Friday, February 15, 2013

ሰበር ዜና!!!
የመርካቶ ወጣቶች መማርያ እና ማረፌያ የነበረው ኢስላህ ትምህርና ልማት ማህበር ትላንት በመንግስት ተዘጋ!!!

በአዲስ አበባ መርካቶ በተለምዶ አደሬ ሠፈር እየተባለ በሚጠራው አካባቢ በሚገኘው የባዩሽ መስጊድ ወጣቶች ጀምአ መስራችነት በካባቢው ህብረተሠብ ተሣትፎ 1997 ተመስርቶ የነበረው ኢስላህ ትምህርና ልማት ማህበር ትላንት ከቀኑ 10 ሠዓት ጀምሮ በፓሊሶች ታሽጓል፡፡ ውስጡ የነበሩ የቢሮ መገልገያ ኮምፒተሮች እና የተለያዩ እቃዋችም በፓሊስ ተወስደዋል፡፡

... ኢስላህ የትምህርት እና እውቀት ማህበር በፍትህ ሚኒስተር እውቅና ያለውና በሀገር በቀል እርዳታ ድርጅትነት የተመዘገበ ሲሆን በባዩሽ መስጊድ ውስጥ የቤተመፅሀፍ አገልግሎት አና በወቅቱ ከቀበሌው አስተዳደር ባገኘው ቤት ለአካባቢው ህዝብ አና አጎራባች ቀበሌ ነዎሪዋች ለሆኑ የቲሞች፤ ትምህርት ጨርሰው ቤት ለተቀመጡ ወጣቶች፤ እንዲሁም ስራ ለሌላቸው ወጣቶች የተለያየ የሞያ ስልጠና ሲሰጥ እና ሲረዳ የቆየ ሲሆን በዚህ ስራውም ብዙ ወጣቶችን ራሳቸውን እንዲችሉ ከፍተኛ አስተዋፅኦ አድርጓል፡፡ ለዚህ ስራውም በክ/ከተማው አስተዳደር ዘውትር ሲመሠገን እና አንደ ሞዴል ሲታይ ቆይቷል፡፡

ትላንት ወደ ድርጅቱ የመጡት ፓሊሦች " ይህ ኢስላህ የትምህርት እና እውቀት ማህበር፡ የአሸባሪዋች እና የአክራሪዋች መፈልፈያ ነው፡፡ " በማለት ያሸጉት ሲሆን እስካሁንም በፓሊስ እየተጠበቀ ነው፡፡ በዚህ የመንግስት ፀረኢስላምና ፀረልማት ድርጊት የአካባቢው ህብረተሠብ በጣም አዝኗል::

No comments: