Wednesday, August 6, 2014

ለጋዜጠኛ አዚዛ መሐመድና የሰማያዊ ፓርቲ አባል ወይንሸት ሞላ የተፈቀደው ዋስትና ተከለከለ

August6/2014
  • 135
    Share
aziza ena weyeneshetከአሸናፊ ደምሴ
በአንዋር መስጊድና አካባቢው ሐምሌ 11 ቀን 2006 ዓ.ም በተፈጠረ ግጭትና ሁከት ተሳትፈዋል በሚል ፖሊስ ምርመራ እያደረገባቸው ከሚገኙ 14 ተጠርጣሪዎች መካከል ጋዜጠኛ አዚዛ መሐመድና የሰማያዊ ፓርቲ አባል ወይንሸት ሞላን ጨምሮ ለሦስት ሰዎች ፍርድ ቤት ትናንት ጠዋት ፈቅዶት የነበረው የ5 ሺህ ብር የዋስትና መብት ከሰዓት በኋላ በፖሊስ በቀረበ ይግባኝ ውድቅ ሆኖ ዋስትናው ተከለከለ።
ሜክስኮ በሚገኘው የፌዴራሉ የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት የፖሊስ ኮሚሽን ጉዳዮች የምርመራ ጊዜ ቀጠሮ ማስቻያ ችሎት የዛሬ ሳምንት የተሰጣቸውን የጊዜ ቀጠሮ ተከትሎ በችሎት ካቀረቡት 14 ተጠርጣሪዎች መካከል የአዲስ ጉዳይ መጽሔት ፎቶ ጋዜጠኛዋ አዚዛ መሐመድና የሰማያዊ ፓርቲ የብሔራዊ ምክር ቤት አባል የሆነችውን ወ/ት ወይንሸት ሞላን ጨምሮ አራት የፖሊስ አባላት (ማለትም አንድ ኢንስፔክተር፣ አንድ ምክትል ኢንስፔክተርና አንድ ምክትል ሳጅንና አንድ የኮንስታብል ማዕረግ ያላቸው) እና ሌሎች ስምንት ተጠርጣሪዎች በችሎች ሲያቀርብ የተቀሩት ከሁለተኛው የጊዜ ቀጠሮ በኋላ ፖሊስ ምርመራዬን ጨርሼባቸዋለሁ ሲል ማሰናበቱን ለፍርድ ቤት ማስታወቁ ይታወሳል።
አሁን ድረስ በምርመራ ላይ የሚገኙት ተጠርጣሪዎች ጠበቃ ያልቆመላቸው ሲሆን፤ በትናንት ጠዋቱ የችሎት ውሏቸውም በባለፈው የጊዜ ቀጠሮ ወቅት ለፍርድ ቤቱ ባቀረቡት የዋስትና ጥያቄያቸው መሠረት ፍርድ ቤቱ፤ አዚዛ መሐመድ፣ ወይንሸት ሞላ እና ኡዝታዝ መንሱር የ5 ሺህ ብር ዋስ አቅርበው እንዲሄዱ ትዕዛዝ ቢሰጥም፤ በቀደመው ችሎት ያቀረባቸውንና ምላሽ ያላቀረበባቸውን የዋስትና መቃወሚያዎች ፖሊስ ለችሎቱ አቅርቦ አስረድቷል። ይኸውም ምርመራዬን አልጨረስኩምና ዋስትና ሊፈቀድላቸው አይገባም፤ በሕክምና ላይ ያሉና ጉዳት የደረሰባቸውን የፖሊስ አባላትንም መጨረሻ ማወቅ ያስፈልጋል በሚል ለፍርድ ቤቱ ባቀረበው ይግባኝ መሠረት ችሎቱ ጠዋት ላይ የተፈቀደ ዋስትና በከሰዓት ላይ ውድቅ ሆኖ ወደ አዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ማረፊያ እንዲመለሱ ተደርጓል።
የምርመራ ተግባራቶቼን አላገባደድኩም ሲል ተጨማሪ የጊዜ ቀጠሮን የጠየቀው ፖሊስ በጥቁር አንበሳ እና በፖሊስ ሆስፒታል የሚገኙትንና በብጥብጡ ወቅት ጉዳት ደርሶባቸዋል የተባሉትን ሰዎች ሁኔታና ቃል ተቀብሎ ለማቅረብ ፍርድ ቤቱን በጠየቀው ተጨማሪ የጊዜ ቀጠሮ መሠረት የ7 ቀናት የምርመራ ጊዜ የተፈቀደለት ሲሆን፤ ለመጪው ነሐሴ 7 ቀን 2006 ዓ.ም ተለዋጭ ቀጠሮ ተሰጥቷል።

እነ ወይንሸት ሞላ ዋስትና ተከልክለው እንደገና ታሰሩ

Augest 6/2014
(ኢ.ኤም.ኤፍ) በዛሬ ጠዋት ዘገባችን ወይንሸት ሞላ, አዚዛ አህመድ እና ኡስታዝ መንሱር እያንዳንዳቸው በ5ሺህ ብር ዋስትና ከ እስር ቤት እንዲወጡ ፍርድ ቤቱ ት እዛዝ ሰጥቶ ነበር:: ሆኖም ይህ ውሳኔ ከተሰጠ በኋላ ዳኞቹን በማስፈራራት ይሁን በምን ባልታወቀ መንገድ ጉዳዩ በቢሮ ውስጥ እንዲታይ ተብሎ; አቃቤ ህጉ ለፖሊስ ተጨማሪ ሰባት የምርመራ ቀናት እንዲሰጠው በጠየቀው መሰረት; በዋስ እንዲፈቱ ተብለው የነበሩት ወይንሸት, አዚዛ እና ኡስታዝ መንሱር እንደገና እንዲታሰሩ ተብሏል::
ከሁለት ሳምንት በፊት አርብ የጁም ዓ ቀን በስፍራው ተገኝተው ከነበሩት መካከል የሰማያዊ ፓርቲዋ ወይንሸት ሞላ እና የአዲስ ጉዳይ መጽሄት ፎቶ አንሺ አዚዛ አህመድ በማይገባ ሁኔታ ታስረው መክረማቸው ይታወሳል። በተለይም ወይንሸት ሞላ ላይ በደረሰው ድብደባ እጇ እስከመሰበር ደረጃ ደርሶ እንደነበር የሚታወስ ነው። ዛሬ ያገኘነው መረጃ እንዳመለከተው ከሆነ ሁለቱም ሴት እህቶች በ5ሺህ ብር ዋስ ለግዜው ከ እስር እንዲፈቱ ልደታ የሚገኘው ከፍተኛ ፍርድ ቤት ውሳኔ ከሰጠ በኋላ ውሳኔው ተቀልብሶ, ለሰባት ቀናት እንደገና እንዲታሰሩ ተደርጓል።
ወይንሸት ሞላ

Ethiopians held huge protest in Washington D.C.(Video)

Augest6/2014
Washington D.C. – Huge Ethiopians protest against TPLF official’s presence at US Africa Summit 2014. (Reporting by Captain Abraham Takele). Watch the video below.

Is the US still giving aid money to Africa’s dictators?

Augest6/2014
By Lorenzo Piccio
desalegneFive years ago, during his first visit to sub-Saharan Africa as U.S. president, Barack Obama memorably told Ghana’s parliament that “Africa does not need strong men. It needs strong institutions.” And months before his re-election, Obama stressed strengthening democratic institutions as one of four pillars of his administration’s sub-Saharan Africa strategy.
“Our message to those who would derail the democratic process is clear and unequivocal: the United States will not stand idly by when actors threaten legitimately elected governments or manipulate the fairness and integrity of democratic processes,” Obama said in the strategy.
Obama’s strident and lofty rhetoric on democracy in Africa may make for odd bedfellows this week as 50 African heads of state gather in Washington for the first-ever U.S.-Africa Leaders Summit.
While sub-Saharan Africa as a whole has made marked progress toward democracy and institution building since the 1990s, more than a dozen of the African leaders expected in Washington can aptly be called strongmen — President Yoweri Museveni of Uganda and President Paul Kagame of Rwanda included.
Source:-devex.com

Tuesday, August 5, 2014

የሕወሓት ጄኔራሎች ሲታመሱ ዋሉ ። በሰራዊቱ ውስጥ አለመተማመን ነግሷል።

August5/2014
ምንሊክ ሳልሳዊ
በጥርጣሬ/ግምት ካልሆነ በቀር አስራ አራቱ መኮንኖች የት እንደገቡ አይታወቅም።
ሁለት ከፍተና የጦር መሃንዲስች ዱካቸው ደብረዘይት ከሚገኘው እስር ቤት ተገኝቷል።


ወደ መቀሌ ከዲያስፖራው ጋር ለዘረፋ የንግድ ሽርክና ኢንቨስተሮች ለመመልመል ያመሩት ጄኔራሎች ሳይቀሩ በምን እንደመጡ በማይታወቅበት ሁኔታ አዲስ አበባ ደርሰው የመሃል አገር መኮንኖች መጥፋትን ተከትሎ ያመጣውን ውጥረት በስብሰባ ሲያሹት እና ከተለያዩ ወታደራዊ ደህንነቶች መረጃ ሲሰበስቡ እንደዋሉ ታውቋል።

በሰራዊቱ ውስጥ አለመተማመን የተፈጠረው ከምን የመነጨ ነው የሚል ጥናት በዚህ ሳምንት በተካሄደበት የመሃል አገር መከላከያ መምሪያዎች ውስጥ አጋጣሚ በተገኘ መረጃ 16 ከፍተኛ የጦር መኮንኖች የት እንደገቡ አይታወቅም ሲል ሪፖርት ያቀረበው የወታደራዊ ደህንነት ቡድን የቀረበለትን ጥቆማ ለበላይ አካላት ሪፖርት ሳያድርግ ፍተሻውን አጧጡፎት የነበረ ቢሆንም ምንም አይነት ፍንጭ ባለማግኘቱ ትላንትና የተነገረው የበላይ አካል በከፍተኛ ድንጋጤ ተውጦ የዋለ መሆኑን ለጦር ክፍሎቹ ቅርብ የሆኑ ምንጮቻችን ከመከላከያ ያደረሱን መረጃ ጠቁሟል።

ከመሃል አገር በተለያየ የጦር መምሪያ ውስጥ ተመድበው ይሰሩ የነበሩት እና የአንድ ኮርስ ምሩቅ ናቸው የተባሉት ወታደራዊ መኮንኖች ውስጥ የሕወሓት ጄኔራሎች ላይ ጥርሱን እንደነከሰ የሚነገርለት ኮሎኔል አለም የሚባለውን የተንቤን ተውላጅ ጨምሮ አስረ አንዱ ወደ ደቡብ ሱዳን ዘልቀው ገብተዋል የሚል መረጃዎች ቢኖሩም እስካሁን ማረጋገጥ እንዳልቻለ ለመከላከያ ደህንነት ቢሮ ምንጮቻችን የገለጹ ሲሆን የሶስቱ ዱካ አለመገኘቱን እና ሁለት ከፍተኛ የጦር መሃንዲሶች ከየት ታፍነው በማን ታፍነው እንደተወሰዱ ሳይታወቅ በደብረዘይት የምድር ውስጥ እስር ቤት እንደሚገኙ ተረጋግጧል።

የሕወሓት ጄኔራሎችን ያመሳቸው ጉዳይ የተንቤን ተወላጆች ሌሎች የደቡብ እና የአማራ ተወላጆች ተያይዞ መጥፋት ሲሆን እንዲሁም በጦር ሰራዊቱ ውስጥ እየላላ መጥቷል ሲሉ የደነፉበት የወታደራዊ ደህንነት ቁጥጥር መላላት ለነገው የስልጣን እድሜያቸው ከፍተኛ ስጋት እንዳጠላበታ ያሳያል ሲሉ መረጃውን የላኩልን የመከላከያ ምንጮቻችን ተናግረዋል። በሙሉ የሃገሪት እዞች ከፍተኛ ቁጥጥር እና ፍተሻ እንዲካሄድ በዛሬው ስብሰባ ጥብቅ ትእዛዝ ያስተላለፉት የሕወሓት ጄኔራሎች በደቡብ እና በምእራብ ድንበሮች አከባቢ ያሉ እንቅስቃሴዎች እንዲፈተሹ በወጪ ገቢው ላይ ከፍተኛ ቁጥጥር እንዲደረግ እና የየቀኑ ሪፖርት እንዲላክ እንዲሁም በመሃል አገር ያሉ የቶር መኮንኖች በየቀኑ ለቅርብ አለቃቸው ዝርዝር የአባላት እንቅስቃሴ ሪፖርት እንዲያቀርቡ ጥብቅ ትእዛዝ አውርደዋል።እንዲሁም ተጨማሪ ወታደራዊ ደህንነቶች በየእዙ እንዲመደቡ አዘዋል።

በዚህ ዙሪያ ያለውን ጉዳይ በተመለከተ የወታደራዊ ደህንነት ሪፖርቶቹን እየተከታተልን የምናቀርብ መሆኑን ቃል እንገባለን።

“ስለእኔ አታልቅሱ!”(ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ )

August 5, 2014

“ዋይ ዋይ ከሚሉና ሙሾ ከሚያወጡ ሴቶችና ከሕዝቡ እጅግ ብዙዎች ተከተሉት፡፡ ኢየሱስ ግን ወደ እነርሱ ዘወር ብሎ እንዲህ አለ፡- እናንተ የኢየሩሳሌም ልጆች ለእኔስ አታልቅሱልኝ፤ ዳሩ ግን፡- መካኖችና ያልወለዱ ማኀፀኖች፣ ያላጠቡ ጡቶችም ብፁአን ናቸው የሚሉበት ጊዜ እነሆ ይመጣልና ለራሳችሁና ለልጆቻችሁ አልቅሱ፡፡” (የሉቃስ ወንጌል ም. 23 ቁ. 27-30) ከቅዱስ መጽሐፉ ይህን የመሲሁ የመጨረሻ ምክር የመረጥኩት (ምንም እንኳ ረቢው የተናገረው ስለመለኮታዊው ትምህርት ቢሆንም) ዓለማዊው ፍች የኢትዮጵያችንን የወቅቱን መንፈስ ለመረዳት ከማስቻሉም በዘለለ፤ በየጊዜው እያየን፣ እየሰማን ያለነውን የፖለቲካ ተቃውሞው የጥምዝምዞሽ መንገድ በአርምሞ ለመመርመር መልካም ምሳሌ ይሆናል በሚል እሳቤም ነው፡፡

የሠላማዊ ትግሉ መቀልበሻ ስልቶች

እፍኝ በማይሞሉ ፋኖዎች ከአርባ ዓመታት በፊት “ደደቢት” በተሰኘ የሰሜን በርሃ የተመሰረተው ህወሓት ከተራዘመ የትግል ጉዙ በኋላ፤ ታጋይ ሕላዊ ዮሴፍ “እልፍ ሆነናል” እንዲል፤ ራሱን አጠናክሮ “እልፍ” በመሆን ሥልጣን ይዞ፣ የሀገሪቷን አንጡራ-ሀብት አመራሩ መምነሽነሺያው ካደረገ፣ እነሆ ሃያ ሶስት ዓመታት እንደዘበት ነጎዱ፡፡ ርግጥ ነው ይህች የዳንኪራ እና ፌሽታ ዘመን እውን ትሆን ዘንድ፣ የቡድኑ ዋና ዋና መሪዎችም ሆኑ መላው ታጋይ (የበረከቱ ተቋዳሽ ባይሆንም) በቃላት ሊገለፅ የማይችል የመከራ ዓመታትን በቆራጥነት ማሳለፋቸው የሚስተባበል ታሪክ አይደለም፡፡ ሥልጣን እጃቸው ከገባ በኋላም የአገር ጥቅም መገበርን ጨምሮ እየገደሉ፣ እያሰሩና እያሰደዱ… በሕዝብ ላይ ወደር የለሽ ጭካኔን በመፈፀም ዘላቂነቱን እንዲህ ስለማስረገጣቸውም ተወርቶ የተዘጋ አጀንዳ ከሆነ ሰነባብቷል፡፡ ይሁንና ከዕለት ዕለት እየመረረና እየከፋ የመጣው ይህ ኩነት፣ ምድሪቷ የአንድ እውነት መዝጊያና የአዲስ ዓመት ምዕራፍ መክፈቻ ላይ መድረሷን ስለማመላከቱ ለመመስከር ጠቢብነትን አይጠይቅም፤ የዘመኑ መንፈስ እያሰማን ያለው “ፋኖ ተሰማራ”ም የሶስተኛው አብዮት ደውል ስለመሆኑ ለመረዳት የቀደሙ ነብያቶችን ትንበያ መጠበቅ አያሻም፡፡

ገዥዎቻችን፣ መግደልና ማሰርን ሱፍ ለብሶ፣ ከረባት አስሮ፤ ጠዋት ወደ ቢሮ ተገብቶ፣ ማታ የሚወጣበት መደበኛ ሥራ ከማድረጋቸውም ባለፈ፣ የሥልጣን ግዛታቸውን እንዲህ ነቅተው (ታጥበውና ታጥነው) ባይጠብቁት ኖሮ፣ ለሃያ ሶስት ዓመት ቀርቶ፣ ለሃያ ሶስት ሰዓት እንኳን በቤተ-መንግስቱ መቆየት እንደማይችሉ አብጠርጥረው ያውቁታል፡፡ የዚህ ጽሑፍ ፍሬ-ሃሳብም በዚህ መልኩ የሥልጣን ዕድሜውን ገና የማቱሳላን ያህል ማራዘም የሚፈልገው ኢህአዴግ፣ ተቃዋሚ ድርጅቶች የሚያቀነቅኑት የሠላማዊ ትግል አቅጣጫን የሚቀይስበትን እና የሚወስንበትን የሴራ ፖለቲካ፣ ለውጥ ፈላጊው ኢትዮጵያዊ ነቅቶ እንዲያከሽፈው መቀስቀስ ነው፡፡

