Saturday, May 3, 2014

በዝዋይ የሚገኙ የፖለቲካና የህሊና እስረኞች መልዕክት አስተላለፉ፤ (የረሃብ አድማ መምታት ጀምረዋል)

May 2/2014
በዝዋይ የሚገኙ የፖለቲካና የህሊና እስረኞች የተለያዩ ጥያቄዎችን በማንሳት ጥያቄያቸው እንዲመለስ ጫና ለመፍጠር የምግብ ማቆም አድማ ጀመሩ። አድማው ለ3 ቀን እንደሚቆይ ታውቋል፡፡ ጥያቄያቸውም፡-

1ኛ፦ የፖለቲካው ሥነ -ምህዳር እንዲሰፋና የፓርቲዎች በነፃነት የመንቀሳቀስና የመደራጀት መብት ሳይሸራረፍ እንዲከበር፣

2ኛ፦ አፋኝ የሆኑት የመያዶች ህግ፣ የፀረ-ሽብር ህግ፣ የፕሬስ ህግ እንዲሻሩና ነፃ የሙያ ማህበራት ላይ የሚደረገው አፈና እንዲቀም፣

3ኛ፦ በግሉ ሚዲያ ላይ የሚደረገው ማስፈራሪትና አፈና በአስቸኳይ እንዲቆምና የፕሬስ ነፃነት ሳይሸራረፍ እንዲከበር፣

4ኛ፦ የመከላከያ፣ የፖሊስና የደህንነት አካላት በህገ መንግሥቱ መሠረት የተሰጣቸውን ኃላፊነት በገለልተኝነት እንዲወጡ፣

5ኛ፦ ፍርድ ቤቶች፣ የምርጫ ቦርድ፣ የህዝብ ሚዲያው ነፃና ገለልተኛ ሆኖ እንዲዋቀር፣

6ኛ፦ የፖለቲካ እስረኞች፣ የታሰሩ ጋዜጠኞች እና የህዝበ ሙስሊሙ ተወካዮች ያለምንም ቅድመ ሁኔታ በአስቸኳይ እንዲፈቱ፣

7ኛ፦ በመላ ሀገሪቱ የሚገኙ እስር ቤቶችን በተመለከተ፡-

ሀ) የሰብአዊ መብት ጥሰትን የፈፀሙ ማለትም በድብደባ አካል ያጎደሉና በድብደባ የሰው ህይወት ያሳለፉ የተቋሙ አባላት ህግ ፊት እንዲቀርቡ፣

ለ) በደረቅ ወንጀል ለታሰሩ እስረኞች የሚደረግ ዝውውር፣ ይቅርታ፣ ምህረት እና አመክሮ ህግ በሚፈቅደውና መድሎ በሌለበት ሁኔታ እንዲፈፀም፣

ሐ) በሁሉም እስር ቤቶች ውስጥ ‹‹ጨለማ ቤት›› በመባል በሚጠሩት የብቻ እስር ቤቶች ውስጥ የታሰሩ እስረኞች ከጨለማ ቤቶቹ ወጥተው ከሌሎች እስረኞች ጋር እንዲቀላቀሉ።

መ) የምግብ፣ የውሃ፣ የአልባሳት፣ የግል ንጽህና መጠበቂያ ቁሳቁሶች አቅርቦት በአስቸኳይ እንዲሻሻል እንዲሁም እስረኞች ከሚጎበኟቸው ሰዎች በወር የሚፈቀድላቸው 1ዐዐ ብር በቂ ባለመሆኑ ክልከላው እንዲነሳ፣ የመረጃ በነፃነት የማግኘት መብታችን እንዲከበር (ሬድዩ የማዳመጥና የግሉ ሚዲያ ውጤቶች የሆኑ ጋዜጦች እንዲገቡልን) የርቀት ትምህርት መማር እንዲፈቀድ፣ ከውጭ የሚላኩልንን ፖስታዎች በአግባቡ እንዲደርሱን።

8ኛ፦ በህገ መንግሥቱ አንቀጽ 28 ላይ በተደነገገው መሠረት በሰው ልጆች ላይ አሰቃቂ ድብደባና አካል ማጉደል ወንጀል መሆኑን በመፃረር በሀገሪቱ ያሉ የምርመራ ጣቢያዎች በተለይም በፌዴራል ፖሊስ ወንጀል ምርመራ (ማእከላዊ) ውስጥ ይህንን ወንጀል የፈፀሙና እየፈፀሙ ያሉ የፖሊስና የደህንነት አባላት ለፍርድ እንዲቀርቡ።

9ኛ፦ በሀገራችን ያለውን የፖለቲካ፣ የኢኮኖሚና ማህበራዊ ምስቅልቅል በዘላቂነት ለመፍታት መንግሥትና ተቃዋሚ የፖለቲካ ኃይሎች ብሔራዊ መግባባትና እርቅ እንዲያወርዱ። በመጨረሻም በአሁኑ ወቅት ሀገሪቱ ያለችበትን አሳሳቢ ሁኔታ በአግባቡ በመረዳት ልዩነትንና ህልውናን ጠብቆ ለጋራ የነፃነት አጀንዳ በጋራ ተባብሮ መታገል የወቅቱ ዋነኛ ጥያቄ በመሆኑ የሀገሪቱ የፖለቲካ ኃይሎች ሁሉ ተባብረው እንዲታገሉና የኢትዮጵያ ህዝብም ከጎናቸው እንዲቆም ጥሪያችንን እናቀርባለን። በመጨረሻም ከዚህ በላይ በዝርዝር ያቀረብናቸው ጥያቄዎች ተገቢውን ትኩረትና ምላሽ ያገኙ ዘንድ ለጊዜው ስማችን ከዚህ በታች የተዘረዘረው የፖለቲካ እስረኞች ከአርብ ሚያዚያ 24 ቀን እስከ እሁድ ሚያዚያ 26 ቀን የሚቆይ የ3 ቀን የረሃብ አድማ አድርገናል።

ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ!!
1ኛ አቶ ዘሪሁን ገ/እግዚአብሔር
2ኛ አቶ ደረጀ አበበ
3ኛ አቶ ናትናኤል መኮንን
4ኛ አቶ ክንፈ ሚካኤል ደበበ (አበበ ቀስቶ)
5ኛ አቶ አንዷለም አያሌው
6ኛ ሻ/ል የሽዋስ ይሁንአለም
7ኛ አቶ ምትኩ ዳምጤ
8ኛ አቶ አበበ መልኬ
9ኛ አቶ ማንደፍሮ አካልነው
1ዐኛ አቶ ገበየሁ ብዙነህ
11ኛ አቶ ዩሐንስ ተረፈ
12ኛ አቶ መሠለ ድንቁ
13ኛ አቶ ፍቃዱ ባሳዝን
14ኛ አቶ የገባው አለሙ
15ኛ አቶ እሱባለው አሌ
16ኛ አቶ ጥላሁን ባለው
17ኛ አቶ አስቻለው አራጋው
18ኛ አቶ በእውቀት ደሳለኝ
19ኛ አቶ ካሳሁን ጌጡ

ግልባጭ
- ለኢትዮጵያ ተቃዋሚ የፖለቲካ ድርጅቶች በሙሉ
- ለተባበሩት መንገሥታት ድረጅት የሰብአዊ መብት ኮሚሽን
- ለአውሮፓ ህብረት የሰብአዊ መብት ኮሚሽን
- ለአሜሪካ መንግሥት የውጭ ጉዳይ መ/ቤት
- ለአፍሪካ ህብረት የሰብአዊ መብት ኮሚች
- ለ Human Rights watch
- ለ Amnesty international
- ለ CPJ እና ለሀገር ውስጥና ለውጭ የሚዲያ ተቋማት በሙሉ፡፡

Addis Ababa’s brutal regime on a killing spree again

May 2/2014
The brutal TPLF minority regime has been arresting, torturing and mercilessly killing Ethiopians for the past 23 years. As recently as last week, the regime in Ethiopia made a house to house search and arrested Blue Party leaders and members who were in the process of staging a peaceful demonstration. This week the regime’s security forces arrested three journalists, social media activists and six pro-democracy bloggers (founders of a group known as Zone Nine). Yesterday, Addis Ababa’s killing machine that has zero tolerance for dissent struck again, killing Oromo students and innocent civilians who protested Addis Ababa’s new Master Plan that enlarges the area of the city by evicting poor Oromo peasants from their ancestral land and annexing surrounding towns against the will of the Oromo people.
On April 30, 2014 armed security forces opened fire on Oromo students who were waging a peaceful protest in the town of Ambo, Western Oromia. According to CNN iReport and eye witness testimonies, the TPLF security forces shot and killed more than 30 people including 8 students, and wounded unspecified amount of protesters.
Ginbot 7, Movement for Justice, Freedom and Democracy condemns the killing of peaceful demonstrators in its strongest terms and holds the Ethiopian regime fully accountable for its indiscriminate killing of innocent civilians, and for all political and social unrests that unfold with the killing. Ginbot 7 strongly believes that regardless of their ethnic and religious background, all citizens of Ethiopia have the right to freely express their ideas and wage peaceful demonstrations. Ginbot 7 urges the TPLF regime to immediately and unconditionally alienate itself from the “Gun solves everything” attitude and understand or comprehend that it’s about time to be civil.
The TPLF regime must understand that the Oromo students have every right to protest when the regime uproots their mothers and fathers from their ancestral land and sells the land to foreigners and its surrogates. The demand of the Oromo students is simple and unambiguous; it is to halt the forced eviction of the Oromos from their land. The answer to this legitimate demand is not and will never be killing people.
The recent crackdown and arrest of journalists, bloggers and human right activists took place days before US Secretary of State John Kerry set his foot on the soil of Ethiopia, and yesterday’s killing of peaceful demonstrators happened while Kerry was having talks with those who ordered the killing. It is clear now that the TPLF regime with its ethno-biased economic and political policies is taking Ethiopia to the brink of civil war with impunity. Ginbot 7 believes that if such a scenario unfolds, it could unravel this great multi-ethnic nation and has the potential to destabilize the entire Horn of Africa. It is the responsibility and strong desire of Ginbot 7 to remind the international community, especially the United States and other donor nations to save Ethiopia from this seemingly imminent danger of disintegration. Ginbot 7 also uses this opportunity to make a call to all Ethiopians to come together and save our great nation from the grave danger of disintegration.

Rest in Peace to those who gave their life to the cause of freedom,
We shall overcome !

Friday, May 2, 2014

Ethiopia protest: Ambo - A witness told the BBC that 47 were killed by the security forces

May 2/2014
MINILIK SALSAWI
At least nine students have died during days of protests in Ethiopia's Oromia state, the government has said.

However, a witness told the BBC that 47 were killed by the security forces.

She said the protests in Ambo, 125km (80 miles) west of Addis Ababa began last Friday over plans to expand the capital into Oromia state.

The government did not say how most of the deaths had been caused but the Ambo resident said she had seen the army firing live ammunition

"I saw more than 20 bodies on the streets," she said.

"I am hiding in my house because I am scared."

The Ambo resident said that four students had been killed on Monday and another 43 in a huge security crackdown on Tuesday, after a huge demonstration including many non-students.

Since then, the town's streets have been deserted, she said, with banks and shops closed and no transport.

She said teaching had been suspended at Ambo University, where the protests began, and students prevented from leaving.

In a statement, the government said eight people had died during violent protests led by "anti-peace forces" in the towns of Ambo and Tokeekutayu, as well as Meda Welabu University, also in Oromia state.

It said one person had been killed "in a related development" when a hand grenade was thrown at students watching a football match.

The statement blamed the protests on "baseless rumours" being spread about the "integrated development master plan" for the capital.

BBC Ethiopia analyst Hewete Haileselassie says some ethnic Oromos feel the government is dominated by members of the Tigre and Amhara communities and they would be loath to see the size of "their" territory diminish with the expansion of Addis Ababa, which is claimed by both Oromos and Amharas.

Image

The student protestors are from Ethiopia's biggest ethnic group, the Oromo, numbering around 27 million people.

Oromia is the country's largest region, completely surrounding the capital Addis Ababa, although the city is itself part of the Amhara region.

Its people speak their own language - Oromifa - and see themselves as very different from the Amhara.

The protesters believe they face losing their regional and cultural identity if plans to extend Addis Ababa's administrative control into parts of Oromia get the go-ahead.

Some have also raised fears of the potential for land grabs.

The so called "master-plan" for Addis Ababa is currently out for public consultation and the government says people are being given opportunities to raise their concerns.

Officials say the plan has been well publicised and will bring city services to poor rural areas.

The protestors claim they merely wanted to raise questions about the plan - but were answered with violence and intimidation.
http://www.bbc.com/news/world-africa-27251331
 

ኢቲቪ የአንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ (አንድነት) እሁድ የሚያደርገውን ሰላማዊ ሰልፍ ማስታወቂያ አላስተናግድም አለ፡፡

May 2/2014
የአንድነት ፓርቲ የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ሀብታሙ አያሌው
አንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ (አንድነት) እሁድ ሚያዝያ 26 ቀን 2006 ዓ.ም ለሚያደርገው ሰላማዊ ሰልፍ የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ድርጅት አላስተናግድም ማለቱን የአንድነት ፓርቲ የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ሀብታሙ አያሌው ገለጹ፡፡ የህ/ግ ኃላፊው እንደገለጹት ከሆነ ማንኛውንም ህጋዊ አካል ወይንም ዜጋ በእኩልነት ማስተናገድ የሚገባው የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ምንም አይነት ህጋዊ ምክንያት ሳያቀርብ አናስተናግድም ማለቱ አንድ የሕዝብ አገልጋይ ነኝ ከሚል ተቋም የማይጠበቅ እና ተቋሙ በእርግጥም የህዝብ አገልጋይ አለመሆኑን በድጋሚ በተግባር ያረጋገጠበት ነው ሲሉ ገልጸዋል፡፡ እንደ ህዝብ ግንኙነቱ ገለፃ ፓርቲው ጉዳዩን በቸልታ እንደማያየው እና ወደ ፍርድ ቤት እንደሚወስደውም ታውቋል፡፡ የኢትዮጵያ ቴሌቪዢን የማስታወቂያ ክፍል ኃላፊ አቶ ሰይፉ አለምሰገድና ወ/ት ሸዋዬ የማስታወቂያ ክፍል ኤክስፐርት በእጅ ስልካቸው ደውለን ምላሽ ለመስጠት ፈቃደኛ ባለመሆናቸው የነሱን ሀሳብ ልናካትት አልቻልንም፡፡

etv

ሰበር ዜና- የኢትዮጵያ ጋዜጠኞች መድረክ (ኢጋመ) ፕሬዝደንት ጋዜጠኛ በትረ ያቆብ ተሰደደ

May 2, 2014
Journalist Betre Yakobከሳምንት በፊት የኢትዮጵያ ጋዜጠኞች መድረክ ፕሬዝዳንትና ምክትል ፕሬዝዳንት በአፍሪካ ህብረት ጋባዥነት የኢትዮጵያን ችግርና አፈና በተለይ በሚዲያው ላይ ያለውን ጫና እና ጋዜጠኞች ላይ የሚደርሰውን አፈና ለመግለጽ ወደ አንጎላ አቅንተው ነበር፡፡ በጉዳዩ ላይ ሰፊ ማብራሪያ የሰጡ ሲሆን ለአፍካ ህብረትም የመፍትሄ ሀሳብ ማቅረቡና ለሰብአዊ መብት ኮሚሽነሩም መልስ መስጠቱ ይታወቃል፡፡
ጋዜጠኛ በትረ ያቆብ ስብሰባው ከተጠናቀቀ በኋላ ወደ አገሩ ለመመለስ በሚዘጋጅበት ወቅት የዓለም አቀፍ የጋዜጠኛ ማህበራትን ጨምሮ ሌሎች የዓለም አቀፍ ተቋማት ሳይቀሩ እሱን ለማሰር የተደረገው ዝግጅት በተጨባጭ ማስረጃ ስላቀረቡለት መሰደዱን የነገረ ኢትዮጵያ ምንጮች ገልጸዋል፡፡ የዞን ዘጠኝ ጦማሪዎች በታሰሩበት ወቅት ፖሊስ የበትረ ያቆብን ቤት በመፈተሸ ያገኘውን ወረቀት ሁሉ እንደወሰደም ምንጮቻችን ጨምረው ገልጸዋል፡፡
ጋዜጠኛ በትረ ያቆብ አንጎላ በተደረገው የአፍሪካ ህብረት ስብሰባ ኮሚሽነሩን በግል እንዳገኛቸውና ኮሚሽነሩም በቅርቡ ወደ ኢትዮጵያ እንደሚመጡ በመግለጽ እንዲሚያገኙት ቃል ገብተውለት እንደነበር ተገልጿል፡፡ በተጨማም ከበርካታ የአፍሪካ ህብረት ባለስልጣናት ጋር ስለ ኢትዮጵያ ወቅታዊ ሁኔታና በሚዲያው ላይ ስለሚደረገው ጫና የተወያዩ ሲሆን አብዛኛዎቹ በተለያዩ መንገዶች እገዛ ለማድረግ ቃል ገብተውለት እንደነበር ከታማኝ ምንጮች ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡ በስብሰባው ወቅት ኢትዮጵያንና የኢትዮጵያ ጋዜጠኞች መድረክን ወቅታዊ ሁኔታ የሚገልጹ ጽሁፎች ለተሰብሰብሳቢዎቹ ተበትነዋል፡፡
የኢትዮጵያ ጋዜጠኞች መድረክ መቋቋም ያስፈራቸው ሌሎች የጋዜጠኞች ማህበራት በትረ ያቆብን ለሂውማን ራይትስ ዎች፣ ለሲፒጄ፣ ለአርቲክል 19ና ሌሎች የጋዜጠኞች ማህበራት ይሰራል፣ ይሰልላል፣ የእነዚህ ድርጅቶች ተላላኪ ነው፣ ሪፖርት ይጽፋል በሚል በመግለጫቸውና ‹‹የጋዜጠኞች ክብ ጠረጴዛ›› በተባለው ፕሮግራም ይከሱት እንደነበር ጋዜጠኛ በትረ ያቆብ አገር ውስጥ በነበረበት ወቅት ለነገረ ኢትዮጵያ ገልጻል፡፡
ነገረ ኢትዮጵያ / Negere Ethiopia

ከአዲስ አበባ ካርታ ጋር በተያያዘ የሚደረገው ተቃውሞ እንደቀጠለ ነው

May1/2014
ኢሳት ዜና :












የመስተዳድሩ  ባለስልጣናት ያወጡትን የከተማዋን አዲስ ማስተር ፕላን ተከትሎ በተለያዩ ዩኒቨርስቲዎች የሚገኙ የኦሮሞ ተወላጆች የጀመሩት ተቃውሞ ወደ ተለያዩ ዩኒቨርስቲዎችና ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች በመዛመት ላይ ነው። በአምቦ ቁጥራቸው በውል ያልታወቁ ተማሪዎች በፌደራል ፖሊሶች ሲገደሉ በድሬዳዋ ደግሞ በመቶዎች የሚቆጠሩ ተማሪዎች ታስረዋል። በአዳማ የተጀመረው ተቃውሞ የረገበ ቢመስልም ውጥረቱ ግን አሁንም እንዳለ ነው።

ዛሬ ደግሞ በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የ6 ኪሎ ተማሪዎች ተቃውሞ ለማድረግ እንቅስቃሴ በጀመሩበት ወቅት የዩኒቨርስቲው ሃላፊዎች ተማሪዎችን አነጋገርው ተቃውሞውን ጋብ እንዲል አድርገውታል። የክልሉ ባለስልጣናት በነገው እለት ተማሪዎችን ያነጋግራሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ ለማወቅ ተችሎአል። በግንደ በረት የሁለተኛ ደረጃ ተማሪዎች ባስነሱት ተቃውሞም እንዲሁ በርካታ ተማሪዎች ተጎድተዋል።

ተማሪዎች አርሶደሮችን ከመሬታቸው በህገወጥ መንገድ ማፈናቀሉ እንዲቆም እየጠየቁ ሲሆን፣ የመንግስት ባለስልጣናት በበኩላቸው እቅዱ በአዲስ አበባ ዙሪያ ያሉ አርሶ አደሮች ከልማቱ ተጠቃሚ ይሆናል በማለት ህዝቡን ለማሳመን እየጣሩ ነው።

ይህ በእንዲህ እንዳለ የአሜሪካየውጪጉዳይሚኒስትርሚስተርጆንኬሪ  አዲስአበባበገቡበትዕለትበኢትዮጽያ የአሜሪካኤምባሲከአዲስአበባ እናኦሮሚያየጋራየማስተርፕላንጋርተያይዞበዩኒቨርሲቲተማሪዎች የተቀጣጠለውንተቃውሞመነሻበማድረግአሜሪካዊያንበተለይወደ አምቦአካባቢእንዳይጓዙመግለጫ አውጥቷል።

ኢምባሲው በአምቦ የተነሳውን ከፍተኛ ተቃውሞ ተከትሎ ወደ አካባቢው የሚሄዱ አሜሪካውያን ጥንቃቄ እንዲያደርጉ አሳስቧል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ ግንቦት7 የፍትህ ፣ የነጻነትና ዲሞክራሲ ንቅናቄ  የመንግስት የጸጥታ ሃይሎች በኦሮሞ ሕዝብና ወጣቶች ላይ እያካሄደው ያለውን አረመኔያዊ ጭፍጨፋ፣ እስርና አፈናን በጥብቅ አውግዟል። ህወሓት፣ ኦህዴድ እና በዚህ ጭፍጨፋ እጃቸው ያለበት ሁሉ ከተጠያቂነት የማያመልጡ መሆኑንም ገልጿል።

“የኦሮሚያ ወጣቶች በአዲስ አበባ ማስተር ፕላን ስም የድሀ ገበሬዎች መፈናቀልን መቃወማቸው ፍትሀዊ ነው” ያለው ግንቦት7፣  የወያኔ “ማስተር ፕላኖች” የወያኔ የዘረፋ እቅዶች መሆናቸው በተደጋጋሚ የታየ ጉዳይ ነው ሲል አክሏል።

ወያኔ ኦሮሚያን ብቻ ሳይሆን መላዋን ኢትዮጵያ በምስለኔዎቹ አማካይነት እየገዛ የኢትዮጵያን ውድ ልጆች በራሳቸው ጉዳይ ባይተዋር አድርጓቸዋልሲል የሚኮንነው ግንቦት7፣  ወጣቶች በአካባቢያቸው ጉዳይ ብቻ ሳይሆን በመላው ኢትዮጵያ ጉዳይ እንደሚያገባቸው፣ ድምፃቸው ሊሰማ እንደሚገባ ገልጿል።

“የሌላው አካባቢም ወጣት የኦሮሚያ ገበሬ መፈናቀል እንደሚያገባው፣ ኢትዮጵያዊያን በኢትዮጵያ ውስጥ በሚደረግ ጉዳይ ሁሉ እንደሚያገባውና፣ በየትኛውም የኢትዮጵያ ክልል ውስጥ ወያኔ የራሱን እቅድ እንዲጭንብን አንፈልግም። ” ሲል አቋሙን አንጸባርቋል።

ግንቦት 7: የፍትህ፣ የነፃነትና የዲሞክራሲ ንቅናቄ፣ መላው የኢትዮጵያ ሕዝብ፣ የኦሮሞ ወጣቶች ጥያቄ የመላው ኢትዮጵያ ሕዝብ ጥያቄ አድርጎ እንዲወስድም ጥሪ  አድርጓል።  ”

በጉራፈርዳና በቤንሻንጉል የተጀመረው መፈናቀል ዛሬ አዲስ አበባ አጎራባች ከተሞች ደርሷል። በአምቦ ይህንን የተቃወሙ ወጣቶች በግፍ ተጨፍጭፈዋል፤ በሌሎች ቦታዎችም ላይ ግድያውና እስሩ በርትቷል። ወጣቱ  የጥይት እራት ሆኖ እስኪያልቅ መጠበቅ አንችልም፤ ሁሉም ትግሉን ይቀላቀል።” ብሎአል።

በአንድ ወይም በሌላ መንገድ የወያኔን አምባገንነት የተቃወሙ በሙሉ የጥቃቱ ሰላባዎች ሆነዋል የሚለው ግንቦት7፣ ለሰልፍ ቅስቀሳ አደረጋችሁ በሚል የታሰሩ የሰማያዊ ፓርቲ ወጣቶች ሰልፉ ተደርጎ  ካለቀ በኋላም አለመፈታታቸውን ፣ ሀሳባቸውን በቲዩተር እና ፌስ ቡክ ማኅበራዊ ሚዲያዎች ሲገልጹ የነበሩ የዞን ዘጠኝ አባላት በአሸባሪ ድራማ በታጀበ ትዕይንት ወደ ማሰቃያ ሥፍራ ከተወሰዱ ቀናት መቆጠራቸውን” በመግለጽ ይህ ሰቆቃ ፣ ጭፍጨፋና አፈና ይቁም” ብሎአል።

አንድነት ፓርቲ ለኢሳት በላከው መግለጫም እንዲሁ በሰፊው የኦሮሞ ህዝብ እና ልጆች ላይ እየተፈፀመ ያለውን ግፍ በአጽንኦት እናወግዛለን ብሎአል።

“ምንም አይነት ህዝባዊ ውይይት ሳይደረግበት ከሰማይ ዱብ ያለው የአዲስ አበባ እና ኦሮሚያ ልዩ ዞን የተቀናጀ የልማት መሪ ፕላን ያስቆጣቸው የኦሮሞ የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ሰልፍ በማድረጋቸው የደረሰባቸውን ህገ ወጥ ድብደባና እስራት” አንድነት በእጅጉ እንደሚቃወመው ገልጿል።

ተማሪዎቹ ለተቃውሞ አደባባይ ቢወጡ ተፈጥሯዊ እና ህገ መንግስታዊ መብታቸው ሊከበር በተገባ ነበር ያለው ፓርቲው፣ ነገር ግን ሁሉን ነገር ካልጋትኳችሁ የሚለውና ለዴሞክራሲያዊ ሽንፈት የማይገዛው ኢህአዴግ በተማሪዎቹ ላይ ያደረሰውን ጥቃት እንቃወማለን ብሎአል።

የታሰሩ ተማሪዎችም በአስቸኳይ እንዲፈቱ፣  የኦሮሞ ተማሪዎችን በገፍ ከዩኒቨርሲቲ የትምህር ገበታቸው በማባረር የሚታወቀው የኢህአዴግ መንግስት ከዚህ ተደጋጋሚ ተግባሩ ታቅቦ ልጆቹን በአስቸኳይ ወደ ትምህርት ገበታቸው እንዲመልስም ጠይቋል።በአጠቃላይ መሬት የዜጎች መያዣ መሆኑ እንዲቀር እንታገላለን ያለው አንድነት፣  ዜጎች በመሬታቸው የመደራደር እውነተኛ መብት ሊኖራቸው እንደሚገባ ተቃውሞ የሚያነሱ ዜጎችም ድምፅ እንዲሰማም አሳስቧል።

ጋዜጠኛ ነብዩና የአንድነት ሊቀመንበር ታሰሩ – ፖሊስ ህገ ወጥ እስሩን ቀጥሏል አንድነቶችም በእስሩ አልበረገጉም

May1/2014
ዳዊት ሰሎሞን
ጋዜጠኛ ነብዩና የአንድነት ሊቀመንበር ታሰሩ
ጋዜጠኛ ነብዩ ሃይሉ የቀስቃሾቹን እንቅስቃሴ ለመዘገብ በወጣበት ለእስር ተዳርጓል፡፡በካዛንቺስ ፖሊስ ጣብያ ከነብዩ ጋር የአዲስ አበባ የአንድነት ሊቀመንበር ዘካሪያስ የማነብርሃንና ዘላለም ደበበ ይገኙበታል፡፡የጣብያው ኃላፊዎች ‹‹ቤተ መንግስት አካባቢ ቀስቅሳችኋል››የሚል ውንጀላ አቅርበውባቸዋል፡፡
ፖሊስ ህገ ወጥ እስሩን ቀጥሏል አንድነቶችም በእስሩ አልበረገጉም
ከአዲስ አበባ መስተዳድር እውቅና ለተቸረው ሰላማዊ ሰልፍ የአንድነት አባላት በራሪ ወረቀት በማደል፣ፖስተሮችን በመለጠፍና በመኪና ቅስቀሳ ሲያደርጉ የእውቅናው ደብዳቤ እውቅና ግልባጭ የደረሰው ፖሊስ አባላቱን በማሰር ስራ መጠመዱ አስገራሚ ቢሆንም የፓርቲው አባላት ቅስቀሳውን ከማድረግ አልተቆጠቡም፡፡
ፖሊሶቹ ለያዟቸው የአንድነት አባላት ወረቀት ለመበተን፣ፖስተር ለመለጠፍና የመኪና ላይ ቅሰቀሳ ለማድረግ ፈቃድ አምጡ በማለት ይጠይቃሉ፡፡ነገር ግን ለሰላማዊ ሰልፍ እውቅና ከሚሰጥ ወረቀት በስተቀር ለቅስቀሳ ተብሎ የሚሰጥ ወረቀት ባለመኖሩ የፖሊስን እስር አስገራሚም አስተዛዛቢም አድርጎታል፡፡ 
የአንድነት አባላት በአሁኑ ወቅት በካዛንቺስ፣በቦሌና ንፋስ ስልክ ፖሊስ ጣብያዎች ታስረው ይገኛሉ፡፡
6110

miilion v 2

Leave a Reply

- See more at: http://satenaw.com/amharic/?p=439#sthash.h4pkwR8I.dpuf

Thursday, May 1, 2014

በሕገ ወጡ መጅሊስ ውስጥ መፈንቅለ ስልጣን መደረጉ ተነገረ!

May 1/2014

በሕገ ወጡ መጅሊስ ውስጥ መፈንቅለ ስልጣን መደረጉ ተነገረ!
ፕሬዚዳንቱ በሌሉበት ሥልጣናቸውን ተነጥቀዋል!
ረቡእ ሚያዝያ 22/2006

በዶ/ር ሽፈራው እና በደህንነት መስሪያ ቤቱ አማካኝነት የሚመሩት የአዲስ አበባ እና የአማራ መጅሊስ አመራሮች መፈንቅለ ሥልጣን ዛሬ መፈጸማቸውን የቅርብ ምንጮች ገለጹ! ይኸው መፈንቅለ ስልጣን የፌዴራል መጅሊስና የአዲስ አበባ መጅሊስን ያመሰ እንደሆነም ተገልጿል፡፡ በዛሬው መፈንቅለ ስልጣን የፌዴራል መጅሊስ ፕሬዚዳንት ሸኽ ኪያር ሸኽ መሀመድ አማን፣ የፌዴራል መጅሊስ ዋና ጸሀፊ አቶ ሙሀመድ አሊ፣ ከአዲስ አበባ መጅሊስ ደግሞ ኢንጂነር ተማምና ሌላ አንድ ሀላፊ መነሳታቸውን ምንጮች ገልጸዋል፡፡
ከስልጣናቸው ተነሱ የተባሉት ፕሬዝደንቱ ሸኽ ኪያር በአሁኑ ሰአት ከአገር ውጪ በሳኡዲ አረቢያ የሚገኙ መሆናቸው ታውቋል፡፡ በዛሬው መፈንቅለ ሥልጣን በሸኽ ኪያር ቦታ የኦሮሚያ ክልል ተወካዩ መተካታቸው ሲገለጽ፣ የአማራው ክልል ተወካይም የኡለማ ም/ቤቱን መረከባቸው ተሰምቷል፡፡

በዚህ ዛሬ ተጠናቀቀ በተባለው መፈንቅለ ስልጣን ታጋይ የነበሩት የትግራይ ተወካይና ም/ፕሬዝደንት ሸኽ ከድር፣ የአዲስ አበባው መጅሊስ ፕሬዝደንት ዶ/ር አህመድ እና የአማራ መጅሊስ ተወካይ አይነተኛ ሚና እንደነበራቸው የታወቀ ሲሆን ከኋላቸውም ዶ/ር ሽፈራውና የደህንነት ሀላፊዎች ሲመሩት ቆይቷል፡፡ የስልጣን ሽኩቻው ረዘም ላለ ጊዜ የቆየ ሲሆን በድሬዳዋ ከተማ በተካሄደው ጉባኤ ላይም ፈንድቶ እስከመውጣት ደርሶ ነበር፡፡ የሽኩቻው ዋነኛ ምክንያትም ከመንግስት በኩል በግዳጅ ህዝበ ሙስሊሙ ላይ ለመጫን ሲሞከር የነበረው የአህባሽ አስተሳሰብ ዳግም በህዝበ ሙስሊሙ ላይ መጫኑ እንዲቀጥል በሚፈልጉት ወገኖች እና ‹‹ህዝበ ሙስሊሙ ሲቃወመው የነበረው የግዳጅ ጠመቃ ቆሞ መጅሊሱ ሁሉንም ሙስሊም በአንድነት ሰብስቦ እና አቻችሎ መቀጠል አለበት›› በሚሉት ዛሬ ከስልጣን በተወገዱት ሀላፊዎች መካከል ያለው የአቋም ልዩነት መሆኑ ታውቋል፡፡

እስካሁን በነበረው ሂደት የመጅሊሱ ፕሬዝደንት ‹‹መጅሊሱ ህዝበ ሙስሊሙን የሚጠቅም እና በሰላም እንዲኖር የሚያደርግ እንጂ ችግር ውስጥ የሚያስገባ አካል መሆን የለበትም›› የሚል ፅኑ አቋም ይዘው የነበረ ሲሆን በሸኽ ከድር በሚመራው ቡድን እየተደረገ ያለውን ህዝበ ሙስሊሙን ዳግም ወደ ተቃውሞ ሊያስገባ የሚችል ትንኮሳ በመቃወምም ለተለያዩ የመንግስት አካላት ደብዳቤ መፃፋቸው ታውቋል፡፡

በሕገ ወጡ መጅሊስ ውስጥ ከላይ እስከታች የሚታየው የስልጣን ሽኩቻ የተቋሙን አመራር ሕገ ወጥነት አመላካች ከመሆኑም በላይ በመንግስት የተሰጠውን የቤት ስራ ለመፈጸም የተሰባሰበ ቡድን መሆኑንም ክስተቱ እማኝነት ሰጥቷል፡፡

በጉዳዩ ዙሪያ ተጨማሪ መረጃዎችና ማብራሪያዎች በነገው እለት ይኖሩናል - ኢንሻአላህ!

ትግላችን እስከድል ደጃፎች ይቀጥላል!
ድምፃችን ይሰማ!
አላሁ አክበር!

በኖርዌይ የዲሞክራሲያዊ ለውጥ በኢትዮጵያ ድጋፍ ድርጅት ኖርዌይ አባሎች አንድነትና ሰማያዊ ፓርቲ የሚያደርጉትን ሰላማዊ ትግል እንደሚደግፍ አጋርነታቸውን አሳዩ

 May 1/2014 

በዛሬው ቀን በኖርዌይ በተከበረው አለም አቀፍ የሰራተኞች ቀን ላይ በመገኛት የዲሞክራሲያዊ ለውጥ በኢትዮጵያ ድጋፍ ድርጅት ኖርዌይ አባሎች አንድነትና ሰማያዊ ፓርቲ  በሀገር ቤት እያደረጉ ያሉትን ሰላማዊ ትግል እንደሚደግፋ አጋርነታቸውን ሲያሳዩ ውለዋል::

May 1/2014 በዛሬው ቀን በኖርዌይ በተከበረው አለም አቀፍ የሰራተኞች ቀን ላይ በመገኛት የዲሞክራሲያዊ ለውጥ በኢትዮጵያ ድጋፍ ድርጅት ኖርዌይ አንድነትና ሰማያዊ ፓርቲ በሀገር ቤት የሚደረገውን ሰላማዊ ትግል እንደሚደግፍ አጋርነቱን አሳያ::
ሜይ 1, አለም አቀፍ የላብ አደሮችና የሰራተኞች ቀን በየአመቱ በመላው አለም በተለያዩ አህጉራት በደማቅ ሁኔታ እንደሚከበር ይታወቃል:: ይህ መከበር ከጀመረ ከመቶ ሃያ አመት በላይ የሆነው የላብ አደሮችና የሰራተኞች ቀን ዘንድሮም ሜይ 1 ቀን 2014 (ሚያዚያ 23 ቀን 2006 ዓ.ም ) በተለያዩ አህጉራት ተከብሮል::
በዛሬውም ቀን ሜይ 1 ቀን 2014 በኦስሎና በኖርዌይ በተለያዩ ከተሞች በደማቃ ሁኔታ የተከበረ ሲሆን የተለያዩ የፖለቲካ ድርጅቶች፣ በሰብአዊ መብትድርጅቶች፣ ሌሎችም ድርጅቶች እንዲሁም በኖርዊይ የሚኖሩ የተለያዩ ሀገራት ማህበረሰብ ክፍሎች (community) የየሀገራቸውን ባንዲራ እና የየድርጅታቸውን አርማ በመያዝ የሰራተኛውን መብት መከበር የሚጠይቁና ሌሎችንም የተለያዩ መፈክሮችን፣ አርማዎችን መያዝ በደማቅ ሁኔታ አክብረዋል::
በኦስሎ እና በተለያዩ ከተሞች የሚኖሩ የዲሞክራሲያዊ ለውጥ በኢትዮጵያ ድጋፍ ድርጅት ኖርዌይ አባሎች የድጋፍ ድርጅቱ ለአባሎቹ ባደረገላቸው የሰልፍ ጥሪ መሰረት ተሳታፊ የሆኑ ሲሆን በዚሁ በኢትዮጵያ ሕዝብ ላይ የሚደርሰውን የሰብዊ መብት እረገጣ የተቃወሙ ሲሆን ለአንድነት እና ሰማያዊ ፓርቲ ያላቸውንም ድጋፍ አሳይተዋል:: በአሁኑ ሰአት የወያኔ መንግስት በኢትዮጵያሕዝብ ላይ እያደረሰ ያለውን የሰበሃዊ መብት እረገጣ ፣አፈና፣ እስራትና ግድያ በመቃወም አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ (አንድነት) እና ሰማያዊ ፓርቲ ሰለማዊ ትግል እያደረጉ እንዳለና በሰላማዊ ትግል የወያኔን መንግስት እየተፋለሙት እንደሆነ ይታወቃል::

የዲሞክራሲያዊ ለውጥ በኢትዮጵያ ድጋፍ ድርጅት ኖርዌይ አባሎችና አመራሮች የተለያዩ መፈክሮችን በመያዝ እና በማሰማት ለአንድነት እና ሰማያዊ ፓርቲ ያላቸውን የድጋፍ አጋርነታቸውን በማሳየት በደማቅ ሁኔታ አክብረዋል::
ድል ለኢትዮጵያ ሕዝብ !!! 

ዲሞክራሲያዊ ለውጥ በኢትዮጵያ ድጋፍ ድርጅት ኖርዌይ

ጭፍጨፋውና አፈናው ይቁም፤ ወያኔ ይወገድ !!!

May 1/2014

ግንቦት 7: የፍትህ፣ የነፃነትና የዲሞክራሲንቅናቄ፣ ዘረኛው ወያኔ በኦሮሚያ ሕዝብና ወጣቶች ላይ እያካሄደው ያለውን አረመኔያዊ ጭፍጨፋ፣ እስርና አፈናን በጥብቅ ይቃወማል። ህወሓት፣ ኦህዴድ እና በዚህ ጭፍጨፋ እጃቸው ያለበት ሁሉ ከተጠያቂነት የማያመልጡ መሆኑን ያስገነዝባል።
የአሮሚያ ወጣቶች በአዲስ አበባ ማስተር ፕላን ስም የድሀ ገበሬዎች መፈናቀልን መቃወማቸው ፍትሀዊ ነው። የወያኔ “ማስተር ፕላኖች” የወያኔ የዘረፋ እቅዶች መሆናቸው በተደጋጋሚ የታየ ጉዳይ ነው። ነዋሪዎቹን ያላማከረ፣ ግንባር ቀደም ባለጉዳዮችን ባለቤት ያላደረገ፣ የሕዝብ ይሁንታ ያላገኘ ማስተር ፕላን ተፈፃሚ ማድረግ አይቻልም።
ወያኔ ኦሮሚያን ብቻ ሳይሆን መላዋን ኢትዮጵያ በምስለኔዎቹ አማካይነት እየገዛ የኢትዮጵያን ውድ ልጆች በራሳቸው ጉዳይ ባይተዋር አድርጓቸዋል። ኦህዴድ በወያኔ ቅጥረኛነት የኦሮሚያ ወጣቶችን በማስጨፍጨፍ ላይ ያለ እኩይ የአድርባዮች ስብስብ ነው።  ወጣቶች የተቃወሙት ይህንን ነው።እነዚህ ወጣቶች በአካባቢያቸው ጉዳይ ብቻ ሳይሆን በመላው ኢትዮጵያ ጉዳይ ያገባቸዋል። ድምፃቸው ሊሰማ ይገባል። የሌላው አካባቢም ወጣት የኦሮሚያ ገበሬ መፈናቀል ያገባዋል። ኢትዮጵያዊያን በኢትዮጵያ ውስጥ በሚደረግ ጉዳይ ሁሉ ያገባናል። በየትኛውም የኢትዮጵያ ክልል ውስጥ ወያኔ የራሱን እቅድ እንዲጭንብን አንፈልግም።
ግንቦት 7: የፍትህ፣ የነፃነትና የዲሞክራሲ ንቅናቄ፣ መላው የኢትዮጵያ ሕዝብ፣ የኦሮሞ ወጣቶች ጥያቄ የመላው ኢትዮጵያ ሕዝብ ጥያቄ አድርጎ እንዲወስድ ጥሪ ያደርጋል።  በጉራፈርዳና በቤንሻንጉል የተጀመረው መፈናቀል ዛሬ አዲስ አበባ አጎራባች ከተሞች ደርሷል። በአምቦ ይህንን የተቃወሙ ወጣቶች በግፍ ተጨፍጭፈዋል፤ በሌሎች ቦታዎችም ላይ ግድያውና እስሩ በርትቷል። ወጣቱ  የጥይት እራት ሆኖ እስኪያልቅ መጠበቅ አንችልም፤ ሁሉም ትግሉን ይቀላቀል።
የወያኔ የጥቃት ሰለባ የሆኑት የአዲስ አበባ ማስተር ፕላን ጉዳይን ያነሱ ወጣቶች ብቻ  አይደሉም። በአንድ ወይም በሌላ መንገድ የወያኔን አምባገንነት የተቃወሙ በሙሉ የጥቃቱ ሰላባዎች ናቸው። ለሰልፍ ቅስቀሳ አደረጋችሁ በሚል የታሰሩ የሰማያዊ ፓርቲ ወጣቶች ሰልፉ ተደርጎ  ካለቀ በኋላም አልተፈቱም።  ይህ ሰቆቃ ማብቃት አለበት።
ጭፍጨፋውና አፈናው ይቁም፤ ወያኔ ይወገድ !!!
ድል ለኢትዮጵያ ሕዝብ !!!

በኦሮሚያ የተጀመረው ተቃውሞ መካረረ ስጋት ፈጥሯል

ኦህዴድ የተከፋፈለ አቋም ይዟል፤ ኢህአዴግ ጉልበት መርጧል
demo


በኦሮሚያ የተለያዩ ከተሞች የተቃውሞ ድምጽ ለማሰማት በሞከሩና ተቃውሟቸውን ለመግለጽ ሰልፍ በወጡ ወገኖች ላይ አገዛዙ የ”ከፋ” ነው የተባለ ሃይል መጠቀሙ ተሰማ። ቁጥራቸው በውል የማይታወቅ ታስረዋል። ለተቃውሞ መነሻ በሆነው አዲሱ የአዲስ አበባ ማስተር ፕላን ላይ ኦህአዴድ ተመሳሳይ አቋም መያዝ አልቻለም። ችግሩን በሰላማዊ መንገድ መፍታት ያልቻለው ኢህአዴግ ጉልበት መምረጡ አገሪቱ ውስጥ ካለው የተከማቸ ብሶቶች ጋር ተዳምሮ አለመረጋጋቱን ያሰፋዋል የሚል ስጋት አለ።
ከኦሮሚያ ክልል አስተዳደር የጎልጉል ምንጮች እንዳሉት በአቀራረቡ ቢለያይም ከተለያዩ ሚዲያዎች የሚሰሙት ዜናዎች ሊስተባበሉ የሚችሉ አይደሉም። በታችኛው እርከን የሚገኙትን ጨምሮ የሁለተኛ ደረጃ ተማሪዎች፣ የዩኒቨርሲቲ ማህበረሰብ በጥቅሉ፣ ገሃድ አይውጣ እንጂ በመዋቅር ውስጥ ያሉ ሰራተኞችና ካድሬዎች የተቃውሞው ተሳታፊና ደጋፊ መሆናቸውን ክልሉም ሆነ ኢህአዴግ አረጋግጠዋል።
የአዲስ አበባ አዲሱ ማስተር ፕላን በዙሪያዋ ያሉትን ስድስት የኦሮሚያን ከተሞችና ስድስት የገጠር ቀበሌዎች የተካተቱበት መሆኑ ያስነሳው ተቃውሞ ቀደም ሲል በክልሉ በምክር ቤት ደረጀ በካድሬዎች ተቃውሞ አጋጠመው። ይህንኑ ተከትሎ ከሳምንት በፊት በአንዳንድ የትምህርት ተቋማት ብልጭ ድርግም ሲል የነበረው ተቃውሞ እየጠነከረ መጣ። የክልሉ የጎልጉል ምንጭ “ተቃውሞው እንደሚጨምር፣ ካድሬውም የተቃውሞው ስውር አጋር እንደሆነ፣ በመረጃ ትንተና አስቀድሞ ይታወቅ ነበር። በዚሁ መሰረት አስቀድሞ አመጹን ማምከን ካልተቻለ የማያዳግም ርምጃ እንዲወሰድ ለፌዴራልና ለመከላከያ አባላት መመሪያ ተሰጥቷል”።
የሰላማዊ ሰልፍ በሚጀመርበት አካባቢ ሌላውን “ሊያስተምር” የሚችል ከበድ ያለ የሃይል ርምጃ እንዲወሰድ በተላለፈው መመሪያ መሰረት ተግባራዊ ቢደረግም ረብሻውና የተቃውሞ እንቅስቃሴው እየሰፋ መሄዱን የጎልጉል መረጃ አቀባይ ይናገራሉ። ከከተማ ወደ ከተማ እየሰፋ የሄደው ተቃውሞ፣ የተቃውሞው አካል በሚመስሉ የስለላ ሰራተኞች በሚያቀብሉት መረጃ መሰረት ለማስታገስ ቢሞከርም አለመቻሉ ኢህአዴግ ውስጥ ጭንቀት ፈጥሯል።
የኦህዴድ አባላት በከፍተኛ አመራር ላይ ያሉትን ጨምሮ ተመሳሳይ አቋም ያልያዙበት አዲሱ የአዲስ አበባ ማስተር ፕላን ጉዳይ በኦሮሚያ የተላዘበውን የፖለቲካ ችግር ሊያባብሰው ይችላል በሚል ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው የኢህአዴግ የፖሊስ የመከላከያ ሃይላት ከልዩ መመሪያ ጋር በተጠንቀቅ እንደቆሙ ምንጩ አመልክተዋል። ይሁን እንጂ በኦህዴድ የታችኛው የቀበሌ መዋቅር ጭምር ተቃውሞው ስለሚደገፍ የአቋም መንሸራተት ሊፈጠር ይችላል የሚለው ስጋት ከፍተኛ መሆኑንንም አልሸሸጉም።
ከተለያዩ የማህበረሰብ አምዶች ሲደመጥ እንደሰነበተውና ሚያዚያ 22፤2006 (ኤፕሪል 30/2014) ቀን የአሜሪካ ሬዲዮ ከስፍራው ሰዎችን በማነጋገር እንደገለጸው ጅማ፣ አዳማ፣ ነቀምት፣ አምቦ፣ ሃሮማያ፣ ድሬዳዋ፣ በመሳሰሉት ከተሞችና የትምህርት ተቋማት ማህበረሰብ ላሰሙት የተቃውሞ ድምጽ የተሰጣቸው ምላሽ ዱላና እስር ነው። ከአምቦ በስልክ ስለሁኔታው የተናገሩ እንዳሉት አላፊ አግዳሚው ሳይቀር “ተጨፍጭፏል”።
በተጠቀሰው ቀን ረፋዱ ላይ የሁለተኛ ደረጃ ተማሪዎች፣ ከሰዓት በኋላ የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ለተቃውሞ ሲወጡ የመከላከያ አንጋቾችና የፌዴራል ፖሊስ አባላት በወሰዱት የሃይል ርምጃ በርካቶች መቁሰላቸውን፣ በነፍስ አውጪኝ አጥር ዘለው የሸሹትን በማሳደድ ጨፍጭፈዋቸዋል። እኚሁ ሰው በስልክ እንደተናገሩት “ሸሽተው ወደ መኖሪያ ቤታቸው የመጡትን ተማሪዎች ለምን ቤትህ አስገባህ ተብዬ ተጨፈጨፍኩ፣ ነፍሴን ለማትረፍ መሬት እየተንከባለልኩ ጮህኩ። ሁለት ልጆቼን ወሰዱ” በማለት ሃዘናቸውን ገልጸዋል። የአምቦ ቤተመንግሥትም እስረኛ እንደሞላው አመልክተዋል።
ለማቅረብ ከያዟቸው ሶስት ጥያቄዎች መካከል አንዱ “ፊንፊኔ ያለው የአጼ ሚኒሊክ ሃውልት ይነሳ የሚል ነው” በማለት ፈርቶ እንደተሸሸገ የተናገረ ተማሪ ከአዳማ ለቪኦኤ ተናግሯል። የቪኦኤው ዘጋቢ ባለስልጣናትን ለማነጋገር ሞክሮ እንዳልተሳካለት፣ በመጨረሻም ከኦሮሚያ ምክር ቤት ያገናቸው ሰው መልስ ሳይመልሱ እንደመሳቅ እያሉ ስልኩን እንደዘጉት በግብር አሳይቷል።
ከምርጫ 97 በፊት አዳማን የኦሮሚያ ዋና ከተማ መደረጓን ተከትሎ የተቀሰቀሰው ችግር ከምርጫ 97 በኋላ ቀውሱ እልባት እንደተበጀለት ይታወሳል። በወቅቱ በሜጫና ቱለማ ማህበር አስተባባሪነት አዲስ አበባ ላይ የተካረረ ሁኔታ ተፈጥሮ እንደነበርም አይዘነጋም። በዚያን ወቅትም የማህበሩ ሊቀመንበር አቶ ድሪቢን ጨምሮ በርካቶች ታስረው ነበር። ኢህአዴግ አቋሙን ለምርጫ ቀውስ ማርገቢያ በሚል ሲቀይር፣ ድርጊቱን አስቀድመው በመቃወማቸው የተገረፉ፣ የታሰሩና ከስራ እንዲሰናበቱ የተደረጉ ካሳ ሊሰጣቸው እንደሚገባ በወቅቱ ተገልጾ ነበር።
አገሪቱ ላይ ከተንሰራፋው የተለያየ ችግር ጋር ተዳምሮ በኦሮሚያ የተጀመረው ተቃውሞ እንዳይካረር ስጋት የገባቸው ክፍሎች “ኢህአዴግ ጉልበት እየተጠቀመ የሚዘራውን ቂምና ቁርሾ ካላቆመ፣ ጠብመንጃ እጄ ላይ ነው በማለት የሚፈጽመውን ግፍ በማቆም ለእርቅ ካልሰራ አሁን ባለው ሁኔታ ነገሮች ከቁጥጥር ሊወጡ” እንደሚችሉ ማስጠንቀቂያ ይሰጣሉ፤ ጂኒው አንዴ ከሳጥኑ ከወጣ በኋላ ልዩነት ሳያደርግ የሚያመጣው መዘዝ ለህወሃት/ኢህአዴግና በቅድሚያ ከዚያም ለሥርዓቱ ባለሟሎች በተዋረድ የሚባላ እሣት እንደሚሆን ታስቦ ካሁኑ መፍትሔ ሊበጅለት ይገባል ይላሉ።

ሰሚ ጆሮ ያጣ የሕዝብ እሮሮና ጩኸት እስከመቼ? ገዛኸኝ አበበ ከኖርዌይ ሌና

By Gezahegn Abee (Norway Lena )

 ዛሬ ሀገራችን ኢትዮጵያ ካለችበት የኢህአዲግ ስርአት ለመላቀቅ እና ከገባችበት ፖለቲካዊ ማህበራዊ እና ኢኮኖሜያዊ ውድቀት ወጥታ ህዝቡም ከወያኔ ስርዓት ተላቋ ወደ ተሻለ እና ወደ ተረጋጋ ሕይወት ለመድረስ ሁሉም ዜጋ የበኩሉን ድርሻ መወጣት እና በሁሉም አቅጣጫ እና በሚችለው መንገድ መታገል ይጠበቅበታል:: ዛሬ ላይ ወያኔ ኢህአዲግ የእምነታችንን ነጻነት እያሳጣን የዜጎቻችን ሰብዓዊ መብት እየረገጠ እና የዜግነት ክብራችንን እና ነፃነታችንን በመግፈፍ የባርነት ኑሮ እየኖርን እንገኛለን::  መቼም በአሁኑ ጊዜ በጨቋኙ የወያኔ ስርአት ያልተማረረ የህብረተሰብ ክፍል ያለ አይመስለኝም ስለሆነም ማንኛውም ኢትዮጵያዊ ዜጋ ሁሉ ሀይማኖት፣ ዘርና፣ቋንቋ
ሳይዘው ሊጠይቀው የሚገባ የመብትና የነጻነት ጥያቄ ሊሆን የሚገባው  እስከ መቼ ? በወያኔ መንግስት የግፍ ስርዓት  እየተጨቆኑ መኖር ብለን እራሳችንን ልንጠይቅ ያስፈልጋል::

በርግጥ በአሁኑ ሰአት ሁሉም ኢትዮጵያዊ ዜጋ ሀገር ቤትም የሚኖረው ከሀገር ውጭ ተሰዶ የሚኖረውም (ዲያስፖራ) ኢትዮጵያዊ በሚችለው መንገድ ሁሉ ወያኔንን በመቃወም እና በመፋለም የወያኔ መንግስት በኢትዮጵያ ሕዝብ ላይ እያደረሰ ያለውንም ግፍ እና በደል ለአለም ህዝብ እና መንግስታቶች ለማሳወቅ የበኩሉን ድርሻ እየተወጣ  እንዳለ ይታወቃል::በተለይም  በወያኔ መንግስት ጨቋኝ እና ዘረኛ አገዛዝ ተጠቂ የሆነው በሀገር ውስጥ የሚኖረው ኢትዮጵያዊ ሕዝባችን ከማንኛውም ጊዜ  በባሰ ችግር ውስጥ እንደሚገኝ እና እየደረሰበት ካላው ችግር የተነሳ በየጊዜው ድምጹን እያሰማ እንዳለ ይታወቃል:: በሀገር ውስጥም ሆነው መሰዋህትነትን  እየከፈሉ ያሉ  በሰለማዊ ትግል የወያኔን አቅም ማሽመድመድ እና ከስልጣን ማስወገድ ይቻላል በማለት አምነው እና ቆርጠው የተነሱት እንደ ሰመያዊ ፓርቲ እና አንድነት ለፍትህና ለዲሞክራሲ የመሰሉ ፓርቲዎች ሕዝቡ ብሶቱን እና ምሪቱን በአደባባይ እንዲያሰማ  እያደረጉት ያለው ሰላማዊ ትግል የሚያስመሰግናቸው ነው :: እነዚህ ፓርቲዎችም  የኢትዮጵያ ሕዝብ ህገ መንግስታዊ መብቱን እንዲያስከብርና ለነጻነቱም እንዲታገል እያነቁት ሲሆን ፣ በአሁኑ ሰአት ለመብቱ እና ለነጻነቱ በየጊዜው ድምጹን እያሰማ እና በአደባባይ እየጮኸ  ይገኛል :: ቢሆንም ሀገርን እመራለው ሕዝብንም አስተዳድራለው ብሎ ከተመጠው መንግስት ነኝ ባይ አካል ግን ምንም አይነት የሕዝቡን እሮሮና ጩኸት አዳምጦ የሕዝብን ጥያቄ የመመለስ ነገር አይታይም::

የኢትዮጵያ ሕዝብም ሕገ መንግስታዊ መብቱን ተጠቅሞ ሀገርን እመራላው ብሎ ለተቀመጠው አካል ድምጹን ማሰመትና መብቱን መጠየቅ ሕገ መንግስታዊ መብቱ ቢሆንም ነገር ግን ይሄ መብቱ ሲከበርለት አይታይም :: በወያኔ መንግስት በኩል በተቃራኒው የሚሆነው ግን ሌላ ነው ሕዝቡ ብሶቱን ለማሰማት በተነሳ ጊዜ ዜጓችን ማዋከብ፣ ማስፈራራት፣ ማሰርና፣ የተለያዩ በደሎችን በዜጎቹ ላይ መፈጸመ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተባባሰ የመጣ አሳሳቢ የሆነና የወያኔ መንግስት የለመደው የእለት በእለት ተግባሩ ሆኖል::

በርግጥ በአሁኑ ጌዜ የምርጫም ጊዜም እየደረሰ ከመሆኑም የተነሳ ሕዝብን ለማታለልና በኢትዮጵያ ላይ ዲምክራሲ እንዳለ ለማስመሰል በምህራባውያን ዘንድ የፖለቲካ ቁማሩ እንዳይበላሽበት በፓርቲዎች ጥያቄ ሳይወድም ቢሆን በስንት መከራ ሰላማዊ ሰልፎችን የማድረግ መብትን የፈቀደ ቢመስልም  ሕዝብን እና የፖለቲካ ድርጅት አመራሮችን ግን በአይነ ቁራኛ በመከታተል ፣ በማዋከብ፣በማሰር ላይ ይገኛል:: ሕዝቡ በተለያያ ጊዜ በሰላማዊ ሰልፎች በየጊዜው ጩኸቱን እያሰማ ቢሆንም የሕዝብ ጩኸት ግን  አዳማጭ ያገኘ አይመስልም:: በአሁኑ ጊዜ በተለያዩ ሰላማዊ ሰልፎች ሕዝቡ  እየጠየቀ ላለው ጥያቄ የወያኔ መንግስት የሕዝብን ጩኸት ሰምቶና አዳምጦ መልስ ይሰጣል ብሎ ማሰብ ሲበዛ እጅግ የዋህነት ይመስለኛል:: የወያኔ መንግስት ለኢትዮጵያ ሕዝብ ችግር፣ መከራ ምንም የማያሳስበው መንግስት እንደሆነ በተለያየ ጊዜ ያየነውና የተረዳነው ነገር ሲሆን በአለም ላይ በተለያዩ ሀገራት ከሚኖሮ ሕዝቦች መካካል በአሁኑ ጊዜ እንደ ኢትዮጵያ ሕዝብ እየተዋረደና መከራ እየደረሰበት የሚኖር ያለ ሕዝብ ያለ አይመስለኝም በቅርቡ እንኮን እንደምናስታውሰው በሳውድ አረቢያ በጨካኝ አረመኔ አረቦች ሕዝባችን በአደባባይ እንደ በግ ሲታረድ በአለም ዙሪያ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ሁሉ ከዳር እስከ ዳር በአንድነት በኢትዮጵያዊ ስሜት በጩኸት ድምጻቸውን ሲያሰሙ በጊዜው በወያኔ መንግስታቶች ዘንድ የሕዝባችን እንደ በግ በአደባባይ መገደል እንደ ምንም ነገር ቦታ ያልተሰጠው ጉዳይ እንደነበር እና የወያኔን መንግስት በብዙዎች ዘንድ ለትዝብት የዳረጋቸው ክስተት እንነበር የቅርብ ጊዜ ትዝታችን ነው ::

ይህ የኢትዮጵያ ሕዝብ በሀገሩ ላይም መኖር አቅቶታል ጮኸቱንም ያሰማል የሕዝቡም ጩኸት ማብቂያ ያለው አይመስልም ሰመያዊ ፓርቲም ቢሆን አንድነት ለፍትህና ለዲሞክራሲ ፓርቲ በአሁን ሰአት ሕዝቡ ብሶቱንና በመንግስት ላይ ያለውን ተቃውሞ እንዲያሰማ በየጊዜው የሰለማዊ የተቀውሞ ሰልፎችን እያዘጋጁ እና በወያኔ መንግስት ላይ የተቃውሞ ድምጻቸውን እያሰሙ ቢሆኑም  የወያኔ መንግስት ግን የሕዝብን ጥያቄ የመመለስ አዝማሚያ አይታይበትም  ነገር ግን  በስልጣን ላይ ያለው መንግስት የሕዝብን እሮሮና ብሶት ማዳመጥ ሕገ መንግሥታዊ ግዴታው ነው፡፡ እነ እስክንድር ፣ርዕዮትና ፣ አንዶለም ሌሎቹም የፖለቲካ እስረኞችና ጋዜጠኞች  በየእስር ቤቶች ውስጥ በእስር በማቀቅ ላይ ባሉበት ሁኔታ መላው የኢትዮጵያ ሕዝብና የአለም የሰባሃዊ መብት ተከራካሪዎች ሳይቀሩ ያለበደላቸውና ያለሀጢያታቸው በግፍ በእስር ላይ ያሉ እስረኞች  ከእስር እንዲፈቱ በየጊዜው በመጠየቅና በውጭ ሀገርም በሀገር ውስም የሚኖሩ ኢትዮጵያ ዜጎች በተለያዩ ሰላማዊ ሰልፎች በመሰብሰብ ስለወገኖቻችን ቢጮኽምጩኸቱም ሰሚ ጆሮ ያጣ ጩኸት እየሆነ ይገኛል::

የኢትዮጵያ ሕዝብ በየጊዜው ጋዜጠኞችና የፖለቲካ እስረኞች ከእስር እንዲፈቱ በሰላማዊ ሰልፎች ይጮኻል ነገር ግን የወያኔ መንግስት ህገ መንግስቱን አክብሮና የሕዝብን ጩኸት ሰምቶ ለሕዝብ ጥያቄ መልስ መስጠት ሲገባው ያለምክንያት ያስራቸውን ዜጓች ከእስር ከመፍታት ይልቅ የሕዝብን ጩኸት ጆሮ ዳባ ልበስ በማለት ከቀን ወደ ቀን ሕዝብን በማተራማስና ሌሎች ንጹሃን ዜጎችንም እያደኑ በመያዝና በማሰር ስራ ላይ ተደምጦል::

 እነ አንዷለም አራጌ ፣እነ በቀለ ገርባ ፣ እና ናትናሄል እና ሌሎችም እስረኞች ከቃሊቲ እንዲወጡ ሕዝብ እየጮኸ ባለበት ሁኔታ ሌሎች በብዙዎች የሚቆጠሩ አንዷለሞች፣ ሌሎች በቀለዎች፣ ሌሎች ናትኖሄሎች ለእስር እየተዳረጉ ነው እነ ርዕዮት አለሙ፣ እስክንድር ነጋ፣ ውብሸትንና ሌሎች በግፍ የታሰሩ ጋዜጠኞች ከእስር እንዲፈቱ እየጮኽን ባለንበት ሁኔታ ሌሎች ርዕዮቶችና ሌሎች እስክንድሮች፣ ሌሎች ውብሸቶች ወያኔ በሚያቀርባቸው የሃሰት ውንጀላዎች እየተከሰሡ ወደ እስር ቤት እየተወረወሩ ሲሆን  ሰሞኑንም እያየን ያለነው ያለነው ይኼንኑ ነው :: ሕዝብን አስሮ የማሰቃየት ሀባዜ የተጠናወጠው አንባ ገነኑ የወያኔ መንግስት በማን አለብኝነት የዞን ዘጠኝ ጦማርያን እና ሌሎች  ጋዜጠኞችን በማያዝ አስሯቸዋል::እነዚህ ወገኖቻችን  ምንም የተደበቀ አጀንዳ የሌላቸው ግን ህገ መንግስቱ ላይ የሰፈረው ሃሳብን በነፃነት የመግለፅ መብት ይከበር ያሉና በህገ መንግስቱ መስረት የሕገ መንግስቱን አንቀፅ እየጠቀሱ የሃሳብ የመግለፅ መብታቸውን የተጠቀሙ ሶስት ጋዜጠኞችን እና ስድስት ብሎገሮችን በተለያየ የሀሰት ወንጀል በመወንጀል ለእስር መዳረጉ ወያኔ ምን ያህል በእምቢርተኝነት ልቡን እያደነደነ ያለ አንባ ገነን መንግስት እንደሆነ በገሃድ ቁልጭ አድርጎ ያሳይ ሀቅ ነው::  ይህ ሁሉ ግን የሚያሳያው ወያኔ በስልጣን ላይ እስካለ ድረስ ዜጎችን በተለያየ የሀሰት ውንጀላ በመወንጀል ማሰረኑንና ሕዝብን ማሰቃየቱ እንደማይቀር የሕዝቡም ስቃይ፣ መከራ፣ እስራታ እና ግድያ እስከ መቼ እንደዚህ ይቀጥላል ? የእኔም ጥያቄ የብዙዎቻችን ጥያቄ የወያኔ አንባ ገነንተ እስከ መቼ ? ሰሚ ጆሮ ያጣው የሕዝብ ሮሮ እና  ጮኸትስ እስከ መቼ ?

እንደእኔ አመለካከት ህዝባችን በሚያደርገው ሰላማዊ ሰልፎች አረመኔው የወያኔ መንግስት ለሕዝቡ ጥያቄ  መቼም ቢሆን መልስ ለመስጠት ፍቃደኛ  ይሆናል ብዪ አላስብም::ነገር ግን የወያኔን መንግስት ይበልጥ ሊያዳክሙ የሚችሉትን ስልቶችን ( strategy) በመንደፍ ትግላችንን ብንቀጥል ወያኔን ማንበርከክ ይችላል የሚል እምነት አለኝ:: ለነገ የሕዝብ እሮሮ እና ጩኸት ተሰምቶ ህገ መንግስቱ የሚከበርባትንና ዜጎች በነጻነት የሚኖሩባት ኢትዮጵያን እየተመኛው ለዛሬ ጹሁፊን ላጠቃል ::

ውድቀት ለአንባ ገነኖች!!
  gezapower@gmail.com

Wednesday, April 30, 2014

በ10 ብር ከገበሬው ተነጥቆ በ19 ሺህ ብር እንደሚሸጥ አንድነት አጋለጠ (በኦሮሞ ተማሪዎች ዙሪያ የአንድነትን መግለጫ ይዘናል)

April 30/2014

ኢሕአዴግ በተለያዩ የአገራችን ክፍሎች በንጹሃን ኢትዮጵያዉያን ላይ ፣ በተለይም ሰሞኑን በኦሮሞ ተማሪዎች ላይ እያደረሰ ያለዉ ሕግ ወጥና ኢሰብአዊ ጥቃት አወገዘ። ዜጎችን የሚያምኑበትን የመናገር ሙሉ መብት እንዳላቸው ያስቀመጠው የአንድነት መግለጫ፣ ተቃዉሞ የሚያስሙ ወገኖች ሊደመጡ እንጂ ሊደበደቡና ሊታሰሩ እንደማይገባም ይገልጻል።

አንድነት፣ በቅርቡ የሚሊዮኖች ድምጽ ለመሬት ባለቤትነት በሚል መርህ፣ አዲስ አበባን ጨመሮ በበርካታ የአገሪቷ ክፍሎች እንቅስቃሴ በማድረግ ላይ ይገኛል። ኢሕአዴግ መሬትን እንደ መጨቆኛና መበዝበዣ መሳሪያ አድርጎ እየተጠቀመበት እንዳለ የሚገልጸው የአንድነት መግለጭ፣ ከድሃው ገበሬ አሥር ብቻ በመስጠት የነጠቀዉን መሬት በ 17 ሺህ ብር በጨረታ እንደሚሽጥ እና ልማት ሳይሆን ገበሬዉን በማፈናቀልና በማደህየት የሚደረግ ዘረፋ እያደረገ እንዳለ ለማሳየት ሞክሯል።
ከጥቂት አመታት በፊት በመቀሌ ፣ በተለይም ከኤርትራ የመጡ ስደተኞች ከሚኖርባቸው ቤቶች፣ የሚኖሩበት አካባቢ ለልማት ያስፈልጋል ተብሎ በሃይል እንዲፈናቀሉ መደረጉ፣ በጋምቤላ ደግሞ ከመሬት ጋር በተገናኘ በሺሆች የሚቆጠር በአገዛዙ በግፍ መገደላቸዉ ይታወቃል። በቤኔሻንጉል ጉሙዝ፣ በአምቦ አካባቢ ፣ በወለጋ እንዲሁም ሌሎች በርካታ ቦታዎች ፣ ዜጎች «ይሄ አገራችሁ አይደለም» በሚል፣ ከአንድ ብሄረሰብ በመሆናቸው ብቻ የተፈናቀሉበት ሁኔታ እንዳለ በስፋት ተዘግቧል።
የአንድነት ፓርቲ በመገለጫዉ፣ የታሰሩ የኦሮሞ ተማሪዎች በአስቸኳይ ተፈተዉ ወደ ትምህርት ገበታቸው እንዲመለሱ ጥይቋል።
በአንዳንድ የኦሮሞ ተማሪዎች አካባቢ «ኦሮሚያ የኦሮሞዎች ናት፣ አዲስ አበባ የኦሮሚያ ናት» የሚሉ፣ በአንዳንድ ዉጭ ባሉ አክራሪዎች የሚሰማ መፈክር በስፋት ሲስተጋማ እንደነበረ፣ ከዚህም የተነሳ ብዙዎች የኦሮሞ ተማሪዎች በሚያነሱት ጥያቄ ላይ ቅሬታ እንዳደረባቸው በመግልጽ እየጻፉ ነው።
በኦሮሚያን እና በአዲስ መካከል ግዛቱ የትና እንዴት መሆን እንዳለበት፣ የአንድነት ፓርቲ አስተያየት ከመስጠት ተቆጥቧል። እንደዚያም ቢሆን ግን ፣ ፓርቲዉ አሁን ያለው በቋንቋ ላይ የተመሰረተዉ ፌዴራል አወቃቀር፣ ያለ ሕዝብ ፍቃድ በጉልበት በሕዝቡ ላይ የተጫነ በመሆኑ፣ እንደገና ቋንቋን ጨምሮ፣ የሕዝቡን አሰፋፈር፣ ጂዮግራፊን፣ ኢኮኖሚን ፣ የሕዥቡን ፍላጎት እንደኢሁም ሌሎች ነጥቦች ባካተተ መልኩ እንደገና መዋቀር አለበት እንደሚያምን በፖለቲካ ፕሮግራሙ በግልጽ አስቀምጧል። ለፓርቲዉ ቅርበት ያላቸው እንደሚናገሩት፣ አሁን በኦሮሚያና በአዲስ መካከል የተፈጠረው ዉዝግብ አሁን ያለው ፌደራል አወቃቀር ያመጣው ጣጣ እንደሆነ በማስረዳት፣ የፌደራል አወቃቀሩ እንደገና ፣ ሁሉን አቀፍና ዴምክራሲያዊ በሆነ መንገድ ከተዋቀረ፣ ብዙ ችግሮች እልባት እንደሚያገኙ ይናገራሉ።

ሰማያዊ ፓርቲ የአርበኞችን ቀን ሊያከብር ነው – በተጨማሪም የሰማያዊ ፓርቲ አመራሮችና አባላት ቅጣት ተጣለባቸው

April 30/2014

ሰማያዊ ፓርቲ ሚያዝያ 27/2006 ዓ.ም የአርበኞችን ቀን በጽ/ቤቱ ታዋቂ የታሪክ ተመራማሪዎችንና ሌሎች ምሁራንን ጋብዞ እንደሚያወያይ ምክትል የህዝብ ግንኙነቱ አቶ እምላዕሉ ፍስሃ ለነገረ ኢትዮጵያ ገልጸዋል፡፡

ምክትል የህዝብ ግንኙነቱ እንዳስታወቁት ስነ ስርዓቱ ሰኞ ሚያዝያ 27 ከጠዋቱ 3 ሰዓት የሚጀምር ሲሆን ማንኛውምኢትዮጵያዊ በፕሮግራሙ መሳተፍ ይችላል ብለዋል፡፡ ‹‹የስነ ጽሁፍ ተሰጥዖ ያላቸውና በበዓሉ ስራቸውን ማቅረብ የሚፈልጉ ኢትዮጵያውያንንም እንዲሳተፉ እንፈልጋለን ያሉት ኃላፊው›› ፕሮግራሙን ወጣቶች ስለ አባቶቻቸው ታሪክ እንዲያውቁ ከማድረግም ባሻገር ስራቸውን በማስታወስ ታካቸውን ለመዘከር እንደሚፈልጉ አክለው ገልጸዋል፡፡

 የሰማያዊ ፓርቲ አመራሮችና አባላት ህግን ለማስከበር በመጣራቸው ተጨማሪ ቅጣት ተጣለባቸው 

ሚያዝያ 19/2006 ዓ.ም ለተካሄደው ሰላማዊ ሰልፍ በቅስቀሳ ላይ የታሰሩት የሰማያዊ ፓርቲ አመራሮችና አባላት በ1000 (አንድ ሺህ ብር) ዋስ እንዲወጡ መወሰኑን ተከትሎ ‹‹እኛ ነጻ ነን፡፡ ገንዘብ አስይዘን እንወጣም፡፡ ስራችን ህግ ማስከበር እስከሆነ ድረስ እየታሰርንም ቢሆን ህግ
እናስከብራለን፡፡ በመሆኑም ነጻ እስካልተለቀቅን ድረስ እሰሩን፡፡›› በማለታቸው ተጨማሪ ክሶችና ቅጣቶች እየተጣለባቸው ነው፡፡ በትናትናው ዕለት ሜሮን አለማየሁና ትግስት ወንዲፍራው ‹‹ግቢ በመረበሸ›› ተጨማሪ ክስ መከሰሳቸው ይታወቃል፡፡ በአሁኑ ወቅት በቤላፖሊስ ጣቢያ የሚገኙ 14 ያህል የሰማያዊ ፓር አመራሮችና አባላትም ተመሳሳይ ክስየተመሰረተባቸው ሲሆን ባለፈው ከፍላችሁ ውጡ ከተባሉት 1000 (አንድ ሺህ ብር) በተጨማ 600 (ስድስት መቶ ብር) ጨምረው ከፍለው እንዲወጡ ተፈርዶባቸዋል፡፡

እነዚህ አመራሮችና አባላት መጀመሪያ የካ ፖሊስ ጣቢያ ታስረው የነበሩ ቢሆንም እስረኛውን በማሳመጽና በመረበሽ
ከመከሰሳቸውም በተጨማሪ ወደ ቤላ ፖሊስ ጣቢያ ተዛውረዋል፡፡ በወቅቱ ድብደባና ማዋከብ እንደደረሰባቸው የሚናገሩት
ታሳሪዎቹ ‹‹ህግን ለማስከበር የምናደርገውን ጥረት እንደ ህገ ወጥነት ተቆጥሮ ተጨማሪ ክስና በደል ቢፈጸምብንም እኛ ህግ
ማስከበራችንን እንቅጥላለን›› ብለዋል፡፡

በተመሳሳይ በጉለሌ ፖሊስ ጣቢያ የሚገኙትና ዛሬ ስምንት ሰዓት ላይ ፍርድ ቤት የቀረቡት የሰማያዊ ፓርቲ አመራሮችና አባላት
እያንዳንዳቸው 5500 ብር አስይዘው እንዲወጡ ተፈርዶባቸዋል፡፡ ታሳሪዎቹ ይህንን ውሳኔ በመቃወም ‹‹ነጻ ካልተለቀቅን
አንወጣም!›› ያሉ ሲሆን ከዳኛው የተሰጣቸው መልስ እንዳሳዘናቸው ለነገረ ኢትዮጵያ ገልጸዋል፡፡ ‹‹ዳኛውና አቃቤ ህጉ
ተመካክለው ነው የገቡት፡፡ በእያንዳንዳችን 5500 ብር እንድንከፍል ሲፈርዱ፤ ‹እኛ ተማሪዎችና የመንግስት ሰራተኞች ነን
ከየትም አምጥተን መክፈል አንችልም!› አልናቸው፡፡ እነሱ ልክ አንድ ሰው እቃ ሲገዛ እንደሚከራከረው ‹በቃ! 2000 ብር
ይሁንላችሁ› አሉን፡፡›› ያሉት ታሳሪዎቹ በህግ ሳይሆን በዘፈቀደ እየተሰራ መሆኑ አሳዝኗቸዋል፡፡ በሌላ በኩል ‹‹ህገ ወጥ
ቢሆንም በሌላ አካባቢ የታሰሩት የእኛ ጓደኞች 1000 ብር ነው እንዲከፍሉ የተወሰነባቸው፡፡ የእኛውን ለምንድን ነው 5500
ያደረጋችሁት?›› ብለው ሲጠይቁ ዳኛው ‹‹ቅጣቱ ከጣቢያ ጣቢያ ይለያያል፡፡›› የሚል አስገራሚ መልስ እንደሰጧቸው
ገልጸውልናል፡፡

የግሉ ፕሬስ ፈተናዎች የፕሬስ ነፃነትን እየተፈታተኑ ናቸው!

April 30/2014

የፊታችን ቅዳሜ እ.ኤ.አ. ሜይ 3 ቀን 2014 የዓለም የፕሬስ ነፃነት ቀን ይዘከራል፡፡ ‹‹የሚዲያ ነፃነት ለተሻለ መፃኢ ጊዜ-የድኅረ 2015 የልማት አጀንዳን ለመቅረፅ›› በሚል መሪ ቃል በመላው ዓለም የሚዘከረው ይህ ቀን፣ የፕሬስ ነፃነት በአሁኑ ጊዜ በዓለም ዙሪያ ምን ዓይነት ገጽታ እንዳለው ያሳየናል፡፡ እኛም እግረ መንገዳችንን አገራችን ኢትዮጵያን ጨምሮ በተለያዩ አገሮች የሚታዩ የግሉ ፕሬስ ፈተናዎችን እንቃኝበታለን፡፡

 የፕሬስ ነፃነት ቀን በሚታሰብበት ዋዜማ ላይ ሆነን ሰሞኑን በአገራችን ውስጥ በርካታ ቁጥር ያላቸው ጋዜጠኞችና ጦማሪያን (Bloggers) በቁጥጥር ሥር ውለዋል፡፡ ፍርድ ቤት ቀርበውም የጊዜ ቀጠሮ ተጠይቆባቸዋል፡፡ በሕግ በተያዘ ጉዳይ ላይ ለጊዜው በዝርዝር የምናነሳው ጉዳይ ባይኖርም፣ የፕሬስ ነፃነትን ከሚጋፉ ወይም ሐሳብን በነፃነት የመግለጽ መብትን ከሚገዳደሩ ጉዳዮች መካከል አንደኛው የጋዜጠኞች እስራት እንደሆነ ግን የምናልፈው ጉዳይ አይሆንም፡፡ በአንድ ጊዜ በርካታ ጋዜጠኞች ታሰሩ ሲባል ድባቡ ደስ አይልምና፡፡ እስቲ በአገራችን የፕሬስ ነፃነትን የሚጋፉ ዋነኛ የግሉ ፕሬስ ችግሮችን እንቃኝ፡፡

የሙያ ክህሎት ችግር  

እንደሚታወቀው የኢትዮጵያ የፕሬስ ጉዞ አንድ ክፍለ ዘመን ያህል አስቆጥሯል፡፡ ይሁንና ባለመታደል በአገራችን አሁን ያለው የግል ፕሬስ ሥራ ላይ ከዋለ ገና የ22 ዓመታት ዕድሜ ነው ያስቆጠረው፡፡ እነዚህ ሁለት አሥርት ዓመታት የሚያሳዩን የፕሬስ ሙያ ገና በጨቅላ ዕድሜ ላይ መሆኑን ነው፡፡ ይህ ለጋነትና የልምድ አናሳነት በግሉ ፕሬስ የዕለት ተዕለት ሥራ ውስጥ ከፍተኛ የሆነ ችግር እየጋረጠ ነው፡፡ የግሉ ፕሬስ ከሚፈታተኑት ዋነኛ ችግሮች መካከል ተጠቃሽ የሚባለው የሙያ ክህሎት (Professionalism) የሚባለው ነው፡፡ በአገሪቱ ውስጥ የሚገኙ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት አስተምረው የሚያወጡት የሰው ኃይል የገበያውን ፍላጎት የሚመጥን አይደለም፡፡ በዚህም ምክንያት ክህሎት ያላቸውን ባለሙያዎች ማግኘት አዳጋች ሆኗል፡፡

የፕሬስ ተቋማት አቅም ውስንነትና ደካማነት ተባብረው ብቃት ያላቸው ባለሙያዎችን ማፍራት አልተቻለም፡፡ በቂ የሆነ የሙያ ክህሎት ሥልጠና ባለመኖሩ ምክንያት በሚያሳዝን ሁኔታ የሙያ ሥነ ምግባር የለም የማይባልበት ደረጃ ላይ ነው ያለነው፡፡ የሙያ ሥነ ምግባር ባለመኖሩ ምክንያት የግሉ ፕሬስ ከምርመራ ዘገባ ይልቅ በአመዛኙ የግል አስተያየትና ሐተታ ውስጥ ተሰማርቷል፡፡ በተለይ ቁጥራቸው በማይናቅ የፕሬስ ውጤቶች ውስጥ ጋዜጠኝነትና የፖለቲካ አቀንቃኝነት ተደበላልቀው ይታያሉ፡፡ በዚህም ምክንያት በዜና ዘገባና በግል አስተያየት መካከል ያለው ድንበር ባለመታወቁ የሙያውን ሥነ ምግባር ማስጠበቅ አልተቻለም፡፡ ሌላው ቀርቶ በጋዜጠኝነት ስም የሚንቀሳቀሱ ማኅበራት ስያሜውን ከመያዛቸው ውጪ እዚህ ግባ የሚባል ሚና የላቸውም፡፡ ፈተናው ግን እየከበደ ነው፡፡

አንድ ሐኪም የተሰማራበት የሙያ ሥነ ምግባር ከሚጠይቀው ውጪ የእምነት ወይም የፖለቲካ ሰባኪ መሆን እንደሌለበት ሁሉ፣ ጋዜጠኛም የሲቪል ማኅበረሰቡን ወይም የፖለቲካ ፓርቲዎችን ሥራ ተክቶ መሥራት የለበትም፡፡ መሐንዲስ መንገድ፣ ድልድይ ወይም ግድብ ሲገነባ ከሙያ ሥነ ምግባር ወጥቶ አላስፈላጊ ድርጊት ቢፈጽም የሚያደርሰው አደጋ ከፍተኛ እንደመሆኑ መጠን፣ ጋዜጠኛው የሙያ ሥነ ምግባሩን ባለመከተሉና ሙያውን በብቃት ባለመወጣቱ ምክንያት የከፋ አደጋ ይፈጥራል፡፡ ይህም በተለያዩ አገሮች ውስጥ በተፈጸሙ ዘርን ማዕከል ያደረጉ ግጭቶችና ውድመቶች ታይቷል፡፡ ስለዚህ የሙያ ክህሎት ችግር የዘመናችን የግሉ ፕሬስ ፈተና ሆኗል፡፡

የኅብረተሰቡ ግንዛቤ ማነስ

በኅብረተሰባችን ዘንድ ያለው የፕሬስ ሙያ ግንዛቤ አነስተኛ ከመሆኑ አንፃር፣ መረጃን ሙያዊ ሥነ ምግባር ተላብሰው ከሚያቀርቡ ጋዜጦች ይልቅ ለፕሮፓጋንዳና ቅስቀሳ ዓይነት ውጤቶች ትኩረት ሲሰጥ ይታያል፡፡ ጋዜጠኝነት ራሱን የቻለ ሙያ፣ በሥነ ምግባር ደንብ የሚመራና በዚህም ምክንያት በዓለም አቀፍ ደረጃ አንቱታ የተቸረው ሙያ ነው፡፡ በኅብረተሰባችን ዘንድ ግንዛቤው አነስተኛ በመሆኑ፣ ለሙያ ሥነ ምግባር ጥሰት የራሱን አዎንታዊ ሚና ይጫወታል፡፡ ጋዜጠኛው ሙስናን በተጨባጭ እንዳያጋልጥ፣ የመልካም አስተዳደር ተግዳሮቶችን እንዳይጠቁም፣ ለዲሞክራሲና ለሰብዓዊ መብት መከበር እንቅፋት የሚሆኑ ኃይሎችን ተቋቁሞ ዘገባዎችን እንዳይሠራ፣ የሕግ የበላይነት እንዲከበር የራሱን አስተዋጽኦ እንዳያደርግ እንቅፋት እየተፈጠረ ነው፡፡ በተቃራኒው ጋዜጠኞች ከሙያ ሥነ ምግባራቸው እያፈነገጡ የፖለቲከኞችን ሚና ሲተኩና የሙያው ሥነ ምግባር አቅጣጫውን ሲስት በኅብረተሰቡ ዘንድ በቀና መታየቱ የግሉን ፕሬስ ሚና ፈተና ውስጥ ከቶታል፡፡ በተለይ ምሁራን ይህንን የተደበላለቀ አካሄድ ከማቃናት ይልቅ ዝም ብለው ማየታቸው ችግሩን አባብሶታል፡፡ 

የፖለቲካ ፓርቲዎች ያልተገባ አካሄድ

ጋዜጠኝነት በገለልተኝነት መርህ የሚከናወን የተከበረ ሙያ መሆኑ የታወቀ ቢሆንም፣ በአገራችን ገዥውን ፓርቲ ጨምሮ የተለያዩ የፖለቲካ ፓርቲዎች ተላላኪ ሲያደርጉት ይታያሉ፡፡ ጋዜጠኝነት ለማኅበረሰቡ መረጃ የመስጠት ሚናው እየተንኳሰሰ የፖለቲካ ጽንፎች ውስጥ እንዲሸጎጥ ይፈለጋል፡፡ ገዥው ፓርቲ በቁጥጥሩ ሥር ያሉ የመንግሥት ሚዲያዎችን በራሱ አምሳያ ቀርፆ እንደፈለገው ሲጠቀምባቸው፣ ተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲዎችም የግሉ ፕሬስ የእነሱ አፈ ቀላጤ እንዲሆን ይፈልጋሉ፡፡ ሁለቱም ኃይሎች ጋዜጠኞችን እንደፈለጉ በማሽከርከር የፖለቲካ አቋማቸው ማስፈጸሚያ እንዲሆን በሚያደርጉት ጥረት ሙያውን በአሳዛኝ ሁኔታ እየፈተኑት ናቸው፡፡ በዚህም ምክንያት የግሉ ፕሬስ ነፃነትና ገለልተኝነት ጥያቄ ውስጥ እንዲወድቅ በመደረጉ ፈተናው ከብዷል፡፡

የመንግሥት ግዴለሽነት

የቀድሞው የፕሬስ ነፃነት አዋጅ 34/85 ከወጣበት ጊዜ ጀምሮ ላለፉት ሁለት አሥርት በሥራ ላይ ያለው የግሉ ፕሬስ የመንግሥት ድጋፍ ሊያገኝ ቀርቶ በቀና ዓይን እየታየ አይደለም፡፡ መንግሥትና የግሉ ፕሬስ የሚተያዩት በበጎ ዓይን ባለመሆኑ ምክንያት ግንኙነቱ የሻከረ ነው፡፡ በተለያዩ ጊዜያት በተፈጠሩ ችግሮች ምክንያት በርካታ የፕሬስ ውጤቶች ከገበያ ወጥተዋል፡፡ ብዙ ቁጥር ያላቸው ጋዜጠኞች ተሰደዋል፡፡ በእስር ላይ ያሉም አሉ፡፡ የመንግሥትና የግሉ ፕሬስ ግንኙነት ተበላሽቶ ለዓመታት ቢዘልቅም መንግሥት ግዴለሽነት ነው የሚታይበት፡፡ በግሉ ፕሬስና በመንግሥት መካከል መተማመን የለም፡፡ ይህ ያለመተማመን መንፈስ ሁለቱን ወገኖች እንደ ጠላት እንዲተያዩ አድርጓቸዋል፡፡ ውጤቱንም እያየነው ነው፡፡ በመንግሥት ቁጥጥር ሥር ያሉ ሚዲያዎች ከፍተኛ በጀት ተመድቦላቸው ፍትሐዊ ባልሆነ መንገድ የግሉን ፕሬስ ገበያ ውስጥ ይወዳደራሉ፡፡ የግሉ ፕሬስ እንደ ሌሎች ኢንቨስትመንቶች ከቀረጥ ነፃና ማበረታቻ አለማግኘቱ ብቻ ሳይሆን፣ በማተሚያ ቤት የተጋነነ የሕትመት ዋጋ ሲጎሳቆል፣ በሕትመት መጓተት ሲንገላታ፣ ከዚያም አልፎ ተርፎ የሕትመት አገልግሎት ሲከለከል ጠያቂ የለም፡፡ ተጠያቂም የለም፡፡ የግንኙነቱ መበላሸት የግሉን ፕሬስ ፈተና አክፍቶታል፡፡ የነገውን ብሩህ ቀን ለማሰብም ከብዷል፡፡

የግሉ ፕሬስ ባለ ክህሎቶችን እያጣ ነው

የግሉ ፕሬስ ፈተናዎችና ውክቢያዎች ሲባባሱ ወደ ግሉ ፕሬስ መምጣት የሚገባቸው ባለ ክህሎት ወጣቶች እየሸሹ ናቸው፡፡ ሙያውንና የሥነ ምግባር ደንቡን በሚገባ ተረድተው የሚሠሩ ትጉህ ጋዜጠኞች እየተሸማቀቁ ወደ ሌላ የሥራ መስኮች እየተመሙ ናቸው፡፡ ጠንካራ የግል ሚዲያ ለመፍጠር መሠረት ሊሆኑ የሚችሉ እነዚህ ባለ ክህሎቶች በሸሹ ቁጥር የግሉ ፕሬስ የፖለቲካ አቀንቃኞችና ፕሮፓጋንዲስቶች ሰለባ ይሆናል፡፡ ከሁሉም የሚያሳስበው ግን ወጣቱ ትውልድ በዚህ ደስ የማይል ድባብ ምክንያት ሙያውን እየፈለገው ለመሸሽ ተገዷል፡፡ ይህ በራሱ አስከፊ ፈተና ነው፡፡

የግሉ ፕሬስ ኢንቨስትመንት መሳብ አልቻለም

አሁን ባለው ደስ የማይል ድባብና የጥላቻ ስሜት የተከበበው የግሉ ፕሬስ በመስኩ ሊሰማሩ የሚችሉ ኢንቨስተሮች ጭምር እየሸሹት ነው፡፡ በዘመናዊ ቴክኖሎጂዎች እየታገዘ በሙያ ሥነ ምግባር ተገርቶ ሥራውን የሚያከናውን የግል ፕሬስ በመዋዕለ ንዋይ መደገፍ ሲገባው ከአነስተኛና ጥቃቅን ሥራዎች ባልተሻለ ሁኔታ ላይ ይገኛል፡፡ በዚህ ጊዜ የሚዲያ ኢንዱስትሪ ተፈጠረ ብለን መኩራራት ሲገባን ከሱቅ በደረቴ ጋር የሚወዳደር ይመስላል፡፡ የግሉ ፕሬስ በአመርቂ ኢንቨስትመንት እየታገዘ የራሱ ማተሚያ ቤት፣ የቢሮ ሕንፃና የበርካታ ቴክኖሎጂ ውጤቶች ባለቤት መሆን ሲገባው፣ ህልውናው ሳይቀር አስተማማኝ ያልሆነበት ጊዜ ላይ እንገኛለን፡፡ ይህ ራሱ ትልቁ ራስ ምታትና ፈተና ነው፡፡

ምን ይደረግ?

በአገሪቱ ውስጥ ጠንካራ፣ አስተማማኝ፣ በሙያ ሥነ ምግባር የዳበረና የአገሪቱን ተጨባጭ ሁኔታ በሙሉ አቅሙ መግለጽ የሚችል የግል ፕሬስ መኖር አለበት፡፡ መንግሥት የግሉ ሚዲያ ዲሞክራሲያዊት አገር እንድትመሠረት ሚና እንዳለው ይቀበል፡፡ ዕውቅና ይስጥ፡፡ የግሉን ፕሬስ በሚመለከት አሁን ያለው የመንግሥት ፖሊሲ መለወጥ አለበት፡፡ በመንግሥትና በግሉ ሚዲያ መካከል ጥሩ ስሜት ስለሌለ በግልጽ የሚታየው አድልኦ በአስቸኳይ ይገታ፡፡ በአሁኑ ወቅት ያለው የግሉ ፕሬስ ውጤቶች ዋጋ የሕዝቡን የመግዛት አቅም የሚፈታተን በመሆኑ ከውጭ በሚገባ የወረቀት ምርት  ላይ የተጣለው ታክስ ይነሳ፡፡ ለግሉ ፕሬስ ከቀረጥ ነፃና የታክስ ማበረታቻ ይደረግ፡፡ በግሉ ፕሬስ ላይ የሚደረገው ተፅዕኖና ውክቢያ ይቁም፡፡ ለሕግ የበላይነት ቅድሚያ ይሰጥ፡፡ በሕገ መንግሥቱ የሠፈሩ መብቶች ይከበሩ፡፡ በተለይ የፕሬስ ነፃነትን የሚመለከተው ከተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ሁለንተናዊ የሰብዓዊ መብት ድንጋጌዎች አንቀጽ 19 (Article 19) ሙሉ በሙሉ የተቀዳው የሕገ መንግሥቱ አንቀጽ 29 ድንጋጌ ይከበር፡፡ ሕግ ሲከበር የፕሬስ ነፃነት ይከበራል፡፡

በሌላ በኩል ፖለቲከኞችና የፖለቲካ አቀንቃኞች የግሉን ፕሬስ በመቀላቀል ጽንፍ ውስጥ አይክተቱት፡፡ ጋዜጠኝነት ራሱን የቻለ ሙያ ነው፡፡ የራሱ የሥነ ምግባር ደንብና ደረጃ አለው፡፡ ጋዜጠኝነት በገለልተኝነት መርህ ላይ ተመሥርቶ ለማንም ሳያዳላ ማንንም ሳይፈራ የሚከናወን ሙያ በመሆኑ የፖለቲካ መሣሪያ አይሁን፡፡ የፕሬስ ነፃነት ቀንን ስንዘክር በፕሬስ ነፃነት ላይ የተጋረጡ ፈተናዎችን እያሰብን ነው፡፡ ስለሆነም ለፕሬስ ነፃነት የሚታገሉ ወገኖች ሁሉ ይህንን ነፃነት የወረሩ ፈተናዎችን ሊረዱ የግድ ይላል፡፡ የግሉ ፕሬስ ፈተናዎች ከራሱ ጀምሮ ውጭ ድረስ የተንሰራፉ በመሆናቸው ሁላችንንም ሊያሳስበን ይገባል፡፡ ነፃ ፕሬስ፣ ነፃ ሐሳብ፣ ነፃ መንፈስ ስንል የግሉ ፕሬስ የነፃነት አየር ይተንፍስ ማለታችን ነው፡፡ ይህ ነፃነት ደግሞ በኃላፊነት ስሜት ተግባራዊ ይሆን ዘንድ የሚመለከታቸው ሁሉ አፅንኦት ሊሰጡት ይገባል፡፡ የግሉ ፕሬስ ፈተናዎች የፕሬስ ነፃነትን እየተፈታተኑ ናቸው!        

የታሰሩት የሰማያዊ ፓርቲ አመራሮችና አባላት ለሁለተኛ ጊዜ ፍርድ ቤት ይቀርባሉ

April 30/2014

-በዋስ ይለቀቁ የተባሉ አባላት በነፃ ካልሆነ አንወጣም አሉ

-በሊቀመንበሩ መሪነት ሰላማዊ ሠልፍ አደረጉ

ከአዲስ አበባ አስተዳደር ሰላማዊ ሠልፍ ማድረግ እንደሚችሉ ማረጋገጫ ካገኙ በኋላ ቅስቀሳ ሲጀምሩ፣ በፀጥታ ኃይሎች በቁጥጥር ሥር ውለው የታሰሩት የሰማያዊ ፓርቲ

አመራሮችና (ከሊቀመንበሩ በስተቀር) ቁጥጥራቸው 28 የሚደርሱ አባላት ሚያዝያ 22 ቀን 2006 ዓ.ም. ፍርድ ቤት ይቀርባሉ፡፡

ሚያዝያ 16 ቀን 2006 ዓ.ም. በቁጥጥር ሥር ውለው የታሰሩት የፓርቲው የፖለቲካ አደረጃጀት ጉዳይ ኃላፊ አቶ ጌታነህ ባልቻን ጨምሮ 14 አባላት በየካ ክፍለ ከተማ ቤላ ፖሊስ ጣቢያ መታሰራቸውን፣ የብሔራዊ ምክር ቤት ምክትል ሰብሳቢውን አቶ የሸዋስ አሰፋን ጨምሮ ስድስት አባላት ደግሞ ቀጨኔ መድኃኔዓለም አካባቢ ላዛሪስት ትምህርት ቤት አጠገብ በሚገኘው ፖሊስ ጣቢያ መታሰራቸውን የፓርቲው ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ እንደሻው እምሻው አስታውቀዋል፡፡ ሚያዝያ 17 ቀን 2006 ዓ.ም. ምክትል ሊቀመንበሩ አቶ ስለሺ ፈይሳ፣ የሕዝብ ግንኙነቱ አቶ ብርሃኑ ተክለያሬድና ስምንት አባላት የካ ፖሊስ ጣቢያ ታስረው እንደሚገኙ የፓርቲው ጽሕፈት ቤት ኃላፊ ጨምረው ገልጸዋል፡፡

አቶ ስለሺን ጨምሮ የተወሰኑት አባላት አዲስ አበባ ከተማ የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ቀበና ችሎት ሚያዝያ 20 ቀን 2006 ዓ.ም. ቀርበው በአንድ ሺሕ ብርና መታወቂያ ዋስ እንዲለቀቁ ፍርድ ቤቱ ያዘዘ ቢሆንም፣ የፓርቲው አባላት ግን ከእስር ቤት እንደማይወጡ ተናግረዋል፡፡ ምክንያታቸው ደግሞ ፖሊስ ያሰረበትን ምክንያት ፍርድ ቤት ሲጠይቀው ለሰላማዊ ሠልፍ እያሉ ሕዝቡን ሲቀሰቅሱና ሲበጠብጡ በመገኘታቸው መሆኑን ገልጾ ቢያስረዳም፣ ፓርቲያቸው ሰላማዊ ሠልፉን አድርጐ ያለምንም ችግር በሰላም በማጠናቀቁ እነሱም በነፃ እንዲሰናበቱ መጠየቃቸው ነው፡፡

ላዛሪስት ትምህርት ቤት አካባቢ በሚገኘው ፖሊስ ጣቢያና ቤላ ፖሊስ ጣቢያ የታሰሩ የፓርቲው አባላት ሚያዝያ 17 ቀን 2006 ዓ.ም. ፍርድ ቤት ቀርበው ፖሊስ የሰባት ቀን ተጨማሪ የምርመራ ቀን ጠይቆ ስለተፈቀደለት፣ ሚያዝያ 22 ቀን 2006 ዓ.ም. እንደሚቀርቡ ተጠቁሟል፡፡

የፓርቲውን አመራሮቹና አባላቱን ለእስር የዳረገው የሚያዝያ 19 ቀን 2006 ዓ.ም. ሰላማዊ ሠልፍ እንደራሴ አካባቢ ከሚገኘው ቢሮ በተወሰኑ ደጋፊዎች ሊቀመንበሩ ኢንጂነር ይልቃል ጌትነት በሚመሩት አባላት ጉዞውን ወደ ባልደራስ አድርጓል፡፡ ‹‹አትነሳም ወይ አትነሳም ወይ ይኼ ባንዲራ ያንተ አይደለም ወይ? ራበን፣ ጠማን፣ በጨለማ ተዋጥን፣ ኔትወርክ የለም፣ መንገድ የለም…›› የሚሉ መፈክሮችን አንግበውና በድምፅ ማጉያ በማስተጋባት ዓደዋ ድልድይ አደባባይ የደረሰው ሠልፈኛ ለተወሰነ ደቂቃ እንደፈለገው መሄድ አልቻለም፡፡ ከዓደዋ አደባባይ ወደ እንግሊዝ ኤምባሲ በሚያስወጣው መንገድ ሠልፈኛው ሊሄድ ሲሞክር፣ መንገዱ በፖሊሶች የጐንዮሽ ሠልፍ ታጥሮ ‹‹መሄድ ያለባችሁ ወደ መገናኛ በሚወስደው መንገድ ነው፤›› በመባላቸው መግባባት ሳይቻል ቀርቷል፡፡

የፓርቲው ሊቀመንበር ኢንጂነር ይልቃል በጉልበታቸው በርከክ ብለው እጃቸውን ወደ ላይ ሲዘረጉ አንዱ የፓርቲው አባል ሰላማዊ ሠልፉ ከየት ተነስቶ የት እንደሚያበቃ የሚፈቅደውን ወረቀት ለአንድ የፖሊስ ኃላፊ ሲያሳዩአቸው ‹‹መንገዱን ክፈቱት ይሂዱ›› የሚል ትዘዝ በመስጠታቸው በጥሩንባ፣ በፊሽካ፣ በድምፅ ማጉያና በጩኸት የታጀበው ሠልፍ በርከት ባሉ ፖሊሶች እየተመራ ወደ እንግሊዝ ኤምባሲ መውጫ አመራ፡፡ ‹‹We need Electricity, We need Water, We need Transportation, No Network, Free Reeyot, Eskindr, Wubshet, Muslim Brothers, Freedom, Freedom›› የሚሉ መፈክሮችን በእንግሊዝ ኤምባሲ መግቢያ በር ፊት ለፊት በጩኸትና የተለያዩ ድምፆችን ካሰሙ በኋላ፣ ጉዞአቸውን ሰላማዊ ሠልፉ የሚጠናቀቅበት በየካ ክፍለ ከተማ ወረዳ 8 ድንበሯ የእናቶችና ሕፃናት ሆስፒታል ጀርባ አድርጓል፡፡

መንግሥት ፖሊሲውን እንዲያሻሽል ወይም ሥልጣኑን እንዲያስረክብ፣ ዜጐች የመናገር፣ የመጻፍና ሐሳባቸውን በነፃነት የመግለጽ ሕገ መንግሥታዊ መብታቸው እንዲከበር እንዲያደርግ፣ የሚሉ መፈክሮችንና ሌሎችንም በማንሳት ሰላማዊ ሠልፉ ተጠናቋል፡፡ ታስረዋል ስለተባሉት የፓርቲው አመራሮችና አባላትን በሚመለከት ፖሊስ ማብራሪያ እንዲሰጥ ሪፖርተር ተደጋጋሚ ጥረት ቢያደርግም ሊሳካ አልቻለም፡፡    

የታሰሩት ጋዜጠኞችና ጦማርያን ጉዳይ እያነጋገረ ነው

April 30/2014

-ዓለም አቀፍ የሰብዓዊ መብት ተሟጋቾች በነፃ እንዲለቀቁ እየጠየቁ ነው

-መንግሥት አደገኛ ወንጀል ፈጽመዋል እያለ ነው

የመብት ተሟጋቾች ነን ከሚሉ የውጭ ድርጅቶች ጋር በገንዘብና በሐሳብ በመስማማት፣ ሕዝብን ለአመፅ ለማነሳሳትና ለማተራመስ በኢንተርኔትና በተለያዩ ማኅበራዊ ድረ ገጾች ላይ

ቀስቃሽ መጣጥፎችን ለማሰራጨት ሲዘጋጁ ተደርሶባቸዋል በሚል፣ በወንጀል ተጠርጥረው የታሰሩ ጋዜጠኞችና ጦማርያን (Bloggers) ጉዳይ እያነጋገረ ነው፡፡

ሚያዝያ 25 እና 26 ቀን 2006 ዓ.ም. በፀጥታ ኃይሎች ቁጥጥር ሥር ከዋሉ በኋላ በ48 ሰዓታት ውስጥ በዕለተ እሑድ ሚያዝያ 19 ቀን 2006 ዓ.ም. በፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ አንደኛ ወንጀል ችሎት በቀረቡበት ወቅት፣ የፌዴራል ፖሊስ ወንጀል ምርመራ ማዕከል (ማዕከላዊ) መርማሪ ፖሊስ፣  ተጠርጣሪዎቹ ከውጭ ድርጅቶች ጋር በገንዘብና በሐሳብ ተስማምተው ሕዝቡን ለአመፅ ለማነሳሳት ሲንቀሳቀሱ ተደርሶባቸዋል ከሚል የወንጀል የጥርጣሬ ውጪ ያለው ነገር ስለሌለ፣ ‹‹ወንጀሉ ምድነው?›› የሚል ጥያቄ ከማንሳት ጀምሮ የተለያዩ መላ ምቶችን በማንሳት የተለያዩ አካላት እየተነጋገሩበት ነው፡፡

ሲፒጄ (ዓለም አቀፍ የጋዜጠኞች መብት ተከራካሪ ድርጅት)፣ ‹‹ሐሳብን በነፃነት የመግለጽ መብት ላይ የከፋ ከሚባሉ ዕርምጃዎች አንዱ ነው፤›› በማለት በጋዜጠኞቹና በጦማርያኑ ላይ በኢትዮጵያ መንግሥት የተወሰደውን ዕርምጃ አውግዟል፡፡ ያለምንም ቅድመ ሁኔታ እንዲለቀቁም ጠይቋል፡፡

አምኒስቲ ኢንተርናሽናል በበኩሉ፣ ‹‹ይኼ የሰብዓዊ መብት ተሟጋቾች፣ ጋዜጠኞችና ተቃዋሚ ፖለቲከኞችን የማሰር የረዥም ጊዜ ልምድ ነው፤›› በማለት ጋዜጠኞቹንና ጦማርያኑን ማሰር ተገቢ አለመሆኑን አስታውቆ በአስቸኳይ እንዲፈቱም ጠይቋል፡፡

ዓለም አቀፍ የመብት ተሟጋች ድርጅቶች የኢትዮጵያን መንግሥት በማውገዝ የጋዜጠኞቹንና ጦማርያኑን መታሰር የሚያነሱትን ወቀሳና ጥያቄ ተከትሎ የጠቅላይ ሚኒስትሩ የኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች አማካሪ አቶ ጌታቸው ረዳ ለውጭ ሚዲያ በሰጡት ምላሽ፣ ‹‹ተጠርጣሪዎቹ በአደገኛ ወንጀል የተጠረጠሩ ናቸው፡፡ ፖሊስ በተጠረጠሩበት ጉዳይ ዙሪያ ምርምራ እያደረገ ነው፤›› ብለዋል፡፡

ሒዩማን ራይትስ ዎች ሚያዝያ 21 ቀን 2006 ዓ.ም. ወደ ኢትዮጵያ ይመጣሉ የተባሉት የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጆን ኬሪ ጋር ባደረገው የስልክ ውይይት፣ የኢትዮጵያ መንግሥት የታሰሩትን ጋዜጠኞችና ጦማርያን ያለምንም ቅድመ ሁኔታ እንዲፈታ ግፊት እንዲያደርጉ ጠይቋል፡፡

የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ድርጅት ጆን ኬሪ ተጠርጣሪዎቹን እንዲፈቱ በኢትዮጵያ መንግሥት ላይ ግፊት እንዲያደርጉ በስልክ ያስተላለፈውን መልዕክት አስመልክቶ አቶ ጌታቸው በሰጡት ምላሽ፣ ‹‹መንግሥት የጋዜጠኞችን የመናገር መብት አላፈነም፣ አንዳንዶች ሙያውን ተገን በማድረግ የወንጀል ድርጊት ውስጥ ሲሳተፉ ይገኛሉ፣ ይኼን ደግሞ የኢትዮጵያ መንግሥት አይፈቅድም፤›› ካሉ በኋላ፣ ‹‹የዓለም አቀፍ የሰብዓዊ መብት ተሟጋቾችን ትዕዛዝን አንቀበልም፤›› ብለዋል፡፡

በፀጥታ ኃይሎች በቁጥጥር ሥር የዋሉት ጋዜጠኞችና ጦማርያን ሚያዝያ 19 ቀን 2006 ዓ.ም. ፍርድ ቤት ሲቀርቡ በሦስት የምርመራ መዝገብ ተከፋፍለው ሲሆን፣ ቀደም ሲል በአዲስ ነገር ጋዜጣ፣ በፎርቹን ጋዜጣና በአዲስ ስታንዳርድ ጋዜጣ ላይ ይሠራ የነበረው ጋዜጠኛ ተስፋዓለም ወልደየስ፣ በአምቦ ዩኒቨርሲቲ የሕግ መምህር ነው የተባለው ጦማሪ ዘለዓለም ክብረትና የአዲስ ጉዳይ መጽሔት ከፍተኛ አዘጋጅ አስማማው ኃይለ ጊዮርጊስ አንድ ላይ ናቸው፡፡

በሁለተኛው የምርምራ መዝገብ የተካተቱት የአዲስ ዘመን ጋዜጠኛ የነበረችው ጋዜጠኛ ኤዶም ካሳዬ፣ ጦማሪ ናትናኤል ፈለቀና ጦማሪ አጥናፉ ብርሃኔ ሲሆኑ፣ የአየር መንገድ ሠራተኛ ነው የተባለው ጦማሪ አቤል ዋበላ፣ ጦማሪ በፍቃዱ ኃይሉና ጦማሪ ማህሌት ፋንታሁን በሦስተኛው የምርምራ መዝገብ ተካተው ለሚያዝያ 29 እና 30 ቀን 2006 ዓ.ም. መቀጠራቸው ታውቋል፡፡

በምሥረታ ላይ ያለው የኢትዮጵያ ጋዜጠኞች መድረክ (ኢጋማ) የጋዜጠኞቹንና ጦማርያኑን መታሰር በማስመልከት ባወጣው መግለጫ፣ መንግሥት የተጠረጠሩበትን ጉዳይ ለሕዝብ ይፋ ማድረግ እንደሚገባው ጠቁሞ፣ መታሰራቸው ግን እንዳሳሰበው ገልጿል፡፡ ባስቸኳይ እንዲፈቱም ጠይቋል፡፡

በአገር ውስጥ ያሉ የግል የኤሌክትሮኒክስና የሕትመት መገናኛ ብዙኃን፣ ከመንግሥትና ከቅርብ ወዳጆቻቸው እንዳገኙት አድርገው በተጠርጣሪዎቹ ጋዜጠኞችና ጦማርያን ላይ እያስተላለፉት ያለው መረጃ፣ መርማሪ ፖሊስ ለፍርድ ቤቱ ሲያስረዳ ፍርድ ቤቱ በምርመራ መዝገቡ ላይ ካሰፈረው የተለየ በመሆኑ፣ በተጠርጣሪዎቹ ላይ በቀጣይ የሚቀርበውን የምርምራ ውጤት ከመጠባበቅ ባለፈ ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት የተደረገው ጥረት አልተሳካም፡፡

ከዞን ዘጠኖች አንዱ ከጆን ኬሪ ጋር – ፎቶ ይዘናል

April 29/2014
አቦጊዳ

የአሜሪካ የዉጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት የታሰሩ ብሎገሮች ጉዳያቸው በአስቸኳይ ታይቶ እንዲፈቱ በቀጥታ የኢትዮዮጵያን መንግስት መጠየቃቸው ቃለ አቀባይዋ ሚሲስ ፕሳኪ ገለጹ።
የኢትዮጵያ መንግስት በሕገ መንግስቱ የተደነገጉትን መብቶች ማክበር እንዳለበት፣ አሜሪካ ጠንካራ አቋም እንደሆኑ የገለጹት ሚሲስ ፕሳኪ፣ የዉጭ ጉዳይ ሚኒስተሩ ጆን ኬሪ በአፍሪካ ጉብኘት ባደረጉበት ጊዜ ሁሉ የሰባአዊ መብት ጉዳይ ባገኙት አጋጣሚ ሁሉ እንደሚያነሱ ለመጠቆም ሞክረዋል።
ከታሰሩ ብሎገሮች መካካል አንዱ ናትናኤል ፈለቀ፣ ከአሜሪካዉ የዉጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ጆን ኬሪ ጋር የተነሳዉን ፎቶ ይመልከቱ።
zone9_kerry1
የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት ቃል አቀባይ፣ በኢትዮጵያ ጉድያ ላይ ከተናገሩት ጥቂቱን ከዚህ በታች ማንበብ ይችላሉ።
======================
State Department Daily Briefing regarding Secretary Kerry’s visit to Ethiopia.
MS. PSAKI: Sure, I can. We are aware that six independent bloggers and three independent journalists were detained by Ethiopian police April 25th through 26th. We urge the Government of Ethiopia to expeditiously review the cases of these detainees and promptly release them. We have raised these concerns on the ground directly with the Government of Ethiopia.
And we, of course, reiterate our longstanding concern about the abridgment of the freedom of press and the freedom of expression in Ethiopia, and urge the Government of Ethiopia to fully adhere to its constitutional guarantees. And certainly while the Secretary is there as part of his trip to Africa, he often raises, at every opportunity, issues surrounding human rights, whether it’s media freedoms or equal treatment, freedom of speech, and I expect that will be the case this time as well.

Tuesday, April 29, 2014

አንዷለም አራጌ እና የቃሊቲው ህይወት

April 29/2014

አንዷለም-አራጌ-እና-የቃሊቲው-ህይወት/አንዷለም-አራጌ-እና-የቃሊቲው-ህይወት/
fe236-andualem-aragie5b15d
(EMF) – አንዷለም አራጌ የአንድነት ፓርቲ አመራር አባል የነበረ ወጣት ነው። በኋላ ላይ የኢህ አዴግ ሰዎች ባቀናበሩት ድራማ አሸባሪ ተብሎ ለእስር ተዳረገ። ቃሊቲ በእስር ላይ ሆኖ ብቻውን በጨለማ ቤት ውስጥ ከመታሰር ጀምሮ ብዙ እንግልት እና መከራን እየተቀበለ ይገኛል። ይህ ሁሉ የሆነው አንዷለም በተቃዋሚው ጎራ በመቆሙ ብቻ ሳይሆን፤ ጎበዝ መሪ በመሆኑም ጭምር ነው። አሁን በ እስር ላይ ሆኖም እንኳን፤ ስሜቱን ለመጉዳት ሲባል እሱን ለመጠየቅ የሚሄዱ ጠያቂዎች ይዋከባሉ፤ እንዲጠይቁትም አይፈቀድላቸውም።
ከትላንት በስትያ አንዷለምን ለመጠየቅ ወደ እስር ቤት ያመሩት፤ ብቸኛው የፓርላማ ውስጥ ተቃዋሚ ክቡር አቶ ግርማ ሰይፉ ትዝብታቸውን ገልጸዋል። የአቶ ግርማ ትዝብት “አንዱዓለምን ለመጠየቅ ቃሊቲ ጎራ ብዬ ነበር፡፡” በማለት ይጀምሩና በአንዷለም ላይ እየደረሰ ያለውን እንግልት በዝርዝር ገልጸውታል። እንዲህ በማለት ይቀጥላሉ አቶ ግርማ….
አንዱዓለም እንደተለመደው በጠንካራ ሞራልና ለሰው ልጅ ክብር በሚሰጠው መንፈሱ ላይ ምንም ለውጥ አይታይም፡፡ የሚበድሉትን ቢሆን ለምን? ብሎ ይጠይቃል እንጂ የበቀለኝነት ሰሜት የለበትም፡፡ ነገር ግን በፍፁም ተሰፋ እያሰቆረጠው ምን አልባት ወደ ርሃብ አድማ ሊገፋኝ ይችላል ብሎ የሰጋው ከብዙ ሺ ከሚቆጠሩ እሰረኞች በተለየ ሁኔታ የሚሰተናገድበት አያያዝ ምቾት አልሰጠውም፡፡ መብቱን እያስደፈረ እንደሆነ ይሰማዋል፡፡
እሱን ለመጠየቅ ከባለቤቱ እና ከእኔ በስተቀር ይህን ሁሉ ኪሎ ሜትር አቋርጠው የመጡ ሰዎችን እየመለሱ ችግር እየፈጠሩበት እንደሆነ ነግሮኛል፡፡ ማንም ጠያቂ እርሱ እንዲጠይቅ አይፈቀድለትም፡፡ ይህ ደግሞ ፌዝ የሚሆነው ለእርሱ ደህንነት ብለን ነው የሚሉት መልስ ነው፡፡ በተለይ ትላንት ምሽት ድንገት በተደረገ ብረበራ ከማረሚያ ቤቱ ላይብረሪ ተውሶ ሲያነባቸው ከነበሩተ መፅኃፎች ላይ የያዛቸውን ማስታወሻዎች በሙሉ ወስደውበታል፡፡ በማረሚያ ቤቱ ደንብ ላይ ይህ ክልከላ ስለመኖሩ ጠይቄው የማረሚያ ቤቱን ደንብና መመሪያ እንዲሰጡኝ ከጠየቅሁ ስድሰት ወር ያለፈ ቢሆንም እስከ አሁን እንዳልሰጡት ነግሮኛል፡፡
ማረሚያ ቤቱ ከህገ መንግሰት በተቃራኒ የሆነ መመሪያ የማውጣት መብትም የለውም፡፡ በነገራችን ላይ የአንዱዓለም ጠያቂዎች እንዳይጎበኙት የተጣለበትን ክልከላ አምሳደር ጥሩነህ ዜናም እንደሚያውቁት ነገር ግን ይህ መመሪያ ስለሆነ እንደሆነ ገልፀውልኝ፣ መመሪያው ከህገመንግሰት ጋር የሚጋጭ ነገር ካለው እንደሚያዩት መደበኛ ባልሆነ ውይይት ገልፀውልኝ ነበር፡፡ አንድ እስረኛ በተለየ ሁኔታ በዘመድ አዝማድ ጓደኛ እንዳይጠየቅ ገደብ ለምን እንደሚደረግበት ሊገባኝ ባይችልም፡፡ ማረሚያ ቤቱ ውስጥ ከመደበኛው በተለይ የሚደረጉ ተግባራትን ተዉ የሚል ያለ አይመስልም፡፡
አንዱዓለም ቃሊቲ ከገባ ጀምሮ በልዩ ቅጣት ክፍል የሚገኝ ሲሆን በዚህ ክፍልም ልዩ ጥበቃ ይደረግበታል፡፡ አንዱዓለም የሚላኩለት መፅሃፎች በጊዜው እንደማይገቡለትና ከተላከለት ስምንት መፅሃፍ ውስጥ 2 አይገባም ከተባለ በኋላ ወደ ቤተሰቦቹም አለመመለሱንም ገልጾልኛል፡፡ ለክፉም ለደጉ አንዱዓለም ለመጉዳት የሚንቀሳቀሱ የመንግሰት ኃላፊዎችም ሆኖ ልወደድ ባይ የማረሚያ ቤት ሹሞች ከዚህ ተግባራቸው ቢቆጠቡ ጥቅሙ የጋራ ነው፡፡ አንዱዓለም ሰርቆ ወይም ሀገር ከድቶ አይደለም በእስር ላይ የሚገኘው፡፡ ለሀገሩ ነፃነት የድርሻዬን እውጣለሁ ብሎ በሰላማዊ መንገድ ሲንቀሳቀስ ይህ ዜጋ ለወንበራችን ጠር ነው ብለው በፈሩ እና በሀሰት በወነጀሉት አካላት ምክንያት ነው፡፡ ሌቦችን ወንጀለኞች እንደፈለጉ በሚሆኑበት እስር ቤት ጀግኖችን ማሰቃየት ማንገላታ አሁንም ፍርሃታቸው እንዳለቀቃቸው ከማሳየት ውጭ አንዱዓለምን መንፈስ እንደማይጎዳው እርግጠኛ ነኝ፡፡ የአሳሪዎቹን በቀለኝነት ግን ቁልጭ አድርጎ ያሳያል፡፡