Thursday, June 30, 2016

ህወሃት በሰሜኑ ግንባር ተጨናንቋል ም/መቶ አለቃ ደጀኔ እና ወታደር በኩር ይናገራሉ!

June30,2016
በልኡል አለም
በሰሜኑ የሀገራችን ክፍል በምእራብ ትግራይ ሂሞራ በታች የማይካድራ ነዳጅ ማጠራቀሚያ አካባቢና እስከ ሰቲት ሁመራ እንዲሁም ጉናና ኡማህጂር ምስራቅ ትግራይና ዓዲ ግራት ድረስ የተሰማራዉ ከተለያዩ ክፍለ ጦሮችና ልዩ ኃይል እንዲሁም አካባቢ ሚሊሻዎች ተወጣቶ በስምሪት ላይ የሚገኘዉ የጸረ ሽብር ቡድን ወደ ግንባር እንዲሰማራ ባለመ መልኩ እየተበተነና እየተሰባጠረ እንደሚገኝ ታማኝ የመከላከያ ምንጮች ገልጸዋል።Ethiopian Soldiers
ይህዉ የጸረ ሽብር ቡድን በተለይም ከደረሰበትና እየደረሰበት ከሚገነዉ ድንገተኛ ጥቃት ምክንያት እጅግ በመመናመኑና በመዳከሙ ለስምሪት የአካባቢዉ ክፍለ/ጦሮች እንዲተኩ የተወሰነ ሲሆን ከላይ የተጠቀሱት አካባቢዎች ላይ የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን ወገኖቻችን በአካባቢዉ ላይ ከሚደረገዉ ወታደራዊ መሯሯጥ የተነሳ ስጋት ስላደረባቸዉ አካባቢያቸዉን ወደ መልቀቁ ደረጃ ሊሸጋገሩ እንደሚችሉ እማኞች እየተናገሩ ይገኛሉ።
የህወሃት አዲስ ምልምልና ቅጥር ወታደሮች በመክዳት ምክንያት ከፍተኛ አደጋ እያስከተሉ በመምጣታቸዉ ወደ ደጀን ጦር በሚደረገዉ ዝዉዉር ከሰቲት ሁመራ ጀርባ ሲካተቱ ነባሮች ስምሪት እና ጸረ ሽብር ስምሪቱን እንደቆጣጠሩ ሆኗል።
በሰሜን ጎንደርና በምእራብ ትግራይ አካባቢ ተሰማርቶ የሚገኘው 24ተኛ ክ/ጦር ከ 25ተኛ ክ/ጦር ጋር ቅይጥ ብረት ለበስ ሜካናይዝድ በማደራጀት የጥምር ዉህድ የሚመስል ስልታዊ ክንዉን እያደረጉ ሲሆን ለዚህ ያለመረጋጋትና የመበታተን ጦስ ዋነኛዉ ምክንያት በየእለቱ በሰራዊቱ ላይ የሚደርሱ አነስተኛ ጥቃቶች እና የዉስጥ አርበኞች የፈጠሩት ጫና በአንኳርነት ተጠቃሽ ከመሆኑ በተጨማሪ የኢትዮ-ኤርትራ የጦርነት ስጋት የፈጠረዉ ትርምስ በራሱ የተያያዘ መጨናነቅ መፍጠሩን ባሳለፍነዉ ሳምንት ከሰሜኑ ግንባር ተነጥለዉ በጎረቤት ሐገር በተጠለሉ ም/መቶ አለቃ ደጀኔ ጥላሁን እና ወታደር በኩር ገ/ስላሴ ለታማኝ ምንጮቻችን ተናገረዋል።
ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ ! !

No comments: