Monday, April 8, 2013

ምርጫ እስኪያልፍ ሙዚቃ ቤቶች የቴዲ አፍሮና የፀጋዬ እሸቱን ዘፈኖች መክፈት ተከለከሉ


በአዲስ አበባ የተለያዩ ስፍራዎች በሚገኙ መዝናኛዎችና ሙዚቃ ቤቶች በሚያዝያ መጀመሪያ የሚደረገው የአካባቢ ምርጫ ሳያልፍ ሀገር ፍቅር ስሜት የሚቀሰቅሱ ዘፈኖችን እንዳይከፍቱ ክልከላ ተደረገ፡፡

ከጥቂት ቀናት በኋላ በሚደረገው የከተማ መስተዳድርና የአካባቢ ምርጫ ብቻውን የሚወዳደረው ኢህአዴግ በካድሬዎቹ አስገራሚ ትዕዛዞችን እየሰጠ እንደሚገኝ የፍኖተ ነፃነት ምንጮች ጠቆሙ፡፡

በአዲሱ ትዕዛዝ መሰረት ምርጫው እስኪያልቅ ድረስ ሙዚቃ ከፍ አድርገው የሚያጫውቱ ሙዚቃ ቤቶችና የመዝናኛ ስፍራዎች የሀገር ፍቅር ስሜት የሚቀሰቅሱና ስለባንዲራ የተዜሙ ዘፈኖችን መክፈት ተከልክለዋል፡፡በትዕዛዙ በተለይ የተከለከሉት የቴዲ አፍሮና የፀጋዬ እሸቱ አዲሱ አልበም ላይ የተካተቱት ዜማዎች ይጠቀሳሉ፡፡

ነጋዴዎቹ “ክልከላው ከምርጫው ጋር ምን እንዳያያዘው አልገባንም፣ሆኖም ከመንግስት የመጣ ትዕዛዝ ስለሆነ ላለፉት ሁለት ሳምንታት ዘፈኖቹን ማጫወት አቁመናል” ብለዋል፡፡

 ነጋዴዎቹ ጨምረው ለፍኖተ ነፃነት እንደገለፁት በተለያየ ጊዜ ለቁጥጥር የሚመጡት የወረዳ ካድሬዎች የተከለከሉትን ዘፈኖች ተከፍቶ ከሰሙ ዛቻና ማስፈራሪያ እንደሚያደርሱባቸው ፡፡ “የቴዲን ዘፈን በተለያዩ ወቅቶች አትክፈቱ ተብለን እናውቃለን” የሚሉት ነጋዴዎቹ የፀጋዬ እሸቱ አዲሱ አልበም ውስጥ ያሉት ሀገርንና ባንዲራን የሚመለከቱ ዘፈኖች በሬዲዮ እየተለቀቁ እነሱ እንዳይከፍቱ መደረጋቸው እንዳስገረማቸው ገለፀዋል፡፡

ምንጮቻችን ተዘዋውረው ያነጋገሯቸው ነጋዴዎች እንደገለፁት ይህ ክልከላ ጎልቶ የታየው በመርካቶና በፒያሳ አካባቢ ነው፡፡

ምንጭ ፍኖተ ነፃነት http://www.fnotenetsanet.com/?p=3853

Sunday, April 7, 2013

የህወሓት/ኢሕአዴግ የዘር ማጽዳትና የዘር ማጥፋት ዘመቻ በአስቸኳይ መቆም አለበት!

የኢትዮጵያ ሕዝባዊ አብዮታዊ ፓርቲ (ኢሕአፓ)
Ethiopian People’s Revolutionary Party (EPRP) (ዴሞክራሲያዊ/Democratic)

ዜጎች በሀገራቸው ውስጥ በመረጡት ሥፍራ የመኖር፤ ሠርቶ ሃብት የማፍራት፤ ቤተሰብ የመመሥረት…ወዘተ በማንም ሊሰጣቸው ወይም ሊነፈጋቸው የማይችል ሁለንተናዊ የዜግነትEthiopian People's Revolutionary Party (EPRP Democratic) መብቶቻቸው ናቸው። ከቅርብ ዓመታት ወዲህ ግን በዓለማችን የተነሱ የጎሣ እንቅስቃሴዎች ሁለንተናዊ የዜጎችን መብቶች በሚፃረር መልኩ አንድ-ወጥ የሆነ ወይም ከሌሎች ዘር የፀዳ ሀገርና መንግሥት ለመፍጠር ጥረዋል። ዓላማቸውን ሊያሳኩ ባልተቻሉባቸው ኅብረብሄር በሆኑ አገሮች ውስጥ ደግሞ የኤኮኖሚ፤ የፓለቲካና የወታደራዊ ኃይሉን በአንድ ዘር የበላይነት ለመያዝ ሲባል የዘር ማጽዳት ዘመቻ (ኤትንክ ክለዚንግ)ና የዘር ማጥፋት ዘመቻ (ጄኖሳይድ) ወንጀል መፈጸም የተለመደ ክስተት ሆኗል።
በዘጠናዎቹ መጀመሪያ ላይ የምሥራቁ የሶሻሊስት ካብ በተፈረካከሰበትና የሥልጣን ክፍተት በተፈጠረበት ወቅት፤ እነዚህ የጎሣ የወንጀል ቡድኖች በሕዝብ ውስጥ የነበሩ የፍትህ፤ የእኩልነትና የነፃነት ትክክለኛ ጥያቄዎችን በማጣመምና ለራስ እኩይ ዓላማ በማዋልና ሕዝብን በማሳሳት የጎሣ ወታደራዊ ኃይሎችን በማቋቋም አሰቃቂ የዘር ማጽዳትና የዘር ማጥፋት ወንጀሎችን ፈጽመዋል። ዓለምአቀፍ የዜና ሽፋን ባገኙት ሀገሮች፤ ለምሳሌ በዩጎዝላቪያ፤ በሩዋንዳ፤ በኮንጎ፤ በሱዳን….ወዘተ ወንጀለኞቹ በዓለምአቀፍ ፍርድ ቤት መፈለጋቸውና አንዳንዶቹም ተይዘው ለፍርድ በመቅረባቸው ዘግናኝ ወንጀላቸውን እንዲያቆሙ ወይም እንዲሰወሩ አድርጓቸዋል። እንደ ኢትዮጵያ ባሉ ሀገሮች ግን ዓለምአቀፍ የመገናኛ ብዙሃን ሽፋን ባለማግኘታቸው ወንጀሉ አሁንም በማንአለብኝነት በሰፊ እየተካሄደ ነው።
በኢትዮጵያ ውስጥ ይህ ዓይነቱ ወንጀል የተጀመረው የትግራይን ሪፕብሊክ እንመሠርታለን ባሉት እንደ መለሰ ዜናዊና ስብሃት ነጋ በመሳሰሉት በዘር ጥላቻ አባዜ የተለከፋ ግለሰቦች በድርጅቻቸው ውስጥ የበላይነት ከያዙበት ጊዜ ጀምሮ ነበር። መሠረታዊ ማጠንጠኛቸው በኢትዮጵያ ውስጥ ለነበረው የባላባታዊ ሥርዓት ጭቆናዎች ተጠያቂው የአማራ ሕዝብ ነው የሚል ነው። ለዚህም ነው ለትግራይ ሪፕብሊክ ምሥረታም እንቅፋት ሊሆን የሚችለው አማርኛ ተናጋሪው ነው በማለት በኢትዮጵያ ውስጥ ፀረ-አማራ ኃይል እንዲፈጥሩና በአማራው ላይ እንዲዘምቱ ያደረጋቸው። አሁንም ከሃያ ሁለት ዓመት አምባገነናዊ አገዛዝ በኋላ የምናየው ይኼው የፀረ-አማራነት ፖሊሲ በተግባር ሲተረጎም ነው። ይህንንም መርዘኛ የህወሓት ፓሊሲ በየቦታው በፈጠሯቸው ተለጣፊ ጅርጅቶችና ባደራጇቸው የጎሣ ወታደራዊ ኃይሎች አማካኝነት የዘር ማጽዳት ዘመቻውን በስፋት ተያይዘውታል።
ከጥቂት ወራት በፊት በጉራፈርዳ ወረዳ የታየው አሁን ደግሞ በቤኔሻጉል-ጉምዝ አካባቢ በሚኖሩ አማርኛ ተናጋሪ ዜጎች ላይ እየተደገመ ነው። ንብረትን ቀምቶ፤ ነፍሰጡርንና አራስን ሳይቀር አፈናቅሎ ማባረርና የድብደባና የግድያ ወንጀሎች በአማራው ሕዝብ ላይ መፈጸሙ ከበፊቱም የነበረውን ፖሊሲያቸውን ተግባራዊ እያደረጉት እንደሆነ የሚያሳይ ነው። ይህ ዓይነቱ ዘግናኝ ወንጀል በተለያዩ ጊዜያትና አካባቢዎች በተለይም በአኝዋኩ፤ በኦጋዴኑ፤ በኦሮሞው፤ በአፋሩ፤ በሙርሲው …ወዘተ ማህበረሰቦች ላይ በአሰቃቂ ሁኔታ ተፈጽሟል፤ አሁንም እየተፈጸመ ነው። ህወሓት/ኢህአዴግ ይህንን የዘር ማጽዳትና የዘር ማጥፋት ወንጀል የሚፈጽመበት ዋናው ምክንያት የፓለቲካ፤ የኤኮኖሚና ወታደራዊ የበላይነቱን ለማስጠበቅ ስለሆነ ለዚህ እኩይ ዓላማው መሳካት እንቅፋት ናቸው ብሎ በሚገምታቸው የኅብረተሰብ ክፍሎች ላይ ወደፊትም ተመሳሳይ ድርጊት ከመፈጸም እንደማይቆጠብ ግልጽ ነው።
ህወሓት/ኢህአዴግና ተላጣፊ ድርጅቶቹ አንድ ኢትዮጵያዊ በኢትዮጵያ ግዛት ውስጥ በመረጠው ቦታ የመኖር፤ የመሥራት በሕጋዊ መንገድ ንብረት የማፍራት፤ ቤተሰብ የመመሥረትና ልጆች የማሳደግ የማይገሰስ የዜግነት ሁለንተናዊ መብቱ እንደሆነና ማንም ፈቃድ ሰጪም ከልካይም ሊሆን እንደማይችል፤ ነፃ ፍርድ ቤቶች ባሉባቸው ሀገሮች በዘር ማጽዳት ወይም በዘር ፍጅት የተሰለፉ ቡድኖችም ሆኑ ግለሰቦች ተከሰው በፍርድ ቤት ቅጣት እንደሚበየንባቸው የተገነዘቡት አይመስልም ወይም ሊቀበሉት አይፈልጉም። የአገር ሉዓላዊነት በሚል ሽፋን ከሕግ ተጠያቂነት ማምለጥ እንደማይቻል ሊገነዘቡት ይገባል። በመሆኑም ማንኛውም ለሀገሩ የሚቆረቆር ኢትዮጵያዊ/ት በሀገራችን ውስጥ እየተካሄደ ያለውን የዘር ማጽዳትና የዘር ማጥፋት ወንጀል ለዓለም ኅብረተሰብ እንዲያሳውቀና ዓለምአቀፋዊ የዜና ሽፋን እንዲያገኝ ማድረግ ግዴታ አለበት። እንዲሁም በወንጀለኛ ግለሰቦችና ቡድኖች ላይ መረጃዎችን በመሰብሰብ በዓለምአቀፍ ፍርድ ቤት ክስ መመሥረትም መታለፍ የሌለበት ጉዳይ እንደሆነ ልናሳስብ እንወዳለን።
በመጨረሻም ይህን በአደባባይ የሚፈጸመውን የዘር ማጽዳትና የዘር ማጥፋት ወንጀል ለአንዴና ለሁል ጊዜ ለማስቆም የሚቻለው የፖሊሲው አራማጅ የሆነውን አምባገነን አገዛዝ በተባበረው የሕዝብ ክንድ ድባቅ ሲመታ ብቻ እንደሆነ ነው። አምባገነኑ አገዛዝ በዴሞክራሲያዊ አስተዳደር እስካልተተካ ድረስ ይህ እኩይ ተግባር እየተስፋፋ መቀጠሉ የማይቀር ነው፤ የእያንዳንዱን ኢትዮጵያዊ ቤት የሚያንኳኳበት ጊዜም ሩቅ አይሆንም።
የዘር ማጽዳትና የዘር ማጥፋት ተዋናኞች ባለፈው ሰሞን የኢህአዴግ ዘጠነኛ ጉባዔ ተብዮው ላይ ዓይናቸውን በጨው ታጥበው ስለ ዴሞክራሲ፤ ስለመልካም አስተዳደርና ስለሙስና…ወዘተ በመናገር በኢትዮጵያ ሕዝብ ላይ ሲያላግጡና ሲመፃደቁ ተስተውለዋል። “ጽድቁ ቀርቶ በወጉ በኮነነኝ” የሚል ይትባሀል እንዳለ እያስታወስን ድምፃችንን ከፍ አድርገን ለህወሓት/ኢህአዴግ ልንነግረው የምንፈልገው በአምባገነኑ አገዛዝ የሚወራለት ዴሞክራሲውና መልካም አስተዳደሩ ቀርቶ ይህን ዘግናኝ የዘር ማጽዳትና የዘር ማጥፋት ወንጀል ባስቸኳይ እንዲያቆም ነው!
ዜጎች መብቶቻቸውን በትግላቸው ይጎናፀፋሉ!
የኢትዮጵያ ሕዝብ በአንድነት ለዘለዓለም ይኖራል!

ም/ጠ ሚኒስትሩ «እስክንድር ነጋን እንፍታ» አሉ

ጠቅላይ ፍርድ ቤት፣ ሰኞ መጋቢት 30 ቀን 2005 ዓ.ም በእነ አቶ እስክንድር ነጋ፣ አንዱዋለም አራጌና ሌሎች ባቀረቡት የይግባኝ ጥያቄ ላይ ዉሳኔ ያሳልፋል ተብሎ ይጠበቃል። በጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ ዙሪያ በሚኒስትሮች ምክር ቤት ዉስጥ ዉይይት እንደተደረገ ፣ ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ መጋቢት 18 2005 ዓ.ም ባቀረበዉ ጽሁፍ ዘግቧል።

 read more http://ethioforum.org/wp-content/uploads/2013/04/eskinder2.pdf

Saturday, April 6, 2013

ለ3ኛ ጊዜ ህትመቱ የተቋረጠበት ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ ” ከእንግዲህ ከጫካ መለስ ባሉ መታገያ መንገዶች በመጠቀም መብታችን እናስከብራለን” አለ

መጋቢት ፳፰ (ሀያ ስምንት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም

ኢሳት ዜና:-እውቁ ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ ይህን የተናገረው ልእልና ጋዜጣ በመንግስት ጫና እንዳድታተም ከታገደች በሁዋላ ነው። ጋዜጠኛ ተመስገን ” የንግድ ሚኒስቴር በልእልና ጋዜጣ የቀድሞ ባለቤትና በአዲሱ ባለቤት መካከል ህገወጥ የሆነ የስም ዝውውር ተደርጓል በማለት የንግድ ፈቃዱ ” እንዲሰረዝ መደረጉን ተነግሯል።

ፍትህ ጋዜጣ በህገወጥ መንገድ እንዳይታተም ከተደረገ በሁዋላ፣ ጋዜጠኛው አዲስ ታይምስ መጽሄትን ከሌላ አሳታሚ ላይ በመግዛት ለተወሰኑ ሳምንታት ሲያሳትም ቆይቷል። መጽሄቷ በተመሳሳይ መንገድ እንድትዘጋ ከተደረገ በሁዋላ፣ ጋዜጠኛ ተመስገን እንደገና ልእልና ጋዜጣን ከሌላ አሳታሚ ላይ በመግዛት ስራውን ለመስራት ሞክሮ ነበር። ይሁን እንጅ ከ100 ሺ ብር በላይ በሆነ ወጪ የገዛው ጋዜጣ ከመንግስት በተላለፈው ጫና እንዳይታተም በድጋሜ ታግዶበታል

ተመስገን በራሱ ስም ፈቃድ አውጥቶ መስራት ከተከለከለ፣ ከእንግዲህ ወዲያ ስለሚኖረው አማራጭ ሲጠየቅ፣ “ያለኝ አማራጭ ከሲቪክ ተቋማት ጋር በመተባበር ፣ ከጫካ ትግል በመለስ ያሉትን የሰላማዋ ትግል አማራጮች በመጠቀም ፣ አስገዳጅ ሁኔታ በመፍጠር መብታችንን እናስከብራለን” ብሎአል።

ጋዜጠኛ ተመስገን ሰሞኑን በገዢው ፓርቲ ደጋፊዎች ከፍተኛ ወከባ ሲደርስበት እንደነበር መዘገባችን ይታወሳል። ተመስገን፣ ከ106 ያላነሱ ክሶችም እንዳሉበት ይታወቃል።

ወያኔ በአማራ ተወላጆች ላይ የጀመረውን የዘር ማጥፋት ዘመቻ እንደቀጠለ ነው

 
ወያኔ ለአማራ ህዝብ፤ ባህልና ታሪክ ያለዉን ጥላቻ ከተራ ጥላቻ አልፎ በተግባር አማራዉን ወደ ማጥቃት ዘመቻ አደገ እንጂ ለአንድም ቀን ቀንሶ አያውቅም። አማራው እንደ ሰው ልጅ የመኖር መብቱ፣ ስብእናው ተገፎ ከቀየው፣ ከመንደሩ የአፈራውን ንብረትና ገንዘብ እየተቀማ መባረሩ፣ መሰደዱ፣ እንግልቱ ሁሉ የወያኔ የበቀል እርምጃ ነው።

በአሶሳ፤ በደኖና በአርባጉጉ ውስጥ አማራ በመሆናቸዉ ብቻ ህጻናት፤ሴቶችና አረጋዉያን በግፍ ተገድለዋል። ባለፈዉ አመት በደቡብ ክልል ጉራ ፈርዳ እየተባለ በሚጠራዉ አካባቢ ለረጂም አመታት ከአካባቢዉ ኢትዮጵያዊ ወገናቸው ጋር ተግባብተዉ ይኖሩ የነበሩ የአማራ ብሄረሰብ አማራ በመሆናቸዉ ብቻ ለአመታት ያፈሩትን ንብረት ይዞ የመሄጃ ግዜ እንኳን ሳይሰጣቸዉ አከባቢዉን ያለ ምንም ቅድመ ሁኔታ ለቅቀዉ እንዲወጡ እንዲፈናቀሉ ተደርጓል።
ከመጋቢት ወር መጀመሪያ ጀምሮ ወያኔ በአማራዉ ህዝብ ላይ አዲስና ሰፋ ያለ የጥቃት ዘመቻ ጀምሯል። በደቡቡ የአገራችን ክልል በጉራፈርዳ የጀመረዉን አማራውን ነጥሎ የማጥቃትና የማንገላታት ዘመቻ አሁን ደግሞ በሰሜን ምስራቅ የአገራችን ክፍል በቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል ቀጥሏል።

የቅርብ ግዜው ደግሞ ከቤንሻንጉል ጉሙዝ ተፈናቅለው በምእራብ ጎጃም ዞን በፍኖተሰላም ከተማ ሜዳ ላይ ወድቀው የሚገኙት አማራ አርሶደአሮች የድረሱልን ጥሪ ማሰማታቸውና፤ ብሄረ አማራን እወክላለሁ ባዩ ብአዴን (የህወሃት ቡችላ) ጠበንጃ ደቅኖብን ወደ መጣችሁበት ተመለሱ ከዚህ ጥፉ ሲል አዋከበን፤ የወገን ያለህ ድረሱልን የት እንግባ ልጆቻችን የአውሬ ራት ሆኑ ሲሉ ስቃያቸውን አሰምተዋል። በርግጥ የህወሃት ተለጣፊው ብአዴን ሆዳቸው ስለሞላ ህሊናቸው ታውሮ ይህ በደል የሰው ልጅን የማጥፋት ሴራ መሆኑን እና በዘር ማጥፋት ወንጀል እንደሚያስጠይቅ የተረዱ አይደሉም።
ሰሞኑን በቤንሻንጉል ጉሙዝ ለረጂም አመታት ከአካባቢዉ ህብረተሰብ ጋር ተቀላቅለው ይኖሩ የነበሩ አያሌ የአማራ ብሄረስብ ተወላጆች ያፈሩትን ንብረት ለመሰብሰብ እንኳን ግዜ ሳይሰጣቸዉ የኔ ብለው ከሚጠሩት የመኖሪያ ቦታቸዉ እንደባዳ እየተገፉ እንዲወጡ ሲደረጉ በአንጻሩ በባህርዳር ከተማ ብአዴን የቱባ ባለስልጣናቱን ከርስ ለመሙላት የክልሉን ህዝብ ጮኸት ጀሮ ዳባ ብሎ ሽርጉድ ሲል የነበረ መሆንን ያገናዘበ ኢትዮጵያዊ ቁጭት በርካታ ነው ።

የኢትዮጵያ ህዝብ ሆይ፡ እርግጥ ነው ይህን ዘረኛ ቡድን ለማስወገድ በሚደረገው መራራ ትግል ሂደት ውስጥ በደልና ሰቆቃው እየበዛ እንደሚሄድ ቢታወቅም ተባብረን ከታገልነው ግን ይህን ልናሳጥረው እንችላለን። አለበለዚያ ግን እስከ መቼ ነው ወገኖቻችን በትውልድ መንደራቸው የሀገር ውስጥ ጥገኛ ጠያቂ የሚሆኑት? የአማራ ብሄረሰብ ተወላጆች ከቀያቸው የተባረሩት በኢትዮጵያዊ ዜግነታቸው ነው።

ግንቦት 7 ንቅናቄ ይህ የወያኔ ስርአት እስካልተወገደ ድረስ በአማራው የተጀመረው ጭፍጨፋ፣ እንግልት፣ ስደት፣ መከራና ግድያ፤ ህወሃት በሌሎችም አጠናክሮ ይቀጥልበታል ብሎ ያምናል። ስለዚህ ምን እንጠብቃለን በወያኔ ያልተበደለ፣ ያልታሰረ፣ ያልተደበደበ፣ ያልተሰደደ፣ ያልተፈናቀለ፣ ያልተራበ፣ ያልተዋረደ፣ ያልተገደለ ህዝብ የለም። የኢትዮጵያ ህዝብ በወያኔ ጨካኝ ስርአት አማካኝነት በጨለማ ሂዎት ውስጥ እየኖረ ነው።

የሀገራችን ወጣት ሆይ፡ ወጣትነት ሀገር ተረካቢ፣ ባላደራ፣ ለውጥ ፈላጊ፣ ሀገሩን ጠባቂ ነው። ወገንህ ሲገረፍ ሲንገላታ ሲሰደድ ማየት እና ከንፈር መምጠት እሰከ መቼ ይሆን? ሰቆቃቸው፣ ቁስላቸው የድረሱልን ዋይታቸው መቼ ይሆን ተሰምቶን እንባቸውን በአለንላችሁ የወገን ደራሽነት የምንደርስላቸው? የምንጠርግላቸው? ግንቦት 7 ትግሉን የማቀጣጠያ ሰአት ጊዜው አሁን ነው ይላል። ወጣት፣ አዋቂ፣ ጎልማሳ፣ ሽማግሌ፣ ዘር ጾታ ቋንቋ ሳይለየን ወያኔን ለማስወገድ በሚደረገው ትግል ምላሽ ስጡ፣ ተቀላቀሉ። በኢትዮጵያ የጠቆረውን ጨለማ በብርሃን መተኪያ ጊዜ ዛሬ ነው። ይህ ትውልድ የታሪክ ባለእዳ አይሁን።

በወያኔ ውስጥ ያላችሁ ይህ በደል ና ሰቆቃ የሚሰማችሁ ወገኖቻችን የውስጥ አርበኛ የምትሆኑበት ሰአት ላይ ናችሁ። ራሳችሁን እና ወገናችሁን ከቀን ጅብ ስርአት አድኑ። ከነጻነት ማግስት በኋላ ከሚመጣባችሁ ከየት ነበራችሁ ክስ ለመጽዳት ከነጻነት ታጋዮች ጋር አብሩ። ወያኔ ለ21 አመታት ህዝቡን ለማጋጨትና ለማባላት የሚያደርገው ስልት መሆኑን ተረድታችሁ የውስጥ ታጋዮች መሆናችሁን ማሳያ ጊዜው አሁን ነው። አሊያ ግን በአማራው ህዝብና በሌላው ማህበረሰብ ላይ እየተፈጸመ ባለው እጅግ አስከፊ ወንጀል በግልም ሆነ በቡድን፣ የንጹሀንን ደም እያፈሰሳችሁ ያላችሁ ወንጀለኞችና ተባባሪዎች ተብላችሁ፣ ከያላችሁበት ታድናችሁ ለፍርድ እንድትቀርቡ ንቅናቂያችን የሚቻለውን ሁሉ ለማድረግ ያለውን ቁርጠኝነት በግልጽ እንድታውቁት ይገባል።

የሀገራችን ህዝብ ሆይ፡ ዛሬ ኢትዮጵያን ከገባችበት ዘረኛ መቀመቅ ስርአት ውስጥ የሚያወጣት ብቸኛ መፍትሄ፣ ፍርሃታችንን በጥሰን በተባበረ ጉልበትና ድፍረት ወያኔን በሚገባው ቋንቋ ስናናግረው፣ ታግለን ስናስወግደው ብቻ ነው ኢትዮጵያና ኢትዮጵያዊነት ኩራትና ክብርን፣ ተሳስቦና ተፈቃቅሮ፣ ተከባብሮና ተቻችሎ የመኖር ጸጋን የምናመጣው። ስለሆነም በየትኛውም አቅጣጫ የሚደረገውን የነጻነት ጉዞ ትግል ትቀላቀሉ ዘንድ ግንቦት 7 የፍትህ የነጻነትና የዴሞክራሲ ንቅናቄ ጥሪውን በድጋሜ ያቀርባል።
ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ!!
 

Friday, April 5, 2013

ዳምጠው ወያኔ/ኢሕአዴግና አፈና በኢትዮጵያ

ፕ/ር መስፍን ወልደማርያም
መጋቢት 2005
በቀልድ ልጀምር፤ አንድ ጮሌ የአስመራ ልጅ የእኔ ተማሪ ነበር፤ አንድ ጊዜ የጂኦግራፊ ክፍል ተማሪዎች አንድ ጃፓናዊ አስተማሪ ለመሸኘት ግብዣ አድርገው ነበር፤ በግብዣው ላይProfessor Mesfin Woldemariam is one of Ethiopia's well-known intellectuals የጠቀስሁት ነገረኛ የአስመራ ልጅ (የአስመራ ልጅ የምለው ላርቀው ፈልጌ እንዳይመስላችሁ፤) በአስተማሪዎች ላይ ቀልድ ያሰማ ነበረ፤ ስለኔ ሲናገር፤– መስፍን ወልደ ማርያም የቢሮውን በር ሁልጊዜ ክፍት አድርጎ የሚቀመጠው ለምንድን ነው? ይልና እሱው ሲመልስ፣ በሩን የመዝጋት ሌሎች ዘዴዎች ስላሉ ነዋ! ቀልዱ ለእኔ እንደገባኝ ፊቱን ስለሚያኮሳትር ሰዎች በሩን አልፈው እንዲገቡ አይጋብዝም ማለት ነው፤ በዚያን ጊዜ እኔም እየሳቅሁ እንደተናገርሁት የሱን ፈሪነት በእኔ መልከ-ክፉነት መደበቁ ነው፤ ቀልዱን ያመጣሁበት ምክንያት ወያኔ ለነጻነት የቆመ መስሎ ለመታየት ሳንሱር የሚባለውን የሚታተሙ ጽሑፎችን በቅድሚያ የማስፈተሽ ቀንበር በሕግ አነሣ፤ ሰዎች እውነት መስሎአቸው ቅሪታቸውን እያነጠፉ ጋዜጦችና መጽሔቶችን ማሳተም ጀመሩ፤ ጋዜጦች እንደአሸን ፈሉ፤ መጻሕፍት ታተሙ፤ ጥቂት ቲያትሮችም ታዩ፤ ዘፈኖች ተመረቱ! ነገር ግን የግል ራድዮና ቴሌቪዥን እንዲሁ የብዙ ሰዎች ሕልም ሆኖ ቀረ፤ ብዙ ሰዎች ብዙ ገንዘብ ከሰሩ፡፡
በሕዝቡ ዘንድ የነጻነት ፍቅር እየለመለመ መሄዱን ሲያየው ወያኔ ሆዱ ተንቦጨቦጨ፤ እንቅልፍ እያጣ ሄደ፤ ቀስ በቀስ ግራ እጁን በሕገ መንግሥቱ ላይ ጭኖ በቀኝ እጁ ጎራዴውን መዘዘ፤ ቀስ በቀስ፣ አንድ በአንድ የተለያዩ መብቶችን ለማስከበር የቆሙትን አንቀጾች ሁሉ አስተኛቸው፤ በተገላቢጦሽ መብቶቻቸውን የሚጠይቁ ሰዎችን፣ ስለመብቶች የሚጽፉ ሰዎችን፣ መብቶችን ከጥቃት ለመከላለከል የቆሙ ድርጅቶችን፣ ከወያኔ አመለካከት ውጭ የሆኑ ሰዎችን ሁሉ መንግሥት በመገልበጥ ሴራ፣ ወይም በሽብርተኛነት እየያዘና እያሰረ በመክሰስና በማስፈረድ የማፈን እርምጃዎችን ሁሉ አጠናከረ፤ አንዲህ ያለውን አፈና ማየትና መስማት እየተለመደ መጣ፤ በኢትዮጵያ ውስጥ በሽብር ስም የሚካሄደው ጥቃትና የሰብአዊ መብቶች ረገጣ እንኳን እኛንና በሽብር ላይ ዓለም-አቀፍ ጦርነት ያወጁትን አሜሪካኖችንም እያስደነገጠ ነው፤ የዓለም የሰብአዊ መብቶች ድርጅቶች ሁሉ፣ የተባበሩት መንግሥታት የሰብአዊ መብቶች ኮሚሽንን ጨምሮ በምሬት እየጮሁ ነው፤ ጋዜጠኞች፣ የሠራተኞች ማኅበሮች፣ የፖሊቲካ ቡድኖች ጭጭ እንዲሉና ምንም ዓይነት እንቅስቃሴ እንዳያደርጉ መንገዱ ሁሉ እየተዘጋባቸው ነው፤ በትግራይ አብርሃ ደስታ የሚባል ወጣት የአፈናውን ድቅድቅ ጨለማ ጥሶ በመውጣት ስለጻፈ አፈናና ማስፈራራት ደረሰበት፤ ‹‹ጭቆናን ስላጋለጥሁ የሕዝብ ጠላት ተባልሁ›› ይላል፤ በቅርቡ እንኳን ሰማያዊ ፓርቲ በዋቢ ሸበሌ ሆቴል የጠራው የራት ግብዣ እንግዶቹ በተጠሩበት ሰዓት ተሰርዞ ተመልሰዋል፤ ለግራዚያኒ ስለሚሠራው ሐውልት የተቃውሞ ሰልፍ ለማድረግ የሞከሩ ኢትዮጵያውያን ታሰሩ፤ እነዚህን ኢትዮጵያውያንን ያሰሩትን ምን እንላቸዋለን? እንግዲህ በኢትዮጵያ ውስጥ ምን የማያሳስር ነገር ሊኖር ይችላል?
የአፈናውን ነገር እነእስክንድር ነጋ፣ እነርእዮት ዓለሙ፣ ውብሸት ታየ … ይመሰክራሉ፤ ለመሆኑ ወደዘጠና ሚልዮን የሚሆን ሕዝብ ያላት አገር ስንት ጋዜጣ፣ ስንት የራድዮ ጣቢያ፣ ስንት የቴሌቪዥን ጣቢያ አላት? ኤርትራ ሦስት የራድዮ ጣቢያዎችና ስድስት ጋዜጦች፣ ጂቡቲ ሦስት የራድዮ ጣቢያዎችና አምስት ጋዜጦች፣ ኬንያ አሥራ ስምንት የቴሌቪዥን ጣቢያዎች፣ ከሠላሳ በላይ የራድዮ ጣቢያዎች፣ ዘጠኝ ጋዜጦች አሉት፤ ትናንት የተፈጠረው ደቡብ ሱዳን እንኳን ሁለት የቴሌቪዥን ጣቢያዎች፣ አምስት የራድዮ ጣቢያዎች፣ አምስት ጋዜጦች አሉት፤ ኢትዮጵያ ያላትን እናውቃለን፡፡
ሰንጠረጅ አንድ
የኪስ ስልክ (ሞባይል) እድገት
እ.አ.አ.2008200920102011
አገሮች ሞባይል ለ100 ሰዎች
በደቡብአፍ
91
93
100
127
ኢትዮጵያ
2
5
8
17
ኬንያ
42
49
62
65
ሱዳን
29
36
42
56
ኤርትራ
2
3
4
4
ሶማልያ
7
7
7
7
ጂቡቲ
13
15
19
21
ምንጭ፡- የዓለም ባንክና የዓለም ቴሌኮሚዩኒኬሽን ድርጅት
የአፈናውን ልክ በሁለቱ ሰንጠረጆች ማየት ይቻላል፤ ለንጽጽር የቀረቡት አገሮች የአፍሪካ ቀንድ ጎረቤቶች ናቸው፤ ነገር ግን ላቅ ያለ ግብ ለማመልከት ደቡብ አፍሪካ ተጨምሮአል፤ ለምሳሌ የኪስ ስልኩን ብንወስድ በደቡብ አፍሪካ በመጀመሪያው ዓመት እአአ በ2008 ለአንድ መቶ ሰዎች 91 የኪስ ሰልኮች ነበሩ በ2011 ለመቶ ሰዎች ወደ አንድ መቶ ሃያ ሰባት ደረሱ፤ ይህም አንዳንድ ሰዎች ከአንድ በላይ የኪስ ስልክ አላቸው ማለት ነው፤ከጎረቤቶቻችን መሀል ኬንያ በ42 የኪስ ስልኮች ለአንድ መቶ ሰዎች ጀምሮ በአራተኛው ዓመት ላይ ወደስድሳ አምስት ማደጉ ይታያል፤ ሱዳንም ከሃያ ዘጠኝ ተነሥቶ በአራተኛው ዓመት ወደሃምሳ ስድስት አድጎአል፤ ጂቡቲም ከ13 ጀምራ ወደ 21 ገብታለች፤ ትልቅዋ አገር ኢትዮጵያ በሁለት ጀምራ ከአራት ዓመታት በኋላ ለመቶ ሰዎች አሥራ ሰባት የኪስ ስልኮች አስቆጥራለች፤ በአፍሪካ ቀንድ በኪስ ስልክ የመጨረሻውን ዝቅተኛ ቦታ የያዘች አገር ትልቅዋና በዓመት ከአሥራ አንድ ከመቶ በላይ እድገት ታስመዘግባለች የሚባልላት ኢትዮጵያ ነች፡፡
ሁለተኛው የአፈናው መገለጫ የኢንተርኔት አገልግሎት ነው፤ በኬንያ በ2008 ከአንድ መቶ ሰዎች ውስጥ የኢንተርኔት ተጠቃሚ የነበረው 42 ሲሆን በ2011 ወደ ስድሳ አምስት አደገ፤ በኤርትራ ከ4 ወደ 6 ሲያድግ፣ በኢትዮጵያ አላደገም፡፡
እነዚህ ሁለቱም የመረጃና የእውቀት መተላለፊያ ዘዴዎች ለማናቸውም እድገት ቁልፍ መሆናቸው አያጠራጥርም፤ በተለይም ለነጻነትና ለእውቀት እድገት አስፈላጊዎች በመሆናቸው ለአምባ-ገነኖች እንደጠላት መሣሪያ የሚቆጠሩ ናቸው፤ ችግሩ እውቀት አለነጻነት አይገኝም፤ ነጻነትም አለእውቀት አይገኝም፤ እውቀትና ነጻነት ተነጣጥለው አይገኙም፤ ስለዚህም ነጻነትን ለመግደል የፈለገ እውቀትንም ይገድላል፤ ስለዚህም አምባ-ገነኖች ሞባይልንና (ተንቀሳቃሽ ወይም የኪስ ስልክ) ኢንተርኔትን ማፈን ዋና ተግባራቸው ያደርጉታል፤ በዚህም ምክንያት ሕዝቦቻቸውን በድንቁርና ያዳፍናሉ፤ በደሀነት ያሰቃያሉ፤ በዘመናችን ዋናው የአውቀት መተላለፊያ ኢንተርኔት ነው፡፡
ሰንጠረጅ ሁለት
የኢንተርኔት አገልግሎት እድገት
እ.አ.አ.2008200920102011
አገሮችየኢንተርኔት አገልግሎት ለመቶ ሰዎች
ደቡብአፍ8.510.118.120.9
ኢትዮጵያ0.50.50.81.1
ሱዳን10.2
ኤርትራ4.14.95.46.2
ሶማልያ1.11.21.3
ጂቡቲ2.34.06.57.0
ደቡብ አፍሪካ የገባው ለንጽጽር ነው፤
ምንጭ፡- የዓለም ባንክና የዓለም የቴሌኮሚዩኒኬሽን ድርጅት
የኢንተርኔት አገልግሎት በቅርቡና በርካሽ ወይም በነጻ ከተገኘ ብዙ ሳይለፉ ምንም ዓይነት እውቀት ሊገኝ ይቻላል፤ በሠለጠኑት አገሮች በአንዳንድ ቡና ቤቶች ነጻ የኢንተርኔት አገልግሎት ይገኛል፤ በኢትዮጵያ ውስጥ በኢንተርኔት ለመጠቀም ደህና ገቢ ያለው መሆን ያስፈልጋል፤ከደሀነት ለመውጣትም ሀብታም መሆን ያስፈልጋል!

Fate of stranded Ethiopian migrants in Yemen

Fate of stranded migrants in Yemen ‘very grim’
GENEVA: The plight of thousands of migrants stranded in Yemen after trying to reach Saudi Arabia and the Gulf has
Ethiopian migrants sleep out in the open near a transit centre
Ethiopian migrants sleep out in the open near a transit centre where they wait to be repatriated in the western Yemeni town of Haradh, on the border with Saudi Arabia, March 29, 2012. REUTERS/Khaled Abdullah
reached desperate proportions, the International Organisation for Migration (IOM) warned yesterday.
“The situation of migrants in Yemen is very grim,” IOM spokesman Jumbe Omari Jumbe said.
Yemen has seen a spike in the number of migrants and refugees from the Horn of Africa who risk their lives to cross the Red Sea in smugglers’ boats only to find themselves blocked at the Saudi border.
Numbers have doubled from around 53,000 in 2010 to more than 107,000 last year. Ethiopians make up the overwhelming majority, but others hail from countries such as Somalia and Eritrea.
“In Haradh town, which the migrants see as a gateway to Saudi Arabia and beyond, thousands of migrants roam the streets and sleep rough in the open with no money for food or medicine,” Jumbe said.
“Many migrants visiting IOM’s offices have been rescued from unscrupulous gangs of kidnappers, traffickers and smugglers and are injured, some with broken limbs. Criminal gangs are also reportedly trading in human organs,” he added.
In addition, the hospital mortuary in the northern Yemen town of Haradh is now filled with the unclaimed bodies of migrants, he said.
Funding shortages have forced the IOM to curtail a programme providing free meals to stranded migrants in Haradh from 3,000 a day to just 300 – with only women, the elderly and unaccompanied youngsters now receiving food.
The lack of cash has also forced the organisation to suspend a voluntary repatriation programme which provides migrants with flights home.
The IOM is also working in Ethiopia to try to discourage would-be migrants from making the Red Sea crossing.
“But people are desperate. And because of that desperation, people are sometimes willing to risk everything,” Jumbe said.

All of us can be Part of the Solution

by Abebe Kassa, April 05,2013
To sell Ethiopian agricultural lands to foreign investors, the weyane regime continued with increasing vigor its policy of forced eviction of ethiopians from their own land. The number of evicted people and their sufferings are growing. As Ethiopians hearing the news from different medias the anger is flowing from everywhere. Often news about atrocities committed by the weyane regime ends up being a week or some weeks long concern. It has to be be changed at some point. The anger has to be transformed in to meaningful action. The regime has to feel these atrocities will have consequences.

The recurrent questions among Ethiopians when we hear this kind of atrocities commited by the weyane regime is: what can we do to stop this from happening again? what is the solution? The questions often followed by demand for opposition forces to unite and make formidable force to challenge the regime. Since 2005 the call is not bearing fruit as we wanted it. In 2005 election Kinjit and Hibret did that in Ethiopia when opportunity arised and shaken the regime to its core. Ofcourse many people yearn to see that being repeated to bring back vitality to the struggle. Currently the opposition being fragmented and weyane controlling almost all the resources and institutions in Ethiopia might appear for some weyane is invincible. Gene sharp who wrote extensively on resistance against dictatorship pointed out that the perception of dictators invulnerability against powerlessness feelings by the opposition makes effective resistance unlikely. The wrong perceptions impede effort. In Ethiopian struggle one factor that is oppositions working together can alter that power equation significantly. Many are demanding it too. We know even the news that oppositions are working together will rattle the weyane camp. The challenge is how to achieve that.

We can’t leave the responsibility only for political parties and civic organizations leaders to unite the opposition force and bring the desired change we want. I believe the way is those of us who wants regime change in Ethiopia to involve in the struggle actively. We can be member or supporter of a political party or civic organization. Political parties and civic organizations are not in short supply and most of us can get the choice of our own. No waiting game while we can be part of those who make it happen. We can play part in shaping the struggle. we can not continue to be bystanders till the unity we demand arrives. We can search the solutions while working in the organizations framework. We might start participating in different organizations however as the struggle goes its course and with time we might meet at some point like tributaries merge together to form a river. Intra-organizations negotiations and discussions will bring the ways to cooperate and work together. This way we can accelerate the disintegration of weyane regime. If we involve and contribute what we can in the effort to bring oppositions to work together, we will dismantle the weyane regime for good and lay the foundation of democratic Ethiopia.
To act is to involve in the struggle.

የ እስክንድር ወንጀሉ መምከሩና ኣቅጣጫ ማሳየቱ ብቻ ነው

(ገለታው ዘለቀ)

eskinder_opt
ኣንድ ጊዜ ኣባባ ተስፋየ ከዚያ ከሚያምርባቸው የ ልጆች ክፍለ ጊዜ ዝግጅታቸው ጠፉብኝና ኸረ የት ገቡ? ብየ ኣንዱን ጠየኩ።
“ኣልሰማህም እንዴ ?”
በፍጹም ምን ሆኑ? ደንገጥ ብየ እንደገና ጠየኩ።
 
ያ ሰው እየሳቀ “ባለፈው ጊዜ ኣዲሱ ኣመት የሰላምና የእርቅ ያድርግልን ብለው በመናገራቸው የመንግስት ሰዎች ማን ሲጣላ ኣዩ? ብለው ኣባረሩዋቸው እኮ!” ሲለኝ ለደቂቃዎች እንደዚያ የሳቅኩበት ጊዜ ትዝ ኣይለኝም። የሁለታችንም ሳቅ ካለቀ በሁዋላ እውነተኛው ስሜት ሲመጣ ደሞ ያስለቅሳችሁዋል። ነገሩ እውነት መሆን ኣለመሆኑን ኣጥብቄ ኣልጠየኩም፣ ለነገሩ ከዚያ ቀን በሁዋላም ከብዙ ሰው ይህንኑ ሰማሁ። ነገሩ በትክክል ሆነም ኣልሆነም ያ ሁሉ ሰው መንግስት እንደዚያ ሊያደርግ ይችላል ብሎ ማሰቡ ራሱ ነገሩ መሆኑን ኣለያም ሊሆን መቻሉን ያሳያል። በዚያች ኣገር ምን የማይሆን ኣለና።
 
በዚህ ስደነቅ ስደመም ደሞ ኣንዴ እንዲህ ሆነላችሁ። እንዲሁ ኣንድ ሻይ ቤት ተቀምጨ ወጪ ወራጁን እማትራለሁ። በመሃል ኣንድ ሰው ሳምሶናይት የሚባለውን ቦርሳ ጠልጠል ኣርጎ ገባና ወዲያ ወዲህ ካየ በሁዋላ የኔን ጠረንጴዛ ተጋርቶ ለመቀመጥ በትህትና ጠየቀኝ። ወንበሩን ሳብኩለት። እንደኔው ሻይ በሎሚ ኣዞ ቁጭ ኣለ። ጥቂት ቆየት ካለ በሁዋላ ያቺን ቦርሳውን ከፈተና ኣንዲት ጋዜጣ ኣውጥቶ ዘረጋጋና ማንበብ ጀመረ። ብዙም ሳይቆይ ሁለት ሰዎች ወደ ሻይ ቤቱ ገቡና ከኛ መቀመጫ ትይዩ ተሰየሙ። ኣንዱ የቀኝ እግሩን ቀጥ ኣርጎ ዘርግቶ ነበር የተቀመጠው። በሁዋላ ኬክ ሊመርጡ ሲነሱ እንደሚያነክስ ሳይ እግሩ ኣርቴፊሻል መሰለኝና ኣለ ኣይደለም ኣሳዘነኝ። የሚጠጣውን እየጠጡ ኬካቸውን እየበሉ ያወካሉ። እኔና ከፊቴ ያለው ሰውየ ግን ጸጥ ብለናል። ትንሽ እንደቆየ ያቺን ጋዜጣውን በሽንጡዋ ሸመለለና ወደ ቦርሳው ከተተ። ደሞ ወዲያው ኣጨበጨበና ሂሳብ ከፈለ።
 
እኔም እስካሁን ባናወራም ኣብርን ለትንሽ ሰኣትም ቢሆን ባንድ ጠረንጴዛ በልተን ጠጥተናል ዝም ኣይባልም ብየ ነው መሰለኝ ቻው ለማለት ምንም ኣልቀረኝም።በመሃል ያ ያነክሳል ያልኩዋችሁ ሰውየ ድንገት ወደኛ ዞረና
“ምን ኣልክ ኣንተ? ምን ኣልክ? ድገመው እንጂ…… ልብ በሉ… ሰዎች ልብ ኣርጉ.. ምን ኣልክ ኣንተ?…” እያለ ይጮሃል። ሁላችንም ተደናገጥን። ያ ከኔ ጋር ጠረንጴዛ ተጋርቶ የነበረው ሳምሶናይቱን እንዳንጠለጠለ “ኸረ እኔ ምንም ኣልወጣኝም ጌታየ ምን ነካዎት” ይላል ኣስር ጊዜ። ከዚያ ከሚያነክሰው ጋር ያለው ሰውየም ኣብሮ ያጫፍራል። በሁዋላ ይሄ ከኔጋር የነበረው ሰው መንጨቅ ብሎ ሲወጣ ሁለቱም ተከተሉትና ጭቅጭቁ ከውጭ ቀጠለ።
 
ያው መቼም ሃይ ሃይ ማለት ያገር ባህል ነውና ወደ ውጭ ወጥቼ ኸረ እሱ ምንም ኣላለም ፣ ምንም ሲል ኣልሰማሁትም ተረጋጉ እያልኩ ለመምከር መቼም ያቅሜን ሞከርኩ።
 
ያ የሚያነክሰው እንባው ሁሉ የመጣ ይመስላል። ይገርማል ዋሽቶ የሚያለቅስ ሰው ቢገጥማችሁ ምን ትላላችሁ?
“እንዴት ትሰድበኛለህ……” እያለ ሲሙዋገት ጓደኛውን ጠጋ ብዬ እናገላግላቸው እባክህ ምን ኣለ? ምንም ኣላልም እኮ ኣልኩት።
“የለም የለም እኔ ራሴ ሰማሁት እኮ ወራዳ ነው ሽባ ብሎ ሰደበው እኮ”
ደነገጥኩና መቼ? ብየ ጠየኩ::
 
ወደዚህኛው ሰውየ ዞሬ ትተዋወቃላችሁ እንዴብዬ ጠየኩ::
“በፍጹም ኣንተዋወቅም ኣለ” ግራ የተጋባው ባለ ሳምሶናይቱ ፈጠን ብሎ
“ሂሳብ ከከፈለ በሁዋላ ድምጹን ከፍ ኣርጎ እኮ ነው የሰደበው”
በውነት ግራ ግብት ኣለኝ። ሁዋላ ላይ ይሄ የሚያናግረኝ ሰው ስልኩን ኣወጣና ኣንድ ሁለት ቁጥሮችን ነካካና ወደዛ ዞር ብሎ ጥቂት ኣወራ መሰለኝ። ወዲያው እንደተመለሰ ኣንድ ፖሊስ መጣና ያንን ባለ ሳምሶናይት
“ቅደም ኣለው።
በዚህ ጊዜ ወደ ፖሊሱ ጠጋ ብዬ ምንም እኮ ኣላለም እኔ እዚህ ነበርኩ
ምንድነው ችግሩ ለማለት ሞከርኩ። ፖሊሱ በግንባሩ ጥሩ ኣርጎ ገረፈና ኣስቆመኝ። ባለ ሳምሶናይቱ እንዲሁ “ምን ኣጠፋሁ” እንዳለ ይነዱት ጀመር። ሁኔታው ገርሞኝ ነበርና ባጭር ርቀት መከተል ጀመርኩ። የሚገርማችሁ ያ ቅድም ቀኝ እግሩን ይጎትት የነበረው “ሽባ” ተብየ ተሰድቢያለሁ የሚለው ሰውየ ኣሁን በግራው ማንከስ መጀመሩን ትኩር ብዬ ኣስተዋልኩና የሆነ ነገር እየሆነ እንደሆነ ገባኝ። ብዙም ሳልርቅ ወደ ሁዋላየ ሂሳቤን ለመክፈል ተመለስኩ። ወደ ሻይ ቤቱ በር ስቃረብ ኣንዱ “ወሰዱት ኣይደል?” ኣለኝ:: ኣዎ ወሰዱት ኣልኩና ግን ምንም ኣለማጥፋቱን ኣስረግጨ ነገርኩት። ጥቂት ኣየኝና “ወንድሜ ተጠንቀቅ ከዚህ ከሚያነክሰው ጋር ያለው ሰውየ የነሱ ጆሮ ነው የተለያየ ልብስ እየለበሰ ሲሰልል ነው የሚውለው ተነቅቶበታል” ኣለኝ። እኔም ወዲያው ጠርጥሬ ስለነበረ ገባኝ። እንግዲህ ያን ሰው በዚህ ርካሽ ስራቸው ኣወናጅለው የሆነ ነገር ኣርገውታል ማለት ነው።
 
ባለፈው ጊዜ ግራዚያኒን ለመቃወም ሰልፍ ወጥተው ከነበሩት መካከል ኣንዱ በኢሳት ቴሌቪዥን ኢንተርቪው ተደርጎለት ሲናገር ልብ ይነካል። ሲቪል እየለበሱ መገናኛ እየያዙ እንዴት የስነ ልቡና ጫና እየፈጠሩ እንደሆነ ገለጸ። ኑሮ ኣይደለም የምንኖረው ኣለ። ያሳዝናል። ሃሳብን መግለጽ ጥቂት ኣስተያየት መሰንዘር በስነ ልቡናና በኣካል የሚያስቀጣ ነገር የሆነባት ሃገር ናት ኢትዮጵያ።
መነሻየኮ ስለ እስክንድር ነጋ ነው። ይህን ያመጣሁት በእንዲህ ባለ ኣገር፣ እስክንድርን የመሰለ ፖሊሲ የሚያመነጭ፣ የሰባዊ መብት እንዲከበር ለማድረግ የሚታገል ሰው ስንት ስነ ልቦናዊ ቅጣት እንደሚቀበል ለመገመት እንዲያስችለን ነው ።
 
እስክንድር የታሰረበትን ምክንያት ኣለም ኣውቆታል። እስክንድር የታሰረው በውስጡ ያለው የእኩልነትና የፍትህ ራእይ እንቅልፍ ኣልሰጥ ስላላቸው ነው። ያንን በገቢ ኣለመመጣጠን የሚሰቃየውን ህዝብ እህል በልቶ እኩልነት ሰፍኖ ማየት የሚፈልግ ሰው መሆኑ ነው የ እስክንድር ሃጢያቱ።እስክንድር ቅንና ርህሩህ ነው። የጻፋቸው ጽሁፎች ዋቢዎች ናቸው። የሱ ወንጀል መምከሩ፣ ኣቅጣጫ ማሳየቱ ብቻ ነው።
 የነ ርእዮት ኣለሙም ወንጀል ይሄው ነው። መናገር፣ መምከራቸው ነው ወንጀላቸው።
ግን እውነት ሊሞት ይችላል። መሞት ብቻ ኣይደለም ሊቀበርም ይችላል። ግን ደሞ እውነት መቃብር ፈንቅሎም የመነሳት ሃይል ኣለው። መንግስት ይህን መረዳት ኣለበት።
 
እግዚኣብሄር ኢትዮጵያን ይባርክ
geletawzeleke@gmail.com

Thursday, April 4, 2013

“አይቴ ብሔሩ ለአማራ . . . የአማራ አገሩ ወዴት ነው?” ኢትዮጵያ አይደለምን?


(ኤፍሬም እሸቴ – www.adebabay.com)፦ በንግግርም ይሁን በጽሑፍ ለማንሣትም ሆነ ለመጥቀስ፣ ለመወያየትም ሆነ ለመከራከር ከማይመቹኝ (discomfort እንዲል ፈረንጅ) የኢትዮጵያ ርዕሰ ጉዳዮች ሁሉ ዘርን፣ ብሔረሰብን የተመለከተው ዋነኛውና አንዱ ነው። ጉዳዩ በዕለት ተዕለት የአገራችን ሕይወት ውስጥ ወሳኙ እና በሁነኛ መልክ ማኅበረሰባዊ ማንነታችንን እየበየነ እንዳለ እያወቅኹም እንዲህ እንደ አሁኑ በአደባባይ ለመውጣት ግን ብዙም አይቀለኝም። ምክንያቱ ሌላ ምንም ሳይሆን ጉዳዩ ያለው ስሱነት (sensitivity) ነው። አሁን ግን ላልፈው አልቻልኩም። አይገባምም። ለምን?
መነሻ
ከአማራ ክልል ወደ ቤኒ-ሻንጉል ጉሙዝ ክልል ያሶ ወረዳ ተጉዘው የከተሙ በርካታ ሰዎች በወረዳው ባለሥልጣናትና ፖሊሶች፤ ሰብአዊ መብታቸው ተጥሶ ከቀያቸው መፈናቀላቸውን የሚያትት ዜና የሰሞኑ ኢትዮጵያውያን ድረ ገጾች/መገናኛዎች ዋነኛ ትኩረት ነው። ስለዚሁ ጉዳይ ዜና ያስነበበው “አዲስ አድማስ” ጋዜጣ ጉዳዩን በተመለከተ የሚከተሉትን ቁም ነገሮች አስፍሯል።
  • በሚኖሩበት አካባቢ የእርሻ ቦታ በማጣታቸውና የተሻለ ሥራ ፍለጋ ከ1997 ዓ.ም ጀምሮ ከአማራ ክልል ወደ ቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ያሶ ወረዳ መሔዳቸውን፣
  • “ከሌላ ቦታ እየመጣችሁና እየሠራችሁ የአካባቢውን ተወላጅ ሰነፍ አደረጋችሁት” በሚል ምክንያት ያፈሩትን ሀብትና ንብረት ሳይሰበስቡ ከክልሉ እንዲወጡ መደረጋቸውን፣
  • አንዳንዶቹ በያሶ ወረዳ ውስጥ የከተማ ነዋሪነትና የንግድ ፈቃድ በማውጣት ላለፉት ሰባት ዓመታት በሥራ ላይ መቆየታቸውን፣ ገሚሶቹ ደግሞ ከ1997 ጀምሮ የቀበሌው ነዋሪ በመሆን ከክልሉ ተወላጆች ጋር በስምምነት መሬት የእኩል እያረሱ የራሳቸውንም የባለመሬቱንም ሕይወት መቀየራቸውን፣
  • በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ከማይ ዞን በያሶ ወረዳ ውስጥ በሀሎ ትክሻ፣ ሆኒ፣ ሊጐ፣ ባብርኮ፣ ሻብቲ፣ ድልድል፣ ቲኒጆ መጢና በመሰል ቀበሌዎች በግምት ከስድስት እስከ ዘጠኝ ሺህ የሚጠጉ ከአማራ ክልል የመጡ ሰዎች እንደሚገኙበት፣
  • “የክልሉ ነዋሪ ወዶንና ተቀብሎን በሰላም ነበር የምንኖረው” ማለታቸውን፣
  • ጐጐታ በተባለ ቀበሌ ከአማራ ክልል የመጡ 43 ሰዎች እንዲሁም በሀሎ ሙከአርባ ቀበሌ የ25 ሰዎች መታወቂያ ተቀዳዶ ሲጣል መመልከታቸውን፣
  • “እስከአሁን በወረዳው ፖሊስ ጣቢያ ከታሠሩት በርካታ ሰዎች በተጨማሪ በመኪና ተጭነው ነቀምትና ጊንቢ የተወሰዱት ሰዎች” መኖራቸውን፤ ስንቅ ሊያቀብሉ የሔዱ ሰዎችም መታሰራቸውን፤
  • ወደመጡበት እንዲመለሱ የተወሰነው፤ በብአዴን፣ ኦህዴድ እና የኢሕአዴግ አጋር ፓርቲ በኾነው ቤኒሻንጉል ጉሙዝ ብሔራዊ ክልላዊ ፓርቲ (ቤጉብዴፓ) በጋራ ተወያይተው በደረሱበት ውሳኔ መኾኑን ሥራው የወረዳው ብቻ ሳይሆን ከክልል እስከ ቀበሌ ድረስ በትስስር እየተሠራ መኾኑን የያሶ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ታደሰ ሻምበል ዳኛ መግለጻቸውን ዘግቧል።
ይህንን ዜና ከሌላ ተመሳሳይ የቅርብ ጊዜ ታሪክ ጋር ካመሳከርነው ከደቡብ ክልል ጉራ ፈርዳ ወረዳ ከተፈናቀሉት/ እየተፈናቀሉ ካሉት ሌሎች ዜጎች ጉዳይ ጋር ልናነጻጽረው እንችላለን። ሁለቱንም አንድ የሚያደርጋቸው ደግሞ አማርኛ ተናጋሪዎች (አማሮች) መሆናቸው ነው።
ሊወገዝ የሚገባው ተግባር
መነሻው ምንም ይሁን ምን፣ የክልሉ ፓርቲ ከማንም ጋር ይስማማ አይስማማ በነዚህ ዜጎች ላይ የተደረገው ተገቢነት የሌለው ነገር ነው። የዜጎች በአገራቸው ውስጥ የመዘዋወር፣ የመኖር መብት እንዲህ በጥቂት የፓርቲ ሹመኞች መወሰኑ የሚያስጨንቅም የሚያስደነግጥም ምልክት ነው። ከጉራ ፈርዳም ከቤንሻንጉል የተፈናቀሉት ሰዎች “አማሮች” መሆናቸው ደግሞ አጋጣሚ ነው ለማለት በጣም የዋህ (ሲገፋም ጅል) መሆን ይጠይቃል።
በቋንቋ ማንነት ላይ ብቻ በተመረኮዘው የአገራችን ፖለቲካ “አማራ” የሚባል ለብዙዎቹ “ብሔሮች ብሔረሰቦች እና ሕዝቦች” ጠላት የሆነ አካል እንዳለ በጓዳም በአደባባይም ሲነገር ብዙ ጊዜ ሰምተናል። ይህ ‘ፖለቲካ ያባውን – መፈናቀል ቢያወጣው’ (ሆድ ያባውን … እንደሚባለው) ምንጩ የማይታወቅ የማይሆነውም ለዚህ ነው።
ከደቡብም ከቤንሻንጉልም ለመፈናቀል “አማራነቱ” ምክንያት የሚሆንበት ከሆነ “አይቴ ብሔሩ ለአማራ? … የአማራ አገሩ የት ነው?” የትስ ሔዶ ይኑር? ኢትዮጵያ አገሩ አይደለምን?” ለማለት ያስገድደኛል። ደግሞስ አንድ ሰው አማርኛ ስለተናገረ የግድ ወደ አማራ ክልል መሔድ አለበት? ሁሉም ወደየክልሉ የሚለውን አዋጅ ያወጣውስ ማን ነው? አማርኛ የሚናገሩ ነገር ግን “የአማራ ክልል አገራቸው ያልሆኑ” ኢትዮጵያውያን የነገ ዕጣ ፈንታ ምንድር ነው?
የመታወቂያ ነገር
ለረዥም ጊዜ የቀበሌ መታወቂያ ሳይኖረኝ እኖር ነበር። ከዕለታት በአንዱ ቀን ግን የግድ የቀበሌ መታወቂያ ማውጣት የሚያስፈልገኝ ጊዜ ደረሰና እኖርበት ወደነበረው ቀበሌ ሔድኩ። ፎርም ሞላኹ። ከዚያም መታወቂያው ላይ መስፈር ያለበት የብሔረሰብ (እነርሱ እንኳን ብሔር ነው ያሉት) ነገር ተነሣ። መናገር አልፈለኩም። ቀበልዬው ካልተናገርኩ እንደማይሰጠኝ እርግጥ አደረገው። መሞላት አለበት። የዘር ማንዘሬን “ደም” ሁሉ እስኪሰለቸው ደረደርኩለት። በምን ፎርሙላ እንደሆነ ባላውቅም እርሱ ደስ ያለውን አንዱን ቋንቋ ብቻ መርጦ ብሔሬን ሞላው። በመታወቂያዬ መሠረት ቀብልዬው የሞላው ክልልና ብሔር አባል ሆንኩ። መታወቂያ እየታየ ሰልፍ መያዝ ሲጀመር እኔም አቶ ቀበልዬው በሞላው ተርታ የግዴን ልገባ ነው ማለት ነው።
ማንነትን በማወቅ ሰበብ ማንነትን ማጣት
ማንነትን ማወቅ፣ ባህልን መጠንቀቅ፣ ቋንቋን ጠብቆ መቆየት የሚደገፍ ብቻ ሳይሆን መብትም ነው። ነገር ግን አሁን ባለው መንገድ ድንበር እያጠሩ ሰውን ያለ ፍላጎቱ “ሰልፍህ በየት በኩል ነው?” የሚያስብል ብሔረሰባዊ አሰላለፍ ግን ጤናማ ካለመሆኑም በላይ አገር ብለን በጋራ የምንኖርባትን ጎጆ የሚያፈርስ ከፋፋይ አስተሳሰብ ነው። በተለይ እዚህ አሜሪካን አገር ከመጣኹ በኋላ ያየሁት እና እንኳን ቋንቋን ቀለምን ማለትም ነጭ፣ ጥቁር፣ እስያዊ፣ ሂስፓኒክ የሚለውን እንኳን ፎርም ላይ ለመሙላት የሰውየው ብቸኛ ፍላጎት መሆኑን ማወቄ በግዳቸው “ብሔረሰብ እንዲመርጡ” ለሚደረጉ ኢትዮጵያውያን እንዳዝንም፣ እንድቆጭም፣ እንድበሳጭም ያደርገኛል።
ዛሬ አማራ ተብለው እንዲወጡ የተደረጉት ዜጎች ሌላው ሰው “አማራ” ይላቸው ካልሆነ ምናልባት ራሳቸውን በቀበሌያቸውና በትውልድ ቀዬያቸው ከመጥራት የዘለለ ነገር የሚኖራቸው አይመስለኝም። እንዳሁኑ “አማራ ናችሁ” የሚለው አንድ ቃል ሳይጫንባቸው በፊት “አገራችን ጎጃም ነው” ወይም “መንዝ ነው” ይሉ ይሆናል። ኦሮሞውም “ሜታ ነኝ” ወይም “ቦረና ነኝ፣ ወለጋ ነኝ” ይል እንደሁ እንጂ እንደአሁኑ “ኦሮሞነት” አልተጫነበትም ነበር። ሌላውም ሌላውም። ማንነትህን እወቅ በማለት ሰበብ የተጫነበት የቋንቋ ቀንበር ከጎረቤቱ የሚለየውና አርሶ ከሚያድርበት ቀዬ የሚያፈናቅለው ከሆነ ማንነቱ እንደ ዕዳ ተቆጥሮበታል ማለት ነው።
ሌላው የሚያስጨንቀው ጉዳይ ምንነትን በማጠር ሰበብ ክፉ የፖለቲካ ጨዋታ የሚጫወቱ ቡድኖች መኖራቸው ነው። የዚህ ጨዋታ ግንባር ቀደሙ ደግሞ ኢሕአዴግ ራሱ መሆኑን መናገር አገራዊ ግዴታ እየሆነ ነው። ፓርቲው ለጊዜያዊ ፖለቲካዊ ጥቅም አገርን የሚያክል ትልቅ ቤት የሚያፈርስ ቁማር ውስጥ ነው ያለው። የሌሎች ብሔረሰቦችን ድጋፍ ለማግኘት አማራውን የመስዋዕት በግ አድርጎ የማቅረብ ቁማር። ዞሮ ተመልሶ ወደራስ ሊተኮስ (Backfire ሊያደርግ) የሚችል መድፍ መጫወቻ ማድረግ።
መረጫጨት ተጀመረ?
አንድ ሰሞን ዝነኛ የነበረች ቀልድ “መረጫጨት ተጀመረ” ትል ነበር። የንስሐ አባት ጸበል ሲረጩ ለጨዋታ የመሰለው ትንሽ ነካ ያደረገው ሰው “መረጫጨት ተጀመረ?” ብሎ ውኃ ያነሳበት ታሪክ። በዚህ ዓይነቱ ከባድ ርዕስ ላይ ይኼ ቀልድ ስላቅ ሆኖ በውስጤ ብቅ አለ። ዛሬ ያባረሩ ሰዎች በሌላው ዘንድ “መረጫጨት ተጀመረ?” እንደማያሰኝባቸው ማወቅ ተስኗቸው ነውን? ምናልባትም ይህ እንዲሆን ፍላጎት እንዳላቸው ማን ያውቃል። እንደመንደር ጎረምሳ “ሰፈሬ ለምን መጣህ?” ሲሉ ሌላው በተራው እነርሱን “ሰፈሬ ለምን መጣችሁ?” እንዲላቸው ፈልገዋል ማለት ነው? ከዚያስ? ተጠቃሚው ማን ሊሆን? ወይስ ካርዱን የሚጫወተው ዋናው ሰውዬ ከኋላ ሆኖ እንዲስቅ? ኢትዮጵያችን እንደማትጠቀም በርግጠኝነት መናገር እችላለኹ።
ለጊዜው
በእኔ ትንሽ ግምገማ ኢትዮጵያውያን በመታወቂያቸው እና በስማቸው እየተገማመቱ እንዲደባደቡ ትልቅ ፍላጎት አለ። እስካሁን ፍላጎቱ ያልተሳካው በኢትዮጵያውያን አርቆ አሳቢነት ነው። ይህንን የኢትዮጵያውያን አርቆ አሳቢነት በሕይወቱ ያልተረዳ እና በዚህ የዘር ፖለቲካ የተጠመቀ ትውልድ አገሪቱን እየተረከበ ሲመጣ እንዴት እንደምንሆን ግን እግዜር ይወቀው። ባለ ራእዩ ሰውዬ “አንተርሐሙዌ” (Interahamwe) ብለው ያሟረቱት ነገር ላለመድረሱ ማረጋገጫ የሚሰጥ ባገኘኹ በተደሰትኩ።
የቤንሻንጉል ክልል ሰዎችም ሆኑ ጉዳዩ የሚመለከታቸው አካላት በሙሉ ለዚህ ዕብደት አፋጣኝ መፍትሔ መስጠት አለባቸው። በዚህ ነገር መጠየቅ ሲመጣ ማዕከላዊው መንግሥትም “አልነበርኩበትም፣ የክልሉ ጉዳይ ነው” ማለት አይችልም። መሬት ለሕንዶች በነጻ በማከፋፈሉ ላይ እጁን የሚያስገባው የቤተ መንግሥት አካል ድሃ ገበሬዎች ሲፈናቀሉ የለኹበትም ሊለን አይችልም። የሚሰማውም አያገኝ።
መቼም የእምነት መሪዎቻችን ራሳቸውን ችለው ቆመው “ተዉ” ይላሉ ብለን አንጠብቃቸውም። እንዲህ ዓይነቱ ኢ-ሰብዓዊ ድርጊት እንዲገታ መጠየቅ የሚገባቸው እነርሱ ቢሆኑም – በቅድሚያ። እነርሱ ባይናገሩም ሥልጣን ያላቸው ብቻ ሳይሆኑ ሐሳባቸውን መግለጽ የሚችሉ ኢትዮጵያውያን በሙሉ ነገሩ ወንጀል መሆኑን መናገር አለባቸው። “ትክክል አይደለም” ለማለት የግድ የአማራነት ቆብ መድፋት አያስፈልገንም። ሰብዓዊነት የሚሰማው በሙሉ ግድ ይለዋል። ለታሪክም ቢሆን። ከጊዜያዊ የፖለቲካ ወገንተኝነት ውጪ ማሰብ የሚያስፈልገው በዚህ ዓይነቱ ጉዳይ ነው። የገዢው ፓርቲ ደጋፊና መሪ የሆኑትም ቢሆኑ ይህንን መቃወም ኢሕአዴግን መቃወም አድርገው መቁጠር አይገባቸውም። እንዲያውም ያስመሰግናቸዋል። ለኅሊናችንና ለልጅ ልጆቻችን ስለምናስረክባት ኢትዮጵያ ስንል “ኧረ በሕግ አምላክ፣ ኧረ በባንዲራው” እንበል።

ይቆየን – ያቆየን

አቶ ስብሐት ነጋ ኤርትራውያንንና ኢትዮጵያውያንን በአንድነት ስብሰባ ጠሩ

መጋቢት ፳፭ (ሀያ አምስት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም

ኢሳት ዜና:-በውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር ስር የሚገኘውና በቀድሞ የህወሃት መስራችና አመራር አባል አቶ ስብሃት ነጋ የሚመራው
የኢትዮጵያ የሰላምና የልማት ዓለም አቀፍ ኢንስቲትዩት የፊታችን ቅዳሜ የኢትዮጵያና ኤርትራ የሕዝብ ለሕዝብ
ግንኙነት ተጠናክሮ በሚቀጥልበት ሁኔታ ላይ የሚመክር ሕዝባዊ ስብሰባ በአዲስአበባ ጠራ፡፡
በትጥቅ ትግሉ ወቅት እና ወደመንግስት ስልጣን ከመጡም በኃላ በመጀመሪያዎቹ 10 ዓመታት ሃይለኛ ፍቅር ውስጥ
የነበሩት ሻዕቢያና ኢህአዴግ በድንገት የፈጠሩት አለመግባባት ተካርሮ ከ15 ዓመታት በፊት ጦርነት ካስነሳና
በሁለቱም ወገኖች ዘንድ በሺ የሚቆጠሩ ሰዎች ካለቁ በኃላ በመንግስት ደረጃ የዚህ ዓይነቱ የውይይት መድረክ
ሲዘጋጅ ይህ የመጀመሪያ እንደሆነ ምንጮቻችን ጠቁመዋል፡፡
ከቀድሞ ጠ/ሚኒስትር አቶ መለስ ዜናዊ ሕልፈት በኃላ የተሾሙት አቶ ኃይለማርያም ደሳለኝ በቅርቡ ለአልጀዚራ
ቴሌቪዥን በሰጡት ቃለምልልስ ኤርትራ ድረስ ሔደው ለመወያየት ፍላጎት እንዳላቸው መግለጻቸው የሚታወስ ሲሆን
የአሁኑ የሕዝብ ለሕዝብ ግንኙነት የተባለው ከሳቸው አቋም ጋር በቀጥታ ስለመያያዙ ወይም አለመያያዙ የታወቀ ነገር
የለም፡፡
አቶ መለስ በሕይወት በነበሩበት ጊዜ ከኤርትራ መንግስት ጋር በሔግ ተከራክረው በይፋ ከተሸነፉ በሃላ ኤርትራዊያን
ከጦርነቱ ጋር ተያይዞ በኢትዮጵያ ጥለውት የሄዱትን ንብረት መልሰው ማግኘት እንዲችሉ መፍቀዳቸውን ተከትሎ በርካታ
ኤርትራዊያን በዕድሉ በመጠቀም ከተለያዩ ዓለማት ወደኢትዮጵያ በመሄድ የቀድሞ ንብረታቸውን አስከብረዋል፡፡
በተጨማሪም ድንበር አቋርጠው ወደኢትዮጵያ የሚገቡ ስደተኛ ኤርትራዊያን በአገር ውስጥ ዩኒቨርሲቲዎች ሳይቀር በልዩ
ድጋፍ ገብተው እንዲማሩ እንደተፈቀደላቸው ሟቹ ጠቅላይ ሚኒሰትር መለስ ዜናዊ መግለጻቸው ይታወሳል።
በ1990 ዓ.ም ድንገት በሁለቱ አገራት መካከል ጦርነቱ ሲቀሰቀስ በአሰብ ወደብ ላይ የሚገኝ ንብረታቸው የተወሰደባቸው ኢትዮጽያዊያን ነጋዴዎች ንብረቶች ብቻ ከ500 ሚሊየን ብር በላይ ይገመት ነበር፡፡ ያኮና ኢንጂነሪንግ፣ኮስ ትሬዲንግ እና የመሳሰሉ አገር በቀል ኩባንያዎች ከዘረፋው ጋር ተያይዞ በደረሰባቸው ኪሳራ ከገበያ መውጣታቸው የሚታወስ ነው፡፡የቀድሞ ጠ/ሚኒስትር አቶ መለስ የኢትዮጵያዊያንን ጥቅም ሳያስጠብቁ የኤርትራዊያን እንዲጠበቅ በማደረግ ሚዛን የሳተ ውስኔ አሳልፈዋል በሚል ክፉኛ ሲተቹም እንደነበር አይዘነጋም፡፡
አቶ ስብሃት ነጋ የሚመሩት ድርጅት መጋቢት 28 ቀን 2005 ዓ.ም በአዲስአበባ ሒልተን ሆቴል የጠራው ስብሰባም
ፋይዳው ይህንኑ ግንኙነት አጠናክሮ ለማስቀጠል ያለመ ነው መሆኑን ምንጫችን ተናግሯል፡፡
የሁለቱ አገራት መንግስታት ዕርቀ ሰላም ባላወረዱበት ሁኔታ ያውም ገለልተኛ ባልሆነ ተቋም አማካይነት ለማምጣት
የታሰበው የሕዝብ ለሕዝብ ግንኙነት ምን እንደሚመስል እነአቶ ስብሃት ያስረዱናል ያለው ምንጫችን፣ በአጠቃላይ ሒደቱ
በኢትዮጵያ መንግስት ላይ የተጣበቁ ጥቂት የኤርትራ መንግስት ተቃዋሚዎችን ለመጥቀም የታስበ ይመስላል በማለት ገልጿል፡፡

የሌንጮ ለታ አዲሱ ትግል – እንዴት?

 
“ከእንግዲህ የቀድሞው መንገድ አይሰራም”
odf
ላለፉት አርባ ዓመታት ለኦሮሞ ህዝብ ነጻነት ሲታገል የቆየው ኦነግ አመራሮቹ ሲጣሉና ሲታረቁ መስማት የተለመደ ነው። የግለሰብ ጸብ የሚመስለው የድርጅት በሽታ ሲንጠው የቆየው ኦነግ በውል ባይታወቅም ተሰነጣጥቆ ለሰሚው ግራ የሚያጋባ ድርጅት ከሆነም ዓመታት ተቆጥረዋል። ስህተትን ገምግሞ የትግል አቅጣጫና ፕሮግራም ከመቀየር ይልቅ ጊዜው ባለፈበት አስተሳሰብ ባለበት ሲረግጥ እድሜውን የፈጀ ድርጅት እንደሆነ ተደርጎም ይወሰዳል።
ስለ ኦነግ ሲነሳ አብዛኞች በመገረም የሚናገሩትና ሚዛን የሚደፋው አስተያየት የሚሰነዘረው በድርጅቱ መከፋፈልና መበጣጠስ ሳይሆን ተለያይተውም አስመራን የሙጥኝ ያሉበት ምክንያት ነው። ኢህአዴግ ህጻን እያለ ሻዕቢያ እንዳሻው ይነዳው እንደነበር የሚያስታውሱ አስተያየት ሰጪዎች ከሽግግር መንግስት ምስረታ በኋላ ኦነግ አገር ለቆ እንዲወጣ መንገዱን የጠረገው ሻዕቢያ መሆኑንን በቁጭት ይናገራሉ።
ኢህአዴግ ለስልጣን አዲስ በሆነበት የጨቅላነት ዘመኑ፣ ኦነግ በታሪኩ ያልነበረውን ሰራዊት በመገንባት አስጨንቆት እንደነበር በመጠቆም በወቅቱ አስተያየት የሰጡ ኢህአዴግ በተለይም መለስ በሻዕቢያ በኩል ኦነግን ለመታረቅ አቅርበውት የነበረውን የሽምግልና ጥያቄ ኦነግ እንዳይቀበል ሰሚ ባያገኙም በአጽዕኖት ምክራቸውን ሰጥተው ነበር።
በኦነግ ታጣቂ ሃይሎችና በኢህአዴግ ሰራዊት መካከል እኩል ሊባል በሚችል ደረጃ የጡንቻ መፈታተን ነበር። ደርግ ሲበታተን ኦነግን የተቀላቀሉ የቀድሞው የኢትዮጵያ ሰራዊት አካላት ወያኔን የማዳፋት አቅሙ ነበራቸው። በወቅቱ የንስር ያህል ጉልበትና ሃይል ቢኖራቸውም ራሳቸውን ጫጩት አድርገው ተመለከቱ። አዲስ አበባ ሲገቡ የነበራቸውን የህዝብ ድጋፍ አራግፈው ጣሉት። በስሜት እየተነዱ ከሚወዷቸው ሁሉ ተቀያየሙ። ህወሃት አጋጣሚውን ለቅስቀሳና ለስም ማቆሸሻ ሰራበት። በስተመጨረሻ ኦነግ ሃይሉንና አቅሙን ዘንግቶ በአመራር ችግርና በአቋም ሸውራራነት ሃይሉን በሙሉ ወደ ካምፕ በማስገባት የኢህአዴግን የእርቅ ጥያቄ ተቀበለ። ሰራዊቱን እየነዳ በፈቃደኛት አሳሰራቸው።
በሻዕቢያ አደራዳሪነት ሁርሶ፣ ደዴሳና መስኖ የገባው ሰራዊት “በደባ” ተከቦ ትጥቁን እንዲፈታ ተደረገ። አብጦ የነበረው የኦነግ ጡንቻ በቅጽበት ከሰመ፤ ሰለለ። ኦነግ ሲቆጣጠራቸው የነበሩትን ቦታዎች ለማስተዳደርና በኦህዴድ ለመተካት ኢህአዴግ እንደ እባብ ተሹለክልኮ ዓላማውን አሳካ። ሻዕቢያም በዚሁ ውለታው ኢትዮጵያንና ኢኮኖሚዋን ብሎም የኢትዮጵያን ስነልቦና እንዳሻው እንዲጋልብ ተፈቀደለት። ብዙ አሻጥር ተፈጠረ፤ ተፈጸመም። ደንዳና ቆዳ ያላት ኢትዮጵያና ህዝቧ ተቦጠቦጡ። ተዘረፉ። አንድ እግር የቡና ተክል የሌላት ኤርትራ ቡና ላኪ ከሚባሉት ቀዳሚ አገራት ዝርዝር ውስጥ ተሰለፈች። አፈርን።
“አገሬን ከወራሪ አጸዳሁ” በማለት ከበሮ እየመታ ጦርነት አልቋል ብለው እጅ የሰጡ የወገን ወታደሮችን የረሸነው ሻዕቢያ ኢትዮጵያንም ያስተዳድር ጀመር። ዛሬ የሚማልባቸውና “ውርሳቸውን ሳናዛባ እናስጠብቃለን” የሚባልላቸው አቶ መለስ እንደ ባዕድ መሪ የኢትዮጵያን ክብርና ጥቅም ለሻዕቢያ አሳልፈው ሰጡ። የሻዕቢያ ታጣቂዎችና ኢትዮጵያ አብልታ ያሳደገቻቸው ጎረቤቶቻችን ሳይቀሩ ናጠጡብን። በየደጃቸው መሳሪያ ወደላይ እየተኮሱ በደስታ ውለታ ባስቀመጠችላቸው አገር ላይ ተሳለቁ። ምስኪኖችን ቤት እያስለቀቁ ወረሱ። የሌላቸውን ሃብትና ንብረት ሰበሰቡ። በኤርትራ ምድር በግፍ ለተረሸኑ የኢትዮጵያ ልጆች ተከራካሪ ጠፋና የሞት ሞት ሞቱ። አገራችን የግፈኞች መፈንጫ እንድትሆን መለስ በበረገዱት በር የገባው ሻዕቢያ ከርሱ ሲጎድል፣ “ልክህን እወቅ” የሚሉ ሲነሱ፣ ስርዓት ያዝ ሲባል ደሙ ተንተከተከና የሃይደር ህጻናትን በጠራራ ጸሃይ በላቸው። ትግራይን ወረረ። ሲሰርቁ ኅብረት የነበራቸው ሲከፋፈሉ ተጣሉና አገር ውርደት ገባው።
ይህንኑ ተከትሎ አገር አልበቃ ብሏቸው የነበሩና ወያኔን ሲያገለግሉ የነበሩ ቅጥረኞች የሰበሰቡትን ሳይበሉ ወደ “ከባርነት ናፅነት” ብለው ድምጻቸውን ወደሰጡላት “እናት አገራቸው ኤርትራ” ተጋዙ። ንብረታቸውን በትነው አገር ለቀው ወጡ። ከነጻነት በኋላ “ታይላንድ ትሆናለች፣ ሲንጋፖር ትሆናለች፤ ሆንግኮንግ ትሆናለች” በተባለላት አገራቸው ለመኖር ተገደዱ። ዳቦ ተሰልፈው ለመግዛት ታደሉ። ኬክ በለመደው፣ ቁርጥ በቆርጠው፣ “ሹካ ባስለመደው” እጃቸው ይድሁበት ገቡ። ወታደር ሆኑ። የሰገዱለትና ቅጥረኛ ሆነው ያገለገሉት ህወሃት መልሶ በረሃ በተናቸው። የሚያሳዝነው ግን ኤርትራዊያን ከየመንደሩ ተለቅመው ወደ አገራቸው ሲሄዱ የአዲስ አበባ ነዋሪዎች አውቶቡስ ከብበው ደረት እየመቱ ያለቅሱላቸው ነበር። ደብቀው ያስቀሩዋቸውም አሉ። ጨርቃቸውን ጥለው አውቶቡስ እንዳይነሳ በፍቅር አምላክ የተንፈራፈሩ ነበሩ። ሁኔታውን የሚያስታውሱ ድርጊቱን “የሞኝ” ተግባር አድርገው ሲወሰዱት ሌሎች ደግሞ “ክፉ ላደረገብህ ክፉ አትመልስ” የሚለው ግብረገብነት የገባቸው የፈጸሙት የጀግንነት ተግባር ነው በማለት የአዲስአበባ ነዋሪዎችን የመንፈስ ልዕልና ያደንቃሉ፡፡
ይህ ከመሆኑ በፊት ጀምሮ ኦነግ ሻዕቢያን ሲለማመነውና እግሩን ሲልሰው የኖረ ድርጅት ዛሬ ድረስ ተበጣጥሶም እዛው አስመራ አምልኮ ደጅ ይገኛል። ከአመት ዓመት ያለ ለውጥ እዛው ይንፏቀቃል። እንደሚሰማው ከሆነ ወታደሮቹ የሻዕቢያ አግልጋዮች ሆነዋል። አመራሮቹም ቢሆኑ አስመራን ለቀው የመውጣትና እንዳሻቸው የመንቀሳቀስ መብት የላቸውም። በዚህም ይሁን በሌላ መነሻ ኤርትራ በከተሙት የተለያዩ የኦነግ ሃይሎች ላይ ከያቅጣጫው ስሞታ መቅረብ ከጀመረ ሰንብቷል። ኤርትራን ለቀው መውጣት አለባቸው የሚለው የኦሮሞ ልጆች ድምጽም በርክቷል። ጥያቄው አያሌ ፖለቲካዊ ማብራሪያ የሚጠይቅና አማራጭ መፍትሄ የሚያሻው ቢሆንም ኤርትራ ውስጥ አሉ በሚባሉ ታጣቂ ተቃዋሚዎች ያልተማረሩና ያልተሰላቹ ቢኖሩ አፍቃሪ ሻዕቢያዎች ወይም ራሳቸው የሻዕቢያ ሰዎች ወይም በማወቅም ሆነ ባለማወቅ የሻዕቢያን ዓላማ የሚያስፈጽሙ ብቻ ናቸው።
እንግዲህ በዚህ መሃል ነው አስመራን ተሳልመው ከነበሩት የኦነግ አመራሮች መካከል አቶ ሌንጮ ለታ፣ አቶ ዲማ ነገዎና ሌሎች ሰሞኑን አዲስ ዜና ይዘው ብቅ ያሉት። አዲስ ፓርቲ በማቋቋም ድፍረት የተሞላው አቋም በማራመድ “አዲሲቷን ኢትዮጵያ በጋራ ለመመስረት ተነስተናል። የቀድሞው የትግል ስልት አያዋጣም” ያሉት። ሃሳቡ መልካም ቢሆንም እንዴት? የሚለው ጥያቄ የበርካቶች ነው። ምክንያቱም በግልጽ “የቀጣዩ ትግል ሜዳ አገር ቤት ነው፤ አገር ቤት ገብተን እንታገላለን” ተብሏልና!
“የኦሮሞ ዴሞክራሲያዊ ግንባር” ODF የሚባል አዲስ ግንባር መቋቋሙ ከአሜሪካ የሚኖሶታ ጠቅላይግዛት ከተሰማበት ጊዜ ጀምሮ በርካታ አስተያየቶችና ጥያቄዎች እየተወረወሩ ሲሆን ከሚመለከታቸው አካላት ጥርት ያለ መልስ አልተሰጠም። ግንባሩ መመስረቱ ይፋ ከሆነ በኋላ መጋቢት 22፤2005ዓም (ማርች 31/2013) በዚያው ጠቅላይግዛት በሚኒያፖሊስ ከተማ በተካሄደ ስብሰባ አንዳንድ ጉዳዮች ይፋ ሆነዋል።
ከብሪታንያ፣ ስዊትዘርላንድ፣ ከካናዳ፣ ከአውስትራሊያ፣ ከጀርመንና ከተለያዩ አገራት የተሰባሰቡ ቁጥራቸው 400 የሚጠጋ ተሰብሳቢዎች ባካሄዱት ውይይት አስፈላጊ የተባሉ ጥያቄዎች ተሰንዝረዋል። ኢትዮጵያን “ኢምፔሪያሊዝም፣ ቅኝ ገዢና ጠላት” አድርገው በመሳል ጥያቄ የሰነዘሩትን ጨምሮ ስለ ቀጣዩ ትግል ትግበራና ሰለ ኦሮሞ ህዝብ ነጻነት መከበር በስፋት ለተነሱ ጥያቄዎች አቶ ሌንጮ ለታ አስገራሚ መልስ ሰንዝረዋል።
“ያለፈውን በመውቀስ የትም አንደርስም። አሁን ማየትና ማሰብ ያለብን ወደፊት ነው። ሌሎች ወገኖችን አግልለን ብንታገል የትም አንደርስም። ያለፈው የትግል መንገድ ስህተት ነበር” ብለዋል። ስለ ኦሮሞ ህዝብ ነጻነት መከበር ሲናገሩ “የሁሉም ኢትዮጵያዊ መብት ካልተከበረ የኦሮሞ መብት ብቻውን ሊከበር አይችልም” በማለት መመለሳቸውን ለማወቅ ተችሏል።
“ጊዜው ተለውጧል። ጊዜው አዲስ ነው። አዲስ ምዕራፍ ላይ ነን። አዲሱ ምዕራፍ ለኦሮሞ ብቻ ሳይሆን ለሁሉም ኢትዮጵያዊ ነው” በማለት የተናገሩት አቶ ሌንጮ፣ “አገር ቤት እንዴት ገብቶ መታገል ይቻላል?” በሚል ለተነሳው ጥያቄ የሰጡት መልስ አዲሱን ድርጅታቸውንና እርሳቸውን የሚፈትን እንደሆነ ያመላከተ ነው።
ቀጣዩ ትግል ኤርትራ ላይ እንደማይሆን በግልጽ የተናገሩት አቶ ሌንጮ፣ አገር ውስጥ በመግባት ለማደራጀት፣ ለመታገል፣ ለመንቀሳቀስ ይቻል ዘንድ “መንገድ እንፈልጋለን” ብለዋል። ኢህአዴግ በተደጋጋሚ እንደሚለው ለድርድር የሚቀመጡ ወገኖች መጀመሪያ ህገመንግስቱን መቀበልና ህግመንግስቱን አክብሮ ለመስራት መማል አለባቸው። ይህ ወደፊት የሚታይ ቢሆንም አገር ቤት ለመግባትና ለመታገል እነ አቶ ሌንጮ ቢስማሙ እንኳን ሌላ መሰረታዊ ችግር እንዳለ ከወዲሁ እየተጠቆመ ነው።
በኦሮሞነታቸው በሚያነሱት ጥያቄ እስር ቤት የታጎሩ የኦሮሞ ልጆች ቁጥራቸው ከፍተኛ ነው – በአስር ሺዎች እንደሚቆጠር ይገመታል። በየቦታው ባሉ እስር ቤቶች ዋናው የመግባቢያ ቋንቋ ኦሮሚኛ እስከመሆን የደረሰበት ሁኔታ ነው የሚታየው። ይህ እውነታ ባለበት አቶ ሌንጮ የሚመሩት አዲሱ ድርጅት እንዴት አድርጎ ይታገላል? ወይም ደግሞ አባላቶቹ እስርና እንግልት እንዳያጋጣማቸው ምን ዓይነት ማረጋገጫና መተማማኛ ማግኘት ይቻላል?
“መልሱ ግልጽ ነው” በሚል ይመስላል “የፈለገው ቢመጣ፣ አስፈላጊው ህግን የጠበቀ ትግል ይካሄዳል። አገሪቱ ላይ ያለውን ህዝብ አስሮ ይችል እንደሆነ የሚታይ ይሆናል” የሚል እንደምታ ያለው ምላሽ ነው እየተሰነዘረ ነው ያለው። በሌላ በኩል አገር ቤት ገብቶ መታገል ብቸኛ አማራጭ ተደርጎ ሲወሰድ አዲሱ ጉዳይ የቀድሞው ሌሎችን ሲያገልና “ልዕልናና ነጻነት ለኦሮሞ ብቻ” በሚል የፖለቲካ ሾፌር ሲደወር የነበረው የትግል ስልት መቀየሩ ነው። በዚህም የተነሳ ይመስላል “ከማናቸውም በኢትዮጵያ ለዴሞክራሲ መረጋገጥና ለህዝብ እኩልነት ከሚሰሩ ድርጅቶችና ፓርቲዎች ጋር አብረን እንሰራለን። የቀድሞው መንገድ አይዋጣም” የሚል ምላሽ የሰጡት።
በኢትዮጵያ ፖለቲካ “እኔን ተከተል፣ ስትቃወም ከኔ ቀመር አትዛነፍ” የሚለውን አመለካከት ጨምሮ በድፍን የአንድ እንቅስቃሴ እርግጠኛ መነሻ ሳይታወቅ አስቀድሞ “የማብከትና የማበስበስ” ስራ መስራት የተለመደ በመሆኑ ከሁሉም ወገን እርጋታ እንደሚጠበቅ፣ ረጋ ብሎ መመርመር እንደሚያስፈልግ ከወዲሁ እየተነገረ ነው።
ላለፉት 20 ዓመታት ኢህአዴግ በብሄር እየለየ በፈጠረው ገደል እየተወረወሩ የሚገቡ ፖለቲከኞች በሰሩት ጥፋት ህዝብ ለከፍተኛ የአእምሮ ጉዳት ተዳርጓል። ኢህአዴግ የ50 ዓመት የቤት ስራ እንደሰጠ አድርጎ የሚያስበውም እነዚሁ የፖለቲካ መሪዎች የህወሃትን የሳሳ ፖለቲካ መረዳት ባለመቻላቸውና ከዋናው ጠላታቸው ይልቅ እርስ በርስ ለመቧቀስ የፈጠኑ መሆናቸውን በቀላሉ ስለሚያሳዩት ነው።
ከ40 ዓመታት የስህተት ጉዞ በኋላ አገር ቤት በመግባት “ሁሉም ነጻ ካልወጡ ኦሮሞ ብቻውን ነጻ አይወጣም” በሚል የትግል መርህ መነሳት በራሱ አስደሳች እንደሆነ አቶ ኦባንግ ሜቶ ለጎልጉል በስልክ ባደረጉት አጭር ቃለምልልስ ተናግረዋል።
“ድንበርና ክልልን ሳይሆን የምንጋራው አብሮነትን ነው” ያሉት የአዲሲቷ ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄ ዋና ዳይሬክተር “በዲኤንኤ ምርመራ ጎሳ አይታወቅም። ተመሳሳይ ዲኤንኤ ያላቸው ጎሳዎችም የሉም። ሁሉም ነጻ ካልወጡ ማንም ነጻ እንደማይወጣ መስማት ታላቅ ብስራት ነው” በማለት ከዓመታት ትግልና ውትወታ በኋላ ድርጅታቸው ሲታገልለትና ሲሟገትለት የቆየው ዓላማ የሌሎችም መርህ ሆኖ በማየታቸውና በመስማታቸው መደሰታቸውን ተናግረዋል።
ከኢትዮጵያ ሕዝብ አብላጫውን ቁጥር የሚይዘው የኦሮሞ ህዝብ ለዚህ ዓይነቱ መርህ ለዘመናት የቆየው ሥርዓቱም ሆነ አኗኗሩ ቅርብ እንደሆነ አቶ ኦባንግ አመልክተዋል፡፡ ድርጅታቸው ከተመሰረተበት ጊዜ ጀምሮ “ከጎሣ ይልቅ ለሰብዓዊነት ቅድሚያ እንስጥ” በሚል የከበረ መመሪያ ላይ ሲሰራ መቆየቱን የገለጹት አቶ ኦባንግ ከዚህ መመሪያ በተጨማሪ “ሁላችንም ነጻ ካልወጣን ማንም ብቻውን ነጻ ሊሆን አይችልም” በሚለው የትግል መርህ በርካታ ስኬቶች መመዝገባቸውን ጠቁመዋል፡፡ ይህንን መፈክር አሁን ደግሞ ኦሮሞ ወገኖቻችን ሲያነሱ መስማት ለድርጅታቸው ታላቅ ድል እንደሆነ ተናግረዋል፡፡
ስብሰባው ላይ ማንም ሳይጠራቸው በራሳቸው አነሳሽነት እንደሄዱ ያስታወቁት አቶ ኦባንግ “የኦሮሞ ተወላጆች ስብሰባ ሲቀመጡ የሚነጋገሩት ስለ ኢትዮጵያ ነው። ኢትዮጵያዊ ነኝና ውይይቱ ይመለከተኛል። ስለዚህ ተገኘሁ። በደስታ ተቀበሉኝ። በስብሰባው ውስጥ በሰማሁት አዲስ ሃሳብ ተደሰትኩ” ብለዋል።
ላለፉት 20 ዓመታት አንዱ ስለ ሌላው ሲያወራ መኖሩን ያመለከቱት አቶ ኦባንግ ሜቶ አሁን አንድ ላይ በመሆን ለመመካከርና “ለአዲሲቷ ኢትዮጵያ” ግንባታ በጋራ ለመታገል መወሰን ከልምድ የተገኘ የፖለቲካ ተሃድሶ መሆኑን አስታውቀዋል። አያይዘውም ድሮም ቢሆን ፖለቲከኞች እንጂ ህዝብ አእምሮ ውስጥ ያልነበረ አስተሳሰብ በማቀንቀን ለህወሃት ፖለቲካ ማዳበሪያ የማቅረብ ስራ ሲሰራ እንደነበር አመልክተዋል።
አቶ ሌንጮ ለታ እንጀምረዋለን ያሉት አዲሱ መንገድ ሁሉንም ህዝብና የፖለቲካ ድርጅቶች ማዕከል በማድረግ ለመስራት ወስኖ የተነሳ እንደሆነ ሲያስታውቁ ያሰመሩበት ጉዳይ ቢኖር “ያለፈውን አናስብም። አሁን አዲስ ምዕራፍ ላይ ነን። አዲሱ ምዕራፍ ሁሉም የኢትዮጵያ ልጆች ተያይዘው የሚፈጥሯትን አዲስ አገር ማየት ነው፡፡” እርሳቸው እንዳሉት 40 ዓመት ባክኗል። አሁንም መንቃት አግባብ ነው። ነገር ግን ድጋፉም ሆነ ተቃውሞው በተራ የድጋፍና ተቃውሞ ስሜት ሳይሆን ረጋ ብሎ በመመርመር እንደሆነ የሚመክሩ ጥቂቶች አይደሉም።
 
 
(ፎቶዎቹን የወሰድነው ከ Hegeree Media channel ቪዲዮ ላይ ነው)

Wednesday, April 3, 2013

አንድነት በህሊና እስረኞች ላይ የሚደርሰውን በደል በመቃወም የተቃውሞ እንቅስቃሴ ሊጀምር ነው

 

የአንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ አመራር አባል የሆነው አቶ ናትናኤል መኮንን ከአንድ ሳምንት በላይ በርሀብ አድማ ላይ እንደሚገኝ የፍኖተ ነፃነት ምንጮች ገለፁ፡፡

በቂሊንጦ ወህኒ ቤት በቅርቡ በተደረገ ስብሰባ ላይ አልሳተፍም በማለቱ ብቻ ለአንድ ወር ከቤተሰቦቹ ጋር እንዳይገናኝ የተከለከለው አቶ ናትናኤል የወህኒ ቤቱን ውሳኔ በመቃወም ከአንድ ሳምንት በላይ በርሀብ አድማ ላይ እንደሚገኝ ታውቋል፡፡
የአንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ ከፍተኛ አመራር አቶ ናትናኤል መኮንን ከቤተሰቦቻቸው እንዳይገናኙ መደረጉን በመቃወም የአንድነት ፓርቲ ከፍተኛ አመራሮች ወደ ወህኒ ቤት በማምራት ማብራሪያ እንደሚጠይቁና ምክንያቱን እንደሚያጣሩ ፓርቲው ለፍኖተ ነፃነት አስታውቋል፡፡

የአንድነት ፓርቲ የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ዳንኤል ተፈራ ለፍኖተ ነፃነት እንደተናገሩት አንባገነኑ የኢህአዴግ መንግስት በፖለቲካ አመለካከታቸው ብቻ ዜጎችን ማሰሩ ሳያንስ በወህኒ ቤት ውስጥ የሚያደርሰውን ኢሰብአዊ ድርጊት ፓርቲው ያወግዘዋል፡፡ በተለይም በህሊና እስረኞች ላይ የሚደርሰውን በደል በመቃወም ሊወስድ ላሰበው የተቃውሞ እንቅስቃሴ መረጃ ለማሰባሰብ ይረዳው ዘንድ የፓርቲውን ሊቀመንበርና ሁለት ከፍተኛ አመራሮችን ያካተተ ቡድን አቋቁሟል፡፡ ቡድኑ ከወህኒ ቤቱ የሚያገኙትን መልስ መሰረት አድርጎ ፓርቲው የራሱን እርምጃ ይወስዳል፡፡

በፍኖተ ነፃነት አቶ ናትናኤል ስላሉበት ሁኔታ እንዲያስረዱ የተጠየቁት ባለቤታቸው ወ/ሮ ፍቅርተ…. ከአንድ ሳምንት በላይ አቶ ናትናኤልን እንዳላያቸው ገልፀው፤ “ካለፈው ሳምንት ጀምሮ የሚላክለትን ምግብ አልተቀበለም፤ ያለበት ሁኔታም አሳስቦኛል” ብለዋል፡፡

Tuesday, April 2, 2013

ጋዜጠኛ ርዮት አለሙ በቃሊቲዎች ክስ ቀረበባት!


አቤ ቶኪቻው
መምህርት እና ጋዜጠኛ ርዮት አለሙ በቃሊቲ እስር ቤት የሚገኙትን የአስተዳደር እና የጥበቃ ሰራተኞች ትንቂያለሽ፣ትሰደቢያለሽ እንዲሁም “የምትሰሩትን በሚዲያ እና ድረ ገፆችReeyot Alemu, the 31 year-2012 Courage in Journalism Award winner. አጋልጣለሁ” ብለሽ ትዝቺያለሽ በሚል ክስ ቀርቦባት መጋቢት 25 /2005 ዓ.ም ቃሏን መስጠቷ ተሰማ፡፡
ጋዜጠኛይቱ ክሱን አስመልክቶ ቃሏን እንድተሰጥ የተጠየቀቸችው መጋቢት 19 /2005 ዓ.ም ምሽት ከመኝታዋ ተቀስቅሳ የነበረ ቢሆንም ከጠበቃዬ ጋር ሳልነጋገር ምንም የምሰጠው ቃል የለኝም በማለቷ እስከ መጋቢት 25 ሊዘገይላት ችሏል፡፡
ርዮት የተከሰሰችው በፌደራል ታራሚዎች አያያዝ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ ቁጥር 139/1999 አንቀፅ 36 መ እና ሠ ላይ በተቀመጠው መሰረት ሲሆን ይህ አንቀፅ “ከባድ የዲሲፒሊን ቅጣት የሚያስከትሉ ድርጊቶች” ተብሎ የተዘረዘረ ነው፡፡
ርዮት ቅጣቱ ተግባራዊ ከተደረገባት፤
ከአንድ ወር እስከ አራት ወር ለሚደርስ ጊዜ በወዳጅ ዘመዶቿ እንዳትጎበኝ፤ ደብዳቤ እንዳትልክ እና እንዳትቀበል (ይሄ እንኳ አሁንም ተግባራዊ ተደርጎባታል) የእስር ቤቱን ቤተ መጻህፍት እንዳትጠቀም፣ በእስር ቤቱ በሚደረግ የጋራ ዝግጅት እና መዝናኛ ላይ እንዳትሳተፍ እንዲሁም ከአንድ ወር እስከ ሁለት ወር ለሚደርስ ጊዜ ለብቻ እስር ትዳረጋለች፡፡
እንዲህ ከሆነ ደግሞ ያቺ በቃሊቲዊቹ ውቃቢ ትፈቀድ የነበረች አመክሮም ልትከለከል ነው ማለት ነው፡፡
በነገራችን ላይ ወጣቱ ፖለቲከኛ ናትናኤልም በእስር ቤቱ እየደረሰበት ያለውን አበሳ በመቃወም የርሃብ አድማ ላይ መሆኑ ተሰምቷል፡፡ የሙስሊሙ መፍትሄ አፈላላጊ አባላትም ቅጥ ያጣውን የእስር ስርዓት ሃይ ለማለት የርሃብ አድማ ላይ ናቸው፡፡
ወይ ጣጣ… ብዬ የራሴን አስተያየት በአዲስ መስመር አቀርባለሁ…
እኔ የምለው ግን ኢህአዴግ ምነው እንዲህ መካሪ አጣ…? እርሱ እኛን በስንቱ መከራ እንዳልመከረን እርሱን የሚመክረው ማጣቱ የሚገርም ነው፡፡
እስቲ አሁን በእስር ላይ የሚገኙ ሰዎችን እስሩ አንሶ አሳር የሚያበላው ምን ይሁነኝ ብሎ ነው? እንደሰማነው በርካታ የህሊና እስረኞች በታመሙ ጊዜ የሚያክሟቸው የእስር ቤቱ ሀኪሞች “መግደል ነበር አንተን” “መጨረስ ነበር አንቺን” እያሉ ያስፈራራሉ፡፡ እውነቱን ለመናገር ይሄ የመጨረሻው ዘመን ምልክት ነውና ነቅታችሁ ጠብቁ፡፡ መንግስታችን “ባትሪ ሎው” እያለ ይመስለኛል!

ሰበር ዜና ማንም የወያኔ ካድሬም ሆነ የመንግሥት ሠራተኛ ከፌደራል ጀምሮ እንዲገመገም፣ ልዩና ጥብቅ ትዕዛዝ ተላልፏል።

የፋሽስት ጣሊያን አሽከሮች የሹምባሽ አስረስ ተሰማ የልጅ ልጅን እና የሹምባሽ ዜናዊ አስረስ ልጅን የመለስ ዜናዊ አስረስን ፀረ-ኢትዮጵያዊነትና በተለይም የፀረ-አማራነት ራዕይ ጅምር ለማስፈፀም፤ ዘረኛ ትግሬዎች በተለይም ወጣቶቹ የተጀመረውን ኢትዮጵያን የማፈራረስ እና አማራውን የማጥፋት ዘመቻ እስከመጨረሻው እንዲያስፈጽሙ በመለስ ዜናዊ ስም የፋሽስቶች ፋውንዴሽን ሊመሠረት ነው። ሙዚዬምም ይሠራለታል በመማለት ወያኔ በትናንትናው ምሽት ዜና ቢያስታውቅም፤
በአሸባሪው ወያኔ መንደር ግን ከፍተኛ ሽብርና ጭንቀት ገብቷል፣ ማንም የወያኔ ካድሬም ሆነ የመንግሥት ሠራተኛ ከፌደራል ጀምሮ እስከ ቀበሌ ድረስ እንዲገመገም፣ ዕረፍት እንዳይኖረውና ሌላ ነገር እንዳያስብ ልዩና ጥብቅ ትዕዛዝ ተላልፏል።
የራሱን ሕዝብ በማሸበር በሚታወቀው በወያኔ መንደር ከፍተኛ ሽብርና ጭንቀት ገብቷል። የኢትዮጵያ ግብርና ምርት ዕድገት በተከታታይ ዓመታት ከ10 በመቶ በላይ አደገ እያለ በሀሰት ሲመፃደቅ የከረመው የወያኔ መንግሥት፤ የውሸቱ ክምር በአገሪቱ የሚያስፈልገውን የምርት መጠን ሊያስገኝ ባለመቻሉ፣ የግብርና ግብዓት ዋጋ በየዓመቱ እየናረ ባለበትና የአርሶ አደሩ የግብዓት አጠቃቀም እየቀነሰ በሄደበት ሁኔታ፣ የግብርና ባለሙያዎች ሙሉ ጊዜያቸውን የኢህአዴግን ፖለቲካ ብቻ እያስፈፀሙ በመገደዳቸውና አርሶ አደሩ ከግብርና ባለሙያዎች ምንም ዓይነት የሙያ ድጋፍና የምርት ዕድገት ማግኜት ስላልቻሉ ተስፋ በመቁረጣቸው፣ በተለይ ባለፉት ሁለት ዓመታት አርሶ አደሮች ተገድደው ከሚሠሩት የአፈርና ውሃ ጥበቃ ሥራ በስተቀር፤ ከ1989 ዓ.ም. በኋላ በግብርናው ዘርፍ ተመዘገበ የሚባለው የምርት ዕድገት የሀሰት ቁጥር ክምር መሆኑን፣ ለመጀመሪያ ጊዜ ኢህአዴግ ባለፈው 9ኛ ጉባኤው ላይ በይፋ አምኗል።
ከዚህም በተጨማሪ በተለይ በአማራው፣ በኦሮሞው ፣ በጉራጌው፣ በአኝዋኩ፣ በአፋሩና በኢሳው ወዘተ ሕዝብ መካከል በህወሃት አቀነባበሪነት የሚደርሰውን በደል እና ሕዝብን እርስ በእርስ ለማጋጨት የሚደርገውን ሴራ ሕዝቡ እየተረዳ በመሄዱ፣ በትግራይ ሕዝብ ስም ህወሃቶች በተለይም ጥቂት የአድዋ የባንዳ ርዝራዦች እየነገዱበት እና የትግራይን ሕዝብ ከቀሪ የኢትዮጵያ ወገኑ ጋር ለማቆራረጥ እየጣሩ መሆኑን በመረዳቱ የትግራይ ሕዝብም ፊቱን ወደ አረና ትግራይ እያዞረ በመሄዱ፣ እንዲሁም የሙስሊሙ እና የክርስቲያኑ አንድነት ህወሃት እንዳሰበው ወደ ግጭት ሊያመራለት ባለመቻሉ፣ እንዲያውም አንድነቱን እያጠናከረ በመሄዱ፣ ወዘተ ወያኔ ተጨንቋል፣ ተሸብሯል።
ይህ ሁሉ ሽብር የመጣው የኢትዮጵያ ሕዝብ በውስጡ ማንም ሊፍቀው የማይችለው የአንድነት፣ አብሮ የመኖርና የመቻቻል ባህሉ በወያኔ ሴራ ሊናጋ ባለመቻሉ፣ በተለይም ከቅርብ ዓመታት ወዲህ ወደ ትጥቅ ትግሉ የሚቀላቀሉ ወጣቶች ቁጥር እየተበራከተ በመምጣቱ፣ የሕዝቡን አንድነትና ዝምታ ክፉኛ በመፍራት ነው።
ስለዚህ የተጀመረው የተቀናጀ ሁለገብ ትግል በተጠናከረ መልኩ መቀጠል አለበት። አንድነት ሃይል ነው። በተባበረ የሕዝቦች ትግል ወያኔ ይወገዳል። ድል ለኢትዮጵያ ሕዝብ። እግዚአብሔር ኢትዮጵያን ይባርክ።
አማርኛ ተናጋሪ ኢትዮጵያውያንን ማፈናቀል የዘር ማጥፋት ወንጀል ነው (ሸንጎ)
መግለጫ
የኢትዮጵያ ህዝብ የጋራ ትግል ሸንጎ (ሸንጎ)
Click here for PDF
ህወሀት/ኢህአዴግ በህዝባችን ላይ የጫነው የጎሳ ፖለቲካ አስከፊ ገጽታው ላለፉት 22 አመታት በግልጽ እየሰፋ መጥቷል። የአንዱ ቋንቋ ተናጋሪ ከሌላው ጋር፣ የአንዱ አካባቢ ነዋሪ ከሌላውEthiopian People's Congress for United Struggle (Congress) ጋር በአይነ ቁራኛ፣ በአጥፊና ጠፊነት እንዲተያይ አድርጓል። በዚህም የተነሳ የጎሳ ግጭት እጅግ ተስፋፍቷል። የህዝብ ህይወት እና ንብረትም በሰፊው ጠፍቷል። የዜጎች የተረጋጋ ህይወትም ተናግቷል። ይህ አጥፊ ፖሊሲም በአስቸኳይ ካልተገታ ቀጣይና ምስቅልቅል ቀውስን እንደሚወልድ ግልጽ ሲሆን የዚህንም ቀውስ መጨረሻ ምን ሊሆን እንደሚችል መገመት እጅግ ይዘገንናል። ይቀጥላል…
 

ለዜጎች መሞት፣ መፈናቀልና መሰደድ ተጠያቂው መንግስት ነው!!!

አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትሕ ፓርቲ (አንድነት) የተሰጠ መግለጫ
አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትሕ ፓርቲ (አንድነት)
UNITY FOR DEMOCRACY AND JUSTICE PARTY (UDJ)
ወንጀለኞች በአስቸኳይ ለፍርድ እንዲቀርቡ እንጠይቃለን
በተደጋጋሚ ፓርቲያችን እንደሚገልፀው አምባገነኑ የኢህአዴግ መንግስት የሚከተለው ቋንቋን መሰረት ያደረገ ፌደራሊዝምና የስርዓቱ አራማጆች ካላቸው የስልጣን እድሜን የማራዘም ጉጉት ተደማምረው ለሃገራችን እንዲሁም ተቻችሎ፣ ተዋልዶ፣ ተዛምዶና ተዋድዶ ለዘመናት ይኖር ለነበረው የኢትዮጵያ ህዝብ ግልፅና አስፈሪ አደጋ ወደ መሆን እንደደረሱ በግላጭ እየታየ ነው፡፡ለዜጎች መሞት፣ መፈናቀልና መሰደድ ተጠያቂው መንግስት ነው!!!
ያ ለዘመናት አብሮን የቆየው በጋራ የመኖር ዕሴት እየተደመሰሰ በምትኩ የሚያጋጩ ስልቶች እየተፈጠሩና እየተተገበሩ ወደ ሰቆቃ ተለውጠው ይገኛሉ፡፡ የዜጎች ሰዋዊና ህጋዊ መብት እየተጣሰም ነው፡፡ በኢትዮጵያችን ውስጥ አብሮ የመኖር፣ ከቦታ ቦታ የመዘዋወርና በፈለጉት ቦታ ሃብት የማፍራት ህልውና እያከተመ መጥቷል፡፡ ለዚህ ክፉ ድርጊት ተጠያቂ የሚሆነው ደግሞ የዜጎችን መዘዋወር መብትና ሃብት የማፍራት መብት ማረጋገጥ የተሳነው መንግስትና መንግስት ብቻ ነው፡፡
የከዚህ በፊቱን የማፈናቀል ግፍ ትተን በቅርቡ እንኳ በጉረፈርዳና በሌሎች አካባቢዎች በቀጥታ በክልሉ ባለስልጣናት በተፃፈ ደብዳቤ ይሄ ሀገራችሁ አይደለም ተብለው፣ ሃብትና ንብረታቸው ተዘርፎ፣ የወለዱ አራሶች እንኳን የማገገሚያ ጊዜ ሳይሰጣቸው ደማቸውን እያዘሩ ሲባረሩ ከመንግስት የተሰጠው ምላሽ ‹‹ሞፈር ዘመቶች ናቸው (ማረሻውን ብቻ ተሸክሞ ወደ ሌላ ሀገር የሚሰደድ ለማለት ይመስለናል)›› የሚል ነበር፡፡ ይሄም ቢሆን የማንኛውም ዜጋ መብት ነው፡፡ መንግስት እነዚህ ዜጎች ‹‹ሃገራችን የት ነው?›› በማለት ለሚያነሱት ጥያቄ መልስ የለውም፡፡
ገዥው ፓርቲ ሃላፊነትን መዘንጋትንና ስህተትን በማረም ፈንታ አፋፍሞ በመቀጠል ዜጎች ሃብትና ንብረታቸው እየተዘረፈ መባረራቸውን ቀጥለዋል፡፡ ይህም በጋምቤላና ቤኒሻንጉል በከፋ መልኩ ቀጥሏል፡፡ በተለይ ከቤኒሻንጉል ክልል የአማራ ተወላጅ የሆኑትን ዜጎች የዘመናችን ሹመኞች ከኢ-ሰብዓዊነት ባፈነገጠ መልኩ ከእቃ ለሚሰጥ ክብር ባነሰ ሁኔታ ንብረታቸውን ሳይሰበስቡ በጅምላ እየተጫኑ መጣላቸውን ቀጥለዋል፡፡ በርካታ ህፃናትም የዚህ ግፍ ሰለባ ሆነዋል፤ እየታፈኑ የሚሞቱትም ቁጥራቸው በርካታ ነው፤ በጣም የሚያሳቅቀው ደግሞ የዚህ ግፍ ሰለባ የሆኑት 59 ሰዎች ሞት ጉዳይ ነው፡፡ ካላግባብ በጭካኔ ለብዙ ዓመታት ከኖሩበት፣ ከወለዱበትና ከከበዱበት ስፍራ ሃላፊነት በጎደለው ሁኔታ በአንድ መኪና እየታጨቁ እንዲወጡ በማድረግ ገደል ውስጥ ገብተው እንዲሞቱ የተፈረደባቸው ዜጎችን ህይወት እንዲቀጠፍ ያደረገውም በቸልታ እየገዛ ያለው የኢህአዴግ መንግስት ነው፡፡ መንግስት በነዚህ ዜጎች ላይ ለደረሰው ኢ- ሰብዓዊ ድርጊትና ህይወት ማጣት ተጠያቂ ነው በማለት ፓርቲያችን ያምናል፡፡
ፓርቲያችን አንድነትም ጥያቄ ያነሳል፡፡ ለውጭ ዜጎች እንዲበለፅጉበት በትንሽ ሳንቲም፤ ግልፅነት በጎደለውና በሙስና በተተበተበ አሰራር ለቻይና ኩባንያዎች፣ ለህንድ ኩባንያዎች፣ ለሳዑዲ አረቢያ ኩባንያዎች ወዘተ ለዜጎቻቸው ቀለብ እንዲያመርቱበት በገመድ እየተለካ የሚሰጠው የአዲስ አበባን ስፋት አምስት ጊዜ የሚበልጥ መሬት እንዴት ለዜጎቹ ይነፈጋል? ለምንስ ኢትዮጵያውያን ተዘዋውረው በኩርማን መሬት ላይ ሃብት የማፍራት መብታቸውን ተነፈጉ? ይህንን ኢሰብኣዊነት ዓለማቀፉ ማህበረሰብ፣ የሰብዓዊ መብት ድርጅቶችና ኢትዮጵያውያን ሁሉ እንዲያውቁት እንፈልጋለን፡፡ ኢህአዴግንንና በእሱ የሚመራውን መንግስት ታሪክና ሕዝብ ይፋረደዋል፡፡ ይህንንም በደል እያዩና እየሰሙ ዝም ማለት የወንጀሉ ተባባሪ መሆን ማለት ነው፡፡ ዛሬውኑ ተቃውሞአችንን፣ ጩኸታችንን እናሰማ፤ በደል ሰቆቃ በቃ እንላለን፡፡

UN FINDS IMPRISONMENT OF ETHIOPIAN JOURNALIST ESKINDER NEGA ARBITRARY UNDER INTERNATIONAL LAW AND CALLS FOR IMMEDIATE RELEASE

April 1, 2013 -

For Immediate Release - Also read the UN General Assembly Report – WGAD opinion

Washington, D.C.: In an opinion released today by Freedom Now, the UN Working Group on Arbitrary Detention found the Government of Ethiopia’s continued detention of independent Ethiopian journalist and blogger Eskinder Nega a violation of international law. The panel of five independent experts from four continents held that the government violated Mr. Nega’s rights to free expression and due process. The UN Working Group called for his immediate release.

Mr. Nega is serving an 18-year prison sentence on terror and treason charges in response to his online articles and public speeches about the Arab Spring and the possible impact of such movements on the political situation in Ethiopia. Arrested in September 2011, Mr. Nega was held without charge or access to an attorney for nearly two months before authorities charged him under Ethiopia’s widely criticized anti-terror laws. This is the eighth time during his 20-year career as an independent journalist and publisher that the Ethiopian government has detained Mr. Nega. His appeal has been repeatedly postponed, most recently on March 27, 2013.

In the attached opinion, released in conjunction with an op-ed by the renowned Ethiopian opposition leader and former prisoner of conscience Birtukan Mideksa, the UN Working Group found that the application of overly broad anti-terror laws against Mr. Nega constituted an “unjustified restriction” on his right to freedom of expression. The UN Working Group’s opinion also recognized “several breaches of Mr. Nega’s fair trial rights,” further rendering his continued detention arbitrary under international law.

“The Ethiopian government cannot continue to use anti-terrorism legislation to muzzle the work of independent journalists, even when it does not like what is being reported,” said Freedom Now Executive Director Maran Turner. “The targeting of journalists by resorting to overly broad anti-terror laws, just like the use of anti-state charges in the pre-9/11 era, is a violation of the internationally protected right to free expression and undermines international efforts to address real security threats.”

Freedom Now represents Mr. Nega as his international pro bono counsel.

Monday, April 1, 2013

በአማራ ህዝብ ላይ እየተፈጸመ ያለው ግፍ በኢትዮጵያ ህዝብ ላይ እየተፈጸመ ያለው ግፍ አካል ነዉ! (ግንቦት 7)

መግለጫ
ግንቦት 7 የፍትህ የነጻነትና የዲሞክራሲ ንቅናቄ
Click here for PDF
የወያኔ መሪዎች እነ መለስ ዜናዊና ስብሐት ነጋ በ1967 ዓም ለትግል ደደቢት በረሀ እንዲገቡ ያነሳሳቸዉና ያሰባሰባቸዉ በአማራዉ ህዝብ ላይ ያላቸው ጥላቻና የበቀል ስሜት እንጂGinbot 7 press release in Amharic የኢትዮጵያ ህዝብ በደልና እሮሮ አንገፍግፏቸዉ እንዳልሆነ በተለያዩ ግዜዎች ለህዝብ ይፋ የሆኑት የወያኔ መግለጫዎችና ለረጂም ግዜ ወያኔን የመሩት መለስ ዜናዊና ስብሐት ነጋ በየአደባባዩ ላይ ያደረጓቸዉ ንግግሮች በግልጽ ያሳያሉ። እነዚህ ከወጣትነት ግዜያቸዉ ጀምሮ በአማራ ህዝብ ላይ ጥርሳቸዉን የነከሱ የወያኔ መስራቾች በለስ ቀንቷቸዉ አዲስ አበባን ከተቆጣጠሩ በኋላም ቢሆን ለአማራ ህዝብ፤ ባህልና ታሪክ ያለቻዉ ጥላቻ ከተራ ጥላቻ አልፎ በተግባር አማራዉን ወደ ማጥቃት ዘመቻ አደገ እንጂ ለአንድም ቀን ቀንሶ አያውቅም።
የወያኔ አገዛዝ ኢትዮጵያ ውስጥ ያከበረዉ ወይም የኤኮኖሚና የፖለቲካ ጥቅሙን ያስጠበቀለት ብሔረሰብ ባይኖርም በግለሰብ ደረጃም ሆነ በቡድን የወያኔ ዘረኞች የአማራን ህዝብ ከተቀሩት ኢትዮጵያዉያን ወንድሞቹና እህቶቹ ነጥለዉ ለማጥቃትና የስነ ልቦና ዘይቤውን ለመስበር ከፍተኛ ጥረት አድርገዋል። በአጠቃላይ የወያኔ ዘረኛ ባለስልጣኖች አማራውን በተከታታይ ሲዘልፉ ቆይተዋል፤አዋርደው አስረዋል፤ ከአገር እንዲሰደድ አድረገዋል፤ አፈናቅለዋል ገድለዋል። ለምሳሌ ወያኔ ስልጣን በያዘባቸዉ በመጀመሪያዎቹ አምስት አመታት ዉስጥ ብቻ አሶሳ፤ በደኖና አርባጉጉ ውስጥ አማራ በመሆናቸዉ ብቻ ህጻናት፤ሴቶችና አረጋዉያን በግፍ ተገድለዋል።
ባለፈዉ አመት በደቡብ ክልል ጉራ ፈርዳ እየተባለ በሚጠራዉ አካባቢ ለረጂም አመታት ከአካባቢዉ ኢትዮጵያዊ ወገናቸው ጋር ተግባብተዉ ይኖሩ የነበሩ የአማራ ተወላጆች አማራ በመሆናቸዉ ብቻ ለአመታት ያፈሩትን ንብረት ይዞ የመሄጃ ግዜ እንኳን ሳይሰጣቸዉ አከባቢዉን ያለ ምንም ቅድመ ሁኔታ ለቅቀዉ እንዲወጡና እንዲፈናቀሉ ተደርጓል። የወያኔ ባለስልጣኖችና በየአካባቢዉ የኮለኮሏቸዉ ምስለኔዎች አካባቢዉን በግድ እንዲለቅ የተደረገ ህግ አክባሪ ዜጋ የለም፤ የተባረሩት ህግ የጣሱ ግለሰቦች ብቻ ናቸው፣ በማለት አሳፋሪ ድርጊታቸዉን ለመደበቅ ሲሞክሩ ታይተዋል። ሆኖም ከጉራ ፈርዳና ከአካባቢዉ ተፈናቅለዉ ወደ መጣችሁበት አካባቢ ተመለሱ ተብለው በየሜዳው ያለምግብ፣ ውኃና፤መጠለያ የተበተኑ በብዙ ሺዎች የሚቆጠሩ የአማራ ተወላጆች ለወገኖቻቸውና ለአለም አቀፉ ህብረተሰብ የድረሱልን ጩኸት ሲያሰሙ መሰንበታቸዉ የቅርብ ግዜ ትዝታ ነዉ።
ወያኔ በዚህ በያዝነዉ አመት ከመጋቢት ወር መጀመሪያ ጀምሮ በአማራዉ ህዝብ ላይ አዲስና ሰፋ ያለ የጥቃት ዘመቻ ጀምሯል። በደቡቡ የአገራችን ክልል በጉራፈርዳ የጀመረዉን አማራውን ነጥሎ የማጥቃትና የማንገላታት ዘመቻ አሁን ደግሞ በሰሜን ምስራቅ የአገራችን ክፍል በቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል ቀጥሏል። ሰሞኑን በቤንሻንጉል ጉሙዝ ለረጂም አመታት ከአካባቢዉ ህብረተሰብ ጋር ተቀላቅለው ይኖሩ የነበሩ አያሌ የአማራ ተወላጆች ያፈሩትን ንብረት ለመሰብሰብ እንኳን ግዜ ሳይሰጣቸዉ የኔ ብለው ከሚጠሩት የመኖሪያ ቦታቸዉ እንደባዳ እየተገፉ እንዲወጡ ተደርገዋል። እዚህ ላይ አንድ እጅግ የሚያሳዝን ነገር ቢኖር በገዢዉ ፓርቲ ኢህአዴግ ዉስጥ አማራን እወክላለሁ ባዩ ብአዴን ወያኔ በአማራዉ ህዝብ ላይ የሚያደርሰውን በደል ዝም ብሎ መመልከቱ ብቻ ሳይሆን ባለፈው አመት ከጉራ ፈርዳ ዘንድሮ ደግሞ ከቤንሻንጉል ጉሙዝ እየተባረሩ እየወጡ ባሉ አማራዎች ላይ እየተፈጸመ ባለው ወንጀል ላይ ተባባሪ መሆኑን አሳይቷል።
ግንቦት ሰባት የፍትህ የነጻነትና የዲሞክራሲ ንቅናቄ ወያኔ በአማራዉ ህዝብ ላይ ያደረሰውንና በማድረስ ላይ ያለውን ይህ ነዉ የማይባል ግፍና መከራ ከዚህ ቀደም እንዳደረገዉ ሁሉ አሁንም አጥብቆ ያወግዛል። ከዚህ በተጨማሪ ወያኔ በዚህ በኢትዮጵያ አንድነትና ነጻነት የትግል ምእራፍ ውስጥ በደም የተቀባ፣ የቀለመ አኩሪ ታሪክ ያለውን የአማራውን ህዝብ መልሶ መላልሶ የሚያጠቃውና ይህንን ታላቅ ህዝብ ከየቦታዉ የሚያፈናቅለው ኢትዮጵያና ኢትዮጵያዊነትን ከአማራዉ ህዝብ ጋር ብቻ በማያያዝ አገራችንን ለማዳከምና አንዱ ኢትዮጵያዊ በሌላዉ ኢትዮጵያዊ ላይ የሚደርሰዉን ግፍና መከራ “ምን አገባኝ” ብሎ እንዲመለከት ለማድረግ ባለው እጅግ አደገኛ ዕቅድ መሠረት መሆኑን የኢትዮጵያ ህዝብ እንዲገነዘብ በጥብቅ ያሳስባል።
ከዚህም በተጨማሪ በአማራው ህዝብ ላይ እየተፈጸመ ባለው እጅግ አስከፊ ወንጀል በግልም ሆነ በቡድን፣ የንጹሀንን ደም እያፈሰሳችሁ ያላችሁ ወንጀለኞችና ተባባሪዎች፣ ከያላችሁበት ታድናችሁ ለፍርድ እንድትቀርቡ ንቅናቂያችን የሚቻለውን ሁሉ ለማድረግ ያለውን ቁርጠኝነት በግልጽ እንድታውቁት ይገባል።
በአማራው የደረሰው ጥቃት የሁሉም ኢትዮጵያውያን ዜጎች ጥቃት ነው እንላለን። ግንቦት ሰባት ይህንን አጋጣሚ በመጠቀም በግለሰብ ደረጃ የምንደሰትበትን ነጻነት የምናስጠብቀው በህብረት ነውና ወያኔ በአሁኑ ግዜ በአማራው ወገናችን ላይ የሚያደርሰውን ግፍ፤ መከራና መፈናቀል በእያንዳንዳችን ላይ እንደደረሰ በመቁጠር ይህንን ግፍ በመፈጸም የማይሰለቸውን ዘረኛ አገዛዝ በተባበረ ህዝባዊ ትግል ከአገራችን ለማስወገድ ለሁሉም ኢትዮጵያዊ የጋራ ትግል ጥሪ ያስተላልፋል።
ግንቦት 7 የፍትህ የነጻነትና የዲሞክራሲ ንቅናቄ
መጋቢት 2005 ዓ. ም