Wednesday, January 29, 2014

“የኢትዮጵያ ፓርቲዎች የሃቀኝነት ጥያቄ ይነሳባቸዋል”

January 28/2014




















ለ46 ዓመታት በፖለቲካ ትግል ውስጥ እንደቆዩ የሚናገሩት የ70 ዓመቱ አዛውንት የቀድሞ የኢፌዲሪ ኘሬዚዳንት ኋላም

የተቃዋሚው አንድነት ፓርቲ ሊቀመንበር ዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳ፤ በቅርቡ ከፓርቲ-ፖለቲካ ራሳቸውን አግልለዋል።
ዶ/ር ነጋሶ፤ ለምን ከአንድነት ፓርቲ ለቀቁ? ስለተቃዋሚዎችና ስለኢህአዴግ ምን ይላሉ? በስጋት ስለሚኖሩበት

የመንግስት ቤት ጉዳይስ?
በእነዚህና ተያያዥ ጉዳዮች ዙሪያ የአዲስ አድማስ ጋዜጠኛ አለማየሁ አንበሴ፤ ብሥራተ ገብርኤል በሚገኘው መኖሪያ

ቤታቸው አግኝቶ  በስፋት አነጋግሯቸዋል፡፡

በስጋት ነው የምኖረው መውደቂያዬን አላውቀውም
እኔ የታገልኩት ቁስ ለመሰብሰብ አይደለም
ታጋይ እንጂ ዲኘሎማት አይደለሁም

ለ46 ዓመታት በፖለቲካ ትግል ውስጥ እንደቆዩ የሚናገሩት የ70 ዓመቱ አዛውንት የቀድሞ የኢፌዲሪ ኘሬዚዳንት ኋላም የተቃዋሚው አንድነት ፓርቲ ሊቀመንበር ዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳ፤ በቅርቡ ከፓርቲ-ፖለቲካ ራሳቸውን አግልለዋል። ዶ/ር ነጋሶ፤ ለምን ከአንድነት ፓርቲ ለቀቁ? ስለተቃዋሚዎችና ስለኢህአዴግ ምን ይላሉ? በስጋት ስለሚኖሩበት የመንግስት ቤት ጉዳይስ? በእነዚህና ተያያዥ ጉዳዮች ዙሪያ የአዲስ አድማስ ጋዜጠኛ አለማየሁ አንበሴ፤ ብሥራተ ገብርኤል በሚገኘው መኖሪያ ቤታቸው አግኝቶ በስፋት አነጋግሯቸዋል፡፡ በስጋት ነው የምኖረው መውደቂያዬን አላውቀውም እኔ የታገልኩት ቁስ ለመሰብሰብ አይደለም ታጋይ እንጂ ዲኘሎማት አይደለሁም ለምንድነው የፓርቲ-ፖለቲካ በቃኝ ያሉት? አንደኛው፤ የእድሜ ጉዳይ ነው፡፡ ጳጉሜ 3 ቀን 2005 ዓ.ም 70 ዓመት ሞልቻለሁ፡፡ ለ46 ዓመት ያህል በቀጥታ ህይወቴን ከፖለቲካ እንቅስቃሴ ጋር አቆራኝቼ ኖሬያለሁ፡፡ አሁን ይበቃል የሚል ስሜት አደረብኝ፡፡ ከአሁን በኋላ ለወጣቶች ቦታውን መልቀቅ አስፈላጊ ሆኖ አግኝቸዋለሁ፡፡ በኔ በኩል የተቻለኝን ያህል በፓርቲ-ፖለቲካ ውስጥ አገልግያለሁ፡፡

አሁን ይበቃኛል፡፡ ይህን ስል ትግሉን አቆማለሁ ማለቴ አይደለም፡፡ ሁለተኛ፤ የጤንነት ጉዳይ ነው፡፡ የስኳር ህመምተኛ ነኝ፡፡ በክኒን ነው የምኖረው፡፡ የደም ግፊትም አለብኝ፡፡ እንደልቤ መንቀሣቀስ አልችልም፡፡ በሊቀመንበርነት ከመሩት “አንድነት” ፓርቲ ጋር ስላለዎት የአመለካከት ልዩነት ይንገሩን? ለእኔ ከፓርቲ-ፖለቲካ መገለል ከላይ ከጠቀስኳቸው ምክንያቶች በበለጠ ይሄኛው ዋናው ምክንያቴ ነው፡፡ ጠቅላላ ጉባኤው ሊደረግ በታቀደ ጊዜ፣ በአመራር ውስጥ መግባት የሚፈልጉ እንዲወዳደሩ ብለን ነበር፡፡ ነገር ግን እኔ ለሊቀመንበርነትም ሆነ ለብሔራዊ ምክር ቤት ለመወዳደር አልፈለግሁም። ያልፈለግሁበት ምክንያት ደግሞ እኔ ወደ አንድነት የመጣሁት በመድረክ ምክንያት ነው፡፡ ከአንድ ዓመት በላይ በፈጀ ውይይት ነው መድረክ የተመሠረተው፡፡ መጀመሪያ መድረክ ወደ ጥምረት ሲሸጋገር ድርጅቶች ናቸው ተስማምተው ጥምረቱን ያቋቋሙት፡፡ እኔ ደግሞ በወቅቱ በየትኛውም ድርጅት ያልታቀፍኩ ስለነበርኩ ሁለት ምርጫ ብቻ ነበረኝ፡፡

ወይ ከመድረክ ጋር ያለኝን ግንኙነት ማቆም አለያም በፓርቲ ጥላ ስር ሆኜ መንቀሣቀስ፡፡ ተሣትፎዬ እንዲቀጥል ስለፈለኩ፣ የግድ ወደ አንድ ፓርቲ መግባት ነበረብኝ። ኘሮግራሙን በማዘጋጀት ብዙ ረድቻለሁ፤ የተለያዩ የፖለቲካ ፓርቲዎች በጋራ ሊሠሩ የሚችሉበት ጠንካራ ኘሮግራም ነው፣ በጣምም ደስ ስለሚለኝ ተሣትፎዬን መቀጠል ፍላጐቴ ነበር፡፡ ስለዚህ በፓርቲ ለመታቀፍ ከስድስቱ የመድረክ ተጣማሪ ፓርቲዎች የትኛው ኘሮግራም የበለጠ ለኔ ይስማማኛል መምረጥ ነበረብኝ፡፡ እናም አንድነትን መረጥኩ፡፡ በዚህ መልኩ ነበር ወደ አንድነት የመጣሁት፡፡ ከመጣሁ በኋላም መድረክ ራሱን አሣድጐ ወደ ግንባር ተሸጋገርን፡፡ ይህን ስናደርግ በሥራ አስፈጻሚ ደረጃ ብዙ ውይይቶች ነበሩ፡፡ ከየድርጅቱ ሁለት ሰዎች የተወከሉበት የሥራ አስፈጻሚ አለ፡፡ የዚያም አባል ነበርኩ፡፡ የአንድነት ፓርቲ ኘሮግራም ያስቀመጠው አቅጣጫ፤ ሁሉም ፓርቲዎች ቢዋሃዱ ለዚህች ሀገር ጠቀሜታ እንዳለው የሚገልጽ ነው፡፡ ህዝቡም ተመሣሣይ ግፊት ያደርግ ነበር፡፡ በዚህ መሠረት ነው መድረኩ ከጥምረት ወደ ግንባር የተሸጋገረው። የመድረኩ ሥራ አስፈጻሚ፤ የግንባሩን ኘሮግራም እና የወደፊት አቅጣጫዎች ሠርቶ ለየፓርቲዎቹ ሥራ አስፈጻሚዎች አቀረበ፡፡ የድርጅቶቹ ሥራ አስፈጻሚዎች ከተወያዩበት በኋላ በኘሮግራሙ ተስማሙ፣ አንድነትም ተስማማ፡፡ የአንድነት ሥራ አስፈጻሚ ከተስማማ በኋላ፣ የመጨረሻ ወሣኝ የሆኑት ሁለት አካላት ውሣኔ ይጠበቅ ነበር፡፡ አንደኛው፤ ብሔራዊ ምክር ቤት ሲሆን ሁለተኛው ጠቅላላ ጉባኤው ነው፡፡

በዚህ ተዋረድ መሠረት፣ ሥራ አስፈጻሚው የተስማማበትን የግንባሩን ኘሮግራም ወደ ብሔራዊ ምክር ቤት አወረደ፡፡ ብሔራዊ ምክር ቤቱ ተቀበለው፡፡ ከዚህ በኋላ የመጨረሻ ወሣኙ ጠቅላላ ጉባኤው ነው፡፡ አስቸኳይ ጠቅላላ ጉባኤ ጠራንና፣ ጠቅላላ ጉባኤው በበጐ ተቀበለው፡፡ ይሄን አካሄድ እንግዲህ ሁሉም የመድረክ ተጣማሪ ድርጅቶች ናቸው የተገበሩት፡፡ አንድነትን ጨምሮ ሁሉም ድርጅቶች በዚህ ሂደት “ግንባሩ ይፈጠር” የሚለውን ከወሰኑ በኋላ የመድረክ ጠቅላላ ጉባኤ ተጠራ፡፡ ከእያንዳንዱ ድርጅት በደንቡ መሠረት 10 ሰው ተወከለ፡፡ 10 የአንድነት ወኪሎችም በመድረኩ ጉባኤ ተገኙ፡፡ በዚህ ሂደት ውስጥ አንዳንድ ችግሮች ነበሩ፡፡ አንደኛ፤ መድረክ የገንዘብ ችግር ነበረበት፡፡ ሁለተኛ፤ ደግሞ ሰዎች በትርፍ ጊዜያቸው ነበር የሚሠሩት፡፡ እነዚህ የስራ መጓተቶች ፈጠሩ፡፡ በዚህ የተነሳም አንዳንድ ጭቅጭቆች ተነሱ፡፡ ለምሣሌ ኘ/ር በየነ፤ በግርማ ሠይፉ ላይ ሲሠጡ የነበረው አስተያየት፣ ግርማም ሲሰጠው የነበረው ምላሽ፤ አቶ ቡልቻም በአንድነት ላይ ሲሰነዝሩት የነበረው አሉታዊ አስተያየት…፤ እነዚህ ሁኔታዎች በአንድነት አባላት ላይ ቀላል የማይባል ተጽዕኖ ፈጥረዋል፡፡ እንዴት የመድረክ አባል ሆነን አሉታዊ አስተያየት ይሰነዘርብናል የሚሉ ቅሬታዎች ነበሩ፡፡ ይሄ አሉታዊ ሁኔታ እያለ ከአንድነት አባላት አንድ ሃሣብ መጣ፡፡ “የመድረክን ሂደት እንገምግም” የሚል፡፡ በብሔራዊ ምክር ቤቱም ሂደቱን ገምግመን ማጠናከር አለብን የሚል ውሣኔ ላይ ተደረሰ፡፡ አንድ ኮሚቴም ተቋቋመ፡፡ ድጋሚ የተቋቋመው ኮሚቴ፤ በአጭር ጊዜ ውስጥ ግምገማውን አጠናቆ፣ ውጤቱን ለብሔራዊ ምክር ቤቱ አቀረበ፡፡ እዚያ ላይ ነው እንግዲህ ችግሮች መፈጠር የጀመሩት፡፡

ገምጋሚ ኮሚቴ ያመጣው አንደኛው የግምገማ ውጤት፤ የመድረክ አባል ድርጅቶች ከአንድነት ኘሮግራም ጋር የማይስማሙ አቋሞችና አላማዎች አሉት፤ በዚህ ሁኔታ ግንባር ፈጥሮ አብሮ መሥራት አይቻልም የሚል ነው፡፡ሁለተኛው ደግሞ ግንባር እንዲሆን የተወሰነው በደንብ ጥናት ተደርጐበትና በቂ ውይይት ተካሂዶበት ሳይሆን አመራሩ ብቻ ያደረገው ነው የሚል ሆነ፡፡ ይሄ ነው በእኔና በአንድነት አባላት መካከል ልዩነት የተፈጠረው፡፡ በእርግጥ ቀድሞም ቢሆን መድረክ እና አንድነት የሚለያዩባቸው አንዳንድ ነጥቦች እንዳሉ ይታወቃል፡፡ ለምሣሌ የህገ-መንግስቱ አንቀጽ 39 ጉዳይ፣ የግለሰብና የቡድን መብት ጉዳይ፣ የመሬት ጥያቄ አፈታት፣ የፌዴራሊዝም ጥያቄ የመሣሠሉት ላይ ልዩነት ነበረው፡፡ እንዴት እነዚህ ልዩነቶች እያሉ ግንባር እናቋቁማለን የሚል ጉዳይም ተነስቷል፡፡ በወቅቱ እኔያቀረብኩት አስተያየት “እነዚህ ልዩነቶች ሊኖሩ ይችላሉ፤ ዋናው በዴሞክራሲያዊ አካሄድ ወደፊት ልዩነቶቹ የሚፈቱበት ሁኔታ በኘሮግራሙ መቀመጡ ነው” የሚል ነበር፡፡ በመድረክ ያሉ ፓርቲዎች ፌዴራሊዝምን የሚደግፉ ቢሆንም በኢትዮጵያ አንድነት እምነት አላቸው፡፡ በኘሮግራሙም መገንጠልን አንደግፍም የሚል አቋም ላይ ተደርሷል። “ልዩነቶች ሊያለያዩን አይገባም፤ አብረን እየሠራን ከምርጫው በፊት ዴሞክራሲያዊ የምርጫ ምህዳር እንዲፈጠር በማድረግ፣ የጋራ ማኒፊስቶ አዘጋጅተን፣ ወደ ፓርላማ እንገባለን ነበር የተስማማነው፤ እኛ ብቻ ሣንሆን ኢህአዴግን ጨምሮ ሌሎች ድርጅቶችም ፓርላማ ይገባሉ፣ ይህን መነሻ አድርገን የጋራ መንግስት እናቋቁማለን፡፡ ዴሞክራሲያዊ የመንግስት መዋቅር ከተፈጠረ በኋላ፣ የመድረኩ ግንባር ተጣማሪዎች የየራሣቸውን ኘሮግራም ይዘው ወጥተው አሊያም አንድ ሆነው የመሠላቸውን ትግል” ይቀጥላሉ በሚል ይሄን ስምምነት የፓርቲው ግምገማ አፈረሰው። በዚህ የተነሣ በሃሣብ ተለያየን፡፡ ብሔራዊ ምክር ቤቱ ግምገማውን ተቀበለው እኔ ተቃወምኩኝ፡፡

ይሄ የሆነው በ2005 ሚያዚያ ወር ነው፡፡ ሁለተኛው ልዩነት የተፈጠረው ደግሞ የግምገማው ውጤት ምን ይሁን በሚለው ላይ ነው፡፡ የግምገማው ውጤት ወደ መድረክ ይሂድና ለውይይት ይቅረብ፤ በሌላ በኩል ወደ ሚዲያ ወጥቶ ህዝቡ ይወያይበት፤ ይሄ በሁለት ሣምንት ጊዜ ውስጥ ተግባራዊ ይደረግ በሚል ብሔራዊ ምክር ቤቱ ወሰነ። ነገር ግን ጉዳዩ በማግስቱ ከውሣኔው ውጪ ሚዲያ ላይ ቀድሞ ወጣ፡፡ አንድ ግለሰብ ጋዜጣ ላይ በስፋት አወጣው፡፡ ይሄን የመድረክ ሰዎች ሲያዩት ትልቅ ቁጣ አስነሣ፡፡ በዚህ ብቻ አላበቃም፡፡ አንድነት ራሱን ሂስ ያድርግና ማስተባበያውን በጋዜጣ ያውጣ ወይም ይሄን ባደረገው ሰው ላይ እርምጃ ውሰዱ የሚል ማስጠንቀቂያ ከመድረክ ቀረበ፡፡ የእኔ አቋም “በሚዲያ ቢወጣ ምናለበት፣ ሂስም ማድረጉ ክፋት የለውም” የሚል ነበር፡፡ ሌሎች ግን አልተስማሙም። እንግዲህ በዚህ ላይም በእኔና በሌሎች የፓርቲው አመራሮች መካከል ልዩነት ተፈጠረ ማለት ነው፡፡ ከዚያ በኋላ በመድረኩ ስብሰባዎች ላይ በሙሉ ህሊናዬ ሆኜ አንድነትን ለመወከል አስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ ገባሁ፡፡ እንደ ሊቀመንበር የግድ አንድነትን መወከልና የፓርቲውን ሃሣብ ማስተጋባት አለብኝ በሌላ በኩል ደግሞ ህሊናዬ ይሞግተኛል፡፡ በዚህ ምክንያት ዘንድሮ የመድረክ ሥራ አስፈጻሚ ውስጥ ከመግባት ተቆጠብኩ፡፡ ይህ በእንዲህ እንዳለ ደግሞ የውህደት ጉዳይ ተጀመረ፡፡ መኢአድ እና አንድነት ይዋሃዱ ተብሎ ድርድር ተጀመረ፡፡ የቅድመ ውህደት ሠነድም ተዘጋጀ፡፡ በዚያ ሰነድ ላይ እኔና ብሔራዊ ምክር ቤቱ አሁንም ተለያየን፡፡ ብዙ የልዩነት ነጥቦች ናቸው፡፡ እነሱን አሁን መዘርዘር አልፈልግም፡፡ እርስዎ ውህደቱን አይደግፉም ማለት ነው? ውህደት እደግፋለሁ፤ ነገር ግን ሲዋሃዱ በምን ላይ ነው የተመሠረቱት፤ የውህደት ስምምነቱስ ምንድን ነው? በሚለው ላይ አንዳንድ ጥልቀት ያለው ውይይት ሊካሄድባቸው የሚገቡ ጉዳዮች ነበሩ፡፡ የአንድነት ብሔራዊ ምክር ቤት ግን እነዚህን ውይይት የሚያስፈልጋቸውን ጉዳዮች እንዳለ ተቀብሏል። ለምሣሌ የህገ-መንግስቱ አንቀጽ 39 ጉዳይ አለ። አንቀጹ የመገንጠል መብትንም ያካትታል፡፡ ይሄን አንቀጽ የውህደቱ ተደራዳሪ ኮሚቴ አይደግፍም፤ ከህገ መንግስቱም መሰረዝ አለበት ሲል ተስማምቶበታል፡፡ በእኔ በኩል ደግሞ ይሄ የማይቻል ነው፡፡ አንቀጽ 39ን ይደግፋሉ? አዎ! እደግፋለሁ፡፡ ምክንያቱም ጥያቄው የመብት ነው፡፡ መብቱ ይከበር ነው እንጂ መገንጠል ይኖራል ማለት አይደለም፡፡

ስለዚህ እኔ አንቀጽ 39 ከህገ መንግስቱ ይሠረዝ የሚለውን አልደግፍም፡፡ ይህን ተቃውሞዬን በማሠማበት ጊዜ፣ እኛ በኢትዮጵያ አንድነት ላይ አንደራደርም የምትል ማሻሻያ በድርድር ሰነድ ላይ ቀረበች፡፡ ብሔራዊ ምክር ቤቱ ይሄን ሙሉ ለሙሉ ተቀበለው፡፡ በእኔ በኩል አሁንም ይሄ አባባል አስቸጋሪ ነው አልኩ፡፡ መብት አክብረህም አንድ ክፍለ ህዝብ መብቴ አልተከበረም፤ እገነጠላለሁ ካለ ምንድነው የሚሆነው? ወደ ጦርነት ነው የሚኬደው ወይስ ሌላ አማራጭ አለ? እዚህ ላይ ልዩነቶች ተፈጠሩ፡፡ አሁን መጨረሻ ላይ ደግሞ በአንድነት ጠቅላላ ጉባኤ ላይ የምረጡኝ ቅስቀሣ ሲካሄድ ነበር። እዚያ ላይ ጠቅላላ ጉባኤው፤”ውህደቱ ያስፈልጋል በማለት በ3 ወር ጊዜ ውስጥ ከመኢአድ፣ ከአረና እና ከመሣሠሉት ፓርቲዎች ጋር ውህደት እንዲፈጸም” ብሎ የወሰነውን ውሣኔ ኢ/ር ግዛቸው ወሰደና፣ “እንዲያውም ለውህደቱ የተሰጠው ጊዜ ዘግይቷል በአጭር ቀናት ውስጥ እንዲጠናቀቅ አደርጋለሁ” ሲል ቅስቀሣ ማካሄድ ጀመረ፡፡ በተጨማሪም “ከአሁን ጀምሮ በጥምረት፣ በግንባር በመሣሠሉት ጊዜ ማጥፋት አያስፈልግም፤ ውህደት ብቻ ነው የሚያስፈልገው፤ በዚህ አካሄድ ነው የምሠራው” ሲል አቋሙን ገለፀ ፤ በዚህም በከፍተኛ ድምጽ ተመረጠ፡፡ ይሄ ለኔ ሌላ ትርጉም አለው፡፡ የእኔ ግልጽ አቋም ምን መሠለህ? ከተቻለ ውህደት ጥሩ ነው፤ ወደ ውህደት የምትደርሰው ግን ከብዙ ውጣ ውረድ በኋላ ነው እንጂ አድርጉ ስለተባለ መሆን የለበትም፡፡ ውህደት ላይ ሁሉም በአንድ እጅ ማጨብጨብ አለበት፤ በኘሮግራም ሙሉ ለሙሉ መስማማት አለበት፡፡ ይሄን ለማድረግ ደግሞ አሁን ባለው ተጨባጭ ሁኔታ ብዙ ውይይት ያስፈልጋል፡፡ እንግዲህ ይሄ የመጨረሻው ውሣኔ ላይ እንድደርስ እና ከፓርቲው እንድወጣ ያደረገኝ ጉዳይ ነው፡፡

በዚህና ከላይ ባስቀመጥኳቸው ምክንያት አቅጣጫው የተለወጠ ይመስለኛል፡፡ እኔ ደግሞ ከአቅጣጫ ለውጡ ጋር ህሊናዬ ተስማምቶ ሊሠራ አልቻለም፡፡ በዚህ ምክንያት ከአንድነት ልወጣ ችያለሁ፡፡ ከፓርቲው ከወጣሁ በኋላ ምን ማድረግ አለብኝ ብዬ ሣስብም የደረስኩበት ድምዳሜ የፓርቲ-ፖለቲካ ይበቃኛል የሚለው ሆነ፡፡ አብዛኞቹ ፖለቲከኞች ከፓርቲ ፖለቲካ ሲገለሉ መጽሀፍ ይጽፋሉ፣ልምዳቸውን ያካፍላሉ፡፡ እርስዎ ምን አሰቡ? ርዕሱንና ይዘቱን መግለጽ አልፈልግም እንጂ መጽሃፍ እየጻፍኩ ነው፡፡ በሌላ በኩል የፖለቲካ ምክር መስጠትና ልምድ ማካፈልም አለ፡፡ እኔ እንዲታወቅልኝ የምፈልገው በአንድነትም ሆነ በመድረክ ላይ “ትክክል አይደሉም” ብዬ ጫና ለመፍጠር አልፈልግም፡፡ እንዲጐዱም አልፈልግም፡፡ ለዚህች ሀገር ፖለቲካ አስፈላጊ ኃይሎች መሆናቸውን በሚገባ አምናለሁ፡፡ ከአንድነት የድርጅት ጉዳይ ኃላፊ ከነበሩት ኢንጂነር ዘለቀ ረዲ ጋርም አለመግባባቶች ተፈጥረው እንደነበር ይታወቃል፡፡ መነሻው ምን ነበር? ኢ/ር ዘለቀ የድርጅት ኮሚቴ ሰብሳቢ ነበር፡፡ የፓርቲውን የድርጅት ስራ ማንቀሣቀስ ነበረበት፡፡ ግን እንደታሰበው ሣይሆን ድክመት ተፈጠረ፡፡ ኃላፊነቱን እንዲወጣ የተቻለውን ያህል መከርን፤ ግን አልሆነም፡፡ እኔ ነበርኩ ኃላፊነቱን የሠጠሁት፡፡ ሥራው ከተዳከመ አልንና ኃላፊነቱን እንዲለቅ አደረግን፡፡ እሱ ግን ደብዳቤ አልደረሰኝም ብሎ ጋዜጣ ላይ አወጀ፡፡ ይሄ ግን አይደለም፤ በወቅቱ ደብዳቤውን ሰጥቼዋለሁ፡፡ ይሄ ነው የግል ፀብ ያስመሰለው እንጂ የአለመግባባቱ መንስኤ የአሠራር ጉዳይ ነው፡፡ ብሔራዊ ምክር ቤቱ ራሱ በአንዳንድ የዲስፒሊን ግድፈቶች የተነሳ በአባልነቱ ላይ ጥያቄ አንስቶ ነበር፡፡ በእኔና በአሥራት ላይም በየጋዜጦቹ ያወጣቸው ጉዳዮች ነበሩ፡፡

አሁን ደግሞ ኢ/ር ግዛቸው በሥራ አስፈጻሚነት መልምሎታል፡፡ እኔ በዚህ ምንም ቅር አይለኝም፡፡ በግል ግን እኔና እሱ ፀብ የለንም፤ እንቀራረባለን፡፡ በ46 ዓመታት የፖለቲካ ህይወትዎ ለኢትዮጵያ ህዝብ አበርክቻለሁ የሚሉት ጉልህ አስተዋጽኦ ምንድን ነው? ዴሞክራሲና ፍትህ ከሌለ፣ ጭቆናና የሰብአዊ መብት ጥሰት ከተንሰራፋ፣ ሰው ሁሉ መታገል አለበት የሚል እምነት አለኝ፡፡ እኔም በዚህ መርህ መሠረት፣ የራሴን ድርሻ ህሊናዬ በፈቀደው መንገድ እየተጓዝኩ አበርክቻለሁ ብዬ አምናለሁ፡፡ ዴሞክራሲ እንዲኖር፣ የሰብአዊ መብቶች እንዲከበሩ አነቃቅቻለሁ ለማለት እችላለሁ፡፡ ለህሊና መኖር እንደሚቻል ያሣየሁም ይመስለኛል፡፡ ዋናው ነገር ሰው ሁልጊዜ መብቶቹ ካልተከበሩ መታገል አለበት፡፡ ባላደርግሁት ብለው የሚቆጩበት ፖለቲካዊ ውሣኔ ይኖርዎት ይሆን? አየህ… አሁን ለምሣሌ ሶሻሊዝምን እደግፍ ነበር። ደርግ ሶሻሊስት ነኝ ባለ ጊዜ ልደግፈው እችል ነበር፤ ነገር ግን አምባገነን ነው፡፡ ወጣቶችን የሚገድልና መብቶችን የሚደፈጥጥ ነበር፤ በዚያ ሶሻሊስት ስለሆነ ብቻ ሁሉን ሃጢያቶቹን ትቼ እሱን ለመደገፍ ህሊናዬ አይፈቅድልኝም ነበር፡፡ ኦነግን ረድቻለሁ፤ ነገር ግን ኋላ ላይ ተጣላን፤ የተጣላንበት ምክንያት ተበታትኖ በየጐጡ እየተደራጁ የሚደረጉ ትግሎችን ተቃውሜ፣ ወደ አንድ መድረክ መሰባሰብ ይገባል የሚል አቋም በመያዜ ነበር፡፡ በአውሮፓ ይገኙ የነበሩ ሁለት የኦሮሞ ድርጅቶችን ለማቀራረብ ስንቀሣቀስ አንደኛው ድርጅት፤ “ይሄ ጐበና ዳጩ /የሚኒልክ ጦር አዝማች የነበሩት/ ነው “አለኝና አገለለኝ፡፡ ከዚያ በኋላ ኦፒኤልኤፍ ከሚባል ድርጅት ጋር እየሠራን እያለ፣ በ1983 “ዱለ ወልቂጡማ ቢሊሱማ” /ዘመቻ ለነጻነትና ለእኩልነት/ ሲታወጅና ጦሩ ከጐጃም ተነስቶ ወደ ወለጋ ሲጓዝ “ይሄ ደግሞ ቅኝ ግዛት ነው” አሉ፡፡ እኔ በወቅቱ “ይሄ ዳግም ቅኝ ግዛት ሊሆን አይችልም።

ምክንያቱም ደርግ ሌላ ቦታ ተሸንፎ መሠረት ያደረገው ኦሮሚያ ውስጥ ነው፤ ስለዚህ ይህን ኃይል ለመደምሰስ የሚደረግን ዘመቻ ዳግም ቅኝ ግዛት ነው ብሎ ያለመደገፍ ደርግ እንዲቀጥል ማድረግ ነው ብዬ አቋም በመያዝ ከእነሱ ጋር ተለያየን፡፡ እንደገና ወደ ኦህዴድ ከመጣሁ በኋላ በ1993 ዓ.ም ከኢህአዴግ የተለየሁት በአቅጣጫ ልዩነት ነው፡፡ ሶሻሊስት ነን ብዬ አብሬ ስሰራ እነሱ ነጭ ካፒታሊዝምን ነው የምንከተለው ብለው በድንገት አወጁ፤ እኔ ደግሞ በካፒታሊዝም አላምንም፡፡ ምክንያቴም ካፒታሊዝምን እንከተላለን ሲባል እንዲሁ የውሸት በመሆኑ ነው፡፡ ፓርቲዎች በነጻነት መንቀሣቀስ ባልቻሉበት እና የብሔር ጥያቄ ባልተፈታበት ሁኔታ ካፒታሊዝምን እንከተላለን ማለት ሌላ ችግር ያመጣል ብዬ ተለያየን ፡፡ ከዚህ አንጻር ህሊናዬ በሚፈቅደው መንገድ ነው ስሄድ የነበረው ማለት ነው፡፡ ህሊናህ በፈቀደው መንገድ ስትጓዝ ደግሞ የሚቆጭህ ነገር የለም፡፡ ስለዚህ እኔ አንዳችም የሚቆጨኝ ነገር የለም በውሣኔዎቼ ሁሉ ደስተኛ ነኝ፤ የራስን ሃሣብና የህሊና ጥያቄ ገፍቶ ለድርጅታዊ ውሣኔ ብቻ መገዛት በእኔ በኩል ትክክል አይደለም፡፡ አንዳንድ ሰዎች “ልዩነት ቢኖርህም ልዩነትህን ውጠህ እዚያው ብትቆይ ይሻልህ ነበር” የሚል ሃሣብ ያመጣሉ፤ ለኔ ግን ይሄ ትክክል አይደለም፡፡ አንዳንዶች እርስዎ ዶ/ር ነጋሶ፤ “ቀጥተኛ ሁሉን ነገር በግልጽ የሚናገሩ ስለሆኑ ለፖለቲካው የሚሆኑ ሰው አይደሉም ይላሉ…. አዎ! እኔ ዲኘሎማት አይደለሁም፡፡ ቀጥተኛ ታጋይ ነኝ፡፡ ፖለቲካው ወደዞረበት እየዞረ የሚሄድ ፖለቲከኛ ዲኘሎማት አይደለሁም፡፡ ዲኘሎማት የሆኑ ሰዎች ብዙ ጊዜ በዚህም በዚያም ብለው ግባቸው ላይ ለመድረስ ነው የሚጥሩት፡፡ እኔ ያንን አልችልበትም ፡፡ ቀጥተኛ መሆንዎ ያሣጣዎት ነገር አለ? ምን ያሣጣኝ ነገር አለ? /ረጅም ሣቅ/ ምናልባት በቁሣቁስ አሣጥቶኝ ሊሆን ይችላል፡፡ ማቴሪያል ደግሞ ድሮም አልነበረኝም፤ አሁንም የለኝም፡፡ ሰዎች ከኢህአዴግ ጋር ባትጣላ ኖሮ ቢያንስ እንደ መቶ አለቃ ግርማ ትኖር ነበር ይሉኛል፡፡

ያንን ካየህ በቁስ ደረጃ ያጣሁት ነገር አለ ተብሎ ሊታሠብ ይችላል፡፡ ይሄ ያለሁበት ቤትም የኔ አይደለም፤ ከዚህም ውጣ ከተባልኩ ቆይቷል፡፡ መውደቂያ ስለሌለኝ እምቢ ብዬ ነው እንጂ፡፡ አበል የለኝም፣ ከአንድነት ትሠጠኝ የነበረች 3 ሺ 800 ብር አበልም ከበቀደም ጀምሮ ቆማለች፡፡ የምኖረው እንግዲህ ከቀበሌ በማገኛት 1300 ብር ጡረታዬ ነው፡፡ ባለቤቴም መጠነኛ ገቢ የምታገኝባት ሥራ አላት፡፡ እንግዲህ አሁን ያለሁበትን የኑሮ ደረጃ ካየህ፣ አጥተሃል የሚሉኝ ሰዎች ሃሣብ ትክክል ነው ልትል ትችላለህ፤ ነገር ግን ይሄ ለኔ አይቆጨኝም፤ ስሜትም አይሰጠኝም፤ ምክንያቱም እኔ በዚህ አይደለም የታገልኩት ቁስ ለመሰብሰብ አይደለም ፡፡ እስቲ ስለፖለቲካ ፓርቲዎች ደግሞ አናውራ…. በአሁኑ ወቅት ለህዝብ መብትና ጥቅም በሃቀኝነት የሚታገሉ ፓርቲዎች አሉ? በጣም አስቸጋሪ ነው፡፡ ሃቀኛ ናቸው አይደሉም የሚለው ግምገማ አስቸጋሪ ነው፡፡ ሁሉም በመሠለው መንገድ እየታገለ ነው፡፡ ለኔ ግን ካየኋቸው ተሞክሮዎች፣ በእርግጥም ሃቀኛ ድርጅት ነው ብዬ የማምነው የህዝብን ሉአላዊ የስልጣን ባለቤትነትን የሚቀበል ፓርቲ ነው፡፡

ለዚህ ተግባራዊነት የሚንቀሣቀስ መሆን አለበት እንጂ ለፓርቲ ኘሮግራም እና ዓላማ ብቻ የሚሠራ መሆን የለበትም፡፡ እዚህ አገር ሁሉም ፓርቲዎች ለህዝብ ነው የሚታገሉት ይባላል። ግን ከገዥው ፓርቲ ጀምሮ በሁሉም ላይ ችግር አያለሁ፡፡ ኢህአዴግ ለስሙ መልካም አስተዳደር፣ ዴሞክራሲ ምናምን ይላል፤ የሚሠራው ግን ሌላ ነው፡፡ ሌሎች ፓርቲዎችም የምንታገለው ለህዝብ የስልጣን ባለቤትነትና ለዴሞክራሲ ነው ይላሉ፤ ያ ከሆነ በጋራ መሥራትን ለምን ይፈሩታል? ከዚህ አኳያ ከተመለከትነው ሁሉም ፓርቲዎች ላይ የሃቀኝነት ጥያቄ ይነሣባቸዋል ማለት ነው፡፡ እርሶ ሲመሩት የነበረው አንድነት፤ “ገዥው ፓርቲ ሀገሪቱን በብሔር ከፋፍሎ ኢትዮጵያዊነትን ሸርሽሯል” የሚል አመለካከት አለው፣ በሌላ በኩል ደግሞ በቅርቡ “የቁጫ ብሔረሰብ ማንነቱ ለምን አይከበርም ሲል የብሔር መብት ጥያቄ ያነሣል፡፡ እነዚህ ነገሮች እርስ በእርሣቸው አይጋጩም? በአንድነት ኘሮግራም ላይ አንድ አንቀጽ አለ። የኘሮግራሙ 3.1.5 አንቀጽ፤ “አብይ የፖለቲካ ጥያቄዎች በፖለቲካዊ መንገድ ነው የሚመለሱት፤ ይሄም በህጋዊና በዲሞክራሲያዊ መንገድ፤ በውይይት እና በድርድር ነው፤ በዚህ መንገድ አብይ ጥያቄዎች ካልተፈቱ ወደ ህዝብ ነው የሚሄደው” ይላል፡፡ ይሄ አንቀጽ እውነት ይታመንበታል ወይ የሚለው ለኔ ጥያቄ ነው፤ ለእኔ ከፖለቲካ ጥያቄዎች አንዱ የብሔር ጥያቄ ነው፡፡ አብይ የፖለቲካ ጥያቄ እንደሚኖር የምታምን ከሆነ፣ አንቀጽ 39ን መቃወም የለብህም ማለት ነው፡፡ የብሔር ጥያቄ የምታምንበት ከሆነ “በኢትዮጵያ አንድነት አልደራደርም” አትልም ማለት ነው፡፡ እኔ ተቃርኖውን በዚህ መንገድ ነው የማየው፡፡የቁጫን ህዝብ በተመለከተ ግን የአንድነት ኘሮግራም ላይ የግለሰብ እና የቡድን መብት መከበር እንዳለበት ተቀምጧል፡፡ የቁጫ ህዝብ አንድ ቡድን ነው፤ አንድነት የማንነት ጥያቄ ሣይሆን የመብት ጥያቄውን ነው የደገፈው፡፡

ጥያቄያቸው ይሰማ ነው ያለው። እነሱ የጠየቁት ይሰማ ከሚለው አኳያ ነው እንጂ ማንነታቸው ይታወቅ የሚል አይደለም፡፡ ከተቃዋሚ ፓርቲዎች መካከል ጥሩ አቅጣጫ ይዟል፤ በቀጣይ ምርጫም የስልጣን ባለቤት ሊሆን ይችላል ብለው ተስፋ የጣሉበት ፓርቲ አለ? አሁን ይህን ማለት ጥሩ አይደለም፡፡ ይሄኛው ከዚህ የተሻለ ነው ብዬ መወሰንም አልችልም፡፡ ፓርቲዎች ይደራጁ፣ ይሞክሩ፤ ከተመረጡ ይመረጡ፤ አሁን አለ ወይም የለም የሉም ብዬ ከደመደምኩኝ ጥሩ አይሆንም ነገር ግን ሁሉም በተቻለ መጠን ከልባቸው ለህዝብ የስልጣን ባለቤትነት ይታገሉ፡፡ በኢህአዴግ በኩልም የፖለቲካ ምህዳሩን መክፈትና ሁሉንም ፓርቲዎች በእኩል ማስተናገድ አለበት፡፡ ፓርቲዎች ከአሁን ጀምረው ተሰባስበው፣ ለዲሞክራሲ መሥራት አለባቸው፡፡ አሁን ጥሩ እየሠሩ ነው የሚሏቸው ፓርቲዎች የሉም? እየሞከሩ ነው ሶስተኛ አማራጭ አለ። አክትቪዝምን የሚከተሉ አሉ፣ አንድነትም፣ መድረክም…. ሌሎችም አሉ፡፡ በአሁኑ ሁኔታ ግን ይሄኛው ይሻላል ያኛው አይሻልም ወይም ሁሉም አይረቡም በሚለው ላይ ግን አስተያየት መስጠት አልፈልግም፡፡ ከፓርቲ ፖለቲካ ራስዎን ቢያገሉም በግልዎ የፖለቲካ ተሳትፎ እንደሚያደርጉ ገልጸዋል፡፡ በግልዎ ለፓርላማ መወዳደርስ? የለም ይበቃኛል፡፡ ወደ ፓርላማው መግባትም አልፈልግም፡፡ ምናልባት በፓርቲዎች መካከል ስምምነት ለመፍጠር፣ በኢህአዴግና በተቃዋሚዎች መካከል መቻቻል እንዲኖር፤ ሁሉም በብሔራዊ ጉዳይ እንዲስማማ የማድረግ እንቅስቃሴዎች ለመሳተፍ እሞክራለሁ፡፡ ምናልባት ኢህአዴግ፤ ለሁለተኛ ጊዜ አብረውት እንዲሰሩ ወይም በማማከር እንዲያግዙት ቢጠይቅዎ ፈቃደኛ ይሆናሉ? ምክር ከፈለገ አብሬ ብሠራ ምንም ችግር የለብኝም፡፡

ስብሰባዎች ካሉ እሣተፋለሁ፡፡ በቅርቡ አቶ ስብሃት ነጋ በሂልተን ሆቴል አንድ ሴሚናር አዘጋጅቶ ጋብዞኝ ነበር፡፡ እዚያ ላይ ተሣትፌያለሁ፡፡ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የጆርናሊዝምና ኮሚኒኬሽን ኢንስቲትዩት የፌዴራሊዝም ጥያቄ ላይ በተደረገ ውይይት ጋብዞኝ አስተያየቴን ሰጥቻለሁ፡፡ በቅርቡም ሌላ ውይይት ላይ እንድገኝ ጠይቀውኛል፡፡ የዚህ ዓይነት ሁኔታ ከተፈጠረ ለምን እምቢ እላለሁ፡፡ የመድረክ ሰዎች ብዙዎቹ እኮ የዩኒቨርሲቲ መምህራን ናቸው፡፡ ዩኒቨርሲቲ ከቀጠረኝ የመንግስት ስለሆነ አልፈልግም አልልም፡፡ ኢህአዴግም በምክር ከፈለገኝ አማክረዋለሁ፤ “ይሄን ብታደርግ ይሻላል፤ ይሄ ጥሩ አይደለም” ለሚለው ሃሣብ በሩን ከከፈተ ጥሩ ነው፡፡ ድሮ የትግል አጋርዎ የነበሩት የቀድሞ የኦነግ አመራር አቶ ሌንጮ ለታ “ወደ ሠላማዊ ትግል ተመልሻለሁ አዲስ ፓርቲም አቋቁሜያለሁ” ማለታቸው ለኢትዮጵያ ፋይዳው ምንድን ነው? ተቀባይነትስ ያገኛሉ ብለው ያስባሉ? በአገር ውስጥ 72 ፓርቲዎች ስላሉ የእነሱ አዲስ ፓርቲ ይዞ መምጣት ብዙም ፋይዳ የለውም፡፡ ከሌሎች ጋር ቢቀናጁ ይሻላል የሚል ሃሣብ አለኝ። ምክንያቱም በኦሮሞ ስም የተደራጁ ብዙ አሉ፡፡ “በኢትዮጵያ ጥላ ስር መኖር ይቻላል” ከሚለው አኳያ ስንመለከተው የእነ ሌንጮ መምጣት የሚጨምረው እሴት ይኖራል፡፡

በሌላ በኩል በአጠቃላይ በኦሮሚያ ውስጥ የሚንቀሣቀሱ ፖርቲዎች ሁለት አቅጣጫ ነው የያዙት፡፡ አንዱ እንገንጠል፣ ሌላው በኢትዮጵያ ጥላ ስር ሆነን እንኑር የሚሉ ናቸው፡፡ በኢትዮጵያ ጥላ ሥር እንኑር ለሚሉት የእነ ሌንጮ መመለስ ድጋፍ ሲሆን እንገንጠል ለሚሉት ደግሞ ድጋፉን ያጐድልባቸዋል፡፡ አገር ውስጥ በሠላማዊ መንገድ ሲታገሉ የቆዩትን የኦሮሞ ድርጅቶችና የእነ ሌንጮ ፓርቲ ውዝግብ ውስጥ እንዳይገቡ እፈራለሁ፡፡ በሌላ በኩል ኦነግ በእነ ሌንጮ ላይ ትግሉን ገድለውታል የሚል ሃሣብ የሚያነሣ ይመስለኛል፡፡ በተለይ ለኦሮሚያ “ህዝብ በኢትዮጵያ ማዕቀፍ እንኑር” የሚለውን አስተሣሠብ የበለጠ ያጠናክራል፡፡ በእኔ እይታም የኦሮሞ ህዝብ ይሄንን ነው የሚፈልገው፡፡ የዳያስፓራውን ፖለቲካ እንዴት ይገመገሙታል? አንዳንዶች የሃይማኖት ተቋማትን በዘር እስከ መከፋፈል ደርሰዋል በሚል ይተቻሉ… ጨለምተኛነት አለ፣ አክራሪነት አለ፣ በሀይማኖትና በጐሣ መከፋፈል የእነ ሌንጮ ፓርቲ ተቀባይነት ያገኛል ወይ የሚለው አስቸጋሪ ጥያቄ ነው፡፡ እኔ 17 ዓመት ጀርመን ሀገር ስለኖርኩ አውቀዋለሁ፤ ከአንዳንድ የኦሮሞ ጓደኞቼ ጋር የምጣላው ለዚህ ነበር፡፡ ለምሣሌ እኔ ከኢትዮጵያ ኤምባሲ “አዲስ ዘመን” ጋዜጣ አስመጥቼ ሳነብ ሲያዩ፡፡ “እንዴት ይሄን የአማራ ጋዜጣ ታነባለህ?” ይሉኛል ወይም መንገድ ላይ ሰውን በአማርኛ ሰላም ስል ደስ አይላቸውም ነበር፡፡ እንዲህ ያሉ ሁኔታዎች ዛሬም አሉ፡፡ እዚያ ነጻነት አለ፤ ግን ነጻነት በዚህን ያህል ደረጃ መከፋፈላቸው፤ በአገር ቤቱ ፖለቲካ ላይ ተጽዕኖ አለው፡፡ ከኢህአዴንም ከአንድነትም የወጡት በአቅጣጫና በአመለካከት ልዩነት ነው፡፡ ከሁለቱ የበለጠ ያልተመቾት የቱ ነው? በጣም አስቸጋሪ ነው፡፡

የኢህአዴጉ በአንድ በኩል “የህወኃት አንጃ” ያላቸውን ሰዎች ያስተናገደበት መንገድ አስከፊ ነው፡፡ ያኔ እኔ ምርጫ ቦርድ ብሆን ኖሮ፣ ኢህአዴግን ሠርተፊኬቱን እሠርዝበት ነበር። ምክንያቱም ሰዎቹ ህገ-መንግስቱና የምርጫ ህጉ በሚፈቅደው መንገድ አይደለም የተባረሩት፡፡ ዴሞክራሲያዊ መብታቸው አልተጠበቀም ያ ለኔ ብዙ ራስ ምታት ፈጥሮብኛል፡፡ ከዚያ በኋላ ደግሞ በሰኔ ላይ አቅጣጫ መቀየር መጣ፡፡ እንግዲህ እሱ እና አሁን በአንድነት ያጋጠመኝ ይመሣሠላል፡፡ እኔ ላይ ጭቅጭቅና አለመግባባት በመፍጠር ረገድ ግን የኢህአዴጉ ነው የሚበዛው፡፡ ከአንድነት ስወጣ በእድሜ መግፋት እና በጤና እንደምለቅ አስቀድሜ ስለገለፀኩ ከጭቅጭቅ ያመለጥኩ ይመስለኛል። አንድነት በዚህ በኩል ሊበራል ነው፡፡ ሃሣብን ያከብራል፤ ያለ ቅሬታ ነው የተለያየነው፡፡ የኢህአዴጉ ግን የልብ ድካም ሁሉ ያመጣብኝ ነበር፡፡ አዲሱን የኢፌዲሪ ኘሬዚዳንት በተመለከተ አስተያየት አለዎት? የኘሬዚዳንት ተቋም ኃላፊነትና ተግባር እንዲሆን የተፈለገው የእንግሊዙ ሲስተም ነው፡፡ በእንግሊዝ ንግስቲቱ ሀገርን ትወክላለች፤ ሆኖም ግን እዚያ ብዙ ጥንቃቄ አለ ንግስቲቱ ጠቅላይ ሚኒስትሩን ትደግፋለች፤ ጠቅላይ ሚኒስትሩ በፊናው እያንዳንዷን ነገር ማማከር፣ ሪፖርት ማድረግና የውሣኔ ሃሣቦችን መቀበል አለበት፡፡

እዚህ ያ የለም፤ አሁን ተፈጥሮ እንደሆነ አላውቅም፡፡ እኔ ባለሁበት ጊዜ ጠቅላይ ሚኒስትሩ አማክሮኝ አያውቅም፡፡ እኔም ብዙ ጊዜ የኦህዴድን የድርጅት ሥራ በመሥራት ላይ ተጠምጄ ስለነበር በሌሎቹ ሥራዎች ላይ አልተንቀሣቀስኩም። ኘሬዘዳንት ግርማም በህመም ምክንያት አልተንቀሣቀሱም፡፡ የአሁኑ እንግዲህ እየተንቀሣቀሱ እንደሆነ አላውቅሁም፡፡ ሆኖም ግን በእድሜም በጤናም ደህና ናቸው፡፡ በትምህርትም ደህና ናቸው፤ በግርማ ሞገስም ገጽታቸው ለኘሬዚዳንትነት አይከፋም፡፡ ነገር ግን የኛ ህገ መንግስት ለኘሬዚዳንቱ ስልጣን አይሠጥም፡፡ በግል ቂም አለው ወይ እንዳትለኝ እንጂ የአሁኑ ኘሬዘዳንት ዶ/ር ሙላቱ ተሾመ እና ዳዊት ዮሐንስ ነበሩ ያኔ በእኔ ላይ የፈረዱት። ሁሉን ነገር እንዳጣ የወሰኑት እነሱ ናቸው፡፡ በ97 ዓ.ም ምርጫ ጊዜ ምርጫ ውስጥ ገብተሃል፤ ብሎ አዋጅ ጥሰሃል ስለዚህ ጥቅማ ጥቅሞችህንና መብትህን ታጣለህ” ብለው የወሰኑት እነሱ ናቸው፡፡ ዶ/ር ሙላቱ ያኔ የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ-ጉባኤ ነበር፡፡ አሁን የሚኖሩበት ቤት ከኘሬዚዳንትነት ሲለቁ የተሰጥዎ ነው? ከኘሬዚዳንትነት የለቀቅሁ እለት የት እንደሚያስገቡኝ ጨንቋቸው፣ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አጠገብ ካለች አንዲት ቤት ነበር ያስገቡኝ፡፡ እዚያ 6 ወር ከኖርን በኋላ ወደ ቦሌ ወሰዱን፤ ጥሩ ቤት ነበረች፤ 3 መኝታ ቤት አላት፣ ቢሮ ግን የላትም፡፡ ግድግዳውና መስታወቱ ተሠነጣጥቆ በጋዜጣ ነበር እየሸፈንን ሁለት አመት ቆየን፡፡ ከዚያ አሁን ያለሁበት ቤት አመጡን፡፡ አሁን ከፓርቲ ፖለቲካ ሲገለሉ ጥቅማ ጥቅሜን መለሼ ላገኝ እችላለሁ የሚል ተስፋ የሎትም? የቀድሞ ኘሬዚዳንት ከወገንተኛ የፖለቲካ እንቅስቃሴ መገለል አለበት ይላል፡፡ አተረጓጐሙ እንግዲህ በኢህአዴግ እይታ አፍህን ዘግተህ ተቀመጥ ነው፡፡ የመጀመሪያው ማስጠንቀቂያ የደረሰኝ አዳማ ላይ የሮያል ዩኒቨርሲቲ ኮሌጅ በክብር እንግድነት ጋብዞኝ ባደረግሁት ንግግር ነው በወቅቱ ኢህአዴግ እንደሚለው “ልማት ያስፈልገናል፣ ልማት እንዲመጣ ዴሞክራሲ ያስፈልገናል፣ ዴሞክራሲ እንዲመጣ የመብት ጥያቄዎች መልስ ያስፈልጋቸዋል” አልኩ። አክዬም፤ “በኦሮሚያ ሠላም ስለሌለ እንደሌሎች አካባቢዎች ልማት እየተፋጠነ አይደለም፣ ይህ የሆነው ደግሞ ዲሞክራሲ ስለሌለ ነው” ብዬ ተናገርኩ፡፡ ከሁለት ሣምንት በኋላ ዳዊት ዮሐንስ ጠራኝና የኦሮሚያ ክልል ከሶሃል አለኝ፡፡ “ፖለቲካ ውስጥ እየገባህ ነው፤ ከአሁን ሰዓት ጀምሮ በዚህ ሁኔታ የምትቀጥል ከሆነ ጥቅማ ጥቅምህን ታጣለህ” አለኝ፡፡ “የፈለከውን አድርግ፤ እኔ አቋሜን ከማራመድ ወደ ኋላ አልልም” አልኩትና ሄድኩ፡፡ በዚያው ውሣኔያቸውን ተግባራዊ ማድረግ ጀመሩ እኔም ክስ መስርቼ፣ ከስሼ ሰበር ደርሶ ለእነሱ ተወሰነ፡፡

የሚሠጠኝ አበል፣ መኪና፣ ሠራተኞች፣ ቤት የመሣሠለውን አጣሁ እኔ አሁን ከፓርቲ ፖለቲካ በመውጣቴ በድጋሚ ጥቅማ ጥቅሜን አገኛለሁ የሚል ተስፋ የለኝም፡፡ ኢህአዴግ ይህን ካደረገ ተለውጧል ማለት ነው፡፡ እኔ ግን አሁንም አስፈላጊ በሆነ ጊዜ ሁሉ መተቸቴንና መቃወሜን እቀጥላለሁ፡፡ ለኘሬዚዳንት ግርማ ወ/ጊዮርጊስ በ4ዐዐሺህ ብር መኖሪያ ቤት መከራየቱን የሚተቹ ወገኖች አሉ? እርስዎ ምን ይላሉ? እኔም ከሚቃወሙት ወገን ነኝ፡፡ በዚህች ድሃ ሀገር ለምን ይሄ አስፈለገ? አንደኛ እኔ እንደሠማሁት ቤቱ 2ዐ ክፍሎች ነው ያሉት፡፡ አሁን በተሻሻለው ህግ ደግሞ ኘሬዚዳንቱ ከ3 እስከ 4 ክፍል ቤት ይሠጠዋል ነው የሚለው፡፡ በሀገራችን የድህነት ሁኔታ በ4ዐዐ ሺህ ብር ቤት መከራየት ያስፈልጋል ወይ?” የሚለውን ጥያቄ ከሚያቀርቡት ወገን ነኝ፡፡ አሁን እርስዎ የሚተዳደሩት በምንድነው? እስከአሁን ድረስ ለኢኮኖሚ የሚጠቅመኝን ሥራ አልሠራሁም፡፡ ለፒኤችዲ የጻፍኳት መጽሃፍ አለች ከዚያች ትንሽ ገንዘብ አግኝቻለሁ፡፡ ከዚያ “ዳንዲ የነጋሶ መንገድ” ከሚለው መጽሃፌ ደግሞ ሩብ ያህሉን አግኝቻለሁ፡፡ ሌላው ኦሮሚያ ኢንተርናሽናል ባንክ ሲቋቋም፣ ዘመዶች አክስዮን ግዛ ብለውኝ በ4 ሺህ ብር የገዛሁት አለኝ፡፡ ከዚያ በስተቀር ምንም የኔ የምለው ሃብት የለኝም፡፡ ደምቢዶሎ ያለው የወላጆቻችን ቦታ ተወስዷል፡፡ እዚህም የራሴ የምለው ቤትም ሆነ ቦታ የለኝም፡፡ ከዚህ ከምኖርበት ቤትም ውጣ ብለውኝ ነበር፡፡ ነገር ግን አቤቱታ በማቅረቤ እስከአሁን ድረስ ዝም ብለውኛል፡፡ ግን በፈለጉ ጊዜ እንደሚወስዱት አውቃለሁ፡፡ ዋስትና የለኝም፤ በስጋት ነው የምኖረው፤ ቀጣይ መውደቂያዬንም አላውቀውም፡፡ ልጆችዎ የት ናቸው? ልጃችን አሁን የፊልም ትምህርቷን ጨርሳ ሎስአንጀለስ ውስጥ ሥራ እያፈላለገች ነው፡፡ ከቀድሞዋ ባለቤቴ የወለድኳቸው ደግሞ አንደኛው ጀርመን ሀገር ይሠራል፤ ሴቷ ደግሞ ለንደን ነው ያለችው፡፡

ልጅ ወልዳለች አሁን የእነሱ ጉዳይ አያሣስበኝም፡፡ እኔ አንድ ነገር ብሆን ባለቤቴ ምን ትሆናለች የሚለው ነው የሚያስበኝ፡፡ በቅርቡ በኢቲቪ በተላለፈ ዶክመንተሪ ላይ እርስዎና ሌሎች የአንድነት አመራሮች በ“ኢሳት” ጣቢያ ላይ ቃለ ምልልስ መስጠታችሁ ተተችቷል... ዶክመንተሪውን ተከታትየዋለሁ፡፡ የመጀመሪያው ላይ አሥራት ጣሴ፣ እኔ እና ዳንኤልን ነበር የሚያሳዩት ሁለተኛው ላይ እኔና ዳንኤል ኢንተርቪው ሰጥተዋል የሚል ትችት አቀረቡ ያቀረቡት፡፡ በቃለ ምልልሱ ምን እንዳልን ግን አላቀረቡም፡፡ ይህ እንግዲህ እነ ነጋሶ ከሽብርተኛ ድርጅት ጋር ግንኙነት አላቸው ለማለት ተፈልጐ እንደሆነ ይገባኛል፡፡ ይህ የአሁኑ ሌላ የኘሮፖጋንዳ ሥራ ነው፡፡ የዚህ ዓይነት ጨዋታ ጥሩ አይደለም፡፡ የትም አያደርሣቸውም፡፡ ቢተውት ጥሩ ነው፡፡ ለወደፊት እርሶ ምን ዓይነቷን ኢትዮጵያ ለማየት ይመኛሉ? መብትና ነጻነት የተከበረባት፣ ሁሉም የፈለገውን የሚያስብባትና ያሻውን አቋም የሚገልጽባት ኢትዮጵያን ባይ ደስ ይለኛል፡፡ ሰው በፈለገው መንገድ እየተደራጀ የፈለገውን ተቃውሞ በመንግስት ላይ የሚያቀርብባት፣ የፈለገውን ግለሰብ እና ፓርቲ የሚመርጥባት፣ዜጐች በሁሉም ጉዳዮች ላይ ወሣኝ የሚሆኑባት ኢትዮጵያን ማየት ምኞቴ ነው፡፡ የሰው ልጅ ሙሉ ነጻነቱ ከተከበረለት፣ አቅሙን መጠቀም ይችላል፤ ያኔም ልማት ይመጣል፡፡ ይች ሀገር በተፈጥሮ ሀብት እግዚአብሔር የባረካት ነች፣ ይህን ተጠቅመን ድህነትን የምንቀርፍባትን ኢትዮጵያ እመኛለሁ፡፡

Tuesday, January 28, 2014

Ethiopia – Land for Sale

January 28, 2014

As the economy thrives, we examine the plight of Ethiopians forced from their land to make way for foreign investors.

NGO’s and policy advocates say the true consequences of the land grabs are almost all negative [Reuters]
NGO’s and policy advocates say the true consequences of the land grabs are almost all negative [Reuters]
Just a few decades ago, Ethiopia was a country defined by its famines, particularly between 1983-1985 when in excess of half a million people starved to death as a consequence of drought, crop failure and a brutal civil war.
Against this backdrop, it is impressive that in recent years, Ethiopia has been experiencing stellar economic growth. The headline statistics are certainly remarkable: the country is creating millionaires faster than any other in Africa; output from farming, Ethiopia’s dominant industry, has tripled in a decade; the capital Addis Ababa is experiencing a massive construction boom; and the last six years have seen the nation’s GDP grow by a staggering 108 percent.
But it is not all positive news, because for all the good figures there are still plenty of bad ones.
Around 90 percent of the population of 87 million still suffers from numerous deprivations, ranging from insufficient access to education to inadequate health care; average incomes are still well below $1500 a year; and more than 30 million people still face chronic food shortages.
And while there are a number of positive and genuine reasons for the growth spurt – business and legislative reforms, more professional governance, the achievements of a thriving service sector – many critics say that the growth seen in agriculture, which accounts for almost half of Ethiopia’s economic activity and a great deal of its recent success, is actually being driven by an out of control ‘land grab’, as  multinational companies and private speculators vie to lease millions of acres of the country’s most fertile territory from the government at bargain basement prices.
At the ministry of agriculture in Addis Ababa, this land-lease programme is often described as a “win-win” because it brings in new technologies and employment and, supposedly, makes it easier to improve health care, education and other services in rural areas.
“Ethiopia needs to develop to fight poverty, increase food supplies and improve livelihoods and is doing so in a sustainable way,” said one official.
But according to a host of NGO’s and policy advocates, including Oxfam, Human Rights Watch and the Oakland Institute, the true consequences of the land grabs are almost all negative. They say that in order to make such huge areas available for foreign investors to grow foodstuffs and bio-fuels for export – and in direct contravention of Ethiopia’s obligations under international law – the authorities are displacing hundreds of thousands of indigenous peoples, abusing their human rights, destroying their traditions, trashing the environment, and making them more dependent on food aid  than ever before.
“The benefits for the local populations are very little,” said renowned Ethiopian sociologist Dessalegn Rahmato. “They’ve taken away their land. They’ve taken away their natural resource, because these investors are clearing the land, destroying the forest, cutting down the trees. The government claims that one of the aims of this investment was to enable local areas to benefit by investing in infrastructure, social services … but these benefits are not included in the contract. It’s only left up to the magnanimity of the investor.”
And those investors, he continued, are simply not interested in anything other than serving their own needs: “They can grow any crop they want, when they want it, they can sell in any market they want, whether it’s a global market or a local market. In fact most of them are not interested in the local markets.”
He cited as an example a massive Saudi-owned plantation in the fertile Gambella region of south west Ethiopia, a prime target area for investors: “They have 10,000 hectares and they are producing rice. This rice is going to be exported to the Middle East, to Saudi Arabia and other places. The local people in that area don’t eat rice.”
But the most controversial element of the government’s programme is known as ‘villagisation’ – the displacement of people from land they have occupied for generations and their subsequent resettlement in artificial communities.
In Gambella, where two ethnic groups, the Anuaks and the Nuers, predominate, it has meant tens of thousands of people have been forced to abandon a traditional way of life. One such is Moot, an Anuak farmer who now lives in a government village far from his home.
“When investors showed up, we were told to pack up our things and to go to the village. If we had decided not to go, they would have destroyed our crops, our houses and our belongings. We couldn’t even claim compensation because the government decided that those lands belonged to the investors. We were scared … if you get upset and say that someone stole your land, you are put in prison. If you complain about being arrested, they will kill you. It’s not our land anymore; we have been deprived of our rights.”
Despite growing internal opposition and international criticism, the Ethiopian government shows no sign of scaling the programme back. According to the Oakland Institute, since 2008, an area the size of France has already been handed over to foreign corporations. Over the next few years an area twice that size is thought to be earmarked for leasing to investors.
Source: ALJAZEERA

“የሰንደቅ” ጋዜጣ አዘጋጆች ተከሰሱ

January 28/2014

ዋና አዘጋጁ በ5ሺህ ብር ዋስ ተለቋል

 “ሰንደቅ” ጋዜጣ ስለ ጉዲፈቻ በሰራው ሰፊ ዘገባ ላይ የሴቶች፣ ህፃናትና ወጣቶች ሚኒስቴር  በስም ማጥፋት አቤቱታ እንዳቀረበበት የገለፀው ዋና አዘጋጁ ፍሬው አበበ፤ ባለፈው ሀሙስ ጠዋት ማዕከላዊ ምርመራ ቀርቦ ቃሉን ከሰጠ በኋላ በ5ሺህ ብር ዋስ መለቀቁን ተናገረ፡፡

ጋዜጣው ታህሣሥ 23 ቀን 2ዐዐ6 ዓ.ም ‹‹የጉዲፈቻ ዘመቻ በተጠያቂነት መጀመር አለበት›› ርዕስ አንቀጽና በሕግ አምዱ ላይ ‹‹ጉዲፈቻና የሕጎቻችን ክፍተቶች›› በሚል ዘገባ ማውጣቱን ዋና አዘጋጁ ተናግራል፡፡ የሴቶች፣ህፃናትና ወጣቶች ሚኒስቴር በጋዜጣው የአገርን ገፅታ የሚያበላሽ፣ የፍትህ ስርዓቱን ተዓማኒነት የሚያሳጣና የሚኒስትሯን ክብር የሚያዋርድ ዘገባ አውጥቷል ሲል ለፓሊስ አቤቱታ ማቅረቡን የተናገረው ዋና አዘጋጁ፤ ከትላንት በስቲያ በፌደራል ወንጀል ምርመራ ዘርፍ ቀርቦ ቃሉን ከሰጠ በኋላ፣ በ5ሺህ ብር ዋስ መለቀቁን ገልጿል፡፡

በጉዲፈቻ ዙሪያ ባወጡት ዘገባ ስም በማጥፋት በመንጀላቸው እንዳሳዘነው የገለጸው ዋና አዘጋጁ ፍሬው፤ “የተፈለገው ሙስናና ኪራይ ሰብሳቢነትን እንዳናጋልጥ ቢሆንም ፈርተን ወደ ኋላ አንልም፤ ሞያው የሚጠይቀውን  መስዋዕትነት ሁሉ እንከፍላለን” ብሏል፡፡ 

ሂውማን ራይትስ ዎች በኢትዮጵያ የፖለቲካ ምህዳሩ ይበልጥ ጠቧል አለ

January 28/2014



















መንግስት፤ ተቋሙ የተቃዋሚዎች የፕሮፖጋንዳ ማስፈፀሚያ ነው
“በኢትዮጵያ የነፃ ሚዲያ ህልውና አደጋ ላይ ነው”
“በኤርትራ የመብት ጥያቄ ማንሳት ነውር ሆኗል” ብሏል

የኢትዮጵያ መንግስት የዜጐችን  ሰብአዊ መብት በስፋት ይጥሳል በማለት ተደጋጋሚ ወቀሳና ስሞታ የሚያቀርበው ሂውማን ራይትስ ዎች የተሰኘው አለማቀፍ የመብት ተቋም፤  ሰሞኑን ይፋ ባደረገው አመታዊ ሪፖርቱ፣ በኢትዮጵያ የፖለቲካ ነፃነት ይበልጥ መጥበቡንና የነጻ ሚዲያ ህልውና አደጋ ላይ መውደቁን ገለፀ፡፡

የኢትዮጵያ መንግስት በበኩሉ፤ የተቋሙን ሪፖርት ያጣጥላል፡፡ በአገሪቱ ውስጥ የፖለቲካ ነፃነትና የፖለቲካ እንቅስቃሴ የማካሄድ እድል (የፖለቲካ ምህዳር) እየጠበበ የመጣው ከምርጫ 97 በኋላ መሆኑን የገለፀው ሂውማን ራይትስ ዎች፤ ከዚያ ወዲህ በመንግስት የፀደቁትን የፀረ - ሽብር እና የበጐ አድራጐት ማህበራት አዋጆችን በምሳሌነት ጠቅሷል፡፡ በፀረ - ሽብር አዋጁ መነሻነት ፖለቲከኞችና ጋዜጠኞች ሽብርተኛ ተብለው እንደታሠሩና እንደተፈረደባቸው የተቋሙ ሪፖርት ጠቅሶ፣ በህጋዊና ሰላማዊ መንገድ የሚንቀሳቀሱ የፖለቲካ ፓርቲዎች በፍርሃት እንዲሸበቡ ተደርገዋል ብሏል፡፡
ጋዜጠኞች የፀረ-ሽብር አዋጁን በመፍራት የሙያ ተግባራቸውን እንዳያከናውኑ መታፈናቸውን ሲገልጽም፤ የአዋጁ አንቀፅ እየተጠቀሰ እሥራት የተፈረደባቸው ጋዜጠኞች መኖራቸውንም አውስቷል፡፡

በኢትዮጵያ ጐልተው የሚታዩት የሰብአዊ መብት ጥሰቶች የፖለቲካ ምህዳር መጥበብና የኘሬሶች አፈና ቢሆኑም፤ ሌሎች የሰብዓዊ መብት ጥሰቶችም መሻሻል አላሣዩም ብሏል ሪፖርቱ፡፡

በማረሚያ ቤት ያሉ እሥረኞች በገለልተኛ አካላት እንዳይጐበኙ መከልከል፣ ያልተፈረደባቸው ግለሰቦችን አስሮ ማቆየትና ለፍርድ ቤት አቤቱታ እንዳይቀርቡ ማገድ፤ ያልተፈረደባቸውን ሰዎች በብሔራዊ ቴሌቪዥን ጣቢያ በሚሠራጩ ፕሮግራሞች ላይ እንደ ወንጀለኛ መፈረጅ… በአገሪቱ ከሚታዩ የሰብአዊ መብት ጥሰቶች ውስጥ የሚካተቱ መሆናቸውን ሪፖርቱ ዘርዝሯል፡፡

ሠላማዊ ሠልፍ የማካሄድ፣ የመብት ጥያቄ የማቅረብና ተቃውሞን የማሰማት መብቶችንም ፈትሼያለሁ የሚለው ሂውማን ራይትስ ዎች፤ ጥያቄ ባቀረቡና ሰላማዊ ሰልፍ ባካሄዱ ሙስሊሞች ላይ እንግልት፣ ድብደባና እሥር ተፈጽሟል ብሏል፡፡ በተቃዋሚ ፓርቲዎች የተጠሩ ሠላማዊ ሠልፎችም  በአፈና ውስጥ የተካሄዱ መሆናቸው በሪፖርቱ ተጠቅሷል፡፡
በአለማቀፍ ደረጃ ከፍተኛ የመብት ጥሰት ይፈጸምባቸዋል ከተባሉት አገራት መካከል ኤርትራ በቀዳሚዎቹ ተርታ ውስጥ እንደምትመደብ ተቋሙ ገልፆ፤ ጋዜጠኞች ለእሥራት እና ለእንግልት፤ ብዙ ዜጐችም ለስደት መዳረጋቸውን ዘርዝሯል፡፡
በኤርትራ የመብት ጥያቄ ማንሣት ነውር ሆኗል ያለው ይሄው ሪፖርት፤ የኤርትራ ሁኔታ ከሁሉም የአፍሪካ ሀገራት እጅግ በጣም አሣሣቢ ነው ብሏል፡፡

ሃሣብን በነጻነት መግለጽ፣ መደራጀትና የፈለጉትን አቋም መያዝ ለኤርትራውያን እንደማይፈቀድ በመጥቀስም፤ ከፍርድ ቤት ትዕዛዝ ውጪ ሰዎች እየተያዙ ይታሠራሉ፤ እስር ቤት የታጐሩ  ጋዜጠኞች፣ ፖለቲከኞችና ሌሎች ዜጐች  ያለምንም ፍርድ ከ10 ዓመት በላይ ሆኗቸዋል ብሏል፡፡

የኢትዮጵያ መንግስት ሂውማን ራይትስ ዎች የሚያወጣቸውን ሪፖርቶች ሙሉ ለሙሉ እንደማይቀበል በተደጋጋሚ ያስታወቀ ሲሆን፤ ተቋሙ ከሽብርተኛ ድርጅቶች ጋር በመቀናጀት የሚሠራ ነው፤  የተቃዋሚ ሃይሎች የኘሮፖጋንዳ ማስፈጸሚያ ነው ሲል ይከሳል፡፡

ሰሞኑን የተሰራጨውን አመታዊ ሪፖርት በተመለከተ የጠየቅናቸው የመንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ሽመልስ ከማል፤ “ሂውማን ራይትስ ዎች የሚያወጣው ሪፖርት ተአማኒነት የሌለውና ገጽታን ለማጠልሸት ያለመ ነው” ብለዋል፡፡
ተቋሙ ሀገር ውስጥ ሣይገኝ ወይም መርማሪዎቹን ሣይልክ፣ ኬንያናና ሌላ ሀገር ተቀምጦ ከተቃዋሚዎች በሚቃርመው ያልተጣራ ተባራሪ ወሬ ላይ ተመስርቶ፣ ከመንግስት ምላሽ ሳይጠይቅ የሚያወጣው መናኛ ሪፖርት ኢትዮጵያ ውስጥ ያለውን ነባራዊ ሁኔታ ፈጽሞ አይገልጽም ብለዋል ሚኒስትር ዴኤታው፡፡

ተቋሙ የኢትዮጵያን መንግስት ለማጥላላት  አቅዶ የሚሠራ ነው ያሉት አቶ ሽመልስ፤ የተቋሙ የምስራቅ አፍሪካ ወኪል አቶ ዳንኤል በቀለ፣ ህገ-መንግስቱን የማፍረስ ነውጥ በማስነሳት የተከሰሱና የተፈረደባቸው፣ ይቅርታ ጠይቀው ቢለቀቁም በኢትዮጵያ መንግስት ላይ ቂም የቋጠሩ በመሆናቸው ሪፖርታቸው ገለልተኛ ሊሆን አይችልም ብለዋል። ይህ ሲባል ግን ሀገራችን ታዳጊ ሀገር እንደመሆኗ ችግሮች አይኖሩም ማለት አይደለም ያሉት ኃላፊው፤ የኘሬስ ነጻነትና የጋዜጠኞች መብት ሙሉ ለሙሉ ተጠብቆ ኘሬሱ እንዲጠናከርና  እንዲስፋፋ እየተደረገ ነው፣ ከባለሙያዎች ጋርም እየተመካከርን በጋራ እየሠራን ነው ብለዋል፡፡

በልቡ የሸፈተ ህዝብ የካድሬዎች ጋጋታና ሽብር አይገታውም

January 28, 2014
በዲያስፖራ የአረና ትግራይ ድጋፍ አስተባባሪ ኮሚቴ የተሰጠ መግለጫ

ሰሞኑሰሞኑን በትግራይ የህወሓት መሪዎችና ካድሬዎቻቸው ከየመንደሩ የተውጣጡ ነብሰ ገዳይ፣ ስብሰባ በታኝና አፋኝ የዱሪየ ቡድኖችን በተለያየ መልኩ በማደራጀት በአረና ትግራይ አባላትና አመራር ላይ የከፈቱትን አዲስ የመንጥርና የድብደባ ዘመቻን አስመልክቶ

ህወሓት/ኢሕአዴግ በትረ ስልጣኑን ከተጎናፀፈና ካደላደለ ወዲህ ከሱ የተለየ አመለካከትና ሃሳብ ያላቸው ወገኖች ሁሉ የተለያዩ ቀለማ ቀለሞችን በመቅባት፣ የፈጠራ ስም በመለጠፍና ሰበብ አስባብ በመፈለግ በቀጥታም ሆነ በረቀቀ መንገድ የመመንጠር፣ የማፅዳት፣ የመሰወር፣ የማሰር፣ የመግደልና እርስ በርስ የማናቆር ስራ ዋነኛ የስርዓቱን ባህርይ መገለጫ ሆኖ መቆየቱ እሙን ነው። የእርምጃው ዋናው ምክንያትም እውነት ተቃዋሚዎቹ የሀገርና የህዝብ ጠላቶች ስለሆኑ አይደለም። ነገር ግን ጥያቄያቸው “ስለ ሀገራችንና ህዝባችን ጉዳይ እኛም ያገባናል!! አባቶቻችን ደም ከፍለው ያቆዩልንን ሀገር የመጠበቅ የኛም ግዴታ ነው!! ዘላቂ ልማትና ዕድገት የሚመጣው እውነተኛ ዲሞክራሲ፣ የሕግ ልዕልና፣ ፍትሕ፣ ነፃነት፣ ሰላምና አንድነት ሲረጋገጥ እንጂ በጡንቻ አይደለም!! ሕገ መንግስቱ የሰጠንን የመናገር፣ የመፃፍ፣ የመደራጀት፣ የመንቀሳቀስ፣ የእምነት፣ የመምረጥና የመመረጥ ነፃነታችንን ይከበር!!” ብለው ሰላማዊና ሕጋዊ መንገድን ተከትለው በቆራጥነት ስለተንቀሳቀሱና ስለጠየቁ ብቻ መሆኑን ማንም ቅን ህሊና ያለው ኢትዮጵያዊ ሊገነዘበው የሚችል ጉዳይ ነው።
ሰሞኑን የመድረክ አባል ከሆኑት የፓለቲካ ድርጅቶች አንዱ “በአረና ትግራይ ለሉዓላዊነትና ለዲሞክራሲ” አባላትና ከፍተኛ አመራር ላይ እየደረሰ ያለው ግፍና አፈና ማየቱ በቂ ይመስለናል። የአረና ትግራይ ፈጣን ዕድገትና በህዝቡ ዘንድ ተቀባይነት እያገኘ መሄድ ያስደነጋጣቸው የህወሓት ካድሬዎችና መሪዎቻቸው እንቅስቃሴውን ለመግታት የማይፈንቅሉት ድንጋይና የማይሸርቡት ተንኰል እንደሌለ በተደጋጋሚ አይተናል። ዛሬም እንደለመዱት አዲስ የማጥቃት ስልት በመቀየስ ነብሰ ገዳይ፣ በታኝና አፋኝ የዱሩየዎች ቡድን በተለያየ መልኩ በሕቡእና በግልፅ በማደረጃት በአረና አባላትና መሪዎች ላይ አዲስ የመንጥር ዘመቻና ጥቃት ጀምሯል።
የማጥቃት ዘመቻው ቀደም ብሎ በሽሬ እንዳስላሴ የተጀመረ ሲሆን ሰሞኑን ደግሞ በባሰ መልኩ በአዲ ግራት ከተማና በሌሎች አካባቢዎችም በስፋት ቀጥሏል። በዚሁ ተከታታይ ዘመቻቸው ያነጣጠሩት አረና ትግራይ የጠራውን ስብሰባ እየተከታተሉ መበተን፣ ህዝቡን ወደ ስብሰባው እንዳይሄድ በተለያዩ ዘዴዎች ማስፈራራትና ማሰናከል፣ በታኝ የዱሩየዎች በዱን በማደራጀት ለመበጥበጥና ለማወክ ያለ የሌለ ሀይላቸውን በማንቀሳቀስ ስብሰባዎችን እንዲቋረጡ አድርጓል።
ጉዳዩን በቅርብ ተከታትለን እንዳረጋገጥነው የሚያሳዝነውና የሚያስገርመው ስብሰባውን መበተኑና መቋረጡ ብቻ ሳይሆን ህዝቡን ለመቀስቀስ በአካባቢው የተሰማሩ በሶስት ከፍተኛ የአረና ትግራይ መሪዎች በአፋኝና በታኝ ቡድን እንዲደበደቡ ማደረጋቸውና ማሰራቸው ነው። የዚሁ ጥቃት ሰለባ ከሆኑት ሰዎች ውስጥ አቶ አስገደ ገብረስላሴ የቀድሞ የህወሓት መስራችና አስልጣኝ የነበሩ፣ አቶ አብርሃ ደስታ የመቀሌ ዩኒቨርሲቲ የፓለቲካ ሳይንስ መምህርና ተመራማሪ፣ አቶ ዓንዶም ገብረስላሴ የዓረና ማእከላይ ኮሚቴ አባልና የህዝብ ግንኙነት ሃላፊ ይገኙባቸዋል።
በአንጋፋ ወንድሞቻችን ላይ የደረሰባቸው ኢ ሰብኣዊ ጥቃት እጅጉን ያስቆጣንና ያስገረመን ቢሆንም በኛ እምነት ይህ ሁሉ ግፍና መሰሪ ተግባር በድምር ሲታይ የሚከተሉትን ሓቆችንና ክስቶችን የሚያመላክቱ የስርዓቱን ባህርይ ገላጭ ናቸው ብለን እናምናለን።
1. ህወሓት ታሪክ፣ ባህልና ሕግ የማይገዛው፣ መሰረታዊ እውነታዎችንና ዲሞክራሲያዊ መርሆዎችን የሚፃረርና የህዝቡን ሉዓላዊ ህልውና የሚያፈርስ የጥፋት መንገድ እየተከተለ በመሄድ ላይ እንደሆነ የሚያሳይ የቀቢፀ ተስፋ እርምጃ መሆኑን ራሱ በራሱ ጋሃድ እየሆነ መምጣቱ የሚያመላክት ነው።
2. ይህ ዓይነቱ ጭካኔ የተሞላበት ድርጊት የሚያሳየን ህወሓት ራሱን ከመንግስትነት ወደ ተራ ዘራፊነትና ማፊያነት በመቀየር የዜጎችን ድህንነት ለመጠበቅ የማይችል ሕገ አልባና የሻገተ ስርዓት መሆኑን ራሱን በራሱ እያስመሰከረ ያለ ድርጅት መሆኑን እንገነዘባለን። አንድ መንግስት በራሱ ህዝብና በገዛ ወገኑ ላይ ነብሰ ገዳይና አፋኝ ቡድንን በማደራጀት ዜጎቹን በአደባባይ ማስደብደብ ማለት የባዕድ ወራሪ እንኳን ያላደረገው ከዚህ የባሰ ጭካኔ፣ ውድቀትና ዝቅጠት አለ ብለን አናምንም።
3. የህወሓት ፀረ ህዝብ ተግባር ለይስሙላ ስለዲሞክራሲና ስለየብዙሃን ፓርቲ ስርዓት ይናገር እንጂ በተግባር በህዝብ ፊት ቀርቦ ለመከራከርና ለመዳኘት አቅምና ሞራል የሌለው፣ በህዝቡ ዘንድ ምን ያህል የተተፋና ጊዜ የጣለው ድርጅት መሆኑን ቁልጭ አድርጎ የሚያሳይ ነው። ህወሓት የትግራይ ህዝብን ነፃነትና ደህንነት ጠባቂ ለመሆን ቀርቶ የነገ የሀገር ተረካቢና ተስፋ የሆነውን ወጣት በነፃነት አየር ተኰትኵቶና የወገንና የሀገሩን ፍቅር ተላብሶ እንዳያድግ ወኔን የሚያኰላሽ ትውልድ ገዳይ ድርጅት መሆኑን ከተግባሩ በላይ ሌላ ምስክር የሚያሻ አይደለም።
4. ህወሓት የትግራይ መንግስት ነኝ ይበል እንጂ ራሱ የፃፈውን ሕገ መንግስት እንኳ ጠንቅቆ የማያውቅ፣ በተግባር የሕገ መንግስቱን መሰረታዊ መርሆዎችን የሚፃረር ስራ የሚሰራ አፍራሽ ድርጅት መሆኑን ራሱን በራሱ እያስመሰከረ ይገኛል። የትግራይ ህዝብ እየተዳደረ ያለው ራሱ ባፀደቀው ሕገ መንግስት መሰረት ሳይሆን ገና በበረሃ የነበረው የደደቢት የካድሬ ሕግ መሆኑን ካለው ተጨባጭ ሁኔታና ከተግባራቸው መረዳት ይቻላል።
5. ህወሓት የትግራይ ህዝብ ነፃ አውጪ ነኝ በማለት የትግራይ ህዝብ ነብዪ መስሎ ለመቅረብ ይሞክር እንጂ በተግባር ግን የታገለለትን አላማ የሚፃረር ስራ የሚሰራና የህዝቡን ተስፋ እያጨለመ የሚገኝ ድርጅት መሆኑን ራሱ በራሱ እያስመሰከረ ይገኛል።
6. የጥቃቱ መንሲኤ ካድሬዎቹ እንደሚሉት የአረና ትግራይ አባላትና ደጋፊዎቻቸው የህዝብ ጠላት ስለሆኑ፣ ሕግ ስለጣሱ፣ የትምክሕተኞች አመለካከት ስለሚያራምዱ ወይም የደርግ ስርዓትን ዳግም ለመመለስ የሚታገሉ ስለሆኑ አይደለም። አረና ትግራይ ሕገ መንግስቱ የሚጠይቃቸው መመዘኛዎችን አሟልቶ በሕጋዊ መንገድ ተመዝግቦ በሰላማዊ መንገድ የሚታገል ድርጅት መሆኑን ይታወቃል። ይሁን እንጂ “አያ ጅቦ ሳታማኸኝ ብላኝ” እንደሚባለው ሁሉ ከጥቃቱ በስተጀርባ ያለው ሚስጢር ግን ባንድ በኩል ገዢው ፓርቲ በሀገር ደረጃ በተለይም በትግራይ ምድር እነሱ የማይቆጣጠሩት ትርጉም ያለው ነፃ የፓለቲካ ድርጅት እንዲፈጠር ፍፁም አይፈልጉም። በሌላ በኩል ደግሞ በትግራይ ህዝብ ላይ ያላቸው ንቀትና ዝቅተኛ ግምት የሚያሳይ ነው። ሕብረተሰቡ በፓለቲካ ድርጅትና በህዝብ መካከል ያለው ግንኙነትና ነፃነት፣ የዲሞክረሲ “ሀ ሁ”፣ ሕገ መንግስታዊ መብቱንና ታሪኩን በትንሹ ያውቃል ብለው ቢገምቱት ኖሮ እንዲህ ዓይነቱ ዓይን
ያወጣ አረሜናዊ ተግባር አይፈፁምም ነበር።
የተከበራችሁ በሀገር ውስጥና በውጭ የምትኖሩ ውድ ኢትዮጵያውያን!!
እኛ በዲያስፓራ የምንኖረው የአረና ትግራይ የድጋፍ አስተባባሪ ኮሚቴና መላ የትግራይ ተወላጆች በሀገራችን ኢትዮጵያ ውስጥ በየማዕዝናቱ በተለይም በበንሻንጉል፣ በጋምቤላ፣ በደቡብና በሌሎች ቦታዎች በወገኖቻችን ላይ የሚፈፀሙ አፈናዎችና እንግልት በቅርብ ስንከታተልና በተለያየ መልኩ ድምፃችንን ስናሰማ ቆይተናል። በቅርቡ በሳውዲ ዓረቢያ በሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ወንድሞቻችንና እህቶቻችን ላይ የደረሰው ልብ ሰባሪ የሆነ አሳዛኝና አሳፋሪ ዜና ስንሰማም በቁጣ ስሜት በመነሳሳት በያለንበት ከሌሎች ወገኖቻችን ጎን በአደባባይ ቆመን ጭኾናል። አውግዘናልም። ዛሬም በተመሳሳይ መልኩ እንደተለመደው በትግራይ በወገኖቻችን ላይ እየተካሄደ ያለው ጥቃትም ከዚሁ ተለይቶ የማይታይ ስለሆነ አሁንም የተሰማንን ቁጣና ብሶት ይህንን የጋራ መግለጫ በይፋ እንድናወጣ ተገደናል። ያልታደለች ሀገር ሁሉጊዜ መርዶ ነውና!!
ትግራይ እንደነ አሉላ አባ ነጋና ዮሐንስ የመሳሰሉ የብዙ ጀግኖች ዓፅም የተቀበረባትና አኩሪ ታሪክ ያላት ምድር ብትሆንም ዛሬ ህዝብዋ በአንድ ቤተሰባዊ ቡድን ለሚመራ ፓለቲካዊ ድርጅት በሞኖፓልና በንብረትነት ለማገልገል የተፈጠረ ህዝብ አድርገው በመቁጠር እንደ ህፃን ልጅ አፍህን ያዝ እየተባለ በካድሬ ዱላ እየተኰረኰመ ሲኖር ማየች እጅግ የሚያሳዝን የታሪክ ጠባሳ ነው። ስለሆነም ህወሓት በህዝቡም ሆነ የተለየ አመለካከት ይዘው በሚንቀሳቀሱ ወገኖቻችን ላይ የሚያካሂደው የስነ ልቦናና የአክል ጥቃት የዲሞክራሲ መርህ የሚፃረር ኢ ሰብኣዊ ተግባር ብቻ ሳይሆን የዜጎች ሕገ መንግስታዊ መብት የሚጥስ ሕገ ወጥ ተግባር ስለሆነ ድርጊቱን እናወግዛን። እንዲሁም በግፍ የታሰሩ ወገኖቻችን ከእስር እንዲፈቱና በነሱ ላይ ድብደባ ያደረሱ የማፊያና የነብሰ ገዳይ ቡድን አባላትም በአስቸኳ ለፍርድ እንዲቀርቡ አበክረን እንጠይቃለን። በስልጣን ላይ ያለው ገዢው ፓርቲ ዜጎቻችንን ለያይተህ ግዛ በሚል ፈሊጥ በየተራ እንደ ፈለገ እያጠቃን እንዲኖር ምቹ ሁኔታ የፈጠርንለት እኛው ራሳችን በተለያየ ጎራ የየራሳችን ጎጆ አበጅተን በረባም ባልረባም በመነጣጠላችን መሆኑን እሙን ነው። ህዝብ ከተባበረ ምን ዓይነት ለውጥ ሊያመጣ እንደሚችል በሌሎች አጋጣሚዎች አይተናል። ስለዚህ በሀገር ቤትም በውጭም የምንኖር ኢትዮጵያውያን ሁሉ ለሀገርና ለወገን ሲባል መለስተኛ ልዩነታችንን ወደ ጎን ትተን በዜጎቻችን ላይ እየደረሰ ያለው አስነዋሪ ጥቃት በጋራ ልንቆምላቸው ይገባል። በመሆኑም ዛሬ በትግራይ ወገኖቻችን ላይ እየደረሰ ያለው በደል ነገ በሌሎች ክልሎችም የሚደርስ ጉዳይ ስለሚሆን ድርጊቱን በጋራ እንድናወግዘው ወገናዊ ጥሪያችንን እናቀርባለን።
ጀግናው ኩሩና ታጋሽ የትግራይ ህዝብም በአካል ይቆጣጠሩት ይሆናል እንጂ የህወሓት ካድሬዎችና መሪዎቻቸው የሚሰሩትን አስቂኝና አሳዛኝ ድራማ ይስቷል ብለን አናምንም። ማን በሙሱና ተነክሮ ጨለማ ለብሶ የሀገርና የህዝብ ሀብት እየዘረፈና ወደ ዉጭ እያሸለከ እንዳለ ማን ደግሞ ለሀገሩና ለወገኑ በፅናት እየታገለ እንዳለ በውል ይገነዘባል። ትላንት ማን ከጎኑ እንደቆመ ማን ደግሞ ለሻዕቢያ ወረራ ለጅብ አሳልፎ እንደሰጠው ስለሚያስታውስ የጊዜ ጉዳይ እንጂ ልቡ ከማን ጋር እንዳለ ጠንቅቀን እናውቃለን። በአጠቃላይ የትግራይ ህዝብ ክብሩንና ማንነቱን በሻዕቢያ በመደፈሩ፣ ለም መሬቱንና አንጡራ ሀብቱን ለባዕድ አሳልፎ በመሰጠቱ፣ ራሱ የሰራውን ቤት፣ በደሙና በአጥንቱ ራሱ የገነባትን ሀገር ፈርሶ የባሕር በር የሌላት ጎራዳና ሽባ ሀገር ይዞ በመቅረቱ ደስተኛ ነው ብለን በፍፁም አናምንም።
ስለሆነም ዛሬም ለገዢው ፓርቲ ህወሓት/ኢሕአዴግ መሪዎችና ካድሬዎቻቸው ደግመን ደጋግመን ልናስገነዝባቸው የምንፈልገው ጉዳይ አንድና አንድ ብቻ ነው። በሀገራችን ፍትሕ የጠማው፣ በረሃብ አለንጋ የሚገረፍና በልቡ የሸፈተ ህዝብ እስካለ ድረስ እናንተ የምትፈፅሙትን ጊዜው ያለፈበትና አረሜናዊ የቀቢፀ ተስፋ እርምጃ ትግሉን የበለጠ እንዲግልና እንዲጎለብት ያደርገዋል እንጂ በፍፁም አይገታውም። እኛም የበለጠ እንድንጠነክርና ቀና ብለን በፅናት ከህዝባችን ጎን እንድንቆም ያደርገናል እንጂ አንገታችንን እንደማንደፋ ደግመን ልናረጋግጥላችሁ እንወዳለን።
ኢትዮጵያ ሀገራችን ለዘላለም ትኑር

Ethiopian refugee misunderstands South Sudan curfew, nearly loses life

January 28/2013

Ochalla receives treatment for a bullet wound at a UNHCR-run clinc in Gorom settlement near Juba, home to some 2,400 Ethiopian refugees.

GOROM SETTLEMENT, South Sudan, January 27 (UNHCR) – Punctuality is usually praised as a virtue, but how often is tardiness fatal? For Ochalla Omot, an Ethiopian refugee, a misunderstanding over an hour and a half nearly cost his life.

“I just could not believe I was going to die like that,” the 27-year-old says while receiving treatment for a bullet wound incurred after he got the hours of a government-imposed curfew wrong. He’s receiving treatment in a UN-run clinic in Gorom Settlement, some 25 kilometres west of Juba, the South Sudanese capital. The settlement is home to 2,400 Ethiopian refugees who live in their own small houses and compounds.

After fighting broke out in Juba last month and quickly spread to seven of the country’s 10 states, the government imposed a curfew requiring all civilians to stay off the streets during specified hours. It was relaxed slightly last week, but for more than a month, civilian movement was banned in the capital from 6 p.m. to 6 a.m.

However, Ochalla was firmly convinced he could stay out two hours later. He set out for Juba one morning earlier this month to look for work as a casual laborer and got caught up in the crisis, which is taking a heavy toll on South Sudanese. UN reports show the month-old conflict has claimed more than 1,000 lives and displaced more than 500,000 people, including more than 120,000 who fled to neighbouring countries as refugees.

“I spent the day looking for work and it was about 7:30 pm when I finally set out to go to the area of Juba where I sleep with friends,” he says, still visibly shaken, despite receiving medical care.
He was stopped by armed men who ordered him to sit by the side of the road – still unaware he had violated the curfew. “I sat down, but when I saw one of them preparing his gun to shoot, I started running without even knowing it, with bullets being shot at me.”

One of the bullets hit his left arm. But he kept running, ignoring the blood gushing from his arm. When he finally reached his destination, the only thing his hosts could do was tie a cloth around his arm to staunch the bleeding. “They could not take me to a health centre because of the curfew.” He only got medical care the next day when he returned to this settlement.

Since he fled ethnic tensions in Ethiopia’s Gambella region in 2008, Ochalla has occasionally worked in Juba to earn money to supplement his monthly food rations. It’s also an escape from the boredom of the camp.
He had been an 11th Grade student when he had to flee Ethiopia, but for one reason or another, has never been able to complete his education in South Sudan.

Now, he says, his close brush with death has rekindled an old dream – to become a doctor. “The fact that I survived all the shooting in Juba means that I will live long enough to achieve my dream,” he says, as a medic – a fellow refugee – tends to his bullet wound.

By Kisut Gebre Egziabher in Gorom Settlement, South Sudan

Source: UNHCR
Author: UNHCR

ህወሓቶች አደብ ግዙ! (አብርሃ ደስታ)

January 28, 2014
በሌሎች ላይ የምትፈፅሙት ተግባር ሁሉ በራሳቹ ላይ እንደምትፈፅሙ (እንደሚፈፀም) አስቡ። በስልጣን ላይ ያለ ሁሉ በስልጣን አይኖርም። የስልጣን ዕድምያቹ በጣም አጪር መሆኑ እናንተም ታውቁታላቹ። በሰዎች ላይ ግፍ ስትፈፅሙ ሰዎች ይጠሏችኋል። በሰዎች ስትጠሉ የስልጣን ዕድምያቹ ያጥራል። እናንተ ያላቹ የህዝብ ድጋፍ ሳይሆን ጠመንጃ ነው። ጠመንጃ ስልጣን ለመያዝ ይረዳ እንደሆነ እንጂ በስልጣን ለመቆየት አያስችልም። ስለዚህ በጠመንጃ አፈሙዝ የስልጣን ዕድምያቹ ለማራዘም የምታደርጉት ጥረት ከንቱ ልፋት ነው።
Abraha Desta the facebook
አብረሃ ደስታ
እናንተ ከስልጣን ወርዳቹ ስልጣን የህዝብ ሲሆን፣ ፍትሕ ሲነግስ፣ እኩልነት ሲሰፍን ለፈፀማችሁት ወንጀልና ላደረሳችሁት በደል በሕግ እንደምትጠየቁ አያጠራጥርም። በስልጣን የኖረ የለም። እንኳን አምባገነኖች ዴሞክራሲያዊ ስርዓቶችም በስልጣን ኮረቻ ተቀምጠው ለዘላለም አይኖሩም።
ምናልባት እናንተ ምግባራችሁ አውቃቹ በህዝብ ስትተፉ ሀገር ለቃችሁ በመውጣት ለማምለጥ ትሞክሩ ይሆናል። ገንዘቡም አላቹ። ሁሉም ካድሬዎች (በሰዎች ላይ ግፍ እንዲፈፅሙ እየታዘዙ ያሉ የህወሓት አባላት) ግን እንደናንተ (እንደ ህወሓት መሪዎች) ከሀገር ወጥተው ለማምለጥ ዓቅሙ የላቸውም። ደግሞ ዓቅሙ ቢኖራቸውስ ለምን በሰሩት ጥፋት ከሀገራቸው ለመሰደድ ይወሰንባቸባል? የህወሓት ባለስልጣንናት ከስልጣን ወርደው በሀገራቸው በሰላም የሚኖሩበት ሁኔታ ለምን አያመቻቹም? ለምን መርሃቸውን ከ “ስልጣን ወይ ሞት” ወደ “ስልጣን ለህዝብ አስረክቦ በሀገር በሰላም መኖር” አይቀይሩም? ለካድሬዎቹስ አያስቡም እንዴ? የህወሓት ዕድሜኮ ትንሽ ነው። ህወሓት ሲሞት የህወሓት አባላትም ከህወሓት ድርጅት ጋር አብረው መሞት የለባቸውም። ህወሓትም ስልጣን ለህዝብ አስረክቦ ተቃዋሚ ፓርቲ ሁኖ መቀጠል ይችል የለ?! ዕድምያችሁ ከህወሓት ድርጅት ዕድሜ በላይ እንዲሆን አድርጉ።
እኛ ሰለማዊ ታጋዮች ነን። ያላቹ ሃብትና ጠመንጃ በመጠቀም እኛን መደብደብ፣ ማሳሰር፣ ማሰቃየት፣ መግደል ትችላላቹ። አምባገነን ስርዓት የሚችለው ነገር ቢኖር ሰው ማሳሰርና መግደል ነው። የዓላም አምባገነን መሪዎች በማሳሰርና በመግደል የስልጣን ዕድምያቸው ዘለአለማዊ ማድረግ ከቶ አይቻላቸውም። ዛሬ እኛን ብትደበድቡና ብትገድሉ ዕድምያቹ እያሳጠራቹ እንጂ እያሸነፋቹ አይደላችሁም። እኛ ብንገደል ሌላ ሰው አለ። ሁሉም ሰው መግደል አይቻልም። ምክንያቱም ሁሉም ሰው ከተገደለ ማንን ትጨቁናላቹ? የሚጨቆን ሰው ያስፈልጋችኋል። ሰው ጭቆና ሲበዛት በመሪዎቹ ላይ ያምፃል። እናም ትሸነፋላቹ። አምባገነን ተሸናፊ ነው። የማይሸነፍ ህዝብ ብቻ ነው። ምክንያቱም ህዝብ ለጭቆና አይነሳም።
እኛን በማሰቃየት ሰለማዊ ትግሉ መግደል አይቻልም። ሰለማዊ ትግሉ በመግደል የሰዎች የነፃነት ጥያቄ መግደል አይቻልም። የሰዎች የነፃነት ጥያቄ በመግደል ሰዎችን ለዘላለም መጨቆን አይቻልም። ስለዚህ መሸነፋቹ አይቀርም።
የሰለማዊ ትግል በር ባትዘግቡን መልካም ነው። ምክንያቱም ደም መፋሰሱ፣ ጦርነቱ፣ መጠፋፋቱ አንፈልገውም። እኛ የምንፈልገው ሰላም ነው። መንገዳችንም ሰለማዊ ነው። የሰላም በር ሲዘጋብን እጆቻችንና እግሮቻችን አጣጥፈን እንቀመጣለን ማለት ግን አይደለም። አንድ በር ሲዘጋ ሌላ በር ማንኳኳታችን ግድ ነው። ነፃነት እንፈልጋለንና። “መታፈን ይብቃን!” ብለን ተነስተናል። ስለዚህ ትግላችን በምንም ዓይነት ስትራተጂ ማስቆም አይቻልም። የሚቻለው ስልጣን ለህዝብ ማስረከብ ነው። ዴሞክራሲ ማስፈን ነው።
ገዢዎች በሐሳብ መከራከር ሳይችሉ ሲቀሩ ወደ ሀይል እርምጃ እንደሚወርዱ እናውቃለን። ሐይል መጠቀም የሽንፈት ምልክት ነው። ህወሓት የፈሪዎችና የጨካኞች ስብሰብ መሆኑ አውቅ ነበረ፤ ወደ ድንጋይ ውርወራ ፖለቲካ ይወርዳል የሚል ግምት ግን ፈፅሞ አልነበረኝም። መንግስት ወንጀልን መከላከል ሲገባው ወንጀል ፈፃሚ ሆነ።
ህወሓት ዉስጧ መበስበሱ እየሸተተን ነው። ምናለ ድንጋይ ባለመወርወር ገመናችሁ ባታጋልጡ? ለማንኛውም አደብ ግዙ የምትሰሩትን እወቁ። በሃይል የሚሆን ነገር እንደሌለ ተረዱ። ካለፉ ስርዓታት ታሪክ ተማሩ። ህዝብ እያያቹ ነው።
It is so!!!

2014 Golden Pen of Freedom awarded to jailed Ethiopian journalist

January 27, 2014
World Association of Newspapers and News Publishers (WAN-IFRA)
Eskinder Nega, an Ethiopian publisher, journalist and blogger
Eskinder Nega
Eskinder Nega, an Ethiopian publisher, journalist and blogger who is serving an 18-year jail sentence under anti-terror legislation, has been awarded the 2014 Golden Pen of Freedom, the annual press freedom prize of the World Association of Newspapers and News Publishers (WAN-IFRA).
Mr Nega was arrested on September 14, 2011 after publishing an article criticising his government’s use of the 2009 Anti-Terror Proclamation to jail and silence critics, including Ethiopian actor and activist Debebe Eshetu.  He was sentenced on 23 January 2012 and denounced as belonging to a terrorist organisation.
In making the award, the WAN-IFRA Board sent a message to the Ethiopian government that misusing anti-terror legislation to jail journalists and those critical of his government is unwarranted and against international protocols, including the Vienna Declaration on Terrorism, Media and the Law.
“This award recognises the courage of Eskinder Nega to speak out despite the risks that saw him jailed under his country’s draconian and overly broad anti-terror laws,” said WAN-IFRA President Tomas Brunegård, speaking on behalf of the Board.
“We call on the Ethiopian government to release Eskinder Nega and all journalists convicted under the sedition provisions, including Solomon KebedeWubset TayeReyot Alemu,and Yusuf Getachew”, said Mr Brunegård, who recently visited Ethiopia as part of an international mission that found that the country’s publishers and journalists practice journalism in a climate of fear.
The Golden Pen of Freedom is an annual award made by WAN-IFRA since 1961 to recognise the outstanding action, in writing or deed, of an individual, a group or an institution in the cause of press freedom. More on the Golden Pen can be found athttp://www.wan-ifra.org/node/31099
The award will be presented on 9 June during the opening ceremonies of the World Newspaper Congress, World Editors Forum and World Advertising Forum, the global summit meetings of the world’s press, to be held in Torino, Italy.
In an opinion piece published in the New York Times, Mr Nega said of his imprisonment: “I’ve never conspired to overthrow the government; all I did was report on the Arab Spring and suggest that something similar might happen in Ethiopia if the authoritarian regime didn’t reform… I also dared to question the government’s ludicrous claim that jailed journalists were terrorists.”
WAN-IFRA has been vocal in their opposition to Ethiopia’s misuse of anti-terror legislation, writing to late Prime Minister H.E. Meles Zenawi in 2012 requesting the immediate release of Mr Nega and most recently demanding his release, along with four other imprisoned journalists, in a joint international press freedom mission to Ethiopia, conducted with the International Press Institute. The full report from the international press freedom mission can be found at http://www.wan-ifra.org/node/97172
Mr Nega opened his first newspaper, Ethiopis, in 1993, which was soon shut down by authorities due to its critical reporting. He then, along with his wife Serkalem Fasil, managed Serkalem Publishing House, responsible for newspapers such as Asqual, Satenaw and Menelik, all of which are currently banned in Ethiopia.  He has also had his journalist’s licence revoked since 2005, but continued to publish articles despite the ban.
Mr Nega is no stranger to being imprisoned due to his writings. He was detained at least seven times under Prime Minister Meles Zenawi.  This included a 17-month jail sentence, along with his wife, on treason charges for their critical reporting on the Meles government’s violent response to peaceful protests that followed the disputed 2005 elections.
WAN-IFRA, based in Paris, France, and Darmstadt, Germany, with subsidiaries in Singapore and India, is the global organisation of the world’s newspapers and news publishers. It represents more than 18,000 publications, 15,000 online sites and over 3,000 companies in more than 120 countries. Its core mission is to defend and promote press freedom, quality journalism and editorial integrity and the development of prosperous businesses.

አንድነት ህወሓት/ኢህአዴግ የትግራይ ህዝብ አማራጭ ሀሳብ እንዳያገኝ እያካሄደ ያለውን አፈና አጥብቆ እንደሚቃወም ገለጸ

January 28/2014
(ዘ-ሐበሻ) አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ ለዘ-ሐበሻ በላከው መግለጫው “ህወሓት/ኢህአዴግ የትግራይ ህዝብ አማራጭ ሀሳብ እንዳያገኝ እያካሄደ ያለውን አፈና አጥብቀን እንቃወማለን” ሲል አወገዘ።

የትግራይ ህዝብ እንደ ሌላው ኢትዮጵያዊ ሁሉ የዴሞክራሲ ዕጦት ሰለባ እንደሆነ ፓርቲያችን ያምናል ያለው አንድነት ስርዓቱ በየትኛውም የኢትዮጵያ ክልል እንደሚያደርገው በትግራይም ሰብዓዊ መብት ይረግጣል፣ ፍትህ ይደፈጥጣል፣ በካድሬዎች ይደበደባል፣ ይንገላታል፣ እንዲሰደድ ይደረጋል፡፡ ስርዓቱና በስርዓቱ ውስጥ የደላቸው ሹማምንት በስሙ ከመነገድ በዘለለ ዋጋ የተከፈለበትን ዴሞክራሲያዊ ስርዓት ዘርግቶ ተጠቃሚ ማድረግ አልቻለም ሲል በመግለጫው ላይ አስቀምጧል።


     
        የመቀሌ ከተማ (ፋይል)

“ህወሓት/ኢህአደግ ክልሉን እንደዋና ካምፕ በማየት በአፈና ውስጥ እንዲኖር አድርጎታል፡፡ የትግራይ ህዝብ የነፃ ፕሬስ ውጤቶችን እንዳያገኝ፤ አማራጭ የፖለቲካ ፓርቲዎችን እንዳያዳምጥ የተፈረደበት ሕዝብ ነው ማለት ማጋነን አይደለም፡፡ ይሄ እውነትም ሕወሓት/ኢህአዴግ በተለያየ ጊዜ በህዝቡ ላይ በፈፀማቸው ኢ-ዴሞክራሲያዊና ኢ-ፍትሃዊ ድርጊቶች የታየ ነው፡፡” የሚለው የአንድነት መግለጫ ” ለዚህ ማሳያ የሚሆነው አምባገነኑ ህወሓት/ኢህአዴግ አረና ባለፈው ሳምንት በትግራይ ክልል አዲግራት ከተማ ሊያደርግ የነበረው ሕዝባዊ ስብሰባ ልክ እንደ ከዚህ ቀደሙ ሁሉ ታፍኖበታል፣ አባላቱ ተደብድበዋል እንዲሁም ታስረዋል፡፡ ይሄ የሆነበት ምክንያት የትግራይ ህዝብ አማራጭ እንዳያገኝና በጉልበት የህወሓት አንጡራ ሀብት ብቻ ሁኖ እንዲያገለግል ከመፈለግ ነው፡፡ ከዚህ በፊትም ፓርቲያችን በመቀሌ ከተማ ሊያደርግ የነበረው የተቃውሞ ሰልፍ በከፍተኛ አፈናና እስር እንዲያስተጓጉል መደረጉ የቅርብ ግዜ ትዝታ ነው፡፡ አንድነት ፓርቲ የትግራይ ህዝብ አማራጭ ሓሳብ የማዳመጥ፣ የሚጠቅመውን የመምረጥና የመቃወም ሕገ-መንግስታዊ መብቱ የተጠበቀ መሆኑን በፅኑ ያምናል፡፡” ብሏል።

አማራጭ ሓሳብ በሚያቀርቡ ፓርቲዎች ላይ ህወሓት/ኢህአዴግ እየወሰደ ያለውን ኢ-ዴሞክራሲያዊ ርምጃና አፈና በጥብቅ እንደሚያወግዝ ያስታወቀው አንድነት “አንድነት የአረና ፓርቲ የሚያደርገውን ዴሞክራሲያዊ እንቅስቃሴ ተከትሎ ህወሓት/ኢህአደግ ለማደናቀፍ የሚያደርገውን ህገወጥ ዘመቻ እንዲያቆም እየጠየቀ አሁንም ተቃዋሚዎችን ‹‹ከጠላቶቻችን ጋር የሚተባበሩ›› በማለት የትግራይን ህዝብ ከሌላው ኢትዮጵያዊ ለመነጠል የሚካሄደውን ዘረኝነት የተሞላበት ከፋፋይ ርምጃ ለአገራችን እጅግ አደገኛ እንደሆነ አምኖ እንደ ሌላው ህዝብ ሁሉ ለነፃነቱ መከበር የሚያደርገውን ትግል አጠናክሮ እንዲቀጥልና ሰላማዊ ትግሉን በመደገፍ ዴሞክራሲያዊ ስርዓት እውን እንዲሆን የከበረ ጥሪ እናቀርባለን፡፡” ሲል መግለጫውን ቋጭቷል።

በኖርዌይ ኢትዮጵያውያን የተቃውሞ ሰልፍ አደረጉ

January 28/2014

ጥር ፲፱ (አስራ ዘጠኝ) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- “ባልመረጥነው መጅሊስ  አንተዳደርም!  ያላመንንበትን የሀይማኖት አስተምህሮ አንቀበልም! የህዝበ-ሙስሊሙ የትምህርት ተቋም የሆነው አወሊያ ትምህርት ቤት  በገለልተኝነት ይተዳደር” የሚሉ የመብት ጥያቄዎችን በማንሳታቸው የ አሸባሪነት ክስ የተመሰረተባቸው የሙስሊም አመራሮች ወደ ወህኒ ከወረዱ ከሁለት ዓመታት በላይ ተቆጠሩ።
























ለሁለት ዓመታት ከዘለቀው የፍትህ ሂደት በሁዋላ  በቅርቡ  ለብይን  በተቀጠረው  ችሎት ላይ በብዘዎች ሰንድ ታሳሪዎቹ  በሙሉ ይፈታሉ የሚል ተስፋ የነበረ ቢሆንም፤  አብዘኞቹ እና ወሳኞቹ አመራሮች በፍርድ ቤት ጥፋተኛ ተብለው እንዲከላከሉ ውሳኔ መተላለፉ፤   የሙስሊሙን ህብረተሰብ ብቻ ሳይሆን  የፍትህና የሰብዓዊ መብት ጉዳይ የሚያሣስባቸውን ሌሎች ወገኖችም ጭምር ያሳዘነ ሆኗል።

ይህ የፍርድ ቤቱ ውሳኔ ከሲህም ባሻገር ለተወሰነ ጊዜ  ከተቃውሟቸው “ፋታ” በመውሰድ  የመሪዎቻቸውን መፈታት በተስፋ ሢጠባበቁ የነበሩትን በርካታ ሙስሊሞች  በማስቆጣት ዳግም  የተቃውሞ ትግላቸውን እንዲቀጥሉ ምክንያት መሆኑ ይነገራል።
ባለፈው ሳምንት መገባደጃ ላይ  በዋለው ጁምአ፤ በኢትዮጵያ  ከ40 በሚበልጡ ከተሞች  በሚገኙ መስጊዶች ውስጥ  በእስር ላይ የሚገኙ የሙስሊም አመራሮችን ለመሰከር የተዘጋጀው የሰደቃ እና የዱዓ ሥነ-ስርዓት በስኬት መጠናቀቁ ይታወሳል።
ይህቀንበተለያዩ  የውጪአገሮችጭምር የሚኖሩ ሙስሊምና ክርስቲያን ኢትዮጵያውያኖች በአንድነት ሆነው ከፍተኛ ተቃውሞ ያሰሙበት እለት  ነበር። የተቃውሞ መርሐ-ግብሩ፣ ዱአ  (ጸሎት)  በማድረግ፤ ሰደቃ  (ምጽዋት) በመስጠት፣ ስብሰባ በማካሄድ በተቃውሞ ሰልፍና   በተለያዩ የአለም ክፍሎች ተካሂዷል።

በተለያዩ የውጪ አገራት ከተካሄዱት ሰልፎች መካከል-በኖርወይ ዋና ከተማ በኦስሎ የተካሄደውየተቃውሞ ሰልፍ ይገኝበታል።
የሰልፉ አላማ በአሁኑ ወቅት በኢትዮጵያ በተለያዩ እስር ቤቶች ውስጥ የሚገኙ የእስልምና ሀይማኖት መሪዎች፣ ጋዜጠኛችና ፖለቲከኞች  ያለ ምንም ቅድመ ሁኔታ እንዲፈቱ፣ በሀገሪቱ የእምነት ነጻነት እንዲከበርና መንግስት እጁን ከሀይማኖቶች ላይ እንዲያነሳ ለመጠየቅ፣ እንደነበር የሰልፉ አስተባባሪ ኮሚቴ ገልጿል።

የኦስሎ ሰልፈኛች፣ በ14 ሰዓት ሴንትራል ስቴሺን ፊት ለፊትካለው ከነብር ሀውልት አጠገብ  ከተሰባሰቡ በሁዋላ “ካርል ዮሀን” ተብሎ የሚጠራውን መንገድ ይዘው  ተቃውሟቸውን እያሰሙ ወደፓርላማው ተጉዘዋል።

ሰልፈኞቹ የኢትዮጵያን ሰንደቅ ዓላማ በማውለብለብ ፣  እንዲሁም የአቡበከር አህመድንና የያሲን ኑሩን ጨምሮ የሌሎች የታሰሩት  የሙስሊሙ መፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴ አባላትን ፣የእነ እስክንድር ነጋን፣   የእነ ርዕዮት አለሙን፣ የነበቀለ ገርባን፣ የነ አንዷለም አራጌን፣ የነውብሸት ታዬን እና የሌሎች የህሊና እስረኞችን  ፎቶ ግራፎች በማንገብ  እና መፈክሮችን በማሰማት በ ኢትዮጵያ እየተፈፀመ ያለውን ነገር ለኦስሎ ማህበረሰብ እና ለኖርዌይ ፓርላማ አባላት አሳይተዋል።

ሰልፈኞቹ ኖርዌጂያን ፓርላማ ጋር እንደደረሱ  ከመካከላቸው የተወከሉ ሁለት ኢትዮጵያውያን ወደ ፓርላማው ጽህፈት ቤት በመግባት የተዘጋጀውን ደብዳቤ ለፓርላማው ተወካይ አስረክብዋል።

የደብዳቤው ይዘት በኢትዮጵያ እየቀጠለ ያለው የሰብአዊ መብት ጥሰት ይገታ እና የታሰሩትም የህሊና እስረኞች ይፈቱ ዘንድ  የኖርወይ መንግስት በኢትዮጵያ መንግስት ላይ ዲፕሎማሲያዊ ጫና እንዲያደርግ  የሚጠይቅ ነው።
በሰልፉ ላይ በኖርዌይ የኢትዮጵያውያን ሙስሊም ተወካይ፣  በኖርዌይ የኢትዮጵያ ኮሚኒቲ ሊቀመንበር እና የስደተኛች ማህበር ጸሀፊ በየተራ  ንግግር አድርገዋል።

የበረዶው  ቁልል ለአይን የሚያስፈራና የቅዝቃዜውም መጠን ከባድ የነበረ ቢሆንም፤  ሰልፎኛቹ በብርቱ ጽናትና ዲሲፕሊን   ሁሉንም ተቋቁመው ፕሮግራሙን  በታሰበው መልኩ አካሂደዋል።

በሰልፉ ላይ ሙስሊምና ክርስቲያን ኢትዮጵያውያን በአንድ ላይ  እጅ ለእጅ ተያይሰው ከመሳተፋቸውም በላይ፤ “አንድ ህዝብ ነን፣ መቼም መቼም አንለያይም”ሲሉ ተደምጠዋል።



በሽብርተኝነት ህጉ ውይይት ስም የአዲስ አበባ ህዝብ እየተሸበረ ነው ሲሉ አንዳንድ ተወያዮች ገለጹ

January 28/2014

ጥር ፲፱ (አስራ ዘጠኝ) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በቅርቡ በአዲስ አበባ ውስጥ ለሚሰሩ የመንግስት ሰራተኞችና በተዋረድም ከህዝቡ ጋር እተደረገ ባለው የሽብርተኝነት ህግ ውይይት፣  ነዋሪዎች ጥላቸውን እንኳን ማመን እንደሌለባቸው በአሰልጣኞች እየተነገራቸው ሲሆን፣ በስልጠናው ላይ የተካፈሉ አንዳንድ የመንግስት ሰራተኞች፣ ስለሽብረተኝነት ልንማር ሂደን ተሸብረን መጣን ሲሉ ተናግረዋል።

በመንግስት  ከፍተኛ አመራሮች የተዘጋጀው የማሰልጠኛ ሰነድ ኢሳት እጅ የገባ ሲሆን፣ ሰነዱ ህብረተሰቡ ከመንግስት ጎን ቆሞ ልማቱን እንዲጠብቅና እንዲያፋጥን ይጠይቃል። በመስተዳድሩ የሚገኙ  የቢሮ ሃላፊዎች፣ በአዲስ አበባ ከፍተኛ የፖለቲካ አመራር በሆኑት በአቶ ተወልደ ወ/ጻዲቅ መሪነት በሰነዱ ላይ ውይይት አድርገውበታል ። በሰነዱ ላይ የመስተዳድሩ የየደረጃው  አመራሮችና ሲቪል ሰራተኞች እንዲሁም የከተማው  ህዝብ እየተወያዩበት ነው።

እስካሁን ባተካሄደው ውይይት እንደታየው የመንግስት ሰራተኞች በስልጠናው ላይ የሚገኙት የስም ምዝገባ ስላለ  እንጅ በዝግጀቱ አምነውበት አይደለም ይላሉ ተሳታፊዎች።

በውይይቶች ወቅት የመንግስት ባለስልጣኖች ከፍተኛ ትኩረት የሚሰጡት ከህዝቡ ስለሚጠበቀው ግዴታ መሆኑን የሚናገሩት ተሳታፊዎች ፣ የአገሪቷን ደህንነት ፖሊስና የደህንነት ሃይሉ ጠብቆ ስለማይችል፣ ህዝቡ ከኮሚኒቲ ፖሊስ ጋር በመተባበር ነቅቶ መጠበቅ እንዳለበት ባለስልጣኖች ማሳሰቢያ መስጠታቸውን ተሰታፊዎች ይገልጻሉ።

የፌደራል ፖሊስ ሽብርተኝነትን ለመከላከልና ወንጀለኛን ለመለየት የአፍና የጸጉር ምርመራ ሊያደርግ እንደሚችል፣ ምርምራው እንዲደረግበት የተጠረጠረ ሰው ፈቃደኛ ካልሆነ ተመጣጣኝ ሃይል በፖሊስ ሊወሰድበት እንደሚችል፣  በማንኛውም ጊዜ በድነገት በከተማ ባስና በታክሲ ላይ ፍተሻ ሊደረግ ስለሚችል ህዝቡ መተባበር እንዳለበት የመንግስት ባለስልጣናት ተናግረዋል።
የመንግስት ሰራተኞች  ቦርሳ፣ፌስታልና መሰል ቁሳቁሶችን ቢሮ ውስጥ ጥለው እንዳይሄዱ የተነገራቸው ሲሆን ፣ ቢሮ ውሰጥ የተገኙ ፌስታሎችና ቦርሳዎች ለአደጋ ከማጋለጣቸው በፊት በጥንቃቄ እንዲታዩ ምክር ተሰጥቷል።

ለማወያያነት በቀረበው ሰነድ ላይ በግልጽ እንደሚታየው “ከፍርድ ቤት ፈቃድ በመውሰድ በሽብርተኝነት የተጠረጠረን ሰው የስልክ፣ የሬዲዮ፣ የኢንተርኔት የኤሌክትሮኒክስ፣ የፋክስ፣ የፖስታ ግንኙነት እና የመሳሰሉ ግንኙነቶችን ለመጥለፍ ወይም ለመከታተል፣ ጠለፋውን ለማስፈፀም ወደ ማንኛውም ቤት በሚስጢር የመግባት ወይም ይህንኑ ለመፈጸም የሚያስችሉ መሳሪያዎችን ለማስቀመጥ ወይም ለማንሳት የፌደራል ፖሊስ ስልጣን ተሰጥቶታል።

እንዲሁም “ ማስረጃ ከሚሰበሰብባቸው የተለያዩ ዘዴዎች መካከል አንዱ በሽብርተኝነት ወንጀል ከተጠረጠረው ሠው ላይ ናሙናዎችን መውሰድ እና የህክምና ምርመራ እንዲያደርግ ማድረግ በመሆኑ ፣ ተጠርጣሪውም በምርመራ ሂደት ናሙናውን ለመስጠት ወይም የህክምና ምርመራ ለማድረግ ፍቃደኛ ካልሆነ ፖሊስ ተመጣጣኝ ኃይል ተጠቅሞ ናሙናውን የመውሰድ ሥልጣን ተሰጥቶታል፡፡

ሰነዱ “ የሀይማኖት አክራሪነትና አሸባሪነት ዋናው ምንጭ ድህነትና ተስፋ መቁረጥ ” መሆኑን ከገለጸ በሁዋላ ፣  ”ፍትሀዊ በሆነ መንገድ ተጠቃሚ የሚሆንበትን ፈጣን ልማት ለማረጋገጥ በመንግስት የወጡ ፖሊሲዎች፣ ስትራቴጂዎችና እቅዶች ተግባራዊ በማድረግ ሂደት ሰፊ ርብርብ ማድረግ” ከህብረተሰቡ እንደሚጠበቅ ይገልጻል።

ኢሳት አስተያታቸውን የጠየቃቸው ሰልጣኞች እንዳሉት ውይይቱ ህዝቡን የበለጠ የሚያሽብር ቢሆንም መንግስትም ሽብር ውስጥ መግባቱን ያመለክታል።

በሰነዱ ላይ  ኦነግ፣ ኦብነግ፣ ግንቦት7፣ አልሸባብና አልቃይዳ አሸባሪ ድርጅቶች ተብለዋል

Monday, January 27, 2014

ይግባኝ ተጠይቆባቸው ከነበሩት 6ሙስሊሞች መካከል የ2ቱን ይግባኝ ፍርድ ቤቱ ውድቅ አደረገው

January 27/2014

በዛሬው ዕለት አቃቤ ህጉ ይግባኝ ጠይቆባቸው የፌደራሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት 1ኛ ምድብ ችሎት ቀርበው ከነበሩት 6 ሙስሊሞች መካከል የህዝበ ሙስሊሙ መፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴ አባል በሆኑት ኡስታዝ ጀማል ያሲን እና በ ኡስታዝ ሃሰን አሊ ላይ አቃቤ ህጉ አቅርቦት የነበረውን የይግባኝ ጥያቄ ማንሳቱ አስታውቋል፡፡
በተቀሩት ላይ ግን ይግባኙን ያፀና ሲሆን ፍርድ ቤቱም ጉዳዩን ለማየት ለየካቲት 20 ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል፡፡
በታህሳስ 3 ቀን የፌደራሉ ከፍተኛው ፍረድ ቤት 4ኛው ምድብ ችሎት በኮሚቴዎቻችን እና በወንድሞቻችን ላይ የጥፋተኝነት ብያኔ ማስተላለፉ እና 10 የሚጠጉትን ደግሞ በነፃ እንዲፈቱ መወሰኑ የሚታወስ ነው፡፡
ይህንንም ውሳኔ ተከትሎ አቃቤ ህጉ በ 6ቱ ላይ ይግባኝ የጠየቀ ሲሆን በመጀመርያው የፍርድ ቤት ቀጠሮ ይግባኝ የተጠቀባቸው 6ቱም ሙስሊሞቸ መጥሪያ አልደረሳቸውመ በሚል ፍርድ ቤት ሳይገኙ በመቅረታቸው ፍርድ ቤቱ ተሟልተው እንዲቀርቡ ለጥር 19 ቀነ ቀጠሮ ሰጥቶ እንደነበር ይታወሳል፡፡
በዚህም ቀነ ቀጠሮ መሰረት ጉዳዩን የተመለከተው 6 ኪሎ መነን አካባቢ የሚገኘው ፍርድ ቤት ይግባኙን በመመርመር በ 2 ሙስሊሞች ላይ የቀረበውን ይግባኝ ውድቅ ያደረገ ሲሆን በተቀሩት 4 ሙስሊሞች ላይ ግን ሌላ ተለዋጭ ቀጠሮ ለየካቲት 20 መስጠቱን ምንጮች አስታውቀዋል፡፡
በህዝበ ሙስሊሙ መፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴ አባል በሆኑት በኡስታዝ ጀማል ያሲን እና በ ኡስታዝ ሃሰን አሊ ላይ አቃቤ ህጉ ያቀረበውን ይግባኝ ፍርድ ቤቱ ውድቅ ያደረገው ሲሆን በተቀሩት በሼህ ሃጂ ኢብራሂም ቱፋ፣በሼህ አብዱራህማን፣በወንድም አሊ መኪ እና በወ/ሮ ሃባ መሃመድ ላይ ቀረበውን ይግባኝ ለመመርመር ተጨማሪ ቀነ ቀጠሮ ለየካቲት 20 መስጠቱን ምንጮች አስታውቀዋል፡፡
ይግባኙ ውድቅ የተደረገላቸው
1.የህዝበ ሙስሊሙ መፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴ አባል የሆኑት ኡስታዝ ጀማል ያሲን
2. ኢስታዝ ሃሰን አሊ
ለየካቲት 20 ተለዋጭ ቀነ ቀጠሮ የተሰጣቸው
1. በሼህ ሃጂ ኢብራሂም ቱፋ
2. በሼህ አብዱራህማን፣
3. በወንድም አሊ መኪ እና
4. በወ/ሮ ሃባ መሃመድ ናቸው
በተያያዘም ዜና ፍርድ ቤቱ የጥፋተኝነት ውሳኔ ያስተላለፈባቸው የህዝበ ሙስሊሙ መፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴ አባላት እና የተቀሩት ወንድሞች ከ 3 ቀናት ቡሃላ በጥር 22 ፍርድ ቤት በመቅረብ የመከላከያ ምስክራቸውን ለተከታታይ 5 የስራ ቀናት ለፍርድ ቤቱ ማቅረብ እንደሚጀምሩ ለማወቅ ተችሏል፡፡
አላህ ፍትህን ያስፍንላቸው!!!

ሁለት ከፍተኛ የኦብነግ አመራሮች ከኬንያ በሕወሃት የደህንነት ሃይሎች ታፈኑ::

January 27/2014

የሕወሓት የጸጥታ እና የደህንነት ሰራተኞች አቶ ሱሉብ አህመድ እና አቶ አሊ ሁሴን የተባሉ የኦብነግ ( የኦጋዴን ብሄራዊ ነጻነት ግንባር ) አመራሮችን ትላንትና ከሰአት በኋላ ከናይሮቢ ከተማ አፍኖ መውሰዱ ተሰምቷል:; እነዚህ የታፈሁ ሁለት አመራሮች ባለፈው ጊዜ ወያኔ በናይሮቢ ከኦብነግ ጋር ባደረገው ምስጢራዊ የድርድር መድረክ ላይ ድርጅታቸውን ወክለው የተሳተፉ እና ለሶስተኛው ዙር ድርድር እየተዘጋጁ ያሉ ነበሩ:: ይህ አፈና የመጀመሪያው ሳይሆን ከዚህ ቀደም በተለያዩ ጊዜያት የሕወሓት የደህንነት ሃይሎች ወደ ኬንያ ዘልቀው በመግባት እጅግ በሚያሰቅቅ እና በኢሰብኣዊ ሁኔታ በሰላም ድርድሮች ላይ የተሳተፉ የተለያዩ የኦብነግ አባላትን አፍኖ በመውሰድ በመግደል ይታወቃል:: በ1998 የሕወሓት ሰራዊት ሶስት የኦብነግ የተደራዳሪ ቡድን አባላትን ገድሎ ሁለቱን በሃይል አፍኖ የወሰዳቸው ሲሆን ከግንባሩ ጋር በተደረገ ድርድር ወደ እብነግ የጦር ሰፈር እንዲመለሱ ተደርጓል::ከሁለት አመት በፊት እንዲሁ በናይሮቢ ከፍተኛ የኦብነግ አመራርን በአደባባይ ገድለዋል:: ምንሊክሳልሳዊ Via ኦጋዴንኔት

TPLF: The Dog That Can no longer Bark

January 27, 2014
by Amanuel Biedemariam
On January 15, 2014, ESAT reported that the Ethiopian People’s Revolutionary Front (EPRDF) conducted organizational evaluation and quoted Bereket Simon, former Ethiopia’s Information Minister and new advisor to Prime Minister Hailemariam Desalgen, on how he characterized the differences amongst the EPRDF leaders during their deliberations. He said:
Before we replaced Revolutionary Democracy with Developmental Democracy, the Front has been divided into three groups. One group of the leadership had argued that our problem was internal and that we need to first check that, while the other group held that our problem was Shabia/Eritrea and that we need to fight them first, but the third position which said that after fighting Shabia/Eritrea, we should then look at our internal problems had become the winning idea.
According to the statement, the EPRDF is no longer a Revolutionary Democracy. It is now Developmental Democracy (whatever that means). In order to come up to that determination however, the group was divided to three camps but the final outcome was a decision to fight “Shaebia/Eritrea” as a primary focus and address their issues later.
Some of TPLF ‘Mafia group’ that remained to bleed the people of Ethiopia
Some of TPLF ‘Mafia group’ that remained to bleed the people of Ethiopia
The irony, one prerequisite to development or any progress for any nation is peace. When a nation ensures relative peace then there is a foundation for progress. The decision by the EPRDF to “Fight Shaebia/Eritrea” as a prerequisite to their developmental democracy is simply absurd, laughable and dangerous at the same time.
After a 15 year period that started with a border war and morphed into the current so called No-War No- Peace strategy; the Tigrayan People’s Liberation Front (TPLF/EPRDF) decided to continue on the same path albeit with a dressed-up name. The question is, at what cost? Who paid for it initially? Who is responsible for the last 15 years? The TPLF evaluation did not entertain peace with Eritrea; does that mean they have no intention to make peace with Eritrea ever? Furthermore, on what grounds does Ethiopia’s current regime, the TPLF/EPRDF is trying to continue the path of hostility? What is the ultimate goal? How will Eritrea deal with the intransigent TPLF? And ultimately, what constituency of Ethiopia will support this intransigence?
Moreover, how did Ethiopia do without peace with Eritrea? Could it have done better?   How have the people of Ethiopia and Eritrea fared? Is the past 15 years a model by which two neighboring countries should conduct their affairs for the future? Who pays for all these? Who paid for the past?
The key question, why did Bereket Simon come-out now and made these absurd statements? Moreover, why now, when many particularly the US, for the first time in over 15 years is talking peace did Bereket Simon roll-out this war agenda? The questions are endless.
The answer to all these questions are found on a statement one astute Eritrean political figure made a while back. When asked to respond about outrageous repeated statements by the TPLF against Eritrea, he answered, “When a dog barks uncontrollably disturbing peace, the best option is to talk to the owners of the dog.”
There are three key reasons why Bereket Simon decided to come out and declared the continuation of the hostilities.
1) The current chatter that the US is on the verge reestablishing ties with Eritrea is a concern and they are crying for some attention. They want to make sure that the US does not abandon them. Ambassador David Shinn’s comment that we will not have relations with Eritrea at the expense of our important ally Ethiopia is designed to do just that; allay concerns. That however, is not working because the reaction to Ambassador Shinn has been very harsh.
2) Improved Eritrea US relations are a serious concern for the pocket books of the minority regime. Ethiopia has provided boots for the West that funds its military. In turn the TPLF controls its army with the billions in funding received from the West specifically the US by using it as incentive. Those who are loyal are rewarded by assignments on peacekeeping missions for lucrative pay. That means there is a security dimension to it as well because the funds pacify multi ethnic military that could turn on them.
3) Peace is the greatest threat to the very existence of the TPLF/EPRDF. Therefore, they must perpetuate these conflicts particularly with Eritrea. The TPLF is using the border issue to control the people of Ethiopia by misleading them as if the border is a negotiating ploy hence continues the declared No-Peace No-War agenda indefinitely.
Time the enemy
The TPLF/EPRDF has run out of time. There has been tremendous regional and global changes that lead to change of attitude and approach in dealing with the countries of the region. Their strategy to subdue Eritrea failed. To the contrary all economic signals indicate that Eritrea is forging ahead independently. The US waited for over a decade and half to bring regime change in Eritrea using Ethiopia and failed.
China’s influence in the region is forcing changes on US Africa policy. The changes on Western global Geo-Strategic shift away from Middle East to Asia plays a factor. Military and other budget cuts in the US will certainly affect changes. In addition, the death of Meles Zenawi and, the power transition that ensued has created a precarious power- sharing leadership arrangement that generated a great deal of uncertainty.
Moreover, countries in the region are working for their interests diligently. Recent activities by countries in the region particularly Egypt, Sudan and Eritrea are something to pay attention to for many reasons.
To Conclude
The US holds the key to Eritrea Ethiopia future relations simply because Ethiopia as a client state and dependent on US for political, diplomatic, economic, food and military support/aid is amenable to US demands. Thus, when and if the US decides it is on the best interest of the US for the TPLF to create peace with Eritrea then there will be no choice left but to acquiesce to US demands. That is the reality.
The question however remains, after paying dear lives of over 20,000 Eritrean souls, thousands more wounded; after having millions displaced; after decades of hostility that impacted families negatively in many ways; in short, after Eritrea paid the price with dear blood why on earth will the people of Eritrea throw a lifeline to the TPLF? Will they?
That simply means the neck of the TPLF is on the table. The US is at a critical point where they have to make a choice whether to save Ethiopia or the TPLF. When an organization with no constituency and according to Bereket Simon not clear about the future-direction of the nation  decide to place their fate on hostilities with a neighboring country Eritrea; the US has a lot to worry about.  When the perception remains Bereket Simon is the key figure rendering Prime Minister Hailmariam Desalegne as a figurehead, the US has a lot to worry about. Is TPLF/EPRDF Ethiopia?  These are some sticky points. Ambassador David Shinn tried to address these conundrum but no takers. He said,
“Although the United States might decide to try again to improve relations with Eritrea, it will not do so at the expense of its ties with Ethiopia.”
The statement above said Ethiopia, not TPLF/EPRDF. The US is cognizant of these complexities. The US at this stage is desperate to save Ethiopia because the current states of affairs are unsustainable.
Ambassador Hank Cohen’s approach is therefore commendable as he is trying to thread a thin line to save a nation from embedded ethnic-political-system that can spell disaster with long term consequences for the region and US long term interests.
Eritrea therefore holds the key.
Awetnnayu@hotmail.com

የአገር አቋራጭ አውቶቡስ ተገልብጦ 17 ሰዎች ሕይወታቸው አለፈ፤ የ2 ዓመት ህፃን ሕይወቱ ተረፈ

January 26/2014


(ዘ-ሐበሻ) ከሞያሌ ወደ ሻሸመኔ ተጓጓዦችን ጭኖ ይጓዝ የነበረ አንድ አገር አቋራጭ አውቶቡስ ተገልብጦ የ17 ሰዎች ሕይወት ማለፉ ተሰማ። የ2 ዓመቱ ህፃን ምንም ጉዳት ሳይደርስበት ሲተርፍ፤ ሌሎች 31 የሚሆኑ ሰዎች ግን ከባድ የአካል ጉዳት እንደደረሰባቸው ለዘ-ሐበሻ የደረሱት መረጃዎች አመልክተዋል።

ትናንት ማምሻውን ከሞያሌ ወደ ሻሸመኔ ሲጓዝ የነበረው ሃገር አቋራጭ አውቶቡስ የተገለበጠው በይርጋ ጨፌ ወረዳ ቆንጋ ቀበሌ እንደሆነ ሲገለጽ የአካባቢው የትራፊክ ፖሊስ በሰጠው መግለጫ ለአደጋው መንስኤ በፍጥነት ማሽከርከር ነው ተብሏል። ፖሊስ ጨምሮም መንገዱ ከፍተኛ ቁልቁለት የነበረው ሲሆን ሹፌሩ ሃላፊነት በጎደለው መልኩ በፍጥነት በማሽከርከሩ አደጋው ሊከሰት እንደቻለ ገልጿል።

በዚህ አካባቢ የተለያዩ የትራፊክ አደጋዎች በተለያየ ጊዜ እንደሚደርስ የጠቆሙት የአካባቢው ነዋሪዎች አደጋዎች በሹፌሮች አማካኝነት ይፈጠሩ እንጂ መንግስትም ተጠያቂ ነው ይላሉ። በተለይ ይህ ቦታ ብዙ የመኪና አደጋ የሚደርስበት ቢሆንም ትራፊክ ፖሊስ በሙስና በመጨማለቅ በፍጥነት በሚያሽከረክሩ ሰዎች ላይ ተገቢውን ቅጣት እንደማይጥሉባቸው የገለጹት እነዚሁ ታዛቢዎች ከአስተዳዳሪው ጀምሮ በሙስና የተጨማለቁ በመሆናቸውና ትራፊክ ፖሊስም የሚገባውን ሥራ ስለማይሰራ ለአደጋዎቹ መበራከትም ምክንያት ነው። በተለይ በኢትዮጵያ በአሁኑ ወቅት የአንድ ትራፊክ የወር ደመወዝ አንድ ሰው ለአንድ ምሽት በሬስቶራንት 2 ሰው ራት የሚጋብዝበት ሂሳብ መሆኑ ፖሊሶቹ በሙስና ላይ እንደሚሰማሩ ታዛቢዎች ለዘ-ሐበሻ ዘጋቢዎች ገልጸዋል። በተጨማሪም በይርጋ ጨፌ ወረዳ በቂ የትራፊክ ምልክቶች አለመኖራቸው ለአደጋው መበራከት እንደምክንያት ያቀርባሉ።

በዚህ የመኪና አደጋ የሞቱ ሰዎች ቁጥር ሊጨምር እንደሚችል የታወቀ ሲሆን አብዛኞቹ በዲላ ሆስፒታል ህክምና ላይ እንደሚገኙ ጨምሮ የደረሰን መረጃ ያመለክታል።

ከዚህ ቀደም በዘ-ሐበሻ ድረ ገጽ ላይ ይህን ጥናት ስለመኪና አደጋ አቅርበን ነበር። በድጋሚ እነሆ፦
በዓለም የጤና ድርጅት (WHO) የ2012 ሪፖርት መሰረት በዓለማችን በዓመት 1ሚሊየን 3 መቶ ሺ ህዝብ በትራፊክ አደጋ ህይወታቸው እንደሚያልፍ ሲታወቅ በኢትዮጵያ በተደረገ ጥናት ደግሞ በዓመት ክ2000 ሰዎች በላይ በመኪና አደጋ ሕይወታቸው ያልፋል።
ለመኪና አደጋ መንስኤ ተብለው ከሚጠቀሱት መካከል በፍጥነት ማሽከርከር፣ ለእግረኞች ቅድሚያ አለመስጠት፣ የሌሊት ጉዞ፣ ደርቦ ማለፍ፣ ከአቅም በላይ መጫን፣ አደንዛዥ ዕፅ መጠቀምና ጠጥቶ ማሽከርከር ከመንስኤዎቹን መሀል ዋነኞቹ እንደሆኑ ታውቋል፡፡ ከዚህም በተጨማሪ የተሽከርካሪ የቴክኒክ ጉድለት ወይም ብልሽት፣ የእግረኛ ግራ መንገድ ይዞ አለመሄድና የማቋረጫ ምልክቶችን (ዜብራ) በአግባቡ አለመጠቀም፣ የመንገዶች በጥራት አለመሰራትና የመንገድ ላይ ምልክቶች ተሟልተው አለመዘጋጀት ለአደጋው እንደመንስኤ የቀረቡ ናቸው፡፡

ዘ -ሐበሻ