Sunday, December 22, 2013

ሻምበል ፍቅረሥላሴ ወግደረስ ጻፉ ክንፉ አሰፋ

December 22/2013


ፀሃይ አሳታሚ ድርጅት በታኅሣሥ 16, 2006 ዓ/ም (Dec. 25, 2013) የቀድሞ የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር የነበሩትን የሻምበል ፍቅረሥላሴ ወግደረስን ‘እኛና አብዮቱ’ የሚል
መጽሃፍ ለገበያ እንደሚያበቃ አስታወቀ። ሻምበል ፍቅረሥላሴ እንደ ደርግ አባልነታቸው በጋራ ያመኑበትን፣ የተማከሩትን፣ የወሰኑትን፣ የሰሩትን፣ የገጠማቸውንና በቅርብ በዓይን ምስክርነት ያዩትን ተንትነው በ‘እኛና አብዮቱ’ ያስነብቡናል። የራሳቸውን ዕይታ ያካፍሉናል።
9781599070780-Perfect.indd
ልጅ ሆነን አንድ አባባል እሰማ ነበር።"አበላል እንደ ደርግ አባል። አለባበስ እንደ ፍቅረሥላሴ ወግደረስ!" - የሚል። በተለይ በኔ ትውልድ ያለን ሰዎች፣ ከዚህ ውጭ ስለኝህ ሰው የምናውቀው ብዙም ነገር አልነበረም። ግና እኝህ ሰው በልባቸው መክሊት ለአመታት የቋጠሩትን መረጃ ጀባ ሲሉን፤”... አጻጻፍም እንደ ፍቅረሥላሴ ወግደረስ" የሚያሰኝ ሆኖ አገኘሁት።
ሻምበል ፍቅረሥላሴ ወግደረስ ለአስራ አምስት ዓመታት አብዮቱን ሲመሩ ቆይተው ወደ መጨረሻው ከሥልጣን በጡረታ ስም እንዲሰናበቱ ተደርገዋል። ደርግን በጣለው በወያኔ
መንግሥትም ለ፳ ዓመታት ታስረው፣ የሞት ፍርድ የተበየነባቸውና በመጨረሻ ፍርዱ ወደ ዕድሜ ልክ ተዛውሮላቸው ከእሥር ቤት በአመክሮ የወጡ ግለሰብ ናቸው።
ጸሃፊው በድራማ መልክ በመጽሃፋቸው ካሰፈሩዋቸው እውነታዎችና ግለ-ሂሶች ውስጥ አንዳንዶቹን ለአንባቢያን ማካፈሉ አይከፋም። ደርጎች መፈንቅለ መንግስት አድርገው ሲያበቁ ቀዳማዊ ሃይለስላሴ ዘንድ ቀርበው ከንጉሱ የገጠማቸውን አስገራሚ ምላሽ ሻምበል ፍቅረሥላሴ ወግደረስ በመጽሃፋቸው እንዲህ ሲሉ አስፍረዋል።
የፖለቲካ እሥረኞች በሙሉ እንዲፊቱ የሚለው ጥያቄ እንደተነበበ ንጉሡ ጣልቃ ገብተው “ለመሆኑ የፖለቲካ እሥረኞቹ እነማን ናቸው?” የሚል ጥያቄ አቀረቡ። “በእርግጥ የምናውቃቸው የፖለቲካ እሥረኞች ባይኖሩም ማንኛውም የፖለቲካ እሥረኛ እንዲፈታ ነው የምንጠይቀው” አሉ ሻለቃ ተስፋዬ ገብረኪዳን። ንጉሡ ራሳቸውን ነቅነቅ አድርገው ጽሑፉን የሚያነበውን የደርግ አባል እየተመለከቱ “አልገባችሁም!” ብለው ዝም አሉ። በእርግጥም አልገባንም። ተማሪዎችና የተለየ ዓላማ የነበራቸው የተማሩ ሰዎች የሰነዘሩትን መፈክር ብቻ ነበር ይዘን ንጉሡ ፊት የቀረብነው። በፖለቲካ እሥረኝነት ስም በከፍተኛ ደረጃ ለጣሊያን ወራሪ መንግሥት በባንዳነት አድረው አገራችንን የወጉ፣ ለቅኝ ተገዥነትም የዳረጉትን እንደ ኃይለሥላሴ ጉግሳ ያሉ ወንጀለኞች የፖለቲካ እሥረኞች ተብለው ከግዞትና ከእሥር ቤት አስወጥተን እንደ ጀግና ራሳቸውን እንዲቆጥሩ አደረግናቸው።
የነ ጄነራል ተፈሪ በንቲ ጉዳይን አስመልክቶ የሰፈረው ታሪክ ደግሞ እንዲህ ይነበባል። “በሊቀመንበርነት ስብሰባውን የሚመሩት ጄነራል ተፈሪ 'የቋሚ ኮሚቴው'በዛሬው ቀን የሚወያይበትን ጉዳይ አስመልክቶ የመቶ አለቃ ዓለማየሁ የደርጉ ዋና ፀሐፊ ይገልጽልናል' ብለው ስብሰባው መጀመሩን ካበሰሩ በኋላ ዓለማየሁ በአጀንዳው ላይ አጭር ገለጣ ማድረግ ሲጀምር ስልክ ተደወለ። ስልኩ ሌ/ኮሎኔል መንግሥቱ አጠገብ ስለነበር ወዲያው ቅጭል እንዳለ መነጋገሪያውን በማንሳት ሃሎ አሉ።
ከሌላው ጫፍ ማን እንደደወለ አላወቀንም። በኋላ እንደታወቀው ሌ/ኮሎኔል ዳንኤል ነበር የደወለው።
ምን እንደተነጋገሩ አልተሰማም። ሌ/ኮሎኔል መንግሥቱ ብቻ “እሺ እሺ” ብለው ስልኩን ዘጉት። ስልኩን እንደዘጉ “ይቅርታ ስልኩ የተደወለው ከጎንደር ነው። ጎንደር ውስጥ ችግር አለ። እናንተ ቀጥሉ” ብለው ከጀርባቸው ባለው በር በኩል ውልቅ አሉ። በዚህን ጊዜ ዓለማየሁና ሞገስ ጥርጣሬ የገባቸው መሰለ።
ዓለማየሁ ንግግሩን አቋርጦ በመስኮት በኩል ውጭ ውጭዉን መመልከት ጀመረ። ዓይኖቹ አላርፍ አሉ። ግራና ቀኝ ይመለከታል። አጠገቡ ያሉትን ሰዎች ሁሉ በጥርጣሬ ተመለከተ። ሻምበል ሞገስም በር በሩን ይመለከታል። ከአሁን አሁን አንድ ችግር ይከሰታል የሚል ፍርሃት ያደረበት ይመስላል። ሁሉም የኢሕአፓ አባላትና ደጋፊዎች ፈርተዋል። እንደፈሩት አልቀረም ሌ/ኮሎኔል መንግሥቱ ከወጡ ሁለት ደቂቃ እንኳን አልሞላም ከበስተጀርባ ባለው ኮሪደር የወታደሮችን እርምጃ ሰማን። ወታደሮች ሲንቀሳቀሱ በፊት ለፊታችን ባሉት መስኮቶች በኩል ተመለከትን። በዚህን ጊዜ ፍስሐ ደስታ “ተከብበናል” አለ። ወዲያው ሁለቱም በሮች በኃይል ተበረገዱ። ሁላችንም ደነገጥን፣ ቀልባችን ተገፈፈ፣ እጢአችንም የወደቀ መሰለን። ድርቅ ብለን በተቀመጥንበት ቀረን።...
ሻምበል ፍቅረሥላሴ ወግደረስ ሰለ ልጅ ሚካኤልን አስተዋይነት ሲያስታውሱ እንዲህ የሚል ግለሂስም ያስነብቡናል። እኛ በችኮላ ውሳኔ መስጠታችን፣ ሕዝቡን በደንብ አለማወቃችን፣ ሰፊ የሕዝብ አመራር ልምድ ማጣታችን፣ የአገርና የውጭውን ፖለቲካ ውስብሰባዊ ግንኙነት አለመገንዘባችን፣ የመንግሥትን አሠራር ደንብና ሥርዓት አለመረዳታችን፣ የፖለቲካና ኢኮኖሚ ጥመርታዊ ግንኙነትን መመልከት አለመቻላችን፣ የተለያየ ገንቢም ሆነ አፍራሽ ተልዕኮ ያላቸው ኃይሎች ተጽዕኖ እንደሚያሳድሩብ ያለማጤናችን፣ በየዋህነትና በቅንነት ብቻ እንደምንሠራ በመገንዘባቸው ሊሆን ይችላል ልጅ ሚካኤል ከእኛ ጋር መቆየት የሚችሉት ለአጭር ጊዜ ብቻ እንደሚሆን የጠቆሙት...
በወቅቱ ስለ ህዝቡ የእርስ በርስ መጨካከንና መወነጃጀል ባሰፈሩት ክፍል ውስጥ እንዲህ የሚል ታሪክ እናገኛለን።
..የሥራ ዕድገት የተከለከለ፣ በሌብነትም ሆነ በስካር ወይም በሌላ ጥፋት የተቀጣ፣ በግል ጉዳይም ሆነ በመንግሥት ሥራ ከአለቃው ጋር የተጣላ፣ በአጋጣሚው ተጠቅሞ አዲስ ሹመት ወይንም ዕድገት
ለማግኘት የሚፈልግ ሁሉ ጠቋሚ፣ ወንጃይ፣ ከሳሽ፣ ተበዳይ ነው። የተወሰነ ጥቅም ለማግኘት ወይም ሌላውን ለመጉዳት ብለው “ኢትዮጵያ ትቅደምን ይቃወማል፣ ከታሠሩት ባለሥልጣናት ወይም ሚኒስትሮች የቅርብ ዝምድና አለው። ስለሆነም ሥራ ይበድላል፣ ሠራተኛውን ያጉላላል፣ ውሳኔ አይሰጥም” በማለት አለቆቻቸውን የሚከሱ፣ የሚወነጅሉ በርካታ ናቸው። ለደርግ አባላት ቤታቸው ድረስ በመሄድ በማስረጃ የተደገፈ ቢሆንም ባይሆንም ተቆርቋሪ በመምሰል የክስ ማመልከቻ የሚያቀርቡም ነበሩ። እንታሠራለን ብለው በፍርሃት
የተደበቁ ባለሥልጣናትን የቅርብ ዘመዶቻቸው ወይም አሽከሮቻቸው ወይም ጎረቤቶቻቸው ደርግ ጽሕፈት ቤት ድረስ በመምጣት ያጋልጧቸው ነበር። የመሥሪያ ቤቶችን ሰነዶች ፎቶ ኮፒ በማድረግ ወይም ሰነዱን እንዳለ ከፋይሉ አውጥተው በማቅረብ “በመንግሥት ንብረት፣ ሀብት ወይንም ገንዘብ ላይ አላግባብ ተወስኗል” ብለው ጥቆማና መረጃ የሚያቀርቡም ነበሩ።
ሠራተኞች አሠሪዎቻቸውን ይከሳሉ፣ ይወነጅላሉ። ገበሬዎች ለዘመናት በደል አደረሱብን የሚሏቸውን የአካባቢ ባለሥልጣናት ይወነጅላሉ። ውንጀላው በርካታ ነው።
አሽከሮች፣ ዘበኞች፣ ገረዶች... መረጃ ይሰጣሉ፣ ይጠቁማሉ። የተደበቀ የጦር መሣሪያ፣ የተደበቀ ገንዘብ፣ ወደሌላ ቦታ የተወሰደ ወይም የሸሸ ሀብት እንዳለም የሚጠቁሙን እነሱ ናቸው።
በአንድ ቦታ በርከት ያሉ ሰዎች ተሰብስበው ምሽት ከአሳላፉ “ሲያድሙ ነበር” ብለው ከነስም ዝርዝራቸው መረጃውን ደርግ ጽሕፈት ቤት ድረስ ያመጣሉ። “እኛ እስከዛሬ የበይ ተመልካች ነበርን ዛሬ ዕድሜ ለእናንተ እንጀራ ሊወጣልን ነው! ከእናንተ ጎን ተሰልፈን አቆርቋዦቹን እንታገላለን! በማንኛውም ጊዜ ትዕዛዝ ብትሰጡን ለመፈጸም ዝግጁ ነን!” እያሉ ታማኝነታቸውንና ተባባሪነታቸውን የሚገልጡም ብዙዎች ነበሩ። በጣም የሚያስደንቀው አባቶቻቸውን፣ ልጆቻቸውን፣ ወንድሞቻቸውን፣ እህቶቻቸውን፣ ባሎቻቸውን፣ ሚስቶቻቸውን በመክሰስ፣ በመወንጀል፣ በማጋለጥ፣ በመጠቆም ብሎም በማሳሰር ጉዳት ያደረሱ በርካቶች መሆናቸው ነው።
እንግዲህ ስለ አዲሱ ‘እኛና አብዮቱ’ መጽሃፍ ይህንን ካልኩ ቀሪውን ለአንባቢ መተው ይበጃል። ሁሉም ሰው መጽሃፉን አንብቦ የራሱን ፍርድ ይስጥ።
ህይወት በሩጫ ትመሰላለች። የተፈጥሮ ህግጋት ነውና የሰው ልጅ እስትንፋሱ እስኪቋረጥ ይሮጣል። ከዚያም ሩጫውን ይጨርሳል። ሩጫውን ሳይጨርስ በልቡ ቋጥኝ የያዘውን እምቅ ቋጠሮ የሚተነፍስ ደግሞ እድለኛ ነው። በአንጻሩ ደግሞ በአእምሮው የቋጠረውን የእውቀት ምስጢር ሳያካፍል የሚያልፍ ሁሉ ያሳዝናል።
ያለውን የወረወረ ንፉግ አይደለምና መንቀፍም ካለብን የሚወረውረውን ሳይሆን የማይወረውረውን ነው። መተቸት ካለብነም ሃሳቡን እንጂ ግለሰቡን ባይሆን ይመረጣል። በሃሳብ ላይ መወያየትና መተሻሸት ደግሞ አዋቂነት ነው።
በመጨረሻም የመጽሃፉ አርታኢ ኤልያስ ወንድሙ በመግቢያው ላይ ባሰፈረው መልእክት ጽሁፌን ልቋጭ። የተማረ፣ ያወቀና ያደገ ትውልድና ዜጋ ምልክቱ የተጻፈን ማንበቡ፣ ያነበበውን ማብላላቱና ካነበበው ውስጥ ስንዴውን ከእንክርዳዱ መለየቱ ሲሆን፤ እራሱም አስተውሎና አገናዝቦ መጻፉ ደግሞ መማሩን ብቻ ሳይሆን መመራመሩንና ማወቁን የሚያሳይ ታላቅ ተግባር ነው። ለዚህም ደግሞ ግላዊ ነጻነት ያስፈልገዋልና ጫንቃው ላይ ያሉትን ግላዊና ታሪካዊ ቀንበሮች የሰበረ ነጻ ሰው መሆን ይጠበቅበታል። ትምህርትና ዕውቀት አስተዋይነትንና ጥልቀትን ከራስ በላይ ለትውልድ አሳቢነትን የሚያመለክት ታላቅ ኃላፊነት ነው። ለዚህም እንደ ትናንቱ ‘የተማረ ይግደለን’ ሳይሆን፤ የተማረ ያስተምረን፣ ያስተዳድረን ብሎም ይምራን በምንልበት ዘመን ከምናነብበው ውስጥ ያልተስማማንበትን በጨዋነት የመቃወም፣ የፈቀድነውን እንደ ስሜታችን የመደገፍና ተሳሳተ የምንለውን ለእርማት መጠቆም ግላዊ መብታችን
ነው።...
* ፀሃይ አሳታሚ ድርጅት ከዚህ በፊት የቀድሞው የኢትዮጵያ ፕሬዝዳንት ኮሎኔል መንግስቱ ኃይለማርያምን፣ የቀድሞውን የህወሃት መሪ ዶ/ር አረጋዊ በርሄን፣ የቀድሞውን የኢህአፓን አመራር አባል የዶ/ር መላኩ ገኝን፣ የቀድሞው ሚንስትር የአቶ ተካልኝ ገዳሙን መጽሃፍትና ከስልሳ በላይ የሆኑ በኢትዮጵያ ታሪክና ጥናት ላይ ያተኮሩ መጽሃፍትን ማሳታሙ ይታወሳል። ‘እኛና አብዮቱ’ የሚለው ይህ አዲስ መጽሃፍ በwww.tsehaipublishers.com ድረገጽና በቀርቡ በየሱቁ አንደሚገኝ ከሎስ አንጀነሰ
የደረሰን ዘገባ አስታውቋል። ሁላችንም ገዘተን እናንብብ።
መጽሃፉን አንብቤ እንደጨረስኩ በሂሳዊ ግምገማ እመለስበታለሁ።  መጸሃፉን ለማግኘት ይህንን ይጫኑ

በጋዜጠኛርዕዮት አለሙ ጉዳይ… የፍርድ ብይኑ ለዳኛው በጽሁፍ እንደተሰጠው ተጋለጠ!!

December 22/2013

EMF=ርዕዮት አለሙ ጋዜጠኛ ናት። ሆኖም የኢህአዴግ ስርአት ወጣቷን ጋዜጠኛ “አሸባሪ” በማለት ክስ ከመሰረቱባት በኋላ፤ የ14 አመት እስራት ፈርደውባታል። ይህ ብይን እንደተሰጠ… የፖለቲካ ውሳኔ እንጂ የዳኞች ውሳኔ እንዳልሆነ ውስጥ ውስጡን ሲወራ ነበር። ይህ ወሬ እውነት መሆኑን የሚያረጋግጡ መረጃዎች እየተገኙ መሆናቸውን በተለይ የቤተሰብ ምንጮች ገልጸዋል።

qqየጋዜጠኛ ርዕዮት አለሙ ታናሽ እህት እንዳሳወቀችው ከሆነ፡ “በዚህ ሂደት ያገኘኋቸው ሁለት ማስረጃዎች አሉ፡፡ አንደኛው በዳኛው የተነበበው የጥፋተኝነት ውሳኔ የእጅ ጽሁፍ ሲሆን ሁለተኛው የዳኛው የእጅ ጽሁፍ ናቸው፡፡ እነዚህ ሁለት ማስረጃዎች በእርግጥም የጥፋተኝነት ውሳኔው በዳኛው እንዳልተጻፈ የሚያረጋግጡ ሆነው አግኝቻቸዋለሁ” ብላለች።

አሁን ብዙዎችን እያነጋገረ ያለው፤ “ከችሎቱ ጀርባ ያለው ድብቅ ዳኛ ማነው?” የሚለው ይሆናል። ይህ በ’ጅ ጽሁፍ ተጽፎ የተሰጠ ብይን የማን እጅ ጽሁፍ ይሆን? ጋዜጠኛ ርዕዮት አለሙ ላይ ብይን በተሰጠበት ወቅት፤ አቶ መለስ በህይወት ነበሩ… የሳቸው ይሆን? ወይንስ የሽመልስ ከማል እጅ ጽሁፍ ነው?

ህዝቡ በዚህ ጉዳይ የራሱን ትዝብት እንዲወስድ፤ በተለይም የፍርድ ውሳኔው ጸሃፊው ማን እንደነበር ለማወቅ ይህ ደብዳቤ ይፋ ይሆናል። ይህ መረጃ ለህዝብ ይፋ የሚሆነው ጋዜጠኛ ርዕዮት የታሰረችበት 30ኛ ወር በታስቦ በሚልበት፤ ታህሳስ 14 2006 ዓ.ም መሆኑ ታውቋል

የአቦይ ስብሀት ነገር!

December 22/2013
ከአሁን በፊት በዚሁ ርዕስ ፅሁፍ እንደፃፍኩ አስታውሳለሁ . አጋጣሚ ሆኖ ዛሬም ይህን ፅሁፍ ለመፃፍ በምነሳበት ወቅት ከዚሁ ርዕስ ሌላ ሀሳቤን በአንድነት ጭምቅ አድርጎ ሊገልፅልኝ የሚችል ርዕስ ሊመጣልኝ ስላልቻለ እንደገና በዚሁ ርዕስ መጠቀሙን ወደድኩ አባይ ስብሀት በልበወለድ ዓለም የተፈጠሩ ሰው *ቢሆኑ ኖሮ እጅግ በጣም አጨቃቃጪ , አነጋጋሪና የተለየ ስብዕና ያላቸው ገፀ ባህርይ ሆነው የተቀረፁ እጅግ በጣም የተዋጣለት ገፀ ባህርይ ይሆኑ ነበር . የሚገርመው ነገር በእውኑ ዓለም ያሉ ሰው ሆኖው ሳለ እንዲህ ዐይነት አነጋጋረና ግራ አጋቢ የሆነ ገፀ ባህርይ ያላችው ሰው መሆናቸው ነው .:: ለዚህ ሳይሆን አይቀርም ብዙውን ጊዜ በሚናገሩት ነገር ሁሉ ትኩረት ሳቢ ሆነው የምናገኛቸው . ለዛሬ ባለፈው በህዳር 17 ቀን 2006 ዓ.ም. በአዲስ አባባ ዩኒቨርሲቲ የጋዜጠኝነትና ኮሙኒኬሽን ዲፓርትመንት ተጋብዘው በተናገሩት ላይ ይሆናል ትኩረት የማደርግው . አቦይ ስብሀት በዩኒርሰቲው ተገኝተው ፖለቲካዊ ሀሳባቸውን ለተማሪዎች እንደሚያካፍሉ ዜናውን እንደሰማሁ ደግሞ ምን ሊሉ ይሆን ብዬ ነበር ከተወሰኑ ጓደኞቼ ጋር በመሆን እዚያ የተገኘሁት . እኔም የዩኒቨርሲቲው ተማሪ መሆኔ ጠቀመኝና የተማሪነት መታወቂያን አሳይቼ ወደ አዳራሹ ዘለኩ . አባይ ስብሀት ሙሉ ለሙሉ ጥቁር የሆነ ሱፍ ለብሰው , ከፊት ለፊት በተደረደሩ መደዳ ወንበሮች ላይ ተሰይመዋል . ከዚያ ድፎ ዳቦ እንዲቆርሱ ተደረገና ወደ ዝግጅቱ , ዋናው ጉዳይ ተገባ . በአንድ የጋዜጠኝነትና ኮሙኒኬሽን ዲፓርትመንት ተማሪ ጥያቄ አቅራቢነት አቦይ ስብሀት ለጥያቄዎቹ ሰፋ ያለ መልስ መስጠት ጀመሩ . ለዛሬ ትኩረቴን እጅግ ከሳቡኝና ግርምት ከፈጠሩብኝ የአቦይ ስብሀት ንግግሮች የተወሰኑትን እዚህ ላይ እያነሳሁ ሀሳብ እሰጥባቸዋለሁ ::
1, . ሀገር ማለት
አቦይ ስብሀት " ሀገር ማለት ህገ መንግስቱ ነው ; . ሌላ ነገር አይደለም " . የሚል ነገር ተናግሯል ይሄ ለእኔ ምን ማለት እንደሆነ ግለፀው ብባል ; . እንዲህ በሌላ ምሳሌ ላስቀምጠው እችላለሁ ትዳር ምንድነው ለሚለው ጥያቄ " . ትዳር ማለት የጋብቻ ሰርቴፍኬት ማለት ነው 
ብሎ የመመለስ ያህል ነው . ይሄ አነጋገር ስሜት ሊሰጥ ይችላል ? ! ትዳርን ትዳር የሚያድርገው የጋብቻ ሰርቴፍኬት አይደለም ; የጋብቻ ሰርቴፍኬት ትዳሩን ህጋዊ ያደርገው እንደሆነ እንጂ ራሱ ትዳር ሊሆን የሚችል ነገር አይደለም ሀገርም እንደዚያ ነው ; . ያለ ህገ መንግስት ሀገር ሊኖር ይችላል ; ሀገር ከሌለ ግን ህግ መንግስት የሚባል ነገር አይኖርም ህገ መንግስት የተፈጠረው በጣም ትናንት በሚባል ጊዜ ሲሆን ; ሀገሮች የተፈረጡትና የኖሩት ግን ለብዙ ሺህ ዓመታት ነው ለምሳሌ ; . የእኛ ሀገር ታሪክ ብንወስድ እንኳ የሀገሪቷ ታሪክ ከሶስት ሺህ ዓመት በላይ ሲሆን በህገ መንግስት ስም መተዳዳር የጀመርንበት ጊዜ ሲታይ ደግሞ አንድ መቶ ዓመትም አልሞላንም . ለነገሩ በሀገራችን በጠመንጃ ጉልበት እንጂ በአግባቡ በህገ መንግስት የሚያስተዳድረን መንግስት እስከዛሬ አላገኘንም ወይም አልፈጠርንም .

2 . ስለኤርትራውያን 

አቦይ ስብሀት ስለኤርትራውያን ሲናገሩ " ኤርትራውያን ከኢትዮጵያውያን በላይ ነው ኢትዮጵያዊነትን በጣም ይፈልጋሉ ; በአንፃሩ ኢትዮጵያውያን የሚፈልጉት የኤርትራ መሬት ነው ህዝቡ አይደለም . አሰብ ቀይ ምናምን ይላሉ . ​​" ብለው እርፍ ! ምንም እንኳ ንግግሩ እጅግ በጣም የሚገርም ቢሆንም የአርትራውያንን ኢትዮጵያዊነት ከአቦይ ስብሀት መስማቴ ጥሩ ለውጥ ነው እላለሁ ; ኤርትራውያን ከእኛ በላይ , ከኢትዮጵያውያን በላይ ኢትዮጵያዊነትን ይሰማቸዋል የሚለውን ግን ቀልድ ነው ሊሆን የሚችለው . ሲጀመር እንዲህ ብሎ ለመናገር በመጀመርያ ህዝቡ ስለዚህ ጉዳይ ያለው አቋም ተጠንቶ ; በደንብ በተጠናቀረ መረጃ ተደግፎ ነው መቅረብ የነበረበት ከሁሉም በላይ እጅግ አድርጎ የሚያሳዝነው ደግሞ ኢትዮጵያውያን የኤርትራን መሬት እንጂ ህዝቡ አይፈልጉትም መባሉ ነው . እኔ የማውቀው በተቃራኒው ነው ; የኢትዮጵያ ህዝብ ለኤርትራውያን ጥልቅ የሆነ ፍቅር እንዳለው ነው ; አሁን ይሄ ሁሉ ነገር ከተፈጠረ በኋላ እንኳ እንደ ራሱ ህዝብ እንደወንድም ህዝብ እንጂ እንደ ጎሮቤት ህዝብ ወይም እንደባዕድ ህዝብ የሚያያቸው አይደለም አቦይ ስብሀት የኤርትራ እና የኢትዮጵያ ህዝቦች የጊዜ ጉዳይ ካልሆነ በስተቀር ነገሮች እየሰከኑ ሲሄዱ ለምሳሌ በኤርትራ ያለውን ስርዓት ሲቀየር በሆኑ ቅርፅ ተባብረው የፖለቲካና የኢኮኖሚ ግንኙነታውን ማጠናከር የሚችሉበት እንድል እንዳለ ; በፌዴሬሽንም በኮንፌደረሽንም በሌላም መልኩ የነበራቸውን አንድነት መመለስ የሚችሉበት ሁኔታ ይፈጠራል ብለው እንደሚያምኑ የተናገሩት በዚያን ቀን ከተናገሯቸው አዎንታዊ ንግግሮች አንዱ ነበር . ስለ ኤርትራው ፕሬዚደንት ሲናገሩ ኢሳይያስ የሚፈልገው አጀብና እዩኝ እዩኝ ማለት እንጂ ሌላ ነገር አይደለም ብሏል ; . እርሱ ገንዘብም አይፈልግም ብሏል የምን ገንዘብ እንደሆነ ግልፅ ባያደርጉትም የእርዳታ ገንዘብ ማለታቸው ሊሆን እንደሚችል መገመት የሚቻል ነው ሀበሻ አይደሉ ; . እኛ እና እርሱ ልዩነታን እዚህ ላይ ነው ማለታቸው መሆን አለበት በቅኔ ! ይልቅ የሰሞኑ አንዱ ገጠመኝ ልንገራችሁ አንድ ኤርትራዊ ከሳውዲ አረቢያ ኢትዮጵያዊ ነኝ ብሎ ከኢትዮጵያውያን ጋር ተደባልቆ ኢትዮጵዊነት ተቀብለው ነው እንደዚህ ወጣት ያሉ ኤርትራውያን በነፃ ከእኛ ዜጎች ጋር ወደ ሀገራችን እያመጡ ያሉት ያስባል . ሻዕቢያ ካልላካቸው ምንም ችግር የለውም ; ኢትዮጵያም ሀገራቸው ነው ድሮም ቢሆን በሻዕቢያ ፕሮፖጋንዳ ተታልለው ነው እንገንጠል ብለው የሄዱት እንጂ የኢትዮጵያ ህዝብ ስለጠላቸው አልነበረም . አቦይ ስብሀት እንዳሉት እነዚህ ኤርትራውያን እየመጡ ያሉት ትክክለኛ ኢትየጵያውያን እነርሱ ናቸው ተብሎ ከሆነ ግን በማን መንግስት እየተዳደርን እንደሆነ መጠየቃችን አይወሬ ይሆናል . " እናንተ 
ከኤርትራውያን ያነሳችሁ ኢትዮጵያውያን ናችሁ " የሚለን መንግስት መቼውም ቢሆን ጤነኛ መንግስት ሊሆን አይችልም ; መንግስትም የመሆን እድል የለውም .

3, የቀበጡ ፖለቲከኞችና ጋዜጠኞች

በእስር ላይ ስለሚገኙ ጋዜጠኞችና ፖለቲከኞች ተጠይቀው ሲመልሱ " ይሄ ስርዓት በስንት መስዋዕትነት የመጣ ስርዓት ነው ; በዚህ ላይ ሁኔታ በመጣ ስርዓት ላይ ማንንም እንዲቀብጥ ሊፈቀድለት አይገባም . መለስ በፓርላማ ስላንዳንድ ፖለቲከኞችና ጋዜጠኞች አስመልክቶ ሲናገር ጉዳት እስካላደረሱ ድረስ ወንጀለኛ መሆናቸውን እያወቅንም እንታገሳቸዋለን ሲል ሰምታችሁት ይሆናል ተሳስቷል ማንም ሰው በህገ መንግስቱ ላይ በስርዓቱ ላይ የመቅበጥ ምልክት ሲያሳይ ጊዜ ሊሰጠው አይገባም ; እርምጃ መውሰድ ያስፈልጋል :: ስለዚህ ማንም ቀበጥ በስርዓቱ ላይ እንዲጫወትበት አንፈቅድም " ብሏል . እንግዲህ በእርሳ c ው አባባል ከሄድን እነ አንዷለም አራጌ , እነ ርዕዮት ዓለሙ ; እነ ውብሸት ታዬ , እነ እስክንድር ነጋ በቅብጠት ነው የታሰሩት ማለት ነው በእስር ጉዳይ ላይ ቀብጠት አለ እንዴ . !ለዚያውም ብእኛ ሀገር ! የኖርዌይ መንግስት እንደዚያ ቢል ብዙም ላይገርም ይችላል ; ምክንያቱም የእስር ቤታቸው ሁኔታ እጅግ የሚያማልል ነው . ከእኛ አንፃር ስታየው ! በቃልቲ ለመታሰር እንዴት ነው ቅብጠት የሚሆነው . እነርሱ የታሰሩት የነፃነት የፍትህ ጥያቄ እንስተው እንጂ ቀብጠው አይመስለኝም . እኔም ይሄን ጉዳይ አንስቼ ቅብጠት ሊሆን እኮ ነው በአቦይ ስብሀት አተያይ ! ጠያቂው በመቀጠል " እነዚህ የታሰሩት ጋዜጦኞች በአንድ በእኩል ወንጀለኛ ተብለው ታስሯል በሌላ በእኩል የሀሳብን በነፃነት የመግለፅ ታጋዮች ተብለው በዓለም አቀፍ እየተሸለሙ ነው ይሄ ሁለቱ ነገር አይጋጭም ወይ ? " ብሎ ሲጠይቃቸው , ፈገግ ብለው ያሰራው አካል እኮ አይደለም እየሸለማቸው ያለው ! በማለት ተሳልቋል ::

4 . ስለሰማያዊ ፓርቲ

" ሰማያዊ ፓርቲ የምን ፓርቲ እንደሆነ ግራ የሚገባ ነው ; የሃይማኖት ፓርቲ ይሁን የፖለቲካ ፓርቲ ይሁን አይታወቅም " አሉ .በመቀጠል ደግሞ " ሰማያዊ ፓርቲ ሙስሊም ወንድሞቻችን ሲል ሰምታችሁ ይሆናል . እነርሱ ናቸው የሞስሊሞች ወንድም የሚሆኑት ! አቤት ሙስሊሞቹ ሲጠሏቸው ብታዩ ! ወደ እኛ እየመጡ ለምን እንዚህን አታሳርፉልንም ነው እኮ የሚሉን . " በማለት ተናግሯል . ላይም መረጃ ሰብስበው ጥናት አድርገው አይደለም የተናገሩት . የተወሰኑ ሙስሊም ጓደኞቻቸው ጋር በጉዳዩ ላይ እውርተው ሊሆን ይችላል ; ነገር ግን በጣት የሚቆጠሩ ሙስሊሞች በዚህ ጉዳይ ላይ ያላቸውን ሀሳብ ማወቅና በብዙ ሚሊዮን የሚገመቱ ሙስሊሞች ለሰማያዊ ያላቸውን አመለካከት ማወቅ የተለያየ ነገር ነው .

5 . ስለሀብት ክፍፍል እና ስለኢህአዴግ ርዕዮተ ዓለም

ስለሀብት ክፍፍል ሲናገሩ ደግሞ " በአለም አንደኛ ፍትሀዊት ሀገር ዶብብ ኮርያ ስትሆን ; ኢትዮጵያ ደግሞ ሁለተኛ ናት ; አሜሪካ ደግሞ የመጨረሻዋ ነች አሉ እንግዲህ አሜረካን በደንብ የምታውቁ መስክሩ ; ኢትዮጵያ ውስጥ ስላለው ሁኔታ እንኳ በቅርብ እናውቀዋለን ;ምስክር መጥራት የሚያስፈልገን ነገር አይደለም አቦይ ስብሀት ስለኢህአዴግ ርዕዮተ ዓለም ሲናገሩ ; . " ኢህአዴግ ቀኝ ዘምም ግራ ዘመምም አይደለም ; ' sentrums ' ነው ' pragmatisk ' ነው " . አሉ አቶ ልደቱ አያሌው " ሶስተኛ አማራጭ " የሚሉትም ይሄ " sentrums " የሚባለውን በሌበራል ዴሞክራሲ ውስጥ የሚመደብ ርዕዮተ ዓለም ነው . ማንም ሰው ወይም ፓርቲ በቀኝ አክራሪነት ወይም በግራ አክራነት ላለመመደብ በስም " sentrums " መባለን ይፈልጋል . እንደ እውነቱ ከሆነ ግን በእኛ ሀገር በትክክል " sentrums " ሊባሉ የሚችሉ ፓርቲዎች ያሉ አይመስለኝም . በፓርቲው ውስጥ ወደ ቀኝ ጥግ የመሄድ ዝንባሌ እንዳለ ሆኖ በፕሮግራም ደረጃ ወደ " sentrums " የሚጠጋ አቋም ያለው አንድነት ፓርቲ ብቻ ይመስለኛል . ሌላው ሁሉ አንድም በቀኝ , አንድም በግራ የሚመደብ ነው . የኢህአዴግ የሚጠጋ አቋም ያለው አንድነት ፓርቲ ብቻ ይመስለኛል . ሌላው ሁሉ አንድም በቀኝ , አንድም በግራ የሚመደብ ነው . የኢህአዴግ እንኳ ግራ ዘመምም ለመሆኑ ክርክር ውስጥም የሚገባ አይደለም .አቦይ ስብሀት ወደ ጫካ ሲገቡ እድሜያቸው ሰላሳ ዘጠኝ እንደነበረ ራሳቸው በዚያው መድረክ ላይ የተናገሩ ሲሆን አስራ ሰባት ዓመት በትግል 23 ዓመት ደግሞ በስልጣን የቆዩ ከመሆናቸው አንፃር አሁን የሰባ ዘጠኝ ዓመት አዛውንት ናቸው ማለት ነው . ነገር ግን አሁንም ጠንካራ እንደሆኑ ታዝቤያለሁ ; . የዓይን መነፅር እንኳ ሳያድርጉ ነው ሲንቀሳቀሱ የነበረው ነገር ግን አነጋገራቸው ሁሉም አይቶ እንዳሳለፈ ሰው ሆኖ አላገኘሁትም ; ይልቅ ገና የፖለቲካ ስሜቱ እንዳልነበረደለት ጎረምሳ ነው በትዕቢትና በማን አህሎኝነት ሲናገሩ የነበሩት . በተለይ ስለተቃዋሚዎች ሲናገሩ ያላቸውን ጥላቻ በግልፅ ያስታውቅ ነበር . ጥላቻ በዚህ ዕድሜ በጣምም ጥሩ አይደለም::



                                                                                                              





.




 .








.


.









.






 .



























.


Saturday, December 21, 2013

በ ‹‹በመለስ ራዕይ ተቃዋሚን ዜሮ እናስገባለን›› የሚል ዘመቻ ተጀምሯል

December 21/2013

 የአቶ መለስ ዜናዊን ራዕይ ለማስቀጠል ተቃዋሚዎችን ዜሮ እናስገባለን የሚል ቅስቀሳ በጎንደር የኢህአዴግ ካድሬዎች መጀመራቸውን ተከትሎ ተቃዋሚዎችን እንደሚደግፉ በሚገመቱና በጎንደር የአንድነት አባላት ላይ ማስፈራሪያ፣ውክቢያና ዛቻ እየተፈጸመ ነው፡፡ በመለስ ራዕይ ሰበብ ከገዢው ፓርቲ የተለየ አመለካከት በሚያራምዱ ዜጎች ላይ ቅስቀሳ መጀመሩና ይህንኑ ተከትሎም አደጋ እያንዣበባቸው እንደሚገኝ በጎንደር የሚገኙ የአንድነት አባላቶች አስታውቀዋል፡፡ ተቃዋሚዎችን ዜሮ ማስገባት የሚለው ዘመቻው ከተቻለ በፈቃደኝነት ተቃዋሚዎቹ ኢህአዴግን መቃወም እንዲያቆሙ ካልሆነ ግን ጫና በመፍጠር እንቅስቃሴያቸውን ማኮላሸት ላይ ያነጣጠረ እንደሆነ ታውቋል፡፡በ2002 ምርጫ 545 ወንበር ማግኘቱን ያወጀው ኢህአዴግ አውራ ፓርቲ ነኝ ማለቱን ተከትሎ ዳዴ ማለት የተሳነው የመድብለ ፓርቲ የፖለቲካ ስርዓት በከፋ ሁኔታ ውስጥ ይገኛል፡፡



በምኒልክ ሳልሳዊ

የሕወሓት አደገኛ የዘረኝነት መርዝ እና የናዚ ፍልስፍና

December 21 /2013

መጀመርያው ዓለም ጦርነት ማገባደጃ ቦኋላ በጀርመን ማደግ ጀምሮ የነበርው ´´የናሺናል ሶሻሊስት ፓርቲ´´ የናዚ የፖለቲካ ዘይቤን በማስፋፋት ፣ የፋሺስቶች የቀኝ ክንፍ እንቅስቃሴ በዛን ወቅት በዋናነት ይታገል ፣ ይዋጋ ነበረው አንዱ ኮሚኒስቶችን ነበር ፡፡ እነዚህን ክፍሎች ዒላማ ካደረገበት ምክንያት አንዱ ፣ በወቅቱ በዓለማችን ዙርያ እየተጠናከረ የነበረውን ፣ የኮሚኒስቶች እንቅስቃሴ ለመቋቋምና ፣ በስራቸው እየተደራጀ የነበረውን የሰራተኛውን ክፍል (working class ) ከኮሚኒስቶች ነጥሎ በናዚስቶች ስር ለማሰለፍና ነበር ፡፡

የናዚ ፍልስፍና መሰረት ፣ የ አርያን ታላቅ ዘር (Aryan master race ) ከሌሎች የሰው ፍጠረት ዘሮች ሁሉ የላቀና ፣ የተመረጠ ሕዝብ እንደሆነ ያምናሉ ፡፡ እነሱ የሚሰጡትን ገጸ-ባህሪያት የማያሟላ ፣ እንደ ሰው ካለመቁጠራችወም በላይ ``በስህተት ወይም ሳይፈለጉ ተፈጥረው ``የተገኙ ነገሮች ተደርገው ስለሚታዩ ፣ መደምሰስ ወይም መጥፋት አለባቸው ብለው ያምኑ ነበር ፡፡ በዚህም የተነሳ ታሪክ እንደመዘገበው ከነሱ ዝርያ ውጪ ናቸው ብለው ፣ በተለያየ ዘርፍ የመደብዋቸውን ፣ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሌሎች ዜጎችን በየማጎርያ ካንፑና (concentration camp)፣ በየእስር ቤቱ እየተሰበሰቡ በሚያሰቅቅ ሁኔታ በጋዝ ጢስ ፣ በጥይት እሩምታና በተለያየ መንገድ እንደጨረሱዋቸውና ፣ ከፊሎቹንም ፣ በጣም አሰቃቂና ፣ኢ-ሰባዊ በሆነ መንገድ ፣ ሰውነታቸውን ለህክምና ምርምር ይጠቀሙባቸው ነበር ፡፡ ከዚያም አልፈው ሄደው፣ የሰውን ልጅ ክቡር ፍጡር ከእንሳት በታች አድርገው በመቁጠር ፣ ቆዳቸውን ለማስታዎሻ (souvenir) ለመብራት አንፖል ማጌጫና ፣ ለቤት ማሳመርያ ቁሳቁስ ይጠቀምባቸው እንደነበር ፣ ዛሬ ከነማስረጃው በተለያዩ የማጎርያ ካንፕ ፣ ሙዝየም ውስጥ ተቀምጠው ማየት ይቻላል ፡፡

እነዚህ ከአርያን ዘር ውጪ ያሉትን ፣ መፈጠር አይገባቸውም ነበር ብለው የመደቧቸውን ፣ ይሁዲዎችን ፣ ጂብሲዎችን ፣ የአዕምሮ ህመምተኞችን ፣ አካለ ስንኩላንን፣ ጥቁሮችን ፣ ከነሱ ሃይማኖት ውጪ ያሉትን ፣ እንደ የጆሃቫ እምነት ተከታዮችን ፣ የፖለቲካ ተቀናቃኞቻቸውንና ፣ የተለየ ጾታዊ አቀራረብ እምነት የነበራቸውን ፣ ከሰባዊ ማንኛውም ፍጡር በታች አድርገው ከማየታቸውም በላይ እንደ የግል መገልገያ ቁሳቁስ አድርገው ፣ አዕምሮዋችን መገመት ከሚችለው በላይ ፣ ኢሰባዊ ድርጊት ይፈጽሙባቸው ነበር ፡፡ የፓርቲ መመሪያቸውም ከላይ የተዘረዘሩትን ከነሱ ውጭ የተፈጠሩትን ፣ የማጥፋት መብት እንዳላቸው ተደርጎ እንዲታመንበት ተቃኝቶ የተዘጋጀ ንድፈ -ሃሳብ ወይም የፖለቲካ ዘይቤ( ideology) ስለነበር ፣ አብዛኛው ሕዝባቸውን በዚህ ፍልስፍና አሳምነው ፣ አሳስተው ከጎናቸው ማሰለፍ ችለው ነበር ፡፡

አርያን የሚለውን ፣ ቃሉን መጠቀም የጀመሩት ሰዎች ፣ ለዚህ የዘረኝነት ተግባር መጠርያ ለማድረግ ሳይሆን ፣ ለአንድ አካባቢ ሕዝብ (ፖርቶ ፣ ኢንዶ አውሮፓውያን ...ወዘተ) መጠርያ ወይም መለያ ለማድረግ ብቻ ነበር፡፡ ሆኖም ናዚዎች ይህንን እውነታ ቀይረው ፣ ትክክለኛ ሕዝብ ማለት በነሱ በነሱ እምነት ፣ ነጭ ፣ ሰማያዊ የዓይን ቀለም ያለውና ፣ ወርቃዊ ቀለም ጸጉር ያለውና ፣ (white, blue eyes and blond hair) የነሱን የፖለቲካ መስመር የሚከተል ...ወዘተ ብለው ያምናሉ፡፡

ይህ አደገኛ በታሪካችን የሚታወቅ በዓለም ሕዝብ ላይ ያደረስው እልቂት ፣ ያስከተለው አካላዊና ስነ-ልቦናዊ ጉዳት በግልጽ ከመታወቁም በላይ ፣ ዛሬም የነሱ ርዝራዦች ፣ በተለያየ ቅርጽ ፣ እንደ አዲሱ የፋሺስት ንቅናቄ (neonazi´s ) እና ፣ በአውሮፓ በህጋዊ የፖሊቲካ ሽፋን ስር ተደራጅተው በግልጽ ይንቀሳቀሳሉ ፡፡ ቅርጻቸውንና ፣ ዘዴያቸውን በመቀያየርና ፣ ያለውን ዲሞክራሲያዊ ህጋዊ መንገድ እንደ ሽፋን በመጠቀም፣ እጅግ ወደ ቀኝ ያጋደለ የዘረኛነትን ዓላማ ፣ የሚያራምዱ ፣ ይፋዊና ፣ ህቡዕ የፖለቲካ ድርጅቶች በማቋቋም እስካሁን ድረስ፣ በምዕራቡ ዓለም በይፋ ሲንቀሳቀሱ እናያለን ፡፡ አንዳንዴ በዓለም ዓቀፍ የኤኮኖሚ ቀውስ ምክንያት ፣ የሃገራቸው ኤኮኖሚ ሲዳከምና ፣ ችግራቸው ሲጠና ፣ ተራውን ሕዝባቸውን ፣ ለዚህ ችግር ምክንያት አድርገው የሚያቀርቡት ፣ የውጪ ዜጎችን ወደ ሃገራቸው ባብዛት መግባትና ፣ የነሱን ሕዝብ ስራና ጥቅም ስለሚካፈሉ እንደሆነ አድርገው ምክንያት እየሰጡ ፣ በተለይ በቀውሱ የተጠቁትን ያሳምኗቸዋል ፡፡

ሕዝብ እነሱን ቢመርጥ ፣ የውጪ ዜጎችን አባረው ፣ ለነሱ የሚጠፋው ንዋይ ለሃገራቸው እንደሚያውሉና ከችግር እንደሚያወጧቸው ቃል ይገቡላቸውል ፡፡ በዚህ የምርጫ አጀንዳ በለስ ቀንቷቸው ስልጣን ሲይዙ ፣ አዳዲስ ጸረ የውጪ ዜጎች ህጎች በማውጣት ከነሱ የተለየ ዘር ፣ ቀለምና ፣ የሃይማኖት እምነት ያላቸውን ፣ የሃገሪቷ ዜጎች ባልሆኑት ላይ ፣ ከፍተኛ ጫና በመፍጠር ፣ ሃገራቸውን ጥለውላቸው እንዲወጡ ከፍተኛ ግፊት ያሳድራሉ ፡፡ ይህ በተለይ እንደ
ብዙዎቻችን ሃገራችንን ጥለን በተሰደድነው ዜጎች ላይ የሚያደርሱብን መንፈሳዊ ጫናና መሸማቀቅ ቀላል እንዳልሆነ እናቀዋለን ፡፡
የናዚዎች የፖለቲካ አካሄድ ከነሞሶሎኒ ፋሺስቶቹ ጋር ብዙ የሚጋሩት እምነት ስለነበራቸው፣ በሃገራችንም ለአጭር ጊዜም ቢሆን ፣ በፋሺስት ወራሪ ጠላት በግድ ተጭኖብን ከነበረው የዘረኝነት ህግና ፣ በወቅቱ በነበሩት ወገኖቻችን ላይም ሆነ በሌሎች ሃገሮች ላይ ይደርስ የነበረው መከራ ስንሰማ ፣ ዘረኝነት ምን ያህል አስከፊ ገጽታ እንደነበረው ከወላጆቻችንና በአህጉራችን ላይ በዚህ ጨካኝ የዘረኝነት ስርዓት ውስጥ ካለፉት ሃገሮች ታሪክ ብዙ ተምረናል ፡፡

በሃገራችንም ፣ በአንዳንድ ኋላ ቀር ባህላችንንና ፣ ካለማወቅ ፣ ከብዙዎቻችን የተለየ የአኗኗር እምነት፣ ልዩ ሙያዊ ተሰጥኦ የነበራቸውን ፣ ወገኖቻችንን ፣ ቡዳ ፣ ፋቂ ፣ ቀጥቃጭ፣ መጫኛ ነካሽ ፣ .....ወዘተ እየተባለ አንዱ ከሌላው የተሻለ ወይም ያነሰ ሆኖ የሚታይበት ፣ የዘር ፣ የሙያና ፣ የእምነት አድሎዋዊ አካሄድ ስለነበር ፣ ከነዚህ ወገኖቻችን ጋር ፣ በጋብቻና በማህበራዊ ኑሮ የማንቀላቀልበት ፣ አሳፋሪ ባህል ነበረን ፡፡ ሆኖም ይህንን አስቀያሚ ባህል ፣ ባለፉት ዓመታት በሂደት ፣ በዓለማዊም ሆነ ሃይማኖታዊ ትምህርት ፣ በሕገ-ደንባችን ...ወዘተ ፣ ለማስወገድ እየተጣረ ነበር ፡፡

ሆኖም ካለፉት 21 ዓመታት ወዲህ ወያኔ ስልጣን ላይ ከወጣ ቦኋላ ፣ ጎጠኝነት ሕጋዊ ሽፋን ተሰጥቶት አንቀጽ ወጥቶለት ፣ በአዋጅ አጊጦ ፣ ሕዝባችንን ዘረኛ በሆነ ፣ ጎጥንና ቋንቋን መሰረት ባደረገ ``ፌደራላዊ አስተዳደር`´ በሕዝባችን ላይ በሃይል ጭኖ ለየት ባለ መልክ ተኳኩሎ ቀረበልን ፡፡ የህንን የማይቀበሉ ወገኖቻችንን ሲያሳድድ ሲያጠፋና ፣ በግልጽ ኢፍትሃዊ -የዘረኛነት አካሄድ ሲከተል እድሜያችንን አጋምሰናል ፡፡ ይህ ዘረኛ ስርዓት ከተዘረጋ ቦኋላ ፣ ለረዥም ዘመናት አብሮ በኖረ ሕዝባችን ማሃል ፣ በዘመናችን አይተን የማናውቀው ፣ የጎጥና ፣ የሃይማኖት ጥላቻ ውስጥ ለውስጥ በአገዛዙ ፣ እንደ ፖሊሲ እየተነደፉ ልዩነትን በማስፋፋት ፣ እርስ በእርስ ከፋፍለው ፣ አዳክመውን የነሱን ሥርዓት ለማራዘም ሲሞክሩ ማየት የተለመደ ሆንዋል ፡፡

ይህ በአገዛዙ ፣ ዘዴውንና ፣ ቅርጹን እየቀያየረ ፣ ተራ በተራ በሕዝባችንና ፣ በዕምነታችን መሃል ጣልቃ እየገባ እርስ በእርስ በማናቆር ያደርስ የነበረው ችግር በመጠኑ ተሳክቶለት ቢሆንም ፣ በእቅዳቸው መሰረት እንደፈለጉት ገና አልተሳካም ፡፡ ይህ ተንኮል የገባቸው ክፍሎች እንዲያውም በተቃራኒው ፣ አልፎ አልፎም ቢሆን ፣ የተለያዩ የኃይማኖት አባቶችና ፣ በፖለቲካውም መስመር ፣ አብረው ተቃውሞዋቸውን ማሰማት ጀምረዋል ፡፡

ይህ ፍልሚያ ቀጣይነት ባለው መንገድና ፣ በተሻለ በተቀናጀ ዘዴ እየተደራጀ ፣ እየተሰባሰበ ፣ ትግሉን አስተባብሮ ወደ አንድ አቅጣጫ ለማምጣት እየተካሄደ ያለው አዝማሚያ ግን ገና አስተማማኝ ባይሆንም፣ ጅምሩ ተስፋ የሚሰጥ ነው፡፡
ምክንያቱም ፣ አብዛኛው የተቃዋሚ የፖለቲካ ድርጅቶች ፣ ውስጥ ለውስጥ እያደገና ፣እየተስፋፋ የመጣውን የዘረኝነት አደጋ አሳሳቢ ደርጃ ላይ መድረሱን አልተቀበሉም ፡፡ በዚህም ምክንያት አገዛዙ በቀላሉ ይወገዳል ብለው ስለሚያምኑ ፣ አብዛኛው ጉልበታቸውን የሚያጠፉት ፣ የሌለ የምርጫ ውድድር መድረክ እንደተፈጠረ ፣ እኔ እበልጥ ፣ እኔ እበልጥ አይነት ፉክክር በማድረግ ነው ፡፡ የአንድነቱ ክፍል ነኝ ከሚለው ፣ በተሻለ የጎጥ ፖለቲከኞቹ እየተቀናጁና ፣ እየተደራጁ፣ እየተቻቻሉ ፣ አጀንዳቸውን በማገባደድ ላይ ናቸው ፡፡ ባጠቃላይ ለአንድነት ቆምኩኝ የሚለው ክፍል ፣ ይህንን አደጋ አጢኖ ስላላየው ፣ በወሬ ፣ ስለ ሕብረት ፣ ጥምረት ፣ ውሕደት ፣ አስፈላጊነት ከመቆዘም ውጪ ፣ ተቻችለው የእውነት ተባብረው ለመቆም ገና አልወሰኑም ፡፡

አንዳንድ የምናያቸውም ሙከራዎችም ፣ በራሳቸው የፖለቲካ አጀንዳ ዙርያ የሚቀራረቡ ፣ ለስልጣን ክፍፍልና ፣ ሚዛን ለመድፊያ የተማከለ ሆኖ ፣ በአዕምሮዋቸው ለፈጠሩት ``የምርጫ ውድድር`` የተነደፈ እንጂ ፣ በእውነት ይህንን ስርዓት ለማስወገድ ተፈልጎ ፣ለጊዜው ልዩነትን ፣ ለእውነተኛ የምርጫ ጊዜ አቆይቶ ፣ መጀመርያ ሃገራችንን ከአንባገነናዊ ሥርዓት ነጻ ለማውጣት ተብሎ ፣ ተቻችሎ አብሮ ለመቆም የታለመ አይደለም ፡፡ እንዲያውም አሁን ፣ የኅብረት አሰባሳቢዎቹ ብዛት የተቃዋሚ የፖለቲካ ድርጅቶችን ቁጥር አልፎ ሊሄድ ስለሆነ ፣ ለነሱም ሌላ ``የኅብረት አሰባሳቢ `` ቡድን ማቋቋም አስፈላጊ እንደሆነ መገመት አይከብድም ፡፡
የአገዛዙ ዓላማው ፣ የጎጥ ፖለቲካን በሕዝባችን መሃል ማስፋፋትና ፣ ይህም ቦኋላ ሊያስከትል የሚችለውን የመገነጣጠል አደጋ ያሰጋናል እስካልን ድረስ ፣ በማንኛውም መንገድ ይህንን ከፋፋይ ሥርዓት ተባብሮ ለማስወገድ አለመጣር፣ ወይም እነሱ በሚሄዱበት መንገድ እየተጓዝን የችግሩ ተባባሪ መሆን ፣ መሀከል ምንም ልዩነት የለውም፡፡ የዚህን አደጋ ክብደት መቀበል ካልፈለግን ፣ ምርጫችን የሕዝባችንን ስቃይ ማርዘም ፣ አገዛዙ እንዲቆይ መርዳትና በመጨረሻም ፣ ለሃገራችን መበታተን ምክንያት መሆኑን መቀበል አለብን ፡፡

የዚህ ጽሁፍ ዋናው ዓላማ ፣ ከላይ በአጭሩ ጠቅሼ ለማሳየት የሞከርኩት ፣ በሃያኛው ክፍለዘመናችን በጀርመን ተከስቶ የነበረው አስቀያሚ የናዚ /የፋሺስቶች የዘር አድልዎ ፖሊሲ ምልክቶቹን ፣ በሃገራችን ፣ በአንዳንድ በተቃዋሚው አካባቢ ባሉም ምሁራንም ጭምር ፣ በአንዳንድ ድህረ-ገጾችና የፓልቶክ የመወያያ ክፍሎች ሲሰሙና ፣ ሲንጸባረቁ ያየሁትን አደገኛ አዝማሚያ፣ ስጋቴን ለወገኖቼ ለማካፈል እንጂ ፣ ባለሙያው ሆኜ አንባቢያንን ለማስተማር አይደለም፡፡
የናዚዝም ፣ ወይም እራሳቸውን የአርያን ማስተር ሬስ (Aryan master race ) ብለው የሚጠሩት ዘርኞች ዋና መለያ አካሄዳቸው ፣ የሌላውን ሰው ሕልውና መካድ ፣ በሕዝብ መሃል ያለውን ታሪካዊ ትስስርን አለመቀበል ፣ ከአንድነቱ ይልቅ በልዩነቱ ላይ ማተኮር ፣ በሕዝቦች መሃል አጥር ማጠር ፣ የግንኙነቱን ድልድይ ማፍረስ ፣ በሰዎች ልጆች መሃከል ሰፊ የማበላለጥና ፣ ሚዛኑ የተንሻፈፈና ቅጥ ያጣ የወገንተኛነት አካሄድ ማስፋፋት ነው ፡፡

ይህ አይነት ግልጽ የዘረኛነት አካሄድ ፣ ትላንት የወያኔው መሪ ፣ `` ከወርቅ ዘር በመወለዴ እኮራለሁ `` ያሉን ፣ ሕዝብን ከሕዝብ የማበላለጥ ዘረኛ ዓላማ ስንቃወም ሰንብተን ፣ ዛሬ ደግሞ ፣ አውቀው ሆነ ሊያስከትል የሚችለውን አደጋ ሳያጤኑት ፣ እንደዚህ አይነት ከፋፋይ ፣ የፋሺስት ዘረኛ ፖለቲካዊ ቋዋንቋ ማሰማት የጀመሩትን ፣ ቁጭ ብሎ ማዳመጥ እየተለመደ መምጣት ጀምሮዋል ፡፡
ዛሬ ከአንዳንድ ተቃውሞን እናስተባብራለን ከሚሉ ፣ ሊያስወግዱ ከሚፈልጉት ስርዓት ባልተለየ መንገድ እየተጓዙ ፣ ቆመንለታል የሚሉት ሕዝብ ያልጠየቃቸውን ፣ እሱ ከሌላው የምበልጥ ነኝ ያላለውን ፣ እሱ ያልፈለገውን በስሙ እንወክለዋለን እያሉ ፣ በሕዝባችን መሃል ፣ ጥላቻንና ፣ መራራቅን የሚጋብዝ ፣ አላስፈላጊ ማበላለጥ ፣ ባልተለመደ መልኩ ሲካሄድ ስንሰማ ፣ ከማሳዘኑም በላይ እያሰጋን ሄድዋል ፡፡
በአንድ የታሪክ ሂደት አስገዳጅነት በተከሰተ ሁኔታም ይሁን ፣ ተፈጥሮ በቸረው ልዩነት ፣ እንደ ጌጣችን ልናየው ፣ የሚገባን ታሪካችንን ፣ አንዱ ከሌላው ፣ የተመረጠ ፣ የተሻለ ፣ ቆንጆ ፣ ጸጉረ ዞማ ፣ አፍንጫ ሰልካካ ፣ ጎበዝ ተዋጊ ፣ ታላቅ ሕዝብ ፣ ወርቅ ሕዝብ .......ወዘተ የመሳሰሉ ፣ በጣም ኋላ ቀር የሆኑ ዘረኛ ፣ ቅጽላዊ ማበላለጦችን በሕዝባችን መሃል ፣ በአለንበት በሃያ አንደኛው ዘመን ማዳመጡ ጆሮ ያሳምማል ፤ አንገት ያስደፋል ፣ ተስፋ ያጨልማል ፡፡ ይህ አይነት አላስፈላጊ ወገንተኝነት ፣ ቆመንለታል ለሚሉት ክፍል ከሌላው ወገኑ እንዲነጠልና ፣ የጥቃት ኢላማ እንዲሆን ከመርዳት ባሻገር የሚጠቅመው ነገር የለም ፡፡
በእርግጥ በማንኛውም ወገናችን ላይ በተናጠል የሚደርሰው ፣ በጎም ይሁን ጉዳት የጋራችን መሆኑን መቀበል አለብን፡፡ የማንኛውም ክፍል ወጋናችን በተናጠልና በተራ በሚደርስበት ፣ መሰቃየት ፣ መታሰር፣ መፈናቀል ፣ መጋዝ ፣ መዋረድ ፣ ለሌላውም ህመም ሆኖ ሲሰማው ኖርዋል ፡፡ ለመፍትሄውም አብሮ ተዋድቋል ፣ ታግሏል ፣ አብሮ በደም የተሳሰረ አንድነት ገንብቷል ፡፡ ያም እየተደናቀፈም ቢሆን ወደፊ ይቀጥላል ፡፡

በተለምዶ ፣ በአባቴ የትውልድ ሃረጌ የዚህኛው ዘር ነኝ ፣ በእናቴ የዚያኛው የእከሌ ወገን ነኝ እንደምንለው ሁሉ ፣ ሁላችንም በኢትዮጵያዊነታችን ከአማራውም ፣ ከኦሮሞውም ፣ ከሃዲያውም ከሁሉም የሐገራችን ሕዝብ ጋር ትስስር ስላለን ፣ የትኛውም ወገናችን ፣ በተናጠልም ይሁን በጋራ ለሚደርስባቸው ጥቃት፣ የራሳችን ጥቃት መሆኑ ተሰምቶን፣ ከማንኛውም የተገፋ ወገናችን ጎን ቆመን ጥቃቱን በጋራ ልንከላከል ይገባል ፡፡ ኢትዮጵያ የሚለው ሁላችንንም የሚያገናኝ ማእከል ነው ካልን ? እኔ በኢትዮጵያዊነቴ ዶርዜነት አለብኝ፣ በኢትዮጵያዊነቴ አፋርነት አለብኝ ፣ በኢትዮጵያዊነቴ አማራነት ፣ በኢትዮጵያዊነቴ ኦሮሞነት ....ወዘተ አለብኝ ብለን አምነን ፣ በተግባር በክፉም ሆነ በደጉ ጊዜ አብረን ተደጋግፈን ስንቆም ነው ፣ እውነተኛ ኢትዮጵያዊነታችንን በተግባር የምናስመሰክረው፡፡

አንዳንዴ ሰዎች እራሳቸው ባልመረጡት መንገድ እንዲሄዱ ፣ ስለሚገፉ ፣ ሰዎች በተናጠል ለሚደርስባቸው ጥቃት እራሳቸውን ለመከላከል በሚያደርጉት ጥረት ፣ የሌላውን ህልውናና ፣ መብት እስካልተጋፉና ፣ ላጠቃላዩ ሕብረት ችግር እስካልሆኑ ድረስ ፣ በሚያመቻቸው መንገድ የመታገል መብታቸውን መቀበል ብቻ ሳይሆን ማገዝና ፣ ከጎናቸው ሆኖ ብቻቸውን አለመሆናቸውን ማሳየት ወገናዊ ግዴታ ነው ፡፡
ይህ አይነት ወገናዊ ትብብር ፣ ለየብቻ መፍትሄ ፍለጋን ለማበረታት ሳይሆን ፣ የላላውን ለማጥበቅ ፣ የራቀውን ልብ ለማቅረብ ፣ የተጎዳውን መንፈስ ለመጠገን ፣ ይበልጥ የሚያስተሳስረን ፣ በሂደት የገነባነውን በጎ ትሪካችንን የሚንከባከብና ፣ የማይጠቅመንን አስወግደን ለሃገራችን አንድነትና ፣ ለሕዝቦቿ እኩልነት ለሚደረገው ትግል ጽኑ የአንድነት መሰረት እንደሚገነባ በማመን ነው ፡፡
ለሰባዊ መብቶች (human rights)መቅደም ስንታገል ፣ ዘር ፣ ሃይማኖት ፣ ቀለም ፣ ጾታ ፣ ታላቅነት ፣ ጀግነት ፣ የመሳሰሉትን ``እንደ መለኪያ `` አስቀምጠን ሳይሆን ፣ ወይም በቡድንና ፣ በግለሰብ የተደራጁና ያልተደራጁ በሚል ስሌት ከፋፍለን ሳይሆን ፣ በዚህ ምድር ላይ ለተፈጠረ ፣ ለሰው ልጅ የተሰጠው ተፈጥሮዋዊ መብቱ የተጣሰ በመሆኑ ብቻ ነው ፡፡
በሌላው ወገናችን ላይ የሚደርሰው፣ እስር፣ እንግልት ፣ መፈናቀል ፣ የሚሰማን ፣ የእኛ በምንለው ላይ ብቻ ሲደርስ ከሆነ ? የሌላው ወገናችን ስቃይና መከራ ፣ እንደራሳችን የማይሰማን ከሆነ ? ሕዝባችንን ያስተሳሰረውን ሰንሰለት እየበጣጠስን ፣ ለጎጣችን ፣ ለመንደራችን ፣ ብቻ የምንጨነቅ ከሆነ፣ በእውነት እንደ ናዚዎቹ ፣ በዘረኞች በሽታ እንደተለከፍን መቀበል አለብን ፡፡

ትላንት ያልተመችን ፣ ሌሎች ብቻቸውን የሄዱበት ጸረ አንድነት የጥፋት መንገድ ነበር ብለን አሁንም የምናምን ከሆነ ? ፣ ይህንን አካሄድ እኛ ስንደግመው ልክ የሚሆንበት መንገድ ስለሌለ ፣ የምንከተለው የትግል አቅጣጫ ፣ ለጋራ ችግራችን ወደ የጋራ መፍትሄ የሚያደርሰ መንገድ የሚያመቻችልን እቅድ ስንነድፍ ነው ፡፡ በጋራ ታግለን ፣ የምናመጣው ሰላም ፣ ዕድገትና ፣ ፍትህ የሰፈነበት ዲሞክራሲያዊ ስርዓት የብዙውን ፣ አለ የምንላቸውን ችግሮቻችንን መፍቻ ቁልፍ ስለሆነ ፣ በየትኛውም አቅጣጫ የምናደርገው ግፊት ፣ ወደ እዚህ አቅጣጫ አቅርቦ የሚያሰባስበን መሆን ይኖርበታል፡፡

የሕዝባችን ጥያቄም ባይሆን ፣ ለረዥም ጊዜ ፊደል በቆጠረው ጎጠኛ (elite) እንወክለዋለን ብለው ወደ ሕዝባችን በሚገፉት አጀንዳ የተጎዳው አንድነታችንን ለመጠገን ፣ በተመሳሳይ መንገድ በእልህ መሄድ ፣ እነሱን መተባበር እንጂ ለሃገር እንደማይጠቅም መታወቅ አለበት ፡፡ በእልህ የሚወሰድ አቅዋም ፣ ለማንኛችንም የሚበጅ አይሆንም ፣ ይበታትነናል፣ በዚህ ደግሞ ማንም አይጠቀምም ፡፡ በሳይንስ እንደተረጋገጠው ፣ ስሜታዊነት ሚዛኑ በዝቶ ካጋደለ ፣ ዕውቀት ወይም ጥበብን የያዘው የአዕምሮ ክፍላችን ስራውን ይቀንሳ፡፡(when emotions is high intelligence is low) የዚህም ውጤት የሚያስከትለውን አደጋ ለማስረዳት አንባቢዎቼን መናቅ ይሆንብኛል ፡፡

ወደድንም ጠላንም የመገንጠልን ዓላማ በሚገፉ ጎጠኛ ኢሊቶችና ፣ በሥርዓቱ ተባባሪነት ይገፋ የነበርው የዘረኞች ዓላማ ፣ ወደ ሕዝባችን እየገባ ፣ ከምንገምተው በላይ እየተራባ ፣ በብሔራዊ አንደንታችን ላይ አደጋ እንዳንዣበበ ያስተዋሉት ጥቂቶች ናቸው ፡፡ የአንድነቱ ደጋፊዎች ነን ከምንል ፣ የጎጥ ፖለቲካ አራማጆች በተሻለ እይተደራጁ ፣ እየተሰባሰቡ እንደሆን መካድ የዋህነት ነው ፡፡
ሕዝብ ደግሞ ፣ መሪ እስከሌለውና ፣ አደራጅቶ ትክክለኛውን አቅጣጫ የሚመራው እስከሌለው ድረስ፣ ቁጥሩ ስለበዛ ምንም ሊሰራ አይችልም ፡፡ በተግባር የምናየውም የተቃዋሚ የፖለቲካ ድርጅቶች ሕዝባችን ብቻውን እንደተውት ነው፡፡ በዚህ ላይ ከአንድ አቅጣጫ ብቻ በቀጣይነት በሚፈስለት ጥንፈኛ አመለካከት አይሳሳትም ማለት አይቻልም ፡፡ በተለያዩ የታሪክ አጋጣሚ ፣ ሕዝብ የተሳሳተ አቅዋም ሊወስድ እንደሚችል በተደጋጋሚ ታይቷል ፡፡

በእነዚህ ጎጠኛ አስተሳሰብ ባላቸው የሚገፋውን የዘረኝነት ጥፋት ፣ እንወክለዋለን የሚሉት ሕዝብ አቅዋም እንደሆነ አድርገን ተስፋ ቆርጠን ፣ በወገኖቻችን ላይ ዕምነት ማጣት የለብንም ፡፡ እንደዛ ማመን የጀመርን ከሆነ ፣ ለጎጠኞች እጅ እየሰጠን እንደሆነና ፣ እኛም የችግሩ ተባባሪ መሆን እንደጀመርን ማመን አለብን ፡፡ በሕዝባችን የሚቀርበው መሰረታዊ ጥያቄና ፣ የተማረው (ኢሊት) በሚፈጥረው ችግር መሃከል ያለውን ልዩነት ማስመር ካልቻልንና ፣ ሁለቱን ካምታታን ፣ ወደ ተሳሳተ ድምዳሜ እንዳይወስደን መጠንቀቅ አለብን ፡፡ እየመጣ ያለውን ችግር አቃለንም ሆነ አጋነን ሳናየው ፣ እንደ ሁኔታው ቅደም ተከተል ተደራጅተን ልንታገለው ይገባል፡፡
ያለው አገዛዝ ፣ የጎጠኞችን ፍላጎት በእጥፍ አጩሆ የሚያደነቁረን እንጂ ፣ የአብዛኛውን ፣ አንድነቱን የሚፈልገው ሕዝባችን ድምጽ ስለታፈነ ፣ ባለመስማታችን ልንጠራጠር አይገባም ፡፡ የሕዝባችንን እውነተኛ ፍላጎት በተለያየ አጋጣሚ ቀዳዳ ሲያገኝ አሳይቶናልና ፣ አሁንም ምንም የተለወጠለት ዓዲስ ነገር ስለሌለ ትግሉ ይቀጥላል ፡፡ እስሩ ፣ እመቃው ፣ ችግሩ ፣ ስደቱ ፣ እንደቀጠለ ሆኖ ፣ አሁንም አብዛኛውን ክፍል ያገለለ አንባገነናዊ ሥርዓት በሰፈነበት ሁኔታ፣ ከመታገል ሰንፈን ፣ እንዲሆንልን የምንመኘውን ፣ ከላይ እንዲፈቀድልን በተስፋ ደጅ እየጠናን ተጃጅለል ማጃጃሉ አይጠቅመንም ፡፡
ካለፈው እንኳን የቅርብ ታሪካችን ፣ ይህ ሥርዓት ሁሌ ግፊት በሚደርስበት ወቅት ፣ ``ለመደራደር `` በሚል ስንት አዛውንቶች ፣ ስልጣን እንቁልልጭ እያላቸው ፣ ሰነድ እያስፈረመ ፣ ከሕዝብ አጋጭቶ ሁኔታውን ፣ በግልባጩ ለራሱ እንደተጠቀመበት መርሳት፣ ትልቅ የፖለቲካ የዋህነት ነው ፡፡ መደራደር የሚባል እንኳን ነገር ቢኖር ፣ ትግልን ሳያቀዘቅዙ ፣ ትጥቅን ሳያላሉ ፣ በስልት ግፊት በማሳደር እንጂ ፣ የገነባነውን የትግል ስሜት እራሳችን ከናድንለት ቦኋላ ፣
ተርግጦ መገዛት እንጂ ፣ አገዛዙስ ለምንድነው ለመደራደር የሚፈልገው? ለዛውም እኛው መላ እየመታንላቸውና ፣ እየተረጎምንላቸው እንጂ ፣ ከእነሱ የሰማነው ምንም ተስፋ የለም ፡፡
እንዲያውም አገዛዙ ከሃገራችን አልፎ እጁን አርዝሞ ፣ በሚሊዮኖች የሚቆጠር ዶላር በየስርቻው ለአድር ባዮች እየዘራ፣ በጅት መድቦ፣ ያሰማራቸውን የውሸት ተቃዋሚዎች ፣ ``በየስብስቡና፣ በየሕብረቱ `` ውስጥ እየጠቀጠቀ አመራሩን በራሱ ሰርጎ ገቦች ሊያሲዝና ፣ መድረኩን ሊያጣብብ ሲሞክር እየታዘብን ነው ፡፡ ይህ ቀድመው መድረኩን ይዘው ሊሰራ ባማይችል መንገድ ጀምረው ካኮላሹት ቦኋላ ፣ ሰዉ ተስፋ ቆርጦ ሁለተኛ የእውነቱንም እንዳይሞክር ፣ ወይም በእውነቱ እና እነሱ በፈጠሩት መሃከል የተምታታ ሁኔታ ለመፍጠር የሚያደርጉት ጥረት ነው ፡፡

እነዚህ ሰረገው የሚያስገብዋቸው የሰለጠኑ አደናባሪዎች ፣ መንገድ ለይ እንደተንጠለጠለ የሕዝብ ቴሌፎን ፣ ገንዘብ እያቃሙዋቸው ፣ በቀሚስና ፣ በንዋይ እያባበሉዋቸው የሚያስለፈልፋቸው ፣ አስመሳይ ተቃዋሚዎች አንዱ እግራቸውን ጠላት ሰፈር ፣ ሌላውን ተቃዋሚው ሰፈር ተክለው ፣ እንደ ቱቦ አስተላልፉ የተባሉትን ውዥንብር (disinformation) በመረጃ ስም እየበተኑ ፣ አሁንም የተቃዋሚው ክፍል ተጠናክሮ እንዳይደራጅ የሚችሉትን ሁሉ እንደቀድሞው ለማደናገር ሲሞክሩ የምናየው ነው ፡፡ ተቃዋሚውም ፣ ማን ምን እንደነበር የራሱ (trackrecord) ስለሌለው ፣ ትላንት ከውስጣችን ወጥተው ፣ አስር ጊዜ እየካዱን ሲመለሱ ፣ የሚቀበላቸው በእቅፍ አበባ ነው ፡፡

ከአዲሱም ጠቅላይ ሚኒስቴራችን በትክክል በሚገባን ቋዋንቋ የሰማነው ነገር ቢኖር፣ ሊመልሱ የተዘጋጁት የሕዝባችንን ጥያቄ ሳይሆን ፣ የቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስቴር የጀመሩትን ``ራዕይ`` በተጠናከረ መንገድ እውን ማድረግን ነው ፡፡ በሚሊዮን የሚቆጠር ሕዝብ ወጥቶ ``የሃዘናቸው ተካፋይ መሆኑን`` ለዓለም ሕዝብና ፣ ለእኛ ሊያሳዩን ሲነሱ ፣ ከፍተኛ ድጋፍ አለን ፣ በጀመርነው መንገድ እንቀጥላለን ማለት መሆኑን የማይገባን ከሆነ ፣ አስተርጓሚ ሊያስፈልገን ነው ፡፡ ወይንም አንዳንዶች በሌላ ዘረኛ ስሌት ሊነግሩን እንደሚፈልጉት `` ችግራችን ሥርዓቱ ሳይሆን ፣ የመሪው ማንነትና ፣ የመጣበት ክፍልን ነበር የምንቃወም`` ብለው በግልጽ ይነግሩን እንደሆን እንጂ፣ ተስፋ ማየት ገና ምንም አልጀመርንምና ለገላጋይነት አንጣደፍ ፡፡

ባጠቃላይ ይህን ሁሉ ዘርፈ ብዙ የጋራ ችግራችንን፣ ለማስወገድና አደጋውን ለመከላከል የምንችለው፣ ባልሆነ ተስፋ እራሳችንን በማታለል ፣ ወይም በእልህ እነሱ በሄዱበት የጎጥ መንገድ በግልባጩ ተጉዘን ሳይሆን ፣ ሰከን ብለን ፣ ትግላችንን ሳናቀዘቅዝ ፣ ትጥቃችንን ሳናላላ ፣ ለዋናው ብሔራዊ ደህንነታችን ስንል መለስተኛ ልዩነቶቻችንን በይደር አቆይተን ``cease-fire`` ይህች ሓገር እንደ ሃገር እንድትቀጥል የምንፈልግ የአንድነት ሃይሎች ፣ ጋባዥ ሳይጠራን ፣ አስተናጋጅ ሳያስፈልገን፣ ግርግር ፣ ድግስ ፣ አሜሪካ ኦባማ እያልን ``መቀላወጥ`` ሳናበዛ ፣ እንደ ጥንቱ አባቶቻችን ፣ ተፈላልገን ፣ ተጠቃቅሰን ፣ ተሰባስበን ፣ ተደራጅተን፣ ብሔራዊ አጀንዳችንን ቀርጸን በጋራ አምርረን መታገል ስንጀምር ብቻ ነው፡፡

እግዚአብሔር ኢትዮጵያን ሁሌ በራሱ መንገድ ይጠብቃታል ፡፡ብስራት ኢብሳእኛም በቀና የአንድነት መንፈስ እንተባበረው ፡፡

ምኒልክ ሳልሳዊ

ኢትዮጵያ ጋዜጠኞችን በማሰር ከዓለም 2ኛ ደረጃ ተቀምጣለች

December 21/2013

መቀመጫውን በኒዮርክ ያደረገው የጋዜጠኞች መብት ተቆርቋሪ ቡድኑ /CPJ/  ባለፈው ረቡዕ  ይፋ ባደረገው ሪፖርት፤ ጋዜጠኞችን በማሰር ከአለም አስር አገሮች መካከል ኢትዮጵያን በሁለተኛ ደረጃ ያስቀመጠ ሲሆን ኤርትራ ቀዳሚ ሆና፣ ግብፅ በሶስተኝነት ተቀምጣለች፡፡

ሲፔጂ 34 አፍሪካዊ ጋዜጠኞች በሰሜንና ምስራቅ አፍሪካ በእስር ላይ እንደሚገኙ የገለፀው ሲፒጄ፤ በኢትዮጵያ ሰባት ጋዜጠኞች በጻፉት ጽሑፍ ሣይሆን “አሸባሪ” ተብለው በእስር ላይ እንደሚገኙ ጠቁሟል፡፡

አለም አቀፍ የመብት ቡድን (Global rights group) የተባለው ተቋም በበኩሉ፤ የኢትዮጵያ መንግስት ጋዜጠኞቹን ያሰራቸው ሚዲያውን ዝም ለማሰኘት ስለሚፈልግ ነው ብሏል። በኤርትራ 22 ጋዜጠኞች በእስር ላይ እንደሚገኙና አንዳቸውም ፍርድ ቤት እንዳልቀረቡ የገለፀው ሲፒጄ፤ እስረኞቹን በተመለከተ ከኤርትራ መንግስት ምንም አይነት መረጃ ለማግኘት እንደተቸገረ ጠቁሟል፡፡ ጋዜጠኞችን በማሰር የ3ኛ ደረጃን በያዘችው ግብፅም ጋዜጠኞች መታሰር የጀመሩት ፕሬዚዳንት መሀመድ ሙርሲ ወደ ስልጣን ከመጡበት ቀን ጀምሮ ነው ብሏል ሲፒጄ፡፡ የሰሜን ምስራቅ አፍሪካ ጋዜጠኞች ተወካይ ቶም ሮዲስ በናይሮቢ ለCPJ እንደተናገረው፤ በአፍሪካ ቀንድ አገራት የተለያዩ ችግሮች እንዳሉና መንግስታት ስለ ችግሩ መወያየት እንደማይፈልጉ ገልጿል፡፡ ሲፒጄ ጋዜጠኞችን በማሰር ቀዳሚዎቹ 10 አገራት በሚል ከዘረዘራቸው መካከል ቬትናም፣ ሶሪያ፣ ፓኪስታንና ቤልጂየም ይገኙበታል፡፡

Thursday, December 19, 2013

ከወያኔ ክፋትና እብሪት እንጂ ፍትህ አይጠበቅም

December 19/2013

ወያኔ ባለፉት ሃያ ሁለት አመታት የአገራችንን የፍትህ ተቋሞች አንዴ አንደ ቂም መበቀያ ሌላ ግዜ ደግሞ እንደ ማጥቂያ መሳሪያ እየተጠቀመባቸዉ የፖለቲካ ተቀናቃኞቹንና ጥርስ የነከሰባቸዉን የህብረተሰብ አባላት እያሰረ፤ እያሳደደና እየገደለ ከርሞ ዛሬ ላይ ደርሷል። በተለይ ከግንቦት 1997ቱ ምርጫ በኋላ ወያኔ ብዕርና ወረቀት ይዘዉ በሃሳብና በአመክኖ የታገሉትን ሰላማዊ ዜጎች “ሽብርተኞች”፤ ድምጻችን ይሰማ ብለዉ የመብትና የነጻነት ጥያቄ አንግበዉ በሰላማዊ መንገድ የታገሉትን ኢትዮጵያዉያን የእስልምና እምነት ተከታዮች ደግሞ “አክራሪዎች” እያለ ፍርድ ቤት በማቅረብ በፍትህ ተቋሞች በኩል የፖለቲካ ዉሳኔ በማሳለፍ ሠላማዊ ዜጎችን ለረጂም ግዜ እስርና እንግልት ዳርጓል።
ወያኔ ለኢትዮጵያና ለዜጎቿ ደንታ የሌለዉ እና ከስህተቱ የማይማር የግብዞችና የዘረኞች ስብስብ ስለሆነ አሁንም የአገሪቱን የፍትህ ተቋሞች እንደ ማጥቂያ መሳሪያ እየተጠቀመ የኢትዮጵያን ህዝብ በፍርሃት ጨለማ ዉስጥ ሸብቦ እየገዛ ለመኖር የቆረጠ ይመስላል። ባለፈዉ ሳምንት አጋማሽ ላይ የወያኔ አገዛዝ ከአንድ አመት ተኩል በላይ እስር ቤት ዉስጥ አጉሮ ያቆያቸዉን የድምጻችን ይሰማ መሪዎች ከፊሎቹን በነፃ ተለቅቀዋል የሚል ከፊሎቹን ደግሞ ተከላከሉ የሚል ትርጉም የለሽ ብይን ሰጥቷል። በህወሀት ታጋዮች የተሞላዉ ፍርደ ገምድሉ የወያኔ ፍርድ ቤት እንኳን ተከሳሾቹ በተከሰሱበት ሽብር የመፈጸም ወንጀል ምንም አይነት ማስረጃ አልተገኘባቸዉም ሲል አገዛዙ ግን የፖለቲካ ክንዱን በመጠቀም ማስረጃ ያልተገኘባቸዉን ሠላማዊ ዜጎች የተከሰሱበትን መሰረተ ቢስ ክስ ተከላከሉ የሚል የፖለቲካ ዉሳኔ ሰጥቷል።
የወያኔ አገዛዝ የሙስሊሙን ህብረተሰብ የመፍትሄ አፈላላጊ ቡድን መሪዎች ፍርድ ቤት ያቀረባቸዉ ለምዕራባዉያን ለጋሾቹና ለአለም አቀፍ አበዳሪ ድርጅቶች ኢትዮጵያ ዉስጥ ፍትህ ያለ ለማስመሰል ነዉ እንጂ ወያኔ የድምጻችን ይሰማ መሪዎችን የፈረደባቸዉ ያሰራቸዉ ቀን ነዉ። የወያኔ የፍትህ ታሪክ በግልጽ እንደሚያሳየን ወያኔ ግለሰቦችን የሚያስረዉ ለክስ የሚያበቃ ማስረጃ አግኝቶባቸዉ አይደለም፤ ይልቁንም ወያኔ ማስረጃዎችን እየፈበረከ ለፍረድ ቤቶች የሚያቀርበዉ ግለሰቦችን ካሰረና ሰብዓዊ መብታቸዉን ከገፈፈ በኋላ ነዉ። ለምሳሌ የድምጻችን ይሰማ መሪዎችን አስሮ ብዙም ሳይቆይ የእነዚህን ሰላማዊ ዜጎች ተክለ ሰዉነት ጥላሸት የቀባና ግለሰቦቹን ያለ ማስረጃ ወንጀለኛ አድርጎ የፈረጀዉን “ጂሐዳዊ ሀረካት” የሚል የፈጠራ ድራማ ሰርቶ ለህዝብ አቅርቧል።
የፌዴራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ሽብር በመፈጸም ወንጀል ተጠርጥረዉ የቀረቡለትን ግለሰቦች በተከሰሱበት ወንጀል ማስረጃ አላገኘሁባቸዉም ካለ በኋላ ሁሉንም በነጻ አለማሰናበቱ የሚያሳየን የወያኔ ፍርድ ቤቶች ከፖለቲካ ተፅዕኖ ነጻ አለመሆናቸዉን ብቻ ሳይሆን፤ ኢትዮጵያ ዉስጥ ፍርድ ቤቶች የገዢዉ ፓርቲ የማጥቂያ መሳሪያዎች መሆናቸዉን ጭምር ነዉ። የወያኔን አገዛዝ ከሌሎች አምባገነኖች ለይቶ አደገኛ የሚያደርገዉና በምዕራባዉያን መንግስታትና በቀላጤዎቻቸዉ እንዲወደስ ያደረገዉም ይሄዉ አገዛዙ የሚቃወሙትን ኃይሎች የሚያጠፋቸዉ እንደሌሎቹ አምባገነኖች በግልጽ ሳይሆን በህግ ሽፋን ዉስጥ በስዉር መሆኑ ነዉ።
የወያኔዉ ፍርድ ቤት በተመሳሳይ ወንጀል ተከስሰዉ የቀረቡለትን ነገር ግን ምንም መረጃ ያላገኘባቸዉን የድምጻችን ይሰማ መሪዎች ገሚሶቹን በነፃ ለቅቆ የተቀሩትን ጥፋተኛ አለመሆናችሁን አረጋግጡ ብሎ መወሰኑ የወያኔን ሁለት እኩይ አላማዎች ያሳየናል። የመጀመሪያዉ የወያኔ አላማ በአላማቸዉ ጸንተዉ የቆሙትን የድምጻችን ይሰማ መሪዎች መከፋፈል ሲሆን፤ ሁለተኛ አላማዉ ደግሞ የኢትዮጵያ ፍርድ ቤቶች የቀረቡላቸዉን የክስ መዝገቦች በሚገባ አጣርተዉ ዉሳኔ የሚሰጡ መሆናቸዉን ለአለም አቀፉ ህብረተሰብ ለማሳየት ነዉ።
የኢትዮጵያ ህዝብ ግን እንደዚህ አይነቶቹን የወያኔ እኩይ ተግባሮች ካወቀ ዉሎ አድሯል፤ ስለሆነም ከወያኔ ፍትህ ጠብቆ አያዉቅም፤ ወያኔ የክፋትና የበቀል ምንጭ ነዉና ለደፊትም አይጠብቅም። የድምጻችን ይሰማ መሪዎችም ሆኑ ከእነሱ በፊት በግፍ ታስረዉ መከራቸዉን የሚያዩት የፖለቲካ ፓርቲ መሪዎች፤ ጋዜጠኞችና የሲቪክ ማህበራት መሪዎች የታሰሩት ለቆሙለት የፍትህ፤ የነጻነትና የእኩልነት አላማ እንደ አለት ጸንተዉ በመቆማቸዉ ነዉ። እነዚህ ጀግኖች የታሰሩለት አላማ የሁላችንም አላማ ነዉና ፍትህ፤ እኩልነትና ነጻነት የጠማን ኢትዮጵያዉያን ክንዳችንን አስተባብረን የችግሮቻችን ሁሉ ምንጭ በሆነዉ በወያኔ ስርዐት ላይ ክንዳችንን በጋራ እናንሳ!
ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ!!!

በአዲስ አበባ ከዩኒቨርሲቲ ተመርቆ ለመንግስት ከሚሠራ ሰው፤ የቀን ሠራተኛ ደመወዝ ይበልጣል

December 19/2013

ቱሉ ከአዲስ አበባ

አምና ከዩኒቨርስቲ ‹‹ከነሙሉ ክብሩና ጥቅሙ›› ‹በተሰጠው› የመጀመሪያ ዲግሪ ተመርቆ ዘንድሮ በ2006 የመንግስት ስራ የያዘ ጀማሪ ሰራተኛ ጠቅላላ ደሞዙ 1600 ብር ነው፡፡ የጡረታ መዋጮና ሌሎች ተቆራጮች ሳይታሰቡ የመንግስት የስራ ግብር ሲቀነስ ተከፋይ ደሞዙ ከ1300 ብር ያንሳል፡፡ ይህ ለ30 ቀናት ሲካፈል የቀን ገቢው ብር 45 ያህል ይሆናል፡፡ ይህ ደግሞ በወቅቱ ያዲሳባ የጉልበት ስራ ገበያ ከቀን ሰራተኛ ደሞዝ (ብር 60) ያንሳል፡፡ የቀን ሰራተኛ ማለት ምንም የሙያ ስልጠናና ትምህርት የሌለውና ተፈጥሯዊ ጉልበቱን ብቻ የሚሸጥ ሰራተኛ ማለት ነው፡፡ ይህም በዛሬ ሁኔታ መማር ምንም ክብርና ጥቅም እንደማያስገኝ ከማሳየቱም በላይ ኪሳራ መሆኑንም ይጠቁማል፡፡

ይህ አስከፊ ሁኔታ በዚህ የሚቆም አይመስልም፡፡ የቀን ሰራተኛ ደሞዝ ካሁኑ ደረጃ የደረሰው የየጊዜውን የኑሮ ውድነት መነሻ በማድረግ ባሳየው ለውጥ እንጂ ከአምስት ዓመት በፊት 20 ብር እና ከዚያም በታች ነበር፡፡ ዛሬ በሦስት እጥፍ አድጓል፡፡ ባለፉት አምስት ዓመታት ከሁለት እስከ አምስት እጥፍና ከዚያ በላይ ጭማሪ ያሳዩ ለኑሮ አስፈላጊ የሆኑ ብዙ ነገሮች አሉ፡፡ ምግብ፣ የሚከራይ ቤትና ትራንስፖርትን ብቻ ማንሳት ይበቃል፡፡ 800 ብር የነበረው ባለ አንድ ክፍል የኮንዶሚንየም ቤት ከ1600 ብር በላይ ሆኗል፡፡ ባዲሳባ ስርቻዎች ውስጥ ከሚገኙ ቤቶች አንድ ዝቅተኛ መጠለያ ለመከራየትም ከ800 ብር በላይ ይጠይቃል፡፡ የወር ገቢው 1300 ብር የሆነ አንድ የመንግስት ሰራተኛ የደሞዙን ሁለት ሦስተኛ (ብር 800) ለቤት ኪራይ ከፍሎ በሚቀረው በቀን ከ16 ብር በታች በሆነ ገንዘብ ጎስቋላ ኑሮ ለመኖር ይገደዳል፡፡

የመንግስት ደሞዝ የገበያውን ለውጥ ተከትሎ ስለማይለወጥ የመንግስት ሰራተኛው መሽቶ በነጋ ቁጥር የሚቆለለውን የኑሮ ሸክም ለመቋቋም እየተንገዳገደ ፍዳውን ያያል፡፡ በዝቅተኛ የመንደር ምግብ ቤቶች አንድ የሽሮ ምግብ 17 ብር በሚያወጣበት በዚህ የኑሮ ውድነት አንድ ሰው ከ16 ብር ባነሰ ገንዘብ እንዴት መኖር እንደሚችል ለመግለጽ ኢኮኖሚክስ ብቁ ዘዴ አይደለም፡፡ ከሱ ይልቅ ሰው ረሀብን፣ ጉስቁልናንና አዋራጅ ኑሮን ለመቋቋም ያለውን አቅም የሚያጠና ሌላ ሳይንስ ያስፈልጋል፡፡

ይህን አዋራጅ ሁኔታ ከሚገልጹት ነገሮች መካከል ዋነኛው የመንግስት ሰራተኛው ለአገልግሎቱ የሚገባውን ዋጋ የመወሰን ነጻነት የሌለው መሆኑ ነው፡፡ ገበያው ለጫማ ጠራጊው ያገልግሎት ዋጋን የመወሰን አንጻራዊ ነጻነት ይሰጠዋል፡፡ ስለዚህ ጫማ ጠራጊው ባለፉት አምስት ዓመታት አንድ ጫማ ለመጥረግ የሚጠይቀውን ዋጋ ከ1ብር ወደ 2ብር፣ ከ2ብር ወደ 3ብርና ከዚያም በላይ ከፍ በማድረግ የቀን ገቢውን ከ60 ብር በላይ አሳድጓል፡፡ የየወቅቱ ገበያ የሚወሰነውም የአገልግሎታቸውንና የምርታቸውን ዋጋ ገበያ በሚሰጣቸው አንጻራዊ ነጻነት እየተጠቀሙ ከፍ በሚያደርጉ አምራቾች፣ አገልግሎት ሰጪዎችና ነጋዴዎች ነው፡፡ የመንግስት ሰራተኛው ሁሉም የገበያ ሸክማቸውን ለማቅለል በምርታቸውና አገልግሎታቸው ላይ በየጊዜው የሚጨምሩትን ጭማሪ በራሱ የአገልግሎት ዋጋ ላይ አምስት ሳንቲም ሳይጨምር መሸከም ግዴታው ነው፡፡ ያለው ነጻነት የተሰጠውን ክፍያ ተቀብሎና ሌሎች የገበያ ኃይሎችና ግብር ጣዩ መንግስት በየጊዜው የሚቆልሉበትን የኑሮ አሳር ተሸክሞ ማገልገል ወይም ስራውን መተው ብቻ ነው፡፡

ይህ ሁኔታ የተማረው የመንግስት አገልጋይ ክብርና ጥቅም ከቀን ሰራተኛውና ከጫማ ጠራጊው ክብርና ጥቅም ማነሱን ከማመልከቱም በላይ የመንግስት ስራ ክብር ማጣቱንና ውስጣዊ ጤናማነቱም ፈተና ላይ መውደቁን ያሳያል፡፡ የመንግስት ሰራተኛው አገልጋይነት ወደ ባርነት በመቀየር ላይ መሆኑ የችግሩ መነሻ ነው፡፡ ባርያ ማህበራዊ ፍትህን ሊያገለግል የሚችለው እንዴት ነው? ይህ ነው ፈተናው፡፡ መንግስት የሚባለው ተቋም ፍትሀዊ ህሊና እንዳለው ይታመናል፡፡ የመንግስት ሰራተኛው ገበያ የሚነፍገውን ነጻነት የሚያካካስለትም ለገዛ ተቀጣሪው ማህበራዊ ደህንነት የሚቆረቀረው ይኸው ፍትሀዊ ህሊና ነው፡፡ ይህ ህሊና ግን አሁን እየሰራ አይመስልም፡፡ ሰራተኛው እያደር በሚያሸቅበው የገበያ ሁኔታ በአስከፊ የኑሮ አረንቋ እየተዋጠ፣ ወደ አዘቅት እየወረደ ነው፡፡ የተማረው የመንግስት አገልጋይ ‹‹ሙሉ ክብርና ጥቅም›› ገደል ገብቷል፡፡

የቀድሞ የአሜሪካ ረዳት ሚኒስትር ኢትዮጵያንና ኤርትራን ለማስታረቅ ‹‹ጊዜው አሁን ነው›› አሉ

December 19/2013


-የፀጥታው ምክር ቤት በኤርትራ ላይ የጣለውን ማዕቀብ እንዲያነሳ ጠይቀዋል
ቀደም ሲል የኢትዮጵያንና የኤርትራን የድንበር ግጭት በቅርበት ከሚከታተሉት መካከልበአሜሪካ ውጭ ጉዳይ መምርያ ቤት የአፍሪካ ጉዳዮች ረዳት ሚኒስትር የነበሩት፣ ሚስተር ኸርማን ሐንክ ኮኸን፣ ኢትዮጵያንና ኤርትራን በማስታረቅ‹‹ጊዜው አሁን ነው›› በማለት የመፍትሔ ሐሳብ ይዘው ቀረቡ፡፡ 
“Time to Bring Eritrea in from the Cold” [ኤርትራን መታደግ አሁን ነው]
በሚል ርዕስ ‹አፍሪካን አርጉመንትስ› በሚባል ታዋቂ ሚዲያ ላይ በታተመው ጽሑፋቸው፣ በድንበር ግጭቱ የተነሳ ‹‹ሰላምና ጦርነት አልባ›› ሁኔታ ውስጥ የሚገኙት ኢትዮጵያና ኤርትራን ለማስታረቅ ትክክለኛ ጊዜው አሁን ነው ያሉበትን ምክንያት አብራርተዋል፡፡ 
ቀደም ሲል ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊንና ፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂን አቀራርበው በችግሩ ላይ ለማነጋገር ሙከራ ማድረጋቸው የሚነገርላቸው ኸርማን ኮኸን፣ በአሜሪካ መንግሥት በአፍሪካ ጉዳዮች ተሰሚነት ካላቸው መካከል ይጠቀሳሉ፡፡ በሁለቱም አገሮች መካከል ዕርቅ መፍጠር ትክክለኛ ጊዜው አሁን ለመሆኑ አንዳንድ መንደርደርያ ሐሳቦች ጠቁመዋል፡፡ 
ከአልቃይዳ ጋር ቀጥተኛ ትስስር ያለውንና በሶማሊያ ለሚንቀሳቀሰው አክራሪ ቡድን አልሸባብ ወታደራዊና የሎጂስቲክስ ድጋፍ ታደርጋለች በማለት በኤርትራ ላይ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት (ተመድ) ሁለት ጊዜ በጦር መሣሪያ ዝውውርና በአንዳንድ ባለሥልጣናት እንቅስቃሴ ላይ ማዕቀብ የጣለ መሆኑ ሲታወስ፣ ኸርማን ኮኸን ግን እ.ኤ.አ. ከ2009 ጀምሮ የኤርትራ መንግሥት ለአልሸባብ ድጋፍ ስለማድረጉ አንድም ማስረጃ የለም ብለዋል፡፡ 
እሳቸው ራሳቸውን እንደ እማኝ በመቁጠር፣ ‹‹እኛ ኤርትራን በደንብ የምናውቃት ሰዎች፣ የኤርትራ መንግሥት በአፍሪካ ቀንድ እስላማዊ አክራሪነት እንዳይስፋፋ ከሚፈሩ አገሮች እኩል ሥጋት ያለው እንደሆነ እንገነዘባለን፤›› ብለዋል፡፡ 
ቀደም ሲል ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለ ማርያም ደሳለኝ፣ ‹‹አስመራ ድረስ በመሄድ መደራደር እፈልጋለሁ፤›› ማለታቸውንና በቅርቡም ፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ፣ ‹‹ኤርትራ ያለ ኢትዮጵያ ዕጣ ፈንታዋ ጨለማ ነው፤›› መናገራቸውን አውስተው፣ በድንበር ግጭቱ ሳቢያ የተካሄደው ጦርነት ሁለቱ አገሮች አሁን ባሉበት ሁኔታ እንዲቀጥሉ ምንም ምክንያት እንደሌለ ጽፈዋል፡፡
ቀደም ሲል በቀረበው ምክንያት ከኤርትራ ጋር መልካም ግንኙነቱን ጠብቆ ቆይቷል ያሉት የፀጥታው ምክር ቤት ቋሚ አባል የሆነው የአውሮፓ ኅብረት አባል አገር ጥያቄ አቅራቢነት፣ በኤርትራ ላይ የተጣለው ‹‹ሪዞሉሽን 1907›› በመባል የሚታወቀው ማዕቀብ እንዲነሳ ቅድመ ሁኔታ አስቀምጠዋል፡፡ 
በኤርትራ ላይ የተጣለው ማዕቀብ በአሜሪካ አነሳሽነት መሆኑን በጽሑፋቸው ያሰፈሩት ኸርማ ኮኸን፣ አሜሪካ ማዕቀቡ እንዲነሳ ለሚቀርብ ጥያቄ ድምፅን በድምፅ የመሻር መብቷን ተጠቅማ ውድቅ ከማድረግ ይልቅ የመፍትሔ ሐሳቡ ተባባሪ እንድትሆን ጠይቀዋል፡፡ 
ቀጥለውም የሁለቱም አገሮች የድንበር ውዝግብ አጣብቂኝ ያበቃ ዘንድ ኢትዮጵያ በድንበር ኮሚሽኑ ውሳኔ መሠረት ለኤርትራ የተወሰነውን ግዛት ለመስጠት ፈቃደኛ እንድትሆን፣ ሁለቱ አገሮች ግንኙነታቸው ቀድሞ ወደነበረበት እንዲመለስ አጠቃላይና ግልጽ ውይይት እንዲያደርጉ መፍትሔ ያሉትን ሐሳብ አቅርበዋል፡፡ አንድ ገለልተኛ የሆነ አውሮፓዊ አገር ይህንን ዕርቅ እንዲጀምር በመጠየቅ፡፡  
የዕርቁ ውጤት በሁለቱም አገሮች መካከል ተቋርጦ የነበረው ንግድ እንዲቀጥል፣ ኢትዮጵያ የኤርትራን የባህር ወደቦች እንድትጠቀም፣ ሁለቱም አገሮች ከዚህ ግንኙነት ተጠቃሚነታቸውን ለማረጋገጥ መስማማቱ ይረዳቸዋል ብለዋል፡፡ ይህም በሁለቱ አገሮች ይፈጸማል በሚባለው የሰብዓዊ መብት ጥሰት ላይ ለመነጋገር እንደሚያመችና በአፍሪካ ቀንድ ሽብርተኝነትን ለመዋጋት በአሜሪካና በኤርትራ መካከል ወታደራዊ ትስስር ለማድረግ በር ይከፍታል ሲሉ አማራጭ ሐሳባቸውን ይደመድማሉ፡፡  
ኸርማን ሐንክ ኮኸን የዛሬ 23 ዓመት ገደማ በደርግ መንግሥትና በኢሕአዴግ መካከል በለንደን ሊደረግ ታስቦ የከሸፈው ውይይት አደራዳሪ እንደነበሩ ይታወሳል፡፡ ድርድሩ የከሸፈው ኢሕአዴግ በፍጥነት እየገፋ አዲስ አበባ በመቃረቡ ነበር፡፡   

የአማራው ክልል ፕሬዘደንት የነበሩት አቶ አያሌው ጎበዜ ስልጣቸውን ለቀቁ!!

December 19/2013

(EMF) ለረዥም አመታት የአማራው ክልል ፕሬዘደንት የነበሩት አቶ አያሌው ጎበዜ በትላንትናው እለት ከስልጣናቸው እንዲነሱ ተደርጓል። በሳቸውም ምትክ የብአዴን እና የክልሉ ምክትል ፕሬዘደንት የሆኑት አቶ ድጉ አንዳርጋቸው በምትካቸው ስልጣኑን ተረክበዋል። የኢህአዴግ ከፍተኛ ባለስልጣናት እንዳሉት ከሆነ፤ “የአሁኑ የስልጣን ሽግሽግ፤ የቀድሞዎቹን ባለስልጣናት በአዳዲስ ሰዎች የመተካት ስራ ነው” ብለዋል። ይህ አባባል ግን በብዙዎች ዘንድ እምብዛም ተቀባይነት ያገኘ አይመስልም።

ሆኖም ሌሎች አስተያየት ሰጪዎች ለየት ያለ አስተያየት ይሰጣሉ። “አቶ አያሌው ጎበዜ ስልጣናቸውን የለቀቁት፤ ቀደም ሲል የማራ ክልል የነበረው እና አሁን የትግራይ ክልል የወሰደው ሰፊ እና ለም መሬት ለሱዳን መሰጠቱን በመቃወማቸው ነው” ይላሉ። ለዚህም እንደማስረጃ የሚያቀርቡት ከ3 ወራት በፊት፤ በመስከረም ወር ላይ በባህር ዳር ተደርጎ በነበረው የድንበር ጉዳዮች ውይይት ላይ፤ አቶ አያሌው ግልጽ በሆነ መንገድ የሃሳብ ልዩነት ማቅረባቸው እንደሆነ ይነገራል። በወቅቱ ከትግራይ ክልል ሰዎች ጠንካራ የሆነ ተቃውሞ ቀርቦባቸው ነበር። ስልጣናቸውን የለቀቁትም ለህዝብ ጥቅም ሲሉ እራሳቸውን አሳልፈው ለመስጠት ካላቸው ፍላጎት በመነሳት እንደሆነ፤ የራሳቸው ሰዎች ከሚሰጡት አስተያየት ለማወቅ ችለናል።
Ayalew Gobeze
Ayalew Gobeze
በተለይም ከቅርብ ጊዜ ወዲህ፤ በወልቃይት የሚገኙ የአማራ ተወላጅ ተማሪዎች፤ የትምህርት አሰጣጡን በመቃወም “በትግርኛ አንማርም” በማለታቸው ምክንያት ቁጥራቸው 3ሺህ የሚደርሱ አማሮች፤ “በትግርኛ ካልተማራቹህ ወደ አማራ ክልል መሄድ ትችላላቹህ።” ተብለው ክልሉን ለቀው እንዲወጡ በመባላቸው፤ እንዲሁም ለረዥም አመታት የአማራ ክልል ውስጥ የነበረው የራስ ዳሽን ተራራ ግርጌ የሚገኙ ቦታዎችን የትግራይ ሚሊሻዎች እየወሰዱት በመሆናቸው ከዚህ ጋር ተያይዞ በተነሳው ውዝግብ፤ በተጨማሪም የትግራይ እና የአማራ ክልል ባለስልጣናት በድንበር ጉዳይ የሚያነሱትን እልህ አስጨራሽ ድርጊት መሸከም ስላቃታቸው ስልጣናቸውን በፈቃዳቸው እንዲለቁ ግፊት የተደረገባቸው መሆኑን የቅርብ ምንጮች ይገልጻሉ። እንደዚህ አይነት አለመግባባት ሲፈጠር ሁለቱም ወገኖች ይፈሯቸው የነበሩት አቶ መለስ ዜናዊ ጣልቃ በመግባባት ለማግባባት ጥረት ያደርጉ እንደነበር የገለጹት ምንጮቻችን፤ አሁን ግን የትግራይ ባለስልጣናት በማን አለብኝነት ክልሉ ማድረግ የሚገባውን ለማዘዝ እንደሚሞክሩ ተገልጿል። በአገር ውስጥ ክልሎች በድንበር ጉዳይ ሲወዛገቡ፤ በህገ መንግስቱ መሰረት ጉዳዩን የሚመለከተው የፌዴሬሽን ምክር ቤት ነው። የፌዴሬሽን ምክር ቤቱ ደግሞ ቀደም ሲል በአባይ ጸሃዬ አሁን ደግሞ በካሳ ተክለ ብርሃን (ሁለቱም የህወሃት አባላት ናቸው) የሚመራ መሆኑ፤ በአማራ እና በትግራይ መካከል የሚነሱ የድንበር ጉዳዮችን በአድሏዊነት ፍርድ ሲሰጡ ቆይተዋል። አሁን ግን አለመግባባቱ ግን ግልጽ እየሆነ መጥቶ የአማራ ክልል ፕሬዘደንት ስልጣናቸውን እንዲለቁ አድርጓቸዋል።

ይህ የሰሜን ኢትዮጵያ ክልል በኢትዮጵያ ታሪክ ውስጥ በዋግ ሹሞች፣ በራስ እና በንጉሥ ይተዳደር የነበረ ቦታ ነው። ከሸዋ ጀምሮ እስከ ላስታ፣ ወሎ፣ አንጎት፣ ደምብያ፣ ጎጃም፣ ጎንደር እና በጌምድር በአማራ ክልል ውስጥ የሚገኙ ናቸው። አሁንም ሆነ ወደፊት አወዛጋቢ የሆኑት የሰሜን ወሎ እና የበጌምድር ክፍለ ግዛቶች ግን፤ በግድ ወደ ትግራይ ክልል ተወስደዋል። ከነዚህ ውስጥ ደግሞ የበጌምድርን ምዕራባዊ ክፍል፤ የትግራይ ባለስልጣናት ለሱዳን ለመስጠት የሚያደርጉት ድርድር ብዙዎችን ቅር ማሰኘቱ አልቀረም። አሁን ስልጣናቸውን የለቀቁት አቶ አያሌው ጎበዜም በዚህ ቅሬታ ውስጥ እንዳሉ፤ ስልጣናቸውን የለቀቁ መሆናቸው በሰፊው ይነገራል።

አቶ አያሌው ጎበዜ በትጥቅ ትግል ውስጥ የነበሩ፤ ከነታምራት ላይኔ፣ አዲሱ ለገሰ፣ ተፈራ ዋልዋ፣ ህላዌ ዮሴፍ ጋር ሆነው በኢህዴን ውስጥ ያገለገሉ ሰው ናቸው። አዲሱ ለገሰ የክልሉ ፕሬዘደንት በነበረበት ወቅት፤ አቶ አያሌው ጎበዜ ደግሞ የክልሉ ከፍተኛ ተጠሪ ሆነው እንደአውሮፓውያን አቆጣጠር እስከ 2008 ድረስ አገልግለዋል። ከ2008 ጀምሮ አሁን ስልጣናቸውን እስከለቀቁበት ጊዜ ድረስ ደግሞ የክልሉ ፕሬዘደንት ነበሩ። እስከቅርብ ጊዜ ድረስ ከሚያደርጉት እንቅስቃሴ አንጻር፤ ስልጣናቸውን የመልቀቅ ምንም ምልክት እንዳልነበረና በመስከረም ወር በኢትዮጵያ እና በሱዳን መካከል ከተደረገው ስብሰባ በኋላ፤ በተለይም ከትግራይ ባለስልጣናት ጋር ልዩነት ውስጥ መግባታቸው በሰፊው ይነገራል።
Degu Andargachew, the new president of Amara region.
Degu Andargachew, the new president of Amara region.
አዲሱ የአማራ ክልል ፕሬዘዳንት የሆኑት አቶ ድጉ አንዳርጋቸው፤ በሰሜን ወሎ ዳውንት ወረዳ ተወለደው ያደጉ ሲሆን፤ ምክትል ፕሬዘዳንት በነበሩበት ወቅት በዘመድ አዝማድ እንደሚሰሩ በሰፊው ይታማሉ። ለምሳሌ እሳቸው በተወለዱበት ስፍራ ከቀበሌ ጀምሮ እስከወረዳ ድረስ ከፍተኛ ባለስልጣን ናቸው። የዳውንት ወረዳ አቃቤ ህግ አቶ ጥላዬ ወንድምነህ፣ የአቅም ግንባታ ሃላፊ አቶ ጌትዬ ወርቁ ሁለቱም የአቶ ደጉ አንዳርጋቸው የ እህት ልጆች ናቸው። የፍትህ ጽ/ቤት ሃላፊዋ ወ/ሮ በላይነሽ ጥላዬ የአጎት ልጅ ናት። የሰሜን ወሎ አስተዳደር አፈ ጉባዔ አቶ አጥናፉ፣ የውሃ ልማት ሃላፊ አቶ ብርሃኑ ደምሴ ሌሎች ቤተሰቦች ናቸው። አቶ ድጉ አንዳርጋቸው ምክትል ፕሬዘዳንት ተብለው ወደ ባህር ዳር ሲሄዱ የአክስታቸውን ልጅ አቶ ጸጋ አራጌን በስፍራው ሾመው ነበር የሄዱት። አቶ ጸጋ አራጌ ለትምህርት ሲላክ ቦታውን፤ ማለትም የዳውንት ወረዳ አስተዳዳሪ የሆኑትነትን ለአቶ ዣንጥራር የአቶ ገዱ የወንድም ልጅ ሰጥተው ነበር የሄዱት። የወረዳው የጸጥታ ዘርፍ ሃላፊው የአቶ ዣንጥራር ወንድም ናቸው። እንዲህ ያለው የርስ በርስ መጠቃቀም ወይም በስልጣን የመጠቀም ነገር ዝርዝሩ በዛ ያለ ነው። ለአሁኑ ስለአዲሱ ፕሬዘዳንት ማለት የሚቻለው ግን ይህን ያህል ነው።

ሕወሓት እና መስእዋትነት (የሕዝብ ልጆችን መስእዋትነት በክህደት የተካ መንግስት)

December 19/2013

 ሕወሓት እቃወማለሁ የምትሉ ሰዎች የሕወሓት ድርጊት የሆነውን ዘረኝነት ባትረጩ መልካም ነው:: የትግራይ ህዝብ ንጹህ ኢትዮጵያዊ ነው:: የትግሉ ጊዜ የነበረው እና አሁን ያለው የሕወሓት እና የትግራይ ሕዝብ ግንኙነት በጣም ሻክሯል:: የትግራይ ሕዘብ የሕወሓት ደጋፊ ቢሆን ኖሮ በአሁን ወቅት ሕወሓት እርስ በርሱ ባልተባላ ነበር የትግራይ ህዝብ እንደሌላው የኢትዮጵያ ህዝብ ሁሉ እያከከ የታጋዩ እናት ..ልጅሽ በረሃ የገባው ተርቦ ነው እንጂ፤ ለኛ ብሎ አልወጣም.. እየተባለች እያለቀሰች ትገኛለች ፡፡ እነኛ ፈንጅ እርገጥ ካንተ መስዋእትነት በስተጀርባ ድል አለ፤ ብልጽግና አለ ይሉት የነበሩ መሪዎች አሁን በስልጣን ኮርቻቸው ላይ ተፈናጠው ፍጹም ጸረ-ዴሞክራሲና ሙሰኞች ሆነው ይገኛሉ፡፡ ተወዳዳሪ የማይገኝላቸው ጉበኞች ፣ የመሬት ሻጮች ፣ አገር ሻጮች ሆነው አርፈውታል፡፡

በትጥቅ ትግል ጊዜ አንድ አንድ ሰዎች የህወሓትን ስብስብ "የሰዎች ስብስብ" ነው ወይስ "ሰዎች መስለው መላእክት ናቸው የተሰባሰቡበት.. "የሚል ጥርጣሬ ውስጥ ሁሉ እስከመግባት ደርሰው እንደነበር አስታውሳለሁ፡፡ እንደ ዛሬ አያድርገውና በጊዜው የህዝብን ችግር ለመፍታት ህወሓት መስዋእትነት ለመክፈል ተወዳዳሪ አልነበረውም፡፡ የህወሓት መሪዎች ታጋዩ ለመስዋእትነት እንደተፈጠረና የሱ መስዋእትነት ሰላም፣ ብልጽግና፣ ለሁሉም ዜጋ እኩል የስራ እድል፣ ትምህርት እንደሚያገኝ፣ በህግ ፊት ሁሉም ዜጋ እኩል እንደሚሆን በማስተማርና በማሳመን ፈንጅ እንዲረግጥ አድርገውታል፡፡ የዚያ ዘመን ትውልድ የመስዋእት ትውልድ እንደሆነ ተቀብሎና አምኖ ታሪክ ሰርቶ አልፎዋል፡፡

አንድ ግዳጅ አለና ቅድሚያ መስዋእት ለመክፈል ዝግጁ የሆነ ማን ነው ተብሎ በሚጠየቅበት ጊዜ ልክ ተማሪዎች ክፍል ውስጥ ጥያቄ ሲቀርብላቸው ለመመለስ እኔ እኔ እያሉ እንደሚሽቀዳደሙ ሁሉ ታጋዩ ለአንዴና ለመጨረሻ ህይወቱን ለመክፈል ይሽቀዳደም ነበር፡፡ አሁን ያለው ሁኔታ ይመጣል ብሎ አልገመተማ፡፡ በዚሁ ጊዜ አድልዎ ተፈጸመ ሊባል የሚችለው ለመስዋእትነት ቅድሚያ አልሰጠም በማለት ታጋዩ ለበላይ አለቃው (ጠርናፊው) ሂስ ማቅረብ ነበር፡፡ እንደ ዛሬ የህዝብና የመንግስት ሃብት መውረር የሚባለ ነገር አልነበረም፡፡
ታጋዩ ለመስዋእትነት ..እኔ ልቅደም.. እና ..የለም እኔ ነኝ መቅደም ያለብኝ.. ሲል ግን ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ህይወቱን እያጣ መሆኑን ዘንግቶት አልነበረም፡፡ ዳግም ተመልሶ በሱ መስዋእትነት የተገኘውን ድል እንደማያየው አስረግጦ ያውቅ ነበር፡፡ በእኔ መስዋእትነት ጥቂቶች ያውም ፈንጅ እርገጥ ብለው ትእዛዝ በመስጠት የህዝብ መስዋእትነት ከንቱ ነገር ያተርፉበታል የሚል እምነት አልነበረውም፡፡ መስዋእትነቱን ከድተው በስልጣን ይጨማለቃሉ ብሎ አልገመተም ነበር፡፡ ጀግናው አሞራው በደርግ ቁጥጥር ስር ወድቆ ለምንድን ነው በረሃ የሄድከው ሲሉት እንደሚገድሉት እያወቀ ስልጣኑን በህዝብ ለሚመረጥ መንግስት ለማስረከብ ነው አለ፡፡ ለዚህም መስዋእትነት የግድ እንደሚልና ለመስዋእትነት ዝግጁ እንደሆነ በጠላቶቹ ፊት ሆኖ የመለሰው የውስጡን እምነት ደብቆ ጠላት ወይም ደርግ የሚፈልገውን ሃሳብ ተናግሮ ህይወቱን ማትረፍ አቅቶት አልነበረም፡፡ ወይም ደርግ እንደሚረሽነው ዘንግቶትም አይደለም፡፡ ነገር ግን በእሱ መስዋእትነት ህዝቡ ሰላምና ብልጽግና ያገኛል፤ ሁሉም ዜጋ በነፃ የሚኖርባት ኢትዮጵያ ትመጣለች በሚል ቅንነት ነበር፡፡ ህዝብ የመረጠው መንግስት ይመሰረታል፤ ህዝብ የሚቆጣጠረው መንግስት እንጂ መንግስት ህዝብን የሚቆጣጠርበት እና የሚያስፈራራበት አመራር በእኔ መስዋእትነት ይወገዳል የሚል እምነትም ስለነበረው ነው፡፡ በሱ መስዋእትነት፣ በታጋዮች ቤተሰብ እና በጭቁኑ ህዝብ የተመረጠው መንግስት ህዝብ የሚቆጣጠረው ይሆናል ብሎ ነበር፡፡ በተገላቢጦሽ በዚሁ ጊዜ በጠላትነት ተሰልፈው ይዋጉት የነበሩና አሁን ከመስዋእትነት ከተረፉ በስልጣን ላይ ያሉ ታጋዮች የታጋዩን እናት አባትና ልጆች እንደ ጠላት ፈርጀው ያሰቃዩታል የሚል እምነት አልነበረውም፡፡ ፈንጅ እርገጥ እያሉ መስዋእትነት እንድንከፍል ትእዛዝ ይሰጡን የነበሩ ሰዎች በወላጆቻችንና ልጆቻችን ላይ ክህደት ይፈጽማሉ ብሎ ማን ይገምታል፡፡ ግን በተግባር ክህደት ተፈጸመ፡፡
የታጋዩ እናት ..ልጅሽ በረሃ የገባው ተርቦ ነው እንጂ፤ ለኛ ብሎ አልወጣም.. እየተባለች እያለቀሰች ትገኛለች ፡፡ እነኛ ፈንጅ እርገጥ ካንተ መስዋእትነት በስተጀርባ ድል አለ፤ ብልጽግና አለ ይሉት የነበሩ መሪዎች አሁን በስልጣን ኮርቻቸው ላይ ተፈናጠው ፍጹም ጸረ-ዴሞክራሲና ሙሰኞች ሆነው ይገኛሉ፡፡ ተወዳዳሪ የማይገኝላቸው ጉበኞች ፣ የመሬት ሻጮች ፣ አገር ሻጮች ሆነው አርፈውታል፡፡ ክህደት የፈፀመ ልዩ መንግስት የተባለበትም ለዚሁ ነው፡፡

ከወያኔ ክፋትና እብሪት እንጂ ፍትህ አይጠበቅም

December 19/2013

ወያኔ ባለፉት ሃያ ሁለት አመታት የአገራችንን የፍትህ ተቋሞች አንዴ አንደ ቂም መበቀያ ሌላ ግዜ ደግሞ እንደ ማጥቂያ መሳሪያ እየተጠቀመባቸዉ የፖለቲካ ተቀናቃኞቹንና ጥርስ የነከሰባቸዉን የህብረተሰብ አባላት እያሰረ፤ እያሳደደና እየገደለ ከርሞ ዛሬ ላይ ደርሷል። በተለይ ከግንቦት 1997ቱ ምርጫ በኋላ ወያኔ ብዕርና ወረቀት ይዘዉ በሃሳብና በአመክኖ የታገሉትን ሰላማዊ ዜጎች “ሽብርተኞች”፤ ድምጻችን ይሰማ ብለዉ የመብትና የነጻነት ጥያቄ አንግበዉ በሰላማዊ መንገድ የታገሉትን ኢትዮጵያዉያን የእስልምና እምነት ተከታዮች ደግሞ “አክራሪዎች” እያለ ፍርድ ቤት በማቅረብ በፍትህ ተቋሞች በኩል የፖለቲካ ዉሳኔ በማሳለፍ ሠላማዊ ዜጎችን ለረጂም ግዜ እስርና እንግልት ዳርጓል።
ወያኔ ለኢትዮጵያና ለዜጎቿ ደንታ የሌለዉ እና ከስህተቱ የማይማር የግብዞችና የዘረኞች ስብስብ ስለሆነ አሁንም የአገሪቱን የፍትህ ተቋሞች እንደ ማጥቂያ መሳሪያ እየተጠቀመ የኢትዮጵያን ህዝብ በፍርሃት ጨለማ ዉስጥ ሸብቦ እየገዛ ለመኖር የቆረጠ ይመስላል። ባለፈዉ ሳምንት አጋማሽ ላይ የወያኔ አገዛዝ ከአንድ አመት ተኩል በላይ እስር ቤት ዉስጥ አጉሮ ያቆያቸዉን የድምጻችን ይሰማ መሪዎች ከፊሎቹን በነፃ ተለቅቀዋል የሚል ከፊሎቹን ደግሞ ተከላከሉ የሚል ትርጉም የለሽ ብይን ሰጥቷል። በህወሀት ታጋዮች የተሞላዉ ፍርደ ገምድሉ የወያኔ ፍርድ ቤት እንኳን ተከሳሾቹ በተከሰሱበት ሽብር የመፈጸም ወንጀል ምንም አይነት ማስረጃ አልተገኘባቸዉም ሲል አገዛዙ ግን የፖለቲካ ክንዱን በመጠቀም ማስረጃ ያልተገኘባቸዉን ሠላማዊ ዜጎች የተከሰሱበትን መሰረተ ቢስ ክስ ተከላከሉ የሚል የፖለቲካ ዉሳኔ ሰጥቷል።
የወያኔ አገዛዝ የሙስሊሙን ህብረተሰብ የመፍትሄ አፈላላጊ ቡድን መሪዎች ፍርድ ቤት ያቀረባቸዉ ለምዕራባዉያን ለጋሾቹና ለአለም አቀፍ አበዳሪ ድርጅቶች ኢትዮጵያ ዉስጥ ፍትህ ያለ ለማስመሰል ነዉ እንጂ ወያኔ የድምጻችን ይሰማ መሪዎችን የፈረደባቸዉ ያሰራቸዉ ቀን ነዉ። የወያኔ የፍትህ ታሪክ በግልጽ እንደሚያሳየን ወያኔ ግለሰቦችን የሚያስረዉ ለክስ የሚያበቃ ማስረጃ አግኝቶባቸዉ አይደለም፤ ይልቁንም ወያኔ ማስረጃዎችን እየፈበረከ ለፍረድ ቤቶች የሚያቀርበዉ ግለሰቦችን ካሰረና ሰብዓዊ መብታቸዉን ከገፈፈ በኋላ ነዉ። ለምሳሌ የድምጻችን ይሰማ መሪዎችን አስሮ ብዙም ሳይቆይ የእነዚህን ሰላማዊ ዜጎች ተክለ ሰዉነት ጥላሸት የቀባና ግለሰቦቹን ያለ ማስረጃ ወንጀለኛ አድርጎ የፈረጀዉን “ጂሐዳዊ ሀረካት” የሚል የፈጠራ ድራማ ሰርቶ ለህዝብ አቅርቧል።
የፌዴራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ሽብር በመፈጸም ወንጀል ተጠርጥረዉ የቀረቡለትን ግለሰቦች በተከሰሱበት ወንጀል ማስረጃ አላገኘሁባቸዉም ካለ በኋላ ሁሉንም በነጻ አለማሰናበቱ የሚያሳየን የወያኔ ፍርድ ቤቶች ከፖለቲካ ተፅዕኖ ነጻ አለመሆናቸዉን ብቻ ሳይሆን፤ ኢትዮጵያ ዉስጥ ፍርድ ቤቶች የገዢዉ ፓርቲ የማጥቂያ መሳሪያዎች መሆናቸዉን ጭምር ነዉ። የወያኔን አገዛዝ ከሌሎች አምባገነኖች ለይቶ አደገኛ የሚያደርገዉና በምዕራባዉያን መንግስታትና በቀላጤዎቻቸዉ እንዲወደስ ያደረገዉም ይሄዉ አገዛዙ የሚቃወሙትን ኃይሎች የሚያጠፋቸዉ እንደሌሎቹ አምባገነኖች በግልጽ ሳይሆን በህግ ሽፋን ዉስጥ በስዉር መሆኑ ነዉ።
የወያኔዉ ፍርድ ቤት በተመሳሳይ ወንጀል ተከስሰዉ የቀረቡለትን ነገር ግን ምንም መረጃ ያላገኘባቸዉን የድምጻችን ይሰማ መሪዎች ገሚሶቹን በነፃ ለቅቆ የተቀሩትን ጥፋተኛ አለመሆናችሁን አረጋግጡ ብሎ መወሰኑ የወያኔን ሁለት እኩይ አላማዎች ያሳየናል። የመጀመሪያዉ የወያኔ አላማ በአላማቸዉ ጸንተዉ የቆሙትን የድምጻችን ይሰማ መሪዎች መከፋፈል ሲሆን፤ ሁለተኛ አላማዉ ደግሞ የኢትዮጵያ ፍርድ ቤቶች የቀረቡላቸዉን የክስ መዝገቦች በሚገባ አጣርተዉ ዉሳኔ የሚሰጡ መሆናቸዉን ለአለም አቀፉ ህብረተሰብ ለማሳየት ነዉ።
የኢትዮጵያ ህዝብ ግን እንደዚህ አይነቶቹን የወያኔ እኩይ ተግባሮች ካወቀ ዉሎ አድሯል፤ ስለሆነም ከወያኔ ፍትህ ጠብቆ አያዉቅም፤ ወያኔ የክፋትና የበቀል ምንጭ ነዉና ለደፊትም አይጠብቅም። የድምጻችን ይሰማ መሪዎችም ሆኑ ከእነሱ በፊት በግፍ ታስረዉ መከራቸዉን የሚያዩት የፖለቲካ ፓርቲ መሪዎች፤ ጋዜጠኞችና የሲቪክ ማህበራት መሪዎች የታሰሩት ለቆሙለት የፍትህ፤ የነጻነትና የእኩልነት አላማ እንደ አለት ጸንተዉ በመቆማቸዉ ነዉ። እነዚህ ጀግኖች የታሰሩለት አላማ የሁላችንም አላማ ነዉና ፍትህ፤ እኩልነትና ነጻነት የጠማን ኢትዮጵያዉያን ክንዳችንን አስተባብረን የችግሮቻችን ሁሉ ምንጭ በሆነዉ በወያኔ ስርዐት ላይ ክንዳችንን በጋራ እናንሳ!
ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ!!!

Ayalew Gobeze, president of the Amhara Regional State, has resigned

December 19/2013

Amhara Regional State Changes Top Leader

Image

Ayalew Gobeze, president of the Amhara Regional State, has resigned from his office today, and replaced by his deputy, Gedu Andargachew, sources disclosed to Fortune.

The congress of the Amhara National Democratic Movement (ANDM), the ruling party in the region, is currently undergoing in Bahir Dar, the seat of the regional state. It has not been clear what transpired this change. But senior leaders in the party say it is part of the succession plan the party has been carrying out in recent years.

Ayalew has been serving the regional state as president since 2008, where he began his debut as a senior official of the regional cabinet in 2005, under Addisu Legesse. He is also a member of the House of Federation, since 2005. However, his ascendance in the ruling party began in 2006, when he was first elected as an executive committee member of the ANDM, during the sixth congress of the party.

A former teacher when the insurgents advancing downward to the centre in the early 1990s, Ayalew represents a generation of EPRDFites that have joined the party after the fall of the military government, in May 1991. He is the peer of Demeke Mekonnen, now chairman of the ANDM and deputy prime minister, and Gegu. The latter began his ascendancy in 2005, after he was appointed to be member the Budget Subsidy & Revenues Affairs Standing Committee of the House of Federation. Chaired by Ayalew, the 10-member committee had comprised politicians such as Shiferaw Shenkute, now minister of Education, Redwan Hussien, now director general of Government Communications Affairs Office, Abadula Gemeda, speaker of Parliament, and Abay Woldu, president of the Tigray Regional State. He became an executive committee member of the ANDM in the same year as that of Ayalew, although both have been members of the party’s central committee since 1999.

Ayalew’s next move has yet to be disclosed, although it is possible that he will be appointed as an ambassador to one of Ethiopia’s overseas missions, sources close to the congress disclosed to Fortune.

Ethiopian Airlines Boeing 767 runway excursion in Tanzania

December 19, 2013

Incident: Ethiopian B763 at Arusha on Dec 18th 2013, fuel emergency, landing on short runway and runway excursion

Flight ET-815 from Addis Ababa (Ethiopia) to Kilimanjaro (Tanzania)
An Ethiopian Airlines Boeing 767-300, registration ET-AQW performing flight ET-815 from Addis Ababa (Ethiopia) to Kilimanjaro (Tanzania), could not land in Kilimanjaro due to a disabled light aircraft on the runway and entered a holding. The crew subsequently declared emergency due to low fuel and diverted to Arusha for a safe landing on runway 27 (length 1620 meters/5300 feet) at 13:15L (10:15Z). At the end of the runway the aircraft turned left as if attempting to turn around for backtracking and came to a stop with all gear on soft ground. No injuries occurred, the aircraft received no visible damage.
The airline confirmed the aircraft diverted because a Cessna was disabled on the runway of Kilimanjaro, however, did not explain why the aircraft diverted to Arusha (27nm from Kilimanjaro Airport) with too short a runway rather than diverting to Mombasa (Kenya, 154nm from Kilimanjaro) or Nairobi (Kenya, 127nm from Kilimanjaro) featuring suitable runways.
An investigation has been opened into the occurrence.
Ground witnesses report, that the crew managed to bring the aircraft to a full stop just before the end of the runway, but then attempted to maneouver the aircraft to backtrack the runway which is when they went off paved surface.
A listener on frequency reported the aircraft was sent into a holding at Kilimanjaro NDB (KB, 293kHz) southwest of Kilimanjaro Airport and south of Arusha Airport. Arusha’s runway was visible from the holding with the same orientation as Kilimanjaro’s runway (09/27 at 3600 meters length). The crew thus obviously believing to land at Kilimanjaro Airport touched down at Arusha.
Metars Kilimanjaro:
HTKJ 181100Z 09010KT 9999 FEW032CB SCT033 31/17 Q1012 NOSIG
HTKJ 181000Z 09012KT 9999 FEW030CB SCT031 31/17 Q1012 NOSIG
HTKJ 180900Z 09010KT 9999 FEW028SC SCT280 30/18 Q1013 NOSIG
Metars Arusha:
HTAR 181100Z 33010KT 9999 FEW026 FEW027CB 26/15 Q1016
HTAR 181000Z 33015KT 9999 FEW026CB BKN026 26/15 Q1017
HTAR 180900Z 33010KT 9999 FEW026CB SCT026 26/15 Q1018
Metars Nairobi:
HKJK 181200Z 04010KT 9999 FEW027CB BKN028 25/15 Q1017 NOSIG
HKJK 181130Z 07010KT 9999 BKN027 25/14 Q1017 NOSIG
HKJK 181100Z 06012KT 9999 BKN027 24/14 Q1018 NOSIG
HKJK 181030Z 06011KT 9999 BKN027 25/15 Q1018 NOSIG
HKJK 181000Z 05011KT 9999 BKN027 25/14 Q1019 NOSIG
HKJK 180930Z 06010KT 9999 SCT026 24/14 Q1019 NOSIG
HKJK 180900Z 02010KT 9999 SCT026 23/13 Q1020 NOSIG
Metars Mombasa:
HKMO 181300Z 06008KT 9999 FEW027 31/24 Q1007 NOSIG
HKMO 181200Z 07012KT 9999 SCT027 31/24 Q1007 NOSIG
HKMO 181100Z 35005KT 9999 SCT027 33/21 Q1008 NOSIG
HKMO 181000Z 33015KT 9999 FEW025CB BKN026TCU 32/23 Q1010 NOSIG
HKMO 180900Z 34010KT 9999 FEW025CB BKN026TCU 31/23 Q1011 NOSIG