Thursday, September 25, 2014

ለህወሃት የማስጠንቀቂያ ደወል!

September 25,2014
አማራጩ “የተሃድሶ ዕርቅ” ብቻ ነው
bell
የአዲሲቷ ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄ (አኢጋን) ዋና ዳይሬክተር ለህወሃት ሊቀመንበር በቀጥታ ወደ ዕርቅ ሊያመጣ የሚችል ደብዳቤ ላኩ፡፡ በደብዳቤው ለህወሃት ከፍተኛ አመራሮች እንዲሁም ለትግራይ ተወላጆች በግልጽ ማስጠንቀቂያ የተሰጠ ሲሆን ህወሃት የፈጸመው ወንጀልም በተወሰነ መልኩ ቀርቧል፡፡ መግለጫው ጥፋትን ዘርዝሮ ወደ እውነተኛና ፍትሃዊ የተሃድሶ ዕርቅ ለመምጣት ነው፡፡ ሙሉቃሉ ከዚህ በታች ይነበባል፡፡

ለአዲሲቷ ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄ (አኢጋን)
ግልጽ ደብዳቤ ለህወሃት!
smne1
“ጊዜ መልኩን ሳይቀይር አሁን ባላችሁ ዕድል ተጠቀሙ!
… ቀናነት ነጻ ያወጣችኋል!”
አባይ ወልዱ
የህወሃት ሊቀመንበር
መቀሌ፤ ትግራይ
አቶ አባይና መላው የህወሃት ማዕከላዊ ኮሚቴ አባላት፤
ይህንን ደብዳቤ የምጽፍላችሁ ከተለያዩ ኢትዮጵያውያን በተውጣጣው የማኅበራዊ ፍትሕ እንቅስቃሴ ከሚመራው በአዲሲቷ ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄ (አኢጋን) ስም ቢሆንም በተለይ ግን ሁላችንም የኢትዮጵያ ልጆች እንደመሆናችን እኔም እንደ አንድ ኢትዮጵያዊ ቤተሰብ አባል የላኩላችሁ ደብዳቤ መሆኑን እንድታውቁልኝ እወዳለሁ። በአንድ ቤተሰብ ውስጥ አለመግባባት ሲከሰት ሁኔታውን ማብረድና ወደ መልካም ማምጣት የቤተሰቡ አባላትና ስለቤተሰቡ በጥልቀት የሚያስቡ ሽማግሌዎች ዋንኛ ተግባር ነው። ታዲያ እኛም አንድ አገርና አንድ ተስፋ በፊታችን ያለ እንደመሆኑ በመካከላችን ያለውን ችግርና ግጭት በእውነትና በታማኝነት ልንነጋገር ይገባል ብዬ ከማመን ነው ይህንን የምጽፍላችሁ።
የዚህ ደብዳቤ ዋና ዓላማ የህወሃትን ሊቀመንበር፣ የህወሃት ማዕከላዊ ኮሚቴ አባላትን እንዲሁም የትግራይ ተወላጅ ወንድምና እህቶቻችንን በሙሉ፤ ስለ እያንዳንዳችን ጣት እንድንጠቋቆም ሳይሆን እርስበርሳችን መነጋገር እንችል ዘንድ ለመጋበዝ ነው። ይህም ንግግርና ውይይት ከፍ ብሎ ወደ ብሔራዊ ዕርቅ እንዲያመራ ለማድረግ ነው። ከዚህ አንጻር ይህንን ደብዳቤ በምጽፍበት ጊዜ ህወሃትን ከትግራይ ሕዝብ በመለየት ለማስቀመጥ ያደረኩትን ሙከራዎች በሙሉ ልብ እንድትሏቸው እሻለሁ። የዚህ ደብዳቤ አግባብ በሥልጣን ላይ ላሉቱና ላጋዦቻቸው ነው እንጂ ብዙውን ጊዜ አለአግባብ ከህወሃት ጋር አብረው የሚወቀጡት የትግራይ ወገኖችን ደርቤ እየተናገርኩ አለመሆኑን እንድታስተውሉልኝ ይሁን።
ይህንን ደብዳቤ የምጽፍላችሁ በጥላቻ በመነሳሳት ሳይሆን በፍቅርና መልካምን ሁሉ በማሰብ እንደሆነ እንድታውቁልኝ እፈልጋለሁ። ምክንያቱም የህወሃት ዘረኛ ፖሊሲ ከህዝቡ ጋር ተቆራኝቶ በአገራችን በቂ ምሬትና ጥላቻ በትግራይ ወንድሞችና እህቶቻችን ላይ እንዲኖር በማድረጉ እኔ በዚያ ላይ ሌላ ጥላቻ የመጨመር ምንም ፍላጎት የለኝም። እንዲያውም ከአምስት ዓመት በፊት የአደባባይ ምስጢር የሆነውን እውነታ በማፍረጥረጥ በህወሃት እየተገበረ ያለው የዘር መድሎና አፓርታይድ ሥርዓት እያደረሰ ያለውን በግልጽ አስረድቼ ነበር። የዚያን ጊዜ የጻፍኩት ደብዳቤ እዚህ ላይ ይገኛል። (http://www.solidaritymovement.org/090611OpenLetterToMyFellowTigrayans.php)
ይህ የአሁኑ ደብዳቤ ከዚያ የቀጠለ ሲሆን የዚያን ጊዜ እንዳልኩት ጉዳዩን እያቀረብኩት ያለሁት እንደ አንድ ባለሙያ ሳይሆን እንደ አንድ ተራ ሰው ለማኅበረሰቤ መልካም በማሰብ ማበርከት የሚገባኝን ከመጠቆምና ለወደፊቱ ኢትዮጵያውያን እንዲሁም ለእናንተ ለራሳችሁ የሚጠቅም ነገር ከማሳየት አኳያ ነው። ስለሆነም በዚህ ደብዳቤ ውስጥ እናንተ ለመስማት የምትፈልጉትንና ለጆሯችሁ የሚጥም ነገር የምዳስስ ሳይሆን እውነትን ቁልጭ አድርጌ ነው የማቀርበው። “እውነትን ተናግሮ የመሸበት ማደር” እንደሚባለው ውሸትን ተናግሬ በሰዎች ዘንድ ተቀባይነትን ከማግኘት ይልቅ እውነትን ተናግሬ ብጠላና ብገለል እመርጣለሁ። ምክንያቱም ያለንበት የአገራችን ሁኔታ በውሸት እንድንነጋገር አይፈቅድልንም። እኔ እዚህ ደብዳቤ ላይ እውነቱን አሰፍራለሁ ብልም በተጻፈው ነገር ሁሉ ከኔ ጋር ትስማማላችሁ ብዬ አልጠብቅም፤ ነገር ግን ሁለታችንንም የሚያስማማ አንዳንድ ነጥቦችን እናገኛለን ብዬ አምናለሁ።
እኛ ማነን?
ኢትዮጵያ በምትባለው አገር በመወለዳችን ወይም በአንድም ይሁን በሌላ መንገድ ከኢትዮጵያ ጋር ግንኙነት ያለን በመሆኑ ኢትዮጵያውያን ነን።በውጭ አገር ያሉትም ከዚህ የተለዩ አይደሉም፤ ምክንያቱም በውጭ አገር ቢኖሩም ወይም አስተዳደጋቸው በውጭ ቢሆንም የቤተሰባቸው የዘር ሃረግና ማንነት ከኢትዮጵያ ባሕል ጋር የተሳሰረ ነው። በመሆኑም ማንም ሰው ከዚህኛው አካባቢ ወይም ዘር ወይም ጎሣ ልወለድ ብሎ ሳይሆን በፈጣሪ ፈቃድ በዚህ አገር ላይ ተወልዷል፤ ዕድሉም ከኢትዮጵያ አገር ጋር ተሳስሯል። ከሚታወቀው ፍጥረተ-ዓለም ውስጥ የሰው ልጅ በሚኖርባት በዚህች ምድር፤ ሁላችንም በውቅያኖስ፣ በአህጉር፣ በተራራ፣ በአገራትና ሰው ሰራሽ በሆኑ ድንበሮች ተከልለን እንገኛለን። በዚህ ውስጥ ሁሉ በልዩነታችን የምንከፋፈል ሰዎችም ነን።
በኢትዮጵያ ውስጥ የራሳቸው ቋንቋ፣ ባሕልና ልዩ አኗኗር ያላቸው ከ80 በላይ የጎሣ ቡድኖች ይገኛሉ። በእርግጥ አሁን ባለው የኢትዮጵያ ሕገመንግሥት እነዚህን ቡድኖች “ብሔር ብሔረሰቦች” ተብለው ይጠራሉ። የዚህ ዓይነቱ የመንግሥት አስተዳደር በተለያዩ ቡድኖች መካከል እኩልነት እንዲኖር ማድረግ ሲገባው እውነታው ግን አብዛኛው ኢትዮጵያዊ የተገፋና የተተወ መሆኑን ነው የሚያሳየው። በአንድ ቤተሰብ ውስጥ ሊኖር የሚገባው ጤናማ መተሳሰብና መረዳዳት በኢትዮጵያችን ውስጥ በሚገኙ “የብሔር ቤተሰቦች” ሲከሰት አይታይም። ከዚህ ይልቅ ለሕዝብ የቆመ ሆኖ እንደተመሠረተ የሚናገረው የህወሃት/ኢህአዴግ አገዛዝ እንደ ብርቅያ ልጆች ለሚያያቸው ትግሬዎችና ህወሃት የቆመ መንግሥት መሆኑ በግልጽ የሚታይ ሐቅ ነው፤ አብዛኛው የኢትዮጵያ ሕዝብ ከዚህ ውጭ ተደርጓል።
በአሁኑ ጊዜ አንዳንዶች ከዚህ “የብርቅየ ልጅነት” ጎራ ለመመደብ በመፈለግ ደፋ ቀና ይላሉ፤ ሌሎች ደግሞ እንደ እውነተኛ ኢትዮጵያውያን ባለመቆጠራቸው ምክንያት አሁን አለ የሚባለውን ግንኙነት “መቁረጥ” ይፈልጋሉ። የእነዚህኛዎቹ አቋም ጠንከር ያለ ከመሆኑ የተነሳ አንዳንዶቹ እናንተ ህወሃቶችን ሥልጣን እንድትለቁ የሚጠይቁ ሲሆኑ ከዚያ ጋር አብሮ ለራሳችሁ ያጋበሳችሁትን ልዩ መብትና ጥቅማጥቅም አብራችሁ እንድትሰጡ ይጠብቁባችኋል። ይህ አስቸጋሪ እንደሚሆን አጠያያቂ አይደለም፤ ሆኖም እናንት ህወሃቶች በማታለል፣ በሙስና እና በጠብመንጃ በማስገደድ የራሳችሁን ጥቅም ስታስከብሩ የቆያችሁ በመሆናችሁ የፈጸማችሁት ነገር ስህተት ብቻ ሳይሆን ህጋዊ፣ ማኅበራዊ እና ግብረገባዊ መብታቸውን በጣሳችሁት ወገኖች ዘንድ ከፍተኛ ችግር ውስጥ እንድትገቡ አድርጓችኋል።
እናንት ህወሃቶች የራሳችሁን ጥቅም ለማስከበር ስትሉ ፍትህን እንዴት እንዳጣመማችሁ፣ ፍርድ ቤቶችን የፖለቲካ መጠቀሚያ እንዳደረጋችሁ፣ መብቶችን እንዴት እንደረገጣችሁ፣ የኢኮኖሚና ንግድ ክፍሉን እንዴት እንደተቆጣጠራችሁ፣ የሃሰት ፕሮፓጋንዳ እንዴት ስትነፉ እንደኖራችሁ፣ የማኅበረሰቡን ዘርፎች (የሃይማኖት ድርጅቶችን፣ ማኅበራዊ ስብስቦችን፣ ወዘተ) በሙሉ እንዴት እንደተቆጣጠራችሁ እና የራሳችሁን ሰዎች (ማለትም ትግሬዎችን) በወታደራዊ፣ በደኅንነትና በሌሎች ቁልፍ ቦታዎች እንዴት እንደሰገሰጋችሁ የኢትዮጵያ ሕዝብ ሳያውቅ የቀረ እንዳይመስላችሁ!
እንደዚህ ወገናዊ እና ሁሉንም እኩል በማይመለከት ቤት ውስጥ እንዴት ነው ሌሎች ኢትዮጵያውያን መኖር የሚችሉት? እንዴትስ ነው በእንደዚህች ዓይነት ኢትዮጵያ ውስጥ መኖር የሚመኙት? እስካሁን እየታየ ያለው ተቃውሞ እና ንቅናቄ እናንተ ህወሃቶች በአንድም ይሁን በሌላ ሁኔታ መላ እንድትፈልጉ እያስገደዳችሁ ያለ ሁኔታ ነው። ስለዚህ የወቅቱ ጥያቄ ጊዜው እስኪያልፍባችሁ ነው የምትጠብቁት ወይስ ከዚህ በላይ የሆነውንና የመንፈስ ልዕልና የሚጠይቀውን የዕርቅና የተግባራዊ ተሃድሶ መንገድን በመከተል ፍትህን እንደገና ታሰፍናላችሁ? ይህንን መንገድ የምትከተሉት ግን በዕርቅና ተሃድሶ ስም ከዚህ በፊት እንዳደረጋችሁት በሥልጣናችሁ ለመቆየት የምታደርጉት ብልጣብልጥ አካሄድ ሳይሆን መደረግ ያለበት አስፈላጊና እውነተኛ ነገር በመሆኑ ልትፈጽሙት የሚገባ ስለሆነ ነው።
ፈጣሪ የሰጠውን ዓለምአቀፋዊ ሕግ መከተል ሰላምን ያወርዳል!
ፈጣሪ ኃያሉ አምላክ ለማንም አያዳላም፤ እኛንም እንዲሁ እንድንሆን ይመክረናል። ፍትሕን ለታናናሾችም ሆነ ለታላላቆች እንዲሁም ከእኛ ጋር ላሉትም ሆነ ከእኛ ውጭ ለሆኑት እንድናሰፍን ይጠበቅብናል። ሌሎችን ስንንቅ፣ ከሰው በታች ስናደርግ፣ ስናገልል፣ ስናጣጥል፣ ስንበድል ወይም ስናጎሳቁል ይህንን ሁሉ ቆጥሮ በእኛ ላይ ተመልሶ መምጣቱ የማይቀር ሐቅ ነው። እኛ እንደ ኢትዮጵያዊ የሌሎችን መብት ስንጠብቅ፣ ማንነታቸውን ስናከብር ፈጣሪ የለገሳቸውን መብት ሁሉ በግልም ሆነ በጋራ ስናከብር የሥራችንን መልካም ውጤት እናገኛለን። ይህንን ሳንፈጽም ከቀረን ግን የዘራነውን ማጨዳችን የማይቀር ነው። ከዚህ አንጻር እናንት ህወሃቶች ባለፉት ሁለት ዓስርተ ዓመታት ስትዘሩ የኖራችሁትን የምታጭዱበት ቀን ሲመጣ እንዴት ልትሆኑ እንደምትችሉ አስባችሁበታል?
በአሁኑ ጊዜ በኢትዮጵያ ሁሉም በራሱ ንዑስ ማንነት ላይ በማተኮር በሌሎች ላይ የሚደረገውን ኢሰብዓዊ ድርጊት ትክክለኛነት ለማስረዳት ሲጠቀምበት ይስተዋላል። ይህም ኃያሉ ፈጣሪ በሌሎች ወንድሞችና እህቶቻችን (ሌሎች ብሔረሰቦች/ጎሣዎች) ላይ ያስቀመጠውን የራሱን ምስል ለማየት ካለመቻል የመነጨ ነው። አኢጋን የተቋቋመውም ይህንን የተሳሳተ አመለካከት ለመቀየርና “ሌሎች” እያልን የምንጠራቸውን የራሳችን አድርገን እንድንወስድና ከፈጣሪ ጋር ስምምነት እንዲኖር ለማድረግ ነው። እንደው እውነቱን እንነጋገር ከተባለ ኃያሉ ፈጣሪ አንድ ሰው እንደ “እኛ ካልተናገረ” ወይም “እኛን ካልመሰለ” ወይም “የእኛን ዓይነት” ሃይማኖት ከሌለው ወይም “ከእኛ ጎሣ/ብሔር” ውጭ ከሆነ ወዘተ ለይቶ የሚያየው ይመስለናል? ወይም ይህ ሰው “የእኛን ዓይነት” የፖለቲካ አመለካከት ከሌለው ወይም በጣም ዝቅተኛና የተዋረዱ ከሚባሉ ጎሣዎች የመጣ በመሆኑ አምላክ ከእኛ አሳንሶ ይመለከተዋል ብለን እናስባለን እንዴ?
“ልዩነታችን ውበታችን” በማለት ትልልቅ ማስታወቂያ (ቢልቦርድ) መለጠፍ ብቻ አይደለም የሚያዋጣው። ከዚህ በማለፍ ፈጣሪ ለጎረቤታችን እንድንሰጥ የጠየቀንን ፍቅር፣ መልካምነትና ፍትሕ በተግባር ማስፈን ይገባናል። ልናስታውስ የሚገባን ነገር ቢኖር ከአካል ሰውነታችን አንዲቷም ክፍል ብትሆን ከታመመች ሌላው የአካል ክፍላችን በጠና ይታመማል፤ ሰላም አይኖረውም። ታዲያ ህወሃት በኢትዮጵያችን ውስጥ ያሰራጨው የዘርና የጎሣ ፖለቲካ ያመረቀዘው ቁስል ህመም እናንተንስ ተሰምቷችሁ ያውቅ ይሆን?
በዘር ላይ የተመሠረተ ፌዴራላዊ አወቃቀር የጎጠኝነት፣ የፊውዳላዊነትና የማርክሲስታዊነት ጣምራ ውጤት ነው።
ህወሃት/ኢህአዴግ የሚከተለው በዘር ላይ የተመሠረተው ፌዴራላዊ አወቃቀር በኢትዮጵያ ውስጥ ያሉትን ቡድኖች በሙሉ የሚያቅፍና የራሳቸውን ዕድል በራሳቸው የመወሰን መብት የሚያጎናጽፍ ነው እያለ ቢናገርም በተግባር ግን ይህ አዲስ ያልሆነና ከቁሻሻ ወጥቶ እንደገና በተግባር የዋለ የጎጠኝነት፣ የፊውዳላዊነትና የማርክሲስታዊነት የወረደ ጣምራ ውጤት ነው።
  1. ጎጠኝነት – አንድን ጎሣ ወይም ጎጥ (የትግሬን) ከፍ በማድረግ በአፓርታይዳዊ አሠራር “አንዱ ጎሣ/ጎጥ ሁሉንም ነገር ለራሱ ማድረግ አለበት” ወይም “የመብላት ተራው የእኛ ነው” በሚል ከፋፋይነት ላይ የተመሠረተ ነው
  2. ፊውዳላዊነት – አንድን ቡድን ወይም ጎሣ ወይም ወገን ከሌላው የተለየ፣ የተሻለ፣ የተመረጠ፣ የበቃ፣ ስለሆነ የመግዛት/የመምራት መብት አለው፤ “ወርቃማ ዘር” ስለሆነ ትርፉንም ለራሱ የማድረግ ሥልጣን ተሰጥቶታል፤ ሌሎች ዕድለቢሶች በሥሩ የመሆን ግዴታ አለባቸው የሚል ነው።
  3. ማርክሲስታዊነት – የሚቃወሙትን ሁሉ – ትግሬዎችንም ጭምር – የመርገጥ ባህርይ ሲሆን ከፊውዳላዊነት በተለየ መልኩ ህወሃት በማርክሲስታዊ አስተሳሰብ “ሰፊውን ሕዝብ” እየጠቀምኩ ነው ቢልም በተግባር ግን “በጭቁኑ ሕዝብ” ስም የራሱን ሥልጣን ያመቻቸ ሆኗል። ይህ ዓይነቱ አታላይ ስልት ብዙሃኑን የአገራችንን ሕዝብ ከሌላው እንዲከፋፈል ያደረገ ብቻ ሳይሆን ብዙሃኑ ያልተማረ፣ በድህነት ላይ የሚገኝና ኑሮን ለማሸነፍ ደፋ ቀና የሚለውን በልዩ ሁኔታ በቁጥጥር ሥር ለማዋል የተደረገ ነው።
ማርክሲስታዊነት በውስጡ ካሉት መርኾዎች አንዱ ሕዝብን መከፋፈል ነው። ይህ ዓይነቱ መርህ ተግባራዊ በመሆኑ ስንቱ የአገራችን ሕዝብ ተከፋፍሎ ቀረ? ስንቱስ “እርስ በርሱ በጠላትነት” እየተያየ ያለፈውንና አዲስ ግጭቶችን እያጎላ “ሰፊውን ሕዝብ” ለራሱ መጠቀሚያነት ያዋለው ስንቱ ነው? ህወሃት ይህንን መሠሪ ስልት በመጠቀም ተዋደውና ተከባብረው የኖሩትን፣ ለምሳሌ አማራና ኦሮሞዎችን፣ እርስበርስ በማጋጨት ክፉ ተግባር ላይ አውሎታል። በገሃድ ሲነገር ባንሰማውም፤ ዋንኛው ምክንያት የእነዚህ ሁለት ወገኖች መተባበርና መስማማት የሚያመጣው ታላቅ ለውጥ ምን ሊሆን ይችላል በሚል ፍርሃቻ እንደሆነ ብዙዎች ያውቁታል።
ይህ ከሆነ ዘንዳ ታዲያ በግማሽ ኦሮሞ እና በግማሽ አማራ የሆኑ ወይም ሌላ ተመሳሳይ ዓይነት ጥምረት ውልድ የሆኑ የት ይድረሱ? የእንደነዚህ ዓይነት ኢትዮጵያውያን እርስበርስ ግጭትና አለመግባባት በእናንተ ህወሃቶች እየዳበረና እየተደጎመ ቆይቶ እዚህ ደርሰናል። ለመሆኑ እናንተ ባመጣችሁት በዘር ላይ የተመሠረተ የጥላቻ ፖሊሲዎች ምክንያት ምን ያህል ግጭቶች እንደተከሰቱና ምን ያህል ሕዝብ እንዳለቀ ታውቁታላችሁ?በዋንኛነትና በዓላማ ስታራምዱት የቆያችሁበት ስለሆነ እያንዳንዷ መረጃ ከእናንተ የተሰወረች ልትሆን አትችልም።
ይህ ብቻ አይደለም፤ እናንተ ህወሃቶች ለአገሪቷ እጅግ የሚጠቅሙ የተማሩ ሰዎችን አሁን እናንተ ለምታራምዱት ፖሊሲ ተቃዋሚ በመሆናቸው ብቻ አስወግዳችኋል፤ እስካሁንም ጥቃት እያደረሳችሁባቸው ይገኛል። እነዚህ በምሁራን ብቻ የሚወሰኑ ሳይሆኑ የእናንተ ጥቃት የደረሰባቸው በኅብረተሰቡ ዘንድ በፖለቲካ፣ በሃይማኖት፣ በኢኮኖሚ፣ በማኅበራዊ ጉዳይ፣ ተቀባይነት ያላቸውን ግለሰቦች፤ እንዲሁም ከእናንተ ውሸትና በሃሰት ለፈጠራችኋትና የጥቂቶች ብቻ ላደረጋችኋት ኢትዮጵያ አልገዛም የሚል ሁሉ በሁሉም ብሔር የሚገኝ የእናንተ የጥቃት ሰላባ ሆኗል። እናንተ ብትክዱትም ግፉን የተቀበሉትና ታሪክ ግን ፈጽሞ ሊረሳቸው አይችልም።
ሌላው በእኩል ደረጃ ሊጠቀስ የሚገባው ነገር ቢኖር ያለማቋረጥ የሚለፈፈው ውሸት ነው። ዓይን ያወጣው ውሸት እንዳለ ሆኖ በማርክሲስታዊ ርዕዮት መልክ የሚቀርበው “የአገም ጠቀም” እና መልካም የሚመስለውን ብቻ ለይቶ በማቅረብ ሕዝቡ እንዲወናበድ የሚደረገው አካሄድ በአጸያፊነቱና በአሳፋሪነቱ የሚጠቀስ ነው። ይህንን በማድረጋችሁ ሕዝብን ሳያውቅ በጭፍን ለመምራት ያስቻላችሁ ቢመስላችሁም በምላሹ ግን በሕዝቡ ዘንድ ውሸት፣ አለመተማመን እንዲሁም እናንተኑ መልሶ የሚያወድም ስትራቴጂ መሆኑን የተረዳችሁት አይመስልም። እንደ ምሳሌ የሚጠቀሰው ከትግሬ ሌላ የሆኑ ኢትዮጵያውያንን በሥልጣን እርከን ላይ በማስቀመጥ ሕዝቡ ሁሉም ተወክሏል ብሎ እንዲያምን የምትጠቀሙበት ወራዳ አካሄድ ነው። የዚህ ማታለያ ሰለባ በጠቅላይ ሚኒስትርነት የተቀመጡት ኃይለማርያም ደሳለኝና ሌሎች እንደ እርሳቸው የተመደቡ ተጠቃሾች ናቸው። በኢትዮጵያ ሰላም እንዲኖር ካስፈለገ ይህ ዓይነቱ አጸያፊና እጅግ ነውረኛ አካሄድ መቆም አለበት።
ህወሃት የተለየ ሊሆን ይችል ነበር! ዕድሎች ነበሯችሁ ግን አልተጠቀማችሁበትም!
ህወሃት በተመሠረተበት ወቅት እንደ ምክንያት አድርጎ ያቀረበው ትግሬዎች በደርግ አገዛዝ በደል ደርሶባቸዋል፣ ተገልለዋል፣ … የሚል እንደነበረና ይህም በረሃ እንዳስገባችሁ ራሳችሁ የምትመሰክሩት ነው። ሆኖም የሥልጣን መንበሩን በተቆጣጠራችሁበት ጊዜ ለውጥ የማምጣት ምርጫ ነበራችሁ። ከፊውዳላዊውም ሆነ ከደርግ አገዛዝ የተለያችሁ መሆን ትችሉ ነበር። በርግጥ የተለያችሁ ሆናችኋል፤ የሚያሳዝነው የተለያችሁት በመልካም ሳይሆን በክፉ፣ በዘረኝነት፣ በስግብግብነት፣ በወገናዊነት፣ በሙስና፣ በራስ ወዳድነት፣ ብዙሃኑን በመበደል፣ ለራሳችሁ ሃብትና ንብረት በማከማቸት፣ በጭቆና፣ በግፍ፣ … ከበፊቶቹ እጅግ በከፋና አጸያፊ በሆነ መንገድ የተለያችሁ ሆናችኋል።
ህወሃት እንደ ማርክሲስታዊው ደርግ የተቃወሙትን ሁሉ በማፈን እና ጦርነት በማወጅ “ገርስሼዋለሁ” የሚለው የደርግ ውላጅ ሆኗል።በሥልጣን በቆየ መጠንም ከደርግ እጅግ እያስከፋና እያስመረረ መጥቷል። ነጻ አውጪ ግምባራችሁ “ለውጥ አመጣለሁ” በማለት ሥልጣን የተረከበ ቢሆንም በጨበጠውን ሥልጣን በመጠቀም የራሱን ጦር ሠራዊት መሥርቷል፤ የኢትዮጵያን የተፈጥሮ ሃብት ንብረት በራሳችሁ ስምና በህወሃት ቁጥጥር ሥር አደረጋችሁ፤ የቀረውንም የአገራችን ሃብት ለቤተሰቦቻችሁና ለዋና የጥቅም ተካፋዮቻችሁ አከፋፍላችኋል፤ ዋንኞቹ የጥቅም ተካፋዮችም ትግሬዎች ናቸው!!
በአገራችን የተለያዩ ክፍሎች በጋምቤላ፣ በኦጋዴን፣ በአፋር፣ በኦሮሚያ፣ በቤንሻንጉል፣ በአማራ እና በአዲስ አበባ ሕዝቡ ተቃውሞውን ሲያሰማ በእናንተ ቁጥጥር ሥር ያለው የጦር ሠራዊትና ፖሊስ ተቃውሞ የሚያሰሙትን ወይ ያስወግዳቸዋል ወይም በግድ ዝም እንዲሉ ያደርጋል። ይህ የሚፈጸመው ደግሞ በመግደል፣ በማሰር፣ የሰብዓዊ መብት በመርገጥ፣ ሕዝብን በማሸበር፣ ወደ ሌላ አገር እንዲሰደድ በማድረግ፣ ወዘተ ሲሆን አገር ቤት የሚቀረው ደግሞ በግድ ጸጥ ይደረጋል፤ ይህ ሁሉ ሲሆን ግን እናንተም ሆነ ህወሃት ምንም ነገር እንዳልተከሰተ ነው የምታስመስሉት።ወጥታችሁ መግለጫ ስትሰጡም ሆነ ስለ ልማት ስታወሩ ይህ ሁሉ ግፍ በአገራችን ላይ እንዳልተፈጸመ ስታስመስሉ ሁለት ዓስርተ ዓመታትን አሳልፋችኋል። “ለብሔር ብሔረሰቦች” መብት መከበር በሚል ራሳችሁ ያቋቋማችሁት የራስን ዕድል በራስ የመወሰን መብት እስከ መገንጠል የሚል ቢሆንም በተቃራኒው የኢትዮጵያን ሕዝብ እስከ ቀበሌና ቤተሰብ ድረስ በራሳችሁ ቁጥጥር (ጥርነፋ) ሥር በማዋል እኩይም ቢሆን ራሳችሁ ላወጣችሁት መመሪያ እንኳን የማትገዙ መሆናችሁን በተደጋጋሚ አስመስክራችኋል።
አገራችንን ላለፉት 23ዓመታት ስታልቧት ከቆያችሁ በኋላ በረሃ በነበራችሁበት ወቅት እና እስካሁን ድረስ “ነፍጠኛ አማራ” እያላችሁ ስታማርሩት የነበረው መላው የኢትዮጵያ ሕዝብ እናንተ በደርግ ላይ ከነበራችሁ መራርነት ባለፈ ሁኔታ ውስጥ ይገኛል። ይህ ሁኔታ ነው ለአዲሲቷ ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄ መመሥረት አንዱ ምክንያት። እናንተ እስካሁን ስታደርጉት የቆያችሁት ፍጹም የተሳሳተና መሰሪ ነው። በዚህ ምክንያት ሕዝብ ቢማረርባችሁና ግፉ አንገቱ ቢደርስ ልትደነቁ አይገባችሁም፤ ምክንያቱም ሕዝቡ በቅቶታል፤ አንገፍግፎታል። ላለፉት ዓመታት ሕዝቡን አንድ የማድረግና ለውጥ የማምጣት ዕድል ነበራችሁ። ከዚህ ይልቅ ግን በአገሪቷና በሕዝቡ ላይ መከፋፈልን እንዲሁም መተላለቅን የሚፈቅድ ወራዳ ሥርዓት ነው የፈጠራችሁት። ታዲያ በራሳችሁ ያመጣችሁትን ይህንን ሁሉ ችግር እንዴት ነው ልትጋፈጡት የምትችሉት?
ይህ ብቻ አይደለም እውነትን እጅግ በጣም የምትፈሩት ነገር ነው። “ብሔር ብሔረሰቦች” በሚል ቅዠት ኢትዮጵያን መሠረትን አላችሁ። ይህ ትክክል እንዳልሆነ በማስረዳት እውነቱን የተናገሩትን ሁሉ በመግደል፣ በማሰር፣ በማስወገድ፣ ደብዛቸውን በማጥፋት፣ ወዘተ ህወሃት ከእውነት ጋር በሚጋፈጥበት ጊዜ የሚያሳየውን አሳፋሪ ገጽታ ቁልጭ አድጋችሁ በገሃድ አሳያችሁ። ይህ ድርጊት እናንተን ለኅሊና ወቀሳና ውርደት የሚያጋልጣችሁ ብቻ ሳይሆን መቅኒያችሁን የሚመጥ፤ ነፍሳችሁን ቅርጥፍ አድርጎ የሚበላ ቅንቅን ነው። ከእናንተ መካከል አንዳንዶች አሁንም እልኸኛና እብሪተኛ በመሆን ልባቸውን አደንድነው ሊሆን ይችላል፤ ለብዙዎች ግን ሐቅን መካድ ለእብደትና ለሞት የሚያደርስ እንደሆነ እሙን ነው።
ህወሃት የሚዲያውን መስክ ለራሱ ጥቅም እንደተቆጣጠረው የተመሰከረ ቢሆንም በተለይ ሰሞኑን የወጣ መረጃ እንዳመለከተው በየድረገጹ ለሚወጡ ጦማሮች እና አስተያየቶች እናንተ በገንዘብ የገዛችኋቸው ቅጥረኞች ማንነታቸውን በመደበቅ ምላሽ እየሰጡ የህወሃትን መልካምነት እንደሚሰብኩና የአጸፋ ፕሮፓጋንዳ እንደሚነዙ የተደረሰባቸው መሆኑ ታውቋል። አገር እንመራለን ብላችሁ ተቀምጣችሁ እንዲህ ዓይነቱ ተግባር ስታስደርጉ ኅሊናችን ነጻ ነው ብትሉ ማን ሊያምናችሁ ይችላል? በአገራችን “መከበር በከንፈር” እንደሚባል ይህንን ሁሉ ግፍ ስትፈጽሙ ቆይታችሁ በሕዝቡ ለመከበር መፈለጋችሁ ለራሳችሁ ሊገርማችሁ ይገባ ነበር። የፈለጋችሁትን ዓይነት መሸፋፈን ብታደርጉ፤ አሳምራችሁ ብታቀርቡት፣ የሕዝቡን ምሬት ግን በምንም ልታፍኑት አትችሉም!
ለተሻለ ወደፊት አማራጩ እውነተኛ ለውጥ ብቻ ነው! የይስሙላ ተሃድሶ ተቀባይነት የለውም!
ሁኔታዎች አሁን ባሉበት ዓይነት እንደማይቀጥሉ እሙን ነው፤ መጨረሻው ይመጣል። አገሪቷ ወደ ሁከትና ቀውስ ውስጥ ከገባች እጅግ ከፍ ያለውን ክፍያ የምትከፍሉት እናንተና ልጆቻችሁ እንዲሁም ዝርያችሁ ነው። ሆኖም ማናችንም ብንሆን ይህ ሲከሰት ማየት አንፈልግም። ስለዚህ የዚህ ደብዳቤ ዋንኛ ዓላማም እናንተ ይህንን እንድትረዱ ለማድረግና ሁኔታው እንዳይከሰት ምን ማድረግ እንዳለባችሁ ለማሳወቅ ነው።
እናንተ አሁን ድረስ የምትከተሉት ፖሊሲዎች ሁሉ ሲወጡና ሲቀምሙ የኖሩት በቀድሞው ጠ/ሚ/ር መለስ ዜናዊ ነበር። ጊዜውን ጠብቆ የሚፈነዳውን ፈንጂ ለእናንተ አውርሰው እርሳቸው አልፈዋል። እናንተስ ምንድነው የምታደርጉት? ከአጠቃላዩ የኢትዮጵያ ሕዝብ ትግሬዎች 6በመቶ ናችሁ። ይህ ሲነገራችሁ ምንም እንዳልሆነ እና እንደማይሆን ለማስመሰል አትሞክሩ። ቁጥራችሁ ትንሽ ሆኖ ያደረሳችሁት በደል እጅግ ግዙፍና ፈጽሞ የማይረሳ ነው። በአንድ አገር ላይ አንድ ቡድን ለብቻው ሁሉንም ነገር ሲቆጣጠር የሚከሰተውን ለማወቅ ሩቅ መሄድ አያስፈልግም – ሩዋንዳ ቅርባችን ናት። መለስ ሲቀምሙት ከቆዩት የማታለያና ብልጣብልጥ ታክቲክ ጋር ተደምሮ የኢትዮጵያ ሁኔታ ከሩዋንዳም የባሰ ይሆናል ብሎ መናገር ይቻላል። መለስ ጥሎት የሄደውን እሣት በጉያችሁ አቅፋችሁ ነው ያላችሁት።
በመጋቢት ወር 1988ዓም በሩዋንዳ የሆነው አሳዛኝና ሰቅጣጭ ድርጊት የተጀመረው በዚያው በመጋቢት ወር አይደለም። ይልቁንም ለዓመታት የወሰደ አፓርታይዳዊ የዘር ፖሊሲ አንዱን ዘር የበላይ በማድረግ፣ ሥልጣን ለራስ ወገን ብቻ በማድረግ፣ ኃብትን ለራስ ወገን በማግበስበስ፣ ሌሎችን በማሰር፣ በመግደል፣ በማሰቃየት፣ … ዓመታት ካለፉ በኋላ ነበር። በወቅቱ የተጮኹ የማስጠንቀቂያ ደወሎች ነበሩ፤ የሰማቸው ግን አልነበረም።አሁን ግን ከ20 ዓመታት በኋላ ሩዋንዳውያን እስካሁን ቁስላቸውን ለማሻር አልቻሉም፤ ለውጦች ቢኖሩም የቁስሉ ጥልቀት እና የፈሰሰው ደም ያረጠበው መሬትና የሞላው ወንዝ አለመተማመንን ቢያሰፍንም ዕርቅን ብቸኛ አማራጭ በማድረግ በፈውስ ሂደት ውስጥ ይገኛሉ። ይህ ሁሉ ከመሆኑ በፊት ግን የተሰጡት ማስጠንቀቂያዎች አድማጭ ሊኖራቸው ይገባ ነበር።
ብዙዎች በአሁኑ ጊዜ ኢትዮጵያ ቀጣይ ሩዋንዳ ልትሆን ትችላለች እያሉ ነው። በ1997 ምርጫ መለስና የህወሃት ማዕከላዊ ኮሚቴ የቅንጅት አመራሮችን በትግሬዎች ላይ የዘር ማጥፋት ወንጀል ፈጽመዋል ብላችሁ የፈጠራ ክስ መስርታችሁ ነበር። የቅንጅት አመራሮች ይህንን በጭራሽ ያደረጉት ባይሆንም እናንተ ግን በአገሪቷ ላይ ያለውን አደጋ ለራሳችሁ የፖለቲካ መጠቀሚያ በማድረግ በራሳችሁ ሕዝብ ላይ ፈርዳችሁበታል፤ ሁኔታው ባይከሰተም በሰው አእምሮ ውስጥ ይህ ክፉ አሳብ እንዲገባ በማድረግ እንወክለዋለን የምትሉትን የትግራይ ሕዝብ ለዕልቂት ዳረጋችሁታል። በወቅቱ በሥልጣን ለመቆየት ስትሉ እና ተቃዋሚዎቻችሁን ለማክሸፍ ብትጠቀሙበትም ተክላችሁ የሄዳችሁት ግን በአገራችን የዘር እልቂት እንዲነሳ የሚያደርግ ፈንጂ እንደሆነ ራሳችሁ ምስክርና ተጠያቂ ናችሁ።
እኔ በግሌም ሆነ የጋራ ንቅናቄያችን በድርጅት ደረጃ ይህ በጭራሽ እንዲከሰት የማንፈልገው ቢሆንም ፍርሃቻው ግን አለ። ባልነደደበት እንደማይጨስ ሁሉ ፍርሃትና ስጋት ደግሞ እንዲሁ ያለምክንያት አይከሰትም። ሕዝቡ ያለውን ፍርሃቻ እኔ በግሌም ሆነ የጋራ ንቅናቄያችን ባለው የመገናኛ መስመር አገር ቤት ጎብኝተው ከሚመጡም ሆነ እዚያው ኢትዮጵያ ውስጥ ካሉትና ሌሎች ሰፋ ያለ ጥናት ከሚያካሂዱ በየጊዜው የምንሰማው ነው። ከእነዚህ ሁሉ የምናገኘው መረጃ የሚያመለክተው ሕዝቡ ምን ያህል በህወሃትና በትግሬዎች ላይ እያመረረ መምጣቱን ነው።ሁኔታው ያሳሰባቸው ኢትዮጵያውያን ለአገሪቷም ሆነ ለቤተሰቦቻቸው በማሰብ አንድ መላ መፈለግ እንዳለበት ይወተውታሉ።
“ልማት፣ ህዳሴ፣ …” እያላችሁ እውነታውን ለመደበቅ ብትሞክሩም ውጥረት ከነገሠ ግን ቆይቷል። በትግሬዎችና በሌሎች ኢትዮጵያውያን መካከል ያለው ልዩነት በተለይ ከውጭ ለሚመጡ ኢትዮጵያውያንም ሆነ ሌሎች በግልጽ የሚታይ ነው፤ ልዩነቱ የሚታየውም ከቦሌ ኤርፖርት ጀምሮ ነው። ወደ አገር ሲገቡ ትግሬ በመሆናቸው ብቻ የተለየ መስተንግዶና አገልግሎት ሲሰጣቸው ማየት ለብዙዎች አዲስ አይደለም። በኤርፖርቱ ውስጥ ያሉት የጉምሩክ ሠራተኞች ትግሬዎች መሆናቸው አንዱ ማረጋገጫ ነው። (በነገራችን ላይ ይህ በራሱ ወደ አገር ውስጥ ማን እንደሚገባ ማን ከአገር እንደሚወጣ በታማኞች ለመቆጣጠር ሆን ተብሎ የተደረገ ነው።)
ከበርካታ ክስተቶች መካከል አንድ የቅርብ ጊዜ ምሳሌ ልጥቀስ፤ የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች የያዘ አንድ ኢትዮጵያዊ ወደ አገሩ በቦሌ በሚገባበት ወቅት የጉምሩክ ሠራተኛው እጅግ ከፍተኛ የሆነ ቀረጥ ይጭንበታል (በብዙ ሺዎች የሚቆጠር)። ግለሰቡም ይህንን ያህል ለመክፈል እንደማይችል ይናገራል። ይህን ጊዜ የጉምሩክ ሠራተኛው ዕቃው እንደሚወረስ (ወደ ጉምሩክ እንደሚገባ) ይነግረዋል። በመጨረሻ ላይ በአማርኛ ይናገር የነበረው የዕቃዎቹ ባለቤት የቋንቋ ማርሹን በመቀየር በትግሪኛ መናገር ይጀምራል። የጉምሩክ ሠራተኛውም በመደነቅ ለግለሰቡ በሰጠው ምላሽ አስቀድሞ ለምን ትግሬ መሆኑን እንዳልተናገረ የሚጠይቅ ነበር። በጉዳዩ ላይ ገብቶበት የነበረው ሱፐርቫይዘርም ዕቃዎቹን ወደ ሻንጣው መልሶ ያለ አንዳች ክፍያ እንዲሰናበት አድርጎታል። ሲሰናበትም ሱፐርቫይዘሩ ግለሰቡን እንዲህ ይለዋል፤ “አንተ የኛ ነህ እንዴ!? – እኛ እኮ የታገልነው፤ ወደ በረሃ የሄድነው ላንተ ነው – በል እቃህን ያዝና ወደ ቤትህ ሂድ” በማለት አሰናብቶታል። እውነቱ ግን ግለሰቡ ትግሬ ሳይሆን አብሮ በማደጉ ቋንቋውን አቀላጥፎ የሚናገር ነበር። ታዲያ እንዲህ ዓይነቱና ከዚህም ያለፈ የረቀቀ ስንት ኢፍትሃዊነት ይፈጸም ይሆን? ለዚህም ነው በአሁኑ ጊዜ ሰዎች በኢትዮጵያ ውስጥ ሁለት ዓይነት ሕግጋት ናቸው ያሉት የሚሉት፤ አንዱ ለትግሬዎች የሚሠራ ሌላው ደግሞ ለተቀረው ኢትዮጵያዊ!
በርካታ ኢትዮጵያውያን እኔንም ጨምሮ ለአገራችን ሰላማዊና ዘላቂ ፍትህ እንዲሁም ሕጋዊ መንገድ የሚከናወን ዕርቅ እንጂ የሩዋንዳ ዓይነት ወይም በጎረቤት ደቡብ ሱዳን የሆነውን ዓይነት መተላለቅና ውድመት በጭራሽ አንመኝም። በአሁኑ ወቅት ባለው ሁኔታ ለበርካታ መቶሺዎች ለሚሆኑት ደቡብ ሱዳናውያን ስደተኞች ዕርዳታ ለማደረግ የማይቻልበት ደረጃ ተደርሷል። አስቀድሞ መፍትሔ ካልተፈለገ በኢትዮጵያስ ይህ ከመሆን የሚከለክለው ምን አለ? ጥፋቱ ሲመጣስ እናንተን የሚታደግ ማን ይሆን? ከዚህስ የምታመልጡ ይመስላችኋል?
ባለፉት ቅርብ ዘመናት በአገራችን ይህንን ተግባራዊ ለማድረግ ሳንችል ቀርተናል – መንግሥቱ አልሆነለትም፣ መለስ አላደረገውም፣ አሁን ደግሞ የተተካችሁት እናንተ ህወሃት/ኢህአዴጎች እየከሰራችሁ ነው። ከደገማችሁት ሁላችንም እንደገና አብረን እንወድቃለን። አወዳደቁ የሚከፋው ግን ለእናንተ ነው፤ እጅግ ብዙ የምታጡት አላችሁና፤ ቀሪው የኢትዮጵያ ሕዝብ 23ዓመታት ሲያጣ ስለኖረ የቀረው ነገር ስለሌለ የሚያጣው እንደ እናንተ አይከፋም። ስለዚህ ዕርቅ አማራጭ የሌለው መፍትሔ ነው፤ ይህ ግን ጭፍን “አንተም ተው፤ አንቺም ተው” ዓይነት ጭፍን ዕርቅ ሳይሆን ጥፋትን ማመን፣ እውነትን መቀበል፣ በደልን ማመን፣ እውነተኛ ተሃድሶ ማምጣትና ፍትሕን ማስፈን የሚጠይቅ ነው። እንዲህ ዓይነት እውነተኛ ለውጥ ካልመጣ ህወሃት ለቀጣዩ ትውልድ ጥላቻና ቂም በቀል ነው የሚያስተላልፈው። ይህ ደግሞ በህወሃትና በአመራር ላይ ባላችሁት ብቻ የሚያነጣጥር ሳይሆን በትግሬዎች ስም አገር ስትገዙ እንደመኖራችሁ አደጋው የትግሬዎች በሙሉ ይሆናል። ከመለስ ጋር ተደምሮ የእናንተም እውነተኛ ውርስ/ሌጋሲ ይህ ይሆናል።
ስለዚህ ለዚህ የተቀደሰ ዓላማ ያላችሁን ፈቃደኛነት በግልጽ አሳዩ። ወደ ድርድሩ ጠረጴዛ ኑ! የፖለቲካ እስረኞችን፣ ጋዜጠኞችን፣ የሰብዓዊ መብት ተሟጋቾችን፣ የሃይማኖት መሪዎችን እና የተቀናቃኝ ፓርቲ መሪዎችን ከእስር በመፍታት ፈቃደኛነታችሁን አሳዩ። ከእናንተ ጋር ሚቃወመውን ሁሉ “አሸባሪ” በማለት ማሰራችሁን አቁሙ! ኃይልን ወይም ጉልበትን በመጠቀም እስከመጨረሻው በሥልጣን አትቆዩም! በዓለም ታሪክ ያልተከሰ ስለሆነ እናንተ ልትከውኑት አትችሉም። እናንተ አለን ከምትሉት ጉልበት በብዙ እጥፍ የሚበልጥ የነበራቸውም ተንኮታኩተዋል። ስለዚህ ከትዕቢታችሁ ተንፍሱ፤ ትህትና አሳዩ፤ ከፍ ብላችሁ የተሰቀላችሁበት ከመሰላችሁ “ፎቅ” ውረዱ! ለለውጥ ያላችሁን ግልጽነት አሳዩ! ለዓመታት ሳታቋርጡ ስታወሩ የነበራችሁትን ውሸት አቁሙ፤ እውነትን መናገር ተለማመዱ። የሃሰትን መንገድ ሳይሆን ትክክለኛውን በመከተል በዜጎች መካከል መተማመን እንዲፈጠር የሚያስችል ሥራ ማከናወን ጀምሩ!
ይህንን ወርቃማ ዕድል አታባክኑት!
ባለፉት 60ዓመታት በላይ ኢትዮጵያ በአምባገነናዊ ሥርዓት ሥር ስትገዛ ኖራለች። ከዚህ አንጻር ሕዝባችን በቂ ግፍ፣ መከራ፣ ስቃይ፣ ደም መፍሰስ፣ ሰቆቃ፣ … አልተቀበለም ትላላችሁ? የብዙዎች ቤት ፈርሷል፣ የበርካታዎች ንጹህ ደም ፈሷል፣ የብዙዎች ልብ ደግሞ በቂም፣ በበቀል፣ በጥላቻ፣ በምሬት ተወጥሯል። ተራው ደርሶ እነርሱም ደም እስኪያፈሱና የተቀማባቸውን መልሰው እስኪዘርፉ ቀናቸውን የሚጠብቁ ጥቂቶች አይደሉም።
እስቲ ለጥቂት ጊዜ ቆም ብለን እናስብ፤ እናንተም ለበርካታ ዓመታት ከተጠመቃችሁበትና ከተዘፈቃችሁበት የማርክሳዊና ሌኒናዊ አመለካከት ትንሽ ቆም ብላችሁ ሁላችንም ወደ ፈጣሪ አምላክ እንመልከት። ማን እንደነበርን እና አምላክ የሰጠንን ሰብዓዊነት ለጥቂት ጊዜ እናጢን። እጅግ በጣም ወድቀናል፤ ከመስመሩ ርቀን ሄደናል፤ ስህተታችንን እንቀበል። ነገር ግን በፈጣሪ ኃይል ከወደቅንበት እንነሳለን፤ እንደገናም እንደ አንድ ሕዝብ እርስበርስ መዋደድም እንችላለን።
የሰዎች ስግብግብነት በመንግሥታት ሕግ ውስጥ እየተሰነቀረ ለሕዝባችንና ለመጪው ትውልድ እርግማን አትርፈናል። ከራስ ወዳድነት እና ለራስ ወገን ወይም ዘር ብቻ ከማሰብና ከመሥራት ይልቅ በአገራችን በበርካታ ወገኖች ዘንድ እንደሚታወቀው ያለውን ማካፈል የተለመደና የተቀደሰ ተግባር እንደገና የምንፈጽምበት ጊዜ አሁን ነው። ይህንን አምላካዊ የሆነ ነገር ትተን ከወዴት ይሆን ለራሴ ወገን፣ ለራሴ ሕዝብ፣ ለራሴ ዘር፣ … የሚል አጥፊ ነቀርሳ ውስጥ የገባነው? በተለይ እናንተ በህወሃት/ኢህአዴግ አማካኝነት ሥልጣን ከጨበጣችሁ በኋላ የራስ ወዳድነቱና ወገናዊነቱ መጠን እየከፋ ከመሄዱ የተነሳ ባሁኑ ወቅት ሲከሰት ማየት ምንም የማይገርም ነገር ሆኗል።
በአገራችን የተለመደው አብሮ የመካፈል ባህል የግራው አስተሳሰብ አቀንቃኞች እንደሚሉት ሃብትን ማሰራጨት አይደለም። የአንዱን ሃብት ወስዶ ለሌላው መስጠት በፍጹም ትክክለኛ ተግባር አይደለም፤ ሌላው ዓይነት ሌብነት ነው። የአገራችን ባህል ግን አብሮ መካፈልን ከፍቅር፣ ከለጋስነት፣ ከመተሳሰብ የመነጨና ወገናዊነትን የሚጻረር ነው። ኢትዮጵያችን አንዲህ ዓይነት ነበረች፤ አሁንም ተመልሳ እንዲህ መሆን ትችላለች። እንዲህ ዓይነቷን ኢትዮጵያ ውስጥ ለመኖር እኔም ሆንኩ ሌሎች የማይፈልጉበት ምንም ምክንያት የለም። ለመጪው ትውልድም ማውረስ የምፈልገው ይህንኑ ነው። እናንተስ? እውነትን መካድ ማንም አይችልም! ሥልጣን በወሰዳችሁበት ጊዜ አንድ ወርቃማ ዕድል አመለጣችሁ። ሌሎችን ሁሉ ማስተባበር ስትችሉ አሻፈረኝ አላችሁ። ደርግንም እንኳን ቢሆን ጨምሮ ለሁሉም መንገዱን መክፈት ስትችሉ የራሳችሁን ነጻ አውጪ ድርጅትና ዘር ብቻ ይዛችሁ ሁሉንም ከህወሃት እና ከትግሬ በታች ማድረጉን ተያያዛችሁበት። ብዙዎችን አስመረራችሁ፤ አስከፋችሁ። እናንተ በበረሃ ተሰማን ያላችሁትን ስሜት ባሁኑ ጊዜ በሚሊዮኖች በናንተ ላይ እየተሰማቸው ነው። “ብሶት የሚወልደው” እናንተን ብቻ እንዳልሆነ ታውቁታላችሁ፤ አገሪቷን ከሰሜንና ደቡብ እንዲሁም ከምስራቅና ምዕራብ በማጠርና በመድፈን “የማንበገር ሆነናል” ብትሉም “ብሶት የሚወልደው” እዚያው አራት ኪሎ አፍንጫችሁ ሥር ስላለመኖሩ አንዳች ማረጋገጫ ሊኖራችሁ አይችልም። ስለዚህ ቀን ሳለ፤ ጊዜ መልኩን ሳይቀይር አሁን ባላችሁ ዕድል ተጠቀሙ! ይህ ሳይሆን ቀርቶ እናንተ በሥልጣን ላይ ባላችሁበት ባሁኑ ወቅት ያልዘረጋችሁት ዕድል ዘመን ፊቱን ሲቀይር ለእናንተ የሚዘረጋላችሁ ይመሰልላችኋል?
እናንተ ለበቀል የነበራችሁ ዓይነት ምርጫ እኔ ሳይኖረኝ የቀረ አይምሰላችሁ! በእናንተ በህወሃት ታጣቂዎች የቅርብ ወገኖቼና ዘመዶቼ በጋምቤላ ተጨፍጭፈዋል፤ ደማቸው ፈሷል፤ ካገር ተሰድደዋል። ነገር ግን ከእኔ ብቀላና ጥላቻ በላይ የሆነችና የወደፊቱ ትውልድ በኔ የደረሰው ዓይነት እንዳይደርስባት የምመኛት ኢትዮጵያ በውስጤ ስላለችና ያችንም ኢትዮጵያ ለማየት ስለምመኝ የይቅርታ እና የዕርቅን አማራጭ መንገድ ተከትያለሁ። ለዚህም ነበር ለቀድሞው መሪያችሁ መለስ፣ ለትግሬዎችና ለሌሎች ኢትዮጵያውያን ከዚህ በፊት በላኩት ደብዳቤ ሁኔታዎችን ሁሉ ዘርዝሬ ለማስረዳት የሞከርኩት። ያንን በጻፍኩበት ወቅት በአገሪቷ ውስጥ በከፍተኛ ሁኔታ የተዛባ የሃብት ስርጭት መኖሩንና በተለይ የዚህ ዋንኛ ተጠቃሚ ትግሬዎች መሆናቸውን ጠቅሼ ነበር። ይህንን ከጻፍኩ በኋላ በርካታ የተለያዩ ምላሾችን ከትግሬዎች ያገኘሁ ሲሆን በዚህ አግባብነት በሌለው የሃብት ስርጭት ዙሪያ ትግሬዎች ስለመጠቀማቸው የሰበሰብኩትን ምላሽ በዚህ መልኩ ጠቅለል አድርጌ አቅርቤዋለሁ።
1. ሁሉም ትግሬ እኩል አልተጠቀመም፤ ብዙዎች ድሆች ናቸው እንደሌላው ኢትዮጵያዊ ዕርዳታ ይሻሉ፤
ይህ አስተሳሰብ እውነተኛ ነው ተብሎ ሊወሰድ ይችላል። ብዙዎቻችን ስለ ትግራይ ስናስብ ትግሬ የሆነ ሁሉ ደልቶታል፣ ተጠቀሟል በሚል ማጠቃለያ ሁሉንም በአንድ በመፈረጅ ስህተት እንፈጽማለን። በትግራይ የሚገኙትን ድሆች ለመርዳት ትልልቅ ፕሮጀክቶች ይካሄዳሉ፤ ይህ በመሠረቱ መልካም ነገር ነው፤ እንደ ዜጋ ቢረዱ ልንደሰት ይገባናል። ችግር የሚሆነው ግን “ትግራይ በጦርነት ተጎድቷል” እየተባለ ከሌሎች ክልሎች በተለየመልኩ ትግራይን ብቻ ለማልማት የሚደረገው አሰራር ፍጹም ኢፍትሃዊና ዘረኛ ነው። ለምሳሌ እኔ ራሴ በ1993ዓም በጋምቤላ የልማት ፕሮጀክት ለማቋቋም በምንቀሳቀስበት ጊዜ ወደ ትግራይ እንድሄድና እዚያ ኢንቨስት እንዳደርግ ግፊት ተደርጎብኝ ነበር። የተሰጠኝም ምክንያት “እዚያ በርካታ መረዳት ያለባቸው አሉ” የሚል ነበር። ባላውቅ ኖሮ እታለል ነበር፤ ነገር ግን ጥያቄውን ውድቅ አደረኩት።
ህወሃት ሥልጣን በመቆጣጠሩ ሁሉም ትግሬ ደልቶታል ማለት አይቻልም። ፕ/ር መስፍን ወልደ-ማርያም የወያኔ ጥላቻ ፍሬ በሚል ርዕስ በቅርቡ በጻፉት ጦማር እንዲህ ይላሉ፡- “የትግራይ ሕዝብ መደህየቱ አልበቃ ብሎት ሲለምንም እየተሳቀቀ ነው፤ የሚለምነው ትግሬ ለብዙ ሰዎች ትግሬና ወያኔ አንድ መስሎ እንደሚታየው ያውቃል፤ አብዛኛው ሰው በወያኔ ላይ ያለውን ስሜት ያውቃል፤ ስለዚህም ሲለምን ሰዎች በወያኔ ላይ ያላቸውን ስሜት ስለሚያራግፉበት እየተሸማቀቀ ነው፤ አንድ የትግራይ ቄስ ከአርሲ ነኝ አሉኝና ለምን እውነቱን አይናገሩም ስላቸው እውነቱን ስናገር የማገኘው ስድብ ብቻ ነው አሉኝ፤ እኒህ ሰው ምን በወጣቸው የወያኔን ኃጢአት ተሸካሚ ይሆናሉ፤ በሌላ በኩል ደግሞ በትግሬነቱ የተጠቀመ አለ፤ እኔ የማውቀው የደርግ ወታደር የነበረ ትግሬ ቆስሎ ከውትድርና ወጣና በአንድ የመንግሥት መሥሪያ ቤት የጥበቃ ሥራ ላይ ነበር፤ በጣም ይቸግረው ነበር፤ ሚስቱ ሕመምተኛ ነበረች፤ የቤት ኪራይ መክፈል ይቸገር ነበር፤ ዛሬ ግን የሚለብሰው ልብስ ሌላ ነው፤ ከኑሮውም ተርፎ ለሲጃራና ለጫት እያወጣ ነው፤ ወይም ሌሎች እያወጡለት ነው፤ ትግሬነታቸው ብቻ እንዲህ የደላቸው በጣም፣ በጣም ጥቂቶች ናቸው፤ ስለዚህም በወያኔ አገዛዝ ትግሬ ሁሉ ተጠቅሞአል ማለት ከጉልሁ እውነት ጋር የሚጋጭ ስሕተት ነው፤ አብርሃ ሰዎች ትግሬ ሁሉ ተጠቃሚ ሆኗል ሲሉ “ያመኛል” ማለቱ ይገባኛል።”
ከዚህ አንጻር ሁሉም ተጠቃሚ እንዳልሆነና የትግራይ ሰዎች የተገለሉ መሆናቸው ግልጽ ነው። ይህም የሆነው አፓርታይዳዊውን ሥርዓት በመቃወማቸው ሲሆን የተቀሩት ግን ከትክክለኛው ዘር – ከአድዋ – ባለመሆናቸው ነው።
2.  ህወሃት ደርግን አሸንፏል ስለዚህ ሽልማቱ ይገባናል፤
ይህንን አስተሳሰብ ከሚያራምዱት መካከል አንዱ ወገን በትግራይ ልማቱ እየተካሄደ መሆኑን እና ለትግራይ ሰዎችም የተሻለ ዕድል እንደተሰጣቸው ያምንና ይህ ሁሉ መሆን ያስፈለገው ትግሬዎች ይህ ስለሚገባቸው ነው የሚል ነው። ደርግን የተፋለሙት ሌሎቹስ? በእርግጥ ትግሬዎች ብቻ ናቸው ደርግን ያስወገዱት? ትልቁን ድርሻ ተወጥተው ይሆናል፤ ግን ሌሎችም በዘር ተደራጅተው ሲፋለሙ እንደነበር ታሪካቸው ይመሰክራል። ከእነዚህ መካከል የኦሮሞ፣ የኦጋዴን፣ የጋምቤላ፣ የሲዳሞ፣ የአፋር፣ የቤንሻንጉል፣ … አርነት ንቅናቄዎች ተጠቃሽ ናቸው። ሌሎች አናሳ ናቸው በሚል ቅድሚያ እንዳይኖራቸው ለማድረግ በምን ያህል ማነስ አለባቸው? ሌሎችን በኢትዮጵያዊነት ተጠቃሚ ላለማድረግ ምን ያህል በቁጥርና በመስዋዕትነት መብለጥ ይገባቸዋል? እናንተስ በምን ያህል መስዋዕትነት በልጣችሁ ነው የበላይነቱን ለመውሰድ የቻላችሁ? ወይስ በትጥቅ ትግሉ ዘመን የእናንተ የህይወት መስዋዕትነት ሌላው ከከፈለው ይበልጣል? መለስ እንዳለው “የወርቅ ዘር” ደም ከሌላው ስለሚበልጥ የማሸነፉ “ሽልማት” ይገባችኋል?
3.  አማራዎች ተመሳሳይ ነገር ፈጽመውብናል፤ በሥልጣን ካልቀጠልን ሌላው ተመሳሳይ ያደርግብናል፤
ይህ መከራከሪያ የተሳሳተ ብቻ ሳይሆን ከሞራልም አኳያ ውዳቂ ነው። በፈጣሪ ዘንድ እናንተ አደረጋችሁትም ሌሎችም በናንተ ላይ አደረጉት የሚለወጥ ነገር የለም፤ የሁሉንም በደል የሚመለከት ነውና። ይልቅ ይህ ዓይነቱ አስተሳሰብ ሌሎችን ለመጉዳት ሆን ተብሎ የተቀነባበረ ሴራ ነው። እንዲህ ያለው በራስ ወዳድነት የታጠረ አስተሳሰብ ነው ለዘመናት የአገራችንን ሕዝብ ሲያንገላታና ሲያሰቃይ የኖረው።
በቅድሚያ በአማራ ስም በደሉን የፈጸመና ኃላፊነት የወሰደ የለም። ሲቀጥል የቅርብ ታሪካችን ስንመለከት እናንተ በትግሬ ስም አገር አየገዛችሁት እንዳላችሁት እንደ እናንተ በአማራ ስም ድርጅትና ፓርቲ አቋቁሞ አገር የገዛ የለም። ለመሆኑ አማራ ብላችሁ የምትጠሩት የትኛውን ነው? ወይስ እናንተ እንደምትሉትና ከሟቹ መሪያችሁ አንደበት ሲነገር እንደሰማነው “የአማራ አስተሳሰብ” ነው? ይህ ሁሉ ይሁን እንበልና “አማራ ገዝቷልና … ” በሚለው ሃሳብ እንኳን ብንሄድ አሁን እናንተ እንዲህ አድርጋችሁ ስላፈናችሁት ወደፊት ጊዜውን ጠብቆ የጠጣውን ፍዳ የማያስከፍላችሁ ይመስላችኋል? ለዚህ ነው ይህ አስተሳሰብ ከሞራል አኳያ የዘቀጠ ነው ያልኩት።
ይልቁንም ባልንጀራህን/ጎረቤትህን እንደ ራስህ ውደድ በሚለው የላቀ መመሪያ መሠረት ሌሎች ለእናንተ ጊዜውን ጠብቀው እንዲቆሙላችሁ እናንተ አሁን ለሌሎች ልትቆሙ ይገባችኋል። ከዘራችሁ ሳጥን ወጥታችሁ፤ ይህ ተደርጎብናልና ይህንን እናደርጋለን ከሚል ጠባብነት ተላቅቃችሁ ለሰብዓዊነት መቆም ዋንኛ መመሪያችሁ ብታደርጉ ራሳችሁንና መጪውን ትውልድ ታተርፋላችሁ። እናንተም ብቻ ሳትሆኑም ሌሎችም በዘርና በጎሣ የጠበቡ ሁሉ ይህንን ሊያስተውሉትና ሊገነዘቡት ይገባል።
4.  ህወሃት ለወገኖቹ፣ ለዘሩ እና ለክልሉ የሚያደርገውን አድሎአዊነት በጭፍን የሚክዱ፤
በዚህ ሥር የሚጠቀሱት በአገሪቷ የሚካሄደውን አድሏዊነት ሽምጥጥ አድርገው የሚክዱ ናቸው። እስቲ በየክልሉ ያለውን ልዩነት እንመልከትና ራሳችሁ ፍርድ ስጡ። እጅግ በጣም ጥቂቱን ልጥቀስ።
የትግራይ ክልል
  • ዓለምአቀፋዊ የልማት ፕሮጀክቶች በቅድሚያ እንዲሄዱ የሚደረግበት
  • የኤፈርት ዋና ጽ/ቤት የሚገኝበትና በቅርቡ ዊኪሊክስ (ሹልክዓምድ) እንዳጋለጠው ለኢትዮጵያ ተብለው ለሚሰጡ ዓለምአቀፋዊ ዕርዳታዎችንና ድጎማዎችን ኤፈርት ለትግራይና ለህወሃት እንዲውሉ ያደረገበትና በሥሩ ያሉት ድርጅቶች በህወሃት ቁልፍ ሰዎችና ተባባሪዎቻቸው ቁጥጥር ሥር በመሆኑ ለትግራይ ክልል የተለየ እንክብካቤ የሚከናወንበት
  • የኢትዮጵያ ወታደራዊ ሥልጣን ዘጠና ስድስት በመቶ የሚሆነው በትግሬዎች ከመያዙ በላይ ወታደራዊ ተቋማት ዋና መሥሪያ ቤታቸው ያደረጉበት
  • ትግሬዎች ከአጠቃላይ የኢትዮጵያ ሕዝብ ስድስት በመቶ አካባቢ ሆነው ክልሉ ግን ከየትኛውም ክልል በበለጠ ሁኔታ ሆስፒታሎች፣ ዩኒቨርሲቲዎችና ሌሎች ተመሳሳይ ተቋማት የተከማቹበት መሆኑ
  • በአገሪቷ ብቸኛ የቴክኖሎጂ ተቋም ያለበት፤ ከሚወጡ መረጃዎች ለመረዳት እንደሚቻለው በዚህ ተቋም ለመግባት ትግሬ መሆን ወሳኝነት ያለው እንዲሁም በሌሎቹ የኢትዮጵያ ክልሎች ያለውን አሠራር ለመቆጣጠር ተማሪዎቹ ከትግሪኛ በተጨማሪ ኦሮምኛ፣ አማርኛ እና እንግሊዝኛ የሚናገሩ እንዲሆን መደረጉ እንዲሁም የተቋሙ በር ጠባቂዎች የቀድሞ ተመራቂዎች እንዲሆኑ በማድረግ በአገሪቷ ውስጥ ምንም ዓይነት ተቋም ተፎካካሪው እንዳይሆን የተደረገበት ክልል መሆኑ
  • በመንግሥታዊ መዋቅር ውስጥ ያሉት ከፍተኛ ባለሥልጣናት ከዚሁ ክልል የመጡበት መሆኑ
  • ኢህአዴግ ብላችሁ በፈጠራችሁት ድርጅት ውስጥ የትግራይ ክልል ሕዝብ ከበርካታዎቹ ጋር ሲነጻጸር አናሳ ሆኖ ሳለ ከአማራውና ከኦሮሞው ድርጅት ጋር በመሆን በማዕከላዊ ኮሚቴ ውስጥ ትግራይ ብቸኛ ተወካይነት እንዲኖረው የተደረገበትና ሌሎቹ በደቡብ ስም የተጠቃለሉበት የተቀሩት አምስት ክልሎች ከነጭራሹም ያልተወከሉበት አድሏዊነት በግልጽ የሚታይበት ክልል ነው።
ለመሆኑ ህወሃት/ኢህአዴግ በዘር ላይ የተመሠረ አፓርታይዳዊ ሥርዓት ነውን?
ይህንን ጥያቄ ለመመለስ በኢትዮጵያ ያሉትን ዋንኛ ተቋማት ማን እንደሚቆጣጠር መመልከቱ በቂ ይመስለኛል። ዝርዝሩ እዚህ ላይ ይገኛል (http://www.solidaritymovement.org/downloads/140731-leaders-key-institutions-in-Ethiopia.pdf) እስቲ ተመልከቱትና ለራሳችሁ ወስኑ! እንደምትሉት በእውነት ኢትዮጵያ “የብሔር ብሔረሰቦች እኩልነት የተረጋገጠባት” ነች ወይስ የ-ተ-ረ-ጋ-ገ-ጠ-ባ-ት ነች? የፌዴራል ጉዳዮች ሚ/ር፣ የውጭ ጉዳይ ሚ/ር፣ የፍትሕ ሚ/ር፣ የብሔራዊ ደኅንነት አገልግሎት (NISS)፣ የመገናኛና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ሚ/ር (MCIT)፣ ፌዴራል ፖሊስ፣ የመከላከያ ሚ/ር፣ የፋይናንስና ኢኮኖሚ ልማት ሚ/ር፣ የገቢዎችና ጉምሩክ ባለሥልጣን፣ የሬዲዮና ዜና አገልግሎት – እነዚህ ሁሉ ታላላቅ ተቋማት የአገሪቱን ስድስት በመቶ በሚወክሉ ትግሬዎችና የህወሃት አባላት ቁጥጥር ሥር ያሉ ናቸው።
tplf eprdfከእነዚህም ሌላ ሌሎች አስፈላጊ የሆኑ ድርጅቶች፣ የሲቪክ ማኅበረሰቦች፣ … በትግሬዎች፣ በህወሃት አባላት፣ በህወሃት ደጋፊዎች፣ … በሞኖፖል የተያዙ ናቸው። እንደ ጠ/ሚ/ር ኃይለማርያም ደሳለኝ ከሌላ ዓይነት ወገን የሆኑ ሰዎች ሥልጣኑን በሚይዙበት ጊዜ አቅራቢያቸውን በሙሉ በትግሬዎች በማጠር እውነተኛውን ሥልጣን በእናንተ እጅ ይወድቃል።
እንደሚታወቀው ነጻ የሆኑ ተቋማት በአንድ ነጻና የተረጋጋ ማኅበረሰብ ውስጥ ወሳኝነት ያላቸው ናቸው። ከዚህ አንጻር እንደነዚህ ያሉ ድርጅቶች ብቃት ባላቸውና ነጻ በሆኑ ግለሰቦች መመራታቸው ከአድልዖ የጸዱ እንዲሆኑ ያደርጋቸዋል። በአምባገነን ሥርዓቶች ግን እንዲህ ያሉትን ተቋማት በሥልጣን ባሉት ጥቂት ግለሰቦች ወይም በተላላኪዎቻቸው እንዲያዙ በማድረግ የሥልጣን ዘመናቸውን ለማስረዘም የሚጠቀሙበት ዓይነተኛ መሣሪያ ነው። ከዚህ ጋር ተያይዞ ሙስና፣ ወገናዊነት፣ ኢፍትሐዊነት፣ ጭቆና፣ … እየተስፋፋ እንዲሄድ የሚያደርግ ከመሆኑ ኅብረተሰቡ በተቋማቱም ሆነ በመሪዎቹ ላይ ያለው እምነት እየተመናመነ ይሄዳል።
በዘር ላይ የተመሠረተ አፓርታይዳዊ ሥርዓት የሚያራምዱ ሁሉ ቁልፍ የሆኑ የሥልጣን ቦታዎችን በአንድ ዘር ወይም ጎሣ አባላት ወይም የአንድ ዘር አባላት በመሠረቱት ፓርቲ ወይም ድርጅት አባላት ብቻ እንዲያዙ ያደርጋሉ። እንዲህ ያሉት ዘረኛ ጥቅመኞች ለሚከፍሉት ታማኝነት በምላሹ ከፍተኛ ሥልጣን፣ ሹመት፣ ዕድልና ሌሎች ጥቅማጥቅሞች እንዲያገኙ ይደረጋሉ። ይህ ሲሆን ያላቸው ታማኝነት በየጊዜው እየተለካ የሚያገኙት ጥቅም በዚሁ መልኩ እየጨመረ እንዲሄድ ይደረጋል። ከዚህ አንጻር ህወሃት/ኢህአዴግ በዘር ላይ የተመሠረተ አፓርታይዳዊ ሥርዓት የሚከተል ለመሆኑ ራሳችሁ ፍርዱን እንድትሰጡ እጠይቃችኋለሁ። ይህንን ጽሁፍ (http://www.solidaritymovement.org/downloads/140731-leaders-key-institutions-in-Ethiopia.pdf) ብትመለከቱ በአገሪቷ ውስጥ ያሉትን ተቋማት ማን እየመራቸው እንደሆነና ከየትኛው ዘር እንደሆነ በግልጽ ልትመለከቱት ትችላላችሁ። ይህ ሕዝብ የሚያውቀው መረጃ ነው፤ የፈለገውን የብሔር ብሔረሰቦች መብት ተከብሯል ብትሉም ኢትዮጵያን በአፓርታይዳዊ የዘር ሥርዓት እየገዛችሁ መሆኑን ልትሸሽጉ ከቶውንም አትችሉም።
እነዚህን ሁሉ ማስረጃዎች እየዘረዘርኩ ለመናገር የሞከርኩት ከተያዛችሁበት የዘረኝነት፣ የወገናዊነት፣ የጠባብነት፣ የጎጠኝነት እና ሁሉን ለኔ ወይም ለዘሬ ከሚል ስግብግብነት በሽታዎች እንድትላቀቁ ነው። በዚህ ነጥብ ላይ የምለምናችሁ ነገር የለም። ከእነዚህ የዘመናት በሽታዎች ብትላቀቁ ራሳችሁንና መጪውን ትውልዳችሁን ታድናላችሁ። ከኅሊና ፍርድ ነጻ ትሆናላችሁ። ተዋግተንለታል የምትሉት ዘራችሁን በጭፍን ከመፈረጅ አድናችሁ አንገት ከመድፋትና በእናንተ ግፍ መላውን የትግራይ ሕዝብ ከማስወንጀልና ይህንን ተከትሎ ሊነሳ ከሚችል በቀል ትታደጉታላችሁ።የኢትዮጵያ ሕዝብ ለ23 ዓመታት መከራውን ስታበሉት ስለኖራችሁ ከዚህ በኋላ የሚያጣው ብዙም ነገር አይኖርም። ለእናንተና ለዘራችሁ ግን ብዙ እጅግ ብዙ የምታጡት አለ። መጠኑ የማይለካ ፍዳ ቁጭ ብሎ እየጠበቃችሁ ነው። ከሰው ብታመልጡ ከፈጣሪ ፍርድ አንዳች የሚያመልጥ የለምና ጊዜ ፊቷን ያዞረችባችሁ ቀን እንዲህ ዓይነቱን የምህረት ተግሳጽ የትም ብትፈልጉት አታገኙትም።
ከዚህ መሰሉ መቅሰፍት ለማምለጥ እንድትችሉ በዋንኛ ኃላፊነት ላይ የምትገኙት የማዕከላዊ ኮሚቴ አባላት ቀዳሚው ስትሆኑ እናንተን የሚደግፉት የትግራይ ተወላጆች በሙሉ ቀጣዩ ኃላፊነት የወደቀባቸው ናቸው። በሦስተኛነት በኢህአዴግ ስም ከእናንተ ጋር ተቀላቅለው የሚሰሩት – የኦሮሞ፣ የአማራና የደቡብ ሰዎች – እንዲሁም ሌሎች ለጥቅም ያደሩ፣ ኅሊናቸውን የሸጡ ኢትዮጵያውያን ኃላፊነት ነው።
ከዚህ ሌላ በፍጹም መዘንጋት የሌለባቸው አሉ። ከእነዚህም መካከል ጋሻ ለኢትዮጵያ ያለውን ችግር በግልጽ ከመናገር አኳያ ቀዳሚው ነው። በግለሰብ ደረጃ ቀድሞ የህወሃት አባል የነበሩትና የህወሃትን አደገኛ አካሄድ ካወቁበት ጊዜ ጀምሮ እስካሁን አቅጣጫውን እንዲቀይር በአደባባይ የሚመሰክሩት አቶ ገብረመድኅን አርአያ፣ ከአገር ውስጥ ሆነው በብዙ መከራና ስቃይ ውስጥ እንኳን እውነትን ከመናገር ወደኋላ የማይሉት፣ እሳቸውና ልጆቻቸው ቢታሰሩም፣ ስቃይ ቢቀበሉም በዓላማቸው የጸኑት አዛውንት አቶ አሰግደ ገብረሥላሴ፣ ደፋሩና አስተዋዩ ወጣት የኮሌጅ መምህር በዘር መጠጥ ያልሰከረውና እናንተን ህወሃቶች በትግራይ ሕዝብ ስም የምታደርጉትን በመቃወም ሌሎቹን ትግሬዎችን “ይህ በኔ ስም መደረግ የለበትም” ብለው እንዲሟገቱ በድፍረት በመናገሩ በግፍ ያሰራችሁት አብርሃ ደስታ ለብዙዎች መዳኛ ይሆኑ ዘንድ የሚጠቀሱ ናቸው።ፕ/ር መስፍን ወልደ-ማርያም እንዳሉት እኔም “አሥር ቢሞሉልኝ ደስ ይለኝ ነበር!” ጥቂትም ቢሆኑ የራሳችሁ ወገኖች የሆኑ እና ከራሳችሁ ድርጅት ጋር ሲሰሩ የነበሩ ምስጢራችሁን ሁሉ የሚያውቁት በግልጽ እየተናገሩ ከጥፋት መንገዳችሁ እንድትመለሱ ሲመክሯችሁ እምቢ በማለት ለእስር ስትዳርጉ ከቶውንም አታፍሩም?! ወዮ የምትሉበት ጊዜ አሁን ነው። ጊዜ ሳያልፍ፤ ቀን ሳይጨልም!
ከትግራይ ማኅበረሰብ በርካታዎች እናንተ የምታደርጉትን አፓርታይዳዊ የዘር ፖሊሲ እንደሚቃወሙ አምናለሁ፤ ነገር ግን በገሃድ ወጥተው ለመቃወም እንደሚፈሩ አስተውላቸኋለሁ። የሌሎች ፍርሃቻ ደግሞ ህወሃት ከሥልጣን ከወረደ ማን ይተካዋል የሚል ነው። ለዚህም ነው የትግሬዎች በይፋ መውጣትና ኃላፊነት በመውሰድ ለመፍትሔ መነሳት አስፈላጊ የሆነው። ዝምታው ድጋፍ ከመስጠት ተለይቶ አይታይምና።
እንዲሁም ከተለያዩ ክፍሎች የሆናችሁ ኢትዮጵያውያን በሙሉ ራሳቸውን በማነጽ ለልጆቻቸውና ለመጪው ትውልድ መልካም ለማድረግ የሚነሱትን ትግሬዎች መደገፍ እንደሚገባችሁ ላሳስብ እወዳለሁ። ስለሌሎች “እነሱ” እያሉ ከማውራት ይልቅ “እኛ” እያላችሁ ለሁሉም የሚሆን መፍትሔ እንዲመጣ እንድትወያዩና እንድትቀራረቡ ይሁን። ከፈጣሪ የተሰጠንን ልዩ መብት የምታከብር አገር ለሁላችንም የምትሆን ኢትዮጵያ እንድትኖረን ውይይቱ ይጀመር። የአንዱ ጉዳት የሁላችንም ሆኖ ይሰማን፤ በ“እኔ ከሞትኩ …” ጭፍን አስተሳሰብ አንታወር፤ መልሶ የራሳችንን የአስተሳሰብ ዓይን ያጠፋዋል። ስለዚህ ሁላችንም እንደ አንድ ትልቅ ቤተሰብ ተከባብረንና ተሳስበን ለመኖር የምንችልባት አገር ለመሥራት እንትጋ።
የህወሃት ማዕከላዊ ኮሚቴ እነዚህን ሁሉ ችግሮች የማያርም ከሆነ ጉዳዩ በርትቶ ወደ ዓመጽ ተቀይሮ ከፈነዳ በኃላፊነት የምትጠየቁት ራሳችሁ ናችሁ። ፍርዳችሁንም ከሁሉም መስመር ትቀበላላችሁ። ይህንን ዓይነቱን ማስጠንቀቂያ ደቡብ አፍሪካውያን አሻግረው ተመለከቱትና በተግባር አዋሉት፤ ሩዋንዳውያን ግን ሰምተው ዝም አሉ። ውሳኔ አለመስጠት በራሱ ውሳኔ ነው። ስለዚህ እናንተም በህወሃት ማዕከላዊ ኮሚቴ ያላችሁ ይህንን ማስጠንቀቂያ ችላ ልትሉት ትችላላችሁ፤ አላወቅንም ማለት ግን በጭራሽ አትችሉም። ሁሉ ይቅርና ይህ ደብዳቤ ራሱ በበቂ ማስረጃነት ይቀርብባችኋል፤ ለዚህም እንዲያግዝ የእንግሊዝኛውም ሆነ ይህ ትርጉም ለመንግሥታት፣ ለሚዲያ ተቋማት፣ ለዓለምአቀፍ ድርጅቶች፣ … በግልባጭ እንዲደርስ ተደርጎ በሰነድነት ተቀምጧል፤ በጊዜው እንዲወጣ ይደረጋል። የዚያን ጊዜ የት ትሸሸጋላችሁ?
ህወሃትን ለምትቃወሙ የትግራይ ወንድሞችና እህቶቻችን፤
ለስኬት ለመብቃት እና ህወሃት ለ23 ዓመታት የመሠረተውን የጥላቻና የዘር ግምብ ለማፍረስ ጠለቅ ያለ ከልብ የሆነ መሠረታዊ ለውጥ ያስፈልጋል። ህወሃት በሚለው መጠሪያ ውስጥ “ትግራይ” ተጠቅሷል። ይህ ደግሞ እናንተን ሁሉ የሚጠቀልል ነው። ስለዚህ ይህንን የህወሃት ፖሊሲ የማትደግፉ ከሆነ ድምጻችሁን ከፍ አድርጋችሁ “ይህ በኔ ስም አይሆንም” ማለት አለባችሁ።
እውነትን በቤታችሁንና በትናንሽ ቡድኖቻችሁ ውስጥ ሳይሆን በገሃድ የምትናገሩበት ጊዜ አሁን ነው። ሊፈነዳ ደቂቃውን እየቆጠረ ያለውን ቦምብ ማክሸፍ የሚቻለው “ቦምብ የለም” ብሎ በማስመሰል፤ ወይም “ሁሉም ሰላም ነው” በማለት አይደለም። ለጥፋታችን ሌላውን በመወንጀል ብቻ እውነትን ሳንናገር ተሸሽገን እንዴት ነው ለሁላችንም የምትሆን ኢትዮጵያ መመሥረት የምንችለው? “አልሰማም” ብለን ጆሮአችንን ከመስማት ብናርቅ እውነትን ልናመልጥ እንዴት እንችላለን? ልባችንን ብናደነድን፣ ብናሳብጥ፣ ስህተታችን ከማረም ብንታቀብ፣ ጥለን ብንሄድ፣ እውነትን በተጋፈጥን ቁጥር በንዴትና በቁጣ ምላሽ ብንሰጥ፣ … ምን ይረባል? ከእውነት እውነተኛነትስ እንዴት መሸሽ ይቻላል? በህወሃት ሲደሰኮር የቆየውና በአሁኑ ጊዜ በኢትዮጵያችን የሚታየው “ቅድሚያ ለዘሬ” የሚለው አመለካከት ሌላው የመጥበብ ፖለቲካ ውጤት ነውና የትም አያደርስም። በወቅቱ የንዴት ማብረጃና የበቀል መወጫ መስሎ ቢወሰድም ለመጪው ትውልድ ግን የማይጠፋ እሣት ነው የሚለኩሰው።
ስለዚህ በትግራይ ማኅበረሰብ ውስጥ ያላችሁትን ሁሉ የአንድ ዘር የበላይነትን የማትደግፉ የለውጥ ሐዋሪያት በመሆን ለእርቅ እና ለፍትሕ እንዲሁም ለእውነተኛ ተሃድሶ ፈርቀዳጅ እንድትሆኑ ላደፋፍራችሁ እፈልጋለሁ። የዘር በሽታውን ለማምከን የመጀመሪያው ሥራ መሥራት የሚገባችሁ እናንተ ናችሁ። ልትግባቡና ልትተማመኑ በምትችሉበት መንገድ በመነጋገር አንድ አቋም ላይ መድረስ አለባችሁ። ማኅበራሰባችሁን ማነጋገርና ማሳመን የእናንተ ቀዳሚ ኃላፊነት መሆን ይገባዋል። መተማመንን ማዳበር የምትችሉት እናንተ ናችሁ። ከዚያም ከሌሎች ጋር ለመነጋገርና ለመወያየት በር እየተከፈተ ይሄዳል። የዕርቅ መሠረትንም መዘርጋት የሚቻልበትን ሁኔታ ማመቻቸት ያስችላል። ራሳችሁን ነጻ አውጥታችሁ ለሌሎች ነጻነት በጽናት የምትቆሙበት ወቅት ቢኖር አሁን ነው፤ ይህንን አዲስ ዓመት ለዚህ ዓላማ ተጠቀሙበት።
ሌሎችም በዘር ላይ የተመረኮዘ እንቅስቃሴ የምታደርጉ ራዕያችሁን በማስፋት መላው የኢትዮጵያ ሕዝብ ነጻ እስካልወጣ ድረስ የራሳችሁን ዘር ብቻ ነጻ ማውጣት እንደማትችሉ መገንዘብ ይኖርባችኋል። ስለዚህ ከእናንተም የሚጠበቀው ከትግራይ ወገኖች ከሚጠበቀው ያነሰ አይደለም።
በህወሃት አመራር ያላችሁ በሙሉ፤ ይህንን ግልጽ ደብዳቤ በራሴና በአዲሲቷ ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄ ስም ልኬላችኋለሁ። ከሰከራችሁበት የዘር ፖለቲካ የምትነቁ ከሆነ በጣም ጥቂት የሆነውን በዚህ ደብዳቤ ለማስፈር ሞክሬአለሁ። ለመንቃት ለሚፈልግ ከበቂ በላይ ነው። አንገት በማደንደን፣ ልብ በማሳበጥና በትዕቢት በመወጠር የጀመርነውን እንቀጥላለን የምትሉ ከሆነ ውሳኔው የራሳችሁ ነው። ሁሉም ነገር ግን ጊዜውን ጠብቆ ለፍርድ ይቀርባል። “ነጻ አውጪ” ነን በሚል ድንፋታ ብትቀጥሉ ከሁሉ የሚበልጠው የነፍስ ነጻነት እንደሆነ ልታውቁ ይገባችኋል። ይህ ደግሞ በነጻ አውጪ ግምባር የሚመጣ አይደለም።
ከዚህ ሁሉ በላይ በደልን የሚቆጥርና ግፍን የሚመልስ ፈጣሪ አለ። የበቀል ሰይፍ ከመመዘዙ በፊት አምላክ ለሁላችንም የማስተዋል አእምሮ ይስጠን። እውነትን በድፍረት የምንናገር፣ የዘር ቦምብ የምናከሽፍ፣ ለጎረቤታችን የምንራራ፣ በፍቅርና በትህትና የምንመራ፣ ለፍትሕ፣ ለይቅርታና ለዕርቅ የምንሰራ፣ ከጥላቻ ይልቅ የመቻቻልን መንፈስ የምናራምድ ያድርገን። ይህ ሲሆን ብቻ ነው ለሁላችንም እና ለመጪው ትውልድ የምትሆን አዲስ ኢትዮጵያ የምትኖረን። ልቦና ይስጠን!
መልሳችሁን እጠብቃለሁ።
አክባሪ ወንድማችሁ፤
ኦባንግ ሜቶ
ዋና ዳይሬክተር፤ የአዲሲቷ ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄ (አኢጋን)
አድራሻ፡ 910- 17th St. NW, Suite 419.
Washington, DC 20006 USA
Email: Obang@solidaritymovement.org.  Website: www.solidaritymovement.org
smne banner1
ይህ ደብዳቤ ለሚከተሉት ግልባጭ ተደርጓል፡-  ለጠ/ሚ/ር ኃይለማርያም ደሳለኝ፣ ለኢህአዴግ፣ ለኦህዴድ፣ ለብአዴን፣ ለደኢህአዴን እና ለህወሃት ማዕከላዊ ኮሚቴ አባላት፣ ለኢትዮጵያ ተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲዎች፣ ለኢትዮጵውያን የሲቪክና የሰብዓዊ መብት ድርጅቶች፣ ለሃይማኖት መሪዎች፣ በዳያስፖራ ለሚገኙ ድርጅቶች፣ የእንግሊዝኛው ቅጂ ለአሜሪካው ፕሬዚዳንት ባራክ ኦባማ፣ ለውጭ ጉዳይ ሚ/ር ጆን ኬሪ፣ ብሔራዊ ደኅንነት አማካሪ ሱዛን ራይስ፣ ምክትል የብሔራዊ ደኅንነት አማካሪ በስትራቴጂክ ግንኙነት ዘርግ ቤን ሮድስ፣ በውጭ ጉዳይ ሚ/ር የዴሞክራሲ፣ ሰብዓዊ መብትና ሠራተኞች ጉዳይ ረዳት ጸሃፊ ቶም ማሊኖውስኪ፣ በብሔራዊ ደኅንነት ም/ቤት የአፍሪካ ጉዳዮች ከፍተኛ ዳይሬክተር ግራንት ሃሪስ፣ በብሔራዊ ደኅንነት ም/ቤት የልማትና የዴሞክራሲ ከፍተኛ ዳይሬክተር ጌይል ስሚዝ፣ በውጭ ጉዳይ ሚ/ር የአፍሪካ ጉዳዮች ቢሮ ረዳት ጸሃፊ አምባሳደር ሊንዳ ቶማስ-ግሪንፊልድ፣ ለዩኤስ ኤይድ ረዳት አስተዳዳሪ ኧርል ጋስት፣ በአሜሪካ ሕግመወሰኛ ምክርቤት የውጭ ጉዳዮች ኮሚቴ ሊቀመንበር ሮበርት ሜኔንዴዝ፣ የውጭ ጉዳይ ኮሚቴ ከፍተኛ አባል ቦብ ክሮከር፣ በሕግ መወሰኛ ም/ቤት የአፍሪካ ጉዳዮች ንዑስ ኮሚቴ ሊቀመንበር ክሪስቶፈር ኩንስ፣ ለሌሎች የሕግ መወሰኛ ም/ቤት ከፍተኛ አባላት (ሴናተሮች) ሚች ማኮኔል፣ ዳያን ፋይንስታይን፣ ጆን ማኬይን፣ ሪቻርድ ደርቢን፣ ኤድዋርድ ሮይስ፣ በእንደራሴዎች ም/ቤት የውጭ ጉዳይ ኮሚቴ የአፍሪካ ጉዳይ ንዑስ ኮሚቴ ሊቀመንበር ክሪስቶፈር ስሚዝ፤ ለእንግሊዝ የውጭ ጉዳይ ሚ/ር፣ ለአውሮጳ ማህበር የውጭ ጉዳይ ኮሚቴ ሊቀመንበር፣ ለጀርመን የውጭ ጉዳይ ሚ/ር፣ ለኖርዌይ የውጭ ጉዳይ ሚ/ር፣ ለአፍሪካ ኅብረት፣ ለአውሮጳ ኅብረት፣ ለአውሮጳ ኮሚሲዮን፣ ለካናዳ መንግሥት፣ ለታላቋ ብሪታኒያ መንግሥት፣ ለካናዳ ዓለምአቀፍ ተራድዖ ድርጅት (ሲዳ)፣ ለአሜሪካ የዓለም አቀፍ ልማት ተቋም (ዩኤስኤይድ)፣ ለእንግሊዝ ዓለምአቀፍ ልማት መምሪያ፣ ለጃፓን የዓለምአቀፍ ትብብር ባንክ፣ ለጃፓን ዓለምአቀፍ ትብብር ኤጀንሲ፣ ለቻይና ዓለምአቀፍ ትብብር ካውንስል፣ ለህንድ ዓለምአቀፍ ልማት ትብብር ኤጀንሲ፣ ለህንድ ኤግዚም ባንክ፣ ለቻይና ኤግዚም ባንክ፣ ለዳኒሽ ዓለምአቀፍ ልማት ኤጀንሲ (ዳኒዳ)፣ ለፊንላንድ ዓለምአቀፍ ልማት ትብብር (ፊኒዳ)፣ ለፈረንሣይ ዓለምአቀፍ ትብብር መምሪያ፣ ለፈረንሣይ ልማት ኤጀንሲ፣ ለጀርመን ዓለምአቀፍ ልማት፣ ለኔዘርላንድስ የልማት ትብበር ሚ/ር፣ ለኖርዌይ ዓለምአቀፍ ልማት ኤጀንሲ (ኖራድ)፣ ለስዊድን ዓለምአቀፍ ልማት ትብብር (ሲዳ)፣ ለስዊዝ ዓለምአቀፍ ልማት ኤጀንሲ፣ ለቱርክ ዓለምአቀፍ ልማት ትብብር ኤጀንሲ (ቲካ)፣
ለሚከተሉት የተለያዩ ድርጅቶችና መ/ቤቶች ግልባጩ ተልኳል፡- Amnesty International, Human Rights Watch, International Commission of Jurists (ICJ), Physicians for Human Rights, The International Justice Resource Center (IJRC), The African Court of Justice and Human Rights, International Criminal Court (ICC), International Justice Project, United to End Genocide, Humanity United, Never Again Coalition, GlobalSolutions.org, The World Council of Churches (WCC), ACTION AID, AFRICA HERITAGE FOUNDATION, AFRICA LEGAL AID, AFRICAN DEVELOPMENT ASSOCIATION, ALLIANCE FOR FINANCIAL INCLUSION, BUSINESS ACTION AGAINST CORRUPTION, CARE INTERNATIONAL, CATHOLIC AGENCY FOR OVERSEAS DEVELOPMENT, CENTER FOR INTERNATIONAL PRIVATE ENTERPRISE, CORRUPTION WATCH, COUNCIL ON FOREIGN RELATIONS, CREATE TRUST, DEMOCRACY WATCH, FORD FOUNDATION, FREEDOM NOW, Free Africa Foundation, GENOCIDE WATCH, Global Advice Network, GLOBAL HUMAN RIGHTS DEFENSE, Global Integrity, INTERNATIONAL CRISIS GROUP, INTERNATIONAL LEGAL ALLIEANCE, Least Developed Countries Watch (LDC Watch), MELINDA & GATES FOUNDATION, Development Research Institute NYU, THE AFRICAN CHAMBER OF COMMERCE IN THE US, THE AFRICAN INSTITUTE OF CORPORATE CITIZENSHIP, The Bertelsmann Foundation, THE COMMONWEALTH BUSINESS COUNCIL, THE CORPORATE COUNCIL ON AFRICA, THE FINANCIAL ACTION TASK FORCE (FATF), THE GLOBAL CLEARINGHOUSE FOR DEVELOPMENT FINANCE, TRANSPARENCY INTERNATIONAL, TRUST Africa, U.K. Anti-Corruption Forum, Overseas Development Institute UK, OXFAM, PARTNERSHIP AFRICA CANADA, PAC, World Vision International, World Accord, HOPE International Development Agency, CARE- Cooperative for Assistance and Relief, Africa Governance Monitoring and Advocacy Project (AfriMAP), AFRICAN DEVELOPMENT BANK, AFRICAN UNION, The African Economic Community (AEC)-AU, Common Market for Eastern and Southern Africa (COMESA), East African Court of Justice (EAC), BANK FOR INTERNATIONAL SETTLEMENTS,ECONOMIC COMMISSION FOR AFRICA (ECA), INTERNATIONAL FUND FOR AGRICULTURAL DEVELOPMENT (IFAD), INSTITUTE FOR INTERNATIONAL COOPERATION AND DEVELOPMENT (IICD), Multilateral Investment Guarantee Agency-World Bank, INTERNATIONAL BANK FOR RECONSTRUCTION AND DEVELOPMENT WORLD BANK, International Monitory Fund (IMF), INTERNATIONAL LABOUR ORGANIZATION, Investment Climate Facilities for Africa Trust (ICF), ORGANIZATION FOR ECONOMIC CO-OPERATION AND DEVELOPMENT, Development Assistance Group (DAG), United Nations (UN)-Sectary, United Nations Human Rights Council, United Nations Development Programme (UNDP), United Nations Conference on Trade and Development (UNCTAD), Multilateral Investment Guarantee Agency, United Nations Industrial Development Organization UNIDO, Jeffrey Sachs (earth institute), Kofi Annan (Africa progress panel)
የደብዳቤው ግልባጭ ከዚህ በታች ለተዘረዘሩት በአዲስ አበባ ለሚገኙት ኤምባሲዎች አምባሳደሮች በስማቸው ተልኳል፡- ለአሜሪካ፣ ለታላቋ ብሪታኒያ፣ ለስዊድን፣ ለፈረንሣይ፣ ለእስራኤል፣ ለዴንማርክ፣ ለፊንላንድ፣ ለሩዋንዳ፣ ለካናዳ፣ ለብራዚል፣ ለሕንድ፣ ለኬኒያ፣ ለጀርመን፣ ለጣሊያን፣ ለአውሮጳ ኅብረት፣ ለአውስትራሊያ፣ ለቱርክ፣ ለስዊትዘርላንድ፣ ለጃፓን፣ ለዴሞክራቲክ ሪፑብሊክ ኮሪያ፣ ለኢንዶኔዢያ፣ ለሳውዲ አረቢያ፣ ለሩሲያ ፌዴሬሽን፣ ለኖርዌይ፣ ለታንዛኒያ፣ ለግብጽ፣ ለቤልጂየም፣ ለጅቡቲ፣ ለሱዳን፣ ለቻይና ፣ ለደቡብ አፍሪካ እና ለኔዘርላንድስ ኤምባሲ አምባሳደሮች።
ለአገር ውስጥና ለውጭ የሚዲያ ተቋማት እንደ ቋንቋው ተጠቃሚነታቸው ተልኳል። እነዚህም፡ Africa Confidential, Al Jazeera, BBC, the Guardian, New York Times, Washington Post, Wall Street Journal, Bloomberg News, MSNBC, CNN, INDIAN OCEAN NEWSLETTER, REUTERS AFRICA, The East Africa, Business Daily, African Review, Deutsche Welle Radio, VOA Amharic, VOA-English, ESAT, Addis Fortune, ለሪፖርተርና ለሌሎች በአገር ውስጥ እና በዳያስፖራ ለሚገኙ ድረገጾች፣ የራዲዮ ፕሮግራሞች፣ መጦመሪያዎች፣ ወዘተ።

ጥቃቅንና አነስተኞች ቀጣዩን ምርጫ ‹እንዲያሳኩ› ታዘዙ

September 25,2014
• ‹‹ቃላችንን ካጠፍን የመለስን ቀን ይስጠን›› ባለስልጣናቱ

ከመስከረም 10/2007 ዓ.ም እስከ መስከረም 12/2007 ዓ.ም በጥቃቅንና አነስተኛ ለተደራጁ የአዲስ አበባ ነዋሪዎች በተሰጠው የ‹‹አብዮታዊ ዴሞክራሲ›› የማጥመቅ ስልጠና በምርጫው ንቁ ተሳትፎ በማድረግ ኢህአዴግ እንዲመረጥ እንዲሰሩ ትዕዛዝ እንደተሰጣቸውና እቅዱን ካላሳኩ ሸዳቸውን መስሪያ ቦታውን እንደሚያጡ ማስጠንቀቂያ እንደተሰጣቸው ለነገረ ኢትዮጵያ ገለጹ፡፡

ሰልጣኞቹ ‹‹ግብር በዝቶብናል፣ ደንብ አስከባሪዎች በየጊዜው እየመጡ ገንዘብ ይወስዱብናል፣ በየወረዳው የመልካም አስተዳደር ችግር መፍትሄ ልናኝ አልቻልንም፣ ስለዚህ እናንተን እንዴት ነው የምንመርጠው? በየምርጫው ቃል ትገባላችሁ? ካለፈ በኋላ ትረሱናላችሁ እንዴት እነመንላችሁ?›› ሲሉ ቅሬታቸውንና በገዥው ፓርቲ እምነት እንደሌላቸው መግለጻቸውን ምንጮች ለነገረ ኢትዮጵያ ገልጸዋል፡፡

በሌላ በኩል በስልጠናው የተገኙት ባለስልጣናት ገዥው ፓርቲ ቃሉን እንደሚያከብርና በአነስተኛና ጥቃቅን የተደራጁት ዜጎች የተባሉትን ስራ ካከናወኑ ተጠቃሚ እንደሚሆኑ ቃል ገብተውላቸዋል ተብሏል፡፡ ተሰብሳቢው በተደጋጋሚ ችግሮችንና ኢህአዴግ ቃል ገብቶ የማይተገብራቸውን ነገሮች በማንሳታቸው በስልጠናው ከተገኙት ባለስልጣናት መካከል አንዱ ‹‹ቃላችንን አናጥፍም፣ ቃላችንን ካጠፍን የመለስን ቀን ይስጠን›› ብለው እንደማሉ ሰልጣኞቹ ለነገረ ኢትዮጵያ ገልጸዋል፡፡

ሰልጣኞቹ በስተመጨረሻም የምስክር ወረቀት የተሰጣቸው ቢሆንም የምስክር ወረቀቱ ላይ የሰፈረውና የሰለጠኑት ግንኙነት እንደሌላቸው ተናግረዋል፡፡ ቀደም ሲል፣ ከስልጠናው በፊት በስልጠናው ያልተገኘ በሸድ ስራ እንደማይቀጥል የማስጠንቀቂያ ደብዳቤ ደርሷቸው እንደነበር ሰነዱን አያይዘን መዘገባችን ይታወሳል፡፡
ነገረ-ኢትዮጵያ

Wednesday, September 24, 2014

ዳኞቹ የኢህአዴግ አባል እንዲሆኑ እንደሚገደዱ ገለጹ

September 24,2014
ከሳምንት በፊት በአቶ በረከት ስምኦን የተከፈተውና 15 ቀን የሚፈጀው የ‹‹ፍትህ አካላት›› ባህር ዳር ላይ እያደረጉት በሚገኘው ስብሰባ ላይ ዳኞች ቅሬታቸውን እንዳሰሙ የነገረ ኢትዮጵያ ምንጮች ገለጹ፡፡
ልማታዊ መንግስት ግንባታ ላይ ያተኮረ ነው በተባለው ስልጠና ላይ የክልሉ የከፍተኛ ፍርድ ቤት ዳኞች፣ በክልሉ የሚገኙ ወረዳዎች የህግ ጉዳይ የስራ ሂደት አስተባባሪዎች፣ የክልሉ ማረሚያ ቤቶች፣ ጸረ ሙስና እና ሌሎችም አስተዳደርና ጸጥታ ጋር የተያያዙ መስሪያ ቤቶች ውስጥ የሚሰሩ አካላት መሳተፋቸው ተገልጾአል፡፡
በስብሰባው በተለይም ዳኞች በዳኝነት ስርዓቱ የፖለቲካ ጣልቃ ገብነት እንዳለና የገዥው ፓርቲ አባል ካልሆኑ መስራት እንደማይችሉ በመግለጽ ቅሬታቸውን እንዳቀረቡ ተገልጾአል፡፡
የክልሉ አስተዳደር የሆኑት አቶ ገዱ አንዳርጋቸው በሚመሩት በዚህ ስብሰባ ዳኞች አባል እንዲሆኑ እንደሚጠየቁ በመጥቀስ ‹‹አባል ሁኑ እየተባልን እንዴት ነጻ ዳኝነት አለ ይባላል?›› ሲሉ መጠየቃቸውን ምንጮች ለነገረ ኢትዮጵያ ገልጸዋል፡፡
ከዚህም ባሻገር የአንድ ፓርቲ የበላይነትና ዴሞክራሲ፣ የፌደራል አወቃቀር፣ በኢህአዴግ አባል ድርጅቶች ስር የሚገኙ ድርጅቶች ሃብት፣ የመሬት ጉዳይና የዳኝነት ነጻነት የመሳሰሉት ጉዳዮች ላይ ጥያቄና አስተያየቶች ቢቀርቡም መልስ እንዳልተሰጠባቸው ምንጮቹ ገልጸዋል፡፡

ስዊድን የኤርትራ ዲፕሎማቶች በ48 ሰዓት ለቀው እንዲወጡ አዘዘች

September 24,2014
ኢሳያስ አፈወርቂ ጉዳዩ የኢትዮጵያና የአሜሪካ ሴራ ነው አሉ
ስዊድንና ኤርትራ በዲፕሎማቲክ የእሰጣ እገባ ውስጥ ከገቡ በርከት ያሉ ጊዜያት የተቆጠሩ ሲሆን በስዊድን የኤርትራ ኤምባሲ ዲፕሎማቶች ባልተገባ ተግባር ተገኝተዋል በሚል የሀገሪቱ ዲፕሎማቶች ስዊድንን በ48 ሰዓት ለቀው እንዲወጡ የስዊድን መንግስት ውሳኔ ያስተላለፈ ሲሆን ፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ ድርጊቱ የኢትዮጵያና የአሜሪካ እጅ አለበት ብለዋል። በስዊድን የወጣውን አዲስ ሕግ ተከትሎ የስዊድን መንግስት በኤርትራ ሰብዓዊ መብት ጥሰት ፈፅመዋል ባላቸው ከፍተኛ የኤርትራ መንግስት ባለስልጣናት ላይ በዚያው በስዊድን ክስ መመስረቱ የሁለቱን ሀገራት ግንኙነት አሻክሯል።
isayas afewerki
የኤርትራ መንግስት ዋነኛ የውጪ ምንዛሪ ገቢ በተለያዩ ሀገራት በሚኖሩ ኤርትራውያን ዲያስፖራዎች ላይ የጣለው ሁለት በመቶ የገቢ ታክስ ሲሆን በድርጊት በተለያዩ ሀገራት የሚገኙ ኤርትራውያን በኢምባሲያቸው ላይ ቅሬታ ሲያሰሙ ቆይተዋል። በስዊድን የሚገኙ ኤርትራውያንም ኢምባሲያቸው የሚጠበቅባቸውን የታክስ መጠን ካልከፈሉ የተለያዩ የዜግነትና የጉዞ ዶክመንቶችን ከመከልከል ባለፈ በኤርትራ የሚገኙ ቤተሰቦቻቸው በማያዣነት ተጠቅሞ እስከማስፈራራት ደርሷል በሚል ለስዊድን መንግስት ክስ ሲያሰሙ መቆየታቸው ታውቋል። የኤርትራ መንግስት በስዊድን በሚገኙ ኤርትራውያን እና የስዊድን ዜግነት ባላቸው ትውልደ ኤርትራውያን የተደራጀ ተቃውሞ እየገጠመው ሲሆን የተቃውሞ አደራጅ ግለሰቦችን ለይቶ ለመከታተል በስዊድን የሚገኘውን ኤምባሲውን እና ዲፕሎማቶችን ይጠቀማል በሚልም ጭምር ነው የስዊድን ባለስልጣት የኤርትራ ዲፕሎማቶችን ለማባረር በምክንያትነት ያስቀመጡት።
የኤርትራ መንግስት በየሀገሩ በሚገኙ ኤምባሲዎቹ አማካኝነት ከኤርትራ ዲያስፖራዎች በታክስ መልኩ በሚሰበሰበው ሁለት በመቶ ገቢ ሽብርተኞችና በፋይናንስ እያገዘ ነው በሚል በተባበሩት መንግስታት የፀጥታው ምክር ቤት አማካኝነት ማዕቀብ ከተጣለበት ዓመታት ተቆጥረዋል። ሆኖም ከማዕቀቡ በኋላ የፕሬዝዳንት ኢሳያስ መንግስት በተለያየ ሀገራት ኤምባሲዎች በኩል ታክሱን ለመሰብሰብ የሚያደርገው ሙከራ በየሀገራቱ መንግስታት ተቃውሞ እያስነሳበት ነው። ከዚህ ቀድም በተመሳሳይ መልኩ ካናዳና ኤርትራ ውዝግብ ውስጥ መግባታቸውን ተከትሎ የካናዳ መንግስት በቶሮንቶ የሚገኙ የኤርትራ ዲፕሎማቶችን በ48 ሰዓታት ውስጥ እስከማባረር ደርሷል።
የስዊድን እርምጃ ተከትሎ ፕሬዝዳንት ኢሳያስ በሰጡት ማብራሪያ ድርጊቱ የኢትዮጵያና የአሜሪካ ሴራ ነው ብለውታል፡፡ ሁለቱ ሀገራት የኤርትራ መንግስት ሁለት በመቶ ታክሱን የምስራቅ አፍሪካ ሀገራትን በሽብርተኝነት ለማተራመስ ይጠቀምበታል በሚል ማዕቀቡ እንዲጣልበት ሰፊ የዲፕሎማሲ ሚናን መጫወታቸውን በምስራቅ አፍሪካ ላይ ትኩረቱን አድርጎ የሚሠራው ጂስካ አፍሪካ ኦንላይን ዘግቧል። (ሰንደቅ ጋዜጣ እንደዘገበው)

“ኣብራሃ ደስታን ኣላሰርኩም” የመቐለ ህወሓት (አምዶም ገብረስላሴ – ከትግራይ)

September 24,2014

የትግራይዋ ህወሓት ማለቴ በሰማእታት ሓወልት ፅሕፈት ቤትዋ ያደረገችው ህወሓት( ኣዲስ ኣበባ የህወሓት ኣንጃ ሰላለች ነው) “ኣብራሃ ደስታ የታሰረበት ምክንያት ኣላውቅም” ኣለች።

ይህ ኑዛዜ የተሰማው በኣገር ደረጃ ለመንግስት ሰራተኞች እየተሰጠ ያለው ስልጠና የሚሉት(ተቃዋሚና ያለፉት ስርዓቶች የሚሰድቡበት መድረክ ስለመሰለ ነው) በትግራይ ክልል ፅህፈት ቤት(ደጀን ቢሮ) የሚሰሩ ሰራቶኞች በፕላኔት ሆቴል እየተካሄደ ባለው መድረክ ነው።

በዚህ መድረክ እየተነሱ ያሉት ጥያቄዎችና ሃሳቦች እጅጉን ጠንካሮችና የህወሓት ተራ ኣባላትና ጥቂት ፈላጭ ቆራጭ መሪዎች ፍፁም ታላቅ ልዩነት መነሩ የሚያሳዩ ናቸው።

በዚህ መድረክ “…ኣብራሃ ደስታ ህገ መንግስት የስጠው ሃሳብን በነፃነት የመግለፅ መብቱን በኣግባቡ በመጠቀሙ ለምን በሽብር ኣምካኝታቹ ኣሰራቹት?…” ለሚለው ጥያቄ ሲመልሱ ነው የመቐለዋ ህወሓት ኣብራሃን እንዳላሰረችና” የማሳሰርያው ምክንያትም ኣላውቅም” ብላ የካደችው።

ስብሰባው እየመሩት የነበሩት የትግራይ ክልል ጤና ቢሮ ምክትል ሃላፊ “..ስለ ኣብራሃ ደስታ መታፈንና መታሰር በፌስቡክ ስሰማ በቀጥታ ወደ ህወሓት ቢሮ ሂጀ ኣነጋጋርኳቸው። ከህወሓት ፅህፈት ቤት ያገኘሁት መልስ ምንም የሚያውቁት እንደሌለና ህወሓት እንዳላሳሰረው ረግረውኛል..” ሲሉ በስብሰባው ገልፀዋል።

ኣብራሃ ደስታን የመቐለዋ ህወሓት ካላሳሰርችው ሌላዋ ተጠያቂ የኣዲስ ኣበባዋ የህወሓት ኣንጃ ናት ማለት ነው።

ከፍተኛ ቁጣ የተላበሰው የፕላኔት ሆቴል ተስብሳቢ ህዝብ ለህወሓት መሪዎች ኣስፈሪ ነበር።

ኣገሪትዋ እየበጠበጥዋት ያሉት መላ የህወሓት ኣባላት ሳይሆኑ የተወሰኑና ጥቂት ሰዎች መሆናቸው በግልፅ በመላ ትግራይ ያሉ ስብሰባዎች የተነሱ ሃሳቦች ቁልጭ ኣድረገው እያሳዩ ናቸው።

ሌላው ከፍተኛ የመወያያ ኣጀንዳ በዓረና ኣባላት እየደረሰ ያለው ዓፈና፣ እንግልት፣ ድብደባ፣ ኣማራጭ ሃሳብ ወደ ህዝቡ እንዳይቀርብ ማደናቀፍ የኣዲስ ኣበባዋ ኣንጃ ሳትሆን የመቐለዋ ኣንጃ ስራ መሆኑ በግልፅ ተነግራቸዋል።

እጅጉን ያስደስታል ህዝቡ ነፃነት ፈልጓል፣ ዲሞክራሲን ናፍቆታል፣ መልካም ኣስተዳደርን ቋምጣል። ለዚህ ማሳያ በዓረና የሚደረገው የማፍረስ፣ እንዳይንቀሳቀስ የመከልከል ተግባር ውጉዝ ከመኣርዮስ እያለው ይገኛል።

ወ/ሮ አዜብ መስፍን ጋዜጠኛ ሲሳይ አጌና ላይ ዋሽተው ስልኩን ጆሮው ላይ ዘጉት

September 24,2014
የኢሳቱ ጋዜጠኛ ሲሳይ አጌና መረጃ ፍለጋ ወ/ሮ አዜብ ጋር ደውሎ ድምፃቸውን ኢሳት ራድዮ ላይ አሰምቶናል። ጋዜጠኛ ሲሳይ ወ/ሮ አዜብ መሆናቸውን ካረጋገጡለት በኋላ መረጃ እንዲሰጡት ጠየቃቸው። አድዋ ስለሆንኩ መረጃ የለኝም በሚል ስልኩን ዘጉት። ለሁለተኛ ጊዜ ደወለላቸውና “ዶ/ር ካሱ ኢላላ ከእርስዎ ጋር ባላቸው አለመግባባት ስላላቸው የመለስን ፋውንዴሽን ለቀዋል የሚባል ነገር አለና ይህን እንዲያረጋገጡልኝ ወይም እንዲያስተባብሉልን ነው የደወልኩት” አላቸው። ምንም አይነት ችግር እንደሌለባቸው ከተናገሩ በኋላ መልሰው እርሳቸው ወ/ሮ አዜብ እንዳልሆኑ በድምጽ ተናግረው ዋሹ። “ድምጽዎት እኮ የአዜብ መስፍንን ይመስላል” አላቸው እርሳቸው ግን ልክ ይህን ሲላቸው ለሁለተኛ ጊዜ ስልኩን ዘግተውበታል። የዛሬው ኢሳት ራድዮ ለዚህ ዘገባ ምላሽ አለው ያድምጡት።

የኮብላዩ ሚኒስትር ወጎች – ከተመስገን ደሳለኝ (ጋዜጠኛ)

September 24,2014

በዚህ ተጠየቅ ጨርፈን የምንመለከተው በኮሙኑዮኬሽን ጽ/ቤት ሚኒስትር ዴኤታ የነበረውና ዛሬ በስደት የሚገኘው የአቶ ኤርሚያስ ለገሰን “የመለስ ትሩፋቶች፣ ባለቤት አልባ ከተማ” የተሰኘው መጽሐፍን ነው፡፡ የመድብሉ ጻሐፊ ኤርሚያስን በግል አላውቀውም፤ ለመጀመሪያ ጊዜ በአካል ያየሁት አቶ በረከት ስምዖን እርሱን እና ሽመልስ ከማልን ምክትሎቹ አድርጐ በሚኒስቴር ዲኤታ ማዕረግ መሾሙን በግዮን ሆቴል ለጋዜጠኞች ይፋ ባደረገበት ዝግጅት ላይ ነው፡፡ ከዚህ ለጥቆ፣ በኢትዮጵያ የቀድሞው የአሜሪካ አምባሳደር ዶናልድ ቡዝ በኤምባሲው ግቢ በሚገኝ መኖሪያ ቤታቸው ባዘጋጁት የዕራት ግብዣ ላይ (ግንቦት 19/2001 ዓ.ም) ድንገት ተገናኝተን እጅ ለእጅ ተጨባብጠን ሰላምታ ተለዋውጠናል፤ ለመጨረሻ ጊዜ የተያየነው፣ በኮሙኒኬሽን ጽ/ቤት ግንቦት 7 እና እነጀነራል ተፈራ ማሞን በተመለከተ መግለጫ በተሰጠበት ዕለት እንደ አፄ ኃይለሥላሴ የክብር ዘብ፣ ከሽመልስ ከማል ጋር በረከት ስምዖንን ግራና ቀኝ አጅቦ በተገኘበት ወቅት ነው፡፡ በተቀረ በመንግስት ሥልጣን ሲገለጥ ብዙም አላስተዋልኩም፡፡ ከዚህ ይልቅም ኢህአዴግነቱን ለማሳየት የሞከረበትን አንድ ገጠመኝ አስታውሳለሁ፤ ይኸውም “የፍትሕ” ጋዜጣ ስራ አስኪያጅ የነበረው እና አሁን በስደት ሀገር የሚገኘው ባልደረባዬ ማስተዋል ብርሃኑን ኮሙኒኬሽን ጽ/ቤት ባለው ቢሮው ድረስ በመጥራት ከባድ ዛቻና ማስፈራሪያ ከሰነዘረበት በኋላ፣ ዛሬ የቀድሞ ጓዶቹ ሥራዬ ብለው እንደቀጠሉበት አይነት በጋዜጣው ላይ የሀሰት ውንጀላ ደርድሮ ሲያበቃ፣ ከኃላፊነቱ ራሱን እንዲያገል አስጠንቅቆት እንደነበር ከራሱ ከባልደረባዬ ማስተዋል አንደበት ሰምቻለሁ፡፡
የሆነው ሆኖ አቶ ኤርሚያስ ከላይ በተጠቀሰው መጽሐፉ በተመላኪው ሰው አመራር “ሁሉን አዋቂነት” ላይ የቆመው መንግስት ምን ያህል በጠባብ የወንዝ ልጅነት የተተበተበ እና በዘራፊ ባለሥልጣናት የተዋቀረ እንደሆነ በስፋት ተርኮልናል፡፡ በተለይም ሙስና እና የህወሓት ካድሬዎች የበላይነትን በተመለከተ በማስረጃ አስደግፎ በተዋበ ስነ-ጽሑፋዊ ቋንቋ ዘርዝሮልናል (በርግጥ “የጋዜጠኛው” አሊያም “የደራሲው ማስታወሻ” የሚያነቡ እስኪመስልዎ ድረስ የመጽሐፉን አርትኦት ተስፋዬ ገ/አብ ወይም የተስፋዬ ብዕር ተፅእኖ ያለበት ደራሲ ብዙ እንደለፋበት በግልፅ ማስታወቁን መካድ አይቻልም)፡፡ ከዚሁ ጎን ለጎንም ዛሬም ከአገዛዙ ጋር የተሰለፉ የቀድሞ ጓዶቹ ለህሊናቸው ሲሉ በድብቅ የሚፈፀሙ ሕገ-ወጥ ድርጊቶችን ደፍረው እንዲያጋልጡ በጠየቀበት ብዕሩ፣ የራሱንም ጥፋቶች እና በትዕዛዝም ይሁን በግል ተነሳሽነት በደል ያደረሰባቸውን ንፁሃን በይፋ ይቅርታ ቢጠይቅ መልካም ነበር፤ አሁንም ቢሆን ለዚህ አይነቱ ቅንነትና በጎ አርአያነት ገና አልረፈደም፡፡ ርግጥ ነው የስደት ምርጫው ባደረጋት ሀገረ-አሜሪካ ባሳተመው መጽሐፉ ውስጥ ድርጅቱ ኢህአዴግ ይሰራው በነበረው ሕገ-ወጥ ድርጊትና የጭካኔ እርምጃ አልፎ አልፎ ቢሮውን ዘግቶ እንደሚያለቅስ፣ ባስ ሲልም ህሊናውን ቆጥቁጦት ታምሞ አልጋ ላይ እንደሚውል በመግለፅ የራሱን ጲላጦሳዊነት ለመስበክ መልፋቱን ስናስተውል፤ ጸሐፊው የሥርዓቱ ጋሻ-ጃግሪ በነበረበት ወቅት የበደለውን ሕዝብ ይቅርታ የመጠየቅ ዝግጁነትም ሆነ ፍላጎት (ቢያንስ በዚህ ሰዓት) የለውም ብለን ማዘናችን አይቀርም፡፡
እንዲሁም ከሀገር እንዲወጣ የተገደደበት ምክንያት ተብሎ ስለተናፈሰው ወሬ ትንፍሽ አለማለቱ በበኩሌ አስተዛዛቢ ሆኖ አግኝቸዋለሁ፤ በወቅቱ የስደቱ መነሾ ተደርጎ በከተማዋ በስፋት የተናኘው፣ ከፍተኛ ወታደራዊ መኮንኖቹ እና “የግንቦት 7 አባላት ናችሁ” የተባሉ ግለሰቦች ለእስር መዳረጋቸውን ተከትሎ ለአንድ ዓለም አቀፍ ሚዲያ “ሙከራው መፈንቅለ መንግስት ነው” የሚል መግለጫ በመስጠቱ እንደነበረ ነው፤ በዚህም እጅግ የተበሳጨው ጠ/ሚኒስትሩ፣ አለቃው በረከት ስምዖን ላይ ጭምር የጭቃ-ጅራፉን ከማወናጨፉም በላይ፣ ኤርሚያስን ያለ ሥራ እንዳንሳፈፈው መወራቱን አስታውሳለሁ፤ ይህንን መረጃ አምኖ ወደመቀበሉ የሚገፋን ደግሞ በዚያው ሰሞን መለስ ዜናዊ ራሱ በቴሌቪዥን ቀርቦ ‘…የተደረገው ነገር እዚህ ግባ የሚባል አይደለም፣ ከአልቃይዳና አልሸባብ ጋር ሲነፃፀሩ የእኛዎቹ አማተሪሽ (ልምድ አልባ) ናቸው’ እያለ የሚኒስትር ዴኤታውን ንግግር ለማስተባበል ሲዳክር የመስተዋሉ እውነታ
ነው፡፡ እርሱም ቢሆን ከዚህ ግልፅ ሹክሹክታ በኋላ በትምህርት ሰበብ ሀገር ለቅቆ መሰደዱ የአንድ ሰሞን የከተማ ወሬ ሆኖ ነበር፡፡ እነሆም ወንድም ኤርሚያስ ለገሰ ይህንን ጉዳይ ዳጉስ ባለው መጽሐፉ ውስጥ ሽራፊ ገፅ ሊሰጠው አለመቻሉ እዚህ ጋ በትዝብት እንዳነሳው መገደዴን በትህትና እገልፃለሁ፡፡ አሸንፈሀልና በዝብዘህ ብላ!
ህወሓት-ኢህአዴግ ወደ ሥልጣን ከመጣበት ጊዜ ጀምሮ፣ በግርማ ብሩ አነጋገር “ደሀ-ዘመም” (በመጽሐፉ የተጠቀሰ) እንደሆነ ለማሳመን የሚሞክርበት ብልጠት፣ ራሱን ለሙስና ፅዩፍ አስመስሎ በማቅረብ ነው፤ ይህን አይነቱን ስሁት አመለካከት በሕዝብ ውስጥ ለማስረፅ ጥቂት የፖለቲካ መታመን-ጉድለት ጥርስ ያስነከሰባቸውን ጉምቱ ጓዶቹን “ሙሰኛ” በሚል ወንጅሎ በወህኒ የቃየል መስዋዕት ሲያደርጋቸው ተስተውሏል፤ እርምጃውንም በፓርላማው መድረክ ሳይቀር ሲኩራራበትና ለፕሮፓጋንዳ ፍጆታ ሲያውለው ተመልክተናል (ከሩቁ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ታምራት ላይኔ እና መከላከያ ሚኒስትሩ ስዬ አብርሃ፤ ከቅርቡ ደግሞ የገቢዎችና ጉምሩክ ዳይሬክተር መላኩ ፈንቴ፣ የደህንነት ኃላፊው ወ/ስላሴ እና መሰል ባለሥልጣናትን እስር ልብ ይሏል)፡፡ የሚኒስትር ዴኤታው መጽሐፍ፣ መለስ እና ጓዶቹ ካደነቆሩን በግልባጩ ‘የዘረፋ መሪዎች’ የሚላቸው ሁለት የህወሓት ሰዎች፣ በባላንጣነት ተሰልፈው እንዴት የሀገር ሀብት ለመቀራመት ይሽቀዳደሙ እንደነበር አጋልጧል፤ አዜብ መስፍንን እና አርከበ እቁባይን፡፡
“እነ አርከበ ከትግራይ ወደ አዲስ አበባ ከመምጣታቸው ጥቂት ወራት በፊት በህወሓት ውስጥ መደናገጥ ተፈጥሮ ነበር፡፡ የህወሓት ዳግም መከፋፈል ምክንያት ደግሞ በወ/ሮ አዜብ እና አርከብ ቡድኖች መካከል አለመግባባቶች መፈጠራቸው ነበር፡፡ መነሻው መረን የለቀቀ የጥቅም ግጭት ሲሆን ዓላማው የህወሓት ኢንዶመንቶችን መቆጣጠር ታሳቢ ያደረገ ነበር፡፡” (ገፅ 25) ከዕለት ተዕለትም ይህ ሁኔታ የተካረረ ልዩነት ፈጥሮ፣ ፖለቲካዊ ቁመና በመላበሱ፤ አርከበ እቁባይ፣ ህወሓት መገፋቱን እና መለስ በበረከት በኩል የድርጅቱን ካድሬዎች እያስጠቃ ነው የሚል ክስ ከማጎኑም ባሻገር፤ ወደኋላ ተጉዞ የኢትዮ-ኤርትራ ጦርነት የተጠናቀቀበትን መዛግብት አቧራ በማራገፍ፣ ተጠያቂነቱን ከፍ ሲል ወደ መለስ ዜናዊ፣ ዝቅ ሲል ደግሞ ወደ በረከት ስምዖን በመወርወር ማጠቋቆሩ ያመጣውን ውጤት እንዲህ ሲል ገልፆታል፡- “በሂደት አቶ አርከበ ይዞ ብቅ ያለው መቀስቀሻ የካድሬውን እና አባሉን ቁስል የነካ በመሆኑ ተቀባይነት አገኘ፡፡ በትግራይ ፕሮፓጋንዳ እና ድርጅት ተመድበው የሚሰሩ ቁልፍ ካድሬዎች ተቀላቀሉት፡፡” (ገፅ 26)
ይህንን ተከትሎ ወትሮም በደፋር ንግግሯ የምትታወቀውና አንጋፋ ታጋዮችን ሳይቀር በቁጣ የምታስረግደው ቀዳማዊት እመቤት የሰነዘረችው የመልስ ምት በመጽሐፉ ላይ እንደሚከተለው ሰፍሯል፡- “ወ/ሮ አዜብ በበኩሏ አርከበና ቡድኖቹ በሙስና ተዘፍቀዋል የሚል ክስ ይዛ ብቅ አለች፡፡ አርከበ በሚስቱና ቤተሰቦቹ የያዘውን ንብረት በመረጃ አስደግፋ አራገበች፡፡ ላውንደሪ ቤት፣ ፋርማሲ፣ ክሊኒክ፣ ሱፐር ማርኬት፣ መስታወት ማስመጣትና መሸጥ…፡፡ በትግራይና አዲስ አበባ የተፈጠሩት አዳዲስ ባለሀብቶች የአርከበና ቡድኖቹ እንደሆኑ በስም ዘርዝራ አሳወቀች፡፡ ስዬ በታሰረበት የሌብነት ወንጀል አርከበ እጁ እንደነበረ፣ በተለይም የስዬ ወንድም ለገዛቸው በርካታ መኪናዎች ቅናሽ እንዲያገኝ ማግባባቱን የፈፀመው አርከበ መሆኑን አጋለጠች፡፡” (ገፅ 26)
እዚህ ጋ አቶ ኤርሚያስ ‹‹አርከበ በሚስቱና በቤተሰቦቹ…›› ስለያዛቸውና አዜብ መስፍን በስም እየጠራች አጋለጠች ስላላቸው የንግድ ድርጅቶች በስም አንድ በአንድ እየጠቀሰ ይፋ ቢያደርግልን ኖሮ መረጃው ምሉዕ (ከ‹ኮሪደር ሀሜት› የዘለለ) ይሆን ነበር ብዬ አስባለሁ፡፡ ከሁሉም ቁጭታችንን የሚያንረው፣ ደራሲው የንግድ ተቋማቱን ባለቤቶች በስም መጥቀስ እየቻለ (አቀራረቡ ለይቶ እንደሚያውቅ ያሳብቃልና) በደፈናው ያለፈው ወንጀል (ሕገ-ወጥ ዘረፋ) ይህ ብቻ አለመሆኑ ሲገባን ነው፤ በዚሁ ገፅ ዝቅ ብሎ የሰፈረው እንዲህ ይላልና፡- “በወቅቱ ሁለቱም ቡድኖች ‹ያለ ኢኮኖሚ የበላይነት፣ የፖለቲካ የበላይነት አይመጣም› የሚል ፖሊሲ ቀርፀው የህወሓት ባለሀብቶችን ለመፍጠር ተንቀሳቅሰዋል፡፡ በዚህ ፖሊሲ ምክንያት በአንድ ሌሊት ከሹፌርነት ወደ አስመጪና ላኪነት፣ ከጋራዥ ሰራተኛነት ወደ መኪና ዕቃ መለዋወጫ አስመጪነት፣ ከታጋይነት ወደ ሪል እስቴት ባለቤትነት፣ ከወታደርነት ወደ ፋብሪካ ባለቤትነት፣ ከህወሓት ምድብተኛ ካድሬ ወደግል ባንክ ከፍተኛ አክሲዮን ባለድርሻነት የተቀየሩ ሰዎችን መስማት የተለመደ ነበር፡፡” (ገፅ 26) እነዚህ ‹‹ተላላኪ›› እና ‹‹ሹፌር›› ባለሀብቶችን በስም አለመጥቀሱ ያስቆጫል፤ በተለይም ለመረጃው ከነበረው ቅርበት አኳያ ይሄ ጉዳይ እንደተራ ነገር በደፈናው ባይታለፍ ኖሮ፣ ለተቃውሞው ስብስብ በዋናነት ሁለት ታላላቅ የፖለቲካ ትርፍ ማስገኘቱ አይቀሬ ነበር፡፡
የመጀመሪያው በጅምላ ህወሓት፣ መላው ትግሪኛ ቋንቋ ተናጋሪን ተጠቃሚ ያደረገ የሚመስለው ኢትዮጵያዊ ስህተቱን እንዲያጠራ ስለሚያስችለው፣ በድርጅቱ እና በብሔሩ መሀከል ያለውን ነጭና ጥቁር ልዩነት እንዲያስተውል ይረዳው ነበር፤ ሌላው ደግሞ እነዚህን በፖለቲካ ውሳኔ ወደሀብት ማማ የወጡትን ግለሰቦች የትላንት ማንነት አብጠርጥሮ የሚያውቀው ቤተሰብ፣ ጎረቤት፣ ዘመድ አዝማድ… የዘረፋ ወንጀላቸውን ተፀይፎ በኢኮኖሚያዊ ማግለል (ሸቀጦቻቸውን ባለመግዛትም ሆነ አገልግሎታቸውን ባለመጠቀም) በተቃውሞ ጎራ እንዲሰለፍ ገፊ-ምክንያት ይሆነው ነበር የሚለው ጭብጥ ነው፡፡ ‹‹የመለስ ትሩፋቶች›› መጽሐፍ በሀገሪቱ ውስጥ ከመጋረጃው ጀርባ ስለተፈፅሙ ህልቆ-መሳፍርት ያሌላቸው አሳፋሪ የህወሓት ሕገ-ወጥ ድርጊቶች እና እብሪቶችን ተንትኖ አስነብቦናል፡፡ ከእነዚህ መሀልም የስምንቱ ኮሎኔሎች ‹‹ጀብድ››ን እዚህ ጋ መጥቀሱ አግባብነት አለው ብዬ አምናለሁ፤ ከ268-269 ባሉ ገፆች እንደተተረከው፣ በምርጫ 97 ማግስት በአንዱ ዕለት በወታደራዊ የደንብ ልብስ የተንቆጠቆጡ ስምንት ከፍተኛ መኮንኖች በሶስት ሄሌኮፕተር ተሳፍረው አሮጌው አውሮፕላን ማረፊያ ይደርሳሉ፤ በቀጥታም የኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ ከንቲባ ወደነበረው አባተ ስጦታው ቢሮ በማምራት፣ መሬት እንደሚሰጥ መረጃ ደርሷቸው ከጦር ግንባር እንደመጡ ይነግሩታል፤ እያንዳንዳቸውም ‹‹ዘመቻ ፀሀይ ግባት የቤት ማሕበር››፣ ‹‹ኃየሎም አርአያ የቤት ማሕበር››፣ ‹‹ዛላአንበሳ የቤት ማሕበር››… የሚል እና መሰል የማህደር ስያሜ ያላቸው የአስራ ሁለት መኮንኖች ስም ዝርዝርና ፊርማ የያዘ ወረቀት ይሰጡታል፤ እንደ ብራ መብረቅ ድንገት ባጋጠመው ክስተት ክፉኛ የተረበሸው ከንቲባም እንዲህ ያለ መመሪያ እንዳልወረደ ለማስረዳት ሲሞክር፣ ለዚህ ዓይነቱ እሰጥ-ገባ ጊዜ ያልነበራቸው የጦር አበጋዞቹ አብረቅራቂ ሽጉጦቻቸውን በመምዘዝ ግንባሩ ላይ ደቅነው በወቅቱ ፋሽን በነበረው ኢህአዴጋዊ ፍረጃ ‹‹የቅንጅት ተላላኪ መሆንህን ደርሰንበታል››፣ ‹‹ኢህአዴግ እንዲሸነፍ ያደረጋችሁት እንዳንተ ያሉ ሰርጎ-ገቦች ናቸው››፣ ‹‹እዚሁ ደፍተንህ እንሄዳለን››… የሚሉ ማስፈራሪያዎችን አዥጎድጉደው በማስጠንቀቅ ነፍስ-ውጪ፣ ነፍስ ግቢ ወጥረው ይይዙታል፤ ይህን ጊዜ የህወሓት አባል የሆነው ምክትል ከንቲባው ነጋ በርሔ፣ የአባተን ቢሮ በርግዶ ሳይታሰብ ዘው በማለቱ፣ አንደኛው ኮሎኔል ያነጣጠረውን መሳሪያ ከአይን በፈጠነ ቅፅበት አዙሮ ይደቅንበታል፡፡ ሁኔታውን ከጉዳይ ያልጣፈው ነጋ በርሔም ባለሽጉጦቹን የጦር አበጋዞች በባዶ እጁ እንዲህ ሲል ተጋፈጣቸው፡-
“ነፍጥ ከእናንተ በፊት አንግበን ተራራ ደርምሰናል፡፡ የምታስፈራሩትን ሂዱና ሌላ ቦታ አስፈራሩ!”
ከፍተኛ መኮንኖቹም በድንጋጤ መሳሪያዎቻቸውን በመዘዙበት ፍጥነት ወደአፎቱ መልሰውና የምክትል ከንቲባውን የስድብ ውርጅብኝ በፀጥታ አዳምጠው ሲያበቁ፣ አባተን ይቅርታ እንዲጠይቁት ይታዘዛሉ፤ እንዲያ በጥንካሬያቸው ለማንም የሰው ልጅ የማይበገሩ መስለው ሲንጎማለሉ የነበሩት ቆፍጣናዎቹ ኮሎኔሎች ባንዴ እንደፊኛ ተንፍሰው በፍርሃት የታዘዙትን ይፈፅማሉ፤ ከዚህ በኋላም ህወሓቱ ነጋ በርሔ በተረጋጋ አንደበት ዋናው ከንቲባውም ጭምር እንዲሰማ ድምፁን አጉልቶ የሚከተለውን ‹‹ምርጥ›› ምክር ለገሳቸው፡ –
“ዲሞክራሲያዊ በሆነ መንገድ ጥያቄያችሁን ብታቀርቡ ኖሮ አባተ እንኳን ቤተሰባችሁን ጥላችሁ ግንባራችሁን ለጥይት ለምትሰጡት ቀርቶ ለሌላውም አይጨክንም፡፡ ያውም ከቀናት በኋላ ጠላት (ቅንጅት) ተረክቦ ለሚዘርፋት አዲስ አበባ!” (ገፅ 255) ከንቲባውም መሬቱን ፈቀደ፤ ነጋም ወደ መቀሌ እንዲዘዋወር ተደርጎ፣ የህወሓት ማዕከላዊ ኮሚቴን እና የትግራይ ክልል ካቢኔን ተቀላቀለ፤ ከጊዜ በኋላም በበረከት ስምዖን በተመራ ግምገማ ላይ በአስቸኳይ አዲስ አበባ መጥቶ ይህንን ጉዳይ እንዲያስረዳ ቢጠየቅ አሻፈረኝ ብሎ ይቀራል፡፡ ደራሲውም ‹‹ዘመን አለፈና አዲሱ ለገሰን ለማገዝ ኢህአዴግ ቢሮ የሥልጠና ማዕከል በምክትል ሚኒስትርነት ማዕርግ ተመደበ›› ሲል የሆሊውድ ፊልምን የሚያስንቀውን ታሪክ ይደመድማል፡፡ በርግጥ አባተም ቢሆን ይህ አስፈሪ ገጠመኙ እንደድንቅ ቃለ-ተውኔት ሁሉ፣ በህወሓት መሪዎች ተደርሶ በኮሎኔሎቹ እና በነጋ የተተወነ መሆኑን ለመረዳት በርካታ ወራት እንደፈጀበት ተጠቅሷል፡፡
በሌላ ምዕራፍ ደግሞ፤ በምርጫው ቀን እኩለ ሌሊት ተቋቁሞ፣ በአርከበ እቁባይ እና በጄነራል ታደሰ ወረደ እንዲመራ የተደረገው ‹‹የፖለቲካ ፀጥታ ጥምር ኮሚቴ››፣ ከ1978 ዓ.ም በፊት ወደ ትግል የገቡና ማዕረጋቸው ከኮሎኔል በላይ የሆነ የህወሓት መኮንኖች ቦሌ ላይ መሬት እንዲያገኙ ማመቻቸቱን አስነብቦናል፡፡ በአናቱም፣ ከኮሎኔል በታች ያሉ የህወሓት ታጋዮች በሌሎች ማስፋፊያ ከተሞች መሬት ማግኘታቸውን ተከትሎ የተፈጠረውን ሁኔታ ሚኒስትር ዴኤታው እንዲህ ያወጋናል፡- “…ወሬው ባድመና ጾረና ጦር ግንባር ድረስ ተዳረሰ፡፡ ወታደራዊ መኮንኖቹ ምሽጋቸውን እየለቀቁ በጦር ሂሊኮፕተሮች ጭምር እየተሳፈሩ አዲሳባን ወረሯት፡፡ የክፍለ ከተሞች ግቢ አቧራ በጠጣ የኮከብ ጋሻና ጦር ክምር የተሸከመ ካኪ ተጥለቀለቀ፡፡” (ገፅ 255-256) ዘመነኛው የኢትዮጵያ ፖለቲካ ‹‹…አንዳንድ እንሰሳት ይበልጥ እኩል ናቸው›› በሚል ያልተፃፈ ሕግ ማደሩን ከውስጥ-አወቅ ምስክርነት የምንረዳው ከህወሓት ውጪ ያሉት ኢህአዴግን የመሰረቱ ድርጅቶች የአመራር አባላት ብቻ የወሰዷትን መሬት በግምገማ እንዲመልሱ መገደዳቸው በዚሁ መጽሐፍ መስፈሩን ስናስተውል ነው፡፡ በወቅቱም በግምገማው ፊት-አውራሪ በረከት ስምዖን የተዘጋጀ ‹‹ከምርጫው በኋላ የድርጅታችንን ስም ያጎደፉና የሕዝቡን ቅሬታ ያባባሱ ተግባራት›› የሚል ሃያ ገፅ ሰነድ የመነሻ ሃሳብ ሆኖ ቀርቦ ነበር፤ የግምገማው ውጤትም የተዘረፈ መሬት ማስመለሻ ፎርምን ህወሓት ያልሆኑ ከ600 በላይ የኢህአዴግ ካድሬዎች እንዲሞሉ አስገድዶ ተጠናቅቋል፡፡
ለአብነትም ደራሲው ‹‹ለታሪክ የተቀመጠው የይቅርታ ፎርም›› ብሎ በመጽሐፉ ያሰፈረውንና በአንድ የብአዴን አመራር የተሞላውን እንደወረደ ልጥቀሰው፡- “ለቦሌ ክፍለ ከተማ መሬት አስተዳደር እኔ ህላዊ ዮሴፍ ድርጅቴ ኢህአዴግና መንግስት የጣለብኝን አደራና ኃላፊነት ወደጎን በመተው ሕገ-ወጥ በሆነ መንገድ የመሬት ወረራ ላይ በመሰማራት አንድ መሬት ወስጃለሁ፡፡ በመሆኑም ይህን ያለአግባብ የወሰድኩትን መሬት አስተዳደሩ እንዲረከበኝ በማክበር እጠይቃለሁ፡፡ ድርጅቴ ኢህአዴግና በእሱ የሚመራው መንግስትም ይቅርታ እንዲያደርግልኝና ከእንግዲህ ወዲያ በየትኛውም የድርጅቴንና የመንግስት ስም በሚያጎድፍ ተግባራት ላለመሰማራት ቃል እገባለሁ፡፡
ከሰላምታ ጋር ህላዊ ዮሴፍ
ግልባጭ
ለአዲስ አበባ ጊዜያዊ ባለአደራ አስተዳደር
ለቦሌ ክፍለ ከተማ ጊዜያዊ ባለአደራ አስተዳደር
ለኢህአዴግ ጽ/ቤት” (ገፅ 257)
የሆነው ሆነ ኤርሚያስ ለገሰ በዚህ መጽሔት ላይ እንዲህ በቀላሉ ጠቅሰን የማንጨርሳቸውን በርካታ አይን ያወጡ ድርጅታዊ እና ግለሰባዊ ዘረፋዎችን ልባችን ቀጥ እስኪል ድረስ አስነብቦናል፡፡ ሌላው ቀርቶ ዛሬ በየመድረኩ ‹ኢህአዴግ ጌታ ነው!›፣ ‹መለስ መሲህ ነው!›… አይነት ፕሮፓጋንዳ በማድመቅ ግንባር-ቀደም እየሆነ የመጣው ጀግናው አትሌት ኃይሌ ገ/ስላሴ ራሱ የዘረፋው ተቋዳሽእንደነበረ እንዲህ ሲል ነግሮናል፡-
“ከሁሉም የሚያሳዝነው ሀገራችንን በዓለም መድረክ በማስጠራቱ የምንወደው ኃይሌ፣ በአስታራቂ ሽማግሌነቱ የምናመሰግነው ኃይሌ፣ በዓለም አደባባይ አልቅሶ ያስለቀሰን ኃይሌ ‹ኃይሌና አለም ሪል ስቴት› በሚል የድርጅት ስም በመስከረም 7/1998 ዓ.ም በቦሌ ክፍለ ከተማ ቀበሌ 18 ውስጥ 50,000 ካሬ ሜትር ሕጋዊ ሰውነት በነዋሪው ድምፅ ከተገፈፈው አርከበ እቁባይ እጅ ወስዷል፡፡ መቼም ታላቁ ሯጭ እየተካሄደ ያለው ውንብድና አዲስ አበባን ማጥፋት እንደሆነ ሳይገባው ቀርቶ አይመስለኝም፡፡” (ገፅ 400-401)
…የወዶ ተሳዳጁ የኦህዴድ ካድሬ፣ ከሁለት ዓስርታት በላይ ሲነገርና ሲፃፍ የነበረውን ርዕሰ-ጉዳይ ለማጠናከር በርካታ የመጽሐፉን ገጾች ሰውቷል፡፡ ይህ የህወሓት ብቸኛ የፖለቲካና ኢኮኖሚ ጠቅላይነት ትርክት፣ ገዢ የተቃውሞው መከራከሪያ መሆኑን በሚገባ የሚያውቀው ኤርሚያስ፣ በተለይም ባገለገለበት አዲስ አበባ ዙሪያ ያልተገለጡ የሚመስሉ ሁነቶችን አስተሳስሮ ለመተረክ ጥሯል፡፡ በርግጥ ለእግረ-መንገድ ያህል አንድ ጥርጣሬ ጥለን እንለፍ፤ ይህን መስመር አብዝቶ ማብራራት፣ ተደማጭነትን እና የፖለቲካ ሁለተኛ ዕድልን እንደሚሰጥ ሚኒስትሩ ከመረዳቱ አኳያ፤ የተባሉትን በምልዐት መቀበሉ ጥቂትም ቢሆን አስቸጋሪ መሆኑ መዘንጋት የለበትም፡፡ አልፎም፣ የትግሪኛ ተናጋሪውን እና ህወሓትን ቀላቅሎ ወደመመልከት እንዳያሻግረን ብርቱ ጥንቃቄ ማድረጉም ሊታወስ ይገባል፡፡
(በሚቀጥለው ሳምንት ይህንኑ መጽሐፍ በማጣቀሻነት እያወሳን፣ የህወሓትን የፖለቲካ የበላይነት እና ጠቅላይነት የሚያሳዩ ወጎችን እንዳስሳለን)

Tuesday, September 23, 2014

የሰማያዊ ፓርቲ አመራሮች መስከረም 23 ፍርድ ቤት ይቀርባሉ

September 23,2014
የሰማያዊ ፓርቲ አመራሮች መስከረም 23 ፍርድ ቤት ይቀርባሉ

 በሽብርተኝነት ተከሰው ማዕከላዊ የሚገኙት የሰማያዊ ፓርቲ የጋሞጎፋ ዞን አመራሮች መስከረም 23/2007 ዓ.ም ከሰዓት በኋላ 8፡00 አራዳ ችሎት እንደሚቀርቡ የሰማያዊ ፓርቲ የአደረጃጀት ጉዳይ ኃላፊ አቶ ብርሃኑ ተክለያሬድ ለነገረ ኢትዮጵያ ገልጸዋል፡፡

የሰማያዊ ፓርቲ የጋሞጎፋ ዞን ምክትል ሊቀመንበር አቶ ፍቃዱ አበበ እንዲሁም የዞኑ የድርጅት ጉዳይ ኃላፊ ኢንጅነር ጌታሁን አርባምንጭ ውስጥ ወር ከ15 ቀን ያህል ታስረው የነበር ሲሆን ወደ ማዕከላዊ ከተዛወሩ ሁለት ሳምንት እንደሆናቸው የአደረጃጀት ጉዳይ ኃላፊው ገልጸዋል፡፡

ታሳሪዎቹ በቤተሰብ፣ በኃይማኖት አባትና በጠበቃ እንዳይጠየቁ የተከለከሉ ሲሆን የምክትል ሊቀመንበሩ አቶ በፈቃዱ ባለቤትና አባት እንዳይጠይቁ መከልከላቸውን ኃላፊው ጨምረው ገልጸዋል፡: (ነገረ ኢትዮጵያ ጋዜጣ)
blue_party_ethiopia101370869814 (1)

የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ኤክስፐርቶች ኢትዮጵያ ፀረ ሽብርተኝነት አዋጁን ለሰብዓዊ መብት ጥሰት ትጠቀማለች ሲሉ ከሰሱ

September 23.2014
-ተቃዋሚዎች ተገቢ ሪፖርት ብለውታል
United-Nations-01-300x220የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት (ተመድ) የሰብዓዊ መብት ሁሉን አቀፍ የአቻ ለአቻ ግምገማ የውሳኔ ሐሳቦችን ለመገምገም የተሰበሰበው የተመድ ከፍተኛ የሰብዓዊ መብት ኤክስፐርቶች ቡድን መስከረም 8 ቀን 2008 ዓ.ም. በጀኔቭ ስዊዘርላንድ ባደረገው ስብሰባ፣ የኢትዮጵያ መንግሥት የፀረ ሽብረተኝነት አዋጁን ሐሳብን በነፃነት የመግለጽና የመደራጀት መብትን ለመጣስ መጠቀሙን እንዲያቆም አሳሰበ፡፡
ባለፈው ዓመት ኢትዮጵያ ያቀረበችውን ብሔራዊ የሰብዓዊ መብት አፈጻጸም ሪፖርትና የሰብዓዊ መብት ይዞታን በአገሪቱ ለማሻሻል የተወሰዱትን ሕጋዊና አስተዳደራዊ ዕርምጃዎች ተከትሎ፣ አባል አገሮች የተለያዩ የውሳኔ ሐሳቦችን መስጠታቸው ይታወሳል፡፡ ያደጉ አገሮች ከፍተኛ ትኩረት ሰጥተው እንዲሻሻል ወይም እንዲሰረዝ የጠየቁት ደግሞ የፀረ ሽብርተኝነት አዋጁን ነው፡፡
የፀረ ሽብርተኝነት ሕግና የሰብዓዊ መብት ጥበቃ፣ የመደራጀትና የሰላማዊ ስብሰባ፣ ሐሳብን በነፃነት የመግለጽ፣ የሰብዓዊ መብት ተሟጋቾች፣ የዳኞችና የጠበቆች ነፃነትና የኢሰብዓዊ አያያዝና ክብርን የሚያዋርድ ቅጣት መብቶች ልዩ ራፖርተሮች የሆኑት ቤን ኤመርሰን፣ ማይና ካያ፣ ዴቪድ ካዬ፣ ሚቸል ፎርስት፣ ጋብሪኤላ ክናውልና ጁአን ሜንዴዝ በጋራ ያወጡት ሪፖርት የፀረ ሽብርተኝነት ሕጉ ጋዜጠኞች፣ ጦማሪያን፣ የሰብዓዊ መብት ተሟጋቾችና የተቃዋሚ ፖለቲካ ፓርቲ አባላት ላይ ያነጣጠረ እንደሆነ ባለፉት ሁለት ዓመታት ከኢትዮጵያ የወጡ ሪፖርቶች ማመላከታቸውን ይገልጻል፡፡ ‹‹ግርፋትና ኢሰብዓዊ አያያዝ በኢትዮጵያ ማቆያዎች ውስጥ መስተዋሉ ከፍተኛ የመሠረታዊ የሰብዓዊ መብት ጥሰት ነው፤›› ሲልም ሪፖርቱ ይጠቁማል፡፡
የኤክስፐርቶች ቡድኑ ሽብርተኝነትን መዋጋት አስፈላጊ ድርጊት ቢሆንም፣ ትግሉ የዓለም አቀፍ የሰብዓዊ መብት መሥፈርቶችን ሳይጣረስ መከናወን እንዳለበት ግን አስምሮበታል፡፡ ‹‹ፀረ ሽብርተኝነትን የሚደነግጉ አንቀጾች በኢትዮጵያ የወንጀል ሕግጋት ውስጥ ግልጽ በሆነ ሁኔታ መተርጎም አለባቸው፡፡ ሕጎቹም ላልተገባ ዓላማ ጥቅም ላይ ሊውሉ አይገባም፤›› ሲልም ሪፖርቱ ያትታል፡፡
ሪፖርቱ በፀረ ሽብርተኝነት አዋጁ የተከሰሱ ግለሰቦች ፍትሐዊ የሆነ የፍርድ ሒደት እያገኙ እንዳልሆነም ይወቅሳል፡፡ በተለይም ከሕግ አማካሪዎችና ከጠበቆች ጋር የመገናኘት መብት እንደማይተገበርም ያስረዳል፡፡ ‹‹ፍትሐዊ የሆነ የፍርድ ሒደት የማግኘት መብት፣ ሐሳብን በነፃነት የመግለጽ መብትና የመደራጀት መብት በፀረ ሽብርተኝነት ሕጉ አፈጻጸም መጣሳቸው ቀጥሏል፤›› ሲሉም ኤክስፐርቶቹ ያሳስባሉ፡፡
‹‹የኢትዮጵያ መንግሥት ሽብርተኝነትን በመዋጋት ስም በዘፈቀደ በቁጥጥር ሥር ያዋላቸውን ሁሉንም ሰዎች እንዲፈታ እንጠይቃለን፡፡ ጋዜጠኞች፣ የሰብዓዊ መብት ተሟጋቾች፣ ተቃዋሚ ፖለቲከኞችና የሃይማኖት መሪዎች መደበኛና ሕጋዊ ሥራቸውን ያለ ዛቻና እስር ሳይፈሩ እንዲቀጥሉ ሊፈቀድላቸው ይገባል፤›› ሲሉም የተመድ ኤክስፐርቶች ጠይቀዋል፡፡ ኤክስፐርቶቹ ኢትዮጵያ የአዋጁን አፈጻጸም ከገባቻቸው ዓለም አቀፍ የሰብዓዊ መብት ግዴታዎች ጋር እያገናዘበች እንድታስኬድም ጥሪ አድርገዋል፡፡
የፀረ ሽብርተኝነት አዋጁን በመቃወም የሕዝብ ፊርማ እስከማሰባሰብ የደረሰው የአንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትሕ (አንድነት) ፓርቲ ፕሬዚዳንት አቶ ግዛቸው ሽፈራው (ኢንጂነር) ሪፖርቱን አስመልከቶ ከሪፖርተር ለቀረበላቸው ጥያቄ ሲመልሱ፣ ‹‹ፓርቲያችን አንድነት የፀረ ሽብርተኝነት አዋጅ የሕግ ሳይሆን የፖለቲካ ሰነድ ነው ያለው ከየትኛውም ፓርቲ ቀድሞ ነው፡፡ አዋጁ የፖለቲካ ፓርቲዎችን፣ ከኢሕአዴግ የተለየ አቋም የሚያንፀባርቁ ግለሰቦችና ጋዜጠኞችን ለማፈን ታሳቢ ተደርጎ የወጣ ነው፤›› ብለዋል፡፡ አቶ ግዛቸው የሕጉን ተፅዕኖ በማየት ፓርቲያቸው በ2005 እና በ2006 ዓ.ም. ሕጉን ለማሰረዝ ፊርማ የማሰባሰብ ሥራ መሥራቱንም አስታውሰዋል፡፡
የተመድ ኤክስፐርቶች ሪፖርት በኢትዮጵያ ላይ ጫና ለመፍጠር ምን ያህል ጠቃሚ ነው በሚል የተጠየቁት አቶ ግዛቸው፣ ተመድ ሕጉ ጉድለት አለበት ስላለ ሳይሆን አዋጁ ከኢፌዲሪ ሕገ መንግሥት ጋር የማይጣጣም በመሆኑ ፓርቲያቸው ተቃውሞውን እንደጀመረ ገልጸዋል፡፡ ዜጎች ሐሳባቸውን በነፃነት የመግለጽ፣ የመሰብሰብና የመደራጀት መብታቸው በሕገ መንግሥቱ ቢከበርም እነዚህን መብቶች በመጣስ በሕጉ አማካይነት በርካታ የህሊና እስረኞችን ኢትዮጵያ እንዳፈራችም አመልክተዋል፡፡ አዋጁ ከሕገ መንግሥቱ ጋር ይጋጫል የሚሉ ከሆነ ለምን ጥያቄአቸውን ለፌዴሬሽን ምክር ቤት ወይም ለሕገ መንግሥታዊ አጣሪ ጉባዔ እንዳላቀረቡ የተጠየቁት አቶ ግዛቸው፣ ከሕግ ክፍላቸው ጋር እየተነጋገሩ እንደሆነና በቅርቡ እንደሚያቀርቡ ጠቁመዋል፡፡
እንደ አንድነት ፓርቲ ሁሉ በአዋጁ ላይ የሰላ ተቃውሞ በማቅረብ የሚታወቀው የሰማያዊ ፓርቲ ፕሬዚዳንት አቶ ይልቃል ጌትነት (ኢንጂነር) በበኩላቸው፣ የኤክስፐርቶቹ ሪፖርት የፓርቲያቸውን አቋም እንደሚያንፀባርቅ ገልጸዋል፡፡ ‹‹እንደ ፓርቲም እንደ ግለሰብም በሪፖርቱ በጣም ደስተኛ ነን፡፡ ኤክስፐርቶቹ ገለልተኛና በጉዳዮቹ ላይ ጥልቅ ዕውቀት ያላቸው ናቸው፡፡ ተዓማኒነት ያለው ሪፖርትም በማውጣት ይታወቃሉ፡፡ ይኼ ዲፕሎማሲያዊ ጫና ከመፍጠር አልፎ ተግባራዊ ዕርምጃ ለመውሰድም የሚያስችል ተፅዕኖ ይፈጥራል፤›› ሲሉም አስረድተዋል፡፡
ከነሐሴ 22 ቀን 2001 ዓ.ም. ጀምሮ የፀናው የፀረ ሽብርተኝነት አዋጅ ቁጥር 652/2001 ተጠቅሶ በርካታ የተቃዋሚ ፖለቲካ ፓርቲ አባላት፣ ጋዜጠኞች፣ ጦማሪያንና የሰብዓዊ መብት ተሟጋቾች ተከሰው ፍርድ ያገኙ ሲሆን፣ በቅርቡም በቁጥጥር ሥር የዋሉ ፖለቲከኞችና ጋዜጠኞች በዚሁ አዋጅ ተከሰው ጉዳያቸው በመታየት ላይ ነው፡፡ መንግሥት ግን ይሠሩት ከነበረው ሙያዊ እንቅስቃሴ ባሻገር በሽብር ተግባር ሲሳተፉ እንደያዛቸው በመግለጽ ራሱን ይከላከላል፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለ ማርያም ደሳለኝ በኢትዮጵያ ውስጥ አንድም የህሊና እስረኛ እንደሌለ መግለጻቸውን ባለፈው ረቡዕ ዕትም መዘገባችን ይታወሳል፡፡ በአሁኑ የተመድ ኤክስፐርቶች ሪፖርት ላይ የመንግሥትን ምላሽ ለማግኘት ሪፖርተር ያደረገው ጥረት አልተሳካም፡፡

አሳዛኝ ዜና (ከቂልንጦ እስር ቤት)

September 23,2014
ዛሬ ከወደ ቂልንጦ የደረሰኝ መረጃ እጅግ የሚዘግንና እንቅልፍ የሚነሳ ነው ነገሩ እንዲህ ነው””
አበበ ካሴ ግንቦት ሰባት ነህ ተብሎ የታሰረ ወጣት . በቂልንጦ ይገኛል፡፡ በሚዘገንን መልኩ ቅጣት ብለው የ10 ጣቶቹን ጥፍሮች ነቅለዋቸዋል፡፡ ብልቱ ላይ ሀይላንድ እያንጠለጠሉ ሲያሰቃዩት ቆይተዋል፡፡ ከብልቱ ፈሳሽ መውጣት ጀምሯል ፡፡ እንዲያሳክሙት ቢጠይቅም እምቢ ብለዉ ህክምና ከልክለውታል፡፡ ይባስ ብለው የእስረኛ መለያ መታወቂያውን ቀምተውታል፡፡ በአሁኑ ጊዜ በከፍተኛ ስቃይ ውስጥ ይገኛል፡፡ ይህ የጭካኔ ተግባር በምን አይነት ቋንቋ እንደሚገለጽ አላውቅም።

Systemic human rights concerns demand action by both Ethiopia and the Human Rights Council

September 23, 2014

amnesty.jpgAMNESTY INTERNATIONAL
PUBLIC STATEMENT
AI Index: AFR 25/005/2014
Systemic human rights concerns demand action by both Ethiopia and the Human Rights Council
Human Rights Council adopts Universal Periodic Review outcome on Ethiopia
With elections coming up in May 2015, urgent and concrete steps are needed to reduce violations of civil and political rights in Ethiopia.� Considering the scale of violations associated with general elections in 2005 and 2010, Amnesty International is deeply concerned that Ethiopia has rejected more than 20 key recommendations on freedom of expression and association relevant to the free participation in the elections and the monitoring and reporting on these. These include in particular recommendations to amend the Anti-Terrorism Proclamation, which continues to be used to silence critical voices and stifle dissent, and recommendations to remove severe restrictions on NGO funding in the Charities and Societies Proclamation.� The independent journalists and bloggers arrested just days before Ethiopia’s review by the UPR Working Group in May 2014 have since been charged with terrorism offences. Four opposition party members were arrested in July on terror accusations, and, in August, the publishers of five magazines and one newspaper were reported to be facing similar charges.
While Amnesty International welcomes Ethiopia’s statement of ‘zero tolerance’ for torture and cruel, inhuman or degrading treatment, and its commitment to adopt preventative measures,� it is concerned by its rejection of recommendations to investigate and prosecute all alleged cases of torture and other ill-treatment and to ratify the Optional Protocol to the Convention against Torture and Other Cruel, Inhuman or Degrading Treatment or Punishment.� The organization continues to receive frequent reports of the use of torture and other ill-treatment against perceived dissenters, political opposition party supporters, and suspected supporters of armed insurgent groups, including in the Oromia region. Amnesty International urges Ethiopia to demonstrate its commitment to strengthening cooperation with the Special Procedures by inviting the Special Rapporteur on Torture to visit the country.� Unfettered access by independent monitors to all places of detention is essential to reduce the risk of torture.
Ethiopia’s refusal to ratify the Convention for the Protection of All Persons from Enforced Disappearance is also deeply concerning in light of regular reports of individuals being held incommunicado in arbitrary detention without charge or trial and without their families being informed of their detention – often amounting to enforced disappearances.�
Ethiopia’s UPR has highlighted the scale of serious human rights concerns in the country. Amnesty International urges the Human Rights Council to ensure more sustained attention to the situation in Ethiopia beyond this review.
Background
The UN Human Rights Council adopted the outcome of the Universal Periodic Review of Ethiopia on 19 September 2014 during its 27th session. Prior to the adoption of the review outcome, Amnesty International delivered the oral statement above.
Amnesty International had earlier submitted information on the situation of human rights in Ethiopia: http://www.amnesty.org/en/library/asset/AFR25/004/2013/en/95f2e891-accc-408d-b1c4-75f20c83eceb/afr250042013en.pdf
Public Document
International Secretariat, Amnesty International, 1 Easton St., London WC1X 0DW, UK www.amnesty.org
****************************************
� Ethiopia accepted a recommendation to ‘take concrete steps to ensure the 2015 national elections are more representative and participative than those in 2010, especially around freedom of assembly and encouraging debate among political parties,’ A/HRC/27/14/Add.1, paragraph 14 (UK)
� A/HRC/27/14, paragraphs 158.22 (United States), 158.32 (Czech Republic), 158. 33 (Switzerland), 158.34 (Czech Republic), 158.35 (Slovenia), 158.36 (Slovakia), 158.37 (France), 158.38 (Ireland), 158.39 (Czech Republic), 158.40 (United States), 158.41 (Australia), 158.42 (Austria), 158.43 (Belgium), 158.44 (Netherlands), 158.45 (Norway), 158.46 (Sweden), 158.47 (Germany), 158.48 (Czech Republic), 158.49 (Hungary), 158.50 (Australia), 158.51 (Austria), 158.52 (Sweden) and 158.53 (United States).
� A/HRC/27/14, paragraph 11; A/HRC/27/14/Add.1, paragraph 10 (Spain).
� Ibid, paragraphs 158.2 (Tunisia), 158.3 (Uruguay), 158.7 (Denmark), 158.8 (Estonia) (Togo), 158.9 (Hungary), 158.13 (Paraguay), 158.29 (Costa Rica) and 158.30 (Austria);
� Ibid, paragraphs 155.48 (Hungary), 155.49 (Chile), 155.50 (Netherlands), 155.51 (Spain) and 157.9 (United Kingdom).
� A/HRC/27/14/Add.1, paragraphs 1 (Madagascar) and 2 (Cape Verde); A/HRC/27/14, paragraphs 158.2 (Tunisia), 158.3 (Uruguay) and 158.11 (France).

ሰኞን በቃሊቲ (ኤልያስ ገብሩ ጎዳና)

September 23, 2014

‹‹መጽሐፉ በመውጣቱ በጣም ደስ ብሎኛል፡፡

‹‹መጽሐፌን በውጭ ሀገር የሚገኙ ኢትዮጵያዊ ወገኖቼም ቢያነቡት ደስ ይለኛል›› ጋዜጠኛ ውብሸት ታዬ

ዛሬ ረፋድ ላይ ከወዳጄ አቤል አለማየሁ ጋር ቃሊቲ ሄደን የቀድሞ የአውራምባ ታይምስ ጋዜጣ ባልደረባችን የነበረውን ጋዜጠኛ ውብሸት ታዬን ለመጠየቅ ተቀጣጥረን ነበር፡፡ አቤል፣ ከቀጠሯችን 20 ደቂቃ ያህል ዘግይቶ መስቀል አደባባይ ደረሰና ደወሎ ተገናኘኝ፡፡ ሁለታችንም በ2007 ዓ.ም በአካል የተገናኘነው ዛሬ ነበር፡፡ ‹‹በ2007 ም ቀጠሮ አታከብርም?›› ብዬ ቀለድኩበት፡፡

ሚኒባስ ታክሲ ተሳፍረን ቃሊቲ ደረስን፡፡ የተለመደ ፍተሻውም ታለፈ፡፡ ነገር ግን፣ እስከዛሬ አጋጥሞኝ የማያውቀው አዲስ ፍተሻ መኖሩን አቤል ነገረኝ፡፡ በዘመናዊ ኤሌክትሮኒክስ ማሽን ጫማ እና ቀበቶን አውልቆ በድጋሚ መፈተሽ ግድ ነበር፡፡ ይህም ታለፈና ‹‹ሸራተን›› ተብሎ ወደሚጠራው የቃሊቲ እስር ቤት አመራን፡፡ ይህንንም የእስረኛ መጠየቂያ ቦታ ስመለከተው ለመጀመሪያ ጊዜ በመሆኑ በማያቸውን ነገሮች ላይ ትኩረት መስጠቴ አልቀረም፡፡

አንድ ጥግ ላይ፣ በአጭር ርዝመት በእንጨት የተሰራች መጠየቂያ ጋር ደርሰን ቆምን፡፡ ለአንዱ ጥበቃ ፖሊስ ውብሸትን
እንዲያሥጠራልን ነገርነው፡፡ ውብሸትም ከደቂቃዎች በኋላ ወደእኛ መጣ፡፡ ፊቱ በፈገግታ ተሞልቶ ነበር፡፡ ብርቱካናማ ቲ-ሸርት
አድርጓል፡፡ በቅድሚያ ያገኘሁት እኔ ነበርኩ፡፡ ተቃቅፈን ሰላምታ እየተለዋዋጥን እያለ ከለበሰው ልብስ አኳያ ‹‹የቀለም አብዮት
ልትጀምር ነው እንዴ?›› አልኩትና ትንሽ ተሳሳቅን፡፡ ከአቤልም ጋር ሰላምታ ከተለዋወጡ በኋላ የጋራ ወጋችንን ቀጠልን፡፡ ብዙ
ሃሳቦች የተወያየነው በቅርቡ ለንባብ ስላበቃው ‹‹የነጻነት ድምጾች›› የሚል ርዕሥ ስላለው የመጽሐፍ ሁኔታ ነበር፡፡ በመጽሐፉ
መውጣት በጣም ደስ ብሎታል፤ ይህም ፊቱ ላይ በግልጽ ይነበባል፡፡ ብዙ መከራን አሳልፎ ይህንን ማየት መቻሉ በጨለማ ውስጥ
እንዳለች ሻማ ይቆጠራል፡፡

ለረዥም ወራት በኩላሊት ህመም እየተሰቃየ ከዝዋይ ወደቃሊቲ ለሕክምና መጥቶ እንኳን የረባ ሕክምና ሳይደረግለት ውሃ ጠጣ
ነበር የተባለው፡፡ ልብ አድርጉ፣ የዝዋይ ውሃ ጠጠር ያለበት መሆኑ እየታወቀ ወደ ዝዋይ እንዲመለስ ተደርጓል፡፡ የወላጅ አባቱን የሞት መርዶ የሰማው በዘዋይ እስር ቤት ነው፡፡ ሌሎች አስቸጋሪ ነገሮች በውብሸት ሕይወት ውስጥ አልፈዋል፡፡ የሚቀየር ነገር ከሌለ ደግሞ 11 የእስር ዓመታቶች ከፊቱ ይጠብቁታል፡፡ ይህ ሁሉ ታልፎ ይህቺን የተስፋ ብርሃን
እንኳ በእስር ቤት ማየቱ ከምር ደስ ይላል – ለሞራሉ!…ይህህ መጽሐፉን ሙሉ በሙሉ አንብቦ የጨረሰው ዓቤል፣ አንዳንድ ጥያቄዎችን ከመጽሐፉ በመነሳት ሲያቀርብለት እሱም ሲያስረዳ እና ሲመልስለት እያለ ወዳጃችን ሰለሞን ሞገስ አጠገባችን ደረሠ፡፡ የውብሸት ጠያቂዎችም ሶስት ሆንን፡፡

‹‹አሁን ከማን ጋር ነው የታሰርከው?›› ስል ጥያቄዬን አቀረብኩለት፡፡ ከገብረዋድ (የቀድሞ የገቢዎች እና ጉምሩክ ባለሥልጣን መ/ቤት ምክትል ዳይሬክተር እና በሙስና ወንጀል ተጠርጥረው ጉዳቸው በፍርድ ቤት እየታየ የሚገኝ) እና ከአንድ ሌላ ልጅ ጋር አንድ ክፍል ውስጥ ነኝ›› አለን፡፡ ገረመኝ፤ አብረው ይሆናሉ ብዬ አልገመትኩም ነበር፡፡

‹‹ለአቶ ገብረዋድ አንድ ጥያቄ ጠይቅልኝ?›› አልኩት ለውብሸት፡፡
‹‹ምን?››

‹‹ከሙስና ወንጀል ተጠርጥረው ከፍተኛ ፍርድ ቤት ሲቀርቡ ለፍርድ ቤቱ አንድ አቤቱታ አቅርበው ነበር፡፡ በወቅቱ እኔም በችሎት ነበርኩ፡፡ ‹በማዕከላዊ ሰብዓዊ መብታቸው መጣሱን ሲናገሩ ገርሞኝ ነበር ያዳመጥኩት፡፡ በእርግጥ ማንም ሰው በእስር ላይ እያለ ሰብዓዊ መብቱ መጣስ የለበትም፡፡ ነገር ግን፣ አቶ ገብረዋድ የመንግሥት ከፍተኛ ሹመኛ በነበሩበት ጊዜ የተቃውሞ ፓርቲ አመራሮች፣አባላት፣ ጋዜጠኞችና በተለያዩ የሙያ ዘርፎች ላይ የሚገኙ ዜጎች በተለያየ ምክንያት ተጠርጥረው ፍርድ ቤት ሲቀርቡ፣ በማዕከላዊ የምርመራ እስር ቤት ሰብዓዊ መብታቸው መጣሱን ለፍርድ ቤት አቤቱታ በተደጋጋሚ ሲያቀርቡ በቀጥታም ይሁን በተዘዋዋሪ መስማታቸው አይርቀም፡፡ ያኔ ዝም ብለው አሁን በራሳቸው ላይ ሲደርስ ስለመብት ጥሰት መናገራቸው ተገቢ ነበር ወይ? የመብት ጥሰት በራስ ላይ ሲደርስ ብቻ ነው ወይ ድምጽን ማሰማት የሚገባው?!›› አልኩት፡፡

ጥያቄዬን አድምጦ እጠይቅልሃለሁ አለኝ፡፡

የተለያዩ ነገሮችን እየተወያየን እያለ አንዲት ወጣት ልጅ ምግብ እና አነስተኛ ጥራቱን የጠበቀ ፍራሽ ይዛ በአቅራቢያችን መጣች፡፡ አቤል ‹‹ገብረዋድ ጋር ነች›› አለ፡፡ ወዲያው አቶ ገብረዋድ መጣ፡፡ ምቾት እና ነጻነት ባልተሰማው መንገድ ‹‹ሰላም ናችሁ›› የሚል ቃል ከአንደበቱ ወጣና ከውብሸት ጀርባ አልፎ ከምትጠይቀው ልጅ ጋር በትግርኛ ቋንቋ መነጋገራቸውን ቀጠሉ፡፡ ጠይቀን እንደተረዳነው ከሆነ ልጁ ነች፡፡ እኔም ጥያቄዬን ለአቶ ገብረዋድ ላቀርብለት አስቤ ከውስጤ ጋር አውርቼ ነበር፡፡ ነገር ግን፣ ከነበርንበት ቦታ አኳያ አመቺ ስላልነበረ ተውኩት፡፡ አቶ ገብረዋድም፣ ቀድሞን ወጣና ፍራሽ እና ምግቡን ይዞ ቻው ብሎን ሄደ፡፡
ውብሸትም መጽሐፉን አስመልክቶ እንዲህ አለን፡- ‹‹መጽሐፉ በመውጣቱ በጣም ደስ ብሎኛል፡፡ መጽሐፉን ሁሉም ሰው ቢያነበውም ደስ ይለኛል፡፡ ስለሀገራችን የእስር ቤት አስቸጋሪ ሁኔታ እና ስለሌሎች ሀገራዊ ጉዳዮች መጠነኛ መረጃ ያገኛል፡፡መጽሐፌን በሀገር ውስጥ ብቻ ሳይሆን በውጭ ሀገር የሚገኙ ኢትዮጵያዊ ወገኖቼም ቢያነቡት ደስ ይለኛል፡፡›› ካለ በኋላ የዳያስፖራ ማኅበረሰብን በተመለከተ ይህቺን ሃሳብ አከለ፡፡

‹‹ዳያስፖራዎች ስለሀገራችን ሁኔታ ያገባናል ስለሚሉ ነው በተለያየ ጊዜ የተለያዩ ጉዳዮች ላይ ድምጻቸውን በማሰማት ሰልፍ የሚወጡት፡፡ ይህን ባያስቡ ኖሮ በየካፌው ቡና እየተጠጣ ዝም ማለት ይቻላል፡፡ ከታሰርኩ በኋላ ‹‹ፍኖተ ነጻነት›› ጋዜጣን የማንበብ ዕድሉን አግኝቼ ነበር፡፡ አንዲት ሴት የእኔን ፎቶግራፍ ደረቷ ላይ አድርጋ [የታሰሩ ጋዜጠኞች እና ፖለቲከኞች ይፈቱ! የሚል] የተቃውሞ ሰልፍ ላይ ድምጻን ያሰማችበትን ምስል ተመለከትኩና፡፡ ሴትየዋ እኔን አታውቀኝም፡፡ ግን የእኔን የእስር ጉዳት ለመቃወም አደባባይ ወጥታለች፡፡ ይህ ለሀገር ከመቆርቆር የሚመነጭ ነው›› ባለኝ መረጃ መሰረት የውብሸት መጽሐፍ ጥሩ እየተሸጠ ይገኛል፡፡ ሁለተኛ ዕትምም በቅርቡ ይገባል፡፡

ከእኛ ራቅ ብሎ የሚገኘው ፖሊስ ከሌሎች ፖሊሶች ጋር ተነጋገረና ‹‹ሰዓት ሞልቷን፤ በቃችሁ›› አለን፡፡ እኛም ውቤን ‹‹አይዞን!›› በማለት አቀፈን የስንበት ሰላምታ ሰጥተነው ተለየነው፡፡ ‹‹አቶ ገብረዋድን ጠይቅልኝ ያልኩህን እንዳትረሳ›› በማለትም በድጋሚ አስታወስኩት፡፡

Monday, September 22, 2014

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ለስራ አጦች በየቤታቸው ለማባበያ ካርድ እያደለ ነው

September 22,2014
• ‹‹ምርጫ ሲደርስ የሚደረግ ነው››
• ‹‹ለኢህአዴግ ጥላቻ አለሽ በሚል አንመዘግብም ብለውኛል››

ነገረ ኢትዮጵያ እንደዘገበው የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሰራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ሴክተር ለስራ አጦች ‹‹ስራ እንሰጣችኋለን›› በሚል በየቤታቸው የስራ ፈላጊዎች መለያ መታወቂያ ካርድ እያደለ መሆኑን የነገረ ኢትዮጵያ ምንጮች ገለጹ፡፡
የስራ ፈላጊዎች መለያ መታወቂያ ካርዱ የሚሰጠው የተማረም ሆነ ያልተማረ እስከ 60 አመት እድሜ ለሚገኝ ማንኛውም ስራ አጥ ነው እንደተባለ ታውቋል፡፡ በሌላ በኩል ከዩኒቨርሲቲ የተመረቁት አዲስ ተማሪዎችና ከአሁን ቀደም ተመርቀው ስራ ያላገኙ ተማሪዎች ‹‹ቀበሌ መጥታችሁ ተመዝገቡ›› እንደተባለ ለማወቅ ተችሏል፡፡
ካርድ የተሰጣቸው ነዋሪዎች የመዘገቧቸው ሰዎች ‹‹ስራ እንሰጣችኋለን፤ ተከታታይ ስብሰባ ስላለ ስራ ለማግኘት ስብሰባውን መሳተፍ ይጠበቅባችኋል›› እንዳሏቸው ገልጸዋል፡፡ካርዱ ከተሰጣቸው መካከል ያልተማሩም የሚገኙበት ሲሆን በተለያየ መስክ በዲግሪ ተመርቀው ስራ ያጡ የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎችን ጨምሮ በርካታ ስራ አጦች እንዳሉ በመጠቆም ስራ የማግኘት ተስፋቸውን እንዲገልጹልን የጠየቅናቸው ነዋሪ ‹‹ስራ እንሰጣችኋለን ብለዋል፤ ከሰጡን ማየት ነው፡፡ ግን ለምርጫ ሳይሆን አይቀርም›› ሲሉ ጥርጣሬያቸውን ገልጸዋል፡፡
በተመሳሳይ ከአሁን ቀደም በቤተሰብ ደረጃ 1ለ5 ተደራጁ ተብለው ሳይደራጁ የቀሩ የቤት እመቤት ‹‹ከአሁን ቀደምም በቤተሰብ ደረጃ 1ለ5 እንድንደራጅ ተጠይቀን ነበር፡፡ አልተደራጀንም፡፡ ምን አልባት ያ አልሰራ ሲል ይሆናል፡፡ ያው ምርጫ ሲመጣ ብዙ ነገር ይመጣል›› ሲሉ የተሰጣቸው ካርድ የምርጫ ማባበያ ሊሆን እንደሚችል ለነገረ ኢትዮጵያ ገልጸዋል፡፡በሌላ በኩል ለገዥው ፓርቲ አሉታዊ አመለካከት አላቸው የሚባሉ ዜጎች እንዳይመዘገቡ የተደረገ ሲሆን እንድትመዘገብ በተጠየቀችበት ወቅት ‹‹ካርዱን ተቀብለን ስንሰበሰብ አባል እንድንሆን አትጠይቁንም?›› የሚል ጥያቄ በማንሳቷ ‹‹ለኢህአዴግ ጥላቻ አለሽ፡፡ አንመዘግብሽም›› እንደተባለች ገልጻለች፡፡
ምንም እንኳ መዝጋቢዎቹ ‹‹ሊስትሮም ቢሆን ስራ ካለው እንዳትመዘግቡ›› መባላቸውን የሚገልጹ ቢሆንም ሱቅና በመሳሰሉት የንግድ ስራዎች የተሰማሩ ዜጎች ‹‹ስራ አጥ›› ተብለው እየተመዘገቡ ይገኛሉ፡፡ ይህም ስራ ከመስጠት ይልቅ ለምርጫ ለማባበልና መረጃ ለመሰብሰብ ሊሆን እንደሚችል ካርድ የተሰጣቸው ነዋሪዎች ለነገረ ኢትዮጵያ ተናግረዋል፡፡

የዓለም ባንክ ኢትዮጵያ ለብድር ዕዳ አደጋዎች የመጋለጥ ዕድሏ እየሰፋ ነው አለ

September22,2014
ሰሞኑን ለሦስት ቀናት ጉብኝት ወደ ኢትዮጵያ መጥተው የነበሩት የዓለም ባንክ ማኔጂንግ ዳይሬክተርና የኦፕሬሽን ዋና ኃላፊ ስሪ ሙሊያኒ ኢንድራዋቲ፣ እያደገ የመጣው የብድር ዕዳ መጠን በኢትዮጵያ ላይ አደጋዎችን ሊያስከትል እንደሚችል ገለጹ፡፡
ኢንድራዋቲ ባለፈው ረቡዕ ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ እንዳስታወቁት፣ ምንም እንኳን የአገሪቱ የብድር ዕዳ መጠን ከጠቅላላ የአገር ውስጥ ምርት አኳያ ያለው ድርሻ አነስተኛ ቢሆንም፣ የዕዳውን መጠን በግልጽነት ለማስተዳደር የሚችልና ግልጽነት የሰፈነበት አስተዳደር ማስፈን የመንግሥት ግዴታ መሆኑን አስታውቀዋል፡፡
የገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስቴር ይፋ ያደረገው መረጃ እንደሚያመለክተው፣ አገሪቱ ያለባት ጠቅላላ የብድር መጠን 20 ቢሊዮን ዶላር ደርሷል፡፡ ከዚህ ውስጥ 12 ቢሊዮን ዶላር ከውጭ ምንጮች የተገኙ ብድሮችን የሚሸፍን የዕዳ መጠን ነው፡፡ በዚህ መሠረት ከጠቅላላ አገር ውስጥ ምርት አኳያ የዕዳው ድርሻ 44 ከመቶ መድረሱን ይጠቁማል፡፡
ኢንድራዋቲ እንደሚገልጹት፣ ይህ አኃዝ ዝቅተኛ በሚባለው የዕዳ ደረጃ ላይ የሚገኝ ነው፡፡ ነገር ግን የመንግሥት የኢንቨስትመንት ወጪዎች እየተበራከቱ በመምጣታቸው ምክንያት የዕዳ መጠኑን በዚያው ልክ እያደገ በመሆኑ፣ የመንግሥት የልማት ድርጅቶችን በሚመለከት ከጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለ ማርያም ደሳለኝና ከሚመለከታቸው ሚኒስትሮች ጋር መነጋገራቸውን አስረድተዋል፡፡ ከውይይቶቹ መካከልም በመንግሥት አስተዳደር ማሻሻያ ሪፎርሞች ላይ ያተኮረው አንዱ እንደነበር አስታውሰዋል፡፡ በዚህም መንግሥት በአስተዳደራዊ መዋቅሮቹ ላይ ማሻሻያ በማድረግ፣ ግልጽነትና ኢኮኖሚውን በብቃት የማስተዳደር ጉዳዮች ላይ ተወያይተዋል፡፡
የመንግሥት የልማት ድርጅቶች በየጊዜው እየጨመረ የመጣውን የኢንቨስትመንት ወጪን መነሻ በማድረግ፣ በኢትዮጵያ እየጨመረ የሚገኘውን የብድር ዕዳ መጠንና ሊከሰት የሚችለውን አደጋ ለመቋቋም የሚያስችል አሠራር ማምጣት እንደሚገባቸው መክረዋል፡፡
‹‹ይህንን ለማከናወን አስተማማኝ የፋናይናንስ ሪፖርት ያስፈልጋል፡፡ ግልጽነትና ወጥነት በጣም ጠቃሚ ነው፡፡ ተዓማኒነት ያለው መረጃ መኖሩ ግድ ይላል፡፡ አሁን እየታየ ያለው የብድር ሁኔታ በኢትዮጵያ ላይ ተጨማሪ የተጋላጭነት አደጋ ማስከተሉ በእርግጠኝነት የማይቀር ነው፤›› ብለዋል፡፡ ኢትዮጵያ የብድር ዕዳዋን ለማቃለል የወጪ ንግድ ሚዛኗ ወሳኝ መሆኑን ኢንድራዋቲ ገልጸዋል፡፡ ሆኖም ባለፉት ሦስት ዓመታት በወጪ ንግድ መስክ አገሪቱ ዝቅተኛ ውጤት ስታዝመገዘብ መቆየቷ ለብድር ዕዳ ያላትን ተጋላጭነት አስፍቶታል ይባላል፡፡
አገሪቱ ስታዝመግብ የቆየችው የኢኮኖሚ ዕድገት መልካም የሚባል መሆኑን የጠቀሱት ኢንድራዋቲ፣ ይህም ሆኖ ኢኮኖሚው መዋቅራዊ ለውጥ ለማምጣት ብዙ እንደሚቀረው ገልጸዋል፡፡ የኢኮኖሚው ዕድገት በርካታ የሥራ መስኮችን ሊፈጥሩ የሚችሉ አምራች ኢንዱስትሪዎችን ለማምጣት ብዙ መንገድ ይቀረዋል ያሉት ማኔጂንግ ዳይሬክተሯ፣ ባንኩ የኢንዲስትሪ ዞኖች ግንባታን ፋይናንስ እያደረገ እንደሚገኝም አስታውሰዋል፡፡ በአዲስ አበባ ቦሌ ለሚ ሁለተኛ ምዕራፍና በአቃቂ ቃሊቲ ቂልንጦ አካባቢ ለሚገነቡ ሁለት የኢንዱስትሪ ዞኖች የሚውል የ250 ሚሊዮን ዶላር ብድር መፍቀዱን፣ በኢትዮጵያ የባንኩ ዳይሬክተር ጉዋንግ ዚ ቼን ገልጸዋል፡፡
ባንኩ ለመሠረተ ልማት ከሚሰጠው ድጋፍ በተጨማሪ በኢትዮጵያ ለመሠረታዊ ሴፍቲኔት ፕሮግራምም ድጋፍ ያደርጋል፡፡ ተዘዋውረው በጎበኟቸው የሴፍቲኔት ጣቢያዎች ጥሩ ውጤት እንዳዩ ማኔጂንግ ዳይሬክተሯ ተናግረው፣ እየጨመረ በመጣው የከተሞች የምግብ እጥረት ተጋላጭነት ሳቢያ በድምሩ አሥር ሚሊዮን ሰዎች በሴፍቲኔት ፕሮግራም ይታቀፋሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ ይፋ አድርገዋል፡፡
ስሪ ሙልያኒ ኢንድራዋቲ የዓለም ባንክን ከመቀላቀላቸው አስቀድሞ የኢንዶኔዥያ የፋይናንስ ሚኒስትር በመሆን አገልግለዋል፡፡ ከዚህ በተጨማሪም የኢኮኖሚ ጉዳዮች አስተባባሪ ሚኒስትር በመሆንም ሠርተዋል፡፡ እ.ኤ.አ. በ2010 የዓለም ባንክን የተቀላቀሉት ኢንድራዋቲ፣ በምክትል ፕሬዚዳንትነት ደረጃ የሚመሯቸው በርካታ መስኮች አሉ፡፡ በማኔጂንግ ዳይሬክተርነት ሥልጣናቸው የባንኩን የአካባቢያዊ ሥራዎች በጠቅላላ የመምራት ኃላፊነት ተሰጥቷቸዋል፡፡

Sunday, September 21, 2014

የወያኔውን የከፋፍለህ ግዛ ስርዓት ለመጣል በአንድነት እንነሳ!!!

Septenber21,2014
ዛሬም እንደ ትናንቱ ምንም የማያውቁ ህጻናት ዋይታ!!! የሴቶችና አረጋዊያን ሌላ ዙር መፈናቀል! ሌላ ዙር የጅምላ ስደት መራር መርዶ ከወደ ጋምቤላ
የግጭቱ ስረ መሰረት እንዲህ ነው። የህወሓት አገዛዝየአካባቢውን ማኅበረሰብ በማፈናቀልና ለም መሬታቸውን ቀምቶ በኢንቨስትመንት ስም ባብዛኛው ካንድ አካባቢ ለመጡ የወያኔ አባላት ቀደም ሲል ለሰሩት ወንጀል ማካካሻ እንዲሆን ታስቦ ካቅማቸው በላይ ቸራቸው። እነሱም ያለምንም ይሉኝታና ያካባቢውን ማኅበረስብ ያኗኗር ሁኔታ በጭራሽ ከግምት ሳያስገቡ ጌታዋን እንደተማመነች በግ ያካባቢው ማኅበረሰብ ለዘመናት ሲወርድና ሲዋረድ ጠብቆ ያቆየውን ጥብቅ ደን እየመነጠሩ የጣውላና የከሰል ንግድ ላይ ተሰማሩ።
የአካባቢው ማኅበረሰብ ግን የበይ ተመልካች ሆነ፣ ቅሬታውን ለባለስልጣናት አቤት ቢልም ሰሚ አላገኘም። ጭራሽ ይባስ ብለው በቀየው የተገኘውን ሴት ወንድ ሳይመርጡ በፌደራል ፖሊስ በመቀጥቀጥ ብዙዎችን ለሞት ሲዳርጓቸው ሌሎችን ደግሞ ቁስለኛ አድርገዋል። ከሞትና ከመቁለት የተረፉትም ተፈናቅለው ዱር ገደሉን ቤታቸው አድርገዋል። በሌላም በኩል የግጭቱ ሰለባ የሆኑት ከሌላ ክልል መጥተው ለረዝም ጊዜ ባካባቢው ኑዋሪ የሆኑ ኢትዮጵያዊን ዜጎችም የግጭቱ ሰለባ ከመሆነ አልተረፉም ፣እነሱም ሞትና ቁስለኛ ሆነዋል። ከሞትና ከመቁሰልም የተረፉት በቴፒ ከተማ አውላላ ሜዳ ላይ ተበትነው ምንም የማያውቁ ሴቶችና ህጻናት ቀን በጸሀይ ሌሊት በቁር እየተጠበሱ ይገኛሉ። እጅግ የሚያሳዝነው ግጭቱን የሚባብሱትና በዋና ተዋናይነት የሚተውኑት የወያኔው ቅጥረኞች የሆኑ የአካባቢ ካድሬዎችና መሬቱን ያላግባብ የቀሙ ያንድ አካባቢ ተወላጆችና ያንድ አካባቢ የፌደራል ፖሊስና የመከላከያ የበላይ ሹማምንት መሆናቸው ነው።
እንዲህ ዓይነቱ የወያኔ ሴራ ዛሬ የተጀመረ አዲስ ክስተት አይደለም። ህወሓት ገና ከመጀመሪው ሲፈጠር አብሮት የነበረና ላለፉት ሃያ ሶስት ዓመታት የቀጠለ እዳ ነው። ይህ ህወሓት ኢትዮጵያዊያንን እርስ በራስ በማጋጨት ለዘመናት ለመግዛት አስቦና አልሞ የተነሳበትና ከኢጣሊያን ቅኝ ገዝ የተማረው ስልት ነው፤ ይህ የህወሓት ባንዳነት ውጤት ነው።
ባለፉት አመታት በጉራ ፈርዳና በቤንሻንጉል ክልል የተፈናቀሉትን ኢትዮጵያዊን ለዘመናት ከኖሩበት ስፍራ ሲፈናቀሉ ያየነውም ይህንኑ የፋሽስታዊ ስርዓታቸው መገለጫው የሆነውን ዘር ለይቶ ማፈናቀልና ማሳደድን ነው።
በጋምቤላ ክልል በሜጢ ከተማና አካባቢው የንጹሀን ዋይታና ሰሚ ያጣ ጩኸት ሁላችንንም፤ ማለትም ኢትዮጵያዊያንን ሁሉ በእጅጉ ሊያሳስበንና ይገባል። በቶሎ ባንድነት ተረባርበን ካላስቆምነው መዘዙ የምንወዳት ሀገራችንን እንዳልነበረች ሊያደርግ የሚችል አደገኛ ሁኔታ ነው።
ግንቦት 7 የፍትህ የነጻነትና የዲሞክራሲ ንቅናቄ ይህንን ተገነዝቦ ስርዓቱን በሁለገብ ትግል ለመስወገድ ወሳኝ ምዕራፍ ላይ ይገኛል፣ በመሆኑም የህዝብ ወገኖች በሙሉ ትኩረታችንን ወያኔ ላይ ብቻ እናድርግ። የወያኔን ከፋፍለህ ግዛ እምቢ በማለት ስርዓቱን ከጫንቃችን አውርደን ለመጣል በሚደረገው ትግል ላይ እንድንረባረብ ግንቦት 7 ጥሪውን ያቀርባል።
ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ!!!