Friday, February 15, 2013

የነ አንዱዓለም አራጌ እና ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ ይግባኝ ክስ ፍርድ ሳይሰጥ ቀረ


በፌደራሉ አቃቤ ህግ በሸባሪነት ክስ ተመስርቶባቸው በከፍተኛው ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 3ኛ ወንጀል ችሎት የጥፋተኝነት ውሳኔ የተላለፈባቸው የአንድነት ፓርቲ ከፍተኛ አመራር አቶ አንዱዓለም አራጌ እና ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ፣ አቶ ናትናኤል መኮንን፣ አቶ አንዱዓለም አያሌው ፣ አቶ ክንፈሚካኤል ደበበ የስር ፍርድ ቤቱን ውሳኔ በመቃወም 6 ኪሎ ለሚገኘው የፌደራሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኛ በጠየቁት መሰረት ለየካቲት 8 ቀን 2005 ዓ.ም. ለውሳኔ ተቀጥሮ ነበር፡፡ ነገር ግን በዕለቱ የፌደራሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት የመሐል ዳኛው ሳይገኙ ቀርተዋል፡፡
ጠቅላይ ፍርድ ቤትም ውሳኔውን ለመስጠት ጉዳዩ ሰፋ ያለ ጊዜ ስለሚፈልግ አይተን አልጨረስንም ብሏል፡፡ በዚህም ምክንያት የይግባኙን የመጨረሻ ፍርድ ውሳኔ ለመስጠት ለ3ኛ ጊዜ ለመጋቢት 18 ቀን 2005 ዓ.ም. ተለዋጭ ቀነ ቀጠሮ ሰጥቷል፡፡

No comments: