Monday, June 9, 2014

የሕዳሴ አብዮት አተገባበር!

June 9/2014
(ተመስገን ደሳለኝ)

  ባለፉት ሁለት ሳምንታት በተከታታይ ባቀረብኳቸው ጽሑፎች ገዥው-ግንባር የመረጠው ስሁት መንገድ፣ ኢትዮጵያችንን ለሳልሳዊው አብዮት እያዘጋጃት መሆኑን ማውሳቴ ይታወሳል፡፡ ይህ የለወጥ መስመርም “የሕዳሴ አብዮት” የሚል ስያሜ ኖሮት፣ ሁሉን አሳታፊ ፖለቲካዊና ማሕበራዊ ንቅናቄ በመፍጠር አገሪቱን በዳግም ውልደት ለማንፃት ብቸኛ አመራጭ የመሆኑ ጉዳይ በስነ-አመክንዮ ተሰናስሎ ቀርቦበት ነበር፡፡ በዚህ ተጠየቅ ደግሞ አብዮቱን ከዳር ለማድረስ ሊተገበሩ የሚችሉ (በሰላማዊ ትግል ማዕቀፍ ውስጥ ያሉ) ስልቶች እና በመጀመሪያው የንቅናቄው ምዕራፍ ሥርዓቱ ለመመለስ ሊገደድባቸው የሚገቡ ጥያቄዎችን እንዳስሳለን፡፡

 ለምን እንሞታለን? 
 የዓለም ታሪክ አምባ-ገነኖች እብደታቸውን እንዲተገብሩ የሚያስችላቸው የታጠቀው ኃይል (ጦር ሠራዊት፣ ደህንነት እና ፖሊስ) ስለመሆኑ አያሌ ማሳያዎችን ዘርዝሮ ያስረግጣል፡፡ የኢትዮጵያችን የቅርብ ጊዜ ታሪክንም ብንመለከት፣ የአፄ ኃይለስላሴ ጨቋኝ አስተዳደርን ግማሽ ክፍለ ዘመን አፋፍ ድረስ ተሸክመው የተጓዙት እነዚህ ኃይሎች መሆናቸው ጉዳዩን አምነን እንድንቀበል ያስገድደናል፡፡ የኮሎኔል መንግስቱ ኃይለማርያም በላኤ-ሰብ ዘመን በታሪክነት ተመዝግቦ ለመታወስ የቻለውም ይህንኑ ክፍል አጥብቆ በመያዙ መሆኑ የትላንት ክስተት ነው፡፡ ባለፉት ሁለት አስርታት ያስተናገድነው የኢህአዴግ ብልጣ ብልጥ አምባ-ገነን አስተዳደርም ከከፋፍለህ-ግዛ ስልቱ በተጨማሪ ዋና መሰረቱ ጠብ-መንጃ አንጋቹ አካል ለመሆኑ ይህ ትውልድ የአይን እማኝ ነው፡፡ አዲሱ የሕዳሴ አብዮታችንም በዚህ ኃይል ላይ ትኩረት ያደርግ ዘንድ የተገደደበት መግፍኤ ይኸው ነው፡፡

 ከግፉአኑ (ከጭቁኖቹ) አብራክ የወጣው ጦር ሠራዊት ‹‹ተኩስ!?›› ተብሎ በታዘዘ ቁጥር ስለምን አምሳያው የመከራ ተቸንካሪ ላይ ሁሌ ጥይት እንደሚያዘንብ እጅግ ግራ አጋቢ ነው፡፡ እውን የህፃናትን ግንባር የሚበረቅሰው፣ እህት-ወንድሙን አነጣጥሮ የሚጥለው ሥርዓቱን ተቀብሎት፣ ትዕዛዙንም አምኖበት ነው ወይ? በጉልበትም ሆነ በሥነ-ምግባር ከሚልቃቸው ግለሰቦች የሚተላለፍለትን መመሪያ እየተገበረ ሰጥ-ለጥ ብሎ የሚገዛው የግል ጥቅም አመዝኖበት? ወይስ ለአለቆቹ የዘፈቀደ ተግባር ሎሌ ሆኖ? …የደህንነት መ/ቤቱ አባላትስ እንዲህ ታች ወርደውና አጎንብሰው የፓርቲ አገልጋይ የመሆናቸው ምስጢር ምን ይሆን? ከገዥው-ግንባር የተለየ የፖለቲካ አመለካከት ያላቸውን ድርጅቶች ቢሮ፣ አመራሩን እና ጋዜጠኞችን በመሰለል መጠመዳቸው የ‹‹እንጀራ›› ጉዳይ ብቻ ሆኖባቸው ነውን? ንፁሀንን በጠራራ ፀሀይ ሳይቀር አፍነው ለስቅየት አሳልፈው እንዲሰጡ የተገደዱበት መነሾስ ምንድር ነው? …የፖሊስ ሠራዊትስ የሥርዓቱ የማጥቂያ መሳሪያ በመሆን እንዲህ ማዕረጉን አቅልሎ ለሀፍረት የተዳረገበት ጉዳይ በማን እርግማን ይሆን? …እኮ ለምንድር ነው የእነርሱንም ጭምር ነፃነትና ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት የሚያውጅ ጥያቄ ባነሳን ቁጥር ደማችንን ደመ-ከልብ የሚያደርጉት?

እነዚህን ጥያቄዎች ለመመለስ ሰፊ ጥናት የሚጠይቅ መሆኑ ሳይዘነጋ፣ የንቃተ ህሊና ማነስ እና ነፍሰ-ገዳይን አወዳሹ ነባር ባሕላችን ከገፊ-ምክንያቶቹ መካከል ስለመጠቀሳቸው ለመናገር ግን የምሁራን ትንተና የሚያስፈልገው አይመስለኝም፡፡ ከዚህ አኳያም ሕዳሴን መሰረት የሚያደርገው አብዮታችን ከትኩረት ማዕከሉ ቀዳሚ አድርጎ መጠነ ሰፊ ቅስቀሳና የንቃት ሥራ በመስራት፣ ባለፉት ዘመናት የጭቆናው አስፈፃሚ ሆኖ በታሪክ ጥቁር መዝገብ የሰፈረውን ታጣቂ ኃይል፣ ወደ ተባባሪነት (ሕዝባዊነት) መለወጥ እንደሚኖርበት ተረድቶ መፍትሔ ካላበጀለት በታሪክ ፊት ከሥሉስ ውድቀቱ የሚታደገው አይኖርም፡፡ በአናቱም አብዮቱ ክብሩን ሊመልስለት እንጂ፣ ነቅንቆ ሊበትነው የተነሳሳ እንዳልሆነ ታጣቂ ኃይሉን ማሳመን የእኛ ዓብይ ተግባር ነው፡፡ እነርሱ አንድም በኑሮ ውድነት፣ ሁለትም ነገን በመስጋት ስር እንዲያድሩ ተቀይደው ነጻነታቸውና መብታቸው የተገፈፈ የመሆኑን እውነታ አስረግጦ ነግሮ ከሕዝብ ጎን በመቆም ሚናቸውን ይወጡ ዘንድ ማግባባት አብዮታዊ ግዴታ ለመሆኑ ነጋሪ አያሻም፡፡ ከለውጡ በኋላም ሠራዊቱ ከአገር አለኝታነቱ በዘለለ፣ ከአድሎአዊነትና ከእርስ በርስ (ከዘውጋዊ) ጥላቻ በፀዳ ፍትሓዊ አስተዳደር ተጠቃሚ የመሆኑን ጉዳይ ማሳመኑ በቀውጢው ሰዓት ወሳኝ ድጋፍ ለማግኘት ጠቃሚ ነው፡፡ የጥቂት ጀነራሎች የሙስና ወንጀልም፣ አቻ ባልደረቦቻቸውንም ሆነ መላ ሠራዊቱን የሚወክል አለመሆኑን ከዘለፋ በራቁ ጨዋ ቃላት መወትወት ጉልህ አስተዋፅኦ አለው፡፡ ይህን ታላቅ ተልዕኮ ለማሳካት በተለይም የአዛዦቹም ሆነ የተራው ወታደር ቤተሰብ፣ ጎረቤት፣ ጓደኞች፣ ዘመድ-ወዳጅ ወገኖች ቀዳሚውን ኃላፊነት መሸከም ይጠበቅባቸዋል ብዬ አስባለሁ፡፡

 የትግሉ ስልቶች… 
 ‹‹የከፋ ጭቆና ቢኖርም ሥርዓቱን የተሸከሙት ብዙ ሰዎች ለረጅም ጊዜ ትብብር ከነፈጉት ጨቋኙ አገዛዝ ተዳክሞ በመጨረሻ መውደቁ አይቀርም›› የሚለው ጄን ሻርፕ፤ የትብብር መንፈግ ፅንሰ-ሀሳብን የሰላማዊ ተቃውሞው ዋነኛው የትግል ማዕከል አድርጎ ያቀርበዋል፡፡ ለዚህ ስልት መተግበር ሀሳብን የማሰራጫ መንገዶች ያስፈልጋሉ፡፡ በይፋ የማይታወቁ የትግሉ መሪዎች/ቡድኖች፣ ሐሳቡ ጨቋኞቹን ለመጣል በሚካሄደው መሬት አንቀጥቅ አብዮት ላይ እንዴት ከፍተኛ ሚና ሊኖረው እንደሚችል፣ ለማሕበረሰቡ ማስገንዘብ ይገባቸዋል፡፡ ይህን ማሕበረሰባዊ ጠንካራ መረዳት ለመፍጠርም፣ በራሪ ጽሑፎችን፣ ማሕበራዊ ድረ-ገፆችን፣ ሕብረ-ዜማዎችን፣ አጫጭር አነቃቂ  ፊልሞችንና የሞባይል ስልክ መልዕክት መለዋወጫ ዘዴዎችን ጨምሮ የተለያዩ የምስልና የድምፅ ሚዲያዎችን ማመቻቸት (መዘርጋት) ይጠበቅባቸዋል፡፡ እነዚህ ከግብፅ እስከ ዩክሬን ተሞክረው የተሳኩ አማራጮችን በኢትዮጵያችንም ለመተግበር፣ በሚገባ መደራጀትና በኃላፊነት መስራት በእጅጉ አስፈላጊና ግዴታ የመሆኑ ጉዳይ አያከራክርም፡፡ እንዲሁም ከሕዝበ-ሙስሊሙ የ‹‹ድምፃችን ይሰማ›› የተፈተነ እንቅስቃሴ ስኬታማ ተሞክሮዎችን ማጎልበትና ወደ ፖለቲካዊው ተቃውሞ መቀላቀል እንደሚቻል መዘንጋት የለበትም፡፡ የአደባባይ ተቃውሞ የሚፈቅደውን ሕገ-መንግስታዊ መብት በምልአት አንጠፍጥፎ መጠቀም ለሰላማዊ ትግሉ ዋነኛ መሰረት እንደሆነ አምኖ መቀበልም ሌላው መረሳት የሌለበት ጭብጥ ነው፡፡ እነዚህን ኩነቶች ለመተግበር የማይነጣጠሉትን እንቅስቃሴዎችም በሶስት በመክፈል በደምሳሳው እንመለከታቸዋለን፡፡

 የአደባባይ እምቢተኛነት… 
 ዛሬ ላይ ስለመታገያ መንገዶቹ ብዙ ነጥቦችን ዘርዝሮ ማቅረቡ ላያስፈልግ እንደሚችል ይሰማኛል፡፡ ምክንያቱም በአገዛዝ ውስጥ የሚመረጡ የትግል ስልቶች በይፋ ከመቅረብ ይልቅ፣ በተቃውሞው አደረጃጀት ጥልቅ ዝግጅት እንደየአውዱ እየተመረጡ ቢተገበሩ የተሻለ ውጤታማ እንደሚሆኑ አምናለሁና፡፡ ሆኖም በዚህ መነሻነት ጥቂት ነጥቦችን ብቻ አንስቼ አልፋለሁ፡፡ በእነ ጄን ሻርፕ እና መሰል የትግሉ መምህራን ተደጋግሞ የሚጠቀሰው ‹‹የአደባባይ መቀመጥ›› የሚባለው ለሰላማዊው አመፅ ግንባር ቀደም ተደርጎ ይጠቀሳል፡፡ ለረዘሙ ቀናት/ሳምንታት አደባባዮችን ሞልቶ፣ ተጨባጭ ፖለቲካዊ ማሻሻያም ሆነ መሰረታዊ የሥልጣን ሽግግር እስኪደረግ ድረስ የመተካካት ስልት በተከተለ እና ግላዊ የዕለት ተዕለት የኑሮ መመሰቃቀሎችን ባገናዘበ (በእጅጉ ጉዳቶቹን በሚቀንስ) መልኩ በፈረቃ ፕሮግራም የሚደረግ እንደሆነ ይታመናል፡፡ በትእምርትነትም የእስልምናን፣ የክርስትናን እና የአይሁድ እምነት ምልክቶችን ለመሰባሰቢነት በመጠቀም፣ በዋና ዋና ግልፅ ሕዝባዊ የመሰባሰቢያ ስፍራዎች ላይ የሰላም ድንኳኖችን መዘርጋት፣ የመማፀኛ ፊርማ ማሰባሰብ፣ በሕንፃዎች አናትና በግድግዳዎች ላይ ለውጥ የሚጠይቁ መፈክሮችንና ምስሎችን መለጠፍ፣ የመኪና ጥሩንባንና ሌሎች ከፍተኛ ድምፅ ሰጪ መሳሪያዎችን ያለማቋረጥ ማስጮኽ፣ የቤት ውስጥ መቀመጥ፣ የሥራ፣ የትምህርትና የረሃብ አድማዎችን መምታት፣ በማሕበራዊ ጉዳዮች ላይ ማደም፣ በየእምነት ተቋማቱ በጋራ ፀሎት ማድረግ… በዚሁ ስር የሚካተቱ ተግባራት ናቸው፡፡

 በርግጥ ይህ ሁሉ ሲሆን የአገዛዙ መሪዎች ሕዝባዊ አብዮቱን በታጠቀው ኃይል ለመቀልበስ ሙከራ ማድረጋቸው የሚጠበቅ ነው፡፡ ይሁንና በዚህን ጊዜ ከፀጥታ አስከባሪዎች ጋር እሰጥ-ገባ ውስጥ ባለመግባት፣ ምንም አይነት አፀፌታዊ ግብረ-መልስ ባለመስጠት፣ በተንኳሽ የቁጣ ቃላት በመጎነታተል ለማበሳጨት ባለመሞከር፣ ተቀጣጣይና ስለት ነገሮችን ከአካባቢው በማራቅ ወይም በፍፁም ባለመያዝ… የተቀኙ ስልቶችን መከተል የሕዳሴ አብዮታችን መገለጫ ነውና፤ በዚሁ መንገድ መፅናት ግዴታ ይሆናል፡፡ በተጨማሪም ይህ አካሄድ በአንዳንድ አገራት እንደተስተዋለው አጋጣሚውን በመጠቀም አብዮቱን ለመጥለፍም ሆነ ሰርገው በመግባት ወደ ደም-አፋሳሽ ነውጥ ለመግፋት የሚሞክሩትን ለመከላከል ያስችላል፡፡

 ሌላኛው ጭብጥ፣ የትግሉን ግብ በግልፅ ቋንቋ ካስቀመጡ በኋላ፣ የተለያዩ ሀገራትና ተቋማት ለሥርዓቱ የሚሰጡትን ድጋፍ እንዲያቋርጡ መወትወት ነው፡፡ ቀጥታዊዎቹን ሰብአዊ ዕርዳታዎች ሳይጨምር ኢህአዴግ በቀዳሚነት የባጀት ድጋፎቹን ከነዚህ ሀገራትና ተቋማት እንዳያገኝ ጠንካራ ዲፕሎማሲያዊ ጫና የሚካሄድበትን ስልት መቅረፅ በእጅጉ አስፈላጊ ነው፡፡ ከዚሁ ጋር ተያይዞ፣ አፈናውን ለማራዘም በርትተው በሚሰሩት የሥርዓቱ ፊት-አውራሪዎች ላይ፤ የጉዞ ማዕቀቦችን ጨምሮ ሌሎች ወደ ድርድሩ ማዕቀፍ እንዲመጡ የሚያስገድዱ ግላዊ ጫናዎች እንዲጠናከሩባቸው መጣር፣ ተጨማሪ የትግሉ መንገድ መሆን ይኖርበታል፡፡

 አብዛኛዎቹ የአለማችን ጨካኝ አገዛዞችን ለታሪካዊ ሽንፈት የዳረገው ሌላው የመታገያ ስልት፣ አፋኝ ሕጎቻቸውን በግልጭ መጣስ መሆኑ በቀዳሚነት የሚወሳ ነው፡፡ በእርግጥ ይህን መሰል የአደባባይ የኢ-ፍትሓዊ ሕጎች ጥሰት ብዙ ዜጐችን ለእስር ይዳርጋል፡፡ ሆኖም የሰላማዊ አብዮት ውጤት መገለጫ፣ የዜጐች እስርን የመዳፈር ብርታት እንደሆነ ከመታወቁ አኳያ፣ ይህኛው አካሄድ ከፍተኛ ሚና አለው፡፡ በእኛም ምድር እስርን የሚዳፈሩ ብርቱና ቆራጥ ጎበዛዝት በተበራከቱ ቁጥር፣ የተቃውሞ አድራጊዎች መጠን በሂደት እየጨመረ እንደሚመጣና ግንባሩም ስጋት አድሮበት ከአፈና እርምጃዎቹ መቆጠቡ ስለማይቀር፣ ለምንፈልገው ሥርዓታዊ ሽግግር አስገዳጅ ፈቃደኝነት ውስጥ ልንከተው እንደሚቻለን ማመን ተገቢ ይመስለኛል፡፡ ይሁንና ውጥረቱ እየበረታ በሄደ ቁጥር ሥርዓቱ ተቃውሞውን ለማክሸፍ በብዛት ወደ እስር መላኩ አይቀሬ ቢሆንም ‹ስለኔ አታልቅሱ› እንዲል መጽሐፉ፣ በእርምጃው ሳይደናገጡ በአቋም በመፅናት ከአደባባዩ ሳያፈገፍጉ፣ ታሳሪዎቹን በጀግንነት እያወደሱ፣ ለእስር የሚዳርጉ ሕጎችን በመጣስ ጀግኖቹን መቀላቀልና ማጎሪያዎቹን አለቅጥ ማጨናነቅ አገዛዙን ለማሽመድመድ ጠቃሚነቱ በተግባር የተሞከረ ስልት መሆኑን ማስታወስ ያሻል፡፡ ነፃነቱን በነፃ ያገኘ ከቶም ቢሆን የለምና! በሰላም ጊዜ እንጂ በእንዲህ አይነቱ የንቅናቄ ወቅት እስር ቤት ቅንጣት ታህል የሚያስፍራ አለመሆኑን በልበ-ሕሊና ማሳደሩ ጠቃሚ ነው ብዬ አስባለሁ፡፡

