Wednesday, August 7, 2013

ሰላማዊ የመብት ጥያቄ በሠለጠነ ውይይት እንጂ በአፈናና ግድያ መቼም ቢሆን አይፈታም!

የኢትዮጵያ ህዝብ የጋራ ትግል ሸንጎ
ኅምሌ 27 ቀን 2005 ዓ/ም

22 ዓመት ሙሉ ነፍጡን ከፊት አስቀድሞ የተፈጥሮ፣ ዴሞከራሲያዊና ሕጋዊ የሆኑ መብቶቹን ለማሰከበር በግምባር ሲታገል የቆየውን ምስኪን ህዝብ በገፍ እያሠረ፤ ኢሰብዓዊ በሆነ መንገድ እያሠቃየውና ግፍ በተሞላበት ግድያም እየቀጣው የቆየው የህወሓት/ኢሕአዴግ ግፈኛ አገዛዝ፣ ይኸው ዛሬም በሰላማዊው ሕዝብ ላይ ባፈናና ግድያው ቀጥሎበት ይገኛል።

 ሐምሌ 25 ቀን 2005 ዓ/ም በምዕራብ አሩሲና በሻሸመኔ አካባቢ ኢማሞቻችን/መሪዎቻችን ይፈቱ እያሉ በሰላማዊ መንገድ ድምጻቸውን ባሰሙ ሙስሊም ኢትዮጵያውያን ላይ የግፍ ግድያ መፈጸሙን ሽንጎው የተገነዘበው በከፍተኛ ሃዘን ነው። ልጆቻችሁ፣ አባቶቻችሁ፤ እናቶቻችሁ፣ እህቶቻችሁና ወንድሞቻችሁ ለህወሓት/ኢሕአዴግ ጥይት ሰለባ ለሆኑባችሁ ወገኖች ሁሉ ጽናቱንና ቁርጠኝነቱን ይስጣችሁ እያልን፤ ዛሬም እንደትናንቱ የታፈነ ድምጻችሁን በማስተጋባትና ጥያቄያችሁም ፍትሃዊ ምላሸ እንዲያገኝ ከጎናችሁ በመቆም ለመታገል ቃል እንገባላችሁዋለን።

የህወሓት/ኢሕአዴግን ማንቁርት ይዞና ሥልጣኑን ጠቅልሎ በመያዝ ከፋፋይ የፖለቲካ መርዙን ሲረጭ የኖረው አምባገነን መሪያቸው የዛሬ ዓመት ገደማ ሲሞት ምናልባት የፖለቲካ ምህዳሩ በመጠኑም ቢሆን ተከፍቶና ተለሳልሶ ቢያንስ አፈናና ጭፍጭፋ ይቆምና የፖለቲካ እሥረኞችም ይፈቱ ይሆናል የሚል እጅግ አናሳም ቢሆን ግምት ተንጸባርቆ ነበር። ባመቱ የመሠከርነው ዕውነታ ግን ያው የተለመደው አፈናና ግድያ በማናለብኝነት መቀጠሉን ነው። ከዚህ ካሁኑ ግድያ አንድ ቀን አስቀድሞ ባዲሱ የፖሊስ ኮሚሸነር ትዕዛዝ ባገር ውስጥ የዜና ማሠራጫ ተነገረ እንደተባለው ማስጠንቀቂያ ከሆነ፤ ደም አፍስሰው ያልጠገቡትና ወሳኝ ሚና እየተጫወቱ ያሉ መሪዎች የግፍ ዱላቸውን በሌሎችም አካባቢዎች ሊቀጥሉበት የወሰኑ ይመስላል።

ከዘመን ብዛትና ከኢትዮጰያ ህዝብ ቁርጠኝነት እነዚህ የዘመናችን ገዢዎቹ የተማሩትና ሊማሩም ያሰቡት ነገር ምን ይሆን እያልንና ሥልጣኔ በጎደለው ድርጊታቸው እየተደመምን፤ ሕዝባችን ግን በገዥዎች ትንኮሳ ሳይረበሽ ባጠመዱለትም ወጥመድ ሳይጠለፍ የጀመረውንም እልህ አሰጨራሽ እና የሰለጠነ ትግል አጠናክሮ እንዲገፋ አደራ እያልን፤ እኛም ከጎኑ ቆመን ከመታገል ወደሁዋላ እንደማንል ቃል እንገባለን።

ሁሉም ኢትዮጵያውያንም ይህን የህወሓትን/ኢሕአዴግን ኋላቀር አረመኔአዊ ጭፍጨፋ አጥበቀው እንዲያወግዙና የመብት ጥያቄን ከሚያነሱ ሁሉ ጎን በመሰለፍ ገዳዮች ለፍርድ እንዲቀርቡ፤ የዕምነት ነጻነት እንዲከበር፣ እንዲሁም የታሰሩት እንዲፈቱ ትግሉን እንዲያጠናሩ ጥሪአችንን እናቀርባልን።

ድል ለኢትዮጵያ ሕዝብ

Tuesday, August 6, 2013

ወያኔዎች ኢትዮጵያውያን ሙስሊሞችን በሽብር ተግባር ለመወንጀል ቦምብ አያፈነዱም ብሎ ማሰብ የዋህነት ነው

August 6, 2013
እንደልቡ ወርቁ

A bomb exploded near a court in the west of Ethiopia's capital Addis Ababaባለፉት ሀያ አንድ አመታት ኢትዮጵያ ውስጥ “የሽብር ተግባራት” የሚመስሉ “ሽብሮች” ተከናውነዋል። በሚኒባስ ዉስጥ፣ በሆቴሎች ዉስጥ፣ በቤተ ክርስትያን ቅጥር ግቢ ዉስጥ ወዘተ… ይሁንና ለአንዳቸውም የሽብር ጥቃቶች ባለቤት ተገኝቶላቸው አያውቅም፣ ባለቤት መገኘቱ ይቅርና የረባ ተጠርጣሪ ተይዞ ፍርድ ቤት ሲመላለስ እንኳ አልታየም።

የኢትዮጵያ ተቃዋሚ ፖለቲከኞችና ህዝቡ ግን “ሽብሮቹን” የሚፈጽመው እራሱ ወያኔ ነው በማለት ያጉረመርሙ ነበር።
ህዝቡም ሆነ ተቃዋሚዎች በሽብር ተግባራቱ ወያኔን ክፉኛ ከሚጠረጥሩባቸው ምክንያቶች ውስጥ፣

1) ወያኔዎች በህዝብ ዘንድ ከፍተኛ ጥላቻን እንዳተረፉ ስለሚረዱ ማናቸውም አይነት የፖለቲካ ድርጅት ሀገር ውስጥ መንቀሳቀስ ከቻለ ህልውናቸው እንደሚያከትም እርግጠኛ ሆነዋል። ስለዚህም የሚያስፈራቸውን የተቃዋሚ ድርጅት በሽብር ተግባራት ፈርጆ ከጫወታ ውጭ ማድረግ የዘወትር ተግባራቸው ነው። ታድያ እንዚህን ያስፈሯቸውን ፖለቲከኞችና የፖለቲካ ድርጅቶች በሽብር ተግባር ለመወንጀልና ለመክሰስ ሽብር ቢጤ መከናወን አለበት።
 
2) ሌላው ወያኔዎች በኢትዮጵያ ውስጥ ሽብር አለ ብለው እራሳቸውን የምዕራባውያን የጸረ-ሽብር አጋር አድርገው ለማቅረብ ያላቸው ፍላጎት ነው። ሶማሊያ ውስጥ ያሉትን አክራሪዎች እጃቸው ኢትዮጵያም ይደርሳል በማለት ምዕራባውያንን ማሳመንና ማግባባት ያስፈልጋቸዋል፣ ለዚህም ደግሞ እዚህና እዚያ በአካራሪዎች የተፈጸመ የሚመስል የሽብር ተግባር እንዲኖር ያስፈልጋል።
 
ይህን የህዝቡንና የተቃዋሚዎቹን ጥርጣሬ እውነት ነው የሚያስብል ሁኔታ የተከሰተው ግን ዘግይቶም ቢሆን “ዊኪሊክስ” የአሜሪካ ሚስጥራዊ ሰነዶችን ይፋ ባደረገ ማግስት ነው። የአሜሪካ ዲፕሎማቶች “በአዲስ አበባ የሚፈነዱት ቦንቦች የአሸባሪዎች ጥቃት ናቸው ብለው እንደማያምኑ” የሚያመላክቱ መልዕክቶችን በተደጋጋሚ ከአዲስ አበባ ወደ ዋሽንግቶን ዲሲ ሰደዋል።
ቦታ እየቀያየረ መጫወት የማይሆንለት የጥንቱ የጥዋቱ የደደቢቱ ወያኔ ዛሬም ድረስ ይህኑ ተጨፈኑ ላሞኛችሁ “ሽብር መጣባችሁ” ድርጊቱን ገፍቶበት ይገኛል።

ኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች በሀይማኖታቸው ጉዳይ መንግስት ጣልቃ በመግባቱ ፍጹም ሰላማዊና ስልጡን በሆነ መንገድ ከአንድ አመት በላይ ድምጻቸውን ከፍ አድርገው የፍትህ ያለህ በማለት ላይ ናቸው።

ምንም እንኳ ወያኔ በጸረ-ሽብር አጋርነቱ ታውቆ ከአሜሪካና ምዕራባውያን አሳዳሪዎቹ ዘንድ እርጥባንና የፖለቲካ ድጋፍ እየተቸረው የዘለቀ ቢሆንም፣ ኢትዮጵያውያን ሙስሊሞችን “አሸባሪ” ናቸው ብሎ ለማስፈረጅ ግን አልተቻለውም።
ሰሞኑን የፊታችን አርብ ኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች የኢድን በዓል አስመልክተው በመላ ሀገሪቱ ሊያደረጉ ያሰቡት ተቃውሞ ወያኔን አስደንግጦታል። በኮፈሌ ከ25 በላይ ንጹሀን ሙስሊሞችን በአጋዚ የጎሳ ወታደሮቹ አስጨፍጭፎ ሲያበቃ በአዲስ አበባ ደግሞ ሙስሊም ወላጆችን ሰብስቦ ልጆቻችሁ ለተቃውሞ እንዳይወጡ እያለ ይማጸናል።

ወያኔ ጭንቀቱ እንደበረታበት የሚያሳየው ሌላው ትዕይንት ደግሞ፣ መቀመጫቸውን አዲስ አበባ ላደረጉ ከ30 በላይ ኤምባሲዎች የፊታችን አርብ የሽብር ጥቃት ሊፈፀም እንደሚችል በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መስሪያ ቤት በኩል መልዕክት ማስተላለፉ ነው።
ወያኔዎች ኢትዮጵያውያን ሙስሊሞችን በሽብር ተግባር ለመወንጀል ቦምብ አያፈነዱም ብሎ ማሰብ የዋህነት ነው። በዚህ ወቅት ነቃ ብሎ አካባቢን እያጠኑ መንቀሳቀስ ደግሞ ብልህነት ነው።

ሰባር ዜና-አቃቤ ህግ ቴድሮስ ባህሩ ከአገር ሸሽተው ጥገኝነት በመጠየቅ አሜሪካ ገቡ!

August 6, 2013
ድምፃችን ይሰማ
ማክሰኞ ሐምሌ 30/2005
‹‹ህሊናዬ የማያምንበትን እንድሰራ ተገድጃለሁ›› አቃቤ ህግ ቴድሮስ ባህሩ
የመንግስት ክስ መጨረሻው በውል እንኳ አልታወቀም፤ ቀጠሮውም ም እንደሆነ የሚታወቅ ነገር የለም!
የሙስሊም መፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴዎችን፣ አሊሞችንና ዳኢዎችን መንግስት በሀሰት በሽብር ወንጀል ጠርጠሮ ከከሰሳቸዉ አንድ አመት ቢያልፍም እስካሁን እልባት ላይ አለመደረሱ ይታወቃል፡፡ በዚህ ክስ ውስጥ ከከሳሽ መንግስት አቃቢያን ህግ መካከል አንዱ የሆኑት አቶ ቴድሮስ ባህሩ ‹‹ህሊናየ የማያምንበትን እንድሰራ ተገድጃለሁ›› በማለት አገራቸውንና ስራቸዉን ጥለዉ ከአገር ሸሽተው ጥገኝነት በመጠየቅ አሜሪካ መግባታቸው ተረጋገጠ፡፡ አቃቤ ሕግ ቴዎድሮስ ባህሩ ሲሰሩ የነበረበትን የስራ ጉዳይ ሰነድ እንኳን ሳያስረክቡ ጥገኝነት ጠይቀዉ ከነቤተሰባቸዉ አሜሪካ እንደገቡ ለማረጋገጥ ተችሏል፡፡Ethiopian Musilms
እንደ ታማኝ ምንጫችን ገለፃ ከመጀመሪያዉ የክስ ምስረታ ጊዜ ጀምሮ በተለይ የማእከላዊ ወንጀል ምርመራ ፖሊሶች በሙያቸዉ ጣልቃ እየገቡባቸዉ ብዙ አቃቢያን ህግ ባለሙያዎች ከፍተኛ ምሬት እንዳለባቸው አስታውሶ፤ የአሁኑ የአቶ ቴዎድሮስ ሙያቸዉን ለቀዉ ከሀገር እንዲሰደዱ ያደረጋቸዉ ዋናዉ ምክንያትም እንደሚታወቀዉ ለረጅም ጊዜ በተጠርጣሪ የመፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴ አባላቶች ላይ ስልጠና የተሰጣቸው ሰዎች የሀሰት የሰዉ ምስክርነት ጋዜጠኛም ሆነ ቤተሰብ እንዲገባ ባልተፈቀደበት ሁኔታ በዝግ ችሎት ሲሰማ የቆየ ሲሆን ይህም ተጠናቆ የቪዲዮ መረጃ መቅረብ ተጀምሮ ነበር፡፡
ለጥቂት ቀናት የታየዉ ቪዲዮ መረጃ ለረጂም ጊዜ ሲሰማ የነበረዉን የሀሰት የሰዉ ምሰክርነት ሙሉ በሙሉ ከንቱ ስላስቀረባቸዉ በአቃቢያን ህግ፣ በደህንነትና በፖሊስ መካካከል ከፍተኛ ዉጥረት ተፈጥሯል፡፡ ለዚህም ይመስላል የፍርድ ቤት ቀጠሮዉ አለመከበሩ ብቻ ሳይሆን ለመቼ እንኳ እንደሚቀጥል ሳይታወቅ ሂደቱ ሁን ተንጠልጥሎ የቀረዉ፡፡ አቶ ቴድሮስ ካሉበት ሁነው ሙሉ የነበረዉን ሂደትና መረጃዉን ለህዝብና ሚዲያ ይፋ ያደርጋሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡

Monday, August 5, 2013

የአንድነት ሰልፎች የመጀመሪያ ድሎች መንግስት ከ4 ዓመት በኋላ በፀረሽብርተኝነት ህጉ ላይ የውይይት መድረክ አዘጋጀ

ስኬት አንድ!!!!!!!!!!!! የአንድነት ሰልፎች የመጀመሪያ ድሎች መንግስት ከ4 ዓመት በኋላ በፀረሽብርተኝነት ህጉ ላይ የውይይት መድረክ አዘጋጀ ሪፖርት ጥንቅር በምንሊክ ሳልሳዊ ====================== አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ የፀረ ሽብርተኝነት ህጉን ለማሻር የጀመረው የፊርማ ማሰባሰብ ዘመቻ በሀገር ውስጥና በአለም አቀፍ ደረጃ ተቀባይነት ማግኘቱንና የመዋያያ አጀንዳ መሆኑን ተከትሎ የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ድርጅት ህጉ ከፀደቀ ከ4 ዓመት በኋላ ፓርቲዎች በህጉ ላይ ያላቸውን አቋም የሚያስረዱበት መድረክ አዘጋጀ፡፡

 ኢቲቪ አንድነት ፓርቲን ጨምሮ ለተለያዩ ፓርቲዎች ደብዳቤ የላከ ሲሆን አንድነት ፓርቲ በበኩሉ በ5 የክልል ከተሞች ለሚያደርገው ህዝባዊ ንቅናቄ አመራሮቹን ስላሰማራ የውይይት መድረኩ እንዲራዘምለት ጥያቄ አቅርቧል፡፡ አንድነት ፓርቲ የሚሊዮኖች ድምፅ ለነፃነት በሚል መሪ ቃል የጀመረው ህዝባዊ ንቅናቄ በስኬት እየተካሄደ መሆኑ ይታወቃል፡፡

ዘላቂ ሰላምን ለማስፈን ወያኔን እናስወግድ!!

ከግንቦት 7 ንቅናቄ የተሰጠ መግለጫ
ሐምሌ 28 2005 ዓ.ም.
ወያኔ ወገኖቻችንን እየገደለ፤ አገራችንን እና ሕዝቧን በሽብር እያመሰ ነው። ከአርብ ሐምሌ 26 ቀን 2005 ዓም ጀምሮ በአገራችን የተለያዩ ክፍሎች የወያኔ ሠራዊት ባልታጠቁና ባልተዘጋጁ ሰላማዊ ዜጎች ላይ ጥይት እያዘነበ ይገኛል። እስካሁን የሞቱና የቆሰሉ ሰዎች ቁጥር ማወቅ ቀርቶ መገመት እንኳን አዳጋች ነው። ሞስሊም ወገኖቻችን፣ በሕጋዊ መንገድ ለውጥ እናመጣለን ብለው የሚያምኑ ሰላማዊ ታጋዮች፣ ሕፃናትና አዛውንት የጥቃቱ ሰለባ ናቸው።

የወያኔ ግንባር ቀደም የጥቃት ሰለባዎች ሰላማዊነታቸው ለማሳየት እጆቻቸውን አስረው ፍትህ ሲማፀኑ የነበሩ ዜጎች ናቸው። ሕግ የማያውቀው ወያኔን በሕጋዊ መንገድ ታግለን መሠረታዊ መብቶቻችንን እናስከብራለን ያሉ ወገኖቻችን በግፍ ተግደዋል፤ ተደብድበዋል፤ ተግዘዋል። የምዕራብ አርሲ ከተሞችና መንደሮች በአጋዚ ጦር ተወረዋል። አዲስ አበባም ውስጥ ዋይታ በርክቷል።

ግንቦት 7: የፍትህ፣ የነፃነትና የዲሞክራሲ ንቅናቄ በወያኔ ፋሽስታዊ እርምጃ ሕይወታቸውን ላጡ ወገኖቻችን ቤተሰቦች ሁሉ የተሰማው መሪር ሀዘን ይገልፃል። እንደዚሁም ለአካል ጉዳት ለተዳረጉ፣ ለተዋከቡ፣ ለተረገጡ፣ ለጅምላ እስር ለተዳረጉ ወገኖቻችን ሁሉ በደረሰባቸው በደል መቆጨቱን ይገልፃል።

ወያኔ በሥልጣን ላይ እስካለ ድረስ የእምነትም ሆነ ሌላ ማናቸውን ነፃነት ሊኖር እንደማይችል የትናትናና የዛሬው ድርጊት አንድ ተጨማሪ ማስረጃ ነው። ወያኔ በሥልጣን መንበር ላይ ውሎ ባደረ መጠን እንዲህ ዓይነቱ መርዶ መስማታችን የማይቀር ነው ብሎ ግንቦት 7 ያምናል። የኢትዮጵያ ሕዝብ መከራ እንዲያበቃ ወያኔ ከሥልጣን መወደግ አለበት፤ ገዳዮች ለፍርድ መቅረብ አለባቸው።
ግንቦት 7: የፍትህ፣ የነፃነትና የዲሞክራሲ ንቅናቄ የሰላማችን ዋስትና የወያኔ መወገድና በምትኩ የሕዝብ ይሁንታ ያገኘ መንግሥት መተካት ነው ብሎ ያምናል። ስለሆነም በአገራችን ሰላም እንዲሰፍን እና መሠረታዊ መብቶቻችን ተከብረውልን መኖር እንድንችል ወያኔን ለማስወገድ ቆርጠን እንነሳ።

መጽናናት ለተገዱ ወገኖቻችን ቤተሰቦች!!!

ድል ለኢትዮጵያ ሕዝብ!!!

The same regime, another massacre

FOR IMMEDIATE RELEASE
August 5 2013

The same regime, another massacre

The TPLF dictatorial regime that indiscriminately killed more than 200 demonstrators in the aftermath of the infamous 2005 election has struck again killing more than 25 innocent demonstrators and wounding, assaulting, and rounding up thousands more. In a bizarre and disgraceful move, the same regime that claimed 99.6% electoral victory just a little more than three years ago, has gone to the same precincts and localities and mercilessly killed the same people that it said – “The People have spoken”.

The abuse and the killing over the weekend targeted Muslim communities all over the nation who for the past 32 months have peacefully been demanding the regime to respect their constitutional right to worship. According to eye witnesses, the heavy-handed attack that resembled a battle field planned operation took place in the town of Kofle about 275 km south of the capital, in Arsi zone of Oromia state. An elderly imam, a five year old child and four teens were among the dead in a killing spree that continued for two days and covered cities, towns, and villages across the nation.

Ethiopia and its tyrant rulers are not new to mass arrests and street massacres; in fact, Ethiopia arrests and kills its own citizens more than any other nation on earth. What’s new and difficult to comprehend is that, the killers in Ethiopia also enjoy one of the largest inflows of foreign aid in the world, and the killing of political disinters and peaceful demonstrators seems to increase as the amount of foreign aid to the killers increases. Ginbot 7, Movement for Justice, Freedom and Democracy condemns the recent mass killing in Ethiopia and holds the TPLF regime and its enables responsible for the innocent life lost.

The political impasse in Ethiopia has come to a dangerous crossroads where the minority regime cannot continue governing the nation without mass arrests and random killings. Ginbot 7 urges the international community, especially those who call themselves ‘defenders of freedom and democracy’ to not quietly watch when citizens in Ethiopian who practice their constitutional right get massacred by their own government.

Ginbot 7 re-affirms its commitment to the proud and courageous people of Ethiopia, and it also wants to use this opportunity to make a call to Muslim and Christian Ethiopians to stand together and show the world that their 1600 years of peaceful co-existence will never be tarnished by the divide and rule policy of the TPLF regime. The time to view and wage the struggle for freedom and justice across religious and ethnic lines has come, and it is now.

Together, we shall overcome!

OLF: Indiscriminate Killing of Innocent Peoples is a Crime Against Humanity!

OLF IMMEDIATE PRESS RELEASE
olf-logo
The Oromo Liberation Front has learned the cold blooded massacre of our people by TPLF/EPRDF Federal police on August 3, 2013 in Wabe gafarsa village, Kofale town, West Arsi Zone, Oromia state.

The TPLF/EPRDF federal police massacred at least 25 innocent people and wounded hundreds who were peacefully demonstrating against illegal detention of their Imams / mosque leaders/ without arrest warrant. The wounded were taken to local hospitals. After killing and wounding many people, the TPLF/EPRDF federal police has engaged in indiscriminate arrest of thousands innocent people from surrounding communities/ towns/. We strongly condemn this terrorist act of the TLF/EPRDF regime against our people.

Since it came to power, the TPLF/EPRDF regime targeted for massacre the Oromo people in general and the Arsi Oromo in particular that it perceived a threat to its dictatorial minority regime.

This egregious crime against innocent people whom their crime was demanding the release of their leaders who were illegal detained through peaceful demonstration even guaranteed under the TPLF/EPRDF nominal constitution should be condemned by all peace loving community of the world .

We also recall with great rage a recent devilish action by late TPLF/EPRDF tyrant Melse Zenawi who said, “there is Al-Qada cell" in Arsi -Bale regions. Following his declaration, the TPLF/EPRDF regime murdered innocent people who were gathered for Friday pray in Asaasaa town, Arsi Region. What happened yesterday is the continuation of the TPLF/EPRDF plan to exterminate the Arsi Oromo people.

It should be known to anybody by now that the TPLF/EPDRF has no more moral & legal authority to call itself the government of Ethiopian peoples. The Ethiopia peoples should use all means to protect themselves from this terrorist regime destined to massacre them when even they demand their simple inalienable rights to worship their God without the interference of the TPLF/EPRDF regime

ለንጹሃን የደም ጥሪ ተገቢው ምላሽ ትጥቅ አንስቶ ነፍሰ ገዳዮችን መፋለም ብቻ ነው!

August 5, 2013
Ginbot 7 Popular Force logoየግንቦት 7 ሕዝባዊ ኃይል (መግለጫ)
Ginbot 7 Popular Force


ከሃምሌ 26 _ 2005 አንስቶ  ይህ መግለጫ እስከወጣበት እስከ ሃምሌ 28_ 2005 አ.ም እለት የወያኔ ዘረኛ ጉጅሌ ቅጥር ነፍሰ ገዳዮቹን በማሰማራት በመላው ኢትዮጵያ፣ በእስልምና እምነት ተከታይ የሃገሪቱ ዜጎች  ላይ በስፋት የግድያ እርምጃ እየወሰደ ነው። ክቡር ህይወታቸውን በግፈኛው የወያኔ የአፈና ሃይል ያጡት ወገኖች ቁጥር በርካታ ሆኗል። ክፉኛ የቆሰሉት ወገኖቻችን ቁጥር ከተገደሉት እጅጉን የገዘፈ ነው። ፍጹም አረመኔያዊነት  በተሞላው መንገድ በወያኔ ቅልብ ጦር የተቀጠቀጡትና እንደከብት ተሰብሰብው በየእስር ቤቱ የታጎሩት ወገኖቻችን ቁጥር በሽዎች የሚቆጠር ሆኗል። እጅግ ሰላማዊና  ስልጡን በሆነ  መንገድ ፍትሃዊ ጥያቄ ባነሱ ወገኖቻችን ላይ የደረሰውን እልቂት የግንቦት 7  ህዝባዊ ሃይል የራሱ እልቂት አድርጎ  ያየዋል። የደረሰባቸውን  መከራና እንግልት የራሱ መከራና እንግልት አድርጎ  ወስዶታል።

የግንቦት 7 ህዝባዊ ሃይል ወያኔን አያወግዝም ወይም ወያኔ በኢትዮጵያውያን ላይ የሚፈጽመውን ግፍ በገንዘብና በስልጠና  በዲፕሎማሲ ድጋፍ የሚያበረታቱን የምእራብና  ሌሎች የወጭ መንግስታት ከድርጊታቸው እንዲታቀቡ አይማጸንም። ባለፉት 22 አመታት ውግዘትና መማጸን የትም እንዳላደረሱን በሚገባ እናውቃለንና። ግንቦት 7  ህዝባዊ ሃይል ደግሞ ደጋግሞ  ግልጽ እንዳደረገው የኢትዮጵያ  ህዝብ መከራ የሚያበቃው ህዝብ የወያኔን በእብሪት የተሞላ ግፈኛ ማንነት የሚመጥንና  የሚስማማ የትግል ስልት መርጦ አምሮ  ወያኔን ታግሎ  በመደምሰስ ብቻ ነው። ሙስሊሙም ሆነ የሌሎች እምነት  ተከታዮች መረዳት የሚገባን ወያኔ ስላማዊና  ስልጡን ከሆነው የእኛ አለምና  መርህ ጋር የማይተዋወቅ ዘረኛ  ገዳይ  ሃይል መሆኑን ነው። ይህ በእብሪትና  በድንቁርና የታጀለ የወያኔ  ሃይል የእናንተን ትእግስት ከፍርሃት፣ አርቆ አሳቢነታችሁን ከሞኝነት ጋር አስተሳስሮ የሚያይ ነው። “የምንገድልለት አላማ ባይኖረን የምንሞትለት አላማ አለን” የሚለውን ድንቅና ክቡር እመነታችሁን ወያኔ የሚያየው እናንተን በመግደል ፍትሃዊ ጥያቂያችሁን ማዳፈን ይቻላል በሚል ትርጓሜ ነው።ወያኔ ይህን የተቀደሰ እምነታችሁንና እንዲሁም  ቅንነትና ትእግስታችሁን ለእናንተ የሚመጥን ስልጡን ምላሽ  ማፈላለጊያ አድርጎ  አያየውም። አላየውም።

የትግል ስልት የሚቀየሰው የባላንጣን ማንነት በሚገባ ግምት ውስጥ በማስገባት እንጂ እኛ የምንፈልገው የትግል ስልት ስለሆነ  ብቻ መሆን አይችልም ብለን እናምናለን። እኛ በግንቦት 7 ውስጥ የተሰባሰብን አባላት የወያኔን የእብሪት አመጽ ማስቆም የሚቻለው የወያኔ አፈሙዝ ብቻ   ሳይሆን የእኛም ጠመንጃ እሳት የሚተፋ እንደሆነ በተግባር በማረጋገጥ ብቻ ነው የሚል ጽኑ እምነት አለን።

ምንም አይነት የስልጣኔና የሞራል ማእቀብ  ከማይገዛው  ወያኔን ከመሰለ እኩይ ሃይል እራስን ከጥቃት መከላከል ብሎም በወያኔ መቃብር ላይ ሰላምና ነጻነት ማስፈን የተፈጥሮና የዜግነት መብታችን ብቻ ሳይሆን የአላህም ፈቃድና  ፍላጎት ለመሆኑ ጥርጥር የለንም።  በዚህ አጋጣሚ የግንቦት 7 ህዝባዊ ሃይል ለእስልምና ተከታይ ወንድሞቻችንና እህቶቻችን ሆነ ለመላው የኢትዮጵያ  ህዝብ የሚያስተላልፈው ጥሪ የሚከተለው ነው። “የወያኔን የእብሪት አመጽ በፍትሃዊና ህዝባዊ አመጽ ለመመከት በያላችሁበት ተደራጁ።

የግንቦት 7 ህዝባዊ ሃይልን ተቀላቀሉ። የወያኔን የግፈኛነት እብጠት በህዝባዊና ፍትሃዊ የመሳሪያ አመጽ እናስተንፍስ” የሚል ነው።

ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ!!!!

ሞት የንጹሃን ደም በከንቱ ለሚያፈሱ በሙሉ !!!!

Sunday, August 4, 2013

በኦሮሚያ አርሲ ዞን የሟቾች ቁጥር 11 ደርሰ!

August 4, 2013
 Free Our Heroes

አንዲት ሴት እና ህጻን ልጅ ከሟቾቹ ውስጥ ይገኙበታል!

ትናንት ማለዳ ጀምሮ የመንግስት ታጣቂዎች በኦሮሚያ ክልል አርሲ ዞን ገብተው በሰነዘሩት ጥቃት የሟቾች ቁጥር 11 ደርሰ፡፡ ከሻሸመኔ እስከ ኮፈሌ እና ዶዶላ ድረስ በሚያካልለው በዚህ የመንግስት ወታደሮች ጥቃት ከፍተኛ ጉዳት የደረሰባቸው እና የታሰሩ ሰዎች ቁጥርም በከፍተኛ ሁኔታ አሻቅቧል፡፡ በእለተ ቅዳሜ ምንም አይነት ተቃውሞም ሆነ መሰል እንቅስቃሰሴዎች በማይካሄድበት እና ባልተካሄደበት እለት የመንግስት ወታደሮች እስከገጠር ቀበሌዎች ድረስ ዘልቆ በመግባት ያለርህራሄ የቀጥታ ጥይት በመጠቀም የአካባቢውን ዜጎች ሲገድሉ ውለዋል፡፡

የመንግስት ቴሌቪዥን በተለመደ መልኩ ‹‹ጂሀድ ሲቀሰቅሱ እርምጃ ተወሰደባቸው›› የሚል ዜና ያሰራጨ ሲሆን የሞቱት ሰዎች ቁጥርም 3 ብቻ መሆኑን ገልጾ ነበር፡፡ መንግስት ቀድሞ በታሰበበት መልኩ በአካባቢው ከፍተኛ የወታደር ሰፈራ በማድረግና በተጠንቀቅ በማስቆም በፌዴራል ፖሊስ፣ አድማ በታኝ እና በወታደሮች በመታጀብ በአካባቢው ሕዝብ ላይ ከማለዳ ጀምሮ ጥቃት ሰንዝሯል፡፡ አራት ኦራል መኪኖች ላይ የተጫኑ ወታደሮች አካባቢውን በመክበብ መስጂዶች እና መኖሪያ ቤቶች ላይ ጭምር ጥይት ሲተኩሱ እንደነበር የታወቀ ሲሆን በዚሁም የአካባበውን ታዋቂ የሃይማኖት መምህር፣ አንዲት ሴት እና ህጻን ልጅን ጨምሮ የሟቾች ቁጥር 10 ደርሷል፡፡ የፌዴራል ፖሊስ አባላት የራሳቸውን መኪና መስታወት በመሳሪያ ሰደፋቸው በመስበር ‹‹ሕዝቡ ሰበረው›› የሚል ፕሮፖጋንዳ ለመስራት የሚያስችል ጥረት ሲያደርጉም ታይተዋል፡፡

መንግስት ምላሽ መስጠት የተሳነውን ሕገ መንግስታዊ የህዝብ ጥያቄ በጥይት በዚህ መልኩ ምላሽ ሲሰጥ ይህ የመጀመሪያው አይደለም፡፡ ባለፈው አመት በአርሲ ዞን አሳሳ ላይ ተመሳሳይ ጥቃት ፈጽሞ አራት ሰዎች መገደላቸው ይታወቃል፡፡ ከዚያም በመቀጠል በአማራ ክልል ገርባ ከተማና በሐረር ኢማን መስጂድ ላይ ተመሳሳይ ጥቃት ፈጽሞ በድምሩ ከ13 ሰዎች በላይ ህይወታቸው በመንግስት ታጣቂዎች ጥይት ተቀጥፏል፡፡ መንግስት የገደላቸውን ሰዎች በሙሉ ‹‹ለጂሃድ ሲያነሳሱ ገደልኳቸው›› የሚል ማስተባበያ ሲሰጥ ቢቆይም ተቀባይነት ሳያገኝ ቀርቷል፡፡ አሁንም ይህ የመንግስት ጭካኔ የተሞላበት ጥቃት ቀጥሏል፡፡

አሁንም ሙስሊሙ ኅብረተሰብ መንግስት ሊፈጥር እያሰበ ያለውን ተጨማሪ ኹከት በመገንዘብና ሊፈጠር የሚችለውን አደጋ በማሰብ የመንግስትን ትንኮሳ ቸል እንዲልና በትእግስት እንዲያሳልፍ አስቸኳይ መልእክት እናስተላልፋለን፡፡ የመንግስት ቀዳሚው ፍላጎት መጀመሪያ እንደታየውም ኹከትና ግጭት በመፍጠርና ጥፋት በማድረስ፣ ሙስሊሙን ኅብረተሰብ ለመወንጀልና ለፕሮፖጋንዳ ፍጆታ ለመጠቀም በመሆኑና ይህም በሁሉም ዘንድ የሚታወቅ በመሆኑ፤ መንግስት ኹከት ሲቀሰቅስ በቸልታና አይቶ በማሳለፍ በመንግስት ወጥመድ ላለመውደቅ ሁሉም ጥረት እንዲያደርግ እንጠይቃለን፡፡ ከምንም በላይ ሰላማዊነታችን ዋጋ የምንሰጠው መሆኑን ሁላችንም ከግንዛቤ በመክተት ሰላማችንን ሊነጥቁ የሚመጡ ኃይሎን በሰላም ብቻ እነድንመልሳቸው አደራ እንላለን፡፡

Breaking News Genocide in Totolamo Village, Ethiopia

August 4, 2013
The Horn Times Breaking News August 4, 2013
by Getahune Bekele-South Africa

Genocide: 11 Ethiopian Muslims mowed down in the Totolamo village blood bath

A five year old kid, an elderly imam and four teens are among the dead
The small maize and potato farming Muslim village of Totolamo in south west oromiyya near the strategic town of Shashemene is in deep mourning after 11 of her citizens gunned down in cold blood by the genocidal Tigre People Liberation Front/ TPLF federal police commandos on Saturday August 3, 2013.

A five year old kid, an elderly imam and four teens are among the dead according to information obtained from Shashemne general hospital where the bodies are stashed in a tiny morgue. The number of the wounded is still unknown.

The fate of hundreds who took refuge inside the Erob Gebya Mosque in the troubled village and surrounded by the federal police is also not yet known. Several others are in detention at the nearby Kofele town police station and the town along with Totolamo village is under total control of the TPLF gunmen in police uniform. Today August 4, 2013 residents are warned to stay indoors as the situation remain frighteningly tense.

The brutal attack on unarmed and benevolent villagers began at nine o’clock yesterday morning after the faithful gathered for their routine prayer meeting. Then the commandos poured into the village and started firing indiscriminately, causing massive chaos and mayhem.

Although genocide has become synonymous with the ruling minority junta for 22 years, the Totelamo blood bath is the first mass killing for newly appointed federal police commander Assefa Abiyo who is said to be more ruthless and ferocious than his predecessor Workneh Gebeyhu.

Scores of relatives from the town of Shashemene are currently waiting to hear the names of the dead or the wounded at the main gate of the general hospital.

Furthermore, in the latest update posted on Minilik Salsawi’s Facebook account, Federal police commandos are among the dead in the Totolamo blood bath as the people tried to defend themselves by throwing stones at the heavily armed attackers backed by deafening machinegun fire.
In related news coming out of yet another nearby western Oromiyya town of Dodola, federal police rapid intervention force unit members were chased away from the area about fifteen hours ago by residents after they made an attempt to arrest a highly regarded local imam.

According to updates reaching the Horn Times from Dodola, angry residents followed the fleeing police force to the region’s administration offices and the Jarolis (elders) are still locked in negotiations with the authorities.

The Horn Times will post further updates in the coming hours.
infihorntimes@gmail.com
@infohorntimes

የወያኔ ደህንነቶች የአንድነት ፓርቲ የመቀስቀሻ መኪና ከስራ ውጭ አደረጉ!


የወያኔ ደህንነቶች እና አባሎች ለሊቱን በኢህአዴግ ደህንነቶች የመቀስቀሻ የተዘጋጀችዉን የሰሌዳ ቁጥሩ 39400 አዲስ አበባ የሆነው ላንድ ክሩዘር ቶዮታ መኪናቸው አራቱም ጎማ የተነፈሰባቸው ሲሆን የአንድነት ፓርቲ አመራሮች ጉዳዩን ለአርባምንጭ ከተማው አስተዳደር አሳውቀው የተነፈሰውን ጎማ ጥገና እንዲያገኝ በማድረግ ቅስቀሳ ሊጀምሩ ቅድመ ሁኔታዎችን አጠናቀዋል፡፡

ሆኖም ግን ለአርባምንጭ ሰላማዊ ሰልፍ በቅስቀሳ ላይ መሰማራቷ ያልተወደደላት መኪና እንቅስቃሴዋን ለመግታት ከ6 የቱሪስት መኪናዎች ተለይታ 4ቱም ጎማዎቿ ተንፍሰው ተገኙ ለሴቻ ወረዳ ፖሊሶች ሪፖርት ቢደርሳቸውም የበላይ አካል ካላዘዘን መጥተን ልንመለከት አንችልም የሚል ምላሽ በመስጠት የአለቆቻቸውን ትዕዛዝ እየተጠባበቁ ሲሆን የሰው ልጆችን ለመርዳት እና የፖሊስ ሃይል ልኮ ችግሩን ለመቅረፍ የሚያደርግ ግብረ ሃይል አለመኖሩን የሚያሳይ መጥፎ የመንግስት ገጸ ባህርይ ነው ሲሉ አባሎቹ ተናግረዋል፡፡
ለሊቱን በኢህአዴግ ደህንነቶች የመቀስቀሻ መኪናቸው አራቱም ጎማ የተነፈሰባቸው የአንድነት ፓርቲ አመራሮች ጉዳዩን ለአርባምንጭ ከተማው አስተዳደር አሳውቀው የተነፈሰውን ጎማ ጥገና እንዲያገኝ በማድረግ ቅስቀሳ ሊጀምሩ ቅድመ ሁኔታዎችን አጠናቀዋል፡፡ለአርባምንጭ ሰላማዊ ሰልፍ በቅስቀሳ ላይ መሰማራቷ ያልተወደደላት መኪና እንቅስቃሴዋን ለመግታት ከ6 የቱሪስት መኪናዎች ተለይታ 4ቱም ጎማዎቿ ተንፍሰው ተገኙ ለሴቻ ወረዳ ፖሊሶች ሪፖርት ቢደርሳቸውም የበላይ አካል ካላዘዘን መጥተን ልንመለከት አንችልም የሚል ምላሽ በመስጠት የአለቆቻቸውን ትዕዛዝ እየተጠባበቁ ነው፡፡

ህገ-መንግስታዊ መብታችንን ሳንገል እየሞትን እናስከብራለን! አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትሕ ፓርቲ (አንድነት)

August 4, 2013
አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትሕ ፓርቲ (አንድነት)
UNITY FOR DEMOCRACY AND JUSTICE PARTY (UDJ)

አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ የሚሊዮኖች ድምፅ ለነፃነት ህዝባዊ ንቅናቄ ሰኔ 13 ቀን 2005 ዓ.ም በጋዜጣዊ መግለጫ አሳውቆ ወደ ንቅናቄው ከገባ ጊዜ ጀምሮ በርካታ ህዝባዊ ድጋፍና በህብረተሰቡ ዘንድ ከፍተኛ መነቃቃት እና የነፃነት ጥያቄ ድምፅ ከሁሉም የኢትዮጵያ ክልሎች በመደመጥ ላይ ይገኛል፡፡

በአንፃሩ ገዥው ፓርቲ የህዝቡን የነፃነት ድምፅ ለማፈን ንቅናቄያአችንን ከጀመርን እለት ጀምሮ በርካታ መሰናክሎችን እየፈፀመ ይገኛል፡፡
Unity for Democracy and Justice (UDJ) partyበጎንደርና በደሴ ያደረግነውን ሰላማዊ ሰልፍ በተደራጀ መንግስታዊ ሽብር ለማደናቀፍ የተሞከረውን ሙከራ በህዝቡ ንቁ ተሳትፎ ከሽፎ የህዝቡን የነፃነት ድምፅ ማሰማታችን የቅርብ ጊዜ ትዝታ ነው፡፡ ይህንን የነፃነት ድምፅ በሌሎች ከተሞች ተቀጣጥሎ እንዳይዘልቅ ከሼክ ኑር ኢማም አሟሟት ጋር በማያያዝ ገዢው ፓርቲ ይህ መግለጫ እስከወጣበት ቀን ድረስ በተለያዩ ከተሞች ህዝቡን በማስገደድ አንድነት ፓርቲን እንዲያወግዝ በየቀኑ ሰልፍ በማስወጣት ላይ ይገኛል፡፡

ሐምሌ 28 ቀን 2005 ዓ.ም በጂንካ ፣ ወላይታ ፣ ባህርዳር ፣ አርባምንጭ እና መቀሌ ሰላማዊ ሠልፍ እና ህዝባዊ ስብሰባ እናደርጋለን ብሎ አንድነት ካሳወቀ ጊዜ ጀምሮ በአካባቢው በሚገኙ አባሎቻችን ላይ ማዋከብና ከፍተኛ ጫና ማሳደሩ ተጠናክሮ ቀጥሏል፡፡

ሐምሌ 27 ቀን 2005 ዓ.ም ወላይታ ለቅስቀሳ የገባው የአዲስ አበባ ልዑክ በአካባቢው ባለስልጣኖች  መንግስታዊ ውንብድና ተፈፅሞበታል፡፡ ታርጋ የሌላቸው ሞተር ሳይክሎች በብዛት በማሰማራት ለቅስቀሳ በተንቀሳቀሱ አባሎቻችን ይዘው የወጡትን በራሪ የቅስቀሳ ወረቀቶችንና የፀረሽብር ህጉን ለማሰረዝ የተሰባሰቡ ፊርማዎችን ከእጃቸው ላይ ነጥቀዋቸዋል፡፡ የፀጥታ ኃይሎችም ዘራፊዎችን ለማስቆም ፍቃደኛ አልነበሩም፡፡ ለቅስቀሳ የተሰማራውንም መኪና አራቱንም ጎማ በማተንፈስና ሹፌሩን በመደብደብ ከተማውን ለቆ እንዲወጣ ማስጠንቀቂያ ተሰጥቶታል ፡፡ በድምፅ ማጉያ መሳሪያም  ቅስቀሳ እንዳናደርግ ተከልክለናል፡፡

የአንድነት ፓርቲ የወላይታ የዞን አመራር አባል የሆነችው  ወ/ሮ ሀድያ መሀመድ ከትላንት ሐምሌ 26 ቀን 2005 ዓ.ም እለት ጀምሮ በግፍ ታስራ ትገኛለች፡፡ በእስር ቤትም የማታምንበትን ሰነድ እንድትፈርም መገደድዋን ለማወቅ ችለናል፡፡ የአንድነት ፓርቲ ህዝበ ሙስሊሙን ለአመፅ እንደሚያነሳሳ አድርገው ያቀረቡትን ሰነድ አልፈርምም ፓርቲዬም ይህንን አልፈፀመም በማለት ፓርቲውን ለመወንጀል በተዘጋጀው የሀሰት ሰነድ ላይ ሳትፈርም ቀርታለች፡፡ በአጠቃላይ የመንግስት የፀጥታ ኃላፊዎች እና የአስተዳድር ኃላፊዎች የህገ-መንግስት ጥሰት በአንድነት ፓርቲ ላይ ፈፅመዋል፡፡ በዚህ አስጨናቂ ሁኔታ ላይ ሆነንም በወላይታ ህዝባዊ ስብሰባውን በነገው ዕለት ሐምሌ 28 ቀን 2005 ዓ.ም በተያዘለት እቅድ መሰረት በህዝባችን ድጋፍ ይከናወናል፡፡

በጂንካ ፣ በአርባምንጭ እና በባህርዳር  ቅስቀሳው ተጠናክሮ የቀጠለ ሲሆን  ህዝቡም  ድጋፉን በአደባባይ እየገለፀ ይገኛል፡፡

በተለይም በባህርዳር የባጃጅ ሹፌሮች በግል ተነሳሽነት የቅስቀሳው አካል በመሆናቸው የባህርዳርን ህዝባዊ ሰልፍ በጉጉት እንዲጠበቅ አድርጎታል፡፡

በአንፃሩ በመቀሌ ከተማ ከሐምሌ 25 ቀን 2005 ዓ.ም ጀምሮ ቅስቀሳ ለማድረግ ጥረት ሲያደርግ የሰነበተው ልዑክ ምንም ዓይነት የድምፅ ማጉያ መሣሪያ እንዳይጠቀም ከመታገዱም በላይ ለቅስቀሳ ያዘጋጀውን ሞንታርቮ በአደባባይ በፖሊስ ተቀምቷል፡፡ በቅስቀሳ ላይ የነበሩት የአንድነት ፓርቲ ብ/ም/ቤት አባል አቶ እንግዳ ወ/ፃዲቅ እንዲሁም የትግራይ ዞን የአንድነት ፓርቲ አመራሮች የሆኑት አቶ ክብሮም ብርሃነ እና አቶ አርአያ ፀጋይ በቀዳማይ ወያኔ ፖሊስ ጣቢያ በአሁኑ ሰአት በዕስር ላይ ይገኛሉ፡፡ ይህንን በደል በተቀነባበረ መልኩ እየፈፀሙ ያሉት የከተማው አስተዳደር እና የፀጥታ ዘርፍ ክፍሉ በጋራ ሲሆኑ ህገ-መንግስቱን በጉልበት በመናድ በመቀሌ ሰላማዊ ሰልፍ እንዳናደርግ በኃይል አደናቅፎናል፡፡ ይህንን የህገ-መንግስት ጥሰት አንድነት ፓርቲ በፍፁም በዝምታ አይመለከተውም፡፡ የጀመርነውን ሠላማዊ ትግል አጠናክረን ከሰፊው የትግራይ ህዝብ ጋር በመሆን እንቀጥላለን በቅርብ ቀን በድጋሚ በመቀሌ ከተማ ሠላማዊ ሰልፍ የምንጠራ መሆናችንን እያሳወቅን ገዢው ፓርቲ ያለ ምንም ቅድመ ሁኔታ በግፍ ያሰራቸውን የፓርቲያችንን አመራሮች በአስቸኳይ እንዲፈታ እንጠይቃለን፡፡ የመቀሌ ነዋሪዎች መንግስት በአንድነት ፓርቲ አመራሮችና አባላት ላይ የፈፀመውን አፈና ፊት ለፊት በመቃወም ያሳዩትን አጋርነት ሳናደንቅ አናልፍም፡፡ አንድነት ፓርቲ ሳይገድል እየሞተ ህገ-መንግስቱን የማስከበር ትግሉን አጠንክሮ ዛሬም ወደፊትም ይቀጥላል፡፡

መንግስት ህገ-መንግስቱን ያክብር!!!

አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትሕ ፓርቲ (አንድነት)

ሐምሌ 26 ቀን 2005 ዓ.ም
አዲስ አበባ

Saturday, August 3, 2013

የቀባሪን ልብ የሰበረ የሕይወት ታሪክ (ከአዲስ አበባ)

ይሄይስ አእምሮ

ወያኔዎች በጣም እየከፉ ነው፡፡ ክፋታቸው ጠርዝ እየለቀቀ መጥቷል፡፡ ይሉኝታና ሀፍረት ወትሮውንም ወያኔዎች ጋ እንደሌለ የታወቀ ቢሆንም አሁን አሁን ግን በጣም የለየላቸው ጋጠ ወጦችና ኅሊናቢሶች እየሆኑ ነው፡፡ እነሱን በሰው ልጅነት ለመፈረጅ እንኳን በጭራሽ የማይሞከር የሚገርሙ ፍጡራን ናቸው፡፡ ይቅርታችሁንና ወያኔዎች ዞሮ የሚያይ አንገት ያልፈጠረባቸው ባልጩት ራስ መሆን አለባቸው፡፡ የሚሠሯቸውን የሕጻን አይሏቸው የዐዋቂ ሞኛሞኝ ሥራዎች ስታዩ ከዚህም በላይ ልትናገሯቸው ትችላላችሁ፡፡ ሞኛሞኝ ማለቴ የሚያደርጓቸው ነገሮች ቁልጭ ያሉ አንጎል የሚባል ያልፈጠረበት የንክር ሰው ሥራ በመሆናቸው ነው እንጂ የሚሠሩት ሁሉ እነሱን የማይጠቅም ነው ለማለት ፈልጌ አይደለም፡፡ ለምሳሌ አንድ ዓይነት አገልግሎት ለማግኘት አንድ መስኮት ላይ ሁለት ሰዎች ቀርባችኋል እንበል፤ አንቺ ትግሬ ስላልሆንሽ ዐርባ ብር ትከፍያለሽ – አጠገብሽ ያለችው ሌላዋ ደግሞ ትግሬ በመሆኗ ብቻ ዐርባ ሣንቲም ትከፍላለች፡፡ እውነተኛ ገጠመኝ ነው እየነገርኳችሁ ያለሁት፡፡

(ለምን አሁኑኑ አልነግራችሁም፡- ቀደም ያለ ጊዜ ነው፡፡ ቦታው ዋናው ፖስታ ቤት ነው፡፡ ትግሬዋ የ‹ሕዝብ አገልጋይ› ሰዎችን በየተራ ታስተናግዳለች፡፡ ነገሩ በፖስታ ቤት በኩል ለመጣ ዕቃ የሚከናወን የቀረጥ ክፍያ ነበር፡፡ አንዷ ትግሬ ለአንድ አነስተኛ ዕቃ ዐርባ ብር እንድትከፍል ስትጠየቅ ‹ቧይ! እዚ ኩሉ ቐርሺ ነቲኣ ቅሩብ ክስታይ…› ትልና በትግርኛ ሥልት ትጮሃለች፡፡ ወቅቱ ወያኔዎች የትም ሥፍራ የሚገኘውን ‹የታገሉለትን የትግራይ ሕዝብ› እንደንብና እንደተርብ እየተራወጡ በወረት የሚያገለግሉበት ስለነበር – ለነገሩ አሁንም ያው ናቸው – ያቺ መስኮት ውስጥ የነበረችው ትግሬ፣ ‹ትግራዋይ ዲኺ? እንተኾንክን አየናይ ወገን?› ብላ ትጠይቃታለች፡፡(‹ትግሬ ነሽ እንዴ? ከሆንሽ ትግራይ ውስጥ የት ቦታ?› ማለቷ ነው) እርሷም ትግሬ መሆንዋን፣ ከትግሬም ዋናው የወቅቱ ነገሥታት መፍለቂያ ዐድዋ ውስጥ መሆንዋን እንደእፉኝት በመነፋፋት በኩራት ትነግራታለች፡፡ ያኔ ዐርባ ብር የተጻፈበትን ወረቀት አምጪው ብላ ትቀበላትና እሱን ‘void’(ዋጋቢስ) አድርጋ ዐርባ ሣንቲም ትጽፍና በራሷ ታሪፍ ታስከፍላታለች – ትግሬ ናታ! ተገልጋይዋም ትግሬ ነቻ! ይህች ትንሽዬ ግን እውነተኛ ታሪክ ናት፡፡ ውስጧ ግን የጊዜውን የወያኔ ኢትዮጵያ ቁልጭ አድርጋ ታሳያለች፤ በጉምሩክ አካባቢ፣ በአየር መንገድ አካባቢ፣ በምርትና አቅርቦት አካባቢ፣ በንግዱ አካባቢ፣ በባንኮች አካባቢ፣ በግንባታው አካባቢ፣ በምግብና መጠጦችና በሸቀጦች አካባቢ፣ በጨረታ ግዢና ሽያጭ አካባቢ፣ በትምህርት አካባቢ፣ በመሬት አስተዳደር አካባቢ፣ በኮንዶምኒየም ቤቶች ዕደላና ክፍፍል አካባቢ፣ … ስንቱ ተጠቅሶ … ብቻ በሁሉም አካባቢ የትግሬው የገዢ መደብ ሌሎችን በሰማይ ጠቀስ ዋጋ እየገረፈና ከጨዋታው ሜዳ እያስወጣ ለትግሬዎች ብቻ መቆሙን ስናይ ‹እነዚህ ሰዎች በርግጥ ሰዎች ይሆኑ ይሆን ወይንስ ሰው ለመሆን የሚቀራቸው አንዳንድ ተፈጥሯዊ ንጥረ ነገር አለ?› ብለን ለነሱም ለራሳችንም ልንጨነቅ እንችላለን – በተፈጥሮ የሚከሰት አንዳች ጉድለት ከሌለባቸው በስተቀር እንዲህ ነፍሰ በላ ይሉኝታቢስ ይሆናሉ ብየ በበኩሌ ማመን ያቅተኛል፡፡ እርግጥ ነው ይሄ ‹ይሉኝታ› ወይም ‹ሀፍረት› የሚባል ቅመም በነዚህ ሰዎች ሰውነት ውስጥ ዜሮ መሆኑን ከተረዳሁ ቆይቻለሁ – ከዚህ የተለዬ ጄኔቲክ ጉድለት እንዳለባቸው እየተጠራጠርኩ መጥቻለሁ – ሰው በጤናው መቼም ለሥልጣንና ለገንዘብ ሲል ብቻ ወንድሞቹንና እህቶቹን እንዲሁም ሀገሩን ይህን ያህል በግፍና በበደል ያጥለቀልቃል ብዬ መቀበል በእውነቱ ይከብደኛል፡፡

 [ለዲፕሎማሲ ያህል ‹አብዛኞቹ ወያኔዎች› የሚል ማባበያ ልጠቀም ይሆን?] አዎ፣ አብዛኞቹ ወያኔ ትግሬዎች እንዲህ ናቸው፤ ከመነሻው እንዲህ ያደርጉ ነበር፤ አሁንም እንዲህ ያደርጋሉ፡፡ ይህ ‹ወርቃማ› ሀገርን የማጥፋት ዕድል በነሱው እጅ እስካለ ድረስም ለወደፊትም እንዲህ ማድረጋቸውን ያለሀፍረትና ያለአንዳች ይሉኝታ በስፋትና በጥልቀት እንደሚቀጥሉ ሳይታለም የተፈታ ነው፡፡ ማንን ፈርተው ሊተውት?

ወደርዕሴ ልመልሳችሁ፡፡ ባለፈው ሰሞን አንድ ተወልደ የሚባል ትግሬ ሞቶ ለቀብር ሄጄ ነበር፡፡ ሰውዬውን ሳይሆን ከሰውዬው ጋር በተገናኘ የማውቀው ሌላ ሰው ስለነበር እሱን ላጽናናና ቀብር ላይ መገኘቴን ለማሳወቅ ግምባሬን ላስመታ ነበር ወደ ቀብሩ ሥፍራ የካ ደብረ ሣህል ቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን ያቀናሁት፡፡ እዚያ የገጠመኝ ነገር ግና አለመሄዴን የሚያስመርጥ ነበር፤ በኢትዮጵያ ውስጥ ስለመኖሬም እርግጠኛ መሆን ተሣነኝ፤ ትግሬዎች በሚባሉ ልዩ ሰብኣዊ ፍጡራን በምትመራና የነሱ ብቻም በሆነች የምናብ ሳይሆን የእውነት ሀገር ውስጥ በስደትና በግዞት የምኖር ያህል ተሰማኝ፡፡ እነኚህ በወያኔ ቡድን ሥር የተኮለኮሉ ትግሬዎች ለይቶላቸው ዐይናውጣዎች መሆናቸውን እስካሁን በእንደዚያን ዕለቱ ሁኔታ አልተረዳሁላቸውም ነበር – ግዴላችሁም አይሆኑ ሆነው ተበለሻሽተውላችኋል፡፡ እንደተለመደው በወንድሞቻቸው ጥጋብና ዕብሪት የሚበሳጩ ጤናማና ሰላማዊ ትግሬዎችን ይቅርታ መጠየቅ ካለብኝ ብዙ ሳይረፍድብኝ እዚችው አንቀጽ ግርጌ ይሄውና ጠየቅሁ፡፡

ሟች ትግሬ በደርግ ዘመን ለስምንት ዓመታት ታስሮ ተፈትቷል፡፡ የታሰረበትም ምክንያት በትግሬነቱ ሳይሆን በወሬ አቀባባይነቱና ለወያኔ በነበረው ቅርበት በደኅንነት ሰዎች ተደርሶበት እንደነበር አጠያይቄ ደርሼበታለሁ፡፡ ሞኙ የደርግ መንግሥት የዘረኝነት ባሕርይ ፈጽሞውን ስላልነበረበት – ይህን ዐረፍተ ነገር እባካችሁን ልድገመው – የደርግ ኅብረብሔራዊ መንግሥት ፈጽሞውን የዘረኝነት ጠባይ ስላልነበረው ዜጎችን በብሔረሰባቸው ምክንያት የሚያስር ወይ የሚገድል እንዳልነበረ በበኩሌ በሚገባ አስታውሳለሁ፡፡ ሰውም ሆነ ተቋም መታማት ካለበት በእውነተኛ ሥራው እንጂ በፈጠራ ወሬ ሊሆን አይገባም ብዬ አምናለሁ፤ ሰውዬው ወይም ድርጅቱ ሞተ ወይም ወደቀ ተብሎ አለሥራው ማማት ትልቅ ስህተትና ኩነኔም ነው፡፡ ደርግ የሚወቀስበትና የሚወነጀልበት ስንትና ስንት ኃጢኣትና የጭካኔ ተግባር ሞልቶ ሳለ “ዘረኛ ነበር፤ የአንድን አካባቢ ሕዝብ ለይቶ ያጠቃ ነበር” ብሎ በአደባባይ መናገር ለትዝብት ከመዳረጉም በላይ የራስን ማንነት በገሃድ አውጥቶ ማሳየት ነው፡፡ የዘመኑ ከፍተኛ ትግሬ ባለሥልጣን ጓድ ፍስሐ ደስታ አጠገብ “ትግሬዎችን አርቀን ቀብረናቸዋል!” እያለ በትዕቢትና በምፀት የሚናር የደርግ ባለሥልጣን አልነበረም፡፡ ከዚህ ነጥብ አንጻር የማፈሪያ ታሪክ ባለቤቶች ፀረ-ኢትዮጵያ ወያኔዎች እንጂ ደርግም ሆነ ከዚያ በፊት የነበሩ ኢትዮጵያውያን መንግሥታት አይደሉም፡፡

በበቀደሙ የወያኔው ሰውዬ ቀብር የታዘብኩት ነገር በቀላሉ የማይታለፍ ሆኖ አግኝቼዋለሁ፡፡ ታሪክ ጸሐፊዎች መዝግቡት፤ መጣጥፍ ጸሐፊዎችም ለጽሑፎቻችሁ ፈርጥ አድርጉት፤ ሕዝቡም ይወቀውና እነዚህን በመካከላችን የበቀሉ የታሪክ መጭና እንክርዳዶችን ለይቶ በተቻለው ሁሉ አምርሮ ይታገላቸው፡፡ እርግጥ ነው – የኢትዮጵያ ሕዝብ ለጊዜው ያለው መሣሪያ ጸሎቱና ዕንባው ነው፡፡ ጸሎትና ዕንባ ደግሞ አንድን ዕብሪተኛ ኃይል እንዴት አድርገው ድራሽን እንደሚያጠፉ በኢትዮጵያ ውስጥ በተደጋጋሚ አይተናል፡፡

ክፉ የሠሩ መሪዎች የመጨረሻ ዕጣ ምን እንደሆነ በጉልህ ከታሪክ ተምረናል፡፡ በጨካኞች የሚፈስ የደም ጎርፍና የግፍ ዕንባ የሚያስከትለው መለኮታዊ መዘዝ የሥርዓት ቁንጮዎችን ሳይቀር ዘር ማንዘር ሳይወጣላቸው ተበታትነው እንዲቀሩ የማድረግ ኃይል አለው – የትናንት መለስ ዜናዊን መቅኖ አጥቶ መቅረት ያስቧል፡፡ ስለዚህ ይህ የትግሬዎች ጎጠኛ የገዢ መደብ በጀመረው የመበስበስና በብርሃን ፍጥነት የመንኮታኮት መንገድ ቀጥሎ የኢትዮጵያ ትንሣኤ በቅርብ እውን እንዲሆን ሁላችን እንጸልይ፤ የሚቻለንንም ሁሉ ያለመታከት እናድርግ፡፡ መንጋቱ አይቀርምና የጠወለገ ተስፋችንን አለምልመን ሀገራችንን በጋራ ነጻ ለማውጣት እንበርታ እንጂ የተጫነብን መርግ እንደማይነሣ ቆጥረን አንቆዝም፡፡ የነሱ ዋና ተግባር ሕዝቡ የሕይወቱ ድርና ማግ ውል እንዲጠፋበትና በተስፋ መቁረጥ ማዕበል እንዲቀዝፍ ለማድረግ በሰበቡም የኛ አይደሉም የሚሏቸው ዜጎች እንደጪስ በንነው እንደጉም ተንነውና እንደጤዛ ረግፈው እንዲቀሩ ነውና ለዚህ ወጥመዳቸው ምቹ ሆነን መገኘት እንደሌለብን እንወቅ፡፡ ተስፋችንም ፈጣሪያችን ነውና ከርሱ ጋር ሆነን የምናምንባቸውንም የተቃውሞ ኃይላት በአመራር ሰጪነት አቅፈንና ደግፈን ትግላችንን ለፍሬ እናብቃ፡፡ እንዲያ ካደረግን የድላችን ቀን በዓመታት ሳይሆን በቀናትና በሣምንታት የሚቆጠር ይሆናል፡፡ …

በተወልደ የቀብር ሥነ ሥርዓት ላይ ያየሁት ጉድ ይሄ ነው – ነገር ነገርን እየጎተተብኝ ዋናውን ጉዳይ በማዘግየቴ ይቅርታ እጠይቃለሁ፡፡ የሰውዬው ማለትም የወያኔ ትግሬው ቀብር አለቀ፤ ለማሣረጊያ ጸሎት ወደዐውደ ምሕረቱ መጣን፤ ካህኑ ቃለ እግዚአብሔርን አሰሙ፤ ከማሣራጊያው የ‹ሥረይ ሎሙ ኃጢኣተ ሕዝብከ…› ጸሎት በፊት የሟች የሕይወት ታሪክ ይነበብ ያዘ – አንባቢው በወያኔያዊ አንደበት እንደሚከተለው ማንበቡን ቀጠለ፤ እኛም እየተገረምን ማዳመጣችንን ቀጠልን፡፡
አቶ ተወልደ እንትና በትግራይ ክልል በእንዲህ ያለ ቦታ ከአባታቸው ከአቶ እንትና ከእናታቸው ከወይዘሮ እንትና በዚህን ዓመተ ምሕረት ተወለዱ፡፡ ዕድሜያቸው ለትምህርት እንደደረሰ …..

የደርግ መንግሥት በትግራይ ሕዝብ ላይ በነበረው ከፍተኛ ጥላቻ ምክንያት የትግራይን ሕዝብ በጅምላ እያፈሰ ያስር በነበረባቸው የ1970ዎቹ አጋማሽ አካባቢ አቶ ተወልደንም ከመንገድ አፍሶ ማዕከላዊ በማስገባት ለስምንት ዓመታት አስሯቸዋል፡፡ …

የሕይወት ታሪክ ንባቡ በዚህ መልክ ቀጠለ፡፡ የሕዝቡን ስሜት ዘወርወር እያልኩ ሳጤነው ትግሬ ያልሆነው ሰው በተለይ ፊቱ ቅጭም እያለ ተቃውሞውን በአካላዊ እንቅስቃሴ ይገልጽ ነበር፡፡ በበኩሌ መሬት ተሰንጥቃ ብትውጠኝ በወደድኩ – በአንድ ልቅሶ ሁለት ልቅሶ ይሏል እንዲህ ነው፡፡ በአንድ ሀገር ሁለት ዜጎች የሚኖሩበት ሁኔታም ፍንትው ብሎ ታየኝ፡፡ አማካሪ ማጣት እንጅ፣ የሰውዬውን ወያኔያዊ አስተዋፅዖ ለማጉላት ሲሉ እንዲህ ዓይነት ፀያፍ ነገር ውስጥ ገቡ እንጂ እንዲያ ብሎ መናገር ስህተት መሆኑን ሊረዱ በተገባቸው ነበር፡፡ እነዚህ ወያኔዎች ሕዝብን የሚንቁ በመሆናቸው ለሚናገሩት ቀርቶ ለሚያደርጉት ነገር ደንታቢስ ናቸው – ‹ሕዝብ ምን ይለናል?› የሚል አንዳችም የማስተዋል ነገር የለባቸውም፡፡ እንደዚሁ በገደምዳሜው ‹ኢትዮጵያን ከደርግ አፈና ነጻ ለማውጣትና የኢትዮጵያን ሕዝብ ነጻነት በማረጋገጥ አሁን ለምንገኝበት ዴሞክራሲ ለማብቃት በከተማ ወስጥ በኅቡዕ ካደረጉት ትግል ጋር በተያያዘ የደርግ ሥርዓት ለስምንት ዓመታት አሥሯቸዋል፡፡ ይህን ተጋድሏቸውንም ቀጣዩ ትውልድና ታሪክ ሲዘክሯቸው ይኖራሉ፡፡› ቢሉ በተሻላቸው ነበር፡፡ ለነገሩ ይህኛውም ከመጀመሪያው በባሰ የብዙዎቻችንን ልብ መስበሩ አይቀርምና ጥሩ አማራጭ ላገኝላቸው የምችል አይመስለኝም፤ ምናልባት ‹አቶ ተወልደ የቆሙለትን የሕወሓት ዓላማ በመደገፋቸው ምክንያት ለስምንት ዓመታት ለደርግ እሥር ተዳርገዋል› ቢባል የሚቀል ይመስለኛል፡፡ ያኔ የተናሩት ግን ታላቅ ትዝብትን ነው ያተረፈላቸው፡፡

ወያኔዎች ሀገርን ከመበታተንና ድህነትን ከማስፋፋት፤ መሬትን ለውጭ ባለሀብት ባወጣ ከመቸብቸብና ሀገርን ለእጅ አዙር ቅኝ አገዛዝ ከማጋለጥ፣ በዘረኝነት ልክፍት ታውሮ አንዱን የበላይ ሌላውን የበታች ከማድረግ ባለፈ የማይፈልጓቸውን ዜጎች በገቡበት እያሳደዱ ከመፍጀት በስተቀር ምን ያመጡልን መልካም ነገር አለ?…

ከዚሁ ‹ታላቅ› ወያኔያዊ ቀብር በተያያዘ ሌላውና ትልቁ ትዝብት በየትኛውም የቀብር ሥነ ሥርዓት በፍጹም የማይፈቀደው የቤተ ክርስቲያኑ የማይክሮፎን አገልግሎት ባልተለመደና ሕዝብን ባስገረመ ሁኔታ ለዚህ ሰውዬ የሕይወት ታሪክ ማስነገሪያነት መፈቀዱ ነው፡፡ በዚህም ነገር ያልተደነቀ አልነበረም፡፡ ለነገሩ የሀገርን ሀብት ሙሉ በሙሉና ከላይ እስከታች ብቻውን የተቆጣጠረ ኃይል ይህችን አነስተኛ የቤተ ክርስቲያን ንብረት አለደንቡ መጠቀሙ ያን ያህል ሚዛን ደፍቶ ሊነገር የሚገባው ጉዳይ አይደለም፤ የዜጎችን ሕይወት ጨምሮ ሁሉም የኢትዮጵያ ሀብትና ንብረት የማን ሆነና? እንኳንስ የየካ ሚካኤልን ማጉሊያ የቅድስት ሥላሤ ካቴድራልን ግቢ እንዳለ ቀምተው በሕይወት ዘመኑ ሃይማኖት ላልነበረው መለስ ዜናዊ አስከሬን ሲሰጡትና ቤተ ክርስቲያንን በአረማውያን ሲያረክሷት፣ በብኤልዘቡሉ የመለስ ስዕል ቤተ ክርስቲያን ከእግር እስከራሷ ‹ስታሸበርቅና ስትዋብ› እዚቺው አጠገባቸው ቁጭ ብለን በዐይናችን በብረቱ እያየን ጉድ ብለን የለምን? በድኑ የት እንደተጣለ ወይም እንደተቀበረ (ተቀብሮም ከሆነ) እንኳን ያልታወቀው የዚህ መፃጉዕ ሰውዬ ሬሣ በሣጥን ውስጥ ያለ በማስመሰል ያን ሁሉ የቁጭ በሉ የሀዘን ትርዒት ካሳዩ በኋላ ወያኔዎች በሚቆጣጠሩት ቤተ ክርስቲያን ውስጥ በፌዴራል እየተጠበቀ ግቢው ወፍ ዝር እንዳይልበትና ለምዕመናን ሳይቀር አስፈሪ እንዲሆን ተደርጎ ካቴድራሉ የጣዖት ማምለኪያ ቦታ እንደመሰለ አሁን ድረስ አለ፤ ቤተ ክርስቲያንም በወንበዴዎች እጅ ገብታ የዲያብሎስ መንጋ በዲያብሎሳዊ ሥሮት እየፈነጨባት፣ በጎቿንም ቀበሮና ተኩላ ከሥር ከሥር እየሞጨለፉባት እንዲሁ እንደክርስቶስ በላማሰበቅታኒ የ‹ኢትግድፈኒ› ጸሎተ ምህላ ኤሎሄ እያለች ትገኛለች፡፡ ካህናቷም ለፊታውራሪ ሊቀ ሣጥናኤል እጅ ሰጥተውና በሥጋ ቅንጦት ተማርከው ከዲያብሎስ መንጋ ጋር አብረው የዛር ዳንኪራ እየረገጡ የውሸት ኑሮ እንዲኖሩ ጨካኙ ታሪክ አመክሮ የሌለው ብያኔውን አስተላልፎባቸዋል – ቢያንስ አሁንና እስካሁን፡፡ ዛሬና አሁን ያለን ብቸኛ ምርጫ ነገም ሌላ ቀን ነውና ፈጣሪ የሚያሳየንን የመጨረሻ ፍርድ በጸሎትና በትግስት መጠበቅ ነው፡፡
ይህን እውነተኛ ታሪክ የምታነቡ ወያኔዎች ግን በአሳቻ ሥፍራና ሰዓት በምታድርጓት በዚያች የምናውቃት ዝግ ስብሰባችሁ ‹አብዚ አብዚ› ተባብላችሁ ብትነጋገሩበትና ይህን በኢትዮጵያ የሃይማኖትና የባህል ትውፊቶች ላይ የምታወርዱትን መቅሰፍታዊ ውርጅብኝ ለመተው ወይም ለመቀነስ ብትሞክሩ አወዳደቃችሁን መልክ ያለው ለማድረግ ይረዳችኋልና ጊዜ ባትሰጡት የተሻለ ነው እላለሁ፡፡

‹ምክር የድሃ ነበርሽ፣ ማን ቢሰማሽ› ሆነና ነገሩ ሰሚ እየጠፋ ተቸገርን እንጂ ‹እዩኝ እዩኝ› ያለ ‹ደብቁኝ ደብቁኝ› የሚልበት ወቅት መምጣቱ በጭራሽ አይቀርምና ቢያንስ ለልጆቻችሁና ለልጅ ልጆቻችሁ ብታስቡላቸው ጥሩ ነው፡፡ ዛሬ የጠገበ ነገ የሚራብ የማይመስለው የመሆኑ መጥፎ ዕጣ በሚጥልብን አእምሯዊ ሞራ እየተወናበድን ብዙዎቻችን የምንገባበት አዘቅት ከኛ ተርፎ ሌሎችን የሚጎዳበት አጋጣሚ እንዳለው በጊዜ መገንዘብና ራስን ከጠማማ መንገድ ባፋጣኝ ማውጣት ከአስተዋይ ጥጋበኛ ይጠበቃልና ወያኔዎች እባካችሁን አሁን አመሻሽ ላይም ቢሆን ከገባችሁበት የስህተት አረንቋ በቶሎ ውጡ፡፡ ዛሬ ጊዜ አላችሁ፤ ነገ ግን ላይኖራችሁ ይችላል፡፡ የሆድን ነገር አያችሁት፤ በላችሁ፤ጠጣችሁ፤ በመጠጥና በምግብ ከሰምበሌጥነት ተነስታችሁ ጌታዋን የገደለች በቅሎ ሆናችሁ፤ ሁሉን አያችሁት፤ ጎናችሁንም በሚመች ቦታ ላይ አሣርፋችሁ ሰላም ያጣ እንቅልፋችሁን ስትደቁ ይሄውና 22 ዓመታትን አስቆጠራችሁ – ምን የቀራችሁ ነገር አለ? ታዲያ በሰው ስቃይ መደሰታችሁን ከአሁን በኋላ ማቆም የለባችሁምን?

 በሌሎች ስቃይና እንግልት እየተደሰታችሁ እስከመቼ ልትኖሩ ትፈልጋላችሁ ? ከሰማይ ወርዶ ወይም ከመሬት ውስጥ ወጥቶ ይህን ክፉ ሥራችሁን እንድትተው ሊመክራችሁ የሚችልስ ማን ነው? ‹ሕዝቡን እስከመቼ ነው የምናስለቅሰው?› ብላችሁ ወደ ኅሊናችሁ በመመለስ ኢትዮጵያን ለመካስ የምትጀምሩት መቼ ይሆን? የኅሊና ዕውርነትና የልቦና ድንቁርና ምን ዓይነት አደጋ እንደሚያስከትልስ አስባችሁ ታውቃላችሁን?… ያሳዝናል በጣም፡፡

ግን ግን በቁማችሁም በሞታችሁም አካላችንንና ኅሊናችንን እየጎዳችሁ መቀጠሉን ከመረጣችሁ ጥጋባችሁን የሚያበርድ ነገር እንዲልክላችሁ አምላክን ከመማጸን በስተቀር ለጊዜው ሌላ ምርጫ የለንም፡፡ የሁላችንም አባት ኅያው እግዚአብሔር ፍርዱን በአጭር ጊዜ ውስጥ ይስጥ፡፡ ዙሪያ ገብ ዳፋው ይጠነክራል እንጂ መስጠቱ ደግሞ አይቀርም፡፡ ለማንኛውም ሁላችንንም ልቦና ይስጠንና የጋራ ሀገራችንን እንዳሁኑ በተናጠል ሳይሆን በጋራ የምንጠቀምበትን ሁኔታ እንድንፈጥር ኅያው እግዚአብሔር ይርዳን፤ አሜን፡፡

Revolution is a Must! What must be considered? Next is…

August  2013
by Leqa Naqamtee,
 
Before 22 years:

I grow up in small town with my “colorful” friends whose his father and mother are from Eritrea, Mendefera, another friend his father from Eritrea  Kessela ,Mother from Ethiopia Wollega Hro Guduru, other 2 friends father   from Tigray Axum and Mother from Wollga Mendi. As young friends we were happy and free from any evil thinking about each other. We have been living in love and joy; I don’t remember a single hostile day among us, except childish quarreler immediately dropped. This is just to bring back a good memory of that day. My feeling of that day about the situation in Eritrea and Tigray was not different from what I am feeling about my country today. That day I was highly concerned about the” civil war” in Eritrea and Tigray. I was questioning why Derge doesn’t allow for peace dialogue. Because of this reasons I have put myself out of sight to not participate in to that day free military services.
After 22 years:
As we all know, finally the ethnic based “revolutions” carried in most part of the country completed and have introduced fundamental change in Ethiopia. The changes were followed by opening of new constitution, arrangements of federal political system and establishment of 1 big and other 9 ”small” governments. The Big government is not the federal one. No! I am mentioning TPLF ruled “empire” federal system. The Big one is now the Tgray government. This is undeniable, because of so many facts that I can bring under this article, which is not the case of my today article. To give a dote example; the economic sector is under the control of few ethnic members. Remember the economic sector I mentioned here is the past 22 year’s economic sector. Just simply visit someone from your village affiliated to TPLEF and check the following indicators.
  •  What was  the source of his/ her  livelihood  pre TPLF ruled government, living standard etc
  • Does any change observed in the past 22 years, what are contributing factors for the observed economic development / improvements etc
To be honest today we are living totally in different Ethiopia and “no one” is ready to bring back the old day good memory for the betterment of our today and future because of the evil political seed germinated in the country and growing selfishness in TPLF villages. This is a tragedy. Much selfishness and greed for wealth accumulation from our brother’s side has changed our social values. Our “Tigray” brothers would like to continue to be dominant in every aspects of our life. They don’t care about our “old day” attachments, free from ethnic based feelings we have been sharing on the civil and evil war of that day, secretly shared resources, ideas based on firmly established brotherhoods/ sisterhoods. Regardless of all evil attempts made in the past 22 years to divide us along ethnic political line and attitudes, I am still confident that most of our Tigray brothers and sisters are sharing the same feeling of that day or must work hard to recover it.

Calmly please evaluate the past 22 years overall situations of our country, the majority of Ethiopians have denied basic human rights for which most of our brothers and sisters are sacrificed for. Selfishness sentiment from our “Tigray” brothers are keeping working intensively and aggressively to make all of us slave of our home country. Our politics, struggle and aspiration for democracy is at grave. In the past 10 years new laws are crafted and applied to limit and incriminate our” natural movements, aspirations, determinations, thinking, developments etc”. Our genuine contribution to the development of our nation and homeland is, discouraged, neglected, will be incriminated or systematically protected by TPLF brutal political system. Our brothers and sisters are sentenced a decades and above because of their political thinking and independent attitudes. According to Derge, the yesterday “petro dollar looters”  “prisoners”, “terrorists”, “dangers elements of the country”, TPLF members, are using the same terminology and sentences at their court to incriminate , to keep our peace loving brothers and sisters like Bekele Gerba, Eskinder Nega, Riot Alemu, many other thousands of Ethiopians in prisons. This is a painful experience for which a human being with healthy consciences does not tolerate.   Therefore,

In conclusion
  1. It is clear without further investigations, from overall political, economical and social conditions of Ethiopia; it is observed that change is inevitable. It clearly that arrogance is observed in the villages of few ethnic group family members. In case Ethiopian people tolerate the situation for their good and deep-rooted social values,   God doesn’t accept it. God is always against the arrogances.
  2.  It is observed that change is inevitable. Change is inevitable not because we all are suffering from hate syndrome towards existing government or we all are “chronically mad” not to seek stability. No! It is because we are in a country where there is no “relative” equality between nations. Where few are taking the resources, working to sustain a political firework, the power and the politics to fulfill their selfish lust for “absolute” dominance, this is intolerable!!! At this critical climax change is inevitable. The bell is ringing!!!  Few are not hearing!!! Or decide to not hear!!! This is very dangerous!!! We need to propose the way to out.
  3. The revolution will be supported by the majority of Ethiopians, advised to be carried out in the form of free from antagonism, racism, ethnic divides, and hatred, shrewdness, which is geared towards social and political reconciliations. In this case the political groups, Ethiopian elites , other peace loving groups, democracy loving nations   are expected to prepare “EPRDF inclusive”  “roadmap”, communicate this roadmap widely throughout “preparation for revolution phase”, and convince the Ethiopian people, at least the major actors,  that the roadmap will be in place immediately after the revolution. I called it “Revolution Management Roadmap”. Our inner motive for change should be clean and trustful. God wants from us to prove this if we are exceed positively from the “arrogances “.
  4. It is time to pray and to call for wise, visionary and revolutionary leaders to be successful in managing the inevitable revolution or equally important to prepare for the otherwise revolutionary outcomes i.e. the blessing or the curse.
  5. Above all, “the fear of God must be the beginning of our wisdom”. The failures of others who don’t feared God and keep sustain their arrogances until the end of their history was not good.  Motivation, courage  is one thing, is not everything, wisdom will make us perfect, therefore,   let us pick responsibly the followings at the eve of the inevitable  revolution,
    1. Let’s do the revolution in the lenses of learning  from others  failure (past 100 years)
    2. Let’s do the revolution in the lenses of learning  from our failures (at least past 150 years)
    3. Let’s do the revolution in the lenses of learning  from others success (Past 50 years)
These are important issues protect us from “starting from zero syndromes” and not to be trapped in the middle of “back to square one journey syndrome”, which is usually end up with “stacked in the vicious circle” gambling.
God bless Ethiopia and the nation

የአንድነት ፓርቲ አባላት ከአጉራ-ዘለል የወያኔ ካድሬዎች ጋር ግብግብ ይዘዋል

August 3, 2013
 
አንድነት ፓርቲ እሁድ ሐምሌ 28፣ 2005 “የሚሊዮኖች ድምፅ ለነፃነት” በሚል መሪ መፈክር ስር በተለያዩ የክልል ከተሞች የሰላማዊ ሰልፍ ለማድረግ አባላቱ ቅስቀሳ በማድረግ ላይ ናቸው። ይሁንና ከወያኔ አጉራ-ዘለል ካድሬዎችና ታጣቂዎች እየደረሰባቸው ያለው ወከባ ተባብሶ ቀጥሏል። ነብዩ ሀይሉ እና ሌሎችም በፌስ-ቡክ ገጾቻቸው ሁኔታውን እንደሚከተለው ይገልጹታል፣

UDJ calling for protest in Bahirdar
በባህርዳር የአድነት ፓርቲ አባላት በቅስቀሳ ላይ። ፎቶ Bisrat Woldemichael
 
በወላይታ የተሸጠ ጀነሬተር እንዲመለስ ተደረገ

በወላይታ ሶዶ ዙሪያ ወረዳ አዳራሽ(አዳራሹ ከ200 ሰው በላይ የመያዝ አቅም የለውም) አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ ለሚያከናውነው ስብሰባ ህዝቡን ለመቀስቀስ ሞንታርቦና ጀነሬተር የሚያከራይ ነጋዴ በመጥፋቱ(በከተማው ጀነሬተር በማከራየት ህይወታቸውን የሚገፉ ነጋዴዎች በብዛት የሚገኙ ቢሆንም ካድሬዎች ቀጠን ያለ ትዕዛዝ በማስተላለፋቸው መከራየት አልተቻለም)የጄነሬተር መጥፋት ያሳሰባት ወ/ሮ ጸሀይ ወ/ጊዮርጊስ አነስተኛ ጀነሬተር በ2300ብር ትገዛለች፡፡
ሻጩ ጀነሬተሩን በህጋዊ መንገድ ከሸጠና መኪናው ላይ እንዲጫን ከተደረገ በኋላ ግለሰቡ እንባውን እያዝረከረከ የተከፈለውን ገንዘብ በመያዝ ጀነሬተሬን መልሱልኝ በስህተት ነው የሸጥኩላችሁ››ይላል ፡፡ነጋዴው ለምን እንደዚህ እንደህጻን እያለቀሰ መልሱልኝ ማለቱን የተረዱ የፓርቲው አባሎችም ጀነሬቱን መልሰውለታል፡፡
—————————
መቀሌ፣ የአንድነት አመራሮች ከነ መቀስቀሻ ሞንታረቮአቸው በቀዳማይ ወያኔ ፖሊስ ጣቢያ ታሰሩ

የአንድነት ፓርቲ አመራር የሆኑት አቶ አርአያ፣ የአንድነት ፓርቲ ከፍተኛ አመራር የሆኑት አቶ እንግዳ ወ/ፃዲቅ እና የአንድነት ፓርቲ የትግራይ ዞን ፀሀፊ አቶ ክብሮም ብርሀነ በመቀሌ ከነ መቀስቀሺያ ሞንታረቮአቸው ቀዳማይ ወያነ ክፍለከተማ ፖሊስ ጣቢያ ታስሩ፡፡ አቶ እንግዳ ወ/ፃዲቅ እና አቶ ክብሮም ብርሀነ ለሁለተኛ ጊዜ እንደታሰሩ ልብ በሉ!!! የመቀሌ ነዋሪዎች አመራሮቹን ለማስፈታት ከፖሊስ ጋር እየተከራከሩ ነው፡፡‪
—————————-
ባህርዳር፣ አንድነት ፓርቲ በባህር ዳር ነገ ሐምሌ 28 ለሚደረገው ሰላማዊ ሰልፍ የተጠናከረ ቅስቀሳ እየተደረገ ነው

የባህር ዳር እና የአካባቢዋ ነዋሪዎችም በተቃውሞው ሰልፉ ላይ በንቃት ለመሳተፍ መዘጋጀታቸውን ለፍኖተ ነፃነት ዘጋቢዎች ተናግረዋል፡፡
ኢህአዴግም የባህር ዳር ህዝብ ባሳየው ንቁ ተሳትፎ በመደናገጡ በተለያዩ ቤተ ክርስትያኖች ቅዳሴ ዘግይቶ እንዲጀምር ትዕዛዝ አስተላልፏል፡፡ ቀበሌዎችም የተለያዩ ስብሰባዎችን አስጠርቷል፡፡ ባህር ዳሮችም ነገ ሰላማዊ ሰልፉን ለማድመቅ የተለያዩ መፈክሮችን በየቤታቸው በማዘጋጀት ላይ ናቸው፡፡
—————————-
አርባምንጭ፣ በአንድነት ፓርቲ በሁለት መኪናዎች አርባምንጭን በቅስቀሳ አድምቋታል፡

በራሪ ወረቀቶች እየተበተኑ ነው ፖስተሮችም በብዛት እየተለጠፉ ነው፡፡ የኢህአዴግ ካድሬዎች “ሰልፉ ላይ እንዳትወጡ” የሚል ቅስቀሳ ቢያደርጉም የአርባምንጭ ነዋሪዎች በሰልፍ ላይ ለመገኘት መወሰናቸውን እየተናገሩ ነው፡፡
—————————-
ጅንካ፣ ከትናንት ጀምሮ ከፍተኛ ቅስቀሳ እየተደረገ ነው

ከአጎራባች አካባቢዎች በሰልፉ ላይ የሚሳተፉ ዜጎች ወደ ጅንካ እየገቡ ነው፡፡ ከትላንት ጀምሮ ፖስተሮች እንዳይቀደዱ የአካባቢው ህዝብ እየጠበቀ ነው፡፡ በኢህአዴግ ካድሬዎች በ 1 ለ 5 መዋቅር ሰልፍ አትውጡ በሚል የጀመረው ቅስቀሳ ከሽፏል፡፡

Friday, August 2, 2013

ጋዜጠኛ ወይስ ካድሬ? (ከኢየሩሳሌም አርአያ)

August 2, 2013
 
Ethiopian Journalist Araya Tesfamariamየሪፖርተር ጋዜጠኛ የማነ ናግሽ በጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ ዙሪያ ያቀናበረውን የተንኮል ወጥመድ ተመርኩዤ በሰጠሁት ምላሽ ዙሪያ የማነ አስገራሚና ከርእሰ ጉዳዩ ጋር የማይገናኝ “መልስ” ለመስጠት ሞክሯል። ካድሬ ሆኖ የቀረበው የሪፖርተሩ የማነ ምላሹን ሲጀምር በኢትኦጵ ጋዜጣ በኢየሩሳሌም…ይቀርብ የነበረውን ዘገባና የፃሓፊውን ማንነት ከጠቀሰ በኋላ « በ2005 እ.ኤ.አ ችግር ውስጥ ሊከቱን ከነበሩ…» ይላል። መለስ ዜናዊ የሚመሩት ፓርቲ 18 ጋዜጠኞችን እስር ቤት በመወርወር፣ ከጋዜጣ ዝግጅት ክፍሎቹ ንብረትና ገንዘብ በሃይል በመዝረፍና ሁሉንም ነፃ ፕሬሶች በሃይል በመዝጋት የወሰዱትን እርምጃ ነው…የማነ «ችግር ውስጥ ሊከቱን..» ሲል የመለስ/በረከትን የፈጠራ ክስ ..እርሱም ቃል በቃል የደገመው።

በተጨማሪ በነፃው ፕሬስ ጋዜጠኞች ላይ በጅምላ የተወሰደውን እርምጃ አለቃው አማረ አረጋዊ በጋዜጣው በወቅቱ ደጋግሞ በርእሰ አንቀፅ በ<አቋም> ደረጃ የፃፈውን « አርፋችሁ ተቀመጡ ያልነው ይህ እንዳይመጣ ነበር..» እያለ የቸከቸከውን እንድናስታውስ አድርጎናል። ከዚህ አልፎ የቅንጅት መሪዎች ላይ በማላገጥ ለገዢው ፓርቲ ግልፅ የሆነ ድጋፍ እንዳለው ያረጋገጠበትን አንዘነጋውም።

 “ኢህአዴግ በምርጫ መሸነፉን በዘገበና “ የሽግግር መንግስት ይቋቋም” ብሎ በፃፈ ማግስት ነበር፥ ተግልብጦ የጋዜጠኞችን፣ የተቃዋሚ አመራሮችን መታሰር በመደገፍ በየጎዳናው የተረፈረፉ ንፁሃን ዜጎች ደም ላይ ሲያላግጥ የታየው። እንዲያውም « እነኢንጂነር ሃይሉ ሻውል በቃሊቲ እስር ቤት መንግስት መሰረቱ» ሲል ለመሳለቅና በህዝቡ ቁስል ለማላገጥ ሞክሯል።

ዛሬም እነ የማነ ናግሽ የህዝብን ያልሻረ ቁስል እየቆሰቆሱና የተወሰደውን እርምጃ እያቆለጳጰሱ እግረ መንገዳቸውን የገዢው ፓርቲ ደጋፊነታቸውን በአደባባይ ሊነግሩን ይዳዳቸዋል። አንድ ነገር ማወቅ ያለብህ አንተ የምትሰራበት ጋዜጣ 10ሺህ የማይሞላ ኮፒ ሲያሳትም እነኢትኦጵ፣ ነፃነት፣ ምኒሊክ፣ አስኳል…የመሳሰሉት ጋዜጦች እስከ 160 ሺህ ኮፒ በማሳተም በህዝቡ ከፍተኛ ተቀባይነት ነበራቸው። ይህ እውነተኛ ታሪክ ነው!! ሪፖርተር ብቻውን ቀርቶም 10ሺህ ኮፒ መድረስ አልቻለም።

ሽመልስና አለቃው ይህንኑ ጠቅሰው አማረን ፊት ለፊት አብጠልጥለውታል። « ፍትህ » ጋዜጣ እስከ 40ሺህ ኮፒ ያሳትም የነበረው ከናንተ ኋላ መጥቶ ነው። ህዝብ ሁሉንም ስለሚያውቅ መርጦ ያነባል። በህብረተሰቡ ተቀባይነት የማጣቱ ምስጢር “ የምታራምዱት ፅንፈኛ አቋም ወይም ወገንተኛነታችሁ” ነው። በዚህ ያላበቃውና ራሱን “ ፕሮፌሽናል ጋዜጠኛ ነኝ” ሲል የገለፀው የማነ ናግሽ፥ “በሪፖርተር ጋዜጣ ላይ ስለሙስሊሙ ማህበረሰብ የመብትና የነፃነት ጥያቄ ዘገባ እንደሚቀርብ፤ ከፈለገም የጋዜጣው ድረገፅ ላይ በመግባት መመልከት እንደሚቻል” ያለሃፍረት ሊገልፅ ሞክሯል። በእርግጥ የበረከት ልሳኖች ኢ.ት.ቪና ራዲዮ እንደሚያቀርቡት « በሽብርተኛነት የተከሰሰው እስክንድር ነጋ ማስረጃና ምስክር ቀረበበት..ተፈረደበት» ዜናዎች በሪፖርተር ጋዜጣ ሲወጡ እንደነበር አይካድም።

ይህንን ነው « ዘግበናል» የምትለው?..ይህንን ድራማ የመንግስት ሚዲያዎቹ ቀርቶ ካንጋሮው ፍ/ቤት አስቀድሞ ተፅፎ የተሰጠውና ያሳለፈው ፍርደ ገምድል ውሳኔ፣ ከመነሻው የበረከት « ድርሰት» ለመሆኑ « አኬልዳማና ጀሃዳዊ ሃረካት» በቂ ማስረጃ ናቸው። አንተም አለቃህም እውነቱን ሸፍናችሁ የገዢውን ፓርቲ ድርሰት ስለደገማችሁ ይሆን? .. በእስክንድርና በሌሎቹም ንፁሃን ዙሪያ « ዘገባ ሰራን፣ ዜና ለጠፍን..» እያልክ የምትቀባጥረው?…በጣም የሚያሳፍረው የሙስሊሙን ጥያቄና ሰላማዊ ተቃውሞ በተመለከተ « በየጊዜው ዘግበናል» ብለህ ያለአንዳች ህፍረት ልትናገር መሞከርህ ነው። እውነታውን ታዛቢው ወገን ይፍረድ! ?..ይልቅ ሰላማዊ የሆነ የሃይማኖት ነፃነት ጥያቄን በማንሳታቸው በድሬዳዋ በፖሊሶች የተወሰደውን እርምጃ እንዴት እንደዘገባችሁት ላስታውስህ?..« በድሬዳዋ በተፈጠረው ግጭት አንድ የዘጠኝ አመት ታዳጊ ከመሞቱ በቀር የከፋ ጉዳት አልደረሰም» ብላችሁ በጋዜጣው ፃፋችሁ። እንዲህ አይነት ዜና “ዘገባ” ይሰራል?…”የከፋ ጉዳት ደረሰ” የሚባለው ስንት ታዳጊዎች ሲገደሉ ይሆን?..ይህን ልትነግሩን ትችላላችሁ?..ደግሞም ስለሙስሊሙ ፍትሃዊ ጥያቄ አንድም መስመር እንዳልፃፋችሁ አስረግጬ ልነግርህ እወዳለሁ!! ቀጠልክና፥ « ሕገ መንግስቱን እናከብራለን፣ አንተና መሰሎችህ ምን እንድንፅፍ እንደምትፈልጉ እናውቃለን..» ስትል አስገራሚና የተደበቀ የሚመስለው ማንነትህን ግልፅ አውጥተሃል።

የሙስሊሙ ማህበረሰብ ጥያቄም ፥ “በህገመንግስቱ የተቀመጠው የሃይማኖት ነፃነት ይከበር፤ መንግስት በሃማኖት ጣልቃ መግባቱን ያቁም፤ የሃይማኖት መሪዎቻችንን የመምረጥ መብት ይረጋገጥልን፤” የሚሉ ናቸው። በአንፃሩ ከተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎችና ተቃዋሚ ፓርቲዎች ደጋግመው የሚቀርቡት ጥያቄዎች ገዢው ፓርቲ ራሱ ላወጣው ሕገመንግስት ተገዢ እንዲሆንና የዜጎች መብትና ነፃነት ይከበር የሚል ነው። ሃቁ ይህ ሆኖ ሳለ « ህገመንግስቱን እናከብራለን» በማለት መግለፅህ ሌላውን በህገወጥነት ለመወንጀል በማሰብ ይሆን?..ይህቺ ገለፃህ የነበረከትን የሰለቸ የማስፈራሪያና ሌላውን የመወንጀያ ዲስኩር ቃል በቃል የደገመች ናት። አያያዝክና፥ « አንተና መሰሎችህ የምትፈልጉት..» ብለሃል፤ “ምንድነው የምንፈልገው?.” ግልፅ ብታደርገው ጥሩ ነበር። ነገር ግን ምን ለማለት እንደፈለክ ከግምት በላይ መናገር ይቻላል፤ ይኸውም « ስለሕወሐት ምንም አንፅፍም፤ ስለነአዜብና ተከታዮቻቸው ዘረፋ አናጋልጥም፣ የምንፅፈው አማረ ስለሚጠላውና አጥብቆ ስለሚቃወመው በረከት ስሞኦን፣ ስለአላሙዲና አብነት..ብቻ ነው የምንፅፈው» ለማለት እንደፈለክ አያከራክርም። የሚያሳዝነው « ፕሮፌሽናል ጋዜጠኛ ነኝ » ባልክበት ብእር መልሰህ ጋዜጠኞችን በጅምላ ለመፈረጅና እንደገዢው ፓርቲ የተለመደ የፈጠራ < ታፔላ> ለመስጠት መሞከርህ ነው። በጣም አሳፋሪ ነው!! ባጭሩ “ ሚናህን ለይተህ” አደባባይ መውጣትህ የበለጠ የአንተና የአለቃህ « አቋም» እንዲታወቅ ማድረግህን ልገልፅልህ እሻለሁ።

Tensions high between the Borena Community and Gov’t

The efforts of the government including Prime Minister Hailemariam Dessalgn to resolve its conflict with the Borena elders have been unsuccessful. The problem started after the government began to resettle Geri Communities of the Somali region and the residents of Borena Zone, South Ethiopia, have refused to cooperate with the government on any matter including the resettlement program.

Just before the recent conflict of the two communities that took the lives of over 50 people from both communities, the Administrator of the Zone Kanu Jilo had told the residents of the Zone that the government had planned to resettle the Geri in Boerna Zone. The government went on with plan and made some administrative changes in the Zone by replacing officials of the Zone with new officials that came from the Oromia region.  As the Bornea community refused to accept the new appointments, the government stalled its resettlement plan and in the mean time, the two communities have mediated and resolved their differences by themselves. The government that did not seem to be pleased with what has happened, arrested over 18 top officials of the Zone including the Zonal Administrator and Police Head for “inciting clan conflicts”.

In the middle of the openings and disagreements, the Oromo Liberation Front (OLF) got the opportunity to come back in the Zone and carry out attacks. The Zone has been wrecked with conflicts.

Last Friday, the Aba Geda of the Borena Community, Guya Geba and 10 other elders met with different officials of the government in Addis Abeba including the Prime Minister. They urged the government that the detained officials should be released first for proper negotiations to kick off. The government began to soften its position.

The government last week promised the elders that it will first release the main officials of the Zone and the rest will be released within 14 days once the Court process is completed.  The Borena communities refused to accept the government’s new conditions and urged that they all be released together. The elders have held another discussion with the Justice Minister. The outcomes of the discussion are not yet known.

ESAT’s efforts to speak with the officials of the Zone were unsuccessful.

ኬኒያዊው ጠበቃ ስለየሱስ የሞት ፍርድ ሔግ ክስ ከፈተ!

ጲላጦስን ሔሮድስን ጣልያንና የእስራኤል መንግሥታትን ከስሷል
 
dola-indidis
                   
የየሱስ ክርስቶስ ክስ፣ ፍርድና ሞት ተገቢው የሕግ አሠራር የተከተለ አይደለም፤ ጉዳዩም እንደገና መታየት አለበት በማለት ኬኒያዊው ጠበቃ ዶላ ኢንዲዲስ ሔግ ለሚገኘው ዓለምአቀፉ ፍርድቤት ክስ ማሰማቱን ጀሩሳሌም ፖስት ኬኒያ የሚታተመውን ናይሮቢያን ጋዜጣን ጠቅሶ ዘግቧል፡፡
 
የቀድሞ የኬኒያ ፍርድቤት አፈቀላጤ የነበረው ይኸው ጠበቃ በወቅቱ የሮም ቄሣር የነበረውን ጢባሪዮስ ቄሣር፣ ጲላጦስን፣ የአይሁድ መሪዎችን፣ ንጉሥ ሔሮድስን፣ የአሁኑን የጣልያንና የእስራኤል መንግሥታትን ከስሷል፡፡
 
“ማስረጃው በመጽሐፍቅዱስ ላይ ይገኛል፤ ይህንን ደግሞ ማንም ሊክድ አይችልም” የሚለው ጠበቃ የሱስ በወቅቱ ተገቢውን ፍርድ እንዳላገኘ ጉዳዩም በትክክል በፍርድ ሒደት ውስጥ እንዳላላፈ ጠቁሟል፡፡ ጉዳዩ ሁለት ሺህ ዓመታት ያስቆጠረ ቢሆንም አሁን ያሉት የጣሊያንና የእስራኤል መንግሥታት በዚያን ጊዜ (በስቅለት) የነበረውን የሮም ህግጋትን አሁንም በሕጋቸው ውስጥ በተግባር እየተረጎሙ ስለሆነ ተጠያቂ ናቸው ብሏል፡፡
 
ክሱን የማቀርበው የየሱስ ወዳጅ (ጓደኛ) በመሆን ነው ያለው ጠበቃ አስቀድሞ ለኬኒያ ከፍተኛ ፍርድቤት ተመሳሳይ ክስ አቅርቦ ውድቅ በመደረጉ ጉዳዩን ወደ ለዓለምአቀፉ ፍ/ቤት መውሰዱ ተጠቁሟል፡፡
 
በወቅቱ ተገቢው ምርመራና የፍርድ አሠራር እንዳልተፈጸመ የተናገረው ጠበቃ በቦታው የነበረ “ተፍተውበታል፣ በበትርና በጡጫና በጥፊ መትተውታል፣ አሠቃይተውታል በመጨረሻም ላይ ሞት እንደሚገባው ፈርደውበታል” የሚለው ጠበቃ ኢንዲዲስ የሱስ እንዲናገር እንኳን ዕድል እንዳልተሰጠው ተናግሯል፡፡
 
ስለ ጉዳዩ እንደሚያውቁ የተጠየቁ አንድ የዓለምአቀፉ ፍ/ቤት ኃላፊ ሲመልሱ “ፍርድቤቱ ይህንን ክስ የማየት ሥልጣን የለውም፤ ፍ/ቤቱ የሚመለከተው በመንግሥታት መካከል የሚከሰት ክርክርና ክስ ነው፤ ይህንን ክስ ለመመልከት በጽንሰሃሳብ ደረጃ እንኳን የማይቻል ነው” በማለት መልስ ሰጥተዋል፡፡
 
ጠበቃ ኢንዲዲስ ግን ተገቢና ትክክለኛ ክስ እንዳቀረበ በእርሱ የሕይወት ዘመንም ፍትህ ተፈጽሞ ለማየት እንደሚበቃ ያለውን ተስፋ ተናግሯል፡፡
 
በጌትሰማኒ የመጨረሻውን ጸሎት ኢየሱስ ካደረገ በኋላ የሮም ወታደሮችና የካህናት አለቆች መጥተው በያዙት ጊዜ በሁኔታው ህገወጥነት የተናደደው አንደኛው ደቀመዝሙር (ጴጥሮስ) በሰይፉ የአንዱን አገልጋይ ጆሮ ቆርጦ ነበር፡፡ የጴጥሮስን ድርጊት የተቃወመው የሱስ ሲመልስ አስፈላጊ ከሆነ “12 ሌጊዮን (ከ60ሺህ – 90ሺህ) መላዕክት” በቅጽበት በማዘዝ ራሱን መከላከል ይችል እንደነበር መናገሩን መጽሐፍ ቅዱስ በግልጽ ይናገራል፡፡ (ማቲዎስ፡26፤53)

Thursday, August 1, 2013

የወያኔ “የድህነት ቅነሳ ፓሊሲ” ለድሀው – “ላም አለኝ በሰማይ …”

ከወያኔ አሰልቺ ዲስኩሮች አንዱ “ልማት” በተለይም “ድህነት ቅነሳ” ነው። ወያኔ ስለ ፈጣን ልማትና ስለ ድህነት ቅነሳ ሲነገረን እነሆ ሁለት አስርታት አለፉ!!!
እርግጥ ነው ወያኔ የራሱን አባላት ድህነት ቀንሷል። የሌላው ኢትዮጵያዊ ድሀ ድህነት ግን እየጨመረ ነው። ያም ሆኖ ግን ወያኔ የራሱ ሹማምንት ከሕዝብ በዘረፉት ገንዘብ የገነቧቸውን ፎቆች እያሳየን “እነሆ ልማታችሁ” እያለ ይሳለቅብናል። በውሸቱ የተሞሉ የምርት መጠንና ምርታማነት መስፈርቶችን እያስነበበን እየራበን “ጠገብን”፤ እየታርዝን “ለበስን” እንድንል ያደርገናል። “ኮንዶሚኒየም አድላለሁ” እያለ እያጓጓን ያችኑ ትንሿ ጥሪታችንን ይነጥቀናል።
ወያኔ በልማት ስም ምን ያላደረገን ነገር አለ? ትምህርት ሳይኖር ዲግሪ እያሸከመ ቀልዶብን ዲግሪ ይዘን ለኮብልስቶን ማንጠፍ ሥራ ተወዳድረናል። ህክምና ሳይኖር በክሊኒኮች መብዛት ተደስታችሁ ጨፍሩ ብሎናል። በጨለማ ውስጥ ተቀምጠን ስለግድቦች መብዛትና ስለ መብራት ኃይል ምርት መትረፍረፍ መስክሩ ይለናል።
ስንቶቻችን ነን የዕለት ተዕለት ኑሮዓችን እና የወያኔ የልማት ዲስኩሮች አልጣጣም እያሉን የተቸገርነው? ፈረንጆችም እነዚያኑ የወያኔ ቁጥሮችን መልሰው ሲነግሩን ስንቶቻችን ነው ከቁጥሮች ጋር የተጣላነው? የወያኔ ልማት፤ የወያኔ ድህነት ቅነሳ ፓሊሲ “ላም አለኝ በሰማይ፤ ወተትዋን እማላይ” የሆነብን ስንቶቻችን ነን?
ወያኔ ሰጠኋቸው በሚለው ሳይሆን እኛ በበላነውና በለበስነው፣ ባገኘው የትምህርትና የጤና አገልግሎቶች ኑሮዓችን ቢለካ ደረጃችን የት ይሆናል? በሚነገረን ሳይሆን በምንኖረው መጠን ትዳራችን ቢለካ ደረጃችን የት ነው?
ከድህነት መለኪያዎች ሁሉ የተሻለና የተሟላ ነው የሚባለው በእንግሊዝኛ Multidimensional Poverty Index የሚባለው ዘርፈ ብዙ የድህነት መለኪያ ነው። ይህን መለኪያ ሰዎች በእርግጥ ባገኙትና በተጠቀሙት ምርትና አገልግሎት መጠን ይነሳል። ሌሎች የድህነት መለኪያዎች መንግሥት አመረትኩ ወይም ሰጠሁ በሚለው ቁጥር ነው የሚነሱት። ውሸት በማይበዛባቸው አገራት በዚህም ተለካ በዚያ እጅግም ለውጥ የለውም። እኛጋ ግን ልዩነቱ የትየለሌ ነው።
ወያኔ የሚወዳቸው መለኪያዎች መካከለኛ ገቢ ካላቸው አገራት ተርታ ልንገባ መቃረባችንን ይነግሩናል። እነሱ መሠረት ያደረጉት ወያኔ አመረትኩ፣ ሰጠሁ የሚለውን ነው። ኑሮዓችን እኛ የተቀበልነው መሠረት በሚያደርገው ዘርፈ ብዙ የድህነት መለኪያ ሲለካ ግን ውጤቱ ፈጽሞ ሌላ ነው።
የ2013 የአውሮፓውያን ዓመት የዓለም ዘርፈ ብዙ የድህነት መለኪያ ስታትስቲክስ ባለፈው ሣምንት ይፋ ተደርጓል። ዘገባው እንደሚያሳየው የዓለማችን የመጨረሻዎቹ አስር ድሀ አገሮች በሙሉ አፍሪቃ ውስጥ ነው ያሉት። ከእነዚህ የመጨረሻ አስር ድሀ አገሮች አንዷ ኢትዮጵያ አገራችን ናት።
አሳዛኙ ዜና ይህ ብቻ አይደለም።
ከአስሩ የመጨረሻ ድሀ አገሮች የመጨረሻዋ ኒጀር ስትሆን ከዚያ ቀጥላ የምትመጣው ኢትዮጵያ ነች። በሌላ አነጋገር ኢትዮጵያ ከዓለም ሁለተኛ የመጨረሻ ድሀ አገር ናት። በድህነት ለኢትዮጵያ የባሰች አገር ኒጀር ብቻ ነች። ጅቡቲ እና ደቡብ ሱዳን ብቻ ሳይሆን ሶማሊያ እንኳ ከእኛ በተሻለ ሁኔታ ላይ ነው ያለችው።
ይህ ምንን ይነግረናል?
በወያኔ ቴሌቪዥን የሚቀርብልን ማዕድ ምግብ አይሆነንም። ጆሮዓችን እስኪደነቁር “ልማት፤ ልማት” እየተባለ ስለተጮኸብን ማጀታችን አይሞላም። መራብና መታረዛችን ሳያንስ “ጠግባችኋል” እየተባለ የሚቀለድን መሆኑ በእጅጉ ያሳዝናል። እኛ እየተራብንና እየታረዝን ባዕዳን ቱጃሮች በመሬታችን ላይ በሀብት ላይ ሀብት የሚጨምሩ መሆኑ ያስከፋናል። እኛ በጨለማ ተውጠን የመብራት ኃይል የሚሸጥ መሆኑ ይቆጨናል።
እኛ ኢትዮጵያዊያን ሳንበላ በጥጋብ እንድናገሳ፤ ደሳሳ ጎጆዓችን እየፈረሰ “ልማት መጣ” እያልን እንድንጨፍር፤ በጨለማ እየኖርን ለግድብ መዋጮ የምንገፈግፍ ምስኪኖች ሆነናል።
ግንቦት 7: የፍትህ፣ የነፃነትና የዲሞክራሲ ንቅናቄ ወያኔ በድህነታችን ላይ መጫወቱ መቆም አለበት ይላል። ግንቦት 7: “መሮናል፤ ከፍቶናል። ወያኔን ከነውሸቱ ልናወስግድ ተነስተናል። ለወያኔ የውሸት “ድህነት ቅነሳ” ጆሮዓችንን አንስጥ። ይልቁንም ወያኔን አስወግደን የመልማት እድላችንን በእጃችን እናስገባ፤ ኃላፊነት የሚሰማው መንግሥት ሲኖር ደግሞ የውሸት ሳይሆን የእውነት እንደምንለማ ባለሙሉ ተስፋዎች ነን” ይላል።
ድል ለኢትዮጵያ ሕዝብ!!