Saturday, July 18, 2015

የቀድሞ የ‹‹አንድነት ለፍትህና ለዴሞክራሲ›› ፓርቲ የአዲስ አበባ ወጣቶች አደረጃጀት የፋይናንስ ኮሚቴ አባል ፍቃዱ በቀለ ታሰረ

July 18,2015
ዛሬ ጥዋት ሌላ የእስር ዜና ሰማን፡፡ የታሰረው፣ የቀድሞ የ‹‹አንድነት ለፍትህና ለዴሞክራሲ›› ፓርቲ የአዲስ አበባ ወጣቶች አደረጃጀት ውስጥ የፋይናንስ ኮሚቴ አባል እና የወረዳ 15 ሰብሳቢ የነበረው ፍቃዱ በቀለ ነበር፡፡ አጋጣሚ ከወዳጄ አናንያ ሶሪ ጋር ስለነበርን ‹‹በምን ይሆን ደግሞ?›› ብለን ራሳችንን መጠየቃችን አልቀረም፡፡ ወላጅ እናቱና እህቱን በአካል ጠይቀን እንደተረዳነው፣ አንድ ጓደኛው ‹‹አሸባሪ ነው›› ብሎ ጠቁሞበት መሆኑን ነው፡፡ እኛም ካዛንቺስ ስድስተኛ ፖሊስ ጣቢያ ልንጠይቀው ሄደን ‹‹እሱን ማግኘት አይቻልም›› ብሎ አንድ ፖሊስ ቢነግረንም በአጋጣሚ ከርቀት አይተነው ሰላም ልንለው ችለናል፡፡
እንግዲህ፣ በየዕለቱ የዜጎችን እስር መስማት የተለመደ ሁነት ሆኗል፡፡ የባለፈው ሳምንት ሐሙስ ዕለትየ‹‹ቀዳሚ ገጽ›› ሥራ አስኪያጅ እና የቀድሞ የ‹‹ሚሊየኖች ድምጽ›› ሪፖርተር የነበረው ሃብታሙ ምናለም ‹‹የአልሸባብ ሴል ነህ፤ ኦባማ በሚገኝበት ስብሰባ ላይ የቨብር ተግባር ልትፈጽም አሲረሃል›› ተብሎ ተጠርጥሮ መያዙንና ፍርድ ቤት ቀርቦም ለድጋሚ ቀጠሮ ለሐምሌ 20 ቀን 2007 ዓ.ም መቀጠሩ ይታወሳል፡፡ ከዚህ በተጨማሪም ከቀናቶች በፊት ሌላ የቀድሞ አንድነት ሴት አባል ከታሰረች በኋላ መፈታቷም የሚታወቅ ሲሆን አበበ ቁምላቸው የሚባል የቀድሞ አንድነት በአሁን ወቅት የሰማያዊ ፓርቲ አባልም ‹‹ወደኤርትራ ሰው ትመለምል ነበር፣ አንተም ወደዚያ ልትሄድ አስበሃል›› ተብሎ አሁንም ድረስ በካሳንቺስ ስድስተኛ ፖሊስ ጣቢያ ታስሮ ይገኛል፡፡
Elias Gebru Godana's photo.

No comments: