Wednesday, June 17, 2015

ብርሃነ ገብረ ክርስቶስ በድብቅ ጅዳ ገቡ

June 17,2015
ልማታዊ “ዲፕሎማት” በምስጢር ካድሬዎችን ሰብስበዋል
berhane

የውጭ ጉዳይ ምክትል ሚ/ር አቶ ብርሃነ ገ/ክርስቶስ በድብቅ ጅዳ ማምሻውን ገብተዋል፡፡ ወደ ሳዑዲ አረቢያ የመጡበት ምክንያት ባይታወቅም በዚያው የሚገኙ የኢህአዴግ ሹሞችና ልማታዊ ዲፕሎማቶች ድንገተኛውን ጉብኝት ተከትሎ ከብርሃነ ጋር ለመወያየት ሽርጉድ ይሉ ለነበሩ የጅዳና አካባቢው ካድሬዎች፣ ለልማት ማህበራት ተወካዮችና ለደጋፊዎቻቸው በሚስጥር ጥሪ አስተላልፈዋል፡፡

ምስጢራዊውን ጥሪ የሚቃወሙ ኢትዮጵያውያን አንድ ባለስልጣን በዚህ መልክ ወደ ጃዳ መግባታቸው ዲፕሎማት ብለው ለሾሟቸው አገልጋዮቻቸው ያላቸውን ንቀት የሚያሳይ ብቻ ሳይሆን በዲፕሎማቱ ላይ እምነት እንደሌላቸው አመላካች መሆኑን ይናገራሉ።
berhane jeddah
ልማታውያንና የልማት አጋሮች ብርሃነን ለውይይት ሲጠብቁ
ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የኢህአዴግ ከፍተኛ ባለሥልጣናት ለስራ ጉብኝትም ይሁን ለህክምና ወደ ሳውዲ አረቢያ ሲገቡ የኤምባሲው ዲፕሎማቶች መረጃ የሚያገኙት ከተለያዩ ድህረ ገጾች መሆኑን የሚናገሩ ውስጥ አዋቂዎች ከዚህ በፊት በረከት ስምዖን በምስጢር ለህክምና ሲገቡ ዲፕሎማቱ በተመሳሳይ ሁኔታ መረጃ እንዳልነበራቸው ያስታውሳሉ፡፡
ከአንድ ዓመት በፊት በረከት በመሐመድ አላሙዲን የግል አውሮፕላን ተጭንው እኩለ ሌሊት ሳውዲ ገብተው ጅዳ ከተማ በሚገኝ አንድ ሆስፒታል ውስጥ በህክምና ላይ መሆናቸውን የቆንሳላ ጽ/ቤቱም ይሁን በሪያድ የኢትዮጵያ ኤምባሲ ያወቁት ጎልጉል እና ዘሃበሻ ሚዲያ ላይ በተለቀቀው መረጃ መሆኑን የሚያስታውሱ እነዚህ ወገኖች በዲፕሎማቱና በኢህአዴግ መሃከል ከፍተኛ የሆነ የመረጃ ክፍተት መኖሩን ያወሳሉ፡፡ በመሆኑም የመረጃ ክፍተቱን ለማሟላት ዲፕሎማቱ ሚስጥራዊ መረጃዎችን ለማግኘት የተጠቀሱትን ሚዲያዎች መከታተል አማራጭ የሌለው መፍትሄ እንደሆነባቸው ይነገራል።
ዛሬ በጅዳ ቆንስላ ጽ/ቤት በተደረገው ስብሰባ ላይ የታዩት ብርሃነ ገብረክርስቶስ በሙስና ስለሚታመሰው በጅዳ የኢትዮጵያ ኮሚኒቲ ት/ቤትና ህልውናው ስላከተመው በሪያድ የኢትዮጵያ ኮሚኒቲ ማህበር ንብረት መባከን ምንም መረጃ እንደሌላቸው ለማወቅ ተችሏል።
አንድ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መ/ቤት ሠራተኛ አስከትለው ትላንት ጅዳ ሳውዲ አረቢያ ስለገቡት አቶ ብርሃነ ገብረክርስቶስ ጉብኝት በሳውዲም ሆነ አገር ቤት ከሚገኘው የኢህአዴግ ጽ/ቤትና መገናኛ ብዙሃን እስካሁን ምንም የተባለ ነገር የለም፡፡ አሁን ዘግይቶ በደረሰን ዜና ብርሃነ ወደ ሪያድ ከተማ ያቀናሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡ (Ethiopian Hagere Jed Bewadi )

No comments: