Wednesday, September 18, 2013

4 የአየር ሀይል አብራሪዎች እና አስተማሪዎች ግንቦት 7 ተቀላቀሉ

September 18/2013
By Gezahegn Abebe

ይለያል ይለያል ዘንድሮ የወያኔ ኑሮ!!! 


ኢሳት ዛሬ ማምሻውን በ ሰበር ዜናው እንዳሰራጨው በቅርቡ በሱማሊያና በዳርፉር የሰላም ማስከበር ስራ ላይ ተሰማርተው የነበሩ 4 የኢትዮጵያ ዓየር ሀይል አብራሪውች እና የበረራ አስተማሪዎች የግንቦት 7 ንቅናቄን መቀላቀላቸውን አስታውቋል:: ከኢትዮጵያ አየር ሀይል በመለየት ግንቦት 7ትን መቀላቀላቸውን ለኢሳት ያረጋገጡት የበረራ ባለሙያዎች በአየር ሀይል ውስጥ የተንሰራፋውን ዘረኝነትና አድሎ ለርምጃው እንደገፋፋቸው አመልክተዋል።


በኢትዮጵያ አየር ሀይል ውስጥ ከዘረኝነትና አድሎው ባሻገር በሰራዊቱ ውስጥ የተስፋፋው ሙስና ተቋሙን ለቀው የነጻነት ታጋዮችን ለመቀላቀል እንዳስወሰናቸው ገልጸዋል።
በኢትዮጵያ አየር ሀይል ውስጥ በአብራሪትና በበረራ አስተማሪነት ሲያገለግሉ ቆይተው ስርአቱን የተለዩት አራቱ የበረራ ባለሙያዎች ካፒቴን አክሊሉ መዘነ፣ ካፒቴን ጥላሁን ቱፋ፣ ካፒቴን ጌቱ ወርቁና ካፒቴን ቢንአም ግዛው ናቸው።
በ1998 ኣም በሶማሊያ ከእስላማዊ ህብረት ሀይሎች ጋር በተደረገው ውጊያ ተሰታፊ እንዲሁም በዳርፉር የሰራዊት ማስከበር ተልእኮ የዘመቱት እነዚህ የበረራ ባለሙያዎች ሁለቱ ለከፍተኛ ትምህርት ከተላኩት ቻይና ተመልሰው ትግሉን መቀላቀላቸውን ሲገልጹ ሁለቱ ደግሞ ከሳምንት በፊት ድሬዳዋ ከሚገኘው የአየር ሀይል ምድብ ተነስተው ስርአቱን መክዳታቸው ተመልክቷል።
በቅርቡ የመረጃ መኮንን የነበረው ሻለቃ መሳፍንት ጥጋቡ ግንቦት7ትን መቀላቀሉን መዘገባችን ይታወሳል።
በአሁኑ ጊዜ በርካታ ወጣቶች ንቅናቄውን እየተቀላቀሉ መሆኑን የሚደርሱን መረጃዎች ያመለክታሉ። አንዳንድ እግረኛ የሰራዊት አባላትም ድርጅቱን እየተቀላቀሉና ለመቀላቀልም ጥያቄዎችን እያቀረቡ መሆኑን ለማወቅ ተችሎአል።

የወያኔን አስተዳደር ከድተው ግንቦት 7ትን  የተቀላቀሉት እነዚህ የዓየር ሀይል ከፍተኛ የጦር መኮንኖች 2ቱ ሻለቃ እንዲሁም ካፒቴኖች መሆናቸው ታውቋል::

 ግንቦት ሰባትን የተቀላቀሉት የኢትዬ አየር ሃይል አብራሪ ኣባላቶች ስም ዝርዝር
ካፒቴን አክሊሉ መዘነ
ካፒቴን ጥላሁን ቱፋ
ካፒቴን ጌቱ ዎርቁ
ካፒቴን ቢንያም ግዛው

No comments: