Saturday, July 5, 2014

አንዳርጋቸው ጽጌ፣ የስደተኛው “ሲኦል ምድር ” የመን እና የእኛ ስጋት …

Andargachew TsigeJuly5/2014
እግረ መንገድ…
   ሰሞነኛው የአቶ አንዳርጋቸው ፅጌ በየመን መታገትና ወደ ኢትዮጵያ የመተላለፍ ዜና ብዙዎችን እያነጋገረ ያለ ጉዳይ ሆኗል። በአረብ ሃገር የሚገኙን ጨምሮ ኢትዮጵያውያንን በመላ አለም ከአድማስ አድማስ በተቃውሞና በድጋፍ እያነቃነቀም ይገኛል። 
   
   ምሽቱን በፊስ ቡክ በ Facebook ማህበራዊ ገጽ ከተንሸራሸሩት አስተያየቶችና ወቅታዊ መወያያ ርዕሶች መካከል የአቶ አንዳርጋቸው ጽጌ መታገት ሲሰማ የመን አቶ አንዳርጋቸው ጽጌን ለኢትዮጵያ መንግስት አሳልፋ እንደምትሰጥ ምንጩን ሳይነግረን መረጃ ያቀበለን የአውራምባ ታይምስ አዘጋጅ ዳዊት ከበደ ያስተላለፈው የማወያያ መጠይቅ አስገርሞ አሳዝኖኛል። ዳዊት በዚህ መጠይቁ”…አቶ አንዳርጋቸው የኢትዮጵያ ፖስፖር ይዞ መቆየት የለበትም ትላላችሁ ? ” በማለት ዳዊት ራሱ ለመረጃ ቅርብ እንደሆነ ባለሙያ በአለማችን ነባራዊ ሁኔታ የነጻነት ታጋዮችን ሁለንተናዊ እንቅስቃሴ እያወቀ እንዳላወቀ ሆኖ በለቀቀው በሚመስለኝ መጠይቁ ሊያወያየን ከጅሏል…

    ወዳጀ የአውራንባው ታይምስ ጋዜጠኛ  ዳዊት Dawit Kebede ይህን ጉዳይ ሲያነሳ በዘመነ ደርግ  “ሽፍታ ፣ ወንበዴ እና ገንጣይ! ” በሚል ስም ይወገዙ የነበሩት የወያኔ መሪዎች በሃገር ቤት ፣ እውቁ የነጻነት ታጋይ ኔልሰን ማንዴላ ፣ የኩርዱ ነጻነት ታጋይ ኦጀላንን ጨምሮ በርካታ በአለማችን የምናውቃቸው የነጻነት ታጋዮች አንባገነን የሚሉትን መንግስት ለመጣል የሃገራቸው ፖስፖርት ይዘው እንዳልነበር ጠፍቶት አይመስለኝም። ሌላው ይቅርና በኢትዮጵያ ውስጥ የኤትራውን ጨቋኝ የኢሳያስን መንግስትን ለመጣል በኢትዮጵያ የሚንቀሳቀሰው ቡድን መሪዎች በኤርትራ ፖስፖርት ይሆን የሚንቀሳቀሱት ?  ብየ ዳዊትን እንድጠይቀውም አድርጎኛል። ይህ በዳዊት አፍንጫ ስር ያለ መረጃ ነውና ወዳጀ ዳዊት እንዲፈትሸው በማሳሰብ ዳዊት የአቶ አንዳርጋቸውን እንቅስቃሴ የማይደግፍ ከሆነ እንደ ዜጋ በግልጽ የራሱን ሃሳብ የማቅረብ መብቱ የተጠበቀ እንደሆነ የወንድም ምክሬን መክሬዋለሁ። በእኔ በኩል ግን ከላይ በሰጠው የወረደ ማወያያ ሃሳብ መነሻ ሚዛናዊነት መጉደል አካሄዱ ስላላማረኝም። ይህም በመሆኑ ወዳጀ ጋዜጠኛ ዳዊት ያነሳው ማወያያ ሃሳብ አላስደሰተኝም!  … ዳዊት የጀመረው ተራ ብሽሽቅ እንጅ መረጃ ቅበላ አልመሰለኝምና አዝኛለሁ! እግዚአብሔር ዳዊትንም እኛንም ይታረቀን ብየ ብዘለው ይሻለኛል: ( ከመነሻ እግረ መንገዴ ይህን ካልኩ ወደ የመን ሰሞነኛ እርምጃ እና እርምጃው ወዳስከተለው ስጋት በጨረፍታ ላምራ …

     የየመን መንግስት በኢትዮጵያ መንግስት “ቀንደኛ” ተፈላጊ የሆኑትን አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ በማገትና በማስተላለፉ ረገድ ያሳየው ፍጥነት ብዙዎችን አስገርሟል። ላለፉት አስርት አመታት በየመን ምድር ታይቶ ተሰምቶ የማይታወቅ ግፍ በኢትዮጵያውያን ላይ ሲፈጸም ተመልካች የሆነው የየመን መንግስት የዛሬ አርምጃ ፍጥነት ብዙዎችን አስገርሟል።

   ያልታደሉ ስደተኞች ኢትዮጵያውያን ግፍ ከተበራከተባቸው አረብ ሃገራት መካከል የመንን የሚተካከላት የለም። ግፍ ተፈጽሞባቸው እዚህ ሳውዲ አረቢያ ያገኘኋቸው ግፉአን ኢትዮጵያውያን ስደተኞች በየመንን ምድር እንደ እንስሳ ተቆጥረው ያዩትን የስደትና እንግልትና እገታ ሲገልጹት “የሲኦል ምድር!” ማለት ይቀናቸዋል።  ስደተኛ ወገኖቻችን ዛሬ ድረስ በየመን ከተማ ፣ጉራንጉሮችና በየበርሃው የከፋ በደል እየተፈጸመባቸው ለመሆኑ የአደባበይ ሚስጥር በመሆኑ ዋቢ የሚያሻው አይደለም። የኢህአዴግ መንግስት  በኢኮኖሚ ሰደተኞች በሆኑ ዜጎቹ ላይ በየመን ምድር የሚፈጸመውን ግፍ ተቃውሞ አርባና ያለው እርምጃ መውሰድ ባለመቻሉ እስካሁን ያለው የስደተኞች ይዞታ አሳሳቢ እንደሆነ ቀጥሏል ።  በግዛት መሬቱ ላይ በዜጎቹ ግፍ ሲፈጸምብን መገደብ የተሳነው የየመን ስንኩል መንግስትም ቢሆን አለም አቀፍ ህግጋትን አክብሮ የወሰደው ቅንጣት እርምጃ ካለማሳየቱ በተዛማጅ የዛሬ አቶ አንዳርጋቸውን የማስረከብ እርምጃ ለኢትዮጵያ ሰላም በማሰብ ሳይሆን የፖለቲካ ጥቅምን ለማጋበስ የወሰደው እርምጃ ነው በሚል ብዙዎችን ቂም አስቋጥሯል።  

     በየመን በሽዎች የሚቆጠሩ ወገኖቻችን በግፍ በየባህሩና በርሃው ወድቀው ሲቀሩ የኢትዮጵያ መንግስት ተወካዮች የዜጎቻቸውን መብት ሲያስከብሩ አይተን ለማናውቅ ዜጎች የመንና ኢትዮጵያ  “አሸባሪ! ” ያሏቸውን ግለሰብ በታገቱበት ጥቂት ቀናት ውስጥ ወደ ሃገር ቤት ማስተላለፋቸው ዜና መሰማቱ ብዙዎቻችን አስደምሟል። ይህ ያልተጠበቀ ክስተትና በየመን የተወሰደ የማስተላለፍ እርምጃን ተከትሎ ኢትዮጵያውያን በየአቅጣጫው የተለያየ አስተያየት በመስጠት ላይ ናቸው። በርካታ ነዋሪዎች  ” አቶ  አንዳርጋቸውንና የሚመሩትን ድርጅት ስም ማንሳት በወንጀለኝነት ያስቀጣል ” የሚለውን ማስጠንቀቂያ እየጣሱ መንግስት “በአሸባሪነት ” ስለፈረጃቸው የቀድሞ የኢህአዴግ ከፍተኛ ባለስልጣን አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ ጉዳይ የመጣው ይምጣ በሚል አንድምታ ድፍረት በተቀላቀለበት መንገድ ዋንኛ መነጋገሪያ ሆኗል።

  በኢትዮጵያ መንግስት  “ነውጠኛ አሸባሪ ” የተፈረጁት እና በኢህአዴግ ላይ ጦር የሰበቀው የግንቦት 7 ድርጅት” አራጊ ፈጣሪ ናቸው” የሚባሉት አቶ አንዳርጋቸው ጽጌን ” ለዲሞክራሲና ነጻነታቸው የተጉ፣ ብርቱ አርበኛና ታጋይ !” እያለ ከንፈሩን የሚጥላቸው እና የሚያደንቋቸው ብዙ ነዋሪዎች አጋጥመውኛል። የመንግስት ደጋፊዎች በበኩላቸው “ትልቁ አሳ ወጥመድ ውስጥ ገብቷል!” ብለው ያምናሉና ጮቤ ከመርገጥ ባለፈ በትምክህት ” እኛ እንዲህ ነን! ” በሚል በኩራት ሲናገሩ አድምጫለሁ  ! በማህበራዊ ድረ ገጾችና በሰሚ ሰሚ ወሬው ደርሶት አስተያየት ላለመስጠት የሚሸሸው ነዋሪ ብዙ ቢሆንም በሆነው ሁሉ ያደረበትን ስጋት ከመግለጽ የተቆጠበ ግን የለም ። በአቶ አንዳርጋቸው ጽጌ መታገትና ለኢትዮጵያ መንግስት መተላለፍ ከተደሰቱት ውጭ ያለው ብዙ ነዋሪ የበቀል እርምጃ እንደሚፈጽሚ ሲዝቱ ተስተውሏል። 

     “ዲሞክራሲና ሰብአዊ መብትን አላስከበራችሁም !” በሚሉ ተቃዋሚ ቡድኖችና ” በሁለት አስርት አመታት ዲሞክራሲን አስፍኛለሁ፣ ሰብአዊ መብት አስከብሬያለሁ! ” በሚለው ኢህአዴግ መካከል አመታት የዘለቀው መጓተት ባመጣው ጣጣ በርካቶች “ከግንቦት 7 ጋር ግንኙነት አላችሁ !” በሚል ዘብጥያ ወርደዋል። አቶ አንዳረጋቸውም ቢሆን በኢህአዲግ ላይ ጠንስሰዋል በተባለው መፈንቅለ መንግስት በሌሉበት የሞት ፍርድ የተበየነባቸው መሆኑ ሲታወስ “ተይዘው ወደ ኢህአዲግ እጅ  ተላልፈዋል !” የመባሉ ዜና በቀል አስቋጥሮ ፣ በዛቻና ፉከራው ታጅቦ ዳግም በፖለቲካ ትርምስ ፍጥጫ እንዳይከታትና ኢትዮጵያን ወደ ሌላ የመጠፋፋት አዙሪት እና ብጥብጥ እንዳይዶላት በነዋሪው ላይ ታይቶ የማይታወቅ ስጋት አጭሯል ። 
   
  አዎ !  አረብ ሃገራት እንዲህ ናቸው ፣ በአረብ ሃገር  ያለን ስደተኞች መከራ ብዙ ነው :( እኔም የሃገሬ ህዝብ በነቂስ ስለሚነጋገርበት ሰሞነኛ አጀንዳ ቢያገባኝ ይህችን ታክል መረጃ አቀብል ዘንድ ነፍሴ ፈቅዳለች ። ከዚህ ባለፈ መጻፍና መናገር ግን አቅሙ የለኝም ልበል ይሆን? 

እስኪ ቸር ያሰማን !

ነቢዩ ሲራክ

ከኢትዮጵያ ሕዝብ አርበኞች ግንባር እርምጃ እወስዳለሁ አለ

July 5, 2014
ከኢትዮጵያ ሕዝብ አርበኞች ግንባር/ኢሕአግ/የተሰጠ መግለጫ


የማፈኛ መዋቅሩን መሰረት በማድረግ በርካቶች ጀግኖች ኢትዮጵያዊያን እጅግ በከፋና በሚዘገንን ሁኔታ በማጥፋት እኩይ ተግባሩ የሚታወቀው አረመኔው የወያኔ ስርዓት በአገራችን የተንሰራፋውን መጠነ-ሰፊ ተግዳሮት ከመሰረቱ ለመንቀል በሚደረገው ትግል ብርቱ ጥረትና እንቅስቃሴ ሲያደርጉ በነበሩት አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ ከየመን መንግስት ጋር በማበር የአንድን ሰው ከአገር አገር የመንቀሳቀስ መብት በመጣስ የየመን መንግስት ለወያኔው ማስረከቡ አጥብቀን የምናወግዘውና የምንቃወመው ሲሆን ድርጅታችን የኢትዮጵያ ሕዝብ አርበኞች ግንባር በአቶ አንዳርጋቸው ጽጌ ላይ በደረሰው አፈና መሰረት በማድረግ ማንኛውንም አይነት እርምጃ የምንወስድ መሆናችንን አበክረን እናስታውቅለን።

ለአገርና ለወገን ዕድገት ብልጽግና ሲሉ በመታገላቸው ሳቢያ የየመን መንግስት እሳቸውን አፍኖ በማስረከቡ ምክንያት አገር ውስጥ እየተካሄደ ያለውን ትግል ለአንድም ደቂቃ ቢሆን የሚገታው አለመሆኑን እብሪተኛው ቡድን ሊረዳው ይገባል።በአቶ አንዳርጋቸው ጽጌ በደረሰው የተቀነባበረ አፈና ዛሬ ላይ መግለጫ የማውጣታችን ምክንያት ጉዳዩ እስኪረጋገጥ በሚል እንጂ ቀደም ባሉት ቀናቶች መግለጫ ማውጣት ይጠበቅብን እንደነበረ እናምናለን ስለሆነም መላው የአገራችን ለውጥ ናፋቂ ወገናችን ሁሉ ይሄንኑ ሃሳባችንን በቅጡ እንዲረዳልን እናስገነዝባለን።

እንደ አንድ ታጋይና አታጋይ እሳቸውን በተቃውሞ ትግል ማጣታችን ቃላት ሊገልጸው ከሚችለው በላይ በውስጣችን ቁጣን ፈጥሯል ። አገዛዙ አቶ አንዳርጋቸውን ከየመን መንግስት መረከቡ ለውጥ ናፋቂው ሕዝብ በፍርሃት ተሸብቦ ለትግል እንዳይነሳሳና ማንኛውም ተቃዋሚ የትም ሄደ የትም ከገባበት ገብተን በእጃችን ለማስገባት የሚያስችለን የዲፕሎማሲ ግንኙነት አለን በሚል ስጋት ለመፍጠር የተሰራ ቀመር ስለመሆኑ ለማንም የተሰወረ አይደለም ።

ትምተኛውና ዘራፊው ቡድን ያልተረዳው ነገር ቢኖር ሕዝቡ ለሚያነሳቸው መሰረታዊ ጥያቄዎች ትኩረት ሰጥቶ በማዳመጥ አግባባዊ በሆነ መልኩና ሕዝቡን ተጠቃሚ ሊያደርግ በሚችል መልኩ ምላሽ እስካልሰጠ ድረስ በማፈን፣ በማሳደድ፣ በማዋከብና በመግደል የሚመጣ መፍትሄ አለመኖሩን ብቻም ሳይሆን በሕዝብ ላይ የሚወሰዱ ጭፍን ኢ-ሰብአዊድርጊቶች በጨመሩ ቁጥር ስርዓቱ ራሱን ወደ መቃብር ጉድጓድ እያስጠጋ እንዳለ ሊረዳው ይገባል።

አንድነት ሃይል ነው!
የኢትዮጵያ ሕዝብ አርበኞች ግንባር /ኢሕአግ/
ሰኔ 28 -2006 ዓ/ም

አዜብ መስፍን በጠና ታመዋል፤ የአባዱላ ገመዳ ልጅ አረፈ – (ከኢየሩሳሌም አርአያ)

July5/2014
ከባለቤታቸው ህልፈት በኋላ ከፖለቲካው መድረክ እየተገለሉ የመጡት ወ/ሮ አዜብ መስፍን በጠና መታመማቸውን ቅርበት ያላቸው ታማኝ ምንጮች አስታወቁ። በስኳር ህመምና በደም ግፊት እየተሰቃዩ የሚገኙት አዜብ መስፍን የሰውነት ክብደታቸው እንደቀነሰና የመጎሳቆል ሁኔታ በገጽታቸው እንደሚታይ የጠቆሙት ምንጮቹ ለስኳር በሽታ በየእለቱ ከሚወስዱት መድሃኒት በተጨማሪ ለደም ግፊትም እንክብሎችን እንደሚወስዱ ምንጮቹ አረጋግጠዋል። አዜብ በመኖሪያቸው አብዛኛውን ቀናት እንደሚያሳልፉ የጠቆሙት ምንጮቹ በፖለቲካው የደረሰባቸው ኪሳራ ብስጭት ውስጥ እንደከተታቸውና ለበሽታ እንደዳረጋቸው አያይዘው ገለጸዋል።
ቦሌ ከሳይ ኬክ ቤት ወደ ውስጥ ገባ ብሎ የሚገኘውና አቶ ስዩም መስፍን ለ19ዓመት የኖሩበት እንዲሁም አቶ ሙክታር ከድር ለሁለት አመት የኖሩበት መኖሪያ ቪላ ውስጥ የሚኖሩት አዜብ መስፍን ከዚህ በተጨማሪ ቦሌ ሩዋንዳ መታጠፊያ ላይ የሚገኘውን የቀድሞ የደህንነት ቢሮ ለአዜብ በቢሮ መልክ እንደተሰጣቸው ምንጮቹ ጠቁመዋል።
azeb
ቀን ቀን በዚህ ቢሮ ለብቻቸው ያሳልፉ የነበሩት አዜብ መስፍን በጠና ከታመሙ ወዲህ ላለፉት አምስት ሳምንታት ወደዚህ ቢሮ ገብተው እንደማያውቁና በቤታቸው እንደሚያሳልፉ ያስታወቁት ምንጮቹ አክለውም ፓርቲው በሚያካሂዳቸው ስብሰባዎች መገኘት እንዳቆሙና ለመጨረሻ ጊዜ የተገኙት ከሁለት ወር በፊት ኢህአዴግ ባካሄደው መደበኛ ጉባኤ ላይ መሆኑን አስገንዝበዋል። በዚሁ ጉባኤ ከተሰብሳቢው ኋላ ለብቻቸው ተቀምጠው የታዩት አዜብ ምንም ሳይናገሩና አስተያየት ሳይሰጡ ስብሰባውን ከመጨረሳቸው ባሻገር ከስተውና ተጐሳቁለው እንደነበር ምንጮቹ አስታውሰው ከዚያ ወዲህ ህመሙ እየጠናባቸው እንደሄደ አያይዘው ገለፀዋል። አዜብ የባለቤታቸውን ቦታ በመተካት የጠ/ሚ/ርነቱንና ፓርቲውን የመምራት እቅድና ምኞት በተቀናቃኛቸው ስብሃት ነጋ ከከሸፈባቸውና የሚተማመኑባቸው የደህንነት ባለስልጣናትና የፓርቲው ቁልፍ ሰዎች እስር ቤት መወርወርና መባበረር ለከፍተኛ የሞራል ድቀትና ለበሽታ እንደዳረጋቸው ምንጮቹ አመልክተዋል። አዜብ የኤፈርት ኤክስኪውቲቭ ዳይሬክተር ተብለው ቢሰየሙም ምንም አይነት የአመራር ሚና እንደሌላቸው የጠቆሙት ምንጮቹ በነስብሃት ተመድበው ተቋሙን ሲመሩ የቆዩት አቶ ብርሃነ ኪዳነማርያም ወደ ራዲዮና ቴሌቪዥን ስራ አስኪያጅ እንደሆኑና ከርሳቸው በኋላ ደግሞ የአርከበ እቁባይ ታናሽ ወንድም ጌታቸው እቁባይ እየመሩት መሆኑን አያይዘው ገልፀዋል።
ከአዜብ ጋር በተፈጠረ ያለመግባባት ከኤፈርት ለቀው የቆዩት ጌታቸው እቁባይ የአቶ መለስ ዜናዊን ሞት ተከትሎ እንዲመለሱ መደረጉን አመልክተዋል። አዜብ ወደ ትግራይ -መቀሌ ከተጓዙ 6 ወር እንዳለፋቸው አክለዋል። በኤፈርት ውስጥ የአዜብ ደጋፊዎች በነስብሃት ተለቅመው መውጣታቸውን ያስታወሱት ምንጮቹ በቅርቡ ኤክስኪውቲቭ ዳይሬክተር የሚለውን የአዜብ ስልጣን በመግፈፍ ሊያባርሯቸው መሆኑን አረጋግጠዋል። …ይህ በእንዲህ እንዳለ የአባዱላ ገመዳ ልጅ ወጣት ኮሚያስ አባዱላ ከዚህ አለም በሞት እንደተለየ ታውቋል። የ26 አመቱ ወጣት ኮሚያስ አባዱላ በጉበት በሽታ ምክንያት ወደ ታይላንድ- ባንኮክ ተልኮ ለአንድ አመት ሲታከም ከቆየ በኋላ ሊድን ባለመቻሉ ከአራት ሳምንት በፊት ህይወቱ አልፏል። በባንኮክ ለአንድ አመት የሆስፒታል ቆይታው ለህክምና ብቻ ከ880ሺህ ዶላር ወጪ እንደተረገለት ታውቋል። በተመሰሳሳይ ሶስተኛ ታናሽ እህቱ (የአባዱላና ራሄል ልጅ) ከአምስት አመት በፊት በገጠማት የሳንባ፣ የአንጀትና የአእምሮ በሽታ በባንኮክ ሆ/ል ለሁለት አመት ህክምና የተከታተለች ሲሆን፣ ለህክምናው ጠቅላላ የወጣው 2.5ሚሊዮን ዶላር እንደሆነ ከዚህ ቀደም ይፋ በተረገው መረጃ መገለፁ ይታወሳል። ይህ ሁሉ ገንዘብ ከህዝብ የተዘረፈ ለመሆኑ አያጠያይቅም። ይህቺ ናት አገሬ! ..ለማንኛውም የአባዱላ ወንጀል ልጁን አይመለከተውም። ወጣት ኮሚያስ በአባቱ ድርጊት ነፃናነት ስለማይሰማው – በየእለቱ አልኮል ይጠጣና ይበሳጭ እንደነበረ ቅርብ የሆኑ ጓደኞቹ ተናግረዋል። የጉበት በሽታውም መንስኤ ይኸው ነው። 

ኢሳት ከኢትዮጵያ ውስጥ በሚደወሉ የስልክ ደወሎች መጨናነቁን እየገለጸ ነው።

July 4, 2014
ጋዜጠኛ ፋሲል የኔአለም በፌስቡክ ላይ ባስቀመጠው መልክት ላይ በርካታ በሽዎች የሚቆጠሩ ስልኮች የቴሌቪዥን እና ሬዲዮ ጣቢያውን ማጫናነቁን ሲገልጽ ስልክ በመመለስ ተጠምደን ነው የዋልነው በርካታዎቹ ግንቦት 7 አሁኑኑ ለመቀላቀል እና የጀግናውን አንዳርጋቸው ጽጌን ሃሳብና ፍላጎት ለማሳካት መዘጋጀታቸውን እየገለጹ ነው። በሁሉም እድሜ ክልል የሚገኘው ኢትዮጵያዊ ስልክ በመደወል ማዘኑና መቆጨቱን እየገለጸ ሲሆን ሁላችንም አንዳርጋቸው ነን የሚሉ መፈክሮችን ሁሉ እያስቀመጡ ነው።
በተያያዘ ዜና ግንቦት 7 ትግሉ ይፋ መጀመሩን አስታውቋል። ከአዲስ አበባ በደረሰን መረጃ መሰረት ደግሞ የህወሃት/ ወያኔ ባለስልጣናት ከዚህ ጋር በተያያዘ ስብሰባ ላይ መቀመጣቸውን ያረጋገጥን ሲሆን ይህም ከፍተኛ የሆነ የፌድራል ሰራዊቱን የማዘጋጀትና በተጠንቀቅ እንዲሆን ለማዘዝ መሆኑን ዘግቢያችን ጨምሮ ተናግሯል። በአዲስ አበባ ጎዳናዎች ምንም አይነት ከወትሮው የተለየ እንቅስቃሴ ባይኖርም በአብዛኛው የኢትዮጵያ ህዝብ ግን በየቤቱ እየተነጋገረ መሆን በተዘዋወረበት መንደሮች ለመረዳት ችሏል። በቦሌ ክፍለ ከተማ መድሃኒያለም አካባቢ ፍሪ አንዳርጋቸው ጽጌ የሚል ጽሁፍ በአውቶብስ መጠበቂያ ተጽፎ መመልከቱንም አክሎ ዘግቦል።
bole_church_ethiopia
ይህ በእንዲህ እንዳለ የወያኔ መንግስት በሀገርና ከሀገር ውስጥ እየተነሳ የመጣውን ቁጣ ሽሽት በሚመስል አንዳርጋቸው ጽጌን አላየሁትም የሚል ወሬ እያስወራ ነው።
ይህ ጠንካራ ታጋይ ወያኔዎቹ ከዚህ በኋላ እያንዳንዷን ጣቶቹ እንኳን እየቆረጡ መግደል ቢጀምሩ አንዳርጋቸው እየሳቀባቸውነው የሚሞተው ያሉት ዶ/ር ብርሃኑ ከዚህ በኋላ ትግሉን ወያኔዎች አስጀምረውታል እየሞትን ልንገድልም ዝግጁ ነን። የኢትዮጵያ ህዝብ ለአንዳርጋቸው አታልቅሱ የጀመረውን ትግል ከግብ አድርሱ ያኔ ነው አንዳርጋቸውን የምታስደስቱት። አንዳርጋቸው ስራውን ጨርሶ ተቀምጧል። ማየት የሚፈልገው ልጆቹን ነው። ሲሉ ተናግረዋል፡፡
10409455_647654315329663_5484929445468543318_n


    የህዝባዊ ሃይሉን ተጠሪ ለማናገር ያደረግነው ሙከራ አልተሳካልንም።

    Friday, July 4, 2014

    የአፍሪቃ መሪዎች ያለመከሰስ መብት

    June4/2014
    ሸዋዬ ለገሠ
    ተክሌ የኋላ

    የአፍሪቃ መሪዎች ባለፈዉ ሳምንት ባካሄዱት ጉባኤ አንድ መሪ በስልጣን ላይ እያለ ክስ እንዳይመሠረትበት መስማማታቸዉ ትችት አስከትሏል። የአፍሪቃ የፍትህና የሰብዓዊ መብቶች ፍርድ ቤት የተሰኘዉ መድረክ ስልጣን ላይ የሚገኙ መሪዎችና ባለስልጣናትን መክሰስ እንዳይችል የታገደ ነዉ።

    የመብት ተሟጋቾች ከወዲሁ የተጣለዉ እገዳ ወንጀል ፈፃሚዎች ሳይጠየቁ በነፃ እንዲኖሩ ያደርጋል እያሉ ነዉ። የአፍሪቃ መሪዎች ይህን ዉሳኔ ያሳለፉት ባለፈዉ ሳምንት ዓርብ ዕለት ኢኳቶሪያል ጊኒ ላይ ባካሄዱት ጉባኤ ነዉ። አሶሲየትድ ፕረስ እንደሚለዉ የመሪዎቹ ስብሰባ ጋዜጠኞች እንዳይገቡ ተደርጎ በዝግ ነዉ የተካሄደዉ። የዝግ ስብሰባዉ ዉሳኔም ሰኞ ዕለት ማምሻዉ ላይ በመግለጫ መልክ በድርጅቱ ይፋ ሆነ። መሪዎቹ አፍሪቃዊ መሪም ሆነ የመንግስት ባለስልጣን ስልጣን ላይ እያለ ክስ ሊመሠረትበት አይገባም ማለታቸዉን 42 የአፍሪቃ እና ዓለም ዓቀፍ ሲቪል ማኅበራትና የመብት ተሟጋች ቡድኖች ተቃዉመዋል።
    በሎንዶን የአምነስቲ ኢንተርናሽናል የህግ አማካሪ ኮላዋሊ ኦላኒያ( kolawole Olaniyan) የመብት ተሟጋቻቾች የተቃወሙበትን ምክንያት ያስረዳሉ፤
    “የተደረገዉ ማሻሻያ አምነስቲ ኢንተርናሽናልን ያሳስበዋል፤ ምክንያቱም ለአፍሪቃ ሃገራት መሪዎች፣ የመንግስት ከፍተኛ ባልስልጣናትና መራሄ መንግስታት በጅምላ ጭፍጨፋ፣ በጦር ወንጀልና በሰብዓዊነት ላይ በሚፈፀሙ ወንጀሎች ያለመከሰስን ከለላ ይሰጣል። ያለመከሰስ መብት ደግሞ እንደሚታወቀዉ ወንጀል ፈፅሞ በነፃነት መንቀሳቀስን ያስከትላል። ይህም የሰብዓዊ መብት ጥሰት ሰለባዎችን ይጎዳል። ለዚህ ነዉ እኛ የተቃዉምነዉ።»
    እንደአምነስቲ እምነትም ስልጣን ላይ የሚገኙት ፖለቲከኞች የማይከሰሱ ከሆነ የመብት ጥሰቶችና የጦር ወንጀሎች ቢፈፀሙም ተጠያቂዉ በነፃነት እንዲኖር ያስችላል። አፍሪቃ ለከፍተኛ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች ተጠያቂነት እንዲኖር ለማስቻል ጥረት እያደረገች በምትገኝበት በዚህ ወቅትም መሪዎቿ ይህንን ተግባራዊ ለማድረግ መስማማታቸዉ ትርጉም እንደሚያጣ ነዉ የተገለፀዉ። የአምነስቲ ኢንተርናሽናል የህግ አማካሪ ኮላዋሊ ኦላኒያ እንደሚሉት የአፍሪቃ መሪዎች ይህን ማሻሻያ ያደረጉበት ወቅት አነጋጋሪ ነዉ፤
    0,,17403235_404,00
    “ይህ ነገር የመጣዉ የአፍሪቃ መሪዎች ዓለም ዓቀፉን የወንጀል ተመልካች ፍርድ ቤት ላይ ከፍተኛ ተቃዉሞ ባሰሙበት ወቅት ነዉ። ፖለቲካዊ ስሌት እንዳለዉ አናዉቅም። ነገር ግን ቀደም ብዬ እንዳልኩት ይህ ፍርድ ቤት የአፍሪቃ መሪዎች በስልጣን ላይ እስካሉና እስከቆዩ ድረስ ከሶ ከችሎት ማቆም አይችልም።»
    የአፍሪቃ ኅብረት ICC በኬንያ ፕሬዝደንት ዑሁሩ ኬንያታና በምክትላቸዉ ላይ የመሠረተዉን ክስ እንዲያስነሳ የተመድ ላይ ያደረገዉ ግፊት ዉጤት አላመጣም። ሁለቱም በጎርጎሪዮሳዊዉ 2007ዓ,ም በሀገራቸዉ ከተካሄደዉ ምርጫ በኋላ በተፈጠረዉ ግጭት በሰብዓዊነት ላይ ከተፈፀሙ ወንጀሎች ጋ በተገናኘ ICC ክስ መስርቶባቸዋል።ሁለቱም ግን የቀረበባቸዉን ክስ ያስተባብላሉ። የአፍሪቃ መሪዎችም አፍሪቃ ላይ ብቻ ያተኩራል ያሉት ICC በመንበረ ስልጣናቸዉ ላይ የሚገኙ መሪዎች ላይ ክስ መመስረቱን በአንድ ድምፅ እየተቃወሙ ነዉ። ችሎቱ ከተመሠረተበት የሮማ ዉል ፈራሚ የአፍሪቃ ሃገራት ቦትስዋና ብቻ ይህን ተቃዉማለች።ተቺዎችም እንዲሁ የICC አባል ያልሆነችዉ ዩናይትድ ስቴትስ በአንድም ሆነ በሌላ መልኩ በፍርድ ቤቱ አሰራር እጇን እንደምትከት በማመልከት የአፍሪቃ መሪዎች በራሳቸዉ ላይ ያነጣጠረ ነዉ የሚሉትን ፍርድ ቤት አሠራር መቃወማቸዉ አይደንቅም ይላሉ። ኮላዋሊ ኦላኒያ በዚህ ላይ አስተያየታቸዉን እንዲሰጥተዋል፤
    0,,17399307_404,00
    “እዉነታዉ አብዛኞቹ የአፍሪቃ መንግስታት ዓለም ዓቀፉ የወንጀል ችሎት የተመሠረተበት የሮም ዉል ፈራሚዎች ናቸዉ። እናም ይህን ተጠቅመዉ ለራሳቸዉ ያለመከሰስ መብት ማጎናጸም መሞከራቸዉ ስህተት ነዉ። ምክንያቱም ይህ ከመተዳደሪያ ደንባቸዉ የሚጻረር ነዉ። የኅብረቱን የመተዳደሪያ ደንቡን ብትመለከቺ የአፍሪቃ መንግስታት ወንጀል ፈጽሞ ሳይጠየቁ መኖርን ለመዋጋት ዝግጁና ፈቃደኛ ናቸዉ ይላል። ምክንያቱም ቀደም ብዬ እንዳልኩት ያለመከሰስ መብት መኖር ማለት ወንጀል ፈፅሞ በነፃ የመንቀሳቀስ መብት ያጎናፅፋል። ይህ ነዉ እየኛ አቋም፣ ለዚህም ነዉ የአፍሪቃ ኅብረትና የአፍሪቃ መሪዎች በዚህ ላይ ያደረጉትን ማሻሻያ እንዲያጤኑት የምንጠይቀዉ።»
    አምነስቲ ኢንተርናሽናል የICC አካል ባለመሆኑ የክስ አቀራረብ ሂደትና አሠራሩን እንደማያዉቅ ያመለከቱት የድርጅቱ የሕግ አማካሪ ፍርድ ቤቱ ምንም ቢያደርግ በሰብዓዊነት ላይ ወንጀል የሚፈፅሙ መሪዎች ግን ስልጣን ላይ እስካሉ ድረስ አይከሰሱ የሚለዉን አጥብቆ እንደሚቃወም ገልጸዋል። ICC ከኬንያንያ መሪዎች በተጨማሪ በሱዳኑ ፕሬዝደንት ኦማር አልበሽር ላይ የቆረጠዉ የእስር ማዘዣ እስካሁን እልባት ያልተገኘለት መከራከሪያ እንደሆነ ነዉ።
    Source: dw

    በወያኔ የተቀነባበረ ሴራ የአቶ አንዳርጋቸው ጽጌ በየመን መታገትና ለወያኔዎች ተላልፎ መሰጠት ለተቀዋሚዎች የማንቂያ ደውል ነው (ገዛኸኝ አበበ ከኖርዌ)

    June4/2014
    Gezahegn Abebe

    Photo: የግንቦት7 ንቅናቄ ዋና ጸሃፊ የሆኑት የአቶ አንዳርጋቸው በየመን መታፈን ሁላችንንም ኢትዮጵያኖችን የወያኔን መሰሪነት አውቀን በቁጣ በወያኔ መንግስት ላይ መነሳት ይገባናል ::የወያኔ መንግስት እሱን በሚቃወሙ ባሉ ሰዎች ላይ ሁሉ እየወሰዳቸው ያለው በግፍ የተሞሉ እርምጃዎች ምን ያህል አንባገነን መንግስት እንደሆነ አመላካች ሲሆን የአቶ አንዳርጋቸው ፅጌ በየመን መታፈንም አመላካች ሲሆን በወያኔ ሴራ የተቀነባበረ መሆኑ ምንም ጥርጥር የለኝም :: የወያኔ መንግስት ማወቅ ያለበት ነገር ቢኖር በነፃነት ታጋዩ አቶ አንዳርጋቸው ላይ የሆነው ነገር የኢትዮጵያን ሕዝብና ተቃወሚዎችን ይበልጥ የሚያጠነክርና ለትግል ይበልጥኑ እንዲነሳሱ የሚያደርግ መሆኑ ነው:: የእንዳርጋቸው በየመን መታሰር ለተቃዋሚ መሪዎች ሊያነቃቸው ያለ ትልቅ ደውል የተደወለ ነው የሚመስለኝ :: በሀገርም ውስጥ በውጭም ያሉ የተቀዋሚ ድርጅቶች አንድ በመሆንና በመተባበር ልዮነታችንን ወደ ጎን በመተው የኢትዮጵያ ሕዝብንም 
በማስተባበር በጋራ ጠላታችን ላይ በመዝመት ይሄን አረመኔ መንግስት ለማስወገድ በጋራ እንናሳ:: 

ድል ለኢትዮጵያ ሕዝብ!!!
ውድቀት ለወያኔ!!
    የግንቦት7 ንቅናቄ ዋና ጸሃፊ የሆኑት የአቶ አንዳርጋቸው በየመን መታፈንን ከሰማን ጊዜ ጀምሮ አብዛኛው ሀገር ወዳድና የኢትዮጵያን የነጻነት ቀን ናፋቂ ወገኖችን ያሳሰበና እረፍት የነሳ ጉዳይ እንደሆነ በየቀኑ በየማህበራዊ ድህረ ገጽ ከሚወጡት ነገሮች መረዳት እንችላለን :: በርግጥ ወያኔ በስልጣን በቆየባቸው በእነዚህ ሃያ ሶስት አመታቶች ብዙ የተማሩ ኢትዮጵያን ሙህሮች፣ ብዙ የፖለቲካ ሰዎች በወያኔ የተቀነባበረ ሴራ ለብዙ ነገር ሰላባ ሲሆኑና ህይወታቸውን እስከሚያጡ ድረስ ሆነዋል :: ሰሞኑን ግን በነጻነት ታጋያችን በአቶ አንዳርጋቸው ጽጌ ላይ በወያኔ የተቀነባበረ ሴራ በየመን የደረሰው እገታና ለነብሰ በላው የወያኔ መንግስት ተላልፎ መሰጠቱ እውን እንደሆነ ስሰማ እንደማንኛውም ኢትዮጵያዊ በእኔም ላይ በጣም ከባድ የሆነ የሀዘን መንፈስ የፈጠረብኝ ሲሆን በወያኔ መንግስት ላይ ያለኝን ጥላቻ ይበልጥኑ ከፍ እንዲል ያደረገ ክስተት ሆኖል  እንዳርጋቸው ወደ ትግል ሲገባ እራሱን ለሞት በማዘጋጀት ሊደርስበት ያለውን ማንኛውንም መሰዋትነት ለመክፈልና ሁሉንም መከራ ለመቀበል ዝግጅነቱን በማሳየት እንደሆነ ከሚሰራቸው ስራዎች መረዳት ይቻላል ::በርግጥ እውነተኛ ትግል መስዋህትነትን እንደሚያስከፍል ባውቅም የእኝህ እድሜያቸውን በሙሉ ለነጻነት ሲታገሉ የኖሩ የነጻነት ታጋይ ላይ የደረሰው ነገር ግን በውስጤ ሁለት ነገሮችን ጭሮብኛል ያለፈ ሲሆን አንድን ነገር ግን እንዳውቅ ረድቶኛል:: አንዱ እንዳርጋቸው ቢታሰርና  የፈለገው ነገር በእሱ ላይ ቢደርስ እንኮን  ለወያኔዎች የእግር እሳት የሆኑ እንዳርጋቸው የወለዳቸው ብዙ ሚሊዩኖች የነጻነት ታጋዮች ኢትዮጵያኖች በየስፍራው ተወልደዋልና ደስ ይለኛል::

    አሁን ላይ ነገሮች ሁሉ የተቀየሩ ነው የሚመስለው የአቶ እንዳርጋቸው ጉዳይ  የአንድ የፖለቲካ ድርጅት ከመሆን  አልፏል :: በአሁኑ ሰአት አብዛኛው ኢትዮጵያዊ የፖለቲካ እና የአመለካከት ልዩነቱን ወደ ኋላ በመተው እኔም አንዳርጋቸው ጽጌ ነኝ በሚል ቃል ጉዳዮን በንቃት እየተከታተለው ሲሆን የታጋይ አንዳርጋቸው ጽጌ በየመን መያዝና በወያኔ እጅ ላይ መውደቅ ለአንዳንድ ሆድ አደር ወያኔዎች ብቻ ፈንጠዝያ የፈጠረና ያስደሰተ ቢመስልም ብዙ ኢትዮጵያ ወገኖችን ግን ከሌላዉ ጊዜ በተለየ መልኩ በእልህና በቁጭት ለትግል እንዲነሳሱ ያደረገ ክስተት እንደሆነ በፊስ ቡክ በውስጥ መልክት ከሚደርሰኝ ደስ የሚልና የሚያበረታታ ጽሁፍ ለመረዳት ችያለው::

    ድርጊቱ ለተቃዋሚዎች የማንቂያ ደውል መሆን ይገበዋል ለነጸነት እንታገላለን የሚሉ ማንኛውም የፖለቲካ ድርጅቶችም ሆኑ ለነጻነት እየታገልን ያለን  ኢትዮጵያኖች የወያኔን መሰሪነት አውቀን ከመቼውም ጊዜ በተለየ መልኩ በቁጣ በወያኔ መንግስት ላይ መነሳትና በወያኔ ላይ ያለንን የከረረ ጥላቻ በእንቢተኝነትና በሕዝባዊ አመጽ ልንገልጽ ይገባናል ::የወያኔ መንግስት ስልጣኑን በሀይልና በጉልበት ከተቆናጠጠበት ጊዜ ጀምሮ  እሱን በሚቃወሙ ባሉ ኢትዮጵያዊ ወገኖቻችን ላይ ሁሉ  ይኼው አረመኔው የወንበዴ ስብስብ  እየወሰዳቸው ያለው በግፍ የተሞሉ እርምጃዎች ምን ያህል አንባገነን መንግስት እንደሆነ አመላካች ሲሆን የአቶ አንዳርጋቸው ፅጌ በየመን መታፈንም የዚሁ አመላካች ነው::ዛሬ ላይ የአንዳርጋቸው መታፈን በርግጥ የወንበዴዎችን ቡድን ጮቤ እያስረገጣቸው እንደሆነ አስባለው  የወያኔ መንግስት ማወቅ ያለበት ነገር ቢኖር በነፃነት ታጋዩ አቶ አንዳርጋቸው ላይ የሆነው ነገር የኢትዮጵያን ሕዝብና ተቃወሚዎችን ይበልጥ የሚያጠነክርና ለትግል በጥንካሬ እንዲነሳሱ የሚያደርግ መሆኑ ነው:: የእንዳርጋቸው በየመን መታገትና በወያኔዎች የተቀነባበረ ሴራ ለወያኔዎች ተላልፎ መሰጠት የየመንን መንግስት ባደረገው ከህግ ውጭ የሆነ አሳፋሪ ድርጊት ለወደፊት የታሪክ ተወቃሽ የሚያደርገው ቢሆንም የመኖች በሰሩት ስራ ወደ ፊት ተጠያቂ እንደሚሆኑበት ምንም ጥርጥር የለኝም::ዋናው መታወቅ ያለበት ግን ድርጊቱ  ለተቃዋሚ መሪዎች ትልቅ የቤት ስራ የሰጠና ሊያነቃቸው ያለ ደውል የተደወለ ነው የሚመስለኝ ::

    በሀገርም ውስጥ በውጭም ያሉ የተቀዋሚ ድርጅቶች በስሜትና፣ በደመነብስ የምንጓዝበት ዘመን ያብቃ፣ እየሰራን ያለውንም ስራ እንመርምር ፣እንንቃ የወያኔን መሰሪ ሴራ ለማክሸፍ አንድ በመሆንና በመተባበር ልዮነታችንን ወደ ጎን በመተው የኢትዮጵያ ሕዝብንም በማስተባበር ነጻነታችንን ህውን ለማድረግ  በጋራ ጠላታችን ላይ በመዝመት ይሄን አረመኔ መንግስት ለማስወገድ በጋራ መነሳት ይጠበቅብናል::

    በመጨረሻም ለወያኔዎች የማስተላልፈው መልእክት ቢኖር እውነተኛ ታጋይ ሊታሰር ሊሞትም ይችላል የተጀመረውን ትግል ግን ልታስሩትም ሆነ ልትገሉት ከቱ አትችሉም ::ኢትዮጵያ አንድ እንዳርጋቸው ብቻ ሳይሆን ሚሊዮን እንዳርጋቸው ፈጥራለችና  በከንቱ አትደከሙ:: ወደዳችሁም ጠላችሁም የእንዳርጋቸውን ፈለግ በመከተል  ሁላችንም  የነጻነት ታጋዮች ነን!!!

    አቶ አንዳርጋቸው አምላክ ከአንተ ጋር ይሁን

    ድል ለኢትዮጵያ ሕዝብ!!!
    gezapower@gmail.com

    Thursday, July 3, 2014

    በአቶ አንዳርጋቸው ጽጌ ጉዳይ… ኤርትራ እና የመን ተፋጠዋል (መልእክተ ዜና – በዳዊት ከበደ ወየሳ)

    July3/2014
    ኤርትራ የየመንን አየር መንገድ እንደምትዘጋ አሳወቀች (ምክንያቱ የአቶ አንዳርጋቸው ጽጌ መታሰር ነው)
    (ኢ.ኤም.ኤፍ) አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ ሰና፣ የመን ውስጥ በየመን የጸጥታ ሃይሎች ታፍኖ መታሰሩ ብሎም አሁን በምን ሁኔታ ላይ እንደሚገኝ አለመታወቁ ብዙዎችን እያነጋገረ ነው። አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ የመን ላይ ትራንዚት እያደረገ በነበረበት ወቅት ነበር በየመን ታጣቂዎች ታፍኖ የተወሰደው። ከዚያን ጊዜ ጀምሮ ኢትዮጵያውያን በየቦታው ድምጻቸውን ለማሰማት ጥረት በማድረግ ላይ ናቸው። ከ’ነዚያ ሁሉ ድምጾች ግን ጎልቶ የወጣው በኤርትራ በኩል የተላለፈው መግለጫ ነው። ይህን የኤርትራን መግለጫ መሰረት በማድረግ፤ ሌሎች ምን ማድረግ እንዳለባቸው የራሳችንን ሃሳብ እንሰጣለን።
    ኤርትራ ለየመን በላከችው መልዕክት መሰረት አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ ካልተፈታ፤ በኤርትራ አየር ላይ የሚሄዱትንም ሆነ፤ ምድር ላይ የሚያርፉት የየመን አውሮፕላኖች የሚታገዱ መሆኑን ገልጿል። ይህ ደግሞ እያደገ ለመጣው የየመን አየር መንገድ ትልቅ ኪሳራን የሚያስከትል ነው። ኤርትራ የጀርመኑን ሉፍታንዛ ካገደች ወዲህ፤ የየመን አየር መንገድ ሉፍታንዛን ተክቶ፤ አስመራ ውስጥ በመስራት ላይ ይገኛል። በዚህም መሰረት ወደ አውሮፓ የሚሄዱም ሆኑ የሚመጡ አውሮፕላኖች በየመን በኩል አድርገው ማለፍ ከጀመሩ ሰነባብተዋል። አሁን ኤርትራ የየመን አየር መንገድን እንደሉፍታንዛ የምታገድ ከሆነ፤ የየመን መንግስት የሚያገኘው ከፍተኛ ገቢ ሊቀንስበት ይችላል።
    ከዚህ በፊት ባቀረብነው ዘገባ ላይ አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ የእንግሊዝ አገር ዜግነት ያለው እና የእንግሊዝን ፓስፖርት ይዞ የሚንቀሳቀስ መሆኑ ይታወቃል። በዚህም መሰረት ስለአቶ አንዳርጋቸው ጽጌ ስናወራ፤ የ እንግሊዝንም መንግስት የጉዳዩ ባለቤት ማድረግ ያስፈልጋል። እንግሊዝ ዜጋዋ በየመን ታስሮ ወደ ኢትዮጵያ እንዳይላክ በአውሮፓ ዲፕሎማሲያዊ ስራ መስራት ተገቢ ነው። ኢትዮጵያ እና የመን እስረኛን አሳልፎ የመስጠት ስምምነት ቢኖራቸውም፤ የመን የ እንግሊዝ ዜግነት ያለውን ሰው አሳልፋ እንዳትሰጥ በዛቻ ሳይሆን፤ በህጋዊ መንገድ የመንን መሞገት ያስፈልጋል።
    ከ እንግሊዝ በተጨማሪ የአሜሪካ ዲፕሎማቶችም በጉዳዩ ጣልቃ እንዲገቡ ማድረግ ሌላው ብልሃት ነው። አሜሪካ ከየመን ጋር ያላትን መልካም ግንኙነት በመጠቀም አቶ አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ እንዲፈታ በየመን የአሜሪካ ኢምባሲ ጥረት እንዲያደርግ ጫና መፍጠር ያስፈልጋል። በአሁኑ ወቅት ግንቦት ሰባት የሚያወጣቸው የማስፈራሪያ መግለጫዎች ድምጸታቸውን በማስተካከል እንደአንድ በሳል የፖለቲካ ድርጅት የሚታይ ዲፕሎማሲያዊ ስራ በመስራት ለውጤት መብቃት አለባቸው። በመሆኑም ከማስፈራሪያ መግለጫዎች ይልቅ፤ ከዲፕሎማሲያዊው ዘመቻ ጎን ለጎን… ህጋዊ ጠበቃ በየመን አዘጋጅቶ፤ ጉዳዩ በኢሚግሬሽን እና በዋናው ፍርድ ቤት እንዲታይ በማድረግ፤ ቢያንስ አቶ አንዳርጋቸው ወደ ኢትዮጵያ እንዳይላክ ጊዜ መግዛት ይቻላል።
    አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ የእንግሊዝ ዜግነት ያለው እንደመሆኑ መጠን ዲፕሎማሲያዊው ዘመቻ በእንግሊዛውያን ጭምር እንዲሰራ፤ ቢቢሲን ጨምሮ ሌሎች የአገሪቱ ሚዲያዎች ለጉዳዩ ትኩረት እንዲሰጡ ማድረግ ተገቢ ነው። የምናወጣቸውም መግለጫዎች በአማርኛ ሳይሆን ሁሉም አገራት በሚረዱት እንግሊዘኛ ቋንቋ ሊሆን ይገባዋል። ከዚያ ውጪ ግን “አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ ባስቸኳይ ካልተፈታ በኢትዮጵያ እና በየመን ባለስልጣናት ላይ እርምጃ እንወስዳለን” አይነት መግለጫዎች፤ ወያኔ ኢህአዴግ “ግንቦት ሰባት የአሸባሪዎች ድርጅት ነው” የሚለውን አባባል ከማጠናከር ውጪ ብዙም ፋይዳ ላይሰጥ ይችላል።
    ይህ ብቻም አይደለም። በማህበራዊ ድረ ገጾች እና ሌሎች ሚዲያዎች ላይ አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ ከዚህ በፊት ያደረጓቸው ንግግሮች እየተለጠፉ መሆኑን ታዝበናል። እንዲህ አይነቶቹ… ቀደም ሲል የተደረጉ ንግግሮችን አሁን ለእይታ ማቅረቡ አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ እስሩ እንዲጸናባቸው እንጂ፤ እንዲፈቱ ስለማይረዳቸው፤ በዚህ ረገድ ሌላ ጥንቃቄ ማድረግ አስፈላጊ ነው። በድጋሚ ለማሳሰብ ያህል… ግንቦት ሰባትም የማስፈራሪያ መግለጫዎችን ከማውጣት ይልቅ፤ በሌሎች ዜጎች እየተደረጉ ያለውን ጥረት ማስተባበር እና ዲፕሎማሲያዊ ይዘት እንዲኖራቸው ማድረግ አለበት። ኤርትራ ያደረገችውን ውሳኔ በማድነቅ፤ ሌሎች አገሮችም ተመሳሳይ እርምጃ እንዲወስዱ ማበረታታት ከግንቦት ሰባት አመራሮች የሚጠበቅ ነው።
    አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ በሌሉበት ሞት የተፈረደባቸው መሆኑን፣ ንብረታቸው በወያኔ ኢህአዴግ መወረሱን፣ ወላጅ አባታቸው እና ቤተሰባቸው በእስር መንገላታቱን አጉልቶ በማውጣት የወያኔ ኢህአዴግን አስከፊ ገጽታ ማሳየት ይቻላል። አሁንም የየመን መንግስት አቶ አንዳርጋቸው ጽጌን ወደ ኢትዮጵያ ብትመልስ በወያኔ ኢህአዴግ ሊደርስባቸው የሚችለውን የግድያ ወንጀል ማሳወቅ እንጂ፤ “አቶ አንዳርጋቸው ካልተፈታ ወዮላቹህ!” የሚለው አይነት ማስፈራሪያ ህሊና ለሌላቸው የሁለቱም አገራት አምባገነን መሪዎች ላይሰራ ይችላል። ህዝብ እና አገር የሚመሩት በእውቀት እና በጥበብ ጭምር በመሆኑ፤ ህጋዊ እና ሰላማዊ በሆነ መንገድ በመከተል… ነገር ግን በጠንካራ ዲፕሎማሲያዊ ዘመቻ አቶ አንዳርጋቸውን የማስፈታቱን ሂደት እንቀጥል – የዛሬው ዜና መልእክታችን ነው።

    የአማራ ጉዳይ፤ አለ? ወይስ የለም?

    July 2/2014
    መስፍን ወልደ ማርያም
    ግንቦት 2006
    mesfinተናግሬ ነበር ማለት ዋጋ የሌለው የወሬ ማጌጫ ነው፤ እስቲ ፍቀዱልኝና ልጠቀምበት፤ ከወያኔ ዋና ምሁር፣ ከመለስ ጋር ለመጀመሪያና ለመጨረሻ ጊዜ ፊት-ለፊት በቴሌቪዥን በተገኛኘን ጊዜ ‹‹አማራ የሚባል ጎሣ የለም፡›› በማለቴ መለስ ዜናዊና ጭፍሮቹ ብቻ ሳይሆኑ ‹‹አማራ-ነን ባዮች›› በቃልም፣ በጽሑፍም፣ በቴሌፎንም ልክ-ልኬን እየነገሩኝ አንጀታቸውን ቅቤ አጠጥተው ነበር፤ ‹አንዲት ሴት ደውለው እብድና ዘበናይ የልቡን ይናገራል፤› ብለውኛል፤ አንድ ሰው የተናገረው ስሕተት ከሆነ ስሕተቱን በማስረጃ ማጋለጥና የራስን ሀሳብ በማስረጃ መትከል ነው፤ እውቀት የሚዳብረው፣ ሰዎች የሚማሩትና በእድገት ጎዳና የሚጓዙት በተጨባጭ ማስረጃ መነጋገር ሲችሉ ብቻ ነው፤ እኔ አማራ የለም፣ ዜሮ (0) ነው፤ አልሁ፤ አማራ አለ፣ አንድ አለ፤ (1) ነው ያለ ሰው የአንድን ዋጋ ማሳየት አለበት፤ አማራ የለም የሚል ዜሮ ነው ማለቱ ስለሆነ ከሌለ ነገር ምንም አይጠብቅም፤ ከአለ ነገር (ከ1) ብዙ ነገሮችን መጠበቅ ይቻላል።
    ዱሮ በልጅነታችን ጭራቅ የሚሉት ማስፈራሪያ ነበረ፤ በአለፉት ሃያ ሦስት ዓመታት አማራ የሚባል ጭራቅ ማስፈራሪያ፣ የኢትዮጵያ ችግሮች ሁሉ ቋት እንደሆነ ሲነገር ቆየ፤ መለስ ዜናዊም እየደጋገመ ‹አከርካሪቱን ሰብረን ሁለተኛ እንዳያንሰራራ› እናደርገዋለን እያለ እንደዛተ የተሰበረውን አከርካሪት ሳያይ ሞተ፤ በሕይወትም እያለ ቢሆን መለስ ዜናዊ አከርካሪቱን እሰብረዋለሁ የሚለውን አማራ የተባለ ስያሜ እንደሹመት ለነበረከት ስምዖንና ለነተፈራ ዋልዋ ይሰጥ ነበር፤ የክብር ጎሣ እንበለው! ራሱም ቢሆን ከዚህ የክብር ጎሣ ቤተሰብነት አልራቀም፤ አከርካሪቱ እንኳን ሊሰበር አልተገኘም!
    ስንት ሺህ ሰዎች አማራ ናችሁ እየተባሉ ከስንት ስፍራ ተፈናቀሉ? አማራ ማለት እነዚሁ የተፈናቀሉት፣ በየጫካው የተገደሉትና የተሰደዱት ብቻ ናቸው? ሌሎችም ካሉ የጎሣ ዝምድና ሳይስባቸውና ከተፈናቀሉት ጋር አብሮ ለመቆም ለምን አልቻሉም? በጋምቤላ በደረገው ጭፍጨፋ የተጨፈጨፉት ጎሣዎች በጣም ትንሽም ቢሆኑ ከካናዳ እስከ አውስትራልያ ዓለምን ያዳራሱት የጎሣ ዝምድና ስሜት ለምን ለእነዚህ አማራ ለተባሉት ተፈናቃዮች አልሠራም? እንግዲህ አማራ እየተባሉ የሚፈናቀሉት፣ የሚገደሉትና የሚሰቃዩት ዘመድና ደጋፊ የሌላቸው ሰዎች ናቸው ማለት ነው፤ ሰውነታቸውም ቢሆን በሕግ ያልተረጋገጠላቸው፣ ሕግ የማይመክትላቸው ናቸው ማለት ነው፤ ይህንን ክርክር ከገፋንበት ዜግነታቸውንም የምንጠራጠርበት ደረጃ ላይ እንደርሳለን፤ ደርግ በጎሣ ላይ የተመሠረተ የውትድርና ሥልጠና ያደረገ ይመስለኛልና በዚህ ጉዳይ ላይ የደርግ ባለሥልጣኖች፣ በተለይም ኮሎኔል መንግሥቱ ኃይለ ማርያም አንድ ቀን የሚነግሩን ይኖራል የሚል ግምት አለኝ።
    አጥቂና ጨቋኝ ነፍጠኛ የሚባለው ሕዝብ ሲጠቃና ሲበደል ከኡኡታ በቀር ድምጹ የማይሰማው ትርጉሙ የህልውና ነው? ወይስ የወኔ? በሌላ አነጋገር አማራ የሚባል ጎሣ በእርግጥ አለ? ወይስ የለም? ከአለ የሚወራለትን ነፍጠኛነትና ወኔ ምን ዓይነት ብል በላው? ይህ ክርክር ከሃያ ሦስት ዓመታት በፊት አማራ የሚባል ጎሣ አለ ብለው የሞገቱኝን ሰዎች (የሞተውን መለስንና ያሉትን ጓደኞቹን ጭምር)፣ የመላው አማራ ይባል የነበረውን ድርጅት፣ ብአዴን የሚባለውን የወያኔ ድርጅት መሠረተ-አልባነት ለማሳየት እንጂ የሌለውንና ከዚህ በፊት ተቆስቁሶ ያልተነሣውን ጎሣ ለማነሣሣት አይደለም፤ የሌለ ነገር ቢቆሰቁሱት አይነሣም,
    በአለፉት ሃያ ሁለት ዓመታት ውስጥ እነዚህን አማራ እየተባሉ የሚፈናቀሉትን፣ የሚገደሉትን፣ የሚሰቃዩትን ሁሉ ‹‹ሰዎች›› ብናደርጋቸውና ሰዎች ብንላቸውስ? ሰው መሆን የተፈጥሮ ነው፤ ልለውጥህ ቢሉት አይለወጥም፤ ሰው ሆኖ ተወልዶ ሰው ሆኖ ይሞታል፤ ሰው መሆናቸውን ወንጀል የማድረግ ዝንባሌ የሚኖረው ሰይጣን ብቻ ይመስለኛል።
    ወይም አማራ የክርስቲያን ሃይማኖትን ተከታይነት የሚገልጽ ስያሜ አድርገን ብንወስደው የእነዚህ ሰዎች መፈናቀል፣ መገደል፣ መሰቃየትና መሰደድ ክርስቲያኖች እንዲጠፉ ለማድረግ ነው? ይህ ከሆነ አንድ ጸረ-ክርስቲያን ኃይል አለ ማለት ይመስለኛል፤ ይህ መደምደሚያ ችግር አለበት፤ ፓትርያርክና ሊቃነ ጳጳሳት ሰይሞ ጸረ-ክርስቲያን ተግባር ነጋ-ጠባ ማከሄድ አታላዩንና ተታላዩን ለመለየት ያስቸግራል።
    እነዚህን አማራ እየተባሉ የሚፈናቀሉትን ‹‹ኢትዮጵያውያን›› ብንላቸውስ? ኢትዮጵያዊነት ታሪካዊ ዜግነት ነው፤ ዜግነት አንድ ሕዝብ በደሙና በአጥንቱ የሚገነባው ነው፤ ዜግነት የሕግ ከለላ አለው፤ ይህንን የሕግ ከላላ ተነፍገው በኢትዮጵያ ምድር ከያለበት የሚፈናቀሉት፣ የሚገደሉት፣ የሚሰቃዩትና የሚሰደዱት ኢትዮጵያዊ ዜግነትን ለማጥፋት የተደራጀ ኃይል አለ ማለት ነው።
    አንግዲህ አማራ የሚባሉት ነፍጥ የሌላቸው ነፍጠኞች በምድረ ኢትዮጵያ ሰዎችም ሆነው፣ ክርስቲያኖችም ሆነው፣ ኢትዮጵያውያንም ሆነው መኖር አይፈቀድላቸውም ማለት ነው ወደሚል መደምደሚያ በግድ መድረሳችን ነው፤ ያዋጣል ወይ?
    ግራም ነፈሰ ቀኝ አማራ የሚባል ጎሣ እንደሌላ በስያሜው ላይ የሚደርስበትን ጥቃት ለመመከት እንኳን ባለመቻሉ አስመስክሯል፤ በሕይወት ላለ በህልውና ላይ የሚደርስበትን ጥቃት መመከትና መከላከል የተፈጥሮ ነው፤ ይህ ሳይሆን ሲቀር ህልውና የለም።

    Wednesday, July 2, 2014

    ሎሚ መጽሄት ከአብርሃ ደስታ ጋር ያደረገው ቃለ ምልልስ

    July2/2014
    “ሕወሓት በ2007 ምርጫ እንደማይመረጥ አውቋል”
    “ዓረናን ለማፍረስ ቢሞከርም አልተሳካም”
    “ዓረና ሕወሓትን ያስደነገጠ እንቅስቃሴ አድርጓል”
    ===============================
    አቶ አብረሃ ደስታ (የዓረና የፖሊት ቢሮ አባል)
    የአረና ፖሊት ቢሮ አባል የሆነው አቶ አብረሃ ደስታ በወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ ከሎሚ መጽሔት ምክትል ማኔጂንግ ዳይሬክተር ቶማስ አያሌው ጋር እንደሚከተለው አውግቷል፡፡
    ሎሚ መጽሄት የፊት ገጽ
    ሎሚ መጽሄት የፊት ገጽ
    ሎሚ፡- በአሁኑ ወቅት የአረና እንቅስቃሴ ምን ይመስላል?
    አብረሃ፡- ዓረና ሦስተኛ መደበኛ ጉባኤውን ካካሄደ በኋላ ከህዝብ ጋር ለመገናኘት፣ ህዝብን ለመሰብሰብ፣ ለማስተማርና ለማደራጀት እንዲሁም ለነፃነቱ እንዲነሳ ለመቀስቀስ ባቀደው መሰረት በተሳካ ሁኔታ ተግባሩን እያከናወነ ይገኛል። እስካሁን ድረስ በአስራ አምስት ከተሞች ህዝባዊ ስብሰባ ጠርተናል። በአስራ አንዱ የተሳካ ስብሰባ ሲደረግ በሽረ እንዳስላሴ፣ ዓዲግራት፣ ሑመራና ሐውዜን ግን በካድሬዎች ሴራ ተስተጓጉሏል። በሰባ አንድ የትግራይ ከተሞችና የገጠር መንደሮች የተሳካ ቅሰቀሳ ተደርጓል። የዓረናን አማራጭ ፖሊሲ የያዘ በራሪ ወረቀት ታድሏል። ዓረና ከምንም ግዜ በላይ በጥሩ ሁኔታ እየተንቀሳቀሰ ይገኛል፤ ተስፋም ተጥሎበታል። የህወሓት አባላትም ዓረናን ወደ መደገፍ የሚሸጋገሩበት አጋጣሚ ተፈጥሯል። ባጠቃላይ ዓረና ያደረገው እንቅስቃሴና እያገኘ ያለው የህዝብ ድጋፍ ህወሓትን አስደንግጦታል።
    ሎሚ፡- በፓርቲያችሁ ውስጥ ልዩነት ስለመኖሩ ይነገራል፤ ካለስ ምክንያቱ ምንድነው?
    አብረሃ፡- በዓረና ውስጥ ልዩነት አልተፈጠረም። ቅሬታ የሚያነሱ ግለሰቦች ግን አሉ። ቅሬታውም ከዓረና ዕቅድና ህወሓት በዓረና አባላት ላይ እያሳረፈው ካለው ጫና ይመነጫል። ዓረና ሰፊ እንቅስቃሴ ለማድረግ ሲወስን ገና ከጅምሩ ያልተዋጠለት አንድ አባል ነበር። ዕቅዱ የአብዛኛውን ድምፅ አገኘና ፀደቀ። የዓረና አመራር አባላት ወደ ህዝብ ወርደው መንቀሳቀስ እንዳለባቸው ተስማማን። በዚሁ መሰረት ሁሉም የማእከላዊ ኮሚቴና የቁጥጥር ኮሚሽን አባላት የየራሳቸው የስራ ድርሻ ተሰጣቸው።
    ሁሉም የዓረና አመራር አባላት በተሰጣቸው የስራ መስክ ሲሰማሩ ሁለት አመራሮች ግን የተሰጣቸውን የስራ ድርሻ ሳይቀበሉ ቀሩ። ከሃያ አምስት የማዕከላዊ ኮሚቴ አባላት አንዱ ወደ ህዝብ ወርዶ የፓርቲ ስራ ለመስራት ፍቃደኛ ሳይሆን ሲቀር ከሰባቱ የቁጥጥር ኮሚሽን አባላትም አንድ አባል ላለመስራት ወሰነ። ስለዚህ ከሰላሳ ሁለት ሰዎች ሁለት ብቻ የፓርቲ ስራ ለመስራት ፍቃደኞች ሳይሆኑ ቀሩ። ሰላሳዎቹ ግን በየተመደቡበት የስራ ዘርፍ ተሰማርተው እነሆ ህወሓትን ያንቀጠቀጠ ዉጤት አስመዝግበዋል።
    በዓረና ፓርቲ እንቅስቃሴ ለመሳተፍና የበኩሉን ለመወጣት ፍቃደኛ ያልሆነ የማእከላዊ ኮሚቴ አባል አቶ ሺሻይ አዘናው ሲሆን፤ የቁጥጥር ኮሚሽኑ አባል ደግሞ ገብሩ ሳሙኤል ነው። እነዚህ ሁለት ግለሰቦች ከዓረና ጉባኤ ጀምሮ እስካሁን ድረስ በማንኛውም የፓርቲ እንቅስቃሴ፣ ስልጠና፣ ስብሰባ ወይ የፓርቲ ስራ አልተሳተፉም። እንደ አባላት የፓርቲ ወርሃዊ ክፍያም አላደረጉም። በዚህ ምክንያት በጉባኤ ተመርጠው ሓላፊነት ተሸክመው የተሰጣቸውን ሓላፊነት በአግባቡ ባለመወጣታቸው በማእከላዊ ኮሚቴ ስብሰባ ሊገመገሙና ለያዙት አፍራሽ ተልእኮ ሊከሰሱ ዕቅድ ተይዟል።
    ሌላ ለችግሩ ምንጭ ነው ብለን የምንወስደው የህወሓትን ጫና መቋቋምህ አለመቻል ነው። ህወሓት በዓረና እንቅስቃሴ በመሸበሩ ምክንያት ዓረናን ለማዳከም፣ ከህዝብ ጋር እንዳይገናኝ ለማድረግ እንዲሁም ለማፍረስ ዕቅድ ይዞ እየተንቀሳቀሰ ነው። የህወሓት ዋነኛ ጠላት ዓረና ሆኗል። በዚህ ምክንያት በመከላከያ ደህንነት አማካኝነት በዓረና አባላት ላይ ጫና ለመፍጠር እያንዳንዱ የዓረና አባል ተጠንቷል። ጥናቱ ምን ይፈልጋል? በምን ሊደለል ይችላል? ይፈራል ወይ? ቢታሰር ነው የሚሻለው ወይስ ቢመከር? ወይስ ቢደበደብ? ወዘተ በሚሉ ነጥቦች ላይ ያተኩራል።
    እንደ ውጤቱም ብዙ የዓረና አባላት አባልነታቸውን ከለቀቁ ገንዘብና መሬት እንደሚሰጣቸው፣ ስልጣን እንደሚሰጣቸው ወዘተ ተነግሯቸዋል። ሌሎችም አባልነታቸውን ካላቆሙ እንደሚደበደቡ፣ እንደሚታሰሩ፣ እንደሚገረፉ፣ ከስራ እንደሚባረሩ፣ ንብረታቸውን እንደሚነጠቁ፣ እንደሚገለሉ፣ እንደሚገደሉ ተነግሯቸዋል። በተነገራቸው መሰረት ጥቅም ያገኙ አሉ። ከስራቸው የተባረሩ አሉ። የታሰሩና የተገረፉ አሉ። ሃብት ንብረታቸውን የተነጠቁ አሉ። ሲቀሰቅሱ በድንጋይ የተወገሩ አሉ። አሁን ብዙ የዓረና አባላት በእስር ላይ ይገኛሉ፤ ቃላቸውን በመጠበቃቸው እና በህወሓት ሊደለሉ ባለመቻላቸው።
    ስለዚህ ጥቂቶች ህወሓት በሚፈጥረው ጫና ሲደናገጡ ብዙዎች ግን በቆራጥነት እየታገሉ ነው። አቶ ሺሻይ አዘናውና ገብሩ ሳሙኤል በዓረና እንቅስቃሴ ለመሳተፍ ያልፈለጉበት ምክንያት ምናልባት በዓዲግራት በድንጋይ ስንወገር ስላዩ ይሆናል። ፍርሓትም አንድ ምክንያት ሊሆን ይችላል። በዓረና መርህ መሰረት አንድ የተቃዋሚ ፓርቲ አመራር አባል ግንባር ቀደም ሁኖ መሳተፍ ይጠበቅበታል። መፍራት የለበትም። በጥቅም ሊደለል አይገባም። ከህወሓት ጎን ተሰልፎ ዓረናን ለማፍረስ ጥረት ማድረግ የለበትም።
    በፓርቲ ውስጥ ችግር ካለ በፓርቲ ስብሰባ ይገመገማል፤ ይጣራል፤ ይፈታል። በዓረና ፓርቲ የተፈጠረው የነ ሺሻይና ገብሩ በስራ ምክንያት አለመገኘት ችግር በማዕከላዊ ኮሚቴ ስብሰባ እንዲነሳ ተወስኗል። ማንኛውም የውስጥ ችግር በውስጠ ደንብ ነው የሚታየው። ዓረና የነኚህ ሁለት የአመራር አባላት እምቢተኝነት በማዕከላዊ ስብሰባ አጀንዳ እንደሚሆን ሲነገራቸው ግን “ጉባኤ መጥራት እንፈልጋለን” የሚል ደብዳቤ ለዓረና ፅህፈት ቤት አስገቡ፡፡ ራሳቸው የፈጠሩትን ችግር ላማድበስበስ በፓርቲው ውስጥ ችግር እንዳለ አስመስለው አቀረቡ። “ጉባኤ እንጠራለን” የሚል ጥያቄያቸውም በማዕከላዊ ኮሚቴ ስብሰባ እንደሚታይ ተነገራቸው።
    እነሱ ደብዳቤ ሲያስገቡ ህወሓትም ዓረና እየፈረሰ ነው የሚል ወሬ መንዛት ጀመረ። በተመሳሳይ ግዜ አቶ ሺሻይ አዘናው፣ አቶ ገብሩ ሳሙኤልና አቶ አስገደ ገብረስላሴ “ፓርቲው እየፈረሰ ነው፣ አንባገነንነት እየሰፈነ ነው፣ የዓረና አባላት እየወጡ ነው፣ አስቸኳይ ጉባኤ እንድንጠራ ይፈቀድልን” የሚል መልእክት ያለው ቅሬታ ለዓረና ፅህፈት ቤት አስገቡ። “ጉዳያችሁን በስብሰባ እናየዋለን። እስከዛ ድረስ ግን እንደ አባላት በፓርቲው ስራ ተሳተፉ፣ መብታችሁን ለመጠየቅ ግዴታችሁን ተወጡ” የሚል መልስ ተሰጣቸው። አቶ አስገደ በፓርቲው ስራ ሲሳተፍ አቶ ሺሻይና አቶ ገብሩ ግን አሻፈረን አሉ።
    ቀጥለውም ዓረና በተለያዩ ከተሞች ህዝባዊ ስብሰባዎችና ቅስቀሳዎች በሚያደርግበት ግዜ፣ የዓረና አመራር አባላት በስራ በተጠመዱበት ግዜ በስራ ከመሰማራት ይልቅ “ፓርቲው እየፈረሰ ነው፣ አስቸኳይ ጉባኤ እንጠራለን” የሚል ፅሑፍ ድጋሚ አስገቡ። ህወሓትም ተመሳሳይ አጀንዳ ፈጠረ። ዓረና እየፈረሰ ነው እያለ ፕሮፓጋንዳ መንዛት ጀመረ። ጉዳዩ ሌላ ተልእኮ እንዳይኖረው በመጠርጠር መቐለ የሚገኙ የዓረና የስራ አስፈፃሚ አባላት ተሰብስበው “የአስቸኳይ ጉባኤ” ጥያቄ ለመመለስ ያህል ጥያቄው ፕሮሲጀሩን (Procedure) ጠብቆ መምጣት እንዳለበት ወሰኑ።
    በዚሁ መሰረት ሦስቱ ቅሬታ አቅራቢዎች የዓረናን ህገ ደንብ አክብረው ህገ-ደንቡ በሚፈቅደው መሰረት ጥያቄያቸውን እንዲያቀርቡ ተነገራቸው። አቶ አስገደ ገብረስላሴ ተራ አባል እንደመሆኑ መጠን ማንኛውም ጥያቄ ለመሰረታዊ አደረጃጀት ያቀርባል። መሰረታዊ አደረጃጀቱ ጥያቄውን መርምሮ ከተቀበለው ለክልል ፅህፈት ቤት ያስገባል። ስለዚህ አስገደ በዓረና ህገ-ደንብ መሰረት ጥያቄውን በመሰረታዊ አደረጃጀቱ በኩል እንዲያስገባ ተጠየቀ፤ ህገ ደንቡ የሚፈቅደው ይሄ ነውና። አስገደ ያለበት መሰረታዊ አደረጃጀት አባላትና ሐላፊዎች ግን የአስገደን ጥያቄ እንደማያውቁ፣ ቅሬታም እንዳላስገባላቸው መሰከሩ። ስለዚህ አስገደ ለሚመለከታቸው አካላት ቅሬታውን አለማቅረቡ ታወቀ። በህገ-ደንቡ መሰረት አንድ ተራ አባል መሰረታዊ አደረጃጀትን ሳያሳውቅ ዘው ብሎ ወደ ክልል ፅሕፈት ቤት አያስገባም። አንድ ተራ አባል አስቸኳይ ጉባኤ ለመጥራት የመሰረታዊ አደረጃጀቱ አባላት ሊቀበሉትና ሊያፀድቁት ይገባል።
    አቶ ሺሻይ አዘናው የማዕከላዊ ኮሚቴ አባል በመሆኑ ጥያቄውን ለማዕከላዊ ኮሚቴ እንዲያቀርብ ተነገረው። የማዕከላዊ ኮሚቴ አባል “አስቸኳይ ጉባኤ” ለመጥራት ከማእከላዊ ኮሚቴ አባላት ቢያንስ አንድ ሦስተኛ ሊቀበሉት ይገባል። ከሃያ አምስቱ የዓረና ማእከላዊ ኮሚቴ አባላት ሺሻይ አዘናው አንድ ነው። አንድ የማእከላዊ ኮሚቴ አባል አስቸኳይ ጉባኤ የመጥራት ስልጣን የለውም፤ በህገ-ደንቡ መሰረት። የሺሻይ ጥያቄ በማዕከላዊ ኮሚቴ ስብሰባ እንደሚታይ ግን ተነግሮታል። የዓረና ማዕከላዊ ኮሚቴ ስብሰባ በሁለት ሳምንታት ግዜ ውስጥ እንደሚካሄድም ተነግሮታል። የማዕከላዊ ኮሚቴ አባል ጥያቄ በማዕከላዊ ኮሚቴ ስብሰባ ይፈታል።
    ሦስተኛው ቅሬታ አቅራቢ አቶ ገብሩ ሳሙኤል ደግሞ የቁጥጥር ኮሚሽን አባል በመሆኑ ቅሬታው ይሁን የአስቸኳይ ጉባኤ ጥያቄ ለሚሰራበት የቁጥጥር ኮሚቴ ማቅረብ ይጠበቅበታል። ጥያቄው ለኮሚሽኑ ካቀረበ በኋላ የኮሚሽኑ አንድ አራተኛ አባላት ከተቀበሉት ጥያቄው ተቀባይነት ይኖረዋል። አቶ ገብሩ ሳሙኤል ግን ለቁጥጥር ኮሚሽን ያቀረበው ጥያቄ የለም። በመሆኑም የገብሩ ጥያቄ ወደ ቁጥጥር ኮሚሽን መሆን እንዳለበት ተነግሮታል።
    የሦስቱም ጥያቄዎች በዓረና ህገ-ደንብ መሰረት procedure ጠብቀው መምጣት እንዳለባቸው ሲነገራቸው አቶ ሺሻይና አቶ ገብሩ “ጥያቄያችን ታፍኗል” ብለው የዓረናን ስም የሚያጠፋ ፅሑፍ በተኑ። “በፓርቲው ህገደንብ መሰረት አስገደ ወደ መሰረታዊ አደራጃጀትህ አስገባ፣ ሺሻይ ወደ ማእከላዊ ኮሚቴ ስብሰባ አቅርበው፣ ገብሩ ሳሙኤል ደግሞ ወደ ቁጥጥር ኮሚሽን አቅርብ። ከዛ ጥያቄያቹ መስመራቸውን ጠብቀው ይፈታሉ” የሚል መልስ ሲሰጣቸው “ታፈንን” አሉ። በፓርቲው ብዙ ችግሮች እንዳሉ ተናገሩ። “ፕሮሲጀር (procedure) ተከተሉ” ማለት ጥያቄን ማፈን አልነበረም። ግን አደረጉት። ፓርቲ የፈረሰ አስመስለው ደጋፊዎቻችንን ለማደናገር ሞከሩ። ይህ ተግባር ህወሓት ከሚሰራው ጋር ይመሳሰላል። የዓረና ፓርቲ ችግሮች ያሏቸውን ዘረዘሩ። ግን እንዴት ማወቅ ቻሉ? ከፓርቲው እንቅስቃሴ ከተሰናበቱ ኮ ዘጠኝ ወራት አስቆጥረዋል። በምናደርገው ስብሰባም ይሁን ስልጠና ወይ ሌላ እንቅስቃሴ አይሳተፉምኮ። የፓርቲውን ውስጣዊ አሰራር ለመገምገም ኮ በፓርቲው እንቅስቃሴ መሳተፍ ግድ ይላል።
    እንግዲህ ጥያቄያችሁን በአግባቡ አቅርቡ ስለተባሉ ነው “ታፍነናል” ብለው ፀረ ዓረና እንቅስቃሴ ያደረጉት። ዓረና ቢሆኑ ኑሮ ዓረናን ለማስተካከል ጥረት ባደረጉ ነበር። “በአስቸኳይ ጉባኤ ጥሪ” ስም ባለፈውም ዓረናን ለማፍረስ ተሞክሮ እንደነበር አውቃለሁ። አልተሳካም፤ አሁንም አይሳካም። ጉዳያቸው ግን በማዕከላዊ ኮሚቴ ስብሰባ ይታያል።
    ሎሚ፡- የፓርቲያችሁ ፀሐፊ ፓርቲውን ለቅቋል፤ ምክንያቱ ምንድነው?
    አብረሃ፡- አዎ! የፓርቲያችን የአደረጃጀት ጉዳዮች ሓላፊ የነበረው አቶ ስልጣኑ ሕሸ ከፓርቲው ለመልቀቅ ደብዳቤ አስገብቷል። እንደ ዓረና መርህ ማንኛውም ሰው ፖሊሲያችንና የፖለቲካ አቅጣጫችን እስከተስማማው ድረስ ወደ ፓርቲያችን የመግባት መብት አለው። በፈለገው ግዜም ከፓርቲያችን መልቀቅ ይችላል። መብቱ ነው። ያለ ፍላጎቱ ተጨቁኖ የሚኖር አባል መኖር የለበትም። አቶ ስልጣኑም መልቀቅ ፈልጓል። ለመልቀቅ ያቀረበው ምክንያት አሳማኝ ሆኖ አላገኘሁትም። ግን መልቀቅ መፈለጉ በራሱ በቂ ምክንያት ነው። ፖለቲካ የህሊና ስራ ነውና።
    አቶ ስልጣኑ ሕሸ በመልቀቁ ምክንያት ዓረና ብዙ ነገር አጥቷል ብዬ አስባለሁ። ምክንያቱም አቶ ስልጣኑ ጠንካራና ጀግና ከሚባሉ የዓረና መሪዎች አንዱ ነበረ። ዓረናን ይመራል ተብሎ ተስፋ የተጣለበት ወጣት ነበር። የስልጣኑን ጥንካሬ ግምት ውስጥ በማስገባት ያቀረበው የመልቀቅያ ምክንያት አሳማኝ ሊሆን አይችልም። በፓርቲው ስብሰባ ወይ ግምገማ ማቅረብ ይችል ነበር። እንደግፈው ነበር። የምናምነውና የምንኮራበት ጓዳችን ነበርና ነው። ስለዚህ መውጣት ፈልጓል። ምክንያቱን በግልፅ ስላልነገረን የመውጣት ፍላጎቱን መከልከል አልፈለግንም፤ አንችልምም። ግን እስካሁን ብዙ ነገር ሰርቷል፤ ብዙ አባል አፍርቷል፤ ብዙ አስተዋፅዖ አበርክቷል። የፓርቲውን ግዴታ በአግባቡ የተወጣ ጀግና ነው። ላበረከተው አስተዋፅዖ የምስጋና ደብዳቤም ያስፈልገዋል።
    ሎሚ፡- አንዳንድ አስተያየት ሰጪዎች አረና ውስጥ የሕወሓት ሰርጎ ገቦች ገብተዋል ይላሉ፤
    አብረሃ፡- አዎ! ዓረና ውስጥ የህወሓት አባላት ሳይገቡ አልቀረም። የሚናገሩትና የሚሰሩት ዓረናን ለማፍረስ ያለመ ይመስላል። ግን አጣርተናል ብለን ነው የምናምነው። ህወሓት ሆነው ወደ ዓረና የገቡ፣ ዓረና ሆነው በጥቅም ተደልለው ለህወሓት የሚሰልሉ ቅጥረኞችም ይኖራሉ። መረጃው ቶሎ ይደርሰናል። አፋጣኝ መፍትሄ እናደርጋለን። ስለዚህ የህወሓት በዓረና መግባት ብዙ ችግር አይፈጥርብንም። ችግር እየፈጠረብን ያለው ጠንካራ አባሎቻችን መታሰራቸው ነው። ጉዳት እየደረሰባቸው ነው። አሁን ያለውን የህዝብ መነሳሳት በአግባቡ ለመምራት ብዙ ቋሚ ሰራተኞች መቅጠር ይጠበቅብናል።
    ሎሚ፡- ከአንድነት ጋር ልትዋሃዱ ነው የሚባለው ነገር ምን ያህል እውነት ነው?
    አብረሃ፡- ለመዋሃድ ያሰብነው ከመድረክ አባላት ጋር ነው። በመድረክ ውስጥ ደግሞ አንድነት፣ ኦፌኮና ደቡብ ሕብረት ኢሦዴፓ እንዲሁም ሲአን አሉ። ስለዚህ ከተቻለ እነዚህ ፓርቲዎች በሙሉ ከዓረና ጋር ቢወሃዱ ምርጫችን ነው። ምክንያቱም አንድ ጠንካራ ሀገራዊ ፓርቲ መመስረት ነው የምንፈልገው። ይህ ካልተቻለ ግን ከኦፌኮ ወይ ከአንድነት ወይ ከደቡብ ሕብረት ወይ ከሲአን ጋር እንወሃዳለን። አንድነቶች ከመኢአድ ጋር ለመወሃድ ጥረት እያደረጉ ነው። ውህደቱ ከተሳካ ጥሩ ነው። ዓረናም ተመሳሳይ አጀንዳ ከሚያራምዱ ፓርቲዎች ጋር የመወሃድ ዕቅዱ ይተገብራል። ባጭሩ ባሁኑ ግዜ አንድነት ከዓረና ሳይሆን ከመኢአድ ጋር ለመዋሃድ ነው ጥረት እያደረገ ያለው። ዓረናም የአንድነትና የመኢአድ ውህደት ይደግፋል። ምክንያቱም ዓረና ጠንካራ ውሁድ ሀገራዊ የተቃውሞ ፓርቲ የማየት ራዕይ አለው።
    ሎሚ፡- ፓርቲያችሁ በስፋት በሚንቀሳቀስበት ትግራይ ያለው ተቀባይነት ምን ይመስላል?
    አብረሃ፡- ዓረና በትግራይ ደረጃ እየተንቀሳቀሰ ነው። ሰፊ ድጋፍ እንዳለውም አረጋግጠናል። የትግራይ ህዝብ ሙሉ በሙሉ ለውጥ እንደሚፈልግ ለማወቅ ችለናል። ህወሓትም ይህንን ጉዳይ በሚገባ ተረድቶታል። እናም ብዙ እንቅፋቶች ለመፍጠር እየሞከረ ነው። “ዓረና አያድናችሁም፣ ከፈለግኩ አስራቸዋለሁ ከፈለግኩ እለቃችዋለሁ” እያለ ህዝብን እያስፈራራ ነው። “ዓረና እየፈረሰ ነው። ዓረና አስፓልት መንገድ፣ ባቡር ሃዲድ፣ ሆስፒታል፣ ትምህርት ቤት ወዘተ ሰርቶ አያውቅም” እያሉ ህዝብን እያጭበረበረ ይገኛል። ስም የማጥፋት ዘመቻ ተከፍቶብናል። የህወሓት የደህንነት ሰዎች ራሳቸው አሳስረው ራሳቸው “እናስፈታችኋለን” እያሉ ህዝብን እያስደነገጡ ነው። ፍትሕ ግን ሊሰጡ አልቻሉም።
    ሎሚ፡- አሁን ላይ ሆነህ ቀጣዩን የ2007 ምርጫ እንዴት ትመለከተዋለህ?
    አብረሃ፡- የ2007 ምርጫ ከባድ ነው የሚሆነው። ምክንያቱም ህወሓት ምንም የህዝብ ድጋፍ እንደሌለው ከወዲሁ አረጋግጧል። ስለዚህ ፍትሓዊ ምርጫ ከተደረገ፣ የህዝብ ድምፅ ከተከበረ መሸነፉ አይቀርም። ህወሓት ግን ሽንፈቱን ለመቀበል ዝግጁ አይሆንም፤ ስልጣን መልቀቅ አይፈልግምና። ስለዚህ ጥሩ እንቅስቃሴ የሚያደርጉ የተቃዋሚ ፓርቲ አመራር አባላትን ማሰሩ አይቀርም። የምርጫ ታዛቢዎችን መከልከሉ አይቀርም። የምርጫ ኮሮጆውን በጠመንጃ መጠበቁ አይቀርም። ህዝቡ ግን ለውጥ ይፈልጋል። እኛ ለለውጥ ቀስቅሰን፣ አነሳስተን የህዝብ ድምፅ ሲታፈን ህዝቡ ምን ሊያደርግ እንደሚችል ስለማይታወቅ ህወሓት ተጨናንቋል። ስለዚህ የህወሓት ጭንቀት ላልመረጥ እችላለሁ የሚል አይደለም፤ እንደማይመረጥማ አውቋል። የህወሓት ጭንቀት ህዝቡን እንዴት መቆጣጠር ይቻላል የሚል ነው።
    ዓረና እስከ 2007 ምርጫ አሁን ባለው መንፈስና ጥንካሬ መንቀሳቀስ ከቻለ ግን አብዛኞቹ የህወሓት ካድሬዎችም ጭምር የማሳመን ከፍተኛ ዕድል አለው። የምርጫን ውጤት ሊያጭበረብሩና ሊሰርቁ የሚችሉ ካድሬዎች በለውጥ ማዕበሉ ሰጥመው ለፓርቲ ሳይሆን ለሀገርና ህዝብ እንዲሰሩ የማድረግ አቅም አለን። በተንቀሳቀስንባቸው አካባቢዎች ያገኘናቸው ካድሬዎች ፈጣን የሆነ የአመለካከት ለውጥ ታይቶባቸዋል። ስለዚህ የጨዋታ ካርዱ በህዝቡ አይደለም ያለው፤ በካድሬዎቹ ነው። ምክንያቱም ህዝቡማ ህወሓትን እንደማይመርጥ ተረጋግጧል። ጥያቄው የህዝቡ ድምፅ ይጭበረበራል ወይ የሚል ነው። ህወሓት የራሱ ካድሬዎች እንኳን የዓረናን እንቅስቃሴ አይተው እየካዱት ነው። ስለዚህ የ2007 ምርጫ ወሳኝ ነው።

    Letter to Yemeni Presidnt on the Detention of Andargachew Tsege, Secretary General of Ginbot 7 Movement for Justice, Freedom and Democracy


    July2, 2014
    H.E. Field Marshall Abdu Rabu Mansour Hadi
    President,
    Republic of Yemen
    Sana’a, Yemen
    Your Excellency:
    Re: Yemeni: Detention of Andargachew Tsege, Secretary General of Ginbot 7 Movement for Justice, Freedom and Democracy
    We are writing to express our grave concerns regarding the unlawful and unwarranted detention of Andargachew Tsege, Secretary General of Ginbot 7 Movement for Justice Freedom and Democracy while in transit at Sanaa International Airport on June 23, 2014.
    We are particularly concerned that the continued illegal detention of Mr. Tsege, a renowned critic of the Ethiopian government is politically motivated and against international law.
    We urge the Government of Yemen to release him immediately and unconditionally.
    Mr. Tsege a well-known pro-democracy and human rights advocate in his ancestral homeland, Ethiopia, presents no threat to Yemen or to the Yemeni authorities.
    Mr. Tsege was imprisoned in Ethiopia for his political activities during the ill-fated election of 2005 and has escaped assassination attempts by the dictatorship whose brutality, is well documented even by the United States State Department.
    It is now universally recognized that the Ethiopian regime subjects political opposition, human rights defenders, journalists and critics of the government in general, to persecution including threats, intimidation, arbitrary arrests and detentions, politically motivated trials, enforced disappearances and extra-judicial killings.
    It’s unconscionable that the Government of Yemen would hand Mr. Tsege over summarily to the security forces of the country whose persecution of its critics at home and abroad is well documented.
    We would like to call your Excellency’s attention to the doctrine of non-refoulement, now recognized as a norm of customary international law. As such all persons are protected under international human rights law from return to any country where they would be in danger of being subjected to torture and extra-judicial killings. Such is the case of Mr. Tsege and we urge your government to adhere to these recognized principles aimed at protecting human rights.
    We respectfully write this letter:
    • To convey our profound concerns for the security of Mr. Tsege and to request his immediate and unconditional release.
    • To call upon the Government of Yemen to respect its solemn obligations under international law to protect Mr. Tsege from arbitrary detention
    • To request your Excellency to use the powers vested in your office to stop any illegal renditions the government of Ethiopia may have requested
    We would like to impress upon you the long and historical ties between the Yemeni and Ethiopian people and we urge you to protect the security of our compatriot and to release him immediately.
    We also trust that Yemeni authorities would not engage in any harmful acts that would endanger the well-being, safety and security of Mr. Tsege. It should be self-evident that such acts would only bring about adverse consequences for the future relations between the peoples of Yemen and Ethiopia.
    Please accept, Your Excellency, the assurance of our highest considerations.
    Sincerely,

    Berhanu Nega, Ph.D.
    Chairman
    Ginbot 7 Movement for Justice Freedom and Democracy

    አቶ አንዳርጋቸው በየመን መንግስት ከታገቱ በሁዋላ የኢትዮጵያ ትምባሆ ድርጅት ለየመን ኩባንያ ተሰጠ

    June2/2014
    የግንቦት 7 አመራር አባል በየመን መንግስት ታግተው ከተያዙ ከአንድ ሳምንት ወዲህ የፕራይቬታይዜይሽንና የመንግሥት የልማት ድርጅቶች ተቆጣጣሪ ኤጀንሲ ውሳኔ መስጠት በተቸገረበት የብሔራዊ ትምባሆ ድርጅት ሽያጭ ጉዳይ ላይ፣ የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት ውሳኔ በመስጠት ለየመን ኩባንያዎች ከፍተኛ የአክሲዮን ድርሻ እንዲወስዱ ተደረገ::
    andargachew
    በአሁኑ ወቅት የመን አቶ አንዳርጋቸው ጽጌን አግታ ባለችበት ወቅት የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት የየመኑ ኩባንያ ሼባ ኢንቨስትመንት የብሔራዊ ትምባሆ ድርጅት 60 በመቶ ባለቤት እንዲሆን መወሰኑ በርካታ ፖለቲከኞችን እያነጋገረ ይገኛል;:
    ሪፖርተር ጋዜጣ እንደዘገበው የ70 ዓመት ዕድሜ ባለቤት የሆነው ብሔራዊ ትምባሆ ድርጅት 22 በመቶ የሚሆነው አክሲዮን ከ1991 ዓ.ም. ጀምሮ በየመኑ ሼባ ኢንቨስትመንት ሲያዝ፣ ቀሪው 78 በመቶ አክሲዮን ደግሞ በመንግሥት የተያዘ ነበር፡፡
    የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት በወሰነው አዲስ ውሳኔ ሼባ ኢንቨስትመንት ተጨማሪ 38 በመቶ አክሲዮን ከመንግሥት ላይ እንዲገዛ የሚፈቅድ በመሆኑ፣ ሼባ ኢንቨስትመንት በብሔራዊ ትምባሆ ድርጅት አክሲዮን ላይ አንበሳውን ድርሻ 60 በመቶ ሲይዝ፣ መንግሥት ደግሞ 40 በመቶ ድርሻ ይዞ ይቀጥላል፡፡
    ሼባ ኢንቨስትመንት እንዲገዛ ለተፈቀደለት 38 በመቶ አክሲዮን 1.3 ቢሊዮን ብር መክፈል እንደሚጠበቅበት የፕራይቬታይዜሽንና የመንግሥት የልማት ድርጅቶች ተቆጣጣሪ ኤጀንሲ ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ኃላፊ አቶ ወንዳፍራሽ አሰፋ ለሪፖርተር ገልጸው፣ ኩባንያው ይህንኑ ገንዘብ እንደከፈለ የስም ዝውውር እንደሚደረግ አስታውቀዋል፡፡
    ብዙም ባልተመለመደ ሁኔታ የብሔራዊ ትምባሆ ድርጅት አክሲዮን ሽያጭ ላይ የፕራይቬታይዜሽን ኤጀንሲ የሥራ አመራር ቦርድ ውሳኔ ለመስጠት የተቸገረው በሁለት ምክንያቶች መሆኑን ምንጮች ይገልጻሉ፡፡ የመጀመርያው ድርጅቱ በሲጋራ ላይ ብቸኛ መብት (ሞኖፖሊ ራይት) ያለው በመሆኑ፣ ይህ የብቸኝነት መብት የየመኑ ኩባንያ ከፍተኛ ድርሻ በሚይዝበት ወቅት ምን መሆን አለበት? የሚለው ጉዳይ ላይ አቋም መያዝ ባለመቻሉ ነው፡፡ ሁለተኛው ጉዳይ ደግሞ ትምባሆ ድርጅት በተለያዩ የታክስ ዓይነቶች በየዓመቱ ከ1.3 ቢሊዮን ብር በላይ ለመንግሥት የሚያስገባ ከመሆኑም በተጨማሪ፣ ትርፋማ ከሆኑ የመንግሥት የልማት ድርጅቶች መካከል አንዱ በመሆኑ፣ ለመንግሥት ግምጃ ቤት ከፍተኛ ገንዘብ ፈሰስ የሚያደርግ ነው የሚለው ጉዳይ ቦርዱ በአክሲዮኑ ሽያጭ ላይ ለመወሰን እንዲቸገር ማድረጉ ነው፡፡
    በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ማዕረግ የሲቪል ሰርቪስና የመልካም አስተዳደር ክላስተር አስተባባሪና የሲቪል ሰርቪስ ሚኒስትር በሆኑት ወ/ሮ አስቴር ማሞ የሚመራው የፕራይቬታይዜሽን ቦርድ በእነዚህ ጉዳዮች ላይ የመንግሥትን አቅጣጫ በግልጽ ባለመረዳቱ፣ የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት አቅጣጫ እንዲሰጠው መጠየቁን መዘገባችን ይታወሳል፡፡ ነገር ግን የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት ሁለቱም ጉዳዮች እንዳሉ ሆነው የአክሲዮን ሽያጩ እንዲከናወን በማዘዙ፣ ባለፈው ሳምንት ሐሙስ የተሰበሰበው የፕራይቬይታዜሽን ቦርድ የየመኑ ኩባንያ ከፍተኛ ባለድርሻ መሆን የሚያስችለውን ውሳኔ እንዲወስን ማድረጉን ምንጮች ገልጸዋል፡፡
    ትምባሆ ድርጅት በተለያዩ አካባቢዎች የትምባሆ ልማት የሚያካሂድባቸው የእርሻ መሬቶች ባለቤት ነው፡፡ የድርጅቱ መሥርያ ቤት ከሜክሲኮ አደባባይ ወደ ሳር ቤት በሚወስደው መንገድ ከአፍሪካ ኅብረት ፊት ለፊት የሚገኝ ሲሆን፣ ለፀጥታ አመቺ አይደለም በሚል መሥርያ ቤቱ ከዚህ ቦታ ተነስቶ ወደ አቃቂ አካባቢ እንዲዛወር ተወስኗል፡፡ ምንጮቹ እንደገለጹት ድርጅቱ ቃሊቲ አካባቢ ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በተረከበው ቦታ ላይ የሚያካሂደውን ግንባታ ሲያጠናቅቅ፣ ለበርካታ ዓመታት ከነበረበት ቦታ ይነሳል ሲል ሪፖርተር ዘገባውን አጠናቁአል::
    ውድ አንባቢያን በኢትዮጵያ አትራፊና ከፍተኛ ታክስ ከፋይ ከሆኑ ትላልቅ የመንግስ ኩባንያዎች መካከል አንዱ የሆነው የብሔራዊ ትምባሆ ድርጅት አቶ አንዳርጋቸው ከታሰሩ ወዲህ ለየመኑ ኩባንያ በጠቅላይ ሚኒስተር መስሪያ ቤት ትዕዛዝ ሙሉ በሙሉ እንዲተላለፍ መደረጉ ዙሪያ ምን ትላላችሁ?

    አንዳርጋቸውን ፍለጋ በየመን…ወዳጄ የሀገር ሰው የት ይሆን የታሰርከው?

    July 1/2014
    በግሩም ተ/ሀይማኖት

    ትላንት ነው አስደንጋጭ ዜና የሰማሁት፡፡ ስለ አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ በየመን መታሰር፡፡ ከምር በጣም ደንግጫለሁ፡፡ የመን ያለውን ሁኔታ ስለምኖርበት በደንብ አውቀዋለሁ፡፡ የመን አሁን ያሉም በፊት የኖሩም በትክክል ያውቁታል፡፡ ድንጋጤዬን እንደያዝኩ በተለያየ ሀሳብ እና መላምት ስታትር፣ ነግቶ የት እንዳለ ለመፈለግ የት የት ሄጄ መፈለግ እንዳለብኝ ውስጤ በእቅድ ስነድፍ ቆየሁ፡፡ እቅዴ ተወስኖ ሳያልቅ ከተለያየ አቅጣጫ የሚያውቁኝ ጉዳዩ ያሳሰባቸው ሰዎች ተንቀሳቃሽ ስልኬ(ሞባይሌ) ላይ እየደወሉ ስለሁኔታው ይጠይቁኛል፡፡ የማውቀው እንደሌለ እና ምን ማድረግ እንደምችል ግራ እንደገባኝ ከመንገር ውጭ መልስ አጣሁ፡፡ ከተለያዩ መገናኛ ብዙሀን ለሚደወልልኝም መልስ አጠረኝ፡፡ ሌሊቱ እስኪጋመስ ድንጋጤዬ አለቀቀኝም፡፡ የድንጋጤዬ መንስኤ ሶስት ነገር ነበር፡፡

    1ኛ፡- የመን እንደገባሁ ተይዤ እስር ቤቶቹን ስላየኋቸው፡፡ እኔን አንድ ጋዜጠኛ ወደ ሀገሬ ለመመለስ ‹‹ወኪል ኒያባ›› የሚባለው ፍርድ ቤት እስከማቆም የወያኔ ካድሬዎች ያደረጉትን በማሰብ…


    2ኛ፡- ከኢትዮጵያ ውጭ የወያኔ ካድሬዎች እንደልብ ከሚንቀሳቀሱባቸው ሀገሮች የመን የመጀመሪያዋ እና በሺህ የሚቆጠሩ ካድሬዎች ያሉባት በመሆንዋ…


    3ኛ፡- የመንና ኢትዮጵያ እ.አ.አቆጣር ከ2004 ጀምሮ በየአመቱ የሚታደስ ወንጀለኛ የመለዋወጥ የሁለትዮሽ ስምምነት ያላቸው በመሆኑ ነው ድንጋጤዬ ልክ ያጣው፡፡


    ባሰብኩት መሰረት ፍለጋዬን ለመቀጠል በዛሬው እለት ጠዋት…የኢሳቱ ጋዜጠኛ ፋሲል የኔአለም ጋር በመደወል መታሰሩን ሲሰሙ የታሰረበትን እስር ቤት ሰምተው እንደሆነ ጠየኩኝ፡፡ ምንም ፍንጭ የለም ትራንዚት ሲያደርግ መያዙን ብቻ ነው የሚያውቁት፡፡ ፍለጋዬን ከሚግሬሽን እስር ቤት ጀመርኩ፡፡ ሞባይል ስልኬ ግን በሁኔታው የተጨነቁ ሰዎች ሲደውሉ ተጨናንቆ ዋለ፡፡ ኢሚግሬሽን እስር ቤት አስፈልጌ የለም፡፡ ወደ ኤርፖርት በመሄድ እዛው ባለው ጊዜያዊ እስር ቤት ታስሮ ከሆነ አስጠየኩ፡፡ የለም፡፡ በመቀጠል የደህንነት ቢሮ በእነሱ አጠራር ‹‹አምንስቲያሲ..›› ሄጄ የሚታወቅ ነገር እንዳለ ጠየኩ፡፡ የረመዳን ጾም በመሆኑ የፍጡር ሰዓት ደርሷል እና ከፈለክ ክፍጡር በኋላ ካልሆነም ነገ ጠዋት መተህ ጠይቅ አሉኝ፡፡ ምን አስችሎኝ ነገ ድረስ ልቆይ…ከምሽቱ ሶስት ሰዓት አካባቢ ሄጄ ባስፈልግም የለም ሆነ ያገኘሁት ምላሽ፡፡


    ‹‹..ወዳጄ የሀገሬ ሰው የት ይሆን የታሰርከው?..›› የሚል እሳቤ ውስጤ ተላወሰ፡፡ ለነገሩ የታሰረበትን ባውቅስ ምን ማድረግ እችል ይሆን? የሚል እሳቤም ሰቅዞ ያዘኝ፡፡ በእርግጥ የመን ከታሰረ ያለው ሁኔታ በጥሩ መንፈስ አይሸትም እና ሁላችንም ተላልፎ እንዳይሰጥ ድምጽ እንድናሰማ ለራሴ አሳሰብኩኝ፡፡…ፍለጋው አያልቅም ነገ ቸር ያሰማኝ ይሆን?...ፍለጋው አያልቅም ነገ ቸር ይገመኝ ይሆን?

    Tuesday, July 1, 2014

    የአቶ አንዳርጋቸውን ጽጌን በየመን መታፈን ተከትሎ ኢትዮጵያውያን የተለያዩ አስተያየቶችን እያሰጡ ነው

    July 1/2014
    ሰኔ ፳፬(ሃያ አራት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የየመን የጸጥታ ሃይሎች የግንቦት7 ንቅናቄ ዋና ጸሃፊ የሆኑትን አቶ አንዳርጋቸውን ማፈናቸውን ተከትሎ በፌስቡክ፣ በቲውቲርና በድረገጾች ላይ የተለያዩ አስተያየቶች ተሰጥተዋል።

    አክቲቪስት አበበ ገላው በበኩሉ የመን አቶ አንዳርጋቸው ጽጌን ማገቷ   ሌላአደገኛና በጣም አሳሳቢ ክስተት ነው።የአንባገነኑየህወሃትስርወመንግስትተቃዋሚዎችንማንምአገርበምንምአይነትሁኔታማፈን፣ማሰርናማንገገላታትአለምአቀፍህግንየሚጥስህገወጥድርጊትነው።የመንአቶአንዳርጋቸውንለወያኔአሳልፋእንዳትሰጥናያለምንምቅድመሁኔታእንድትለቅሁሉምነጻነትናፋቂኢትዮጵያዊሁሉበጋራጥረትሊያደርግይገባል።የየመንኤምባሲዎችንበያሉበትበተቃውሞማጨናነቅናእንቅልፍመንሳትእንዲሁምአለምአቀፍጫናማድረግያስፈልጋል።ግዜሳይረፍድይህንንየቁርጥቀንኢትዮጵያዊለመታደግበያለንበትበጋራእንረባረብ።” ሲል ጥሪ አቅርቧል።

    ፕራይድ ዲ ባሰፈረው ጽሁፍ ደግሞ ” እውነተኛ ታጋይ ሊታሰር ሊሞት ይችላል፣ የተጀመረውን ትግል ግን ሊያስሩትም ሆነ ሊገሉት ከቶ አይቻላቸውም። ኢትዮጵያም አንድ አንዳርጋቸውን ብቻ ሳይሆን ሚሊዮን አንዳርጋቸውን ፈጥራለችና በከንቱ አትድከሙ፣ ወደዳችሁም ጠላችሁም ሁላችንም ግንቦት 7 ነን።” ብሎአል።

    የአረና ፓርቲ አመራር አባል የሆነው ወጣቱ ፖለቲከኛና መምህር አብራሀ ደስታ ከመቀሌ ባሰፈረው ጽሁፍ ደግሞ ” በርካታኢትዮጵያውያንስደተኞች በየመን ሲሰቃዩ የኢህአዴግ መንግስት ዝምታመምረጡይገርመኝ ነበር።ኢትዮጵያውያን በየመንይታሰራሉ፣ይገረፋሉ፣ይገደላሉ።መንግስትናሀገርየሌላቸውይመስልማንምየሚደርስላቸውየለም።ይህንነገርእንቆቅልሽሆኖብኝነበር።ለካኢትዮጵያውያንስደተኞችበየመንሲሰቃዩየኢትዮጵያመንግስትሰምቶእንዳልሰማየሆነውየየመንመንግስትየግንቦት 7ንአመራርአባላትበመያዝእንዲተባበረውለማግባባትነው።ይሄው ኢህአዴግለዜጎች ደህንነት ሳይሆን ለስልጣኑ የቆመ   የማፍያዎችድርጅትመሆኑአስመሰከረ።መንግስትየሚመሰረተውየህዝብናሀገርደህንነትለመጠበቅነው።ኢህአዴግግንየስደተኞችንደህንነትወደጎንትቶለስልጣኑየሚፈታተኑትንግለሰቦችበመያዝስራተጠምዷል።ለስልጣንጥበቃየሚውልንያህልለዜጎችደህንነትምየሚውልቢኖርመልካምነውእላለሁ።” ብሎአል።

    ዘላለም ጸጋየ በበኩሉ ” በሀገራችንመኖርሲያቅተንእንሰደዳለን፡፡
    ተሰደንእንኳንእንታደናለን፡፡ኦአምላክሆይምነውእረሳኸን፡፡ኢትዮጵያውያንልጆችህእንደራሄልእንባቸውጸባዖትየሚደርሰውመቸነው፡፡ ጃያስተሰርያ” ያለ ሲሆን፣ ነጻነት ይበልጣል ደግሞ”የመንበኢትዮጵያህዝብየነፃነትትግልላይጣልቃመግባቷንእንድታቆምለጫትናለርካሽለሆነጥቅምየወንበዴስብስብየሆነውወያኔኢህአዴግጋርበማበርታጋዮቿላይእየደረሰላለውአፍናመከራእንግልትተባበሪበመሆንየሀገራችንታሪካዊጠላትእየሆነችእንደምትገኝሊገነዘቡትይገባል:፡” ብሎአል።

    የነፃነት ትግል ሁሉንም መራራ መከራ ለመቀበል መፍቀድ ነው በሚል ርእስ ሥርጉተሥላሴ ባወጣችው ጽሁፍ ደግሞ ” የነፃነትትግልመከራንለመቀበልተፈቅዶናተወዶየሚወሰድእርምጃነው።የነፃነትትግልየጫጉላጊዜሽርሽርአይደለም።ሊሆንምከቶውንምአይችልም።ስለዚህ ዛሬ በግንቦት 7ጸሐፊ በአቶ አንዳርጋቸው ጽጌ የደረሰው እግታ ከትግልመስምር አንዱ በመሆ ኑ ሊያደናግጥ የሚገባው የዓለም ፍጻሜ አይደለም። ጀግኖች አባቶቻችንና እናቶቻችን እራሳቸውን ሰጥተው ነው ኢትዮጵያሀገራችንከክብሯጋርያቆዩን።” ብላለች።

    ሙላት ሃይሉ ለየመኑ ፕሬዚዳንት በጻፈው ደብዳቤ ደግሞ ” የየመን መንግስት ከኢትዮጵያ ጋር የሚኖረውን የረጅም ጊዜ የጥቅም ግንኙነት በመመርመር አቶ አንዳርጋቸውን አሳልፎ እንዳይሰጥ ጠይቋል። ሙላት አቶ አንዳርጋቸው በኢትዮጵያ ውስጥ ዲሞክራሲያዊ ስርአት እንዲሰፍን እራሱን አሳልፎ የሰጠ ሰው መሆኑን ገልጿል።

    ለኢሳት በኢሜል ከደረሱት መልእከቶች መካከል ፣ አዱኛ የተባሉ ሰው “ለነጻነት በሚደረግ ትግል  ውስጥ መሪ ወይም ታጋይ ቢሞት፣ ቢታሰር ወይም ቢሰደድ ትግል አይቆምም፣ ትግል የሚቆመው ወይም ቅርጹ የሚቀየረው የተፈለገው ነጻነት ሲመጣ ብቻ ነው። አንድ መሪ በመታሰሩ ወይም በመሞቱ ትግል የሚቆም ቢሆን ኖሮ የጆን ጋራንግ ደቡብ ሱዳን ወይም የማንዴላዋ ደቡብ አፍሪካ እስከዛሬም አይወለዱም ነበር። አንዳርጋቸው ጽጌ ኢትዮጵያ ካፈራቻቸው ጀግና የነጻነት ታጋዮች መካካል በመጀመሪያው ረድፍ የሚሰለፍ ነው። አንድም ቀን ለልጆቹና ለኑሮው ሳያስብ በረሃ ለበረሃ የሚንከራተት፣ ለአገሩ ነጻነት ሲል ውድ ህይወቱን ለመስጠት ቆርጦ የተነሳ እውነተኛና ጀግና መሪ ነው።  አንዳርጋቸው ቆራጥና ጀግና ሰው ነው። የአገሩ ጉዳይ ሁሌም ስለሚያንገበግበው እረፍት የለውም። የየመን መንግስት አንዳርጋቸውን ለወያኔ ጅቦች አሳልፎ እንደማይሰጠው ተስፋ አደርጋለሁ፣  ቢያደርገው እንኳን ለነጻነት የሚደረገው ትግል መልኩን ቀይሮ፣ እስካሁን ከታየውም በበለጠ ቆራጥነትና አንዳንዴም ጭካኔ በተሞላበት መንገድ ይካሄዳል እንጅ አይደበዝዝም።  ” ብሎአል።


    የኢትዮጵያ ህዝብ በዝምታ እየተቀበላቸው የሚገኙት በደሎች

    July 1/2014
    የኢትዮጵያ ህዝብ በዝምታ እየተቀበላቸው የሚገኙት በደሎች
    ከአንድነት ሃይሌ
    በየመን የአቶ አንዳርጋቸው ፅጌ መታገትን በመስማቴ አዘንኩ፤ የኢትዮጵያ ህዝብ በዝምታ እየተቀበላቸው የሚገኙትን በደሎችም መለስ አድርጌ ባጭሩ እንድቃኝ አስገደደኝ።
    ያሳዝናል! በአመት ከ70 ሺህ በላይ ኢትዮጵያውያን ህፃናት በማደጎነት ሲሸጡ እያየን፣ እየሰማን፤ ከ45 ሺህ በላይ ሴቶቻችን ለሳውዲ አረቢያ በቤት ሰራተኝነት ሲቸረቸሩና፤ ቁጥር ስፍር የሌላቸው ዜጎቻችን በተመሳሳይ መልኩ ለሌሎች አረብ ሃገራት በሃራጭ ሲሸጡ እያየን፣ እየሰማን፤ ሴቶቻችን በየ አረብ ሃገሩ ለመስማት እጅግ በሚያዳግት ሁኔታ አሰቃቂ በደሎች ባደባባይ ሲፈፀምባቸው እያየን፣ እየሰማን፤ አያሌ ኢትዮጵያውያን ዜጎች ህይወታቸውን ለማትረፍና ለማሻሻል ወደተለያዩ ሃገራት ተሰደው ስቃይ ውስጥ እንደሚገኙ እያየን፣ እየሰማን፤ ከዚህም በላይ ደግሞ ይህ ሁሉ በደል በዜጎች ላይ ሲፈፀም ቢያንስ ተቃውሞውን ሊያሰማ ፈፅሞ ፍላጎት የሌለው፤ ይባስ ብሎ በደሉን በተቃወሙ ዜጎች ላይ ከበዳዮቹ ሃገራት ጋር በማበር ንፁሃን ዜጎችን የሚደበድብ፣ የሚያስር ጭካኝ ስርዓት በጫንቃችን ተሸክመን፤ አንጀታችን እያረረ፣ ልባችን በሃዘን እየተጎዳ፣ ሞራላችን በውድቀት እየተሰበረ፣ አንገታችንን ደፍተን በዝምታ እየኖርን እንገኛለን።
    ሁላችንም እንደምናቀው የኬኒያ፣ የሱዳን፣ የጅቡቲና፣ ሌሎች የጎረቤት ሃገራት በወያኔ በደል ምክንያት ሳይወዱ ተገደው ህይወታቸውን ለማዳን ከሃገራቸው በተሰደዱ ኢትዮጵያውያን ላይ በተደጋጋሚ አፈና እየፈፀሙ ይገኛሉ። በቅርቡ በኬኒያ መንግስት ታፍኖ ለወያኔ ከተሰጠ በኋላ ህይወቱ እስክታልፍ ድረስ ለአመታት በወያኔ እስር ቤት በተሰቃየው በወንድማችን ወጣት ተስፋሁን ጨመዳ ላይ የተፈፀመውን አሳዛኝ በደልና በኦብነግ አመራር አባላት ላይ የተደረገው አፈና፤ በደቡብ ሱዳን በአቶ ኦኬሎ አኩአይና ሌሎች የጋምቤላ ንቅናቄ አባላት ላይ በተመሳሳይ መልኩ የተደረገው አፈና ያለምንም ተጨባጭ እርምጃ በዝምታ ታልፈዋል። ዛሬ ደግሞ የየመን መንግስት በአሳዛኝ ሁኔታ አቶ አንዳርጋቸው ፅጌን ማገቱ በመገናኛ ብዙሃን ተነግሯል።
    በዜጎቻችን ላይ እየደረሱ ለሚገኙት አሰቃቂ በደሎች በዋነኝነት ተጠያቂው የወያኔ መንግስት ቢሆንም፤ በስደት የሚኖሩ ዜጎቻችን ላይ ከወያኔ መንግስት ጋር በመተባበር በተደጋጋሚ አፈና እየፈፀሙና አጋልጠው እየሰጡ የሚገኙ የጎረቤት ሃገራት ወደፊት በኢትዮጵያ ህዝብና መንግስት ተጠያቂ እንደሚሆኑ ምንም ጥርጥር የለኝም። ነገር ግን ወገኖቼ ይህ አፈና እስከመቼ ይቀጥላል!? ዜጎች ጭቆናን በመቃወማቸው ብቻ በስደት ከሚደርስባቸው ስቃይ በላይ ለምን በየ ጎረቤት ሃገሩ ይታፈናሉ!? እኛ ኢትዮጵያውያን እስከመቼ እየተናቅን እንኖራለን!? ጎበዝ ዝምታውና መነጣጠሉ ይብቃ! የሚደርስብንን አፈና ለማስቆምና ራሳችንን ለመከላከል ሁላችንም በአንድነት ጫና መፍጠርና ማስገደድ ግድ ስለሚለን፤ በምንችለው ሁሉ መረባረብና መተባበር ይኖርብናል እላለሁ።
    አፈናው ይብቃ!

    Open Letter to President of Yemen

    July 1, 2014

    Open letter to Abd Rabbuh Mansur Hadi: President of Yemen Arab Republic

    by Mulat Hailu
    yemen-andargachew
    The people of Ethiopia are Shocked and disappointed over the illegal detention of Andargachew Tsige, Secretary General of Ginbot7 Movement for Justice, Freedom and Democracy by Yemen security forces during his transit flight in Yemen.
    Mr. Andargachew is an Ethiopian origin and British citizen who has been struggling for prevalence of democracy in Ethiopia. He has devoted himself to the true cause of Ethiopian people, the inevitable desire for democracy. Though foiled successfully, the criminal dictatorial regime in Ethiopia has attempted to assassinate the leader Andargachew in November 2013. Mr. Andargachew is hero for Ethiopian people and is one of the icons of democracy in the nation.
    The Senna Security forum that has been signed under former president of Yemen, Ali Abdullah Saleh and former dictator of Ethiopia Melse Zenawi which lead TPLF to establish surveillance base in Yemen for surveillance and phone tapping on Ethiopian opposition has been serious concern for Ethiopian people. The illegal detention of Mr. Andargachew, by Yemen Security forces since June 23, 2014 has no ground and is grave concern for the people of Ethiopia. We urge the government of Yemen to immediately free Mr. Andargachew and the Yemen security forces not to transfer him to the criminal regime in Addis under any circumstance. Yemen has no ground to detain Mr. Andargachew who has been tirelessly working for prevalence of democracy in Ethiopia. We request the government of Yemen to carefully evaluate its long term interest and lasting cooperation with the people of Ethiopia and avoid short termism in dealing with dictatorial regime in Ethiopia. The long historical relationship between the people of the two sisterly nations has endured, in spite of changing regimes, on the basis of mutual cooperation. The people of Ethiopia considers the act of transferring Mr. Andargachew to the dictatorial regime in Ethiopia as direct attack on its long aspiration and struggle for genuine democracy in the nation. We hereby request President Hadi not to take any steps that will jeopardies the long lasting relationship between the people of the two sisterly nations and to order the immediate release of Mr. Andargachew. Thank you in advance for your serious consideration.