ዛሬ በርካቶች በቁጭት እንደሚብሰለሰሉት ኢህአዴግ በመንበሩ ላይ ከሁለት አስርታት በላይ ተደላድሎ የመቆየቱ ምስጢር በውስጣዊ ጥንካሬው፣ አሊያም ሲቪል ጀግኖች በመጥፋታቸው ሳቢያ አይደለም (ወላድ በድባብ ትሂድና፤ ሀገሪቱ የሚሞትላት ጀግና ትውልድ ከመፍጠር መክና አታውቅም)፡፡ የግንባሩ ዋነኛ የጥንካሬ ምንጭ የተቃዋሚውንም ወገን የቤት ሥራ ጠቅልሎ እየሰራ በመሆኑ ነው ብዬ አምናለሁ፡፡ ወደኋላ ሄደን በአደረጃጀትም ሆነ በድጋፍ መሰረታቸው ‹‹የተሻሉ›› ሊባሉ የሚችሉ ተቀናቃኝ ፓርቲዎችን ሂደት ብንመረምር፣ መራራውን እውነታ እየጎመዘዘንም ቢሆን መጋታችን አያጠራጥርም፡፡ ለማሳያ ያህልም በአገዛዙ የማስቀየሻ እርምጃ ተጠልፈው ከከሸፉ ሕዝባዊ ንቅናቄዎች መካከል ጥቂቶቹን በአዲስ መስመር እንመልከት፡፡

ኦነግ

የኦሮሞ ነፃ አውጪ ግንባር፣ መለስ ዜናዊና ጓዶቹ ቆንጥረው ከሰጡት የሽግግር መንግስት ሥልጣኑ ተገፍቶ ከወጣ በኋላ ወደለመደው በርሃ በገባበት ወቅት፣ በአንፃራዊነት ቀድሞ መገንባት ከቻለው ጥንካሬ ባሻገር፣ በኦሮምኛ ተናጋሪው ማሕበረሰብ ዘንድ የሚሊዮኖችን ልብ ይበልጥ ማማለል ችሎ እንደነበረ የአደባባይ ሐቅ ነው፡፡ ወቅታዊውን የኃይል አሰላለፍ ጠንቅቆ የተረዳው “አባ መላ”ው ኢህአዴግም የጠብ-መንጃ ግብግቡ ከመጀመሩ አስቀድሞ፣ ከተማውን ለቆ ያልወጣውን የአመራር አባሉን ኢብሳ ጉተማን ወደ እስር ቤት ወረወረ፤ ይህንን ተከትሎም ኦነግ ከመቼውም ጊዜ በላይ በእልህና በቁጭት ተነሳስቶ አርሲና ሐረርን አስተባብሮ፣ ወለጋን በታንክ አቋርጦ፣ ባቱ ተራራን በመድፍ ጩኸት አንቀጥቅጦ፣ በባሌ ተሻግሮ ፊንፊኔ ላይ በድል ሊንጎማለል ነው ተብሎ ሲጠበቅ፤ በግልባጩ ዋና ፀሀፊው ሌንጮ ለታ እና የተወሰኑ መሪዎቹ በቦሌ በኩል በመመለስ “ወይ እኛንም አብራችሁ እሰሩን፤ አሊያም ጓደኛችንን መልሱልን?” በማለት ከመረጡት የኃይል ትግል ጋር የማይጣጣም ስልት ተግብረው አረፉት፤ በዚህም የልብ ልብ የተሰማው ኢህአዴግ፣ የድርጅቱን አባላትም ሆነ ኦሮምኛ ተናጋሪውን በጅምላ በ “ስመ-ኦነግ” እየወነጀለ ለአስከፊ እስር መዳረጉ፣ በክልሉ ላይ ከባድ ፍርሃት አነበረ፡፡ ይህ ፖለቲካዊ ስህተትም ለዛሬው ሽንፈቱ ዋነኛ ተጠቃሽ ሲሆን፤ የተቃውሞ ጎራ ትግሉንም ከሥርዓት ለውጥ ወደ እስረኛ ማስፈታት ያወረደ ቀዳሚ ኩነት ሆኖ በታሪክ ተከትቧል፡፡

መአሕድ

የፕ/ር አስራት ወልደየስ የመላው አማራ ሕዝብ ድርጅት (መአሕድ) ውድቀትም ከኦነግ ጋር ተመሳሳይ ነው፡፡ መአሕድ በምስረታው ማግስት ያገኘው መጠነ-ሰፊ የሕዝብ ድጋፍ፣ ህወሓት/ኢህአዴግ በ17 ዓመታት ከሰበሰበው ሁሉ ይልቅ እንደነበረ አይዘነጋም፡፡ ይህ አይነቱ ፈጣን ግስጋሴም ሊያስከትለው የሚችለውን የቁጣ ናዳ አስቀድሞ የተረዳው ‹‹ብልጣ-ብልጡ›› ኢህአዴግ፣ ሊቀ-መንበሩን ጉምቱ የሕክምና ሊቅ ጨምሮ ጥቂት የአመራር አባላቱን እስር ቤት ወረወረ፡፡ ከዚያማ ድርጅቱ ‹‹እታገልለታለሁ›› የሚለውን የፖለቲካ ሥልጣን የመቆጣጠር ዓላማውን ‹‹መሪዎቻችን ይፈቱ!›› ወደሚል አኮስሶ ባለበት ሲረግጥና ሲዳክር ለ13 ዓመታት ከቆየ በኋላ፣ በስተመጨረሻ ህላዊነቱ አክትሞ ወደ ሕብረ-ብሔር (መኢአድ) ድርጅትነት መሸጋገሩ ታወጀ፡፡ ክስተቱም አብዮታዊው ግንባሩ የተቃውሞ ጎራውን እንቅስቃሴ ወደፈለገው አቅጣጫ መዘወሩን በሚገባ እንደተካነበት ያስረገጠ ሆኖ አልፏል፡፡

ቅንጅት

ዛሬ ዛሬ እንደ ንግስት ሳባ ዘመን የሩቅ ጊዜ ታሪክ ያህል ይሰማኝ የጀመረው ምርጫ 97ም ሌላኛው የነገረ-አውዱ አስረጂ ነው፡፡ በጥቂት ወራት ውስጥ ከጫፍ ጫፍ ሀገራዊ ንቅናቄ መፍጠር የቻለው ግዙፉ ቅንጅት በአብዛኞቹ የምርጫ ጣቢያዎች በይበልጥ ደግሞ በገጠር አካባቢዎች አሸናፊ መሆኑ በተለያዩ አጣሪ አካላት በመረጋገጡ፤ የኢህአዴግን‹‹መንግስት ለመመስረት የሚያስችለኝ ድምፅ አግኝቻለሁ›› ጨዋታን ከውስጥም ከውጭም አምኖ የተቀበለ አንድም እንኳ አልነበረም፡፡ በአዲስ አበባ አንዳንድ አካባቢዎች ይህንንዓይን ያወጣ ስርቆት በሠላማዊ መንገድ ለመቃወም በሞከሩ ዜጎች ላይ በተወሰደው ርህራሄ አልባ የኃይል እርምጃ በርካታ ንፁሀን ለህልፈት እና ለአካል ጉዳት ሲዳረጉ፣ በተወሰኑየክልል ከተሞች ደግሞ ከፍተኛ ሕዝባዊ ማጉረምረም ተፈጥሮ እንደነበረ ይታወሳል፡፡ ግና፣ ‹‹ብልሆቹ›› የኢህአዴግ ኤጲስ ቆጶሳት በተካኑት ስልት የቅንጅቱን መሪዎች ከያሉበትሰብስበው እስር ቤት ከተቱ፤ ትግሉም ከተነሳበት ‹‹የገጠሩ ወገኖቻችን ድምፅ ይመለስ!›› ወደ ‹‹መሪዎቻችን ይፈቱ!›› ቀኝ ኋላ ዞሮ፣ የሥርዓቱ ዕድሜ እንዲቀጥል ስለመፍቀዱ የእኔ ትውልድ የአይን ምስክር መሆኑ ርግጥ ነው፡፡

ሕዝበ-ሙስሊሙ

ለሶስት ዓመት ተመንፈቅ (ከ‹‹እፎይታ ጊዜ››ው በቀር) ካለማቋረጥ በተቀጣጠለው የሙስሊሙ ኃይማኖታዊ ነፃነትን የማስከበር ትግልም፣ የንቅናቄው አስተባባሪዎች ‹ቃሊቲ የታጎሩትን መሪዎች የማስፈታት ዓላማ በአራተኛነት የተያዘ ነው› ቢሉም (‹‹አህባሽን በግዴታ ማጥመቅ ይቁም››፣ ‹‹መጅሊሱ ወደ ሕዝቡ ይመለስ›› እና ‹‹ነፃ ሕዝባዊ ምርጫ ይካሄድ›› የሚሉት ሶስቱ መሪ ጥያቄዎች የተቃውሞ መነሾ እንደሆኑ ልብ ይሏል)፤ የሕዝበ-ሙስሊሙ በተለይም የቅርብ ጊዜዎቹ የመስጂዶቹ እምቢ-ባይነቶች፣ ሥርዓቱ ለማደነቃቀፍ (ዓላማውን ለማስቀየስ) ባዘጋጀው የ‹‹ይፈቱ›› ማዕቀፍ ስር የተገደበ የመምሰል አዝማሚያው ነው በዚህ አውድ እንድጠቅሰው ያስገደደኝ፡፡ በርግጥ የሁለት አስርታቱን የተቃውሞ ልምድ በቅጡ የመረመሩ የሚመስሉት የ‹‹ድምፃችን ይሰማ›› ወጣቶች፣ በዚህ የተለመደ የትግል ቅልበሳ ላለመጠለፍ የሚያደርጉት ብርቱ ሙከራ እንዳለ ብገነዘብም፣ ከቀደመው ‹‹ጥቁር ሽብር›› ወዲህ በቀጣይ በሚኖሩት የትግል ወቅቶች ዋነኛ የትግል ጥያቄያቸውን ነፃነታቸውን በማስከበር ማዕቀፍ ስር እንደሚያደራጁት አምናለሁ፡፡

ማልቀስስ ለማን?

በ1983ቱ የመንግስት ለውጥ ዓለም አቀፋዊው አውድ፣ ለሽፍቶቹ ስብስብ እርግማንም በረከትም ይዞ ነበር፡፡ እርግማኑ፣ በቀደመ-ፖለቲካዊ ዝማሜያቸው ዝግ ሶሻሊስት ሥርዓት መመስረት አለመቻላቸው ሲሆን፤ በረከቱ ደግሞ በረዥሙ የእርስ በእርስ ጦርነት ክፉኛ የተመታችውን አገር በተለይም ተቋሞቿን ለመገንባት ከሚያስፈልገው ጊዜ አኳያ የምዕራባውያኑን ‹‹ዕድል እንስጣቸው›› የድጋፍ ልብ ማግኘታቸው ነው፡፡ በእነ ሳሙኤል ሀንቲንግተን ‹‹መድበለ-ፓርቲ ሥርዓትን እርሱት፤ አውራ ፓርቲነት ያዋጣችኋል›› ምክረ- ሐሳብ አማካኝነት የወቅቱ ምዕራባውያን አለቆቻቸውን መንፈስ መረዳታቸውን ወደኋላ ስንገነዘብ፤ ቢያንስ እስከ 97 ድህረ-ምርጫ ውጥንቅጥ ድረስ በተጓዙበት የአምባ-ገነንነት መንገድ በጥብቅ አለመወገዛቸውን እንረዳለን፡፡ በአናቱም በህወሓትና መሰል ነፍጥ አንጋቢ የድህረ-ቀዝቃዛው ጦርነት ቡድኖች ላይ ተስፋ የነበራቸው ዓለም አቀፍ ተቋማት እና ምሁራንም ዘግይተውም ቢሆን ቡድኖቹ ወደ ቋሚ ሽፍትነት መቀየራቸውን ከመመልከት አልዳኑም፡፡ የዚህ አይነት ስብስብ ቋሚ መለዮ፣ በመሰረተ ልማት ግንባታዎች ላይ ሙሉ ሀገራዊ ሀብት ማፍሰስ ነው፤ መግፍኤውም ግልፅ ነው፤ የሕብረተሰቡ የአምራችነት ማሕበረ-ኢኮኖሚያዊ አቅም ሲጎለብት፣ እነርሱም የሚያግበሰብሱት ሀብት እየሰፋና እየበዛ እንዲሄድ የማስቻሉ ሀቅ ነው፤ እንደ ህወሓት ያሉ የነፃ-አውጪነት የኋላ ታሪክ ያላቸው ገዢ ቡድኖች፣ በምርጫ ፖለቲካ የማይነቀነቁባቸው ምክንያቶችም ከዚሁ ጋር ይተሳሰራል፤ ከሰላማዊ ሕዝባዊ ዓመፅ ውጪ ይህን ነውረኛ ቡድን ማስቆም እንደማይቻል በ‹‹ሕዳሴ አብዮት›› ርዕሰ-ጉዳይ ለመከራከር የሞከርኩትም ለዚሁ ነው፡፡ እንግዲህ ከእስክንድር ነጋ እስከ ርዕዮት አለሙ፤ ከውብሸት ታዬ እስከ የሱፍ ጌታቸው፤ ከአንዱአለም አራጌ እስከ በቀለ ገርባ፤ ከጦማሪያኑ እስከ እነ ሐብታሙ አያሌው… ድረስ ዘርዝረን የማንጨርሳቸው የእልፍ አእላፍ ለውጥ ፈላጊ ኢትዮጵያውያን መታሰር አሳዛኝ ቢሆንም፤ ለእነርሱም ሆነ ለሀገር የሚበጀው ‹‹ታጋይ እንጂ ትግል አይሞትም!›› የሚለውን የጊዜውን አስገዳጅ ሕዝባዊ ጥሪ በመቀበል አደባባዩን በቁጣ ማጥለቅለቅ ብቻ ነው፡፡ ከዚህ ውጪ ዛሬ እያየነው እንዳለው የግፉአኑን መፈክር አንግቦ መነሳትን ገሸሽ አድርጎ፣ የ‹‹ይፈቱ›› ጥያቄ የትግሉን መንፈስ ይመራው ዘንድ መፍቀድ ሂደቱን ለሥርዓቱ ሴራ አሳልፎ እንደመስጠት የሚቆጠር ይመስለኛል፡፡

መግቢያዬ ላይ የጠቀስኩት የመምህሩ ቃል የሚነግረንም ለእነሱ ከማልቀስ ይልቅ፣ የአምባ-ገነኑን ሥርዓት ቀንበር ተሸክመን በአሳረ-ፍዳ ኑሮአችንን ስለምንገፋው ስለራሳችን ብናለቅስ የተሻለ መሆኑን ነው፡፡ ከዚህ ጎን ለጎንም አብዝተን ነፃነታቸውን የምንሻላቸው ጀግኖቻችን እንደምኞታችን ቢፈቱና መፃኢ ዕድላቸው ምን ሊሆን እንደሚችል ራሳችንን ብንጠይቅ፣ የምንፋጠጠው ‹ተመልሰው በኢህአዴግ የብረት ጫማ ስር ለጥ-ሰጥ ብሎ ማደር› ከሚል እውነታ ጋር ብቻ ነው፡፡የተለመደውን ‹‹የይቅርታ ቃጭል›› አጥልቀው፣ በተሰበረ መንፈስ ከትግሉ ርቀው አንደበታቸውን ሸብበው አሊያም ከሀገር ወጥተው ቀሪውን ህይወታቸውን በስደት እንዲያሳልፉ ከማድረግ ያለፈ የምንፈጥርላቸው ወይም የምናመቻችላቸው ምንም ነገር አለመኖሩ ርግጥ ነውና፡፡ ያውም ብርቱካን ሜደቅሳን ለቅቆ፤ ርእዮት ዓለሙን የሚያስርበትን የቆየ የፖለቲካ ጨዋታውን ሳንዘነጋ፡፡ ይህም ነው ሕዝብን የማዳመጥ አንዳችም ልምድ ለሌለው ሥርዓት ‹‹ይፈቱ!››፣ ‹‹ይለቀቁ!›› እያልን ከመጮኽ በመቆጠብ፣ ታሳሪዎቹ ስለተዋደቁባቸው የነፃነት እሴቶች መተግበር መታገልን ግድ ያደርገው፡፡

በጥቅሉ በመከራው ዳገት ላይ ያሉት ወገኖቻችን የገጠማቸውን ሁነት ያስነሳው፣ ማናችንም በነፃነትና በእኩልነት ልንኖርባት የምትገባዋን አገር የመናፈቅ እንደሆነ ከተስማማን ዘንዳ፣ በየእስር እርምጃው የተፈጠሩትን ክፍተቶች እየደፈንን፣ የነፃነቱን ቀን ለማቅረብ መታተር የወቅቱ አስገዳጅ ጉዳይ ነው ብዬ አምናለሁ፡፡ በቀድሞው የቅንጅት አመራሮች የገፍ እስር ማግስት፣ የከተሞቹን ንቅናቄዎች ከ‹‹ይፈቱልን›› ይልቅ፣ ‹‹ድምፃችን ይመለስልን!›› በሚለው መሠረታዊ ጥያቄ አጥብቀን ይዘን ትግላችንን ብናራዝመው ኖሮ፣ ፖለቲካዊ ለውጦችን መጨበጥ እንችል እንደነበር ማናችንም ብንሆን የምንጠራጠር አይመስለኝም፡፡ ከዚህ አኳያም የሚያስማማን ዋነኛ ጭብጥ፣ ቢያንስ የ2002ቱ ምርጫ በተካሄደበት አስቂኝ ድራማ ልክ ተከናውኖ እና ተቀልዶብን የማለፉ ዕድል እጅጉን ያነሰ የመሆኑ ጉዳይ ነበር፡፡

ባለፉት ጥቂት ወራት ውስጥ ያየናቸው የጦማሪያኑና የሶስቱ ፓርቲዎች ወጣት አመራሮች እስር፣ በተለመደው የ‹‹ይፈቱ›› ደካማ የትግል ስልት የመሄድ ዳርዳርታውን ገርተን፣ ከአደባባዩ መራቃቸውን ተከትሎ እየተፈጠረ ያለ የሚመስለውን (ከማሕበራዊ ድረ-ገፆች እስከ የዕለት ተዕለት የፓርቲዎቹ እንቅስቃሴ ድረስ) ክፍተት መሻገሩ፣ የተሻለ ብቻም ሳይሆን ገዢዎቻችን እንድንሰምጥበት ከሚሹት የሽንፈት ማጥ ውስጥ ከመነከርም የሚገታ አማራጭ ነው፡፡

እነሆም ለማንስ ማልቀስ ይገባል? የሚለውን ጥያቄ መመለስ የሚያስፈልገን እንግዲህ በዚህ ከባድ ወቅት ላይ ነው፡፡ …እንደየተነሱበት አውድ ለሚያምኑባቸው ክቡድ ዕሴቶች ዘብጥያ ለተጣሉት ዜጎች መብሰልሰልን በመምረጥ ከጎናቸው መሰለፍን ላንገራገርነው ለኛ ማዘን የበለጠ የተገባ ነውና፣ እነርሱ ድርሻቸውን ስለመወጣታቸው እያመሰገንን፣ ፍትሃዊ አቋሞቻቸውን በገዘፈ ጉልበት ወደፊት መውሰድ ብቸኛው ምርጫችን መሆን ይኖርበታል፡፡ የ‹‹ሕዳሴው አብዮት›› ተግባሮትም አስፈላጊው ሥነ-ልቦና ይኸው ነው ብዬ አምናለሁ፡፡

ድል ለግፉአን ኢትዮጵያውያን

አዲስ መረጃ በአቶ በረከት ዙሪያ፡ ምስጢር አወጡ የተባሉትን የጂዳ ቆንስላ ጽ/ቤት እያመሰ ነው

August5/2014
ሰበር ዜና አቶ በረከት ስሞኦን ዛሬ August 5, 2014 የሆስፒታል ቀጠሮቸውን ያጠናቅቃሉ !
« በአቶ በረከት ጉዳይ ካድሬዎች ጅዳ ቆንስላ ጽ/ቤትን ሲያምሱ ዋሉ »
bereket alamudi demeke
ሳውዲ አረቢያ በህክምና ላይ የሚገኙት አቶ በረከት ስሞኦን ከህመማቸው አገግመው ሼክ አላሙዲን ወደ አዘጋጁላቸው ሚስጥራዊ ሆቴል ካቀኑ ወዲህ እኚህ ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣን ስላሉበት የጤነነት ሁኔታ በእርግጠኝነት መናገር ባይቻለም ከሁለት ቀን በፊት የሼክ አላሙዲን ወደ አሜሪካ ማቅናት ተከትሎ የአቶ በረከት ስሞኦን የ ጤንነት ሁኔታ በመላካም ሁኔታ ላይ እንደሚገኝ መረጃዎች ያመላክታሉ ። አቶ በረከት ስሞኦን እስካሁን ሳውዲ አረቢያ ከሚገኙ ዲፕሎማቶች ጋር በስልክም ሆነ በአካል እንዳለተጋናኙ የሚገልጹ እነዚህ ምንጮች እኚህ የመንግስት ከፍተኛው ባለስልጣን ያረፉበት ሆቴል ምሲጥራዊነቱ በከፍተኛ ጥንቃቄ የተጠበቀ መሆኑን ይናገራሉ።
የአቶ በረከት የጤንነት ሁኔታ በማህበራዊ ገጾች መነጋገሪያ ከሆነ ወዲህ ጭቀት ውስጥ የገቡት ሼክ አልሙዲን የተለያዩ ሆቴሎችን እየቀያየሩ እኚህን የመንግስት ባለስልጣን ደብቀው ሲያስታምሙ እና አሰፈላጊውን ድጋፍ ሲያደርጉላቸው መክረማቸውን ለማውቀ ተችሏል። አቶ በረከት ከሆስፒታል ከወጡ ወዲህ የተለያዩ ሆቴሎች እንዳረፉ የሚገልጹ መረጃዎች ሼኩ ወደ አሜሪካ ከማቅናታቸው በፊት በግል ከተከራዩላቸው ምርጥ ሆቴሎች ምናልባተም የመጨረሻ የአቶ በረከት ሚስጥራዊ ማገገሚያ ይሆናል ተብሎ ከሚነገርለት ሆቴል ነገ ወደ «ቡግሻን» hospital በማቅናት የመጭረሻ የህክምና ቀጠሮአቸውን ካጠናቀቁ በሃላ በአጭር ቀን ውስጥ፡ ወደ ሃገር ይመለሳሉ ተብሎ ይጠበቃል። በተያያዘ ዜና በህክምና ላይ የምትገኘው የ6 አመቷ የአቶ በረከት ልጅ ህጻን ህሊና በረከት በመልካም ጤነት ላይ መሆኗን የኢትዮጵያ ሃገሬ የሆስፒታል ምንጮች አረጋግጠዋል ።
ይህ በዚህ እንዳለ በጅዳ የኢ.ህ.አ.ዴ.ግ ካድሬዎች የአቶ በረከትን ገበና አጋለጣችሁ በሚል ጅዳ ቆንስላ ጽ/ቤት ዛሬ የመጡ ኢትዮጵያውያን ሲያዋኩቡ መዋላቸው በጅዳ እና አካባቢው ኢትዮጵያውያን ማህበረሰብ ዘንድ ከፍተናኛ ቁጣን ማስነሳቱ ን ለማረጋገጥ ተችሎል ። ጅዳ ቆንስላ ጽ/ቤት የተለያዩ ጉዳዮቹን ለማስፈፀም በጠራራ ጸሃይ ሲነፍሩ የነበሩ ኢትዮጵያዊያንን እንደ ዜጋ አዝነው በአግባቡ ከማስተናገድ ይልቅ አቶ በረከት መታመማቸውን መረጃ ያወጣችሁት እናንተ ናችሁ የተቃዋሚ ወሬ አቀባዩች እናተን ሰብስቦ ማቃጠል ነበር በሚል ዛቻ ፍጹም ኢትዮጵያዊ ነኝ ከሚል የድርጀት አባል በማይጠበቅ ቃላት በኢ.ህ.ዴ.ን ካድሬዎች እና የህወሃት ካድሬዎች ሲያዋክቡ ሲዋከቡ መዋላቸውን በደሉ የተፈፀመባቸው ወገኖች ገልፀውልናል። በተለይ እራሳቸውን ብቸኛ በጅዳ የኢትዮጵያ ቆንስላ ጽ/ቤት ፈላጭ ቆራጭ አድርገው ያስቀመጡት የህወሃት የቀድሞ ታጋይ አቶ ገሬ እና መዝገብ ቤት ሃላፊ የሆነው የትግራይ ተወላጁ የቀድሞው የህወሃት ታጋይ አቶ ሽፋ ባለጉዳዮችን ሲያንገራግሩ ከነበሩ መሃከል ግንባር ቀደም እንደነበሩ ታውቋል።
የጅዳ ቆንስል ሃላፊ የነበሩትን ቆንስል ዘነበን በተጽዕኖ ያስነሱት እንዚህ የጅዳ ኢህአዴግ ካድሬዎች የጅዳን ቆንስላ ጽ/ቤት በመቆጣጠር ደካማ ዲፕሎማቶችን በመናቅ እንዳሻቸው በማድረግ ከማድረጋቸውም በላይ ለጉዳይ የመጣውን ኢትዮጵያዊ ማጉላላት እና ፓስፖርት እስከ መንጠቅ የደረሱ ወንጀለኞች መሆናቸው በአብዛኛው የጅዳ ማህበረሰብ ዘንድ ይነገራል። ከዚህ መሰሪ ተግባራቸው ያልታቀቡት እንዚህ ግለሰቦች የአቶ በረከትን ለህክምና መምጣትን መረጃ አወጣችሁ የሚሏቸውን ወገኖች ወደ ቆንስላው ግቢ ሲገቡ በመተናኮል ሁከት ቀሰቀሱ ብለው ለማሳሰር በዝግጅት ላይ መሆናቸውን ከጽ/ቤት የወጡ መረጃዎቻችን ጠቁመዋል።
Ethiopian Hagere ጅዳ በዋዲ

የዋሽንግተኑን የአፍሪቃ መሪዎች ጉባኤ ኢትዮጵያውያን ተቃወሙት

August 5/2014
"ኦባማ ዝምታው ይብቃ"
ethio us


ኢትዮጵያውንና ኢትዮጵያውያን አሜሪካውያን በትናትናው እለት በዋሽንግተን ዲሲ የተከፈተውንና በዩናይትድ ስቴትሱ ፕሬዝዳንት ባራክ ኦባማ ከአፍሪቃ መሪዎች ጋር የሚያደርጉትን ጉባኤ በመቃወም አደባባይ ወጥተዋል።
“በኢትዮጵያ የሚታየው የሰብዓዊ መብት ረገጣ እንዲቆም አዎንታዊና ተጨባጭ ግፊት በማድረግ ፋንታ፤ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶቹን አራማጆች በመደገፍ ሁኔታው ይበልጥ እንዲባባስ እያደረገ ነው፤” ሲሉ ከተለያዩ የዩናይትድ ስቴትስ ግዛቶች የመጡ መሆናቸውን ያስታወቁት የሰልፉ ተሳታፊዎች የኦባማን አስተዳደር ኮንነዋል።
ስብሰባውን አስመልክቶ የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ባራክ ኦባማ ወደ ርዕሰ-ብሔርነቱ በዘለቁ ወቅት ሃገራቸው ከነበረችበት የምጣኔ ኃብት ድቀት አሁን እያገገመች በመሆኗ ትኩረታቸውን ለአፍሪካ እየሰጡ መሆኑን የሚያሳዩ ክንዋኔዎችን እያደረጉ ነው በማለት ቀድሞ በኢትዮጵያ የአሜሪካ አምባሣደር የነበሩትና የጆርጅ ዋሽንግተን ዩኒቨርሲቲ ረዳት ፕሮፌሰር ዴቪድ ሺን መናገራቸውን ያሜሪካ ድምጽ ሬዲዮ ዘግቦ ነበር፡፡
ከሱዳኑ ፕሬዚዳንት በስተቀር ያልተጋበዙት መሪዎች አለመጋበዝ ትክክለኛ ውሣኔ ነው ብለው እንደማያስቡም ተናግረዋል – አምባሳደር ሺን፡፡
በሌላ በኩል ደግሞ የመጭው ሣምንት የአፍሪካ መሪዎች የዋሺንግተን ጉባዔ ይህንን ጉባዔ የረጥነው ከአፍሪካ ጋር ያለንን ግንኙነት ለማሳደግ መወሰናችንን መልዕክት ለማስተላለፍ ነው ሲሉ የዩናይትድ ስቴትስ የሥልታዊ ግንኙቶች የብሄራዊ ፀጥታ ምክትል አማካሪ ቤን ሮድስ ተናግረዋል፡፡
ሚስተር ሮድስ፣ የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የአፍሪካ ጉዳዮች ረዳት ሚኒስትር ሊንዳ ቶማስ-ግሪንፊልድ እና የዩናይትድ ስቴትስ የብሔራዊ ፀጥታ ምክር ቤት የልማትና የዴሞክራሲ ከፍተኛ ዳይሬክተር ጌል ስሚዝ ጉባዔውን አስመልክቶ ከትናንት በስተያ ምሽት ላይ ከጋዜጠኞች ጋር ባካሄዱት የአንድ ሰዓት የስልክ ቃለ-ምልልስ የመጭውን ሣምንት ጉባዔ ይዘትና አካሄድ አብራርተዋል፡፡
የተቃውሞ ሰልፉን በተመለከተ በድምጽ የተጠናቀረውን ለማዳመጥ እዚህ  ወይም እዚህኛው ላይ ይጫኑ::

ኢህአዴግ በድሆች ጉሮሮ ላይ ቁማር መጫወቱን ቀጥሎበታል፡፡ የደመወዝ ማሻሻያ ርካሽ የፓለቲካ ትርፍና ተግዳሮቱ

August4/2014
ምንሊክ ሳልሳዊ
***የደመወዝ ማሻሻያ ርካሽ የፓለቲካ ትርፍና ተግዳሮቱ….***
በድሆች ጉሮሮ ላይ ፓለቲካውን የሚያካብተው ኢህአዴግ በተቀጣሪዎቹ ላይ ቁማር መጫወቱን ቀጥሎበታል፡፡

ተቀጣሪው የኢትዮጵያ ህዝብም ባርነትን ወዶ መኖሩን ተያይዞታል፤ የሰውን ልጅ ከጫማህ ስር በባርነት ለማኖር ከፈለግክ ቤተሰብ መጦር ድሮ ቀረን እያዜመ በቤተሰብ የሚጦረው የዘመናችን የመንግስት ሠራተኛ አያድርሰው እንጅ ቢታመም ጉድ ፈላ! ያው ጤና አዳሙን፣ዳማከሲዩን፣ዝንጅብሉን አጥር ያፈራውን ሐረግ ሬሳ ይታጠናታል እንጅ እንኳንስ የግል ሆስፒታል በቀበሌው ያለ ጤና ጣቢያ ሔዶ በሐኪም ሊታይ አይችልም፤ በዓመት በዓል እንኳን ከመንግስት ሠራተኛ ቤት የልኳንዳ ፌስታል እንጅ የበግ ቆዳ የገባው በደጉ ዘመን ነበር፤ለመማር እራስን ለመለወጥ ገንዘብ ያስፈልጋል፤ከተማርክ ደግሞ ጥያቄ ማንሳትህ አይቀርም! የዛሬን ካልቸገረህ ስለ ነገህ ትሞግታለህ! ማኩረፊያ ካለህ ምሰህን አስከብረህ ለእራትህም ትተርፋለህ! ቅሉ ግን ከምሳ ባሻገር እንድትኖር አይፈለግም፡፡ ከምሳ ያለፈ እንድታስብ አይፈለግም! ሆድህ ከሞላ ቁንጣንህ ወንበር ያሰይሃል ተብሎ ይታመናል-በኢህአህዴግ ቤት! እራትህን እርግጠኛ ከሆንክ መታረዝህ ያሳስብሃል! ቁርሳቸውን ላላሟሹቱ ማሰብ ትጀምራለህ! ሌሎች መብቶችህም ትውስ ይሉህ ይሆናል! ከራስህ አልፈህ አገሬ ብለህም ትነሳ ይሆናል፡፡ ስለዚህ ሆድህ ይሞላ ዘንዳ አይፈለግም፡፡ ደንደስህ ከወፈረ ለማነቆ አይመችም! የኢትዮጵያ የተቀጣሪዎች የደመወዝ እስኬል ዝቅተኛ ነው ብለህ ማንሾካሾ አትችልም፤ አደሃሪ ጓደኛህ ይቺ አገር ከዚህ በላይ ደመወዝ ለመክፈል አቅሟ አይፈቅድም ብሎ በሐገርህ ፍቅርህ ስስ ጎንህ በኩል ዘልቆ ይሞግትና ዝም ያሰኝሃል! አዎ! ይኢ አገር የተትረፈረፈ ደመወዝ መክፈል ያቅታት ይሆናል፤ እነ እንቶኔ ከጓሯቸው እንደ ባህር ዛፍ የሚያበቅሉትን ህንጻ መስሪያ የሚያክል ደመወዝ አልተመኘህም! ከእርሀብና ከእርዛት፣ከጥማትና ድቆሳ የሚያላቅቅ ገንዘብ ግን ኢትዮጵያ መክፈል አይሳናትም፤ ደግሞስ የመሬቷ ኢትዮጵያ ይፋ የምትሆነው ደመወዝ ላይ ብቻ ነው እንዴ? የኢትቪዋ ኢትዮጵያ የት ገባች?

ካርል ማርክስና የሶሻሊስት ኮሚዩኒዝም ፅንሠ ሃሳብ አራማጆች “ያላቸው” በ “ሌላቸው” ላይ ካፒታሊስቶች በመሆን ላባቸውን እና ደማቸውን በመምጠጥ በድሆች ሞት ላይ ጉልበታቸውን እያጠናከሩ ነው፤በላብ አደሩ ሞት ላይ ካፒታሊስቶቹ እስትንፋሳቸውን እያራዘሙ ነው የሚል ክስ ነበር ይዘው የተነሱት፡፡ እዚህ አገር ግን ካፒታሊስት የሆኑት ግለሰቦች ብቻ ሳይሆኑ ኢህአዴጋዊው መንግስት ነው፤ በቀን ለስምነት ሰዓታት ሠርተህ መንጋጋዎችህ ሁሉ ምግብ ረግጠው አያድሩም፤ ጉንጮችህ በምግብ ተጨንቀው የበላህበትን አታስታውሰውም፤ በተንደላቀቀ ቢሮ ውስጥ በመንግስት ወንበር ላይ ስትሽከረከር ውለህ ማታ ቤትህ ስትገባ የሚጠብቅህ 45 ድግሪ ያዘመመ ቤት ነው፤ እሱንም ከአይጦች ጋር ተዳልበህ የምትኖርበት ነው፤ አልጋ ብርቅህ ነው፤ ያው ኬሻ በጠረባህ ነው፡፡

በመንግስት ተቋማት ውስጥ ተቀጥሮ መስራት በፈቃደኝነት ድህነትን ለመውረስ ዝግጁ መሆን ማለት ነው፡፡ የመንግስት ተቋማቶች ብቃት ባላቸው ባለሙያዎች ድርቅ ተመትተዋል፡፡ ተስፋ የቆረጡ፤በሙያቸው የማይተማመኑ ወይም ሙያ አልቦዎች፣ በሠራተኛው ገበያ ውስጥ ተወዳዳሪ ያልሆኑ የእውቀት የክህሎት፣ የዝግጅት እና የተነሳሽት ድኩማኖች መናኸሪያ እየሆኑ መጥተዋል፡፡ አማራጭ አጥቶ የመንግስትን ቤት ሙጥኝ ያለ ፈጻሚ እንኳንስ አገር ሊገነባና የአፍራሽነት ሚና ነው የሚጫወተው፡፡ መንግስት በክህሎት አልቦ እና በሙያ ለምኔ ፈጻሚዎች ተከብቦ እንዴትስ ህዝብን ማገልገል ይችላል? የግሉ ዘርፍ በሰው ኃይል አደረጃጀቱ በልጦት ከተገኘ መንግስት የግሉን ዘርፍ መምራት ቀርቆ መንግስት በግሉ ዘርፍ ይመራል፡፡ መጨረሻ ላይም ፓለቲካል ሙስናና እና የሐገር ምርኮ (State capture) ገቢራዊ ይሆናሉ፡፡ ኢትዮጵያችን የቁልቁለት ሩጫውን ተያይዘዋለች፡፡ ሙያ አልቦ ፈጻሚዎችን ተይዞ እንዴት ያለ መልካም አስተዳደር ሊኖር ይችላል? የእለት ጉርሱ የሚያቃዠው ፈጻሚን አሰባስቦ እንዴት አገርን ከሙስና ማዕበል መታደግ ይቻልል? ከእለት ጉርሱ ባሻገር እንዳያስብ የተደረገ ሎሌ ሆዱ ስለሚጠግብበት የስርቆት አጋጣሚ ከማሰብ አይቦዝንም፡፡ በሩ ተከፍቶ ሞሰቡ ሳይከደን ባገኘም ጊዜ ተደብቆ ማሻማዱ አይቀርም፡፡ መና አገኝበታለሁ ወዳለሁ ሁሉ ማጮለቁ አይቀርም፡፡ ድሃ ሎሌ ሆኜ እቀር ዘንዳ ጥረዋል በሚል ቀበጸ-ተሥፋነትም ድሃ ሊያደርጋቸው ከመጣርም አይታቀብም፡፡ በሐገሩ ጥቅም ላይ ደርሻ የሌለው ሎሌ “ሺ ቢታለብ ያው በገሌን” እያዜመ ወተት ከመስረቅና ከመድፋት አይቦዝንም፡፡ ለሆዱ ጩኸት መልሽ ያጣ ፈጻሚ እንዴት የተገልጋይ ጩኸት ሊሰማ ይችላል? ከቶስ እንዴ ልማታዊ የለውጥ ሃዋሪያ ይሆን ዘንድ ይከጀላል? የባለፉትን ሁለትና ሦስት አመታት የመንግስት መስሪያ ቤቶች የሰራተኛ ፍልሰት በኢትዮጵያ ታሪክ ከፍተኛ ደረጃ የደረሰበት ነው፡፡ ታላላቅ የሚባሉትና ከፍተኛ ደመወዝ ይከፍላሉ የሚባሉት መስሪያቤቶች ጭምር በዚህ አለመረጋጋት ሲናጡ ነው የከረሙት፡፡አንድ ሺህ የዩኒቨርሲቲ ወጣት አድስ ምርቆችን ጥቅምት ላይ የቀጠረው መስሪያ ቤት ታህሳስ ላይ አንድ ሺህ አምስት መቶ ሆነው እየለቀቁበት የተቸገሩ ባለስልጣን መ/ቤቶች በርካቶች ናቸው፡፡ይህን ተጨባጭ መዋጥ ያቃታቸው አመራሮች ገባያው በሥራ ፈላጊ የሰው ኃይል ተጥለቅልቋልና የፈለገ ይልቀቅ እያሉ ሲያቅራሩ ነው የከረሙት፡፡


እንዳይሞት እንዳይሽር እያደረግክ አፉ ላይ የእለት ጉርሱን ጣል አድርግለት” የሚለውን መርሕ የሚከተለው ኢህአዴግ መርሑ የሰመረለት ይመስላል፤ ከእለት ጉርሱ ባሻገር እንዳይኖር ቅጽር አበጀህለት ማለት ነው፤ የእንጨት ሆነ የብረት ቀንበር ጫንከው በሆዱ ከማልጎምጎም ባሻገር አንዳች ሳይላወስ ሰጥ ለጥ ብሎ ይኖራል- ወርሐዊ ምንደኛ፡፡ኢትዮጵያዊው ተቀጣሪ “እረኛ ቢቆጣ ምሳው እራቱ ነውን” እያዜመ ማነቆውን ለሚያጠብቁበቱ የኢህአዴግ አመራሮቹ ታማኝ ሎሌ ሆኖ መኖርን ሙዱ አድርጎታል፤አበሻ ካርቶን ሙሉ ሐንድ አውት ጠግርራ ተመርቃ በአንድ ሽህ ስምንት መቶ ብር ትቀጠርና አንድ ሺ ሦስት መቶ ብሩን ኩሽና መሰል ቤት ትከራይበትና ቀሪውን አምስት መቶ ብር “ተመስገን ጽሐዩ መንግስታችን!” እያለች መኖሩን ለምዳዋለች፡፡

የኪራይ ሰብሳቢነት አመለካከቱ ተውሳክ ከወንበረኞቹ ወደ ህዝቡ በሰፊው ተዛምቷል፤ የደመወዝ ማሻሻያ ፕሮግራም ገና ይፋ ከመደረጉ ቤት ኪራይ፣ አስሰቤዛው፣ አልባሳቱና አገልግሎቱ ሁሉም በአንድ ጊዜ ዋጋቸው ጣሪያ ይነካል፡፡ አግባብ ያልሆነ ዋጋ ጨምረው ከፍተኛ ፕሮፊት ማርጅንን ከመሻት የተጨመረችዋን ደመወዝ ብቻ ሳይሆን ከዚህ በፊት የነበረውንም አብረው ይወስዱታል፡፡ሕዝብ ራስ ወዳድ መሆን ሲጀምር የፓለቲካውም ቁማር ይሰምራል፡፡ ነጋዴው በአንድ ቀን አዳር ቢሊየነር መሆንን ሲመኝ፣ ቤት አከራዮች ቤተ ተርፏቸው ቤት ለሌላቸው እያከራዩ ቤት የሌላቸውን ደፍቀው ሌላ ጎጆ መቀለስ ካማራቸው ኢትዮጵያችን በቁሟ መፍረሷን አያበሰሩህ ነው፡፡ በእርግጥ ለዚህ መፍትሔ ነበረው፤ ችግሩ በደመወዝተኛው ሞት ላይ የፓለቲካው ቁማር መግዘፉ ነው እንጅ! የደመወዝ ማሻሻያ ተቀዳሚ አላማ ተቀጣሪውን የሕዝብ ክፍል ኑሮ ለማሻሻል ታስቦ መሆን ነበረበት፡፡ ግና ምን ዋጋ አለው!! ሁለት መቶ ብር ለመጨመር የሁለት መቶ ሺህ ብር ጭማሪ ፕሮፓጋንዳ በመገናኛ ብዙሐን የሚለፍፉ የደመወዝ ማሻሻያ ስግብግብ ፓለቲከኞች የፓለቲካ ትርፍ ለማጋበስ ሽተው ያደረጉት ሴራ ነውና-“ሺ ቢታለብ ያው በገሌን” እንድታዜም ትገደዳለህ፡፡

የኢትዮጵያ ፓለቲከኛ ኢኮኖሚስቶች ባለ ባንክ ኪሶቹን የዘነጋ ተቀጣሪ ምንዱባንን መሰረት ያደረገ የማክሮ ኢኮኖሚ ማረጋጊያ ፓሊሲ ይቀምሩልሃል፤ ልክ የእኔና የእርሰዎን መኖር እየተፈታተነ ያለው የኑሮ ውድነት ምክንያቶቹ በርካቶች ናቸው፡፡ከነዚህ አንዱ በርካታ ገንዘቦች በህብረተሰቡ እጅ ሲገቡ ብዙ ብሮች ትቂት ምርቶችን የማሳደድ አደጋ ይገጥማቸዋል፤በዚህ ጊዜ መንግስት የዋጋ ንረቱን ለማረጋጋት በህዝቡ እጅ የሚገኙትን ገንዘቦች መጠን ለመቀነስ በርካታ መንገዶችን ቀይሶ መንቀሳቀስ ይገባዋል፡፡በሌላ በኩል ደግሞ መንግስት ወደ ህዝቡ እየጎረፈ ያለውን የገንዘብ ጅረትም ቆጣሪ ሊያበጅለት ይገባል፡፡ ይህ የኢኮኖሚክስ መርህ ነው፤ በርካታ ሐገሮች የሚተገብሩት! እንዳመታደል ሆኖ በአገራችን ግን ያለው ከዚህ የተለየ ነው፡፡ በህዝቦች እጅ የሚገኝን በርካታ ገንዘብ መቀነስ አለብን ብለው ሲነሱ የኛዎቹ ፓለቲከኛ ኢኮኖሚስቶችና መሪዎች ትዝ የሚሏቸው በስሮቻቸው ያሉ ተቀጣሪ ምንዱባን ናቸው፡፡ከተቀጣሪው ደመወዝ ላይ የአባይ፣የምንትስ የምንትስ በሚል በመሸቃቀብ የዘጠና ሚሊዬን ሕዝብን በር በአስር ሚሊዬኖች መስከኮት ሊከርችሙ ይጥራሉ፡፡ለልማት የሚውለውን እንኳን ትተነው በአሻጥር ወደ ጥገኞቻቸውና የትርፍ አጋሮቻቸው የሚጎርፈውን የገንዘበ ፍሰት አጠናክረው የተቀጣሪን ደመወዝ በመሻቀብ የሞኒታሪ ፓሊሲን ገቢራዊ እያደረግን ነው ሲሉ ያላግጡብናል፡፡

የደመወዝ ማሻሻያ በኢትቪ ካልተለፈፈ ማሻሻያ ፕሮግራም አይሰራም የሚል የኢኮኖሚክስ ህግ አልተከተበም፡፡የደመወዝ ጭማሪው የተቀጣሪውን ኑሮ ለማሻሻል ታስቦ ቢሆን ኖሮ ውስጥ ለውሥጥ ለዚያውም የተለያዩ የሐገሪቱ ዘርፎችን በክላስተሮች ከፋፍሎ በሒደትና በወራት ከፋፍሎ የደመወዝ ማሻሻያውን ገቢራዊ ማድረግ ይቻል ነበር፡፡ ግና የኛዎቹ የፈለጉት የሎሌዎቻቸውን ኑሮ በማድቀቅ ፍጹም ተገዢ ይሆኑላቸው የሰሩት ሴራ ነው፡፡ የደመወዝ ማሻሻያ ፕሮግራሙ ሳይጠናቀቅ፤የእድገት ስኬሉ ሳይሰላ የረከሰ በፓለቲካን ትርፍ ከመሻት ገና በውጥን ላይ ትቂት ፓለቲከኞች በቤቶቻቸው ያወሩትን ለሚዲያ በማቅረብ ምርጫ 2007ን ከማሰብ የተሰራ ደባ ነው፡፡አገር በተጻፈ ስርዓትና ህግ ካልተመራች ፍጻሜው ይሔው ነው፡፡ በሚመለከታቸው አካላት ያልጸደቀን አሉባልታ ለፕሮፓጋንዳ ፍጆታ በማዋል ምንደኞችን ለመርገጥ የተሰራ ሴራ ነው፡፡

እንግዲህ የኑሮ ውድነት መንስኤዎቹ ብዙ ቢሆኑም ዋናወናዎቹ ከምርት እጥረት ወይም (Supply shock)፣ከፍላጎት ማደግ እና ከስነ-ልቦና (Expectation) እንደሚመጣ ኢኮኖሚስቶቹ ይስማማሉ፡፡ ከሥነ-ልቦና ጫና ማለትም ኑሮ እንደሚወደድና እየተወደደ መሔዱን ተፈጥሯዊ የኢኮኖሚ ባህሪ አድርጎ ያመነ ህዝብ የተጠየቀውን ከመክፈል ውጭ ማቅማማት አይችልም፤ አቅራቢውም ይህችን እንደ ሽፋን እየተጠቀመ ሸማቹን እንደ አልቀት ከመምጠጥ አይታቀብም፡፡ የሸማቹን ልብ ለማረጋጋትና የመደራደር አቅሙን ለመጨመር መገናኛ ብዙሐን የሚጫወቱት ሚና ከፍተኛ በመሆኑ ኢኮኖሚስቶች ክትባቱ ሚዲያ ነው ይላሉ፡፡ ያለመታደል ሆኖ የኛ አገር ሚዲያዎች የተረትና የውሸት አባት በመሆናቸው አበሻ ገልብጦ ነው የሚሰማቸው፡፡ ገባያ ላይ ሁለት ሺህ ብር የሚሸጥን ጤፍ በመቶዎች ይነግሩህና “አይ ኢቲቪ-ቱልቱላ ሁላ!” እያልክ ወደ ሸመታህ ትቃናለህ፡፡መንገድ ላይ ተሰልፈው በልመና የሚያስቸግሩህ ገበሬዎች ዞረው በኢቲቪ ልማታዊ ባለሀብት ሆነው ቁጭ ሲሉ ኢቲቪ ያስኮመኩመናል፡፡እናም ወንድሞቼ ኢኮኖምክስ በሐበሻ ምድር ላይ ከሽፏል፡፡ ምንደኛ የእለት ጉሮሮውን ከማራስ ባሻገር ያሉ አጀንዳዎችን እንዳያስብ በማድረግ ሚሊዬን ምንደኞችን ደጋፊ የማድረግ ኢህአዴጋዊው ፓሊሲም ያለ አንዳች እንቅፋት ግስጋሴውን ቀጥሏል፡፡ባካችሁ በቃኝ!...

Monday, August 4, 2014

“እኛ አባቶች ከእንግዲህ ሀላፊነት ለወጣቶች በመስጠት በምክርና የተለያየ ተሞክሯችን በመስጠት ከጎናቸው መቆም አለብን፣

August 4/2014
hqdefault
በቅርቡ ኢንጂነር ግዛቸው ሽፈራው የአንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ ሊቀመንበር ለመሆን በዕጩነት ቀዳሚ ሆነው ማለፋቸው የፓርቲው ልሳን የሆነው ፍኖተ ነጻነት አስታውቋል፡ ፡በዚህ ጉዳያ ያልተናደደና ያልተበሳጨ ሀገር ወዳድ ኢትዮጵያዊ ይኖራል ብሎ መገመት ይከብዳል፡፡ በተለይ ያእቆብ ሀ/ማሪያም በግንቦት 25/2005 በሰማያዊ ፓርቲ ሰልፍ ላይ በኩባ አደባባይ ለሰልፈኛው አቅርበውት በነበረው ንግግቸው ላይ “እኛ አባቶች ከእንግዲህ ሀላፊነት ለወጣቶች በመስጠት በምክርና የተለያየ ተሞክሯችን በመስጠት ከጎናቸው መቆም አለብን፣ከእንግዲህ የእኛ ሀላፊነት ወንበሩን ለወጣቱ ለአዲሱ ተውልድ መልቀቅ ነው፣ “ብለው ነበር፡፡ ኢንጂነር ግዛቸው ግን እንዲህ ቅዱስ ነገር ለመስማት ፍላጎትም ያላቸው አይመስልም፡፡ ኢህአዴግም የእሳቸው ወደ ፊት መምጣት እንደ ሰማይ መና የሚቆጥረው ነገር ነው፡፡ ለምን? ፣ሰውዬው ታሰረው ከነበሩትና በኋላም በይቅርታ ከተለቀቁት የቅንጅት አመራሮች አንዱ ነበሩ፡፡እና ምን አለበት ሊባል ይችላል፡፡በጣም ከባድ ችግር ነው ያለበት፡፡ዋናው ነገር ምን አይነት ይቅርታ ጠይቀው ነው የወጡት የሚለው ነው፣ እንዲህ የሚል ነው
….ህገ መንግስቱንና ህገመንግስታዊ ስርአቱን በሀይልና በአመጽ ለመናድ በህገወጥ መንገድ ተንቀሳሰናል በዚህም ምክንት ብዙ ጥፋትና ውድመት ተከስቷል፤እንዲህ አይነት ነገሩ ውስጥ በማድረግ ህዝባችንና መንገስታችንን በመበደላችን አጥፍተኛል ተጸጽተናል፣ከእንግዲህም አይለመደንም ይቅርታ ይደረግልን… የሚል አይነት ነበር፡፡
ኢህአዴግ በእንዲህ አይነት ሁኔታ ይቅርታ እንዲጠይቁ ያደረገው በትክክል የተባለው ነገር ስለፈጸሙ ሳይሆን፣፣ከእስር ትፈታላችሁ ነገር ግን ካሁን በኋላ እኔ ከምላችሁ አንዳች ፍንክች ብትሉ ተመልሳችሁ ትገቧታላችሁ ማለቱ እንደሆነ ትርጉሙ ግልጽነው፡፡ለዚህም የብርቱካን ሚደቅሳ ነገር ማየት ረዘም ተደርጋ እንዳተሰረች ዶሮ እንጂ እኝደወፍ እንድትበር አልተፈቀደላትም፡፡ስዊድን ሀገር ሄዳ ኢህአዴግ የማይፈቅደው ነገር ተናግራ ወደ ሀገር ቤት ስትመጣ ብዝብ ፊት ይቅርታ ጠይቂ አለበለዛ በተስማማስ መሰረት ወደነበርሽበት ትመለሻለሥ ጠባለች፡፡እምቢ አለች፡፡ተመለሰች፡፡በወቅቱ አብዛኛው የአንድነት አመራሮች በፊርማ የወጡ ስለነበሩ ለምን ብለው ሊከራከሩላት አልቻሉም፣እንዳውም የሚሉሽን አትሰሚምና የእጅሽን ነው ያገኘሽው በሚል አይነት ሁኔታ በብዙ መንገድ ሊኮንኗትና ሊያሳጧት ሞክረዋል፡፡
በወቅቱ ደግሞ ድርጅቱን በሀላፊነት ይመሩ የነበሩት ዛሬ ቲፎዞ አሰልፈው የመጡት ኢንጂነር ግዛቸው ሽፈራው ነበሩ፡፡እኚህ ሰው በወቅቱ ብርቱካን የታሰረችው እስርቤት የገባችውን የፊርማውን ቃል ስላቃለለች ነው የሚል በሚመስል የብርቱካንን ስም የሚያነሳ ሁል በድንጋይ ሳይቀር እስከማስደብበብ ደርሰዋል ውሸታም የሚለኝ ያ አይመስለኝም፡፡ከድርጅቱ አግደዋል አባረዋል፡፡ለዚህም የዛሬዎቹ የሰማያዊ ፓርቲ መሪዎችና አባላትን መጥቀስ ይቻላል፡፡ሰውዬው ድርጅቱን ይመሩት እስርቤት የፈረሙትንነገር በህልማቸውና በቅዠታቸው እየመጣባቸው ነበር፡፡ ለኢህአዴግ የገቡትን ቃል ለማክበር ብዙ የደርጅቱን ወጣቶችና ስም አባክነዋል፡፡ዘሬም ያ ፍርሀታቸው ደብቀው በፍርሀት ሊመሩት ከነቲፎዟቸው ብቅ ብለዋል፡፡በነገራችን ላይ ይህ ሰው በ97 ምርጫ ወቅት ፓርላማ እንግባ አንግባ በሚባልበት ወቅት እንግባ (ኢህአዴግ የሰጠንን ተቀብለን እንግባ) ብለው ይከራከሩ የነበሩ ከዚህም የሀገር ፍቅር ይኖራቸው ይሆናል እንጂ ወደፊት ገፍቶ ኢህአዴግን ለመታገል የሚጎላቸው ነገር እንዳለ ማወቅ ይቻላል፡፡ለጫማው በኋላ ይታሰብበታል ላሁኑ ማምለጥ ነው የሚሉ አይነት ሰው ናቸው፡፡
እና ምን ለማለት ነው ? ሰውዬ የአንድነት መሪ ቢሆኑ ድርጅቱን የሚመሩት ያኔ በፈረሙት ፊርማ ታስረውና ተሸብሽበው ነው፡፡አንዷል አተራጌ አፌን ሞልቼ ስለነጻነት አወራለሁ ሲል አትችል እንዲህ ማድረግ እንደማትችል እስርቤት ፈርመሀል ተብሎ ይኀው የትእንዳለ እናውቃለን፡፡ዶ/ር ብርሀኑ ነጋ የፈረው ፊርማ በሀገር ቤት የትም እንደማያደርሰው አውቆ ይኸውየት እንዳለ እናውቃለን፣እዛም አልቀረለትም የሞት ፍርድ ተፈርዶበታል፡፡ዶ/ር ያእቆብ ቃሊቲ እያለሁ የፈረምኩት ፊርማ እያሰብኩኝ የኢትዮጵያን ህዝብ ትግል ከምጎዳ አርፌ ብቀመጥ ይሻላል ብለው ይመስላል ይኸው መሪ አይደለም የየትኛውም የፖለቲካ ፓርቲ አባልም አይደሉም፡፡ብርቱካንም በውሸት ታስራችሁ በተጭበረበረ መንገድ የፈረማችሁት ፊርማ እፈራችሁ የምትኖሩ ከሆነና ሌላውም ሲታሰር ፍርዳችሁና ና ምላሻችሁ ይሄ ከሆነ ብላ ሀገሩም ትግሉም ጥላ ተደብቃ እየኖረች ነው፡፡
ኢንጂነር ሀይሉሻውል መለስን ጎንበስ ብለው እጅ ነስቻለሁ ያሉት ወደው አይደለም፣ የፈረሙት ፊርማ ምን ያህል ቀልባቸውና ቅስማቸውን እንደሰበራቸው መገመት ይቻላል፡፡ያኔ ታስረው የነበሩ ጋዜጠኞች ሀገር ጥለው ያሉት ቃሊትን ብቻ ሳይሆን የፈረሙትንም ፊርማ ስለሚፈሩ ጭምር ነው፡፡ኢህአዴግ ሰማያዊ ፓርቲ በአደረጃጀትም ሆነ በዐጣቃላይ ጥንካሬ ከአንድነት ስለሚበልጠው አይደለም እንዲህ ልቡ የተሸበረው፣የቀሊቲን ፊርማ እያሰቡ የሚመሩ ሰዎች ስላልሆኑ ጭምር ነው፡፡
ስለዚህ ኢንጂነር ግዛቸው ሽፈራው የአንድት መሪ ሆኑ ማለት ድርግቱ ክንፍ ብቻ ያለው የማይበር የታሰረ ዶሮ ከመሆን ውጪ ምንም አያመጡም፡፡ ስለዚህ በገዛ ፈቃዳቸው በቃኝ ብለው ከጎን ሆነው የትግል ልዳምቸውና ምክርብቻ ማካፈል አለባቸው፡፡ ደግሞም ባለፈው 22 ውስጥ ፖለቲካ ውስጥ ብዙ ጊዜጣቸውን ያሳለፉት እንደ በየነ ጴጥሮስና ዶ/ር መራራ ጉዲና በድርጅት አመራርነት በተለያየ ቦታ ተለጥፈው ተጣብቀው ነው ነው፡፡ለኢህአዴግ የጣሉት እንጂ ያስጣሉት ነገር የለም፡፡ሸክም መሆን ብቻ፡፡መአድ ውስጥ አመራር ውስጥ ነበሩ፣መኢአድ ውስጥ እንዲሁ፣ቅንጅት ውስጥ የታሰሩት አመራር ላይ ስለነበሩ ነው፣አንድነት እሰካሁን የሚያሳማውን ስም ያሰጡትም አመራር ላይ ስለነበሩ ነው፡፡አይተናቸዋል ፣በቃ አሁን ቦታውን ለሌላ ይልቀቁ!!በተለይ የእሳቸው ወደ ስልጣን መምጣት ድርጅቱን እንደእነ ቡልቻ ባሉ “የበራላቸው” ሰዎች በብሄር (በተለይ መዐአድ ውስጥ የነበሩ ሰው ከመሆናቸው አንጻር)በጣም የሚያሳማና ኢህዴግም የያኔው አንዳንድ የቅንጅት ስህተቶችን እያነሳ ህዝብ የሚያስትበት አጀንዳና የትግል መግደያ ከመሆን አያልፉም!

የጦማሪያኑና ጋዜጠኞቹ የክስ መቃወሚያ ቀጠሮ ተላለፈ

August 4/2014

የዞን ዘጠኝ ስድስት ጦማርያንና ሶሰት ጋዜጠኞች በወንጀለኛ መቅጫ ህግና በፀረ ሽብር አዋጁ ላይ የተመለከተውን በመተላለፍ የሽብር ወንጀል ለመፈፀም አቅደዋል፣ ተዘጋጅተዋል፣ አሲረዋል፣ አነሳስተዋል እንዲሁም ህገ መንግሥታዊ ሥርዓቱን በሁከትና በአመፅ ለመለወጥ አስበዋል ተብለው በዋና ወንጀል አድራጊነት በፈፀሙት በህገ መንግሥትና በህገ መንግሥታዊ ሥርዓት ላይ በሚደረግ የሙከራ ወንጀል ተከሰው ባለፈው ሐምሌ 11 ቀን 2006 ዓ.ም ፍርድ ቤት መቅረባቸው ይታወሳል፡፡

ከሦስት ወራት የምርመራ ጊዜ በኃላ የፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 8ኛ የወንጀል ችሎት የቀረቡት ተከሳሾች በፅሑፍ የቀረበላቸውን ክስ ካደመጡ በኃላ በአቃቢ ህግና በጠበቆቻቸው መካከል በተደረገ የዋስትና ጥያቄ ክርክር ብይን ለመስጠትና የክስ መቃወሚያ ለማዳመጥ ፍርድ ቤቱ ለሐምሌ 28 ቀን 2006 ዓ.ም የጊዜ ቀጠሮ መስጠቱ ይታወሳል፡፡

በዛሬው ቀጠሮ ዘጠኙም ተከሳሾች ፍርድ ቤት የቀረቡ ቢሆንም በዋስትና መብት ጉዳይ በጠበቃና በአቃቢ ሕግ መካከል የተደረገው ክርክር የህግ ትርጓሜ እንደሚያስፈልገው ጠበቃዎች በጠየቁት መሰረት ከመቅረጸ ድምጹ ላይ ተገልብጦ ለህግ አስተርጓሚ እንዲላክ እንዲሁም በሌለችበት ክስ የተመሰረተባት 1ኛ ተከሳሽ ሶሊያና ሽመልስ በጋዜጣ ጥሪ እንዲደረግላት የተሰጠው ትዕዛዝ ባለመፈፀሙ ፍርድ ቤቱ ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል።

ባለፈው ቀጠሮ ተከሳሾች የክስ መቃወሚያቸውን እንዲያቀርቡ ከፍርድ ቤቱ ብይን ተሰጥቶ የነበረ ቢሆንም ፍርድ ቤቱ በዛሬው ቀጠሮ የሰጣቸው ትዕዛዞች ተፈጻሚ ባለመሆናቸው ለብይን ያስቸግረናል በሚል የክስ መቃወሚያቸውን ሳያደምጥ ቀርቷል፡፡
ጠበቆቹ ለፍርድ ቤቱ በሰጡት አስተያየት በመጀመሪያው የፍርድ ቤት ውሎ ለዛሬ ቀጠሮ የክስ መቃወሚያ እንዲቀርብ ብይን የተሰጠ መሆኑን አስታውሰው ፍርድ ቤቱም ሆነ አቃቢ ህጉ የክስ መቃመወሚውን ለማየት በቂ ጊዜ የሚሰጥ በመሆኑ የክስ መቃወሚያ በጽሁፍ እንድናቀርብ ይፈቀድልን ብለው ጠይቀዋል፡፡ ችሎቱም የጠበቆችን ጥያቄ በመቀበሉ የክስ መቃወሚያው ለአቃቢ ህግና ለፍርድ ቤቱ በጽሁፍ ቀርቦ በቀጣዩ ቀጠሮ በንባብ እንዲሰማ አዟል።

በ1ኛ ክስ ላይ ለተዘረዘሩ የወንጀል ድርጊቶች 5 መቃወሚያ እንዲሁም በ2ኛ ክስ ለቀረቡት የወንጀል ድርጊቶች 4 መቃወሚያ ነጥቦች የተዘረዘረበት ሰነድ “የቀረበው ክስ ከተጠቀሰው የህግ አነጋገር ጋር የሚቀራረብ አለመሆኑን፣ ተከሳሾች ፈጽመዋቸዋል የተባሉት በክስ ዝርዝሩ የተመለከቱ ተግባራት በህግ የተፈቀዱና ሕገ መንግስታዊ ጥበቃም የተደረገባቸው ሰብአዊና ዲሞክራሲያዊ መብቶች መሆናቸውን፣ የቀረበው ክስ ግልፅ አለመሆኑን፣ ወስደዋል የተባሉት ሥልጠናዎችና ለመገናኛ ብዙኃን ያስተላለፉት መረጃ ወንጀል አለመሆኑን የተመለከቱ መቃወሚያዎችን የያዘ ነው፡፡

በ2ኛ ክስ የቀረበው የክስ መቃወሚያ ደግሞ ጠበቃው ማሰብ የማያስከስስና የማያስቀጣ መሆኑን፣ መደራጀት፣ የሥራ ክፍፍል መፍጠር እና የተለያዩ ሥልጠናዎችን መውሰድ ወንጀል አለመሆኑን፣ በአንድ ድርጊት ሁለት ክስ መቅረቡ አግባብ አለመሆኑ፣ የቀረበው የማስረጃ ሰነድ አለመሟላትን በተመለከተ ከወንጀለኛ መቅጫ እና ከጸረሽብር አዋጁ አንቀጽ ጠቅሰው ተቃውሞዎቻቸውን በጽሑፍ በዝርዝር አቅርበዋል፡፡

የዕለቱን ችሎት የሚመሩት ዳኛ ባስተላለፉት ውሳኔ የዋስትና መብት ጥያቄ ክርክር ከመቅረጸ ድምጽ ተገልብጦ ከመዝገቡ ጋር ተያይዞ ለህግ አውጪ አካል እንዲልክ እንዲሁም ለ1ኛ ተከሳሽ በፕሬስ ጥሪ እንዲደረግና የክስ መቃወሚያ በንባብ እንዲደመጥ ትዕዛዝ አስተላልፈው ለነሐሴ 14 ቀን 2006 ዓ.ም ቀጠሮ ሰጥተዋል፡፡

አንድ መቶ ሰባ አምስት ኪሎ ወርቅ ከሃገር ሊወጣ ሲል ቢያዝም በሳሞራ የኑስ ትእዛዝ እንዲያልፍ ተደርጓል።

August 4/2014
ምንሊክ ሳልሳዊ

  • 661
    Share
የጄኔራል ሳሞራ የኑስ እንደሆነ የሚጠረጠረው አንድ መቶ ሰባ አምስት ኪሎ ወርቅ ከአገር ሊወጣ ሲል ተይዞ የነበረ ቢሆንም በጄኔራሉ ትእዛዝ ከአገር እንዲወጣ መደረጉን የአየር መንገዱ የደህንነት ምንጮች ጠቁመዋል። ይህ በሁለት ካርቶን ታሽጎ በበረራ ቁጥር 600 እና 612 ወደ ዱባይ ሊሻገር ሲል በቁጥጥር ስር የዋለው ወርቅ በጊዜው ባለንብረቱ ተፈልገው ባለመገኘታቸው እንዲቆይ ቢደረግም ጄኔራል ሳሞራ የኑስ ቦታው ድረስ አሽከሮቹን በመላክ እንዲለቀቅ እና እንዲያልፍ/እንዲጫን የተደረገ መሆኑ ታውቋል።

ይህ የሃገር ሃብት የሆነን ወርቅ የወያኔ ባለስልጣናት ካለምንም ገደብ በማሸሽ እና በመዝረፍ ላይ የተሰማሩ ሲሆን ፒያሳ አከባቢ በሚገኘው በአፍሪካ ወርቅ ቤት ሽፋን እንዳልካቸው እና ዳንኤል በሚባሉ ስሞች በሚሊዮን ዶላሮች የሚገመት የወርቅ መጠን ከአገር በማስወጣት እና እንዲሁም የውጪ ወርቆችን ካለምንም የቀረጥ ክፍያ ወደ ሃገር ውስጥ በማስገባት ስራ ላይ መሰማራታቸው በተጨማሪም ሃገሪቷ የምታገኛቸው የውጪ ምንዛሬዎች በጥሬው እየታሸጉ ከሃገር እንደሚወጡ ታውቋል።

Sunday, August 3, 2014

ሠራዊቱ የህዝብ ወገንተኛነቱን የሚያስመሰክርበት ግዜ እየመጣ ነው

Augest3/2014
በኢትዮጵያ ታሪክ ውስጥ የቀደመው ትውልድ ከቱርክ ኤምፓየር፤ ከግብፅ እና ከደረቡሽ፤ ከጣሊያን ወራሪ፤ ከሶማሊያ ተስፋፊ ኃይል እና ከሌሎችም የኢትዮጵያ ጠላቶች ጋር ተዋግቶ አገሪቷን ለአሁኑ ትውልድ ለማቆየት ትልቅ መስዋዕትነት ከፍሏል። በተለይ ነፍጥ አንግቦ የተሠለፈው ኃይል የከፈለው የህይወት መሥዋዕትነት የሚረሳ አይደለም። አገራችን ኢትዮጵያ ለዛሬው ትውልድ የቆየችው ከራሱ ይልቅ ለአገርና ለወገን የሚያስብ ትውልድ በመኖሩ መሆኑ የሚያከራክረን ጉዳይ አይሆንም።
የአገር መከላከያ ሠራዊት እና የአገር ደህንነት ኃይል የቆመው አገርን ከጥቃት ለመከላከል ነው። አገር በጠላት እጅ ወድቃ በወገን ላይ ስቃይ እንዳይደርስ፤ ህዝቡም አገር አልባ እንዳይሆን መጠበቅ የአገሪቷ የሠራዊትና የደህንነት ኃይል ዋና ተግባር ነበር። ህወሃት መራሹ መንግስት አገሪቷን ከተቆጣጠረ ዘመን ጀምሮ በኢትዮጵያ ሥም የቆመው ሠራዊት እና የደህንነት ኃይል ተግባሩ ሌላ ሁኗል።
በዚህ ዘመን ሠራዊቱና የደህንነት ኃይሉ የአገርን ብሄራዊ ደህንነት የሚጠብቅ ሳይሆን ህወሃት የተባለውን ዘረኛና ዘራፊውን ቡድን የሚጠብቅ ኃይል መሆንን እንዲመርጥ ሁኖ አገርን ከጠላት የመከላከል ተግባሩን ረስቷል። ይህን ኃይል የሚመሩትም ደማቸውንና አጥንታቸውን ቆጥረው ከአንድ መንደር/ጎሣ የተሰባሰቡ እና ካርታ ይዘው የቆሙበትን ሥፍራ እንኳን ለመለየት የማይችሉ መሃይማን መሆናቸው አገሪቷ ያለችበትን አደጋ ከሚያመላክቱ ምልክቶች መካከል አንዱ ነው። ህወሃቶች የደርግ ሠራዊት እያሉ ሊሳለቁበት የሚሞክሩት የቀድሞው የአገሪቷ መከላከያ ኃይል ሲመራ የነበረው አውሮፓና አሜሪካን ድረስ ተጉዘው በተማሩ፤ ማዕረጋቸውም የዓለም ዓቀፉን ደረጃ የጠበቀ፤ አገሪቷን ወክለው አደባባይ ቢወጡ የሚያኮሩ እንደነበረ የታወቀ ነው። የሹመታቸው መሠረትም ደምና አጥንት ሳይሆን እውቀታቸው፤ ችሎታቸውና ወታዳራዊ ብቃታቸው ነበረ።በህወሃት የሚመራውን ሠራዊትና የደህንነት ኃይል የሚመሩት ቡድኖች ከቀድሞዎቹ ሥርዓት የጦር መሪዎች ጋር ሲወዳደሩ የጫማቸውን ጠፍር እንኳ ለመፍታት የሚታጩ አይሆኑም።ግዜ የሰጠው ቅል ድንጋይ ይሰብራል እንደሚባለው ሆነና ጨካኞችና ነፍሰ ገዳዮች በወንበሩ ቁጭ ብለው የአገሪቷን ውድቀት እያፋጠኑት ይገኛሉ።
ዛሬ ህወሃቶች በወንበሩ ቁጭ ብለዋል። እነዚህ ከጭካኔ በቀር እንጥፍጣፊ የአገር ፍቅር የሌላቸው ቡድኖች አቋቋምን ያሉት ሠራዊትና የደህንነት ኃይልም አገሩንና ወገኑን ከመጠበቅ ይልቅ የገዛ ወገኑን የሚያሸበር ቡድን እንዲሆን ተደርጓል። ሠራዊቱ እና የደህንነት ኃይሉ ለአገርና ለትውልድ እንዲያስብ ሳይሆን የጥቂት ዘረኞችን ዕድሜ ለማራዘም ዘብ የቆመ ኃይል እንዲሆንም ሁኗል። ህወሃት እየፈጠረ ያለው ሠራዊትና የደህንነት ኃይል በጀግና ማዕረግ አገሩንና ህዝቡን ከጥቃት ተከላክሎ በህዝቡ ተከብሮና ተወዶ እንዲኖር ሳይሆን በጭካኔው ታውቆ እና የወገኑን ፍቅር አጥቶ በስነ ልቦና ቀውስ ውስጥ የሚኖርን ኃይል ነው። እንዲህም ሁኖ በመቀረፁ ግደል ሲባል ገስግሶ ሂዶ የገዛ ወገኑን ይገድላል። አፍርስ ሲባል ፈጥኖ በብዙ ድካምና ወጪ የተገነባውን የወገኑን መኖሪያ ቤት ያፈርሳል። እሠር ሲባል ህፃን ከአዛውንት ሳይለይ ያገኘውን ሁሉ ወደ ወይኒ ቤት ያግዛል። በእንዲህ ሁኔታ ከወገኑ ተለይቶ፤ በወገኑ ላይ ዘምቶ፤ ወገኑን ወግቶ፤ ወገኑን አሥሮና አሰቃይቶ ራሡም እንደገና በክፉ ድርጊቱ ታሥሮ እንዲኖር ሁኗል።
ህወሃት የፈጠራችሁ እና በአገር መከላከያ እና ደህንነት ኃይል ሥም ቁማችሁ በወገኖቻችሁ ላይ እንድትዘመቱ የተደረጋችሁ የሠራዊቱና የደህንነት ኃይሎች አድምጡ። አሁን አገራችን ባለችበት ሁኔታ ለኢትዮጵያና ለህዝቧ ዋነኛው ጠላት ህወሃት ነው። ህወሃት የዘረኞችና የዘራፊዎች ስብሰብ ነው። የዘረኝነታቸው መገለጫ ብዙ ነው። የሚያዙህ ጄኔራል ተብየዎች ደማቸውን ቆጥረው የተጫኑብህ መሆናቸውን ተመለከት። እነዚህ ጄኔራሎች አገሪቷን ከተቆጣጠሩ ዘመን ጀምሮ ያካበቱትን የሃብት ብዛት ተመልከት። ሁሉም በሚሊዮን የሚቆጠር ሃብት ባለቤት ናቸው። ልጆቻቸው በአውሮፓና በአሜሪካን ይማራሉ። ሚስቶቻቸው አውሮፓና አሜሪካን እየሄዱ እንዲወልዱ ይደረጋል።ይሄን ለምን ያደርጋሉ ቢባል እየገዙ ያሉት አገር የራሳቸው አገር ስለመሆኗ ብርቱ ጥርጣሬ ስላላቸው ነው። ህዝቧንም እንደ ወገኖቻቸው ለማየት ሥር የሰደደ ጥላቻማላቸው። አንተ እና ወገኖችህ ግን ከሙታን ትንሽ ከፍ ብላችሁ፤ ከሚኖሩት እገር ሥር ተረግጣችሁ የህወሃቶች አኗኗሪ ሁናችሁ የመከራውን ዘመን ትቆጥራላችሁ። በድህነት የሚወቅሯችሁ እንሷቸው ይሄና አስባችሁ፤ ያንን ተናገረችሁ እያሉ በዓለም ላይ በተከለከለ የቶርቸር ዓይነት እንድትሰቃዩ ትደረጋላችሁ። ይህ የጠላት ተግባር ነው።አሁን ባለንበት ዘመንም የኢትጵያ ዋነኛው ጠላት ህወሃት መሆኑን ያለምንም ጥርጣሬ ማመን ይኖርባችኋል።
ህወሃትን ጠላት የሚያድረገው ምንድ ነው ?
ህወሃቶች ወደ ስልጣን ከመጡ ዘመን ጀምሮ ሁለት ሚሊዮን አማራ ጠፍቷል። ይሄ ሁሉ አማራ የት እንደገባ ህወሃት እስከ አሁን አልተናገረም። ይሄ ዘረኛ ቡድን አገሪቷን ከተቆጣጠረ ዘመን ጀምሮ በዜጎች መካከል ሊኖር የሚገባው መተማመን ጠፍቷል። በዚህም ምክንያት ዜጎች ከኖሩበት ሥፍራ እየተነቀሉ ሜዳ ላይ እንዲወድቁ ሁኗል። ይሄ ዘራፊ ቡድን አገሪቷን ከተቆጣጠረ ግዜ ጀምሮ ከአገሪቷ ውስጥ በስምንት ዓመታት ውስጥ ብቻ ከ11 ቢሊዮን ዶላር በላይ ተዘርፎ በውጪ አገራት ባንኮች ውስጥ ተደብቋል። ይህ ቡድን ስልጣኑን ከተቆጣጠረ ዘመን ጀምሮ ከአገሪቷ በሚሰደዱ ምሁራን፤ ጋዜጠኞች፤ የኃይማኖት አባቶች እና በሌሎች ዜጎች ቁጥር ኢትዮጵያን የሚያክል አልተገኘም። ህወሃት የተባለው ዘረኛ እና ዘራፊ ቡድን አገሪቷን ከተቆጣጠረ በኋላ አባቶች በደምና አጥንታቸው ያቆዩት ድንበር እየፈረሰ እና ኢትዮጵያዊያን እየተፈናቀሉ ሜዳ ላይ ተጥለው መሬቱ ለባእዳን እየተሰጠ ነው። ይሄ ቡድን አገሪቷን ከተቆጣጠረ ዘመን ጀምሮ ድሃ ሜዳ ላይ ተጥሎ የድሃውን መሬት ህወሃቶች እየነጠቁ ባለሃብት ነን ብለዋል። ይሄ ቡድን አገሪቷን ከተቆጣጠረ ዘመን ጀምሮ ሃሳብን በነፃ መግለፅ አሸባሪነት ሁኗል። ህወሃትን መንቀፍ በሞት የሚያሰቀጣ ወንጀል እስከመሆን ደርሷል። ኢትዮጵያ ይህን በሚመስለው ጠላት እጅ ተይዛለች።
ኢትዮጵያን ከዚህ ጠላት እጅ ለማላቀቅ የሠራዊቱና የአገር ደህንነት ኃይሉ ከፍተኛ ሚና መጫወት አለበት። ከህወሃት የበለጠ ጠላት ኢትዮጵያ የላትም፤ በታሪኳም እንዲህ ዓይነት ጠላት አይታ አታውቅም። ይህን ጠላት ወደ ከርሰ መቃብሩ የሚከት የለውጥ ባቡር እየገሰገሰ ነው። ይሄን የለወጥ ባቡር ፈፅሞ ማቆም አይቻልም። ህወሃቶች የለውጡ ባቡር በፍጥነት እየገሰገሰ እንደሆነ እያዩት ነው። በዚህም አንዳንዶቹ የዘረፉትን ሃብት ይዘው እየሸሹ ነው። ሌሎቹም የሚያደርጉትን አጥተው በዜጎች ላይ በስቃይ ላይ ስቃይ እያበዙ ነው። የሠራዊቱና የደህንነቱ ኃይል የኢትዮጵያዊያን ጠላት መሆንን ከመረጡ ዘረኞች ጎራ ራሱን ለይቶ የህዝብ ልጅ፤ የአገር ጥላ ከለላ መሆኑን አሁኑኑ ማሳየት መጀመር ይጠበቅበታል። የአገር መከላከያ አባል ስትሆን አገርህን ከጠላት ለመከላከል እንጂ ከጠላት ጋር አብረህ የገዛ ወገንህን ስቃይ ለማብዛት አይደለም። ከጠላት ጋር መወገንን ከመረጥክ ግን የተነሳው የለውጥ ባቡር አንተንም ጨፍልቆ እና ታሪክህን ከዘረኞችና ከዘራፊዎች ጎራ ፅፎ እንደሚያልፍ ቅንጣት ታክል ጥርጣሬ አይኑርህ።
የእኛ እምነት ግን ከህወሃቶች ጎን ቁመህ ወንድሞችህን ትወጋለህ የሚል አይደለም። ህወሃቶች ለአንት ወንድምም ጋሻም መከታም የሚሆኑ አይደሉም። በአሁን ሠዓት የህወሃቶች ጭንቀት የዘረፉትን ሃብት የሚያሸሹበትን ሥፍራ የማግኘት ነው እንጂ የአንተ ደህንነት አይደለም። ህወሃቶችን እንቅልፍ የሚነሳቸው የሠሯቸው ትላልቅ ህንፃዎች ፍፃሜ እንጂ የኢትዮጵያዊያኑ በሠላም የመኖር ጉዳይ አይደለም። ህወሃቶች የሚሞቱለትም ሆነ የሚኖሩለት አንድ እና አንድ ምክንያት ዘርፈው ያካባቱት ሃብት እንጂ ኢትዮጵያ የምትባል አገር እንዳልሆነች የታወቀ ነው። አንተ የሠራዊቱ አባል ግን የእነዚህን ዘረኞችና ዘራፊ ህወሃቶችን እድሜ ለማራዘም የምትሞተውና የምትገድለው ለምንድ ነው? የእነርሱን እድሜ ለማራዘም ብለህ ብትሞት ለህወሃቶች ወግኖ ኢትዮጵያዊያንን ሲወጋ ሞተ ተብለህ መሳለቂያ ሆነህ መቅረትህን አታውቅምን ?
እኛ ግን እንዲህ እንልሃለን ለአገርህ መሞት ክብር ነው። ለአገር መሞት ማለትም በዚያች አገር ውስጥ ለፍትህ፤ ለህግ የበላይነት፤ ለነፃነት፤ ለእኩልነት እና ለእውነተኛ ዴሞክራሲያዊ ሥርዓት ግንባታ ራስን አሳልፎ መስጠት ማለት ነው።በዚህ ሞትህ ማንም ማንንም ሳይጫን፤ ማንም ማንንም ሳይሸከም መኖር የሚቻልባት አገር ተፈጥራ እኩልነት ሲሰፍን የአንት ስም በአገሪቷ እስከ ዘላለሙ ሲታወስ ይኖራል። ልጆችህና ልጅ ልጆችህ በአንተ ሥራ ኮርተውና አንገታቸውን ቀና አድርገው የሚሄዱ ይሆናሉ። ለዚህ ዘላቂ ክብር ብለህ ብትሞት ሞትህ የክብር ሞት ይሆናል። የሣሞራንና የጓደኞቹን የሥልጣን ጥም ለማርካት ብለህ ብትገልና ብትሞት ግን አሟሟትህ ከንቱ ይሆናል። ለነፃነት፤ ለእኩልነት እና ለህግ የበላይነት ብለው የተነሱ ነፁሃን ዜጎችን ለመግደል የታጠከውን ነፍጥ ብታነሳ ፍፃሜህ ከንቱ ሁኖ እንደሚቀር አትጠራጠር። የምትሞትለትም ሆነ የምትኖርለት ዋናው ቁም ነገር ሊሆን የሚገባው በህወሃቶች የተጣመመውን ፍትህ ለማቃናት፤ ወገኖችህና አንተ የተነጠቃችሁትን ነፃነት ለመቀዳጀት፤ እውነተኛ ዴሞክራሲዊ ሥርዓት በአገርህ እንዲሠፍን፤ ጥቂት ዘረኞች ብዙሃኑን ተጭነው፤ ብዙሃኑም እነዚህ ጥቂት ዘረኞችን ተሸክመው የሚኖሩበት ሥርዓት እንዲያበቃ ሊሆን ይገባዋል። ለእነዚህ ድንቅ ሃሳቦች ብለህ ብትሰዋ መስዋዕትነትህ የጀግና መሥዋዕትነት ይሆናል። እንዲህ ዓይነቱ መሰዋዕትነት ለአገርና ለወገን የሚሰጥ ውድ እና ታላቅ ስጦታ ነው። ይሄን ውድ እና ታላቅ ስጦታ የሰጠ ደግሞ በታሪክ ማህደራት ውስጥ ስሙ ለዘላለም ሲታወስ ይኖራልና የለወጡን ባቡር እንድትሳፈር እንመክርሃለን።
ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ !!!

እነ ህሊና መቼ አባታቸውን ያገኛሉ? [በዳዊት ሰለሞን]

August3/2014
Yeshiwassew, Habtamu, Danial
ነገረ ኢትዮጵያ ጋዜጣን ዛሬ አነበብኳት ፡፡የጋዜጣዋ ባልደረባ የሆነው በላይ ማናዬ በቅርቡ ለእስር የተዳረገው የሰማያዊ ፓርቲ ብሄራዊ ምክር ቤት ምክትል ሰብሳቢ የሆነው የሺዋስ አሰፋ ቤት ተገኝተው የየሺዋስን ሁለት ህጻናት ልጆች ማግኘታቸውንና ህጻናቱም ስለ አባታቸው የሚያስቡትን እንደነገሩት ይተርካል፡፡
ህሊና የየሺዋስ ሁለተኛ ልጅ ስትሆን የ5 ዓመት ህጻን ናት፡፡‹‹አባቴ ደሴ ሄዷል››እንዳለችው በላይ ይገልጻል፡፡ጋዜጠኛው አባቷ ደሴ እንዳልሄደና ሰው እንዳይጠይቀው ተደርጎ መታሰሩን ቢያውቅም መቼ ነው ከደሴ የሚመለሰው ብላ ስትጠይቀው መልስ ፍለጋ መዋተቱን ይነግረናል፡፡የየሺዋስ የመጀመሪያ ልጅ ከህሊና በእድሜ ከፍ ያለ በመሆኑ ደሴ ሄዷል መባሉን ለመቀበል የተቸገረ ይመስላል፡፡
እንደ ህሊና ሁሉ የጋዜጠኛ ውብሸት ታዬ ብቸኛ ልጅም አባቱ ‹‹አስተማሪ በመሆኑ ዝዋይ እያስተማረ እንደሆነ ለጠየቀው ሁሉ ይናገራል፡፡ፍትህ ሁልግዜም ወላጅ እናቱን ‹‹አባቴ የሚያስተምረው ትምህርት መቼ ነው የሚያበቃው››በማለት በጥያቄ ይወጥራት እንደነበር ትናገራለች፡፡Wibishet Taye
የጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ ልጅ የተወለደው እስር ቤት ውስጥ ነው፡፡አባቱ ለዘጠነኛ ጊዜ ለእስር ሲዳረግም ፖሊሶች እስክንድርን ከእጁ ፈልቅቀውት ሲወስዱት ተመልክቷል፡፡ፖሊሶችን በተመለከተ ቁጥር እናቱን ‹‹እኔንም ሊያስሩኝ ነው?››እያለ ይጠይቃት ነበር፡፡አሁን ናፍቆት ከአባቱ በስጋ ተለይቶ አሜሪካን አገር ይገኛል፡፡ናፍቆት እንደ ልጅ የመጫወት ዕድል አላገኘም በማለት ብዙ መስዋዕትነት የከፈለችው ሰርካለም ፋሲል ትናገራለች፡፡Andualem-Eskindir-300x165
አንዷለም አራጌ በድጋሚ ለእስር ሲዳረግና ፖሊሶች ቤቱን ለመፈተሸ ነፍጥ አንግተው ጎራ ሲሉ የአንዷለም ሁለት ልጆች በቤቱ መጋረጃ ተደብቀው ሂደቱን በፍርሃት ይከታተሉ እንደነበር አባታቸው ያልተሄደበት መንገድ በማለት በሰየመው መጽሐፉ መስክሯል፡፡
የአንዷለም ልጆች አባታቸውን ለመጠየቅ ቃሊቲ በሚያመሩበት ወቅት ሁሌም የምትፈቀድላቸው 30 ደቂቃ የምታበቃው በለቅሶ ነው፡፡ልጆቹ አባታቸው እንዲያጫውታቸው እየጠየቁ ሰዓት ማለቁ እየተነገራቸው በእንባ ይመለሳሉ፡፡እናታቸው ህጻናቱን ሳምንቱን በሙሉ ስታባብል ማሳለፍን እየተላመደችው መጥታለች፡፡
ናትናኤል መኮንን ልጆቹን በትምህርት ትልቅ ደረጃ የማድረስ ህልም እንደሁሉም ኢትዮጵያዊ አባት የነበረው ነው፡፡አጠገባቸው ሆኖ ሊመራቸው ባይችልም እናታቸው የአባታቸውን ህልም ልጆቹ እንዲኖሩ ለማድረግ ብዙ ታትራለች፡፡አሁን የናቲ ልጆች የትምህርት ቤታቸው ሰቃዮች ሆነዋል፡፡
የናትናኤልን መኖሪያ ለመፈተሸ መጥተው ከነበሩ ሰዎች መካከል አንዱ ህጻኑን የናቲን ልጅ ይዞ‹‹እንደ አባትህ እንዳትሆን››ይለዋል፡፡ህጻኑ መልሶ ‹‹መሆን የምፈልገው እንደ አባቴ ነው››በማለት መልሶለታል፡፡
ዳንኤል ሺበሺ ትዳር ቢኖረውም ልጅ አልወለደም፡፡የህዝብ ልጅ የሚል ስያሜ ከበጎ አድራጎት ስራው የተነሳ የወጣለት ዳንኤል ሁለት ልጆችን በመኖሪያ ቤቱ ተቀብሎ እያሳደገ ይገኛል፡፡ዳንኤል በመታሰሩ ግን የሚጎድልባቸው ህጻናት ሁለቱ ብቻ አይደሉም፡፡ዳንኤል ለብዙዎች ደራሽ ነበር፡፡
ሐብታሙ አያሌው የልጁን ሁለተኛ ዓመት የልደት በዓል ለማክበር እየተዘጋጀ ሳለ ነበር ለእስር የተዳረገው፡፡ባለቤቱ ልጃቸው የመኖሪያ ቤታቸው በር በተንኳኳና ስልክ በተደወለ ቁጥር የምታሳየውን ናፍቆት እየተመለከተች በእንባ ትዋጣለች፡፡
ሌሎች በጣም ብዙ አባቶችና እናቶች አልያም ለቤተሰቦቻቸው እንደ ልጅ የሚታዩ ዜጎች ሽብርተኛ ተብለው ዘብጥያ እንዲወርዱ ተደርገዋል፡፡አስደሳቹ ነገር ግን እነዚህ አባቶች፣እናቶች፣እህቶችና ወንድሞች የታሰሩት ስልጣናቸውን ያለ አግባብ በመጠቀማቸው፣ሙስና በመፈጸማቸው፣በሀሰት በመመስከራቸው፣ሰው በመግደላቸውና ህሊናቸውን ጥለው ለሆዳቸው በማደራቸው አለመሆኑ ነው፡፡የታሰሩት ይህች አገር ወዴት እያመራች እንደሆነ በመጠየቃቸው ነው፡፡እነ ህሊና አባታቸውን የሚያገኙትም ይህች አገር የጥቂቶች መሆኗ ሲያበቃ ብቻ ነው፡፡ጥቂቶችን ሐይ ለማለት ግን ብዙዎች ከእንቅልፋቸው መባነን ግድ ይላቸዋል፡፡እስከዛው የየሺዋስ ፣የሐብታሙ ፣የያሲን ኑሩ፣የዳንኤል፣የናትናኤልና የሌሎቹም የእኔ ልጆች ናቸው ማለት ይኖርብናል፡፡

በአንዋር መስጊድ ብጥብጥ ፖሊሶችም መሳተፋቸው ተገለጸ

August 3/2014

-ኮማ ውስጥ ያሉ ተጎጂዎች ሁኔታ እስኪታወቅ ተጨማሪ የምርመራ ጊዜ ተፈቀደ 

ሐምሌ 11 ቀን 2006 ዓ.ም. በመርካቶ አንዋር መስጊድና በአካባቢው ላይ በተፈጠረ ግጭትና ብጥብጥ፣ አራት የፖሊስ አባላት መሳተፋቸው በፍርድ ቤት ተገለጸ፡፡ 

ፖሊስ ለሦስተኛ ጊዜ ሐምሌ 24 ቀን 2006 ዓ.ም. በአዲስ አበባ ከተማ የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት የፖሊስ ኮሚሽን ጉዳዮች ምርመራ ጊዜ ቀጠሮ ማስቻያ ችሎት 14 ተጠርጣሪዎችን ያቀረበ ሲሆን፣ ሌሎች ተጠርጣሪዎችን እያጣራ መልቀቁን ገልጾ በችሎቱ የቀረቡት ተጠርጣሪዎች ላይ ለሚቀረው ተጨማሪ ምርመራ 14 ቀናት ተጨማሪ ጊዜ ጠይቋል፡፡

ፖሊስ ተጨማሪ ጊዜ የፈለገበትን ምክንያት ለፍርድ ቤቱ እንዳስረዳው አንድ ኢንስፔክተር፣ አንድ ምክትል ኢንስፔክተር፣ አንድ ምክትል ሳጂንና አንድ ኮንስታብል ግጭትና ብጥብጥ ከፈጠሩት ጋር በመተባበር ፀጥታ ለማስከበር በወጡ የሥራ ባልደረቦቻቸውና ሌሎች ሰላማዊ ሰዎች ላይ ጉዳት በማድረስ መጠርጠራቸውን መርማሪ ፖሊስ ለፍርድ ቤቱ አስረድቷል፡፡ ተጎጂዎቹ በጥቁር አንበሳና በፖሊስ ሆስፒታል ኮማ ውስጥ ስለሆኑ በመሆናቸው ቃል አለመቀበሉን ገልጿል፡፡ ተጎጂዎቹን አሁን ባሉበት ሁኔታ ማናገርና ቃል መቀበል ባለመቻሉ፣ በቀጣይ የሚሻላቸው ከሆነ የእነሱን ቃል ለመቀበልና ተጨማሪ የምስክሮችን ቃል የመቀበል ሥራ እንደሚቀረው ለፍርድ ቤት አስረድቷል፡፡

ሌሎች በግጭቱና ብጥብጡ የተሳተፉና የሚይዛቸው ተጠርጣሪዎች እንዳሉት ፖሊስ አስረድቶ፣ በሆስፒታል ውስጥ በሞትና በሕይወት መካከል ያሉት ተጎጂዎች ሁኔታ ሳይለይለት ለተጠርጣሪዎቹ ዋስትና ሊፈቀድ እንደማይገባ አመልክቷል፡፡

የተጎዱት ሰዎች ቢሞቱ ተጠርጣሪዎቹ የሚቀርብባቸው ክስ የመግደል ወንጀል ክስ ሊሆን ስለሚችል፣ በወንጀል ሕግ ሥነ ሥርዓት ቁጥር 63 መሠረት ዋስትና ሊከለከሉ እንደሚችሉ መርማሪ ፖሊስ በመጠቆም የዋስትና ጥያቄውን ተቃውሟል፡፡

በግጭቱ ወቅት አንድ ተጠርጣሪ ሆዱ አካባቢ በጥይት ተመትቶ የነበረ ሲሆን፣ ቀዶ ሕክምና የተደረገለት ቢሆንም ጥይቱ ከሆዱ ሊወጣ ባይችልም፣ በወቅቱ በግጭቱ በነበረው ተሳትፎ ምክንያት ፍርድ ቤት እንዲቀርብ ተደርጓል፡፡ ግለሰቡ በጥይት እንዴት ሊመታ እንደቻለና ማን እንደመታው ፖሊስ ምርመራ እያደረገ መሆኑን ለፍርድ ቤት ተናግሯል፡፡ የአዲስ ጉዳይ ፎቶ ጋዜጠኛ አዚዛ መሐመድና የሰማያዊ ፓርቲ አባል ወ/ት ወይንሸት ሞላ፣ ተጨማሪ የምርመራ ቀናት ከተጠየቀባቸው ተጠርጣሪዎች መካከል ናቸው፡፡ ፖሊስ ስለነሱ የወንጀል ተሳትፎ ለፍርድ ቤቱ ሲያስረዳ፣ በግጭቱ ወቅት ሕዝቡ ሲሸሽ ‹‹ወንድ ሆነህ የት ነው የምትሸሸው?›› በማለትና ወደ ግጭቱ እንዲመለሱ በማድረግ፣ ግጭቱን ሲያባብሱ እንደነበር የሚያሳይ በቪዲዮ የተደገፈ ማስረጃ እንዳለው በማስረዳት ዋስትናቸውን ተቃውሟል፡፡ እነሱ አደፋፍረው ባባባሱት ግጭት የተጎዱና በሆስፒታል ኮማ ውስጥ ያሉ ተጎጂዎች ጉዳይ እልባት ሳያገኝ ዋስትና እንዳይፈቀድላቸው ፖሊስ አመልክቷል፡፡

የግራ ቀኙን ክርክር ያዳመጠው ፍርድ ቤቱ የጥቁር አንበሳ ሆስፒታልና ፖሊስ ሆስፒታል፣ ተጎጂዎቹ ያሉበትን ደረጃ የሚገልጽ ማስረጃ እንዲልኩ በችሎት በመንገርና ፖሊስ ቀረኝ የሚለውን ምርመራ በአጭር ቀናት እንዲያጠናቅቅ በማዘዝ ለሐምሌ 29 ቀን 2006 ዓ.ም. ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል፡፡

Saturday, August 2, 2014

በእስር ቆይታቸው 100 ቀናት ለደፈኑት ጦማርያን የተማጽኖ ደብዳቤ ለጠቅላይ ሚኒስተሩ ተላከ፡፡

August2/2014
‹‹ዞን ዘጠኝ››  የጦማሪያን ቡድን አባላት ዘለዓለም ክብረት፣ ናትናኤል ፈለቀ፣ ማህሌት ፋንታሁን፣ በፍቃዱ ኃይሉ፣ አቤል ዋበላና ሶልያና ሺመልስ ሲሆኑ፣ ተስፋለም ወልደየሱስ፣ አስማማው ኃይለ ጊዮርጊስና ኤዶም ካሳዬ ደግሞ ጋዜጠኞች ናቸው፡፡ ሶልያና የተከሰሰችው በሌለችበት ነው፡፡
በቅርቡም ቀደም ሲል መንግሥት በአሸባሪነት የፈረጀው የግንቦት ሰባት ዋና ጸሐፊ አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ ከየመን ዋና ከተማ ሰነዓ በቁጥጥር ሥር ውለው ይገኛሉ፡፡ እንዲሁም ደግሞ በተመሳሳይ ጊዜ በሽብርተኝነት ተጠርጥረው አራት የተቃዋሚ ፖለቲካ ፓርቲዎች አመራሮችን (አብርሃ ደስታ፣ ሀብታሙ አያሌው፣ ዳንኤል ሺበሺና ስለሺ አሰፋ) መንግሥት በቁጥጥር አውሏል፡፡
ethopia-bloggersመንግሥት የፀረ ሽብርተኝነት አዋጅ ካፀደቀ ጊዜ ጀምሮ በርካቶች በዚህ ሕግ እየጠየቀ ይገኛል፡፡ ይህንን ሕግ፣ የሲቪል ማኅበራት አዋጅ፣ እንዲሁም የፕሬሱ አዋጅ ከዓለም አቀፍ ማኅበረሰብ ትችት ሲቀርብበት የቆየ መሆኑም አይዘነጋም፡፡
ይህ በእንዲህ እንዳለ ሰሞኑን በርካታ ዓለም አቀፍ የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ድርጅቶች ለጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለ ማርያም ደሳለኝ የተማፅኖ ደብዳቤ ልከዋል፡፡ ከደብዳቤው ፈራሚዎች መካከል ሂዩማን ራይትስ ዎችና አምነስቲ ኢንተርናሽናል በግንባር ቀደምትነት የሚገኙበት ሲሆን፣ እነዚህ ድርጅቶች ኢትዮጵያ ውስጥ ባለው የሰብዓዊ መብት አያያዝና የፕሬስ ነፃነት ከኢትዮጵያ መንግሥት ጋር ተስማምተው አያውቁም፡፡
እነዚህ ድርጅቶች በየጊዜው በሚያወጡዋቸው ሪፖርቶች ከመንግሥት ጋር ሲጋጩ የቆዩ ሲሆን፣ በተለይ የኢትዮጵያ የፀጥታ ኃይሎች በሶማሊያና በኦጋዴን ተፈጸመ ባሉት የሰብዓዊ መብት ጥሰት ምክንያት ግንኙነታቸው እጅግ እንዲሻክር ምክንያት ሆኖ ነበር፡፡
አምነስቲ ኢንተርናሽናልና ሂዩማን ራይትስ ዎች አንዳንዴም የአሜሪካ ስቴት ዲፓርትመንት በዓመታዊ ሪፖርታቸው በኢትዮጵያ መንግሥት የሰብዓዊ መብት አያያዝ ላይ ከፍተኛ ትችት የሚሰነዝሩ ሲሆን፣ መንግሥትም አንዳንዴ ዘጋቢ ፊልሞችን በመሥራት የአፀፋ ምላሽ ሲሰጥ ይስተዋላል፡፡
ሰሞኑን ለጠቅላይ ሚኒስትሩ የተላከው ደብዳቤም አርቲክል 19 እና እነዚህ ሁለት ድርጅቶች በግንባር ቀደምትነት ያሉበት ሲሆን፣ በአጠቃላይ ደብዳቤው ላይ ፊርማቸውን ያሳረፉ ግን ቁጥራቸው አርባ አንድ ነው፡፡
መንግሥት የተቃዋሚ ፖለቲካ ፓርቲ አመራሮችንም ሆነ ጋዜጠኞችን ወይም  የፖለቲካ ተሟጋቾች በእስር ሲያውል እንዲህ ዓይነት ደብዳቤ መጻፍና የታቃውሞ መግለጫ ማውጣት የተለመደ ቢሆንም፣ በዚህ ደረጃ በዓለም ዙሪያ ያሉት የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ድርጅቶች (ብዙዎቹም አፍሪካ ውስጥ የሚገኙ ናቸው) በአንድ ላይ መንግሥትን ሲቃወሙ ለመጀመርያ ጊዜ ነው፡፡
የኢትዮጵያ መንግሥት እነዚህ የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ድርጅቶች፣ በተለይ የምዕራባዊያን የፖለቲካ አቋም ኒዮ ሊብራሊዝምን አራማጆች በሚል ምንም ዓይነት መለሳለስ የማያሳይ ሲሆን፣ የአገሪቱ የፖለቲካ ዕድል በራሷ ሕዝቦችና በራሷ መንግሥት ብቻ እንዲወሰን የፀና አቋም አለው፡፡
ጠንካራና ነፃ የሰብዓዊ መብት ተቋም በሌለበት በየትኛውም አካባቢ በሚኖር ሕዝብ የሚፈጸም የሰብዓዊ መብት ጥሰት ያገባኛል የሚል አቋም ያላቸው እነዚህ ድርጅቶች ግን፣ ሰብዓዊ መብት የዓለም አቀፋዊነት (ዩኒቨርሳል) ጉዳይ መሆኑን በመከራከሪያነት ያቀርባሉ፡፡
ደብዳቤው ክብደት ይኖረው ይሆን?
አርባ አንድ ድርጅቶች ፊርማቸውን ያሳረፉበትና “Detention of Bloggers is a Violation of International Law” [ጦማርያንን ማሰር ዓለም አቀፍ ሕግን መጣስ ነው] በሚል ለጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለ ማርያም የተላከው ይኸው ደብዳቤ፣ ዋና ይዘቱ ላለፉት ሦስት ወራት በእስር የቆዩትና በቅርቡ ክስ የተመሠረተባቸውን ጦማሪያን መንግሥት በነፃ እንዲለቃቸው የሚጠይቅ ሲሆን፣ ሌሎች ቀደም ሲል ሲያነሱዋቸው የነበሩት ቅሬታዎችም ተካተውበታል፡፡
በመጀመሪያ ኢትዮጵያ በርካታ ዓለም አቀፍ የሰብዓዊ መብት ስምምነቶችንና የአፍሪካ ቻርተሮችን ፈራሚ መሆኗ ተጠቅሶ፣ የኢትዮጵያ ፀረ ሽብርተኝነት ሕግ እነዚህን ዓለም አቀፍ ስምምነቶችና የአገሪቱ ሕገ መንግሥት ይጥሳል በሚል ነው፡፡ ለዚህም እንደ ማስረጃ ያቀረቡት፣ አንዳንድ የተመድ አጣሪ ቡድኖች ቀደም ሲል በሽብር የተፈረደባቸው የፖለቲካ አቀንቃኝ እስክንድር ነጋ፣ ጋዜጠኛ ውብሸት ታዬ፣ መምህርትና ዓምደኛ ርዕዮት አለሙና አንዱዓለም አራጌ ላይ ያቀረቡዋቸውን ሪፖርቶች ዋቢ በማድረግ ነው፡፡ በእነዚህ ግለሰቦች ላይ ተፈጸመ ያሉት የሰብዓዊ መብት ጥሰት፣ የፀረ ሽብርተኝነት አዋጅ መንግሥት ተቃዋሚዎችንና ጋዜጠኞችን ለማፈን እንደ መሣሪያ ተጠቅሞበታል የሚለውን ድምዳሜ ዓለም አቀፍ ተቀባይነት ያገኘ ሐሳብ እንደሆነ አቅርበዋል፡፡ የፀረ ሽብርተኝነት አዋጁ እንዲከለስም የደብዳቤው ሌላ ዋና ይዘት ነው፡፡
በደብዳቤው ፊርማቸውን ካሳረፉት ድርጅቶች መካከል የአራቱ ተቀማጭነታቸው በናይጄሪያ፣ የሦስቱ በደቡብ ሱዳን፣ የሁለቱ በግብፅ፣ የሁለቱ ደግሞ በብሩንዲ ሲሆኑ የተቀሩት ማዕከላዊ አፍሪካ፣ ታንዛኒያ፣ ዛምቢያ፣ ዚምባቡዌ፣ ጋምቢያ፣ ምዕራብ አፍሪካና ኬንያ ውስጥ ነው፡፡ የተቀሩት ደግሞ ከዞን ዘጠኝ ጋር በተያያዘ ስሙ ተደጋግሞ ሲነሳ የነበረው አርቲክል 19ን ጨምሮ ተቀማጭነታቸው በአውሮፓና በአሜሪካ ነው፡፡
ደብዳቤው በተመድ፣ በአውሮፓ ኅብረትና በአፍሪካ ኅብረት ድርጅቶች ውስጥ በኢትዮጵያ መንግሥት ላይ ተፅዕኖ ለመፍጠር ዓላማ ያደረገ ይመስላል፡፡
‹‹መንግሥት አቋሙ መመርመር አለበት›› 
የኢትዮጵያውያን ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (ኢዴፓ) የቀድሞ ሊቀመንበር አቶ ሙሼ ሰሙ፣ የደብዳቤውን ተፅዕኖ ፈጣሪነት በሁለት አቅጣጫ አይተውታል፡፡ ቀደም ሲል በተመሳሳይ የተለያዩ የተቃውሞ ሪፖርቶች ቢወጡም እዚህ ግባ የሚባል ለውጥ በመንግሥት አሠራር ላይ አለማምጣታቸውን ያስታውሳሉ፡፡ መንግሥትም በራሱ መንገድ ድርጅቶችን መፈረጁን እንደቀጠለ ያስረዳሉ፡፡ እነዚህ ዓይነት ሪፖርቶች ተፅዕኖ ያልነበራቸው አንድም በመንግሥት ቀድመው የተፈረጁ በመሆናቸው ለመቀበል የሚያሳየው ባህሪ አነስተኛ መሆኑን፣ እንዲሁም ድርጅቶቹ የሪፖርት እወጃቸው በመንግሥት ተቀባይነት ሲያጣ ቀጥለው የሚሠሩት ሥራ አለመኖሩ እንደሆነ ይናገራሉ፡፡ ‹‹እስከምን ድረስ ይሄዳሉ?›› የሚል ጥያቄም ሰንዝረዋል፡፡
አቶ ሙሼ በተጨማሪ የትም ቢሄዱ ‹‹ምን ያህል ተፅዕኖ መፍጠር ይችላሉ?›› የሚል ሌላ ጥያቄ ያነሳሉ፡፡ ‹‹ድርጅቶቹ ቀጥተኛ ተፅዕኖ መፍጠር አይችሉም፡፡ የተቀመጡባቸው አገሮች መንግሥታት ኢትዮጵያ ላይ አንዳንድ የዕርዳታና የብድር ማዕቀብ እንዲጥሉ የሚወተውቱ ቢሆንም፣ እስካሁን ተግባራዊነቱ አልታየም፤›› ሲሉም አክለዋል፡፡
መንግሥታት በእነዚህ ድርጅቶች ከሚቀርብላቸው ጥያቄ የበለጠ አቋማቸውን የሚመለከቱት ከአጠቃላይ የሕዝብ ፍላጎትና የአገር ለአገር ግንኙነት አንፃር መሆኑንም ተናግረዋል፡፡
አቶ ሙሼ እንደሚሉት ደብዳቤው ሌላ ፋይዳ ግን አለው፡፡ በዚህ ደረጃ ለኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር የቅሬታ ደብዳቤ ሲጻፍ ለመጀመሪያ ጊዜ መሆኑን የጠቆሙት አቶ ሙሼ፣ ለድርጅቶቹ ቁጥር ትልቅ ሥፍራ ሰጥተውታል፡፡ ‹‹በያሉበት የራሳቸውን ተፅዕኖ ይፈጥራሉ፤›› ብለዋል፡፡
እሳቸው እንደሚሉት፣ መንግሥት ጥያቄው ከእነሱ ስለመጣ ሳይሆን የተጻፈውን በትዕግሥት አይቶ ክፍተቱን ለመሙላት አቋሙን በመፈተሽ ቢጠቀምበት መልካም ነው፡፡ ዋናው ተፅዕኖ አገር ውስጥ ከሚገኙት ከሕዝብና ከተቃዋሚ ፖለቲካ ፓርቲዎች መሆን እንዳለበትም መክረዋል፡፡ ‹‹ሰው በአስተሳሰቡ ምክንያት መታሰር የለበትም፤›› በማለት በፍርድ ቤት በተያዘ ጉዳይ ላይ ከዚህ የዘለለ አስተያየት ከመስጠት አቶ ሙሼ ተቆጥበዋል፡፡
ቀደም ሲል እንዲህ ዓይነት ሪፖርት ከሰብዓዊ መብት ተሟጋች ድርጅቶች ሲወጣ መንግሥት አፋጣኝ ምላሽ የሚሰጥ ሲሆን፣ ለዚህኛው ደብዳቤ መልስ በሚመስል ሁኔታ ስለድርጅቶቹ ሪፖርት እንከንና ስለኢትዮጵያ አቋም የሚያሳይ ዶክመንተሪ በኢቲቪ ማክሰኞ ምሽት ቀርቧል፡፡
የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ በሰጡት አጭር ምላሽ የመማር፣ የመጻፍና የማሰብ ነፃነት የመሳሰሉ የሰብዓዊ መብት ጉዳዮች የኢትዮጵያ መንግሥት የዴሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ አካል መሆናቸውን አስረድተዋል፡፡ ከዚህም በመነሳት፣ ‹‹ሰብዓዊ መብት የኢትዮጵያ ፖሊሲ እምብርት ነው፣ የህልውናችን ጥያቄ ነው፤›› በማለትም፣ ኢትዮጵያ ውስጥ ግልጽ የሆነ የሕግ ጥሰት ካልተፈጸመ በስተቀር ሰዎች የመሰላቸውን በመጻፋቸው እንደማይታሰሩ አስረድተው፣ የውጭ ድርጅቶችን የሚመለከት ጉዳይ እንዳልሆነም ገልጸዋል፡፡ ‹‹በአንድ ሉዓላዊ አገር ፖለቲካ ውስጥ እየገቡ እገሌን ፍቱ፣ እገሌን እሰሩ የማለት መብት የላቸውም፣ በእነሱ ጥያቄ የሚመጣ ለውጥ አይኖርም፤›› ብለዋል፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለ ማርያም ለተማፅኖው ደብዳቤ ግልጽ ምላሽ ያልሰጡ ቢሆንም፣ ቀደም ሲል ለእስር የተዳረጉ ጋዜጠኞችንና ጦማሪያንን አስመልክቶ ለቀረበላቸው ጥያቄ ሲመልሱ፣ ‹‹አንድም በሙያው የታሰረ ሰው የለም፡፡ ኢትዮጵያን ለማናጋት የተዘረጋው የሽብር መረብ እስኪበጣጠስ ግን ከዚህ መረብ ጋር የተገናኘ ማናቸውም ሰው ላይ ዕርምጃ መውሰዳችን እንቀጥላለን፤›› በማለት የመንግሥታቸውን አቋም ግልጽ አድርገዋል፡፡

ስለ ዳተኛ ምሁራንቸል አንበል

August2/2014
ዳኛቸው ቢያድግልኝ
ምሁር የሚለው ስያሜ እውቀት የተካነ ጥበብን አፍላቂ የዐለምን ምስጢር መርማሪ፣ እውነት መስካሪና አስተማሪ ለሆኑ የሚሰጥ መጠርያ ነው ወይንስ በአንዱ ወይም በሌላው ተቋም ውስጥ ያለፉና ያንን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት (ከአርከበ ሱቅ ከሚገዛው በቀር) ለተቀበሉ ሁሉ የሚሰጥ ነው? የሚል ጥያቄ በየወቅቱ ይነሳል። ብዙ ባለምስክር ወረቀቶች ግራና ቀኝ ማየት የማይደፍሩ፣ እውነት የማይመሰክሩ የተሻለ ደሞዝ፣ ዝናና ክብር የሚያማልላቸው ስምና የትምህርት ደረጃቸውን ለመተዳደርያ ብቻ የሚያደርጉ ሆነዋል የሚል ወቀሳም እየበዛ ነው። እንዲያውም ‘መማር እንደዚህ ከሆነ’ የሚሉ የተሳሳተ አቅጣጫ የሚይዙ ሰዎች የመጡበትም አንደኛው ምክንያት ይኸው ነው። ይህ ማለት የተማሩ ሰዎች ሁሉ እንደ ኃይለማርያም ደሳለኝ ፖለቲከኛ ለምን አልሆኑም ማለት አይደለም። ፖለቲካ ሳይንስ ነው ካልን ሰዎች ባልተካኑበት ቢቀድሱ ከመዕመናን ጆሮ ላይደርሱ ቢደርሱም እንደሳቸው ተደናግረው ሊያደናግሩ ይችላሉ። ይሁን እንጂ ነፃነት፣ መብትና ፍትህን መፈለግ የፖለቲካ ጠበብትነትን አይሻም፣ ሰው መሆንን ብቻ እንጂ። በተለያየ ሙያ ከሰለጠኑ ምሁራንም በትንሹ የሚጠበቀው ለመብትና ለነፃነት ቀናዒ እንዲሆኑ ነው።

ለመጻፍ መነሳሳቴን የፈጠረው ዛሬ ያነበብኩት በኢያሱ ለበኑ የተጻፈው Ethiopia: The Tale of Two Minister D’états የሚለው ጽሁፍ ነው። ይህ በእንግሊዝኛ የተጻፈው ጦማር ሁለት የአባትና የልጅ ያህል ልዩነት ያላቸውን ሚኒስትር ደኤታዎችን የሚያነጻጽርና አንደኛው በጣም የተማሩና አዛውንቱ ዶር ተቀዳ አለሙ ከሁሉም አገዛዞች ጋር እጅና ጓንት ሆነው የሚሄዱ ለሁሉም አገልጋይ ስለመሆናቸውና ሌላኛው ኤርምያስ (ወያኔ ሲገባ እድሜው ሃያ ያልገባ) ከመንግስት ጋር ሆኜ አገር መግደልና ሕዝብ መበደል ይብቃኝ ብለው አለቃቸውን ስለነበረን ጊዜ አመሰግናለሁ በሚል ደብዳቤ ወደ እውነት ለመጠጋት ምቾትንና ስልጣንን ጥለው ስለሄዱት ግለሰብ የሚመለከተው ነው። ወያኔ ሲገባ የነበረው ሞቅ ሞቅና በደርግ ላይ የነበረው አፍላ ጥላቻ የልጅነት መልቀቂያ ፈተና ተቀብሎ ወደ ጉርምስና የሚሸጋገር እንደ ኤርምያስ ላለ ወጣት የሚመርጠውን መንገድ መሞገት አሰቸጋሪ ነው። ወደ ጉልምስና ሲሻገር ግን እውነት ማየት ከተሳነው ችግር እንዳለ ያመለክታልና ኤርምያስም እውነትን አሻግሬ ተመለከትኩ ያለሁበትንም ጠላሁ ብለው የራሣቸውን እድል በራሳቸው ወሰኑ። ዶክተሩ ደግሞ ወደ አዲስ የመንግስት የስልጣን ግምጃ ቤት እየተቀዱና በቀላሉ እየተደባለቁ ስለመኖራቸው የሚያነጻጽረው ጦማር ጊዜያችንን ገላጭና ጥያቄ አጫሪም ነው።

የኢያሱ ለበኑ ጦማር በኦሪየንታሊዝም ጽሁፉና በሌሎችም ስራዎቹ ታዋቂ የሆነው ፕሮፌሰር ኤድዋርድ ሰይድን (1935 – 2003) ሃሳብ የሚጋራ ይመስለኛል። ፕሮፌሰሩ በአንድ ጽሁፉ …

“Nothing in my view is more reprehensible than those habits of mind in the intellectual that induce avoidance, that characteristic turning away from a difficult and principled position which you know to be the right one, but which you decide not to take. You do not want to appear too political; you are afraid of seeming controversial; you need the approval of a boss or an authority figure; you want to keep a reputation for being balanced, objective, moderate; your hope is to be asked back, to consult, to be on a board or prestigious committee, and so to remain within the responsible mainstream; someday you hope to get an honorary degree, a big prize, perhaps even an ambassadorship. For an intellectual these habits of mind are corrupting par excellence. If anything can denature, neutralize, and finally kill a passionate intellectual life it is the internalization of such habits.” (Edward Said, 1994, Representations of the Intellectual, pp.100-101)

ሃሳቡ ወደ አማርኛ ሲመለስ “… እንደ እኔ አመለካከት በመርህ ላይ የተመሰረተ አስቸጋሪ ግን ትክክለኛ አቋም ከመያዝ ሆን ብለው የሚሸሹ ምሁራንን ያህል አሳፋሪ ነገር የለም። ፖለቲከኛ ላለመምሰል ተሟጋችና አስቸጋሪ ላለመባል የአለቃን ወይም የበላይን መልካም ፈቃድ ብቻ በመጠበቅ ሚዛናዊና ተጨባጭ ሁኔታን ያገናዘቡ ናቸው በመባል በትላልቅ ስፍራ ለመጋበዝ አማካሪ ለመሆን የከፍተኛ ኮሚቴዎች አባል ለመሆንና በትላልቅ የቦርድ ስብሰባዎች ለመገኘት፣  ከሃላፊዎች ተርታ ለመቆም እናም አንድ ቀን የክብር ዲግሪ ለማግኘት፣ ትላልቅ ሽልማቶች ለመሸለም ምናልባትም አምባሰደር ለመሆን ይጥራሉ። ይህ አይነቱ ባህርይ ምሁርን ከምንም ነገር በላይ የሚያረክስና እርባናቢስ አድርጎ የሚያከሽፍ ልማድ ነው…”

በርካቶቻችን በዘልማድ ለዚህ አይነት ሰዎች ሞገስና ክብር መስጠታችን ደግሞ እጅጉን ጎድቶናል። ስለ ጨዋነትና ጥሩ ሰውነት መገለጫው ዝምተኛነትና ዳተኛነት ነው። ‘እሳቸው ዝም ነው… አይቶ እንዳላየ ናቸው… ሰው ቀና ብለው አያዩም… ከሁሉም ጋር አብረው ይሄዳሉ…. ምንም ውስጥ የሉበትም.. ኑሮአቸውን ብቻ ነው የሚኖሩት…ወዘተ። በሚሉ አባባሎች ውስጥ መልካም ነገሮች ቢኖሩም አንኳ እነዚሀ የባህርይ መገለጫዎች ለመብትና ነፃነት ተቆርቋሪ የሆኑትን ፍትህ ፈላጊዎች አሳናሽ ናቸው። ስለዚህ የመብት ታጋዮችን ‘ነገረኞች’ “አሳዳሚዎች’ ያስብላል። በነኚህ ‘ነገረኞችና አሳዳሚዎች’ ጥንካሬና ትግል ሳቢያ የሚመጣውን ጥቅም ግን ቀድመው የሚቋደሱት ምንም ውስጥ የሌሉበት ‘ጨዋዎቹ’ ናቸው። ጉዳት ቢኖረው መስቀል ተሸካሚዎቹ ‘ነገረኞቹና’ ‘አሳዳሚዎቹ’ ይሆኑና “ሳይቸግራቸው… አርፈው ቢቀመጡ ኖሮ” ተብለው ይወገዛሉ።

ለዚህም ይሆናል ዛሬ በሀገርቤትም ይሁን በውጪው አለም በተለያዩ ተቋማት ውስጥ የሚሰሩ ኢትዮጵያዊ ‘ምሁራን’ በደልንና መብት ረገጣን አይቶ እንዳላየ ሲያልፉ የምንመለከተው። ከዚያ የሚብሰው ደግሞ የመፍትሄ አካል ከመሆን ይልቅ እንደ ክህሎታቸው የሚሞክሩትን ሁሉ ማብጠልጠል ማዋረድና መመፃደቅን እንደ ትልቅ ነገር በመቁጠር ሲኮፈሱ የምናያቸውም የበዙበት ምክንያትም ይህ ዳተኝነት ምንም ዋጋ ስለማያስከፍልም ነው። ከዚህ አይነት ስነምግባር በመቆጠብ እውቀታቸውን ቢፈትሹና የሚተርፋቸውን ቢያካፍሉ ከሌሎች ጋርም ቢመክሩ በስሜትና ፍላጎት ብቻ ሳይሆን በእውቀት፣ በአመክንዮና በብልህነት ወደፊት እንድንገሰግስ እገዛቸውን ቢለግሱ የተሻለ ይሆናል። መድረክ ላይ ወጥቶ መናገር ወይም ጽሁፍ መጻፍ ብቻ ሳይሆን ተቋማትን ማጠናከር፣ አዳዲስና ዘርፈ ብዙ እንቅስቃሴዎችን መፍጠር፣ የተራራቀው እንዲቀራረብ የከረረው እንዲረግብ ማድረግ፣ የእውቀት ፍላጎትን በማሳደግ የመረጃ ተፋሰስን በማስፋት ምሁራዊ አስተዋጽኦ የሚደረግባቸውን መንገዶች መፈለግና ሃሳብ ማቅረብ ድርሻቸው ነው እንዲያውም የዜግነት ግዴታቸው ጭምር ነው። ምሁራን የሃሳብ ልዩነቶቻቸውን አንደጠላትነት ሲመለከቱ ክርክራቸውን ወደ ተራ ስድብነት ሲቀይሩት ቂመኝነት የዛሬውን አይናቸውን ሲጋርደው ግን የጥፋት ጥፋት ይሆናል። ሃሳቤን በዚሁ የሃርቫርድ ፕሮፌሰር ኤድዋርድ ሰይድ ጽሁፍ ላጠቃልለው ፈቀድኩ እንዲህ ይላል…

“And finally a word about the mode of intellectual intervention. The intellectual does not climb a mountain or pulpit and declaim from the heights. Obviously you want to speak your piece where it can be heard best; and also you want it represented in such a way as to influence with an ongoing and actual process, for instance, the cause of peace and justice. Yes, the intellectual’s voice is lonely, but it has resonance only because it associates itself freely with the reality of a movement, the aspirations of a people, and the common pursuit of a shared ideal.”

ወደ አማርኛ ሲመለስ “በመጨረሻም ስለምሁራን አስተዋጽኦ እንዲህ እላለሁ። ምሁር ከተራራው ጫፍ ወጥቶ ወይም ከመድረክ ላይ ቆሞ ድል አድርጌአለሁ አይልም። ይልቁንም ሃሳብህን አድማጮችህን በሚገባ ልትደርስበት በምትችለው መንገድ ተናገር። ንግግርህም እየሆነ ባለ አንገብጋቢ ጉዳይ ላይ ይሁን ለምሳሌ ስለ ሰላምና ፍትህ። አዎ የምሁር ድምጽ ብቸኛ ሊሆን ቢችልም እንኳ ስለ ሕዝቡ ፍላጎት ስለ ትግሉ ስለጋራ ግብና የጋራ ስምምነት እስከሆነ ድረስ እንደ ገደልማሚቶ ያስተጋባል።” ይለናል።

ምሁራን እውቀትና ብልህነታቸውን፤ የሕዝባቸውን የነጻነትና የፍትህ ጥማት አገናዝበው ከያሉበት የሚያሰሙት ድምፅ የሚያንኳኩት በር እንደ ገደልማሚቶ እያስተጋባ የሚያስተባብረን ወደ ነጻነትና አንድነት የምናደርገውን ጎዳና የሚያሳምርልን በፍጥነትም የሚያደርሰን ይሆናልና ለዚህ ቢተጉልን በልባችን ውስጥ ሀውልት እንሰራላቸው ዘንድ እውነት ነው። ጠብታ ተጠራቅሞ ጎርፍ ጎርፍም ጎልብቶ ወንዝ እንዲሆን ሁሉ ከያላችሁበት ድምጻችሁ ይሰማ ክፋትን ጠራርጎ የሚወስድ ሕዝባዊ አመጽም ይወለዳል።

ነፃነትና ሰላም ፍትህና ብልጽግና ለኢትዮጵያችን ይሁን
biyadegelgne@hotmail.com