Tuesday, February 4, 2014

አራተኛው ሰው ጉድ አፈሉ!

Feb.4/2014

ጋዜጠኛ መስፍን ኣብርሃ - ጀርመን

p leayh



ኢትዮጵያና አሜሪካ የሁለትዮሽ ግንኙነታቸውን ከጀመሩ ዘንድሮ 111ኛ ዓመታቸውን ይዘዋል። በቀድሞው የኢትዮጵያ ንጉስ አፄ ምንሊክና በአሜሪካው አቻቸው ፕሬዚዳንት ቴዎዶር ሩዝቬልት ልዑካን መካከል ለዘጠኝ ቀናት ድርድር ከተካሄደ በሁዋላ ነበር ግንኙነቱ በይፋ የተጀመረው። ከአንድ ክፍለ-ዘመን በላይ ያስቆጠረው የአገራቱን ግንኙነት በመጠቀም ኢትዮጵያ ጠቀም ያለ እርዳታዎችን ተቀብላለች።በአሁኑ  ወቅትም በየዓመቱ ከ500 ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር በላይ የልማትና የወታደራዊ እርዳታ ተጠቃሚ ናት። አሜሪካም ብትሆን ፖለቲካዊ ወታደራዊና ኢኮኖሚያዊ ጥቅም ከአገራችን ታገኛለች።ሆኖም ከቅርብ ጊዚያት ወዲህ አሜሪካ በኢትዮጵያ ባሉ የሰብዓዊና የዴሞክራሲያዊ መብቶች መከበር ዙሪያ ቅር መሰኘቷን ደጋግማ ስትገልፅ ቆይታለች። በየዓመቱ በአሜሪካ መንግስት ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በሚወጣው የአገራት የሰብዓዊ መብት ሪፖርትም ኢትዮጵያ ባላት ሪከርድ በአሜሪካ ክፉኛ ስትተች ነበር።
ይህን ተከትሎም ይመስላል የአሜሪካ ህግ አውጪ ምክር ቤት/ኮንግረንስ ጥር 7/2006 ዓ.ም ባወጣው ዓመታዊ የበጀት ድልድል ቀመር ለኢትዮጵያ በሚሰጠው የልማትና ወታደራዊ ድጋፍ ላይ ቅድመ ሁኔታዎችን ያዘለ አንቀጽ ያካተተ ሕግ አፅድቋል።
ሕጉ የአገሪቱን ዓመታዊ የ2014 በጀት አሜሪካ እርዳታ የምትሰጣቸውን አገሮች እርዳታ ሰጪ ድርጅቶች የገንዘብ ተቋማት የሰብዓዊ መብት ተቋማትና የመሳሰሉትን በጀት ያካተተ ነው። በዚህ ዳጎስ ያለ ሕግ ላይ በአንቀጽ 70ሺ42 ገፅ 1ሺ294 ላይ የአሜሪካ መንግስት ለኢትዮጵያ የሚሰጠውን ወታደራዊና የልማት እርዳታዎች የሚመለከት ሆኖ እናገኘዋለን።
ከፕሬዚዳንት ባራክ ኦባማ ከምክትሉ ጆ ባይደን ከአሜሪካ የህግ አውጪ ምክር ቤት አፈ-ጉባኤ ጆን ቤይነር ቀጥሎ የሴኔቱ ፕሬዚዳንት በስልጣን ተዋረዳቸው ደግሞ አራተኛው ሰው በመባል የሚታወቁት ከፍተኛ ሴናተርና ዴሞክራቱ ፓትሪክ ሌሂ አማካኝነት አንቀፁ እንዲካተት መደረጉ የሚገለፀው ይኸው ህግ እንደ ኦክላንድ ኢንስቲትዩት የማህበረሰብ ተቋም የፖሊሲ ዳይሬክተር ፍሬድሪክ ሙሶ ታሪካዊ ህግ ተብሎ እየተወደሰ ይገኛል።
ከዚህ ቀደም የኢትዮጵያ መንግስትን አስተዳደር የሚቃወሙትና ኤችአር 2003 በመባል የሚታወቀውን ህግ ያረቀቁት እንደራሴዎች ዶናልድ ፔይንና ክሪስ ስሚዝ በጉዳዩ ላይ ምንም አይነት እውቀት ሳይኖራቸው በአሜሪካ የሚገኙ የኢትዮጵያ መንግስት አግባቢዎች/ሎቢስት እንዲሁም በአምባሳደር ግርማ ብሩ የሚመራው በአሜሪካ የኢትዮጵያ ኤምባሲ ህግ አነፍናፊ አታሼዎች እውቅና በላይ ሳይታሰብ በድንገት ህግ ሆኖ የወጣው ይኸው አንቀጽ የሁለቱን አገራት መንግስታት ግንኙነት ሊፈታተነው እንደሚችልም ከወዲሁ ተገምቷል።
የህጉ አንቀጽ እንደሚያስገድደው የአሜሪካ መንግስት ለኢትዮጵያ የሚሰጠው እርዳታ በትክክል ለታለመለት ዓላማ መዋሉን የአሜሪካ ውጭ ጉዳይና የገንዘብ ሚኒስትሮቹ ማረጋገጥ አለባቸው። በጀቱ በስራ ላይ ከመዋሉም በተጨማሪ በጀቱን በቀጣይ ለመልቀቅ፤
  1. ገለልተኛ ዳኝነት መኖሩን ማረጋገጥ ወይም ወደ ገለልተኛ ዳኝነት ለማምራት ጥረት እንደሚደረግ ውጤታማ እቅዶች በስራ ላይ መዋላቸውን ማረጋገጥ
  2. የኢትዮጵያ መንግስት የመናገር ራስን የመግለፅ መብት መጠበቁን ሰላማዊ ስብሰባዎች ማካሄድን በእምነት ተቋማት ላይ ተፅዕኖ ያለማ ድረግ ተቃዋሚ ፓርቲዎች በነፃነት እንዲሰሩ ዜጎች ከህግ ውጭ የማይታሰሩና ማዋከብ የሌለ መሆኑን ማረጋገጥ
  3. የሰብዓዊ መብት ተከራካሪዎች በኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል የመጎብኘት ዕድል እንዳይነፈጉ፤ በክልሉ የሰብዓዊ መብት ጥሰት በፈፀሙ የፖሊስና የመከላከያ ሃይሎች ላይ ክስ እንዲመሰረት
  4. በኦሞ ሸለቆና በጋምቤላ ክልል አካባቢዎች በሰፈራ ስም ዜጎች ከመሬታቸው እንዳይፈናቀሉና እንዳይሰደዱ ማረጋገጥ
  5. ከአሜሪካ ህዝብ ቀረጥ ከፋዮች ተሰብስቦ ለኢትዮጵያ እርዳታ የሚውለው ገንዘብ የዜጎቹን ህይወት የሚያሻሽል እንጂ ድህነቱን የሚያባብስ እንዳይሆን ሁለቱም ሚኒስትሮች አረጋግጠው ለበጀት ኮሚቴው ሪፖርት ማድረግ እንዳለባቸው የህጉ አንቀጽ ያስገድዳል።
በአጠቃላይ በኢትዮጵያ የዴሞክራሲ ስርዓቱ መሻሻልና የመልካም አስተዳደር መስፈንን በቅድመ ሁኔታነት የሚያስቀምጥ ህግ ነው ማለት ይቻላል።
ከዚህ ቀደም በሚሰጡ እርዳታዎች ላይ እርዳታውን ከመስጠት የዘለለ የቁጥጥር ነገር ስለማይደረግ ከፍተኛ ንብረትና ሃብት ተመዝብሯል የሚል ክስ የሚደመጥበት የኢትዮጵያ መንግስት ከአሁን በሁዋላ እያንዳንዷ ዶላር የት እንደዋለች የማሳመን ሃላፊነት ተጥሎበታል።
ሴናተር ሌሂ በተደጋጋሚ ጊዚያት በኢትዮጵያ ያለውን የሰብዓዊና የዴሞክራሲ መብቶች አያያዝ ላይ የተለያዩ ሪፖርቶችን አቅርበዋል። በተለይ በቅንጅት አመራሮችና በእስክንድር ነጋ መታሰር በሰብዓዊ መብት ጥሰቶች ላይ ሰፊ ንግግር አድርገዋል። እኝህ ሰው ታዲያ ያላቸውን የካበተ ልምድና የ40 ዓመት የሴናተርነት አገልግሎታቸውን በመጠቀም አንቀፁ እንዲካተት በማድረጋቸው በሰብዓዊ መብት ተሟጋች ድርጅቶች በማህበረሰብ ተቋማት በኢትዮጵያውያን አክቲቪስቶችና በዲያስፖራ በሚገኙ አንዳንድ ኢትዮጵያውያን ከፍተኛ ምሁራን ምስጋና እየተቸራቸው ይገኛል።
የህጉ አንደምታ
ህጉ የዜጎች መብት እስካልተጣሰ ድረስ እርዳታ መሰጠቱን አይቃወምም። ድንጋጌው በሐምሌ 2013 ተጠንስሶ በቅርቡ ህግ ሆኖ የወጣው ይኸው አስገዳጅ አንቀጽ ለኢትዮጵያ መንግስት ከፍተኛ የቤት ስራ የሰጠ ሆኗል። ተጠያቂነት አስቀምጧል። ይሄ ካልተፈፀመ እርዳታውን በቀጣይ ዓመት ማግኘት አስቸጋሪ ይሆናል።
ኢትዮጵያ ደግሞ በየዓመቱ በቢሊዮን የሚቆጠር ብር ከአሜሪካ መንግስት በእርዳታ የምታገኝ በመሆኑ ይህን ርዳታ ለማግኘት ቅድመ ሁኔታዎቹን ቢያንስ በአጭር ጊዜ የማሟላት ግዴታ ይኖርበታል። እንዲህ በቀላሉ ከማንም የማታገኘው እርዳታ ስለሆነም የኢትዮጵያን መንግስት ቢያንስ የተወሰነ የፖሊሲ ማስተካከያ እርምጃ እንዲወስድ ያስገድደዋል። በቅርቡ አቶ በረከት ስምኦን እንዳሉት ገበሬው ተኛ ስንለው ይተኛል ሩጥ ስንለው ይሮጣል ምንም ብናደርገው ተሸክሞን ይዞራል ያሉት ነገር የሚሆን አልመሰለኝም።ህዝቡን እንደፈለክ በተለይ በእኛ ገንዘብ ልታሽከረክር ከአሁን በሁዋላ አትችልም እየተባለ ነውና። ያው ገበሬውም ቢሆን የሚያገኘው የእርዳታ እህል በአብዛኛው የሚገኘው ከዚቹ ከአሜሪካ አይደል? ስለዚህ ቀደም ብሎ ነበር እንጂ አሁን እንኳን የአሜሪካ መንገድ የካሮትና የዱላው አማራጭ ይመስላል።meles and obama
የኦባማ አስተዳደር   
የሕጉን አንቀጽ የኦባማ አስተዳደር እንዴት ሊያልፈው ቻለ? የሚለው ጉዳይ በአሁኑ ወቅት በጣም አነጋጋሪ ሆኗል። የአብዛኞቹ ምሁራን ሃሳብ ወደ አንድ ያዘነበለ ነው። እሱም አንቀጹ የተካተተው በአንድ በሺዎች በሚቆጠሩ ገፆች ባሉት የበጀት ህግ ውስጥ በመሆኑና በዴሞክራቶቹና በሪፐብሊካኖቹ መካከል በርካታ አጨቃጫቂ አንቀፆች የነበሩ በመሆናቸው ብዙ ትኩረት ሳይሰጡበት ሾልኮ አምልጧል የሚል ነው። ምክንያቱም የኦባማ አስተዳደር ከኢትዮጵያ መንግስት ጋር ያለው ጥብቅ ግንኙነት በዚህ ሁኔታ እንዲሻክር አይፈልግምና። የህጉን አንቀጽ አስተዳደሩ አውቆት ቢሆን ኖሮ ህግ ሆኖ እንዳይወጣ ያደርገው እንደነበርም መገመት ተገቢ ነው። የአሜሪካ መንግስት አቋሙ ምን እንደሆነ እስካሁን በይፋ የገለፀው ነገር የለም። ለህጉ ከመገዛት ግን ሌላ የተሻለ አማራጭ አይኖረውም። መንግስቱ ለፓርላማው ተገዥ ነውና።
የህጉ ተግባራዊነት
የህጉ ተግባራዊነት የግድ ይላል። ምክንያቱም በማወቅም ይሁን ባለማወቅ አንቀጹ በህጉ ተካቶ ፀድቋል። ይህን የህግ አንቀጽ ይዘው ማንኛቸውም የኮንግረንሱ አባላት ይመለከተኛል የሚልም ዜጋና ተቋም የአሜሪካ ባለስልጣናትን ፍርድ ቤት አቁሞ ለተግባራዊነቱ ሊሞግታቸው ይችላልና።የኦባማ አስተዳደር በዚህ ሁኔታ ከኢትዮጵያ መንግስት ጋር ያለው ግንኙነት እንዲሻክር ባይፈልግም የፓርላማውን ውሳኔ የማስፈፀም ሃላፊነት ስላለበት አዎንታዊ ጫና ሊያሳድር ይችላል።
የኢትዮጵያ መንግስት ምላሽ/ስጋት
በእርግጥ በጉዳዩ ላይ መንግስት እስካሁን ያለው ነገር የለም። ከነበረው ሪከርዱ መረዳት እንደሚቻለው ግን የአሜሪካ መንግስት የሚሰጠው እርዳታ አነስተኛ ነው። ከአሜሪካ የምናገኘውን እርዳታ ጨምራ ቻይና ትሰጠናለች።መንገዳቸውን ጨርቅ ያድርግላቸው። የሚሉ ምላሾች እንደሚሰጡ ይጠበቃል።
ነፍሳቸውን ይማርና የቀድሞው ጠ/ሚ መለስ ዜናዊ የቀጥታ ስርጭት በሚተላለፍበት በአንድ የፓርላማ ስብሰባ ላይ በሶማሊያ የተካሄደውን ጦርነት አስመልክተው ስለ አሜሪካ የገንዘብ ድጋፍ ተጠይቀው አሜሪካ ኮንዶም ነው የምትረዳን በኮንዶም ነው ወይ ሶማሊያ የምንዋጋው? ብለው መናገራቸውን አስታውሳለሁ። ከዚህ በመነሳት የራዕያቸው ተረካቢዎችም ቃላት ለዋውጠው ወይ ይህንኑ ወርሰው ሊናገሩ ይችላሉ። አንዳንዶቹም አሜሪካ ሉዓላዊነታችንን ትነካለች ስለዚህ እርዳታው ይቅርብን ሊሉም ይችላሉ። የኦባማ አስተዳደርም አንቀጹ ሙሉ ለሙሉ ተግባራዊ እንዳይሆን የመከላከል በአንዳንድ ጉዳዮችም ላይ የተለየ አቋም ሊይዝ ይችላል።
በእኔ የህግ እውቀት ከሆነ ይህ ህግ ሆኖ የጸደቀው አንቀጽ ራሱን ችሎ ያልወጣ በመሆኑና በበጀት ህጉ ውስጥ ተካቶ በመፅደቁ ብሎም ከህጉ በግልፅ መረዳት እንደሚቻለው የ2014 የዩናይትድ ስቴትስ የበጀት ህግ በመሆኑ የኦባማ አስተዳደር ካላመነበት ከአንድ ዓመት የዘለለ እድሜ ስለማይኖረው የተደረጉት ጥረቶች በድል ተጠናቀዋል /mission accomplished/ ማለት አያስችልም።
መልካም እድሎች
የኢትዮጵያ መንግስት የአሜሪካ እርዳታ ይቅርብኝ ቻይና አለችልኝ የሚል ምላሽ መስጠት አያዋጣውም። ምክንያቱም ቻይና የኢትዮጵያ መንግስት ህዝቡን ረገጠም በህዝቡ ተረገጠም ጉዳዬ ብላ አትከታተልም። ንግዷን እስካጧጧፈች ድረስ መስጠት የምትፈልገውን ትሰጣለች። ስለዚህ የአሜሪካ እርዳታ መቅረት ከፍተኛ ችግር እንደሚፈጥር በመረዳትና ወደአላስፈላጊ ግጭት እንዳይሄድ በመፍራት የኢትዮጵያ መንግስት በአፈቀላጤዎቹ/ሎቢስት ጭምር ሳይቀር ለመደራደር የሚገደድበት ሁኔታ ይፈጠር ይሆናል። ብሎም የአውሮፓ ህብረት ከአሜሪካ በላይ ለኢትዮጵያ ገንዘብ የሚረዳ ተቋም ነውና እሱም የአሜሪካ መንግስትን አቋም ደግፎ ተመሳሳይ ውሳኔ ላይ ከደረሰ የኢትዮጵያ መንግስት እጅግ ከፍተኛ አጣብቂኝ ውስጥ ነው የሚገባው። ስለዚህ ቢያንስ ቢያንስ ለፕሮፓጋንዳ እምቢኝ ዘራፍ ቢልም ቀስ በቀስ ጉዳዩን እኛም በትራንስፎርሜሽኑ እቅዳችን ይዘነው ነበር በማለት ፖሊሲዎቹን የማስተካከል እርምጃ እንደሚወስድ መገመት ይቻላል።
መደምደሚያ
ያም ሆነ ይህ ይሄ ሸንቋጭ ህግ በኮንግረንሱ ፀድቆ ወጥቷል።አሜሪካም ከመግለጫ ያለፈ እርምጃ እንድትወስድ ሲጨቀጭቋት ለነበሩት አካላት መጠነኛ እፎይታ እንዲያገኙ አድርጋለች። እሰጣ ገባው የሚወሰነው ግን በዋነኝነት የኢትዮጵያ መንግስት በሚይዘው አቋም ላይ ይሆናል።
በአሜሪካ ኮንግረንስ የፀደቀው የህግ አንቀፅ እመራዋለሁ አስተዳድረዋለሁ አገሬ ነው ዜጋዬ ነው ለሚል ስርዓት አጋዥ እንጂ ፀሩ የሚሆንበት ሁኔታ ስለማይኖር የኢትዮጵያ መንግስት የተጣለበትን ሃላፊነት ተረክቦ ለህዝቡም ለአገሪቱም የሚበጀውን ይሄን ውሳኔ ያስተግብር!አራት ነጥብ። (ፎቶ: KAREN BLEIER/AFP/Getty Images)
ጎልጉል

የሙስሊም መፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴ አባላት ፍርድ ቤት ቀረቡ

Feb. 4 /2014

ጥር ፳፯ (ሃያ ሰባት) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የታሳሪ ቤተሰቦች፣ የሚዲያ ባለሞያዎችና የውጭ አገራት ዲፕሎማቶች  በተገኙበት በተካሄደው ችሎት  የታሳሪ ጠበቆች የምስክሮቻቸውን አድራሻ አሟልተው አለማቅረባቸው በፍርድ ቤቱ ተገልጿል።
ጠበቆቹ የምስክሮችን ስም በፍጥነት ለማስታወቅ ያልቻሉት ጂሃዳዊ ሐረካት ፊልም ለህዝብ መለቀቁን ተከትሎ በምስክሮች ላይ ፍርሀት በማደሩና የተለያዩ አካላት ስለሚያስፈራሯቸው ለደህንነታቸው በመስጋታቸው መሆኑን እንዲሁም የሰነድና የቪዲዮ ማስረጃዎች ለማቅረብ ደግሞ ተጨማሪ ጊዜ የሚያስፈልግ መሆኑን በመግለጽ ተከራክረዋል።

አቃቤ ህግ የጠበቆችን ንግግር ተቃውሞአል። ጠበቆቹ የወሰዱት ጊዜ በቂ በመሆኑ ማስረጃዎችን አጠናክረው እንዲያቀርቡም ጠይቋል።

የሙስሊሙ መፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴ ሰብሳቢ ኡስታዝ አቡበከር አህመድ በበኩላቸው በሺዎች የሚቆጠሩ ምስክሮችን አዘጋጅተው የነበረ ቢሆንም በተደጋጋሚ ከፖሊስና ከደህንነት በሚደርስባቸው ማስፈራሪያ ሳቢያ ‹‹የሚደርስብንን ችግር ተቋቁመን ለመመስከር ዝግጁ ነን›› ያሉትን ስም ዝርዝር ብቻ ማስገባታቸውን፣ የእነዚሁ መስካሪዎች አድራሻ ያልተጠቀሰውም ከደህንነት ስጋት እንደሆነ በመግለጽ ለማስረዳት ሞክረዋል።

ዳኛው በበለኩላቸው የምስክሮች ስምና አድራሻ፣ የሚመሰክሩለት ግለሰብና የሚመሰክሩት ጭብጥ በሙሉ ተሟልቶ መቅረብ እንዳለበት አሳስበዋል፡፡

አቶ አህመዲን ጀበል በበኩላቸው ታሳሪዎች ችሎት ፊት የቀረቡት ለታሪክ ምስክርነት እንጂ ፍትህን ጠብቀው እንዳልሆነ ገልጸው ‹‹የአቃቤ ህግ ምስክሮችን ደህንነት ለመጠበቅ›› በሚል ፍርድ ቤቱ ሲፈቅድ የነበራቸውን አሰራሮች በመጥቀስና በማነጻጸር ችሎቱን በመስቀለኛ ጥያቄ አፋጠዋል፡፡

‹‹የአቃቤ ህግ ምስክሮች የፖሊስም፣ የወታደርም የመንግስትም ድጋፍ እየተደረገላቸው እንኳ ደህንነታቸውን ለመጠበቅ በሚል ስም ዝርዝርና አድራሻቸው ሳይደርሳቸው ምስክርነታቸው እንዲሰማ ተፈቅዶ ሳለ፣ የተከሳሽ ምስክሮች ግን የግድ አድራሻቸው መታወቅ አለበት ተብሎ መነገሩ ትክክል አይደለም በማለት ተከራክረዋል።

ኡስታዝ አቡበክር ተጨማሪ ነገሮችን ለመናገር ሲጀምሩ  የጥበቃ ሐላፊው ያለዳኞቹ ትእዛዝ አስቁመውታል፡፡

ዳኞች በመጨረሻም የታሳሪ ጠበቆች የምስክሮች ስምና አድራሻ፣ የሚመሰክሩለትን ግለሰብና የሚመሰክሩበትን ጭብጥ በሙሉ አሟልተው ከሰነድና ቪዲዮ ማስረጃዎች ጭምር ለመጋቢት 16 እንዲያቀርቡና ለ15 ቀናት ያህልም ለችሎቱ እንዲያሰሙ ውሳኔ በመስጠት ችሎቱን አሰናብተዋል፡፡

የመፍትሄ አፈላላጊ አባላት ምንም አይነት የመንፈስ መረበሽ እንዳልታየባቸው በስፍራው የነበሩ ታዛቢዎች ገልጸዋል።

Another Oromo Politician Dies In An Ethiopian Prison!

Feb. 4, 2014
In less than six months since the death of Kassahun Chemeda, an Oromo rights activist, who died under detention in Kaliti Prison, another Oromo rights activist and a member of the opposition Oromo People’s Congress (OPC), Ahmed Nejash, has died in prison.
ESAT Radio reported last night that Ahmed, who was detained in Kaliti prison and was a candidate of OPC in the 2010 Ethiopian general election representing his constituency in Dire Dawa, was detained two years ago.In less than six months since the death of Kassahun Chemeda, an Oromo rights activist, who died under detention in Kaliti Prison, another Oromo rights activist and a member of the opposition Oromo People’s Congress (OPC), Ahmed Nejash, has died in prison.
His wife, Feriyah Abdurhman, said to the Radio that the cause of his death has not been known and no one knows where is buried. She said he was kept in solitary confinement for four months.
He is survived by his wife and his daughter.



More Ethiopian Migrants hunting, smuggling on Yemen-Saudi border

Feb4/2014

his grubby sling, Ali Yusef let out a gasp as his mangled forearm dropped limply to his side. Jumping out of a speeding pick-up truck to evade kidnappers last week, the young Ethiopian was lucky to get away with only a broken arm.
























       Ethiopian migrants walk on the side of a highway leading to the western Yemeni town of Haradh, on the border with Saudi Arabia March 28, 2012. Plagued by sandstorms, drought, gun runners and drug smugglers, the 1,800-km (1,100-mile) strip of land along the Yemeni-Saudi border has long been a desolate, dangerous place. But crumbling government control and a surge of migrants, driven out of the Horn of Africa by poverty and persecution, have turned it into a kind of hell where criminal gangs roam freely, 
         trading migrants like commodities. Picture   taken on March 28, 2012.
               REUTERS/Khaled Abdullah

“It (jumping) was worth the risk,” said Yusef, showing the blisters on his palms. “I’d rather die than let them catch me.”Yusef is one of thousands of Ethiopians lured by the promise of a better life in wealthy oil-rich Gulf Arab states who have found themselves trapped in a lawless and violent stretch of territory on the Yemeni side of the border with Saudi Arabia.

Plagued by sandstorms, drought, gun runners and drug smugglers, the 1,800-km (1,100-mile) strip of land along the Yemeni-Saudi border has long been a desolate, dangerous place.
But crumbling government control and a surge of migrants, driven out of the Horn of Africa by drought, poverty and persecution, have turned it into a kind of hell where criminal gangs roam freely, trading migrants like commodities.

Aid workers in Haradh, a smugglers’ outpost on the border, say that the kidnapping of migrants for ransom is now common practice.
“Kidnap, robbery, [deleted] abuse, it’s part of everyday life here,” said Ali Al-Jafri, a logistics officer from the International Organization for Migration (IOM), which runs a camp in Haradh for 3,000 Ethiopians awaiting repatriation.
“It’s become a business, an industry in itself.”
Exploiting the chaos in the country after mass protests forced President Ali Abdullah Saleh to step down after 33 years in office, more than 103,000 men and women crossed the Red Sea into Yemen in 2011 – double the previous year’s figure, according to the U.N. Refugee Agency (UNHCR).

The increased numbers are part of an exodus from the Horn of Africa that the UNHCR and IOM say represents one of the largest flows of economic refugees on earth.

“What you see in Yemen is just the tip of the iceberg,” said Yacoub El Hillo, the director of the UNHCR’s Bureau for the Middle East and North Africa.
“This is a lucrative business, it is a criminal business, and it is growing.”
RISING INFLUX
Chris Horwood, director of the Nairobi-based Mixed Migration Secretariat, said the kidnapping racket is already well established in the Sinai and more recently in eastern Sudan.
“We are calling it the ‘commoditization’ of migrants,” Horwood said.
“It is a lucrative, underground cash-cow. The proliferation of mobile phone networks and money transfer systems that so assist migrants to communicate and fund their journeys have become a curse used by criminals to extort what little the poorest have left.”
About 75 percent of the migrants who come to Yemen are Ethiopians, most heading to wealthy Gulf Arab states, especially Saudi Arabia, in search of work.

Hussein Regin Suri, a stick-thin Ethiopian in flip-flops trudging along a coastal road toward the Saudi border, said he had left his wife, job and nine-month-old child behind in Addis Ababa.

“What I earn in two months teaching in Ethiopia, my brother makes in a week chopping vegetables in Riyadh,” Suri said.

For most in Yemen – a country with the highest rate of chronic child malnutrition after Afghanistan – the migrants are a burden, another competitor in an already fierce scrap for limited resources.

Criminal gangs have scented opportunity, however. They snatch migrants from the roadside and detain and torture them to extract payment from their relatives abroad.

Nineteen-year-old Aisha Saeed Indris relates how her captors pressed lit cigarettes into her forearm to get her father’s telephone number after they bought her from a Yemeni border patrol.
“They poured liniment in my eyes. Then they beat me all over my body with a metal chain,” Indris told Reuters in a Haradh hospital where she was receiving treatment for her injuries. 
“They took it in turns,” she said, her voice faltering. “One of them held me down while the other raped me. Then they called my father in Ethiopia and told him that if he didn’t wire them money, they’d shoot me.”
It was only when a fellow migrant escaped and informed the police of her whereabouts that Indris was released.

LIKE FIGHTING AN INSURGENCY

Rattled by the flow of illegal immigrants, drugs and weapons, Saudi authorities have invested billions of dollars shoring up the border over the last decade.

Construction of a 75-km (45-mile) iron fence commenced in 2008. Floodlights, thermal cameras and electric wires have all made the crossing more perilous than before.

Sometimes, migrants say, Saudi border guards resort to brute force to repel those trying to sneak across the border into the kingdom in search of work.

The damp floor of a rundown hospital in Haradh is where many of those who attempt the journey end up. One man named Yusuf hoisted up yellow shorts to reveal a pair of bulging pink scars running up the backs of his thighs.

After shooting him in the legs, he said, Saudi patrolmen slung him in the back of a truck, drove him across the border and left him in a ditch under the baking sun. If not for a Yemeni farmer who found him and took him to the clinic, he would have died.


ethiopian migrants gather outside a transit center where they wait to be repatriated, in the western Yemeni town of Haradh, on the border with Saudi Arabia March 28, 2012. Plagued by sandstorms, drought, gun runners and drug smugglers, the 1,800-km (1,100-mile) strip of land along the Yemeni-Saudi border has long been a desolate, dangerous place. But crumbling government control and a surge of migrants, driven out of the Horn of Africa by poverty and persecution, have turned it into a kind of hell where criminal gangs roam freely, trading 
                      migrants like commodities. Picture taken onMarch 28, 2012.
                      REUTERS/Khaled Abdullah

Yemeni officials are frustrated by the Saudi policy of ditching the would-be migrants they apprehend back across the border.

“The Saudis are a thousand times richer than us, they’re supposed to build camps, repatriate them to their home countries,” said Ibrahim Zaydaan, an official from Yemen’s Ministry of Human Rights, who is tasked with documenting migrant abuse. “But instead they just shove them back over the border.

“It’s like trying to dam a fast-moving river – in the short term you stop some water getting through, but eventually it’s going to overflow.”

A spokesman for the Saudi Interior Ministry said half a million people try to sneak into the country annually, and that border guards only open fire when they were fired upon.
“Our border security system is no different from other countries … Those who arrive are sent back to where they came from,” said the spokesman.

On Yemen’s side of the border a climate of collusion and low political will to apprehend and prosecute smugglers is allowing the trade and abuse of migrants to flourish.

Ahmed, a military officer from Haradh who would only give his first name, is one of a handful of Yemeni security officials who have made a fortune helping smugglers move Africans into the world’s top oil exporter.

In a country where more than 40 percent of the people live on less than two dollars a day, Ahmed’s coordination with smugglers earns him around $20,000 a month.

Asked whether he runs into trouble moving migrants through government checkpoints, he laughed: “What checkpoints? This country is run by tribes not policemen: these people are my friends.”

The Defense Ministry refuses to comment on the matter. But local authorities in Haradh say there is collusion between Yemeni border guards and smugglers but say they are overwhelmed, lacking both the authority and firepower to flush the smugglers out.

“Is there facilitation? Of course there’s facilitation. I have no control over the border guards, they are under the Ministry of Defense,” said Colonel Mohammed Ahmed Najd, Chief of Police for Haradh district.
“When we raid the smugglers’ houses we face fierce resistance and shootouts. It’s like fighting an insurgency,” he said. “As long as these people keep arriving the smugglers will keep taking them. There is nothing we can do.”

Source: Reuters (by Sami Aboudi and Sonya Hepinstall)

ጉራማይሌ ፖለቲካ! – ከተመስገን ደሳለኝ (ጋዜጠኛ)

Feb.4/2014

በምንወዳት ኢትዮጵያችን ከኑሮ እስከ ሮሮ፤ ከማሕበራዊ እስከ ፖለቲካ፤ ከኢኮኖሚ እስከ ትምህርት ፖሊሲ፤ ከመንፈሳዊ እስከ ዓለማዊ… ያሉ ጉዳዮች ጉራማይሌነት ከቀን ወደ ቀን እየጎላ ነው፡፡ በዚህ ፅሁፍም ጥቂት ያህል ማሳያዎችን በአዲስ መስመር እንመለከታለን፡፡
ጎንደር እና ጥምቀት

የሁሉም መነሻና መድረሻ ዓላማ መንፈሳዊ ይሁን እንጂ እንደ መስቀል፣ ጥምቀትና ሬቻ… ያሉ አንዳንድ በዓላት ከመንፈሳዊነታቸው በተጨማሪ የባሕል መገለጫ እስከመሆን ደርሰዋል፡፡ ከዚህ የተነሳም በዓላቶቹ በሚከበሩባቸው ቦታዎች የሚገኘው ስፍር ቁጥር የሌለው ሕዝብ፣ ሰማያዊውን ፅድቅ ብቻ ሳይሆን፣ በባህላዊው አከባበርም በእጅጉ ስለሚማርክ ጭምር ነው፡፡

የሆነው ሆኖ በወዳጆቼ ጋባዥነት የዛሬ አስራ አምስት ቀን በጎንደር ከተማ በተከበረው የጥምቀት በዓል ላይ ተገኝቼ ነበር፤ በወቅቱም የታዘብኩት ጉዳይ ከሺህ ዓመታት በፊት የተፈፀመ አንድ ክስተትን እንዳስታውስ ገፊ-ምክንያት ሆኖኛል፤ ይኸውም በዘመነ ኦሪት የምድረ ባቢሎን ሰዎች አምላካቸውን ከመንበረ ሥልጣኑ ለመገልበጥ አሲረው ወደ ሰማይ የሚያወጣቸውን ታላቅ ግንብ መገንባት የጀመሩ ጊዜ አምላክ በድርጊታቸው ተቆጥቶ ቋንቋቸውን በማደበላለቁ ውጥናቸው በአጭር እንደተቀጨባቸው በመፅሀፉ የተተረከ ነው፡፡ …እነሆም ይህ በሆነ ከሺህ ዓመታት በኋላም የጎንደር ሕዝብ እና መንግስት በአንድ አደባባይ፣ በአንድ ድግስ ላይ ከመቼውም ጊዜ የበለጠ የመግባባት መንፈስ ርቆባቸው፣ ጉራማይሌነታቸው ደምቆ አስተውያለሁ፡፡

እንደሚታወቀው ኢህአዴግ መራሹ-መንግስት ከበረሃ ‹የብሔር ፖለቲካ› የተሰኘ መርዝ ቀምሞ መምጣቱ ሳያንስ፣ አረንጓዴ፣ ቢጫ፣ ቀይ ሰንደቃችን (ባንዲራችን) ላይም ኮከብ ይሉት ዲሪቶ ለጥፎ ‹ጨው ቢጠቀለልበት፣ ስኳር ቢቋጠርበት… ምንድን ነው? ያው ጨርቅ ነው!› ማለቱ ብዙሃኑን ኢትዮጵያዊ እጅግ አስቆጥቶት ነበር፡፡ በነዚህና መሰል ድርጊቶቹም የተነሳ ግንባሩ በሀገር ጉዳይ ላይ ዛሬም ድረስ መናፍቅ
ተደርጎ ተቆጥሯል፤ ደግሞም ነው! ምክንያቱም ያቺ ልባችንን በደስታ የምትሞላው ባንዲራ እስከ ደርግ ውድቀት ጧትና ማታ በክብር ስትሰቀልና በክብር ስትወርድ ነው የኖረችው፡፡ ያን ጊዜ በየመንገዱ መኪና ውስጥ ያለው ከመኪናው ወርዶ፣ እግረኛውም የደረሰበት ቦታ ላይ ቀጥ ብሎ ቆሞ፣ ጠዋት ከፍ አድርጎ ሲያውለበልባት፣ አመሻሻ ላይ ደግሞ በዝማሬ አውርዶ በክብር አጣጥፎ ሲያስቀምጣት ማየት በእውነቱ ልብን በከፍተኛ ሃሴት ይሞላ እንደነበር አይዘነጋም፡፡

ግና! ዛሬ ዘመን ተቀይሮ፣ ታሪክ ተሽሮ ስንት የደም መስዋዕትነት የተከፈለባት ውድ ባንዲራችን በተሰቀለችበት ዞር ብሎ የሚያያት ጠፍቶ ተበጫጭቃ ሰርግ ቤት የተጎዘጎዘ ወረቀት መስላ መታየቷ በቁጭት አንገብግቦ፣ በሀዘን ልብ ይሰብራል፡፡ እናም ብዙሃኑ ባንዲራ የሚያውለበልብበት አጋጣሚ በተፈጠረ ቁጥር ከፍ የሚያደርጋት ያችኑ ንፅኋን (የድሮዋን) ሰንደቅ ሆኖ ዘልቋል፡፡ ይሁንና ካለፉት ጥቂት ዓመታት ወዲህ ድንገት ከእንቅልፉ የባነነው ኢህአዴግ በየትኛውም ጊዜና ቦታ ሁሉ መውለብለብ ያለበት ኮከብ የታተመበት ባንዲራ ብቻ እንዲሆን በአዋጅ እስከመደንገግ ደርሷል፡፡ ይህንንም አዋጅ ተከትሎ በተለይም አዲስ አበባን ጨምሮ በዋና ዋና ከተሞች ባንዲራን በተመለከተ ጠበቅ ያለ ቁጥጥር ሲያደርግ ተስተውሏል፡፡

ሰሞኑን በጎንደር ከተማ ያያሁት ግን የዚህን ተቃራኒ ነው፤ ባንዲራችን የባህላዊም ሆነ ኃይማኖታዊ በዓላት ዋነኛ አድማቂ መሆኗ ነባር ልማድ ነው፤ እናም ጎንደር ላይ ዘንድሮ የጥምቀት በዓል በተከበረበት ወቅት በታቦታቱ ዙሪያ በተለያየ መልኩ የተዘጋጀውም ሆነ ሕዝቡ ያነገበው ሰንደቅ፣ አገዛዙ ‹‹ከዚህ ውጪ…›› ብሎ ለእስር እንደሚዳርግ በአዋጅ የለፈፈለትን ባለ ኮከቡን አይደለም፤ ይልቁንም በብዙሃኑ የሀገሬ ሕዝብ ልብ ላይ የታተመችውን ያችን ንፁህ አረንጓዴ፣ ቢጫ፣ ቀይ ባንዲራ ብቻ ነበር፡፡ …ኩነቱም የፓርቲ ‹ፖለቲካዊ ፍቺ› ሰጥቶ ሰንደቁን ላዥጎረጎረው ኢህአዴግ ‹‹እመራዋለሁ›› ከሚለው ሕዝብ ያለውን ዕርቀት አመላካች ሆኖ አልፏል፡፡

ሌላው የዕለቱ ጉራማይሌ ክስተት በተለያየ ቅርፅ የተሰሩ፣ የኢትዮጵያን መልከዓ-ምድር የሚያሳዩ ሶስት ግዙፍ ካርታዎች በመኪኖች ላይ ተጭነው ለዕይታ አደባባይ መቅረባቸው ነው፤ እነዚህ ካርታዎች የሚያመላክቱት የሀገራችን ሰሜናዊ ድንበር መለስ ዜናዊ እና ጓደኞቹ ትግራይ ላይ ተገድቦ እንዲቀር ከሻዕቢያ ጋር የተዋዋሉበትን አይደለም፤ ስመ-ጥሩው ጀግና አሉላ አባነጋ ጦሩን ሰብቆ ‹ቼ ፈረሴ› ብሎ እስከጋለበበት ቀይ ባህር ድረስ የሚዘረጋውን የቀድሞውን የኢትዮጵያ ይዞታ ያካተተ እንጂ፡፡

ይህ መሳጭ ትዕይንትም ሕዝብና መንግስት ያለፉትን ሃያ ሁለት ዓመታት መደማመጥ የማይችሉ (ቋንቋቸው የተደበላለቀባቸው) ሆነው እዚህ እንደደረሱ ማሳያ ተደርጎ ሊወሰድ ይችላል፡፡ ለዚህ አይነቱ ጉራማይሌ ግንኙነት ገፊ-ምክንያት ደግሞ የጎንደር ሕዝብ ሕገ-ወጥ በመሆኑ አልነበረም፤ ገዥው ፓርቲ ይቺን ሀገር ለመመስረት እልፍ አእላፍ ቀደምት አባቶች የሞቱላትን፣ ታሪክ የተሰራባትን ባንዲራ በማን ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ አህሎኝነት ያሻውን የለጠፈባት ከመሆኑም በላይ የኢትዮጵያን ጥቅም ያላስከበረ የሀገር ግንጠላ ላይ መሳተፉ የፈጠረው ቁጭት ነው፡፡…መቼም የዕለቱን ኩነት ቋራ ሆቴል በረንዳ ላይ ከእኛ በጥቂት ሜትሮች ዕርቀት ተቀምጦ ቁልቁል ሲከታተል የነበረው በረከት ስምዖንየተጠናወተው የእብሪት ፖለቲካ አይነ-ልቦናውን ካልጋረደበት በቀር ይህ ጉዳይ የሚያስተላልፍለት አንዳች አገራዊ ምስጢር ያለው መሆኑ አይጠፋውም፡፡

ዛሬም መሬት ማስወሰዱ ቀጥሏልን?

ከእነዚህ ክስተቶች በተጨማሪ በአካባቢው የተመለከትኩት ከባድ ውጥረት አለ፤ ይኸውም ‹ለሱዳን ሊሰጥ ነው› እየተባለ የሚነገርለት የመሬት ጉዳይ ካመጣው ጣጣ ጋር የሚጋመድ ነው፤ በርግጥ በአንዳንዶች ዘንድ መሬቱ ወደ ውስጥ ስልሳ (60)፣ ወደ ጎን ደግሞ አንድ ሺህ (1000) ኪሎ ሜትር ድረስ እንደተሰጠ ይታመናል፡፡ ይሁንና በግሌ ይህ ክስ ማረጋገጫ የሚቀርብበት ሆኖ አላገኘሁትም፡፡

በጉዳዩ ላይ ምክንያታዊ ለመሆንም በዚህ በተጠቀሰው የመሬት ስፋት ውስጥ ሊካተቱ የሚችሉ ከተሞችን መመልከቱ የተሻለ በመሆኑ፣ በቀጥታ ከሱዳን ጋር ከሚዋሰኑ ሁለት ከተሞች አንስተን እናስላው፤ እናም ከመተማ ከተነሳን ሸህዲን፣ ወህኒ፣ ነጋዴ ባሕር እያልን ጭልጋን እናገኛለን፡፡ መነሻችን ከሌላኛው የወሰን ከተማ ተሂ ከሆነ ደግሞ ምንጁግጁግ፣ ወዲ በርዚን፣ ኩሊት፣ ሸንፋ፣ ማሕበረ-ስላሴ ገዳምን አልፈን ደንገል እንደርሳለን፡፡ እንግዲህ የሰማነው ወሬ እውነት ከሆነ እነዚህ መሬቶች ሁሉ ለሱዳን ተሰጥተዋል ማለት ነው፡፡ ግን ለምን? ኢህአዴግ እንዲህ ሙጭጭ ብሎ የያዘውን ሥልጣን ሊያሳጣው የሚችል ውሳኔ ላይ ለመድረስ (ከተሞቹን ለሱዳን ለመስጠት) የተገደደበት ምን ምክንያት አለ? በነገራችን ላይ ይህ አስተያየት ስርዓቱ ለሀገር ጥቅም ይቆረቆራል እንደማለት አይደለም፡፡ ምክንያቱም በሆነ ክፉ ቀን ሥልጣኑን አጣብቂኝ ውስጥ የሚከት ሁኔታ ከገጠመው ሀገር ከመበታተንና ከማፈራረስ የሚመለስ አለመሆኑን የቀድሞው ተሞክሮዎቹ ይነግሩናል፡፡

የሆነው ሆኖ ሊተኮርበት የሚገባው ኢህአዴግ እስከአሁን በጉዳዩ ላይ ምላሽ ሳይሰጥ ያደፈጠበት አንዳች የሸሸገው ሚስጥር ቢኖር ነው የሚለው ይመስለኛል፤ የዚህ መነሻ ምክንያታችን ደግሞ ወደ ሥልጣን ከመጣ በኋላ በድብቅ ለሱዳን የሰጣቸው (ዛሬ ተወሰዱ ከሚባሉት ውስጥ የማይካተቱ) መሬቶች የመኖራቸው እውነታ ነው፤ ይኸውም ብአዴን የመሰረተው ‹‹ዘለቀ እርሻ›› የተሰኘው ድርጅት በአንድ ወቅት ያስተዳድራቸው የነበሩት አብደረግ እና ደሎል (ሽመል ጋራ እና ምዕራብ አርማጭሆ) ውስጥ በቁጥር ከአንድ እስከ ስምንት የተሰየሙ ግዙፍ የእርሻ መሬቶች ነበሩ፤ ይሁንና በአሁኑ ወቅት ከቁጥር ሁለት እስከ ስምንት ያሉትን (በድምሩ ወደ ሁለት መቶ ሺህ ሄክታር የሚደርሱ) መሬቶችን አሳልፎ ሰጥቷል፤ ይህንንም ተከትሎ ‹‹ዘለቀ እርሻ›› እንቅስቃሴ አልባ ሆኗል፡፡ በርግጥ ‹ቆራጦቹ› የብአዴን አመራሮችም ቢሆኑ እንዲህ አይነቱን ጥሬ ሀቅ አይክዱም፤ ይልቁንም ‹ቀድሞውንም ግማሹ ይዞታ የእነርሱ ነበር› ብለው ያስተባብላሉ እንጂ፡፡ …ግና! ማን ነበር ‹‹ከሱዳን ነጥቀን የወሰድነው መሬት አለ!›› ያለው? መለስ ዜናዊ ይሆን?4

እንዲሁም ‹‹ስናር›› የተባለው ከፊል ቦታ ለሱዳኖች መሰጠቱን ከታማኝ ምንጭ ሰምቻለሁ፤ ርግጥ ስናርን ሱዳኖች እንዲቆጣጠሩት በር የተከፈተላቸው የደርግ መንግስት በወደቀበት ማግስት (በ1983 ዓ.ም መጨረሻ) ነው፤ የዚህ ስጦታ መግፍኤ በትግሉ ዘመን ሱዳን ኢህአዴግን ‹አቅፋና ደግፋ› ለድል እንዲበቃ ያበረከተችው ውለታን ታሳቢ ያደረገ እንደሆነም ይነገራል፡፡ እናም ሱዳኖች እንደ መና የወረደላቸውን ያልታሰበ ገፀ-በረከት ለመጠበቅ ወደ አስራ ሁለት ገደማ የሚደርሱ ወታደራዊ ካምፖችን መስርተው እስከ 1988 ዓ.ም ድረስ የምድሪቱን በረከት ሲቀራመቱ መቆየታቸው እውነት ነው፡፡ ይሁንና በ1988 ዓ.ም በወቅቱ የሱዳን መንግስት አፈ-ጉባኤ የነበረው ሃሰን አል-ቱራቢ እጅ እንዳለበት የተጠረጠረውን በአዲስ አበባ በቀድሞ የግብፅ ፕሬዚዳንነት ሆስኒ ሙባረክ ላይ የተቃጣውን የግድያ ሙከራ ተከትሎ ኢትዮጵያና ሱዳን (በተለይም ተጠርጣሪዎችን አሳልፎ በመስጠትና ባለመስጠት ጉዳይ) ግጭት ውስጥ ይገባሉ፡፡ ይህን ጊዜም ኢህአዴግ የአካባቢውን አርሶ አደሮች ‹‹መሬታችሁን አስመልሱ›› በሚል ቀስቅሶ በሱዳናውያን ላይ ያዘምታቸውና ድል ያደርጋሉ፤ ስናርም ተመልሳ በኢትዮጵያውያን ይዞታ ለመጠቃለል በቃች፡፡ ግና! አሁንም እንቆቅልሽ በሆነ ሁኔታ (ከ1999 እስከ 2000 ዓ.ም ድረስ ባለው ጊዜ) እንደገና ወደ ሱዳን ተላልፋ ተሰጠች፤ በነገራችን ላይ ስናር በሃያ ስድስት ‹‹ኮርድኔት›› የተከፋፈለች ስትሆን፣ ዛሬ የኢትዮጵያውያን ይዞታ ሊባል የሚችለው ‹‹ኮርድኔት 24›› በተሰኘው ውስጥ ባለፈው ዓመት ህይወታቸው ያለፈውና በርካታ
ታጣቂዎችን ማስከተሉ የሰመረላቸው ባሻ ጥበቡ እና አስመሮም መኮንን የተባሉ ግለሰቦች ለሱዳናውያን ሳያስረክቡ፣ በራሳቸው ኃይል ተገዳድረው ያቆዩት መሬት ነው፡፡ በተቀረ በአካባቢው የምናገኛቸው ኢትዮጵያውያን ከሱዳናውያን ላይ በአረብኛና እንግሊዘኛ በተፃፈ ውል በተከራዩት መሬት ላይ ብቻ ነው፡፡

በአናቱም በአሁኑ ወቅት ለሱዳን ሊሰጡ ነው እየተባለ የሚነገረው እንደ መተማ-ዮሀንስ፣ ዳፋ፣ ሽመል ጋራ፣ ፎርኹመር፣ አብዱራፊ፣ ነፍስ ገብያ፣ አለቃሽ (በረሃማ አካባቢ ነው)… የመሳሰሉ ከተሞች ስማቸው ተደጋግሞ በመነሳቱ፣ አካባቢውን ውጥረት ውስጥ ከትቶታል፡፡ በርግጥም ከአገዛዙ ያደረ ታሪክ አኳያ መሬቶቹን አይሰጥም ተብሎ አይታሰብም፤ በተለይም ጉዳዩን ለጥጠን የሰሜን አፍሪካ አብዮት በፈጠረበት ስጋት፣ በድንገቴ ውሳኔ እየገነባ ካለው የ‹‹ህዳሴ ግድብ›› ጋር አነፃፅረን ካየነው፣ የሱዳንን ድጋፍ ለማግኘት መሬቶቹን አሳልፎ ሊሰጥ ይችላል ወደሚል ጠርዝ እንገፋለን፡፡ …ግና! ይህ አይነቱ ኢህአዲጋዊ ድፍረት ‹‹አባትየው ቢሞት የለም ወይ ልጅየው?›› በሚል ሕዝባዊ ተቃውሞ መቀስቀሱ አይቀሬ ነው፡፡ ከዚህ ውጪ ዛሬ ‹‹ተሰጡ›› ወይም ‹‹ሊሰጡ›› ነው ብለን የምንጫጫባቸው መሬቶች‹‹የይገባኛል›› ጥያቄ ያልቀረበባቸው በመሆኑ፣ ኦቦ ሌንጮ ለታ ‹በባሌ ሲጠብቁን፣ በቦሌ ገባን› እንዲል፣ ስርዓቱ ሆነ ብሎ ከእውነታውአርቆ ለማደናገር የሚጠቀምባቸው አጀንዳዎች ሊሆኑ ይችላሉ ብሎ መጠርጠሩ አስተዋይነት ይመስለኛል፡፡ በርግጥም ጉራማይሌ ፖለቲካ ማለት ይህ ነው፡፡

ሌላው ትኩረት የሚያሻው ጉዳይ ኢህአዴግ በእነዚህ አካባቢዎች እያደረገ ያለው የሚከተለው መሆኑ ነው፡- ከኩሊት እስከ ቋራ ድንበር ድረስ ከወሎ፣ ከጎጃም እና ከጎንደር ነዋሪዎች አሰባስቦ የመልሶ ማስፈር ስራ ሰርቷል፤ የሰፈራው ዋነኛ አላማም ለም መሬት ይዘው እያረሱ ቤተሰብ መስርተው እንዲቀመጡ ያማቻቸላቸውን ሰፋሪዎች መሳሪያ በማስታጠቅ በአካባቢው በኩል ሊመጡ የሚችሉ የኃይል አማራጭን የሚከተሉ ተቃዋሚዎችን እንዲከላከሉ እና ከአቅማቸው በላይ ሲሆን ደግሞ አስቀድመው መሬት ለሰጣቸው መንግስት እንዲያሳውቁ ማድረግን ያሰላ ነው፡፡ በዚህም ለሥልጣኑ አስጊ የሆነውን ቀዳዳ ለመድፈን እየሞከረ እንደሆነ መረዳት ይቻላል (በነገራችን ላይ ከጎንደር ተቆርሶ ለትግራይ መሬት ተሰጥቷል የሚል አደገኛ ቅስቀሳም እየተካሄደ ነው፤ በግሌ ይህ ጉዳይ የሚያወዛግብ አይመስለኝም፤ ስርዓቱ ያነበረውን ቋንቋ ተኮር ፌደራሊዝም የማንደግፈው እስከሆነ ድረስ መሬቱ ወደ የትኛውም የሀገሪቱ ክልል ቢሄድ ለውጥ አይኖረውም፤ ምክንያቱም በኢህአዴግ ግብዓተ-መሬት ላይ የሚያብበው መልከዓ-ምድራዊ ፌደራሊዝም (Geographical Federalism) እነዚህን አጨቃጫቂ መሬቶች ለአስተዳደር አመች በሆነ መልኩ ማዋቀሩ አይቀሬ ነውና)

አያሌው ጎበዜና ባሕር ዳር

አቶ አያሌው ጎበዜ ድርጅቱን የተቀላቀለው አስተማሪ ሆኖ እየሰራ በነበረበት አዲስ ዘመን ከተማ በ1984 ዓ.ም ቢሆንም በተፋጠነ ሂደት የሽግግር መንግስቱ የስራ አስፈፃሚ አባል መሆን ችሎ ነበር፤ ከ1987-1992 ዓ.ም የክልሉ አስተዳዳሪ አዲሱ ለገሰ ምክትል ሆኖ ተሹሟል፤ በዮሴፍ ረታ የአስተዳደር ዘመን (ከ1992-97 ዓ.ም) ደግሞ መጀመሪያ የክልሉ ገንዘብና ኢኮኖሚ ኃላፊ፣ ቀጥሎ አፈ-ጉባኤ ሆኖ ሰርቷል፡፡

ይሁንና በምርጫ 97 ዮሴፍ በተወዳደረበት ሰሜን ሸዋ በቅንጅት እጩ ሲሸነፍ፣ አያሌው ደግሞ በማርቆስ ከተማ በባሶ ሊበን ወረዳ ሊያሸንፍ ችሏል (አሸናፊነቱ ምንም እንኳ እንደ ሌሎቹ የኢህአዴግ ተወዳዳሪዎች በድርጅታዊ የድምፅ ስርቆት የተገኘ ቢሆንም) ከ1998 ዓ.ም አንስቶ እስከያዝነው አመት መጀመሪያ ወራት ድረስ የክልሉ ፕሬዚዳንት ሆኖ የቆየው አያሌው ጎበዜ ‹‹ለሱዳን ተሰጠ›› ወይም ‹‹ሊሰጥ ነው›› ከተባለ መሬት ጋር ተያይዞ የማጀገኑና የማንፃቱ ቅስቀሳ የኑፋቄን መንገድ የተከተለ ይመስለኛል (የጉዳዩ ስሁትነት የኛይቷን ‹ፋክት› መፅሄትንም ይጨምራል) በደፈናው ከዚህ ቀደም ‹አያሌው ለሱዳን በሚሰጥ መሬት ላይ አልፈርምም በማለቱ፣ ደመቀ መኮንን ፈረመ› የሚባል ምንጩ የማይታወቅ ወሬ ሁላችንም ጋ ደርሶ እንደነበረ ይታወሳል፡፡ ይሁንና ከብአዴን የመረጃ ምንጮቼ እንዳረጋገጥኩት፣ አያሌው ያውም ርህራሄ አልባ የነበረውን የጉልበታሙ ጠቅላይ ሚንስትር መለስ ዜናዊን ውሳኔ ተቃውሞ ‹ፈርም›፣ ‹አልፈርምም› አይነት አንጃ ግራንጃ የሚፈጥር ደፋር ልብ ያሌለው መሆኑን ነው፡፡ በግልባጩ ፖለቲካችን ጉራማይሌ ነውና ለብአዴን ፍቅር በሌላት ባሕር ዳር አያሌው ተወዳጅ እንደሆነ ይነገራል፤ ይህ የተወዳጅነቱ ሚስጥር ግን ከድርጅቱ ይልቅ ‹‹መረጠኝ›› ለሚለው ሕዝብ ታማኝ በመሆኑ እና በሀገር ጥቅም ከእነ ‹ኦቦ› አዲሱ ለገሰ ተሽሎ ሳይሆን፣ ከራሱ የግል ባህሪና ሰብዕና ጋር ስለሚያያዝ ነው፤ ይኸውም በመኖሪያ ቤቱ አካባቢ ካሉ ነዋሪዎች እና አብረውት ከሚሰሩ የበታች ሰራተኞች ጋር የመሰረተው ማሕበራዊ ግንኙነት ዋነኛው ነው፤ በርግጥም የሚያውቀውም ሆነ የማያውቀው ሰው ሲሞት ቀብር ላይ ይገኛል፤ ማታም እዝን ይዞ በመሄድ ሲያፅናና ያመሻል፤ ሰርግን በመሳሰሉ የደስታ ዝግጅቶችም ላይ እንዲሁ ይሳተፋል፤ እነበረከት ስምዖን ለሚያቀነቅኑት ግራ ዘመም ፖለቲካም ሩቅ በመሆኑ፣ እጅግ መንፈሳዊ የሆነ ባህሪይ ይስተዋልበታል፤ ለአብነት እምነቱ የሚያዝዘውን (ከመፆም ጀምሮ በቤተ-ክርስቲያን ተገኝቶ እስከ ማስቀደስ ያሉ ጉዳዮችን) እንደ ባለሥልጣን ግብዝ ሳይሆን እንደ ማንኛውም ተራ አማኝ ዕለት ተዕለት ሲፈፅም ይታያል፡፡ በቤተሰብ አስተዳደርም ቢሆን አራት ልጆቹን መንግስት ትምህርት ቤት ከማስተማር አልፎ በኢትዮጵያዊ ጨዋ ስነ-ምግባር ማሳደጉን፣ ብልሹ አድርገው ልጆቻቸውን እያሳደጉ ካሉ ከአንዳንድ ኃላፊነት ከማይሰማቸው ባለሥልጣናት ጋር አነፃፅረው የሚያመሰግኑት የድርጅቱ የቅርብ ሰዎች አጋጥመውኛል፤ ከጥቂት ወራት በፊት በህክምና በማዕረግ የተመረቀችውን ብቸኛና የመጀመሪያ ሴት ልጁንም እንደ ምሳሌ ይጠቅሳሉ፡፡

በአናቱም የትኛውም ባለ ጉዳይ ቢሮው ሲመጣ ያለ ቢሮክራሲ ማስተናገዱም ሆነ ለሚቀርብለት አቤቱታም ጥያቄ ‹አይሆንም› አለማለቱን እንደ በጎ ተግባር የቆጠሩለት ሰዎች ለሰውየው ገፅታ ግንባታ የራሳቸውን ሚና ተጫውተዋል፡፡ በተቀረ ኢህአዴግ እንደ አሰባሰባቸው በርካታ ባለስልጣናት እርሱም አለቆቹን አብዝቶ የሚፈራ ሽቁጥቁጥ ሰው መሆኑን በቅርብ የሚያውቁት ይናገራሉ፡፡ በተለይም የብአዴን ካድሬዎች ‹‹ሽማግሌው›› እያሉ በሹክሹክታ የሚጠሩትን አዲሱ ለገሰን እና ሞገደኛውን በረከት ስምዖንን የ‹መለአኩ ገብርኤል› ያህል እንደሚፈራቸው ሰምቻለሁ፡፡

ይህ ፍራቻውም በፍትሕ እና በሙስና ቢሮዎች አካባቢ ከብቃት ይልቅ ‹‹የራሴ›› የሚላቸውን የትውልድ መንደሩን ሰዎች በመሾሙ ‹‹እመራዋለሁ›› የሚለውን ሕዝብ ለከፋ ብሶትና መከራ አጋልጦ ነው ከሥልጣኑ የተሰናበተው፡፡ ይህም ሆኖ ከኃላፊነቱ ለመልቀቅ ጥያቄ ካቀረበ ከአንድ አመት በኋላ ነው ፓርቲው ያፃደቀለት፤ ያለፈውን ሙሉ ዓመትም በቢሮው ከመገኘቱ እና በትላልቅ ጉዳዮች ላይ ከመሳተፉ ባለፈ፣ ሁሉንም ሥራ ሲሰራ የነበረው ዛሬ በምትኩ የተሾመው የዋድላ ደላንታው ገዱ አንዳርጋቸው ነው፤ ገዱ ድርጅቱን የተቀላቀለው ከአያሌው አንድ ዓመት ቀደም ብሎ ዋድላ ደላንታን ኢህአዴግ ከደርግ መዳፍ በኃይል ነጥቆ በወሰደበት ወቅት ነበር፤ ያን ጊዜ የገበሬ ማሕበር ሕብረት ሱቅ ሠራተኛ የነበረው ገዱ ዛሬ የክልሉ ፕሬዚዳንት ለመሆን ችሏል፤ በርግጥ ይህ ሰው ጠንካራ ሠራተኛ እና የበላይአመራሮችን ተጋፋጭ እንደሆነ ይነገርለታል፤ እንዲሁም እንደ አያሌው ከሙስና ጋር ብዙም ንክኪ የለውም (በነገራችን ላይ የብአዴን ዋነኛአመራሮች ለሙስና ሩቅ እንደሆኑ በወሬ ደረጃ ይሰማል፤ ግና! ይህንን እንደምን ማመን ይቻላል? …በርግጥ በክልሉ በተዘዋዋሪ መንገድ የጀነራል አበባው ታደሰ ነው ከሚባለው ባለ አራት ፎቁ ‹‹አልዋቅ›› ሆቴል ሌላ በወሬ ደረጃ የአመራር አባላቱ ንብረት የሆነ አላጋጠመኝም፤ ነገር ግን እኔን አላጋጠመኝም ማለት ሰዎቹ ንፁሃን ናቸው እንደ ማለት አይደለም)



 አቶ በረከት እና አዲሱ 


የሆነው ሆኖ ብአዴን በበረከት ስምዖን፣ በአዲሱ ለገሰ፣ በካሳ ተክለብርሃን፣ በታደሰ ጥንቅሹ እና በከበደ ጫኔ ስም የመሰረተው ‹‹ጥረት›› የተሰኘው ኮርፕሬሽን ዳሽን ቢራ፣ ጥቁር አባይ ትራንስፖርት፣ ዘለቀ እርሻ፣ አምባሰል አስመጪና ላኪ፣ ጣና ሞባይል እና ጣና ፍሎራ የተሰኙ የንግድ ድርጅቶችን ያስተዳድራል፡፡ ከእነዚህም ውስጥ አትራፊ የሚባለው ዳሽን 49 ፐርሰንቱን እንግሊዝ አገር ለሚገኝ አንድ ቢራ አምራች ድርጅት ሲሸጥ፤ ጣና ሞባይልም በአሜሪካን ሀገር የታወቀው የሶፍት ዌር ኢንጂነር ባለሙያው ወልደሉዑል ካሳን ጨምሮ ለአራት ሰዎች የአክሲዮን ድርሻን አስተላልፏል፡፡ ይህ ሁኔታም ድርጅቶቹ ትርፍና ኪሳራቸውን በውጪ ኦዲተር እንዲያስመረምሩ የሚያስገድድ መደላድል ፈጥሮላቸዋል፡፡ በርግጥም እንዲህ አይነቱ አሰራር የእነ አዜብ መስፍን መቀለጃ ከሆነው ‹‹ኤፈርት›› በተሻለ መልኩ ለዘረፋ እንዳይጋለጥ መታደጉ አከራካሪ አይደለም፡፡ ምክንያቱም እንግሊዛዊው ድርጅት የዳሽን ቢራ 49 ፐርሰንት ድርሻን ገዝቶ ሲያበቃ፣ ወጪና ገቢውን አይከታተልም ማለቱ ሩቅ ነውና፡፡

በትግራይ ሕዝብ ስም እየነገደ፣ ለህወሓት አመራር አባላትና ቤተሰቦች ብቻ መምነሽነሺያ የሆነው ‹‹ኤፈርት››ም በእንዲህ አይነት መልኩ ለውጭ ድርጅቶች ድርሻ እንዲሸጥ ካልተገደደ በቀር ለቁጥጥር አስቸጋሪ ሆኖ መቀጠሉ ሳይታለም የተፈታ እውነታ ነው፤ ይህ ሁኔታም የፖለቲካ ሥልጣን የጨበጠ ሁሉ የቻለውን የሚዘግንለት ከመሆን የሚተርፍበትን እድል ያመቻችለታል (በነገራችን ላይ እንደሚወራው የብአዴን አመራሮች ወደ ሙስና አለመግባታቸው እውነት ከሆነ፣ ምክንያቱ ጠፍጥፎ የሰራቸውን ህወሓት በመፍራት ብቻ ነው ሊሆን የሚችለው፡፡ በግልባጩ ህወሓት በኢትዮጵያ ሰማይ ስር የሚፈራው የለምና እንዲህ እንደቀለደ በሚቀጥለው ወር የተመሰረተበትን 39 ዓመት ለማክበር ሽር-ጉዱን ከወዲሁ ተያይዞታል)
ሌላው የብአዴን አመራሮች አስገራሚ ታሪክ ከዋነኞቹ መካከል ታምራት ላይኔ፣ በረከት ስምዖን፣ አዲሱ ለገሰ፣ ሕላዊ ዮሴፍን… የመሳሰሉት የትዳር አጋራቸውን ያጩላቸው አንዲት ሴት መሆናቸው ነው፡፡ እኚህ የዋግ ኡምራ ተወላጅ በታጋዮች ዘንድ ‹‹ማዘር›› እየተባሉ ሲጠሩ፣ ኢህአዴግ ውስጥ ባሉ አንዳንድ አሽሟጣጮች ደግሞ ‹‹ጣይቱ›› በሚል ቅፅል ስም ይታወቃሉ፤ ይህ ስያሜ የአጼ ምንሊክ ባለቤት የነበሩት እቴጌ ጣይቱ ታላላቅ መኳንቶችን እየመረጡ ከቅርብ ዘመዶቻቸው ጋር ያጋቡ ነበር ከሚለው ትርክት የሚነሳ ነው፡፡ የሆነው ሆኖ ይህንን ኩነት ጉራማይሌ የሚያደርገው የ1993ቱን የህወሓት ክፍፍል ተከትሎ የብአዴን መሪዎች ‹‹ቦና-ፓርቲዝም››ን በአደባባይ ሲያወግዙና ሲተቹ መስማታችን ነው፡፡
(ቀሪውን ጉራማይሌ የፖለቲካ ወጋችንን በሚቀጥለው ሳምንት እመለስበታለሁ)

ከ ዘ -ሐበሻ የተወሰደ

ሕወሃት ከመለስ ጋር አብሮ ተቀብሮአል

Feb 4/2014

ይህ የያዝነው ወርሓ የካቲት “የህወሓት ልደት የትግራይ ህዝብ ልደት ነው፣ ህወሓት ብቸኛ የትግራይ ህዝብ ነፃ አውጪ ነው፣ የትግራይ ህዝብታሪክ ከደደቢት ይጀምራል፣ የህወሓት አላማና ፍላጎት የትግራይ ህዝብ አላማና ፍላጎት ነው፣ የትግራይ ህዝብ ከህወሓት ሌላ አማራጭየለውም ዙሪያው ሁሉ ገደል ወይም ጠላት ነው፣ በአጠቃላይ የትግራይ ህዝብ ህልውና ከህወሓት ህልውና ጋር የተቆራኘና ድርጅቱ ስልጣን ላይሲኖር ትግራይም የምትኖር ድርጅቱ ከጠፋ ወይም ስልጣን ላይ ከሌለ ደግሞ የትግራይ ህዝብም አብሮ የሚጠፋ ነው”……..እያሉ በመስበክበሰማእታት መቃብር ላይ ቆሞው የውሸት ድራማ የሚሰሩበት፣ በትግራይ ህዝብ ደምና አንጡራ ሃብት ላይ የሚነግዱበት፣ በድምሩ “ጆሮውንቆርጠው የሰጡት ውሻ ሥጋ የሰጡት ይመስለዋል” እንዲሉ የትግራይ ህዝብ ብሄራዊ ክብሩ፣ ዳር ድንበሩንና ብሄራዊ ጥቅሙን ለባዕድ ሽጠውሲያበቁ ነፃ አውጥተናሃል!! ልማት አምጥተንልሃል!! እያሉ የሚዘምሩበትና የሚመፃደቁበት የካቲት 11 በዓል እየመጣ ነው። ይህ ዓይነቱ ጭፍንየፕሮፓጋንዳ መርዝ ደግሞ ዛሬ የመጣ ባህል አይደለም። ህወሓት ከተፈጠረበት ቀን አንስቶ እስካሁን ድረስ ለአርባ ዓመታት ያህል ለጀሮእስከሚሰለች ድረስ በካድሬዎቹ አማካይነት ነጋ ጠባ በዚያች በተቀደሰች ምድር ትግራይ በአሁኑ በሃያ አንደኛ ክፍለ ዘመን የሚሰበክ የደደቢትየአደንቁረህ ግዛ ፍልስፍና መሆኑን ተራ የገጠር እረኛም ሳይቀር ያውቀዋል።
 
ይሁን እንጂ ህወሓት ከድርጅትነት ወደ ቡድናዊ አምባ ገነንነት፣ በኋላም ከቡድናዊ አገዛዝ ወደ ፍፁም የቤተሰባዊ መዝርፊያና የማፈኛ የግል
ኩባንያ ሆኖ ከተሸጋገረ ወዲህ እኖሆ ዓሰርቱ ዓመታት አስቆጥሯል። በመጨረሻም “ጊዜ ዳኛ ታሪክ ምስክሩ ነውና” ድርጅቱ ከባለቤቱ ከቀድሞ
ጠቅላይ ሚኒስቴር መለስ ዜናዊ ጋር አብሮ ግብኣተ መሬት ገብቷል። ላይመለስ አብሮ ተቀብሯል። አሁን ያለው “በድርቆሽ የተሞላ ህይወት
የሌለው የቆዳ ግሳንግስ ወደ(ዓርሲ)” ተለውጦ ባንድ በኩል በአቶ ስብሓት ነጋ የ80 ዓመት ጎበዝ አለቃ የሚመራ ሲሆን በሌላ በኩል ደግሞ
በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ በኤርትራውያን የሚገፋ አሮጌ ጋሪና በወታደር የሚጠበቅ የደረቀ ሬሳ ሆኖ ቀርቷል” የሚሉ ብዙዎች በሚሊዮኖች
የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያን ናቸው።

ይህ ምን ያህል እውነትነት አለው? አንድ የፓለቲካ ድርጅት ሞቷል ወይም ህይወት የለዉም ሲባልስ ምን ሲሆን ነው? ህወሓት ከበረሃ ጀግንነት
ወደ ዱር አራዊትነት የተቀየረበት ጊዜስ መቼ ነው? እውነት የጥቂት ወሮ-በላና ከሃዲ መሪዎች በረሃ የገቡበትን ቀን የታላቁ የትግራይ ህዝብ
ልደት ነውን? የትግራይ ህዝብ ከሌላው ሰማንያ ሚሊዮን የኢትዮጵያ ህዝብ ምን የተለየ ጥቅም ስላገኘ ነው የአንድ መርሲነሪ የፓለቲካ ድርጅት
ልደት የህዝቡን ብሄራዊ በዓል ተደርጎ የሚያከብረው? ለመሆኑ የትግላችን ውጤት ነው እየተባለ የሚነገርለት ሕገ መንግስት እውነት ለትግራይ
ህዝብ ይመለከተዋልን? የሚሉና ሌሎች ተዛማጅ ጥያቄዎችን እንድንመልስ ግድ ይለናል።

ወደ ዋናው የጥያቄው መልስና አርእስተ ጉዳይ ከመግባቴ በፊት ግን ለአንባቢዎቼና ለነፃ ሚዲያ ደንበኞቼ በአክብሮት የምጠይቀው በዚሁ
ፅሑፍ ዙሪያ በመቃወምም ሆነ በመደገፍ ከቂም በቀል፣ ከስሜታዊ አስተሳሰብ፣ ከጭፍን ደጋፊነት፣ በአጠቃላይ የግለ ስብእና፣ የሃሳብ ነፃነትና
ሰብኣዊ መብት በማይጋፋ መልኩ በዋናው ጉዳይ ላይ ያተኰረ ክርክር ወይም ሃሳብ ቢያቀርቡ ለመማማርና በቂ መልስ ለመስጠት ዝግጁ
መሆኔን በዚሁ አጋጣሚ ለመግለፅ እወዳለሁ። ፍርሃትን አስወግዶ የህሊና ባርነትን ሰብሮ በመውጣት የሀገርና የህዝብ ወገን ሆኖ መከራከር፣
ለሃቅ መመስከርና በፅናት መቆም ምንኛ ያኰራል!!!

በዘመነ መሳፍንት አንዲት የጎጃም አልቃሽ ““ጎጃሜ ቡዳ ነው ቡዳ ነው ስትሉ ስትሉ አላየህም ወይ ትግሬ እርስ በርስ ሲባሉ” ብላ ተናግራለች”
በማለት ከዛሬ አስራ አንድ ዓመት በፊት የህወሓት አመራር ለሁለት ተሰንጥቆ ሲፈረካከስ ያዩ አንድ አዛውንት ያለፉትን የትግራይ ባላባቶችና
መሳፍንቶች ታሪክ ከህወሓት ታሪክ ጋር በማነፃፀር እንደዋዛ አጫውተውኝ እንደነበር አስታውሳለሁ። በሌላ መልኩ ደግሞ ስለ ህዝቡ ጀግንነት፣
ጨዋነት፣ ታጋሽነትና አትንኩኝ ባይነት እያስታወሱ የዛሬው ትውልድ ግን ሐሙት የፈሰሰ እንዲሁ ወኔው ተኰላሽቶ መቅረቱ በጣም ያሳዘናቸው
መሆኑን በቁጭት ገልፀውልኛል። ነገር ግን በወቅቱ የነገሩኝን ሁሉ ብዙም ልብ አላልኩትም ነበር። በኋላ ግን ስለ ህወሓት የተፃፉ መፃሕፍቶች
በተለይም የቀድሞ የህወሓት ታጋይና አታጋይ የነበሩት አቶ አስገደ ገብረ ስላሴ የፃፉትን ጋህዲ በሚል ሶስት ተከታታይ መፃሕፍቶችን ሳነብ
“ማየት ማመን ነውና” የትግሉ ባለቤትና የድርጅቱን መስራች የነበሩት ሰዎች እንኳን ሳይቀር የመሰከሩለት ህወሓት ከተፈጠረበት ቀን ጀምሮ
እስካሁን ድረስ ተግባሩ ሲመረመር ከላይ አዛውንቱ የነገሩኝ አባባል በትክክል የሚገልፅ መሆኑን ለመረዳት ችያለሁ።

“““የህወሓት “ የህወሓት ታሪክ የርስ በርስ መላላት፣ ህዝብ ለህዝብ የማናቆርና ሀገርን የማፍረስ ታሪክ ነው” ” ” ” ቢባል ከእውነት የራቀ አይደለም። ይህን
በሚመለከት ዝርዝሩን ለታሪክ ፃፊዎች ትቼ አንድ ሁለት አብነቶችን ብቻ ልጥቀስ። ህወሓት ከትጥቁ ትግል ዘመን ጀምሮ እስካሁን ድረስ ለ40
ዓመታት ያህል የዘለቀው አንድ ገዢ መፈክር ነበረው። እሱም “ የቻለ ይሩጥ!! ያልቻለ ያዝግም!! ያበቃለት ይለይለት!!? በትግርኛ (ዝኻኣለ ይጉየ!
ዘይካኣለ ይሳለ! ዘብቀዐ ይታኣለ) የሚል ነው። ከመፈክሩም ጎን ለጎን በድርጅቱ የኪነት ቡድን የተሰራ ከአቶ መለስ መልክ ጋር የሚመሳሰል ፊት
ለፊቱ ደግሞ ጣቱን ወደ ሰዎች ቀስሮ የሚያስፈራራ ሥዕል በየስብሰባውና ታጋዮች ባሉበት ሁሉ የሚለጠፍ ነበር።

ስዕሉ በጋሃድ በአደባባይ መውጣት የጀመረው ደግሞ ልክ እነ ዶ/ር አረጋዊ በርሄና አቶ ግደይ ዘርኣፅዮን ከድርጅቱ ተለይተው ከወጡ በኋላና
“ማርክሰ ሌኒስት ሊግ ትግራይ (ማሌሊት)” ከተመሰረተ አንድ ዓመት ባልሞላ ውስጥ ነበር። ስዕሉ ያልተለመደ ነገር ስለነበረ ብዙ ታጋዮችን
በተለይም ያልተማሩ የገበሬ ልጆች የሆኑትን ታጋዮች ግራ አጋብቷል። አንዳንድ ቦታም ሌሊት በሳንጃ እየቀደዱ ይጥሉት ነበር። ከጊዜ በኋላ ግን
ስዕሉ ተለመደ። የሚገርመው ግን በወቅቱ የድርጅቱን የኪነ ጥበብ አባል ሆኖ ስዕሉን ያቀነባበረ ሳኣሊውንም ጭምር ከጥቂት ወራት በኋላ
ድርጅቱን ለቆ በመውጣት ዛሬ በስደት ዓለም በህወይት ይገኛል። ስሙን ያልጠቀስኩበት ምክንያት ደግሞ የሱ ፍቃደኝነት መጠየቅ ስላለብኝ
ነው። የመፈክሩ ዋና አላማና ስትራተጂም የሚከተሉትን ሶስት ዋና ዋና ነገሮችን ያቀፈ ነው፡- 1. አንደኛ የአቶ መለስ ዜናዊና የአቶ ስብሓት ነጋ ቡድን ተቀናቃኝ ወይሞ ሞጎደኛ ተብለው የሚጠረጠሩትን ያመራር አባላት፣ ምሁራንና የጦሩ አለቆችን (ይህችን ባቄላ ካደረች አትቆረጠምም) በማለት ቀስ በቀስ የማፅዳት ስልትና ስትራተጂ ነው። ይህንንም ሰሞኑን በኢትዮ-ሚዲያ ድሕረ ገፅ የወጣውን የነ ሙሴ፣ ዶ/ር አታክልት፣ ገሰሰው አየለን ጨምሮ ተኩሉ ሃዋዝ፣ መለስ ካሕሳይ፣ ዶ/ር አረጋዊ በርሄ፣ ግደይ ዘርኣፅዮንና ሌሎች በሽዎች የሚቆጠሩት የድርጅቱን ከፍተኛና መካከለኛ የአመራር አባላትን ያካትታል።
2. ሁለተኛው የመፈክሩ አላማና ስትራተጂ የትግራይ ብሄረተኝነትንና ብሎም የኢትዮጵያዊነት ስሜትን ከትግራይ ምድርና ከህዝቡ አስተሳሰብ
ከስረ መሰረቱ በመፋቅና በማጥፋት በምትኩ በትግራይ ብሎም በሀገራችን የኤርትራ ሻዕቢያዊ አመለካከት የበላይነት እንዲይዝ ማረጋገጥ
ነው። በዚሁ ዙሪያ በቅድሚያ የተመቱት የድሮ አስተሳሰብ፣ ሀገራዊ ስሜትና እንዲሁም በኤርትራ ጉዳይና በአገር አንድነት ጉዳይ ላይ
የከረረ አመለካከት አላቸው ተብለው የሚገመቱትን ባላባቶችንና የሀገር አዛውንቶችን ናቸው። ቀጥሎም የተመቱት የትግራይ መሁራኖች
ናቸው። በኤርትራና በሀገር ጉዳይ ዙሪያ የሚከራከሩና ጥያቄ የሚያነሱ ምሁራን እንደ ኤለክትሪክ ይፈሩዋቸው ነበር። በዚህ መሰረት
“ሽዋውያን ተጋሩ” የሚል የቅፅል ስም መለጥፍ ብቻ ሳይሆን በዘፈንም ሳይቀር ቅስማቸው እንዲሰበርና አንገታቸው እንዲደፉ ተደርጓል።
በዚህ ምክንያት የቻሉትን ከድርጅቱ ሸሽተው እንዲያመልጡ ያልቻሉት ደግሞ ለእስርና ለግድያ ተዳርጓል። በዚህ ምክንያት በሀገር
ውስጥም ሆነ በውጭ የሚኖሩ የትግራይ ምሁራን ዛሬም ስለህዝባቸውና ሀገራቸው ጉዳይ ደፍረው ጥያቄ እንዳያነሱ ፍርሃት እንደ ወባ
በሽታ በደማቸው ውስጥ ገብቶ እያዩ እንዳላዩ ዝም እንዲሉ ትልቅ ምክንያት የሆነውን ጠባሳ እስካሁን ድረስ አልሻረም።
ዛሬ በአረና ትግራይ አባላትና ደጋፊዎቻቸው እየደረሰ ያለው ዱላም ከዚሁ የተለየ አይደለም። ለአንድ የአረና አባል ከአምስት በላይ ሰላዮች
በመመደብ ኮቲያቸውን እየተከተሉ መውጫና መግቢያ ያሳጧቸዋል። ዛሬ ትግራይ ለነ ስብሓት ነጋና ሌሎች መሪዎች ታማኝ የሆኑትን
የኤርትራ ተቃዋሚ ነን የሚሉ ድርጅቶች በነፃነትና በልበ ሙሉነት የሚንቀሳቀሱባት በአንፃሩ ከህዝቡ አብራክ የተፈጠሩ ለነ አረና ትግራይና
ሌሎች ሀገር በቀል ድርጅቶች ግን በገዛ ሀገራቸው ተሸማቅቀውና በአደባባይ በዱላ እየተመቱ የሚኖሩባት ምድራዊ ሲኦል ሆና ትገኛለች።
በመሆኑም ዛሬ ሰፊው የትግራይ ህዝብ ባንድ በኩል የትግራይ ሻዕቢያ በሌላ በኩል ደግሞ የኤርትራ ሻዕቢያ አጣብቅኝ ውስጥ ገብቶ
በሁለት አለንጋ እየተገረፈ የሚገኝ ህዝብ ሆኗል። ታዲያ!! ለዘህ ሚስኪን ህዝብ አለሁልህ የሚል ወገን ማን ይሆን?
 
3. ሶስተኛው የመፈክሩ አላማና ስትራተጂ በህዝቡ የስነ ልቦናና የአካል ጥቃት በማድረስ በተለይም በትግራይ ምድር ፍርሃት፣ ሽብር፣
ጥርጣሬና ህወከት በማንገስና የህዝቡን ሁለንትናዊ አስተሳሰብ በመቆጣጠርና በማደንዘዝ ፀጥ ረጭ ብሎ እንዲገዛና ለጥቂት መሪዎች
ዘላለማዊ ስልጣን አገልጋይ ሆኖ እንዲኖር ለማድረግ ነው። በሌላ አነጋገር ትግራይ ወፍ እንኳን ዞር የማይልባት፣ ሌላው ኢትዮጵያዊ
በትግራይ ህዝብ ጉዳይ ላይ እንደማያገባው ተደርጎ መፈናፈኛ በማሳጣት በስመ ልማት እንደፈለጉ የሚግጥዋት የህወሓት የጓሮ አትክልት
ሆና እንድትኖር ለማድረግ ነው።
ልበ በሉ!! የትግራይ ህዝብ በጦርነት የደቀቀ ህዝብ ነው። ትግራይ ደርግ፣ ኢዲዩ፣ ጀብሃ፣ ሻዕቢያ፣ ኢሕአፓ፣ ህወሓትና ሌሎች ብረት
ያነገቡ ሀይሎች የሚንቀሳቀሱባት ለአስራ ሰባት ዓመታት ያህል የጦርነት አውድማ ሆና ቆይታለች። ዛሬም ህዝቡ ከጥይት ጭኾት
አልተላቀቀም። በኤርትራና በኢትዮጵያ በሁለቱም ሀገሮች ድንበር ከሩብ ሚሊዮን በላይ ሰራዊት በመሸገበትና በተፋጠጠበት የጦርነት
ደመና ስር ሆኖ ዛሬ ነገ ውጊያ ይጀመራል እያለ በፍርሃት ተውጦ የሚገኝ ህዝብ ነው። በዚህም ላይ በየጊዜው ከያሉበት በታጣቂዎች
እየታፈኑ ወደ ኤርትራ ተወስደው ደብዛቸው የማይታወቁ ንፁኃን ዜጎች ቁጥራቸው ቀላል አይደለም። በዚሁ ፍርሃት ቀያቸውንና
ቤታቸውን እየለቀቁ ወደ ዓረብ ዓለም የሚሻገሩና ወደ ማሀል ሀገር በመሸሽ የኢትዮጵያ ዋና ዋና ከተሞችን በልመና ያጥለቀለቁት የየተኛው
አካባቢ እንደሆኑ ማንም ኢትዮጵያዊ ያውቃል። እነዚህ ግጭቶችም እንደ ፓለቲካ መሳሪያና ማስፈራሪያ እየተጠቀሙ “እኛ ከሌለን ያ ሁሉ
ጠላት ይመለሳል፣ ሻዕቢያ ተመልሶ ይውጥሃል፣ ኦነግና ትምክሕተኞች ቂማቸው ይወጡቡሃል፣ የሽብርተኞች ዒላማ ትሆናለህ፣ በትግራይ
የተተከሉ ፋብሪካዎች ተነቅለው ወደ ማሃል ሀገር ይወሰዳሉ፣ በትግልህ የቀበርካቸው ጠላቶች ከመቃብር ተነስተው ይመጣሉ፣ ወዘተ እያሉ
ነጋ ጠባ ህዝቡን ማሸበርና ማደንቆር የተካኑበት ዋነኛ የአገዛዝ ጥበባቸው ሆኖ ይገኛል።
 
ወንድሞቼ ሆይ!! ታዲያ እንዲህ ዓይነቱ የቆሸሸ ታሪክ ያለው ድርጅት ዛሬ በትግራይ ህዝብና በተለይም በአረና አባላትና ደጋፊዎቻቸው ላይ
የአራዊት ስራ ቢሰራ የሚያስገርም አይደለም። ህዝብን ሁሉ ጊዜ ማታለል የማይቻል መሆኑን ያልገባቸውና ጊዜውም ጥሏቸው እየሄደ
መሆኑንም የማይቀበሉ እንደ ሾላ ፍሬ ውስጣቸው የበሰበሱ መሪዎች እስከ ህልፈተ ቀናቸው ድረስ “የደንቆ ልቅሶ መልሶ መላልሶ” እንዲሉ
ዛሬም የሚናገሩት ቋንቋና የሚሰሩት ስራ ያው በጫካ የለመዱት ዓይነት ነው። ከላይ የተጠቀሰው የመፈክራቸው አላማና ስትራተጂም
በትክክል ሲተረጎም “እምቢ ያለ ሰው ጥይት አጉርሰው” ከሚለው የደርግ ስርዓት መፈክርና ተግባር ጋር አንድ ዓይነት መሆኑን የኢትዮጵያ
ህዝብ ይስቷል ብዬ አልገምትም።
 
የሚያሳዝነውና የሚያስገርመው ነገር ግን ትግራይን የጥፋትና የመከራ ሞዴል በማድረግ የሚፈፅሙትን ጉድ እንደ ኤይድስ ወረርሽኝ በሽታ
ወደ ሌሎቹ ክፍላተ ሀገራትም እየተዛመተ መምጣቱ ነው። በዚሁ ነጥብ ዙሪያ በቀጣዩ ፅሑፌ ተመልሼ እመጣለሁ። ቸር ሰንብቱ።

በነጻነት አድማሱ
 

Two police officers arrested over abduction of Ethiopian officials

February 4, 2014
by CYRUS OMBATI
STANDARD Digital

Kenyan police officers arrested
NAIROBI, KENYA: Two Kenyan police officers were Monday arrested in connection with the abduction of two top officials of Ethiopia’s Ogaden National Liberation Front (ONLF) from outside a popular restaurant in Upper Hill, Nairobi last week

.
The officers, an inspector and a constable attached to Nairobi Area CID are expected to face charges of espionage for Ethiopia’s intelligence services.

Nairobi head of CID Nicholas Kamwende confirmed the arrests and said the officers expected in court Monday morning.

“They will face various charges following the abduction of the two ONLF officials,” said Kamwende.
He added the officers had been identified by witnesses as having participated in the abduction of Mr Sulub Ahmed and Ali Hussein who were members of the ONLF negotiation team that was in Nairobi for a proposed third round of talks.

Ahmed and Hussein were members of ONLF central committee and were abducted on January 26 from outside Arabian Cuisine in Upper Hill area.
They were later driven out of the country to Ethiopia by intelligence officials from Addis Ababa and their whereabouts are not known.

ONLF officials who asked not to be named had said security agencies from Ethiopia and Kenya were involved in the kidnapping.

They had been invited for a lunch date at the restaurant near TSC headquarters when they were abducted by men who were in three waiting cars.

One of the cars, a black Toyota Prado and the driver were seized and detained at the Turbi police station the following day but the two were missing amid speculation they had been taken across to Ethiopia.
The ONLF officials who spoke in Nairobi said the two officials were invited by the Kenyan government for peace negotiations. Their whereabouts in Ethiopia are yet to be known.

“This is not the first time that such an incident happens and we urge that the government of Kenya provides us with security. We do not know the fate of our officials but we know they were taken to Ethiopia,” said an official who asked not to be named.

Analysts say that this move may affect diplomatic negotiations between ONLF and Ethiopia brokered by Kenyan Government on 2012.

ONLF is a separatist rebel group fighting to make the region of Ogaden in eastern Ethiopia an independent state.

ONLF, established in 1984, demands for the autonomy of this region, and claimed responsibility for several attacks since the beginning of 2007 aimed at Ethiopian forces in the area, which the government considers a region under the new federal system.

ህግ እና ስርኣት ለባለስልጣናት የሚገዛበት አገር ..

Feb.4/2014
በሃገሪቱ የተፈጠሩ ስብርባሪ ህወሓት መራሽ መንግስታት የህዝቦችን የመኖር መብት ደፍጥጠዋል::
 ባለስልጣናት ለህግ እና ለስርኣት ተገዢ አለመሆናቸው ህግና ስርኣት ለእነሱ ተገዢ እንዲሆን ማድረጋቸው ጸሃይ የሞቀው ሃቅ ነው;: የህግን የበላይነት ማረጋገጥ የተሳነው ስርኣት የወለዳቸው ስብርባሪ ህወሓት መራሽ መንግስታት የህዝቦችን የመኖር መብት ደፍጥጠዋል::በሃገራችን ውስጥ ላለፉት 22 አመታት ተንሰራፍቶ ያለው የአንድ ፓርቲ ህገወጥ አገዛዝ ለህዝቦች ነጻነት የሚከፈለውን መስእዋትነት እንደ መንግስት ሳይከፍል ህዝብን በማሸበር እና በማወናበድ የህግ የበላይነትን ደፍጥጦ ለስልጣኑ ብቻ እየተራወጠ ይገኛል::በሃገሪቱ የህግ የበላይነት የተከበረ ጊዜ ስልታንህ ያበቃል የተባለ ይመስል ከበላይ ባለስልጣናት ጀምሮ እስከ በታች ካድሬዎች ድረስ የህግን የበላይነት ክደዋል:: ማንም ማንንም ማዘዝ በማይችልበት እና የተሰባበሩ ትንንሽ በንግስታት በራሳቸው ሂደት የተፈጠሩባት ኢትዮጵያ ባለስልጣናቱ መናበብ አለመቻላቸው ህዝቡ በፍትህ ላይ ተስፋ ከቆረጠ ውሎ አደረ አድሮም ኖረ::
የአንድ ሃገር ህግ የህዝብን ትኩሳት እና ጥያቄዎች ይዞ መጓዝ ሲኖርበት በሃገራችን ግን የህግ የበላይነትን የፖለቲካ ትኩሳቶች እያሽመደመዱት እንዳይከበር እና እንዲደፈጠጥ እያደረጉት ይገኛሉ:; አንድ ህዝብ ባላረቀቀው እና ባላጸደቀው ህግ ሲገዛ የህግን ትርጉም እንደማያውቅ ታሳቢ አድርጎ በህዝብ ነጻነት ላይ የሚደረጉ የፖለቲካ ጨዋታዎች እንኳን በበሰለው የኢትዮጵያ ህዝብ ላይ ይቅር እና በሌላውም ባልሰለጠነ ህዝብ ላይ ሊተገበር መድፈር ራስን እንደመናቅ ይቆጠራል:: ወያኔ ራሱ አርቅቆ እና አጽድቆ ህጎችን በማውጣት ከፈለገም በመሻር በመቀየር በመገለባበጥ በመተርጎም ህዝቦች የራሳቸውን መብት እና ነጻነት እንዳያገኙ በከፍተኛ ደረጃ መሸራረፎችን እየፈጠረ ነው::ምንሊክ ሳልሳዊ
ባለስልጣናት የወንበር ግዝፈታቸውን ተጠቅመው የተለያዩ ውሳኔዎችን ትእዛዞችን ተግባራትን በስልክ በደብዳቤ በቀላጤ ወዘተ የህግን ስርኣት ባልተከተለ መልኩ እያሽከረከሩት ከህግ የበላይነት ላይ በድንፋታና በትእቢት በመጓዝ ላይ ሲሆኑ ይህንን ያየ የበታች ካድሬ እንዲሁ ህግን እና ስራትን ባልትየከተለ መንግድ የህዝቦችን ህልውና ገደል ከቶታል:: ከበላይ ባለስልጣናት ባልተናነሰ እንዲሁም በበለጠ ማለት ይቻላል የወያኔ ካድሬዎች እና ተባባሪዎቻቸው በአገሪቱ ላይ ስርኣት አልበኝነት እና ህገወጥነት እንዲሰፍን እየሰሩ ነው::ይህ ደግሞ ህዝብ በስርኣቱ ላይ ተስፋ እንዲቆርጥ አድርጎታል::
በከፍተኛ ደረጃ ህግን እየበረዙ አድርገው በሙስና የተዘፈቁ የወያኔ ባለስልጣናት እና ደጋፊ ታዛዥ ካድሬዎቻቸው በሃገሪቱ ራሳቸው ያወጡትን ህግ ራሳቸው እየጣሱ የሚገኙ ሲሆን በራሳቸው ህግ ራሳቸው እንደሚጠየቁበት እየዘነጉ መሆኑን አለማወቃቸው ለህዝብ ያላቸውን ንቀት ያመለክታል::የምናነበው ሕጉና የምንመለከተው ተግባሩ የተለያየ ነው፡፡በሙስና ከተዘፈቁበት አንዱ የመሬት እደላ እና አሰጣጥ ነው መሬትን በተመለከተ ህጉ የሚለውን የሚከተል ባለስልጣን ማግኘት አስቸጋሪ ነው ህጉን የሚያስፈጽም ካድሬ ሹመኛም ማግኘት አይታሰብም::ይህ ማለት ደሞ ሁሉም ከመሬት እደላ ጋር በተያያዘ ህጉን ተከትለው የሚሰሩት ሳይሆን የግለሰቡ ብሄር እና የፋይናንስ አቅም ተመልክተው ይፈጽሙለታል:; ለእውነት እና ለሃገር የሚሰራ ኢንቨስተር ከአከባቢው ይነቀላል ሌባው እና ሙሰኛው ኢንቨስተር በአደባባይ በመንግስት ባለስልጣናት እንክብካቤ ይደረግለታል አፋሽ አጎንባሽ ካድሬዎችን ይበዙለታል::
የህግ የበላይነት በሃገሪቱ አለመስፈኑ ኢኮኖሚውን ከማንኮታኮቱም በላይ ባለስልታናት በዝርፊያ እና በሽሽት ላይ እንዲያተኩሩ አድርጓቸዋል::ህዝቡም ይህን ተከትሎ እንዲሁም በፖሊሶች በደህንነት አባላት በቅጥረኛ የመንግስት አሸባሪዎች በጥቂት የከተማ ወታደራዊ ኮማንዶዎች ህግ ሲጣስ እየተመለከተ ስለሆነ አንድም መንፈሱ ሲጎዳ ሌላም አለው ስርኣት ላይ አመኔታ በማጣቱ ድምጹን እንዲቋጥር አስገድዶታል::በሃገሪቱ የፍትህ አካላት ላይ የመንግስት ባለስልጣናት ጣልቃ ገብነት የፖለቲካ የበላይነት መከሰቱ ህዝቦች አንገታቸውን በፍትህ አካላት ፊት እንዲሰብሩ እንዲሸማቀቁ አድርጎታል::
በየመንግስት ተቋማት፣ ከሚኒስቴር ጀምሮ እስከ ተራ የቀበሌ ካድሬ ቢሮ ጠረጴዛ፣ በፍርድ ቤቶች እና በፍትህ አካላት ፍትሕ የተነፈጉ፣ ሕገ መንግሥትና ሥርዓት እንዲከበር የሚጠይቁና አቤት የሚሉ በርካታ መዝገቦች ሰሚ ጆሮ አጥተዋል፡፡ ለሕግና ለሥርዓት ቅድሚያ የሚሰጥ አዕምሮ፣ ጆሮና ዓይን ተነፍገዋል፡፡ ልዩ ትኩረት ሊሰጣቸው ይገባል፡፡ ምንሊክ ሳልሳዊ ሕገ መንግሥቱና ሕግ ያስገድዳሉ፡፡ቢሆንም ምንም አይነት መልስ ሲሰጣቸው ይሁን ሲገመገሙ ታይቶ አይታወቅም በተዋረድ የመንግስት አሰራር አለመኖር በስልክ እና በቀላጤ ህግ እየተጣሰ ከህዝብ በሚሰበሰብ ግብር የሚተዳደሩት ፖሊስ እና የፍትህ አካላት በግለሰቦች ትእዛዝ ህዝባዊ ሂደቶችን ሲያመክኑ ህግን ሲጥሱ ህገወጥ እርምጃዎች ሲፈጸሙ ከህግ ውጭ የህዝቦችን መብት ሲደፍሩ እየታየ መንግስት ነኝ የሚለው አካል ዝምታን መርጧል::ይህ ደግሞ የሚያመለክተው በሃገሪቱ ውስጥ ስብርባሪ ትንንሽ መንግስታት መፈጠራቸውን ነው::ባለስልጣናት ለህግ እና ለስርኣት ተገዢ አለመሆናቸው ህግና ስርኣት ለእነሱ ተገዢ እንዲሆን ማድረጋቸው ጸሃይ የሞቀው ሃቅ ነው;: እነዚህ ስርኣቱ የወለዳቸውን ባለስልጣናት እና ካድሬዎች ከኢትዮጵያ ምድር ወደ ከርሰ መቃብራቸው ከቶ ህዝብን ለነጻነት ለማብቃት በጋራ መታገል ግዴታችን መሆኑን አውቀን በአንድነት ስርኣቱን ማስወገድ ማንኛውም ሃገሬን እወዳለሁ የሚል ዜጋ ሊነሳለት እና ሊተገብረው የሚገባ መሆኑን ለማስገንዘብ እወዳለሁ::ምንሊክ ሳልሳዊ

የአማራውን ሕዝብ ክብር የደፈሩና ያዋረዱ አምባገነን ገዥዎች ለፍርድ ይቅረቡ!!!

february 3/2014

ከአንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትሕ ፓርቲ(አንድነት) የተሰጠ መግለጫ


‹‹ጉድ ሳይሰማ…›› እንደሚባለው የኢትዮጵያ ሕዝብ በስርዓቱ እየተፈፀመበት ካለው ጭቆናና በደል፤ ሰብዓዊና ዴሞክራሲያዊ መብት ገፈፋ፤ አፈናና ስደት፤ ሙስናና የመልካም አስተዳደር እጦት በተጨማሪም በአምባገነን ገዥዎች እየተዋረደ፣ በአደባባይ እየተሰደበና ሰብዓዊ ክብሩ እየተጣሰ ይገኛል፡፡ እንዳለመታደል ሆኖም ሀገራችን ላይ ያለው ስርዓት ህዝቡን የሚያዋርድ፣ ከህዝብ ጥቅም ይልቅ ስልጣኑን የሚያስቀድም፣ ለህዝብ ጆሮ የሚሰጥ አስተዋይ መሪ የሌለው ነው፡፡ ለዘመናት ያልተፈቱ ችግሮችና በመሪዎቹ የሚፈጠሩ ችግሮች ትከሻውን ያጎበጡት የኢትዮጵያ ህዝብም ስርዓቱን ከነችግሩ መሸከሙ አልበቃ ብሎ መሪ ነን በሚሉት እየተበሻቀጠና ለውርደት እየተዳረገ ይገኛል፡፡

ፓርቲያችን በትኩረት እየተከታተለው ያለውና ሰሞኑን የተለያዩ ማህበራዊ ሚዲያዎች ላይና በኢሳት ይፋ የተደረገው የአማራ ክልል ም/ ፕሬዘዳንትና የብአዴን ፅ/ቤት ኃላፊ የሆኑት አቶ አለምነው መኮንን የአማራውን ህዝብ በአደባባይ መሳደባቸውንና ማዋረዳቸውን የሚያሳዩ መረጃዎች መለቀቃቸውና የክልሉ መንግስት ለማስተባበል እንኳ ዝግጁ አለመሆኑ የሚያሳየው ንቀትንና ጥላቻን ብቻ ሳይሆን እንመራዋለን የሚሉት ህዝብ ትከሻ ላይ ተቀምጠው ፀረ ህዝብ አቋም እንደሚያራምዱ ነው፡፡ ፓርቲያችን የብአዴን/ኢህአዴግ ባለስልጣን በአማራ ህዝብ ላይ የፈፀሙትን ክብር የሚነካ አሳፋሪ ድርጊት በቸልታ ሊመለከተው እንደማይችል አስረግጦ ለመናገር ይወዳል፡፡ ፀረ ህዝብ አቋም የሚያራምዱ አምባገነኖችንም ከህዝብ ትክሻ ለማውረድ ትግሉን አጠናክሮ እንደሚቀጥል ያረጋግጣል፡፡ አንድነት በቅርቡ በጉራ ፈርዳና በቤኒሻንጉል ጉሙዝ በዜጎች ላይ የተወሰደው የማፈናቀል ተግባር ስርዓቱና የስርዓቱ መሪዎች የፈጠሩት ችግር እንጅ የአካባቢው ሕዝብ የፈጠረው እንዳልሆነ ያምናል፡፡

አቶ አለምነው መኮንን የተባሉት ባለስልጣን የአለቆቻቸውን የዘወትር አባባል በማስረገጥ እመራዋለሁ የሚሉትን የአማራ ህዝብ ‹‹ሰንፋጭ የሆነ ትምክህተኝነት የተጠናወተው፣ ትምክህተኝነቱን ያልተወ፣ በባዶ እግሩ እየሄደ መርዝ ንግግር የሚናገር ወዘተ›› ካሉ በኋላ ‹‹የትምክህት ልጋጉን ማራገፍ አለበት›› በማለት እንደሌሎች ብሄረሰቦች ሁሉ ለዚች ሀገር ደከመኝ፣ ሰለቸኝ ሳይል ዋጋ የከፈለውን የአማራ ህዝብ ዋጋ በማሳጣትና የሌሎች ጠላት አድርጎ በማቅረብ የማጥላላት ዘመቻ ከፍተዋል፡፡

ፓርቲያችንም ይህንን አሳፋሪና የዜጎችን ክብር የደፈረ የባለስልጣኑ አባባል በቸልታ የሚታይ ሆኖ አላገኘውም፡፡

ስለዚህ፡-

1. ግለሰቡ በዚህ የተዛባ አመለካከቱ ለአማራ ህዝብ መሪ ሊሆን ስለማይችል በአስቸኳይ ከፓርቲና ከመንግስት ኃላፊነቱ እንዲነሳና ለህዝቡ ይፋ እንዲደረግ፤

2. ህዝቡን ያዋረደው ባለስልጣን ላይ ርምጃ የማይወሰድ ከሆነ ግን የግለሰቡ አመለካከት የብአዴንና የክልሉ መንግስት አቋም አድርገን የምንወስድ መሆኑ እንዲታወቅ፤

3. አንድነት ፓርቲ ፀረ-ህዝብ አቋም ያለው ግለሰብ ባደረገው የህዝብ ጥላቻ ንግግር (Hate speech) ተነስቶ ለሕግ የሚያቀርብ መሆኑ እንዲታወቅ፤

4. ፓርቲያችን ህዝቡን በማስተባበር በባህርዳር ከተማ ታላቅ የተቃውሞ ሰልፍ እንደሚጠራና ድርጊቱን የማውገዝና እንዲቆም የማድረግ ርምጃ የሚወስድ መሆኑን እንገልፃለን፡፡

ስለዚህ አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ የክልሉን ህዝብ እየመራው ያለው ብአዴን/ኢህአዴግ ለህዝብ ክብር የሌለው ድርጅት መሆኑን አውቆ ከፓቲያችን ጎን በመቆም እንዲታገለው ጥሪ እናቀርባለን፡፡

ዘላለማዊ ክብር ለኢትዮጵያና ኢትዮጵያውያን!!!

አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትሕ ፓርቲ (አንድነት)

ጥር 26 ቀን 2006 ዓ.ም

አዲስ አበባ


Source :-fnotenetsanet

Monday, February 3, 2014

ሕወሃት ከመለስ ጋር አብሮ ተቀብሮአል

Feb 3/2014

ይህ የያዝነው ወርሓ የካቲት “የህወሓት ልደት የትግራይ ህዝብ ልደት ነው፣ ህወሓት ብቸኛ የትግራይ ህዝብ ነፃ አውጪ ነው፣ የትግራይ ህዝብታሪክ ከደደቢት ይጀምራል፣ የህወሓት አላማና ፍላጎት የትግራይ ህዝብ አላማና ፍላጎት ነው፣ የትግራይ ህዝብ ከህወሓት ሌላ አማራጭየለውም ዙሪያው ሁሉ ገደል ወይም ጠላት ነው፣ በአጠቃላይ የትግራይ ህዝብ ህልውና ከህወሓት ህልውና ጋር የተቆራኘና ድርጅቱ ስልጣን ላይሲኖር ትግራይም የምትኖር ድርጅቱ ከጠፋ ወይም ስልጣን ላይ ከሌለ ደግሞ የትግራይ ህዝብም አብሮ የሚጠፋ ነው”……..እያሉ በመስበክበሰማእታት መቃብር ላይ ቆሞው የውሸት ድራማ የሚሰሩበት፣ በትግራይ ህዝብ ደምና አንጡራ ሃብት ላይ የሚነግዱበት፣ በድምሩ “ጆሮውንቆርጠው የሰጡት ውሻ ሥጋ የሰጡት ይመስለዋል” እንዲሉ የትግራይ ህዝብ ብሄራዊ ክብሩ፣ ዳር ድንበሩንና ብሄራዊ ጥቅሙን ለባዕድ ሽጠውሲያበቁ ነፃ አውጥተናሃል!! ልማት አምጥተንልሃል!! እያሉ የሚዘምሩበትና የሚመፃደቁበት የካቲት 11 በዓል እየመጣ ነው። ይህ ዓይነቱ ጭፍንየፕሮፓጋንዳ መርዝ ደግሞ ዛሬ የመጣ ባህል አይደለም። ህወሓት ከተፈጠረበት ቀን አንስቶ እስካሁን ድረስ ለአርባ ዓመታት ያህል ለጀሮእስከሚሰለች ድረስ በካድሬዎቹ አማካይነት ነጋ ጠባ በዚያች በተቀደሰች ምድር ትግራይ በአሁኑ በሃያ አንደኛ ክፍለ ዘመን የሚሰበክ የደደቢትየአደንቁረህ ግዛ ፍልስፍና መሆኑን ተራ የገጠር እረኛም ሳይቀር ያውቀዋል።

ይሁን እንጂ ህወሓት ከድርጅትነት ወደ ቡድናዊ አምባ ገነንነት፣ በኋላም ከቡድናዊ አገዛዝ ወደ ፍፁም የቤተሰባዊ መዝርፊያና የማፈኛ የግል
ኩባንያ ሆኖ ከተሸጋገረ ወዲህ እኖሆ ዓሰርቱ ዓመታት አስቆጥሯል። በመጨረሻም “ጊዜ ዳኛ ታሪክ ምስክሩ ነውና” ድርጅቱ ከባለቤቱ ከቀድሞ
ጠቅላይ ሚኒስቴር መለስ ዜናዊ ጋር አብሮ ግብኣተ መሬት ገብቷል። ላይመለስ አብሮ ተቀብሯል። አሁን ያለው “በድርቆሽ የተሞላ ህይወት
የሌለው የቆዳ ግሳንግስ ወደ(ዓርሲ)” ተለውጦ ባንድ በኩል በአቶ ስብሓት ነጋ የ80 ዓመት ጎበዝ አለቃ የሚመራ ሲሆን በሌላ በኩል ደግሞ
በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ በኤርትራውያን የሚገፋ አሮጌ ጋሪና በወታደር የሚጠበቅ የደረቀ ሬሳ ሆኖ ቀርቷል” የሚሉ ብዙዎች በሚሊዮኖች
የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያን ናቸው።

ይህ ምን ያህል እውነትነት አለው? አንድ የፓለቲካ ድርጅት ሞቷል ወይም ህይወት የለዉም ሲባልስ ምን ሲሆን ነው? ህወሓት ከበረሃ ጀግንነት
ወደ ዱር አራዊትነት የተቀየረበት ጊዜስ መቼ ነው? እውነት የጥቂት ወሮ-በላና ከሃዲ መሪዎች በረሃ የገቡበትን ቀን የታላቁ የትግራይ ህዝብ
ልደት ነውን? የትግራይ ህዝብ ከሌላው ሰማንያ ሚሊዮን የኢትዮጵያ ህዝብ ምን የተለየ ጥቅም ስላገኘ ነው የአንድ መርሲነሪ የፓለቲካ ድርጅት
ልደት የህዝቡን ብሄራዊ በዓል ተደርጎ የሚያከብረው? ለመሆኑ የትግላችን ውጤት ነው እየተባለ የሚነገርለት ሕገ መንግስት እውነት ለትግራይ
ህዝብ ይመለከተዋልን? የሚሉና ሌሎች ተዛማጅ ጥያቄዎችን እንድንመልስ ግድ ይለናል።

ወደ ዋናው የጥያቄው መልስና አርእስተ ጉዳይ ከመግባቴ በፊት ግን ለአንባቢዎቼና ለነፃ ሚዲያ ደንበኞቼ በአክብሮት የምጠይቀው በዚሁ
ፅሑፍ ዙሪያ በመቃወምም ሆነ በመደገፍ ከቂም በቀል፣ ከስሜታዊ አስተሳሰብ፣ ከጭፍን ደጋፊነት፣ በአጠቃላይ የግለ ስብእና፣ የሃሳብ ነፃነትና
ሰብኣዊ መብት በማይጋፋ መልኩ በዋናው ጉዳይ ላይ ያተኰረ ክርክር ወይም ሃሳብ ቢያቀርቡ ለመማማርና በቂ መልስ ለመስጠት ዝግጁ
መሆኔን በዚሁ አጋጣሚ ለመግለፅ እወዳለሁ። ፍርሃትን አስወግዶ የህሊና ባርነትን ሰብሮ በመውጣት የሀገርና የህዝብ ወገን ሆኖ መከራከር፣
ለሃቅ መመስከርና በፅናት መቆም ምንኛ ያኰራል!!!

በዘመነ መሳፍንት አንዲት የጎጃም አልቃሽ ““ጎጃሜ ቡዳ ነው ቡዳ ነው ስትሉ ስትሉ አላየህም ወይ ትግሬ እርስ በርስ ሲባሉ” ብላ ተናግራለች”
በማለት ከዛሬ አስራ አንድ ዓመት በፊት የህወሓት አመራር ለሁለት ተሰንጥቆ ሲፈረካከስ ያዩ አንድ አዛውንት ያለፉትን የትግራይ ባላባቶችና
መሳፍንቶች ታሪክ ከህወሓት ታሪክ ጋር በማነፃፀር እንደዋዛ አጫውተውኝ እንደነበር አስታውሳለሁ። በሌላ መልኩ ደግሞ ስለ ህዝቡ ጀግንነት፣
ጨዋነት፣ ታጋሽነትና አትንኩኝ ባይነት እያስታወሱ የዛሬው ትውልድ ግን ሐሙት የፈሰሰ እንዲሁ ወኔው ተኰላሽቶ መቅረቱ በጣም ያሳዘናቸው
መሆኑን በቁጭት ገልፀውልኛል። ነገር ግን በወቅቱ የነገሩኝን ሁሉ ብዙም ልብ አላልኩትም ነበር። በኋላ ግን ስለ ህወሓት የተፃፉ መፃሕፍቶች
በተለይም የቀድሞ የህወሓት ታጋይና አታጋይ የነበሩት አቶ አስገደ ገብረ ስላሴ የፃፉትን ጋህዲ በሚል ሶስት ተከታታይ መፃሕፍቶችን ሳነብ
“ማየት ማመን ነውና” የትግሉ ባለቤትና የድርጅቱን መስራች የነበሩት ሰዎች እንኳን ሳይቀር የመሰከሩለት ህወሓት ከተፈጠረበት ቀን ጀምሮ
እስካሁን ድረስ ተግባሩ ሲመረመር ከላይ አዛውንቱ የነገሩኝ አባባል በትክክል የሚገልፅ መሆኑን ለመረዳት ችያለሁ።

“““የህወሓት “ የህወሓት ታሪክ የርስ በርስ መላላት፣ ህዝብ ለህዝብ የማናቆርና ሀገርን የማፍረስ ታሪክ ነው” ” ” ” ቢባል ከእውነት የራቀ አይደለም። ይህን
በሚመለከት ዝርዝሩን ለታሪክ ፃፊዎች ትቼ አንድ ሁለት አብነቶችን ብቻ ልጥቀስ። ህወሓት ከትጥቁ ትግል ዘመን ጀምሮ እስካሁን ድረስ ለ40
ዓመታት ያህል የዘለቀው አንድ ገዢ መፈክር ነበረው። እሱም “ የቻለ ይሩጥ!! ያልቻለ ያዝግም!! ያበቃለት ይለይለት!!? በትግርኛ (ዝኻኣለ ይጉየ!
ዘይካኣለ ይሳለ! ዘብቀዐ ይታኣለ) የሚል ነው። ከመፈክሩም ጎን ለጎን በድርጅቱ የኪነት ቡድን የተሰራ ከአቶ መለስ መልክ ጋር የሚመሳሰል ፊት
ለፊቱ ደግሞ ጣቱን ወደ ሰዎች ቀስሮ የሚያስፈራራ ሥዕል በየስብሰባውና ታጋዮች ባሉበት ሁሉ የሚለጠፍ ነበር።

ስዕሉ በጋሃድ በአደባባይ መውጣት የጀመረው ደግሞ ልክ እነ ዶ/ር አረጋዊ በርሄና አቶ ግደይ ዘርኣፅዮን ከድርጅቱ ተለይተው ከወጡ በኋላና
“ማርክሰ ሌኒስት ሊግ ትግራይ (ማሌሊት)” ከተመሰረተ አንድ ዓመት ባልሞላ ውስጥ ነበር። ስዕሉ ያልተለመደ ነገር ስለነበረ ብዙ ታጋዮችን
በተለይም ያልተማሩ የገበሬ ልጆች የሆኑትን ታጋዮች ግራ አጋብቷል። አንዳንድ ቦታም ሌሊት በሳንጃ እየቀደዱ ይጥሉት ነበር። ከጊዜ በኋላ ግን
ስዕሉ ተለመደ። የሚገርመው ግን በወቅቱ የድርጅቱን የኪነ ጥበብ አባል ሆኖ ስዕሉን ያቀነባበረ ሳኣሊውንም ጭምር ከጥቂት ወራት በኋላ
ድርጅቱን ለቆ በመውጣት ዛሬ በስደት ዓለም በህወይት ይገኛል። ስሙን ያልጠቀስኩበት ምክንያት ደግሞ የሱ ፍቃደኝነት መጠየቅ ስላለብኝ
ነው። የመፈክሩ ዋና አላማና ስትራተጂም የሚከተሉትን ሶስት ዋና ዋና ነገሮችን ያቀፈ ነው፡- 1. አንደኛ የአቶ መለስ ዜናዊና የአቶ ስብሓት ነጋ ቡድን ተቀናቃኝ ወይሞ ሞጎደኛ ተብለው የሚጠረጠሩትን ያመራር አባላት፣ ምሁራንና የጦሩ አለቆችን (ይህችን ባቄላ ካደረች አትቆረጠምም) በማለት ቀስ በቀስ የማፅዳት ስልትና ስትራተጂ ነው። ይህንንም ሰሞኑን በኢትዮ-ሚዲያ ድሕረ ገፅ የወጣውን የነ ሙሴ፣ ዶ/ር አታክልት፣ ገሰሰው አየለን ጨምሮ ተኩሉ ሃዋዝ፣ መለስ ካሕሳይ፣ ዶ/ር አረጋዊ በርሄ፣ ግደይ ዘርኣፅዮንና ሌሎች በሽዎች የሚቆጠሩት የድርጅቱን ከፍተኛና መካከለኛ የአመራር አባላትን ያካትታል።

2. ሁለተኛው የመፈክሩ አላማና ስትራተጂ የትግራይ ብሄረተኝነትንና ብሎም የኢትዮጵያዊነት ስሜትን ከትግራይ ምድርና ከህዝቡ አስተሳሰብ
ከስረ መሰረቱ በመፋቅና በማጥፋት በምትኩ በትግራይ ብሎም በሀገራችን የኤርትራ ሻዕቢያዊ አመለካከት የበላይነት እንዲይዝ ማረጋገጥ
ነው። በዚሁ ዙሪያ በቅድሚያ የተመቱት የድሮ አስተሳሰብ፣ ሀገራዊ ስሜትና እንዲሁም በኤርትራ ጉዳይና በአገር አንድነት ጉዳይ ላይ
የከረረ አመለካከት አላቸው ተብለው የሚገመቱትን ባላባቶችንና የሀገር አዛውንቶችን ናቸው። ቀጥሎም የተመቱት የትግራይ መሁራኖች
ናቸው። በኤርትራና በሀገር ጉዳይ ዙሪያ የሚከራከሩና ጥያቄ የሚያነሱ ምሁራን እንደ ኤለክትሪክ ይፈሩዋቸው ነበር። በዚህ መሰረት
“ሽዋውያን ተጋሩ” የሚል የቅፅል ስም መለጥፍ ብቻ ሳይሆን በዘፈንም ሳይቀር ቅስማቸው እንዲሰበርና አንገታቸው እንዲደፉ ተደርጓል።
በዚህ ምክንያት የቻሉትን ከድርጅቱ ሸሽተው እንዲያመልጡ ያልቻሉት ደግሞ ለእስርና ለግድያ ተዳርጓል። በዚህ ምክንያት በሀገር
ውስጥም ሆነ በውጭ የሚኖሩ የትግራይ ምሁራን ዛሬም ስለህዝባቸውና ሀገራቸው ጉዳይ ደፍረው ጥያቄ እንዳያነሱ ፍርሃት እንደ ወባ
በሽታ በደማቸው ውስጥ ገብቶ እያዩ እንዳላዩ ዝም እንዲሉ ትልቅ ምክንያት የሆነውን ጠባሳ እስካሁን ድረስ አልሻረም።

ዛሬ በአረና ትግራይ አባላትና ደጋፊዎቻቸው እየደረሰ ያለው ዱላም ከዚሁ የተለየ አይደለም። ለአንድ የአረና አባል ከአምስት በላይ ሰላዮች
በመመደብ ኮቲያቸውን እየተከተሉ መውጫና መግቢያ ያሳጧቸዋል። ዛሬ ትግራይ ለነ ስብሓት ነጋና ሌሎች መሪዎች ታማኝ የሆኑትን
የኤርትራ ተቃዋሚ ነን የሚሉ ድርጅቶች በነፃነትና በልበ ሙሉነት የሚንቀሳቀሱባት በአንፃሩ ከህዝቡ አብራክ የተፈጠሩ ለነ አረና ትግራይና
ሌሎች ሀገር በቀል ድርጅቶች ግን በገዛ ሀገራቸው ተሸማቅቀውና በአደባባይ በዱላ እየተመቱ የሚኖሩባት ምድራዊ ሲኦል ሆና ትገኛለች።
በመሆኑም ዛሬ ሰፊው የትግራይ ህዝብ ባንድ በኩል የትግራይ ሻዕቢያ በሌላ በኩል ደግሞ የኤርትራ ሻዕቢያ አጣብቅኝ ውስጥ ገብቶ
በሁለት አለንጋ እየተገረፈ የሚገኝ ህዝብ ሆኗል። ታዲያ!! ለዘህ ሚስኪን ህዝብ አለሁልህ የሚል ወገን ማን ይሆን?

3. ሶስተኛው የመፈክሩ አላማና ስትራተጂ በህዝቡ የስነ ልቦናና የአካል ጥቃት በማድረስ በተለይም በትግራይ ምድር ፍርሃት፣ ሽብር፣
ጥርጣሬና ህወከት በማንገስና የህዝቡን ሁለንትናዊ አስተሳሰብ በመቆጣጠርና በማደንዘዝ ፀጥ ረጭ ብሎ እንዲገዛና ለጥቂት መሪዎች
ዘላለማዊ ስልጣን አገልጋይ ሆኖ እንዲኖር ለማድረግ ነው። በሌላ አነጋገር ትግራይ ወፍ እንኳን ዞር የማይልባት፣ ሌላው ኢትዮጵያዊ
በትግራይ ህዝብ ጉዳይ ላይ እንደማያገባው ተደርጎ መፈናፈኛ በማሳጣት በስመ ልማት እንደፈለጉ የሚግጥዋት የህወሓት የጓሮ አትክልት
ሆና እንድትኖር ለማድረግ ነው።

ልበ በሉ!! የትግራይ ህዝብ በጦርነት የደቀቀ ህዝብ ነው። ትግራይ ደርግ፣ ኢዲዩ፣ ጀብሃ፣ ሻዕቢያ፣ ኢሕአፓ፣ ህወሓትና ሌሎች ብረት
ያነገቡ ሀይሎች የሚንቀሳቀሱባት ለአስራ ሰባት ዓመታት ያህል የጦርነት አውድማ ሆና ቆይታለች። ዛሬም ህዝቡ ከጥይት ጭኾት
አልተላቀቀም። በኤርትራና በኢትዮጵያ በሁለቱም ሀገሮች ድንበር ከሩብ ሚሊዮን በላይ ሰራዊት በመሸገበትና በተፋጠጠበት የጦርነት
ደመና ስር ሆኖ ዛሬ ነገ ውጊያ ይጀመራል እያለ በፍርሃት ተውጦ የሚገኝ ህዝብ ነው። በዚህም ላይ በየጊዜው ከያሉበት በታጣቂዎች
እየታፈኑ ወደ ኤርትራ ተወስደው ደብዛቸው የማይታወቁ ንፁኃን ዜጎች ቁጥራቸው ቀላል አይደለም። በዚሁ ፍርሃት ቀያቸውንና
ቤታቸውን እየለቀቁ ወደ ዓረብ ዓለም የሚሻገሩና ወደ ማሀል ሀገር በመሸሽ የኢትዮጵያ ዋና ዋና ከተሞችን በልመና ያጥለቀለቁት የየተኛው
አካባቢ እንደሆኑ ማንም ኢትዮጵያዊ ያውቃል። እነዚህ ግጭቶችም እንደ ፓለቲካ መሳሪያና ማስፈራሪያ እየተጠቀሙ “እኛ ከሌለን ያ ሁሉ
ጠላት ይመለሳል፣ ሻዕቢያ ተመልሶ ይውጥሃል፣ ኦነግና ትምክሕተኞች ቂማቸው ይወጡቡሃል፣ የሽብርተኞች ዒላማ ትሆናለህ፣ በትግራይ
የተተከሉ ፋብሪካዎች ተነቅለው ወደ ማሃል ሀገር ይወሰዳሉ፣ በትግልህ የቀበርካቸው ጠላቶች ከመቃብር ተነስተው ይመጣሉ፣ ወዘተ እያሉ
ነጋ ጠባ ህዝቡን ማሸበርና ማደንቆር የተካኑበት ዋነኛ የአገዛዝ ጥበባቸው ሆኖ ይገኛል።

ወንድሞቼ ሆይ!! ታዲያ እንዲህ ዓይነቱ የቆሸሸ ታሪክ ያለው ድርጅት ዛሬ በትግራይ ህዝብና በተለይም በአረና አባላትና ደጋፊዎቻቸው ላይ
የአራዊት ስራ ቢሰራ የሚያስገርም አይደለም። ህዝብን ሁሉ ጊዜ ማታለል የማይቻል መሆኑን ያልገባቸውና ጊዜውም ጥሏቸው እየሄደ
መሆኑንም የማይቀበሉ እንደ ሾላ ፍሬ ውስጣቸው የበሰበሱ መሪዎች እስከ ህልፈተ ቀናቸው ድረስ “የደንቆ ልቅሶ መልሶ መላልሶ” እንዲሉ
ዛሬም የሚናገሩት ቋንቋና የሚሰሩት ስራ ያው በጫካ የለመዱት ዓይነት ነው። ከላይ የተጠቀሰው የመፈክራቸው አላማና ስትራተጂም
በትክክል ሲተረጎም “እምቢ ያለ ሰው ጥይት አጉርሰው” ከሚለው የደርግ ስርዓት መፈክርና ተግባር ጋር አንድ ዓይነት መሆኑን የኢትዮጵያ
ህዝብ ይስቷል ብዬ አልገምትም።

የሚያሳዝነውና የሚያስገርመው ነገር ግን ትግራይን የጥፋትና የመከራ ሞዴል በማድረግ የሚፈፅሙትን ጉድ እንደ ኤይድስ ወረርሽኝ በሽታ
ወደ ሌሎቹ ክፍላተ ሀገራትም እየተዛመተ መምጣቱ ነው። በዚሁ ነጥብ ዙሪያ በቀጣዩ ፅሑፌ ተመልሼ እመጣለሁ። ቸር ሰንብቱ።

በርካታ የአዲስ አበባ ቤት ተመዝጋቢዎች ገንዘባቸውን ከባንክ እያወጡ ነው

Feb.3/2014

ጥር ፳፮ (ሃያ ስድት) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ከውስጥ አዋቂ ምንጮች ለማዎቅ እንደተቻለው የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በአዲስ አበባ ከተማ ውስጥ የሚታየውን የመኖሪያ ቤቶች ችግር በዘላቂነት ለማቃለል በሚል ከዚህ በፊት ከነበረው የ 20/80 የጋራ መኖሪያ ቤት ልማት ፕሮግራም በተጨማሪ በአማራጭ የ 10/90 አነስተኛ ገቢ ላላቸው የህብረተሰብ ክፍሎች እና ለመለስተኛና መካከለኛ ገቢ ላላቸው በ40/60 የቁጠባ ቤት ፕሮግራም መቅረጹን ተከትሎ እስከ አንድ ሚሊዮን የሚጠጋ ህዝብ ተመዝግቦ ነበር።

ይሁን እንጅ በአሁኑ ወቅት እጅግ በርካታ ቁጥር ያላቸው የተለያዩ የቤት ልማት ፕሮግራም ተሳታፊ ዜጎች ከፕሮግራሙ እየወጡ መሆኑ ታውቋል። ይህን ዜና እስካጠናከርንበት ጊዜ ድረስ ከ30 ሺ በላይ የሚሆኑ ነዋሪዎች ገንዘባቸውን ከባንክ አውጥተዋል።

ባንክ ቤቶች ከዚህ በፊት ለምዝገባ ስራ ሲጨናነቁ ከነበረው ባልተናነሰ በአሁኑ ጊዜ በከፍተኛ የስራ ጫና ውስጥ እንዳሉና ለዚህ አገልግሎት ብቻ አንድ መስኮት ለመልቀቅ እንደተገደዱ የደረሰን መረጃ ያመለክታል።

የ20 /80፣ የ10/90 እና የ40/60 ቤቶችን ለመገንባት ከገንዘብ እጥረት በተጨማሪ የቦታ እጥረት ማጋጠሙን ኢሳት የውስጥ መረጃዎችን በማሰባሰብ መዘገቡ ይታወሳል። በተለይም የኦሮሚያ ክልል በአዲስ አበባ ዙሪያ ያሉ ከተሞችን በአዲስ አበባ ታላቁ ካርታ ውስጥ ለማስገባት ፈቃደኛ ሆኖ ባለመገኘቱ የፕሮጀክቱ ተፈጻሚነት አደጋ ውስጥ ወድቋል።
መንግስት ወደ 10 ቢሊዮን ብር የሚጠጋ ገንዘብ ከባንክ በመበደር ቤቶችን ለመስራት ቢያስብም፣ ንግድ ባንክ በርካታ የብድር አገልግሎቶችን በመሰረዝ ለማግኘት የቻለው 6 ቢሊዮን ብር ነው። መንግስት በተለይ 40 በ60ን ተግባራዊ ለማድረግ ያወጣው እቅድ ቅጅው ለኢሳት ደርሶአል። በዚህ እስካሁን ይፋ ባልተደረገው እቅድ የቤቶች ዋጋ ቀድሞ ከተያዘለት በእጥፍ ጨምሮ በግል ከሚሰሩ ቤቶችም ጋር ሲነጻጸር እጅግ ውድ ሆኖ ተግኝቷል።

በነአቡበከር መሀመድ የክስ መዝገብ የመከላከያ ማስረጃ ለመከታተል የተያዘው ቀጠሮ ወደ መጋቢት 20 ተሸጋገረ።

Feb 3/2014
18 ተከሳሾች ያሉበት ይህ መዝገብ ዛሬ በፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት 4ኛ የወንጀል ችሎት ቃሊቲ ነበር ሊታይ ቀጠሮ ተይዞ የነበረው።ተከሳሾቹ በጠበቆቻቸው አማካኝነት ከ400 በላይ የሚሆኑ የመከላከያ ማስረጃዎችን ማዘጋጀታቸውን አስታውቀዋል።
ከሳሽ የፌደራል አቃቢህግ አቀራረባቸውን አስመልክቶ ለፍርድ ቤቱ ተቃውሞ ያቀረበ ሲሆን ፥ ማን ለማን እንደሚመሰክር እና ጭብጡን እንዲያቀርቡ ጠይቋል።ግራ ቀኙን የመረመረው ፍርድ ቤቱ የአቃቢህግን አቤቱታ በመቀበል ጭብጥ አስይዙ ብሎ ሲበይን ፥ የተከሳሽ ጠበቆች ይህን ለማድረግ የአንድ ወር ጊዜ ጠይቀዋል።ችሎቱ የራሱን የጊዜ ሰሌዳ ከግምት ውስጥ በማስገባት ፥ በብይኑ መሰረት መዝገቡን ለመመልከት ለመጋቢት 20 2006 ዓ.ም ተለዋጭ ቀጠሮ ይዟል።