Wednesday, June 12, 2013

ኢትዮጵያና ግብጽ የቃላት ጦርነት መወራወር ጀምረዋል።

<<ማናቸውንም እርምጃ ለመውሰድ በሩ ክፍት ነው>>ግብጽ

<<በቀረርቶ ተደናግጠን ለሰከንድ የግድብ ግንባታውን አናቆምም>>-ኢትዮጵያ

በሁለቱ አገሮች መካከል መተነኳኮሱ እየባሰ የመጣው ዘንድሮ ግንቦት 20 ቀን የተከበረውን የገዥውን ፓርቲ በኣል ምክንያት በማድረግ ኢትዮጵያ ፦” የአባይ ወንዝን የተፋሰስ አቅጣጫ አስቀየስኩ” ብላ ማወጇን ተከትሎ ነው።
ይህን ተከትሎ በተለይ የግብጽ መንግስት -ከተቃዋሚዎቹ ጋር በመሆን በኢትዮጵያ ላይ እስከ ወታደራዊ ጥቃት ድረስ የሚደርስ እርምጃ ለመውሰድ የመከሩበት ስብሰባ በይፋ ታየ፤

 ይሁንና የግብጽ መንግስት-ከተቃዋሚዎቹ ጋር በመሆን ኢትዮጵያ ላይ ለመውሰድ ስለታሰበው እርምጃ ሲመክሩበት የነበረው ስብሰባ በቀጥታ የቴሌቪዥን ስርጭት መተላለፉ፤ግብጽ -ኢትዮጵያን ለማስፈራራት መፈለጓን የሚያሳይ ተራ ጨዋታ ነው በሚል ብዙዎች ትኩረት ሳይሰጡት ቆይተዋል
ይህ በ እንዲህ እንዳለ ትናንት የግብጹ ፕሬዚዳንት መሀመድ ሙርሲ ፦ኢትዮጵያ በምትሠራው ግድብ ሳቢያ ወደ ግብጽ ከሚፈሰው የ አባይ ወንዝ የጠብታ ያህል ከቀነሰ አገራቸው ግብጽ ማናቸውንም እርምጃዎች ኢትዮጵያ ላይ ለመውሰድ ዝግጁነቱ እንዳላት አስታውቀዋል።

 ከ ኢትዮጵያ ጋር ጦርነት እንደማይፈልጉ፤ ግድቡን ለማስቆም የሚያደርጉት ጥረት ካልተሳካ ግን ሁሉንም አማራጭ እርምጃዎች ለመውሰድ እንደሚገደዱ ነው ፕሬዚዳንቱ የተናገሩት።
ኢትዮጵያ - አቅጣጫውን የቀየረው የወንዙ ፍሰት ሀይል ካመነጨ በሁዋላ ተመልሶ በመደበኛው መስመር እንደሚፈስ እና በግብጽም ሆነ በሱዳን ላይ የሚፈጥረው ነገር እንደማይኖር ደጋግማ ብታሳውቅም፤ፕሬዚዳንት ሙርሲ ፈጽሞ የግብጽ የውሀ ደህንነት ሊነካ አይገባም! በማለት የ ኢትዮጵያን ምላሽ እንደማይቀበሉት አስታውቀዋል።
“የ አገሪቱ ፕሬዚዳንት እንደመሆኔ መጠን ሁሉንም እርምጃዎች ለመውሰዱ በሩ ክፍት መሆኑን አሳውቃለሁ” ነው ያሉት -ፕሬዚዳንት ሙርሲ።
በማያያዝም፦”ግብጽ የዓባይ ስጦታ ከሆነች፤ዓባይ የግብጽ ስጦታ ነው”ብለዋል-በስሜት ውስጥ ሆነው በቴሌቪዥን ባደረጉት ንግግር።
እንደ አንድ ታላቅ ህዝብ የግብፃውያን ህይወትና ኑሮ ከ ዓባይ ጋር የተያያዘ ነው ያሉት ፕሬዚዳንት ሙርሲ፤ ፍሰቱ በ አንዲት ጠብታ ከቀነሰ ያለን ቀሪ አማራጭ ደማችን ነው”ብለዋል።
የግብጽን ተደጋጋሚ ዛቻ ተከትሎ የ ትዮጵያ የውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር ዛሬ ባወጣው መግለጫ፦<<ኢትዮጵያ በቀረርቶ ተደናግጣ ለሰከንድ የግድብ ግንባታዋን አታቆምም>>ብሏል።

ኢትዮጵያ ከምንም በላይ ለትብብር ፣ ለወዳጅነትና ለጋራ ጥቅም ያላትንም ፅኑ እምነት በወቅቱ ግልፅ አድርጋለች ያለው የሚኒስቴሩ መግለጫ ፥ ይህ በእንዲህ እንዳለ ትናንት ብሄራዊ የናይል ጉባኤ በተሰኘው ስብሰባ ላይ የግብጽ ፕሬዚዳንት ፣ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ፣ ሚኒስትሮችና ሌሎችም በተገኙበት ታላቁን የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ አስመልክቶ አፍራሽ መልዕክቶች ተላልፈዋል ብላል ።
በዚህ ረገድ በግብፅም ሆነ በሌላ ማንኛውም ወገን የሚቀርብ የግድቡን ግንባታ የማዘግየት ወይም ከነአካቴው የማቋረጥ ነገር ፈፅሞ ተቀባይነት እንደማይኖረው የውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር ገልጿል ።

 ጦርነትና ሌሎች አፍራሽ ስልቶችን ስለመጠቀም የሚቀርቡት ሀሳቦች ያረጁና ያፈጁ ፣ የ21ኛውን ክፍለ ዘመን አስተሳሰብ የማይሸከሙ ፣ እና ጤናማ ያልሆኑ አስተሳሰቦች እንደሆኑ የገለጸው የውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር፤ ኢትዮጵያ በዚህ ቀረርቶ ተደናግጣ ግንባታውን ለሰኮንድም አታቆምም ብላል።

 ጉዳዩን በትኩረት እየተከታተሉ ያሉ የፖለቲካ ተንታኞች ግን ሁለቱ መንግስታት የቃላት ጦርነት ውስጥ የገቡት በውስጣዊ አስተዳደራቸው የተፈጠረባቸውን ፖለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ ቀውስ ለመጠምዘዝ እንደሆነ በስፋት አስተያየት ሢሰጡ ይደመጣሉ።

Federal police clash with residents in Afar

ESAT News

June 11, 2013

Following the assassination of Muhammad Kayeb, 20, by the Issa clan in the presence of Federal Police yesterday, the Afar people have been fighting with the Federal Police near Gewane Wlegeli, Afar, in Eastern Ethiopia. The shot out has continued until we entered the Studio.

The residents began the shooting because they believed that the Police were trying to generate conflict between the two people. ESAT had reported last week that the pastoralists of this same area were asked to give their weapons to the police but the police left the area and the clash was calmed. Residents state that the current clash is also linked to clashes of the previous week.

The extent of causality and death has not been established yet. ESAT’s attempt to speak with the officials of Afar has been unsuccessful.

Tuesday, June 11, 2013

‹መድረክ›| ያለፈው ሰልፍ ድራማ ሊሆን ይችላል – እኛም አቅደናል

ተቃዋሚዎች ሰላማዊ ሰልፉ “የኢህአዴግ ድራማ” ሊሆን ይችላል አሉ
Beyene Petros

ባለፈው እሁድ በሰማያዊ ፓርቲ አስተባባሪነት የተካሄደው የተቃውሞ ሰልፍ፣ ከ97 ምርጫ ወዲህ ለመጀመሪያ ጊዜ የተደረገ መሆኑን የሚናገሩት ተቃዋሚ ፓርቲዎች፤ ላለፉት ስምንት ዓመታት እንኳን ሰልፍ ስብሰባም ማካሄድ እንዳልቻሉ በመግለጽ፤ የእሁዱም ሰልፍ “የኢህአዴግ ድራማ ሊሆን ይችላል” በማለት እንደሚጠራጠሩ ገለፁ ፡፡ የኢህአዴግ ፅ/ቤት ሃላፊ አቶ ሬድዋን ሁሴን በበኩላቸው፣ ህገመንግስቱን መሰረት ባደረገ መልኩ የሚፈፀሙ ሰላማዊ ሰልፎች እንደማይከለከሉና ድሮም የነበረ አሰራር መሆኑን ተናግረዋል፡፡ የመድረክ ፓርቲ ምክትል ሊቀመንበርና የህዝብ ግንኙነት ሃላፊ ፕ/ር በየነ ጴጥሮስ፤ እስከአሁን ሰላማዊ ሰልፍ ለማድረግ ይቅርና አዳራሽ ለመከራየት እንኳን ሆቴሎች የመስተዳድሩን ፈቃድ አምጡ እያሉ ሲያስቸግሯቸው እንደነበር ገልፀው፤ የሰሞኑ የሰማያዊ ፓርቲ ሰልፍም ምናልባትም ከአፍሪካ ህብረት ጋር በተያያዘ ኢህአዴግ ያደረገው ጨዋታ ሊሆን ይችላል ብለዋል፡፡

“ሰላማዊ ሰልፍ ለመጥራት እኛም ዕቅድ ይዘን እየተነጋገርን ነው” የሚሉት ፕ/ር በየነ፤ ኢቴቪ ሰልፉን መዘገቡን ብቻ በማየት መሻሻሉን ለማወቅ እንደማይቻል ገልፀዋል፡፡ “ኢቴቪም ቢሆን ድራማውን እየሰራ ይሆናል” በማለት ዘገባውን የሰራው አንዳንድ የሚያስወነጅሉ ጉዳዩች ላይ በማተኮር ነው ብለዋል፡፡ “አላማቸውና መሻሻላቸው የሚታወቀው ወደፊት መቀጠሉ ሲታይ ነው” ብለዋል – ፕሮፌሰሩ፡፡ የመድረክ ምክትል ሊቀመንበርና የድርጅት ጉዳይ ሃላፊ ዶ/ር መረራ ጉዲና በበኩላቸው፤ ሰላማዊ ሰልፉ መካሄዱ ችግሮችን ካልፈታ ልክ በአረብ አገራት ላይ እንደታየው አይነት ችግሮች ሊከሰት እንደሚችል ይናገራሉ፡፡ “የህዝብ ችግር እስካልተፈታ ድረስ ህዝብ አንድ ቀን በቃኝ ሊል ይችላል – መብቱ ካልተከበረለትና የሚበላው ካጣ ችሎ የሚቀመጥበት መንገድ የለም፡፡ ይሄ ህዝብ መብቱ እንዲከበርለት፣ ነፃነት እንዲያገኝ፣ በልቶ እንዲያድር ይፈልጋል፡፡ ኢህአዴግ ይህንን ችግር መፍታት ካልቻለ፣ ህዝቡ አሁንም “መሪውን ይበላል” የሚባለውን ሊተገብር ይችላል፡፡” የሚሉት ዶ/ር መራራ፤ እኛን አዳራሽ እየከለከሉ ለሌላው ሰላማዊ ሰልፍ የሚፈቅዱት የህዝብ ሙቀት ለመፍጠር በማሰብ ሊሆን ይችላል ብለዋል፡፡

“ምናልባትም የኢህአዴግ አዲስ አሰራር ከሆነ ይበል የሚያሰኝ በመሆኑ፣ በነካ እጁ ለመድረክና ለሌሎች ፓርቲዎችም እንዲፈቅድ ጥያቄያችን ነው” ብለዋል፡፡ አቶ ሬድዋን በበኩላቸው፤ ተቃዋሚዎች ሰልፍ ተከለከልን ማለታቸውን አይቀበሉትም፡፡ “በራሳቸው ምክንያት ሳይካሄዱ የቀሩ ካልሆኑ በስተቀር፣ ሰላማዊ ሰልፍ ማካሄድ በፊትም ነበር፤ አሁንም ተካሂዷል፡፡ ሃሳብን በነፃነት በአደባባይ ወጥቶ የመግለጽ መብት አዲስ አሠራር ነው ብለን አናስብም” ብለዋል፡፡ ብዙ ጊዜ ተቃዋሚ ፓርቲዎች አዳራሽ ተከለከልን፣ ሰልፍ አልተፈቀደልንም የሚል ቅሬታ ያነሳሉ የሚሉት አቶ ሬድዋን፤ የአዳራሽ ጉዳይ የባለ አዳራሾች እንጂ የመንግስት አለመሆኑን ጠቅሰው፣ “መንግስት አዳራሽ አያከራይም፡፡ ለዚህኛው ፓርቲ አከራይ፣ ለዚህኛው አታከራይ የሚል ነገርም የለም” ይላሉ፡፡

በአደባባይ ሃሳብን በነፃነት የመግለጽና ሰላማዊ ሰልፍ ማድረግን በተመለከተም፤ “ነፃና ክፍት በሆነ ሰዓትና ቦታ፣ ህጉን ጠብቀውና ፎርማሊቲውን አሟልተው እስካካሄዱ ድረስ የሚከለከሉበት ሁኔታ የለም፡፡ ከዚህ በኋላም አይኖርም” ብለዋል፡፡ የኢትዮጵያ ሬዲዮና ቴሌቪዥን በአዘጋገብ ላይ ያሳየውን ለውጥ በተመለከተ የተጠየቁት አቶ ሬድዋን፤ “ከዚህ በፊትም የማውቀው ኢቴቪ፤ ሁሉንም ወገን ለማናገር ጥረት ሲያደርግ ነው፡፡ ብዙ ጊዜ ሲያጋጥም የነበረው ግን ተቃዋሚ ፓርቲዎች፣ ኢቴቪ እንዳይመጣና እንዳይዘግብብን፣ ከዘገበም ሙሉውን እንዳይቀርጽብን የሚል አቋም እንደነበራቸው ነው፡፡ ተቋሙ የሚሰጣቸውን እድል ያለመጠቀም፣ አትግቡብን የሚል የራሳቸው የሆነ ችግር እንዳለባቸው ነው የማውቀው፡፡ የሆኖ ሆኖ ፕሮግራሙን የሚያየው ተመልካች የራሱን ፍርድ መስጠት ይችላል” በማለትም መልሰዋል፡፡

“መድረክ” ለሰኔ 17 ህዝባዊ ስብሰባ ሊጠራ ነው

ዋና ኦዲተርና የስነምግባርና ፀረ ሙስና ኮሚሽን ሰሞኑን ለፓርላማ ያቀረቡትን ሪፖርት መነሻ በማድረግ በነገው ዕለት በመድረክ፣ በመኢአድ፣ በአንድነትና በሰማያዊ ፓርቲ ቢሮዎች የፓርቲዎቹ አመራሮች ውይይት እንደሚያደርጉና መድረክ ለሰኔ 17 ህዝባዊ ስብሰባ እንደሚጠራ ተገለፀ፡፡

የመድረክ ስራ አስፈፃሚ አቶ አስራት ጣሴ ለአዲስ አድማስ እንደገለፁት፤ የፓርቲዎቹ አመራሮች በነገው ውይይት የሚደርሱበትን የጋራ መግባባት በመያዝ፣ መድረክ ለሰኔ 17 ህዝባዊ ስብሰባ ለመጥራትና በአዲስ አበባ ከተማ በመዘዋወር የመኪና ቅስቀሳ ለማድረግ ተዘጋጅቷል፡፡ ሙስና የስርአቱ መገለጫ በሆነበት፣ የህዝብ ሃብት እየባከነና የዲሞክራሲ መብቶች እየተጣሱ ባለበት በአሁኑ ወቅት፣ መንግስት እምቢተኝነቱን ትቶ ከተቃዋሚ ፓርቲዎች ጋር ውይይት እንዲያደርግ ጥሪ እንደሚተላለፍለት ገልፀዋል፡፡ ገዢው ፓርቲ የሚቀርብለትን የውይይት ሃሳብ ተቀብሎ ወደ ውይይት ካልመጣ፣ 33ቱ ፖርቲዎች ሰላማዊ ትግሉን ተጠቅመው አገራዊ ንቅናቄ በማድረግ፣ እንደ ሰማያዊ ፓርቲ ሰላማዊ ሰልፍ ለማድረግ ማቀዳቸውንም አስረድተዋል፡፡

Monday, June 10, 2013

በአፋር ፌደራል ፖሊሶች ከህዝቡ ጋር ሲታኮሱ ዋሉ

ሰኔ ፫ (ሦስት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም

ኢሳት ዜና:-በትናንትናው እለት የ20 አመቱ ወጣት የሆነው ሙሀመድ ካይብ የፌደራል ፖሊስ አባላት በቅርበት ባሉበት በኢሳዎች መገደሉን ተከትሎ፣ አፋሮች ገዋኔ ወለጌሊ እየተባለ በሚጠራ ስፍራ ከፌደራል ፖሊስ ጋር ዛሬ ሲታኮሱ ውለዋል። ስቱዲዮ እስከገባንበት ጊዜ ድረስ ተኩሱ አለመቆሙን ለማወቅ ተችሎአል።

ነዋሪዎች በፌደራል ፖሊስ አባላት ላይ ተኩስ የከፈቱት ፣ ፖሊሶቹ ሆን ብለው ሁለቱን ብሄረሰቦች ለማጋጨት እየጣሩ ነው በሚል ምክንያት ነው። ከሳምንት በፊት በዚሁ አካባቢ የሚኖሩ አርብቶ አደሮች መሳሪያቸውን እንዲያስረክቡ በተጠየቁበት ጊዜ ተኩስ በመክፈታቸው ፖሊሶቹ አካባቢውን ለቀው መሄዳቸውንና ግጭቱ መብረዱን መዘገባችን ይታወሳል። ዛሬ የተፈጠረው ግጭት ባለፈው ሳምንት ከተካሄደው ግጭት ጋር እንደሚያያዝ ነዋሪዎች ይናገራሉ።

በግጭቱ ምን ያክል ሰዎች እንደቆሰሉ ወይም እንደሞቱ ለማወቅ አልተቻለም። በጉዳዩ ዙሪያ የአፋር ባለስልጣናትን ለማነጋገር ያደረግነው ሙከራ አልተሳካም።

Sunday, June 9, 2013

አንድነት ፓርቲ የሰኔ 1 ሰማዕታትን በልዩልዩ ዝግጅቶች ዘከረ

ሰኔ 1 ቀን 1997 ዓ.ም በመንግስት ሀይሎች በግፍ የተጨፈጨፉ የሰላማዊ ትግል ሰማዕታትን ለመዘከር አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ የአዲስ አበባ ዞን ያዘጋጀው መርሀግብር ትላንት ተካሄደ፡፡

 ቀበና አካባቢ በሚገኘው አንድነት ፓርቲ ዋና ጽ/ቤት ሰማዕታቱን ለማሰብ በህሊና ፀሎት በተጀመረው በዚሁ መርሀ ግብር ላይ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የፓርቲው ሊቀመንበር ዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳ ሲሆኑ ከሳቸው በመቀጠል የአንድነት ፓርቲ አዲስ አበባ ዞን ሰብሳቢ አቶ ትዕግስቱ አወሉ ዕለቱን የሚመለከት ንግግር አድርገዋል፡፡

ከ300 በላይ ታዳሚዎች በተሳተፉነት በዚህ መርሀግብር ላይዕለቱን የተመለከቱ ግጥሞች በገጣሚ መላኩ ጌታቸው ቀርበዋል፡፡ የፍኖተ ነፃነት ጋዜጣ ዋና አዘጋጅ ነብዩ ኃይሉ ዕለቱን አስመልክቶ የነበረውን ትዕውስታ ለታዳሚው አካፍሏል:: የመርሀግብሩ አዘጋጆች ሰኔ አንድ በግፍ ከተገደሉ ዜጎች መካከል 42 የሚሆኑትን ስምና የአገዳደል ሁኔታ በመቀንጨብ አቅርበዋል፡፡ የታሳሪዋ ጋዜጠኛ ርዕዮት አለሙ አባት አቶ አለሙ ጌቤቦ የመዝጊያ ንግግር ካደረጉ በኋላ በቅርቡ በማዕከላዊ ታስሮ ድብባና እስር ሲፈፀምበት በነበረው ወጣት ብርሀኑ ተክለያሬድ የተመራ የጧፍ ማብራት ስነስርአት ተካሂዶ መርሀግብሩ ተጠናቋል፡፡ 

Saturday, June 8, 2013

መድረክ ለሰኔ 17 ህዝባዊ ስብሰባ ሊጠራ ነው

መንግስት ለውይይት ካልተዘጋጀ 33ቱ ፓርቲዎች ሰላማዊ ሰልፍ ለማድረግ አቅደዋል ዋና ኦዲተርና የስነምግባርና ፀረ ሙስና ኮሚሽን ሰሞኑን ለፓርላማ ያቀረቡትን ሪፖርት መነሻ በማድረግ በነገው ዕለት በመድረክ፣ በመኢአድ፣ በአንድነትና በሰማያዊ ፓርቲ ቢሮዎች የፓርቲዎቹ አመራሮች ውይይት እንደሚያደርጉና መድረክ ለሰኔ 17 ህዝባዊ ስብሰባ እንደሚጠራ ተገለፀ፡፡

የመድረክ ስራ አስፈፃሚ አቶ አስራት ጣሴ ለአዲስ አድማስ እንደገለፁት፤ የፓርቲዎቹ አመራሮች በነገው ውይይት የሚደርሱበትን የጋራ መግባባት በመያዝ፣ መድረክ ለሰኔ 17 ህዝባዊ ስብሰባ ለመጥራትና በአዲስ አበባ ከተማ በመዘዋወር የመኪና ቅስቀሳ ለማድረግ ተዘጋጅቷል፡፡ ሙስና የስርአቱ መገለጫ በሆነበት፣ የህዝብ ሃብት እየባከነና የዲሞክራሲ መብቶች እየተጣሱ ባለበት በአሁኑ ወቅት፣ መንግስት እምቢተኝነቱን ትቶ ከተቃዋሚ ፓርቲዎች ጋር ውይይት እንዲያደርግ ጥሪ እንደሚተላለፍለት ገልፀዋል፡፡ ገዢው ፓርቲ የሚቀርብለትን የውይይት ሃሳብ ተቀብሎ ወደ ውይይት ካልመጣ፣ 33ቱ ፖርቲዎች ሰላማዊ ትግሉን ተጠቅመው አገራዊ ንቅናቄ በማድረግ፣ እንደ ሰማያዊ ፓርቲ ሰላማዊ ሰልፍ ለማድረግ ማቀዳቸውንም አስረድተዋል፡፡
ምንጭ አዲስ አድማስ

Thursday, June 6, 2013

ወያኔ የፈጠረዉ የፍርሀት ድባብ ሲሰበር . . .

         
በኢትዮጵያ ህዝብ ላይ የሚደርሰዉ በደልና መከራ ወለደን ብለዉ ለትግል ጫካ የገቡት ዘረኞቹ የወያኔ መሪዎች አዲስ አበባ ገብተዉ ከተደላደሉ በኋላ በህዝብ መብትና ነጻነት፤ በአገር አንድነትና በአጠቃላይ በኢትዮጵያ ህዝብ ብሄራዊ ጥቆሞች ላይ ይህ ነዉ ተብሎ ሊነገር የማይችልና ከእነሱ በፊት ከነበሩት መንግስታት ጋር ሲተያይ እጅግ በጣም የከፋ በደል ፈጽመዋል እየፈጸሙም ይገኛሉ። ዘረኞቹ የወያኔ መሪዎች አዲስ አበባ ገብተዉ የኢትዮጵያን መንበረ ስልጣን ከመቆጣጠራቸዉ በፊት ዕቅድ አዉጥተዉና ተዘጋጅተዉ የመጡት የኢትዮጵያን ህዝብ በዘር፤ በሐይማኖትና በክልል በመከፋፈል በጠመንጃ ኃይል የያዙት ስልጣን በግዜና በህገመንግስት ያልተገደበ መሆኑን ለማረጋገጥና የእኛ ነዉ ለሚሉት የህብረሰተብ ክፍልና ለሚተባበሯቸዉ ሆዳሞች ተቆጥሮ የማያልቅ ሀብት ማጋበስ የሚችሉበትን መንገድ ለመፍጠር ነዉ። የወያኔ መሪዎች ይህንን አገራዊ በደል ያለምንም ተቃዉሞ መፈጸም እንዲችሉ ከአገሩ ይልቅ የተወለደበትን ክልል ብቻ፤ ከብሔራዊ አንድነቱና አጋራዊ ጥቅሙ ይልቅ የራሱን ጥቅም ብቻ የሚመለከትና የእነሱን ኃይለኝነትና የተለየ ጀግንነት እየሰበከ የሚኖር በፍርሀት የተሸበበ ፈሪ ትዉልድ ለመፍጠር ከፍተኛ ጥረት አድርገዋል።

የወያኔ ክፋት፤ ዘረኝነትና “ልማት” በሚል ሽፋን የተደበቀ አገር የማፍረስ ሴራ ከወዲሁ የገባቸዉ የኢትዮጵያ የቁርጥ ልጆች ከ1997ቱ ምርጫ በፊትም ሆነ በኋላ የወያኔን ገመና ለማጋለጥና የኢትዮጵያ ህዝብ ለመብቱ፤ ለነጻነቱና ለእኩልነቱ እንዲታገል ለማድረግ እንደሻማ እየቀለጡ ብርሀን ሆነዉ አልፈዋል። ይህ የዕልፍ አዕላፋት የትግል መስዋእትነትና ምሳሌነት ፍሬ እያፈራ መጥቶ በላፈዉ እሁድ ግንቦት 25 ቀን የተካሄደዉንና ወያኔ ከሃያ አመታት በላይ ሲቋጥር የከረመዉን የፍርሀት መቀነት የበጠሰ እጅግ በጣም የሚያበረታታ ትዕይንተ ህዝብ እንዲደረግ አስተዋጽኦ እድርጓል፡፡ ይህ ባለፈዉ እሁድ የተካሄደዉ ሰላማዊ ሰልፍ የኢትዮጵያ ህዝብ የሚያስተባብሩት፤ አቅጣጫ የሚያሳዩትና ጉያዉ ዉስጥ ገብተዉ እያበረታቱ የሚመሩት መሪዎችን ካገኘ እንኳን ምንም አይነት ህዝባዊ መሠረት የሌለዉን ወያኔን የመሰለ ፀረ ህዝብ ሃይል ቀርቶ ለማንም የማይበገር ህዝብ መሆኑን ያስመሰከረ ሰልፍ ነዉ።

በሰማያዊ ፓርቲ የተጠራዉና የብዙ ኢትዮጵያዉያንን ይሁንታ ያገኘዉ የእሁዱ ሰላማዊ ሰልፍ ወያኔ ያስረናል ወይም ይገድለናል እየተባለ አላግባብ እየተፈራ በቀጠሮ ሲተላለፍ የቆየዉን ህዝባዊ ትግል ከፍርሀትና እንደ ገመድ ከረዘመ ቀጠሮ ዉስጥ በጣጥሶ ያወጣና የህዝብን የትግል መንፈስ ያነቃቃ ሰላማዊ ሰልፍ እንደነበር በሰልፉ ላይ የታየዉ የህዝብ ስሜትና ለኢትዮጵያ ህዝብ የተላለፉት መልዕክቶች በግልጽ ይናገራሉ። ባለፈዉ እሁድ በተደረገዉ ሰላማዊ ሰልፍ ላይ የታየዉ ህዝብዊ መነሳሳት ሊበረታታ የሚገባዉና እንዲሁም በአገር ዉስጥና በዉጭ አገር የሚገኙ ኢትዮጵየዉያን የመብትና የነጻነት ትግላቸዉ አካል አድርገዉ ሊቀላቀሉት፤ ሊረዱት፤ሊተባሩትና ህዝባዊ ትግሉ የሚጠይቁዉን አመራር ሊሰጡት የሚገባ እጅግ በጣም አበራታች ጅምር ነዉ። ለትግልና ለመስዋዕትነት ዝግጁ የሆነዉ የኢትዮጵያ ህዝብ ያጣዉ መሪ ነዉ እያልን አግባብ የሌለዉ ጩከት ከመጮህ ይልቅ አገራችንን የምንወድ የኢትዮጵያ ልጆች ሁሉ መሪዎችን በትግል ሂደት ዉስጥ የምንፈጥረዉ እኛዉ እራሳችን መሆናችንን ተረድተን ይህንን የሚያበረታታ ተስፋ የሰጠንን ሰላማዊ ሰልፍ የምናጠናክርበትንና ተከታታይነት ኖሮት ብዙ የህብረተሰብ ክፍሎችን የሚያካትትበትን መንገድ ልንቀይስ ይገባል።

የኢትዮጵያ ህዝብ አሁንም ቢሆን ለመብቱ፤ለነጻነቱና ለአንድነቱ ማናቸውንም አይነት መስዋዕትነት ለመክፈል ዝግጁ መሆኑን ባለፈዉ እሁድ በግልጽ አሳይቷል። አሁን የሚቀረዉ ህዝባዊ ትግሉን የመምራት ታሪካዊ ሀላፊነት የወደቀበት የህብረተሰብ ክፍል ጨርቄን ማቄን ማለቱን ትቶ ወቅቱ የሚፈልገዉን የትግል አመራር መስጠት ብቻ ነዉ።

ዘረኛዉ የወያኔ አገዛዝ አንዴ የታጠቀዉን ጠመንጃ በመጠቀም ሌላ ግዜ ደግሞ ፓርላማዉንና የህግ ተቋሞችን ተጠቅሞ ተቃዋሚ ኃይሎችን የሚያጠፋ ህግ በማዉጣት የኢትዮጵያን ህዝብ የፍትህና የነጻነት ፍላጎት ለማፈን ብዙ ጥሯል፤ ከሁሉም በላይ ደግሞ እራሱን “ተራሮችን ያንቀጠቀጠ” ትዉልድ ብሎ በመጥራት ህዘብ በፍርሃት ጨለማ ዉስጥ እንዲኖር ለማድረግ ብዙ ታግሏል።
ቆራጡ የኢትዮጵያ ህዝብ ግን ስድቡን፤ ንቀቱን፤ እስራቱን፤ግድያዉንና ስደቱን እንዳመጣጡ መክቶ በፍርሀት ዉስጥ የማይኖር ህዝብ መሆኑን ባለፈዉ እሁድ ለወዳጁም ለጠላቱም በግልጽ አሳይቷል። ይህ እሁድ ግንቦት 25 ቀን 2005 ዓም አዲስ አበባ ዉስጥ የታየዉ የትግል መነሳሳት ሁሉንም የህብረተሰብ ክፍሎች በማቀፍ ወያኔና በጠመንጃ ኃይል የመሰረተዉ ዘረኛ ስርአቱ እስከተወገዱና ኢትዮጵያ ፍትህ፤ ነጻነትን ዲሞክራሲ የነገሱባት ምድር እስክትሆን ድረስ መቀጠል ይኖርበታል፤ ይህንን ለማድረግ ደግሞ በአገር ዉስጥና በዉጭ አገር የሚኖረዉ ኢትዮጵያዊ እንደ አንድ ሰዉ ቆሞ መታገል ይኖርበታል።

ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ!!

ከሰማያዊ ፓርቲ የተሰጠ መግለጫ (መንግስት ለሕዝብ ጥያቄዎች ምላሽ እንዲሰጥ አሁንም እንጠይቃለን!)

Blue Party Ethiopia
ሰማያዊ ፓርቲ

ሰማያዊ ፓርቲ የጠራው ታላቅ ሰላማዊ የተቃውሞ ሰልፍ ግንቦት 25 ቀን 2005 ዓ.ም በርካታ ሕዝብ በተገኘበት ደማቅ ሆኖ ተካሂዷል፡፡ ለዚህ ሰልፍ መሳካት ከፍተኛ ድጋፍና አስተዋፅኦ ላደረጉ የፖለቲካ ፓርቲዎች፣ የሲቪክ ማህበራት፣ የመገናኛ ብዙኃንና በሰልፉ ለተሳተፉ ዜጎች እንዲሁም ሰልፉ በሰላም እንዲጠናቀቅ ለረዱ የፀጥታ ኃይሎች ፓርቲያችን ልባዊ ምስጋናውን ያቀርባል፡፡

ከዚህ በተቃራኒ ግን ይህንን ሰላማዊ የተቃውሞ ሰልፍ ተከትሎ የገዥው ፓርቲ ባለስልጣናትና የመንግስት ተወካዮች የተለመደውን ተልካሻ አስተያየቶች ሰጥተዋል፡፡ የገዥው ፓርቲ ተወካይ ሰልፉን አስመልክቶ በሰጡት አስተያየት “የሐይማኖት አክራሪነት አጀንዳው አድርጎ ሲንቀሳቀስ የነበረው ሰማያዊ ፓርቲ ዛሬ በጠራው ሰላማዊ ሰልፍ ድብቅ አጀንዳው ገሃድ ወጣ” በማለት በሰጡት አስተያየት ፓርቲውን ለማንቋሸሽና ለማራከስ ሞክረዋል፡፡

 ይህም ፓርቲውን በእጅጉ ያስቆጣ ነው፡፡ ይህ ዓይነቱ መሰረተ ቢስ ፍረጃ የገዥው ቡድን አባላት ለንግግራቸውና ለሚሰጡት አስተያየት ሚዛን የሌላቸው ከመሆኑ ውጭ በፓርቲው ፕሮግራምም ሆነ እንቅስቃሴ ከአሸባሪነት ጋር የሚያገናኘውን አንዳችም ነገር አልጠቀሱም፡፡ ፓርቲው በሕጋዊ መንገድ ተመዝግቦ እየተንቀሳቀሰ የሚገኝ እና በሕገ መንግስቱ በተሰጠው መብት ተጠቅሞ በሕጋዊ ሥነስርዓት ያደራጀውን ሰላማዊ የተቃውሞ ሰልፍ በእንዲህ አይነት መንገድ መፈረጅ ሰልፉ ከተጠራበት ዓላማና መንፈስ በእጅጉ የራቀ አስተያየት ሆኖ አግኝቶታል፡፡

ፓርቲው ከዚህ በፊትም በተደጋጋሚ በሰጣቸው መግለጫዎች በእስልምና እምነት ተከታዮች ላይ የሚደረገውን ጣልቃ ገብነት መቃወሙ ይታወሳል፡፡ ይህንኑ ጥያቄ በተቃውሞ ሰልፉ ላይ ወደ አደባባይ ይዞ መውጣቱ ሕገ መንግስታዊ የመብት ጥያቄ መሆኑን ይገነዘባል፡፡ ከባለሥልጣኑ የተሰጠው አስተያየት ግን የእስልምና ሐይማኖት ተከታይ ዜጎች በሰላማዊ መንገድ የተቃውሞ ጥያቄ ማቅረባቸውን ገዥው ፓርቲ በበጎ ጎን አለማየቱንና የመብት ጥያቄ የሚያነሱ ዜጎችን ሁሉ ወደ ሽብርተኝነት ፍረጃ ለመክተት የሚያደርገውን ጥረት የሚያመላክት ሆኖ አግኝተነዋል፡፡ በተጨማሪም ገዥው ፓርቲ የእስልምና እምነት ተከታዮችን ኢትዮጵያውያን ዜጎች እንደሆኑ አድርጎ እንደማያያቸውም ሰማያዊ ፓርቲ ተገንዝቧል፡፡

የመንግስት ተወካይ የሆኑት ባለስልጣን በበኩላቸው በሰጡት አስተያየት በሰላማዊ መንገድ ተጠይቆና ታውቆ መንግስት ራሱ ያመነውና እጅግ ሰላማዊ የሆነ የተቃውሞ ሰልፍ እንዲካሄድ ያደረገን ፓርቲ ውጭ የሚገኙ ኃይሎች ተላላኪ አድርጎ ማቅረብ የአብዬን ወደእምዬ እንደሚባለው መሆኑን እየገለፅን ይልቁንም በሕጋዊ መንገድ ተመዝግቦ የሚንቀሳቀሰውን ፓርቲያችንን መንግስት ከልቡ ሊቀበለው እንዳልቻለ አስገንዝቦናል፡፡ በተጨማሪም ይህ አባባል ሰማያዊ ፓርቲን የማይመጥን፤ ፓርቲውም በተግባር እያሳየ ያለውን ሰላማዊ የፖለቲካ እንቅስቃሴ የሚጥስ በመሆኑ አጥብቀን እናወግዘዋለን፡፡ እኝሁ የመንግስት ባለስልጣን በሰላማዊ ሰልፉ የተላለፉት መልዕክቶች ህገ መንግስቱን የሚንዱ ናቸው በማለት በደፈናው ህዝብን ለማታለል ከመሞከራቸው በተለየ የትኛው ሃሳብ የትኛውን የሕገ መንግስት ድንጋጌ እንደሚፃረር ካለማመልከታቸውም በላይ ፓርቲው በፍርድ ቤት ጉዳይ ጣልቃ እንደገባ አድርጎ ለማሳየት መሞከር የመንግስትን ግብር ለሰማያዊ ፓርቲ መስጠት ከመሆኑም ሌላ ላም ባልዋለበት ኩበት ለቀማ ያደርገዋል፡፡

በመጨረሻም የእስልምና እምነት ተከታይ ዜጎቻችን ማንኛውንም የመብት ጥያቄ ከሌሎች ወገኖቻቸው ጋር በሰላማዊ መንገድ የማቅረብ ሕገ መንግስታዊ መብታቸው መሆኑን መንግስትም ሆነ ገዥው ፓርቲ እንዲያውቀው እያሳሰብን፤ ሰማያዊ ፓርቲ ከመንግስትም ሆነ ከገዥው ፓርቲ በሚሰጥ ማንኛውም ማስፈራሪያ ከጀመረው የሰላማዊ ትግል ጉዞ ፍፁም ወደ ኋላ እንደማይል፤ ይልቁንም የተነሱትን የሕዝብ ጥያቄዎች መንግስት በሦስት ወራት ውስጥ ምላሽ እንዲሰጥ አሁንም በድጋሚ ማሳሰብ እንፈልጋለን፡፡
ግንቦት 29 ቀን 2005 ዓ.ም
አዲስ አበባ

በግብጽ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን የድረሱልን ጥሪ እያሰሙ ነው

በዛሬው እለት ለማለዳ ታይምስ ቅርበት ያላቸውን ወገኖች እንዳነጋገርናቸው ከሆነ በግብጽ መንግስት ክፉኛ የሆነ ክትትል እየተደረገብን ነው
እኛ ምንም አቅም የለንም በስራም በኩል ሆነ በጎዳናዎች ላይ ህብረተሰቡ ጥላቻውን አድርቶብናል ፣በተለያዩ ካፍቴሪያዎች ወንድሞቻችን እና
እህቶቻችን ተደብድበዋል በማለት ስሜታቸውን የገለጹት በተለይም በአሁኑ የኢትዮ-ግብጽ አጣብቂኝ ሁኔታ ሁላችንንም ውስጥ በመከራ
ከቶናል ሲሉ ተናግረዋል ።
በግብጽ የሚገኘውም የኢትዮጵያ ኮሙኒቲ ማናቸውንም ዜጎች ለጊዜው ኢትዮጵያዊ ነኝ ብለው እራሳቸውን ለአደጋ
እንዳያጋልጡ ማስጠንቀቂያ መስጠቱን ጠቁመዋል ።
በአባይ ግድብ ምክንያት እና መስመሩን በመቀየሱ ምክንያት ውጥረቱን ማየሉን
አስመልክቶ የተለያዩ የውጭ ዜጎችም ለውጭ ዜጎች ለግብጽ ማስጠንቀቂያ እሰጡ ቢሆንም ፣ በሌላም በኩል ደግሞ የኢትዮጵያ ኤምባሴ
በግብጽ ሰራዊት መከበቡን ከስፍራው የደረሰን ዘገባ አረጋግጦአል ። ይህ በእንዲህ እንዳለ ዜጎችን የማዳን እና ካሉበት ስፍራ ወደ ተሻለ ሁኔታ
ለማኖር የሚያስችለውን ተግባር የማድረግ ጥረት እንዲደረግ ርብርቦሹ እንዲጠናከር የማለዳ ታይምስ መረጃ ማእከል ይመክራል።

Wednesday, June 5, 2013

በጦርነቱ ሰበብ በተዘረፈ ሐብት የሕወሃት ጄነራሎች ሚሊየነር ሆነዋል፡፡

ማን ያውራ የነበረ…….ማን ያርዳ የቀበረ……”

 “….የጦር መኮንን ሆነህ እንደባለሙያ ስታየው ውጊያው በጥቅሉ የሙያ ብቃት ያልታየበት አሳፋሪ ጦርነት ነበር ማለት ይቻላል፡፡በጃንሆይ እና በደርግ ዘመን ኤርትራ ላይ ውጊያ ተደርጎ የተሰዋው ዜጋችን ቁጥር ከ250 ሺ እስከ 300 ሺ ይደርሳል፡ከዚህ አንፃር ወያኔ በአንድ ዓመት ውስጥ ኤርትራ ላይ ያስፈጀው የወታደር ቁጥር በጣም አሳፋሪ ነው፡፡ከመከላከያ የሰው ኃይል አስተዳደርና ልማት መምሪያ ሰነዶች ያገኘሁት መረጃ እንደሚያሳየው በጠቅላላ በኢትዮ ኤርትራ ውጊያ 98,700 ወታደር ሲሞትብን 194¸300 ቁስለኛ ተረክበናል፡፡

ከኦርዲናንስ እዝ ያገኘሁት መረጃ ደግሞ መጀመሪያ ለውጊያ ከተዘጋጀው ከባድ መሳሪያ 2ሐ3ኛው መውደሙን ነግረውኛል፡፡ ይህንን ትርጉም አልባጦርነት የመሩት መሪዎች ሰዓረ መኮንን፣ ሳሞራ የኑስ፣ዮሀንስ ገብረመስቀል፣ታደሰ ወረደ፣ኳርተር /አብርሃ ወልደማርያም/፣ ብርሃነ ነጋሽ የተባሉት ጄነራሎች ናቸው፡፡ የጦርነቱ ማዕከላዊ እዝ አባላት ደግሞ መለስ ዜናዊ፣ ስዬ አብርሃ፣ ተወልደ ወልደማርያም፣ አለምሰገድ ገብረአምላክ፣ ተፈራ ዋልዋ፣ ፃድቃን ገብረትንሳኤ እና ክንፈ ገብረመድሕን ነበሩ፡፡

 ያ ሁሉ ዜጋ ያለቀበትና ያ ሁሉ የሀገር ሀብት የወደመበት ጦርነት ከጦርነት አመራር ችግር መሆኑ በግልፅ እየታወቀ አንድም የጦርነቱ መሪ ተጠያቂ ሳይሆን እንዲሁ መቅረቱ በጣም ያሳዝናል፡፡…….”
ኮሎኔል አለበል አማረ

 የአጋዚ ኮማንዶ አመራር አባል የነበሩ እና በግንቦት 7 መፈንቅለ መንግስት ሙከራ ተጠርጥረው ዕድሜ ልክ ፅኑ እስራት የተፈረደባቸው

 ሌላኛው ኮሎኔል ደግሞ እንዲህ ይሉናል፡

“……የኢትዮ ኤርትራ ጦርነት ለጦርነቱ መሪዎች የሐብት ምንጭ ሆኖ ማገልገሉን ማየት ችያለሁ፡፡ በጦርነቱ ሰበብ በተዘረፈ ሐብት የሕወሃት ጄነራሎች ሚሊየነር ሆነዋል፡፡ ፃድቃን፣ ጀቤ፣ ብርሃነ ነጋሽ፣ ገዛኢ አበራ፣ አባዱላ ገመዳ፣ አበባው ታደሰ፣ ባጫ ደበሌ፣ ታደሰ ወረደ፣ ሰዓረ መኮንን፣ እና ሌሎችም ጄነራሎች በአዲስ አበባ በባህርዳርና በመቀሌ ያስገነቡት ቪላና ፎቅ ውበቱ አይንን ያፈዛል፡፡ የቤት እቃዎቻቸው፣ ምንጣፎቹ፣ መብራቶቻቸውና ኮርኒሶቻቸው በውድ ዋጋ ከአውሮፓ እየተጫኑ የመጡ ናቸው፡፡ የመጨረሻውን ቴክኖሎጂ እየተጠቀሙ ለቪላዎቻቸው ማሞቂያና ማቀዝቀዣ ተክለውላቸዋል፡፡ ከዚያ ሁሉ እልቂት በኋላ ጄነራሎቹ በቀጥታ ወደ ሃብት ፉክክር ነው የገቡት፡፡ የሚፈሰው ገንዘብ በጦርነቱ ወቅት የተዘረፈ ነው፡፡ …..”
ኮሎኔል አበበ ገረሱ
ጎበዝ የአበበችን ጠባሳ ያየ በእሳት አይጫወትም ይባላል፡፡ በኢትዮ ኤርትራ ጦርነት ለሀገራቸው ዳር ድንበር መከበር ሲሉ በኢትዮጵያዊነት የሀገር ፍቅር ስሜት ግን ደግሞ የወያኔን መሰሪ ባህርይ ባለመረዳት ውድ ሕይወታቸውን መስዋዕት ያደረጉት የነ በረከት፣ አባዱላ፣ ስዩም፣ አዲሱ እና ከላይ ያየናቸው ጄነራሎች እና የወያኔ ባለስልጣናት ልጆች አልነበሩም፡፡ የምስኪኑ ደሃ ኢትዮጵያዊ ልጆች እንጂ፡፡ ለዚያውም እኮ ያ ሁሉ ጀግና ወታደር ያለቀበት መሬት በጀርባ በተደረገ ስምምነት የኢዮጵያን ሕዝብ አጭበርብሮ ለወራሪው ሃገር እንዲመለስ አድርጓል፡፡ እነዚህ መስዋዕት የሆኑ ልጆቻችን ግን ለቤተሰባቸው መርዶ ማድረስ ቀርቶ ለአንድ ደቂቃ እንኳን የሕሊና ፀሎት እንዲደረግላቸው ያስታወሰ አንድም የወያኔ ባለስልጣን የለም፡፡ ባጭሩ ወያኔ ድሃውን ኢትዮጵያዊ የሚያየው ልክ እንደ ኮንደም ነው፡፡ በአፀያፊ ሁኔታ ይጠቀምባቸውና እንደ ቆሻሻ ይጥላቸዋል፡፡

 ይኸው አሁን ደግሞ ግብፅ፤ ልትወረን ነው በማለት የጦርነት ነጋሪት እንደለመደው እያስጎሰመ ነው፡፡ ኢትዮጵያ በታሪኳ ከግብፅ ጋር ባደረገችው ጦርነት አንድም ጊዜ ተሸንፋ አታውቅም፡፡ ይኸውም የአባቶቻችን ወኔ እንዳለ ሆኖ በዋናነት የጦር መሪዎቹ አመራር ወሳኝ ነበር፡፡ ዘንድሮ ግን የዚህ ዓይነት ጄነራሎችን ይዘን ወደ ጦርነት ብንገባ ዳግም ድሃውን ኢትዮጵያዊ ማስጨረስና ለወያኔ ጄኔራሎች የሐብት ዝርፊያ መመቻቸት መስሎ ይታየኛል፡፡ በዋናነትም የወያኔ የሰሞኑ ልፍለፋ እንደለመደው የሀገር ውስጥ ችግርን ለማስቀየስ የሸረበው አዲስ ተንኮል እንጂ ከልቡ ለአባይና ሀገር ተቆርቋሪ ሆኖ በማሰብ ነው ብዬ በግሌ አምናለሁ፡፡ ከዚህ በኋ በወያኔ ቆስቋሽት በሚነሳ ጦርነት የአንድም ኢትዮጵያዊ ደም መሬት ላይ ይፈስ ዘንድ ፈፅሞ አልሻም፡፡

አባይ ቢገደብ በጣም ደስ ይለኛል ከሁሉም በላይ ደግሞ ወደ ውጭ ሀገር በመሰደድ ላይ ያለው የሀገሬ የተማረ ሰው ፍልሰት ቢገደብ እንዲሁም ከአባይ የበለጠ ሀገርን ሊያሳድግ የሚችል ፈጠራና ግኝቶችን ማውጣት የሚችለው የሰው ልጅ ሕይወትና ሕሊና በአባይ ሰበብ መስዋዕት ይሆን ዘንድ ተገቢ ነው ብዬ አላምንም፡፡

 ደብተራው ፀጋዬ

Breaking News: Armoured Vehicles Surround Ethiopian Embassy In Cairo

Awramba Times – The Ethiopian embassy in Cairo is surrounded by heavily armed personnel and armoured vehicles. Ethiopian citizens, both refugees and Ethiopian-passport holders, are savagely harassed and beaten by ordinary Egyptians and the police everywhere they move.

According to our sources, it is very difficult for Ethiopians to move around and many people are starving as they fear for their life to go out and buy foodstuff and drinking water. Egyptians are preparing a massive demonstration against Ethiopia to be held next Friday.

On the other hand, Ethiopian Ambassador to Egypt Mohamed Dirrir met with Egyptian opposition leader and former Secretary General of the Arab League, Amr Moussa in Cairo today. Ambassador Mohamed Drirr has a two hours meeting with Amr Moussa on the recent developments on the Nile and has made clear that Ethiopia has no any intention of harming egypt or affecting its access to the Nile waters.

source: awrambatimes.com

EPRDF going bankrupt due to few readerships: Document

ESAT News    June 3, 2013
  
The ruling Ethiopian People’s Revolutionary Democratic Front (EPRDF) has said that it was going bankrupt due to lack of readership of its Party Organ newspapers and magazines.

 Although the Front attempted to change the contents of its Abiyotawi Democracy newspaper and Addis Raeye magazine, both the leadership and members are not willing to read. Abiyotawi Democracy is mainly produced for farmers and those with primary education while Addis Raeye is prepared for members with advanced education.

This was revealed in a document that ANDM, member party of the EPRDF, prepared for its senior and mid level leadership titled “the evaluations of the 10th Organizational Congress: Decisions and Future Directions”. The 43 page document explains the problems that both ANDM and EPRDF have faced.

The document states that many members join the ruling party with the aim of finding jobs and other benefits but as they fail to succeed in that, they leave the party. Although many members have been recruited in the rural areas, they are only good at helping themselves than leading, supporting and empowering others. In cities, the document states, very few people working in small and micro business, the civil service and educational institutions have been recruited and those few have many limitations in their allegiances.

It stated that although Abiyotawi Democracy offers analytical articles few members pay attention to it, feel unhappy to purchase copies and deliberate on them. Similarly, the report said little attention has been given to the biannual magazine, Addis Raeye. The main problem, the report said, is within “the leadership”. Problems in distribution, participation and quality were mentioned as the shortcomings of the magazine.

The document said that the leadership and members of the Front seriously lack theoretical, reading culture, political and ideological knowledge.

According to the report, poor leadership is the basic cause of poverty, bad governance and social problems in the Amhara region particularly

ESAT Daily News Amsterdam June 04, 2013 Ethiopia


ከተቃውሞ ሰልፉ በሁዋላ በመካከለኛ ደረጃ ላይ የሚገኙ አመራሮች እየተገመገሙ ነው

ግንቦት ፳፯ (ሀያ ሰባት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም

ኢሳት ዜና:-ባለፈው እሁድ ሰማያዊ ፓርቲ ያካሄደውን የተቃውሞ ሰልፍ ተከትሎ በማግስቱ የኢህአዴግ ባለስልጣናት በተለያዩ ክልሎች የሚገኙ አመራሮችን እንዲሁም በፕሮፓጋንዳ መስክ ላይ የተሰማሩትን በመጥራት ዜናውን እስካጠናከርንበት ጊዜ ድረስ ግምገማ እያካሄደ መሆኑን ለማወቅ ተችሎአል።

 አብዛኞቹ አመራሮች ሂስና ግለሂሳቸውን እንዲያወርዱ የተጠየቁ ሲሆን፣ የድርጅቱ አባሎች በጸረ ህዝቦች ፕሮፓጋንዳ በመወናበድ እና ለግንባሩ ርእዮተ አለም ትኩረት ባለመስጠት ድርጅቱን ከውስጥ እያዳከሙት ነው የሚል ወቀሳ ከከፍተኛ አመራሮች ተስምቷል።
ግምገማው በክልል ከተሞችም በመካሄድ ላይ መሆኑን ለማወቅ ተችሎአል። አብዛኞቹ ነባር አመራሮች ” በጦር ያልተፈታው ኢህአዴግ በወሬ አይፈታም” በማለት በመካከለኛ ደረጃ ላይ የሚገኙ አመራሮች፣ ጸረ ሰላም ሀይሎች ከሚነዙት ፕሮፓጋንዳ ራሳቸውን እንዲያቅቡ ተነግሮአቸዋል።

በግምገማው የተሳተፈ አንድ የድርጅት አባል “እንዲህ አይነት ግምገማ በድርጅቱ ታሪክ ውስጥ አጋጥሞኝ አያውቅም፣ ከእሁድ በሁዋላ ድርጅታችን ታምሷል፣ መሪዎቻችን በጣም ተበሳጭተው መግቢያ እያሳጡን ነው” በማለት ለኢሳት ተናግሯል።
ይህ በእንዲህ እንዳለ በአቶ አዲሱ ለገሰ የሚመራ ቡድን በደቡብ ኢትዮጵያ እየተዘዋወረ የህዝብ አስተያየት በመሰብሰብ ላይ ነው።  አቶ አዲሱ ትናንት በዴቻ ወረዳ  160 ሰዎችን ሰብስበው ስለመልካም አስተዳደርና ስለሌሎች ጉዳዮች አወያይተዋል። በስብሰባው ላይ ለመሳተፍ የጠየቁ ወጣቶች ስብሰባውን እንዳይካፈሉ መደረጋቸው ታውቋል።

Tuesday, June 4, 2013

አርበኞች ግንባር በሁመራ አካባቢ በወያኔ 35ኛ ክፍለጦር ላይ ጥቃት ሰነዘረ

ነበልባሉ የኢትዮጵያ ሕዝብ አርበኞች ግንባር ሰራዊት በሉግዲና በበረከት ተከታታይ ወታደራዊ ጥቃት ፈፀመ።

ነበልባሉ የኢትዮጵያ ሕዝብ አርበኞች ግንባር ሰራዊት በግንቦት 24-2005 ዓ.ም ከወያኔ መከላከያ ጋር በሉግዲ ባካሔደው ውጊያ ከፍተኛ ድል መቀዳጀቱ ይታወሳል።

Ethiopian People Patriotic Frontበግንቦት 25-2005 ዓ.ም በቀጠለው ውጊያ በሁመራ ልዩ ስሙ በረከት በተሰኘ ስፍራ ከአምባገነኑ አገዛዝ 35ኛ ክፍለጦር እና ከሚሊሻ ሰራዊት ጋር በተካሄደው ውጊያ በተከታታይ በስምንት/8/ ዙር ፋታ የለሽና እልህ አስጨራሽ ውጊያ 148 ሙት፣ 374 ቁስለኛ፣ 31 ክላሽንኮፍ፣ጠመንጃ 47 የእጅ ቦንብ ፣2 ስናይፐር፣ 3 መትረየስና የተለያዩ ወታደራዊ ቁሳቁሶች ማርኳል።

በእለቱ በተካሄደው ውጊያ የአካባቢው ማህበረሰብ የኢትዮጵያ ሕዝብ አርበኞች ግንባር ባሳየው ከፍተኛ ወታደራዊ ጀብድ መደነቃቸውንና ድርጅቱ ያለውን ወታደራዊና ፖለቲካዊ ብቃት ያሳየ መሆኑን ገልፀው ፣ ወጣቶችም በዚህ ሃይል ጠላት ማሽመድመድ የሚችል ድርጅት መሆኑን አስመስክሯል ሲሉ ተናግረዋል።

ለስምንት ዙር ያህል በተካሄደው ውጊያ የአገዛዙ ቅጥረኛ ጦር ቁስለኞች ወደ ዳንሻ፣ ማይካድራ፣ ሁመራ የመሳሰሉት ቦታዎች በሚገኙ የጠላት የሕክምና ተቋማት ቁስለኞችን እየጫኑ ማጓጓዝ ላይ ተጠምደው እንደዋሉና ገሚሶቹ ከፉኛ በመቁሰላቸው ሕክምና እርዳታ ሳይጀመርላቸው መሞታቸው ታውቋል።

ከኢትዮጵያ ሕዝብ አርበኞች ግንባር ሰራዊት በደረሰበት ድንገተኛ ጥቃት አከርካሪው የተሰበረው 35ኛ ክፍለ ጦር በድንጋጤና ፍርሃት ውስጥ ተሸብቦ በመጨነቅ ላይ በመሆናቸው የአካባቢውን ማህበረሰብ ያለስራው እየተንገላታ እንደሚገኝ ታውቋል።
የኢትዮጵያ ሕዝብ አርበኞች ግንባር ሰራዊት አሁንም ቢሆን ወያኔው ለሕዝብ መሰረታዊ ጥያቄዎች መልስ ባለመስጠት አቋሙ የሚቀጥል ከሆነና ስለ አባይ ግድብ እያወሩ ሕዝብን ኢ-ፍትሃዊ በሆነ መንገድ መግዛቴን እቀጥላለሁ የሚል ከሆነ በሁመራ ልዩ ስሙ በረከት እንዲሁም በሉግዲ በ35ኛ ክፍለ ጦርና በሚሊሻ ላይ የተወሰደው አኩሪ ወታደራዊ እርምጃ አይነቱን ቀይሮና ተጠናክሮ የሚቀጥል መሆኑን ያስታውቃል።

በግንቦት 24 እና  25-2005 ዓ.ም በተካሄደው ውጊያ በድምሩ 192 ሙት 440 ቁስለኛ ቁጥራቸው የበዛ ተተኳሽ መሳሪያዎችን ከነትጥቃቸው በመማረክ የታሪኩ አካል የሆኑ  ተዋጊ አርበኞች እንዳሉት እኛ ለሀገራችን ኢትዮጵያና ሕዝቧ እስከ ሕይወት መስዋዕትነት ለመክፈል ፊት ለፊት በጠመንጃ አረር እየተፋለሙ እንደሚገኙና ትግሉ ለመላው የኢትዮጵያ ሕዝብ ጥቅም ሲባል የሚደረግ እንደመሆኑ መጠን የሁሉም ርብርብና ተሳትፎ አስፈላጊና የውዴታ ግዴታ በመሆኑ የአገራችን ችግር መፍትሔ ለመስጠት በአምባገነኑ የወንበዴ ቡድን በሆነው ወያኔ ላይ እንዝመት ሲሉ ጥሪያቸውን አስተላልፈዋል።

በሰስዊዘርላድ-ጄኔቭ ኢህአዴግ የጠራው የቦንድ ሽያጭ ስብሰባ “ከ ዓባይ በፊት የሰብዓዊ መብት ጥሰት ይገደብ!” የሚል መፈክር ባነገቡ ኢትዮጵያውያን ብርቱ ተቃውሞ ከሸፈ

ግንቦት ፳፮ (ሀያ ስድስት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም

ኢሳት ዜና:-ኢህዴግ -በጄኔቭ  ለ ዓባይ ግድብ ቦንድ ሽያጭ ለማካሄድ ካለፉት ሁለት ወራት ወዲህ በምስጢር ከፍተኛ ዝግጅት ሲያደርግ ከቆየ በሁዋላ በቅርቡ ለደጋፊዎቹ ብቻ የዝግጅቱን ዕለት፣ቦታ እና ሰዓት አስመልክቶ ጥሪ ያቀርባል።

ይሁንና ኢህአዴግ  መቼ እና የት ዝግጅቱን ሊያደርግ እንዳሰበ የውስጥ መረጃ የደረሳቸው በጄኔቭ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ጎን ለጎን የተቃውሞ ዝግጅት ሲያስተባብሩ ይከርማሉ።

ከተቃውሞ ሰልፉ አስተባባሪዎች አንዱ የሆኑት አቶ ጴጥሮስ አሸናፊ እንደገለጹት፤በስፍራው የሚገኙት  የ ኢህአዴግ ካድሬዎች ተቃውሞ እንዳይነሳ በማሰብ ዝግጅቱን ከጄኔቭ ወጣ ብሎ በሚገኝና ለትራንስፖር ፈጽሞ አመች ባልሆነ ጭር ባለ ስፍራ እንዲሆን ቢያደርጉም በ ኢትዮጵያኑ ብርቱ ተቃውሞ ሊሳካላቸው አልቻለም።

እንደ አቶ ጴጥሮስ ገለፃ ከትናንት በስቲያ  ቅዳሜ በ ኢትዮጵያ ሰ ዓት አቆጣጠር ከቀኑ 10 ሰ ዓት ጀምሮ ሊካሄድ የታሰበውን የቦንድ ሽያጭ ለመቃወም ከዙሪክ፣ከበርገን፣ከሎዛን እና ከባዝል-ከተሞች  ከ 200 በላይ ኢትዮጵያውያን  አውቶቡሶችንና ሚኒባሶችን በመከራየትና የግል መኪኖቻቸውን በማሽከርከር በዝግጅቱ ቦታ የተገኙት  አንድ ሰ ዓት በመቅደም ነበር።

የ ኢትዮጵያውያን ማህበር በስዊዘርላንድ፣ ግንቦት 7 ለፍትህ ለነፃነትና ለዲሞክራሲ ንቅናቄ፣የ ኦሮሞ ነፃነት ግንባር፣የቢላል ኢትዮ-ስዊዝ ማህበር፣የዲሞክራሲያዊና የሰብዓዊ መብቶች አስተባባሪ ወጣቶች ግብረ-ሀይልና የስዊዘርላን ድምፃችን ይሰማ ኮሜቴ በጋራ በመሆን ባስተባበሩት በዚህ ሰልፍ ፦”ከዓባይ በፊት ዘረኝነት ይገደብ! በግፍ የታሰሩ ጋዜጠኞች፣የህዝበ-ሙስሉሙ መሪዎችና የፖለቲካ እስረኞች ይፈቱ!” የሚሉት መፈክሮች መስተጋባት የጀመሩት ገና የ ኢህአዴግ ዝግጅት ሳይጀመር ነው።

ተቃውሞው እያየለ በመምጣቱ የ ኢህአዴግ ደጋፊዎች እንደተጠበቀው ወደ አዳራሹ ሊመጡ አለመቻላቸውን የገለጹት አቶ ጴጥሮስ እስከ ምሽቱ አራት ሰ ዓት ድረስ  ራሳቸውን ተሸፋፍነውና አቀርቅረው ወደ አዳራሹ የገቡት ሰዎች ከ 30 እንደማይበልጡ ተናግረዋል።

በተቃውሞው ማየል ፕሮግራሙ ይጀመራል በተባለበት ሰ ዓት ካለመጀመሩም ባሻገር የዝግጅቱ እንግዳ የነበሩት በስዊዝ የ ኢትዮጵያ አምባሳደር እና ሌሎች የ ኢህአዴግ ባለስልጣናት ወደ ስፍራው ዝር ሳይሉ ቀርተዋል።

በስፍራው የሚገኘው የ ኢሳት ወኪል እንዳጠናቀረው ሪፖርትም፤በሰልፈኞቹ ጩኸት የተደናገጡት ጥቂት ተሰብሳቢዎች ወደፖሊስ በመደወል ተጨማሪ ሀይል እንዲመጣላቸው ባቀረቡት ተማጽኖ መሰረት የፖሊስ ሀይል ቢመጣም፣ ዝናቡ ጉሉበቱን ጨምሮ ቢወርድም፣ ኢትዮጵያውያኑ ያለ አንዳች መነቃነቅ በከፍተኛ ወኔ እና አገራዊ ስሜት ተቃውሟቸውን ቀጥለዋል።

የተቃውሞ ሰልፈኞቹ ከዚህም ባሻገር በዝግጅቱ አዳራሽ ተሰቅሎ የነበረውን ባለ ኮከብ ባንዲራ በማውረድና ፦”ኢትዮጵያውያንን የሚወክለው ባንዲራ ይሄ ነው”በማለት ትክክለኛውን የ ኢትዮጵያ ባንዲራ ሰቅለዋል።

ሰልፈኞቹ በዚህም ሳይወሰኑ   በአዳራሹ ውስጥ የጋዜጠኞችን፣የፖለቲካ እስረኞችንና የታሰሩትን የሙስሊም አመራሮች ፎቶግራፎች ለጥፈዋል።

“በኦሮሞ ነፃነት ግንባር መካከል መለስተኛ ልዩነት የተፈጠረ ቢሆንም፣ በዚህ ሰልፍ ላይ ግን ከሁለቱም ወገኖች ያሉት የግንባሩ አባላት ተገኝተው ከሁላችንም ጋር በአንድ ላይ ድምፃቸውን ማሰማታቸው በጣም ደስ የሚያሰኝና ልዩ ስሜትን የፈጠረብን ክስተት ነበር”ብለዋል-አቶ ጴጥሮስ።

ዕለቱ የሰማያዊ ፓርቲ ሰልፍ የሚካሄድበት ዋዜማ መሆኑም ለሰልፈኞቹ ትልቅ ደስታን የሰጠና ተስፋን የፈነጠቀ ነበርም ብለዋል-አስባባሪው።

በ ኢትዮጵያውያኑ ብርቱ ተቃውሞ ገንዘብ የመሰብሰብ እቅዳቸው የከሸፈባቸው የ ኢህአዴግ ካድሬዎች በስተመጨረሻም ያዘጋጁትን ምግብ ሳይቀር የውጪ ዜጎችን በመጥራት በነፃ እስከመጋበዝ ደርሰዋል።

“የ አባይ መገደብ የሁላችንም ደስታ ነው፤ ዓባይ እንዲገደብ እንሻለን። ሰውን ያለ አግባብ እየገደሉና እያሰሩ በሰው ደም ላይ የሚደረግን ልማት ግን እንቃወማለን!ዓባይም ከልማት አልፎ ለፖለቲካ ንግድ መዋሉን ም ፈጽሞ አንቀበለውም! ቅድሚያ ፍትህ፤ነፃነት፣ዲሞክራሲ በአገራችን ይንገስ! ያኔ ዓባይን በጋራ ክንድ እንገነባዋለን!”ብለዋል-አስተባባሪው ስለተቃውሞ ሰልፉ ዓላማ ሲያብራሩ።

ሰማያዊ ፓርቲ በጠራው የተቃውሞ ሰልፍ ላይ መንግስት የሰጠውን ማስፈራሪያ አመራሮች እና የህግ ባለሙያዎች ውድቅ አደረጉት

ግንቦት ፳፮ (ሀያ ስድስት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም

ኢሳት ዜና:-እሁድ ግንቦት25 ከፍተኛ ህዝብ የተገኘበትን የተቃውሞ ሰልፍ በተመለከተ የኢህአዴግ የጽህፈት ቤት ሀላፊ የሆኑት አቶ ሬድዋን ሁሴን ለሬዲዮ ፋና ሲናገሩ ” የሃይማኖት አክራሪነትን አጀንዳው አድርጎ ሲንቀሳቀስ የነበረው ሰማያዊ የፖለቲካ ፓርቲ ጸረ ህገ መንግስታዊ እንቅስቃሴው ዛሬ በጠራው ሰልፍ ተጋልጧል ” ብለዋል።

ፓርቲው ያዘጋጀውን ሰላማዊ ሰልፍ ላልተፈለገ አላማ አውሎታል ያሉት አቶ ሬድዋን ፣ በሰልፉ በአብዛኛው የተንጸባረቀው የሙስሊም መፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴዎች ይፈቱ እየተባለ መስተጋባቱ ፥ ፓርቲው ህገ መንግስቱን በመጣስ በሃይማኖት እጁን መክተቱና በህግ የበላይነት አምናለሁ እያለ በፍርድ ቤት ጉዳያቸው የተያዘባቸው ሰዎች በሁካታ ይፈቱልን ማሰኘቱ ተጠያቂ ያደርገዋል ሲሉ አክለዋል።

የኮሚኒኬሽን ጽህፈት ቤት ሚኒስትር ዲኤታ የሆኑት አቶ ሽመልስ ከማልም እንዲሁ የአቶ ሬድዋንን ንግግር የሚያጠናከር አስተያየት ለኢቲቪ ሰጥተዋል

