Wednesday, September 4, 2013

የወያኔ ጁንታ ለሚወርደው ፕሬዚዳንት ግርማ ወልደጊዮርጊስ በወር የአምስት መቶ ሺህ ብር መኖርያ ቤት ተከራየ::

September 04, 2013
by Minelik S

አገር በኢኮኖሚ እየደቀቅች ለግል ምቾት ገንዘብ ይዘረገፋል:: የወያኔ ጁንታ ለሚወርደው ፕሬዚዳንት ግርማ ወልደጊዮርጊስ በወር የአምስት መቶ ሺህ ብር መኖርያ ቤት ተከራየ:: አዲስ አበባ የሚገኘው የፕሬዚዳንቱ ቢሮ እንዳሳወቀው የወያነ ጁንታ በቅርቡ ለሚወርዱት ሹመኛው ፕሬዚዳንት የ500.000 ሺህ ብር መኖሪያ ቤት መከራየቱን ካፒታል ጋዜጣ ዘግቧል::ታምኝ ምንጮች ለጋዜጣው እንዳሉት የመኖሪአይ ቤቱ የኪራይ ውል ስምምነት ሰነድ ከአቶ ኤሊያስ አራጌ   የመኖሪያ ቤቱ ባለቤት ጋር ተፈርሞ ሙሉ ለሙሉ በውል እና ማስረጃ ክፍል ጸድቆ የተጠናቀቀ ሲሆን መኖሪያ ቤቱ ከነሙሉ ኢቃዎቹ እና የምቾት አቅርቦቶች ጋር ማንኛውንም ነገር ያሟላ ነው::

ምንጮቹ ቤቱ የሚገኝበትን አከባቢ ባይጠቅሱም እዚሁ አዲስ አበባ ውስጥ እንደሆነ ጠቁመው ይህ ውል የተፈጸመው የወያኔን አዋጅ ቁጥር 255/2001 እና በመስከረም 2009 የተሻሻለውን ተመርኩዞ ሲሆን በኢኮኖሚ እየደቀቀች ባለች አገር ላይ የህን ያህል ምቾት ለባለስልጣናት ከመስጠት በአመት የሚወጣው ውጪ አስፈላጊ የአገልግሎት መስጫዎችን ሊገነባ እንደሚችል ተቺዎች ይናገራሉ::

ዝርዝሩን እዚህ ላይ ያገኙታል:- http://www.ethiopianreview.com/forum/viewtopic.php?f=2&t=60420&p=366853#p366853


No comments: