Tuesday, June 28, 2016

አስፋልቱ “አብስትራክት” የሆነው የደምቢዶሎ ኤርፖርት

June 28,2016
“የቀረው በwifi ይሠራል”
d d airport
ህወሃት በግፍ በሚመራት ኢትዮጵያ የማይጠፋ ነገር የለም፡፡ ምናልባት መብራት ብቻ ነው የሚጠፋው ብሎ የሚያስብ የቅርቡን ክስትት ያልተከታተለ ብቻ ሊሆን ይችላል ቢባል ማጋነን አይሆንም፡፡
boy
መሃንዲሱን ተዋወቁ
መብራት፣ ውሃ፣ የስልክ ኔትወርክ፣ ወርቅ፣ … ብቻ ሳይሆን ጋዜጠኞች፣ ፖለቲከኞች፣ የሥርዓቱ ተቃዋሚዎች … በሚጠፉባት አገር ከሰማኒያ በላይ ኮንዶሚኒየም ይጠፋል፤ ሰሞኑን ደግሞ በኢትዮጵያ የህወሃት ተጠሪ ኃይለማርያም በነቀምቴ ከተማ  አውሮፕላን ማረፊያ ያስቀመጡት የመሠረት ድንጋይ ጠፍቷል ተብሎ የማኅበራዊ ሚዲያውን ሰፈር አድምቆታል፡፡
የነቀምቴው ሳያንስ ደምቢዶሎ ደግሞ ተመረቀ የተባለው የአፈር አየር ማረፊያ ህወሃትን ለከፍተኛ ስላቅና ፌዝ አጋልጦታል፡፡ የሥርዓቱ ደጋፊ የሆኑት ሳይቀሩ “ገንዘቡ ተበልቷል” ያሉበት የዚህ አውሮፕላን ማረፊያ የማኮብኮቢያና የማረፊያ መንገድ ከአፈር መሆኑ ብቻ ሳይሆን ተሳፋሪዎችንም ከአውሮፕላኑ ሲወርዱ የሚያጠልቁት ጭቃ መከላከያ እንዲኖራቸው የሚያስገድድ ሆኗል፡፡ ከአየር መንገድ ንግድ አንጻር ይህ በራሱ በኢትዮጵያ አየርመንገድ መሸፈን ያለበት ወጪ በመሆኑ ከረሜላ፣ ለስላሳና ጣፋጭ ምግቦችን ከአንዳንድ ቦቲ ጋር አብሮ ለተሳፋሪዎች በበረራ አስተናጋጆቹ ማቅረብ እንደሚገባው ፌዘኞች አላግጠዋል፡፡
ddairportየተለያዩ ፎቶዎችን በመገጣጠምም በርካታ ትችት በማኅበራዊ ሚዲያ የቀረበበበት ይህ ጉዳይ አንዳንዶችም ህወሃት በትግራይና በኦሮሚያ የሚያደርገው “ልማታዊ ሥራ” እንዴት የተለያየ መሆኑን በትግራይ የሚገኙ ኤርፖርቶችን ከደምቢዶሎው ጋር በማነጻጸር ምሬታቸውን የገለጹበት ሆኗል፡፡
በዚህ የዜና ዘገባ፥ እፍረት አያውቅም እንጂ፤ የቀድሞው ኢቲቪ ያሁኑ ኢቢሲ እስካሁን 50ዓመት አገልግያለሁ ከዚህ በኋላ በቃኝ ብሎ “ለሰፊው ሕዝብ ጥቅም ሲል” ራሱን ማጥፋት ነበረበት ተብሏል፡፡
እጅግ ከፍተኛ የሥራአጥ ቁጥር ባለበት አገር ይህ ኤርፖርት የሥራ ዕድል ከፍቷል ብለው የተሳለቁ ይህንን ማስታወቂያ በትነዋል፡-
ክፍት የስራ ቦታ ማስታወቂያ
በዚህ ሳምንት የተመረቀው ዘመናዊው የደምቢ ዶሎ አየር ማረፊያ መስፈርቱን የሚያሟሉ ማንኛቸውንም አመልካቾች ያለ ውድድር በቀጥታ ለመቅጠር ይፈልጋል። መስፈርቱን እናሟላለን የምትሉ ደምቢ ዶሎ ግብርና ምርምር በአካል ቀርባችሁ መመዝገብ የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን።
የቅጥር መስፈርት፡- የ11 በሞቶ እድገታችንን ታሳቢ በማድረግ ለ11 ዓመት የሰመጠ ባቡር በማንጠልጠል የጡንቻ ማዳበርያ የአካል ብቃት መስራቱን የሚያረጋገጥ ማስረጃ ማቅረብ ብቻ።
የስራ ቦታ፡- ደምቢ ዶሎ የታረሰ ማሳ ላይ።dd air port
የስራው አይነት፡- በጭቃ የተያዘ አውሮፕላን መግፋት።
“ይህ የሚታያችሁ አፈር ወይም ጭቃ ሊመስል ይችላል፤ አውሮፕላን ማረፊያው በአስፋልት ነው የተሰራው – አብስትራክት ስለሆነ በደንብ አልታችሁም፤ የቀረው ደግሞ በwifi ይጠናቀቃል፥ እንደጀመርን እንጨርሰዋለን” ብሏል ብለው የኢቢሲውን ተመስገን “ጋዜጠኛዊ ብቃት” ለማድነቅ አንዳንድ ፌዘኞች ስልክ ቢደውሉ ኔትወርክ ጠፍቷል ተብለዋል፡፡
airport(ጎልጉል: የድረገጽ ጋዜጣ)

No comments: