Sunday, November 16, 2014

የተወሰደው እርምጃ የስርዓቱን ፍርሃት ደረጃ እንደሚያሳይ ኢ/ር ይልቃል ገለጹ

November 16,2014
9ኙ ፓርቲዎች በትብብር የጠሩትን የአደባባይ ህዝባዊ ስብሰባ በኃይል መበተኑ የስርዓቱ የፍርሃት ደረጃ ጫፍ መድረሱን ያሳያል ሲሉ የትብብሩ ሊቀመንበር ኢ/ር ይልቃል ጌትነት ለነገረ ኢትዮጵያ ገለጹ፡፡

ኢንጅነር ይልቃል በተለይ ሰማያዊ ፓርቲ ከአሁን ቀደም እንደሚያደርገው ለምን እስከመጨረሻው አንበተንምአላላችሁም? ብለን ላቀረብንላቸው ጥያቄ ‹‹የአንድ ወር መርሃ ግብር አውጥተናል፡፡ ምርጫው ነጻና ፍትሓዊ እስኪሆን ድረስ የነጻነት ትግሉ የሚቀጥል ነው፡፡ በአራት ኪሎ አካባቢ የሚኖሩ ዜጎችን ጠርተን ልናነጋግር በሞከርንበት ወቅት ብዙ እስርና ደብደባ ተፈጽሟል፡፡ ከዚህ የስርዓቱ ፍርሃት አንጻር ገና በመጀመሪያው ስራችን ወደኃይል እንዲገባ አልፈለግንም፡፡ ለሚቀጥሉት ስራዎቻችን ስንል ነው፡፡ ለሚቀጥለው ያንን በሚመጥን ደረጃ መዘጋጀት አለብን፡፡›› ብለዋል፡፡

ኢንጅነር ይልቃል ጌትነት አክለውም ‹‹እኛ ዛሬ የአራት ኪሎን አካባቢ ሰዎች ነው የጠራነው፡፡ በዚህ ደረጃ ፈርተው ይህን ስብሰባ ያግዳሉ ብሎ ለመገመት ይከብዳል፡፡ ድሮውንም የሌላቸው የህዝብ ድጋፍ ጭራሹን እንደተሟጠ ነው የሚያሳየው፡፡ ትንሹም ነገር ለስልጣናቸው አስጊ ነው ብለው ማሰባቸው የፍርሃት ደረጃቸው ጫፍ እንደደረሰ ያሳያል፡፡›› ብለዋል፡፡
Photo: የተወሰደው እርምጃ የስርዓቱን ፍርሃት ደረጃ እንደሚያሳይ ኢ/ር ይልቃል ገለጹ

9ኙ ፓርቲዎች በትብብር የጠሩትን የአደባባይ ህዝባዊ ስብሰባ በኃይል መበተኑ የስርዓቱ የፍርሃት ደረጃ ጫፍ መድረሱን ያሳያል ሲሉ የትብብሩ ሊቀመንበር ኢ/ር ይልቃል ጌትነት ለነገረ ኢትዮጵያ ገለጹ፡፡ 

ኢንጅነር ይልቃል በተለይ ሰማያዊ ፓርቲ ከአሁን ቀደም እንደሚያደርገው ለምን እስከመጨረሻው አንበተንም አላላችሁም? ብለን ላቀረብንላቸው ጥያቄ ‹‹የአንድ ወር መርሃ ግብር አውጥተናል፡፡ ምርጫው ነጻና ፍትሓዊ እስኪሆን ድረስ የነጻነት ትግሉ የሚቀጥል ነው፡፡ በአራት ኪሎ አካባቢ የሚኖሩ ዜጎችን ጠርተን ልናነጋግር በሞከርንበት ወቅት ብዙ እስርና ደብደባ ተፈጽሟል፡፡ ከዚህ የስርዓቱ ፍርሃት አንጻር ገና በመጀመሪያው ስራችን ወደኃይል እንዲገባ አልፈለግንም፡፡ ለሚቀጥሉት ስራዎቻችን ስንል ነው፡፡ ለሚቀጥለው ያንን በሚመጥን ደረጃ መዘጋጀት አለብን፡፡›› ብለዋል፡፡  

ኢንጅነር ይልቃል ጌትነት አክለውም ‹‹እኛ ዛሬ የአራት ኪሎን አካባቢ ሰዎች ነው የጠራነው፡፡ በዚህ ደረጃ ፈርተው ይህን ስብሰባ ያግዳሉ ብሎ ለመገመት ይከብዳል፡፡ ድሮውንም የሌላቸው የህዝብ ድጋፍ ጭራሹን እንደተሟጠ ነው የሚያሳየው፡፡ ትንሹም ነገር ለስልጣናቸው አስጊ ነው ብለው ማሰባቸው የፍርሃት ደረጃቸው ጫፍ እንደደረሰ ያሳያል፡፡›› ብለዋል፡፡

እንግሊዝ አቶ አንዳርጋቸው ፅጌን በተመለከተ ደብዳቤ መጻፏን ወያኔ አረጋገጠ

November 15,2014
የእንግሊዙ ጠቅላይ ሚኒስትር ዴቪድ ካሜሮን አቶ አንዳርጋቸው ፅጌን በተመለከተ ለወያኔዉ ጠቅላይ ሚኒስትር ደብዳቤ መጻፋቸውንና ወያኔም አቋሙን ግልጽ ማድረጓን የወያኔዉ ኮሙዩኒኬሽን ጽሕፈት ቤት ሚኒስትሩ አቶ ሬድዋን ሁሴን ተናገረ። ሬድዋን በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ባለፈዉ ማክሰኞ በሰጠዉ ጋዜጣዊ መግለጫ፣ ዴቪድ ካሜሩን ለጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለ ማርያም ደብዳቤ መጻፋቸውን የተለያዩ የውጭ ሚዲያዎች መዘገባቸውን ሰምቻለሁ ካለ በኋለ “ለምን ጻፉ ማለት አይቻልም፤ ጥያቄዉ መሆን ያለበት ምን መለሳችሁ ነው፤” በማለት የተለመደ የማጭበርበሪያ ቃላት ደርድሯል።
የተለያዩ የእንግሊዝ ሚዲያዎች ኢትዮጵያ አቶ አንዳርጋቸው ፅጌ ላይ ቀደም ሲል የተፈረደውን የሞት ቅጣት እንዳትተገብር እንዲሁም ኢትዮጵያ ለሚገኘው የእንግሊዝ ኤምባሲ አቶ አንዳርጋቸውን የመጐብኘት ቋሚ ፈቃድ እንዲሰጥ በደብዳቤያቸው መጠየቃቸውንም ሬድዋን ሁሴን ተናግሯል።
ለዴቪድ ካሜሮን ደብዳቤ መልስ መሰጠቱን ያረጋገጠዉ ሬድዋን፣ “በተጨባጭ የተፈረደበትን ግለሰብ ነው የያዝነው፤ እንዲህ ብታደርጉት ባታደርጉት ብሎ ማንሳት ይቻላል። ምክንያቱም እነሱም የሚመለከታቸው በመሆኑ። በዚህ ምክንያት ግን የእኛ መልስ በራሳችን ሕግ መሠረት ዓለም አቀፍ ሕጉም በሚለው መሠረት የምናደርገውን እናደርጋለን፤” ብሏል። ኢትዮጵያ የምትተገብረው የራሷን ሕግ መሆኑን የገለጹት አቶ ሬድዋን፣ “ከነጭም ከጥቁርም የሚመጣን ደብዳቤ ተንተርሰን ምንም አንተገብርም፤” ብሏል። ከዚህ በተጨማሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዴቪድ ካሜሮን ደብዳቤ ጽፈው፣ በኢትዮጵያ በኩልም መልስ ተስጥቷል ያለዉ ሬድዋን ሁሴን በደብዳቤው የቀረቡ ጥያቄዎች ቅሬታ እንዳላስነሱ ሁሉ መልሱም ቅሬታ አያስነሳም የሚል ተስፋ በኢትዮጵያ በኩል መኖሩን ተናግረዋል።
“እነሱ ዜጋዬ ነው ብለዋል፤ የእነሱ ዜጋ እንደ ቼ ጉቬራ ነፃ አውጣ ተብሎ ኢትዮጵያ ውስጥ አልተላከም። የእነሱ ዜጋ ከነበረ የእንግሊዝን ዴሞክራሲ ይበልጥ ለመጨመር መታገል ይችል ነበር። ነገር ግን በኢትዮጵያ በቅጥር ነብሰ ገዳይነት ካልተሰማራ በስተቀር ሌላ ሚና አልነበረውም፤” ብለዋል።

የሰንደቅ አላማችን ጠላት ወያኔና ወያኔ ብቻ ነዉ!

November 15,2014
ሰንደቅ አላማ ለአንድ አገር ህዝብ የኩራት፤ የአልበገር ባይነት፤ የአንድነትና የታሪክ ተከታታይነት ምልክት ነዉ። ሰንደቅ አላማ በአንድ በኩል የወደፊቱን ብሩህ ተስፋ ክወዲሁ እያሳየን እየዟችሁ የሚለን፤ በሌላ በኩል ደግሞ በምናብ ወደኋላ እየወሰደን የድልና የመስዋዕትነት ታሪላችንን የሚያስታዉሰን የነጻነት፤ የሠላምና የብሩህ ተስፋ ማህደር ነዉ። የአገራቸን የኢትዮጵያ አረንጓዴ፤ ቢጫና ቀይ ሰንደቅ አላማ ትናንትናና ከትናንት ወዲያ በተስፋፊዎች አለመደፈራችንን ብቻ ሳይሆን ዛሬም ዘረኞች የጫኑብንን የመከራ ቀንበር በቆራጥነት ሰብረን ነገና ከነገ ወዲያ የነፃነት አየር እንድንተነፍስ አስረግጦ የሚነግረን የአንድነታችን፤ የተገጋድሏችንና የድላችን ልዩ ምልክት ነዉ። አንድን ኢትዮጵያዊ ሰንደቅ አላማ ላንተ ምንህ ነዉ ብለን ብንጠይቀዉ ጥያቄዉን ዕድሜህ ስንት ነዉ ተብሎ እንደሚጠየቅ አንድና ሁለት ቃል ብቻ ተናግሮ አይመልስም። ሰንደቅ አላማም በአንድና በሁለት ቃላት ምንነቱ የሚገለጽ ተራ ቃል አይደለም። ኢትዮጵያዉያን ተማሩ አልተማሩ፤ ደሃ ሆኑ ኃብታም ፤ወንጀለኛ ሆኑ ወይም ሠላማዊ ለአገራቸዉ ሰንደቅ አላማ የተለየ ቦታ አላቸዉ። ሰዎች የአገራቸዉን ሰንደቅ አላማ የሚወዱትና ለሰንደቅ አላማዉ በክብር መዉለብለብ የህይወት መስዋዕትነት የሚከፍሉት ስለታዘዙ ወይም ስለ ሰንደቅ አላማዉ ተነግሯቸዉ አይደለም። በእርግጥም የሰንደቅ አላማ ክብርና የአገር ፍቅር ለሰዎች ሰንደቅ አላማዉን አክብሩ፤ አገራችሁን አፍቅሩ እየተባለ የሚነገር ነገር አይደለም። አገርንና ወገንን ማክበርና መዉደድ ሰንደቅ አላማን ከማክበርና ከማፍቀር ጋር በቀጥታ የተገናኘ ነዉ።የሰንደቅ አላማ ልዪ ክብርና የአገር ፍቅር ሰዎች ተወልደዉ ከሚያድጉበት ማህበረሰብ፤ ከቤተሰብ፤ ከጎረቤትና ከጓደኛ እንደ ምግብና እንደ ዉኃ እየበሉና እየጠጡ የሚያገኙት የሰዉነትና የዜግነት መገለጫ ታላቅ እሴት ነዉ።
ለዚህም ነዉ የማንም አገር ዜጋ አገሩ ዉስጥ ቢኖር ወይም ካገሩ ዉጭ፤ ቢታሰር ባይታሰር፤ ሀብታም ቢሆን ወይም ደሃ፤ የኔ ነዉ የሚለዉን የእናት አገሩን ሰንደቅ አላማ በፍጹም የማይረሳዉ። ከአገራቸዉ ዉጭ የሚኖሩ ሰዎች ደግሞ በተለይም ኢትዮጵያዉያን በተለያዩ ምክንያቶች የሚኖሩባቸዉን አገር ዜግነት ቢወስዱ እንኳን ሰንደቅ አላማቸዉን ባዩና ባስታወሱ ቁጥር የሚሰማቸዉ አገራዊ ስሜት እጅግ በጣም ከፍተኛ ነዉ – እንዲያዉም ከአገራቸዉ ተሰድደዉም ሆነ በልዩ ልዩ ምክንያቶች ከአገራቸዉ ዉጭ የሚኖሩ ኢትዮጵያዉያን ሰንደቅ አላማቸዉን ባዩ ቁጥር የአገራቸዉ፤ የወንዛቸዉ ፤ ተወልደዉ ያደጉበት መንደርና የልጅነት ትዝታቸዉ ባአይናቸዉ ላይ እየመጣ ዕንባ በዕንባ ይተናነቃሉ። ሰንደቅ አላማ ለአንድ አገር ህዝብ አንድ ነገር ነዉ፤ ብዙ ነገር ነዉ፤ ሁሉም ነገር ነዉ። ሰንደቅ አላማ ህዝብን ያስተባብራል፤ ያከባብራል፤ ያዋድዳል፤ መስዋዕትነትን፤ ፍቅርንና ብልፅግናን ያመለክታል።
ዛሬ የሰንደቅ አላማችንን ጉዳይ አቢይ የመወያያ አርዕት አድርገን የወሰድነዉ አለምክንያት አይደለም። በአገር ጥላቻቸዉና በስንደቅ አላማ ንቀታቸዉ የሚታወቁት የወያኔ ዘረኞች “የአብዬን ወደ እምዩ” እንዲሉ ሰንደቅ አላማቸዉ ተዋርዶ ከሚያዪ የቁም ሞታቸዉን የሚመር ትን ዉድ የኢትዮጵያ ልጆች ባንዲራዉን አዋረዱበለዉ መናገራቸዉን ስለማን ነዉ። ኢትዮጵያን ጨምሮ ብዙ አገሮች ተስማምተዉ የሚያከብሩት አለም አቀፉ የሰንደቅ አላማ አያያዝ ፕሮቶኮል በአለም አቀፍ መድረኮች ላይ የሁሉም አገሮች ሰንደቅ አላማ በእኩል ደረጃ መቀመጥና መሰቀል አለበት፤ አንድ ላይ መሰቀልና አንድ ላይ መዉረድ አለበት ይላል። ይህንን ፕሮቶኮል ረስቶና ሰንደቅ አላማችንን ንቆ በአለም አቀፍ መድረክ ላይ ከሌሎች አገሮች መሪዎች ጋር የኢትዮጵያን ሰንደቅ አላማ እንደ አለባሌ ዕቃ ዘቅዝቆ ይዞ ያዋረደዉ ወያኔዎች “ታላቁ መሪ” ብለዉ የሚጠሩት ነገር ግን የለየለት የአገርና የህዝብ ጠላት የሆነዉ ዘረኛዉ መለስ ዜናዊ ነዉ። የህወሓትን ባንዲራ በየቦታዉ እየሰቀሉ የኢትዮጵያን ሰንደቅ አላማ ተራ ጨርቅ ነዉ ብለዉ የሸቀጥ መጠቅለያ ያደረጉትም መለስ ዜናዊና ጓደኞቹ ናቸዉ። ዛሬ ደማቅ ሰንደቅ አላማዉን አስመልክቶ በወያኔና በኢትዮጵያ ህዝብ መካከል ያለዉ ትልቅ ልዩነት ትክክለኛዉና ህዝብ የኔ ነዉ ብሎ የተቀበለዉ የኢትዮጵያ ሰንደቅ አላማ የትኛዉ ነዉ የሚለዉ ጥያቄ ላይ ነዉ አንጂ ባንዲራዉን ማክበር አለማክበር ወይም ማዋረድ ላይ አይደለም።
የኢትዮጵያ ሰንደቅ አላማ የእናት አገራችንን የኢትዮጵያንና የህዝቦቿን ታሪካዊ ተከታታይነትና ዘለዓለማዊነት አጉልቶ የሚያሳየን ከሁላችንም በላይ የገዘፈ ግዙፍ አርማ ነዉ፤ ይህ ማለት ደግሞ ሰንደቅ አላማችን ያቻትና ብሎ እንደሚያሳየን አገር አንደ ኢትዮጵያ ሙሉ ህልዉና ያለዉ ህያዉ አካል ነዉ ማለት ነዉ። ሰንደቅ አላማችንን የምንወደዉና የምናከብረዉም ህያዉ አገራችንን የሚወክል ህያዉ አካል በመሆኑ ነዉ። መለስ ዜናዊንና ስብሀት ነጋን የመሳሰሉ በጣት የሚቆጠሩ የትዉልድ ጭንጋፎች ለራሳቸዉ አገር ሰንደቅ አላማ ደንታ ላይኖራቸዉ ይችላል። የኢትዮጵያ ህዝብ እንዳለ ግን የህልዉናዉና የአንድንቱ መገለጫ የሆነዉን ሰንደቅ አላማ አይንቅም ወይም አያዋርድም፤ አንድ ህዝብ ባንዲራዉን የማይቀበልና የማያከብር ከሆነ ባንዲራዉ አይወክለዉም ማለት ነዉ፡ ኢትዮጵያ ዉስጥ ዛሬ ያለዉ እዉነታም ይሄዉ ነዉ፡ የኢትዮጵያ ህዝብ ወያኔ ባዕድ አካል የለጠፈበትን ባንዲራ የኔ ነዉ ብሎ አልተቀበለዉም ወይም ባንዲራዉ ይወክለኛል ብሎ አያምንም።
ዘርዓይ ደረስ በ1937 ዓም ሮም ዉስጥ የፋሺስት ጣሊያኖችን ጭንቅላት በገዛ አገራቸዉ እንደ ቅጠል እየጨረገደ ከጣለ በኋላ በጣሊያኖች ጥይት ቆስሎ ሲያዝ የተናገዉ የመጨረሻ ቃል ይህ የጣሊያኖች ባንዲራ ይዉረድና የኢትዮጵያ ሰንደቅ አላማ ይሰቀል የሚል የጀግንነትና የአገር ፍቅር ቃል ነበር። ጀግናዉ አብዲሳ አጋ በጣሊያን በረሃዎች ጣሊያኖችን እያሳደደ ሲገድል የኢትዮጵያ ባንዲራ ከአጠገቡ አልተለየችም። በቀዳማዊ ኃ/ስላሤና በደርግ ዘመነ መንግስት ተማሪዎች ጧት ወደ ክፍል ከመግባታቸዉ በፊት ተሰልፈዉ የኢትዮጵያን ሰንደቅ አላማ በክብር ይሰቅሉ ነበር፤ ማታም ወደ ቤታቸዉ ከመሄዳቸዉ በፊት ጧት በክብር የሰቀሉትን ባንዲራ በክብር አዉርደዉ ነበር ወደየቤታቸዉ የሚሄዱት። ዛሬ የኢትዮጵያን ሰንደቅ አላማ ጨርቅ ነዉ ብለዉ የተሳደቡና በዚህ ሰንደቅ አላማ ከገበያ የገዙትን ሸቀጥ እየጠቀለሉ አስራ ሰባት አመት የከረሙ ምናምንቴዎች ናቸዉ በሰንደቅ አላማ ክብርና በአገር ፍቅር ታንጾ ያደገዉን ኢትዮጵያዊ ሰንደቅ አላማዉን አዋረደ እያሉ የአዞ እምባ የሚያነቡት።
ሰንደቅ አላማ በዜጎች ልብ ዉስጥ አንደ እሳት የሚቀጣጠል የአገር፤ የህዝብና የዜግነት መገለጫ የሆነ ታላቅ አርማ ነዉ። ይህ አርማ ደግሞ ከእኛነታችንና ከህልዉናችን ጋር የተጣበቀ አርማ ነዉና መንግስት በተለዋወጠ ቁጥር አይለዋወጥም። ዛሬ ወያኔ የኢትዮጵያን ሰንደቅ አላማ አስመልክቶ ከኢትዮጵያ ህዝብ ጋር የገባዉ የማይታረቅ ቅራኔም የሚመነጨዉ ከዚሁ ከወያኔ ግራ የተጋባ እዉነታ ነዉ። የዚህ ዘመን ትዉልድም ሆነ ለዚህ ዘመን ትዉልድ አገርና ሰንደቅ አላማ አስረክቦ ያለፈዉ የቀድሞዉ ትዉልድ ሰንደቅ አላማዬ ብሎ የሚጠራዉና ወያኔ የኢትዮጵያ ባንዲራ እያለ የሚጠራዉ ነገር የተለያዩ ናቸዉ።
ባለፉት 75 አመታት አራት ኪሎ ቤ/መንግስትን የተቆጣጠሩት ሦስት ኃይሎች ማለትም የቀኃስ፤ የደርግና የወያኔ አገዛዞች ሁሉም የኢትዮጵያን ሰንደቅ አላማ ከራሳቸዉ ጋር ለማያያዝ ሞክረዋል። በንጉሡና በደርግ ዘመነ መንግስት የኢትዮጵያ ሰንደቅ አላማ የይሁዳ አንበሳና የወታደራዊዉ መንግስት አርማ ነበረበት፤ ሆኖም እነዚህ ሁለት አርማዎች ያረፈበት የኢትዮጵያ ሰንደቅ አላማ በቤተመንግስትና ንጉሡና ፕሬዚዳንቱ በሚጓዙባቸዉ ኦቶሞቢሎች ላይ እንጂ ሌላ ቦታ አይታዩም ነበር። በመላዉ አገሪቱ በየቀኑ ጧት እየወጣ ማታ ሲመሽ የሚወርደዉና በየግለሰቦች ቤት የሚገኛዉ ሌጣዉ አረንጓዴ፤ ቢጫና ቀዩ ሰንደቅ አላማ ነበር። የኢትዮጵያ ህዝብም ሰንደቅ አላማዬ ነዉ ብሎ የሚያምነዉና የሚቀበለዉ ይህንኑ ምንም አይነት ባዕድ አካላ የሌለበትን አረንጓዴ፤ ቢጫና ቀይ ሰንደቅ አላማ ነዉ።
ወያኔዎች ጫካ ዉስጥ ሆነዉ የትጥቅ ትግል በሚያካሄዱበት ወቅት ያነገቡትና ነጻ አወጣን ባሉበት ቦታ ሁሉ የሰቀሉት የኢትዮጵያን ሰንደቅ አላማ ሳይሆን የህወሓትን ባንዲራ ነበር። ከብዙ መረጃዎች እንደተረዳነዉ ወያኔዎች የኢትዮጵያን ሰንደቅ አላማ አንደ ተራ ጨርቅ ቆጥረዉ ዕቃ መጠቅለያ አድርገዉት ነበር፤ ይህ ደግሞ የለየለት የጥላቻና የንቀት ምልክት ነዉ።
በአርግጥም ዋና ዋናዎቹ የወያኔ መሪዎች እነ ነመለስ ዜናዊና እነ ስብሐት ነጋ ኢትዮጵያንና የኢትዮጵያን ህዝብ ይጠሉ ስለነበር ለነሱ ትልቁ ቁም ነገር ህወሐትና የዘረኝነት ምልክት የሆነዉ የህወሓት ባንዲራ ነዉ እንጂ ኢትዮጵያና የኢትዮጵያ ሰንደቅ አላማ አልነበረም። ይህ ፀረ ህዝብና ፀረ አገር ባህሪያቸዉ ደግሞ ጫካ ዉስጥ ብቻ ተወስኖ የቆየ ባህሪ ሳይሆን አዲስ አበባ ገብተዉ ክህዝብ ጋር ሲቀላቀሉም በግልጽ የታየና ምን ግዜም ሊደበቅ የማይችል ባህሪይ ነዉ። የወያኔዉ ቁንጮ መለስ ዜናዊ እኛ ኢትዮጵያዉያን የምናከብዉንና የምንወደዉን ሰንደቅ አላማ “ጨርቅ” ብሎ መጥራቱ አዲስ የጀመረዉ ነገር ሳይሆን ከጫካ ይዞት የመጣዉ የተለመደ አባባል ነዉ። መለስ ዜናዊ ይህንን ጸያፍ ድፍረቱንና ፀረ ሰንደቅ አላማነቱን ለማረሳሳት የባንዲራ ቀን ብሎ ቢያዉጅም የኢትዮጵያ ህዝብ ግን ልጆቹ፤ አባቶቹ፤ አያቶቹና ቅድም አያቶቹ የተሰዉለት ሰንደቅ አላማ በአለባሌ ሰዉ አንደበት “ጨርቅ” ተብሎ የተጠራበትን ቀን ምን ግዜም አይረሳም።
ከቅርብ ግዜ ወዲህ የወያኔ ዘረኞች ኢትዮጵያዉያንን በተለይም በዉጭ አገሮች የሚኖሩ ኢትዮጵያዉያንን ባንዲራቸዉን አያከብሩም ወይም ባንዲራዉን አዋረዱ እያሉ መክስስ ጀምረዋል። በነገራችን ላይ ከወያኔዎችና ከጥቂት ሆዳም ተከታዮቻቸዉ ዉጭ የኢትዮጵያ ህዝብ አገር ዉስጥም በዉጭ አገሮችም በሰንደቅ አላማዉ ላይ ያለዉ አቋም ተመሳሳይ ነዉ። ወያኔ ሰንደቅ አላማዉ ላይ ባዕድ አካል ለጥፎ ከዛሬ ጀምሮ ሰንደቅ አላማችሁ ይህ ነዉ ብሎ አዋጅ ሲያወጣ አዋጁን የሰማለት አንድም ሰዉ አልነበረም። እንዲያዉም ህዘብ ሰላማዊ ሰልፍ ሲወጣ፤ ሰርግ ሲደግስ፤ ኳስ ጨዋታ ሲሄድና በተለያዪ ቦታዎች ደስታዉንና ኃዘኑን ሲገልጽ አንግቦ የሚወጣዉ የወያኔን ባንዲራ ሳይሆን አረንጓዴ፤ ቢጫና ቀዩን ሰንደቅ አላማ ነበር። ወያኔ የኢትዮጵያን ሰንደቅ አላማ የቀየረዉ በጠመንጃ ሀይል እንደሆነ ሁሉ የኢትዮጵያ ህዝብ ይህንን የማይወደዉንና በሀይል የተጫነበትን ባንዲራ ተቀብሎ እንዲኖር ያደረገዉም በጠመንጃ ሀይል ነዉ።
ለመሆኑ እነሱ እራሳቸዉ የለየላቸዉ የኢትዮጵያና የኢትዮጵያዊነት ጠላት የሆኑት የወያኔ መሪዎች በዉጭ አገሮች የሚኖሩና አክርረዉ የሚቃወሟቸዉን የኢትዮጵያ ልጆች ባንዲራዉን አዋረዱ እያሉ ተደጋጋሚ ክስ የሚያሰሙት ለምንድነዉ? አንዳንድ ከህልዉናቸዉ ይልቅ ለማይጠረቃዉ ሆዳቸዉ ያደሩ ደካማ ግለሰቦችስ ይህንን የወያኔ መሠረተ ቢስ ክስ እየሰሙ አንደ ገደል ማሚቶ ደግመዉ ደጋግመዉ የሚያስተጋቡት ለምንድነዉ? አገራችን ኢትዮጵያ ሁለት የተለያዩ ባንዲራዎች ሊኖራት እንደማይችል ሁላችንም እናዉቃለን። ለመሆኑ ይህ እኛ ሰንደቅ አላማ እነሱ ባንዲራ እያልን የምንጠራዉ ነገር አንድና ተመሳሳይ ነዉ? ወያኔና በየቦታዉ ያስቀመጣቸዉ የገደል ማሚቶዎች ከሁሉም ነገር አስቀድመዉ መመለስ ያለባቸዉ ይህንን ጥያቄ ነዉ። እኛ ኢትዮጵያዉያን ከህጻንነታችን ጀምሮ የኛ ነዉ እያልን ያሳደገንን፤ የመራንን፤ አቅጣጫ ያሳየንነና በተለይ በልጅነታችን ት/ቤት እያለን ጧት በክብር ሰቅለን ማታ ላይ በክብር እያወርድን በክብር እናስቀምጥ የነበረዉን አረንጓዴ፤ ቢጫና ቀይ ሰንደቅ አላማችንን ማክበርና መዉደድ ብቻ ሳይሆን ለዚህ ሰንደቅ አላማ ዘለዓለማዊነት አንድ ህይወታችንን እንሰጣለን። ሰንደቅ አላማዉን የማያከብር ህዝብ የለም፤ እኛም ኢትዮጵያዉያን ሰንደቅ አላማችንን እንወዳለን፤ እናከብራለንም፤ የምንወደዉና የምናከብረዉ ሰንደቅ አላማ ግን ባዕድ አካል የተለጠፈበትን የወያኔን ባንዲራ ሳይሆን የነፃነታችን፤ የእንድነታችን፤ የሰላማችንና የመዋዕትነታችን ምልክት የሆነዉን አረንጓዴ፤ ቢጫና ቀዩን ሰንደቅ አላማ ነዉ። ይህንን ሰንደቅ አላማ ደግሞ እኛ ኢትዮጵያዉያን ብቻ ሳንሆን ይህንን የጥቁር ህዝብ የነጻነትና የመስዋዕትነት ታሪክ ምልክት የሆነ ደማቅ ሰንደቅ አላማ አያሌ አፍሪካዉያንም ያከብሩታል። ለምሳሌ የስምንት የአፍሪካ አገሮች ባንዲራ አቀማመጡ ይለያያል አንጂ ቀለሙ አረንጓዴ፤ ቢጫና ቀይ ነዉ፤ ከዚህ በተጨማሪ የሌሎች 23 አፍሪካ አገሮች ባንዲራ ደግሞ ቀዩና አረንጓዴዉ ቀለም አለበት። ይህ ሁሉ የሚያሳየን ሰንደቅ አላማችን የፓን አፍሪካ ባንዲራ እየተባለ በተለያዩ የአፍሪካ አገሮችም የሚከበርና የብዙ አፍሪካ አገሮች ሰንደቅ አላማ መሰረት መሆኑን ነዉ።
የወያኔ ዘረኞች ኢትዮጵያ ዉስጥ የነበሩትንና በዉጭ አገሮች የሚገኙ አማራጭ የመረጃ ምንጮች ሁሉ ጥርቅም አድርገዉ ዘግተዉ እንደቤት ዉስጥ ዕቃቸዉ በሚቆጣጠሩት ቴሌቪዥን፤ ሬዲዮና ጋዜጣ “በሬ ወለደ” አይነት ዉሸታቸዉን ጧትና ማታ በተደጋጋሚ አየተናገሩ ለግዜዉም ቢሆን ህዝብን ማደናገር ይችሉ ይሆናል። ሰንደቅ አላማዉን የሚወደዉንና የሚያከብረዉን ኢትዮጵያዊም እነሱን ስለተቃወመ ብቻ ባንዲራዉን አዋረደ እያሉ ህዝብን ሊያታልሉ አንዳንድ ወደ ገባዎችንና ጥቂት የዋሆችን ሊያሳምኑ ይችሉ ይሆናል። ሆኖም የኢትዮጵያን ህዝብ እንወዳለን ፤ ለኢትዮጵያ አንድነት እንቆማለን፤ የዚህ አንድነት ምልክት የሆነዉን ሰንደቅ አላማም እናከብራለን አያሉ ታቦት ተሸክመዉ ቢምሉም የሚያምናቸዉ ቀርቶ ከጉዳይ ቆጥሮ የሚሰማቸዉ አንድም ዜጋ የለም። የወያኔ ዘረኞችና ቡችሎቻቸዉ የሚባቸዉ ቢሆን ኖሮ ዉስጣችን ያለዉን ከፍተኛ የአገር፤ የወገን፤ የባንዲራና የሉዓላዊነት ስሜት ደግመን ደጋግመን እንነግራቸዉ ነበር፡ ሀኖም እነሱን ከማስወገድ ጀምሮ አገራችንን እስከማረጋጋት ድረስ ብዙ አስቸኳይ የሆነ አገራዊ አደራና አገራዊ ስራ ይጠብቀናልና ለዛሬዉ እዚህ ላይ እናብቃ።
የኢትዮጵያ ህዝብ ትግል ያሸንፋል!

ሰበር ዜና – የቅ/ሲኖዶሱን ልዕልናና ሕገ ቤተ ክርስቲያንን መፃረራቸውን የቀጠሉት አቡነ ማትያስ ማኅበረ ቅዱሳንን ‹‹የቤተ ክርስቲያን ቅኝ ገዥ›› አሉት – ‹‹አባ ማትያስ አላበደም፤ በዚኽ መግለጫ እንድትሠሩበት ነው የምነግራችኹ›› ሲሉም በማኅበሩ ላይ የጥፋት መልእክታቸውን ዐዋጁበት!

November 16,2014
  • ጥቂት አማሳኞች በማንጨብጨብ ሲከተሏቸው፣ ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳቱን ጨምሮ ብዙኃን ጉባኤተኞች በድንጋጤና በተደምሞ አዳምጠዋቸዋል፡፡ ፓትርያርኩ በቀቢጸ ተስፋ ውስጥ እንዳሉም አመላካች ኾኗል፡፡
  • ማኅበረ ቅዱሳን÷ በጉባኤያት፣ በኅትመትና በኤሌክትሮኒክስ የስብከተ ወንጌል ስርጭት፣ በቅዱሳት መካናት ልማት፣ በአብነት ት/ቤቶችና በካህናት ማሠልጠኛዎች ድጎማና ሞያዊ እገዛዎች ያከናወናቸው ተግባራት በብፁዕ ጠቅላይ ሥራ አስኪያጁ ሪፖርት በስፋት ተዳስሰዋል፤ ጉባኤተኞች ማኅበሩ ላስመዘገባቸው የሥራ ፍሬዎች ደማቅ ድጋፋቸውን ገልጸዋል፡፡
his-hholiness00ዛሬ፣ ጥቅምት ፭ ቀን ፳፻፯ ዓ.ም. በጠቅላይ ቤተ ክህነት የስብሰባ አዳራሽ በተጀመረው ፴፫ኛው የመንበረ ፓትርያርክ አጠቃላይ ሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤ ዓመታዊ መደበኛ ስብሰባ ላይ የጉባኤ መክፈቻ ቃለ በረከት እንዲሰጡ የተጋበዙት ፓትርያርክ አባ ማትያስ፣ ማኅበረ ቅዱሳንን ‹‹የቤተ ክርስቲያን ቅኝ ገዥ›› በማለት ‹‹በቁጥጥር ሥር እንዲውል›› ቅስቀሳ እንዳካሔዱበት ተሰማ፡፡
ፓትርያርኩ የጉባኤ መክፈቻ ‹ቃለ በረከታቸው› ማሳረጊያ ላደረጉት ቅስቀሳ መሰል ንግግራቸው መግቢያ ያደረጉት፣ ‹‹ስለ ቤተ ክርስቲያን ወቅታዊ ኹኔታ ልገልጽ እፈልጋለኹ፤ ይህ ጉባኤ በዓመት አንዴ የሚገኝ ነው፤ ዕድሉ እንዲያመልጠኝ አልፈልግም፤›› በሚል ቃለ አጽንዖት ነበር፡፡
ከዚያም ‹‹ቤተ ክርስቲያናችን በቅኝ ገዥዎች ተይዛለች›› ካሉ በኋላ ‹‹ቅኝ ገዥው ማን ነው?››ሲሉ ጠይቁ፡፡ ምላሹን ራሳቸው ሲሰጡ፣ ‹‹ኹላችኁም የምታውቁት አንድ ማኅበር ነው›› ሲሉ ጠቆሙ፡፡ ‹‹በምን?›› ሲሉ ዳግመኛ ጠየቁና ‹‹በገንዘብ፤ በራስዋ ገንዘብ፤ ይኼን እንድታውቁ እፈልጋለኹ›› ሲሉ መለሱ፤ ‹‹እኔ ይኽን ጉዳይ ከራሴ አወርዳለኹ፤ የቤተ ክርስቲያናችን ገንዘቧ፣ ክብሯ ተወስዷል፤›› በማለትም አስረገጡ፡፡
በአምናው ዓመታዊ ስብሰባ፣ ‹‹ማኅበሩ በቁጥጥር ሥር እንዲውል›› አጠቃላይ ጉባኤው ውሳኔ አሳልፎ ነበር ያሉት ፓትርያርክ አባ ማትያስ፣ ‹‹ገንዘቡ፣ ንብረቱ በቁጥጥር ሥር እንዲውል የወሰናችኁት አንድም አልተፈጸመም፤ እነርሱም ፈቃደኛ አልኾኑም፤ ማን ጠይቆ?›› ሲሉ ኹኔታው ከአቅማቸው በላይ እንደኾነ ገልጸዋል፡፡
አስከትለውም ‹‹ቤተ ክርስቲያን ከቅኝ ተገዥነት ትውጣ፤ ካህናቱ ከመከራ ይውጡ›› በማለት መልእክታቸውን በማንኛውም ቦታ እንደሚያስተላልፉ ከተናገሩ በኋላ፣ በሓላፊነት የተቀመጡት ‹‹ይህችን ቤተ ክርስቲያን ለመጠበቅ፤ አንዷን ቅድስት፣ ኦርቶዶክሳዊትና ታሪካዊት ቤተ ክርስቲያን ልመራ እንጂ ኹለት ቤተ ክርስቲያን የለችም፤›› ብለዋል፡፡
በመጨረሻም ‹‹የቤተ ክርስቲያን ቅኝ ገዥ ነው፤›› ባሉት ማኅበረ ቅዱሳን ላይ የጥፋት መልእክታቸውን ያስተላለፉት በሚከተለው መልክ ነበር፡-
‹‹እኔ ብቻዬን የምሠራው ነገር የለም፤ በዚኽ መግለጫ እንድትሠሩበት ነው የምነግራችኹ፤ አባ ማትያስ አላበደም፤ መልእክቴን እያስተላለፍኹ ነው ያለኹት፤ መልእክቴን ተቀበሉ ብዬ እማፀናችኋለኹ፡፡››
የፓትርያርኩ አቋም ብዙም ያልተጠበቀ አልነበረም፡፡ ይኹንና የአዲስ አበባ ገዳማትና አድባራት አስተዳዳሪዎች ከተቀመጡበት አካባቢ ጥቂት አማሳኞች ቢያንጨበጭቡላቸውም በብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳቱና በጉባኤተኞች ላይ ሰፍኖ ይታይ በነበረው መደመምና ድንጋጤ የተዋጠ እንደነበር ተገልጧል፡፡ ‹‹የመልካም አስተዳደር አስተሳሰብን ማበልጸግ›› በሚል ሰበብ መስከረም ፳፯ ቀን በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት አዳራሽ፣ መስከረም ፳፱ ቀን በጠቅላይ ቤተ ክህነት አዳራሽ በማኅበረ ቅዱሳንና በቅዱስ ሲኖዶስ አባላት ላይ ከርእሱ በመውጣት በከፈቱት ዘመቻ፤ ብፁዕ ጠቅላይ ሥራ አስኪያጁንና ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳቱን ጨምሮ ከቤተ ክርስቲያናችን ከፍተኛ ሓላፊዎችና በብዙኃን መገናኛ አውታሮች ከተስተጋባው የብዙኃን አገልጋዮችና ምእመናን ብርቱ ተቃውሞ የተነሣ በቀቢጸ ተስፋ ውስጥ እንዳሉ አመላካች ተደርጎም ተወስዷል፡፡
የጉባኤተኞችን ቀልብና ስሜት ለመግዛት የተጠቀሙበት ቅስቀሳ ‹‹ከልጆቹ ጋራ እልክ መጋባታቸውን›› ያሳያል ያሉ አንዳንድ ተሳታፊዎች፣ አባ ማትያስ በፕትርክና በተሾሙበት ቀን አበ ብዙኃን ለመኾን ቃል የገቡበትን መሐላ በግላጭና በተደጋጋሚ ከመጣስ በላይ እብደት ባለመኖሩ በተጣለባቸው ታላቅ የቤተ ክርስቲያን ሓላፊነትና አባትነት ጉዳዩን በጥሞናና በተረጋጋ መንፈስ ሊመለከቱት እንደሚገባ ያሳስባሉ፡፡ የአጠቃላይ ጉባኤው መርሐ ግብር በመንበረ ፓትርያርክ ቅድስተ ቅዱሳን ማርያም ካህናት በጸሎተ ወንጌል ሲከፈት ፓትርያርኩ በንባብ ያሰሙት ቃልም‹‹ወንድምኽ ቢበድልኽ ምከረው፣ ይቅር በለው›› (ማቴ. ፲፰÷፲፭) የሚል ነበር – የማኅበረ አመራር ከፓትርያርኩ ጋራ የውይይት መርሐ ግብር እንዲያዝለት በተደጋጋሚ ባመለከተበት ኹኔታ ቀርቦ የተጠየቀበትና ምላሹ ተሰምቶ ጥፋተኝነቱ የተረጋገጠበት በደሉ ባይታወቅም!
MK on the 33rd gen assembly of Sebeka Gubae
(ፎቶ: ማኅበረ ቅዱሳን)
አባ ማትያስ የጠቀሱት ‹‹ገንዘብና የንብረት ቁጥጥር›› ጉዳይ በተመለከተ አጠቃላይ ጉባኤው ባለፈው ዓመታዊ ስብሰባው ያወጣው የጋራ ያአቋም መግለጫው፣ ‹‹እየተሠራበት ያለውን የገቢና የወጪ ሒሳብ በቤቱ የቁጥጥር አገልግሎት እያስመረመረ፣ በቤቱ ሞዴላሞዴሎች እየተገለገለ ማእከልንም በመጠበቅ አገልግሎቱን እንዲቀጥል›› ያስገነዘበበት ነበር፡፡
ማእከላዊነትን ጠብቆ ከማገልገል አንጻር፣ ማኅበሩ በ፲፱፻፺፬ ዓ.ም. ለሦስተኛ ጊዜ በቅዱስ ሲኖዶስ ተሻሽሎ በጸደቀለት መተዳደርያ ደንቡ መሠረት ከዋናው ማእከል አንሥቶ በየአህጉረ ስብከቱ በዘረጋው መዋቅሩ ከየአህጉረ ስብከቱ ሊቃነ ጳጳሳት ጋራ በመመካከርና መመሪያ በመቀበል የቤተ ክርስቲያንን ኹለንተናዊ አገልግሎት የሚደግፉ ተግባራትን እያከናወነ እንዳለ ገልጧል፡፡ በየጊዜው የአገልግሎት ዕቅዱን በማሳወቅ በየስድስት ወሩ የአገልግሎት የሥራ ዕቅድ አፈጻጸምና የሒሳብ ሪፖርት ለጠቅላይ ቤተ ክህነቱ ያቀርባል፤ ተገቢውን መመሪያም ከመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽ/ቤቱ ይቀበላል፡፡
የገቢና የወጪ ሒሳብ እንቅስቃሴውን ስለመቆጣጠርም፣ ሒሳቡን በየጊዜው በውስጥ ኦዲተር እያስመረመረ ቆይቶ በየዓመቱ ደግሞ ዓለም አቀፍ ዕውቅና ባለው ሕጋዊ የውጭ ኦዲተር አስመርምሮ ለሚመለከታቸው የቤተ ክህነት አካላት እያቀረበ የሚሰጠውን መመሪያ ተከትሎ አገልግሎቱን በማከናወን ፳፫ ዓመታትን ማስቆጠሩን ገልጧል፡፡
የጠቅላይ ቤተ ክህነቱ የቁጥጥር አገልግሎት የማኅበሩን የገቢና ወጪ እንቅስቃሴ መቆጣጠር በፈለገበት ጊዜ ኹሉ ማኅበሩ በውስጥ ይኹን በውጭ ኦዲተር ያስመረመረውን ሒሳብ ማየት አልያም በማንኛውም ጊዜ በራሱ ኦዲተሮች ወይም የውጭ ኦዲተሮች አወዳድሮ በመመደብ ማስመርመር እንደሚችል አበክሮ የገለጸው ማኅበረ ቅዱሳን፣ ስንኳን የራሱን የሒሳብ አያያዝ ቀርቶ የቤተ ክርስቲያናችን የሒሳብ አሠራር በሙሉ ዘመናዊና ለኦዲት የሚመች እንዲኾን የሚያግዝ ማኅበር መኾኑን አረጋግጧል፡፡
ይኹንና የማኅበሩ የሒሳብ አሠራር ዘመናዊና በሕግ ተቀባይነት ያለው የኹለትዮሽ የሒሳብ አመዘጋገብ ሥርዐት(double entry accounting system) የሚከተል በመኾኑ፤ እጅግ ኋላ ቀር፣ በዘመናዊ የሒሳብ መዝገብ አያያዝ ሥርዐትም ተቀባይነት እንደሌለው ቋሚ ሲኖዶስና የጠቅላይ ቤተ ክህነቱ ጽ/ቤት ሰሞኑን በቀረበላቸው የሦስት የበጀት ዓመታት የውጭ ኦዲት ምርመራ ሪፖርት አጋጣሚ ያመኑበትን የቤተ ክህነቱን የነጠላ የሒሳብ አመዘጋገብ ሥርዐት(single entry accounting system) ለመከተል እንደሚቸግረው በተደጋጋሚ አስተያየቱን አቅርቧል፡
በተመሳሳይ አኳኋን የጠቅላይ ቤተ ክህነቱ የገንዘብና ንብረት ገቢና ወጪ መመዝገቢያ ሰነዶች (ሞዴላሞዴሎች) ሥራ ላይ ማዋል የማኅበሩን የሒሳብ አሠራር ወደ ኋላ የሚጎትት እንደኾነ ነው የገለጸው፡፡ ማንኛውም ሕጋዊና ዘመናዊ የሒሳብ ምርመራ(ኦዲት) አሠራር በተለይም የውጭ ኦዲት የኹለትዮሽ የሒሳብ መዝገብ አያያዝ ሥርዐትን ተግባራዊነት በተሻሻለ ደረጃ የሚጠይቅ በመኾኑና በዚኽ የኦዲት ሥርዐት የቤተ ክህነቱ ሞዴላሞዴሎች ተቀባይነት እንደሌላቸው ሞያዊ አስተያየቱን ሰጥቷል፡፡
እስከ አኹን ባለው አሠራርና እውነታ ሞዴላሞዴሎቹን መጠቀም የቤተ ክርስቲያናችንን ገንዘብ፣ ሀብትና ንብረት ከብኩንነት፣ ከመዘረፍና ከመጭበርበር ማዳን እንዳልተቻለ ጥናታዊ ሪፖርቶች ያመለክታሉ፡፡ የሞዴላሞዴል አሠራር (የነጠላ የሒሳብ መዝገብ አያያዝ) ማንኛውንም ወጪ(ቋሚ ዕቃም ቢኾን) በወጪነት የሚመዘግብ እንጂ አንድ ተቋም ስላለው ሀብት በአግባቡ የሚያሳይ አይደለም፡፡ የፓትርያርኩንም ኾነ የቱኪና ጯኺ አማሳኞች የ‹‹ተቆጣጠሩት›› ዐዋጅ የሚረዳና ጥያቄያቸውን የሚመልስም አይደለም፡፡
በርግጥም ጥያቄው የማኅበሩን የገንዘብና ንብረት እንቅስቃሴ በአግባቡ ለመቆጣጠርና ተቋማዊ ለውጡን እንደ ጥርስና ከንፈር ተደጋግፎ የማራመድ ከኾነ፣ በማንኛውም የዘርፉን ሞያ በሚረዳ ወገን ዘንድ ተቀባይነት ያለው የመፍትሔ ሐሳብ በማኅበሩ ቀርቧል፡፡ ይኸውም ቁጥጥሩ፡-የማኅበር ሕገ ተፈጥሮን የተገነዘበ፣ ዓለም አቀፍ የፋይናንስ ሕግንና የቁጥጥር መርሕን የጠበቀ፣ ለቁጥጥር አመቺ የኾነና በሕግም ተቀባይነት ያላቸውን ዘመናዊ መንገዶች በመከተል ላይ ያተኩራል፡፡
ከማኅበር ሕገ ተፈጥሮ አኳያ፣ ማኅበረ ቅዱሳን ከቤተ ክህነት በሚመደብ በጀት እንደሚተዳደሩት መምሪያዎች ወይም ድርጅቶች ሳይኾን በበጎ ፈቃድ ክፍተቶችን ለመሙላት፣ አባቶችን በፍቅር ለመታዘዝና ለማገዝ የተሰባሰቡ አባላቱ ያቋቋሙት ራሱን የቻለ የቤተ ክርስቲያን አጋዥና ድጋፍ ሰጭ አካል በመኾኑ በአባላቱ መዋጮና በበጎ አድራጊዎች ርዳታ/ድጋፍ ነው የሚንቀሳቀሰው፡፡ የማኅበሩን ሒሳብ ሊያንቀሳቅስና ንብረቱን ሊያስተዳድር የሚችለው ጠቅላላ ጉባኤው የመረጠው የማኅበሩ አባልና አካል የኾነ ብቻ ነው፡፡
ተቆጣጣሪው አካል በዕለት ተዕለት የሥራ እንቅስቃሴው ውስጥ ከገባ ዓለም አቀፍ የቁጥጥር መርሕን ይጥሳል፡፡ ይኹንና ተቆጣጣሪው አካልቁጥጥሩን ሊያጠብቁለት የሚችሉ ሥርዐቶችን መዘርጋትና ተግባራቱን በአግባቡ መከታተል ብቻ የማኅበሩን አገልግሎት፣ የገንዘብና ንብረት እንቅስቃሴ ለመቆጣጠር ያስችለዋል፡፡
በአግባቡ ከተደራጀ ተቆጣጣሪ አካል የሚጠበቁት እኒኽ የሥርዐት ዝርጋታዎችና ክትትሎችም፡-
  • የኦዲት ሥራን ማሠራትና ከውጤቱ ተነሥቶ ተገቢውን አስተያየትና መመሪያ መስጠት፤
  • ዕቅዶችንና ሪፖርቶችን በመገምገም አስተያየት መስጠት፤
  • የገንዘብና ንብረት የገቢና የወጪ ሰነዶች ኅትመት በተቆጣጣሪነት መፍቀድ፤
  • የባንክ ሒሳብ እንዲከፈት ማኅበሩ ሲጠይቅ ለባንክ ማሳወቅ፤
  • የባንክ ፈራሚዎችን ስም ማኅበሩ ሲያቀርብ ለባንክ ማሳወቅ፤
  • በማኅበሩ ጠቅላላ ጉባኤያት ላይ እየተገኙ ሐሳብን መስጠት… የመሳሰሉት ናቸው፡፡
በማኅበሩ መተዳደርያ ደንብ መሠረት ማኅበሩ አገልግሎቱን የሚያቆመው፣ ትክክለኛነቱ በቅ/ሲኖዶስ በተረጋገጠ የጠቅላላ አባላቱ ውሳኔ አልያም በቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ ውሳኔ ሲኾን ያፈራው የማይንቀሳቀስ፣ ተንቀሳቃሽ የኾነና ጥሬ ገንዘብ በሙሉ ንብረትነቱና ሀብትነቱ ለኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን እንደኾነ ሰፍሯል፡፡ ማኅበሩ ከሚከተለው የሒሳብ አያያዝ ሥርዐት አኳያ የንብረት መሸጥና መለወጥ፣ ቱኪዎቹ እንደሚሉት ‹‹ማሸሽ›› ሳይኾን፤ በአጠቃላይ ንብረቱ ላይ የሚያመጣው ለውጥም የለም፤ የሚጨምረውና የሚቀንሰው ነገር በግልጽ በሚረዳ መንገድ በአሠራሩ የሚታይ ነውና፡፡፡፡
በአጠቃላይ የማኅበረ ቅዱሳን የማገልገል አቅም ከፍተኛ ደረጃ ላይ መድረሱ በቤተ ክርስቲያናችን ከፍተኛ አካል በታመነበትና የሚገኝበትን የዕድገት ደረጃ የሚመጥን፣ ለቤተ ክርስቲያን ኹለንተናዊ ዕድገት የሚጠቅም፣ የላቀና የተሻለ መንፈሳዊና ማኅበራዊ አገልግሎት ለማበርከት የሚያስችለው መዋቅራዊ አደረጃጀትና ምቹ ኹኔታ እንዲፈጠርለት እየተጠየቀ ባለበት ወቅት፣ የፓትርያርክ አባ ማትያስ ቅኝ ገዥ ነው፤ አጥፉትቅስቀሳ በእጅጉ አሳዛኝና በብርቱ ሊታሰብበት የሚያስፈልግ ነው፡፡
ደጉ ነገር! በዛሬው የአጠቃላይ ጉባኤው ዓመታዊ ስብሰባ በስፋት የተደመጠው የጠቅላይ ሥራ አስኪያጁ አጠቃላይ ሪፖርት፣ ይህን በአማሳኞች፣ ጎጠኞች፣ አድርብዬ ፖሊቲከኞችና የፕሮቴስታንታዊ ተሐድሶ ግንባር ቀደም መሪዎች ክፉ ምክር የተፈጠረ እልከኝነትና ምናልባትም የውጭ ኃይልን አጀንዳ በሌላ ገጽታ የሚገፋ የውክልና ጫና የወለደው ክሥ ከንቱ የሚያደርግ መኾኑ ነው፡፡
ጠቅላይ ሥራ አስኪያጁ በጥቅልና በዝርዝር ያቀረቧቸው የማኅበሩ የሥራ ፍሬዎች፣ አባ ማትያስ ማኅበሩን በቅኝ ገዥነት እንደወረፉት ሳይኾን፤ለታሪካዊት፣ ብሔራዊትና ሐዋርያዊት ቤተ ክርስቲያን ክብርና መብት መጠበቅ፤ ለትምህርተ ሃይማኖቷ፣ ሥርዐተ እምነቷና ክርስቲያናዊ ትውፊቷ ከትውልድ ወደ ትውልድ ሳይበረዝና ሳይከለስ መተላለፍ ትጉህ ዘኢይነውም ኾኖ ጥብቅና መቆሙን ነው፡፡
ከአጥቢያ ቤተ ክርስቲያን እስከ ልዩ ጽ/ቤት በተዘረጋው የአማሳኞች፣ ጎጠኞችና አድርብዬ ፖሊቲከኞች የሙስና ኤምፓየር የቤተ ክርስቲያንን‹‹ክብሯንና ገንዘቧን በቅኝ ገዥነት የወሰደ›› ሳይኾን፤ የሰበካ ጉባኤ ማደራጃ መምሪያ ሓላፊ ሊቀ ማእምራን ፋንታኹን ሙጬ የዘንድሮውን የአህጉረ ስብከት ውጤታማነት በገለጹበት ቋንቋ ‹‹የቤተ ክርስቲያናችን ምጣኔ ሀብት በዓለት ላይ የተመሠረተ ይኾን ዘንድ›› የአባላቱንና የበጎ አድራጊ ምእመናንን ጉልበት፣ ሞያና ገንዘብ አስተባብሮ ስኬታማ የልማት ሥራ የሠራ መኾኑን ነው፡፡
‹‹ካህናቱን ለጭቆናና ለመከራ ቀንበር የዳረገ›› ሳይኾን ከማንኛውም ክፍያ ነፃ በኾነና ያለስስት በልግስና በሚናኘው ሞያዊ አበርክቶው፣ ለተቀደሰው የክህነት ሞያቸው መከበርና ለኑሯቸው መመቻቸት የተጠበበና ከአማሳኞች፣ ጎጠኞችና ዐምባገነኖች ጋራ በየመድረኩ ፊት ለፊት የተሟገተ መኾኑን ነው፡፡
ፓትርያርኩም ኾነ መላው ኦርቶዶክሳዊ የሚጨነቅለት የኦርቶዶክሳውያን ቁጥር መቀነስ አሳስቦት፣ በንግግር ብዛት ሳይኾን በተግባር፣ ሚልዮኖችና መቶ ሺሕዎች የቃለ እግዚአብሔርን ማዕድ በሚቋደሱባቸው ሐዋርያዊ ጉዞዎችና በዘመናዊ ቴክኖሎጂ በታገዙ አውታሮች ስብከተ ወንጌልን ማስፋፋቱንና ማጠናከሩን ነው፡፡

Friday, November 14, 2014

ፌደራል ፖሊሶች ለሚፈጽሟቸው ግድያዎች ተጠያቂው ማን ነው?

November 14,2014
ከዳዊት ሰለሞን
dawitይህ ጥያቄ በቀጥታ በመንግስት ትዕዛዝ የተፈጸሙ ግድያዎችን አይመለከትም፡፡እንደውም በፓርላማ ከቀረበው ረቂቅ አዋጅ አንዱ ‹‹በግዳጅ ላይ ያለ የመንግስት ታጣቂ ለሚፈጽመው ጥፋት ተጠያቂ እንዳይሆን ››የሚሞግት ነው፡፡
ፓርላማው 446 ለ 1 የሚመራ በመሆኑም ገዢው ፓርቲ የፈለገውን አዋጅ የማውጣት መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡በዚህ ገጽ ግን ለማንሳት የወደድኩት ታጣቂዎች ከስራ ገበታቸው ውጪ እየፈጸሟቸው የሚገኙ ግድያዎች ሀላፊ ማን ይሆናል የሚለውን ነው፡፡
ንፋስ ስልክ አካባቢ የመንግስት የሰላም አስከባሪ አባል የነበረ አንድ መቶ አለቃ ጎረቤቶቹን በ35 የክላሽ ጥይት መግደሉና ህጻናቱን ያለ ወላጅ ማስቀረቱ አይዘነጋም፡፡
መቶ አለቃው ከታሰረ በኋላ በልዩ እንክብካቤ ተይዞ ወላጆቻቸውን ባጡ ህጻናት ላይ ይዘት እንደነበርና በኋላም አመለጠ ተባለ፡፡መቶ አለቃው መጨረሻ ላይ ስለመያዙ ተነገረ፡፡
ባህርዳር የተፈጸመውን አሰቃቂ ግድያ አንዘነጋውም፡፡አፍቅሪያታለሁ ያለ ፌደራል ፖሊስ የ18 ሰዎችን ህይወት ቀጥፎ ወንዝ ውስጥ ገብቶ ሞተ የሚል ወሬ ተናፈሰ፡፡
ቂርቆስ መንደር በምትገኝ የሴተኛ አዳሪዎች ሰፈር እንዲሁ የእኔ የሚላትን ሴተኛ አዳሪ ከሌላ ወንድ ጋር ተኝታ በማግኘቱ ፌደራሉ በሁለት ጥይት ደረቷን መትቶ ለህልፈት ዳረጋት ፣ከሴትየዋ ጋር የነበረው ጎልማሳም እግሩን በጥይት ለመቆረጥ በቅቷል፡፡
ይህ ፎቶ ግራፍም በተመሳሳይ መንገድ በፌደራል ፖሊስ ህይወቱን በግፍ ስለ ተነጠቀ ወጣት የሚጮህ ነው፡፡
ጅማን በእንባ፣በድንጋጤና በተቃውሞ የሞላ ክስተት የተስተናገደው በፌደራል ፖሊስ ነው፡፡በምሽት ሰው ቤት ሰብሮ የገባው ፖሊሱ አንዲት አይነ ስውር እናትና ልጃቸውን ቀጥፏል፡፡
ግለሰቡ ስለ መያዙም ተነግሯል፡፡ግን ይህ ነገር በገዳዮቹ መያዝ ብቻ የሚያበቃ መሆን የለበትም፡፡ተጠያቂነቱ ወደ ላይም መውጣት አለበት፡፡መሳሪያ መያዝ የማይገባቸው፣ሰብዓዊነት ምን ማለት እንደሆነ የማይረዱ፣ግደሉ ሲባሉ ከመግደል የማያመነቱ፣መሳሪያ ሲጨብጡ ጭንቅላታቸውን ቃታው ጋር የሚያደርጉ ሰዎችን መለዮ እያለበሱ ስልጣናቸውን ለማራዘም እስከጠቀሟቸው ድረስ ስለሚፈጽሙት ዘግናኝ ድርጊት ደንታ የሌላቸው አካላትም መጠየቅ ግድ ይላቸዋል፡፡
የሟቾቹ ደምም በተኳሾቹ ላይ ብቻ ሳይሆን ነፍጥ ባሸከሟቸው ሀይሎች ላይም ይጮሃል፡፡

የአዲስ አበባ ነዋሪዎች ፖሊስ ጣቢያዎችን እንዲሰሩ ተጠየቁ

November 14,2014
የአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪዎች በየ አካባቢያቸው ለሚሰሩት አዳዲስ ፖሊስ ጣቢያዎች ገንዘብ እንዲያዋጡ መጠየቃቸውን ለነገረ ኢትዮጵያ ገለጹ፡፡ በየ አካባቢው የሚገኙት የፖሊስ ጣቢያዎች ነዋሪዎች ገንዘብ እንዲያዋጡ በየ ቤታቸው ደብዳቤና የገንዘብ መክፈያ ቅጽ እየሰጡ ሲሆን ነዋሪዎቹ ገንዘብ እንዲከፍሉ የተጠየቁበትን ቅጽ ሳይሞሉ መመለስ አይችሉም ተብሏል፡፡

ደብዳቤው ላይ ባለው የፖሊስ ጣቢያው ስልክ ቁጥር ደውለን ያነጋገርናቸውና ስማቸውን ለመግለጽ ፈቃደኛ ያልሆኑ አንድ የፖሊስ አባል ‹‹ህዝቡን ለምን ፖሊስ ጣቢያ እንዲሰራ ታስገድዳላችሁ?›› በሚል ላነሳነላቸው ጥያቄ ‹‹ህዝቡኮ ራሱ ነው ሴት ልጆቻችን በሰላም መግባት አልቻሉም እያለ ያለው፡፡ ፖሊስ የህዝብ እስከሆነ ድረስ ህዝብ ፖሊስ ጣቢያ ቢያሰራ ምን ችግር አለው? ህዝቡ አልከፍልም ካለ ሊቀር ይችላል፡፡ እናንተ ግን ይህን እንደጥያቄ የምታነሱት ስብሰባው ላይ ስላልነበራችሁ ነው፡፡›› ብለውናል፡፡

ከወራት በፊት ‹‹ማህበረሰብ አቀፍ ፖሊስ›› በሚል አደረጃጀት ህዝቡ በየቤቱና ከጎረቤት ጋር 1ለ5 በመደራጀት ከፖሊስ ጋር ግንኙነት እንዲኖረው የሚያዝ ህግ መውጣቱና ነዋሪዎቹንም ማደራጀት መጀመሩን ነገረ ኢትዮጵያ መዘገቧ ይታወቃል፡፡


የሶዶ ከተማ ጎዳና ተዳዳሪዎች በግዳጅ ካምፕ እንዲገቡ ተደረገ

November 13,2014
ከህዳር 6/2007 ዓ.ም እስከ ህዳር 10/2007 ዓ.ም በሶዶ ከተማ የሚደረገውን የደኢህዴን ድርጅታዊ ጉባዔ አስመልክቶ ሶዶ ከተማ ውስጥ የሚገኙ ጎዳና ተዳዳሪዎች በግዳጅ ወደ ካምፕ እንዲገቡ መደረጋቸውን የነገረ ኢትዮጵያ ምንጮች ገለጹ፡፡ 

በመቶዎቹ የሚቆጠሩ ሴት፣ አዛውንትና ህጻናት ጎዳና ተዳዳሪዎች ሶዶ ውስጥ አራዳ ክፍለ ከተማ ተብሎ በሚጠራውና አዲስ እየተሰራ በሚገኘው ገለሜ የተባለ እስር ቤት ውስጥ በግዳጅ እንዲገቡ መደረጉን የነገረ ኢትዮጵያ ምንጮች ገልጸዋል፡፡ ካምፕ ውስጥ የገቡትን የጎዳና ተዳዳሪዎችም የቃለ ህይወት ቤተ ክርስቲያን ለሳምንት ቀለብ እንደሚያቀርብላቸውና ጉባዔው ካለቀ በኋላ ወደነበሩበት እንደሚመለሱም ምንጮቻችን አክለው ገልጸዋል፡፡

‹‹ለጉባኤው ሲባል ዜጎችን በግዳጅ ወደ ካምፕ ማስገባቱ ደኢህዴን በከተማዋ ልማት እንደተመዘገበና ህዝቡን ከድህነት እንዳላቀቀ ለማስመሰል ያደረገው አስነዋሪ ተግባር ነው›› ያሉት የሰማያዊ ፓርቲ የወላይታ ዞን የአደረጃጀት ኃላፊ አቶ ታደመ ፈቃዱ ‹‹እስካሁን ሶዶ ከተማ ውስጥ መብራት ስለማይኖር በርካቶች ተዘርፈዋል፡፡ የተገደሉም አሉ፡፡ የከተማዋ ውበትም እምብዛም የተጠበቀ አልነበረም፡፡ አሁን ግን ከተማዋን ለማጽዳት እየተሯሯጡ ነው፡፡ መብራት ባልነበረበት ከተማ መንገዱ ሁሉ ባውዛ ሆኗል›› ሲሉ ስለሁኔታው አስረድተዋል፡፡

ለደኢህአዴን ጉባዔ ተብሎ የከተማዋ ውበት እንዲጠበቅና የጠፉት አገልግሎቶች ለጊዜው እንዲስተካከሉ መደረጉም በህዝቡ ዘንድ መነጋገሪያ ሆኗል ተብሏል፡፡ ስለ ጉዳዩ ያነጋገርናቸው አንድ የከተማዋ ነዋሪም ‹‹ህዝቡ በአገልግሎቶች መጥፋት ተማሯል፡፡ የከተማው ውበት ለሚኒስትሮቹ እንጅ ለእኛ አይደለም፡፡ እንዲህ ከሆነ ደኢህዴን በየ15 ቀኑ ጉባዔ ቢያደርግ ጥሩ ነበር›› ሲሉ ስለሁኔታው ገልጸውልናል፡፡

ለጉባዔው ሲባልም በጸጥታ ስም በተቃዋሚዎች ላይ ክትትል እየተጠናከረ ይገኛል ያሉት አቶ ታደመ ‹‹ከተማዋ በፖሊስ ተጥለቅልቃለች፡፡ ፖሊሶች በየ 10 ሜትሩ ቆመው ነው የሚታዩት፡፡›› ብለዋል፡፡

Thursday, November 13, 2014

ጊዜው የሕዝባዊ እምቢተኝነት ነው!!!

November 13,2014
በአሁኑ ወቅት በአገራችን በከተሞችና በገጠሮች እየታዩ ያሉ ምልክቶችን በጥንቃቄ የመረመረ ማንኛውም ሰው የሚከተሉትን መታዘቡ አይቀርም።
በአንድ በኩል፣ ወያኔ የተወገደባት፣ ፍትህ የሰፈነባትና የበለፀገች ኢትዮጵያ እውን ሆና የማየት ተስፋችን እየለመለመ ነው። በዚህም ምክንያት ኢትዮጵያ ዉስጥ ለረጂም ዓመታት በሕዝብ ላይ ሰፍኖ የነበረው የፍርሀት ደመና እየገለጠ በመሆኑ ተዘግተው የቆዩ አንደበቶች መናገርና “ይኸ ሁሉ ግፍ ለምን?” ብለው መጠየቅ ጀምረዋል። ይህንን መነቃቃት በአስተሳሰብም፣ በተግባርም፣ በኪነጥበብም እያየነው ነው። የኢትዮጵያ ወጣቶች ለውጥ በአገራችን ሊመጣ እንደሚችል ከማመን አልፎ ራሳቸውን በለውጥ አምጭ ኃይልነት መመልከት ጀምረዋል። በርካታ ወጣቶች ወያኔን በትጥቅ ለመገዳደር የወሰኑ ወገኖቻችንን እየተቀላቀሉ በዚህም ምክንያት ጉልበታቸውን እያፈረጠሙ ነው። የለውጡ እርሾ ከሲቪሉ አልፎ በመከላከያ ሠራዊቱ እና በኢሕአዴግ ድርጅቶች ውስጥም እየተብሰለሰለ ነው። የኢትዮጵያ የመከላከያ ሠራዊት፣ ህወሓት ኢትዮጵያን ለማጥፋት የሚጠቀምበት ኃይል መሆኑ እያበቃ በአንፃሩ የትግሉ አጋር የሚሆንባቸው ሁኔታዎች እየታዩ ነው። በሁሉም የሠራዊቱ ክፍሎች ጉምጉምታው ወደ ጩኸት እየተቀየረ በመሆኑ ሠራዊቱ በአለቆቹ ላይ የሚነሳበት ጊዜ እሩቅ አይደለም። በተለያዩ ምክንያቶች ህወሓትን ወይም ህወሓት የፈጠራቸውን ድርጅቶች የተጠጉ በአጠቃላይ ኢሕአዴግ በሚባለው ስብስብ ውስጥ የሚገኙ ወገኖቻችንም “ለመሆኑ ማንን ነው እያገለገልን ያለነው?” ብለው በመጠየቅ ላይ ናቸው። በዚህም ምክንያት ወያኔ ውስጡ እየተረበሸ ነው። ከኢትዮጵያም ውጭ በሚገኘው ኢትዮጵያዊ ዘንድ ያለው ቁጣና ዝግጁነት ከወትሮው እጅግ የላቀ ነው። በአጭሩ፣ በሁሉም አቅጣጫ፣ ደረጃ በደረጃ የሕዝባዊ እምቢተኝነት እንቅስቃሴዎች ተጀምረዋል።
በአንፃሩ ደግሞ፣ የጨለማ ንጉሥ የሆነው ወያኔ፣ የኢትዮጵያ ሕዝብን ወደ ፍርሀት ቆፈን ለመመለስ እስሩን ከመቸውም በላይ ያጧጧፈበት ጊዜ ነው። በትግራይ፣ በአማራ፣ በኦሮሚያ፣ በደቡብ፣ በአፋር በሶማሊ … በመላው ኢትዮጵያ ብሩህ ራዕይ የሰነቁ ወጣቶችና አዛውንት ታድነው እየታሰሩ ናቸው። የወያኔ እስር ቤቶች በአርቆ አስተዋይ ዜጎቻችን ተሞልተዋል። ወትሮም ከፍተኛ የነበረው ስደት ብሶበታል፤ ለእውነት በጽናት የቆሙ ጋዜጠኞች ወይ ታስረው፣ አልያም ተሰደው አልቀዋል። የወያኔ የግዴታ ስልጠና አገሩን እያመሰው ነው። የኢትዮጵያዊያን ኑሮ በእጦቶች የታጀበ ሆኗል። የነፃነት እጦት፣ የፍትህ እጦት፣ የመብራት እጦት፣ የስኳር እጦት፣ የዘይት እጦት፣ የታክሲ እጦት፣ የመኖሪያ ቤት እጦት፣ እጦት፣ …. እጦት።
እነዚህ ሁለት ተፃራሪ እውነታዎች ሁለት ተፃራሪ ኃይሎች ለወሳኝ ፍልሚያ ፊት ለፊት መፋጠጣቸዉን በግልጽ ያሳያሉ። ዛሬ አገራችን ኢትዮጵያ ውስጥ ነፃነትና ባርነት፣ ፍትህና ጭቆና፣ ደስታና ሀዘን፣ ተስፋና ተስፋ መቁረጥ፣ ብልጽግናና ድህነት፣ እውቀትና ድንቁርና፣ ብርሃንና ጨለማ፣ ለወሳኝ ግጥሚያ ተፋጠዋል። ይህ ፍጥጫ የኢትዮጵያን የወደፊት እጣ ፈንታን በመወሰን ረገድ አቢይ ሚና የሚኖረው ወሳኙ ግጥሚያ – ሕዝባዊ እምቢተኝነት – መጀመሩን አብሳሪ ነው። የነፃነት፣ የፍትህ፣ የተስፋ፣ የብልጽግና፣ የእውቀትና የብርሃን ወገኖች ነን የምንል ኢትዮጵያዊያን ሁሉ ይህንን ፍልሚያ በድል መወጣት ግዴታችን ነው።
ወያኔ ታጋዮችን ቢያስር ትግሉን አያስርም። በእጦት ኑሮዓችን በማመሰቃቀል በድህነት ሊያንበረክከን ቢሻም፣ በፍጹም አንበረከክለትም። በተዘረፈ የድሆች ድካም ህንፃዎችን ቢገነቡም የራስ ባልሆነ ጌጥ አንኮራም። የወያኔ የሆነ የኛ አይደለም፤ የእነሱ መክበር የኛ መክበር አይደለም። ወያኔ እና የኢትዮጵያ ሕዝብ ገዢና ተገዢ፤ በዳይና ተበዳይ፣ ገፊና ተገፊ ናቸው።
ተበዳይና ተገፊ የሆነው የኢትዮጵያ ሕዝብ በዘረኞች፣ ሙሰኞችና ከፋፋዮች የህወሓት ባለሥልጣኖቻቸውና ሎሌዎቻቸው ላይ ይነሳሉ። የተጀመረው ሕዝባዊ እምቢተኝነት አመቺ በሆኑ መንገዶች ሁሉ ይጧጧፋል።
የወያኔ ትዕዛዛትን መሻር፤ በሥራ ላይ መለገም፤ ግብር አለመክፈል፤ አድማ መምታት፤ የወያኔ ካድሬዎችን ማግለልና ማዋረድ፤ የነፃነት ኃይሎችን መደገፍ፤ የፓሊስና የጦር ሠራዊት አባላትን ማቅረብ እና በተገኘው አጋጣሚ ሁሉ እነሱም የትግሉ አካል እንዲሆኑ ማበረታታት፤ ህሊና ያላቸው የኢሕአዴግ አባላት የሕዝቡን ትግል እንዲያግዙ ማበረታታት … – እነዚህንና እነዚህን የመሳሰሉ በርካታ የትግል ስልቶች ከአሁን ጀምሮ በተከታታይ በሥራ ላይ መዋል ይኖርባቸዋል። የወያኔን የጭቆና ምሽግ ከውስጥ መሸርሸር፤ ከውጭ መደርመስ ይኖርበታል። የመሸርሸርና የመደርመስ ሥራዎች ተደጋግፈው እንዲሄዱ ማድረግ ይገባል። ጊዜው የእምቢተኝነት ነው።
ግንቦት 7: የፍትህ፣ የዲሞክራሲና የነፃነት ንቅናቄ የኢትዮጵያ ሕዝብ አጠገቡ ባሉት መሪዎቹ አስተባባሪነት በአንድነት እንዲነሳ ጥሪ ያቀርባል፤ በመላው ዓለም ላይ የሚገኙ ኢትዮጵያዊያንም በኢትዮጵያ ውስጥ የሚደረገው ሁለገብ ትግል በጽናት እንዲደግፉ ያሳስባል። ይህንን ትግል በድል መወጣት ግዴታችን ነው፤ እንወጣዋለንም!
ድል ለኢትዮጵያ ሕዝብ!

Wednesday, November 12, 2014

የዞን 9 ጦማርያን እና ወዳጅ ጋዜጠኞች አስራአንደኛ የፍርድ ቤት ውሎ

November 12,2014
በዛሬው እለት በነሶልያና ሽመልስ የክስ መዝገብ 10 ተከሳሾቸን ጉዳይ ሊያይ የተሰየመው ችሎት በጦማርያኑ እና በጋዜጠኞቹ ላይ የቀረበውን ክስ አቃቤ ህግ አንዲያሻሽል ትእዛዝ ሰጥቷል፡፡
ባለፈው ሳምንት የክስ ፋይሉን አስመልክቶ የህግ እና የፍሬ ነገር ችግር አለበት በሚል የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ ያቀረቡትን የተከሳሾች ጠበቆች አንዲሁም መሻሻል የሚገባው ነገር የለውም ያለውን የአቃቤ ህግን መልስ ተከትሎ ብይን ለመስጠት ተቀጥሮ በዳኞች ለውጥ ተለዋጭ ቀጠሮ ተሰጥቶ የነበረው ችሎት ዛሬ ክሱ ላይ መሰረታዊ ማሻሻያ እንዲደረግ ብይን ሰጥቷል፡፡
ብይኑም በአጠቃላይ ሲታይ
1. በመጀመሪያው ክስ የጸረ ሽብር ህጉን አንቀጽ አራት በመጥቀስ በደፈናው የሽብር ስራ ተብሎ ቀርቦ ነበረውን ክስ አስመልክቶ ፍርድ ቤቱ ክሱ ፈጸሙትን ወይም ሊፈጽሙ ያሰቡትን የሽብር ተግባር በአንቀጽ ሶስት መሰረት አቃቤ ህግ በዝርዝር አንዲያስቀምጥ መቼ እና እንዴት አንደፈጸሙት ተግባሩም ምን እነደሆነ አንዲገለጽ
2. የሽብር ቡድን ፣ ግንቦት ሰባት አንዲሁም ኦነግ በማለት በተለያየ ቦታ የተጠቀሱ ስሞች ከመኖራቸው ባሻገር ግልጽ የሆነ ነገር ባለመኖሩ የተባለው የሽብር ቡድን ማን እነደሆነ በግልጽ አንዲቀመጥ ( አቃቤ ህግ በክሱ አንድም ቦታ ላይ ዞን 9 የሚል ቃል አለመጠቀሙን ያስታውሷል)
3. ስትራቴጂ እና ተልእኮ በመቀበል የሚለው ክስ ምን አይነት ስትራቴጂ እና ምን አይነት ተልእኮ ከማን ለእነማን ተከሳሾች አንደሆነ በግልጽ እንዲቀመጥ
4. የገንዘብ ድጋፍን አስመልክቶ ለሽብር ተግባር ተቀበሉት የተባለው ገንዘብ ከማን እነደተላከና ለምን ሽብር ተግባር አንደዋለ በዝርዝር አንዲገለጽ
5. የተከሳሾችን የስራ ክፍፍል አስልመልክቶ አቃቤ ህግ አቃቤ ህግ ለይቶ እነማን ምን የሽብር ስራ ክፍፍል አንደነበራቸው ለይቶ እንዲያቀርብ
6. ህገ መንግስቱን በሃይል መናድ የሚለው ክስ በአንደኛ ክስ ላይ ከተጠቀሱ ተግባራት ጋር ተመሳሳይ በመሆኑ ሙሉ ለሙሉ ውድቅ አንዲሆን እና ጉዳዩ በጸረ ሽብር ህጉ ብቻ አንዲታይ ብይን ሰጥቷል፡፡
በተመሳሳይ ፍርድ ቤቱ ሁለቱ ሴት ተከሳሾች ማህሌት ፋንታሁን እና ኤዶም ካሳዬን የማረሚያ ቤት አያያዝን አስመልክቶ ማረሚያ ቤት ሃላፌ ቀርበው መልስ አንዲሰጡ ባዘዘው መሰረት የማረሚያ ቤት ተወካይ መጥተው የእስረኞቹ አያያዝ እንደማንኛውም እስረኛ ነው ብለው የካዱ ሲሆን በተጨማሪም ማንኛውንም አይነት ችግር ካለ ከተከሳሾች ጋር በመነጋገር ለመፍታት ፍቃደኛ መሆኑን ገልጸዋል፡፡ ፍርድ ቤቱም የፍርድ ሂደቱን ላለማጓተት የተከሳሽ ጠበቆች ከማረሚያ ቤቱ ጋር አንዲነጋገሩ እና መፍትሄ ላይ እነዲደርሱ አንዲሁም ለውጥ ከሌላው ግን የተከሳሽ ቤተሰቦችን ምስክርነት ለመስማት የሚገደድ መሆኑን ገልጿል። አቃቤ ህግ ክሱን አሻሽሎ ተከሳሾች አንደተለመደው በሙሉ የስሜትና የአካል ደህንነት ላይ ሆነው ወዳጆቸን ሰላም ሲሉ እና እርስ በርሳቸው ሲወያዩ ተስተውለዋል፡።
ማስታወሻ - ዞን 9 የጦማርያን ቡድን ፍርድ ቤቱ የክስ ማሻሻል ትእዛዝ በበጎ ጎን የምንመለከተው ሲሆን የፍትህ ስርአቱ የሚታማበትን የተለመደውን ገለልተኛነት የማጣት ችግር አስወግዶ ጦማሪ ጓደኞቻችንን እና ወዳጅ ጋዜጠኞችን ከክሱ በነጻ በማሰናበት ታሪካዊ ሃላፌነቱን አንደሚወጣም ተስፋ አናደርጋለን፡፡ የዞን ዘጠኝ ጦማርያን ምንም አይነት የሽብር ተግባር ላይ ተሰማርተን የማናውቅ መሆኑን ክሱም ሃሳባችንን በነጻነት ከመግለጽ ተግባራችንን ጋር ተያያዘ መሆኑን አጥብቀን እንደምናምን እያስታወስን መንግሰት ክሱን ሙሉለሙሉ ውድቅ በማድረግ የጉዳዩን ፓለቲካዊ አለመሆን አንዲያረጋግጥልን ጥሪ እናስተላለፍለን ፡፡
አሁንም ስለሚያገባን እንጦምራለን!

Tuesday, November 11, 2014

ኢትዮጵያ በሰብዓዊ መብቶች ላይ የምትፈጽመውን ጥሰት ካላቆመች የአፍሪካ ህብረት መቀመጫውን ከአዲስ አበባ መቀየር አለበት ተባለ።

ImageNovember 11,2014

ኢትዮጵያ በሰብዓዊ መብቶች ላይ የምትፈጽመውን ጥሰት ካላቆመች የአፍሪካ ህብረት መቀመጫውን ከአዲስ አበባ መቀየር አለበት ተባለ። በደቡብ አፍሪካ ዊትስ ዩኒቨርሲቲ በተካሄደ የአፍሪካ የምርመራ ጋዜጠኝነት ጉባኤ ላይ አንጎላዊው ጋዜጠኛ ራፋኤል ማርኩዌዝ ደ ሞራይዝ የኢትዮጵያ መንግስት ያሰራቸውን ጋዜጠኞች መፍታት አለበት ብሏል።

ራፋኤል ማርኩዌዝ ደ ሞራይዝ አንጎላዊ ጋዜጠኛ ነው። በሙያው በሃገሩ አንጎላ በርካታ ክስ እና እስር እንደገጠመው ይነገራል። ባለፈው ወር በደቡብ አፍሪካ ዊትስ በተካሄደው የአፍሪካ የምርመራ ጋዜጠኝነት ጉባኤ ላይ ኢትዮጵያ ሃሳብን በነጻነት የመግለጽን ጨምሮ በሰብዓዊ መብቶች ላይ ጥሰት በመፈጸም ከአፍሪካ ህብረት ህልም በተቃራኒ ቆማለች በማለት ተችቷል። ''የአፍሪካ ህብረት መቀመጫ በቀዳሚነት የመላ አፍሪካውያንን ህልም ይወክላል። የሰው ልጅ ክብር እና የሰብዓዊ መብት ክብር ደግሞ የሁሉም አፍሪካውያን የጋራ ህልም ነው። ኢትዮጵያ በዚህ ረገድ የሰዎችን ሰብዓዊ መብት በመጣስ በተቃራኒው መንገድ እየተጓዘች ነው። ይህ ደግሞ የአፍሪካውያንን ህልም አይወክልም። የኢትዮጵያ መንግስት ያሰራቸውን ጋዜጠኞች በመፍታት ሃሳብን በነጻነት የመግለጽ ነጻነትን እንዲያከብር እና ዜጎች እና ጋዜጠኞች ህገ-መንግስታዊ መብታቸውን በተግባር እንዲያውሉ እንዲፈቅድ የአፍሪካ ህብረት ጫና ማድረግ ይኖርበታል። ''

ራፋኤል በጉባኤው የዞን ዘጠኝ ጦማሪዎችን እስር እና ክስ እንዲሁም የቀድሞው ፍትህ ጋዜጣ አዘጋጅ ተመስገን ደሳለኝን የሶስት አመት ብያኔ በማሳያነት አንስቷል። አፍሪካውያን ጋዜጠኞችና የሰብዓዊ መብት ተሟጋቾች በኢትዮጵያ ያለውን ሁኔታ በቸልታ አልፈዋል ሲልም ተችቷል። ኢትዮጵያ የሰብዓዊ መብትን ማክበር ካልቻለች የአፍሪካ ህብረት ከአዲስ አበባ መነሳት ይኖርበታል ብሎ ያምናል።

''የተወሰኑ ጋዜጠኞችን አውቃለሁ። በ2005 ተኩስ ሲጀመር እና ተቃዋሚ ፖለቲከኞች ሲታሰሩ በአዲስ አበባ ነበርኩ። አሁን በሃገሪቱ ስላለው ሁኔታ በቂ ግንዛቤ አለኝ። ከኢትዮጵያውያን ምሁራን እና አሁን ባለው መንግስት የተለያየ ጫና የደረሰባቸውን ሰዎች አገኛለሁ። የአፍሪካ ህብረትን ለመወከል በመጀመሪያ ሰብዓዊ መብትን የሚያከብር ሃገር እንፈልጋለን። ኢትዮጵያ ይህንን ማድረግ ካልቻለች እንደ አፍሪካዊነታችን የአፍሪካ ህብረት መቀመጫውን ዜጎች ራሳቸውን የመግለጽ እና ሰብዓዊ መብት ወደ ተከበረበት ሃገር እንዲዛወር መጠየቅ ይኖርብናል። ምክንያቱም ግለሰቦች የሚከበሩባት መንግስታት የህዝብ አገልጋይ እንጂ ከህግ በላይ ያልሆኑባት አጋርነት የጠነከረባት አፍሪካን እንሻለን። ኢትዮጵያ ደግሞ በአሁኑ ወቅት ይህን እያደረገች አይደለም። ''''

ድንበር የለሽ የጋዜጠኞች ቡድን ባለፈው ሳምንት ባወጣው ዘገባ ባለፈው አመት ብቻ በኢትዮጵያ ስድስት የህትመት ውጤቶች ሲዘጉ ከ ሰላሳ በላይ ጋዜጠኞች መሰደዳቸውን ይፋ አድርጓል። በምህጻሩ ሲፒጄ ተብሎ በሚጠራው የጋዜጠኞች መብት ተከራካሪ ተቋም መሰረት ደግሞ ቢያንስ 17 ጋዜጠኞች በኢትዮጵያ በእስር ላይ ይገኛሉ። ራፋኤል ማርኩዌዝ በእስር ላይ ያሉ ጋዜጠኞች እንዲፈቱ አፍሪካውያን ሊተባበሩ ይገባል ሲል ይናገራል።

''አፍሪካውያን በሙሉ በተለይም ጋዜጠኞችና የሰብዓዊ መብት ተሟጋቾች በትብብር ከሰራን የኢትዮጵያ መንግስት ቆም ብሎ ራሱን እንዲፈትሽ ማድረግ እንችላለን። አላማችን ኢትዮጵያን ማግለል አይደለም። አላማችን ኢትዮጵያ ጋዜጠኞችን እንድታከብር ሃሳባቸውን በነጻነት የመግለጽ መብታቸውን በመጠቀማቸው የታሰሩትንም እንድትፈታ ነው።''

 source http://www.dw.de/%E1%8A%A2%E1%89%B5%E1% ... a-18051929

ግልጽ ደብዳቤ ”ለጠቅላይ ሚኒስትር” ኃይለማርያም ደሳለኝ : ከታሳሪ ዞን9 ጦማርያን እና ጋዜጠኞች

November 10,2014
ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ሕገ መንግስታችንን ያክብሩ!
ሠላም ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር!? እንዴት ነዎት? ያስታውሱ ከሆነ የዛሬ ሁለት ዓመት አካባቢከፊሉ የዚህ ማስታወሻ ፀሃፊዎች  ‘ግልፅ ደብዳቤ ለጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማሪያም ደሳለኝ’
“ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር እባክዎትን የተለያዩ የመንግስት አካላት የሕገ መንግስታችንን ድንጋጌዎች እየጣሱ ነውና እርስዎም በሕገ መንግስቱ አንቀፅ 74/13/ መሠረት ሕገ መንስቱን የማስከበርና የማክበር ግዴታ ስላለብዎት ሕገ መንግስቱን ያክብሩ” በማለት አንዲት አጭር ደብዳቤ ፅፈንልዎት ነበር፡፡
zone9ድንገት በተለያዩ ምክንያቶች የጻፍንልዎትን ደብዳቤ ካላነበቡት ወይም ማስታወስ ካልቻሉ ዛሬ ይሄን ማስታወሻ ስለምንፅፍልዎት ግለሰቦች አንድ ሌላ ማስታወሻ እንስጥዎ፡ ከ6ወራት በፊት /በሚያዚያ 2006 ዓ.ም/ ሶስት  ጋዜጠኞችንና ስድስት ጦማሪያንን ‘ሕገ መንግስቱንና ሕገ መንግስታዊ ስርዓቱን በኃይል ለመናድ በመሞከር ወንጀል ጠርጥሬያችኋለሁ’ በማለት መንግስትዎ ልማታዊ ርምጃ (አብዮታዊ ርምጃ እንደሚባለው) ወስዶ ነበር፡፡
እኛም የዚህ ማስታወሻ ፀሃፊዎች የዚህ ‘ልማታዊ ርምጃ’ ሰለባ የሆንን ግለሰቦች ነን፡፡በርግጥ ከሁለት ዓመታት በፊት ‘ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ሕገ መንግስቱን’ ያስከብሩልን በማለት ጥያቄ ያቀረብንልዎት ግለሰቦች ‘ከ6 ወራትበፊት ሕገ መንግስቱን ለመናድ  ሞክራችኋል’ በማለት መንግስትዎ ሲያስረን ሕገ መንግስቱ እንዲከበር ጠይቀን ሕገ መንግስቱን ለመናድ በመሞከር ወንጀል ተጠርጥረን ስንታሰር እስሩ በጣም ግራ አጋብቶን ነበር፡፡በዚህ ያልቆመው መንግስትዎ ክሱን ‘ሕብረተሰቡንና ሀገሪቱን ለማሸበር አቅዳችኋል ሞክራችኋል አሲራችኋል…’ በማለት ወደ ‘ሽብርተኝነት’ያሳደገው ሲሆን እርስዎም ከዚህ ጋር በተያያዘ ሃሳብዎትን ሲሰጡ ስለተመለከትንዎ ትንሽ ቅሬታ ይዘን መጣን፡፡
በቅድሚያ አሁን ያለንበትን ሁኔታ በትንሹ ብናስረዳዎት ቅሬታችንን ለመረዳት ያስችልዎታልና አንዳንድ ጉዳዮችን እንንገርዎት፡፡
ይሄን ማስታወሻ በምንፅፍልዎት ወቅት ከታሰርን ከ 200 ቀናት የተቆጠሩ ሲሆን፣ነገር ግንጉዳያችን ገና በቅድመ ክስ (Pre Trial) የክርክር ሂደት ላይ ይገኛል፡፡ ይሄ የሆነበት ዋነኛ ምክንያትም መንግስትዎ እንኳን ለእኛ ለተከሳሾች ለከሳሽ አካልም ግልፅ ያልሆነ ክስ በማቅረቡ ነው፡፡ ይሄንንም ስንል ልትፈፅሙት ነበር የተባለው ‘የሽብርተኝነት ድርጊት’ ሳይጠቀስ ‘በቃ የሽብርተኝነት ድርጊት ልትፈፅሙ ነበር’ በማለት በጨበጣ ስለመጣብን ነው፡፡
ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር እንግዲህ የብዙ ድብደባ፣ ዛቻ እና ስድብ ሰለባዎች ከሆንን በኋላምየቀረበው ይሄ  ክስ ነው ከ6 ወራት በኋላም ተከሳሾች ከሳሾቻችንምሳንረዳው በየቀጠሮው እየታሸ ነው የሚገኘው፡፡ ‘የተፋጠነ ፍትህ’ ሕገ መንግስትዊ መብት ነውና የተፋጠነ ፍትህ ይሰጠን፣ እርስዎምይሄን ሕገ መንግስታዊ መብት ያክብሩ እያልንዎት አይደለም ‘ሕገ መንግስቱ ተከብሮ እያለ ሕገ መንግስቱ ይከበር በማለቴ ጥፋተኛ ነኝ’በማለት ‘ጥፋት የሚያሳምን’ ( አንዱ የዚህ ደብዳቤ ጸሃፌ ጦማሪ ጥፋት ብሎ አንዲፈርም የተገደደው ህገ መንግስቱ ተከብሮ እያለህገመንግስቱ ይከበር ማለቴ ጥፋት ነው ብሎ መሆኑ መንግስትዎን መልክ ግልጽ አድርጎ ያሳያል) መንግስት አለዎትና ይህ ጥያቄ አንደሚበዛብዎትእናውቃለን፡፡
ይልቁንም ቀላልና ግልፅ ቅሬታን ነው ይዘን የመጣነው፡፡ ይሄውም የኢፌድሪ ሕገ መንግስትበአንቀፅ 20/3/ ላይ
‘የተከሠሡ ሰዎች[…]  በፍርድ ሂደት ባሉበት ጊዜ በተከሰሱበት ወንጀል እንደ ጥፋተኛ ያለመቆጠር[…]መብት አላቸው::’
በማለት የደነገገ ሲሆን፣ ይሄንን ሕገ መንግስታዊ መብትም ማንኛውም የመንግስት አካል እንዲሁም ግለሰብ የማክበር ግዴታ አለበት፡፡
ክቡር ጠቅላይ ሚኒስቴር እርስዎና መንግስትዎም በተደጋጋሚ ‘ሕገ መንግስቱ ሳይሸራረፍ እናስከብራለን’ ይላሉና ይሄን ሕገ መንግስታዊ ድንጋጌ የምታውቁት ይመስለናል፡፡ ነገር ግን ከታሰርን ወዲህ ስለእኛ የእስር ጉዳይ በተጠየቁባቸውጊዜያት ይሄን ሕገ መንግስታዊ ድንጋጌ በመጣስ ‘ፍርድዎትን’ በተደጋጋሚ ሲሰጡ ታዝበናል፡፡ እናስረዳዎ፡- ሐምሌ 12/2006 ዓ.ም በሰጡት ጋዜጣሚ መግለጫ ላይ ስለእኛ እስር ጉዳይ ለቀረበልዎት ጥያቄ ሲመልሱ፡-

‘ከአስመራ እስከ ሞቃዲሾ የተዘረጋው የሽብር ሰንሰለት ውስጥ አንዴከገቡ በኋላ ብሎገር ነኝ፣ ጋዜጠኛ ነኝ ማለት ዋጋ የለውም’
በማለት ብዙ ነገሮችን ተናገሩ፡፡ ይሔውልዎት ስህተትዎ፡-
1.     የክሳችን ዋነኛ ጭብጥ በሃገርውስጥ ‘የሽብርተኛ ድርጅት በማቋቋም ‘የሽብርተኝነት’ ተግባራትን ለመፈጸም አሲረዋል፡ አቅደዋል… የሚል እንጂ፣ እርስዎም እንደሚሉት ‘ሰንሰለት’ ምናምን አይደለም፣
2.    እሺ አሸባሪዎችም ይበሉን፣ነገር ግን ሕገ መንግስቱ እንደሚደነግገው በፍርድ ቤት ‘ጥፋተኝነታችን’ እስሚረጋገጥ ቢጠብቁስ ምናለበት? ይህ የሚያመለክተው እርስዎም እንደ ማእከላዊ መርማሪዎች ነፃ ሆኖ የመገመት (presumption of innocence) መብታችንን እያከበሩልን እንዳይደለ ነው፡፡
ይሄ ነገር የሆነው በድንገት ሊሆን ይችላል ብለንዝም ብንልም እርስዎ ግን በድጋሚ ጥቅምት 6/2007 ዓ.ም በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ቀርበው ከምክር ቤቱ አባል ለቀረበልዎ ጥያቄሲመልሱ፡-

“የብሎገር ጭምብልአጥልቆና በጋዜጠኝነት ሙያ ውስጥ ተሸሽጎ ከተከሳሽነት ማምለጥ አይቻልም፡፡ ሽብርተኝነትን መዋጋታችን ይቀጥላል…” እያሉ እርስዎ ያሉትን የብሎገር ጭምብል አውልቀውና ተሸሸጉበት ያሉትን የጋዜጠኝነት ሙያመሸሸጊያ አፍርሰው ባንዴ ‘የአሸባሪነት’ ካባ ደረቡልን፡፡
ክቡር ጥቅላይ ሚኒስቴር፣ እያልን ያለነው የአንድ ሰው ‘አሸባሪነት/ወንጀለኝነት’ የሚረጋገጠው በፍርድ ቤት እንደሆነ ሕገ መንግስቱ ደንግጎ እያለ፣ እርስዎ ግን ነፃ ሆኖ የመገመት መብታችን ወደ ጎን ብለው እንደ ከሳሽም እንደፈራጅም በመሆን ‘አሸባሪዎች’… እያሉን ይገኛሉ ነው፡፡
ምናልባት ‘ስራ አስፈጻሚው ከሳሽ ነውና እኔም የስራ አስፈጻሚው አካል መሪ ስለሆንኩ የፈለኩትን አስተያየት የመስጠት መብት አለኝ’ ብለው ከሆነ፣ ሕገ መንግስቱን የማክበር ጉዳይ ‘ርስዎን ጨምሮ ሁሉም ዜጎች ላይ የተጣለ ግዴታነው፡፡ እርስዎ ‘L’e’tat, c’est moi’ ይሉት አይነት የራስ ግምት ውስጥዎ ከሌለ በስተቀር እንዲህ በግልፅ እየጠየቅንዎት ‘ሕገ መንግስትቱን  አላከብርም’ በማለት ገና ዋነኛ ክርክሩ እንኳንያ ልተጀመረ ክስን (ዋነኛ ክርክር ካለው) መሠረት በማድረግ ከዚህ በኋላ እኛን ‘አሸባሪዎች’ አይሉንም ብለን ተስፋ እናደርጋለን፡፡ይህን ተመሳሳይ ምላሽ “በእርግጠኝነት አሸባሪ ናቸው” በሚል ቃና ለቢቢሲ ለኢንቢሲ ለመሳሰሉት አለም አቀፍ ሚዲያ  ተቋማትም መስጠትዎን ሰምተናል፡፡
ሌላው ልናስታውስዎ የምንፈልገው ጉዳይ እንደኛ አይነት የተራገበ( በሰፊው በታወቀ የአደባባይ)የፍርድ ጉዳይ ([un] popular case) ላይ የመንግስት አካላት አስተያየት (say) ያለውን ተፅእኖ እንዲያስቡት ነው፡፡እርስዎ በምክር ቤት ቀርበው የአሸባሪነት ፍርድ ከበየኑብን (አሁን እያደረጉት እንዳሉት) ፍርድ ቤትም ሆነ ሌሎች የመንግስትዎ አካላትምን ሊያስቡ እንደሚችሉ አስተውለውታልን?!
ይሄን ሁሉ ስንልዎ እንዲያው ሕጉን ያክብሩልን ለማለት ያክል ነው እንጅ፣ ከሽብርተኝነትጋር የሚያገናኘን ቅንጣት ያክል እውነት /A segment of fact/ እንደሌለና የሰው ልጆች መልካምና ደስተኛ ሕይወት እንዲኖራቸውከመመኘትና ለአገራችን ያገባናል ከማለት ያለፈ ሕይወትም ፍላጎትም እንደሌለን እኛም እናውቀዋለን እርስዎና መንግስትዎም ያውቁታል፡፡ነገር ግን ካለፉት ስድስት ወራት አንስቶ ጨዋታውን በግድ ካልተጫወታችሁ ተብለናልና እየተጫወትን ነው፡፡ የአሁኑ ጥያቄያችን ግን በጣም ቀላል ነው፣ ጨዋታው ገና በደንብ እንኳን ሳይጀመር ውጤቱን እይወስኑት ነው፡፡
እርስዎ ወደ ጠቅላይ ሚኒስትርነት የስልጣን ደረጃ በወጡ ሰሞን አብዛኞች የዚህ ማስታወሻፀሃፊዎች መጠነኛ ለውጥና ማሻሻዎች ያደርጋሉ የሚል ተስፋ ሰንቀን “The First 100 Days” ወዘተ እያልን ብዙ ጠብቀንዎት ነበር፡፡ ከሁለት ዓመት በሚበልጥ ግዜ እንደተመለከትንዎ ግን ተስፋችን ፍሬ ሊያፈራልን አልቻለም፡፡ አሁንም አዲስ ተስፋ ሰንቀን ግን ፡-“ክቡር ጠቅላይ ሚኒስቴር እባክዎትን ሕገ መንግስቱን ያክብሩ! የእኛንም መብት ያክብሩልን” እንላለን፡፡

‘’የብሎገር ካልሲ አድርጎ፣ የጋዜጠኝነት ጫማ ተጫምቶ የሽብረተኝነት ሰንሰለት ውስጥ ከገቡ በኋላ ሕገ መንግስቱን ያክብሩልኝ ማለት ዋጋ የለውም!’’በማለት ተስፋችን ዋጋ እንደማያሳጡት ተስፋ አለን፡፡

ከአክብሮት ጋር

 ጦማርያን                    ጋዜጠኞች
ዘላለም ክብረት                 ኤዶም ካሳዬ
ናትናኤል ፈለቀ                ተስፋለው ወ/የስ
በፍቃዱ ሃይሉ                አስማማው ኃ/ጊዮርጊስ
አጥናፍ ብርሃኔ
አቤል ዋበላ
ማህሌት ፋንታሁን

ታላቁ ረኃብ፡ ህወሀት አሁንም ቢሆን ለመስረቅ እና ለመዝረፍ ፈቃድ አለው ከፕሮፌሰር አለማየሁ ገብረማርያም

November 10,2014
ትርጉም በነጻነት ለሀገሬ
TPLF Cash.. 1984 የተከሰተውየኢትዮጵያ ታላቁ ረኃብ ሲታወስ፡ክፍል 2
ባለፈው ሳምንት ባቀረብኩት ትችቴ (እ.ኤ.አ በ1984 የተከሰተው የኢትዮጵያ ታላቁ ረኃብ ሲታወስ፡ ክፍል1)፣ ላለፉት በርካታ ዓመታት ረኃብን በማስመልከት ሳቀርባቸው በነበሩት ትችቶች የህዝባዊ ወያኔ ሀርነት ትግራይ እና አሁን በህይወት የሌለው መሪው መለስ ዜናዊ እ.ኤ.አ ከ1991 ጀምሮ በኢትዮጵያ ውስጥ ምንም ዓይነት ረኃብ የለም በማለት ሙልጭ አድርገው በመካድ ሲያደርጉት የነበረውን ተራ ቅጥፈት በማጋለጥ በተጨባጭ መረጃዎች ላይ በመመስረት ስሞግት የቆየሁባቸውን ዋና ዋና ጭብጦች በማካተት ክለሳ ማድረጌ ይታወሳል፡፡ መለስ እና ጓደኞቹ ከዓለም አቀፍ ለጋሾች እና አበዳሪ ድርጅቶች ጋር በመሞዳሞድ ለረኃብ ስያሜ የተለያዩ የማስመሰያ እና የማደናገሪያ ስሞችን በመስጠት በኢትዮጵያ የተለያዩ ክፍሎች ከሁለት አስርት ዓመታት በላይ ተንሰራፍቶ ህዝብን ሲፈጅ እና ሲያሰቃይ የቆየውን ረኃብ በመደበቅ በሀገሪቱ ውስጥ በየትኛውም ቦታ ቢሆን እንደሌለ አድርገው በረኃብ ሲሰቃዩ በቆዩት እና በረኃቡ ምክንያት ባለቁት ወገኖቻችን ላይ ሸፍጥ ሲሰሩ ቆይተዋል፡፡ ለዚህም አጽንኦ በመስጠት በኢትዮጵያ ያለው ረኃብ የፈለገውን ያህል በማስመሰያ እና በማደናገሪያ ቃላት እና ሀረጎች ተሸፋፍኖ እና ታጅቦ ቢቀርብም ያው አሁንም ቢሆን ረኃብ ነው! በማለት ማጠቃለያ መስጠቴ የሚታወስ ነው፡፡
በዚህ በክፍል ሁለት ትችቴ ደግሞ እ.ኤ.አ ከ1984 – 85 ድረስ ህወሀት በተከሰተው በታላቁ ረኃብ ምክንያት የረኃብ ሰለባ ለሆኑት ወገኖች ነብስ ማዳኛ ለሰብአዊ እርዳታ የመጣውን እርዳታ ለጦር መሳሪያ ግዥ እና ለግል ጥቅም ለማዋል ሲያደርገው የነበረውን የዥዋዥዌ ጨዋታ ለመዳሰስ ሞክሪያለሁ፡፡ በመጀመሪያ ጊዜ እ.ኤ.አ ሜይ 2011 በሁፊንግተን ፖስት “ለመስረቅ ፈቃድ ማግኘት” በሚል ርዕስ ባቀረብኩት የመጀመሪያ ትችት ህወሀት የሰረቀ መሆኑን ከሁለት የቀድሞ የህወሀት የአመራር አባላት ጋር የተደረገን ቃለ መጠይቅ ዋቢ በማድረግ ለሰብአዊ እርዳታ ተብሎ የመጣን የእርዳታ እህል ከታለመለት ዓላማ ውጭ ህወሀት ለመሳሪያ መግዣ እና ለሌላ ለግል ጥቅሙ ያዋለ መሆኑን በማጋለጥ ትችት አቅርቤ ነበር፡፡ ይህ ቡድን እ.ኤ.አ በ1984 ጫካ በነበረበት ጊዜ የጀመረው የዓለም አቀፍ የእርዳታ ስርቆት፣ ዘረፋ እና ሙስና የማይላቀቁት መናጢ አመል ሆኖበት አሁንም እስካለንበት ጊዜ እስከ 2014 ድረስ በተለያየ እና በተወሳሰበ መልኩ ቀጥሎ ይገኛል፡፡
“አሊ ባባ”፣ መለስ እና 40 የህወሀት/ማረት (TPLF/REST) የ1984- 85 የእርዳታ እህል እና ዶላር ሌቦች እና ዘራፊዎች፣
እ.ኤ.አ በ1984 – 85 በሰሜን ኢትዮጵያ ተከስቶ በነበረው አስከፊ እና አሰቃቂ ረኃብ ምክንያት የረኃቡ ሰለባ ለሆኑ ህዝቦች በሚል ከዓለም አቀፉ ህብረተሰብ ሩብ ሚሊዮን ዶላር ተሰብስቦ ነበር፡፡ ያ ረኃብ እጅግ በጣም አስከፊ ገጽታ ያለው እና ባልተጠበቀ መልኩ የተከሰተ ነበር፡፡ እ.ኤ.አ በ1984 የትግራይን አካባቢ የጎበኘው የቢቢሲው ጋዜጠኛ ሚካኤል ቡርክ የረኃቡን አስከፊነት እንደሚከተለው ገልጾት ነበር፣ “የ20ኛው ክፍለ ዘመን የመጽሐፍ ቅዱስ ረኃብ“ እና “በመሬት ላይ ለሲኦል የቀረበ ነገር“፡፡
እ.ኤ.አ በ1984 – 85 በአማጺያን ኃይሎች እንቅስቃሴ እና በደርግ ወታደራዊ አምባገነን መንግስት የአውሮፕላን ድብደባ ምክንያት በትግራይ ክልል እና በሌሎች የሰሜን ኢትዮጵያ የተለያዩ አካባቢዎች የአስቸኳይ ጊዜ እርዳታን በተለመደው የእርዳታ አሰጣጥ ሁኔታ ማቅረብ እጅግ በጣም አስቸጋሪ ነበር፡፡ በርካታ የዓለም አቀፍ መንግስታዊ ያልሆኑ ለጋሽ ድርጅቶች እርዳታውን አማጺያን ቡድኖች በተቆጣጠሯቸው አካባቢዎች በአስከፊው ረኃብ የጥቃት ሰለባ ለሆኑት ወገኖች ፈጣን በሆነ መልኩ የህይወት አድን እርዳታውን ለማድረስ ሌሎች ተለዋጭ መንገዶችን እና ዘዴዎችን ማግኘት ነበረባቸው፡፡
እንደ አማራጭ በመውሰድ በርካታዎቹ መንግስታዊ ያልሆኑ እርዳታ ሰጭ ድርጅቶች ለረኃብ ጥቃት ሰለባ ለሆኑ ወገኖች በቀላሉ ምግብ ማድረስ እንዲቻል በማሰብ በምስራቃዊ የሱዳን ጠረፍ በትግራይ ወሰን አካባቢ የማከፋፈያ ጣቢያ ከፈቱ፡፡ በሱዳን ወሰን አካባቢ በርካታ መንግስታዊ ያልሆኑ እርዳታ ሰጭ ድርጅቶች በብዛት መከማቸት እና ገንዘብ በማዋጣት እረገድ ይደረጉ በነበሩት የህዝብ ግንኙነት ጥረቶች ምክንያት ለህወሀት አመራሮች እና ለአማጺያኑ ወታደሮቻቸው ትርፋማ የሆነ የንግድ አጋጣሚ ፈጠረላቸው፡፡ አማጺያኑ እነርሱ በተቆጣጠሯቸው አካባቢዎች ጥሩ የእርዳታ ማስተላለፊያ መንገዶች እንዳሉ በማሳወቅ እና የእርዳታ እህሉንም ሆነ ሌላ ማንኛውንም ዓይነት ቁሳቁስ እነርሱ ማከፋፈል ቢችሉ ስራው የተሳካ እንደሚሆን እና ለዘለቄታው ውጤታማ እንደሚሆኑ መንግስታዊ ላልሆኑ ለጋሽ ድርጅቶች ሀሳብ አቀረቡ፡፡
የቀድሞው የህወሀት የገንዘብ ግምጃ ቤት ኃላፊ የነበሩት እንደ ገብረመድህን አርአያ እና የአማጺያኑ መስራች የነበሩት እንደ ዶ/ር አረጋዊ በርሄ ገለጻ ከሆነ የህወሀት ቁልፍ መሪዎች መለስ ዜናዊን ጨምሮ በዓለም አቀፍ የረኃብ እርዳታ ሰጭ ድርጅቶች አማካይነት በረኃቡ ሰለባ ለሆኑት ተብሎ የተመደበውን በሚሊዮን ዶላር የሚቆጠር የእርዳታ እህል የማጭበርበሪያ ስልት ነድፈው ከተያዘለት ዓላማ ውጭ ለጦር መሳሪያ መግዣ እና ለግል ጥቅማቸው አዋሉ፡፡ ገብረ መድህን እና አረጋዊ ግልጽ እንዳደረጉት መለስ እና ቁንጮ ካድሬዎቹ አንድ የማጭበርበሪያ ዕቅድ በመንደፍ የሰብአዊ እርዳታ የሚያቀርብ ድርጅት በሚል ማህበረ ረዲኤት ትግራይ/ማረት (Relief Society of Tigray/REST) ተብሎ የሚጠራ የማስመሰያ እርዳታ ሰጭ ድርጅት አቋቋሙ፡፡ ውስጡ ለቄስ ነው እና በአንድ ወቅት አሁን በህይወት የሌለው መለስ ዜናዊ እንዳለው የዚህ ድርጅት ልብ እንደ ፈጣን ሎተሪ ተፍቆ ቢታይ እንደ ስሙ እርዳታ ሰጭ ድርጅት እንዲሁም ለሰው ልጆች ክብር በፍቅር ተቃጥሎ ህይወትን ለማዳን ከልቡ የሚሰራ ርህራሄን የተላበሰ እውነተኛ ሰብአዊ ድርጅት ሳይሆን ሌባ፣ ዘራፊ እና በቅጥፈት የተሞላ የማፊያ ድርጅት ሆኖ ይገኛል፡፡ በዚያን ወቅት የህወሀት አመራሮች ማረት ከህወሀት ወታደራዊ ክንፍ ጋር ፈጽሞ ግንኙነት የሌለው እና የተለዬ ሀቀኛ የእርዳታ ሰጭ/አከፋፋይ ለጋሽ ድርጅት እንደሆነ በማስመሰል የተለያዩ ዓለም አቀፋዊ የእርዳታ ሰጭ ድርጅቶችን ለማሳመን ሌት ከቀን ጥረት አደረጉ፡፡ እውነታው እንደሚያሳየው በእርግጥ ማረት እና ህወሀት የአንድ ሳንቲም ሁለት ገጽታዎች ናቸው፡፡
በአሁኑ ጊዜ በስደት በውጭ ሀገር የሚኖሩት ዶ/ር አረጋዊ በርሄ የህወሀትን የረቀቀ የእርዳታ ማጭበርበር ባህሪ ለቢቢሲ ጋዜጠኛ ለማርቲን ፕላውት እንዲህ በማለት ገልጸው ነበር፣
“… አንዳንድ ጊዜ የእርዳታን ገንዘብ እንደ ሁለተኛ አማራጭ በመውሰድ የጦር መሳሪያ እንገዛበት ነበር፡፡ ገንዘቡ ካለህ መካከለኛው ምስራቅ በመምጣት መሳሪያ መግዛት ትችላለህ፡፡ ስለሆነም የተወሰነውን ገንዘብ ለመሳሪያ ግዥ በማዋል እንጠቀምበት ነበር፡፡ ይህንን ማረት እየተባለ በአህጽሮ ቃል የሚጠራውን ድርጅት ታውቀዋለህ፣ ሲተነተን ማህበረ ረድኤት ትግራይ ማለት ነው፡፡ የህወሀት የሰብአዊ እርዳታ ክንፍ ነው፣ እና በማረት ስም የእርዳታ ገንዘብ ወደ ህወሀት ይመጣ ነበር፡፡ ከዚያ ይህንን የእርዳታ ገንዘብ ካገኘህ በኋላ ለእርዳታ፣ ለጦር ግንባር ወይም ደግሞ ለጦር መሳሪያ ግዥ፣ ለመድኃኒት፣ ወዘተ በሚል በጀት ታዘጋጃለህ፡፡ የእርዳታን ገንዘብ ትግሉን ለማስቀጠል እንጠቀምበት ነበር ለማለት እችላለሁ፡፡
ከዚህም በላይ በብዙ ሚሊዮን ስለሚቆጠር ዶላር ጉዳይ እንነጋገር ነበር፡፡ ለዚህ አንድ ተጨባጭነት ያለው ምሳሌ ልነግርህ እችላለሁ፡፡ እ.ኤ.አ በ1985 ትግራይ አሰቃቂ በሆነ ረኃብ በተጠቃች ጊዜ የእርዳታ ገንዘብ በማረት በኩል አድርጎ ወደ ህወሀት ይጎርፍ ነበር፡፡ ስለሆነም ከሞላ ጎደል አንድ ዓይነት ዓላማ ያላቸው እና ምንም ዓይነት ልዩነት የሌላቸው ማርክሲስት ሌኒኒስት ሊግ ትግራይ/ ማሌሊት/Marxist Leninist League of Tigrai (MLLT) እና የህወሀት አመራሮች 100 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር ለተለያዩ ተግባራት እንዲውል መመደብ ነበረባቸው፡፡ በዚህም መሰረት መለስ ዜናዊ ከዚህ ገንዘብ ውስጥ 50 በመቶ የሚሆነው ለህወሀት እንቅስቃሴዎች፣ 45 በመቶ የሚሆነው ለማሌሊት ማደራጃ እና 5 በመቶ የሚሆነው ብቻ በረኃብ ሰለባ ለወደቁት ተረጅዎች መዋል አለበት የሚል ሀሳብ አቅርቦ እንደነበር አስታውሳለሁ…እነዚህን ሁለት ሰዎች (አርዓያ ገብረመድህን እና ተክለወይነ አሰፋ) አውቃቸዋለሁ፡፡ የህወሀት ተዋጊዎች ናቸው፡፡ አንዱ እራሱን ነጋዴ በማስመሰል ይቀርባል፡፡ ሁለተኛው ደግሞ ከነጋዴው ማሽላ የሚገዛ በመምሰል ይቀርባል፡፡ ሁለቱም የህወሀት ነባር ካድሬዎች ናቸው፣ እናም ነጋዴ ለመምሰል ትወና በመተወን ላይ ናቸው፡፡ እነዚህ ሁሉ ነገሮች የሚተወኑት ገንዘቡን ለማግኘት ሲባል ነው፡፡ [በፎቶግራፉ ላይ ከላይ የሚታዩት የመንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች ተወካይ የነበረው ፔርቤዲ ከመካከል ሆኖ የታሰረ ረብጣ ብር ለተወካይ ተብዬዎች ሲያስታቅፍ ነበር] እናም ይህ ዜጋ መቶ በመቶ ተታሏል፡፡”
ገብረ መድህን የዓረጋዊንን ሀሳብ ትክክለኛነት አረጋግጠዋል፡፡ ገብረ መድህን (ከላይ በስዕሉ ላይ በስተግራ በኩል ሆነው ገንዘብ ሲቆጥሩ የሚታዩት) እራሳቸው በግንባር በመቅረብ በመቶዎች እና በሺዎች የሚቆጠር ዶላር ለመለስ ዜናዊ እና እንደ እባብ ተስለክላኪው እና የህወሀት የክርስትና አባት ለሆነው ለስብሀት ነጋ በወቅቱ በእጃቸው ያስረከቡ መሆናቸውን ገልጸዋል፡፡ ሁለቱ የህወሀት አድራጊ ፈጣሪዎች መለስ እና ስብሀት የህወሀትን የገንዘብ ፍሰት ይቆጣጠሩ ነበር፡፡ ገብረመድህን የህወሀት ዋና የገንዘብ ኃላፊ ሹም የነበረ ቢሆንም መንግስታዊ ካልሆኑ ድርጅቶች በእርዳታ ስም የሚመጣውን ገንዘብ ለመለስ እና ለስብሀት ካስረከበ በኋላ ስለገንዘቡ አወጣጥ እና ከጥቅም ላይ እንዴት ሆኖ እንደሚውል እንዲያውቅ አይደረግም ነበር፡፡ ያም ሆነ ይህ ገብረመድህን ገንዘቡ በትክክል ለታለመለት ዓላማ ጉዳይ ስለመዋሉ እና አለመዋሉ ጥርጣሬ ነበረው፡፡ ሆኖም ግን የጥፋተኝነት ማስረጃው (ሁለቱን የህወሀት ካድሬዎች እና ማክስ ፔርቤዲ የተባለውን ከእንግሊዝ መንግስታዊ ያልሆኑ የእርዳታ ሰጭ ድርጅቶች መካከል ታላቅ ከሆነው የክርስቲያን እርዳታ/Christian Aid ተብሎ ከሚጠራው ተወካይ እጅ እየቆጠሩ በመረከብ በወለሉ ላይ በትልቅ ቦርሳ ውስጥ በርካታ ገንዘብ ሲያጭቁ የሚያሳየው ፎቶግራፍ) በምንም ዓይነት መልኩ ማስተባበያ ሊቀርብበት የማይችል አስደንጋጭ ነገር ነው፡፡
የችግሩን ስፋት እና ጥልቀት እንዲሁም የረኃቡን አስከፊነት እና አሳሳቢነት መንግስታዊ ላልሆኑት እርዳታ ሰጭ ድርጅቶች በውሸት በትወና መልክ ለማሳየት ሲባል የህወሀት አመራሮች እጅግ ብዛት ያለውን የረኃብ ሰለባ ህዝብ ከትግራይ ወደ ሱዳን በማምጣት በኢትዮ-ሱዳን ሰሜናዊ የድንበር አካባቢዎች ላይ በአንድ ጀንበር ምሽት እንደ አሸን የፈሉ የእርዳታ መስጫ ጣቢያዎችን በማዘጋጀት የተረጅዎችን ቁጥር ከመጠን በላይ አበዙት፡፡ የተለያዩ ዘዴዎችን እና ስልቶችን በመጠቀም የህወሀት አመራሮች መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች በትግራይ ውስጥ በረኃብ ለተጠቃው ህዝብ የእርዳታ እጃቸውን እንዲሰነዝሩ ለማስቻል ዝርዝር የሆነ የገበያ ተውኔት በማዘጋጀት ለመድረክ እይታ አበቁ፡፡ ይህ የተደረገው ለእነርሱ በጣም ታማኝ የሆኑ የድርጅቱን ጥቂት የውስጥ አባላት በመምረጥ እና በማደራጀት የእህል ነጋዴ ሆነው እንዲቀርቡ እና መንግስታዊ ካልሆኑ ድርጅቶች እርዳታ የማሰባሰብ ንግድን ማጧጧፍ ነበር፡፡
መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶችን የማታለሉ ጨዋታዎች ወይም ደግሞ የበለጠ ግልጽ ለማድረግ የምዕራቡን ዓለም መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች የረኃብ እርዳታ የማታለል ዕቅድ የተለያዩ መገለጫዎችን ያካተተ ነበር፡፡ በማጭበርበሩ የመጀመሪያ ደረጃ ላይ የህወሀት አመራሮች ሶስት ደረጃዎችን ያካተተ ሂደትን ተጠቅመዋል፡፡ በመጀመሪያው ደረጃ አንድ የህወሀት/ማረት የባለስልጣኖች ቡድን ህጋዊ የእህል ነጋዴዎች በመምሰል በርካታ መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶችን ይቀርባሉ፣ እናም በረኃብ ለተጠቃው ህዝብ እርዳታ በፍጥነት እንዲደርስ በርካታ ብዛት ያለው እህል እንዲሸጥላቸው ይጠይቃሉ፡፡ በዚያን ጊዜ የህወሀት አታላዮች በመቶዎች የሚቆጠሩ ከባድ የጭነት ማምላለሻ መኪናዎች ያገኙ እና በጣም ሚስጥራዊ በሆነ መልኩ ከመሬት ውስጥ በተዘጋጀ ሰፊ ማጠራቀሚያ ከተለያዩ ምንጮች ያገኗቸውን የእርዳታ እህሎች መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶችን ጨምሮ ለእራሳቸው ተዋጊዎች መጠቀሚያ በሚል ያጭቁታል፡፡ እነዚህ በከባድ ሚስጥር ከመሬት ውስጥ ታጭቀው የሚገኙ የእህል ቁልሎች በእርግጠኝነት ዓላማው መንግስታዊ ላልሆኑ ድርጅቶች ለመሸጥ ነው፡፡ የህወሀት/ማረት እህል አዳዮች መንግስታዊ ካልሆኑ ድርጅቶች ጋር እህልን ለመሸጥ ይደራደራሉ፣ ከዚያም ሽያጩን ያጠናቅቁ እና ከሽያጩ ያገኙትን በርካታ ገንዘብ ተሸክመው እህሉን ወደ ደበቁበት ቦታ ይመለሳሉ፡፡ ገብረመድህን እራሳቸው በዚህ እህል የመግዛት እና የመሸጥ ትወና ላይ የእህል ማደል ቀጥተኛ ተሳታፊ ነበሩ፡፡ ከዚህ አንጻር የእርሳቸውን ሚና እንዲህ በማለት በግልጽ አስቀምተውታል፣
የሙስሊም ነጋዴ እንድመስል የሙስልም ልብሶች እንድለብስ ይሰጡኝ ነበር፡፡ መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች እኔን አያውቁኝም ምክንያቱም የእኔ ስም መሀመድ ነበር፡፡ ይኸ ስም የመቀየር የማጭበርበር ስራ የተደረገው መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶችን ለማታለል በህወሀት የበላይ አመራሮች የተዘየደ የማጭበርበሪያ ስልት ነበር፡፡ መንግስታዊ ካልሆኑ ድርጅቶች በርካታ የሆነ ገንዘብ እቀበል ነበር፣ እናም የተቀበልኩት ገንዘብ ወዲያውኑ በህወሀት መሪዎች ይወሰድ ነበር፡፡ ከወሰዱት ገንዘብ ውስጥ በርካታውን የህወሀት አመራሮች በግል የሂሳብ ቁጥራቸው በምዕራብ አውሮፓ ባንኮች ያስቀምጡ ነበር፡፡ ከዚህ ገንዘብ ጥቂቱ ደግሞ ለመሳሪያ መግዣ ያውሉት ነበር፡፡ የአስከፊው ረኃብ የጥቃት ሰለባ የሆነው ተረጅው ህዝብ ግማሽ ኪሎ ግራም ያህል በቆሎ እንኳ አያገኝም ነበር፡፡ አንድ ጊዜ የእህል መግዛቱ ስራ ከተከናወነ በኋላ ሌላው የህወሀት/ማረት ቡድን ደግሞ የተገኘውን የእርዳታ እህል በትግራይ ውስጥ በተለያዩ ቦታዎች በመሄድ የማከፋፈሉን ስራ ይሰራል፡፡
በሁለተኛው ደረጃ የተዋቀረው የህወሀት/ማረት ባለስልጣኖች በሚስጥር ከመሬት ውስጥ ያከማቹትን የእህል ክምችት ድንገተኛ ፍተሻ በማድረግ ስራውን ያቀላጥፋሉ፡፡ ሆኖም ግን የእህል ማስቀመጫ መጋዘኑ በሌላ ማሳሳቻ ነገር ተሞልቶ ይቀመጣል፡፡ ገብረመድህን እንዲህ ብለው ነበር፣ “እዚያ ብትሄድ ግማሽ የሚሆነው የመጋዘኑ የእህል መያዣ ጆንያ በአሸዋ ተሞልቶ ነው የሚገኘው“ ገብረመድህን እንዳሉት ከሆነ የመንግስታዊ ያልሆኑ የእርዳታ ሰጭ ድርጅቶች ተወካይ ወደ መጋዘኑ ከመጣ በኋላ በችኮላ እና በዓይን ውጫዊ የገረፍ ገረፍ እይታ ብቻ በመመልከት የእራሱን መተማመኛ ይሰጣል፣ ከዚያም ክፍያ ፈጽሞ ወደ ሱዳን ተመልሶ በመሄድ ሌላ ተጨማሪ እህል ለመግዛት ዝግጅቱን ያደርጋል፡፡
በሶስተኛ ደረጃ የተመደበው አንድ ዓይነት ወይም ደግሞ ሌላ የህወሀት/ማረት ቡድን ወደ መንግስታዊ ያልሆኑ እርዳታ ሰጭ ድርጅቶች ይሄድ እና ወደተለያዩ የትግራይ አካባቢዎች በመውሰድ ለህዝቡ ማደል እንድንችል ሌላ ተጨማሪ እህል እንዲሸጥልን በማለት ሌላ የውሸት ማታለያ መጫወቻ ሜዳ በማዘጋጀት ጥያቄውን ለእርዳታ ሰጭ ደርጅቶቹ ያቀርባል፡፡ በዚህን ጊዜ ከእርዳታ ሰጭ ድርጅቶች የተገኘው አዲስ የእርዳታ እህል ወደተባለው ህዝብ እንዲሄድ አይደረግም፡፡ ይልቁንም ከመሬት ውስጥ ባለው መጋዘን ውስጥ ታጭቆ የሚገኘው እህል ወደ ሌሎች የትግራይ የተለያዩ ክፍሎች እንዲሄድ በማድረግ መንግስታዊ ላልሆኑት የእርዳታ ሰጭ ድርጅቶች ግን አዲሱ እና ከዚያ ተገዝቶ እንዲሰጥ የተባለውን እህል ያሰራጩ እና ያከፋፈሉ በማስመሰል የማታለል ስራቸውን በስፋት ይቀጥላሉ፡፡ የእርዳታ ሰጭ ድርጅቶች ነጻ በሆነ መልኩ የተሰጠው እርዳታ ወደ እርዳታ ፈላጊው ህዝብ ሄዶ በትክክል መከፋፈሉን የሚያረጋግጡበት ምንም ዓይነት መንገድ ስለሌላቸው ከአንድ ቦታ ወደ ሌላ ቦታ ለሚጓጓዘው  ተመሳሳይ የማደናገሪያ እህል ሁሉ ይከፍላሉ፡፡ በዚያ መልኩ የረቀቀ የማታለል ዘዴን በመጠቀም ህወሀት/ማረት ቀደም ሲል የነበራቸውን የእህል እና የአሸዋ ክምችት ብዙ ጊዜ መንግስታዊ ላልሆኑ ድርጅቶች ደጋግመው በመሸጥ በሚሊዮኖች የሚቆጠር ዶላር በገቢነት ይሰበስባሉ፡፡
ማርቲን ፕላውት ከቢቢሲ በሰሜን ኢትዮጵያ እ.ኤ.አ በ1970ዎቹ ተከስቶ የነበረውን ረኃብ እ.ኤ.አ ማርች 2010 ባወጣው ዘገባው እ.ኤ.አ በ1985 የሲአይኤ መረጃ ያወጣውን ዋቢ በማድረግ እንዲህ የሚል መደምደሚያ ሰጥቶ ነበር፣ “ለተራቡት ወገኖች እርዳታ በሚል የሽምቅ ተዋጊዎች የሚያሰባስቡትን እርዳታ ዓለም በስፋት እያወቀው ሲመጣ እና የእርዳታው መጠንም እየጨመረ ሲመጣ ለእርዳታው ተብሎ የሚመጣው ሁሉ ሙሉ በሙሉ በሚባል መልኩ ለጦር መሳሪያ መግዣ ይውል ጀመር፡፡“ በ1980ዎቹ መጨረሻ አካባቢ ሮበርት ሁደክ የተባሉ በኢትዮጵያ የዩኤስ አሜሪካ ነባር ዲፕሎማት የህወሀት አባላት በዚያን ወቅት ለእርዳታ የሚሰጣቸውን እህል ለመሳሪያ መግዣ ያውሉ ነበር በማለት የተናገሩትን ቢቢሲ እንዳለ ቃላቸውን ወስዶ እንዲህ በማለት ዘግቦ ነበር፡፡ “አንድ ማክስ ፔቤርዲ የሚባል የእርዳታ ሰራተኛ በግንባር በመገኘት ለህወሀት/ማረት ባለስልጣኖች 500,000 ዶላር በኢትዮጵያ ገንዘብ ተቀይሮ እህል እንዲገዙበት በእጃቸው የሰጣቸው መሆኑን ተናግሯል“ በማለት ገልጸው ነበር፡፡
ገብረመድህን በጽሁፋቸው በዝርዝር ግልጽ እንዳደረጉት እ.ኤ.አ በ1984 – 85 ተከስቶ የነበረውን ታላቁን ረኃብ ሰበብ በማድረግ ህወሀት አብዛኛውን እርዳታ ለመሳሪያ መግዣ እና ለአመራሩ አባላት የግል ጥቅም አውለውታል የሚለው የመጀመሪያ ማስረጃ አሳማኝ ይመስላል (የገብረመድህንን ክፍል አንድ የአማርኛ ጽሁፍ እዚህ ጋ ይጫኑ፡፡ ለክፍል ሁለት ደግሞ እዚህ ይጫኑ)
የህወሀት የእርዳታ ስርቆት እና እርዳታውን ለሌላ ዓላማ ማዋል የሚለውን ፕሮፌሰር ሀሰን ሰይድ “መንግስታዊ ጥቃት በኢትዮጵያ፡ ሰብአዊ እርዳታ እና ሙስና“ (መነበብ ያለበት ጽሁፍ) በሚል ርዕስ ባዘጋጁት ዝርዝር እና ጥልቀት ባለው ጥናታዊ ጽሁፋቸው ውስጥ እንዲህ የሚል ማጠቃለያ ሰጥተዋል፣ “በጥናቴ ውስጥ የመረመርኳቸው ሰነዶች እና ያደርግኋቸው ቃለ መጠይቆች እንዲሁም የሰበሰብኳቸው የምስክርነት ማስረጃዎች እንደሚያረጋግጡት ለጋሽ እና እርዳታ ሰጭ ድርጅቶች ማህበረ ረድኤት ትግራይ/ማረት ከህወሀት ጋር የአንድ ሳንቲም ሁለት ገጽታዎች መሆናቸውን እንደሚያውቁ የሚጠቁሙ መሆናቸው፣ እንደዚሁም ደግሞ የህወሀት እና የእርዳታ ሰጭ ድርጅቶች ሰራተኛ ለሰብአዊ እርዳታ ተብሎ የሚመጣ እርዳታ ለመሳሪያ ግዥ እና ለጦር ግንባር ዓላማ ይውል እንደነበር ያውቁ ነበር…“
በዚህ አሳፋሪ እና የወረደ ድርጊት ስህተት ውስጥ ተሳትፈው የነበሩት መቅንየለሾች ማስረጃዎችን ቆሻሻ በማለት ዘለፋ ከማቅረብ ውጭ በእውነተኛ መረጃ ላይ በተመሰረተ መልኩ አጣሪ እና እውነታ አፈላላጊ ኮሚቴ በማቋቋም ማስተባበል እና እራሳቸውን ከዚህ ከባድ እና ጠንካራ ክስ ነጻ ማድረግ ተስኗቸው ቀርቷል፡፡ እውነት በሀሰት ተቀብራ አትቀርማ! እንደዚህ ያለ ምርመራ እስከሚካሄድ ድረስ የእርዳታ ምንተፋ ስግብግብነት እና ሌብነት የማይደፈር እና ሊስተባበል የማይችል መደበኛ ዘረፋ ሆኖ የቆያል፡፡ ቦብ ጌልዶፍ እ.ኤ.አ በ1984 የሙዚቃ ባንድ በማስተባበር በአስር ሚሊዮኖች የሚቆጠር ዶላር ለእርዳታው እንዲሰበሰብ አድርጓል፣ የረኃብ እርዳታው በተሳሳተ መልኩ ለጦር መሳሪያ መግዣ ውሏል እየተባለ የሚሰማውን ውንጀላ ምክንያት በማድረግ እንዲህ ብሎ ነበር፣ “ምንም ዓይነት ገንዘብ ያለአግባብ የጠፋ ካለ የኢትዮጵያን መንግስት በህግ እጠይቃለሁ፡፡“
እ.ኤ.አ በ1980ዎቹ አጋማሽ (እንዲሁም ባለፉት 23 ዓመታት) መንግስታዊ ካልሆኑ የእርዳታ ሰጭ ድርጅቶች በአስር ሚሊዮኖች የሚሆን ለእርዳታ የተመደበ ዶላር የህወሀት አታላዮች ለራሳቸው ተራ ተስፈኝነት፣ በሚሊዮን የሚቆጠር ዶላር በብልጣብልጥነት እየዘረፉ ለግል ጥቅማቸው እና ለመሳሪያ መግዣ ያዋሉትን ሰው ዝም ብሎ በዘፈቀደ ሊያደንቅ ይችላል፡፡ እውነት ለመናገር አሊ ባባ እና የእርሱ 40 የወያኔ ሌቦች እንደዚህ ዓይነት ብልጣብልጥነት የተሞላበት የማጭበርበር ዕቅድ በመጠቀም መንግስታዊ ላልሆኑ የእርዳታ ሰጭ ድርጅቶች እራሳቸው እርዳታ ሰጭ ድርጅቶች የለገሱትን እህል እና አሸዋ የተሞላባቸውን ጆንያዎች እየደጋገሙ መሸጥ አልነበረባቸውም፡፡ የግሪክ የሌቦች አምላክ የነበረው ሄርምስ እንኳ እንደዚህ ያለ በጣም የሚያስገርም ዕንከንየለሽ የሸፍጥ ዕቅድ በማውጣት በሚሊዮኖች የሚቆጠር ዶላር ለመውሰድ መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶችን ለማታለል እና በቀላሉ ለማሞኘት አልቻለም ነበር፡፡ የህወሀት አመራሮች “አዲስ የአፍሪካ የሌቦች ዝርያ” የሚለው ስም የሚገባቸው ነው፡፡
ማረት የህወሀት ባተሌ ፍጹም አያውቅ እረፍት፣
በኢትዮጵያ የዩናይትድ ስቴትስ የምግብ እርዳታ በሶስት የውጭ መንግስታዊ ያልሆኑ የእርዳታ ሰጭ ድርጅቶች በብቸኝነት ይተዳደራል፡፡ እነርሱም ምግብ ለተራቡ/Food for the Hungry (FH) (እራሱን የክርስቲያን ድርጅት/Christian Organization እያለ የሚጠራ እና እ.ኤ.አ ከ1971 ጀምሮ በዓለም አቀፍ ደረጃ ድሆችን በመርዳት ላይ ያለ)፣ የህጻናት አድን ድርጅት/Save the Children (እራሱን የዓለም የተቸገሩ ህጻናት ቁንጮ እርዳታ ሰጭ ድርጅት እያለ የሚጠራ)፣ የካቶሊክ እርዳታ አገልግሎት/Catholic Relief Services (CRS) (በዩናይትድ ስቴትስ ለካቶሊክ ማህበረሰብ ዓለም አቀፍ የሰብአዊ እርዳታ ድርጅት) እና ማህበረ ረድኤት ትግራይ/ማረት የሚባል አንድ የሀገር ውስጥ መንግስታዊ ያልሆነ እርዳታ ሰጭ ድርጅት ናቸው፡፡ እ.ኤ.አ በ1984 – 86 የረሀብ ሰለባ ለነበሩ ወገኖቻችን ከእርዳታ ሰጭ ድርጅቶች ቀርቦ የነበረውን የምግብ እርዳታ ያለምንም ይሉኝታ በረሀብተኞች ጉሮሮ ላይ በመቆም የተለያዩ ሸፍጦችን እና የማታለያ ዘዴዎችን እየፈበረከ ሙልጭ አድርጎ የበላ እና ለእራሱ የውንብድና ሀራራው የመሳሪያ ግዥ ያዋለ ማህበረ ረድኤት ትግራይ/ማረት የተባለው ያው ድርጅት አሁንም በ2014 በኢትዮጵያ ለተከሰተው ረሀብ ዓይን ባወጣ መልኩ እርዳታ አከፋፋይ ሆኖ ቀርቧል፡፡ የሌባ ዓይነደረቅ መልሶ ልብ ያወልቅ እንዲሉ!
እ.ኤ.አ በ2010 እና በ2014 (እንዲሁም ከ2010 በፊት) ማረት ከ1.5 ቢሊዮን ዶላር በላይ የሚሆን የምግብ እርዳታ ተቀብሎ በማከፋፈል ስራው ላይ ተሳታፊ የነበረ ብቸኛው የሀገር ውስጥ መንግስታዊ ያልሆነ ድርጅት ነው፡፡ እ.ኤ.አ ኦገስት 15/2014 ዩኤስኤአይዲ/USAID እንዳወጣው ዘገባ ከሆነ ዩኤኤአይዲ በእራሱ ምግብ ለሰላም ጽ/ቤት/Office of Food for Peace እያለ በሚጠራው ጽ/ቤቱ በኩል እ.ኤ.አ በ2014 ለማረት እና ለሌሎች መንግስታዊ ያልሆኑ ዓለም አቀፋዊ ድርጅቶች 237 ሚሊዮን ዶላር፣ እ.ኤ.አ በ2013 ደግሞ 236 ሚሊዮን ዶላር፣ እ.ኤ.አ በ2012 ደግሞ 307 ሚሊዮን ዶላር፣ እንዲሁም እ.ኤ.አ በ2011 ሌላ 313 ሚሊዮን ዶላር እና እ.ኤ.አ በ2010 ደግሞ 452 ሚሊዮን ዶላር አድሏል፡፡
ማረት እስከ አሁንም ድረስ እራሱን “የህዝባዊ ወያኔ ሀርነት ትግራይ/ህወሀት የሰብአዊ እርዳታ ክንፍ” አድርጎ ይቆጥራል፡፡ በእርግጥ ማረት እ.ኤ.አ በ2014 በሞኖፖል የያዘ መንግስታዊ ያልሆነ የሀገር ውስጥ ድርጅት እና ልክ እ.ኤ.አ በ1984 ሲያደርግ እንደነበረው ሁሉ በኢትዮጵያ ይህንን ግዙፍ የሆነ ዓለም አቀፍ እርዳታን በማጭበርበር በእራሱ የማስተላለፊያ ቱቦ ለህወሀት የሚያስተላልፍ በእርዳታ ሰጭ ድርጅት ስም የሀሰት ጭምብላ ያጠለቀ መንታፊ ድርጅት ነው፡፡ በኢትዮጵያ ውስጥ ዓለም አቀፋዊ እርዳታን ለማከፋፈል የሚወዳደሩ ሌሎች ሀገር በቀል መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች የሉም፡፡ በእርግጥ የበጎ አድራጎት እና ማህበራት አዋጅ እየተባለ የሚጠራው መንግስታዊ ተቋም በኢትዮጵያ ያሉትን ሁሉንም መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች ሲያከስም (እ.ኤ.አ በ2010 አዋጁ ከወጣ በኋላ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ብዛት በሶስት ወራት ጊዜ ውስጥ ከ4,600 ወደ 1,400 ወርደዋል) ለማረት ጥሩ እድል በመፍጠር ምንም ዓይነት ተቀናቃኝ የሌለው ብቸኛው የሀገር ውስጥ ጠቅላይ ለመሆን በቅቷል፡፡
እንደ አንድ ኢትዮጵያዊ ምሁር ዘገባ ከሆነ ማረት የህወሀት የገንዘብ እና ቁሳቁስ ማስተላለፊያ ቱቦ ነው፡፡ በአሁኑ ጊዜ የህወሀት የንግድ ግዛት የመነሻ ካፒታል ከተለያዩ ምንጮች ይመጣል፡፡ አንዱ እና ዋናው የማስተላለፊያ ምንጩ የረኃብ እርዳታ የህወሀት ክንፍ የሆነው ማህበረ ረድኤት ትግራይ (ማረት) ነው፡፡ ማረት የእርዳታ ገንዘብን እና ሌሎች ቁሳቁሶችን ካልተጠበቁ እና በፈቃዳቸው ከሚሰጡ የውጭ የእርዳታ ሰጭ ድርጅቶች በመቀበል ገንዘብ እና ቁሳቁሶችን ወደ ህወሀት የገንዘብ ሳጥን ውስጥ የሚያስተላልፍ ድርጅት መሆኑ በስፋት ይታወቃል፡፡
የበጎ አድራጎት ድርጅት አዋጅ እየተባለ የሚጠራው መንግስታዊ ተቋም የሚያሳየው እውነታ አገር በቀል የሆኑ እና በሀገር ውስጥ መንቀሳቀስ የሚችሉት በህወሀት ስር ተጠቃለው የተያዙ ወይም ደግሞ ሌሎች ከህወሀት ጋር ወይም እርሱ ከሚፈልግላቸው ድርጅቶች ጋር በጋራ ለመንቀሳቀስ የሚችሉ ድርጅቶች ብቻ ናቸው፡፡ እ.ኤ.አ በ1984 ህወሀት በማረት በኩል ዓለም አቀፋዊ የሰብአዊ እርዳታን ለመሳሪያ መግዣ እና ለግል ጥቅሙ አውሏል፡፡ እ.ኤ.አ በ2014 ህወሀት ዓለም አቀፍ የሰብአዊ እርዳታን በማረት በኩል በመጠቀም አሁንም ለግል ጥቅሙ በማዋል ላይ ይገኛል፡፡ ምን ያህል! ነገሮች የበለጠ በተለዋወጡ ቁጥር የበለጠ አንድ ዓይነት እየሆኑ ይሄዳሉ!
ከመላ አፍሪካ ዩኤስኤአይዲ ትልቅ የእርዳታ ፕሮግራም ያለው በኢትዮጵያ ነው፡፡ ባለፉት 23 ዓመታት ብቻ በአስር ቢሊዮን የሚቆጠር ዶላር ከዩናይትድ ስቴትስ አሜሪካ ለህወሀት በእርዳታ ስም የተሰጠው ገንዘብ ከምን ላይ ዋለ? ለዚህ ጥያቄ የሚሰጠው መልስ እዕምሮን የሚበጠብጥ አስቸጋሪ ይሆናል! ማንም ሊያውቅ አይችልም፡፡ ዩኤስኤአይዲ/USAID እራሱ በቢሊዮን የሚቆጠር ዶላር ወደ ህወሀት የገንዘብ ካዝና ውስጥ የሚረጨው እንኳ አያውቀውም! ለዚያም ነበር የዩናይትድ ስቴትስ የመንግስት መምሪያ ጽ/ቤት ኢንስፔክተር በዘገባቸው ላይ እንዲህ የሚል መደምደሚያ የሰጡት፣ “የዩኤስኤአይዲ ኦዲት የምርመራ አገልግሎት የኢትዮጵያን የግብርና ምርታማነት ተግባራት (የኦዲት ዘገባ ቁጥር 4-6663-10-003-P (እ.ኤ.አ ማርች 30, 2010)“ በሚከተለው መልክ አስቀምጦታል፡
….የኦዲት ኢንስፔክተር [የግብርና ዘርፍ ምርታማነት] ፕሮግራም  የገበያ መር የኢኮኖሚ ዕድገት ማምጣቱን እና ገበሬዎች፣ አርብቶ አደሮች፣ እና ሌሎች በኢትዮጵያ የሚገኙት ተጠቃሚዎች ሁሉ መሻሻል እያሳዩ መሆናቸውን በጥናቱ አግኝቷል፡፡ ሆኖም ግን ያ የተገኘው ውጤት ምን ያህል እንደሆነ በአፈጻጸም አያያዝ እና የስራ አፈጻጸም ዘገባ ማቅረብ ደካማነት ምክንያት መወሰን አይቻልም፡፡ በተለይም ድርጅቱ በተለያዩ አካባቢዎች የስራውን ሂደት እና አፈጻጸሙን ለመከታተል እንዲቻል በሚል የስራ አፈጻጸም መለኪያ አመልካቾች እና ግቦችን በማስቀመጥ የሚጠቀም ቢሆንም… ለአብዛኞቹ መለኪያ አመልካቾች በዘገባ የቀረበው ውጤት ግን በግብነት ከተያዙት ጋር አልተነጻጸረም፡፡ ከዚህም በተጨማሪ የቀረበው የኦዲት ዘገባ በዩኤስኤአይዲ/ኢትዮጵያ የቀረቡት  የአፈጻጸም ውጤቶች ተይዞ ከነበረው ዕቅድ ጋር መነጻጸር መቻል አለመቻላቸውን ለመወሰን አይቻልም ምክንያቱም የድርጅቱ ሰራተኞች እነዚህ ውጤቶች እንዴት እንደተገኙ መግለጽ አይችሉም ወይም ደግሞ ለእነዚያ ተገኙ ለተባሉት የስራ ውጤቶች ድጋፍ አይሰጡም፡፡ በእርግጥ የኦዲት ቡድኑ በዘገባው የቀረቡ የአፈጻጸም ውጤቶችን ተገቢነት ያላቸው እንዲሆኑ ለማድረግ ሙከራ ያደረጉ ቢሆንም ይህንን ለመስራት በድርጅቱ ወይም ደግሞ የድርጅቱ ተባባሪ አስፈጻሚዎች ሳይቻል ቀርቷል (ከገጽ 6 – 12)…
እ.ኤ.አ ኦክቶበር 2010 ሂዩማን ራይትስ ዎች የተባለው ዓለም አቀፋዊ የሰብአዊ መብት ተሟጋች ድርጅት በኢትዮጵያ እርዳታ ከዓላማው ውጭ ለሌላ ጉዳይ መዋሉን አስመልከቶ መግለጫ አውጥቶ ለህዝብ ከመልቀቁ ከጥቂት ቀናት በፊት ዩኤስኤአይዲ/USAID እና የልማት እርዳታ ቡድን/Development Assistance Group (ለኢትዮጵያ እርዳታ የሚሰጡ 27ቱ የሁለትዮሽ እና በይነ መንግስታት የልማት ድርጅቶች (አንዳንድ ጊዜም በጥቅሉ ዓለም አቀፍ የድህነት ወትዋቾች/አቃጣሪዎች እየተባሉ የሚጠሩት) በኢትዮጵያ የልማት እርዳታ ላይ መጠነ ሰፊ እና ስልታዊ የሆነ ገንዘቡን ከታለመለት ዓላማ ውጭ የዋለ የለም ብለዋል፡፡ የእኛ ጥናት ስልታዊ የሆነ የእርዳታ ገንዘብ የጠፋ ወይም ደግሞ ለሌላ ዓላማ የዋለ ለመሆኑ ያገኘው ማስረጃ የለም ብለዋል፡፡ የወፍ ምስክሯ ድንቢጥ እንደሚባለው! ዳምቢሳ ሞዮ አሳማኝ በሆነ መልኩ እንደምትሞግተው ሁሉ ዓለም አቀፍ እርዳታ ለኢትዮጵያ እና ለሌሎች የአፍሪካ አገሮች ወጥመድ ሆኖ ቆይቷል፡፡ አሁንም ወጥመድ ነው፡፡ የዓለም አቀፉ የእርዳታ ምጽዋት ለኢትዮጵያ የጥገኝነት አዙሪትን፣ የተንሰራፋ ሙስናን፣ የገበያ መመሰቃቀልን፣ ስር የሰደደ ድህነት ማስፋፋትን እና ዘላለማዊ የእርዳታ ሱስ ውስጥ የሚያስገባ አደገኛ መርዝ ነው፡፡
ድህረ ጽሑፍ፣
በኢትዮጵያ ለበርካታ አስርት ዓመታት ሲከሰት በቆየው ረኃብ ላይ ጥናት በማካሄድ ዘገባ በማቅረብ ጠቃሚ አስተዋጽኦ ሲያደርጉ የቆዩ ሁለት ያልተዘመረላቸው ጀግኖች አሉ፡፡ እ.ኤ.አ በ1984 ተከስቶ ለነበረው በኢትዮጵያ ታላቁ ረኃብ 30ኛ ዓመት በሚታወስበት ዕለት እኔ በግሌ እንግሊዛዊውን ጋዜጠኛው ሚካኤል ቡርክን ከልብ ላመሰግን እወዳለሁ፡፡ ይህ ጀግና ጋዜጠኛ የኢትዮጵያን የ1984 ረኃብ በመዘገብ ሙዚቀኛ ቦብ ጌልዶፍን በማነሳሳት በቀጥታ በሚተላለፍ የእርዳታ ማሰባሰቢያ ኮንሰርት በመጠቀም ግዙፍ የሆነ ገንዘብ እንዲሰበሰብ በማድረጉ ብቻ አይደለም ሆኖም ግን በአስከፊው ረኃብ ምክንያት በመርገፍ እና በመሰቃየት ላይ የሚገኙትን የኢትዮጵያን ህዝቦች ሁኔታ ለዓለም አቀፉ ማህበረሰብ በማስተዋወቅ በፈጠረው ከፍተኛ የሆነ ግንዛቤ ጭምር እንጅ፡፡ እንደዚሁም ደግሞ የቢቢሲ ዘጋቢ እና በኋላም የአፍሪካ አርታኢ ሆኖ ሲሰራ የነበረውን እና እ.ኤ.አ በ1984 – 85 በተከሰተው ረኃብ ሰበብ ከምዕራቡ ዓለም ለተራቡት ወገኖቻችን የመጣውን በብዙ ሚሊዮን ዶላር የሚቆጠረውን እርዳታ በአቋራጭ ለመሳሪያ መግዣ እና ለግል ጥቅም ውሎ የነበረበትን እኩይ ምግባር ያጋለጠውን ጀግና ጋዜጠኛ ማርቲን ፕላውትን ከልብ ለማመስገን እወዳለሁ፡፡
የጋዜጠኝነትን ክቡር ሙያ በማስመልከት ታዋቂው የአሜሪካ ጸሐፊ፣ ዘጋቢ እና የፖለቲካ ተንታኝ የሚከተለውን አስፍሮ ነበር፣ “በጋዜጠኝነት ሙያ እውነታውን ከመናገር እና ሰይጣናዊ ድርጊትን ከማሳፈር እና ከማጋለጥ የበለጠ ትልቅ ህግ የለም፡፡“ እውነታን አፍርጦ በመናገር እና ሰይጣናዊ ድርጊትን በማሳፈር እና በማጋለጥ የ1984-85ን የኢትዮጵያን ታላቅ ረኃብ የዘገበ ከቡርክ እና ፕላውት ውጭ ማንም ጋዜጠኛ ይኖራል የሚል እምነት የለኝም፡፡ ኢትዮጵያዊ/ት የሆን ሁሉ እነዚህን ጀግኖች የማመስገን ዕዳ አለብን፡፡
ዓለም አቀፋዊ እርዳታ ለኢትዮጵያውያን/ት የድህነት አዙሪት ቀለበት ወጥመድ ሲሆን ለህወሀት ግን የመስረቅ እና የመዝረፍ ፈቃድ ነው!
ኢትዮጵያ በክብር ለዘላለም ትኑር!
ጥቅምት 25 ቀን 2007 .