Tuesday, April 8, 2014

Egypt’s Potential Presidential Candidate Threatens to Use Force Against Ethiopia’s Dam

April8/2014

Lawyer and head of a renowned Egyptian soccer club Mortada Mansour speaks during a press conference in the Egyptian capital, Cairo, on 6 April 2014 (AP)

Washington — An Egyptian potential presidential candidate hopeful announced today that he will order the use of military force against Ethiopia if the latter does not suspend the construction of the Grand Renaissance dam.

In announcing his presidential bid at a press conference on Sunday, lawyer Mortada Mansour said that “water for Egypt is Egypt’s life”.

“There are signed international conventions… .There are two agreements, one in 1929 and the other in 1959 to regulate water usage between Egypt and Sudan,” Mansour added.

The controversial figure, who was elected last week as head of Cairo’s Zamalek Club, accused Israel of standing behind the Ethiopian dam project and dismissed popular initiatives to resolve the dispute with Addis Ababa.

“There are international organizations that failed [to mediate] and Ethiopia stuck to its position. Just like they threatened to use their army, Egypt has an army. If Israel which is inciting Ethiopia learned a lesson from the Egyptian army in 1973 [war], you are threatening my life. I will not allow you to build your dam and block water from me and in the end famine occurs among the Egyptian people and we kill each other for a drop of water,” Mansour said.

“Just like they showed off and brought their generals around the dam and said if Egypt can come. No we also have generals and planes O’ Ethiopia that can reclaim Egypt’s rights because we will not allow a drop of water to be cut, to have drought in the country, in agriculture, people can’t find a drop of water. This is vital for us. I thought that for subsequent Egyptian administrations that the issue of water is a life or death issue. This is not up for discussion” he added.

Egypt fears that the $4.6 billion hydropower plant will diminish its share of the river’s water flows, arguing its historic water rights must be maintained.

Ethiopia is the source of about 85% of the Nile’s water, mainly through rainfall in its highlands, with over 90% of Egyptians relying on water from the Nile’s flows.

In June 2012, a panel of international experts tasked with studying the impacts of the Ethiopian dam on lower riparian countries, including Sudan and Egypt, found that the dam project will not cause significant harm to either country.

Cairo remains unconvinced and has sought further studies and consultation with Khartoum and Addis Ababa.

If Mansour’s candidacy is endorsed by the presidential commission he will face the former Egyptian defense minister Field Marshal Abdel-Fatah El-Sisi who is widely seen as almost certain to win. The leftist political figure Hamdeen Sabahi has also pledged to compete in the elections.
Mansour has made a failed bid to run for president in the 2012 elections but was disqualified by the elections committee.

According to a profile by the Daily News Egypt, Mansour said in 2011 that he did not “have the right to run” for president because he is “ill-tempered”.
In April 2011, Mansour was accused of being involved in Tahrir clashes commonly dubbed “the Battle of the Camel” on 2 February, which left 11 demonstrators dead and hundreds injured. He was later acquitted of all charges however.

He ran in four parliamentary elections in 1990, 1995, 2000 and 2012, but only won in the 2000 elections. In 2012, he lost to an opponent from the Muslim Brotherhood.
He is well known for his hot temper and was taken off air in TV phone interviews a number of times for using obscene language.

Mansour is also seen as someone who is obsessed with filing numerous police complaints and lawsuits against figures he has disputes with.

በአዲስ አበባ ባለፈው ሳምንት ቅስቀሳ በማደረጋቸው የታሰሩት የአንድነት አባላት የርሃብ አድማ መቱ

April 7/2014

አንድነት ፓርቲ ለመጋቢት 28/2006 ጠርቶት በነበረው ሰላማዊ ሰልፍ ለህዝብ የተዘጋጀ በራሪ ወረቀት ሲበትኑ በህገ ወጥ መንገድ በቁጥጥር ስር ከዋሉት የአንድነት ፓርቲ አባላት መካከል በስድስተኛ ፖሊስ ጣብያ የሚገኙት አክሊሉ ሰይፉና ወርቁ እንድሮ መታሰራቸውን በመቃወም የርሃብ አድማ መምታታቸው ታውቋል፡፡ ሁለቱ ወጣቶች እስከ ነገ የማይለቀቁ ከሆነ ሚክሲኮ በሚገኘው ፍርድ ቤት ከፖሊስ ጣብያ እንደሚቀርቡ ይጠበቃል፡፡
አንድነት የጠራው ሰላማዊ ሰልፍ በቀጣዩ እሁድ እንደሚደረግም ፓርቲው ማስታወቁ አይዘነጋም፡፡



1978773_10201809671544371_4553591674619978710_n

እነ አብርሃ ደስታ ታስረው ተፈቱ (አፈናው ትግራይ ውስጥ ተባብሷል)

April7/2014


 በትግራይ ውስጥ በግልጽ ህወሃትን በመቃወም ከሚንቀሳቀሱት ተቃዋሚ ፓርቲዎች መካከል አረና አንደኛው እና ዋነኛው ነው። ትላንት እሁድ መጋቢት 28 ቀን፣ 2006 ዓ.ም. በአፅቢ ወንበርታ ወረዳ ሓይቂመስ ሓል ከተማ ስብሰባ ለማድረግ እቅድ አድርገው ነበር። ከስብሰባው በፊት ግን ቅስቀሳ ሲያደርጉ በነበሩ ሰዎች ላይ ህጻናት ድንጋይ እንዲወረውሩባቸው ነው የተደረገው። ቀላል ድብደባም ተፈጽሞባቸዋል። ከያዙት ሆቴል እንዲወጡ አልጋ ያከራየውን ሰው ሲያስፈራሩት ነበር። ይህ አልበቃ ብሎ የተደበደቡት ሰዎች ሶስቱ በፖሊስ ተይዘው ታስረዋል።
ከስፍራው ሁኔታውን ሲዘግብ የነበረው አብርሃ ደስታ ከመታሰሩ በፊት እንዲህ ብሎ ነበር። “በአስተዳዳሪዎች ትእዛዝ የእንዳስላሴ ቤተክርስትያን ሐላፊዎች የቤተክርስቲያኒቱ ማይክሮፎን በመጠቀም የአፅቢ ህዝብ እሁድ (ዓረና ስብሰባ በጠራበት ሰዓት) በእንዳስላሴ ቤተክርስትያን እንዲገኝ እያወጁ ይገኛሉ። እሁድ በእንዳስላሴ ቤተክርስትያን ያልተገኘ “ክርስትያን አይደለም!” እያሉ ህዝብን እያስፈራሩ ነው። …ህወሓት ኢህአዴግ በሁሉም ሀይማኖቶች ጣልቃ መግባት የሚፈልገው እንደዚህ የሀይማኖት መሪዎች የህወሓት የፖለቲካ መሳርያ እንዲሆኑ ስለሚፈልግ ነው። ከወራት በፊት ቄሳውስት ህዝብ ህወሓትን እንዲደግፍ በመስቀል እንዲያስምሉት ታዘው ህዝቡ ፍቃደኛ እንዳልሆነ ይታወሳል።
የህወሓት ስጋት ይህን ያህል ነው። ምንም የህዝብ መሰረት እንደሌለው ስለሚያውቅ ህዝብ በስብሰባ እንዳይገኝ ማድረግ፣ ቅስቀሳ የሚያደርጉም መረበሽ፣ መደብደብ ነው ስራው።” ይህን ያለው አብርሃ ደስታ ስብሰባውን ካደረገ በኋላ ከሌሎች ጋር  ታሰረ። ከዚህ በመቀጠል የምናቀርብላቹህ፤ የአረና አመራሮችና ደጋፊዎች ታስረው በነበረበት ወቅት፤ የፓርቲው ፕሬዘዳንት የሆኑት አቶ ብርሃኑ በርኼ የጻፉትን ነው። እንዲህ ይላል የአቶ ብርሃኑ መልዕክት።
እሁድ መጋቢት 28 ቀን 2006 ዓ/ም ዓረና ትግራይ ህዝባዊ ፖለቲካዊ ስብሰባ በምስራቃዊ ዞን አፅቢ ወንበርታ ወረዳ ጠርቶ ያካሄደ ሲሆን ከትናትና ጀምሮ ህዝቡን ወደ ስብሰባው እንዲመጣ የሚቀሰቅሱ አባሎችና አመራሮች ከድንጋይ ውርወራ ና የቡድን ረብሻ ባለፈ ከተከራዩት አልጋ አስወጥቶ ለሊት የትም ተጥለው እንዲወድቁ ለማድረግ እጅግ ኢ-ሰብአዊ ተግባር መፈፀሙን ተገልፆ ነበር ፡፡ የአፅቢ ፖሊስ አባላቶቻችን ከተከራየትና ገንዘቡን ከፍለው የክፍሉ ቁልፍ ተረክበው በእጃቸው ከሚገኝ ቤት ካለወጣቹህ በማለት ቅዳሜ መጋቢት 27 ቀን 2006 ዓ/ም አቶ አምዶም ገ/ሰላሴ ፣ አቶ ስልጣኑ ሕሸ ፣ መም/የማነ ንጉሰ እስከምሽቱ 2፡30 በአፅቢ ፖሊስ በእስር ነበሩ ፡፡ በዚሁ ቀን የወረዳ አስተዳዳዎች የሚመሩት ለህዝብ የሚታደል በራሪ ፅሑፍ መቅደድና በአረና አባላት ላይ ድንጋይ በመወርበር ሲያውኩ ዛሬ ጥዋት ደግሞ ህፃናትና ምልምል ካድሬዎች ገብረ ማርያም የተባለው የታጠቁ ሚልሻ ጭምር በዓረና አባላት ላይ መጠነ ሰፊ የማወክ ተግባር እንደጀመሩና ስብሰባው እንዳይካሄድ ከፍተኛ ጥረት እንዳደረጉ ተገልፆ ነበር ፡፡
እሁድ ከሰኣት በሁዋላ የህዝብ ስብሰባው እንደተጠናቀቀ ደግሞ የአረና ከፍተኛ አመራሮችና አባሎች እንዲሁም በስብሰባው የተገኙ ወደ 61 የሚሆኑ ገበሬዎች በአፅቢ ከተማ ፖሊስ ጣብያ ታስረዋል ፡፡ የእስሩ መነሻ ምክንያት ተደባዳቢ የወንጀለኞች ቡድን የአረና አባላትን ሲደበድቡና ስብሳባው እንዳይጀመር ሲያውኩ የሚያሳይ መረጃ በሞባይል ቀርፃችኋል የሚል ሆኖ ተቀረፀ የተባለው ፊልም ከተገኘበት የሞባይል ስልክ አውጥቶ ለመንጠቅና ለማጥፋት ያለመ ነው፡፡
የአቶ አብርሃ ደስታ ሞባይል ተወስዶ እየተፈተሸ ሲሆን የሌሎቹ የአረና ከፍተኛ የአመራር አባላትና አባላት ሞባይል ስልኮችም እንዲሁም በስብሰባው የነበሩ ገበሬዎች ሞባይል በፖሊስ ተነጥቆ በአፅቢ ፖሊስ ጣብያ እስር ቤት እየተፈተሸ እንደሆነ ቦታው ያሉ የአረና አባላት ሪፖርት አድርገውልኛል ፡፡
ሁኔታው ለትግራይ ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ዘአማኑኤል ለገሠ በሞባይል ስልካቸው 0914 300868 ልክ ዛሬ እሁድ ከሰአቱ 9፡30 ደውየላቸው ስልኩን እንዳነሱ የምደውልላቸው ያለሁኝ ብርሃኑ በርሀ መሆኔን ገልጨ ልክ በኩሓ አፀያፊ እስርና መንግላታት በዓረና አባለት እየተፈፀመ እንዳለ ሪፖርት ሳደርግላቸው እኔን መሆኔን እንዳወቁ ወዲያው ስልካቸውን የዘጉብኝ እንዳይሆን ብየ ስልኩን እንዳይዘጉብይ በፍጥነት በአፅቢ ስብሰባ የሚያካሂዱ አባላቶቻችን መታሰራቸው ስነግራቸው ንግግሬን ሳልጨርስ ስልኩን ዘጉት ፡፡
ፖሊስ ወንጀል ስለመሰራቱ ማስረጃ የያዘለት ይሸልማል እንጂ ወንጀል መሰራቱን የሚያረጋግጥ መረጃ ለማጥፋት ፖሊስ የሚሰራ ከሆነ ይህ ዓይነቱ ፖሊስ የሰላም አባት ወይስ የወንጀል አባት እንበለው ?
አሁን በፖሊስ ምርመራ በአፅቢ ፖሊስ ጣብያ የሚገኙት 1- አቶ ስልጣኑ ሕሸ የዓረና የድርጅት ጉዳይ ሃላፊና የፅሕፈት ቤት ሃላፊ 2- አቶ ዓምዶም ገብረ ስላሴ የዓረና የህዝብ ግንኙነት ሃላፊ 3- አቶ አብርሃ ደሰታ የዓረና የህዝብ ግንኙነት ኮሚቴ አባልና ስራ አስፈፃሚ አባል 4- መም/ ታደሰ ቢተውልኝ የዓረና ማእከላዊ ኮሚቴ አባል 5- አቶ አስገደ ገብረ ስላሴ 6 – መም/የማነ ንጉሴ 7 አቶ ሃይለ ኪሮስ ታፈረ 8- መም/ ሃይለ 9 አቶ ቴወድሮስ 10 – መምህር ክፍሎም እና ሌሎች የአረና አባላትና 61 የስብሰባው ተሳታፊ የአከባቢው ገበሬዎች ናቸው፡፡
ዓረና ትገራይ ፓርቲ ይህንኑ ዘግናኝ የገዢው ፓርቲ የዓፈና ተግባር እንዲቃወምና እንዲያጋልጥ ለሁሉም ኢትዮጵያዊያን ዜጎች ፣ ለሰብአዊ መብት መከበር የሚሰሩ ተnማት ፣ በኢትዮጵያ ለሚሰሩ የውጭ መንግስታት ኢንባሲዎች እንዲሁም ድምፃቸው ለታፈኑ ድምፅ ለመሆን ለሚሰሩ የሃገር ውስጥና የውጭ ሚድያዎች ጥሪውን ያቀርባል ፡፡ በተጨማሪም እነዚህ የጠራራ ፀሃይ ወንጀለኛች በሕግ ፊት ለመፋለም ይረዳ ዘንድ የቻለ ሁሉ ኢትዮጵያዊ ለዓረና ትገራይ ፓርቲ የገንዘብና የሙያ ድጋፍ እንዲያደርጉ ለሁሉም ወንጀል የሚፀየፉ ወገኖች ጥሪውን ያቀርባል ፡፡
ይህ ዓይነቱ ዓይን ያወጣ ወንጀል የትግራይ ህዝብ ከደርግ አፈና ለመታደግ በ 17 የትጥቅ ትግል ዓመታት ሂወታቸውና ንብረታቸው ለከፈሉ በሂወት ያሉ ለውጥ ፈላጊዎቹ የህወሓት አባለትና ደጋፊዎች እንዲሁም መላ የትግራይ ህዝብ በአማራጭ ሰላማዊ ትግል ለሚያካሂድ ፓርቲ የሚፈፀም ጭፍጨፋ በእራሱ መብት የተቃጣ ወንጀል መሆኑን አውቆ በምሬት እንዲቃወመው ጥሪውን ያቀርባል፡፡
ጭፍን ዓፈና የነፃት ባለ ራአዮችን በማጠናከር የነፃነት ራእይ ገዳዮችን የሚያዳክም ግብዝ ውሳኔ መሆኑን የትግራይ ህዝብ አኩሪ ፀረ ባእዳዊ ገዥዎችና ፀረ ፋሽት ደርግ ተጋድሎ በሚገባ ያስተማረን በመሆኑ በዚሁ እኩይ የደርግን አሻራ የወረሱ የአምባገነኖች ተግባር ዓረና ፓርቲና አባላቱ እንደማይንበረከኩ ሁሉም ሊያቀው ይገባል ፡፡ የዓረና ሃገራዊ ራዕይ የሃገር አጀንዳ ሆኖ በሃገረዊ ለውጥ ይደምቅ ዘንድ ዓረና ጠንክሮ እንደሚሰራም ደግሞ ያረጋግጣል ፡፡
ዓረና ትግራይ ለዴሞክራሲና ለሉእላዊነት ፓርቲ
መጋቢት 28 ቀን 2006 ዓ/ም ከቀኑ 10፡20
መቐለ
ዛሬ አብርሃ ደስታ ከ እስር ተፈቷል። ስለነበረው ሁኔታ እሱ ራሱ ያስተላለፈውን መልእክት ለአንባቢዎቻችን በማስተላለፍ ዘገባችንን እናበቃለን። እንዲህ ይላል የአብርሃ ደስታ የመጨረሻ ዘገባ።
ጓዶች ህወሓት ምንም የህዝብ (በተለይ የትግራይ) እንደሌለው በማረጋገጡ በምርጫ ሙሉ በሙሉ ቢሸነፍ እንኳ ስልጣን በሰለማዊ መንገድ ለማስረከብ ፍቃደኛ እንደማይሆን ከወዲሁ እያረጋገጠልን ነው። በትግራይ ምርጫ ስለመፈቀዱም እርግጠኛ አይደለሁም። ባለፈው ቅዳሜና እሁድ የዓረና አባላት በአፅቢ ከተማ ምግብና አልጋ እንዳያገኙ ተደርጓል። በህፅናትና የህወሓት መሪዎች ተደብድበዋል። እሁድ በዓረና ስብሰባ ለመሳተፍ የመጡ የአፅቢ ኗሪዎች በአዳራሹ በር አከባቢ በድንጋይ ተወግረዋል። እሁድ ማምሻውን የዓረና አባላት በፖሊስ ጣብያ ለሁለት ሰዓት ያህል ታስረዋል (ስለተደበድቡ ታስረዋል)። ተሳታፊዎችና የዓረና አባላት ድብደባ ሲፈፀምባቸው የተቀረፀ ቪድዮ ከዞን (ዓዲግራት) በመጡ ባለስልጣናት በሃይል ተፈትሿል። ሞባይሌ ያለ ፍቃዴ በፖሊስ ሃይል ተነጥቄ የቀረፅኩት የድብደባ ማስረጃ ተፈትሾ ተሰርዟል። የሞባይል ቆፎዬ ተበላሽቷል። አሁን ቅስቀሳችንና ስብሰባችን እንቀጥላለን። ምክንያቱም ህዝብ የራሱን ድምፅ በራሱ የሚያስከብርበት ዓቅም እስኪገነባ ድረስ ማስተማራችን እንቀጥላለን። ህዝብ ራሱ የራሱን ድምፅ ካላከበረ ህወሓት እንዲያከብርለት አይጠበቅምና።

Monday, April 7, 2014

ስለፍትሕ ሲባል፤ ሥርዓቱ ይፍረስ!

April 7/2014
(ተመስገን ደሳለኝ)
 
 ባለፉት አራት አስርታት ሀገሪቱ አያሌ ተግዳሮቶችን መጋፈጧ ባይዘነጋም፤ በተለያየ ጊዜ ሚሊዮኖችን ካረገፈው አሰቃቂው ረሃብ በማይተናነስ መልኩ ሕዝቦቿን ዋጋ ያስከፈለ ጉዳይ ቢኖር የፍትሕ አለመከበር ያስከተለው ሁለንተናዊ ምስቅልቅሎሽ ነው ብሎ ለመናገር የሚያስደፍሩ በርካታ ማሳያዎች አሉ፡፡ የየካቲቱን አብዮት ጠልፎ ሥልጣኑን የተቆጣጠረው ወታደራዊው ደርግ፣ የፍርድ ቤት ደጆችን በጓጉንቸር ቆልፎ ሲያበቃ፣ የራሱ አባላት እጃቸውን እያወጡ ድምፅ በመስጠት በአፄው ባለስልጣናትንም ሆነ ግብረ-አበሮቹ በነበሩ መኮንኖች ላይ የሞት ቅጣትን ያህል የመጨረሻ ከባድ ውሳኔ የማሳለፍን አስደንጋጭ ክስተት ጨምሮ፤ ከከተማ እስከ ገጠር ያደራጃቸው የአብዮት ጠባቂዎችና የገበሬ ማሕበራት ከየቤቱ አንቀው እያወጡ “ነፃ እርምጃ” እንዲወስዱ፣ ከየእስር ቤቱ እየለቃቀሙ በጅምላ እንዲረሽኑ በአዋጅ የፈቀደበት ጊዜ የፍትሕ ምኩራቡ ፈርሶ በግላጭ የተቀበረበት ዕለት ነው ቢባል ማጋነን አይሆንም፡፡ በርግጥ ይህ የማን-አለብኝነት አረመኔያዊ አገዛዝ የታቃውሞውን ጎራ በማጠናከር ታሪካዊ ውድቀቱ እንዲፋጠን ካደረጉ ምክንያቶች አንዱ እንደነበር ለመረዳት 17 ዓመታትን መውሰዱ አይዘነጋም፡፡

 “ፍትሕ አልባው አምባ-ገነናዊ የደርግ ስርዓት አማርሮ በርሃ ያስወጣንና ብሶት የወለደን የለውጥ ሃዋርያት ነን፤ በመቃብሩም ላይ
ፍትሕ-ርትዕ የሰፈነባት ዲሞክራሲያዊት አገር እንመሰርታለ” በማለት ከበሮ ይደስቁ የነበሩት የያኔው “ነፃ አውጪዎች”ም፣ ደርግ አፍርሶ የቀበረውን የፍትሕ ምኩራብ አመዱን አራግፈው ቢያነሱትም፤ ባነበሩት አስመሳይ ሥርዓት በኩል በዘውግ ማንነት፣ በሙስናና በሙያ አልባ ዜጎች በክለው ክብር የለሽ ሲያደርጉት በጣት የሚቆጠሩ ወራት እንኳ አልፈጀባቸውም፡፡ ‹‹አዲስ ንጉስ አንጂ ለውጥ መቼ መጣ!›› እንዲል ከያኒው፤ ካስወገዱት የደርግ መንግስት ጋር ልዩነታቸው-ደርጉ ያልቻለበትን የተቃውሞ ድምፆች በአዋጅ እንዲንቀሳቀሱ በአንድ በኩል ፈቅደው፣ በሌላ በኩል መልሶ ለመጨፍለቅ የፍርድ ቤቶችን ባረኮት የመጠቀም ባለ ሁለት ገፅ ብልጠታቸው ብቻ ነው፡፡

 ይህ አይነቱ አገዛዝም ሥልጣን በያዘ ማግስት ሀገሪቱን እንዳሻው ለመርገጥ ሲቪል ቢሮክራሲውን ብቻ ሳይሆን የፍትሕ ስርዓቱንም በአምሳሉ አፍርሶ መስራት ነበረበት፡፡ ይሁንና ተቋሙን በዚህ መልኩ ለማዋቀር ጊዜ እንደሚያስፈልግ በመረዳቱ አሁን ድረስ በቂ
መከራከሪያ ሊቀርብላቸው የማይችሉ ጉዳዮችን ከፍትሕ ሥርዓቱ ነጥቆ ሕገ-መንግስቱ ውስጥ በመዶል ለሌሎች ሰጥቷል፡፡ ለዚህ ደግሞ በቂ ማሳያ የሚሆነው፤ ሕገ-መንግስታዊነትን አስመልክቶ የሚነሱ የማጣራት ኃላፊነቶችን ለፌዴሬሽን ምክር ቤት መስጠቱ ነው፡:

በርግጥ አንዳንድ የወቅቱ ዘገባዎች እንደሚያሳዩት ሕገ-መንግስቱ በተረቀቀበት ሰሞን፣ ከሕገ-መንግስቱ የሚጣረሱ አዋጆች፣ ክሶች
አሊያም ኩነቶች ሲፈጠሩ፣ የማጣራቱ ኃላፊነት የፍርድ ቤት መሆን አለበት ሲሉ የተከራከሩ ድምፆች ነበሩ፡፡ ዳሩ ውሎ-አድሮ ምን
እንደሚሰሩ አስቀደመው የሚያውቁት ታጋዮች፣ በዛ ካድሬ-ዳኞች ባላፈሩበት ወቅት እንዳሻቸው ሕገ-መንግስቱን እየናዱ ቢያስሩ፣ አዋጅ ቢያወጡና ቢያስፈርዱ ድጋፉን የሚሰጣቸው ተቋም፣ በኢሠፓውያን እንደተሞላ የሚጠረጥሩት ፍርድ ቤት ሳይሆን፣ እንደ ልብ ሊቆጣጠሩት የሚችሉት የፌዴሬሽን ምክር ቤት መሆኑን በመረዳታቸው፣ በፓርላሜንታዊ ሥርዓት ትመራለች በተባለች ሀገር ብዙም ባልተለመደ አኳኋን ሕገ-መንግስታዊ ትርጉም የሚሻቸውን ጉዳዮች የማጣራት ስራን ለዚሁ ምክር ቤት ሰጡት፡፡ ከዚሁ ጎን ለጎንም በጥቂት ዓመታት ውስጥ የፍትሕ ተቋሙን በፓርቲ ፖለቲካ የተተበተበ፣ ለጉልበተኛ የሚገብር፣ ገንዘብ ሊገዛው የሚችል፣ ተቀናቃኝ ድምፆችን የማፈኛ መሳሪያ… አድርጎ የመቅረፅ ዓላማቸውን ማሳካት ችለዋል፡፡ በውጤቱም ተቋሙ የህግ የበላይነት የተደፈጠጠበት አድሎአዊና በየጊዜው ደካሞችን የሚያጠቃ ከሆነ እነሆ ከሁለት አስርት በላይ አስቆጥሯል፡፡

 የሆነው ሆኖ የሥርዓቱን ፍትሕ ረጋጭነት በተጨባጭ ፍፃሜዎች አስደግፎ ለማቅረብ ሁለት አብነቶችን እጠቅሳለሁ፡፡ ቀዳሚው
የበርካታ ግፉአንን እሪታ ሲወክል፤ ተከታዩ ደግሞ የገዥዎቹን የሙስና እና የጓዳ ፖለቲካ ትስስሮች ይጠቁመናል ብዬ አምናለሁ፡፡

የሞገስ ወልዱ-ጩኸት

 ሰማይ ከመፍገጓ በፊት፣ ሁሌ ንጋት ላይ ኮተቤ አካባቢ ከሚገኘው መኖሪያ ቤቱ ተነስቶ፣ በእግሩ ሰከም ሰከም እያለ ከጠዋቱ ሶስት
ሰዓት ግድም ልደታ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ይደርስና ዋናው በር ፊት ለፊት ቆሞ ከአንድ ሰዓት ላላነሰ ጊዜ ‹‹ሌባ ዳኛ!›› እያለ ይጮኻል፡፡ ያፏጫል፡፡ ‹‹እናንተ ገላችሁኛል፤ ቀብራችሁኛል፤ አምላክ ፍርዱን ይሰጣል!›› በማለትም ተስፋው በሰማያዊው መንግስት ላይ ብቻ እንደሆነ ያውጃል፡፡ …ይህ ሰው እንደምን ያለ ከባድ በደል ቢደርስበት ይሆን ምሬቱ እንዲህ ጣራ የነካው?

 አሳዛኙ የሞገስ ታሪክ እንዲህ ይጀምራል፡- በ1997 ዓ.ም የወላጅ እናቱን ወ/ሮ አስካለ ቢፋ ህልፈት ተከትሎ፣ ወንድሙ ኃይሉ
ወልደአማኑኤል የወራሽነት ድርሻውን እንዲያካፍለው ክስ መስርቶ ሲያበቃ፤ ሶስት ጥያቄዎችን ለፍርድ ቤቱ ያቀርባል፡-
‹‹ንብረትነቱ የእናታችን የሆነ ቀበሌ 14/15 ውስጥ የሚገኝ 250 ካሬ ሜ. ላይ ያረፈ መኖሪያ ቤት፣ ሁለት ማሳ የእርሻ መሬት እና በንግድ ባንክ አራት ኪሎ ስላሴና መገናኛ ቅርንጫፍ የተቀመጠ መጠኑ ያልታወቀ ገንዘብን ያካፍለኝ፡፡›› 

 የከሳሽ ወንድም የሆነው ኃይሉም ፍርድ ቤት ቀርቦ ‹‹ቤትም ሆነ የእርሻ መሬት የሚባል ነገር የለም፤ በባንክ አለ ስለሚባለው
ገንዘብም አላውቅም፤ እናታችን በሞተችበት ወቅት ስሟን ለማስጠራት ስል የእርሷ የነበረውን መሬት በ30 ሺህ ብር ሸጬ፤ ለአርባ፣ለመንፈቅ፣ ለተስካር 10 ሺህ ብር ያወጣሁ ሲሆን፤ ቀሪውን 20 ሺህ ደግሞ ለወንድሜ ማረፊያ የሚሆን ቤት ሰርቼበታለሁ›› ሲል ምላሽ ይሰጣል፡፡ ችሎቱም ‹ቤቱንና የእርሻ መሬቱን በተመለከተ የቀረበ ማስረጃ አለመኖሩን› ገልፆ ‹የ30 ሺህው ጉዳይ ግን ያለይግባኝ ባይ ፍቃድ ወጪ የተደረገ ስለሆነ፤ የገንዘቡ ግማሽ 15 ሺህ ብር ድርሻው ስለሆነ እንዲሰጠው› በማለት ወስኖ መዝገቡን ይዘጋል፡፡ በውሳኔው እጅግ በጣም የተበሳጨው ሞገስ፣ ጉዳዩን በይግባኝ ከፍተኛው ፍርድ ቤት ይወስደዋል፤ ይግባኝ ሰሚውም ‹‹ቤቱ ይገኝበታል›› የተባለው ቀበሌ የእናታቸውን ማህደር እንዲያቀርብ ትዕዛዝ ይሰጣል፡፡ ግና፣ ሀገሪቷ ኢትዮጵያ ናትና፤ ቀበሌው ማህደሩ መጥፋቱን፣ ሟችም በተከሳሽ ቤት ይኖሩ እንደነበረ በደብዳቤ ያሳውቃል፡፡ ሆኖም ቀበሌው ይህንን ምላሽ ከሰጠ ከ14 ቀን በኋላ ‹የቀድሞውን አስተዳደር ጠይቄ ያገኘሁት መረጃ ነው› በማለት ለፍርድ ቤቱ እንዲህ የሚል ሌላ ደብዳቤ ይልካል፡- ‹ወ/ሮ አስካለ የግል መኖሪያ ቤት የነበራቸው ሲሆን፣ ቤቱ ያረፈበት መሬት ለ‹‹ሪል እስቴት›› በመሰጠቱ፤ ምትክ ቦታና ስድስት ሺህ ብር ወስደዋል›፡፡ የሰው ምስክሮችም ቀርበው ሟች እናት ቤት ሰርተው እንደነበረ ያረጋግጣሉ፡፡ ይህም ሆኖ የወ/ሮ አስካለ ማህደር ከቀበሌው ‹‹ጠፍቷል›› በመባሉ ምንም አይነት ማስረጃ ስላልቀረበ የቀድሞው ውሳኔ በይግባኝ ሰሚው ችሎትም ሊለወጥ አልቻለም፡፡ ከዚያን ጊዜ ጀምሮም ላለፉት ሁለት ዓመታት ከፍተኛው ፍርድ ቤት በር ላይ ቆሞ መጮኽን ስራዬ ብሎ ይዞታል፡፡ በርግጥ ከቀን ቀን አካላዊ መዳከም እየበረታበት መሄዱ በግልፅ ቢታይም የ40 ዓመቱ ጎልማሳ ሞገስ ወልዱ ዛሬም ከፍርድ ቤት ደጅ ቆሞ መጮኹና ማፏጨቱ የበርካታ ግፉአንን ድምፅ የሚወክል ይመስለኛል፡:

 ይህ ጉዳይ የሚያሳየው፣ የመንግስት ደመወዝ እየተከፈላቸው በዜጎች ሕይወት ላይ ሊወስን የሚችል እንዲህ አይነቱን ማስረጃ
ያለአንዳች ጭንቀት ‹‹ጠፋ›› ብሎ ለመናገር የሚደፍሩ፣ ስለሕዝብ ብሶትና ችግር ምንም ግድ የሌላቸው ካድሬዎች እየተበራከቱ
መምጣታቸውን ብቻ አይደለም፡፡ ይልቁንም እንደ ሞገስ ያሉ የፍትሕ እጦት ረመጥ ሆኖ ያንገበገባቸው ምስኪኖች በአደባባይ ሲጮኹ ውለው፤ ሲጮኹ ቢያድሩ ‹‹ምን ይሆን ችግራቸው?›› ብሎ ለማድመጥ የሚሞክር አንድ እንኳን ባለሥልጣን መታጣቱንም ጭምር ነው፡፡ ‹‹ሳይሰሙ ቀርተው ይሆናል!›› ማለቱን ከባድ የሚያደርገው ደግሞ፣ በልደታ ከፍተኛ ፍርድ ቤት አካባቢ የሚተላለፉ መንገደኞችም ሆኑ ወደ ተቋሙ የሚመጡ ባለጉዳዮች ክስተቱን የማወቃቸው እውነታ ነው፡፡ ከፖለቲካ ጋር በተያያዘ ፍርድ ቤት የሚቀርቡ ሰዎችን የችሎት ውሎ ለመሰለል ከተከሳሾች ቀድመው የሚደርሱ የደህንነት ሰራተኞችም ሞገስን ለማወቃቸው እኔው ራሴ ምስክር ነኝ፡፡ በአናቱም ከዚህ ቀደም በሸገር ራዲዮ ‹‹ኧረ በሕግ›› የሚል ፕሮግራም ያዘጋጅ የነበረውና በአሁኑ ወቅት በ97.1 ኤፍ.ኤም ‹‹የእኔ መንገድ›› የተሰኘ በተመሳሳይ ጭብጥ ዙሪያ የሚያተኩር ፕሮግራም የሚያዘጋጀው በሳሉ የሕግ ባለሙያ ሰለሞን ጓንጉል፣ ይህንን ታሪክ ከአንዴም ሁለቴ ለአድማጭ አድርሶታል፡፡ እንግዲህ እነዚህ ሁሉ ተደማምረው ነው ከቀበሌ አንስቶ ላይ ድረስ ያሉ መንግስታዊ መዋቅሮችን የዘረጋውና የሚቆጣጠረው የኢህአዴግ አመራር አባላት፣ የሞገስን ጩኸት ‹‹አልሰሙም›› ማለቱን ከባድ ያደረገው (በነገራችን ላይ በጠቅላይ ፍርድ ቤት ግቢ ለአስር አመት ያህል በየቀኑ እየተመላለሱ የሚቆሙ አንዲት አዛውንት እና በፍትሕ ሚኒስቴር በር ላይ ቆማ መዋል ከጀመረች ስድስት ዓመት ያለፋት ራሄል የተባለች አቤት ባይ እንስት… መኖራቸውን አልዘነጋሁም)

ሙስና እና የጓዳ ፖለቲካ ትስስሮሽ 

 አገሪቷ በዚህ ሁሉ መፍትሔ እጦትና በፍትሕ መዛባት እየተመሰቃቀለችና በሕዝቦቿም ዋይታ እየተናወፀች ቢሆንም፤ መጽሐፉ ‹‹ዓይን አላቸው አያዩም፤ ጆሮ አላቸው አይሰሙም›› እንዲል፤ ገዥዎቻችን ይህን መሰሉን የድሆችና የአቅመ ደካሞች ብሶት መስማትን ፍፁም አይሹም፡፡ እነርሱ የታጋሉትም ሆነ የሚሰሙት አለቆቻቸውንና ባለፀጋዎችን ብቻ እንደሆነ ከሚያሳዩን በርካታ ማስረጃዎች መሃል ለአብነት አንድ ምሳሌ ላቅርብ፡-ጉዳዩ በሙስና ተጠርጥሮ በእስር ላይ ከሚገኘው የቀድሞ ገቢዎችና ጉምሩክ ዳይሬክተር መላኩ ፈንቴ ጋር ይያያዛል፡፡ ከዚህ ሰው ሃያ አንድ ገፅ ከፈጀ የእምነት ክህደት ቃል ውስጥ ኮነ ምህረቱ የተባለ ግለሰብ በአራጣ ማበደር ተጠርጥሮ ከተያዘ በኋላ ‹‹እነአየለ ደበላ ለዳኛ ጉቦ ሰጥተው በዋስ ከእስር ተፈትተው፣ ከሀገር ለመውጣት ያስባሉ›› የሚል ‹‹መረጃ›› በመስጠት መተባበሩን ገብረዋህድ ወ/ጊዮርጊስ እንደነገረው ገልፆ፣ ከእስር እንዲለቀቅ መደረጉን እናገኛለን፡፡ መቼም በሙስና ወንጀል ከተጠያቂነት የሚድን ተከሳሽ የሚሰጠው መረጃ ተጠርጣሪዎችን በሕግ ለመጠየቅ የሚጠቅም ሲሆን እንጂ፤ እንዲህ ባለ ከዋናው ክስ ጋር በማይዛመድ ተራና የአሉባልታ ወሬ አለመሆኑን እነገብረዋህድና እነመላኩ ቀርቶ ማንኛውም መንገደኛ እንኳ ሊጠፋው አይችልም፡፡ አውቆ የተኛ… እንደሚባለው ካልሆነ በቀር፡: የሆነው ሆኖ ከመላኩ ፈንቴ የእምነት-ክህደት ቃል ትኩረት የሚስበው፣ ግለሰቡ በዚህ መልኩ ከሱ ተነስቶለት ከእስር ከተፈታ በኋላ ንብረቱና የባንክ ሒሳቡ መታገዱን አስመልክቶ የተፈጠረው ኩነት ነው፡፡ አቶ መላኩ ጉዳዩን ለመርማሪዎቹ ሲያብራራ ቃል-በቃል እንዲህ ነበር ያለው፡-

‹አቶ አባይ ፀሀዬ እና አቶ ደመቀ መኮንን ደውለው ‹ግለሰቡ አቤቱታ እያቀረበ ነው፡፡ ለምን አታዳምጡትም? ሲሉኝ፤ እኔም ከዚህ በኋላ  ነው ግለሰቡን እቢሮዬ አግኝቼ ከላይ በገለፅኩት ሁኔታ እንዲስተናገድ ያደረኩት፡፡››

እነዚህ ሰዎች ‹‹ነፃ አወጣነው›› የሚሉትን ሕዝብ ለስቃይ ዳርገው፣ ጥቂት ባለፀጎችን ብቻ ለማገልገል የቆሙ መሆናቸውን ለማስረገጥ ከዚሁ የእምነት-ክህደት ቃል አንድ ማሳያ ልጨምር፡- ዶ/ር ፍቅሩ ማሩ የተባለ የአዲስ ልብ ህክምና ክሊኒክ ባለቤት ከፍተኛ ዋጋ ያላቸው የሕክምና መሳሪያዎች (የልብ ፒስ ሜከር ተብሎ ተጠቅሷል) በሕገ-ወጥ መንገድ ሲያስገባ በቦሌ ኤርፖርት ጉምሩክ ሠራተኞች እጅ ከፍንጅ ከተያዘ በኋላ መለቀቁን በተመለከተ የህወሓት ከፍተኛ አመራር አባል የሆነው ዶ/ር ቴዎድሮስ አድህኖም ስልክ ደውሎ ‹‹ክሱን ብታነሱላቸውና በአስተዳደራዊ መፍትሔ ብትሰጧቸው›› ብሎ ከመንገሩም በላይ የግለሰቡ ክስ እንዲቋረጥ የሚጠይቅ ደብዳቤ  እንደፃፈላቸው መላኩ ፈንቴ ለመርማሪዎቹ መናገሩ በመዝገቡ ላይ ተጽፎ ይገኛል፡፡ ይህንን ሁናቴም ከወቅቱ የፖለቲካ አሰላለፍ አኳያ ስንተነትነው አቶ መላኩ ‹ዶ/ር ቴዎድሮስን መስማት፤ ህወሓትን እንደመታዘዝ ነው› የሚል እምነት አድሮበት የተባለውን ፈፀመ ብለን ብንደመድም ተምኔታውያን አያሰኘንም፡፡

 እነዚህ ከፍተኛ ባለሥልጣናት ያውም ሀገር በሚጎዳ ወንጀል የተከሰሰ ተጠርጣሪን በተመለከተ ከሥልጣን ገደባቸው አልፈው
‹‹አድምጥ!›› እያሉ የማዘዛቸው ምስጢር ሥርዓቱ ለፍትሕ ያለውን ግድየለሽነት እና በዚህ ሥርዓት የሕግ የበላይነት ብሎ ነገር 3 እንጦሮጦስ መውረዱን ፍንትው አድርጎ ያሳያል ብዬ አምናለሁ፡፡ በርግጥ ይህንን ጉዳይ እጅ ከፍንጅ ከተያዘ በኋላ መለቀቁን በተመለከተ የህወሓት ከፍተኛ አመራር አባል የሆነው ዶ/ር ቴዎድሮስ አድህኖም ስልክ ደውሎ ‹‹ክሱን ብታነሱላቸውና በአስተዳደራዊ መፍትሔ ብትሰጧቸው›› ብሎ ከመንገሩም በላይ የግለሰቡ ክስ እንዲቋረጥ የሚጠይቅ ደብዳቤ እንደፃፈላቸው መላኩ ፈንቴ ለመርማሪዎቹ መናገሩ በመዝገቡ ላይ ተጽፎ ይገኛል፡፡ ይህንን ሁናቴም ከወቅቱ የፖለቲካ አሰላለፍ አኳያ ስንተነትነው አቶ መላኩ ‹ዶ/ር ቴዎድሮስን መስማት፤ ህወሓትን እንደመታዘዝ ነው› የሚል እምነት አድሮበት የተባለውን ፈፀመ ብለን
ብንደመድም ተምኔታውያን አያሰኘንም፡፡

 እነዚህ ከፍተኛ ባለሥልጣናት ያውም ሀገር በሚጎዳ ወንጀል የተከሰሰ ተጠርጣሪን በተመለከተ ከሥልጣን ገደባቸው አልፈው
‹‹አድምጥ!›› እያሉ የማዘዛቸው ምስጢር ሥርዓቱ ለፍትሕ ያለውን ግድየለሽነት እና በዚህ ሥርዓት የሕግ የበላይነት ብሎ ነገር
እንጦሮጦስ መውረዱን ፍንትው አድርጎ ያሳያል ብዬ አምናለሁ፡፡ በርግጥ ይህንን ጉዳይ ለጥጠን ከተመለከትነው ‹‹…ለምን
አታዳምጡትም?›› የምትለዋን ቃል ሰምና ወርቅ የለበሰች ቅኔ አድርገን በመውሰድ ልንፈታት እንችላለን፤ በተለይም መላኩ ፈንቴ
ከዚህች ጥያቄ መሰል ትዕዛዝ በኋላ ግለሰቡን ቢሮ ጠርቶ ማስተናገዱን ስናስተውል፡፡ ምንም እንኳን አባይ ፀሀዬ በጊዜው በጉዳዩ ላይ መላኩን ሊያዝበት የሚያስችል መንግስታዊ ሥልጣን /የዕዝ ተዋረድ/ ባይኖረውም፤ አንጋፋ የህወሓት አመራር አባልና የበለጠ የፖለቲካ ጉልበት ያለው መሆኑ፤ ደመቀ መኮንን ደግሞ በብአዴን በኩል የአለቃነቱ ነገር ሲታሰብ፣ አሁንም መላኩ ፈንቴ የተጠየቀውን ‹‹ጥያቄ››ከማስተናገድ ውጪ ሌላ አማራጭ አይኖረውም ወደሚል ጠርዝ ይገፋናል፡፡ በርግጥ እውነታው ይህ ቢሆንም፣ መላኩ ዛሬም እስር ቤት ውስጥ ሆኖ የቀድሞ አለቆቹንም ሆነ ራሱን ተጠያቂ ለማድረግ አልደፈረም፡፡ በግልባጩ ለቀረቡበት ክሶች በሙሉ ተጠያቂው ገብረዋህድ እንደሆነ ከመናገሩም በላይ እንዲህ በማለት ወንጅሎታል፡- ‹‹የአያት ባለቤት በግብር ማጭበርበር ተከሶ በነበረበት ወቅት የተከሳሹ ቤተሰብ የሆነ ሰው እቢሮዬ መጥቶ ‹ገብረዋህድ ምንም ጥፋት ሳያጠፋ ነው የአያት አክሲዮን ማሕበር ባለቤትን ያሳሰረው፤ አሁንም አንድ ሚሊዮን ብር ካመጣችሁ ከእስር ይፈታል ብሎናል› የሚል ጥቆማ አመጣልኝ፡፡ …ገብረዋህድ እና ነጋ ገ/እግዚአብሔር (የነፃ ትሬዲንግ ባለቤት ነው) ጓደኛሞች ናቸው፡፡ ነጋ ዕቃ ሲያስመጣ
አያስፈትሽም፤ የነጋም ጓደኞች እነ አልሳም፣ ጌት አስ የመሳሰሉት ድርጅቶች ዕቃ በቀላል ቀረጥና ታክስ እንዲሁም አልፎ አልፎ ሳይፈተሹ ያልፋሉ፤ …ባለቤቱ ሃይማኖትም፣ በነጋ ድርጅት ውስጥ ትሰራለች…›› መላኩ ፈንቴ ይህንን ጉዳይ ለጠቅላይ ሚኒስትር መለስ መናገሩንና ጠቅላይ ሚኒስትሩም፣ ፀጋዬ በርሄን ‹‹ተከታተል›› ብሎት እንደነበረ ከአስረዳ በኋላእንደሚከተለው ይቀጥላል፡-
‹‹ገብረዋህድ በኋላ እንደነገረኝ ባለቤቱን ከነጋ ድርጅት አስወጥቶ በአዜብ ትዕዛዝ መሰረት ኤፈርት ውስጥ ያስቀጠራት መሆኑን ገልፆልኝ ‹አንተም ላይ የሚወራው ስለምትታገል ነው ብላኛለች አዜብ› ሲለኝ እኔም ተከታትዬ ፀጋዬ በርሄ ከምን እንዳደረሱት አልጠየኩም፡፡መጠየቅ ነበረብኝ፤ ጥፋት ነው፡፡ በአጠቃላይ ገብረዋህድ ላይ ብዙ ነገር ይባል ነበር፡፡›› 

 መቼም ይህ ምላሽ በ1981 ዓ.ም ከአስመራ ዩንቨርስቲ በኢኮኖሚክስ ዲግሪውን፣ ከአውስትራሊያ በገቢ አስተዳደር ሁለተኛ
ዲግሪውን፤ ከለንደንም በቢዝነስ አስተዳደር በተመሳሳይ መልኩ ትምህርቱን ካጠናቀቀና የረዥም ዓመታት የስራና የፖለቲካ ተሞክሮ ካለው ሰው የተሰጠ መሆኑን ስናስተውል፤ ሀገሪቱ የአምባገነን ባለሥልጣናት መቀለጃ ብቻ ሳትሆን፤ የሰዎቹንም ያመላክታል፡፡ እንዲሁም እነሞገስ ሰሚ ያላገኙበትን ምክንያትም ሆነ በዚህች ሀገር ገንዘብ ያለው የፈቀደውን መፈፀም የመቻሉን
ምስጢር ይገለፅልናል፡፡

ኢህአዴጋዊ ዕድሜ ማራዘሚያ…

 ገዥው ስብስብ የፍትሕ ስርዓቱን ተቋማዊነት ሳይነካ፣ ለጨቋኝነቱ መጠቀሚያ የሚያደርግበት አንዱ መንገድ ከጠቅላይ እስከ ታች በተዋረድ የሚገኙ ፍርድ ቤቶች ድረስ ያሉ ዳኞችን የሚመድብበት አካሄድ ነው፡፡ በርግጥ እንዲህ አይነቱ ሀገርና ሕዝብ አልያም
ሞራላዊ ልዕልና እና የሕግ-የበላይነት የማያስጨንቀው አገዛዝ፣ የፍትሕ ስርዓቱ ቅጥ የለሽ ተባባሪነት ሳይታከልበት የሥልጣን ዕድሜውን ማራዘም እንደማይችል መረዳት አይሳነውም፡፡ ይህን ለማድረግም ያለው ብቸኛ ምርጫ ዳኞቹን ከስሩ መሰብሰብ ይሆናል፡፡ ለዚህ ደግሞ ኢህአዴግ መሩ-መንግስት ሁለት አካሄዶችን ለመተግበሩ ያሳለፋቸው ሁለት አስርታት በሚገባ ያሳያሉ፡፡

 የመጀመሪያው የሚሾሙት ዳኞች፣ የግንባሩ ከፍተኛ የካድሬ ማሰልጠኛ እንደሆነ ከሚነገርለት ሲቪል ሰርቪስ ኮሌጅ ተማሪዎች
መካከል ማድረጉ ነው፡፡ ከዚህ ‹‹የትምህርት›› ተቋም ውስጥ የሚወጡ የሕግ ምሩቃን ደግሞ ስለጥልቅ ዘመናዊ የሕግ ፅንሰ-ሃሳብ
ለማወቅ ከመትጋት ይልቅ፤ የኢህአዴግ ፖሊሲዎች እና አብዮታዊ ዲሞክራሲ ሕግን እንዴት ‹‹ለመደብ ጠላት›› መጠቀም
እንደሚያስችሉ በሚሰብኩ መምህራን ስር እንዲያልፉ ይገደዳሉ (ስለመምህሮቹ ምሁራዊ ልሽቀት ለመረዳት የሕዝብ ሙስሊሙን ጥያቄ በሽብር ተግባር ለመፈረጅ እና ማሕበረ ቅዱሳንን በአክራሪነት ለመወንጀል በ‹‹ጥናታዊ ጽሑፍ›› ስም የተጓዙበትን ርቀት ማየቱ ብቻ በቂ ይመስለኛል)፡፡ ተማሪዎቹም በዚህን መሰሉ የካድሬ ተቋም ስልጠና ስር ሰንብተው ሲወጡ፤ በፍፅምና ሊታመኑላቸው ይገቡ የነበሩትን ፍትሓዊ ዳኝነትና ህሊና የሚባሉ ጉዳዮችን ጨፍልቀው፣ በተለይም ፖለቲካዊ ነክ በሆኑ አይረቤ ክሶች ፊታቸው በሚቆሙ ንፁሀን ዜጎች ላይ መከራን የሚያዘንቡ አሽከሮች ይሆናሉ::፡ ይህንን አስነዋሪነት ካለመታከት የሚፈፅሙትም፣ ሥልጣንን እና ተያያዥ ጥቅማ-ጥቅሞችን እያጋበሱ ወደ ከፍታ ሲወጡ ተመልክተናል፡፡

 ሁለተኛው የግንባሩ አካሄድ ከካድሬ ማሰልጠኛውም ሆነ የተሻለ ነው ከሚባለው የአ.አ.ዩ. የሕግ ፋካሊቲ የሚመረቁትን፣ በተከታታይ ርዕዮተ-ዓለማዊ ጠመቃ የሥርዓቱ ጋሻ-ጃግሬ ማድረግ ላይ ያተኮረው ነው፡፡ በሀገሪቱ ከፍተኛ ፍርድ ቤቶች ሲያገለግሉ ቆይተው ስደትን የመረጡ ዳኞችና ዐቃቢ-ህግያት በተለያየ ጊዜ እንደ መሰከሩትም አሰልቺ የርዕዮተ-ዓለም ጠመቃ የፍትሕ ሥርዓቱን ነፃነት ጽልመት ካላበሱት ሂደቶች በዋነኛነት ተጠቃሽ ነው፡፡ በአንድ ወቅትም ሟቹ አቶ መለስ ዜናዊ የሀገሪቱን ዳኞች ሰብስቦ ስለሕገ-መንግስት እና ሕገ አተረጓጎም መርህ ሲያስተምር ለማየት የተገደድነው የዚሁ የጠመቃው አንድ አካል በመሆኑ ይመስለኛል፡፡ ዳሩስ፣ ይህማ ባይሆን ኖሮ እስክንድር ነጋ ላይ 18 ዓመት መፍረድ ሕሊና እንዴት ይፈቅድ ነበር? ኦልባና ሌሊሳንስ ለ11 ዓመታት ወህኒ ያስወረወረው ጥፋት ምን ተብሎ በአሳማኝ መልኩ ሊጠቀስ ይችል ይሆን?

… ቀሪው ለሳምንት ይቆየን!

የአንባ ገነኖች የስልጣን ጥም አባዜ (ገዛኸኝ አበበ ከኖርዌይ ሌና)

በገዛኸኝ አበበ (ኖርዌይ ሌና)


 ዛሬ በአለማችን ላይ አንባ ገነን መንግስታቶች ሊመሩት እና ሊያስተዳድሩት በላው ሕዝብ ላይ  የሰብሃዊ መብት ረገጣ እስራት እና ግድያ በሕዝባቸው ላይ እንደሚያደርሱ ይታወቃል በተለይም የአፍሪካ መሪዎች እና መንግስታቶች በአንባ ገነንት እና የሕዝባቸውን ሰብሃዊ መብት በመርገጥ ግንባር ቀደም ተጠቃሾች ሲሆኑ ከእነዚህም ውስጥ አገራችን ኢትዮጵያ አንዶ ናት :: በአሁኑ ሰአት በሀገራችን ኢትዮጵያ በስልጣን ላይ ያለው መንግስት ከጊዜ ወደ ጊዜ አይን ያወጣ የሰበሃዊ መብት ጥሰት በዜጎች ላይ እየፈጸመ እንዳለ ይታወቃል ይህም የወያኔ የዜጎችን የሰብሃዊ መብት መርገጥ እና ሕዝብና እያስፈራሩ ረግጦ መግዛት ከምንም ነገረ የመነጨ ሳይሆን ሕዝቡ ስለ ዜግነት መብቱ እንዳያስብ በታጠቀ ኃይል እያስፈራሩ የሥልጣን እድሜን ለማራዘም ወያኔዎች ያዋጣናል ብለው የመረጡት መንገድ ሲሆን  ዜጎችን መረበሽ፣ መዝረፍ፣ ማሰር እና መግደልን ተያይዘውት ይገኛሉ::

ዜጎችን ማሰቃየት፣ ማሰር እና መግደል የአንባ ገነን መንግስታቶች መገለጫና መታወቂያ ሲሆን        አንባ ገነን መንግስታቶች  በሰለም እና በመረጋጋት ሊመሩት እና ሊያስተዳድሩት የበላይ ሆነው የተሾሙለት ሕዝብ ሰበሃዊ መብት በመርገጥ  ግፍና በደል እንደሚፈጽሙባቸው በገሀድ የታወቀ ሲሆን እነዚህ አምባ ገነን መሪዎች ለምንድ ነው ግን ሕዝባቸውን የሚያሰቃዩት፣ የሚያስሩት እና  የሚገደሉት ብለን ማሰባችን እና መጠየቃችን አይቀርም በየትኛውም አለም እንደምናየው አንባ ገነኖች ያለምንም ተቀናቃኝ በስልጣን ዙፋናቸው ላይ ለመቀመጥ ከመሻት የተነሳ  ዜጎቻቸውን  ያሰቃያሉ፣ ያስራሉ፣ይገድላሉ

 በተለይም እኛ ኢትዮጵያኖች በሀገራችን መንግስት በየጊዜው በግፍ ስለሚያሰቃዩት፣ ስለሚታሰሩት እና  ስለሚገደሉት ወገኖቻችን ሁል ጊዜ እንዳለቀስን እና እንደጮህን እንገኛለን::

ምክንያቱም ወያኔ /ኢህአዲግ  ወደ ስልጣን  ከመጣበትና የኢትዮጵያንም ሕዝብ  በሀይል መምራት  ከጀመረበት ጊዜ አንስቱ እስከ አሁን ድረስ ከሁለት አስርት ከአመታት በላይ መሆኑ ነው አንድም ቀን በሰላም እና በተረጋጋ ሁኔታ የኖረበት እና የኢትዮጵያ ሕዝብንም በሰላም የመራበት ጊዜ የለም ብል ማጋነን አይሁንብኝም::ይኼው የወያኔ ኢህአዴግ አገዛዝ ሁልጊዜ እንደፈራ ሕዝቡንም እንዳስፈራራ ሁል ጊዜ እንደተረበሸ ሕዝቡንም እንደረበሸ የሚኖር ሲሆን ይህም የወያኔ  ባህሪና መገለጫዎች ናቸው:: ከዚህም የተነሳ ሀገራችን ኢትዮጵያ በወያኔ ኢህአዲግ መንግስት መገዛት ከጀመረችበት ጊዜ  አንስቶ ወያኔ ያሰረው እና የገደለው ሀገሩንም ጥሎ እንዲሰደድ ያደረገው ሕዝብ ቁጥሩ እጅግ ብዙ ሲሆን የዜጎችንም ሰላም በመረበሽ እና በሀገራቸው ተረጋግተው እንዳይቀመጡ በማድረግ ላይ ይገኛል::

 ከዚህ በታች  የአንባ ገነኖችን ማንነት መገለጫ የሆኑትን ነገሩች  በአጭሩ የተወሰኑ ነጥቦችን በማንሳት ለመዳሰስ እሞክራለው

    1,አምባገነኖች ያለ ሕዝብ ፍላጎት ለብዙ አመታት በስልጣን ላይ የመቆየት ማንነት ይታይባቸዋል         (የስልጣን ሱሠኞች) ናቸው ::

  ብዙዎን ጊዜ እንደ  አፍሪካ እና አረብ ሀገራት ያሉ አምባ ገነን  የሀገር መሪዎች ወደ ስልጣን ሲመጡ የሕዝብን ህውቅና አግኝተው ወይም በሕዝብ ድምጽ በምርጫ ተመርጠው ሳይሆን አንድም በመፈንቅለ መንግስት አንድም በጦርነት በሀይል ስልጣንን መቆጣጠር ወይም በዘር ውርስ የስልጣን እርክብክቦሽ አማካይነት መሆኑ ይታወቃል:: ስለሆነም  ወደ ስልጣን ከመጡበት ጊዜ ጀምሮ  ስልጣናቸው ወይም መንግስታቸው በሀገራቸው ዜጎች እውቅና ሲሰጠው አይታይም :: ከዚህም የተነሳ ከሕዝባቸው ጋር አይጥ እና ድመት በመሆን ተፈራርተው ሕዝባቸውን  ሲያስፈራሩና ሲረብሹ ይኖራሉ ::  እንደነዚህ ያሉ ሀገራቶች  በማን አለብኝነት ያለምም ተቀናቃኝ ለብዙ አመታት የስልጣንን ወንበር ተቆጣጥረው ስልጣንንም መከታ በማድረግ የሕዝብን መብት በመርገጥም  ሲኖሩ ይታያሉ:: እነዚህ አንባ ገነን መንግስታቶች በሕዝባቸው ላይ አመኔታ የላቸውም ሕዝቡም በእነሱ ላይ አመኔታ የለውም ስለዚህ ሁል ጊዜ በዜጎቻቸው እንደተረገሙ እነሱም ሁል ጊዜ ዜጎቻቸውን እንደረገሙ ይኖራሉ::እየወለ እየደር ግን የአንባ ገነኖች መጨረሻቸው በሕዝብ ቁጣ ተርፍረክርኮ መውደቅ ነው::

 በግብጽ በቱኒዚያ በየመን እና በሌሎችም ሀገሮች እንዳየነው አንባገነኖች ለብዙ አመታት ስልጣንን በማውረስ እና በመረካከብ ሕዝብን በመጨፍለቅ ሲገዙ እንደነበር የቅርብ ጊዜ ትዝታችን ነው ለምሳሌ በግብጽ ጀማል ሙባረክ የሚቀጥለው የግብጽ መሪነትን ከአባቱ ለመውረስ እና ለመረከብ በመዘጋጀት እያለ ነበር ድነገት ባልጠበቁት ሰአት የቱኒዚያው ሱናሜ የተነሳው እና ያለሙትን አላማ ሳይተገብሩ በአንባ ገነኖች መገዛት በሰለቸው ሕዝብ ቁጣ እንደ ሰም ቀልጠው የቀሩት:: እነዚህን ሀገሮች እንደ ምሳሌ አነሳው እንጂ እንደነ ምሮኮ እና ኮንጎ የመሳሰሉ አብዛኞች ሀገሮች ስልጣንን በሀይል ወይም በውርስ በማውረስ እና በመረካከብ  ያለ ሕዝብ ፍላጎትና ህውቅና  ለዘመናት በማን አለብኝነት ስልጣንን በግላቻው በመቆጣጠር የሕዝቦችን ሰብሃዊ መብት ሲጨፈልቁ የሚኖሩ ሀገሮችን መጥቀስ ይቻላል::አንባ ገነኖች  እነሱን ከሚመስላቸው ውጭ  ለሌላ የፖለቲካ ፓርቲ ድርጅትም ሆነ ሀገርን ለመምራት አቅምም ሆነ ብቃቱ ላላቸው ሰዎች በማንኛውም መንገድ ቢሆን ስልጣንን ለመልቀቅ ፍቃደኞች ሲሆኑ አይታዩም::

ወደ ሀገራችን ኢትዮጵያ ስንመጣ ይህንኑ ነው የምናየው በአሁኑ ሰአት ሀገራችንን ኢትዮጵያን እየመራው ነው የሚለው የወያኔ  መንግስት ስልጣንን በዘር ሲወራረሱ እንደነበሩ  እንደ አንዳንድ አረብ  እና አፍሪካ ሀገራት አንባ ገነን መሪዎች በዘር አይወራረሱ እንጂ   ያለ  ሕዝብ ፍቃድ እና ፍላጎት ውጭ ለዘመናት የስልጣን ወንበሩን በማን አለብኝነት በሀይል ተቆጣጥሮ የዜጎችን ሰብሃዊ መብት እየረገጠ ያለ መንግስት መሆኑ ይታወቃል::አሁን ባለው አካሄድ እና አንዳንድ የወያኔ ባለስልጣኖች  ጊዜ አፋቸው እያመለጣቸው እንደሚናገሩት እነዚህ የስልጣን ጡመኞች የሆኑት የወያኔ ባለስልጣኖች በፈቃዳቸው ስልጣንን ይለቃሉ ተብሎ የማይታሰብ ቢሆንም ድንገት ግን የሕዝብ ቁጣ ገንፍሎ ወያኔ የሚባል የአንባ ገነን የማፊያ ቡድን ዳግመኛ እንዳያንሰራራ በግብጽ ፣ በቱኒዚያ እና በሌሎችም ሀገሮች እንደ ሆነው ሁሉ የአንባ ገነኑን የወያኔን መንግስት  ስርአት ወደ መቃብር ያስገበዋል የሚል ከፍተኛ የሆነ እምነት አለኝ::

የሰሜን አፍሪቃ እና መካከለኛው ምሥራቅ አገራት ዜጎች ለአስርት ዓመታት በአምባገነን አገዛዝ ተገዝተዋል። እኛ ደግሞ ለአስርት ዓመታት አምባገነን ብቻ ሳይሆን ዘረኛም ጭምር በሆነ የስልጣን ጥም አባዜ በተጠናወጠወ አገዛዝ እየተገዛን ነው። እኛ እየደረሰብን ያለውን ዓይነት አዋራጅ ዘረኝነት እነሱ ላይ አልደረሰባቸውም። አምባነንነት እነሱን አስመርሮ በገዚዎቻቸው ላይ በአንድነት እንዲነሱ አድርጓቸዋል። እኛ ዘንድ ደግሞ አምባገነንነትና ዘረኝነት ተዳብለውብናልና ከእነሱ በላይ አምርረን በህብረት እንነሳለን።

   2,አምባገነኖች በራስ የመተማመን (self confidence)ስለሌላቸው ለሁሉም ሃይል መጠቀም ይወዳሉ።

 አንባ ገነን መንግስታቶች ሕዝብን በአግባቡ መምራት ሕዝብ የሚጠይቀውን ማንኛውንም አይነት ጥያቄ ለመመለስ ፍቃደኛ አይደሉም:: አንባ ገነን መንግስታቱች በነገሱበት ሀገር የመብት የነፃነት የፍትህ ጥያቄ መጠየቅ በፍጹም የማይታሰብ ሲሆን ዛሬ ስንቶች ናቸው መብታቸውን  ስለጠየቁ  ብቻ በአንባገነኖች ጥይት በየሀገሩ እንደ ቅጠል እየረገፉ ያሉት::

እዚህ ላይ መታወቅ ያለበት ነገር የኛዎቹ አንባ ገነኖች (የወያኔ መንግስት)  መጀመሪያውኑ   ወደ ስልጣን ሲመጡ እና  ለዘመናት ከሁለት አስርት አመታት በላይ በስልጣን ላይ  ሲቀመጡ በሕዝብ ፍላጎት እና ነጻ ምርጫ ሳይሆን ሌሎች አንባ ገነን መንግስታቶች እንደሚያደርጉት ሁሉ ሕዝብን እያስፈራሩ እና ሃይልን በመጠቀም የሕዝብን ናጻነትና መብትን በማፈን እንደሆነ ይታወቃል ::  በመሆምኑ የስልጣንን ወንበር ከያዙበት ጊዜ ጀምሮ መንግስታቸው የሕዝብ ተቀባይነት የለውም:: ስለሆነም   ፈጽመው ተረጋግተው መኖር በማይችሉበት ሁኔታ ውስጥ ሲገኙ  ሁልጊዜ መንግስታቸው በስጋት ውስጥ ነው :: 

አንባ ገነኑ የወያኔ መንግስት በራሱ የማይተማመንና በስጋት ውስጥ የሚኖር መንግስት  እንደሆነ በቅርቡ  የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ድርጅት ሒዩማን ራይትስ ዎች የወያኔን መንግስት አሳፋሪ ድርጊት በመኮነን ያወጣው ሪፖርት አመላካች ነው::እንደ  የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ድርጅቱ ሪፖርት  ውስጥና በውጭ የሚገኙ ኢትዮጵያውያንንና ሌሎች ባለሙያዎችን በማነጋገር አዘጋጀሁት ባለውና በተጠናቀቀው  ሳምንት ይፋ ባደረገው  የኢትዮጵያ መንግሥትን የሰብዓዊ መብት ጥሰት እየፈጸመ እንዳለ እና  ከተቃዋሚ ፓርቲዎች ወይም አገር ውስጥ እንዳይንቀሳቀስ ከታገደ የፖለቲካ ድርጅት ጋር በማንኛውም መንገድ ቅርበት ያላቸው ኢትዮጵያውያኖች በወያኔ መንግስት እንደሚሰለሉ እና እነዚህ ሰዎች የሚያደርጉት የስልክ ንግግር በተለይ ደግሞ ከውጭ አገር የተደወለ ከሆነ ያለ ግለሰቦቹ ፈቃድ ወይም ዕውቅና ተጠልፎ እንደሚቀዳ ሒዩማን ራይትስ ዎች በሪፖርት ላይ ይፋ አድርጎል  ለዚህም የስለላ ተግባሩን ለመፈጸመ  የሚያገለግሉ መሣሪያዎችን ከተለያዩ አገሮች እንዳገኘ፣ሪፖርቱ ጨምሮ ይፋ አድርጓል::

  የወያኔ መንግስት በራስ መተማመን የጎደለው እና በፍርሃት የተሞላ መግስት መሆኑን በአደባባይ ያስመሰከረ አንባ ገነን መንግስት ነው ::መሪዎቹ በጭራሽ በራስ መተማመን ብሎ ነገር ስላልፈጠረባቸው መተማመኛቸው ጠብመንጃ፤በጦሩ ጉያ ተሸጉጠው ሃገርና ሕዝብን ለእልቂት ለረሃብ ለመከራ የሚያበቁበትን ቆመውም ተቀምጠው ተኝተውም ማውጠንጠን ነው፡፡ ይህንንም ስል እንዴው ዝም ብዬ ከመሬት ተነስቼ እንዳይደለ ይታወቅልኝ:: እኔ እስከማቀው ድረስ የወያኔ መንግስት ስልጣኑን ሀ ብሎ የኢትዮጵያን ሕዝብ ማስተዳደር ከጀመረበት ጊዜ አንስቱ እስከ አሁን ድረስ ከ22 አመት በላይ መሆኑ ነው አንድም ቀን በሰላም እና በተረጋጋ ሁኔታ የኖረበት እና የኢትዮጵያ ሕዝብንም በሰላም የመራበት ጊዜ የለም ብል የተሳሳትኩኝ አይመስለኝም:: ከዚህ ስጋታቸውም የተነሳ የኢትዮጵያን ሕዝብ አፍነው ይዘውታል::

 ዜጓች ሕገ መንግስታዊ  መብታቸውን ተጠቅመው  የሚደርስባቸው ጭቆናና የሰበሃዊ መብት ጥሰት   በነጻነት መቃወም አልቻሉም :: አንባ ገነኑ ወያኔ ይኼን ያክል ዘመን በስልጣን ላይ ሲቆይ ስልጣኑን መከታ በማድረግ  ስንቶችን ሲገርፍ፣ ሲያስር ፣ ሲያሰቃይ እና ሲገድል እንደኖረ በአደባባይ የተገለጠ ሀቅ ነው::ሕዝብም ስለመብቱ እና ነጻነቱ የጠየቀ ከሆነ ይታሰራል ፣ይገረፋል ይገደላል::

ኢትዮጵያን በዘር ፣ በቋንቋ እና በሃይማኖት ከፋፍሎ የህዝቡን አንድነት ለማጥፋት የሚጥረውን አገዛዝ መቃወም ደግሞ “አሸባሪ’’ የሚል ታርጋ አስለጥፎ ዘብጥያ ያስወረውራል።  ዛሬ የኛዎቹ እነ እስክንድር ነጋ ፣ርዕዮት አለሙ እና ሌሎችም ወጣት ወገኖቻችን በሽበርተኝነት ስም ተወንጅለው በአንባ ገነኖች እስር ቤት ውስጥ ተጥለው እየተሰቃዩ ያሉት የወያኔ መንግስት እንደሚለው ሽብርተኛ  ሳይሆኑ  የነጻነት እና የፍትህ ታጋይ ጀግኖች እንደሆኑ በድፍረት መናገር እችላለው::

በወያኔ አንባ ገነናዊ እኩየ ስራዓት የህግ የበላይነት የለም፤ ዲሞክራሲ ተደፍጥጡዋል፤ የደህንነት ዋስትና የለም፤ ነፃ ፕሬስ ተረት ሆኗል፣ የብዙሃን ፓርቲ ያልምንም እፍረት ተገፍትሮል። የሲቪክና ሙያ ማህበራት የማሽመድመዱ ተግባር ተከናውኗል።ይለቁንም ዘረኞች ግፈኞች፣ ወንጀልኞች፣ አምባገነኖች፣ ሙሰኞች እንዳሻቸው ዛሬም እየፈነጩ፤  በተቃራኒው ደግሞ ለፍትህ ለእኩልነትና፣ለነጻነት ሲሉ ለህሊናቸው፣ የሚታገሉ የሚዋረዱበት፣ የሚሰደዱበትና የሚታስሩበት አገር መሆኑ በጣም ያንገበግባል፣ ያስቆጫል።

ነገርግን አንባ ገነኖች የስልጣን ሃይላቸውን በመጠቀም ማሰር፣ መግደል ሕዝብን ማሰቃየት ከያዛቸው የስልጣን ጥም አባዜ የተነሳ በስልጣን ላይ ረጅም ጌዜ ለመቆየት የሚጠቀሙበት መንገድ ሲሆን ይህም በራስ መተማመን እንደሌላቸው ያሳያል ::ነገር ግን እዚህ ላይ ማወቅ ያለብን ነገር ይህ አይነት አካሄድ አንባ ገነን መንግስታቶችን የትም ሊያደርሳቸው እንደማይችል ሲሆን አንባ ገነኖችም ይህን ሊገነዘቡትና ሊያውቁት ይገባል ባይ ነኝ ::በርግጥ የታፈኑ ብሶት ገንፍሎ የነጻነት ደማቅ ፀሐይ የምናይበት ጊዜ እንደሚመጣ ቅንጣት ያክል አልጠራጠርም። 

የሰሜን አፍሪቃ እና መካከለኛው ምሥራቅ አገራት ዜጎች በያገራቸው ፍትህ በመጓደሉ ተማረዋል። እኛ አገር ደግሞ ፍትህ ራስዋ ተዋርዳለች። ፍርድ ቤቶች ማጥቂያዎች ሆነዋል። አገራችን እስር ቤት ሆናለች። አብዮት ከቀሰቀሱት ጎረቤቶቻችን በባሰ እኛ ተበድለናልና  ከእነሱ በባሰ አምርረን ልንነሳና አንባ ገነኖችን ዳግም እንዳይነሱ ልንቀብራቸው ያስፈልጋል።

     3,አምባገነኖች ከሀገር እና ከሕዝብ ጥቅም ይልቅ የራሳቸውን ጥቅም ያስቀድማሉ (ሙሰኞች ናቸው)

የአንባ ገነኖች ሌላው የባህሪያቸው ዋንኛ መታወቂያቸው ሙሰኝነት ሲሆን ይህንንም ተከትሎ  አገራችንን ኢትዮጵያን ጨምሮ አፍሪካ  አንባ ገነኖች በስፋት የነገሱባት  ሙሰኝነት እና ሙሰኞች የተንሰራፉበት አህጉር በመሆን ትታወቃለች :: በአፍሪካ ሀገራት የሚነሱ መሪዎች ወደ ስልጣን ከመጡ እና ስልጣን ከያዙ በኋላ ስለ ሀገር እና ስለ ሕዝባቸው ግድ የለሾች ሲሆኑ ስለ ሀገር እና ስለ ሕዝባቸው ግድ የማይላቸው ሆዳሞችና የራሳቸውን ጥቅም ብቻ የሚያሳድዱ ገንዘብ ወዳዱች ናቸው::

 በሀገራችን ኢትዮጵያ በስልጣና ላይ ያለው አምባ ገነኑ የወያኔ መንግስት ባለስልጣኖች  ከላይ እስከታች በተዘረጋው የወያኔ ስርአት ውስጥ ከቁንጮ ባለስልጣናት እስከታችኛው አገልጋይ ድረስ በሙስናና በሌብነት ያልተዘፈቀ የስርአቱ አገልጋይ ቢፈለግ አይገኝም :: በአሁኑ ሰአት መላው የኢትዮጵያ ሕዝብ አዲስ አበባን ነዋሪ ጨምሮ ሕዝቡ በከፍተኛ የኖሮ ችግር እንዳለ ይታወቃል:: ካለውም ታላቅ የኑሮ ውድነትና የስራ ማጣት ፣ ያለው ብልሹ የመንግስት ፖለቲካዊ አስተዳደር ተደምሮበት ሕዝቡ ሀገሮን ጥሎ ወደ ተለያየ ሀገር እየተሰደደ በተለይም ወጣቶች ወንዶችና ሴቶች እህቶቻችን ሀገራቸውን ጥለው ሲወጡ በየድንበሩ እየሙቱና ወደ ተለያየ ሀረብ ሀገራትም ሄደው ለተለያየ መከራ ስቃይ እና ችግር ሲደርስባቸው እና ዜጓቻችን ሲገደሉ ምንም ግድ የማይሰጣቸው ነገር ግን   እኔ ከሞትኩኝ ሰርዶ አይብቀል እንደሚባለው የወያኔ  አንባ ገነን መሪዎች ሙሰኞች ከኢትዮጵያ ሕዝብ የዘረፉትን  በመቶ ሚሊየኖች የሚቆጠር ዶላር ከኢትዮጵያ ህዝብ በማሸሽ በውጪ አገር ባንኮች በማካበት ላይ እንደሚገኙ ግሎባል ፋይናንሻል ኢንቴግሪቲ 11 ቢሊዮን ዶላር የሚጠጋ የአገሪቱ ገንዘብ በውጭ ባንኮች መቀመጡን ይፋ ማድረጉ ይታወቃል ።

በወር ስድስት ሺህ ብር ደሞዝተኛ እንደነበሩ በባለቤታቸው የተነገረላቸው አንባ ገነን የነበሩት የቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስቴር ሞቹ አቶ መለስ ዜናዊ ሁላችንም እንደምናስታውሰው ከጥቂት ዓመታት በፊት የትንሳኤ ሬድዮ የኢትዮጵያን ሕዝብ ሀብት የዘረፉ የወያኔ መንግስት ባለስልጣኖችን፥ የቀድሞውን ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊን ጨምሮ የዘረፉትን ሀብት መጠንና ገንዘቡን ያስቀመ ጡበትን አገር ጭምር ይፋ አድርጎ እንደነበር አስታውሳለው።  ።  አቶ መለስ ዜናዊ በማሌዥያ በባንክ ፬፪ (አርባ ሁለት) ሚሊዮን ዶላር እንዳስቀመጡ ገልጾ ነበር።ይታያችው እንግዲህ  በተከታዩቻቸውና የአቶ መለስ አፍቃሪ በሆኑ ሰዎች እስከ አሁን ድረስ ሰውየው ስለ ሀገራቸውና ስሉሕዝባቸው ፍቅር የነበራቸው ባለራእይ መሪ እንደነበሩ ሲወደሱ እና ሲዘመርላቸው እንሰማለን እውነታው ግን የሚያሳየው ሌላ ነው አንባ ገነኖች አንድም ቀን የሀገር እና የሕዝባቸው ፍቅር ኖሮቸው አያውቅም እኝው አንባ ገነን የቀድሞ መሪ ሕዝባቸውን ሲያዋርዱና ሲያንቋሽሹ ለሀገራቸውም ቅንጣት ያከል ፍቅር እንደሌላቸው የሚያሳይ ስራ ይሰሩ የነበሩና ጀግኖች አባቶቻችን የታወደቁለትን ባንዲራ ጠቅላይ ሚኒስትሩ አንዴ ሲዘቀዝቁት አንዴ ጨርቅ ነው ሲሉት እንደነበር እናስታውሳለን::


 በአሁኑ ሰአት የወያኔ መንግስት ሙስናን ለማጥፋት እየታገለ እንዳለ በተለያዩ መድረኮችና ሚድያዎች ከመግለፅ ኣልፎ። ራሱ የፀረ ሙስና ኮምሽን ብሎ ባደራጀውና  በሚጠራው ተቋም ሙሰኞች ባላቸው ግለ ሰቦች  ላይ ክስ በበመመስረት ወደ ፍርድ ሲያቀርባቸውና እስርቤት ውስጥ ሲያጉራቸው ይስተዋላል፣ ነገር ግን ይህ የወያኔ መሰሪ ተንኮል ሆነ ብሎ ለህዝብና ለኣለም ማህበረሰብ ወያኔ እራሱን የብርሃን መላእክት አድርጎ በማቅረብ ለማታለል ተብሎ እየተሰራበት ያለ ተንኮል ነው:: 

ወያኔ እራሱን ፀረ-ሙስና ድርጅት ለመምሰል ለህዝብና ለኣለም ማህበረሰብ ለማታለል እየተሰራበት ያለ ድብቅ ተንኮል     ነገር ግን ለስርኣቱ ተገዢ ሆነህ እስካገለገልክ ድረስ በአስተሳሰብ የተለየ እስካልሆንክ ሰው ብትገድል እንኳ በእርቅ ነፃ መውጣት ትችላለህ፡፡ስልጣንህን ተገን በማድረግ የህዝብ ንብረትና ገንዘብ ለመስርቅ ሙሉ ዋስትና እንደሚሰጥህ፣ የፈለከውን ያክል ገንዘብ ብትዘርፍ ዘመነኛ ተብለህ ልትሸለማለህ ትችል እንደሆነ እንጂ ሙሰኛ አያሰኝህም፡፡ ነገር ግን ከእነሱ ትንሽ ለየት ያለ የፖለቲካ ልዩነት ያላቸው እና ለበላይ ኣለቆቻቸው  ያላጎበደዱና ያልተስማሙ ግን ሙስናን ተገን በማድረግ በቁጥጥር ውስጥ እንደሚውሉ ይታወቃል:: ይህም  የወያኔ  ስርአት ምን ያህል አንባ ገነን መሆኑንና ስርኣቱ የስልጣን ጥም አባዜ በተጠናወጣቸው የስልጣን ሙሰኞች  የተሞላ ኣስመሳይ ፀረ ህዝብ ኣሰራር መሆኑንን ያመለክታል::

ሙስና የአንባ ገነን መንግስታቶች መገለጫ ሲሆን የሰሜን አፍሪቃ እና መካከለኛው ምሥራቅ አገራት የነበሩት አንባ ገነን ሹሞች በሙስና ያካበቱት ሃብት በቢሊዮን ዶላሮች እንደሚገመትና ሕዝቡንም ለአመጽ ያነሳሳው ይኸው የአምባ ገነኖች ከልክ ያለፈ ሙሰኝነትና ሌብነት እንደሆነ ይታወቃል። የእኛ የመጨረሻይቱ ድሃ አገር አንባ ገነን የወያኔ ሹሞችም በሙስና ያካበቱት ሃብት እንደዚያው ነው። እርግጥ ነው በከተሞቻችን ህንፃዎች በርክተዋል ሆኖም ግን የሙሰኞቹ እንጂ የለፍቶ አዳሪዎቹ አይደሉም። በሃብት መበላለጥ የተቆጩት እና በሙስና መብዛት በአንባ ገነንና በስልጣን ሱሰኞች መሪዎቻቸው የተናደዱ የአህጉራችን  የሰሜን አፍሪቃ ዜጎች በገዢዎቻቸው ላይ ተነስተዋል እኛ ደግሞ  ከእነሱ በላይ ተጎድተናልና ከእነሱ በላይ አምርረን ልንነሳ ሙሰኛውን፣ የሀገርና የሕዝብ ፍቅር የሌለው አንባ ገነኑ የወያኔ መንግስት ላይ መነሳት ይጠበቅብናል።
   
ድል ለኢትዮጵያ ሕዝብ !!!
ውድቀት ለአምባገነኖች!!!
gezapower@gmail.com



ኖርዌይ ኢህአዴግ ያሰረባትን ዜጋዋን ጉዳይ እየተከታተለች ነው

April7/2014

ማዕከላዊ እስርቤት ከፍተኛ ስቃይ ይደርስባቸዋል በሚል ተሰግቷል
okello


የኢህአዴግን ካዝና የምትሞላዋ ኖርዌይ በማዕከላዊ እስር ቤት የሚገኙትን ዜጋዋን አስመልክቶ በዲፕሎማሲያዊ መንገድ እየሰራች መሆንዋ ታወቀ። በማዕከላዊ እስር ቤት የታሰሩት ዜጋዋ ድብደባና ቶርቸር እንዳይካሄድባቸው በቅርብ ክትትል እያደረገች መሆንዋን ለጉዳዩ ቅርብ የሆኑ ክፍሎች ለጎልጉል አስታውቀዋል።
ኢህአዴግን ከልጅነቱ ጀምራ ስትደጉም የኖረቸውና አሁን ደግሞ “በልማታዊ መንግሥትነት” መድባ ድጋፏን የምትዘረጋለት ኖርዌይ ዜጋዋን አስመልክቶ አስፈላጊውን ሁሉ የማድረግ ግዴታ እንዳለባት ይታወቃል። በዚሁ መሰረት የኖርዌይ ትልቁ ጋዜጣ ቀደም ሲል ጎልጉል ምንጮቹን ጠቅሶ ይፋ ያደረገውን ዜና የሚያረጋግጥ ዜና አሰራጭቷል።
ደቡብ ሱዳን የጸጥታ ሃይሎች አሳልፈው ለኢህአዴግ የሰጧቸው የቀድሞ የጋምቤላ ርዕሰ መስተዳድር አቶ ኦኬሎ አኳይ የኖርዌይ ዜግነት እንዳለቸው በማረጋገጥ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ጉዳዩን በቅርበት እንደሚከታተለው፣ አዲስ አበባ የሚገኘው የኖርዌይ ኤምባሲም ስራውን እየሰራ እንደሆነ አፍተን ፖስት አመልክቷል።
አፍተን ፖስት “የሰብአዊ መብት ተከራካሪ” ሲል በዜናው መክፈቻ የጠቀሳቸውን አቶ ኦኬሎ አኳይን አስመልክቶ የውጪጉዳይ ሚኒስቴር የኮሙኒኬሽን አማካሪ ስቫይን ሚኬልሰንን ጠቅሶ “አቶ ኦኬሎ የደቡብ ሱዳን የደህንነት ሃይሎች በደቡብ ሱዳንና በዩጋንዳ ድንበር መካከል ይዘዋቸዋል። አንደተያዙም ወደ ጁባ ሳይወሰዱ ተላልፈው ተሰጥተዋል” በማለት የጉዳዩን አካሄድ አመላክቷል።
የኢህአዴግን የገቢ ምንጭ የሆነችው ኖርዌይ በጉዳዩ አቋም በመያዝ ያስታወቀችው ስለመኖሩ ዜናውን የዘገበው አፍተን ፖስት ያለው ነገር የለም። ይሁን አንጂ ድርጊቱን በዲፕሎማሲያዊ መንገድ ኖርዌይ እንደምትቃወመው አልሸሸገም። አቶ አኳይ ለምን ወደ ስፍራው እንደተጓዙ በውል የተገለጸ ነገር እንደሌለ ዜናው ጠቁሟል። “በተመሳሳይ” በማለት ከዜናው ግርጌ ኢህአዴግ ለዴሞክራሲና ለሰብአዊ መብት ክብር እንደሌለው፣ በነጻ ፕሬስና በተቃዋሚ ፓርቲዎች ላይ እያደር የከረረ ርምጃ በመውሰዱ ክፉኛ የሚዘለፍበት ጉዳይ እንደሆነ አጣቅሷል።
ጎልጉል መጋቢት 19 ቀን 2006 ዓም (March 28, 2014) ቀን ዜናውን ይፋ በማውጣት ቅድሚያ ወስዶ ሲዘገብ አቶ ኦኬሎ ከደቡብ ሱዳን ከሆቴል ውስጥ ታፍነው መወሰዳቸውን ጠቁመን ነበር። አሁን አዲስ በመጣው መረጃ በዩጋንዳና በደቡብ ሱዳን ድንበር ላይ ተያዙ መባሉ ምን አልባትም ኢህአዴግ ሊመሰርትባቸው ላሰበው ክስ አመቺ ሁኔታ ለመፍጠር ታስቦ እንደሚሆን ጥርጣሬ አለ። የዜናው ምንጭ አቶ ኦኬሎ ከጁባ በሄሊኮፕትር መወሰዳቸውን እንደሚያውቁ ገልጸዋል።
በመለስ ዜናዊ ውሳኔና ትዕዛዝ በአኙዋክ ተወላጆች ላይ በጅምላ የተከናወነውን ጭፍጨፋ አስመልከቶ ተቃውሞ በማሰማት፣ አድርጉ ተብለው የታዘዙትን ባለመቀበል አገር ጥለው የኮበለሉት አቶ ኦኬሎ ስለ ኢትዮጵያና ኢትዮጵያዊያን ያገባናል በሚሉ “አክቲቪስቶች”፣ የፖለቲካ ድርጅቶችና፣ ማህበራት ዘንድ ዋንኛ ርዕስ ያለመሆናቸው ምክንያት አስገራሚ እንደሆነባቸው የሚጠቁሙ ዲያስፖራዎች ጥቂት አይደሉም። ከዚያም አልፎ አሁንም የመታሰራቸው እና እርሳቸውን ለማስፈታት በሚደረገው ሁኔታ ላይ የተፈጠረው ዝምታ አጠያያቂ እንደሆነ ተጠቁሟል፡፡
አቶ ኦኬሎ ማዕከላዊ እስር ቤት እንደሚገኙና፣ በዚያም በከፍተኛ ደረጃ ቶርቸር ይደረጋሉ በሚል ስጋት ሁኔታውን ለሚመለከታቸው በማሳወቅ በኩል አንዳንድ ወገኖች እንቅስቃሴ መጀመራቸው ታውቋል። ኢህአዴግ እስካሁን ፍርድ ቤት ያላቀረባቸው አቶ ኦኬሎ “አሁን ስለሚገኙበት የጤና ሁኔታ የኖርዌይ ኤምባሲ የጉብኝት ሪፖርትና ይጠበቃል” ሲሉ እኚሁ ክፍሎች አመላክተዋል።
ከቤተሰባቸው ተነጥለው በስደት ከሚኖሩበት ኖርዌይ ወደ ደቡብ ሱዳን ያመሩት የቀድሞው የጋምቤላ ርዕሰ መስተዳድር ደቡብ ሱዳን በህወሃት ሙሉ ቁጥጥርና ፈቃድ የምትንቀሳቀስ አገር መሆኗን እያወቁ ወደዚያ ማቅናታቸውን “ታላቅ ጥፋት” መባሉን መዘገባችን ይታወሳል። ቤተሰቦቻቸውን ለማግኘት ያደረግነው ሙከራ አሁንም አልተሳካም። ባምቤላ የአኙዋኮች ጭፍጨፋ ላይ ቀጥተኛ ተሳታፊ የነበሩት አቶ ኦሞት ኦባንግ በቅርቡ መኮብለላቸውና በብዙዎች ዘንድ አውሮጳ እንዳሉ ቢነገርም በትክክል ያሉበት አገር በይፋ አለመታወቁን መዘገባችን አይዘነጋም።

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ

የሪያዱ ሚስጥራዊ ቦንድ ሽያጭ ከሸፈ!

April 6/2014

ሐሙስ ጅዳ ላይ ያልቀናው ቦንድ ሽያጭ ትናንት ሪያድ ከተማም ከሽፏል።

የሁለቱም ከተሞች እቅድ መክሸፍ ምክንያት የሕወሐት ሰዎች ጉልበት የመጠቀም ስሕተት መሆኑ ያመሳስለዋል።ጅዳ ኮሚዩኒቲ አዳራሽ አቶ ከድር የሚባል የሕወሐት ሰው አንዲትን ስብሰባ የምትሳተፍ እህት በጥፊ መትቶ ሞባይሏን ለመንጠቅ ባደረገው ትንቅንቅ ስብሰባው ወደሁከት ተቀይሮ መበተኑ ይታወሳል።ሪያድ ስለሆነው ደግሞ እንከታተል ።

የትናንቱ የሪያድ ስብሰባ ለኤምባሲው ሩቅ ያልሆኑ ከየብሄሩ ሐያ ሰዎች በድምሩ አንድ መቶ ሃምሳ ሰዎች ብቻ በሚስጥር የተጠሩበት ነበር።መረጃው ለህዝብ ይፋ ከተደረገ በኋላ በርካታ ሰው ወደኮሚዩኒቲው አዳራሽ በማምራት ለመግባት ይጠይቃል።ከመግቢያ በር “የጥሪ ካርድ አምጡ” ይባላል ።”የለንም” ይላል ህዝብ።”ከየትኛው ብሔር ናችሁ?”ብለው በረኞች ሲጠይቁ “ኢትዮጵያውያን ነን።ጉዳዩ እንደዜጋ ይመለከተናል።”ይላሉ።

በዚህ ምልልስ መሐል አንድ ሰው ሞባይል ሲቀርፅ የሕወሐት አባል የሆነ ግለሰብ ይመታውና ሞባይሉን ሊነጥቀው ይሞክራል ።በር ላይ የተሰበሰበው ኢትዮጵያዊ የዚህ ሕወሐት እብሪት አበሳጭቶት ግብግብ ሲጀመር ከአዳራሹ ውስጥ የነበሩ ሌሎች ህወሀቶች መቀመጫ ወንበር በማንሳት የአዳራሹ መስተዋት በመሰባበር ህዝቡን ለመደብደብ ወደውጭ ይወጣሉ።

የኮሚዩኒቲው ፀጥታ አስከባሪ የሳዑዲ ፖሊሶች በመሐል ገብተው ነገሮች በቁጥጥር ስር ዋለ።የችግሩን መከሰት የሰሙት አምባሳደር መሐመድ ሐሰን መጀመርያ ላይ ፀብ ያጫረውን ሰው አምጡልኝ።የኤምባሲው ሰራተኛ ቢሆን እንኳ በህግ ይከሰሳል።”አሉ።ሰውየውን ህወሀቶች አስቀድመው ቢያሸሹትም በሕዝብ ጥቆማ ያሸሸው ሰው ይያዛል።አምባሳደሩ ሰውየው ህወሐት መሆኑን ሲያውቁ አፈገፈጉ።”በቃ ጉዳዩን ጸውስጥ እንጨርሰዋለን።አሁን ወደጉዳያችን እንግባ።”ብለው በግርግሩ ያለጥሪ ከገቡት ሰዎች ጭምር ስብሰባው ተጀመረ።

ገና እንደተጀመረ አንድ ሰው ብድግ ብሎ “ሀገራችን ውስጥ በሃይማኖታችን ምክንያት ቁምስቅል የምታሳዩን አንሶ በሰው ሐገር እንዴት ትደበድቡናላችሁ?”ብሎ እምባ እየተናነቀው ተናገረ!

ከበር ላይ የህወሓት እብሪተኞች የፈፀሙት የንቀት ድርጊት ከዚህ ሰው ንግግር ታክሎ የመንግሥት ደጋፊ የሚባሉ ሰዎችን ሳይቀር አስከፍቶ እያንዳንዱ ሰው ከወንበሩ ብድግ አዳራሹን ለቆ ወጣ!

ኢትዮጵያ የግል መኝታ ቤታቸው የምትመስላቸውና በሌላው ዜጋ የሐገር ባለቤትነት የማያምኑ ጭፍን የህወሓት ግልፍተኞች የሪያድና ጅዳን የህዳሴ ግድብ የልማት ውይይት(የቦንድ ሽያጭ) በዚህ መልኩ አኮላሽተውታል!!

የጠበቆች ማህበር በአርቲስት ግሩም ኤርሚያስ ላይ የወንጀል ክስ መመስረታቸው ተሰማ

April 6/2014



በአዲስ አበባ ታትሞ የሚወጣው ማራኪ መጽሔት እንደዘገበው በቅርቡ በሰይፉ ፋንታሁን የኢቢኤስ ሾው ላይ ቀርቦ በአዲስ ፊልሙ ላይ አደንዛዥ ዕፅ ተጠቅሞ መስራቱን ለማህበረሰቡ ያሳየው አርቲስት ግሩም ኤርሚያስ የጠበቆች ህብረት በጋራ የወንጀል ክስ አቅርበውበታል።

ጠበቃ ማቲያስ ግርማ ለማራኪ መፅሄት እንዳስረዱት በክሱ ላይ ሰይፉ ፋንታሁንና አለማየሁ ታደሰ ደጋፊ ሀሳብ በመስጠታቸው ክስ ይመሰረትባቸዋል ብለዋል። አርቲስቱ ምንም እንኳ ለፊልም ግብዓት “መስለው ሳይሆን ሆነው” ለመስራት ያደረጉት ተግባር ቢሆንም ህብረተሰቡን ከወንጀል ለመጠበቅ ሲባል ክስ እንደተመሰረተባቸው የጠበቆች ተወካዩ አስረድተዋል።

አርቲስት ግሩም ኤርሚያስ በፊልሙ ላይ
አርቲስት ግሩም ኤርሚያስ በፊልሙ ላይ
“ይህንን የበለጠ ማጣራት የነበረባቸው ፖሊስና አቃቤ ህግ ቢሆኑም ፣ በግልፅ በሀገሪቱ የአየር ክልል የተላለፈውን መረጃ ዝም ማለታቸው እንዳሳዘናቸውም ገልፀዋል። በሀገሪቱ የወንጀል ህግ ስርዓት በተለይ ግሩም በክሱ ጥፋተኛ ከተባለ እስከ ሰባት አመት እንዲሁም የ50ሺ ብር ቅጣት ይጠብቀዋል::
በኢትዮጵያ የወንጀል ህግ 1996/97 አንቀፅ 525 ንዑስ አንቀፅ/ሀ መሰረት እስከ ” አደንዛዥ ዕፅን እራሱ ወይም ሌላ ሰው ሊጠቀምበት በማሰብ የገዛ፣የተጠቀመ፣ እንዲጠቀም ያደረገ፣,,,” ከ7 ዓመት እስከ 50ሺ ብር ቅጣት ይጠብቀዋል። እነ ሰይፉ ደግሞ “ወንጀልን ባለማወቅ” ክስ ተመስርቶባቸዋል።

መጽሔቱ ዘገባውን ሲያጠናቅቅ ለግሩም በቅርብ መጥሪያ ይደርሰዋል ተብሎ ይጠበቃል ብሏል።

ዘ- ሐበሻ

Sunday, April 6, 2014

ከ60 ሺህ በላይ የከተማው ነዋሪዎች የተሳተፉበት ይህ ሰላማዊ ሰልፍ በተሳካ ሁኔታ ተጠናቀቀ!! “እድሜ ለአንድነት አስተነፈሰን !!! ” የደሴ ነዋሪዎች

April 6/2014

የሚሊዮኖች ድምፅ ለመሬት ባለቤትነት” በሚል መሪቃል በደሴ የተደረገው የተቃውሞ ሰልፍ በተሳካ ሁኔታ ተጠናቋል፡፡ በስፍራው የሚገኙት የአንድነት ፓርቲ ከፍተና አመራሮችና የዞን አመራሮች በሰልፉ ለተሳተፈው የደሴ ህዝብ ምስጋና አቅርበዋል፡፡ ‪የደሴ ነዋሪዎችም “እድሜ ለአንድነት አስተነፈሰን” በማለት ደስታቸውን ገልጸዋል።

የሚሊዮኖች ድምጽ ለመሬት ባለቤትነት በሚል መሪ ቃል አንድነት ፓርቲ የጀመረውን ዘመቻ በማስመልከት የመጀመሪያውን ሰላማዊ ሰልፍ በደሴ ከተማ በተሳካ ሁኔታ ማድረጉ ታውቋል።

ከቅስቀሳ ጀምሮ በደህንነቶች እና በፖሊስ ሃይሎች ወከባ እና መንግስታዊ ውንብድና የተደረገበት የደሴው ሰልፍ ህዝቡ ከፓርቲው ጎን በመቆም ለመብቱ እና ለነጻነት ያለውን ቀናኢነት በማሳየት ትልቅ ትብብር አድርግዋል። በደሴ ከተማ በዛሬው እለት የተደረገው ሰልፍ ከጠዋት ጀምሮ ህዝቡ ፍርሃቱን በመስበር ወደ አደባባይ ወጥቶ ብሶቱን ያሰማ ሲሆን ፖሊሶች መንገድ በመዝጋት ሽብር ለመፍጠር ቢሞክሩም ህዝቡ እያሳበረ በሰልፉ ላይ በመገኘት ተቃውሞውን አሰምቷል።
ከ60 ሺህ በላይ የከተማው ነዋሪዎች የተሳተፉበት ይህ ሰላማዊ ሰልፍ በተለያዩ መፈክሮች ደምቆ ነበር።ህዝቡ አንግቦት ክንበሩት መፈክሮች ውስጥ ፦
-መሬት ከካድሬው ወደ ህዝቡ ይመለስ – አንድነት ኃይል ነው
- የፖለቲካ እስረኞች ይፈቱ – መሬት ለህዝብ ይመለስ
- ጭቆና በቃን – ድል የህዝብ ነው – በግፍ የታሰሩ ይፈቱ ……… የሚሉ ይገኙበታል።

የደሴው ሰላማዊ ሰልፍ በተሳካ ሁኔታ እየተካሄደ በነበረበት ወቅት የአዲስ አበባ ፖሊሶች እና ደህንነቶች ቀበና ሼል አከባቢ የሚገኘውን የአንድነት ዋና ጽ/ቤት በመክበብ ወከባ ሲፈጽሙ ተስተውሏል።

በደሴው ሰላማው ሰላፍ ላይ የአንድነት ከፍተኛ አመራሮች የሆኑት ተቀዳሚ ም/ፕሬዝዳንቱ አቶ ተክሌ በቀለ እንዲሁም የውጪ ጉዳይ ሃላፊው ዘለቅ ረዲ የደሴ የአንድነት ሰብሳቢ ንግግር ማድረጋቸው ታውቋል። የሚሊዮኖች ድምፅ ለመሬት ባለቤትነት” በሚል መሪቃል በደሴ የተደረገው የተቃውሞ ሰልፍ በተሳካ ሁኔታ ተጠናቋል፡፡ በስፍራው የሚገኙት የአንድነት ፓርቲ ከፍተና አመራሮችና የዞን አመራሮች በሰልፉ ለተሳተፈው የደሴ ህዝብ ምስጋና አቅርበዋል፡፡10015653_835736346442828_702939082745029919_n
10152391_835736339776162_7351371086334858666_n
10153092_836259806390482_8153608612627631063_n
10155032_616009748483963_362900362438077475_n
10155823_835669356449527_3760871470725215523_n
10167954_836259836390479_6240097630066552294_n
10169237_836259799723816_864490525410169866_n
10173673_836259819723814_4324534385503670790_n
10174878_702665629792189_7683975017900055174_n
10174887_702670359791716_622918347144100597_n
10174963_835669536449509_993779596150300973_n
10178024_616009418483996_7236771988187809640_n
10246832_835736313109498_4232990120556389759_n (1)

የእንግሊዝ ኩባንያዎች ቅሬታ ለጠቅላይ ሚኒስትሩ ቀረበ

April5/2014

ኢትዮጵያ ውስጥ በተለያዩ የኢንቨስትመንት ሥራዎች የተሰማሩ የእንግሊዝ ኩባንያዎች በርካታ ችግሮች እያጋጠማቸው ነው በማለት የእንግሊዝ ኤምባሲ ቅሬታውን ለጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት አቀረበ፡፡
እንግሊዝ ኤምባሲ ሰሞኑን ለጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት በኩባንያዎቹ ላይ እየደረሰ ያለውን ችግር በመዘርዘር በደብዳቤ አሳውቋል፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለ ማርያም ደሳለኝ ለጉዳዩ ትኩረት በመስጠት ከእንግሊዝ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ባለሥልጣናትና ከእንግሊዝ ኩባንያዎች ተወካዮች ጋር ተነጋግረዋል፡፡
‹‹ጠቅላይ ሚኒስትሩ የእንግሊዝ የንግድ አባላትን ለማነጋገር መፍቀዳቸው የሚያበረታታ ነው፡፡ ስብሰባው በአሁኑ ወቅት የሚታዩት ችግሮች ምን እንደሆኑ እንዲረዱ አስችሏቸዋል፡፡ አንዳንዶቹን ችግሮች ለመፍታት እንደሚሞክሩም አስታውቀዋል፡፡ ኩባንያዎቹ በኢትዮጵያ ቢዝነስ ለመሥራት ያላቸውን ፅኑ ፍላጎትም ተረድተዋል፡፡ በኢትዮጵያ የረጅም ጊዜ ቆይታ እንዲኖራቸው ቆርጠው መምጣታቸውንም እንዲሁ፤›› በማለት በኢትዮጵያ የእንግሊዝ አምባሳደር ግሬግ ዶሪ በኢሜል ለሪፖርተር ገልጸዋል፡፡
በኢትዮጵያ ከ18 በላይ የእንግሊዝ ኩባንያዎች በተለያዩ የኢንቨስትመንት ሥራዎች ላይ ተሰማርተው ይገኛሉ፡፡ ከእነዚህ ውስጥ ሜታ አቦ ቢራ ፋብሪካን የገዛው ዲያጆ፣ ከዳሸን ቢራ ፋብሪካ ጋር በሽርክና ደብረ ብርሃን ላይ አዲስ የቢራ ፋብሪካ በመገንባት ላይ የሚገኘው ዱት፣ ኢትዮጵያ ቆዳ ፋብሪካን የገዛው ፒታርድስ፣ በማዕድን ፍለጋ ላይ የተሰማራው ኒዮታ፣ በደቡብ ኦሞ በነዳጅ ፍለጋ ላይ የተሰማራው ታሎው ኦይል፣ የወጥ ቅመም የሆነውን ክኖር የሚያመርተው ዩኒሊቨር፣ በኦጋዴን በነዳጅ ፍለጋ ላይ የተሰማራው ኤጃ፣ በአፋርና በትግራይ ወርቅ ፍለጋ ላይ የሚገኘው ስትራቲክስ ኢንተርናሽናል ይገኙበታል፡፡
እነዚህ ኩባንያዎች እየደረሱባቸው ካሉ ችግሮች መካከል የሎጂስቲክስ አገልግሎትና የትራንስፖርት ችግር፣ በጉምሩክ ሥነ ሥርዓት አፈጻጸም የቆይታ ጊዜ የተራዘመ መሆኑና በንግድ ሒደት የሚያጋጥም ከፍተኛ ወጪ ይጠቀሳሉ፡፡
እነዚህ ችግሮች ቢፈቱ በቀላሉ የመንግሥትን ወጪ ከመቆጠብ ባሻገር የሙስና በር ይዘጋል በማለት ኤምባሲው አስተያየቱን ሰንዝሯል፡፡
ከዚህ በተጨማሪም የማዕድን ፍለጋ ፈቃድ ለማውጣት ረዥም ጊዜ መወሰዱ፣ የነዳጅና ጋዝ ፍለጋ እየተፋጠነ ቢሆንም የኤሌክትሪክ ኃይል አቅርቦት አለመኖርና የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ በቅርቡ ባወጣው መመርያ የውጭ ኩባንያዎች የገንዘብ አቅርቦት 50/50 እንዲሆኑ መደረጉ እንደ ችግር ተነስተዋል፡፡
ምንጮች እንደገለጹት ጠቅላይ ማኒስትር ኃይለ ማርያም የሚመለከታቸው መሥሪያ ቤቶች ይህንን ችግር እንዲፈቱ ትዕዛዝ ሰጥተዋል፡፡
እንግሊዝ በዓመት ለኢትዮጵያ 16 ቢሊዮን ብር ቀጥተኛ የበጀት ድጋፍ የምታደርግ ብቸኛ አገር ናት፡፡
የእንግሊዝ መንግሥት በበርካታ ዘርፎች ከኢትዮጵያ ጋር የሚሠራ ሲሆን፣ የመከላከያ ሠራዊት ትራንስፎርሜሽንና የ25 ዓመት የኤሌክትሪክ ኃይል ማስተር ፕላን ጥናቶችን ይሠራል፡፡
በሁለቱ አገሮች መካከል ያለው የንግድ ሚዛን ወደ እንግሊዝ ያደላ ቢሆንም፣ በኢትዮጵያ በኩልም ዕድገት እያሳየ ነው፡፡ በ2001 ዓ.ም. እንግሊዝ ከኢትዮጵያ 48 ሚሊዮን ፓውንድ የሚያወጣ ዕቃ ገዝታለች፡፡ ይህ ቁጥር በ2005 ዓ.ም. 70 ሚሊዮን ፓውንድ ደርሷል፡፡ በተመሳሳይ ወቅት ኢትዮጵያ 77 ሚሊዮን ፓውንድ የሚያወጡ ዕቃዎችን ከእንግሊዝ ገዝታለች፡፡ በ2005 ዓ.ም. ይኼ ገንዘብ 99 ሚሊዮን ፓውንድ ደርሷል፡፡

Saturday, April 5, 2014

ህወሓት በአፅቢ (እንዳስላሴ) ረብሻ ለመቀስቀስ እየሞከረ ነው፤ ነገ እሁድ አረና ለጠራው የተቃውሞ ሰልፍ ቅስቀሳውን ቀጥሏል

April 5/2014
አብርሃ ደስታ ከመቀሌ
የዓረና አባላት ለነገ እሁድ መጋቢት 28 በአፅቢ (እንዳስላሴ) ከተማ ለሚደረግ ህዝባዊ ስብሰባ ቅስቀሳ እያደረጉ ይገኛሉ። በዓድዋ ቅስቀሳ ስናደርግ “እንዳትነኳቸው፣ በሰላም ይቀስቅሱ!” ብሎ መመርያ የሰጠ በመቐለ ከተማ የሚገኝ የህወሓት ከፍተኛ አመራር ዛሬ በአፅቢ ከተማ በምናደርገው ቅስቀሳ ረብሻ እንዲነሳ መመርያ መስጠቱ ከአንድ ሰዓት በፊት ሰማሁ። አላመንኩም ነበረ። ለማረጋገጥ ወደ አፅቢ ደወልኩ።

የዓረና አባላት ቅስቀሳ ሲያደርጉ ገብረማርያም የተባለ የወረዳው የሚልሻ አዛዥ ወጣቶችን አሰባስቦ የሚታደለውን ወረቀት መቅደድና መሳደብ መጀመራቸው ተነገረኝ። በራሪ ወረቀቱ መቅደድና መሳደብ የጀመረው የወረዳው ዋና አስተዳድሪ ሲሆን እሱን ተከትለው የሚረብሹ የተደረጁ ወጣቶችም ነበሩ። አሁን ህዝቡ ጣልቃ ገብቶ የሚረብሹ ወጣቶችን አስፈራርቷል። ዋና አስተዳዳሪውን በህዝብ ተሰድቧል። አሁን ሁኔታው ተረጋግተዋል። አቅጣጫው ግን በተደራጀ መልኩ የሚከናወን የዓዲግራትን ዓይነት ይመስላል። በአፅቢ ወንበርታ በጣም ብዙ የዓረና አባላትና ደጋፊዎች አሉ። ከወራት በፊት ህወሓትን ተቃውመው ዓመፅ አስነስተው እንደነበር ይታወሳል። አሁን ወደ አፅቢ እየሄድኩ ነው።

የተጋላቢጦሽ! ተቃዋሚ ፓርቲ ሰላምና ፀጥታ እንዲከበር ጥረት ሲያደርግ ገዥው ፓርቲ (መንግስት) ደግሞ ረብሻ ለመቀስቀስ ጥረት ያደርጋል፤ ስልጣኑ ተጠቅሞ የህዝብን ሰላም የሚበጠብጡ ወጣቶች በክፍያ ያደራጃል፣ ሰለማዊ ሰው እንዲደበድቡ ያበረታታል። ዓመፅ መቀስቀስ ለምዷቸው ይሆን?! ዓረና ግን ሰለማዊ ፓርቲ ነው። ለህዝብ ነፃነት ስንል እንደበደባለን፤ ለሰላም ስንል መስዋእት እንሆናለን። ምክንያቱም የሰላም መንገድ ሰለማዊ መሆን መሆኑ እንረዳለን። ትግሉ ስንጀምር ብዙ መስዋእትነት እንደሚያስከፍለን እናውቃለን። የአፅቢ ህዝብ እንደሚተባበረንም እርግጠኞች ነን።

ፓይለት ሃይለመድህን አበራን ለማስመለስ ጄኔቭ የመጣው የኢህአዴግ ልኡካን

April 4/2014
ረዳት ፓይለት ሃይለመድህን አበራን ለማስመለስ የኢህአዴግ ልኡካን በጄኔቫረዳት ፓይለት ሃይለመድህን አበራን ወደ ኢትዮጵያ ለማስመለስ በአቶ አስመላሽ ወልደ-ስላሴ የተመራከፍተኛ የኢህአዴግ ልኡካን ቡድን ጄኔቭ፣ ስዊዘርላንድ ከርሞ ባለፈው ሳምንት ተመልሷል።በፓርላማው የህግ እና የአስተዳደር ጉዳይ ቋሚ ኮሚቴ ሊቀ-መንበር የሆኑት አቶ አስመላሽ ወልደ-ስላሴ የተመራውይህ ቡድን ከሜይ 13፣ 2014 ጀምሮ የስዊዘርላንድ መንግስት አካላት ጋር በሃይለመድህን ጉዳይ ላይ ለቀናት ተወያይቷል።ስዊዘርላንድ ረዳት ፓይለቱን አሳልፋ እንድትሰጥም ቡድኑ ብዙ ሙከራ አድርጎ እንደነበርና ሙካራው ሁሉ ሳይሳካመቅረቱንም ለማወቅ ችለናል።

ቡድኑ የስዊስ ፌዴሬሽን የህግ አካላትን ለማሳመን ካቀረበው ምክንያት ዋነኛው፣ ረዳት ፓይለት ሃይለመድህንአበራ የአእምሮ በሽተኛ መሆኑን እና ይህንንም ከራሱ ቤተሰብ አባላት እንዳረጋገጡላቸው ገልጸዋል። የስዊዝ መንግስት ግንጥያቄውን ውድቅ አድርጎታል። ለዚህም የሰጠው ዋነኛ ምክንያት፤ የሞት ፍርድን ተግባራዊ ለሚያደርግ መንግስት ማንንምአሳልፌ አልሰጥም የሚል ሲሆን ይህ ባይሆንም፣ በስዊዘርላንድ እና በኢትዮጵያ መሃል ተጠርጣሪ እስረኛን የማስመለስ ውልየለም ብለዋል።በተያያዘ ዜና ወንድሙ ዶ/ር እንዳላማው አበራ እና በጀርመን የምትኖር እህቱ ሃይማኖት አበራ ጄኔቭ ድረስበመምጣት የረዳት ፓይለት ሃይለመድህን አበራን ከሚገኝበት እስር ቤት ጎብኝተውታል። የስዊስ ጠበቆችም የፓይለቱመብት እንዲከበር አጥብቀው እየሰሩ ይገኛሉ። 

መገናኛ ብዙሃን ላይ ሲደሰኩሩ የነበሩ አንዳንድ የኢትዮጵያ የህግ ባለሞያዎችእዚህ ጉዳይ ላይ እንዲተባበሩ ሲጠየቁ አሳፋሪ ምላሽ መስጠታቸውንም ጉዳዩን በቅርብ ከሚከታተሉት ኢትዮጵያውያንለመረዳት ችለናል።ረዳት ፓይለት ሃይለመድህን አበራ ባለፈው የካቲት 10፣ 2006 ዓ.ም. የኢትዮጵያ አየር መንገድ ንብረት የሆነውንቦይንግ 767 አግቶ ጄኔቭ ስዊዘርላንድ ላይ በማሳረፍ እዚያው የፖለቲካ ጥገኝነት መጠየቁ ይታወሳል። የአለም ዜና ርዕስሁሉ ትኩረት ስቦ የነበረው ይህ ልዩ ክስተት የኢትዮጵያን የሰብአዊ መብት ሁኔታና የአስተዳደር በደል አደባባይ በማውጣቱየገዢው ፓርቲ አባላትን እጅግ እንዳበሳጨ ይነገራል።አንዳንድ መገናኘ ብዙሃን እንደገለጹት የአጎቱ ድንገተና ህልፈት ርዳት ፓይለቱን አስቆጥቶት ነበር። የሃይለመድህንአበራ አጎት፤ ዶ/ር እምሩ ሥዩም ህይወት በድንገት ማለፍ ለብዙዎች ያልተፈታ እንቆቅልሽ ነው። ዶ/ር እምሩ ሥዩም የአዲስአበባ ዩኒቨርሲቲ መምህር ነበሩ።በአለም ዙሪያ ያሉ ኢትዮጵያውያን ወጣቱ ፓይለት ሃይለመድህን አበራን መደገፋቸውን እንደቀጠሉ ሲሆን በረዳትፓይለቱ ስም የተከፈቱ ድረ-ገጾች እና የፌስቡክ መድረኮች ላይ ሰፊ ዘመቻ በማድረግ ላይ ይገኛል።የስዊዝ ቴሌቭዥን በረዳት ፓይለት ሃይለመድህን አበራ ዙርያ አንድ ዘጋቢ ፊልም የሰራ ሲሆን ይህ ዘገባ ለትንሽግዜ እንዲዘገይ ተደርጓል። ዘጋቢ ፊልሙ አየር ላይ ያልዋለበት ምክንያት የረዳት ፓይለት ሃይለመድህን አበራ ጠበቆችእንዲዘገይ በመጠየቃቸው ነው ሲሉ ጉዳዩን የሚከታተሉት ኢትዮጵያውያን ገልጸዋል።

Friday, April 4, 2014

ረዳት ፓይለት ሃይለመድህን አበራን ለማስመለስ የኢህአዴግ ልኡካን በጄኔቫ

April 4/2014

ረዳት ፓይለት ሃይለመድህን አበራን ወደ ኢትዮጵያ ለማስመለስ በአቶ አስመላሽ ወልደ-ስላሴ የተመራ ከፍተኛ የኢህአዴግ ልኡካን ቡድን ጄኔቭ፣ ስዊዘርላንድ ከርሞ ባለፈው ሳምንት ተመልሷል።
በፓርላማው የህግ እና የአስተዳደር ጉዳይ ቋሚ ኮሚቴ ሊቀ-መንበር የሆኑት አቶ አስመላሽ ወልደ-ስላሴ የተመራው ይህ ቡድን ከሜይ 13፣ 2014 ጀምሮ የስዊዘርላንድ መንግስት አካላት ጋር በሃይለመድህን ጉዳይ ላይ ለቀናት ተወያይቷል።  ስዊዘርላንድ ረዳት ፓይለቱን አሳልፋ እንድትሰጥም ቡድኑ ብዙ ሙከራ አድርጎ እንደነበርና ሙካራው ሁሉ ሳይሳካ መቅረቱንም ለማወቅ ችለናል።

ቡድኑ የስዊስ ፌዴሬሽን የህግ አካላትን ለማሳመን ካቀረበው ምክንያት ዋነኛው፣ ረዳት ፓይለት ሃይለመድህን አበራ የአእምሮ በሽተኛ መሆኑን እና ይህንንም ከራሱ ቤተሰብ አባላት እንዳረጋገጡላቸው ገልጸዋል።  የስዊዝ መንግስት ግን ጥያቄውን ውድቅ አድርጎታል። ለዚህም የሰጠው ዋነኛ ምክንያት፤ የሞት ፍርድን ተግባራዊ ለሚያደርግ መንግስት ማንንም አሳልፌ አልሰጥም የሚል ሲሆን ይህ ባይሆንም፣  በስዊዘርላንድ እና በኢትዮጵያ መሃል ተጠርጣሪ እስረኛን የማስመለስ ውል የለም ብለዋል።

በተያያዘ ዜና ወንድሙ ዶ/ር እንዳላማው አበራ እና በጀርመን የምትኖር እህቱ ሃይማኖት አበራ ጄኔቭ ድረስ በመምጣት የረዳት ፓይለት ሃይለመድህን አበራን ከሚገኝበት እስር ቤት ጎብኝተውታል። የስዊስ ጠበቆችም የፓይለቱ መብት እንዲከበር አጥብቀው እየሰሩ ይገኛሉ። መገናኛ ብዙሃን ላይ ሲደሰኩሩ የነበሩ አንዳንድ የኢትዮጵያ የህግ ባለሞያዎች እዚህ ጉዳይ ላይ እንዲተባበሩ ሲጠየቁ አሳፋሪ ምላሽ መስጠታቸውንም ጉዳዩን በቅርብ ከሚከታተሉት ኢትዮጵያውያን ለመረዳት ችለናል።

ረዳት ፓይለት ሃይለመድህን አበራ ባለፈው የካቲት 10፣ 2006 ዓ.ም. የኢትዮጵያ አየር መንገድ ንብረት የሆነውን ቦይንግ 767 አግቶ ጄኔቭ ስዊዘርላንድ ላይ በማሳረፍ እዚያው የፖለቲካ ጥገኝነት መጠየቁ ይታወሳል። የአለም ዜና ርዕስ ሁሉ ትኩረት ስቦ የነበረው ይህ ልዩ ክስተት የኢትዮጵያን የሰብአዊ መብት ሁኔታና የአስተዳደር በደል አደባባይ በማውጣቱ የገዢው ፓርቲ አባላትን እጅግ እንዳበሳጨ ይነገራል።

አንዳንድ መገናኘ ብዙሃን እንደገለጹት የአጎቱ ድንገተና ህልፈት ርዳት ፓይለቱን አስቆጥቶት ነበር። የሃይለመድህን አበራ አጎት፤ ዶ/ር እምሩ ሥዩም ህይወት በድንገት ማለፍ ለብዙዎች ያልተፈታ እንቆቅልሽ ነው።  ዶ/ር እምሩ ሥዩም የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ መምህር ነበሩ።

በአለም ዙሪያ ያሉ ኢትዮጵያውያን ወጣቱ ፓይለት ሃይለመድህን አበራን መደገፋቸውን እንደቀጠሉ ሲሆን በረዳት ፓይለቱ ስም የተከፈቱ ድረ-ገጾች እና የፌስቡክ መድረኮች ላይ ሰፊ ዘመቻ በማድረግ ላይ ይገኛል።

የስዊዝ ቴሌቭዥን በረዳት ፓይለት ሃይለመድህን አበራ ዙርያ አንድ ዘጋቢ ፊልም የሰራ ሲሆን ይህ ዘገባ ለትንሽ ግዜ እንዲዘገይ ተደርጓል። ዘጋቢ ፊልሙ አየር ላይ ያልዋለበት ምክንያት የረዳት ፓይለት ሃይለመድህን አበራ ጠበቆች እንዲዘገይ በመጠየቃቸው ነው ሲሉ ጉዳዩን የሚከታተሉት ኢትዮጵያውያን ገልጸዋል::

ዘ-ሐበሻ

ያልዘሩትን ማጨድ ከቶ አይቻልም!!

April 4/2014

የወያኔ መንግስት የኢትዮጵያን ብሄር ብሄረሰቦች አጋጭቶ በመካከላቸው ጥርጣሬና መፈራራት አንግሶና የታሪክ ጠባሳዎችን እንደ አዲስ በመጓጐጥ እያደማ ከፋፍሎ ለመግዛት ካለመታከት ያደረጋቸው ሙከራዎች ገና ፍሬ ባያፈሩም
 ቁጥቋጦዎቹ መብቀል ጀምረዋል። እዚህም እዚያም በካድሬዎች የውስጥ ለውስጥ ተልእኮ የሚለኮሱ እሳቶች መብለጭለጭ ጀምረዋል። ሌላው ቀርቶ በአንድ ብሄረሰብ መሃል ሳይቀር በከባቢ ልዩነቶች ብቻ መናቆሮችና መጋደሎች እያስተዋልን ነው። ሰሞኑን በጉጂና በቦረና ኦሮሞዎች መካከል የወያኔ ሎሌዎች በሚያበረታቱት አተካሮ የብዙ ወገኖቻችን ህይወት ጠፍቷል። ሰዎች ከኑሮአቸው ተፈናቅለዋል። ወያኔ እንደኳስ ጨዋታ ተመልካች ዳር ሆኖ ይመለከታል፣ ያጨብጭባል።
ሰሞኑን ባህርዳር ከተማ ውስጥ በተካሄደ የስፖርት ውድድር ላይ አሳፋሪ ክስተት ነበር። ለሰሚው የሚቀፍ ብልግና የተቀላቀለበት ስድብና ቁርቋሶ አይተናል። ከበስተጀርባ ሆነው ይህንን ለፍቅር ብቻ ሊውል የሚገባ የስፖርት ዝግጅት መርዝ ረጭተውበታል። ከዚህ ላቅ ያሉ የተንኮል ድግሶችም ተደግሰው ህዝብ ውስጥ በወያኔ ከተነዙ የመርዝ ቢልቃቶች ውስጥ ስራ ላይ ሳይውሉ ቀርተዋል።
ይህ በታሪካችን ታይቶ የማይታወቅ ዘር የሚዘራው ወያኔ ያልተከፋፈለ ህዝብ አይገዛልኝም በሚል ፍልስፍና እንደሆነ በተደጋጋሚ እያየን ነው። ሶማሌ ክልል ውስጥ በተቋቋሙ ልዩ ፖሊስ በሚል ስያሜ በሚጠሩ የመንግስት ሃይሎች ጥቃት ቁጥሩ እጅግ በርካታ የሆነ የኦሮሞ ማህበረሰብ ከኖረበት መሬት ተጠራርጎ እንዲወጣ ተደርጓል። ብዙዎቹ ተገድለዋል። ብዙ ደም መቃበት ተፈጥሯል። በየክልሉ ምስኪን የአማራ ገበሬዎችን መሬት ንብረት በመንጠቅ አከባቢውን ለቀው እንዲሄዱ አድርገዋል። መሄጃ የለንም ያሉትንም ቀጥቅጠው እንደገደሏቸው ሰሞኑን ከጅባትና ሜጫ አካባቢ ያሉ መረጃዎችን አይተናል።
እነዚህ በየቦታው የሚብለጨለጩ እሳቶች በዚህ ከቀጠሉ ሁላችንም ወደ ሚያቃጥልና የሚለበልብ የሰደድ እሳት ማደጉ አይቀርም። የወያኔ ባለሟሎች ካለምንም ይሉኝታና ማሰላሰል ይህንን እሳት እያራገቡ ይገኛሉ።
ይህንን አደገኛ አዝማሚያ በንጭጩ ማስወገድ የሚችለው ራሱ ህዝቡና የኢትዮጵያ ዲሞክራሲያዊ የነጻነት ሃይሎች ድምጽና ህብረት እንጂ የወያኔ መንግስት አይደለም። ስለዚህ ህዝቡ በተለይም ወጣቶች ከዚህ ወጥመድ ሰብረው እንዲወጡ ግንቦት 7 የነጻነት፣ የፍትህና የዲሞክራሲ ንቅናቄ አጥብቆ ያሳስባል። ተመሳሳይ ተንኮሎችንም ማጋለጡን ይቀጥላል። የብሄርሰብ ልሂቃንም ይህንን መርዝ እንዲቋቋሙ፣ ይልቁንም ወያኔ እንዳይመቸው ይበልጥ መቀራረብና ፈተናውን በጋራ እንድንቋቋም ጥሪያችን በድጋሜ እናቀርባለን።
ያልተዘራ አይታጨድም። ወያኔ የዘራልን መርዝ የሚያፈራው መርዝን እንጂ ሌላ አይደለም። ልዩነቶቻችን እንደዘመኑ በሰለጠነ ዲሞክራሲያዊ መንገድ እንጂ በተያዘው መንገድ ማስወገድ አይቻልም።
ዞሮ ዞሮ በዚህ ሳይጣናዊ የወያኔ መሰሪ ሴራ ለምትፈስ ለእያንዳንዶ የደም ጠብታ ተጠያቂው የወያኔ ጉጅሌ መሆኑን አጥብቀን እናሳስባለን። በመሆኑም ለመከፋፈል ከመመቻቸት ይልቅ አንድነታችን በማጥበቅ የነጻነት ሃይሎችን በመቀላቀል ራሳችን እና የሀገራችንን ህልውና ከዚህ ከወያኔ የመከፋፈል መርዝ እንታደግ።
ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ!!!

የአምባገነኑን የወያኔ ቡድን እድሜ ለማሳጠር በአንድነት እንሰራለን!

April 4/2014


የኢትዮጵያ ሕዝብ አርበኞች ግንባር እና የአማራ ዲሞክራሲያዊ ሃይል ንቅናቄ የጋራ መግለጫ

        የስልጣን እድሜውን ለማራዘም የተለያዩ  ምክንያቶችን እየፈጠረ እና በሱ ላይ የተነሱትን የተቃውሞ  ሃይላት በ አሸባሪነት ከመፈረጅ አልፎም በመግደል በማሰር እና የተለያዩ  ወከባዎችን  በመፍጠር ከትግሉ ጎራ ጋሳቸውን እንዲያገሉ ማድረጉና እያደረገም መሆኑ ህዝብ የሚያውቀው ሃቅ ነው::

       ይህን ተከትሎም በመሳሪያ ሃይል ስልጣን ላይ የወጣውን የወያኔን ቡድን ለስልጣን በበቃበት መንገድ ካልሆነ በስተቀር በሰላማዊ መንገድ የስልጣን ሽግግር እንደማያደርግ የተረዱ የተቃውሞ  ሃይላት በተለያዩ  ጎራ ተከፍለው  የትጥቅ ትግል እያደረጉ መሆኑ ይታወቃል ::

        የወያኔ አምባገነን ቡድን እድሜው ሊያጥር የሚችለው ኢትዮ0ያዊያን በአንድነት ሆነው መታገል ሲችሉና ህዝቡንም አንድ ማድረግ ሲችሉ ነው የሚለውን የመላው የኢትዮጵያዊ ጥያቄን ለመመለስ በሚል ከአሁን በፊት የተለያዩ የትብብር ሂደቶችን ቢኖሩም አመርቂ ስራ ሊሰሩም ሆነ የኢትዮጵያን ህዝብ የዘወትር ጥያቄ ሊመልሱ አልታደሉም::

         በመሆኑም ድርጅቶች አንድ ሆነው ህዝቡን አንድ አድርገው ትግሉ ሊፋጠን የሚችለው እየተባበርን ነው ብሎ  ለህዝብ ማወጅ ሳይሆን የተባበረ ሃይል የሰራውን ስራ ለህዝብ ይፋ  ማድረግና በቀጣይ የሚኖረው የትግል ሂደት ድርጅቶችም ሆኑ ህዝቡ በአንድነት በመታገሉ ሂደት በጠራ መንገድ እንዲጓዝ እገዛ ያደርጋል ::

          በዚህም መሰረት እነዚህ ከላይ የተጠቀሱት ቁም ነገሮች መቅደም አለባቸው በሚል መርህ ጥልቀት ያለቅ ውይይት በማድረግ በሚስጥር ወታደራዊ ግንባር የፈጠሩት የኢትዮጵያ ህዝብ አርበኞች ግንባር እና የአማራ ዲሞ ክራሲያዊ ሃይል ንቅናቄ በመጀመርያ እኛ ግንባር መፍጠራችንን ለህዝብ ይፋ ከማድረጋችን በፊት የጋራ ግንባሩ ህዝብ ሊያየው የሚችል በጋራ መስዋእትነት የመክፈል ሂደት መኖር አለበት የሚል የጋራ ግንባሩ ስምምነት በመኖሩና ይህንንም ተግባራዊ ለማድረግ ከሁለቱ ድርጅቶች የተውጣጣ ሰራዊት ሰሞኑን በተለያዩ  መገናኛ ዘዴዎች የተገለጸውን ስራ እንዲሰሩ ሆኗል ::

          ግቡን በአንድነት ተዋህዶ ለመስራት የተነሳው የኢትዮጵያ ህዝብ አርበኞች ግንባር እና የአማራ ዲሞክራሲያዊ ሃይል ንቅናቄ ባለፈው ሳምንት ማለትም መጋቢት 12/2006 ዓ/ም በጠገዴ ወረዳ ግጨው በተባለ አካባቢ ከወያኔ ሚሊሻ ታጣ ቂሃይል ጋር ባደረጉት ውጊያ ሶስት የሚልሻ አመራሮች ሲማርክ 17 ገድሎ 14 ማቁሰሉን እና የተለያዩ  የጦር መሳሪያዎች ከመሰል ጥይቶቻቸው እንዲሁምሁለት (2) ሽጉጥ  መማረኩንና የተማረኩትንም የሚልሽያ አመራሮች ስለ ድርጅቶቹ አላማና ፕሮግራም በማሳወቅ በሰላም ወደቀያቸው ተዘኝተዋል ::

        ኢትዮጵያንና ኢትዮጵያዊነትን ማዳን አድርገን የተነሳነው የኢትዮጵያ ህዝብ አርበኞች ግንባር እና የአማራ ዲሞክራሲያዊ ሃይል ንቅናቄ የጀመርነው ተግባራዊ እንቅስቃሴ በአንድነት መስመር ጥላ ስር መሆኑ ለህዝቡተስፋ ከመሆን አልፎ በተናጠል እየተጓዙ ላሉ ድርጅቶችም አብነት ይሆናል የሚል እምነት በማሳደር ወደ ውህደት የምንመጣበትን ሂደት እያመቻቸን መሆኑን ለመላው የኢትዮጵያ ህዝብ ለመግለጽ እንወዳለን ::

        በመሆኑም አምባገነኑ የወያኔ ቡድን እድሜው ሊያጥር የሚችለው የኤትዮጵያዊያን በተናጠል ሳይሆ ን በአንድነት ስንታገል መሆኑ ታምኖበት መላው የኢትዮጵያ ህዝብ ድርጅቶች ወደ አንድነቱ መስመር እንዲመጡ ግፊት በማድረጉ ረገድ የበኩሉን ድርሻ እንዲወጣ ጥሪ እያደረግን በተለያየ ጎራ ተከፋፍለው የሚታገሉ የወያኔ ተቃዋሚሃይሎችም እኛ የጀመርነውን አብሮ መስዋእትነት የመክፈል ሂደት በመከተል ሃገራችንንና ህዝባችንን ልናድን የምንችልበትን መንገድ እናመቻች ስንል ጥሪያችንን እናስተላልፋለን ::

የአዲስ አበባ አስተዳደር ከሕገ ወጥ ተግባሩ ታቀበ – ሰልፉ በሌላ ቀን እንዲደረግም ጠየቀ

April 4/2014
የአዲስ አበባ አስተዳደር መጋቢት 26 ቀን ለአንድነት ፓርቲ በላከው ደብዳቤ ፣ አንድነት መጋቢት 28 ቀን ሊያደርግ ያሰበዉ ሰላማዊ ሰልፍ ፣ ለሌላ ጊዜ እንዲተላለፍ ጠየቀ። ሰልፉ በታሰበበት ቀን ሌሎች ዝግጅቶች እንዳሉ የገለጸዉ የአስተዳደሩ ደብዳቤ «ተጨማሪ መስመርና ቦታ በመጥቀስ (ሰልፉን) የምታካሂዱበትን ሌላ ቀን ጭምር እንድታሳዉቁን እንገልጻለን» ሲል አስተዳደር ሕግና ስርዓቱን በጠበቀ መልኩ ምላሽ ሰጧል።
በመጋቢት 28 ቀን ምን አይነት ሌላ ዝግጅት በአዲስ አበባ እንዳለ ለማወቅ ያደረግነው ሙከራ አልተሳካም።
አስተዳደሩ አሁን የላከው ደብዳቤ ሶስተኛ ሲሆን፣ ቀደም ሲል የላካቸው ሁለት ደብዳቤዎች ሕገ መንግስቱን የሚጻረሩ ፣ ደንብን ስርዓትን ያልተከተሉ በመሆናቸው የአንድነት ፓርቲ እንደማይቀበላቸው ማሳወቁ ይታወሳል።«ለሕገ ወጥ እርምጃ ተባባሪ» አንሆንም ያለው አንድነት፣ አባላቱና ደጋፊዎቹ ትልናት መጋቢት 25 ቀን በአዲስ አበባ አራቱም ማእዘናት በራሪ ወረቀቶች ሲያሰራጩ እንደነበረ ይታወቃል።
የአንድነይ ፓርቲ አመራሮች ለአስተዳደር ምላሽ ለመስጠት ስብሰባ ላይ ሲሆኑ፣ ሕጉን ተከትሎ የቀረበ ደብዳቤ በመሆኑ፣ የአስተዳደሩ ጥያቀ በመቀበል የሰልፉን ቀን ይለዉጣሉ ተብሎ ይጠበቃል።፡
በዚህ ጉዳይ ያነጋገርናቸው የፖለቲካ ተንታኝ ፣ የመጀመሪያዎቹ ሁለት ሕገ ወጥ ደብዳቤ የጻፉትን ባለስልጣናት በሕጝ መጠየቅ እንዳለባቸው ገለጸው፣ የአንድነት ፓርቲ ሕግ ወጥ ደብዳቤዎችን ዉድቅ አደርጎ አባላቱ በድፍረት መቀስቀሳቸዉን፣ አንዳንዶቹም መአትሰራቸውን አድንቀዋል። «አንድነት ቀኑን የሚያራዝመው ከሆነ፣ የበለጠ ለቅስቀሳ ጊዜ ያገኛል» ያሉት እኝሁ ተንታኝ ፣ የአስተዳደሩን ደብዳቤ ድርብ ድርል ብልዉታል።
በተያያዘ ዜናም ሌላው በመጋቢት 28 ቀን ይደረጋል ተብሎ የሚጠበቀዉ የደሴ ሰልፍ የቅስቀሳ ዘመቻ በተጧጧፈ ሁኔታ እየተቀጣጠለ እንደሆነ ከስፍራዉ የደረሰን ዘገባ ይጠቁማል።