Friday, December 6, 2013

የፍርሃት ባህልን (culture of fear) (culture of fear) (culture of fear) እያነገሰ ያለው የኢትዮጵያ ፖለቲካ፤ አንድ እርምጃ ወደፊት ሁለት ወደ ኋላ

ክፍል አንድ
December 6/2013
.ያሬድ ኃይለማርያም ኃይለማርያም ኃይለማርያም
ከቤልጅየም፤ ከቤልጅየም፤ ብራስልስ
ፍርሃት የግለሰቦች ባህሪ መገለጫ ስለሆነ በማኅበረሰብ በማኅበረሰብ በማኅበረሰብ ደረጃ የሚኖረውን ገጽታ እና ትርጓሜ ማስቀመጥ ያስቸግራል። ያስቸግራል። ያስቸግራል። አንዱ ሰው
የሚፈራውን ነገር ሌላው ላይፈራው ስለሚችል ፍርሃት እንደ የግለሰቡ ባህሪ እና ጥንካሬ ወይም ስነ----ልቦናዊ ሁኔታ የተለያየ መልክ
ይኖረዋል።። ይሁንና በአንድ ማኅበረሰብ ውስጥ የሚገኙ ሰዎች የሚጋሩት ባህልና ስነ----ልቦናዊ ሁኔታ እንደመኖሩ ሁሉ የሚጋሩትም
ፍርሃት ወይም ደስታ ወይም ሃዘን ወይም ድፍረት ወይም ሌሎች ባህሪያት ይኖራል።።። በዚህም ምክንያት አንዳንድ ሰዋዊ ባህሪያት
ለአንድ ማህበረሰብ ወይም ለበርካታ ሰዎች የወል መገለጫ ተደርጎ ሲገለጽ ይስተዋላል።።።። ‘‘‘‘የዚህ አካባቢ ሰዎች ጀግኖች ወይም ጸብ
ፈሪዎች ወይም እሩህ ሩህዎች ወይም ጨካኞች ወይም ቂመኞች ወይም ገራገሮች ወይም ተንኮለኖች ወይም ጎጠኞች ወይም ሌላ
ባህሪ ያላቸው ናቸው’ ’ ’ ’ የሚል አገላለጽ የተለመደ ነው።።። ይህ አይነቱ አነጋገር ሳይንሳዊ መሰረት ያለው ባይሆንም በአካባቢው ላይ
ጎላ ብለው በሚታዩ ሰዎች ላይ ተደጋግሞና ተዘውትረው የሚታዩ ተመሳሳይ ባህሪያት የአካባቢው ሰው ሁሉ መገለጫ ተደርገው
ስለሚወሰዱ ድምዳሜው ለስህተት የተጋለጠ ሊሆን እንደሚችል ከወዲሁ ለመግለጽ እወዳለሁ።።።። ከዚህ መንደርደሪያ መንደርደሪያ መንደርደሪያ በመነሳት
በዚህ ጥልቅ ጥናት ባላካሄድኩበት ባላካሄድኩበት ባላካሄድኩበት ነገር ግን ደጋግሜ ሳብሰለስለው ሳብሰለስለው ሳብሰለስለው በቆየሁት የፍርሃት ባህል እና በኢትዮጵያ የፖለቲካ ድባብ ዙሪያ
ያለኝን ምልከታ ለአንባቢያን ለአንባቢያን ለአንባቢያን ለማካፈልና በጉዳዩም ላይ ለመወያየት ወሰንኩ።

በአንድ ማኅበረሰብ ውስጥ የፍርሃት ድባብ እንዲሰፍን እና ከዚያም አልፎ ባህል እንዲሆን ምክንያት ከሆኑት በርካታ ነገሮች
መካከል የተወሰኑትን የተወሰኑትን የተወሰኑትን ልጥቀስና በእኛ ማኅበረሰብ ውስጥ ያላቸውን ገጽታ በመጠኑ ለመዳሰስ እሞክራለሁ። እሞክራለሁ። እሞክራለሁ። በስነ----ልቦና ጠበብቶች
ከሚጠቀሱት ዋና ዋና የፍርሃት ምንጮች መካከል፤ ነፃነትን ማጣት፣ ነገ የሚሆነውን ማወቅ አለመቻል፣ የህሊና እና የአካል ቁስልን
ባስከተሉ ትላንቶች ውስጥ ማለፍ፣ የማያቋርጥ ብስጭት ወይም ንዴት፣ ድህነት በሚያስከትለው ሚያስከትለው ሚያስከትለው ስቃይ ውስጥ መማቀቅ፣ አጋር እና
አለኝታ ማጣት፣ በሌሎች ክፉኛ መነቀፍ፣ መንጓጠጥ፣ መጠላት እና መገለል፣ በሚኖሩበት ማኅበረሰብ ዘንድ ተቀባይነትን ተቀባይነትን ተቀባይነትን ማጣት፣
የሞት አደጋን ማሰብ፣ ሽንፈት ወይም ስኬት አልባ ሆኖ መቆየት፣ እና ሌሎችም ይገኙበታል።።።። ከእነኝህ መክንያቶች ውስጥ የአንዱ
መከሰት አንድን ሰው ወደ ፍርሃት ውስጥ ሊከት እንደሚችል ጥናቶች ይጠቁማሉ።። ይጠቁማሉ። እነኝህ ምክንያቶች ተደራርበውና ተደራርበውና ተደራርበውና በአንድ ጊዜ
በአንድ ሰው ወይም በአንድ ማኅበረሰብ አባላት ላይ ሲከሰቱና ዕልባት ሳያገኙ እረዘም ላለ ጊዜ ሲቆዩ ደግሞ አደጋቸው የከፋ ነው
የሚሆነው።። ከዚህም በመነሳት ወደ እኛ ማህበረሰ ስንመለስ በግላችንም ሆነ በጋራ ህይወታችን ከላይ ከተጠቀሱት የፍርሃት
መንሰዔዎች መካከል ስንቶቹ በህይወታችን በህይወታችን በህይወታችን ውስጥ ተከስተዋል፣ ተከስተዋል፣ ተከስተዋል፣ ስንቶቹን በአሸናፊነት በአሸናፊነት በአሸናፊነት አለፍናቸዋል፣ አለፍናቸዋል፣ አለፍናቸዋል፣ ስንቶቹስ ዛሬም ድረስ
አብረውን ይኖራሉ፤ የሚሊቱን ጥያቄዎች እያንዳንዱ ሰው እራሱን እንዲጠይቅ እየተውኩ በወል በምንጋራቸው በምንጋራቸው በምንጋራቸው ጥቂት የፍርሃት
መንሰዔዎች ላይ ላተኩር።።።
የነፃነት ማጣት
ሰብአዊ መብቶች በገፍ በሚጣሱበት እና ዜጎች የሰውነት ክብራቸው ተገፎ፣ ተዋርደውና ነፃነታቸውን ነፃነታቸውን ነፃነታቸውን ተነጥቀው በሚኖሩበት አገር
ሁሉ ፍርሃት ትልቁ ገዢ ኃይል ነው።።። በእንዲህ ያለው ማህበረሰብ ውስጥ የፍርሃት ሰለባ የሆኑት እና ነፃነት አልባ ሕይወትን
የሚገፉት ተጨቋኞቹ ብቻ ሳይሆኑ ጨቋኞቹም ጭምር ናቸው።።። ተጨቋኖቹ በግፍ ልንገደል፣ ልንታሰር፣ የስቃይ ሰለባ ልንሆን፣
ታፍነን ልንሰወር፣ ከሃገር ልንሰደድ፣ ከሥራ ልንባረር፣ ንብረታችን ሊወረስ፣ በግዞት ከቦታ ቦታ ልንዛወር፣ ከቅያችን ልንፈናቀል፣ ልንፈናቀል፣ ልንፈናቀል፣
በሃሰት ክስ ልንወነጀል፣ ልንወነጀል፣ ልንወነጀል፣ ደሞዛችንን ልንነጠቅ፣ ከሥራ ደረጃችን ልንቀነስ፣ ወዘት … … … … እያሉ አደጋዎችን እያሰቡ በሽብርና በፍርሃት
ቆፈን ተይዘው ‘‘‘‘ጎመን በጤና’ ’ ’ ’ በሚል የማፈግፈጊያ የማፈግፈጊያ የማፈግፈጊያ ስልት መብቶቻቸውን መብቶቻቸውን መብቶቻቸውን አሳልፈው በመስጠት የግፍ እንቆቋቸውን እንቆቋቸውን እንቆቋቸውን እየተጎነጩ
መራራ ሕይወታቸውን ሕይወታቸውን ሕይወታቸውን ይመራሉ።።። ጨቋኞቹም ይህን በነፍጥ እና በሕግ አንበርክከው አንበርክከው አንበርክከው ነፃነቱን የነጠቁትና ለስቃይ የዳረጉት ሕዝብ
በአንድ አይነት ተአምር በቁጣ ገንፍሎ ከተነሳ አንድም ቀን እንደማያሳድራቸው እንደማያሳድራቸው እንደማያሳድራቸው ጠንቅቀው ስለሚያውቁ እያንዳንዱን እያንዳንዱን እያንዳንዱን ደቂቃና
ሰዓታት ልክ እንደ ተጨቋኙ በፍርሃት እና በሽብር ነው የሚያሳልፉት። የሚያሳልፉት። የሚያሳልፉት። ከቦታ ቦታ ሲንቀሳቀሱም፣ ሲንቀሳቀሱም፣ ሲንቀሳቀሱም፣ የእለት ሥራቸውንም
ሲያከናውኑ፣ ሲያከናውኑ፣ ሲተኙም ሆነ ሲዝናኑ በሠራዊትና በመሣሪያዎች ጋጋታ ታጅበው ነው።።። ምናልባትም ከተጨቋኞቹም ከተጨቋኞቹም ከተጨቋኞቹም በባሰ ፍርሃት
ውስጥ ነው የሚኖሩት።። የሚኖሩት።
ዛሬ ኢትዮጵያ ውስጥ ያለውን ሁኔታ በቅጡ ያጤንን እንደሆነ ገዢና ተገዢ እርስ በእርስ የሚፈራሩበት፤ የሚፈራሩበት፤ የሚፈራሩበት፤ መንግሥት ተቃዋሚ
ፓርቲዎችን፣ ፓርቲዎችን፣ ተቃዋሚዎች መንግሥትን የሚፈሩበትና የሚፈሩበትና የሚፈሩበትና አንዱ ሌላውን የማያምንበት የማያምንበት የማያምንበት ሁኔታ ነው የተፈጠረው። የተፈጠረው። የተፈጠረው። የመንግሥት ፍርሃት ከተቀናቃኝ የፖለቲካ ኃይሎች አልፎ የሲቪክ ማኅበረሰቡን፣ ማኅበረሰቡን፣ ማኅበረሰቡን፣ የሙያ ማኅበራትን፣ ማኅበራትን፣ ማኅበራትን፣ ነጋዴውን፣ ምሁራኑን፣ ገበሬውን፣ ወጣቱን እና
ሌላውንም የኅብረተሰብ የኅብረተሰብ የኅብረተሰብ ክፍል ክፉኛ የሚፈራበትና በቁራኛ የሚከታተልበት የሚከታተልበት የሚከታተልበት፤ እነሱም መንግስትን እንደ ተናካሽ አውሬ የሚፈሩበት
ሁኔታ ተፈጥሯል።። ተፈጥሯል። በመንግሥትና በመንግሥትና በመንግሥትና በሕዝቡ፣ በተቃዋሚ ፓርቲዎችና በመንግሥት፣ በመንግሥት፣ በመንግሥት፣ በሕዝቡና በተቃዋሚ ፓርቲዎች መካከል
ካለመተማመን ካለመተማመን የመነጨው ይህ ጥልቅ ፍርሃት በአገሪቱ የኢኮኖሚ፣ የፖለቲካ እና ማኅበራዊ እንቅስቃሴዎች እንቅስቃሴዎች እንቅስቃሴዎች ላይ ጥቁር ደመናን
ጋርዷል።።።። በገዢው ኃይል በኩል ያለውን የፍርሃት ድባብ ለመመልከት በየጊዜው መንግሥት የሚወስዳቸውን የሚወስዳቸውን የሚወስዳቸውን የኃይል እርምጃዎች፣ እርምጃዎች፣ እርምጃዎች፣
የሚያወጣቸውን የሚያወጣቸውን የማፈኛ ሕጎች፣ እያጠናከረ የሄደውን የሥለላና የአፈና መዋቅር፣ በመገናኛ ብዙሃን የሚያሰራጫቸውን የሚያሰራጫቸውን የሚያሰራጫቸውን ሕግን
ያልተከተሉ እና በሽብር መንፈስ የተዋጡ መግለጫና ዘገባዎችን መመልከት በቂ ነው።።። በተለይም የ1997ቱን ምርጫ ተከትሎ
የተቀሰቀሰው የተቀሰቀሰው የሕዝብ ቁጣ ያስደነበረው ያስደነበረው ያስደነበረው የወያኔ መንግሥት ከላይ የጠቀስኳቸውን የጠቀስኳቸውን የጠቀስኳቸውን እና አጥብቆ የሚፈራቸውን የሚፈራቸውን የሚፈራቸውን የኅብረተሰብ የኅብረተሰብ የኅብረተሰብ
ክፍሎች ቀፍድዶ ለመያዝና እንቅስቃሴዎቻቸውን እንቅስቃሴዎቻቸውን እንቅስቃሴዎቻቸውን ለመገደብ ባወጣቸው የጸረ----ሽብር፣ የሲቪክ እና የበጎ አድራጎት ድርጅቶች
መተዳደሪያ፣ መተዳደሪያ፣ የፕሬስ እና የፖለቲካ ፓርቲዎችን ምዝገባ፣ የፀረ----ሙስና እና ሌሎች አዋጆች ሥርዓቱ የአፈና እና የመብት እረገጣ
ተግባሩን ሕጋዊ ወደማድረግ ሂደት የተሸጋገረ መሆኑን ያሳያሉ።።። ፍጹም ሰላማዊ እና ሕጋዊ በሆነ መልኩ የመብት ጥያቄዎችን ባነሱ
ዜጎች ላይ፤ አቅመ ደካሞችን እንኳን ሳይለይ ‘‘‘‘የፈሪ በትሩን’ ’ ’ ’ ሲያሳርፍ በተደጋጋሚ ተስተውሏል። ተስተውሏል። ተስተውሏል።
ባለፉት ሃያ አመታት የአገዛዝ ሥርዓቱ የፈሪ በትሩን በተለያዩ የኅብረተሰብ የኅብረተሰብ የኅብረተሰብ ክፍሎች ላይ አሳርፏል።። አሳርፏል። ብዕርና ወረቀት በያዙ
ከከፍተኛ ደረጃ ተማሪዎች እስከ አንደኛ ደረጃ ትመህርት ቤት ሕፃናት ጋር ሳይቀር በተደጋጋሚ ጊዜያት ተላትሟል።። ተላትሟል። በርካቶችን
ገድሏል፣ አስሮ አሰቃይቷል፣ አሰቃይቷል፣ አሰቃይቷል፣ ደብድቧል፣ ከትምህርት ገበታቸው ላይ አፈናቅሏል፣ አፈናቅሏል፣ አፈናቅሏል፣ ከአገር አሰድዷል፣ በሃሰት ወንጅሎ አስፈርዷል። አስፈርዷል። አስፈርዷል።
በእምነት ቤቶች ውስጥ ገብቶ ከአማኞች፣ ከመንፈሳዊ አባቶች እና ይህን አለም ሸሽተው በገዳም ከከተሙ መነኮሳት ጋር ሳይቀር
ተላትሟል።። የኃይማኖት ተቋማት እንዲከፋፈሉና እንዲከፋፈሉና እንዲከፋፈሉና በገዢው ፓርቲ የፖለቲካ ተሿሚዎች ቁጥጥር ስር እንዲወድቁ ተደርገዋል። ተደርገዋል። ተደርገዋል።
ምእመናን በመስጊዶችና በመስጊዶችና በመስጊዶችና በቤተክርስቲያን በቤተክርስቲያን በቤተክርስቲያን ውስጥ እያሉ በታጠቁ ኃይሎች ተገድለዋል፣ ተገድለዋል፣ ተገድለዋል፣ ተደብድበዋል፣ ደብድበዋል፣ ደብድበዋል፣ ተዋርደዋል። ተዋርደዋል። ተዋርደዋል። ቀሳውስት
ጥምጥማቸውን ጥምጥማቸውን እንዲያወልቁ እንዲያወልቁ እንዲያወልቁ እና መስቀላቸውን መስቀላቸውን መስቀላቸውን እንዲጥሉ ተደርጎ በማጎሪያ ካምፖች ውስጥ የማሰቃየት ተግባር
ተፈጽሞቻቸውል። ተፈጽሞቻቸውል። ኢማሞች ጺማቸው እየተጎተተ ተወስደው ተደብድበዋል፣ ተደብድበዋል፣ ተደብድበዋል፣ ታስረዋል።። ታስረዋል። ይህ ሕዝብን የማዋረድ እና የማሸበር
ተግባር የመነጨው እንደ እኔ እምነት የገዢው ኃይል እየተባባሰበት እየተባባሰበት እየተባባሰበት ከመጣው የፍርሃት እና የመሸበር ስሜት የተነሳ በራስ
የመተማመን ስሜቱ እየተቦረቦረ እየተቦረቦረ እየተቦረቦረ በመሄዱ ነው።።። ዛሬ ሥርዓቱ የገዛ ጥላውንም የሚፈራበት፣ የሚፈራበት፣ የሚፈራበት፣ አባላቱ ላይ እንኳን እምነት ያጣበት
ደረጃ ላይ ደርሷል።።። ለእዚህም አንዱ ማሳያው በነጋ በጠባ ቁጥር ማቆሚያ በሌለው የግምገማ ስብሰባ አባላቱን ሲያስጨንቅ
መታየቱ እና ለዚሁ የሚያባክነው የሚያባክነው የሚያባክነው ጌዜ እና የሕዝብ ገንዘብ፣ የባለሥልጣናት የባለሥልጣናት የባለሥልጣናት ተደጋጋሚ ሹም ሽር እና ከአገር ከድተው የሚወጡ
ባለሥልጣናት ባለሥልጣናት እና የወያኔ አባላት ቁጥር መጨመሩ ነው።።።
ይህ የገዢው ኃይል የሕግን ልጓም በመበጣጠስ የፈረጠመ ክንዱን ይቀናቀኑኛል ይቀናቀኑኛል ይቀናቀኑኛል ባላቸው ግለሰቦች፣ ጋዜጠኞች፣ የፖለቲካ
ኃይሎችና የሙያ ማኅበራትና አባላቶቻቸው አባላቶቻቸው አባላቶቻቸው ላይ ሁሉ ማሳረፉ ቀሪውን የኅብረተሰብ የኅብረተሰብ የኅብረተሰብ ክፍል ክፉኛ እንዲደነብርና እንዲደነብርና እንዲደነብርና በፍርሃት ቆፈን
እንዲሸማቀቅ እንዲሸማቀቅ አድርጎታል። አድርጎታል። አድርጎታል። ዛሬ ኢትዮጵያ ውስጥ የሰብአዊ መብቶች መከበር፣ የዴሞክራሲ ጥያቄዎች እና የሕግ የበላይነት
መረጋገጥ የሁሉንም የኅብረተሰብ የኅብረተሰብ የኅብረተሰብ ክፍል የዕለት ተዕለት ሕይወት የሚነካ ቢሆንም የጥቂቶች ጉዳይ ተደርጎ ተወስዷል።። ተወስዷል። በእነዚህ
ጉዳዮች ላይ ጥቂት የሲቪክ ማኅበራት፣ ጥቂት ጋዜጠኞች፣ የተቃዋሚ ፓርቲዎች እና በጠአት የሚቆጠሩ ግለሰቦ ብቻ ናቸው
ባላቸው ውሱን ጉልበት እና አቅም ሲወያዩ፣ የምንግሥትን የምንግሥትን የምንግሥትን መጥፎ ተግባራት ሲቃወሙ፣ ለዜጎች መብት ሲሟገቱ እና ባደባባይ
ሲጮሁ የሚስተዋለው። የሚስተዋለው። የሚስተዋለው።
በድህነት አረንቋ ውስጥ ተዘፍቆ መቆየት
ሌላው እና ትልቁ የፍርሃት ምንጭ በከፋ ድህነት ውስጥ ለረዥም ጊዜ እየማቀቁ መቆየት እና ድህነቱ ባስከተለው የስቃይ ህይወት
አካላዊና መንፈሳው አቅም ተሸርሽሮ ክፉኛ መጎዳት እና መዳከም ነው።።። ሕዝብን በድህነት ውስጥ አምቆ በማቆየት ለሰው ልጅ
ከሚገባው ክብር ወርዶና ከእንስሳ ያልተሻለ ሕይወት እንዲኖር በማድረግ ቅስሙን መስበር የአምባገነኖች የአምባገነኖች የአምባገነኖች አንዱ የሥልጣን
እድሜአቸውን እድሜአቸውን ማራዘሚያ ሥልት ነው።።። የድህነት ክፋቱ ኪስን ብቻ ሳይሆን የሚያራቁተው የሚያራቁተው የሚያራቁተው ክብርንም ጭምር ነው።።። አንድ ሰው
በመንገድ ላይ ቆሞና እራሱን ከመጽዋቾቹ ሥር ዝቅ አድርጎ ቁራሽ ምግብ ወይም ቤሳ ሲለምንና ሲማጸን በኩራትና በደስታ ስሜት
ውስጥ ሆኖ አይደለም።። አይደለም። እያፈረ እና እየተሸማቀቀ እየተሸማቀቀ እየተሸማቀቀ በተሸናፊነትና በተሸናፊነትና በተሸናፊነትና በዝቅተኝነት በዝቅተኝነት በዝቅተኝነት ስሜት ውስጥ ሆኖ ነው።።። ይህ ክስተት በሙሉ
ጤንነት እና በወጣትነት ወይም በጉልምስና እድሜ ላይ ባሉ ሰዎች ውስጥ ሲሆን ደግሞ ያለው የውስጥ ሕመም እና የሕሊና ቁስል
እጅግ የከፋ ነው።።። የድህነት ክፋቱ ያፈሩትን ቅሪት ብቻ ሳይሆን የሚያሳጣው ወይም ኑሮን ለማሸነፍ የሚያስችል አቅምን ብቻ
ሳይሆን የሚሸረሽረው የሚሸረሽረው የሚሸረሽረው መንፋሳዊ ወኔንም ጭምር ነው ከላያችን ገፎ የሚወስደው። የሚወስደው። የሚወስደው። ከሰውነት ደረጃ ላይ የሚያቆመንን የሚያቆመንን የሚያቆመንን መንፈሳዊ
ልዕልና ካጣን በኋላ ቁሳዊ ድህነቱን ብናሸንፈው እንኳን መንፈሳዊ ድህነቱ ይከተለናል። ይከተለናል። ይከተለናል። እዚህ ላይ ለማሳሰብ የምወደው ነገር ድሃ
ሁሉ ፈሪ ነው ወይም በፍርሃት ቆፈን የተተበተበ ነው የሚል የተሳሳተ ግንዛቤ እንዳይወሰድ እንዳይወሰድ እንዳይወሰድ ነው።።። በከፋ የኢኮኖሚ ድህነት ውስጥ
እየኖሩ ክብራቸውን አስጠብቀውና አስጠብቀውና አስጠብቀውና እና በላቀ የመንፈሳዊ ወኔያቸው እራሳቸውንና እራሳቸውንና እራሳቸውንና አገራቸውን አስከብረው ያለፉ ድሃ አያት ቅድመ
አያቶቻችንን አያቶቻችንን ማሰብ የግድ ይላል።።። ዛሬም የገንዘብ እጦትና ድህነት ያላላሸዋቸውና ያላላሸዋቸውና ያላላሸዋቸውና መንፈሳዊ ልዕልናቸውን አስጠብቀው በክብር
የሚሞቱ ወገኖች አሉን፤ ትቂቶች ቢሆኑም።።። የዚህ ጽሁፍ ትኩረት ግን በቁሳዊውም ሆነ በመንፈሳዊ ማንነታቸው ውስጥ ድህነትና ፍርሃት ተረባርበው ወይም ከሁለቱ በአንዱ
ተጠልፈው ስብእናቸው ፈተና ውስጥ የወደቀባቸውን የወደቀባቸውን የወደቀባቸውን ሰዎች የሚመለከት ነው።።። በተለይም በዚህ ግለኝነት በነገሠበት እና ገንዘብ
በሚመለክበት በሚመለክበት የአለም ወቅታዊ ሁኔታ ውስጥ መናጢ ድሃ ሆኖ ለዘመናት መቆየት መዘዙ ብዙ ነው።።። ብዙዎች ከዚህ መቋጫው
ከጠፋው የድህነት አረንቋ ለማምለጥ ስደትን አማራጭ አድርገው በተለያዩ አቅጣጫዎች አገሪቷን ለቀው ለአረብ አገራት ባርነት
ተሰደዋል።። ቀሪዎች ደግሞ የአገዛዝ ሥርዓቱ ሎሌ በመሆን ነፃነታቸው በቤሳ መሸቀጥን ቀጥለዋል።። ቀጥለዋል። ለሁለቱም እድሉን ያጡ
በሚሊዮን የሚቆጠሩ ድሆች ደግሞ በየጎዳናው ላይ ተበትነው ዝናብ፣ ውርጭና ፀሃይ እየተፈራረቁባቸው እየተፈራረቁባቸው እየተፈራረቁባቸው የመጽዋቾቻቸው ደጅ
ጠኞች ሆነዋል።።።
ከተወሰኑ አሥርት አመታት በፊት አንድ ሰው በድህነቱ ምክንያት እራሱንና ልጆቹ የትምህርት፣ የትምህርት፣ የትምህርት፣ የጤና አገልግሎት፣ አገልግሎት፣ አገልግሎት፣ መሰረታዊ የሆን
አልባሳትና መጠለያ ጎጆ ባለቤት ለማድረግ የሚገጥመው ፈተና ቢኖርም ይህን ያህል የመረረ አልነበረም። አልነበረም። አልነበረም። ዜጎች በወር ከሁለት ብር
አንስቶ እንደ የአቅማቸው የቀበሌ እና የኪራይ ቤቶችን ቤቶች ተከራይተው የመጠለያ ችግራቸውን ይቀርፉ ነበር።።። በአገሪቷ ውስጥ
የነበሩ በርካታ የሕዝብ ትምህርት ቤቶች ከመመዝገቢያ ከመመዝገቢያ ከመመዝገቢያ ያልዘለለ አነስተኛ ገንዘብ እየተቀበሉ ተማሪዎችን በነጻ ያስተናግዱ ነበር።።።
ብዙ ምሁራንንም አፍርተዋል። አፍርተዋል። አፍርተዋል። በየቀበሌው ከተደራጁ ጤና ጣቢያዎች አንስቶ በተለያዩ የመንግሥት ሆስፒታሎች ዜጎች በነፃና
እጅግ ተመጣታኝ በሆነ ክፍያ ጥሩ ሕክምና የማግኘት እድል ነበራቸው።። ነበራቸው። በአንድ ብር በሚገዛው አስር ትንንሽ ዳቦ ወላጆች
ልጆቻቸውን አብልተው ያሳድሩ ነበር።።። ዛሬ አገሪቱ በልማት እየገስገሰች እየገስገሰች እየገስገሰች እንደሆነ በሚነገርበት በሚነገርበት በሚነገርበት በዚህ ወቅት ዜጎች በኑሮ ውድነትና
ዋስትና ማጣት በጨለማ ህይወት ውስጥ እየተደናበሩ ይገኛሉ።።።
መንግሥት በኢኮኖሚውም፣ በኢኮኖሚውም፣ በኢኮኖሚውም፣ በፖለቲካውም በፖለቲካውም በፖለቲካውም ሆነ በሌሎች ኃይማኖታዊና ኃይማኖታዊና ኃይማኖታዊና ማኅበራዊ ጉዳዮች ያሻውን ቢያደርግ በሕዝብ በኩል
መላሹ ዝምታ ሆኗል።።።። አብዛኛው ሕዝብ ከተዘፈቀበት ከተዘፈቀበት ከተዘፈቀበት የድህነት አረንቋ ሳይወጣ በርካታ ነገሮች ተቀይረዋል። ተቀይረዋል። ተቀይረዋል። በመቶና በሁለት መቶ
ይገዛ የነበር ጤፍ በሺዎች ሲያወጣ ምላሹ ዝምታ ሆኗል።።። ቲማቲም እንኳን ባቅሟ በኪሎ ከሁለት ብር ወደ ሃያ ብር ስትጠጋ
አንዳንዴም ስትዘል ዝምታ፣ የቤት ኪራይ ከመቶዎች ወደ ሺዎች ሲንር ዝምታ፣ የነዳጅ ዋጋ በየጊዜው ሲያሻቅብ ዝምታ፣
የመብራት፣ የውሃ፣ የስልክ እና የኢንተርኔት የኢንተርኔት የኢንተርኔት አገልግሎቶች አገልግሎቶች አገልግሎቶች በሰአታት፣ ከዚያም ለቀናት አንዳንዴም በተወሰኑ ቦታዎች ለሳምንታት
ሲጠፉ ዝምታ፣ መነኮሳት እና አድባራት ሲዘረፉና ሲዋረዱ ዝምታ፣ መስጊዶች እና ኢማሞች ሲዋክቡና ሲታሰሩ ዝምታ፣ የአገር
ሽማግሌዎች፣ ሽማግሌዎች፣ ፖለቲከኞች፣ ፖለቲከኞች፣ ፖለቲከኞች፣ ጋዜጠኞች እና የሰብአዊ መብት ተሟጋቾች ሲደበደቡ፣ ሲታሰሩና ሲሳደዱ ዝምታ፣ የንግዱ ማኅበረሰቡ
ሲዋክብና ሲጉላላ ዝምታ፣ ገበሬዎች በማዳበሪያ እዳ ንብረታቸውን ንብረታቸውን ንብረታቸውን ሲነጠቁና ከዛም አልፎ ከትውልድ ትውልድ ያቆዩትን
ይዞታቸውን እየተነጠቀ ለውጪ ቱጃሮች ሲቸበቸብ ዝምታ፣ ወንዶች ሚስቶቻቸውና ሚስቶቻቸውና ሚስቶቻቸውና ሴት ልጆቻቸው እፊታቸው ሲደፈሩና ሲጠቁ
እያዩ ዝምታ፣ እናቶች ልጆቻቸውና ባሎቻቸው በየወጡበት ሲቀሩ እያዩ ዝምታ፣ በየከተማው የሚገኙ ነዋሪዎች ቤታቸ በላያቸው
ላይ እንዲፈርስ እየተደረገ ከነልጆቻቸ በየሜዳው ተበትነው ይዞታቸው ለስግብግብ ባለሃብቶች ሲሰጥ ዝምታ፣ የሙያ ማኅበራት
ሲጠቁ ዝምታ፣ መምህራኖች ሲዋከቡ ዝምታ፣ በብዙ ሺዎች የሚቆጠሩ ሠራተኞች ከሥራ ገበታቸው ‘‘‘‘በድህነት ቅነሳ እስትራቴጂ’’’’
ስም ሲፈናቀሉና ለርሃብ ሲዳረጉ ዝምታ፣ ባለሥልጣናት ባለሥልጣናት ባለሥልጣናት የከፋ ሙስና ውስጥ ተዘፍቀው ሲንቦጫረቁ ዝምታ፣ ሕፃናት ሳይቀሩ
በየአደባባዩ በየአደባባዩ ግንባራቸው በጥይት እየተቦደሰ ሲረሸኑ ዝምታ፣ የአገሪቷ የትምህርት ሥርዓት ክፉኛ አቆልቁሎ ትውልድን ወደማክሰም
ደረጃ ላይ ሲደርስ እየተመለከትን እየተመለከትን እየተመለከትን ዝምታ፣ መንግሥት ድህነትን ሸሽተው ከሃገር የሚሰደዱ ወጣቶችን መንገዱን ጨርቅ
ያድርግላችው ያድርግላችው እያለና ገንዘብ እየቃረመ ለዘመናዊው ባርነት እያዘጋጀ ፓስፖርት ሰጥቶ ሲያሰድድ ዝምታ፣ በየጎዳናው የወደቁ
ሕፃናቶችን በጉዲፈቻ ስም መንግስት ለውጪ ዜጎች በብዙ ሺ ዶላር ሲቸበችብ እያየን ዝም፣ መንግስት የራሱን ሕገ----መንግስት
እየናደ የፈቀደውን ሁሉ በዜጎች ላይ ሲፈጽም የህዝብ ምላሽ ዝምታ፣ ዝምታ፣ ዝምታ…………........።።።። ስንቱ ተጠቅሶ ይቻላል?
አንድ ሕዝብ ይህ ሁሉ ውርጅብኝ ያለፋታ ሲዥጎደጎድበት ሲዥጎደጎድበት ሲዥጎደጎድበት እና መገለጫ የሌልውን ግፍ እና ጭቆና በጫንቃው ላይ ሲጫንበት
ውስጥ ውስጡን እያጉረመረመ፣ እያጉረመረመ፣ እያጉረመረመ፣ እያለቀሰና ልቡ እየደማ እንዴት ነህ ሲሉት ደህንነቱን ለመግለጽ ‘‘‘‘እግዚያብሄር እግዚያብሄር እግዚያብሄር/ አላህ ይመስገን’ ’ ’ ’
እያለ የውሸት ሳቅ እየሳቀ እንዲኖር ያስገደደው ምንድን ነው? መንፈሱና አካሉ በቁሙ ተሸርሽረው እያለቁ ባልሞትኩም ባይነት
የአያቶቹን ገድል በህሊናው እያመነዥከ በዘመኑ ለተጋረጡበት ለተጋረጡበት ለተጋረጡበት ፈተናዎች፤ በተለይም ድህነት፣ የፖለቲካና የኢኮኖሚ ጭቆዎችና
በገዛ አገሩ ተዋርዶ መኖርን ለመሸሽ ስደትን ወይም ልመናን ወይም ሕሊናን ቀብሮ ለሥርዓቱ አገልጋይ መሆንን ከማን ተማረ? ይህ
ጥልቅ የሆነው ዝምታችን የፍርሃት? ወይስ የትእግስት? ወይስ በፍርሃትና በትእግስተኛነት በትእግስተኛነት በትእግስተኛነት መካከል ሌላ ደሴት ወይም መንጠልጠያ
ስፍራ አለ? እራሳችንን እንጠይቅ!
በቀጣዩ ክፍል እስከምንገናኝ እስከምንገናኝ እስከምንገናኝ በቸር እንሰንብት!

ኔልሰን ማንዴላ በሕይወት ቢለዩንም በመንፈስ አብረውን ይቆያሉ

Decenber6/2013

በአፓርታይድ የደቡብ አፍሪቃ መንግሥት ብቻ ሳይሆን በዩ. ኤስ. አሜሪካ ጭምር ሽብርተኛ ተብለው ሲሳደዱ፣ ሲታሰሩና ሲሰቃዩ የሕይወታቸውን አጋማሽ የጨረሱ፤ በመሣሪያ የታገዘ አመጽንና ሕዝባዊ እምቢተኝነትን አጣምሮ የያዘ ሁለ-ገብ ትግል በመምራት ለአፓርታይድ አገዛዝ ማብቃት ከፍተኛ ድርሻ ያለው የትግል አስተዋጽዖ ያደረጉ፤ ለመላው ዓለም የነፃነት ታጋዮች አርአያ የሆኑት ኔልሰን ማንዴላ አረፉ።
ኔልሰን ማንዴላ የነፃነት ትግልን በግንባር በመሰለፍ መርተዋል። ኢትዮጵያ ድረስ በመምጣት ወታደራዊ ሥልጠና ወስደው ዘረኛዉን የፕሪቶሪያ አገዛዝ በመሣሪያ ታግለዋል። የእሳቸው ጠመንጃ ማንሳት ለበርካታ ወጣት ታጋዮች አርዓያ ሆኗል። እስር ቤት በቆዩባቸው 27 ዓመታት ደግሞ የድርጅታቸውንና የትግሉን አመራሩ ለጓዶቻቸው በመተው እርሳቸው ለነፃነትና ለእኩልነት በመታሰርና ስቃይን በመቀበል ትግሉን መርተዋል። በዚህም ምክንያት በትግል ሜዳም በእስር ቤትም መሪ እንደሆኑ የዘለቁ ታላቅ አፍሪቃዊ ናቸው።
ከነፃነት በኋላ ደግሞ ኔልሰን ማንዴላ በሕዝብ ነፃ ፈቃድ የተመረጡ የአዲሲቷ ደቡብ አፍሪካ የመጀመሪያ ፕሬዚዳንትነት ሆነዋል። በየምርጫው ተወዳድሬ አሸንፌ በፕሬዚዳንትነት ልቀጥል ሳይሉ በአፍሪቃ ባልተለመደ ሁኔታም አንድ ዙር ብቻ አገልግለው ደግመው ላለመወዳደር ወስነው በጊዜ ሥልጣናቸውን በመልቀቅ መርተዋል። በመሆኑም ኔልሰን ማንዴላ ሥልጣን ላይ ሆነውም ሥልጣን ለቅቀውም መሪ መሆን የቻሉ ድንቅ አፍሪቃዊ ናቸው።
ኔልሰን ማንዴላ ታላቅ የነፃነት አርበኛ፣ ታላቅ የለውጥ አራማጅ፣ ታላቅ መምህር እና ታላቅ የእርቅ ሰው ነበሩ። ዛሬ ዓለም እኚህን ታላቅ አፍሪቃዊ አጣች።
ግንቦት 7: የፍትህ፣ የነፃነትና የዲሞክራሲ ንቅናቄ በኔልሰን ማንዴላ ሕልፈት የተሰማውን ጥልቅ ሐዘን ይገልፃል። ከእንግዲህ ማንዴላን የምናስባቸው ከእሳቸው ተሞክሮ የምንማረው ሲኖር ነው። በዘረኝነት እየተጠቃን ላለነው ኢትዮጵያዊያን የማንዴላ ትምህርት ሕያው ሊሆን ይገባል።
ግንቦት 7: የፍትህ፣ የነፃነትና የዲሞክራሲ ንቅናቄ፣ ዘረኝነትን በጽናት የመታገል ሆኖም ግን ይቅር ባይ የመሆንን እሴቶች ተግባራዊ በማድረግ ማንዴላ በሕይወት ቢለዩንም በመንፈስ ሁሌም አብረውን እንዲኖሩ እናድርግ ይላል።
የግንቦት 7: የፍትህ፣ የነፃነትና የዲሞክራሲ ንቅናቄ ህዝብ ግንኙነት

የችግሮቻችን የመፍትሔ ቁልፍ – ወያኔን አስወግዶ ፍትህን ማስፈን

December 6/2013

አሁንም በሳውዲ አረቢያ እና አካባቢው አገሮች የሚገኙ ወገኖቻችን የድረሱን ጥሪዎች እያሰሙ ነው። የወገኖቻችን ዋይታና ሰቆቃ አልበረደም። ዛሬም እህቶቻን እየተደፈሩ፣ እየተዋረዱ፣ እየተገደሉ ናቸው። በጥጋብ አገር ውስጥ ሆነው ኢትዮጵያዊያን ሕፃናት በረሀብና በጥም እየሞቱ ነው። በርካታ ኢትዮጵያዊያን ለከፋ የአዕምሮ ህመም እየተዳረጉ ነው።
በተለያዩ የዓለም አገራት የሚገኙ ኢትዮጵያዊያን በመካከለኛው ምሥራቅ የሚገኙ ወገኖቻቸውን ሕመም እየታመሙ፤ ስቃያቸውን እየተሰቃዩ ይገኛሉ። አስቸኳይ እርዳታ ለማድረስም አቅማቸው የቻለውን ሁሉ ለማድረግ በመረባረብ ላይ ናቸው።
ባለፉት ጥቂት ሣምንታት ኢትዮጵያዊያን ባደረጓቸው ብርቱ ጥረቶች ጥቂት አበረታች ውጤቶች ተገኝተዋል። ከደረሰባቸው የመብት ረገጣ ጋር ፈጽሞ ተመጣጣኝ ባይሆንም ቢቢሲን ጨምሮ አንዳንድ የዓለም ዓቀፍ የዜና አውታሮች በወገኖቻችን ላይ ስለሚደርሰው በደል እንዲዘግቡ ማድረግ ተችሏል። እስካሁን ምን ያህል ወገኖቻችን እድሉን እንዳገኙ ማረጋገጥ ባይቻልም የሳውዲ መንግሥት ሙሉ የትራንስፓርት ወጪ ችሎ ወገኖቻችን ማጓጓዝ ጀምሯል። ዓለም ዓቀፍ የሰብዓዊ መብት ጥበቃ ድርጅቶች ለኢትዮጵያዊያን መብት መከራከር ጀምረዋል።
በአንፃሩ ግን አሁንም ሕሊናን የሚረብሹ ነገሮች እየተሰሙ ነው።
  1. ከሳውዲ እየታፈሱ የመን ድንበር ላይ የተጣሉ፤ የደረሱበት የማይታወቁ ኢትዮጵያን ቁጥር በየእለቱ እየጨመረ ነው። እነዚህ ወገኖቻችን በየመን በረሀ ላይ የሚደርስባቸው ሰቆቃ ሳውዲ ውስጥ ከነበረው የባሰ ነው።
  2. አሁንም በሳውዲ ተደብቀው የሚገኙ፤ “እጃቸውን ለመንግሥት ሰጥተው” እንደ ወንጀለኛ በእስር ቤቶች የሚማቅቁ በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያዊያን አሉ። እነዚህ ወገኖቻችን ያሉበት ሁኔታ ሕሊና ሊሸከመው ከሚችል በላይ ነው።
ከዚህ ሁሉ በላይ ኢትዮጵያዊያንን እየረበሸ ያለው የወያኔ ባህርይ ነው።
ወያኔ በእንዲህ ዓይነት የመከራ ወቅትም በወገኖቻችን ላይ ዘርፈ ብዙ ንግድ እያጧጧፈ ነው። በሳውዲ አረቢያ መንግሥት ወጪ የተመለሰሉትን ወገኖቻችን ለምርጫ ቅሰቀሳ ፕሮፖጋንዳ ሥራ እየተጠቀሙባቸው መሆኑ ሳያንስ ለእለት ጉርስ የሚሰጣቸው የእርዳታ ገንዘብ በወያኔ እየተዘረፉ ነው። ገንዘብ ባለበት ሁሉ ወያኔ አለ። ወያኔ ለተመላሽ ስደተኞች የእለት ጉርስ የተሰጠውንም እርዳታ እየቀማ የሚበላ እኩይ ኃይል ነው።
ድሆች ኢትዮጵያዊያን ወደ አረብ አገራት ሲሰደዱ ለወያኔ ድርጅቶች ገንዘብ ከፍለው ነው። እዚያ በነበሩበት ጊዜም ለወያኔ ገንዘብ እንዲከፍሉ ይደረግ ነበር። በግፍ ተፈናቅለው፤ ሀብታቸው ተዘርፎ ባዶ እጃቸውን ሲመለሱም ለወያኔ የእርዳታ ገንዘብ መለመኛ ሆነዋል። ወያኔ በድሆች ኢትዮጵያዊያን ድህነት የሚከብር በታሪካችን ውስጥ ታይቶ የማይታወቅ ስግብግብ ነው። ወያኔ ኢትዮጵያዊያን ፈጽሞ ሊጠየፉት የሚገባ ነው ስብስብ ነው።
ግንቦት 7: የፍትህ፣ የነፃነትና የዲሞክራሲ ንቅናቄ በችግር ላይ የሚገኙ ወገኖቻችንን ከመርዳት ጎን ዓይኖቻችንን ከወያኔ እንዳንነቅል በአጽንዖት ያሳስባል። ወያኔ ከሥልጣን ሳይወገድ ችግሮቻችንን መፍታት አንችልም። የኢትዮጵያዊያን ችግሮች ለወያኔ የገቢ ምንጮች ናቸና ወያኔ እስካለ ድረስ ችግሮችን መፍጠሩና ማስፋፋቱ አይቀርም።
የኛ የኢትዮጵያዊያን ችግሮች የመፍትሔ ቁልፍ ያለው ወያኔን በማስወገድ ፍትሀዊ አመራር ማስፈን ላይ በመሆኑ የጋራ ትኩረታችን እዚያ ላይ እንዲሆን ግንቦት 7 ያሳስባል።
 ድል ለኢትዮጵያ ሕዝብ!!!

የመለስ ጎጂ ሃሳቦችና ድርጊቶች

የኢትዮጵያ ሲቪክ ንቅናቄ  (Ethiopian Civic Movement )
 ሕዳር 2006
December 6/2013
የኢትዮጵያ አንድነትንና የመንግስት ስርዓቱን የሚመለከቱት የመለስ ሃሳቦችና ድርጊቶች ለኢትዮጵያ ህዝብ ከባድና አሳሳቢ ትርጉም አላቸው፡፡ የአንድነቱ ጥያቄ የኢትዮጵያ እንደ አገር የመኖርና ያለመኖር ጉዳይ ሲሆን፣ ስርአቱ ደግሞ በኢትዮጵያ ህዝብ መብቶች ላይ ማን መወሰን እንደሚችል ያመለክታል፡፡ የአገር ህልውና እና የህዝብ መብትን ያህል ትልቅ ጉዳይ ሊኖር ስለማይችል ክብደቱና አሳሳቢነቱ አያጠያይቅም፡፡
መለስ አንድነትን በሚመለከተው ሃሳቡ ትግራይን ከመገንጠል ኣላማ ጀምሮ ሳይተገብረው ቢቀርም፤ ኢትዮጵያን ወደብ አልባ አድርጓል፤ ህዝብን በቋንቋ ክልሎች ከፋፍሎ በጉራ ፈርዳና ቤኒሻንጉል-ጉሙዝ ለተከሰቱት አማሮችን የማፈናቀል ግፍ መሰረት ጥሏል፤ የመገንጠል “ህገ መንግስታዊ” አንቀፅ አዘጋጅቷል፤ ለሱዳን መሬት አድሏል፤ ዜጎችን አፈናቅሎ ለም መሬት ለውጭ ድርጅቶች በርካሽ ለረዥም ጊዜ አከራይቷል፡፡
የመንግስት ስርዓቱ በቃላት መድብለ ፓርቲ በተግባር ያንድ ፓርቲ አፋኝ ስርዓት ነው፡ስለዚህም ስርዓቱ በኢትዮጵያና በኢትዮጵያውያን ላይ ወሳኙ መለስ እንደነበረ ለ21 ዓመታት ደጋግሞ አረጋግጧል፡፡ ሰውየው በኢትዮጵያ በነበሩ መንግስታት በተለመደ መሳሪያ ማለትም የፈላጭ ቆራጭነት ስልጣንን በመጠቀም፣ በኢትዮጵያ ግን ያልተለመደና በውጭ ሃይሎችም ያልተሳካ፣ ኢትዮጵያን የማፍረስ ዓላማ ለመተግበር ሞክሯል፤ በከፊልም ተሳክቶለታል፡፡
አሁን ጥያቄው ከመለስ ህልፈተ-ህይወት በሁዋላ የኢትዮጵያ ህዝብን አፍኖ አንድነቱን የሚሸረሽረው ስርዓት ምን ይሁን? ነው፡፡ መልሱም የመለስ ስርዓት መፍረስ፣ አስተሳሰቡም መወገዝ አለበት እንደሆነ ለኢትዮጵያውን አሻሚ መሆን የለበትም፡፡
በዚህ መሰረት ካልታረሙ ለወደፊቱም ሊቀጥሉ የሚችሉ፣ ህወሓት የትጥቅ ትግል ከጀመረበት ጀምሮ እሰካሁን ያሉ በዋናነት ከመለስ የፈለቁ ጎጂ አስተሳሰቦችና አሰራሮች ባጭሩ መቃኘት ያስፈልጋል፡፡
ያልተፃፈ የጥንት ታሪክ አሁን ሲፃፍ ያልተረጋገጡ ወሬዎችና ግምቶች እንደ እውነተኛ ታሪክ የመፃፈቸው አደጋ ከፍተኛ ቢሆን የሚጠበቅ ነው፡፡ ታሪኩ ሲፈፀም የነበሩ ሰዎች በህይወት እያሉና የፅሁፍ ማስረጃዎች ሳይታጡ ያልተፈፀመ ታሪክ ብቻ ሳይሆን የእውነቱ ተፃራሪ የሆነ ታሪክ ሲፃፍና ሲነገር ግን በጣም ያሰገርማል፡፡ ጠንቁም ብዙ ነው፡፡ እንደዚህ ዓይነት ውሸት የሚያሰራጩ ሰዎችን እንዴት ማመን ይቻላል? ለምንስ በዚህ መልክ ይቀጥላሉ? |ብለን መልስ-አዘል ጥያቄን በማቅረብ ጉዳዩን ላንባቢዎች ፍርድ መተው እንችል ነበር፡፡ ይሁን እንጂ በመለስ ትእዛዝ ውሸቱን የሚያሰራጩት ሰዎች ደግሞ በበኩላቸው በውሸቱ የሚያምኑ ሰዎችን መፍጠር ችለዋል፤ ምክንያቱም በጉልበት መገናኛ ብዙሃንን ለሁለት አሰርት ዓመታት በብችኝነት በመቆጣጠር የተወሰነ ህዝብ ጀሮን አይንና አእምሮን ተቆጣጥረው ህዝቡ መስማት፣ ማየትና መግለፅ ያለበትን ሲወስኑ ቆይተዋል፡፡ ስለዚህ ውሸቱ እውነት መስሎ ህዝብን ማወናበዱ እንዳይቀጥል የሚያመዛዝን አእምሮ ያላቸው ዜጎች እውነቱን ለማወቅና ለማሳወቅ ጥረት ማድረግ አለባቸው፡፡ ባንድ በኩል በውሸት ላይ በተመሰረተ ቅስቀሳ የተስፋፋውን ድንቁርና ማጋለጥና ማስወገድ፤ በሌላ በኩል ለዘለቄታዊ የህዝብ ደህንነት ጥፋት የሚያስከትሉትን ሃሳቦችና አሰራሮች እንደ አደገኛ ቆሻሻ ላንዴና ለሁሌ መቅበር ያስፈልጋል፡፡
መለስና ግብረ-አበሮቹ በ1968 ባወጡት የህወሓት (የዚያን ጊዜ ተሓህት) መግለጫ (ማኒፌስቶ) ትግራይን ከኢትዮጵያ የመገንጠል ዓላማ እንደነበራቸው በይፋ ስለገለፁ፣ መለስ ኢትዮጵያን የሚያፈርስ እንጂ ኢትዮጵያን የሚጠቅም ራእይ ይዞ ለትግል አልተሰለፈም፡፡ ሰውየው የፈለገው ራእይ ቢኖረው ኢትዮጵያን የሚመለከት በጎ ነገር ሊሆን አይችልም፡፡ ሃቁ ይህ ነው፤ በቃ፡፡
የመለስ ፍጡራን ማኒፌስቶው መታረሙን በመጥቀስ ቁም ነገር የተናገሩ ሊመስላቸው ይችላል፡፡ ቁምነገሩን ጭራሽ የሳቱት ቢሆኑም፣ ማኒፌስቶው እንደታረመ የሚገልፁት ሰዎች ቢያንስ የእርማቱን አስፈላጊነት ስለሚገነዘቡ ይህንን ግንዛቤ ከሌላቸው ሰዎች ይሻላሉ፡፡ ሆኖም፡
1ኛ ትግራይን ከኢትዮጵያ የመገንጠል ዓላማ ማንሳቱ ራሱ በኢትዮጵያዊነቱ በሚያምን ሰው ሊነሳ እንደማይችል ሊያስተባብሉ አይችሉም፡፡
2ኛ እርማቱ (በ1971 የህወሓት ጉባኤ) በመገንጠል ፈንታ የትግራይ ህዝብ የራሱን እድል በራሱ እንዲወስን መታገል እንደ ድርጅታዊ ዓላማ ማስቀመጥ ስለነበረ ከማጭበርበር የተለየ ትርጉም የለውም፡፡ ምክንያቱም በአንድነትና በመገንጠል አማራጮች አንድ ህዝብ ድምፁን በመስጠት መወሰን የሚያስፈልገው የአንድነትና የመገንጠል ሃይሎች ሲኖሩ ነው፡፡ ደርግ ፀረ ዴሞክራሲ ቢሆንም አቋሙ ላንድነት ነበር፤ የትግራይ ህዝብም የመገንጠል ጥያቄ አላነሳም፡፡ ስለዚህ የመገንጠል ፍላጎቱ የመለስና ግብረ-አበሮቹ አቋም ነበር፡፡ መለስና ግብረ-አበሮቹ በመገንጠል ፍላጎታቸው ያልቀጠሉበት አንዱ ምክንያት በተለይ ህዝብን አፍነው ከመቆጣጠራቸው በፊት ለዓላማቸው የህዝብ ሰፊ ድጋፍና ያንዳንድ ታጋዮች ትብብር እንደማያገኙ ስለተገነዘቡ ነው፡፡ በዛም ምክንያት በድርጅታቸው ውስጥ በ68 የፃፉትን ማኒፌስቶ ለድርጅቱ አባሎች ሳያሰራጩ ቀርተዋል፡ ሁለተኛው ምክንያት የህወሓት ሰራዊት በኢትዮጵያ ደረጃ ስልጣን ለመያዝ የሚያስችል ጥንካሬ ስላካበተና እነ መለስ ራሳቸው በጠፈጠፏቸው አሻንጉሊት ድርጅቶች መሳሪያነት ኢትዮጵያውያንን እየከፋፈሉና እጨፈጨፉ መግዛትና መዝረፍ ስለቻሉ ነው፡፡ ትግራይን የመገንጠል ቅሰቃሳ ከቆመ በሁዋላም የመለስ ነገድ-ተኮር ፖለቲካ በመገንጠል መብት ስም ህጋዊ ልባስ እንዲያገኝ በህገ መንግስት ተካትቷል፡፡
እውነቱ ከላይ እንደተገለፀው የማሻማ እያለ መለስ የተቆጣጠረው ህወሓት ከመጀመሪያ ጀምሮ ለኢትዮጵያ አንድነት እንደታገለ፣ ያ ቡድን ዓላማው ኢትዮጵያን ለመታደግ እንደነበረ አሁን የሚወራው የፈጠራ ታሪክ ከየት መጣ? በኢህአዴግ የረቀቀው ህገ መንግስት ኢትዮጵያን ከመገነጣጠል እንዳዳነ የሚሰራጨው ቅስቀሳ በታሪክ ውሸት፣ በአመክንዮ የተዛባ ነው፡፡ ሻዕብያ በራሱ አቅምና በመለስ ጥረት ኤርትራን መገንጠል ችሏል፤ በኢትዮጵያ የመገንጠል ጥያቄ ካነሱት በቂ ወታደራዊ አቅም ያልገነቡ ድርጅቶች ከማስገንጠል የተገቱት በኢህአዴግ ጉልበት እንጂ በህገ መንግስቱ አይደለም፡፡ ስለሆነም የመለስ ነገድ-ተኮር ፖለቲካ አንድነትን የሚያጠናክር ሳይሆን በአገራችን በመታየት ላይ እንዳለው ህዝብን የሚያጋጭና የሚያፈነቅል መርዝ በመሆኑ መወገድ አለበት፡፡
መለስ በህወሓት ውስጥ በ1968 ተጠባባቂ የማእከላዊ ኮሚቴ አባል ከሆነ ጀምሮ እሰከ 2004 ህልፈተ ህይወቱ ድረስ ለ36 ዓመታት በሰው ህይወት ላይ ለመወሰን የሚያስችለው ስልጣን ይዞ የዜጎች ህይወት እየቀጨ ቆይቷል፡፡ የመለስን አገዛዝ መገለጫዎች በሚከተሉት አርእስት ስር ማየትና የያንዳነዱ ባህርይ፣ አቋምና ድርጊት እውነታ በማስረጃ እያረጋገጥን እያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ ሰብአዊ ክብሩ እንዲጠበቅ የመለስ እኩይ ስርኣት ተወግዞ ካገራችን እንዲወገድ ከፍተኛ ጥረት እንደሚያስፈልግ እናሳስባለን፡፡
የህወሓት/ኢህአዴግ ማለትም የመለስ የስልጣን መሰረት ጉልበት ነው፡፡ ውሸትና ሙስና የተንሰራፉትም ከጀርባቸው ጉልበት ስላለ እንጂ በቀላሉ ተጋልጠው ሊወገዱ ይችሉ ነበር፡፡ ስለዚህ ህወሓት/ኢህአዴግ የመለስ ፈር መከተሉን ከቀጠለ በሰላማዊ ህዝብ ላይ ጉልበት ስለሚጠቀም ብዙ ዓይነት ወንጀሎች መፈፀም ይችላል፡፡ ሌሎች ፀረ ህዝብ ድርጊቶቹም ህዝብን በማሸማቀቅ ስለሚፈፅማቸው ጉልበት ሰውን እንደመጉጃና እንደማስፈራሪያ ለፖሊሲዎቹ ተፈፃሚነት የሚፈጥረው አመቺ ሁኔታ መገንዘብ ይቻላል፡፡
1.   ፈላጭ ቆራጭነት
በኢትዮጵያ ያንድ ግለ-ሰብ ፈላጭ-ቆራጭ አምባገነንነት አዲስ ክስተት አይደለም፡፡ ቢሆንም ከተካሄደው ረዥም ትግልና፣ ከተከፈለው እጅግ ከባድ መሰዋእት አንፃር ሲታይ ትውልዱን በበላ ትግል ፈላጭ-ቆራጭ ግለ-ሰብ መንገሱ ባንድ በኩል የሰውየው ኢሰብአዊነት አረገግጧል፡፡ የመለስ ፈላጭ ቆራጭነት በህወሓት ውስጥ ከማሌሊት ምስረታ ጋር የሚፈልጋቸውን ካድሬዎች መልምሎ፣ የማይፈልጋቸውን አባላት ካጠቃ በሁዋላ የጀመረ ነው፡፡ በሌላ በኩልም ታጥቆ ከታገለው ሃይል ጥቂቱ ባለው ሙስና ጎልቶ እንደሚታየው ለዝርፊያ የቆመ እንደሆነ፣ አብዛኛው የድርጅቱ አባል ደግሞ ታግሎ ዴሞክራሲያዊ ስርአት የመገንባት ብቃት እንደሌለውና የአምባገነን መሳሪያ ሆኖ የግለ-ሰብ አምባገነንነት በመመስረቱ፣ ሰብአዊና ዴሞክራሲያዊ መብቶች በመረገጣቸው፣ ፍትሕና የህግ የበላይነት ባለመኖራቸው ተረጋግጧል፡፡ ስለዚህ የመለስ ፈላጭ ቆራጭነትና የህወሓት/ኢህአዴግ አባላት አድርባይነትና መሰሪያነት ህዝብን የሚያሸማቅቅ ገዳይና አፋኝ ስርኣት ፈጥሯል፡፡
2.   ተከታታይ የጅምላና የተናጠል ግድያዎች
ቀደም ብሎ የደርግ ግፎች የታዛቢዎችን ቀልብ በሳቡበት የትጥቅ ትግል ጊዜ ግልፅነትና ተጠያቂነት ባልነበረበት ሁኔታ የህወሓት አመራር በድርጅቱ አባላት እና በሰላማዊ ህዝቡ ላይ በምስጢር ብዙ ግድያዎች ይፈፀሙ ነበር፡፡ ብዙ የትግራይ ህዝብና የህወሓት ተራ አባሎች በዝምድና፣ በጐረቤትነትና በጓደኝነት የሚያውቃቸው የህወሓት ሰለባዎች መኖራቸውን ቢያውቁም ባገዛዙ ስለታፈኑ፣ ከስርዓቱ ጋር በጥቅም ስለተሳሰሩ፣ ወይም የህወሓት ወታደራዊ ድል እንደ ጀብድ ስለሚያዩና ጀብዱን በመጋራት ዝና የሚያገኙ ስለሚመስላቸው በህወሓት ስለተፈፀሙት ወንጀሎች በይፋ አይናገሩም፡፡
በትጥቅ ትግሉ ጊዜ በተለይ በሲቪሎች በድብቅ የተፈፀሙት ግድያዎች ተደብቀው አይቀሩም፤ በግድያው ጊዜ ህፃናት የነበሩና ባገር ቤትና በስደት ያደጉም በቤተሰብ መረጃው ስለተላለፈላቸው ያውቁታል፡፡ ስለዚህ የድብቅ ግድያዎቹ፣ በአዲስ አበባ በተደጋጋሚ (1985፣ 1993፣ 1997፣ 1998) እና በሌሎች ከተሞች በይፋ እንደተፈፀሙት ጭፍጨፋዎች በታሪክ ይመዘገባሉ፡፡ ስለዚህም ግፍ ከፈፀመው ሃይል ጋር የወገኑት ዜጎች ቆም ብለው ማሰብ አለባቸው፡፡
3.   የፖለቲካ ሙስና እና ጎጠኝነት
ብዙ ጊዜ ስለ ሙስና ሲወራ ከጉቦና ስልጣንን ካለአግባብ ከመጠቀምና ሃብት ከማካበት ጋር ይያያዛል፡፡ ባለስልጣኖች የሚፈፅሟቸውን የሙስና ድርጊቶች ለመፈፀም የሚያስችላቸው መሰረት ግን ስልጣኑን ለመያዝ የሚፈፅሙት በጉልበት የታጀበ ቅጥፈት ነው፡፡ ህወሓት/ኢህአዴግ በውሸት ምርጫ ስልጣኑን በህዝብ ፍላጎት እንዳገኘ የሚገልፀው በጉልበት የሚፈልገውን ማድረግ ስለሚችል እንጂ ማጭበርበሩ፣ ህዝብን ማስገደዱና ድምፅን መዝረፉ ህዝብ ስለማይነቃበት አይደለም፡፡ በውሸት ምርጫ ከፍተኛውን የስልጣን እርከን የመያዝ አሰራር የስርዓቱ መገለጫ እስከሆነ ድረስ ለሙስና ድርጊቶች አመቺ ሆኖ ይቀጥላል፡፡ ከላይ ከፈተኛውን መንግስታዊ ስልጣን በጉልበትና ቅጥፈት የሚቆጣጠሩና ስልጣኑን ለዝርፊያና ለግል ምቾት የሚጠቀሙ ሰዎች አስካሉና ለዚህ ድርጊት በውስጣቸው መተማመን እንዲኖራቸው በነገድ፣ በጎጥና በዝምድና የተሳሰሩ ሰዎች እስከገዙ ድረስ፣ ከታች የገዢዎቹን አርአያ እየተከተለ ሙሰኛ የሚሆን መብዛቱ የሚገርም አይደለም፡፡
መለስ ሙስናን በቅንነት የሚቃወም ቢሆን ኖሮ በነበረው ፍፁም ስልጣን ሊገታው እየቻለ ከሱ በፊት ከነበሩት አገዛዞች ባጠረ ጊዜ ውስጥ ለከት የሌለው ሙስና አይስፋፋም ነበር፡፡ በተፃራሪው ግን መለስ ገና ከትጥቅ ትግሉ ጀምሮ ለተራበ ህዝብ የመጣውን እርዳታ ለምሳሌ ተጋይ የነበረውን ገብረመድህን አርአያን እህል የሚሸጥ ነጋዴ መስሎ ገንዘብ ከእርዳታ ሰጪዎች እንዲቀበል ያደርግ ነበር (Tigray, Ethiopia’s untold story, by Max Peberdy)፡፡ ትእምትን (ኢፈርት) ለመመስረት የተጠቀመበት ገንዘብ ከእርዳታ ተጭበርብሮ የተወሰደ ነው፡፡ የመለስ ሚስት የትእምት ከፍተኛ ስልጣን የያዘችው በቤተሰባዊ የሙስና አሰራር ነው፡፡ መለስ ያገዛዙ አካል ሆነው የተፈጠሩት ሙሰኞች ለስርዓቱ የቆሙ የሱ ደጋፊዎች እንደሆኑና እንደሚያስፈልጉት አያውቅም ማለት የዋህነት ነው፡፡
ሰውየው ግን ደርጊቶቹን በቃላቱ፣ ቃላቱን በድርጊቶቹ የማፍረስ አመል ነበረው፡፡ ዴሞክራሲን የማይፈልገው ወንጀሎቹ እንዳይጋለጡ ስለሚሰጋ መሆኑ እየታወቀ፣ ዴሞክራሲያዊ ስርዓትን እንዳይገነባ ሙስና እንዳደናቅፈው ለውጭ ዜጎች እንደሚከተለው ይገልፅ ነበር፡፡ ለምሳሌ አሌከስ ዴ ዋል (Alex de Waal) መለስ በተቃዋሚ የፖለቲካ ድርጅቶችና ሲቪክ ማህበራት ላይ በሚወስዳቸው እርምጃዎች ምክንያት ለሚያወግዙት ሰዎች መልሱ ምን እንደሆነ ጠይቆት መለስ ሲመልስ „የአባታዊነትና የሙስና የበላይነት ባለበት የፖለቲካ ኢኮኖሚ (በሚወስዳቸው እርምጃዎች ምክንያት እሱን) የሚያወግዙት ሰዎች ዴሞክራሲን እንዴት እንደሚገልፁትና ወደ ዴሞክራሲ የሚወስደው አዋጪ መንገድ እንዴት እንደሚፈልጉ ያውቃሉ ወይ?“ ብሎ በመጠየቅ ዴሞክራሲ እንደሌለ ከማመን አልፎ ጥያቄውን ማንሳቱን ስህተት ሊያስመስለው ይሞክራል፡፡ (Alex de Waal ፣ Dec. 06, 2012፣ ጉግል) የዜጎች መብቶችን ያፈነው ራሱ፣ ሙስና ያንሰራፋውም ራሱ መሆኑ ቢታወቅም መለስ ለኢትዮጵያውያን ዴሞክራሲያዊ ስርዓት እንደገነባ ከመግለፅ ቦዝኖ አያቅም፡፡
4.   ህዝቡን በአንድ ሰው ሃሳብ እንዲመራ ማስገደድ
የተለያዩ ሃሳቦች ሲገለፁ እየተፋተጉ ስህተቶች ይታረማሉ፤ ከተለያዩ ሃሳቦች የተሻሉ ሃሳቦች ሊፈልቁ እና በተግባር እየተፈተኑ ሲጎለብቱ እውቀት በሂደት ያድጋል፡፡ መለስ የራሱ ሃሳብ ቢይዝና በፍላጎት ለሚቀበሉት ሃሳቡን ለማስፋፋት ቢሞክር ችግር አይሆንም ነበር፡፡ ችግሩ የፖሊቲካ ስልጣኑን፣ መገናኛ ብዙሃንን፣ የሚቆጣጠረው አስተዳደርንና ከተነገራቸው ውጪ የራሳቸውን ሃሳብ መግለፅ የማይፈቀድላቸው አሻንጉሊት ካድሬዎችን እየተጠቀመ የዜጎች ሃሳብ የሚቆጣጠርበት ስርዓት መመስረቱ ነበር፡፡
የመለስ ሃሳብ በጉልበት ከሚሰራጭ የሃይማኖት ስብከት የማይለይ፤ አማራጭ ስለሚከለክል ሚዛናዊ አስተሳሰብ ከነፃነት ጋር የሚያፍን፤ በማስረፅ (indoctrination) መልክ የሚሰራጭ፣ ካለ ደራሲው ፍላጎት አዲስ ግብአት ስለማይቀበል የማያድግና፤ የተለየ ሃሳብ የሚያቀርቡ ዜጎችን በጠላትነት በመፈረጅ በዜጎች መካከል የጠላትነት መንፈስ የሚፈጠር ቀኖና ነበር፡፡ ሰውየው ዜጎች በሱ ትእዛዝ እንዲተዳደሩ ብቻ ሳይሆን እሱ ራሱ ቢያምነበትም ባያምነበትም ላጭር ጊዜም ቢሆን ዜጎች በሱ ሃሳብ እንዲመሩ ያደርግ ነበር፡፡ በዚህ አሰራሩም ማመዛዘን የማይችሉ አምላኪዎችና አምላኪዎች በመምሰል የግል ጥቅማቸውን የሚያሳድዱ አድርባዮች ፈጥሯል፡፡ መለስ በትጥቅ ትግሉ ጊዜ የማሌሊትን እምነት ያልተቀበሉ እንደ ጠላት ያሳድዳቸውና የጋንግሪን ስም አውጥተላቸው በጋንግሪን እንደተለከፈ አካል እዲቆረጡ ይቀሰቅስና በተግባር የተለየ ሃሳብን ለማጥፋት የተለየ ሃሳብ ባላቸው አባላት ላይ ግፍ ይፈፅም ነበር፡፡
መለስ ማሌሊትን በህወሓት ውስጥ ፍፁም ስልጣን ለመጠቅለል ከተጠቀመባት በሁዋላ ስለ ነጭ ካፒታሊዝም ማውራት ጀመረ፡፡ ስለዚህ ሰውየው የተወሰነ ሃሳብ ሲያሰራጭ በመርህ ደረጃ አምኖበት ሳይሆን ሃሳቡን ለስልጣን መሳሪያ ለመጠቀም ነበር፡፡ እሱ ራሱ ሃሳቡን መቀየር ስለሚችል፣ ይዞት ቆይቶ የሚጥለው ሃሳብ ትክክል እንዳልነበረ ማመኑን ያመለክታል፡፡ መሳሳቱን የሚገነዘብ ሰው ደግሞ ሌሎች ሰዎችም ትክክል ሊሆኑም ሊሳሳቱም እንደሚችሉ መገንዘብ መቻል አለበት፡፡ መለስ ሁሉንም የሱ ተከታዮች ያልሆኑትን በራሳቸው ፖለቲካዊ ሃሳብ የሚመሩትን ዜጎች በራሱ ብቻ ሳይሆን በህዝብ ጠላትነት እየፈረጀ አልፏል፡፡ ስለዚህ ማመዛዘን የሚችሉና ቅንነት ያላቸው የኢህአዴግ አባሎች ካሉ የመለስን መንገድ መከተል የለባቸውም፡፡
5.   የሰብአዊና ዴሞክራሲያዊ መብቶች መርገጥ
የኢህአዴግ ህገ መንግስት ብዙ ሰብአዊና ዴሞክራሲያዊ መብቶች ቢያካትትም የኢህአዴግ ባለስልጣኖች ህገ መንግስቱን ባያከብሩ አያስገርምም፡፡ ህገ መንግስቱ የተዘጋጀው በወንጀለኞች ማለትም በመለስና ግብረ-አበሮቹ ይሁንታ ስለሆነ በትጥቅ ትግሉ ጊዜ ወንጀል ሲፈፅሙ የቆዩ ሰዎች መንግስታዊ ስልጣን ከያዙም በሁዋላ በተራ ቁጥር 1 እንደጠቀስነው ወንጀል መፈፀማቸውን ቀጥለዋል፡፡ ግፈኛ ገዳዮች “እያንዳንዱ ዜጋ በህይወት የመኖር መብት” እንዳለው ቢገልፁ ምን ትርጉም አለው?
የኢህአዴግ አባሎችና ደጋፊዎች ህገ መንግስቱን በታጋዮች ደም እንደተፃፈ ተኩራርተው ሲገልፁ ታጋዮቹ ራሳቸው የራሳቸውን መብት አስከብረው እንደማያውቁ የተገንዘቡ አይመስሉም፤ ወይም እውነቱ እንዲገለፅ አይፈልጉም፡፡ በትግሉ ጊዜ ድርጅቱን መለስና ጥቂት ግብረ-አበሮቹ ታጋዮችን ሲያስገድሉ፣ አስረው ሲያሰቃዩና ሲያባርሩ እንኳንና ተቃውሞ ማቅረብ መጠየቅም በአመራሩ የተወሰዱ እርምጃዎችን ትክክለኛነት እንደ መጠራጠር፣ በአመራሩ እምነት ማጣትና ሌሎችም እምነት እንዲያጡ በማድረግ ድርጅቱን ለማፈረስ እንደመሞከር እየተተረጐመ ያስወነጅል ነበር፡፡ ሁሉም እንደ በቀቀን የተባለውን እንዲደግም ስለሚፈለግም ዝምታም ያስጠረጥር ነበር፡፡ የድርጅቱን ማለትም የኢህአዴግን በተለይም የህወሓትን ታሪክ የማያውቁ አንባቢዎች ታሪኩን ማጥናት ሳያስፈልገቸው ከኢህአዴግ መንግስት ባህሪ የዜጎች ሰብአዊና ዴሞክራሲያዊ መብቶች እንደሚረግጡ ያውቃሉ፤ የተለየ ሃሳብ ያላቸውና መብታቸው እንዲከበር የሚጠይቁ ሰዎች እንዴት በቅጥፈት እየተወንጀሉ እንደሚጠቁ ማንም በቅን ህሊና የሚያስተውል ኢትዮጵያዊ ሊያረጋግጥ ይችላል፡:
6.   በግድ ማደራጀትና ነፃ ድርጅቶች እንዳይኖሩ/እንዲዳከሙ ማድረግ 
የተማሩና በከተሞች የሚኖሩ ዜጎች ራሳቸውን ማደራጀት ይችላሉ፤ በገጠር የሚኖረው ህዝብ ግን የመደራጀት ልምድ ስለሚያንሰው፣ እንደፈለገው በዘመናዊ መጓጓዣ መጠቀም ይሁን በስልክ መገናኘት ስለማይችል፣ ከማሃይምነት ስላልተላቀቀና፣ የኑሮረው ሁኔታ ፋታ ስለማይሰጠው ራሱን የማደራጀት አቅሙ የተወሰነ ነው፡፡
የተማሩና በከተሞች የሚኖሩ ዜጎች የገጠሩን ህዝብ እንዲደራጅ ሊያግዙት ይችላሉ፡፡ ይሁን እንጂ ኢህአዴግ የመንግስት ስልጣን፣ ጉልበት፣ አስተዳደርና የመንግስት ንብረት እየተጠቀመ ስጋት በማስፈን ህዝቡን እንደመሳሪያ ለማሽከርከርና ትእዛዙን ለማስፈፀም በመለሳዊ ነገድ-ተኮር ስልትና እስከ ቤተሰብ ድረስ ለመቆጣጠር በሚያመች መልክ በራሱ ሹመኞች ስር ያደራጃል፡፡ ይህ ኣይነት ስልት አፋኝና አማራጭን የሚነፍግ የሁሉም ጠርናፊ (totalitarian) ስርዓቶች አደረጃጀት ነው፡፡ ከኢህአዴግ ነፃ ሆነው በሙያ፣ እንደ ሲቪክ ማህበራትና እንደ የፖለቲካ ፓርቲዎች ለመደራጀት የሚሞክሩ ዜጎች በአገዛዙ ይዋከባሉ፤ እንቅስቃሴያቸው ይገታል፤ ፍርሃት በማስፈን አባላትና ደጋፊዎች እንዳይጠጓቸው፣ ለህይወታቸውና ነፃነታቸው ዋስትና እንዲያጡ ይደረጋሉ፤ ህይወታቸው የተቀጨም አሉ፡፡ በዚህ አሰራር አገዛዙ በቃላት ስለ መድብለ ፓርቲ እያወራ በተግባር የአንድ ፓርቲ ስርዓት አስፍኗል፡፡
7.   ህዝብን በቋንቋ መከፋፈል
የአገራችን ክፍለ ሀገሮች በቋንቋ ላይ የተመሰረቱ እንዲሆኑና የነገድ ድርጅቶች በብዛት እንዲመሰረቱ መደረጋቸው በተወሰኑ ምሁራን መካከል የነበረውን ነገዳዊ ቅራኔ ተቋማዊ በሆነ መልክ፣ ማለትም በቋንቋ ክልሎች፣ በነገድ ድርጅቶችና ባስተዳደራዊ መዋቅር ለሁሉም ህዝብ እንዲዳረስ ተድርጓል፡፡
የብሄር ብሄረሰቦች መብት መከበር የሚደገፍ መሠረታዊ የዴሞክራሲ ጥያቄ ቢሆንም፣ የመለስ ነገድ-ተኮር ፖለቲካ ግን በዋናነት የኢትዮጵያ ህዝብን ከፋፍሎ ለመግዛት የተጠቀመበት ስልት ነው፡፡ ስለሆነም የኢትዮጵያ ህዝብ አንድነት እየተሸረሸረ ይገኛል፡፡ የሱማሌ ክልል ፕረዚደንት ትግሬዎች አማሮች ወደ ስልጣን እንዲመለሱ እንደማይፈልጉ መናገሩ፣ አማሮች በአገራቸው ውስጥ ከጉራ ፈርዳና ከቤኒ ሻንወጉል-ገሙዝ በግፍ እንዲባረሩ መደረጉ፣ ባገሪቱ እስር ቤቶች የኦሮሞዎች ቁጥር መብዛቱ እና ባንዳንድ ወገኖች መለስና ተከታዮቹ ለፈፀሟቸው ወንጀሎች የትግራይ ህዝብ ተጠያቂና እንዲሁም በልማት ተጠቃሚ ተደርጎ መታየቱ መለስ በመሃንዲስነት የመሰረተው መርዘኛ ስርአት ውጤት ነው፡፡
8.   የተቋሞች ወገንተኝነት
መለስ ስልጣን ከመያዙ በፊት የነበሩ የተማሩና ልምድ ያካበቱ ኢትዮጵያውያን የሲቪልና የሰራዊት አባሎችን እንደ ባእድ አባርሮ ከነበቴሰባቸው ለስራ አጥነትና ለችግር እንዲጋለጡ አድርጓል፡፡ ቀጥሎ ሁሉም ታጣቂ ሃይሎች፣ ህግ አውጪው፣ ያስተዳደርና የፍርድ ቤት ተቋሞች፣ የሙያና የሃይማኖት ድርጅቶች ሳይቀሩ ያንድ ፖሊቲካ ድርጅት(መለስ በህይወት እስከነበረበት ጊዜም ያንድ ግለ-ሰብ) መሳሪያ እንዲሆኑ አድርጓል፡፡ እነዚህ ተቋሞች ለራሳቸው ተነፃፃሪ ነፃነት እንዲኖራቸውና ህዝብን በእኩልነት እንዲያገለግሉ ያንድ ፓርቲ ስርዓቱ ፈርሶ፤ በቃላት ብቻ ሳይሆን በተግባር የመድብለ ፓርቲ ስርዓት መገንባት አለበት፡፡
9.   መርዘኛ የጥላቻ ቅስቀሳ
በኢትዮጵያዊነቱ የሚያምን ማንም ዜጋ ኢትዮጵያውያንን እንደ ወገኑ ማየትና ለራሱ የሚፈልገው የዜግንት ክብር ለማንም ኢትዮጵያዊም እንደሚገባ መቀበል አለበት፡፡ ፖለቲካው ነገድ-ተኮር ከመሆኑ ጋር ተያይዞ በዋናነት በቅንጅት ላይ ተመስርቶ የነበረው የዘር ማጥፋት ክስ የጥፋት ዒላማ ተደርጎ የተገለፀው የህዝብ ወገን (የትግራይ ህዝብ) አጥፊ ተደርጎ በተወነጀለው ወገን ላይ (በዋናነት በአማራው) የጥላቻ ስሜት ለመቀስቀስ ነው፡፡
ተከሳሹ ኢንተርሃምዌን መስሎ እንዲታይ ቅስቀሳ ተደርጓል፡፡ ኢንተርሃምዌ በሩዋንዳ በ1994 እ.አ.አ. እስከ 800 000 የሚደርሱ ሰላማዊ ሰዎችን (በዋናነት ቱትሲዎችንና እንዲሁም ለዘብተኛ ሁቱዎችን) የገደለ የመንግስት አካል የሆነ የሁቱ ሚሊሽያ ነበር፡፡ በቅንጅት አባላትና ሌሎች ዜጎች ላይ የተመሰረተው የፈጠራ የዘር ማጥፋት ክስ ውድቅ ቢሆንም የቅስቀሳ መልእክቱ ተላልፏል፤ በህዝብ አለመተማመን አሰራጭቷል፡፡ ኢንተርሃምዌ፣ ትምክህተኛ፣ ነፍጠኛ፣ ጥግተኛ፣ ቅንጅት ወዘተ ተመሳሳይ ትርጉም እንዲኖራቸውና በተወሰነ የህዝብ ክፍል ላይ የኢትዮጵያ አንድነትን በሚፈልጉ ዜጎች ላይ የጥላቻ መቀስቀሻና ማስፈራሪያ ተደርገዋል፡፡
10.  አስፀያፊ ባህል
አገዛዙ ህዝቡን እያሸበረ አሸማቅቆና አፍኖ ስለሚገዛ ተቃዋሚዎች፣ ጋዜጤኞችና የህዝብን መብቶች ለማስከበር የሚሞክሩ ህዝባዊ (ሲቪክ) ድርጅቶች ሊያድጉ አልቻሉም፡፡ በእንቅርት ላይ ጀሮ ደግፍ እንደሚባለው ግን መለስ አገዛዙን አሰፀያፊ የሆነ ዜጎችን የማዋረድና የማሰቃየት አመል አስለምዶታል፡፡
መለስ ሁሉንም ስለተቆጣጠረ ተቃዋሚዎቹም በቁጥጥሩ ስር እንዳሉና ምንም እንደማያሰጉት እያወቀ የሚፈፅማቸው ድርጊቶችና የሚረጫቸው ቃላት የቆሰለ ምርኮኛን ረግጦ እንደሚደበድብ፣ በላዩ ላይ እንደሚተፋና እንደሚቅራራ ሰው ነበር፡፡ ለምሳሌ በ2002ቱ የህወሓት 37ኛ ዓመት ሲያከብር ለውሸት ምርጫም ይቀሰቅስ ስለነበረ፤ በህዝብ ድምፅ ላይ እሱ ራሱ ወሳኝ መሆኑ እያወቀ አስነዋሪ ንግግር ከማድረግ አልተቆጠበም፡፡ የድሮ ጓደኞቹን በይፋ ገለባ፣ እንጉብላይ፣ ለህዝብ ጠላቶች ሽፋን የሆኑ እያለ ሰደባቸው፡፡ ህዝባችን ጨዋነትን እንደ ትልቅ እሴት ያያል፡፡ መለስ ግን ባህላችንን የሚበክልና ለነበረው የራሱ ስልጣንም ክብር የማይሰጥ አመሉ አስፀያፊ ነበር፡፡ መለስ የተለየ ሃሳብ የገለፁ ሰዎችን አመክንዮ ባለው አቀራረብ ስህተት የሚለውን ሃሳባቸው በመግለፅ ፈንታ የሰዎቹ ጭንቅላት እንደበሰበሰ ይሰድብ ነበር፡ ሰው በፅኑ ካልታመመ ጭንቅላቱ አይበሰብስም፤ ጭንቅላቱ እስኪበሰብስ ከታመመም ተቃዋሚ አይሆንም፡፡ ስለዚህ በመለስ የሚሰደቡት ጤኔኛ ሰዎች ናቸው፡፡
አገዛዙ ራሱ ሊያስከበረው የሚገባውን ህግ በመጣስ ሊያጠቃው የሚፈልገውን ሰው (ለምሳሌ ስየን) ካሰረ በሁዋላ ያሰረውን ሰው የሚጎዳ አዲስ ህግ በማውጣት፣ ህግ ወደ ሁዋላ ተመልሶ ተፈፃሚነት እንዲኖረው ማድረጉ አሰፀያፊና ፍርደ ገምደላዊ የበቀል ድርጊት ነው፡፡ በውሸት ተከሰው ታስረው የሚሰቃዩ ዜጎችን በሽምግልና ስም እርቅ ፈላጊ መስሎ በመታየት ህዝብን ለማወናበድ የሚደረግ ቅስቀሳ፣ ነፃነታቸው የተነፈጉ እስረኞች በስነ-ልቡና በማሰቃየት ራሳቸውን እንዲወነጅሉ (ቅንጅት ወዘተ.. ብርቱካን ሚደቅሳ ለሁለተኛ ጊዜ) ማድረግ መለስ ምን ያህል የሰውን ሰብአዊ ክብር የማንቋሸሽ አመል እንደነበረው ያመለክታሉ፡፡ መለስ በአንድ በኩል ለሰብአዊና ዴሞክራሲአዊ መብቶች በሚታገሉ ዜጎች ላይ የጭካኔና አስፀያፊ ድርጊቶች ሲፈፅም በሌላ በኩል ጤንነትን ለሚጎዱና የስነ ምግባር ብልሹነት ለሚያስከትሉ የጫትና አደንዥ እፆች ሱስ መስፋፋት ሊበራል ዴሞክራሲያዊ ሆኖ አልፎአል፡፡
የውሸት ምርጫ ማካሄዱ ራሱ ብዙ አሰፀያፊ ድርጊቶችን ያጠቃልላል፤ ህዝቡንና ተቃዋሚዎችን ያሸማቅቃል፣ የምርጫ ቦርዱን፣ ዳኞቹን፣ የመንግስት ሰራተኞቹንና ካድሬዎቹን ለቅጥፈት፣ ታጣቂዎቹን ለጉልበት ተግባሮች ያሰማራል፤ ማጭበርበር፣ ጉልበት መጠቀምና፣ መዋሸት ስልጣንን ለመያዝ፣ በስልጣን ተጠቅሞም የህዝብና የእርዳታ ሃብት መዝረፍ መጥፎ አርአያ የሆኑ የአገዛኡ መገለጫዎች ሆነዋል፡፡
ከላይ የተጠቀሱት ዘርፈ-ብዙ ጎጂ ድርጊቶችና ጠባዮች ስንገልፅ ባገዛዙ የተጀመሩ ጠቃሚ ድርጊቶች የሉም ለማለት አይደለም፡፡ በተለይ የመሰረተ ልማት ጥሩ ጀማሮዎች አሉ፡፡ ያሉትም በጥራት እንዲያድጉ ማድረግ አስፈላጊ ነው፡፡
ጥሩ ስራዎች እንዳሉ በመጥቀስ ጎጂዎቹን ለመደበቅ መሞከር ግን ጉዳቶቹ እንዲቀጥሉ ከማድረግ አይለይም፤ ስታሊን ከኢንዱስትሪ እድገት፣ ጋዳፊ ከውሃ አቅርቦት ጋር መንግስቱ ሃይለማርያምም ማሃይምነትን በማጥፋት ሙከራ በአዎንታዊ ሚናቸው ይጠቀሳሉ፤ በዚህ ምክንያት ግን አረሜኔያዊ ድርጊቶቻቸው እየተወገዙ እንዳይደገሙ የሚደረገው ጥረት አልተገታም፡፡ ስለዚህ ባገራችንም በዋናነት መለስ ያመጣቸው የአረሜኔው ስርአት መገለጫዎች እንዲወገዱ ጥረታችን መጧጧፍ አለበት፡፡
ከላይ እንደተገለፀው መለስ በአገርና በህዝብ ዘርፈ-ብዙ ወንጀሎች የፈፀመ፣ በወንጀሎቹ ህዝባዊ ፍርድ ሳያገኝ ያለፈ ሰው ነው፡፡ ቢሆንም እሱ ያሳደጋቸው ደጋፊዎቹና ተከታዮቹ የስልጣን እድሜቸውን ለማራዘም ታላቅ አገራዊ ራእይ የነበረው መሪ ነበር እያሉ በሚቆጣጠሩት የመገናኛ ብዙሃን ህዝብን ሲያደነቁሩ ከርመዋል፤ አሁንም ይቀጥላሉ፡፡
በተለይም መለስ „ዴሞክራሲያዊ ልማታዊ መንግስት“ እንደተመሰረተና ኢትዮጵያም በኢኪኖሚ በጣም እንዳደገች ያልተቆጠበ የውሸት ፕሮፓጋንዳ በመንዛት ላይ ይገኛሉ፡፡ ለዚህ የውሸት ፕሮፓጋንዳ መሠረት ደግሞ በመለስ አገዛዝ ተሰሩ የተባሉትን ወይም እሱ ያቀዳቸው ናቸው የተባሉትን የመሰረተ ልማት ፕሮጀክቶችን በመጥቀስ ነው፡፡ ሃቁ ግን ከዚህ ነጭ ውሸት የተለየ ነው፡፡
በመሠረቱ ማንኛውም ስርዓት ወይም መንግስት፣ ዴሞክራሲያዊ የሆነም ያልሆነም፣ የተወሰኑ የመሠረተ ልማት ስራዎች መስራቱ የሚጠበቅ ነው፡፡ እጅና እግሩን አጣጥፎ የሚቀመጥ ስርኣት የለም፡፡ በተለይም ዴሞክራሲያዊ ተቀባይነት (legitimacy) የሌላቸው ስርአቶች በልማት ለውጥ አምጥተናል እያሉ አገዛዛቸውን ለማራዘም እንደሚጠቀሙ በታሪክ የታየ አሁንም በተለያዩ አገሮች የሚታይ ክስተት ነው፡፡ መለስ ባጭበረበራቸው ምርጫዎችና በፈፀማቸው የሰብአዊ መብት ጥሰቶች ዴሞክራሲያዊ እንዳልነበረ እንኳን የኢትዮጵያ ህዝበ ይቅርና የሚደግፉት የውጭ መንግስታትና እንዲሁም አለም አቀፍ የሰብአዊ መብት ተሟጋች ድርጅቶች የሚመሰክሩት ሃቅ ነው፡፡ ስለሆነም መለስ „ልማታዊ መንግስት“ የአገዛዙን እድሜ ለማራዘምና እሱና ተከታዮቹ የህዝብ ሃብትን ለመዝረፍ የተጠቀሙበት ስልት ነው፡፡
በመለስ አገዛዝ የተሰሩ የመሰረተ ልማት አውታሮች በአብዛኛው አገሪቱ ከውጭ ባገኘችው በብዙ ሚልዮን ዶላር የሚቆጠር ብድርና እርዳታ ነው፡፡ ህወሓት/ኢህአዴግ በሚፈፅመው ሙስናና ዘረፋ አይጠየቅምና በቀጥታም ይሁን በተዘዋዋሪ በአብዛኛው የመሰረተ ልማት ግንባታዎች ህወሓት/ኢህአዴግ ተጠቃሚ መሆኑ የሚካድ አይደለም፡፡ ለአብነት የአባይ ወንዝ ግድብ ስሚንቶና ብረታ ብረት የሚያቀርበው የህወሓት ትእምት (EFFORT) መሆኑ የአደባባይ ምስጢር ነው፡፡
ባጠቃላይ በመለስ አምባገነናዊ አገዛዝ በዘረፋ የበለፀጉት የሱ ተከታዮችና ደጋፊዎች ሲሆኑ፣ አብዛኛው የኢትዮጵያ ህዝብ ግን ተጠቃሚ አይደለም፡፡ የኢኮኖሚ እድገት ቢኖር አብዛኛው የከተማ ህዝብ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየከፋ በሚሄደው የኑሮ ውድነት አይሰቃይም ነበር፡፡ አርሶ አደሩም የማዳበሪያ ዕዳ መክፈል አቅቶት ሳይቸገር የምርቱ ተጠቃሚ በሆነ ነበር፡፡ በብዙ ሺ የሚቆጠር የአገሪቱ የተማረ ሃይልና ወጣት ለስደት ተጋልጦ በሳወዲ አረብያ የግፍና ውርዴት ሰለባ አይሆንም ነበር፡፡
በመጨረሻምው ኢትዮጵያውያን መለስ የፈፀማቸው ወንጀሎች አደገኛነት በመገንዘብ፣ በተለይም የቀበራቸው የአገር አንድነትን የሚሸረሽሩ ፈንጂዎችን ለማፅዳትና የአገራችን አንድነትን ለማጠናከር ከመቸውም ጊዜ በበለጠ በአንድነት መታገል ታሪካዊ ግዴታችን ነው፡፡

የቀድሞ የደህንነት ሀላፊ አቶ ወልደስላሴ ወልደሚካኤል ተጨማሪ ክስ ተመሰረተባቸው

December 6/2013
አዲስ አበባ ፣ ህዳር 26፣ 2006 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የብሄራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት ሰራተኛ የነበሩት አቶ ወልደስላሴ ወልደሚካኤል ከሁለት ቤተሰቦቻቸው ጋር በተጠረጠሩበት የሙስና ወንጀል ተጨማሪ ክስ ተመሰረተባቸው።
ተከሳሾቹ  አቶ ወልደስላሴ ወልደሚካኤል፣ የመከላከያ ሚኒስቴር ባልደረባ የነበሩት ወንድማቸው ዘርአይ ወልደሚካኤል፣ እህታቸው ወይዘሪት ትርሃስ ወልደሚካኤልና የቅርብ ጓደኛቸው ዶሪ ከበደ ናቸው ።
ተከሳሹ በ 2002 ዓ.ም ቱሪዝም ኢን ኢትዮዽያ ኤንድ ዘ ሆርን ኦፍ አፍሪካ የተሰኘ መጽሃፍ ያሳተሙ ሲሆን ፥ ይህንን መጽሃፋቸውን በስፖንሰር ለማሳተም ባደረጉት እንቅስቃሴም  የመንግስት የልማት ድርጅቶች ተቆጣጣሪ ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር የሆኑትን አቶ በየነ ገብረስላሴ የነበራቸውን ቀና አስተሳሰብ ተጠቅመው ያለአግባብ በልጽገዋል ነው የሚለው የክስ መዝገቡ።
መጽሃፉ በመስሪያቤታቸው ስም እንደተዘጋጀ በሚያስመስል ሁኔታ አቶ በየነ የሚመሯቸው የቦሌ፣ የብርሃንና ሰላምና የአርቲስቲክ ማተሚያ ቤት ሃላፊዎች በጋራ የአቶ ወልደስላሴን 3 ሺህ መጻህፍት በ124 ሺህ ብር እንዲያሳትሙ ተደርጓል ነው የሚለው ክሱ።
ማተሚያ ቤቶቹ በርካሽ ያሳተሙት አቶ ወልደስላሴ ከነበራቸው ተሰሚነትና ስልጣን መነሻነት መሆኑንና ይህንን መጽሃፍ ኢትዮ ቴሌኮም ምንም በማይመለከተው 10 ሺህ መጻህፍት የሚታተሙበትን የ385 ሺህ ብር ክፍያ  ለአቶ ወልደስላሴ እንዲከፍልም መደረጉንም ነው  የክስ መዝገቡ የሚያስረዳው።
አቶ ወልደስላሴ የሙገር ሲሚንቶ ኢንተርፕራይዝና የአትክልትና  ፍራፍሬ ገበያ ማህበር የቦርድ ሰብሳቢ በነበሩበት ጊዜ ሃላፊነታቸውነ ተጠቅመው ፥ ሁለቱ ድርጅቶች 310  ኮፒዎችን በግድ እንዲገዙ መደረጉም ተመልክቷል።
26 የሚሆኑ ግለሰቦችና ድርጅቶችም እያንዳንዳቸው ከ 25 እስከ 1ሺህ 500 ፥  በጥቅሉ ከ73 ሺህ የሚልቁ ኪፒዎችን ሳይወዱ በግድ  እንዲገዙ መደረጉ ፣ ይሄ ሁሉ ሲደረግ ተቋማቱ ለመጻህፍቱ ገንዘብ ከፍለው መጻህፍቱን አለመረከባቸውም ጭምር ነው በክስ መዝገቡ የተዘረዘረው።
ተከሳሹ አቶ ወልደስላሴ ባልደረባቸወ የሆኑ አንዲት ሴት ጋር በነበራቸው መቀራረብ የመስሪያቤቱን  መኪና በህገ ወጥ መንገድ ነዳጅ እያስሞሉ ግለሰቧ እንደልባቸው በአዲስ አበበባና ከከተማ ውጪ እንዲጠቀሙበት አስደርገዋል የሚለውም ተጠቅሶባቸዋል።
ተከሳሹ ከ2003 እስከ 2004 ዓ.ም አቶ ሳቢር አርጋው የተሰኙ ነጋዴን ለምሰራው ቤት ሴራሚክ ስለጎደለኝ የጣሊያን ስሪት ገዝተህ ስጠኝ በማለት ፥ በስልጣናቸው አስፈራርተዋቸው የ65 ሺህ ብር ሴራሚክ  ተቀብለዋል ፣ ከ 2001 እስከ 2005 ባሉት የግብር አመታት አሳትሞ ከሸጣቸው መጻህፍት ካገኘው ገቢ ላይ መክፈል የነበረበትን ከ496 ሺህ ብር በላይ ለመንግስት አስታውቆ አለመክፈሉም ተጠቅሷል።
ተከሳሹ ባለ4 ፎቅ የግል ቤቱን ወንድሙ ለሆነው ሁለተኛ ተከሳሽ ዘርአይ ወልደስላሴ ውክልና ሰጥቶና ከመኖሪያ ቤት ውጭ ለሆነ አገልግሎት እንዲውል አድርጎ በ14 ወራት ውስጥ 790 ሺህ ብር ገቢ አግኝቷል ፤ ከገቢው 126 ሺህ ብር የሚሆነው የመንግስት ግብርን ለግብር አስገቢው መስሪያቤት ሃሰተኛ መግለጫ በማቅረብ ሳይከፍል መቅረቱም በክሱ ተመልክቷል።
ከዚሁ ቤት ኪራይ መንግስት ከተርን ኦቨር ታክስ ማግኘት የነበረበትን ከ119 ሺህ ብር በላይ ገቢ ሳያገኝ መቅረቱና ተከሳሹ በህገ ወጥ መነገድ ያገኘውን ገንዘብ ማንም እንዳያውቅበት ለማድረግ በሰኔ 28 1998 ዓ.ም ለሁለተኛው ተከሳሽ (ወንድም) ዘርአይ ወልደሚካኤል ሙሉ ውክልና መስጠቱ ተዘርዝሯል።
እንዲሁም ምንም አይነት የገንዘብ ልውውጥ ሳያደርጉ ከ3ኛዋ ተከሳሽ እህቱ ትርሃስ ጋር መጋቢት 24፣ 2005 ዓ.ም የብድር ውል ማድረጋቸውም ተጠቅሷል።
በተጨማሪም ተከሳሹ ከእህቱና ወንድሙ ጋር ያለአግባብ አፈሯቸው የተባሉ የገንዘብና የአይነት ሃብቶች በክስ መዝገቡ ተጠቅሰዋል።
1ኛው ተከሳሽ ወልደስላሴ ወደሚካአል ከ1983 እስከ የካቲት 2005 ዓ.ም የብሄራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት የውስጥ ሰራተኛ ሆኖ ሲሰራ ፥ ወርሀዊ ደመወዙ ከ 1,600 እስከ 6,000 ብር የነበር ሲሆን ፥ ነገር ግን ስልጣኑን እና የነበረውን ተሰሚነት በመጠቀም በፈጸመው የሙስና ወንጀል ከባለ4 ደረጃ ህንጻ ውጪ ፣ ከ3 ሚሊየን ብር በላይ በተለያዩ የግልና የመንግስት ባንኮች ተቀማጭ ማድረጉም ተመልክቷል።
2ኛ ተከሳሽ አቶ ዘርአይ ወልደስላሴ ከመከላከያ ሚኒስቴር በጡረታ እስከሚገለል ድረስ ወርሀዊ ደመወዙ 532 ብር የነበር ሲሆን ፥ በክስ መዝገቡ ተከሳሹ በተለያዩ ባንኮች 5 ሚሊየን ብር የሚጠጋ ገንዘብ ማስቀመጡ ፣ በአዲስ አበባ ቤቴል ቁጥር 3 በተባለ አካባቢ  በ74 ካሬ ሜትር ይዞታ ላይ መሰረት የተጀመረበት ቦታ ፣ በአፋር ክልል ከ 1 ነጥብ 4 ሚሊየን ብር በላይ ግምት ያላቸው ሁለት የእርሻ  ኢንቨስትመንቶችና 2 ነጥብ 7 ሚሊየን ብር ግምት ያላቸው ሁለት ሎደር ማሽነሪዎችም በስሙ መኖራቸው ተመዝግቧል ።
3ኛዋ ተከሳሽ የአቶ ወልደስላሴ እህት የ8ኛ ክፍል ተማሪ ስትሆን ፥ ምንም አይነት የገቢ ምንጭ የሌላት እንደሆነች ነው በክስ መዝገቡ የተገለጸው።
ግለሰቧ በ 81 ሺ ዩሮ የተገዛ አንድ ስካቫተር ፣ አውቶሞቢል መኪና፣ በአዲስ አበባ ቦሌና የካ ክፍለ ከተሞች እንዲሁም በለገጣፎ ፣ በመቀሌና አክሱም ከተሞች 3 ሺህ 266 ካሬ ሜትር ቦታዎች በስሟ ተመዝግቧል ፤ በተለያዩ ባንኮችም ከ 8 ሚሊየን ብር በላይ ተቀማጭ ገንዘብም እንዲሁ ተመዝግቧል።
የአቶ ወልደስላሴ የረዥም ጊዜ ጓደኛ እንደሆነ የሚነገርለት 4ኛው ተከሳሽ ዶሪ ከበደ አቶ ወልደስላሴ በቤተሰቦቹ ስም በሚስጥር የያዘውን ከፍተኛ ሃብት ይዞ በማቆየት የወንጀል ተሳትፎ አድርጓል ነው የሚለው ክሱ።
በአጠቃላይ ተከሳሾቹ ንብረትና ገንዘብ ለማፍራት የሚያስችል ምንም አይነት አቅም ሳይኖራቸው በፈጸሙት ምንጩ ያልታወቀ  ንብረትና ገንዘብ ይዞ በመገኘት የሙስና ወንጀል ተከሰዋል።
ከአቶ ወልደስላሴ እና ከወንድማቸው በስተቀር ወይዘሪት ትርሃስ እና አቶ ዶሪ የዋስትና መብት ጥያቄ አቀርበው ፥ ከሳሽ አቃቤሀግ የተመሰረተባቸው ክሰ ከ10 አመት በላይ የሚያስቀጣ በመሆኑ በህጉ መሰረት የዋስትና መብት ሊፈቀድላቸው አይገባም ሲል ቅዋሜ አቅርቧል።
ግራ ቀኙን የመረመረው የፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድቤት 15ኛ ወንጀል ችሎት በተከሳሽ ጠበቆች የቀረበውን የዋስትና ጥያቄ ውድቅ በማድረግና ጉዳያቸውን ማረሚያ ሆነወው እንዲከታተሉ በመወሰን ፤ የክስ መቃወሚያቸውን ለመስማት ለታህሳስ 7   2006 ዓ.ም ተለዋጨ ቀጠሮ ይዟል።


ድብልቅልቁ የወጣው ‹‹አብዮታዊ ዴሞክራሲ›› ኢህአዴግን ጨርቁን አስጥሎታል፡፡

December 5/2013

ፋሽስቶች ለኢትዮጵያውያንና ለሌሎች ካልሆነ በስተቀር ለአገራቸው ህዝብ ክብር ነበራቸው፡፡ እነ ሌኒንም ቢሆን ለአገራቸው አንድነት እንጅ ተገንጣይነት አልሰሩም፡፡ አረቦቹ ለአገራቸው ጥቅም ሲሉ ነው ኢትዮጵያን ይጠሉ የነበሩት፡፡ የአስተሳሰባቸው መርዝነት ለእኛ እንጅ ለራሳቸው ህዝብ አልነበረም፡፡ ምንም ያህል ቢያብዱና ቢሰክሩ ለአገራቸው ህዝብ ክብር ነበራቸው፡፡ ለብሄራዊ ጥቅማቸው ይጨነቁ ነበር፡፡ በግራዚያኒ ላይ የጣሊያን ግራ ዘመም ፓርቲዎች በነጻነት ተቃውሞ አሰምተው በሰላም ገብተዋል፡፡ ኢትዮጵያውያን ግንወገኖቻቸው በተጨፈጨፉበት ጎዳና እንደገና ተደብድበዋል፡፡ ታስረዋል፡፡ ይህ በአብዮታዊ ዴሞክራሲ የተለከፈ መንግስት ከያኔው ጨፍጫፊዎችም በላይ ይሆንብኛል፡፡ ስካር ሱስ ነው፡፡ 
በሽታም ጭምር፡:

 እንዲህ የጠደባለቀ መርዛማ አልኮል መጎንጨትን ልማዱ ያደረገ ድሮ ሰክሮ የሚሰራውን ጉዳይ ምሎና ተዘክሮ እተዋለሁ ቢልም የሚሰራው ግን ያው የስካሩን፣ የእብደት ተግባሩን ነው፡፡ ለግራዚያኒ የቆመው ኢህአዴግ ከውስጥም ከውጭም ተቃውሞ ሲገጥመው ስህተቱ ስካሩ መሆኑን ሳይረዳው ቀርቶ አይደልም፡፡ ግን ለሳውዲዎች ቆሞ ደገመው፡፡ ድብልቅልቁ የወጣው ‹‹አብዮታዊ ዴሞክራሲ›› ግን ኢህአዴግን ጨርቁን አስጥሎታል፡፡ ለዛም ነው ይህን ያህል ያበዱት የ‹‹አብዮታዊ ዴሞክራሲ›› የአልኮል መጠን ስንት ቢሆን ነው?›› ብየ የጠየቁት፡፡ ከወራት በፊት ለግራዚያ ሲቆም አብዮታዊ ዴሞክራሲ ምን ያህል እንደሚያሰክር፣ እንደሚያሰብድ አሰይቶናል፡፡ ይህ ከእነ ሞሶሎኒ የተወሰደው የአልኮል ክፍል መሆኑ ነው፡፡ ከሳምንታት በፊት ኢትዮጵያውያንን በአረብ ዱላ ገረፈ፡፡ ይህኛው ከአረቦቹ ጥላቻ የተዘነቀው የአብዮታዊ ዴሞክራሲ አልኮል ነው፡፡ አሁን ደግሞ የአጤ ምኒልክን ሙት አመት አታከብሩም ብሎ ከልክሏል፡፡ ይህኛው የሁሉም ውጤት ነው፡፡ ህወሓት/ኢህአዴግ መጨረሻ ቀላቅሎ ያለ አቅሙ አይኑን ጨፍኖ የተጎነጨው ይህኛውን አልኮል ነው፡፡ ጸረ ኢትዮጵያውይነት! የአሁኑ ጣሊያኖች የምኒልክ ታሪክ እንዳይወደስ የሚፈልጉበት ምንም አይነት ምክንያት የለም፡፡ እነ ሌኒን በሚሉት መልኩ ‹‹አብዮታዊ ዴሞክራሲ›› የሚባለው አገራችን ውስጥ የለም፡፡

 የስታሊን ጠባብ ብሄርተኝነት፣ የምዕባራዊያኑ ‹‹ካፒታሊዝምና ዴሞክራሲ›› በስም ደረጃ፣ የአልባኒያና የቻይና አምባገነንነት፣ የሻዕቢያና አረብ አገራት ጥላቻ፣ የሞሶሎኒ ፋሽዝም……ተደባልቀው የተሰራ ውጥንቅጡ የጠፋበት ‹‹ርዕዮት ዓለም›› ነው፡፡ የአሁኑ አብዮታዊ ዴሞክራሲ ከሁሉም ጎን የወሰደው መጥፎ ጎናቸውን እንጅ መልካሙን አይደለም፡፡ እነዚህ የየዘመኑን ትውልድ ያሰከሩ አስተሳሰቦችን መጠናቸውን ሳያውቅ የደባለቀው አብዮታዊ ዴሞክራሲ ከአልኮንነትም አልፎ መርዝ ወደመሆን ደርሷል፡፡ አልኮል ብቻውን ከሚወሰደው በላይ ሲደባለቅ ያሰክራል፡፡ ያሳብዳልም፡፡ አሁን ደገሞ ለድሮዎቹ፣ አድዋ ላይ ለተሸነፊት ጣሊያኖች ቆሞ ከለከለ፡፡ ኢህአዴግ ከአረቦቹ፣ ከፋሽስቶቹ፣ ከእነ ስታሊን….የደባለቀውን የውስጡን ጥላቻ በአብዮታዊ ዴሞክራሲው አልኮል አወጣው፡፡ ይህን ታዲያ ከስካርና ከእብደት ውጭ ምን ይሉታል? እኔ ይህን ናላ አስቶ፣ ጨርቅ አስጥሎ በአገር ህዝብ ላይ የሚያዘምት፣ ህዝብ ላይ የሚያስጨክን፣ ብሄራዊ ጥቅምን የሚያስጠላ ‹‹አብዮታዊ ዴሞክራሲ›› የአልኮል መጠኑን መገመት አልቻልኩም፡፡ ከመጠን በላይ መሆኑን፣ መርዛማነቱ ማመዘኑን ከመገመት ውጭ! ግን ኢህአዴግ እስከመቼ እንዲህ ጨርቁን ጥሎ ይዘልብናል?

 ሚኒልክ ሳልሳዊ  አትላንታ

ከሳውድ አረቢያ ከሚመለሱ ኢትዮጵያውያን ጋር በተያያዘ የመንግስት እንቅስቃሴ እየተተቸ ነው

December 5/2013
ህዳር (ሃያ ስድስ)ቀን ፳፻፮ / ኢሳት ዜና :-የመኖሪያና የስራ ፈቃድ የላችሁም በሚል ከሳዑዲዓረቢያ ወደ አገራቸው የሚመለሱ ኢትዮጵያዊያን ቁጥር በከፍተኛ ሁኔታ እየጨመረ ሲሆን ቁጥሩ መንግስት አስቀድሞ ካሰበው እጅግ አሻቅቧል፡፡ በዚህ ም ምክንያት ተመላሾቹን ለመቀበልና ለማቋቋም  መንግስት በቂ በጀት አለመያዙ እንደ አገር አሳፋሪ መሆኑን ለጉዳዩ ቅርበት ያላቸው ምንጮች ገልጸዋል፡፡
መንግስት የተመላሾቹ ቁጥር 23 ሺ ገደማ መሆኑንና እነዚህም ወገኖች ለመመለስ መመዝገባቸውን በመግለጽ ለተመላሾቹ 50 ሚሊየን ብር እንደመበ መግለጹ ይታወቃል፡፡ ይህም ሆኖ የተመላሾቹ ቁጥር ከፍተኛ መሆኑ ከታወቀ በሁዋላ እንደገና መረጃውን በማሻሻል ተመላሾቹ ከ50 እስከ 80 ሺ እንደሚገመቱ ይፋ አደርጎአል፡፡ ይሁን እንጅ እስትናንት ድረስ ከ100 ሺ በላይ ሰዎች መመለሳቸውን የመንግስት መገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል፡፡ከነዚህ መካከል 8 ሺህ የሚሆኑት ነፍሰ ጡር መሆናቸው ተገልጿል ፡፡
መንግስት ለተመላሾቹ 50 ሚሊየን ብር መመደቡን ከመግለጽ ውጪ መልሶ ለማቋቋም ምንም ያሰበው
ነገር አለመኖሩን የጠቀሱት ምንጮቹ  ተመላሾቹን ተቀብሎ በሲቪል ሰርቪስ ዩኒቨርሲቲ ጊዜያዊ ማረፊያ ካቆየ በኃላ ክልሎች ስራ ይሰጡዋቹሃል በማለት እያባበለ ወደትውልድ አካባቢቸው እንዲሄዱ እያደረገ መሆኑን  ጠቁመዋል፡፡ተመላሾቹ  በሰው አገር መከራና ስቃይን ከማሳለፍ ባሻገር  ያፈሩትን ሐብትና ገንዘብ ይዘው መመለስ አለመቻላቸውን ያስታወሱት እነዚሁ ምንጮች በዚህ ሁኔታ ላይ ያሉትንና  በተስፋ መቁረጥ የተጎዱትን ወገኖች በባዶ እጅ ወደ ቤተሰብ መስደድ እጅግ አሳዛኝ ነው ብለዋል ፡፡
በፌዴራል ዋና ኦዲተር ሪፖርት መሰረት መከላከያና ሌሎች መንግስታዊ መ/ቤቶች  በ2004 የበጀት አመት 3 ነጥብ 6 ቢሊየን ብር ያለበቂ ሰነድና ተጠያቂነት በባከኑበት አገር፤ በአንጻሩ ከስደት ተመላሽ ዜጎች በበቂ ሁኔታ እንኩዋን መረዳት የሚችሉበት ሁኔታ አለመመቻቸቱ፣ ጉዳያቸውም ለፖለቲካ ፍጆታ መጠቀሚያ ብቻ መዋሉ ያስቆጫል ብለዋል᎗ የኢሳት የአዲስ አበባ ዘጋቢ ያነጋገራቸው ወገኖች፡፡
መንግስት ለተመላሽ ወገኞች ህዝቡ እርዳታ እንዲደርግ ባቀረበው ጥሪ መሰረት ባላሃብቶች ሰባት ሚሊየን ብር ለመለገስ ቃል የገቡ ሲሆን ከዚህም ውስጥ ሁለት ሚሊየን ብሩ  የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን የለገሰችው ነው፡፡ በአጠቃላይ እስካሁን ያለው የዕርዳታ ጥያቄ ምላሽ አጥጋቢ አለመሆኑ ብቻ ሳይሆን በመንግስት በኩልም ተጨማሪ በጀት መድቦ ሰዎቹን በዘላቂነት ለማቋቋም ፍላጎት አለመታየቱ አሳዛኝ መሆኑን ለጉዳዩ ቅርበት ያላቸው ወገኖች እየገለጹ ነው ።
ከዚሁ ጋር በተያያዘ በሳዑዲ አረቢያ በኢትዮጵያውያን ላይ የሚፈፀመውን ግፍ በመቃወም በስዊዘርላንድ ለሁለተኛ ጊዜ የተቃውሞ ሰልፍ ተደርጓል።
ከሳምንት በፊት በስዊዘርላንድ-በርን በሚገኘው የሳኡዲ አረቢያ ኤምባሲ ፊት ለፊት በመውጣት ተቃውሟቸውን የገለጹት ኢትዮጵያውያን፤ በጀኔቭ ከተማ ለሁለተኛ ጊዜ ባደረጉት ሰልፍ በወንድሞቻቸውና እህቶቻቸው ላይ እየተፈፀመ ያለውንና ሊያባራ ያልቻለውን ግፍና ሰቆቃ አውግዘዋል።
በጀኔቭ የተባበሩት መንግስታት ዋና ጽህፈት ቤት  በተደረገው ሰልፍ ኢትዮጵያውያኑ በዜጎቻቸው ላይ እየተፈፀመ ያለውን ግፍ ድምፃቸውን ከፍ በማድረግ ከማሰማታቸውም ባሻገር የቪዲዮ ማስረጃዎቸን  በ አንድ ላይ አሰባስበው በማደራጀት ለጽህፈት ቤቱ እንዲደርስ አድርገዋል።
ከቀኑ 14 ሰዓት እስከ 17 ሰዓት በቆየው በዚሁ ሰልፍ ላይ ፓርቲያቸውን በውጭ ሃገራት የማስተዋወቅ ተግባር እያከናወኑ ያሉት የሰማያዊ ፓርቲ ሊቀ-መንበር ኢንጂነር ይልቃል ጌትነት ተሳትፈዋል።
ከአስተባባሪዎቹ -አንዱ የሆነው ወጣት አክቲቪስት ጴጥሮስ አሸናፊ ሰልፉን አስመልክቶ ከኢሳት ጋር ባደረገው አጭር ቆይታ፤የወገኖቻችን ሰቆቃ እስኪያባራ ድረስ ያለድካምና መታከት ጩኸታችንን  ለዓለማቀፉ ማህበረሰብ ማሰማታችንን እንቀጥላለን ብሏል።
በሰልፉ ላይ የኢትዮጵያውያኑን ስሜት የነካ ግጥም ያቀረበችው ወጣት ነጃት በበኩሏ-ከሁሉም በተለየ መልኩ ግፉና መከራው ኢትዮጵያውያን ላይ ብቻ ማየሉ እረፍት እንደነሳት ትናገራለች።
ለሰልፈኞቹ ንግግር እንዲያደርጉ የተጋበዙት የሰማያዊነፓርቲ ሊቀመንበር ኢንጂነር ይልቃል ጌትነት በበኩላቸው፤በኢትዮጵያ ለወገኖቻቸው ድምፃቸውን ለማሰማት ባልቻሉበት ወቅት ወደ  ወጪ አገር መጥተው  ለመሰለፍ  መብቃታቸው እንዳስገረማቸው ተናግረዋል።

Thursday, December 5, 2013

Nelson Mandela, anti-apartheid icon and father of modern South Africa, dies

December 5, 2013
(CNN) — Nelson Mandela, the revered statesman who emerged from prison after 27 years to lead South Africa out of decades of apartheid, has died, South African President Jacob Zuma announced late Thursday.
Nelson Mandela has died
Mandela was 95.
“He is now resting. He is now at peace,” Zuma said. “Our nation has lost its greatest son. Our people have lost a father.”
“What made Nelson Mandela great was precisely what made him human,” the president said in his late-night address. “We saw in him what we seek in ourselves.”
Mandela will have a state funeral. Zuma ordered all flags in the nation to be flown at half-staff from Friday through that funeral.
Mandela, a former president, battled health issues in recent months, including a recurring lung infection that led to numerous hospitalizations.
With advancing age and bouts of illness, Mandela retreated to a quiet life at his boyhood home in the nation’s Eastern Cape Province, where he said he was most at peace.
Despite rare public appearances, he held a special place in the consciousness of the nation and the world.
A hero to blacks and whites
In a nation healing from the scars of apartheid, Mandela became a moral compass.
His defiance of white minority rule and incarceration for fighting against segregation focused the world’s attention on apartheid, the legalized racial segregation enforced by the South African government until 1994.
In his lifetime, he was a man of complexities. He went from a militant freedom fighter, to a prisoner, to a unifying figure, to an elder statesman.
Years after his 1999 retirement from the presidency, Mandela was considered the ideal head of state. He became a yardstick for African leaders, who consistently fell short when measured against him.
Warm, lanky and charismatic in his silk, earth-toned dashikis, he was quick to admit to his shortcomings, endearing him further in a culture in which leaders rarely do.
His steely gaze disarmed opponents. So did his flashy smile.
Former South African President F.W. de Klerk, who was awarded the Nobel Peace Prize with Mandela in 1993 for transitioning the nation from a system of racial segregation, described their first meeting.
“I had read, of course, everything I could read about him beforehand. I was well-briefed,” he said last year.
“I was impressed, however, by how tall he was. By the ramrod straightness of his stature, and realized that this is a very special man. He had an aura around him. He’s truly a very dignified and a very admirable person.”
For many South Africans, he was simply Madiba, his traditional clan name. Others affectionately called him Tata, the Xhosa word for father.
A nation on edge
Mandela last appeared in public during the 2010 World Cup hosted by South Africa. His absences from the limelight and frequent hospitalizations left the nation on edge, prompting Zuma to reassure citizens every time he fell sick.
“Mandela is woven into the fabric of the country and the world,” said Ayo Johnson, director of Viewpoint Africa, which sells content about the continent to media outlets.
When he was around, South Africans had faith that their leaders would live up to the nation’s ideals, according to Johnson.
“He was a father figure, elder statesman and global ambassador,” Johnson said. “He was the guarantee, almost like an insurance policy, that South Africa’s young democracy and its leaders will pursue the nation’s best interests.”
There are telling nuggets of Mandela’s character in the many autobiographies about him.
An unmovable stubbornness. A quick, easy smile. An even quicker frown when accosted with a discussion he wanted no part of.
War averted
Despite chronic political violence in the years preceding the vote that put him in office in 1994, South Africa avoided a full-fledged civil war in its transition from apartheid to multiparty democracy. The peace was due in large part to the leadership and vision of Mandela and de Klerk.
“We were expected by the world to self-destruct in the bloodiest civil war along racial grounds,” Mandela said during a 2004 celebration to mark a decade of democracy in South Africa.
“Not only did we avert such racial conflagration, we created amongst ourselves one of the most exemplary and progressive nonracial and nonsexist democratic orders in the contemporary world.”
Mandela represented a new breed of African liberation leaders, breaking from others of his era such as Robert Mugabe by serving one term.
In neighboring Zimbabwe, Mugabe has been president since 1987. A lot of African leaders overstayed their welcomes and remained in office for years, sometimes decades, making Mandela an anomaly.
But he was not always popular in world capitals.
Until 2008, the United States had placed him and other members of the African National Congress on its terror list because of their militant fight against the apartheid regime.
Humble beginnings
Rolihlahla Mandela started his journey in the tiny village of Mvezo, in the hills of the Eastern Cape, where he was born on July 18, 1918. His teacher later named him Nelson as part of a custom to give all schoolchildren Christian names.
His father died when he was 9, and the local tribal chief took him in and educated him.
Mandela attended school in rural Qunu, where he retreated in 2011 before returning to Johannesburg and later Pretoria to be near medical facilities.
He briefly attended University College of Fort Hare but was expelled after taking part in a protest with Oliver Tambo, with whom he later operated the nation’s first black law firm.
In subsequent years, he completed a bachelor’s degree through correspondence courses and studied law at the University of Witwatersrand in Johannesburg, but left without graduating in 1948.
Four years before he left the university, he helped form the youth league of the African National Congress, hoping to transform the organization into a more radical movement. He was dissatisfied with the ANC and its old-guard politics.
And so began Mandela’s civil disobedience and lifelong commitment to breaking the shackles of segregation in South Africa.
Escalating trouble
In 1956, Mandela and dozens of other political activists were charged with high treason for activities against the government. His trial lasted five years, but he was ultimately acquitted.
Meanwhile, the fight for equality got bloodier.
Four years after his treason charges, police shot 69 unarmed black protesters in Sharpeville township as they demonstrated outside a station. The Sharpeville Massacre was condemned worldwide, and it spurred Mandela to take a more militant tone in the fight against apartheid.
The South African government outlawed the ANC after the massacre, and an angry Mandela went underground to form a new military wing of the organization.
“There are many people who feel that it is useless and futile for us to continue talking peace and nonviolence against a government whose reply is only savage attacks on an unarmed and defenseless people,” Mandela said during his time on the run.
During that period, he left South Africa and secretly traveled under a fake name. The press nicknamed him “the Black Pimpernel” because of his police evasion tactics.
Militant resistance
The African National Congress heeded calls for stronger action against the apartheid regime, and Mandela helped launch an armed wing to attack government symbols, including post offices and offices.
The armed struggle was a defense mechanism against government violence, he said.
“My people, Africans, are turning to deliberate acts of violence and of force against the government, in order to persuade the government, in the only language which this government shows by its own behavior that it understands,” Mandela said during a hearing in 1962.
“If there is no dawning of sanity on the part of the government — ultimately, the dispute between the government and my people will finish up by being settled in violence and by force. ”
The campaign of violence against the state resulted in civilian casualties.
Long imprisonment
In 1962, Mandela secretly received military training in Morocco and Ethiopia. When he returned home later that year, he was arrested and charged with illegal exit of the country and incitement to strike.
Mandela represented himself at the trial and was briefly imprisoned before being returned to court. In 1964, after the famous Rivonia trial, he was sentenced to life in prison for sabotage and conspiracy to overthrow the government.
At the trial, instead of testifying, he opted to give a speech that was more than four hours long, and ended with a defiant statement.
“I have fought against white domination, and I have fought against black domination,” he said. “I have cherished the ideal of a democratic and free society in which all persons live together in harmony and with equal opportunities. It is an ideal which I hope to live for and to achieve. But if needs be, it is an ideal for which I am prepared to die.”
His next stop was the Robben Island prison, where he spent 18 of his 27 years in detention. He described his early days there as harsh.
“There was a lot of physical abuse, and many of my colleagues went through that humiliation,” he said.
One of those colleagues was Khehla Shubane, 57, who was imprisoned in Robben Island during Mandela’s last years there. Though they were in different sections of the prison, he said, Mandela was a towering figure.
“He demanded better rights for us all in prison. The right to get more letters, get newspapers, listen to the radio, better food, right to study,” Shubane said. “It may not sound like much to the outside world, but when you are in prison, that’s all you have.”
And Mandela’s khaki prison pants, he said, were always crisp and ironed.
“Most of us chaps were lazy, we would hang our clothes out to dry and wear them with creases. We were in a prison, we didn’t care. But Mandela, every time I saw him, he looked sharp.”
After 18 years, he was transferred to other prisons, where he experienced better conditions until he was freed in 1990.
Months before his release, he obtained a bachelor’s in law in absentia from the University of South Africa.
Calls for release
His freedom followed years of an international outcry led by Winnie Mandela, a social worker whom he married in 1958, three months after divorcing his first wife.
Mandela was banned from reading newspapers, but his wife provided a link to the outside world.
She told him of the growing calls for his release and updated him on the fight against apartheid.
World pressure mounted to free Mandela with the imposition of political, economic and sporting sanctions, and the white minority government became more isolated.
In 1988 at age 70, Mandela was hospitalized with tuberculosis, a disease whose effects plagued him until the day he died. He recovered and was sent to a minimum security prison farm, where he was given his own quarters and could receive additional visitors.
Among them, in an unprecedented meeting, was South Africa’s president, P.W. Botha.
Change was in the air.
When Botha’s successor, de Klerk, took over, he pledged to negotiate an end to apartheid.
Free at last
On February 11, 1990, Mandela walked out of prison to thunderous applause, his clenched right fist raised above his head.
Still as upright and proud, he would say, as the day he walked into prison nearly three decades earlier.
“As I walked out the door toward the gate that would lead to my freedom, I knew if I didn’t leave my bitterness and hatred behind, I’d still be in prison,” he said at the time.
He reassured ANC supporters that his release was not part of a government deal and informed whites that he intended to work toward reconciliation.
Four years after his release, in South Africa’s first multiracial elections, he became the nation’s first black president.
“The day he was inducted as president, we stood on the terraces of the Union Building,” de Klerk remembered years later. “He took my hand and lifted it up. He put his arm around me, and we showed a unity that resounded through South Africa and the world.”
Broken marriage, then love
His union to Winnie Mandela, however, did not have such a happy ending. They officially divorced in 1996 after several years of separation.
For the two, it was a fiery love story, derailed by his ambition to end apartheid. During his time in prison, Mandela wrote his wife long letters, expressing his guilt at putting political activism before family. Before the separation, Winnie Mandela was implicated in violence, including a conviction for being an accessory to assault in the death of a teenage township activist.
Mandela found love again two years after the divorce.
On his 80th birthday, he married Graca Machel, the widow of former Mozambique president, Samora Machel.
Only three of Mandela’s children are still alive. He has 17 grandchildren and 12 great-grandchildren
Symbolic rugby
South Africa’s fight for reconciliation was epitomized at the 1995 rugby World Cup Final in Johannesburg, when it played heavily favored New Zealand.
As the dominant sport of white Afrikaners, rugby was reviled by blacks in South Africa. They often cheered for rivals playing their national team.
Mandela’s deft use of the national team to heal South Africa was captured in director Clint Eastwood’s 2009 feature film “Invictus,” starring Morgan Freeman as Mandela and Matt Damon as Francois Pienaar, the white South African captain of the rugby team.
Before the real-life game, Mandela walked onto the pitch, wearing a green-and-gold South African jersey bearing Pienaar’s number on the back.
“I will never forget the goosebumps that stood on my arms when he walked out onto the pitch before the game started,” said Rory Steyn, his bodyguard for most of his presidency.
“That crowd, which was almost exclusively white … started to chant his name. That one act of putting on a No. 6 jersey did more than any other statement in bringing white South Africans and Afrikaners on side with new South Africa.”
During his presidency, Mandela established the Truth and Reconciliation Commission to investigate human rights abuses during apartheid. He also introduced housing, education and economic development initiatives designed to improve the living standards of the black majority.
A promise honored
In 1999, Mandela did not seek a second term as president, keeping his promise to serve only one term. Thabo Mbeki succeeded him in June of the same year.
After leaving the presidency, he retired from active politics, but remained in the public eye, championing causes such as human rights, world peace and the fight against AIDS.
It was a decision born of tragedy: His only surviving son, Makgatho Mandela, died of AIDS at age 55 in 2005. Another son, Madiba Thembekile, was killed in a car crash in 1969.
Mandela’s 90th birthday party in London’s Hyde Park was dedicated to HIV awareness and prevention, and was titled 46664, his prison number on Robben Island.
A resounding voice
Mandela continued to be a voice for developing nations.
He criticized U.S. President George W. Bush for launching the 2003 war against Iraq, and accused the United States of “wanting to plunge the world into a Holocaust.”
And as he was acclaimed as the force behind ending apartheid, he made it clear he was only one of many who helped transform South Africa into a democracy.
In 2004, a few weeks before he turned 86, he announced his retirement from public life to spend more time with his loved ones.
“Don’t call me, I’ll call you,” he said as he stepped away from his hectic schedule.
‘Like a boy of 15′
But there was a big treat in store for the avid sportsman.
When South Africa was awarded the 2010 football World Cup, Mandela said he felt “like a boy of 15.”
In July that year, he beamed and waved at fans during the final of the tournament in Johannesburg’s Soccer City. It was his last public appearance.
“I would like to be remembered not as anyone unique or special, but as part of a great team in this country that has struggled for many years, for decades and even centuries,” he said. “The greatest glory of living lies not in never falling, but in rising every time you fall.”

ከሳውዲ ዓረቢያ ከተመለሱ ስደተኞች መካከል 8 ሺህ ሴቶች ነብሰ ጡር ናቸው ተባለ::


December 5/2013

ከሳውዲ ዓረቢያ ከተመለሱ ስደተኞች መካከል 8 ሺህ ሴቶች ነብሰ ጡሮች መሆናቸውን FBC (Fana Broadcasting Corporate S.C.)በውጭ ጉዳይ ሚንስቴር የመካከለኛው ምስራቅ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ጀማል በክር ዋቢ በማድረግ ዘገበ ። 

ከተጠቀሱት ነፍሰጡር እህቶቻችን መሃከል በሪያድ እና በጅዳ የሚገኙ የኮሚኒ ግዜያዊ መጠለያ ከገቡ በሃላ አስገድዶ መድፈር ወንጀል ሳይፈጸምባቸው እንዳልቀረ ምንጮች ገለጹ ።

እስከ ትናንት ባለው መረጃ መሰረት የወንዶች ቁጥር 58 ሺህ 529 ፣ የሴቶች ቁጥር 28 ሺህ 943 ሲሆኑ ከእነዚህ ውስጥ 8 ሺ ሴቶች ነፍሰ ጡሮች መሆናቸው ታውቋል።

የህጻናት ቁጥር ደግሞ 4 ሺህ 51 መድረሱ ለማወቅ ተችሏል።

በአሁኑ ወቅት ካሳዑዲ ተመላሽ ኢትዮጵያን እንግልት እንዳይገጥማቸው ከመንገዶች ባለስልጣን ጋር በመተባበር ጊዜያዊ መናኻሪያ እንደተቋቋመና ለአብነትም በትናንትናው እለት ብቻ ከ 4 ሺህ 20 በላይ ዜጎች ወደየቅያቸው እንዲመለሱ መደረጉን በውጭ ጉዳይ ሚንስቴር የመካከለኛው ምስራቅ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ጀማል በክር ተናግረዋል።

ይህ በዚህ እንዳለ አሰሪዎቻቸው ከሚፈጽሙባቸው ግፍ እና በደል ለመታደግ ቀደም ሲል ባዲራቸው ወደ ተሰቀለችበት በሪያድ የኢትዮጵያ ኮሚኒት እና በጅዳ ቆንስላ ግቢ ተጠልለው ከነብሩ እህቶቻችን መሃከል ከ 15 በላይ ነፍሰጡሮች መሆናቸው መዘገቡ ይታወሳል ።

እነዚህ ለስራ ወደ ሳውዲ አረቢያ አቅንተው በለስ ያልቀናቸው ወገኖች በተጠቀሱት የኮሚኒት ማዕከላት ለጥያቄ ትፈለጋላችሁ እየተባለ ማታማታ ባዶ ክፍል ውስጥ ለሰአታት ቆይተው ይወጡ እንደነበር የሚናገሩ ምንጮች በተጠቀሱት እህቶቻችን ላይ የአስገድዶ መድፈር ወንጀል በኮሚኒቲው አላፊዎች አሊያም በሪያድ የኢትዮጵያ ዲፕሎማቶች ሳይፈጸምባቸው እንዳልቀረ አክለው ይገለጻሉ። የተጠቀሰውን መረጃ መሰረት በማድረግ አንዳንድ ወገኖች ጉዳዩን ለማጣራት ያደረጉት ሙከራ በሁለቱም « በጅዳ እና በሪያድ » ኮሚኒት ግቢ ውስጥ ተጠልለው የነብሩ እህቶቻችን የሪያዱን ግርግር ተከትሎ በዲፕሎማቱ ተዕዛዝ ወደ አልታወቀ እስርቤት መወስዳቸው የሚገልጹ የአይን እማኞች ነፍሰጡሮቹ እስካሁን ያሉበትን እና የተፈጸመውን ወንጀል ለማጣራት እንዳልተቻለ ይገልጻሉ።

ይህንን ጉዳይ በተመለክተ በሪያድ የኢትዮጵያ ኮሚኒት ግቢ ተጠልለው የነበሩ 12 ነፍሰጡር እህቶቻችን ስም ዘርዝር እና የኢትዮጵያ አድራሻቸው እጃችው እንደገባ የሚገልጹ እንዚህ ወገኖች ወደፊት የእህቶቻችንን ሞራል በማይነካ ሁኔታ እንደአስፈላጊነቱ በወገኖቻችን ላይ የተፈጸመውን አሳዛኝ እና ዘግናኝ ድርጊት ለህዝብ ይፋ ለማድረግ ይሞከራል ብለዋል ።

Ethiopian Hagere ጅዳ በዋዲ