Thursday, August 21, 2014

መለስን ቅበሩት!(ተመስገን ደሳለኝ)

August 21, 2014

ከኢትዮጵያ ሀገሬ የደቀቀ ኢኮኖሚ ላይ በማን አህሎኝነት ወጪ ተደርጎ፣ ቅጥ ባጣ መልኩ በመላ አገሪቱ እየተከበረ ስላለው የቀድሞ አምባገነን ጠ/ሚኒስትር ሁለተኛ ሙት ዓመት ዝክርም ሆነ ሰውየውን ዛሬም በአፀደ-ህይወት ያለ ለማስመሰል እየሞከሩ ላሉት ጓዶቹ አንዲት ምክር ብጤ ጣል ማድረጉ ተገቢ ነው ብዬ ስለማስብ በአዲስ መስመር እንዲህ እላለሁ፡-

አብዮታዊው ገዥ-ግንባር ግንቦት ሃያ፣ የህወሓት ምስረታ፣ የብአዴን አፈጣጠር፣ የኦህዴድና የደኢህዴን ውልደት፣ የብሔር ብሔረሰቦች በዓል፣ የባንዲራ ቀን፣ የመከላከያ ሳምንት፣ የፍትሕ ሳምንት፣ የሕዳሴ ግድብ መሰረት ድንጋይ የተጣለበት… ጅኒ-ቁልቋል እያለ ዓመቱን ሙሉ በማይጨበጥ ተራ ፕሮፓጋንዳ ማሰልቸትን መንግስታዊ ኃላፊነት አድርጎታል፡፡ ይህ እንግዲህ ለቁጥር የሚያታክቱ፣ በነጭ ውሸት የታጨቁ እና በአብዮታዊ ዲሞክራሲ ቅኝት የተንሸዋረሩ ‹ዶክመንተሪ ፊልሞቹ›ን ረስተንለት ነው፡፡

ይህ ሁሉ ያልበቃው ‹‹ጀግናው›› ኢህአዴግ ከጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ህልፈት ወዲህ፣ ወርሃ-ነሐሴንም እንደ ግንቦት ሃያው ሁሉ የሟቹን ታጋይነትና አብዮታዊነት፤ ሕዝባዊነትና አርቆ አስተዋይነት፤ የርዕዮተ-ዓለም ተራቃቂነትና የአየር ንብረት ተካራካሪነት፤ በፖለቲካ ቢሉ በኢኮኖሚ ቁጥር አንድ ጠቢብነትና ባለራዕይነት፤ ፍፁም ፃድቅነትና ሰማዕትነት…. የሚተረክበት ሲያደርገው ቅንጣት ታህል ሀፍረት አልተሰማውም፡፡ ሰሞኑን በ‹‹ኢትዮጵያ›› ቴሌቪዥን ግድ ሆኖብን ተመልክተንና ሰምተን በትዝብት ካሳለፍናቸው ‹‹መለስ፣ መለስ›› ከሚሉ የከንቱ ውዳሴ አደንቋሪ ድምፆች በተጨማሪ፣ የኦሮሞን ባሕላዊ ልብስ ሲያለብሱት፣ ሐረሪዎች ጋቢ ሲደርቡለት፤ በደቡብ የሚገኙ ብሔሮች የየራሳቸውን ባሕል የሚወክሉ አልባሳት ሲሸልሙት፣ ስለወላይታነቱ ሲመሰክሩለት…

ደጋግመን ለመመልከት ተገደናል፤ ይሁንና ድርጅቱ ስለ ቀድሞ ሊቀ-መንበሩ አልፋና ኦሜጋነት ለመስበክ ዙሪያ ጥምዝ ከዳከረለት ከእንዲህ አይነቱ የተንዛዛ ፕሮፓጋንዳ ይልቅ፣ በዚሁ የቴሌቪዥን መስኮት የቀረበ አንድ ጎልማሳ ‹‹መለስ ሁሉም ማለት ነው›› ሲል የሰጠው አስተያየት፣ ቅልብጭ አድርጎ ይገልፅለት ነበር ብዬ አምናለሁ፡፡ የዚህ አይነቱ ምጥን አስተያየትም በጥራዝ ነጠቅነት ዘላብዶ የኋላ ኋላ በሀፍረት ከማቀርቀር ያድናል፡፡ ለምሳሌ እናንተ የግንባሩ ካድሬዎች ስለመለስ ምሁርነት ለመናገር ስትዳዱ ሁሌ የምትደጋግሙት፣  ያንኑ የአብዮታዊ ዴሞክራሲ አርቃቂነቱ እና የልማታዊ ዴሞክራሲያዊ መንግስት ኀልዮት አዋቃሪነቱ ነው፡፡ ግና፣ ይህ ‹‹ንድፈ-ሃሳብ›› ተብዬ ራሱ በርዕዮተ-ዓለምነት ለመጠራት የማይበቃ የተውሸለሸለ ጭብጥ ስለመሆኑ በርካታ ምሁራን በጥናቶቻቸው ከማስረገጣቸው ባሻገር፣ አገሪቷን ለከባድ ኢኮኖሚያዊ ድቀት፣ ሕዝቧን ደግሞ ለጥልቅ ድህነት መዳረጉን ብቻ ማስታወሱ በቂ ይሆናል፡፡ ስለልማታዊ መንግስት አዋጭነት በብቸኝነት እንደተከራከረ ተደርጎ የሚለፈፈውን እንኳን ንቆ መተው ሳይሻል አይቀርም፡፡ ከታንዲካ ማካንደዋሬና መሰል የፅንሰ-ሃሳቡ አበጂዎች የዘረፋቸውን መከራከሪያዎች ማን ዘርዝሮ ይዘልቀውና፡፡ ‹መለስን ቅበሩት› የምለውም፣ እንዲህ ያሉ አስነዋሪ ማንነቶቹን ማስታወስ ስለሚያም ነው፡፡

እናም እውነት እውነት እላችኋለሁ፡- ስለሰውዬው የምትነግሩን እና የምታስቀጥሉት ‹ሌጋሲ›ም ሆነ የምትተገብሩት ረብ ያለው አንድም ራዕይ የለምና ዝም፣ ፀጥ ብላችሁ የምራችሁን ቅበሩት፡፡ እስቲ! ኦጋዴንን ተመልከቱ፤ ካሻችሁም ወደ አኝዋኮች ተሻገሩ፤ ያን ጊዜ እናንተ በአርያም የሰቀላችሁት ሰው፣ ለነዚህ ሁለት ብሔሮች የቀትር ደም የጠማው ጨካኝ መሪ እንደነበር፣ በክፋት ትዕዛዞቹ ጥፋት ከተረፈ ጠባሳ ትረዱታላችሁ፡፡ ለአቅመ-ሔዋን ያልደረሱ ህፃናት በሰልፍ የሚደፈሩባት፣ ወጣቶች እንጀራ ፍለጋ በተስፋ-ቢስነት ጥልቁን ውቅያኖስ ሰንጥቀው ለመሰደድ የማያመነቱባት፣ የጤና ኬላ ማግኘት ተስኗቸው በልምሻ የሚባትቱ ብላቴኖችን በአቅም-የለሽነትና በቁጭት የምናስተውልባት ደካማ አገር አስረክቦን እንዳለፈ ከወዴት ተሰወረባችሁ? ከቀዬዎቻቸው በጉልበት ለተፈናቀሉ ወገኖች በመቆርቆር ‹‹ሕግ ይከበር!›› ባሉ በየጉራንጉሩ ወድቀው እንዲቀሩ የተፈረደባቸው ጎበዛዝትን ሬሳ እንድንቆጠር ያደረገን ደመ-ቀዝቃዛ ‹መሪ› እንደነበረስ ስንት ጊዜ እያስታወስን እንቆዝም? ቀደምት አባቶች ወራሪውን ፋሽስት ለማንበርከክ የተዋደቁባቸው ጢሻና ኮረብቶች በዚህ ዘመን የዜጎች ወደሞት አገራት መሸጋገሪያ ጽልማሞቶች የሆኑት በማን ሆነና ነው? ከሕግ ተጠያቂነት ቢያመልጥ፣ ከታሪክ ተወቃሽነት ልትታደጉት የምትችሉ ይመስላችኋልን?

…ይልቅ እመኑኝ! ፀጥ ብላችሁ ላንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ጥልቅ ጉድጓድ ቆፍራችሁ ቅበሩት! ላይመለስ በመሄዱም እንደ ግልግል ቆጥራችሁት እርሱት!! መቼም በገዛ ራሱ ሕዝብ ላይ ትውልዶች ይቅር ሊሉት የሚሳናቸውን ይህን መሰሉ መከራ ላዘነበ ሰው በአፀደ-ስጋ ሳለም ሆነ በበድን የሙት መንፈሱ ስር በየዓመቱ ለአምላኪነት መንበርከክ፣ የናንተን አልቦ ማንነት እንጂ ሌላ አንዳች የሚነገረን ቁም ነገር ጠብ ሊለው አይችልም፡፡ ይህም ሆኖ ለመለስ አምልኮ እጅ መስጠት አሳፋሪነቱ፣ ለካዳሚዎቹ ብቻ መሆኑን መስክሮ ማለፉ የቀሪዎቻችን ዕዳ እንደሆነ መገንዘብ አለብን፡፡

ዳኞች ካድሬ ሲሆኑ እንደማየት የመሰለ የአገር ዉድቀት የለም – ግርማ ካሳ

August21/2014
አገሩን እና ሕዝቡን የሚወድ ። እንደ ሌሎች በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያዉያን፣ ኢትዮጵያ ከግፍ አገዛዝ ተላቃ ዜጎች መብታቸዉና ነጻነታቸው ተጠበቆ፣ ተከባብረዉ በስላም የሚኖሩባት አገር እንድትሆን፣ የሚያደርጉትን ትግል የተቀላቀለ ነው። ወጣት ነው። ጉልበትና አቅም አለው። እንደ አንዳንዶች በጥቅም ተታሎ አደርባይነትን መምረጥ ይችል ነበር። ነገር ግን አላደረገዉም። «ሰዉ ያለ ነጻነቱ ምንድን ነው ? » ብሎ ለነጻነቱ ቆመ። የባለ ራእዩ ወጣቶች ማህብርን ከዚያም የአንድነት ፓርቲን ተቀላቀለ። በአንድነት ፓርቲ የአዲስ አበባ መዋቅር የቦሌ ወረዳ አመራር አባል ሆኖ ይሰራ ነበር። በሶሻል ሜዲያዉም ብዙ ጊዜ ድምጹን ያሰማል። አይፈራም። ወኔ አለው።
ጥላዬ
በቅርቡ በአንድነት ፓርቲ ዉስጥ እየተደረገ በነበረዉ፣ ዉህዱን ፓርቲ ለመምራት በተደረገው የምርጫ ፉክክር «አዲስ አመራር ያስፈልጋል» በሚል ለአቶ በላይ ፍቃደ ይቀሰቅስ ነበር። ለዉጥ ፈላጊ ነው።
ነሐሴ 4 ቀን 2006 ዓ.ም ፣ ዜጎችን ማሰርና ማሰቃየት የለመደባቸው የአገዛዙ ታጣቂዎች ከየአቅጣጫው ተረባረቡበት። ምክንያቱ ለጊዘው ባልታወቀ ሁኔታ ወደ ወህኒ ወረወሩት። ይህ ወጣት ፣ ብዙዎች የማያወቁት፣ የማደንቀዉን የማከብረው ጥላዬ ታረቀኝ ይባላል።
ፖሊሲ ፍርድ ቤት ይዞት በቀረበ ጊዜ፣ «በሰው ላይ ጉዳት አድርሷል» የሚል ክስ ነበር ያቀረበበት። ፖሊሲ በሰው ላይ ጉዳት አደረሰ የሚል ክስ አቅርቦ ጉዳት ደረሰበትን የተባለው ግለሰብ ግን ለማቅረብ አልቻለም። «ጉዳይ ደረሰበት የተባለውን ሰው ማግኘት አልቻልኩም» ብሎ መረጃዎችን ለማሰባሰብ ጊዜ እንዲሰጠው ጠየቀ። ወጣት ጥላዬ ግን ለፍርድ ቤቱ ፣ «የያዙኝ ደህንነቶች እየመጡ ከእኛ ጋር ለመስራት ፈቃደኛ እስካልሆንክና የምንሰጥህን ተልዕኮ እስካልፈፀምክ እዚህ ትበሰብሳለህ እንጂ አትወጣም» እያሉ እንደሚዝቱበት አስረዳ። ዳኛው ግን መረጃ ባልቀረበበት እና በወጣት ጥላዬ ላይ በፖሊሶች ዛቻና ማስፈራሪያ እየተሰጠ ባለበት ሁኔታ፣ በዋስ እንዲፈታ ሳይፈቅ ቀረ። ለነሐሴ 12 ፖሊሲ መረጃዎቹን አጠናቆ እንዲያቀርብ ትእዛዝ ሰጠ።
ጉዳት ደረሰ የተባለው ከሁለት ወራት በፊት፣ በሰኔ 12 ቀን 2006 ዓ.ም ነው። በቀጠሮዉ ቀን፣ ፍርድ ቤቱ «ሁለት ወራት ሙሉ የት ነበራችሁ? ለምንስ ጉዳት የደረሰበት ሰው አላቀረባችሁም ? » ሲል ጠየቀ። ፖሊሶች «ጉዳይ የደረሰበትን ሰው ልናገኘው አልቻልንም። የሕክምና ማስረጃ እንድናቀርብ ይፈቀድልን» ብለው ተጨማሪ ቀናት እንዲሰጣቸው ጠየቁ። ወጣት ጥላዬ «የአንድነት ፓርቲ አባል በመሆኔ፣ ባለኝ የፖለቲካ አመለካከት ጫና ለማሳደር የተወጠነ ውጥን» ነው ሲል ከፍርድ ቤቱ ፍትህን ጠየቀ።ፍርድ ቤቱ ግን አሁን ለሰላማዊ ዜጎች ፍትህን ነፈገ። ወጣት ጥላዬ በወህኒ እንዲቆይ ተደርጎ ተለዋጭ ቀጠሮ ለነሐሴ 14 ቀን 2006 ዓ.ም ተሰጠ።
አስቡት፣ የሕክምና መረጃ ያለ ባሌበቱ ሆስፒታሎች መስጠት የለባቸውም። (የአገር ደህንነትን የሚነካ ካልሆነ በቀር)። አሁን፣ ፖሊስ እያለ ያለው፣ ታከመ የተባለው ሰው ፍቃድ ሳይጠየቅ፣ የህክማን ማስረጃ ከሃኪም ቤቶች እንደሚያቀርብ ነው። ለነገሩማ የሆስፒታል አስተዳዳሪዎች ዉሸትን ጨማምረው፣ ያለዉን እንደሌለ፣ የሌለዉን እንዳለ አድርገው መረጃ መስጠታቸው አይቀርም። በተለያዩ ጊዜያት በሌሊት የሚገደሉ፣ በረሃብና በጠኔ የሚሞቱ ብዙ ናቸው። በአገር ቤት ችግር እንደሌለ የዉሸት ገጽታ ለማቅረብ የሚፈልገው አገዛዙ፣ ሆስፒታሎች የዉሸት አታብሲ (የሞት ይሕክምና ማረጋገጫ) እንዲጽፉ እንደሚያደርጓቸውም ያው አገር ሁሉ የሚያወቀው ሐቅ ነው።
እንግዲህ ይሄ ሁሉ የሚያሳየው ሁለት ትላልቅ ነጥቦች አሉ።
1. ብዙዎቻችን በጣም የሚታወቁ ግለሰቦች ሲታሰሩ ነው የአገዛዙ ዜጎችን የማሸበርና የማወክ ተግባር የሚታየን። ነገር ግን በአገራችን እየተደረገ ላለው እልህ አስጨራሽ ትግል፣ ብዙ የማናውቃቸው ወገኖቻችን ትልቅ ዋጋ እየከፈሉ ነው። ከነዚህም አንዱ ወጣት ጥላዬ ታረቀኝ ነው።
2. በኢትዮጵያ አገራችን ባሉ ፍርድ ቤቶች እየታየ ያለው፣ ፍትህን የማስከበር ሥራ ሳይሆን፣ ፍጹም አሳፋሪ፣ ኋላ ቀርና አሳዛኝ የፍርድ መዛባት እንደሆነ ነው። ፖሊስ ዜጎችን እንደፈለገ ሲያስርና ሲያሸብር፣ በፈለገ ጊዜ ተጨማሪ ቀጠሮ ሲጠይቅ፣ ዳኞች ቅንጣት እንኳን የሕግ ባለሞያዎች የስነ-ምግባር ኮድ (ኤቲክስ) ሕሊናቸውን ወቅሷቸው፣ ትክክለኛ ነገር ሲሰሩ እንደማይታዩ ነው። ዳኞች ካድሬ ሲሆኑ ደግሞ ከዚህ የበለጠ ለአገር ዉድቀት የለም።
ገዢዎች ይኸው ስልጣን ከያዙ ጀመሮ እንደገደሉና እንዳሰሩ ናቸው። ሕግን መቀለጃ እያደረጉ ናቸው። ነገር ግን በዱላ፣ በጠመንጃ፣ በማስፈራራት፣ በዛቻ ኢትዮጵያዉያን ለመብታቸው፣ ለነጻነታቸውና ለአንድነታቸው የሚያደርጉት ትግል ሊገቱ አይችሉም። እሳት የለበሱ፣ በወኔ የተሞሉ፣ የስለጠነ ፖለቲካ የሚያራምዱ፣ በአንድ ቦታ ብቻ ሳይሆን በመላ አገሪቷ የሚኖሩ፣ አገዛዙ ከዘረጋዉን የጎሳ ድንበር አልፈው በሰብእናና በኢትዮጵያዊነት የተሳሰሩ በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ እንደ ጥላዬ ታረቀኝ ኢትዮጵያ አፍርታለች።

መኢአድ ከአንድነት ጋር ለሚካሄደው ውህደት ምርጫ ቦርድ እንቅፋት ሆኗል አለ

August 21/2014
ከመኢአድ የተገለለው ቡድን የምርጫ ቦርድን ሐሳብ ይደግፋል
መኢአድ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ከአንድነት ጋር ልፈጽም ያቀድኩትን ውህደት እያስናከለ ነው ሲል ከሰሰ፡፡
33b5461297b045e11af9807754b39b7f_Lየመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት (መኢአድ) እና አንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትሕ ፓርቲ (አንድነት) ውህደት ለመፈጸም ሲያካሂዱ የቆዩት ድርድር በመግባባት ቢጠናቀቅም፣ በመኢአድ ጠቅላላ ጉባዔ ሒደት ላይ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ጥያቄ በማንሳቱ ሊቋጭ እንዳልቻለ መኢአድ አስታውቋል፡፡
መኢአድ ነሐሴ 13 ቀን 2006 ዓ.ም. በጽሕፈት ቤቱ በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የተለያዩ ምክንያቶችን በመፍጠር ውህደቱ እንዳይሳካ በመሥራት ላይ እንደሚገኝ አስታውቋል፡፡
የመኢአድ ፕሬዚዳንት አቶ አበባው መሐሪ እንደገለጹት፣ የመኢአድ ጠቅላላ ጉባዔ አባላት 600 ናቸው፡፡ ፓርቲያቸው ሐምሌ 13 እና 14 2005 ዓ.ም. ባካሄደው ጠቅላላ ጉባዔ 390 አባላት ተገኝተዋል፡፡ ነገር ግን ምርጫ ቦርድ በስብሰባው የተገኙ የጠቅላላ ጉባዔ አባላት 285 ብቻ በመሆናቸው ምልዓተ ጉባዔው አልተሟላም በሚል ምክንያት በጉባዔው የተላለፉ ውሳኔዎችን አልተቀበለም፡፡
ምንም እንኳን እርሳቸው ይኼን ቢሉም፣ በኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድ የአገልግሎትና ግንኙነት ዘርፍ ቢሮ ምክትል መምርያ ኃላፊ አቶ ወንድሙ ጎላ፣ ‹‹በወቅቱ አባሎቻችን በርካታ ስለነበሩ የጠቅላላ ጉባዔ አባላትን ቁጥር 600 አድርገናል፡፡ አሁን ግን አባሎቻችን ስለቀነሱ ያን ማድረግ አንችልም፡፡ ያለን 285 ነው፡፡ የምትቀበሉን ከሆነ አስተያየት አድርጋችሁ ተቀበሉን፡፡ አለበለዚያ ምንም ማድረግ አንችልም፤›› የሚል ምላሽ ማግኘታቸውን መዘገባችን ይታወሳል፡፡
‹‹ጉባዔው በ390 አባላት የተካሄደ ስለመሆኑ በቂ መረጃ አለ፡፡ ምርጫ ቦርድ ሆን ብሎ ፓርቲውን ለማፍረስ ከሚንቀሳቀሱ ኃይሎች ጋር እያበረ ነው፤›› ሲሉ አቶ አበባው በምሬት ተናግረዋል፡፡
ምርጫ ቦርድ እዚህ ውሳኔ ላይ ሊደርስ አይገባውም የሚለው የመኢአድ መግለጫ፣ ከምርጫ ቦርድ በተጨማሪ እየተፈጠሩ ላሉት ችግሮች ቀደም ሲል የመኢአድ አባል የነበሩና በዲሲፕሊን ጥሰት ምክንያት ከፓርቲው የተወገዱ አባላትን ተጠያቂ አድርገዋል፡፡
ፓርቲው እንደሚለው በዲሲፕሊን ምክንያት የተወገዱ 14 አባላት ሲሆኑ፣ እነዚህ የተወገዱ አባላት ባለፈው እሑድ ነሐሴ 11 ቀን 2006 ዓ.ም. ከማለዳ ጀምሮ ከመንግሥት የፀጥታ ኃይሎችና ከኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ባልደረቦች ጋር የፓርቲው ጽሕፈት ቤት ላይ ወረራ ፈጽመዋል ብሏል፡፡
በዚህ ሒደት ጽሕፈት ቤት ውስጥ የነበሩት አባላት እንዳይወጡ፣ ለመግባት የሞከሩ አባላት ደግሞ ወደ ጽሕፈት ቤቱ እንዳይገቡ እስከ ቀትር ድረስ አግተው ውለዋል በማለት አቶ አበባው ገልጸዋል፡፡
ይህ ቡድን ከአራት ዓመት በፊት በዲሲፕሊን ጥሰት ከፓርቲው የተወገደና በፍርድ ቤትም እንዲወገድ የተወሰነበት መሆኑን መኢአድ በመግለጫው ጠቅሶ፣ ነገር ግን ከመንግሥት የፀጥታ ኃይሎች ጋር በመሆን ፓርቲው ላይ ከፍተኛ ጥፋት በመፈጸም ላይ መሆኑን አብራርቷል፡፡
የፓርቲው ፕሬዚዳንት አቶ አበባው እንደገለጹት በዲሲፕሊን የተወገደው ቡድን ወደ ፓርቲው ለመመለስ ፍላጐት አሳይቷል፡፡ ነገር ግን ዕርምጃ የተወሰደበት ቡድን በመሆኑ የመኢአድ የሥራ አስፈጻሚ በሽማግሌዎች አማካይነት የቡድኑን ጥያቄ ለጠቅላላ ጉባዔ ለማቅረብ በሒደት ላይ እያለ፣ ቡድኑ ይህንን ተግባር መፈጸሙ እንዳሳዘናቸው ጠቅሰዋል፡፡
መኢአድ በዲሲፕሊን ተወግደዋል ካላቸው የቀድሞ አመራሮች አንዱ የሆኑት የፓርቲው የቀድሞ ዋና ጸሐፊ አቶ ማሙሸት አማረ ለኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ድርጅት እንደገለጹት፣ መኢአድ ከአንድነት ጋር ውህደት ለማድረግ ፍላጐት ያለው ቢሆንም፣ ድርጅቱ ጠቅላላ ጉባዔውን ባለማካሄዱ ከብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ጉድለቶቹን እንዲያሟላ በተሰጠው አቅጣጫ መሠረት ለማሟላት አመራሮችና አባላት ለስብሰባ ወደ ፓርቲው ጽሕፈት ቤት ሲያመሩ በር ላይ እንዳይገቡ መታገዳቸውን ተናግረዋል፡፡ ፓርቲው ያወጣው የመተዳደሪያ ደንብ እየተጣሰ ነው ብለው፣ የምርጫ ቦርድ ሕግና መመርያ ወደጎን እየተደረገ ሕገወጥ ድርጊቶች እየተከናወኑ መሆናቸውን አቶ ማሙሸት ገልጸዋል፡፡
ነገር ግን የመኢአድ ፕሬዚዳንት እንደሚናገሩት ደግሞ እነዚህ ሰዎች የታገዱ በመሆናቸው፣ በሽምግልናው መሠረት ቀኑ ደርሶ ጉዳያቸው በጠቅላላ ጉባዔ እስኪታይ ድረስ ቦታ የላቸውም፡፡
ቡድኑ ከምርጫ ቦርድ ጋር ሆኖ እያደረገ ያለው ተግባር የተጀመረው ውህደት እንዳይካሄድ፣ ቢያንስ ለ2007 ዓ.ም. ምርጫ ውህደት ፈጽመው ጠንካራ ተወዳዳሪ ሆነው ለመቅረብ የሚያደርጉትን ዝግጅት የሚያሰናክል ሕገወጥ ተግባር መሆኑን መኢአድ አስታውቋል፡፡

Wednesday, August 20, 2014

የወያኔ ጁንታ በግዳጅ እየሰጠ ባለው ስልጠና ከባድ ተቃውሞ ከሰልጣኞች እየገጠመው ነው ።

August 20/2014
ምንሊክ ሳልሳዊ
የመንግስት ሰራተኛው እና የዩንቨርስቲው ተማሪዎች የከተቱት ስልጣና ላይ ወያኔ በጥያቄዎች ተወጥሯል፡፤

በሚቀርቡ የስልጠና ርእሶች ላይ ከፍተኛ አለመግባባት እና ጩኽት እየተከሰተ ነው፡፡


ከኑሮ ውድነቱ በባሰ ያቆሰሉን የሕወሓት አባላት ናቸው ።" የመንግስት ሰራተኛው


መልካም የልማት አስተዳደር በሚል ሽፋን ለመንግስት ሰራተኞች እና ለዩንቨርስቲ ተማሪዎች በተከታታይ ለ15 ቀን እየተሰጠ ያለው ስልጠና የወያኔን አመራሮች እና ከፍተኛ ካድሬዎች አጣብቂኝ ውስጥ የከተታቸው መሆኑን እና ተቀባይነት ማግኘት እንዳልቻሉ ከሰልጣኞች የሚመጡ መረጃዎች ጠቁመዋል።

ሰራተኞቹ እና ተማሪዎቹ በየፊናቸው ያነሱት ፖለቲካዊ ኢኮኖሚያዊ እና ማህበራዊ ወቅታዊ ጥያቄዎች ወያኔዎች ፊታቸው ላይ ከፍተኛ ድንጋጤ ከመነበቡም በላይ ለመመለስ ሲደናበሩ እና እፍረት ሲሰማቸው የታየ መሆኑን እና መጭውን እንደማይችሉት ስሜታቸው ላይ ሲነበብ እንደነበረ የጠቆመው መረጃ ከወያኔ ካድሪዎች አከባቢ የተገኘ መረጃ እንደጠቆመው ይህን ያህል አስጨናቂ ነገር ይነሳል የሚል ግምት ስላልነበረ ለአሰልጣኝ ካድሪዎች ቀድሞ የተሰጠው ስልጠና ምንም ውጤት ላይ ባለማሳየቱ አዳራሾች በተማሪዎቹ በፉጨት እና በከፍተኛ ተቃውሞ እንደተሞሉ መሆኑ ታውቋል።

የኢትዮጵያን ታሪክ በተመለከተ በክፍተኛ ደረጃ ለማጣጣል ከመሞከር አንስቶ የቀድሞ መሪዎችን በመራገም ላይ ያተኮረው ስልጠና እንዲሁም በይበልጥ የአፄ ምንሊክን ታሪክ አፈር ለማስገባት የታቀደ እንደሆነ ተሰምቷል። የኢትዮጵያን ታሪክ ያለፉት 23 አመታት ብቻ ለማድረግ የታቀደውን ሂደት ያልደገፉት ተማሪዎቹም ይሁኑ ሰራተኞቹ ከፍተኛ ተቃውሞ በማሰማት አደራሾችን በጩሀት ሞልተውታል ። ከናንተ በተሻለ እኛ የአያት ቅድመአያቶቻችንን ታሪክ ስለምናውቅ እናንተ የምትነግሩን ታሪክ የፈጠራ እና የጥላቻ ነው ስለዚህ አናዳምጣችሁም የሚል መልእክት አስተላልፈዋል። የቀድሞ ባለታሪኮችን በማጣጣል ኢትዮጵያ የምትባል አገር እንድትኖር ያደረጋት ኢሕአዴግ ነው የሚል አደምታ ያለው ስልጠና ተቀባይነት ሊያገኝ ባለመቻሉ በከፍተኛ ክርክር እና ጩሐት ውስጥ ያለፈ መሆኑን ተገልጿል።

በኢትዮጵያ ውስጥ ያለውን ሰው ልጆች መብት እና ሃሳብን በነጻነት የመግለጽ መብት ዙሪያ ከፍተና የሆነ አለመግባብቶች የተከሰቱ ሲሆን ካድሪውቹ መምእልስ አቅቷቸው ሲይስቀይሱ እና ሲያደናቡ ቢስተዋልም የወያኒ ለማደናበር መሞከር ፉጨት እና ጩኽትን እንዳስከተለ በየአደራሹ ስልጠናውን እየተከታተሉ ከሚገኙ ተማሪዎች የደረሰን መረጃ ሲያመለክት በየመንግስት ተቋማት ውስጥ ያለውን የበላይነት እና የሕዝብን መጉላላት በተመለክተ
ጥያቄ ያነሱት የመንግስት ሰራተኞች ስራችንን መስራት አልቻልንም ከኑሮ ውድነቱ በባሰ ያቆሰሉን የሕወሓት አባላት ናቸው ሲሉ አማረዋል። ደሞዝ ተጨመረ ሲባል ማንን ለማጭበርበር ነው ያሉት ሰራተኞቹ ጠብ ለማይል ነገር ከስራ ተባረራችሁ ቢባል ይሻለን ነበር ሲሉ ተናግረዋል። ዝግጅት ሳይደረግበት ለነጋዲዎች አቀባብላችሁ ሰጣችሁን ሌላ ኑሮ ውድነትን አመጣችሁብን እንጂ ምንም በደሞዝ ጭማሪው ያተረፍነው ነገር የለም። ሚዲያው የሚናገረው ከተጨመረው ጋር አይገናኝም ዝም እንዳላችሁ ዝም ብለን እየቆዘምን ብንኖር ይቻል ነበር ሲሉ ድምጻቸውን በስልጠናው ላይ አሰምተዋል፡፡

በተማሪዎቹ ዘንድ እየተሰጠ ባለው ስልጠና እጅግ ዘርፈ ብዙ ጥያቄዎች የተነሱ ሲሆን ሕገመንግስቱ ለምን አልተተረጎመም ከወሬ ውጪ ህገመንግስቱን ኢህአዲግ እየጣሰው ነው፡፤ የሚከሰሱት ግን ህገመንግስቱ ይከበር ያሉ
ዜጎች ናቸው የሚል ጠንካራ ጥያቄ ጨምሮ የሽብር ትርጉም ይነገርን ሽብርተኛ ምንድነው አሸባሪውስ ማነው የሚሉ ትድጋጋሚ ጥያቂውች እና ከሃይማኖት ነጻነት አንጻር ያለውን እደምታ ልታስርዱን አልቻልችሁም አታደናብሩን የሃገሪቷ ጥቅም እና የዜጎች ክብር ለምእራባውያን ብሄራዊ ጥቅም እና ለፖለቲካ አጀንዳ ሲባል ተዋርዷል፡ የሚሉ አስተያየቶችቸንአ ጥያቂዎች ተደምጠዋል። የሃገሪቱ ኢኮኖሚ አደገ ይባላል እንጂ ባለስልጣናት ቱጃር በሆኑበት እና በሙስና በትዘፈቁበት የአንድ ብሄር አባላት በድንገት በሃብት በተንበሸበሹበት ሁኔታ እንዴት ድህነት ተንሰራፋ ሲሉ ተማሪዎቹ አሰልጣኝ ካድሬዎቹን አፍጠዋቸዋል።

እጅግ የሚሰለች እና የሚያስጠላ ስልጠና ነው ይሉት ሰራተኞቹም ይሁኑ ተማሪዎቹ ምንም አይነት ፍላጎት አለማሳየታቸው እና ለጠየቁት ጥያቄ መልስ አለማግኘታቸው ከአሰልጣኞቹ ጋር ይመደብበርረና ስልጠናውን ጥለው እስከመውጣት የደረሱ መሆኑ ታውቋል። ስልጠናውን ጥለው ቢወጡም ከግቢ መውጣት እንደማይችሉ ተናግረዋል፤ለመጭው ምርጫ ድምጽ ለማሰባሰብ እየሮጠ የሚገኘው ወያኔ ድርጊቱ የሚያመለክተው በመፈረካከስ ላይ እንደሚገኝ እንዲሁም ሕዝቡ ፍርሃቱን እየለቀቀ የመብት እና የነጻነት ጥያቄዎችን እያነሳ መሆኑ አስደንግጧቸዋል።

የየቀኑን ስልጠናውን ውሎ በተመለከተ ማታ ማታ በከፍተኛ የወያኔ አመራሮች የሚመራ ስብሰባ የሚደረግ ሲሆን በተማሪዎቹ እና በሰራተኞቹ እየተሰጠ ያለውን አስተያየት እና ጥያቄዎች ዙሪያ የሚቀርብ ሪፖርት ለበላይ አካሎቻቸው እንደሚተላለፍ ታውቋል።

መኢአድን ለማፍረስ እየተፈጸሙ ያሉ ሴራዎችና ደባዎች

August20/2014
የመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት (መኢአድ) በሰላማዊ መንገድ እየታገሉ ካሉ የፖለቲካ ፓርቲዎች መካከል አንጋፋውና ጠንካራው ፓርቲ ነው፡፡
aeupበዚሁ መሠረትም የተለያዩ ፓርቲዎችን በማጠናከር ቅንጅት እንዲፈጠር ካደረጉ የፖለቲካ ፓርቲዎች መካከል ታላቁን ድርሻ የወሰደና ለውጤትም የበቃ ነው፡፡ ዛሬም የቅንጅትን መንፈስ በመመለስ ህዝባችን ለሠላማዊ ትግሉ እንዲነሳሳ ለማድረግ ከአንድነት ጋር ለመዋሃድ ከፍተኛ ጥረት በማድረግ ከጫፍ ላይ ደርሶ ነበር፡፡ ይሁን እንጂ በህውሓት/ኢህአዴግ መንግሥት የሚመራው ምርጫ ቦርድ የተለያዩ ምክንያቶችን በመፍጠር ውህደቱ እንዳይሳካ በመስራት ላይ ይገኛል፡፡
በአገር ውስጥ ሆነ በውጭ የምትገኙ የመኢአድ ደጋፊዎችና የኢትዮጵያ ሕዝብ ሆይ!
በአቶ ማሙሽት አማረ የሚመሩት ጥቂት ግለሰቦች እሁድ ነሐሴ 11 ቀን 2006 ዓ.ም ከጠዋቱ 12፡00 ሠዓት ጀምሮ የታርጋ ቁጥሩ አ.አ ኮድ3-43511 የሆነች ተሽከርካሪ መኪና በያዙ የደህንነት አባላትና ካሜራቸውን ከፓርቲው በር ላይ በጠመዱ የኢቲቪ ጋዜጠኞች በመመራት የፓርቲውን ጽ/ቤት ወረሩ፡፡ በውስጥ የነበሩት እንዳይወጡ እና በውጭ የነበሩት ወደ ጽ/ቤቱ እንዳይገቡ አግተው እስከ 9፡00 ሰዓት ድረስ ውለዋል፡፡ ይህ ቡድን ከአራት አመት በፊት በዲስኘሊን ጥሰት ከፓርቲው የተወገደ እና በፍ/ቤትም እንዲወገድ የተወሰነበት ነው፡፡ ይሁን እንጂ ይህ ቡድን በህውሓት/ኢህአዴግ የደህንነት አባላት በመመራት በፓርቲው ላይ ከፍተኛ ጥፋት በመፈፀም ላይ መሆኑ በግልጽ ሊታወቅ ይገባል፡፡ ይህ ጥፋትም ሆን ተብሎ የኢትዮጵያን ሕዝብ ትግል ለማዳከምና ብሎም ጨርሶ ለማጥፋት ከተያዙ እቅዶች አንዱ ነው፡፡
የኢትዮጵያ ሕዝብ ሆይ!
እንግዲህ ይህ ቡድን ለእውነት እና ለኢትዮጵያ ሕዝብ ትግል የቆመ ቢሆን ኖሮ በደህንነቱና በኢቲቪ መሪነት የፓርቲውን ጽ/ቤት መውረር ነበረበትን? እውን የዚህ ቡድን መሪዎች ለኢቲቪ በሰጡት ቃለ ምልልስ ላይ ምርጫ ቦርድ ለመኢአድ ፍቃዱን እንዳይሰጥ መጠየቅ ነበረባቸውን? ከዚህ ላይ ልብ ልንለው የሚገባው ጉዳይ እነዚህ ግለሰቦች ለኢትዮጵያ እውነተኛና ለሕዝቧ ነፃነት የሚታገሉ ቢሆኑ ኖሮ ከገዢው ፓርቲ ደህንነትና የገዢው ፓርቲ ከሚቆጣጠረው የኢትዮጵያ ቴሌቪዥንና ሬዲዮ እንዲሁም ከምርጫ ቦርድ ጋር አብሮ መስራትና በእነዚህ ድርጅቶችም ተመርቶ መምጣት አልነበረበትም፡፡
መኢአድ የብዙ ታጋዮቹ ደም የፈሰሰበት፣ ቤት ንብረታቸውን ያጡበትና አገር ጥለው የተሰደዱበት አሁንም ቢሆን የስቃይ እና የጭቆና ቀምበር ተሸክመው እየታገሉ ባሉበት ባሁኑ ወቅት ይህ ቡድን ፓርቲውን ለማፍረስ ከገዢው ፓርቲ ጋር ማበር አልነበረበትም፡፡
የኢትዮጵያ መንግሥት ከሥልጣን እወገዳለሁ በሚል ስጋት ውስጥ በመውደቁ የተነሳ በሚያደርገው መፍጨርጨር ለሕዝብ መረጃ የሚያቀርቡ እውነተኛ መጽሔቶችንና ጋዜጦችን ለመዝጋት ጥረት በማድረግ ላይ መሆኑ ግልጽ ነው፡፡ እንደሁም ጠንካራ ፓርቲዎችን ለማጥፋት በያዘው እቅድ መሠረትም ከአራት አመታት በፊት ከፓርቲው ክስ ቀርቦ በፍ/ቤት የተወገዱትን ጥቂት ግለቦች በማበረታታት መኢአድን ለማፍረስ ጥረት ያደርጋል፡፡
ዛሬ በአገሪቱ ላይ ሕግና ሥርዓት እየጠፋ መምጣቱን የተረዳነው ሕግ እንዲያስከብሩልን ለአራዳ ፖሊስ ጣቢያ አቤት በማለት ያመጣናቸው ፖሊሶች በደህንነቱ ሥራቸውን እንዳያከናውኑ መከልከላቸውንና ወደመጡበት እንዲመለሱ መደረጉን ስንመለከት ነው፡፡
ስለዚህ የኢትዮጵያ ሕዝብ ሆይ! በድህነትና በጭቆና ቀንበር ውስጥ ወድቀህ አቅምህን እንድታጣ የተሰራብህ ብትሆንም ቅሉ ባለን አቅም ለምናደርገው ሰላማዊ ትግሉ ሁሉ ከጎናችን እንድትቆም እንጠይቃለን፡፡
ህውሓት/ኢህአዴግ እየተጫወተ ያለው የፖለቲካ ቁማር እነ ማሙሸት አማረን በፓርቲው ማፍረስ ላይ በማነሳሳትና በመኢአድ የውስጥ ችግር ያለ በማስመሰል የውጭውን እንድንረሳ ለማድረግ የሚያደርገውን ጥረት ለአገራችንም ሆነ ለሕዝባችን የሚጠቅም ስላልሆነ እንዲያስብበት እንመክራለን፡፡
እነዚህን በተሳሳተ ጐዳና እየተጓዙ ያሉ ወንድሞችና እህቶችን የኢትዮጵያን ሕዝብ ትግል ከማዳከም እንዲቆጠቡ በዱላና በአመጽ ከመሔድ ይልቅ ወደ ሰለጠነ መንገድ እንዲመጡ ምክርህን እንድትለግሳቸው እናሳስባለን፡
የመኢአድ አባላትም በያላችሁበት በጥንካሬ በመቆም ፓርቲያችሁን በንቃት እንድትጠብቁ፣ በተለመው መንገድም የሰላማዊ ትግላችሁን እንድታጧጡፉ ፓርቲያችሁ መኢአድ ጥሪውን ያቀርብላችኋል፡፡
አንዲት ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር!!!
ነሐሴ 13 ቀን 2006 ዓ.ም

የዶ/ር ቴድሮስ አድሃኖም የአፍ ወለምታ (ኤፍሬም ማዴቦ)

August 20/2014
የዶ/ር ቴድሮስ አድሃኖም የአፍ ወለምታ (ኤፍሬም ማዴቦ)
የዶ/ር ቴድሮስ አድሃኖም የአፍ ወለምታ (ኤፍሬም ማዴቦ)
ባለፈዉ ሰሞን ቻይና አፍሪካ ዉስጥ ሰላሳ አመት በማይሞላ ግዜ ዉስጥ ያደረገችዉ የኤኮኖሚና የፖለቲካ መስፋፋት ያሳሰባቸዉ የአሜሪካዉ ፕሬዚዳንት ባራክ ኦባማ ምነዉ ምን አድረግናችሁና ነዉ ፊታችሁን ያዞራችሁብን ብለዉ ለመጠየቅ በርከት ያሉ የአፍሪካ መሪዎችን ቤተ መንግስታቸዉ ድረስ ጋብዘዋቸዉ ነበር። በዚህ የሃሳብ ልዉዉጥ፤ ምክር፤ የእራት ግብዣና የዋሺንግተን ዲሲን ጉብኝት ባጠቃለለዉ የፕሬዚዳንት ኦባማ ድግስ ላይ በመልካም የዲሞክራሲ ጅምራቸዉ የሚወደሱት የጋናና የደቡብ አፍሪካን መሪዎች ጨምሮ እንመራሀለን የሚሉትን ህዝብ በየቀኑ የሚያስሩት፤ የሚደበድቡትና የሚገድሉት የወያኔ መሪዎችም ተገኝተዋል። በዚህ የመሪዎች ስብሰባ ላይ ጠ/ሚ ደሳለኝ ኃ/ማሪያምን አጅበዉ ከመጡት የወያኔ ሹማምንት አንዱ የዉጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ዶ./ር ቴድሮስ አድሃኖም ነበሩ። ዶ/ር ቴድሮስ በዋሽንግተን ዲሲ ቆይታቸዉ ብዙዎቻችንን እየዋለ ሲያድር ደግሞ እራሳቸዉንም ግራ ያጋባ የሬድዮ ቃለ መጠይቅ ሰጥተዉ ነበር።
“በአፍ ይጠፉ በለፈለፉ” የአገራችን ባለቅኔዎች አፉ እንዳመጣለትና እንዳሻዉ የሚናገርን ሰዉ . . .  ዋ ተጠንቀቅ በአፍ የሚነገር ነገር ዋጋ ያስከፍላል ለማለት የተረቱት ተረት ነዉ።  አዎ! ባለቅኔዎቹ እዉነታቸዉን ነዉ።  የሚያዳምጡንን ሰዎች ለማስደሰት ስንል ብቻ አፋችን እንዳመጣ የባጥ የቆጡን የምንዘባርቅ ሰዎች የምንላቸዉ ነገሮች እኛዉ ዘንድ ዞረዉ መጥተዉ መጥፊያችን ሊሆኑ ይችላሉ። በቅርቡ ዋሺንግተን ዲሲ ብቅ ብለዉ የነበሩትን የኢትዮጵያ የዉጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ዶ/ር ቴድሮስ አድሃኖምን ያጋጠማቸዉ ይሄዉ በጋዛ አፍ ተናግሮ የመጥፋት ቅሌት ነበር። ዶ/ር ቴድሮስ እዚህ ዋሽንግተን ዲሲ ዉስጥ መንግስታቸዉ የሰራተኛ ደሞዝና የአየር ላይ ወጪ እየከፈለ በሚያስተዳድረዉ ሬድዮ አፋቸዉን ሞልተዉ የተናገሩትን ነገር አዲስ አበባ ተመልሰዉ በፌስ ቡካቸዉ በለቀቁት መልዕክት ለማስተባበል ቢሞክሩም ነገሩ “ከአፍ ከወጣ አፋፍ” ሆኖባቸዉ በስህተት ላይ ስህተት እየፈጸሙ ይገኛሉ።
ሬድዮ አገር ፍቅር በመባል ከሚታወቀዉ ሳምንታዊ ሬድዮ ጣቢያ ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ ዶ/ር ቴድሮስ አድሃኖም በእስር ላይ የሚገኙት የድምጻችን ይሰማ መሪዎች የአሜሪካ መንግስት ጓንታናሞ ዉስጥ ካሰራቸዉ የአልቃይዳ አባላት ጋር ግንኙነት እንዳላቸዉ ማረጋገጫ አግኝተናል ካሉ በኋላ የአሜሪካ መንግስት ይህንን ግኑኝነት አስመልክቶ የድምጻችን ይሰማ መሪዎችን ኢትዮጵያ ድረስ ሄዶ ለማነጋገር ለመንግስታቸዉ ጥያቄ እንዳቀረበ ተናግረዋል። ያልነገሩን ነገር ቢኖር የአሜሪካ መንግስት ባቀረበዉ ጥያቄ መሰረት ቃሊቲ ድረስ ሄዶ የድምጻችን ይሰማ መሪዎችን ማነጋገሩንና አለማነጋገሩን ብቻ ነዉ።
ዶ/ር ቴዎድሮስ ብቻ ሳይሆኑ እሳቸዉ በአባልነት የሚገኙበት ህወሃት የሚባዉ ድርጅት ሃያ ሦስት አመት ሙሉ እየዋሸ የዘለቀ ድርጅት ነዉና የዶ/ር ቴድሮስ ዉሸት ብዙም ላይገርመን ይችላል። ሆኖም ግን ዶ/ር ቴድሮስ ግማሽ ደቂቃ በማይሞላ ግዜ ዉስጥ ሁለት ቱባ ቱባ ዉሸቶችን ሲዋሹ “ከማንም ጋር አንወግንም፤ የቆምነዉ ለእዉነት ብቻ ነዉ” የሚለዉ የአገር ፍቅር ሬድዮ ጣቢያ አዘጋጅ ካለምንም ተከታይ የማብራሪያ ጥያቄ የዶ/ር ቴድሮስን ቆሞ የሚሄድ ዉሸት እንዳለ ተቀብሎ ጭራሽ ዶ/ር ቴድሮስን ማመስገኑ የወያኔ ስርዐት ዉሸትና ቅጥፈት አገር ዉስጥ ብቻ ሳይሆን በዉጭ አገሮችም ምን ያክል ህብረተሰባችንን አንደበከለ ያሳያል።
የኢትዮጵያን የእስልምና እምነት ተከታዮች ከአልቃይዳ ጋር ማገናኘት እነዚህ ወንድሞቻችንና እህቶቻችን ያነሱትን ህጋዊ የመብትና የነጻነት ጥያቄ ላለመመለስ የሚደረግ አጉል ዉጣ ዉረድ ከመሆኑ አልፎ ማንም ማየትና ማሰብ የሚችል ሰዉ የማይቀበለዉ ከንቱ ቅጥፈት ነዉ። ደግሞም ይብላኝ ለዶ/ር ቴድሮስ አፋቸዉን ላዳለጣቸዉ እንጂ ወጣቶቹ የድምጻችን ይሰማ መሪዎችኮ የጓንታናሞ አስር ቤት ሲከፈት ከአልቃይዳ ጋር ግንኙነት መፍጠር ቀርቶ አልቃይዳ የሚባል ነገር መኖሩን እንኳን ሰምተዉ የማያዉቁ አንድ ፍሬ ልጆች ነበሩ።
ሌላዉ የዶ/ር ቴድሮስ ትልቁ ዉሸት የአሜሪካ መንግስት ከአልቃይዳ ጋር  የነበራቸዉን ግንኙነት አስመልክቶ የድምጻችን ይሰማ መሪዎችን የታሰሩበት ቦታ ድረስ ሄዶ ላናግራቸዉ ብሎ ጠየቀን ማለታቸዉ ነዉ። እኔ እንደሚመስለኝ ዶ/ር ቴድሮስ አደስ አበባ ከገቡ በኋላ “ምን ነካኝ” ብለዉ ዉሸታቸዉን በፌስ ቡክ ገጻቸዉ ለማስተባበል የቸኮሉት ደጋግመዉ ወዳጃችን ነዉ ብለዉ በተናገሩት በአሜሪካ መንግስት ስም የዋሹት ዉሸት ከንክኗቸዉ ይመስለኛል፤ አለዚያማ ወያኔም ሆነ የዉጭ ጉዳይ ሚኒስቴሩ ዶ/ር ቴድሮስ በዋሹ ቁጥር ዉሸታቸዉን የሚያስተባብሉ ቢሆን ኖሮ የወያኔ አገዛዝ መሪዎች ስራቸዉ እየዋሹ ማስተባበል ብቻ ይሆን ነበር።
የሚገርመዉ ዶ/ር ቴድሮስ ከአሜሪካ ተመልሰዉ አዲስ አበባ ከገቡ በኋላ የመጀመሪያዉን አንድ ሳምንት ያሳለፉት አንድም አሜሪካ ዉስጥ የዋሹትን ዉሸት በማስተባበል ሌላ ግዜ ደግሞ ሌሎች አዳዲስ ዉሸቶችን በመዋሸት ነበር። በእርግጥም ዶ/ር ቴድሮስ አድሃኖም በየአገሩ የሚገኙትን አምባሳደሮቻቸዉን ሰብስበዉ የኢትዮጵያን ህዝብ ከት አድርጎ ያሳቀ ነጭ ዉሸት ዋሽተዋል። ለምሳሌ አሜሪካ ዉስጥ የህዳሴዉ ግድብ ቦንድ ሽያጭ እጅግ በጣም ዝቅተኛ መሆኑን ከተናገሩ በኋላ ምክንያቱን ሲገልጹ የአሜሪካ ህግ ለቦንድ ሽያጩ አመቺ አለመሆኑን ገልጸዉ ይህንን ለማሻሻል መንግስታቸዉ ከአሜሪካ መንግስት ጋር አብሮ እየሰራ መሆኑን ተናግረዋል። መቼም ለራሱ አገር ይህ ነዉ ተብሎ ሊጠቀስ የሚችል ህግ አዉጥቶ የማያወቀዉ እንቅልፋሙ የኢትዮጵያ ፓርላማ የአሜሪካንን መንግስት የሚገዛ ህግ ካላወጣ በቀር ዶ/ር ቴድሮስ አደራ የተጣለባቸዉን የቦንድ ሽያጭ እንዴት አሜሪካ ዉስጥ እንደሚወጡት ባላዉቅም መንግስታቸዉ የኢትዮጵያ ዳያስፖራ ባለበት ቦታ ሁሉ ሁሉ ቦንድ መሸጥ ያልቸለዉ የየአገሮቹ ህግ ችግር ፈጥሮበት ሳይሆን ለወገኖቹ መብትና ነጻነት የሚታገለዉ ኢትዮጵያዊ ወንድሞቼንና እህቶቼን እየገደላችሁ የምትሸጡልኝ ቦንድ ባፍንጫዬ ይዉጣ ብሎ እምቢ ስላላቸዉ ነዉ። ይህንን ደግሞ መዋሸት እንጂ እዉነትን ሸፍኖ ማስቀረት ያልቻሉት ዶ/ር ቴድሮስም ከተባበሩት ዓረብ ኤምሬትስ በስተቀር የሁሉም አገሮች የቦንድ ሽያጭ እጅግ በጣም ደካማ እንደነበር ለሰበሰቧቸዉ አምባሳደሮች ተናግረዋል፡፡
ከዶ/ር ቴድሮስ በፊትም ሆነ እሳቸዉ እያሉ የዉጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ከትዉልድ አገሩ ርቆ የሚኖረዉን የኢትዮጵያ ዳያስፖራ በጥቅማ ጥቅም እየደለለ ከአገዛዙ ጎን ለማሰለፍ ተደጋጋሚ ጥረቶችን አድርጓል። በተለይ የህዳሴዉን ግድብ ቦንድ ሽያጭና  የዕድገትና ትራንስፎርሜሺኑን ዕቅድ ተግባራዊ ለማድረግ የወያኔ/ኢህአዴግ አገዛዝ ዳያስፖራዉን አንደ ከፍተኛ የዉጭ ምንዛሬ ምንጭ ተመልክቶት ነበር፤ ሆኖም አብዛኛዉ ዳያስፖራ ከአገዛዙ ጎን ተሰልፎ ከሚያገኘዉ ግዜያዊ ጥቅም ይልቅ ዘላቂ የሆነዉን የእናት አገሩን አንድነትና የወገኖቹን ፍትህ፤ ነጻነትና እኩልነት በመምረጡ የወያኔ/ኢህአዴግ አገዛዝ ከዳያስፖራዉ እዝቃለሁ ብሎ የተመኘዉ የዉጭ ምንዛሬ ህልም ሆኖ ቀርቷል።
ሌላዉ የወያኔ/ኢህአዴግ አገዛዝ ከፍተኛ በጀትና የሰዉ ኃይል መድቦ ዳያስፖራዉን ለማማለል በሙሉ ሀይሉ የተንቀሳቀሰበት አካባቢ ቢኖር የከተማ ቦታና ቤት ሽያጭ ዘመቻ ነዉ። በእርግጥ አንዳንድ ከህዝብና ከአገር ጥቅም ይልቅ የራሳቸዉን ጥቅም ያስቀደሙ የዳያስፖራዉ አባላት ኢትዮጵያ ዉስጥ የሚካሄደዉን የመሬት ቅርምት በይፋ እየተቃወሙ የቅርምቱ ድግስ የእነሱን ቤት ሲያንኳኳ ግን በራቸዉን ወለል አድርገዉ ከፍተዉ የድግሱ ተሳታፊዎች ሆነዋል። አብዛኛዉ የኢትዮጵያ ዳያስፖራ ግን እናትና አባቴን እያፈናቀላችሁ የምትሰጡኝን መሬትም ሆነ ቤት አልፈልግም ብሎ በቦንድ ሽያጩ ላይ የወሰደዉን ጠንካራ አቋም በከተማ መሬትና ቤት ሽያጭ ላይም ደግሞታል። የወገኖቹን ነጻነትና ፍትህ ለማስከበር በህይወቱ የተወራረደዉን የኢትዮጵያ ዳያስፖራ የማያወላዉል አቋም ያልተረዱት ዶ/ር ቴድሮስ ግን ያንን የለመዱትን በጥቅማ ጥቅም የመደለል ሴራቸዉን አሁንም እንደቀጠሉበት ነዉ። ለምሳሌ ዳያስፖራዉ በመጪዉ አመት በሚደረገዉ የምርጫ ድራማ ላይ ያለዉን እይታ እንዲለዉጥ ለማድረግ ሲባል ብቻ 40 በ60 በሚባለው የቤቶች መርሃግብር የታቀፉ የዲያስፖራ አባላት የከፈሉበት ቤት የ2007ቱ ምርጫ ከመጀመሩ በፊት በአስቸኳይ ተጠናቅቆ እንዲሰጣቸዉ ትዕዛዝ ተላልፏል። እዚህ ላይ አንድ እጅግ በጣም የገረመኝም ያሳዘነኝም ነገር ቢኖር በአንድ በኩል ግብር ከፋይ በሌላ በኩል ደግሞ ቤት አልባ የሆነዉና እነ ዶ/ር ቴድሮስ አድሃኖም 99.6% መረጠን የሚሉት አገር ዉስጥ የሚኖረዉ ኢትዮጵያዊ ተረስቶ ትርፍ ቤት ፈላጊዉ ዳያስፖራ ቅድሚያ እንዲሰጠዉ መደረጉ ነዉ።
ለመሆኑ ዶ/ር ቴድሮስና መንግስታቸዉ ሁሌም አክራሪዉ ዳያስፖራ እያሉ የሚያሙትን ማህበረስብ ወድደዉ ሊስሙት ነዉ ወይን ተጠግተዉ ሊያልቡት እንዲህ የተንሰፈሰፉለት? የዳያስፖራዉን አባት፤ እናት፤ ወንድምና እህት እያሰሩ፤ እየገደሉና የመብትና የነጻነት ጥያቄ የሚያነሳባቸዉን የዳያስፖራ አባል ደግሞ አገርህ አትገባም ብለዉ አገር እየነሱት እነሱ ግን የልመና ኮሮጇቸዉን ተሽክመዉ አሜሪካና አዉሮፓ እየመጡ አገርህን እናሳድግልሃለን ገንዘብ ስጠን ብለዉ የሚጠይቁት በማን አገር ማን ለሚጠቀምበት ልማት ነዉ? እነ ዶ/ር ቴድሮስ እነሱን ከመሰለ ፀረ ህዝብ አገዛዝ ጋር ተመሳጥረዉ የዳያስፖራዉን አባል በህገ ወጥ መንገድ አግተዉ እየደበደቡና መታሰሩን ሰምታ ልትጠይቀዉ የሄደችዉን እህቱን ተወልዳ ካደገችበትና እትብቷ ከተቀበረበት አገር በ24 ሰዐት ዉስጥ ዉጪ ብለዉ እያስገደዱ እንዴት ቢገምቱንና እንዴት ቢመለከቱን ነዉ ዞር ብለዉ እኛኑ ገንዘብ ስጡን ብለዉ የሚጠይቁን?
ዶ/ር ቴድሮስ ከአገር ፍቅር ሬድዮ ጋር ያደረጉትን ቃለ መጠይቅ ከማጠቃለላቸዉ በፊት ደጋግመዉ የተናገሩት ኢትዮጵያን ምን ያክል እንደሚወዱና ይህ የሚወዱት አገር ህዝብ በእድገት ወደ ፊት ከገፉ አገሮች ተርታ ተሰልፎ ማየት አንደሚቸኩሉ ነዉ። መልካም ምኞት ነዉ። ሆኖም ይህ ምኞት የዚያችን የሚወዷትን አገር ህዝብ ሲናገር አፉን እየዘጉ፤ ሲጽፍ እጁን እያሰሩ፤ ሃሳቡን ሲገልጽ ማዕከላዊ ወስደዉ ሰቅለዉ እየገረፉና  ሰላማዊ ሠልፍ ተሰልፎ መብቴንና ነጻነቴን አክብሩልኝ ብሎ የጠየቃቸዉን ደግሞ ደረቱንና ጭንቅላቱን በጥይት እያፈረሱ የሚሳካ ምኞት አይደለም።  ዶ/ር ቴድሮስ በአፋቸዉ ብቻ የሚናገሩት ምኞት ዳያስፖራዉ በአፉም በልቡም ዉስጥ ያለ፤ የነበረና ለወደፊትም የሚኖር ምኞት ነዉ። ምኞታችንና ምኞታቸዉ ገጥሞ ኢትዮጵያ አድጋና በልጽጋ የምናያት  ግን ዶ/ር ቴድሮስ  እኛም እንደሳቸዉ በአገራችን ጉዳይ እንደሚያገባን በዉል ሲረዱና ይህንን ሃያ ሦስት አመት ሙሉ በችንካር ቀርቅረዉ የዘጉብንን በር ወለል አድርገዉ ሲከፍቱ ብቻ ነዉ።
የኢትዮጵያ ትንሳኤ በልጆቿ መስዋዕትነት ይረጋገጣል!!!!

የፀጥታ ሃይሎች በጭፍን ታዛዥነት የሚጥሷቸው መሰረታዊ መርሆች

August 19/2014
ድምፃችን ይሰማ!
muslim 2በሃገራችን ኢትዮጵያ ህገ መንግስት መግቢያ ላይ በግልፅ እንደሰፈረው ሃገራችንን እንዲመራ የሚመሰረተው መንግስት በኢትዮጵያ ህዝቦች ነፃ ፍላጎት፣ በህግ የበላይነት እና በህዝቦች ፈቃድ የህዝቡን የጋራ ጥቅም፣ መብት እና ነፃነት እንዲያስከብር የሚመሰረት የፖለቲካ ተቋም ነው፡፡ ይህ የፖለቲካ ተቋምም ህዝባችንን በትጋት እና በህግ በታቀፈ አካሄድ እንዲያገለግል ተደርጎ የተመሰረተ ሊሆን እንደሚገባው ህገ መንግስቱ በጥብቅ ያሳስባል፡፡ በመቀጠልም ህገ መንግስቱ በአንቀፅ 8 ንዑስ አንቀፅ 1 ህዝቦች የሃገራችን ኢትዮጵያ ሉአላዊ ስልጣን ባለቤቶች መሆናቸውን ረጋግጣል፡፡ ከዚያም በመቀጠል በአንቀፅ 9 ንዑስ አንቀፅ 1 ከህገ መንግስቱ ጋር የሚቃረን ማንኛውም የውስጥ ደንብም ይሁን መመሪያ ውድቅ መሆን ያለበት መሆኑን በማስገንዘብ ያሰፈረ ሲሆን በአንቀፅ 9 ንዑስ አንቀፅ 2 ደግሞ ማንኛውም የመንግስት አካልም ሆነ የፖለቲካ ድርጅት ለህገ መንግስቱ ተገዢ መሆን እንዳለበት በጥብቅ ያስገነዝባል፡፡
እንግዲህ በህገ መንግስቱ መግቢያና በአንቀፆቹ የተገለፁትን ሃሳቦች ጠቅለል ባለ መልኩ ከተመለከትናቸው በሃገራችን የሚመሰረተው መንግስት ህዝብን ለማገልገል የሚመሰረት ተቋም መሆኑን እና የመንግስት አካል ሆነው የሚፈጠሩ ማናቸውም ክፍሎች ለህገ መንግስቱ ተገዢዎች፣ እንዲሁም ህገ መንግስቱን በተግባር ለመተርጎም የሚፈጠሩ መሆን እንዳለባቸው እንረዳለን፡፡ በተቃራኒው ህገ መንግስቱን የማፋለስ እና የመርገጥ መብት የሌላቸው መሆኑንም እንገነዘባለን፡፡ በተጨማሪም በማንኛውም የመንግስት ተቋማት ተቀጥሮ የሚሰራ ግለሰብ ዋነኛ እና ከፍተኛ ኃላፊነቱ ህዝብን ማገልገል እና የህዝቡን ጥቅም እና ነፃነት መጠበቅ መሆኑን እንረዳለን፡፡
ከዚህ መሰረታዊ ሃሳብ ከተነሳን በመንግስት ተቋማት ውስጥ በመቀጠር የህዝብን መብት እና ነፃነት የሚጋፉ፣ ወይም የማህበረሰባቸውን መብት እና ነፃነት የሚገፍ ማንኛውንም ትዕዛዝ የሚቀበሉ፣ የሚፈፅሙ እና የሚያስፈፅሙ አካላት ቢያንስ የሚከተሉትን ሶስት መሰረታዊ የህገ መንግስት ጥሰቶች መፈፀማቸውን ልንገነዘብ እንችላለን፡-
1. አንድ ግለሰብ በሃገራችን ሉዓላዊው አካል እና ከፍተኛ የስልጣን ባለቤት ህዝብ መሆኑን እያወቀ የህዝብን ደህንነት እና ነፃነት የሚጋፉ ድርጊቶችን እንዲፈፅም የሚሰጠውን ትዕዛዝ መቀበሉ እሱም የህዝቡ አካል ነውና በቅድሚያ የራሱ ህገ መንግስታዊ መብት እንዲረገጥ በፍቃደኝነት የተቀበለና ለህገ መንግስቱ ክብር የሌለው መሆኑን ያረጋግጣል፤
2. ግለሰቡ የህብረተሰቡን መብት የሚጥሱና ነፃነቱን የሚያቃውሱ ድርጊቶችን እንዲፈፅም ታዝዞ ድርጊቱን ከፈፀመ የወገኖቹን የህገ መንግስት መብት የሚጥስ እና የሚረግጥ በመሆኑ ዳግም ህገ መንግስቱን ይጥሳል፤ ይረግጣል፤
3. ህገ መንግስታዊ መብታችን ተጥሷል በማለት ተቃውሞ የሚያሰሙ የህብረተሰብ ክፍሎችን ለማፈን እና ይህን መብታቸውንም ለመግፈፍ የተሰማራ ከሆነ በሶስተኛ ደረጃ ህገ መንግስቱን ይጥሳል፤
በመሆኑም እያንዳንዱ ዜጋ በሚያደርገው ድርጊት ዛሬ መንግስትን በታማኝነት ሲያገለግል ድርጊቱ ከህገ መንግስቱ ጋር የሚጣጣም እና የህገ መንግስቱን መንፈስ የተከተለ መሆን አለመሆኑን የማጣራት ግዳጅ ያለበት ሲሆን ይህንን ችላ ብሎ ህገ መንግስቱን የሚፃረሩ ድርጊቶችን መፈፀሙ ነገ የህግ የበላይነት በሃገሪቱ ሲሰፍር እና እኛ የኢትዮጵያ ህዝቦች መብታችንን በፍትሃዊ ፍርድ ቤት የምናከብርበት ወቅት ሲመጣ በህገ መንግስቱ መሰረት ለፍርድ የሚቀርብ መሆኑን ሊገነዘብ ይገባዋል፡፡ ይህን ከግምት በመክተት እያንዳንዱ ዜጋ ህገ መንግስቱን ተገንዝቦ የራሱን መብት አክብሮ የሌላውን ወገኑን መብት እንዲያከብር አጥብቀን በወገናዊነት ስሜት እንጠይቃለን፡፡ ታማኝነት ለህግ እና ለህገ መንግስቱ እንጂ ራሳቸውን ‹‹የህዝብ ተወካዮች›› ሲሉ ሰይመው ህዝብን ለመርገጥና መብት ለመግፈፍ ለቆሙ ጥቂት አምባገነኖች አይደለም! የአምባገነኖች አገልጋይና መሳሪያ በመሆን ካገለገሉ በኋላ ‹‹ህዝብ ላይ በደል የፈጸምኩት በእነሱ ትዕዛዝ ነው›› ማለት ከተጠያቂነት አያድንም!
ህገ መንግስቱን ማክበር እና ማስከበር ህዝባዊ ሀላፊነታችን ነው!!!
ትግላችን እስከድል ደጃፎች በአላህ ፈቃድ ይቀጥላል!

Tuesday, August 19, 2014

ጠብ-መንጃ አናነሳም! (ተመስገን ደሳለኝ)

August 19/2014
Journalist Temesgen Desalegn
Journalist Temesgen Desalegn
“ብሶት የወለደው” ኢህአዴግ ከሁለት አስርታት በፊት በሰሜን ተራሮች ላይ ከኢትዮጵያ መንግስት ወታደሮች ጋር ያደረገውን የጎሬላ ውጊያ “አጃኢብ” በሚያሰኝ ቆራጥነት በድል መወጣቱ የማይታበል እውነትነው፤ ሥልጣን ከተቆናጠጠ በኋላም ለሚሰነዘርበት ማንኛውም አይነት የኃይል ጥቃት፣ ያውም ማቸነፍ አለማሸነፉን ሳያሰላ በፍጥነት ዘሎ ለመዘፈቅ ሲያንገራግር የተስተዋለበት ጊዜም አልነበረም፤ አሀዱ ብሎ የአመፅ ትግል ከጀመረበት ዕለት አንስቶ ላለፉት አርባ ዓመታት ከጀብሃ እስከ ኢህአፓ፤ ከኦነግ እስከ ኦብነግ፤ ከትህዴን እስከ አርበኞች ግንባር፤ ከሻዕቢያ እስከ አልሸባብ… በስም ተዘርዝረው ከማያልቁ ብረት-ነካሽ ድርጅቶች ጋር ወደ ፍልሚያ ለመግባት ከመወሰኑ በፊት ሰላማዊ መፍትሄዎችን ግራና ቀኝ የመፈተሽ ትዕግስትም ሆነ ልባዊ ፍላጎት እንዳልነበረው የራሱ የታሪክ ድርሳናት ሳይቀሩ በግላጭ ይናገራሉ፡፡ በተለይም ሀገር በቀሎቹ ተቃዋሚ ድርጅቶች በእንዲህ አይነቱ አስገዳጅ ሁኔታ ነፍጥ አንግበው የመገኘታቸው ምስጢር በቀጥታም ሆነ በዘወርዋራው የሥርዓቱ እጅ ስላለበት መሆኑን የሚያስረዱ ማሳያዎች የበዙ ናቸው፡፡ ከነዚህ መሀል አንዱና ዋነኛው በርሱ አጋፋሪነት የፀደቀውን ሕገ-መንግስት፤ በፕሮፍ መስፍን ወልደማርያም አገላለፅ “በሕገ-አራዊት”ነት ቀይሮ በአደባባይ መብቶቻቸውን መጨፍለቁ ነው፤ ከሁሉም በላይ ደግሞ በነፃ ምርጫ ማሸነፍም ሆነ ሥልጣን መጋራትን ‹ግመል በመርፌ ቀዳዳ…›ን ያህል ማጥበቡ እና “መንገዱን ጨርቅ ያድርግላችሁ” የምትለዋ የከረምች እብሪት ድርጅቶቹ “ዱር ቤቴ” እንዲሉ ያስገደዷቸው ገፊ-ምክንያቶች ስለመሆናቸው ቅንጣት ያህል አያጠራጥርም፡፡
በግልባጩ በበርካታ ድርሳናት ስለጀብዱውና ተጋድሎው የተተረከለት አብዮታዊ-ግንባሩ፣ ለሕዝባዊ እምቢተኝነት ፈሪ እና ድንጉጥ የመሆኑ ነገር ተደጋግሞ መወሳቱ ሌላ እውነት ነው፡፡ ብረት ያነሱ ተቀናቃኞቹን በብረት ለመጋፈጥ ካለው ወኔ  ይልቅ፣ ሰላማዊ ትግልን በተመሳሳይ ቋንቋ የማስተናገድ ፍርሃቱ እጥፍ ድርብ እንደሚልቅ በተጨባጭ የተረጋገጠ ጉዳይ ነው፡፡ በተለያየ አጋጣሚ በድንጋጤ ሲርበተበት፣ እንቅልፍ ሲያጣ፣ ግብታዊ እርምጃ ሲወስድ… የተስተዋለውም በሕግ የደነገገውን መብት ተንተርሰው የተቀሰቀሱየተቃውሞ ትግሎች የተጠናከሩበት ጊዜያት ላይ ብቻ ነው ብዬ አምናለሁ፡፡ የሰሞኑም ዘመቻ ነፃ-ፕሬስ ግባት ከዚሁ የሚመደብ ነው፡፡
በሰላማዊ የትግል ስልቶች ማዕቀፍ ስር የሚገኙ መብቶታቸውን የተጠቀሙ ቆራጦች ለተቃውሞ በወጡ ቁጥር፣ ቅጥ-ባጣ መልኩ መፍረክረኩን እና የእውር-ድንብር እርምጃ የመውሰዱን እውነታ ለማስረገጥ በተለያየ ጊዜ የተመለከትናቸው ማሳያዎችን እየጠቀሱ መሟገቱ አስቸጋሪ አይደለምና ጥቂቶቹን በአዲስ መስመር ላስታውስ፡-
በ1993 ዓ.ም በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ተማሪዎች የተነሳውንና የአካዳሚያዊ ነፃነትን የጠየቀውን ሰላማዊ ተቃውሞ ተከትሎ በመዲናይቱ የተከሰተው ሕዝባዊ ንቅናቄ ምን ያህል የሚይዝ የሚጨብጠውን አሳጥቶት እንደነበረ ለመረዳት፣ በሃያና ሰላሳ ሺዎች የሚቆጠሩ የከተማይቱን ኗሪዎች (አብዛኛዎቹ በተቃውሞ ያልተሳተፉ) ከየቤታቸው እንዴት አፋፍሶ ለግፍ እስር እንደዳረጋቸው ማስታወሱ በቂ ነው፡፡ በወቅቱ ክስተቱ አገሪቱን ለሁለት ቀናት መንግስት-አልባ አስመስሏት እንደነበረ በተሳታፊነትም በታዛቢነትም ሁኔታውን የተከታተልን ዜጎች ሁሉ አንዘነጋውም፡፡

በ1995 ዓ.ም የሲዳማ ተወላጆች፣ ክልላዊነትን እና የሀዋሳ ከተማ ዕጣ-ፈንታን በሚመለከት ጥያቄ አንስተው በደቡብ ክልል ርዕሰ- መዲና ለተቃውሞ አደባባይ የወጡ ጊዜም፣ አብዮታዊ-ግንባሩ ምን ያህል ፈታኝ ሁኔታ ውስጥ ወድቆ እንደነበረ ማስታወሱ ለዛሬው ጠ/ሚንስትርም ሆነ ለብዙዎቻችን የሚከብድ አይሆንም፤ ሥርዓቱ ያዘመታቸው የመከላከያና የፌደራል ፖሊስ ሠራዊት አባላት ሕጋዊውን የሲዳማ ተወላጆች ጥያቄ ለመቀልበስ፣ ጎዳናዎቹን በደም-አባላ በማጥለቅለቅ የፈፀሙት አሳዛኝ ጅምላ ጭፍጨፋ (ዘር ማጥፋት) በታሪክ መዝገብ ጥቁር ገፅ ላይ በማይፋቅ መልኩ ተከትቦ አልፏል፡፡ ይህም ሆኖ የዚህ ሰላማዊ ተቃውሞ ውጤት፣ ለፌደራል መንግስቱ፣ ክልሉን በኃላፊነት ሲመራ የነበረውን ኃይለማርያም ደሳለኝን፣ በሽፈራው ሽጉጤ እንዲተካ ያስገደደ የሽንፈት ፅዋ ማስጎንጨቱ ይታወሳል፡፡

በምርጫ 97 ዋዜማ ሚያዝያ 30 ‹‹ዴሞክራሲን እናወድስ›› በሚል መሪሕ-ቃል ‹‹ቅንጅት›› በጠራው ስብሰባ ላይ ተገኝቶ መስቀል አደባባይን ያጥለቀለቀው የሕዝብ ‹‹ሱናሜ››፣ ሥርዓቱን ለከባድ ድንጋጤ አጋልጦ፣ በሀፍረት አኮራምቶ፣ ለከፋ ስቃይ ዳርጎት እንደነበረስ ከቶ ማን ሊዘነጋው ይቻለዋል? ያኔ የተመለከትነው ገዥው-ፓርቲን ከፍተኛ ፍርሃት ላይ የጣለ አስደንጋጭ ትዕይንት፣ ዛሬም ድረስ ለሚተገብረው የቅድመ-ምርጫ አደን መስዋዕት እየዳረገን እንደሆነ ሁላችንንም የሚያስማማ እውነታ ነው (በዕለቱ ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ‹ምን አልባት ሕዝቡ በቁጣ የቤተ-መንግስቱን አጥር ገርስሶ ሊገባ ይችል ይሆናል› በሚል ፍርሃት ከእነ ቤተሰቡ ደብረዘይት አየር ኃይል ግቢ ተሸሽጎ አሳልፏል የሚለው ወሬ ከሹክሹክታም በዘለለ በከተማዋ በስፋት ተናፍሶ ነበር)፡፡

ሕዝበ-ሙስሊሙ ያቀጣጠለው ከሁለት ዓመት በላይ ያስቆጠረው የተቃውሞ ትግልም፣ አገዛዙን እንዴት በፍርሃት እንዳራደው ለመረዳት በጉዳዩ ዙሪያ በየጊዜው የሚወጡ እርስ-በርስ የተምታቱ መግለጫዎችን እና ረብ-የለሽ ‹‹ዘጋቢ›› ፊልሞቹን መመልከቱ በቂ ነው፡፡ ይህንን ፍፁም ሰላማዊና ስልጡን የተቃውሞ ንቅናቄን ለማፈን የተወሰዱት የኃይል እርምጃዎችም፣ የእነ አባይ ፀሀዬን የይስሙላ ዲሞክራሲያዊ ባህሪ ለዓለም አቀፉ ማሕበረሰብ ከማጋለጡ ባለፈ፣ ድርጅታቸው-ኢህአዴግን ለሳልሳዊ የውስጥ ክፍፍል መዳረጉን የመረጃ ምንጮች ያወሳሉ፡፡
በአናቱም ግንባሩ፣ በተቃውሞ ጎራ በተሰለፉ ሕጋዊ የፖለቲካ ድርጅቶች ውስጥ ነውረኝነቱን በግላጭ በሚያሳይ መልኩ የራሱን ሰዎች አስርጎ በማስገባት ለመከፋፈል ከሚሞክርበት ማኪያቬሊያዊ ሴራ በተጨማሪ፣ አመራሩን እና የነቃ ተሳትፎ የሚያደርጉ አባሎቻቸውን በጥቅማ ጥቅም በመደለል፣ ከሀገር በማሳደድ፣ ከፖለቲካ ተሳትፎ ራሳቸውን አግልለው በፍርሃት ‹‹ጎመን በጤና››ን እያጉረመረሙ የበይ-ተመልካች ሆነው አርፈው እንዲቀመጡ የብረት መዳፉን ለመጫን እና ለመሰል ሕገ-ወጥ ድርጊቶቹ ማስፈፀሚያነት በቢሊዮን የሚቆጠር የአገር ሀብት አፍስሶ ጠንክሮ የመስራቱ (እየሰራም የመሆኑ) ጉዳይ አከራካሪ አይደለም፡፡ ይህንን ኩነት በምኩንያዊነት ለማስረገጥ በኮሙኒኬሽን ጽ/ቤት የአቶ በረከት ስምዖን ምክትል የነበረውና ሀገር ጥሎ የተሰደደውን የቀድሞ ሚኒስቴር ዲኤታን የአቶ ኤርምያስ ለገሰን ምስክርነት መጥቀስ ተገቢ በመሆኑ፣ በቅርቡ ‹‹የመለስ ትሩፋቶች›› በሚል ርዕስ ለንባብ ካበቃው መጽሐፉ አንድ ማሳያ ላቅርብ፡-
‹‹በምርጫ 92 ኢህአዴግ መሸነፉን አስቀድሞ ካረጋገጠ በኋላ የተከተለው ስትራቴጂ የሕዝቡን ውሳኔ ባይቀይረውም ለማጭበርበር ጠቅሞታል፡፡ …የምርጫውን ዴሞክራሲያዊነት የሚያጠፉ ሶስት እርስ በእርስ የሚመጋገቡ ስትራቴጂዎችን ነደፈ፡፡ ስትራቴጂዎቹ እንደሚከተለው ነበሩ፤ በእጩ ምዝገባ ወቅት በተቃዋሚ ፓርቲ እጩዎች ውስጥ ለኢህአዴግ የሚሰራ አስርጎ ማስገባት፤ በየወረዳው ምርጫ ቦርድ በሚፈቅደው መሰረት የተፎካካሪ እጩዎችን ከተቻለ በማሳመን ካልተቻለ በመደለልና በማስገደድ ራሳቸውን እንዲያገሉ ማድረግ የሚሉ ነበሩ፡፡›› (ገጽ 58-59)
በነገራችን ላይ ኤርሚያስ ለገሰ በዚህ መጽሐፉ ለእንዲህ አይነቱ እኩይ ሴራ ስላልተበገረ አንድ ያልተዘመረለት ጀግና በዝርዝር አስፍሮልናል፡፡ ሰውየው በቅፅል ስሙ ‹‹አበበ ቀስቶ›› ተብሎ የሚታወቀው እና በምርጫ 92 በአዲስ አበባ ከተማ በወረዳ 24 ኢዴፓን ወክሎ ለውድድር የቀረበው ክንፈ ሚካኤል ደበበ ነው፡፡ የአገዛዙ ካድሬዎች ክንፈ በአካባቢው ጠንካራ ድጋፍ እንዳለው ጠንቅቀው ያውቁ ስለነበረ ብርቱ ስጋት ላይ ይወድቃሉ፤ በዚህም ‹‹ምርጥ›› የሆነ አደናቃፊ ስልት ተነድፎ ለመተግበር መሞከሩን አቶ ኤርሚያስ እንደሚከተለው ይነግረናል፡-
‹‹(ክንፈ) ከምርጫው ፉክክር ገለል የሚልበት አማራጮች ታሰቡ፡፡ እሱን ማስፈራራቱ የሚታሰብ አልነበረም፡፡ ምድር ቢንቀጠቀጥም የሚፈራ ሰው አይደለም፡፡ በቁጥጥር ስር ለማዋል ደግሞ ወንጀል ሲሰራ እጅ ከፈንጅ መያዝ አለበት፡፡ ስለዚህ የቀረው የመጨረሻ አማራጭ በገንዘብ መደለል ሆነ፡፡›› (ገጽ 65)
ተራኪው ይቀጥላል፤ ለድለላው 50 ሺ ብር ወጪ ይደረጋል፤ በደላይነት ደግሞ ዳኛ ልዑል ገ/ማሪያም (ይህ ሰው የወቅቱ የፍትህ ሚኒስቴር ሚኒስትር ዲኤታ መሆኑን ልብ ይሏል) እና ኪሮስ የተባሉ የህወሓት አባላት ይመደባሉ፤ አቤም ሊያግባቡት ቤቱ ድረስ በመጡ ግለሰቦች ሃሳብ በመስማማቱ፣ ልዑልና ግብረ-አበሩ 35 ሺውን ለራሳቸው አስቀርተው 15ሺ ብር ይሰጡታል፤ የወረዳው የኢህአዴግ አመራርም በተከተለው ‹‹እፁብ-ድንቅ›› መፍትሔ ለጊዜው ከስጋት ነፃ ይሆናል፤ ግና፣ ይህ ሁኔታ ብዙ አልቆየም፡፡
ከሳምንታት በኋላ፣ ምርጫው ሊካሄድ ጥቂት ቀናት ሲቀሩት ሸገር ተወልዶ፣ ሸገር ያደገው የአራዳ ልጅ አበበ ቀስቶም በታሪክ ሲዘከር የሚኖርበት ውሳኔውን እንዲህ ሲል አረዳቸው፡‹‹የተጋበዝኩትና ብራችሁን የተጠቀምኩት እናንተ ጋር የማይነጥፍ የብር ማምረቻ ስላለ ነው፡፡ ምርጫ የምወዳደረው ግን ለገንዘብ ሳይሆን ይህን አስከፊ ሥርዓት ለመጣልና ለነፃነቴ ነው፡፡ በዚህ ላይ ለመደራደር ህሊናዬ አይፈቅድም፡፡›› (ገጽ 65-66)
ዛሬ ‹‹አሸባሪ›› በሚል ክስ ተወንጅሎ፣ የሃያ አመት የእስር ቅጣት ተላልፎበት፣ በአሰቃቂው የቃሊቲ ወህኒ ተጥሎ የሚገኘው አበበ ቀስቶ እንዲህ ያለ ድፍረትና ቁርጠኝነት የነበረው ጀግና ስለመሆኑ አብዮታዊ ግንባሩን አደግድገው ያገለገሉት ካድሬዎች ጭምር እየመሰከሩለት ይገኛሉ፡፡
ከግል ገጠመኜ ደግሞ አንድ ልመርቅ፤
የ‹‹ፍትሕ›› ጋዜጣ ዋና አዘጋጅ ሆኜ በምሰራበት ወቅት፣ አቤ በ‹‹አሸባሪ››ነት ተከሶ ፍርድ ቤት ይመላለስ ነበር፤ ከዕለታት በአንዱ ቀንም እጅግ የሚያሳዝንና የግፉአን እናቶችን የሀዘን እንባ የሚወክል ጽሑፍ ከወህኒ ቤት ይልክና በጋዜጣችን ላይ ይታተማል፡፡ ቀደም ብሎ እስክንድር ነጋ፣ አንዱአለም አራጌ እና ናትናኤል መኮንንም በተመሳሳይ መልኩ የላኳቸው ጽሑፎች ተስተናግደዋል፤ ይህ ከሆነ ሁለት ሳምንት በኋላ ‹‹የተከበረው›› ፍርድ ቤት እነዚህን ጽሑፎች እንዲታተሙ በመፍቀዴ ‹‹ችሎት መድፈር›› የሚል ክስ መስርቶብኝ ዳኞች ፊት ቀረብኩ፤ ከአራቱ ታሳሪዎች መካከልም አቤ ተለይቶ ተጠርቷል፤ የመሀል ዳኛውም አንድ ጥያቄ ጠየቀው፡-
‹‹ይህንን ጽሑፍ አንተ ነህ የጻፍከው?››
አበበ ቀስቶ መልስ ለመስጠት አልተቻኮለም፤ ዳኞቹ፣ ዓቃቢ-ሕግጋን እና የችሎቱ ታዳሚዎች በሙሉ ምን ሊል ይችላ ይሆናል? በሚል ጉጉት እየጠበቁት ነው፤ የእኔ አይደለም ቢልስ? ማን ያውቃል? …ጥቂት ሰከንዶች በአስጨናቂ ዝምታ ካለፉ በኋላም፣ ልበ-ሙሉ ፖለቲከኛ ፈገግ ብሎ መናገር ጀመረ፡-
‹‹አዎ፣ እኔነኝ የጻፍኩት! ፍላጎቴም እዚህ እናንተ ፊት ላነብላችሁ ነበር፤ ሆኖም ሰዓት የለንም ብላችሁ ስትከለክሉኝ ጊዜ ነው፣ ለተመስገን የላኩለት!››
(በቀጣዩ ሳምንት ስለመጽሐፉ በስፋት ለመወያየት ቀጠሮ ይዘን፣ ወደጀመርነው ርዕሰ-ጉዳይ እንመለስ)
ስለምን ነፍጥ አናነሳም?
በኢሕአዴግ ዘመነ-አገዛዝ ብረት የማንሳትን ተገቢነት የሚያቀነቅኑ ልሂቃን፣ ለትግሉ ስልት አግባብነት የሚያነሷቸውን መከራከሪያዎች በሁለት መልኩ ልናያቸው እንችላለን፡-
በቀዳሚነት ከገዥው-ፓርቲ ተፈጥሯዊ ባህሪ ጋር አያይዘው፣ ለአቻቻይ ዴሞክራሲያዊ ሥርዓት ግንባታ የሚያስፈልጉ ባህሪያት በፍፁም የማይስተዋሉበት፣ ይልቁንም ‹ሕገ-መንግስታዊነትን፣ የሕግ የበላይነትን፣ የተቋማት ነፃነት፣ ሃሳብን በነፃነት የመግለፅ መብትን፣ የመሰሉ ዕሴቶችን በመጨፍለቅ የሚታወቅ ነው› የሚል ጥቅል መከራከሪያ ያቀርባሉ፡፡ እውነታው እነርሱ እንደሚሉት ቢሆንም እንኳ፣ ብረት የሚቀላቀልበት ትግል የሚያፈራርሳቸውን ማሕበረ-ኢኮኖሚያዊ ተቋማትን እንደገና ከፍርስራሹ ዓመድ ላይ ለመጀመር የሚያስገድድ መሆኑን ግን የዘነጉት ይመስለኛል፡፡
ሁለተኛው ጭብጥ፣ የማሕበረሰቡን የፖለቲካ ባህል እና የአንድ ወቅት የሰላማዊ ትግልን ሙከራ ክሽፈት በማውሳት የሚቀነቀነው ነው፡፡ የፖለቲካ ባህላችን ለጦረኛነት፣ ተዋስኦን ለሚጨፈለቅ የመጠፋፋት መንገድ የቀረበ የመሆኑን መሞገቻ ለክርክር በመግፋት የሃሳባቸው ማጠንጠኛ ያደርጉታል፡፡ ይሁንና የመድበለ-ፓርቲ ሥርዓትን እና ነፃ የአደባባይ ክርክርን ያልተላመደ ማሕበረሰብን አሁንም ለትጥቅ ትግል መጥራት ይህንኑ አሉታዊ ሕዝባዊ ባህርይ ከማጠናከር የዘለለ አንዳች ፋይዳ እንደሌለው ለመሟገት የሚያስችሉ በርካታ ነጥቦች አሉ፡፡ ‹ማሕበረሰቡ ለተራዘመ ሰላማዊ ትግል አይሆንም› ብለው የሚከራከሩ ጸሐፍት የሚጠቅሱት፣ 97 ላይ የተጨናገፈውን እንቅስቃሴና መሰል ሕዝባዊ ተቃውሞን መሰረት በማድረግ ነው፡፡ በተለይም የቅንጅት ጉምቱ ፖለቲከኞች እስኪበቃን እንደነገሩን፣ ስህተቱን ሁላችንም የምንጋራው ይሆናል (የኢሕአዴግ ቢልቅም ቅሉ!)፡፡ ግና፣ የወቅቱ ክስተት ከሰላማዊ ትግል አማራጮች አነስተኛ ሚና የሚሰጠውን የምርጫ ፖለቲካን ብቻ ግብ ያደረገ መሆኑ ‹ትግሉን ሞክረነዋል› የሚለውን መከራከሪያ ያጎደለው ይመስለኛል፡፡
ከዚህ ይልቅ፣ ሰላማዊ ሕዝባዊ አብዮትን አንድም ጊዜ በቅጡ ሳንሞክር (በቀቢፀ-ተስፋ ተሞልተው የሥልጣን ጥማት ካሰከራቸው ቀልባሾች ሳንታደገው) ጠብ-መንጃ ወደማንገብ መመለስ ቢያንስ በቂ መከራከሪያዎችን ያሳጣል ብዬ አምናለሁ፡፡
ከላይ በጥቅሉ ከጠቀስኳቸው ጭብጦች ባለፈ፣ እነዚህ ኢህአዴግ ሥልጣን ከተቆናጠጠበት ማግስት አንስቶ ነፍጥ የነከሱ ቡድኖች፣ንፁሃን ዜጎችን እንዳሻው እንዲያስር እና እንዲያሰድድ ፖለቲካዊ ሰበባ-ሰበቦች ከመስጠት ባሻገር ያዋጡት በጎ አበርክቶ (ተጨባጭውጤት) አለመኖሩን ልብ ማለት ያሻል፡፡
የሆነው ሆኖ የዚህ ጽሑፍ ተጠየቅ ከተለመዱት ሁለቱ የትግል ስልቶች አንዱን መባረክ እና ሌላኛውን ማውገዝ አይደለም፡፡ ይልቁንም በህወሓት ጠቅላይነት የሚመራው ገዥው-ግንባር፣ ከብረት ትግል ይልቅ፣ በሕገ-መንግስቱ ማዕቀፍ ስር ለሚጠቃለሉ ሕዝባዊ ንቅናቄዎች ብርክ የሚይዘው መሆኑን በማውሳት፤ ባለፉት እትሞች በ‹‹ሕዳሴ አብዮት›› የጠቀስኳቸውን አተገባበሮች በበቂ ሕዝባዊ ጉልበት መግፋት እንደሚያዋጣ ዳግም አፅንኦት ለመስጠት ነው፡፡ ርግጥ ነው ሁላችንንም ግራ-ገቡ ኢህአዴግ ፍርሃት በናጠው ቁጥር ሲያሻው በገፍ ወህኒ እያጎረ፤ ሲፈልግ የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርታቸውን እንኳን ያልጨረሱ ብላቴኖችን ግንባር በጥይት እያፈረሰ፣ በል ሲለው ደግሞ ይህንን መከራ እና ስቃያችንን የምንተነፍስበት ሚዲያ እያሳጣን በምሬት እንደሞላን አንክድም፡፡ ይህ ሁሉ ሆኖም ግን ድርጅቱ የተካነበትንና ለፍልሚያ የሚመርጠውን ጠብ-መንጃ አናነሳም፡፡ ጠብ-መንጃ የማናነሳው ልበ-ሙሉነታችን ከህወሓት-ኢህዴን መስራቾች የጉብዝና ዘመን ያነሰ ሆኖ በመገኘቱ አይደለም፤ ሚሊዮናት ዘመን ተጋሪዎቼ ለሀገር ጉዳይ፣ ለሕዝብ ጥቅም ግንባራቸውን እንደማያጥፉ አውቃለሁና፡፡ የደኑ መመንጠር ምሽግ ስላሳጣን ወይም የምናፈገፍግበት መሬት ስለጠፋንም አይደለም፡፡ ብረት-ጠል የሆንነው፣ በሰላማዊ ሕዝባዊ ዓመፅ ይህን ሥርዓት አስቁሞ፣ ኢትዮጵያን ማደስ እንደሚቻል ካለን የፀና እምነት ባሻገር፣ ነባራዊውም ሁነት ጮኾ የሚያስረግጥልን ይሄንን በመሆኑ ብቻ ነው፡፡ ይህ ሰላማዊ የመጨረሻ ሙከራ በኢትዮጵያ ሰማይ ስር ዳግም ነፍጥ እንዳይነሳ አስተማማኝ ዋስትናን ሰጥቶ እንደሚጠናቀቅም አልጠራጠርም፡፡ በረዥሙ የጭቆና አገዛዝ በተለይም በእርስ በርስ ጦርነት ለተጎዳና ለደኸየ ሕዝብ፣ የወጣቶቹን ደም ለሚያስገብር ትግል አሳልፎ መስጠት፣ የነገይቱን ኢትዮጵያ ባድማነት ማወጅ ነውም ብዬ አምናለሁ፡፡ እንደዚያም ሆኖ ግን ‹ብረት ያዋጣል› የሚሉ ኃይሎች በመረጡት መንገድ ሥርዓቱን አስገድደው ወደ ብሔራዊ እርቅና አገራዊ ሕዳሴ ሊያመጡልን ከቻሉ፣ የትግላቸው ታላቅ አበርክቶ እንደሚሆን ይሰማኛል፡፡ ወደምናልመው ሁለንተናዊ ሕዳሴ ለመድረስም የሚኖራቸውን ሚና በምንም አይነት መነሾ ላሳንሰው አይቻለኝም፡፡
ከዚህ በላቀ በተከታታይ የተወያየንበት የ‹‹ሕዳሴ አብዮት›› ማዕቀፍ፣ በሕዝባዊ የአደባባይ ዓመፅ ሥርዓቱን ከማውረዱ በዘለለ፣ በደም-እልባት ያጣነውን አንድ ዋነኛ እሴት አውሶን የሚያልፍ ይመስለኛል፡፡ በሰላማዊ አብዮት የሚሳተፍ ዜጋ አገራዊ ሕዳሴን በማምጣት፤ ሁላችንንም በእኩልነትና በነጻነት የሚያኖር ፖለቲካዊ ሥርዓት ማዋለዱ አይቀሬ ነው፡፡ በመጪው አስተዳደር የሚከወኑትን ሀገራዊ ጉዳዮች በያገባኛል የሚከታተል፣ እያንዳንዱን የዜግነት መብቱን አጠንክሮ የሚጠይቅ እና በውይይት (በሃሳብ ብዙሃነት) የሚያምን ትውልድ በ‹‹ሕዳሴ አብዮት›› ሂደት እንደሚፈጠር በእርግጠኝነት መናገር ይቻላል፡፡ የንቅናቄው አድማስ ሁሉን አቀፍ መሆኑ ከተሳካለት ደግሞ በድህረ-ለውጡ የሚነብረውን የፖለቲካ ባህል በእጅጉ የዘመነ ያደርገዋል፡፡ ‹የአብዮተኞች አባት› ተብሎ የሚወደሰው ካርል ማርክስ ከጓዱ ፍሬዴሬክ ኤንግለስ ጋር በጻፈው መድብል ላይ ይህን እውነት አስረግጦ አልፏል፡፡ ‹‹German Ideology›› በሚለው ያሰላሳዮቹ የጋራ ስራ ላይ የአብዮት ሂደት ዋና ፋይዳ ከለውጡ በኋላ የሚፈጠር ማሕበረሰብ የነቃ እንደመሆኑ፣
መጪዎቹ የሥልጣን ተረካቢዎች በቁመቱ ልክ ካልሆኑ (ካልመጠኑት) ለእነርሱም አስቸጋሪ እንደሚሆን የማስረገጡ እውነታ ነው፡፡
ለዚህም የቅርቡን የአረቡ መነቃቃት ማየት ያዋጣል፡፡ የግብፅ ሕዝብ ከአብዮቱ በፊትና በኋላ ያለውን የንቃት ልዩነት ማንም የሚያስተውለው ነው፤ ዛሬ ላይ የምናየው ማሕበረሰብ የሆስኒ ሙባረክ አገዛዝ ከነበረበት አንፃር ሲታይ ፍፁም ፖለቲካዊ ስለመሆኑ በብዙዎች ተወስቷል፡፡ ለእያንዳንዱ አገራዊ ጉዳይ ያገባኛል በማለት መሟገትን የዕለት ተዕለት ስራው አድርጎታል፡፡ ከዚህ አብዮታዊ ሃሳብ ትይዩ በብረት የሚመጣ ለውጥ፣ ተመልሶ ማሕበረሰባዊ ፍዝነት ውስጥ እንደሚጥለን መረዳታችንም፣ መጪውን የአብዮት አማራጭ ብቸኛው ትውልዳዊ ዕዳ ወደማድረጉ ገፍቶታል፡፡ ከሞት ይልቅ ህይወት፣ ከድቀት ይልቅ ጥንካሬ፣ ከመበታተን ይልቅ አንድነት የሚሰጠንን ሰላማዊ የለውጥ ንቅናቄ በቀጣዩ ዓመት ስለመከወን ደግመን ደጋግመን ማሰላሰል ደግሞ የዘመኑ አስገዳጅ ኃላፊነት ነው ብዬ አምናለሁ፡፡
ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር!

ሻእቢያ ከከረን እና ከአስመራ ጦሩን ወደ ተሰንይ ማስፈሩን ተከትሎ ወያኔ ተጨማሪ ጦር ሲያጓጉዝ ዋለ።

August19/2014
ምንሊክ ሳልሳዊ
የመከላከያ ሰራዊቱ ሊከዳ ይችላል በሚል ስጋት የወያኔ ጄኔራሎች ሲመክሩ ውለዋል።
ከሩሲያ ጋር የጦር ልምምድ ስምምነት እንዳደረገ የሚነገርለት የኤርትራ ገዥ ቡድን ሻእቢያ ከባለፉት ወራቶች ጀምሮ ጦሩን ወደ ደቡባዊ የኤርትራ ግዛቶቹ በመሰብሰብ ላይ መሆኑን ተከትሎ ወያኔም እንዲሁ ባለፈው ካሰፈረው ሰራዊት በተጨማሪ ከትላንትና ጀምሮ ከባድ የጦር ተሽከርካሪዎችን እና ተጨማሪ የጦር ሰራዊት በአከባቢው በማስፈር ላይ መሆኑ ታውቋል።
Ethio-army2 (1)አሜሪካ እና ሩሲያ በአከባቢው ያላቸውን የበላይነት ለመቀዳጀት ፉክክር በገቡበት በዚህ ወቅት አከባቢው የጦርነት ቀጠና እንደሚሆን ቀድማ አሜሪካ በበረራ ደህንንነ ሰበብ ሹክ ባለችበት ሰአት እንዲሁም የሻእቢያ ተቃዋሚ ሃይሎችን ወያኔ በገንዘብ እና በቅስቁስ እየረዳ ባለበት ጊዜ በተጨማሪም በአግል ወያኔያዊ ትእቢት እየዛተ እንዳለ ሲሆን ለወያኔ ከፍተኛ ስጋት የሆኑበት ኢርታራ ውስት የመሸጉ ተቃዋሚ ሃይላት ስለሆኑበት በጭቆና የተምረረው ምከልከያ ሰራዊት ተቃዋሚዎችን ይቀላቅላል የሚል ከባድ ስጋት በሕወሓት ጄኔራሎች ላይ መከሰቱን ምንጮች ጠቁመውል።
ወያኔ በቅርቡ ከዩክሬይን ያስገባችቸን ቲ-72 ዘመናዊ ታንኮች በጦርነት ላይ ለማሰለፍ ወደ ሰሜን እያጓጓዘ ሲሆን ሻእቢያ በበኩሉ ሩሲያ ሰራሽ የሆኑ ዘመናዊ ታንኮች ሚሳኤሎች እና ከባባድ መሳሪያዎች፡ጸረ አይሮፕላን መድፎችን በአከባቢው አስፍሯል። ወያኔ ዘመናዊ መሳሪያ እና በታንክ ላይ የተጠመዱ መድፎችን ቢያምጣም በመክላከያ ሰራዊቱ ላይ ምንም አይነት መተማመን እንዳሌለው እየተናገረ ሲሆን በሰሜናዊ ትግራይ ብግብርና ሙያ ላይ ከነሙሉ ትጥቃቸው ያሰፈራቸውን የቀድሞ ታጋዮች እየቀሰቀሰ መሆኑ ሲታወቅ ህዝቡ ጦርነት እንደተሰላቸ እና ባለው ስርአት ላይ እምነት እንዳጣ በግልጽ እየተናገረ መሆኑ ታውቋል።
በሰራዊቱ ያልተማመነው ወያኔ አንድ የወሰደው እርምጃ ከሱዳን ጋር ያደረገውን የሰራዊት ቅልቅል ሲሆን ይህም ተቀላቅሎ መስራት በሰራዊቱ መኮንኖች ዘንድ ተቀባይነት አለማግኘቱ ታውቋል። የምዕራብ ኢትዮጵያን መሬት ለሱዳን ለመስጠት ያሰበውን አገር የማጥፋት ሴራ ተግባራዊ ለማድረግ መሆኑን እና ሰራዊቱም ይህንን ተረድቶ ላገሩ ክብርና ታሪክ እንዲቆም ህዝቡ እየትናግረ ሲሆን የተደረገው የሰራዊት ውህደት ሱዳን በዳርፍርና ምስራቅ ሱዳን እንዲሁም ከደቡብ ሱዳን አቅጣጫ ላለበት ጦርነት በስምምነታቸው መሰረት የኢትዮጵያ ወታደሮች እንዲዋጉለት ለማድረግና ወያኔም በዚህ ጉዳይ ላይ መስማማቱን እናም በመከላከያ ሰራዊት ያለ የኢትዮጵያ ወጣት በጎረቤት አገሮች የበረሃ ሲሳይ ከመሆን ራስን እንዲታደግ አስተያየት ሰጪዎች አሳስበዋል።
ይህ በእንዲህ እንዳለ ከአዲስ አበባ የሚወጡ ዘገባዎች መጭውን የወያኔ የጦርነት ዝግጅት ተከትሎ የመከላከያ ሰራዊቱ በመክዳት ከተቃዋሚ ሃይሎች ጋር ሊቀላቀል ይሽላል በሚል ስጋት ስብሰባ ተቀምጠው መዋላችውን ምንጮች ጠቁመዋል። በኤርትራ የሚንቀሳቀሱ የተቃዋሚ ሃይሎች የሚያወጡት መግለጫ በሰራዊቱ ላይ የሚፈጸመው ዘረኝነት እንዲሁም ብዝበዛ እና ከሃገሪቱ ጥቅሞች አንጻር እየተደረገ ያለው ብሄራዊ ውርድት በእጅጉ አሳሳቢ ደረጅ ልይ መድረሱ ሕዝቡ ለስር አቱ ያለው ጥላቻ መበራከቱ እንዲሁም ከዚህ ቀደም በባድመ ጉዳይ የተፈጸሙ መንግስታዊ ማጭበርበሮች እና የመሳሰሉት ግኡዳዮች ሰራዊቱ ይከዳል የሚል ከባድ ስጋት ያላቸው መሆኑን ያወሱት ጄኔራሎቹ በመከላከያ ሰራዊቱ ላይ እምነት በማጣትቸው ትግራይ ያለው የሕወሓት ታጣቂ ሃይል ከጀርባ እንደ ደጀን እንደ መተማመኛ እንደሚወስዱት መክረዋል።
ሰራዊቱ ያለውን ስርአት በተመለከት ደስተኛ ስላልሆነ እንዲሁም ሕዝቡ የሚፈልገው ለውጥ እንጂ ጦርንት ስላልሆነ ወያኔ በመጭው ሊያደርገው ያሰበው ጦርነት ከባድ ኪሳራ ያስክትልበታል ተብሎ ተገምቷል።

Monday, August 18, 2014

የዩኒቨርስቲተማሪዎችየሚያነሱዋቸው ጥያቄዎች ለኢህአዴግ ፈታኝ እንደሆኑበት ተሰብሳቢዎች ገለጹ

August18/2014

ኢሳት ዜና :-የትምህርት ሚኒስቴር ከ360 ሺህ በላይ ነባርና አዳዲስ የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች የመንግሥትን ፖሊሲና ስትራቴጂን እንዲሰለጥኑ አስገዳጅ መመሪያ ማውጣቱን ተከትሎ በጎንደር ዩኒቨርስቲ የተሰበሰቡ ከ1500 በላይ ተማሪዎች ያነሱዋቸው ጥያያቄዎች ለኢህአዴግ ካድሬዎች ፈታኝ እንደሆኑባቸው ውይይቱን የሚከታተሉት ወኪሎቻችን ገልጸዋል። በከፍተኛ መሰላቸትና ጫጫታ የሚካሄደው ስብሰባ ዋና አላማ ተማሪውን ስለመጪው ምርጫ ማዘጋጀትና አዳዲስ አባላትን መመልመል ነው። ባለፈው አርብ በተደረገው የመጀመሪያ ቀን ስብሰባ ተማሪዎች ከመብት ፣ ከዲሞክራሲና ከኢኮኖሚ ጋር የተያያዙ ጥያቄዎችን አንስተዋል። እውን በአገራችን የብሄር እኩልነት አለ ወይ ሲሉ የጠየቁት ተማሪዎች፣ በተለያዩ መስሪያ ቤቶች በሚገኙ ከፍተኛ የስልጣን ቦታዎች የአንድ ብሄር የበላይነት ጎልቶ እንደሚታይ፣ ብሄሮች እኩል ናቸው ብሎ መናገር እንደማይቻልና በተለይ የአማራ ብሄር እንወክለዋለን ብለው በተቀመጡ ባለስልጣኖች ሳይቀር እየተሰደበ መሆኑን ገልጸዋል።

በአገሪቱ ዲሞክራሲ የሚባል ነገር እንደሌለ የተናገሩት ተማሪዎች፣  የሃይማኖት እኩልነት አለ መባሉንም በጥርጣሬ ተመልክተውታል። ኢህአዴግ ስለ ደርግ ደጋግሞ ቢያወራም፣ የእስካሁን የሰራው ከደርግ የማይሻልና ኢህአዴግና ደርግ የተለያዩ ናቸው ብሎ ለመውሰድ እንደማይቻል ተማሪዎች ገልጸዋል። በኢኮኖሚው ረገድ የተለየ ነገር አለመምጣቱን የገለጹት ተማሪዎች፣ የተጀመሩ መንገዶች አይጠናቀቁም፣ ስኳር ጠፍቷል፣ መንግስት ኢኮኖሚው አድጓል ቢልም በቅርቡ የወጡ መረጃዎች ኢትዮጵያን ከአለም የመጨረሻዋ ደሃ አገር እንዳደረጋትና አብዛኛው ግንባታዎች የሚካሄዱት ከቻይና በተገኘ ብድር መሆኑን ተናግረዋል።

 የቀድሞ መንግስታት በራሳቸው ወጪ ግንባታዎችን ያካሂዱ ነበር ያሉት ተማሪዎች፣ በኢህአዴግ የምንሰማው ግን ቻይና ብድር ፈቀደች፣ ቻይና ብድር ሰረዘች የሚል መሆኑን ጠቅሰዋል። የኢትዮጵያን ታሪክ ከእናንተ በተሻለ እናውቀዋለን በማለት  ተማሪዎች በታሪክ ላይ ተመስርቶ የሚሰጣቸውን ተንተና እንደማይቀበሉት ገልጸዋል። በሱዳን እና በኢትዮጵያ መካከል ስላለው ድንበር እና ኢትዮጵያ ለሱዳን ስለሰጠችው መሬትም ጥያቄ ተነስቷል። ዩኒቨርስቲዎችን የፖለቲካ ማራመጃ መደረጋቸውን የተቃወሙት ተማሪዎች፣ በእረፍት ሰአታቸው ላይ ተማሪዎችን ያስፈለገበት  አላማ እንዲገለጽላቸውም ጠይቀዋል። አንዳንድ ተማሪዎች ግን ምርጫ ሲደርስ ነው የምታስታወሱን በማለት የስብሰባው አላማ ከምርጫ ጋር የተያያዘ መሆኑን ጠቅሰዋል። ተማሪዎች አሰልቺ ነው ባሉት ስብሰባ፣ የገዢው ፓርቲ ተወካዮች ለተነሱት ጥያቄዎች በቂ መልስ ለመስጠት ባለመቻላቸው ተማሪዎችን ይበልጥ ማበሳጨቱን ወኪሎቻችን ገልጸዋል። በሥልጠናውላይተሳትፎየምስክርወረቀትያልያዘተማሪ በዩኒቨርሲቲዎቹትምህርቱንመቀጠል እንደማይችልሉ ተነግሮአቸዋል።

የትምህርት ሚኒስትሩ አቶ ሺፈራው ሽጉጤ ሰሞኑን ለጋዜጠኞች እንደገለጹት በመንግሥት ፖሊሲዎችና ስትራቴጂዎች ላይ ከ250 ሺህ በላይ ነባር የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች እናከ116 ሺህ በላይ አዳዲስ ተማሪዎች ለተከታታይ 15 ቀናት አበል በመክፈል ባሉበት አካባቢ   በፕላዝማ ሥልጠና እንደሚሰጥቃል የገቡ ቢሆንም፣ ከገጠር አካባቢ ለመጡት መጠነኛ አበል ከመስጠት በስተቀር ሌሎች ተማሪዎች አላገኙም። በዚህም በተማሪዎችና በባለስልጣኖች መካከል ጭቅጭቅ ተፈጥሮ እንደነበር ለማወቅ ተችሎአል።

ሥልጠናውንየሚሰጡትከፍተኛየመንግሥትባለስልጣናትመሆናቸውንየሥልጠናውዝርዝርእናየሚፈጀውወጪምንያህል እንደሆነእስካሁን ግልጽ አይደለም። ይህሥልጠና ኢህአዴግበመንግሥትወጪለቀጣዩምርጫድጋፍለማግኘትእንዲሁም ነባር አባላቱን በዩኒቨርስቲ ተማሪዎች ለመተካት ለዘረጋው መርሃ ግብር ማስፈጸሚያ ነው ኢሳት ያነጋገራቸው ተማሪዎች እንደሚሉት ኢህአዴግን የስልጠናውን አላማ ግልጽ አላደረገም። ስብሰባውን ለመሰታፍ በተማሪዎች በኩል ያለው ስሜትም ቀዝቃዛ ከመሆኑ
በተጨማሪ በርካታ ተማሪዎች ስብሰባውን ጀምረው ጥለው ይወጣሉ። የቀድሞው ም/ል ጠ/ሚኒስትር  አዲሱ ለገሰ በቅርቡ ባወጡት ጽሁፍ ኢህአዴግ አሁን ያለውን አመራር ይዞ ረጅም እርቀት እንደማይጓዝና ነባር አመራሩን በዩኒቨርስቲ ተማሪዎች
ለመተካት መንቀሳቀስ እንደሚገባ አመላክተው ነበር።

የወያኔው ኢንሳ በአዲስ መልክ የፌስቡክ ስም አጥፊ ፔጆችን/ገጾችን ሊያደራጅ ነው

August 18/2014
=================ነቢል አህመድ ዘገፈርሳ=====================
facebookወያኔ የኢትዮጵያን ሕዝብ አንድነት እና ነጻነት ለመሸራረፍ ብሎም ለመበታተን ከሚጠቀምባቸው ዘዴዎች አንዱ በማህበራዊ ድህረገጹ ያሰማራቸውን ከተቃዋሚ ሃይላት ጋር ተመሳስለው የተቃዋሚ የፖለቲካ ድርጅት መስለው የተቃዋሚ ሃይሎችን ሎግ በመጠቀም እንዲሁም ለሽፋንነት በየመሃሉ የተቃዋሚ ድርጅቶችን መግለጫ እንደወሽመጥ በማስገባት በማታለል እና በማጭበርበር ላይ ተመስርተው ሲሰሩ የነበሩ ስም አጥፊ ገጾችን/ ፔጆችን በአዲስ መልክ ለማደራጀት በዚህ ሳምንት እረፍት እንዲወስዱ ያደረጋቸው መሆኑ ታውቋል።
ስም በማጥፋት ለውጥ ፈላጊ ሃይሎች በተለያዩ አክቲቪስቶች ላይ መጠራጠር እንዲያሳድሩ እና ጠቃሚ የተባሉ ጦማርያንን እንዲያጡ እና ትግሉ አቅጣጫውን እንዲስት በስፋት አዲስ የአሰራር ዘይቤ ለመቀየስ የተሳዳቢዎች የተዛልፊዎች እና የስም አጥፊዎች የማህበራዊ አካውንት እና ፔጆች እረፍት ላይ መሆናቸውን እና በተጠናከረ መልኩ ወደ ስራ እንደሚመለሱ በቅርብ የሚያውቋቸው ወዳጆቻቸው ተናግረዋል።
በዚሁም መሰረት በዜጎች መካከል ከባድ ጥርጣሬን ያጭራሉ የተባሉ የፈጠራ ጽሁፎች እና የሞቱ ሰዎች ፎቶዎችን በመጠቀም የተለያዩ የፌክ ወንጀሎችን በመጻፍ እንድሁም ከብልግና እና የሰውን ክብር ከሚያዋርዱ አዳዲስ ብካይ የሃሰት መረጃዎች ጋር ወዘተ ተያይዘው ወደ ማህበራዊ ድህረገጾች እርፍታቸውን ጨርሰው እንደሚመጡ ታውቋል።

አቶ ብርሃኑ በርሀ የዓረና ትግራይ ፓርቲ ሊቀ መንበር በወቅታዊ የሀገራችን ጉዳይ ላይ ለ ሎሚ መፅሄት የሰጡት ቃለ መጠይቅ

Augest 18/2014
ሎሚ* ለመሆኑ አሁን ፓርቲያችሁ በምን አይነት ሁኔታ እየተንቀሳቀሰ ይገኛል?


አቶ ብርሃኑ በርሀ የዓረና ትግራይ ፓርቲ ሊቀ መንበርአቶ ብርሃኑ:- ፓርቲያችን ዓረና ትግራይ የሚያደርጋቸው እንቅስቃሴዎች የፓቲርው ጠቅላላ ጉባኤ ያሳለፋቸው ውሳኔዎች ተግባራዊ ማድረግ መሰረት ያደረገ ሆኖ ጠቅለል ብሎ ሲገለፅ የዓረና አማራጭ ፖሊሲና በወቅታዊ ሃገራዊና ክልላዊ ጉዳዮች ያለው አ ም ለህዝብ በማስተዋወቅ የአረና አማራጭ ፖሊሲዊች የህዝቡ አጀንዳና የፍላጎቱ መገለጫ ሆነው ከፓርቲ ፖለቲካ ወደ የህዝብ ፖለቲካ በማሸጋገር የነፃና ፍትሃዊ ምርጫ እድል ተፈፃሚነት በህዝቡ የነቃ ተሳትፎ ዋስትና እንዲያገኝ ለማስቻል ተከታታይ የህዝብ ፖለቲካዊ ስብሰባዎች ማካሄድ ፣ አማራጭ ፖሊሲያችን በማስተዋወቅ የምንፈጥረው ተቀባይነትና ድጋፍ የፈጠረልን ምቹ ሁኔታ በመጠቀም ፓርቲያችን በአባላትና በደጋፊዎች ብዛት እንዲሁም በአደረጃጀት መዋቅራችን በማስፋት እራሳችንን ለሰላማዊ ፣ሕጋዊና ዴሞክራሲያዊ የምርጫ ውድድር ብቁ ሆኖ መገኘትን ያለመ ነው ፡፣ የዓረና አማራጭ ፖሊሲ የህዝቡ አጀንዳ ሆኖ ህዝቡ ይጠቅመ’ል የሚል ግንዛቤ ወስዶ የራሱ አጀንዳ አድርጎት ለውጤታማነቱም ወሳኙ ራሱ ህዝብ መሆኑን እንዲገነዘብና ያን ለማድረግ ህዝብ ብቃቱም ችሎታውም እንዳለው እንዲገነዘብ ማስቻል የፖለቲካ ስራችን አቅጣጫና የሰላማዊ ትግላችን ስትራተጂ መመርያም በተግባር ለመፈፀም ነው የምንንቀሳቀሰው፣፣

 ሎሚ* ዘመቻ አብርሃ ደስታ ብላችሁ ያዘጋጃችሁት ፕሮግራም እንዴት ነበር?  

አቶ ብርሃኑ:- አብርሃ ደስታ ሀገራዊ ራኢ ከሰነቁና የአረና አመራር ወራሾች ይሆናሉ ተብለው ከምንገምታቸው ንቁ የአረና ወጣት አመራሮች አንዱ ነበር፡፣ አካዳሚያዊና ፖለቲካዊ ብቃቱ ተስፋ የሚጣልበት መሆኑን በተግባር አሳይቶአል ፣ ለማነበት ራኢ ግብራዊነት የማይታጠፍ የፀና አ ም አሳይቶአል ፣ አጠቃላይ ፖለቲካዊ ስብእናውና የመቀስቀስ ችሎታው የሚደነቅ ነው፣ የኤሌክትሮኒክስ ቴክኒዮሎጂ በመጠቀም የፌስቡክ ንጉስ እስኪመስል ሰርቶአል ፣ አስተምሮአል አሳምኖአል ተደናቂነትም አትርፎአል፣ ይህ በመሆኑ ለአብርሃ ደስታ ብቻ ሳይሆን ውለታና ምስጋና ለሚገባቸው ወጣት መሪዎች ክብርና አድናቆታችን ለመግለፅ ከመታሰሩ በፊት ህዝባዊ ፖለቲካዊ ስብሰባ እንዲካሄድባቸው አብሮን ውሳኔ የሰጠባቸው የራያ አዘቦ ወረዳ አከባቢ ያካሄድነው ህዝባዊ ፖለቲካዊ ስብሰባ ዘመቻ አብርሃ ደስታ ብለናቸዋል ፣
[ሙሉውን ለማንበብ እዚህ ይጫኑ]—

የኢትዮጵያችን ችግር ገዢዎች እና አደርባዮቻቸው የሚፈጥሩት የፖለቲካ ካንሰር ነው::…. .. እየተገፋን እስከመቼ?? ተነስ እንጂ ወገን !! - ምንሊክሳልሳዊ

August18/2014
ሁኔታዎች ገዢው ፓርቲ ብቻ በሚፈልገው መንገድ የሚቀጥል ከሆነ ደጋግሜ ለመናገር የምንፈልገው ለሃገርም ለህዝብም ከባድ እና አደገና አደጋ እንዳለው ነው:: በፖለቲካ ታማኝነት ያልተማሩ እና ከካድሬ ትምህርት ቤት ተመርቀው የወጡ በፖለቲካ ጥላቻ የተሞሉ ሰዎች የአገርን አመራር እና የህዝብን አንድነት ሊጠብቁ ስለማይችሉ በሃገሪቱ የፖለቲካ መስክ ትልቅ በሽታ ሆነዋል::

በሃገሪቱ የተከሰተውን ደዌ ከማዳመጥ ይልቅ በሽሙጥ አንዱ አንዱን እየወገረው በመብረር ላይ እንገኛለን :; እርስ በእርስ ከመወጋገር ያድነን እንዳንል እየተወጋገርን ጸሎት ለቅጽበት ነው::ማን ከማን ይማር ሎሌ ከንጉሱ ሆኖብን ሆነና የራሳችንንም ሆነ የሃገራችንን ህመም ተጋግዘን እንዳናድን ራሳችን በሽታ ሆነናል::ምን እንደተባልን እንኳን ማዳመጥ አለመቻላችን አንዱ ደንቃራችን ሲሆን የምንናገረውንም ከማንነገርው መራርጠን መተንፈስ እስኪያቅተን ድረስ እያቃተትን በሽታችንን እያባስን ብዙሃዊ ተላላፊ ህመም አድርገነዋል ከዚህ ይሰውረን እንዳንል ራሳችን አሁንም ደንቃራ ሆነናል::

የኢትዮጵያችን ችግር ገዢዎች የሚፈጥሩት የፖለቲካ ካንሰር ነው::ልዩነት እንዳለ ሆኖ በጋራ ሃገራዊ መርህ ላይ ያልተመሰረተ ፖለቲካ እንዴት ህዝባዊ መተሳሰብ ሊፈጥር እንደሚችል በሃገራችን የሚገኙ ፖለቲከኛ ነን የሚሉ አልተረዱትም ወይንም አውቀው እየተባሉ እያባሉን እያነካከሱን ነው:: በጋራ መተሳሰብ ላይ ያልተመሰረተው ፖለቲካችን እና በመጭበርበር የሚያጭበረብሩን ገዢዎቻችን ለነገ ሃገር ተረካቢ ትውልድ አደገኛ የሆነ የፖለቲካ በሽታ እያወረሱ ይገኛሉ፤ የፖለቲካ በሽታ ብቻ ሳይሆን በአንድ ወጥ መርህ ላይ የተመሰረተ እና የደቀቀ ኢኮኖሚ ጭምር:: ይህ በተጭበረበረ ፖለቲካ ላይ የተገነባ ኢኮኖሚ የህዝቦችን የጋራ መደጋገፍ በማስመጥ ገዢው መደብ በፍጹም ከኔ ውጪ የሚነካ ካለ እሳት እንደነካ ነው በማለት በፍራቻ ላይ የተመሰረተ ማስጠንቀቂያ በመስጠት ዜጎች በሃገራቸው ብሄራዊ አጀንዳ ጉዳይ እንዳይሳተፉ እንዳይተሳሰቡ እንዳይደጋገፉ እንቅፋት ሆኖ ይገኛል::ከማህበረሰቡ ተገልሎ እየተሰራ ያለውን ውጤት እያየነው ነው::

በሃገራችን በመጀመሪያ ደረጃ ሁሌ ለገዢዎቹ የሚኒነግራቸው ቢኖር የህግ የበላይነት እንዲከበር ነው:: የስልጣን እድሜ ለማስረዘም ሲባል በሃገሪቱ ገንዘብ የተገዙ የፓርቲ ካድሬዎች በህዝቡ ላይ ከህግ በላይ በመሆን አሳር እና አበሳ እያሳዩን ሲሆን ይህንንም ከተራ ዜጋ ጀምሮ እስከ ሃይማኖት መሪዎች ድረስ አበቱታ እያሰሙ የህግ ያለህ የመንግስት ያለህ እያሉ ነው::ሲታይ ግን ምንም መፍትሄ ያለው አይመስልም ይህ ደግሞ ገዢ ነኝ ባዩ አካል የስርኣት ለውጥ ማምጣት ስለማይችል በህዝቦች የጋራ ትግል ለውጡን ተከትሎ ህግና ደንብ ሊከበር እንደሚችል የሚታወቅ እና የተጠና ነው::በዚሁ ከቀጠለ ግን አገር ከገባችበት አደጋ ወደ ሌላ አደገኛ አደጋ እንደምትሸጋገር ለመናገር እወዳለሁ::

ሌላው የተንሰራፋው ሙስና የሃገር ሃብትን በተገቢው ቦታ ላይ እንዳናውል እንቅፋት ሆኗል:: ሁሉም በተደጋጋሚ ታግለው ስልጣን እንደያዙ የሚደነፉት የወያኔ ጁንታ አባላት በሙስና ውስጥ ተዘፍቀው አገሪቷን እርቃኗን አስቀርተዋታል:: ይህ አደገኛ የሙስና ሂደት ህዝብን ወደ ኑር ውድነት እና ድህነት እስር ውስጥ ከቶታል:: ተናግረን የማንጨርሳቸው እስር፣ ስደት ፣ስራ አጥነት ፣ግድያ ፣ክስራ መፈናቀል፣ ተመሳሳይ ምእንግስታዊ ውንብድናዎችቸና ሽብሮች በዜጎች ላይ እየተፈጸሙ በገሃድ እየታዩ እንዲሁም መንግስትዊ ቅጥፈት/ውሸቶች በአደባባይ እየተደሰኮሩ የትውልድን ሞራል ለመግደል ካለመታከት እየተውተረተሩ ነው። ራሳችንን ማንቃት ለለውጥ መነሳት ግድ ይለናል ፤ ደጋግመን እንናገራለን በሕዝብ ልጆች አፋጣኝ ትግል እጅግ ሊለወጥ የሚገባው ጉዳይ መሆኑን ለማሳወቅ እወዳለሁ :: በተጨማሪ በፖለቲካ ታማኝነት ያልተማሩ እና ከካድሬ ትምህርት ቤት ተመርቀው የወጡ በፖለቲካ ጥላቻ የተሞሉ ሰዎች የአገርን አመራር እና የህዝብን አንድነት ሊጠብቁ ስለማይችሉ በሃገሪቱ የፖለቲካ መስክ ትልቅ በሽታ ሆነዋል::

የፖለቲካ ካንሰራችንን ተነጋግረን እና በጋራ ሆነን ከማዳን በጉልበት በሽሙጥ እና እኔ አውቅልሃለሁ በሚል አባዜ እስከመቼ ድረስ እንደምንቀጥል አልታወቀም:: ሁኔታዎች ገዢው ፓርቲ ብቻ በሚፈልገው መንገድ የሚቀጥል ከሆነ ደጋግሜ ለመናገር የምንፈልገው ለሃገርም ለህዝብም ከባድ እና አደገና አደጋ እንዳለው ነው:: ሁላችንም ዜጋ እስከሆንን ድረስ ለሃገራችን እኩል አስታውጾ ማበርከት አለብን ።….እየተገፋን እስከመቼ?? ተነስ እንጂ ወገን !! #ምንሊክሳልሳዊ

Sunday, August 17, 2014

እንደገና ይድረስ ለሠራዊቱ

August17/2014
“የትግሬ” ነፃ አውጪ ነኝ ብሎ ራሱን የሠየመው የዘረኞችና የዘራፊዎች ቡድን አገሪቷን እያጎሳቆለ ያለው ከሠራዊቱ ጀርባ ተንጠላጥሎ መሆኑ ይታወቃል። ይህ የዘረኞችና የዘራፊዎች ቡድን የተሸከመውን ሠራዊት ሳይቀር በጉስቁልናና በድንቁርና እንዲኖር ፈርዶበታል። ህወሃት ሠራዊቱ እንዲማር፤ ዘመኑ ከሚፈቅደው የቴክኖሎጂ እውቀት ጋር ራሱን እንዲያዋህድ እና በራሱ የሚተማመን የዘመነ ሠራዊት እንዲሆን ፍላጎት የለውም።አሜሪካን በአገሯ በሚገኙ የጦር ትምህርት ተቋማት ውስጥ ወታዶሮችን ለማሰልጠን ፍላጎት ብታሳይም ሳሞራ የኑስና መለስ ዜናዊ እምቢ ማለታቸውን አብዛኛው የሠራዊቱ አባላት የሰሙት አይመስልም። አሜሪካን በሁለት ዓመት ውስጥ ብቻ 42 ወታደሮችን አገሯ ወስዳ ለማስለጠን በጠየቀች ግዜ ሳሞራ የፈቀደው 13 ወታደሮች ብቻ ሂደው እንዲማሩ ነው። እነዚህም ከህወሃቶች መካከል ፊደል የቆጠሩ ተፈልገው በመገኘታቸው መሆኑም ታውቋል። በሠራዊቱ ውስጥ የሚገኙ ሌሎች የትምህርት ዝግጅት ቢኖራቸውም የትምህርት እድሉን ተከልክለዋል።
ህወሃት ከራሱ ውጪ ያሉት ሌሎች ላይ ምንም ዕምነት እንደሌለው በተለያየ አጋጣሚ ተናግሮታል። የትምህርት ዕድሉን ለምን መጠቀም እንዳልፈለጉ ሲጠየቅ ሳሞራ የኑስ “ሌሎችን አናምናቸውም አሜሪካን ሂደው ይቀራሉ” ብሎ መልስ መስጠቱም ተመዝግቦ ይገኛል። 11ኛ ክፍልን ያልዘለለው የህወሃቱ ኢታማዦር ሹም ሳሞራ የኑስ ሠራዊቱን ታማኝና የማይታመኑ በሚል ይከፍላቸዋል። የህወሃት አባል የሆነ ወታደር ታማኝ ፤ ሌሎች የሠራዊቱ አባላት የማይታመኑ።
አሁንም የሠራዊቱ አባላት ስሙ !
እናንተ ምንም ያክል ጥሩ ዜጋ ለመሆን ብትጥሩ በህወሃቶች ዘንድ የምትታመኑ አይደላችሁም። ህወሃቶች ከእነርሱ ውጪ ባሉ ሌሎች ላይ ጥርሳቸውን እንደነከሱ እስከ ዛሬ አሉ። በሌሎች ዜጎች ላይ የመዘዙት የበቀል ሰይፍም ወደ ሰገባው የሚመለስ አልሆነም። በሁለት ዓመት ውስጥ 42 ወታደሮችን አሜሪካን ወደ አገሯ ወስዳ ለማስልጠን ብትጠይቅም 13ቱን ብቻ ተቀብለው 29ኙን አንፈልግም ማለታቸው የተመዘዘው የበቀል ሰይፋቸው አንዱ አንጓ መሆኑን የትምህርት ዕድሉን የተነፈገው የሠራዊቱ አባል ልብ ሊለው ይገባል። እነ ሳሞራ የኑስ ከእነርሱ ውጪ ያሉ ሌሎች ዜጎች በድንቁርናና በችጋር እየተሰቃዩ ይኖሩ ዘንድ ፈርደውበታል። በእንዲህ ሁኔታ እንዲኖር የተፈረደበት ሠራዊት፤ ውጪ አገር ሂዶ እንዳይማር የተከለከለ ሠራዊት፤ ዘር ሃረጉ እና ድርጅታዊ ታማኝነቱ እየታየ ለሹመት የሚበቃው የሠራዊት አባል ይህን ውስኔ ለወሰነበት ለመለስ ዜናዊ ፋውንዴሽን ከሚያገኛት ከወር ደመወዙ ላይ ቆርጦ እንዲከፍል ይደረጋል። እንዲህ ዓይነት በደል በየትኛውም አገር ታይቶ አይታወቅም።
በችጋር እንድትኖሩ ከምታገኟት ከወር ደመወዝችሁ ላይ ይወሰዳል፤ ተምራችሁ ራሳችሁን እንዳትቀይሩ በነፃ የሚገኘውን የትምህርት ዕድል እንኳ እንዳትጠቀሙ ተከልክላችኋል። በዚህ ሁኔታ እንድትኖሩ ከተፈረደባችሁ በኋላ የገዛ ወገኖቻችሁን ደም በከንቱ እንድታፈሱ ትደረጋላችሁ። የቀደመው ትውልድ በደሙ ያቆመው ድንበር ፈርሶ እና ዜጎች ተፈናቅለው መሬቱ ለባዕድ ሲሰጥ አናንተ ቁማችሁ ትመለከታላችሁ። ያ የሚፈሰው ደም የራሳችሁ ደም፤ ተፈናቅሎ ሜዳ ላይ የሚወድቀው የገዛ ወገናችሁ መሆኑን ለማሰብ እንኳ ነፃነት ያጣችሁ ትመስላላችሁ። የህፃን ደም በአዲስ አበባ ጎዳና ላይ ሲፈስ ለምን ስትሉ አልተሰማም፤ ጋምቤላዎች ለዘለዓለም ከኖሩበት መሬት ተፈናቅለው መሬታቸውን ሌሎች ሲቀራመቱት ይሄ አይሆንም ለማለት የያዛችሁት ነፍጥ የሸንበቆ ምርኩዝ ሁኖባችኋል። በኦጋዴን ላይ የዘር ማጥፋት ወንጀል ሲፈፀም ተባባሪ ትሆናላችሁ። ህወሃቶች በዚያች አገር ለሚፈፅሙት ማንኛውም ወንጀል እናንተ የእነርሱ በትር ሁናችሁ ታገለግላላችሁ። ከዚያች አገር ከሚገኘው ሃብት ግን ተካፋይ አትሆኑም። እነርሱ ሚሊየነር ሁነው የሚያደርጉትን ሲያጡ፤ አናንተ የሠራዊቱ አባላት ግን በችጋር ከነ-ቤተሰቦቻችሁ ትሰቃያላችሁ። ይሄ ሁኔታ ማብቃት የኖርበታል።
የአገሪቷ መከላከያ ኃይል ራዕይ ተብሎ የተነገረህ እንዲህ ይላል “. . . ለህገ-መንግስቱ እና ለህዝቡ ፍፁም ታማኝ የሆነ . . . የሃገራችን ህዝቦች ተምሳሊት የሆነ . . . የእውቀት መፍለቂያ የሆነ ሠራዊት መገንባት “
ምንም እንኳ ጥሩ ራዕይ ተቀርፆ የተቀመጠ ቢሆንም አንተ የሠራዊቱ አባል ግን የዚህ ራዕይ ተካፋይ አይደለህም።አንተ የምትካፈልው መከራውን እንጂ መልካሙን ራዕይ አይደለም። ለህገ-መንግስቱ እና ለህዝቡ ፍፁም ታማኝ የሆነ ሠራዊት መገንባት የሚለውን ራዕይ መልሰህ መልሰህ እንድታስብ እንመክርሃለን። በእኛ በኩል ግን ህወሃት በአገሪቷ ጫንቃ ላይ ከተቆናጠጠ ዘመን ጀምሮ ህዝቡን ሲያዋርድ ኖረ እንጂ ለህዝብ ታማኝ ሲሆን አልታየም። ህገ-መንግስት ብሎ ራሱ እዚያ ጫካ ሁኖ የፃፈውን ራሱ ሲያፈርሰው ኖረ እንጂ ሲያከብረው አላየንም። ህወሃት ለህገ-ማንግስቱ እና ለህዝቡ ታማኝ ሁኖም አያውቅም። ወደ ፊትም ራሱን ከህዝብ እና ከህግ-በታች አድርጎ እንዳይኖር እሰከ ዛሬ ሲፈፅመው የኖረው ወንጀል የሚያስችለው አይሆንም። ህወሃቶች ከነ እድፋቸው ወደ ማይቀረው መቃብራቸው መሄድን የመረጡ ስለሆነ ሠራዊቱ ራሱን ከእነዚህ ነውረኞች ለይቶ ለህገ-መንግስቱና ለህዝቡ ፍፁም ታማኝ መሆኑን ማስመስከር ይጠበቅበታል።
ሌላው ከህወሃት ውጪ ያላችሁ የሠራዊቱ አባላት ልታስቡበት የሚገባው ዓቢይ ነገር ደግሞ ‘የሃገራችን ህዝቦች ተምሳሊት የሆነ ሠራዊት መገንባት ‘ የሚለውን ራዕይ ነው። ሃገራችን ከ80 በላይ ብሄሮች የሚኖሩባት መሆኑ ይታወቃል።ለዚህች አገር ምሳሌ ሊሆን የሚችል መከላከያ ኃይል መገንባት እንደ ራዕይ የተቀመጠ ቢሆንም በተግባር የሆነው ግን ሌላ ነው። አሁን ባለው የአገሪቷ መከላከያ ኃይል ውስጥ ያሉ የጦር አዛዦችን ቀና ብለህ አይተህ እውነት መከላከያ ሃይሉ የህዝቦቿ ተምሳሊት የሆነ ሠራዊት መሆኑን ራስህ እንድትመልስ እንጠይቅሃለን። በአገሪቷ የተሾሙ ጄኔራሎች ከአንድ ጎጥ እና መንደር የተሰባሰቡ መሆናቸው በምን መልኩ የሃገራችን ህዝቦች ተምሳሊት የሆነ ሠራዊት ሊሆን እንደሚችል ህወሃቶችን ደግሞ ደጋግሞ መጠየቅ ተገቢ ይሆናል።
በመጨረሻም ‘የዕውቀት ምንጭ የሆነ ሠራዊት መገንባት’ የሚል ራዕይም በጉልህ ተፅፎ ተቀምጧል። የህወሃት የጦር አበጋዞች ከ7ኛ ክፍል ያልዘለሉ፤ካርታ ይዘው የቆሙበትን ሥፍራ እንኳ ለማሳየት የሚደናበሩ መሆናቸው የታወቀ ነው። እነዚህ ፊደል ቆጥረው ያልዘለቁ ቡድኖች የሚመሩት ተቋም እንደምን ሁኖ የዕውቀት ምንጭ ሊሆን እንደሚችል የሚያውቅ የለም። የህወሃቶች እውቀት የንፁሃን ደም ማፍሰስ፤ የድሃ ሃብት መዝረፍ፤ እኔ ብቻ ባይነት እንጂ ከዝህ የዘለለ ሌላ እውቀት ያላቸው አይደሉም። እነርሱ ባለመማራቸው የጎደለባቸው ነገር አለመኖሩን እያዩት ለትምህርትና ለተለየ ዕውቀት ዋጋ ይሰጣሉ ማለት አይቻልም። ሌሎቹም ተምረው እውቀት እንዲገበዩ ለማድረግ ስብዕናቸው አይፈቅድላቸውም። በዚህም ምክንያት ከውጭ አገራት በነፃ የሚገኘውን የትምህርት ዕድል እንኳ ወታደሩ ተጠቅሞ ራሱን በእውቀት እንዳያዳብር ይከለክላሉ። እንዳይማር የተከለከል የሠራዊት አባል እንደምን ሁኖ የዕውቀት መፍለቂያ ሊሆን እንደሚችል የሠራዊቱ አባላት የሽፍቶቹን ቡድኖች መጠየቅ ይኖርባችኋል።
የሠራዊቱ አባል የህዝብ አካል መሆንህን አትርሳው። ነገ ዞረህ የምትገባውም እዚያው ከወጣህበት ህዝብ መሆኑን እኛ ልናስታውስህ እንወዳለን። አሁን ባለው አካሄድህ የወጣህበትህን ድንኳን፤ በዚያች ድንኳን ውስጥ ሁነህ ያሳደጉህ ወገኖችህን እያሳደድክ መሆንህን አስታውስ። የወጣህበትንም ድንኳን እያፈረስክ ነው። ድንኳንህንም አፍርሰህ ከጨረስከው ነገ ዞሮ ማረፊያ እንደማይኖርህ ደግሞ እኛ ልናስታውሰህ እንፈልጋለን። ጥሪያችንን መስማት ከማንም በላይ ለራስህ ይበጅሃል። የወገኖችህን ጥሪ ሰምተህ በወገኖችህ ላይ የተመዘዘውን የበቀል ሰይፍ ለማቆም ከህዝብ ጎን መሆንን አልመርጥ ካልክ መጨረሻህ አያምርም። እነ ሳሞራ የኑስ ጠላቶችህ እንጂ ወገኖችህ አይደሉም። እነ ሳሞራ የኑስ አንተንና ልጅ ልጆችህን ጭምር በድንቁርና አዘቅት ውስጥ አኑረው ቀጥቅጠው ለመግዛት ያላቸው ፍላጎት ወሰን እንደሌለው ማወቅ ይኖርብሃል። የተሸከምከው መሣሪያ ለፍትህ ለእኩልነት፤ ለነፃነት እና ለእውነተኛ ዴሞክራሲያዊ ሥርዓት ግንባታ እንቅፋት የሚሆኑትን የሚፋለም ሊሆን ይገባዋል እንጂ እነዚህን ጥያቄዎች ባነሱ ወገኖች ላይ የሚያነጣጥር መሆን አይኖርበትም።
እንግዲህ ምን እናድርግ እያላችሁ የምትጠይቁን አላችሁ። ለዚህ ጥያቄ መልሱ ያለው ከእናተው ደጅ ነው። እኛ ያነሳነውን ጥያቄ ባላችሁበት ሁናችሁ ማንሳት ትችላላችሁ። አብዛኛው ሠራዊት ጥቂት ዘረኞችንና ዘራፊዎችን ተሸክሞ የሚኖሩበት ሁኔታ ለመቀየር ሦስትም አራትም እየሆናችሁ እምቢ ማለት መጀመር አለባችሁ። ህወሃቶችን ተሸክማችሁ፤ የህዝባችሁ ጠላቶች ሁናችሁ፤ አገራችሁንና ህዝባችሁን አዋርዳችሁ የምትኖሩት ኑሮ ኑሮ አይደለምና እምቢ አይሆንም ማለት ጀምሩ። ለዘረኞቹና ለዘራፊዎቹ ህወሃቶች ከመሞት ይልቅ ለፍትህ፤ ለእኩልነት እና ለነፃነት ብላችሁ ብትሠው መሥዋእትነታችሁ ለዘላለም ሲዘከር ይኖራል፤ ስማችሁም ከመቃብር በላይ ይሆናል።ፍፃሜያችሁም የጀግና ፍፃሜ ይሆናል።
ፍፃሜያችሁ የጀግና ፍፃሜ እንዲሆን ለፍትህ፤ ለነፃነት እና ለእኩልነት ዘብ የምትቆሙ ሁኑ እንጂ የአንድን ዘረኛና ዘራፊ ቡድን እድሜ ለማራዘም የምትቆሙ አትሁኑ።
ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ !!!

የግል ሚዲያዎች ክስ ለምን? – በግርማ ሰይፉ

August17/2014
Girma Seifu
በዚህ የፋክት ዕትም ከ“ግል ሚዲያ” ውጪ ስለ ሌላ ነገር መፃፍ ትክክል መስሎ አልታየኝም፡፡ ይህን ሳስብ ደግሞ ባለፈው ዕትም በፋክት መፅሔት በከፊል የተነሳውን የኢህአዴግ የፖሊሲ ወረቀት “የዴሞክራሲ ሰርአት ግንባታ ትግልና አብዮታዊ ዲሞክራሲ” በሚል በመጋቢት 1999 ዓ.ም የወጣውን መሰረት ማድረግ ወሰንኩ፡፡ ከዚህ የፖሊሲ ወረቀት ውስጥም “ሚዲያና ዲሞክራሲ” በሚለው ንዑስ ርዕስ ላይ አተኩራለሁ፡፡ ለዚህም ምክንያቴ፣ አሁን መንግስት እንደሚለው እየወሰደ ያለው እርምጃ  ህግን የማስከበርና የህዝብ ጥያቄን የመመለስ ሳይሆን፤ በፖለቲካ ሰነዱ ላይ ያስቀመጠውን በግል ሚዲያዎች ላይ መወሰድ ያለበት ተከታታይ እርምጃ ክፍል መሆኑን በመጥቀስ ይህን የፖለቲካ ሰነድ አግኝተው ለማንበብ እድል ላልገጠማቸው አንባቢያን ማስረዳት ነው፡፡ ከዚያም በማስከተል ይህ ሰነድ፣ በፈለገው መንገድ ተተርጉሞ ህገወጦች ይለናል በሚል ነፃነታችንን አሳልፈን ለመስጠት አለመዘጋጀታችንን ይፋ ለማድረግ ነው፡፡ ነፃነት በነፃ አይገኝምና፡፡

ይህ የምርጫ 97 ዝረራ የወለደው የፖለቲካ ሰነድ ሚዲያን በሚዳስስበት ንዑስ ክፍል መግቢያ ላይ “ሚዲያ የዴሞክራሲ ስርአትን በመገንባት ረገድ ወሳኝ ድርሻ ካላቸው ተቋሞች አንዱ ነው” ብሎ የሚጀምር ቢሆንም፤ ዋና ግቡ ግን ሚዲያን እንዴት ማጥፋት እንደሚቻል የሚተነትን ነው፡፡ የሩዋንዳን እልቂት ፈጣሪ ሚዲያዎችን ፣ የምዕራባዊያንን የሚዲያ ተቋማትን እንዲሁም በአረቡ ዓለም ያሉትን አልዓረቢያና አልጀዚራን የመሳሰሉ ሚዲያዎችን በመጠቃቀስ “ኪራይ ሰብሳቢ ሚዲያዎች” የሚል ፅንሰ ሀሳብ ለማዋለድ በሚረዳ መልኩ “የኪራይ ሰብሳቢነት ፖለቲካ ኢኮኖሚ በልማታዊ ፖለቲካዊ ኢኮኖሚ በተሟላ መልኩ መተካት አለበት” ብሎ ይደመድማል፡፡ ስለዚህ ከዚህ በኋላ ኪራይ ስብሳቢ ሚዲያ ሲባል አቤት ማለት ይኖርብናል፡፡ ልዩነት ለዘላለም ይኑር ብለን የምንዘምር ሰዎች የኢህአዴግ “ልማታዊ ፖለቲካው ኢኮኖሚ”ን እንደ አንድ አስተሳሰብ መቀበል ብንችል እንኳን፣ ይህን አስተሳሰብ ለራሳችን ለማድረግ የምንቸገር ሰዎች አለን፡፡ ይልቁንም ከዚህ የተሻለ አማራጭ አለን ስንል፣ ይህ አስተሳሰብ በኢህአዴጎች ሰፈር “ኪራይ ስብሳቢነት” ቢሆንም በነፃነት ልናራምድ የምንችልበትን መድረክ ለመንፈግ፣ ይህ ሰነድ የማይፈነቅለው ድንጋይ የለም፡፡

የሚዲያ ነፃነትና የዲሞክራሲ ስርአት ግንባታን በሚመለከት የፖለቲካ ሰነዱ  “ሚዲያውን በነፃነትና በጤናማ አኳኋን እንዲያድግ ማድረግ ለማንም ሲባል የሚሰራ ስራ ሳይሆን በአገራችን የዴሞክራሲ ስርአትን እውን ለማድረግ ተብሎ የሚከናወን በመሆኑ ለሌሎች የዴሞክራሲ ሰርአት ግንባታ ስራዎች ከምንሰጠው ትኩረት የማይተናነስ ትኩረት ለዚህም ስራ መሰጠት አለበት” ይላል፡፡ ይህን አባባል በጥሬው ስንመለከተው ምንም ክፋት የለበትም፡፡ ነገር ግን ምን ዓይነት ‹ነፃነት› እና ምን ዓይነት ‹ጤንነት› እንደሆነ ስንመረምር ችግሩን መረዳት ይቻላል፡፡ ኢህአዴግ ሌሎችንም የዴሞክራሲያዊ ተቋማትን ማለትም የብዙኃን ማኅበራትን፣ የፖለቲካ ፓርቲዎችን፣ የህዝብ ምክር ቤቶች እንዲሁም የዳኝነት ስርዓቱን ምን ያህል ነፃነት እየከለከለ ጤና እንደሚነሳቸው ስንረዳ፣ ምን ዓይነት ነፃነትና ጤና እንደታዘዘልንም መረዳት ቀላል ነው፡፡ የግል ሚዲያውም ከላይ እንደገለፅኳቸው የዴሞክራሲ ተቋማት ሸፋፋ እንዲሆን የመጨረሻው ምዕራፍ ላይ እንገኛለን፡፡ ስለዚህ ኢህአዴግ ሚዲያውን እንደሌሎቹ የዲሞክራሲ ተቋማት ሙት እንዲሆን መፈለጉን እንረዳለን፡፡ በሙታን ውስጥ የሚገኝን ነፃነት እና ጤና የሚያውቁት ሙታኖች ብቻ ናቸው፡፡

ኢህአዴግ እንደ መንግስት የሚዲያውን አቅም መገንባት ሳይሆን እንዴት አድርጎ መዋጋት እንዳለበት በዝርዝር አስቀምጧል፡፡ ይህንንም ለማድረግ በፖለቲካ ሰነዱ ውስጥ የተቀረፀውም በአቅም ግንባታ ሞዴል ሳይሆን በውጊያ ሞዴል ነው፤ “ኪራይ ስብሳቢነትን መዋጋት” በሚል ርዕስ ነው የተቀመጠው፡፡ በዚህ ንዑስ ርዕስ ስር በዋነኝነት የተቀመጠው የውጊያ ግንባር “የሚዲያ አውታሮች ገቢና ወጪያቸውን በትክክል እንዲያስመዘግቡና በየጊዜውም ጥብቅ ቁጥጥር እንዲደረግበት ማድረግ ወሳኝ ጉዳይ ነው፡፡” ይላል፡፡ ይህም የሚረዳው “በውጭ ሃይሎችና በፀረ ሰላም ድርጅቶች ፋይናንስ እንዳይደረግ በጥብቅ መከላከልና መቆጣጠር በጣም አስፈላጊ ይሆናል፡፡” በሚል ነው፡፡ ይህን በተመለከተ በግል ሚዲያዎች ላይ ማስረጃ ማቅረብ የተሳነው መንግስት በቴሌቪዥን በኩል ለሆዳቸው ያደሩ ሹሞችን እና ባለሞያ ነን የሚሉትን ሰብሰቦ በዘጋቢ ፊልም ‹‹መረጃ አለን፤ ከሚያትሙት አርባ አምስት ሺ፣ ሁለት ሺውን ብቻ ነው የሚሸጡት›› የሚል ፕሮፖጋንዳ ለመስራት ይዳክራል፡፡ ማስረጃ ማቅረብ ያልቻለ መንግሰት ‹መረጃ› እያመረተ ይገኛል፡፡ ወደፊት እነዚህ መረጃዎች በማስረጃ ደረጃ ፍርድ ቤት ይቀርባሉ ብለን ብንጠረጥር አስገራሚ አይሆንም፡፡ ለነገሩ ያቃጥሉት ነበር የሚል አዳፍኔ ምስክር ይጠፋል ብላችሁ ነው፡፡

በዚህ መስመር አንድም ማስረጃ ማግኘት የተሳነው መንግስት፣ በቀጣይ በሚዲያ ተቋማት ላይ ከማስታወቂያ እና ከአንባቢ በሚገኝ ገቢ ላይ እርምጃ መውሰድን እንደ ዋነኛ የኢኮኖሚ ቁጥጥር ስርአት አድርጎ ይዞታል፡፡ አንባቢዎችም እንደምትረዱት የመንግስትና የግል ድርጅቶች ማስታወቂያ እንዳያወጡ ከፍተኛ ጫና በመዳረጉ አሁን ጥርስ የተነከሰባቸው መፅሔቶች ማስታወቂያ ሳያወጡ በመፅሃፍ መግዣ ዋጋ መፅሔት ለመሸጥ በመገደዳቸው መንግስት ወደ ሌላ እርምጃ ተሸጋግሯል፡፡ ሌላኛው እርምጃ ከሰሞኑ የተሰማው ክስ ነው፡፡ በነገራችን ላይ ይህ ነውረኛ የፖለቲካ ሰነድ ጥርስ የተነከሰባቸውን የግል ሚዲያዎች የሚገልፃቸው ነውረኛ በሆነ አገላለፅ ነው፡፡ በኢህአዴግ ሰፈር መገበርም አያስከብርም፡፡ እነዚህ የግል ሚዲያዎች አብዮታዊ ዲሞክራሲን ባይቀበሉም የመንግሰትን ስትራቴጂ የተቀበሉ ኪራይ ስብሳቢዎች በማለት ይገልፃቸዋል፡፡ ለእነርሱም “በሕጉ መሰረት የሚሰሩ ጥገኞችን በተመለከተ ግን ለስራቸው የተመቻቸ ሁኔታ የመፍጠር አሰራር ልንከተል ይገባናል” በማለት ይሰድባቸዋል፡፡ በቅርቡ ለነዚህ ጥገኞች ምን ተጨማሪ ነገር እንደሚደረግላቸው የምናየው ይሆናል፡፡ እንደምታስታውሱት ለጥገኛ የፖለቲካ ፓርቲዎች ድጎማ ሲሰጣቸው፣ የሌሎቹ ፓርቲ አባላት ደግሞ በእስር ላይ ይገኛሉ፡፡

በኢህአዴግ አብዮታዊ ዲሞክራሲ መስመር ያልገባ ሁሉ ህገወጥ እና ጤና የሌለው ተደርጎ ይቆጠራል፡፡ በዲሞክራሲ፣ ሰላም እና ነፃነት ላይ የቆመ ደንቃራም አድርገው ይቦድኑታል፡፡ ህዝቡ ኢህአዴግ የሚያወራውን ይህን ሽብርና መዓት ወደ ጎን በማለት ኪራይ ሰብሳቢ ለሚላቸው የግል ሚዲያዎች መተማመኛው የፈለገውን ያህል ውድ ቢሆኑ፣ ተሻምቶ በመግዛት የአለንላችሁ መተማመኛ መስጠቱ አልተዋጠላቸውም፡፡ ሹሞቻችን ይህን የህዝብ መተማመኛ ተቀብለው ለመሄድ ፈቃዳቸው አይደለም፡፡ ይልቁንም ከህዝብ ውጭ አለቃ የለንም እያሉ በየመድረኩ የሚገዘቱ ሹማምንት፤ ህዝብን በሚንቅ መልኩ፤ ‹በህዝብ ጥያቄ መሰረት በግል ሚዲያዎች ላይ እርምጃ ወስደናል› ይሉናል፡፡ ህዝቡ እርምጃው ለምን ተወሰደ ሳይሆን የሚለው ለምን ዘገየ እያለ ነው፡፡ ህዝቡ፣ ህዝቡ፣ ህዝቡ እያሉ በመንግሰት ሚዲያ ላይ ቀርበው ይዘባበታሉ፡፡

ለማንኛውም ከላይ እንደተረዳነው የኢህአዴግ የፖለቲካ ሰነድ የሚያስቀምጠው “ዋነኛው መቆጣጠሪያ መንገዱ ኢኮኖሚያዊ ስለሆነ … ልዩ ትኩረት ሰጥተን ልንረባረብበት ይገባል፡፡ ከዚህ ጎን ለጎን በህገወጥ ሚዲያዎች ላይ አስተዳደራዊ እርምጃ እንዲወሰድባቸው የሚደረገው ሂደት በአስተዳደራዊ ገፅታው ብቻ ሳይሆን በፖለቲካው ገፅታው መታየት አለበት፡፡” በማለት ነው፡፡ ስለዚህ ሰሞኑን እየተወሰደ ያለው እርምጃ በምንም መመዘኛ የግል ሚዲያዎቹ በሀገርና በህዝብ ላይ ሽብር በመፍጠራቸው ሳይሆን በአብዮታዊ ዴሞክራሲ አስተሳሰብ ላይ በፈጠሩት ሽብር መነሻ ብቻ ነው፡፡ እርምጃውም ፖለቲካዊ በመሆኑ፣ ከቀጣዩ ምርጫ ጋር ተያይዞ በመጣ ፍርሃት የተነሳ ነው፡፡ ስለዚህ የግል ሚዲያዎች ለአብዮታዊ ዲሞክራሲ አንገብርም በማለታቸው “ህገወጥ” በሚል ሽፋን አስተዳደራዊ እርምጃ ለመውሰድ ክስ ተመስርቶባቸዋል፡፡ ከላይ ለመጥቀስ እንደሞከርኩትም፣ ይህ አቅጣጫ የተቀመጠው በመጋቢት 1999ዓ.ም ከምርጫ 1997 ሽንፈት ማግስት ነው፡፡

ይህ ጉደኛ ሰነድ “አስተዳደራዊ እርምጃ ተገቢ መሆኑን ህዝቡና ከዚያም አልፎ ብዙሃኑ የሚዲያው ተዋንያን የሚቀበሉበት ሁኔታ መፍጠር አለብን፡፡” ይላል፡፡ ለዚህ ነው እንግዲህ፣ መንግስት ወገቡን ታጥቆ እርምጃው ተገቢ ነው እያለ የሚሰብክን፡፡ ይህን ድራማ ለመስራት የሚጋበዙትም ሰዎች ይህን መረዳት ያለመቻላቸው አስገራሚ ነው፡፡ ሰነዱ በመጨረሻም “ለውጭው አለም በዚህ ረገድ የምንወስዳቸውን እርምጃዎች ተገቢነት ለማስረዳት ጥረት ማድረግ ያለብን ቢሆንም ጋዜጠኞች በምንም አይነት ምክንያት መታሰራቸውን የማይቀበሉ ሃይሎች በርካታ በመሆናቸው እነዚህን ለማሳመን ከመንገዳችን ወጥተን መሄድ የሚጠይቀን መኖር የለበትም፡፡” ብሎ ያጠናቅቃል፡፡ አንድም ጋዜጠኛ፣ ጋዜጠኛ በመሆኑ አይታሰርም በሚል ድርቅ ብለው የሚከራከሩን ሹሞቻችን ጋዜጠኞችን ለምን እንደሚያስሩ ግን በሰነዳቸው ላይ በፅሁፍ አስቀምጠዋል፡፡ ጋዜጠኞች የሚታሰሩት በጋዜጠኝነታቸው ብቻ ሳይሆን እንደ ሰው በያዙት አመለካከትም ጭምር ነው፡፡ ጥገኛ ለመሆን ባለመፍቀዳቸው እና ለነፃነታቸው በመቆማቸው ነው፡፡
እንግዲህ አስተዳደራዊውን እርምጃ ተከትሎ የሚመጣው  እስር መሆኑን ልብ ማለት አለብን፡፡ የዚያን ጊዜ ደግሞ ኢህአዴግ ከመስመር መውጣት ሳያስፈልገው “ጋዜጠኛ አላሰርንም፣ ጋዜጠኛ መሆን ወንጀል ለመስራት ሰርተፊኬት አይደለም” እያለ በመስመሩ ላይ ሆኖ ያላግጣል፡፡ ለማነኛውም በፖለቲካም ሆነ በጋዜጠኝነት ተሳትፎ የሚያደርጉ ሁሉ፣ የሚሳተፉት ይህ ጠፍቷቸው ሳይሆን ነፃነታቸው ከዚህ በላይ መሆኑን የሚረዱ በመሆናቸው ነው፡፡ ለነፃነት ሲባል ከእስርም በላይ ሞትን ለመቀበል የቆረጠን ሰው ማቆም እንደማይቻል መረዳት ግን ተገቢ እና አስፈላጊ ነው፡፡ይህን ፅሁፍ ለምታነቡ የኢህአዴግ አባላት አንድ ጥያቄ አለኝ፤ “ከጥገኝነት እና ከነፃነት” የቱ ይሻላል?

Saturday, August 16, 2014

ከግብረሰዶማውያኑ ጀርባ (አርአያ ተስፋማሪያም)

August16/2014

ከጥቂት አመት በፊት በኢትዮጵያ በተለይ አዲስ አበባ የሚገኙ ግብረሰዶማውያን ያቀረቡትን ጥያቄ ተከትሎ በሸራተን ሆቴል የሃይማኖት አባቶች ጋዜጣዊ መግለጫ ለመስጠት በስፍራው ተገኝተዋል። ፕሮግራሙ ሊጀመር 15 ደቂቃ ሲቀረው በድንገት የደህንነት ሰዎች ይገቡና ጋዜጠኞች እንዲወጡ ያደርጋሉ። ቀጥሎ ለሃይማኖት መሪዎቹ « ይህን መግለጫ መስጠት አትችሉም» ተባሉ። « ማነው ከልካዩ?..» ሲሉ ጠየቁ፤ ጭራሽ ማስጠንቀቂያ ተሰጣቸው። የተቃውሞ መግለጫው በዚህ መልኩ ተደናቀፈ። በመቀጠል ሰላማዊ ሰልፍ ለማድረግ ተጠየቀ። የሸራተኑን መግለጫ ያደናቀፈው ባለስልጣን ጣልቃ ገብቶ ሰልፉን አስከለከለ። ይህን ሁሉ ያደረጉት የወቅቱ የጤና ጥበቃ ሚ/ር ዶ/ር ቴዎድሮስ አድሃኖም መሆናቸውን የቅርብ ምንጮች ያረጋግጣሉ። በቅርቡ አሜሪካ መጥተው የነበሩት ዶ/ር ቴዎድሮስ በአፍሪካ ከጤና ጋር በተያያዘ አንድ ተቋም በሃላፊነት እንዲመሩ ተፈልገዋል። ከያዙት ስልጣን ፓርቲያቸው እንዲለቃቸውና አሜሪካኖቹ ወደሚፈለጉት ቦታ ዶክተሩን ለመውሰድ እቅድ መኖሩን አንዲት ከፍተኛ ሃላፊን በመጥቀስ ምንጮች ገልፀዋል።
ዶ/ር ቴዎድሮስ ስለዚህ ጉዳይ ይነጋገሩ አይነጋገሩ የታወቀ ነገር የለም። ዶክተሩ የተመረጡት « በኢትዮጵያ የጤና ጥበቃ ሚ/ር ሆነው ብዙ ነገር ሰርተዋል፤ ለምሳሌ ኤ.ች.አይ.ቪ/ ኤድስ፣ የወሊድ ቁጥጥር፣ የጤና ተቋማት ግንባታ..» ወዘተ በሚል ይጠቅሳሉ። ነገሩ ወዲህ ነው..የሚሉ ወገኖች ባለስልጣኑ የተፈለጉት « ለግብረሰዶማውያን መብት ዘብ በመቆም አሜሪካ በዚህ ዙሪያ ለምታራምደው አቋም ዶ/ር ቴዎድሮስ በተደጋጋሚ አጋርነታቸውን በማሳየታቸውና በተጨማሪ ስለግብረሰዶማውያን መብት ደግፈው ስለሚፅፉ ነው» ይላሉ። የሚያሳዝነው ዶ/ር ቴዎድሮስ « የማሰር ሱስ የለብንም..» ከማለት አልፈው የታሰሩትን ሙስሊሞች ከጓንታናሞ ጋር ለማያያዝ መሞከራቸውና ቀጥሎ ለማስተባበል መሯሯጣቸው ነው። እውነት ለመብት የቆሙ ቢሆን ኖሮ ከአምላክ ድንጋጌና ተፈጥሮ ላፈነገጡ ሳይሆን ካለሃጢያታቸው በእስር እየተሰቃዩ ለሚገኙ ወገኖች መሆን ነበረበት።