 ኢኮኖሚያዊ ትብብር መንፈግ
 ስለትብብር መንፈስ መንፈግ ጉዳይ አስቀድመን ልናነሳው የሚገባን ኢኮኖሚ ተኮር የሆነውን የትግል ስልት ነው፡፡ ይህ ሥርዓት ለጭቆናው መሰረት ካደረጋቸው መካከል፣ በዝባዥ የምጣኔ-ሀብት ተቋማትን ማቋቋሙ አንዱ እንደሆነ ይታወቃል፡፡ እናም የኢኮኖሚ ትብብር መንፈግን ቀዳሚው የትግል አማራጫችን ብናደርገው የሕዳሴውን አብዮት ግቦች በአጭር ጊዜ ለማሳካት የማስቻሉ ዕድል የሰፋ ይሆናል፡፡ ለዚህም በዋናነት ልናተኩርባቸው የሚገቡ ሁለት ጉዳዮች አሉ፡፡ አንደኛው በማዕከላዊ መንግስቱ በቀጥታ እንደሚመሩና እንደሚደገፉ ከሚነገርላቸው ድርጅቶች፣ ምርቶችን ባለመግዛትና የምርት ሂደቱንም ከውስጥ በማጨናገፍ፣ እንዲዳከሙ ማድረግን የሚመለከት ነው፡፡ ረዥሙ ትግል ከባድ ዋጋ እንደሚጠይቀን ከተማመንን፣ ለህልውናችን የቀን ተቀን ኑሮ እጅግ ወሳኝ የሆኑትን የምርት 3 ውጤቶች ከመንግስታዊ ተቋማቱ አለመግዛት፣ ሥርዓቱን ለማሽመድመድ ውጤታማ መሆኑ አይቀርም፡፡ ከዚህ ጋር ተያይዞ፣ በእነዚህ ተቋማት ውስጥ የሚሰሩ ሠራተኞችንና መሀከለኛ የአመራሩን አባላት፣ የምርት ሂደቱን እንዲያስተጓጉሉ በማግባባት፣ ተቋማቱን በዝግመታዊ ሂደት አቅማቸውን ማድቀቅ አንዱ የትብብር መንፈግ አማራጭ ነው፡፡ ይህ መንገድ ከዛሬው ነባራዊ ሁኔታችን አንፃር የማይቻል ቢመስልም፤ ፕሬዚዳንት ባራክ ኦባማ ‹‹በርግጥ! እንችላለን!!›› እንዲል፤ እኛም የነቃንለትን ሃሳብ ለመፈፀም የማንፈነቅለው ድንጋይ እንደማይኖር በተግባር ማሳየት ይጠበቅብናል፡፡ ደግሞም በቀላሉ በማይደበዝዝ መነቃቃት ካልታደስን መጪው ጊዜ አደገኛ ይሆን ዘንድ እንደመፍቀድ ይቆጥራልና፤ በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች በሚገኙ መንግስታዊ የንግድ ተቋማት ውስጥ ያሉትን ሠራተኞች በአንድ የግንኙነት መስመር በማስተሳሰር ሁኔታዎች ግድ ባሉ ቀን በተመሳሳይ ጊዜ በማንቀሳቀስ፣ ሥርዓቱን ክፉኛ ማዳካሙ ተግዳሮት የበዛ አለመሆኑ አከራካሪ አይመስለኝም፡፡ የኢኮኖሚ ትብብር መንፈግን የግድ የሚያደርገው ሌላው ጉዳይ፣ ግብር (ታክስ) ያለመክፈል ሕዝባዊ እምቢተኝነትንም ስለሚያጠቃልል ነው፡፡ የጭቆናው አገዛዝ ተጠናክሮ የቆመው በታክስ ሥርዓቱ ላይ መሆኑንም ሆነ ለሥልጣን ዕድሜ ማራዘሚያው መጥቀሙን በቅጡ መገንዘብ ከቻልን ታክስ ባለመክፈል፣ የቆመበትን መሰረት መቦርቦር የሚቻልበት ዕድል መኖሩን ማስታወስ አስፈላጊ ነው ብዬ አስባለሁ፡፡

 ሁለተኛው ደግሞ የኢትዮጵያችን ነባራዊ ሀቅ፣ አብዮቶቹ ከተተገበረባቸው ሀገራት አንድ ለየት የሚል ገፅ ያለው ከመሆኑ ጋር የሚነሳ ነው፡፡ ይኸውም የገዢው ግንባር አባላት ተከፋፍለው በሀገሪቷ ኢኮኖሚ የአንበሳውን ድርሻ መያዛቸው ነው፡፡ ከማዕድን ቁፋሮ እስከ ጨርቃጨርቅ ኢንዱስትሪ፤ ከፋይናንሺያል ተቋማት እስከ አልኮል ምርቶች ድረስ የተቆጣጠሩበትን መንገድ ማዳከም፤ ሕዝባዊ ጉዳት ሳይከተል ቀጥታ የሥርዓቱን የመጨቆኛ ምንጭ ማድረቁን ቀላል ያደርገዋል፡፡ በርግጥ አገዛዙ ከእነዚህ የፓርቲዎቹ ተቋማት ምንም አይነት አገልግሎት ላለመጠቀም የሚደረገውን አድማ በመመዝመዝ፣ ሂደቱን በአንድ ቋንቋ ተናጋሪ ላይ ያነጣጠረና ብሔሩን ሆን ተብሎ ለመጉዳት ታስቦ እንደተደረገ አስመስሎ የሚነዛውን መርዛም ፕሮፓጋንዳ ከወዲሁ ለማጨናገፍ፣ ከድርጅቶቹ ምርቶቹን ያለመግዛት ውሳኔ፣ ከማንኛውም ብሔር ጋር እንደማይገናኝ ማመን እና መተማመንን መፍጠር ቀዳሚው ተግባር መሆኑ ይኖርበታል፡፡ በ‹‹ኤፈርት›› የበለፀገች ትግራይ፣ በ‹‹ዲንሾ›› ያደገች ኦሮሚያ፣ አልያም በ‹‹ጥረት›› የተጠቀመ የአማራ ክልል አለመኖሩን፣ መጀመሪያውኑ ከልብ ተገንዝበን ከተንቀሳቀስን፣ ፓርቲ ተኮር ድርጅቶቹን ማግለል አስቸጋሪ አይሆንብንም፡፡ የተቃውሞ እንቅስቃሴው ቀጣይ ቅቡል መሪዎችም ይህን ጭብጥ ሕዝቡ ዘንድ በሚገባ ማስረፅ አንዱ ኃላፊነታቸው መሆኑን ሊዘነጉት አይገባም፡፡

 የገዥው ፓርቲ አባላት… 
 ሶስተኛው ልንዘጋጅበት የሚገባው ጉዳይ፣ በመጀመሪያው የአብዮቱ እርከን ለዘብተኞቹን የግንባሩ አባላት በእንቅስቃሴው እንዲሳተፉ ማመቻቸት ነው፡፡ በተለይም ከድህረ-97ቱ የምርጫ ፖለቲካ ድቀት እና ይህን ተከትሎ በመጣው የተቃውሞ ስብስብ መዳከም የተነሳ፣ ‹ፓርቲውን በአዝጋሚው መንገድም ቢሆን እየገሩ መሄድ ይቻላል› በሚል የተቀላቀሉ እንዳሉ ይታወቃልና፤ እነዚህን ወንድሞችና እህቶች በሂደቱ ውስጥ ለማሳተፍ፣ የአብዮቱን መሪ ህልም እንዲያምኑበት ማድረጉ የግድ ነው፡፡ እነርሱን እያካተትን በተጓዝን መጠን፣ ሌሎቹም የፓርቲው አባላት ትግሉን በመቀላቀል፣ የራሳቸውን ጥያቄዎች አንግበው ሥርዓቱ ወደመነጋገር እንዲመጣ ያስችሉታል ብዬ አምናለሁ፡፡ የታቀደ አብዮት ስኬቶችን ስንመረምር እነዚህን መሰል ክስተቶችንም የለውጡ አካል ማድረጉን መረዳታችን አይቀርም፡፡ በነገራችን ላይ በመታደሳችን ዘመን ለቀደሙ ወንጀሎችም ሆነ ሀገራዊ ውድመቶች ሂሳብ ማወራረድን ታሳቢ ማድረግ ፍፁም አብዮቱን መጎተት ከመሆኑም በላይ፣ የታሪካችንን አስቀያሚ ገፅ በመድገም ቁልቁል መዝቀጥ እንደሆነ መተማመን ይኖርብናል፡፡ ግባችን ኢትዮጵያን እያደሱ ወደፊት ማራመድ እስከሆነ ዘንዳ፣ የተሻለ ዴሞክራሲያዊ ሥርዓትን የመፍጠሪያው መንገድ ላይ ብቻ ማተኮር ብቸኛው መፍትሄ ነው፡፡ ያለፈው ዘመን ሰማዕታትን እየዘከርን፣ ለአጥፊዎቹ ምህረት እያደረግን በይቅርባይነትና በመቻቻል ላይ የምታብበውን ኢትዮጵያን መመስረት የሕዳሴው አብዮት ግብ ሊሆን ይገባል፡፡

 የንቅናቄው ፊት መሪዎች 
 ይህን የለውጥ መንፈስ በፊት መሪነት ማስተባበር የሚችሉ ጠንካራ የሲቪክ ተቋማት በሀገሪቱ ያለመኖራቸው ጉዳይ፣ ለሂደቱ መፍጠን የግድ ሌላ አማራጭ እንድንፈልግ ያስገድደናል፡፡ በርግጥ አንዳንድ ወገኖች ለእንዲህ አይነቱ ጊዜ በሰላማዊ መንገድ የሚንቀሳቀሱ የፖለቲካ ፓርቲዎችን መጠቀምን ይመክራሉ፡፡ ይህ ግን አደገኛና ያልተጠበቀ ክስረት ሊያስከትል የሚችል ይመስለኛል፡፡ ምክንያቱም ድርጅቶቹ የየራሳቸው የተለያየ ዓላማ አንግበው የሚታገሉ በመሆኑ ከተሳታፊነት አልፈው በመሪነት መምጣታቸው፣ ሁነቱን ከሁሉን አሳታፊነት ወደ ቡድንነት፤ ከዲሞክራሲያዊ ሽግግር ወደ ሥልጣን ነጠቃነት (መፈንቅለ መንግስት) የመቀየር አደገኛ ክስተት ውስጥ ሊያስገባው ይችላል፡፡ ይህ አካሄድ በሌሎች ሀገራት ለከሸፉ አብዮቶች በማሳያነት መጠቀሱንም ታሳቢ በማድረግ፣ ለእኛ ችግር መፍትሔውን አዲስ (ከዚህ ቀደም ያልተሞከረ) አማራጭን ከራሳችን ወቅታዊ ሁኔታ አንፃር መፈለግ ላይ ማተኮሩ ይበጃል፡፡ በግሌም ይህንን ታላቅ ሀገራዊ ግዴታ ለመሸከም የተሻሉ ናቸው ብዬ የማስበው ዩንቨርስቲዎቻችንን ነው፡፡ በመላ ሀገሪቱ በተመሳሳይ ወቅት መጀመር የሚኖርበትን የሕዳሴ አብዮት፣ ሁሉም መንግስታዊ ዩኒቨርስቲዎች የሚገኙበትን ከተሞች ጨምሮ አጎራባች አካባቢዎችን ለማስተባበር ኃላፊነት የሚወስዱበት መንገድን ማማቻቸቱ የሚሳካበትን ስልት ከወዲሁ መቀየስ የሚቻል ይመስለኛል፡፡ ርግጥ ነው በዛሬው እውነታ ላይ ሆነን በተለይም የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የገዢው ፓርቲ የፖለቲካ መናኸሪያ የመሆናቸውን ነገር ግምት ውስጥ አስገብተን ስናምሰለስለው፣ ሁነቶቹ አልጋ በአልጋ ሊሆኑ እንደማይችሉ ከማንም የተሰወረ አይሆንም፡፡ ግና፣ በየተቋማቱ የየትኛውም ፓርቲ አባል ያልሆኑ ለውጥ አራማጅ መምህራንና ተማሪዎች በራስ ተነሳሽነት በመሰባሰብ የማስተባበሩን ኃላፊነት ተረክበው ከፊት መስመር እንዲሰለፉ የማንቃትና ማብቃት ሥራ ቢሰራ፣ አንድም እዚህ ግባ የሚባል ተግዳሮት ባለመኖሩ ሂደቱን ለማፋጠን ይጠቅማል፤ ሁለትም ከንቅናቄው ስፋት አኳያ ለከበደ መስዋዕትነት የመዳረጉ አጋጣሚ እጅግ የጠበበ በመሆኑ ግንባር ቀደም ተሰላፊ ደፋሮችን ማግኘት አዳጋች አያደርገውም፡፡ ይህ ዕቅድ የሚሳካ ከሆነ ደግሞ ዩኒቨርስቲዎቹ በዕኩል ውክልና የጋራ ማዕከል (አዲስ አበባ ለዚህ አመቺ ሊሆን ይችላል) አቋቁመው አብዮቱን በሀገርና ሕዝብ ጥቅም አስተሳስረው መምራት እንደሚኖርባቸው እንደማይዘነጉት ተስፋ አደርጋለሁ፡፡

 የአብዮቱ የመጀመሪያ ጥያቄዎች
 ሕዝባዊ ንቅናቄው በሚገባ ተጠናክሮ ከቀጠለ በኋላ መንግስት እጁን ተጠምዝዞ እንዲተገብራቸው መነሳት ያለባቸው ቀዳሚ ጥያቄዎች (ለለውጡ መደላድል የሚሆኑት) የሚከተሉት ቢሆኑ መልካም ነው፡- በመላ ሀገሪቱ ባሉ ማረሚያ ቤቶች የሚገኙ የፖለቲካ፣ የሕሊና እና የሀይማኖት እስረኞችን ያለምንም ቅድመ ሁኔታ መፍታት፤ በውጪ ሀገር ያሉ ተቃዋሚ ድርጅቶች፣ ምሁራን፣ ጋዜጠኞች እና የመብት ተሟጋቾች ያለልዩነት ወደ ሀገር ቤት ገብተው በነፃ እንዲንቀሳቀሱ መፍቀድ፤ ባለፉት ጥቂት ዓመታት የወጡ አፋኝ ሕጎችን መሰረዝ፤ በሀገሪቱ የመንግስት ምሥረታ ላይ የአፈና መዋቅር ሆኖ የሚያገለግለውን ምርጫ ቦርድ አፍርሶ አብዛሃ ኢትዮጵያዊን ሊያሳምን በሚችል ገፅ እንደገና ማዋቀር፤ ለዴሞክራሲ ጠቃሚ የሆኑ የተለያዩ ተቋማትን ነፃ ማድረግ፤ የብዙሃን (የመንግስት) ሚዲያን እውነተኛ የሕዝብ ልሳን የሚሆኑበትን አሰራር መዘርጋት፤ መከላከያ ሰራዊቱ፣ የደህንነት ሰራተኛው እና የፖሊስ አባላት በነቢብ ሳይሆን በገቢር ተጠሪነታቸውን ለሕገ-መንግስቱ ማድረግ… ሲሆን፤ እነዚህ ሁኔታዎች ከተሟሉ በኋላ በ2007 ዓ.ም. የሚካሄደውን ምርጫ ለተጨማሪ አንድ አመት በማራዘም፤ ለሁሉም ተወዳዳሪዎች (ለነባሮቹም ሆነ አዲስ ለሚደራጁት) መድረኩን ክፍት አድርጐ የሕዳሴውን አብዮት ለውጥ መተግበር ይቻላል ብዬ አምናለሁ፡፡ እዚህ ጋ መዘንጋት የሌለበት ዋነኛው ጉዳይ አብዮቱ በራሱ በገዥው-ፓርቲ ውስጥ ያሉ በፖለቲካ ቀኖናዊነት ያልተጠለፉና ሀገራዊ ለውጥ ፈላጊ የአመራር አባላት ‹የኢህአዴግ መንግስት ወይም ሞት!› የሚሉ ግትር ጓዶቻቸውን አግልለው፣ ይህንን ኃላፊነት እንዲወስዱ ጫና ማድረግ ላይ የሚያተኩር እንጂ፤ በደፈናው ግንባሩን በጠላትነት ፈርጆ የሚያሳድድ አለመሆኑን ግንዛቤ መውስድ ያስፈልጋል፡፡ የሕዳሴው አብዮታችን የ‹ጊሎትን› ማሽን የማይታጠቅና ልጆቹንም የማይበላ፤ በአጥፍቶ መጥፋት ጨዋታ ሕግ የማይመራ መሆኑን ማስረገጥ ቀዳሚው ተግባር ይሆናል፡፡ ጎን ለጎንም የለውጡን (የጥያቄዎቹን) መፈፀም የሚከታተል ከንቅናቄው አስተባባሪዎች፣ ከንግዱ ማሕበረሰብ፣ ከኃይማኖት ተቋማት፣ ከሲቪክ ማሕበራት፣ ከልሂቃኑ እና ከሀገር ሽማግሌዎች መካከል በተወጣጡ ግለሰቦች የጋራ ምክር ቤት አዋቅሮ ቁጥጥር ማድረግ የሚቻልበትን አሰራር መቀየሱ ሌላኛው ጠቃሚ ክዋኔ ነው፡፡ ይህ መንገድ በድህረ-ኢህአዴጓ ኢትዮጵያችን ፖለቲካዊና ማሕበራዊ ምስቅልቅሎሽ ቦታ እንዳይኖራቸው የመታደግ አቅምንም ለመገንባት ማስቻሉ መዘንጋት የለበትም፡፡

 የተባረከችዋ ቀን መቼ ትሆን? 
 ይህን መሰል የለውጥ ጥያቄ ማቅረቡ ሥርዓቱ ከሃያ ሶስት ዓመት በላይ ከመቆየቱ አኳያ የተቻኮለ እንደማይሆን አምናለሁና፤ ከላይ ከተጠቀሱት ዋና ዋና አብዮታዊ ጉዳዮች አንፃር፤ እንዲሁም በአንድ ወቅት አቶ መለስ ዜናዊ ‹‹ልጄ ፋኖ ተሰማራ እንድትል አልፈልግም›› እንዳለው ሁሉ፤ ህወሓት የታሪካችን የመጨረሻው ‹‹ነፃ አውጪ›› ድርጅት ይሆን ዘንድ የሚታወጅበት ዕለትን ከወዲሁ መወሰኑ ላይ ከተስማማን፣ የ2007ቱ ወርሃ መስከረም በሁለት ጉዳዮች ቢመረጥ የተሻለ ይመስለኛል፡፡ የመጀመሪያው በቀጣዩ ዓመት የሚደረገውን አምስተኛ ዙር ሀገር አቀፍ ምርጫን የማራዘሙ አስፈላጊነት ከሕዝባዊ ጥያቄው መካከል ግንባር-ቀደም በመሆኑ ለአገዛዙ በቂ የጥሞና ጊዜ መስጠት የማስቻሉ ጠቀሜታ ሲሆን፤ ሁለተኛው ደግሞ የአዲስ ዓመት ጅማሮ ከመሆኑ አኳያ ባሕላዊም ሆነ ስነ-ልቦናዊ መነቃቃት የመፍጠር አቅሙ የራሱ በጎ አበርክቶ ይኖረዋል ተብሎ ስለሚታሰብ ነው፡፡

 ከሞላ ጎደል ለሶስት ሳምንታት ያህል የተነጋገርንባቸው እነዚህ ታላላቅ አጀንዳዎች እውን ይሆኑ ዘንድ ቀጠሮውን በልቦናችን ይዘን፣ ራስን በውስጥ ዝግጅት ማሰናዳቱ ለነገ የማይተው የቤት ስራችን መሆኑንም ጨምሮ መረዳት ያሻል፤ በዚህም የሕዳሴያችን ንቅናቄ እንደ ቀዳሚዎቹ ሁለት አብዮቶች አዲስ መዘዝ፣ ሳይሆን አዲስ ተስፋ እንዲያመጣ እናስችላለን ብዬ አስባለሁ፡፡ በመጨረሻም ያቺ ትንሳኤ አብሳሪ ዕለት በኢትዮጵያችን ምድር ከቶም ቢሆን አቻ የላትምና፣ በአያሌ ናፍቆት ስለመጠበቋ ዛሬ ላይ እንዲህ መመስከሩ ከምኞት የተሻገረ መሆኑን አስረግጬ ብናገር ማጋነን አይሆንም፡፡

 ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር!


Who is afraid of the Ethiopian bloggers?

June 9, 2014
Who is afraid of  Eskinder Nega, Reeyout Alemu, Woubshet Taye, Zone Nine bloggers…?Who is afraid of  Eskinder Nega, Reeyout Alemu, Woubshet Taye, Zone Nine bloggers…?
The “dean” of independent Ethiopian journalists and blogger extraordinaire, Eskinder Nega, is serving an 18 year sentence for blogging. The late Meles Zenawi personally ordered Eskinder’s arrest and even determined his sentence. Meles Zenawi feared and hated Eskinder Nega more than any other journalist in Ethiopia. Meles feared Eskinder for the same illogical reason elephants “fear” mice.
In a recent “open letter” from prison to his eight year-old son Nafkot, Eskinder wrote, “ I have reluctantly become an absent father because I ache for what the French in the late 18th Century expressed in three simple words: liberté, egalité, fraternité.” Eskinder is a blogger for liberty, equality and brotherhood. That is why he is my personal hero!
Reeyot Alemu, the 34 year-old undisputed Ethiopian heroine of press freedom, was also jailed by Meles Zenawi for 14 years. She has been internationally recognized as  “Ethiopia’s Jailed Truth Teller.”  Reeyot was jailed for writing a  “scathing critique of the ruling political party’s fundraising methods for a national dam project, and drew “parallels between the late Libyan despot Muammar Gaddafi and Meles Zenawi.” Reeyot refused to be gagged and muzzled even in prison and courageously kept on speaking truth to the abusers of  power. “I believe that I must contribute something to bring a better future [in Ethiopia]. Since there are a lot of injustices and oppressions in Ethiopia, I must reveal and oppose them in my articles… I knew that I would pay the price for my courage and I was ready to accept that price,” said Reeyot in her moving handwritten letter smuggled out of prison.  The regime has denied Reeyot basic medical care to punish her for unyielding defiance.  According to the London-based Media Legal Defence Initiative reported in Al Jazeera, Reeyot “has received severely inadequate treatment for the fibroadenoma she was diagnosed with. She has had surgery without anaesthesia, has been left with surgical stitches in her breast for over a year and never received proper aftercare.” She is my personal heroine!
The indomitable journalist and editor Woubshet Taye has also been silenced and languishes in a hell-hole called Zwai (“Zenawi”) prison. He is sentenced to 14 years. Woubshet would not back down from using his newspaper as a watchdog on the regime’s corruption and abuses of power. Woubshet has also been denied medical care for a severe kidney condition. Denial of medical care (a crime against humanity) is a routine punishment imposed on prisoners of conscience in Ethiopia. Woubshet’s five year-old son Fiteh (meaning “justice”) keeps asking, “When I grow up will I go to jail like my dad?”  Fiteh is too young to realize that he is already in an open air prison now.
A few weeks ago, Ethiopia’s “Zone Nine Bloggers” (named after a prison block  holding political prisoners at  the infamous “Meles Zenawi Kality Prison” a few kilometers outside of the capital) and other journalists including Atnaf Berahane, Zelalem Kibret, Befeqadu Hailu, Abel Wabela, Mahlet Fantahun, Natnael Feleke, Asmamaw Hailegeorgis, Tesfalem Waldyes and Edom Kassaye were arrested and detained on unknown charges. The “police” are trying to figure out what charges to bring against them(Ethiopia is the ONLY country in the world where the police arrest and detain a suspect and then go out looking for evidence of wrongdoing!!! The “courts” deny bail to detainees and grant endless continuances and delays to “prosecutors” to enable them to fabricate evidence. That’s one of the reasons I call them “kangaroo courts”.) The real crime of the “Zone 9ers” is  “advocating freedom of expression and what they call Dreaming of a Better Ethiopia.” A recent scheduled “court” hearing for the “Zone 9ers” was closed to the public and diplomatic observers.
Why they are afraid of  Eskinder Nega, Reeyout Alemu, Woubshet Taye, Zone Nine bloggers… ?
“Four hostile newspapers are more to be feared than a thousand bayonets,” fretted Napoleon Bonaparte, dictator of France, as he declared war on that country’s independent press. For the regime in Ethiopia, the pens and computer keyboards of a handful of independent journalists and bloggers are more to be feared than ten thousand bayonets mounted on AK-47s.  All dictators and tyrants in history have feared the enlightening powers of the independent press. The benighted dictators in Ethiopia fear the enlightening powers of an independent press more than the firepower of several fully equipped infantry divisions.
Total control of the media and suppression of independent journalists remains the wicked obsession of the regime. They believe that by controlling the flow of information, they can control the hearts and minds of the people. They believe they can fabricate truth out of falsehood by controlling the media. By crushing the independent press, they believe they can fool all of the people all of the time. But they know deep down in their stone cold hearts that “truth will not forever remain on the scaffold, nor wrong remain forever on the throne.” They live each day in the land of living lies fearful of losing their throne.
The benighted dictators in Ethiopia today confront a reality Napoleon confronted long ago. “A journalist is a grumbler, a censurer, a giver of advice, a regent of sovereigns and a tutor of nations.” It was the fact of “tutoring nations” — teaching, informing, enlightening and empowering the people with knowledge– that was Napoleon’s greatest fear of a free press. He understood the power of the independent press to effectively countercheck his tyrannical rule and hold him accountable before the people. He spared no effort to harass, jail, censor and muzzle journalists for criticizing his use of a vast network of spies to terrorize French society. The press exposed his military failures, condemned his indiscriminate massacres of unarmed protesters in the streets and  for jailing, persecuting and killing his political opponents. Ethiopia’s dictators now face Napoleon’s nightmare and are jailing and persecuting young bloggers and independent journalists. They spend sleepless nights in cold sweat afraid of the truth!
The E bloggers and journalists are special Ethiopian heroes and heroines. They are truth-tellers and -warriors. They fight tyranny with their pens and computer keyboards. Their ammunition are truth, words, ideas, facts and opinions. They slay falsehoods with the sword of truth. They chase bad ideas with good ones and advocate replacing old ideas with new ones. They fight the people’s despair with words of hope. They teach the people that fear is overcome with acts of courage. They fight ignorance and powerful ignoramuses with knowledge and reason. They stand up to arrogance and hubris with defiant humility. They seek to transform intolerance with forbearance; resist oppression with perseverance and defeat doubt with faith. They fight with their pens and keyboards on the battleground that is the hearts and minds of the Ethiopian people.
Living on Planet denial-istan, lies and fear
The regime in Ethiopia lives on a planet of its own where lies are truth, the truth is mangled daily and the con artists live in fear. The regime has upended the Cartesian principle. “We think, therefore things exist or do not exist.” The demigod of the regime, the late Meles Zenawi, was a master of denial. He always denied the existence of political prisoners in his prisons: “There are no political prisoners in Ethiopia at the moment. Those in prison are insurgents. So it is difficult to explain a situation of political prisoners, because there are none.” He denied the occurence of famine and starvation during his overlordship; he said there were only  pockets of severe malnutrition in some districts in the south and an emergency situation in the Somali region.” He denied any violations of human rights. “We are supposed to have burned villages [in the Ogaden]. I can tell you, not a single village, and as far as I know not a single hut has been burned. We have been accused of dislocating thousands of people from their villages and keeping them in camps. Nobody has come up with a shred of evidence.” The fact that the American Association for the Advancement of Science confirmed the burning of Ogadeni villages with satellite images meant nothing on Planet Zenawi. Meles declared with a straight face that his press law which has resulted in the imprisonment and exile of dozens of  Ethiopia’s topindependent journalists and bloggersa  is “on par with the best [press laws] in the world.” Following the 2010 “election”, Meles said his party won the 2010 “election” by 99.6 percent because the people love his party. Meles was an Orwellian archetype. He used “political language to make lies sound truthful and murder respectable, and give an appearance of solidity to pure wind.”
There are certain undeniable truths about those running the regime in Ethiopia today. They all live in FEAR. They live in FEAR of the TRUTH.  They fear the power of the free press as the exposer of the truth. They fear the press as much as their one-time ideological master V.I. Lenin: “Why should freedom of speech and freedom of the press be allowed? Why should a government which is doing what it believes to be right allow itself to be criticized? It would not allow opposition by lethal weapons. Ideas are much more fatal things than guns. Why should any man be allowed to buy a printing press and disseminate pernicious opinion calculated to embarrass the government?”
They fear the TRUTH because they know the TRUTH makes the people free. They fear FREEDOM because they fear new IDEAS. They fear new ideas because they fear CHANGE. A free people armed with the truth, animated with ideas of freedom is free to change its form of government at will.
What is the truth about the regime in Ethiopia? The truth is that they are  criminals against humanity; they have no legitimacy; they cling to power by force of arms; they steal elections; they are corrupt to the core; they abuse and misuse their power;  they flout the rule of law and they are outlaws who rule by the law of the jungle.  The truth is they are total frauds practicing bushcraft as statecraft. The truth is that they are thugtators who operate Africa’s most ruthless thugtatorship.
They fear independent journalists and bloggers because these journalists and bloggers expose the truth about their crimes and corruption, failed policies, incompetence and ignorance. They fear the independent journalists and bloggers as much as the demons who possess their victims fear exorcists and holy water. They have done everything in their power to keep the truth from the people for whom the truth is manifest. They have jammed satellite transmissions, clamped down on internet access, shuttered newspapers and jailed journalists. Just last week, Arabsat informed the International Communication Union and the Arab League that Ethiopia is jamming its transmissions and vowed to take “all appropriate actions to prosecute the culprit” and recover compensation for “any damage already incurred or to be incurred as a result of the jamming.”  The regime is today harassing, threatening and arresting newspaper peddlers on the streets who sell copies of the few newspapers mildly critical of the regime.
The truth is that the Chinese are the invisible hands behind the suppression of free expression in Ethiopia. They provide not only the electronic jamming technology to the regime but also the telecommunication  infrastructure used for mobile and internet services. They are the one stop shop for the whole kit and caboodle used to suppress and constrict the free flow of information into and out of Ethiopia. Two years ago almost to the day, former U.S. Secretary of State Hilary Clinton visiting Zambia said of China in Africa, “We saw that during colonial times, it is easy to come in, take out natural resources, pay off leaders and leave. And when you leave, you don’t leave much behind for the people who are there. We don’t want to see a new colonialism in Africa.” The truth is that the Chinese are not only staying and expanding their neocolonial hegemony in Ethiopia, they are principally responsible for the suppression of free expression by providing the regime technical support and equipment used in audio and video surveillance and electronic jamming.
They fear FREEDOM. What is freedom? The essence of all human freedom is the freedom from FEAR. In practical terms, freedom is not fearing to speak one’s mind; not fearing to write what one pleases; not fearing to believe or not believe in any idea, religion or philosophy; not fearing to come together with anyone one chooses. The ultimate freedom any human being can experience is to live in a society where those in power fear and respect the people who have given them power.
They fear IDEAS. “Ideas are much more fatal things than guns,” warned Lenin. Ideas power change in science, politics and all other areas of human endeavors. The world is not flat after all. But the dictators in Ethiopia are the new flat-earthers. They think they can rule like kings, czars and maharajahs without the consent (or stolen consent) of the people. They have few wholesome ideas and do not have the intellectual capacity to understand and appreciate new ones. But their minds are supreme diabolical workshops for destructive ideas that create ethnic division, perpetuate bigotry and hatred, incite strife, provoke conflict, spread and proliferate corruption, instigate disunity and animosity and arouse suspicion and distrust among the people. They are incapable of generating ideas that unite people, create ethnic harmony, forge national unity, build consensus, establish solidarity and inspire faith.
The centophobic (those who fear new ideas) dictators in Ethiopia pretend to be visionaries, men of new and grand ideas. They want the people and the world to believe they are forward looking, imaginative and creative dreamers and innovators; but one cannot dream living a nightmare of fear. They are clueless about what it takes to be visionary leaders: integrity, acceptance of personal responsibility, ability to inspire others, learning from mistakes and failures instead of repeating them mindlessly, saying “I am sorry” when they make mistakes, open mindedness, fairness and passion about doing the right thing. They are myopic “leaders” who are passionate about doing the wrong thing. They can clearly see the wads of stolen loot bulging their pockets but they are completely blind to the dire consequences of what they are doing now in the foreseeable future. A powerful idea — an idea whose time has come — is unstoppable. The yearning for freedom by the people of Ethiopia is unstoppable and once unleashed, it will sweep away everything in its path with tornadic force.
They fear CHANGE. What is change? Change is that eternal universal law which governs the processes of growth and decay in all things. The regime in Ethiopia fears change because they fear they will lose their dominant economic and political position in society. They will crush any attempt, including peaceful ones, to bring about change. They fail to understand that “Those who make peaceful revolution impossible will make violent revolution inevitable.”
Because of lack of political legitimacy and lack of state capacity, Ethiopia today is in a state of terminal political decay; it has become a failed state. For the past quarter century, the policy of ethnic division (“ethnic federalism”) has left Ethiopia with two options, despite the silly propaganda about the “developmental state” surging forward with  “double-digit growth.” Only their lies are growing with double and triple digits.
Ethiopia stands at the crossroads today. It may go forward as a nation united, or splinter into mini-“thugistans” carved out of the so-called “kilils” (Ethiopia’s version of apartheid-style bantustans). If Ethiopia becomes a collection of mini-thugistans, the biggest losers will be the regime in power, their cronies and supporters. Not only will they lose political power, they will lose all of the loot they have stolen and accumulated, at least inside the country. It is in the rational self-interest of those in power to work for peaceful change and for political regeneration and bring the people together as one nation. It is in their self-interest to harmonize relations with opposition groups and leaders and provide for political space. Change in Ethiopia may be like a train that arrives late. The winds of change that blew over Eastern Europe and the Middle East will certainly blow over Ethiopia too. The only question is whether those winds will be breezy or hurricane-force.
The TRUTH shall make you free if you are free but torments those who are not
It is written that the “truth shall make you free.” Free and fear are mutually exclusive. The sole purpose of the independent press and bloggers is to tell the truth as they see it. They are free to give their opinions of the truth without fear. But the people already know the truth. Despite the bold-faced lies that “Ethiopia is growing by double digits”, the people know the truth. They know they do not have enough to eat and millions starve every day; they do not have adequate water supply or electrical power; they receive little medical care; the young people are under-educated and unemployed;  the regime is corrupt and routinely commits crimes against humanity. The people know they live in an open-air prison.
The crime of the independent journalists and bloggers is disclosing to the people what they already know. Their crime is digging 24/7 at the mine of corruption and abuse, unearthing new evidence of crimes against humanity.  That is why the regime is are afraid of them. The regime wants the truth to remain buried and forgotten. The regime believes  that by suppressing the truth and jailing and silencing the truth-tellers, they could permanently silence and kill the truth. As George Orwell observed, “In a time of deceit telling the truth is a revolutionary act.” The E-bloggers are Ethiopia’s revolutionary vanguards today.
Weaponization of fear in the media
The regime has long decided to use its quintessential weakness into its forte. It has used fear as its preferred weapon of mass confusion, division, deception, demonization and distraction.  The regime has used the public media to conduct a relentless campaign of fear, smear and demonization. They have broadcast much-ballyhooed “documentaries” (“docutrash”) to paint all who oppose the regime as “terrorists”. In a revolting and scandalous docutrash entitled “Akeldama”, they depicted  Ethiopia as a country under withering terrorist attack by Ethiopian Diaspora opposition elements and their co-conspirators inside the country and other “terrorist” groups. “Akeldama” stitched revolting and gruesome video clips and photomontage of terrorist carnage and destruction throughout the world to tar and feather all opponents of the late Meles Zenawi as stooges of Al-Qaeda and Al-Shabaab in Somalia.
In another docutrash entitled  “Jihadawi Harakat”, they tried to stoke the fires of Islamophobia by spreading fear and loathing between Christians and Muslims. They thought they could scare Ethiopian Christians into believing that the same Muslims with whom they have coexisted peacefully for a millennia have been suddenly transformed into bloodthirsty “Islamic terrorists” secretly planning to wage a jihadist war to establish an Islamic government.
They have used Ethiophobia and ethnophobia  to spread fear and loathing among the people, and place themselves as the only salvation to an imaginary ethnic and sectarian strife and carnage. They have played one ethnic group against another. They have used ethnic cleansing in the name of “ethnic federalism”. They have resurrected historical grievances to stoke the fires of ethnic hatred. They have used their own fears as a weapon against the people.
The war on Ethiopian journalists and bloggers is a war on truth itself
The regime’s war on Ethiopia’s independent journalists and bloggers is a war on truth itself. The regime has been the victor in all of the battles and skirmishes over the last quarter of a century. But there will be a final decisive war  between the dictators who swing swords and brandish AK47s and the journalists and bloggers who wield pens and computer keyboards. That war will be waged in the hearts and minds of the Ethiopian people. I have no doubts whatsoever that the outcome of that war is foreordained. In fact, I believe that war has already been won. For as Edward Bulwer-Lytton penned in his verse, in the war between sword holders and pen holders, final victory always goes to the pen holders:
‘True, This! –
Beneath the rule of men entirely great,
The pen is mightier than the sword. Behold
The arch-enchanters wand! – itself a nothing! –
But taking sorcery from the master-hand
To paralyze the Caesars, and to strike
The loud earth breathless! – Take away the sword –
States can be saved without it!’
But if the paramount question is to save the regime in Ethiopia or to save Ethiopia’s independent press and bloggers, I would, as Thomas Jefferson chose,  save the latter: “The basis of our government being the opinion of the people, the very first object should be to keep that right; and were it left to me to decide whether we should have a government without newspapers or newspapers without a government, I should not hesitate a moment to prefer the latter. But I should mean that every man should receive those papers & be capable of reading them.”
Were it left to me to decide whether we should have a regime without independent journalists and bloggers or independent journalists and bloggers without a regime, I should not hesitate a moment to prefer the latter. After all, I am a hard-core, proud-as-hell, dyed-in-the wool, rootin’-tootin’, foot stompin’, unapologetic, unabashed and unrelenting E-blogger!!!
Power to independent journalists and E-bloggers!
Professor Alemayehu G. Mariam teaches political science at California State University, San Bernardino and is a practicing defense lawyer.
Previous commentaries by the author are available at:
Amharic translations of recent commentaries by the author may be found at:

Sunday, June 8, 2014

ሱዳን በዓባይ ጉዳይ በግብፅ ላይ ፊቷን አዙራለች

June 8/2014

-ብፅ በቅድመ ሁኔታ የታጠረ የድርድር ጥያቄ አቀረበች
-ኢትዮጵያ ቅድመ ሁኔታውን አልተቀበለችም 
ኢትዮጵያ የታላቁ ህዳሴ ግድብ ግንባታን ለመጀመር የዓባይን ወንዝ የፍሰት አቅጣጫ በጊዜያዊነት ከቀየረች በኋላ፣ ግብፅ የፈጠረችው ፖለቲካዊ ውጥረት ባለፈው ሳምንት የተለየ መልክ ይዟል፡፡
ሱዳን በግድቡ ላይ ተቃውሞ እንደሌላት በመግለጽ ግብፅን ብቸኛዋ ተቃዋሚ አገር እንድትሆን አድርጋታለች፡፡ በሌላ በኩል ግብፅ በጉዳዩ ላይ የተለሳለሰ የሚመስል አቋም በማሳየት በቅድመ ሁኔታ የታጠረ የድርድር ጥያቄ ለኢትዮጵያ አቅርባለች፡፡ መንግሥት በበኩሉ የግብፅ ጥያቄ በሳይንስ ላይ ያልተመረኮዘና ግልጽነት የሚጎድለው ነው ብሏል፡፡ የግድቡ ግንባታ እንዲቋረጥ የቀረበው ሐሳብም ፈጽሞ ተቀባይነት የለውም ሲል ቁርጥ ያለ አቋሙን ገልጾ፣ በእንዲህ ዓይነቱ ሁኔታ ውስጥም ድርድር እንደማይኖር አስታውቋል፡፡

ኢትዮጵያ የዓባይን የፍሰት አቅጣጫ ከቀየረች በኋላ የግብፅ መንግሥት ከፍተኛ ተቃውሞውን እያሰማ ሰንብቷል፡፡ ኢትዮጵያ፣ ሱዳንና ግብፅ በጋራ ያቋቋሙት የባለሙያዎች ቡድን በግድቡ ተፅዕኖ ላይ ያቀረበውንም ሪፖርት እንደማትቀበል ግብፅ አሳውቃለች፡፡ ኢትዮጵያ በዓባይ ወንዝ ላይ የጀመረችው የኃይል ማመንጫ ግድብ ግብፅና ሱዳን በቅኝ ግዛት ዘመን ውል መሠረት የሚያገኙትን የውኃ ኮታ የሚቀንስ በመሆኑ፣ የግብፅን ህልውና አደጋ ላይ ይጥላል የሚለው የግብፅ ዋነኛ መከራከሪያ መሆኑ ይታወቃል፡፡

የግብፅ ፕሬዚዳንት መሐመድ ሙርሲ ከአገሪቱ ተቃዋሚ ፓርቲዎች ጋር በጉዳዩ ላይ ውይይት ማድረጋቸው የተዘገበ ሲሆን፣ ከተወያዮቹ ዕውቅና ውጭ በቀጥታ የቴሌቪዥን ሥርጭት በተላለፈው በዚህ ውይይት ላይ፣ አክራሪ የተቃዋሚ ፓርቲ አመራሮች በኢትዮጵያ ላይ ወታደራዊ ጥቃት መክፈት እንደሚገባ ፕሬዚዳንቱን ሲመክሩ ታይተዋል፡፡ በዚሁ ውይይት ላይ የተሳተፉትና የኢትዮጵያ ተቃዋሚ ኃይሎችን በመደገፍ አገሪቱን ማተራመስ ወይም በግብፅ የደኅንነት ኃይል ግድቡ እንዲወድም መደረግ አለበት የሚል ምክራቸውን ሲሰጡ የነበሩት አይማን ኑር የተባሉ የተቃዋሚ ፓርቲ አመራር፣ በሱዳን ላይም ትችታቸውን ሰንዝረው ነበር፡፡

በዓባይ ውኃ ፖለቲካ ዙሪያ ከግብፅ በተለየ ሁኔታ ዝምታን እየመረጠች ያለችው የሱዳን አቋም የሚያበሳጭ ነው ነበር ያሉት አይማን ኑር፡፡

የግለሰቡ ንግግር ያበሳጫት ሱዳን በውጭ ጉዳይ ሚኒስትርና የመንግሥት ቃል አቀባይ በሆኑት ሚስተር አህመድ ቢላል ኦስማን በኩል ምላሽ ሰጥታለች፡፡ በሱዳን ቴሌቪዥን ቃለ ምልልስ ያደረጉት ሚኒስትሩ የግብፅ ባለሥልጣናት ሱዳንን ከመዝለፍ እንዲቆጠቡ ጥሪ ያቀረቡ ሲሆን፣ ‹‹በዓባይ ወንዝ ጉዳይ ሱዳን የያዘችው አቋም ግብፅን የሚያስደስት አይደለም፤›› ብለዋል፡፡

የግብፅ ፖለቲከኞች በሱዳን ላይ የሰነዘሩት ዘለፋ ለግብፅ ፖለቲካዊ ፍላጐት ጥቅም የለውም ሲሉ አክለዋል፡፡

በዚሁ ቃለ ምልልሳቸው ወቅት ኢትዮጵያ እየገነባች ባለችው ግድብ ላይ የመንግሥታቸው አቋም ኢትዮጵያን የሚደግፍ መሆኑን፣ ምክንያቱ ደግሞ ሱዳንም በውጤቱ ተጠቃሚ ስለምትሆን ነው ብለዋል፡፡

‹‹የኢትዮጵያ ግድቡን መገንባት የዓባይን የውኃ ፍሰት የሚያሻሽል በመሆኑ ሱዳን በዝናብ ላይ ብቻ የነበራትን ጥገኝነት የሚቀንስ ነው፤›› ብለዋል፡፡

ካለፈው ሳምንት ጀምሮ በዓባይ ፖለቲካ ተወጥረው የሰነበቱት የግብፅ ባለሥልጣናት፣ በሳምንቱ መጨረሻ ላይም አለ የሚሉትን ችግር ከኢትዮጵያ ጋር ውይይት በማድረግ ለመፍታት የመምረጥ ፍላጐት አሳይተዋል፡፡

የግብፅን የውኃ ፍላጐት ለማስከበር የተሻለ ነው ባሉት ፖለቲካዊ ውይይት መሠረት ለኢትዮጵያ መንግሥት የውይይት ጥያቄ ያቀረቡ ቢሆንም፣ ኢትዮጵያ የግድቡን ግንባታ በማቆም ውይይቱ መጀመር እንዳለባት ጠይቀዋል፡፡

ኢትዮጵያ በዚህ የድርድር ጥያቄ ተስማምታ በጉዳዩ ላይ እልባት ካልተገኘ ግን፣ ግብፅ ማንኛውንም አማራጭ በመጠቀም ብሔራዊ ደኅንነቷን ለማስከበር እንደምትገደድ፣ የፕሬዚዳንት ሙርሲ የፖለቲካ አማካሪ የሆኑት አይማን አሊ መናገራቸውን የግብፅ መገናኛ ብዙኀን ዘግበዋል፡፡

‹‹ግብፅ የራሷን ፍላጐት የማስከበር ፍላጐት እንዳላት ሁሉ የሌላው አገር መንግሥትና ሕዝብ የራሳቸውን ፍላጐት መከተል ይችላሉ፡፡ ነገር ግን ኢትዮጵያ የምትገነባው ግድብ በግብፅ ላይ ምንም ዓይነት ጉዳት እንደማያስከትል ልታረጋግጥ ይገባል፡፡ በተጨባጭ ዋስትና መስጠት ይኖርባታል፡፡ ይህ ካልሆነ ግን ግብፅ ያሏትን አማራጮች በሙሉ ተጠቅማ ጥቅሟ እንዲከበር ታደርጋለች፤›› ሲሉ በማስጠንቀቂያ የታጀበ ዛቻ ሰንዝረዋል፡፡

ግብፅ በዓባይ ወንዝ ላይ የተፈጠረውን የፖለቲካ ውጥረት በማርገብ ረገድ እየሄደችበት ያለው መንገድ የተደበላለቀ የሚመስል ሲሆን፣ በውይይት ለመፍታት ያሳየችው ፍላጐት በቅድመ ሁኔታ ታጥሯል፡፡ በሌላ በኩል ወታደራዊ ጉልበት የመጠቀም ፍላጐት እንዳላትም ለማሳየት እየሞከረች ነው፡፡ ባለፈው ሳምንት መጀመርያ ላይ በቀጥታ ሥርጭት የተላለፈው የባለሥልጣናቱ ውይይት ሆን ተብሎ የተደረገ ሊሆን እንደሚችል እየተነገረ ነው፡፡

ባለፈው ሳምንት ረቡዕ ዕለት የግብፅ የደኅንነት ኃላፊ በሆኑት መሐመድ ራፋት ሸሃታ የተመራ ልዑካን ቡድን ሱዳንን መጐብኘቱን የግብፅ ሚዲያዎች ዘግበዋል፡፡ ነገር ግን የሱዳን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዘገባውን አስተባብለዋል፡፡

ግብፅ ወታደራዊ ጥቃት የመጠቀም አማራጭ እንዳላትና ልትጠቀም እንደምትችልም በተደጋጋሚ መዘገቡን አስመልክቶ ምላሽ እንዲሰጡ የተጠየቁት በሚኒስትር ዴኤታ ማዕረግ የጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለ ማርያም ደሳለኝ የሕዝብ ግንኙነት አማካሪ አቶ ጌታቸው ረዳ፣ የግብፅን ወታደራዊ አማራጭ ‹‹የቀን ቅዠት ነው›› ሲሉ ገልጸውታል፡፡ አቶ ጌታቸው ግድቡን ለማውደም ወይም ኢትዮጵያን ለማተራመስ በግብፅ ፖለቲከኞች ስለተሰነዘረው አስተያየት በሰጡት ምላሽ፣ ኢትዮጵያን ደካማ በነበረችበት ጊዜ እንኳ ለማተራመስ የተደረገው ሙከራ አለመሥራቱን፣ አሁን ደግሞ እጅግ በጣም በተሻለ ደረጃ ላይ ስለምትገኝ ከግብፅም ሆነ ከሌላ አገር የሚቃጣን ጥቃት ታከሽፋለች ብለዋል፡፡ የግብፅ ፕሬዚዳንት ምክንያታዊ ሆነው ወደ ግጭት የማይገባበት ሁኔታ ይፈጠራል ብለው እንደሚያምኑ ገልጸዋል፡፡ በሆስኒ ሙባረክ ዘመን ኢትዮጵያን በአማፂያን አማካይነት ለማተራመስ የተደረገው ሙከራ መክሸፉንም አስረድተዋል፡፡

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዶ/ር ቴድሮስ አድሃኖም በበኩላቸው፣ የግብፅ የውይይት ጥያቄ ተቀባይነት ያለው መሆኑን፣ ነገር ግን የግድቡ ግንባታ መቆም አለበት በማለት ግብፅ ያስቀመጠችውን ቅድመ ሁኔታ ‹‹የማይታሰብ›› ሲሉ በትዊተር ድረ ገጽ ገልጸዋል፡፡

መንግሥት ከግብፅ ጋር ያለው ግንኙነት ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት አስታውቆ፣ አንዳንድ የግብፅ ፖለቲከኞችና ባለሥልጣናት የሕዝብ ለሕዝብ ግንኙነትን የሚጎዳ ፕሮፓጋንዳ መንዛታቸው እንዳሳዘነው ገልጿል፡፡ በትዕግስት አንዳንድ ጉዳዮችን ለማለፍ ቢፈልግም ገንቢ ያልሆኑ የፕሮፓጋንዳ ዘመቻዎች በመነዛታቸው፣ በኢትዮጵያ የግብፅ አምባሳደርን በመጥራት የመንግሥታቸውን አቋም ጠይቀው ማብራሪያ እንዲሰጡ መጠየቁንና ምላሽ እየጠበቀ መሆኑን አስታውቋል፡፡ የግብፅ መንግሥት እስካሁን ለተጠየቀው ማብራሪያም ሆነ ማስተባበያ አልሰጠም፡፡ 

Saturday, June 7, 2014

የኢትዮ-ኤርትራ የድንበር ጉዳይ ለምን አይቋጭም?

June 7/2014
"የለዘብተኞችና የእስስት” ፖለቲካ ልዩነት እየፈጠረ ነው
ethio er


መለስ በሁለቱ አገሮች ድንበር ላይ “የጅራፍ ድምጽ እንኳን አይሰማም” በማለት ሲመጻደቁበት የነበረው የኢትዮ-ኤርትራ ጦርነት በ”ወረራ” እና “ወረራን መቀልበስ” በሚል ድራማ ተጀምሮ ከተቋጨ አስራ አምስት ዓመት አልፎታል። ኢህአዴግና ሻዕቢያ ጉዳያቸውን በጠረጴዛ ዙሪያ ወይም በጡንቻ መቋጨት ያልቻሉበት ምክንያት ለብዙዎች እንቆቅልሽ ሆኖ እስካሁን አለ። ሁለቱም ወገኖች ድንበር ላይ ወታደር አፍስሰው መቀመጣቸውን አስመልከቶ “አውቀው ነው” ከሚለው ውሃ የማይቋጥርአስተያየት ጀምሮ በርካታ ጉዳዮች በገሃድና በሹክሹክታ ሲሰማ ቆይቷል።
የጎልጉል የዜና ምንጮች ሰሞኑን ከአዲስ አበባ የላኩት መረጃ ግን በይዘቱ የተለየ ነው። ይህንኑ አዲስ ጉዳይ የሚመለከታቸው ክፍሎች አስተያት እንዲሰጡበት ያደረግነው ሙከራ ባይሳካም ዜናው ለውይይት የሚጋብዝ በመሆኑ አትመነዋል።
የድንበር ውዝግቡ አንዲቋጭ ይፈለጋል?
የኢትዮ-ኤርትራ የድንበር ውዝግብ ጦርነት ከኢትዮጵያ ወገን ብቻ ከ100 ሺህ በላይ ጉዳዩ በውል ያልገባቸው ወገኖች ህይወት የተገበረበት ነው። የአይደር ትምህርት ቤት ህጻናትን ጨምሮ የበርካታ ሰላማዊ ዜጎችንና ህጻናትን ህይወትም ቀጥፎ አልፏል። አቶ መለስ ለዚህ ሁሉ ቀውስ ተጠያቂ ቢሆኑም በድንገት ተስፈንጥረው ፍርድ ቤት ህግ ሳይጠቀስባቸው አልፈዋል። “ታላቁ መሪ” በህይወት እያሉ በኤርትራ ጉዳይ በተፈጠረ አለመግባባት ትግራይ ውስጥ እስከመታገት ቢደርሱም ከጥንቃቄ ጉድለት በአንጋቾቻቸው ፈጥኖ ደራሽነት ተርፈው ተቃዋሚዎቻቸውን “ውህዳን” በማለት በየተራ አራግፈው ብቻቸውን “ውርስና ቅርስ” ለመሆን በቅተዋል።
ayider
አይደር
ከህንፍሽፍሽ፣ የልዩነት ጊዜ ጀምሮ አደባባይ የወጣው የልዩነት መሰረት በወቅቱ ይፋ ሲደርግ ኢትዮጵያውያንን አሳዝኖና አስቆጥቶ እንደነበር በወቅቱ በስፋት የተዘገበበት ጉዳይ ነው። ዛሬም ይህ ወቅት ዳግም እየተመለሰ እንደሆነ እየተሰማ ነው። “የኤርትራን ጉዳይ እንቋጭ” የሚሉ የከረረ አቋም ያላቸው ተነስተዋል። እነዚህ ወገኖች ሁለት አማራጭ በማቅረብ ሃሳባቸው ተግባራዊ ሊሆን እንደሚችል እየወተወቱ ነው።
የመጀመሪያው አሁን ያለው የመከላከያ አቅም የድንበሩን ውዝግብ በሃይል ለመቋጨት አቅም እንዳለው እየታመነ ለምን “ቸልተኛነት ተመረጠ” በሚል በቂ ጡንቻ ስለመገንባቱ አበክረው የሚከራከሩበት አግባብ ነው። ሁለተኛው ደግሞ “የኤርትራን ተቃዋሚዎች አደራጅተናል፤ ለምን እነሱ ወደ ኦፕሬሽን አይገቡም” የሚል እንደሆነ መረጃዎቻችን ያስረዳሉ።
ቸልተኞቹ ምን ይላሉ?
በዚህ ጉዳይ ቸልተኛ የሚባሉት የተለየ ምክንያት ያላቸው፣ ነገር ግን “ጦርነት አያዋጣም” በሚል በገሃድ የሚከራከሩ ወገኖች ናቸው። እነዚህ ውስን የብአዴንና የህወሃት ቁልፍ ሰዎች በትግራይ ድንበር አካባቢ አስተዳደር የሚሰሩትን ጨምሮ የኤርትራ ደም አላቸው። በደህንነትና በጸጥታ ክፍሉ አጠቃላይ መዋቀር ላይ ቁልፍ ቦታ ተጎናጽፈዋል። የመረጃ ምንጮቹ ማብራሪያ እንደሚያመለክተው እነዚህ ወገኖች “ኢሳያስን የክፉ ቀን መጠባበቂያ” ነው የሚሏቸው። ሰዎቹ ኢህአዴግ ላይ አንዳችም አይነት ስጋት እንደማይሆኑ የሚታወቅ ሲሆን ዋና ዓላማቸው “ከመሃል አገር ወይም ከመካከል ለውጥ ካልተነሳ አርፈህ ተቀመጥ” የሚል ዓይነት መንገድ የሚከተሉ ናቸው።
ሃሳቡን ሲያብራሩ “ጉዳዩ ስትራቴጂክ ነው” በሚል ነው የሚጀምሩት። ኢትዮጵያዊነት ለሚያንገበግባቸው ህወሃቶች የማይገባቸው ይህ “ቁልፍ ስትራቴጂ” ለማመን የሚከብድ መረጃ ነው። እንደ መረጃው ምንጮች ከሆነ “የመሀሉ አገር ለለውጥ ከተነሳ የመጨረሻ መመሸጊያችን ኤርትራ ናት” የሚል ነው፡፡ እነዚህ የተቀላቀለ ደም ያላቸው ክፍሎች የሚያራምዱት “ቁልፍ” የተባለው ስትራቴጂ “የከፋ ቀን ከመጣ ወንድሞቻችን አይጥሉንም” የሚል ነው። ይህም ተግባራዊ የሚሆነው የቁርጥ ቀን ሲመጣ ለኢሳያስ የሚፈልጉትን በማድረግና በመስጠት ሰላም አውርዶ ህወሃት በገነባው ኢኮኖሚ አማካይነት የንግድ ትስስር መፍጠርና መኖር ነው። በኢትዮጵያ ውስጥ “በማንምና በምንም የማይገሰስ” የንግድ ኤምፓየር በመገንባት ኤርትራን በኢኮኖሚ ድቀት እንድትቀጥል የማድረጉ አካሄድ የ“ቁልፉ” ስትራቴጂ አንደኛው ግብዓት እንደሆነም ይነገራል፡፡
ኢሳያስን “አስልሎ መጣል” በሚለው መርህ ሻዕቢያን መጣል ከተቻለ ኢህአዴግ ያደራጃቸውን ተቃዋሚዎች በመያዝ የሚፈልገውን መንግስት ኤርትራ ላይ የመትከልና ከህወሃት ጋር ተዳቅለው የኖሩት የኤርትራ ደም ያላቸው የኤርትራ ተወላጆችን ወደ ግንባር ማምጣት ነው። በነዚህ ሁለት አማራጭ ሃሳቦች የተተከሉት ከላይ የተጠቀሱት ዓይነት “ለዘብተኞች” ይህንን ሃሳብ ይፋ አውጥተው መከራከርና ማሳመን ስለማይችሉ ጉዳዩ ውስጥ ውስጡን እየተብላላ ወደ ልዩነት እንዳያመራ ስጋት አለ። እነዚህ ስጋት የገባቸው ክፍሎች “ቁልፍ” የሚባለውን ስትራቴጂ “የህወሃት የለዘብተኞችና የእስስት ፖለቲካ” ሲሉ ይጠሩታል።
ከኤርትራና ከኢትዮጵያ የሚንደረደሩ ኃይሎች
ህወሃት/ኢህአዴግና ሻዕቢያ/ኤርትራ አንዱ የሌላውን ተቃዋሚ በይፋ በመደገፍ ሃይል ማደራጀት ከጀመሩ ቆይተዋል። ከሁለቱም ወገን ከፍተኛ የሚባል ሃይል ያላቸው የተቃዋሚ ክፍሎች፣ ድርጅቶች፣ ፓርቲዎች አሏቸው በሚባለው ሃይል ተጠቅመው አንዱ ሌላውን በማጥቃት ነጻ መሬት እስካሁን መያዝ አልቻሉም። ከዚህም ከዚያም ከሚሰሙት መጠነኛ የጦርነት ሪፖርቶች ውጪ ተለቅ ያለ ድል ስለመገኘቱ ከሁሉም ወገን አልተሰማም። ሰፊ ሃይል አለው የሚባለው ደሚትም ሆነ ኤርትራ ላይ መሳሪያ አነሳ የሚባለው የአፋር ቀይ ባህርና ኩናማ ንቅናቄ ስለ ሃይል ግንባታ ከመናገር ውጪ ይህ ነው የሚባል ድል እስካሁን አልጨበጡም።eritrea-opposition-conference
ምንም እንኳን ጥንቃቄና ማስተዋል የሚጠይቅ ቢሆንም ከኤርትራ የሚንደረደሩት የኢትዮጵያ ተቃዋሚ ሃይሎች፣ ከኢትዮጵያ ይወናጨፋሉ የተባሉት የኤርትራ ተቃዋሚዎች ወደ ተግባር ሳይገቡ ጊዜ መፍጀታቸው “ቁልፍ” የተባለው ስትራቴጂ ሊመረመር የሚገባው እንደሆነ አመላካች እንደሆነ የመረጃው ምንጮችይጠቁማሉ። የኤርትራ ተቃዋሚዎች አዲስ አበባ ላይ የሽግግር መንግስት አቋቁመው፣ መሪያቸውን ሰይመው፣ ህገ መንግሰት አዘጋጅተው፣ ሽግግር ወቅት መተዳደሪያ አርቅቀው፣ የሃይማኖትና የሲቪክ ተቋማትን አካትተው በዝግጅት ላይ እንዲቀመጡ መደረጉ፣ ምናልባትም በኢህአዴግ በኩል ያለው ዝግጅት “ቸልተኛ” በሚባሉት “እስስት ፖለቲከኞች” ታልሞና ታቅዶ የሚከናወን ስለመሆኑ አመላካች አይመስልም? በኢትዮጵያ ወገን ግን ተቃዋሚዎች “እኔ በጠራሁት ሰልፍ ላይ አትገኝም” እየተባባሉ እርስበርስ እየተቆራቆሱ፣ በገጽ ብዛት ብቻ የሚለያይ ተመሳሳይ ማኒፌስቶና ፕሮግራም ይዘው ትግሉን የርስ በርስ አድርገውታል። ከኢትዮጵያ ውጪ ያሉትም በመቀዳደምና በመጠላለፍ ፖለቲካው ተክነውበት የኢትዮጵያ ነጻነት ያደላደሉትን መደብ የሚያፈርስባቸው ይመስል አትላንቲክን ማቋረጥ አስግቷቸዋል፡፡ ሁሉም “እስስት ፖለቲከኛ” መሆን አልቻሉም። የአብዛኛዎቹ የትግል ሁሉ መጀመሪያና መጨረሻ “የምትታገለውን ዋና ባላንጣ ትተህ ያንተው ቢጤውን በመቃረን ዕድሜህን አርዝም” የሚል ያልተጻፈ የፖለቲካ ፕሮግራም፣ የጸና እምነትና ግብ ያላቸው ይመስላሉ።

የእናት ሀገር የድረሱልኝ ጥሪ ???…

June 7/2014
(ሠዓሊ አምሳሉ ገ/ኪዳን አርጋው)
ethio poor


ባለፈው ሰሞን ወያኔ ኢሕአዴግ ላለመው የጥፋት ተልእኮ ወሳኝ ክንውኑን መተግበሩ ይታወሳል፡፡ ወያኔ ለጥፋት ተልእኮው በእጅጉ የሚረዳውን ወሳኝ የጥፋት ሥራ የመሥራቱን ያህል ከእምነተ-አሥትዳደር (ፖለቲካ) ፓርቲዎች (ቡድኖች) አንሥቶ እስከ ሕዝባዊ ማኅበራት (Civic organizations) ድረስ ያሉ ሁሉ ልብ ሳይሉት ወይም በቅጡ ሳይረዱት ቀርተው ይሁን ምን አላውቅም ተገቢውን ትኩረት ሳይሰጡት ሲቀሩ ሳይ እጅግ ተገርሜያለሁ፡፡
ወያኔ በአሩሲ ሔጦሳና በሐረር ጨለንቆ ላይ ፋሽትት ጣሊያን ለሰበው የቅኝ ግዛት ይዞታ ዘለቄታ ሲል በነበረው ስልት (Strategy) ተአማኒነት እንዲኖረው በእውነተኛው ታሪካችን ላይ ሆን ብሎ በክፋት የፈጠረውን ፈጠራ በርዞ የሕዝባችንን አንድነት፣ ሰላም፣ ጥምረት፣ ወንድማማችነት (እኅትማማችነት)፣ መተማመን ለመፈረካከስና ለአገዛዙ ምቹ ሁኔታ ለመፍጠር ሲጠቀምበት የነበረውን ድርሰት ወያኔ ሐሰት እንደሆነ እያወቀ ነገር ግን ላለው ተመሳሳይ የጥፋት ዓላማ ከወደቀበት በማንሣት የፈጠራ ሠማዕታትን የሚዘክር የመታሰቢያ ሐውልት አስገንብቶ አስመርቋል፡፡ እንደሚታወቀው ፋሺስት ጣሊያን አስቀድሞ የኢትዮጵያን ሰሜናዊ ክፍል በኋላም መላውን ኢትዮጵያን ይዞ በነበረበት ወቅት ሕዝቡን አዳክሞ ቅኝ አገዛዙን ለማጽናት እንዲያስችለው በፋሺስታዊና የቅኝ አገዛዝ ስልት (Strategy) ሕዝቡን በዘር፣ በሃይማኖት፣ በሞያ ወይም በሥራ ዓይነቶች ሳይቀር ከፋፍሎ ያናቁር ለማፋጀትና ለማባላት ይጥር እንደነበር ታሪክ ዘግቧል፡፡
ፋሺት ጣሊያን ይህ እኩይ ሴራው ያሰበውን ያህል ሳይሠምርለት ቀርቶ በጀግኖች አርበኞቻችን ድል ተመትቶ ተባረረ፡፡ ነገር ግን ሰላዮቹ ሚሲዮኖችና ሀገር አሳሾቹ ሀገራችንን ለመበቀል ሰላምና አንድነት እንዳይኖራት ለማድረግ ብዙ እኩይ ፈጠራዎቻቸውን እውነት አስመስለው በመጽሐፍ አሳትመዋል፡፡ ይህ እንዳለ ሆኖ ዛሬ አሸባሪዎቹ ወያኔ ኦነግና ሻቢያ የኦሮሞን ሕዝብ በሔጦሳና በጨለንቆ ተፈጽሞብሀል የሚሉትን በጅምላ ጡት እጅና ብልት የመቁረጥ ቅጣት ወይም ግፍ ተፈጽሟል ብሎ የጻፈ ሚሲዮን ወይም አሳሽ አንድ እንኳን የለም፡፡ እነዚህ የጥፋት ኃይሎች እከሌ እከሌ የተባለ ታሪክ ጸሐፊ እንደዚህ በሚለው መጽሐፍ እነደጻፈው እያሉ የጠቀሷቸውን መጻሕፍትም ከሀገር ውጪ ያሉ ወዳጆቻችንን ሳይቀር  አስቸግረን  መጻሕፍቱ አሉበት በተባሉ ቦታዎች አፈላልገን ስናነብም በሚገርም ሁኔታ ከሚሉት ጋራ ጨርሶ የማይገናኝና የሌለ ፈጠራ ሆኗል፡፡ ይሄ ምንን ያመለክታል ወገን?
ይሄን ብለው የሚያወሩ ወገኖች ዐፄ ምኒልክ ሀገርን መልሶ አንድ ለማድረግ በዘመቱበት ወቅት ከጦር አበጋዞቻቸው ዋናዋናዎቹ የኦሮሞ ተወላጆች እንደነበሩ አያውቁም፡፡ ለምሳሌ የጦሩ አበጋዝ (ዋና ሹም ወይም ኃላፊ) ራስ ጎበና ዳጬ ነበሩ፡፡
ጥቂት የማንባል ዜጎች በየሕሊናችን “ወያኔ ይሄንን ሐውልት የሠራው እውን ከማስተዋል ማነስ ብቻ ነው ወይስ ከጀርባው እንዳች ነገር አለው?” የሚለው ጥያቄ እየፈራነውም ልናስበው ሳንፈልገውም ገፍቶ ይመጣብናል፡፡ ገፍቶ ከመጣም በኋላ ልንተወው ወይ ልንመልሰው ለማንፈልገው ለዚህ ጥያቄ መልስ ለመመለስ ስንሞክር የሆነ አስጨናቂ ስሜት ይጫጫነናል፡፡ የምናውቀውን እውነታም ላለማመን ከራሳችን ጋር ከባድና የማያዋጣ ሙግት እንገጥማለን፡፡ ሳንቋጨውም ባለበት መተውን እንመርጣለን፡፡ አደጋው እንግዲህ ያለው እዚህ ላይ ነው፡፡ እንዲህ ያለው አደገኛ ነገር በእንጭጩ መታረም መቀጨት ካልቻለና ጊዜ እያገኘ በሄደ ቁጥር ስር እየሰደደ፣ እየከበደ፣ እየጠነከረ የሚሔድ መሆኑና ካደገ፣ ከከበደ፣ ስር ከሰደደ፣ ከጠነከረና ከአደጋ ቀለበት ውስጥ ከከተተን በኋላ የጠነሰሰውን አደጋ ከመጋት ውጭ ለማረም ለማስተካከል የማንችል መሆኑ፡፡ ከዚህ የሔጦሳና የጨለንቆ የፈጠራ ሠማዕታት የመታሰቢያ ሐውልቶች ከማንም በላይ የደነገጡ ግራ የተጋቡና ያዘኑት በተቃውሞ የፖለቲካ ፓርቲ ውስጥ ያሉትን ጨምሮ ታዋቂ የኦሮሞ ልኂቃን ናቸው፡፡ ተፈጽሟል የተባለው ድርጊት እንዲሁ ከመወራቱ ውጪ ለመፈጸሙ አንድም መረጃ እንደሌላ በመግለጽ ጭምር፡፡
ወያኔ ይሄንን የጥፋት ሥራ ከመሥራቱ በፊት ከዚህ ሥራ መቅደም የነበረበትን ሥራ ሥልጣን ከያዘ ጊዜ ጀምሮ ያለ እንዳች ማሰለስ ሥራዬ ብሎ በሚገባ ሲሠራ ቆይቷል፡፡ የኢትዮጵያ ሕዝብ የነበረውን በዘርና በጎጥ ያልተገደበ ያልታጠረ የአንድን ሕዝብና የአንዲት ሀገር አስተሳሰቡን በማፈራረስ ዜጎችን “ወደ ክልልህ” እየተባሉ እስከ መፈናቀልና መሰደድ የደረሰ በዘርና “ክልል” ብሎ በጠራው የሀገር ቅርጫ አጥብቦ ከፋፈለው፡፡ ኢትዮጵያዊነት የመጥፋት ያህል ደበዘዘ፣ ብሔርተኝነት ነገሠ፣ በኢትዮጵያዊነት መለያና ቀለም ቦታ ዘርና ብሔርተኝነት ተተካ፣  ዜግነት በብሔር ተተካ፡፡ በውጤቱም ሀገራዊ (ብሔራዊ) ስሜት ጠፋ ሕዝቡ ተፈራቀቀ ተራራቀ፡፡ ወያኔ ይሄንን እኩይ ሥራ በአጥጋቢ ውጤት እንደሠራ ካመነ በኋላ የእኩይ ዓላማውን ቀጣይ ምዕራፍ በቅርቡ ተግብሯል፡፡ ሦስተኛውንና የዚህን እኩይ ድርጊት የመጨረሻ ምዕራፍ በያዘለት የጊዜ ቀጠሮ ለመከወን ያስባል፡፡
ይህ ዓይነት ዘውጋዊ የእምነተ-አሥተዳደር (የፖለቲካ) አስተሳሰብ ሀገራትን ለምን ዓይነት ችግር እንደዳረገ የዓለም ታሪክ በሚገባ ያስረዳናል፡፡ ሩቅ ሳንሔድ ሩዋንዳን የወሰድን እንደሆነ ለምን ዓይነት አደጋና እልቂት እንደዳረጋት ሁሉም የሚየውቀው የቅርብ ጊዜ ታሪክ ነው፡፡ ሩዋንዳዊያን ጣሊያን በእኛ ላይ እንዳደረገው ሁሉ ቅኝ ገዥዎቻቸው በሠሩት የመከፋፈልና የማባላት ሴራ ከደረሰባቸው ከዚያ አሳዛኝና ዘግናኝ የእርስ በእርስ እልቂት በኋላ ዛሬ ላይ ሩዋንዳ ውስጥ እኔ ሁቱ ነኝ እኔ ቱትሲ ነኝ እኔ ትዋ ነኝ በማለት ማንነትን በዘር ለመግለጽ መሞከር የተወገዘና በሕግ የተከለከለ ሆኗል፡፡ አንድ ሩዋንዳዊ ራሱን ማንነቱን ለመግለጽ በፈለገ ጊዜ እኔ ሩዋንዳዊ ነኝ በማለት ነው እራሱን የሚገልጸው፡፡
እኛ ታዲያ ዘርን መሠረት ካደረገው የዘውግ እምነተ-አስተዳደር (ፖለቲካ) አስተሳሰብ ለመውጣትና እኔ ትግሬ ነኝ፣ እኔ ኦሮሞ ነኝ፣ እኔ ጉራጌ ነኝ፣ እኔ አማራ ወዘተ. እያልን ማንነታችንን ከኢትዮጵያዊነት አጥበን በዘራችን በመግለጽና አንድነታችንን ከሚከፋፍል የዘውግ ፖለቲካን ለመተው ለመጣል የግድ እንደ ሩዋንዳ ያለ የዘር ፍጅት ውስጥ ማለፍ ይኖርብናል ወይ? ብልጥ ከሌላ ይማራል ነበር ብሂላችን፡፡ ይህ እንዲሆን ካልተፈለገ በስተቀር ይሄንን መረዳት ይሳናቸዋል ብዬ አላምንም፡፡ ሂደቱም ቁልጭ አድርጎ እያሳየን ያለው ይሄንን እውነት ነው፡፡ የእኛ መሪዎች አቶ መለስን ጨምሮ ሩዋንዳ በየጊዜው የዚህን የዘር ፍጅት ለማሰብ በዓል ባዘጋጀች ቁጥር ይሄዳሉ ሥነ ሥርዓቱንም ተካፍለው ይመጣሉ፡፡ እጅግ የሚገርመኝ ነገር ቢኖር እያደረጉት ካለው አደገኛና እጅግ ኃላፊነት የጎደለው ሥራቸው መረዳት እንደሚቻለው ሩዋንዳ የሚመላለሱት የዘር ፍጅትን እንዴት ማነሣሣት እንደሚቻልና ከሩዋንዳው የዘር ማጥፋት ወንጀል ድክመት ጥንካሬውን ተምረው በተሻለ አፈጻጸም እንዴት መከወን እንደሚችሉ ለማጥናት ይመስላል፡፡ አንድነት የነበረውን ሕዝብ እስኪበቃቸው ድረስ እየሰበኩ በዘር በሃይማኖት ከለያዩና ካራራቁ በኋላ ሐሰተኛ ወሬ በመንዛት ቂምና በቀልን በመፍጠር የዘር ፍጅት ለመፍጠር አንዱን ሕዝብ በሌላው ላይ ያነሣሣሉ ይቀሰቅሳሉና፡፡
ይህ እኩይና ሳይጣናዊ ዓላማ ባይኖራቸው ኖሮ ከአንድ መንግሥት በሚጠበቅ ኃላፊነት፤ እንኳን ጠላት ለጥፋት ዓላማው የፈጠረውን ፈጠራ አንሥተው ሊቀሰቅሱ ሊያነሣሱ ይቅርና በትክክል የተፈጸመ የተደረገ ጉዳይ ቢሆንም እንኳ ጉዳዩ ሊፈጥር ከሚችለው የማይፈልግ አደገኛ አሉታዊ ውጤት አንጻር አሁን እያደረጉት ካለው ድርጊት ሁሉ በተቆጠቡ ነበር፡፡ እያደረጉት ያሉት ግን ከዚህ ፍጹም የተቃረነውን ነው፡፡ በሔጦሳና በጨለንቆ ያስገነቧቸውን ሐውልቶች ብናይ እኔ ምን ዓይነት የሞራል (የግብረ ገብ) ደረጃና ሰብእና ቢኖራቸው እንደዚያ ያለ የሚያየውን ሁሉ የሚሰቀጥጥ የሚያስደነግጥና የሚዘገንን ቅርጽና ገጽታ ያለው ሐውልት ለምን ሊያቆሙ እንደቻሉና እንደፈለጉ ሊገባኝ አልቻለም፡፡ የዚያ ድርጊት ሰለባ ናቸው ለሚሏቸው ወገኖች የሕሊናና የሥነ ልቡና ጤና እና ደኅንነት እንኳን አልተጠነቀቁም አልተጨነቁም፡፡  የእነዚያ የተሠው የተባሉ ወገኖች ወገን ነኝ የሚል ሁሉ ይሄንን ሰቅጣጭ አስደንጋጭ ሐውልት ባየ ቁጥር ሕሊናው ይቆስላል ይደማል ይህ ስሜትም ወዲያውኑ የበቀል ስሜትን ይወልዳል፡፡ የሐውልቶቹ ቅርጽና ገጽታ እንዲህ ዓይነት ስሜት ሊፈጥር በሚችል መልኩ የተቀረጹት ሆን ተብሎ እንደሆነ በግልጽ መረዳት ይቻላል፡፡
ከዚህ ይልቅ ይሄንን ያስገነቡ ወገኖቻች ቀና ቢያስቡ ኖሮ እንኳንና ድርጊቱ አለመፈጸሙን እያወቁ ድርጊቱ ተፈጽሟል ብለው የሚያምኑ ቢሆኑም እንኳ በሆስፒታል (ዐቢይ የህክምና ማዕከል) እና መሰል የአገልግሎት መስጫ የልማት ግንባታዎች ተገልጾ ቢሆን ኖሮ ኅብረተሰቡ በአገልግሎቱ ከመቀጠሙም ባሻገር ከእንደዚያ ያለ ሐውልቱን በመመልከት ከሚፈጠር የሥነ-ልቡናና የሕሊና ሁከት ቁስለትና ጉዳት በተገላገሉ በተረፉ ነበር፡፡
በተለይ ከነዚህ ሐውልቶች መገንባት በኋላ በየአካባቢው ያሉ የአማራ ብሔረሰብ ተወላጆች ላይ በቀጥታና በተዘዋዋሪ የሚደርስባቸው ጥቃት በዓይነትና በመጠን ጨምሯል ተባብሷል፡፡ “እንናንተ የሚኒልክ ዘሮች ናቹህ” የምትባል ቃል በመጠቀም ብቻ ከፍተኛ የሆነ የሥነ ልቡና ጥቃት እያደረሱባቸው ለከባድ ሰቀቀን ጭንቀት እና ሥጋት እየዳረጓቸው ይገኛሉ፡፡ ጥቂት የማይባሉ ወገኖቻችንን ዛቻ ማስፈራሪያውን በመፍራት ወልደው የከበዱበትንና ሀገራቸውን ጥለው ለቀው ለመውጣት ተገደዋል፡፡  በብዙኃን መገኛኛዎች እንደተሰማውም በተለያዩ አካባቢዎች እዚህ ከቅርብ ስሉልታ ሳይቀር ልቀቁ እየተባልን አደጋም እየተጣለብን ነው፡፡
ወያኔ ከትናንት እስከ ዛሬ የሕዝብ (የመንግሥት) የብዙኃን መገናኛዎችን በመጠቀም ኢንተርሀምዌዮቹ ያደርጉት እንደነበረው ሁሉ የተለያዩ መንገዶቹን በመጠቀም ያነጣጠሩበትን ብሔረሰብ ለማስመታት በአቶ ጥልማሞት ትእዛዝ ተደርሶ በሬዲዮ ፋና (Radio Mille Collines) ይተላለፍ ከነበረው እጅግ አረመኔያዊ ሕዝብን በሕዝብ ላይ የሚያነሣሣ ረጅም የማፋጃ ድርሰትን ጨምሮ እስከ ትናንትናው የባህርዳሩ የመላው ኢትዮጵያ ስፖርት ውድድር እስከ ተደረገው ሴራ ድረስ የሕዝብ (የመንግሥት) የብዙኃን መገናኛዎችን በመጠቀም ለማጫረስ ለማፋጀት ያልተጣረ ጥረት የለም፡፡ በባህር ዳሩ የስፖርት ዝግጅት ላይ ወያኔ የኦሮሞ ብሔረሰብን የሚዘልፉ የሚሰድቡ ምንደኞችን አዘጋጅቶ እያስጨፈረ በማሰደብ ያንኑ ድርጊትም በኦሮሚያ ቴሌቪዥኑ (RTLMC, Radio Television Libre des Mille Collines) የቀጥታ ሥርጭት ለኦሮሞ ሕዝብ ያሳይ ነበር፡፡ የወያኔ ቅጥረኞች ይሄንን ሲያደርጉ ሥራው የወያኔ ነበርና የፌዴራል ፖሊስ አጠገባቸው ሆኖ አንዳችም ዓይነት ፍርሐትና መጨነቅ አይታይባቸውም ነበር፡፡ ፌዴራሎቹም በእነሱ ላይ አንዳችም ዓይነት የእርምት እርምጃ አልወሰዱም ነበር፡፡
እንደ የፖለቲካ ፓርቲ የገባው ንቁና ኃላፊነት የሚሰማው የፖለቲካ ፓርቲ ኢትዮጵያ ውስጥ ካለ ከምንም ነገር በላይ በታላቅ ንቃት እልህና ቁጭት ማስተዋልና ቁርጠኝነት ይሄንን የራሱን የተቀናበረ ሸረኛና እኩይ ሒደት ጠብቆ ዛሬ ላይ ሐውልት ግንባታ ድረስ የደረሰውን የማፋጃ፣ የማባያ፣ የማስተላላቂያ እንቅስቃሴ ሰላማዊ የተቃውሞ ሰልፍን ጨምሬ የተለያዩ የመቃወሚያ መንገዶችን በመጠቀም አሸባሪዎቹ ወያኔና አጋሮቹ ኦነግና ሻቢያ እየመረዙት ያለውን ሕዝብ ትክክለኛውን መረጃ እንዲደርሰው በማድረግ ሀገርንና ሕዝብን መቀመቅ ለመክተት ከሚጠነጠነው ሴራ እራሱን እንዲያርቅ እንዲጠብቅ ተባባሪ እንዳይሆን ማድረግ ማስቻልና ለዓለም ዓቀፉ ማኅበረሰብም እየተሠራብን ያለውን የኢንተርሀምዌዮች እንቅስቃሴ ሴራ ማጋለጥ ይኖርባቸዋል፡፡ ይሄንን በማድረግ ችግሩ ቢረፍድብንም ሳይመሽብን ከወዲሁ ሊቀረፉ እንዲችሉና የየዋህነት ይሁን የምን ምንነቱ በቅጡ ባልታወቀው ዝምታችን ድነገት ነገ ከተፍ ከሚልብን ከአስፈሪው አደጋ ሕዝብንና ሀገርን ይታደጉ፡፡ የተጣለባቸውን ሀገራዊና ሕዝባዊ አደራ ሳይመሽ ይወጡ፡፡ እኩዩን ሰይጣናዊ ሴራ ያክሽፉ፡፡ ይህ ኃላፊነት የእነዚህ አካላት ብቻ ሳይሆን የእያንዳንዱ ዜጋም ጭምር ነው፡፡
ከዚህ ሁሉ ዓመታትም በኋላ በፖለቲካ ፓርቲ (በእምነተ-አሥተዳደር ቡድን) ደረጃ ተመሥርተው ወያኔ በግላጭ በዓይናቸው ሥር እየሠራው ያለውን እኩይና ሰይጣናዊ ሴራ ማወቅ፣ መረዳት፣ መገንዘብ፣ የሚያስከትለውን አደጋ ከርቀት ማየት፣ ማሽተት ካልቻሉና እንደፖለቲካ ፓርቲ መውሰድ ያለባቸውን ተገቢና ወቅታዊ እርምጃ በሰዓቱ መውሰድ ካልቻሉ ጨርሶ ምኑም አልገባቸውምና፣ አልበሰሉምና አልነቁምና አልበቁምና ፓርቲዎቻቸውን አፈራርሰው እየቤታቸው ይቀመጡ፡፡
ወያኔ ለማንም የሀገር ልጅ በማይገባና ሊገባም በማይችል የጥፋት ዓላማ ሀገርንና ሕዝብን መርዞ ለዚህ አድርሶናል፡፡ በእርግጥ ምንጊዜም ቢሆን በአንድ ማኅበረሰብ ውስጥ ምንም ቢደረጉ ቢመከሩ ቢዘከሩም የማይሰሙና የማይገባቸው ፈጽሞ ኃላፊነት የማይሰማቸው ፀረ-ማኅበረሰባዊ ሰብእና (Anti-social personality) ያላቸው ዜጎች ይኖራሉ፡፡ ይህ ሰብእና ያለባቸው ግለሰቦች “መቸም ቢጤ ከቢጤው ጋር” ነውና የሚወዳጀው አውቀውትም ይሁን ሳያውቁት ተሳስበው በአንድ የመቧደን ዕድል ያገኛሉ፡፡ ይህ ሰብእና ያለባቸው ቡድኖች የጠላት መጠቀሚያ ለመሆን እጅግ የተመቹ ናቸው፡፡ በሀገራችን ከዐሥርት ዓመታት ወዲህ እንዲህ ዓይነት ሰብእና ያላቸው ዜጎች የመንግሥትን ሥልጣን የመጨበጥ ዕድሉን አግኝተው ብዙ ነገሮችን እያበላሹ እያጠፉ እንዳሉ ዐይተናል እያየንም ነው፡፡ ከተበላሹትና ከጠፉት እሴት ሀብቶቻችን ብዙዎች በሚያሳዝን ሁኔታ ድጋሚ ላናገኛቸው ያጣናቸውና የምናጣቸውም ናቸው፡፡ በይነ ሕዝባዊ (ዴሞክራሲያዊ) ሥርዓት በሌለበት ሀገር እንዲህ ዓይነት ሰብእና ያላቸው ዜጎች ሥልጣን ለመጨበጥ ሰፊ ዕድል አላቸው፡፡
አንድ ሕዝብ በእነዚህ ዓይነት እኩያን ቡድኖች ላይ ነቅቶ መከላከል ካልቻለና ድርጊቶቻቸውን በዝምታ ለመመልከት ከመረጠ ሕልውናውን እስከማጣት ድረስ የሚያደርሰውን ዋጋ መክፈሉ የማይቀር ይሆናል፡፡ ይህ ችግር በሀገራችን እንደመኖሩ እኛንም ዝምታችን ከባባድ ዋጋ አስከፍሎናል እያስከፈለንም ይገኛል፡፡ ዓለም እንደ አንድ መንደር መጥበቧ ታላቅ እንቅፋት ሆነባቸው እንጂ እንደ ጥንቱ እንደድሮው በአንድ ቦታ የተደረገውን በሌላው ያለው የማያውቅበት የማይሰማበት ዘመን ላይ ብንሆን ኖሮ ወያኔ በተለይም አማራን ከምድረገጽ ሳያጠፋ እንድ ምሽት ማሳለፍ ባልመረጠ ነበር፡፡ እነዚህ ሰዎች በዘመነ ሉላዊነትም (Globalization) ቢሆን ዓለም የደረሰበት ዘመናዊ አስተሳሰብ ሳያግዳቸው ለ 23 ዓመታት ጥፋት እያሴሩ ሲዳዳቸው እንዳየናቸው ዝንባሌያቸው ይሄንን ማድረግ ነው፡፡ ከዓለም ዕይታ ውጪ ሆኖ እንዴት ለማድረግ እንደሚቻል ቸገራቸው እንጂ፡፡ በጅምላ ማለቴ ነው እንጅ በተናጠል ወይም በጥቂት በጥቂቱ መመንጠሩንማ ከተያያዙት ይሄው 23ዓመታት ሆኗቸዋል፡፡
 የአንድ ሀገር ሕዝብ መሆናችንና አንድ የጋራ ሀገር ያለን ወንድማማች (እኅትማማች) መሆናችን ተዘንግቶ “አንተ አማራ ነህ ውጣ ልቀቅ” ከተባለ ቆንጨራ አለመጨመሩ ነው እንጅ ከሩዋንዳው የኢንተርሀምዌ ፍጅት በምን ተለየ? ለነገሩማ ቆንጨራን ከሩዋንዳ ቀድመው በበደኖ፣ በአቦምሳ፣ በአርባጉጉ፣ በወለጋ ወዘተ. የፈጁበት የእኞቹ አልነበሩም? በሩዋንዳ ያ ዘግናኝ የዘር ፍጅት ከመከሰቱ በፊት የነበረው እንቅስቃሴ ይሄው ነበር፡፡ አንድን ዘር ነጥሎ በጥላቻ በመመልከት “ሀገራችንን ልቀቁ” የሚል፡፡ ያ እልቂት በሩዋንዳ በድንገት ከመከሰቱ በፊት ለሁለት ዐሥርት ዓመታት ያህል የጥላቻ ፖለቲካ ሲነዛ ከርሞ ነበር፡፡ ያሰቡትን ጥቃት ጥቃቱ የታሰበባቸውን ዘሮች ብቻ ነጥሎ ለማጥቃት እንዲያስችላቸውም መታወቂያቸው ላይ ብሔረሰባቸው እንዲሰፍር ተደርጎ ነበር፡፡ እኛንም እኮ ለዚህ ሲያመቻቹን ነው መታወቂያችን ላይ ብሔረሰባችን ከየት እንደሆነ እንዲሰፍር ማድረጋቸው፡፡ አሸባሪዎቹ ወያኔና አጋሮቹ ኦነግና ሻቢያ የቤት ሥራዎቻቸውን እንደማጠናቀቃቸው መጠን ክርስቶስ ይታደገን እንጂ ከፊታችን ባሉ ጊዜያት ቆንጨራ ላለመጨመሩ ምን ማረጋገጫ አለን?
አቶ መለስ ይሄንን ማለትም ሕዝብን በዘሩ ምክንያት እያፈናቀሉ “ውጡልን ልቀቁልን” ስለሚለው ጉዳይ ተጠይቀው ሲመልሱ “የክልሉ መንግሥት መብት ነው እንደመሰለው ማድረግ ይችላል” ብለው እንደነበር ይታወሳል፡፡ አቶ መለስ አልገባቸውም እንጂ ይሄንን ሲሉ “በእርግጥ እኔ ተብሏል የሚል እምነት የለኝም ሐሰተኛ ውንጀላ ነው” ነገር ግን ወያኔ ተብሏል እያለ እንደለፈፈው ሁሉ በምርጫ 97ዓ.ም  ዋዜማ ተቃዋሚዎች “እቃ ወደ ቀበሌ ትግሬ ወደ መቀሌ” ብለዋል እያለ ይከስ የነበረውን ክስ ጥፋት አይደለም ትክክለኛ አባባል ነው ብለው እያረጋገጡ ነው፡፡
ሐሰተኛ የፋሺስት ሴራ መሆኑ እየታወቀ ከግብር አባታቸው ፋሺስት ይሄንን እኩይ ሴራ በመውረስ “እንዲህ አድርገውህ ነበር” እያሉ መቀስቀስ አጸፋውን እንዲመልስ መገፋፋት ማነሣሣት የቆንጨራን መተላለቅ ለመጋበዝ ካልሆነ ፍቅርን መተሳሰብን እንድነትን ለማምጣት ለመመሥረት እንዳልሆነ ለማንም ግልጽ ነው፡፡ እመኑኝ እነዚህ ወገኖች እንዲህ ዓይነት እኩይ ሰይጣናዊ ሐሳብ ባይኖራቸው ኖሮ እንኳን እውነት ያልሆነውን እውነት ቢሆን ኖሮም እንኳ እያደረጉት ያለውን ፍጹም ኃላፊነት የጎደለው አድራጎት በፍጹም በፍጹም ባልሞከሩት ነበር፡፡ ይህ ሁሉ ሴራ እንደ አያጅባጅቦ ሁሉ አመሃኝቶ ለመብላት የሚደረግ ጥረት ነው፡፡
መጨረሻ የሚሉት ሰዓት ሲደርስ ወይም ለእነሱ አስቸጋሪ ሆኖ የታያቸው ሰዓት ሲመጣባቸው ምንም ነገር ሳያሳስባቸው ልክ የተቀበረን ፈንጂ አንዲት ቁልፍ በመጫን ማፈንዳት እንደሚቻል ሁሉ መቀመጫችን ላይ የቀበሩብንን ዘርንና ሃይማኖትን መሠረት ያደረጉ የጥላቻ ፈንጅ ስስ ብልቱ የት እንደሆነ በሚገባ እንደማወቃቸው መጠን የሆነ ቦታ አንዲት ነገር በማድረግ ብቻ አፈንድተው ሊያባሉን ሊያፋጁን ሊያጫርሱን በሚችሉበት ሁኔታ አመቻችተው አስቀምጠውናል፡፡ ወገን ሆይ! እባክህ ይሄንን የተሸረበብህን የተተበተበብህን የተጠነሰሰብህን የተቆመረብህን የእልቂት ሴራ ጠንቅቀህ ዐውቀህ የትም ቦታ፣ መችም ቢሆን፣ ምንም ቢፈጠር የሕዝብ ደም የተጠሙ አጋንንትን ነቅቸብሀለሁ “እንቢ” በማለት ተፋቅረህ ተዋደህ ተከባብረህ ጠላትህን አሳፍር፡፡ ከተደገሰልህ እልቂት፣ ሞት፣ ጥፋት አምልጥ ዳን፣ ሀገርን ከመፍረስ ታደግ፡፡ አምላክ ይርዳህ፡፡
 ወያኔ ይሄንን ሐሰተኛ የጥፋት የፈጠራ ታሪክ አዲስ በቀረጸው የኢትዮጵያ ታሪክ የትምህርት ዓይነት እንዳካተተው ይነገራል፡፡ እርግጡን ከጥቂት ጊዜያት በኋላ የምንረዳው ይሆናል፡፡ አገዛዙ ካለውና ከምናውቀው እኩይ ዓላማው እንጻር ስናየው ግን ይሄን አይደለም ከዚህም የከፋ ሊያደርግ እንደሚችል ግልጽ ነው፡፡
ሌላው አበክሬ ማስገንዘብ የምሻው ነገር ቢኖር የምዕራቡ ዓለም መንግሥታትና የሰብአዊ መብት ተሟጋች ድርጅቶች “ከሩዋንዳው የዘር ማጥፋት ጀርባ ማን ነበረ” የሚለውን ለጊዜው እንተወውና በሰው ልጆች ታሪክ “እጅግ ዘግናኙና ተወዳዳሪ የሌለው የዘር ማጥፋት”  በመባል የሚታወቀውን የሩዋንዳውን የዘር ፍጅት እንዳይከሰት ማድረግ እየቻሉ በመዘናጋታቸው ይህ በመሆኑ እየተጸጸቱ ያ የዘር ፍጅት በየዓመቱ በታሰበ ቁጥር በሚያወጧቸው መግለጫዎች ያረጋግጣሉ፡፡ በእንደዚህ ዓይነቱ ወንጀልና የወንጀል ሰለባዎች (victims) ያላቸው የያገባኛል መንፈስ (concern) ይሄንን ያህል ከሆነ ወያኔ ኢሕአዴግ ሥልጣን ከያዘ ጊዜ ጀምሮ ምን ለማድረግ ምን እየሠራ እንደሆነ ጠንቅቀው ያውቃሉና ያለፈው ስሕተታቸው እንዳይደገም ምን እያደረጉ ነው? የወያኔን እኩይ ሴራ ጠንቅቀው እንደሚያውቁ ቅንጣት ታክል አልጠራጠርም፡፡ አይደለምና ይሄንን ያህል ግዙፍ ጉዳይ የዕለት ተዕለት ጥቃቅን ጉዳዮቻችን እንኳን ከእኛ ቀድመው በወቅቱ በሰዓቱ ዐውቀው ለእኛም ሳይቀር የሚያሳውቁን እነሱው ናቸውና፡፡
ሠዓሊ አምሳሉ ገ/ኪዳን አርጋው
ሠዓሊ አምሳሉ ገ/ኪዳን አርጋው
ታዲያ ነገሩ እንዲህ ከሆነ ዝምታው ለምንና ምንስ እስኪሆን ድረስ ነው? በዚህ ኃላፊነት የጎደለው ዝምታና ዳተኝነት በሚፈጠር  ችግር ዳግም እንደገና “በመዘናጋታችን እንዳይከሰት ልናደርግ እንችል የነበረው ችግር በመከሰቱ እናዝናለን እንጸጸታለንም” እያላቹህ የአዞ እንባ በማንባት እንድታላዝኑልን ከቶውንም አንሻም፡፡ ኃላፊነታቹህንና ግዴታቹህን መወጣት ካለባቹህ በቋፍ ካለ አደጋ ላይ ነንና ነገ ሳይሆን ዛሬ ከዛሬም አሁን ድረሱልን፡፡ ታሪክና አጋጣሚ የጣለባቹህን ኃላፊነት ሳትወጡ ቀርታቹህ በምትደጉሙትና በምትረዱት በምትደግፉት “መንግሥት” ለሚፈጠረውና ለሚፈጸምብን አደጋና ችግር ሁሉ ሙሉ ኃላፊነትን ትወስዳላቹህ፡፡ በውጪ የምትኖሩ ዜጎቻችን ሁሉ ሳትዘገዩ ይሄንን ጉዳይ በሰላማዊ ሰልፎችና በተለያዩ መንገዶች ለሚመለከተው ሁሉ እንድታስገነዝቡ አበክሬ ማሳሰብ እወዳለሁ፡፡ ይህ የታፈነው የኢትዮጵያ ሕዝብ ድምፅ ነው፡፡
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር!!!

Friday, June 6, 2014

ኡስታዝ አቡበከር አህመድ በጨለማ ክፍል መታሰራቸው ተሰማ

June 6/2014
በአቡ ዳውድ ኡስማን -
(ድምጻችን ይሰማ እንደዘገበው)

በቂሊንጦ ማረሚያ ቤት በሃሰት በሽብርተኝነት ተወንጅለው በእስር የሚገኙት ኮሚቴዎቻችንን የማረሚያ ቤቱ አስተዳር ሆን ብሎየማሸማቀቅ እና የማዋከብ ተግባር እየፈፀመባቸው እንደሚገኝ መዘገባችን ይታወቃል:: በማረሚያ ቤቱ ከሚገኙ ህግ ታራሚዎች እና እስረኞች በተለየ መልኩ ከቅርብ ጊዜ ጀምሮ በኮሚቴዎቻችን አመራሮች እና አብረዋቸው በታሰሩት ወንድሞች ላይ ትኩረት በማድረግ አቃቂር የ መፈለግ እና ባገኙትም ነገር ጉዳዩን በማግነን ለማሸማቀቅ እና ለማንገላታት የማረሚያ ቤቱ አስተዳደር አቶ አምባዬ እና የደህንነት ሃላፊ አቶ ኤርሚያስ እየተንቀሳቀሱ መሆናቸወየተገለፀ ሲሆን ሲዝቱባቸው በነበረው መሰረትም የህዝበ ሙስሊሙን መፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴ ሰብሳቢ የሆኑትን ኡስታዝአቡበከር አህመድን በጨለማ ክፍል ውስጥ እንዲታሰሩ መደረጉን ምንጮች አስታውቀዋል፡፡

በኮሚቴዎቻን እና በወንድሞቻችን ላይ ልዩ ክትትል በማድረግ በጨለማ ክፍ ውስጥ እንዲሰቃዩ ለማድረግ ከበላይ የደህንንትአካላቶች ትዕዛዝ የተላለፈ ሲሆን ይህንንም ተግባራዊ ለማድረግ ድንገተኛ ፍተሸ በማድረግ ማንኛው እስረኛ ጠያቂዎች ሊሰጡት የሚችሉትን ገንዘብ ይዛችሁ ተገኝታቹሃል በሚል ኡስታዝ አቡበከር አህመድን እና ሼህ መከተ ሞሄን የማስፈራራት እና ቃላቸውን እንዲሰጡ የማድረግ እንቅስቃሴ ሲየደርጉባቸው ቆይተዋል፡፡በትላንትናው ዕለት ሃሙስም ኡስታዝ አቡበከር አህመድን በጨለማ ክፍል ውስጥ እንዲታሰር ማድረገቻውን ምንጮች አስታውቀዋል፡፡

ከሌላ እስረኞች በተለየ ሁኔታ ኮሚቴውን የማዋከቡ እና በጨለማ ቤት ለመቅጣት የማስፈራቱ ድርጊታቸው ህገ ወጥ መሆኑን ኡስታዝ አቡበከር አህመድ ለማረሚያ ቤቱ ደህንነት ሃላፊዎች ሲያሳስቡ ቢቆዩም የማረሚያ ቤቱ ሃላፊዎች ግን ኡታስዝ አቡበከርን በጨለማ ክፍል ውስጥ እንዲታሰር ማድረጋቸው ታውቋል፡፡

ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ከህግ እና ክፍርድ ቤቱ ተዕዛዝ ሁሉ የበላይ በሆኑ የደህንነት ሃይሎች በኮሚቴዎቻችን አመራሮች ላይ እና በተወሰኑ ወንድሞች ላይ እየተደረገ ባለው ጥብቅ ክትትል እና የዚህ መሰሉ የጨለማ ቤት ቅጣት የሚፈፀም ከሆነ ኮሚቴዎቸችን ለፍርድ ቤቱ እያቀረቡ የሚገኙትን የመከላከያ ምስክር እስከማቆም ሊደርሱ እንደሚችሉ ታውቋል፡፡ ህግ ተፅፎ ባለበት ሃገር ህጉ እየተጣሰ ንፁሃን እንዲንገላቱ መደረጉ የፍርድ ቤቱን ሚና ከቁብ የማያስገባ መሆኑን የሚያረጋግጥ በመሆኑ በችሎቱ የመቀጠሉ ሁኔታ አጠያያቂ ሊሆን እንደሚችል ተገምቷል፡፡

ሼህ መከተ ሞሄ እና ኡስታዝ አቡበከር አህመድ ላይ በጨለማ ክፍል አስገብተው እንደሚቀጧቸው የማረሚያ ቤቱ ሃላፊዎች ሲዝቱባቸው የቆዩ ሲሆን ዛቻቸውን በተግባር በመለወጥ በጨለማ ክፍል ውስጥ እንዳስገቧቸው ታውቋል፡፡
ኡስታዝ አቡበከር አህመድ እየተፈጸመባቸው የሚገኘውን ህገ ወጥ ተግባር ለፍርድ ቤቱ ያሳውቃሉ ተብሎ ይጠበቃል ኡስታዞቻችንን እና ወንድሞቻንን አላህ ይጠብቅልን!!!

የጠቅላይ ሚኒስትሩ አማካሪ… አለቃ ጸጋዬ በርሄ ሰክሮ የሰው ሚስት ይዤ ካላደርኩ በማለቱ በቡጢ ተዘረረ

June 6/2014
ማለቂያ የሌለው የወያኔዎች ጉድ …. የጠቅላይ ሚኒስትሩ አማካሪ የሆነው አለቃ ጸጋዬ በርሄ ሰክሮ የሰው ሚስት ይዤ ካላደርኩ በማለቱ በቡጢ ተዘረረ።
አለቃ ጸጋዬ በርሄ በሴሰኝነታቸው የመጣ በአውስትራሊያ በቡጢ ተደብድበዋል።
“ወደዳችሁም ጠላችሁም ሁሉም አድፍጦ ሊበቀላችሁ እየጠበቀ ነው። ” በኬንዊክ የሚኖሩ የትግራይ ልጆች
(በምንሊክ ሳልሳዊ)
በምእራብ አውስትራሊያ ኬንዊክ ግዛት በሚገኘው የትግራይ ተወላጆች ኮሚኒቲ ማእከል ግንቦት ሃያን በማስመልከት በተድረገ ዝግጅት ላይ ለመታደም የዘመቱት የወያኔ ባለስልጣናት በገዛ ወዳጆቻቸው ተዋርደው ተመልሰዋል። በፖለቲካው መስክም ይሁን በሴሰኝነታቸው እድል ያልሰመረላቸው የወያኔ ባለስልጣናት አብሯቸው ከተጓዘው አንዱ የጠቅላይ ሚኒስትሩ አማካሪ የሆነው አለቃ ጸጋዬ በርሄ ሰክሮ የሰው ሚስት ይዤ ካላደርኩ በማለት ከፕሮቶኮል ውጪ በመንቀሳቀሱ የራያው ተወላጅ አቶ ተከስተ በትደጋጋሚ ለ4 ጊዜ ቡጢ ሲያቀምሳቸው በክፍተኛ ደረጃ በማእከሉ ውስጥ ድንጋጤ ተፈጥሮ ነበር።
ጸጋየ በርኸ
ጸጋየ በርኸ
ሁኔታውን ለማረጋጋት ቢሞከርም ከሌሎች የጸጋዬ ባለሟሎች ጋር ግብግብ በመያያዝ .. እኔ ወዲ ራያ በማለት አቶ ተከስተ በጸጋዬ እና ተከታዮቹ ላይ ጉዳት አድርሰዋል። በትግራይ የራያ ተወላጅ እና የቀድሞ የሕወሃት አባል የሆኑት አቶ ተከስተ ባለቤታቸው ይዘው በዝግጅቱ ላይ የመጡ ቢሆንም በወቅቱ በነበረው ክፍተኛ የመጠጥ ብዛት ከልክ በላይ የጠጡት አለቃ ጸጋዬ በቆንጆ የራያ ልብስ ደምቃ በሹሩባ ያጌጠችው የአቶ ተከስተ ሚስት አይናቸው ገብታ እንዲያመጡላቸው ቢያዙም የሰው ሚስት እንደሆነችና ባለቤቷ አብሮ እንዳለ ቢነገራቸውም ሊሰሙ ባለመቻላቸው ያለችበት ቦታ ድረስ በስካር መንፈስ ሰተት ብለው ሲሄዱ ነገሩ የገባው የቀድሞ የሕወሓት አባል አቶ ተከስተ በቡጢ ተቀብሏቸው መሬት ላይ ዘርግፏቸዋል።
ይህ በእንዲህ እንዳለ በምእራብ አውስትራሊያ ኬንዊኪ የሚገኘው የትግራይ ኮሚኒቲ ለሁለት ተከፍሎ የወያኔ መሪዎችን በማፋጠጥ ክባድ የፖለቲካ ኪሳራ እንደተፈጠረ ወዳጆቻችን ገልጸውልናል። ሕወሓት በኢትዮጵያ የሚያደርገው ድርጊት ለነገ ልጆቻችን ቂም ማትረፍ ነው ወደዳችሁም ጠላችሁን ሕዝቡ ተለያየ ብላችሁ እያሰበችሁ ከሆነ አትሳሳቱ ሁሉ አድፍጦ እየጠበቀ ነው ድንገት የፈነዳ እለት ይበቀላቹሃል። በቀሉም ለትግራይ ተወላጆች ይተርፋል መፍትሄ አምጡ በማለት የመከሩ ሲሆን በሌላው ወገን ደሞ አማራው አድብቷል የአማራው ጅብ እንዳይበላችሁ እናንተ እርስ በርስ እየተባላችሁ ነው አታናቆሩ ሲሉ መካሪዎችን ሮሮ አስምተዋል።
ከእራት በፊት በቤተክርስቲያናት መካከል የተከፋፈለውን አካል ለማስታረቅ የሞከሩት የወያኔ ባለስልጣናት በፍጹም ለማስማማት ባለመቻላቸው በአቡነ ማትያስ ስም ለማስፈራራት ቢሞክሩም መሳቂያ ሆነዋል። የተዋህዶ ቤትክርስቲያን በመንደርተኖች የተክፈለች ሲሆን የአድዋ እና የተንቤን ተብለው የሚጠሩት ቤተክርስቲያኖች ሲኖሩ በኮሚኒቲ ማእከሉ ውስጥ ያለውን ከሕወሓት ቢሮ ጋር አብሮ የተጣበቀውን አድዋዎች ሲያስተዳድሩት ተንቤኖች ደሞ የራሳቸውን ቤተክርስቲያን በመመስረት ተገንጥለው ወተዋል። ይህንን ግኡዳይ ለመፍታት እና ወደ አንድነት ለማምጣት በቦትው የተገኙት የፖለቲካ ባለስልጣናት አለቃ ጸጋዬ እና የአባይ ወልዱ ባለቤት እንዳልተሳካላቸው ሲታወቅ ከተንቤን ተወላጆች ጠንካራ ሂስ ቀርቦባቸዋል።
# ምንሊክሳልሳዊ

የደህንነት ኃይሎች በጋዜጣ አዙዋሪዎች ላይ እርምጃ መወሰድ ጀመሩ

June 6, 2014
 በቅርቡ ገዥው ፓርቲ የግሉን ሚዲያ ለማፈን እንዲያስችል ጋዜጣ አዙዋሪዎችና አከፋፋዮችን በጥቃቅንና አነስተኛ ለማደራጀት የሚያስችል አሰራር እንደጀመረ ታውቋል፡፡ በዚህ አሰራር መሰረት ገዥው ፓርቲን የሚተቹ ጋዜጦችና መጽሄቶች ከገበያ በማስወጣት በቀጣዩ ምርጫ የሚደርስበትን ጫና ለመቀነስ እንደፈለገም ሲነገር ቆይቷል፡፡
ይህ በአዙዋሪዎች ላይ ሊወሰድ የታቀደው እርምጃ ዛሬ አመሻሹ ላይ የጀመረ ሲሆን በተለያዩ የአዲስ አበባ ክፍሎች ጋዜጣ አዙዋሪዎች በገዥው ፓርቲ የደህንነት ኃይሎች ታግተው አምሽተዋል፡፡ በእገታው ወቅት የደህንነት ኃይሎች ‹‹ለማዞር የተደራጃችሁበትንና ፈቃድ የተሰጣችሁበትን ወረቀት አምጡ›› በማለት ወደ ጣቢያ ሊወስዱዋቸው እንደነበርና አዙዋሪዎቹም ‹‹መደራጀት አይጠበቅብንም፣ ጣቢያም አንሄድም›› ብለው የደህንነቶቹን ትዕዛዝ መቃወማቸውን ለነገረ ኢትዮጵያ ገልጸዋል፡፡
በተጨማሪም መንግስት የሚተቹትን ጋዜጦችና መጽሄቶች እንዲያዞሩ እንደማይፈልግና እሱ በሚፈልገው እያደራጀ መሆኑን ለነገረ ኢትዮጵያ ገልጸዋል፡፡ እርምጃው መጠነ ሰፊ መሆኑን የጠቆሙት ታጋቾቹ ‹‹መንግስት ይህንን ለመተግበርም በእኛ ብቻ ሳይሆን ጋዜጣ በምናስነብብባቸው ካፌዎች ላይም ጫና ተጀምሯል፡፡ ካፌዎቹ ለአንድ ሰው ከአንድ ጋዜጣ በላይ እንዳንሰጥና አንዳንዶቹም ጭራሹን እንዳናስነብብና እንዳንሸጥ እየከለከሉን ነው፡፡›› ያሉት አዙዋሪዎቹ እስካሁን ይወሰዳል የተባለው እርምጃ ዛሬ በግልጽ መጀመሩን ገልጸዋል፡፡
Reading newspapers in Addis Ababa, Ethiopia

አንድነት ቅስቀሳውን አፋፍሞታል፤ ፖሊስ 19 አባላትን አስሯል

June 5/2014
አንድነት ፓርቲ በመጪው ዕሁድ ሰኔ 1 ቀን 2006 በደብረማርቆስ፣ በአዳማ/ናዝሬት እና በቁጫ/ሰላም በር ከተማ የሚሊዮኖች ድምፅ ለመሬት ባለቤትነት በሚል መሪ ቃል ለሚያካሂደው የተቃውሞ ሰልፍ፤ የቅስቀሳ ስራውን የሚያስተባብሩ ሶስት ቡድኖች ከትላንት ጀምሮ ከዋናው ጽ/ቤት መንቀሳቀስ ጀምረዋል፡፡ ዛሬ በቁጫ/ሰላም በር ከተማ የሚደረገውን ቅስቀሳ የሚያስተባብረው ቡድን ወደ ስፍራው አቅንቷል፡፡ በደብረ ማርቆስና በአዳማ የተጠናከረ ቅስቀሳ ከተሰራ በኋላ የፖሊስ የተሟላ የዕውቅና ማስረጃ የያዙት 10 የአንድነትን ደብረ ማርቆስ ላይ እንሁም 9 የአንድነት ፓርቲ አመራሮችና አባላትን ደግሞ አዳማላይ አስሯል፤ በተጨማሪም የአንድነት ፓርቲ የአዳማ ከተማ የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ የሆነው አቶ ተስፋዬ ዋቅቶላን ከሌሎች አመራሮችና አባላት ተነጥሎ እንደታሰረም ለወቅ ተችሏል፡፡10390527_646975422054062_5390340408407620827_n
10414571_646975815387356_5317420916539631797_n
1959393_646975445387393_1642782545267051048_n ‪

የቦሌ ሁለተኛ ደረጃ ት/.ቤት ተማሪዎች የህዝብን ጥያቄ አነሱ።

June 6/2014
የቦሌ ሁለተኛ ደረጃ ት/.ቤት ተማሪዎች የህዝብን ጥያቄ አነሱ። በርካቶች ታፍሰዋል። ታስረዋል በዛሬው እለት በቦሌ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማሪዎች በመሰባሰብ ፈተና ከጨረሱ በኋላ ከጠዋት ጀምረው አቤቱታቸውን ሲያሰሙ እንደነበር በቦታው ሁኔታውን የተከታተለው ጥላዬ ታረቀኝ ለምንሊክ ሳልሳዊ ባደረሰው መረጃ ገልጽዋል። ኑሮ ተወደደ ቤተሰቦቻችን በጭንቀት እያሳተማሩን ነው ፡፤ ምግብ ውሃ መብራት የሚሉ ጥያቄዎች ተነስተው እንደነበር ተዘግቧል። ነጻነት እንፈልጋለን ኑሮ እየመረረን ነው ከብድናል ይእሚሉ ተማሪዎችን ለምበተን ከ100 በላይ የፌዴራል ፖሊስ ወደ ትምህርት ቤቱ በመግባት ከ40 በላይ ተማሪዎችን አፍሶ የወሰደ ሲሆን ተማሪውን ከግቢ በማስወጣት በቡድን ተሰብስበው የቆሙ ተማሪዎችን ሲያፍስ እና ስበትን ይነበር ሲሆን በርካታ ተማሪዎች ወደ ቦሌ መድሃኒያለም ቤተክርስቲያን ሸሽተው መሄዳቸው እና መሸሸጋቸው ተጠቁሟል። የኢትዮጵያ ህዝብ በኑሮ ውድነት ምክንያት በከፈተን ድእረጃ በመማረሩ ወጣቶች በወያኔ ላይ ጥርሳቸውን የነከሱ ሲሆን በድንገት አድፍተው የለውጥ አብዮት ያመጣሉ በሚል ወያኔ በስጋት በመራዱ የጸጥታ ሃይሎቹን እያሰማራ በመደብደብ እና በማሰር ላይ ሲገኝ በቅርቡ በኦሮሚያ ክልል ተማሪዎች ላይ የተፈጸመው ተጠቃሽ ነው።bole 4bolebole1
bole2


Thursday, June 5, 2014

ወጣቶች እየመጡ ነው!!!

June 5/2014
ግንቦት 7: የፍትህ፣ የነፃነትና የዲሞክራሲ ንቅናቄ፣ “ወጣት፤ የነብር ጣት!” በሚል ርዕስ ጥር 26 ቀን 2003 ዓ.ም. በቁጥር 142 ባወጣው ርዕሰ አንቀጹ “ወጣት በነብር ጣት መመሰል ያንሰው እንደሆን እንጂ አይበዛበትም። የኢትዮጵያም ወጣት የነብር ጣት ሆኖ ያውቃል … አሁንም ነው” ብሎ ነበር። በዚያ ጽሁፍ እና በሌሎችም አጋጣሚዎች በተደጋጋሚ እንዳብራራው ግንቦት 7 በወጣቱ ችሎታና ተነሳሽነት ላይ ከፍተኛ እምነት አለው። የወደፊቷ ብቻ ሳይሆን የአሁኗ ኢትዮጵያም የወጣቱ መሆኗን ግንቦት 7 ያምናል። ግንቦት 7: ወጣቶችን ለማሳተፍና ለመሪነት ለማብቃት የሚጥር፤ ራሱም በወጣቶች የተገነባ ድርጅት ነው።
ኢትዮጵያ አገራችንና ሕዝቧን ከወያኔ አደንቋሪ አገዛዝ ለማላቀቅ ቆርጠው የተነሱ ወጣቶች እየበረከቱ መምጣታቸው የግንቦት 7 እምነትን የሚያጠናክር ሆኗል። አምባገነኑን የወያኔ አገዛዝን በትጥቅ ትግል መፋለም ይኖርብናል ብለው የተነሱ ወጣቶች በከፍተኛ ፍጥነት እየተደራጁ መሆናቸውን እንሰማለን። እድሜያቸው በሀያዎችና በሠላሳዎች መጀመሪያ ላይ የሚገኙ ለጋ ወጣቶች ናቸው የግንቦት 7 ሕዝባዊ ኃይል የሚባለውን የትግል ድርጅትን የፈጠሩት። ይህ ኃይል ሰሞኑን ለአራተኛ ጊዜ እጩዎችን አሰልጥኖ ማስመረቁን በተለያዩ ሚዲያዎች ባሰራጨው ዜና ገልጿል። በተመሳሳይም የትግራይ ህዝብ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ (ትህዴን) በሺህ የሚቆጠሩ ወጣቶችን አሰልጥኖ ለወሳኝ ትግል ዝግጁ መሆኑን አብስሯል። የኢትዮጵያ አርበኖች ግንባርም በወጣቶች የተሞላ ለትግል የተዘጋጀ ድርጅት ነው። ሌሎችም አሉ። እነዚህን ድርጅቶች ድርጅት ያደረጓቸው ወጣቶች ናቸው።
በሰላማዊ የትግል ዘርፍም ወያኔ የሚያደርስባቸው እስር፣ ዱላና እንግልት እየተቋቋሙ በየእለቱ እየበረቱ የመጡ ጀግኖች ወጣቶችን ማየት ችለናል። ወያኔ፣ በማኅበረሰቡ ውስጥ ብሩህ አዕምሮና ልብ ያላቸው ወጣቶችን አስሬ፣ አሸማቅቄ ጨረስኩ ሲል ከዚያ የባሱ እየፈለቁ ነው። በነፃነት ሲጽፉ የነበሩ እነ እስክንድር ነጋ፣ ውብሸት ታየ እና ርዕዮተ ዓለሙ በሀሰት ክስና ምስክር ሲታሰሩ ወያኔ ተስፋ እንዳደረገው ወጣቶች በፍርሃት ተሸማቀው ልሳኖቻቸውን አልዘጉም። እንዲያውም ከነሱ የባሱ፣ የበሰሉ ጦማርተኞች መጡ። ሰላማዊ ታጋዮቹ እነ አንዱ ዓለም አራጌና ናትናኤል መኮንንን ሲያስር ከእነሱ የበለጡ ወጣት ወንድና ሴት ታጋዮች መጡ። እስከ ድል ድረስ ይህ ዑደት ይቀጥላል፤ ኢትዮጵያ ወጣት ጀግኖችን ማፍራቷ አያቋርጥም።
ወያኔ “ኢህአዴግ” በሚባል ቀፎ በሰበሰባቸው አድርባይ ድርጅት ውስጥ የተሰባሰቡ ወጣቶችም ወደ ህሊናቸው እየተመለሱ፣ ድፍረት እያገኙና እየከዱት ነው። በአሁኑ ወቅት በተለያዩ ምክንያቶች በወያኔ ድርጅቶች ውስጥ የገቡ ህሊና ያላቸው ወጣቶች “ምን እናርግ?” እያሉ ነው። ለእነዚህ ወገኖቻችን ግንቦት 7 አጭር ምላሽ አለው – “ከቻላችሁ ጥላችሁ ውጡና የነፃነት ትግሉን በይፋ ተቀላቀሉ፤ ካልቻላችሁ ኢህአዴግን ከውስጥ ሆናችሁ ውጉት፣ አዳክሙት፣ ግደሉት” ።
በሁሉም ረገድ በኢትዮጵያ ወጣት ላይ ያለ ተስፋን የሚያጠናክሩ ነገሮችን የምናስተውልበት ወቅት ላይ መሆናችን የሚያስደስት ነገር ነው። “እንዴት ልታገል? ከማን ጋር ልታገል?” የሚሉ ጥያቄዎች ምላሽ አግኝተዋል። ነፃነቱን የሚወድ ወጣት ሁሉ እንደ ፍላጎቱና ዝንባሌው የሚሳተፍበት መድረክ ተዘጋጅቶለታል።
ወያኔ፣ ወጣቱን ያህል የጎዳው የኢትዮጵያ የኅበረተሰብ ክፍል የለም። የህወሓት መሪዎች በወጣትነታቸው ዘመን “መብት ተነፈግን” ብለው ብረት አንስተዋል፤ የዛሬው ወጣት ግን እነሱ ያኔ የነበራቸውን እኩሌታ ያህል እንኳን መብት እንዳያገኝ አድርገዋል። የህወሓት ሁሉንም ጠቅልሎ የመግዛት ፍላጎት ወጣቱን መናገርም ሆነ መፃፍ ብቻ ሳይሆን ማሰብ እንኳን እንዳይችል ለማድረግ እየሞከረ ነው።
የኑሮ እድሎች የሚከፋፈሉት በዘርና በፓለቲካ ወገንተኝተኝነት በመሆኑ ከሁለቱም ያልሆነው ወጣት ኑሮው የተጎሳቆለ፤ የነገ ተስፋውም የጨለመ ሆኗል። ስደት የኢትዮጵያ ወጣት እጣ ፈንታ ሆኗል። ዛሬ የተማረውና ከተሜው ብቻ ሳይሆን በትምህርት ያልገፋውና በገጠር በግብርና የሚተዳደረውም ወጣት ስደተኛ ሆኗል። አረብ አገራት፣ ሱዳን፣ ኬኒያ፣ ደቡብ አፍሪቃ በኢትዮጵያውያን ወጣት ወንዶችና ሴቶች ተጨናንቀዋል። ወያኔ ወጣቱን በእድሜና በዝንባሌ ሳይሆን በዘር በማደራጀት የጎንደሩ ለባሌ፤ የሸዋው ለአሩሲ፤ የትግራዩ ለባህርዳር፣ የደሴው ለለቀምት ፈጽሞ ባዕድ እንዲሆን፤ በጥርጣሬም እንዲጠባበቅ፤ በሰበብ አስባቡም እንዲቆራቆስ አድርጓል። ወያኔ፣ የኢትዮጵያን ወጣት በኢትዮጵያ ወጣት ላይ እንዲዘምት አድርጓል።
ያም ሆኖ ግን የወያኔ ፋሺስታዊ የጥፋት ፕሮጀክት እየተናደ ነው። በተስፋና በወኔ የተሞሉ ከሁሉም የኢትዮጵያ አካባቢዎች የተውጣጡ ወጣቶች በበረሃዎችና በሜዳዎች ላይ በአንድነት ሲዘምሩ ስናይ የኢትዮጵያ ትንሳኤ ቅርብ መሆኑ ይሰማናል። አዎ!!! የኢትዮጵያ ወጣቶች ከየአቅጣጫው እየመጡ ነው። መላው የኢትዮጵያ ሕዝብ ህልማቸውን ያልማል፤ ዜማቸውን ያዜማል። ግንቦት 7: የፍትህ፣ የነፃነትና የዲሞክራሲ ንቅናቄ ሁሌም አብሯቸው ነው። ኢትዮጵያ በወጣቶቿ ብርቱ ትግል ከአገዛዝ ነፃ ትወጣለች።
ድል ለኢትዮጵያ ሕዝብ!!!

ሕወሓት ስድስት የኦሮሞ ተወላጆች አለባቸው ጫካ ወስዶ እንደረሸናቸው ተጋለጠ ።

June 5/2014
ምንሊክ ሳልሳዊ
በትግራይ ክልል 14 የኦሮሞ ተወላጆች ከጨለማ ክፍል ታስረዋል።

ወጣት አራርሳ ኤዴሳ የተባል የጅባት እና ሜጫ ሰው በቶርች እንዲሞት ተደርጓል።
አምባገነኑ የሕወሓት ጁንታ ቢትዮጵያውያን ኦሮሞዎች ላይ የሚያደርሰው አድገኛ የሆነ ዘረኝነትን ያዘለ የጥላቻ መከፋፈል እና እንዲሁም የተማሩ የኦሮሞ ወጣቶችን ለማጥፋት የሚደረገው ሩጫ እየተጋለጠበት መሆኑን የደረሱን መረጃዎች ያመለክታሉ። 

የኦሮሞን ሕዝብ ነጻነት እና የመብት እኩልነት ጥያቄዎችን የሚያነሱ ለሕወሃት አስጊ ናቸው ሕዝብን ይቀሰቅሳሉ ተብለው የሚፈሩ እና ከየመንገዱ እና ጎረቤት አገሮች ታፍነው የተወሰዱ የኦሮሞ ተወላጆች በትግራይ ክልል ውስጥ በከፍተኛ ጥበቃ በ እስር ቤት ስቃይ ላይ መሆናቸው ታውቋል። እነዚህ ቁጥራቸው 14 የሚሆኑ ታሳሪዎች የደረሱበት አይታወቅም ተብሎ ነገሩ ተደፋፍኖ ሕወሓት በከፍተኛ ደረጃ እያሰቃያቸው መሆኑ ታውቋል። ከ እስረኞቹ መካከል ከዚህ ቀደም ወጣት አራርሳ ኤዴሳ የተባለ እና ከበጮ አከባቢ ታፍኖ የተወሰደ ተማሪ በግርፋት እና በድብደባ ሕይወቱ እንዳለፈ ታውቋል። እንዲሁም እስር ቤቱ ውስጥ ከየመንገዱ ታፍነው የተወሰዱ የኢሕኣፓ የቀድሞ አባላት እንደሚገኙ ተጠቁሟል።

ይህ በኢንዲህ እንዳለ በሰሜን ሸዋ አለባቸው ጫካ ውስጥ ሕወሓት ስድስት የኦሮሞ ተወላጆችን እንደረሸናቸው መርጃዎች አጋልተዋል። ወያኔ በተለያየ ጊዜያት ለኦሮሞ ህዝብ መብት የሚከራከሩ እና ከጅቡቲ እና ኬንያ ታፍነው የመጡ እነዚህን 6 የኦሮሞ ተወላጆች ሰብስቦ በመውሰድ ከገደላቸው በኋላ በጅምላ እንደቀበራቸው ታውቋል። አለባቸው ጫካ ማለት የወያኔ እስር ቤቶች እና የማሰቃያ ቦታዎች አንዱ ሲሆን በትግሉ ወቅት የተለያዩ የደርግ መኮንኖች እንዲሁም የሻእቢያ ተቃዋሚዎች እንደተረሸኑበት ይታወቃል። አሁንም በከፍተኛ ጥበቃ ብዛት ያላቸው ዜጎች ታስረው እንደሚገኙ ይታወቃል።

ዚጎቻችን ደብዛቸው ጠፋ እንደወጡ አልተመለሱም ወዘተ እየተባለ በተለያየ ጊዜ ሮሮ ቢሰማም ምንም አይነት ፍንጮች እንዳልነበሩ ሲታወቅ በአሁን ሰአት ግን የተለያዩ መረጃዎች እንደሚጠቁሙት ኢትዮጵያውያን ክየመንገዱ እና ጎረቤት አገር እየታፈኑ ካለፍርድ በምስጢራዊ ወህኒ ቤቶች እየተሰቃዩ እንደሆነ ተጋልጧል።