Friday, April 4, 2014

የአንባ ገነኖች የስልጣን ጥም አባዜ

በገዛኸኝ አበበ (ኖርዌይ ሌና) 

 ዛሬ በአለማችን ላይ መንግስታቶች ሊመሩት እና ሊያስተዳድሩት በላው ሕዝብ ላይ  የሰብሃዊ መብት ረገጣ እስራት እና ግድያ በሕዝባቸው ላይ እንደሚያደርሱ ይታወቃል በተለይም የአፍሪካ መሪዎች እና መንግስታቶች በአንባ ገነንት እና የሕዝባቸውን ሰብሃዊ መብት በመርገጥ ግንባር ቀደም ተጠቃሾች ሲሆኑ ከእነዚህም ውስጥ አገራችን ኢትዮጵያ አንዶ ናት :: በአሁኑ ሰአት በሀገራችን ኢትዮጵያ በስልጣን ላይ ያለው መንግስት ከጊዜ ወደ ጊዜ አይን ያወጣ የሰበሃዊ መብት ጥሰት በዜጎች ላይ እየፈጸመ እንዳለ ይታወቃል ይህም የወያኔ የዜጎችን የሰብሃዊ መብት መርገጥ እና ሕዝብና እያስፈራሩ ረግጦ መግዛት ከምንም ነገረ የመነጨ ሳይሆን ሕዝቡ ስለ ዜግነት መብቱ እንዳያስብ በታጠቀ ኃይል እያስፈራሩ የሥልጣን እድሜን ለማራዘም ወያኔዎች ያዋጣናል ብለው የመረጡት መንገድ ሲሆን  ዜጎችን መረበሽ፣ መዝረፍ፣ ማሰር እና መግደልን ተያይዘውት ይገኛሉ::

ዜጎችን ማሰቃየት፣ ማሰር እና መግደል የአንባ ገነን መንግስታቶች መገለጫና መታወቂያ ሲሆን        አንባ ገነን መንግስታቶች  በሰለም እና በመረጋጋት ሊመሩት እና ሊያስተዳድሩት የበላይ ሆነው የተሾሙለት ሕዝብ ሰበሃዊ መብት በመርገጥ  ግፍና በደል እንደሚፈጽሙባቸው በገሀድ የታወቀ ሲሆን እነዚህ አምባ ገነን መሪዎች ለምንድ ነው ግን ሕዝባቸውን የሚያሰቃዩት፣ የሚያስሩት እና  የሚገደሉት ብለን ማሰባችን እና መጠየቃችን አይቀርም በየትኛውም አለም እንደምናየው አንባ ገነኖች ያለምንም ተቀናቃኝ በስልጣን ዙፋናቸው ላይ ለመቀመጥ ከመሻት የተነሳ  ዜጎቻቸውን  ያሰቃያሉ፣ ያስራሉ፣ይገድላሉ

 በተለይም እኛ ኢትዮጵያኖች በሀገራችን መንግስት በየጊዜው በግፍ ስለሚያሰቃዩት፣ ስለሚታሰሩት እና  ስለሚገደሉት ወገኖቻችን ሁል ጊዜ እንዳለቀስን እና እንደጮህን እንገኛለን::

ምክንያቱም ወያኔ /ኢህአዲግ  ወደ ስልጣን  ከመጣበትና የኢትዮጵያንም ሕዝብ  በሀይል መምራት  ከጀመረበት ጊዜ አንስቱ እስከ አሁን ድረስ ከሁለት አስርት ከአመታት በላይ መሆኑ ነው አንድም ቀን በሰላም እና በተረጋጋ ሁኔታ የኖረበት እና የኢትዮጵያ ሕዝብንም በሰላም የመራበት ጊዜ የለም ብል ማጋነን አይሁንብኝም::ይኼው የወያኔ ኢህአዴግ አገዛዝ ሁልጊዜ እንደፈራ ሕዝቡንም እንዳስፈራራ ሁል ጊዜ እንደተረበሸ ሕዝቡንም እንደረበሸ የሚኖር ሲሆን ይህም የወያኔ  ባህሪና መገለጫዎች ናቸው:: ከዚህም የተነሳ ሀገራችን ኢትዮጵያ በወያኔ ኢህአዲግ መንግስት መገዛት ከጀመረችበት ጊዜ  አንስቶ ወያኔ ያሰረው እና የገደለው ሀገሩንም ጥሎ እንዲሰደድ ያደረገው ሕዝብ ቁጥሩ እጅግ ብዙ ሲሆን የዜጎችንም ሰላም በመረበሽ እና በሀገራቸው ተረጋግተው እንዳይቀመጡ በማድረግ ላይ ይገኛል::

 ከዚህ በታች  የአንባ ገነኖችን ማንነት መገለጫ የሆኑትን ነገሩች  በአጭሩ የተወሰኑ ነጥቦችን በማንሳት ለመዳሰስ እሞክራለው

    1,አምባገነኖች ያለ ሕዝብ ፍላጎት ለብዙ አመታት በስልጣን ላይ የመቆየት ማንነት ይታይባቸዋል (የስልጣን ሱሠኞች) ናቸው ::

  ብዙዎን ጊዜ እንደ  አፍሪካ እና አረብ ሀገራት ያሉ አምባ ገነን  የሀገር መሪዎች ወደ ስልጣን ሲመጡ የሕዝብን ህውቅና አግኝተው ወይም በሕዝብ ድምጽ በምርጫ ተመርጠው ሳይሆን አንድም በመፈንቅለ መንግስት አንድም በጦርነት በሀይል ስልጣንን መቆጣጠር ወይም በዘር ውርስ የስልጣን እርክብክቦሽ አማካይነት መሆኑ ይታወቃል:: ስለሆነም  ወደ ስልጣን ከመጡበት ጊዜ ጀምሮ  ስልጣናቸው ወይም መንግስታቸው በሀገራቸው ዜጎች እውቅና ሲሰጠው አይታይም :: ከዚህም የተነሳ ከሕዝባቸው ጋር አይጥ እና ድመት በመሆን ተፈራርተው ሕዝባቸውን  ሲያስፈራሩና ሲረብሹ ይኖራሉ ::  እንደነዚህ ያሉ ሀገራቶች  በማን አለብኝነት ያለምም ተቀናቃኝ ለብዙ አመታት የስልጣንን ወንበር ተቆጣጥረው ስልጣንንም መከታ በማድረግ የሕዝብን መብት በመርገጥም  ሲኖሩ ይታያሉ:: እነዚህ አንባ ገነን መንግስታቶች በሕዝባቸው ላይ አመኔታ የላቸውም ሕዝቡም በእነሱ ላይ አመኔታ የለውም ስለዚህ ሁል ጊዜ በዜጎቻቸው እንደተረገሙ እነሱም ሁል ጊዜ ዜጎቻቸውን እንደረገሙ ይኖራሉ::እየወለ እየደር ግን የአንባ ገነኖች መጨረሻቸው በሕዝብ ቁጣ ተርፍረክርኮ መውደቅ ነው::

 በግብጽ በቱኒዚያ በየመን እና በሌሎችም ሀገሮች እንዳየነው አንባገነኖች ለብዙ አመታት ስልጣንን በማውረስ እና በመረካከብ ሕዝብን በመጨፍለቅ ሲገዙ እንደነበር የቅርብ ጊዜ ትዝታችን ነው ለምሳሌ በግብጽ ጀማል ሙባረክ የሚቀጥለው የግብጽ መሪነትን ከአባቱ ለመውረስ እና ለመረከብ በመዘጋጀት እያለ ነበር ድነገት ባልጠበቁት ሰአት የቱኒዚያው ሱናሜ የተነሳው እና ያለሙትን አላማ ሳይተገብሩ በአንባ ገነኖች መገዛት በሰለቸው ሕዝብ ቁጣ እንደ ሰም ቀልጠው የቀሩት:: እነዚህን ሀገሮች እንደ ምሳሌ አነሳው እንጂ እንደነ ምሮኮ እና ኮንጎ የመሳሰሉ አብዛኞች ሀገሮች ስልጣንን በሀይል ወይም በውርስ በማውረስ እና በመረካከብ  ያለ ሕዝብ ፍላጎትና ህውቅና  ለዘመናት በማን አለብኝነት ስልጣንን በግላቻው በመቆጣጠር የሕዝቦችን ሰብሃዊ መብት ሲጨፈልቁ የሚኖሩ ሀገሮችን መጥቀስ ይቻላል::አንባ ገነኖች  እነሱን ከሚመስላቸው ውጭ  ለሌላ የፖለቲካ ፓርቲ ድርጅትም ሆነ ሀገርን ለመምራት አቅምም ሆነ ብቃቱ ላላቸው ሰዎች በማንኛውም መንገድ ቢሆን ስልጣንን ለመልቀቅ ፍቃደኞች ሲሆኑ አይታዩም::

ወደ ሀገራችን ኢትዮጵያ ስንመጣ ይህንኑ ነው የምናየው በአሁኑ ሰአት ሀገራችንን ኢትዮጵያን እየመራው ነው የሚለው የወያኔ  መንግስት ስልጣንን በዘር ሲወራረሱ እንደነበሩ  እንደ አንዳንድ አረብ  እና አፍሪካ ሀገራት አንባ ገነን መሪዎች በዘር አይወራረሱ እንጂ  ከሕዝብ ፍቃድ እና ፍላጎት ውጭ ለዘመናት የስልጣን ወንበሩን በማን አለብኝነት በሀይል ተቆጣጥሮ የዜጎችን ሰብሃዊ መብት እየረገጠ ያለ መንግስት መሆኑ ይታወቃል::አሁን ባለው አካሄድ እና አንዳንድ የወያኔ ባለስልጣኖች አንዳንድ ጊዜ አፋቸው እያመለጣቸው እንደሚናገሩት እነዚህ የስልጣን ሱሠኞች የሆኑት የወያኔ ባለስልጣኖች በፈቃዳቸው ስልጣንን ይለቃሉ ተብሎ የማይታሰብ ቢሆንም ድንገት ግን የሕዝብ ቁጣ ገንፍሎ ወያኔ የሚባል የአንባ ገነን የማፊያ ቡድን ዳግመኛ እንዳያንሰራራ በግብጽ ፣ በቱኒዚያ እና በሌሎችም ሀገሮች እንደ ሆነው ሁሉ የአንባ ገነኑን የወያኔን መንግስት  ስርአት ወደ መቃብር ያስገበዋል የሚል ከፍተኛ የሆነ እምነት አለኝ::

የሰሜን አፍሪቃ እና መካከለኛው ምሥራቅ አገራት ዜጎች ለአስርት ዓመታት በአምባገነን አገዛዝ ተገዝተዋል። እኛ ደግሞ ለአስርት ዓመታት አምባገነን ብቻ ሳይሆን ዘረኛም ጭምር በሆነ የስልጣን ጥም አባዜ በተጠናወጠወ አገዛዝ እየተገዛን ነው። እኛ እየደረሰብን ያለውን ዓይነት አዋራጅ ዘረኝነት እነሱ ላይ አልደረሰባቸውም። አምባነንነት እነሱን አስመርሮ በገዚዎቻቸው ላይ በአንድነት እንዲነሱ አድርጓቸዋል። እኛ ዘንድ ደግሞ አምባገነንነትና ዘረኝነት ተዳብለውብናልና ከእነሱ በላይ አምርረን በህብረት የስልጣን ሡስ በተጠናወጣቸው አንባገነኖች ላይ እንነሳለን።

   2,አምባገነኖች በራስ የመተማመን (self confidence)ስለሌላቸው ለሁሉም ሃይል መጠቀም ይወዳሉ።

 አንባ ገነን መንግስታቶች ሕዝብን በአግባቡ መምራት ሕዝብ የሚጠይቀውን ማንኛውንም አይነት ጥያቄ ለመመለስ ፍቃደኛ አይደሉም:: አንባ ገነን መንግስታቱች በነገሱበት ሀገር የመብት የነፃነት የፍትህ ጥያቄ መጠየቅ በፍጹም የማይታሰብ ሲሆን ዛሬ ስንቶች ናቸው መብታቸውን  ስለጠየቁ  ብቻ በአንባገነኖች ጥይት በየሀገሩ እንደ ቅጠል እየረገፉ ያሉት::

እዚህ ላይ መታወቅ ያለበት ነገር የኛዎቹ አንባ ገነኖች የወያኔዎች መጀመሪያውኑ ወደ ስልጣን ሲመጡ እና  ለዘመናት ከሁለት አስርት አመታት በላይ በስልጣን ላይ  ሲቀመጡ በሕዝብ ፍላጎት እና ነጻ ምርጫ ሳይሆን ሌሎች አንባ ገነን መንግስታቶች እንደሚያደርጉት ሁሉ ሕዝብን እያስፈራሩ እና ሃይልን በመጠቀም የሕዝብን ናጻነትና መብትን በማፈን እንደሆነ ይታወቃል::   በመሆኑም የስልጣንን ወንበር ከያዙበት ጊዜ ጀምሮ መንግስታቸው የሕዝብ ተቀባይነት የለውም:: ስለሆነም   ፈጽመው ተረጋግተው መኖር በማይችሉበት ሁኔታ ውስጥ ሲገኙ  ሁልጊዜ መንግስታቸው በስጋት ውስጥ ነው የሚኖረው:: 

አንባ ገነኑ የወያኔ መንግስት በራሱ የማይተማመንና በስጋት ውስጥ የሚኖር መንግስት  እንደሆነ በቅርቡ  የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ድርጅት ሒዩማን ራይትስ ዎች የወያኔን መንግስት አሳፋሪ ድርጊት በመኮነን ያወጣው ሪፖርት አመላካች ነው::እንደ  የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ድርጅቱ ሪፖርት  ውስጥና በውጭ የሚገኙ ኢትዮጵያውያንንና ሌሎች ባለሙያዎችን በማነጋገር አዘጋጀሁት ባለውና ባለፈው  ሳምንት ይፋ ባደረገው  የኢትዮጵያ መንግሥትን የሰብዓዊ መብት ጥሰት እየፈጸመ እንዳለ እና  ከተቃዋሚ ፓርቲዎች ወይም አገር ውስጥ እንዳይንቀሳቀስ ከታገደ የፖለቲካ ድርጅት ጋር በማንኛውም መንገድ ቅርበት ያላቸው ኢትዮጵያውያኖች በወያኔ መንግስት እንደሚሰለሉ እና እነዚህ ሰዎች የሚያደርጉት የስልክ ንግግር በተለይ ደግሞ ከውጭ አገር የተደወለ ከሆነ ያለ ግለሰቦቹ ፈቃድ ወይም ዕውቅና ተጠልፎ እንደሚቀዳ ሒዩማን ራይትስ ዎች በሪፖርት ላይ ይፋ አድርጎል  ለዚህም የስለላ ተግባሩን ለመፈጸመ  የሚያገለግሉ መሣሪያዎችን ከተለያዩ አገሮች እንዳገኘ፣ሪፖርቱ ጨምሮ ይፋ አድርጓል::

  የወያኔ መንግስት በራስ መተማመን የጎደለው እና በፍርሃት የተሞላ መግስት መሆኑን በአደባባይ ያስመሰከረ አንባ ገነን መንግስት ነው ::መሪዎቹ በጭራሽ በራስ መተማመን ብሎ ነገር ስላልፈጠረባቸው መተማመኛቸው ጠብመንጃ፤በጦሩ ጉያ ተሸጉጠው ሃገርና ሕዝብን ለእልቂት ለረሃብ ለመከራ የሚያበቁበትን ቆመውም ተቀምጠው ተኝተውም ማውጠንጠን ነው፡፡ ይህንንም ስል እንዴው ዝም ብዬ ከመሬት ተነስቼ እንዳለ ይታወቅልኝ:: እኔ እስከማቀው ድረስ የወያኔ መንግስት ስልጣኑን ሀ ብሎ የኢትዮጵያን ሕዝብ ማስተዳደር ከጀመረበት ጊዜ አንስቱ እስከ አሁን ድረስ ከ22 አመት በላይ መሆኑ ነው አንድም ቀን በሰላም እና በተረጋጋ ሁኔታ የኖረበት እና የኢትዮጵያ ሕዝብንም በሰላም የመራበት ጊዜ የለም ብል የተሳሳትኩኝ አይመስለኝም:: ከዚህ ስጋታቸውም የተነሳ የኢትዮጵያን ሕዝብ አፍነው ይዘውታል::

 ዜጓች ሕገ መንግስታዊ  መብታቸውን ተጠቅመው  የሚደርስባቸው ጭቆናና የሰበሃዊ መብት ጥሰት   በነጻነት መቃወም አልቻሉም :: አንባ ገነኑ ወያኔ ይኼን ያክል ዘመን በስልጣን ላይ ሲቆይ ስልጣኑን መከታ በማድረግ  ስንቶችን ሲገርፍ፣ ሲያስር ፣ ሲያሰቃይ እና ሲገድል እንደኖረ በአደባባይ የተገለጠ ሀቅ ነው::ሕዝብም ስለመብቱ እና ነጻነቱ የጠየቀ ከሆነ ይታሰራል ፣ይገረፋል ይገደላል::

ኢትዮጵያን በዘር ፣ በቋንቋ እና በሃይማኖት ከፋፍሎ የህዝቡን አንድነት ለማጥፋት የሚጥረውን አገዛዝ መቃወም ደግሞ “አሸባሪ’’ የሚል ታርጋ አስለጥፎ ዘብጥያ ያስወረውራል።  ዛሬ የኛዎቹ እነ እስክንድር ነጋ ፣ርዕዮት አለሙ እና ሌሎችም ወጣት ወገኖቻችን በሽበርተኝነት ስም ተወንጅለው በአንባ ገነኖች እስር ቤት ውስጥ ተጥለው እየተሰቃዩ ያሉት የወያኔ መንግስት እንደሚለው ሽብርተኛ  ሳይሆኑ  የነጻነት እና የፍትህ ታጋይ ጀግኖች እንደሆኑ በድፍረት መናገር እችላለው::

በወያኔ አንባ ገነናዊ እኩየ ስራዓት የህግ የበላይነት የለም፤ ዲሞክራሲ ተደፍጥጡዋል፤ የደህንነት ዋስትና የለም፤ ነፃ ፕሬስ ተረት ሆኗል፣ የብዙሃን ፓርቲ ያልምንም እፍረት ተገፍትሮል። የሲቪክና ሙያ ማህበራት የማሽመድመዱ ተግባር ተከናውኗል።ይለቁንም ዘረኞች ግፈኞች፣ ወንጀልኞች፣ አምባገነኖች፣ ሙሰኞች እንዳሻቸው ዛሬም እየፈነጩ፤  በተቃራኒው ደግሞ ለፍትህ ለእኩልነትና፣ለነጻነት ሲሉ ለህሊናቸው፣ የሚታገሉ የሚዋረዱበት፣ የሚሰደዱበትና የሚታስሩበት አገር መሆኑ በጣም ያንገበግባል፣ ያስቆጫል።

ነገርግን አንባ ገነኖች የስልጣን ሃይላቸውን በመጠቀም ማሰር፣ መግደል ሕዝብን ማሰቃየት ከያዛቸው የስልጣን ጥም አባዜ የተነሳ በስልጣን ላይ ረጅም ጌዜ ለመቆየት የሚጠቀሙበት መንገድ ሲሆን ይህም በራስ መተማመን እንደሌላቸው ያሳያል ::ነገር ግን እዚህ ላይ ማወቅ ያለብን ነገር ይህ አይነት አካሄድ አንባ ገነን መንግስታቶችን የትም ሊያደርሳቸው እንደማይችል ሲሆን አንባ ገነኖችም ይህን ሊገነዘቡትና ሊያውቁት ይገባል ባይ ነኝ ::በርግጥ የታፈኑ ብሶት ገንፍሎ የነጻነት ደማቅ ፀሐይ የምናይበት ጊዜ እንደሚመጣ ቅንጣት ያክል አልጠራጠርም። 

የሰሜን አፍሪቃ እና መካከለኛው ምሥራቅ አገራት ዜጎች በያገራቸው ፍትህ በመጓደሉ ተማረዋል። እኛ አገር ደግሞ ፍትህ ራስዋ ተዋርዳለች። ፍርድ ቤቶች ማጥቂያዎች ሆነዋል። አገራችን እስር ቤት ሆናለች። አብዮት ከቀሰቀሱት ጎረቤቶቻችን በባሰ እኛ ተበድለናልና  ከእነሱ በባሰ አምርረን ልንነሳና አንባ ገነኖችን ዳግም እንዳይነሱ ልንቀብራቸው ያስፈልጋል።
     3,አምባገነኖች ከሀገር እና ከሕዝብ ጥቅም ይልቅ የራሳቸውን ጥቅም ያስቀድማሉ (ሙሰኞች ናቸው)

የአንባ ገነኖች ሌላው የባህሪያቸው ዋንኛ መታወቂያቸው ሙሰኝነት ሲሆን ይህንንም ተከትሎ  አገራችንን ኢትዮጵያን ጨምሮ አፍሪካ  አንባ ገነኖች በስፋት የነገሱባት  ሙሰኝነት እና ሙሰኞች የተንሰራፉበት አህጉር በመሆን ትታወቃለች :: በአፍሪካ ሀገራት የሚነሱ መሪዎች ወደ ስልጣን ከመጡ እና ስልጣን ከያዙ በኋላ ስለ ሀገር እና ስለ ሕዝባቸው ግድ የለሾች ሲሆኑ ስለ ሀገር እና ስለ ሕዝባቸው ግድ የማይላቸው ሆዳሞችና የራሳቸውን ጥቅም ብቻ የሚያሳድዱ ገንዘብ ወዳዱች ናቸው::

 በሀገራችን ኢትዮጵያ በስልጣና ላይ ያለው አምባ ገነኑ የወያኔ መንግስት ባለስልጣኖች  ከላይ እስከታች በተዘረጋው የወያኔ ስርአት ውስጥ ከቁንጮ ባለስልጣናት እስከታችኛው አገልጋይ ድረስ በሙስናና በሌብነት ያልተዘፈቀ የስርአቱ አገልጋይ ቢፈለግ አይገኝም ብል ማጋነን አይመስለኝም:: በአሁኑ ሰአት መላው የኢትዮጵያ ሕዝብ አዲስ አበባን ነዋሪ ጨምሮ ሕዝቡ በከፍተኛ የኖሮ ችግር ውስጥ እንዳለ ይታወቃል:: ካለውም ታላቅ የኑሮ ውድነትና፣ የስራ ማጣትና ያለው ብልሹ የመንግስት ፖለቲካዊ አስተዳደር ተደምሮበት ሕዝቡ ሀገሮን ጥሎ ወደ ተለያየ ሀገር እየተሰደደ በተለይም ወጣቶች ወንዶችና ሴቶች እህቶቻችን ሀገራቸውን ጥለው ሲወጡ በየድንበሩ እየሙቱና ወደ ተለያየ ሀረብ ሀገራትም ሄደው ለተለያየ መከራ ስቃይ እና ችግር ሲደርስባቸው እና ዜጓቻችን ሲገደሉ ምንም ግድ የማይሰጣቸው ነገር ግን   እኔ ከሞትኩኝ ሰርዶ አይብቀል እንደሚባለው የወያኔ  አንባ ገነን መሪዎች ሙሰኞች ከኢትዮጵያ ሕዝብ የዘረፉትን  በመቶ ሚሊየኖች የሚቆጠር ዶላር ከኢትዮጵያ ህዝብ በማሸሽ በውጪ አገር ባንኮች በማካበት ላይ እንደሚገኙ ግሎባል ፋይናንሻል ኢንቴግሪቲ 11 ቢሊዮን ዶላር የሚጠጋ የአገሪቱ ገንዘብ በውጭ ባንኮች መቀመጡን ይፋ ማድረጉ ይታወቃል ።

በወር ስድስት ሺህ ብር ደሞዝተኛ እንደነበሩ በባለቤታቸው የተነገረላቸው አንባ ገነን የነበሩት የቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስቴር ሟቹ አቶ መለስ ዜናዊ ሁላችንም እንደምናስታውሰው ከጥቂት ዓመታት በፊት የትንሳኤ ሬድዮ የኢትዮጵያን ሕዝብ ሀብት የዘረፉ የወያኔ መንግስት ባለስልጣኖችን፥ የቀድሞውን ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊን ጨምሮ የዘረፉትን ሀብት መጠንና ገንዘቡን ያስቀመጡበትን አገር ጭምር ይፋ አድርጎ እንደነበር አስታውሳለው።  ይሄ ሬድዮ ጣቢያ አቶ መለስ ዜናዊ በማሌዥያ በባንክ ፬፪ (አርባ ሁለት) ሚሊዮን ዶላር እንዳስቀመጡ ገልጾ ነበር።ይታያችው እንግዲህ  በተከታዩቻቸውና የአቶ መለስ አፍቃሪ በሆኑ ሰዎች እስከ አሁን ድረስ ሰውየው ስለ ሀገራቸውና ስለ ሕዝባቸው ፍቅር የነበራቸው፣ ባለራእይ መሪ እንደነበሩ ሲወደሱ እና ሲዘመርላቸው መስማት የሰለቸን ጉዳይ ነው:: እውነታው ግን የሚያሳየው ሌላ ነው ተከታዩቻቸውና የአቶ መለስ አፍቃሪ እንደሚሉት ሳይሆን አንባ ገነኖች አንድም ቀን የሀገር እና የሕዝባቸው ፍቅር ኖሯቸው አያውቅም እኝው አንባ ገነን የቀድሞ መሪ ሕዝባቸውን ሲያዋርዱና ሲያንቋሽሹ ለሀገራቸውም ቅንጣት ያከል ፍቅር እንደሌላቸው የሚያሳይ ስራ ይሰሩ የነበሩ እና ጀግኖች አባቶቻችን የታወደቁለትን ባንዲራ እንኳን ሳይቀር ጠቅላይ ሚኒስትር ተብዬ የነበሩት አንዴ ሲዘቀዝቁት አንዴ ጨርቅ ነው ሲሉት እንደነበር እናስታውሳለን::

 በአሁኑ ሰአት የወያኔ መንግስት ሙስናን ለማጥፋት እየታገለ እንዳለ በተለያዩ መድረኮችና ሚድያዎች ከመግለፅ ኣልፎ። ራሱ የፀረ ሙስና ኮምሽን ብሎ ባደራጀውና  በሚጠራው ተቋም ሙሰኞች ባላቸው ግለሰቦች  ላይ ክስ በበመመስረት ወደ ፍርድ ሲያቀርባቸውና እስርቤት ውስጥ ሲያጉራቸው ይስተዋላል ነገር ግን ይህ የወያኔ መሰሪ ተንኮል ሆነ ብሎ ለህዝብና ለኣለም ማህበረሰብ ወያኔ እራሱን የብርሃን መላእክት አድርጎ በማቅረብ ለማታለል ተብሎ እየተሰራበት ያለ ተንኮል ነው:: 

ወያኔ እራሱን ፀረ-ሙስና ድርጅት ለመምሰል ለህዝብና ለኣለም ማህበረሰብ ለማታለል እየተሰራበት ያለ ድብቅ ተንኮል     ነገር ግን ለስርኣቱ ተገዢ ሆነህ እስካገለገልክ ድረስ በአስተሳሰብ የተለየ እስካልሆንክ ሰው ብትገድል እንኳ በእርቅ ነፃ መውጣት ትችላለህ፡፡ስልጣንህን ተገን በማድረግ የህዝብ ንብረትና ገንዘብ ለመስርቅ ሙሉ ዋስትና እንደሚሰጥህ፣ የፈለከውን ያክል ገንዘብ ብትዘርፍ ዘመነኛ ተብለህ ልትሸለማለህ ትችል እንደሆነ እንጂ ሙሰኛ አያሰኝህም፡፡ ነገር ግን ከእነሱ ትንሽ ለየት ያለ የፖለቲካ ልዩነት ያላቸው እና ለበላይ ኣለቆቻቸው  ያላጎበደዱና ያልተስማሙ ግን ሙስናን ተገን በማድረግ በቁጥጥር ውስጥ እንደሚውሉ ይታወቃል:: ይህም  የወያኔ  ስርአት ምን ያህል አንባ ገነን መሆኑንና ስርኣቱ የስልጣን ጥም አባዜ በተጠናወጣቸው የስልጣን ሙሰኞች  የተሞላ ኣስመሳይ ፀረ ህዝብ ኣሰራር መሆኑንን ያመለክታል::

ሙስና የአንባ ገነን መንግስታቶች መገለጫ ሲሆን የሰሜን አፍሪቃ እና መካከለኛው ምሥራቅ አገራት የነበሩት አንባ ገነን ሹሞች በሙስና ያካበቱት ሃብት በቢሊዮን ዶላሮች እንደሚገመትና ሕዝቡንም ለአመጽ ያነሳሳው ይኸው የአምባ ገነኖች ከልክ ያለፈ ሙሰኝነትና ሌብነት እንደሆነ ይታወቃል። የእኛ የመጨረሻይቱ ድሃ አገር አንባ ገነን የወያኔ ሹሞችም በሙስና ያካበቱት ሃብት እንደዚያው ነው። እርግጥ ነው በከተሞቻችን ህንፃዎች በርክተዋል ሆኖም ግን የሙሰኞቹ እንጂ የለፍቶ አዳሪዎቹ አይደሉም። ስለዚህ በአሁኑ ሰአት እያደጉት ያሉት አንባ ገነኖች እና ሙሰኞች እንጂ ሀገራችን ኢትዮጵያ እንዳይደለች መታወቅ አለበት የሀገሬ ምስኪንና ደሃ ሕዝብማ በየቦታው በረሃብ እያለቀ ነው የሚገኘው:: በሃብት መበላለጥ የተቆጩት እና በሙስና መብዛት በአንባ ገነንና በስልጣን ሱሰኞች መሪዎቻቸው የተናደዱ የአህጉራችን  የሰሜን አፍሪቃ ዜጎች በገዢዎቻቸው ላይ ተነስተዋል እኛ ደግሞ  ከእነሱ በላይ ተጎድተናልና ከእነሱ በላይ አምርረን ልንነሳ ሙሰኛውን፣ የሀገርና የሕዝብ ፍቅር የሌለው አንባ ገነኑ የወያኔ መንግስት ልንፋለመው ይገባል እያልኩኝ ጹሁፊን ላጠቃላል ፈጣሪ ቸረ ወሬ ያሰማን ።

የአንባ ገነኖች መጨረሻቸው ውርደት ነው !!! ድል ለሀገር ወዳድ ኢትዮጵያውያን !!

gezapower@gmail.com

የሕወሓቱ ልሳን ወይን ጋዜጣ አዘጋጅ ደብዛው ጠፋ

April 3/2014

አብርሃ ደስታ ከመቀሌ



የወይን ጋዜጣ አዘጋጅ በመሆን ህወሓትን ለረጅም ግዜ ሲያገለግል የነበረው ጋዜጠኛ ሐገዞም መኮነን አዲስ አበባ ከሚገኝ ቤቱ ከጠፋ ሁለት ሳምንታት አለፉ። ጋዜጠኛ ሐገዞም መኮነን ወይን ጋዜጣ ሲያዘጋጅ ቆይቶ ከቅርብ ግዜ ወዲህ የህወሓት የዓፈና ተግባራትና አካሄድ በግልፅ መቃወም ከጀመረ ወራት አስቆጥሯል።

ከወይን ጋዜጣ አዘጋጅነት ለቆ የወይን ጋዜጣና የህወሓት የዓፈና ስትራተጂዎች የሚያጋልጥ መፅሓፍ ፅፎ ሊያስመርቅ በዝግጅት ላይ እያለ ያልታወቁ የፀጥታ አካላት በሌሊት ከቤቱ እንደወሰዱትና እስካሁን ያለበት እንደማይታወቅ ተገልፀዋል። ከወራት በፊት ማህተመስላሴ ገብረእግዚአብሄር የተባለ የሰሜን የፌደራል ፖሊስ የሎጂስቲክስና ፋይናንስ ሓላፊ በመቐለ ከተማ 16 ቀበሌ በፀጥታ ሃይሎች መገደሉ ይታወሳል።

በፀጥታ ሃይሎች የተፈፀመ ሙስና እንዳያጋልጥ በሚል ምክንያት ነው የተገደለው። በህወሓት አባላት ላይ ተደጋጋሚ ዓፈናና ግድያ ይፈፀማል፤ ግን አይጋለጥም። የማይጋለጥበት ምክንያት ግልፅ ነው።

Thursday, April 3, 2014

“የእሪታ ቀን” እንዲሰረዝ የኢህአዴግ መንግስት ጠየቀ

April3/2014

በአንድነት ፓርቲ አማካኝነት – መጋቢት 28 ቀን፣ 2006 ሊደረግ የነበረው የ እሪታ ቀን በአዲስ አበባ መስተዳድር ተቃውሞ ገጥሞታል። ከአዲስ አበባ አስተዳደር ከንቲባ ጽ/ቤት የወጣው ደብዳቤ እንደሚያመለክተው ከሆነ፡ ሰልፈኞቹ የሚሄዱበት ስፍራ የተከለከለ በመሆኑ የሰላማዊ ሰልፉን ጥያቄ እውቅና አንሰጠውም ብሏል። ቀበና መድሃኔአለም ከሚገኘው የአንድነት ፓርቲ ጽ/ቤት ተነስቶ በፒያሳ እና ቸርችል ጎዳና አድርጎ፤ ጥቁር አንበሳ ድላችን ሃውልት ጋር ይጠናቀቅ የነበረውን ሰላማዊ ሰልፍ፤ የአዲስ አበባ አስተዳደር ጽ/ቤት… መንገዱ የባቡር መስመር የሚዘረጋበት፣ ትራፊክ የሚበዛበት እና ሆስፒታል የሚገኝበት መሆኑን በመግለጽ ነው፤ ለሰልፉ እውቅና የነፈገው። ይህ በ’ንዲህ እንዳለ የአንድነት ፓርቲ በዚህ ጉዳይ ላይ ሰልፉን የሚያካሂድ መሆኑን ገልጿል። ሆኖም በፓርቲው በኩል የተሰጠ ዝርዝር ማብራሪያ ወይም ኦፊሴላዊ መግለጫ የለም። ምናልባት ፓርቲው ተለዋጭ ቀን እና ቦታ ይጠይቅ ይሆናል… እውቅና ከተነፈገና ለሌላ ጊዜ የሚያስተላልፈው ከሆነ ጉዳዩን በቴሌቪዥን እና በሬድዮ ማሳወቅ ሳይኖርበት አይቀርም። ለማንኛውም ከአንድነት ፓርቲ የሚሰጥ ኦፊሴላዊ መግለጫ ካለ ይዘንላቹህ እንቀርባለን።

የወላይታ ዞን የሰማያዊ ፓርቲ አመራሮች ታሰሩ

April3/2014

መጋቢት 20/ 2006 ዓ.ም የወላይታ ዞን የሰማያዊ ፓርቲ አመራሮች ሶዶ ውስጥ ስብሰባ ለማድረግ ዝግጅት እያደረጉ በነበረበት ወቅት ፖሊስ ምንም አይነት ምክንያት ሳይሰጥ ሰብስቦ እንዳሰራቸው ከአካባቢው የፓርቲው ተወካዮች ለማወቅ ተችሏል፡፡ በአሁኑ ወቅት አመራሮቹ ድል በትግል በተባለው የፖሊስ ጣቢያ ታስረው ይገኛሉ፡፡

blue_welayta
በአሁኑ ወቅትም እስር ላይ ከሚገኙት መካከልም፡-
1. ወጨፎ ሳዳሞ የወላይታ ዞን ምክትል ሰብሳቢ
2. ታደመ ፍቃዱ የወላይታ ዞን አደረጃጀት ጉዳይ ኃላፊ
3. አቶ ጻድቁ ወ/ስላሴ የወላይታ ዞን የፋይናንስ ኃላፊ
4. አቶ ቴዎድሮስ ጌታ የዞኑ የወጣቶች ጉዳይ ኃላፊ
5. ቦጋለ የፓርቲው አባል
ይገኙበታል። እነዚህ አመራሮች መታሰራቸውን ተከትሎ የዞኑ የፓርቲው ሌሎች አመራሮችና አባላት፣ ድል በትግል ፖሊስ ጣቢያ ሄደው ታሳሪዎችን ለመጠየቅም ሆነ የታሰሩበትን ምክንያት ለማጣራት ያደረጉት ጥረት ሳይሳካ መቅረቱን ማወቅ ተችሏል፡፡
ጠዋት 4 ሰዓት ላይ የታሰሩት የዞኑ አመራሮች ምግብ፣ ውሃና ልብስ እንዳይገባላቸው መከልከሉንም የአካባቢው አመራሮች ለነገረ ኢትዮጵያ ገልጸዋል፡፡ ከሁለት ሳምንት በፊት የፓርቲው አመራሮች ለስብሰባ ወደ አካባቢው በሄዱበት ወቅት በተመሳሳይ ሁኔታ ታስረው እንደነበር ይታወቃል፡፡ በወቅቱ ከታሰሩት የፓርቲው ኃላፊዎች መካከል የህዝብ ግንኙነት ኃላፊው አቶ ብርሃኑ ተክለያሬድ በወላይታ ዞን በተቃዋሚዎች በተለይም ሰማያዊ ፓርቲ ላይ የሚደረገው አፈና መጠናከሩን በመጥቀስ፣ ይህንን አፈና በመቃወም ፓርቲው በቅርብ ጊዜ በአካባቢው ህዝባዊ ንቅናቄ እንደሚያደርግ ገልጸዋል፡፡ በዞኑ የሚደረገው አፈና ህገ ወጥ መሆኑንና በአሁኑ ወቅት እስር ቤት ውስጥ የሚገኙት የዞኑ የፓርቲያቸው አመራሮችም በአስቸኳይ እንዲፈቱ ጠይቀዋል፡፡

ትንሽ ምላጭ አገር ትላጭ! መጠላለፍ ወደየትኛው ገደል እየመራን ነው?

April3/2014

መስፍን ወልደ ማርያም
የአዲስ አበባን መኪናዎች በተለይም በጫት የሚሽከረከሩት ታክሲዎችን በማንኛውም መስቀልኛ መንገድ ላይ ለአምስት ደቂቃ ቆሞ የተመለከተ ሰው በቀላሉ እንደሚረዳው ‹እኔ ካላለፍሁ ማንም አያልፍም!› በሚል መመሪያ መኪናዎቹ ተቆላልፈው እንዲቆሙ ማድረግ ነው፤ እንደሚመስለኝ የአባቶቻችንን ዕዳ እየከፈልን ነው፤ ዱሮ በደጉ ዘመን ሁለት ኢትዮጵያውያን መስቀልኛ መንገድ ላይ ሲገናኙ አንተ-እለፍ አንተ-እለፍ እየተባባሉ የሰማዕታቱንና የቅዱሳኑን ስም እየጠሩ ይገባበዙ ነበር! ይህ ባህል በጠንካራ የሥልጣኔ ላጲስ ተደምስሶ ጠፍቶ በምትኩ እኔ ካላለፍሁ ማንም አያልፍም መንገዱን ሁሉ መቆላለፍ አዲስ የመጠላለፍ ባህል እየተተከለ ነው፤ የመጠላለፍ ባህል የሚታየው በባቡር መንገዶች ላይ ብቻ አይደለም፤ በብዙ ነገር መጠላለፍ ባህል እየሆነ ነው! የዚህ ዝንባሌ መጨረሻው አሸናፊ የሌለበት ሙሉ ጥፋት ነው።

በመንገዶች ላይ ጥቂት በጫት የሚነዱ መኪናዎች በመቶ የሚቆጠሩ መኪናዎች እንዳይንቀሳቀሱ ለማድረግ ይችላሉ፤ ሲያደርጉም በየቀኑ እየታየ ነው፤ በማኅበረሰባዊና በፖሊቲካ ግንኙነትም አንድ ሰው የሚዘራው መርዝ የጊዜው ሁኔታ በሚፈቅድለት ፍጥነት የማኅበረሰቡን አባላት ያዳርሳል፤ እንቆቅልሹ እንደሚለው ትንሽ ምላጭ አገር ትላጭ! ማለት መርዝ፣ እሳት፣ ተላላፊ በሽታ በሕዝቡ ላይ ማሰራጨት ከአምስትና ከአሥር ዓመታት በኋላ ውጤቱ ምን እንደሚሆን መገመት አያቅትም።

ድብብቆሽ አይጠቅምም፤ሁለት ነገሮችን በግልጽ ማውጣት አለብን፤አንደኛ በአሜሪካና በአውሮፓ መሽጎ ፍርሃቱንና ሽቁጥቁጥነቱን ለመሸሸግ መርዙን በኢትዮጵያውያን ላይ የሚረጨው ለምንድን ነው? አገዛዙ ይህንን የሚያደርግበት ምክንያት ግልጽ ነው፤ ከፋፍሎ የመግዛት ዘዴ ነው፤ ከአገዛዙ ጋር በሚደረግ ትግል ከታች ሆነው ከሥልጣን ውጭ የሆኑ ዜጎች በሥልጣን ላይ ከተቀመጡት ጋር እየተቆራቆዙና እየተጋጩ ናቸው፤ ይህንን እኔ የላይና-የታች ግጭት (vertical conflict) የምለው ነው፤ ከወያኔ/ኢሕአዴግ ጋር የሚደረገው ትግል ይህ ነው፤ ይህንን ለማክሸፍ ወያኔ/ኢሕአዴግ ትግሉን ከላይና-ታች አውጥቶ ወደጎን-ለጎን ግጭት (horizontal conflict) ሊለውጠው ይፈልጋል፤ ከወያኔ/ኢሕአዴግም ውጭ በጎሠኛነትና በሃይማኖት አክራሪነት የደነዘዙ ሰዎችም ትግሉን ጎን-ለጎን ሊያደርጉት እየሞከሩ ናቸው።

የፖሊቲካ ትግልን የሚመሩ ሰዎች በጎሠኛነትና በሃይማኖት አክራሪነት ስሜት እየተሳቡ ትግሉን የላይና-የታችነቱን ጠብቀው በተደራቢነት የጎን-ለጎን ትግሉን ይጨምሩበታል፤ ይህ ሲሆን ሀሳብ፣ ጉልበትና ሀብት ይከፋፈላል፤ ይበታተናል፤ ወደዓላማ ለመድረስም ያስቸግራል፤ ወያኔ ወደመጨረሻው ላይ ኢሕአዴግ ብሎ የሰየመውን ቀፎ አስቲፈጥር ድረስ በስሙ ውስጥ ኢትዮጵያን የሚያነሣ ነገር አልነበረውም፤ ወያኔን ለድል ያበቃው የማታለያ ስሙ እንደሆነ በበኩሌ አልጠራጠርም፤ ከሃያ ሁለት ዓመታት የጎሣ ሥርዓት በኋላ ኢትዮጵያ ቆስላለች እንጂ አልሞተችም፤ የአሐዝ ማስረጃ ለማቅረብ ባልችልም በብዙ ጎሣዎች መሀከል ጋብቻ እንደዱሮው እየቀጠለ ነው፤ ይህንን የቆየ የዝምድና ሰንሰለት ለመበጠስ የሚጥሩም አሉ።
ኒው ዮርክ ተቀምጦ ትኩስ ውሻ (ሆት ዶግ!) እየበላ ለእስላም ኦሮሞዎች የመገዳደያ መመሪያ የሚሰጥ ሰው የመንፈስ ጤንነቱን እጠራጠራለሁ፤ ይህንን የኒው ዮርክ ቀረርቶ ተከትሎ ሌላ የመጠላለፍ አዋጅ ሰማን፤ ቴዎድሮስ ካሣሁን ለአጼ ምኒልክ ስለዘፈነ ከበዴሌ ቢራ ፋብሪካ ጋር ለማስታወቂያ የገባው ውል ሥራ ላይ ከዋለ የበዴሌን ቢራ አንጠጣም ተባለና ማስታወቂያው ተሰረዘ ይመስለኛል፤ ማን እንዳሸነፈ ወደፊት ጊዜ ይነግረናል፤ አሁን ደግሞ ሌላ ማዘዣ ሰማሁ፤ ‹‹የስ›› በሚለው ውሀ ጠርሙስ ላይ እንስራ የተሸከመችው ኮረዳ መስቀል አድርጋ ነበር፤ ልጅቱ ከነመስቀልዋ የምትታይበትን ውሀ እስላሞች አንገዛም ስላሉ ነጋዴዎቹ መስቀሉን አወለቁባት! ይህንን ማዘዣ ላወጣው አክራሪ እስላም ወረባቦ ቅዳሜ ገበያ ሄዶ እንዲጎበኝ አሳስበዋለሁ፤ ዛሬ ተለውጦ እንደሆነ አላውቅም እንጂ እኔ ብዙ ጊዜ ተመላልሼ እንዳየሁት የወረባቦ ኮረዶች ሁሉ ትልልቅ መስቀል በአንገታቸው ላይ ይታይ ነበር፤ መስቀል የእምነት መግለጫ ይሆናል፤ አያጠራጥርም፤ ግን መስቀል ጌጥም ይሆናል! መስቀል የናዚ ምልክትም ሆኖ ነበር! ለማናቸውም የዚህ ዓይነቱን መጠላለፊያ ለኢትዮጵያ ሕዝብ የሚገምዱ ሰዎች ዓላማቸው ማንንም ለመጥቀም ሳይሆን ፍቅርንና ሰላምን ለማደፍረስ ነው፤ የኢየሱስ ክርስቶስ መሠረታዊ ትምህርት ክፉን በክፉ አትመልሱ ነውና ለተበጠሰው መስቀል አጸፋውን ለመመለስ ማሰብ አይገባም።

ከኒው ዮርክ የተሰማው ቀረርቶም ሆነ የመስቀል ማስወለቁ ጉዳይ የተከሰተበትን ጊዜ ልብ ልንለው ይገባል፤ እስላሞች ስለነጻነት የሚያደርጉት ንቅናቄ በጣም እየጋለ በመሄድ ላይ እያለ ክርስቲያኖችም የዜግነት ግዳጃቸው አድርገውት ድጋፋቸውን በሚሰጡበት ጊዜ ነበር፤ ይህ መሆኑ ጥርጣሬን ይጋብዛል፤ የገጠመውን የእስላሞችና የክርስቲያኖች ሰልፍ በማደፍረስ ወይም በመክፈል የሚጠቀም ማን ነው? የሚጎዳውስ ማን ነው? ሁሉም የትግል አጋፋሪዎች ለዚህ ጉዳይ የሚያስፈልገውን ክብደት ቢሰጡት ትግሉ በጎን-ለጎን እንዳይሄድና እንዳይዳከም ይረዳል፤ ከዚያም በላይ አክራሪነት የሚባለውና የሚያስከትለውም ሽብርተኛነት የሚመጣው እንዲህ እያለ ነው፤ እግዚአብሔር ከዚያ ያውጣን!

የማለዳ ወግ … በጨለመው የሳውዲ ወህኒም ይነጋል …

April2/2014



ግፍ ከበዛበት ወህኒ የአክብሮት ስላምታየ ይድረሳችሁ!
እነሆ ለሁለተኛ ጊዜ ለአፍታ ያህል እድሉን አግኝቸ ወህኒ የመውረዴን እውነታ ላስረዳችሁ ግድ አለኝ ። ዛሬ አስረግጨ የምነግራችሁ ወህኒ የመውረዴ ምክንያት ሚስጥር ግምሽ እድሜየን ህግና ስርአቷን አክበሬ የኖርኩባትን የሳውዲት አረቢያን ህግ ተላልፊ አይደለም ! የስደተኛው ጉዳይ ያገባኛል በሚል የማቀርበው መረጃ ቅበላየ የማይመቻቸው ፣ ያመማቸው ከተሰረሰውና እየተሰራ ካለው ከእገታው ጀርባ ስለመኖራቸው አልጠራጠርም ። ... ዛሬ በዚህ ዙሪያ ብዙ አልልም!
አላወቁትም እንጅ ክፉዎች ጠቅመውኛል ፣ ያላየሁትን እንዳይ አድርገውኛል። መንገዱ የከፋ ቢሆንም በወሰዱኝ መንገድ ተመርቸ እሰማው የነበረውን የወገኖቸ የወህኒ የከፋ ኑሮና ህመም ፣ በተቆርቋሪ ጠያቂ ማጣት ፣ በፍትህ መነፈግ እይሆኑ ያሉትን ከመስማት ማየት ማመን ነውና በአካል ማየት ችያለሁ !
ከመታሰሬ ጥቂት ቀናት በፊት በግፍ ለተደበደበው፣ ሁለት አይኑን ላጣውና " አይሆኑ ከሚሆን ቢሞት ይሻላል "ተብሎ የፎቶ መረጃው ሳይቀር በእጀ የገባውን ወጣት ምንዱብ የወህኒ ህይወትን ተጨባጭ ታሪክ ከአይን እማኞች ቃርሜያለሁ! እሱም ያለው ከታሰርኩበት የቅርብ ርቀት ነው ። ... አትጠራጠሩ አገኘውም ይሆናል !
በዚህ የጭንቅ ሰአት ከእኔና ከቤተሰቦቸ ጎን ሆናችሁ አለኝታችሁን ለገለጻችሁልን ምስጋናየ ከፍ ያለ ነው ! ዛሬ ወደ ዝርዝር ጉዳዩ አንገባም ። በላይ በመላ አለም የምትገኙ ወገኖቸ ያሳያችሁኝ ድጋፍና መቆርቆር ከጨለማው ቤት ደርሶኝ ጽናት አጎናጽፎኝ ሰንብቷል። ይህም በአረብ ሃገር ስደተኛ ዙሪያ ሳቀርነው ለነበረው መረጃ ያገኘሁት ክብርና ሞገስ ሆኖ መከራውን አስረስቶኛል: ) ምስጋናየ አይለያችሁ!
ወገኖቸ ወዳጆች ፣ ዛሬ ሰላም መሆኔን ብቻ ተረዱ ብየ እንጅ በሰፊው ስለሚሆነው አቅም በፈቀደ መጠን እናወራለን ! ዝምታው ከናፈቅኳቸው ልጆቸ ፣ ከቤተሰቦቸና ከእናንተ ጋር የሚያደርሰው መንገድ ውል እንዲይዝ የሚደረገው ሙከራ ውል እንዲይዝ የሚተጉ ወገኖችን ሂደት ላለማደናቀፍ ብቻ ለመረጋጋት ሲባል ብቻ ነው !
በጨለመው የሳውዲ ወህኒም ይነጋል ፣ በንጋቱ ጮራ ታግዘን የምናወጋው የማለዳ ወግ ናፍቆኛል: ) ይህን ለማድረግ የሚከፈለውን ሁሉ ለመክፈል ደግሞ ልቤ ብርቱ ነው ...
ሰላም ለሁላችሁ !
ነቢዩ ሲራክ
ከአንዱ የሳውዲ ወህኒ ቤት

በእጅ አዙር የኢ.ህ.አ.ዴ.ግ መግስት ስለባ የሆነው ጋዜጠኛ ነብዩ ሲራክ ለወግኖቹ ክበር እስከ መስወአትነት እንደሚቆም ከስርቤት አረጋገጠ !

April2/2014

በእጅ አዙር የኢ.ህ.አ.ዴ.ግ መግስት ስለባ የሆነው ጋዜጠኛ ነብዩ ሲራክ ለወግኖቹ ክበር እስከ መስወአትነት እንደሚቆም ከስርቤት አረጋገጠ !
ባልታወቀ ምንክንያት ክቀርብ ግዜህ ወዲህ በሳውዲ ጸጥታ ሃይሎች ለእስር የተዳረገው ጋዜጠኛ ነብዩ ሲራክ ሳውዲ አረቢያ ውስጥ በወገኖቹ ላይ የሚፈጸመውን በደል እይተከታተለ ለሚዲያ የሚያበቃ በአረቡ አለም የሚገኝ ብቸኛ ኢትዮጵያዊ ጋዜጠኛ ነው ። ጋዜጠኛ ነብዩ ሲራክ ለወህኒ ከመዳረጉ በፊት ባለፉት አመታት በወገኖቹ ላይ የሚደርስውን ግፍ እና በደል አስመለክቶ ያቀርብ በነበረው የማለዳ ወግ መረጃ ቅበላው ያልተደሱቱ የኢ.ህ.አ.ዴ.ግ መንግስት ሹማምንቶች እና በወገኖቻቸው ህይወት ዶላር ሲሰበስቡ በከረሙ አፋኞች ማስፈራያ ይደርሰበት እነደበር ለማወቅ ተችሏል ።

 ጀግናው ጋዜጠኛ ለነዚህ ወሮበሎች ሳይበረከ እስከመጨረሻው ለወገኑ ክበር የህይወት መስወአትነት ለመክፈል የግባውን ቃልኪዳን ጠብቆ በእሳት ተፈትኖል። ዛሬ በዚህ ጀግና ጋዜጠኛ ላይ የተፈጸመውን ደባ እና ከጀርባው እና ማን እንዳሉ በስፋት መግለጽ ጋዜጠኛ ነብዩ ሲራክ ነጻ ለማውጣት ለወህኒ ከተዳረገበት ግዜ ጀምሮ እሳካሁን እተደረገ ያለውን ጥረት ስለሚያወሳስበው ወደ ዝርዝር ሃስቡ ከመግባት መቆጠብ ግድ ብሏል ። ይህን ታላቅ ጋዜጠኛ ከተቻለ ከሳውዲ አረቢያ እንዲባረር አሊያም ወህኒ እንዲማቅቅ ጋዜጠኛ ነብዩ ሲራክ ያለፈጸመውን ፈጸመ በሚል የጥላቻ ዘመቻ ከፌስ ቡክ አንስተው ለሳውዲ ጸጥታ ሃይሎች የተሳሳተ መረጃ እስከመስጠት የድረሱ ዛሬም ዛሬም እንቅልፍ አጥተው የሚያማትሩ የህዝብ ጠላቶችን የሃሰት ውንጀላ በመከላለከል ይህን ኢትዮጵያዊ ጋዜጠኛ ከደረሰበት አደጋ ልንታደገው ይገባል። 
Ethiopian Hagere ጅዳ በዋዲ

Wednesday, April 2, 2014

ግብፅ በህዳሴው ግድብ ላይ ‹‹የተቀናጀ የድርጊት መርሐ ግብር›› አለኝ አለች

April 2, 2014

-የኢትዮጵያና የግብፅ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ብራሰልስ ይገናኛሉ

ግብፅ በህዳሴው ግድብ ላይ ‹‹የተቀናጀ የድርጊት መርሐ ግብር›› አለኝ አለች

የታላቁ የኢትዮጵያ የህዳሴ ግድብ ግንባታ ሦስተኛ ዓመት እየተከበረ ባለበት በዚህ ወቅት፣ በግድቡ ላይ የተለየ አዲስ ፖሊሲ የለኝም ያለችው ግብፅ ቀስ በቀስ ተግባራዊ የሚደረግ ‹‹የተቀናጀ የድርጊት መርሐ ግብር›› እንዳላት አስታወቀች፡፡

ይህ የግብፅን የውኃ ደኅንነት ያስጠብቃል የተባለለት መርሐ ግብር ‹‹ፖለቲካዊ፣ ሕጋዊና ሌሎች ቴክኒካዊ›› የሚባሉ ጉዳዮችን ያቀፈ መሆኑን የግብፅ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አስታውቀዋል፡፡

የግብፅ ዴይሊ ኒውስ ጋዜጣ እንደዘገበው፣ ግብፅ በታላቁ የህዳሴ ግድብ ላይ የተለየ ፖሊሲ ባይኖራትም፣ ነገር ግን ግድቡን በተመለከተ የምታራምደው አቋም የተለመደው መሆኑን ቃል አቀባዩ ተናግረዋል፡፡

የዓባይን ውኃ በተመለከተ ከብሔራዊ ደኅንነቷ ጋር ያስተሳሰረችው ግብፅ ግድቡን በተመለከተ ግልጽ የሆነ አቋም እንዳላት የጠቆሙት ቃል አቀባዩ፣ የግብፅን ፍላጎት በሚፃረር ጉዳይ ላይ ምንም ዓይነት ድርድር እንደማይኖር በግልጽ አስታውቀዋል፡፡ የግብፅን ፍላጎት የሚፃረር ያሉት የግድቡ ግንባታ ነው፡፡

ከፖለቲካዊና ከሕጋዊ ማዕቀፎች ውጪ የግብፅ ‹‹የተቀናጀ የድርጊት መርሐ ግብር›› ያካተተው ‹‹ቴክኒካዊ ጉዳዮች›› የተባለው ምንን ለማመልከት እንደሆነ ቃል አቀባዩ ባይገልጹትም፣ የፖለቲካ ተንታኞች ግን የተለመደው የግብፆች ማስፈራሪያ ነው ብለውታል፡፡ የግብፅ ባለሥልጣናት ከኢትዮጵያ ጋር መነጋገር ሲኖርባቸው ለምን ይህንን ዓይነቱን ማስፈራሪያ እንደሚጠቀሙ ግራ ያጋባል ይላሉ፡፡

ኢትዮጵያ ላለፉት ሦስት ዓመታት እየገነባችው ያለው የታላቁ ህዳሴ ግድብ በአሁኑ ወቅት 33 በመቶው መጠናቀቁ ሲገለጽ፣ ግብፅ በበኩሏ የግድቡ ግንባታ ሕገወጥ ነው በማለት በመግለጽ ላይ ናት፡፡ በግብፅ የውኃ ደኅንነት ላይ የሚከሰት ችግር እንደሌለ በኢትዮጵያ ባለሥልጣናት በተደጋጋሚ ቢገለጽም፣ ግብፅ አሁንም በግድቡ ምክንያት ብሔራዊ ደኅንነቴ ተነክቷል ማለቷን ቀጥላለች፡፡

ይህ በዚህ እንዳለ፣ የግብፅ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ነቢል ፋህሚ ከኢትዮጵያ አቻቸው ዶ/ር ቴድሮስ አድሃኖም ጋር በብራሰልስ ለመነጋገር ቀጠሮ መያዛቸው ታውቋል፡፡ በአውሮፓ ኅብረትና በአፍሪካ ጉባዔ ላይ ለመገኘት ሁለቱ ሚኒስትሮች ብራሰልስ ይገኛሉ፡፡ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮቹ በታላቁ የህዳሴ ግድብ ላይ እንደሚነጋገሩም ተሰምቷል፡፡

ዶ/ር ቴድሮስና ሚስተር ፋህሚ እ.ኤ.አ. ሴፕቴምበር 2013 ካይሮ ተገናኝተው በግድቡ ምክንያት የተፈጠረውን ውጥረት ለማርገብ ስምምነት ላይ መድረሳቸው ይታወሳል፡፡

የግብፅ ባለሥልጣናት ግድቡን በተመለከተ በተለያዩ ጊዜያት የተለያዩ አቋሞችን እያራመዱ ሲሆን፣ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ደግሞ እ.ኤ.አ. በ1902 ኢትዮጵያና እንግሊዝ የዓባይን ውኃ በተመለከተ አድርገውታል የተባለውን ስምምነት በመጥቀስ ወደ ዓለም አቀፍ ፍርድ ቤት እንሄዳለን እያሉ ናቸው፡፡ እነሱ ያልነበሩበትን ስምምነት ይዘው የትም መድረስ እንደማይችሉ የፖለቲካ ተንታኞች እየገለጹ ሲሆን፣ ያ ስምምነት በትርጉም ስህተት ምክንያት ሥራ ላይ አለመዋሉ ይነገራል፡፡

የግብፅ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ፋህሚ በተጨማሪ ግድቡን በተመለከተ ከአውሮፓ ኅብረት የውጭ ጉዳይ ፖሊሲ ኃላፊ ካትሪን አሽተን ጋር ተነጋግረዋል፡፡ የሁለቱ ባለሥልጣናት ውይይት ውጤት ግን አልተሰማም፡፡

ግብፅ ከኢትዮጵያና ከሱዳን ጋር ጀምራቸው የነበሩ ሦስት ዙር ውይይቶችን በተለያዩ ምክንያቶች ካሰናከለች በኋላ፣ በግድቡ ላይ የተለያዩ ዘመቻዎችን መጀመሯ አይዘነጋም፡፡ ከእነዚህ ዘመቻዎች መካከል የቅርቡ ግድቡን ዓለም አቀፍ ገጽታ ማላበስ ሲሆን፣ አሁን ደግሞ ‹‹የተቀናጀ የድርጊት መርሐ ግብር›› የሚሉት ብዙዎችን ግራ አጋብቷል፡፡

በኢትዮጵያ የታላቁ ህዳሴ ግድብን ሦስተኛ ዓመት በማስመልከት በተለያዩ መርሐ ግብሮች የተለያዩ ዝግጅቶች የተደረጉ ሲሆን፣ መጋቢት 24 ቀን 2006 ዓ.ም. ግድቡ በሚገነባበት ሥፍራ በከፍተኛ ሥነ ሥርዓት አከባበር ተደርጓል፡፡

ሕወሓት በምርጫ 2007 በትግራይ ክልል ሊሸነፍ እንደሚችል አመነ

April 2, 2014

አብርሃ ደስታ ከመቀሌ

ዓረና ፓርቲ በትግራይ ክልል ወረዳዎች በመዘዋውር ባሰብሰበው መረጃ መሰረት በ2007 በሚደረገው ሀገራዊ ምርጫ ገዥው ፓርቲ የህዝብን ድምፅ ካከበረ ህወሓት በመላው ትግራይ ሙሉ በሙሉ ይሸነፋል። አንድ የህወሓት የስራ አስፈፃሚ አባል (ለግዜው ስሙ ይቅር) በዓዲግራት ከተማ ለተሰበሰቡ ከምስራቃዊ ዞን የተውጣጡ የህወሓት ካድሬዎች “እናንተ በምትፈፅሙት በደል ምክንያት በ2007 ምርጫ እንሸነፋለን። ግን አንዳንድ የምናደርጋቸው ነገሮች ስለሚኖሩ ሙሉ በሙሉ ተስፋ አትቁረጡ። ለራሳችሁ ዕጣ ፈንታ ስትሉ በደንብ ስሩ” ማለቱ ታውቋል። ካድሬዎቹም “በናንተ (የላይኞቹ አመራሮች) ችግር ነው የምንሸነፈው፤ ህዝብ የማይቀበለውን ነገር እንድናሳምን ታስገድዱናላቹ” የሚል መልስ በመስጠታቸው የእርስበርስ ንትርክ መከፈቱ ታውቋል። ከስብሰባው በኋላ ካድሬዎቹ የንትርኩ ነጥቦች ለዓረና አባላት አስረድተዋል።

በዓረና እንቅስቃሴ የሰጉ የህወሓት መሪዎች ህዝብን በገንዘብ መደለል ጀምረዋል። ባሁኑ ግዜ የትግራይ ህዝብ በህወሓቶች በሦስት ደረጃዎች ተከፍሎ ግሬድ ተሰጥቶታል። ግሬድ A, B ና C። ግሬድ “A” ታማኝ የህወሓት ካድሬ፣ ግሬድ “B” መሓል ሰፋሪ፣ ግሬድ “C” ተቃዋሚ (ዓረና)። በዚሁ መሰረት ህወሓትን ለማገልገል ፍቃደኛ የሆነ ሰው (ታማኝ ካድሬ A) ለስብሰባ ይጠራና የማዳበርያን ዕዳ ለመክፈል የሚያግዘው 3000 ብር የውሎ አበል ተብሎ ይሰጠዋል። 3000 ብር ከተቀበለ በኋላ ተቃዋሚዎችን ይታገላል፣ ህወሓት እንዲመረጥ ያግዛል፣ ታማኝ የህወሓት አገልጋይ ይሆናል። ለህወሓት ታማኝ ያልሆነ ለስብሰባ አይጠራም፤ ገንዘብም አይሰጠውም። በ3000 ብር የምርጫ ድምፅ መግዛት ይሉታል እንዲህ ነው። የምርጫ ድምፅ እየተገዛበት ያለ ገንዘብ የህወሓት ሳይሆን በግብር መልክ የተሰበሰበ የመንግስት ገንዘብ ነው። መንግስት ብር አነሰኝ እያለ ግብር እየጨመረ ነጋዴዎች ንግዳቸውን ይዘጋሉ። ህወሓቶች ደግሞ የሰበሰቡትን ገንዘብ ለምርጫ ጅንጀና ይጠቀሙታል።

                  (ከዚህ ቀደም የአረናን ሕዝባዊ ስብሰባ እንዳይሳተፉ የተከለከሉ የሽሬ ነዋሪዎች – ፎቶ ከአብርሃ ደስታ) – ፎቶ ፋይል

የትግራይ አርሶአደሮች እንደዚህ በፖለቲካ ታማኝነት በዉሎ አበል መልክ ገንዘብ እየተሰጣቸው የማዳበርያ ዕዳቸውን መክፈል ከቻሉ ጥሩ ነው። ባንዳንድ አከባቢዎች ግን የዉሎ አበሉ መጠን ይለያያል። ለምሳሌ በደቡባዊ ምስራቅ ዞን ለየት ያለ አጋጣሚ ተፈጥሯል። ህወሓቶች በሁሉም ዞኖች እንደሚያደርጉት ሁሉ ታማኝ የተባሉ (ለምርጫ ሊያገለግሉ የሚችሉ) 200 የሳምረ አርሶአደሮች መለመሉ። አርሶአደሮቹ ሲመለመሉ “ለስብሰባ ትሄዳላቹ፣ 3000 ብር አበል ይሰጣችኋል፤ ስለዚህ 3000 ብሩን ለማግኘት በመጪው ሰኔ ላይ ለምትወስዱት ማዳበርያ 1200 ብር አሁን ክፈሉ” ይሏቸዋል። አርሶአደሮቹም 3000 ብሩን ለማግኘት 1200 ብር እንደምንም ብለው ከፈሉ። ከሳምረ ለስብሰባ ተብሎ ወደ ሕዋነ ተወሰዱ፤ ፖለቲካ ተጀነጀኑ። በመጨረሻ እነሱ 3000 ብር እየጠበቁ 640 ብር ብቻ እንደሚሰጣቸው ተነገራቸው። ከ640 ም 600 ው መቆጠብ አለባቹ በሚል ሰበብ በህወሓቶች እጅ ሲቀር 40 ብር ብቻ ለትራንስፖርት ተሰጣቸው። አርሶአደሮቹ አሁን ቅሬታቸው አካፍለውናል።


አዎ! የህዝብ ድምፅ ከተከበረ ዓረና ሙሉ በሙሉ ያሸንፋል። እናም ህወሓቶች በሰለማዊ መንገድ ስልጣን ያስረክባል። የህወሓት ካድሬዎችም መብታቸው ተጠብቆላቸው በሰላም በሀገራቸው ይኖራሉ። ከፈለጉ በመንግስት መስራቤት በሙያቸው ተቀጥረው ይሰራሉ፣ ወይም ህወሓት ተቃዋሚ ፓርቲ አድርገው ለሚቀጥለው ምርጫ ለመወዳደርና ለማሸነፍ ይሞክራሉ። በሰለማዊ መንገድ ስልጣን ለማስረከብ ካልፈለጉ ግን በሃይል እስኪወገዱ ድረስ በስልጣን ይቆያሉ። በሃይል ከተሸነፉ እንደ የደርጎቹ ከሀገር ተጠርገው ይባረራሉ፤ የደርግ ባለስልጣናት ዕጣ ፈንታ ይቀምሳሉ።
ስልጣን ለህዝብ እናስረክብ፤ ሰለማዊ የስልጣን ሽግግር ይኑር። ስልጣን ለህዝብ ካላስረከብን ግን ሌላ ታጣቂ ሃይል ይነጥቀዋል። ከዛ ስልጣን ባላንጣን መምችያ ዱላ ይሆናል። ዱላው ከህዝብ ጋር መሆን አለበት።
==================
ሰላማዊ ሰልፍ በደርግና ህወሓት
“የትግራይ ህዝብ ሰለማዊ ሰልፍ የማድረግ መብቱ ከተነፈገ እነሆ 22 ዓመታት አለፉ” ብዬ ለፃፍኩት “ከ22 ዓመታት በፊት ሰለማዊ ሰልፍ ማድረግ ይፈቀድ ነበር እንዴ? በደርግ ግዜስ ሰለማዊ ሰልፍ ይፈቀድ ነበር ማለት ነው?” የሚል ጥያቄ መጣብኝ።

የደርግ ዘመን በትግራይ ክልል የጦርነት ግዜ ነበረ። በጦርነት ግዜ ሰለማዊ ሰልፍ አይፈቀድም። በደርግ ግዜ ሰለማዊ ሰልፍ ማድረግ በህገመንግስት የተደነገገ መብት አልነበረም። በደርግ ዘመን ስርዓት አልነበረም። ደርግ ትግራይን አልተቆጣጠረም ነበር። ግማሹ የትግራይ መሬት በደርግ ወታድሮች ቁጥጥር ሲሆን ግማሹ ደግሞ በህወሓቶች እጅ ነበረ (ሓራ መሬት ትግራይ)። ስለዚህ አንድ መንግስት የዜጎችን መብት ለማስከበር መጀመርያ ስርዓት መመስረት አለበት። በሁሉም አከባቢዎች አስተዳዳራዊ ስራና ቁጥጥር ሊኖረው ይገባል። ደርግ በትግራይ አስተዳዳራዊ ቁጥጥር አልነበረውም። የዜጎችን መብት ለማስከበር ሕገመንግስት መደንገግ አለበት። በደርግ ግዜ ሕገመንግስት አልተደነገገም ነበር ማለት ይቻላል። ምክንያቱም ደርግ ወታደራዊ መንግስት ነበርና። ወታደራዊ መንግስት ሕግ አያከብርም፤ ስለ ስልጣኑ እንጂ ስለ ህዝብ መብት አይጨነቅም።
ስለዚህ የትግራይ ህዝብ ሰለማዊ ሰልፍ የማድረግ መብቱ ተነፈገ ሲል በደርግ ግዜ መብቱ ተከብሮለት ነበር ማለቴ አይደለም። መልእክቱ ህወሓትም ከደርግ እሻላለሁ፣ ደርግን አስወግጄ የህዝብ መብት አስከብራለሁ፣ ነፃነት እፈቅዳለሁ እያለ የትግራይን ህዝብ ድጋፍ አሰባስቦ ቤተመንግስት ከገባ በኋላ ሌላ ደርግ ሆነብን ለማለት ተፈልጎ ነው።

ህወሓት ራሱ ከደርግ ጋር ማወዳደር ቢተው ጥሩ ይመስለኛል። ምክንያቱም በደርግ ግዜኮ (በትግራይ ማለቴ ነው) ስርዓት አልነበረም። የደርግ ዘመንኮ የጦርነት ዘመን ነው የነበረው። ስለዚህ አንድ መንግስትነት ተቆጣጥርያለሁ የሚል ስርዓት ራሱ ከጦርነት ዘመን ጋር እንዴት ያወዳድራል? ህወሓት ራሱ መፈተሽ ያለበት አሁን መስራት ካለበትና መስራት ከሚጠበቅበት አንፃር መሆን አለበት።

[በአባይ ግድብ ዙሪያ የተጻፈ አጭር ሀተታ] ትንሹዋ ወያኔና ትልቁ ወያኔ አላኖሩኝም

April 2, 2014
ነፃነት ዘለቀ (አዲስ አበባ) 
ለለውጥ ያህል ከራሴ ችግር ብጀምር ምን አለበት? ግለሰብ ካልኖረ ማኅበረስብ አይኖርም፡፡ ደሞም የኔ ችግር የሁሉም ፣ የሁሉም ችግር የኔ መሆኑን የማያምን አንባቢ ቢኖር ችግር አለበት ማለት ነውና በጊዜ ራሱን ፈትሾ መድሓኒት ቢጤ ቢያፈላልግ ሳይሻለው አይቀርም፡፡TPLF is just like a Rat
ትንሹዋ ወያኔ ጠምሳኛለች፡፡ እኔን ብቻም አይደለም የጠመሰችው፡፡ ብዙዎች ኢትዮጵያውያንንም እንጂ ነው፡፡ ከወያኔ ባልተናነሰ ሁኔታ ኑሯችንን እያቃወሰችው ትገኛለች – ትልቁ ወያኔ በደጅና በቤት ውስጥ እርሷ ደግሞ በቤት ውስጥ ብቻ በተናጠልና በቡድን እየተጋገዙ ወዲያ ወዲህ ውልፊት ልንል በማይቻለን ሁኔታ ወጥረውናል፡፡ ምን እንደምናደርግም ጨንቆናአለ፡፡ ይቺ የቤት ውስጥ ወያኔ ዐይጥ ናት፡፡
ዘመኑ ለይቶለት የዐይጦችና  የወያኔዎች ሆኗል ወንድሞቼና እህቶቼ ማለትም ኢትዮጵያውያን፡፡ በኔ ቤት የተረፋት ነገር የለም፤ ለወትሮው ካልሲና ጨርቃ ጨርቅ እየለቃቀመች ነበር ወደጎሬዋ እምትወስድ፡፡ ዛሬ ግን ዘመን ተቀይሮ ባዶ ሞሰብ ሣይቀር መቆርጠም፣ አልሙኒየም የምጣድ አከንባሎ መጎርደም፣ ቁም ሣጥን መቀርጠፍ ይዛለች፤ ወያኔነት ከዚህ በላይ አለ? መጽሐፎችን አንብባ ላታነብ ነገር በጥርሶቿ መከታተፍ፣ ምግቦችን ከጉሮሮዋችን እየነጠቀች ማንከት፣ በሌሊትና አንዳንዴ ደግሞ በማንአለብኝነትና ወደር በሌለው ዕብሪት በቀንም ቤትን ተቆጣጥራ ሰላምን ማወክ የዘመናችን ትንሹዋ ወያኔ ገደቡን ያለፈ የድፍረት ተግባር ሊሆን በቅቷል – ወያኔን ተማምና መሆን አለበት መቼም፡፡ ድፍረቷ እኮ ድፍረት እንዳይመስላችሁ፡፡ ኧረረረረረ…. እንዳቃጠልሽኝ የሚያቃጥል ይዘዝብሽ፡፡ ብዙ ሰዎች በርሷ እንደተቸገሩና ዘመኑ ለርሷና ለወያኔ ዓይነቶቹ ምሥጥ መሠሪዎች የሰጠ መሆኑን ይህን ችግር የማወያያቸው ሰዎች ሁሉ ይነግሩኛል፡፡
ዛሬና አሁን በኢትዮጵያ የሰዓት አቆጣጠር ከሌሊቱ 6፡30 ገደማ ሲሆን ቀን የገዛሁትን እንትን በስምንት የጦር ግምባር አጥምጄ ወደብሶት አደባባይ መውጣቴ ነው – እንዳትሰማኝና እንዳታውቅብኝ ነው የገዛሁትን ነገር በእንትን የገለጸኩላችሁ ታዲያን – እንጂ “እዚያው በላች እዚያው ቀረች” የሚል አደገኛ መርዝ መግዛቴን ለመናገር አፍሬ እንዳይመስላችሁ፡፡ ለነገሩ ወያኔና ዐይጥ ከጠላታቸው የሚከላከሉበት ብዙ ተለዋዋጭ ዘዴ ስላላቸው በበሶ ዱዔት ያዘጋጀሁትን ግብዣ እንደሚቀበሉትና እንደማይቀበሉት አላውቅም – ውጤቱን ነገ አያለሁ፤ ዲዲቲና ወባ እንኳን ተለማምደው ጓደኛሞች መሆናቸውን ቀደም ሲል ሰምተን የለም? የሆነው ሆኖ ችግሩ ቀላል እንዳይመስላችሁ፤ ከአራት ኪሎ ቤተ መንግሥት የተለቀቁ ነው የሚመስሉት – እንደደፋርነታቸውና እንደሆዳምነታቸው፡፡ የሚምሩት ነገር እኮ የላቸውም፡፡ የሚሆንልኝ መስሎኝ “ዕቃ አትንኩብኝ፤ ቤቱ እንደሆነ ይበቃናል፡፡ ካለኝ አልፎ አልፎ ቀለብ እቆርጥላችኋለሁ – ከሌለኝ ግን ምን አደርጋለሁ? ብቻ አትተናኮሉኝ እንጂ እኔ መርዝ አላጠምድባችሁም፤ የዛሬን ኑሮ መቼም እናንተም ታውቁታላችሁ፡፡ ከመጠለቁ እግርን የሚፋጀው እሳተ መለኮቱ የቻይና ካልሲ እንኳን ባቅሙ ሠላሣና ዐርባ ብር በገባበት ወቅት እባካችሁን ተከባብረን እንኑር፡፡…” ብዬ ቃል ገብቼ በቤቴ ውስጥ የሚያደርሱትን ጉዳት ሰምቼ እንዳልሰማሁና ዐይቼም እንዳላየሁ ለብዙ ጊዜ ትቻቸው ነበር፡፡ እነሱ ግን የእንጀራ ሞሰብ አልጋችን ላይ አስቀምጠን ከባለቤቴ ጋር በየተራ እየጠበቅን እስክናድር ድረስ አሰቃዩን – የቤት ውስጥ ወያኔዎች! አሁን ባሰብኝና ቃሌን አፈረስኩ፡፡ እናም … የነሱስ አብነቱ ቀላል ነው፡፡ አለ እንጂ ወያኔ ለያዥ ለገራዥ ያስቸገረ! የወያኔስ ሰማያዊ መርዝ ካልተጨመረበት በምድራዊ መርዝ ብቻ አይጠራም፡፡ እናም ጎበዝ ግዴላችሁም ለላይኛውም በርትተን እንጩህ፡፡ የቃመ ብቻ ሣይሆን የጮኸም ተጠቀመ ሲባል ሰምቻለሁ፡፡
ወያኔና ዐይጥ አንድ ናቸው፡፡ ይሉኝታ አያውቁ፤ ፍቅር አያውቁ፤ ሀፍረትና ኅሊና እሚባል የላቸው፤ የተረገሙ ፀረ-ሕዝቦች፡፡
የሰሞኑ የወያኔ ኢቲቪ ወሬ የአባይ የህዳሴ ግድብ ብቻ ሆኗል፡፡ ነገሩ “አንድ ያላት እንቅልፍ የላት” ዓይነት ነው፡፡ በሌሎች ሀገራት በየአሥር ኪሎ ሜትሩ የሚገኝ ግድብ ኢትዮጵያ ውስጥ ብርቅ ሆኖ ጆሯችን እስኪደነቁርና እጅ እጅ እስኪለን ድረስ አባይን እየተጋትን ነው፡፡ ይህ ግድብ ከኢኮኖሚያዊ ጠቀሜታው ይልቅ ፖለቲካዊ ፋይዳው እንደሚያመዝን ቀድሞውንም የታወቀ ነው፡፡ ፈረንጆቹ አንድን ነገር “politicized” ሆኗል ሲሉ ያ እንዲያ ሆነ የሚሉት ነገር በፊት ለፊት ከቆመለትና ከሚወራለት ዓላማ ውጪ ለሌላ ጉዳይ ውሏል ማለታቸው ነው፡፡ የወያኔ የህዳሴ ግድብም ወያኔ እንደሚለው ለሀገሪቱ የሚሰጠው የተለዬ ጥቅም ኖሮ ሣይሆን ሕዝብን ለማዘናጊያነትና ሊጠቀስም ሣይጠቀስ ሊዘለልም ለሚችል የተለዬ ፖለቲካዊ ፍጆታ መሆኑን እናውቃለን፡፡ አለበለዚያ የስድስት ሺህ ሜጋ ዋት ኮረንቲ ከቁም ነገር ተጥፎ እስከዚህን ድረስ 24 ሰዓት ከበሮ የሚያስደልቅና ይቀምሰውና ይልሰው ያጣን ድሃ ሕዝብ ያለ ርህራሄ የሚያዘርፍ ሆኖ አይደለም፡፡ “አንቺ ቁም ነገርሽ የጎመን ወጥሽ” እንደምንል ወያኔም በዚህች ድልድይ ማነው ግድብ ዕንቅልፍ አጥቶ እኛንም እንደሱ አትተኙብኝ እያለን ነው፡፡
በማለፊያ ክርስቶሳዊ አባባል አንድ የአደባባይ ምሥጢር እንድናገር መልካም ፈቃዳችሁ ይሁንልኝ፤ “እውነት እውነት እላችኋለሁ” አባይ ተገድቦ ቢያልቅ በኔም ሆነ በሌሎች ወገኖቼ ሕይወት ላይ አንዳችም ቁሣዊም ሆነ መንፈሣዊ ለውጥ አያመጣም፡፡ በምንም ዓይነት መንገድ፡፡ እርግጥ ነው – የተሟላ የቴክኒክ ዕውቀት ያለው የሰው ኃይል ካለና እንዳሁኑ በተጭበረበረ የግዢ ሂደት አማካይነት ፎርጅድና የአገልግሎት ዘመኑን ጨርሶ የተጣለ የማቴሪያል አቅርቦት ከተወገደ እንዲሁም የሕዝብ ብዛት በቁጥጥር ሥር ከዋለ ምናልባት ልክ እንዳሁኑ በመብራት ዕጦት ዳፍንት ውስጥ ላንገባ እንችል ይሆናል፡፡ እንዲያም ሆኖ ግን አሁንም ልክ እንዳሁኑ ሁሉ ለማይጠረቃው የመንግሥት ባለሥልጣናት ኪስ ማደለቢያና ለአነስተኛ የሀገር ገቢ ሲባል ቤት ያለው ሰው ሳይጠግብ ለዬጎረቤት ሀገር ኮረንቲ መቸብቸቡ ከቀጠለ የዚያኔም ቢሆን – አባይም ተገድቦ ማለት ነው – የመብራት ፈረቃው ላይቀርልን ይችላል፡፡ እናም በአባይ ግድብ ሳቢያ ከወያኔ ጋ ድብን ያለ ፍቅር የገባችሁ ወገኖች እውነቱን ከወዲሁ እንድትረዱት ላሳስብ እወዳለሁ፡፡ ወጥመድ ውስጥ ዘው ብላችሁ አትግቡ፡፡ ሀገር ካላችሁ ሁሉም አለና፡፡
ኢትዮጵያዊ መንግሥት ቢኖረን አንድ አይደለም አሥርና ከዚያም በላይ ትላልቅ ግድቦች ሊኖሩን የመቻላቸው ዕድል ሰፊ ነው፡፡ “ልማታዊ መንግሥታችን፤ ባለራዕዩና አባይን የደፈረ ጠቅላይ ሰይጣናችን ማነው ሚኒስትራችን” እያላችሁ ሟቹን ወያኔ የምታንቆለጳጵሱ ጥቅመኞች ሁሉ ዐይናችሁን ወደጭቁኑ የኢትዮጵያ ሕዝብ አዙሩና እውነቱን ለመረዳት ሞክሩ፡፡ ወያኔ ከኢትዮጵያ ታሪክ አንጻር ዕድሜው የጤዛ ያህል ነው፡፡ በማታለልና በማጭበርበር 23 ዓመታትን መኖሩም የሚገርም ነው፡፡ ለዚህ ቆይታው ግን ተጠያቂው ወያኔ ብቻ ሣይሆን በተንሸዋረረ ልማት ስም አንጀታቸው ለወያኔ የሚንቦጫቦጭ አድር ባዮችና እበላ ባይ ሆዳሞች የሚያደርጉለት ሁለገብ እገዛም ጭምር ነው፡፡ የኛም አንድ አለመሆንና በሃሳብ መለያየት ለወያኔ ዕድሜ መርዘም የድርሻውን አበርክቷል፡፡ ሌላ ሌላውን ምክንያት እናንተም ታውቃላችሁ፡፡
ወያኔ የአባይን ግድብ ብቻ ሣይሆን ሌሎች በሃያና ሠላሣ የሚቆጠሩ ታላላቅ ግድቦችን መሥራት ይችላል፡፡ እንዴት? በየተራ እንይ፡፡
ለአንድ ጡረተኛ ፕሬዚደንት መኖሪያ ቤት የተከራዩት በወር ስንት ብር ነው? (ልብ አድርግ – ከ400 ሺ ብር በላይ ነው!) በየወሩ የተመደበው ሌላ ሌላ ጥቅማ ጥቅምስ ስንት ነው ? ይህ በራሱ ቢደማመር በዓመትና በሁለት ዓመት ጊዜ ውስጥ – የሙስና መርዝ ካልተጠናወተው በቀር- አንድ መለስተኛ ግድብ ይሠራል፡፡ ለአንዲት ድሃ ሀገር ተጧሪ “ፕሬዚደንት” – ለዚያውም ፈርም የሚባልን ወያኔያዊ ደብዳቤ ለሚፈርም ከዘበኛ ያነሰ ሥልጣን ለነበረው ሰው – ይህን ሁሉ ወጪ መመደብ በስተጀርባው ሌላ ቤተኛን በእግረ መንገድ ለመጥቀም የተሸረበ ሤራ አለ ማለት ነው እንጂ አሳማኝነቱና ምክንያታዊነቱ በፍጹም አይተየኝም – “ራቁቱን ለተወለደ … “ ምን አነሰው ነበር እንዴ የሚባል? ይህ ነገር ራስን ያለማወቅ ችግር ወይም ስለሀገር ያለማሰብና በእልህ የሀገርን ሀብት የማባከን አዝማሚያ ይመስለኛል፡፡ እንደኢቲቪ የቁጭ በሉ አገላለጽ ሣይሆን እንደተጨባጩ እውነታ ከአጠቃላዩ ሕዝብ ከ85 በመቶ በላይ በባዶ እግሩ በሚሄድባት የድሃ ገበሬዎች ሀገር ውስጥ አንድን ተጧሪ ባለሥልጣን እንዲህ አንቀባርሮ የሚይዝ መንግሥት ደግሞ አንድ ግድብ ለመገንባት በሚል ሰበብ ከኔ ቢጤው ተራ ዜጋ – የወር ደመወዙ ከልመና ካላወጣው፣ እየሠራ ከሚደኸይና የኗሪ አኗኗሪ ከሆነ ምንዱብ ሠራተኛ መዋጮ መጠየቅ አልነበረበትም – አሣፋሪ ነው፡፡ እኔ እንዴት እንደምኖር አውቃለሁ፡፡ እንኳንስ ከደመወዜ ተቆርጦ ይቅርና አሁን የሚከፈለኝ ደመወዝ ተብዬ ዕጥፍ ድርብ ቢከፈለኝ እንኳን የኑሮውን ክብደት ሊያቃልልኝ አይችልም፤ የኔ ቢጤዎች የምንኖረው አንዷን ኪሎ ቅቤ በ“አጠቃቀስኩሽ” ሥልት ለዓመት እንደተጠቀመችባት ብልህ ሴት ዓይነት የኑሮን ጨውና ቅመም በብልሃት ‹አጠቃቀስኩሽ› እያልን ነው፡፡ ይህን የአባይ መዋጮ በተመለከተ የወያኔ መንግሥት ደደብነትና አስተዋይነትን ማጣት በእጅጉ ይገርመኛል – ለነገሩ ደደብነትና ወያኔ ለካንስ ሞክሼዎች ናቸውና፡፡ ስንቶችን እያዘባነነ የሚያኖር መንግሥት ጦሙን ከሚያድር ዜጋ በግድ የወር ደመወዙን ሲቆርጥ በዚህ መንግሥት ባለሥልጣናት ጭንቅላት ውስጥ የሚገኘው ነጭ ጭቃ ምን እንደሆነ ወይም የምን እንደሆነ ለማወቅ በከንቱ የምንዳክር አንጠፋም – በበኩሌ በራስ ቅላቸው ውስጥ ምን ተሸክመው እንደሚዞሩ ለመረዳት ሞክሬ ሲሰለቸኝ ደክሞኝ ትቸዋለሁ – እንዲያው ግን አምባርጭቃ ይሆን እንዴ? ሲገርሙ!
ወያኔዎች ኢንሳ በሚሉት የስለላ ድርጅታቸው ኢሳትን በዋናነት ጨምሮ የተቃዋሚ ሚዲያዎችን ሲቻላቸው ከዓለም ለማጥፋት ያ ባይቻል ደግሞ ወደ ሀገር ገብተው ሕዝብን በማንቃት የወያኔ ቅሌትና ውርደት እንዲሁም ከብረት የጠነከረ ፈርዖናዊና ናቡከደነፆራዊ የግፍ አገዛዛቸው ሕዝብ ላይ በዬጊዜው የሚፈጥረው ጭቆናና ግፍና በደል እንዳይገለጥባቸው በማሰብ በየወሩ የሚከሰክሱት የሀገር ሀብት አንድ አባይን ብቻ ሳይሆን አሥር ባሮና አሥር አዋሽን ያስገድባል፡፡ በዚያ ረገድ እኛን ብቻ ሣይሆን ሌላውን ዓለምም በሚያስደምም ሁኔታ እንደጉድ ነው ገንዘባችንን ለኛው መጨቆኛ የሚመዠርጡት፡፡ ይህን የማናውቅ እየመሰላቸው ከሆነ ተሞኝተዋል፡፡ በብዙ ሚሊዮን የሚቆጠር ዶላር ለትርኪ ምርኪ የሚዲያ ማፈኛ ቁሣቁስና የውጪ ኤክስፐርቶች እንዲሁም የስለላ ቫይረስ ለመግዛት ሜዳ ላይ ከሚበትኑት ለሀገር ዕድገት ቢያውሉት ከጉራማይሌያዊ የልመና ባህላቸው በወጡ ነበር፡፡ እንደነሱ የገንዘብ አወጣጥ እኮ ኢትዮጵያ እጅግ ሀብታም ናት፡፡ እነሱ ገንዘብን በሚሊዮንና በቢሊዮን መዝረጥ የሚያደርጉት የነሱን ሥልጣን ለማስጠበቅ መሆኑ ከፋ እንጂ እንዳመነዛዘራቸው ለጭቁኑ ሕዝብ ቢሆን ኖሮ ረሀብና እርዛት ከሀገራችን ጠቅልለው ከወጡ በትንሹ 23 ዓመታትን ባስቆጠሩ ነበር፡፡ ለደኅንነት የተቃዋሚ ክትትልና የፀረ-ስለላ ስለላ አባላት በገፍ የሚወጣው መዝገብ የማያውቀው ወጪ፣ በወያኔ አገዛዝ የፊጥኝ ከታሰረው ምሥኪን ሕዝብ ተቀምቶ የወያኔን ወንበር ለመጠበቅ ለተሠማራው የሀገር መከላከያ ሠራዊት ተብዬ የሚገፈገፈው ገንዘብ፤ ለመሣሪያ ግዢና በግዢው ሰበብ በሙስና ወደግል ካዝና የሚዶለው ቁጥር የማይገልጸው እጅግ ብዙ ገንዘብ፣ በመከላከያና በደኅንነት እንዲሁም በመሰል የፀጥታ ተቋማት ለሚርመሰመሰው ጆሮ ጠቢና አፋዳሽ ሁላ ካለበቂ ሥራ እንደ ቅጠል የሚረግፈው የሀገር ገንዘብ፣ ካበቂ ጥናትና ካለተጨባጭ ሀገራዊ ፋይዳ በዬጊዜው ለሚቋቋሙ አዳዲስ መሥሪያ ቤቶችና አደረጃጀቶች የሚወጣው ገንዘብ፣ ውጤቱ አስቀድሞ ለሚታወቅ የማይረባ ምርጫ የሚከሰከሰው ብዙ ሚሊዮን ገንዘብ፣ ለአብዮታቸው ጥበቃ ሲባል ለዬግልገል ካድሬው የሚዘራው ብር፣ሕወሓትን በዋናነት ይዞ ለዬአጋር ድርጅት ተብዎች ዓመታዊ የምሥረታ በዓላት ለፈንጠዝያና ለቸበርቻቻ የሚወጣው ገንዘብ፣ በሀገር ውስጥም ከሀገር ውጪም በባለሥልጣናት የሚመዘበረው የሀገር ሀብትና ንብረት … ሁሉ ቢደማመር ሀገራዊ ልመና ሱስ ላልሆነበት የመንግሥት መዋቅር ያለ አንዳች ምፅዋትና ቡገታ  አንድ አይደለም ከመቶ በላይ ግድብና ሌላም የልማት ዕቅድ ያሠራል፡፡ ዓለም አቀፍ ደረጃውን የጠበቀ አንድ ብሔራዊ እስቴዲየም ለማሠራት ወገቤን የሚል መንግሥት ያላት ኢትዮጵያ 200 ታንኮችንና በአሥራዎች የሚቆጠሩ የጦር አውሮፕላኖችን በአንዴ ሲገዛ በሰበቡም ከፍ ሲል ለመግለጽ እንደተሞከረው በመቶ ሚሊዮን የሚገመት ገንዘብ በየማይማን የጦር “ጄኔራሎች” የግል ካዝና ሲገባ ስናይ “የነዚህ ሰዎች ዜግነት ምን ይሆን? በውነቱ ኢትዮጵያዊነቱ ይቅርና ጤናማነታቸው የማያጠራጥር ሰዎችስ ናቸው ወይ?” ብለን መጨነቃችን አይቀርም፡፡ ሰው እኮ አንድ ዓመት ይዘርፋል፤ አንድ ዓመት ይዋሻል፤ አንድ ዓመት ይሰርቃል፤ አንድ ዓመት ይሞስናል፤ አንድ ዓመት ይዘሙታል፣ አንድ ዓመት ያጭበረብራል፣ አንድ ዓመት … አዎ፣ በወረት ለተወሰነ ጊዜ ከመስመር መሠወር/መጥፋት ያለ ነው፡ አንድ ሰው የሀብት ፍቅር ካራዠው  መቼስ ምን ይደረጋል በሚፈልገው ነገር እስኪጠረቃ ድረስ ወይም በቃኝን እስያውቅ ድረስ ለተወሰነ ጊዜ መጥፎ ነገርን እያደረገ ይቆያል፤ ሰው ከሆነ ግና በሕይወት ውጣ ውረድ መማር አለበት፡፡ የተሸከመው አንጎል ጭቃ ሣይሆን ዛሬን ከነገና ትናንትን ከትናንት በስቲያ እያመዛዘነ ገምቢ ግንዛቤን ሊያስጨብጠው የሚችል ትልቅ መለኮታዊ ስጦታ ስለሆነ በሕይወት ፈተና ተሸንፎ ከተዘፈቀበት ሰውነትን ከሚያሳንስና ኅሊናን ከሚያጎድፍ ወደእንስሳነት ደረጃም ከሚያወርድ አዘቅት ለመውጣት መሞከር አለበት – ከወያኔ እንዲያውም ብዙ እንስሳት የተሻሉ “ሞራላዊ” ፍጡራን ናቸው፡፡ ዕድሜ ልኩን በክፋትና በመጥፎ ድርጊቶች ተበክሎና በዚያው ቆርቦ መኖር ለታዛቢም ይሰቀጥጣል፡፡ ወያኔዎች ከጧት እስከማታ ቢያጋፍሩ በቃኝን የማያውቁና በቂምና በበቀል የታጀሉ ትንግርተኛ ፍጡራን ናቸው – “የሞኝ ዘፈን ሁልጊዜ አበባዬ” እንዳትሉኝ እንጂ ለምሳሌ በዐሥራዎቹ ዕድሜ ሳሉ የጀመራቸው ፀረ-ኢትዮጵያና ፀረ-አማራ ጥላቻ አሁን ድረስ በስተርጅናም አብሮ ዘልቆ እነስብሃትንና ሣሞራን ምን ያህል እያሰቃያቸው እንደሆነ የምናውቀው ነው፡፡ ይሄ ታዲያ መረገም አይደለም ትላላችሁ? ብቻ ይህንን የምለውን ሁሉ የማናውቅና ሁኔታዎች ሲያመቹና ጊዜው ሲደርስ የማንጠይቅ ከመሰላቸው አሁንም ተሞኝተዋል፡፡
ካሉት ጥቂት መጻሕፍት ውጪ ምንም ምድራዊ ሀብትና ንብረት እንዳልነበረው ካላንዳች ሀፍረት በራሱ አንደበት ሲናገር የነበረውና የባሕርይ አምሳያው ወላጅ አባቱም “ [በድህነቱ ምክንያት] የአምስት ብርና የአሥር ብር ኖቶችን እንኳን መለየት አይችልም” በማለት የወፍ ምሥክሯ ድምቢጥ ዓይነት የዋቢነት ቃሉን የሰጠለት መለስ ዜናዊ 3.7 ቢሊዮን ዶላር በስሙ ተመዝግቦ መገኘቱን አንድ ዓለም አቀፍ ተቋም በቅርቡ አጋልጧል፡፡ ከዚያም ቀደም ብሎ በዚሁ ብዔል ዘቡል የበኩር ልጅ በሰምሃል መለስ ስም ከአምስት ቢሊዮን ዶላር (ሚሊዮን አይደለም!) – ልድገመው ከአምስት ቢሊዮን ዶላር በላይ ተቀማጭ ገንዘብ እንደተገኘ ተዘግቧል፡፡ በአባትና ልጅ ስም የተገኘው ገንዘብ ብቻውን ከሁለት በላይ የአባይን መሰል ግድቦችን ያስገነባል፡፡ ታዲያ የምን ቧጋችነትና ማራሪነት ነው? የምንስ ማስመሰል ነው? የቆሎ ተማሪ የሀብታምም ልጅ ቢሆን ቧግቶ መብላቱ፣ ለምኖ ካልበላ ትምህርቱ ስለማይገባው ነው የሚል አፈ ታሪክ ስላለ ነው፡፡ ኢትዮጵያስ ካልቧገተችና ድሃ ልጆቿን ራቁታቸውን ካላስቀረች ልትለማ አትችልም ማለት ነው? ምን ዓይነት ዕንቆቅልሽ ነው? ኢትዮጵያየን ከ30 ዓመታት በላይ በሙያዬ ያገለገልኳት ሰውዬ የእኔ ልጅ በወያኔ ወለድ የኑሮ ውድነት ሳቢያ በቀን አንዴም መመገብ እያቃተው ከኔ ከአባቱ መናኛ የወር ደሞዝ ለአባይ አዋጣ ስባል ሰምሃል መለስ ደግሞ የኢትዮጵያን አንጡራ ሀብት በሎንዶን ታላላቅ ሆቴሎች እየተዘዋወረች ከሎንዶናውያንና ወያኔያውያን ወሮበሎች ጋር በዬምሽት ክበባቱ ጢምቢራዋ እስኪዞር እየጠጣች ስታስታውክበትና አለመላው ስትዘባነንበት ሲታይ ምን ዓይነት ሀገራዊ ስዕል ነው የምናስተውለው? የዚህን አስገራሚ እውነት ተፈጥሯዊ ፍትህስ መቼ ነው የምናየው? የሆነ የሚያበሳጭ ሀገራዊ ምስል በአእምሯችሁ ብልጭ አላለባችሁም? ስንቱ ባለሥልጣንና የጦር አበጋዝ ነው ከነየልጁ በዚህ መልክ በሀገር ሀብት እየተጫወተ የሚገኘው? ታዲያ ይሄ ሁሉ አላግባብ በሙስናና በዝርፊያ የሚባክን ሀብት ስንት ግድብ፣ ስንት የባቡር መንገድ፣ ስንት አውራ ጎዳና፣ ስንት ሆስፒታል፣ ስንት ትምህርት ቤት፣ ስንት ኮሌጅና ዩኒቨርስቲ (ያልተማሩ መምህራን የታጨቁበት ባዶና ከርክክብ ሥነ ሥርዓቱ ቀድሞ የሚሰነጣጠቅ – ጥቂት ቆይቶም የሚፈራርስ ሕንፃ ሣይሆን በሁሉም ረገድ ደረጃውን የጠበቀ ማለቴ እንደሆነ ተረዱልኝ)፣ ስንት የበጎ አድራት ተቋም፣ ስንት ክሊኒክና የጤና ኬላ፣ ስንትና ስንት የመኖሪያ ቤቶችና ሕንፃዎች አይሠራም ነበርን? ይህ ሁሉ ገንዘብ ቅን ተገዢ ያደረገንን ማይምነት ከኢትዮጵያ ምድር ጠራርጎ አያወጣውም ነበርን? ይህንንም ሕዝቡ አያውቅብንም ዘመኑ ሲደርስም አይጠይቀንም ብለው ከሆነ በርግጥም ተጃጅለዋል፡፡ ለነገሩ ሆድ አለልክ ሲጠግብ እኮ ጭንቅላት ፉዞ ይሆናል አሉ፡፡
በቀዳማዊ ኃ/ሥ ጊዜ ስንት ብድርና ዕርዳታ ወደ ሀገር ገባ? በደርጉስ? በአሁኑ የወያኔ ጉጅሌስ? በዕርዳታና በብድር መልክ ከሚገባው ገንዘብ ምን ያህሉ ነው በትክክል በታለመበት ሥራ ላይ የሚውለው? አሁን የሚባለውን እንስማ ካልን ወደ ሀገር ከሚገባው የብድርም ሆነ የዕርዳታ ገንዘብ ውስጥ ሩብ ያህሉ እንኳን የሀገር ጥቅም ላይ አይውልም፡፡ ይመዘበራል፤ የግለሰቦችን ኪስ ያሞቃል፡፡ ለሀገር የሚቆረቆር ባለሥልጣንም ሆነ ተቆጣጣሪ ለጋሽና አበዳሪ ሀገር ባለመኖሩ በኢትዮጵያ ስም የተቃፈፈው የዕርዳታም ይሁን የብድር ገንዘብ እሳት ውስጥ የገባ ቅቤ ሆኖ ይቀራል፡፡ በመሠረቱ ሙሰኝነት ዱሮም ነበር – ግን እንደዛሬው ዐይኑን ያፈጠጠና ግዘፍ ነስቶ በአደባባይ ሲራመድ የሚታይ አልነበረም፤ ይሉኝታ የሚባል የኅሊና ዳኛ በመጠኑም ቢሆን  ነበር፡፡ ዛሬ ግን ደመወዙን የምናውቀው አነስተኛ ባለሥልጣንና የሥራ ኃላፊ ሁሉ የወር ገቢው ለሦስት ቀንም እንደማይበቃው እየተረዳን ወር ከወር ጮማ ሲቆርጥና ዊስኪ ሲጨልጥ ነው የሚገኘው – የሚመነዝረው ረብጣ ብርማ አይነሣ፡፡ ከየት አመጣው? ባለፈው ከአንድ መጽሔት እንዳነበብኩት እርሱና ሚስቱ ተኝተው ባደረጉት ነገር ምክንያት ፈጣሪ የሰጣቸውን ሦስተኛ ልጅ ሚስቱ ብቻ እንደሰጠችው በመቁጠር ትልቅ የፌሽታ ድግስ በቤቱ ውስጥ አድርጎ የ2.5 ሚሊዮን ብር መኪና ቁልፍ ለምሽቱ የሸለመው ወያኔ ሀብታም ያን የሚጫወትበትን ገንዘብ ከየት አባቱ እንዳመጣው ብንጠይቅ መልስ የሚሰጠን የለም፡፡ እነዚህን መሰል የወያኔ ንፋስ ወለድ ሀብታሞች በከንቱ የሚቀዳድዱትን ብር ለቁም ነገር ቢያውሉት አንድ ቀርቶ አምስት ስድስት ግድብ አይሠሩም ነበር ወይ? የኔ ቢጤን የሥጋን ምግብ ተውትና በቅጡ የተሠራች ኩርጥ ያለች የአተር ወጥ እንኳን ካዬ ወራት ያስቆጠረ መንዳካ ድሃ ያለችውን መናኛ ሣንቲም በግድ ከሚቀሙ እነዚህንና አላሙዲንን የመሳሰሉ ደደብ ሀብታሞችንና ቱጃር የባለሥልጣን ነቀዞችን  ቢያስተባብሩ አባይን የሚያስንቅ ስንትና ስንት ግንባታ ሊሠሩ አይችሉም ነበር ወይ? እነሱ እንደልባቸው ለሚምነሸነሹባት ሀገር እኔ ምን ቤት ነኝና የሌለኝን ልስጥ? ይህኛው ግፍ ከሁሉም ግፎች አይበልጥምን? አሁን ኢትዮጵያ በርግጥ የማን ናት? ከትንሽ ጣት ምን ተቆርጦ ይወሰዳል? እነዚህ የመንግሥት ሰዎች ግፍ ማለት ምን ማለት እንደሆነ አያውቁም ማለት ነው? ጤፍ በኩንታል ከብር 1600 በላይ በሆነበትና የአንድ ወዛደር ወርሃዊ ደሞዝ ከ400 ባልበለጠበት ሁኔታ ምኑን ነው ከምኑ የሚቆርጡት? ምነው እስከዚህን አቅል አሳጣቸው? …
አባይን ተገድቦ ማየት ማንም አይጠላም፡፡ “አሻራውን አባይ ላይ የማያስቀምጥ ኢትዮጵያዊ አይደለም” የሚሉት ፈሊጥ ደግሞ የእውነት መሠረት የሌለውና ጠርዝ የለቀቀ የግድብ ‹ፖሊቲሳይዜሽን› ነው፡፡ ከእውነቱ ፍጹም የራቀ የማጨናበሪያ ፕሮፓጋንዳ ነው፡፡ መቼም ቢሆን አባይ ቢገድብ የሚጠላ ኢትዮጵያዊ ሊኖር አይችልም – መንግሥት ቀርቶ የመንግሥት ጳጳስ ቢያወግዘንም የአባይን መገደብ ሣይሆን የምንቃወመው ጠንጋራ አካሄዱንና የወያኔን ገደብ የለሽ ቱልቱላ ነው፡፡ ለምሳሌ ከፍ ሲል እንደተገለጸው ግድቡ ለሆነ ችግር ማስተንፈሻ ድንገት ጣልቃ ገባ እንጂ ሕዝብ አልመከረበትም፤ የሥራው ኮንትራት አሰጣጥም ብዙ ችግር እንዳለበት፣ ዕቃ አቀራረብና ሌላ ሌላ ሂደት ላይም ወያኔያውያን ባለጠጎችና ሞሰቦን የመሳሰሉ የወያኔው መርዝአቀባይ  ደንገጡር ድርጅቶች ይበልጥ እንዲከብሩበት ተደርጎ እየተካሄደ መሆኑ ከታማኝ የዜና ምንጮች ሰምተናል፤ ታዲያስ? ለምን እንታለላለን? እንጂ በመሠረቱማ ወያኔን መጥላትና የአባይ መገደብ የግድ የሆነ ግንኙነት ሊኖራቸው አይችልም፡፡ ችግሩ ተደጋግሞ እንደተነገረው ዘረኝነትን በዋነኛነት ጨምሮ ከአባይ በፊት መገደብ ያለባቸው ብዙ ወያኔያዊ የመጥፎ አገዛዝ ጎርፎች መኖራቸው ነው፡፡ እኔ ለምሳሌ ለአባይ ድምቡሎ አላዋጣም፤ ፍላጎቴ ራሱ ዜሮ ነው፡፡ የኔ ሰዎች የያዙት ስለማይመስለኝና ስላልሆኑም እንዲያውም ስለአባይ ወሬው ራሱ ባይነሳብኝ እመርጣለሁ – ወያኔን ብሎ ለኢትዮጵያ አሳቢ ይታያችሁ! አንድስ አንድስ እሚያህል መሬት እየገነደሰ ለባዕድ የሚሸጥ ወያኔ እንዴት ለሀገር ተቆርቁሮ ይህን ታላቅ ፕሮጀክት ሊጀምር ይችላል? እደግመዋለሁ – ግድቡን ግን ጠልቼ አይደለም፡፡ በሌላም በኩል ካየነው እኔን እየራበኝ፣ ኑሮየ የጎሪጥ እያየኝ ነጋ ጠባ እያላገጠብኝ ከኔ ተርፎ ለአባይ ማለት ከጅብ ተርፎ ለውሻ እንደማለት ስለሆነ ላዋጣ ብዬ ልግደርደር ብል እንኳን እንደስድብ ተቆጥሮ “ተው አንተ፣ አቅምህን ዕወቅ፣ ዕረፍ እንጂ፣ አንተን አይመለከትም፤ ምን አለህና! “ ነው ልባል እሚገባ፡፡ ዐይን አይቶ ልብ ይፈርዳል ይባላል፡፡ በቀን አንዴ መቅመስ ያቃተው ሰው፣ የነተበ ሸሚዝና አቧራ የቃመ የሸራ ይሁን የላስቲክ ጫማ ማድረጉ የማይታወቅ ሰው፣ ወር በገባ በአምስተኛውና ስድሰተኛው ቀን ሁሉም የቤት አስቤዛው ተመካክሮ በአንዴ የሚያልቅበትና ኑሮውን በብድርና እልፍ ሲልም በውጭ ሀገራት በሚኖሩ ዘመዶቹ መጠነኛ የበጀት ድጋፍ ተሰናባቹን ወር ከአዲሱ ወር ለማገጣጠም የሚፍጨረጨር ሰው፣ ልብሱ እላዩ ላይ አልቆ – ከአንሶላ ጋር ተቆራርጦ – ከሶፋና አዳዲስ የቤት ዕቃዎች ግዢና ጥገና ጋር እስከወዲያኛው ተፋትቶ፣ … በደመ ነፍስ ብቻ (ጌታ) ናስቲለው የሚኖር ሰው የግድብ ወሬ አይገባውም – እንዲገባው መጠበቅ ራሱ ቂልነትና ለተቀማጭ ሰማይ ቅርቡን የሚያስተርት ፌዝና ቀልድ ነገር ይመስለኛል፡፡ ይህ ግድብና የግድብ ቱሪናፋ የቅንጦት ወሬና እውነትም ለቡትለካ እንዲያመች ለወያኔ ዕድሜ ማራዘሚያነት ተለክቶ የተሰፋ መለስ ዜናዊያዊ የማጭበርበሪያ ካባ ነው – ካባ አሰፋፍ እንደሱ እንደመለስ የሚሆን ደግሞ በዓለም የለም፤ ማገብት፣ ተሓት፣ ተሓህት፣ ሕወሓት፣ማሌሊት፣ ኢማሌኃ፣ ኢዴመአን፣ ኢሕዲን፣ ብኣዴን፣ ደኢሕዴግ፣ ኦሕዴድ፣ ብዙ ንቅናቄዎች፣ ብዙ ዴዶች … ስልቻ ቀልቀሎ፣ ቀልቀሎ ስልቻ …ይህ ሁሉ ካባ ወያኔ ላይ የሚጠለቅና በአብዛኛው በኢንጂኔር መለስ ዜናዊ የተሰፋ ነውና ነበርም – አማርኛውም ጠፋኝ ልጄ፡፡ በዚህ በአባይ ግድብ የውሸት ካባ ደግሞ ኢትዮጵያዊነት አይለካም – መለካት ካለበት እንግዲያውስ ይህን ወያኔያዊ ቅራቅንቦና የነፃነት ትግልን የማደናቀፊያ ሥልት ተከትሎ ራሱ በመወናበድ ሌሎችን የሚያወናብድ ቀፎ ዜጋ ነው – በቃ ቀፎ፡፡ አናቱን በመዶሻ እየወቀጡት እግሩን ሲያኩት መታለሉ የማይገባው ዝንጉ ካለ ቀፎ ብቻ ሣይሆን ድንጋይ ራስም ሆዳምም ደንቆሮም ነው፡፡ ለእኔ ሀገርና መሪ ሲኖረኝ ሁሉም ይደርሳል፡፡ ዝንጀሮ “ቀድሞ የመቀመጫየን” እንዳለችው  ሀገራዊ ነፃነት ሣይኖረኝ አንድ ሺህ ግድብና አንድ ሌላ ሺህ ባቡር ከነሃዲዱ ቢኖረኝ ምንም አይፈይድልኝም፡፡ ጣሊያን በአምስት ዓመት የሠራቸው የልማት አውታሮች ጥቅማቸው እንዳለ ሆኖ ቅኝ ገዢውን ግን ወደ መልአክነት አልለወጡትም፤ በአፓርታይድ ዘመን ደቡብ አፍሪካ ውስጥ የታዩና ሀገሪቷን ከበለጸጉ የዓለም ሀገሮች ተርታ ያስሰለፉ የዕድገትና ልማት እመርታዎች የአፓርታይድን ሥርዓት ከመገርሰስ ካለማዳናቸውም በላይ ሥርዓቱን ከዓለም አቀፍ ውግዘትና መነጠል አውጥተው ለጽድቅና ለበረከት አላበቁትም፡፡ ኦ!ኦ! አሁንስ በቃኝ እባክህን፡፡ ዕንቅልፌ እያዳፋኝ ነው፡፡ እነዚያ እርጉም ትናንሽ ወያኔዎችም ግብዣየን መቀበል አለመቀበላቸውን ላረጋግጥና ጋደም ልበል፡፡ ከቅብዥር ነፃ የሆነ እውነተኛ ዕንቅልፍ ባይኖርም ዐረፍ ማለቱ አይከፋም፡፡ እነዚህ ነቀዝ ወያኔዎች እያሉ በቅጡ መተኛትም እኮ ቀረ፡፡ 11፡30 ሌሊት (ንጋት?)፡፡ 24/7/2006ዓ.ም

Tuesday, April 1, 2014

ዶክተር ዳኛቸው አሰፋን ከዩኒቨርስቲ ለማባረር የተሰራው ሴራ ከሸፈ::


ኑሯቸውን ከመሰረቱባት አሜሪካ ጓዛቸውን ጠቅልለው አገራቸው በ1997 ግድም የገቡት ዶክተር ዳኛቸው አሰፋ ላለፉት ሰባት አመታት በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የፍልስፍና መምህር በመሆን ሲያገለግሉ ቆይተዋል፡፡
ዶክተሩ በአደባባይ ሀሳባቸውን መግለጽ በመጀመራቸውና ተማሪዎቻቸውም በሀሳብ ላይ ተመስርተው ሀሳባቸውን እንዲገልጹ ማደፋፈር መጀመራቸው በገዢው ፓርቲ ሰዎች በስጋት እንዲታዩ አድርጓቸዋል፡፡
ዳኛቸው የቀድሞዋ የትምህርት ሚኒስትር ገነት ዘውዴ የቅርብ ዘመድ በመሆናቸውም‹‹የራሳችን ሰው እንዴት በአደባባይ ይተቸናል››የሚል ክፉ መንፈስ የተጠናወታቸው ለኢህአዴግ ቅርበት አለን የሚሉ ካድሬዎች ዶክተሩን ከዩኒቨርስቲው ለማስወጣት የተለያዩ ሴራዎችን በመጎንጎን ላይ ታች ሲሉ ቆይተዋል፡፡
የፍልስፍና ምሁሩ የአመት እረፍታቸውን አጠናቅቀው በቅርቡ ወደ ስራ ገበታቸው እንደተመለሱ ዩኒቨርስቲው የቅጥር ኮንትራታቸውን ለማደስ መዝገብ ቤት የሚገኘውን መረጃቸውን ፈልጎ በማጣቱ ኮንትራታቸውን ለማደስ መቸገሩን ያረዳቸዋል፡፡
አስተማሪነትን ለእንጀራ የማይፈልጉት ዳኛቸው በሰሙት ነገር ሳይደናገጡ በየመዝገብ ቤቱ መረጃቸውን ማፈላለጉን ይያያዙታል፡፡አራት መዝገብ ቤት የጠፋው ፋይል ዛሬ ከመዝገብ ቤት ውጪ በአንድ ሰው አማካኝነት በመገኘቱም የመምህሩ የቅጥር ኮንትራት እንዲታደስ ትዕዛዝ ተላልፏል፡፡
ለዳኛቸው ቅርበት ያላቸው ምንጮቼ እንደነገሩኝ ከሆነ‹‹ዛሬ የድል ቀኔ ነው››በማለት ዶክተሩ ለወዳጆቻቸው ተናግረዋል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የሰላማዊ ሰልፍና ስብሰባ ማሳወቂያ ክፍል ህገ ወጥ ደብዳቤ ለአንድነት ጻፈ

ምላሹን አልቀበልም በማለቱም በፖስታ ቤት ተልኮለታል ህገ መንግስቱ እውቅና የቸረው ሰላማዊ ሰልፍ የማድረግ መብት ሳይሸራረፍ መተግበሩን እንዲከታተል በአዋጅ የተቋቋመው የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የሰላማዊ ሰልፍና ስብሰባ ማሳወቂያ ክፍል አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ መጋቢት 28/2006 ዓ.ም መነሻውን ፓርቲው ከሚገኝበት ቀበና በማድረግ በአራት ኪሎ አደባባይ በመዞር ጠቅላይ ሚኒስትሩ ጽ/ቤት ፊት ለፊት የሚጠናቀቅ ሰላማዊ ሰልፍ እንደሚያደርግ በመግለጽ ለኦፊሰሩ ደብዳቤ አስገብቶ የነበረ ቢሆንም መስተዳድሩ በአዋጅ የተሰጠውን ጊዜ ገደብ አሳልፎ ምላሽ ሰጥቷል፡፡

ኦፊሰሩ በደብዳቤያቸው ‹‹በርካታ ትምህርት ቤቶች ዩኒቨርስቲና ፣የመንግስት ተቋማት በሚገኙበት አካባቢ ሰላማዊ ሰልፍ ለማካሄድ የማይቻል በመሆኑ የተጠየቀውን የሰላማዊ ሰልፍ እውቅና ጥያቄ ተቀባይነት ያላገኘ መሆኑን እንገልጻለን፡፡››ብሏል፡፡ የአገሪቱ ፓርላማ ‹‹ስለ ሰላማዊ ሰልፍና ሕዝባዊ የፖለቲካ ስብሰባ ስነ ስርዓት ባወጣው አዋጅ ‹‹የከተማው ወይም የአውራጃው አስተዳደር ጽ/ቤት ሰላማዊ ሰልፉ ወይም ሕዝባዊ የፖለቲካ ስብሰባው ምን ግዜም በየትኛውም ቦታ ሊካሄድ አይችልም ማለት አይችልም››(አዋጅ ቁጥር 3/1983 )በማለት ያወጀውን በአዋጁ ስር የተቋቋመው ጽ/ቤት በማን አለብኝነት በመሻር የሰላማዊ ሰልፍ ጥያቄውን አልተቀበኩትም ብሏል፡፡ አንድነት አዋጁን የጣሰውን ደብዳቤ እንደማይቀበል በመግለጽ ለኦፊሰሩ ደብዳቤ በመጻፍ በአካል ቢሯቸው በመገኘት ለመስጠት ቢሞክርም በአስገራሚ ሁኔታ ኦፊሰሩ ደብዳቤውን አልቀበልም ብለዋል፡፡
የኦፊሰሩ ድርጊት ህገ ወጥ መሆኑን የተገነዘበው ፓርቲያችን ደብዳቤውን ቢሯቸው ጠረጴዛ ላይ ትቶ ከመውጣቱም በላይ በሪኮማንዴ እንዲደርሳቸው አድርጓል፡፡ ኦፊሰሩ እየሰሩ የሚገኙት ነገር ህገ ወጥ መሆኑን እንዲገነዘቡም ለፌደራል ፖሊስ፣ለአዲስ አበባ ከተማ ፖሊስ በግልባጭ ደብዳቤው እንዲደርሳቸው መደረጉን የአንድነት የአዲስ አበባ ዋና ጸሐፊ አቶ ነብዩ ባዘዘው ተናግረዋል፡፡ በህገ ወጥ ደብዳቤ የሚሰረዝ ሰላማዊ የህዝብ ጥያቄ ባለመኖሩም ሰላማዊ ሰልፉ በተያዘለት ቀነ ገደብ እንደሚደረግ አቶ ነብዩ ጨምረው ገልጸዋል፡፡

በስድስት ወር ውስጥ 41 ሰዎች በመንገድ ጉድጓዶችና ኩሬዎች ውስጥ ገብተው ሞተዋል

April 1/2014


  • “በመንገድ ላይ ለሚደርሱ አደጋዎች የአዲስ አበባ መንገዶች ባለስልጣን ተጠያቂ ነው”
  • “መንግሥትን በሰራው ጥፋት መክሰስ ህገ-መንግስታዊ መብት ነው” - የህግ ባለሙያ

ለአዛውንቱ አቶ ተስፋዬ ኪዳኔ መስከረም 10 ቀን 2006 ዓ.ም መልካም ቀን አልነበረም፡፡ ከመ/ቤታቸው ወጥተው ወደ ቤታቸው እያመሩ ነበር፡፡ ከ5ኛ ፖሊስ ጣቢያ ወደ ጌጃ ሰፈር በሚወስደው መንገድ ኮንዶሚኒየም ቤቶች አካባቢ ሲደርሱ በፍፁም ያልጠበቁት አስደንጋጭ አደጋ አጋጠማቸው፡፡ መንገድ ዳር ከሚገኝ ጉድጓድ ውስጥ ገብተው እግራቸው ተሰበረ፡፡

ከድንጋጤ ጋር ሙሉ ኃይላቸውን አሰባስበው ባሰሙት የድረሱልኝ ጥሪ፣ የአካባቢው ሰዎችና የእሳት አደጋ ሰራተኞች ተረባርበው ከጉድጓዱ በማውጣት ወደ ባልቻ ሆስፒታል ለህክምና ወሰዷቸው፡፡ በሆስፒታሉ ለ20 ቀን ተኝተው ከ23 ሺህ ብር በላይ አውጥተው ቢታከሙም እንደተመኙት በፍጥነት ከጉዳታቸው አገግመው በእግራቸው ቆመው ለመሄድ አልቻሉም። ይኸውና ላለፉት 7 ወራት ከሰውና ከክራንች ድጋፍ መላቀቅ አቅቷቸዋል፡፡

አሁንም በተመላላሽ ህክምናቸውን እየተከታተሉ ሲሆን አቶ ተስፋዬ ለደረሰባቸው ጉዳት ኃላፊነት የሚወስድ አካል የትኛው እንደሆነ ባለማወቃቸው መብታቸውን ማስከበርና ካሳ ማግኘት እንዳልቻሉ ይናገራሉ። “መንገዱ ላይ የተቆፈረ ጉድጓድ ውስጥ ነው የገባሁት፣ ኃላፊነቱን መውሰድ የሚገባው የአዲስ አበባ መንገዶች ባለስልጣን ነው የሚል እምነት አለኝ። ነገር ግን አንድ ሰው የዚህ ዓይነት አደጋ ሲደርስበት በየትኛው የህግ አግባብ፣ ማንን መክሰስና መጠየቅ እንዳለበት አላውቅም” ብለዋል፡፡

እንደ አቶ ተስፋዬ ሁሉ ባለፉት 6 ወራት መንገድ ዳር ተቆፍረው ባልተከደኑ ጉድጓዶችና በአዲስ አበባ ዙሪያ ባሉ ኩሬዎች ውስጥ ገብተው 41 ሰዎች መሞታቸውን፣106 ሰዎች መቁሰላቸውን ከአዲስ አበባ እሳትና ድንገተኛ አደጋዎች መከላከልና መቆጣጠሪያ ኤጀንሲ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡ ዓምና በግማሽ አመት ውስጥ 28 ሰዎች በተመሳሳይ አደጋ ሲሞቱ፣ 88 ሰዎች ቆስለዋል፡፡ ይህም ዘንድሮ የአደጋው መጠመን መጨመሩን ያመለክታል፡፡

“በአዲስ አበባ መንገዶች ላይ በየአምስት ሜትሩ ጉድጓድ አለ፡፡ አብዛኞቹ ጉድጓዶቹ በአዲስ አበባ ውሃና ፍሳሽ ባለሥልጣን ለፍሳሽ (ድሬኔጅ) መውረጃ የተቆፈሩ ናቸው፡፡ ለቴሌኮም፣ ለመብራት ኃይል ኬብሎችና ለመሰል አገልግሎት የሚቆፈሩም አሉ፡፡ ጉድጓዶቹ ትላልቅ ስለሆኑ ከሰው ቁመት በላይ እስከ 2 ሜትር ጥልቀት ያላቸው ናቸው” ይላሉ፤የአዲስ አበባ እሳትና ድንገተኛ አደጋዎች መከላከልና መቆጣጠር የኮሙኒኬሽ ኦፊሰር አቶ ንጋቱ ማሞ፡፡

ጉድጓዶቹ፣ በተለያዩ ምክንያቶች ክፍት ሊሆኑ ይችላሉ ያሉት አቶ ንጋቱ፤ ሕገ-ወጦች ክዳኑ  ላይ ያለውን ፌሮና ሌሎች ነገሮች ወስደው ክፍት ይተዋቸዋል፡፡ አንዳንድ ጊዜ ደግሞ የጉድጓዶቹ ባለቤት የሆኑ ድርጅት ሠራተኞች ለሥራ ይከፍቱትና ሳይዘጉ ይተዋቸዋል፡፡ ሁሉም ጉድጓዶች ያሉት መንገድ ላይ ነው፡፡ እነዚህ ጉድጓዶች ብዙውን ጊዜ ጉዳት የሚያደርሱት በክረምትና በጭለማ ነው፡፡ በክረምት ፍሳሹ ሞልቶ አስፋልቱን ስለሚያጥለቀልቀው ጉድጓድ መኖሩ አይታወቅም፡፡ በጭለማም አይታይም፡፡ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ደግሞ ለመንገድ ግንባታ ጉድጓዶች ይቆፈራሉ፡፡ ጧት ሥራ ስትሄድ ያልነበረ ጉድጓድ፣ ማታ ስትመለስ ተቆፍሮ ይጠብቅሃል፡፡ በሥራ መግቢያና መውጫ ሰዓት ጉድጓድ ስለመኖሩ የማያውቅ እንግዳና ሌላውም ሰው ትራንስፖርት ለመያዝ ሲጋፋ ጉድጓዶቹ ውስጥ ወድቆ ሊጎዳ ይችላል፡፡

ይኼ በከተማው መኸልም የሚታይ ነው፡፡ ከመዲናዋ ወጣ ብለው በሚገኙ የልማት ማስፋፊያ አካባቢዎችም ለኢንቨስትመንት በማለት ንፋስ ስልክ ላፍቶ ወረዳ አንድና ሁለት፣ ቦሌ ቡልቡላ ወረዳ አንድ፣ ቦሌ ኤርፖርቶች ድርጅት ጀርባ፣ ኮልፌ ቀራንዮ ሚኪሌይላንድ አካባቢ፣ ሐና ማርያም፣ ገርጂ ጊዮርጊስ … አካባቢዎች ድንጋይና ማዕድን ለማውጣት ፈቃድ ወስደው የሚቆፍሩ አሉ። የሚፈልጉትን ነገር ካገኙ በኋላ ለቀው ሲሄዱ የቆፈሩትን ጉድጓድ ሳይከድኑት ክፍቱን ትተው ነው የሚሄዱት፡፡ ያ ቦታ ውሃ ይቋጥርና ኩሬ ይፈጥራል። እዚያ ውስጥ ዋና የማይችሉ ታዳጊዎችና ወጣቶች ገብተው ሲዋኙ ወይም ኮብልስቶን ጠራጊዎች የግል ንፅህና ለመጠበቅ ገብተው ሲታጠቡ ሰምጠው ይሞታሉ፡፡

ሰሞኑን እንኳ ሐና ማርያም አካባቢ ባለ ኩሬ ውስጥ አንድ የ10 ዓመት ታዳጊ ገብቶ ሬሳውን አውጥተናል፡፡ ኩሬው ብዙ ህይወት ነው የቀጠፈው። አቃቂ አካባቢ የውሃ ችግር ስላለ እዚያ አካባቢ ካለ ኩሬ ውሃ ለመቅዳት የሄደ የጋሪ ፈረስ  ከነጋሪው ኩሬው ውስጥ  ሰጥሞ ሞቶ አውጥተናል፡፡

ለእነዚህ አደጋዎች ተጠያቂዎቹ ድንጋይ ወይም ማዕድን ለማውጣት ቦታውን ቆፍረው ሲያበቁ ቦታውን ቀድሞ ወደነበረበት ሳይመልሱ ክፍቱን ትተው የሚሄዱ ድርጅቶችና አስፈጻሚ አካላት ናቸው፡፡ ቦታውን ለመቆፈር ከአካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን ፈቃድ ሲያወጡ፣ ሲበቃቸው መልሰው ለመክደን ግዴታ ይገባሉ፡፡ ባለስልጣን መ/ቤቱም “ቃላችሁን ባታከብሩ” ብሎ ጉድጓዱን መክደን የሚያስችል ከፍተኛ ገንዘብ በመያዣ ይቀበላል። ነገር ግን ድርጅቶቹ በቸልተኝነት ወይም በሌላ ምክንያት የቆፈሩትን ጉድጓድ ሳይዘጉ ቢሄዱ አይጠየቁም ወይም አስፈጻሚው አካል ተከታትሎ ለመያዣ በተቀበለው ገንዘብ ጉድጓዱ እንዲዘጋ አያደርግም፡፡ እኛ አገር ጥሩ ጥሩ ሕጎች አሉ፡፡ ነገር ግን ተከታትሎ የሚያስፈጽም አካል የለም፡፡

በዚህ የተነሳ ባለፉት 6 ወራት ውስጥ ብቻ 41 ሰዎች ባልተከደነ የመንገድ ጉድጓድና ኩሬ ውስጥ ገብተው ሕይወታቸውን አጥተዋል፡፡ ከ15 ቀን በፊት ሜክሲኮ ከፌዴራል ፖሊስ ዋና ጽ/ቤት ፊት ለፊት አንድ የ32 ዓመት ወጣት ለቀላል ባቡር መንገድ በተቆፈረ ጉድጓድ ውስጥ ገብቶ ሞቷል፡፡ ጊዜው ትንሽ ቆየት ብሏል እንጂ አንድ ሰው በቀድሞው የአፍሪካ ኅብረት ድርጅት፣ በአሁኑ የአፍሪካ አንድነት አካባቢ ባለ ጉድጓድ ውስጥ ገብቶ 5 ቀን ከቆየ በኋላ እንዳጋጣሚ ሆኖ ከእነሕይወቱ ሊወጣ ችሏል፡፡ ያ ሰው ዕድለኛ ነው ማለት ይቻላል፡፡ አንዲት ልጅ በአጋጣሚ ከጉድጓድ ውስጥ ድምፅ ትሰማለች። ለማረጋገጥ ጠጋ ስትል ሰው አየች፡፡ ልጅቷ እዚህ (እሳት አደጋ) የሚሰራ ወንድም ስለነበራት፣ ደውላ ስላየችው ነገር ነገረችው፡፡ በአጋጣሚ ወንድምየው ዕረፍት ላይ ስለነበር፣ ደውሎ ነገረንና ሄደን አወጣነው፡፡ ያ ሰው አሁንም በሕይወት አለ፡፡ የሀይገር ሹፌር ሲሆን ትዳር መስርቶ እየኖረ ነው። ይኼ አደጋው ሲደርስ ዘመድ ወይም በአካባቢው የነበሩት ሰዎች ደውለውልን ያወጣናቸው ናቸው። ለእኛ ሳይደወል ዘመድ ወይም የአካባቢው ሰዎች ከጉድጓድ አውጥተው ወደ ቤትና ወደ ሐኪም ቤት የወሰዷቸው ወይም የቀበሯቸው በርካታ ናቸው፤ ቤት ይቁጠራቸው፡፡

በዚህ ጉዳይ ላይ ከአዲስ አበባ መንገዶች ባለሥልጣን ጋር ብዙ ጊዜ ተወያይተናል፡፡ እኔ ራሴ ከባለሥልጣኑ ኃላፊ ከኢንጂነር ፍቃዱ ኃይሌ ጋር ተነጋግሬአለሁ፡፡ ምንም መፍትሔ ያልተገኘለት ችግር ሆኖ ቆይቷል፡፡ ለልማት ተብሎ ተቆፍሮ በሚፈጠር ኩሬ ውስጥ በሳምንት አንድ ወይም ሁለት ሰው ገብቶ ይሞታል፡፡ በዚህ የተነሳ በዜጎች ላይ ከፍተኛ ጉዳት እየደረሰ ነው፡፡ እኛ ማድረግ የምንችለው ጉድጓድ ወይም ኩሬ ውስጥ ገብተው የሞቱትን ሬሳ አውጥተን ለፖሊስ ማስረከብ፣ አምቡላንስ ስላለን ተጎድተው በህይወት ያሉትን ህክምና ወደሚያገኙበት ማድረስ ነው፡፡ ከዚህ በተረፈ ከኩሬ ውስጥ ሬሳ ስናወጣ በአካባቢው ላሉ ሰዎች ትምህርት እንሰጣለን፡፡ ነገር ግን እዋኛለሁ ብሎ ለሚሄድ ሰው ጠባቂ ማቆም አንችልም፡፡ ልማት ሲካሄድ ያለ ቁፋሮ ሊካሄድ አይችልም፡፡ ስለዚህ ጉድጓድ ሲፈጠር መከለል አለበት፡፡ በአካባቢው አደጋ መኖሩን የሚጠቁሙ ዓለም አቀፍ ምልክቶች ስላሉ፣ እነሱ ጉድጓዱ ጋ ከመድረሱ ከ5 ሜትር በፊት መተከል አለባቸው፡፡

ለምሽት ደግሞ አንፀባራቂ ምልክት ማኖር ያስፈልጋል፡፡ በኮንስትራክሽን ቦታዎች ብዙ ጊዜ አደጋ የሚደርሰው በዝቅተኛ ሰራተኞች ላይ ነው፡፡ ባለሙያዎቹማ አደጋ ሊኖር እንደሚችል ስለሚያውቁ ይጠነቀቃሉ፡፡ ስለዚህ ለአደጋ የተጋለጡትን ሰራተኞች ማስተማርና የአደጋ መከላከያ ቆብ እንዲደፉ፣ ቦት ጫማ እንዲያደርጉና ጓንት እንዲያጠልቁ … ማስገደድ ያስፈልጋል በማለት አቶ ንጋቱ አሳስበዋል፡፡

በጉዳዩ ላይ የመስሪያ ቤታቸው አቋም ምን እንደሆነ የተጠየቁት የአዲስ አበባ መንገዶች ባለስልጣን ሥራ አስኪያጅ ኢ/ር ፍቃዱ ኃይሌ፣የሚያስተዳድሩት መስሪያ ቤት የከተማዋን መንገድ የሚሰራና የሚያስተዳድር እንደመሆኑ መሰል አደጋዎች ሲደርሱ ተጠያቂ የማይሆንበት ምክንያት እንደሌለ ይገልፃሉ፡፡

መንገድ ላይ ያሉ ጉዳዮችን እየተከታተለ መዝጋትና መድፈን የባለስልጣኑ ድርሻ ከመሆኑም በላይ ህብረተሰቡም ጥቆማ በመስጠት ሊተባበር ይገባል ያሉት ኢንጂነሩ፤ እስካሁን ወደ መስሪያቤታቸው “ጉዳት ደርሶብኛልና ካሳ ይገባኛል” የሚል አቤቱታ ይዞ የቀረበ ተጎጂ ባይኖርም እንዲህ ያለ አቤቱታ ከቀረበ መስሪያቤታቸው ኢንሹራንስ ገብቶም ቢሆን ማሳከም እንዳለበትና ተጠያቂ መሆን እንደሚችል ተናግረዋል፡፡

መንገድ ሲሰራ ከሰዎች ንክኪ ተከልሎ መሆን እንዳለበት የሚያስገነዝቡት ኢ/ር ፍቃዱ፤ ከዚህ አግባብ ውጪ የመንገድ ግንባታ ሲከናወን አደጋውን ያደረሰው ሥራ ተቋራጭ ከሆነ ባለስልጣኑ ተጠያቂ ይሆናል፡፡ አንዳንድ ተሽከርካሪዎች በእግረኛ መንገድ ላይ ወጥተው የፍሳሽ ማስተላለፊያ ቱቦ ክዳኖችን መስበራቸው ለጉድጓዶቹ መፈጠር መንስኤ ነው ያሉት ኃላፊው፤ በቀለበት መንገድ ላይ ያሉ የፍሳሽ ማስወገጃ ቱቦ የብረት ክዳኖችም በሌቦች መዘረፋቸው ለባለስልጣን መስሪያቤቱ ፈታኝ እየሆነ መምጣቱን ገልጸዋል፡፡ በዚህ ምክንያት ተሽከርካሪዎችና እግረኞች በጉድጓድ እየገቡ ከፍተኛ አደጋ እየደረሰባቸው እንደሚገኝ መረጃው አለን ያሉት ኢ/ር ፍቃዱ፤ ተጠያቂነትን የሚያሰፍን ጠንካራ የህግ አፈፃፀም ያስፈልጋል፤ ኅብረተሰቡም ጉድጓዶች ሲያጋጥሙት ለባለስልጣኑ መጠቆም አለበት ብለዋል፡፡

ችግሩን ለመቅረፍ የባለስልጣን መስሪያቤቱ ሰራተኞች የቱቦ ክዳኖችን ከፍተው ቆሻሻ ካፀዱ በኋላ በአፋጣኝ መልሰው እንዲደፍኑ፣ ኮንትራክተሮችም መንገድ ሲሰሩ ከልለው እንዲሰሩ ጥብቅ ትዕዛዝ እየተላለፈ መሆኑን ኢ/ሩ ገልፀዋል፡፡
ስሜ አይጠቀስ ያሉ አንድ የሕግ ባለሙያ፤ መንገድም ይሁን ህንፃ በአጠቃላይ የመሰረተ ልማት መዋቅር ሲሰራ በሰዎች ደህንነትና አካል ላይ ጉዳት በማያደርስ መልኩ መሆን እንዳለበት የወንጀለኛ መቅጫ ህጉ እንደሚደነግግ ጠቅሰው፤ የግንባታ ስራው ተጠናቅቆ አገልግሎት በመስጠት ላይ ባለ መንገድ ላይ ለሚደርስ ጉዳት የአዲስ አበባ መንገዶች ባለስልጣንና የኢትዮጵያ መንገዶች ባለስልጣን፣አደጋው የደረሰበት መንገድ ተጠቅሶ ክስ ሊቀርብባቸው ይችላል ብለዋል፡፡

በኮንስትራክሽን ሂደት ላይ ባለ መንገድ ውስጥ የደረሰ አደጋ ካጋጠመ ግን፣ ተጎጂው መንገዱን የሚያሠራውን ባለስልጣን መስሪያቤትና ሥራ ተቋራጩን በአንድነት በመጥቀስ ኃላፊነት ሊወስድ የሚገባውን አካል ፍ/ቤት ይወስንልኝ ብሎ ክስ ሊመሰርት እንደሚችል ባለሙያው አብራርተዋል። ይህ የክስ አቀራረብ ተመራጭ የሆነው፤ ሥራ ተቋራጩን መቆጣጠር ያለበት አሠሪው መስሪያ ቤት ስለሆነና በመካከላቸው ያለው ውል ስለማይታወቅ ነው ብለዋል፤ ባለሙያው፡፡

በእኛ ሀገር እንደ ልማድ ሆኖ መንገድ ሲሰራ የጥንቃቄ ምልክቶች እንደማይቀመጡ መታዘባቸውን የተናገሩት ባለሙያው፤ በአንዳንድ የሰለጠኑ ሀገሮች ከ5 ሜትር ርቀት ላይ ምልክቶችና አቅጣጫዎች እንደሚቀመጡ በመጠቆም በእኛም ሀገር ይህ አስገዳጅ ህግ ተፈፃሚ መደረግ አለበት ሲሉ ይመክራሉ፡፡ በቴሌ ኬብል ቀበራ ወቅት ጉድጓዶች ሳይከደኑ ከቀሩም የቴሌ መሆኑን በማረጋገጥ፣ አሊያም ፍ/ቤት ያጣራልኝ በማለት የመንገዶች ባለስልጣንና ቴሌን አጣምሮ ክስ መመስረት ይቻላል ብለዋል፡፡

በእኛ ሀገር የመንግሥት መስሪያ ቤቶችን በወንጀል መክሰስ (ኮርፖሬት ክሪሚናል ሊያቢሊቲ) በሚለው ፅንሰ ሐሳብ መነሻነት የወንጀለኛ መቅጫ ህጉ እንደሚከለክል የጠቆሙት የህግ ባለሙያው፤ ተጎጂው የደረሰበትን የጉዳት መጠን ጠቅሶ “ልካስ ይገባኛል” ብሎ የፍትሐብሔር ክስ ማቅረብ ይችላል ብለዋል፡፡ “መንግሥትን ከስሼ ካሣ አገኛለሁ” የሚለው ሐሳብ በራሱ በኛ ሀገር ካለመለመዱም በላይ በፍ/ቤቶች የተንዛዛ አሰራር ምክንያት ተጎጂዎች መብታቸውን እንዳያስከብሩ ዳተኛ ያደርጋል ያሉት ባለሙያው፤ ይህ ባህል መቀረፍ እንዳለበትና ሰዎች ሕጉ የሰጣቸውን መብት እንዲያስከብሩ አሳስበዋል።

በጉዳዩ ላይ የሚመለከታቸውን የአዲስ አበባ ውሃና ፍሳሽ አገልግሎት እና የአካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን መስሪያ ቤትን አስተያየት ለማካተት ያደረግነው ሙከራ ስልካቸው ባለመነሣቱ ሳይሳካ ቀርቷል፡፡

ከምዕራብ ሸዋ ዞን መሬት ተቀማን ያሉ የአማራ ተወላጆች ሰሚ አጣን አሉ

March 31/2014
1510357_10201735795417514_1563874087_n

“ወደ አንድነት ፓርቲ የመጣነው መሬት ያስመልስልናል ብለን አይደለም” 
 ስምንቱ በአዲስ አበባ ከተማ ክፍለ ከተማ ፖሊስ ጣቢያ ታስረው አድረዋል  
“ያለ አግባብ የተያዘ መሬት ላይ ሁሌም እግድ ይጣላል” - የዞኑ አስተዳደር 
በኦሮሚያ ክልል በምዕራብ ሸዋ ዞን ዳኖ ወረዳ አዋዲ ጉልፋ ቀበሌ፤ የመጡ 29 የአማራ ተወላጅ አርሶ አደሮች “መሬት እንዳናርስ ተከለከልን፤ ቅሬታችንን የሚሰማን አጣን” ሲሉ አማረሩ፡፡ ከ29ኙ ስምንቱ በአዲስ ከተማ ክ/ከተማ፣ ወረዳ ሰባት ፖሊስ ጣቢያ፣ ረቡዕ ማታ ታስረው ማደራቸውንና ሀሙስ ረፋድ ላይ መለቀቃቸውን አርሶ አደሮቹ ለአዲስ አድማስ ተናግረዋል፡፡ አርሶ አደሮቹ አብዛኞቹ ከ1986 ዓ.ም ጀምሮ ከጎንደርና ከሌሎች የአማራ አካባቢዎች መሸኛ በማምጣት መሬት እንደተሰጣቸው፣ በአዋዲ ጉልፋ፣ በአጂላ ዳሌና በዙሪያው መሬት በማልማት፣ ቤተእምነት በመገንባትና ሌሎት መሰረተ ልማቶችን በመስራት ከ20 ዓመታት በላይ በሰላም እንደኖሩ ገልፀው፣ ከ2004 ዓ.ም ወዲህ ግን በአማራ ተወላጅ አርሶ አደሮች ላይ የመሬት እቀባ እንደተጣለ ተናግረዋል፡፡ 
አቶ ቢያዝን አበራ የ65 ዓመት አዛውንት ናቸው። ትውልድና እድገታቸው ጎንደር ቢሆንም በመሬት ጥበትና በተፈጥሮ መጎዳት ሳቢያ ወደ ምዕራብ ሸዋ ዞን ዳኖ ወረዳ አዋዲ ጎልፋ ቀበሌ በ1986 ዓ.ም መጥተው መኖር እንደጀመሩ ይናገራሉ፡፡ ላለፉት 20 ዓመታት መሬታቸውን እያረሱ፣ ለመሰረተ ልማት መዋጮ እያዋጡ፣ አካባቢያቸውን እያለሙ ዘጠኝ ልጆቻውን ሲያሳድጉ መኖራቸውን ገልፀዋል፡፡ ይሁን እንጂ ከ2004 ዓ.ም በኋላ ነገሮች እየተቀየሩ፣ የአካባቢው ባለስልጣናት ባህሪ እየተለወጠና በአማራ ተወላጆች ላይ ጫናው እየበረታ እንደመጣ ገልፀዋል፡፡ “በ2004 ዓ.ም የአማራ ህዝብ ከሰፈረባቸው ቀበሌዎች አንዱ በሆነው አጂላዳሌ ቀበሌ፣ ከሰሜን ሸዋ የመጡ የ150 አባወራዎች ቤት በእሳት ጋይቶ ሰዎቹ የት እንደደረሱ ጠፍተዋል” ያሉት አቶ ቢያዝን፤እርሳቸው በሚኖሩበት አዋዲ ጉልፋ ቀበሌም “ለአማራ ተወላጆች ሁለት ሁለት ሄክታር መሬት ይበቃል፤ ቀሪውን ለኦሮሚያ ወጣቶች እንሰጣለን” በሚል መሬታቸውን አርሰው እንዳይበሉ እንዳደረጉዋቸው ተናግረዋል፡፡ “ከዚያን ጊዜ ጀምሮ ከወረዳ ወደ ዞን፣ ከዞን ወደ ክልል አቤት ብለን ሰሚ በማጣታችን ወደ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ጽ/ቤት እና ወደ ፌዴሬሽን ም/ቤት አቤት ብለናል” ያሉት አዛውንቱ፤ “ይህን የሚያደርገው የአስተሳሰብ እጥረት ያለበት ነው፤ ወደ ቦታችሁ ተመለሱ ውሳኔ እንሰጣለን” ብንባልም እስካሁን ምንም ውሳኔ አላገኘንም ብለዋል፡፡ “ጉዳዩ በእንጥልጥል እያለ መጋቢት 8 ቀን 2006 ዓ.ም አንድም በአማራ ተወላጆች የተያዘ መሬት እንዳይታረስና እንዳይዘራ የሚል እግድ ደብዳቤ ወጣብን” በማለት የእግድ ደብዳቤውን በማስረጃነት አቅርበዋል፡፡ 
ደሳለኝ በላቸው የተባሉት ሌላው የ43 ዓመት ጎልማሳ፤ ከ1978 ዓ.ም ጀምሮ ከአባታቸው ጋር ወደ ናኖ ወረዳ እንደመጡ ገልፀው፣ ከናኖ ወደ ዳኖ የመጡበት ምክንያት በወረዳው ሰዎች በተደረገላቸው የአብረን እንኑር ጥሪ መሆኑን ገልፀዋል፡፡ ከደቡብ ጎንደር በልጅነታቸው እንደመጡ የገለፁት አቶ ደሳለኝ፤ ከዚያን ጊዜ ጀምሮ ስምንት ልጆችን አፍርተው በሰላም መኖር እንደ ጀመሩ ገልፀዋል፡፡ ከ29ኙ የአማራ ተወላጅ አርሶ አደሮች ጋር በአንድነት ለፍትህና ለዴሞክራሲ ፓርቲ ቢሮ ውስጥ በተነጠፈ ጂባ ላይ ተቀምጠው ያገኘናቸው ጎልማሳው፤ በወረዳው ባለስልጣናት ከፍተኛ የመብት ጥሰት እየደረሰ እንደሆነ ገልጸው በአካባቢው ያሉ የመኪና መንገዶችን፣ ቤተ እምነቶችን እና መሰል መሰረተ ልማቶችን ከመሰሎቻቸው ጋር መገንባታቸውን፣ ጠፍ የነበረውን መሬት አልምተው ግብር እየከፈሉ፣ ለመሰረተ ልማትና ለአባይ ግድብ እንደ ማንኛውም ዜጋ እያዋጡ እየኖሩ “አማራ ነህ ፤መሬት አይገባህም” መባላቸውን ተቃውመዋል፡፡ 
“ትምህርት የሚሰጠው በኦሮምኛ ብቻ በመሆኑ ልጆቻችንን ወሊሶና ወልቂጤ ልከን በስንቅ እናስተምራለን” ያሉት አቶ ደሳለኝ፤ “በወረዳውና በቀበሌው ኃላፊዎች ስብሰባ ተጠርተን ሄደን በኦሮምኛ ተጀምሮ በኦሮምኛ ያልቃል፤ ስብሰባው እኛን የማያሳትፍ ከሆነ ለምን ጠራችሁን ስንል፤ ግዴታችሁ ነው እንባላለን” ብለዋል፡፡ 
“ይባስ ብለው መሬት ለምን ትቀሙናላችሁ? አብረናችሁ የኖርን፣ አካባቢውን ያለማን ነን ስንል ድብደባና ግርፋት ደርሶብናል” ያሉት አቶ ደሳለኝ፤ በዚህ ሳቢያ ጌጡ ክብረት የተባለ የአጂላ ፉዳሌ ቀበሌ ነዋሪ የአማራ ተወላጅ፣ህግና ፖሊስ ባለበት ተደብድቦ ሞቷል፤ እስካሁን ገዳዮቹም አልተያዙም፤ ክስም አልተመሰረተም” ሲሉ አማረዋል፡፡ ከ20 ዓመት በላይ ኖረን ጥሩ ልማትና ጥሩ ስራ ስንሰራ “ህገ-ወጥ ሰፋሪዎች ናችሁ፤ ወደ ክልላችሁ ሂዱ፤ መሬቱ ለኦሮሞ ወጣቶች ይፈለጋል” ተባልን ያሉት ቅሬታ አቅራቢዎቹ፤ ይሄም ኢትዮጵያዊነታችንን እንድንጠራጠር አድርጎናል ብለዋል፡፡ 
ለፌዴሬሽን ም/ቤት በተደጋጋሚ አቤት ማለታቸውንና ምላሽ አለማግኘታቸውን የገለፁት አርሶ አደሮቹ፤ በድጋሚም መምጣታቸውን ጠቁመው፤ “የፌዴሬሽን ም/ቤት አፈጉባኤ ስለሌሉ ወደ ቦታችሁ ተመለሱ” የሚል ምላሽ እንደተሰጣቸው ተናግረዋል፡፡ የመጣችሁት ፌዴሬሽን ም/ቤት ከሆነ እንዴት ወደ አንድነት ፓርቲ ጽ/ቤት መጣችሁ በማለት ላቀረብነው ጥያቄም፤ “በአገሪቱ መሪ በኢህአዴጋችን ምላሽ በማጣታችን ጉዳያችንን ለኢትዮጵያ እና ለዓለም ሚዲያ እንዲያሰሙልን በሚል ነው የመጣነው” ብለዋል አቶ ደሳለኝ፡፡ በአሁኑ ሰዓት በአማራ ተወላጅ አርሶ አደሮች ላይ በአካባቢው ባለስልጣናት እየደረሰ ያለው ግፍና በደል ቆሞ፣ መሬታቸውን እንዳያርሱ የተጣለው እግድ ተነስቶ፣ በሰላም መኖር እንደሚፈልጉ የገለፁት አርሶ አደሮቹ፤ይህ ምላሽ የሚገኘውም ከገዢው ፓርቲ እንደሆነ በመጠቆም አስቸኳይ እርምጃ እንዲወሰድላቸው ተማፅነዋል፡፡ 
“ወደ አንድነት ፓርቲ የመጣነው መሬት ያስመልስልናል ብለን አይደለም” ያሉት ሌላው አርሶ አደር፤ በመንግስት በኩል ምላሽ አጥተን መተንፈሻ በማጣታችን ነው ብለዋል፡፡ “የትኛውንም የአካባቢው ተወላጆች የሚያደርጉትን መዋጮ ለአባይ ግድብ፣ ለመንገድ ስራ እያዋጣንና ግብር እየከፈልን ባለበት መሬት እንዳናርስ የታገድንበት ሁኔታ አሳዝኖናል፤ ዜግነታችንና ህልውናችን አደጋ ላይ ወድቋል፤ መንግስት አስቸኳይ መፍትሄ ይስጠን” ሲሉ ጠይቀዋል፡፡ “አሁን ያላችሁበት አካባቢ አትኖሩም ከተባልንም መንግስት ሌላ የምንኖርበት ቦታ ወስዶ እንዲያሰፍረን እንጠይቃለን” ብለዋል፡፡ 
“በአሁኑ ሰዓት ሰሚ አጥን ስንከራተት የአንድነት ፓርቲ አመራሮች ተቀብለው ምግብ እና መኝታ እንድናገኝ አድረገውናል፤ ያለ ስንቅ ነበር የመጣነው” ብለዋል፤አርሶአደሮቹ፡፡ ጉዳያቸውን ለጋዜጠኞች አስረድተው ወደ አገራቸው ሲመለሱ፣ አውቶቡስ ተራ አካባቢ ፖሊሶች ለጥያቄ እንፈልጋችኋለን በማለት ቢያዝን አበራ፣ ደሳለኝ በላቸው፣ ኑሮዬ እንድሪስ፣ ፀጋ ዳምጠውና ሌሎች አራት ሰዎችን በአዲስ ከተማ ክ/ከተማ ወረዳ ሰባት ፖሊስ ጣቢያ እንደወሰዷቸው የገለፁት አርሶ አደሮች፤ ለምን መጣችሁ፣ ወደ አንድነት ፓርቲ የመራችሁ ማን ነው፣ ከየት ነው የመጣችሁት እና ሌሎች ጥያቄዎች ቀርቦላቸው  መልስ ከሰጡ በኋላ፣ ፖሊስ ጣቢያ አድረው ሀሙስ 3፡30 መለቀቃቸውን  ገልፀዋል፡፡ 
የምዕራብ ሸዋ ዞን መስተዳድር ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ቱፋ ቴሶ በበኩላቸው፤ በአማራ ተወላጆች ላይ ደርሷል የተባለውን በደል እንደማያውቁት ገልፀው፣ ችግሮችም ካሉ ለዞኑ ማመልከትና ተበድለናል ያሉት አርሶ አደሮች ተሳታፊ በሆኑበት መንገድ ተወያይቶ መፍታት ይቻል እንደነበር ተናግረዋል፡፡ “ችግሩ ከ2004 ዓ.ም ጀምሮ እንዳለ አላውቅም፣ ወደ ኃላፊነቱ የመጣሁት በቅርብ ነው” ያሉት አቶ ቱፋ፤ ችግራቸውን በተዋረድ ሳያሰሙ ወደ ፌዴሬሽን ም/ቤት መሄዳቸው አግባብ እንዳልሆነና ለዞኑ ያሰሙት ቅሬታ እንደሌለ ተናግረዋል፡፡ “እኛ አማራ ቢሆኑም ከየትኛውም ብሔር ቢመጡም የምናያቸው በወንድምነት ነው“ ያሉት የመስተዳድሩ ጽ/ቤት ኃላፊ፤ አሁንም ቢሆን ችግራቸውን ቀርበው ያወያዩንና በስፍራው ተገኝተን ከወረዳው ኃላፊዎች ጋር ተመካክረን እንፈታዋለን” ብለዋል፡፡ 
የአማራ አርሶ አደሮች፣ልጆቻችን በአማርኛ ቋንቋ መማር አልቻሉም በማለት ባነሱት ቅሬታ ዙሪያ አቶ ቱፋ ሲመልሱ፤ “በአገር አቀፍ ደረጃ ከአንድ ክልል መጥተው ሌላ ክልል ውስጥ ለሚኖሩ ዜጎች ት/ቤት ተከፍቶ በልዩ ሁኔታ በአፍ መፍቻ ቋንቋቸው እንዲማሩ እየተደረገ ነው፡፡ በአጠቃላይ ግን ያለባቸውን ቅሬታ ከዞኑ መስተዳድር ጋር መነጋገር ይኖርባቸዋል” ካሉ በኋላ፣ከዳኖ ወረዳ ወደ ፌደራል መንግስት ቅሬታ ለማሰማት የሄዱ የአማራ አርሶ አደሮች መኖራቸውን የሰሙት በወሬ ደረጃ እንደሆነ ተናግረዋል፡፡ 
“አርሶ አደሮቹ ከአካባቢው ተወላጅ ተለይተው የሚታዩበት መንገድ የለም” ያሉት አቶ ቱፋ፤ ከመጠን በላይ የያዙት መሬት ካለም ሆነ ያለአግባብ ታግደውና መሬት ተወስዶባቸው ከሆነ፣ ሁሉም በህግና በስርዓት እንደሚታይ ገልፀው፤ ከህግ በላይ የሚሆን ማንም እንደሌለ ተናግረዋል፡፡  
የዞኑ ምክትል መስተዳድር አቶ ከሳዬ ገመቹ በበኩላቸው፤ “የታገደ መሬት ካለም ያለ አግባብና በህገ-ወጥ መንገድ የተያዘ ነው” ካሉ በኋላ ከዚህ ቀደም በዚህ ጉዳይ ቅሬታ ያነሱ ሰዎች እንደነበሩና በዞን፣ በወረዳ፣ በክልል እና ከእምባ ጠባቂ ተቋም ተወካዮች መጥተው ጉዳዩ ውሳኔ አግኝቷል ብለዋል፡፡ 
በአማራም ሆነ በአካባቢው ተወላጆች ያለአግባብና ከመጠን በላይ የተያዘ ካለ ታይቶ መሬት ለሌለው ይሰጣል፤ የተረፈው ወደ መንግስት የመሬት ባንክ ይገባል ያሉት ምክትል መስተዳድሩ፤ “በህገ-ወጥ መንገድ ያልተፈቀደ መሬት ይዘው ከአማራ ክልል ስለመጡ የተበደሉ አድርገው ማቅረባቸው፣ህዝብን ከህዝብ ለማጋጨትና ለመከፋፈል ሆነ ብለው የሚያደርጉት ነው ብለዋል፡፡ 

የፕሬዚዳንቱ ጽ/ቤት ኃላፊ ከሥልጣናቸው ተነሡ

March 31/2014


የፕሬዚዳንት ጽ/ቤት ሃላፊ የነበሩት ወ/ሮ አማረች በቃሉ፤ከቀድሞ ፕሬዚዳንት አቶ ግርማ ወልደጊዮርጊስ የቤት ኪራይ ውል አፈፃፀም ጋር በተገናኘ በተፈጠረ የሥራ ዝርክርክነት  ከሃላፊነታቸው እንደተነሱ ምንጮች ጠቆሙ፡፡

መጋቢት 11 ቀን 2006 ዓ.ም በጠቅላይ ሚኒስትሩ በተፃፈ ደብዳቤ ሃላፊዋ፣ በአሰራር ዝርክርክነት ከሃላፊነታቸው እንደተነሱ የጠቆሙት ምንጮች፤በዝርክርክነት ተብሎ የተጠቀሰውም የቀድሞ ፕሬዚዳንት የቤት ኪራይ ውል አፈፃፀም እንደሆነ ተናግረዋል፡፡

ወ/ሮ አማረች ግን ይሄን አይቀበሉም፡፡ ጉዳዩ በኢህአዴግ የተለመደ የስራ ዝውውር እንጂ የአሠራር ዝርክርክነትም ሆነ የቀድሞ ፕሬዚዳንት ጉዳይን የተመለከተ አይደለም ሲሉ አስተባብለዋል፡፡ ምንጮች እንደሚሉት፤ ከአንድ ወር በፊት በፅ/ቤቱ በተደረገ ግምገማ በጽ/ቤቱ የአመራር፣ የአስተዳደርና  የአገልግሎት አሰጣጥ ላይ ዝርክርክነት እንዳለ የተጠቀሰ ሲሆን ወ/ሮ አማረችም በተመሳሳይ ጉዳይ ተገምግመዋል፡፡
ከግምገማው ጋር ግንኙነት እንዳለው ባይታወቅም አዲሱ ፕሬዚዳንት ዶ/ር ሙላቱ ተሾመ ባለፈው ጥር ወር ላይ በፃፉት ደብዳቤ፤ የፅ/ቤቱ ሃላፊ ወ/ሮ አማረች በቃሉ ከሃላፊነታቸው እንዲነሱላቸው ጠይቀው እንደነበር ምንጮች አስታውሰው፤ ሃላፊዋ ላለፉት ሶስት ወራት በሥራቸው ላይ ቆይተው በዚህ ወር ከሃላፊነታቸው እንደተነሱ ገልፀዋል፡፡

ከሃላፊነታቸው በተነሱት ወ/ሮ አማረች በቃሉ ምትክም የአዲስ አበባ ከንቲባ ጽ/ቤት ሃላፊ የነበሩት አቶ ብሩክ ግዛው የተሾሙ ሲሆን ስለአዲሱ ኃላፊነታቸው የጠይቀናቸው አቶ ብሩክ፣መልስ ከመስጠት ተቆጥበዋል፡፡

የቀድሞው ፕሬዚዳንት ግርማ ወ/ጊዮርጊስ አሁን የተከራዩትን መኖርያ ቤት አፈላልጎ ያገኘላቸው የኮሚሽን ሰራተኛ፣በውሉ መሰረት ክፍያ አልተፈፀመልኝም በማለት በፕሬዚዳንቱ ፅ/ቤት፣ በፕሬዚዳንቱና በልጃቸው ላይ ክስ መመስረቱ የሚታወቅ ሲሆን መጀመርያ ላይ ቤት ያከራየው ግለሰብም ከፕሬዚዳንቱ ፅ/ቤት የ2.1 ሚ ብር ካሣ እንዲከፈለው የመጨረሻ የማስጠንቀቂያ ደብዳቤ በማስገባት ቀጣዩ እርምጃ ክስ መመስረት እንደሆነ ተናግሯል፡፡

ምንጮች እንደሚሉት፤ ይሄ ሁሉ ችግር የተፈጠረው በፕሬዚዳንቱ ፅ/ቤት የአመራርና አስተዳደር እንዝላልነት ሲሆን የሃላፊዋ መነሳትም ከዚህ ጋር በቀጥታ የተገናኘ እንደሆነ ይናገራሉ፡፡


በስድስት ወር ውስጥ 41 ሰዎች በመንገድ ጉድጓዶችና ኩሬዎች ውስጥ ገብተው ሞተዋል

March 31/2014


  • “በመንገድ ላይ ለሚደርሱ አደጋዎች የአዲስ አበባ መንገዶች ባለስልጣን ተጠያቂ ነው”
  • “መንግሥትን በሰራው ጥፋት መክሰስ ህገ-መንግስታዊ መብት ነው” - የህግ ባለሙያ

ለአዛውንቱ አቶ ተስፋዬ ኪዳኔ መስከረም 10 ቀን 2006 ዓ.ም መልካም ቀን አልነበረም፡፡ ከመ/ቤታቸው ወጥተው ወደ ቤታቸው እያመሩ ነበር፡፡ ከ5ኛ ፖሊስ ጣቢያ ወደ ጌጃ ሰፈር በሚወስደው መንገድ ኮንዶሚኒየም ቤቶች አካባቢ ሲደርሱ በፍፁም ያልጠበቁት አስደንጋጭ አደጋ አጋጠማቸው፡፡ መንገድ ዳር ከሚገኝ ጉድጓድ ውስጥ ገብተው እግራቸው ተሰበረ፡፡

ከድንጋጤ ጋር ሙሉ ኃይላቸውን አሰባስበው ባሰሙት የድረሱልኝ ጥሪ፣ የአካባቢው ሰዎችና የእሳት አደጋ ሰራተኞች ተረባርበው ከጉድጓዱ በማውጣት ወደ ባልቻ ሆስፒታል ለህክምና ወሰዷቸው፡፡ በሆስፒታሉ ለ20 ቀን ተኝተው ከ23 ሺህ ብር በላይ አውጥተው ቢታከሙም እንደተመኙት በፍጥነት ከጉዳታቸው አገግመው በእግራቸው ቆመው ለመሄድ አልቻሉም። ይኸውና ላለፉት 7 ወራት ከሰውና ከክራንች ድጋፍ መላቀቅ አቅቷቸዋል፡፡

አሁንም በተመላላሽ ህክምናቸውን እየተከታተሉ ሲሆን አቶ ተስፋዬ ለደረሰባቸው ጉዳት ኃላፊነት የሚወስድ አካል የትኛው እንደሆነ ባለማወቃቸው መብታቸውን ማስከበርና ካሳ ማግኘት እንዳልቻሉ ይናገራሉ። “መንገዱ ላይ የተቆፈረ ጉድጓድ ውስጥ ነው የገባሁት፣ ኃላፊነቱን መውሰድ የሚገባው የአዲስ አበባ መንገዶች ባለስልጣን ነው የሚል እምነት አለኝ። ነገር ግን አንድ ሰው የዚህ ዓይነት አደጋ ሲደርስበት በየትኛው የህግ አግባብ፣ ማንን መክሰስና መጠየቅ እንዳለበት አላውቅም” ብለዋል፡፡

እንደ አቶ ተስፋዬ ሁሉ ባለፉት 6 ወራት መንገድ ዳር ተቆፍረው ባልተከደኑ ጉድጓዶችና በአዲስ አበባ ዙሪያ ባሉ ኩሬዎች ውስጥ ገብተው 41 ሰዎች መሞታቸውን፣106 ሰዎች መቁሰላቸውን ከአዲስ አበባ እሳትና ድንገተኛ አደጋዎች መከላከልና መቆጣጠሪያ ኤጀንሲ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡ ዓምና በግማሽ አመት ውስጥ 28 ሰዎች በተመሳሳይ አደጋ ሲሞቱ፣ 88 ሰዎች ቆስለዋል፡፡ ይህም ዘንድሮ የአደጋው መጠመን መጨመሩን ያመለክታል፡፡

“በአዲስ አበባ መንገዶች ላይ በየአምስት ሜትሩ ጉድጓድ አለ፡፡ አብዛኞቹ ጉድጓዶቹ በአዲስ አበባ ውሃና ፍሳሽ ባለሥልጣን ለፍሳሽ (ድሬኔጅ) መውረጃ የተቆፈሩ ናቸው፡፡ ለቴሌኮም፣ ለመብራት ኃይል ኬብሎችና ለመሰል አገልግሎት የሚቆፈሩም አሉ፡፡ ጉድጓዶቹ ትላልቅ ስለሆኑ ከሰው ቁመት በላይ እስከ 2 ሜትር ጥልቀት ያላቸው ናቸው” ይላሉ፤የአዲስ አበባ እሳትና ድንገተኛ አደጋዎች መከላከልና መቆጣጠር የኮሙኒኬሽ ኦፊሰር አቶ ንጋቱ ማሞ፡፡

ጉድጓዶቹ፣ በተለያዩ ምክንያቶች ክፍት ሊሆኑ ይችላሉ ያሉት አቶ ንጋቱ፤ ሕገ-ወጦች ክዳኑ  ላይ ያለውን ፌሮና ሌሎች ነገሮች ወስደው ክፍት ይተዋቸዋል፡፡ አንዳንድ ጊዜ ደግሞ የጉድጓዶቹ ባለቤት የሆኑ ድርጅት ሠራተኞች ለሥራ ይከፍቱትና ሳይዘጉ ይተዋቸዋል፡፡ ሁሉም ጉድጓዶች ያሉት መንገድ ላይ ነው፡፡ እነዚህ ጉድጓዶች ብዙውን ጊዜ ጉዳት የሚያደርሱት በክረምትና በጭለማ ነው፡፡ በክረምት ፍሳሹ ሞልቶ አስፋልቱን ስለሚያጥለቀልቀው ጉድጓድ መኖሩ አይታወቅም፡፡ በጭለማም አይታይም፡፡ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ደግሞ ለመንገድ ግንባታ ጉድጓዶች ይቆፈራሉ፡፡ ጧት ሥራ ስትሄድ ያልነበረ ጉድጓድ፣ ማታ ስትመለስ ተቆፍሮ ይጠብቅሃል፡፡ በሥራ መግቢያና መውጫ ሰዓት ጉድጓድ ስለመኖሩ የማያውቅ እንግዳና ሌላውም ሰው ትራንስፖርት ለመያዝ ሲጋፋ ጉድጓዶቹ ውስጥ ወድቆ ሊጎዳ ይችላል፡፡

ይኼ በከተማው መኸልም የሚታይ ነው፡፡ ከመዲናዋ ወጣ ብለው በሚገኙ የልማት ማስፋፊያ አካባቢዎችም ለኢንቨስትመንት በማለት ንፋስ ስልክ ላፍቶ ወረዳ አንድና ሁለት፣ ቦሌ ቡልቡላ ወረዳ አንድ፣ ቦሌ ኤርፖርቶች ድርጅት ጀርባ፣ ኮልፌ ቀራንዮ ሚኪሌይላንድ አካባቢ፣ ሐና ማርያም፣ ገርጂ ጊዮርጊስ … አካባቢዎች ድንጋይና ማዕድን ለማውጣት ፈቃድ ወስደው የሚቆፍሩ አሉ። የሚፈልጉትን ነገር ካገኙ በኋላ ለቀው ሲሄዱ የቆፈሩትን ጉድጓድ ሳይከድኑት ክፍቱን ትተው ነው የሚሄዱት፡፡ ያ ቦታ ውሃ ይቋጥርና ኩሬ ይፈጥራል። እዚያ ውስጥ ዋና የማይችሉ ታዳጊዎችና ወጣቶች ገብተው ሲዋኙ ወይም ኮብልስቶን ጠራጊዎች የግል ንፅህና ለመጠበቅ ገብተው ሲታጠቡ ሰምጠው ይሞታሉ፡፡

ሰሞኑን እንኳ ሐና ማርያም አካባቢ ባለ ኩሬ ውስጥ አንድ የ10 ዓመት ታዳጊ ገብቶ ሬሳውን አውጥተናል፡፡ ኩሬው ብዙ ህይወት ነው የቀጠፈው። አቃቂ አካባቢ የውሃ ችግር ስላለ እዚያ አካባቢ ካለ ኩሬ ውሃ ለመቅዳት የሄደ የጋሪ ፈረስ  ከነጋሪው ኩሬው ውስጥ  ሰጥሞ ሞቶ አውጥተናል፡፡

ለእነዚህ አደጋዎች ተጠያቂዎቹ ድንጋይ ወይም ማዕድን ለማውጣት ቦታውን ቆፍረው ሲያበቁ ቦታውን ቀድሞ ወደነበረበት ሳይመልሱ ክፍቱን ትተው የሚሄዱ ድርጅቶችና አስፈጻሚ አካላት ናቸው፡፡ ቦታውን ለመቆፈር ከአካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን ፈቃድ ሲያወጡ፣ ሲበቃቸው መልሰው ለመክደን ግዴታ ይገባሉ፡፡ ባለስልጣን መ/ቤቱም “ቃላችሁን ባታከብሩ” ብሎ ጉድጓዱን መክደን የሚያስችል ከፍተኛ ገንዘብ በመያዣ ይቀበላል። ነገር ግን ድርጅቶቹ በቸልተኝነት ወይም በሌላ ምክንያት የቆፈሩትን ጉድጓድ ሳይዘጉ ቢሄዱ አይጠየቁም ወይም አስፈጻሚው አካል ተከታትሎ ለመያዣ በተቀበለው ገንዘብ ጉድጓዱ እንዲዘጋ አያደርግም፡፡ እኛ አገር ጥሩ ጥሩ ሕጎች አሉ፡፡ ነገር ግን ተከታትሎ የሚያስፈጽም አካል የለም፡፡

በዚህ የተነሳ ባለፉት 6 ወራት ውስጥ ብቻ 41 ሰዎች ባልተከደነ የመንገድ ጉድጓድና ኩሬ ውስጥ ገብተው ሕይወታቸውን አጥተዋል፡፡ ከ15 ቀን በፊት ሜክሲኮ ከፌዴራል ፖሊስ ዋና ጽ/ቤት ፊት ለፊት አንድ የ32 ዓመት ወጣት ለቀላል ባቡር መንገድ በተቆፈረ ጉድጓድ ውስጥ ገብቶ ሞቷል፡፡ ጊዜው ትንሽ ቆየት ብሏል እንጂ አንድ ሰው በቀድሞው የአፍሪካ ኅብረት ድርጅት፣ በአሁኑ የአፍሪካ አንድነት አካባቢ ባለ ጉድጓድ ውስጥ ገብቶ 5 ቀን ከቆየ በኋላ እንዳጋጣሚ ሆኖ ከእነሕይወቱ ሊወጣ ችሏል፡፡ ያ ሰው ዕድለኛ ነው ማለት ይቻላል፡፡ አንዲት ልጅ በአጋጣሚ ከጉድጓድ ውስጥ ድምፅ ትሰማለች። ለማረጋገጥ ጠጋ ስትል ሰው አየች፡፡ ልጅቷ እዚህ (እሳት አደጋ) የሚሰራ ወንድም ስለነበራት፣ ደውላ ስላየችው ነገር ነገረችው፡፡ በአጋጣሚ ወንድምየው ዕረፍት ላይ ስለነበር፣ ደውሎ ነገረንና ሄደን አወጣነው፡፡ ያ ሰው አሁንም በሕይወት አለ፡፡ የሀይገር ሹፌር ሲሆን ትዳር መስርቶ እየኖረ ነው። ይኼ አደጋው ሲደርስ ዘመድ ወይም በአካባቢው የነበሩት ሰዎች ደውለውልን ያወጣናቸው ናቸው። ለእኛ ሳይደወል ዘመድ ወይም የአካባቢው ሰዎች ከጉድጓድ አውጥተው ወደ ቤትና ወደ ሐኪም ቤት የወሰዷቸው ወይም የቀበሯቸው በርካታ ናቸው፤ ቤት ይቁጠራቸው፡፡

በዚህ ጉዳይ ላይ ከአዲስ አበባ መንገዶች ባለሥልጣን ጋር ብዙ ጊዜ ተወያይተናል፡፡ እኔ ራሴ ከባለሥልጣኑ ኃላፊ ከኢንጂነር ፍቃዱ ኃይሌ ጋር ተነጋግሬአለሁ፡፡ ምንም መፍትሔ ያልተገኘለት ችግር ሆኖ ቆይቷል፡፡ ለልማት ተብሎ ተቆፍሮ በሚፈጠር ኩሬ ውስጥ በሳምንት አንድ ወይም ሁለት ሰው ገብቶ ይሞታል፡፡ በዚህ የተነሳ በዜጎች ላይ ከፍተኛ ጉዳት እየደረሰ ነው፡፡ እኛ ማድረግ የምንችለው ጉድጓድ ወይም ኩሬ ውስጥ ገብተው የሞቱትን ሬሳ አውጥተን ለፖሊስ ማስረከብ፣ አምቡላንስ ስላለን ተጎድተው በህይወት ያሉትን ህክምና ወደሚያገኙበት ማድረስ ነው፡፡ ከዚህ በተረፈ ከኩሬ ውስጥ ሬሳ ስናወጣ በአካባቢው ላሉ ሰዎች ትምህርት እንሰጣለን፡፡ ነገር ግን እዋኛለሁ ብሎ ለሚሄድ ሰው ጠባቂ ማቆም አንችልም፡፡ ልማት ሲካሄድ ያለ ቁፋሮ ሊካሄድ አይችልም፡፡ ስለዚህ ጉድጓድ ሲፈጠር መከለል አለበት፡፡ በአካባቢው አደጋ መኖሩን የሚጠቁሙ ዓለም አቀፍ ምልክቶች ስላሉ፣ እነሱ ጉድጓዱ ጋ ከመድረሱ ከ5 ሜትር በፊት መተከል አለባቸው፡፡

ለምሽት ደግሞ አንፀባራቂ ምልክት ማኖር ያስፈልጋል፡፡ በኮንስትራክሽን ቦታዎች ብዙ ጊዜ አደጋ የሚደርሰው በዝቅተኛ ሰራተኞች ላይ ነው፡፡ ባለሙያዎቹማ አደጋ ሊኖር እንደሚችል ስለሚያውቁ ይጠነቀቃሉ፡፡ ስለዚህ ለአደጋ የተጋለጡትን ሰራተኞች ማስተማርና የአደጋ መከላከያ ቆብ እንዲደፉ፣ ቦት ጫማ እንዲያደርጉና ጓንት እንዲያጠልቁ … ማስገደድ ያስፈልጋል በማለት አቶ ንጋቱ አሳስበዋል፡፡

በጉዳዩ ላይ የመስሪያ ቤታቸው አቋም ምን እንደሆነ የተጠየቁት የአዲስ አበባ መንገዶች ባለስልጣን ሥራ አስኪያጅ ኢ/ር ፍቃዱ ኃይሌ፣የሚያስተዳድሩት መስሪያ ቤት የከተማዋን መንገድ የሚሰራና የሚያስተዳድር እንደመሆኑ መሰል አደጋዎች ሲደርሱ ተጠያቂ የማይሆንበት ምክንያት እንደሌለ ይገልፃሉ፡፡

መንገድ ላይ ያሉ ጉዳዮችን እየተከታተለ መዝጋትና መድፈን የባለስልጣኑ ድርሻ ከመሆኑም በላይ ህብረተሰቡም ጥቆማ በመስጠት ሊተባበር ይገባል ያሉት ኢንጂነሩ፤ እስካሁን ወደ መስሪያቤታቸው “ጉዳት ደርሶብኛልና ካሳ ይገባኛል” የሚል አቤቱታ ይዞ የቀረበ ተጎጂ ባይኖርም እንዲህ ያለ አቤቱታ ከቀረበ መስሪያቤታቸው ኢንሹራንስ ገብቶም ቢሆን ማሳከም እንዳለበትና ተጠያቂ መሆን እንደሚችል ተናግረዋል፡፡

መንገድ ሲሰራ ከሰዎች ንክኪ ተከልሎ መሆን እንዳለበት የሚያስገነዝቡት ኢ/ር ፍቃዱ፤ ከዚህ አግባብ ውጪ የመንገድ ግንባታ ሲከናወን አደጋውን ያደረሰው ሥራ ተቋራጭ ከሆነ ባለስልጣኑ ተጠያቂ ይሆናል፡፡ አንዳንድ ተሽከርካሪዎች በእግረኛ መንገድ ላይ ወጥተው የፍሳሽ ማስተላለፊያ ቱቦ ክዳኖችን መስበራቸው ለጉድጓዶቹ መፈጠር መንስኤ ነው ያሉት ኃላፊው፤ በቀለበት መንገድ ላይ ያሉ የፍሳሽ ማስወገጃ ቱቦ የብረት ክዳኖችም በሌቦች መዘረፋቸው ለባለስልጣን መስሪያቤቱ ፈታኝ እየሆነ መምጣቱን ገልጸዋል፡፡ በዚህ ምክንያት ተሽከርካሪዎችና እግረኞች በጉድጓድ እየገቡ ከፍተኛ አደጋ እየደረሰባቸው እንደሚገኝ መረጃው አለን ያሉት ኢ/ር ፍቃዱ፤ ተጠያቂነትን የሚያሰፍን ጠንካራ የህግ አፈፃፀም ያስፈልጋል፤ ኅብረተሰቡም ጉድጓዶች ሲያጋጥሙት ለባለስልጣኑ መጠቆም አለበት ብለዋል፡፡

ችግሩን ለመቅረፍ የባለስልጣን መስሪያቤቱ ሰራተኞች የቱቦ ክዳኖችን ከፍተው ቆሻሻ ካፀዱ በኋላ በአፋጣኝ መልሰው እንዲደፍኑ፣ ኮንትራክተሮችም መንገድ ሲሰሩ ከልለው እንዲሰሩ ጥብቅ ትዕዛዝ እየተላለፈ መሆኑን ኢ/ሩ ገልፀዋል፡፡
ስሜ አይጠቀስ ያሉ አንድ የሕግ ባለሙያ፤ መንገድም ይሁን ህንፃ በአጠቃላይ የመሰረተ ልማት መዋቅር ሲሰራ በሰዎች ደህንነትና አካል ላይ ጉዳት በማያደርስ መልኩ መሆን እንዳለበት የወንጀለኛ መቅጫ ህጉ እንደሚደነግግ ጠቅሰው፤ የግንባታ ስራው ተጠናቅቆ አገልግሎት በመስጠት ላይ ባለ መንገድ ላይ ለሚደርስ ጉዳት የአዲስ አበባ መንገዶች ባለስልጣንና የኢትዮጵያ መንገዶች ባለስልጣን፣አደጋው የደረሰበት መንገድ ተጠቅሶ ክስ ሊቀርብባቸው ይችላል ብለዋል፡፡

በኮንስትራክሽን ሂደት ላይ ባለ መንገድ ውስጥ የደረሰ አደጋ ካጋጠመ ግን፣ ተጎጂው መንገዱን የሚያሠራውን ባለስልጣን መስሪያቤትና ሥራ ተቋራጩን በአንድነት በመጥቀስ ኃላፊነት ሊወስድ የሚገባውን አካል ፍ/ቤት ይወስንልኝ ብሎ ክስ ሊመሰርት እንደሚችል ባለሙያው አብራርተዋል። ይህ የክስ አቀራረብ ተመራጭ የሆነው፤ ሥራ ተቋራጩን መቆጣጠር ያለበት አሠሪው መስሪያ ቤት ስለሆነና በመካከላቸው ያለው ውል ስለማይታወቅ ነው ብለዋል፤ ባለሙያው፡፡

በእኛ ሀገር እንደ ልማድ ሆኖ መንገድ ሲሰራ የጥንቃቄ ምልክቶች እንደማይቀመጡ መታዘባቸውን የተናገሩት ባለሙያው፤ በአንዳንድ የሰለጠኑ ሀገሮች ከ5 ሜትር ርቀት ላይ ምልክቶችና አቅጣጫዎች እንደሚቀመጡ በመጠቆም በእኛም ሀገር ይህ አስገዳጅ ህግ ተፈፃሚ መደረግ አለበት ሲሉ ይመክራሉ፡፡ በቴሌ ኬብል ቀበራ ወቅት ጉድጓዶች ሳይከደኑ ከቀሩም የቴሌ መሆኑን በማረጋገጥ፣ አሊያም ፍ/ቤት ያጣራልኝ በማለት የመንገዶች ባለስልጣንና ቴሌን አጣምሮ ክስ መመስረት ይቻላል ብለዋል፡፡

በእኛ ሀገር የመንግሥት መስሪያ ቤቶችን በወንጀል መክሰስ (ኮርፖሬት ክሪሚናል ሊያቢሊቲ) በሚለው ፅንሰ ሐሳብ መነሻነት የወንጀለኛ መቅጫ ህጉ እንደሚከለክል የጠቆሙት የህግ ባለሙያው፤ ተጎጂው የደረሰበትን የጉዳት መጠን ጠቅሶ “ልካስ ይገባኛል” ብሎ የፍትሐብሔር ክስ ማቅረብ ይችላል ብለዋል፡፡ “መንግሥትን ከስሼ ካሣ አገኛለሁ” የሚለው ሐሳብ በራሱ በኛ ሀገር ካለመለመዱም በላይ በፍ/ቤቶች የተንዛዛ አሰራር ምክንያት ተጎጂዎች መብታቸውን እንዳያስከብሩ ዳተኛ ያደርጋል ያሉት ባለሙያው፤ ይህ ባህል መቀረፍ እንዳለበትና ሰዎች ሕጉ የሰጣቸውን መብት እንዲያስከብሩ አሳስበዋል።

በጉዳዩ ላይ የሚመለከታቸውን የአዲስ አበባ ውሃና ፍሳሽ አገልግሎት እና የአካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን መስሪያ ቤትን አስተያየት ለማካተት ያደረግነው ሙከራ ስልካቸው ባለመነሣቱ ሳይሳካ ቀርቷል፡፡

“የአገር ፍቅር ከየትኛውም ሽልማትና ሞገስ በላይ ነው”

March 31/2014



የአሜሪካ መንግሥት “የአፍሪካ ስኬታማ ወጣት መሪ” በሚል የሰማያዊ ፓርቲ ሊቀመንበር ኢንጅነር ይልቃል ጌትነት መርጦ ለመሸለም ጥሪ ማድረጉን የፓርቲው ልሳን ጋዜጣ ባለፈው ሳምንት ዘግቧል፡፡ በሌላ በኩል ከአሜሪካ ኤምባሲ በኩል የተገኙ መረጃዎች የሰማያዊ ፓርቲ መሪ የተመረጡት የአሜሪካ  ስቴት ዲፓርትመንት  በየዓመቱ ለሚያዘጋጀው የሊደርሺፕ ፕሮግራም እንጂ ለሽልማት አይደለም ይላሉ፡፡  የአዲስ አድማስ ጋዜጠኛ አበባየሁ ገበያው የፓርቲውን ሊቀመንበር ኢንጂነር ይልቃልን በጉዳዩና ኤርፖርት ላይ በገጠማቸው ችግር ዙርያ አነጋግራቸዋለች፡፡

ወደ አሜሪካ ለመጓዝ ኤርፖርት ከገቡ በኋላ ችግር እንደገጠመዎት ሰምቻለሁ፡፡ ችግሩ ምን ነበር?

በአሜሪካ መንግስት ተጋብዤ ለሶስት ሳምንት የምቆይበት “ወጣት የአፍሪካ መሪዎች” የሚል ፕሮግራም ነበር፡፡ በሉፍታንዛ ነበረ የምሄደው። በኤርፖርት ውስጥ አስፈላጊውን ሂደት ሁሉ አልፌ የኢሚግሬሽንና ደህንነት ሰዎች ፎቶ ወስደው ፓስፖርቴን ተቀበሉኝና አንደኛው አለቆቹ ጋር ይዞኝ ሄደ፡፡ ለሶስት ሰዓት ያህል አንድ ክፍል ውስጥ አቆዩኝ፡፡ መጨረሻ ላይ ከፓስፖርቴ ውስጥ አንድ ገፅ ነቅለው አውጥተው … “አንድ ገፅ ወጥታለች” ብሎ ቀዶ አመጣልኝ … እቃዬ አውሮፕላኑ ውስጥ ገብቶ ነበር፤ እሱንም አወረዱት፡፡ ባለፈው ሰኞ ነበር አሜሪካ መገኘት የነበረብኝ፤ ለጊዜው ተስተጓጉሏል።

የአሜሪካ መንግስት “የአፍሪካ ስኬታማ ወጣት መሪ” በሚል እንደሸለማችሁ ባለፈው ሳምንት በፓርቲያችሁ ልሳን ላይ ተዘግቧል፡፡ ሰማያዊ ፓርቲ ዕድሜው አጭር ከመሆኑ አንፃር ሽልማቱ ይገባናል ትላላችሁ?

ኢትዮጵያ ከዓለም የመጨረሻ ድሃ አገር ናት፡፡ አገሪቱን ከድህነት ለማውጣት የልጆቻችንን ዕድሜ የሚጠይቅ ተከታታይ ሥራ እና ትግል የሚያስፈልገው ነው፡፡ ሥራችንን የምትለኪው ግን በአንፃራዊነት ነው፡፡ ለምሳሌ ሰልፍ የሚባል ነገር ለስምንት አመት ኢትዮጵያ ውስጥ የማይታሰብ ነበር፡፡ አሁን ግን ሁሉም ፓርቲዎች ሰልፍና የአደባባይ የፖለቲካ ስራን እንደ ባህል እየያዙትና፤ እየተነቃቁም ናቸው። የሌሎች ፓርቲ አመራሮች “ህዝቡ ፈርቷል፤ ሰልፍ አይወጣም፣ አይተባበረንም” በሚል ዝም ብለው የመግለጫ ስራ ነበር የሚሰሩት፡፡ አሁን  ነገሮች ተለውጠዋል፡፡ አዲሱ ትውልድ በፊት ተከታይ እንጂ የራሱ ሀሳብ ኖሮት የሚሳተፍ አልነበረም። በሰማያዊ ፓርቲ ውስጥ ግን ሌት ተቀን የሚተጉ ሰዎችን ታያለሽ… እስከመታሰርም ደርሰዋል፡፡ ይህም የቅርብ ጊዜ ትዝታ ነው፡፡ የሚታየው የተፈጠረው የፖለቲካ መነቃቃትና ግንዛቤ ነው እንጂ የሀገራችንን ችግር ሰማያዊ ፓርቲ ፈትቶ ይጨርሰዋል ወይ ብትይ …. ትውልዱም የሚጨርሰው አይመስለኝም። ብዙ ተከታታይ ስራዎች ይጠይቃል፡፡ ከነበርንበት ጨለማ አንፃር ነው መታየት ያለበት፡፡ ቅንጅት በመፍረሱ ህዝቡ  ተስፋ ቆርጧል፡፡ ኢህአዴግ ጠቅላይ  በመሆኑና አፋኝ አዋጅ በመያዙ ዘላለማዊ ይመስል ነበር፡፡ ሰማያዊ ፓርቲ ያንን አስቸጋሪ ሁኔታ ወደ ይቻላል በማምጣትና መነቃቃት በመፍጠር የፖለቲካ ድባቡን ቀይሮታል፡፡ ይሄ ደግሞ ረጅም ጊዜንና ትልቅ ስራን የሚጠይቅ ነበር፡፡ ሰማያዊ ፓርቲ ግን በአጭር ጊዜ ይሄንን ማድረግ ችሏል፡፡ ከዚህ መንፈስ ነው የሚታየው እንጂ እኛ ብዙ ሰራን ብለን አንኩራራም፡፡ ገና ብዙ ስራ ነው የሚቀረን፤ ወደፊትም ብዙ እንሰራለን፡፡

ሰማያዊ ፓርቲ አሁን በዘረዘሩልኝ ምክንያቶች በአሜሪካ መንግስት “የአፍሪካ ስኬታማ ወጣት መሪ” በሚል ሸልሞታል፤ ሽልማቱም ይገባናል እያሉኝ ነው?

አዎ .. በደንብ ተሸልመናል፡፡ ሽልማቱም ይገባናል፡፡ ሽልማቱ ይገባናል ስንል ግን አሜሪካኖች አይደሉም የሚሸልሙንና የሚያወድሱን፡፡ ግን በራሳቸው መመዘኛ እኛን መምረጣቸው መልካም ነገር ነው፡፡ ሰማያዊ ፓርቲ የሚያድግ ፓርቲ ነው፡፡ በኢትዮጵያ 70 ከመቶ የሚሆነው ህዝብ ወጣት ነው፡፡ ወጣቱን ሊወክል የሚችል ፓርቲ ነው፡፡ አዲስ አስተሳሰብን እንደፈጠረ ሃይል፣ ሽልማትን አስበን አይደለም የምንሰራው፡፡ ከዚህ በላይ ለሃገራችን ብዙ መስራት ይጠበቅብናል፡፡

በየጊዜው የተለያዩ ፖለቲከኞች ለህዝብ የገቡትን ቃል ሳይፈጽሙ ሸርተት ይላሉ፡፡ ህዝቡን ከዚህ ዓይነቱ ጥርጣሬ እንዴት ማውጣት ይቻላል ይላሉ?

ህልም ተፈርቶ ሳይተኛ አይታደርም፡፡ ከዚህ በፊት ኢትዮጵያ ውስጥ በተደጋጋሚ ውጤት ያልመጣው የግለሰብ ፖለቲካ በመሆኑና ፖለቲካው በሰዎቹ ስብዕና ላይ በመመስረቱ ነበር፡፡ ይሄም ትግሉን ጎድቷል፡፡ ለዚህ መፍትሔው ትግሉን ህዝባዊ ማድረግና በአንድ ሰው ላይ አለመንጠልጠል ነው፡፡ ህዝቡ ፖለቲካውን የራሴ ነው ብሎ መያዝ አለበት፡፡ ግለሰቦች ሲሄዱ ሌሎች ይተካሉ፡፡

ኢትዮጵያ የወላድ መካን አይደለችም፤ ብዙ ልጆች አሏት፡፡ ፖለቲካውን የጋራ ካደረግነው የህዝቡ ስጋት ይቀንሳል፡፡ ፖለቲካ የዜግነት ጉዳይ ነው፤ ሁሉም መሳተፍ አለበት፡፡ ያ በሆነ ጊዜ ራሳቸውን ብቻ ለአገር ጠቃሚ አድርገው የሚያስቡ ሰዎች መመፃደቃቸውን ያቆማሉ፡፡ ያኔ መግነንም አምባገነንነትም ይጠፋል፡፡ ፓርቲውም ህዝባዊነት ይኖረዋል ማለት ነው፡፡ የሰማያዊ ፓርቲ ልጆች የትኛውም ቦታ ላይ ተወዳድረውና ሰርተው መኖር የሚችሉ ናቸው፡፡ በዚህ በአሰልቺና በተጠላ ፖለቲካ ውስጥ የገቡት የአገር ፍቅር ስላላቸው ነው፡፡ የአገር ፍቅር ደግሞ ከየትኛውም ሽልማትና ሞገስ በላይ ነው፡፡  

ከወር በፊት ለፓርቲ ሥራ ወደ አሜሪካና አውሮፓ ተጉዘው ነበር፡፡ የተለያዩ ስብሰባዎችንም ከዳያስፖራው ጋር አድርጋችኋል፡፡ በዚህ ጉዞ ዋና ዓላማችሁ ምን ነበር?

ሁለት ወር ነው የቆየሁት፤ አውሮፓ አስራ አምስት ቀን፣ አሜሪካ 45 ቀን ያህል፡፡ አትላንታ፣ ሳንሆዜ፣ ቦስተን፣ ላስቬጋስ፣ ሎስአንጀለስ፣ ሲያትል… ነበርኩ። የመጀመሪያ ስብሰባዬ ዲሲ ነበር፡፡ የስብሰባው ዓላማ ሰማያዊ ፓርቲ የተመሰረተባቸውን መሰረታዊ አላማዎችና ምሰሶዎችን ማስተዋወቅ ነበር፡፡ እዚህም አብዛኛውን ቅዳሜና እሁድ ምሁራንን ቢሮዋችን ውስጥ እየጋበዝን በፀረ ሽብር ህጉ፣ በመሬት ፖሊሲ፣ በአጠቃላይ በኢኮኖሚ በታሪካችን ዙሪያ በመወያየት ሰማያዊ ፓርቲ ያለውን አቋም ለህዝብ በተደጋጋሚ ይገልጽ፣ ያስተምር ነበር፡፡ የአሜሪካና አውሮፓ ጉዞ ዓላማ፣ በውጭ ያለው ኢትዮጵያዊ ለሰማያዊ ፓርቲ ሀሳቦችና ፕሮግራሞች ድጋፍ እንዲሰጥና የትግል ስልቶቻችንንም ጭምር ለማስተዋወቅ ነበር፡፡

ሰማያዊ ፓርቲ የቅስቀሳ ሀይል እንጂ ድርጅታዊ መዋቅር የለውም፤ የንቅናቄ ፓርቲ ነው፤ የበሰለ ፖለቲካ አያራምድም የሚል ትችት ይሰነዘርባችኋል? እርስዎ ምን ይላሉ?

የሞተን ፖለቲካ ልታነሺ የምትችይው፤ ህዝብ ሲከተልሽና መነቃቃትን መፍጠር የምትችይው የአገሪቱን ችግር በሚገባ መረዳት ሲቻል፣ ለዚያ ችግር መፍትሄ ሊሆን የሚችል ቀጥተኛ ፖሊሲ ሲኖር፣ ፖሊሲውን ለማስፈፀም ደግሞ ብቃት ያለው አመራር ሲኖር ነው ህዝቡ የሚነቃነቀው፡፡ በስልጣን ላይ የተቀመጡ ሰዎች ፖሊሲ አላቸው፤ ሰማያዊ ፓርቲዎች ግን ፖሊሲ የላቸውም ቢባል ለአመለካከት የማይመች ነው የሚሆነው፡፡ በመሰረቱ አንድ ሰው ሊነቃነቅ የሚችለው  የሚያምንበት ነገር ሲኖር ነው። መነቃነቅ ከተፈጠረ እምነት አለ፡፡

ተቃዋሚ ፓርቲዎች በህብረት ለመስራት የትብብርና የውህደት እንቅስቃሴ ላይ ቢሆኑም ሰማያዊ ፓርቲ ለውህደት ዳተኝነት ይታይበታል የሚል ትችት ይሰነዘርበታል…

በኢትዮጵያ የ40 ዓመት የፖለቲካ ፓርቲዎች ታሪክ “ዛሬ ተዋህደው፤ ነገ ፈረሱ” ሲባል ነው የምናውቀው፡፡ ይሄ እንዲቀጥል አንፈልግም፡፡ ስለዚህም የውህደትንና የጥምረትን ነገር በጥንቃቄ መመርመር እንፈልጋለን፡፡ በሆይሆይታ የሚፈጠሩ ጥምረቶችና ውህደቶች ውጤቱ ሲያመጡ አልታየም። ለምሳሌ አንድነት ወደ መድረክ የገባው በጣም ፈጥኖ ስለነበር ራሱን ጎድቷል፡፡ እናም አንድነት ከመድረክ ታገደ ተባለ፡፡ ሰላሳ ሶስት ፓርቲዎች ተቋቁመው ምንም ነገር ሳይፈይዱ ነው የከሰሙት። በቅርቡ ደግሞ “አንድነትና መኢአድ ለውህደት እየተነጋገሩ ነው” ሲባል ነበር፡፡ አሁን ደግሞ ተቋረጠ ተብሏል፡፡ እኛ ጥናት ሳይደረግ በፍጥነት ሮጠን ወደ ውህደት አንገባም፡፡ ወደ ፖለቲካው ያልገባ አዲሱ ትውልድ አለ፤ ፓርቲዎች አካባቢ ጊዜ ከምናጠፋ እዛ ላይ አተኩረን ህዝብ ውስጥ ብንሰራ ጉልበትም፣ ሀይልም፣ ዕውቀትም ገንዘብም አለ የሚል አቋም ይዘን ነው የምንንቀሳቀሰው፡፡ በመርህ ደረጃ ግን ከሌሎች ፓርቲዎች ጋር ለመስራት ሰማያዊ ፓርቲ ዝግጁ ነው፡፡

የምርጫ ስነ ምግባር ኮዱን አንፈርምም ብላችኋል፡፡ ለምንድነው ለመፈረም ያልፈለጋችሁት?

አንድ ህግ በሀገር ደረጃ ህግ ሆኖ ከወጣ በኋላ መፈረም አለመፈረም አስገዳጅ አይደለም፤ ትክክለኛም አሰራር አይደለም፡፡ ለምሳሌ የማናምንባቸው አዋጆች ሁሉ ወጥተዋል፡፡ የፀረ-ሽብር አዋጅ፣ የመሬት ሊዝ አዋጅ፣ የሲቪክ ማህበራት ማደራጃ፣ የሚዲያና የመረጃ ነፃነት አዋጅ ወጥተዋል፡፡ እነዚህን አዋጆች ሰማያዊ ፓርቲ አፋኝ አዋጆች ናቸው ብሎ ያምናል፡፡ ህግ ሆነው ከወጡ በኋላ ግን ህገመንግስታዊ በሆነ መንገድ እስከ ምንቀይራቸው ድረስ ለአዋጆቹ መገዛት ግዴታችን ነው፡፡ የስነ ምግባር ደንብና አዋጅ በፓርላማ ህግ ሆኖ ፀድቋል፤ ለእሱ ብቻ መፈረም አያስፈልግም። አዋጅ በወጣ ቁጥር እኮ አንፈርምም፡፡ አጀንዳ ሆኖም መቅረብ የለበትም፡፡ ኢህአዴግ ለድርድር እንቅፋት ለመፍጠር ሲፈልግ ያመጣው ነው፡፡