ጉዳዩን በማስመልከት ጥያቄ የቀረበላቸው   ኢ/ር ይልቃል ጌትነት  መንግስት የሚያቀርበው የሀሰት ውንጀላ ከወደፊቱ ጉዙአቸው እንደማይገታቸው ተናግረዋል **

በእለቱ ተናጋሪ የነበሩት ዶ/ር ያእቆብ ሀይለማርያም ህዝቡ ከ8 አመታት በሁዋላ ለመጀመሪያ ጊዜ የተቀዳጀው መብት መሆኑን ገልጸው፣ ህገመንግስቱን የጣሰው መንግስት እንጅ ፓርቲው ወይም እርሳቸው አለመሆናቸውን ተናግረዋል።

በተመሳሳይ ዜና ደግሞ ሁለት ታዋቂ ህግ ባለሙያዎች መንግስት ያቀረበውን ውንጀላ ውድቅ አድርገውታል።

 የድምጻችን ይሰማ የሙስሊም አመራሮችን የፍርድ ቤት ጉዳይ የያዙት አቶ ተማም አባቡልጉ ሙሰሊም ኢትዮጵያውያን ኢትዮጵያዊ በመሆናቸው ተቃውሞአቸውን የማሰማት መብት እንዳላቸው፣ ገልጸዋል። የእኛ ደንበኞች የህገመንግስት መብታቸው በመጣሱ አመለካከታቸውን  በተቃውሞ ማቅረባቸው መብታቸው መሆኑን የገለጹት አቶ ተማም፣ ህገወጥ የሚሆነው ሰዎች ለምን መብታችሁን ገለጻችሁ ተብለው እንዲሸማቀቁ መደረጋቸው ነው ብለዋል።

የርእዮት አለሙ አባት አቶ አለሙ ጎቤቦ በበኩላቸው ህግ ሰላማዊ ሰልፍ ማድረግን እንደማይከለክል እና በፍርድ ቤት ላይ የሚኖረው ተጽኖ አለመኖሩን ገልጸው መንግስት ህዝቡን ለማስፈራራት እና ሀሳቡን እንዳይገልጽ ለማድረግ የወሰደው ሊሆን እንደሚችል ገልጸዋል::

Monday, June 3, 2013

በሽዎች የተጀመረው እንቅስቃሴ የሚሊዮኖች ይሆናል!

የኢትዮጵያ ሕዝብ የጋራ ትግል ሸንጎ (ሸንጎ)
Ethiopian People’s Congress for United Struggle (Shengo)


ግንቦት ፳፭ ፣ ፳፻፭

Ethiopian People's Congress for United Struggle (Congress)June 2, 2013

የኢትዮጵያ ሕዝብ የጋራ ትግል ሸንጎ (ሸንጎ) በዛሬው እለት  በሰማያዊ ፓርቲ ጠሪነትና በተለያዩ ድርጅቶች ተባባሪነት በአዲስ አበባ ለተካሄደው ሰላማዊ ሰልፍ ያለውን አድናቆትና የትግል አጋርነት በድጋሜ ይገልጣል።

ይህ በሽዎች የሚቆጠሩ ዜጎች ጎሳ፣ዕድሜ፣ጾታና እምነት ሳይነጥላቸው በአንድ ሆነው የሀገራችንን ህብር በሚያንጸባርቅና በታላቅ ሥነስርዓት የጋለ ስሜታቸውን በይፋ የገለጡበት ህዝባዊ ሠልፍ  ፣ በሕዝባችን ላይ የተጫነው የፍርሀት ድባብ እየተሰበረ መምጣቱን የሚያመለከት ታላቅ እርምጃ ነው።

ይህ  እጅግ ብዙ ወጣቶችን ያሳተፈ፣ ስሜት ቀስቃሽና ታላቅ ወኔ የታየበት የህዝብ ቁጣ፣ ህዝባችን ለዓመታት የተጫነበትን የግፍ ቀንበር ሊሸከም የሚችልበት ጀርባ እንደሌለው በግልጥ ያሳየበት ቀን ነው።

ይህ ስላማዊ ሰልፍ የኢትዮጵያ ህዝብ መሰረታዊ መብቶች ሙሉ በሙሉ እንዲከበር፣ ጎሳ ተኮር የህዝብ ማፈናቀል እንዲያበቃ፣ የኑሮ ውድነት እንዲወገድ፣ በፖለቲካ ጉዳይ በእስር ላይ ያሉ የፖለቲካ ድርጅት መሪዎችና ነጻ ጋዜጠኞች  በአስቸኳይ እንዲፈቱ፣ የመደራጀት መብት ሙሉ በሙሉ እንዲከበር፣ በየሃይማኖቶች የውስጥ ጉዳይ የመንግሥት ጣልቃ ገብነት እንዲቆምና የታሰሩት የሙስሊሙ ተወካዮች እንዲፈቱ በመጠየቅ የሀገሪቱን ሕዝብ ብሶት በሚገባ  አንፀባርቋል።

የኢትዮጵያ ሕዝብ የጋራ ትግል ሸንጎ (ሸንጎ) እነዚህና ሌሎች መሰረታዊ የመብት ጥያቄዎች ባሰቸኳይ እንዲመለሱና  ከዚህም አልፎ የአምባገነንነትና የጎጠኛ ስርዓት አክትሞ ህዝብ በምርጫ የራሱን መንግሥት የመመስረት መብቱ እንዲረጋገጥ ለማስቻል ከተለያዩ ኢትዮጵያዊ ሀይሎች ጋር ተባብሮ ትግሉን እንደሚቀጥል አሁንም ያረጋግጣል።

በሀገር ውስጥ ብቻ ሳይሆን፣ ከሀገር ውጭም፣ ዓለምአቀፉ ህብረተሰብ፣ ያለውን ሁኔታ ይበልጥ ተረድቶ፣ በመፍትሄ ፍለጋው አንጻር፣ አወንታዊ ሚና እንዲጫወት፣ ሸንጎው የተለያዩ እንቅስቃሴዎችን አጠናክሮ ይቀጥላል።

የተባበረ የህዝብ ትግልን ሊመክት የሚችል ምንም ሀይል የለምና፣ መብታችንን ለማሰከበር ትግላችን ተጠናክሮ ይቀጥል። ዛሬ የተካሄደው ሕዝባዊ የተቃውሞ ሰልፍ፣ ለተከታታይ ሕዝባዊ ንቅናቄዎች በር ከፋች እንጂ መደምደሚያ እንደማይሆን ሸንጎው ይተማመናል።

ሰላማዊው ትግሉ እንዳይቀጥል የሕወሓት/ኢሕዴግ አሸባሪ አገዛዝ ብዙ ጥረት እንደሚያደርግና ደፍረው በወጡትና ባዘጋጁት ላይም ስበብ እየፈጠረ የሽብር ክንዱን ከመሰንዘር ስለማይመለስ ከወዲሁ ነቅቶ መጠበቅና በጋራ መከላከል የሚቻልበት ዘዴ እንዲፈጠር፣ ተደናግጦና በርግጎም የተጀመረው የነጻነት ጉዞ እንዳይከሽፍና  እንዳይቆም  ሸንጎ ያሳስባል። ሁሉም ዜጋ  የተቻለውን ሁሉ እንዲያደርግም ጥሪ ያደርጋል።

ኢትዮጵያና ኢትዮጵያዊነት በቆራጥ ልጆቿ ትግል ተከብረው ለዘላለም ይኖራሉ

ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ

የኢትዮጵያ ሕዝብ የጋራ ትግል ሸንጎ(ሸንጎ)

Sunday, June 2, 2013

Thousands march for rights in rare Ethiopia protest

(Reuters) - About 10,000 Ethiopians staged an anti-government procession on Sunday in the first large-scale protest since a disputed 2005 election ended in street violence that killed 200 people.
The demonstrators marched through Addis Ababa's northern Arat Kilo and Piazza districts before gathering at Churchill Avenue in front of a looming obelisk with a giant red star perched on top, a relic of Ethiopia's violent Communist past.
Some carried banners reading "Justice! Justice! Justice!" and some bore pictures of imprisoned opposition figures. Others chanted, "We call for respect of the constitution".
A few police officers watched the demonstration, for which the authorities had granted permission.

"We have repeatedly asked the government to release political leaders, journalists and those who asked the government not to intervene in religious affairs," said Yilekal Getachew, chairman of the Semayawi (Blue) Party which organized the protests.
He said the demonstrators also wanted action to tackle unemployment, inflation and corruption.
"If these questions are not resolved and no progress is made in the next three months, we will organize more protests. It is the beginning of our struggle," he told Reuters.
Government officials were not immediately available for comment.
ANTI-TERRORISM LAW
Ethiopian opposition parties routinely accuse the government of harassment and say their candidates are often intimidated in polls. The 547-seat legislature has only one opposition member.
Though its economy is one of the fastest-growing in Africa, Ethiopia is often criticized by human rights watchdogs for clamping down on opposition and the media on national security grounds, a charge the government denies.
Critics point to a 2009 anti-terrorism law that makes anyone caught publishing information that could induce readers into acts of terrorism liable to jail terms of 10 to 20 years.
Last year, an Ethiopian court handed sentences of eight years to life to 20 journalists, opposition figures and others for conspiring with rebels to topple the government.
More than 10 journalists have been charged under the anti-terrorism law, according to the Committee to Protect Journalists, which says Ethiopia has the highest number of exiled journalists in the world.
Muslims, who form about a third of Ethiopia's mostly Christian population, staged mosque sit-ins in 2012, accusing the government of meddling in religious affairs and jailing their leaders.
Ethiopia, long seen by the West as a bulwark against radical Islamists in neighboring Somalia, denies interfering, but says it fears militant Islam is taking root in the country.
(Reporting by Aaron Maasho; Editing by George Obulutsa and Alistair Lyon)