Friday, July 15, 2016

መፍትሄው አንድ ብቻ ነው - ህዝቡን ማክበር (ግርማ ካሳ)

July 14,2016
"አጋዚና ተጨማሪ የመከላከያ ኃይል ወደ ጎንደር ማምሻውን ገብቷል!!" የሚል ዜና አነበብኩ። አጋዚን ወደ ህዝብ መላክ መፍትሄ አይደለም። ነገሩን የበለጠ ነው የሚያባብሰው።

አጋዚ ተቀባይነት የለውም። አጋዚማ በሌሊት እንደ ወንበዴ መጥቶ ሰላማዊ ዜጎችን ለማፈን ሲል አሁን የተፈጠረውን ቀዉስ ያመጣው እርሱ ነው። እዚህ ላይ "አጋዚ አይደለም፣ የፌዴራል ፖሊስ ነው ምናምን .." የምትሉ ልትኖሩ ትችላላችሁ። በኔ ግምት ያው ናቸው። የተለያዩ ስም ያላቸው፣ የተለያየ ልብስ የሚለብሱ፣ ግን አንድ አይነት ተግባር የሚፈጸሙ፣  በሕወሃት ብቻ የሚታዘዙ ጸረ-ህዝብ ታጣቂዎች።

እነዚህ ሃይሎች ህዝብን ሲጠበቁ አላየንም። በጋምቤላ አሸባሪዎች መጥተው ወገኖቻችን ሲገድሉ በዚያ አልነበሩም። በሱዳን ድንበር ሱዳኖች ገበሬዎቻችንን ሲያጠቁ፣ ኢትዮጵያዉያንን ለመጠበቅ አልተንቀሳቀሱም። ሁልጊዜ የነዚህን ታጣቂዎች ጉልበት የምናየው ሰላማዊ ዜጎችን፣ ሕጻናትን አረጋዊያን እና ራሳቸውም መመከት የማይችሉት ሲደበድቡና በጠራራ ጸሃይ ተኩሰው ሲገድሉ ነው። በቅርቡ በኦሮሚያና አዲስ አበባ በንፋስ ስልክ አካባቢ በሕዝቡ ላይ ያደረጉትን ብቻ መመልከት ይበቃል።

ከጎንደር በተለያዩ ገጠሮችና ከተማዎች እያየን እንዳለው፣ ሕዝቡ እጅግ በጣም አምሯል። ከዚህ በኋላ የባርነት እና የጭቆናን ቀንበር ላለመሸከም ተማምሏል።

በነገራችን ላይ በጎንደር የተነሳው ከየትም የመጣ እንቅስቃሴ አይደለም። ወያኔዎች እንደሚሉት ከ ኤርትራ የመጣ አይደለም። የሻእቢያ እጅ  የለበትም። እንደው ሻእቢያ ቢያግዝ የሚያግዘው ወያኔዎችን ነው። ኤረትራ አሉ የሚባሉ ደግሞ  የት እንዳሉ ሁላችንም የምናወቀው ነው። ብዙም በዚያ ዙሪያ መጻፍ አያስፈለግም። እያየን ያለው እንቅስቃሴ፣ በሕዝቡ ዉስጥ ያለ ፣ ገንፍሎ የወጣ የነጻነትና የፍትህ ጥያቄ ነው።  ልክ በኦሮሚያ እንደነበረው፣ በሕዝብ ሃይል ላይ ብቻ የተመሰረተ እንቅስቃሴ ነው።

ወያኔዎች ከማንም በላይ ይሄንን የጎንደር ህዝብ የሚያወቁት ይመስለኛል። ምናልባት ጥጋቡ፣ ጮማዉና ስቡ አይምሯቸዉን ሸፍኖ  ያለፈዉን ታሪክ ካላስረሳቸው በስተቀር።

በመሆኑም ወደ ጎንደር እየላኩት ያለውን አጋዚ ወደ መጣበት ቢመልሱ፣ የገባም ካለ ደግሞ ቢያስወጡ ይሻላቸዋል። ጉዳዩን የክልሉ አስተዳደር በሰለጠነ መልኩ ማስተካከል ይችላል።

ይሄን የምጽፈው ለማስፈራራት አይደለም። በሜዳ ላይ ያለዉን ተጨባጭ ሁኔታ ከግምት በማስገባት እና ወደ ለየለት ጦርነት ከሚኬድ በሚል ነው። አጋዚዎች መጥተው እንደለመዱት እንግደል፣ እንጨፍጭፍ ቢሉ የተለየ ሁኔታ ነው የሚያጋጥማቸው። ተሸናፊ የሚሆኑት፣ የሚያልቁት ራሳቸው ናቸው። የአካባቢው መሬት ከዉጭ ለመጡ አመች አይደለም። ተራራማ ነው። እንኳን የታጠቀ ፣ ገደል ሸንተረሩን የሚያውቅ ህዝብ በነቂስ ወጥቶ ቀርቶ፣ የቆረጡ ፣ ጥቂቶች ብቻ ይሄ የሰላማዊ ዜጎችን ደም እየጠጣ የደለበን የአጋዚ ጦር ድባቅ ማድረግ አያቅታቸዉም።

የወያኔ ባለስልጣኖች ልብ ይግዙ እላለሁ። ሕዝቡ ተናግሯል። አንፈልጋችሁም ብሏቸዋል። ሕዝቡን ይተወት ። አበቃ !!!!!!

ከዚህ በታች የምታይዋቸው የፌዴራል ልብስ የለበሱ የሕወሃት ሚሊሺያዎችን ነው። ሕዝቡ በሰላም በተቀመጠበት በመተንኮሳቸው የወደቁ ናቸው። በጣም ያሳዝናል።እድሜ ለወያኔዎች ለሰላም፣ ለፍቅር፣ ለብሄራዊ እርቅ በሮችን በሙሉ ዘግተው፣  እንደዚህ እንድንተላለቅ እያደረጉን ነው። ያሳዝናል። እስከአሁን ጥይት የሚተኮሰው በአንድ አቅጣጫ ነበር። አሁን ከሁለት አቅጣጫ እየሆነ መጥቷል።

ደግሜ እላለሁ።፡ይሄንን ህዝብ ወያኔዎች ባይተነኩሱት ይሻላል። የሕዝቡ ጥይቄ ቀላል ነው። ሰላም፣ ፍትህ፣ ነጻነትና እኩልነት ነው። በአገራችን ሁለተኛ ዜጋ አንሁን የሚል ነው። የሕዝቡን ጥያቄ ማክበርና መቀበል ነው ብቸኛው የሚያዋጣው መፍትሄ።




Thursday, July 14, 2016

አርበኞች ግንቦት 7 ለጎንደር ህዝብ አጋርነቱን እየገለጸ እንደሚገኝ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ተናገሩ

July 14,2016

አርበኞች ግንቦት 7 መስዋዕትነት እየከፈለ ለሚገኘው የጎንደር ህዝብ አጋርነቱን እየገለጸ እንደሚገኝ ሊቀመንበሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ተናገሩ። የአርበኞች ግንቦት 7 ሊቀመንበር ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ በምስልና ድምፅ ከኤርትራ ረቡዕ ዕለት ባስተላለፉት መልዕክት የአማራም ህዝብ ሆነ መላው የኢትዮጵያ ህዝብ አጋርነቱን እንዲያሳይ ጥሪ አቅርበዋል።


የወልቃይት ህዝብ ማንነቱን በተመለከተ በህጋዊና ሰላማዊ በሆነ መንገድ ያቀረበው ጥያቄ በህወሃት በኩል የሃይል ምላሽ መሰጠቱ የቀሰቀሰው ተቃውሞ ወደግጭት ማምራቱን በጥሪያቸው ያስታወሱት ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ፣ በጎንደር የታየው ህዝባዊ ዕምቢተኝነት በስርዓቱ ሰለባ ለሆኑትና ለውጥ ለሚሹ ሁሉ መነቃቃትን የፈጠረ እንደሆነ አመልክተዋል።

“ከተባበርን አንጸናለን፣ ከተከፋፈልን እንወድቃለን” በማለት ለሁሉም ኢትዮጵያውያን የአጋርነት ጥሪ ያቀረቡት ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ፣ “ዛሬ በጎንደር ከተማ እና አካባቢዋ እየተዋደቁ ካሉ ወገኖቻችን ጎን ካልቆም በህወሃት የሚደርስብን አፈና ማለቂያ አይኖረውም በማለት መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል። የአርበኞች ግንቦት 7 ሊቀመንበር ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ለመከላከያና ለፌዴራል ፖሊስ አባላት ለብዓዴን፣ ኦህዴድ፣ ደህዴን እንዲሁም ለህወሃት አባላት ጭምር በገዳዮችና ዘራፊዎች ላይ ተነሱ በማለት ጥሪ አቅርበዋል።
አገዛዙን በመቃወም የሚደረጉ ህዝባዊ እንቅስቃሴዎች የትግራይን ህዝብ ለማጥቃት የተካሄደ በማስመሰል የሚቀርበውን አሳፋሪ ሴራ እንዲያጋልጥም መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።

የኦሮሚያና የአማራ ክልል የፖሊስና የሚሊሺያ አባላት ለነበራችውና አሁንም ላላችሁ በጎ ሚና ህዝቡ አክብሮቱን ይሰጣችኋል በማለት ከኤርትራ በምስልና በድምፅ መልዕክት ያስተላለፉት ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ከዚህ ውጭ በወንጀል ተባባሪ የሆኑና በግድያ ተሳታፊ የሆኑ የጸጥታ ሃይሎች በማናቸውም መንገድ ከተጠያቂነት ነጻ እንደማይሆኑ አሳስበዋል።

“በአንድነት ከተነሳት የነጻነት ቀን ቀርባለች” በማለት ወደንግግራቸው ማጠቃለያ የመሩት ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ፣ በሁሉም የሃገሪቱ ክልሎች የአርበኞች ግንቦት 7 ታጋዮች እንደሚገኙ አመልክተው፣ “ስትሞቱ እየሞትን ስትቆስሉ እየቆሰልን፣ ሊገድሏችሁ ያኮበኮቡትን እየታገልን እስከመጨረሻው የድል ምዕራፍ ከውስጣቸው እንደማንለይ ዕወቁት” ሲሉ መልዕክታቸውን አጠቃለዋል።

Wednesday, July 13, 2016

በጎንደር ሶስት የፌዴራል ፖሊሶች ሲገደሉ ሕዝቡ ቁጣው አሁንም እንደገነፈለ ነው። የህወሓት ደጋፊ ንግድ ቤቶች ወድመዋል።

July 13,2016
በጎንደር የሕዝቡ ቁጣ የቀጤለ ሲሆን ሕዝቡን ለማጥቃት ወደ ጎንደር የዘለቁ የፌዴራል ፖሊሶች እና የደህንነት ሃይሎች ጥቃት እየደረሰባቸው መሆኑ ተሰምቷል። ብሶቱ ገንፍሎ ኣደባባይ የወጣው ሕዝብ ራሱን በመሰዋት ነጻነቱን ለማረጋገጥ በመታገል ላይ ሲገኝ ለወያኔ ኣገዛዝ ማነቱን ከማሳየቱም በላይ ኣገዛዙን እንደማይፈልግ በሰልፍ ጭምር ኣረጋግጧል፤ ኣገዛዙ ሕዝብን ከሚያዘናጋባቸው እና ከሚያታልልባቸው መንገዶች ኣንዱ ድርድር ሲሆን የወልቃይት ጉዳይን በተመለከተ የተዋቀረውን ኮሚቴ ኣባላት ኣንዱ ከሆኑት ከኮሎኔል ደመቃ ጋር ድርድር ተቀምጧል የሚሉ መረጃዎች እየወጡ ቢሆንም ለኮሎኔሉ ቅርብ የሆኑ ምንጮች ግን ኮሎኔሉ ከማንም ጋር መደራደር እንዳልጀመሩ በመግለጽ ሊደራደሩ ቢሉ እንኳን ከወያኔ በኩል ኣስተማማኝ ነገር እንዳሌለና የታሰሩትም እንዳልተፈቱ ገልጸዋል።
የአማራ ገበሬ ጦር ቦታ ይዞ እዬተጠባበቀ ነው። አራቱ ታፍነው የተወሰዱ ኮሚቴዎቻችን በአስቸኳይ እንዲለቀቁ ጠይቀዋል። ያ ካልሆነ ከፍተኛ አደጋ እንደሚጥሉ ተናግረዋል። በአራቱም አቅጣጫ ወደ ከተማዋ የአማራ ገበሬ ጦር እዬተመመ ነው። ምንም እንኳ በየኬላው የመከላከያ ጦር ዘግቶ ቢጠብቅም አማሮች መግቢያ አላጡም ።በዛሬው እለት ብቻ ሁለት ከፍተኛ የህወሓት ደህንነቶችና ሶስት የፌዴራል ፖሊሶች ተገለዋል። የህወሓት ደጋፊ ንግድ ቤቶች ወድመዋል። ፩ኛ ሁመራ ፔኒስዬን - ፪ኛ ጣና ሆቴል - ፫ኛ ሮማን ሆቴል - ፬ኛ ቋራ ሆቴል …ከቀላል እስከ ከፍተኛ ውድመት የደረሰባቸው ሆቴሎች ናቸው። ወርቅ ቤቶችም አላመለጡም።ህዝቡ በምሬት የህወሓት ደጋፊ የሆኑ የትግራይ ተወላጆች ጎንደርን ለቀው እንዲወጡ ሲያሳስብ ውሏል።
ምንጭ ሚኒሊክ ሳልሳዊ

Monday, July 11, 2016

ዜጎችን ማፈናቀል መግደልና ማሰደድ የህወሃት አይነተኛ መግለጫዎች ናቸው !!!

July 11,2016

አርበኞች ግንቦት7
ህዝባዊ ወያኔ ሃርነት ትግራይ ወደ ስልጣን ከመጣበት ጊዜ አንስቶ በአገራችንና በህዝባችን ላይ ሲፈጽም የቆየውና እየፈጸመ ያለው ግፍና ስቃይ ተዘርዝሮ የሚያልቅ አይደልም። አፈና ፣ እስር፣ ግድያና ዜጎችን ማፈናቀል አይነተኛ መግለጫዎቹ የሆነው ይህ የህወሃት አገዛዝ፣ ሰፋፊ የእርሻ መሬቶችንና የከተማ ቦታዎችን በመቸብቸብ ሃብት ለማካበት ባለው ዕቅድ በ10 ሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎችን እትብታቸው ከተቀበረበት ቀዬና የትውልድ መንደሮቻቸው በግፍ እንዲፈናቀሉ አድርጎአል። አሁንም እያደረገ ነው ።
ሰሞኑን በአዲስ አበባ በንፋስ ስልክ ክፍለ ከተማ ቀርሳና ኮንቶማ በተባሉ ቀበሌዎች ከ30 ሺ በላይ የሚገመት ህዝብ ለአመታት ከኖረበት መኖሪያ ቤቶች በሃይል ተገፍትረው በመውጣት ጎዳና ላይ እንዲበተኑ ተደርጎአል። በዚህም እርምጃ ምክንያት አቅመደካማ የሆኑ አዛውንቶች፤ ነፍሰጡሮችና ከወለዱ ገና ሳምንታት ያልሞላቸው እመጫቶች፤ የሚያጠቡ እናቶች፤ ህጻናትና ለጋ ወጣቶች ለከፋ ችግር ተዳርገው ለቅሶና ዋይታ በማሰማት ላይ ናቸው ። በስንት ልፋትና ድካም ከሰሩዋቸው ቤቶች ተለዋጭ ቦታ ሳይሰጠን ወይም ካሳ ሳይከፈለን አንወጣም በማለት ለማንገራገር የሞከሩ 10 ሰዎች በፖሊስ ጥይት ተገደለዋል፤ በመቶዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ደግሞ ለእስር ተዳርገዋል።
ህወሃት እንዲህ አይነት የጭካኔ እርምጃ እየወሰደ ያለው በክፍለ ከተማው የሰፈሩት ሰዎች "ህገወጦች ናቸው" በሚል ሰበብ ነው። ትናንት ባዶ እግራቸውን ነፍጥ አንግበው ቤተመንግሥቱን የተቆጣጠሩና ጄሌዎቻቸው ከመሃል ከተማው ዜጎችን እያፈናቀሉ ቪላና ሰማይ ጠቀስ ፎቆች ሲገነቡ ህገወጥ ያልተባሉት ሰዎች፣ አረብ አገር ድረስ ተጉዘው በግርድና ሥራ ሳይቀር በመሥራት ባገኙት ገንዘብ በአገራቸው መሬት ላይ ጎጆ የቀለሱ ለምንድነው ህገወጥ የሚባሉት የሚለውን ለታሪክ ፍርድ እንተወውና እነዚህ ህገወጥ የተባሉ ሰዎች በመንግሥት ይዞታ ሥር ካሉ የአገልግሎት ድርጅቶች ጋር ተዋውለው መብራትና ውሃ አስገብተው ሲጠቀሙ መኖራቸው ፤ ገንዘብ በማዋጣት መንገድ ፤ ጤና ጣቢያዎችንና ትምህርት ቤቶችን በከተማው አስተዳደር ድጋፍ ማስገነባታቸው ፤ የህወሃት የንግድ ድርጅቶች በሚሊዮኖች የሚቆጠር ትርፍ ለሚዝቁበት የአባይ ግድብ ቦንድ በየመኖሪያቤታቸው ቁጥር ሲሸጥላቸው የነበረና የምዕራቡን አለም ለማደናገር በየአምስት አመቱ የሚደረገውን የምርጫ ድራማ ለማድመቅ በግዳጅ እንዲመዘገቡና ድምጽ እንዲሰጡ ሲደረጉ መቆየታቸው ብቻውን አገዛዙ ሲመቸው እውቅና ሰጪ ሳይመቸው ደግሞ እውቅና ነሺ መሆኑን የሚያሳይ፣ ለፍትህና ለርእትዕ የማይሰራ የዘራፊዎች ቡድን በመሆኑ፣ የድሆችን ቤቶች ለማፍረስ የወሰደው እርምጃ በየትኛውም መስፈረት ተቀባይነት የሌለው ህገወጥ ድርጊት ነው። ለነገሩ ህገወጥ ከሆነ ቡድን ህጋዊነትን መጠበቅ አይቻልምና ወያኔ በህግ ሽፋን የሚወስዳቸው እርምጃዎች ሁሉ ህገወጥነታቸውን አይለውጠውም።
አባቶቻችን አገራቸውን ከባዕድ ወረራ ለመከላከል ደማቸውን ያፈሰሱትና አጥንታቸውን የከሰከሱ መጪው ትውልድ በአገሪቱ አንገት ማስገቢያ ጎጆ እንዲኖረው በማሰብ እንጅ፣ በደምና በአጥንት የተገዛው መሬት ለውጭ አገር ዜጎች እንዲቸበቸብ ወይም በመንግስት ስም የተደራጁ ሽፍቶች እንዲዘርፉት አልነበረም።
ሌላው አስገራሚና አሳዛኙ ነገር እንዲህ አይነት ሰቆቃ የተፈጸመባቸውና በዚህ ክረምት ወቅት ቤቶቻቸው ፈርሶና ንብረቶቻቸው ወድሞ ወደ ፍጹም ድህነት እንዲገቡ በተደረጉት ዜጎች መሬት ላይ ፣ ህወሃት ኮንዶሚኒዬሞችን ገንብቶ ለዲያስፖራ ለመቸብቸብ ዕቅድ ያለው መሆኑ ነው ። ዲያስፖራው አገዛዙ በወገኖቹ ላይ የሚፈጽማቸውን ሰቆቃና ግድያ በማጋለጥ ሥራ ላይ በመጠመዱ የህወሃት መሪዎች እረፍት አጥተዋል። በተለይ ከምርጫ 97 ወዲህ አጋዚ የተባለው ሃይል በሰብአዊነት ላይ የሚፈጸም ወንጀል የቀን ጉዳይ ካልሆነ በቀር በአለም አቀፍ ወንጀል እንደሚያስጠይቅ ወያኔ ይረዳል። ይህንን ስጋት ለማስቆም የዲያስፖራን እንቅስቃሴ ማዳከም እንደስትራቴጂ ነድፎ መንቀሳቀስ የጀመረው የነ ቴዎድሮስ አድሃኖም አገዛዝ፣ ዲያስፖራውን በጥቅም በመከፋፈል ስጋቱ ይቀነሳል ብሎ ያምናል። ከዚህም በተጨማሪ አገር ውስጥ የሚደረገውን አልገዛም ባይነት ትግል ለማጠናከር የዲያስፖራው እምቅ ሃይል የሚፈጥረውን ተአምር ህወሃት አውቆታል። ላፍቶ ክፈለ ከተማ 40 በ60 በተባለው ፕሮጄክት የኮንዶሚኒዬም ባለቤት በመሆን የአገራቸውንና የወገኖቻቸውን ስቃይ ለማራዘም ላኮበኮቡ የዲያስፖራ አባላት እየተመቻቸች ያለ ሰፈር ነው። ከውስጧ እየተሰማ ያለው ለቅሶና ዋይታ የማይቆረቁራቸው ፤ ኮንዶሚኒዬም ቤት የሚያማልላቸው ዲያስፖራዎች አይኖሩም አይባልም።
አርበኞች ግንቦት 7 የህወሃት አገዛዝ ዜጎችን በመግደልና በማሰር ከቀያቸውና ከመኖሪያቤታቸው በሚያፈናቅለው የከተማም ሆነ የገጠር መሬት ላይ ማንም ሰው በህግ ፊት በዘላቂነት የሚጸና መብት ሊያገኝ ይችላል ብሎ አያምንም። ህወሃት በሚወረውርላቸው የጥቅም ፍርፋሪ የወጎኖቻቸውን ስቃይና መከራ ዕድሜ እያራዘሙ ያሉ ከየማህበረሰቡ የተገዙ ስላሉ በተለመደው ርካሽ ዋጋ በንጽጽር ደህና መኖር እየቻለ ካለው የዲያስፖራ ማህበረሰብ ሰዎችን መሸመት እችላለሁ ብሎ ህወሃት እየተንቀሳቀሰ ነው። በቴዎድሮስ አድሃኖም ጽ/ቤት ተዘጋጅቶ በተግባር እንዲተረጎም በውጪ አገር ባሉ የወያኔ ኤምባሲ ሁሉ የተበተነው የዲያስፖራ ፖሊሲ አላማ ይሄ ነው። ቀርሳና ኮንቶማ በእንዲህ አይነት ርካሽ ጥቅም የሚሸመቱ የዲያስፖራ አባላትን ለማሰባሰብ እየተዘጋጀ ያለ ሰፈር ነው። አርበኞች ግንቦት 7 የሶስት ቀን አራስ በተገደለችበት፤ በርካታ እናቶች ፤ አቅመደካማ አዛውንቶችና ታዳጊ ህጻናት ተፈናቅለው ለጎዳና ተዳዳሪነት በተዳረጉበት ቦታ ላይ የሚገነባውን ኮንዶሚኒዬም፤ ለተለያዩ አገልግሎት የሚሆኑ ህንጻዎች ወይም ሌላ ኢንቬስትመንት ባለቤት ለመሆን በየዋህነት ያሰፈሰፉ ካሉ ውሳኔያቸውን ቆም ብለው እንዲያጠኑት ይመክራል። ከቤታቸው ተፈናቅለው እንባቸውን እያፈሰሱና በየሜዳው ተበትነው የሚንከራተቱ ወገኖቻችን እንባ ሳይደርቅ ህወሃት ወደ መጨረሻው ከርሰመቃብር ይወርዳል። ይህ ምኞት ሳይሆን የቆምንለትና እየሞትንለት ያለው ትግል ውጤት ነው።
ወያኔ ሃብት ለማካበት በሚያጧጡፈው የመሬት ንግድ የሚፈናቀሉ ወገኖቻችን ህይወት ሁላችንንም ይመለከታል። የአገሪቱን ዜጎች ለጎዳና ተዳዳሪነት በመዳረግ የሚገነቡ አዳዲስ ህንጻዎችና መንገዶች ልማት ሳይሆን ማህበራዊ ቀውስ በመፍጠር ህብረተሰቡን ለከፍተኛ ችግር የሚዳርግ አደጋውም ለአገር የሚተርፍ ነው። አልጠግብ ባይ ጥቂት የህወሃት አመራሮች ህዝባችንን ሲያፈናቅሉትና አገር አልባ ሲያደርጉ ዝም ብሎ መመልከት ችግሩ እንዲባባስና እያንዳንዳችን የጥቃቱ ሰለባ እንዲንሆን መጋበዝ ነው። አርበኞች ግንቦት 7 ይህንን የህወሃት ዜጎችን የማፈናቀል እርምጃ ለማስቆምና በግፍ ለተገደሉ ወገኖቻችን በህግ ለመፋረድ ሁሉም ኢትዮጵያዊ በያለበት ጸረ ወያኔ ትግሉን እንዲያፏፉምና ትግሉን እንዲቀላቀል ወገናዊ ጥሪውን ያቀርባል።
ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ!!

Friday, July 8, 2016

ሰበር ዜና… በወያኔ ወታደራዊ ደህንነት አባላት ላይ እርምጃ ተወሰደ

July 8,2016
በልኡል አለም
በሰሜን የሐገራችን ክፍል በህቡእ የተደራጁ የዉስጥ አርበኞችና የትግል አጋሮች በአንድነት በመተባበር ቀንደኛ እና አደገኛ በሆኑ በትግራይ ነጻ አዉጪ ቡድን የመከላከያ ሰራዊት የደህንነት አባላት ላይ እርምጃ ወስደዋል። ቢያንስ ከ6 ወራት በላይ የፈጀዉን ድርጊት ከመራዉ የህቡእ ኃይል ህበረት ወስጥ የወጣዉ መረጃTPLF security officers killed in Gondar እንደሚጠቁመዉ።
ወታደር አሳምን ሃለፎም፣
ወታደር በረከት ድረስ፣
ወታደር ሰይድ ይማም፣
ወታደር የትናየት ላቀዉ፣
ወታደር ጀምበሩ ዘለቀ።
የተባሉ እነዚህ እርምጃ የተወሰደባቸዉ አባላት የሕዝብ ጠላትነታቸዉን በግልጽ ያስመሰከሩ ያለ አግባብ የሚያስሩ፣ የሚገድሉና ወገኖቻችንን የሚያሳድዱ በተለይም በጎንደር አካባቢ መሬታችንን ለሰሜን ሱዳን አሳልፎ ለመስጠት ደፋ ቀና የሚለዉ የወያኔ አገልጋዮች በወልቃይት ጠገዴ አፋኞችና ገዳዮች ሲሆኑ በተለያዩ ወቅቶችና ግዜያቶች ከሰፊዉ ህዝብ ጎን እንዲቆሙ ትእዛዝ ቢሰጣቸዉም አሻፈረኝ በማለታቸዉና በእኩይ ተግባራቸዉ በመቀጠላቸዉ ነዉ።
፣እርምጃዉን የወሰዱት የህቡህ ተደራጅ ሐይ መሪዎች በተለያየ ወቅትና ግዜ እነዚህን የወታደራዊ ደህንነት ሰዎች ካገቷቸዉ በኋላ ከሰሜኑ ግንባር ብሔራዊ ደህንነት ጋር ድርድር ላይ የነበሩ ሲሆን በድርድሩ የወያኔ ጽንፈኛ ቡድን ባደረገዉ ስህተት ምክንያት እርምጃዉን ለመዉሰድ መገደዳቸዉን አስታዉቀዋል።
ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ !

Thursday, July 7, 2016

ግልጽ ደብዳቤ ለአቶ ጌታቸው አሰፋ ለብሄራዊ መረጃና ደህንነት ሃላፊ (ከታማኝ በየነ እና ሲሳይ አጌና)

July 7,2016
ለአቶ ጌታቸው አሰፋ
ለብሄራዊ መረጃና ደህንነት ሃላፊ
ስማችን ከስር የተመለከተው ግለሰቦች በሃገራችን ነጻነት እውን እንዲሆን ከሚፈልጉ በሚሊዮኖች ከሚቆጠሩ ኢትዮጵያን ውስጥ እንገኛለን። በሃገራችን በነጻነት መኖር ወይንም ሃገራችንን በነጻነት ማየት ባንችልም በሰው ሃገር በነጻነት እንኖራለን፥ ሆኖም በሃገራችን ያጣነውን ነጻነታችንን ለማስመለስ፣ በጥቅል ኢትዮጵያ እና ኢትዮጵያውያንም በነጻነት እንዲኖሩ የአቅማቸውን ጥረት ከሚያደርጉት ውስጥ ነን።ይህ ጥረታችን በደህንነት መስሪያ ቤትዎም ሆነ በሕወሀት መንግስት እንደማይወደድ የምናውቅ ቢሆንም ማስፈራሪያና መደለያ በማቅረብ ትደፍሩናላችሁ የሚል ግምት ግን አልነበረንም።Tamagne Beyene and Sisay Agena to Getachew Assefa
ለዚህ መነሻ የሆነን እና ከስራ ባልደርቦቻችን እንዲሁም ካለንበት ተቋም ኢሳት ውጭ በግል ለመጻፍ ያነሳሳን ረቡዕ ሰኔ 22 ቀን 2008 ዓ.ም /June 29/2016/ የተላከልን መልዕክት ነው።የርሶ ማለትም የደህንነት መስሪያ ቤት ሰራተኞች እንዲሁም የገዢው ፓርቲ ባለስልጣናት በየወላጆቻችን ቤት በመገኘትና በመጥራት በተጠቀሰው ቀን የሰጡት ማሳሰቢያ እና መደለያ እንደደረሰን እየገለጽን፣ እ ንደማንቀበል ለማረጋገጥ ይህን ለመጻፍ ተገደናል ።
ወንጀል የፈጸመ ግለሰብ ወይንም ቡድን ቢሆን እንኳን ወንጀል በስጋ ዝምድና እንደማይተላለፍ ለአቅም አዳም ለደረሱ ያውም መንግስታዊ ሃላፊነት ላይ ላሉ ባለስልጣናት እንደማይጠፋቸው ቢታምንም በክፋት፣በጥላቻ እና በዘረፋ ግዚያቸውን ለሚያባክኑት የሕወሓት መሪዎች ይህ አለመከሰቱ አይገርመንም። እኛን ዝም ለማሰኘት አዛውንት እና ሕጻናትን በመያዣነት /hostages/ ለመያዝ ስትወስኑ ምን ያህል አቅም እያነሳችሁና ተስፋ እየቆረጣችሁ እንድሆንም አሳይቶናል።
እናንተ በደል አንገፈገፈን ብላችሁ ለመብታችሁ እሰከመጨረሻው ታግላቹኋል።እናንተ በተራችሁ በበደል ላይ በደል ስትጭኑብን ፡ ኢትዮጵያን በዘረኝነት ስትቀጠቅጡና ስትዘርፉ፣ ዜጎችን በገዛ ሃገራቸው ባይተዋር ስታደርጉ ይህንን በዝምታ እንድንመለከት ማስፈራሪያ እና መደለያ መላካችሁ የሚያናድድ ቢሆንም፣ ይህ ድፍረት ይበልጥ ጉልበት እንደሰጠን ለርስዎም ሆነ በሕወሃት ለሚመራው መንግስት ማስታወስ እንሻለን። ማናቸውም ማሰፈራሪያና መደለያ እንዲሁም ቤተሰቦቻችንን በዕገታ መያዝ ከነጻነት ጉዞ አንዲት ስንዝር እንደማትመልሱን በተግባራዊ ርምጃዎቻችን የምትመለከቱት ይሆናል።

Wednesday, July 6, 2016

በኤርትራ ምድር በምርኮ ተይዘው የሚገኙ የወያኔ ወታደሮች አርበኞች ግንቦት ለመቀላቀል እንደሚፈልጉ አስታወቁ።

july 6/2016
በቅርቡ በፆረና ግንባር ወያኔ በቆሰቆሰው ጦርነት በኤርትራ ወታደሮች ተማርከው በእስር ላይ የሚገኙት የኢትዮጵያ ወታደሮች የኦሮሞና የአማራ እንዲሁም ከተለያዩ ብሄሮች የተውጣጡት ወደዚህ ጦርነት የገቡት በትግሬ የጦር አዛዦች አስገዳጅነት መሆኑን በመናገር የኤርትራ መንግሥት ይቅርታ የሚያደርግላቸው ከሆነ አርበኞች ግንቦት 7ን በመቀላቀል ዘረኛውን ገዳዩን የወያኔ ስርዓት ለመዋጋት እንደሚፈልጉ መናገራቸውን ከኤርትራ ምድር የወጣው መረጃ በታማኝ ምንጮቻችን በኩል ሊረጋገጥ ችሎዋል።

የጦር ምርኮኞቹን ጉዳይ አስመልክቶ የኢትዮጵያ መንግስት ከጋዜጠኞች ለቀረበለት ጥያቄ በአቶ‪ ‎ጌታቸው_ረዳ‬ በኩል የተሰጠው ምላሽ
<<ምንም የተማረከ ወታደር የለም እንዲያው ጀግናው የመከላከያ ሰራዊታችን እስከ 200 ሜትር ድረስ ለትንኮሳ የመጡትን የኤርትራን ወታደሮች እያሳደደ አጥቅቷል>>የሚል እንደነበር የሚታወስ ነው።

የነዚህን የኢትዮጵያ ምርኮኛ ወታደሮች የወደፊት እጣ ፈንታ አስመልክቶ የኤርትራ መንግስት ምን ሊወስን እንደሚችል እስካሁን ድረስ ምንም የታወቀ ነገር ባይኖርም በጉዳዩ ዙሪያ የኤርትራ ባለስልጣናት ከአርበኞች ግንቦት 7 አመራሮች ጋር ሊነጋገሩበት እንደሚችሉ መረጃውን ካደረሱንታማኝ ምንጮቻችን ለመረዳት ችለናል።

Tuesday, July 5, 2016

የህወሃቱ ሹም ራሳቸውን በራሳቸው ካዱ

July 5,2016

“የአምስት ቀን አራስ ልጄን እንደያዝኩ ጥዬ ሸሽቻልሁ” ተፈናቃይ
save
በአዲስ አበባ ከተማ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ሀና ማርያም፣ ፉሪ፣ ማንጎ ጨፌ ሌሎች በክፍለ ከተማው ስር ባሉ መንደሮች ከቤት መፍረስ ጋር በተያያዘ የሰው ሕይወት መጥፋቱ ይታወሳል፡፡ ሁለት ፖሊሶችና አንድ የወረዳው ሥራ አስፈጻሚ ህይወታቸው እንደጠፋ በይፋ ቢነገርም የዚያኑ ያህል ከዚህ ጋር በተያያዘ የተለያዩ መረጃዎች እየወጡ ይገኛሉ፡፡
የአሜሪካ ድምጽ ሬዲዮ ባቀናበረው መረጃ ላይ እንዳመለከተው “መኖሪያ ቤቶቹ ይፈርሳሉ በመባሉ ከአካባቢው ነዋሪዎች የተወሰኑት አቤቱታ እያቀረቡ ባለበት ወቅት የመንግስት አፍራሽ ግብረኃይሎች ቤቱን ለማፍረስ የመብራት ትራንስፎርመር መንቀል እንደጀመሩና በዚህ መካከል ከፍተኛ ግጭት እንደተፈጠር ነዋሪዎች ይናገራሉ”።
ከላይ በተጠቀሱት አካባቢዎች የመኖሪያ ቤቶች በዶዘር በሚፈርሱበት ወቅት ወንዶች በአካባቢው እንዳይጠጉ መከልከሉን ነዋሪዎች ይናገራሉ። ከተነሳው ግጭት ጋር በተያያዘ የአካባቢው ወንዶች እና አባወራዎች ለእስር ተዳርገው አቅመቢስ ህጻናትና ሴቶች ብቻ በግፍ እየተገደዱ ከቤታቸው እንዲወጡ ተደርገዋል፡፡ አንወጣም ያሉትም ቤታቸው ላያቸው እንዲፈርስ በሚደረግበት የመጨረሻ ወቅት ቤታቸውን እየጣሉ እንደወጡ ይናገራሉ፡፡
“የዶዘር ድምጽ እየገፋ ሲመጣ አንድ የ11ዓመት ልጄንና አንድ የ6 ዓመት ልጄን እዚያው ዝናብ ላይ ትቼ የአምስት ቀን ወንድ ልጄን ታቅፌ ሸሽቻለሁ” በማለት በእንባ እየታጠበች የተናገረችው እናት በአሁኑ ሰዓት በጓደኛዋ ቤት ተጠልላ እንደምትገኝ ከቪኦኤ ለቀረበላት ጥያቄ ስትመልስ ተናግራለች፡፡
የየቤተሰቡ አባወራ በአካባቢው እንዳይገን በማድረግ፤ አብዛኛውንም በማሰር በሐምሌ ክረምት መግቢያ ላይ የተደረገው የግፍ አሠራር ምንም እንኳን ቤቶቹ ህገወጥ ናቸው ቢባልም ቢያንስ ለምን በበጋው ወቅት አይደረግም በማለት ነዋሪዎች በምሬት ይጠይቃሉ፡፡
ስማቸው ካሡ ጎዳፋይ መሆኑን እና የወረዳ አንድ ተወካይ መሆናቸውን በትክክል ካረጋገጡ በኋላ የተደወለላቸው demolishedከቪኦኤ መሆኑ ሲነገራቸው ካሱ ጎዳፋይ እንዳልሆኑና ሲመጣ እንደሚነግሩት እርሳቸው ግን የካሡ ወንድም እንደሆኑ የተናገሩት አነጋገራቸው የሚያሳብቅባቸው የህወሃት ሹመኛ፤ ጋዜጠኛ ጽዮን ግርማ እያነጋገረቻቸው ስልኩን ጆሮዋ ላይ ዘግተውባታል፡፡
ይህንን ግፍ የተሞላበት ዘግናኝ አሠራር በተመለከተ ገጣሚ ዮሐንስ ሞላ (Yohanes Molla) ከዚህ ፎቶ ጋር በማያያዝ የሚከተለውን ጽፏል፡- “እንኳን እንዲህ የትም ውጡ ተብሎ፥ ቤት ጣሪያው ተበስቶ ሲያንጠባጥብ እንኳን ይጨንቃል። እንኳን እንዲህ የትም ተበተኑ ተብሎ፥ ካፊያ ጥሎ መጠለያ እስኪያገኙ ድረስም ይጨንቃል። እንኳን እንዲህ በየሜዳው ተወርውሮ፥ ጠና ያለ ነፋስ መጥቶ ቆርቆሮ ሲያንጋጋም ይጨንቃል። እስከመቼ ግን ሕዝብ ላይ እንዲህ ይደረጋል?!”
ድልድይ በማፍረስ “ዝነኝነቱ” የሚታወቀው ህወሃት፤ አሁን እንኳን የሥልጣን መንበር ላይ ሆኖ ማፍረሱ ተያይዞታል፡፡ በላፍቶ አካባቢ የተከሰተው ግን አፍራሽ ሁልጊዜ ሲያፈርስ ብቻ እንደማይኖርና ቀኑ ሲደርስ እርሱም እንደሚፈርስ በማስረጃ የተረጋገጠበት ነው፡፡ (የዜናው ምንጭ: ቪኦኤ)

Sunday, July 3, 2016

Ethiopia: Tigray People’s Liberation Front on the Run

July 3,2016
by Amanuel Biedemariam
For over a decade now this author have repeatedly expressed that the ultimate goal the Tigray People’s Liberation Front is to break away from Ethiopia and declare independent Abay Tigray by invoking Article 39 of Ethiopian constitution which unequivocally states:TPLF officials of the Ethiopian regime
“Every nation, nationality or people in Ethiopia shall have the unrestricted right to self determination up to secession.”
On June 29 Ethiopian Satellite Television Service (ESAT) reported,
“Residents in Lafto Sub City of the Ethiopian capital Addis Ababa (Kersa Kontuma neighborhood) clashed with the regime loyal police forces in attempt to protect their houses from demolition. People are posting pictures of deceased police officer bodies on Social Media. The police officers believed to be killed during the clash with protesters.
Some says the casualty figures could be 10 to 17 police officers.” 
Two weeks after Eritrea accused the TPLF of military aggression ESAT news reported,
“The TPLF regime in Ethiopian has been moving its army and heavy military equipment in large numbers to the north of the country, Acording to eyewitness accounts. The witnesses said public transport buses, as per the instructions given by the regime, have been transporting large numbers of the army from south and central regions of the country to the north.” 
This is move is peculiar because as Mr. Neamin Zeleke on his latest piece, “The Myth of a stable Ethiopia under a Minority Regime” wrote, the army and the people need be on the same page for the army to succeed on all its endeavors.
Clearly, the people of Ethiopia and the TPLF army are not in the same page and that is the reason why the residents in Lafo city in Addis Ababa killed soldiers loyal to the TPLF.  This happened because the people of Ethiopia have now concluded, without a shadow of doubt that the TPLF is not in any way representative of their interests. Furthermore, they have concluded that there is no institution that they can go to and express their grievances effectively.
What this means is that what the TPLF seeded is coming to fruition. The division between the people and the TPLF organ and its army is real. The people are certain now that the TPLF army is not there to protect but harm them. As a result the people are forced to take measures in their own hands to protect their lives and livelihood as in this case. They are raising arms to fight against TPLF. People are running away from authorities even when they are desperately in need of medical attention.
This demonstrates that seeds for civil war are planted by the TPLF and the likelihood that it could spread like wild fire is as real as daylight. Absent of urgent intervention by Washington there is absolutely nothing that can stop this runaway train.
The question, does the TPLF leadership understand the gravity of the situation?
People were concerned when they heard that the TPLF is moving soldiers close to Eritrean borders, rightly. Their fear is legitimate however, this time, it must be clear to the world that the TPLF is running back to Tigray not readying for war against Eritrea. War against Eritrea will destroy them.
For the last 25 years the Tigrayan People’s Liberation Front (TPLF) have been busy making enemies with Afars, Gambella, Ogaden, Amhara, Oromia, Wekait, Somalia and every ethnic group. They have picked a fight with the very country that gave them notoriety and legitimacy, Eritrea.
To pursue US’s interest TPLF cutoff relations with every constituency in the region. With the belief that the US cannot pursue its interests without the TPLF in the region, TPLF wrongly undermined every constituency.
This approach has a very short shelf life. In order to succeed the TPLF needed to succeed by ensuring the regime change agenda and destabilization of Eritrea. Controlling Eritrea would have made controlling the rest of Ethiopia easier. That however, was a tall order. As is evident now the TPLF failed to control Ethiopia and its Eritrea agenda is no longer possible.
The TPLF criminals that have been pillaging Ethiopia and created tremendous hardship in the region have finally come to realize that their time is up and they are running back to their original base of Tigray.
Therefore, the troop movement back has nothing to do with initiating war against Eritrea. It is self protection and move towards Article 39, Greater (Abay) Tigray. It is to protect their interests from their bases in Tigray.
The TPLF has been disconnected from the people of Tigray for a long time. However, recent developments in Ethiopia have reignited their interest because their very lives are at stake and they have nowhere else to go but Tigray.
Of late there has been tremendous PR moves directed at the people of Tigray designed to re-entice their base’s support.  July 2, 2016 ESAT news reported, the TPLF has built a Peugeot car assembly plant in Wikro Ketema in Tigray. It further noted that the TPLF established a pharmaceutical company worth one Billion Birr in Adi Grat.
“Chief executive Officer of the Endowment Fund for the Rehabilitation of Tigray (EFFORT), Azeb Mesfun said the manufacturing sector has a significant contribution to achieve Ethiopia’s target of becoming a middle income country by 2025.” 
EFFORT is abbreviation for Endowment Fund for the Rehabilitation of Tigray. Yet, the wife of the late dictator Meles Zenawi Azeb Mesfun claims that, “The manufacturing sector has a significant contribution to achieveEthiopia’s target of becoming a middle income country by 2025.” Emphasis is added.  However, Azeb is trying to reestablish her base in Tigray In the name of Ethiopia.
Conclusion
The TPLF invested heavily in Oromia and other parts of Ethiopia to loot. That however was short lived and dangerous. Because when people resisted the TPLF went on a killing spree everywhere living no room for any good will. As a result the people of Ethiopia have rejected the regime everywhere. The TPLF has no place inside Ethiopia and has no where else to go but Tigray. Hence, the TPLF is making a last ditch effort to hanker down in Tigray. It will declare article 39 and try to mend fences with Eritrea.  Will this become a saving grace for the dying regime?
No, they will sure be hunted by the people of Ethiopia and Tigray. They have hands that are soaked with blood and they will certainly pay for it.
Awetnayu@hotmail.com

ለመሆኑ ጦርነቱ የማን ነዉ?!

July 3,2016
ከሠራዊቱ ድምፅ ራዲዮ
የኢትዮጵያ ሕዝብ የሚያዉቀዉ ላለፉት 25 አመታት ኢትዮጵያን በነፍጥ እየገዛ ያለዉ የትግሬ ነፃ አዉጭ ነኝ ብሎ ራሱን የሚጠራዉ የሚሊሽያ ዘረኛ ቡድን መሆኑን ነዉ። የሚገርመዉ ግን ለአገዛዙ እዉቅና የሠጡት ከኢትዮጵያ ሕዝብ ይልቅ የአሜሪካ የእንግሊዝ የቻይናና አንዳንድ የአዉሮፖ አገሮች ናቸዉ። ኢትዮጵያ ዉስጥ ስለተዘረጋዉ ዲሞክራሲ እኩልነትና ሰላም የሚነግሩንም እነዚሁ ፈረንጆች ናቸዉ።
እነዚህ ባእዳን አገሮች አረካ አርባጉጉና አሠቦት ላይ የፈሰሰዉ ደም ፧በቅርቡ በኦሮሞ ማህበረሠብ ወገኖቻችን እንቢተኝነት ምክንያት በአገዛዙ ቅልብ ነፍሰገዳይ ወታደሮች የወደቀዉ የ400 ንፁሀን ነፍስ ፧በወልቃይትና በአጠቃላይ በአማራዉ ማህበረሠብ ላይ የሚካሄደዉ መፈናቀልና የዘር ማጥፋት ጭፍጨፋ ፧በአንዳንድ ከተሞች የሚደረጉ የኖርያ ቤቾችን የማፍረስ ዘመቻ ፤በጋምቤላና በኦጋዴን በተከታታይ የተፈፀመዉ የመሬት ዘረፋና የጅምላ ፍጅት ፧በጋዜጠኞችና በፖለቲካ ድርጅቶች ላይ እየተፈፀመ ያለዉ ግፈ ኦርዮን ፧በምንም ሁኔታ ሊሰማቸዉ አይችልም።ዛሬ አንዳንድ የአዉሮፓና የአሜሪካ ዲፕሎማቶችና ጋዜጠኞች ኢትዮጵያን የሚመለከቱት አራት ኪሎ ቤተመንግሥት ሲደርሱ የህወሃት ሃኪም በሚያዝላቸዉ መነፅር ነዉ ማለት ይቻላል።
አሁንም ድረስ  ሕዝቡ በጠመንጃ አፈሙዝ አስገዳጅነት እተገዛ መሆኑን አያምኑም፧ሊያምኑም አይፈልጉም። በተለያዩ አካባቢዎች ሰዎች በአገዛዙ ቅልብ ወታደሮች በጥይት በአደባባይ ተደብድበዉ የመሞታቸዉ ወሬ ሲደርሳቸዉ አገዛዙን በመሸሽ በብዙ መቶ ሽህ የሚቆጠሩ ዜጎች ድንበር ጥሰዉ ባህር አቋርጠዉ ሲሰደዱ የባህርና የዱር አዉሬ ሲበላቸዉ በሽብርተኛ ነፍሠገዳዮች አንገታቸዉ በካራ ሲቀላ፧ከነህይወታቸዉ በእሳት ሲቃጠሉና ከፎቅ ተወርዉረዉ ሲጣሉ ፧አሲድ ፊታቸዉ ላይ ሲከለስና ፧በሥርአተ አልበኛ ወታደሮች ሲደፈሩ እነዚህ አላጋጮች የዲሞክራሲ ሂደት ነዉ ይሉናል።
ስለ ኢትዮጵያ ታላቅነትና ገናናነት ፧የስልጣኔ ቅርስና የጥንታዊ ሰዉ መፍለቂያ አድርገዉ የሚያወሩላት አገር ዛሬ ያለችበት ደረጃ ለወሬም የማይመች ሳይሆንባቸዉ አይቀርም። ወደዘመነ መሳፍንት የመመለሳችን ሁኔታ ደግሞ ጨርሶ አይስተባበልም። አቶ ስብሃት ነጋን አቶ አባይ ፀሃዬን አቶ በረከት ስምኦንን አቶ አላሙዲንንና እነእንቶኔን እንደዘመነ መሣፍንት ገዥዎች ለመቁጠር በግድ ራስ ደጃዝማች ፍታዉራሪ ማለት አስፈላጊ አይደለም። የዘመነ መሳፍንት ይዘት ግን አለ! አየሩም መንፈሱም አለ ዘመነ ወያኔ!!!
አምላክ ኢትዮጵያን የሚታረቃት ለሱም ለሕዝቡም የሚስማማ መሪ ሲሰጣት ሊሆን ይችላል የሚሉ ብዙዎች ናቸዉ። መቼ እንዴት ይነሳል የሚለዉ ጥያቄ ግን መልስ አልተገኘለትም።
እንደሚታወቀዉ የህወሀት ዘረኞች እፍረትና ይሉኝታ የሚባል ነገር አልፈጠረባቸዉም። ጎስቋላ ሕዝብ ይበልጥ እያጎሳቆሉ የተምታታ ፖለቲካ ይበልጥ እያመሱ ፧ደሀ ኢኮኖሚ ይበልጥ እየገደሉ መንግሥት የሚባል ካባ ደርበዉ በመሪነት ሥልጣን ራሳቸዉን ኮፍሰዋል።
ድህነት የኩራት ምንጭ ባይሆንም ቢያንስ ቢያንስ በብሄራዊ ኩራት ሲሸፈን የሞራል ጥንካሬና የባለ አገርነት መንፈስ ያላብሳል። ትልቁ ኪሳራ የአላማ ድህነት፧የእዉቀት ድህነት፣ የአመራር ድህነት ነዉ። ላለፉት 25የህወሀት አገዛዝ በዚህ ረገድ ያለን ሃብት በሽበሽ ነዉ።
የኢትዮጵያን የሦስት ሽህ ዘመን ባለታሪክነት የማያዉቁና ማወቅም የማይፈልጉ ሰዎች  ታሪክ ሲያስተምሩን፧ ፖለቲካ የማያዉቁ ሰዎች እንደእዉር እንምራችሁ ሲሉን የአገርን ዳር ድንበር ምንነት የማያዉቁ ሰዎች በአገር አመራር ላይ ሲቀመጡ፧የኢኮኖሚ ሀሁ የማያዉቁ ሰዎች ኢኮኖሚ አደላዳዮች ሲሆኑ፧ሕግ ያልዳኛቸዉ ሰዎችና ከቶዉንም በተከሣሽ ሳጥን ዉስጥ መሆን የሚገባቸዉ ሰዎች የፍትህ አጋፋሪዎች የሰላም ዳኞች ሲሆኑ፥የአንደኛ ደረጃ ትምህርቱን እንኳ ያላጠናቀቀ የፕሮፊሰርነትና የሙሉ ጄኔራልነት ማዕረግ ሸልሞ የጦር ሃይሎች ጠቅላይ ኤታ ማጆር ሹም ቢሮ ሲቀመጥ ማየት፧ከዚህ የበለጠ አመራር የማጣት ማስረጃ አይገኝም።
ዛሬ አገራችን ኢትዮጵያ ኢትዮጵያዊ አመራር በማጣትዋና በመጥፎ ታሪክ አጋጣሚ የሥልጣን ኮርቻ ላይ የተቀመጡት ፀረ ኢትዮጵያ የህወሀት ቡድኖች ለሕዝቡ ታማኝ ባለመሆናቸዉ ህብረተሰቡ ቀዉስ በቀዉስ ሆኗል።
በመከላከያ ሠራዊቱም ውስጥ ከላይ ጀምሮ እስከ ታች ድረስ ያሉት አዛዦችና ካድሬዎች የትግርኛ ቋንቋ ተናጋሪና የዘረኛዉ የህወሀት አባላት ብቻ ናቸዉ። ቀደም ሲል የነበረዉን የረጅም አመታት የዳበረ የወታደራዊ ሳይንስ እዉቀትና ልምድ ያለዉን ከኢትዮጵያና ከኢትዮጵያዊነት ዉጭ ሌላ አላማ የሌለዉን የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት በትኖ በክልል የተሸነሸነና በጎጥ የተማከለ ሠራዊት በምትኩ አቋቁሟል። ይህ በጎጥ የተደራጀ ሠራዊት ብቃት በሌላቸዉ ከአንድ ጎሳ የፈለሱ ከጫካዉ የጎሬላ ዉጊያ በስተቀር ምንም የወታደራዊ አመራር ሥልጠና የሌላቸዉና የተሸከሙትን ማዕረግ የማይመጥኑ ማፈሪያዎች ናቸዉ። ዉትድርና ጥበብ ነዉ። በየደረጃዉ ያለዉን ወታደራዊ ማዕረግ ለመልበስ በልዩ ልዩ ሥልጠና ዉስጥ ማለፍን ይጠይቃል። በህወሀት ሠራዊት ዉስጥ እንደሚታየዉ ግን ማእረግ የሚታደለዉ አንደገና ዳቦ በስጦታ ነዉ።
በስራቸዉ ያለዉ ተራዉ ወታደር እንደጭቁኑ ሕዝብ ሁሉ ከፍተኛ ጭቆና አለበት። በህወሀት የስለላ መረብ ተተብትቧል። ከትግሬ ዘር በተለይም ደግሞ ከህወሀት አባላት ዉጭ በመሆኑ ብቻ በጥርጣሬ ይታያል አይታመንም።በግምገማ ይዋከባል። በአስቸጋሪ ዉጊያ ወቅት ግንባር መስመር ተሰልፎ የጥይት ማብረጃ ይሆናል። የዉጭ አገር ስልጠና እድልናና ገንዘብ የሚያስገኝ ግዳጅ ሲሆን ደግሞ ከወርቆቹ ጎሳ ተመርጦ ይላካል። አማራ ከሆነ ግንቦት 7 ኦሮሞ ከሆነ ኦነግ እየተባለ ይፈረጃል።በየጥቃቅኑ ምክንያት ዘብጥያ ይጣላል። የሌላዉ ጎሳ አባላት ሰብሰብ ብለዉ ቆመዉ ማዉራት አይፈቀድላቸዉም ለአድማ ነዉ አስብሎ ግምገማ እንደሚያስቀርብ ሥርአቱን ከድተዉ የወጡት የሠራዊቱ አባሎች ገሃድ ያወጡት እዉነታ ነዉ።
ይህ ሠራዊት በማንኛዉም ወቅት መሳርያዉን በአለቆቹ ላይ ሊያዞር እንደሚችል መናገር ነብይ አያሰኝም።
ዛሬም አገዛዙ ጦርነት እየፈበረከ ነዉ። አሸናፊና ተሸናፊ ለሌለዉ ኢትዮ ኤርትራ ጦርነት ከ100ሽህ በላይ ዜጎች አልቀዋል። የጦርነቱ ዉጤት የአገሪቱን ኢኮኖሚ ከማዉደሙም ሌላ ኪሳራና የዉርደት ጠባሳ ጥሎ አልፏል።በዚያ ፍልሚያ ጥቂት የማይባሉ የቀድሞ የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት አባላት ጄኔራሎች ሳይቀሩ በዉዴታ ግዴታ ተሰልፈዉ መሳተፋቸዉ ይታወሳል።በጦርነቱ ፍፃሜ ላይ ግን የወያኔ መሪዎች የመሬትና የገንዘብ ሽልማት እያገኙ ወደሰላማዊ ንሮአቸዉ ሲመለሱ የቀድሞ የኢትዮጵያ ወታደሮች ብዙዎቹ መስዋእት ሆነዉ የተረፉት ባዶ እጃቸዉን ተባረዋል። ከጦርነቱ በኋላ በወቅቱ የዉጭ ጉዳይ ሚኒስትር የነበሩት ስዮም መስፍን ባድመ ለኛ ሆናለች ብለዉ በአደባባይ ሰልፍ በጠሩ ማግሥት ግዙፉ እዉሸታቸዉን በአለም አቀፉ መድረክ በተገላቢጦሽ ሰማነዉ።
ሰሞኑን ከ16 አመት በኋላ ሌላ የጦርነት ከበሮ እየደለቁ ነዉ። ሌላ እልቂት። ሌላ የጦር መሣርያ የቅብብሎሽ ንግድ ፧ሌላ ዉሸት። ትናንት ከማይረባ ሽሮ ይሻላል ወደሽራሮ ያለዉ የበይ ተመልካች ወገኔ ዛሬ በነሱ መልማይ ካድሬዎች የተጣለ የሆቴል ትርፍራፊ ከምትበላና በረሀብ እዚህ ከምትሞት ወትድርና ግባና በልተህ ሙት እያሉት ነዉ።
ይህ ከ16 አመት በኋላ ያገረሸ የኢትዮ ኤርትራ ጦርነት ምክንያቱ ምን ይሆን?! ጦርነቱ የማንና የማን ጦርነት ነዉ?! በጦርነቱ ተጠቃሚዉ አካል ማነዉ?! የሚሉትና የመሳሰሉት ጥያቄዎች ዛሬ ይበልጥ አነጋጋሪ ጉዳዮች ናቸዉ። ለመሆኑ ካለፈዉ የሁለቱ አገራት ጦርነት ሠፊዉ የኢትዮጵያ ሕዝብ ምን ተማረ?! የእዉነት ጦርነት ቢጀመር የኢትዮጵያ ሕዝብ ምላሽ ምን ይሆን?!

Thursday, June 30, 2016

ህወሃት በሰሜኑ ግንባር ተጨናንቋል ም/መቶ አለቃ ደጀኔ እና ወታደር በኩር ይናገራሉ!

June30,2016
በልኡል አለም
በሰሜኑ የሀገራችን ክፍል በምእራብ ትግራይ ሂሞራ በታች የማይካድራ ነዳጅ ማጠራቀሚያ አካባቢና እስከ ሰቲት ሁመራ እንዲሁም ጉናና ኡማህጂር ምስራቅ ትግራይና ዓዲ ግራት ድረስ የተሰማራዉ ከተለያዩ ክፍለ ጦሮችና ልዩ ኃይል እንዲሁም አካባቢ ሚሊሻዎች ተወጣቶ በስምሪት ላይ የሚገኘዉ የጸረ ሽብር ቡድን ወደ ግንባር እንዲሰማራ ባለመ መልኩ እየተበተነና እየተሰባጠረ እንደሚገኝ ታማኝ የመከላከያ ምንጮች ገልጸዋል።Ethiopian Soldiers
ይህዉ የጸረ ሽብር ቡድን በተለይም ከደረሰበትና እየደረሰበት ከሚገነዉ ድንገተኛ ጥቃት ምክንያት እጅግ በመመናመኑና በመዳከሙ ለስምሪት የአካባቢዉ ክፍለ/ጦሮች እንዲተኩ የተወሰነ ሲሆን ከላይ የተጠቀሱት አካባቢዎች ላይ የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን ወገኖቻችን በአካባቢዉ ላይ ከሚደረገዉ ወታደራዊ መሯሯጥ የተነሳ ስጋት ስላደረባቸዉ አካባቢያቸዉን ወደ መልቀቁ ደረጃ ሊሸጋገሩ እንደሚችሉ እማኞች እየተናገሩ ይገኛሉ።
የህወሃት አዲስ ምልምልና ቅጥር ወታደሮች በመክዳት ምክንያት ከፍተኛ አደጋ እያስከተሉ በመምጣታቸዉ ወደ ደጀን ጦር በሚደረገዉ ዝዉዉር ከሰቲት ሁመራ ጀርባ ሲካተቱ ነባሮች ስምሪት እና ጸረ ሽብር ስምሪቱን እንደቆጣጠሩ ሆኗል።
በሰሜን ጎንደርና በምእራብ ትግራይ አካባቢ ተሰማርቶ የሚገኘው 24ተኛ ክ/ጦር ከ 25ተኛ ክ/ጦር ጋር ቅይጥ ብረት ለበስ ሜካናይዝድ በማደራጀት የጥምር ዉህድ የሚመስል ስልታዊ ክንዉን እያደረጉ ሲሆን ለዚህ ያለመረጋጋትና የመበታተን ጦስ ዋነኛዉ ምክንያት በየእለቱ በሰራዊቱ ላይ የሚደርሱ አነስተኛ ጥቃቶች እና የዉስጥ አርበኞች የፈጠሩት ጫና በአንኳርነት ተጠቃሽ ከመሆኑ በተጨማሪ የኢትዮ-ኤርትራ የጦርነት ስጋት የፈጠረዉ ትርምስ በራሱ የተያያዘ መጨናነቅ መፍጠሩን ባሳለፍነዉ ሳምንት ከሰሜኑ ግንባር ተነጥለዉ በጎረቤት ሐገር በተጠለሉ ም/መቶ አለቃ ደጀኔ ጥላሁን እና ወታደር በኩር ገ/ስላሴ ለታማኝ ምንጮቻችን ተናገረዋል።
ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ ! !

Wednesday, June 29, 2016

"ከሁሉ መቅደም ያለበት ሰብዓዊ ልማት ነው" ሃብታሙ አያሌው

June 29,2016
“ሪፎርም [ተሃድሶ] በገዥዉም በተቃዋሚዉም የግድ ያስፈልጋል"
habtamu

ከጥቂት ቀናት በፊት “ሀገር አለኝ!! ወገን አለኝ!!” በማለት በፌስቡክ ገጹ ላይ ይህንን የለጠፈው የአንድነት ፓርቲ አመራር አቶ ሃብታሙ አያሌው በጠና ታምሞ በኮማ ውስጥ ይገኛል፡፡
“እዉነት እዉነት እላችሁአለሁ ስቃይና መከራ የምቀበልላት ብቻ ሳትሆን የምሞትላት ሀገር አለችኝ!!
“ዘጠኝ ሞት መጣ ቢሉት አንዱን ግባ በለዉ” ከሚል ጀግና ህዝብ ተወልጄ በእስካሁኑ ስቃይ ጉልበቴ አይዝልም። እንድበረታ ዛሬም ከጎኔ ላልተለያችሁ ቃሌ ይሄ ነዉ። አመሰግናለሁ” ነበር ያለው!
የትግል አጋሩ ዳንኤል ሺበሺ (Daniel Shibeshi) በጥቂት ሰዓታት በፊት በፌስቡክ ገጹ ላይ ከላይ የሚታየውን የሃብታሙን ፎቶ አድርጎ ያሰራጨው ጽሁፍ እንዲህ ይላል፤
“በሀብታሙ አያሌው ጤና መታወክ፣ እየተረባበሻችሁ ላላችሁ ሁሉ በያላችሁበት ሆናችሁ ፀሎታችሁን ቀጥሉበት። አሁንም በኮማ ውስጥ ነው ያለው። ለውጥ አልታየም። ከትንፋሽ ውጭ ሌላ እንቅስቃሴ የለም። ቤተሰብ በሙሉ ተረባብሿል። ነገር ሁሉ ግራ ገብቶኛል። ወገን ሆይ በክፉዎች እጅ ወድቀናል!!! ከሌሊቱ 8ሰዓት።”
በአንድነት ፓርቲ ውስጥ በነበረው የጎላ ተሳትፎ በህወሃት ዓይን ውስጥ የገባው ወጣቱ ፖለቲከኛ ሃብታሙ በህወሃት “አሸባሪ” ተብሎ ተፈርጆ በእስርቤት ሲማቅቅ በቆየበት ጊዜ ከደረሰበት ግፍና ስቃይ የተነሳ ሁለቱም ኩላሊቶቹ ከፍተኛ ችግር ደርሶባቸው በሃይለኛ ህመምና ስቃይ ውስጥ ሲማቅቅ ቆይቷል፡፡ በአገር ውስጥ መታከም የማይችል በመሆኑ ወደ ውጪ ሄዶ እንዲታከም ከሃኪሞች ቢነገረውም የህወሃት ሹመኛ የሆነው “ወንጀለኛ ዳኛ” ከአለቆቹ በተሰጠው ትዕዛዝ መሠረት ሃብታሙ ወደ ውጪ እንዳይወጣ ከልክሏል፡፡
አሁንም በሰላማዊ መንገድ ለመታገል ቁርጠኛ እንደሆነ የሚናገረው ሃብታሙ ከጥቂት ቀናት በፊት ከጋዜጠኛ ኤልያስ ገብሩ ጋር በአዲስ ገፅ መፅሔት ያደረገው ቃለምልልስ ከዚህ በታች ይገኛል፡፡
ጥያቄ፡- የግንቦት 20 ፍሬን በተመለከተ የምታምንበትን ገልጸሃል፡፡ የተቃውሞ ፓርቲ ትግልም በውጣ ወረድ የታጀበ ነው፡፡ ሀሳብን በነፃነት የመግለጽ መብት ራሱ በገደል አፋፍ ላይ ነው የሚገኘው፡፡ ለሀገርና ለህዝብ የሚጣፍጥ ፍሬ ለማፍራት ምን መደረግ አለበት?
ሐብታሙ አያሌው፡- በኢትዮጵያ ውስጥ ዴሞክራሲያዊ ለውጥ ለማምጣት ከተፈለገ፤ በንጉሱም፣ በደርግም የነበሩ ችግሮች ኢህአዴግ ከ25 አመታት በሁአላም እንዲቀጥላቸዉ መፍቀድ አይገባም። በኢትዮጵያ ታሪክ ውስጥ ብዙ ያልተመለሱ ጥያቄዎች አሉ፡፡ ዋናውና መሰረታዊዉ ጥያቄ የሰብዓዊና የዴሞክራሲያዊ መብት ጥያቄዎች ናቸዉ፡፡ የዴሞክራሲና የሰብዓዊ መብት ጥያቄዎች ለነገ የሚባሉ አይደሉም። ፈጣን ምላሽ ይጠይቃሉ። ኢህአዴግ እነዚህን መሰረታዊ የህዝብ መብቶች ለማክበር ዝግጁ እንዳልሆነና አቅሙም እንደሌለዉ ከመቼዉም ጊዜ በላይ ግልፅ የሆነ ይመስላል።
የምትፈልገውን ነገር የማግኘት፣ የመምረጥ፣ በህይወት የመኖር፡ የመናገር፡ የመፃፍ…የመሳሰሉት መሰረታዊ መብቶች በተጣሱበት ምንም አይነት ጣፋጭ ፍሬ ሊገኝ አይችልም። ኢህአዴግ ስልጣን ለማስጠበቅ ብቻ የሚከተለዉ በልማት ስም የህዝብን መብት የማፈን ስርዓት ሊያፈርሰን ካልሆነ በቀር ሊሰራን አይችልም።
ጣፋጭ ፍሬ ለማግኘት ከሁሉ መቅደም ያለበት ሰብዓዊ ልማት ነው፡፡ ከልማቱ ጋር ተያይዞ ከድህነት የመውጣት ጥያቄ ይመጣል፡፡ መጀመሪያ ህሊና… ህሊና ከሆድ መቅደም አለበት፡፡ የህሊና ነጻነት የሚባል ነገር አለ፡፡ ኢህአዴግ ያልገባዉ ወይም እንዲገባዉ ያልፈለገው ይህ ነዉ ። የምን ጊዜዉም መከራከሪያዉ ሆድን በማስቀደም ላይ ነው፡፡ ‹‹ልማት ይቀድማል›› ይለናል፡፡ የህሊና ጥያቄዎች ሳይመለሱ ሆድ መቅደም የለበትም፡፡ የስርዓቱ ሰዎች የገዛ ህዝባቸውን እየዘረፉ በረሃብ የሚቆሉት እና የሚያፍኑት እኮ ለዚህ ነዉ እነሱ ጋር የህሊና ጥያቄ የሚባል ነገር የለም ። በአፋቸዉ ዴሞክራሲና ልማት ተነጣጥለው አይታዩም ይሉሃል በተግባር ግን ከዚህ የተለዩ ናቸዉ መብት የጠየቀን ያስራሉ ያሰድዳሉ ይገላሉ፡፡ ኢህአዴግ ከባድ የቁርጠኝነትና የማስፈጸም ችግር ያለበት ድርጅት ነዉ፡፡ ላለፉት 25 ዓመታት ነገሮች ሲሻሻሉና ትንሽ ዕድል ሲያገኙ አልታዩም ከአመት አመት ወደ ባሰ ጨለማ እያመራን ነዉ። ኢህአዴግ ለመነጋገር እና ለሪፎርም መዘጋጀት አለበት ተቃዋሚዉም እንደዛዉ አለዚያ መጨረሻችን የፈራነው እንደ ሀገር መፍረስ ይመጣል። መነጋገር መደማመጥ የሁሉ መፍትሄ ነዉ ነገር ግን ተስፋ የሚያሳጣዉ ኢህአዴግ በየጊዜው እየባሰበት እንጂ እየተሻሻለ የማይመጣ ድርጅት መሆኑን ነዉ።habtamu a
ጥያቄ፡- እንዴት?
ሐብታሙ አያሌው፡- ለማስታወስ ያህል፣ በ83 እና 84 ዓ.ም ልጅ ነበርኩ፤ ምንም አላስታውስም፡፡ ግን አንብቤ እና ጠይቄ ከተረዳሁት፣ መሬት ላይ የነበረውም ነገር እንደሚያሳየው ከ83-87 ዓ.ም ድረስ የሚዲያው ነጻነት ከፍተኛ ደረጃ ላይ የደረሰበት ነበር ይባላል፡፡ የፈለከውን መናገር ትችላለህ፣ የፈለከውን መጻፍ ትችላለህ፣ ኢህአዴግ ለማፈንና ለመቆጣጠር የሚያስችል ስልት አልዘረጋም ዴሞክራሲን ለማስመሰል ወይም ለመሞከር ይፈልግ ነበር፡፡
ጥቂት ቆይቶ ግን ወደ ተፈጥሮአዊ የድርጅቱ ባህሪ ተመለሰ። ስለዚህ ወደ አፈናው ሲሄድ፡ ምሁራኖቹን መጀመሪያ በጠላትነት መፈረጅ፣ ዩኒቨርሲቲ አካባቢ ያለውን ነገር ማጽዳት፣ ሚዲያዎችን በሙሉ መቆጣጠር፣ መንግስታዊ ያልሆኑ ተቋማትን ወይም ሲቪል ማኅበራትን በመንግሥት ደጋፊዎች በመሙላት መቆጣጠር፣ የሃይማኖት ተቋማትን መቆጣጠር . . . ፖለቲካውን አረጋግቶ ለመምራት ሁሉንም ተቋማት ‹‹በእኔ ቁጥጥር ሥር ማድረግ አለብኝ›› ወደሚል ተግባር ሄደ፡፡ መሆን የነበረበት ግን ይህ ሳይሆን ተቃራኒው ነው፡፡ የዴሞክራሲ ተቋማትን በካድሬ መቆጣጠር ሳይሆን መፍትሄዉ ገለልተኛ ሆነዉ እንዲጠናከሩ ማድረግ ነበር። መንግሥት ሊሔድና ሊመጣ ይችላል፣ ሲስተሙ ግን መቆም ነበረበት፡፡ ስለዚህ ኢህአዴግ ያተኮረው ሲስተም ላይ ሳይሆን የቁጥጥር ዘዴ ግንባታ ላይ ነው፡፡
እምነት የሚጣልበት ተቋም ተገንብቶ ቢሆን ኖሮ ላለፉት 25 ዓመታት ምርጫ ቦርድ አያከራክርም ነበር፡፡ ዛሬም የዴሞክራሲ ጥያቄ ሀገሪቷን ያልሆነ ችግር ውስጥ አይከታትም፡፡ የሰብዓዊ መብት ተቋም ቢገነባ፣ የሰብዓዊ መብት ኮሚሽን በሚያወጣው ውጤትና በሚነግረን ነገር ላይ ልዩነት አይፈጠርም፡፡ የሚዲያ ተቋሙ (በመንግስት ቁጥጥር ስር ያለው) አንድን ፓርቲ ከማገልገል ይልቅ ሀገራዊ ሚናውን ሊወጣ የሚችል ነጻ የሚዲያ ተቋም እንዲሆን ማድረግ ቢቻል ይሄ ሁሉ ሀገራዊ ቀዉስ አይፈጠርም ነበር፡፡
ጥያቄ፡- እነዚህ ነገሮች በሌሉበት የምታደርገው ምንድን ነው?
ሐብታሙ አያሌው፡- በኢህአዴግ ፕሮግራም ላይ ነጻ የኢኮኖሚ ሥርዓት የሚል አለ፡፡ በነጻ ገበያ እኩል መወዳደር ሚቻልበት ዕድል ግን የለም፡፡ ይልቁንስ እንደምናየውና እንደምንሰማው የመከላከያው ክፍል ተቆጣጥሮታል፡፡ እርግጥ ነው፣ አንድ መከላከያ ሀገርን ከመጠበቅ ባሻገር በልማት ግንባታ ውስጥ ከፍተኛ ሚና እንዲኖረው ማድረግ ይገባል፡፡ ነገር ግን፣ አጠቃላይ የግሉን ሴክተር በሙሉ ከውድድር በሚያወጣ መልኩ የሀገሪቱ ኢኮኖሚ ወደ መከላከያ መሰባሰቡ ተገቢ አይደለም፡፡ በዚህ ጉዳይ ላይ አቋም ይዘን ተከራክረናል፡፡ የግል ዘርፉ ነው መንግስትን መቆጣጠር ያለበት፡፡ መንግስት በገበያ ውስጥ ያለው ተሳትፎ ውስን መሆን አለበት፡፡ መንግስት ኢኮኖሚውንና የፖለቲካ ሥልጣኑን ከተቆጣጠረ አንባገነን ለመሆን ሰፊ ዕድል ይሰጣል፡፡ በዚህም የግለሰቦች ሚና ከፍተኛ ይሆናል፡፡ አየህ ኢህአዴግ በሁሉም ነገር ቁልቁል ሂዶአል የምልህ ለዚህ ነዉ ። በጥቅሉ አንድ ፓርቲ ይወለዳል ያድጋል ይሞይሞታል አሁን ኢህአዴግ በዚህ ሂደት አልፎ እድገቱን ጨርሷል።
ጥያቄ፡- ስለዚህ ምን ማድረግ ይጠበቅበታል?
ሐብታሙ አያሌው፡- ከዚህ በኋላ ኢህአዴግ ሪፎርም ሳያደርግ፣ የዴሞክራሲ አብዩት ሳያመጣ፣ በዴሞክራሲ መንገድ ለውጥ ሳያመጣ፣ በልማቱ ጉዳይ፣ በሰብዓዊ መብት ለውጥ ሳያመጣ እስካሁን በመጣበት መንገድ ለመቀጠል የሚችልበት ዕድል የለም፡፡ ይልቁንስ ወደበለጠ ቀውስ ውስጥ ነው የሚገባው፡፡ ሪፎርም የማምጣት ዕድሉን መጠቀም አለበት፡፡ እንደውም አንድ አባባል መጠቀም እፈልጋለሁ፡፡ ኢህአዴግን በተቃዋሚ ጎራ ላይ ወድቀን ነው የጠበቅነው፡፡ ወድቀን ጠብቀን፣ ለምን ደረሱብን እያልን ነው፡፡ ወድቀን ባንጠብቃቸው አይደርሱብንም ነበር፤ ለዚህ ጥቂት ምሳሌዎች ባነሳ፣ አንዱ የተቃዎሚዎች ጎራ በዴሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ እንቅፋት ሆኖ የቀጠለበት በማይረባ ምክንያቶች፤ የግል ጉዳዩን ለማሳካት የተሰባሰበ ስብስብ፣ ከግል ከፍተኛ ፍላጎት መዝለል ያልቻለ ስብስብ በመሆኑ ነው፡፡
ይህ ሲባል የሚከፋው ሰው ይኖራል፤ ግን የሆነ ሰው ይከፈዋል ብዬ አስተያየት ከመስጠት ወደኋላ አልልም፡፡ አንድነት ፓርቲ በእኔ ዘመን ሊቀ-መንበር ያደረገው ኢንጂነር ግዛቸውን ነበር፤ ኢንጂነር ግዛቸው ከኃላፊነት ሲነሳ ‹‹እኔ ከሄድኩ ፓርቲው ብትንትኑ ይውጣ›› ብሎ አንድነትን በትኖ ሄዷል፡፡ ኢንጂነር ግዛቸው አንድነትን በማፍረስ ከኢህአዴግ የሚለይበትን አንድም ምክንያት የሚጠቅስ ሰው አላገኝም፡፡ ኢህአዴግ አንድነትን ለማፍረስ የሰራውን ያህል ኢንጂነር ግዛቸውም ሰርቷል፡፡ እነትዕግስቱስ አንድነትን ለማፍረስ የተጫወቱት ሚና ከኢህአዴግ የሚለየው በምንድን ነው?! ኢህአዴግ መጥቶ አንድነትን ባያፈርሰው ኖሮ ግዛቸው፣ ትዕግስቱና ሰፊው የሚባሉ ሰዎችን ይዘን ነበር የምንቀጥለው፡፡ ያ ስብስብ በርካታ ችግሮች የነበሩበት ስብስብ ነበር፡፡ ወርቅ በእሳት እንደሚነጠረው የፈተና ቀን ሲመጣ አብዛኛው ተበታትኖ ድራሹ ጠፋ፡፡
በእርግጥ ይህንን ለማድረግ የታወቀ ኢህአዴግ ባህሪ አለ፡፡ በኢትዮጵያ ውስጥም ጠንካራ ተቃዋሚ ፓርቲ እንዳይፈጠር ፍላጎት አለው፡፡ አንድነትን ማፍረስም ለነገ የሚባል ነገር አልነበረም፡፡ ምክንያቱም አንድነት ውስጥ የኢትዮጵያ ፖለቲካ በደንብ የገባቸውና የተረዱ ምርጥ ምርጥ ኃይሎች ነበሩ፡፡ እኔም ወደአንድነት ስገባ እነዚህን ሰዎች አይቼ ነው፡፡ እነዚህን ጥቂት እርሾ የሆኑ ሰዎችን ይዞ በኢትዮጵያ ዴሞክራሲ ውስጥ የኢህአዴግን ሁኔታ ተቋቁሞ ትልቅ ለውጥ ማምጣት ይቻላል፡፡ ነገር ግን ውስብስብ የሆነው የተቃዋሚው ችግር በቀላሉ የሚለቀን አልሆነም፡፡ በፖለቲካ አቋማቸውና እውቀታቸው አንድም ጥያቄ የማይነሳባቸውን እከሌ እከሌ ብሎ ማንሳት ይቻላል፡፡
እኔና ዳንኤል ወደ እስር ቤት ስንገባ ከአንድነት ፓርቲ በጣም ተስፋ የጣልኩባቸው ምርጥ ምርጥ ሰዎች ነበሩ፡፡ ለምሳሌ ተክሌ በቀለን የመሰለ ፖለቲከኛ፣ በላይ ፍቃዱን የመሰለ ስለ ኢትዮጵያ ፖለቲካ በቂ እውቀት ያለው ሰዉ፡ ግርማ ሰይፉን የመሰለ ወሳኝ፡ አስራት አብርሃ፡ አስራት ጣሴ፡ ፀጋዬ አላምረዉ … ነበልባል የሆኑት ወጣቶች እንደነ ዳግም፡ እስማኤል ዳዉድ፡ ስንታየሁ ቸኮል፡ ዳዊት ሰሎሞን፡ ያሬድ አማረ፡ አለነ ማህፀንቱን የመሳሰሉ በርካታ ትንታግ ወጣቶች በኢትዮጵያ ፖለቲካ ውስጥ እድል ቢያገኙ፣ እንደ ኢህአዴግ በር ዘግቶ የሚያፍን ድርጅት ባይሆን ኖሮ የተሻለ ደረጃ የሚደረስበት እድል ነበረ፡፡ መጨረሻ ላይ እኮ እነ አስራት አብርሃ፣ አናንያ ሶሪ፡ ስለሺ ሀጎስ መሃመድ አሊ፡ ሌሎችም በርካታ ሰዎች ተስፋዎች ወደ አንድነት መጥተው ነበር፡፡ እኛም ከታሰርን በኋላ ፓርቲው ሊቀጥል የሚችልበት ሰፊ እድል ነበር፡፡ በላይ ፍቃዱ ተክሌ በቀለ ግርማ ሰይፉ እውቀትና ክህሎታቸዉን ተጠቅመዉ ምርጥ አመራር እየሰጡ ለዉጥ የሚያመጡበ ብሩህ ዕድል ነበረ፤ ነገርግን ይህንን ኢህአዴግ ጠምዝዞ አክሽፎታል፡፡
የኢህአዴግ አንድነትን ማፍረሱ ታሪካዊ ስህተት ነው፡፡ አንድነትን አፍርሶ የኢትዮጵያ ፖለቲካ ላይ ዳግም ጨለማውን የበለጠ አበረታው፡፡ እኛን አሰረ፤ አንድነትን አፈረሰ፡፡ ዉጤቱ ሺህ እልህኛ ወጣቶችን ፈጠረ እንጂ ትግሉን አልቀለበሰዉም፡፡ አንድነት ‹‹በርታ›› ሊባልና ሊደገፍ የሚገባው ድርጅት ነበር፡፡ ድክመቶችን እንዲያርም እድል ሊሰጠው ይገባ ነበር፡፡ አየህ ኢህአዴግ ፈፅሞ ለዴሞክራሲያዊ ስርአት ግንባታ ብቁም ምቹም እንዳልሆነ ሁሉ የተቃዋሚ ጎራው ስብስብም ባለብዙ ችግር ነዉ፡ ከብዙ ሆድ አደሮች ጋር ተጃምለን ለጉዳት ተጋልጠናል እናም መፍትሄዉ ሰከን ብሎ ወደራስ ማየት ራስን መገምገም ነዉ ።
ከሁሉ በፊት ሀገር እናስቀድም ሪፎርም በገዥዉም በተቃዋሚዉም የግድ ያስፈልጋል ባይ ነኝ።
በመጨረሻም እኔ ባሁኑ ወቅት በከባድ የጤና ችግር ዉስጥ እንዳለሁ የምታየው ነዉ። የሀገሬ ጉዳይ ቢያሳስበኝም በደረሰብኝ ግፍ ስቃዬን እንዳዳምጥ ተገድጃለሁ። እናም ከብዙ ከሀዲዎች መካከል የነጠሩ የቀድሞ የአንድነት ሃይሎች እንደ ትላንቱ ዛሬም ስላልተለዩኝ አመሰግናለሁ። ተክሌ፡ በላይ፡ ግርማ፡ ስዩም፡ አስራት ጣሴ፡ አስራት አብርሃ፡ ገበየሁ፡ እስማኤል፡ ሰባህ፡ ፋሲካ፡ እዩኤል፡ አስማማው ሃይለጊዮርጊስ፡ ናትናኤል ፈለቀ፡ ዮናታን ወልዴ፡ ታታሪዉ ጠያቂዬ ተፈሪ፡ ወዳጄ ማይክ መልዐከ … ከፍ ያለ ምስጋና አቀርባለሁ።
ከሁሉ በላይ ጠበቃ አመሃ መኮንን ከግፍ እስር ብቻ ሳይሆን ዛሬም ሂወቴን ለማዳን እያደረክ ላለህዉ ሁሉ ከቤተሰቤ ጋር ምስጋና እናቀርባለን። ኤልያስ እንደ ወንድም አልተለየህኝም ምስጋና ይድረስህ፡ በስም ያልተጠቀሳችሁ በሀገር ዉስጥ እና ዉጭ ያላችሁ ሁሉ አመስግኛለሁ።
ሰላም ለሀገራችን ይሁን!
(ምንጭ:Elias Gebru Godana ፌስቡክ)

Tuesday, June 28, 2016

አስፋልቱ “አብስትራክት” የሆነው የደምቢዶሎ ኤርፖርት

June 28,2016
“የቀረው በwifi ይሠራል”
d d airport
ህወሃት በግፍ በሚመራት ኢትዮጵያ የማይጠፋ ነገር የለም፡፡ ምናልባት መብራት ብቻ ነው የሚጠፋው ብሎ የሚያስብ የቅርቡን ክስትት ያልተከታተለ ብቻ ሊሆን ይችላል ቢባል ማጋነን አይሆንም፡፡
boy
መሃንዲሱን ተዋወቁ
መብራት፣ ውሃ፣ የስልክ ኔትወርክ፣ ወርቅ፣ … ብቻ ሳይሆን ጋዜጠኞች፣ ፖለቲከኞች፣ የሥርዓቱ ተቃዋሚዎች … በሚጠፉባት አገር ከሰማኒያ በላይ ኮንዶሚኒየም ይጠፋል፤ ሰሞኑን ደግሞ በኢትዮጵያ የህወሃት ተጠሪ ኃይለማርያም በነቀምቴ ከተማ  አውሮፕላን ማረፊያ ያስቀመጡት የመሠረት ድንጋይ ጠፍቷል ተብሎ የማኅበራዊ ሚዲያውን ሰፈር አድምቆታል፡፡
የነቀምቴው ሳያንስ ደምቢዶሎ ደግሞ ተመረቀ የተባለው የአፈር አየር ማረፊያ ህወሃትን ለከፍተኛ ስላቅና ፌዝ አጋልጦታል፡፡ የሥርዓቱ ደጋፊ የሆኑት ሳይቀሩ “ገንዘቡ ተበልቷል” ያሉበት የዚህ አውሮፕላን ማረፊያ የማኮብኮቢያና የማረፊያ መንገድ ከአፈር መሆኑ ብቻ ሳይሆን ተሳፋሪዎችንም ከአውሮፕላኑ ሲወርዱ የሚያጠልቁት ጭቃ መከላከያ እንዲኖራቸው የሚያስገድድ ሆኗል፡፡ ከአየር መንገድ ንግድ አንጻር ይህ በራሱ በኢትዮጵያ አየርመንገድ መሸፈን ያለበት ወጪ በመሆኑ ከረሜላ፣ ለስላሳና ጣፋጭ ምግቦችን ከአንዳንድ ቦቲ ጋር አብሮ ለተሳፋሪዎች በበረራ አስተናጋጆቹ ማቅረብ እንደሚገባው ፌዘኞች አላግጠዋል፡፡
ddairportየተለያዩ ፎቶዎችን በመገጣጠምም በርካታ ትችት በማኅበራዊ ሚዲያ የቀረበበበት ይህ ጉዳይ አንዳንዶችም ህወሃት በትግራይና በኦሮሚያ የሚያደርገው “ልማታዊ ሥራ” እንዴት የተለያየ መሆኑን በትግራይ የሚገኙ ኤርፖርቶችን ከደምቢዶሎው ጋር በማነጻጸር ምሬታቸውን የገለጹበት ሆኗል፡፡
በዚህ የዜና ዘገባ፥ እፍረት አያውቅም እንጂ፤ የቀድሞው ኢቲቪ ያሁኑ ኢቢሲ እስካሁን 50ዓመት አገልግያለሁ ከዚህ በኋላ በቃኝ ብሎ “ለሰፊው ሕዝብ ጥቅም ሲል” ራሱን ማጥፋት ነበረበት ተብሏል፡፡
እጅግ ከፍተኛ የሥራአጥ ቁጥር ባለበት አገር ይህ ኤርፖርት የሥራ ዕድል ከፍቷል ብለው የተሳለቁ ይህንን ማስታወቂያ በትነዋል፡-
ክፍት የስራ ቦታ ማስታወቂያ
በዚህ ሳምንት የተመረቀው ዘመናዊው የደምቢ ዶሎ አየር ማረፊያ መስፈርቱን የሚያሟሉ ማንኛቸውንም አመልካቾች ያለ ውድድር በቀጥታ ለመቅጠር ይፈልጋል። መስፈርቱን እናሟላለን የምትሉ ደምቢ ዶሎ ግብርና ምርምር በአካል ቀርባችሁ መመዝገብ የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን።
የቅጥር መስፈርት፡- የ11 በሞቶ እድገታችንን ታሳቢ በማድረግ ለ11 ዓመት የሰመጠ ባቡር በማንጠልጠል የጡንቻ ማዳበርያ የአካል ብቃት መስራቱን የሚያረጋገጥ ማስረጃ ማቅረብ ብቻ።
የስራ ቦታ፡- ደምቢ ዶሎ የታረሰ ማሳ ላይ።dd air port
የስራው አይነት፡- በጭቃ የተያዘ አውሮፕላን መግፋት።
“ይህ የሚታያችሁ አፈር ወይም ጭቃ ሊመስል ይችላል፤ አውሮፕላን ማረፊያው በአስፋልት ነው የተሰራው – አብስትራክት ስለሆነ በደንብ አልታችሁም፤ የቀረው ደግሞ በwifi ይጠናቀቃል፥ እንደጀመርን እንጨርሰዋለን” ብሏል ብለው የኢቢሲውን ተመስገን “ጋዜጠኛዊ ብቃት” ለማድነቅ አንዳንድ ፌዘኞች ስልክ ቢደውሉ ኔትወርክ ጠፍቷል ተብለዋል፡፡
airport(ጎልጉል: የድረገጽ ጋዜጣ)

Saturday, June 25, 2016

አንዳችሁንም አናስተርፍም፤ እንጨርሳችኋልን” የህወሃት ነፍጠኞች

June 25,2016
“ኦጋዴን፤ የኢትዮጵያ [የህወሃት] ድብቅ ኃፍረት

ogaden 4
የኢትዮጵያን ሕዝብ በነጻ አውጪ ስም እስካሁን በግፍ እየገዛ ያለው የትግራይ ህዝብ ነጻ አውጪ ግምባር ሥልጣን በኃይል ከመያዙ በፊት ሲፈጽም የነበረውን የሰብዓዊ መብት ረገጣ፤ ሥልጣን ከያዘም በኋላ ላለፉት 25 ዓመታት ቀጥሎበታል፡፡ ህወሃት ሥልጣን ከያዘ ጀምሮ በኢትዮጵያ ውስጥ ግፍ ያልተፈጸመበት አካባቢ የለም የሚለው አባባል የተጋነነ አይደለም፡፡
ኦጋዴን፤ የኢትዮጵያ [የህወሃት] ድብቅ ኃፍረት” በሚል ርዕስ ጋዜጠኛ ግራሃም ፔብልስ በኦጋዴን የሚካሄደውን የሚዘገንን ግፍ ሰኔ 15፤ 2008ዓም (June 22, 2016) ዩትዩብ ላይ ለቋል፡፡ (ዘጋቢ ፊልሙ እዚህ ላይ ይገኛል)
“በዛፍ ላይ ለተወሰኑ ደቂቃዎች ሰቅለውኝ ነበር፤ በርካታ ደቂቃዎች ካለፉ በኋላ አወረዱኝ፤ … ከዚያም ካሁን በኋላogaden 1 የምንልሽን ታደርጊያለሽ አለበለዚያ እንገድልሻለን አሉኝ” የግፍ ዶፍ የወረደባት አናብ ከተናገረችው፡፡
የሚዲና የዕርዳታ ሥራዎችን የሚያካሂዱ ሁሉ ወደ ኦጋዴን እንዳይገቡ በህወሃት ትዕዛዝ ተደርጎባቸው ባለበት ባሁኑ ወቅት በኦጋዴን የሚካሄደው ግድያ፣ አስገድዶ መድፈር፤ እስር፣ እንግልት፣ ወከባ፣ … በድብቅ ቀጥሏል ይላል ጋዜጠኛ ግራሃም፡፡
ዘጋቢ ፊልሙን ለመሥራት መረጃው የተሰበሰበው ከሚሊታሪው የኮበለሉና ሌሎች ለህይወታቸው ያልሳሱ ደፋሮች በሰጡት ምስክርነት ነው፡፡ በተለይም ከኢትዮጵያ ኮብለለው በቅርቡ ኬኒያ ልትዘጋው ወደ ወሰነችው የዳዳብ የስደተኞች ካምፕ የሚገኙ ሦስት ሴቶች የህወሃት ሠራዊት ስላደረሰባቸው መከራ፣ ሥቃይና አስገድዶ መድፈር ተግባራት ምስክርነታቸውን ሰጥተዋል፡፡
ወደ ዳዳብ በግንቦት 2006ዓም የመጣችው ሚሪያም ለሁለት ዓመት ተኩል እንዴት እንደተሰቃየች፣ አስገድዶ መድፈርና ድብደባ እንዴት እንደተፈጸመባት ትናግራለች፤
“እንደ ማሰቃያ ይሆን ዘንድ እስኪደክመኝ ድረስ ሬሣ አቅፌ እንድቆም ተደርጌአለሁ፤ ከዚያም ሚጥሚጣ የሞላበት ላስቲክ በራሴ ላይ አስረውብኛል፤ ገመዱን ሲያስሩት አጥብቀው ከአንገቴ ጋር በማሰራቸው ራሴን ስቼ ወድቄ ነበር፡፡ ከዚያ ለብዙ ሆነ እየተፈራረቁ አስገድደው ደፈሩኝ …”ogaden 10
“ኦጋዴን በሚገኘው እስርቤት 1097 የምንሆን ነበርን፤ ቁጥሩን በትክክል አውቀዋለሁ ምክንያቱም በየቀኑ ማለዳ ላይ እያሰለፉ ከቆጠሩን በኋላ በቡድን በቡድን እያደረጉ ይከፋፍሉን ነበር፤ …
“(የተያዝን ጊዜ) እህቴን ጉሮሮዋን አንቀው መረጃ አምጪ አሏት፤ ምንም እንደማታውቅ ብትነግራቸውም አልሰሟትም፤ ከሌሎቻችን ጋር ተቀላቅላ እንድትቀመጥ አደረጓት ከዚያም ሁላችን እያየን አራት ቤቶቻችን አቃጠሏቸው፤ ቤቱን እያቃጠሉ እህቴን ከመካከል ነጥለው ግምባሯ ላይ በጥይት መቷት፤ እህቴን እስከሞት ስትደማ አየኋት፤ ከእርሷ አጠገብ ሌላ ሴት ልጅ በድብደባ ብዛት ሞታ ነበር፤ ከዚያም እኔን ሬሣ ባለበት ጉድጓድ ውስጥ ጣሉኝ፤ በዚያ ጉድጓድ ውስጥ አራት ቀንና አራት ምሽት አሳለፍኩ፤ ጥፋተኛ መሆኔን እንድናዘዝ ምርመራ ይካሄድብኝ ነበር፤ አለበለዚያ መጨረሻዬ እንደ ሬሣው እንደሚሆን ይነግሩኝ ነበር፤ እኔም ምንም የምናዘዘው የለኝም የምታርዱኝ ከሆነ እረዱኝ አልኳቸው፤ (ጉድጓድ ውስጥ በነበርኩበት ጊዜ) ከሬሣው መካከል አንዱ ጉሮሮው ታርዶ፤ አንገቱም በዱልዱም ነገር ተቆርጦ ጭንቅላቱ እዚያው የቀረው አካሉ ጎን ነበር፤…”
በመስከረም 2007ዓም ወደ ዳዳብ ካምፕ የመጣቸው አናብ ደግሞ “የኢትዮጵያ ሠራዊት በጅምላ ከገደሉ በኋላ በጅምላ የሚቀብሩበትን ቦታ በመደበቅ ከፍተኛ የሆነ ጥንቃቄ ያደርጋሉ፤ አንዳንዶቹ መቼም አይገኙም፤ አንዳንዶቹ ግን በቁሻሻ ጉድጓዶች ውስጥ ተገኝተዋል” ትላለች፡፡
በእርሷ ላይ የደረሰውን በተመለከተ ስትናገር አናብ እንዲህ ትላለች፤ “ወደ እስር ቤት ተወስጄ በሽቦ ታነቅሁኝ፤ ይህ ዓይነቱን ተግባር በተደጋጋሚ ሲፈጽሙ ቆይተው በኋላ እስርቤት ተዉኝ፤ በተያዝኩ ጊዜ ከፊት፥ ከኋላና ጭኔ ላይ በጎማ ጠፍር ገርፈውናል፤ ከእኔ ጋር የተያዙ አምስት ልጃገረዶች ነበሩ፤ ከተያዙት ውስጥ ትልቋ 19ዓመቷ አካባቢ ነበር፤ ትንሽዋ ደግሞ ወደ 15ዓመት አካባቢ ነበረች፤ በተያዝንበት ወቅት ልጆቹን ክፉኛ ሲደበድቧቸውና በሰደፍ ሲመቷቸው አይቻለሁ፤ ልብሳቸውንም ቀዳድደውባቸው ብጣቂ እራፊ አድርገው ተመልሰዋል፤ ይህንን በየጊዜው የሚያደርጉት ተግባር ነው፤ …Ogaden 11
“መረጃ እንድንሰጣቸው በየጊዜው ይመረምሩን ነበር፤ ሴቶችን ‘አስገድደን እንደፍራችኋለን’ እያሉ ያስፈራራሉ፤ ‘አንደፈርም’ ብለው አሻፈረን የሚሉትን ደግሞ ያንቋቸዋል፤ ሴቶቹ ራሳቸውን ስተው ባሉበት ወቅት እንኳን ይደፍሯቸዋል … እኔ የታሰርኩበት ትንሽ ክፍል ውስጥ ሰባት ሴቶች ነበሩ፤ ከዚያ ክፍል ነጻ የተለቀቀ የለም ማለት ይቻላል፤ ከእኛ በፊት እዚያ ክፍል የነበሩት ታርደዋል፤ ሌሎቹም በረሃብ እንዲሞቱ ተደርገዋል፤ ሬሣቸውንም በየጉድጓዱ ወርውረውታል፤ እኛ የነበርንበት ክፍል ሬሣ ነበር፤ የክፍሉን ሁኔታ ማንም ሊገምት የሚችል አይደልም (መግለጽ አይቻልም)፤ በክፍሉ የነበረው ሬሣ ባብዛኛው የወጣት ወንዶች ነው፤ እስከ አራት ቀናት ሬሣው በክፍሉ እንዲቆይ ይደረጋል፤ ከዚያ አውጥተው በየቦታው፤ በየመንገዱ ይወረውሩታል፤ …”
እንደ ሚሪያም በግንቦት 2006 ዓም ወደ ዳዳብ የመጣችው ፋጡማ “ወታደሮቹ እናንተ የኦጋዴንን ሰዎች እናጠፋችኋለን፤ ምንም ዓይነት ነዋሪ እዚህ አካባቢ አንፈልግም፤ እንጨርሳችኋለን” ይሉናል፡፡ “እስርቤት ሳለሁ አንቀውኝ ነበር፤ በሳንጃም ወግተውኛል፤ በየጊዜው መላ አካላቴን ደብድበውኛል፤ ጭንቅላቴን በኤሌትሪክ ጠብሰውታል፤ የማያደርጉት ዓይነት ስቃይ የለም …” በማለት ምሬት እና ሰቆቃ በተሞላበት ድምጽ ምስክርነቷን ስትሰጥ ትደመጣለች፡፡ ኦብነግ በአካባቢው እንዳለ እና ሠራዊቱ አንድ መቀመጫ ቦታ እንደሌለው፤ በተገኘው አጋጣሚ ወደ ሰፈር እንደሚመጡ እና የሚፈልጉትን እንደሚያገኙ ፋጡማ ትናገራለች፡፡Ogaden 12
ህወሃት በበረሃ በነበረበት ጊዜ ተጋዳላዮቹ በየምሽቱና በየሌሊቱ ወደ መንደራቸውና ሰፈራቸው በሚመጡበት ጊዜ የትግራይ እናቶች ልጆቻቸውን ምግብና መጠጥ እያሲያዙ፤ ስንቅ እንየቋጠሩ ይልኩ ነበር አቶ ስዬ አብርሃ ሲናገሩ ተደምጠዋል፡፡ እንዲያውም የራሳቸውን እናት ጠቅሰው ብዙዎችን ይመግቡ እንደነበርና ለበርካታ ተጋዳላዮች “እናት” እንደነበሩ መናገራቸው ይታወሳል፡፡
በህወሃት አዛዥነት ወደ ሥፍራው የተላከው ሠራዊት አስገድዶ መድፈር አንዱ የጥቃት መሣሪያው ነው፡፡ በወታደራዊ ሠፈሮች ውስጥ ሴቶች ለወሲብ መገልገያ ሆነዋል፤ ከሚደርስባቸው ሰቆቃ በተጨማሪ በተደጋጋሚ በበርካታዎች ይደፈራሉ በሚለው የግራሃም የቪዲዮ ዘገባ ላይ የስቃይ እንባ የምታፈሰውን ሚሪያም “በተደጋጋሚ ተደፍሬአለሁ፤ ድርጊቱ መደበኛ እየሆነ ከመምጣቱ የተነሳ ተቀበልነው” ስትል ያሳያል፡፡ “ብዙዎች በጣም አሳዛኝ በሆነ ሁኔታ ላይ ይገኛሉ፤ አንዳንዶችም የሚጥል በሽታ ይዟቸዋል ሌሎችም እውር ሆነዋል፤ እኔም ራሴ ከደረሰብኝ ስቃይና ድብደባ የተነሳ አሁን እየተሻለኝ ቢሆንም የጡንቻ መኮማተርና የሚጥል በሽታ ይዞኛል፡፡”
የኦጋዴን ጭፍጨፋ መሃንዲሱና ጀማሪው ሞት እንደ ቡሽ ክዳን ያስፈነጠረው መለስ ነው፡፡ የሙት ውርስ እንጠብቃለን የሚሉት አወዳሾቹም በሙት መንፈስ እየተመሩ ግፉን ቀጥለውበታል፡፡Ogaden 13
የኢትዮጵያን ስም ይዞ በኦጋዴን ወገኖቻችን ላይ የዘመተው የትግራይ ህዝብ ነጻ አውጪ ግምባር ሠራዊት ኦጋዴን በደረሰበት ጊዜ የፈጸመውን እማኞቹ በግልጽ ያስረዳሉ፡፡ “የኢትዮጵያ ሠራዊት አባላት ይሁኑ ወይም ልዩ ፖሊስ እኔ አላውቅም” የምትለው ፋጡማ ሰፈሮቻቸው በወራሪው ሠራዊት ከተከበበ በኋላ ከብቶቻቸው፤ ግመሎቻቸው፤ … በአጠቃላይ ንብረታቸው እንደተዘረፈ ትናገራለች፡፡ ከሁለቱ ሴቶች ጋር በመስማማትም ወንዶች እየተነጠሉ እንደተገደሉ ታስረዳለች፡፡ በተለይ የተማሩ የሚባሉ የኦጋዴን ወጣቶችን እየለዩ እንደገደሉ የሟች ቤተሰብ የሆኑት እነዚህ እህቶች በቃለምልልሱ ላይ ሲናገሩ ይደመጣሉ፡፡ ሁልጊዜ የሚባሉትም “አንዳችሁንም አናስተርፍም፤ እንጨርሳችኋልን” መሆኑን ግፍ፤ እልህና ሲቃ በሞላው ድምጽ ይናገራሉ፡፡ ዘጋቢ ፊልሙ ላይ በተሰጠው መረጃ መሠረት ይህንን ግፍ የሚፈጽሙት ግዢው ህወሃት በልዩ ሁኔታ ያሰለጠናቸው በትምህርት ያልታነጹ፤ ወታደራዊ ዲሲፒሊን የሌላቸውና ከወሮበላ የማይተናነስ ባህርይ ያላቸው ጨካኝ ፓራሚሊታሪዎች እንደሆኑ ያስረዳል፡፡
ህወሃትንና ሹሞቹን በዚህ የኦጋዴን ዘር ማጥፋትና በሰብዓዊ ዘር ላይ በሚፈጸም ወንጀል ማስከሰስ፤ ለፍርድ ማቅረብ የኦጋዴን ወገኖችንና የመላ ኢትዮጵያ ልጆችን ትብብር ይጠይቃል፡፡ ስቃይ፣ መከራ፣ ሰቆቃ፣ … ካላስተባበረን ሌላ ምን ሊያስተባብረን ይችላል? ሰዎች ደስታን እንደመሰላቸው ሊተረጉሙት ይችላሉ፤ ግፍ ግን ቋንቋውና ስሜቱ አንድ ዓይነት ነው – እስከ አጥንት ይዘልቃል፤ መቅኔን ይቆጠቁጣል፡፡
Ogaden 15ከአዘጋጆቹ፤ ምንም እንኳን በጋዜጠኛነት ተግባር ላይ የምንገኝ ቢሆንም የእነዚህ እህቶቻችን እና ወንድሞቻችን መከራና ስቃይ ያመናል፤ ያስለቅሰናል፡፡ ከአንዲት እናት የተወለድን ሰብዓዊ ፍጡር እንደመሆናችን የሴቶች ስቃይ ከምንም በላይ ልባችንን ያሳምማል፡፡ እንደ ኢትዮጵያዊ ይህንን ስቃይ ማቅረብ ሌላውን ዜና የመዘገብ ያህል ቀላል አይደለም፡፡ ድርጊቱ አሁን የተፈጸመ ያህል እየተሰማቸው አሁንም ትኩስ እንባ እያፈሰሱ ስቃያቸውን የገለጹት እህቶቻችን ህመም የማያመውና የማያስለቅሰው ህወሃትና በድንቁርና ጭለማ ውስጥ የገቡት ጀሌዎቹ ናቸው፡፡ ህወሃት ይህንን ዓይነቱን ግፍ ሲደርግ ኖሯል፤ አሁንም እያደረገ ነው፤ ኢትዮጵያ ግን አሁንም ከእናንተ የኦጋዴን ግፉአን ጋር ታለቅሳለች፡፡
ከጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ የተወሰደ

Thursday, June 23, 2016

አንዳርጋቸው ጽጌ የታገተበትን ሁለተኛ አመት ስናስታውስ ለነጻነት ትግሉ ያለንን ቁርጠኝነት በማደስ ነው!!!

June 23,2016

የወያኔ አገዛዝ በአቡደራቡህ መንሱር ሃዲ ይመራ ከነበረው የየመን መንግሥት ጸጥታ ሃይል ጋር በመመሳጠር አንጋፋውን መሪያችንንና የትግል ጓዳችንን አንዳርጋቸው ጽጌን ከሰነዓ አውሮፕላን ማረፊያ አግቶ በቁጥጥሩ ስር ካስገባ እነሆ ዛሬ ሁለት አመት ሞላው።
የአለም አቀፉን ህግ በመተላለፍ ህወሃት ድንበር ተሻግሮና ባህር አቁርጦ አንዳርጋቸው ጽጌን ከየመን ሲያግት ቢያንስ ሁለት ውጤቶችን ለማግኘት አሰፍስፎ እንደነበር መገመት አያስቸግርም። አንደኛው ሥልጣን ላይ ተደላድሎ ለብዙ አመታት የመቆየት ምኞቱን አደጋ ላይ የጣለበትን የአርበኞች ግንቦት 7 እንቅስቃሴ አከርካሪ በመምታት ትግሉን አሽመደምደዋለሁ የሚል የተሳሳተ ስሌት ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ ህወሃትን የሚግደራደር ሃይል የትም ቢሆን ሊያመልጥ እንደማይችል በማሳየት የኢትዮጵያን ህዝብ አንገት ለማስደፋትና በፍርሃት አንቀጥቅጦ ለመግዛት የታለመ የእብሪት ውሳኔ ነው።
በዚህም ስሌት ህወሃት አንዳርጋቸው ጽጌን በእጁ ለማስገባት በአፈናው ተግባር ተባባሪ ለሆነው ለመንሱር ሃዲ መንግሥት ዘጠኝ ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር እንደከፈለ በራሱ አንደበት ሳይደብቅ ለደህንነት አባላቶቹ ሲናገር ተደምጧል። ዘጠኝ ሚሊዮን ዶላር ከድህነት ወለል በታች ላለቺው አገራችንና የዕለት ህይወቱን ከአለም አቀፍ ህብረተሰብ በሚለገስ የምግብ ዕርዳታ ለሚገፋው ህዝባችን ምን ማለት እንደሆነ ግልጽ ነው። በግዜያዊ ጥቅም አይናቸው የታወረዉ የየመን መንግሥት ባለስልጣኖችም ቢሆኑ ለፍትህ፥ ለእኩልነትና ለነጻነት የሚታገልን አንድ ኢትዮጵያዊ በአገሩ አየር መንገድ ሲጓዝ አግተዉ ለወያኔ ሲያስረክቡ ለረጂም አመታት በዘለቀዉና ለወደፊትም ጸንቶ በሚቆየዉ የሁለቱ አገሮች ወዳጅነት ላይ ጥሎት የሚያልፈዉ መጥፎ ጠባሳ የታያቸዉ አይመስልም። የሰነዓውን ኦፕሬሽን በህወሃት በኩል የመራውና አንዳርጋቸዉ ጽጌ እጆች ላይ ካቴና አጥልቆ ለወያኔ ያስረከበው አብረሃም መንጁስም ቢሆን በሱልጣን ሽኩቻ ከነበረበት ሃላፊነት ተፈንግሎ ዛሬ የት እንዳለ ከሱ ከራሱ ዉጭ ሌላ ሰዉ የሚያዉቅ አይመስለንም።
የህወሃት አፈናና ጭቆና የመረረው ህዝባችን አንዳርጋቸው ጽጌን ለማገት የተሄደበት ርቀትና የተከፈለው ዋጋ በነጻነቱ ላይ የተቃጣ ድፍረት መሆኑን ያሳየው “እኔም አንዳርጋቸው ነኝ” በሚል ቁጣ ሆ ብሎ በመነሳት ነው። አገር ውስጥና ከአገር ውጪ የተቀጣጠለው ይህ ህዝባዊ ቁጣ በአንድ አንዳርጋቸው መታገት እልፍ አእላፍ አንዳርጋቸውን ከማፍራቱም በላይ የህወሃት መሪዎችንና ጋሻ ጃግሬዎቻቸው እንደለመዱት ደረታቸውን ነፍተው በሠላም እንዳይወጡና እንዳይገቡ ወደ ሚያሸማቅቃቸው የተግባር እርምጃ ተሸጋግሮአል።
አርበኞች ግንቦት 7 ከአንዳርጋቸው መታገት በኋላ የተቀጣጠለው ህዝባዊ ቁጣ የአንዳርጋቸዉ የረጅም ጊዜ ምኞትና ትግል ላይ በነበረባቸዉ አመታት በከፍተኛ ደረጃ የደከመበት የልፋቱ ዉጤት ነው ብሎ ያምናል። አርበኞች ግንቦት 7 ይህንን ህዝባዊ ቁጣና ህዝባዊ መነቃቃት አስተባብሮና የሚያስፈልገውን አመራር ሰጥቶ ትግሉን ከዳር ለማድረስ በሙሉ ሃይሉና ጉልበቱ እየተንቀሳቀሰ መሆኑን በዚህ አጋጣሚ ለወዳጅም ለጠላትም ይገልጻል።
የምንወደውና የምናፈቅረው የትግል ጓዳችን አንዳርጋቸው ጽጌ የታገተበትን ሁለተኛ አመት ስናስታውስ ይህ ጀግና ሰዉ የጀመረውን ትግል ከዳር ለማድረስ ያለንን ቁርጠኝነት በማረጋገጥ ነው። ለፍትህ ለእኩልነትና ለነጻነት ሲታገሉ የወያኔ ሠለባ የሆኑ ወገኖቻችንን በፍጹም እንደማንረሳቸዉና በየዕስር ቤቱ በዘረኞች እብሪት እየተሰቃዩ ያሉ ወገኖቻችን ሁሉ ነጻ እስኪወጡ ድረስ እነሱ አንግበው የተነሱትን ዓላማ ከግብ ለማድረስ ቆራጥነት ትግሉን እንደምንቀጥል ቃል እንገባለን።
የትግል ጓዳችን አንዳርጋቸዉ ሆይ ! ያንተና እንዳንተ በወያኔ ሰቆቃ የሚፈጸምባቸው ጓዶቻችን ሁሉ የመከራ ዘመን የሚያበቃው የወያኔ የሥልጣን ዕድሜ ለማሳጠር የጀመርከውን ትግል ከዳር ስናደርስ መሆኑን አንተም ታውቀዋለህና እንደምንታደግህ አትጠራጠር።
ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ

የአቶ አንዳርጋቸው ጽጌ መታሰር የነጻነት ትግሉን አቀጣጥሎታል ሲል አርበኞች ግንቦት7 ገለጸ

June 23,2016

ኢሳት ዜና :- ንቅናቄው የድርጅቱ ከፍተኛ የአመራር አባል የታሰሩበትን ሁለተኛ አመት ለማስታወስ ባወጣው መግለጫ “ ህወሃት አንዳርጋቸው ጽጌን በእጁ ለማስገባት በአፈናው ተግባር ተባባሪ ለሆነው ለየመኑ የቀድሞ መሪ መንሱር ሃዲ መንግሥት ዘጠኝ ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር ቢከፍልም፣ አፈናው በአገር ውስጥና ከአገር ውጪ ህዝባዊ ቁጣ ከመቀስቀስ እና እኔም አንዳርጋቸው ነኝ የሚሉ ታጋዮች ትግሉን እንዲቀላቀሉ እንዲሁም ወደ ተግባር ትግል እንዲገቡ ከማድረግ ውጭ በድርጅቱ ላይ ያሰበውን ድል አላገኘም ብሎአል።
“የሰነዓውን ኦፕሬሽን በህወሃት በኩል የመራውና አንዳርጋቸዉ ጽጌ እጆች ላይ ካቴና አጥልቆ ለወያኔ ያስረከበው አብረሃም መንጁስም ቢሆን በሱልጣን ሽኩቻ ከነበረበት ሃላፊነት ተፈንግሎ ዛሬ የት እንዳለ ከሱ ከራሱ ዉጭ ሌላ ሰዉ የሚያዉቅ አይመስለንም” የሚለው የአርበኞች ግንቦት 7 መግለጫ፣ የአንዳርጋቸው መያዝ የፈጠረው ህዝባዊ ቁጣ የህወሃት መሪዎችንና ጋሻ ጃግሬዎቻቸው እንደለመዱት ደረታቸውን ነፍተው በሠላም እንዳይወጡና እንዳይገቡ ወደሚያሸማቅቃቸው የተግባር እርምጃ አሸጋግሮታል ብሎአል።
ከአንዳርጋቸው መታገት በኋላ የተቀጣጠለው ህዝባዊ ቁጣ የአንዳርጋቸዉ የረጅም ጊዜ ምኞትና በትግል ላይ በነበረባቸዉ አመታት በከፍተኛ ደረጃ የደከመበት የልፋቱ ዉጤት ነው ብሎ እንደሚያምን የገለጸው ድርጅቱ፣ አርበኞች ግንቦት 7 ይህንን ህዝባዊ ቁጣና ህዝባዊ መነቃቃት አስተባብሮና የሚያስፈልገውን አመራር ሰጥቶ ትግሉን ከዳር ለማድረስ በሙሉ ሃይሉና ጉልበቱ እየተንቀሳቀሰ ነው ሲል አክሏል።
ንቅናቄው “የትግል ጓዳችን አንዳርጋቸው ጽጌ የታገተበትን ሁለተኛ አመት ስናስታውስ ይህ ጀግና ሰዉ የጀመረውን ትግል ከዳር ለማድረስ ያለንን ቁርጠኝነት በማረጋገጥ ነው” ያለ ሲሆን፣  ለፍትህ ለእኩልነትና ለነጻነት ሲታገሉ የአገዛዙ  ሠለባ የሆኑ በየዕስር ቤቱ  እየተሰቃዩ ያሉ ሁሉ ነጻ እስኪወጡ ድረስ ትግሉን እንደሚቀጥል አስታውቋል።
በሌላ በኩል በእንግሊዝ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ቀኑን በማስመልከት በእንግሊዝ የውጭ ጉዳይ ፊት ለፊት የተቃውሞ ሰልፍ አድርገዋል። ሰልፉ በእስር ላይ የሚገኙ የፖለቲካ እስረኞች እንዲፈቱ የሚጠይቅ መሆኑን ጋዜጠኛ መታሰቢያ ቀጸላ ከስፍራው ዘግባለች ።

Wednesday, June 22, 2016

ህወሃት “አምባሳደሮችን” በታማኞቹ ሊተካ ነው

June22,2016
“የማይታመኑ ከሆነ “አለመታመናቸውን” ማሳየት አለባቸው”
ambassadors

በተለያዩ አገራት የሚገኙ አምባሳደሮች በወሳኝ የህወሃት ሰዎች ሊተኩ እንደሆነ ተነገረ፡፡ በህወሃት ውስጥ ያለው ፍርሃቻና አለመረጋጋት ለሁኔታው አስገዳጅነት ምክንያት ሆኖ ቀርቧል፡፡ ህወሃት ለዓመታት ያገለገሉትን ሎሌዎች የማያምናቸው ከሆነ እነርሱም “አለመታመናቸውን” ማሳየት ይገባቸዋል፡፡
በአሜሪካ፤ በአውሮጳ፤ በአውስትራሊያና በኢትዮጵያ አጎራባች በሆኑ አገራት የሚገኙ አምባሳደሮች በቅርቡ ወሳኝ በሆኑ የህወሃት ሰዎች ሊተኩ መታሰቡን ማንነታቸው እንዲገለጽ ያልፈለጉ የጎልጉል መረጃ አቀባይ አስታውቀዋል፡፡ ለመረጃው ቅርብ እንደሆኑና የአገራቱም ዝርዝር እንዳላቸው የተናገሩት መረጃ አቀባይ የሹምሽሩ ምክንያት ይህ ነው ተብሎ በውል ባይታወቅም ህወሃት ከውስጥና ጫና ተጠቃሽ እንደሆነ ይጠቁማሉ፡፡
በኢህአዴግ ተለጣፊና ድቃይ ድርጅቶች ታቅፈው የሥርዓቱ ሎሌ የሆኑት አምባሳደሮች በመጪዎቹ ሳምንታትና በሐምሌ ወር ወደ ኢትዮጵያ እንዲመጡ እንደሚደረግ ታውቋል፡፡ በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የሚደረግ ዓመታዊ ስብሰባና ግምገማ ተብሎ ሽፋን የሚሠጠው ይኸው አምባሳደሮችን የመጥራት ውሳኔ በህወሃት ሰዎች የተቀነባበረና የትኞቹን አምባሳደሮች በማን ለመተካት እንደታሰበ አስቀድሞ የተወሰነ ነው፡፡ በዓለምአቀፍ የዲፕሎማሲ ህግጋት መሠረት የሚነሱት አምባሳደሮች መረጃ ለየአገራቱ ደርሷል፡፡
ለ25 ዓመታት እጅግ አሰቃቂ ወንጀሎችን በመፈጸም በነጻ አውጪ ስም ኢትዮጵያን በፍግ እየገዛ ያለው የትግራይ ነጻ አውጪ ግምባር ከፍተኛ ችግር ውስጥ በሚወድቅበት ጊዜ ታማኝ የትግራይ ተወላጆችን በተለይም ነባር ታጋዮች ላይ አመኔታውን በማድረግ “ክፉ ጊዜያትን” ሲያልፍ ቆይቷል፡፡ የአሁኑም ጉዳይ ከዚህ የተለየ እንዳልሆነ ነገራል፡፡
በተለይ በሰብዓዊ መብት ረገጣ እያደረሰ ያለው ግፍ ከበቂ በላይ በሆነ ማስረጃ በተደጋጋሚ እየወጣበት ባለበት ባሁኑ ጊዜ የወደፊቱ ሁኔታ ምን ሊሆን ይችላል የሚለው መመለስ ያለበት ጥያቄ ሆኗል፡፡ ለዚህም ይመስላል በሰሜኑ ኢትዮጵያ ከአማራው ክልል ጋር ተያይዞ ያለውን አደገኛ ሁኔታ ለማምከን የኤርትራ ካርዱን የመዘዘው በማለት አስተያየት ሰጪዎች ይናገራሉ፡፡ ወራትን ያስቆጠረው የኦሮሞ ወጣቶች ተቃውሞ ከሁሉም በላይ አረመኔነቱንና ለሥልጣኑ ሲል የማይፈጽመው ወንጀል እንደሌለ በግልጽ ያሳየ መሆኑን ሰሞኑን የወጣው የሰብዓዊ መብት ተመልካቹ መ/ቤት (ሂውማን ራይትስ ዎች) ዘገባ ያሳያል፡፡
በተለይም በያዝነው ዓመት ጥር ወር አካባቢ የአውሮጳ ፓርላማ ኢህአዴግን “ልክ የሚያስገባ” ባለ 19 ነጥብ ውሳኔ ማስተላለፉ ይታወቃል፡፡ በወቅቱ ውሳኔው ኢህአዴግ “ልክ ሊገባ ይሆን” የሚል አመለካከት መጫሩን ጎልጉል ጠቅሶ በጻፈበት ወቅት “ረቂቁ ለውይይት እንዳይቀርብ የቻሉትን ያህል የጣሩት ቴድሮስ አድሃኖም “ዲፕሎማሲያቸው” አለመሥራቱን፤ ጉዳዩን በቅርበት የሚከታተሉ ውሳኔው “ውስጡ በብረት የተወጠረ የቦክስ ጓንቲ ነው” ማለታቸውን ጨምሮ ዘግቦ ነበር፡፡ ይህ በዝርዝር መረጃ ቀርቦበት ለውሳኔ የበቃው ሰነድ ቀኑን ጠብቆ ህወሃት ላይ ሰይፉን እንደሚመዝ የወንጀሉ ተዋናዮች ከማንም በላይ የሚረዱት እውነታ ሆኗል፡፡
በአሜሪካ፤ ወሳኝ በሆኑ የአውሮጳ ከተሞች (ህብረቱ ያለበትንም ጨምሮ) እንዲሁም በኢትዮጵያ አጎራባች አገራት ያሉ አምባሳደሮች በታማኝ የህወሃት ተጋዳላዮች ለመተካት መታሰቡ የዲፕሎማሲው ተጽዕኖ ያስከተለው ጫና ብቻ ሳይሆን በህወሃት ውስጥ ሌላም ፍርሃቻ ስለአለ ነው በማለት ጉዳዩን ከሌላ አንጻር የሚመለከቱ ይናገራሉ፡፡
አሊ ኦጃሊ
አሊ ኦጃሊ
ምዕራባውያን ኃይላት ትኩረታቸውን ሊቢያ ላይ አድርገው ጋዳፊን ከሥልጣን ለማውረድ እንቅስቃሴ በጀመሩበት ወቅት ዓመጹ እየተፋፋመ ሲሄድ በየአገሩ የነበሩ የጋዳፊ ታማኞች መክዳታቸው ይታወሳል፡፡ ጋዳፊ ህይወታቸው በOctober 2011 ከማለፉ ስምንት ወራት በፊት በዋሽንግተን ዲሲ ታማኝ አድርገው ያስቀመጧቸው አምባሳደር አሊ ኦጃሊ ጋዳፊን መክዳታቸው ይታወቃል፡፡ ለጋዳፊ ታማኝ በመሆን አርባ ዓመት ያህል ያገለገሉት አምባሳደሩ በወቅቱ ከከዱ በኋላ የአማጺውን ኃይል ተቀላቅለው ነበር፡፡ ከዚህ አልፈው በአሜሪካ የአማጺው አፈቀላጤና ተወካይ በመሆን ሲሰሩ ከቆዩ በኋላ የጋዳፊ መውደቅ እውን እየሆነ ሲሄድ አሜሪካ መልሳ በቦታቸው አስቀምጣቸው ነበር፡፡ ከዚህ አንጻር ህወሃትን ያስፈራው ይህንን መሰል የፖለቲካ ቁማር እንደሆነ ይነገራል፡፡
ከሎሌነት ባላለፈ አገልግሎት የሚሰጡትን “የራሴ፤ ታማኞቼ” ከሚላቸው ጋር ፈጽሞ እኩል ሊያደርጋቸው የማይፈልገው ህወሃት የፖለቲካው ትኩሳት አቅጣጫውን የቀየረ ዕለት የአሊ ኦጃሊን መንገድ ሊከተሉ ይችላሉ ብሎ የጠረጠራቸውን በቶሎ ለመተካት መወሰኑ “ከጋዳፊ ተምረናል” የሚል እንድምታ እንዳለው ይነገራል፡፡ በየትኛውም የለውጥ እንቅስቃሴ ጊዜ በተለይ በጎረቤትና በኃያላን አገራት ያሉ አምባሳደሮች መክዳት አልፎም ንቅናቄውን መቀላቀል የአምባገነኖችን ዕድሜ በማሳጠር በኩል ቁልፍ ሚና ይኖረዋል የሚሉ አስተያየት ሰጪዎች ህወሃት ምዕራባውያን በተገኘው አጋጣሚ ፊታቸውን እንደሚያዞሩበት በመገመት ይህንን መሰሉን ጥንቃቄ ማድረጉ ሥልጣኑን እንዴት እንደሚንከባከብ የሚያሳይ ነው፡፡ በተለይ የኦህዴድ መሸርሸርና በክልሉ ያለው ዓመጽ እስካሁን አለመብረድ ከአምባሳደር ጀምሮ እስከ በታች እርከን የቆንስላ ተግባራት ላ የተሰማሩ ኦሮሞ ዲፕሎማቶችንና ሠራተኞችን በዓይነቁራኛ እንዲታዩ እያደረጋቸው ነው፡፡ ከዚህ አንጻር “ለችግር ጊዜ አትታመኑም” ተብለው እንደሸቀጥ እንዲመለሱ የሚጠሩት አምባሳደሮች ቀን ፊቷን ሳታዞርባቸው ለምንስ በእርግጥ “የማይታመኑ መሆናቸውን” ለህወሃት አያሳዩትም በማለት የዜናው አቀባይ ለዲፕሎማቶቹ ጥሪ አዘል ምክር ለግሰዋል፡፡   (ፎቶ: ያለፈው አመት ሹመኞች)
ምንጭ ጎልጉል

Monday, June 20, 2016

BREAKING: Genzebe Dibaba’s coach arrested in doping raid

June 20,2016
image
BARCELONA, Spain (AP) — The coach of World 1500m champion Genzebe Dibaba and other long-distance runners was arrested near Barcelona after Spanish police raided his hotel room and found traces of EPO and other banned substances on Monday.

Jama Aden, a Somalian, was detained along with one of his unnamed trainers from Morocco, as the IAAF tested 30 athletes who were also guests at the Sabadell hotel, about 25 kilometers from Barcelona, where the coach has established annual training camps since 2013.

Police confirmed Aden and his trainer were under arrest on charges of administering and distributing doping substances and endangering public health. After questioning by law enforcement, both detainees should face prosecution within 72 hours.

Local authorities did not expect further arrests to follow.

The athletes, including Dibaba, at the raided hotel were mainly from Somalia, Sudan, Ethiopia or Djibouti.

Dibaba is a heavy favorite to win the Olympic women’s 1500m in Rio de Janeiro.

A simultaneous police raid in Madrid also yielded 16 arrests related to the trafficking of drugs and anabolic steroids.

Despite coinciding in time, law enforcement officers stressed there was no connection between the Sabadell operation and the bust in the Spanish capital, mainly linked to the bodybuilding underground market for steroid users.

Source: AP

” የኢህአዴግ” እና “ህግደፍ” የሰሙኑ ዉጥረት



June 20,2016
(የግል እይታ) – ዑስማን ካዋጃ
Ethiopiaየዛሬ 25 አመት የዓረቦች ታላቅ ህልም እና አጀንዳ በኢህአዴግ እና ህዝባዊ ግንባር ንዲሞክራሲን ፍትሕን (ህግደፍ) ኣስፈፃሚነት ተግባራዊ ሆነ ፡፡ የኢ/ያ ህዝቦችን በመሳርያ አፈሙዝ በማስገደድ ፡ ኤርትራውያንን የፈጠራ ታሪክ በመጋት እና Mass hallusination በመፍጠር ሁለት አገሮች ተፈጠሩ፡፡ ኤርትራ የግላችን ኢ/ያ የጋራችን የሚል የዝርፍያ እቅድ በ “ህግደፍ” ተነድፎ ሁለቱም ባለግዜዎች ለተግባራዊነቱ ተረባረቡ፡፡ እነ ቀይባህር ኮርፖሬሽን ተመስርተው ኢ/ያ ያለምንም ከልካይ ተዘረፈች፡ እነ Horn international bank በብድር እና እና እርዳታ የተገኘውን የውጭ ምንዛሪ በሰአታት ፍጥነት ህጋዊነትን አላብሰው አስመራ አደረሱት፡፡ ስለ አገር መቆርቆር እንደወንጀል ተቆጠረ፡ ምስጋና ለወቅቱ የትግራይ ክልል አስተዳዳሪ ለነበሩት አቶ ገብሩ አስራት ይህን የዝርፍያ እቅድ በተቻላቸው መጠን ለመከላከል ሞከሩ በውጤቱም በተለምዶ ኢትዮ ኤርትራ የሚባለውን ግጭት ተቀሰቀሰ፡፡
ከ ሁለት ዓመታት ከባድ ጦርነት በኢትዮጵያ ልጆች ከባድ መስዋዕትነት የሻዕብያ ምሽግና ትዕቢት ተናደ፡፡ የኢ/ያ ጦር አሰብን ለመቆጣጠር ጥቂት ኪሎሜትሮች ሲቀሩት ታላቁ ” ባለራአይ” መሪያችን ራዕያችንን እንዳይሆን አድርገው አኮላሹት፡፡
ሰሙኑን የኢትዮ-ኤርትራ ግጭት እንደ አዲስ ተማሙቋል፡ አፍቃሪ ኢህአዴግ ሚድያዎች እና ትናንሽ ካድሬዎት ግቡ ባይታወቅም የጦርነት ነጋሪት እየጎሰሙ ናቸው፡፡ እኔ በግሌ የሰሙኑን የጦርነት አጀንዳ አጥብቄ እቋወማለሁ ለምን ቢባል:
1)ኢህአዴግ ኤርትራ ላይ ባለው ጭንጋፍ አቋም፡
ገዥው ፖርቲ ምን ግዜም ኤርትራ እና ህጋዊ የባህር በር የማግኘት መብታችን በተመለከተ ምን ግዜም ከኢትዮጵያ ህዝቦች በተፃራሪ እነደቆመ ነው፡፡ታድያ ይህን የገዢው ፖርቲ ፀረ ኢ/ያ አቋም ሳይቀየር ምን ለማግኘት ነው ጦርነት ውስጥ የምንገባው? እዚህ ላይ ሻዕብያን አስወግዶ ለኢ/ያ ችግር የማይፈጥር መንግስት ለመመስረት የሚል ውሃ የማይቋጥር ምክንያት በትናንሽ ካድሬዎች ይቀርባል ግን እንበል እና አዲስ የሚመሰረተውስ መንግስት ፀረ ኢ/ያ እንደማይሆን መተማመኛችን ምን ድነው?
2) ቀይ ባህር ላያ የጦር ሰፈሮቻቸው እየገነቡ ባሉ የኢ/ያ ታሪካዊ ባላንጦች ከዚህ አፍራሽ ተግባራቸው በዘላቂነት መከላከል የሚቻለው አስመራ ቤተመንግስት ላይ የሰው ለውጥ በማድረግ ሳይሆን ቀይ ባህርን በቆዋሚነት በመቆጣጠር ነው፡፡ ይህን ማድረግ የሚችል አርቆ አሳቢ መሪ እና ፖርቲ በሌለበት የሚካየድ ጦርነት ኢ/ያን ከባድ ዋጋ ከማስከፈል አልፎ የሚያመጣው ብሄራዊ ጥቅም የለም፡፡
3) የኤርትራውያን ከእንቅልፋቸው አለመንቃት፡
የሆነ ኤርትራዊ የችግራችሁ ምንጭ ምንድነው ብለን ብንጠይቀው መልሳቸው ተመሳሳይ ነው…..ኢሳያስ ኢትዮጵያዊ የደም ሃረግ ስለው ይሉናል ፡፡ታድያ ችግራችሁ እንዴት ይፈታል? የሚል ጥያቄ ብናስከትል አሁንም ገራሚ መልስ ይነግሩናል…..ኤርትራ በንፁህ ኤርትራዊ(ደቂ አባት) ስትመራ ይሉናል፡፡ከኢትዮጵያ ጋር በደም ያልተሳሰረ ንፁህ ኤርትራዊስ ማነው? ማንም ኤርትራዊ ይችን ጥያቄ መመለስ አይችልም፡፡ ታድያ የችግራቸው ምንጭ ትዕቢት፡ክፋት፡ድንቁርና፡ቅዠት፡አዲስ የተፈበረከ የውሸት መንነት: Mass Hallusination መሆኑን መውል ሳይገነዘቡ እና ስህተታቸው ለማረም ከውስጥ እንቅስቃሴ ባልጀመሩበት የኛን በማያገባን ጥልቅ ማለት ምን ለማትረፍ ነው???
እናም የኢህዴግን ባህሪ ባልተቀየረበት ወይም የኢ/ያ ብሄራዊ ጥቅምን ሳይሸራረፍ ሊያስፈፅም የሚችል ፖርቲ ባልተፈጠረበት የሚካየድ ጦርነት ኤርትራውያንን ከኢሳያስ አገዛዝ ነፃ ከማውጣት እና ኢትዮጵያውያን እናቶችን ዳግም ማቅ ከማልበስ ባለፈ ለኢትዮጵያ ዘላቂ ጥቅም ስለማያመጣ አጥብቄ እቋወማለሁ፡፡