Saturday, September 13, 2014

የወያኔ የፖለቲካና የኢኮኖሚ እንቅስቃሲዎች ተሽመድምዷል።ትግሉም ወሳኝ ምእራፍ ላይ መሆኑ ተረጋግጧል :: (ምንሊክ ሳልሳዊ)

September 13,2014
- ወገን የሞተውን ወያኔን ለአንዴ እና ለመጨረሻ ጊዜ የቀብር ስነ ስርአቱን የምንፈጽምበት ወቅት ላይ ነን ። - ለስርኣቱ ቅርበት አላቸው ያሉ ምንጮች ወያኔ ወገቡ እንደተሰበረ እየተናገሩ ነው:: - ወያኔ ስልጣኑን ለህዝብ እንዲያስረክብ በተገኘው የትግል ስልት በመሳተፍ የዜግነት ድርሻችንን እነወጣ።
ወያኔ እየመራው የሚገኘው ኢኮኖሚ ተሽመድምዶ ሃገርን ረመጥ ላይ እየከተታት ሲሆን የወያኔ ሳቦታጅ ጥቂት ሰዎች በሃገር ሀብት በህዝብ ላይ እንዲፈነጩ አድርጓቸዋል::በሃገሪቱ ማንኛውም አይነት የኢኮኖሚ እንቅስቃሴዎች ከበፊቱ በተለየ እና በባሰ ሁኔታ ተንኮታኩተው አፈር መልበሳቸው በይፋ ታውቋል::ለስርኣቱ ቅርበት አላቸው ያሉ ምንጮች ወያኔ ወገቡ እንደተሰበረ እየተናገሩ ነው::በፖለቲካው ረገድ የስርኣቱ ገዢ ፓርቲዎች እርስ በርስ አለመተማመን ደረጃ ላይ ከመድረሳቸውም በላይ አመራሮቹ አድፍጠው አንዱን አንዱን እየጠበቀ በፍራቻ አለም ውስጥ እየዋተቱ ይገኛሉ::አቤት የሚባልበት እየጠፋ ነው፡፡ የውሳኔ ሰጪ ያለህ ቢባል መልስ አይገኝም፡፡ ፋይሎች የሚያያቸውና የሚያነባቸው አጥተዋል፡፡ መልካም አስተዳደር ገደል ገብቷል::በአላማ ሳይሆን በጊዜያዊ የመኖር ሂደት ላይ የተመሰረተው የካድሬዎቹ ሩጫ ድካምን በመፍጠሩ ሁሉም በያለበት ቆም ብሎ እያሰበ ሲሆን አሳቡም የገፈፍኩትን ገፍፌ ሃገርን ድባቅ መትቼ ልሽሽ ሆኗል::
ገበናን ገበና ይገፈዋል እንደሚባለው የወያኔ ጁንታ በተጭበረበረ ፖለቲካ ላይ የገነባው ኢኮኖሚያዊ ገበና በገበና ተጋልጧል:: የማይሰማ ነገር የለም እና እኛም ሰማን አነበብን አየንም እነሆ ታዝበን ዝም አላልንም ገበናዎቹ ገበናውን ሲገልቡት አብረን አልሳቅንም ሀገር ነውና ገበናዎቹን ተመርኩዘን የምንለውን ልንል ይኸው ተከሰትን::
የስርኣቱ ቅርብ ምንጮች የሃገሪቱ ኢኮኖሚ በመሽመድመዱ ወያኔ ወገቡ መቆረጡን እና መምራት አለመቻሉን በለሆሳስ በመተንፈስ ኢኮኖሚው መንኮታኮቱን ሲናገሩ የንግድ ስራዎች ከፓርቲ ድርጅቶች ውሽ በታም ተዳክመው እና ሞተው ያሉ ሲሆን የገንዘብ እንቅስቃሴዎች ጭራሽ ገደል መግባታቸውን እና ደንበኞች በባንኮች ላይ ያላቸው አመነታ በመጥፋቱ ግንኙነቶች መልፈስፈሳቸው በይበልጥ ለግል ባንኮች መዳከም ምክንያት ሆነዋል ሲሉ ይህ ደሞ አሉ የገንዝብ እንቅስቃሴውን ገድሎታል:: ምንሊክ ሳልሳዊ በጣም ድብን ያለ እውነት ነው::በውጭ ምንዛሪ ችግርና እጥረት ምክንያት በጣም የሚያስፈልጉ ዕቃዎች እንደተለመደው ከውጭ እየገቡ አይደለም፡፡ በጥቂቱ የመጡ ካሉም ዋጋቸው የማይቻል እየሆነ ነው፡፡ ብለውም አክለው አስቀምጠዋል::
ወያኔ አስፈላጊውን ገንዘብ ባለማግኘቱ ፕሮጀክቶች የቆሙ የተጓተቱ ሲሆን የሚሰበከው እድገት ለፕሮፓጋንዳዊ የሚዲያ ፍጆታ ብቻ መሆኑ ተረጋግጧል::ወያኔ የፋይናንስ ጥያቄውን ሊጨብጠው አይደለም ሊዳስሰው አልቻለም::በኢንቨስትመንት እንሰማራለን ብለው የመጡ የውጭው አለም ሰዎች በቢሮክራሲው መንተክተክ የተነሳ አስፈላጊውን አስተዳደራዊ ትብብር ማግኘት አለመቻላቸውን ከመናገራቸውም በላይ የጀመሩት ኢንቨስትመት እንደሚቋረጥ የወያነ ባለስልጣናት እንደሚያስቆሟቸው እና ለምን ሲሉ መልስ የሚሰጣቸው አከል እንደሌለ እና ጨረታ ካሸነፉ በኋላ እንደሚሰረዝ ለማን እንደሚሰጥ እንደማያውቁ አማረው እየተናገሩ ነው::
ሌላው የሃገር ውስጥ ታዋቂ ነጋዴዎችን ጨምሮ የወያኔ ባላባቶች ከፍተኛ የውጭ ምንዛሬ እያሸሹ መሆኑ ነው::የተረፈ ካለ ደሞ ወደ ባንክ ከመውሰድ ይልቅ ቤጅ መያዝ እየተመረጠ መቷል::አገር ውስጥ ደሞ ከማስቀመጥ ይልቅ ውጪ አገር መላክ እየተለመደ መቷል::ምንሊክ ሳልሳዊ አገር ውስጥ ባለው የውጭ ምንዛሪ ክምችት ላይ ተጨማሪ ጉልበት ሊፈጥር የሚገባው የውጭ ምንዛሪ ግኝትም ውጭ እንዲቀር እየተደረገ ነው፡፡ የገባ ካለም በጥቁር ገበያ እንደገና እንዲወጣ እየተደረገ በመሆኑ አገሪቱ ተጠቃሚ መሆን አልቻለችም፡፡ብለዋል የስርኣቱ ታማኞች:; ይህ የሚያመለክተው ዜጎች በፖለቲካው ጉዞ ላይ እምነት እንዳሌላቸው ሲሆን እየተሽመደመደ እና እየደቀቀ ያለው የፖለቲካ ስራቲ ምንም ለውጥ ሊያመጣ አለመቻሉ ሰዎች በወንጀለኝነት ሳይሆን በአስተሳሰባቸው ወህኒ መውረዳቸው የፈጠረው ስጋት ነው::
ዜጎች በህግ ላይ እና በንጽህናቸው ላይ ከመተማመን ይልቅ የህግ የበላይነት ከመጥፋቱ አንሳር እጅግ ፍርሃት ውስጥ በመግባታቸው የተማሩ እና በንግዱ አለም የተሰማሩ ሁሉ አፍርሃት ከመርበድበዳቸው እና ከመሰደዳቸው በላይ አሉ የተባሉትም ወያኔ በሙስና ባልደረቦቹ ላይ ፖለቲካዉ ገጀራ ሲያሳርፍ እየተመለከቱ ስራ በማቆም ከመደናበራቸውም ሌላ በራሳቸው አለመተማመን ያለባቸውን ጨምሮ በሙስናው ከባለስልጣናት ጋር የተነከሩ ሲሆን ሌሎች ደሞ እስከሚጣራ ለምን ልታሽ በሚል ባለው የፖለቲካ አመራሩ ላይ እምነት በማጣት የንግዱን ስራ ገለውት ከሃገር በመሸሽ ላይ ናቸው::
የተጭበረበረ አፋኝ ፖለቲካ ያስከተለው የኢኮኖሚ መንኮታኮት የአገሪቱን የፖለቲካ አናቶች ለውጥ እንዳያመጡ በመተብተብ ቀውስ ውስጥ የከተታቸው መሆኑን ከስብሰባዎች እና ከጭብጨባዎች ብዛት እየታዘብን ነው::በሌላ በኩል ሚዲያዎች ህዝብን መዋሸታቸው እና ለፖለቲካ ፍጆታ ብቻ መዋላቸው አገሪቷ እንድትንኮታኮት በር የከፈተ ሲሆን የዚህ መፍትሄ ስልጣን መልቀቅ ነው::ወያኔ ስልጣኑን ልህዝብ እንዲያስረክብ በተገኘው የትግል ስልት በሙሉ በመሳተፍ የዜግነት ድርሻችንን እነወጣ። #ምንሊክሳልሳዊ

ሰበር ዜና፡ ታጋይ ዘመነ የግንቦት 7 ህዝባዊ ሃይል አመራር ከአባይ ሚደያ ጋር አጭር ቆይታ አደረገ

September 13, 2014
ሰበር ዜና፡ ታጋይ ዘመነ የግንቦት 7 ህዝባዊ ሃይል አመራር ከአባይ ሚደያ ጋር አጭር ቆይታ አደረገ።

አባይ ሚዲያ ከግንቦት 7 ህዝባዊ ሃይል የፖለቲካ ሃላፊ ከሆነው ታጋይ ዘመነ ካሴ ጋር የስልክ ውይይት አደረገ። ታጋይ ዘመነ ለአባይ ሚዲያ ሲናገሩ አቶ ኤልያስ ጋዜጠኛ ስለመሆኑም እና እንዴት እና በምን ሂሳብ ወደ ትግል አለም እንደገባም እንደማያውቁ ተናግረዋል።
ወጣቱ ታጋይ ዘመነ ለኢትዮጵያ ህዝብ ባስተላለፈው መልእክት አዲሱ አመት የሰላም እና የድል ዘመን እንዲሆን በመመኘት እና ወንድማችን ታጋይ አንዳርጋቸውን የከፈለውን መሰዋእትነት ከንቱ እንዳይሆን ህዝባዊ ሃይሉ እና ከሌሎች የነጻነት ሃይሎች ጋር እየተደረገ ያለው ሂደት መፋጠኑን በዚህ አመት የምናወራበት ሳይሆን ወደ ትጋበር ተሸጋግረን ወያኔን የምናበረክክበት ዘመን እንደሚሆን አትጠራጠሩ ሲል መልእክቱን አስተላልፉል።
አባይ ሚዲያ ሰሞኑን ስለ ታጋይ ዘመነ እና ግንቦት 7 በኢትዮጵያን ሪቪው ባለቤት አቶ ኤልያስ ክፍሌ እያደረገ ያለውን ግንቦት 7ን የማጥላላት ዘመቻን አስመልክቶ  ላቀረብንለት ጥያቄ ሲመልስ፡-
በመጀመሪያ እንደዚህ አይነት ለወረደ እና ትግልን ለመጉዳት ሲል ቀን ከሌት በሚሰራ ግለሰብ የሚለውን መመለስ ለእኔ ራሱ ተገቢ አይደለም። እኛ ያለነው ተግባራዊ ትግል ላይ ነው እንጂ ምኞት ላይ አይደለም። እናም እኔ ራሴን ዝቅ አድርጌ በተራ ጉዳዮች መግባት አልፈልግም የኢትዮጵያ ህዝብ ከእኛ ብዙ ይጠብቃል። እውነተኛ ታጋይ፣ እውነተኛ ጋዜጠኛ፣ እውነተኛ ሰራተኛ ሀገራችን ካጣች እኮ ቆዪ፤ ስለዚህ ኤልያስም ከእነዚህ ውስጥ አንዱ ነው። የኢትዮጵያ ህዝብ ትግሉን ለመጉዳት ከሚሰሩ ተኩላዎች መጠንቀቅ እና እነሱ የሚመሩትን የግል ዌብሳይት የመረጃ ምንጭ አድርጎ አለመውሰድና አለማየት ተገቢ ነው። ምክንያቱም ለደቂቃም ቢሆን ያዘናጋናል አሁን አንተ ስትደውልም ስራ ትቼ ነው የማናግረው። ብዙ እና በርካታ ስራዎች አሉብን አጣዳፊ የሆኑ።
አባይሚዲያ፡ ሙሉውን ቃለምልልስ ከኢሳት የማክሰኞ ዝግጅት በኋላ ይዞ የሚቀርብ መሆኑን ለአንባቢዎቹ ይገልጻል።
Source: Abbaymedia.com

በቦረና ዞን ነዋሪ የሆኑት አቶ ጎንፋ አበራ ከፖሊስ በተተኮሰ 4 ጥይት ሕይወታቸው አለፈ

September 13,2014
አስከሬኑ ሽኝት ላይ የነበሩ የአባያ ገላና ወረዳ ሰብሳቢ አቶ በድሉ መንግሥቱ በፖሊስ ተደብድው በእስር ላይ ናቸው
(ፍኖተ ነፃነት) በቦረና ዞን ገላና ወረዳ ቶሬ ከተማ ነዋሪ የሆኑት አቶ ጎንፋ አበራ ጳጉሜ 4 ቀን 2006 ዓ.ም በግምት ከምሽቱ 3፡00 ሰዓት ላይ ወታደር ዋቆ ሁቃ በተባለ ፖሊስ በተተኮሰ 4 ጥይት ህይወታቸው ማለፉን የቦረና ዞን የአንድነት አስተባባሪ አቶ ጌታቸው በቀለ ለፍኖተ ነፃነት ገለጹ፡፡ የአቶ ጎንፋ አስከሬን ወደ ቶሬ ከተማ ጤና ጣቢያ ተወስዶ ሐሙስ መስከረም 1 ቀን 2007 ዓ.ም ከቀኑ 6፡00 ሰዓት ቤተሰባቸው ወደሚገኝበት አምቦ ከተማ ሲሸኝ የቶሬ ከተማ ነዋሪዎች አሸኛኘት ያደረጉ ሲሆን የአባያ ገላና ወረዳ ሰብሳቢ የሆኑት አቶ በድሉ መንግሥቱ ከሽኝቱ ሲመለሱ በፖሊስ ተይዘው ድብደባ ከተፈጸመባቸው በኋላ በእስር ላይ መሆናቸውን አስተባባሪው ገልጸዋል፡፡ አቶ በድሉ የተቃዋሚ ፓርቲ አባል በመሆናቸው ብቻ በተደጋጋሚ በገዢው ፓርቲ ካድሬዎች ድብደባና እስር ይፈጸምባቸው የነበረና ባሳለፍነው ዓመትም ይሰሩበት የነበረ የግል ታክሲያቸውን በድንጋይ የሰባበሩባቸው ሲሆን አቶ በድሉና በአካባቢው ያሉ የፓርቲው አባሎች ግን እየደረሰባቸው ያለው ዛቻ፣ ማስፈራሪያና እስር ከትግሉ ፈቀቅ እንደማያደርጋቸው ሰላማዊ ትግሉንም አጠናክረው እንደሚቀጥሉ አስታውቀዋል፡፡ ወደ ቶሬ ወረዳ ፖሊስ ደውለን ሁኔታውን ለማጣራት ያደረግነው ሙከራ አልተሳካም፡፡
Car ethiopiaCar ethiopia1

(ድብቅ ስትራቴጂ) የህወሓት ሥርዓት የአፋር ህዝብን መሬት የትግራይ ነው አለ

September 13,2014
(በአኩ ኢብን አፋር )
በሰሜናዊው የአፋር ክልል የሚገኙ የአፋር ክልል ወረዳዎች ዳሉልን ጨምሮ «የትግራይ መሬት ነው!» በማለት አፋቸው ሞልተው የሚናገሩ የህዋሓት መሪዎች ይደመጣሉ!! እሱም አብዓላ፣ ደሉል፤ ኮናባ፣ ባራህሌ፣ የትግራይ መሬት ነው ከሚባሉ ቦታዎች ይጠቀሳሉ። በኮናባ ወረዳ ከሁለት ሳምንታት በፊት በትግራይ ነዋሪዎችና በአፋር ነዋሪዎች መካከል ግጭት ተፈጥሮ አንድ የአፋር ወጣት ሲሞት 3 ደግሞ መቁሰላቸው ዘግበን ነበር። ችግሩ በሁለት ነዋሪዎች መካከል የሚፈጠር ግጭት አይደለም! የህዋሓት መንግስት የአፋር መሬትን ለመቀራመት የሚያደርገው ሆን ተብለው የሚደረጉ ትንኮሳዎች መሆናቸው ግልፅ ነው! «የኮናባ ወረዳ እና የአፅቢ ወረዳ የድምበር ወዝግብ የቆየ ቢሆንም የዛሬው በመንግስት ሆን ተብሎ የተፈጠረ በመሆኑ አሳስቦናል።» ይላሉ የኮናባ ነዋሪዎች።
afar region
የህዋሓት መንግስት ባለስልጣናት «መሬቱ የእኛ ነው እስከ ዳሉል የትግራይ መሬት ነው ብትፈልጉም ባትፈልጉም መንግስት እርምጃ ይወስዳል» ብለው ይናገራሉ። የአፋር የአገር ሽማግሌዎችን ጨምሮ ብዙ ወጣቶች በነገሩ በመገረም «በመሬታችን እየሞተን ነው! ገና አሁንም እንሞታለን!» በማለት ባለፈው ሳምንት በውቅሮ የተደረገው ስብሰባ ያለ ምንም መፍተሄ ተበትኗል! በስብሰባው የትግራይ ክልልን ወከለው የተገኙት የውቅሮው የዞን አስተዳደር የዞኑ የፀጥታ ቢሮ ኃላፊ እንዲሁም የአፅቢ ወረዳ መስተዳደርና የፀጥታ ቢሮ ኃላፊ ሲሆኑ በአፋር በኩልም እንደዛው። ለእነርሱ ታማኝ የሆኑት የዞን 2 የመንግስት ባለስልጣናትና በርካታ የአገር ሽማግለዎች ተገኝተዋል!! በዚህ ስብሰባ በባለፈው ውግያ የንፁሃን ሰዎችን ህይወት ያጠፉትን ሰዎች የአፅቢ ወረዳ የፀጥታ ኃይሎች ለህግ እንዲያቀርቡ በአፋር ሽማግሌዎች የተጠየቁ ቢሆንም ሰሚ አላገኙም!! «ካሁን በኋላ» ይላሉ የኮናባ ወጣቶች «ካሁን በኋላ ሁላችን በተጠንቀቅ እንቆማለን እንሞታለን!»
ከመንግስት የምንጠብቀው ፍትህ የለም!!

Friday, September 12, 2014

በህወሀት እና በአጋር ፓርቲዎቹ መካከል አለመተማመን እየተፈጠረ ነው

September 12, 2014
ሁኔ አቢሲኒያ

እስከ ጳጉሜ 4 2006 ዓ.ም ድረስ የተካሄደው የኢህአዴግ ምክር ቤት ስብሰባ በርካታ እንግዳ ክስተቶችን ይዞ የተገኘ እንደነበር ውስጥ አዋቂ ምንጮች ገልጸዋል:: በአንድ ወር ውስጥ ብቻ ለሶስተኛ ጊዜ በተካሄደው በዚሁ የድርጅቱ ስብሰባ ብአዴን እና ኦህዴድ ድርጅታዊ ተልእኮዎችን የማስፈጸም ውስንነት እንደታየባቸው አልፎ ተርፎም የኦሮሚያ እና የአማራ ክልሎች በተለይም ከኦሮሚያ ክልል ወለጋ ኢሊባቡር እና አምቦ የኦነግ ምሽግ የሆኑ ሲሆን በአማራ ክልል ሰሜን ጎንደር በአርበኞች ግንባር ቁጥጥር ስር ለመዋል እንደተቃረበ፣ በአመራሩ እንዝህላልነት ህዝቡ ከኢህአዴግ እየራቀ እና ለድርጅቱ ጀርባውን እንደሰጠ ከመድረክ ተገልጽዋል:: በዚህ ጉዳይ ላይ የተናገሩት የብአዴን እና የኦህዴድ አመራሮች የተቀሰው አካባቢ ገብቶ ለመስራት ፍቃደኛ የሚሆኑ አባላት እጥረት እንዳለ፣ ህዝቡ በተደጋጋሚ በአካባቢው አመራሮች ላይ ዛቻ እና ማስፈራሪያ እንደሚያደርስ ገልጸው ይህም ሊሆን የቻለው በአካባቢው ያለው የሀይል እጥረት እንደሆነ ገልጸዋል::

በሌላ በኩል በብኣዴን እና በኦህዴድ ውስጥ የሚገኙ አባላት ድርጅታዊ ታማኝነታቸው ከጊዜ ወደ ጊዜ እየቀነሰ እየመጣ እንደሆነ በርካታ አባላት በየሄዱበት ሀገር ጥገኝነት በመጠየቅ ላይ መሆናቸው የተገለጸ ሲሆን መጪው የ2007 ምርጫ በሰላም ይጠናቀቅ ዘንድ ሁሉም መሰረታዊ ድርጅቶች አባላታቸውን ጠንክረው እንዲያንቀሳቅሱ በተጨማሪም የሚዲያው ክፍል ልማታዊ አርቲስቶች ወደ ህዝቡ ልብ እንዲገቡ መሰራት እንዳለበት ለዚህም እቅድ ተነድፎ በቅርቡ ለሚዲያው ክፍል ገቢ እንደሚሆን እና ስራው ተግባራዊ እንደሚሆን ከመድረክ ተገልጹአል::

በሌላ በኩል ህወሀት በ2007 ቴዎድሮስ አድሀኖምን የድርጅቱ ኮከብ በማድረግ ላቅ ብሎ ለመታየት የሚያደርገው ሙከራ በአንዳንድ የኦህዴድ እና የብአዴን አባላት ተቃውሞ ሊያስነሳ እንደሚችል የተገመተ ሲሆን ከዚህ ሁሉ ነገር ጸድቶ ትክክለኛ የህወሀት ስራ አስፈጻሚ ሆኖ እየሰራ የሚገኘው ደህዴን እንድሆነ ለማወቅ ተችሉአል::

በተያያዘ ዜና ህወሀት እና የተቃዋሚው ቡድን ለእርቀ ሰላም ይቀመጡ ዘንድ በአፍቃሪ ህወሀቶች ዘንድ ውስጥ ውሰጡን ስራ እየተሰራ መሆኑን ለማወቅ ተችሏል፣ ይህንንም ስራ በበላይነት ይዘው እየሰሩ ያሉት አቶ መነገሻ ስዩም እንደሆኑ በተጨማሪም አሜሪካን ሀገር ሜሪላንድ ውስጥ ነዋሪ የሆኑት ዶ/ር ጥላሁን በየነ በቡድኑ ውስጥ እንደሚገኙም ለማወቅ ተችልዋል::

የእርቀ ሰላሙ ጉዳይ ከየትኛው ወገን እንደተነሳ ባይታወቅም የተለያዩ አስተያየት ሰጪ የኢህአዴግ አባላት ህዝቡ ከኢህአዴግ በተቃራኒ በመቆሙ በተለይም በሐገር ውስጥ በትግራይ ክልል የአረና ፓርቲ ተቀባይነት ማግኘት በመሀል ኢትዮጵያ ደግሞ የሰማያዊ እና የአንድነት ፓርቲዎች መጠናከር በሚጠሩት ሰልፍ ላይ የሚገኘው የህዝብ ቁጥረ ከእለት ወደ እለት መጨመር በውጪ ሀገራት ደገሞ ግንቦት ሰባት እና የአርበኞች ግንባር ልዩነታቸውን ወደ ጎን በመተው ወደ አንድ መስመር መምጣት በህወሀት ነባር አመራሮች ለድርጅታቸው እንደ አደጋ በመታየቱ የእርቀ ሰላሙ ጉዳይ ከህወሀት አመራሮች ሊነሳ እንደሚችል ይገመታል፣ በተቃዋሚው በኩል በእርቀ ሰላሙ ዙሪያ ያለው ምላሽ ምን ሊሆን እንደሚችል የታወቀ ነገር የለም።

The timing of ER’s rampage against G7 is a calculated one

Sept 12, 2014
Past trends and patterns of stories published by ER Intelligence Unit prove that ER has no qualms to pen fictions and distortions. Its latest, so-called “special report” is not a special report, but a deliberate act of to attract online traffic. ER’s claim to know many facts is simply hogwash, at least everything that he said and stated regarding Ginbot 7. We at Ginbot 7 can easily refute ER’s obdurate fictions in public line by line, but unlike ER we are indebted to the Ethiopian public. Hence, we spend our valuable time planning and excusing our vital tasks of removing the ethnic minority regime.
It is indeed easy to debunk these fictions in the so called special report and the latest one, the laughable “advice to G7”.Laughable indeed! The ER editor thinks he is an institution by himself, otherwise, where is he getting this inflated sense of self, the moral authority, and the political acumen to give an advice to an organization that has more than enough politically experienced and highly capable leaders and members in thousands?
I have known and worked with ER’s editor for the past so many years to champion human rights and democracy in Ethiopia. He is a hard worker. I admire his dedication. But he fails to see left and right, backwards and forward. He fails to handle contradictions and complexities. He thinks that the world revolves around him; he thinks that he has a monopoly on facts, solutions and ideas about the how, the ways and means of the struggle to bring about the desired end.
ER’s editor had projects, and those projects failed due to several reasons. His failure is not Ginbot 7’s failure. Let it be known that I have no interest to respond and engage the editor of ER further in refuting each of the fabrications and lies. Ginbot 7, as an organization, does not consider diversionary fictional stories deserve a formal reply.
I am writing this last note in my personal capacity and as person who happen to know the details of what ER’s editor otherwise claims them to be the “facts”, the” truth “, and Lo and Behold, the only “truth“ concerning everything about G7, its internal working, its relationships with governments, including the Eritrean government, and other organizations, and many of G7 projects. And unlike ER, there is no way I would dwell on these matters in public. We owe it the struggle; we owe it the Ethiopian people not to do so. That is what any responsible person who understands the stakes involves would do.
Thank you and sincerely,
Neamin Zeleke

ቪኦኤ አማርኛ፣ ከድጡ ወደ ማጡ? – በአበበ ገላው (ጋዜጠኛና አክቲቪስት)

Sep12,2014
የዛሬ ወር ገደማ የቪኦኤ አማርኛ ሪፖርተር የሆነውና አወዛጋቢና የተዛባ መረጃ በማቅረብ በስፋት የሚታወቀው ሄኖክ ሰማእግዜር ሙሉ በሙሉ ሃሰት የሆነ ዘገባ በአሜሪካን ሬድዎ አማካኝነት አሰራጨ። የዘገባው አላማ በካሊፎርኒያ የሚገኘው አዙሳ ፓስፊክ ዩኒቨርሲቲ ለአቶ ሃይለማርያም ደሳለኝ ሰጥቶ የነበረውን የክብር ሽልማት መልሶ መንጠቁንና ዝግጅቱ መሰረዙን በማስመልከት የቀረበው ዘገባ ሃሰት ነው ብሎ ለማስተባበል እና እኔን፣ አለማቀፉን የኢትዮጵያዊያን መብት የጋራ ህብረት እንዲሁም ኢሳትን በሃሰተኝነት ለመወንጀል የታለመ ነበር።
አበበ ገላው
አበበ ገላው
ይሁንና ለእርምጃው ምክንያት የሆነው በኢትዮጵያ ውስጥ እየተካሄደ ያለው መጠነ ሰፊ የሰብአዊ መብት ጥሰት ዩኒቨርሲቲው እንዲመረምርና ሽልማቱን መልሶ እንዲያጤን ስለተደረገ መሆኑ በግልጽ የተነገረ እውነታ ነበር። ዩኒቨርሲቲውም ለክብሩ ስነ ስርአት መሰረዝ የሰጠው ዋነኛ ምክንያት ይሄው የሰብአዊ መብት ጥሰት ጉዳይ መሆኑን በይፋ ደጋግሞ ገልጿል።
አልተሳካም እንጂ ሄኖክ በተለይ በእኔ ላይ ያነጣጠረ በተንኮል የተሞላ ጎጂና የተዛባ ዘገባ ሲያቀርብ ይሄኛው ሶስተኛው ነው። በግንቦት 10, 2004 (May 18, 2012) በአቶ መለስ ዜናዊ ላይ የተቃውሞ ድሞጽ ሳሰማ ሄኖክ በአይኑ ያየው በጆሮው የሰማው ሃቅ ቢሆንም ድምጼን ሳንሱር አርጎ ዘገባውን አዛብቶ ለስርጭት አበቃው። በዚህም ምክንያት ቪኦኤ ከአድማጮቹ ከፍተኛ ተቃውሞ ስለቀረበበት በሳምንቱ ዘጋባውን እንደገና በሌላ ሰው አስተካክሎ ተቆርጦ የቀረውን ድምጼን አስገብቶ ሌላ ዘገባ ለማስተላለፍ ሞከረ። ይሄን በጋዜጠኝነት ስም የተሰራ እርካሽ የፖለቲካ ቁማር ታዝበን አለፍነው።
ከዛም ግኡሽ አበራ የሚባል አንድ የቦስተን ነዋሪ በእኔ ላይ የግድያ ወንጀል ለመፈጸም ሲዶልት ገና ከጥንስሱ በFBI ተደርሶበት ምርመራ እንደተደረገበት ተዘገበ። በዚህ ላይ ወያኔ የተቀናጀ ስራ በመስራት፣ አንዳንድ ድህረ ገጾችን፣ ፓልቶኮችን እና ቪኦኤን በመጠቀም እኔ ግኡሽ አበራን ልክ በሃሰት የወነጀልኩት ለማስመሰል ሌላ ያልተሳካ ጥረት ተደረገ። እንደተለመደው ሄኖክ አሳፋሪ የካድሬ ስራውን በመቀጠል ከፍተኛ መዛባት ለመፍጠር ሞከረ። ትንሽ ብዥታ ቢፈጥሩም ያሰቡትን ያህል ግን አልተሳካም። ፈጽሞ ያላናገረውን የFBI ቃል አቀባይ ጠቅሶ እንደለመደው ድምጽ ሳያስገባ “የጥቅሱ መጀመሪያ፣ የጥቅሱ መጨረሻ” በማለት አድማጭን ግራ የሚያጋባ ዘገባ ለቀቀ። እኔ እንደ ጋዜጠኛ ባይሆንም እንደ ጉዳዩ ባለቤት ከቦስተን FBI ቃል አቀባይ ግሬግ ኮምኮዊች ጋር ያደረኩት ንግግር የድምጽ መረጃ እስካሁን በእጄ ላይ አለ። በተጨማሪም እንደነ ግኡሽ ስራ ቦታው ድረስ ሄደው የFBI መርማሪዎች ካፋጠጡት ግን በሴራው አለመሳተፉ ከተረጋገጠው ቤዛ ጥላሁን ያገኘሁት ዝርዝር መረጃ ጭምር በእጄ ይገኛል።
ዘፋኝና የግኡሽ ደባል የነበረችው አበራሽ የማነ በግዜው የቤዛ ወዳጅ የነበረች ሲሆን አሁን ትዳር መስርተዋል። በወቅቱ ለአበራሽ የማነ መርማሪዎቹ ጥያቄ ቢያቀርቡም ምንም አይነት ውንጀላ ማንም ባያቀርብባትም ፓልቶክ ላይ ብቅ ብላ በሃሰት አበበ ገላው ወነጀለኝ እንድትል ተደረገ። እነ አውራምባ ታምስም ወገንተኛ የሆነና የሚያስተዛዝብ ስራ ሰሩ። ይህንንም በወቅቱ ታዝበን አለፍነው።
peter
FBI በዋነኛነት ትኩረት ያደረገው ግኡሽ ላይ ነበር። ለዚህም ምክንያት ደግሞ እንዳወሩት በፌስቡክ ስለተሳደበ ወይንም ስለዛተ ሳይሆን በግድያ ወንጀል ዱለታ ሊያስጠይቅ የሚችል መረጃ መርማሪዎች እጅ በመግባቱ ነበር። በቀጣይነት በጉዳዩ ላይ ተጨማሪ እርምጃ የመውሰድና ያለመውሰድ መብት የመርማሪዎቹ ሲሆን የዘገባው እውነታ ግን ከላይ የተጠቀሰው ነው።
በግልጽ አፍቃሪ ወያኔ የሆነው ሄኖክ ሰማእግዜር ግን ጥቅስ ብሎ ያነበበውን ብዥታ የሚፈጥርና ከዋናው ጭብጥ ውጭ የሆነና አዛብቶ ያቀረበውን ሃተታ በተውሶ የወሰደው ከሶስተኛ ወገን፣ እንደውም እንደሰማሁት ከሆነ፣ ከትግሪኛ ዝግጅት ክፍል ነበር። ይሁንና ጥረቱ እውነቱን አልቀየረውም። ግኡሽ አበራ እኔን በስም ማጥፋት በፍርድ ቤት እንደሚከስ ወያኔዎች ደጋግመው ከመናገር አልፈው ከፍትኛ ገንዘብ ቢያዋጡም እስካሁን የተሰማ ክስ የለም።
እኔ በወቅቱ ወንጀል ሲዶልት የተደረሰበት ሰው ማንንም በስም ማጥፋት መክሰስ አይቻለውም ያልኩት እውነትን በመተማመን ነበር። አሁንም ፍርድ ቤቶች ክፍት ስለሆኑ ግኡሽ ብቻ ሳይሆን የውሸት ዘገባ በማሰራጨት እጅ ከፍንጅ በመያዝ አደባባይ ያወጣሁት ሄኖክ ሰማእግዜር (እስከ እረዳቶቹ) ዶሴውን ጠርዞ ፍርድ ቤት መሄድ ይችላል። ይሁንና ውሸት ታጥቆ አየር ላይ መውጣትም ይሁን የውሸት ዶሴ ጠርዞ ፍርድ ቤት መሮጥ ፈጽሞ እንደማያዋጣ ከወዲሁ መጠቆም እወዳለሁ።
የአሁኑ ይባስ እንዲሉ ሄኖክ አቶ ሃይለማሪያም አሜሪካ ሳይደርሱ ላስቸኳይ ስራ ተመለሱ፣ ያልደወሉትን ስልክ ደውለው ክብሩ ይቅርብኝ አሉ፣ እኔ ያልጻፍኩትን ደብዳቤ እያነበበና እያጠቀሰ፣ ያልተናገርኩትን ተናገረ፣ ያልዘገብኩትን ዘገበ እያለ ፈጽሞ ያላናገራቸውን ቃል አቀባይ ያላሉትን አሉ እያለ፣ አደባባይ ወጣ። በሁዋላ ስናጠያይቅ እንደውም የተረዳነው አሳፋሪው የቪኦኤ የሃሰት ዘገባ የተሰራው በቡድን ለሶስት መሆኑን ነው።
ታዲያ ምነው ይሄ ሁሉ የቪኦኤ ሰራዊት አንዲት ቅንጣቢ መረጃ ማውጣት ተሰናው? ከሁሉ የሚገርመው ደግሙ ውሸታችን “ቢቢጂ” የተባለ ቦርድ አጸደቀልን ብለው አይናቸውን በጨው አጥበው አደባባይ መውጣታቸው ነው። በእውነቱ በጣም ያሳዝናል። ቢቢጂም ቢሆን በመረጃ የተደገፈ ማስተባበያ ይዞ እስካልመጣ ድረስ አድማጭም አክባሪም በቀላሉ ማግኘት ይችላል ብዬ አላምንም። የተራዳሁት አንድ ጉዳይ ቪኦኤ ውስጡን ለቄስ ነው። ማንንም የመውደድም ይሁን የመጥላት ግላዊ መብታቸውን ብናከብርም ውሸት ታጥቀው አየር ላይ ከወጡ ግን ችላ ሳንል ደግመን በእውነት ሚሳኤል አናወርዳቸዋለን።
እኛ ለህዝባችን ነጻነትና መብት ከመከራከርና ከመታገል አንቆጠብም። ለዚህም ደግሞ ከማንም ፍቃድ አንጠይቅም። አንዳንድ የቪኦኤ አማርኛ ክፍል ባልደረቦች የእነ አቶ ሃይለማሪያም ደሳለኝ ክብር ተነካ ብለው እኛን ለማጥቃት መነሳታቸው ባያስገርምም ያሳዝናል። በከንቱ ይደክማሉ እንጂ አቶ ሃይለማርያምም ሆኑ አዙሳ ፓስፊክ ዩኒቨርሲቲ በዙ ተቀጣሪዎች አሏቸው። ሁለቱም ወገኖች ቪኦኤን በቃል አቀባይነትይሁን በጥብቅና አለመቅጠራቸውን በርግጠኝነት መናገር ይቻላል።
VOA 1
እንኳን በሜድያ ስራ የተሰማራ ጋዜጠኛ ነኝ ባይ ይቅርና ማንም እንደሚያውቀው አንድ ሚድያ ስተት ሲሰራ ባግባቡ እርማት እንዲያደርግ ይጠየቃል። ስህትት ተሰርቶ ከተገኝም አግባብ ባለው መንገድ እርምት አድርጎ ይቅርታ ይጠይቃል።። ቪኦኤን የሚያህል ግዙፍ ተቋም የሌሎችን ስራ ከማኮሰስ አልፎ በውሸት ጭብጦ የእውነትን ተራራ ለመናድ ጥረት ማድረጉ በጣም ግራ የሚያጋባ ጉዳይ ከመሆን አልፎ የምጣዱ እያለ የእንቅቡ ተንጣጣ የሚለውን አባባል ያስታውሰናል።
ሌላው አሳዛኝ ጉዳይ በዚህ የሀሰት ዘገባ ቁልፍ ሚና የተጫወተው ፒተር ሃይንላይን በአጠያያቂ መስፈርት ባለፈው ሳምንት ለሄኖክ ሰማ እግዜር “ሽልማት” ማቀበሉ ነው። ሄኖክም ይህንኑ ሽልማት ከአፍሪካ ክፍል ሃላፊው ከአቶ ንጉሴ መንገሻ እጅ ተቀብሏል። በርግጥ ሄኖክ ለማዛባትና ሃሰትን በይፋ በማሰራጨት ተወዳዳሪ ስላልተገኘለት ታላቅ ሽልማት ይገባው ይሆናል። ለጋዜጠኛነቱ ሽልማት መስጠት ግን ጋዜጠኝነትን መስደብ ነው።
በዚህ አይን ከፋች በሆነ አጋጣሚ ከእነ ሄኖክና ፒተር ሃይህላይን ይልቅ የአማርኛው እና የአፍሪካ ክፍል ሃላፊ የሆኑ ሁለት አንጋፋ ኢትዮጵያዊያን ጋዜጠኞችን በጣም ታዘብኩ።። ክብር ወደ ትዝብት ያለ ምክንያት እንደማይቀየር ለማንም ግልጽ ነው። ለምን ታዘብከን ብለው ከጠየቁኝ ምላሹን በዝርዝር በአደባባይ ላስረዳቸው ዝግጁ ነኝ። እስከዛው ሆድ ይፍጀው በማለት ለዛሬው የኢሳቱ ጋዜጠኛ መሳይ መኮንን የቪኦኤን ከድጡ ወደ ማጡ የሆነውን የሰሞኑን ጉዞ አስመልክቶ ያዘጋጀውን ምርጥ ዝግጅት ካልሰሙት አያምልጥዎ።
መልካም አዲስ አመት ለጭቁኑ የኢትዮጵያ ህዝብ!

Thursday, September 11, 2014

2007 ወሳኝ የትግል ዓመት!!!

Sep11,2014
ሁለት ሺህ ስድስት ዓመተ ምህረት ለኛ ለኢትዮጵያዊያን በአብዛኛው በመጥፎ የሚታወስ ዓመት ነው። 2006፣ በመካከለኛው ምስራቅም ሆነ በአፍሪቃ በስደት ላይ የሚገኙ ወገኖቻችን ላይ የሚደርሰው ስቃይ ከፍተኛ ደረጃ ላይ የደረሰበት ዓመት ነበር። 2006፣ ቀደም ባሉ ዓመታት አገራቸዉን ለቅቀዉ የተሰደዱ ሳይደላቸው በርካታ አዳዲስ ስደኞች ከአገር ወጥተው በበረሃዎችን ቀልጠው፤ በባህር ሰጥመው ያለቁበት አሳዛኝ ዓመት ነው። 2006፣ ጥንቃቄ በተሞላበትና በተቆጠበ መንገድም ቢሆን የተቃውሞ ድምጽ ያሰሙ ወገኖቻችን ወደ እስር ቤቶች የተጋዙበት ዓመት ነው። 2006፣ በአምቦ፣ በለቀምት፣ በጅማ በሀረር በርካታ የዩኒቨርስቲ ተማሪዎች የተገደሉበት፤ በአስር ሺዎች የሚገመቱት ደግሞ የታሰሩበት ዓመት ነው። 2006፣ በአፋር፣ በኦሮሚያ፣ በደቡብ፣ በቤንሻንጉል፣ በጋምቤላ፣ በአዲስ አበባና አካባቢው በ100 ሺዎች የሚገመት ኢትዮጵያዊ የተፈናቀለበት ዓመት ነው። 2006 ቁጥራችው ቀላል ያልሆኑ የነፃነት ታጋዮች ከጎረቤት አገራት ታፍነው ወደ እስር ቤቶች የተጋዙበት ዓመት ነው። 2006 የንቅናቄዓችን ዋና ፀሐፊ አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ በጉዞ ላይ እያለ በትራንዚት አውሮፕላን ለመቀየር ባረፈበት በየመን ዋና ከተማ ሰንዓ በየመን መንግሥት ወንበዴዎች ታፍኖ ለሸሪካቸው ህወሓት በህገወጥ መንገድ አስተላልፈው ለስቃይ እንዲዳረግ የተደረገበት ዓመት ነው። በእነዚህ ሁሉ ምክንያቶች ነው 2006 “ጥቁር ዓመት” የሚል ስያሜ ያገኘው።
ጭንቅላት የሚባል ነገር ያልፈጠረባቸው ድኩማን ሰላዮችና ፈንጋዮች የመጨረሻውን የመንግሥት ሥልጣን የያዙበትና ውሳኔያቸው “እሰረው፣ ክሰሰው፣ ግረፈው፣ ግደለው …” ብቻ የሆነበት ዓመት መሆኑ የ2006 ልዩ መታወቂያው ሆኖ ይቆይ ይሆናል። ይሁን እንጂ በ2006 ጨለማ ውስጥ የታዩ የብርሃን ጨረሮችም እንደነበሩና እንዳሉም መርሳት አይገባም።
በሁለት ሺህ ስድስት ዓመተ ምህረት የኢትዮጵያ ሕዝብ ከመቸውም በላይ በህወሓት አገዛዝ አምርሯል፤ በሁለገብ ትግል የህወሓትን አገዛዝ ለመፋለም የቆረጡ ወገኖች ትብብር ተጠናክሯል። በ2006፣ ኢትዮጵያ ዉስጥም ከኢትዮጵያም ውጭም የንቅናቄዓችን የግንቦት 7 ድርጅታዊ መዋቅር ተጠናክሯል። በ2006፣ ከህወሓት አገዛዝ ጋር ያለው መፋጠጥ ከሯል። እነዚህ ሁኔታዎች 2007 አገራችን በለውጥ ማዕበል የምትናጥበት ዓመት ሊሆን እንደሚችል ያመለክታሉ።
በአዲሱ ሁለት ሺህ ሰባት ዓመተ ምህረት፣ የግንቦት 7 አባላትና ደጋፊዎች ትልቁ ሥራ ድርጅታዊ አቅምን ማጎልበት ነው። በተለይ ወጣቶች በአምባገነን ሥርዓቶች ውስጥ ሕዝባዊ የትግል ድርጅቶችን እንዴት መመሥረት እንደሚቻል ማጥናት እና መፈተሽ ይኖርባቸዋል። ትናንሽ የግንቦት 7 ድርጅታዊ ቋጠሮዎች በመላው አገሪቱ መሠራጨት ይኖርባቸዋል። ወጣቶች ትናንሽ ኢ-መደበኛ ስብስቦችን ቶሎ መፍጠር እና አደጋ ሲያጋጥም ቶሎ ማፍረስ መልመድ ይኖርባቸዋል። ይህንን ክህሎት ደግሞ በቀጥታ ከሌሎች አገራት ከመዋስ ሀገር በቀል ቢሆን ይመረጣል።
በሁለት ሺህ ሰባት ዓመተ ምህረት፣ የጽዋ ማኅበሮች፣ መድረሳዎችና ጀማዎች፣ የስፓርት ቡድኖችና ደጋፊዎች፣ የመንደር ደቦዎችና የቡና ተርቲቦች፣ ስም ያላቸውም፣ ስም የሌላቸውም ስብስቦች የግንቦት 7 አባላት መገናኛዎች ይሆናሉ። በ2007 የግንቦት 7 አባል መሆን የምርጥ ዜግነት ምልክት መሆኑ በስፋት ተቀባይነት የሚያገኝበት ዓመት ይሆናል ብለን ተስፋ እናደርጋለን። በ2007 በህወሓት ካድሬዎች “ሽብርተኛ” መባል የሚያስደስትና እንደ ሽልማት ተደርጎ የሚወሰድበት ዓመት ይሆናል ብለንም ተስፋ እናደርጋለን። በ2007 እስር ማስፈራሪያ መሆኑ ያከትማል። በ2007 የኢትዮጵያ ወጣቶች በአርበኝነታቸው ይታወቃሉ። በ 2007 እያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ የህወሓት ሹማንምትን ዘረፋ የሚያጋልጥበት ዓመት ይሆናል። 2007 ዳኞች “እንቢ፣ በሀሰት አንፈርድም”፤ የመንግሥት ጋዜጠኖች “እውነቱን ደብቀን አንዋሽም”፤ ፓሊሶች “ወገናችንን አንደበድብም፣ አናስርም፣ አንገርፍም”፤ ወታደሮች ደግሞ “በወገናችን ላይ አንተኩስም” የሚሉበት ዓመት ይሆናል ብለን ተስፋ እናደርጋለን።
በዚህም ምክንያት 2007ን የምንቀበለው በታላቅ ተስፋና ዝግጅት ነው። በ 2007 ነፃነትና አምባገነንነት፤ ዘረኛነትና አንድነት፤ እውነትና ውሸት፤ አድርባይነትና አርበኝነት፤ ዝርፊያና ንጽህና፤ ድህነትና ብልጽግና የሚፋጠጡበት ዓመት ይሆናል ብለን እንጠብቃለን። በአጭሩ 2007 የወሳኝ ትግል ዓመት ይሆናል።
ሁለት ሺህ ሰባት ዓመተ ምህረት፣ የኢትዮጵያ መፃዒ እድል የሚወሰንበት ዓመት በመሆኑ ሁላችንም በተነሳሳ የአርበኝነት መንፈስ እንድንቀበለው ግንቦት 7: የፍትህ፣ የነፃነትና የዲሞክራሲ ንቅናቄ ጥሪ ያደርጋል።
መልካም አዲስ ዓመት!
ድል ለኢትዮጵያ ሕዝብ !

ሚሊየነሩ ጄ/ል (ከኢየሩሳሌም አርአያ)

Sep11,2014
ጄ/ል ዮሃንስ ገ/መስቀል
ጄ/ል ዮሃንስ ገ/መስቀል
የሕወሐት ታጋይ ጄ/ል ዮሃንስ ገ/መስቀል ቦሌ ቴሌ መድሃኒያለም ባለ6 ፎቅ ህንፃ እንዳስገነቡ የቅርብ ምንጮች አጋለጡ።
ከ95ሚሊዮን ብር በላይ በሚደርስ ወጪ እንደተገነባ የተነገረለት ይኸው ባለ6 ፎቅ ዘመናዊ ህንፃ ለተለያዩ የግልና የመንግስት ባንኮች፣ ኢንሹራንስ ድርጅቶች፣ ንግድ ቤቶችና የተለያዩ ድርጅት ቢሮዎች እንደተከራየ የጠቆሙት ምንጮቹ በወር ከ2.1 ሚሊዮን ብር የሚገመት ኪራይ ጄኔራሉ እንደሚሰበስቡ አስታውቀዋል።
ሌ/ጄ ዮሃንስ በግላቸው ባለ6 ፎቅ ዘመናዊ ህንፃ በከፍተኛ ወጪ በማስገንባትና ከፍተኛ የኪራይ ሂሳብ በየወሩ በመሰብሰብ ከሌሎቹ በቢዝነስ ከተሰማሩ የሕወሐት/ኢህአዴግ ጄኔራል መኮንኖች የተለየ እንደሚያደርጋቸው ምንጮቹ አመልክተዋል። በአገር መከላከያ ሚኒስቴር የመረጃ ዋና መምሪያ ሃላፊ ሆነው ለረጅም አመታት ሲሰሩ የቆዩት የህወሐቱ ጄኔራል ዮሃንስ ገ/መስቀል ከ1995ዓ.ም ጀምሮ ከጄ/ል ሳሞራ የኑስ ጋር የከረረ ቅራኔ ውስጥ ገብተው እንደቆዩና በሁለቱ የህወሀት ጄኔራሎች መካከል የተፈጠረው ቅራኔ እየተባባሰ ሄዶ ጄ/ል ዮሃንስ ከሃላፊነት እንዲነሱ መደረጉን ያስታወሱት ምንጮቹ የሁለቱ ቅራኔ ሙስናን መሰረት ያደረገ እንደነበረ አስረድተዋል። (በወቅቱ ስለግጭታቸውና መለስ ዜናዊ ዘንድ ቀርበው ስለተነጋገሩት በኢትኦጵ ጋዜጣ መረጃው ይፋ ተደርጐዋል)  ጄ/ል ዮሃንስ ከመከላከያ ሃላፊነታቸው እንዲነሱ የተደረጉት በጄ/ል ሳሞራ መሆኑን ያስታወሱት ምንጮቹ በወቅቱ “ጡረታ” በሚል እንደተነሱና ሲነሱም በሜ/ጄኔራል ማእረግ እንደነበሩ አስታውቀዋል።
በሙስና ባገኙት በመቶ ሚሊዮን የሚገመት ገንዘብ ሕንፃ ወደማስገንባት የግል ቢዝነስ የተሰማሩት ጄ/ል ዮሃንስ ከአራት አመት በኋላ በመከላከያ የሌተና ጄኔራልነት ማእረግ ባሳለፍነው ሰኔ ወር ተሰጥቷቸው በደቡብ ሱዳን የሚሰማራውን የተመድ ሰላም አስከባሪ ሰራዊት በጦር አዛዥነት እንዲመሩ መመደባቸው አስገራሚ ነው ያሉት ምንጮቹ ምክንያቱም ጡረታ ተብለው የተሰናበቱት ዮሃንስ የሌተና ጄኔራል ማእረግ እድገት ተሰጥቷቸው መመለሳቸው በመከላከያ ታሪክ የመጀመሪያው ሊያደርጋቸው ስለሚችል ግርምት ሊፈጥር ችሏል ብለዋል። ዮሃንስ የአገር መከላከያ ሚ/ር የሌ/ጄኔራል ማእረግ እንዲሰጣቸውና በተመድ እንዲመደቡ የተደረገው በአሜሪካ ትእዛዝ መሆኑን ምንጮቹ አመልክተዋል። በቦሌ ለንደን ካፌ ፊት ለፊት ዘመናዊ መኖሪያ ካስገነቡት ጄኔራሎች አንዱ ናቸው።
(በፎቶው ጄ/ል ዮሃንስ ገ/መስቀል)

አንድነት ኃይል ነው፤ መበታተን ጥቃት ነው (ዶ/ር. አክሎግ ቢራራ)

Sep 11,2014
አስተያየት
 ዶ/ር. አክሎግ ቢራራ 
unityበመሳሪያ ኃይልና በውጭ መንግሥታት ድጋፍ የስልጣን እርካብ የተቆናነጠጠው፤ በጠባብ ብሄርተኛው በህወሓት ፍጹም የበላይነት የሚመራው፤ የኢህአዴግ መንግሥት ከተመሰረተበት ጀምሮ የኢትዮጵያ ግዛታዊ አንድነት፤ ደህንነትና ነጻነት፤ የዘጠና አራት ሚሊዮን ሕዝቧ ሉአላዊዊነት፤ እውነተኛ እኩልነት፤ ማህበራዊ ጥቅም፤ መሰረታዊ ትብብር፤ ነጻነትና ዲሞክራሳዊ መብቶች ሙሉ በሙሉ ተናግተዋል፤ ተገፈዋል። በማንኛውም የዘመናዊነት መስፈርት ቢፈረጅ፤ ኢትዮጵያን ከባሰ አደጋ፤ ሕዝቧን ከከፋ ድህነት እና የእርስ በርስ ግጭት፤ ወጣቱን ትውልድ ለሁላችንም ከሚያሳፍር ስደተኛነትና ውርደት ሊያድነው የሚችለው ተተኪ የአገዛዝ ስርአት (አማራጭ) በሕግ የበላይነት፤ በእውነተኛ የኢትዮጵይያውያን እኩልነት፤ በሕዝብ ስልጣን የተመሰረተ ዲሞክራሳዊ አገዛዝ ብቻ ነው። ሰፊ ለም መሬት፤ ዝናብ፤ ወንዝ፤ ተስማሚ አየር፤ ከመሬት በታች ገና የማይታወቅ ሃብት ያላት አገር ለሁሉም አስተናጋጅ ለመሆን እንደምትችል አልጠራጠርም። ፍትህ-ርትእ ከሌለ ይኼን የማይገኝ ሃብት የሚጠቀሙበት የውጭ ኢንቬስተሮችና አጋር የሆኑ የውስጥ ሃብታሞች ሆነው ይቆያሉ። ገዢው ፓርቲና ተቃዋሚዎች የሚስማሙበት አንድ አበይት ጉዳይ አለ። ይኼውም ዲሞክራሳዊ አማራጭ አስፈላጊ ነው የሚል። ከጽንሰ ሃሳብ ባሻገር ግን ሁለቱም ወገኖች ዲሞክራሳዊ አሰራርን በተግባር አላሳዩም፤ ለማሳየትም የተዘጋጁ አይመስልም። አንዱ በሌላው እያመኻኘ ሃያ ሶስት ዓመታት አልፈዋል። የሚቀጥለው ምርጫ ዘጠኝ ወሮች ቀርተውታል። ሑኔታው ከቀጠለ የሚቀጥለው ምርጫ ከአሁኑ ተወስኗል ለማለት እንችላለን፤ የገዢው ፓርቲ የበላይነት ብቻ ይሆናል። መቶ በመቶ አሸነፍኩ ቢል አንገረም። የሚወዳደረው ከራሱ ጋር ይሆናል።
ገዢው ፓርቲ መከፋፈልን ወደ ሳይንስ ለውጦታል። ተቃዋሚው ይኼን ሳይንስ አልቀበም በማለት ፋንታ እርስ በርሱ መናከሱን ቀጥሎበታል። በተደጋጋሚ የሚታየው የራእይ፤ የግብ፤ የአደረጃጀትና የአመራር ደሃነት በቀላሉ አለመፈታቱ ተቃዋሚውን ፍሬ ቢስ አድርጎታል። በአገር ውስጥ ብቻ ያለው ሳይሆን በውጭም ያለው፤ በነጻነት ለመወያየትና አብሮ ለመስራት ገዢው ፓርቲ ሊቆጣጠረው የማይችለው። ቢቀበለውም ባይቀበለውም ተቃዋሚው የገዢው ፓርቲ አገልጋይ ሆኗል ለማለት ያስችላል። የምናውቀው የሃገሪቱን አስተዳደር በቋንቋ የቀየሰው አምባገነን መንግሥት ቆይታውንና የኢኮኖሚ ጥቅሙን ለማጠናከር ህዝብን እርስ በርሱ እንዲጋጭ፤ ተቃዋሚዎች እርስ በርሳቸው እንዲናከሱ በማድረግ ላይ ይገኛል። ይኼ የመከፋፈልና ስልጣንና ሃብትን የማስተማመኛ ስልት ከታወቀ፤ በአገር ቤትም ሆነ በውጭ የሚገኙ ተቃዋሚዎች በሰከነ መንገድ አስበው፤ ተፈላልገው፤ ተከባብረው፤ “ተናበው”፤ በዋናው ዓላማ ላይ ተስማምተው ለመስራት የገዢው ፓርቲ ፈቃድ አያስፈልጋቸውም ነበር። ችግሩ ጥበባዊና ዘመናዊ በሆነ መንገድ የማደራጀትና የመምራት ድክመትና ክፍተት መኖሩ ነው። ስርዓቱ  የራሱን መቆያ ያጠናከረውና የሚያጠናክረው የሃገሪቱን ባጀት፤ የተፈጥሮ ሃብትና ሌላ ጥሪት ለጥቂቶች አገልጋይ የሆነ ተከታታይ የብልጭልጭ እድገት በማሳየት፤ “እኔ እስካለሁ የእድገቱ ተጠቃሚዎች ትሆናላችሁ፤ እኔ ከሌለሁ፤ ትበላላችሁ” በሚል ዘዴ ነው።
ስርዓቱ የሚሰራውን ያውቃል ማለት ነው። የሚሰራውን የማያውቀው ተቃዋሚው ሆኗል። የተበታተነው ተቃዋሚ የሚለው በኢትዮጵያ እድገት የለም አይደለም። ፍትህ የለም። የአብዛኛው ሕዝብ ኑሮ ከጊዜ ወደ ጊዜ ወደ ታች በመሄድ ላይ ይገኛል፤ የኑሮ ውድነት የተራውን ዜጋ የመግዛት አቅም አስጊ በሆነ ደረጃ ቀንሶበታል። የወጣቱ ትውልድ እድል ተምሮ መሰደድ ሆኗል። በዘመነ ኢህአዴግ የሃገሪቱ ለም መሬትና ወንዝ ለውጭ ኢንቬስተሮች በእርካሽ ዋጋ ሲሰጥ ቆይቶ በአሁኑ ጊዜ አላሙዲ ብቻ የሚያመርተው በዓመት አንድ ሚሊዮን ቶን ሩዝ ለሳውዲ ገበያ ይቀርባል። እንደ ካሩቱሪ ያሉ የህንድ ኢኒቨስተሮችም የጋምቤላን ለም መሬት ተረክበው ምርታቸውን ለውጭ ገበያ ያቀርባሉ። በአጠቃላይ ኢትዮጵያ እየተነገደባት ነው። ሳውዲዎች እየተመገቡ  ብዙ ሚሊዮን ኢትዮጵያውያን ይራባሉ፤ አገሪቱ በዓመት ከአንድ ቢሊዮን ዶላር በላይ ለምግብ ግዢ ታወጣለች። ህይወቱ የተናጋው አብዛኛው ሕዝብ መብቱ ሰለታፈነ፤ ድምፁን ለማሰማት ስላልቻለ መከራውን ተቀብሎ ይኖራል ወዘተ የሚሉ ናቸው።
ስለሆነም፤ ተቃዋሚው የጠራ አማራጭ ለማቅረብ ነባራዊው ሁኔታ ይፈቅድለታል። የሚጎድለው የዓላማ አንድነትና የአመራር ብልሃት ነው። እርግጥ ነው፤ የገዢው ፓርቲ አቅም ከፍተኛ ነው። መንግሥትን ከተቆጣጠረ ባጀትንም እንደፈለገው ፈሰስ ለማድረግ ይችላል።

ስንቅ ብቻውን አቅም አይሆንም
የተቃዋሚው ክፍል አቅም ጠንካራ ሊሆን የሚችለው ከሕዝብ ከሚያገኘው ድጋፍ፤ ከመተባበሩ፤ ያለውን የቁሳቁስ አቅም በጋራ ከመጠቀሙ፤ በብልሃት ከመስራቱ፤ በአንድ ድምፅ ከመነሳቱ፤ ለዓላማው ጠንክሮ፤ በውስጥ አመራር ሳይበከል መስዋት ለመክፈል ፈቃደኛ ከመሆኑ ላይ ነው። በውጭ ያለው አገር ወዳድ፤ ዲሞክራትና የሰብአዊ መብቶች ጠበቃ ኃይል ያልተቆጠበ ድጋፍ ለማድረግ አቅምና ፍላጎት አለው። “ተባበሩ ወይንም ተሰባበሩ” እያለ ሲመክር ቆይቷል። ገንዘቡን፤ እውቀቱን፤ ድጋፉን ችሯል። ወደፊትም ይችራል የሚል እምነት አለኝ። ሆኖም፤ ስንቅ አቀባይነት ያለ ድርጅትና አመራር ብቃት ኢትዮጵያን አይለውጥም። ለዚህ ነው፤ ደጋፊዎች ተስፋ እየቆረጡ “ተቃዋሚ ነኝ” ማለቱን ቀልድ አታድርጉት፤ “ጩኸቱን ወደ ተግባር ለውጡት፤ በፍርሃትና በመጠላለፍ ዓለም መኖራችሁን አቁሙ፤ ነጻነት፤ ፍትህና ዲሞክራሳዊ ስርአት ያለ መስዋእትነት ስኬታማ ሊሆኑ አይችሉም። የእርስ በርስ ጦርነቱን አቁሙ። በውጭ ኃይሎች ማምለኩን አቁሙ። ድርጅት አፍርሳችሁ በድርጂት መተካቱን ተውት። አትጠላለፉ። መገናኛ ብዙሃኖችን ለእርስ በርስ ጦርነት አትጠቀሙ፤ አትወነጃጀሉ፡  የራሳችሁን የውስጥ አመራር ሳታጠናክሩ ሁሉን ነገር በገዢው ፓርቲና በሌላው ላይ አታመኻኙ፤ ተቃውሞ ብቻውን የማህበራዊ ጥቅም አይኖረውም” ወዘተ፤ ወዘተ የሚሉት።
በጀ፤ ታዲያ መፍትሄው ምንድን ነው?
ይኼ አጭር የፖለቲካ ኢኮኖሚ ስእል በተደጋጋሚ ያሳየው የኢትዮጵያ ተቃዋሚ ኃይሎች ጥቃቅን ልዩነቶችን ወደ ጎን ትተው ለሃገሪቱ ዘላቂነት እና ለመላው ሕዝቧ ደህንነት ሲባል መተባበር፤ ቢቻል መዋሃድ አለባቸው የሚለውን ባለፉት አስር አመታት በተደጋጋሚ ሁሉን በሚመለከት ያቀርብኩትን ምክርና ጥሪ ነው። ምክር እንጅ ትእዛዝ አይደለም። ማንም ግለሰብ ወይንም ቡድን ከውጭ ሆኖ ትእዛዝ ለመስጠት አይችልም። ትግሉ በአገር ቤት ካልተጠናከረ፤ አገር አቀፍና አሳታፊ ካልሆነ የፈለገው ጥረት ቢደረግ ዲሞክራሳዊ መሰረት ለመጣል አይቻልም። የኢትዮጵያ ሕዝብ የሚፈልገው አብሮና ተሳስቦ መኖርን ነው። ቂም በቀልነትን አይፈልግም። አንዱን አምባገነን በሌላ አምባገነን መተካት አይደፈልግም። ይኼማ ከሆነ ኢህአዴግ ምን አደረገ፤ የተካው ደርግ ምን አደረገ፤ አጼ ኃይለ ሥላሴስ ምን አደረጉ? የኢትዮጵያ ሕዝብ ራሱ የስልጣኑ፤ የመንግሥቱ፤ የመሪዎቹ ባለቤት ለመሆን ይፈልጋል። ለዚህ ብዙ መስ ዋት ከፍሏል። ስለሆነም፤ ሁሉም ተቃዋሚ ኃይሎች በዓላማ እንድነት በመንቀሳቀስ ታሪክ የሚጠይቀውን ሃላፊነት መወጣት አለባቸው። ሕዝብን ካጎለመሱ ተመጣጣኝ አቅም ይኖራቸዋል። ወሳኙ ሕዝብ ብቻ ነው። የኢትዮጵያ ሕዝብ በምርጫ ዘጠና ሰባት ለቅንጅትና ለህብረት የሰጠው ያልተቆጠበ ድጋፍና የከፈለው መስዋእት እንዲያንሰራራ ከተፈለገ በአገር ቤትና ከአገር ውጭ የሚገኙ የፖሌቲካና የማህበረሰብ ድርጅቶች፤ የሞያ ስብስቦች፤ ግለሰሶብችና ሌሎች ከቡድን፤ ከፓርቲ፤ ከግል ዝናና ጥቅም በላይ ለኢትዮጵያ ዘላቂነትና ለመላው ስብጥር ሕዝቧ ደህንነት አብረው መነሳትና አምባገነኑን መንግሥት ማንበርከክ፤ ቢያንስ ለድርድር እንዲስማማ ማድረግ ይኖርብናል። ከሁሉም በላይ የተቀነባበረ የሕዝብ አመፅ አገር አቀፍና ዘላቂነት ባለው ደረጃ ከተካሄደ ገዢው ፓርቲ ለመደራደር ይገደዳል።
ይኼን ትንተና ለማዘጋጀት የተገደድኩበት ዋና ምክንያት የህወሓት/ኢህአዴግ መንግሥት የለመደውን መንገድ እየተጠቀመ፤ ከመጭው ምርጫ በፊት በሰላማዊ መንገድና በሁለገብ ትግል የሚንቀሳቀሱና ተባብረው ለመስራት ፈቃደኛ የሆኑትን ተቃዋሚዎች ሁሉ ተባብረው እንዳይሰሩ በማሰብ በመከፋፈል ላይ ይገኛል። ይኼ አዲስ ነገር አይደለም። የኢትዮጵያ ሕዝብ ተስፋ ጥሎበት የነበረው የመኢአድና የአንድነት ውህደት ሂደት አሳዛኝና ተስፋ በሚያስቆርጥ መልክ ስኬታማ አለመሆኑ ለገዢው ፓርቲ ቆይታ ከፍተኛ አስተዋፅዖ አድርጓል። ይኼ ችግር የገዢው ፓርቲ ሳይሆን የተቃዋሚው ነው። በቅርቡ የተከሰተም ሌላ የተቃዋሚውን ክፍል ከጥያቄ ውስጥ ያስገባ አከራካሪ ጉዳይ አለ።
እንደማንኛውም አገር ወዳድ በ August 28, 2014 ሶስት በውጭ የሚንቀሳቀሱ ተቃዋሚ ድርጅቶች በዜናና በድህረገጾች ያሰራጩትን፤ ኢትዮጵያውያን ከፍተኛ ትኩረት የሰጡትን የጋራ መግለጫ በሰከነ መንገድ ተመልክቻለሁ።  መግለጫው እንዲህ ይላል። “ኢትዮጵዮጵያንና ሕዝቧን ካሉበት አዘቅት በማውጣት ሕዝቡ የስልጣን ባለቤት የሚሆንበትን ሁኔታ ለማመቻቸት የጋራ ትግልና መስዋእትነት የግድ የሚለን ደረጃ ላይ መድረሳችንን፤ የወያኔን ቡድን በሁለገብ ትግል እየተፋለምን ያለን ድርጅቶች ተጣምሮና አንድ ሆኖ መታገል እንዳለብን ካመንን ዓመታት አስቆጥረናል። ስለሆነም፤ ወደፊት ለመዋሃድ የተሰማማነው ድርጅቶች፤
  1. የኢትዮጵያ ሕዝብ አርበኞች ግንባር
  2. የግንቦት 7 የፍትህ፤ የነጻነትና የዲሞክራሲ ንቅናቄ
  3. የአማራ ዲሞክራሳዊ ኃይሎች ንቅናቄ ነን” የሚል መግለጫ ወጥቶ ሲያነጋግር ቆይቷል።
ከአንድ ሳምንት በኋላ በ September 6, 2014, በኮሎኔል አለበል የሚመራው የአማራ ዲሞክራሳዊ ኃይሎች ንቅናቄ ማስተባበያ አውጥቶ “ከግንቦት 7 ጋር አልተዋሃድኩም” ብሏል።
በእኔ ግምትና እምነት ምንም እንኳን የጋራ ስምምነቱ በምን አጀንዳ ላይ እንደተቀረጸ ባላውቅም፤ አሰራሩ በግልፅነት፤ በሃላፊነት፤ በዲሞክራሳዊነት፤ በዘላቂነትና ሌሎችን በሚያበረታታ መንገድ የውህደቱ ድርድር እንዲካሄድ ያለኝን ተስፋና ምኞት ለማቅረብ እፈልጋለሁ። በተመሳሳይ፤ በአንድነትና በመኢአድም በውስጥና በመካከላቸው መካከል የተከሰቱ ልዩነቶችም በውይይት፤ በግልፅነት፤ በሃቀኝነት፤ በብልሃት፤ በዲሞክራሳዊ ስልት እንዲፈቱ የታሪክ አደራ እሰነዝራለሁ። ዛሬ ለፍትህ- ርትእ፤ ለህግ የበላይነት፤ ለሰብአዊ መብቶች መከበር፤ አገርን ከአደጋ ለመከካለክ፤ ለእውነተኛ እኩልነትና ለዲሞክራሲ የሚታገሉ ኃይሎች “ኢህአፓ፤ መኤሶን፤ እሴፓ፤ ፓሪስ አንድ፤ ፓሪስ ሁለት፤ ኢዲዩ፤ እዴፓ፤ ቅንጅት፤ ህብረት፤ ታንድ፤ ኦነግ፤ መድረክ፤ አሬና፤ ግንቦት 7፤ አርበኞች፤ የአማራ ዲሞክራሳዊ ኃይሎች፤ አንድነት፤ ሰማያዊ፤ መኢአድ፤ አንድ ሁለትና ሶስት ወዘተ የሚሉበትና እርስ በርስ የሚወቃቀሱበት ዘመን አልፏል ለማለት የሚያስችሉ ብዙ ክስተቶች አሉ። የኼን ስል፤ ሁላችሁም ተዋሃዱ ማለቴ አይደለም፤ ብዙ ተሞክሮ አለተቻለም። ዲሞክራሳዊ ለውጥ ከተፈለገ ለመተባበርና ለመደጋገፍ ይቻላል። ይኼም ፈቃደኛነት ካለ ብቻ ነው። “አገር ትሸጥ ሲባል ስንት ታወጣለች” የሚል አዲስ ባህልና አዲስ ባለሃብት መደብ መፈጠሩን እያየን እርስ በርሳችን የምንናከስ ከሆነ ከትግሉ ዓለም መውጣት አለብን። አዲሱ ትውልድ ለራሱ ህይወት ሲል ይታገልበት ለማለት መድፈር አለብን። በምትካችን አዲስ ትውልድና አዲስ ዓመራር እየታገለ አመራሩን እንዲይዝ ቦታውን እንልቀቅለት። መሰናክል አንሁን። መቀበል ያለብን፤ እኛ ራሳችን ለመምከር ወይንም ለመመከር ስለማንፈልግ ሌሎች፤ በተለይ ፈረንጆች ለእኛ ተናጋሪ ሆነዋል። ለምሳሌ፤ ለኢትዮጵያ የሚለግሱ መንግሥታትና ድርጅቶች ደጋግመው የሚነግሩን በአንድ ላይ፤ በአንድ ድምፅ ለመናገርና አግባብ ያለው አማራጭ ለኢትዮጵያ ሕዝብ ለማቅረብ እስካልቻላችሁ ድረስ ማንም አያዳምጣችሁም ነው። ሃቁ፤ ያለውን መንግሥት እንደግፋለን ነው የሚሉት። የተበታተነ ተቃዋሚ ውጤቱ ይኼው ነው። አንፈረድባቸው። የሚያኮራ ታሪክ እያለን የራሳችን ህብረተሰብ ለመታገድ ካልቻልን ሌሎች ያዙብናል። እያዘዙብን ነው። ከዚህ የበለጠ የጠነከረ ምክር መጠበቅ ራስን ማታለል ነው።
ለማጠቃለ፤ በሃገር ውስጥም ሆነ ከሃገር ውጭ የሚንቀሳቀሱ ተቃዋሚዎች እንዲያስቡበት የምመኘውና አደራ የምለው የህወሓት/ኢህአዴግ መንግሥት እድሜውን ለማራዘም ለሚያደርገው ያልተቆጠበ ሴራና ሰለባ ምርኮኛ መሆን የለባችሁም/የለብነም የሚል ነው። የኢትዮጵያ ሕዝብ የሚፈልገውና የሚመኘው የእርስ በርስ መጠላለፍና ለስልጣን መሻማትን አይደለም፤ አብሮና ተባብሮ አምባገነኑን ስርዓት በዲሞክራሳዊ ስርዓት መተካትና ዘላቂነትና ፍትሃዊነት ያለው የእድገት በርና መሰረት እንዲከፈትለት ነው። ስለሆነም፤ የተቃዋሚዎች ሙሉ እምነት በኢትዮጵያ ሕዝብ አቅም ላይ ይሁን አላለሁ።

Wednesday, September 10, 2014

ከነጻነት ታጋዮች ጋር በቂሊንጦ

Sep10,2014
ለምሳሌ ያህል ጆን ኬሪ ወደ ኢትዮጵያ የመጣ ወቅት መርማሪዎቹ የሚገርም ጥያቄ አንስተውልን ነበር፡፡ ‹‹ጆን ኬሪ ጓደኛችሁ ነው?›› ብለው ጠይቀውናል፡፡ በጣም የሚገርም ነው፡፡ አንድ የአሜሪካ ከፍተኛ ባለስልጣን የእኛ ጓደኛ እንደሆነ አድርገው አቅርበውታል፡፡ ደግሞም ይህንንም ህገወጥ አድርገው ነው የሚያቀርቡት፡፡

ባለፈው ሳምንት በማህበራዊ ሚዲያው ‹‹ጥቁር ሳምንት›› (black week) በሚል ለአምስት ቀናት ዘመቻ (campaign) መካሄዱ ይታወሳል፡፡ በዚያ የጥቁር ሳምንት ዘመቻ ወቅት በመጨረሻው ቀን አስተባባሪዎቹ አዲስ አመትን በማስመልከት ‹አዲስ አመት በዓልን ከነጻነት ታጋዮች ጋር› በሚል የታሰሩ የነጻነት ታጋዮች እንዲጠየቁ ጥሪ መተላለፉ አይዘነጋም፡፡ በመሆኑም የሰማያዊ ፓርቲ ወጣቶችና የነገረ ኢትዮጵያ ዝግጅት ክፍል ጳጉሜ 5 ቀን 2006 ዓ.ም በቂሊንጦ የሚገኙ የዞን 9 የጡመራ ቡድን አባላትንና የሙስሊሙ መፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴ አባላትን በመጠየቅ የዘመቻውን አካል አከናውነዋል፡፡

ቀጥሎም የጥቂት እስረኞችን መልዕክት በአጭር በአጭሩ አቅርበናል፡፡ ጦማሪ ናትናኤል ፈለቀ ‹‹ሀገሬ ላይ እርግጠኛ የሆንሁበት ጉዳይ ቢኖር እኔን እንደ ዜጋ የሚጠብቀኝ መንግስት የሌለኝ መሆኑን ነው፡፡ ህገ-መንግስቱ አልጠበቀኝም፡፡ ህገ-መንግስቱ ጥሩ ቢሆንም አልተከበረም፡፡ ይህ ሁሌም የሚያሳዝነኝ ጉዳይ ነው፡፡ ታስሬ ባለሁባቸው ቀናት ሁሉ የታዘብኩት ነገር፣ ኢትዮጵያ ውስጥ ከፍተኛ የሆነ የባለሙያ እጥረት በሁሉም ዘርፍ መኖሩን ነው፡፡ አቅም ያላቸው ዜጎች ከስርዓቱ በመገፋታቸው ክፍተቱ እንዲሰፋ ሆኗል፡፡ በጣም ነው የሚያሳዝነው፤ የሚሰሩ ሰዎች በተገቢው ቦታ ላይ አለመኖራቸውን አይቻለሁ፡፡ የሚያሰራ ስርዓት ስለሌለ ብዙዎች ህሊናቸውን መርጠው በመራቃቸው ይመስለኛል አቅም ያላቸው ሰዎች የራቁት፡፡ ይህ ለሀገር አሳሳቢ ነው፡፡ የሚቆጨኝ ነገር በተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎችና በሌሎች ተቋማት በእንግሊዝኛ የተሰሩ የጥናት ስራዎችን በመምረጥ አሰባስበን በአማርኛ ቋንቋ በጆርናል መልክ ለመስራት አስበን ያን ሳንሰራ በመታሰራችን ነው፡፡ አሁን በተለያዩ ሁኔታዎችና ጉዳዮች ላይ ወጣቶች በማህበራዊ ሚዲያው በኩል የሚሰሩ ስራዎች እንዳሉ ስሰማ በጣም ነው ደስ ያለኝ፡፡

እኛን አስረው ሌላው ዝም እንዲል ፈልገው ኖሮ ከሆነ እንዳልተሳካላቸው የሚያሳይ ነው፡፡ ለሀገር የሚያስቡ ብዙ ወጣቶች በየጊዜው ማበባቸው አይቀሬ ነው፡፡ እየታየ ያለውም ይሄው ነው፡፡ ምንግዜም የሚበረቱ ሰዎች ለውጥ ያመጣሉ ብዬ አምናለሁ፡፡›› አይመዲን ጀበል፣ ሙስሊሙ መፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴ አባል ልትጠይቁን ስለመጣችሁ በጣም እናመሰግናለን፡፡ በተለይ ወጣቶቹ እያደረጋችሁ ያለው እንቅስቃሴ እንሰማለን፡፡ በጣም ደስ ይላል፡፡ እስካሁን በአገር ጉዳይ አስተዋጽኦ ሲያደርጉ የቆዩት የ1960ው ትውልድ አባላት ናቸው፡፡ አሁን ወጣቶች እንቅስቃሴ እያደረጉ ነው፡፡ ይህ ይበል የሚያሰኝ ነው፡፡ ነገር ግን በቂ ነው ማለት አይቻልም፡፡ ስለሆነም ተጠናክሮ መቀጠል አለበት፡፡ ያሲን ኑሩ፣ የሙስሊሙ መፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴ አባል ‹‹እስር፣ እንግልትና ሌሎችም በደሎች የአምባገነኖች እርምጃ መለያ ባህሪያት ናቸው፡፡ አምባገነኖችን አንድ የሚያደርጓቸው እነዚህ ባህሪያት ናቸው፡፡ አምባገነኖች ከታሪክ አይማሩም፡፡ የዛሬ 20 አመትም ሆነ 50 አመት ወደ ስልጣን የሚወጣ አምባገነን ይህን ነው የሚደግመው፡፡ መንግስት በኃይማኖቶች መካከል ልዩነት መፍጠር ይፈልጋል፡፡ እናንተ ክርስቲያኖች የኃይማኖት ድንበር ጥሳችሁ ከእኛ ከሙስሊም ወንድሞቻችሁ ጋር መቆማችሁን እናደንቃለን፡፡ በተለይ ሰማያዊ ፓርቲ ለሙስሊሙ ማህበረሰብ መብት በመቆም የሚያደርገውን ጥረት እናደንቃለን፡፡ እኛን ለመጠየቅ እስር ቤት ድረስ ስለመጣችሁ በጣም እናመሰግናለን፡፡ ትግሉ ከዚህም በላይ መስዋዕትነት ያስከፍላልና በርቱ፡፡›› ጦማሪ በፍቃዱ ኃይሉ ‹‹ማዕከላዊ የገባነውን የመጀመሪያ ሰሞን ለእኛ አስቸጋሪ ነበር፡፡ በማንኛውም ጊዜ እስር ሊኖር ይችላል በሚል ማዕከላዊ የሚደረጉትን ነገሮች ለማሳወቅ እንጥራለን፡፡ በተለያዩ ጊዜያት የጻፍናቸው ጽሁፎች ለዚህ ያግዛሉ ብየ አምናለሁ፡፡ በመሆኑም በእኛ ላይ ከደረሱብን ነገሮች ሌሎች ይማሩባቸዋለን ብለን እናምናለን፡፡ ይህ ሲሆን የሚታሰሩ ሰዎች የሚደርስበት ችግር አዲስ እንዳይሆን ያደርጋል፡፡ ወደ ቂሊንጦ ከመጣን በኋላ የተሻለ ነገር ቢኖርም አሁንም ድረስ መጽሃፍና ጋዜጣ አይባልንም፡፡ በጥቁሩ ሳምንት ዘመቻ ያደረጋችሁትን ነገር ሰምተናል፡፡ በጣም ደስ የሚል ስራ ሰርታችኋል፡፡ መጥታችሁ ስለጠየቃችሁን ደስ ብሎናል፡፡ እስሩ ቀጣይነት እንደሚኖረው ቢታወቅም፣ በየትኛውም ሁኔታ በርታትችሁ እንድትቀጥሉ እፈልጋለሁ፡፡ በየቀኑ ጋዜጠኞች በሚደርስባቸው ጫና አገራቸውን ጥለው መሰደዳቸውን እንሰማለን፡፡ ይህ በጣም ያሳዝናል፡፡›› ጋዜጠኛ ተስፋለም ወልደየስ ‹‹ከመታሰሬ በፊት ማዕከላዊ ውስጥ ስለሚፈጸሙ በደሎች በተለያዩ ሪፖርቶች ላይ ማንበብ ችዬ ነበር፡፡ ማዕከላዊ ከገባሁ በኋላ ያየሁት ግን ሰፊና ከጠበኩት በላይ ነው፡፡ በተለይ ትጥቅ ትግልን የመረጡ ተቃዋሚዎች አባላት ናቸው የተባሉ አሊያም በሚዲያው የማይታወቁና ጠያቂ የሌላቸው አካላት ላይ የሚደርሰው በደል ዘግናኝ ነው፡፡ በዩኒቨርሲቲ ተማሪዎችም ተመሳሳይ ድብደባ ደርሶባቸዋል፡፡ ድሮ ማዕከላዊ ውስጥ ይደረጉ እንደነበር ሰምቼ ነገር ግን ይሆናሉ ብዬ የማላምናቸውን ነገሮች ሁሉ እንደሚፈጸሙ ለመገንዘብ ችያለሁ፡፡ የማዕከላዊ መርማሪዎች አስቸጋሪዎች ናቸው፡፡ ምርመራ ማድረግ ሳይሆን ጥፋተኛ መሆናችንን እንድናምንላቸው ነው ሁሌም ተመሳሳይ ጥያቄ የሚያነሱልን፡፡ አንዳንዶቹ ጥያቄዎች በጣም የሚገርሙ ናቸው፡፡ ለምሳሌ ያህል በምርመራ ወቅት ‹‹እከሌ ጋር ሻይ እየጠጣን›› ብለን የተናገርነውን ነገር እነሱ ‹‹ስብሰባ አድርገን›› ብለው ይጽፉታል፡፡ ሻይ መጠጣት በእነሱ ስብሰባ ተብሎ ይተረጎማል፡፡ አንድ ጋዜጠኛ የሚሰራው ህጋዊ ስራ ህገወጥ ተደርጎ ይወሰዳል፡፡ ለአብነት ያህል ሰማያዊ ፓርቲ ግንቦት 25/2004 ዓ.ም ባደረገው ሰልፍ ተገኝቼ ፎቶ አንስቼ ነበር፡፡ ይህ ፎቶ ግራፍ በክስ ቀርቦብኛል፡፡ አስቡት በዚህ ሰልፍ ኢቲቪና ሌሎች የመንግስት ሚዲያዎችም ፎቶ አንስተዋል፣ ቪዲዮ ቀርጸዋል፡፡ መርማሪዎቹን ‹‹ይህ ስራዬ ነው፡፡ አያስወነጅለኝም›› ብትል አያምኑልህም፡፡ ጋዜጠኛ አስማማው ኃ/ጊዮርጊስም ሰማያዊ ፓርቲ ባዘጋጀው ሰልፍ ላይ ተገኝተሃል የሚል ጥያቄ ቀርቦለታል፡፡ በተመሳሳይ ዩጋንዳ እያለሁ ባቋቋምኩት ጋዜጣ ላይ ሙሃመድ ሰልማን ‹‹ፒያሳ ሙሃመድ ጋ ጠብቂኝ›› በሚል ከጻፈው መጽሃፍ ላይ ያሉ ጽሁፎችን ጋዜጣው ላይ አውጥቻቸው ነበር፡፡ ሆኖም ይህም በክስ ቀርቦብኛል፡፡ ‹‹መጽሃፍ ላይ ነው የወሰድኩት፡፡ መጽሃፉ ህጋዊ ሆኖ አገር ውስጥ ይሸጣል›› ብትል ማንም አይሰማህም፡፡ ፖሊስ ህዝብን ለመጠበቅ የቆመ አካል ተደርጎ ነው የሚወሰደው፡፡ ነገር ግን ከገባንበት ጊዜ ጀምሮ ገና ሳይፈረድብን ‹‹እናንተስ ለምን ሽብር ትፈጥራላችሁ?›› ያሉን ፖሊሶች አጋጥመውናል፡፡ ቀድመው ፈረዱብን ማለት ነው፡፡ በምርመራ ወቅት በጣም የሚያስገርሙ ነገሮች ተነስተዋል፡፡ ለምሳሌ ያህል ጆን ኬሪ ወደ ኢትዮጵያ የመጣ ወቅት መርማሪዎቹ የሚገርም ጥያቄ አንስተውልን ነበር፡፡ ‹‹ጆን ኬሪ ጓደኛችሁ ነው?›› ብለው ጠይቀውናል፡፡ በጣም የሚገርም ነው፡፡ አንድ የአሜሪካ ከፍተኛ ባለስልጣን የእኛ ጓደኛ እንደሆነ አድርገው አቅርበውታል፡፡ ደግሞም ይህንንም ህገወጥ አድርገው ነው የሚያቀርቡት፡፡ በሌላ በኩል አንዴ ከሰማያዊ ፓርቲ ጋር፣ ሌላ ጊዜ ከግንቦት ሰባት ሌላ ጊዜ ደግሞ ከኦነግ ጋር ግንኙነት እንዳለን ይገልጹልናል፡፡ እነዚህ ድርጅቶች በምንም መልኩ የሚገናኙ አይደሉም፡፡ በጣም የሚያሳዝነው ጋዜጠኛ የሚከሰሰው በመጻፉ አይደለም፡፡ በጋዜጠኝነት ብትከሰስ አንድ ነገር ነው፡፡ እነሱ ግን የሚያነሱብህ ክስ ሌላ ነው፡፡ ፌስቡክና ሌሎች ሚዲያዎች ላይ ንቁ ተሳታፊ የነበርን ሰዎች ያለመረጃ ስንቀመጥ ከባድ ነው፡፡ በተለይ በመጀመሪያዎቹ 75 ቀናት ነገሮች አስቸጋሪ ነበሩ፡፡ ከዛ በኋላ ግን ቢያንስ ኢቲቪን መመልከት ችለናል፡፡ ኢቲቪ በሚያቀርባቸው ጉዳዮች ላይ የየራሳችን ትርጉም እየሰጠን አገራችን ውስጥ በጥቂቱም ቢሆን ምን እየተካሄደ እንዳለ መረዳት እንችላለን፡፡ ወደ ቂሊንጦ ከመጣን በኋላ ነገሮች የተሻሉ ናቸው፡፡ ከጠያቂዎቻችን መረጃዎችን ማግኘት እንችላለን፡፡››

Tuesday, September 9, 2014

በፕሬሱ ላይ የተመዘዘው ሰይፍ

Sep 9/2014
re4መረጃ የማግኘት ነጻነት ከዋነኞቹ የዴሞክራሲ መገለጫዎች ወይም እሴቶች መካከል ይጠቀሳል፡፡ መረጃ የማግኘት ነጻነቱ የተከበረለት ህዝብ በሀገሩ የስልጣን መንበሩ ላይ የተቀመጠውን አስተዳደር (መንግስት) የመቆጣጠር ኃይሉ ከፍተኛ ነው፡፡ ሙስና፣ ብልሹ አስተዳደርና ሌሎችን ንቅዘቶች በማጋለጥ የመንግስትን ተጠያቂነት በማስፈን ሂደት ውስጥ ህዝብ ንቁ ተሳታፊ ይሆን ዘንድ መረጃ የማግኘት ነጻነቱን ሊጎናጸፍ ይገባዋል፡፡ ለዚህ ደግሞ መረጃ የሚያደርሱት ሚዲያዎች በስፋት መኖር የግድ ነው፡፡ ለዚህም ነው በዴሞክራሲያዊ አስተዳደር ውስጥ የሚዲያ (ፕሬስ) ሚና እንዲጎላ የሚደረገው፡፡
በተቃራኒው በአምባገነን ስርዓት ውስጥ ገዥዎች የሚዲያ (ፕሬስ) ነጻነትን በማፈን ህዝብ መረጃ እንዳያገኝ የተለያዩ እርምጃዎችን ሲወስዱ ይስተዋላል፡፡ አምባገነኖች ስርዓቱን የሚተቹ የፕሬስ ውጤቶችን ይዘጋሉ፣ ጋዜጠኞችን ያስራሉ፣ ያሳድዳሉ፣ አለፍ ሲልም ይገድላሉ፤ ያስገድላሉ፡፡ አምባገነኖች ለይስሙላ የሚዲያ ነጻነት መረጋገጡን የሚያሳዩ ህጎችን በማውጣት በውጭ ሆኖ ለሚመለከታቸው አካል ዴሞክራት በመምሰል በውስጥ ተግባራቸው ግን ካወጧቸው ህጎች ፍጹም ተቃራኒ በመሆን የአፈና ስራ ያከናውናሉ፡፡ የግል ፕሬሶችን በቀጥታም ሆነ በእጃዙር ጨምድዶ በመያዝ፣ ፕሬሶች ህጉን ተከትለው በፈቃዳቸው ያሻቸውን እንዳይሰሩ ያደርጋሉ፡፡ እንዲህ አይነቶቹ የአምባገነኖች ተግባራት በበርካታ ሀገራት ተመሳሳይነት ያላቸው ናቸው፡፡
ለአብነትም ለረጂም አመታት ቻይናን እየገዛ ያለው የቻይና ኮሚኒስት ፓርቲ በሀገሩ የሚንቀሳቀሱ የሚዲያ ውጤቶች ላይ ባሻው ጊዜ ሁሉ ህገ-ወጥ እርምጃዎችን በመውሰድ ይታወቃል፡፡ ይኸው የቻይና ገዥ በ2012 ብቻ ከ16 በላይ ዌብሳይቶችንና ብሎጎችን ከርችሟል፡፡ ይህ አምባገነን ስርዓት በምድረ ቻይና የመረጃ መረብ እቀባ በማድረጉ ምክንያት፣ ሀገሪቱ በተለያየ ጊዜ ከታዋቂዎቹ ዓለም አቀፍ የመረጃ ምንጮች ጎግልና ያሁ ድረ-ገጾች ጋር አተካራ ውስጥ ስትገባም ይታያል፡፡ ከዚህም በተጨማሪ ቻይና በሀገሯ የሚታተሙ ጋዜጦችንና መጽሔቶችንም በመክሰስና በመዝጋት ስሟ በአሉታ ይነሳል፡፡
ቻይና ዲንግ ዲያን የተሰኘውን ከፍተኛ ተነባቢ ሳምንታዊ ጋዜጣ እ.ኤ.አ በ2006 መዝጋቷንም እዚህ ጋር እንደምሳሌ ማንሳት ይቻላል፡፡ የቻይና ገዥዎች ጋዜጣውን የዘጉት በሀገሪቱ ያለውን የማህበራዊ ቀውስ፣ በሙስና የተጨማለቀውን አስተዳደር፣ በከተሞች ያለውን የከፋ የአየር ብክለት፣ ያልተመጣጠነ የዜጎች የደመወዝ ክፍያን፣ ልቅ የመሬት ይዞታን እና ሌሎች ችግሮቹን በተከታታይ ማጋለጡን ተከትሎ እንደነበር ይወሳል፡፡ ከምንም በላይ ደግሞ የቻይና መሪዎች ትችትን ለመቀበል አለመፍቀድ እንዲህ አይነት እርምጃዎችን እንዲወስዱ አድርጓቸዋል፡፡ ቻይናውያን ጋዜጠኞች በቻይና መንግስት የሚወሰደው እርምጃ ፍጹም ህጋዊ መሰረት የሌለው ነው ሲሉ ቢከራከሩም ሰሚ አግኝተው የሚያውቁ አይመስሉም፡፡
በበርካታ የአፍሪካ ሀገራት ያለው እውነታም ተመሳሳይነት ያለው ነው፡፡ በእነዚህ አምባገነን ስርዓቶች ገዥዎች ፕሬሱ በተቋም ደረጃ ጎልብቶ በሁለት እግሩ እንዲቆም የሚፈልጉ አይደሉም፡፡ ስለሆነም የራሳቸውን የግል ስልጣን ጠብቆ ለመቆየት ነጻ ፕሬሶችን ሰለባ ያደርጓቸዋል፡፡ በእርግጥም እንደ ኢትዮጵያ ባሉ፣ አምባገነኖች በነገሱባት ሀገር ፕሬሱና ሙያተኛው በነጻነት ተደራጅቶና ጎልብቶ ተቋም እንዲመሰርት አይፈቀድለትም፡፡ ለዚህም ይመስላል የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ባራክ ኦባማ በ2009 አፍሪካን ሲጎበኙ ጋና አክራ ላይ ‹‹አፍሪካ ጠንካራ ሰዎችን (መሪዎችን) ሳይሆን ጠንካራ ተቋማትን ነው የምትሻው›› ሲሉ ሀቁን የተናገሩት፡፡
በእርግጥም አፍሪካ ጠንካራ ተቋማት የላትም፡፡ በኢትዮጵያ ያለው የጠንካራ ተቋማት እጦት ችግር ደግሞ ከብዙ የአፍሪካ ሀገራትም የከፋ ነው፡፡ በተለይ ለሌሎች ተቋማት መጎልበት አይነተኛ ሚና የሚጫወተው የሚዲያ ተቋም እንደ ኢትዮጵያ ባሉ ሀገራት ምንም በሚባል ደረጃ ላይ የሚገኝ ነው፡፡ ለዚህ ደግሞ አምባገነኖቹ ገዥዎች ድክመቶቻቸውን በሚያጋልጥባቸው ሚዲያ ላይ የሚወስዱት ህገ-ወጥ እርምጃ አሉታዊ ሚና አለው፡፡
ፕሬሱ ላይ የተመዘዘው አዲሱ ሰይፍ
የኢህአዴግ ገዥዎች ፕሬሱን በማዳከም ሂደት ላይ ከቻይና ‹‹ምርጥ ተሞክሮ›› ሳይወስዱ አልቀሩም፡፡ ልክ እንደ ቻይና ሁሉ ጋዜጦችን፣ መጽሔቶችን፣ ዌብሳይቶችን…ይዘጋሉ፤ ይከስሳሉ፡፡ በእርግጥ በኢትዮጵያ ያለው የፕሬስ ነጻነት ህገ-መንግስታዊ እውቅና አግኝቷል፤ ዋስትና ግን የለውም፡፡ ምክንያቱም ህገ-መንግስታዊ እውቅና ያገኘው የፕሬስ ነጻነት በተለያዩ አፋኝ አዋጆች ዋስትናውን አጥቷል፡፡ የፕሬስ ተቋማትም ሆነ ሙያተኞች (ጋዜጠኞች) ህገ-መንግስቱ ላይ በሰፈረው መሰረት ለመስራት ሲንቀሳቀሱ በተለያዩ ተልካሻ ምክንያቶች በህገ-ወጥ እርምጃ በተደጋጋሚ ተደናቅፈዋል፤ እየተደናቀፉም ይገኛሉ፡፡ በዘመቻ መልክ የግሉን ፕሬስና ጋዜጠኞችን የማሳደድ ስራ ከተከናወነበት ምርጫ 97 ጀምሮ ኢህአዴግ መራሹ መንግስት ይህን ህገ-መንግስታዊ እውቅና የተቸረውን ነጻነት ሲገረስስ ታይቷል፡፡
አስገራሚው ጩኸት ደግሞ ኢህአዴግ እነዚህን የአፈና ስራዎች ሲሰራ ‹ህገ-መንግስታዊ ስርዓቱን ለመጠበቅና ለማስጠበቅ› በሚልና በልማት ሽፋን መሆኑ ነው፡፡ ህግን እየጣሱ ህግን ለማስከበር ስል ነው የሚለው የኢህአዴግ መንግስት ከሰሞኑ ደግሞ ሌላ የአፈና መስመርን ዘርግቷል፡፡ ይኸውም ‹‹ህገ-መንግስታዊ ስርዓቱን በአመፅ ለመናድ በማሴር የተጠረጠሩ የህትመት ውጤት አሳታሚዎችና ድርጅቶች›› ላይ በ‹ፍትህ ሚኒስቴር› አማካኝነት ክስ መመስረት ነው፡፡
ተጠርጣሪ ተከሳሽ አሳታሚዎችና ድርጅቶች የክስ ቻርጅ ሳይደርሳቸው እንደማነኛውም ሰው የስርዓቱ አፍ በሆነው በኢቴቪ መስማታቸውን የገለፁት የክስ ይዘት፣ ለብዙዎቻችን ግርምትን የሚያጭር ነው፡፡ የፍትህ ሚኒስቴር መግለጫ ስለጉዳዩ ሲያትት እንዲህ ይላል፤ ‹‹በየጊዜው ህገ-መንግስቱንና ህገ-መንግስታዊ ስርዓቱን በኃይል ለመናድ የአመፅ ቅስቀሳና የሀሰት ወሬዎችን በመንዛት፣ ህገ-መንግስታዊ ስርዓቱ በኃይል እንዲፈረስ እና ህዝብ በመንግስት ላይ ያለአግባብ አመኔታ እንዲያጣ የሚያደርጉ የወንጀል ተግባራትን በመፈፀም ተጠርጥረዋል፡፡››
ተጠርጣሪዎቹ ከፍተኛ ተነባቢነት እንዳላቸው የሚታወቁት አምስት መጽሔቶችና አንድ ጋዜጣ ናቸው፡፡ እነዚህም ፋክት፣ ጃኖ፣ ሎሚ፣ አዲስ ጉዳይ እና እንቁ መፅሄቶችና አፍሮ ታይምስ የሚባል ጋዜጣ አሳታሚዎችና ድርጅቶች ናቸው። ምናልባትም ኢህአዴግ ክሱን ለመመስረት መስፈርቱ ፕሬሶቹ ከፍተኛ ተነባቢነት ማግኘታቸው ሳይሆን አይቀርም፤ አለበለዚያም በምንም አይነት መልኩ ምንም ባደርግ አትተቹኝ ባይነት መሆኑ ነው፡፡ እዚህ ላይ፣ ለመሆኑ ‹‹…ህዝብ በመንግስት ላይ ያለአግባብ አመኔታ እንዲያጣ በማድረግ…›› ማለት ምን ማለት ነው? ሲጀመርስ ስርዓቱ በህዝብ ዘንድ አመኔታ አለው ወይ? ብሎ መጠየቅ ተገቢ ይሆናል፡፡
ይህን መሰሉ የመንግስት እርምጃ የግሉ ፕሬስና ጋዜጠኞቹ ላይ የሚያሳድረውን አሉታዊ ተጽዕኖ ኢህአዴግ ጠንቅቆ የሚያውቀው ይመስላል፡፡ ከአሁን በፊት እንደታየው ከሆነ መንግስት እነዚህን መሰል አሳታሚዎች ክስ ሲመሰርትባቸው ጋዜጠኞቹና አሳታሚዎቹ ወዴት ሊያመሩ እንደሚችሉ የበፊት ተሞክሮው ማህደር የሚነግረው እውነታ አለ፡፡ የኸውም ጋዜጠኞቹና አሳታሚዎቹ ክሱ በሚያሳድርባቸው ጫና ሀገር ጥለው መኮብለል፣ አልያም ስራቸውን እርግፍ አድርገው መተው እንደሆነ አይቶታል፡፡ ይህን አይነት በፍትህ ሚኒስቴር በኩል የሚወጣ ‹መረጃ› እነ አዲስ ነገርና አውራምባ ታይምስን የመሳሰሉ ጋዜጦችን ከህትመት ውጭ አድርጓቸው እንደነበርና ጋዜጠኞችንም ለስደት እንደዳረጋቸው ኢህአዴግ ጠንቅቆ የሚያውቀው ጉዳይ ነው፡፡ የዚህኛው ክስ ጉዳይም ከዚህ ጋር የተመሳሰለ ምላሽን እንዲያስገኝለት በማሰብ የመሰረተው ክስ ሊሆን ይችላል፡፡
የራሷ ሲያርባት…
አንዳንዴ ከራስ ግዙፍ ጉድፍ ይልቅ የሌላን ጥቃቅን ችግር ማየት የተለመደ ይሆናል፡፡ ለምሳሌ መንግስት በእነዚህ አምስት መጽሔቶችና አንድ ጋዜጣ ላይ የመሰረተው ክስ ተገቢነት የሚኖረው ከሆነ ኢህአዴግም በተመሳሳይ የሚከሰስባቸው አግባቦች መኖራቸውን ልብ ያለው አይመስልም፡፡ ይኸውም መንግስት በራሱ ቁጥጥር ስር በሚገኙ ሚዲያዎች ዘወትር ህዝብን ባዶ ተስፋ እየመገበ ከማወናበዱ በተጨማሪ፣ በተቃውሞው ጎራ ያሉትን ኃይላት ከህዝብ ለማራቅ የሚያደርሰው የስም ማጥፋትና ማጥላላት አልታወሰውም፡፡ መቼም በዶክሜንተሪ ፊልም ስም በተለያዩ አካላት ላይ የሚሰራው ስራ ምን ያህል ጤነኛ እንዳልሆነ ከራሱ ከኢህአዴግ ሰዎች የተሰወረ ሊሆን አይችልም፡፡
ስለሆነም መንግስት አሳታሚዎችንና ድርጅቶችን ‹‹…የሀሰት ወሬዎችን በመንዛት ህገ-መንግስታዊ ስርዓቱ በኃይል እንዲፈረስ እና ህዝብ በመንግስት ላይ ያለአግባብ አመኔታ እንዲያጣ የሚያደርጉ የወንጀል ተግባራትን በመፈፀም…›› ከጠረጠረና ከከሰሰ፤ እሱ ህጋዊና ሰላማዊ ተቃዋሚዎችን ‹‹ከአሸባሪ ቡድኖች ጋር ግንኙነት በመፍጠር›› እያለ ስማቸውን ሲያጎድፍ እንዴት አያፍርም ያስብላል፡፡
ያም ሆነ ይህ ግን መንግስት ምርጫ 2007 ዓ.ም ሳይደርስ ህዝብ መረጃ የሚያገኝባቸውን ፕሬሶች ከወዲሁ ከመስመር እንዲወጡ ማድረጉን ተያይዞታል፡፡ ቀደም ብሎ በተለያዩ ፕሬሶችና ጋዜጠኞች እንዲሁም ጦማሪያን ላይ ሲወስደው የቆየውን እርምጃ አሁንም ገፍቶበታል፤ ገናም ይቀጥልበታል፡፡ ለዚህ ማሳያ ምልክቶች የሚሆኑት ደግሞ በአሳታሚዎችና ድርጅቶቹ ላይ የሚወሰደው እርምጃ ቀጣይ መሆኑን ፍትህ ሚኒስቴር ያወጣው መግለጫ በግልጽ መናገሩ ነው፡፡ ‹‹በህገ-መንግስቱ የተበጁትን ገደቦች በማን አለበኝነት በመጣስ ስራዬ ብለው ብሄራዊ ደህንነትን አደጋ ላይ በሚጥል መልክ አመፅና ሁከትን የሚቀሰቅሱ፣ አክራሪነትንና ሽብርተኝነትን የሚያወድሱ እንዲሁም የሚያበረታቱ፣ በህዝቡ መሃከል የዘርና የሃይማኖት ጥላቻን የሚቀሰቅሱ፣ የህዝብ መሪዎችንና የተቋማትን መልካም ስምና ዝና በሀሰት የሚያጠፉና የሚወነጅሉ አንዳንድ ህትመቶች እንዳሉም ሊታወቅ ይገባል›› ሲል ማስፈራሪያ አዘል መግለጫውን አሰምቷል፡፡
‹አያ ጅቦ…›
አሁን በአምስቱ የመጽሔት እና አንድ ጋዜጣ አሳታሚዎች ላይ የተመሰረተው ክስ ብዙ የተንሸዋረሩ ምክንያቶችና ሰበቦችን ተከትሎ የመጣ ነው፡፡ ለምሳሌ ከወራት በፊት የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት ባስጠናው ‹የአዝማሚያ ጥናት›፣ መሰረት ‹‹አብዛኛዎቹ በህትመት ላይ ያሉ መጽሔቶች የጽንፈኛ የፖለቲካ ፓርቲዎች ልሳኖች ናቸው›› ሲል ድምዳሜ ላይ መድረሱ ሲነገር ቆይቷል፡፡ ይህም የኢህአዴግ መንግስት በ‹ጥናት› አረጋግጠናል በሚል ‹‹አያ ጅቦ ሳታማሃኝ ብላኝ›› ማለቱ እንደሆነና በቀጣዩ እርምጃ ሊወሰድባቸው የተመረጡ ፕሬሶች መኖራቸውን ያሳየ ነበር፡፡ በዚህም አሁን ክስ የተመሰረተባቸው የፕሬስ አሳታሚዎች በዚያ ‹ጥናት› ስማቸው በክፉ ተነስቶ ጥርስ የተነከሰባቸው እንደነበሩ ማየቱ በቂ ነው፡፡
ሌላው ማመሃኛ ወይም ማደናገሪያ ደግሞ መንግስት ‹ይኽን ክስ እንድመሰርት የተገደድኩት በህዝብ ግፊት ነው› ለማለት የሞከረበት ድንግርግሮሽ ነው፡፡ ‹‹የጥቃታቸው ሰለባ የሆነው ህዝብ በእነዚህ የህትመት ውጤቶች የህግ ከለላ በተሰጣቸው ጥቅሞቹ ላይ ያለማቋረጥ የሚደርሰውን ጥሰት ለማስቆም መንግስት ህጋዊ እርምጃ እንዲወስድ በተለያዩ መንገዶች ሲጠይቅ ቆይቷል›› ይላል መንግስት በፍትህ ሚኒስቴር በኩል በሰጠው መግለጫው፡፡
በእርግጥ የኢህአዴግ መንግስት ከረጂም ጊዜ ተሞክሮው እንደታየው አካሄዳቸው ያላማረውን (የሚተቹትን፣ ድክመቶቹን የሚያጋልጡትን) ማናቸውንም የግል ህትመት ውጤቶች በተለያዩ ዘዴዎች ከመስመር ማስወጣቱን ልብ ማለት ይቻላል፡፡ መንግስት አዲስ ዘመንን፣ ኢቴቪንና አይጋ ፎረም የመሳሰሉ ሚዲያዎችን በመጠቀም ሰፊ ማጥላላት ሲከፍትባቸው የነበሩትንና ያሉትን ፕሬሶችና ጋዜጠኞች ስንመለከት ኢህአዴግ ህግ የማይገዛው፣ በአንጻሩ ግን ህግን በማስከበር ስም ሌሎች ላይ ጥቃት እያደረሰ የሚገኝ መሆኑን እናያለን፡፡
ተቋም እንዳይኖር ማድረግ
ኢህአዴግ ፕሬሱ በተቋም ደረጃ እንዲጎለብት አይፈቅድም፡፡ ስለሆነም የግል ፕሬሱ እንደ ፕሬስም ሆነ ጋዜጠኞቹ በነጻነት ተደራጅተው ችግሮቻቸውን እንዲፈቱ አይደረግም፡፡ በዚህ አመት ላይ ራሳቸውን በማህበር ለማደራጀት የሞከሩ ጋዜጠኞች እንኳ እጣፈንታቸው ከመበታተን ያለፈ አልሆነም፡፡ ለዚህ ደግሞ የመንግስት ጫና አሉታዊ ሚና አለው፡፡ ለምሳሌ ሁለቱ አመራሮች (የማህበሩ ፕሬዚዳንት ጋዜጠኛ በትረ ያዕቆብ እና የህዝብ ግንኙነት የነበረው ጋዜጠኛ ዘሪሁን ሙሉጌታ) ስርዓቱ ባደረሰባቸው ጫና ሀገር ጥለው ተሰድደዋል፡፡
ኢህአዴግ መደራጀት መብት ነው ሲል፣ በራሱ ማዕቀፍ ጥገኛ እስከተሆነ ድረስ ማለቱ እንደሆነ በተደጋጋሚ የታየ ጉዳይ ነው፡፡ አሁን ላይ ነጻና ገለልተኛ ማህበራትን ማየት ብርቅ ሆኗል፡፡ ምክንያቱም በየማህበራቱ የኢህአዴግ እጅ በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ አለ፡፡ ስለሆነም የፕሬሱን ጉልበት ማዳከሚያ ዋና መሳሪያው ያገባኛል የሚሉ አካላት በነጻነት እንዳይደራጁ ማድረግ ነው፡፡
እስካሁን ድረስ የግል ፕሬሱ አንድ የጋራ ጠንካራ ማተሚያ ቤት እንኳ ሊኖረው አልቻለም፡፡ ፕሬሱ የአንጋፋ የመንግስት ማተሚያ ድርጅት ብርሃንና ሰላም ማተሚያ ቤት ጥገኛ ነው፡፡ ሌሎች የንግድ ማተሚያ ቤቶችም ቢሆን አንድም አቅማቸው የሚያወላዳ አይደለም፤ ሁለትም በተዘዋዋሪ መንገድ በስርዓቱ ተጽዕኖ ስር የወደቁ ናቸው፡፡
የተመዘዘውን ሰይፍ ለማጠፍ…
በአጠቃላይ አሁን ያለው የሀገራችን የፕሬስ ነጻነት እጅግ አሳሳቢና አደገኛ ሁኔታ ላይ የሚገኝ መሆኑ ግልጽ ሆኗል፡፡ እስካሁን ከተለመደው የጋዜጠኞቹ እስርና ድብደባ እንዲሁም ስደት በከፋ ሁኔታ አሁን ደግሞ አሳታሚዎች ላይ ክስ መመስረት መቻሉ መንግስት ምን ያህል የግል ፕሬሱን ማሽመድመድ እንደፈለገ ጉልህ ማሳያ ይሆናል፡፡ ስለሆነም ይህን በፕሬሱ ላይ የተጋረጠውን አደጋ ለማቃለል የተደራጀ ርብርብ በሚመለከታቸው ተቆርቋሪ አካላት ዘንድ መደረግ ይኖርበታል፡፡ መንግስት ህገ-መንግስቱን አክብሮ ፕሬሱ በነጻነት እንዲቀሳቀስ መፍቀድ ግዴታው መሆኑን በተለያዩ ስልቶች (ለምሳሌ የፕሬሱ አባላት የሚያስተባብሩት የተቃውሞ ሰላማዊ ሰልፍ ማካሄድ፣ የተዘጉ ፕሬሶችን የቀደሙ ኮፒዎች ይዞ በአደባባዮች በህብረት መታየት፣ አፍን በጥቁር ፕላስተር አሽጎ ተቃውሞን መግለጽ…) በመሳሰሉት ማስገደድም የተገባ ይሆናል፡፡
ነገረ ኢትዮጵያ

በብሶት የታፈነው ህዝብ አመፅ ከመንግስት ቁጥጥር ውጪ ሊሆን ይችላል የሚል ስጋት ወያኔ አድሮበታል።

Sep 9,2014
 2007 ለለውጥ !
በሳሞራ የኑስ እና በጌታቸው አሰፋ የሚመራ ልዩ የኮማንዶ እና የደህንነት ሃይል አዲስ አበባ ባህር ዳር እና ድሬዳዋን መቆጣጠር የሚችልበትን ስልት እየነደፈ ነው።
- በሳሞራ የኑስ የሚመራው የኮማንዶ ጦር ህገመንግስታዊ ጥያቄ ማንሳቱ ታማኝነቱ ጥርጣሪ ውስጥ ገብቷል
- መጪው ጊዜ በመላው ኢትዮጵያ የአንድነት እና የዲሞክራሲ ሃይሎች ገነው ይወጣሉ።
- ዲያስፖራው ከምንም ጊዜ በበለጠ ለወያኔ የጎን ውጋትና ራስ ምታት ሆኗል።
- ተቃዋሚ ሃይሎች በአሁን ወቅት ከባድ ጥንካሬ እና የትግል ስልት ሊኖራቸው ይገባል።ጊዜው ነው።
ምንሊክ ሳልሳዊ ፦ በብሶት የታፈነው ኢትዮጵያዊ በቀጣዮቹ ጊዜያት ከፍተኛ አመጽ ያስነሳል በሚል ስጋት ያደረበት እና አመፁ ከመንግስት ሃይሎች ቁጥትር ውጪ ይሆናል በሚል ከፍተኛ ውጥረት በስጋት የተደባለቀበት የወያኒው ጁንታ በከፍተኛ ባለስልጣናት ደረጃ ስብስባ የተቀመጠ ሲሆን ካለፉት ሳምንታት ተከታታይ ስብሰባዎች በተገኙ የውይይት ፍሬ ሃሳቦች መሰረት በሳሞራ የኑስ እና በጌታቸው አሰፋ የሚመራ ልዩ የኮማንዶ እና የደህንነት ሃይል አዲስ አበባ ባህር ዳር እና ድሬዳዋን መቆጣጠር የሚችልበትን ስልት እየነደፈ ነው።
በአዲስ አበባ የከፍተኛ ለሕወሓት ባለስልጣናት ቅርብ የሆኑት ምንጮች እንደተናገሩት የሚነደፈው ስልት የሕወሓት ባለስልጣናት እምነት ያልጣሉባቸውን የፖሊስ እና ወታደራዊ ሃይሎችን ጨምሮ ህዝቡን መቆጣጠር በሚቻልበት ሁኒታ ልላ ያተኮረ ሲሆን የፖሊስ እና ወታደሩ ክፍል በባለስልጣናት ላይ እርምጃ ይወስዳል በሚል ከፍተኛ ስጋትም እንዳደረባቸው ታውቋል ። የትግራይ ተወላጆች የሆኑትም ፊታቸውን እንዳዞሩባቸው የጠቆሙት ምንጮቹ በከፍተኛ ገንዘብ ከደቡብ ሱዳን ምስራቃዊ ክፍል የሚገኙ እና በስደተኝነት በኢትዮጵያ የኖሩ አማርኛ ቋንቋን የሚናገሩና የሚሞክሩ እንዲሁም ከኑባ ደማዚን ቅጥረኞችን በመግዛት ከቢንሻንጉል ጉምዝ በማምጣት እንዲሁም አስፈላጊ የሆኑ የቀድሞ ታጋዮችን በፖሊስ መልክ በመመልመል በጥሩ ክፍያ በአዲስ አበባ ባህር ዳር እና ድሬዳዋ ላይ ለማስፈር መታቀዱን ተጠቁሟል። በተለይ በአዲስ አበባ እና በባህር ዳር ይመደባሉ የተባሉ እናበተለያየ ጊዜ በሳሞራ የኑስ የተመረቁ እና በስሩ የሚታዘዙ ኮማንዶዎች እንዲዘጋጁ የተነገራቸው ቢሆንም ባለፈው ሳምንት በነበርቸው ስብሰባ ላይ ህገመንግስታዊ ጥያቂዎችን እንዳነሱ ከታወቀ በኋላ ታማኝነቱ ጥርጣሬ ውስጥ በመግባቱ የወያኒ ስጋቶች ሰፍተው እና ተወጥረው መታየታቸውን ምንጮቹ ተናግረዋል።
የሕዝብ አመጽ ከመንግስት ቁጥጥር ውጪ ይሆናል የሚሉት ባለስልጣናት ወታደሩ ክፍል እና የፖሊስ ሰርዊቱ ስለ ተቃዋሚዎች በጎ አመለካከት እንዳይኖረው ከፍተኛ ፕሮፓጋንዳ በየ ክፍሉ እየረጩ ሲሆን የፖለኢስ እና የጦር ሰራዊቱ ግን ጥያቂዎችን ከማንሳቱም በላይ ከካድሬዎች ጋር ፊት ለፊት እስከመሟገት መድረሱ ከቀረበልቸው ሪፖርት የተረዱት ወያኔዎች እንዲሁን ይህን ሰሞን በተለያየ መልኩ አብዮታዊ ዲሞክራሲ በልማት ስም ሽፋን በማድረግ በስልተና መልክ ሲሰጡ የገጠማችው ተቃውሞ ካድሬዎች ፖሊሰና ሰርዊቱ ሕገመንግስታዊ ጥያቄ እንዲያነሳ ማድረጉን የሚያስገነዝብ ሪፖርት በስፋት እንደቀረበ እና ይህንን ሪፖርት ተገትሎ የህዝብ ብሶት ይፈነዳል የሚል ስጋት ወያኒን እያሯሯጠው እንደሆነ ታውቋል።
ምንጮቹ አያይዘውም መጪው ጊዜ በመላው ኢትዮጵያ የአንድነት እና የዲሞክራሲ ሃይሎች ገነው ይወጣሉ። የሚልው የወያኒ ዋና የስብሰባ ነጥብ ገነው እንዳይወጡ በተለይይ የማምከን ስራ ለመጠቀም ቢያስብም ካሁን በፊት የተጠቀመብት ስልት እንዳላዋጣው እና ተቃዋሚዎች ገነው እንዳይወጡ የሚያደርግ የመጨረሻ እርምጃ ለመውስድ የሚያስችል ጥናት በአቶ በርክት ስምኦን በኩል በአስቸኳያ እንዲጠና ሲል ዲያስፖራው ከምንም ጊዜ በበለጠ ለወያኔ የጎን ውጋትና ራስ ምታት እንደሆነና የሀገር ውስጥ ተቃዋሚዎችን በማደረጀት ረገድ ትልቁን ሚና እየትጫወተ እንደሆነ መወሳቱን እና ይህንን ወያኔ መቆጣጠር እንዳቃተው እንደቀጠለ እንዳለ ተነግሯል። ምንጮቹ አያይዘውም ተቃዋሚ ሃይሎች በአሁን ወቅት ከባድ ጥንካሬ እና የትግል ስልት ሊኖራቸው ይገባል ፤ጊዜው ነው። ሲሉ መረጃውን አድርሰውናል።
በሃገር ውስጥ እና በውጪው ህገር የምንገኝ ተቃዋሚዎች ወያኒ በገባበት ስጋት እና ውጥረት ውስጥ ራሱን በራሱ እንዲቀብር ና በኢትዮጵያ ለአንዲና ለመጨረሻ ጊዜ አምባገነንነት እንዲያከትም የዜግነት ድርሻችንን በጋራ የምንወጣብት ጊዜ አሁን በመሆኑ በጋራ ልዩነቶችን በማቻቻል አንዱ አንዱን ሳይወንጅል እና ሳይፈርጅ በተባበረ ክንድ በተገኘው የትግል ስልት ልይ ሁሉ በተገኘው ድርጅት ጋር ሁሉ በመሳተፍ ለነጻነትችን የምንችለውን አስታውጾ ሁሉ እንድናደርግ ይጠበቅብናል። ነጻነት በእጃችን ነው !!

Monday, September 8, 2014

ህዝባዊ እንቢተኝነት ለነፃነት እና ለፍትህ ! (በይድነቃቸው ከበደ)

Sep8,2014
በአገራችን የፖሊቲካ ሥርዓት ሄደት ውስጥ ስልጣን በሰላማዊ መንገድ ከአንዱ ወደሌላው የተሸጋገረበት አጋጣሚ እጅግ በጣም አናሳነው፡፡ አብዛኛው የስልጣን ሽግግር ጉልበትና ብረትን መሰረት ያደረገ ነው፡፡ እንዲህ ዓይነቱ የስልጣን ሽግግር ጉልበተኞች ሁሌም አሸናፊ የሚሆኑበት ጉልበቱ አናሳ የሆነ ከስልጣን የሚርቅበት ዓይነተኛ መንገድ ነው፡፡ይህም በመሆኑ በህዝብ ፍቃድ እና ምርጫ ወይም በህዝባዊ እንቢተኝነት የመንግስት የአስተዳደር የስርዓት ለውጥ ወይም ጥገናዊ ማስተካከያ ለውጥ ከዚህ ቀደም እንዲሁም ባሁን ወቅት በአገራችን ስለ መደረጉ ምስክርነት ለመስጠት የሚያስችል አጋጣሚ ስለመኖሩ ያጠራጥራል፡፡ ለዚህም ነው ሰላማዊ ትግል በአገራችን ተስፋ አስቆራጭ እና የማይሞከር መስሎ የሚታየው፡፡
ይድነቃቸው ከበደ
ይድነቃቸው ከበደ

እርግጥነው በሰላማዊ ትግል ሂደት ውስጥ ውጣ ውረዶ የበዛ ነው፡፡ በዓለማችን ላይ የተካሄዱት ሠላማዊ ትግሎች ውጤት ያስመዘገብት መተኪያ የሌለውን የሰውልጅ ሕይወትን እስከመንጠቅ በመድረሰ ነው፡፡ ይበልጥ ደግሞ ትግሉ አስቸጋሪ የሚያስመስለው ውጤቱ የሚፈጀው ጊዜ ነው፡፡ ሠላማዊ ትግል ማለት ታጋዩ የሚታገልለትን ውጤት ሣይመለከት በትግሉ ሂደት የሚሰዋበት ነገር ነው እስከመባል ይደርሳል፡፡ እንዲህ ዓይነቱ ደረጃ ለመድረስ ከሌላ ጋር ሣይሆን ከእራስ አስተሳሰብ ጋር ይህ ቀረሽ የማይባል ትግልን ማካሄድ ይጠይቃል፡፡ ይሁን እንጂ እንዲህ-አይነቱ የአስተሳሰብ ልዕልና ለመድረስ ገፊ ምክንያቶች ካሉ፣ ምክንያቶችሁ በስትራቴጂ ከተነደፉ፣ የገዥው ስርዓት ደካማ ጎኖ በሚገባ ከታወቀና ከተለየ፣ ተምሳሌታዊ እንዲሁም ደረጃ በደረጃ የሚያድግ ሰላማዊት ግሉን የሚመራ ጠንካራ ተቋም ካለ የሰላማዊ ትግል የአስተሳሰብ ደረጃ ማሳያ የሚሆን በአመርቂ ውጤት የተደገፈ ተግባር እውን ሆኖ ማያት የማይቻልበት ምንም ምክንያት የለም ፡፡ በመሆኑም የሠላዊ ትግል መገለጫዎች ከሆኑት ውስጥህ ዝባዊ እንቢተኝነት ከአምባገነን አገዛዝ ወደ ዲሞክራሳዊ ስርዓት ለመሸጋገር አይነተኛ መንገድ ነው፡፡ ስለዚህም ህዝባዊ እንቢተኝነት ወንጀልም አጢያትም አይደለም! ህዝባዊ እንቢተኝነት በተለያዩ አገሮች በተለያየ ወቅት የተተገበር እና ውጤት የታየበት ከአምባገነናዊ ስርዓት የመላቀቂያ ቀጥተኛ መንገድ ነው ብሎ መደምደም ባይቻልም ተመራጭ የሰላማዊ ትግል ስትራቴጂ ነው፡፡ ሁላችንም ሊያስማማን የሚችለው ጨቋኝ የመንግስት ሥርዓት ባለበት ህዝባዊ እንቢተኝነት የቅንጦት ጉዳይ ሣይሆን የህልውናምርጫ ይሆናል፡፡ በዚህም ምክንያት ህዝባዊ እንቢተኝነት የትኛውም አይነት ስም ቢሰጠው ተጨቋኝ እና ጨቋኝ እስካለ ድረስ አይቀሬነቱ እርግጥ ነው፡፡

ጨቋኝነት እራስን በክፉ ልቦና እና በጥላቻ በማስገዛት ከሰውነት በታች በራስ ፍቃድ የሰው መጥፎ መሆንን ወዶ መቀበል ነው፡፡ መጮቀን ግን ማንም የትም ፈልጎ የማይቀበለው ጉልበተኛ ጉልበት በሌለው ላይ የሚያሸክመው የግፍ ክምር ነው፡፡መጨቋን በግለሰብ ደረጃ ሲሆን እዳው ገብስ ነው ተብሎ ቀሎ ባይታይም፣ በአገር እና በመንግስት ሲሆን ግን ልብ ይስብራል የማንነትም ክብር ያሳጣል፡፡ ጭቋና በሃይማኖት፣ በጎሣ፣ በአስተሳሰብ እና በፖለቲካ አመለካከት ምክንያት ሲፈፀም የጭቆና ቀንበር መሸከም ይከብዳል፡፡

በመሆኑም በስልጣን ላይ የሚገኝ የህዝብ ፍቃድ ጨርሶ ያላየው በሃይል እየገዛ የሚገኘ መንግስት፡፡በሃይማኖት፣ በጎሣ፣ በአስተሳሰብ እና በፖለቲካ አመለካከት በዜጎቹ ላይ እያደረሰ ያለው ጭቆና መጠኑ እና አይነቱ እየበዛ ከሄደ ለዜጎች እንቢተኝነት ምላሹ የሥርዓት ለውጥ ብቻ ነው፡፡ ይሁን እንጂ በጭንጋፍ አምባገነናዊ የመንግስት አስተዳደር ውስጥህ ዝባዊ እንቢተኝነት ያለው ምልክታ እንደሌሎች ፓለቲካዊ እንቅስቃሴ እና ተቃውሞ የተሸዋረር እይታ አይደለም፡፡
ይሁን እንጂ የአገራችን ወቅታዊ ሁኔታ መነሻ በማድረግ እኛ ኢትዮጵያዊያን ስለ እዝባዊ እንቢተኝነት ለመነጋገር ሳይሆን ተግባራዊ ለማድረግ በቂ ምክንያቶች አሉን፡፡ የመጀመሪያው እና ወሳኙ በህዝብ መልካም ፍቃድ እና ምርጫ ይሁንታ ባላገኘው ጉልበተኛ መንግስት አማካኝነት ነፃነት እና ፍህት በአደባባይ መነጠቃችን እና በተነጠቅነው ምትክ እየደረሰብን ያለው መንግስታዊ ጭቆና ከልክ በላይ መሆኑ ነው፡፡ የህዝብ ስልጣን ባለቤት ቀማኞች ኢትዮጵያዊ ማንነት እና ክብር በማሳጣት ኢትዮጵያንና ኢትዮጵያዊነት ንእንዲጠፋ ለማድረግ እና እነሱ እንደሚፈልጉት አይነት ሃገር ሆና ማየት የቀን የለሊት ምኞታቸው እንዲሁም ጥረታቸውም ጭምር ነው፡፡ ማንነትን ከማሰናከል እና ከማጥፋት የሚጀምረው መንግስታዊ ውንብድና እጅ ሳይሰጡ ለምን ብሎ መጠየቅ ትልቁ እና የመጀመሪያው የነፃነት ጥያቄ ነው፡፡ የጥያቂው ምላሽ ምንም ይሁን ምን በጀግኖች አባቶቻችን እና እናቶቻችን ተከብራና ታፍራ የኖረችው በፈጣሪ ቃልኪዳን እና እገዛ ሁሌም በክብር ትኖራላች፡፡

በአገራችን ሞልቶ በፈሰሰው የግፍ ፅዋ ያልተነካው ማነው ? 23 ዓመት ሙሉ ነፃነት እና ፍትህ በመነጠቅ የቁም እስረኛ በመሆኑ የተጨነቀው ስንቱ ነው? ጭንቀቱ አላስችል ሲለው አገር ጥሎ በሰው አገር የሚኳትነው ምን-ያህል ነው? በአገዛዙ ስርዓት ምክንያት የስንት ሰው ህይወት ተሰዋ ? የታሰረው እና የቆሰለው ቤት ይቁጠረው፡፡ የኑሮ ውድነቱ ትከሻን ከማስጎበጥ አልፍ የስንቱን ህይወት ቀጠፈ? እኛ ኢትዮጵያዊያን ደሰታችን እና ሀዘናችን ከፈጣሪ ጋር የተቆራኘ ነው፤ ይህን እንጂ የአገዛዙ ሥርዓት የለየለት አምባገነን መሆኑ የሚያመላክተው በሃይማኖት ላይ የሚያደርገው ቀጥተኛ ጣልቃ ገብነት እና ያስከተለው ቀውስ ጭምር ነው፡፡ ለሃይማኖት እና ለታሪክ ግድ የማይሰጠው ገዥው መንግስት በዜጎች መካከል ማህበራዊ ቀውስ በመፍጠር ያለተረጋጋ ማህበረሰብ እንዲኖር ያልተደረገ ነገር ምን አለ ? መሬት ቆርሶ መሸጥ የዕለት ገቢ ያደረገው መንግሰት በተለያየ የአገራችን ክፍል ምትክ መሬት ወይም ተገቢውን ካሳ ሳይሰጣቸው የተፈናቀሉ እና ለከፋ ችግር የተጋለጡ ቤት ይቁጠራቸው፡፡ በመሆኑም እነዚህ እና መሰል በደሎች በመንግሰት አማካኝነት ያልተፈፀመበት ማነው ?፡፡ ከተገፉ እና ከተበደሉ ጎን ላለመቆም መወሰን ምንም አልተነካውም የሚለው ነገ ላለመነካቱ ምን ማረጋገጫ አለው ፡፡እርግጥነው የስርዓቱ ቀጥተኛ ተጠቃሚ የሆኑ ጥቂት ግለሰቦች እና ሆድ አደሮች ለህዝባዊ ህንቢተኝነት የወንዝ ዳር ሙጃ ሣራ መሆናቸው አይቀርም ፡፡

በመሆኑም ጥገናዊ ለውጥ የሚያመጣ የመንግሰት አስተዳደር ሳይሆን የስርአት ለውጥ ለመፍጠር የሚያስችል ሁሉን አቀፍህ ዝባዊ እንቢተኝነት በሠላማዊ መንገድ ተግባራዊ ማድረግ እንደ-ዜጋ የመኖር ወይም ያለመኖር ምርጫም ጭምር ነው፡፡ አብዛኛው ኢትዮጵያዊ ከግዴለሽነት እና ምን-ያገባኛል ስሜት ተላቆ በገዥው መንግሰት ላይ “ስልጣን የህዝብ ነው!” ከማለት ባለፍ የስልጣን ባለቤት ለመሆን የሚያስችል ቁጭት አዘል ዝግጅት ስለመኖሩ ብዙ አመላካች ነገሮች አሉ፡፡ ስለሆነም ዓለም አቀፍ ተሞክሮ ያለው የአገራችን ተጨባጭ ሁኔታ ግምት ውስጥ በማስገባት ፣ እጅግ በጣም ሰላማዊ የሆነ መሪ እና ተመሪ ያለው ጠንካራ ስትራቴጂ በመንደፍ ህዝባዊ ህንቢተኝነት ለነፃነት እና ለፍትህ ተግባራዊ ማድረግ ይቻላል፡፡

እንዲህ አይነቱ ህዝባዊ እንቢተኝነት በሁለት መንገድ የሚፈፀም ነው፡፡ የመጀመሪያው ዜጎች በራሳቻው ፍቃድ ተነሳሽነት በሚፈጥሩት ተቋማት የሚመራ ሲሆን፡፡ በአገራችን ተጨባጭ ሁኔታ ነፃ ማህበራዊ ተቋም ስለመኖሩ እና ይህን ስለማስፈፀማቸው እርግጠኛ ለመሆን አይቻልም፡፡ ሌላው ደግሞ በፖለቲካ ፓርቲዎች አማካኝነት ነው፡፡ ይህ ደግሞ አሁን ባለው የተቃዋሚ ፓርቲዎች ከተለመደው እና ውጤቱ በግልፅ ካልታወቀበትና ካልተመዘነበት የቅርብ ጊዜ የተቃውሞ ሰልፍ ልምድ ጋር ሲነፃፀር አዲስ ምዕራፍ ነው፡፡ ሆኖም ግን ለ8 ዓመታት የተዘጋው የተቃውሞ ሰልፍ በሰማያዊ ፓርቲ ፈር-ቀዳጅነት አደባባይ ወጥተን ድምፃችን ለማሰማት መቻላችን ለፓርቲው አድናቆት የሚያሰጥ ነው፡፡ በተጨማሪ የዚህ ፁሁፍ አቅራቢ በመኢአድ እና በአንድነት እንዲሁም በመድረክ አማካኝነት የተካሄዱትን የተለያዩ የተቃውሞ ሰልፎች ያለው አድናቆት እንደተጠበቀ ነው፡፡ ስለሆነም አገር አቀፍ ህዝባዊ እንቢተኝነት በሰላማዊ መንገድ ተግባሪዊ እንዲሆን የፓርቲዎች ፊት አውራሪነት እና አዝማችነት የግድ አስፈላጊ ነው፡፡ በህዝብ የተጣለበትን ሃላፊነት የሚወጣ እና የተለያ የሰላማዊ የትግል ዜዴዎችን ተግባሪዊ የሚያደርግ ጠንካራ የተቃዋሚ ፓርቲ የምናይበት ወቅት እርቁ እንደማይሆን ተስፋ አደርጋለው ፡፡
ኢትዮጵያ በክብር ለዘላለም ትኑር !!!

Sunday, September 7, 2014

የለውጡ አካል መሆኛው ግዜው አሁን ነው

September 7/2014
እኔም አንዳርጋቸው ነኝ የሚል ድምፅ ከአጥናፍ እስከ አጥናፍ እያሰተጋባ ነው። ይሄን ድምፅ የሚያቆመው አንዳችም ምድራዊ ኃይል አልተገኘም። ኢትዮጵያዊ ባለበት ሥፍራ ሁሉ ይሄ ድምፅ ከፍ ብሎ እየተሰማ ነው። ይህንንም ተከትሎ “ላንቺ ነው ኢትዮጵያ፤ ላንቺ ነው ኢትዮጵያ” የሚለው መዝሙር በኢትዮጵያ ተራሮች እናት ላይ እየተዘመረ ነው። ፍትህ ተዋርዳለች፤እኩልነት ጠፍቷል፤ ነፃነት የለም ያሉ ምርጥ ኢትዮጵያዊያን ሳያቅማሙ አያቶቻቸው በተመላለሱበት ተራሮች ላይ ተሠማርተዋል። ሞትንም ንቀው ጋሻ አንስተዋል፤ ሰይፋቸውንም መዘዋል። ለፍትህ፤ ለዕኩልነት እና ለነፃነት የተመዘዘው ሰይፍ ከእንግዲህ ወደ ሰገባው እንደማይመለስ ህወሃቶች እንዲያውቁት እንፈልጋለን።
በኢትዮጵያችን ፍትህ ከጠፋ ብዙ ዘመን ሁኖታል። ከሁሉም ዘመን የህወሃቶች ዘመን ግን የተለየ ነው። ህወሃቶች ህግን ዜጎችን የማጥቂያ መሣሪያ አድርገው መጠቀማቸው ከሌሎች እንዲለዩ ያደርጋቸዋል። እነዚህ ቡድኖች ሥፍር ቁጥር የሌላቸው ቂም መወጣጪያ ህጎችን አውጥተዋል። እንዲህ በማድርጋቸውም ሠላም እናገኛለን ብለው ያስባሉ። የህወሃቶች አስተሳሰብ ደካማና እርባና ቢስ መሆኑን ከሚያሳዩ ተግባሮቻቸው መካከል አንዱ ይሄው በፍትህ ሳይሆን በህግ ብዛት ሠላም እናገኛለን ብለው ተስፋ ማድረጋቸው ነው። የህግ ብዛት ሠላምን አያስገኝም፤ ፍትህንም ማስፈን አይችልም። እንዲያውም ህግ በበዛ ቁጥር ፍትህ እየጎደለች እንደምትሄድ የህወሃቶች ድርጊት ደህና ምስክር ነው። እነርሱ ዜጎችን ለመበቀያ ብለው የሚያወጧቸው ጥቃቅን ህጎች እነርሱ “ህገ መንግስት” ብለው የሚጠሩትን የሚንዱ እና ፍትህን ዋጋ የሚያሳጡ ሁነው እያየናቸው ነው። የፀረ ሽብር ህጉ በህገ መንግስቱ የተቀመጠውን የዜጎችን የመናገር የመደራጀትና በሰላማዊ መንገድ የመንግስትን እኩይ ተግባራት የመቃወምን መብት የገፈፈ ነው። የፀረ ሙስና ህጉም ቢሆን እንዲሁ ነው። በፀረ ሙስና ህጉ የሚጠየቁ በህወሃት የተጠሉ ብቻ ስለመሆናቸው በሙስና የተጨማለቁት የህወሃት ሹማምንት ህያው ምስክሮች ናቸው። በህወሃቶች ህግ ሁሉም ዜጎች እኩል አይደሉም። ህወሃቶች ከሌሎች ይበልጣሉ። የህወሃቶች ምኞት እነርሱ ከህግ በላይ፤ ሌላው ህዝብ ከህግ በታች ሁነው ህወሃትን ተሸክመው እንዲኖሩ ነው። እንዲህ ዓይነቱን ኢ-ፍትሃዊነት መታገል ግዜው የሚጠይቀው ታሪካዊ ግዴታ ነው። መሪያችን አንዳርጋቸው ፅጌ የተነሳውም ህወሃቶች መሣቂያ መሳለቂያ ያደረጓትን ፍትህ ወደ ሚገባት ክብር ለመመለስ ነው። በአገራችን የህግ የበላይነት ሠፍኖ ጥቂቱ ብዙሃኑን ሳይጫን፤ ማንም ማንንም ሳይሸከም ሁሉም በህግ እና በፍትህ እኩል ሁኖ የሚኖሩባት ሠላም የበዛላት ሥፍራ እንድትሆን የመሪያችን የአንዳርጋቸው ምኞት ነው። ይሄን ምኞት ሚሊየኖች አንግበው ተነስተዋል።
ህወሃቶች አገራችንን አደጋ ላይ ከጣሉባቸው አንኳር ድርጊቶቻቸው መካከል አንዱ በዜጎች መካከል እየፈጠሩ ያሉት ግልፅ ልዩነት ነው። ህወሃቶች ከሌሎች ኢትዮጵያውያን ጋር እኩል ነን የሚል እምነት የላቸውም። የህወሃቶች ዕምነት እነርሱ ከሌላው ኢትዮጵያዊ ከፍ እንደሚሉና በዚያች አገር ውስጥ የተለየ መብት እንዳላቸው ነው። ለመገድልም፤ ለመዝረፍም፤ዜጎችን ለማሳቃየት እና ከአገር ለማባረርም መብቱ የእኛ ነው የሚል ጅላጅል እምነት አላቸው። ይህ የሞኝ እምነታቸው በዜጎች መካከል ቂመ በቀል ሊያተርፍ የሚችል አድሎዎ እንዲፈጥሩ አድርጓቸዋል። አድሎአቸውንም ይበልጥ የከፋ የሚያደርገው ህወሃቶች ሁሉን አድራጊ እኛ ነን ብለው ሲያበቁ የህወሃት የበላይነት የለም ብላችሁ እምኑ ብለው ዜጎችን መጫናቸው ነው። ይህ ድርጊታቸው ብዙ ዜጎችን አስቆጥቷል። ህወሃቶች ግን የዜጎችን ቁጣ የሚያይ ዓይን፤ የሚያስተውል ሂሊና ርቋቸዋል። በኢትዮጵያችን በህወሃቶች አማካኝነት እየተፈጠረ ያለው ግልፅ አድልዖ ለአገራችን ህልውና ከፍተኛ አደጋ ነው። በህዝብ መካከል አድልዖ መፈፀም እና ቂምና በቀልን መትከል የህወሃቶች የመኖሪያ ድንኳናቸው ሁኗል። መከፋፈልና አድልዖ ባለበት አገር ውስጥ ሠላም ይኖራል ማለት አይቻልም። አድልዎ የታላላቅ ግጭቶችና ለውጦች ጥሩ ምክንያት መሆኑን መርሳት አይገባንም።መሪያችን አንዳርጋቸውም ሆነ ግንቦት ሰባት ንቅናቄ የተነሳው እንዲህ በዜጎች መካከል የሚፈፀመውን አድልዖ ለማስቆምና ዜጎች በገዛ አገራቸው በእኩልነት የሚኖሩበትን ሁኔታ ለመፍጠር ነው። ይህ የእኩልነት ጥያቄ የግንቦት ሰባት ንቅናቄ ብቻ ሳይሆን የሁሉም ዜጎች ጥያቄ ሁኖ ከኢትዮጵያ እስከ ውጪ አገራት ድረስ እያሰተጋባ ነው።
ሌላው ህወሃቶች አገሪቷን እያዋረዱ ካሉበት ነገሮች መካከል አንዱ የነፃነት ጥያቄ ነው። እኛ ከመጣን በኋላ በኢትዮጵያ ነፃነት ሰፈነ እያሉ ያላዝናሉ። ህወሃቶች ከነፃነት ጋር ተያይዞ ሊመጣ የሚችለውን ኃላፊነት ለመረዳትና ለመሸከም ከፍተኛ የሆነ የአስተሳሰብ ድክመት አለባቸው። ከነፃነት ጋር የሚመጣውን ኃላፊነት ለመሸከም ብቻ ሳይሆን የነፃነትንም ትርጉም ለመረዳት ከፍተኛ የሆነ የእውቀት ማነስ ችግር ያለባቸው መሆኑም ይታወቃል። ራሳቸውን ከታሰሩበት የድንቁርና ሰንሰለት ማስፈታት ሳይችሉ ከሰሞኑ የከፍተኛ ተቋም ተማሪዎችን ሰብስብው የእኛን አብዮታዊ ዲሞክራሲ ካልስተማርናችሁ ትምህርታችሁን አትቀጥሉም ሲሉ ማሰብ ማቆማቸውን ቁልጭ አድርጎ የሚያሳየን አንድ እውነት ሁኖ አግኝተነዋል። ማሰብ የሚችሉ ቢሆኑማ ኑሮ ነፃነት ማለት ‘የእናንተን አብዮታዊ ዲሞክራሲ መስማት አልፈልግም ማለትን’ እንደሚጨምር ያውቁ ነበር። ነፃነትን የማያውቁት ነፃ አውጪዎች ነን ባዮቹ ህወሃቶች ግን ተማሪው መስማት የማይፈልገውን አብዮታዊ ዲሞክራሲ አስገድደው እየጋቱት ይገኛሉ። ለሚቀጥለውም አርባና ሃምሳ ዓመት ስልጣኑን ለማንም አሳልፈን የምንሰጥ አይደለንም ሲሉ በድፍረት ተናግረዋል። የዚህ ሁሉ ድፍረት ምንጭ ህወሃቶችን የተፀናወታቸው እኔ ብቻ ከሚል ከንቱ አስተሳሰብ የመነጨው ስግብግብነታቸው መሆኑን መገነዘብ ያስፈልጋል።
እንግዲህ ፍትህ መቀለጃ ሁናለች፤ እኩልነት ተጓድሏል፤ ነፃነት ጠፍቷል የሚሉ ዜጎች ከሁሉም አቅጣጫዎች ድምፃቸውን እያሰሙ ነው። የህዝቡ ብሶትም ፅዋውን ሞልቶ እየፈሰሰ ነው፤ ቁጭቱም ከመቸውም ግዜ በላይ ግሏል። ከሰሞኑ በሃያ ስድስት ታላላቅ ከተሞች የተደረጉት ውይይቶችም ያሳዩን አንድ እውነት ህዝቡ ይበልጥ መቆጣቱን ነው። ቁጣውም የተገለፀበት መንገድም ሌላው አስደማሚ ጉዳይ ነው።“እኛም አንዳርጋቸው ነን” ሲሉ ድምፃቸውን ከፍ አድርገው አሰምተዋል። ከእንግዲህ ፍርሃት ሆይ መወጊያህ ወዴት አለ የሚሉ ኢትዮጵያዊያን ድምፃቸውን ከፍ አድርገው ላንቺ ነው ኢትዮጵያ፤ ላንቺ ነው ኢትዮጵያ እያሉ ዘምረዋል። ይሄ ለፍትህ፤ ለእኩልነትና ለነፃነት ለሚታገሉ ታጋዮች ተስፋ ሰጪ ምልክት ነው።
ህወሃቶች በሠላማዊ መንገድ ለሚደረገው ትግል መንገዱን ሲያደናቅፉ እሰከ ዛሬ ዘልቀዋል። አሁን ጭራሹን ገና ሃምሳ የመከራ ዘመን እየተመኙልን ነው። ይሄ ምኞታቸው ቅዥት ሁኖ እንደሚቀር እኛ ልናስታውሳቸው እንፈልጋለን። በዚያች አገር ለውጥ መምጣት አለበት። ለውጡ በዛፍ ላይ የተንጠለጠለ የጎመራ ፓፓያ አይደለም በራሱ ወደ ምድር የሚወርድ፤እኛ ራሳችን ልናወርደው የሚገባን እንጂ። ተፈላጊውን ለውጥ ለማምጣት እያንዳንዱ ዜጋ በቻለው መሣሪያና ባለው አቅም ሁሉ ለልውጡ ሳያቅማማ መታገል ይኖርበታል። ህወሃቶች ነፃነታችንን አይሰጡንም፤ ፍትህም ከእነርሱ እጅ የምትገኝ አይደለችም፤ እኩልነትንም የሚያውቁ አይደሉም እነዚህ ወርቃማ እሴቶች በትግል የሚገኙ ናቸው። እነዚህን ክቡር ስጦታዎች አስነጥቆ ዝም ያለ ወደ መታረጃው ሥፍራ የሚነዳ ከብትን ይመስላል። ብዙ ኢትዮጵያዊያን እንዲህ መሆንን የሚምርጡ አይደሉም። በየከተሞቹ በተደረገው ውይይት ከተገነዘብናቸው እውነቶች መካከል አንዱ ዜጎች ለፍትህ፤ለእኩልነት እና ለነፃነት አስፈላጊውን መሥዋዕትነት ለመክፈል ዝግጁ መሆናቸውን ነው።
በህወሃት ዘመነ መንግስት የመከራ እንባችሁን በመዳፋችሁ የምታፍሱ፤ ህወሃት በአገሪቷ ላይ እያደረሰ ያለው የጥፋት ድርጊት የሚያነገበግባችሁ እና ምን እናድርግ መሪ አጣን የምትሉ ስሙን! መሪ ካጣችሁ እንዲህ አድርጉ “ራሳችሁ ተነሱና መሪ ሁኑ!”። ከምታምኗቸው ጥቂት ወዳጆቻችሁ ጋር ሁናችሁ ተደራጁ፤ አንዳችሁ አንዳችሁን አድምጡ፤ ጥሩ ተመሪ መሆን ከቻላችሁ ጥሩ መሪ ወጥቷችኋል ማለት ነው። የአገራችን ፈርጀ ብዙ ችግር በጥቂት ዜጎች ብቻ የሚቀረፍ አይደለም።የሁሉንም ቁርጠኛ ዜጎች ትግል የሚጠይቅ ነውና በየመንደራችሁ ተደራጅታችሁ የጎበዝ አለቃ መርጣችሁ ዘረኞችን፤ ዘራፊዎችንና አድሎዋዊ ሥርዓት የዘረጉባችሁን ታገሏቸው። እንዲህ ካደረጋችሁ ከእኛ ጋር ለመገናኘት መንገዱ ቀላል ይሆናል።
የግንቦት ሰባት ንቅናቄ ጥያቄ አጭርና ግልፅ ነው። ፍትህ፤ ነፃነትና እኩልነት በኢትዮጵያችን ይሰፈን ነው። የህወሃትን ዘረኝነትና አምባገነንነት የሚፀየፍ ሁሉ የንቅናቄያችን ደጋፊ ነው። እነዚህን ነገሮች በኢትዮጵያ ለማስፈን በሚችለው ሁሉ ርምጃ መውሰድ የጀመረ የንቅናቄያችን አካል ነው። እኛም ከጎኑ አለን። እንዲህ በማድረግ የማይቀረውን ለውጥ አናመጣለን። ለውጡ ይመጣል አንድም የተፈጥሮ ህግ ስለሆነ፤ አንድም ደግሞ እኛ ሳናቅማማ የፈለግነውን ለውጥ ለማምጣት ስለተነሳን።
ህወሃቶች መስልጠን የማይችሉ፤ ከአዲስ አስተሳሰብ ጋር ራሳቸውን ማዋሃድ የማይሆንላቸው ፍፁም ግትሮች መሆናቸውን በተዳዳጋሚ አይተናል። ይሄን ግትርነታቸውን እንደ ጀግንነት ይቆጥሩታል። በአገራችን ደህና አባባል አለች እንዲህ የምትል “ሞኝ አሸነፈ ምን ብሎ? እምቢ ብሎ” ይባላል። ህወሃቶችን በዚህ አባባል መግለፅ ሞኝ ያስመስላቸዋል እነርሱ ግን ሞኞች አይደሉም ጨካኞች እንጂ። የጭካኔያቸው ምንጭ ደግሞ በራሳቸው የማይተማመኑ ደካሞች መሆናቸው ነው። እነርሱ ከዛሬ ሠላሳ ዓመት በፊት በመስታወት ውስጥ ያዩትን የራሳቸውን ምሥል ዛሬም መልሰው ያንኑ ምሥል እያዩት ነው። ከሠላሳ ዓመት በኋላም ሊቀየሩ አልቻሉም። ከዚያ ካረጀው ምሥላቸው ላይ ዓይናቸውን ነቅለው ግዜው እና ሁኔታው የፈጠረውን በአካባቢያቸው ያለውን አዲስ ምሥል ለማየት አቅቷቸውል። ስለዚህ ህወሃቶችን ማስወገድ ግድ ነውና ሁሉም በያለበት ለሚመጣው ለውጥ ራሱን ያዘጋጅ፤ የለውጡም አካል ይሁን እንላለን።
ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ !