Wednesday, June 17, 2015

ኣቶ ታደሰ ኣብርሃ የተባሉ የዓረና-መድረክ ኣባልና የምዕራባዊ ዞን የዓረና ኣመራር ኣባል በሶስት ሰዎች ታንቀው ተገደሉ።

June 17,2015
ኣቶ ታደሰ ኣብርሃ የተባሉ የዓረና-መድረክ ኣባልና የምዕራባዊ ዞን የዓረና ኣመራር ኣባል ትናንት ማታ 09 / 10 / 2007 ዓ/ም
በሶስት ሰዎች ታንቀው ተገደሉ።
ኣቶ ታደሰ ኣብራሃ በቓፍታ ሑመራ ወረዳ ማይካድራ ቀበሌ ኑዋሪ ሲሆኑ በዘንድሮው ምርጫ ወቅት በቀበሌው ኣስተዳዳሪዎች፣ ካድሬዎች፣ የሚቀርቧቸው ሰዎች ከዓረና-መድረክ ኣባልነታቸው እንዲለቁ የተሸመገሉ፣ የተለመኑና በመጨረሻም ዛቻዎች ሲደርስባቸው እንደነበረ ይታወቃል።
ኣቶ ታደሰ ማታ 03:00 በ 3 ሰዎች ኣንገታቸው የታነቁ ሲሆን ሶስቱ ሰዎች ሙቷል ብለው የተዋቸው ቢሆኑም ሂወታቸው እስከ 09:15 ኣላለፈችም ነበር። ኣቶ ታደሰ ኣብራሃ የ48 ዕድሜ ጎልማሳ ነበሩ።
ኣደጋው 3 ሰዎች እንደፈፀሙባቸው፣ በኪሳቸውም 300 ብር የነበረ ቢሆንም ሰዎቹ ሊወስዱት እንዳልቻሉ ተናገረው ነበር።
የኣቶ ታደሰ ሬሳ በሑመራ ሆስፒታል ላለማስመርመር የማይካድራ ፖሊስ ትራፊክ በዓረና ኣባላት ላይ ከፍተኛ ጫና የፈጠሩ ሲሆን የተለያዩ የመንግስት ኣካላትም ምርመራው እንዳይካሄድ የተለያዩ ጫናዎች እንደፈጠሩ ኣባሎቻችን ከስፍራው ገልፀውልናል።
ሬሳው ወደ ሑመራ ወስዶ ለማስመርመር የሚጠቅም መኪና ለመከራይ ሲባል ኣባሎቻችን የተካራት ሞተር ሳይክ በፖሊስት ትራፊክ ተከልክላለች።
የኣቶ ታደሰ ኣብራሃ ቤት ኣካራይና ሌሎች ሰዎች ከኣደጋው በተያያዘ ጫና እየተፈጠረባቸው እንደሆነ ለማወቅ ተችለዋል።
የኣቶ ታደሰ ኣብራሃ ግድያ በሳምንት ውስጥ የወጣት ሳሙኤል ኣወቀን ጨምሮ ለሁለተኛ ግዜ በፖለቲከኞች ላይ የተፈፀመ ግድያ ሲሆን ከ2007 ዓ/ም በዓረና-መድረክ ኣባላት ለሁለተኛ ግዜ የተፈፀመ ግድያ ያደርገዋል።
ባለፈው ታህሳስ ወር የደቡባዊ ዞን የዓረና-መድረክ ኣስተባባሪና የማእከላይ ኮሚቴ ኣባል የነበረው ኣቶ ልጃለም ኻልኣዩ በኣዲስ ኣበባ ማንነታቸው ባልታወቁ ሰዎች መገደሉ ይታወቃል።
ይህ ተግባር በስፁም የሚወገዝና በሰላማዊ ትግል ላይ ሽብር የሚፈጥር ተግባር ነው።
በሰለማዊ መንገድ የሚታገሉ ፖለቲከኞች የሚፈፀም ግድያ ይቁም...!
መንግስት ነብሰገዳዮች ወደ ፍርድ ያቅርብ...!
ፈጣሪ ነብሳቸው ገነት ውስጥ ያኑርልን ኣሜን።
ነፃነታችን በእጃችን ነው።
IT IS SO..!
ምንጭ አምዶም ገብረስላሴ

ብርሃነ ገብረ ክርስቶስ በድብቅ ጅዳ ገቡ

June 17,2015
ልማታዊ “ዲፕሎማት” በምስጢር ካድሬዎችን ሰብስበዋል
berhane

የውጭ ጉዳይ ምክትል ሚ/ር አቶ ብርሃነ ገ/ክርስቶስ በድብቅ ጅዳ ማምሻውን ገብተዋል፡፡ ወደ ሳዑዲ አረቢያ የመጡበት ምክንያት ባይታወቅም በዚያው የሚገኙ የኢህአዴግ ሹሞችና ልማታዊ ዲፕሎማቶች ድንገተኛውን ጉብኝት ተከትሎ ከብርሃነ ጋር ለመወያየት ሽርጉድ ይሉ ለነበሩ የጅዳና አካባቢው ካድሬዎች፣ ለልማት ማህበራት ተወካዮችና ለደጋፊዎቻቸው በሚስጥር ጥሪ አስተላልፈዋል፡፡

ምስጢራዊውን ጥሪ የሚቃወሙ ኢትዮጵያውያን አንድ ባለስልጣን በዚህ መልክ ወደ ጃዳ መግባታቸው ዲፕሎማት ብለው ለሾሟቸው አገልጋዮቻቸው ያላቸውን ንቀት የሚያሳይ ብቻ ሳይሆን በዲፕሎማቱ ላይ እምነት እንደሌላቸው አመላካች መሆኑን ይናገራሉ።
berhane jeddah
ልማታውያንና የልማት አጋሮች ብርሃነን ለውይይት ሲጠብቁ
ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የኢህአዴግ ከፍተኛ ባለሥልጣናት ለስራ ጉብኝትም ይሁን ለህክምና ወደ ሳውዲ አረቢያ ሲገቡ የኤምባሲው ዲፕሎማቶች መረጃ የሚያገኙት ከተለያዩ ድህረ ገጾች መሆኑን የሚናገሩ ውስጥ አዋቂዎች ከዚህ በፊት በረከት ስምዖን በምስጢር ለህክምና ሲገቡ ዲፕሎማቱ በተመሳሳይ ሁኔታ መረጃ እንዳልነበራቸው ያስታውሳሉ፡፡
ከአንድ ዓመት በፊት በረከት በመሐመድ አላሙዲን የግል አውሮፕላን ተጭንው እኩለ ሌሊት ሳውዲ ገብተው ጅዳ ከተማ በሚገኝ አንድ ሆስፒታል ውስጥ በህክምና ላይ መሆናቸውን የቆንሳላ ጽ/ቤቱም ይሁን በሪያድ የኢትዮጵያ ኤምባሲ ያወቁት ጎልጉል እና ዘሃበሻ ሚዲያ ላይ በተለቀቀው መረጃ መሆኑን የሚያስታውሱ እነዚህ ወገኖች በዲፕሎማቱና በኢህአዴግ መሃከል ከፍተኛ የሆነ የመረጃ ክፍተት መኖሩን ያወሳሉ፡፡ በመሆኑም የመረጃ ክፍተቱን ለማሟላት ዲፕሎማቱ ሚስጥራዊ መረጃዎችን ለማግኘት የተጠቀሱትን ሚዲያዎች መከታተል አማራጭ የሌለው መፍትሄ እንደሆነባቸው ይነገራል።
ዛሬ በጅዳ ቆንስላ ጽ/ቤት በተደረገው ስብሰባ ላይ የታዩት ብርሃነ ገብረክርስቶስ በሙስና ስለሚታመሰው በጅዳ የኢትዮጵያ ኮሚኒቲ ት/ቤትና ህልውናው ስላከተመው በሪያድ የኢትዮጵያ ኮሚኒቲ ማህበር ንብረት መባከን ምንም መረጃ እንደሌላቸው ለማወቅ ተችሏል።
አንድ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መ/ቤት ሠራተኛ አስከትለው ትላንት ጅዳ ሳውዲ አረቢያ ስለገቡት አቶ ብርሃነ ገብረክርስቶስ ጉብኝት በሳውዲም ሆነ አገር ቤት ከሚገኘው የኢህአዴግ ጽ/ቤትና መገናኛ ብዙሃን እስካሁን ምንም የተባለ ነገር የለም፡፡ አሁን ዘግይቶ በደረሰን ዜና ብርሃነ ወደ ሪያድ ከተማ ያቀናሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡ (Ethiopian Hagere Jed Bewadi )

Monday, June 15, 2015

በማዕከላዊ እዝ የሚገኝ አንድ የኦሮሞ ተወላጅ የሆነ የአስር አለቃ ማዓረግ አይገባህም በመባሉ የተነስ እራሱን አጠፋ

June 15,2015
maekelay ezi ye mareg asetat የሚገኙ የሰራዊት አባላት ለሃምሌ ወር 2007 ዓ/ም የቆይታ ጊዜአቸውን ጨርሰው በሚገኙ የሰራዊት አባላት ላይ እየተካሄደ ባለው የከፋ የዘረኝነት ምልመላ ምክንያት አንድ የኦሮሞ ተወላጅ የሆነ የአስር አለቃ ማዓረግ አይገባህም በመባሉ የተነስ እራሱን እንዳጠፋ ተገለፀ።
በደረሰን መረጃ መሰረት- የ23 ክፍለ ጦር የ2 ሬጅመንት በ3 ሃይል ውስጥ የቲም ምክትል አዛዥ የነበረ አስር አለቃ ጫላ ጋዲሳ የተባለው ወታደር በተለያዩ መድረኮች ላይ ተቃራኒ የሆነ ሃሳቦችን ያቀርባል ለህገ መንግስቱ ታማኝ አይደለም መንግስትን ያማርራል የሚሉ ነጥቦችን አስቀምጠው ማዕረግ አይገባህም ተብሎ ከሃይል አመራር በላይ ያሉ አዛዦች ውሳኔውን በማስተላለፋቸው ምክንያት ስሜቱ የተጎዳው ይህ ወታደር ስብሰባው እንዳለቀ ዋርዲያ ነኝ በሎ በመውጣት እራሱን እንዳጠፋ ከእዙ የደረሰን መረጃ አመለከተ።
በአሁኑ ጊዜ በኢህአዴግ የሰራዊት አባላት ውስጥ ያለው የከፋ የዘረኝነት አድሎዎ ለማዕረግ እድገትና ለተለያዩ ጥቅማጥቅሞች ሲባል በሚደረጉ ምልመላዎች ላይ የሰራዊቱ ከፍተኛ አመራሮች በሰራዊት ውስጥ ኢ- ፍትሃዊ የሆነ አሰራር እየሰሩ መሆናቸውን በተለያዩ የሰራዊት እዞች ውስጥ የሚገኙ ምንጮቻችን የላኩልን መረጃ ያስረዳል።
ምንጭ ዴምህት

Sunday, June 14, 2015

የፍቅር ትርያንግል አዙሪት(Lovers Triangle)፤ ሼህ መሐመድ አላሙዲ-ከመንግስት ባለስልጣናት-ከልማታዊ አርቲስቶቻችን

June 14, 2015
በሥዩም ወርቅነህ
ቱጃሩ ‘ሼክ’ መሐመድ አል አሙዲን፤ጋጠወጦቹ የወያኔ መንግስት ሹማምንቶች፦ የሃገሪቱ ፕሬዚደንት ዶ/ር ሙላቱ ተሾመ፣ የፌደረሽን ምክር ቤት አፈ-ጉባዔ፣ የጠቅላይ ሚኒስትሩ አማካሪ አቶ በረከት ስምዖን፣ እንዲሁም ታላላቅ ‘የተከበሩ’ እንግዶችና የአርቲስት ቤተሰቦች በተገኙበት፤ በትላንትናው እለት የትዝታው ንጉስ ጋሽ ማህሙድ አህመድ 50ኛ ዓመት የሙያ ጉዞ በማስመልከት የተዘጋጀ ዝግጅት ሲከበር፤ ከወጣቷ አክትረስ ማህደር አሰፋ ጋር ከትዳራቸው ውጭ ሲማግጡ ታይተዋል። ይህ ከሃገራችን ባህልና ወግ በእጅጉ የሚፃረርና የወደፊት ተተኪውን ትውልድን ወደ አልባሌ ድርጊት የሚገፋፋ ነውረኛ ተግባር ነው።Sheikh Mohammed Hussein Ali Al Amoudi
ማህደርና ሼሁ ለብዙ ጊዜ ሲታሙ መቆየታቸው ይታወቃል። ነገር ግን ንቀት ካልሆነ በቀር እንደዚህ ጋጠወጥ የሆነን ድርጊት በአደባባይ ማድረጉ ለምን አስፈለገ? የወያኔ ሊቀመናብርት ባለስልጣናትን በመዳፋቸው በማስገባት የሃገሪቱን ሃብት የሚዘርፋት ሼክ መሃመድ አል አሙዲን በልማታዊ አርቲስቶቻችን ሰይፉ ፋንታሁን፣ ሰራዊት ፍቅሬ፣ ሙሉዓለም ታደሰ፣ ማዲንጎ አፈወርቅና በሌሎችም አማካኝነት ታዳጊ ወጣት የሃገራችን ልጃገረዶችን በሃብታቸው በማማለል ከአላማቸው በማሰናከል ንፅህናቸውን እንዲያረክሱ ያስገድዷቸዋል። ይህን ህገ-ወጥ ድርጊት የሚያውቁት የወያኔ ቁንጮ ባለስልጣናት ከድርጊታቸው እንዲቆጠቡ ከማድረግ ይልቅ በተጋበዙበት ግብዣ እንኳን ከትዳራቸው ውጭ እየማገጡ እያዩ በጭብጨባ አጅበዋቸዋል።
ወያኔና ጀሌዎቹ ላለፉት 24 ዓመታት የኃገራችን ሃብትና ንብረትን የዘረፉት አንሷቸው፤ ታሪካችንን ሲያጠለሹ፣ ሲያጠፉ፣ የታሪክ መፅሃፍትና ቅርስ ለባዕድ ሲሸጡ፣ ሲያቃጥሉ፣ ባህልና ወጋችንን ሲያንኳስሱ፣ የእምነትና ሃይማኖት ስፍራዎችን ሲያረክሱና ሲያቃጥሉ፣ እንዲሁም አያሌ ወንጀሎችን ሲፈፅሙ መቆየታቸው ፀሃይ የሞቀው የአደባባይ ሚስጥር ነው። እንደ አንድ ኢትዮጵያዊ ለእኔ በዚህ ደረጃ ተንኮታኩታ ጥበብ በአደባባይ ረክሳ፣ ሃገር ተደፍራና አንገታችንን አስደፍታ ማየት ያመኛል። ልማታዊ አርቲስቶቹና የወያኔ ቁንጮ ባለስልጣናት በሼሁ ፍርፋሪ ገንዘብ ህሊናቸው ታውሯል። ልማታዊ አርቲስቶቹም በጥቅም በመደለል የወያኔ ሎሌ ሆነዋል። በቅኝ ግዛት ተገዝታ የማታውቀው ሃገራችን ኢትዮጵያም ሼክ መሐመድ አል አሙዲን እንደፈለጉ የሚፈነጩባትና እሚያዙባት ሃገር ሆናለች።
ሼህ መሐመድ አል አሙዲን 28 ክርስቲያን ወንድሞቻችን ISIS በሚባለው እስላማዊው አሸባሪ ቡድን ከታረዱ ወዲህ ለብዙ አርስቲስቶች በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ብሮች በስጦታና በሽልማት መልክ አበርክተዋል። ለአብነት ያህል ለአርቲስት ማዲንጎ አፈወርቅና ለንዋይ ደበበ ሁለት ሁለት ሚሊዮን ብር፣ ለመሳፍንት 9 ሚሊዮን ብር እንዲሁም በትላንትናው ዕለት ለአርቲስት ማህሙድ አህመድ 5 ሚሊዮን ብር በሽልማት መልክ ለግሰዋል። እውን ይህን ሁሉ የሚያደርጉት ለአርቲስቶቻችን እውነተኛ አክብሮት ኖሯቸው ይሆን!? እውነተኛ ምክንያታቸው ይህ ቢሆን ኖሮ በርካታ ታላላቅ አርቲስቶቻችንና እውቅ ዜጐቻችን በሼሁ ብሮች በተጥለቀለቁ ነበር። ይልቁኑስ በዙሪያቸው የተሰባሰቡት አርቲስት ተላላኪዎቻቸውና ሎሌዎቻቸው በወንጀል ያደፈ ልባቸውን፣ በዝርፊያ የተጨማለቀ እጃቸውንና፣ ውስጠ ሚስጥራቸውን ስለሚያውቁ በውለታ መልክ ጠፍረው ለመያዝና አንዳንድ የዋህ ዜጐችን ለማምታታት ይመስላል።
ሼሁ በእውነት ለሃገራችን ደራሽ የሆኑ ቅን ሰው ቢሆኑ ኖሮ፤ መላው የኢትዮጵያ ሕዝብ በሃዘን ቅስሙ በተሰበረበት፣ መሪር ሃዘኑ በከፋበት፣ የልጆቹ አንገት በቢላዋ ሲቀላ በአደባባይ ተመልክቶ ባዘነበት በዛ ድቅድቅ ጨለማ፣ ለኢትዮጵያ ህዝብ ሃዘናቸውን በገለፁ ነበር፤ እንደሌላውም ቅን ኢትዮጵያዊ ልጆቻቸው ለታረደባቸው ቤተሰቦች እርዳታ ባደረጉ ነበር። ዛሬ ደግሞ አይናቸውን በጨው አጥበውና የኢትዮያን ህዝብ ንቀው፤ የልጅ ልጃቸው ከምትሆነው ከወጣት ተዋናይት ማህደር አሰፋ ጋር፤ ከኢትዮጵያ ባህልና ወግን ባልተከተለ መልኩ ባደባባይ ባልባለጉ ነበር። ሼሁ በISIS ልጆቻቸው ለተጎዳባቸው ቤተሰቦች ሃዘናቸውን ያልገለፁትና ያለመርዳታቸው፣ ያለሃፍረትም እንዲህ ያስፈነጠዛቸው ምክንያት በሃዘናችን ተደስተው ይሆን!? ወይንስ ሌሎችም እንደሚታሙት ለISIS አጋርነታቸውን እየገለፁ!?~መጠርጠር አይከፋም!።
የኢትዮጵያ ታሪክና ወግን አስጠብቀን ለተተኪ ትውልድ ለማስተላለፍ ወያኔን ማስወገድ አማራጭ የሌለው መፍትሄ ነው።
ኢትዮጵያ ለዘላለም በልጆቿ ተከብራ ትኑር!
እናቸንፋለን!

Saturday, June 13, 2015

ቴድሮስ አድሐኖም በጆሐንስበርግና በፕሪቶሪያ ዙሪያ እንዳይዘዋወሩ ጥብቅ መልእክት እንደደረሳቸው ተነገረ

June 13,2015

በደቡብ አፍሪካ የሚደረገዉን የአፍሪካ ህብረት ስብሰባ ለመካፈል ወደዚያዉ ያመራዉ የወያነኔ የዉጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቴድሮስ አድሐኖም በጆሐንስበርግና በፕሪቶሪያ ዙሪያ እንዳይዘዋወሩ ጥብቅ መልእክት ከወያኔ መረጃ ቢሮ በፕሪቶሪያ ለሚገኘዉ የወያኔ ኢንባሲ መተላለፉን ከዉስጥ የወጣ መረጃ አመለከተ::

ተላላኪዉ ቴድሮስ አድሐኖም በደቡብ አፍሪካ የሚገኙ የወያኔ ደጋፊዎችን ሰብስቦ ሊያነጋግር በሞባይል ስልክ መልክት (text)እያደረገ ሳንድተን ሪክሬሽን ሴንተር ቀጠሮ እያስያዘ መሆኑን የደረሱበት በደቡብ አፍሪካ የሚገኙ ተቃዋሚዎች በንቃት እየተጠባበቁት ሲገኙ ተላላኪዉ ቴድሮስ በማንኛዉም ስፍራዎች ለመዟዟር እንዳይችል ተደርጓል።

በተጨማሪ ኢትዮጵያዊያን በሙሉ ሚኒስተሩን በመቃወም በተገኘበት ስፍራና ቦታ ሁሉ መረጃ ለመስጠት በተጠንቀቅ መቆማቸዉን አሳዉቀዋል። ወያኔና ወያኔይያዊያን በሙሉ በደረሱበት ሁሉ ከመዋረዳቸዉንና ከመሸማቀቃቸዉን በዘለለ መልኩ ህዝብን በመፍራት መደበቃቸዉ በራሱ አንድ ታላቅ ድል ነዉ ሲሉ ከወደ ሳንድተን አንድ ግለሰብ ተናግረዋል፤

መርጋ ደጀኔ እንደዘገበው

የትጥቅ ትግል የሚያካሂዱ የተቃዋሚ ድርጅቶችን ዲሞክራሲያዊ ናቸው ብላችኋል የተባሉ ዜጎች እየታሰሩ ነው

June 13,2015

በአዲስ አበባ ከተማ የሚኖሩ ህዝቦችን የትጥቅ ትግል የሚያካሂዱ የተቃዋሚ ድርጂቶች ዲሞክራሲያዊ ናቸው ብላችኋል በማለት ንፁሃን ዜጎችን እያሰረ መሆኑን ከስፍራው የሚገኙ ምንጮቻችን አስረድተዋል።
በአዲስ አበባ ከተማ ጀሞ በተባለው አካባቢ ግንቦት 7 እና ሌሎችም የትጥቅ ትግል የሚያካሂዱ ድርጂቶች ዲሞክራሲያዊ ናቸው የሚል በራሪ ወረቀት መበተኑን ተከትሎ ለጊዜው ስሙ ያልታወቀ የጀሞ አካባቢ ነዋሪ ግንቦት 22 ቀን 2007 ዓም ይህንን ንግግር አንተም ደግመህዋል ተብሎ የታሰረ ሲሆን በተመሳሳይ ግንቦት 15 ቀን 2007 ዓ/ም ቅዳሜ ምሽት ሁለት አውሮፕላን አብራሪዎች ሸራተን ሆቴል አምሽተው ወደ ቤታቸው ሲሄዱ ምነው የምርጫው ዕለት ቀዘቀዘ ሰው የት ሄደ ብላችሁ ተነጋግራችኋል ተብለው በበርካታ የደህንነትና የፌድራል ፖሊስ ታጣቂዎች ታጅበው ወደ እስርቤት መወሰዳቸውን ምንጮቻችን ከቦታው ገልፀዋል።
ሁለቱ ኢትዮጵያዊያን የትግራይና የአዲስ አበባ ተወላጅ ፓይለቶች ምንም የሰሩት ወንጀል ሳይኖራቸው በጥርጣሬ አይን በመታየት ግንቦት 17 ቀን 2007 ዓ/ም ካሳንቺስ ምድብ ችሎት ቀርበው በተወሰነ ውሳኔ መሰረት ምነው የምርጫው ዕለት ቀዘቀዘ ሰው የት ሄደ ብለሃል የተባለው የትግራይ ክልል ተወላጅ ፓይለት 10ሺህ ብር እንዲከፍል የተወሰነ ሲሆን ሁለተኛው ምንም መልስ ባለመስጠቱ በነፃ ተሰናብቷል።

Thursday, June 11, 2015

ከቴፒ ወጣቶች የምንማራቸው ቁም ነገሮች

June 10, 2015
def-thumbበደቡብ ኢትዮጵያ ሸካ ዞን የሚገኙ የቴፒ ወጣቶች በህወሓት አገዛዝ የሚደርስባቸው በደል አንገሽግሿቸው ራሳቸውን አደራጅተው በአገዛዙ ላይ እርምጃ መውሰድ ከጀመሩ በርካታ ወራት ተቆጥረዋል። እነዚህ ወጣቶች ግንቦት 27 ቀን 2007 ዓ.ም. በአካባቢያቸው የሚገኝን አንድ የፓሊስ ጣቢያ ወረው እስረኞችን ማስፈታታቸው በመላው ኢትዮጵያ እንዲታወቁ ምክንያት ሆኗል፤ የአገዛዙ ሚዲያም ድርጊቱ መፈፀሙ በተዘዋዋሪም ቢሆን አምኗል።
ለፍትህ፣ ለነፃነት፣ ለዲሞክራሲ፣ ለእኩልነት እና ለአገር አንድነት ግድ ያለን ኢትዮጵያዊያን ሁሉ ከቴፒ ወጣቶች የምንማራቸው በርካታ ቁም ነገሮች ያሉ ቢሆንም የሚከተሉት ዋና ዋናዎቹ ናቸው ብለን እናምናለን።
1. “ጥቂቶች ነን፤ ምንም ማድረግ አንችልም” ብለው ተስፋ ቆርጠው በደልን ለመቀበል አልመረጡም፤
2. ዓላማቸው ትልቅና ሀገራዊ ቢሆንም እርጃዎቻቸው አካባቢ ተኮር አድርገዋል፤
3. የሚወስዷቸው እርምጃዎች በአቅማቸው መጠን እንዲሆኑ በማድረግ በራሳቸው ላይ ያለው መተማመን እንዲጎለብት ማድረግ ችለዋል፤
4. እንደሁኔታው በፍጥነት መሰባሰብና መበታተን የሚችል ቀልጣፋስብስብ ማደራደት ችለዋል፤ እና
5. በከፍተኛ ሥነሥርዓት በመታነጽ ከቴፒ ሕዝብ ጋር ያላቸውን ትስስር አጠናክረዋል።
ሁላችንም ከእነዚህ ወጣቶች ልንማር ይገባል። በአምባገነን አገዛዝ ጉያ ውስጥ የሚደራጅ የአመጽ ኃይል የተለያዩ አደረጃጀቶች ሊኖሩት ይችላል። አንዱ አደረጃጀት የቴፒ ወጣቶች በተግባር ያሳዩን ነው – ተንቀሳቃሽ፣ ለግዳጅ ተሰባስቦ በፍጥነት የሚበተን፤ መልሶ ደግሞ የሚሰባሰብ ቀልጣፋ ድርጅት።
በምርጫ 97 በሰላማዊ መንገድ የሰጡትን ድምጽ ይከበርን ያሉ ወገኖታችን በአዲስ አበባ ከተማ በግፍ የተጨፈጨፉበት ሰኔ 1 ቀን 1997 ዓም 10ኛ ዓመት በሀዘን አስታውሰናል። ከዚያ ወዲህ በርካታ ወገኖቻችንን በሰላማዊና ህጋዊ ትግል አጥተናል፤ ብዙዎች ቆስለዋል፤ በሺዎች የሚገመቱ በእስር እየማቀቁ ነው። ሆኖም ግን ያ የትግል መስመር የትም አላደረሰንም። የህወሓት አገዛዝ እንዲያበቃ እና በምትኩም ሕዝብ በነፃነት የመረጠው አስተዳደር እንዲኖር የምንፈልግ ወገኖች ሁሉ ወደግባች የሚያደርሱንን አማራጮችን መፈለግ ግዴታችን ሆኗል።
አርበኞች ግንቦት 7: የአንድነትና የዲሞክራሲ ንቅናቄ “ሁለገብ ትግልን” እንደ ትግል ስትራቴጂ ሲመርጥ በውስጡ ብዙ አማራጭ ስልቶች መኖራቸውን እግንዛቤ በማስገባት ነው። የቴፒ ወጣቶች በተግባር ያሳዩን የተለያዩ የሁለገብ ትግል ስትራቴጂ አካል የሆኑ በርካታ የትግል ስልቶች መኖራቸውን ነው። ቴፔ የተደረገው እንዳለ ሌላ ቦታ ይደረጋል ማለት አይደለም። ከቴፒ የምንማረው ዋናው ቁምነገር በፈጠራ እና በአካባቢ እውቀት በታገዘ ስልት ወያኔ መፋለም ያለብን መሆኑ ነው።
አርበኞች ግንቦት 7 የቴፒ ወጣቶች ላሳዩት ተግባራዊ መነሳሳት አድናቆት እና ለከፈሉት መስዋዕትነት ያለውን ክብር እየገለፀ በሌላው የአገራችን ክፍሎች ያሉ ወጣቶችም ከቴፒ ወንድሞቻቸው ትምህርት እንዲቀስሙ ያበረታታል።
በዚህ አጋጣሚም በየቦታው በራስ አነሳሽነት የሚጀመሩ ተግባራዊ እንቅስቃሴዎች አካባቢ ተኮር ቢሆኑም እንኳን አገራዊ እይታ እንዲኖራቸው፤ ከሌሎች መሰል እንቅስቃሴዎች ጋር እንዲቀናጁና እንዲደጋገፉ ብሎም የሀገራዊ ትግሉ አካል እንዲሆኑ ማድረግ የሚያስፈልግ መሆኑን በዚህ አጋጣሚ ያስገነዝባል፤ ይህ ተግባራዊ እንዲሆንም ይሠራል።
ድል ለኢትዮጵያ ሕዝብ!!!

Wednesday, June 10, 2015

ምርጫ ሲባል፣ መሳይና አስመሳይ (ፕ/ር መስፍን ወልደ ማርያም )

June 10, 2015
ምርጫ ሲባል የነጻነት ዓየር አለ፤ ምርጫ ሲባል ተፎካካሪዎች አሉ፤ ምርጫ ሲባል ተፎካካሪዎች በእኩልነትና በነጻነት የቆሙበት መድረክ አለ፤ ምርጫ ሲባል የራሱን ፍላጎት በትክክል የሚያውቅና ከፍርሃት ነጻ የሆነ መራጭ አለ፤ ምርጫ ሲባል የተፎካካሪዎቹን እኩልነትና ነጻነት፣ የመራጮቹን እኩልነትና ነጻነት የሚያከብሩና የሚያስከብሩ ዳኞች አሉ፤ ምርጫ ሲባል የመራጮቹን ፍላጎት በትክክልና ያለአድልዎ የሚያሳይ ሰነድ የሚያዘጋጁ እግዚአብሔርን የሚፈሩ፣ ሕግን የሚያከብሩ፣ ለሕዝብና ለአገር የሚቆረቆሩ ሰዎች አሉ፤ ምርጫ ሲባል ይኸኛው ከዚህኛው ይሻለኛል ብለው የመወሰን ችሎታ ያላቸው ሰዎች አሉ፤ ምርጫ ሲባል መራጮቹ ተመራጮቹን ማገላበጥ አለ።Prof. Mesfin Woldemariam
ታዲያ እኛ ምርጫ የምንለው ይህንን ሁሉ የያዘ ነው? ከዚህ በላይ ከተዘረዘሩት ውስጥ አንዱም እንኳን ቢጎድል፣ ምርጫ አንለውም፤ ምርጫ-መሳይ ልንለው እንችል ይሆናል፤ አንድ የሁለት ጓደኞች የቆየ ቀልድ ትዝ አለኝ፤ አንዱ ስሙ መሳይ ነው፤ ፊታውራሪ ነው፤ ሌላው ስሙ በፈቃዱ ነው፤ ሀኪም ነው፤ አንድ ቀን በፈቃዱ መሳይን ሲያገኘው በፊታውራሪነቱ ለማሾፍ ፊታውራሪ መሳይ አለ፤ መሳይን ጫን ብሎ፤ መሳይም ሲመልስ በዶክተርነቱ እያሾፈ ዶክተር በፈቃዱ ብሎ ዶክተርን ጫን ብሎ መለሰለት! የኛን ምርጫ-መሳይ ምን ብለን፣ አንዴት ብለን እናሹፍበት? ያውም ማሾፍ ከተፈቀደ! በባህላችን በጣም የተወደደ ምግብ አለ፤ ያንን ምግብ አቅርበው መሣሪያው ሲነፍጉ ሥጋውን ሰጥቶ ቢላዋውን መንሣት ይባላል፤ ንፉግነት ብቻ አይመስለኝም፤ ክፋትም አለበት፤ የደርግና የወያኔ ምርጫ-መሳዮች በአለማወቅና በንፉግነታቸው ይመሳሰላሉ፤ በክፋት ግን አይመሳሰሉም።
ደርግም ሆነ ወያኔ ከሌኒን ለመማር አልቻሉም እንጂ አስመስለዋል፤ ምርጫ-መሳዩንም ያገኙት ከዚያው ነው፤ ሌኒን ጉሮሮን ግጥም አድርጎ በብረት ሰንሰለት አስሮ ነጻ ነህ ይላል! መገንጠል ትችላለህ! ይላል፤ ወያኔም ሲሉ ሰምቶ መገንጠል-መሳይ ሕግ-መሳይ አወጣ! ችግር ነው ጌትነት! ዱሮ ተረት ነበር፤ ዛሬ ግን በእውነት ሲቸግር እያየን ይመስለኛል፤ አንድ ሰው ራሱ ባፈራው ሀብትና በደረሰበት የጌትነት ደረጃ ችግር አይሰማውም፤ ሀብቱ ከየት እንደመጣ፣ እንዴት እንደመጣ፣ ምን ያህል ልፋት እንዳስከተለ መገመት ይቻላል፤ በተዘረፈ ሀብት ጌትነት ሲመጣ ግን ችግርን አዝሎ ነው፤ አንድ ሰው አራት ሚልዮን ብር ወድቆ ቢያገኝ አራት መቶ ካሬ ሜትር መሬት ቢገዛበት አያስደንቅም፤ የገንዘብ አያያዝን ስለማያውቅና በስጋት ስለሚከሳ መሬቱ ላይ መቀመጥ አስተማማኝ መስሎ ይታየዋል፤ ከካስትሮ በፊት የነበረውን የኪዩባ ሁኔታ በትንሹም ቢሆን የሚያውቅ በዛሬው ጊዜ በኢትዮጵያ ካለው ሁኔታ ጋር ተመሳሳይነቱን ለመረዳት አያዳግትም፤ በኪዩባም ሆነ በኢትዮጵያ በተዘረፈ ሀብት ጌትነትን ያስፋፋው አሜሪካ ነው፤ ሕዝብ የሚደኸየውና የሚከብረው በጉልበትና በዝርፊያ ብቻ በሆነበት አገር ጊዜውን ጠብቆ ከሁለት አንዱን አርግዞ ይወልዳል፤ ወይ ዘራፊዎችን ሁሉ ዘርፎ ሙልጭ የሚያወጣቸው ጉልበተኛ ይመጣል፤ ወይ በሕጋዊ መንገድ ከዘራፊዎች እየገፈፈ ሀብትን ለሕዝብ የሚያደላድል ሕጋዊ ሥርዓት ይመሠረታል፤ ሁለቱንም በማስረገዝ ላይ ያሉት በግፍ ሀብታም የሚሆኑት ናቸው።
ሕዝብ የሥልጣን ባለቤት እንደሆነ ለማስመሰል ምርጫ መሳይ አለ፤ ሕዝብ የሀብት ባለቤት እንደሆነ ለማስመሰል ግን ትንሽ ያስቸግራል፤ በኮንዶሚንየም ለማስመሰል ቢሞከርም አልሆነም፤ ለሎሌዎች ሹሞችም አልተዳረሰም! በምርጫ መሳዩ ማሸነፍ ቀላል ነው፤ እንዲያውም መቶ በመቶ ማሸነፍ ይቻላል፤ ችግሩ የሚመጣው ከዚያ በኋላ ነው፤ ደካሞች የፖሊቲካ ቡድኖችንና ደካማውን ሕዝብ ማሸነፍ እንደሚቻል ጉልበተኛው አስመስክሯል፤ ሌላው ቀርቶ ‹‹የኔ›› የሚላቸውን ቡድኖችም አፈር ላይ ሊያስተኛቸው ይችላል፤ እንዲያውም አፈሩ ምቹ ፍራሽ ነው ብለው በደስታ እንዲቀበሉ ሊያደርጋቸው ይችላል፤ አሁን የጉልበተኛው መድረክ እየጠበበ መጣ፤ ችግሩ የሚፈጠረው እዚህ የጠበበው መድረክ ውስጥ ባሉት ጉልበተኞችና ጉልበተኛ መሳዮች ነው፤ በአንድ በኩል በጉልበተኞች መሀከል፣ በሌላ በኩል በጉልበተኛ መሳዮች መሀከል፤ በሌላ በኩል በጉልበተኞችና በጉልበተኛ መሳዮች መሀከል፣ ይህ ትግል ዳካማዎች የፖሊቲካ ቡድኖችን እንደማሸነፍ ቀላል አይደለም፤ በአጥር ላይ እየተንጠለጠሉ የጣሉትን ለመልቀም እየተሻሙ ነው፤ በጉልበተኞቹ መሀከል ክፉ የሥልጣን ችጋር ገብቷል ማለት ነው፤ ጦር መማዘዝ ኪስን እንደሚያራቁት ያውቃሉ፤ ያለሥልጣን ኪስ ሙሉ እንደማይሆንም ያውቃሉ፤ ታዲያ ምን ይሻላል?

Tuesday, June 9, 2015

ገዳይና ሟች – አየር ኃይልና ህውሃት

June 9, 2015
አዲስ (ከሲልቨር ስፕሪንግ)
ለኢትዮጵያ አየር ኃይል ቀናዒነት ስላለኝ በቅርብ እርቀት እከታተላለሁ ። ከአባላቱም ጋር በስደት የቅርብ ወዳጅነት መስርቼ ከልብ ትርታቸው ጋ የእኔን አዛምጄ ፣ በአዘኑበት አዝኜ ፣ ሲደሰቱ ተደስቼ ለማንኛውም ጥሪያቸው በግምባር ቀደምትነት ምላሽ በመስጠት በሁሉም ቦታ ታድሜ እነሆ ዘመናት ተቆጠሩ።Ethiopian air force
እማውቀው – እኔ ከብዙዎቹ አንዱ እንደሆንኩ ነው ። የቀድሞው የኢትዮጵያ አየር ኃይል በብዙሃኑ ኢትዮጵያዊ ልብ ውስጥ በቁጭት አክብሮትና አድናቆትን እንደተጐናፀፈ ከትውልድ ትውልድ እያንፀባረቀ ቢመጣም ፤ የኋላ ኋላ ዕጣ ፋንታው ግን መበተን ፣ መሰደድ ፣ ያለ ፍርድ ለዘመናት መታሰርና ፣ ለሞት ፍርድ ተላልፎ መሰጠት ሆነ ። ይህም እንኳ ሳያግደው ዝናው በጠላቶቹም ጭምር ሳይቀር ከዳር እስከዳር እንደናኘ ዛሬም አለ።
ታድያ ዛሬ የዚህን ታላቅ ወታደራዊ ተቋም ታሪክ በመፅሃፍ ተፅፎ ማየት በህይወት ላሉት ክብር ፣ ለሰፊው ህዝብ ማስታወሻ ፣ ለመጪውም ትውልድ መማሪያ መሆኑ የማንኛውም ቅን ዜጋ ህልም ነው ፤ ለአባላቱና ለቤተሰቦቻቸውም ደግሞ ኩራትና እፎይታ ነው።
ለዚህም ነበር ይህንን ታላቅ አላማ ሰንቀው ለተንቀሳቀሱ የቀድሞው የኢትዮጵያ አየር ኃይል አንጋፋ አባላት በከፍተኛ ሁኔታ ድጋፍ የተሰጠው ። ድጋፍ በገንዘብ ፣ ድጋፍ በማቴሪያል ፣ ድጋፍ በሞራል …. ወዘተ።
የታሪክ መፅሃፉን እውን ለማድረግ ለዘመናት ሲዳክሩ የነበሩት ፣ በአየር ኃይሉ ውስጥ ቀደምትነት ያላቸው የተከበሩ ፣ ስመጥርና ገናና የመሆናቸውን ያክል ፤ አጨራረሱ ላይ ግን በፊት አውራሪነት በኢትዮጵያችን እየተለመደ የመጣው የገዢው ስርዓት ተዋላጆች ዋነኛ ባለቤት እየሆኑ የብዙሃኑን ቀና ግምት ወደ ትዝብት ፣ ሃዘንና ጥርጣሬ የወሰደ አልነበረም ብሎ መደምደም አይቻልም።
ከዚሁ ጋር ተያይዞም የመፅሃፉ ይዘት በምን መልኩ ይቀርብ ይሆን የሚለው ከአገር ቤት እስከ ዲያስፖራው የቀድሞው አባላቱ መካከል የተለያየ ሃሳብ ከየአቅጣጫው ተነስቶ በመግባባትም ፣ ባለመግባባትም እንደተናጠ ነበር መፅሃፉ ከመደብር ሳይሆን በውስጥ አወቆች እዚህ ደጃችን የደረሰው።
ስለዚህ የጥያቄውና የውይይቱ መሰረተ ሃሳብ ለምን የአየር ኃይሉ የታሪክ መፅሃፍ ተፃፈ የሚል አይመስለኝም ። በፍፁም አደለምም ። የተወሰኑ ግለሰቦች ግን ለምን የአየር ኃይል ታሪክ ተፃፈ የሚል ጥያቄ እንደተነሳ አስመስለው ለማቅረብ ሲታገሉ በቅርብ አስተውያቸዋለሁ ። ጥያቄው ለምን መፅሃፉን ወደ ጠላት ጉያ ከተቱት (ምክንያቱም የአየር ኃይልን ቁስልና ጥቃት ለመግለፅ አመቺ ቀጠና ስላልመረጡ) ነው እንጂ ለምን ታሪኩ ተፃፈ አይደለም ብዬም ደጋግሜ አስረድቻቸውም ይህንን ይዘሉታል ። ስለዚህ ሆን ተብሎ የሚሰራ ነገር አለ ማለት ነው።
እንደ ግለሰብ ማንኛውም ሰው ፖለቲካዊም ሆነ ሃይማኖታዊ ወዘተ አመለካከቶች ሊኖሩት ይችላል ። ይህም ሊከበርለትና ሊበረታታም ይገባል ። ሆኖም ግን የዚህ የኢትዮጵያ አየር ኃይል ታሪክ አካሎች የኢትዮጵያ አየር ኃልይ አባላት ናቸው ። ባለቤቱ ደግሞ የኢትዮጵያ ህዝብ ነው ። እንግዲያውስ በዚህ መፅሃፍ ዝግጅት ዙርያ የተለያየ ሃሳብ ቢነሳ ሊደመጥና ከግንዛቤ ውስጥ ገብቶ ትኩረት ተሰጥቶት በሃሳብ ተፋጭቶም ነጥሮ ሊወጣ ይገባዋል ፤ ለመፅሃፉም ግብዓት አስተዋፅዖው ቀላል አይሆንም ፤ የታሪኩንም ሙልዓዊነት ሲያዳብረው ተዓማኒነቱንም ከፍተኛ ያደርገዋል ። ይህንንም ስል እንዲያው መቋጠሪያ በሌለው ውዝግብ ውስጥ ገብቶ መቧቸሩ አስፈላጊ ያለመሆኑን እየተረዳሁ ቢያንስ ግልፀኝነትና ታማኝነት በተሞላበት ሁኔታ በተደራጀ መልኩ (በየአካባቢው) በቡድን ኰፒውን የማየትና ሃሳብ የመለዋወጥ ዕድሉ ሊኖር በተገባ ነበር ። አለፍም ሲል በእድሜም ሆነ በልምድ የተከበሩ የሰራዊቱ አባላት እንደዚህ አይነቱን የግራ ቀኝ የሃሳብ ፍጭት ሃላፊነት ወስደው ማወያየትና ሁሉንም በተቀራረበ ግንዛቤ ሸክፎ በአንድነት እንዲጓዝ ማድረግ ታሪክ የጣለባቸው ትልቅ ሃላፊነት መሆን በተገባው ነበር።
ለመሆኑ ችግሩ ምንድነው ? ለምንስ ወደ አላስፈላጊ ጭቅጭቅ በሚል መሸፈኛ እነዚህ ከስርዓቱ ጋር ወስደው ያጣበቁን ሰዎች የፈለጉትን ለማድረግ በር የሚከፍት አካሄድ ተመረጠ ? ትላልቅ የሚባሉት ሰዎችስ ሃላፊነት በሚሰማው መልኩ መሃል ገብተው ማወያየትና መዳኘት ለምን ወኔ ከዳቸው ? ይህ ሃላፊነት ተወስዶ ቢሆን ኖሮ ቢያንስ ዛሬ ላይ ለተነሳው የክህደት ጥያቄ ባልተጋለጠን ነበር።
አገራችን ኢትዮጵያ በረዥም ዘመን ታሪኳ ውስጥ አሁን እንዳለችበት ጊዜ ችግር ገጥሟት አያውቅም ። ለእናት አገራቸው ደከመን ሰለቸን ሳይሉ በሙያቸው እያገለገሉ ሲዋደቁ የነበሩ ፣ ጊዜው በደረሰበት ቴክኖሎጂ የታነፁ ፣ በአፍሪካ ግምባር ቀደሙን አየር ኃይል የአኩሪ ገደል ባለቤት ያደረጉ ፣ ለኢትዮጵያ አየር መንገድ ፣ ለኢትዮጵያ ሲቪል አቬየሽን ጥንስስና መሰረት የጣሉ ፣ ለተለያዩ ሲቪል ተቋማትና አምራች ድርጅቶች አመራር መፍለቂያ የሆኑ ፣ በጤና ፣ በስፖርት የአገሪቷን ስም በዓለም እንዲናኝ ያደረጉ ወዘተ ታላላቅ ሰዎች ሁሉ ሲዋረዱና እንዲሸማቀቁ ሲደረግ በዓይናችን እንድናይ የተገደድንበት ዘመን ላይ ነን ያለነው።
በኢትዮጵያ የአብዮት ዘመንም ተነሳ ተራመድ ብለው በግንባር ቀደምትነት የህዝብን የለውጥ ፍላጐት በመምራት የህዝብ ዕምባ ጠባቂ በመሆን ያገለገሉ ፤ ረዥሙ የእርስ በርስ ጦርነትም ማብቂያ ይበጅለት ብለው በግንቦት 8፣ 1981 ብርቅዬና ውድ አመራሮቻቸውን የገበሩ ፤ ለእናት አገሩ ዘብ በመቆሙና በማገልገሉ ጀግኖቹ አባላቱ ተዋርደው ፣ ታስረው ፣ ተሰደው ፣ ተገልለውና ተሸማቀው እንዲኖሩ የተደረገበት ። የሞት ፍርድ እንኳ ሳይቀር የተበየነበት ዘመን ነው።
ዛሬም እንኳ ይህቺን ፅሁፍ እየጫጫርኩ ባለሁበት አጋጣሚ የግንቦት 20 ድል እየተከበረ ስለ ጨፍጫፊው የኢትዮጵያ አየር ኃይል ሲያላዝኑ ይሰማል ። ሌላው ቢቀር በአንድ ወቅት አየር ኃይሉን እንዲጐበኙ ለተደረጉት አርቲስቶች እንዳሉት የሞተ ፣ የተማረከ ፣ የተንኰታኰተና የተሽመደመደ አየር ኃይል እንደተረከቡና ዛሬ ግን እነሱ አየር ኃይሉን ከፍተኛ ደረጃ እንዳደረሱ ሲገልፁ መስማት ምንኛ ያማል ? እነዚህ የመፅሃፉ አዘጋጆች እንደዚህ አይነቱ የመንግስት ዘለፋ ሊሞቃቸውም ሆነ ሊበርዳቸውም እንዳልቻለ ማስተዋል ገረሜታን መፍጠሩ አልቀረም።
ታድያ ዛሬ መነሻው በተድበሰበሰ ሁኔታ ተጀቡኖ ፣ በአሳዳጆቹ ዳንኪራ ቤት (ሸራተን) በተሰጠ የችሮታ ድግስ የተጀመረው የመፅሃፍ ዝግጅት ፣ የሌላውን ሃሳብ ባለማዳመጥ በድንገት የምረቃው ዜና አሁንም በአሳዳጆቹ አጋፋሪነት መሰማቱ ከፍተኛ ሃዘንና ድንጋጤ ቢፈጥር ምን ይገርማል ? ክህደትስ ነው ቢባል ምን ያጠራጥራል?
ደግሞስ የመፅሃፉ አወጣጥና አካሄድ አላግባብ በማን አለብኝነት ብሎ መተቸት ከመፅሃፉ ይዘት ጋር ምን ያገናኘዋል ? አዎ ወደ አይቀሬው የመፅሃፉ ይዘት ወደድንም ጠላንም እንገባለን! አወጣጡ ግን የተሽመደመደ ፣ በክህደት የተሞላ ፣ ለአፍራሾቹ በበቂ ሁኔታ ምላሽ ሊሰጥ የማይችል መሆኑን በድፍረት እናገራለሁ ። ወደፊት በመፅሃፉ ባህሪና ይዘት ላይ ብዙ ለማለት እንድችል ከወዲሁ ይህንን ሳልጠቁም ማለፍ ስላልፈለኩ ነው።

Monday, June 8, 2015

Ethiopia: Patriotic Ginbot 7 fighters pictures has gone viral

June 8, 2015
Following the Ethiopian sham election which the Tigrayan People’s Liberation Front (TPLF) claim 100 percent of 442 parliamentary seats, most Ethiopians are talking about the alternative struggle to bring change.
Currently it looks like the Patriotic Ginbot 7 Movement for Unity and Democracy freedom fighters are getting more and more attention.
Below Patriotic Ginbot 7 rebel’s training exercises pictures that has gone viral on social Medias.
Patriotic Ginbot 7 fightersPatriotic Ginbot 7 fighters
Patriotic Ginbot 7 fighters
Patriotic Ginbot 7 fighters
Patriotic Ginbot 7 fighters


በአማራ ክልል የሚገኙት የመንግስት ድርጅቶች በልዩ ሃይል እንዲጠበቁ እያተደረጉ ነው

June 8,2015
bahire
የ2007 ምርጫን የወያኔ መንግስት በሁሉም ክልሎች በከፍተኛ ድምጽ ምርጫውን እነዳሸነፈ ማወጁ ይታወሳል  ይህንንም ተከትሎ በአብዛኛው የሀገሪቱ ክፍሎች ውጥረት የነገሰ  ሲሆን  የምርጫውን የውጤት ማጭበርበር በመቃወም  ከሌላው ክልል በበለጠ በኦሮሚያና፣ በአማራ ክልሎች የህዝቡ ቋጣ በከፍተኛ ሁኔታ ላይ እንደሚገኝ የሚታወቅ ሲሆን፣በዚህም የተነሳ  በአማራ  ክልል የብአዴን/ኢህአዴግ ካድሬዎች በህዝቡ ላይ ያላቸው እምነት እያሽቆለቆለ በመመጣቱ በክልሉ ላይ የሚገኙት የመንግስት ድርጅቶች በልዩ ሃይል እንዲጠበቁ ማድረጋቸውን ተገለፀ::

 ከክልሉ ባገኘነው መረጃ መሰረት ግንቦት 16/2007 ዓ/ም የተካሄደውን የይስሙልና ከምርጫውም በኋላ ወያኔ /ኢህአዴግ መቶ በመቶ እንዳሸነፈ በተለያዩ ሚዲያዎች በተገለፀው ግዜያዊ ውጤት ባለመርካቱ የተነሳ    በአማራ ክልል የሚኖሩ የክልሉ ነዋሪዎች  ድምፃችንን ተሰርቀናል በማለት በተለያየ መንገድ ቁጣቸውን  እየገለፁ ሲሆን ከዚህም የተነሳ  በክልሉ ያሉ የወያኔ ካድሬዎች  ህዝቡ ተቃውሞ ሊያነሳ ይችላል የሚል ትልቅ ስጋት እነደፈጠረባቸውና በፍርሃት ውስጥ እነደሚገኙ ታውቋል ::

 በክልሉ ያለውን የህዝቡን ቋጣ ተከትሉ ለተፈጠረባቸው ስጋት የወያኔ ካድሬዋች እየወሰዱ ያሉት እርምጅ በክልሉ የሚገኙት እንደ ሱር ኮንስትራክሽን፤ ባንኮች፤ ቴሌና የመሳሰሉት ድርጅቶችን ቀደም ሲል በህጋዊ መንገድ ተቀጥረው ሲሰሩ የነበሩ የጥበቃ ሰራተኞችን በማባረር ልዩ ጥበቃ ተብለው በሚታወቁ ታጣቂዎች እንዲጠበቅ እያደረጉ መሆናቸውን ለማወቅ ተችሏል፣ ወያኔዎች ይህንን ማድረጋቸው የበለጠ የህዝቡን ቁጣ እንደሚቀሰቅሰው የአካባቢው ነዋሪዎች እየተናገሩ ይገኛሉ::

ይህ አይነቱ በታጣቂ ሓይሎች ተደርጎ ህዝቡ ዓመፅ እንዳያካሂድ ተብሎ የሚደረግ የተጠናከረ የጥበቃ አካሄድ በአማራ ክልል ብቻ ሳይሆን በመላው ያገራችን አካባቢዎች ውስጥ ለውስጥ እየተሰራበት እንደሆነ።ያገኘነው  መረጃ ያስረዳል::

ሪፖርተር ገዛኸኝ አበበ

Saturday, June 6, 2015

Befeqadu Hailu: An Ethiopian Writer Who Refused to Remain Silent

June 6, 2015
by Nwachukwu Egbunike | Global Voices
Befeqadu Hailu: An Ethiopian Writer
Asmamaw, Befeqadu (middle) and Edom participating in a race organized in Addis Ababa. Photo courtesy of family.
In April 2014, nine bloggers and journalists were arrested in Ethiopia. Several of these men and women had worked with Zone9, a collective blog that covered social and political issues in Ethiopia and promoted human rights and government accountability. And four of them were Global Voices authors. In July 2014, they were charged under the country’s Anti-Terrorism Proclamation. They have been behind bars ever since, their trial postponed time and again.
This marks the third post in our series – “They Have Names” – that seeks to highlight the individual bloggers who are currently in jail. We wish to humanize them, to tell their particular and peculiar stories. This story comes from Nwachukwu Egbunike, a Nigerian poet, writer, and blogger who has worked with Global Voices since 2011.
Befeqadu Hailu is an Ethiopian writer who could not quiet his conscience in the face of brutality and human rights violations in his country. For this, he is currently in behind bars.
His novel, Children of Their Parents won the 2012 Burt Award for African Literature. He also writes poetry. It seemed only natural that his passion found visible expression in blogging, and that he became a co-founder of the Zone9 bloggers collective.
Using the Internet, Befeqadu personified those eternal words of the grandfather of African literature, Chinua Achebe: “an artist, in my understanding of the word, should side with the people against the Emperor that oppresses his or her people.” For doing this, Befequadu was deprived of his freedom.
Befeqadu and eight others have been charged with terrorism and incarcerated since April 2014.  But the real wrongdoers are his jailers: a repressive government that forbids critical dissent. That is indeed the great crime of Befeqadu and his colleagues. They refused to conform to the norm of silence. This trait is obviously innate in any writer, that compulsion not to keep quiet. The poetry in Befequadu’s veins could not be bottled by state intimidation or stifled with the bars in a jail.
Writing from prison, Befeqadu’s strong and unbending will to stand for the truth remains unbroken. In a letter describing his experiences over the first few months of his incarceration, he described repeated interrogations that he underwent in which authorities asked him, “so what do you think is your crime?” He mediated on this question:
“So what do you think is your crime?”
The question is intriguing. It sheds light on our innocence, on our refusal to acknowledge whatever crimes our captors suspect us of committing. Yes, they probed us severely, but each session ended with same question. The investigation was not meant to prove or disprove our offenses. It was meant simply to make us plead guilty.
After two years of writing and working to engage citizens in political debate, we have been apprehended and investigated. Blame is being laid upon us for committing criminal acts, for supposedly being members and “accepting the missions” of [opposition political parties]…
[…]
No matter what, boundaries exist in this country. People who write about Ethiopia’s political reality will face the threat of incarceration as long as they live here.
We believe that everyone who experiences this reality, dreading the consequences of expressing their views, lives in the outer ring of the prison – the nation itself. That is why we call our blog Zone9.
The weight of that question: “so what do you think is your crime?” and the corresponding response shed light on the irony of the jailer (held captive only by fear) and the jailed (who possesses interior freedom). In the words of Wole Soyinka, “books and all forms of writing are terror to those who wish to suppress the truth.”
Befequadu is in jail because he writes.
Weaving stories untold
Befeqadu Hailu is an Ethiopian Writer
Digital drawing of Befeqadu Hailu by Melody Sundberg
Lauding stories unheard 
Shouting for gagged voices
Serving rising voices
From the four compass points
From sun’s rising to its setting
From the Atlantic to the Sahara 
Let a mighty echo arise,#FreeZone9Bloggers!

የህወሓት አምባገነናዊ ስርዓት በመላ አገሪቱ ያሰፈነውን ቅጥያጣ የገበያ ስርዓትና….

June 6, 2015
def-thumb ጭቆና በመቃወም ባለሀብቶችና በሰላማዊ መንገድ ሲታገሉ የቆዩ የተቀናቃኝ ፓርቲዎች አባላት በረሃ እየወረዱ ብረት ማንሳታቸውን ቀጥለዋል፡፡
ሰሞኑን በርካታ ቁጥር ያላቸው ባለሀብቶችና የአንድነት ፓርቲ አባላት በረሃ ወርደው አርበኞች ግንቦት ሰባትን ተቀላቅለዋል፡፡
ህወሓት-ኢህአዴግ የሚያራምደው በጎሰኝነት የተቃኘ የምጣኔ ሀብት ስርዓት አላላውስ ያላቸው ነጋዴዎችና ሰላማዊ ትግል ያበቃለት መሆኑን የተረዱት የአንድነት ፓርቲ አባላት ኢትዮጵያ ውስጥ የስርዓት ለውጥ መጥቶ እውነተኛ ነፃነት እንዲሰፍን ከልብ ከታመነ ብቸኛው መፍትሄ ጠብመንጃ ስለሆነ በአገር ቤት ያሉ ባለሀብቶችና የተቀናቃኝ ፓርቲ አባላት የእነሱን ፈለግ እንዲከተሉ ጠንከር አድርገው አሳስበዋል፡፡
ከሳምንት በፊት የአግአዚ ኮማንዶ ክፍለ ጦር አባላትን ጨምሮ በርካታ የመከላከያ ሰራዊት አባላትና ባለሀብቶች በረሃ ወርደው አርበኞች ግንቦት ሰባትን መቀላቀላቸውን መዘገባችን አይዘነጋም፡፡

Friday, June 5, 2015

በመርካቶ የተቀሰቀሰውን እሳት በቁጥጥር ስር ለማዋል አሁንም ጥረቱ እንደቀጠለ ነው

June 5,2015
ዘጋቢ ገዛኸኝ አበበ
ዛሬ ከቀኑ 9 ሰዓት አካባቢ በአዲስ አበባ መርካቶ በተለምዶ ሸራ ተራ በሚባለው ስፍራ ከባድ የሆነ እሳት ተቀስቅሷል። እሳቱ በሸራ ተራና አብዶ በረንዳ ተብሎ በሚጠረው አካባቢ በአደገኛ ሁኔታ እየተያያዘ ሲሆን የእሳት ቃጠሎው መነሻ ለጊዜው ባይታወቅም  በስፍርው የተቀሰቀሰው እሳት ግን በጣም አስፈሪና ከበድ እንደነበር ለማወቅ ተችሏል ።በአካባቢው የተቀሰቀሰውን እሳት በቁጥጥር ስር ለማዋል  ድረስ ጥረቱ እንደቀጠለ ሲሆን የአሳት ቃጠሎውን ግን  እስከአሁን ድረስ መቆጣጠር እንዳልተቻለ ታውቋል።

 ከሰፍራው  ያገኘነው ዜና እንደሚያስረዳን ከሆነ እሳቱን ለማጥፋት የእሳት አደጋ መኪኖች በስፍራው የነበሩ ሲሆን ነገር ግን  የእሳት አደጋ መኪኖቹ ውሃ ጨርሰው ሲመላለሱ ታይተው ነበር ።

 የአካባቢው ነዋሪና በአካባቢው በንግድ ስራ የተሰማሩት ሰዎች ግን  እሳቱን ለማጥፋት በተቻላቸው  አቅም ሁሉ በመረባረብ ጥረት ያደረጉ ሲሆን የተለያዩ መሳሪያ የታጠቁ ፊደራል ፖሊሶች ግን የእሳት አደጋው በተነሳባቸው ሱቆች ምንም ዓይነት ዝርፊያ እንዳይፈፀም ጥበቃ  በማድረግ በሚል ሰብብ ከተለያዩ የስፍራ በፍጥነት በመምጣት አካባቢውን ወረውታል።

  ህዝቡም በሙሉ አቅሙ እሳቱን ተረባርቡ እንዳያጠፋ በስፍራው የነበሩት የፌዴራል እና የአዲስ አበባ ፖሊሶች ችግር የፈጠሩባቸው ሲሆን እሳቱን ለማጥፋት ሲረባረቡ በነበሩ ወጣቱች ላይም አካባቢውን የወረሩት የወያኔ ፊደራል ፖሊሶች የተለያዩ ወከባ ሲያደርሱባቸው እንደነበር ለማወቅ ተችሏል።

ይህ ዜና  እስከ ተጠናከረበት ጊዜ ድረስ በአካባቢው የሚገኙት የእሳት አደጋ ሰራተኞችም አሁንም እሳቱን ለመቆጣጠር ጥረት በማድረግ ላይ ሲሆኑ። የአዲስ አበባ የእሳትና ድንገተኛ አደጋዎች መከላከልና መቆጣጠር ባለስልጣን በከተማዋ ካሉት ሁሉም ቅርንጫፎች የእሳት ማጥፊያ ተሽከርካሪዎቹን በማሰማራት ቃጠሎውን ለማስቆም ጥረት እያደረገ ሲሆን ህብረተሰቡና የባለ ሱቆች ባለቤትም በእሳት ከተያያዙ ሱቆች ውስጥ ሸቀጦችን ለማዳን ጥረት እያደረጉ ሲሆን ሌላው እሳቱን ላለመቆጣጠር አስቸጋሪ ያደረገው ነገር

በእሳት በተያያዙ ሱቆች ውስጥ የፕላስቲክ ምርቶች የሚገኙ በመሆናቸው እና አከባቢው ተሽከርካሪን እንደልብ የማያንቀሳቅስ በመሆኑ እሳቱን የማጥፋት ዘመቻውን አስቸጋሪ ማድረጉ ተመልክቷል። ሌላው የእሳቱን ቃጠሎ እየተባባሰ  መምጣት አሳሣቢ ያደረገው ጉዳይ በዛው አካባቢ አንድ ትልቅ የዘይት ማምረቻ መኖሩ ሲሆን እሳቱ ወደዛ ከቀጠላ  በአካባቢው ትልቅ ጥፋትና ውድመት ማስከተሉ እንደማይቀር ተሰግቷል።



ሰማያዊ የG-7 መሪዎች በኢህአዴግ ላይ ጫና እንዲያደርጉ አሳሰበ

June 5,2015
በነገረ ኢትዮጵያ ሪፖርተር
ሰማያዊ ፓርቲ ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ ነገ ግንቦት 29/2007 ዓ.ም በሚካሄደው የG-7 ስብሰባ መጋበዛቸውን ተከትሎ የወቅቱ የጉባኤው መሪ ለሆኑት የጀርመን ቻንስለር ለአንጌላ ሜርክል በፃፈው ደብዳቤ መሪዎቹ በኢህአዴግ ላይ ጫና እንዲያደርጉ አሳስቧል፡፡
 
አቶ ኃይለማርያም ደሳለኝ በስብሰባው ላይ መጋበዛቸው ቅር እንዳሰኘው የገለፀው ፓርቲው 24 አመት በስልጣን ላይ የቆየው የጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ፓርቲ አፋኝ ለመሆኑ የ2007 ዓ.ም ጠቅላላ ምርጫን በምሳሌነት ጠቅሷል፡፡ ምርጫው ልምድ ያላቸው የውጭ ታዛቢዎች ያልተገኙበትና የአፍሪካ ህብረት ታዛቢ ቡድንም ‹‹ነፃና ፍትሓዊ›› ነበር ለማለት ያልደፈረበት፣ ሰማያዊን ጨምሮ ሌሎች ተቃዋሚ ፓርቲዎች የተጭበረበረ መሆኑን ማረጋገጣቸውን በደብዳቤው አስታውሷል፡፡
ምርጫው ገዥው ፓርቲ 100% አሸነፍኩ ያለበት፣ ተቃዋሚዎች ላይ ከፍተኛ ጫናና እስር ከዚህም ሲያልፍ ለሞት የተዳረጉበት ነበር ያለው ሰማያዊ ፓርቲ ገለልተኛ ሲቪክ ማህበራት እንዳይታዘቡ መከልከላቸውን ገልጾአል፡፡ ጋዜጠኞችን፣ ጦማሪያንን፣ የሀይማኖት አባቶችንና ፖለቲከኞችን ለማጥቃት በወጣው የፀረ ሽብር ህግ ምክንያት ኢትዮጵያ በፖለቲካ እስረኞች ብዛት ከአፍሪካ ቀዳሚዋ መሆኗን ፓርቲው አስታውሳል፡፡
የጉባኤው አባላት ከኢትዮጵያ ጋር ባላቸው የንግድ ግንኙነትና በሚያበረክቱት እርዳታ ምክንያት በሰብአዊ መብት፣ ዴሞክራሲና ልማት ላይ አዎንታዊ አስተዋጽኦ ማድረግ የሚችሉ ቢሆንም የኃይለማርያም ደሳለኝ ፓርቲ የሚመራው መንግስት ለሰብአዊ መብት፣ ሀሳብን በነፃነት የመግለፅ መብት እየገደበና ተቃዋሚዎች ላይ ከፍተኛ በደል እያደረሰ ይገኛል ብሏል፡፡
ጉባኤው ሰብአዊ መብትና ዴሞክራዊያዊ መብትን ለልማትና የኢኮኖሚ ግንኙነት በቅድመ ሁኔታነት በመውሰድ ጫና ማድረግ ካልቻለ የኢትዮጵያ ዴሞክራሲያዊ ግንባታን እንደሚጎዳም ሰማያዊ ፓርቲ አሳስቧል፡፡ በመሆኑም ጉባኤው የፖለቲካ እስረኞች ያለ ቅድመ ሁኔታ እንዲፈቱ፣ ኢህአዴግ ተቃዋሚዎችን ማሰርና እንቅስቃሴያቸውን ከመገደብ እንዲቆጠብ እና አፋኝ አዋጆች ላይ ማሻሻያዎች እንዲደረግባቸው በኢህአዴግ መንግስት ላይ ጫና እንዲያደርግና ተገቢውን እርምጃ እንዲወስድ አሳስቧል፡፡

Tuesday, June 2, 2015

የመንግስትና የፖሊስን መልካም ስም አጥፍተዋል የተባሉ ወጣቶች ተፈረደባቸው

June 2,2015
 ኢሳት ዜና :-አይ ኤስ የተባለው አሸባሪ ቡድን በኢትዮጵያውያን ላይ የወሰደውን ዘግናኝ እርምጃ ለማውገዝ በተጠራ ሰልፍ ላይ የመንግስትንና የፖሊስን ስም አጥፍተዋል የተባሉ ወጣቶች በእስርና በገንዘብ ተቀጥተዋል።

አስማማው ወልዴ፣ የማነ ወርቅነህ፣ ስንታየሁ ታሪኩ፣ ያሲን ቃሲምና ይግረማቸው አበበ ሚያዚያ 14 ቀን 2007 ዓም ጠ/.ሚ ሃይለማርያም ደሳለኝ ንግግር በሚያደርጉበት ወቅት ድምጻቸውን ከፍ አድርገው ጠ/ሚኒስትሩን መሳደባቸውን በክሱ ላይ ተገልጿል።

አስማማው ወልዴና የማነ ወርቅነህ በመስቀል አደባባይ አድርገው ወደ ቤተመንግስት ሲያልፉ የመንግስትን ስም የሚያጠፉ ቃሎችን በመጠቀም መሳደባቸውን ክሱ በተጨማሪ ያስረዳል።
ፍርድ ቤቱ ወጣቶቹ መንግስትን መሳደባቸውን ማረጋገጡን በመግለጽ፣ ስንታየሁ ታሪኩ፣ ያሲን ቃሲምና ይግረማቸው አበበ በ4 ዓመት ጽኑ እስራት ፣ አስማማው ወልዴና የማነህ ወርቅነህ ደግሞ 500 ብር እንዲቀጡ ውሳኔ አስተላልፏል።

በተመሳሳይ ዜናም ናትናኤል ያለምዘውድ በእለቱ ሁከትና ብጥብጥ ፈጥሯል በሚል በ 3 ዓመት ከ3 ወር እስር እንዲቀጣ ፍርድ ቤት ወስኖበታል። ተመሳሳይ ክስ የተመሰረተባቸው ማቲያስ መኩሪያ፣ ብሌን መስፍን፣ ተዋቸው ዳምጤና መሳይ የተባለ ሌላ ወጣት መከላከያ ምስክር ለማቅረብ ለሰኔ 4 መቀጠራቸውን ነገረ ኢትዮጵያ ዘግቧል። እነ ማቲያስ ‹‹ሰልፉ ላይ ሀሰተኛ ወሬ በማውራት፣ ጠቅላይ ሚኒስትሩ እየተናገሩ በነበረበት ወቅት ወደ ፖሊስ ድንጋይ በመወርወር፣ ህዝቡን አትነሳም ወይ በማለት” ለመቀስቀስ ሞክረዋል የሚል ክስ ቀርቦባቸዋል።

በተመሳሳይ ‹‹ጠቅላይ ሚኒስትሩ እየተናገሩ በነበረበት ወቅት ወደ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ድንጋይ በመወርወር ሰልፉን አውካችኋል›› የተባሉ ሌሎች አምስት ወጣቶች ለሰኔ 4 የመከላከያ ምስክር እንዲያቀርቡ መቀጠራቸውን ጋዜጣው አክሎ ዘግቧል። አይ ኤስን ድርጊት ለማውገዝ የወጡ የአዲስ አበባ ወጣቶች በኢህአዴግ መንግስት ላይ ተቃውሞአቸውን ሲያሰሙ እንደነበር ይታወቃል። በኢትዮጵያ የመንግስትን ስም ማጥፋትና መንግስትን መሳደብ በህግ ያስጠይቃል።

Ethiopia: TPLF’s Deformed Democracy

June 2, 2015

TPLF’s Deformed Democracy: Competing with Themselves and Winning

by Alem Mamo
Ethiopian election 2015: EPRDF election campaign
“If you only have a hammer, you tend to see every problem as a nail.” — Abraham Maslow When you only have a gun in your tool box, you tend to see everyone and everything as a threat to your very existence. The May 24, 2015, “election” was a giant step backward for the development of electoral democracy in Ethiopia. The election drama concocted by the TPLF is nothing more than a fraudulent and futile exercise to legitimize the illegitimate. It was an endeavor marred by gross violations of citizens’ rights and doesn’t even stand the scrutiny of bare minimum benchmark of electoral process. By its very nature, the TPLF stands in stark contradiction with the basic tenants of democracy, which include freedom of assembly, freedom of expression, and respect for the rule of law. How can one expect the political space to be open and fair under such circumstances? Throughout its existence, the TPLF has broken all the sacred tenants of democracy and freedom. Exclusive, extremely violent, and relentlessly committed to dividing and polarizing the public, it has neither the aspiration nor the principled interest to foster democracy in Ethiopia.
The TPLF’s election drama is in the same league with North Korea’s “election” fiasco: one party rule, one candidate, an electoral body created and run by loyal party cadres. When one combines all of these elements, the result is a twisted and deformed version of democracy.
Naturally, authoritarian regimes are no friends of democracy. In fact, they loathe and fear it. Guaranteeing citizens the right to choose their government in a free and fair political competition is against their political agenda and vision. Most importantly, ethnic political parties, like the TPLF, see the emergence of inclusive democracy as an existential threat to the very agenda they promote, which is polarization and division. Their insular and exclusive political consciousness lacks both the intellectual and emotional knowledge to critically understand the nature of broad-based, inclusive democracy, let alone to implement it. In their deformed political world, they develop a narrative that only satisfies their own minimum understanding of freedom and democracy.
Electoral democracy in its actual form is rooted in a competition whereby all competing parties have a level playing field. They have unrestricted and equal access to inform the public about their platform and vision with no harassment or intimidation from anyone. Such transparent political space guarantees, ultimately, that it’s the electorate that decides who should govern. Under the TPLF’s “election”, however, this fundamental principle is non-existent. The TPLF, like many other guerrilla groups who came to power through the barrel of a gun, see their battlefield victory as a permanent and transferable asset that applies to every form of competition, be it political or economic. Admitting defeat in a peaceful and non-violent political competition is considered a denigrating loss to the distant past military victory. The only lens for accessing and evaluating all completion is a through the binary lens of military loss and defeat. It is for this primary reason (mind set) that the TPLF refused to accept the result of the 2005 election, when it was widely defeated. In the end, it declared a state of emergency and deployed a deadly force, killing hundreds and arresting tens of thousands of citizens.
This mindset is clearly demonstrated in the re-enactment of past military victory during the recent election campaign (as reported by Ethiomedia). This enactment has multiple purposes and implicit and explicit messages. First, it is to communicate/remind the public that they are not willing to relinquish power through the electoral process. “Anyone who is thinking otherwise must think again.” Second, for the TPLF and the likes, there is no difference between military victory and electoral victory. The first reinforces the latter. Political psychoanalysts call it “time collapse”: the idea of reactivating and projecting past events into the present such as battlefield or war. In these circumstances the primary objective is not necessarily for the purpose of memorializing or remembrance. Instead the underlying motivation is to blur the time line between the present and the past and to reinstate the past anger and hate against some groups. The other reason for reactivating the past is to play the role of ‘victim’ and ‘hero’ characters. In the reactivation both the ‘victim’ and the hero appear simultaneously. Each side however is exploited for different purposes, the ‘victim’ is played to garner sympathy and support while the ‘hero’ is played to project strength and power. The third objective is to hypnotize the public through the blurred lens of the past and the present so that their woe’s and injustice suffered under TPLF appear in the past.
To embrace electoral democracy, a significant shift in consciousness is required. First and foremost the ability and willingness to play by the rules is a prerequisite. One cannot be a neighborhood bully and embrace a free and fair electoral completion. Accepting a defeat in a peaceful and non-violent arena is the highest form of political maturity and growth. At this stage TPLF doesn’t have either of those qualities. TPLF has grown vertically and horizontally, but it spectacularly failed to grow-up.
The writer can be reached at: alem6711@gmail.com

Monday, June 1, 2015

ከአርበኞች ግንቦት7 ጋር አብራችሁዋል በሚል የተያዙት ክስ ተመሰረተባቸው

June 1,2015
ኢሳት ዜና :-በሰሜን ጎንደር ዞን ማክሰኝት ከተማ ነዋሪ መሆናቸው የተነገረው አቶ ዘመነ ምህረቱ እና ሌሎች የመከላከያ ሰራዊት አባላት የሽብርተኝነት ክስ እንደተመሰረታባቸው ሪፖርተር ዘግቧል። አቶ ዘመነ የመኢአድ ምክትል ፕሬዚዳንት መሆናቸው በክሱ የተመለከተ መሆኑን የዘገበው ጋዜጣው፣ መስከረም 18፣ 2007 ዓም በጎንደር በሚገኘው የመኢአድ ጽ/ቤት ውስጥ አባላትን በመሰብሰብ ” የወያኔ መንግስት መውደቂያው ደርሷል። አንድ የቶር አውሮፕላን፣ 12 የጦር ጄኔራሎች ከድተው ወደ ኤርትራ ገብተዋል። ኢህአዴግ በጦር ካልሆነ በሰላማዊ መንገድ ስልጣን አይለቅም። የህዝብ እምቢተኝነት በመፍጠር የወያኔን መንግስት መጣል አለብን፣ በ2007 ዓ.ም. የሚካሄደው አገራዊ ምርጫ በሰላማዊ መንገድ አይካሄድም፡፡ ወደ ምርጫው አንገባም፡፡ ሌላ አማራጭ መጠቀም አለብን…›› ” የሚል ክስ እንደተሰመረተባቸው ጋዜጣው ዘግቧል።

በዚሁ መዝገብ በአዲስ አበባ ነዋሪ የሆኑት አቶ ጌትነት ደርሶ ተመሳሳይ ክስ የተመሰረተባቸው ሲሆን፣ ወደ ኤርትራ ተሻግረው ከግንቦት7 ከፍተኛ አመራር ከሆኑት ዶ/ር ክፈተው አሰፋ ጋር በመገናኘት ፖለቲካዊና ወታደራዊ ስልጠና ወስደዋል ተብሎአል። በዚሁ መዝገብ ተከሰው የቀረቡት ሌላው የአዲስ አበባ ነዋሪ አቶ መለሰ መንገሻ ሲሆኑ ፣ እርሳቸውም የአርበኞች ግንባር አባል ነበሩ ተብሎአል። ተከሳሹ ሰው በመመልመል ስራ ላይ መሳተፉንና በመንግስት ባለስልጣናትላይ ጠቃት ለመፈጸም ሲያጠና ነበር የሚል ክስ እንደተመሰረተበት ጋዜጣው ዘግቧል። የአየር ኃይል ባልደረባ የሆነው ምክትል መቶ አለቃ አንተነህ ታደሰ ዘውዴ ተመሳሳይ ክስ ተመስርቶበታል።


መኮንንኑ ታኅሳስ 24 ቀን 2007 ዓ.ም. ከደብረ ዘይት አየር ኃይል በመነሳት ወደ ኤርትራ ጉዞ እያደረጉ መንገድ ከሚያሳያቸው ሌላ ሰው ጋር ታኅሳስ 26 ቀን 2007 ዓ.ም. ወሮታ ከተማ ላይ መያዛቸው በክሱ ተመልክቷል፡፡ በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል አሶሳ ዞን ቶንጎ ወረዳ ሻንቦላ ከተማ ሻንቦላ ቀበሌ ገበሬ ማኅበር ውስጥ ነዋሪ ናቸው የተባሉት ሼክ መሐመድ አብዱል ቃድር የሚባሉ ተጠርጣሪ የእስልምና ሃይማኖትን እንደ ሽፋን በመጠቀም፣ በኃይል እስላማዊ መንግሥት ለማቋቋም ሲንቀሳቀሱ ነበር በሚል ክስ ተመስርቶባቸዋል።


ከአርበኞች ግንቦት7 ጋር በተያያዘ የሚታሰሩ የመከላከያ ሰራዊት አባላት ፣ የተቃዋሚ ፓርቲ አባላትና ወጣቶች ቁጥር ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ ነው። በቅርቡ 4 የአየር ሃይል ባልደረቦችና የእግረኛ ሰራዊት አባላት ተመሳሳይ ክስ ተመስርቶባቸዋል። የመኢኢድ፣ የሰማያዊ እና የቀድሞው አንድነት ፓርቲ አንዳንድ አባላት በተመሳሳይ ወንጀል ተከሰው በማእከላዊና በቃሊቲ እስር ቤቶች ይገኛሉ።


ከአርበኞች ግንቦት 7 ዜና ሳንወጣ በኒዉዚላንድ ኦክላንድ ትላንት ለ አርበኞች ግንቦት 7 የአንድነትና ዲሞክራሲ ንቅናቄ የገንዘብ ማሰባሰብ በተደረገዉ ዝግጅት በተሳካ ዉጤት መጠናቀቁን አንዱአለም ሃይለማርያም ከኦክላንድ ዘግቧል። የአርበኞች ግንቦት 7 የአንድነትና ዲሞክራሲ የዉጭ ጉዳይ ዘርፍ ተጠሪ የሆኑት አቶ አበበ ቦጋለ በዝግጅቱ ላይ በመገኘት ድርጅቱ በአሁኑ ሰዓት የደረሰበትን እና በማከናወን ላይ ያለዉን ስራ አብራርተዋል።


አቶ አበበ የአርበኞች ግንቦት 7 በኤርትራ በኩል ስለሚያደርገዉ እንቅስቃሴና በተቃዋሚ ሃይሎች በኩል ከተቻለ ተዋሕዶ አለበለዚያም በጥምረት ለመስራት የሚያደርገዉን እንቅስቃሴ በሰፊዉ ገልፀዋል። በአሁኑ ጊዜ ሃላፊነት የጎደለዉ የሕዉሐት መራሹ መንግስት ምርጫዉን አስመልክቶ በሕዝብ ላይ እና በተቃዋሚ ፓርቲዎች ላይ እየሰራ ያለዉን ቅጥ ያጣ ግፍ የዘረዘሩት አቶ አበበ፣ አሁን ጊዜዉ ብሶታችንን ብቻ የምናወራበት ባለመሆኑ በምንፈልገዉ መንገድ ሁሉ በመደራጀት አገር አድን ጥሪዉን ተቀብለን ለአገራችን ኢትዮጵያና ሕዝቧ ልንደርስላት ይገባል ብለዋል።
በዝግጅቱ ከ20 ሺ ያላነሰ ዶላር መሰባሰቡንም በዘገባው ተመልክቷል።

"ባለፈው ሰረቁ ነው ሚባለው ያሁኑ ግን ዘረፋ ነው" ዶ/ር መረራ

June1,2015
ዋናዎቹ ተቃዋሚዎች  የምርጫ ውጤቱን አንቀበለውም አሉ
* “በየ5 ዓመቱ ምርጫ እያሉ ህዝብን ከማሰቃየት፣ እንደነ ሰሜን ኮርያ እና ቻይና የአንድ ፓርቲ አገዛዝ ነው ብሎ ማወጁ ይመረጣል”
* “ኢህአዴግ ያሸነፈው ወደ ዘረፋ ስለገባ ነው እንጂ ተቃዋሚ ስለተዳከመ አይደለም”
* ዋናዎቹ ተቃዋሚዎች የምርጫ ውጤቱን አንቀበለውም አሉ
* ምርጫ ቦርድ የተቃዋሚዎች ውንጀላ መሰረተቢስ ነው ብሏል
ባለፈው እሁድ በተከናወነው 5ኛው አገር አቀፍ ምርጫ የተወዳደሩ ዋና ዋናዎቹ ተቃዋሚ ፓርቲዎች፣የምርጫውን ፍትሃዊነት ጥያቄ ውስጥ የሚከቱ ግድፈቶችና የህግ ጥሰቶች መፈጸማቸውን ጠቅሰው የምርጫውን ውጤት እንደማይቀበሉ አስታወቁ፡፡ የኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድ በ442 የምርጫ ክልሎች ኢህአዴግ ሙሉ በሙሉ እንዳሸነፈ መግለጹን ተክትሎ  መድረክ፣ ሰማያዊ፣ ኢዴፓና መኢአድ የምርጫውን ውጤት አንቀበለውም ብለዋል፡፡
ገዢው ፓርቲ ኢህአዴግን ተከትሎ ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው እጩዎች ለውድድር ያቀረበው የኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊ አንድነት መድረክ፣ምርጫውን አስመልክቶ ባለፈው ረቡዕ በሰጠው መግለጫ፤ የምርጫውን ፍትሃዊነት ጥያቄ ውስጥ የሚከቱ ግድፈቶችና የህግ ጥሰቶች በመፈጸማቸው የምርጫውን ውጤት ሙሉ ለሙሉ እንደማይቀበለው ጠቁሟል፡፡
በቅስቀሳ ወቅት በአባላትና ደጋፊዎች ላይ ወከባ መፈፀሙንና በምርጫው ዕለት ታዛቢዎች ከምርጫ ጣቢያዎች መባረራቸውን የጠቀሰው መድረክ፤ ጉድለቶቹንና ግድፈቶቹን ዘርዝሮ ለብሄራዊ ምርጫ ቦርድ በደብዳቤ ማመልከቱንና ምላሹን እየተጠባበቀ እንደሚገኝ አስታውቋል፡፡
ባለፈው ረቡዕ የኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድ 442 የምርጫ ክልሎችን ውጤት ያስታወቀ ሲሆን ኢህአዴግ ሁሉም ላይ ማሸነፉን ጠቁሞ፣ የተቃዋሚዎች ውንጀላ ሙሉ በሙሉ መሰረተ-ቢስ አሉባልታ ነው ሲል አጣጥሎታል፡፡
የመድረክ ምክትል ሊቀመንበር ዶ/ር መረራ ጉዲና በበኩላቸው፤ “የዘንድሮ ምርጫ ውጤት ከ2002 ምርጫ የባሰ የሃገሪቱን ዲሞክራሲ ያጨለመ ነው” ብለዋል፡፡ “ባለፈው ምርጫ ቢያንስ ሰረቁ ነው የሚባለው፤ አሁን ግን ዘረፋ ነው ያካሄዱት” ያሉት ዶ/ር መረራ፤ ኢህአዴጐች በሪከርድነት የያዙትን 99.6 በመቶ ውጤት ወደ መቶ ለማሳደግ አስበው ያደረጉት ይመስለኛል ሲሉ አስተያየታቸውን ሰጥተዋል፡፡ “ኢህአዴግ ያሸነፈው ወደ ዘረፋ ስለገባ ነው እንጂ ተቃዋሚ ስለተዳከመ አይደለም” ያሉት የመድረክ አመራር፤ “ምርጫ በዚህ ሀገር ላይ በትክክል የማይካሄድ ከሆነ በየ5 ዓመቱ ምርጫ እያሉ ህዝብን ከማሰቃየት፣ እንደነ ሰሜን ኮርያ እና ቻይና የአንድ ፓርቲ አገዛዝ ነው ብሎ ማወጁ ይመረጣል” ብለዋል፡፡ ገዢው ፓርቲ የምርጫ ውጤቱን ተመልክቶ “ስልጣን ወይም ሞት” የሚለውን አመለካከቱን መፈተሽ እንደሚገባው ጠቁመውም መንገዱ ብዙ ርቀት አያስኬድም ብለዋል፡፡ “ኢህአዴጎች በዚህ አካሄዳቸው ከቀጠሉ ማንንም የማትጠቅም ኢትዮጵያን ትተው እንዳይሄዱ ደግመው ደጋግመው ማሰብ አለባቸው” ሲሉ አሳስበዋል – ዶ/ር መረራ፡፡ “ህዝቡ ሰላማዊና ህጋዊ ትግሉን መቀጠል አለበት” ያሉት የፓርቲው አመራር፤ “ምርጫው ተጭበረበረ ብለን እጃችንን አጣጥፈን አንተኛም፤ ህዝቡ ከኛ ጋር ስለሆነ ትግላችንን እንቀጥላለን” ብለዋል፡፡
በምርጫው ከኢህአዴግ ቀጥሎ የተሻለ ድምፅ ያገኘው ሠማያዊ ፓርቲ ትናንት በሰጠው መግለጫ፤ ምርጫው ከዚህ ቀደም በኢትዮጵያ ከተካሄዱት ምርጫዎች ጋር እንኳ ሊወዳደር የማይችል እጅግ ኢ-ፍትሃዊ፣ ወገንተኛና ተአማኒነት የሌለው በመሆኑ የምርጫውን ሂደትም ሆነ ውጤት አልቀበለውም ብሏል፡፡
“ነፃነት በሌለባት ኢትዮጵያ ህዝባዊ አስተዳደር መትከል ዘበት ነው” ያለው ፓርቲው፤ “በኃይል በተቀማ ድምፅ የሚመሰረት መንግስትም በህዝብ ተቀባይነት የለውም” ብሏል፡፡ በኢትዮጵያ የሰብአዊና ዲሞክራሲያዊ መብቶች እስከሚከበሩ ድረስ የነፃነት ትግሉ በተጠናከረ መልኩ እንደሚቀጥልም ሰማያዊ  አስታውቋል፡፡
በዘንድሮ ምርጫ የተሳተፈው ምርጫውን ሊያስፈፅሙ የሚችሉ ገለልተኛና ብቃት ያላቸው ተቋማት እንደሌሉ እያስገነዘበ መሆኑን የጠቆመው ፓርቲው፤ በምርጫው ምክንያት የተቃዋሚ ተወዳዳሪዎች፣ ታዛቢዎችና አባላት በገዥው ፓርቲ ካድሬዎች አፈናና እንግልት ደርሶባቸዋል ብሏል፡፡ “በህገ ወጥ አሰራሮች ታጅቦ የተከናወነ” ሲል የገለጸው የዘንድሮ ምርጫ፤ በምንም መመዘኛ ነፃ፣ ፍትሃዊና ተአማኒ ሂደት ያልታየበት በመሆኑ ሂደቱንም ውጤቱንም አልቀበለውም ብሏል ሰማያዊ ፓርቲ፡፡
ከኢህአዴግና መድረክ ቀጥሎ በርካታ እጩዎችን ለምርጫው ያቀረበው የኢትዮጵያውያን ዲሞክራሲያዊ ፓርቲ (ኢዴፓ) ፕሬዚዳንት ዶ/ር ጫኔ ከበደ በበኩላቸው፤ በቅድመ ምርጫው ወቅት ኢዴፓ በሚዲያ የሚያስተላልፋቸው መልእክቶች ሳንሱር እየተደረጉበት መሆኑን በተደጋጋሚ መግለጻቸውን አስታውሰው፣ በምርጫው ላይ ችግር መታየት የጀመረው በሂደቱ ላይ እንደነበር ተናግረዋል፡፡ በሂደቱ ወከባዎች በዝተውብን ነበር ያሉት ዶ/ር ጫኔ፤ በነዚህ ችግሮች ውስጥ ሆኖ ፓርቲያቸው በሂደቱ መሳተፍ መቀጠሉን ጠቁመው ሂደቱ ከህግ አፈፃፀም አንፃር ዲሞክራሲያዊ ነበር ማለት አይቻልም ብለዋል፡፡
የኢህአዴግ ፅ/ቤት የህዝብና ኮሚኒኬሽን ኃላፊው አቶ ደስታ ተስፋሁ በሰጡት አስተያየት፤ “ሂደቱ ጥሩ ነው ብለው ወደ ምርጫው ከገቡ በኋላ ውጤት አይቶ ሂደቱ ትክክል አልነበረም ማለት ተቀባይነት የለውም” ሲሉ የኢዴፓን ሃሳብ ተቃውመዋል፡፡ አንዳንድ ፓርቲዎች በሂደቱ አምነው ከገቡ በኋላ ህዝብ እንዳልመረጣቸው ሲያውቁ ምርጫው ተቀባይነት የለውም ማለታቸው እኛ ካላሸነፍን ከሚል አባዜ የሚመነጭ ነው ያሉት  አቶ ደስታ፤ በምርጫው ህዝቡ መብቱን በትክክል ተግባራዊ ስለማድረጉ የአፍሪካ ህብረትን ጨምሮ ሌሎች ታዛቢዎች ያረጋገጡት በመሆኑ የምርጫውን ውጤት አልቀበልም ማለት ለህዝቡ ውሳኔ ያለመገዛት ፀረ ዲሞክራሲያዊ አካሄድ ነው ሲሉ ተችተዋል፡፡ “ፓርቲዎች ህዝብ ለምን አልመረጠኝም ብለው ራሳቸውን መገምገም እንጂ ድክመታቸውን ወደ ሌላ አቅጣጫ ማዞር የለባቸውም” ብለዋል አቶ ደስታ፡፡
ከምርጫው በፊት የገዢው ፓርቲ አባላት ህግ በመጣስ ብዙ አፈናዎችና ወከባዎች ሲፈጽሙ ነበር ያሉት የኢዴፓ ፕሬዚዳንት፤ በምርጫው እለት የፓርቲያቸው ታዛቢዎች ከምርጫ ጣቢያዎች መባረራቸውን ጠቁመው፣ “ታዛቢዎች በሌሉበት የተካሄደው ምርጫ ተአማኒ ነው ብለን አናምንም” ብለዋል፡፡ “ምርጫው ሚስጢራዊ በሆነ ሁኔታ አይደለም የተከናወነው” የሚሉት ፕሬዚዳንቱ፤ “መራጮች እየተገደዱ ሲመርጡ ታዝበናል፣ አሁንም ድረስ ታዛቢዎቻችን ለምን የተቃዋሚ ፓርቲ ታዛቢ ሆናችሁ በሚል እየተዋከቡብን ነው” ሲሉ ቅሬታቸውን ገልጸዋል፡፡
ቅድመ ምርጫውም ሆነ የምርጫው እለት እንዲሁም ውጤት አገላለፁ የምርጫ ደንቦችንና ህጎችን ሙሉ በሙሉ የጣሰ ነው ያሉት ዶ/ር ጫኔ፤ ምርጫ ቦርድ ከአደረጃጀት አኳያ ራሱን ሊፈትሽ የሚያስገድደው ሂደት ተስተውሏል ብለዋል፡፡ የምርጫ ውጤቱ አገላለፅ ህዝቡ ትክክለኛ መረጃ እንዳያገኝ የሚያደርግ መሆኑን የጠቆሙት ፕሬዚዳንቱ፤ ውጤቱን ሙሉ ለሙሉ ለምን መግለፅ እንዳልተቻለ ጠይቀዋል፡፡
“መንግስት ለመመስረት የሚያስችል ድምፅ ለማግኘት አስቸጋሪ የነበረ ቢሆንም የተወሰነ ወንበር በፓርላማ እንደምናገኘን  ጠብቀን ነበር፤ነገር ግን ምርጫው አሳታፊ ባለመሆኑ አልተሳካም” ብለዋል፡፡ ፓርቲያቸው የሚጠብቀው ዓይነት ምርጫ እንዳልተደረገ ጠቁመውም አሳታፊ ባልሆነ ሂደት ሰላማዊ ትግሉን የትም ማድረስ እንደማይቻል ገልፀዋል፡፡
ኢዴፓ ስትራቴጂውን እንደገና በመቀየር ለተሻለ ትግል እንደሚዘጋጅ በመጠቆምም ተመሳሳይ ርዕዮተ ዓለም ከሚከተሉ ተቃዋሚ ፓርቲዎች ጋር ግንባር ፈጥሮ ለመንቀሳቀስ ማቀዱን ተናግረዋል፡፡ ነገር ግን አሁንም ቢሆን ፓርቲው በምክንያታዊነት መንቀሳቀሱን ይቀጥላል ብለዋል፡፡
ፓርቲያቸው ከገዢው ፓርቲ ጋር ከፓርቲዎች የጋራ ም/ቤት ባለፈ በተለየ ሁኔታ መነጋገር እንደሚፈልግም ዶ/ር ጫኔ አስታውቀዋል፡፡ ሌላው የምርጫ ተፎካካሪ የመላ ኢትዮጵያውያን አንድነት ድርጅት (መኢአድ) ፕሬዚዳንት አቶ አበባው መሃሪ እንዲሁ፤ የምርጫውን ውጤት ለመቀበል እንደሚቸገሩ ተናግረዋል፡፡ “የተሰራው ስራ ለሀገር የሚበጅ አይመስለኝም” ያሉት ፕሬዚዳንቱ፤ “ምርጫው ትክክለኛ አይደለም፤ አንቀበልም” ብለዋል፡፡ በሃገሪቱ ትክክለኛ ዲሞክራሲ ለማምጣት ጥረት የሚያደርጉ አካላትን ተስፋ የሚያስቆርጥ የምርጫ ውጤት መሆኑን የጠቆሙት አቶ አበባው፤ በሰላማዊ ትግል ለውጥ ማምጣት የማይቻል ከሆነ የፓርቲዎች መኖር ጥቅም የለውም ብለዋል፡፡ ምርጫ የህዝብ ፍላጎት በትክክል የማይገለፅበት ከሆነ የትግሉ ጉዳይ አጠያያቂ ይሆናል ሲሉም አቶ አበባው አክለዋል፡፡
የምርጫ ውጤቱን ረቡዕ ማታ መስማታቸውን የተናገሩት የአንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትህ ፕሬዚዳንት አቶ ትዕግስቱ አወሉ፤ ስለ ምርጫው መረጃዎች እያሰባሰቡ እንደሆነና አቋማቸውን ለመግለጽ የፓርቲው ስራ አስፈፃሚ መወያየት ስላለበት ምላሽ ለመስጠት እንደማይችሉ ተናግረዋል፡፡ የኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊ ኃይሎች ግንባር (ኢፌድሃግ) በበኩሉ፤ ህዝብ ለመረጠው አካል እውቅና እንደሚሰጥ ጠቁሞ፣ ለቀጣይ ምርጫ  ድክመትና ጥንካሬውን ገምግሞ ዝግጅት እንደሚያደርግ አስታውቋል፡፡
የኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ባለፈው ረቡዕ 442 የምርጫ ክልሎችን ውጤት ይፋ ያደረገ ሲሆን በሁሉም ክልሎች ገዥው ፓርቲ ኢህአዴግና አጋሮቹ ማሸነፋቸውን ገልጧል፡፡
ምርጫው በታሰበለት የጊዜ ሰሌዳ ያለምንም ችግር አሳታፊ፣ ፉክክር የታየበትና ዲሞክራሲያዊ ሆኖ ተጠናቋል ያሉት የቦርዱ አመራሮች፤ ከምርጫው ጋር የተገናኙ የተቃዋሚ ፓርቲዎች ቅሬታዎችን መሰረተቢስ ናቸው በማለት ውድቅ አድርገዋቸዋል፡፡ “በምርጫው እለት ታዛቢዎችን ተባረውብናል፣ ኮሮጆዎች ሳይፈተሹ ድምፅ ተሰጥቷል፣ ኮሮጆዎች ተቀይረዋል፣ ምርጫው ተጭበርብሯል – የሚሉት መሰረተ ቢስ አሉባልታ ነው” ብለዋል – አመራሮቹ፡፡