Saturday, July 4, 2015

አይቀሬዉ የድል ፊሽካ ተነፋ!! አርበኞች ግንቦት 7 ሕዝባዊ ኃይል በወያኔ ሰራዊት የኃይል ጥቃት ሰነዘረ

July 4,2015

 ሀሙስ ዕለት ሰኔ 25 2007 ዓ.ም የአርበኞች ግንቦት 7 ለአንድነትና ዴሞክራሲ ንቅናቄ ሰራዊት በትግራይ ክልል ቀፍታ መሲል፣ ሆርጃሞ እና ማይሰገል ላይ ህወሓት ከሚቆጣጠረው የ24ኛ ክፍለ ጦር፣ ፌደራል ፖሊስና ልዩ ኃይል ጋር ባደረገው ለአራት ሰዓታት የዘለቀ ከባድ ጦርት ከፍተኛ ጉዳት አደረሰ፡፡

የአርበኞች ግንቦት 7 አርበኛ ተጋዮች በትግራይ ቀፍታ መሲልና ሆርጃሞ ላይ መሽጎ ያገኙትን ከሶስት ክፍሎች ማለትም ከ24ኛ ክፍለ ጦር፣ ከፌደራል ፖሊስና ከልዩ ኃይል የተውጣጣና እስከ አፍንጫው የታጣቀ ቁጥር ስፍር የሌለው ጦር ከቀኑ ሰባት ሰዓት እስከ አስር ሰዓት ለተከታታይ ሦስት ሰዓታት በጥይት ቆልተውታል፡፡

በተጨማሪም እዚያው ትግራይ ውስጥ ማይሰገል በተባለው ቦታ ምሽት ከአስራ ሁለት ሰዓት እስከ አንድ ሰዓት በተደረገው ፍልሚያ በጠላት ጦር ሰራዊት ላይ ከፍተኛ እልቂት ደርሷል፡፡ 

ትግራይ ውስጥ በሚገኙ በሦስቱ ቦታዎች በተደረው አራት ሰዓታትን የፈጀ መራራ ውጊያ ከተለያዩ ሶስት ክፍሎች የተደራጀው የጠላት ጦር በአርበኞች ግንቦት ሰባት የነፃነት ፋኖዎች ፈርጣማ ክንድ ክፉኛ ተደቁሶ የተበታተነ ሲሆን በትንሹ ከ50 በላይ ወታደሮች ሲሞቱ ከ60 በላይ ደግሞ ከባድ ቁስለኛ ሆነዋል፡፡ ህወሓት በሚቆጣጠረው ሰራዊት ላይ የደረሰው ጉዳት አሁን ገና በመጣራት ላይ የሚገኝ ሲሆን ውሎ አድሮ ትክክለኛው መረጃ ሲገኝ የሞቱትና የቆሰሉት ወታደሮቹ ቁጥር አሁን ከተገለፀው ከሁለትና ሦስት እጥፍ ሊያሻቅብ እንደሚችል ይገመታል፡፡ 


ስለዚህም በአሁኑ ሰዓት አርበኞች ግንቦት 7 ጦርነት አውጇል በሚል ከሁመራ-ዳንሻ፣ ከሁመራ-ሽሬ እና እንዲሁም በተጨማሪ ከሁመራ-ጎንደር የሚገኙት አውራ ጎዳናዎች ጥርቅም ብለው በጦር ሰራዊት ተዘግተው ምንም አይነት የመኪና እንቅስቃሴ የለም፡፡


እስከ ዛሬ የኢትዮጵያ ህዝብ በጉጉት ሲጠብቀው የኖረው ህወሓትን በጠብመንጃ የማስወገዱ ጦርነት ፍልሚያ አብሳሪ የሆነው ፊሽካ በአርበኞች ግንቦት 7 ለአንድነትና ዴሞክራሲ ንቅናቄ እነሆ ተነፍቷል፡፡ በመሆኑም ነፃነት ፈላጊ የሆነ የኢትዮጵያ ህዝብ/ወጣት ሁሉ በያለበት ትጥቅ ያለው ትጥቁን አንስቶ፣ ድንጋይና ዱላ የጨበጠም በእጁ በሚገኝ ማናቸውም መሳሪያ የዘረኛውን አገዛዝ የህወሓትን ቡድን ራስ ራሱን በመቀጥቀጥ በረሃ ወርደው በመፋለም ውድ ህይወታቸውን እየከፈሉ ከሚገኙት ልጆቹ፣ ወንድሞቹ እና እህቶቹ የሆኑ አርበኛ ታጋዮች ጎን አንዲሰለፍ አርበኞች ግንቦት 7 ለአንድነትና ዴሞክራሲ ንቅናቄ ጥሪውን አቅርቧል፡፡

No comments: