Tuesday, September 24, 2013

የአባይ ቡድን በሁለት ተከፈለ!

September 24/ 2013

ህወሓት በአባይ ወልዱና ደብረፅዮን ቡድኖች በሁለት መከፈሉ ይታወቃል። ባለፈው የህወሓት የማእከላዊ ኮሚቴ ስብሰባ የአባይና የደብረፅዮን ጠብ በጣም በመክረሩ የተነሳ ሽጉጥ መማዘዛቸው ተሰምቷል። ሃይለማርያም ደሳለኝና በረከት ስምዖን ለማስታረቅ የሞከሩ ሲሆን ዉጤቱ አልታወቅም። ይህ በንዲህ እንዳለ የአባይ ቡድንም ሰሞኑ በሁለት ተከፍሏል፤ የአባይ ወልዱና የበየነ መክሩ። ከህወሓት ስብሰባ በኋላ የስልጣን ሽግሽግ ለማድረግ የተሞከረ ቢሆንም በየነ መክሩና ኪሮስ ቢተው ከስልጣናቸው ለመውረድ (ሓላፊነት ለመቀየር) ፍቃደኛ ባለመሆናቸው ከአባይ ወልዱ ጋር ከፍተኛ አምባጓሮ ተፈጥሯል።


ኪሮስ ቢተው የግብርና ቢሮ ሓላፊና የኢንተርፕራይዞች የቦርድ ሰብሳቢ ነበር። አባይ ወደ ሌላ ቢሮ ሊቀይሮው አስቦ ፍቃደኛ ሳይሆን ቀርቷል። የኢንተርፕራይዞች (ብዙ በጀት የሚመደብበት) ስልጣን ግን ቀምቶ ለአለም ገብረዋህድ ሰጥቶታል። ግብርና ቢሮም ለወደ አዳል ታስቦ ነበር። ግን ጠብ ስለተነሳ አልተሳካም። በየነ መክሩም የንግድና ኢንዱስትሪ (የከተማ ልማት ጨምሮ) ስልጣን በእጁ ሲሆን አባይ ቢሮው ለሌላ ሊሰጠው ፈልጎ ፍቃደኛ ባለመሆኑ ግን እስካሁን ውዝግብ ላይ ናቸው። በየነ መክሩ ወደ ሀገሩ (እስራኤል) የመሄድ ሓሳብ ይዟል።
የአባይ ቡድን በሁለት መከፈሉ (አባይና በየነ የሚመሩት) ማሳያ በትግራይ ክልል የዉሃ ሃብት ቢሮ አመራር አባላት የሁለቱ ቡድኖች ደጋፊዎች ተጣልተው እንደተደባደቡና አከባቢው እስካሁን በፌደራል ፖሊስ እየተጠበቀ መሆኑ ተረጋግጧል።
ስርዓት ሲበሰብስ እንዲህ ነው። ለማንኛውም ቸር ያሰማን።

No comments: