Sunday, September 7, 2014

‹‹የፍርድ ሂደቱ ድራማ ነበር›› ከወይንሸት ሞላ ጋር ቃለ ምልልስ

Sep 7,2014
(ኢ.ኤም.ኤፍ) የሰማያዊ ፓርቲ አመራር አባል የሆነችው ወይንሸት ሞላ፤ የሙስሊሙን እንቅስቃሴ ለመከታተል አንዋር መስጊድ ሄዳ በነበረበት ወቅት በደህንነት ታፍና፤ በአሰቃቂ ሁኔታ እየተደበደበች መወሰዷን በድረ ገጻችን ላይ ገልጸን ነበር። ከዚያም ሰውነቷ ተጎድቶ እና ደክሞ ፍርድ ቤት ትመላለስ የነበረ መሆኑን በመጨረሻም በዋስ መፈታቷን በወቅቱ ገልጸናል። ከ”ነገረ ኢትዮጵያ” መጽሄት ጋር ያደረገችው ቃለ ምልልስ ኢትዮጵያ ውስጥ እንዳይታተም በመደረጉ ምክንያት አዘጋጆቹ ቃለ ምልልሱን በማህበራዊ ድረ ገጾች ላይ ለቀውታል። እኛም ይህንኑ ቃለ ምልልስ ለናንተ ልናጋራቹህ ወደድን። ከዚህ በታች አቅርበነዋል።
‹‹የሙስሊሙን እንቅስሴ ተገኝቼ በመታዘቤ ኮርቻለሁ›› ወ/ት ወይንሸት ሞላ፣ የሰማያዊ ፓርቲ ብሔራዊ ም/ቤት አባል
ወ/ት ወይንሸት ሞላ የሰማያዊ ፓርቲ ብሔራዊ ምክር ቤት አባል ስትሆን ፓርቲው በሚያደርጋቸው የፖለቲካ እንቅስቃሴዎች ላይ ንቁ ተሳታፊ ከሆኑት መካከል እንደሆነች ይነገርላታል፡፡ ወጣቷ ፖለቲከኛ ወይንሸት ሞላ ሐምሌ 11 ቀን 2006 ዓ.ም ለዓመታት የዘለቀው የሙስሊሙ ማህበረሰብ የመብት ጥያቄ አካል የሆነውንና በዕለቱ በአኑዋር መስጊድ የተደረገውን የተቃውሞ ሁኔታ ለማየት በቦታው ተገኝታ እንደነበር ትናገራለች፡፡ ወ/ት ወይንሸት በዕለቱ በፖሊስ ቁጥጥር ስር ውላ ለ29 ቀናት በእስር ቆይታ በዋስ ተለቅቃለች፤ ጋዜጠኛ ጌታቸው ሺፈራው ስለጉዳዩ አነጋግሯታል፡፡
ነገረ ኢትዮጵያ፡- አንዋር መስጊድ አካባቢ ተይዘሽ ከታሰርሽ በኋላ ለምን መስጊድ ሄደች የሚሉ አካላት ነበሩ፡፡ ለመሆኑ እንዴትና ለምን ነበር የሄድሽው?
ወይንሸት፡- የሄድኩበት ምክንያት ግልጽ ነው፡፡ በእርግጥ እኔ የሄድኩበትን ብቻ ሳይሆን በተለይ በገዥው ፓርቲ በኩል የሙስሊሙን ማህበረሰብ እንቅስቃሴም ባልሆነ መንገድ ትርጉም እየተሰጠው ነው የሚገኘው፡፡ የሙስሊሙን እንቅስቃሴ እስላማዊ መንግስት ለመመስረት የሚደረግ እንደሆነ አድርገው በተሳሳተ መንገድ ያቀርቡታል፡፡ የእኔንም ከዚህ በተለየ ሁኔታ አይደለም ያቀረቡት፡፡ ምን አልባት የእኔ ይለያል ከተባለ ፖለቲከኛ በመሆኔ ሊሆን ይችል ይሆናል፡፡ ሆኖም እኔም የሄድኩት እንቅስቃሴውን ለማየት ነው፡፡ ይህን ለማየት የሄድኩበት ምክንያት አንደኛ ገዥው ፓርቲ ሙስሊሙ ማህበረሰብ የሚያደርገውን እንቅስቃሴ ሰላማዊ አይደለም ብሎ ስለሚፈርጅ ነው፡፡ ሙስሊሞች ደግሞ እንቅስቃሴው ሰላማዊ እንደሆነ ይናገራሉ፡፡ ለህዝብ እንደቆመ እንደ አንድ የተቃዋሚ ፓርቲ አባልነቴም ሆነ መሪ ለመሆን እንደምትፈልግ አንዲት ሴት ቦታው ላይ ተገኝቼ ነገሮችን ማረጋገጥ ስለነበረብኝ ቦታው ላይ ተገኝቻለሁ፡፡
ነገረ ኢትዮጵያ፡- የተያዝሽበት ሁኔታስ ምን ይመስላል?
ወይንሸት፡- መስጊዱ ፊት ለፊት ባለ አንድ ህንጻ ላይ ሆኜ እንቅስቃሴውን ስከታተል ነው የያዙኝ፡፡ በተለይ ከያዙኝ በኋላ የወሰዱት እርምጃ በጣም ዘግናኝ ነበር፡፡ በድብደባ ከፍተኛ ጉዳት አድርሰውብኛል፡፡ አጸያፊ የሆነ ስድብ ይሳደቡ ነበር፡፡ መንግስት ነኝ ከሚል አካል የመጣ ሰው እንዲህ ይሳደባል ብሎ ለማመን እስኪከብድ ድረስ ነው የሚሳደቡት፡፡ ለሴት ልጅ ምንም አይነት ክብር የላቸውም፡፡ ሲሳደቡ ኢትዮጵያዊ አይመስሉም ነበር፡፡ የህዝቡን ስነ ልቦና ለመስለብም ይሁን ለሌላ ጉዳይ ግፉ ምን ያህል ጫፍ እንደደረሰ የሚያሳይ ነበር፡፡ ድብደባ የፈጸሙብኝ ደህንነቶች ተደብቀውና እኔን ከተያዙት ሌሎች ሰዎች ለይተው ነበር የሚደበድቡኝ፡፡ እንዳይታዩ መስገጃ ተከናንበው ነበር ይደበድቡኝ የነበረው፡፡ ከሌላው ለይተው ሰማያዊ ፓርቲ መጥቶ ያድንሽ እያሉ ነበር ከበው የደበደቡኝ፡፡ ይህ ፍርሃታቸውን ነው የሚያሳየው፡፡ በሚደበድቡኝ ወቅት ሞባይሌን ይጎረጉሩ ነበር፡፡ በድንገት የአባይ ግድብን ፎቶ አግኝተውት ‹‹ደግሞ አባይ ግድብንም ልታፈነዱ ነው?›› ይሉኝ ነበር፡፡ ሌላስ ተልዕኮሽ ምንድን ነው እያሉ ከፍተኛ ደብደባ አድርሰውብኛል፡፡ የመጣው ሁሉ የሌለ ጥያቄ እየጠየቀ ይሳደባል፡፡ ይደባደባል፡፡
በምርመራ ወቅት መረዳት እንደቻልኩትም እኔን ሙስሊሞቹ የደበደቡኝ ለማስመሰል ነው የፈለጉት፡፡ በደህንነት አካላት ተደበደበች የሚሉትን ነገር ማመን አልፈለጉም፡፡ በዱላና አናቴን ደግሞ በእርግጫ ከደበደቡኝ በኋላ ጥለውኝ ሄዱ፡፡ ደም በጣም ይፈሰኝ ነበር፡፡ ፊቴ ሁሉ በደም ታጥቦ ነበር፡፡ ከዚህም በኋላ ወደ አራተኛ ፖሊስ ጣቢያ ወሰዱኝ፡፡ እዛ ፖሊስ ጣቢያ ቤቱ መቆሚያ መቀመጫ እስኪያጣ ድረስ በተጎጅዎች ተሞልቷል፡፡ እኔ ህክምና ያስፈልገኛል ስላቸው አንዲት ነርስ መጥታ አየችኝና ‹‹ከአቅሜ በላይ ነው ቁስሉ መሰፋት አለባት›› ስትል ደህንነቶቹ ግን ‹‹ይህ የአገር ጉዳይ ነው፡፡ አይሆንም›› ብለው ወደ ሶስተኛ ፖሊስ ጣቢያ ወሰዱኝ፡፡ ከቀኑ ሰባት ሰዓት አካባቢ ድብደባ የደረሰብኝ እስከ ምሽቱ አራት ሰዓት አካባቢ ደሜ እየፈሰሰ ነበር፡፡ እስከዛ ሰዓት ድረስ ቁስሉ አልተሰፋም ነበር፡፡ እኔ ብቻ ሳልሆን በርካታ ሰዎች ተመሳሳይ በደል ተፈጽሞባቸዋል፡፡ በፖለቲከኛ ደረጃ እኔ ብቻ ብሆንም እንፈልጋቸዋለን ያሏቸውን ሰዎች ምንም ህክምና ሳይደረግላቸው ወደ ሶስተኛ ፖሊስ ጣቢያ ነበር የሚልኳቸው፡፡ የራሳቸውንም ሰዎች ሰርጎ ገቦች ናቸው እያሉ የፖሊስ መታወቂያ ስለያዙ ብቻ ተመሳሳይ በደል ተፈጽሞባቸው አብረው ልከዋቸዋል፡፡
ለረዥም ጊዜ ህክምና ባለማግኘቴ እራሴን እየሳትኩ ሄድኩ፡፡ ከምሽቱ አራት ሰዓት በኋላ ወደ ራስ ደስታ ሆስፒታል ወሰዱኝ፡፡ ራስ ደስታ ሆስፒታል ላይ የፈጸሙብኝም በጣም የሚያሳዝን ጭካኔ ነበር፡፡ ሐኪሞቹ ቁስሌን ሲያዩ ‹‹ይህ የተፈነከተ ሳይሆን በጩቤ የተወጋ ነው›› እስከማለት ደርሰው ነበር፡፡ ነገር ግን ያንን ያህል ጉዳት ልተኛባቸው ስልሆንኩ ነው መሰለኝ ያለማደንዘዣ ነው የሰፉት፡፡ ውሃ እንኳን የሚሰጠኝ ላገኝ አልቻልኩም፡፡ ጉዳትክን እያዩ ሁሉም ጸጥ ብለው ነው የሚያልፉት፡፡ ቤተሰቦቼ የተሻለ ሐኪም ቤት ይወስዱኛል ብላቸው ሊሰሙኝ አልቻሉም፡፡ ያለ ማደንዘዥ ሲሰፉኝ በጣም እጮህ ነበር፡፡
ነገረ ኢትዮጵያ፡- እንደነገርሽኝ እንደ አንድ ፖለቲከኛ የኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች ጉዳይ ያገባኛል ብለሽ ነው የሄሽው፤ በወቅቱ ምን ታዘብሽ?
ወይንሸት፡- ሙስሊሙ ማህበረሰብ የፈጠረው ችግር የለም፡፡ ሁላችንም እንደሰማነው በእምነታቸው ላይ በሚፈጸምባቸው ጣልቃ ገብነት ትልቅ የተቃውሞ ፕሮግራም አዘጋጅተው ነበር፡፡ ሙስሊሞቹም ያንን ነገር ለመታደም ነው የሄዱት፡፡ በወቅቱ ሙስሊሞቹ ያደረጉት ነገር የለም፡፡ ድንጋይ ወርዋሪዎቹ ደህንነት ነን የሚሉት አካላት ናቸው፡፡ ዘግናኝ ድብደባ ይፈጽሙ የነበሩትም ራሳቸው የደህንነት አካላት ናቸው፡፡ ቀርበህ ስትጠይቃቸው የሚገልጹትም በሙስሊምነታቸው እንደታሰሩ እንጂ ወንጀል ፈጽመው እንዳልሆነ ነው፡፡
በድብደባው በኩል ያለው በጣም ዘግናኝ ነው፡፡ ጦር ሜዳ ነበር የሚመስለው፡፡ ከሰባት ሰዓት ጀምሮ እስከ ምሽቱ 12 ሰዓት መስጊዱ አካባቢ ደብደባ ነበር፡፡ ወደቁ፣ የተፈነከቱና የደሙ እናቶችን፣ ነፍሰ ጥሩዎችን ታያለህ፡፡ ቦታው ላይ ከ2000 በላይ ሰው ተይዟል፡፡ ይህ የተያዘ ሰው ወደ አራተኛ ፖሊስ ጣቢያ ተወሰደ፡፡ አብዛኛው ለመደብደብ እንዲያመች ወደሚኖርበት አካባቢ ፖሊስ ጣቢያ ነው የተወሰደው፡፡ ከፍተኛ ድብደባ የሚያደርሱባቸውን ሰዎች የሚለዩት የእንቅስቃሴው ደጋፊ ነኝ ብለው በመናገራቸውና በአለባበሳቸው ነው፡፡
መጀመሪያ በተለይ ጦር ኃይሎች አካባቢ ወደሚገኝ ፖሊስ ጣቢያ (መደብደቢያ) የተወሰዱት በጣም የሚያሳዝን ግፍ ተፈጽሞባቸዋል፡፡ አራተኛ ፖሊስ ጣቢያ ላይ ጊዜያዊ ህክምና ከሰጡ በኋላ በኒቃብ፣ በሂጃብና በሌሎች ሀይማኖታዊ አለባበሳቸው እየነጠሉ ወደ ጦር ኃይሎች አካባቢ ወደሚገኘው መደብደቢያ ወሰዷቸው፡፡ ሞባይላቸውንና ሌሎች ንብረታቸውን ተቀምተዋል፡፡ ንብረታቸውን መዝግበው አልነበረም የሚቀበሏቸውና ማንም ንብረቱን ያገኘ የለም፡፡ በጣም በሚያሳዝንና በሚያሳፍር ሁኔታ ኒቃባቸውንና ሌሎች ሙስሊሞች በተለይም ሴቶቹ የሚለብሱትን ልብሶችቻውን እያስወለቁ ነበር የሚደበድቧቸው፡፡ መቼም ሙስሊም ሴቶች እምነቱ በሚፈቅደው መሰረት የሚለብሱትን ልብስ ሲያወልቁ ከውስጥ ምን ሊቀር እንደሚችል መገመት ቀላል ነው፡፡ አብዛኛዎቹ እንዲህ ራቁታቸውን ሆነው ወንድ አይቷቸው የማያዉቁ ለጋ ወጣቶች ናቸው፡፡ ይህ ሁሉ በደል ከተፈጸመባቸው በኋላ ንብረታቸውን ሳይመልሱላቸው ከሌሊቱ 9 ሰዓት ላይ ለቀቁዋቸው፡፡ ንብረታቸው አይመዘገብም፡፡ በዛና ሰዓት ሴቶቹ ወደየት ሊሄዱ ይችላሉ?
ነገረ ኢትዮጵያ፡- ለብቻሽ ተለይተሸ ከተደበደብሽ ምርመራ ላይም የተለየ ትኩረት ሊኖር እንደሚችል መገመት ይቻላል፡፡ ምርመራው እንዴት ነበር?
ወይንሸት፡- ዋነኛው የምርመራ አካል ‹‹ተልዕኮ አለሽ ይህን ተልዕኮ ንገሪን›› የሚል ነው፡፡ እንደዛ ጉዳት ደርሶብኝና ቁስሌን ያለ ማደንዘዣ ሰፍተው እስከ ሌሊቱ 9ና 10 ሰዓት ገደማ ምርመራ ላይ ነበርኩ፡፡ እኔ ደግሞ ተልዕኮ እንደሌለኝና ሁኔታውን ለመታዘብ እንደሄድኩ ነበር የምናገረው፡፡ ያው እነሱ ይሳለቃሉ፣ ይዘባበታሉ፡፡ ሶስተኛ ፖሊስ ጣቢያ ውስጥ ድብደባ አልነበረም፡፡ ከዛም በኋላ ቤቴን ፈትሸው መጽሃፍቶችና የዘፈን ሲዲዎችን አግኝተዋል፡፡ ሊፈትሹ የሄዱት ግን ከፍርድ ቤት ፈቃድ አውጥተው የጦር መሳሪያ፣ በራሪ ወረቀቶችና ሁከትና ብጥብጥን የሚያስነሱ ቁሳቁሶች ይገኛል ብለው ነው፡፡ ቤት ያገኙትን ወረቀት መስመር በመስመር እያነበቡ የፈለጉትን ለማግኘት ጥረው ነበር፡፡ ነገር ግን ምንም ሊያገኙ አልቻሉም፡፡ የሰማያዊ ፓርቲ መታወቂያና የዘፈን ሲዲዎችን ብቻ ነው የወሰዱት፡፡
ነገረ ኢትዮጵያ፡- በተለይ ወደመጀመሪያው አካባቢ ማንም ታዛቢ ፍርድ ቤት መግባት ባለመቻሉ መከታተል አልተቻለምና የፍርዱ ሂደቱስ እንዴት ነበር?
ወይንሸት፡- የፍርድ ቤቱ ሂደቱ ድራማ ነበር፡፡ ሌላ ምንም መገለጫ የለውም፡፡ በማይመለከተን ነገር ክሱን ወደ ግድያ ለመቀየር ብዙ ብዙ ጥረዋል፡፡ ክሱ ሁከትና ብጥብጥ አስነስተዋል ነው የሚለው፡፡ በህግ መሰረት ሁከትና ብጥብጥ የዋስትና መብት አያስነጥቅም፡፡ እኛም ለፍርድ ቤቱ የዋስትና መብታችንን ጠይቀናል፡፡ ይህን ስንል ‹‹በእለቱ ዕለት ከፍተኛ አደጋ የደረሰባቸው ሁለት ፖሊሶች አሉ፡፡ የእነዚህ ፖሊሶች የህክምና ውጤት እስኪረጋገጥ ድረስ እነዚህ ልጆች መለቀቅ የለባቸውም›› ብለው ነበር መርማሪዎቹ የሚከራከሩት፡፡ ፍርድ ቤት የቀረብነው 17 ሰዎች የመጣንበትን ምክንያት ተናግረናል፣ የየራሳችን መከራከሪያም አቅርበናል፡፡ መርማሪዎቹ ግን ይከራከሩ የነበሩት ግድያ እንደፈጸምን ነው፡፡ የሞተ ሰው አለ፣ ጥቁር አንበሳ የተኛ ሰው አለ እየተባለ በየ ሳምንቱ የእሱ ውጤት ነበር በመርማሪዎቹ በኩል በመከራከሪያነት ይቀርብና የጊዜ ቀጠሮ ይጠየቅበት የነበረው፡፡ ነገር ግን ሄደው አይጠይቁም፡፡ የሞተ ሰው ኖረም አልኖረም ቦታው ላይ ፖሊስ የከፈለው መስዋዕትነት ይሆናል እንጂ 17ቱም ታሳሪዎች አንድ ጠጠር እስካልወረወርን ድረስ ጥፋተኛ የምንሆንበት አንድም ምክንያት የለም፡፡ ግን ሰው ገድላችኋል ብለው የሚጠይቁት እኛን ነበር፡፡
በተለይ በፖሊስ በኩል የመጨነቅ ስሜት ይታይ ነበር፡፡ በራሳቸው ፈልገው ያደረጉት ነገር እንዳልሆነ ፊታቸው ይናገር ነበር፡፡ እነሱም ህሊናቸው ያውቀዋል፡፡ እንዲያውም እረፍት አጣን እያሉ ያማርሩ ነበር፡፡ በጣም በሚገርም ሁኔታ የአንድ መስጊድ አስተማሪ ኡስታዝ ጭምር ነው የታሰረው፡፡ የጋዜጠኛዋ አዚዛ መሃመድም ቢሆን ተመሳሳይ ነው፡፡ እነሱም እኛን ተከራክረው ጥፋተኛ ለማሰኘት የሚያስችል ምክንያቱም ተነሳሽነቱም አልነበራቸውም፡፡ በዚህም ምክንያት ከፍተኛ ጭንቀት ይታይባቸው ነበር፡፡ የዋስትና መብቱም የሚያሳየው ይህንኑ ነው፡፡ እንድንለቀቅ ተወስኖ አምስትና አስር ደቂቃ ሳይሞላ ነው ወደ ይግባኝ ሰሚ ፍርድ ቤት ሄደን ዋስትናችን የታገደው፡፡ እነሱ ሳይሄዱ እዛው ላይ ሆነው ጨርሰውታል ማለት ነው፡፡
በወቅቱ ተመሳሳይ ምክንያት ነበር የሚያቀርቡት፡፡ ሊሞት የተቃረበ ፖሊስ አለ ነበር የሚሉት፡፡ ያው በግድያ ወንጀል ለመክሰስ ነው፡፡ የግድያ ወንጀል ደግሞ የዋስ መብትን አያስፈቅድም፡፡ የዋስ መብታችን ያገደው የይግባኝ ፍርድ ቤት ቀጠሮውን ለአንድ ሳምንት ሲያራዝም መርማሪዎቹ ጉዳት ደርሶበታል የሚሉትን ፖሊስ የህክምና ምርመራ እንዲያመጡ ቢጠይቅም እነሱ ግን ሊያመጡ አልቻሉም፡፡ በሂደቱ መረዳት እንደቻልኩት ፖሊስም ሆነ ፍርድ ቤት በራሳቸው የሚወስኑት ነገር እንደሌለ ነው፡፡ እንዲያው ዳኛው ላይ የተሻለ ነገር ማየት ችያለሁ፡፡ የተወሰነም ቢሆን ትንሽ ነገር ደፍሮ በራሱ ወስኗል፡፡ ፖሊሶቹ ላይ ግን ሙሉ በሙሉ ጭንቀት ይታያል፡፡
በዋስ ይፈቱ ከተባልን በኋላ እስር ቤት ውስጥ ቆይተናል፡፡ ከዚህም የተረዳሁት መንግስት እኛን ማንገላታትና የእስር ጊዜያችን ማስረዘም እንደሚፈልግ ነው፡፡ የመንግስት እጅ ነበረበት፡፡ ፖሊስም ሆነ ዳኛ በራሳቸው መወሰን አልቻሉም፡፡ አስር አይነት ምክንያት ይዘረዝራሉ፡፡
ነገረ ኢትዮጵያ፡- የፖለቲካ ፓርቲ አባል በመሆንሽ የደረሰብሽ የተለየ ነገር ምንድን ነው?
ወይንሸት፡- ከሌሎች በተለየ በተደጋጋሚ ከምርመራ እጠራ ነበር፡፡ አሰልቺና ተደጋጋሚ የሆኑ ነገሮችን ነው የሚጠይቁኝ፡፡ በምርመራው ወቅት የሶስተኛ ፖሊስ ጣቢያ አባል ያልሆኑ ማንነታቸው የማላውቃቸው ሰዎች ነበር የሚመረምሩኝ፡፡ ከመጠን በላይ ተደጋጋሚ ጥያቄ ይጠይቁኝ ነበር፡፡ ካሜራ እየተቀረጽኩ ነበር የሚያናግሩኝ፡፡ ምርመራው ከተከሰስኩበት ነገር ጋር የሚገናኝ አልነበረም፡፡ እኔ የተከስስኩት በሁከትና ብጥብጥ ነው፡፡ እነሱ የሚጠይቁኝ ግን ስለ ሰማያዊ ፓርቲ ነው፡፡ አንዴ ከፓርቲው እንድወጣ ይመክሩኛል፡፡ ለኢህአዴግ እንድሰልልም ሊያግባቡኝ ይሞክራሉ፡፡ መሰደድ የምፍለግ ከሆነ እንደሚመቻችልኝ፣ ከፖለቲካው ወጥቼ በተለይም ከኢህአዴግ ጋር መስራት ከቻልኩ ሀብታም እንደምሆን ሊመክሩኝ ይጥራሉ፡፡ ምርመራውና ክሱ ምንም አይነት ግንኙነት አልነበራቸውም፡፡
ነገረ ኢትዮጵያ፡- የሙስሊሙን ጉዳይ ለመከታተል ስትሄጂ ከገመትሽው በላይ ያልጠበቅሽው ሆኖ ያገኘሽው ነገር ምንድን ነው?
ወይንሸት፡- ሁሉም ነገር ያልጠበኩት ነው፡፡ በወቅቱ ጉዳዩን ለመታዘብ ስሄድ እንደዛ አይነት ችግር ይፈጠራል ብዬ አልገመትኩም፡፡ መንግስትን ተቃውሞው አስፈርቶታል፡፡ ይህ ግልጽ ነው፡፡ ቦታው ላይ የነበረው አድማ በታኝ ፖሊስ፣ በአካባቢው ከነበረው የሙስሊሙ ማህበረሰብ ይበልጥ ነበር፡፡ ያደረሱባቸው ነገርም ያልጠበኩትና አሰቃቂ ነገር ነው፡፡ የሰው ልጅ እንደዛ ይደበደባል ብሎ ለማሰብ ይከብዳል፡፡ የሙስሊሙን ማህበረሰብ እንቅስቃሴ ሌላ መልክ ለመስጠት እዛው ላይ ድራማ ሲሰሩ ታያለህ፡፡ ለምሳሌ ያህል በጣም ትልቅ ገጀራ ነገር ነው፣ በጨርቅ ነገር ተጠቅልሏል፡፡ የሙስሊሙ ማህበረሰብ ለብጥብጥ ይዞት የመጣ ለማስመስል ሲሞክሩ በርቀት እመለከት ነበር፡፡ በጣም በርካቶች ሙስሊም በመሆናቸው ብቻ ተደብድበዋል፡፡ በሙስሊም ስም መጠራት ህመም እስኪሆን ድረስ ማለት ነው፡፡ ሆን ተብሎ ጥይት ተነጣጥሮ የተተኮሰባቸው ሰዎች ነበሩ፡፡ ለምሳሌ ያህል ከ17 የሙስሊሙ የመፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴ አባላት መካከል አንዱ የሆነው የያሲን ኑሩ ታናሽ ወንድም ፋኢዝ ኑሩን መጥቀስ ይቻላል፡፡ ፋኢዝ ኑሩ ስግደት ላይ እያለ ጥይት ተተኩሶበት እንደተመታ አብረን ታስረን በነበርንበት ወቅት ለማረጋገጥ ችያለሁ፡፡ እሱ ምንም የሚያውቀው ነገር የለም፡፡ እነሱ ደግሞ የሚጠይቁት ስለወንድሙ ነው፡፡ እየሰገደ ስለነበር ከተመታ በኋላ ነው ያየው፡፡ ህክምናም ልክ እንደ እኔ ‹‹የአገር ጉዳይ ነው›› ተብሎ አልታከመም፡፡ ጥይቷ እስኪፈታ ድረስ አልወጣችም ነበር፡፡ ይህን ያህል ርህራሄ በጎደለው መንገድ ነው አገር እየገዙ የሚገኙት፡፡
አብዛኛዎቹ ሴቶች መስጊድ ውስጥ ነው የነበሩት፡፡ ወንዶቹ ናቸው ውጭ ላይ ይሰግዱ የነበሩት፡፡ በእስልምና እምነት መሰረት በሴቶች መስገጃ ወንድ አይገባም፡፡ መስጊድ ውስጥ የሚገኝን ሰው አውጥቶ መደብደብ ይቅርና መግባት አይፈቀድም፡፡ ነገር ግን አድማ በታኞች ከእነ ጫማቸው ሴቶች የሚሰግዱበት ውስጥ ገብተው ተደባድበዋል፡፡ ሁኔታውን አብረውኝ የታሰሩት ሴቶች እያለቀሱ ነበር የነገሩኝ፡፡ ይህ ዘግናኝና እነሱ እምነት አላቸው ወይ? ብለህ እንድትጠይቅ የሚያስገድድ ነው፡፡ አድማ በታኝ ሴቶች መስገጃ ድረስ ገብቶ ህጻናትን፣ እናቶችንና ነፍሰ ጡሮችን በጭካኔ ሲደበድብ በጣም ያሳዝናል፡፡ ሙስሊሙ ማህበረሰብ በጣም አዝኗል፡፡
ነገረ ኢትዮጵያ፡- እንደገለጽሽልኝ ከተያዝሽበት ጊዜ ጀምሮ በደል ደርሶብሻል፡፡ ለ29 ቀናትም እስር ቤት ቆይተሻል፡፡ ባልሄድኩ ብለሽ ይጸጽትሻል?
ወይንሸት፡- ጉዳዩን ተገኝቼ በማየቴ በጣም ደስተኛ ነኝ፡፡ ለማየት ነው የሄድኩት፡፡ ተይዤ የእስር ቤት አያያዙን ጨምሮ በርካታ ነገሮችን መታዘብ ችያለሁ፡፡ በሙስሊሙ ማህበረሰብ ላይ የሚፈጸምበትን ግፍና በደል በአካል ተገኝቼ ማየት ችያለሁ፡፡ ደህንነቶቹ በምርመራ ወቅት የሚያደርጉትን ነገር መታዘብ ችያለሁ፡፡ በአስተሳሰብም ደረጃ ጉዳዩን በአንድ ደረጃ ከፍ ብየ እንዳየው ያደረገኝ በመሆኑ ተገኝቼ የሙስሊሙን እንቅስቃሴ በመታዘቤ ምንም አልጸጸተኝም፡፡ እንዲያውም በመገኘቴ ኮርቻለሁ፡፡
ነገረ ኢትዮጵያ፡- አመሰግናለሁ ወይንሸት!
ወይንሸት፡- እኔም አመሰግናለሁ!

የብኣዴን ካድሬዎች ራሳቸውን ከሕወሓት የበላይነት ማላቀቅ አለብን የሚል ዘመቻ ጀመሩ።

Sep 6/2014
ዘላለማችንን የፖለቲካ የበታችነት የተጠናወተን ጥገኞች ሆነናል::


ምንሊክ ሳልሳዊ እንደዘገበው በባህር ዳር ካለፈው ሳምንት ጀምሮ እየተካሄደ ያለው የብአዴን ካድሬዎች እና የለውጥ ሃዋርያ ብሎ ራሱን የሚጠራው የወጣት አባላት ቡድን በድርጅቱ ውስጥ ያገረሸውን የለውጥ ጥያቄ ተከትሎ በብኣዴን ውስጥ እየተነሳ ስላለው የፖለቲካ መብት ጥያቄ በሰፊው ውይይት የተደረገበት ሲሆን ብአዴን የኢሕኣዴግን መርሆ እንደጠበቀ ከሌሎች ድርጅቶች የበላይነት እና ጥገኝነት መላቀቅ አለበት በሚሉ እና ወደ አመራር የመጡ በትግሉ ያልተሳተፉ ግለሰቦችን አደርባይነት አሳሳቢ ደረጃ ላይ መድረሱን አጽንኦት ሰጥተው ተወያይተውበታል::

የባህር ዳሩ ስብሰባ እንዲሁም ያዝ ለቀቅ እየተደረገ ያለው የክልል ከተሞች የብአዴን ካድሬዎች ስብሰባ በድርጅቱ መካከል መከፋፈልን ለመፍጠር እና አለመተማመንን ለማንገስ እንዲሁም ጥላቻን ለማስፋፋት የታቀደ ነው ሲሉ ካድሬዎቹ ይናገራሉ፤ የብአዴኖች በቡድን እየተከፋፈሉ በተለያዩ አጋጣሚዎች መገናኘት እና መሰብሰብ ለሕወሓት ድንጋጤን የፈጠረ መሆኑን ውስጥ አዋቂ ምንጮች ተናግረዋል:: በፖለቲካ ጥቃት ከድርጅቱ የተገለሉ የቀድሞ አባላት ከድርጅቱ ካድሬዎች ጋር መገናኘታቸው እና ወዳጅ መሆናቸው ለሕወሓት እንዳልተዋጠለት ታውቋል።

ብኣዴን ከፍተኛ የስልጣን እርከኖች ላይ ለምን አይቀመጥም? የጦር ሰራዊቱ በአንድ ብሄር ተወላጆች የበላይነት ተቀፍድዶ ተይዟል በትግሉ ትንሽ እና ትልቅ ሳይባል ብኣዴን መስእዋትነት ከፍሏል ;; ብኣዴን ስሙ የተቀየረው የኢሕዴንን ታሪክ ለማኮላሸት እና ኢሕዴን የሚለውን ስም ከገበሬው እና ከክልሉ ለማጥፋት የተሸረበ ሴራ ነው እንጂ ለአማራው የታዘነ ጉዳይ አይደለም የሚሉ አስተያየቶች የተደመጡ ሲሆን ዘላለማችንን የፖለቲካ የበታችነት የተጠናወተን ጥገኞች ሆነናል እንዳሉ ተጠቁሟል::

የብአዴን ውይይት ያተኮረበት የፖለቲካ የበላይነት በዝርዝር የቀረበ ሲሆን የትግል አቅጣጫዎችን ለምን በራሳችን አንቀይስም የሚል ጥያቄ ሳይቀር እንደተካተተበት ሲታወቅ የስልጣን ክፍፍል የክልልሎች የልማት ስኬት እና ከጀርባ የፖለቲካ ውኪሎች ሙስና እና ጫና ለክልል ልማቶች እንቅፋት እንደሆነ በዝርዝር ተቀምጧል::እንዲሁም በሙስና ስም ስለሚታፈኑ የድርጅቱ አባላቶች የተነሳ ሲሆን እነማን ናቸው በከፍተኛ ደረጃ በሙስና የተዘፈቁት የሚሉ ጥያቄዎችም እንደተነሱ ታውቋል::እንደዚህ አይነት ነጥቦች ካሁን በፊትም ተነስተው ተድበስብሰው እንዲታለፉ የተደረገ እንደነበር ተሰብሳቢዎች የተናገሩ ሲሆን አሁን ግን መልስ ሊሰጥባቸው ይገባል ሲሉ በአንክሮ ተናግረዋል።

Saturday, September 6, 2014

የኢቲቪ ጥያቄዎች እና የእኔ መልሶች (በግርማ ሰይፉ – የፓርላማ አባል)

Sep 5,2014
በሰሞኑ ሰለ ግል ሚዲያው ትንሽ ለማለት ሞክሬ ነበር፡፡ የዚሁ ተከታታይ የሆነውን ይህ ፅሁፍ ደግሞ በዋነኝነት የአሁኑ የኢትዮጵ ብሮድካሰት ኮርፖሬሽን ለዘጋቢ ፊልም መስሪያ ብሎ ያዘጋጀውን ጥያቄ መሰረት አድርጌ አቀርብላችኋለው፡፡ ከጥያቄው መረዳት እንደምትችሉት ጥያቄዎቹ ለውንጀላ በሚያመች መልኩ የተዘጋጁ ሰለሆነ በግልፅነት ጥያቄውን ለመመለስ የሚሞኩሩ ሰዎች እንደ አትሌት ሀይሌ ገብረስላሴ መጠለፋቸው አይቀርም፡፡ ሚዲያ ብላችሁ አዲስ ዘመንን ስትከሱት ኢቲቪ ከሌላ ቦታ ካመጣው ጋር ቆርጦ ቀጥሎ ዘጋቢ ፊልም የግል ሚዲያውን ለመክሰስ ግብዓት ያደርጋችኋል፡፡ ይህን ለመከላከል ኢቲቪን በሩቁ ማለት ሳይሻል አይቀርም፡፡ ለዚህም ነው የቀረቡልኝን ጥያቄዎች ለኢቲቪ ብመልስ ምን ሊሆን እንደሚችል በምትረዱት ሁኔታ ከዚህ በታቸ የማቀርብላችሁ፡፡
Girma Seifu
Girma Seifu
ኢቲቪ እንደ መግቢያ በመጀመሪያ ያቀረበው ጥያቄ “ብሄራዊ ጥቅም ማለት ከኢትዮጵያ አንፃር መገለጫዎቹ ምንድናቸው?” የሚል ነው፡፡ የዚህ ጥያቄ ዓላማ በመጨረሻ ላይ ከሚቀርቡት ጥያቄዎች አንፃር ስታዩት የግል ሚዲያዎቹ እነዚህን ብሔራዊ ጥቅሞች እየተጋፉ ነው የሚል መደምደሚያ ለመስጠት እንዲመቸው ያቀረበው ነው፡፡ በእኔ እምነት በቅርቡ እየሰፋ የመጣውን ሀገር ማለት? የሚለው ተጠየቅ መሬት ሲደመር ሰው (አንድ እና አንድ ሁለት እንደሚባለው) ማለት አይደለም፡፡ ለምሣሌ የዶክተር በድሉ ዋቅጅራ ሀገር ማለት የእኔ ልጅን ልብ ይሏል፡፡ የመለስ ዜናውንም ሀገር ማለት ህዝብ ነውም የሚረሳ አይደለም፡፡ የዶክተር ሀይሉ አርአያን የሀገር ልክፍት ግጥምም ትዝ ይለኛል፡፡ የዚህን ጥያቄ መልስ እንደ እልም ፈቺ፤ ለእልም ፈቺ እንተውው እና በእኔ እምነት ብሔራዊ ጥቅም ወይም የሀገር ጥቅም ማለት በአጭሩ የዜጎች ጥቅም ብዬ ነው የማስበው፡፡ የሀገረ ኢትዮጵያ ጥቅም የሚባል ነገር ሁሉ የኢትዮጵያዊያን ጥቅም ማለት ነው ብዬ ነው የምረዳው፡፡ ኢትዮጵያዊያኖች እንዴት ነው የሚጠቀሙት ብለን ወደ ዝርዝር ሰንገባ ደግሞ በሠላም ወጥቶ መግባት/መኖር፤ የሰውነት መብት መከበር፤ የህግ የበላይነት መኖር፤ ወዘተ ሲሆኑ መንግሰት እነዚህን ኃላፊነቱን ለመወጣት የሚያስችለው መዋቅር እንዲኖረው ማደረግ ደግሞ የህዝቡ ዋነኛ ኃላፊነት ይሆናል፡፡ አንድ አንድ ሰዎች ጥቅም የሚባለውን ነገር ከራሳቸው በላይ ዘለግ አድርገው ማየት ስለማይችሉ ለልጅ ልጆች ሀገርን እንደ ሀገር አስጠብቆ ማለፍ የእነርሱ ድርሻ አይመስላቸውም፡፡ ለዚህም ነው ድንበር ማስከበርም፣ ዛፍ መትከልም፣ ወንዝ ተራራውም እንዲጠበቅ ማድረግ የመሳሰሉት አብይ ጉዳዩች ባለቤት ያጣሉ፡፡ ንቁ ዜጎች ግን ይህን በፍፁም አይዘነጉትም፡፡ ዛፉ ጥላው አድጎ ባይጠቀሙበት እንኳን ችግኝ መትከል ሀገራዊ ሃላፊነታቸው እንደሆነ ይረዳሉ፡፡ ድንበር ማስከበርም እንዲሁ ለልጅ ልጆቻቸው የሚተላለፍ መሆኑን ስለሚገነዘቡ ሀገር ቆርሰው አይሰጡም፡፡ ለኢቲቪ ይህን መልስ ብሰጠው የት ሰፈር እንደሚቆርጠውና ከምን ጋር እንደሚቀጥለው መገመት አያሰቸግርም፡፡
የኢቲቪ ተከታዩ ጥያቄ “የግል ፕሬሶች የሀገሪቱን ብሔራዊ ጥቅሞች በማሰጠበቅ ረገድ ምን ያህል እየሰሩ ነው?” የሚል ሲሆን ከመጀመሪያው ጥያቄ ጋር ያለው ዝምድና ፍንትው ብሎ ይታያችኋል፡፡ በግሌ ለዚህ ጥያቄ ያለኝ መልስ “አንድም የግል ፕሬስ” የኢትዮጵያን ጥቅም አሳልፎ ለአሜሪካ፣ ለአውሮፓ፣ ለሀረብ ወይም ለሌላ አካል አሳልፎ ይሰጣል የሚል እምንት ሊኖረኝ አይችልም፡፡ በሀገራችን እንዳለመታደል ሆኖ መንግሰት የሚባለው አካል ከላይ የዘረዘርኳቸውን የህዝብ ጥቅሞች ማስጠበቅ ሲያቅተው እና ይህን ችግሩን በሌላ ማለከክ ሲፈልግ የግል ሚዲያዎቹ ቅርብ ሆኖ ያገኛቸዋል፡፡ ስለ መንግሰት በጎ በጎውን መዘመር እንጂ የመንግሰትን ኃላፊነት ያለመወጣት እና ደካማነት ሲነሳ “የሀገር/የህዝብ ጥቅም” ተነካ ብሎ ቡራ ከረዩ ማለት ይቀናዋል፡፡ እውነቱን ስንመለከተው ግን ጥቅም የተነካ ከሆነ ወይም ሊነካ ከሆነ የተነካው የሹሞች ጥቅም ነው፡፡ እርሱም እንደ ዜጋ ከሚያገኙት ሳይሆን በወንበር ተገን የሚዘርፉት ነው፡፡ የግል መልሴ ለኢቲቪ ይህ ነበር የሚሆነው፡፡
ሶሰተኛው ጥያቄ “የግል ፕሬሶቹ መሰረታዊ የሆኑ የግለሰብ መብቶቸን በሚጋፋ መልኩ እየሰሩ ይገኛሉ ይባላል፤ በዚህ ላይ እርሶ ይስማማሉ ወይ?” የሚል ነው፡፡ እነዚህ የግል ፕሬሶች ማሰረጃ የሌለው ነገር አትመው የግል መብት ነክተው ከሆነ በማስረጃ ፍርድ ቤት ማቅርብ ይቻላል፡፡ የግለሰብ መብት የሚሉት ግን ሹመኞቹን እንደሆነ መረዳት አይከብድም፡፡ አንድ አንድ ሹመኞች የህዝብ ማስተዳደሪያ የሆኑትን የሹመት ቦታዎች ሲረከቡ አብሮ የሚመጣውን የግል መብትና ነፃነት ገደብ ይዘነጉታል፡፡ የመንግሰት ንብረት ሲያስተዳድሩ በትክክል ካልተጠቀሙ ሚዲያው ይህን ለልጆቻቸው ብሎ ዝም ብሎ ሊያልፋቸው አይችልም፡፡ ይህ በመንግሰት ሹመኞች ላይ ብቻ ሳይሆን የህዝብ ህውቅናን ያገኘ ማነኛውም አይነት ታወቂነት ደረጃ ላይ የሚገኝ አርቲስት፣ ባለሀብት፣ ሯጭ፣ ወዘተ ሊሆን ይቸላል፡፡ ከዚህ በዘለለ ግን የግል ሚዲያዎች የግለሰቦችን መብቶች ሊጥሱ የሚችሉበት ምክንያት የለም፡፡ ማንነቱ ስለማይታወቅ ሰው ቢፅፉ ማንም ሊያነብላቸው አይችልም፡፡ ትርፉ ኪሳራ ነው የሚሆነው፡፡ በእርግጥ እነዚህን የግል መብቶች ከላይ እሰከታች የሚጣሱት ጡንቻና መዋቅር ባለው መንግሰት ነው፡፡ መንግሰት ደግሞ እነዚህን ድርጊቶች የሚፈፅመው ለህዝብ ጥቅም ስል ነው ይላል፡፡ እኛ ደግሞ በህዝብ ስም መብታችንን አትጣስ እያልን ለትግል የወጣነው በግል ሚዲያ ላይ ሳይሆን በመንግሰት ላይ ነው፡፡
አራተኛው ጥያቄ “አሁን በገበያ ላይ ያሉት የግል ፕሬሶች የጋዜጠኝነትን መሰረታዊ የስነ ምግባር መርሆዎችን ጠብቀው በመሰራት ረገድ ምን ዓይነት አዎንታዊና አሉታዊ አስተያየት አለዎት?” የሚል ነበር፡፡ ይህ በተደጋጋሚ ጋዜጠኛ ነኝ የሚሉት ሁሉ የሚያነሱት ነጥብ ሲሆን ሰምምነት ተደርሶበት ሁሉም ሊገዛለት ይገባል የተባለ የሰነ ምግባር መርሆ ግን በዓለም ላይ የለም፡፡ አብዛኞቹ የሚስማሙበት ግን ጋዜጣኛ መርዕ ማድረግ ያለበት ነገር ካለ “ተጠያቂነቱን ለህዝብ” ማድረግ ነው፡፡ ይህም ማለት የህዝቡን የመረጃ ፍላጎት ማርካት ነው፡፡ ከዚህ ተከትሎ የሚመጡ የመረጃ ትክክለኝነት፣ግብረገባዊነት፣የመሳሰሉት ሊመጡ ይችላሉ፡፡ ይህን ጋዜጠኛው ማሟላት ካቃተው ደግሞ ተጠያቂነቱ ለህዝብ ይሁን ካልን ፍርድ ሰጪውም ህዝብ ይሆናል ማለት ነው፡፡ ስለዚህ ህዝብ ዓይንና ጆሮ ሲከለክላቸው ከገበያ ይወጣሉ፡፡ ብሎም ይጠፋሉ፡፡ በዚህ ጊዜ “አከፋፋዮች” ናቸው እንዲህ የሚያደረጉት የሚል ክስ ውሃ አይቋጥርም፡፡ በውጭ ሀይል ግፊት ነው የሚለውም ክስ የትም የሚያደርስ አይሆንም ማለት ነው፡፡
በመጨረሻ የቀረበው ጥያቄ “የፖለቲካ ፓርቲዎችና ፕሬስ አንዱ በሌላው ላይ ያላቸው አዎንታዊና አሉታዊ ተፅህዕኖ እንዴት ይታያል?” የሚል ነው፡፡ የዚህ ጥያቄ ዓላማ የግል ፕሬሶቹ የተቃዋሚ ፓርቲዎች ልሣን ሆኑ የሚል መደምደሚያ ላይ መድረስ ነው፡፡ በእውነቱ ግን ሁልጊዜ ፕሬስ “የWatch Dog – የህዝብን ጥቅም የመጠበቅ” ስራውን መዘንጋት የለበትም – ፓርቲዎች በየተራ ስልጣን የሚይዙ ስለሆነ የፕሬስ ይሁንታን ለማግኘት መጣጣራቸው አይቀርም፡፡ ተገቢም ነው፡፡ በእኛ ሀገር ገዢው ፓርቲ “የህዝብ/የመንግስት” የሚባሉትን ሚዲያዎች ጠቅልሎ የያዘና መረጃም የማይስጥ ስለሆነ፤ የግል ሚዲያዎች ደግሞ በመንግሰት በኩል የተነፈጉትን መረጃ ለማግኘት እና የገዢው ፓርቲ ተግባርም ትክክል እንዳልሆነ ለማሳየት በተቃዋሚ ፓርቲዎች ጋር ቢወግኑ ክፋት የለው፡፡ ለነገሩ መንግስት መረጃ እየሰጣቸውም ቢሆን መንግሰት መደገፍ የማይፈልግ የግል ሚዲያ ማቋቋም ነውር የለውም፡፡ ነውር የሚሆነው በመንግሰት ሚዲያ ገዢውን ፓርቲ ብቻ ማገልገል ነው፡፡

Friday, September 5, 2014

በሰመራ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎችን ካድሬ ለማድረግ የተጠራው ስልጠና በማስፈራራት ተጠናቀቀ

Sep 5,2014
አኩ ኢብን አፋር ለዘ-ሐበሻ እንደዘገበው፦
በአፋር ክልል በረእሰ መዲናው በሰመራ የሚገኘው ብቸኛው ዩኒቨርሲቲ ለ10 ቀናት ሲሰጥ የቆየው የተማሪዎች ሰልጠና ባለፈው ሰኞ ተጠናቀቋል። በስልጠናው የክልሉ የፓለቲካ መሪዎች የተገኙ ሲሆን በአጣቃላይ ሰለ መጭው ምርጫ ቅስቀሳ እንደነበረ ምንጮችን ገልፆል።
afar univercity
እንደ ምንጮቻችን ዘገባ ከሆነ ለመጪውው ምርጫ ኢህአዴግን ምረጡ ካልመረጣቹሁ ግን ስራ አታገኙም በሚል ብዙ ማሰፈራራት የበዛበት ስልጠና እንደነበረ ታውቋል፡
በዚህ አመት ከተለያዩ ዩኒቨርሲቲ የተመረቁ ተማሪዎች በሰልጠናው የተገኙ ሲሆን በተማሪዎች በኩል ለሚነሱ ወቅተዊ ጥያቄዎች ተገቢ ምላሽ ከመስጠት ይልቅ ማስፈራራትና ማስጠንቀቅ እንደነበረ ታይቷል።
በመጪው ምርጫ ኢህአዴግ እና የክልሉ ፓርቲ አብዴፓ በዩኒቨርሲቲ ተመራቂዎች ላይ ያላቸው ድፍራቻ በግልፅ በታየበት በዚህ ስልጠና በክልሉ በግልፅ ስለሚታዩ ችግሮች ላይ የሚናገሩ ተማሪዎች ስማቸው እየተመዘገበ እንደነበረ የአይን እማኞች ገልጸዋል።
በዘንድሮው ምርጫ በመላው ኢትዮጵያ ሊነሳ ስለሚችለው ሁከት ተማሪዎችን ከወዲሁ የማስጠንቀቅ ስልጣና ይመስላል ሲሉ አሰተያየት ሰጪዎች ይናገራሉ።
በኢትዮጵያ ከሚገኙ 9 ክልሎች እስከ አሁን ብዙዎቹም የሚገባቸውን ያህል ባይሆኑም በትምህርት አመስፋፋት ኋላ በመቅረት አፋር ክልል መሪነቱን ይይዛል።

Thursday, September 4, 2014

ወጣቱን ለማደንቆር ያለመው ስልጠና ህወሓትን ለመቅበሪያነት ይዋል!

September 4, 2014 
ህወሓት፣ ከሶስት መቶ ሺህ በላይ የመንግሥት ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተማሪዎችን በየቦታው ሰብስቦ እያሰለጠነ ነው። ይህ ሲያልቅ የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተማሪዎች ስልጠና ይቀጥላል ተብሏል። በድምሩ ወደ ግማሽ ሚሊዮን የሚጠጋ ወጣት አንድ አይነት ሰነድ አንብቦ ለ2007 ትምህርት ይዘጋጃል ማለት ነው። ስልጠናው ወደ መንግሥት ሠራተኞችና ሌሎች የኅብረተሰብ ክፍሎችም ይስፋፋል ተብሎ ይገመታል።
ግንቦት 7: የፍትህ፣ የነፃነትና የዲሞክራሲ ንቅናቄ በዚህ ሥልጠና ላይ ያለውን እይታ በነሐሴ 16 ቀን 2006 ዓም ቁጥር 328 ርዕሰ አንቀጹ መግለጹ ይታወሳል። ግንቦት 7 የዩኒቨርስቲ ተማሪዎች በወያኔ ስልጠናዎች ላይ ተቃውሞ ለማሰማት መድፈራቸው ወጣቱ ለለውጥ የተዘጋጀ እንደሆነ አመላካች መሆኑን ተገንዝቦ ይህ የለውጥ ፍላጎት በድርጅት እንዲታገዝ ወጣቱ በትናንሽ ሕዋሶች ራሱን እንዲያደራጅ መክሯል። ሆኖም ግን ህወሓት ለስልጠናው የሰጠው ትኩረት ቀድሞ ከታሰበው በላይ በመሆኑ ንቅናቄዓችን በዚህ ርዕሰ ጉዳይ ላይ እንደገና ሊመለስበት ወስኗል።
ህወሓት፣ ይህንን ያህል መጠነ ሰፊ ስልጠና ማድረግ ለምን አስፈለገው? የዲሞክራሲ ኃይሎችስ ይህንን ስልጠና እንዴት ለራሳቸው ጥቅም ሊያውሉት ይችላሉ?
ህወሓት ይህንን ትርጉም የለሽ ስልጠና በአሁኑ ሰዓት ለመስጠት የፈለገበትን በርካታ ምክንያቶች ማቅረብ ቢቻልም የሚከተሉት ሁለቱ ግን ዋነኛዎቹ ናቸው ብለን እናምናለን።
አንደኛውና ዋነኛው ምክንያት ህወሓት የተከታዮች ድርቅ የደረሰበት መሆኑ አድርባይ መሪዎቹን ማሳሰቡ ነው። በሚሊዮን ይቆጠራሉ የሚባሉት የኢህአዴግ አባላት ልባቸው ከህወሓት ጋር አለመሆኑ ግልጽ እየሆነ መጥቷል። በተለይ ደግሞ በተላላኪዎቹ ብአዴን፣ ኦህዴድ እና ደህዴግ የተሰባሰቡ አባላት በግልጽ ህወሓትን መቃወም እየጀመሩ ነው። ህወሓት የራሱን መጥፊያ እያደራጀ መሆኑ የተሰማው በመሆኑ አዳዲስ “ምዕመናንን” ከከፍተኛ ትምህርት ተቋማት አካባቢ መመልመል ይፈልጋል። የመንግሥት ንብረትና መዋቅር ለፓርቲ ስልጠና የሚጠቀም በመሆኑ ከብዛት የሚገኝ ትንሽም ቢሆን ጥቅም የሚያገኝ ከሆነ የወጭው ጉዳይ ህወሓትን አያሳስበውም። ስለሆነም ይህ ስልጠና በተቻለ መጠን ብዛት ያላቸዉን የተማተሩ ወጣቶች በአድርባይነት ለህወሓት ማሰለፍን አላማዉ አድርጎ የተነሳ ስልጠና ነዉ።
ሁለተኛው አቢይ ምክንያት ደግሞ ህወሓት ለኢትዮጵያ ወጣት ለማስተላለፍ የፈለገው መልዕክት ወደ እያንዳንዱ የዩኒቨርስቲ ተማሪ ጆሮ መድረሱን ማረጋገጥ መፈለጉ ነው። መልዕክቱም “ሜዳ ውስጥ ያለሁት ተጫዋች እኔ ብቻ ነኝ። ለሚቀጥሉት አርባና አምሳ ዓመታትም እኔን የሚገዳደረኝ አይኖርም፤ ስለሆነም የኢትዮጵያ ወጣት ሆይ ለለውጥ ያለህ ተስፋ ከንቱ ነው። አርፈህ ቁጭ ብለህ ተገዛ” የሚል መልክት ነው።
ስልጠናዎቹ ከላይ የተጠቀሱትን ሁለት ዓላማዎችን በሚገባ ማስፈፀም ይችላሉ ብሎ መገመት ከባድ ነው። የስልጠናው ይዘት እጅግ የወረደ እና የሰልጣኞቹን ብስለት ግንዛቤ ውስጥ ያላስገባ መሆኑ ስልጠናውን ምፀት የበዛበት አድርጎታል፤ አሰልጣኞቹንም ትዝብት ውስጥ ጥሏቸዋል። የስልጠናዎቹ ጽሁፎች (ማንዋሎች) ይዘት ደግሞ የአዘጋጆቹ የእውቀት ማነስ ምን ያህል አሳሳቢ ደረጃ ላይ ያለ መሆኑ ለተማሪዎቹ ተጨባጭ ማስረጃዎች ሆነውላቸዋል። በአጠቃላይ ስልጠናው ለአሰልጣኝ ካድሬዎች ያልተዘጋጁበት ፈተና ደቅኖባቸዋል። የኢትዮጵያ ወጣት ሲሞሉት የሚሞላ ባዶ ጋን አለመሆኑን እያዩት ነው። ወጣቶች ጠጣር ጥያቄዎችን ያነሱባቸዋል፤ አሰልጣኖች እነዚህ ጥያቄዎች እንዴት መመለስ እንዳለባቸው ስለማያውቁ ይደናበራሉ። መልስ ሲጠፋ ቁጣ፣ ዛቻና ማስፈራሪያ ይከተላል።
ይህም ሆኖ እነዚህ ስልጠናዎች ለህወሓት ምንም ውጤት አያስገኙም ብሎ ማለፍ አይቻልም። የስልጠናዎቹ ውጤት የሚወሰነው ግን የኢትዮጵያ ወጣት ከህወሓት ውጭ ለሚመጣ መረጃ ባለው ቅርበት መጠን ነው። ሁሉም የመረጃ ምንጮች ተዘግተውበት የህወሓትን የእድገትና የሰላም መዝሙር ሲሰማ ለኖረ ሰው በስልጠናው የሚሰጡ ባዶ ፕሮፖጋንዳዎችን የመቃወሚያ ምክንያት አይኖረውም። ለተለያዩ የመረጃ ምንጮች ቅርበት ያለው ወጣት ግን የህወሓት መዝሙር ከግራዚያኒ የእድገትና የሰላም መዝሙር የተለየ አለመሆኑን ይረዳል። በፋሺስት ወረራ ወቅት ግራዚያኒም ኢትዮጵያን በመንገድና በህንፃ እየገነባሁ ነው፤ በጥቂት ዓመታት ውስጥ አውሮፓ የደረሰችበት ደረጃ ላይ አደርሳታለሁ ይል እንደነበር ይታወሳል።
የህወሓትን ኢትዮጵያን ለአርባና አምሳ ዓመታት የመግዛት እቅድን ወጣቱ ምክንያታዊ ነው ብሎ ይቀበላል? የራሱን አፋኝ ህጎች አክብረው እየተፍጨረጨሩ ያሉ ተቀናቃኖቹን እንኳን በእንጭጩ እየደፈጠጠ ያለ ሥርዓት “ኃላፊነት የሚሸከም አጣሁ” የሚለው ሰበቡ በወጣቱ ዘንድ ምን ያህል ተቀባይነት ይኖረዋል? በግንቦት 7 እምነት ይኸኛው የስልጠና ዓላማ ሊሳካ የሚችለው በዲሞክራሲያዊ ኃይሎች ድክመት ብቻ ነው። ዘረኛውንና ዘራፊውን ወያኔ መጣል ብቻ ሳይሆን ከወያኔ በኋላ ፍትህ፣ እኩልነትና ብልጽግና የሚሰፍኑበትን ስትራቴጄ ያዘጋጀና ለስትራቴጂዉ ክንዉንራሱን ያዘጋጀ ድርጅት መኖሩን የኢትዮጵያ ወጣት ማወቅ ይኖርበታል። ግንቦት 7: የፍትህ፣ የነፃነትና የዲሞክራሲ ንቅናቄ ከሌሎች ዲሞክራሲያዊ ድርጅቶች ጋር በመተባበር ኢትዮጵያን ወደ ነፃነት፣ እኩልነትና ብልጽግና ጎዳና ለማስገባት እየታገለ መሆኑን ሁሉም ወጣት ሊገነዘብ ይገባል። ይህ ግንዛቤ ካለ የኢትዮጵያ ወጣት ለእብርተኛው፣ ዘረኛው፣ ሙሰኛውና ከፋፋዩ ህወሓት ተገዢ አይሆንም።
በስልት ከተጠቀምንበት ህወሓት ብዙ ሚሊዮኖች የሕዝብ ገንዘብ አውጥቶበት ያዘጋጀው ስልጠና ለራሱ ከሚሰጠው ጥቅም በላይ ለዲሞክራሲያዊ ኃይሎች የሚሰጠው ጠቀሜታ ይበልጣል። ለምሳሌ፣ ግንቦት 7 እነዚህን ስልጠናዎች የኢትዮጵያን ወጣት ለትግል ያላቸውን ዝግጁነት ለመገምገም ተጠቅሞበታል። “የኢትዮጵያ ወጣት ለትግል ዝግጁ ነው – የቀረው ድርጅት ነው” ሲል የግምገማውን ውጤት አሳውቋል። በዚህም ርዕሰ አንቀጽ ይህንኑ መልዕክት ማስረጽ ይፈልጋል።
በአምባገነን ሥርዓቶች ውስጥ የሚኖሩ ዲሞክራሲያዊ ድርጅቶች ከተለመዱ አደረጃጀቾች መለየት አለባቸው። መደበኛ (Formal) አደረጃጀቶች አባላትን ለአደጋ ያጋልጣሉ። በዚህም ምክንያት ነው ግንቦት 7፣ ኢ-መደበኛ (Non Formal) አደረጃጀቶች የሚመርጠው። በእኛ ሁኔታ “ኢ-መደበኛ አደረጃጀት” ስንል አራት ይሁን አምስት የሚተማመኑ ወጣቶች የሚፈጥሩት የግንቦት 7 ሴል ነው። ይህንን ሴል የፈለጉትን ስም ሊሰጡት ይችላሉ – እድር፣ ክበብ፣ የሆነ ስፓርት ቡድን ደጋፊ የተመቻቸውን ስያሜ ይስጡት። የተቋቋመበት ዓላማ ግን ግልጽ ነው – ለፍትህና ለነፃነት የሚደረገውን ትግል ማገዝ ነው። ይህ ኢ-መደበኛ ስብስብ ራሱን የግንቦት 7 አካል አድርጎ ይቁጠር። የግንቦት 7 ፕሮግራሞችንና ጽሁፎችን ያንብብ። ስብስቡ ለመረጃዎች ራሱን ቅርብ ያድርግ። መረጃዎችን ይለዋወጥ። በሂደት ቀጣዩ መንገድ ግልጽ እየሆነለት ይመጣል።
እየተካሄደ ያለው የህወሓት የጅምላ ስልጠና ለኢ-መደበኛ ድርጅቶች መስፋፋት ምቹ ሁኔታ ይፈጥራል። የግንቦት 7 አባላትና ደጋፊዎች እነዚህን ስልጠናዎች የግንቦት 7 ሴሎችን ለማደራጀት እንዲጠቀሙበት እንመክራለን። ግንቦት 7 በኢትዮጵያ ወጣት የፈጠራ ችሎታ ላይ እምነት አለው። የኢትዮጵያ ወጣት አደንቁሮ ሊቀብረው የመጣውን ስልጠና ህወሓትን ለመቅበሪያነት እንደሚጠቀምበት የግንቦት 7 እምነት ነው።
ድል ለኢትዮጵያ ሕዝብ!!!

መልዕክት ከእስክንድር ነጋ፣ ጥቁሩን ሳምንት ተቀላቀሉ

September 4, 2014
እንደሰማሁት ከሆነ ጥቁር ሳምንት በሚል የተጀመረው ዘመቻ ጥሩ ዘመቻ ነው፡፡ በማህራዊ ሚዲያው ሲንቀሳቀሱ የነበሩትም ሆነ ጋዜጠኞች በመታሰራቸው እንቅስቃሴው አለመዳከሙ ያስደስታል፡፡ መጭው ዘመን የነጻነት ይሆን ዘንድ ኢትዮጵያውያን ይህን የመሰሉ እንቅስቃሴዎችን መደገፍ፣ ማበረታታትና መቀላቀል አለባቸው፡፡ በተለይ በአሁኑ ዘመን ማህበራዊ ሚዲያው ትልቅ ለውጥ እያመጣ ነው፡፡ በግብጽና ቱኒዚያ ማህበራዊ ሚዲያው ቀላል የማይባል ለውጥ አምጥቷል፡፡ ህወሓትና ሌሎችም ታጣቂ ኃይሎች ከቻይና እና ከቬትናም ልምድ ቀስመዋል፡፡ ያ ሌላ ዘመኑ ነበር፡፡ አሁን ዘመኑ ተለውጧል፡፡ ዘመኑ የሰጠንን አጋጣሚ ተጠቅመን ለነጻነታችን በሰላማዊ መንገድ መታገል አለብን፡፡ ጥቁር ሳምንት በሚል የተጀመረውን ዘመቻ በርትታችሁ መቀጠል አለባችሁ፡፡ ወጣቱ፣ ዳያስፖራው፣ ጋዜጠኛው በእንደዚህ አይት ዘመቻዎች፣ በሰላማዊ ሰልፎች፣ ማህበራትን በማቋቋማ፣ በውይይቶች መሳተፍ አለበት፡፡

አንዳንዶች ፌስ ቡክ ምንም ለውጥ እንደማያመጣ ሊገምቱ ይችላሉ፡፡ ከፌስ ቡክ አልፎ በአሁኑ ወቅት ያለው እንቅስቃሴ ለውጥ አያመጣም ብለው የሚገምቱ ይኖራሉ፡፡ ግን ያለ ጥርጥር ለውጥ ያመጣል፡፡ ውሃ በ99ንኛው ዲግሪ ሴንቲግሬድ ነው የሚፈላው፡፡ እስከዛ ድረስ ምንም አይነት ለውጥ አይታይበትም፡፡ ውሃ የሚያፈላ ሰው 99 እስኪደርስ ድረስ ማህል ላይ ተስፋ ቆርጦ ሊተውው ይችላል፡፡ ግን 99 ዲግሪ እስኪደርስ ድረስ የራሱ የሆነ የማይታይ ለውጥ ያደርጋል፡፡ ተስፋ ያልቆረጠ በአንድ ዲግሪ ለውጡን ያየዋል፡፡ በፌስ ቡክ የሚደረጉትና ሌሎች እንቅስቃሴዎችም ከዚህ አንጻር ነው መታየት ያለባቸው፡፡ ለውጥ የሚመጣው በእያንዳንዱ እንቅስቃሴ ድምር ውጤት ነው፡፡ 99 ዲግሪ እስኪደርስ ለውጡ ላይታይ ይችላል፡፡ ጥቁር ሳምንትን የመሳሰሉት ተደማምረው ነው የሰላማዊ ትግሉን 99 ዲግሪ የሚያደርሱት፡፡ ተስፋ መቁረጥ የለብንም፡፡

በጥቁር ሳምንት የታሰርነውንና ሌሎች ችግር እየደረሰባቸው የሚገኙትን ኢትዮጵያውያንን በማስታወሳችሁ በግሌ ማመስገን እወዳለሁ፡፡ ኮርቼባችኋለሁ፡፡ የእኛን መታሰር ብቻ ማንሳቱ አሊያም መጨነቁ በቂ አይደለም፡፡ እንደዚህ በተግባር ንቅናቄ መጀመር አለበት፡፡ ውጤት እናመጣለን፡፡ የሰላማዊ ትግሉ ዲግሪ ሴንቲግሬድ 99 የሚደርስበት ጊዜ ሩቅ አይደለም፡፡

መልዕክት ለዳያስፖራው የእኛ አገር ፖለቲካ አንድ ችግር የገንዘብ አቅም ነው፡፡ በሰላማዊ መንገድ የሚንቀሳቀሱ ተቃዋሚ ፓርቲዎች አባላትን ለማደራጀት፣ ቢሮ ለመክፈት፣ ሰላማዊ ሰልፎችን ለማካሄድ፣ ውይይቶችን ለማድረግ፣ ልሳንና በራሪ ወረቀት ለማሳተም ገንዘብ ያጥራቸዋል፡፡ የፖለቲካው አንቀሳቃሽ ኃይል ቢሆኑም በገንዘብ ችግር ምክንያት አጀንዳ ማንሳት ይሳናቸዋል፡፡ በቂ አባላት አያገኙም፡፡ ህዝብ ውስጥ ለመግባትም ይቸገራሉ፡፡ ገንዘብ ከሌለ ምንም ሊሰሩ አይችሉም፡፡ ይህ በእኛ አገር ብቻ የሚደረግ አይደለም፡፡ የአሜሪካ ፖለቲካ ፓርቲዎች መካከል የሚደረገው ትግል የገንዘብ ነው፡፡ በምርጫም ሆነ በሌሎች አጋጣሚዎች ፓርቲዎቹ ከተለያዩ አካላት በሚያገኙት ገንዘብ ነው ውጤታማ እንቅስቃሴ የሚያደርጉት፡፡

የኢትዮጵያ ህዝብ በድህነት ውስጥ የሚኖር እንደመሆኑ የእኛ አገር የፖለቲካ ፓርቲዎች ከአባላቸው አሊያም አገር ውስጥ ከሚገኘው ህዝብ ሰብስበው የተሳካ ስራ ሊሰሩ አይችሉም፡፡ በመሆኑም አማራጭ ሊሆን የሚችለው በዳያስፖራው ነው፡፡ ዳያስፖራው ማህበረሰብ በአገሩ ለውጥ እንዲመጣ ይፈልጋል፡፡ በለውጡ ግን ቀጥተኛ ተሳታፊ አይደለም፡፡ ለዚህም አገር ውስጥ ለሚገኙትና በሰላማዊ መንገድ ለሚንቀሳቀሱትና ለሚደግፋቸው ፓርቲዎች የገንዘብ ድጋፍ ማድረግ ይጠበቅበታል፡፡ ይህ ካልሆነ ለውጥ ሊመጣ አይችልም፡፡ ኢትዮጵያ ውስጥ ሆነው መስዋዕትነት የሚከፍሉትን መደገፍ ካልተቻለ ለውጥ ሊመጣ አይችልም፡፡

ራዕያችን የማይደረስበት አይደለም ከ50ና 60 አመታት በፊት ኢትዮጵያ ከቅኝ ግዛት ነጻ እንዲወጡ ትልቅ እገዛ ያደረገችላቸው አገራት አሁን ዴሞክራሲያዊ ሆነዋል፡፡ ጋና፣ ማላዊና ቤኒንን መጥቀስ ይቻላል፡፡ በእነዚህ አገራት ዴሞክራሲ ሲሰፍን እኛ ወደኋላ ተመልሰናል፡፡ ነጻ ፕሬስ አላቸው፡፡ ነጻ ምርጫ ያካሂዳሉ፡፡ ህዝባቸው በነጻነትና በመረጠው መንግስት መተዳደር ጀምሯል፡፡

በተቃራኒው እኛ በአፈና ውስጥ ገብተናል፡፡ እኛ የምንጠይቀው እንደነዚህ አገራት ህዝቦች ነጻ ሆኖ ለመኖር ነው፡፡ የእንግሊዝንና የአሜሪካን ያህል ባይሆንም የእነዚህን አገራት ያህል ዴሞክራሲ ማስፈን ከቻልን ራዕያችን ተሳካ ማለት ነው፡፡ ስለሆነም የጠየቅነው ነገር ትንሽ ነው፡፡ ይህን ያህል የተለጠጠና የማይደረስበት አይደለም፡፡ ነጻ ያወጣናቸውን አገራት ያህል ዴሞክራሲ ለመገንባት መነሳት ትንሽ ነገር ነው፡፡ በመሆኑም በቀላሉ ልናሳካው የምንችለው ጉዳይ ነው፡፡

Wednesday, September 3, 2014

የወያኔ የጎሳ አፓርታይድ ሥርዓት በዲያስፖራው ኢትዮጵያዊ ላይ

September 2, 2014 
ወያኔ በለስ ቀንቶት የኢትዮጵያን በትረ ስልጣን ከተቆጣጠረ ጊዜ አንስቶ ከጫካ አዝሎት የመጣውን አብዮታዊ ዲሞክራሲና የአንድን ጎሳ ሁለንተናዊ የበላይነት የማስፈን ዓላማ ለማሳካት ባለው አቅም ሁሉ ሲሰራ ኖሯል።
ዘረኛው ወያኔ የትግሬ ጎሳን በመሣሪያነት ለመጠቀም ሲል ጎሳውን በሞራል፤ በኢኮኖሚ፤ በጤናና በትምሕርት ከሌላው የላቀ ደረጃ ላይ ማድረስ በሚለው መርሁ መሠረት የሃገሪቱን ማህበራዊ፤ ኢኮኖሚያዊ፤ ወታደራዊና የደህንነቱን ዘርፍ ሁሉ በትግሬዎች ቁጥጥር ሥር እንዲውል በማድረግ በኢትዮጵያ ውስጥ የጎሳ አፓርታይድ ሥርዓትን ዘርግቶ ይገኛል።
ይህ ብቻም አይደለም የወያኔ አገዛዝ መሣሪያ ይሆነኛል ከሚለው ከትግሬ ህዝብና ከትግራይ ክልል በዘለለ ኢትዮጵያ ስለምትባል ሃገርም ሆነ ኢትዮጵያዊ ስለሚባል ሕዝብ ዘለቄታዊ ጥቅምና ጉዳት ባለማሰብ የሥልጣን ዘመኑን ዘለዓለማዊ ለማድረግ ያስችለኛል በሚለው ጊዚያዊ ጥቅም ላይ ብቻ በማተኮር የሃገሪቱን መሬትና ዳር ድንበር ሳይቀር ለባዕዳን አሳልፎ በመስጠት የጊዚያዊ ፖለቲካና የንዋይ ጥቅም ማጋበሻው እያደረገው ይገኛል።
ሌላው ቀርቶ የሃይማኖት ተቋሙ እንኳ ከትግሬ ጎሳ የበላይነትና ቁጥጥር ውጭ እንዳይሆን ወያኔ ገና ሥልጣን ላይ ከመውጣቱ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተወሕዶ ቤተ ክርስቲያን ፓትሪያርክ የነበሩትን አቡነ መርቆሪዎስን ከመንበራቸው አሽቀንጥሮ በመወርወር በብዙ ሺህ ኪሎሜትር ተጉዞ ባህር ማዶ ድረስ በመሻገር በሃይማኖት ህንጸጽ ተወግዘው በመሰደድ ከኦርቶዶክስ እምነት ይልቅ ወደ ካቶሊኩ እምነት አዘንብለው የነበሩትን አባ ጳውሎስን ትግሬ በመሆናቸው ብቻ መርጦ ፓትርያርክ አድርጎ ሊሾማቸው ችሏል።
ከዛም በኋላ ኢትዮጵያን በምታክል ታላቅ ሃገር የሥልጣን እርከን ላይ ለ20 ዓመታት ያህል ቆይቶ እንኳ ከዚህ ከጠባብ የጎጥ አስተሳሰቡ መላቀቅ ባለመቻሉ ትግሬ በመሆናቸው መርጦ ፓትሪያርክ ያደረጋቸውን አቡነ ጳውሎስ ሞት ሲወስዳቸው አሁንም ከ85 ሚሊዮን በላይ የሆነውን የአማራውን፤ የኦሮሞው፤ የደቡቡን ሕዝብ፤ ጋምቤላውን፤ የቤንሻንጉሉን ሕዝብ ሳይሆን አንድ ትግሬ ፍለጋ ወጪ ሃገር ድረስ በመሄድ እንደገና አቡነ ማትያስ የተባሉ ሌላ ትግሬ ከእየሩሳሌም በማምጣት ፓትሪያርክ አድርጎ ሾሟቸው ይገኛል።
ይህና ይህንን የመሳሰሉ የኢትዮጵያዊነት ስጋና ደም አለው የሚባል ሰው ይፈጽመዋል የማይባል አይን ያወጣ ይሉኝታ ቢስነትና ጋጠ ወጥ የወያኔ የዘረኝነት ተግባር፤ ዛሬ ሥርዓቱን ብቻ ሳይሆን ጎሳውንም ጭምር ምንም ዓይነት ሃፍረትና ይሉኝታ የሚባል ያልፈጠረባቸው ናቸው እያስባለ ይገኛል።
ከቅርብ ጊዜ ጀምሮ ደግሞ የወያኔ አገዛዝ እጁን በማስረዘም በዲያስፖራ የሚገኘውን ኢትዮጵያዊ እንኳ ከዘረኛው አገዛዝ ነጻ ሆኖ በሰላምና በነጻነት እንዳይኖር ስደተኛውን ኢትዮጵያዊ በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ በጎሳ አፓርታይድ ሥርዓቱ ቁጥጥር ሥር ለማዋል ከፍተኛ ጥረት በማድረግ ላይ ይገኛል።
ዲያስፖራው ኢትዮጵያዊ በሃገሩ የተነፈገውን ነጻነት፤ ፍትህና እኩልነት በዲያስፖራ ኑሮው የተጎናጸፈ ቢሆንም፤ ነገር ግን ሃገሬንና ሕዝቤን አልረሳም በማለት ሃገሩ ውስጥ በወያኔ የጎሳ አፓርታይድ ሥርዓት ሥር ለሚገኘው ወገኑ በመቆርቆር፤ ሥለ ኢትዮጵያ ሕዝብ ከመጮህና ድምጹን ከማሰማት ታቅቦ አያውቅም።
ይህንን ድምፁ ለታፈነው ሕዝብ ድምጽ የሆነውን ኢትዮጵያዊ የዲያስፖራ ኃይል ወያኔ በጠላትነት የሚያየው በመሆኑ ይህንን ኃይል ለማዳከምና ለመከፋፈል አያሌ ጥረቶችን ሲያደርግ ኖሯል።
ከእነዚህም ጥረቶቹ ውስጥ ተጠቃሽ የሚሆነው ዲያስፖራው ኢትዮጵያዊ እንኳንስ እትብቱ የተቀበረበት ሃገሩ በአሁኑ ዘመን በማንኛውም ነፃነትና ዲሞክራሲ በሰፈነባቸው የባዕድ ሃገራት ሁሉ እንደ ልብ የመግባትና የመውጣት፤ ከዛም ባሻገር ቤት የመስራትም ሆነ ንብረት ማፍራት ሰብዓዊ መብቱ ሆኖ ሳለ፤ የወያኔ አገዛዝ ግን ይህንን መብት ለዜጎች ፈቃጅና በችሮታ ሰጪ መስሎ በመቅረብ፤ የተለያዩ የመሬት ምሪት፤ የቤተ መሥራትና የኢንቨስትመንት በሮች ለዲያስፖራው ተከፍቷል የሚል የማታለያ ፕሮፓጋንዳ በማሰራጨት ስጦታ ሰጪና ነፋጊ ሆኖ እየቀረበ ዲያስፖራውን ኢትዮጵያዊ የውጪ ምንዛሪ ምንጭ በማድረግና የሰዎችን ዳታ ማግኛ ዘዴ አድርጎ ሲጠቀምበት ኖሯል።
ከዛም በመቀጠል ንብረት ያፈራና ቤት የሰራ የዲያስፖራ ኗሪን ዳታ በመጠቀም የሥርዓቱ ደጋፊ እንዲሆኑ ለመቀስቀስና የሃሰት ፕሮፓጋንዳ መልዕክቶችን ለማስተላለፍ ተጠቅሞበታል።
አሁን፤ አሁን ደግሞ ንብረት ያለህና እንደልብህ ኢትዮጵያ የምትገባና የምትወጣ ሁሉ በወያኔ ላይ ተቃውሞ ብታነሳ በንብረትህ ላይ ወይም የፈቀድኩልክን የመግባትና የመውጣት መብት አግደዋለው ወይም አሸባሪ ብዬ ዘብጥያ አወርድሃለው እያለ በተቀጣሪዎቹ አማካኝነት ዲያስፖራውን ኢትዮጵያዊ እያስፈራራ ይገኛል።
በእርግጥ የወያኔ አገዛዝ ኢትዮጵያ ውስጥ እንደሚያደርገው ሁሉ ዲያስፖራውንም ለመቆጣጠር የሚያስችል የሚዲያም ሆን የሶሻል ሚድያ ቁጥጥር፤ እንዲሁም የፌደራል ፖሊስ፤ የመከላከያና የደህንነት ኃይል የሌለው ሲሆን ሆኖም ግን በተለያየ ዘዴ ዲያስፖራውን በቀጥታና በተዘዋዋሪ መንገድ ለመቆጣጠር የሚያስችሉ ተቋማትን ለማደራጀት ትኩረት ሰጥቶ በመንቀሳቀስ ላይ ይገኛል።
ከእነዚህ የወያኔ አገዛዝ በውጪ ሃገራት ካተኮረባቸው ተቋማት ውስጥም በውጪ ሃገራት የተቋቋሙ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያናት በአንደኛ ደረጃ ተጠቃሽ ናቸው።
እነዚህን ከፍተኛ ተከታይ ያላቸውን በውጪ የተመሠረቱ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያናትን በቁጥጥር ሥር በማዋል ወያኔ የጎሳ አፓርታይድ ሥርዓቱን በዲያስፖራው ኢትዮጵያዊ ውስጥ ለማስፈን ለሚያደርገው ጥረት አንዱ ምሳሌ የሚሆነውም፤ መንበሩ ለንደን ላይ አድርጎ እንዲቋቋም የተደረገው የሰሜን ምዕራብ አውሮፓ ሃገረ ስብከት ነው።
የዚህ ሃገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ በማድረግ የወያኔ አገዛዝ ሹሞ የላካቸው አቡነ እንጦስ የሚባሉ ትግሬ ሲሆኑ የሃገረ ስብከቱ ስራ አስኪያጅ የተደረገውም መጋቢ አዕላፍ ተወልደ ገብሩ የተባለውም እንዲሁ ትግሬ ነው።
ይህ ብቻም አይደለም ሃገረ ስብከት በተባለው ሰበካ አስተዳደር ውስጥ የሚገኙት አብዛኞቹ በጎሳ የተሰባሰቡ ትግሬዎች ናቸው።
ሌላው የደቡብ አውሮፓ ሃገረ ስብከት ተብሎ ጣሊያን ሮም ላይ የተቋቋመውን በሊቀ ጳጳስነት እንዲመሩ የተደረጉት ደግሞ አቡነ ሙሴ የተባሉ እንዲሁ ትግሬ ናቸው።
እንደ አውሮፓ አቆጣጠር በ2005 ምርጫ 97ን ተከትሎ ወያኔ ሕዝብን በግፍ በጨፈጨፈበት ወቅት የለንደኗ ቤተ ክርስቲያን በግፍ ለተገደሉት ኢትዮጵያኖች ፀሎት ለማድረግ ስትዘጋጅ፤ የወያኔ አገዛዝ ለሞቱት ሰዎች አብያተ ክርስቲያናት ጸሎት እንዳያደርሱ በአቡነ ጳውሎስ አማካኝነት መመሪያ አስተላልፎ ስለነበር የወያኔ ወኪሎችና ደጋፊዎች የሆኑ ካህናት ቤተ ክርስቲያኗ ለተገደሉት ሰዎች ጸሎት ማድረግ የለባትም በማለታቸው ይህ በሕዝቡ ውስጥ እንደተሰማ ከፍተኛ የሕዝብ ቁጣን አስነስቶ የቤተ ክርስቲያኗ አባላት አቡነ ጳውሎስን በማውገዝ ከአሁን በኋላ ቤተ ክርስቲያኗ የአቡነ ጳውሎስ ስም ቅዱስ ብላ በጸሎት ላይ እንዳትጠራ ውሳኔ በማስተላለፍ በግፍ ለተገደሉት ኢትዮጵያውያን ሙሉ ጸሎት እንዲካሄድ አደረጉ።
በዚህ ወቅት ለቤተ ክርስቲያኗም ሆነ ለሃገሩ እንግዳ የነበሩት አቡነ ሙሴ በአጭር ጊዜ ቆይታቸው ሕዝበ ክርስቲያኑ ተክለ ሰውነታቸውንና ጭምተኝነታቸውን በማየት እግዚአብሔር ያመጣልን ቅዱስ ሰው በማለት አክብሮ የተቀበላቸው ቢሆንም እሳቸው ግን የወያኔ መመሪያ ሲጣስና ወያኔ ሲወገዝ ወያኔነታቸው ገንፍሎ ወጥቶ በመናደድ “ደንቆሮ ሁሉ!!” በማለት ሕዝብን በመሳደብ ሕዝብንና ቤተ ክርስቲያንን ረግጠው ሊወጡ ችለዋል።
በዚህ ምክንያት ከለንደኗ ማርያም ቤተ ክርስቲያን ከተለዩ በኋላ የመንደር ልጆቻቸው የሆኑትን ትግሬዎች አሰባስበው ሥላሴ ቤተ ክርስቲያንን መሠረቱ።
በመጀመሪያ የጎሳው አባላት ብቻ የተከተሏቸው በመሆኑ ቅዳሴው በትግርኛ ቋንቋ እንዲሆን ጭምር የተጠየቀ ሲሆን ቀጥሎ ግን የዋሁና የጎሳ ፓለቲካው የማይገባው ምስኪኑ ሕዝበ ክርስቲያን ቤተ ክርስቲያን እስከተከፈተ ድረስ ወደ ቀረበኝ እሄዳለሁ በሚል የዋህነት ስሜት የጎሳ ፖለቲከኞች ወደሚመሩት ቤተ ክርስቲያን በመሄድ መገልገል በመጀመሩ በብዛት የሚመጣውን ሕዝብ ገንዘብና ጉልበት ላለማጣት ሲሉ የቅዳሴው ቋንቋ ሳይለወጥ እንዲቀጥል ሊያደርጉት ችለዋል።
አቡነ መሴ የለንደኗን ማርያም ቤተ ክርስቲያን በጎሳ ከከፈሉ በኋላ ከለንደን ወደ ኢትዮጵያ በመሔድ የአቡነ ጳውሎስ ታማኝ ባለሟል ሆነው በመቆየት ከዛ የወያኔ አገዛዝ በውጪ ሃገራት የሚያደርገውን የጎሳ አፓርታይድ ሥርዓት ለማስፋፋት ወደ ጣልያን ሃገር በመላክ የደቡብ አውሮፓን ሃገረ ስብከት እንዲያቋቁሙ ተደርገዋል።
በጣሊያን ሃገር ካሉት አብያተ ክርስቲያናት የሚሰበሰበው ገቢ ዝቅተኛ በመሆኑና የወያኔን ዓላማ ለማሳካት የሚችል ሆኖ ባለመገኘቱ አቡነ ሙሴ ከፍተኛ የሕዝብ ቁጥር ወደ ሚገኝበትና ከፍተኛ ገቢ ሊሰበሰብ ወደሚችልበት ወደ ጀርመን ሃገር በመሄድ መንበራቸውን በጀርመን ሃገር እንዲያደርጉ ተደረገ።
የወያኔ አገዛዝ አቡነ ሙሴን ፍራንክ ፈርት ወደሚገኘው የማሪያም ቤተ ክርስቲያን ሲልክ አስተዳዳሪ ከሆኑት አባ ሲራክ ከሚባሉ ሌላ ትግሬ ጋር በመመሳጠር ስለነበር ጀርመን ሃገር ብዙ አብያተ ክርስቲያናትን በመምራት የሚታወቁትን እንደ እነ ሊቀ ካህናት ዶ/ር መርሀዊ ተበጀም ሆኑ አጠቃላይ ሕዝበ ክርስቲያኑ ምንም ነገር ሳይነገረው አቡነ ሙሴ ታቦት በመያዝ ጀርመን የደረሱት በድንገት በታቦት ንግሥ ቀን ነበር።
በዚህም ዕለት አቡነ ሙሴ ከአሁን ጀምሮ መንበሬ በጀርመን ሃገር ፍራንክፈርት በምትገኘው ማርያም ቤተ ክርስቲያን ነው ብለው በማወጃቸው በሕዝቡ ውስጥ ከፍተኛ ቁጣና ተቃውሞ አስነስቶ ጳጳሱንም ሆነ ሊያቋቁሙት ያሰቡትን ሃገረ ስብከት ሕዝቡ ባለመቀበሉ ጉዳዩ ሲያከራክር ቆይቶ በመጨረሻ በግብጾች ገዳም ውስጥ እንዲቆዩ ተደርገው ወደ ኢትዮጵያ ተመልሰው መሄዳቸው ታውቋል።
ይህ ከሆነ በኋላ በአሁኑ ወቅት ደግሞ ውስጥ ውስጡን ተንኮል ሲሸረብ ቆይቶ ሊቀ ካህናት ዶ/ር መርሃዊ ተበጀን ጭምር በማለሳለስ አቡነ ሙሴ ተመልሰው ወደ ጀርመን በመምጣት እንደለመዱት ሕዝቡን በጎሳ በመከፋፈል የወያኔን የጎሳ አፓርታይድ ሥርዓት ቅርንጫፍ ሃገረ ስብከት መልሰው ለማቋቋም በዝግጅት ላይ እንደሚገኙ ለማወቅ ተችሏል።
በጀርመን የሚገኝ ኢትዮጵያዊ የኦርቶዶክስ እምነት ተከታይ ሁሉ ይህ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ሊዘረጋ የታሰበው የጎሳ አፓርታይድ ሥርዓት ሰለባ ከመሆኑ በፊት ነቅቶ መጠበቅና መከላከል ይገባዋል።
በወያኔ የጎሳ ፖለቲካ መዋቅር መሠረት እንዲመሠረቱ የተደረጉት እነዚህ ሁለቱ ሀገረ ስብከቶች ዓላማ ዲያስፖራው ኢትዮጵያዊ በውጪ ሃገራት የመሠረታቸው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያናት በስደተኛው ሲኖዶስ ሥር በመሆንና ገለልተኛ ነን በማለት ነጻ ሆነው ዘረኛውን የወያኔ አገዛዝ የሚጻረር ድምጽ ከማሰማት እንዳታቀቡ በማድረግ ተግባራቸው ሁሉ የአገዛዙን ሥራ በማወደስና ድጋፍ በመስጠት ብቻ ተወስኖ ለሃገረ ስብከትና ቤተ ክህነት ፈሰስ አድርጉ በማለት የውጪ ምንዛሪ መሰብሰቢያ እንዲሆኑ ታስቦ ነው።
በእንግሊዝ ሃገር የምትገኘው የርዕሰ አድባራት ለንደን ደብረ ጽዮን ቤተ ክርስቲያን በመጀመሪያ በአቡነ ሙሴ ተጠንስሶ በአቡነ እንጦስ ለንደን ላይ የተመሠረተውን የወያኔ የጎሳ አፓርታይድ ቅጥያ ሃገረ ስብከት ሳትቀበል ከአገዛዙ የቀጥታም ሆነ የተዘዋዋሪ ተጽዕኖ ነጻ በመሆን በሃብትና በአደረጃጀት ራሷን ችላ ትተዳደር ነበር።
ሆኖም ግን ሕዝቡ ሃብትና ጉልበቱን አስተባብሮ ህንፃ ቤተ ክርስቲያን ከገዛ በኋላ አምኖ መርጦ የሾመው አባ ግርማ ከበደ (የለንደኑ ዲያቢሎስ) የተባለው መነኩሴና ግብረ አበሮቹ የቤተ ክርስቲያኑን አባላት በመክዳት ለወያኔ ኤምባሲ ሄደው እጅ በመስጠታቸው ምክንያት በአሁኑ ወቅት ይህ ወያኔ ከጎሳው አባላት መርጦ ያቋቋመው ሃገረ ስብከት ከነ አባ ግርማ ጋር ግንባር በመፍጠር ቤተ ክርስቲያኗን ከአባላቱ ነጥቆ ለመቆጣጠር በማድረግ ላይ ያለውን ጥረት የቤተ ክርስቲያኗ አባላት ተቋቁመው በመታገል ከፍተኛ ትንቅንቅ ላይ ይገኛሉ።
አባ ግርማ ከበደ (የለንደኑ ዳቢሎስ)
ሌላው በአሁኑ ወቅት ይፋ እየሆነ የመጣው ወያኔ የጎሳ አፓርታይድ ሥርዓቱን በዲያስፖራው ኢትዮጵያዊ ላይ ለማስፈን በመሣሪያነት ከሚጠቀምባቸው ዘዴዎች ውስጥ በገንዘብና በጥቅማ ጥቅም ቀጥሮ የሚያሰማራቸው የስድብና የፕሮፓጋንዳ ወኪሎቹ ጉዳይ ሲሆን እነዚህ ቅጥረኛ ባንዳዎች የወያኔ የሙሉ ሰዓት ተቀጣሪ ሰራተኛ በመሆን አሉ የሚባሉ ኢትዮጵያዊ ግለሰቦችን ድርጅቶችንና ልዩ ልዩ የዲያስፖራው ተቋማት ላይ የስም ማጥፋት ዘመቻ በማካሄድ የሃሰት ውንጀላዎችን በማሰራጨት ዲያስፖራውን በታትነው በወያኔ ጫማ ስር ለማስገባት ቀን ከሌሊት በመስራት ላይ ይገኛሉ።
ወያኔ ዲያስፖራውን ኢትዮጵያዊ ለመቆጣጠር በሃይማኖት ተቋማት ውስጥ እንዴት ሰርጎ እንደሚገባ ከሚያስገነዝቡት ውስጥ አሁንም በለንደኗ ደብረ ጽዮን ቤተ ክርስቲያን ውስጥ የተፈጸመው ለሌሎች እንደ ትምሕርት ሊሆን የሚችል ጉዳይ ቀጥሎ የተመለከተው ነው።
የቤተ ከርስቲያኗ አባላት ቤተ ክርስቲያናቸውን ከወያኔ ዘረኛ አገዛዝ የሃገረ ስብከት ሹመኞች ጠብቀው ለማኖር ጥረት በሚያደርጉበት ወቅት ወገንና ደጋፊ በመምሰል ዲያቆን ነኝ የሚል አንድ ግለሰብ ወደ ቤተ ክርስቲያኗ ይጠጋል። በመቀጠልም ይኸው ሰው ወደ ፊት ተጠግቶ ካህናቱ ከሚቆሙበት ተርታ ካህን መስሎ በመቆም ይቀላቀላል። ሆኖም ግን ይህ ሰው ከካህናቱ ተርታ ከመቆሙ በስተቀር አንድም ቀን የድቁናም ሆነ የክህነት ተግባር ሲያከናውን ስለማይታይ ጉዳዩ ሰውን ሁሉ የሚያነጋግር ጉዳይ ሆኖ ቢከርምም ጉዳዩን ትኩረት ሰጥቶ ያጣራ ሳይኖር እንዲሁ ይኖራል።
ከጊዜ በኋላም ይህ ሰው የኮሚቴዎች ስብሰባ ሲኖር የካህናቱ ጉባኤ አባል ነው እየተባለ በጉባኤዎች ላይ መገኘት ይጀምራል።
በመጨረሻ ግን የዚህን ሰው ትክክለኛ ማንነት ማንም ሰው ሳያጣራና ሳይመረምር ሰውዬው ራሱን በራሱ ሊያጋልጥ ቻለ።
ይህ ሰው ስሙ መንገሻ መልኬ የሚባል ሲሆን ግለሰቡ ኢትዮጵያ ውስጥ በቤተ ክህነትና በአብያተ ክርስቲያናት አካባቢ በጸሐፊ ረዳትነትና በተላላኪነት ተጠግቶ ከመስራቱ በስተቀር ለድንቁና ቀርቶ ለጽዋኅኆህነት (የቤተ ክርስቲያን በር ከፋች) የሚያበቃ ሃይማኖታዊ እውቀት የሌለውና ከፍተኛ የባህሪ ችግር ያለበት ሰው መሆኑ ሊረጋገጥ ተችሏል።
የመንገሻ መልኬ ወደ ቤተ ክርስቲያኑ መጠጋት ዓላማም ወገን መስሎ በመቅረብ፤ ወደ ካህናቱና ወደ ቤተ ክርስቲያኗ አስተዳደር በመጠጋት የአቡነ እንጦስ (የወያኔ ሃገረ ስብከት) ስውር ሰላይ (Under Cover Agent) በመሆን አስፈላጊውን የስለላ ተግባር ለማከናወን ነበር።
በዚህም መሠረት በሰላሙ ጊዜ የቤተ ክርስቲያኗን መረጃዎች ሁሉ ቤተ ክርስቲያኗን በቁጥጥራቸው ሥር ለማዋል ቀን ከሌሊት ለሚጥሩት ለአቡነ እንጦስ በስውር ሲያቀብል ከኖረ በኋላ በቤተ ክርስቲያን ውስጥ በአስተዳዳሪውና በአባላቱ መካከል ግጭት ሲነሳ ደግሞ ተልኮውን ለማሳካት ግንባር ቀደም የፀቡ አባባሽና አራጋቢ በመሆን የስውር ስራውን በይፋ ወጥቶ ማካሄድ ቀጠለ።
በዚህ ዓይነት የተሸፈነበትን ጭንብል ካወለቀ በኋላ ከለንደኑ ዲያብሎስ መነኩሴ ጋር በመሆን ቤተ ክርስቲያኗን ከአባላቷ ነጥቆ የወያኔው አገዛዝ ሹመኞች እንዲቆጣጠሯት ለማድረግ በተደረገው ጥረት ውስጥ ግንባር ቀደም ተዋናኝ ሆኖ ቀጠለ።
ቤተ ክርስቲያኗን ከአባላቷ ነጥቀው በቁጥጥራቸው ሥር ያስገቡ የመሰላቸው አቡነ እንጦስም ስውር ሰላያቸው የነበረው መንገሻ መልኬን ውለታ ለመክፈልና በሥራው እንዲገፋበት ለማበረታታት “መጋቢ ጥበብ” የሚል ማዕረግ በመስጠት በአሁኑ ወቅት የሃገረ ስብከቱ ዋና ጸሐፊ አድርገው ሾመውት ይገኛሉ ።
(መንገሻ መልኬን ኢትዮጵያ ውስጥ የሚያውቁት የቅርብ ጓደኞቹ፤ “በቀን ጎንደሬ በማታ ደግሞ ትግሬ” ነኝ በማለት በምላሱና በአድር ባይነቱ የሚኖር ሰው መሆኑን ማስረጃ ጠቅሰው ይገልጻሉ።)
ይህንን ባህሪ በመላበስ ነው ወደ ለንደኗ የስደተኞች ቤተ ክርስቲያን በመጠጋት የቅጥረኛ ባንዳነት ሥራ ሲሰራ የቆየው።መንገሻ መልኬ በዚህ ስራው የተሰጠውን ሹመት ሰው አላውቅለት ያለ ስለመሰለውም ይመስላል በቅርቡ በተሰራጨ የYouTube ቪድዮ ላይ የሃገረ ስብከቱ ጸሐፊ ነኝ በማለት ራሱን በራሱ ሲያስተዋውቅ ተስተዉሏል።
በቀን ጎንደሬ፤ በማታ ደግሞ ትግሬ ነኝ ባይ መንገሻ መልኬ።
የቪዲዮው አቀነባባሪና አቅራቢ ደግሞ ሌላው የወያኔ የስድብና የፕሮፓጋንዳ ቅጥረኛ ባንዳ የሆነው እንዳለ ወንዳፍራሽ (Endex) ሲሆን “ግመል ሰርቆ አጎንብሶ” እንደሚባለው የወያኔ ቅጥረኛ ባንዳ መሆኑን ሕዝብ እያወቀው፤ እሱ ግን ራሱን የደበቀ መስሎት ራሱን በኮፊያ፤ ፊቱን ደግሞ በጥቁር መነጽር በመሸፈን ሁሌ ሲቸገር ይታያል።
ይህ ብቻም አይደለም ይኸው የወያኔ ቅጥረኛ በሚያሰራጨው የወያኔ ፕሮፓጋንዳ ቪዲዮ ላይ ሁሉ ምስሉን ደብቆ በድምጹ ብቻ የሚናገር ሲሆን በዚህም ቪዲዮ ላይ በድምጹ ብቻ ጥያቄ የሚያቀርበው ይኸው እንዳለ ወንዳፍራሽ የተባለው የወያኔ ቅጥረኛ ባንዳ ነው።
እንዳለ ወንዳፍራሽ (Endex)
ከእንዳለና ከመንገሻ በተጨማሪ ቄስ አባተ ጎበና እና መሪጌታ ሄኖክ የሚባሉ ሁለት ካህናት በቪዲዮው ቃለ ምልልስ ላይ የተሳተፉ ሲሆን እነዚህ ሁለት ካህናት ለወያኔው የጎሳ አባርታይድ አገዛዝ ሹመኛ ለአቡነ እንጦስና ለነ ተወልደ ገብሩ በማደር የቤተ ክርስቲያኑን አባላት አባረው ቤተ ክርስቲያኗን ለሀገረ ስብከት ተብዬው በማስረከብ ሹመት ሽልማትንና ጥቅማ ጥቅምን ለመቃረም የክህደት ተግባር በመፈጸም ላይ የሚገኙ ናቸው።
“…. ያለበት ዝላይ አይችለም” እንደሚባለው በንግግራቸው ጣልቃ “ወያኔ አይደለንም፤ ወያኔ ማለት አይደለም” እያሉ ሲወተውቱ ይደመጣሉ፤ (ይህቺ የተበላች እቁብ መሆኗን አልተረዱምና ሕዝብን ያታለሉ መስሏቸው ነው)
በርግጥ በዛው ወያኔ አይደለንም ባሉበት አፋቸው ደግሞ ጥቂት ቆይተው ዓለም ያወቀውንና ፀሐይ የሞቀውን የወያኔ አገዛዝ በሃይማኖት ጉዳይ ጣልቃ የመግባትን ከፍተኛ ችግር በመካድ ማስተባበያ ይሰጣሉ።
በተለይ ቄስ አባተ ጎበና የተባለው ካህን በቀኝ እጁ የያዘው የክርስቶስ መስቀል ሳያስፈራው ሰውንም ሆነ ፈጣሪን በመዳፈር “በኢትዮጵያ ውስጥ መንግሥት በሃይማኖት ጣልቃ አይገባም፤ ገብቶም አያውቅም” በማለት በድፍረት በመዋሸት ከወያኔ ባለሥልጣናት የላቀ የሃሰት ማስተባበያ ያቀርባል።
ሙሉውን ቪድዮ ለማየት ቀጥሎ ያለውን ሊንክ ይጫኑ።
(ሙሉ ቪድዮውን ለማየት ረጅም ሰዓታትን ስለሚወስድ በተለይ መንገሻ መልኬ የተባለው የባንዳነት ሹመቱን የሚያረጋግጥበትን በ52፡ 38 ደቂቃ ላይ፤ የቄስ አባተን የወያኔ መንግሥት ጠበቃነት ደግሞ በ 1:4.16 ላይ መመልከት ይችላሉ።)
እንዳለ ወንዳፍራሽ ወደተባለው የወያኔ ቅጥረኛ ባንዳ ስንመለስም፤ የሱ የቅጥረኝነት ተግባር በቤተ ክርስቲያን ዙሪያ ብቻ የተወሰነ ሳይሆን በፖለቲካውም ዙሪያ ዲያስፖራውን ኢትዮጵያዊ ለሃገሩና ለወገኑ ድጋፍ ሰጪ እንዳይሆን ለማዳከም ወያኔ በሚሰጠው መመሪያና ትዕዛዝ መሠረት ግለሰቦችንና ድርጅቶችን የመሳደብና የማዋረድ ተግባርን የሙሉ ሰዓት ሥራው አድርጎት ይገኛል።
ይህ ግለሰብ ወያኔ በኤምባሲ ሽፋንና በስደተኝነት ስም በውጪ ሃገራት ካሰማራቸው ስላዮች ጋር በመመተባበር በቅርብ ጊዚ እንኳ በYou tube፣ viber text እና በሌሎች የSocial media ላይ ካሰራጫቸው የፕሮፓጋንዳ መልዕክቶች ውስጥ የሚከተሉት ይገኙባቸዋል።
በተለይ እድሜውን በሙሉ ለሃገሩ ኢትዮጵያና ለሕዝቧ ሲታገል የኖረው አንዳርጋቸው ጽጌ በዘረኞች ተይዞ ወደ ሰቆቃ የእስር ቦታቸው ሲወሰድ ያዘነው፤ የተቆጨውና የተቆጣው የግንቦት 7 አባል ወይም ደጋፊ ብቻ ሳይሆን አብዛኛው ስደተኛ ኢትዮጵያዊ ቢሆንም በአንጻሩ ግን የአንዳርጋቸው በወያኔ እጅ መግባት ዘረኛ ወያኔዎችንና ደጋፊዎቻቸውን እንዳስደሰተ ደግሞ የማይታበል ነው።
ቀጥሎም ወያኔ አንዳርጋቸውን በኢ.ቲ.ቪ. ላይ ምስሉን አቅርቦ መቶ ቦታ የተከታተፈ ቪዲዮ አሳየ። የቪዲዮው ዓላማም ጀግናችን የምትሉት አንዳርጋቸው ጀግና ሳይሆን ፈሪና የማይረባ ሰው ነው ብሎ በማዋረድ ሰውንም ሆነ ትግሉን ተስፋ ለማስቆረጥ የሚቻለውን ሁሉ አደረገ።
ይህ የወያኔ ድርጊት የሚጠበቅ የወራዳ ባህሪው መግለጫ ሲሆን ነገር ግን ሌላው የሚያስገርመው እንዳለ ወንዳፍራሽን የመሰለ ቅጥረኛ ባንዳ ወያኔን በማስደሰት የሚጥልለትን ፍርፋሪ ለመልቀም ሲል የወያኔን ፕሮፓጋንዳ መሠረት በማድረግ አንዳርጋቸውን ያዋርዳል ብሎ የሚያስበውን የፕሮፓጋንዳ ጽሑፍ እያዘጋጀ በfree Viber text ሌት ተቀን በመልቀቅ ድያስፖራውን ኢትዮጵያዊ ለማደናቆር መሞከሩ ነው።
እንዳለ ወንዳፍራሽ (Endex) የአንዳርጋቸውን መያዝ አስመልክቶ ከሚያስተላልፈው የወያኔ ፕሮፓጋንዳ ውስጥ አንዳርጋቸውን በፈሪነት በመፈረጅ ሌሎችም ስደተኞች ግንቦት 7 እና OLF እየተባሉ በወያኔ እየተለቀሙ እንደሚጋዙ የሚያስፈራራበት የፕሮፓጋንዳ የViber text ውስጥ አንዱ ቀጥሎ የተመለከተው ነበር።
“Andargachew vs Gen Fanta Belay!! Coward vs brave heart! General Fanta Belay was a graduate from sandhurst military academy the best Britain can offer, him n his top rated generals wanted to get rid off the derg junta, unfortunately the coup de tat was compromised and they caught him whilst escaping, they put him in TV to humiliate him but that brave man was still in my mind that he stood for his conviction n never shopped his collaboration, he died in bravery but Andy with in a month he drop names and their alleged involvement in terrorism!! For our church safety and for the pride of religion we thank ful for exposing names that are directly involved in the smear campaign against our church’s integrity, systematic theft and organised criminality of individuals!! But for those members of G7 n OLF elements u got a lesson of cowardice 101! The same will happen here in uk every one of u will shop each other!! N will have our peace and tranquility!! God save Ethiopia!!”
ከቦታ ቦታ በነጻነት የመንቀሳቀስ የዓለም አቀፍ ሕግ ተጥሶ የአንዳርጋቸው ጽጌ በየመን መታፈንና ለወያኔ አገዛዝ ሰቆቃና ግድያ አሳልፎ መሰጠት አስቆጥቶት አንዳርጋቸው ባስቸኳይ ይፈታና ሕጋዊ የዜግነት መብቱ ይጠበቅለት ዘንድ የእንግሊዝ መንግሥት ውጪ ጉዳይ መሥሪያ ቤትን ለመጠየቅ በእንግሊዝ ሃገር ኗሪ የሆኑት በሺህ የሚቆጠሩ ኢትዮጵያዊያን ሰላማዊ ሰልፍ ሲወጡ፤ የወያኔ ቅጥረኛ ባንዳ የሆነው እንዳለ ወንዳፍራሽ ግን በዲያስፖራው ኢትዮጵያዊ መካከል እየኖረ ቀጥሎ የተመለከተውን የወያኔ ፕሮፓጋንዳ በ viber text ያሰራጭ ነበር።
በዚህም ቴክስ ላይ ሰላማዊ ሰልፉን የሚያስተባብሩና ለኢትዮጵያና ለኢትዮጵያውያን ሲሉ ቀን ከለሊት በመድከም የሚታወቁትንና ሰልፉን ሲያስተባብሩ የነበሩትን እነ ዶ/ር ወንድሙ መኮንንና አቶ ዘላለም ተሰማን ለማዋረድ ይሞክራል። እንደውም የአንዳርጋቸው መታፈን ቀደም ሲል ኢትዮጵያውያን በሳዑዲ አረቢያ ግፍና በደል ሲፈጸምባቸው ኢትዮጵያዊው ሰላማዊ ሰልፍ ወጥቶ መቃወሙ ያመጣው መዘዝ ነው በማለት ኢትዮጵያውያኑን ይከሳል።
===============================================================================================
“ I was soo eager to see the video, the Free Andy outside the foreign office! No video, no emotional rant! No burning of flags? But I saw an article from the infamous woizero minitis usually lamenting and blaming every one that is labelled woyaney but herself n her ranting brigade! Last year ZT and her foot soldiers went outside the Saudi embassy showing off their anger by breaking all norms of communication! As invincible entities they released all their clips as if their view and anger would not yield tit for tat retaliation! In less than a year they lost Andy for rendition! For the lasts four years he was traveling through Yemen there were no interception or threat of rendition but because of these emotionally corrupted men of no morale and ethical principles, they brought the jungel rule on themselves, now after realising the legal cautions and possible liabilities they are hiding behind ill composed n unworthy article of woizero Wobdimu and few piX of the usual faces of protestors!!”
==============================================================
ከዚህ በተጨማሪ አንዳርጋቸው ጽጌን በተመለከተ ወያኔ ሌላ ድራማ አዘጋጅቶ በቴሌቪዥን ሊያቀርብ እንደሚችል በመገመት ሕዝቡን አስቀድሞ ለማስገንዘብ ታማኝ በየነ፤ ሲሳይ አጌና፤ ወንድም አገኝና ኤርሚያስ በኢሳት ቲቭ ላይ ያቀረቡትን ትንታኔ በተመለከተ ደግሞ የወያኔው ቅጥረኛ እንዳለ ወንዳፍራሽ በተለይ ለሃገሩም ሆነ ለኢትዮጵያ ሕዝብ እንደ ስሙ ሁሉ ምን ግዜም ታማኝ ሆኖ የኖረውን ታማኝ በየነን ለማዋረድና ለማቃለል ሲል ቀጥሎ የተመለከተውን የviber text አሰራጭቷል።
“Essat commentators such as once who was the toy boy for shek Al mudddeee, the tycoon billionaire and the twat who rained down from helicopter on His wedding day, in the early years of 2004 when the woyaney regime n the tycoon rejected him he was a paid promoter of the political elites, now he is gliding on the fame n glory hunting, a typical character if Narcist he has became the eye sore self promoted political analysit if our country, he is nine other than the reformed woyaney Tamage Beyene! With two other woyaney left overs recently have told us that woyaney is producing a documentary on Andy!! We have got the scoop now!! The star in that documentary is shaleqa Mamo!! Especially his adventure with £100,000 in Ethiopia, the time he wrote his book n got his honey trap wifey! He went to Ethiopia with £100,000 to set up clandestine networks for purpose of political agenda for the political elites of the diaspora; but he consumed the money for his own needs such as throwing a wedding”
ከላይ የተመለከተው የviber text መልዕክት የቅጥረኛ ባንዳው የእንዳለ ወንዳፍራሽ ሲሆን ለማራጋገጫነትም የviber text ኦርጂናል ኮፒ (Screen shot) በገጹ መጨረሻ ላይ መመልከት ይቻላል።
በመጨረሻም
እንዳለ ወንዳፍራሽና ሌሎች የወያኔ ቅጥረኞ ባንዳዎች፤ ለወያኔ ካደሩ ካህናት ጋር በማበር ጨርሶ እውነትነት የሌለውን ነገር እውነት አስመስለው በማሰራጨት በተለይ ወጣት ኢትዮጵያውያንን ለሃይማኖታችሁና ለቤተ ክርስቲያናችሁ ቁሙ! ካህናት ሲዋረዱ ዝም ብላችሁ አትዩ! በዕድሜ የገፋው ሰው ሁሉ ወንጀለኛና ከደርግ፤ ከኢህአፓ፤ ከኦነግና ከመሳሰሉት የጥንት ድርጅቶች የተረፈ ነው እያሉ በማሳሳት ለሃገርና ለሕዝብ በቆሙ ግለሰቦችና ተቋሞች ላይ እንዲነሱ በማድረግ የወያኔ መጠቀሚያ መሣሪያ እያደረጓቸው ይገኛሉ።
ከእነዚህ ወጣቶች ውስጥም የተነገራቸውን በማመን ለትክክለኛ ነገር የቆሙ መስሏቸው ሕግን የተላለፈ ድርጊት ውስጥ በመግባት በወንጀለኛነት እየተመዘገቡ ለመማርም ሆነ ተምሮም ጥሩ ስራ ለመያዝ መስናክል የሚሆን ነገር ውስጥ በማስገባት የወደፊት ዕድላቸ እንዲጨልምባቸው እያደረጓቸው ይገኛሉ።
ይህን ወያኔ በዲያስፖራው ውስጥ በማስፋፋት ላይ ያለውን ሽብርና ምስቅልቅል ለመታደግ፤ “ጠላትማ ምን ጊዜም ጠላት ነው፤ አስቀድሞ መክላት አሾክሿኪውን ነው” እንደተባለው እነዚህ ዲያስፖራው ኢትዮጵያዊን እርስ በርሱ ከፋፍለው በወያኔ ጫማ ሥር እንዲረገጥ ለማድረግ የሚጥሩ ቅጥረኛ ባንዳዎችንና ከሃዲዎችን አውቆና ተገንዝቦ ለይቶ በማወቅ የሚሰሩትን እኩይ ስራ ማምከን ይኖርበታል።
ኢትዮጵያ አንድነቷ ተጠብቆ ታፍራና ተከብራ ለዘለዓለም ትኑር!!
አስፋ ምን ተስኖት

የሸዋስ፣ ሃብታሙ እና ዳንኤል ተጨማሪ 28 ቀን ተቀጠረባቸው

Sep3,2014
• ‹‹2 ጊዜ 28 ቀን ሲቀጠርባቸው ምንም ሳትሰሩ ነው የመጣችሁት›› ጠበቃ ተማም
Habtamu abrhayeshiwas daniel






የሸዋስ አሰፋ፣ ሀብታሙ አያሌውና ዳንኤል ሺበሽ ተጨማሪ 28 ቀን ተቀጠረባቸው፡፡ ታሳሪዎቹ ዛሬ ጠዋት 3፡30 ላይ በአራዳ ምድብ ችሎት እንደሚቀርቡ ተነግሮ የነበር ቢሆንም ቀጠሮው ተቀይሮ 8፡30 ላይ በቀረበው ችሎት ‹‹ተጨማሪ መረጃ ለማሰባሰብ›› በሚል ተመሳሳይ ምክንያት 28 ቀን ተቀጥሮባቸዋል፡፡ መስከረም 22/2007 ዓ.ም ይቀርባሉ ተብሎ እንደሚጠበቅም ጠበቃ ተማም አባ ቡልጉ ገልጸዋል፡፡
ችሎቱ ወደ ከሰዓት የተዛወረበት ምክንያት ‹‹ዳኛ ስላልነበረ ነው›› የተባለ ሲሆን ችሎቱን ለመከታተል የአውሮፓ ህብረትና ሌሎች ተወካዮችን ጨምሮ በርከት ያለ ህዝብ ቢገኝም ቤተሰብም ጭምር ችሎቱን መከታተል ሳይችል ቀርቷል፡፡ ለዚህም የተሰጠው ምክንያት ‹‹ችሎቱ በጽ/ቤት የተካሄደ በመሆኑ ተመልካች አይይዝም›› የሚል መሆኑን ጠበቃ ተማም ገልጸዋል፡፡
ጠበቃ ተማም አባ ቡልጉ ቀጠሮውን አስመልክቶ ‹‹እስካሁን የምታቀርቧቸው ምክንያቶች ተመሳሳይ ናቸው፡፡ 2 ጊዜ 28 ቀን ሲቀጠርባቸው ምንም ሳትሰሩ ነው የመጣችሁት፡፡ አሁንም ተጨማሪ 28 ቀን ተቀጥሮባቸዋል፡፡ በዚህም ምክንያት ደንበኞቼ እየተጉላሉ ነው፡፡›› በሚል ውሳኔውን መቃወማቸውን ለማወቅ ተችሏል፡፡
በተጨማሪም ጠበቃው ታሳሪዎቹን ከቤተሰብ ውጭ ማንም እንዳይጠይቃቸው እየተደረገ መሆኑን በመግለጽ ቅሬታቸውን ያቀረቡ ሲሆን ዳኞቹ እንደተለመደው ‹‹በሌሎች ዘንድም ሊጠየቁ ይገባል›› የሚል ትዕዛዝ እንደሰጡ ታውቋል፡፡ ጠበቃ ተማምም በበኩላቸው ‹‹ፍርድ ቤት ሁል ጊዜም ትዕዛዝ ይሰጣል፡፡ ግን ተግባራዊ ሲሆን አይታይም፡፡›› ሲሉ ፍርድ ቤቱ የሚሰጠው ትዕዛዝ ተግባራዊ እንዲሆን ጠይቀዋል፡፡
ምንጭ ነገረ ኢትዮጵያ

Tuesday, September 2, 2014

አቻምና ኢትርሃሞይ ዘንድሮ ጎንታናሞ ቤይ! – ታደለ መኩሪያ

Sep2,2014
Andargachew Tsige
በ1997 ዓ ም  የቅንጅት በምርጫ  ማሸነፍ ያሰጋቸው የወያኔ መሪዎች  በሕዝብ ውስጥ መጠራጠርንና  መከፋፈልን ለመፍጠር ፤ በ1994 ዓ ም በሩዋንዳ የተፈጠረውን የዘር ማጥፋት ተመስሌት  ‘ኢትርሃሞይን’ ተቃዋሚዎች ሊፈጥሩ ነው ብለው ፕሮበጋንዳ ነዙ፤ የኢትዮጵያ ሕዝብ ለማያውቃችሁ ታጠኑ አላቸቸወ፤ በ1967 ዓ ም  አማርኛ ተናገሪውን ለይተው ለማጥፋት በፕሮገራማቸው ነድፈው መቀሳቀሳቸውን  በእነርሱ ቤት የኢትዮጵያ ሕዝብ አላየም፣ አልሰማም፣ አላነበበም፤ ኩኩ መለኮቴ መሰል  የልጆች ጫወታችሁን ተውና ማለቱን ገና አልገባቸውም፤ በሐምሌ መጨረሻ 2014 ዓ ም    የውጪ ጉዳይ ሚንስትሩ ዶክተር ቴዎድሮስ አድኖምም  በአሜሪካ  በዲሲ  ከተማ ቆይታቸው ባአካባቢው በሚገኝ  ለግል ሬዲዮ ጣቢያ  ቃል መጠየቅ  ሰጥተው ነበር፤ከሁለት ዓመታት  በላይ  በግፍ ታስረው  ሰለሚማቅቁት የእስልምና ሃይማኖት ተከታዮች መፍትሔ አፈላላጊ ተመራጮች  ኮሚቴ ጉዳይ  መጥይቅ ቀርቦላቸው ነበር። የኢትዮጵያ እስልምና ተከታዮችን  በጎንታናሞቤይ ኩባ ሰላጤ፣ በአሜሪካ ባሕር ሃይል መናሕሪያ በአልካይዳነት ተጠርጣረው ከታሰሩት ጋር  አመሳስላዋቸዋል። በጣም የሚያስደነግጥና የሚያስፈራ ፍረጃ፣ ኢትዮጵያ በሃይማኖት መቻቻል በዓለም ሕብረተሰብ የምትጠቀሰውን ሀገር በአንድ ጎርዳፋ ምላስ አፈር አበሏት፤ ከዚህ በፊትም ዶክተሩ ሰለእነዚሁ ‘ደምፃችን ይሰማ’ በማለት ፍትህን ሰለጠየቁት ሙስሊም ወንዶሞቻች ላይ የተዛባ ዘገባ በማቅረባችው ‘ትልቁ  ዳባ ሊጥ ሆነ’   በሚል መጣጣፍ ምክር መስል ሐሳብ አቅረቤላቸው ነበር። መዋሸትን ማደሪያቸው ካደረጉት ካድሬዎች  ከነሺመልስ ከማልና ከበረከት ሰዕሞን ራሶን ያርቁ የሚል ነበር፤ አልተቀበሉኝም፤ ደግመው ደጋግመው ዋሹ፤ የኢትዮጵያ የእሰልምና ተከታዮችን በአልካይዳነት መፈረጁ ሣህለን ማርያም  የሚያሰኝ ነው፣ ሌላው ደግሞ  በሰኔ ወር 2014 ዓ ም አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ  ከየመን ሳና አይሮፕላን ጣቢያ መታፈን  ሲጠየቁ ይሰጡት የነበረው መልስ የውጭ ጉዳይ ሚንስትርን የሚመጥን መልስ አልነበረም። በሌላ ኃይል ከጀርባ እንደሚነዱ የሚያሳይ ነበር፤ በአቶ አባይ ጸሐዬና በአለቃ ጸጋዬ በረሄ የዘር ተፋሰስ ፓለቲካ እየተገፉ  የማይመጥናቸውን አስነዋሪ  ሥራ  መስራታቸው ለቤተሰባቸው ብቻ ሳይሆን ሞያቸወ ከልብ ለሚወስዱቱ ዜጎች ያሳዝናል፤ ሕብረተሰቡ የሞያቸውን አገልግሎት በጥብቅ ይፈልገዋል። የውጭ ጉዳዩን  ሥራ በአፋቸው ጤፍ ለሚቆሉትና ውሸትን መተዳደሪያቸው ላደረጉት  ለሬደዋን ሁሴን ወይም ለሽፈራው  ሽጉጤ ቢለቁላቸው መልካም ነው። በውሸት መኮራኩር ከሚገጫገጨው ከትግራይ ጉጅሌዎች መንገሥት አባል የነበረው ኤርሚያስ ለገሠ ‘የመለስ  ቱሩፋቶች’ ባለቤት የሌላት ከተማ በሚለው መጸሐፉ ውስጥ ጥሩ ሥዕብና እንዳሎት፣ በ1997 ዓ ም ምርጫን አስመልክቶ ያቀረቡትን ሪፖርት፣ መሠረት አድርጎ ትልቅ ሙገሣን ቸሮታል,፤ ሌላው ዶክተር ተብዬው ደግሞ በዘር ፖለቲካ ናላው የዞረ መሆኑንም ሣይገልጽ አላለፈም።
ዶክተር ቴዎድሮስ አባል የሆኑበት የትግራይ ጎጅሌ ዋና አቀንቃኞቹ፤ሟቹ  መለስ ዜናዊ፣ አባይ ጸሐዬ፣ አርከበ ዐቁባይ፣ መስፍን ሰዩም፣ ሰባት ነጋ፣ አለቃ ጸጋዬ በረሄ ሀገር ለመገነጣጠል ለውጭ አገር ምደኞች ያደሩ  መሆናቸውን እያወቁ የእነርሱ አካል መሆኖ ያሳዝናል፡፡ አባቶ ቴዎድሮስ ብለው ሰም ሲያወጥሎት ለአገሩ አንድነት ሕይወቱን የሰዋን የጅግናውን የሐፄ ቴዎድሮሰን ፈለግ ተከትለው ለአንድነት መስዕዋትነት እንዲከፍሉ ነው።  በዘርና በሃይማኖት ሕዝቡን ከሚያለያዩት ከትግራይ ጉጅሌዎች ጋር ሀገርን በሃይማኖትና በዘር እንዲከፋፍሉ አልነበረም፤  ሰምን መላዓክ ያወጣዋል፣አንድአርጋቸውና ቴዎድሮስ  ለሀገር አንድነት  ተመስሌዎች ናቸው፤ ዶክተር ቴዎድሮስ አድኖምና አንድአርጋቸቸች ጽጌ ወንድማማቾች ናቸው፣ ማን ቃኤል ማን  አቤል እንደሆነ ሥራቸውና ትውልድ ይመስክር፤ ዶክተር ቴዎድሮሰ አድኖም  ወይስ አንድአርጋቸው ጽጌ የአባቶችን  ቃል  ያፈረሰው?  አቶ አድኖም ልጃቸውን ቴዎድሮስ በለው ሰመ ሲያወጡለት ለአንድነት በመሰዕዋትነት ክበርን፣  እንደሚያጎናጽፍ አምነውበት ነው። አቶ ጽጌም ልጃቸውን አንድአርጋቸው ብለው ስም ሲያወጡለት  በአንድነት ጸጋን አብስር ማለታቸው ነው። ኢትዮጵያ  የነዚህ የባለራዕይ  አባቶች ሀገር ናት።  ከትንታኔው ማንኛቸው ናቸው የእሣት ልጅ አመድ የሚባሉት?  ዶክተር ቴዎድሮስ አድኖም ወይስ አንድአርጋቸወ ጽጌ? አደራ ያልበላውን አንድአርጋቸውን አድባር ትከተለው፤  ዶክተር ቴዎድሮስ አድኖምም  በሃይማኖትም በዘር ከፋፋይ ከሆኑት  የትግራይ ጉጅሌዎች  እጅ ወጥተው ከሕዝብ ጎራ ይቀላቀሉ።የአባቶን ሕልም ዕውን ያድርጉ እላለሁ። ኢትዮጵያ  ከወደቀችበት በልጆቿ ትነሣለች።

ፑንትላንድና ሶማሌላንድ ከኢትዮጵያ ጋር የመዋሃጃ ሰነድ አቀረቡ

Sep2,2014
ሰነዱ አሜሪካንን ጨምሮ ለኃያላን አገሮች ቀርቧል


ራሳቸውን ራስ ገዝ አገር አድርገው በማስተዳደር ላይ ያሉት ሶማሌላንድና ፑንትላንድ ከኢትዮጵያ ጋር ውህደት ለመፈጸም የሚያስችላቸውን ሰነድ ለአሜሪካው የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መ/ቤት (ስቴት ዲፓርትመንት) ማቅረባቸው ተሰማ። ሰነዱ ለእንግሊዝና ለሌሎች የአውሮፓ ሃያል አገራት መቅረቡም ታውቋል። ለጉዳዩ ቅርብ የሆኑ ክፍሎች “እንሰጋለን” ሲሉ የውህደት ጥያቄው ሊተገበር የሚገባው እንዳልሆነ አመልክተዋል
ከኢትዮጵያ ጋር ለመዋሃድ ጥያቄ ያቀረቡት ሁለቱ የሶማሌ ጠቅላይ ግዛቶች የተጠቀሰውን ሰነድ ማቅረባቸውን የተናገሩት የጎልጉልምንጮች፣ የሰነዱን ዝርዝርና ውህደቱ በምን መልኩ ሊከናወን እንደሚችል ዝርዝር መረጃ ለጊዜው ከመስጠት ተቆጥበዋል።
ፑንትላንድና ሶማሌላንድ ራሳቸውን ከተበጠበጠችው እናት አገራቸው ነጥለው አገር ማስተዳደር ከጀመሩ ዓመታት ቢያስቆጥሩም እስካሁን ድረስ በአገርነት እውቅና አላገኙም። በዚህ መነሻ ይሁን በሌላ፣ ሁለቱ የሶማሌ ጠቅላይ ግዛቶች ኢትዮጵያን እናት አገራቸው ሆና እንድታስተዳድራቸው ሰነድ አዘጋጅተው ከማቅረባቸው በፊት ከኢህአዴግ ጋር ረዘም ላለ ጊዜ ሲመክሩ ቆይተዋል።
“ባለራዕዩና ወደር የሌለው የኢትዮጵያ ልጅ” እየተባሉ የሚጠሩት ሟቹ ጠ/ሚ/ር በህይወት እያሉ የተጀመረው ይህ የውህደት ጥያቄ ተግባራዊ ሊሆን ስለሚችልበት፣ ስለሚያስገኘው ጥቅምና ጉዳት አስተያየት እንዲሰጡ የተጠየቁ ዲፕሎማት “እኔም ሆንኩ ሌሎች ስጋት አለን” ይላሉ። ሲያስረዱም “ወደብ እናገኛለን። ቆዳችን ይሰፋል። ነገር ግን ችግሩ ደግሞ ከዚህ ሁሉ የከፋ ነው” ብለዋል።
mapችግሮቹን መዘርዘር ምን አልባትም በአገር ቤት የተለያዩ የእምነት ተቋማትና ምዕመናን ዘንድ ቅሬታ ሊያስነሳ እንደሚችል ያመለከቱት ዲፕሎማት ኢህአዴግ እጁን ሰብስቦ ሊቀመጥ እንደሚገባ መክረዋል። በሶማሊያ አካባቢ ካለው የአክራሪ ሃይላት መስፋፋት ጋር በተያያዘ ለደህንነት ሲባል ሃያላን አገሮች ጥያቄውን ሊደግፉት እንደሚችሉ ያመለከቱት አስተያየት ሰጪ “ውህደቱ በግፊትና በድጎማ ስም ተግባራዊ ይሁን እንኳን ቢባል ቅድሚያ የኢትዮጵያ ህዝብ በይፋ ደምጽ ሊሰጥበት ይገባል፣ ከፍተኛ የእምነት ቁጥር አለመመጣጠን ያስከትላል” የሚል ጥቅል ሃሳብ ሰንዝረዋል።
ኢህአዴግ በቀድሞ መሪው አማካይነት የሶማሌ ወደቦችን አማራጭ አድርጎ የመጠቀም ስትራቴጂ እንዳለው በተደጋጋሚ ሲገለጽ ነበር። ለዚሁ ተግባራዊነት መጨረሻው በይፋ ባይታወቅም በኢትዮጵያ ወጪ ወደቡ ድረስ ዘልቆ የሚገባ የመኪና መንገድ ግንባታ ተጀምሮ አንደነበር የሚታወስ ነው። በተለይ የፑንትላንድ ፓርላማ ሰዎች በተደጋጋሚ አዲስ አበባ ይመላለሱ አንደነበርም አይዘነጋም።
የህወሃት ሰዎች የወደብ ጉዳይ ካሳሰባቸው የኢትዮጵያ ንብረት የሆነውን የአሰብን የባህር በር ወደ ቀድሞው መንበሩ የመመለስ ስራ አጠንክረው መስራት የሚያስችላቸው ሰፊ የህግና የመብት አግባብ ስለመኖሩ የተናገሩት ዲፕሎማት “ሶማሌ አሁን ችግር ውስጥ ብትሆንም ህጋዊ ክልሎቿን ለመጠቅለል መስማማት የአንድን አገር ሉአላዊነት የመዳፈር ያህል በመሆኑ ጊዜ ጠብቆ ዋጋ ያስከፍላል። የህግ ድጋፍም የለውም፤ በፌዴሬሽን ለመቀላቀልም ቢሆን የሚያስችል አግባብ የለም” ብለዋል።
በቅርቡ ለመጠጥ ውሃ ፕሮጀክት “ፓርላማው” ሳያውቅ ከኢትዮጵያ ተቆርጦ የተሰጠውን መሬት አስመልክቶ ለተፈጠረው ቅሬታ መልስ የሰጡት የውጪ ጉዳይ ሚኒስትር ቃል አቀባይ ዲና ሙፍቲ “ከጅቡቲ ጋር የሚፈጸመው ውህደት አንዱ አካል ነው” በማለት የመሬቱን አላግባብ መሰጠት ማስተባበላቸው የሚታወስ ነው። ሪፖርተር ቃል አቀባዩን ጠቅሶ በወቅቱ እንደጠቆመው ኢህአዴግ ለጅቡቲ ያቀረበው የመሬት ግብር /ስጦታ/ በሂደት “ለመጠቃለል” የሚያስችል ውለታ ተደርጎ የሚቆጠር መሆኑን ነው። ኢትዮጵያ በራሷ ወጪ በጅቡቲ ወደብ ላይ የወደብ ኮሪዶር ለመስራት ከስምምነት መድረሷንም አስቀድሞ በቃል አቀባዩ አማካይነት መገለጹ አይዘነጋም። ይህንን የሚያስታውሱ የቀደመው ወደብ የመገንባት ውል እያለ ባቋራጭ “የውህደት ሃሳብ እንዴት ተሰነቀረ?” ሲሉ ይጠይቃሉ።
በተመሳሳይ ፑንትላንድና ሶማሌላንድ ከኢትዮጵያ ጋር ለመዋሃድ ፍላጎት ቢኖራቸውም በተግባር ሊውል የማይችል ቅዠት እንደሆነ አስተያየት ሰጪዎች አመልክተዋል። ሁለቱ ክፍለ ሃገሮች የኢትዮጵያ አካል ከሆኑ በኋላ በአንቀጽ 39 ንዑስ ቁጥር 1 መሠረት “የራሳቸውን ዕድል በራሳቸው የመወሰን እስከ መገንጠል ድረስ ያለው ያልተገደበ መብት” መሰረት በማድረግ ዳግም የመገንጠል ጥያቄ በማቅረብ ኢህአዴግ አስቀድሞ እውቅና እንዲሰጣቸውና አንደ ኤርትራ ውለታ እንዲሰራላቸው ተመኝተው ሊሆን አንደሚችል የሸረደዱም አሉ።

Monday, September 1, 2014

የተማሪዎች ስልጠናው ወደ ሙስሊሞ ኮሚቴ አፈላላጊ ዞሯል * ‹‹ጠበቆቹ በፖለቲካ ዘመቻ ተጠምደዋል!››

August1,2014
ባለፈው ሳምንት ለተማሪዎች በሚሰጠው ስልጠና ቴዲ አፍሮና ሰማያዊ አጀንዳ መሆናቸውን መግለጻችን ይታወሳል፡፡ በአሁኑ ወቅት ስልጠናው ወደ ሙስሊሙ እንቅስቃሴና የኮሚቴው ጠበቃዎች መዞሩን ለማወቅ ተችሏል፡፡ ለዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች በሚሰጠው በዚህ ስልጠና የሙስሊሙ መፍትሄ አፈላላጊና መንግስት የሙስሊሙ ጉዳይ እልባት እንዲሰጥ የጠየቁ አካላት በአክራሪነት ፈርጇቸዋል፡፡ ‹‹የልማታዊ ዴሞክራሲያዊ ስርዓት ግንባታ ፈተናዎች›› በሚለው ሰነድ የሙስሊሙ ማህረሰብ እንቅስቃሴ ደም ለማፍሳሰስ እየጣረ እንደሚገኝ ይገልጻል፡፡
ከዚህም ባሻገር የሙስሊሙ መፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴ ጠበቆች ከጥብቅና ይልቅ የፖለቲካ ስራ እንደሚሰሩ በሰነዱ ላይ ተጠቅሷል፡፡ በሰነዱ ገጽ 46 ላይ ‹‹ጠበቆቻቸው በእየ ዕለቱ የፍርድ ቤት ትዕዛዝ በመጣስ በሰፊ የፖለቲካ ዘመቻ የተጠመዱ ናቸው፡፡›› ሲል ያትታል፡፡
ሰነዱ ለስርዓት ግንባታ እንቅፋት ናቸው የሚላቸው የሁለቱንም እምነት ተከታዮች ሲሆን ‹‹በክርስትናም ሆነ በእስልምና ሽፋን አገራዊ አጀንዳዎችን አስቀድመው ከሚፈታተኑን ኃይሎች ባልተናነሰ ደረጃ ደግሞ በሚያገኙት የገንዘብ ጥቅማጥቅም ተደልለው አገራችን የጀመረችውን የእኩልነት ጉዞ የሚያጥላሉ፣ ህገ መንግስታዊ ስርዓታችንን ጥላሸት የሚቀቡ ኃይሎች አሉ፡፡›› ሲል የሁለቱን እምነት ተከታዮች ይወቅሳል፡፡
ሰልጣኞቹ የላኩልንን የሰነዱ ክፍል እንደሚከተለው አያይዘነዋል፡፡
blue
blue 2
ምንጭ ነገረ ኢትዮጵያ

የግንቦት 7 የፍትህ የነፃነትና የዲሞክራሲ ንቅናቄ ህዝባዊ ስብሰባና የገቢ ማሰባሰቢያ ዝግጅት በኖርዌ ኦስሎ በተሳካ ሁኔታ ተደረገ !!


በመላው አለም በሀያ ስድስት አገራት እና ታላላቅ ከተሞች ሊደረግ የታሰበው የግንቦት 7 የፍትህ፣ የነፃነትና የዲሞክራሲ ንቅናቄ ህዝባዊ ስብሰባና የገቢ ማሰባሰቢያ ዝግጅት የኖርዌይ ዋና ከተማ በሆነችው በኦስሎ ኦገስት 31, 2014 የንቅናቄው ምክትል ሊቀመንበር አቶ አበበ ቦጋለ በተገኙበት በታላቅና በደማቅ ሁኔታ ተከናወነ።

ህዝባዊ ስብሰባው በዲሞክራሲያዊ ለውጥ በኢትዮጵያ ድጋፍ ድርጅት ኖርዌ አዘጋጅነት ከቀኑ 15፡00 ጀምሮ የተካሄደ ሲሆን  በህዝባዊ ስብሰባው  ቁጥራቸው በርከት ያሉ በኦስሎና በተለያዩ የኖርዌ ከተሞች የሚኖሩ ኢትዮጵያውያኖች ተሳታፊ ሆነዋል። በፕሮግራሙ  መጀመሪያ ህዝቡ በአንድ ላይ ሆነው የግንቦት 7 ህዝባዊ ሀይል መዝሙር የዘመሩ ሲሆን  ከህዝባዊ ሀይሉ መዝሙር በመቀጠልምአቶ አቢ አማረ የዲሞክራሲያዊ ለውጥ በኢትዮጵያ ድጋፍ ድርጅት ኖርዌ የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ አጠር ያለ የእንኳን ደህና መጣችሁ  መልእክት አስተላልፈው በአለፉት ሃያ ሶስት አመታት በወያኔ የግፍ አገዛዝ ለተገደሉ ንፁሀን ዜጎች የአንድ ደቂቃ የህሊና ፀሎት አስደርገዋል።

በፕሮግራሙ ቅድመ ተከተልም የመጀመሪያውን ንግግር ያደረጉት አቶ ደባሱ መለሱ የግብረሃይሉ ዋና ሰብሳቢ ሲሆኑ በንግግራቸው ጠንከር ያሉ ሶስት ዋና ዋና መልክቶችን አስተላልፈዋል፦

አንደኛው መልእክታቸው ለአቶ አንዳርጋቸው ፅጌ ሲሆን፦ መልክቱም የደከምክበትን ዓላማ ያለምንም ጥርጥር እናሳካዋለን ምንም ጥርጥር አይግባህ በአሁኑ ሰአት በወያኔ እስር ቤት ውስጥ እየደረሰብህ ያለውን ስቃይ እናውቃለን ነገር ግን አይዞህ ጠላቶችህን እንበቀላቸዋለን ብለዋል ። ሁለተኛው መልክታቸው ደግሞ ወያኔን ለመፋለም ቆርጠው ለተነሱት ታጋዮች ሲሆን ኢትዮጵያውያኖች በማንኛውም ነገር ከጎናችሁ ነን በርቱ ብዙ ሀገር ወዳድ ኢትዮጵያውያኖች አብረናችሁ ነን ብለው ሶስተኛውን መልክታቸውን ደግሞ ለወያኔዎች ሲሆን መልክቱም፦ በውስጣቸው ያለውን የበታችነት ስሜት ትተው ህዝብን ማሰቃየት፣ መግረፍ ማሰርና መግደል እንዲያቆሙ መልክታቸውን አስተላልፈዋል። ከዚያም የግንቦት 7 አላማ ራእይና ተልኮ የያዘ ስለ ግንቦት 7 ምንነት የሚያስረዳ በቪዲዮ የተደገፈ ሰፋ ያለ ገለፃ ተደርጓል።

በመቀጠል ንግግር ያደረጉት አቶ ዮሐንስ አለሙ የዲሞክራሲያዊ ለውጥ በኢትዮጵያ ድጋፍ ድርጅት ኖርዌ ሊቀመንበር ሲሆኑ እሳቸውም በንግግራቸው  የግንቦት 7 ህዝባዊ ስብሰባ በመላው አለም የሚደረግ መሆኑን በመጥቀስ ይህ ህዝባዊ ስብሰባ በዲሞክራሲያዊ ለውጥ በኢትዮጵያ ድጋፍ ድርጅት ኖርዌ አዘጋጅነት በኖርዌ ኦስሎ መደረጉ እንዳስደሰታቸው ገልፀው በኣሁኑ ሰኣት ከመቼውም ጊዜ በተለየ መልኩ የወያኔ መንግስት በሀገራችን ላይ እያደረሰ ያለውን ስቃይና መከራ እየጨመረ መምጣቱን ገልጸው ይሄ ዘረኛው ቡድን ህዝባችን ላይ እያደረሰ ያለውን መከራና ስቃይ ለማስቆም ዋናው አማራጭ ወያኔን ከስልጣን ማስወገድ ብቻ  ነው ብለዋል ለዚህም አላማ ሁላችንም ያለማቋረጥ ትግላችንን መቀጠል አለብን ብዙ ስብሰባዎችን፣ ሰላማዊ ሰልፎችን፣ የተለያዩ እንቅስቃሴዎችን አድርገናል ነገር ግን አሁን ወደተግባር የምንሸጋገርበት ጊዜ ነው መሆን ያለበት በማለት የተናገሩ ሲሆን ህዝቡ ከስሜታዊነት ወጥቶ ትግሉን በተግባር እንዲያሳይ ጥሪ በማስተላለፍ ለህዝባዊ ስብሰባው መሳካት አስተዋፅኦ ያደረጉትን ክፍሎች ምስጋና አቅርበዋል።

ከአቶ ዮሃንስ ንግግር በመቀጠል ንግግር ያደረጉት የእለቱ ተጋባዥ እንግዳ አቶ አበበ ቦጋለ ሲሆኑ እሳቸውም ይህ ስብሰባ በተለያዩ ሀገሮች እየተደረገ እንዳለ እና በሁሉም ስብሰባዎች ላይ የሚተላለፉ መልክቶች ተመሳሳይነት እንዳላቸው ጠቅሰው እኔም አንዳርጋቸው ፅጌ ነኝ ማለት ምን ማለት ነው በሚል ለተሰብሳቢው ሰፋ ያለ ገለፃ አድርገዋል። ህዝባችን በአሁኑ ሰአት በእየአረብ ሀገራትም ሆነ ወደ ሌሎች ሀገራት ለስደት እየተዳረገ ሲሆን የዚህ ሁሉ መሰረቱ የወያኔ የዘረኝነትና የጭቆና የግፍ አገዛዝ በመሆኑ ይህንን አንባገነን ስርዓት አሽቀንጥረን መጣል የእያንዳንዳችን ኢትዮጵያዊያን ሃላፊነት መሆን ይገባዋል በማለት ወያኔን በስልጣን ላይ እንዲቆይ ያደረጉ ነገሮች ናቸው የሚሏቸውንም በዝርዝር አቅርበዋል። አቶ አበበ ይህንንም ሲያብራሩ በአሁኑ ሰአት የወያኔ መንግስት የኢትዮዽያ ህዝብን የሴት ማህበር፣ የወጣቶች ማህበር፣ ወዘተ... በማለት በተለያዩ ጥቅሞች ጠላልፎ እድሜውን እያራዘመ እንደሆነ ገልጸው የወያኔ ቡድን ለማስወደድ በተለይም ወጣቶች ታላቅ ሃላፊነት አለብን በአሁኑ ሰአት ትግሉ በታላቅ ሁኔታ ተፋፍሞ ይገኛል በቅርብ የውህደት ስምምነት የተፈራረሙት አርበኞች ግንባር፣ የአማራ ህዝባዊ ንቅናቄ እና የግንቦት 7 የፍትህ የነፃነትና የዲሞክራሲ ንቅናቄ ድርጅቶች በአጭር ጊዜ ውስጥ ውህደቱ ይጠናቀቃል ይህ ውህደትም ከትህዲንና ከሌሎች በትጥቅ ትግል ከሚታገሉ ድርጅቶች ጋር ይቀጥላል። ይህ በድርጅቶች መካከል የተጀመረውን የውህደት አንድነት ማገዝ የእያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ ኃላፊነት መሆን ይጠበቅበታል በማለት ንግግራቸውን አጠናቀዋል።

በስብሰባው አቶ ሙላው የትህዲን ሊቀመንበር በስልክ የትህዲንን ራእይና አመሰራረት ከተናገሩ በኋላ በአሁኑ ሰአት ድርጅታቸው የወያኔን መንግስት በከፍተኛ ሁኔት እየተፋለሙትና ብዙ የትግራይ ወጣቶች ትግሉን እየተቀላቀሉ እንደሆነ አስረድተዋል። ድርጅታቸው ለምን የትግራይ ህዝብ ዲሞክራሲ ንቅናቄ በዚህ አይነት የስም ስያሜ መሰየሙ በአላማና በምክንያት የሆነ እንደሆነ በመናገር እየታገሉ የሚገኙት ለትግራይ ህዝብ ብቻ ሳይሆን ለመላው የኢትዮጵያ ህዝብ እንደሆነና እኛ ብቻችንን ለውጥ እናመጣለን ብለን ስለማናምን ወያኔን ከሚፋለሙ ከሌሎች ድርጅቶች ጋር ለመስራት እንደ አገር አላማ ይዘን የተነሳነው እቅድ ነው ብለዋል። በተመሳሳይ የአርበኞች ግንባር እና የግንቦት 7 ህዝባዊ ሃይል ተወካዮችም በስልክ ለተሰብሳቢው መልክታቸውን አስተላልፈዋል።በመቀጠልም የአቶ አንዳርጋቸው ፅጌን ስራዎች የሚዘክር አጭር የቪዲዮ ገለፃ ተላልፎ የመጀመሪያው ዙር ተጠናቆል።

ስብሰባው ለአጭር ደቂቃ እረፍት በመውሰድ የምሳና የሻይ ቡና መስተንግዶ ከተደረገ በኋላ በቀጥታ ወደ ጨረታ ስነስርአት አምርትዋል ለጨረታ የቀረበው የአርበኛው አንዳርጋቸው ፅጌን ምስል የያዘ ፎቶ ግራፍ ሲሆን ፎቶ ግራፉ ወደ ጨረታው ስፍራ  በባንዲራ ታጅቦ ሲመጣ ህዝቡ ከመቀመጫው በመነሳትና በጭብጨባ ደማቅ አቀባበል አድርጓል። በጨረታውን እጅግ በርካታ ሰዎች የተሳተፉ ሲሆን የበርገን የዲሞክራሲያዊ ለውጥ ቅርንጫፍ ፅ/ቤት እና የዲሞክራሲያዊ ለውጥ ዋና ፅ/ቤት በከፍተኛ የገንዘብ መጠን የተፎካከሩ ሲሆን ጨረታው በዲሞክራሲያዊ ለውጥ በኢትዮጵያ ድጋፍ ድርጅት ኖርዌ ዋና ፅ/ቤት አሸናፊነት የተጠናቀቀ ሲሆን ሎተሪዎች፣ መፅሐፍቶች እና ሌሎች የገቢ ማስገኛ ቁሳቁሶችም ለገቢ ማሰባሰቢያው ሽያጭ ላይ ውለው መጠኑ ከፍተኛ የሆነ ገቢ ለማግኘት ተችሏል።

በመጨረሻም የዲሞክራሲያዊ ለውጥ በኢትዮጵያ ድጋፍ ድርጅት ም/ሊቀመንበር የመዝግያ ንግግር ካደረጉ በኋላ ላንቺ ነው ሀገሬ ላንቺ ነው ላንቺ ነው ኢትዮጵያ ላንቺ ነው የተሰኘውን የግንቦት 7 ህዝባዊ ሃይልን መዝሙ ዘማሪዎች እና ተሰብሳቢው በጋራ በመዘመር ዝግጅቱ በተያዘለት ሰአት በተሳካ ሁኔታ ተጠናቋል። የመድረክ መምራቱን ስራ ከመጀመሪያ እስከመጨረሻ በተሳካ ሁኔታ ያከናወኑልን ወ/ሪት ዙፋን አማረ እና አቶ ሳሌ አብርሃ መሆናውንም ለመግለፅ እንወዳለን።

ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ!!
የዲሞክራሲያዊ ለውጥ በኢትዮጵያ ድጋፍ ድርጅት ኖርዌ

ግንቦት 7፤ የኢትዮጵያ ህዝብ አርበኞችና የአማራ ዲሞክራሲያዊ ሃይሎች ንቅናቄ ወደ ውህደት የሚያደርሳቸውን የስምምነት ፊርማ ተፈራረሙ

Sep 1,2014
የፋሽስቱ ወያኔን አገዛዝ ለመገርሰስ በተለያዩ መንገዶች ሲታገሉ የቆዩት 3 ቱ ድርጅቶች ወደ ውህደት የሚያደርሳቸውን የጋራ ስምምነት ፊርማ መፈራረማቸውን ለሬዲዮ ክፍላችን የተላከው መረጃ ያመለክታል። የፋሽስቱ ወያኔን ዕድሜ ለማሳጠር በአንድነት እንሰራለን! በሚል ድርጅቶቹ በጋራ ባወጡት መግለጫ በአገራችን ኢትዮጵያ የተንሰራፋውን ዘረኛና በታኝ ስርአት ከኢትዮጵያ ህዝብ ጫንቃ ላይ ለማውረድና ሕዝቦቿን ካሉበት አዘቅት በማውጣት የስልጣን ባለቤት የሚሆንበትን ሁኔታ ለማመቻቸት የጋራ ትግልና መስዋዕትነት ወሳኝ መሆኑን በማመን አንድ ሆነን አገዛዙን በጠነከረ መንገድ ለመፋለም ተስማምተናል ሲሉ በጋራ የመስራቱን አስፈላጊነት ድርጅቶቹ ገልፀዋል።
ይሀ በእንዲህ እንዳለ ውህደት የፈጸሙት 3 ቱ ድርጅቶች የኢትዮጵያ ህዝብ አርበኞች ግንባር፣ የግንቦት 7፣ የፍትህ፣ የነፃነትና የዲሞክራሲ ንቅናቄ እንዲሁም የአማራ ዲሞክራሲያዊ ኃይሎች ንቅናቄ የተጀመረውን የነፃነት ትግል ከግብ ለማድረስ ህዝባዊ ድጋፍ ይደረግላቸው ዘንድ ጥሪ አቀረቡ የፋሽስቱ ወያኔን ዕድሜ ለማሳጠር በአንድነት እንሰራለን! በሚል በሳምንቱ መጀመሪያ ላይ ድርጅቶቹ በጋራ ባወጡት መግለጫ በአገራችን ኢትዮጵያ የተንሰራፋውን ፋሽስታዊ ስርአት ከኢትዮጵያ ህዝብ ጫንቃ ላይ ለማውረድና ሕዝቦቿን ከገቡበት አዘቅት በማውጣት የስልጣን ባለቤት ለማድረግ የጋራ ትግልና መስዋዕትነት ወሳኝ መሆኑን በማመን አንድ ሆነን አገዛዙን በጠነከረ መንገድ ለመፋለም ተስማምተናል ሲሉ የውህደቱን አስፈላጊነት የገለፁት ድርጅቶቹ አያይዘውም አስፈላጊውን መስዋዕትነት በመክፈል የጉጅሌው ወያኔን እድሜ ለማሳጠር በምናደርገው እልህ አስጨረሽ የነፃነት ትግል የኢትዮጵያ ህዝብ ከጎናቸው በመሰለፍ ድጋፍ ያደርግላቸው ዘንድ ጥሪያቸውን አቅርበዋል። የነፃነት ቀኑ እየተቃረበ መሆኑን ያመላከቱት የድርጅቶቹ ከፍተኛ አመራሮች የኢትዮጵያ ህዝብ ባለበት ቦታ ሆኖ ትግሉን ማፋፋምና መቀላቀል ይኖርበታል ሲሉ መልዕክት አስተላልፈዋል። በአገር ቤት፤ በውጭና በጎረቤት አገር የሚኖር ማንኛውም ኢትዮጵያዊ ከድርጅቶቹ ጎን በመሰለፍ የሞራል፤ የገንዘብና የሃሳብ ድጋፍ በመስጠት የዜግነት ግዴታውን እንዲወጣ ጥሪ እንዳቀረቡም ለማወቅ ተችሏል። እየተደረገ ያለው ትግል ሁለገብ ትግል መሆኑን ያመለከቱት ድርጅቶቹ በተለይ በውጭ አገራት እንደተጀመረው ሁሉ በአገር ቤት ውስጥም ህዝቡ በተቀናጀ ሁኔታ ለወያኔ አልገዛም ብሎ እምቢተኝነቱን ማሳየት መጀመር እንዳለበት፤ የወያኔን ንግድ ድርጅቶች የሚያዳክሙ ማንኛውም እምጃዎችን መውሰድ መጀመር እና የፋሽስቱ ወያኔ ካድሬዎችንና ተከታዮችን በማግለል ቅጥረኞቹ እንዲሸማቀቁ ብሎም አገዛዙን ሸሽተው የነፃነት ትግሉን እንዲደግፉ አልያም እንዲቀላቀሉ ማድረግ የሚቻልባቸውን ርምጃዎች በተጠናከረ ሁኔታ መውሰድ መጀመር እንዳለባቸው አ ሳስበዋል።
የድርጅቶቹ ውህደት በኢትዮጵያውያን ዘንድ እየተወደሰ መሆኑንም ለማወቅ የተቻለ ሲሆን በተለይ ዲሞክራሲያዊ ሃይሎች በጋራ ሆነው መታገል ባለመቻላቸው በተናጠል ያደርጉት የነበረው ትግል ውጤት ባለማምጣቱ አገዛዙ ለ 23 አመታት በስልጣን መቆየት መቻሉን በመግለጽ ይሄ አሁን የተጀመረው ሂደት ይህንን ለወያኔ አገዛዝ የተመቻቸ ትግል ይቀለብሳል በማለት ለነፃነት ናፋቂው የኢትዮጵያ ህዝብ ብስራት መሆኑ በስፋት ተነግሯል። ውህደቱ በሰው ሃይል፤ በእውቀትና በገንዘብ ረገድም ድርጅቶቹን መፈርጠም እንደሚያስችላቸውና የተጀመረውን የነፃነት ትግል ዕድሜ እንደሚያሳጥር በብዙዎች ዘንድ እየተገለጸ እንደሚገኝ ለማወቅ ተችሏል። በመጨረሻም የኢትዮጵያን አንድነት ያስቀደሙት፤ የህዝቦቿን ነፃነት የሚናፍቁና በሁለገብ የትግል እንቅስቃሴ አገዛዙን ለማስወገድ ውህደት ፈፅመው ኢትዮጵያን ለማዳን የተዘጋጁትን እነዚህን ዲሞክራሲያዊ ሃይሎች በተለይ የመከላከያ ሰራዊቱና አገር ተረካቢ የሆነው ወጣት ትውልድ እንዲቀላቀላቸው ጥሪ ማቅረባቸው ታውቋል።