Wednesday, September 25, 2013

እስራቱ ቀጥሏል ፖሊሰ የቀድሞውን የኢትዮጵያ ፕሬዘንዳንት ዶክተር ነጋሶ ጊዳዳን አሰረ

September 25/2013

ከገዛኸኝ አበበ
 
እስራቱና ቅስቀሳው መሳ  ለመሳ እየሄዱ ነው ::  አንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ መስከረም 19, 2006 በመስቀል አደባባይ ለሚያደርገው ታላቅ ሰላማዊ ሰልፍ በዛሬው ዕለት በሞራል እና በንቃት በቅስቀሳ ስራ  ላይ ተሰማርተው  እያሉ ሁል ጌዜ ህዝብን ማሸበር ማሰር እና ማሰቃየት ስራው የሆነው የወያኔ መንግስት በበኩሉ ፖሊሶቹን በማሰማራት  በዛሬው ዕለት ለቅስቀሳ ከወጡ መኪኖች ሁለተኛው በቄራ መታገቱንና በቅስቀሳ ስራ ተሰማርተው የነበሩ አባላት በፖሊስ ቁጥጥር ስር እንዲውሉ ተደርገዋል፡፡

ይህ እንዲህ ባለበት ሁኔታ የቀድሞ የአገሪቱ ፕሬዘንዳንት የነበሩት የአንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ ፕሬዘንዳንት ዶክተር ነጋሶ ጊዳዳን ፓሊስ ያሰራቸው ሲሆን ዶክተር ነጋሶ የታሰሩበት ምክንያት የፓርቲውን የቅስቀሳ ቡድን አባላት ለማስፉታት ወደ ጉለሌ ክፍለ ከተማ የሽሮ ሜዳ ፖሊስ ማዘዣ ጣብያ በማምራት ለፖሊሶቹ ልጆቹ ምንም የፈጸሙት ህገ ወጥ ድርጊት ስለሌል እና ልጆቹም ሲቀሰቅሱ የነበረው በመንግስት እውቅና የተሰጠውን ሰላማዊ ሰልፍ ነው ቅስቀሳው ህገ ወጥ ነው የምትሉም ከሆነ እነዚን ወጣቶች የላኳቸው እኔ ስለሆንኩኝ እኔን ልታስሮኝ ትችላላችው በማለቸው ፖሊሰ የቀድሞውን የኢትዮጵያ ፕሬዘንዳንት ዶክተር ነጋሶ ጊዳዳን በማሰር ወጣቶቹን የለቀቀቸው መሆኑን ለማወቅ ችለናል :: 


ነገር ግን የአንድነት ፓርቲ አባላት እና ቅስቀሳው ላይ የተሰማሮት ግለሰቦች በምንም የሚበገሩ አይመስሉም በትናትናው እለት  መንግስት ቅስቀሳውን ለማስተጓጎል ከ28 በላይ አባላትን አስሯ ፓርቲው የተከራያቸው የቅስቀሳ መኪኖች ታርጋቸውን በመፍታት ዳግመኛ ስራ እንዳይሰሩ በትራፊክ እንዲቀጡ ቢያደረግም የመኪና ባለቤቶቹ ፣ ሾፌሮቹና ረዳቶቻቸው “ስራችን ስለሆነ ብቻ ሳይሆን ጭምር ዓላማችሁንም ስለምንደግፍ ከጎናቹ ነን ምንም አይነት ነገር ቢመጣ ወደ ኋላ አንልም” ማለታቸው ይታወሳል፡፡

  The Voice of Freedom



No comments: