Friday, July 18, 2014

የዘንድሮ እስር ‹‹ጸበል ቅመሱ›› ሁነብኝ ጃል! (ጋዜጠኛ ኤልያስ ገብሩ)

July18/2014

(የህገ-መንግሥቱ አንቀጽ 30 ሳይሻር ተሽሮ ከሆነ መሻሩን ተቃዋሚዎች ይወቁት!)
========
የምንወዳት ኢትዮጵያ ሀገራችን በተለያዩ ሥርዓታት ውስጥ የተለያዩ የሰዎችን እስር አስተናግዳለች፤ ዛሬም እያስተናገደች ትገኛለች፡፡
በ97 ዓ.ም ምርጫውን ተከትሎ የቅንጅት አመራሮች፣ የግል ጋዜጠኞችና የሲቪክ ማኅበራት አመራሮች …ታስረው ከአንድ ዓመት ከዘጠኝ ወራት በኋላ በይቅርታ፣ በነጻ …መፈታቸው ይታወሳል፡፡ ከዚህ ጊዜም በኋላ፣ በተለይ አፋኝ በሆነው የጸረ-ሽብርተኝነት አዋጁ ብዙዎች ታስረዋል፣ እየታሰሩም ይገኛሉ፡፡
ጋዜጠኛ ኤልያስ ገብሩ ጎዳና
ጋዜጠኛ ኤልያስ ገብሩ ጎዳና
በዘንድሮ ዓመት ግን የምናየው እስር የተለየ ሆነብኝ፡፡ የሕገ- መንግሥቱን አንቀ ጽ 30 መሰረት በማድረግ ሰላማዊ ሰልፍ የሚጠሩ የተቃዋሚ ፓርቲ አመራሮች እና አባላቶቻቸው ለሰልፉ ቅስቀሳ በሚያደርጉበት ወቅት እየተያዙ ለቀናቶች ታስረው መፈታት የተለመደ ሆነ፡፡ (ወይ ይህ የሕገ-መንግሥቱ አንቀጽ 30 ሳይሻር ተሽሮ ከሆነ መሻሩን ተቃዋሚዎች ይወቁት!)
አንድነት እና ሰማያዊ ፓርቲዎች ይሄንን እርምጃ ዘንድሮ በደንብ አይተውታል ብል ማጋነን አይሆንብኝም፡፡ ይሄም ብቻ አይደለም፣ ጋዜጠኞች፣ ጦማሪያኖች፣ ፖለቲከኞችና በርካታ ዜጎች በሽብር ወንጀል ተጠርጥረው ታስረዋል፣ ክስም ተመስርቶባቸዋል፡፡
በዛሬው ዕለት ደግሞ የምርጫ ሥነ-ምግባር ደንቡን በመፈረም የፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት አባል የሆነው ኢትዮጵያ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (ኢዴፓ) የፊታችን ቅዳሜ ሜክሲኮ በሚገው የመብራት ሐይል አዳራሽ ህዝባዊ ስብሰባ ለማድረግ አቅዶ ስድስት አባላቱ ዛሬ ቂርቆስ አካባቢ በመኪና ህዝቡን በመቀስቀስ ላይ እያሉ መታሰራቸውን ሰማን፡፡
ፖሊስም ‹‹የስብሰባ እንጂ የቅስቀሳ ፈቃድ አልያዛችሁም›› በማለት ጥዋት አካባቢ በፖሊስ ጣቢያ ውስጥ እንዳሰራቸው እና የፓርቲው አመራሮች በፖሊስ ጣቢያ ድረስ በመገኘት ከኃላፊዎቹ ጋር ቢነጋገሩም ልጆቹ ቃላቸውን መስጠታቸውንና ፖሊስ ልቀቃቸው የሚል ትዕዛዝ ሲደርሰው እለቃቸዋለሁ ማለቱን ወዳቻችን ዳዊት ሰለሞን በፌስ ቡክ ገጹ ዛሬ አስነብቦን ነበር፡፡
እኔም እንደጋዜጠኛ ጉዳዩን ለማጣራት የቀድሞ የኢዴፓ ሊቀመንበር ወደሆኑት አቶ ሙሴ ሰሙ ተንቀሳቃሽ ስልክ ላይ ደውዬ እውነት መሆኑን አረጋግጫለሁ፡፡ እንዲያውም፣ አቶ ሙሼ የተደረገው ነገር አግባብ አለመሆኑን በመጥቀስ በነገው ዕለት በግል መኪናቸው ቅስቀሳ ለማድረግ ማቀዳቸውን አጽንኦት ሰጥተው ነግረውኛል፡፡
እንዲሁም፣ በዛሬው ዕለት በእነሀብታሙ አያሌው የክስ መዝገብ አንድነት ፓርቲ ላቀረበው አቤቱታ የፍርድ ቤቱን ውሳኔ በአራዳ ፍርድ ቤት ለማድመጥ በችሎት ተገኝተው የነበሩ ስድስት የአንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ አባላት (ዳንኤል ፈይሳ፣ አብነት ረጋሳ፣ ጥላዬ ታረቀኝ፣ ፋሲካ አዱኛ፣ ብርሀኑ ይግለጡና መሰለ አድማሴ) በደህነት ሃይሎች ተይዘው በቶዮታ ደብል ጋቢና ኮድ 3-50559 መኪና ወደ ማዕከላዊ መወሰዳቸውን የፍኖተ ነፃነት የማዕከላዊ ምንጮች ገልጸው ነበር፡፡ ከሰዓታት በኋላም የታሰሩት የፓርቲው አባላት ተፈትዋል፡፡
እስያዊቷ ሀገር ማሌዥያ፣ የመንገደኛ አውሮፕሏኖቿ አንዴ ሲሰወሩ፣ አንዴ ሲከሰከሱና በሮኬት ሚሳይል ሲመቱ ዛሬም ድረስ ደርሰዋል፡፡ በዛሬው ዕለት እንኳን ከሆላንድ አመስተርዳም ወደ ማሌዥያ ኩዋላላምፑር ሲጓዝ የነበረ ቦይንግ 777 የመንገደኞች አውሮፕላን በሮኬት ሚሳይል ተመትቶ (በራሽያ መሆኑ እየተነገረ ነው) በዩክሬን ግዛት በመከስከስ 295 ሰዎች አልቀዋል፡፡ 
በሀገራችን ደግሞ ሁሉን ዓቀፍ የእስር እርምጃ በመንግሥታችን እየተወሰደ መመልከቱ ቀጥሏል፡፡ ለዚህም ነው፣ በርዕሴ ‹‹የዘንድሮ እስር ‹‹ጸበል ቅመሱ›› ሁነብኝ ጃል!›› በማለት የገለጽኩት፡፡
ወዳጄ ዳዊት ሰለሞንም “Ethiopia the land of prisoners” (ኢትዮጵያ የእስረኞች ምድር) የሚል መልዕክት ከአምስት ሰዓታቶች በፊት በፌስ ቡክ ገጹ አስፍሮ ተመልክቻለሁ፡፡ ማሌዥያ በአውሮፕላን አሳዛኝ አደጋ ጣጣ በዓለም ስትታወቅ እኛ ደግሞ ዜጎችን በገፍ መማሰር እንታወቅ?!
እኔ ደጋግሜ ብያለሁ፣ እስር መፍትሄ አይደለም፡፡ ዜጎችን ማሰር ብዙ የማይገርምበት ጊዜ ላይ ደርሰናል፡፡ መንግስታችን ሆይ! ዜጎችን የማሰር ጉዞውን በአንክሮ አስብበት! አሊያ… ከባድ ነው! መዘዝ አለው፡፡
ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር! —

በወቅታዊ የአገራችን ጉዳይ… ማን ምን አለ?

July18/2014
ኢ.ኤም.ኤፍ) ሰሞኑን ከታሰሩት ጋዜጠኞች እስከ አንዳርጋቸው ጽጌ እና የሙስሊም ኮሚቴዎች ድረስ ሰዎች የየራሳቸውን ሃሳብ እና አስተያየት ይሰጣሉ። እነዚህ ሃሳብ እና አስተያየቶች ሚዛን የሚደፉ ሆነው ስላገኘናቸው፤ ለናንተም ለታሪክም ለህትመት ማብቃቱ መልካም ነው ብለን አሰብን። በመሆኑም የጋዜጠኛ ኤልያስ ገብሩ፣ አበበ ገላው አቡ ዳውድ ኡስማን እና ዮናታን ተስፋዬ ያሉትን አቅርበንላችኋል። ከዚህ ቀጥሎ ይነበባል።
ኤልያስ ገብሩ ስለሃብታሙ አያሌው የተናገረው….
ዛሬ በእስር ላይ የሚገኘውን የአንድነት ለፍትህና ለዴሞክራሲ ፓርቲ የሕዝብ ግንኘነት ኃላፊ የሆነውን ሀብታሙ አያሌውን በሥራ አጋጣሚ ቅርበት አውቀዋለሁ፡፡
በእሱ ላይ የነበረኝን ጥያቄ አቅርቤለትም ደስ ብሎት፣ በዝርዝር መልሶልኝ አስረድቶኛል፡፡ጥቂት የማይባሉ ሰዎች ‹‹ሀብታሙ ትናንት እንዲህ ነበር፣ እንዲያነው …ወዘተ›› እያሉ ሚዛን የማይደፉ ንግግሮችን ሲናገሩ በእርጋታ አድምጫቸው አውቃለሁ፡፡ ሰዎች ይህንን መሰል ሃሳብ የማንሸራሸር መብት አላቸው ብዬ አምናለሁ፡፡
እኔ ግን፣ ሀብታሙን ሳውቀው ንቁ፣ ብዙ ሃሳቦች ያሉት፣ ስለሀገሩ ያገባኛል የሚል፣ ደፋር ሆኖ ያመነበትን በድፍረት የሚናገር፣ እንደ ንቁ ፖለቲከኛ ለጋዜጠኞች መረጃን በዝርዝር የሚሰጥ፣ ኃይማኖተኛ፣ ፈገግታ የማይለየው፣ ጎበዝ የአደባባይ ፖለቲከኛ የሆነ ኢትዮጵያዊ ነው፡፡
ለሚነሳለት ሃሳብ ወይም ትችት ሃሳብን በሃሳብ የሚመልስ ልጅነው – ሀብታሙ፡፡
(አንዳንዶች የቀረበላቸውን ሀሳብ ወይም ትችት ፊት ለፊት መመለስ ወይም መሞገት ሲያቅታቸው ወደስድብ እና ዘለፋ ወይም ወዳልታሰበ ሀሳብ ሲነጉዱ እያየሁ ፈገግ እላለሁ፣ እስቃለሁ፣ ከምር ያስቁኛል)
ሃብታሙን ግን ሃሳብን በሃሳብ ከሚመልሱ ውስን የኢትዮጵያ ልጆች መካከል አንዱ ሆኖ አገኘሁትና ደስም አለኝ፡፡ ጠንካራ እና ጀግና ልብስላለውም ወደድኩት!
———————————————–
አበበ ገላው ስለወቅታዊ ሁኔታ የተናገረው…
በአሁኑ ግዜ መታሰር የሚያስፈራበት ግዜ አልፏል። ኢትዮጵያ ውስጥ ብዙ ሰው እኛንም እሰሩን እያለ ነው። ሽብረተኛ ተብሎ መከሰስ የሚያስከብር እንጂ የሚያሸማቅቅ መሆኑ ቀርቷል።
የተቃዋሚ ፓርቲዎች በጋራ በሺዎች የሚቆጠሩ አባላቶቻቸውን ሰብስበው እኛም አሸባሪዎች ነን እሰሩን ብለው አደባባይ በየግዜው በተከታታይ እንዲወጡ ቢያደርጉ ብዙ ሰው ፍርሃቱ የበለጠ ይለቀዋል። ለሚታሰሩ ሰዎች እና ለቤተሰቦቻቸው ድጋፍ የሚያደርጉ ስብስቦች በየአካባቢው ሊቋቋሙ ይገባል። አንዱ ሲታሰር ያልታሰረው ድጋፍ ያድርግ። እስኪሚሊዮኖችን ሲያስሩ እናያቸዋለን።
እነርሱ በፍርሃት ሰውን ሁሉ አሸባሪ እያሉ የሚኖርበት ግዜ በጋራ ትግል ማክተም ይገባዋል።
——————————————–
‪አቡ ዳውድ ኡስማን የሙስሊም ኮሚቴዎችን የፍርድ ሂደት አስመልክቶ ያስተላለፈው መልእክት
የኮሚቴዎቻችን እና  የወንድሞቻችን የመከላከያ ምስክር ለፍርድ ቤቱ የማስደመጡ ሂደት በነገው ዕለት ሃምሌ 10 በከፍተኛው ፍርድ ቤት ቦሌ ምድብ ችሎት እንደሚካሄድ ለማወቅ ተችሏል፡፡
ከዚህ ቀደም ሲካሄድበት ከነበረው ከቃሊቲ 08 አዳራሽ ለውጥ ተደርጎ ከሲ ኤም ሲ አደባባይ ወደ ቀኝ 200 ሜትር ገባ ብሎ ባጃጆች ካሉበት ወደ ቀኝ ታጥፎ ዲቦራ ት/ቤት አካባቢ በሚገኘው በከፍተኛ ፍርድ ቤት ቦሌ ምድብ ችሎት እንደሚካሄድ ምንጮች አስታውቀዋል፡፡ ይህ ችሎት አዲስ የተገነባ እና ሰፊ የችሎት አዳራሽ እንዳለው ተዘግቧል፡፡
ህዝበ ሙስሊሙም የተለመደውን አጋርነቱን በችሎቱ በመገኘት ለኮሚቴዎቻችን እና ለወንድሞቻችን ሊገለፅ ይገባል፡፡
ፍትህ ለኮሚቴዎቻችን እና ለመላው ሙስሊም ይሁን!!
አላህ ይፈርጃቸው!!
———————————-
ዮናታን ተስፋዬ ስለፍርድ ቤቶች እና የፍርድ ሂደቱ የተናገረው
ፍርድ ቤት ምንም ፍትህ እንደማይገኝ እያወቅነው ለምን ራሳችንን እንደምናታልል አይገባኝም፡፡ ለምን በፍርድ ቤቱና በፍርድ ሂደቱ ተስፋ እንደምናደርግ ልረዳውአልቻልኩም፡፡ ሁሉ ነገር ታፍኖ ሀግ የማያከብር አምባገነን እንኳን ፍርድ ቤት ቀርበው ገና ሳይታሰሩ ውሳኔ አሳልፎ አይናችን ላይ ድራማ እየሰራ እኛ አሁንም ፍርድ ቤት ላይ አይናችን አልተነቀለም፡፡
ለታገቱት ታጋዮች አጋርነትን ማሳየታችን እንደተጠበቀ ሆኖ ፍርድ ቤቱን ትተን ሁላችንም ተራችን ደርሶ እክንታፈን መታገል አለብን፡፡
መታሰር ተራ ነገር እንደሆነ እስካሁን የሄድንበት መንገድ አመላካች ነው፡፡ ስለዚህ በፍርድ ቤት ውሎ ወሬ ጉጉት ከሚገድለን ሀሳባችንና ጉልበታችንን ከምናባክን ለወያኔም ከምንመቸው ትግሉን ማፋፋም ይሻለናል፡፡ ያኔ ሁላችንም ታስረን ሁላችንም ነፃእንወጣለን፡፡ እስከዚያው ጪአማራጭ የለም፡፡ ማንም ለኛ የሚቆምልን የለም እያንዳንዳችን ስለእውነት በፅናት መቆም አለብን፡፡
ራሳችንን ነፃ እናውጣ!

Thursday, July 17, 2014

ሰበር ዜና:- ጦማሪያኑና ጋዜጠኞቹ ላይ ሽብርተኛ ተብለው ክስ ተመሠረተባቸው

July 17/2014
 
በሽብርተኝነት ወንጀል ተጠርጥረው በቁጥጥር ሥር ውለው የነበሩት ጦማሪያን፣ ሶልያና ሽመልስ (በሌለችበት)፣ በፍቃዱ ኃይሉ፣ ናትናኤል ፈለቀ፣ ማህሌት ፋንታሁን፣ አጥናፉብርሃኔ፣ ዘለዓለም ክብረት፣ አቤል ዋበላ፣ እንዲሁም ጋዜጠኞቹ አስማማው ኃይለ ጊዮርጊስ፣ ኤዶም ካሣዬና ተስፋለም ወልደየስ ላይ ሐምሌ 10 ቀን 2006 ዓ.ም. ክስ ተመሠረተ፡፡

ተጠርጣሪዎቹ የሽብርተኝነት ወንጀል በሚሰጠው ውጤት ሙሉ ተሳታፊ በመሆን ለአመፅ ተግባር በህቡዕ መደራጀታቸውን፣ የፌዴራል ዓቃቤ ሕግ ለፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት 19ኛ ወንጀል ችሎት ያቀረበው የክስ ቻርጅ ይገልጻል፡፡

እንደ ዓቃቤ ሕግ ክስ ተጠርጣሪዎቹ በህቡዕ በመደራጀት፣ የአጭርና የቅርብ ጊዜ ግብ በማቀድና በመንደፍ ከግንቦት 2004 ዓ.ም. ጀምሮ እጃቸው እስከተያዘበት ጊዜ ድረስ በፓርላማ ሽብርተኛ ተብለው ከተሰየሙት የግንቦት 7 እና የኦነግ ድርጅቶች መመርያና ሐሳብ ሲቀበሉ መቆየታቸው ተገልጿል፡፡

ከተጠርጣሪዎቹ አንዷ የሆነችው ሶሊያና ሽመልስ የቡድኑ መሥራችና አስተባባሪ በመሆን ከ2004 እስከ 2006 ዓ.ም. መቆየቷና ከ2006 ዓ.ም. ጀምሮ በውጭ አገር አስተባባሪና የውጭ ግንኙነት ሆና ከመሥራቷም በተጨማሪ፣ ከግንቦት 7 ጋር ግንኙነት ለመፍጠር ተልዕኮ በመቀበል፣ አባላትን በማደራጀትና በመመልመል ስትሠራ መቆየቷን ክሱ ያስረዳል፡፡

የህቡዕ ቡድኑ ከ2004 እስከ 2006 ዓ.ም. ‹‹ሴኩሪቲ ኢን ቦክስ›› የተባለ ሥልጠና እንዲሠለጥንና እንዲደራጅ ስትመራ መቆየቷም በክሱ ተካቷል፡፡

ሌላኛው ተጠርጣሪ በፍቃዱ ኃይሉ የአገር ውስጥ የሽብር ቡድንን በመምራትና የሥራ ክፍፍል በማድረግ፣ እንዲሁም ግብ በማስቀመጥና ስትራቴጂ በመንደፍ ከሽብርተኛ ኃይሎች ጋር ግንኙነት ሲፈጥር መቆየቱ በክሱ ተጠቅሷል፡፡

የዓቃቤ ሕግ ክስ እንደሚያስረዳው ከሆነ ተጠርጣሪ ናትናኤል ፈለቀ ከ2004 ዓ.ም. ጀምሮ ካልተያዙ ግብረ አበሮቹ ጋር በመሆን የህቡዕ ድርጅቱ የአገር ውስጥ አስተባባሪ በመሆን በሥሩ ላሉት አባላት የሥራ ክፍፍል መመርያ በመስጠት፣ ከግንቦት 7 ጋር ግንኙነት በመፍጠር መመርያ ከመቀበሉ በተጨማሪ፣ ለአመፅ ተግባር የሚውል የተላከለትን 48,000 ብር ማከፋፈሉንም ክሱ ያብራራል፡፡

ሌሎቹ ተጠርጣሪዎች በህቡዕ ድርጅቱ ውስጥ ከ2004 ዓ.ም. ጀምሮ መሥራችና አባል በመሆን የግንቦት 7 እና የኦነግን ስትራቴጂና ዕቅድ በመቀበል በውጭና በአገር ውስጥ ባሉ የቡድኑ አባላት ጋር ግንኙነት በመፍጠር፣ በውጭና በአገር ውስጥ ሥልጠና በመውሰድ፣ በዋና ወንጀል አድራጊነት ተካፋይ በመሆን የሽብርተኝነት ድርጊት ለመፈጸም በማቀድ፣ በመዘጋጀት፣ በማሰርና በማነሳሳት ወንጀል መከሰሳቸውን ዓቃቤ ሕግ ያቀረበው ክስ ያስረዳል፡፡

በሁሉም ተጠርጣሪዎች ላይ ዓቃቤ ሕግ ያቀረበው ሁለተኛ ክስ እንደሚያስረዳው ተጠርጣሪዎቹ በወንጀሉና በሚያስገኘው ውጤት ተስማምተው በሕገ መንግሥት ሥርዓት የተቋቋመን መንግሥት በአመፅ፣ በሁከትና በብጥብጥ ለመለወጥ በማሰብ ከግንቦት 2004 ዓ.ም. እስከተያዙበት ዕለት ድረስ በህቡዕ ተደራጅተው፣ የሥራ ክፍፍል በመፍጠር፣ ሥልጠናዎችን በመውሰድ፣ አመፅ የሚቀሰቅሱ ጽሑፎችን በመበተን፣ የአመፅ ቡድኖችን በማደራጀት ሕገ መንግሥቱና ሕገ መንግሥታዊ ሥርዓቱን በአመፅና በሁከት ለመለወጥ በመሞከር ወንጀል መከሰሳቸውን የዓቃቤ ሕግ ክስ ያስረዳል፡፡  

ሰበር ዜና:- ጦማሪያኑና ጋዜጠኞቹ ላይ ሽብርተኛ ተብለው ክስ ተመሠረተባቸው

July 17/2014

በሽብርተኝነት ወንጀል ተጠርጥረው በቁጥጥር ሥር ውለው የነበሩት ጦማሪያን፣ ሶልያና ሽመልስ (በሌለችበት)፣ በፍቃዱ ኃይሉ፣ ናትናኤል ፈለቀ፣ ማህሌት ፋንታሁን፣ አጥናፉ

ብርሃኔ፣ ዘለዓለም ክብረት፣ አቤል ዋበላ፣ እንዲሁም ጋዜጠኞቹ አስማማው ኃይለ ጊዮርጊስ፣ ኤዶም ካሣዬና ተስፋለም ወልደየስ ላይ ሐምሌ 10 ቀን 2006 ዓ.ም. ክስ ተመሠረተ፡፡

ተጠርጣሪዎቹ የሽብርተኝነት ወንጀል በሚሰጠው ውጤት ሙሉ ተሳታፊ በመሆን ለአመፅ ተግባር በህቡዕ መደራጀታቸውን፣ የፌዴራል ዓቃቤ ሕግ ለፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት 19ኛ ወንጀል ችሎት ያቀረበው የክስ ቻርጅ ይገልጻል፡፡

እንደ ዓቃቤ ሕግ ክስ ተጠርጣሪዎቹ በህቡዕ በመደራጀት፣ የአጭርና የቅርብ ጊዜ ግብ በማቀድና በመንደፍ ከግንቦት 2004 ዓ.ም. ጀምሮ እጃቸው እስከተያዘበት ጊዜ ድረስ በፓርላማ ሽብርተኛ ተብለው ከተሰየሙት የግንቦት 7 እና የኦነግ ድርጅቶች መመርያና ሐሳብ ሲቀበሉ መቆየታቸው ተገልጿል፡፡

ከተጠርጣሪዎቹ አንዷ የሆነችው ሶሊያና ሽመልስ የቡድኑ መሥራችና አስተባባሪ በመሆን ከ2004 እስከ 2006 ዓ.ም. መቆየቷና ከ2006 ዓ.ም. ጀምሮ በውጭ አገር አስተባባሪና የውጭ ግንኙነት ሆና ከመሥራቷም በተጨማሪ፣ ከግንቦት 7 ጋር ግንኙነት ለመፍጠር ተልዕኮ በመቀበል፣ አባላትን በማደራጀትና በመመልመል ስትሠራ መቆየቷን ክሱ ያስረዳል፡፡

የህቡዕ ቡድኑ ከ2004 እስከ 2006 ዓ.ም. ‹‹ሴኩሪቲ ኢን ቦክስ›› የተባለ ሥልጠና እንዲሠለጥንና እንዲደራጅ ስትመራ መቆየቷም በክሱ ተካቷል፡፡

ሌላኛው ተጠርጣሪ በፍቃዱ ኃይሉ የአገር ውስጥ የሽብር ቡድንን በመምራትና የሥራ ክፍፍል በማድረግ፣ እንዲሁም ግብ በማስቀመጥና ስትራቴጂ በመንደፍ ከሽብርተኛ ኃይሎች ጋር ግንኙነት ሲፈጥር መቆየቱ በክሱ ተጠቅሷል፡፡

የዓቃቤ ሕግ ክስ እንደሚያስረዳው ከሆነ ተጠርጣሪ ናትናኤል ፈለቀ ከ2004 ዓ.ም. ጀምሮ ካልተያዙ ግብረ አበሮቹ ጋር በመሆን የህቡዕ ድርጅቱ የአገር ውስጥ አስተባባሪ በመሆን በሥሩ ላሉት አባላት የሥራ ክፍፍል መመርያ በመስጠት፣ ከግንቦት 7 ጋር ግንኙነት በመፍጠር መመርያ ከመቀበሉ በተጨማሪ፣ ለአመፅ ተግባር የሚውል የተላከለትን 48,000 ብር ማከፋፈሉንም ክሱ ያብራራል፡፡

ሌሎቹ ተጠርጣሪዎች በህቡዕ ድርጅቱ ውስጥ ከ2004 ዓ.ም. ጀምሮ መሥራችና አባል በመሆን የግንቦት 7 እና የኦነግን ስትራቴጂና ዕቅድ በመቀበል በውጭና በአገር ውስጥ ባሉ የቡድኑ አባላት ጋር ግንኙነት በመፍጠር፣ በውጭና በአገር ውስጥ ሥልጠና በመውሰድ፣ በዋና ወንጀል አድራጊነት ተካፋይ በመሆን የሽብርተኝነት ድርጊት ለመፈጸም በማቀድ፣ በመዘጋጀት፣ በማሰርና በማነሳሳት ወንጀል መከሰሳቸውን ዓቃቤ ሕግ ያቀረበው ክስ ያስረዳል፡፡

በሁሉም ተጠርጣሪዎች ላይ ዓቃቤ ሕግ ያቀረበው ሁለተኛ ክስ እንደሚያስረዳው ተጠርጣሪዎቹ በወንጀሉና በሚያስገኘው ውጤት ተስማምተው በሕገ መንግሥት ሥርዓት የተቋቋመን መንግሥት በአመፅ፣ በሁከትና በብጥብጥ ለመለወጥ በማሰብ ከግንቦት 2004 ዓ.ም. እስከተያዙበት ዕለት ድረስ በህቡዕ ተደራጅተው፣ የሥራ ክፍፍል በመፍጠር፣ ሥልጠናዎችን በመውሰድ፣ አመፅ የሚቀሰቅሱ ጽሑፎችን በመበተን፣ የአመፅ ቡድኖችን በማደራጀት ሕገ መንግሥቱና ሕገ መንግሥታዊ ሥርዓቱን በአመፅና በሁከት ለመለወጥ በመሞከር ወንጀል መከሰሳቸውን የዓቃቤ ሕግ ክስ ያስረዳል፡፡    

የአቶ አንዳርጋቸው ጽጌ ታላቅ እህት በ24 ሰአታት አገር ለቀው እንዲወጡ ታዘዙ

June17/2014
ሐምሌ ፲(አስር)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ለሰአታት በቁም እስር ላይ የነበሩት የታዋቂው ፖለቲከኛና የሰብአዊ መብት ታጋይ የአቶ አንዳርጋቸው ጽጌ ታላቅ እህት ወ/ሮ ብዙአየሁ ጽጌ የወንድማቸውን ጉዳይ ለመከታተል በሚል ከ10 ቀናት በፊት ወደ ኢትዮጵያ ቢያመሩም፣ ከትናንት በስቲያ ደህንነት ጽ/ቤት  ከተጠሩ በሁዋላ አገሪቱን በአስቸኳይ ለቀው እንዲወጡ ተነግሯቸዋል።

በታዘዙበት ሰአት ለመመለስ እንደሚቸገሩ የተናገሩት ወ/ሮ ብዙአየሁ፣ የ 24 ሰአት ጊዜ የጊዜ ገደብ ከተሰጣቸው በሁዋላ ዛሬ ወደ አሜሪካ ተመልሰዋል።  ወ/ሮ ብዙአየሁ የአቶ አንዳርጋቸውን ቤተሰቦች በመወከል ጉዳዩን ለመከታተል በሚል መሄዳቸውን ከቤተሰቦች የተገኘው መረጃ ያመለክታል።

ኢህአዴግ የአቶ አንዳርጋቸው ጉዳይ የእግር እሳት እንደሆነበት የሚደርሱን መረጃዎች ያመለክታሉ። አቶ አንዳርጋቸው የህዝቡ የመነጋገሪያ አጀንዳ መሆናቸውና ከዚሁ ጋር ተያይዞ የግንቦት7 ዝናም ከምንጊዘውም በላይ በመጨመሩ የገዢውን ፓርቲ ከፍተኛ አመራሮችን እያበሳጨ ነው።

ይህ በእንዲህ እንዳለ ለአቶ አንዳርጋቸው ጽጌ ያላቸውን አክብሮት ለመግለጽ በአገር ውስጥም በውጭም የሚገኙ ኢትዮጵያውያን  አሁንም በተከታታይ ስልኮችን እየደወሉ አስተያየቶችን እየሰጡ ነው። በፐርዝ አውስትራሊያ የሚገኙ ኢትዮጵያውያንም ከእንግሊዝ ቆንስላ ጽህፈት ቤት ፊት ለፊት የተቃውሞ ሰልፍ አድርገዋል። ኢትዮጵያውያኑ ለቆንስላው ላቀረቡት ጥያቄ የፐርዝ የእንግሊዝ የቆንስላ ሃላፊ፣ አገራቸው የአቶ አንዳርጋቸውን ጉዳይ ከፍተኛ ትኩረት ሰጥታ እየተከታተለችው ነው የሚል መልስ ሰጥተዋል።

በሱዳን የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ለኢሳት በላኩት ደብዳቤ የአቶ አንዳርጋቸው መታፈን ” ወያኔ  ፍጹም አወሪነቱን ያሳየበት እና ዘላአለም የነጻነት ታጋዮችን ለማስፈራራት እና ከትግሎ ሜዳ ለማስውጣት የተጠቀመበት የትእቤት ስራ ነው። ” መሆኑን ያሳያል ካሉ በሁዋላ፣ የተወሰደው እርምጃ ህዝቡን ለትግል እንደሚያነሳሰው ገልጸዋል።

በሌላ ዜና ደግሞ በሽብርተኝነት ወንጀል ተከሰው ማእከላዊ እስር ቤት እንዲታሰሩ የተደረጉት የአንድነት ፓርቲ የህዝብ ግንኙነት ሃላፊ አቶ ሀብታሙ አያሌው፣ የድርጅቱ የድርጅት ጉዳይ ምክትል ሃላፊ አቶ ዳንኤል ሽበሺ፣ የሰማያዊ ፓርቲ ምክትል የምክር ቤት ሰብሳቤ አቶ የሽዋስ አሰፋ እንዲሁም አረና ፓርቲ የስራ አስፈጻሚና ታዋቂ ጸሃፊ መምህር አብርሃ ደስታ ፍርድ ቤት ይቀርባሉ ተብሎ ቢጠበቅም፣ፍርድ ቤት ሳይቀርቡ ቀርተዋል። አንድነት ፓርቲ የተያዙት ሰዎች በ48 ሰአታት ውስጥ ፍርድ ቤት አለመቅረባቸውን በመግለጽ ክስ መስርቶ ነበር። ይሁን እንጅ ፍርድ ቤቱ የቀረበውን ክስ ውድቅ አድርጎታል።

አገራዊ ጥሪ ለመከላከያና የፓሊስ ሠራዊት አባላት

July17/2014
ግንቦት 7፡ የፍትህ፣ የነፃነትና የዲሞክራሲ ንቅናቄ የኢትዮጵያ የመከላከያና የፓሊስ ሠራዊት አባላትን ከአለቆቻቸው ለይቶ ይመለከታል።
የመከላከያና የፓሊስ ሠራዊት ከፍተኛ ሹማምንት ከህወሓት የተቀዱ፣ ለህወሓት ሥልጣን የቆሙ፣ ዘረኞች፣ ፋሽስቶችና ሙሰኖች መሆናቸው በገሃድ የሚታወቅና በተደጋጋሚ ጥናቶችም የተረጋገጠ ጉዳይ ነው። በዘመነ ወያኔ የሠራዊት አዛዥነት ሹመት መሥፈርቶች ዘር፣ የፓለቲካ አመለካከትና ለህወሓት ያላቸው ታማኝነት ነው። በዚህም ምክንያት ሁሉም ቁልፍ የአዛዥነት ቦታዎች የተያዙት ሙሉ በሙሉ የህወሓት አባላት በሆኑ የትግራይ ተወላጆች ነው። እነዚህ የጦርና የፓሊስ ሹማምንት ኢትዮጵያን ወረው እንደያዙት አገር ሲዘርፉ፣ ሕዝቧንም ሲገሉና ሲገርፉ እንሆ 23 ዓመታት አልፈዋል። በእነዚህ 23 ዓመታት ትግራይን ጨምሮ በደል ያልደረሰበት የኢትዮጵያ ግዛት እና የኅብረተሰብ ክፍል የለም። ሁሉም ኢትዮጵያዊ በእነዚህ ፋሽስቶች ተረግጧል፣ ተዋርዷል፣ ተግዟል። የንቅናቄዓችን ዋና ፀሐፊ አቶ አንዳርጋቸው ጽጌን ጨምሮ በርካታ ኢትዮጵያዊያን የነፃነት አርበኞች በእነዚህ እኩይ የሠራዊቱና የፓሊስ አዛዦች ሰቆቃ እየተፈፀመባቸው ነው። የወያኔ የጦርና የፓሊስ አዛዦች እና ሰላዮች አገራችን እያደሙ፤ ሕዝባችንን እያስለቀሱ ነው። በወያኔ ፋሽስት የጦርና የፓሊስ አዛዦች እና ሰላዮች ጥምረት ሰቆቃ የሚፈፀምበት የኅብረተሰብ ክፍል በየጊዜው እየጨመረ ይገኛል። የወያኔ ማሰቃያዎችን የሞሉት የፓለቲካና የሀይማኖት መሪዎች፣ ጋዜጠኞችና ብሎገሮች መሆናቸው ለዚህ አንድ ማሳያ ነው።
የሠራዊቱ የበታች ሹማምንትና ተራ አባላት ጥንቅር ግን ከአዛዦቹ ፈጽም የተለየ ነው። የመከላከያና የፓሊስ ሠራዊት አባላት ከመላው የኢትዮጵያ ግዛቶች የተውጣጡ፤ እንደሌላው የኢትዮጵያ ሕዝብ ሁሉ በነፃነት እጦት፣ በመብቶች መገፈፍ እና በኑሮ ውድነት የሚሰቃዩ ዜጎች ናቸው። የኢትዮጵያ ወታደር በወያኔ አዛዦቹ እየታዘዘ ወገኑን የሚበድል ቢሆንም ራሱ ከመበደል ግን አይድንም። የኢትዮጵያ ወታደር በወያኔ አዛዡ ታዞ ሌላኛውን ወገኑን ቢያስርም ሹሙ ፊቱን ባዞረበት ጊዜ እራሱ ደግሞ ከመታሰር አይድንም። የኢትዮጵያ ወታደር ወያኔ አዞት ምስኪኖችን ይደበድባል፤ ራሱ ደግሞ በወያኔ ይደበደባል። የኢትዮጵያ ፓሊስ በወያኔ ትዕዛዝ ንጹሀን ዜጎችን ያስራል፣ ያሰቃያል፤ እራሱ ደግሞ በወያኔ ይታሰራል፣ ይሰቃያል። ይህ ምን የሚሉት ባርነት ነው? የወያኔ ሹማምንቶች በሚመሩት የመከላከያና የፓሊስ ሠራዊት ውስጥ ያሉ ወገኖቻችን በህወሓት የሚደርስባቸው በደል ሌላው ኢትዮጵያዊ ከሚደርስበት ይብስ እንደሆን እንጂ የሚያንስ አይደለም።
ግፍ መብቃት አለበት። በጥቂት የህወሓት ሹመኖች ትዕዛዝ በኢትዮጵያዊው ወታደር ላይ የሚደርሰው ውርደት ማብቃት አለበት። ሠራዊቱ የኢትዮጵያ እንጂ የህወሓት ሠራዊት አይደለም፤ ሊሆንም አይገባውም። ሠራዊቱ ለራሱ ነፃነት ብቻ ሳይሆን ለአገርና ለሕዝብ ደህንነት ዘብ የመቆም ኃላፊነት አለበት። የኢትዮጵያ ሠራዊት የህወሓት የባንዳ ሠራዊት ሆኖ ሕዝብን በማሰቃየትና ሀገርን በመበደል ተግባር ላይ ተሠማርቶ ማየት አንሻም። ይህንን ለራሱ ክብር ያለው፤ አገሩንና ሕዝቡን የሚወድ የሠራዊቱ አባልም የሚፈቅደው ጉዳይ አይደለም።
ስለሆነም ግንቦት 7: የፍትህ፣ የነፃነትና የዲሞክራሲ ንቅናቄ የሚከተለው ሀገራዊ ጥሪ ለመላው የመከላከያና የፓሊስ ሠራዊት አባላት ያቀርባል።
ውድ የኢትዮጵያ የመከላከያ ወይም የፓሊስ ሠራዊት አባል! በጥቂት የህወሓት ፋሽስቶች መዳፍ ውስጥ ሆነህ የገዛ ራስህን፣ የቤተሰቦችህን፣ የወገንህን እና የአገርህን ስቃይ ማራዘምህን አቁም። አንተ የኢትዮጵያ ሕዝብ አለኝታ እንጂ የጥቂት ጎጠኞች ሎሌ ልትሆን አይገባም። አንተ የኢትዮጵያ ሕዝብ መከታ እንጂ የእያንዳንዱ ቤተሰብ ስጋት መሆን የለብህም። አንተ የመጪው ትውልድ አርዐያ እንጂ ሕፃናትንና ወጣቶችን ማስፈራሪያ መሆን የለብህም።
የኢትዮጵያ ወታደር ሆይ! ራስህን ተመልከት! ራስህን ታዘብ! ዛሬ ያለህበት ሁኔታ አሳፋሪ ነው። አዛዦችህ አገርን፣ ትውልድንና ታሪክን ለማጥፋት የተነሱ ናቸው። አንተን ተጠቅመው ነው ይህንን ዓላማቸውን የሚያስፈጽሙት። ይህ ላንተ ብቻ ሳይሆን ለልጅ ልጆችህ ውርደት ነው። ከወያኔ ባርነት ራስህን ነፃ አውጣና የነፃነት ታጋዮችን ተቀላቀል። ወያኔ መጥፋቱ አይቀርም። ወያኔ የቀድሞውን ጦር እንደበተነው አንተን ለመበተን የሚሻ የለም። አንተ ዛሬ ከወገን ጋር ወገንተኛነትህን ካሳየህ ከአገዛዙ ጋር እጠፋለሁ ብለህ አትስጋ። ለዚህም ነው አንተ ዛሬ በግልም ሆነ በቡድን የምትወስደው እርምጃ የአገራችንን ብቻ ሳይሆን የሠራዊቱን እጣ ፈንታ ይወስናል ብለን ወገናዊ ጥሪ የምናቀርብልህ።
ውድ የኢትዮጵያ የመከላከያና የፓሊስ ሠራዊት አባላት ወገናችን!ከበዳዮች ጎን ሳይሆን ከተበዳዮች ጎን ቁም። ከገራፊዎችና ገዳዮች ጎን ሳይሆን ከነፃነት ታጋዮች ጎን ሁን። ዛሬውኑ ወስን። አሁን የነፃነት ታጋዮችን መቀላቀል ቀላል ሆኗል። ያሉበትን ታውቃለህ፤ ተቀላቀል። አልያም የጠመንጃህን አፈሙዝ በፋሽስት አለቆችህ ላይ አዙር። ይህንን እርምጃ በመውሰድ ከታሪክ ተወቃሽነት እራስህን በመታደግ ለአገርህና ለወገንህ አለኝታህን አረጋግጥ።
ድል ለኢትዮጵያ ሕዝብ !!!

ስካርና ለቅሶ

July 17/2014
አርአያ ተስፋማሪያም
( በፎቶው ሰመሃል መለስ ከጥቁር አፍሪካዊ ወጣት ጋር…)
የአዜብ መስፍንና የመለስ ዜናዊ ልጅ የሆነችው ሰመሃል መለስ በየቀኑ ከልክ በላይ አልኮል እንደምትጐነጭ የቅርብ ታማኝ ምንጮች አስታውቀዋል። የ27 አመት ወጣቷ ሰመሃል አቅሏን እስክትስት ከጠጣች በኋላ እየተነፋረቀች እንደምታለቅስ ታውቋል። ቦሌ በሚገኘውና የቀድሞ ስዩም መስፍን መኖሪያ ቤት ውስጥ ከወላጅ እናትዋ ጋር የምትኖረው ሰመሃል የሚያስለቅሳት ነገር አስገራሚ ሆኖዋል። ሰመሃል በአባትዋ ሞት አሊያም በእናትዋ መታመምና በደረሰባት የፖለቲካ ኪሳራ እንዲሁም ብዙ ባለስልጣናት ስለማይጠይቋቸው “ተበሳጭታ” ይሆን የምታለቅሰው?..የሚሉት ዋናዎቹ ናቸው።

ሰመሃል ማወቅ ያለባት ነጥብ አለ። በሺህ የሚቆጠሩ ወገኖች እስር ቤት በማጐር፣ በመግደልና ቤተሰብ በመበተን፣ በማሰቃየትና ከአገር እንዲሰደዱ እንዲሁም በስደት እንዲያልቁ በማድረግ ወንጀል የፈፀሙት አባትዋ መለስ ዜናዊ እንደነበሩ ልታውቅ ይገባል። የ3 አመቱ ህፃን ናፍቆት አባቱን እስክንድር ነጋን ከጉያው እየደበደቡ ሲወስዱት ስቅስቅ ብሎ ሲያለቅስ አንቺ ምናልባት ከአባትሽ ጋር ትሳሳቂ ነበር። የ10 እና 13 አመት ታዳጊ ወጣቶች በምርጫ 97 በጥይት ተደብድበው እንዲገደሉ ቀጥታ ትእዛዝ የሰጡት (ያውም በቲቪ ወጥተው) አባትሽ መለስ ዜናዊ ናቸው። የነዛ ሕፃናት ወላጆች ዛሬም ያለቅሳሉ። በ10ሺዎች የሞቱለት የባድመ ጦርነት አስመልክቶ መሬት እንስጥ ያሉት መለስ ዜናዊ ፓርላማ ቀርበው « ቁራሽ መሬት ሄደ ብለን ሃዘን አንቀመጥም፤ ሙሾ አንወርድም» ብለው በጀግኖቹ መስዋእትነት የተሳለቁ ናቸው። የጀግኖቹ እናት ዛሬም ታለቅሳለች። አባትሽ ትተውት የሄዱት የዘርና ጐሳ ፖለቲካ አገሩን እያመሰው ይገኛል። መለስ አስፋፍተውት በሄዱት እስር ቤቶች ዛሬም ዜጐች በጅምላ እየተሰቃዩ ይገኛሉ። ስንቱን ልዘርዝረው!?...እኩል እናልቅስ!?

Ethiopian Ministry of Foreign Affairs says Andargachew cannot visited unless “officials permit”

July 15, 2014
The Ethiopian Ministry of Foreign Affairs, in a letter it sent to the Head of the Africa Section of the United Kingdom (UK) Foreign and Commonwealth Office, said that Andargachew Tsige would only get legal and consular services when “relevant bodies give the permission”.
The Ministry did not name who the “relevant bodies” are. Sources, however, say the so called ‘bodies’ are the security officials.
The Ministry wrote the letter after the Head of the Africa Section at the British Ministry of Foreign Office wrote a letter asking for a permission to “visit Andargachew Tsige”.
The British Office has been saddened by the response and is waiting for further responses, it has been learnt.
A family member of Andargachew Tsige said that Ethiopia’s intelligence officials are refusing Andargahcew from being visited so that they can record what he says due to excessive torture which they will later broadcast to the public with the aim of killing the spirits of the public. The family member said he had also notified this to the Office.
ESAT has received information that in order to force him to utter what he does not want to say, Andargachew has been tortured and denied sleep.
In a meeting held in the Prime Minister’s office last weekend, the officials of the Ethiopian Anti Terror Taskforce have stated that the methods of torture so far used on Anadargachew Tsige did not yield much thus it has been decided that they could execute additional torturing methods.
The inability of the Ethiopian Prime Minister and the Ministry of Foreign Affairs to respond to the visitation requests exposes that the Country is being ruled by few people in the backdoor, said the sources.
Similarly, Ethiopians living in Japan have held protest rallies outside the British and Yemen Embassies today.

የውህደት እንቅስቃሴአችን በተሳካ ሁኔታ ቀጥሏል!! – ከመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት (መኢአድ) እና ከአንድንት ለዴሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ (አንድነት) ከጉባኤ አዘጋጅ ኮሚቴ የተሰጠ ጋዜጣዊ መግለጫ

July17/2014
ለውህደቱ መሳካት ጥረት እና ድጋፍ እያደረጉ ላሉ ኢትዮጵያውያን ምስጋና እናቀርባለን!1እንደሚታወቀው የመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት (መኢአድ) እና አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ (አንድነት) የቅድመ ውህደት ስምምነት ፊርማ ካኖሩ በኋላ ጠቅላላ ጉባኤ በመጥራት ውህደቱን ምሉዕ ለማድረግ የጋራ ኮሚቴ በማቋቋም እየተንቀሳቀሱ ይገኛሉ፡፡
ይሄው ውህደት አመቻች ኮሚቴ በስምምነት ሰነዱ በተቀመጠው መሰረት ለማጠናቀቅ ቀን ከሌሊት እየሰራ ሲሆን የሁለቱ አንጋፋ ፓርቲዎች ውህደት የተሳካ እንዲሆን ትንሽ ግዜ መጨመር አስፈላጊ ሆኖ አግኝቶታል፡፡ በተለይም ለውህደቱ መሳካት የሚያስፈልገው የገንዘብ መጠን ሰፊ በመሆኑ በሀገር ውስጥና በውጭ የሚገኙ ደጋፊዎቻችን የአቅማቸውን ድጋፍ ለማድረግ በስምምነት ሰነዱ የተቀመጠው የውህደት ግዜ ላይ ሁለት ሳምንት መጨመር እንደሚያስፈልግ ታምኖበታል፡፡
ስለዚህ ጉባኤ ጠሪ ኮሚቴው ባደረገው ግምገማ የሁለቱ ፓርቲዎች የውህደት ግዜ ሓምሌ 19 እና 20 እንዲሆን ተስማምቷል፡፡ ከዚህ ውጭ ግን የሁለቱ ፓርቲዎች ረቂቅ ደምብና ፕሮግራም ዝግጅት በተሳካ ሁኔታ የተጠናቀቀቀ ሲሆን የጉባኤ ተሳታፊዎች የውህደቱን ግዜ በጉጉት እየጠበቁ ይገኛሉ፡፡ በመጨረሻም ሁለቱ ፓርቲዎች ተዋህደውና ሌሎች ፓቲዎች ወደ መሰባሰብ መጥተው የተጠናከረ የተቃውሞ ሃይል እንዲፈጠር ብርቱ ድጋፍ ላደረጉ ኢትዮጵያውያንና የውህደት አመቻች ኮሚቴው ስራ የተቀላጠፈ እንዲሆን ድጋፍ እያደረጉ ላሉ ኢትዮጵያውያን ሁሉ ከፍ ያለ ምስጋና እናቀርባለን፡፡
በመቀጠልም እስከ ውህደቱ ፍፃሜ ድረስ በሀገር ውስጥና በውጭ አገር እየተደረገ ያለው ድጋፍ እንደሚቀጥል በመተማመን ለውህደቱ ድጋፍ የምታደርጉ ኢትዮጵያውያን፡-
መኢአድ፤ አቢሲንያ ባንክ፤ ቦሌ ቅርንጫፍ፤ የባንክ አካውንት ቁጥር፡- AEUP – SP 235
አንድነት፤ አቢሲንያ ባንክ፤ ጠመንጃ ያዥ ቅርንጫፍ የባንክ አካውንት፡- UDJ – A/C 47
በኩል እንድታስገቡ የውህደት አመቻች ኮሚቴው አገራዊ ጥሪውን ያቀርባል፡፡
ስንተባባር እናሸንፈላን!!
ሐምሌ 9 ቀን 2006 ዓ.ም
አዲስ አበባudJAEUP

Wednesday, July 16, 2014

Ethiopian Opposition Political Parties Rant Over Recent Crackdown

July 16, 2014
In a recent crackdown, police arrested four opposition political party members and leaders, and members of the parties they belong to have expressed concern about the situation and demand the immediate release of the detainees. Getachew Redda, advisor to the Prime Minister told The Reporter that the individuals were arrested due to their connections with terrorist organizations and said it was unrelated to the upcoming national election, which will be conducted next year.Arena Tigray Party's Executive Committee member Abraha Desta.
“Their involvement in the terrorist organization is the major reason for their arrest,” he stated.
Four of the detained opposition political party members and leaders are head of public relations affairs of Unity for Democracy and Justice Party (UDJ), and vice chairman of organizational affairs of the party Habtamu Ayalew and Daniel Shibeshi respectively, Blue Party’s National Council Deputy Chairperson, Yeshiwas Assefa, and Arena Tigray Party’s Executive Committee member Abraha Desta.
Kidane Yirgu, head of Arena Addis Ababa branch said to The Reporter “Abraha has not appeared before a court of law and the party understood that he came to Addis Ababa on Thursday afternoon around 5:30.”
“Though the party is ready to get him a lawyer it is difficult to communicate with him and the party has not received any official information about his whereabouts, however, some other people have informed the members of the party that Abraha is in Addis Ababa,” Kidane added Regarding the charges the government stated, Kidane told The Reporter that “Abraha is a peaceful person and believes in a non-violent and peaceful struggle, therefore the charge that the government stated has got nothing to do with him.”
Arena also thinks the regime change should come peacefully and does not support any armed struggle to change the system, however we can’t say a certain group is a terrorist or not but we don’t believe in an armed struggle, he further added. On the other hand, the Blue Party condemned the current crackdown of then political figures and the situation of the country and said, “we cannot tolerate TPLF/EPRDF’s [Tigrayan People's Liberation Front/Ethiopian Peoples' Revolutionary Democratic Front] state of terror.” Yilikal Getnet (Eng.) president of Blue Party also told The Reporter, “Members of the party and his family members are not allowed to visit him, and his constitutional right to appear before court within 48 hours has been deprived.”
He said “their arrest boldly hints that the regime’s final days in power are counted and change is inevitable in the near future and hence the party demands the immediate release of the detainees and as well advocates the regime to stop the state of terror.”
Sileshi Feysa, deputy chairperson and head of election affairs of Blue Party on his part told The Reporter, “though we don’t believe in the struggle approach of Ginbot 7, the party still doesn’t accept the labeling made by the ruling party that they are a terrorist group.”
He further added that the party is engaged in a peaceful and non-violent political struggle and thus did not support any movements that aren’t peaceful. The Unity for Democracy and Justice Party (UDJ) also expressed its concerns about the current crackdown and stated the situation as a measure taken by the ruling party to control the upcoming election and demands the immediate release of the detainees.
Engineer Gizachew Shiferaw, president of UDJ said that UDJ believes in a peaceful and non-violent struggle and that the party has no connections with organizations that engage themselves in an armed struggle.
In relation to whether UDJ regards Ginbot 7 as a terrorist organization or not, he told The Reporter, “we don’t have a mandate to do so therefore I don’t want to say anything about it.”
Moreover, the All Ethiopian Union Party (AEUP) and UDJ merger joint committee also condemns the arrest and said arresting political leaders would not stop the process of merging by citing that Habtamu Ayalew was the head of the merging committee that comprised 10 members from both parties.
Source AllAfrica

ጋዜጠኞቹና ጦማሪያኑ ፍርድ ቤት ሳይቀርቡ የምርመራ መዝገቡ መዘጋቱ ሕገወጥ አካሄድ መሆኑ ተገለጸ

June16/2014
-‹‹አሁን ታስረው የሚገኙበት ሁኔታ ሕገወጥና አደገኛ ነው›› የተጠርጣሪዎች ጠበቃ
zone 9999በሽብርተኝነት ወንጀል ተጠርጥረው በክስ ላይ የሚገኙት ሦስት ጋዜጠኞችና ስድስት ጦማርያን ፍርድ ቤት ሳይቀርቡ ፖሊስ ‹‹ምርመራዬን ስለጨረስኩ መዝገቡ ይዘጋልኝ›› በማለት መዝገቡ እንዲዘጋ ማድረጉ ሕጉን ያልተከተለና አደገኛ መሆኑን ጠበቃቸው አስታወቁ፡፡
ተጠርጣሪ ጋዜጠኞች ተስፋለም ወልደየስ፣ አስማማው ኃይለ ጊዮርጊስ፣ ኤዶም ካሳዬና ጦማሪያንና የሕግ መምህር ዘለዓለም ክብረት፣ ናትናኤል ፈለቀና አጥናፉ ብርሃኔ ሐምሌ 5 ቀን 2006 ዓ.ም. በፌዴራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ ችሎት የሚቀርቡበት ዕለት ነበር፡፡ እንደወትሮው ሁሉ የተጠርጣሪዎች ቤተሰቦች፣ የአገር ውስጥና የውጭ አገር ጋዜጠኞች፣ ጓደኞቻቸውና የተለያዩ የችሎት ታዳሚዎች በጠዋት ማልደው በፍርድ ቤት ግቢ የተገኙ ቢሆንም፣ እስከ ቀኑ 5፡30 ሰዓት ድረስ ፖሊስም ሆነ ተጠርጣሪዎቹ ወደ ችሎቱ አልመጡም፡፡ ከ5፡30 ሰዓት በኋላ ሌሎች ፍርድ ቤት የሚቀርቡ ተጠርጣሪዎቹና ፖሊስ ችሎት ቆይተው ሲወጡ፣ የተጠርጣሪዎቹ ጠበቃ አቶ አመሐ መኮንን፣ ደንበኞቻቸው ፍርድ ቤት መቅረብ አለመቅረባቸውን ለማጣራት የዕለቱን ተረኛ ዳኛ ለማነጋገር ገቡ፡፡ ጠበቃው ስለደንበኞቻቸው ፍርድ ቤቱን ሲጠይቁ፣ ፖሊስ ምርመራውን መጨረሱን በማሳወቅ መዝገቡ እንዲዘጋለት ጠይቆ መዘጋቱን ሲያስረዳቸው፣ ‹‹እንዴትና በምን ሁኔታ?›› የሚል ጥያቄ ቢያቀርቡም፣ ከመዘጋቱ ውጪ ምንም ምላሽ ሊያገኙ አለመቻላቸውን ተናግረዋል፡፡
እስረኛ ፍርድ ቤት ሳይቀርብ የምርመራ መዝገቡ ሊዘጋ እንደማይችል የሚናገሩት ጠበቃ አመሐ፣ ተጠርጣሪዎቹ ከሐምሌ 5 ቀን 2006 ዓ.ም. ጀምሮ በእስር ላይ መሆናቸው፣ በሕግ አግባብ በፍርድ ቤት ምንም ትዕዛዝ ባልተሰጠበት ሁኔታ በመሆኑ ድርጊቱ ሕገወጥና አደገኛ መሆኑንም አስረድተዋል፡፡
ፖሊስ ምርመራውን ካጠናቀቀ ተጠርጣሪዎቹን ፍርድ ቤት ይዞ በመቅረብ ለፍርድ ቤቱ ማስረዳትና ክስ እስከሚመሠረትባቸው ድረስ በዋስ እንዲቆዩ ወይም የሕግ ሥርዓቱ በሚፈቅደው መሠረት ስለሚቆዩበት ሁኔታ ፍርድ ቤቱ ትዕዛዝ መስጠት እንደነበረበት አስረድተዋል፡፡
ፍርድ ቤቱ ትዕዛዝ ባልሰጠበት ሁኔታ ተጠርጣሪዎቹ ባሁኑ ወቅት የት እንዳሉ እንደማይታወቅ የሚናገሩት ጠበቃው፣ በወንጀል ሕጉና በሕገ መንግሥቱ በተጠሰው አካልን ነፃ የማውጣት መብት (ሐቢየስ ኮርፐስ) ክስ ሊመሠርቱ እንደሚችሉ ገልጸዋል፡፡
በሌላ የምርመራ መዝገብ የተካተቱት ጦማሪያን ማህሌት ፋንታሁን፣ አቤል ዋበላና በፈቃዱ ኃይሉ ደግሞ ፍርድ ቤት መቅረብ የነበረባቸው ሐምሌ 7 ቀን 2006 ዓ.ም. የነበረ ቢሆንም፣ ተጠርጣሪዎቹም ሆኑ መርማሪ ፖሊስ ሳይቀርቡ መቅረታቸውን ጠበቃው ጠቁመዋል፡፡
ዘጠኙም ተጠርጣሪዎች ‹‹የመብት ተሟጋች ነን›› ከሚሉ የውጭ ኃይሎች ጋር በሙሉ ሐሳብና ገንዘብ በመስማማት ሕዝብን የማተራመስ፣ አገርንና መንግሥትን የማፍረስ ዘገባ በኢንተርኔትና በተለያዩ ድረ ገጾች ያልሆነ መረጃ ሲያስተላልፉ ተገኝተዋል በሚል ፖሊስ ሚያዝያ 17 እና 18 ቀን 2006 ዓ.ም. በቁጥጥር ሥር እንዳዋላቸው መዘገባችን ይታወሳል፡፡ ፖሊስ በተጠርጣሪዎቹ ላይ ለሁለት ጊዜ የ14 ቀናት የምርመራ ጊዜ ጠይቆ ከተፈቀደለት በኋላ፣ በሦስተኛው የፍርድ ቤት ቀጠሮ የተጠርጣሪዎቹ ጉዳይ ውስብስብና ድርጊቱም የሽብርተኝነት ድርጊት መሆኑን በመጥቀስ፣ ለተጨማሪ ምርመራ 28 ቀን እንዲፈቀድለት የፀረ ሽብርተኝነት ሕጉን በመጥቀስ ተፈቅዶለት መመርመር ላይ መሆኑን መዘገባችን አይዘነጋም፡፡ ተጠርጣሪዎቹ በቁጥጥር ሥር ከዋሉ 78 ቀናት ሞልቷቸዋል፡፡

የጨነገፉ የአፍሪካ መንግስታት የሞራል ዝቅጠት (ፕሮፌሰር አለማየሁ ገብረማርያም)

July 16/2014
July 15, 2014
ከፕሮፌሰር አለማየሁ ገብረማርያም
ትርጉም በነጻነት ለሀገሬ
በልጆች ላይ የሚፈጸም ወንጀል በሰው ልጆች ላይ የሚፈጸም ወንጀል ነውን?

የጨነገፉ (ዉድቀት የገጠማቸው) መንግስታትን አስመልክቶ በቅርቡ በወጣ መረጃ መሰረት ከአስሩ የመጀመሪያዎቹ ቁንጮ አገሮች ስድስቱ እና ከ25ቱ የመጀመሪያዎቹ ቁንጮ አገሮች 18ቱ በአፍሪካ የሚገኙ አገሮች ናቸው፡፡ የዚህ ትችት ዓላማ የጨነገፉ የአፍሪካ አገሮችን ሬሳ መደብደብ አይደለም፣ ወይም ደግሞ በብዙ የአፍሪካ አገሮች የአፍሪካን የመንግስት አስተዳደር ውድቀት ትረካ ለማውሳት አይደለም፣ እንደዚሁም ለህዝቦቻቸው መሰረታዊ እና አስፈላጊ የሆኑ አገልግሎቶችን ማቅረብ የማይችሉ፣ የህዝቡን ደህንነት ማስከበር የተሳናቸው፣ እጅግ በጣም እየተስፋፋ የመጣውን ሙስና መቆጣጠር ያልቻሉ፣ መንግስታዊ ወንጀለኝነትን የሚያራምዱ፣ እየተስፋፋ የመጣውን የሰብአዊ መብት ረገጣ ማስቆም የማይችሉ እና ሀብት ባላቸው እና በሌላቸው መካከል ያለውን ልዩነት ለማጥበብ የማይችሉ አቅመቢስ ድሁር የአፍሪካ ሽባ መንግስታት ን ለመንቀፍ አይደለም፡፡ስለአፍሪካ የጨነገፉ መንግስታት የሞራል ዝቅጠት ባሰብኩ ቁጥር ስሜቴ ይረበሻል፡፡

በመጀመሪያ ደረጃ የጨነገፈ (ዉድቀት የገጠማቸው) የአፍሪካ መንግስት ማለት ምን ማለት ነው? የጨነገፈ መንግስት በገሀዱ ዓለም ያለው መንግስት መጥፎ አምሳያ ነው፡፡ የአፍሪካ የጨነገፉ የአፍሪካ መንግስታትን መንግስታት ማለት  ኮካ ኮላ ለሰውነት ጠቃሚ የሆነ መጠጥ ነው አንደማለት ነው (ኮካኮላ የሚባለው መጠጥ በኢትዮጵያ አይጠጣ !)፡፡ ለምዕራባውያን እና ለእነርሱ የብዙሀን የኢኮኖሚ እና የፖለቲካ ተቋማት የአፍሪካ የጨነገፈ መንግስት ለልግስና የተቀመጠ ግኡዝ ነገር ነው፣ የጨነገፈ መንግስት የእዳ ክፍያ ስርዓት መሞከሪያ እና የይስሙላ ልማት ባሪያ ነው፡፡ ለምዕራቡ ዓለም አካዳሚ የአፍሪካ የጨነገፈ መንግስት የአፍሪካን ገዳይ መንግስት የሚያጠኑበት እና ስህተት የሰራ መሆኑን የሚያሳውቁበት ዘዴ ነው፡፡ በጎ አመለካከት ላላቸው እና ለትችት አቅራቢዎች የጨነገፈ መንግስት አታላይ እና አስመሳይ የሆነ መንግስት መሳይ ቡድን ነው፡፡ የሞራል ስብዕና የሌላቸው የአፍሪካ የጨነገፉ መንግስታት በሞራል የበከቱ እና ውግዘት የሚገባቸው ደንቆሮዎች ናቸው፡፡ የጨነገፉ መንግስታትን አመልካች መለኪያዎች (በቋፍ ላይ ያሉ በሚል እንደገና የተሰየሙ እና በ2014 በፖለቲካዊ አካሄድ የጨነገፈ ተብለው የተፈረጁ) የሰላም እና የውጭ ፖሊሲ መጽሄት በጋራ በማተም ባወጣው ዘገባ መሰረት የአፍሪክ የጨነገፉ መንግስታት በ12 በማህበራዊ፣ በኢኮኖሚያዊ እና በፖለቲካ አመልካች መስፈርቶች ዝቀተኛ ውጤት አግኝተዋል፡፡

አሁን በህይወት የሌሉት የዩናይትድ ስቴትስ አሜሪካ ፕሬዚዳንት ሁበርት ምፍሬ እ.ኤ.አ በ1948 ለዴሞክራቲክ ፓርቲ እንዲህ የሚል የተማጽኖ ጥያቄ አቅርበው ነበር፣ “ለሰብአዊ መብቶች መከበር ጥረት አድርጉ“ እናም በመጨረሻ የ1964 የሲቪል መብቶች ደራሲ የሚከተለውን ምልከታ አድርገው ነበር፣ “…የመንግስት የሞራል ጥያቄ ያ መንግስት የህይወት ስንክሳር የተዘባረቀባቸውን ህዝቦች፣ ህጻናት፣ ድንግዝግዝ ባለ ህይወት ውስጥ ላሉ ህዝቦች፣ ለአዛውንቶች፣ በጨለማ ህይወት ውስጥ ላሉ፣ ለታመሙ፣ ለምስኪኖች እና ለአካለ ጎደሎዎች እንዴት በማድረግ ማስተናገድ እንደሚችል የሚመለከትበት ሁኔታ ነው፡፡ “በሞራል ስብዕና የበከቱ የመንግስታት አመላካች መለኪያዎች ብዙዎቹ የአፍሪካ መንግስታት ከመጀመሪያው ረድፍ ላይ ይቀመጣሉ፡፡“ እነዚህ ለመንግስት፣ ገዥ አካል እና ህጋዊ መንግስት የሚደረጉ ደካማ ይቅርታዎች በውድቀት ላይ ያሉትን እንዴት እንደሚያስተናግዱ እና የጧት ህይወታቸው በአሁጉሩ እንዴት እንደሆነ የሚያመላክት አሳፋሪ ድርጊት ነው፡፡
የህጻናት ጠለፋ፣

አሸባሪ ቡድን የናይጀሪያ 300 ልጃገረዶች አፍኖ ከወሰደ ከሶስት ወራት በኋላ ልጆቹ የት እንዳሉ እንኳን ፍንጭ ማግኘት አልቻለም፣ እንዲሁም መንግስት እነዚህን ልጃገረዶች ፈልጎ ለማስፈታት ያደረገው ይህ ነው የሚባል ጥረት የለም፡፡ ሁሉም ንጉሶች እና አጋፋሪዎቻቸው ቢሆኑ ሊፍልጓቸው አልፈለጉም፡፡ በመጀመሪያ ደረጃ የልጃገረዶቹ መታፈን በዓለም አቀፍ ደረጃ የሞራል ቁጣ እና ውግዘትን አስከትሏል፡፡ ቀዳሚ ያሜሪካ እመቤት ሚሸሌ ኦባማ በልጃገረዶቹ መጠለፍ የተሰማቸውን ሀዘን እና ቁጣ ገልጸዋል፡፡ እናም በእጃቸው የተጻፈበት ካርድ ከፍ አድርገው በመያዝ “ልጃገረዶቻችንን መልሱ“ ብለዋል፡፡ ይህንን አስቀያሚ ጉዳይ ግለሰብአዊ አድርገውታል፡፡ ሚስስ ኦባማ እንዲህም ብለው ነበር፣ “ባራክ እና እኔ ልጆቻችንን በዚህ አይተናል“፡፡ በጣም አስቀያሚ ነገር ነው፣ የናይጀሪያ ፕሬዚዳንት እና ሚስስ ጉድላክ ጆናታን የዚህ ዓይነት ስሜት አልተሰማቸውም፡፡ ቢያንሰ እንኳ ምንም ያሉት ነገር የለም፡፡ የአፍሪካ ታላቅ እያለ ከሚመጻደቅ አገር በምን ዓይነት መለኪያ ነው 300 ልጃገረዶች ያለምንም ፍንጭ ሳይኖረው በቀላሉ ሊጠፉ የሚችሉት?

የህጻናት ወታደሮች፣

የሞራል ስብዕና መጥፋት እና የአፍሪካን ህጻናት ህልውና እና ደህንነት ለመጠበቅ ቁርጠኝነት ያለው ውሳኔ ያለመወሰን ሁኔታ በህጻናቱ ችግሮች ላይ ዘገባ ያለማቅረብ የአፍሪካ ወንጀለኛ መሪዎች ስህተት ነው፡፡ በኮንጎ ዴሞክራቲክ ሬፑብሊክ፣ ሩዋንዳ፣ ቡሩንዲ፣ የመካከለኛው አፍሪካ፣ ሶማሊያ፣ ዩጋንዳ፣ ሴራሊዮን፣ ኮትዲቯር፣ ዚምባብዌ፣ ቻድ፣ ሱዳን፣ እና ደቡብ ሱዳን በመቶ ሽዎች የሚቆጠሩ ህጻናት በየዓመቱ በአማጺያን፣ ሚሊሻ እና የመንግስት ኃይሎች ህጻናቱ ወታደር እንዲሆኑ ያስገድዳሉ፡፡ በገጠር የሚኖሩ የአፍሪካ ህጻናት ከቦታ ቦታ በሚንቀሳቀሱበት ጊዜ ወይም ደግሞ ወደ ት/ቤት ሲሄዱ እና ሲመለሱ፣ ለዕለት ጉርሳቸው ሲባዝኑ እና ከሚኖሩበት ካምፕ እንኳ ሳይቀር አሁንም ከየቤታቸው የመታፈናቸው ሁኔታ እንደቀጠለ ነው፡፡ በ10 ዓመት እድሜ ህጻናት ወንዶች እንደወጣት የጦር መሳሪያዎችን መፍታት እና በመግጠም ከእራሳቸው የበለጠ የጦር መሳሪያ ይሸከማሉ፡፡ በዚህም መሰረት ህጻናቱ ሁልጊዜ ይደበደባሉ፣ እናም በሰው ልጆች ላይ የጦር ወንጀል ማለትም ግድያ፣ አስገድዶ መድፈር፣ ማሰቃየት፣ አካለጎደሎ ማድረግ፣ እና ሌሎች ለመናገር የሚዘገንኑ ወንጀሎችን እንዲሰሩ ይገደዳሉ፡፡ የተጠለፉ ልጃገረዶች ሁልጊዜ ይደፈራሉ፣ የስሜት ማርኪያና እንዲሆኑም የቤት ውስጥ ስራዎችን እንዲሰሩ ይገደዳሉ፡፡

ኮንጎ ዴሞክራቲክ ሬፑብሊክ ዉጤቱ ምን ሊሆን እንደሚችል የማይታወቅ ከዓለም ከፍተኛ የሆነ የኅጻናት ወታደር አላት፡፡ በኡጋንዳ የሎርድስ ሬዝንታንሰ እየተባለ የሚጠራው የአማጺያን ኃይል በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ ወንወዶች ልጆችን ለውትድርና እና ልጃገረዶችን ደግሞ በአስገድዶ መድፈር የወሲብ ባሪያ አድርጓቸዋል፡፡ በአስቸጋሪነቱ የሚታወቀው የአገሪቱ መሪ የነበረው ጆሴፍ ኮኒ በሰው ልጆች ላይ በፈጸመው የጠለፋ ወንጀል ምክንያት በዓለም ዓቀፉ የወንጀለኞች ፍርድ ቤት አቃቤ ህግ ክስ ተመስርቶበታል፡፡ ሌሎች ጥቂቶች ደግሞ በህጻናቱ ላይ በፈጸሟቸው ወንጀሎች ምክንያት ተጠያቂ ሆነዋል፡፡ በኮንጎ ዴሞክራቲክ ሬፑበሊክ ጦረኛ ቶማስ ሉባንጋ ዲሎ የተባለው ህጻናትን አስገድዶ ለጦርነት በመመልመል ብቸኛው ተጠርጣሪ እና በዓለም የወንጀለኞች ፍርድ ቤት ክስ የተመሰረተበት ጦረኛ ነው፡፡

የህጻናት ጉልበት ብዝበዛ፤ ብዙዎቹ የአፍሪካ መንግስታት የህጻናትን ጉልበት ብዝበዛ ለመዋጋት እና ለማቆም ያለመቻል ሌላው የሞራል ስብዕናቸው ውድቀት መገለጫ ነው፡፡ የህጻናት ጉልበት ብዝበዛ “የህጻናትን ደህንነት የሚጎዳ ወይም ደግሞ ከትምህርት ገበታ እንዲታቀቡ የሚያደርግ ሁኔታ ነው፡፡“ በ5 እና በ17 ዓመታት የዕድሜ ክልል መካከል የሚገኙ በሚሊዮን የሚቆጠሩ የአፍሪካ ህጻናት በአሁኑ ጊዜ ሰብአዊነት በጎደለው መልኩ እና በአገር አቀፍ እና በዓለም አቀፋዊ ደረጃ ህገወጥነትን ባካተተ ሁኔታ በዝባዥ ወይም ደግሞ በአስቸጋሪ የስራ ሁኔታ ተይዘው ይገኛሉ፡፡ በኮንጎ ዴሞክራቲክ ሬፑብሊክ ዕድሚያቸው ከ15 ዓመታት በታች የሆኑ በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ህጻነት ስግብግቦቹን የቻይና ኩባንያዎች ፍላጎት ለማርካት ሲባል በመዳብ፣ ኮባልት፣ እና ሌሎች ውድ ማዕድናት ፍለጋ አስቀያሚ የሆነ የጉልበት ብዝበዛ ይካሄድባቸዋል፡፡ የተባበሩት መንግስታት አገራዊ ዘገባዎች እንደሚያስረዳው ዕድሚያቸው ከ5 እስከ 1 ዓመት የሆናቸው አንድ ሶስተኛ የሚሆኑት ሁሉም የኬንያ ህጻናት በህጻናት የጉልበት ብዝበዛ ተግባራት ላይ ተይዘው ይገኛሉ፡፡ በናይጀሪያ ከ14 ዓመት ዕድሜ በታች የሆኑ ወደ 20 ሚሊዮን የሚገመቱ ህጻናት በጣም አስቸጋሪ በሆነ እና ለረዥም ሰዓት በሚጠይቅ ስራ ላይ ተጠምደው ይገኛሉ፡፡ እ.ኤ.አ እነደ አሜሪካ የስራ መምሪያ የስራ ጥናት እንዳቀረበው፣በኢትዮያ ያሉ ህጻናት በግብርናው እና በሌሎች የቤት ውስጥ ስራ በጣም አስቀያሚ በሆነ የጉልበት ብዝበዛ ይፈጸምባቸዋል፡፡ የመረጃ ውሱንነት የገደበ ቢሆንም በጣም አስቀያሚ የሆነ የጉልበት ብዝበዛ በአፕል፣ በቡና፣ በሽንኩርት፣ በሙዝ፣ በአበባዎች እና በስኳር አገዳ ምርቶች በጣም አስከፊ የሆነ የጉልበት ብዝበዛ አለ፡፡ በግብርና ላይ የሚሰሩ አደገኛ የሆኑ መሳሪያዎችን ይጠቀማሉ፣ ከባድ ሸክም ይሸከማሉ፣ እንዲሁም ጎጂ የሆኑ ጸረ ተባዮችን ይጠቀማሉ፡፡ እንስሶችን የሚጠብቁ ህጻናት በርካታ ጉዳቶች ማለትም የመነከስ፣ በኃይል የመገፍተር፣ ወይም የመወጋት አደጋ ይደርስባቸዋል፡፡ ህጻናት በተለይም በቤት ውስጥ የሚሰሩ ልጃገረዶች ለአስገድዶ መደፈር ወይም ደግሞ ለሌላ የጥቃት ሰለባ ይሆናሉ፡፡ በኢትዮጵያ የህጻናት ማደጎን በመተግበር ህጻናቱ በልዩ ልዩ የአዕምሮ በሽታ እንዲሰቃዩ ያደርጋል፡፡ የማገዶ እንጨት የሚሰበስቡ እና ውኃ የሚያመላልሱ ከባድ ሽክም ተሸክመው ብዙ ርቀቶችን እንዲጓዙ ይገደዳሉ፡፡

የማይታዩ ህጻናት፤

በኤች አይቪ ኤይድስ ወላጅ የለሽ የሆኑ፣ የኃይል ጥቃት የሚፈጸምባቸው፣ የሚፈናቀሉ እና በጦርነት ጉዳት የሚደርስባቸው በሚሊዮን የሚቆጠሩ የአፍሪካ የማይታዩ ህጻናት አሉ፡፡ በጨነገፉ የአፍሪካ አገሮች መሪዎች የተረሱ ናቸው፡፡ እነዚህ ህጻናት በውስጥ የተፈናቀሉ ወይም ደግሞ በተፋፈገ ሁኔታ በጥገኝነት የሚኖሩ፣ ንጽህናው ባልተጠበቀ እና በሽታን ባዘለ መልኩ ህይወትን በመግፋት ላይ ይገኛሉ፡፡ በወሮበላ ወንጀለኞች በመጠለያ ካምፖች እና በሌሎች ምክንያቶች ብዙውን ጊዜ ሰለባ ላይ እንዲወድቁ ይሆናል፡፡ በተለይ በመጠለያ ካምፖች ያሉ ህጻናት ለጾታ እና ለሌሎች መሰል ጥቃቶች የተጋለጡ ናቸው፡፡ አብዛኞቹ የተፈናቀሉ እና በመጠለያ ካምፖች ውስጥ ያሉ ህጻናት በስነ ልቦና ችግር ማለትም የአዕምሮ ጭንቀት፣ ድብርት፣ ከማህበራዊ ግንኙነት መገለል፣ እና አጠቃላይ የአዕምሮ መታወክ ችግር ሊገጥማቸው ይችላል፡፡

የህጻናት ምግብ እጥረት፣

የሰብ ሰሀራ አፍሪካ አገሮች ከዓለም ከፍተኛ የሆነ የምግብ እጥረት የሚታይባቸው ናቸው፡፡ አስከፊ የምግብ እጥረት አንዳንድ ጊዜም “ድብቅ ረሀብ“ እየተባለ የሚጠራው ህጻናቱ የሚወስዷቸው ንጥረ ነገሮች (ስብ፣ ፕሮቲን፣ ቫይታሚኖች እና ማዕድኖች፣ ወዘተ) የህጻናቱ ሰውነት ከሚፈልገው በታች የሚቀርቡ ናቸው፡፡ በአስከፊ የምግብ እጥረት የተጎዱ ህጻናት በአዕምሮም ሆነ በአካል የኮሰሱ እና በቀላሉ በበሽታ የሚጎዱ ልጆች ናቸው፡፡

በኢትዮጵያ ህጻነት በተመጣጠነ ምግብ እጦት የተጎዱ ናቸው፡፡ እ.ኤ.አ በ2013 በአፍሪካ ህብረት እና በኔፓድ ዕቅድ እና አስተባባሪ ኤጀንሲ፣ በአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን እና በተባበሩት መንግስታት የምግብ ፕሮግራም በጋራ በተደረገ ጥናት “በኢትዮጵያ ከአምስት ህጻናት ሁለቱ በእድገት መቀጨጭ የሚጠቁ ናቸው“፡፡ ይህም ሊከሰት የሚችለው ህጻናቱ ወሳኝ የሆኑ ንጥረ ነገሮችን በማህጸን ላይ እያሉ ወይም ደግሞ በመጀመሪያዎቹ 5 ዓመታት ጊዜ ውስጥ ሳያገኙ ሲቀሩ ነው፡፡ 81 በመቶ የሚሆኑት የህጻናት የምግብ እጥረት እና ከዚህ ጋር ተያይዘው የሚከሰቱ በሽታዎች ህክምና አይደረግላቸውም፣ በኢትዮጵያ 28 በመቶ የህጻናት ሞት በምግብ እጥረት የሚመጣ ነው፣ በአንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች 16 በመቶ ደጋሚዎች ከእድገት መቀጨጭ ጋር የተያያዙ ናቸው፡፡ ከምግብ እጥረት ጋር በተያያዘ መልኩ በሚከሰተው የህጻናት ሞት ምክንያት የስራ ኃይሉን በ8 በመቶ ቀንሶታል፡፡

በኢትዮጵያ 67 በመቶ የሚሆነው ጎልማሳው ትውልድ በህጻንነት ጊዜው በእድገት መቀጨጭ የተጎዳ ነው፡፡ በህጻናት ያልተመጣጠነ ምግብ እጥረት ምክንያት በየዓመቱ 55.5 ቢሊዮን ብር ማለትም 16.5% የሚሆነውን የአገሪቱን ጠቅላላ ሀብት የሚሸፍን ገንዘብ ይባክናል፡፡ የእድገት መቀጨጭን ማስወገድ የእድገት እና ትራንስፎርሜሽን አስፈላጊው ደረጃ ነው፡፡” በዚህ ጥናት መቅድም ላይ አምሃ ከበደ “የኢትዮጵያ የጤና እና ስነምግብ ምርምር“ ከቢሮክራሲያዊ አካሄድ በወጣ መልኩ የሚከተለውን ጠቁመዋል፣ “የኢትዮጵያ መንግስት የእድገት እና ትራንስፎርሜሽን እቅዱን በሚተገብርበት ጊዜ የተመጣጠነ ምግብ እጥረትን የማስወገድን ጠቃሚነት ማጉላት አለብን“፡፡

የስብዕና ድህነትን ወይም የአፍሪካን የኢኮኖሚ እድገት እና ተራንስፎርሜሽንእቅድ መጋረጃን መቅደድ፣

የአፍሪካ መሪዎች፣ የእነርሱ ከፍተኛ ተከፋዮች እና ከመጠን በላይ የድህነት ወትዋቾች እና አዕምሮ የሌላቸው የብዙህን መገናኛ አስመሳይ ጋዜጠኞች አፍሪካ በመነሳት ላይ እንደሆነች እና አስገራሚ በሆነ መልኩ ተሀድሶ እና ልማትን እያካሄደች እንደሆነች እንድናምን ጥረት ያደርጋሉ፡፡ አፍሪካ የኢኮኖሚ እድገት አስመዝግባለች፣ ተሀድሶ እና ተራንስፎርሜሽን እያካሄደች ነው የሚለው የማስመሰያ ንግግር እና ስለአፍሪካ መተረት የውሸት ተረት ነው፡፡ አፍሪካ በአምራች ኢንዱስትሪዎቿ፣ ዓለም አቀፍ ንግድ እና ቱሪዝም አማካይነት በብዙ ቢሊዮን የሚቆጠር የውጭ ምንዛሬ ታገኛለች፡፡ አፍሪካ ለኢንቨስትመንት ዋና ቦታ ናት ብለው ያምናሉ፡፡ ጠቅላላ የሀገር ሀብት መጣኔ በከፍተኛ ሁኔታ እያደገ ነው ይላሉ፣ የነፍስወከፍ ገቢ በእጥፍ እና ሶስት ጊዜ እጥፍ እያደገ ነው፣ ድህነት እየከሰመ ነው እናም የአፍሪካ መካከለኛ ገቢ ያለው የህብረተሰብ ክፍል እያደገ ነው ይላሉ፡፡

አፍሪካ በአሁኑ ጊዜ ከመቸውም ጊዜ በላይ ብዙ ሚሊየነሮች እና ቢሊየነሮች አሏት፡፡ አፍሪካውያን/ት በተንቀሳቃሽ ስልክ እና በሌሎች የመገናኛ ቴክኖሎጂዎች የተገናኘች ናት፡፡ ብልህ ያልሆኑ የአፍሪካ የጨነገፉ መንግስታት መሪዎች አፍሪካ በአንድ ተኩል አስርት ዓመታት ጊዜ ውስጥ የመካከለኛ ጊቢ ያላቸውን የዓለም አገሮች ትቀላቀላለች የሚል ተስፋ አላቸው፡፡ሆኖም ግን በድህነት ወትዋቾች እና በዓለም አቀፍ የጨነገፉ መንግስታት መሪዎች መገናኛ ብዙሀን ማስመሰያ ጀርባ አንድ መሰረታዊ የሆነ ስህተት አለ፡፡ የእነርሱ ተረት ተራኪዎች ሁልጊዜ ስር የሰደደውን ሙስና ትኩረት ባለመስጠት ያናንቃሉ፣ ትልቁን የተቆለለ እዳ እና የጨነገፉ የአፍሪካ መንግስታት ለምዕራቡ ዓለም የእርዳታ እና ብድር ተቋማት ያጎበድዳሉ፡፡ ትንሽ አበጥ ላለችዋ ነገር ለአፍሪካ የኢኮኖሚ ኃይል ጊዚያዊ ችግር እንደሆነች አድርገው የማስመሰል ስራ ይሰራሉ፡፡ የግብርና ምርቶችን፣ ጥሬ እቃዎችን፣ ብረት እና ማዕድናትን ወደ ውጭ በመላክ አፍሪካ ከድህነት ትወጣለች በማለት የአፍሪካ ህዝቦችን ይዋሻሉ፡፡ ስለሆነም በእንቁዎቹ በአፍሪካ ወጣቶች መሰረት ያልተገነባውን የእድገት እና የትራንስፎርሜሽን እቅድ ማን ጉዳይ ሊለው ይችላል? አፍሪካ ልጆቿ በአስከፊ ሁኔታ በምግብ እጦት እየተሰቃዩ፣ ደካማ የትምህርት አቅርቦት እየተተገበረ፣ ዝቅተኛው የደህንነት ሁኔታ ባልተሟላበት ሁኔታ፣ በስደተኞች መጠለያ ጣቢያ ዜጎች ተረስተው በሚቀሩበት ሁኔታ እና ለሁሉም ዓይነት ኃይል እና የመብት ረገጣ በተጋለጠበት ሁኔታ ማንም በእውነተኝነት አፍሪካ አድጋለች ብሎ መከራከር ይቻለዋልን! እንደዴትስ ነው አፍሪካን ከድህነት አራንቋ| መንጥቆ በማውጣት ወደ ብልጽግና ተራራ ለማውጣት የሚቻለው? በእርግጠኝነት የወደቁት እና የስብእና ዝቅጠት ያለባቸው የወደቀችዋ የአፍሪካ መንግስታት መሪዎች አያደርጉትም!

በወጣቱ የህብረተሰብ ክፍል ከፍተኛ የሆነ መዋለ ንዋይ ካልተመደበ አፍሪካ ልታድግ አትችልም፣ ይልቁንም ትወድቃለች፣ ወድቃለችም፡፡ የአፍሪካውያንን/ትን ፍላጎት በመገደብ ተሀድሶ ማምጣት ከቶውንም አይቻልም፡፡ ከልጆች ጠንካራ ትከሻ እና ክንፍ በስተቀር አፍሪካ ከድህነት አራንቋ ልትወጣ አትችልም፣ አፍሪካ በድህነት ወጥመድ ውስጥ ተተብትባ ትቀጥላለች፣ እናም በእዳ ማጥ፣ በገንዘብ ክፍተት፣ በርሀብ፣ በእጥረት፣ በሙስና፣ በኋቀርነት እና በልመና ተቀይዳ ትቀራለች፡፡

ሆኖም ግን ወደፊት ስናይ ለአፍሪካ ወጣቶችዋ ወሳኝ ናቸው ነው፡፡ በሞይ ኢብራሂም ፋውንዴሽን እንደተጠቃለለው በሚቀጥሉት ሶስት ተከታታይ ትውልዶች 41 በመቶ የሚሆነው የአፍሪካ ህዝብ ወጣት ይሆናል፡፡ አፍሪካ በወጣት ኃይል እድገት ብቸኛዋ አህጉር ትሆናለች፡፡ ምዕራብ አውሮፓ በህዝብ ብዛት እየቀነሰ ይሄዳል፣ ላቲን አሜሪካ እና ኤሽያ የተመጣጠነ የህዝብ እድገትን ይይዛሉ፡፡ ያ ዘገባ አፍሪካ እ.ኤ.አ በ2040 የአፍሪካ ሰራተኛ ህዝብ ቁጥር ከቻይና ወይም ህንድ የሚበልጥ ይሆናል፡፡ እ.ኤ.አ በ2050 የአፍሪካ ሰራተኛ ህዝብ ቁጥር ቢያንስ ከአውሮፓ 3 ጊዜ እጥፍ በመብለጥ የዓለምን ህዝብ ሶስት አራተኛ የሚይዝ ይሆናል፡፡ ቁጥር ብቻውን ምንም ማለት አይደለም፣ ነገር ግን የአፍሪካ ወጣቶች በዓለም ገበያ ላይ ተወዳዳሪ እንዲሆኑ ግዛት፣ መንግስታት እና ገዥዎች ካላመቻቹላቸው ማሰብ ብቻውን የሚፈይደው ነገር አይኖርም፡፡

የአፍሪካ ወጣቶች በዓለም ገበያ ተወዳዳሪ ካልሆኑ በስተቀር ቀጥር ብቻውን የሚፈይደው ነገር ለመኖሩ ምን ማረጋገጫ አለ? “ለወደፊቱ ውድ የሆነውን የወጣት ህብታችንን እንዴት ነው ልንፈጥረው የምንችለው?” በማለት የሞ ኢብራሂም ፋውንዴሽን ዘገባ ጥያቄ ያቀርባል፡፡ እኔ በበኩሌም ስብዕናቸው ለዘቀጠው የአፍሪካ መሪዎች ተመሳሳይ ጥያቄ አቀርባለሁ፡፡

ኢትዮጵያ በክብር ለዘላለም ትኑር!
ሀምሌ 5 ቀን 2006 ዓ.ም

ፍርድ ቤቱ በእነ ሐብታሙ ጉዳይ ጠንከር ያለ ትዕዛዝ አስተላለፈ

July15/2014
ከዳዊት ሰለሞን
የዛሬ ሳምንት ማክሰኞ በቁጥጥር ስር እንዲውሉ የተደረጉት የአንድነት ፓርቲ ከፍተኛ አመራሮች ህገ መንግስቱና የጸረ ሸብር አዋጁ በሚያዙት መሰረት እጃቸው ከተያዘበት አንስቶ በ48 ሰዓት ውስጥ ፍርድ ቤት መቅረብ እንደሚገባቸውና በቤተሰቦቻችውና በጠበቃቸው መጉብኘት መብታቸው መሆኑን ከግምት በማስገባት ጠበቆቻቸው ያልተሟሉላቸው መብቶች በፍርድ ቤት ጣልቃ ገብነት ይከበሩ ዘንድ በዛሬው ዕለት ክስ መስርተው የማዕከላዊ አመራሮች ለቀረበባቸው ክስ በአካል በመገኘት ምላሽ ሰጥተዋል፡፡
ሃላፊዎቹ ለፍርድ ቤቱ በሰጡት ምላሽ ሰዎቹን ፍርድ ቤት በ2/11/2006 ዓ.ም ማቅረባቸውን ጠቅሰዋል፡፡የታሳሪዎቹ ጠበቆች የሆኑት ጠበቃ ተማም አባቡልጉና አቶ ገበየሁ ደምበኞቻቸውን ማግኘት አለመቻላቸውን ፍርድ ቤት ሲቀርቡም እንዲያውቁ አለመደረጋቸውን አስረድተዋል፡፡ጠበቆቹ ደምበኞቻቸውን ማየት እንዲፈቀድላቸውና በቤተሰቦቻቸውም እንዲጎበኙ እንዲደረግ ትዕዛዝ እንዲሰጥ አቤት ብለዋል፡፡
ፍርድ ቤቱ ግራ ቀኙን ካደመጠ በኋላ ታሳሪዎቹ በቤተሰቦቻቸው እንዲጎበኙ እንዲደረግና ከጠበቆቻቸው እንዲመካከሩ ይደረግ ሲል ትዕዛዝ ሰጥቷል፡፡ፍርድ ቤቱ ከዚሀ በተጨማሪም በማዕከላዊ እንደሚገኙ የተነገረላቸውን ታሳሪዎች የፊታችን አረብ 4፡00 እንዲቀርቡ ሲል አዟል፡፡የማዕከላዊ ኃላፊም በፍር ቤቱ የተሰጠውን ትዕዛዝ መፈጸሙን እንደሚከታተሉ ተናግረዋል፡፡10557351_10202411521670248_5400861717310665444_n


“አሸባሪ”ዎቹን ፍለጋ – ከተመስገን ደሳለኝ (ጋዜጠኛ)

June 15/2014
 (የሽብር – ዘፍጥረት ፫)
    ….በሁለት ተከታታይ ጽሁፎች የሽብርተኝነትን አነሳስ እና የአልሸባብን አፈጣጠር በደምሳሳውም ቢሆን መቃኘታችን ይታወሳል፡፡ በዚህም የኢትዮጵያ ጦር ወደ ሶማሊያ መግባቱ ለምስራቅ አፍሪካው አደገኛ ቡድን መወለድ መንስኤ ስለመሆኑ ከተለያዩ የመረጃ ምንጮች እና ከሞቋዲሾ እስከ ኪስማዩ በደም ከተፃፈው የሠራዊቱ አባላት ገጠመኝ መረዳት ችለናል፤ ይህ ቡድን ዛሬ ከመንግስታዊ ተቋማት ይልቅ ንፁሀን ዜጐችን ዒላማ አድርጎ፣ የቀንዱን አገራት አካባቢ ወደ ሕግ-አልባ የጦር ቀጠናነት መለወጥ የሚያስችለውን ግዙፍ ኃይል አካብቶ አስፈሪ እየሆነ ስለመምጣቱ ማስተዋሉ አዳጋች አይደለም፡፡ ለርዕሰ-ጉዳያችንም መቋጫ የምናደርገው የኢትዮጵያ መንግስት ‹‹ሽብር››ን እንዴት ለፖለቲካዊ ዓላማ እንደሚጠቀምበትና እነማንን በ‹‹አሸባሪ››ነት  ፈርጆ በመወንጀልና በማሳደድ እኩይ ተግባር ላይ መጠመዱን በጨረፍታ መመልከት በመሆኑ ወደዛው እናልፋለን፡፡
ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ
ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ
   የሽብር ድንበር…
የሽብር ድርጊትን ለዓላማቸው ማስፈፀሚያ መምረጣቸውን በይፋ አውጀው የሚንቀሳቀሱ ቡድኖች፣ በአሰቃቂ አደጋዎች በሚመነዘሩ ጥቃቶች ንፁሃንን ለህልፈትና ለከባድ ፍርሃት በመዳረግ፣ ማሕበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴዎችን በመገደብ ጥያቄዎቻቸውን በኃይል ለማስፈፀም መሞከራቸው የተለመደ ነው፤ ለዚህ ይቅር ለማይባለው ጭካኔያቸውም የድል ችቦ ለኩሰው ጮቤ ሲረግጡ በሀዘን ተመልክተናል፤ በቅርቡ በጎረቤታችን ኬኒያ ውስጥ የተፈፀሙትን ዘግናኝ የጅምላ ጥቃቶችና ፍንዳታዎችን ተከትሎ ቡድኑ የሰጣቸው መግለጫዎችም ይህንኑ ያስረግጣሉ፡፡ ከሁሉም በፊት ግን ‹‹የሽብር ድርጊት ምንድር ነው?›› የሚለው ጥያቄ ተፍታቶ መመለስ የሚኖርበት ይመስለኛል፡፡ ምክንያቱም በዳሰሳችን የምናገኘው ምላሽ ዓለም-አቀፍ ማሕበረሰቡን የሚያቀራርብ ቢሆንም፣ በተግባር ሲገለጥ ግን መጣረስ መኖሩን ማስረጃዎች ይጠቁማሉና፤ ስለዚህም የሽብርን አንድምታ ከየመንግስታቱ ባህርያት አኳያ በሁለት ምድብ ከፍለን እንመለከታለን፡፡
የመጀመሪያው በአንፃራዊነት ዴሞክራሲያዊ አስተዳደርን ማንበር የቻሉ አገራት እና ዓለም-አቀፍ ተቋማት ከሚሰጡት ብያኔ ጋር የሚያያዝ ነው፡፡ በዚህ ምድብ ሽብርተኝነት የሚያቅፈው ትርጓሜም ሆነ አደጋውን ለመከላከል የሚወጡ ሕጎች በውስጣዊ የፖለቲካ ፍላጎት (በተለይ ሥልጣንን ከሕዝባዊ ሰላማዊ ተቃውሞ ለመከላከል) ያልተቃኙ ከመሆናቸው በተጨማሪ፣ ‹የተቃዋሚ ፓርቲ አባላትንና ተቺዎችን ለማጥቃት ይውላሉ› ተብሎ አለመታሰቡ ከሞላ ጎደል ብዙሃኑን የሚያስማሙ (እንከን ባይታጣባቸውም በመግባባት የሚታለፉ) ተደርገው ይወሰዳሉ፤ የእነዚህ አካላት ብቸኛ ዓላማም አገርን እና ሕዝብን ከሰቆቃ መጠበቅ ላይ ያተኮረ እንደሆነ በመረጋገጡ ትርጓሜው ያን ያህል ሲያከራክር አይስተዋልምና ዝርዝር ነገር ከማተት ታቅበን፣ ወደ ሌላኛው ምድብ እንለፍ፡፡
በሁለተኛነት የምናነሳውና ዋነኛው ደግሞ ኢትዮጵያን ጨምሮ ወጥ-አምባገናዊ አገዛዝ በሚያስተዳድሯቸው አገራት የሚበየነውን የሽብር ድርጊት ነው፤ በእነዚህ ሥርዓታት ውስጥ ድርጊቱ አለቅጥ ከመለጠጡ በዘለለ፣ ለትርጉም አሻሚ የሆኑ አንቀፆች እንዲካተቱበት ስለመደረጉ ጉዳዩን ያጠኑ ምሁራን የደረሱበት ድምዳሜም ሆነ በተጨባጭ የታዩ የሐሰት ውንጀላዎች ያስረግጡልናል፡፡ ኩነቱን ከኢትዮጵያ አውድ አኳያ ካየነው ደግሞ ይሁነኝ ተብሎ የገዥው-ፓርቲን ስሁት ፖሊሲዎች እና አምባ-ገነናዊ ባህሪያት በድፍረት የሚተቹትን፤ እንዲሁም በሰላማዊ መንገድ የሚታገሉ የፖለቲካ ድርጅት አባላትን ለማጥቃት በ2001 ዓ.ም የፀደቀው የፀረ-ሽብር አዋጅ አንዳንድ አንቀፆች እንዲካተቱበት መደረጉን በማስረጃነት መጥቀስ እንችላለን፡፡ በተለይም ከአረቡ ፀደይ በኋላ በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ ‹‹ለሥልጣኔ ያሰጉኛል›› በሚል የጠረጠራቸውን የፖለቲካ ፓርቲ አባላት፣ ጋዜጠኞች እና አክቲቪስቶች፣ እንዲሁም ከኦሮሚያ በስመ-ኦነግ አፍሶ ካጎራቸው ንፅሃን እስከ የሙስሊም ኮሚቴዎች ድረስ በሐሰት እየወነጀለ ወህኒ ቤቱን ከአፍ እስከ ገደፉ ለመሙላት ያላዳገተውም በዚህ አስቀድሞ በዘረጋው ወጥመድ ይመስለኛል፡፡
  በርግጥ ይህን መሰሉ የገዥዎቻችን ብልጠት ዛሬ የተጀመረ አለመሆኑ አይካድም፤ ትላንት አርበኛው በላይ ዘለቀ እና ደጃዝማች ታከለ ወልደሐዋርያትን የመሳሰሉ የሀገር ባለውለታዎች፣ በአፄ ኃይለስላሴ አስተዳደር ‹‹አሸባሪ›› (ፀረ-ዘውድ) ተብለው የህይወት መስዋዕትነት መክፈላቸውን እናስታውሳለን፡፡ በኮሎኔል መንግስቱ ኃይለማርያም ዘመነ-መንግስትም ቢሆን፣ ከጄኔራል አማን አምደሚካኤል እስከ ጄኔራል ተፈራ ባንቲ፤ ከኢህአፓ እስከ መኢሶን፣ ከኦነግ እስከ ህወሓት፣ ከጀብሀ እስከ ሻዕቢያ… ያሉ የፖለቲካ ድርጅቶች እና ግለሰቦች ‹‹አሸባሪ›› (ፀረ-ሕዝብ) ተብለው ይሳደዱ፣ ይጨፈለቁና ይገደሉ እንደነበር ከታሪክ ድርሳናት በተጨማሪ እውነታውን ይመሰክሩ ዘንዳ   በህይወት የሰነበቱ የዓይን እማኞች ያስረግጣሉ፤ ኢህአዴግም በምክር ቤቱ በኩል የያዘውን ሥልጣን በመጠቀም አካሄዱን ሕጋዊ ለማስመሰል በአዋጅ የደነገገው ይህንን የቀደመ ስልት በመኮረጅ ነው ብዬ አምናለሁ፡፡
ስጋታችን ማነው?
አሸባሪ ቡድኖች ብዙውን ጊዜ የሚያቀነቅኑትን ፖለቲካዊ እና ኃይማኖታዊ አጀንዳዎችን ለማስፈፀም የየትኛውንም አገር ሕግ ከመጣሳቸውም በዘለለ ደም-አፋሳሽን በመሰለ አሉታዊ ገፅ የሚሸፈኑ መሆኑ እውነት ነው፤ ከዚህ ተነስተንም ስለጉዳዩ በምክንያታዊነት እንነጋገር ከተባለ፣ በዛሬይቷ ኢትዮጵያ ቀንደኛው የስጋት ምንጭ ምንድር ነው? ብሎ ወሳኝ ጥያቄ ከማንሳት መጀመርን ግድ ይላል፡- በተጨባጭ ሀገሪቷን በታሪክ-አልባነት ለማፈራረስ ያንዣበበብን አደጋ የቱ ነው? ሥርዓቱ ያነበረው የጎሳ ፌደራሊዝም ወይስ እስክንድር ነጋ? የዕድገት ማነቆስ? አለቅጥ የተንሰራፋው መንግስታዊ ሙስና ወይስ እነርዕዮት ዓለሙ እና ውብሸት ታዬ? አንገብጋቢው ችግራችንስ? በአስደንጋጭ ሁኔታ እያሻቀበ ያለው ሥራ-አጥነት ወይስ እነአንዱአለም አራጌ እና በቀለ ገርባ? ተቻችሎ የመኖር እንቅፋትስ? የመንግስት በግላጭ በኃይማኖት ጉዳይ ጣልቃ መግባት ወይስ እነአቡበከር መሀመድ? በርሃብ እንደ ቅጠል ለመርገፋችንስ? አስከፊው ድህነት ወይስ አንዳርጋቸው ጽጌ? የዲሞክራሲ ጋሬጣስ? ከአገዛዙ የተለየ የፖለቲካ አመለካከት አራማጆችን በኃይል ማፈን ወይስ እነተስፋዓለም ወልደየስ? ለሕግ የበላይነት አለመከበርስ? ፍትህን በገንዘብ ሊገዛ ለከጀለ ባለጊዜ መቸርቸር ወይስ ‹በሰላማዊ መንገድ የሥርዓት ለውጥ እናመጣለን› በሚል የተደራጁ የፖለቲካ ፓርቲ አባላትን ማሳደድ? …ለእነዚህና መሠል ጥያቄዎች አመክንዮአዊ ምላሽ ማግኘት ቀዳሚው ተግባር ይመስለኛል፤ ምላሾቹም ለአጠቃላይ አገራዊ፣ ፖለቲካዊ፣ ማሕበራዊ እና ኃይማኖታዊ ችግሮች የማያዳግም መፍትሔ መስጠት
አይሳናቸውም ብዬ አስባለሁ፡፡
ማነው አሸባሪ?
ምንም እንኳ ጥያቄው ተራ ቢመስልም፣ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የተስተዋለው የሀገራችን ተጨባጭ እውነታ የሚነግረን ከሚታሰበው በተቃርኖው ነው፡፡ ጉዳዩን ያከረረው ገፊ-ምክንያትም አገዛዙ የሽብርን ትርጓሜ በፈለገ ወቅት ለጥጦ በመጠቀሙ ብቻ አይደለም፤ ይልቁንም ሁሉም የሀገሪቱ ዜጋ በማንኛውም ሰዓት ሊወነጀልበት እንደሚችል እያሰበ በፍራሃት ተሸብቦ ሰጥ-ለጥ ብሎ እንዲያድር በማስገደዱም ጭምር ነው፡፡ ከጥቂት ዓመታት በፊት ኦነግ፣ ኦብነግ እና ግንቦት 7 እንደ አልቃይዳ እና አልሸባብ ሁሉ ‹‹አሸባሪ›› ድርጅቶች ተብለው መፈረጃቸው አይዘነጋም፡፡ ይሁንና እነዚህ አገር-በቀል ድርጅቶች ፖለቲካዊ ጥያቄዎቻቸውን የጦር መሳሪያ በማንገብ ለመፍታት የሚከተሉት መንገድ ‹ትክክል ነው፣ አይደለም›ን ጉንጭ አልፋ እሰጠ-እገባ ለጊዜው ወደጎን ብለን፣ የትጥቅ ትግል መስመርን ለምን መረጡ? የሚለውን የጨረፍታ ፍተሻ አናስቀድም፡፡
በቅድሚያም የኦሮሞ ሕዝብ ነፃ አውጪ ግንባር (ኦነግ) ያለፈበትን ጥምዝምዞሽ ብንመለከት የምናገኘው እውነታ፣ ዛሬ በ‹‹አሸባሪ››ነት ከወነጀለው ኢህአዴግ ጋር በመተባበር የደርግ ሥርዓትን ለመቀየር ከመታገሉም በላይ በድሉ ማግስት የጋራ መንግስት መስርቶ፣ ለአንድ ዓመት ከመንፈቅ አካባቢ በጋራ ሀገር ሲያስተዳድር መቆየቱን የሚያስረግጥ ነው፤ ውሎ አድሮ አብዮታዊ ግንባሩ ‹ኦሮሚያን ያለከልካይ መቆጣጠር› የሚለውን ያደረ ትልሙን ለመተግበር፣ ትልቅ እንቅፋት የሆነበትን ኦነግን ከመንግስታዊው ሥልጣን ማባረር ቀንደኛ የቤት ሥራው በማድረጉ፤ ‹‹ሰላማዊና ሕጋዊ›› ተብሎ የተለፈፈለት የምርጫ ውድድር ሊካሄድ የቀናት ዕድሜ ሲቀሩት በስውር እጁ ጠምዝዞና አዋክቦ ከውድድሩ እንዲወጣ ማስገደዱን እንረዳለን፡፡ ይህንንም ተከትሎ ኦነግ የጣለውን ጠብ-መንጃ አንስቶ በኃይል ሥርዓቱን ለማስወገድ ‹‹ዱር ቤቴ!›› ብሎ ተመልሶ በርሃ መግባቱ ባይካድም፣ ወደዚህ ጠርዝ ለመገፋቱ ግን ዋነኛ ተጠያቂው (ኃላፊነት የሚወስደው›) ማን ነው? ብለን ብንጠይቅ መልሱ ቀላልና ግልፅ ነው፡፡    ሌላው በዚህ አውድ ሊጠቀስ የሚችለው ግንቦት 7 ነው፤ እንደሚታወሰው የዚህ ድርጅት ግንባር ቀደምት መስራቾች፣ በ1997ቱ ሶስተኛው ሀገር-አቀፍ ምርጫ ቅንጅቱን ወክለው ተወዳድረው እንዳሸነፉ ቢነገርም፣ ኢህአዴግ የቀድሞው ልምዱን በመጠቀም ‹‹ጨዋታው ፈረሰ፤ ዳቦ ተቆረሰ›› ብሎ ሁሉንም ከያሉበት ለቃቅሞ ወህኒ ቤት አጉሯቸው ሲያበቃ፤ እንዳሻው በሚቀልድበት ካንጋሮ ፍርድ ቤት አቅርቦ የዕድሜ ልክ እስራት ቅጣት ማስጣሉ የትላንት ትውስታችን ነው፡፡
እንግዲህ በዚህ አይነቱ በተቀነባበረ ሰው-ሰራሽ እሳተ-ጎመራ እንዲፈተኑ የተገደዱ ፖለቲከኞች፣ ያውም በቅድመ-ሁኔታ ከእስር ሲለቀቁ፣ እንደ ኢትዮጵያዊነታቸው ‹ለሀገራችን የሚበጅ ርዕዮተ-ዓለም አለን› ብለው ለትግል ከቆረጡ፣ የሚኖራቸው አማራጭ ምን ሊሆን ይችል ነበር? ብለን ብንጠይቅ፣ ሁላችንንም ሊያሳምን የሚችል ድምዳሜ ላይ መድረስ ቢሳነን እንኳ፣ ዛሬ ለመረጡት የትግል ስልት አሁንም ኃላፊነቱ ዞሮ ዞሮ መንግስታዊ ሥልጣን ከያዘው ኃይል ትከሻ ላይ እንደማይወርድ እሙን ነው፡፡
ከዚህ ባለፈ ኢህአዴግ ሀገሪቷ የ‹‹አሸባሪ››ዎች ዒላማ መሆኗን ለማሳየት የሚጠቅሳቸው (ባለቤት ያላቸውም፣ የሌላቸውም)፣ በአዲስ አበባ አንዳንድ ሆቴሎች እና ሚኒባስ ታክሲዎች ላይ የተፈፀሙ ህይወት-ቀጣፊ አሳዛኝ ፍንዳታዎችን በተመለከተ ከዚህ ቀደም ከ‹‹ፍትሕ›› ጋዜጣ ጀምሮ ‹‹ፋክት›› መጽሔት ድረስ ባሉ የሚዲያ ውጤቶች በስፋት የተዘገቡ በመሆኑ መድገሙ አስፈላጊ አይደለምና አልፈዋለሁ፡፡ በግልባጩ የአልሸባብ አሸባሪነትንም ሆነ በኢትዮጵያ ላይ ጥቃት ለመሰንዘር ያለው ብርቱ ፍላጐት ለማንም ስለማያጠራጥር፣ የመንግስት ቀዳሚ ተግባር ሀገሪቱንና ዜጎቿን ከየትኛውም አደጋ መጠበቅ በመሆኑ፣ ከዚህም በላቀ ለጉዳዩ ከፍተኛ ትኩረት መስጠት እንዳለበት እገነዘባለሁ (ይህ ጥንቃቄ ጥልቅ ከሆነው ድህነታችን አንፃር በጥቅም ተማልለው በግብረ-አበርነት ሊሳተፉ የሚችሉ ወንድም-እህቶችንም በአይነ-ቁራኛ መከታተልን ያካትታል)፡፡ ምክንያቱም እውነተኞቹ የሽብር ኃይሎች (በመለስ ዜናዊ አገላለፅ ‹‹ፕሮፌሽናሎቹ››) የሰናፍጭ ታህል ቀዳዳ ካገኙ ዘግናኝ የሕዝብ እልቂት እና ከባድ የንብረት ውድመት ከማድረስ እንደማይመለሱ ከኬኒያ ክራሞት መረዳት ይቻላል፡፡
በተጨማሪም ከሥርዓቱ የተለየ የፖለቲካ አመለካከት ያላቸው ድርጅቶች፣ ጋዜጠኞች፣ የመብት ተሟጋቾችም ሆኑ ዜጎች… አልሸባብን የመሳሰሉ ኃይሎችን ለመከላከል በሚደረገው ጥረት እኩል ኃላፊነትና ግዴታ እንዳለባቸው አልዘነጋውም፡፡ ይህ ማለት ግን በተጭበረበረ ምርጫ ባሸነፉ የገዢው ፓርቲ አባላት የተሞላው የሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት፣ የዓይኑ ቀለም ያላማረውን በሙሉ ‹‹አሸባሪ›› ብሎ እያሳደደ የሚፈርጀውን እንደወረደ በመቀበል ማውገዝ አለመሆኑን ማስታወስ እወዳለሁ፡፡ በግሌም ከአልቃይዳ እና አልሸባብ በቀር፣ ሌሎቹ ድርጅቶች የሚከተሉት የትግል ስልት ሕጋዊና ሰላማዊ አለመሆኑ ባይካድም፣ የብሔራዊ ቡድናችንን እግር ኳስ ጨዋታ ለመመልከት በአዲስ አበባ ስታዲየም የሚሰበሰበው ዜጋን፣ አሊያም በሕዝብ የመጓጓዣ አገልግሎት ታጭቆ የሚጓዝ ንፁሃንን የጥቃት ዒላማ አድርገው ሲንቀሳቀሱም ሆነ ሲተግብሩ አለመታየታቸውንም፤ አለመሰማታቸውንም እመሰክራለሁ፤ በ‹‹ማኒፌስቶ››አቸውም ውስጥ ሲቪሉ ኢትዮጵያዊን በአሳቻ ቦታ ባጠመዱት ፈንጂ ስለማጋየት የሚያወራ ሽራፊ አንቀፅ አላነበብኩም፤ በአጠቃላይ ሰላማዊ ዜጋን በሽብር ድርጊት ለማመስ የቀመሩትን ‹‹ስትራቴጂ›› የሚያጋልጥ ጥናትም ሆነ የውስጥ-አወቅ መረጃ አጋጥሞኝ አለማወቁን  አልሸሽግም፡፡ …የሆነው ሆኖ በኢትዮጵያችን የ‹‹ሽብር›› ዘፍጥረት ቅድመ-ታሪክ ከሞላ ጎደል ይህን ይመስላል ብዬ አምናለሁ፡፡
   በተቀረ የአል-ቃኢዳውን አይማን አልዘዋሀሪ፣ አሊያም የአልሸባቡን አህመድ አብዲ ጎዳኔ፣ ወይም የቦኮ-ሀራሙን አቡበክር ሼኩ የመሰለ በለዒ-ሰብ፣ ከኢትዮጵያውያን ‹‹አሸባሪ››ዎች መካከል ፈልገን የምናገኝ አይመስለኝም፤ ሌላው ቀርቶ ከሳሹ ኢህአዴግም የታሳሪዎቹን ንፅህና ከማንም በላይ አሳምሮ ያውቀዋል፡፡ ሆኖም ሀገሪቱ ኢትዮጵያ ነችና፣ በደነበረና ምርጫ በተቃረበ ቁጥር ‹‹አሸባሪ›› በሚል የሀሰት ወንጀላ ፖለቲከኞችን፣ ጋዜጠኞችን፣ የመብት ተሟጋቾችን…  ለእስርና ስቅየት የሚዳርግበት በስዩመ ጠብ-መንጃ ሥልጣን ራሱን ከቀባ ከሁለት አስርታት በላይ ተቆጥሯል፤ መስከረም እስኪጠባም ድረስ ይኸው የነፍጠኝነት ዘመን መቀጠሉ አይቀሬ ይሆናል፡፡   በነገራችን ላይ እስከዚያው አቶ አንድአርጋቸው ጽጌ ሰሞኑን ከየመን ተይዞ ሞት ለፈረደበት የኢትዮጵያ መንግስት ተላልፎ መሰጠቱን ሰምተናል፤ በርግጥ የመን ከዚህ የሰው ንግድ ገበያ ምን እንዳተረፈች የተገለፀ ነገር የለም (መቼም በደጉ ዘመን፣ አክሱማውያን ያስገብሯት የነበረችው ምድረ-አረብ፣ ይህ አይነቱን ያውም የራስን ሀገር ክብር የሚነካ ውለታን በብላሽ ፈፀመች ቢባል ማን ያምናል?) እንደዚያም ሆኖ ግን የአምባ-ገነኑ መሪያችን የአቶ መለስ ዜናዊን ህልፈት በሰማን ጊዜ እንደ ሰው እንዳዘንነው ሁሉ፣ እንዳርጋቸው ጽጌም ከአፄው ዘመን ጀምሮ በእምነቱ ፀንቶ ጉልበታም አገዛዞችን ሲገዳድር ከአርባ ዓመት በላይ ዋትቶ ዋትቶ፤ ዛሬ ሞቱን በሚሹ ሰዎች እጅ በመወድቁ ሊደርሰበት በሚችለው መከራና ስቀየት ከልብ ከማዘን ያለፈ የማደርገው ነገር ባይኖርም፣ ‹የኢትዮጵያ አምላክ ብርታቱን ይስጥህ› ማለትን
ወደድኩ፡፡
              እንደ መውጫ
ዘርፈ-ብዙ በሆኑ የግንኙነት ሰንሰለቶች እየተጠላለፈ ከመጣው የዓለም ገፅታ ተገንጥሎ ጉልበተኛ ሥርዓት ይመሰረትበት የነበረው የአምባ-ገነንነት ዘመን ጀምበር እየጠለቀበት ይመስላል፡፡ ከኢኮኖሚያዊ ወዳጅነት እስከ ፖለቲካዊ ስምምነቶች ያሉ የትብብር ውሎችም አስገዳጅ በሆኑ ሕጋዊ ማዕቀፎች መጠፍነግን የመሰለ ጫና ስለማሳረፋቸው ከሁነቱ ለማፈንገጥ የሞከሩ ጥቂት የማይባሉ አገራትን የማታ ውድቀት ማስታወሱ በቂ ነው፡፡ በተለይም ከቀዝቃዛው ጦርነት ወዲህ የተስተዋሉ ታሪካዊ ክስተቶች ዓለምን በማጥበባቸው፣ በተደጋጋሚ አምባ-ገነን አስተዳደርን ያስተናገዱ አገራት እንኳ ሳይቀሩ፣ በአዲስ ፖለቲካዊ ልምምድ እንዲቃኙ የዕድል በር ተከፍቶላቸዋል፡፡ ነገም  የለውጡን መንፈስ በመቃወም ለዲሞክራሲያዊ ሥርዓት ለመንበርከክ አሻፈረኝ የሚሉ መንግስታትም፣ ከድንገቴው ፍርስራሾቻቸው ሥር ትውልዱ የነፃነት ብርሃን ይጎናፀፍ ዘንድ ዘመኑ ስለመፍረዱ ለመናገር ነብይ መሆንን አይጠይቅም፡፡ በእኛይቷ ኢትዮጵያም ተወደደም ተጠላ ከሁለት አስርታት በላይ እንደ ምርጊት የተጣበቀብን ኢህአዴጋዊ አስተዳደር የመጨረሻ ስንብት፣ በዚህ መንገድ ስለመበየኑ አስተማመኝ ፍንጮች መታየታቸውን በድፍረት እመሰክራለሁ፡፡ እልፍ አእላፍ እግሮችም ወደ የለውጥ አደባባዩ የማምራታቸውን ብልጭታ፣ የትኛውም ምድራዊ ኃይል ሊያጨልመው ይችላል ብሎ ማሰቡ ፈርኦናዊ መታበይ ካልሆነ በቀር አንዳችም ፋይዳ አይኖረውም።
ይሁንና አገዛዙ እንዲህ በውድቀቱ ዋዜማ ላይ ቆሞም በክፋት መፀናቱ ጥቂት ጥያቄዎችን እንድናሰላስል ይገፋል፡- ይህ አይነቱ የናዳ መዓት ተንከባሎ እስኪያደባየው ድረስ ስለምን በግትርነት ቆሞ ይጠብቃል? ሊገታው የማይችለውን ማዕበል በመጋፋትስ፣ በእናት አገር የእንባ ጎርፍ ውቂያኖስ መፍጠርን ስለምን መረጠ? እንዲህ የትውልድ ደም በከንቱ ለማፍሰስስ ስለምን አሰፈሰፈ? የሀገሪቱ ዕጣ-ፈንታ በጠብ-መንጃ ብቻ ይወሰን ዘንድ ስለምን ጨከነ? …ርግጥ ነው የእነዚህ ጥያቄዎች ምላሾች ሟርትም ይሁን ገድ፣ በሀገሬ ምድር አዲስ የታሪክምዕራፍ የመገለጡን አይቀሬነት ቅንጣት ጥርጣሬ ውስጥ አይከቱትም፡፡ በአናቱም ዛሬ አገዛዙን በትጥቅ ትግል ለመፋለም ከአስራ አንድ የማያንሱ ቡድኖች ‹‹ክተት›› አውጀው በርሃ መግባታቸው፣ የደርግን የመጨረሻዎቹ ቀናት ማስታወሱ አንዳች የሸሸገው ምስጢር አይኖረውም ማለት ታሪክን በቅጡ አለመረዳት ይሆናል፡፡
የሆነው ሆኖ የኢህአዴግ እምቢ-ተኝነት አውዳሚ ጥፋት ሊያደርስ ቢችልም እንኳ፣ በሂደቱ የምንሻገራቸው አደጋዎች፣ የምንወጣቸው አቀበቶች፣ የምንወርዳቸው ቁልቁለቶች፣ የምናቋርጣቸው ጫካዎች… የማታ ማታ ዴሞክራሲያዊ ሥርዓት ማዋለዳቸው አይቀሬ ነው፡፡ በዚህ ሁሉ ትንቅንቅ መካከልም ለዘመናት የልዩነት መንስኤ የሆኑት፣ ከርዕዮተ-ዓለም እስከ ኃይማኖት፤ ከኢኮኖሚ ሥርዓት እስከ መሬት ይገባኛል ድረስ የሚመዘዙ ጥያቄዎች የሚያደርሱት ኪሳራ በሀገር ፍርሰት፣ በትውልድ እልቂት ሳይወራረድ በፊት፣ በሰላማዊ መንገድ መፍታት ይቻል ዘንድ የኢህአዴግን እጅ ከመጠምዘዝ ጎን ለጎን ብሔራዊ እርቅን አሳክቶ በድል ጎዳና በዝማሬ ለመትመም ሁላችንም የፖለቲካ ልዩነትን ለጊዜው ወደጎን ብለን በአንድነት እንድንቀሳቀስ ያስገድደናል፡፡ ይህንን ተልዕኮ ለማሳካትም ከክር የቀጠነው ብቸኛ አማራጫችን ደጋግመን የተነጋገርንበት ‹‹የሕዳሴ አብዮት›› ነው ብዬ አምናለሁ፡፡
ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር!

Tuesday, July 15, 2014

Ethiopia: CPJ condemns closed court hearings

July 15, 2014

CPJ condemns closed court hearings for nine Ethiopian journalists

Nairobi, July 14, 2014–The Ethiopian government should end its politicized prosecution of nine Ethiopian journalists arrested in April. The journalists and their lawyers were shut out of court room hearings in recent days.Committee to protect journalists
In hearings at the Arada First Instance Court in the capital Addis Ababa on Saturday and Monday, police said that they had wrapped up their investigation into the nine journalists–who were arrested on April 25 and 26–and referred the case for trial to the Federal High Court, according to local journalists, who spoke to the detective leading the investigation. Neither the defendants nor their lawyers were present.
Authorities have held the journalists without informing them of any charges for 80 days at Maekelawi Prison, and only recently allowed family to visit, local journalists told CPJ.
A public prosecutor originally accused the nine detainees–editor Asmamaw Hailegiorgis, freelancers Tesfalem Waldyes and Edom Kassaye, and bloggers Abel Wabella, Atnaf Berhane, Mahlet Fantahun, Natnail Feleke, Zelalem Kibret, and Befekadu Hailu–of working with foreign human rights organizations and using social media to create instability in the country, according to news reports.
“Ethiopian authorities are trying to create the impression that this is a legal matter, when in fact it is retaliation and an attempt to silence government detractors,” said CPJ East Africa Representative Tom Rhodes. “We call on the government to release the journalists immediately and end the practice of jailing its critics.”
The bloggers are part of a critical collective known as Zone 9, a name derived from Kality Prison where political prisoners and journalists are held. The group, who published under the motto, “We Blog Because We Care,” had suspended publishing for seven months after harassment by security agents, according to the blog. The arrests followed an April 23 announcement on Facebook that the group would resume publishing. The bloggers are all young professionals; Ambo University fired one of the detainees, lawyer and lecturer Zelalem Kibret, this month for not showing up for work, according to news reports.
Local journalists say the other three journalists–Asmamaw, senior editor at the influential privately owned weekly magazine Addis Guday, and freelancers Tesfalem and Edom–may have been arrested on suspicion of being affiliated with the Zone 9 group.
The date for the next hearing at the Federal High Court is not clear. The journalists’ defense lawyer, Ameha Mekonnen, told a news website dedicated to the journalists’ plight that he plans to file a lawsuit challenging the legal process at the High Court.
CPJ’s repeated attempts to reach Information Minister Redwan Hussein were unsuccessful.

አብርሃ ደስታ ተደብድቦ ፍርድ ቤት ቀረበ

July 15/2014
 በትግራይ እየተካሄዱ ያሉ ወቅታዊ ጉዳዮችን በመዘገብ ይታወቃል። ለእውነት ሲቆም እንጂ፤ ለህይወቱ ሲሰጋ አይተነው አናውቅም። አብርሃ ደስታ ስራው መምህርነት ሲሆን፤ የአረና ፓርቲ የህዝብ ግንኙነት ሃላፊም ነው። የትግራይ ተወላጅ ሆኖ ስለትግራይ መጥፎ በመዘገቡ የተናደዱበት ይመስላል። ባለፈው ሳምንት ትግራይ ውስጥ ታፍኖ ወደ አዲስ አበባ ማእከላዊ ፖሊስ እስር ቤት መምጣቱን ዘግበን ነበር። እዚህ ማእከላዊ እስር ቤት ውስጥ ብቻውን መታሰሩ እና በከፍተኛ ሁኔታ መደብደቡ አዲስ የደረሰን ዘገባ ነው።
አብርሃ ደስታ ጠያቂም ሆነ ጠበቃ የለውም። ከድብደባው የተነሳ በጣም መዳከሙ ነው የደረሰን ዘገባ የሚያመለክተው። በፍቃዱ ጌታቸው ከአዲስ አበባ እንደዘገበው ከሆነ፤ አብርሃ ደስታ እንዳይታይ በማሰብ ለሊት ነበር እስር ቤት ያስገቡት። ይህ ብቻ አይደለም። በሚገርም ወይም ታይቶ በማይታወቅ ሁኔታ በኢትዮጵያ ሰአት አቆጣጠር ከለሊቱ 6፡30 ለሱ በተሰየመ ፍርድ ቤት ቀርቦ እንደነበር ለማወቅ ተችሏል። ለማወቅ ያልቻልነው ነገር፤ የፍርድ ቤቱ ሂደት፣ የክሱ ጭብጥ እና ይዘት ምን እንደሚመስል ነው። ነገሩን እንደ አንድ ተቃዋሚ ብቻ ሳይሆን እንደሰው ስናስበው ትክክል አይመስልም። አንድን ሰው አፍኖ አምጥቶ፤ ደብድቦ እና አሰቃይቶ ፍርድ ቤት ማቅረብ የደረስንበትን የፍትህ ዝቅጠት የሚያሳይ ነው።
አብርሃ ደስታ በተደጋጋሚ ሲናገር “የትግራይ ህዝብ የህወሃት ደጋፊ አይደለም” ይል ነበር። ለነገሩ የህወሃት ታጋዮች የሞቱት እና የተሰዉት እንደአብርሃ ደስታ ያሉ ሰዎች በግፍ ታፍነው እየተደበደቡ ለፍርድ እንዲቀርቡ ከነበር ያሳዝናል። ህወሃትን እንደግፋለን የሚሉ የትግራይ ተወላጆች ጭምር “የመስዋዕትነት ውጤቱ ይህ ነው?” ብለው እራሳቸውን መጠየቅ አለባቸው።
የአረና ፓርቲም አንድ አባሉ ታፍኖ እና ታስሮ ሲወሰድ በዝምታ መመልከት የለበትም። የመግለጫ ጋጋታ የታሰሩትን ባያስፈታም፤ አቋምን ማሳወቂያ መንገድ ነውና መግለጫ ማውጣት አስፈላጊ ነው። የይስሙላ ቢሆንም ለሰባዊ መብት ጠባቂ ድርጅትም ቢሆን ማሳወቅ ያስፈልጋል። ከምንም በላይ ግን አንድነት ፓርቲ እንዳደረገው በህገወጥ መንገድ ዜጎችን የሚያስሩትን ሰዎች ለፍርድ ማቅረብ ያስፈልጋል። ቢሰራም ባይሰራም የህጉን መንገድ ደጋግመን ልንሄድበት ይገባል። ለዛሬው እዚህ ላይ አበቃን።

በኖርዌ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያኖች በእልህና በቁጣ የተሞላ ታላቅ ሰላማዊ ሰልፍ አደረጉ

July 15/2014
ሰኞ ጁላይ 15, 2014 የዲሞክራሲያዊ ለውጥ በኢትዮጵያ ድጋፍ ድርጅት በኖርዌ አዘጋጅነት በኖርዌ ኦስሎ በተለያዩ ከተሞች የሚኖሩ ቁጥራቸው በርከት ያሉ ኢትዮጵያውያኖች በአንድ ላይ በመሰብሰብ ከቀኑ 13፡00 ጀምሮ በአቶ አንዳርጋቸው ፅጌ የግንቦት 7 የፍትህ የነፃነትና የዲሞክራሲ ንቅናቄ ዋና ፀሃፊ በየመን የፀጥታ ኃይሎች ታፍነው በአምባገነኑ ወያኔ እስር ቤት መታሰራቸውን በመቃወም እና በተጨማሪም አቶ ኦኬሎ አኳይ የኖርዌይ ዜግነት ያላቸውና በኖርዌ ሃገር ይኖሩ የነበሩ የቀድሞው የጋምቤላ ክልል ፕሬዘዳንት ከሱዳን በወያኔ የደህንነት ኃይሎች በግፍ ታፍነው መወሰዳቸውንና በወያኔ እስርቤት ታስረው ለሞት ፍርድ መዳረጋቸውን በመቃወም ድምጻቸውን ሲያሰሙ ውለዋል።

ሰልፈኞቹ መነሻቸውን በኖርዌጅያን የውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር ያደረጉ ሲሆን በዛው በኖርዌጅያን የውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር በመገኘት የወያኔን ህገወጥ አፈና እና እስራት የሚቃወሙ የተለያዩ መፈክሮችን በመያዝና በማሰማት የተቃውሞ ድምጻቸውን አሰምተዋል። በስፍራው የነበሩ ሰልፈኞቹ ሲያሰሟቸው ከነበሩት መፈክሮች መካከል በጥቂቱ ኦኬሎ አኳዮ ይፈታ፣ ኖርዌይ ዜጋሽ ኦኬሎ አኳዮ የት ነው ያለው?፣ ኦኬሎ አኳዮ አሸባሪ አይደለም የሚሉ የተለያዩ መፈክሮች ይገኙበታል ::በማያያዝም ሰልፈኞቹ የኖርዌ መንግስት ለአምባገነኑ የወያኔ መንግስት የምትሰጠውን እርዳታ እንድታቆምም ጠይቀዋል:: በእለቱ የተዘጋጀውን ደብዳቤ የዲሞክራሲያዊ ለውጥ በኢትዮጵያ ድጋፍ ድርጅት ኖርዌይ ምክትል ሊቀመንበር አቶ ዳንኤል አማካኝነት ለውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር ተወካይ አስረክበዋል። ተወካይዋም ደብዳቤውን ከተቀበሉ በኋላ ጉዳዩ ን እንደሚያዩትና ችግሩ አሳሳቢ ከመሆኑም አኳያ በትኩረት እየተከታተሉት እንደሆነ አሣውቀዋል። በመቀጠልም ሰልፈኞቹ በቀጥታ ጉዟቸውን ወደ እንግሊዝ ኢምባሲ በማቅናት ታላቅ እልህና ቁጣ የተቀላቀለበት ደማቅ ሰላማዊ ሰልፍ ያደረጉ ሲሆን በዛው በእንግሊዝ ኢምባሲ ፊት ለፊት በመሆን የተለያዩ መፈክሮችን በመያዝ በታላቅ ጩህትና በስሜት ሲያሰሟቸው ከነበሩት መፈክሮች መካከል Britin were is you citizen, Free Andrgachew Tsige, where is your action, stop discrimination among citizens, we are all Andrgachew Tsige, Brtain dont support terrirost regim in Ethiopia የሚሉት ይገኙበታል::

እነዚሁ በኖርዌ የሚኖሩ ኢትዮጵያ ሰልፈኞች በዚሁ በእንግሊዝ ኢምባሲ ፊት ለፊት በመገኘት ባለፈው ጁላይ 3, 2014 ሰልፍ ማድረጋቸው ይታወሳል::የዛሬው ሰልፍ ከባለፈው ሰልፍ እጅግ በጣም ለየት የሚያደርገው ነገር ቢኖር ሰልፈኞቹ በጠቅላላ እኔም አንዳርጋቸው ፅጌ ነኝ የሚል የአንዳርጋቸውን ምስል የያዘ ቲሸርት የለበሱ ሲሆን ለሰልፉም ድምቀትን በመስጠት ለነጻነት ታጋዩ ለአቶ አንዳርጋቸው ፅጌ ያላችውን ፍቅር በአደባባይ ያስመሰከሩ ሲሆን የተቃውሙ ሰልፉም በሰልፈኞቹ ቁጣና እልህ የተሞላበት እንደነበር ለማየት ተችሏል::ሰልፈኞቹም የያዙትን ደብዳቤ በሰልፉ አዘጋጅ ኮሚቴ ተወካይ በአቶ ዳዊት መኮንን በኩል ለእንግሊዝ ኢምባሲ ተወካይ ያስረከቡ ሲሆነ ተወካይዋም ጉዳዩ እንዳሳሰባቸው፣ በትኩረትና በቅርበት እየሰሩ መሆኑን እንዲሁም አቶ አንዳርጋቸው ፅጌ ነፃ እስኪወጡ ድረስ የተቻላቸውን ሁሉ እንደሚያደርጉና ክትትላቸውን እንደሚቀጥሉ ለሰልፈኛው አሳውቀዋል።

 በመጨረሻም ሰልፈኞቹ በአንድ ላይ በመሆን የግንቦት 7 ህዝባዊ ኃይል መዝሙር ላንቺ ነው ሐገሬ ላንቺ ነው ላንቺ ነው ኢትዮጵያ ላንቺ ነው የሚለውን ህዝባዊ መዝሙር በደማቅና በሀገራዊ ስሜት ዘምረው ዝግጅቱ በተሳካ ሁኔታ ከቀኑ 15፡00 ተጠናቋል።
ሁላችንም አንዳርጋቸው ፅጌ ነን!!!
ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ!!!