Wednesday, August 27, 2014

We struggle in unison to end dictatorship in Ethiopia

August 26, 2014
A Joint Statement (The Ethiopian People Patriotic Front, Ginbot 7 Movement for Justice, Freedom and Democracy, Amhara Democratic Forces Movement)
Many political parties and organizations lacking unity and common goal have fought hard for decades to end dictatorship in Ethiopia. The ever increasing number of the political organizations and their failure to work together has enabled longevity for the minority dictatorial regime that would and should have been in the dustbin of history long time ago.Inside EPPF - Ethiopian People's Patriotic Front Training Camp, part1
We believe it’s about time that all concerned individuals and groups that understand and see the deep hole that our nation finds itself, must pause and reflect on the backbreaking path we traveled and the critical juncture we have reached.
For years, the Ethiopian people have been demanding for a united political front, and we the various political forces that struggle to make the people the only source of power in Ethiopia have envisioned that a united political force and collective struggle is not an option, but an indispensible necessity.
Today, the call of the Ethiopian people for a united political front has been answered with the first and initial step. Our long term vision and desire to create a broader united front that ultimately leads to a strong united Ethiopia has materialized with this initial step. With this initial step, the following three political entities have completed the preconditions to merge their organizations, and have vowed to pay all the necessary sacrifices that the struggle requires to make the Ethiopian people masters of their destiny.
We the three organizations that have reached an agreement towards the merger are:
1. The Ethiopian People Patriotic Front
2. Ginbot 7, Movement for Justice, Freedom and Democracy
3. Amhara Democratic Forces Movement
We want to let the Ethiopian people and friends of Ethiopia know that we the undersigned organizations have agreed to work together in all aspects and facets of the struggle during the transition period.
Unity is power!!!
The Ethiopian People Patriotic Front, Ginbot 7 Movement for Justice, Freedom and Democracy, Amhara Democratic Forces Movement

Tuesday, August 26, 2014

በትግራዮች እና በአፋሮች መካከል በተነሳ የድንበር ይገባኛል ግጭት የአንድ ሰው ሕይወት ማለፉ ተዘገበ

August26/2014
August26/2014
(ዘ-ሐበሻ) አሁን ለዘ-ሐበሻ የደረሰው መረጃ እንደሚያመለክተው በአፋር ክልል በሰሜን ዞን በኮናባ ወረዳ ነዋሪዎች እና በትግራይ ክልል የአፅቢ ወንባርታ ወረዳ ነዋሪዎች መካከል ግጭት የተቀሰቀሰ ሲሆን እስካሁን የአንድ ሰው ሕይወት ማለፉ ተዘግቧል።

አኩ ኢቢን ከአፋር ለዘ-ሐበሻ ባደረሰው መረጃ በኮናባ ወረዳ የዋህደስ ቀበለ አፋሮችና በአፅቢ ወረዳ ኦሳት ቁሼት ከ1 አመት በፊት የድምበር ይገባኛል ያለመገግባባት የነበረ መሆኑ በተደጋጋሚ የተዘገበ ሲሆን ዛሬ ከሳዓት በኋላ በኢትዮጵያ ሰዓት አቆጣጠር 8:30 ጀምሮ ይህ ዜና እስከተጠናከረበት ጊዜ ድረስ ግጭት ላይ ይገኛሉ።

በድንበር ይገባኛል ግጭት የተነሳ በተለያዩ የኢትዮጵያ ከተሞች ከዚህ ቀደም ንጹሃን ዜጎች ሕይወት ማለፉ የሚታወስ ሲሆን አሁንም በአፋሮች እና በትግራዮች መካከል የተነሳው ግጭት ሥርዓቱ የፈጠረው የዘረኝነት አስተዳደር ውጤት ነው የሚሉ አስተያየት ሰጪዎች አሉ።

ለዘ-ሐበሻ መረጃውን ያደረሰው አኩ ኢቢን ኮናባ መተው እየተዋጉ ያሉት የወታደር ልብስ የለበሱ የሚሊሻ አባላት ናቸው ሲል እስካሁን በዚህ ግጭት 1 ሰው ሲሞት 2 ሰዎች ደግሞ ቆስለዋል ብሏል። በሞተው ሰው ጉዳይ ዘ-ሐበሻ ከመንግስት ወገኖች ለማጣራት ያደረገችው ጥረት ባይሳካም የድንበር ግጭቱን ለማብረድ ከመንግስት በኩል እየተደረገ ያለው ዝግመተኛ ሥራ የአካባቢውን ነዋሪዎች እንዳስቆጣ ምንጮች ገልጸውልናል።

በዚህ ግጭት ዙሪያ ተጨማሪ መረጃዎች እንደደረሱን እንመለሳለን።
                                    (የሕወሓት መንግስት ኢትዮጵያን የሚያስ ተዳድርበት ካርታ)

12ኛው ጋዜጠኛ ዳዊት ሰለሞንም ተሰደደ

August 26, 2014

(ኢ.ኤም.ኤፍ) ሰሞኑን በጋዜጠኞች ላይ እየደረሰ ያለውን ማዋከብ ተከትሎ በርካታ ጋዜጠኞች ከአገር መውጣታቸው ይታወሳል። በተለይም ገዢው አካል በአምስት የፕሬስ ውጤቶች፣ ሎሚ፣ አፍሮ ታይምስ፣ እንቁ፣ አዲስ ጉዳይና ጃኖ ፕሬሶች ላይ ግልጽ የሆነ ህገ ወጥ ጥቃት እያደረሰባቸው በመሆኑ አስራ አንድ ጋዜጠኞች አገር ለቀው ለመሰደድ በቅተዋል። አሁን ደግሞ ሌላኛው እና 12ኛው ጋዜጠኛ ዳዊት ሰለሞን ከአገር ለመውጣት መገደዱን በተለይ ለኢ.ኤም.ኤፍ ከላከው መረጃ ለማወቅ ችለናል።

ጋዜጠኛ ዳዊት ሰለሞን በተለይ በአዲስ አበባ እና ከአዲስ አበባ ይደረጉ የነበሩ ሰላማዊ ሰልፎችን በመከታተል የጽሁፍ እና የፎቶ ዘገባ በማቅረብ የሚታወቅ ጋዜጠኛ ነው። ጋዜጠኛ ዳዊት ሰለሞን ባለፈው እሁድ አትላንታ ከሚገኘው ማህደረ አንድነት ጋር ባደረገው ቃለ ምልልስ “በቀጣይ እርምጃ ሊወስዱብኝ እንደሚችሉ መረጃ ስለደረሰኝ ከአገር ለመውጣት ተገድጃለሁ።” በማለት ገልጿል። (ሙሉውን ቃለ ምልልስ እንደደረሰን እናቀርባለን)

በአሁኑ ወቅት ኢትዮጵያ ጋዜጠኞችን በማዋከብ፣ በማሰር እና ለስደት በመዳረግ ከአለም አስር መጥፎ አገሮች ተርታ የተመደበች መሆኗን የሲ.ፒ.ጄ እና ሌሎች የፕሬስ ተቋማት ደጋግመው ይገልጻሉ።

ጋዜጠኛ ዳዊት ሰለሞንን በቀጥታ በማግኘት መርዳት ለምትፈልጉ የኢሜይል አድራሻው dawit341@gmail.com መሆኑን በዚህ አጋጣሚ እናሳውቃለን።

አሰደንጋጭ ዜና ኢቦላ መሰል በሽታ በኢትዮጵያ አሶሳ መከሰቱን አዲስ አድማስ የአካባቢውን የጤና ቢሮ ሃላፊዎች ጥቀሷ ዘገበ ።

August26/2014
አንድ ሰው በበሽታው ሞቷል
የክልሉ ጤና ቢሮ በሽታው ኢቦላ አይደለም ብሏል
በሽተኞች ላይ ደም ማስመለስና ማስቀመጥ ተስተውሏል
በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የምግብ መበከል ሊሆን ይችላል ተብሎ የተጠረጠረ ምንነቱ ያልታወቀ በሽታ በሁለት ሰዎች ላይ መከሰቱንና አንደኛው መሞቱን የክልሉ ጤና ቢሮ ኃላፊ አቶ ሃብታሙ ታዬ ለአዲስ አድማስ የገለፁ ሲሆን የኢቦላ በሽታ በክልሉ በየትኛውም አካባቢ አልተከሰተም ብለዋል፡፡ 
የተለያዩ ማህበራዊ ሚዲያዎች በክልሉ በሚገኘው ባምባሲ የስደተኞች ጣቢያ በሽታው ተከስቷል ሲሉ ያሰራጩት መረጃ የተሳሳተ መሆኑን የጠቆሙት የቢሮ ኃላፊው፤ ለጊዜው በትክክል ምንነቱ ያልታወቀው በሽታ የተከሰተው ከስደተኞች ጋር ምንም አይነት ንክኪ በሌለው የአሶሳ ከተማ መንደር 47 በሚባል አካባቢ መሆኑን ገልፀዋል፡፡ 
በህክምና ባለሙያዎች የምግብ መበከል ሊሆን ይችላል በተባለው በዚህ በሽታ የተያዙት ሁለት ግለሰቦች ላይ የታየው ምልክት ደም ማስመለስና ማስቀመጥ መሆኑን የጠቆሙት አቶ ሃብታሙ፤ በሽተኞቹ ለብቻ ተገልለው በጥንቃቄ እንዲታከሙ ተደርጓል፣ የአንደኛውን ህይወት ማትረፍ ባይቻልም ሌላኛው ቤተሰቦቻቸው ጋር ሆነው ህክምናቸውን እየተከታተሉ ነው ብለዋል፡፡ 
የኢቦላ በሽታ ምልክቶች ከሌሎች በሽታዎች ጋርም ሊመሳሰል ይችላል ያሉት የቢሮ ኃላፊው፤ ነገር ግን በህክምና ባለሙያዎች በሽታው ኢቦላ አለመሆኑ ተረጋግጧል፤ በሽታው የምግብ መበከል ሳይሆን እንዳልቀረ ተጠርጥሯል ብሏል፡፡ 
በድንበር አካባቢ በሽታው ሊገባ ይችላል የሚል ስጋት እንዳለ የጠየቅናቸው ኃላፊው፤ ሱዳን ውስጥ በሽታው ስለሌለ ስጋት የለብንም ብለዋል፡፡
ህብረተሰቡ በሽታው ኢቦላ ነው በሚል እንዳይደናገጥ በክልሉ ኤፍ ኤም ሬዲዮ ጣቢያ ትናንት ጠዋት ቀርበው በሽታው ኢቦላ አለመሆኑን ማስረዳታቸውን አቶ ሃብታሙ ገልፀዋል፡፡ ተጨማሪም ግብረ ሃይል በማቋቋም ምንነቱ በትክክል ያልታወቀውን በሽታ ለማጣራት ባለሙያዎች የተከሰተበት ቦታ ድረስ በመሄድ የማጣራት ስራ መስራታቸውንና ኢቦላ በክልሉ የትኛውም አካባቢ እንዳልተከሰተ ማረጋገጣቸውን ለአዲስ አድማስ አስታውቀዋል፡፡ የጤና ጥበቃ ሚኒስቴር የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ አህመድ አማኖ፤ በሃገሪቱ በየትኛውም አካባቢ ኢቦላ አለመከሰቱን ከየክልሎች በሚሰበሰቡ መረጃዎች መረዳት መቻሉን ለአዲስ አድማስ ገልፀው፤ ምናልባትም ከሙቀት መጨመር ጋር ተያይዞ ትኩሳት፣ የአፍንጫ መንሰር ሊያጋጥም ይችላል ብለዋል፡፡ አሶሳ ተከሰተ ተብሎ በተለያዩ ማህበራዊ ሚዲዎች የተሰራጨውም ትክክለኛ መረጃ አይደለም ብለዋል ኃላፊው፡ ምንጭ አዲስ አድማስ

የወያኔን እድሜ ለማሳጠር በአንድነት እንሠራለን – የውህደት መግለጫ

Augusr25/2014
የወያኔን እድሜ ለማሳጠር በአንድነት እንሠራለን
ቀን 19/12/2006
በአገራችን ኢትዮጵያ ላይ የተንሰራፋውን ዘረኛና በታኝ ሥርዓት ለመቀየርና ከኢትዮጵያ ሕዝብ ጫንቃ ለማውረድ በተለያየ ጎራ ተከፍለው የሚታገሉ ድርጅቶች ቁጥር ከምንጊዜውም በላይ እየበረከተ መምጣቱ የጎጠኛውን ቡድን እድሜ በማራዘም ረገድ ጉልህ ሚና መጫወቱ አሌ የማይባል ሀቅ ነው።
ወቅቱ የሚጠይቀውና አገራችንና ሕዝባችን ያሉበትን ደረጃ በአንክሮ የተረዳ አገርና ሕዝቡን አፍቃሪ የሆነ ድርጅትም ሆነ ቡድን ቆም ብሎ ሊያስብ የሚገባበት ደረጃ ላይ መድረሳችንን የሚያሳይ ነው።
በመሆኑም ኢትዮጵያንና ሕዝቧን ካሉበት አዘቅት በማውጣት ሕዝቡ የስልጣን ባለቤት የሚሆንበትን ሁኔታ ለማመቻቸት የጋራ ትግልና መስዋዕትነት የግድ የሚለን ደረጃ ላይ መድረሳንን፤ የወያኔን ቡድን በሁለገብ ትግል እየተፋለምን ያለን ድርጅቶች ተጣምሮና አንድ ሆኖ መታገል እንዳለብን ካመንን ዓመታት አስቆጥረናል።
በአሁኑ ወቅት ከላይ የጠቀስናቸው ሂደቶች ምላሽ አግኝተው አገራችንና ሕዝባችንን ከአዘቅት ለማውጣት በመጣመር ብቻ ሳይሆን በውህደት አንድ ሆነን አገራችንንና ሕዝባችንን አንድ በማድረጉ ረገድ አስፈላጊው መስዋዕትነት በመክፈል የትግል እድሜ እናሳጥር በሚል ለውህደት የሚያደርሰንን ውይይት ለመጀመር የሚያስችል ሂደቶችን አጠናቀን ወሳኝ ወደሆነው ሂደት ውስጥ መግባታችንን ለመላው የኢትዮጵያ ሕዝብና ወዳጆች ማብሰር እንፈልጋለን።
ወደፊት ለመዋሃድ የተስማማነው ድርጅቶች
1. የኢትዮጵያ ሕዝብ አርበኞች ግንባር
2. የግንቦት 7፣ የፍትህ፣ የነፃነትና የዲሞክራሲ ንቅናቄ
3. የአማራ ዲሞክራሲያዊ ኃይሎች ንቅናቄ
ስንሆን በሚኖረው የሽግግር ሂደት ወቅትም በሁሉም የትግል ዘርፍ በጋራ መሥራት የጀመርን መሆናችንን እየገለጽን የመላው ወገናችን ድጋፉ እንዳይለየን ስንል ጥሪዓችንን እናስተላልፋለን።
አንድነት ኃይል ነው !!!
የኢትዮጵያ ሕዝብ አርበኞች ግንባር — የግንቦት 7: የፍትህ፣ የነፃነትና የዲሞክራሲ ንቅናቄ — የአማራ ዲሞክራሲ ኃይሎች ንቅናቄ

Monday, August 25, 2014

የተማሪዎች ተቃውሞ ተጠናክሮ ቀጥሏል

August25/2014
ነገረ ኢትዮጵያ 
• የኢትዮጵያ የባህር በር ለኤርትራ መሰጠቱ ስህተት ነው

• የኢኮኖሚ እደገቱ እውነት አይደለም 
• የትምህርት ስርዓቱ ወድቋል
• የተማረ ሰው ክብር አይሰጠውም
addis_universityአዲስ አበባ ውስጥ ሳውዝ ካምፓስ (ልደታ)፣ አቃቂ (AASTU)፣ ፍቼ የግብርና ኮሌጅ፣ ስድስት ኪሎ፣ አምስት ኪሎ፣ አራት ኪሎ፣ አአዲስ አበባ የቢዝነስና ኢኮኖሚክስት ትምህርት ክፍልና ሌሎችም አካባቢዎች ከነሃሴ 15 ጀምሮ ልጠና ላይ የሚገኙ የመጀመሪያ ዙር ሰልጣኞች ተቃውሟቸውን መሳማታቸውን እንደቀጠሉ የነገረ ኢትዮጵያ ምንጮች ገለጹ፡፡ ተማሪዎቹ ገዥው ፓርቲ አለ በሚለው እድገት፣ የባህር በር፣ የተማረው የማህበረሰብ በሚደርስበት በደል፣ የትምህርት ጥራት፣ የመምህራን የእውቀት ደረጃ ማነስ፣ ድህነትና አጠቃላይ ኢኮኖሚ ውድቀት ላይ ጠንከር ያለ አስተያየትና ተቃውሞ መሰንዘራቸውን ተገልጾአል፡፡
የኢኮኖሚ እድገት
ተቃውሞ ከገጠማቸው ጉዳዮች መካከል የኢኮኖሚ እድገት አለ የለም የሚለው ሲሆን ተማሪዎቹ ‹‹በአክሱም ዘመን ገናና የነበረችው ኢትዮጵያ በአሁኑ ወቅት በኢኮኖሚው መስክ ጭራ›› መሆኗን በመግለጽ እድገቱ አለ መባሉ ስህተት መሆኑን ገልጸዋል፡፡ ተማሪዎቹ ጨምረውም ‹‹በቀን አንድ ጊዜ እንኳን መመገብ የማይችል ማህበረሰብ ይዘን አድገናል ማለት አንችልም፡፡›› በሚል እድገት አለመኖሩን ተከራክረዋል፡፡ ‹‹ሀገራችን ውስጥ የምግብ፣ የቤት፣ የትምህርት፣ የኔትወርክና ሌሎች ችግሮች አሉ፡፡ ስኳርና ዘይት ለመግዛት ህዝብ ቀበሌ ተሰልፎ ነው የሚውለው፡፡ በ400 ብር ደምወዝ ቤተሰብ የሚያስተዳድር ህዝብ ያለባት ሀገር የሌሎችን እድገት ፈዛ እያየች ያለችን ሀገር አድጋለች ልንል አይገባም፡፡›› ማለታቸው ተገልጾአል፡፡
በተመሳሳይም ‹‹2 በመቶ የሚሆነው የአሜሪካ አርሶ አደር ዓለምን በሚመግብበት በአሁኑ ወቅት 85 በመቶ አርሶ አደር ይዘን ለምን እንራባለን?›› የሚል ጥያቄ ማንሳታቸውንም የነገረ ኢትዮጵያ ምንጮች ጠቅሰዋል፡፡ ተማሪዎቹ ‹‹አድገናል ብለን ራሳችን ማወዳደር ያለብን ከ40 አመት ከነበረ ስርዓት ጋር መሆን የለበትም፡፡ እድገታችን መለካት ካለበት ከሌሎች አገራት ጋር ነው፡፡ መካከለኛ ገቢ ካላቸው አገራት በ2020 እንመደባለን ከተባለ መንግስት መቀየር ይኖርበታል፡፡ ምክንያቱም ይህን ስርዓት ለ20 አመት አይተነዋል፡፡ ባለፉት አመታት ለውጥ ሊያመጣ አልቻለምና በ2020ም ለውጥ ያመጣል ብለን አንጠብቅም፡፡›› የሚል ጠንካር ያለ ሀሳብም አቅርበዋል፡፡
እድገት ላይ ነው የሚባለው የኮንስትራክሽን ዘርፍ የጥራት ደረጃው ዝቅተኛ መሆኑን በተለይ በዘርፉ ትምህርታቸውን እየተከታተሉ የሚገኙ ተማሪዎች አንስተዋል፡፡ ተማሪዎቹ ‹‹እድገት የምንለው የህንጻዎችን ወደላይ ማደግ ወይንም መብዛት ሳይሆን የማህበረሰቡን አስተሳሰብና አኗኗር ዘይቤ መቀየር ነው፡፡›› ሲሉ ተከራክረዋል፡፡ በስልጠናው ወቅት ገዥው ፓርቲ የቻይናን ፈለግ ተከትሎ እድገት ማስመዝገቡን በመቃወም ‹‹ቻይና ከ2.3 እስከ 2.7 በመቶ እያደገች እንደሆነ ይነገራል፡፡ የእሷን ፈለግ ተከተለች የተባለችው ኢትዮጵያ ከ11.2 በመቶ በላይ አደገች ነው የሚባለው ከየት አምጥተነው ነው? ወይስ እንደ ቀን አቆጣጠራችን እድገታችንም ይለያያል?›› ሲሉም አሰልጣኖቹን ጠይቀዋል፡፡
የባህር በር
ተማሪዎቹ ለኤርትራ መሰጠቱ አግባብ እዳልሆነ፣ የባህር በርና ወደቡ ለኢትዮጵያ ቀጣይ እድገት፣ ደህንነትና ታሪክ አንጻር አስፈላጊ መሆኑን በመግለጽ ገዥው ፓርቲ በባህር በር ላይ ያለውን አቋምና ፈጸመ ያሉትን ስህተት ተችተዋል፡፡ ወደብ አልባ በመሆናችን ኢኮኖሚያችን ወደኋላ መቅረቱንም አንስተዋል፡፡ በሌላ በኩል ‹‹በአገራችን የሚመረቱ ሰብሎችና ፍራፍሬዎች ለአገር ውስጥ ገበያ የሚቀርቡት ከውጭ ከተላከው ሲተርፍ ነው፡፡›› በማለት በኤክስፖርት ዘርፍ ያለውን ችግር፣ አገር ውስጥ እየተፈጠረ ያለውን የኑሮ ውድነት ከዚሁ ችግር መመንጨቱን ጠቅሰዋል፡፡
የትምህርት ጥራት
ተማሪዎቹ የራሳቸውን ተሞክሮ በመጥቀስ የትምህርት ስርዓቱ ችግር ያለበት መሆኑን በመከራከሪያነት አቅርበዋል፡፡ ‹‹ለተማረ ሰው ክብር እየተሰጠ አይደለም፡፡›› በሚል የእነሱም እጣ ፈንታ ተመሳሳይ መሆኑን ስጋታቸውን ገልጸዋል፡፡ በተጨማሪም ‹‹የሚያስተምሩን አስተማሪዎች የእውቀት ደረጃ ጥያቄ ምልክት ውስጥ ነው፡፡ በየ ዩኒቨርሲቲው በአመራር ላይ የሚገኙ ግለሰቦች እውቀት የላቸውም፡፡›› በማለት ዩኒቨርሲቲዎች ላይ የተደቀነውን አደጋ አንስተዋል፡፡
ዲግሪ ይዘው በስራ ፈጠራ ስም በጥቃቅንና አነስተኛ እንዲደራጁ የሚደረገውን የተቃወሙት ተማሪዎቹ ‹‹የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ተደራጅተው ካፌ ከፈቱ፣ ኮብልስቶን አነጠፉ ሲባል ነው የምንሰማው፡፡ ለዚህ ስራ ደግሞ ዩኒቨርሲቲ መማር አያስፈልገውም፡፡ ይህን ስራ ለመስራት የሶስት ወር ስልጠና በቂ ሆኖ እያለ ዩኒቨርሲቲ መማር ባላስፈለ›› ሲሉ የትምህርት ስርዓቱ ውድቀት እንደገጠመው መግለጻቸውን ለማወቅ ተችሏል፡፡
ነገረ ኢትዮጵያ በቀጣይም የተማሪዎችን ጉዳይ እየተከታተለች ታቀርባለች!

ወያኔ መንግስት በቅርቡ በፕሬሱ ላይ የከፈተው ዘመቻ ለስደት ከዳረጋቸው ጋዜጠኞች ጋር የተደረገ ቃለ ምልልስ

August 25/2014

በኢትዮጵያ ሕዝብ መራራ ትግል እብሪተኛው የወያኔ መንግስት መውደቁ አይቀርም!!!

August24/2014
Gezahegn Abebe (ገዛኸኝ አበበ)

የኢአዲግ ወያኔ መንግስት   የስልጣን ወንበር በትሩን በሀይል ከተቆናጠጠበት ጊዜ ጀምሮ የኢትዮጵያ ሕዝብ የአኖኖር ሁኔታ ከእለት ወደ እለት እያሽቆለቆለ እና እየወረደ በመምጣቱ ከምቼውም ጊዜ በበለጠ በአሁኑ ወቅት ሕዝቡ ኑሮን መቋቋም በማይችልበት አደገኛ ሁኔታ ውስጥ እንደሚገኝ በኢትዮጵያ ውስጥ ያለውን የኑሮ ውድነት ተቋቁሞ መኖር ከባድ ፈተና እየሆነባቸው እንደሆነ የችግሩ ሰለባና ተጠቂ የሆኑት ሰዎች በየጊዜው ከሚያሰሙት ሮሮና ጩኸት መረዳት ይቻላል:: በአሁኑ ወቅት ጥቂትየስርአቱ  ደጋፊዎች እና የወያኔ ካድሬዎች ካልሆኑ በስተቀር የኑሮ ውድነቱን መቋቋም በማይችሉበት ደረጃ ላይ ደርሰዋል::

  በአሁኑ ሰአት መንግስት የሚያራምደው ፖሊሲ የመላው ኢትዮጵያን ሕዝቡ ፍላጎት እና ጥቅም ማዕከል ያላደረገ ሲሆን የተወሰኑ የህብረተሰብ ክፍሎችን ብቻ ተጠቃሚ እያደረገ እንደሚገኝ ይታወቃል :: ሁሉን የኢትዮያ ህዝብ እና ክልል ተጠቃሚ ያላደረገው የመንግስት የልማት ስትራቲጂ ፖሊሲ እና በመላው ሀገሪቱ ላይ በስፋት ተንሰራፍቶ ያለው ሙሰኝነት ከእለት ወደ እለት የሕዝቡ የአኖኖር ሁኔታ  እያሽቆለቆለ እና እየወረደ እንዲመጣ ካደረጉት ምክንያቶች ውስጥ ተጠቃሽ ሲሆኑ ለኑሮ ውድነቱ ግንባር ቀደም ተጠያቂው ሀገሪቱን እየመራው እና የሀገሪቱን ኢኮኖሚ እድገት በፍጥነት እያሳደጉኝ ነው የሚለው የወያኔ ኢህአዲግ መንግስት ነው:: 

ታስታውሱ እንደሆነ የወያኔ ቁንጮ የነበሩት ሞቹ የቀደሞ ጠቅላይ ሚኒስት መለስ ዜናዊ በአንድ ወቅት  በአሥር አመት ዉስጥ «ኢትዮጵያ በምግብ እራሷን ትችላለች። እያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ በቀን ሶስቴ እንዲመገብ እናደርጋለን» ብለው ነበር ነገር ግን ይህ የአቶ መለስ ዜናዊ ንግግር  የውሃ ላይ ሽታ ሆኖ ቀረ :: በአንጻሩአቶ መለስ  የኢትዮጵያን ሕዝብ በቀን ሶስቴ እንዲመገብ እናደርገዋለን ያሉለት  ኢህአዲግ  ኢትዮጵያን በብቸኝነት በሀይል መግዛት ከጀመረ  23 አመት እየተጠጋ ሲሆነው በእነዚህ አመታቶች ውስጥ  ምንም የተለወጠ ነገር የለም:: የወያኔ መንግስት በተቆጣጠረው በመገናኛ ብዙሃን እንደሚለፈልፉት የኢትዮጵያ ኢኮነሚው ዕድገቱ በፍጥነት ሽቅብ እየገሰገሰ ሳይሆን ወደታች እያሽቆለቆለ ይገኛል::  ኑሮ እጅግ መራራ ከመሆኑ የተነሳ የሰዉ የአኖኖር ሁኔታ አሳሳቢ ደረጃ ላይ በመድረሱ ዉስጥ ዉስጡን የሚያልቁት ወገኖቻችን ብዛት ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ ነዉ።

 በመላው አገሪቱ አዲስ አበባን ጨምሮ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተባባሰ የመጣው የውሃ፣የመብራትና የቴሌኮም አገልግሎት ጥራት መጓደልና የአገልግሎት መቋረጥ እንዲሁም በአገሪቷ እጅግ ከፍተኛ የሆነ የዉጭ ምንዛሪ እጥረት እየታየ ሲሆን  በኢኮኖሚ ችግር  የተነሳ ሕዝቡ ያለውን የኑሮ ውድነት መቋቋም በማይችልበት ሁኔታ ውስጥ በመገገኘቱ በማንኛውም ጊዜና ሰሀት ግባታዊ ሕዝባዊ አመጽ ሊነሳና ትልቅ ችግር ሊፈጠር እንደሚችል የሚሰጉ ብዙዎች ናቸዉ።ደግሞሞ አይቀርም

በአሁኑ ሰአት እንደሚታየው እና መረጃዎች እንደሚጠቁሙት የኢትዮጵያ ሕዝብ ለውጥን ይፈልጋል ህዝቡ ሀገሪቱን እየመራ ባለው የወያኔ መንግስት ለመመራት ፍቃደኛ አይደለም ከየቦታው የሚሰማው እና የሚታያው የሰበዓዊ መብት ረገጣው አፈናና ግድያው ቀጥሎ ባለበት ሁኔታ በየቀኑ እየተባባሰ የመጣው የኑሮው ውድነቱ የኢትዮጵያ ሕዝብ  ከወያኔ ኢህአዲግ መንግስት ጋር ሆድ እና ጀርባ ሆነው እንዲቀጥሉ እያደረጋቸው ነው::ከዚህም የተነሳ መንግስት በየቀበሌው፣በየመስሪያ ቤቱ የሚጠራቸው ሕዝባዊ ስብሰባ ላይ ለመገኛት ፍቃደኛ እና ደስተኛ እንዳይደለ ምንጮቻችን ይገልጻሉ:: ነገሮች በዚህ አይነት ሁኔታ ሊቀጥሉ አይችሉም:: የመረረው የኢትዮጵያ ሕዝብ መብቱን ለማስከበር ሆ ብሎ በወያኔ መንግስት ላይ መነሳቱና አንባገነኖችን ዳግም እንዳይነሱ ገርስሶ መጣሉ አይቀርም:: ስንቶቻችው በእኔ ሀሳብ ትስማማላችው::

   ውድቀት ለአምባገነኑ የወያኔ መንግስት!!!
   ገዛኸኝ አበበ ነኝ ነሀሴ 17/2006

Sunday, August 24, 2014

ወያኔ እስካሁን ድረስ የግንቦት ሰባት የሃገር ቤት መዋቅር በፍጹም እጇ ላይ እንዳልገባ ተረጋግጧል።

August24/2014
ምንሊክ ሳልሳዊ
በሀገሪቱ የስራ ማቆም አድማ እና የተማሪዎች አመጽ ያሰጋል ።

ከመጭው ምርጫ በፊት በኢትዮጵያ ውስጥ የስራ ማቆም አድማ እና የተማሪዎች አመጽ እንደሚያሰጋ ለጠቅላይ ሚኒስትሩ የደህንነት አማካሪ ለሕወሓቱ አለቃ ጸጋይ አርብ እለት የቀረበው ሪፖርት መግለጹን ምንጮች ጠቁመዋል። ምንጮቹ እንዳሉት በወያኔ ውስጥ ስልጣኔን አጣለሁ እፈረካከሳለሁ የሚለው ከፍተኛ ሽብር የፈጠረው ፍራቻ እየተባባሰ መሄዱን እና ወያኔ ለመጭው አርባ አመታት እቆያለሁ የሚለውን ሃሳቡን ሊያኮላሽብኝ ይችላል ያለውን ሁሉ እርምጃ ቢወስድ ምንም አይነት ውጤት እንደማያገኝ እና በይበልጥ ጥላቻ እያሰፋ እንደሚመጣ በተሰበሰበው የመረጃ ሪፖርት ተገልጿል ።

የተቃዋሚ የፖለቲካ ድርጅቶች የሚያስተባብሩ ከሆነ ሕዝቡ የሚከፈለውን መስእዋትነት ለመክፈል ወደኋላ የማይል መሆኑን የጠቆመው ሪፖርት የከተማው የተማረውም ያልተማረውም ሕብረተሰብ በወያኔ ላይ ከፍተኛ ጥላቻ ስላለው ለመጭው ጊዜ ከፍተኛ የሆነ የስራ ማቆም አድማ እና የተማሪዎች አመጽ ያሰጋል ሲል ሪፖርቱ ተናግሯል። እንደ ምንጮቹ አገላለጽ ክሆነ የሃገር ቤት ፓርቲዎች በተለይ ሰማያዊ እና መኢአድ ይህንን እንቅስቃሴ ያስተባብራሉ የሚል የሕዝቡንም አትኩሮት መሳብ እንደቻሉ ሲታወቅ አንድነት እና መድረክ ፓርቲ ውስጥ ያሉ እና ያሰጋሉ የሚባሉ መዋቅሮችን በቁጥጥር ስር ለማዋል ጥረቱ መቀጠሉን ሪፖርቱ አውስቷል።

በወያኔ አስተዳደር እና ባልተማሩ ባለስልጣናቱ እንዲሁም ክድሬዎቹ ሕዝቡ እየተማረረ እንደሆነ እና መንግስታዊው ውሸትና ወመኔነት፣ ሙስና ከፈጠረው የኑሮ ድቀት ጋር ተደማምሮ መጨው ጊዜ ለወያኔ ገሃነም እንደሆነበት በግልጽ የተቀመጠ ሲሆን አብዛኛው የገዢው ፓርቲ አባላት ሳይቀሩ በድርጅቱ ሁኔታ እና ኢዲሞክራሲያዊነት እንደማይደሰቱ እንዲሁም ሕዝቡ እያገለላቸው ሲሆን የሚቀርባቸዉም ሕዝብ ከአንገት በላይ መሆኑን እየገለጹ ስለሆነ የድርጅቱን መኖር እንደማይፈልጉ ታውቋል። አንዳንድ አባላቱ ድርጅቱን ከደርግ ኢሰፓ ጋር እንደሚያመሳስሉት እና በ97 ምርጫ የወሰዱትን እርምጃ በገዢው ፓርቲ በሆነው ድርጅታቸው ላይ ሊወስዱ ይችላሉ ሲል ሪፖርቱ አስቀምጧል።

ከዚህ ጋር በተያያዘ ወያኔ እስካሁን ድረስ የግንቦት ሰባት የሃገር ቤት መዋቅር በፍጹም እጇ ላይ እንዳልገባ ተረጋግጧል። የደህንነት አካላቶች ባደረጉት ማጣራት ግንቦት ሰባት ብለው የተጠቆሙት በራሳቸው መዋቅር ውስጥ ያሉ እና የሃገር ቤት ተቃዋሚዎችን እንዲሰልሉ የተላኩ የገዢው ፓርቲ አባሎች ሆነው ማግኘታቸው ጭራሽ ኢሕአዴግን ውዝግብ ውስጥ እንደከተተው ታውቋል። ከኢሕአዴግ ጽ/ቤት ለደህንነት ቢሮ የተላከው መረጃ እንደሚጠቁመው የግንቦት ሰባት አባልነት የተባሉት አብዛኛዎቹ ለድርጅቱ ጠቃሚ መረጃ የሚያመጡ ሰዎች ሲሆኑ ስለ ግንቦት ሰባት ግን ምንም መረጃ ያላመጡ እና የሚያውቁት ነገር እንደሌለ ይገልጻል።

ወያኔ ምንም አይነት የግንቦት ሰባት መዋቅር ፍንጭ አለማግኘቱ ጭንቀት ውስጥ ስለከተተው በእስር ቤት ያጎራቸውን ወጣቶች በግንቦት ሰባት ዙሪያ ስለላ እንዲሰሩ እና ክትትል እንዲያደርጉ ማሰልጠን ቢፈልግም የመለመላቸው ወጣቶች ፈቅደኛ ሊሆኑለት እንዳልቻሉ ታውቋል፡፤ በቅርቡ እንደተፈታ የሚናገር አንድ ወጣት የላከው መረጃ እንደሚያሳየው የፈለገውን ገንዘብ እንደሚስጡት እና የፈለገው አገር እንደሚልኩት በመግለጽ አብሯቸው እንዲሰራ እና የግንቦት ሰባትን እንቅስቃሴ ተከታትሎ መረጃ እንዲያቀብላቸው ቢያስገድዱት በፍጹም አለመስማማት እንደተለያቸው ተናግሯል። አስተያየት ሰጪዎች ወያኔ ስልጣንን ለማቆየት በሚያደርገው ጥረት የተለያዩ የስለላ መረቦችን እንደሚዘረጋና ተቃዋሚዎች ከዚህ እንዲጠነቀቁ እንዲሁም ተመሳስለው ከሚመጡ ሰርጎ ገቦች ራሳቸውን በመጠበቅ የየፓርቲያቸውን የደህንነት ክፍል እንዲያጠናክሩ አሳስበዋል።#ምንሊክስልሳዊ

Saturday, August 23, 2014

እስክንድር ነጋን ተመልከቱ!

August 23, 2014
በላይ ማናዬ
በአምስት ወራት ብቻ 16 ጋዜጠኞች ኢትዮጵያ ሀገራቸውን ለቅቀው፣ ከስርዓቱ ሸሽተው ወደ ውጭ ሀገር ተሰድደዋል፡፡ አንዳንዶቹ በእውነትም በሀገራቸው ለመስራት ባለመቻላቸውና በመንግስት ክስ የበረገጉ ሲሆኑ ሌሎቹ ደግሞ ሙያቸውን እንደ ሽፋን ተጠቅመው ከሀገር ለመውጣት ያላቸውን ምኞት ያሳኩ ናቸው ማለት እችላለሁ፡፡ (ድፍረት ሳይሆን በትክክል በማውቀው ጉዳይ ላይ ተመስርቼ ነው ይህን የምለው፡፡ ከተሰደዱት ውስጥ በግል የማውቃቸው ስለሚበዙ አቋማቸውን መታዘብ ችዬ ስለነበር የስደታቸው ምክንያት ሊያሳምነኝ ስለማይችል!)

በግሌ ስደትን እንደ መፍትሄ አልቆጥረውም፤ በስደትም ከጋዜጠኝነት መሸሸት የሚቻል አይሆንም፡፡ ጋዜጠኝነት ውስጥ (በተለይ በአምባገነን ስርዓት) የትኛውም አይነት ፈተና አለ፡፡ እስከሞት ድረስ የሚዘልቅ ፈተና፡፡ እስራት፣ ዛቻ፣ ድብደባ፣ ስድብ… ቀላሎቹ ፈተናዎች ናቸው፡፡ ደግሞስ ከማን ነው የሚሸሸው? ከስርዓቱ ወይስ ከራስ እውነት? ከራስ ሸሽቶማ ወዴት ይኬዳል?

ለማነኛውም እስኪ እስክንድር ነጋን ተመልከቱ!

ከሰባት ጊዜ በላይ በመለስ ዜናዊ የአምባገነን መንግስት ታስሯል፡፡ ሀገር ክህደት ከእነሱ ብሶ በሀገር ክህደት ወንጅለው እስር ቤት ልከውታል፡፡ ሲፈታ ሲታሰር፣ ‹ከእንግዲህስ አንተን ማሰር ሰለቸን› ብለውታል፡፡ ግን አልሰለቹም…‹‹አሸባሪ›› ብለው ለ18 ዓመታት ማጎሪያ ቤት እንዲቆይ ፈርደውበታል እስክንድር ግን ይህን ሁሉ መከራ ለእውነቱ ሲል፣ ለጋዜጠኝነት ስብዕናው ሲል፣ ለሀገሩና ለወገኑ ሲል…ሁሉንም ነገር ተቀብሎ በጽናት አስተናግዶታል፤ እያስተናገደውም ይገኛል፡፡ ሂዱና ቃሊቱ እስር ቤት ውስጥ እስክንድርን ጠይቁት፡፡ ገና ወደእናንተ ሲመጣ ምትሃታዊ ፈገግታውን ይመግባችኋል፡፡ ደግሞ ውስጡ ሰላም እንደሚሰማው አግኝታችሁ ስታናግሩት ትረዱታላችሁ!

አዎ፣ እስክንድርን ተመልከቱ! ልጁ በእስር ቤት ተወልዷል፡፡ አሁን ከልጁ ናፍቆት ጋር በሰላም መኖርን ጠልቶ አይደለም በእስር የሚማቅቀው፡፡ ስለእውነት፣ ስለሀገር፣ ስለወገን ሲል ነው፡፡ እስክንድር አሁን የተፈረደበትን የ18 አመታት እስር ቆይታ መጨረስ ግድ ከሆነበት ከእስር ሲወጣ ልጁ ናፍቆት 25 ዓመት ይሞላዋል፡፡ ተመልከቱ! እስክንድር ከልጁ ናፍቆት ጋር ከእስር ቤት ውጭ የሚገናኘው ናፍቆት 25 ዓመት ሲሆነው ነው ማለት ነው፡፡

እስክንድር ግን ይህን ሁሉ እያወቀ ላመነበት ነገር መስዋዕትነት እየከፈለ ነው፡፡ እስክንድር ስደትን ቢመርጥ ለእሱ ቀላል ነበር፤
ከእነጭራሹ ወደ ኢትዮጵያ ሳይገባ በሀገረ አሜሪካ በድሎት መኖርም ይችል ነበር፡፡ ይህ ለእስክንድር የሚዋጥለት አልሆነም፡፡ ሀገሩ
ኢትዮጵያ የእሱን አስተዋጽኦ ትፈልግ ነበር፤ እናም ለሀገሩ ማድረግ የሚችለውን ለማድረግ አላቅማማም!

ከአቅም በላይ በሆነ ምክንያት ሀገር ጥለው የተሰደዱት ወቀሳ አይሰነዘርባቸው ይሆናል፡፡ ግን ግን የእስክንድርን ጫማ መጫማት ስለምን አቃተን ብለው ራሳቸውን መጠየቅ የሚገባቸው ይመስለኛል፡፡ ርዕዮት ዓለሙ (እመቤቲቱ)፣ ውብሸት ታዬ፣ የሱፍ ጌታቸው፣…የሚከፍሉትን መስዋዕትነት እኛ ለመክፈል ስለምን ይከብደናል ብለው ራሳቸውን መጠየቅ ተገቢ ነው ብዬ አምናለሁ፡፡

እስክንድር የፅናት ምልክት! አሁን ላይ በጋዜጠኝነት ሙያ ኢትዮጵያ ውስጥ ላለን ሰዎች እስክንድር የሙያችን የተግባር መምህር መሆኑን እገነዘባለሁ፡፡ ለዚህም እስክንድርን እንመልከት! ጽናቱን እንጋራ፡፡ እነ ኔልሰን ማንዴላም ትናንት ‹‹አሸባሪዎች›› ነበሩ እስክንድር ዛሬ በእነሱ እይታ ‹‹አሸባሪ›› ነው፡፡ እኔ ደግሞ የጽናት ምልክት፣ ላመነበት ሟች መሆኑን አይቻለሁ፡፡ (‹‹አሸባሪ››ን ማድነቅ አሸባሪነት ነው ለካ¡ ቢሆንም ራሴን ሴንሰር አላደርግም፡፡ ያመኑበትን በነጻነት መጻፍ ተምሬያለሁ፤ የምጽፈውን፣ የምናገረውን እኔ እንጂ ሌላ ሰው አይመርጥልኝም!)

አዎ፣ እስክንድር ነጋን ተመልከቱ!

የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ተቃውሞ እንደቀጠለ ነው

August23/2014
 የሸክ ኑሩ ግድያ ሴራ ነው
• ኢህአዴግ በሉዓላዊነት ላይ ያለውን ፖሊሲ ተቃውመዋል
• ‹‹አማኞችን በአሸባሪነት መክሰስ ትውልዱን ለመግደል የተደረገ የኢህአዴግ ሴራ ነው፡፡››
• ህወሓት ከስሯል
• የአንዳርጋቸው ጽጌ ጉዳይ
• አዲሲቷ ኢትዮጵያ የትኛዋ ናት?

ነገረ ኢትዮጵያ ባህርዳር፣ መቀሌ፣ ጎንደር፣ ደብረማርቆስ፣ ደሴ፣ ወልደያ፣ ደብረታቦርና ሌሎችም የሚገኙ የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎችን ባገኘችው መረጃ መሰረት የተነሱትን ዋና ዋና ተቃውሞወች እንደሚከተለው አቅርባለች፡፡

አርሶ አደሩ አሁንም ድረስ ኢህአዴግ እየተደረገ ያለው የመሬት ድልደላ የፓርቲው አባል አይደሉም የሚባሉት አርሶ አደሮችን መሬት አልባ በማድረግ ለደጋፊዎቹ እየሰጠ መሆኑን በውይይቱ ወቅት ተገልጾአል፡፡ ከዚህም በተጨማሪ በ1997 ዓ.ም ምርጫ ቅንጅትን መርጣችኋል እየተባሉ አሁንም ድረስ ጫና እየደረሰባቸው እንደሚገኝና፣ ይህም ለምርጫው ዝግጅት እንዳይሆን ተማሪዎቹ ስጋታቸውን ገልጸዋል፡፡

የእምነት ነጻነት በርካታ ኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች ለሶስት አመታት ሰላማዊ በሆነ መንገድ ድምጻቸው እንዲሰማ ቢጥሩም መንግስት እየወሰደው ያለው አፈና አግባብ አለመሆኑን፣ በተለይም በርካታ ቁጥር ያለውን ሙስሊሙን ማህበረሰብ በጅምላ አሸባሪ ብሎ መፈረጅ ስህተት መሆኑን በተማሪዎቹ ተነስቷል፡፡ በተመሳሳይ ‹‹ኢህአዴግ ማህበረ ቅዱሳንን አሸባሪ የሚልበት ምክንያት ምንድን ነው?›› የሚል ጥያቄ የተነሳ ሲሆን የግቢ ጉባዔ የማህበረ ቅዱሳን አንድ ክንፍ ነው ተብሎ በመፈረጁ አዲስ ህግ ወጥቶ ዩኒቨርሰቲ ውስጥ በጾም ወቅት ይሰጠን የነበረው አገልግሎትን ጨምሮ እምነታችን እንዳንተገብር መከልከላችን ለጣልቃ ገብነቱ ማሳያ ምክንያት ነው›› ብለዋል፡፡

ይህም መንግስት ከመቼውም ጊዜ በበለጠ በእምነት ላይ ጣልቃ እየገባ መሆኑን በውይይቱ ላይ ተነስቷል፡፡ እንደ ምሳሌም በ1989ና 1994 ዓ.ም የኃይማኖት አባቶች በተለይም ቄሶች የጦር መሳሪያ ደብቃችኋል ተብለው ድብደባ እንደደረሰባቸው በመግለጽ የጣልቃገብነቱን አስከፊነት ገልጸዋል፡፡ ሉዓላዊነት ሉዓላዊነትን በተመለከተ በበርካታ ዩኒቨርሲቲዎች ጥያቄ የተነሳ ሲሆን በተለይም በባህርዳር፣ ጎንደር፣ ወልደያ፣ ደሴና ደብረማርቆስ ዪኒቨርሲቲዎች ዋነኛ የመወያያ አጀንዳ እንደነበር ለመረዳት ችለናል፡፡ ተማሪዎቹ ‹‹መሬቱን ቆርሶ የሰጠው ኢህአዴግ ነው፣ በሉዓላዊነት ጉዳይ ላይ አገራችን ከነበራት ክብር እያሳነሰው ነው፣ ኢትዮጵያ አንድነትን ለመጠበቅ የጣረውን ምኒልክን እየወቀሰ ኢህአዴግ በአሁኑ ወቅት መሬት ቆርሶ መስጠቱ አላማውን በግልጽ የሚያሳይ ነው›› በማለት በሉዓላዊነት ላይ የተሳሳተ ፖሊሲ እንዳለው ተከራክረዋል፡፡
በተጨማሪም ‹‹ኤርትራ ተገንጥላለች፣ አሰብን አጥነተናል፣ ባድመ ላይ ወጣቱ አልቆ መሬቱን አሳልፎ ሰጥቷል፣ አሁን ደግሞ የመተማን መሬት አሳልፎ ለመስጠት በድብቅ መፈራረሙ በሉዓላዊነታችን ላይ ያለውን አሉታዊ አቋም የሚያሳይ ነው፡፡›› በሚል በሉዓላዊነት ላይ ያለውን የተሳሳተ ፖሊሲ ተቃውመዋል፡፡ በተመሳሳይ ተማሪዎቹ አያሌው ጎበዜ የፕሬዝዳንትነት ስልጣኑን ሳይጨርስ የወረደው መሬቱን ፈርሜ አልሰጥም ስላለ ነው፡፡›› ያሉት ተማሪዎቹ ለጥያቄዎቻቸው መልስ እንደሚፈልጉ ገልጸዋል፡፡ የሸህ ኑሩ ግድያ ደሴ ላይ የተማሪው ትልቅ መወያያ ከሆኑት ጉዳዮች መካከል የሸህ ኑሩ ግድያ በቀዳሚነት እንደሚገኝ የነገረ ኢትዮጵያ ምንጮች ገልጸዋል፡፡

slide-15ከተወያዮቹ መካከል ‹‹የሸክ ኑሩ ገዳይ የኢህአዴግ ደህንነቶች ናቸው፡፡ ይህም የተደረገው ኢህአዴግ በሙስሊሙ መካከል ልዩነት ለመፍጠርና እርምጃም ለመውሰድ እንዲመቸው የወሰደው ነው፡፡›› ማለታቸውን ለማወቅ ተችሏል፡፡ አንዳርጋቸው ጽጌ ደብረማርቆስ በሚገኙ ተወያዮች አጀንዳ ከነበሩት ጉዳዮች መካከል የአንዳርጋቸው ጽጌ ጉዳይ ይገኝበታል፡፡ ተማሪዎቹ ‹‹የመን አንዳርጋቸውን አሳልፋ መስጠቷ ትክክል አይደለም፣ የአንዳርጋቸው ጉዳይ ሽብርን መዋጋት ነው ወይንስ የፖለቲካ ባላንጣነት? የእንግሊዝ ዜጋ የሆነውንና እንግሊዝ በአሸባሪነት ያልፈረጀችውን ሰው አሸባሪ ማለቱ ጸረ ሽብር ህጉ ከእንግሊዝ ተመሳሳይ ህግ ጋር በምን ቢለያይ ነው? በጸረ ሽብር ኢህአዴግ ከእንግሊዝ በልጦ ነው ወይ? አሁን ያለበት ሁኔታም ለህዝብ ይፋ ሊሆን ይገባል የመሳሰሉ ጥያቄዎች ተነስተዋል፡፡ ማፈናቀል የከተማ ነዋሪዎችን ማፈናቀል በባህርዳር፣ ጎንደርና ደብረማርቆስ ከተማ ውስጥ የሚገኙት የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ተነስቷል፡፡

ተማሪዎቹ ‹‹በተለያዩ ከተሞች ድሃዎችን በማፈናቀልና ቤታቸውን በማፍረስ ለሀብታም እየተሰጠ ነው፡፡ ይህ የጭቆና የመጨረሻው ደረጃ ነው፡፡›› ሲሉ ተከራክረዋል፡፡ ‹‹የመሬት መቀራመት መሬት በቀብሬ ላይ ይቀየራል ከሚለው የኢህአዴግ ፖሊሲ የመነጨ ነው፡፡ የመሬት ክፍፍሉ አርሶ አደሩን ያገለለና ለስርዓቱ መጠቀሚያ የሆነ ነው፡፡ የሊዝ ህጉ መሰረዝ ይገባዋል፣ አርሶ አደሩ ከመሬት እየተነቀለ ነው፣ 1ለ5 አርሶ አደሩን ለማፈን የተደረገ ነው፡፡ መሬት የኢትዮጵያ ህዝብ እንጅ የመንግስትና የፓርቲ መሆን የለበትም›› የሚሉ ተቃውሞዎች ተነስተዋል፡፡ የባህር ዳሩ ግጭት የመላው ኢትዮጵያ ጨዋታዎች ላይ የተፈጠረው ግጭትን በተመለከተ ደሴ፣ ደብረታቦር፣ ባህርዳርና ጎንደር ላይ መወያያ ሆኖ እንደነበር ለማወቅ ተችሏል፡፡

ባህርዳር ላይ በተደረገው የመላው ኢትዮጵያ ጨዋታዎች ላይ የተፈጠረው ግጭት ብአዴን በበላይነት የመራው ሴራ መሆኑን፣ ይህም አማርኛ ተናጋሪውን እንደማይወክል፣ የብአዴን ፖለቲከኞች እንወክለዋለን የሚሉትን ህዝብ በአደባባይ ሲሳደቡ መስተዋላቸው የሚያሳየው ለህዝብ ያልቆሙ እንደሆነ ተማሪዎቹ አጽንኦት ሰጥተው እንደገለጹ ለነገረ ኢትዮጵያ ገልጸዋል፡፡ ርዕዮት-ዓለም በተለይ ባህረዳር ውስጥ ድባንቄ የተባለ ቦታ ላይ የሚገኙት የባህርዳር ዩኒቨርሲቲ ሰልጣኞች በርዕዮት ዓለም ላይ ሰፋ ያለ ውይይት ማድረጋቸውን ለማወቅ ተችሏል፡፡ ‹‹እስከ 1994 ዓ.ም ኢህአዴግ ፖሊሲ አልነበረውም፣ ተቃዋዎችን ፖሊሲ የላቸውም እያለ ለመተቼት ምን ሞራል አለው፣ ሌብራሊዝም ተቃዋሚዎቹ ስለሚከተሉት ብቻ ትክክል እንዳልሆነ እየተነገረን ነው፣ ከቻይና ተገለበጠ የሚባል ርዕዮት ዓለም ለኢትዮጵያ እየጠቀመ አይደለም፣ መነሻውና መድረሻው የማይታወቅ የኢህአዴግ ርዕዮት ዓለም ኢትዮጵያ ውስጥ ለውጥ ሊያመጣ አልቻለም፣ ማህበረቅዱሳንንና ሙስሊሙን ማህበረሰብ አሸባሪ ማለት እምነት አልባ ትውልድ ለመፍጠር የተደረገ ሴራ ነው፣ ይህ ትውልዱን ለመግደል የተደረገ የኢህአዴግ ሴራ ነው፡፡

ትምህርት ‹‹ትምህርትን በኢህአዴግ ዘመን ወድቋል፡፡ ትምህርቱ ጥራት ቢኖረው ኖሮ ተመርቆ ስራ አያጣም ነበር፡፡ አሁንም ስራ እንይዛለን የሚል ተስፋ የለንም፡፡ ኢህአዴግ ዘመን ትምህርት ወድቆ ትምህርት ስርዓቱን የጀመሩትን ስርዓቶች የማውገዝ ሞራል አላችሁ ሆይ?›› የሚሉ ተቃውሞዎች ቀርበዋል፡፡ በተጨማሪም ‹‹በየ ዩኒቨርሲቲው የሚገኙ ሴቶች በትምህርት ስርዓቱ ውድቀትና በድህነት ምክንያት ገላቸውን እየሸጡ ነው፡፡ ኢህአዴግ በግብረ ሰዶማውያን ላይ ያለው አቋም የተሳሳተ ነው፡፡ ይህም የሚደረገው ትውልዱ ማንነቱን ትቶ ውድቀት ላይ እንዲወድቅ ለማድረግ ነው፡፡ ሌሎች ጉዳዮች ላይ ሌብራሊዝምን እያንቋሸሸ የወሲብ ሌብራሊዝምን ግፍ ከሚገባው በላይ ለቆታል፡፡ ይህ ኢህአዴግ ስልጣኑን ለማቆየት የሚያደርገው ስልት ነው፡፡ ይህ በተሳሳተ የኢኮኖሚ ምክንያት በመጣው ድህነት የተነሳ ነው፡፡ በትምህርት ውድቀትና በድህነቱ ምክንያት ተማሪዎች ድንጋይ መቀጥቀጥ አማራጭ ሆኖ በመቅረቡ ሴቶች የወሲብ ንግድን እንዲቀላቀሉ እንዲሁም ወንዶች የጎዳና ተዳዳሪ እንዲሆኑ እየተደረገ ነው፡፡ የሚሉ ተቃውሞዎችን ማቅረባቸውን ለነገረ ኢትዮጵያ ገልጸዋል፡፡›› የሚሉ ተቃውሞዎች ተነስተዋል፡፡

ኢዲሲቷ ኢትዮጵያ የትኛዋ ናት? ለስልጠና በቀረቡት ሰነዶች አብዛኛዎቹ ክፍሎች ውስጥ ‹‹አዲሲቷ ኢትዮጵያ›› የሚል ቃል የተደጋገመ ሲሆን ተማሪዎቹም ‹‹ኢዲሲቷ ኢትዮጵያ የትኛዋ ናት? ኤርትራ የተገነጠለችባት፣ በቋንቋ የተከፋፈልንባት፣ ወደብ አልባ የሆንንባት፣ የኢትዮጵያ ገናናነት የወረደባት ኢትዮጵያ አዲሲቱ ኢትዮጵያ ልትባል ትችላለች? የሚሉ ጥያቄዎችን አንስተዋል፡፡ በተጨማሪም ‹‹ብሄር ማለት ምን ማለት ነው?›› የሚለው ወልደያ፣ ባህርዳር፣ ጎንደር፣ ደብረማርቆስ በሚገኙ ሰልጣኞች ሰፊ ክርክር አስነስቷል፡፡ ፋብሪካዎች ደብረማርቆስ የሚገኙ የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ‹‹ደብረ ማርቆስ ውስጥ ሊገነባ የነበረ የመኪና መገጣጠሚያ እንደገና እንዲቀር ተደርጓል፣ በክልሉ የቢራ እንጅ ሌሎች ፋብሪካዎች እንዲስፋፉ አይደረግም›› የሚል ጥያቄ አንስተዋል፡፡ ከዚህም በተጨማሪ ‹‹በስፋት ደን ይመነጠራል፡፡ ደን እየተመነጠረ እንዴት አረንጓዴ ልማት አለ ይባላል?›› የሚሉ ጥያቄዎችን ተጠይቀዋል፡፡

ህወሓት ከስሯል

በመቀሌ ዪኒቨርሲቲ የሚገኙ ሰልጣኝ ተማሪዎች በተለይም በህወሓት ላይ ጥያቄ ማንሳታቸውን ስማቸው እንዲገለጽ ያልፈለጉ አሰልጣኝ ለነገረ ኢትዮጵያ ገልጸዋል፡፡ ተማሪዎቹ ‹‹የትግራይ ህዝብ በህወሓት አምኖና ከሌላው ህዝብ ተለይቶ እንዲኖር ህወሓት ብዙ ስራ ሰርቶ ነበር፡፡ ከክፍፍሉ በኋላ ግን ህወሓት ከስሯል፡፡ የትግራይ ህዝብን ጥያቄ ያልተመለሰ ለመሆኑ የአረና መፈጠር አንድ ማሳያ ነው፡፡›› ማለታቸውን አሰልጣኙ ለነገረ ኢትዮጵያ ገልጸዋል፡፡ በተጨማሪም አብርሃ ደስታ ላይ የተወሰደው እርምጃም መነጋገሪያ እንደሆነም ለማወቅ ችለናል፡፡ ተማሪዎቹ አብርሃ ደስታ መፈታት እንዳበት መጠየቃቸውንም ለማወቅ ተችሏል፡፡ በሌላ በኩል በአብዛኛዎቹ ዩኒቨርሲቲዎች ጥያቄውን ያነሱት ተማሪዎች በቡድን ውይይት ወቅት ማስፈራሪያ እየደረሰባቸው እንደሆነም ተገልጾአል፡፡ በጅማ፣ አዳ፣ ሀዋሳና ሌሎች ከተሞች የሚሰለጥኑ የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ያሰሙትን ተቃውሞና መከራከሪያዎች በቀጣይነት ለማቅረብ እንሞክራለን፡፡
Minilik Salsawi (ምንሊክ ሳልሳዊ)

Friday, August 22, 2014

ጄ/ል ባጫ ደበሌ በሜሪላንድ ግዛት የ350ሺህ ዶላር ቤት ገዙ

August22/2012
Gen. Bacha Debele (left),  meets Pakistan President Pervez Musharraf.
Gen. Bacha Debele (left), meets Pakistan President Pervez Musharraf.
ጄ/ል ባጫ ደበሌ በአሜሪካ ሜሪላንድ ግዛት በ350ሺህ ዶላር ቤት መግዛታቸው ታውቋል። የባጫ ባለቤትና አንድ ልጃቸው እንደሚኖሩበት ሲታወቅ ልጃቸው በተርም ከ20ሺህ ዶላር በላይ እየተከፈለለት እንደሚማር ማወቅ ተችሏል።
በከፍተኛ ሙስና ውስጥ ከተዘፈቁ የመከላከያ ከፍተኛ የጦር አዛዦች አንዱ የሆኑት ባጫ ደበሌ በቦሌ ከለንደን ካፌ ፊት ለፊት ባለሁለት ፎቅ ዘመናዊ ቪላ ገንብተው እንደሚያከራዩ ይታወቃል። በኢትዮ- ኤርትራ ጦርነት ወቅት አሰብን ለመቆጣጠር ይገሰግስ የነበረውን የኢትዮጵያ ሰራዊት ከመለስ ዜናዊ በተላለፈ ትእዛዝ ግስጋሴው እንዲገታና ወታደራዊ እቅዱ እንዲኮላሽ ከፍተኛ ሚና የተጫወቱት ባጫ ደበሌ መሆናቸውን የቅርብ ምንጮች ያረጋግጣሉ።
ባጫ የአቶ መለስን “ሃሳብ” ተግባራዊ በማድረጋቸው በሙስና ሃብት ጥግ መድረስ ችለዋል ሲሉ ምንጮቹ ያክላሉ።
ይህ በእንዲህ እንዳለ ተስፋዬ ገ/አብ በዲሲ የሃበሻ ሬስቶራንት ውስጥ ሲገባ በርካታ ኢትዮጵያውያን ሬስቶራንቱን ለቀው እንደወጡ ታውቋል። « አንተ ባለህበት መመገብም ሆነ አብረን መቀመጥ አንፈልግም» ሲሉ ነበር የወጡት። ኢትዮጵያውያን ወንድማማቾችን ለማጋጨት ከሻዕቢያ የተቀበለውን መሰሪ አጅንዳ ይዞ የሚንቀሳቀሰው ተስፋዬ ገ/አብ ያሳተመውን መፅሐፍ ተረክበው እንዲሸጡለት የጠየቃቸው የሃበሻ መደብሮች በሙሉ ፈቃደኛ ሳይሆኑ ቀርተዋል። « ኦሮሞ ነኝ» በማለት እያደነገረ የሚገኘው ተስፋዬ ለሻዕቢያው መፅሄት በሰጠው ቃለምልልስ « ኤርትራዊ ነኝ፤ ወላጆቼም ኤርትራውያን ናቸው» ሲል ተናግሮዋል።

ኢትዮጵያውያን በሳዑዲ አረቢያ ሪያድ ከተማ ሲታፈሱ አመሹ

August22/2014
ለዘ-ሐበሻ የዘገበው ኢትዮጵያ ሃገሬ ጅዳ በዋዲ
የሳውዲ አረቢያ መንግስት ያለመኖሪያ ፈቃድ የሚኖሩ ህገወጥ ውጭ ሃገር ዜጎች ሃገሪቱን ለቀው እንዲወጡ የሚገልጸውን መመሪያ ተግባርዊ ለማድረግ የፀጥታ ሃይሉ በወሰዱት እርምጃ ከ1 መቶ 80 ሺህ በላይ እትዮጵያውያን ያለምንም ቅድመ ሁኔታ ከቤት ንብረታቸው ተፈናቅለው የሳውዲን ምድረ ለቀው ወደ ሃገር መመለሳቸው ይታወሳል። ይህ በዚህ እንዳለ የሳውዲ ከስደት ተመላሽ ወገኖችን መልሷ የማቋቋም ከፍተኛ ሃላፊነት የተጣለበት የኢትዮጵያ መንግስት ሁሉንም ለማድረግ በተደጋጋሚ ቃል ቢገባም በወቅቱ የዓለምን ህዝብ ትኩረት ስቦ የነበረው የኢትዮጵያውያኑ ጉዳይ እስኪረጋጋ የውጭ ጉዳይ ሚንስትሩ ዶ/ር ቴድሮስ አድሃኗም ከስደተኛው ጋር ፎቶ በመነሳት በኢቲቪ ሲሰራጭ ከነበረው ሰፊ የዜና ሽፋን ባሻገር ስደተኛው ምንም አይነት ማቋቋሚያም ሆነ ድጋፍ እንዳላደረጉላቸው ይነገራል። በተለይ የስደት አለም ህጻናት ልጆቻቸውን ታቀፈው ለሃገር የበቁ እናቶች ለጎዳና ተዳዳሪነት የተዳረጉበት አስዛኝ ታሪክ የአብዛኛውን ኢትዮጵያዊ ሆድ አላውሷል ። መንግስት በወቅቱ አዲስ አበባ በስደተኞቹ እንዳትጨናነቅ የስደተኞቹ ጉዳይ በየክልሉ ባለስልጣናት የታያል በሚል ሽፋን በመቶሺህ የሚቆጠረውን ስደተኛ በየጉራጉሩ ወሽቆ ነገሮቹን ለማድበስበስ ቢሞክረም አብዛኛው ወገኖች በቋፍ ላይ ያለቸውን ህይወታቸውን ለመታደግ አቀም ያለው አይቀሬውን ሞት በመጋፈጥ፡ በህይወቱ ቆርጦ ሳውዲ አረቢያ ለመግባት ቀይ ባሀርን በጀልባ አቋርጧ ለዳገም ስደት ተዳርጓል።
በአንጻሩ በሰው ሃገር ወልዶ ከብዶ በወቅቱ ያገኛት በነበረች የዕለት ገቢው ከእጅ ወደ አፍ የሆነ የስደት አለም ጎጆውን አሞቆ ያለጥሪት ይኖር የነበረው አባወራ ያቺን ቀውጢ ውቅት መቋቋም ተስኖት የቤተሰቦቹን ህይወት ከወረበሎች ለማዳን ወደ ሃገሩ እግሬ አውጪኝ ቢልም ያለጠበቀው ገጥሞት የሞቀ የስደት ዓለም ትዳሩን መቅኔ ያሳጣውን የመንፉሃው ሁከት እየረገመ በገዛ ሃገሩ ሰማይ ተድፍቶበት ለልጆቹ የዕለት ጉርስ ዳቦ መግዣ አጥቶ የህጻናቱን ስቃይ እና መከራ ላለማየት እግር ወዳ መራው ሲኳተን በረሃ በልቶት እደወጣ የቀረውን ከሳውዲ ስደት ተመላሽ ኢትዮጵያዊ ቤት ይቁጠረው ። ይህ ባለበት ሁኔታ የሳውዲ ፀጥታ ሃይሎች በዛሬው ዕለት ባደረጉት የተጠናከረ የቤት ለቤት ፍተሻ ከ1 ሺሕ በላይ ህገ ወጥ ሰዎች በቁጥጠር ስር መዋላቸውን የሚናገሩ ምንጮች ከግማሽ በላይ የሚሆኑት ኢትዮጵያውያን መሆናቸው ጉዳዩን የበለጠ አሰደንጋጭ ያደረገዋል ። የፀጥታ ሃይሉ ከህብረትሰቡ በሚቀርብላቸው መረጃ መስረት ዘመቻውን በቀጣይነት በሪያድ ከተማ በተለምዶ ነሲም አል ሃማም እና ጉቤራ እይተባሉ የሚጠሩ መንደሮችን በማማከል አጠናክረው እንደሚቀጥሉ ከውስጥ አዋቂ ምንጮች ማረጋገጥ ተችሏል።። ከአንድ ወር በፊት በሪያ ድ ከተማ የአንድ ወህኒ ቤት ግርግዳ ደምርሰው ኢትዮጵያውያኑን ጨምሮ ቁጥሩ በወል የማይታወቅ እስረኞች ማምለጣቸው ይታወሳል ።
በዛሬው ዕለት መንፉሃ ውስጥ በተካሄደው የቤት ለበቤት ፍተሻ በኢትዮጵያውያን ላይ ስለደርሰ እንግለት ወደ ሪያድ የኢትዮጵያ ኤንባሲ ስልክ በመደወል ለማረጋገጥ ባደረኩት ጥረት አንድ ስሜ እንዳይገለጽ ያሉ ዲፕሎማት የቤት ለቤት ፍተሻው በኢትዮጵያውያኖች ላይ ብቻ ያነጣጠረ እንዳልነበረ ገልጸው በዘመቻው ወቀት ከፍተኛ የሳውዲ ፀጥታ ሃይል መኮንኖች እና የመዲናይቱ ባለስልጣናት የቀርብ ክትትል እና ቁጥጠር ያደርጉ እንደነበር በማውሳት እርምጃው በባህር የመጡ የመኖሪያ ፈቃድ በሌላቸው ህገወጥ የአካባቢው ነዋሪዎች ላይ ብቻ ያነጣጠረ እና በየትኛውም ዜጋ ላይ ምንም አይነት እንግለት ያለተፈፀመ ጥናቃቄ የተሞላበት ዘመቻ እንደነበር አረጋግጠናል ብለዋል ።በማስከተል ትላንት የሻኞቸውን ኢትዮጵያውያን ደግማችሁ ዛሬ ስትሸኙ ምን ይሰማችሃል ላልኳቸው ጥያቄ ምላሽ ሳይሰጡኝ ተሰናብተውኛል። ዛሬ ማለዳ መንፉሃ ውስጥ በሳውዲ ፀጥታ ሃይሎች ተካሄደ በተባለው የቤት ለበቤት አፈሳ ዙሪያ ተጨማሪ መረጃዎችን ከአካባቢው ነዋሪዎች እና ወህኒ ከሚገኙ ወገኖች መረጃ በማሰባሰብ በሰፊው ለመዘገብ የማደርገው ጥረት ይቀጥላል ።

saudi ethiopia 2
saudi ethiopia 3
saudi ethiopia 4
saudi ethiopia 1
saudi ethiopia 5

ETHIOPIA – Nine journalists and bloggers still held arbitrarily

August 22/2014

Three journalists and six bloggers who have been held for the past five months were denied bail by a federal court in Addis Ababa yesterday after the prosecution argued that article 3 of the 2009 anti-terrorism law, under which they are detained, precludes release on bail.
The defence said article 3’s bail prohibition does not apply because none of them has been individually charged with a specific crime under the anti-terrorism law. The defence also argued that article 3 violates the constitutional guarantee of the right to release on bail.
The three journalists are Tesfalem Waldyes, Edom Kasaye and Asmamaw Hailegiorgis, and the six bloggers – all members of the Zone 9 collective – are Atnaf Berhane, Mahlet Fantahun, Befekadu Hailu, Abel Wabella, Natnail Feleke and Zelalem Kibret. One of the collective’s co-founders, Soliyana Shimelis, is being prosecuted in absentia.
The Ethiopian government is clearly trying to gag the media,” said Reporters Without Borders secretary-general Christophe Deloire. “These three journalists and nine bloggers have been held for nearly five months without being given the least guarantee of due process. The prosecution still has not said what precisely they are supposed to have done to justify the charges. We call for their immediate release because they have no place being in prison.
The prosecution accused them on 17 July of “organizing themselves into covert sub-groups to overthrow the government by contacting and receiving finance and training from two designated terrorist groups” – the US-based opposition group Ginbot 7 and the separatist Oromo Liberation Front (OLF). They are facing up to 15 years in prison under the anti-terrorism law.
Restrictions on freedom of information have grown in recent months in Ethiopia, where at least six journalists are currently detained in connection with their work. A state broadcaster fired 20 employees because of their political views
on 25 June, and the justice ministry announced on 5 August that it intended to bring criminal charges against six news publications for “encouraging terrorism and endangering national security.”Ethiopia is ranked 143rd out of 180 countries in the 2014 Reporters Without Borders press freedom index

Thursday, August 21, 2014

ከወያኔ የዩኒቨርስቲ ተማሪዎች ስልጠናዎች የተረዳነው:- ወጣቱ ለለውጥ ዝግጁ ነው፤ የቀረው ድርጅት ነው

August21/2014

የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የተመሠረቱበት ዓላማ የእውቀትና ጥበብ መበልፀጊያና ማስፋፊያ እና የምርምር ማዕከላት እንዲሆኑ ነው። እውቀትና ጥበብ እንዲበለፅጉ እና የምርምር ሥራዎች እንዲዳብሩ የአካዳሚ ነፃነት መኖሩ ቁልፍ ጉዳይ ነው። የአካዳሚ ነፃነት ሳይኖር መምህራኑም ተማሪዎቹም በነፃነት ማሰብ፣ አስቸጋሪ ጥያቄዎችን ማንሳት እና ለጥያቄዎቻቸው መልስ ለመሻት መመራመር አይችሉም። የአካዳሚ ነፃነት ሳይኖር የተለያዩ እይታዎችንና ንድፈሀሳቦችን በገለልተኛነትና በሀቀኝነት መመርመር አይቻልም። በከፍተኛ የትምህርት ተቋማት የአካዳሚ ነፃነት እንዲኖር ተቋማቱ ከፓርቲ ፓለቲካ ገለልተኛ መሆን ይኖርባቸዋል። አንድ ከፍተኛ የትምህርት ተቋም የአንድ ፓርቲ ርዕዮተ ዓለም አራማጅ ከሆነ ተቋሙ የፓርቲው ካድሬዎች ማሰልጠኛ ሆነ ማለት ነው። ዛሬ በአገራችን የሚገኙ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የሚገኙበት ሁኔታ ይህ ነው። የአገራችን የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የወያኔ ካድሬዎች ማሰልጠኛ ሆነዋል። ይህ አጅግ አሳሳቢ ጉዳይ ነው።
የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ወደ ህወሓት ካድሬ ማሰልጠኛነት መዝቀጥ አንድ ተጨባጭ ማስረጃ ሰሞኑን ለዩኒቨርስቲ ተማሪዎች በፕላዝማ ቴሌቪዥን አማካይነት በመሰጠት ላይ ያለው ፕሮፖጋንዳ ነው። በዚህ ፕሮፖጋንዳ ያልተጠመቀ ተማሪ የሚቀጥለው ዓመት መደበኛ ትምህርት አይቀጥልም በማለት ተቋማቱ ለካድሬ ማሰልጠኛነታቸው እውቅና ሰጥተዋል።
በዚህ ብዙ የአገር ሀብትና ጊዜ በፈሰሰበት ቅስቀሳ፣ የወያኔ ካድሬዎች ዘረኛና ከፋፋይ ፓሊሲዎቻቸውን ማር ቀብተው ወጣቱን ለመጋት እየጣሩ ነው። ለፓርቲ ቅስቀሳ የመንግሥትን መዋቅር መጠቀም በራሱ ወንጀል ቢሆንም ከዚህ በላይ ጉዳት ያለው ደግሞ የፕሮፖጋንዳው ይዘትና ዓላማ ነው። ወያኔ/ኢሕአዴግ ሁሉንም ነገር የሚያውቅ፤ ሁሉንም ነገር ማድረግ የሚችል ተደርጎ የተዘጋጀው ፕሮፖጋንዳ በትውልድ ላይ የሚያስከትለው የእውቀትና የሥነ ልቦና ኪሳራ ከፍተኛ ነው።
በዚህ “ስልጠና” ተብሎ በሚሞካሸው ርካሽ ፕሮፖጋንዳ አማካይነት አድርባይ የሆነው ወያኔ ወጣቱን ለአድርባይነት እያዘጋጀው ነው። የወያኔ ዓላማ የኢትዮጵያ ወጣት መስሎና ዋሽቶ አዳሪ እንዲሆን ማድረግ ነው። የስልጠናው ዓላማ ወጣቶች ለግል ሕወታቸው ምቾች ሲሉ የወያኔ አባላትና ደጋፊዎች እንዲሆኑ ማድረግ ነው። የስልጠናው ዓላማ “ወይን ለኑሮ” ተቀባይነት ያለው የኑሮ ዘይቤ ለማድረግ ነው። ይህ ደግሞ የከፍተኛ ትምህርትን መሠረተ ሀሳብን ብቻ ሳይሆን የኢትዮጵያዊነት ነፃነት-ወዳድ ባህልንም የሚፃረር ነው። በዚህም ምክንያት ወያኔ የወጣቱን ትውልድ ላይ አዕምሮ ለማላሸቅ የሚነዛውን ፕሮፖጋዳ መቃወም የኢትዮጵያዊያን ሁሉ የዜግነት ግዴታ ነው።
ደግነቱ በአብዛኛዎቹ የስልጠና አዳራሾች እየሆነ ያለው ወያኔ ያሰበውና የተመኘውን አይደለም። የኢትዮጵያ ወጣት የወያኔን ዘረኛ ፕሮፖጋንዳ የሚጋት እንዳልሆነ እያስመሰከረ ነው። በብዙ አዳራሾች የወያኔ ካድሬዎች ሊመልሷቸው ከማይችሏቸው ጥያቄዎች ጋር ተፋጠው እንዲያፍሩ ተደርገዋል። ወጣቶች፣ “የታለ የምታወሩለት እድገት ?” “ቻይና በሠራው እናንተ የምትፎክሩት ለምንድነው?“ “ፍትህ የት አለ?” “የአንድ ብሔር የበላይነትን ነው እኩልነት የምትሉት?” እያለ ካድሬዎችን እያፋጠጠ ነው። ወጣቱ አፈና በበዛበት ሁኔታ ውስጥም ሆኖ መሠረታዊ የሆኑ ጥያቄዎችን ለማንሳት መድፈሩ፤ በአንዳንድ አዳራሾች ደግሞ በጩኸት የፕሮፖጋንዳውን ሥራ ማወኩ ወጣቱን ብቻ ሳይሆን ኢትዮጵያዊያንን ሁሉ የሚያኮራ ተግባር ነው።
ወያኔ፣ ወጣቱን አድርባይነትን ለማስተማር ያዘጋጀው ስልጠና የወጣቱ ቆራጥነትና አርበኝነት ማሳያ ሲሆን፤ ፍርሃት ለማስፈን የተጠራ ስብሰባ ድፍረትን አደባባይ ሲያወጣ ማየት የሚያኮራ ነው። ወጣቱ በዚህ ስልጠና ላይ ባሳየው ድፍረት ለለውጥ ምን ያህል ዝግጁ እንደሆነ አሳይቷል። አሁን የጎደለው ድርጅት ነው። የወጣቱ ለለውጥ ዝግጁ መሆን አንድ ትልቅ የምሥራች ነው። ይህ ዝግጁነት በድርጅት መደገፍ ደግሞ ተከታትሎ መምጣት ያለበት ሥራ ነው። የወጣቱ የመንፈስ ዝግጅትና ድርጅት ከተቀናጁ የወያኔ ውድቀት ቅርብ ነው።
ወጣቱ ከተቃውሞ ባለፈ ሊሠራቸው የሚገቡ በርካታ ጉዳዮች ከፊቱ ተደቅነዋል። ከሁሉ አስቀድሞ ድርጅት ወሳኝ ጉዳይ እንደሆነ ሊጤን ይገባዋል። ግንቦት 7: የፍትህ፣ የነፃነትና የዲሞክራሲ ንቅናቄ በወያኔ አገዛዝ ሥር ባለችው ኢትዮጵያ ውስጥ ምስጢራዊና ማዕከላዊነትን ያልጠበቁ ትናንሽ ስብስቦች ይበልጥ ውጤታማ ይሆናሉ ብሎ ያምናል። ስለሆነም ግንቦት 7፣ እያንዳንዱ ለሀገሩ፣ ለነፃነቱ፣ ለክብሩ፣ ለፍትህ ግድ ያለው ወጣት ከሚመስሉትና ከሚያምናቸው ጥቂት ወዳጆቹ ጋር በምስጢር እንዲደራጅ አጥብቆ ይመክራል። የተደራጁ ስብስቦች ግንቦት 7ን ማግኘት ወይም ግንቦት 7 እነዚህን ስብስቦች ማግኘት አስቸጋሪ አይሆንም። የኢትዮጵያ ወጣት ለለውጥ ዝግጁ ነው። የጎደለው ድርጅት ነው። የጎደለውን ማሟላት ደግሞ የሁላችንም ግዴታ ነው።
ግንቦት 7:የፍትህ፣ የነፃነትና የዲሞክራሲ ንቅናቄ፣ የዩኒቨርስቲ ተማሪዎች በወያኔ ስልጠናዎች ላይ ተቃውሞ ለማሰማት በመድፈራቸው የተሰማውን ደስታ ይገልፃል። ይህ ክስተት ወጣቱ ለለውጥ የተዘጋጀ እንደሆነ በአመላካችነት ወስዶታል። ይህ የለውጥ ፍላጎት በድርጅት ካልታገዘ ውጤት ስለማያመጣ ወጣቱ በትናንሽ ሕዋሶች ራሱን እንዲያደራጅ ይመክራል። ይህንን ካደረግን የወያኔ ፋሺስታዊ አገዛዝን የምናስወግድበት ጊዜ ሩቅ አይሆንም።
ድል ለኢትዮጵያ ሕዝብ!!!

ለነጻነት የሚደረግ እውነተኛ ትግል

ገዛኸኝ አበበበ

ወያኔ ኢህአዲግ የስልጣን ወንበሩን በሀይል ከተቆናጠጠበት ጊዜ ጀምሮ በስልጣን በቆየባቸው በሃያ ሶስት አመታቶች በየጊዜው በህዝባችን ላይ የሚያደርሰው ግፍ እና ጭቆና ከእለት ወደ እለት እየጨመረ መምጣቱ በአደባባይ የሚታይ እውነታ ሲሆን ከዚህም ጨቋኝና ገዳይ ስርዓት የተነሳ የሀገሪቷ ዚጓች  በሀገራቸው ላይ በሰላም መኖርና የነጻነትን ሀየር መተንፈስ በማይችሉበት ክፉ ሁኔታ ውስጥ ይገኛሉ::

በአሁኑ ጊዜ ከማንኛውም ጊዜ በተለየ መልኩ ገበሬው፣  ተማሪው፣  ፣ አስተማሪው ፣ ነጋዲው፣ ጋዜጠኛው ፣ ስፖርተኛው፣ ዘፋኙ፣ አርቲስቱ፣ ወዘተ......በማንኛውም እርከን ላይ የሚገኙ የህብረተሰብ ክፍሎች በሀገራቸው ላይ በነጻነት መኖርን ስላልቻሉ   ባገኙት አጋጣሚ ሁሉ ሀገራቸውን ትተው እየወጡ በየጊዜው ለስደት ሲዳረጉ ይታያሉ:: ምክንያቱም ዜጓች በሀገራቸው በተረጋጋ ሁኔታ ለመኑር የሚያስፈልጋቸው  ዋንኛውና ቁልፉ ነገር ሰላም እና ነጻነት ነውና::ማንኛውም ሰው በሚኖርበት ሀገር በሚኖርበት ሰፈር ወይም አካባቢ እና በሚኖርበት ቤት ውስጥ ሳይቀር በሰላምና በነጻነት መኖርን ይፈልጋል:: ነጻነት በምንም ዋጋ ሊተመን የማይችል ትልቅ ጸጋ ነውና:: ሰላም እና ነጻነት በሌለበት ሀገር የሚኖሩ ዜጓች፣   መብታቸው ይረገጣል ፣ ነጻነታቸው ይታፈናል  ዜጓች ለእስር፣ ለሞት፣ እና ለስደት ይደጋሉ::በሀገራችን ኢትዮጵያ የምናየውም ይህንኑ ነው::

 እንደ አለመታደል ሆኖ ሀገራችን ኢትዮጵያም በአለም ላይ ካሉት ሀገራት በግንባር ቀደምነት  የሰው ልጆች ነጻነታቸውን እና መብታቸውን ከሚገፈፉበት ሀገር ተርታ እንደምትገኝና የሀገሪቷ ዜጓች በጨቋኙ ገዥ ስርዓት ነጻነታቸውን ተገፈው ባሪያ ሆነው የሚኖሩበት ሀገር እንደሆነች በየጊዜው ከሚወጡ አለም አቀፍ ሪፖርቶች መረዳት ይቻላል::::

 ዜጓች በከፍተኛ ሁኔታ ለስደት እየተዳረጉ ባሉበት በአሁኑ ወቅት በኢትዮጵያ ሕዝብ ላይ የሚደረገው አፈና፣ እስራት እና ግድያው በከፍተኛ ሁኔታ ተባብሶ የሚገኝ ሲሆን ይህም በገሃድ እየታየ ያለ እውነታ ነው :: በእነዚህ ሃያ ሶስት አመታቶች በፋሺስቱ የወያኔ ቡድን ነጻነቱ እየተገፈፈና መብቱ እየተረገጠ ያለው የኢትዮጵያ ሕዝብም ከእንግዲህ ወዲህ ይሂን የወረበሎች ቡድን እሽሩሩ እያሉ የመኖር አቅም ያለው አይመሰልም :.: በአሁኑ ጊዜ ከየአቅጣጫው ከሚሰሙ ነጻነት ናፋቂ የኢትዮጵያኖቸ ሕዝብ ጩኸት ድምጽ መረዳት እንደሚቻለው ሕዝባችን ለወያኔያዊ አንባገነን ስርዓት መገዛትን የጠላበትና ከመቺውም ጊዜ በተለየ መልኩ እምቢ አሻፈረኝ ብሎ ነጻነቱን ለማስመለስ በአንድነት ለመቋም የተነሳበት ዘመን ላይ የደረሰን በሚያስመስል መልኩ ከየቦታው የሚሰማው የነጻነትና የሰላም ናፋቂዎች የጀግንነት ድምጽ ምስክር ነው::

በቅርቡ እንኳን እንደምናየው የግንቦት 7 የፍትህ፣ የነፃነትና የዲሞክራሲ ንቅናቄ ዋና ጸሀፊ የአቶ አንዳርጋቸው ጽጌን ከየመን ታግተው በወያኔ እስር ቤት ታስረው በግፍ እየተሰቃዩ እንዳለ ይታወቃል የነጻነት ታጋዩ አቶ አንዳርጋቸው በወያኔ ሴራ ከየመን ታግተው በወያኔ እጅ ላይ መውደቃቸው ከተሰማ ጊዜ ጀምሮ የኢትዮጵያ ሕዝብ የወያኔን አውሬነት በይበልጥ በመረዳት ከዳር እስከ ዳር በአንድነት መቋሙን እያስመሰከረ ሲገኝ የፖለቲካ ግለቱም ጨምሮ የአረመኔው የወያኔን ቡድን በከፍተኛ ሁኔታ አርበድብዶት እንደሚገኝ ወያኔ ከሚሰራው ስራና ከሚያደርጋቸው ድርጊቷች ማወቅ ይቻላል::የአቶ አንዳርጋቸውን መታሰር ተከትሎ  እየከረረ ያለውን የሕዝብን ቁጭትና ቁጣ ለማጥፋት በሚያስመስል መልኩ ይኼ አረመኔው መንግስት በአሁኑ ጊዜ በሀገር ቤት በሰላማዊ መንገድ ለመብታቸው እና ለኢትዮጵያ ሕዝብ ነጻነት በህጋዊ መንገድ እንኮን ሳይቀር እየታገሉ ያሉትን ሰዎች ከየመንገዱ እየለቀመ እስር ቤት አስገብቶ እያሰቃያቸው እንዳለ ይታወቃል ::ይህንንም ተከትሎ  ሁላችንም እንደምናውቀው  የአንድነት ፓርቲ ሥራ አስፈጻሚ አባልና ሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ሀብታሙ አያሌው፣ የፓርቲው ምክር ቤት አባል አቶ ዳንኤል ሺበሺ፣ የአረና የሕዝብ ግንኙንት ኃላፊ አቶ አብረሃ ደስታና የሰማያዊ ፓርቲ ምክር ቤት ምክትል አፈ ጉባዔ አቶ የሸዋስ አሰፋን ጨምሮ ሌሎችም እጅግ ብዙ ለየጻነታቸው የሚታገሉ ኢትዮጵያን ወገኖቻችን  የወያኔ መንግስት በግፍ  አስሯቸው እያሰቃያቸው እንደሚገኝ ይታወቃል::

ይኼ መንግስት እሱን  የሚቃወሙትን ሰዎችንና በድፍረት እየተጋፈጡት ያሉትን የፖለቲካ መሪዎች አአሸባሪ የሚል የታርጋ ስም እየለጠፈላቸው ወደ እስር ቤት መወርወር የተጠናወጠው ክፉ ባህሪው ሆኖል:: የፖለቲካ መሪዎችንና የፖለቲካ ሰዎችን ማፈንና እየያዙ ወደ እስር ቤት መወርወር ይበልጥኑ ትግሉን እያከረረውና የኢትዮጵያን ሕዝብ ይበልጥኑ ለነጻነቱ በመታገል ለድል እያነሳሳው  ነው እንጂ ፈጽሞ ከትግል ወደ ኋላ እይመለሰው እንዳይደለ የወያኔ ባለስልጣኖች ጠንቅቀው ሊያውቁት የሚገባቸው ነገር ይመስለኛል:: የኢትዮጵያ ሕዝብ ነጻነትን ተጠምቷል ::Freedom is more than food  በአሁኑ ሰአት በሀገር ቤትም ሆነው በሰላማዊ መንገድ እየታገሉ ያሉ የፖለቲካ ድርጅቶች ይሁኑ ወይም በውጭ ሆነው በሁለገብ ትግል እየታገሉ ያሉ የፖለቲካ ድርጅቶች አላማቸውም ሆነ ጥያቄያቸው አንድ ነው የስልጣን ወይም የገንዘብ ሳይሆን የነጻነት ጥያቄ ነው :: የኢትዮጵያ ሕዝብ ነጻነት ያስፈልገዋል   ::እኛም  ሰላምና ነጻነት የናፈቀን ህዝቦች መብታችንን ለማስከበር ለነጻነት ከሚታገሉ ድርጅቷች ጎን በመቆም ለነጻነታቸው ሲታገሉ  በወያኔ አንባገነን ትህዛዝ ወደ እስር እየተወረወሩ እና በግፍ እየተሰቃዩ ላሉ ወገኖቻችን  ከመንኛውም ጊዜ በተለየ መልኩ ሀገራዊ ስሜት ተሰሞቶን ልንጮህላቸውና የእነሱንም ፈለግ በመከተል ከሁለት አስርት አመታት በላይ የዜግነት መብታችንና እየረገጠና ነጻነታችንን እያፈነ ህዝባችንን ለስደት እያደረገ ያለውን ያለውን ይኼን ሰይጣናዊና አረመናዊውን  ስርዓት በማንኛውም መንገድ በመታገል፣እውነተኛ ሰላምና ነጻነት በኢትዮጵያ ምድራችን እንዲመጣ ለማድረግ የወያኔን መንግስት ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ዳግም እንዳይነሳ  አከርካሪውን ሰብሮ ለመጣል በእውነተኛ ኢትዮጵያዊ ስሜት መነሳት ይጠበቅብናል እላለው::

  ድል ለኢትዮጵያ ሕዝብ !!!


ሰማያዊ ፓርቲ “ለተማሪዎች በግዳጅ የሚሰጠውን ካድሬያዊ ስልጠና እና ትውልድን የማኮላሸት ሴራ አጥብቀን እናወግዛለን!” አለ

August21/2014
ሰማያዊ ፓርቲ ዛሬ ባወጣው መግለጫው ለተማሪዎች በግዳጅ እየተሰጠ ያለውን ካድሬያዊ ስልጠና በማውገዝ ኢሕአዴግ እየሰራ ያለውን ትውልድን የማኮላሸት ሴራ አጥብቀን እናወግዛለን አለ። መግለጫው እንደወረደ እነሆ፦
blue partyላለፉት 23 ዓመታት ህወሓት/ኢህአዴግ ስራዬ ብሎ ካዳከማቸውና ጉዳዬ ከማይላቸው ዘርፎች ውስጥ የሚመደበው የትምህርት ስርዓቱ ሲሆን ይህም ከኢህአዴግ ስህተቶች ሁሉ ዋነኛው እና አሳፋሪ ተግባሩ ነው፡፡ ለሁለት አስርት አመታት ትውልዱን በማምከን በሀገሩ ተስፋ እንዲቆርጥ ከገፉት ጉዳዮችም ግንባር ቀደሙ የህወሓት/ኢህአዴግ የተምታታበት የትምህርት ፖሊሲ መሆኑም ይታወቃል፡፡ ትምህርት ለአንድ ሀገር እድገት የጀርባ አጥንት መሆኑ እየታመነ የትምህርት ስርዓቱ ሆን ተብሎ በንቀት እና በዝርክር አሰራር እንዳያድግና ጥራት እንዳይኖረው ኢህአዴግ እየተጋ አሁን ድረስ ዘልቋል፡፡

በዚህ አይነቱ አጥፊ አካሄድ ምክንያትም ሀገራችን በዓለም ደሃ ሀገራት ተርታ ቀዳሚዋ ሆናለች፡፡ የተማረ እየተገፋ በስራ አጥነት ሲንከራተት እና ለስደት ሲዳረግ በካድሬነት የስርዓቱ አገልጋይ መሆን ደግሞ በተቃራኒው ተጠቃሚ እያደረገ ይገኛል፡፡ በተለይም ተማሪዎች በዩኒቨርስቲ ቆይታቸው የገዢው ፓርቲ አባል እንዲሆኑ ሲገደዱ መቆየታቸውና የኢህአዲግ አባል ካልሆኑም ስራ ሊያገኙ እንደማይችሉ እየተነገራቸው በፍራቻ ለአባልነት የተመዘገቡ ብዙዎች እንደሆኑ የአደባባይ ሚስጥር ነው፡፡ በዚህ ሳያበቃ አሁን አሁን ደግሞ የገዢውን ፓርቲ ያረጀና ያፈጀ ኋላቀር አስተሳሰብና ርዕዮተ-ዓለም በተማሪዎች ላይ ለመጫን በየዓመቱ መጀመሪያ ‹ስልጠና› በሚል ፈሊጥ በጀት በጅቶ በግድ ሊግታቸው እየሞከረ ይገኛል፡፡
በዚሁ በያዝነው ወርም በሁሉም ዩኒቨርስቲዎች ተማሪዎች እንዲሰበሰቡና ስልጠና እንዲወስዱ ጥሪ የተላለፈ ሲሆን ስልጠናውን ያልተከታተለም መደበኛ ትምህርቱን እንደማይቀጥል ማስፈራሪያ አይሉት ማሳሰቢያ በገዢው ፓርቲ በኩል ተላልፏል፡፡ ሌላው አስገራሚ ዜና ደግሞ ተማሪዎቹ በግድ ስልጠናውን እንዲወስዱ መገደዳቸው ሳያንስ ወደ ግቢ ከገቡ በኋላ ተመልሰው መውጣት እንደማይችሉ መሰማቱ ነው፡፡ ይህም ኢህአዴግ ካድሬዎቹን የሚያሰለጥንበት ዝግ የስብሰባ ስልት መሆኑ ጉዳዩን የበለጠ አስገራሚ ያደርገዋል፡፡
ህወሓት/ኢህአዴግ ይህንን ስልጠና ሲያካሂድም፡-
1. ህግን በጣሰ መልኩ የትምህርት ማዕከላትን የፖለቲካ ማራመጃ እና የአንድ ፓርቲ ርዕዮተ-ዓለም ማስፈፀሚያ አድርጓል፡፡
2. ይህን ፋይዳ ቢስ ስልጠና በሁሉም ዩኒቨርሲቲዎችና ከ800.000 በላይ ለሚሆኑ ተማሪዎች በሚሰጥበት ወቅት ከፍተኛ የህዝብ ሀብት እያባከነ ይገኛል፡፡
3. ተማሪዎች የእረፍት ጊዜያቸውን በነፃነት ማሳለፍ ሳይችሉ በአስቸኳይ ወደ ዩኒቨርስቲዎች እንዲመለሱ ተገድደዋል፡፡
4. በሚሰጠው ስልጠናም ላይ በአክራሪነት በብሔርተኝነትና በመሳሰሉት ጉዳዩች ሽፋን በተማሪዎች ዘንድ መርዛማ ጥላቻን እየረጨ ይገኛል፡፡
5. በአጠቃላይ በስልጠናው ወቅት ርካሽ የፕሮፖጋንዳ ስልትን በመጠቀም መጪውን ምርጫ በማምታታት ለማለፍ እየሞከረ ሲሆን ይህም በአምባገነንነቱ ቀጥሎ ህብረተሰቡን አማራጭ ለማሳጣትና ሀገሪቷን ወዳልተፈለገ አለመረጋጋት ሊወስድ እየሞከረ መሆኑን ያሳያል፡፡

በመሆኑም ሰማያዊ ፓርቲ ይህን የገዢው ፓርቲ ህገ ወጥ አድራጎት አጥብቆ እያወገዘ ጉዳዩን እየተከታተለም አቋሙን ይፋ የሚያደርግ መሆኑንን ይገልፃል፡፡ ተማሪዎችም በዚህ ህገ ወጥ ተግባር ሳይደናገጡ ያለምንም ፍርሃት ህጋዊ በሆነ መንገድ ይህን ካድሬያዊ ስልጠና በማውገዝ፣ የገዢውን ፓርቲ ድብቅ ሴራ በማጋለጥ እና ለህወሓት/ኢህአዴግ የተለመደ አጥፊ ፕሮፖጋንዳ ባለመታለል ተማሪዎች በአንድነት እንዲቆሙ ሰማያዊ ፓርቲ ጥሪውን ያስተላልፋል፡፡

ነሀሴ 15/2006 ዓ.ም ሰማያዊ ፓርቲ
ኢትዮጵያ በክብር ለዘላለም ትኑር!

New charges against Ethiopian publications further diminish critical voices (CPJ)

August21/2014
Five independent magazines and a weekly newspaper have been charged by Ethiopia’s Justice Ministry, a move that may add to the long lists of shuttered publications and Ethiopian journalists in exile. In a press release issued August 4, the ministry accused the journals of publishing false information, inciting violence, and undermining public confidence in the government, news reports said.
The ministry said it pressed charges after running out of patience with the publications for “encouraging radicalism and terrorism.” The state broadcaster aired the ministry’s announcement, but none of the publications received the charge sheet, local journalists told me. The six independent publications are Afro Times, a weekly newspaper, and magazines Addis Guday, Enku, Fact,Jano, and Lomi. All are popular alternatives to the state-run press, which espouses an increasingly positive narrative. Local journalists and news reports said the charges could be a way for the ruling party to silence critics ahead of elections expected in May 2015.
Repeated calls to the Justice Ministry and a government spokesman went unanswered.
The ministry’s charges are not unexpected. In February, the pro-government Ethiopian Press Agency, a state-controlled news wire, conducted a study analyzing the content of the publications and concluded they were responsible for inciting violence and upholding opposition viewpoints, according to local news reports. Many local journalists at the time said they feared the study would be used as a pretext to target the publications later. “It’s a strategy the government uses when they want to stop a newspaper,” Habtamu Seyoum, an editor at popular magazineAddis Guday, told me by phone. “They will prepare an article claiming that a journalist or media house should be closed. The next step is to jail or close the media house; it’s done as a sort of formality.”
The Justice Ministry’s charges reflect a trend of authorities silencing critical media. Since 2009, the government has banned or suspended at least one critical independent publication per year, according to CPJ research.
Addis Guday stopped publishing on August 9. Several staff went into exile shortly after the government announcement, fearing imminent arrest. CPJ research shows their fears are likely justified. “We had police surrounding our offices, insults printed by the government press, constant phone threats–and now [these charges]. It was just too much,” Addis Guday Deputy Editor Ibrahim Shafi told CPJ. A week before the staff members fled, police raided their offices twice in one week, ostensibly to investigate financial records, he said.
The country’s politicized justice system coupled with the ruling party’s near zero-tolerance approach to criticism has led a steady flow of journalists to flee the country. CPJ has directly assisted at least 41 journalists fleeing Ethiopia since 2009, and the total number of exiles is likely higher. Those who have fallen out of favor with authorities, whether from independent or state media, feel exile or imprisonment are their only options.
Authorities arrested another Addis Guday editor, Asmamaw Hailegeorgis, in Aprilon terrorism charges, and arrested photojournalist Aziza Mohamed in July on vague accusations of incitement. Ethiopian authorities have a penchant for sentencing journalists to jail after presenting charges, no matter how spurious the charges may be. Data collected from the registrar of Ethiopia’s Federal High Courtsuggest 95 percent of journalists accused by authorities are found guilty, according to TrialTrackerBlog.org, which publishes news about detained journalists in Ethiopia.
Lomi (“Lemon”) failed to print on August 8 and is unlikely to do so again, local journalists told me, because printers fear publishing anything that has fallen out of the ruling party’s favor. Last month, police searched Lomi‘s offices and accused the staff of working without a license, a charge they denied, local journalists said.
According to the state-run Addis Admas, all but one of the magazines failed to publish recently.
A court in the capital, Addis Ababa, summoned the general managers of three publications–FactAddis Guday, and Lomi–on August 13, but only the general manager of Lomi appeared, according to news reports. Local journalists told CPJ they expect the other three publications to be summoned to court soon.
CPJ was not able to reach journalists from Afro TimesEnkuFact, or Jano.
If these publications close down due to this latest government challenge, Ethiopia’s meager circulation of weekly independent publications–roughly 60,000 for a population of 90 million people–will decrease further. There is only one television station, run by the state, and out of five radio stations, three are staunchly pro-government. The state-run telecommunications company is the sole Internet service provider for a country with the second lowest Internet penetration rates in sub-Saharan Africa, according to the International Telecommunication Union. With limited independent voices, voters’ access to critical news sources and informed debate ahead of Ethiopia’s May 2015 elections may be negligible. The ruling party would probably not want it any other way.
[Reporting from Nairobi]
Tom Rhodes is CPJ’s East Africa representative, based in Nairobi. Rhodes is a founder of southern Sudan’s first independent newspaper. Follow him on Twitter: @africamedia_CPJ

መለስን ቅበሩት!(ተመስገን ደሳለኝ)

August 21, 2014

ከኢትዮጵያ ሀገሬ የደቀቀ ኢኮኖሚ ላይ በማን አህሎኝነት ወጪ ተደርጎ፣ ቅጥ ባጣ መልኩ በመላ አገሪቱ እየተከበረ ስላለው የቀድሞ አምባገነን ጠ/ሚኒስትር ሁለተኛ ሙት ዓመት ዝክርም ሆነ ሰውየውን ዛሬም በአፀደ-ህይወት ያለ ለማስመሰል እየሞከሩ ላሉት ጓዶቹ አንዲት ምክር ብጤ ጣል ማድረጉ ተገቢ ነው ብዬ ስለማስብ በአዲስ መስመር እንዲህ እላለሁ፡-

አብዮታዊው ገዥ-ግንባር ግንቦት ሃያ፣ የህወሓት ምስረታ፣ የብአዴን አፈጣጠር፣ የኦህዴድና የደኢህዴን ውልደት፣ የብሔር ብሔረሰቦች በዓል፣ የባንዲራ ቀን፣ የመከላከያ ሳምንት፣ የፍትሕ ሳምንት፣ የሕዳሴ ግድብ መሰረት ድንጋይ የተጣለበት… ጅኒ-ቁልቋል እያለ ዓመቱን ሙሉ በማይጨበጥ ተራ ፕሮፓጋንዳ ማሰልቸትን መንግስታዊ ኃላፊነት አድርጎታል፡፡ ይህ እንግዲህ ለቁጥር የሚያታክቱ፣ በነጭ ውሸት የታጨቁ እና በአብዮታዊ ዲሞክራሲ ቅኝት የተንሸዋረሩ ‹ዶክመንተሪ ፊልሞቹ›ን ረስተንለት ነው፡፡

ይህ ሁሉ ያልበቃው ‹‹ጀግናው›› ኢህአዴግ ከጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ህልፈት ወዲህ፣ ወርሃ-ነሐሴንም እንደ ግንቦት ሃያው ሁሉ የሟቹን ታጋይነትና አብዮታዊነት፤ ሕዝባዊነትና አርቆ አስተዋይነት፤ የርዕዮተ-ዓለም ተራቃቂነትና የአየር ንብረት ተካራካሪነት፤ በፖለቲካ ቢሉ በኢኮኖሚ ቁጥር አንድ ጠቢብነትና ባለራዕይነት፤ ፍፁም ፃድቅነትና ሰማዕትነት…. የሚተረክበት ሲያደርገው ቅንጣት ታህል ሀፍረት አልተሰማውም፡፡ ሰሞኑን በ‹‹ኢትዮጵያ›› ቴሌቪዥን ግድ ሆኖብን ተመልክተንና ሰምተን በትዝብት ካሳለፍናቸው ‹‹መለስ፣ መለስ›› ከሚሉ የከንቱ ውዳሴ አደንቋሪ ድምፆች በተጨማሪ፣ የኦሮሞን ባሕላዊ ልብስ ሲያለብሱት፣ ሐረሪዎች ጋቢ ሲደርቡለት፤ በደቡብ የሚገኙ ብሔሮች የየራሳቸውን ባሕል የሚወክሉ አልባሳት ሲሸልሙት፣ ስለወላይታነቱ ሲመሰክሩለት…

ደጋግመን ለመመልከት ተገደናል፤ ይሁንና ድርጅቱ ስለ ቀድሞ ሊቀ-መንበሩ አልፋና ኦሜጋነት ለመስበክ ዙሪያ ጥምዝ ከዳከረለት ከእንዲህ አይነቱ የተንዛዛ ፕሮፓጋንዳ ይልቅ፣ በዚሁ የቴሌቪዥን መስኮት የቀረበ አንድ ጎልማሳ ‹‹መለስ ሁሉም ማለት ነው›› ሲል የሰጠው አስተያየት፣ ቅልብጭ አድርጎ ይገልፅለት ነበር ብዬ አምናለሁ፡፡ የዚህ አይነቱ ምጥን አስተያየትም በጥራዝ ነጠቅነት ዘላብዶ የኋላ ኋላ በሀፍረት ከማቀርቀር ያድናል፡፡ ለምሳሌ እናንተ የግንባሩ ካድሬዎች ስለመለስ ምሁርነት ለመናገር ስትዳዱ ሁሌ የምትደጋግሙት፣  ያንኑ የአብዮታዊ ዴሞክራሲ አርቃቂነቱ እና የልማታዊ ዴሞክራሲያዊ መንግስት ኀልዮት አዋቃሪነቱ ነው፡፡ ግና፣ ይህ ‹‹ንድፈ-ሃሳብ›› ተብዬ ራሱ በርዕዮተ-ዓለምነት ለመጠራት የማይበቃ የተውሸለሸለ ጭብጥ ስለመሆኑ በርካታ ምሁራን በጥናቶቻቸው ከማስረገጣቸው ባሻገር፣ አገሪቷን ለከባድ ኢኮኖሚያዊ ድቀት፣ ሕዝቧን ደግሞ ለጥልቅ ድህነት መዳረጉን ብቻ ማስታወሱ በቂ ይሆናል፡፡ ስለልማታዊ መንግስት አዋጭነት በብቸኝነት እንደተከራከረ ተደርጎ የሚለፈፈውን እንኳን ንቆ መተው ሳይሻል አይቀርም፡፡ ከታንዲካ ማካንደዋሬና መሰል የፅንሰ-ሃሳቡ አበጂዎች የዘረፋቸውን መከራከሪያዎች ማን ዘርዝሮ ይዘልቀውና፡፡ ‹መለስን ቅበሩት› የምለውም፣ እንዲህ ያሉ አስነዋሪ ማንነቶቹን ማስታወስ ስለሚያም ነው፡፡

እናም እውነት እውነት እላችኋለሁ፡- ስለሰውዬው የምትነግሩን እና የምታስቀጥሉት ‹ሌጋሲ›ም ሆነ የምትተገብሩት ረብ ያለው አንድም ራዕይ የለምና ዝም፣ ፀጥ ብላችሁ የምራችሁን ቅበሩት፡፡ እስቲ! ኦጋዴንን ተመልከቱ፤ ካሻችሁም ወደ አኝዋኮች ተሻገሩ፤ ያን ጊዜ እናንተ በአርያም የሰቀላችሁት ሰው፣ ለነዚህ ሁለት ብሔሮች የቀትር ደም የጠማው ጨካኝ መሪ እንደነበር፣ በክፋት ትዕዛዞቹ ጥፋት ከተረፈ ጠባሳ ትረዱታላችሁ፡፡ ለአቅመ-ሔዋን ያልደረሱ ህፃናት በሰልፍ የሚደፈሩባት፣ ወጣቶች እንጀራ ፍለጋ በተስፋ-ቢስነት ጥልቁን ውቅያኖስ ሰንጥቀው ለመሰደድ የማያመነቱባት፣ የጤና ኬላ ማግኘት ተስኗቸው በልምሻ የሚባትቱ ብላቴኖችን በአቅም-የለሽነትና በቁጭት የምናስተውልባት ደካማ አገር አስረክቦን እንዳለፈ ከወዴት ተሰወረባችሁ? ከቀዬዎቻቸው በጉልበት ለተፈናቀሉ ወገኖች በመቆርቆር ‹‹ሕግ ይከበር!›› ባሉ በየጉራንጉሩ ወድቀው እንዲቀሩ የተፈረደባቸው ጎበዛዝትን ሬሳ እንድንቆጠር ያደረገን ደመ-ቀዝቃዛ ‹መሪ› እንደነበረስ ስንት ጊዜ እያስታወስን እንቆዝም? ቀደምት አባቶች ወራሪውን ፋሽስት ለማንበርከክ የተዋደቁባቸው ጢሻና ኮረብቶች በዚህ ዘመን የዜጎች ወደሞት አገራት መሸጋገሪያ ጽልማሞቶች የሆኑት በማን ሆነና ነው? ከሕግ ተጠያቂነት ቢያመልጥ፣ ከታሪክ ተወቃሽነት ልትታደጉት የምትችሉ ይመስላችኋልን?

…ይልቅ እመኑኝ! ፀጥ ብላችሁ ላንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ጥልቅ ጉድጓድ ቆፍራችሁ ቅበሩት! ላይመለስ በመሄዱም እንደ ግልግል ቆጥራችሁት እርሱት!! መቼም በገዛ ራሱ ሕዝብ ላይ ትውልዶች ይቅር ሊሉት የሚሳናቸውን ይህን መሰሉ መከራ ላዘነበ ሰው በአፀደ-ስጋ ሳለም ሆነ በበድን የሙት መንፈሱ ስር በየዓመቱ ለአምላኪነት መንበርከክ፣ የናንተን አልቦ ማንነት እንጂ ሌላ አንዳች የሚነገረን ቁም ነገር ጠብ ሊለው አይችልም፡፡ ይህም ሆኖ ለመለስ አምልኮ እጅ መስጠት አሳፋሪነቱ፣ ለካዳሚዎቹ ብቻ መሆኑን መስክሮ ማለፉ የቀሪዎቻችን ዕዳ እንደሆነ መገንዘብ አለብን፡፡