Wednesday, January 22, 2014

ፕሮፌሰሩ – ሰክነው ማዳመጥ ለሚችሉ መናገር ያስደስታቸዋል

January 22/2014

“ችግር ፈጣሪው አንድነት (ፓርቲ) ነው።”
beyene 1



ፕ/ር በየነ ጴጥሮስ የኢትዮጵያ ሶሻል ፓርቲና የደቡብ ህብረት ፓርቲ መሪ ናቸው። በግል የመድረክ መስራች ሲሆኑ፣ የሚመሩት ድርጅትም በመድረክ ጥላ ስር ከተሰባሰቡት ፖለቲካ ድርጅቶች መካከል ይገኝበታል። ፕ/ር በየነን ጨምሮ ላለፉት ሁለት አስርት ዓመታት ኢህአዴግን በመቃወም የሚታወቁ ፖለቲከኞች ተተኪ ፖለቲከኞች አላዘጋጁም በሚል ይወቀሳሉ። በዚህ ጉዳይ ስማቸው ከሚነሱት መካከል አንዱ ፕ/ር በየነ ናቸው። ፕ/ር በየነ አሜሪካ ለሥራ መምጣታቸውን ተከትሎ የጎልጉል ዘጋቢ ቃለ ምልልስ አድርጎላቸዋል። ፕ/ር በየነ በቃለ ምልልሳቸው ወቅት በተደጋጋሚ “እኔ የምናገረው ሰክነው ማዳመጥ ለሚችሉት ነው” በማለት ያሳስባሉ። ለምን?
ጎልጉል፡- ስለ መንግሥትና ተቃዋሚዎች እርቅ ጉዳይ ወሬ ይወራል የሰሙት ነገር አለ?
ፕ/ር በየነ፡- የለም። ምንም አልሰማሁም።
ጎልጉል፡- እርስዎ የሚመሩት ፓርቲ ጥያቄው አልቀረበለትም?
ፕ/ር በየነ፡- በፍጹም። በሚታወቅ ደረጃ ያነጋገረን አካል የለም። ማለቴ በድርጅት ወይም በአገር ደረጃ።
ጎልጉል፡- በግለሰብ ደረጃስ? ፖለቲካ የውትወታ (ሎቢ) ሥራ ነው ስለሚባል፤
ፕ/ር በየነ፡- በርግጥ በዚህ ደረጃ እንቅስቃሴ አለ። እኔ ሁሌም በሎቢ አምናለሁ። በ1997 ምርጫ ወቅት ያ ሁሉ እድል የተከፈተው በሎቢ ነው። በድካም ነው። እኔ ውስጡ ስለነበርኩ ሁሉንም አውቀዋለሁ። አስተውሎ መራመድና በሰከነ መንፈስ ከተሰራበት በሎቢ ብዙ ነገሮችን ማሳካት ይቻላል።
ጎልጉል፡- ግን እኮ 23 ዓመት ሞላ?
ፕ/ር በየነ፡- ቢሞላስ? ከእውነታዎች እንደምንረዳው በተለያዩ አገሮች 40ና 50 ዓመታት የፈጁ የትግል ተሞክሮዎች አሉ። ሎቢ በራሱ ብቻውን ትግል አይደለም። በሎቢ ብቻ ውጤት አይጠበቅም። ለሎቢ የሚያበቃና ሎቢ የምታደርጋቸውን ክፍሎች የምትማርክበት አግባብ ያስፈልጋል።beyene2
ጎልጉል፡- ግልጽ ቢያደርጉልኝ?
ፕ/ር በየነ፡- በየጠርዙ፣ በየጥጉ እየተፈለፈሉ ለኢትዮጵያ ህዝብ እናውቅልሃለን፣ መፍትሄህ ነን የሚሉ ድርጅቶች አሉ። ድርጅቶች መሪያቸውንና መስራቾቻቸውን ይመስላሉ። ሎቢ ስታደርግ ወይ በድርጅት አለያም በመሪነት ነው። ሎቢ ከፍተኛ ስብዕናና ደረጃን ይጠይቃል። በዚህ ደረጃ ስንለካ ፈተናውን ማለፍ አለብን።
ጎልጉል፡- ለሎቢ ፖለቲካ እንኳ የማይመጥን ተቃዋሚዎች አሉ እያሉ ነው?
ፕ/ር በየነ፡- ሁሉንም ማለቴ አይደለም። እኔ የምናገረው አጠቃላይ ጉዳይ ነው።
ጎልጉል፡- በሎቢ የሚፈጠር አንድም ነገር የለም። አሜሪካኖቹ ኢህአዴግን ስለሚደግፉ ሎቢ ጉንጭ አልፋ ነው፣ ጊዜም ይገድላል የሚሉ አሉ፤
ፕ/ር በየነ፦ ተመሳሳይ እምነት ሊኖር አይችልም። ሁሉም በሚያዋጣው መንገድ መሔድ ይችላል። እኔ ግን በሎቢ አምናለሁ። ማንንም አላኮርፍም። በማንም ላይ ቂም ይዤ አላፈገፍግም። ተስፋ ሳልቆርጥ ድሮም እንደማደርገው እገፋበታለሁ። አሜሪካኖች ኢህአዴግን ወደዋል፣ ፈልገዋል በማለት ዳር ሆኖ በመሳደብና በማንጓጠጥ ትርፍ አይገኝም። አንድ እውነት አለ። አሜሪካኖቹ ኢህአዴግን ይረዳሉ። ይደግፋሉ። ይህንን አደረጉ ማለት ግን ኢህአዴግን ወደዱ ማለት አይደለም። በተለይ በኢህአዴግ ፖለቲካ ተሰላችተዋል። ፍርሃቻም አላቸው። የዘር ፖለቲካ መጨረሻው ወዴት እንደሚያመራ ደቡብ ሱዳን እያሳየቻቸው ነው። ኢትዮጵያን ከራሳቸው መሰረታዊ አቋም አንጻር መክሰርም አይፈልጉም። ችግሩ ያለው ከኢህአዴግ እሻላለሁ ሲባል በሚጨበጥና በሚታይ ማሳመኛ መሆን አለበት። ሎቢ የምታደርጋቸው ክፍሎች ሚዛናቸው ላይ ሲያስቀምጡ ሞልቶ መገኘት ያስፈልጋል። አማራጭ ነኝ ሲባል የሚዛኑን ክብደት ማንሳትን ይጠይቃል።የውጪ ኃይሎችን ድጋፍና ተቀባይነት ማግኘት ትልቅ ድል ነው። ብዙ ጉዳዮች አሉ።
ጎልጉል፡- አሜሪካ ቆይተዋል?
ፕ/ር በየነ፡- አዎ ትንሽ ቆይቻለሁ።
ጎልጉል፡- የተቃዋሚ ፓርቲ አመራሮች ወደ አሜሪካ ሲመጡ ሚዲያዎች ላይ ይቀርባሉ። እርስዎ ግን ድምጽዎ አልተሰማም። ለምን?
ፕ/ር በየነ፡- መፈላለግን ይጠይቃል።
ጎልጉል፡- እንዴት?
ፕ/ር በየነ፡- ነገር ከሚገባቸውና ብቃቱ ካላቸው ዜጎች ጋር ነው የምውልው የሚል እምነት አለኝ።
ጎልጉል፡- ቅሬታ ያለዎት ይመስላል?
ፕ/ር በየነ፡- አስቀድሜ የገለጽኩ ይመስለኛል። የአዋዋልና የአረዳድ ጉዳይ ነው። ለኔ ቅርብ በሆኑ ሰዎች ሚዲያ ላይ እንድቀርብ ተጠይቄያለሁ። ግን ጥያቄ ያቀረቡት ክፍሎች በሚሄዱበት መስመር ለመሄድ ስለማልፈልግ ጥያቄው ለጊዜው እንዲቆየኝ አድርጌያለሁ።
ጎልጉል፡- ጥያቄ ቀርቧል እያሉ ነው? ለመሆኑ ከየትኛው ሚዲያ ነው?
ፕ/ር በየነ፡- በተለያዩ መንገዶች ጥያቄዎች ቀርቦልኛል። ያው በመተዋወቅ መንገድ። ይህንን ስል ክፍተት ልዩነት አለ በሚል ደረጃ የሚታይ አይደለም። በቃ የእምነት ጉዳይ ነው።
ጎልጉል፡- አንዳንድ ገለጻዎችዎ ማብራሪያ የሚጠይቁ ናቸው?
ፕ/ር በየነ፡- አስቀድሜ የገለጽኩ መሰለኝ። እኔ የምናገረው በሰከነ መንፈስ ለሚያዳምጡ፣ ከንዴትና ከስሜት ፖለቲካ ራሳቸውን ላቀቡት ነው። ለነዚህ ዜጎች መልዕክቴ ግልጽ ነው።
ጎልጉል፡- ይቆያሉ?
ፕ/ር በየነ፡- እስከ ሐምሌ (ጁላይ) እዚህ ነኝ።beyene_petros
ጎልጉል፡- አገር ቤት ያለውን ፖለቲካ ለጊዜው አቁመውታል ማለት ነው? የፖለቲካ እረፍት ወጡ?
ፕ/ር በየነ፡- ድርጅታችን መዋቅርና በየደረጃው ያሉ አመራሮች አሉት። በተቀመጠ እቅድ መሰረት ያከናውኑታል። በሳምንት ሲያስፈልግም በየቀኑ እንገናኛለን።
ጎልጉል፡- ዶ/ር ነጋሶ “በቃኝ” ብለዋል ሰምተው ከሆነ? እርስዎስ?
ፕ/ር በየነ፡- አንተ አረጀህ ካልከኝ እንጂ እኔ አላረጀሁም። ጤነኛ ነኝ። በደንብ አስባለሁ። እድሜዬም የዶ/ር ነጋሶን ያህል አይደለም። ራሴንም በግል መርጬ ወይም አስመርጬ አላውቅም። ርምጃን ምክንያታዊ በሆነ መንገድ የማውቅ ሰው እንደሆንኩ እረዳለሁ።
ጎልጉል፡- ስለዚህ ራስዎን ከፖለቲካ ስለ ማግለል አያስቡም ማለት ነው?
ፕ/ር በየነ፡- እኔ በቀላሉ ራሴን ከፖለቲካ ሰውሬ ገዳም ለማኖር መወሰን አልችልም። የምትታገልለትን ህዝብ ቃል ገብተህለት ለማን ጥለኸው ነው የምትሄደው? ልክ እኮ እንደ አንድ የሰራዊት መሪ ማለት ነው። ሰራዊቱን በትኖ ወደ ቤቱ የሚገባ!! 22 ዓመት ከታገልኩበት ህዝባዊና አገራዊ ዓላማ ለመገለል ራሴን ጡረታ የማወጣበት ምክንያት የለኝም።
ጎልጉል፡- 22 ዓመታት የተጓዘው የተቃዋሚዎች የፖለቲካ እንቅስቃሴ አድሮ ቃሪያ ነው እየተባለ ነው። ተስፋ ሰጪ ነገ የለም። እንዲያውም ኢህአዴግን ለማጀብ የተፈጠራችሁ እንደሆነ ተደርጎ አስተያየት ይሰጣል፤ እየተሰጠም ነው፣ ለዚህ ዋናው ምክንያት ምንድነው ይላሉ?
ፕ/ር በየነ፡- ተጨባጩ እውነታ ነው።
ጎልጉል ፡- እንዴት?
ፕ/ር በየነ፡- ወያኔ/ኢህአዴግ የሚባለው ቅድመ ዝግጅት ያደረገ ሃይል የአገሪቱን ሃብት፣ ፖሊስ፣ ደኅንነት፣ መከላከያ፣ አጠቃሎ ተቆጣጥሮ ከእኔ ሌላ ማንም ብቅ ካለ አጠፋለሁ ብሎ በመወሰን አገሪቱን ረግጦ መያዙ አንዱና ዋናው መሰረታዊ ችግር ነው። እንግዲህ …
ጎልጉል፡- ይህ የሚታወቅ ነው። ከናንተ በኩል ያለውን ችግር ቢነግሩኝ?
ፕ/ር በየነ፡- መነሻውን ለማስጨበጥ ነው። በገንዘብ፣ በጦር መሳሪያ፣ በቁሳዊ ነገር ይህንን ኃይል መብለጥና ማሸነፍ አይቻልም። ግን በሰብዓዊ ብቃት በልጦ መገኘት ይቻላል። በስዕብና ጥራት፣ በዓላማ ጽናት፣ ለራስ በመታመን፣ ቃል የገቡለትን ህዝብና መጪ ትውልድ በማሰብ ትግሉን ፍጹም ሰላማዊ በሆነ መንገድ ማጠንከር አልተቻለም። ኢህአዴግን እንፎካከራለን የምንለው ክፍሎች መሰረታዊ የስትራቴጂና የታክቲክ ጉዳዮችን መለየት አቅቶን የምንፈረካከስ፣ እርስ በርስ በመጋጨት ጊዜ የምንገድል፣ ቀላል ጉዳይ እንኳ ማለፍ የማንችል መሆናችን ለኢህአዴግ አመችቶታል። የሚያሳዝነው ከዚህ ተደጋጋሚ ጥፋት ትምህርት መውሰድ አለመቻሉ ነው። የመንቦጫረቅ ችግር አለ። አገራችን አንድ ተረት አለ።ለአውራነት/ለኮርማነት የታሰበው በሬ ተመልሶ እናቱን ጠባ ህዝብ ከሚጠብቀን ደረጃ ስንወርድ በተለያየ መልኩ ኪሳራችን ይበዛል ማለት ነው።
ጎልጉል፡- እሺ ምን ይደረግ?
ፕ/ር በየነ፡- ትንንሽ ጠርዝ በመያዝ የሚደረግ ትግል የትም አያደርስም። ይህን ማወቅ ያልቻሉ አሉ። ኢህአዴግ ትንንሽ ሲመሰረት ደስታው እጠፍ ድርብ ነው። ኢህአዴግ ስትደራጅና ስትገዝፍበት አይወድም። እኛ ደግሞ ለመግዘፍና ተደራጅቶ ለመቀጠል አልቻልንም። ቅድም የተነሳው ጥያቄ እዚህ ጋር ይመጣል። የፖለቲካው ስራ የዘመኑን ፖለቲካ መጫወት የሚችሉትን ክፍሎች ይፈልጋል። አሁን ባለው ተጨባጭ ሁኔታ ፖለቲካው አመራር አልባ ሆኗል። ሰው የለውም። ልሂቃኑ ዳር ቆመዋል። በአገራቸው ፖለቲካ መሳተፍ ሲገባቸው እኛን ይተቻሉ። የሞከርነውን ያወግዛሉ። ዳር ቆመው እኛን ከመተቸት ያለፈ አስተዋጽኦ የላቸውም። አገር ቤት በስፋት ያለው ችግር የተማረውና ዘመናዊውን ፖለቲካ ማራመድ የሚችለው ክፍል ዳር እንደቆመ መቅረቱ ሲሆን፣ ዲያስፖራውም በተመሳሳይ ተመሳሳይ ችግር አለበት።beyene petros
ጎልጉል፡- ዲያስፖራው ንቁ ተሳታፊ እንደሆነ ነው የሚነገረው?
ፕ/ር በየነ፡- ችግሩ አገር ቤት ጎልቶ ቢታይም በውጪ አገር በሚኖሩ ወገኖች ዘንድም በተመሳሳይ ይስተዋላል። ስሜታዊነት ትልቁ ችግር ነው። ከስሜት ብዛት መሰረታዊ ጉዳዮችን መለየት አለመቻልና ተስፋ የመቁረጥ ሁኔታ ይታያል። ግለሰቦችን በጀት መድቦና ጊዜ ሰውቶ ስማቸውን የማጥፋት ስራ ላይ መጠመድ አለ። ይህንን ተናገርክ ወይም አሰብክ ብሎ ሰውን ለመስደብና ሰብዕናውን ለማቆሸሽ ጊዜ ሰጥቶ በዘመቻ ይሰራል። ይህ ትልቁ በሽታ ነው። ለዚህ ሁሉ መፍትሄው መስከን ነው። ከስሜት ፖለቲካ መለየት ነው። አገር ልትበተን ነው፣ አገር ልትደማ ነው፣ ኢትዮጵያ አለቀላት፣ ወዘተ በሚል ተስፋ መቁረጥን በራሳችን ላይ በማወጅ ተጠቃሚ አንሆንም። መጥፎውን ብቻ በማሰብ የምንታገል ከሆነ ሩቅ ማየት ይሳነናል። ብስጩ ሆነን እንቀራለን።
ጎልጉል፡- ስለዚህ?
ፕ/ር በየነ፡- ፖለቲካ በባህሪው ክፍተትን አይወድምና አካኪ ዘራፍ ከማለት በመቆጠብ አብረን የምንሰለፍበትን መንገድ ለይተን ማወቅ ይገባናል። አለበለዚያ የፖለቲካው ሥራ እየተንቦጫረቀ ኢህአዴግን ከመጥቀም የዘለለ ፋይዳ አይኖረውም።  በግሌ ቀድሞውንም እንደማደርገው የሰከነ ፖለቲካ ከሚስባቸው፣ ከስሜታዊነት በጻዳ፣ ከተስፋ መቁረጥ በዘለለ ከሚሰሩት ጋር አጠናክሬ እሰራለሁ። መጪውን ምርጫ …
ጎልጉል፡- ስለ ምርጫው እናቆይና ስለመደራጀት ባነሱት ላይ የሚሰማ ተቃውሞ አለ። አብራችሁ መስራት አልቻላችሁም ትባላላችሁ። ቅንጅት ፈረሰ፣ አሁን ደግሞ መድረክም …
ፕ/ር በየነ፡- በርግጥ በመድረክ ደስተኛ አይደለሁም።
 ጎልጉል፡- ይቅርታ ስላቋረጥከዎት፣ ግን መድረክ አለ?
ፕ/ር በየነ፡- መድረክ አለ። አመራርም አለው። ስምንት ድርጅቶች ነበሩበት። ከ2010 (እኤአ) ምርጫ በኋላ ሁለቱ መቀጠል አልቻሉም። አሁን ስድስት ድርጅቶችን በአባልነት አሉበት።
ጎልጉል፡- ደስተኛ አይደለሁም ሲሉ?
ፕ/ር በየነ፡- በህብረትና በቅንጅት ስብስብ ውስጥ መፍረክረክርክ ተፈጠረ። ህዝብን አሰባስቦ የማታግል ጉዳይ ዋጋ አጣ። ጉዳዩ አሳሳቢ ስለነበር እንዴት እናድርግ በሚል ለጉዳዩ ትኩረት የሰጥን ወገኖች መጀመሪያ በግል፣ ቀጥሎ በድርጅት ደረጃ መድረክን ፈጠርን። ከሁለት ዓመት በላይ የተደከመበት ስራ ነው። ህብረትና ቅንጅትን ካገጠሟቸው ችግሮች በቂ ግንዛቤ ተወስዶ ነበር መድረክ የተቋቋመው። ከዚያ ሁሉ ድካም በኋላ አሁን የተፈጠረውን ሳስብ ያሳዝነኛል። እገረማለሁም።
ጎልጉል፡- እንዴት?
ፕ/ር በየነ፡- ከቀድሞው ስህተት ተምረን ትልቅ አገራዊ ዓላማ እናራምዳለን፣ ታግለን እናታግላለን፣ በማለት ተስማምተው በህግ ለመተዳደር ፊርማቸውን ያኖሩ ድርጅቶች ለገቡት ውል ተገዢ አንሆንም አሉ። የፈረሙበትን ውል አናውቀውም አሉ። አንድ ድርጅት ለህግ አልገዛም፣ ለፈረመበት ደንብ አልታዘዝም ካለ ጨዋታው ፈረሰ ማለት ነው። መድረክ ሲቋቋም ከ65 ገጽ በላይ የሚሆን ፕሮግራም ተቀርጾ ሁሉም አባል ድርጅቶች በራሳቸው ጉባኤ አጽድቀውት የተቀበሉት ነው። አንዳንዶቹ ላረቀቁት፣ ለተቀበሉትና በጉባኤ ወስደው ላጸደቁት ደንብ አንገዛም፤ አገር ግን እንመራለን እያሉን ነው።beyene4
ጎልጉል፡- እየከሰሱ ያሉት አንድነትን ነው?
ፕ/ር በየነ፡- አዎ። ምስጢር አይደለም። ችግር ፈጣሪው አንድነት ነው። በአደባባይ ችግራችንን ተነጋግረን የመድረክ የበላይ አመራሮች የወሰኑባቸውን ሰነዶች ይፋ አደረጉ። ይህ አግባብ አይደለም።
ጎልጉል፡- ስለዚህ ከአንድነት ምንም አልጠብቅም እያሉ ነው?
ፕ/ር በየነ፡- ራሳቸውን አስተካክለው ለመስራት ከፈለጉ ከአንድነት ሌላ የምመርጥበት ምክንያት የለኝም። ዋናው ለህግና ለደንብ መገዛት ነው። ከመድረክ የተሻለ ህዝባዊ አመኔታ ያለው ፓርቲ ያለ አይመስለኝም። በውስጡ ስላለሁ ሳይሆን እውነት ነው። ሌላ የተሻለ ድርጅት ካለ ሊገለጽ ይችላል።
ጎልጉል፡- ሕዝብ ተስፋ ይቆርጣል ብለው ያስባሉ?
ፕ/ር በየነ፡- ሕዝብ በመውደቅና በመነሳት ማመን አለበት። ሕዝብ ዓላማ ሊኖረው ይገባል። ተቃዋሚዎች ጥፋት ብናጠፋም ስልጣን ላይ ሆነን ህዝብን የበደልን አይደለንም። ወይም ስልጣን ላይ ተቀምጠን ክህደት አልፈጸምንም። ወደ ተስፋ መቁረጥ የሚያመራ ሁኔታ የለም። የልሂቃኑ ወደ ፓለቲካው አለመግባትና ባገራቸው ጉዳይ ዳር ቆመው ለመኖር መወሰናቸው ሊታሰብበት ይገባል። ኢትዮጵያና ልጆቿ ከነሱ ብዙ ይጠብቃሉ።
ጎልጉል፡- ኢህአዴግ በተለያዩ ሚዲያዎችና በመሪዎቹ ህዝብ በተቃዋሚ ፓርቲዎች መንገሽገሹን እየገለጹ ናቸው፤
ፕ/ር በየነ፡- ይህ የኢህአዴግ አሉባልታ ውድቅ ነው። የሚያስተናግደውም ያለ አይመስለኝም። ወያኔ በራሱ ከተማመነ ምርጫውን ክፍትማድረግ ነው። ህዝቡ ተቃዋሚዎችን የማይመርጥ ከሆነ የአንድ ለአምስት አደረጃጀት ለምን አስፈለገ? ቤተሰብ ድረስ ዘለቀ የደህንነት ሰንሰለት ለምን ዘረጉ? ህዝብን በስለላ ማስጨነቅን ምን አመጣው? ሚዲያዎቹ እግረ መንገዳቸውን እነዚህን ጥያቄዎች መጠየቅ ቢችሉ መልካም ነበር። የተፈጠሩበት ባህሪ ስለማይፈቅድላቸው እነሱን ጨምሮ ለውጥ ፈላጊዎች ናቸው። ህዝብ እኮ መምረጥ እንደሚችል ሲነገረው ማንን እንደሚፈልግ አሳይቶ ድምጹን በኃይል ነው የተነጠቀው። ምርጫ ሲመጣ ህዝብ ድምጹን የሚሰረቀው ለምንድነው? እንዲህ ያለውን የኢህአዴግ አሉባልታ ዋጋ የሌለው ተራ ነገር ነው።
ጎልጉል፡- እርስዎ እንዳሉት ኢህአዴግ የመፎካከሪያ መንገዱን ስለዘጋ፣ በተቃዋሚዎች በኩል አገር ቤት ያለው ትግል ውጤት ማምጣት ባለመቻሉ የኃይል አማራጭ ይሻላል? በማለት የተነሱ አሉ። ምን አስተያየት አለዎት?
ፕ/ር በየነ፡- በስሜታዊነትና አገር ውስጥ ባለው የፖለቲካ ምህዳር ጠበበ በሚል አሁን ባለንበት ወቅት ለአገሬ ጦርነት አልመኝም። እኔ የምመራቸው ድርጅቶችም አይቀበሉትም። በጦርነት ለውጥ ሊመጣ ቢችልም አስተማማኝ አይደለም። ጦርነት የሁለት የጎበዝ አለቆች ጸብ ነው። ወያኔ ነፍጥ ይዞ በረሃ ገባ። ስልጣን ሲይዝ የገባውን ቃል አላከበረም። የኢትዮጵያ ህዝብ ካለው ልምድ የተነሳ ነፍጥ አንስተው የሚታገሉትን የሚያምን አይመስለኝም። በነፍጥ ስልጣን ይዞ ለህዝብ ያስረከበ የለም። በብዙ መልኩ ብክነት ነው።
ጎልጉል፡- በሰላማዊ መንገድ ኢህአዴግን ማስወገድ ካልተቻለ ምን ይደረግ? የሰላማዊ ትግሉን ቁልፎች ኢህአዴግ ብቻውን ይዞታል። እድሜ ከመቁጠር የዘለለ የሚገኝ ነገር የለምና ጦርነት ወቅታዊው አማራጭ ነው የሚሉ አሉ፣
ፕ/ር በየነ፡- አስቀድሜ ባግባቡ የመለስኩ መሰለኝ። ፈጥኖ ተስፋ የመቁረጡ ችግር ወደ አካኪ ዘራፍ ትግል ያዛውራል። ከስሜት በመራቅ በርጋታ ለሚያስቡት ነው የምናገረው ያልኩት ለዚህ ነው። የሰላማዊውን ትግል ለራሳችን ክብር በመስጠት፣ ስብዕናችንን ዝቅ ሳናደርግ፣ ህዝብና መጪውን የልጅ ልጅ ትውልድ እያየን በጽናት ብናከናውነው ውጤታማ ነው። ኢህአዴግም የሚፈራው ይህንን ትግል ነው።
ጎልጉል፡- ከመጪው ምርጫ ለውጥ ይጠብቃሉ?
ፕ/ር በየነ፡- እንግዲህ እኛ ለውጥ እንዲመጣ እየሰራን ነው። ወደ ምርጫ ከመግባታችን በፊት የ1997 ዓ.ም. ዓይነት ሁኔታ እንዲፈጠር እየሰራን ነው። ከምዕራብ አገሮችና ከአሜሪካ ጋር በቀጣዩ ምርጫ የዲፕሎማሲ ስራ ጀምረናል። ከኢህአዴግም ጋር ለመደራደር እንፈልጋለን። ቀጣዩ ምርጫ የተሻለ እንዲሆን እንጥራለን። ለውጥ የሚኖረው ይመስለናል። መጀመሪያ ላይ እንደገለጽኩት በኢህአዴግ የውስጥ ፖለቲካ ምቾት የሌላቸው ተበራክተዋል። ይህንን እንደ ዕድል ለመጠቀም በሎቢ ስራ ላይ ነን። ይህንን ካመቻቸን የደጋፊና የመራጭ ችግር የለብንም።
ጎልጉል፡- ኢህአዴግ በተለይም ህወሃት ውስጥ ከመለስ ሞት በኋላ ውስጡ ችግር ነግሷል። ሊፈራርስ ነው ይባላል? እንደ አንድ ታዛቢ ምን መልስ አለዎት?
ፕ/ር በየነ፡- ከስሜት የሚመነጭ ግምት ልክ አይሆንም። ግምት ሲበላሽ ትግልም መስመሩን ይስታል። በስሜት የተነሳ የትግሉ መስመር ከሳተ አደጋው ዘመንን ሊሻገር ይችላል። በስሜት ፖለቲካና ትግል ውስጥ የሚከሰተው ተስፋ መቁረጥ ደግሞ ከባድ ነው። በመለስ ሞትና በህወሃት ጉዳይ የየዋህነት ፖለቲካ ባንከተል የተሻለ ነው። በማንኛውም የፖለቲካ ስራ ውስጥ ውይይትና ንግግር አለ። ክርክሮችንና ውይይቶችን ወደ መሐል የሚያመጣ ሰው ሊኖር ይችላል። ከዚህ አንጻር መለስ ቀዳሚ ሊሆኑ ይችላሉ። ያ ማለት አሁን ሰው የለም ማለት አይደለም። ህወሃቶች አሁን ያላቸውን የኢኮኖሚ የበላይነት ማስጠበቅ የሚችሉት ሲስማሙ ብቻ እንደሆነ ያውቃሉ። አሁን ያሉበት ደረጃና ስሜታቸው ጨምሯል። ከፍተኛ ሃብት አላቸው። ህወሃት ይህንን ሃብት ይዞ ለመቆየት የፖለቲካው የበላይነት ያስፈልገዋል። ስለዚህ የፖለቲካውን የበላይነት አሳልፎ ለመስጠት እርስ በርስ ይጣላሉ ብሎ መገመት ለኔ የዋህነት ነው። ራስን ማታለል ነው። የመከላከያ ሃይሉ ህዋሃት የሚገጥመውን ማንኛውን ችግር ለመታደግ ተቋጭቶ የተሰራ ነው። የወታደራዊ ኢንዱስትሪው ከፍተኛ ጡንቻ አለው። የደኅንነቱንና የፖሊሱን ኃይል በተመሳሳይ በሚያመቻቸው መልኩ ገንብተውታል። ስለዚህ ዝም ብሎ ኢህአዴግ በጉምጉምታ ይናዳል ብሎ ማሰብ አግባብ አይመስለኝም። ያሳስተናል። የተሳሳተ ግምትና መረጃ ጉዳቱ ለራስ ነው።beyene_petros
ጎልጉል ፡- ወደ ፊት የሚያስፈራዎት ነገር አለ?
ፕ/ር በየነ፡- በኢትዮጵያ ነጻ ምርጫ እንዳይካሄድ አፍኖ መያዝ ተስፋ የሚያስቆርጣቸውን ክፍሎች እያበዛ አገሪቱ ሙሉ በሙሉ ችግር ውስጥ እንዳትገባ እፈራለሁ። በአገሪቱ የፖለቲካ አካሄድ ውስጥ የሚገፉና የሚታፈኑ በበረከቱ ቁጥር እምቢተኛነት ይነሳል። እንዲህ ያለው ነገር ከተነሳ አደገኛ ነው።
ጎልጉል፡- ምን መልዕክት አለዎት? ለማን?
ፕ/ር በየነ፡- በአገራችን ዘመናዊውን ፖለቲካ የመምራት ብቃት ያላቸው ወገኖች ዳር ቆመው መመልከታቸውን እስካላቆሙ ድረስ ለውጥ ለማምጣት ቀላል አይሆንም። የሰላማዊው ትግል ብቃት ያላቸውን ክፍሎችና ልዩ ቃል ኪዳን የተላበሱ አገር ወዳዶችን ያሻዋል። አገሪቱ እንዲህ አይነት ስብዕና ያላቸው ሰዎች ድሃ አይደለችምና ልጆቿ ሊታደጓት ይገባል። ጡረታ እንድንወጣ የሚወተውቱን፣ ጥለን የት እንሂድ በሚል ተቸግረን እንደሆነ በመረዳት እነዚህ ወገኖች /ልሂቃኑን/ ወደ ፖለቲካው ተሳትፎ ፊታቸውን እንዲያመሩ ሊገፋፉዋቸው ያስፈልጋል። ሚዲያውም ላዲስ ሃሳብና ላዳዲስ ባለ ራዕዮች ልዩ ትኩረት በመስጠት ሊሰራ ይገባዋል። አልሰማም ያሉትንም የማሳሰብና የመውቀስ ተግባር ከሚዲያ ይጠበቃል። ዲያስፖራውም ድጋፍ ሲያደርግ በስሜት ሳይሆን በሰከነ አእምሮ በማሰብ ሊሆን ይገባዋል። ከንዴትና ከብሶት የጸዳ ፖለቲካ የሚያራምዱ ክፍሎች እንዲበዙ መስራት ይገባዋል። ስለ ድጋፍ ሲነሳ ዲያስፖራው የሚሰጠውን እገዛ ማንሳት ተገቢ ነው። የዲያስፖራው ድጋፍ ሚዛን በማይደፉ መስፈርቶችና ወገንተኛነት ላይ እንዲያተኩር ተደርጓል። ይህ መለወጥ አለበት።
ጎልጉል፡- ኸርማን ኮኽን በቅርቡ ይፋ ስላደረጉት የኢትዮጵያና የኤርትራ እርቅ ጉዳይ ምን ይላሉ?
ፕ/ር በየነ፡- እርቅ ደግ ነው። ከኤርትራ ጋር የሚደረገው እርቅ ግን የፖለቲካ መሪዎች ተራ መጨባበጥና የነሱን ፍላጎት ብቻ ያሟላ መሆን የለበትም። እርቁ የአልጀርስን ስምምነት በቅድሚያ ተግባራዊ ከማድረግ እንደሚጀምር ነው ኮኽን የተናገረው። በደብዳቤ ውስጥ ከዚህ ዘለለ ቁም ነገር አላየሁበትም። የአልጀርስ ስምምነት ሲባል ባድመን አሳልፎ የሚሰጥ፣ ኢትዮጵያን በርካታ መሬት እንድታጣ የሚያደርጋት ነው። ከዚህ አንጻር ስጋት አለኝ። ፓርላማ በነበርኩበት ወቅት እንዳልኩት ጉዳዩ ጥንቃቄ ያሻዋል። ስለዚህ አዲስ ድርድር ከተደረገም ሰጥቶ በመቀበል መርህ አትራፊ በሚያደርግ መልኩ ሊሆን ይገባል።
ጎልጉል፡- በሰጡት አስተያየት ላይ ተቃውሞ እንደሚገጥምዎት ያስባሉ?
ፕ/ር በየነ፡- በመጀመሪያ ለማን እንደምናገርና አውቃለሁ። እኔ የተናገርኩት በግል የማምንበትንና በድርጅት አቋማችን የሆነውን ነው። ሃሳብ ላይ ተንተርሶ መከራከርና መነጋገር ይቻላል። ሃሳብ ላይ ያላተኮረ ተራ ዘለፋና ትችት ዋጋ የለውም። ከዚህ ሌላ በየነ ይህንን አለ በማለት የዘመቻ ወቀሳ ከተሰነዘረ የምለው ነገር የለም። በጨዋነት ለሚቀርብ የሃሳብ ተቃውሞ ግን የሚቀርበውን ሃሳብ ሰምቼ መልስ ልሰጥ እችላለሁ። ይሄ አሁን የተለመደው አይነት ተራ የስም ማጥፋትና ማቆሸሽ ዘመቻ ግን የመጨረሻው እድገታችን መሆኑ ያሳዝነኛል። ብዙ ነገር እያየን ነው። ሰው ለማቆሸሽና ስም ለማጥፋት ጊዜና ገንዘብ እየባከነ ነው።
ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ 

አንባ ገነኑን የወያኔን መንግስት በቃ ልንለው ይገባል (ገዛኸኝ አበበ ከኖርዌይ )

ከገዛኸኝ አበበ
January 22/2014

ማብቄያ የሌለው የወያኔ አረመናዌ ድርጊት ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ በመጣበት በዚህ ጊዜ ሰሞኑን ለእራሴ አንድ ጥያቄ ጠየቁትኝ እስከመቼ ነው የወያኔ መቀለጃ እና መጫወቻ ሆነን የምንኖረው እስከመቼ ነው ወያኔ ህዝባችንን እያሰቃየ እና እየጨቆነ የሚኖረው እስከመቼ ነው ዜጓች መብታቸው ታፍኖና ነጻነታቸው ተረግጦ በሃገራቸው መብታቸው ሳይከበር እንደ ዜጋ ሳይሆን እንደ ሁለተኛ ዜጋ እየተቋጠሩ የሚኖሮት እኔ እንደማስበው በአሁኑ ጊዜ ሀገራችንን እየመራ ያለው የወያኔ መንግስት  ኢትዮጵያንና ኢትዮጵያውነትን ሊያጠፋ የተነሳ መንግስት ይመስለኛል ግን እስከ መቼ ነው የወያኔ ኢህአዲግ መንግስት በዚህ ርኩስ ባህሪውና ድርጊቱ የሚቀጥለው ? በቃልንለው ይገባል::

መቼም ይህ ጥያቄ የሁላችንም ሀገር ወዳድ እና ነጻነት ናፋቂ ኢትዮጵያኖች ጥያቄ ይሆናል ብዬ አስባለው እስከመቼ _?

 እኛ ኢትዮጵያኖች መብታችን ተረግጦ  ነጻነታችን ተገፎ በዲሞክራሲ ቸነፈር ተመተን መኖር ከጀመርን ይኸው ከድፍን ሁለት አስር አመታቶች በላይ አስቆጠርን በእነዚህ  ዓመታቶች ብዙዎች ለዲሞክራሲ፤ ለፍትህና ለነፃነት ታግለዋል አሁንም ቡዙዎች በሚችሉት መንገድ ሁሉ ይኼ ዘረኛውን እና አንባ ገነኑን የወያኔን መንግስት እየተፋለሙት ይገኛሉ::ነገር ግን ለዲሞክራሲ፤ ለፍትህና ለነፃነት የታገሉ ብዙዎች  በብዙ ሺህ የሚቆጠሩ  ዜጎች አልቀዋል፤ ለስደትም ተዳርገው ለብዙ መከራ ሰለባ ሆነዋል፡፡ ቁጥራቸው እጅግ ብዙ የሆነ የሀገሪቷ ዜጓች ደግሞ በአሁኑ ሰዓት በሀገሪቱ በሚገኙ እስር ቤቶች ታስረው በወያኔ ካድሬዎች ጭካኔ የተሞላበት ኢ ሰበአዊ ድርጊት እየተፈጸመባቸው በሰቃይ እና በመከራ ውስጥ ሲገኙ አንዳንዶቹም በሚደርስባቸው ስቃይ እና በወያኔ መጥፎ ሴራ እዛው ወህኒ ቤት ውስጥ እይውታቸው እያለፈ ይገኛል:: ለዚህ ማሰረጃ የሚሆነን  በቅርቡ ከጅጅጋ 25 ኪሜ ገደማ እርቃ በምትገኘው ቀብሪበያህ እስር ቤት ውስጥ የሞቱት ከ40 በላይ የሚሆኑ ንጹሃን ኢትዮጵያ ዜጓቻችን ምስክር ነው:: አረ ስንቱ ይዘረዘራል የወያኔ መንግስት በኢትዮጵያ ህዝብ ላይ እያደረሰ ያለው በደል ቢዘረዘር ማለቂያ የለውም :: ወያኔ በስልጣን በቆየባቸው በእነዚህ አመታቶች ከጊዜ ወደ ጊዜ ነገሮች መሻሻል እና መስተካከል ሲገባቸው ነገሮች ሁሉ በተገላቢጦሽ  እስራቱ፣ግድያው፣ስደቱ፣ድህነቱ ፣ ሁሉ ነገር እየባሰ እና ከጊዜ ወደ ጊዚ እየጨመረ መምጣቱ ሀገራችን ኢትዮጵያ በጣም አሳሳቤና አስጌ  ሁኔታ ላይ እንደምትገኝ አመልካች ነገር ነው::

ወያኔዎች እኔ ከሞትኩኝ ሰርዶ አይብቀል እንደሚባለው  የሀገሬቱን ሀብት እየዘረፉ እና እየቦጠቦጦ እንዳሻቸው መኖርን አልበቃም ብሏቸው ቅንጣትም ያክል ስለ ኢትዮጵያም ቢሆን ስለ ኢትዮጵያዊነት ግድ እንደሌላቸው በሚያሳይ መንገድ  በማን አለብኝነትና በግድ የለሽነት  ለግል እና ለእራሳቸው የፖለቲካ ጥቅም ቀደምት አባቶቻችን ለሀገራችን ዳር ድንበር መስዋዕት የሆኑለትን እና ደማቸውን ያፈሰሱለትን መሬታችንን ድንበራችንን እንኮን ሳይቀር ለባህድ አገራት በመስጠት ላይ እንዳሉ ሲሰማ ማንንም ኢትዮጵያዊ የሆነ ዜጋ ሁሉ የሚያስቆጣ እና የሚያንገበግብ ነው ብዬ አስባለው:: በጣም የሚገርመው እና የሚያሳዝነው ነገር ወያኔዎች  የገዛ ወገኖቻችንን የሀገሪቱን ዜጓች ሀብት እና ንብረት ካፈሩበት ሀገርና መሬት ላይ ሀብትና ንብረታቸውን እየዘረፉና ቤታቸውን እየፈረሱ ከሚኖሩበት ቄዬ እያባረሩ ለውጭ አገር ሰዎች ደግሞ የሀገሬቷን መሬት እየቸበቸቡ መኖርን የለመዱበት ተግባራቸው መሆኑ ነው :: 

እያደር ብዙ ይሰማል እንደሚባለው የወያኔን መንግስት  አሁንም ዝም ካልነው ሌላ ብዙ አስርት የመከራ አመታትን መጋፈጥ ሊኖርብን ነው፡፡ እስከመቼ ዝም እንደ ምንለው ግን ወገን አይገባኝም ፡፡ ወያኔ እያደረገው ስላለው አረመናዊ ድርጊቶ ፋታ ልንሰጠው አይገባም ::  አሁንም ህፃን፤ ወጣት፤  ጐልምሳና አዛውንት ወገኖቻችን ሲረግፍ፤ ሲሰደዱ ፣ የኢትዮጵያ ገጽታ ሲበላሽና ፣ በደምና በአጥንት መስዋዕትነት ተከብሮ የቆየውን የሃገራችንን ዳር ድንበር የወያኔ መንግስት ለባዕድ አሳልፎ ሲሰጥ ማየት ከሆነ ህልማችን መልካም! ግን ይህንን የሚያልምም ሆነ የሚመኝ ንፁህ ኢትዮጵያዊ ያለ አይመስለኝም፤ ከራሳቸው ከወያኔ ሆድደር ካድሬዎች በስተቀር፡፡ ስለዚህ ወገኔ ሆይ ይህንን መንግስት ዝም ብለን ልናየው አይገባም፡፡ ወይም እንደ ፈለገ ሊፈነጭብን ቦታ መስጠት የለብንም፡፡ እስካሁን በኢትዮጵያ ህዝብ ላይ ያደረሰው ጭቆናና በደል እንዲያውም በምን አለብኝነት የኢትዮጵያን ቅርጽ እና ታሪክ የሚያበላሸውን የወያኔ እንቅስቃሴ  ሁሉም የኢትዮጵያ ዜጋ ዘር፣ ጎሳና ፆታ ሳይለይ ኢትዮጵያንና ኢትዮጵያውነትን እያጠፋ ባለው በወያኔ መንግስት ላይ ሆ ብለን በአንድነት በመነሳትና በመጮህ ይበቃል ልንለው እና ልናስቆመው  የግድ ነው፡፡ 

በቃ በቃ በቃ !!!

      ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኖራለች!!!

ማብቄያ የሌለውን የወያኔ ግፍና በደል ልናስቆመው ይገባል (ገዛኸኝ አበበ ከኖርዌይ )

ከገዛኸኝ አበበ

January 22/2014







ማብቄያ የሌለው የወያኔ አረመናዌ ድርጊት ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ በመጣበት በዚህ ጊዜ ሰሞኑን ለእራሴ አንድ ጥያቄ ጠየቁትኝ እስከመቼ ነው የወያኔ መቀለጃ እና መጫወቻ ሆነን የምንኖረው እስከመቼ ነው ወያኔ ህዝባችንን እያሰቃየ እና እየጨቆነ የሚኖረው እስከመቼ ነው ዜጓች መብታቸው ታፍኖና ነጻነታቸው ተረግጦ በሃገራቸው መብታቸው ሳይከበር እንደ ዜጋ ሳይሆን እንደ ሁለተኛ ዜጋ እየተቋጠሩ የሚኖሮት እኔ እንደማስበው በአሁኑ ጊዜ ሀገራችንን እየመራ ያለው የወያኔ መንግስት  ኢትዮጵያንና ኢትዮጵያውነትን ሊያጠፋ የተነሳ መንግስት ይመስለኛል ግን እስከ መቼ ነው የወያኔ ኢህአዲግ መንግስት በዚህ ርኩስ ባህሪውና ድርጊቱ የሚቀጥለው ?

መቼም ይህ ጥያቄ የሁላችንም ሀገር ወዳድ እና ነጻነት ናፋቂ ኢትዮጵያኖች ጥያቄ ይሆናል ብዬ አስባለው እስከመቼ _?

 እኛ ኢትዮጵያኖች መብታችን ተረግጦ  ነጻነታችን ተገፎ በዲሞክራሲ ቸነፈር ተመተን መኖር ከጀመርን ይኸው ከድፍን ሁለት አስር አመታቶች በላይ አስቆጠርን በእነዚህ  ዓመታቶች ብዙዎች ለዲሞክራሲ፤ ለፍትህና ለነፃነት ታግለዋል አሁንም ቡዙዎች በሚችሉት መንገድ ሁሉ ይኼ ዘረኛውን እና አንባ ገነኑን የወያኔን መንግስት እየተፋለሙት ይገኛሉ::ነገር ግን ለዲሞክራሲ፤ ለፍትህና ለነፃነት የታገሉ ብዙዎች  በብዙ ሺህ የሚቆጠሩ  ዜጎች አልቀዋል፤ ለስደትም ተዳርገው ለብዙ መከራ ሰለባ ሆነዋል፡፡ ቁጥራቸው እጅግ ብዙ የሆነ የሀገሪቷ ዜጓች ደግሞ በአሁኑ ሰዓት በሀገሪቱ በሚገኙ እስር ቤቶች ታስረው በወያኔ ካድሬዎች ጭካኔ የተሞላበት ኢ ሰበአዊ ድርጊት እየተፈጸመባቸው በሰቃይ እና በመከራ ውስጥ ሲገኙ አንዳንዶቹም በሚደርስባቸው ስቃይ እና በወያኔ መጥፎ ሴራ እዛው ወህኒ ቤት ውስጥ እይውታቸው እያለፈ ይገኛል:: ለዚህ ማሰረጃ የሚሆነን  በቅርቡ ከጅጅጋ 25 ኪሜ ገደማ እርቃ በምትገኘው ቀብሪበያህ እስር ቤት ውስጥ የሞቱት ከ40 በላይ የሚሆኑ ንጹሃን ኢትዮጵያ ዜጓቻችን ምስክር ነው:: አረ ስንቱ ይዘረዘራል የወያኔ መንግስት በኢትዮጵያ ህዝብ ላይ እያደረሰ ያለው በደል ቢዘረዘር ማለቂያ የለውም :: ወያኔ በስልጣን በቆየባቸው በእነዚህ አመታቶች ከጊዜ ወደ ጊዜ ነገሮች መሻሻል እና መስተካከል ሲገባቸው ነገሮች ሁሉ በተገላቢጦሽ  እስራቱ፣ግድያው፣ስደቱ፣ድህነቱ ፣ ሁሉ ነገር እየባሰ እና ከጊዜ ወደ ጊዚ እየጨመረ መምጣቱ ሀገራችን ኢትዮጵያ በጣም አሳሳቤና አስጌ  ሁኔታ ላይ እንደምትገኝ አመልካች ነገር ነው::

ወያኔዎች እኔ ከሞትኩኝ ሰርዶ አይብቀል እንደሚባለው  የሀገሬቱን ሀብት እየዘረፉ እና እየቦጠቦጦ እንዳሻቸው መኖርን አልበቃም ብሏቸው ቅንጣትም ያክል ስለ ኢትዮጵያም ቢሆን ስለ ኢትዮጵያዊነት ግድ እንደሌላቸው በሚያሳይ መንገድ  በማን አለብኝነትና በግድ የለሽነት  ለግል እና ለእራሳቸው የፖለቲካ ጥቅም ቀደምት አባቶቻችን ለሀገራችን ዳር ድንበር መስዋዕት የሆኑለትን እና ደማቸውን ያፈሰሱለትን መሬታችንን ድንበራችንን እንኮን ሳይቀር ለባህድ አገራት በመስጠት ላይ እንዳሉ ሲሰማ ማንንም ኢትዮጵያዊ የሆነ ዜጋ ሁሉ የሚያስቆጣ እና የሚያንገበግብ ነው ብዬ አስባለው:: በጣም የሚገርመው እና የሚያሳዝነው ነገር ወያኔዎች  የገዛ ወገኖቻችንን የሀገሪቱን ዜጓች ሀብት እና ንብረት ካፈሩበት ሀገርና መሬት ላይ ሀብትና ንብረታቸውን እየዘረፉና ቤታቸውን እየፈረሱ ከሚኖሩበት ቄዬ እያባረሩ ለውጭ አገር ሰዎች ደግሞ የሀገሬቷን መሬት እየቸበቸቡ መኖርን የለመዱበት ተግባራቸው መሆኑ ነው :: 

እያደር ብዙ ይሰማል እንደሚባለው የወያኔን መንግስት  አሁንም ዝም ካልነው ሌላ ብዙ አስርት የመከራ አመታትን መጋፈጥ ሊኖርብን ነው፡፡ እስከመቼ ዝም እንደ ምንለው ግን ወገን አይገባኝም ፡፡ ወያኔ እያደረገው ስላለው አረመናዊ ድርጊቶ ፋታ ልንሰጠው አይገባም ::  አሁንም ህፃን፤ ወጣት፤  ጐልምሳና አዛውንት ወገኖቻችን ሲረግፍ፤ ሲሰደዱ ፣ የኢትዮጵያ ገጽታ ሲበላሽና ፣ በደምና በአጥንት መስዋዕትነት ተከብሮ የቆየውን የሃገራችንን ዳር ድንበር የወያኔ መንግስት ለባዕድ አሳልፎ ሲሰጥ ማየት ከሆነ ህልማችን መልካም! ግን ይህንን የሚያልምም ሆነ የሚመኝ ንፁህ ኢትዮጵያዊ ያለ አይመስለኝም፤ ከራሳቸው ከወያኔ ሆድደር ካድሬዎች በስተቀር፡፡ ስለዚህ ወገኔ ሆይ ይህንን መንግስት ዝም ብለን ልናየው አይገባም፡፡ ወይም እንደ ፈለገ ሊፈነጭብን ቦታ መስጠት የለብንም፡፡ እስካሁን በኢትዮጵያ ህዝብ ላይ ያደረሰው ጭቆናና በደል እንዲያውም በምን አለብኝነት የኢትዮጵያን ቅርጽ እና ታሪክ የሚያበላሸውን የወያኔ እንቅስቃሴ  ሁሉም የኢትዮጵያ ዜጋ ዘር፣ ጎሳና ፆታ ሳይለይ ኢትዮጵያንና ኢትዮጵያውነትን እያጠፋ ባለው በወያኔ መንግስት ላይ ሆ ብለን በአንድነት በመነሳትና በመጮህ ይበቃል ልንለው እና ልናስቆመው  የግድ ነው፡፡ 

በቃ በቃ በቃ !!!

      ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኖራለች!!!

አዲስ እየተሰራ ያለው የቡሻና ባእታ ለማርያም ገዳም ለጥምቀት እለት በእሳት ጋየ

January22/2014

 ጥር 10 ቀን 2006 ዓ.ም ታቦተ ሕጉ ወደ ባሕረ ጥምቀት ከወጣ በኋላ ከሆሳዕና ከተማ 30 ኪ.ሜ ርቀት ላይ የሚገኘው እና አዲስ በመሰራት ላይ ያለው የቡሻና በአታ ለማርያም ገዳም

በአፅራረ ቤተ ክርስቲያን እንዲህ በእሳት ወድሟል ፡፡በሃገሪቱ ውስጥ ሃይማኖታዊ ሂደቶች በህገ እግዚአብሄር ደንብ እንዲጓዝ የማያደርገው ይሄው የወያኔ መንግስት እንደነዚህ አይነቶች ታሪካዊ ገዳማት እና መስኪዶች  እንዲጠፉ በማድረግ ያላሰለሰ ጥረቱን በማድረግ ቀጥሎአል ።በሃገራችን ኢትዮጵያ  በዚች ሃገር የኦርቶዶክስ ተዋህዶ ሃይማኖት የተሰነዘረው ጥቃት የትየለሌ ነው  ፡፡ በየቀኑ ሶቆቃ በየቀኑ ለቅሶ በየቀኑ መጥፎ ልብን የሚሰበር ዜና እየተነገረ እና እመንቱን ከህብረተሰቡ ልብ ዘንድ ለማውጣት ታቅዶ የተነሳ መንግስት መሆኑን ይታወቃል ። የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ሃይማኖት የአማራው ህዝብ ብቻ መስሎአቸው የሚዘክሩት የወያኔ ባለስልጣናት እና አመራር አካላቶች  ኦርቶዶክስ ከአማራው ኢጅ መንምኖ ወጥቶአል ሲሉ መናገራቸው የሚታወስ ነው ከዚህም በፊት አቦይ ስብሃት ይህንን ቃል በድጋሚ መናገራቸውን ይታወሳል ።


Human Rights Watch WORLD REPORT 2014 – Ethiopian – ”The Semayawi Party (“Blue Party”), a newcomer to Ethiopia’s political scene, held a peaceful protest in June—the first large-scale protest organized by a political opposition party in eight years.”

January 21/2014

Hopes that Ethiopia’s new leadership would pursue human rights reforms following Prime Minister Meles Zenawi’s death in August 2012 have been shattered; there was no tangible change of policy in 2013. Instead, the Ethiopian authorities continue to severely restrict the rights to freedom of expression, association, and peaceful assembly, using repressive laws to constrain civil society and independent media, and target individuals with politically motivated prosecutions.
Muslim protests against perceived government interference in their religious affairs were met by security forces with arbitrary arrests and detentions, beatings, and other mistreatment throughout the year. The trial of 29 protest leaders who were arrested in July 2012 has been closed to the public, media, and family members since January. Others convicted under the country’s deeply flawed antiterrorism law—including opposition leaders and four journalists—remain in prison.
Image
Ethiopia’s ambitious development schemes, funded from domestic revenue sources and foreign assistance, sometimes displace indigenous communities without appropriate consultation or any compensation. Security forces have also used violence, threats, and intimidation to force some groups to relocate, such as in the Lower Omo Valley where indigenous people continue to be displaced from their traditional lands, which are earmarked for state-run irrigated sugar plantations.
Freedom of Peaceful Assembly
Since early 2012, members of Ethiopia’s Muslim community—which constitutes at least 30 percent of the country’s population—have organized regular public protests. Demonstrations were triggered by perceived government interference in the Supreme Council of Islamic Affairs and the Awalia mosque in Addis Ababa.
The government has clamped down heavily on the protests, arbitrarily detaining and beating protesters, including 29 prominent activists and leaders who were arrested in July 2012 and charged in October 2012 under the Anti-Terrorism Proclamation. In January, the High Court closed those hearings to the public, including media, diplomats, and family members. Some defendants have alleged mistreatment in detention and the trials raise a number of due process concerns, including lack of access to legal counsel for some defendants for almost two months, and erratic access to relatives.
The government has also undermined the defendants’ presumption of innocence by broadcasting inflammatory material and accusations against them on state television. In February, the state-run Ethiopian Television (ETV) broadcast a program called “Jihadawi Harakat” (“Jihad War”) that included footage of at least five of the defendants filmed in pretrial detention. The program equated the Muslim protest movement with Islamist extremist groups, casting the protest leaders as terrorists.
Despite the arrests, protests continued throughout 2013. In early August, protests were organized in the capital, Addis Ababa, as well as in other cities to commemorate Eid al Fitr, the end of Ramadan. Witnesses described a heavy police presence in Addis Ababa, and credible sources said that police used excessive force to disperse the demonstrators and detained hundreds, at least temporarily.
The Semayawi Party (“Blue Party”), a newcomer to Ethiopia’s political scene, held a peaceful protest in June—the first large-scale protest organized by a political opposition party in eight years. A planned protest in August was cancelled when the Blue Party offices were raided by security forces, resulting in the arrest of dozens of people and the confiscation of equipment. The Blue Party had earlier been denied a permit by government to hold the protest.
Arbitrary Detention and Ill-Treatment
Arbitrary detention and ill-treatment in detention continues to be a major problem. Students, members of opposition groups, journalists, peaceful protesters, and others seeking to express their rights to freedom of assembly, expression, or association are frequently detained arbitrarily.
Ill-treatment is often reported by people detained for political reasons, particularly in Addis Ababa’s Federal Police Crime Investigation Center, known as Maekelawi, where most individuals are held during pre-charge or pretrial detention. Abuse and coercion that in some cases amount to torture and other ill-treatment are used to extract information, confessions, and statements from detainees.
Individuals are often denied access to legal counsel, particularly during pre-charge detention. Mistreated detainees have little recourse in the courts and there is no regular access to prisons and detention centers by independent investigators. Although the government-affiliated Ethiopian Human Rights Commission has visited some detainees and detention centers, there is no regular monitoring by any independent human rights or other organizations.
In July, a delegation from the European Parliament was denied access to Kaliti prison in Addis Ababa by Ethiopian authorities, despite having received prior authorization.
Freedom of Expression and Association
Since 2009, when the Anti-Terrorism Proclamation and the Charities and Societies Proclamation (CSO Law) were passed, freedoms of expression and association have been severely restricted in Ethiopia. The CSO law is one of the most draconian laws regulating nongovernmental activity in the world. It bars work on human rights, good governance, conflict resolution, and advocacy on the rights of women, children, and people with disabilities if organizations receive more than 10 percent of their funds from foreign sources.
Ethiopia’s most reputable human rights groups have either dramatically scaled down their operations or removed human rights from their mandates. Several of the country’s most prominent human rights activists have fled the country due to threats.
Ethiopian media remains under a tight government stranglehold, and many journalists practice self-censorship. Webpages and blogs critical of the government are regularly blocked, and foreign radio and TV stations are routinely jammed. Journalists working for independent domestic newspapers continue to face regular harassment and threats.
The Anti-Terrorism Proclamation has been used to target political opponents, stifle dissent, and silence journalists. In May, the Supreme Court upheld the 18-year sentence of journalist and blogger Eskinder Nega Fenta, who was convicted in July 2012 for conspiracy to commit terrorist acts and participation in a terrorist organization. Eskinder received the PEN Freedom to Write award in 2012. Reeyot Alemu Gobebo, a journalist for Feteh, was convicted on three counts under the terrorism law for her writings. Her sentence was reduced from 14 to 5 years on appeal, but her appeal of the remaining five-year sentence was dismissed in January. Reeyot was awarded the prestigious 2013 UNESCO/Guillermo Cano World Press Freedom Prize.
Journalists covering the Muslim protests were threatened and arbitrarily detained. Solomon Kebede, chief editor of the now-defunct Yemuslimoch Guday (“Muslim Affairs”), was arrested in January and charged under the Anti-Terrorism Proclamation. Yusuf Getachew, his predecessor, was charged under the same law in 2012. Several other journalists fled Ethiopia in 2013, making it one of the top three countries in the world in terms of the number of journalists in exile.
Forced Displacement Associated with Development Programs
Both the government of Ethiopia and the donor community have failed to adequately investigate allegations of abuses associated with Ethiopia’s “villagization program.” Under this program, 1.5 million rural people are being relocated, ostensibly to improve their access to basic services. However, some of the relocations in the first year of the program in Gambella region were accompanied by violence, including beatings and arbitrary arrests, and insufficient consultation and compensation.
On July 12, the World Bank’s board of executive directors approved the recommendation of the Inspection Panel, the institution’s independent accountability mechanism, to investigate a complaint from ethnic Anuak refugees alleging that the bank violated its own safeguards in Gambella. The investigation was ongoing at time of writing.
Ethiopia is proceeding with development of a sugar plantation in the Lower Omo Valley, clearing 245,000 hectares of land that is home to 200,000 indigenous peoples. Displaced from their ancestral lands, these agro-pastoralists are being moved to permanent villages under the villagization program.
Key International Actors
Ethiopia enjoys warm relations with foreign donors and most of its regional neighbors. Ethiopia has forged strong ties based on its role as the seat of the African Union (AU), its contribution to United Nations peacekeeping, security partnerships with Western nations, and its progress on some of the Millennium Development Goals (MDGs). These strong relationships have contributed to the international community’s silence on Ethiopia’s dismal human rights record.
The year 2013 saw Ethiopia continue to play a mediation role between Sudan and South Sudan, while its troops maintained an uneasy calm in the disputed Abyei region. Ethiopia continues to deploy its troops inside Somalia, but outside the AU mission.
Ethiopia also continues to receive significant amounts of donor assistance—almost US$4 billion in 2013. As partners in Ethiopia’s development, donor nations remain muted in their criticism of Ethiopia’s appalling human rights record and are taking little meaningful action to investigate allegations of abuses associated with development programs.
Relations with Egypt worsened in 2013 due to Egyptian concerns that Ethiopia’s Grand Renaissance Dam will divert valuable water from the Nile River. An estimated 85 percent of the Nile’s waters originate in the Ethiopian highlands and Egypt is completely dependent on the Nile for all its water needs. At 6,000 megawatts of electricity, the dam will be Africa’s largest hydroelectric project. Construction started in 2012 and the dam is scheduled to be completed in 2018.
In addition to Western donors, China, India, and Brazil are increasingly financing a variety of large-scale development initiatives. Foreign private investment into Ethiopia is increasing with agro-business, hydroelectric, mining, and oil exploration all gaining prominence in 2013. Agro-business investment is coming mainly from India, the Gulf, and the Ethiopian diaspora, attracted to very low land prices and labor costs. As seen in several of Ethiopia’s other large-scale development projects, there is a serious risk of forced displacement of people from their land when some of these programs are implemented. 

አዲሱ የብሮድካስት ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ሹመት በግል ጋዜጦች ላይ ለሚወሰደው እርምጃ አመላካች ነው ተባለ

January21/2014

ጥር ፲፫ (አስራ ሦስት) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የኢትዮጵያ ራዲዮና ቴሌቪዥን ድርጅት ዋና ዳይሬክተር የነበሩት የቀድሞ የህወሃት ታጋይ አቶ ዘርዓይ አስገዶምየኢትዮጵኢያ ብሮድካስት ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር በመሆን መሾማቸው መንግስት ከምርጫ 2007 በፊት በፕሬሱ ላይ ለሚወስዳቸው እርምጃዎች ጠንካራ አስፈጻሚ በማስፈለጉ ሊሆን እንደሚችል ኢቲቪን የለቀቁ አንዳንድ ጋዜጠኞች ተናገሩ።


የአቶ ዘርዓይ ከቴሌቪዥን ዳይሬክተርነት መነሳት በአቶ በረከት ስምኦን ምትክ የድርጅቱ ቦርድ ሊቀመንበር ሆነው ከወራት በፊት ከተሾሙት አቶ ሬድዋን ሁሴን ጋር አንዳንድ ወገኞች እያገናኙት መሆኑ ስህሀት ነው ይላሉ ጋዜጠኞቹ።  በተለይ በቀጣዩ አንድ ዓመት በአስተዳደራዊ መልኩ ከሕትመት እንዲወጡ ለማድረግ የታሰቡ ጋዜጦችና መጽሄቶችን ጉዳይ ለማሳካት ቁርጠኝነት እንዳላቸው በመገመት አቶ ዘርአይ መሾማቸውን ይናገራሉ፡፡

አቶ ዘርዓይ በባህርያቸው ግትርና አምባገነን መሆናቸውን ያስታወሱት ጋዜጠኞች፣ ከዚህ ቀደም ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናት በዴሞክራሲ ተቋማት ጉዳይ ላይ ያደረጉት ውይይት ከዕውቅናየ ውጪ እንዲቆራረጥ ተደርጓል በሚል በአንድ የግል ጋዜጣ ተቃውሞ ያቀረበውን አንድ ጋዜጠኛ ያለምንም ማንገራገር ከድርጅቱ እንዲሰናበት ማድረጋቸው የአምባገነንነታቸው አንድ መገለጫ ነው ሲሉ ጋዜጠኞቹ ያወሳሉ።

የኢቴቪ ባልደረባ የሆነ አንድ ጋዜጠኛ ለአዲስ አበባው ዘጋቢ እንደተናገረው አቶ ዘርዓይን እንደዋና ስራ አስኪያጅ በቀላሉአግኝቶ ማነጋገር፣ችግርን ማስረዳት ለሰራተኞች እንኩዋን የሚቻል አለመሆኑን በመጥቀስ ወደእሳቸው ቢሮ ከመግባትጠ/ሚኒስትሩ ቢሮ መግባት ይቀል ነበር ብሎአል፡፡

በእሳቸው አመራር ዘመን በድርጅቱ ጋዜጠኞችና የማስታወቂያ ባለሙያዎች ሳይቀር የኪራይሰብሳቢነት ዝንባሌ ገዝፎ መታየቱን፣ በተለይ የእሳቸው ተከታይ የሆኑ  ጋዜጠኞች ቢያጠፉ እንኩዋን አይቶ ዝም ከማለት ያለፈ እርምጃ አይወስዱም ነበር ብለዋል፡፡
አቶ በረከት ስምኦን የቦርድ ሰብሳቢ በነበሩበት ዓመታት ከአቶ ዘርዓይ ጋር መግባባት እንዳልነበራቸውና ለዚህ ምክንያቱ ደግሞ አቶ ዘርዓይ ታዛዥነታቸው ከማንም ይልቅ ለህወሃት ሰዎች ብቻ በመሆኑ ነው ሲሉ ጋዜጠኞች ይናገራሉ፡፡ በዚህ ምክንያት አቶ በረከት አዛዡን ማንሳትም፣ መቃወምም ተቸግረው መቆየታቸውን ጋዜጠኛው ተናግሯል።

የአቶ ደስታው ከብሮድካስት ባለስልጣን ዳሬክተርነት ሲነሱ ምናልባት በራሱ የሚተማመን ፣ሕግና ስርዓትን ብቻ አክብሮ የሚሰራ ተሹዋሚ ሊመጣ ይችላል የሚለውን ጭላንጭል ተስፋ የአቶ ዘርዓይ ሹመት እንደሻረው ጋዜጠኛው አክሎ ተናግሯል።

Tuesday, January 21, 2014

እጁን በብረት ቀጥቅጠው የሰበሩት ኢትዮጵያዊ ስደተኛ

January 21/2014
በግሩም ተ/ሀይማኖት

ሰነዓ ቁጭ ብዬ የሰዎችን ስቃይ ከመስማት በዘለለ ምንም ልፈይድ አለመቻሌ ሁሌም ይሰማኛል፡፡ አሁን አሁን ደግሞ በየጊዜው ከጅቡቲ፣ ከሶማሊያ በባህር ተሻግረው ወደ የመን የሚገቡትን በብዙ ሺህ የሚቆጠሩ ኢትዮጵያዊያን ስደተኞች እንደ በፊቱ ባይበዛም ይመጣሉ፡፡ በፊት ይዘው ሳዩዋቸው የነበሩት አፋኞችም፡፡ ስራቸውን በተጠናከረ መልኩ ተያይዘውታል፡፡ አፍነው እያሰቃዩ ገንዘብ አስልኩ ማለቱን ቀጥለዋል፡፡ እዚህ ቪዲዮ ላይ የሚታየውም እዛ ጉዳት የደረሰበት ሰው ነው፡፡

ብህሩን ከተሸገሩ በኋላ ወደ ሳዑዲ ጉዞው የማይሆን ሲሆን ወደ ሰነዓ ይገባሉ፡፡ ታዲያ የየመን መንግስት እስረኛ ስለበዛበት በቦታ እና አቅም ማነስ ምክንያት ቶሎ አይቀበሏቸውም፡፡ በዚህ ጊዜእስር ቤቱ ጊቢ በር ላይ ይተኛሉ፡፡ ብርዱ፣ ርገቡ፣ መጸዳጃ ቦታ ማጣቱና ልብስ የሌላቸው መሆኑ አንገብገቢ ችግር ሆነ፡፡

የቻልኩትን ያህል ለማድረግ ጥረት ሳደርግ ከጎኔ የተሰለፉ ጥቂት ሰዎች ነበሩ፡፡ አሁን ደግሞ የልጅነት ጓደኛዬ ካሳሁን የሺጥላ የቻለውን ያህል ለመርዳት ከጎኔ ሆኗል፡፡ የኩዌቱ ውዳጄ ነዛር ዳጊም እኔስ ወገኔን በሚል በጎኔ መሰለፉ ቢያስደሰተኝም ሁሌም በስደተኞች ጉዳይ ከኩዌት ድምጹን የሚያሰማ ወዳጄ ነው፡፡ ካሳሁን የሺጥላንም ሆነ ንዛር ዳጊን ከልብ የማመሰግነው በርሃብ ተጠርዘው በብርድ ተቆልተው መንገድ ዳር ወድቀው ባሉ ስደተኛ ወንድምና እህቶቼ ስም ነው፡፡

ይሄንኑ ተልዕኮዬን ለመፈጸም ሰነዓ ኢሚግሬሽን እስር ቤት በረ ላይ ያሉትን ለማጠየቅ በሄድኩበት ጊዜ አንድ ሰው አገኘሁ፡፡ ከዚህ በፊት ተደጋጋሚ እንደዘገብኩት የመን ውስጥ ባሉ ስደተኞችን አፍነው በማሰቃየት ገንዘብ ከቤተሰብ፣ ወዳጅ ዘመድ እንዲያስልኩ የሚያደርጉት ሰዎች እእ ላይ ወደቀ፡፡ ስልክ ቀጥር አምጣና ደውለን እንዲልኩ እናድርግ ብለው ሲየሰቃዩት በብረት ትከሻው ላይ ምን ያህል ጉዳት እነንዳደረሱበት እያሳየኝ ነው፡፡ የሚያሳዝነው ግን ይህን ያደረrገው ኢትዮጵያዊ የአፋኞቹ ተቀጣሪ እንደሆነ ነው የሚናገረው፡: ሺዲዮውን ይመልከቱ






በርካታ ሙስሊሞች “ሕዝብን ለሽብር ቀስቅሻለሁ” ብላችሁ እመኑ በሚል በእስር ቤት እየተገረፉ መሆኑ ተዘገበ

January 21 /72014

ህወሐት መራሹ የኢትዮጽያ መንግስት ሕዝበ ሙስሊሙ ላይ የሚወስደውን እርምጃ አጠናክሮ እንደቀጠለ ነው ሲል ቢቢኤን ራድዮ ዘገበ። እንደ ራድዮው ዘገባ ከኢዱ ጅምላ ጭፍጨፋ ቡኋላ መንግስት ልዩ ግብረ ኃይል በማቋቋም በአ/አበባ በወልቂጤ እንዲሁም በአዳማ ከተማዎች ላይ የሚገኙ መስጂድ የሚያዘወትሩ ወጣቶችን ከየቦታው አፍኖ በመውሰድ በአገራችን ጏንታናሞ ማእከላዊ እስር ቤት ውስጥ “ሕዝብን ለሽብር ቀስቅሻለሁ” ብላችሁ እመኑ እየተባሉ ቀን ከሌት የስቃይ አይነት ሲያስቆጥራችው ከርሞ ጥር 7 2006 ቁጥራቸው 16 የሚደርሱ ወጣቶችን የወያኔ ፋሽን የሆነውን የሽብርተኝነት ክስ መስርቶ ወደ ቂሊንጦ (ሒጅራ ኮምፓውንድ ) አዛውሯቸዋል::




(ፎቶ ፋይል )


ራድዮው ዘገባውን ቀጥሎ ”አሁንም የስቃይ መአት እየተቀበሉ ያሉ ወንድሞች ደግሞ ዛሬም እዛው ማእከላዊ ይገኛሉ፤ ምንም በማያውቁት ወንጀል የተከሰሱ ወንድሞቻቸው ላይ በግድ እንዲህ ሲያደርጉ ነበር ብላችሁ መስክሩ ተብለው ነው የሚሰቃዩት” ካለ በኋላ በስቃይ ላይ ያሉትን ስም ይጠቅሳል።

1ኛ አብዱላሂ ከሊል፣ ከጀርመን መስጂድ የተያዘ፤
2ኛ. መስፍን ገብሬ (ሀቢብ) ከቄራ መስጂድ
3ኛ. ኡመር ሹክረላህ ከኮልፌ አካባቢ
4ኛ ሙጅብ አሚኖ ናቸው።

“ማንኛውም በሕግ ጥላ ስር የሚገኝ ዜጋ ከሕጋዊ ጠበቃውና ከቤተሰቡ ጋር መገናኘ ትእንደሚችል ወረቀት ላይ ብቻ የቀረው ህገ መንግስት ቢገልፅም መንግስትም ሁሌም በህግ ስም ሲምል ሲገስፅ ቢውል ቢያድርም ለነዚህ እና ለብዙ ዜጎች ሹፈት ሆኖባቸዋል ጠበቃ እንዳያገኛቸው “ጠበቃ አያስፈልገንም “በሉ ተብለው ብቻ የሚደርስባቸው የስቃይ በትር ለአእምሮ ይከብዳል::” ያለው የቢቢኤን ዘገባ ከዚህ ሁሉ የከፋው እውነት ‘ማንኛውም ኢትዮጵያዊ በባህሉ በሃይማኖቱ ተከብሮና የፈለገውን እምነትና አስተሳሰብ ማራመድ ይችላል’ የሚለውን የሕገ መንግስት ማእዘን ገደል የከተተው እርምጃ ወንድማችን መስፍን ገብሬ (ሀቢብ) ላይ የሚደርሰው ‘ለምን ሰለምክ?’ እየተባለ በማእከላዊ ገራፊዎች የሚደርስበት ስቃይ ነው” ብሏል። ራድዮው በመጨረሻም “ይህ ወንድማችን የሁለት ልጆች አባት ሲሆን ከመስከረም10 ቀን ጀምሮ ማእከላዊ እየተሰቃየ ይገኛል፤ እነዚህን ወንድሞች ከጎናቸው ልንቆም ይገባል፤ እንዲሁም የሚደርስባቸውን ኢሰብአዊ ድርጊት ሁላችንም ለማጋለጥ እንነሳ” ሲል መልዕክቱን አስተላልፏል።


 ዘ -ሐበሻ

“ነፃነታችንን መልሱልን!?”

January 21/2014

ከተመስገን ደሳለኝ

 የኢህአዴግ መራሹ መንግስት ‹መዝገበ ቃላት› ለነፃነት የሚሰጠው ትርጓሜ ‹አራምደዋለሁ› ከሚለው ግራ-ዘመሙ አብዮታዊ ዲሞክራሲ ብያኔ አንፃር የሚተነተን በመሆኑ፣ የየትኛውም ተቋም ነፃ ሆኖ የመንቀሳቀስ መብት ላይ ረዣዥም እጆቹን ደጋግሞ እየጫነ ሲጨፈልቅና ሲያስጨፈልቅ ለመኖሩ በርካታ ማሳዎችን ማቅረብ ይቻላል፡፡ ይሁንና ከብዙዎቹ መሀል ለጊዜው የእምነት ተቋማት የነፃነት ወሰን እስከ ምን ድረስ ነው? የሚለውንተጠየቅ በተለይም ከሁለቱ ታላላቅ ሃይማኖቶች (ክርስትና እና እስልምና) አንፃር ተራ በተራ ከፈተሽን በኋላ ተቋማቱን ከእንዲህ አይነቱ ወደ ቅርቃር ከሚገፋ ፈተና የሚታደጋቸውን ብቸኛ የመውጫ መንገድ ለማስታወስ እሞክራለሁ፡፡

      ‹‹እስልምናን መቆጣጠር››

ካለፉት ጥቂት ዓመታት ወዲህ ገዥው ፓርቲ እስልምናን ሙሉ ለሙሉ የመቆጣጠር እቅዱን ዳር ለማድረስ ያልፈነቀለው ድንጋይ፣ 
የአልማሰው ሥር እንዳልነበር ጥቂት የማይባሉ ምልክቶችን አይተናል፡፡ ለምሳሌነትም የቅርቡ በተለምዶ ‹‹የአወሊያ ንቅናቄ›› ተብሎ የሚጠቀሰው ሕዝባዊ ተቃውሞ በቂ ይመስለኛል፡፡ ይህ እንቅስቃሴ (ንቅናቄ) ለመጀመሪያ ጊዜ አደባባይ የወጣው፣ መንግስት የእምነትተቋሙን በማያፈናፍን መልኩ ለመቆጣጠር በፌደራል ጉዳዮች ሚኒስቴር ፊት-አውራሪነት ያለአንዳች ይሉኝታ (የብዙሃኑን የእምነቱ ተከታዮች ይሁንታ ሳያገኝ) ‹‹አህባሽ›› የተሰኘ አስተምህሮ በድፍረት ለመጫን ከሞከረባቸው ጊዜያት አንስቶ ባደረጋቸው ተከታታይ ጣልቃ-ገብነቶች ሳቢያ ነው ወደሚል ድምዳሜ ከሚያደርሱን ምክንያቶች ዋነኛው ሆኖ ይነሳል፡፡ ለመንደርደሪያነት ያህልም የተቃውሞውን ጅማሮ በአዲስ መስመር በጨረፍታ እንዳስሰው፡:

 …ለንቅናቄው መነሾ የሆነው በወቅቱ የመጅሊሱ የአመራር አባል የነበሩት ጀማል መሀመድ፣ ለእምነቱ ብቸኛ የሆነውን ሚሲዮናዊ 
አወሊያ ትምህርት ቤትን በተመለከተ ታሕሳስ 21 ቀን 2004 ዓ.ም ላይ የላኩት ደብዳቤ ነው፤ የደብዳቤው ጭብጥም በርካታ የመስጂድ ኢማሞች፣ መምህራን እና የአረብኛ ተማሪዎች መባረራቸውን የሚያረዳ እንደነበረ አይዘነጋም፡፡

 የመጅሊስ አመራርን ‹ፖለቲካዊ ክንድ› ፈርጣማነት በሚያሳብቅ መልኩ የተሰናዳው ይህ ደብዳቤ የቀሰቀሰው ቁጣ፣ ሕዝበ-ሙስሊሙ ለዓመታት አምቆት የነበረውን ብሶት ሊያፈነዳና በርካታ የመብት ጥያቄዎቹን እንዲያነሳ መግፍኤ ይሆናል ብሎ አስቀድሞ የገመተ ያለ አይመስለኝም፤ የሆነው ግን ይህ ነበር፡፡ የእምነት ነፃነት እንዲከበር ሶስት መሰረታዊ ጭብጦችን የያዙት ጥያቄዎችም፡- ‹‹የመጅሊስ 
አመራሮች አይወክሉንምና ወርደው አዲስ ምርጫ ይካሄድ››፣ ‹‹አህባሽን በምእመኑ ጫንቃ ላይ በግዴታ ለመጫን የሚደረገው ሙኩራ ይቁም›› እና ‹‹አወሊያ ከመጅሊስ ወጥቶ በገለልተኛ ቦርድ ይተዳደር›› በሚል ስር የሚጠቃለሉ ናቸው፡፡ የኋላ ኋላም በአገዛዙ ‹እስላማዊ መንግስት በሽብር ተግባር ለመመስረት›› ወደሚል ተምኔታዊ ውንጀላ የተቀየሩት እነዚሁ ጥያቄዎች ነበሩ፡፡

በርግጥ ‹‹አህባሽ››ን ተከልሎ የመጣው መንግስታዊ ጫና ዋነኛ ዓላማው (ከአንዳንድ የምዕራብ ሀገራት ፍላጎት ባሻገር) አስተምህሮውን ተገን አድርጎ ምእመኑን እርስ በርስ በመከፋፈል፣ የተቋሙን ነፃነት በቀላሉ ለመጋፋት የሚያስችለውን መደላድል መፍጠር ነው፡፡ ይሁንና ስልቱ ምንም እንኳ ከሃሳቡ ተጋፊዎች አንጻር አነስተኛ ቢሆንም፣ መንገድ ጠራጊ ደጋፊዎች ሊያስገኝለት መቻሉን መካድ ግን መሬት ካለው እውነታ ጋር እንደ መላተም ይቆጠራል፤ ምክንያቱም የመጅሊሱ አመራር ሙሉ በሙሉ ከአገዛዙ ጎን በመቆም አጀንዳው ቅቡል እንደሆነ ለማስመሰል የማይናቅ አስተዋጽኦ አድርጓልና፡፡

ይህም ሆኖ አብዛኛው የእምነቱ ተከታይ በአጭር ጊዜ ውስጥ፣ ተቃውሞ በተነሳበት እዛው አወሊያ ግቢ ተሰባስቦ፣ ከሰባት መቶ ሺህ በላይ የውክልና ፊርማ በማሰባሰብ፣ አስራ ሰባት አባላት ያሉት አንድ የመፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴ አዋቅሮ ሲያበቃ ከላይ የተጠቀሰውን ሕገ-መንግስታዊ የመብት መከበር ጥያቄውን መልክ አስይዞ መታገሉ ብዙም አላዳገተውም፡፡ እነሆም በበርካታ የሀገሪቱ ከተሞች ሕዝበ-ሙስሊሙን ከጎኑ በማሰለፍ በዚህ ዓመት መጀመሪያ ላይ እስከተከበረው የዒድ አል-ፈጥር በዓል ድረስ በየመስጊዶቹ ፍፁም ሰላማዊ በሆነ መንገድ ለጥያቄዎቹ ሁነኛ መልስ ይሰጠው ዘንድ ከፍተኛ የተቃውሞ ትግል አድርጓል፤ በተጨማሪም የኮሚቴው አባላት ከተመረጡ ከስምንት ወራት በኋላ (ሐምሌ 10/2004 ዓ.ም) በግፍ መታሰራቸው ሳያንበረክከውና ሳይከፋፍለው፤ ይከተለው ከነበረው ሰላማዊ መንገድ ውልፍት ሳይል ለተራዘመ ጊዜያት መቀጠሉ በዘመናዊቷ ኢትዮጵያ የታሪክ ገፅ ላይ አዲስ አሻራውን ለማሳረፈ ያስቻለው ይመስለኛል፡፡

         አህአዴግአዊ ‹ህቡዕ መዳፍ›…

አገዛዙ በግልፅ የሚታየውን መጅሊስ፣ በማይታይ ስውር ‹መዳፉ› ልጓም ጨብጦ እየጋለበ በኃይማኖታዊ ተቋሙ ላይ በስፋት ጣልቃ መግባቱን የምንረዳው ‹‹መፍትሄ አፈላላጊ›› ተብለው የተመረጡትን የኮሚቴውን አባላት አንድ በአንድ ለቅሞ ወህኒ ቤት ከወረወረ በኋላ፣ የከሰሰበትን የመወንጀያ ጭብጥ እና እንዲከላከሉ የወሰነበትን የማስረጃዎች ይዘት ስንመረምር ነው፡፡ 
 በርግጥ ሁሉም የተከሰሱት በፀረ-ሽብር ሕጉ ሲሆን፣ ከውሳኔው በኋላም አንዳንድ አንቀጾች ከመሻሻላቸው በቀር ምንም የረባ ለውጥ አልታየም፡፡ ይሁንና መንግስት ገና ከመነሻው (ፍርድ ቤት ሳይቀርቡ) በኮሚቴው አባላት ላይ የተለያዩ ‹ዶክመንተሪ ፊልሞች›ን በኢትዮጵያ ቴሌቪዥን በማስተላለፍ የወንጀለኛነት ብያኔ እና የማጠልሸት ቅስቀሳ አድርጎባቸዋል፡፡ ከዚህ በኋላም (ጥቅምት 15 ቀን 2005 ዓ.ም) ‹‹ጥፋቶች›› ያላቸውን አራት ጭብጦች በመዘርዘር መደበኛ ክስ መስርቶባቸዋል፡፡ የክሱ ይዘትም ከሞላ ጎደል እንደሚከተለው ተጠቃሎ ሊቀርብ ይችላል፡-

‹‹…‹መፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴ› በሚል እርስ በእርስ ተመራርጠው ሲያበቁ ከጥር 5 ቀን 2004 ዓ.ም ጀምሮ ሁሌ በየሳምንቱ አርብ ለፀሎት አወሊያ መስጊድ ለሚሰበሰበው ሕዝብ የሽብር ዓላማቸውን ለማራመድ በአዲስ አበባ እና በክልሎች ባዘጋጁት የሰደቃ እና 
የአንድነት ዝግጅቶች ለሚጠሩት ሕዝብ፣ በማሕበራዊ ድህረ-ገፆች፣ ለዚሁ ትግበራ በተቋቋሙት የተለያዩ ኃይማኖታዊ መገናኛ ብዙሀን፣ በመፃህፍት፣ በበራሪ ፅሁፎችና ዘጋቢ ፊልሞች አማካኝነት… የመጨረሻ ግባቸው የሆነውን እስላማዊ መንግስት ለመመስረት የሙስሊሙ ሕዝብ ቁጥር ከ80 በመቶ በላይ ነው በማለት ለሽብር ተግባር ቀስቅሰዋል፤ አነሳስተዋል፡፡››

ጉዳዩንም በዝግ ችሎት ሲመለከት የነበረው ከፍተኛው ፍርድ ቤት ከአንድ ወር በፊት (ታሕሳስ 3 ቀን 2006 ዓ.ም) የሰጠው ውሳኔ 
በሶስት የተከፈለ ሆኖ አግኝቸዋለሁ፡፡ የመጀመሪያው አቡበከር መሀመድ፣ አህመዲ ጀበል፣ ያሲን ኑር እና ካሚል ሸምሱን ጨምሮ አስራ አራት ሰዎች ያሉበት ሲሆን፣ ከተከሰሱበት የወንጀለኛ መቅጫ ሕጉ አንቀጽ 32(1)(ሀ)(ለ) እና 38(1) መካከል፣ በአንቀጽ 32(1)(ሀ) እንዲከላከሉ ተወስኗል፤ በተጨማሪም ‹‹በፀረ-ሽብርተኝነት አዋጅ ቁጥር 652/2001 አንቀጽ 3(1)(2)(4)(6) እና አንቀጽ 4 ሥር የተመለከተውን በመተላለፍ›› ከሚለው ደግሞ አንቀጽ 3 ቀርቶ በአንቀጽ 4 ተመሳሳይ የተከላከሉ ብይን ተሰጥቶባቸዋል፡፡ ሁለተኛው ጋዜጠኛ የሱፍ ጌታቸውን ጨምሮ አራት ሰዎችን የሚመለከት ሲሆን፤ እነርሱም ከእነ አቡበክር ክስ ጋር የተጠቀሰባቸው የወንጀለኛ መቅጫ አንቀጾች ሁሉም ውድቅ ሆነው በፀረ-ሽብርተኝነት ሕጉ አንቀፅ 7(1) ጥፋተኛ ተብለዋል፡፡ ሶስተኛው የአቶ ጁነዲን ሳዶን ባለቤት ወ/ሮ ሀቢብ መሀመድ እና ሁለት የበጎ አድራጎት ድርጅትን ጨምሮ አስራ ሁለት ተከሳሾች ያሉበት ሲሆን፣ የተላለፈው ውሳኔም በነፃ መሰናበታቸውን የሚገልፅ ነው፡፡ 

        ‹‹ማስረጃ›› ፍለጋ… 

ከክሱ ጀርባ ረጅሙ የመንግስት እጅ መኖሩን የሚያመላክተው ‹‹ጥፋተኛ›› በተባሉት ተከሳሾች ላይ የቀረበው ‹‹ማስረጃ›› ነው፡፡ 
እንዲያ ስርዓቱን በኃይል አፈራርሰውና ሌሎች ኃይማኖታዊ ተቋማትን ጨፍልቀው ‹‹እስላማዊ መንግስት›› ሊመሰርቱ ወጥነው 
ሲንቀሳቀሱ እጅ ከፈንጅ ለመያዛቸው በበቂ ሁኔታ ያስረዱልናል ብለው የጠቀሷቸው ‹‹ማስረጃዎች›› በጠቅላላ የሚከተሉት ናቸው፡- ‹ሁሉም ታሳሪዎች ለፖሊስ ሰጡ የተባለው የእምነት-ክህደት ቃል፣ ዓቃቢ-ሕግ ሰብስቦ ያቀረባቸው የሰው ምስክሮች፣ የሞባይል ቀፎዎች፣ ላፕቶፖች፣ ሲዲዎች፣ በራሪ ወረቀቶች፣ ጭልፋና የወጥ-ድስቶች…›፤ በቃ! በአናቱም ‹‹የሙስሊሙ ቁጥር ከሀገሪቱ ሕዝብ ሰማኒያ በመቶውን ይይዛል ብለዋል›› የሚለው ክስ ተራ አሉባልታ መሆኑን ለማስረገጥ፣ ራሳቸው የኮሚቴው አባላት መጋቢት 2004 ዓ.ም ለቀድሞው ጠቅላይ ሚንስትር ከፃፉት ደብዳቤ ውስጥ የሚከተለውን አንቀጽ ብቻ መጥቀሱ በቂ ነው፡-

‹‹…እንደሚታወቀው የሃገሪቱን ሰላሳ ሶስት በመቶ የሚሆነውን የሕብረተሰብ ክፍል የሚወክለው የኢትዮጵያ እስልምና ጠቅላይ ም/ቤት (መጅሊስ) ተገቢው ሕጋዊ ሰውነት የለውም…›› 

እናሳ! ዓቃቢ-ሕግጋኑ 80 በመቶን ከየት አምጥተው ይሆን? …በርግጥ አቶ መለስ ዜናዊ ‹‹መረጃ እንጂ ማስረጃ የለንም›› እንዲል ገዥው ፓርቲ በእነዚህ የ‹‹ሽብር›› ማስፈፀሚያ ቁሳቁሶች ነው መንበረ-መንግስቱን ከመገልበጥም ሆነ ሀገሪቱን ከኃይማኖታዊ ስርዓት ለጥቂት ታድጌያታለሁና ወንዶች በጭብጨባ፣ ሴቶች በእልልታ አመስግኑኝ የሚለው፡፡ 

የክሱን ልብ-ወለድነት በአመክንዮ ለማስረዳት ከ‹‹ማስረጃዎቹ›› ውስጥ ሁለት ጉዳዮችን ብቻ መምዘዙ ይበቃናል፡፡ ተከሳሾቹ ለፖሊስ በምን ሁኔታ ቃላቸውን እንደሰጡ እና የአንድ ምስክር እማኝነትን (ምንም እንኳ ችሎቱ በዝግ የተካሄደ በመሆኑ የሁሉንም የሀሰት መስካሪነት ሙሉ ለሙሉ ማጋለጥ ባይቻልም፣ ዳኞቹ ራሳቸው ባሳለፉት ውሳኔ ላይ የተጠቀሰው የአንድ የምስክር ቃል ይህንን መከራከሪያ ያስረግጥልናል) 

              የመርማሪዎቹ ‹‹ችሎታ››… 

 የጥፋተኝነታቸው ማሳያ የሆነው የኮሚቴው አባላት ለፖሊስ የሰጡት ቃል ተብሎ በሰነድነት የቀረበው በድምሩ 413 ገፅ ሲሆን፤ ይህ ምርመራም በምን መልኩ እንደተካሄደ በቅርቡ ታሳሪዎቹ በተለያዩ ሚዲያዎች ባሰራጩት ደብዳቤ ላይ የፍትሕ ስርዓቱን ገመና እና በዚች አገር ሰብዓዊ መብቶች ምን ያህል ዋጋ እንዳጡ ልብ የሚሰብሩና በድንጋጤ ዓቅል የሚያስቱ መከራዎቻቸውን ጭምር በመዘርዘር ነግረውናል፡፡ በደብዳቤው ላይ ዓቃቢ-ሕግ ክስ መመስረቻ ያደረገውን ቃላቸውን ፖሊሶቹ ፈልፍለው የደረሱበት የመርማሪነት ‹‹ጥበብ››ን እንዲህ በማለት ነበር የገለፁት፡- 

‹‹…በማዕከላዊ እስር ቤት ውስጥ ከፍተኛ የሆነ ስነ-ልቦናዊ እና አካላዊ ስቃይ ደርሶብናል፡፡ ከአስራ አራት ሰዓታት በላይ ያለ እረፍት ቀጥ ብለን እንድንቆም በማድረግ፣ ጀርባችን እስኪላጥ ራቁታችንን በሽቦ በመግረፍ፣ በሰንሰለት በማሰር እና አይናችንን በጨርቅ በመሸፈን የውስጥ እግራችን እስከሚላጥ ገልብጦ በመግረፍ፣ ቀንና ማታ አሰቃቂ በሆነ ምርመራ እና በድብደባ ብዛት እንቅልፍ በመንሳት፣ ፂማችንን በመንጨትና እንድንላጭ በማስገደድ፣ ከአቅም በላይ የሆነ ስፖርት በግድ በማሰራት፣ ብልት በመግረፍ፣ ‹ልጅህን እንገድለዋለን! ሚስትህን አስረን በፊትህ ቶርች እናደርጋታለን! ብልትህ ላይ የውሃ ሃይላንድ በማንጠልጠል መሀን እናደርግሀለን!› እያሉ በማስፈራራት ከፍተኛ የሆነ እንግልትና ስቃይ አድርሰውብናል፡፡ …በክረምት ቀርቶ በበጋ እንኳ ቅዝቃዜው በማይቻለው ‹ሳይቤሪያ› ተብሎ በሚጠራው ጨለማ ክፍል አጉረውናል፡፡ መቋቋም የሚያዳግተውን የማሳቃያ ስሌታቸውን በመጠቀም ያላሰብነውንና ያልሰራነውን ‹እመኑ! ተናገሩ! ፈርሙ!› ብለው አስገድደውናል፡፡››

ወደድንም ጠላንም የሀገራችን እውነተኛ ገፅታ ይሄ ነው፡፡ በአናቱም ታሳሪዎቹ የደረሰባቸውን ግፍና መከራ የሚያረጋግጡልን ገፊ-
ምክንያቶች፣ የመጀመሪያው ከዚህ ቀደም የተለያዩ ዓለም አቀፍ የሰብዓዊ መብት እና የፕሬስ ነፃነት ተሟጋች ድርጅቶች ማዕከላዊን 
በተመለከተ ያወጧቸው ሪፖርቶች ሲሆን፤ ሁለተኛው ታሳሪዎቹ ራሳቸው ይህንኑ የጭካኔ ተግባር በዝርዝር ጠቅሰው በመርማሪ ፖሊሶቹ ላይ በፍርድ ቤት ክስ መስርተው የነበረ መሆኑ ነው፤ ሶስተኛው ደግሞ መንግስት ‹ጅሃዳዊ ሀረካት› በሚል ርዕስ ያዘጋጀው ‹ዶክመንተሪ ፊልም› በድጋሚ እኩለ ሌሊት ላይ በተላለፈበት ወቅት የማዕከላዊ መርማሪዎች የኮሚቴው ሰብሳቢ የሆነውን አቡበከር መሀመድን እጁን በሰንሰለት የፊጥኝ አስረው ሰብዓዊነቱን በሚያንቋሽሽና መንፈሱን በሚያሸማቅቅ ሁናቴ ቃሉን ሲቀበሉ በቴሌቪዥን መስኮት መመልከታችን ነው፡፡

       የዓቃቢ-ሕግ ምስክር ሲባል… 

ለዚህ ሙግት ማሳያ የማደርገው ከዓቃቢ-ሕግ ምስክሮች መሀል አንዱ የሰጠውን የምስክርነት ቃል ነው፤ ይህ ግለሰብ በ21ኛ ተከሳሽ ሼኽ ጣሂር አብዱልቃዲር መኖሪያ ቤት ሽጉጥ ከነጥይቱን ጨምሮ የተለያዩ ማስረጃዎች በብርበራ ሲገኝ መመልከቱን በችሎቱ ፊት በፈጣሪው ስም ምሎ ተናግሯል፤ የሚገርመው ነገር ግን ይህ አይደለም፤ ዳኞቹ በሰጡት ውሳኔ ላይ እንደሚከተለው ማለታቸውን መስማታችን እንጂ፡-

‹‹እነዚህ ማስረጃዎች (ሽጉጡም ጨምር) አልቀረቡም፤ ዓ/ሕግም በማስረጃ ዝርዝርና በሰነድነት አልጠቀሳቸውም፤ ሌላ ማስረጃም 
አልቀረበም፡፡›› 

እንግዲህ በዝምታ ተገርሞ ከማለፍ በቀር ‹ታዲያ ምስክሩ ከየት አምጥቶ ነው ስለመሳሪያው የዘባረቀው?› የሚል ጥያቄ ማቅረብ አይቻልም፤ ቢቀርብም አጥጋቢ መልስ አይገኝለትም፤ ለምን ቢሉ ሀገሪቱ ኢትዮጵያ ነቻ!! ያውም ኢህአዴግ በብረት መዳፉ ጨፍልቆ የሚገዛት ምስኪን ሀገር፡፡ ...መቼም ይህ ተጨባጭ እውነታ እንዲህ ገሀድ መውጣቱ በዚህ ፀያፍ ተግባር ውስጥ የቀጥታ ተሳትፎ ያልነበራቸውን የገዥው ፓርቲ አመራርንም ሆነ አባላትን ጭምር የአትንኩኝ ባይነት ንዴት ይቀሰቅስ እንደሆነ እንጂ፣ ስለሕገ-መንግስት፣ ሕሊና፣ ሕዝብና አገር በድፍረት መናገር (ጥብቅና መቆም) የሚችሉበት ሞራል ይኖራቸዋል ብሎ ማሰብ ተላላነት ነው (በነገራችን ላይ የሀገሬ የፍትሕ ደጆች እንዲህ የዘቀጡ መሆናቸው ሲጋለጥ ይህ የመጀመሪያው አይደለም፡፡ በድህረ-ምርጫ 97ም የፈጠራ ማስረጃዎች እና ሓሳዊ ምስክሮች ምን ያህል ነግሰውበት እንደነበረ ታይቷል፡፡ የጋዜጠኛ ሲሳይ አጌና ‹‹የቃሊቲው መንግስት›› እና የአንተነህ ሙሉጌታ‹‹የተዋረደው ፍርድ ቤት›› መፃህፍት ሂደቱን በቦታው የነበርን እስኪመስለን ድረስ በውብ ቋንቋ ከሽነው በዝርዝር ተርከውልናል) 
    
          ከቤተ-ክህነት ጀርባ… 

 በርግጥ ከቤተ-ክህነት ‹የእምነት ነፃነት ይከበር!› ጥያቄ ጋር በቀጥታ ተያይዞ ለአስከፊው የቃሊቲ ማጎሪያ የተዳረጉ መንፈሳውያን መሪዎች እስካሁን የሉም፡፡ ይህ ግን የአገዛዙ ‹እርኩስ መንፈስ› በደጆቿ ዙሪያ አልረበበም እንደማለት አይደለም፡፡ ፓትሪያርክን አባርሮ ሌላ መሾም፣ እነአቦይ ስብሃትን የመሳሰሉ የፓርቲው አንጋፋ መሪዎች በአደባባይ ‹‹አንድም ከመንግስት ነፃ የሆነ ጳጳስ የለም!›› ከማለት አልፈው፣ ‹‹ነፃ የሆነ ጳጳስ ካለ እሸልመዋለሁ›› እስከሚለው ተሳልቋቸው ድረስ ያሉ ማረጋገጫዎች የሚያሳዩት የመንግስትን ጣልቃ ገብነት ነውና፡፡ በተለይም በያዝነው ዓመት የመጀመሪያዎቹ ሁለቱ ወራት ውስጥ ብቻ በቤተ-ክህነቱ የውስጥ ጉዳይ ጣልቃ የገባውን ስውር እጅ እና የእምነቱን የአስተምህሮ መንገድ፣ ከኑፋቄው በመለየትም ሆነ በተለያዩ መንፈሳዊ ተግባሮቹ ስመ-ገናና የሆነውን ‹‹ማህበረ ቅዱሳን›› ላይ የተሸረበውን መንግስታዊ ተንኮል ‹‹ቀጣዩ የኢህአዴግ ዒላማ ማህበረ ቅዱስን ይሆን?›› እና ‹‹ኢህአዴግና የኃይማኖት ነፃነት›› በሚሉ ፅሁፎች እዚሁ መፅሄት ላይ ቀደም ሲል በስፋት ስላወሳናቸው ዛሬ መድገሙ አስፈላጊ አይመስለኝም፡፡ ይሁንና ጣልቃ ገብነቱን የሚያመላክቱ ሁለት አዳዲስ ማሳያዎችን የአጀንዳውን ተጠይቅ ለማጠናከር እጠቅሳቸዋለሁ፡፡ 

             ወረራ-ሲኖዶስ

ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ኢህአዴግ ለ‹‹አውራ ፓርቲ››ነቱ ዋስትና የእምነት ተቋማትንም በ‹መንፈሳዊ ክንፍ›ነት ከጎኑ የማሰለፍ ግዴታ 
ውስጥ የከተተው ይመስል፣ ከፍተኛ ባጀት መድቦና ትኩረት ሰጥቶ እየሰራበት እንደሆነ መታዘብ ይቻላል፡፡ ባሳለፍነው ወርሃ ጥቅምት መደበኛው የሲኖዶሱ ጉባኤ በተደረገበት ወቅት፣ ለመጪው ግንቦት አጠናቅቀው እንዲያዘጋጁ ኃላፊነት ለሰጣቸው አራት አባላቱ ያስተላለፈው ውሳኔ፡- ‹‹ዘጠኝ እጩ ጳጳሳትን መልምላችሁ አቅርቡ!›› የሚል ነበር፡፡ ሆኖም ከቤተ-ክህነት ምንጮቼ ባገኘሁት መረጃ፣ መንግስት የፊታችን ግንቦት ወር በሚደረገው ጉባኤ ላይ ሹመታቸው ፀድቆ በቀጥታ የሲኖዶሱ አባል መሆን በሚችሉት ዘጠኙ ጳጳሳት ምልመላ ላይ ረዥም እጁን እየከተተ መሆኑን ነው፡፡

እንደሚታወሰው ነባሩ የቤተ-ክህነት የጳጳሳት የአመራረጥ መስፈርት የሚከተሉት ናቸው፡- ‹‹በምንኩስና የኖረ (ትዳርም ልጅም 
ያሌለው)፣ መንፈሳዊውንም ሆነ ዓለማዊው ትምህርቱን በሚገባ ያጠናቀቀ፣ ከአንድ በላይ ቋንቋ መናገር የሚችል፣ እውነትና ሀሰትን የማይናገር፣ አስካሪ መጠጥ የማይጠጣ፣ እድሜው ሃምሳ ዓመት የደረሰ፣ በሚያገለግለበት ቦታ ምስጉን መሆኑ የተረጋገጠ…፡፡›› ይሁንና ጀግናው ኢህአዴግ ደግሞ የፖለቲካ ታማኝነትን በተጨማሪነት ለመክተት ‹አክራሪ ያልሆነ› እና ‹ልማታዊ የሆነ› በሚሉ ሁለት መስፈርቶች ሸፋፍኖ በለመደው ስውር እጁ ተፅእኖ በማድረግ በሲኖዶሱ ውስጥ ያለውን ጉልበት ለማጠናከር እየሞከረ እንደሆነ ማረጋገጤ ለተጠየቁ እንደ አንድ ማሳያ ሊወሰድ ይችላል ብዬ አስባለሁ፡፡

           የለውጡ አንድምታ… 

ከወራት በፊት የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ሊቀ-ጳጳስ ሆነው በሲኖዶሱ የተሾሙት አቡነ እስጢፋኖስ፣ በአቡነ ቴውፍሎስ ዘመን ፀድቆ ይሰራበት የነበረውን ‹ቃለ-አዋዲ› ለማሻሻል ይሁን ለመሻር ባይታወቅም አዲስ ጥናት አጥንቶ እንዲያቀርብላቸው ኃላፊነቱን ለማህበረ ቅዱሳን ይሰጣሉ፡፡ ማህበሩም በአጭር ጊዜ ውስጥ ‹‹የአዲስ አበባ የሀገረ-ስብከት የአደረጃጀትና አሰራር ለውጥ ጥናት›› በሚል ርዕስ የቤት ስራውን አጠናቅቆ ያቀርባል፡፡ 

ነገር ግን የመዋቅርንና የአሰራር ለውጥን ጨምሮ ግልፅነትና ተጠያቂነት ያለበት ዘመናዊ የፋይናንስ ስርዓት እንደተካተተበት የተነገረው የጥናቱ ረቂቅ መሰናዳቱን ተከትሎ ገና ከአሁኑ ከአንዳንድ የደብር አስተዳዳሪዎች ዘንድ ከባድ ተቃውሞ እየደረሰበት ነው፡፡ እንደ ምንጮቼ መረጃ ሁናቴው በጊዜ መፍትሄ ካልተበጀለት ሀገረ-ስብከቱንም ሆነ የደብር አስተዳዳሪዎችን መከፋፈሉ አይቀሬ ነው፡፡

 ይህንን ጉዳይ እዚህ ጋ ያነሳሁት የመንግስትን ጣልቃ ገብነት ያሳያል በሚል ነው፡፡ ይኸውም የጥናቱ ይዘት በወሬ ደረጃ በመናፈሱ ብቻ ‹‹መተግበር የለበትም!›› የሚል ተቃውሞ እያሰሙ ያሉ አንዳንድ ጳጳሳት እና የደብር አስተዳዳሪዎች ‹‹መንግስት ከጎናችን ስለሆነ፣ ከእርሱ ጋር እንነጋገርበታለን››፣ ‹‹ይህ ህግ መፅደቅ የለበትም፣ አለበለዚያ ሪፖርት ለምናቀርብለት አካል ሪፖርት እናደርጋለን››፣ ‹‹አርፋችሁ ብትቀመጡ ይሻላችኋል››፣ ‹‹እርሶንም (አቡነ እስጢፋኖስን) ከሥልጣንዎት እናወርዶታለን››… እና መሰል ማስፈራሪያዎችን አቡኑ ቢሮ ድረስ በመሄድ መናገራቸው ነው፡፡

በጥቅሉ እነዚህ ሁነቶች ስርዓቱ በቤተ-ክህነት የውስጥ አስተዳደር ምን ያህል ጠልቆ እጁን እንደሰደደ ያስረግጡልኛል ብዬ አምናለሁ፡፡

    ‹‹ድምፃችን ይሰማ›› ወዴት ተሰወረ? 
  
ባሳለፍነው ሳምንት ሁለተኛ ዓመቱን የደፈነው የሕዝበ-ሙስሊሙ ‹‹የእምነት ነፃነት ይከበር!›› ጥያቄ፣ በተለይም ‹‹መፍትሄ 
አፈላላጊ›› ተብለው የተመረጡት የኮሚቴ አባላት ለእስር ከተዳረጉ በኋላ የተቃውሞ ንቅናቄው ሲመራ የቆየው ‹‹ድምፃችን ይሰማ!›› የሚል መርህ ባነገቡ አስተባባሪዎች እንደነበረ ይታወሳል፡፡ ፍፁም ሰላማዊውን እና ሕጋዊውን መንገድ በመከተል የጁምዐን ሶላት እየጠበቁ የኮሚቴው አባላት በአስቸኳይ ከተጣሉበት የስቃይ ጎረኖ እንዲወጡና ያነሷቸው የመብት ጥያቄዎችም ያለ አንዳች ቅድመ ሁኔታ እንዲመለሱ አዲስ አበባን ጨምሮ በሌሎችም የሀገሪቱ ከተሞች ያስተባበረው የተቃውሞ ድምፅ ዛሬ በቦታው የለም፡፡ በግልባጩ መስጊዶቹ በከባድ ፀጥታ የተመቱ መስለዋል፡፡ 

 ከማሕበራዊ ሚዲያዎች እስከ የእጅ ስልክ መልዕክት መለዋወጫዎች፤ ከበራሪ ወረቀቶች እስከ ፍትህ ሬዲዮ ድረስ ያሉ የመረጃ 
ማስተላለፊያ ዘዴዎችን እጅግ በሰለጠነ መንገድ ይጠቀም የነበረው የ‹‹ድምፃችን ይሰማ!›› ተቃውሞ፣ በዘንድሮው የዒድ በዓል ወቅት በእምነቱ ተከታዮች ላይ መንግስት ከወሰደው መጠን የለሽ የጭካኔ እርምጃ በኋላ ዳግም አልተከሰተም፡፡ ይሁንና ምንም እንኳ በበዓሉ ዋዜማ አስተባባሪዎቹ የተቃውሞ እንቅስቃሴውን ለጊዜው ለማቋረጥ መወሰናቸውን ቢያሳውቁም፣ በስርዓቱ የአመራር አባላት ዘንድ ያለው አተያይ ግን ተቃውሞውን በኃይል መቆጣጠር እንደተቻለ ነው፡፡ በርግጥም ይህ አይነቱ የተሳሳተ መደምደሚያ ይመስለኛል የኮሚቴው አባላትን ውሃ በማይቋጥር ክስ ‹‹ጥፋተኛ›› ብሎ እንዲከላከሉ እስከመወሰን ድረስ የልብ-ልብ የሰጠው፡፡ 

የሆነው ሆኖ አገዛዙ የእስልምና እምነት ተከታዮችን በአህባሽ እና ሓሳዊ ሰባኪያን ከፋፍሎ ለማዳከም ያደረገው ሙከራ ቢከሽፍም፣ 
ዛሬም የተነሱት ሕጋዊ የመብት ጥያቄዎች መልስ ካለማግኘታቸውም በላይ፣ በእነዛ ፈታኝ ጊዜያት ሚሊዮኖችን ወክለው በድፍረት ከፊት መስመር የተሰለፉት ንፅሃን የኮሚቴው አባላት በእስር እየማቀቁና ለተለመደው የፖለቲካ ፍርደ-ገምድል ውሳኔ እያመቻቿቸው ስለመሆኑ የ‹‹ድምፃችን ይሰማ›› አስተባባሪዎች ይዘነጉታል ተብሎ አይገመትም፡፡ በአናቱም ይህ ሁናቴ እንደ ልጅነት ዘመን፣ የሚታሰረው ታስሮ፣ የሚገደለው ተገድሎ፣ የሚሰደደው ተሰዶ… ሲያበቃ ‹ዳቦ ተቆረሰ፣ ዕቃቃው ፈረሰ› ተብሎ በየፊናችን የምንበታተንበት አይነት ጨዋታ አለመሆኑን ማስታወሱ አግባብ ነው ብዬ አስባለሁ፡፡  

          የመውጫው መንገድ 

ኢህአዴግ ያለፉትን ሃያ ሁለት የሰቆቃ ዓመታት በስሁቱ የ‹አብዮታዊ ዲሞክራሲ› ርዕዮተ-ዓለም ብያኔ ሀገሪቱንና ሕዝቧን ለአስከፊ 
ድህነት፣ ለመራራ ጭቆና ዳርጓል፡፡ ይህንንም ተከትሎ ባነበረው መከፋፈልና አለመተማመን የሥልጣን ዕድሜውን ያለስጋት ማራዘሙ ተሳክቶለታል፡፡ ጥያቄውም ከዚህ የሚነሳ ቢሆንም፣ ምላሹ በቅርቦቹ ሁለት ዓመታት ውስጥ ከታየው የሙስሊሙ ሰላማዊ የትግል ስልት ጋር የሚተሳሰር ይመስለኛል፤ ምክንያቱም ማንኛውም የመብት ጥሰት የሚያሳስበው ዜጋ ይህን ክቡድ መንፈስ ከመቀላቀል የተሻለ አመራጭ የለውምና (በነገራችን ላይ የኮሚቴው አባላት በቀጠሮ ከሚቀርቡበት የፊታችን ጥር 22 ቀን ጀምሮ ችሎቱ ለታዳሚ ክፍት በመሆኑ ያለአንዳች የኃይማኖት ልዩነት ወደ ፍርድ ቤት በመትመም ከጎናቸው ታላቅ የሕዝብ ደጀን መኖሩን ማሳየቱ መንፈሳቸውን ለማበርታት መልካም አጋጣሚ ነው) 

በጥቅሉ ሰማያዊ ነፃነታቸው በፖለቲካ ጉልበት እየተናደ የመጣው የሁለቱ ኃይማኖት ልሂቃንና ተከታዮች ዛሬ ከመቼውም ጊዜ በላይ የጎንዮሽ መተያየታቸውን ገርቶ፣ የብሔር ልዩነትን አዘልሎ በአንድ አውድ ሊያሰባስባቸው የሚችል ገፊ-ምክንያት አላቸው፡፡ እናም ስርዓቱ እርስ በእርስ በጥርጣሬና በስጋት እንዲተያዩ ለማድረግ በተንሸዋረረ የ‹‹መቻቻል›› ፕሮፓጋንዳ ስም እየዘረጋው ያለውን የረቀቀ ወጥመድ በመሻገር፣ የአደባባይ ተቃውሞዎችን በጋራ በማስተባበር የማያቋርጥ ጫና ፈጥረው ለቤተ-አምልኮዎቻቸው ‹‹ነፃነታችንን መልሱልን!?›› አንገብጋቢ ጥያቄ መፍትሄ ማስገኘት ይኖርባቸዋል፡፡ ይህንን የተቀደሰ ዓላማ ከግብ ለማድረስ በተለይም ከ‹‹ድምፃችን ይሰማ›› ውጤታም እንቅስቃሴ ጥቂት ገፆችን በመገንጠል ሰፊ መዋቅር ያለው ‹‹ማሕበረ ቅዱሳን›› ደጋግሞ ቢከልሰው ካለፈ ቁጭት ራሱን መታደግ የሚችልበትን የመውጫ ቀዳዳ ማግኘቱ ብዙ አያለፋውም፡፡

በመጨረሻም ‹‹ድምፃችን ይሰማ›› ከታሳሪዎቹ የኮሚቴው አባላት መካከል አንዱ የሆነው ካሚል ሸምሱ ሐምሌ 8 ቀን 2004 ዓ.ም እንደ ተናገረው ጠቅሶ በማሕበራዊ ድህረ-ገፆች ያሰራጨውን መልዕክት የርዕሰ-ጉዳያችን መደምደሚ ይሆን ዘንድ ወደደሁ፡-

‹‹የዚህች ሀገር ሰላም ፀጥታ ነው፤ ዲሞክራሲን ማስፈን የሚቻለው፤ የሕግ የበላይነትን ማስከበር የሚቻለው በጋራ ነው፤ እኛም የእዛው አካል ስንሆን ነው፤ የአንዱ መብት ተከብሮ የሌላው ተጥሶ ሊሆን አይችልም! አንደኛው የሕገ-መንግስት ክፍል ተከብሮ ሌላኛው ተደፍጥጦ ሊሆን አይችልም! ሰላምን ነው የምንዘምረው! ለሰላም ነው የምንታገለው! ጥያቄያችንን በሰላማዊ መንገድ እንሄድበታለን!››









































































































































ርዕዮት አለሙ ጋዜጠኛ እንጅ አሸባሪ ናት ብየ አላምንም!

January 21/2014

(ነቢዩ ሲራክ)
reeyot


የጋዜጠኛ ርዕዮት አለሙን ስራዎች በቅርብ ተከታትያለሁ! ውንጀላ እስራቷን ፣ ህክምና እንድታገኝ መደረጓን እና የቤተሰብ እና የወዳጆችዋ ጉብኝት እንዳታገኝ መከልከሏን ሰምቻለሁ ! ይህ ሁሉ በዚህች የመናገር የመጻፍ ነጻነቷን ተጠቅማ ህገ መንግስታዊ መብቷን በተጠቀመች ወጣት ጋዜጠኛ ላይ የሚከፈል መስዋዕትነት ቢሆንም ስቃይ መከራዋ ፣ በደል መገፋቷ ያንገበግበኛል!እናም እንደ አንድ ኢትዮጵያዊ ተተገፈፈቸው መብቷ ይመለስ ዘንድ በሚደረገው ሰላማዊ እንቅስቃሴ ደጋፊ ነኝ ! ርዕዮት አሸባሪ አይደለችም ብየ አምናለሁና ፊርማየን ለድጋፍ ሳስቀምጥ ኩራት ይሰማኛል !
ፍትህ ለጋዜጠኛ ርዕዮትና ለመሰሎቿ ስመኝ ለኢትዮጵያስ እንኳንም ተወለድሽ የምላት አሁንም በኩራት ነው! ግጥሙን ለማንበብ እዚህ ላይ ይጫኑ::

በሃይማኖት ጭቆና ስም የሚረጩ አደገኛ መርዞች

January20/2014

ከፋሲል የኔአለም (ጋዜጠኛ)

አራተኛውን የኢቲቪ “ጥናታዊ ፊልም” አየሁት፤ ዝቅ ሲል ለምርጫ ቅስቀሳ፣ ከፍ ሲል ደግሞ ከፋፍሎ ለመግዛት ተብሎ የተዘጋጀ ይመስለኛል። ፊልሙ ኢህአዴግንና የቀድሞ ስርዓቶችን ያነጻጽራል፤ ማንም ነፍስ ያለው ሰው ኢትዮጵያ ውስጥ የሃይማኖት ጭቆና አልነበረም ብሎ አይክድም፤ ልዩነቱ የሚጀመረው “ጨቋኙ ማን ነው? ተጨቋኙስ?” የሚለውን ለመመለስ ሲሞከር ነው። በእኔ እይታ ጨቋኞቹ የኦርቶዶክስ እና የኦርቶዶክስ እምነት ተከታይ መንግስታት ብቻ እንደነበሩ ተደርጎ የሚቀርበው አስተያየት ስህተት ነው፣ ተጨቋኞቹ ከኦርቶዶክስ ውጭ ያሉ ሃይማኖቶች ብቻ እንደነበሩ ተደርጎ የሚቀርበውም አስተያየት በታሪክ ያልተደገፈ፣ የስህተት ትምህርት ነው ። ታሪካችን እንደሚነግረን ከ66ቱ አብዮት በፊት፣ ሁሉም ስልጣን የያዙ ሃይሎች ስልጣናቸውን ለማቆየት ወይም ግዛታቸውን ለማደራጀት እነሱ የሚደግፉትን ሃይማኖት በሌላው ላይ ለመጫን ሙከራ አድርገዋል። የአጼ ሃይለስላሴ መንግስት የመጀመሪያውን የጽሁፍ ህገመንግስት ስላረቀቀና በህገመንግስቱ ላይ “ ኦርቶዶክስ ሃይማኖት” የመንግስት ሃይማኖት መሆኑን በይፋ ስላወጀ ዛሬ እንደ ትልቅ ግኝት ተጋኖ ይቀርባል እንጅ፣ ከዚያ በፊት የነበሩት ገዢዎች ኦርቶዶክስን ብቻ ሳይሆን፣ካቶሊክንና እስልምናን የመንግስት ሃይማኖት ለማድረግ ሞክረዋል። ክርስትናን በይፋ ከተቀበለው ከመጀመሪያው ንጉስ ኢዛና ጀምሮ እስከ አክሱም ስርወ-መንግስት ውድቀት ድረስ ኦሮቶዶክስ ሃይማኖት የመንግስት ድጋፍ ነበራት፤ ዮዲት መጣችና ስርዓቱን ለማፍረስ ሞከረች። ቀደም ብሎ ክርስትናን የማያውቁት አገዎች፣ ክርስትናን ከአክሱሞች ስለተቀበሉ፣ ኦርቶዶክስ ሃይማኖት ያለምንም ችግር የመንግስት ሃይማኖት ሆኖ ቀጠለ። ይኩኖ አምላክ ከዛግዌዎች ስልጣኑን ከቀማበት እስከ ግራኝ አህመድ ዘመቻ ድረስ ኦሮቶዶክስ አሁንም የመንግስት ሃይማኖት ሆና ቆይታለች። ይሁን እንጅ ኦርቶዶክሳዊ የሆኑት ነገስታት ከኦሮቶዶክስ ውጭ ያሉ ሃይማኖቶችን ብቻ ሳይሆን የኦርቶዶክስ ሃይማኖት ተከታዮች ሆነው፣ የአስተምህሮ ልዩነት የነበራቸውን ሳይቀር፣ ሃይማኖታቸውን በነጻነት እንዳያስፋፉ ያግዱ ነበር። የደቂቀ እስጢፋኖሳውያን ታሪክ ለዚህ ጥሩ ምሳሌ ነው። ደቂቀ እስጢፋኖሳውያን እስከመጨረሻው ኦርቶዶክሶች ነበሩ፣ከሙስሊሙ ወይም ከቤተ-እስራኤላውያን ባላነሰ መልኩ ወከባ ደርሶባቸዋል።

ግራኝ አህመድ ዘመቻውን ወደ ሰሜን ባስፋፋበት ወቅት ደግሞ ቀድም ብሎ ክርስቲያን የነበሩት ዜጎች እስልምናን በግድ እንዲቀበሉ ተደርጓል። ግራኝ ለረጅም ጊዜ ስልጣን ላይ ቆይቲ ቢሆን ኖሮ እስልምና የመንግስት ሃይማኖት የመሆን እድሉ ሰፊ ነበር። ግራኝ በስልጣን ላይ በነበረባቸው አመታት እስልምና ዋና የአገሪቱ ሃይማኖት ነበር። ግራኝን ለመውጋት የመጣው የፖርቱጋል ጦር በበኩሉ አንዱ አላማው የካቶሊክ ሃይማኖት በኢትዮጵያ ማስፋፋት ነበር። ገልውዲዎስ ፈቃደኛ ቢሆን ኖሮ ካቶሊክ የመንግስት ሃይማኖት የመሆን እድሉ ሰፊ ነበር፤ አጼ ሱስንዮስ ሲነግሱ ግን ካቶሊክ የመንግስት ሃይማኖት ሆነ ። ኦርቶዶክስ የሆኑትም ያልሆኑትም እኩል ሃይማኖታቸውን እንዲለውጡ ተገደዱ። ካቶሊክ ለአጭር ጊዜም ቢሆን የመንግስት ሃይማኖት ሆነ፣ በዚህም የተነሳ ብዙ ደም ፈሰሰ። አጼ ፋሲል ሲነግሱ ደግሞ ኦርቶዶክስ ተመልሳ ከበሬታ አገኘት- “አጼ ፋሲል ነገሱ፣ ሃይማኖትን መለሱ” ተባሉ። ይሁን እንጅ በእርሳቸውም ጊዜ “ሁለት ልደት ፣ ሶስት ልደት፣ ቅባት ፣ ተዋህዶ” በሚሉ የአስተምህሮ ልዩነቶች ኦርቶዶክስ ትናወጥ ጀመር። ከዚያ በሁዋላ በመጡ መንግስታት ቅባቶች ሲያሸንፉ ተዋህዶዎች ተሳደዱ፣ ተዋህዶዎች ሲያሸንፉ ደግሞ ቅባቶች ተሳደዱ። በዘመነ መሳፍንት ጊዜ ደግሞ ለ90 ዓመታት ገደማ ማእከላዊ መንግስት የሚባልም ነገር ስላልነበር፣ የመንግስት ሃይማኖት የሚባል ነገር አልነበረም፣ መንግስት ነበር ከተባለም የይስሙላ ነበር። ከዚያ በሁዋላ የመጡት አጼ ቴዎድሮስ በኦርቶዶክስ ውስጥ የአስተዳደር“ ተሃድሶ” ለማካሄድ ሞከሩ። አብዛኞቹ አማካሪዎቻቸው ፣ ፈረንጆቹ ማለቴ ነው፣ ፕሮቴስታንቶች ነበሩ። ንጉሱ የኦርቶዶክስ ተከታይ ቢሆኑም ሃይማኖቱን ለማስፋፋት ወይም ሌላው ሰው ሃይማኖቱን እንዲቀይር ሲያስገድዱ አልታየም፤ ከኦርቶዶክስ ጋር የነበራቸው ግንኙነት መበላሸት ለውድቀታቸው አንዱ ምክንያት ሆኗል፣ ታሪክ አስተማሪዎቻችን እንደነገሩን ንጉሱ የፕሮቴስታንቱ ትምህርት እየጣማቸው ሄዶ ነበር። ከዚያ በሁዋላ የመጡት አጼ ዮሃንስ አራተኛ ደግሞ አጥባቂ ኦርቶዶክሳዊ ነበሩ። ኦርቶዶክስ ተዋህዶ በይፋ የመንግስት ሃይማኖት እንዲሆን ቦሩ ሜዳ ላይ ደንግገዋል። ሙስሊሙ ሃይማኖቱን እንዲቀይር አስገድደዋል፤ ከተዋህዶ ውጭ ያሉት፣ በተለይ ቅባቶች በጎጃም ( ምስራቅ ጎጃም) አካባቢ ተጠልለው እንዲቀሩ አድርገዋል። ለእርሳቸው ሃይማኖት ትልቅ ቦታ ነበረው።

እርሳቸውን የተኩዋቸው አጼ ሚኒሊክ ኦርቶዶክስ ቢሆኑም፣ ቀደም ብሎ ሃይማኖት የነበራቸው ሰዎች ፣ በተለይ ሙስሊሞች፣ ሃይማኖታቸውን እንዲቀይሩ ሲያስገድዱ እምብዛም አይታይም፤ ሃይማኖት የላቸውም ተብለው የሚታሰቡት ወይም ከኦርቶዶክስና እስልምና ውጭ ያሉት ግን ኦርቶዶክስን እንዲቀበሉ ተጽእኖ ይደረግባቸው ነበር። ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ግን የመንግስታቸው ሃይማኖት ነበር፡፡ ከእርሳቸው በሁዋላ የመጡት ልጅ እያሱ፣ኦርቶዶክስን የሚወዱ ሰው አልነበሩም፣ ከስልጣን የወረዱትም የመንግስትን ሃይማኖት እስልምና ለማድረግ አስበዋል በሚል ተዶልቶባቸው ነው፤ በእርሳቸው ዘመን፣ ጊዜው አጭር ቢሆንም ከኦርቶዶክሶች ይልቅ ሙስሊሞች የተሻለ ተቀባይነት ነበራቸው፤ በእርግጥ አባታቸውም ቀደም ብሎ ሙስሊም የነበሩ ናቸው። ልጅ እያሱ ለረጅም ጊዜ በስልጣን ላይ ቆይተው ቢሆን ኖሮ፣ እስልምና የመንግስት ሃይማኖት እንኳን ባይሆን፣ እንደ ኦርቶዶክስ እኩል የመንግስት ሃይማኖት የመሆን እደል ይኖረው ነበር ብየ አስባለሁ።

አጼ ሃይለስላሴ ከእያሱ ውድቀት ተምረው ኦርቶዶክስ ተዋህዶን መንግስታዊ ሃይማኖት ሆኗል ብለው በህገመንግስት ደነገጉ፤ እርሳቸውን ዘመናዊውን ትምህርት ያስተሟሩዋቸው ሰው ካቶሊክ ነበሩ። አጼ ሃለስላሴ “ ኦርቶዶክስ ሃይማኖት፣ የመንግስት ሃይማኖት ነው” ቢሉም፣ ሙስሊም በሙሉ በአንድ ጊዜ ኦርቶዶክስ እንዲሆን አላዘዙም፣ በሙስሊሙ፣ በካቶሊኩና በሌላው ሃይማኖት ተከታይ ላይ አስተዳደራዊ ተጽኖዎች አልነበሩም፣ የመንግስት አድልዎ አልነበረም ማለት ግን አይደለም ። ኮሎኔል መንግስቱ ሃየለ-ማርያም መጡና “እግዚአብሄር የሚባል የለም” ብለው ሙስሊሙንም ክርስቲያኑንም ኩምሽሽ አደረጉት፤ ሙስሊሙ የአሁኑ ይባስ አለ፣ ክርስቲያኑም፣ እግዞዎ አለ። ሙስሊሞች “አላህ በኖረና በተጨቆንን ፣ ኦርቶዶክሶች ደግሞ “እግዚአብሄር በኖረና መንግስታዊ ሃይማኖት መሆኑ በቀረብን” ሳይሉ የቀሩ አይመስለኛም ። መንግስቱ በሁሉም ሃይማኖት ላይ ሳያዳላ ነው የተነሳው፤ ያም ሆኖ ግን ጓድ መንግስቱ ሰዎች በአንድ ጀንበር ሃይማኖታቸውን እንዲቀይሩ አላስገደዱም፤ የሚከተለውን ያውቁ ነበርና። ፕሮቴስታንትን በተመለከተም ኮሎኔል መንግስቱ፣ ፕሮቴስታንት ስለሆነ ብቻ፣ የተለየ አሉታዊ ተጽእኖ አላደረጉበትም፤ እርሳቸው ፕሮቴስታንት እንዲስፋፋ ያልፈቀዱት ሌላ ራስ ምታት ላለመጨመር ነው፣ ራሳቸውን ለማዞር ኦርቶዶክስና እስልምና በቂዎች ነበሩ። መንግስቱ ኮሚኒዝምን ትተው የምእራባውያንን ዲሞክራሲ ቢከተሉ ኖሮ፣ ፕሮቴስታንት ሃይማኖት እንደልቡ እንዲንቀሳቀስ ይፈቀድለት ነበር።

በኢህአዴግ ጊዜ ደግሞ ፣ ሙሉ መብትን የማይጠይቁ ሃይማኖቶች እስካልተነሱ ድረስ፣ ማንም የፈለገውን ሃይማኖት መከተል ይችላል። ሙሉ መብትን የሚጠይቁ ሃይማኖቶች ከመጡ ግን በሽብርተኝነት ወንጀል ተከሰው መቀመቅ ይወርዳሉ።
እንግዲህ ሳጠቃልለው፣ ኦርቶዶክስ ሃይማኖትን እና ሃይማኖቱን ይከተሉ የነበሩ ነገስታትን ብቻ ጨቋኝ አድርጎ ማቅርብ ስህተት ነው። የኦርቶዶክስም ሆነ የሌላ ሃይማኖት ተከታይ ገዢዎች፣ ሃይማኖታቸውን በሃይል ለማስፋፋት ጥረት አድርገዋል፤ ገዢዎቹ እነሱ ከሚከተሉት ሀይማኖት ውጭ ያሉትን ዜጎች ብቻ ሳይሆን በአንድ ሃይማኖት ስር እንኳ ሆነው የተለየ አስተምህሮ ይከተሉ የነበሩትን ሳይቀር አሳደዋል። ኦርቶዶክስን ጨቋኝ ፤ ሙስሊሙንም ተጨቋኝ አድርጎ ለማሳየት የሚደረገው ሙከራ እጅግ አደገኛ ነው። ገዢው ፓርቲ ራሱን ለአንዱ የመስቀል ጦረኛ፣ ለሌላው ጂሃዲስት እያደረገ ለማቅረብ የሚያደርገው ሙከራ ከራሱ አልፎ ለአገር እንዳይተርፍ ፣ከአሁኑ እረፍ ሊባል ይገባዋል።

የደህንነት ሰራተኞች ሃላፊነታችን ለአገር ወይስ ለፖለቲካ ስርአቱ ነው የሚል ጥያቄ አነሱ

January 20/2014

ጥር ፱ (አስራ ሁለት) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-መንግስት በመረጃዎች አያያዝ ዝርክርክነት ፣ በሳይበር በሚደረጉ ስለላዎች እና ከውስጥ ባሉ የመንግስት አካላት እየሾለኩ በሚወጡ መረጃዎች ህልውናየ አደጋ ላይ ወድቋል በማለት ግመገማ ማድረጉን ተከትሎ  ”የደህንነት ሰራተኞች ሃላፊነታችን ለማን ነው?” የሚል ጥያቄ ማንሳታቸውን  ከደህንነት መስሪያ ቤት ለኢሳት የደረሰው በድምጽ የተደገፈ መረጃ አመለከተ። በስብሰባው ላይ ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናት እና የመንግስት ሹሞችም ተገኝተው ነበር።

ጥያቄውን ያነሱት በፌደራል ስር የሚገኙ የደህንነት ስራተኞች እና ቀደም ብሎ በአቶ መለስ ዜናዊ ዘመን በትግራይ ውስጥ በመቀሌ ዩኒቨርስቲ ሽፋን የተቋቋመው ኤም አይ ቲ እየተባለ በሚጠራው ከመቀሌ ከተማ 9 ኪሎሜትር ርቀት ላይ በተገነባው ተቋም ውስጥ ተመርቀው የወጡት የደህንነት ሰራተኞች ናቸው።

የደህንነት ሰራተኞቹ “የእኛ ሃለፊነት የአገር ደህንነትን ማስጠበቅ ነው የፖለቲካ ስርአቱን ?” በሚል  ጥያቄ ያነሱ ሲሆን፣ አንድ  የመንግስት ከፍተኛ ባለስልጣን  ” የፖለቲካ ስራ የማይሰራ ደህንነት የለም፣ የደህንነት ስራ ሲጀመር ስርአት የማቆየት ስራ ነው፤ ስርአቱን የምናቆይበት ደግሞ ፕሮፌሽናል ነው፣ በስርአቱ ላይ እምነት ማሳደር የሚጠይቅ ተግባር ነው፣ የግንቦት7ትን አስተሳሰብ የሚያቀነቅንና ስርአቱ በጉልበት መፍረስ አለበት ብሎ የሚያስብ ሰው፣ የተስፋየ ወልደ ስላሴ አይነት የደህንነት ብቃት አለው ቢባል፣ ሞሳድ 20 አመታት አሰልጥኖታል ቢባል ስርአቱን ከማፍረስ ውጭ ደህንነቱን ሊያስጠብቅ አይችልም” ፣ ስለዚህ የደህንነት ስራ ለሚሰሩ ወገኖች የፖለቲካ ወገንተኝነታቸው ወሳኝ ነው የሚል መልስ ሰጥተዋል ።

“የደህንነት ተቋሙ ፣ ሰራዊቱና ሚዲያው በተቃዋሚዎች ዘንድ መቼውንም ቢሆን ገለልተኛ ተደርጎ አይቆጠርም” ያሉት እኝህ ከፍተኛ ባለስልጣን ፣ ገለልተኛ ማድረግ የሚባል አስተሳሰብ ያለው ካለ እንደዛ ሊሆን አይችልም፣ ሊሆን የሚችለው የተቃዋሚዎችን ሰዎች ደህንነት ውስጥ ማስገባት ነው ብለዋል። ” በተለይም በተቋም ደረጃ ፤በምህጻረ ቃል ኢንሳ እየተባለ የሚጠራው የመረጃ ደህንነት መስሪያ ቤት፤ የዜግነት እና ኤምግሬሺን ፤የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር፤በጀኔራል ሳሞራ የኑስ የሚመራው የመከላከያ ደህንነት ፤የአስተዳደር እና ፀጥታ ፤ የፌደራል ፖሊስ ፤ የፀረ ሽብር ግብረ ሃይል በእዝ ሰንሰለት በሚፈጠር ልዩነት እርስ በርስ እየተወዛገቡ ሲሆን፣ ተቋሞቹን በትክክል የሚመሩትን አካላት  ለመለየት አስቸጋሪ ሆኖ መገኘቱና እርስ በርስ በሚፈጥሩት  እሰጥ አገባ  አንዱ አንዱ የሚሰራውን የማጠፋፋት እርምጃ እየወሰዱ መሆኑ በግምገማው ላይ ተነስቷል፡፡

የመንግስት ሚስጥሮች ለሶስተኛ ወገኖች ተላልፈው እየተሰጡ በመሆኑ ሚስጢሮችን  መደበቅ የማይቻልበት ደረጃ ላይ ተደርሷል ሲሉ አንዳንድ ባለስልጣኖች አስተያየቶችን ሰጥተዋል።
ለተነሱት አስተያየቶች መልስ የሰጡት ባለስልጣኑ፣ ኢንሳ የተቋቋመውም ይህን ለመስራት መሆኑን  ገልጸው፣ “አገሮች ሙሉ በሙሉ ከሳይበር ስለላ ነጻ ባለመሆናቸው አቶ ሃይለማርያምም ነጻ ናቸው ብየ አላስብም” ብለዋል። “አሜሪካኖች የምንናገረውን ሁሉ ከፈለጉ ይሰሙታል” የሚሉት እኝሁ ባለስልጣን፣ “እኛም የአቅማችንን ያክል አሜሪካኖች የሚናገሩትን ለማዳመጥ እንሞክራለን” ብለዋል። የሳይበር ስለላ ለማካሄድ ጥሩ ጅምሮች ቢኖሩም፣ ያን ያክል የምንኩራራበት ግን አይደለም በማለት ኢነሳ ያለበትን ደረጃ አመላክተዋል

ከኦሮሚያና ከደቡብ የመጡ የደህንነት ሹሞች ደግሞ “በመከላከያ የደህንነት ተቋሞች ውስጥ የአንድ ብሄር የበላይነት ጎልቶ ይታያል” በሚል ቅሬታ ያነሱ ሲሆን ፣ ባለስልጣኑም “የሰራዊት ማመጣጠን ስራ በረጅም ጊዜ የሚሰራ ስራ  ነው ” በማለት ለመመለስ ሞክረዋል።

” ትግሉን መርተው እዚህ ድረስ የመጡ ሰዎችና በመከላከያ ውስጥ ያለውን የመኮንኖች ቦታ የያዙት ከአንድ አካባቢ የመጡ መሆናቸው ግልጽ ነው የሚሉት ባለስልጣኑ፣ ያም ሆኖ ከትግራይ የመጡ በርካታ ጄኔራሎች ጡረታ እንዲወጡ ቢደረግም ሂደቱ ግን ረጅም ጊዜ የሚወሰድ ነው ሲሉ አክለዋል።

“የብሄር ተዋጽኦ ብቻ የአንድን ሰራዊት ጠንካራና ደካማ ጎን መገለጫ ተደርጎ መወሰድ ካለበት አደጋ አለው ” ያሉት ባለስልጣኑ፣ የአንድ ብሄር የበላይነት አለ ተብሎ በአጭር ጊዜ ለማመጣጠን ብቻ በአንድ አዳር ሁሉንም ነገር መቀየር እንደማይቻል መንግስት ያምናል ሲሉ ተናግረዋል

አቶ መለስ ዜናዊ በውጭ ሃይሎች ተገድለዋል ይባላልና በምን እንደሞቱ በትክክል ይነገረን በሚል ባለስልጣናት ላነሱት ጥያቄም የደህንነት ባለስልጣኑ፣ “አቶ መለስ በውጭ ሃይሎች ተገድለዋል የሚል ትክክለኛ ማስረጃ የለም በማለት መመለስ የጀመሩት ባለስልጣኑ፣ እርሳቸው የሞቱት በስራ ብዛት ተዳክመው እና ህክምናውን መቋቋም ባለመቻላቸው ነው ሲሉ ደምድመዋል።
በተያያዘ ዜናም የሃገሪቱን ደህንነት አደጋ ላይ ለመጣል ከኢሳት ጋር በመሆን እየሰራችሁ ነው፣ ለኢሳትም መረጃ ታቀብላላችሁ  ተብለው የተጠረጠሩ  5 የደህንነት አባላት በቁጥጥር ስር ውለዋል።  ወጣት መብራቴ ታምራት ፤ወጣት ጀማል አወል ፤ወጣት ደጀኔ አድማስ ፤ ወጣት ሃይሉ ጨርቆስ ፤መቶ አለቃ አሰፋ አብርሃ ሰሞኑን በደህንነቶች ቁጥጥር ስር መዋላቸውን የኢሳት የደህንነት ምንጮች ገልጸዋል።

በተመሳሳይ ዜናም በሃገሪቱ በ28ቱ ዩኒቨርስቲዎች የሚገኙ የህወሃት አባላት ተማሪዎች እና የደህንነቶች ሃለፊዎች ግምገማ መጀመራቸውን ለማወቅ ተችሎአል።
በግምገማው ወቅት የኦህዴድ እና የብአዴን መሪዎች የተማሪዎችን እንቅስቃሴ በመከታተል ባሰዩት ውጤት የተገመገሙ ሲሆን፣ ባለፉት ስድስት ወራት የአክሱም ፤ ደብረ ታቦር እና ደብረ ብርሃን የኒቨርስቲዎች ከፍተኛ የአመጽ እንቅስቃሴ የታየባቸው በመሆኑ ልዩ የደህንነት ክትትል እንደሚያስፈልጋቸው ተወስቷል።