Monday, October 12, 2015

ከመድረክ/ሰማያዊ/መኢአድ ጋር ለመነጋገር እንደሚፈልጉ አቶ ሃይለማሪያም ገለጹ - የሚሊዮኖች ድምጽ

October 12,2015
Millions of voices for freedom - UDJ's photo.
“ከስፖርት ጀምሮ እስከ ሥራ በፓርቲ አባላነት ነው “ ወ/ር ጽጌ ጥበቡ
“ እርስዎ ከምለስ ራ፤እይ ተላቀው ይራስዎት ራእይ መቼ ነው የሚኖሮት ? “ ጥያቄ ለአቶ ኃይለማሮያ
ያለፈው አርብ መስከረም 28 እና ቅዳሜ መስከረም 29 ቀን፣ ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማሪያም ደሳለኝ በተገኙበት፣ በአምስቱ አመቱ የእድገትና ትራስንፎርሜሽን እቅድ ዙሪያ፣ ኢሕአዴግ ስብሰባ አድርጓል። በአመስት አመቱ እቅዱ ዙሪያ ከመነጋገር በፊት በሕዝብ የሚነሱ ወቅታዊ የሰብአዊ መብት፣ የፍትህ መጓደልና የብሄራዊ መግብባባት ዙሪያ ዉይይቶች መቅደም አለባቸው በሚል፣ የአራት ደርጅቶች ስብስብ የሆነው መድረክ፣ የሰማያዊ ፓርቲና የመላው ኢትዮጵያ አንድነት ደርጅት (መኢአድ ) ስብሰባዉን አልተሳተፉም።
ከመድረክ ቀጥሎ በ2007 በርካታ ተወዳዳሪዎች በማሰለፍ ሁለተኛ የሆነው ኢዴፓን ፣ ጨመሮ ሌሎች አናሳ ድርጅቶች ስብሰባዉን ተሳትፈዋል። በዶር ጫኔ ከበደ የሚመራው ፣ ኢዴፓ፣ ጥያቄዎችን በማንሳት ጠንካራ ክርክሮች እንዳደረገ ለማረጋገጥ ችለናል። የኢዴፓ ተወካዮች፣ በድፍረትና በግልጽ ያለፈው የአምስት አመት እቅድ እንዳልተሳካ፣ መረጃዎች በማስቀመጥ ለማሳየት የሞከሩ ሲሆን፣ መሰረታዊ የፍትህ የመልካም አስተዳደር፣ የዴሞክራሲ ለዉጦች ተደርገው፣ ሕዝቡን ባቀፈና ባሳተፈ መልኩ ስራ ካልተሰራ፣ መጨው የአምሰት አመት እቅድም አይሳከም ሲሉ ለነ አቶ ሃይለማሪያም ደሳለኝ ተናግረዋል።
ወ/ሮ ጽጌ ጥበቡ የሚባሉ የኢዴፓ ምክር ቤት አባል፣ “ ከስፐርት ጀመሮ እስከ ሥራ፣ የኢሕአዴግ ፓርቲ አባል ካልተኮነ በቀር ምንም ነገር ማደረግ አይቻልም” ሲሉ ሕወሃት/ኢሕአዴግ ኢኮኖሚዉን፣ ፖለቲካዉን፣ ሜዲያዉና ሌሎች ሁሉንም ተቋማት ብቻውን እንደሚቆጣጠር በመገልጽ ፣ ተቋማት ገለልተኛ መሆን እንዳለባቸው አሳስበዋል።
“ እርስዎ የመለስን ፎቶ እየያዙ፣ በመለስ ራእይ እያሉ ነው። የራስዎት ራእይ የልዎትም ወይ ? ሲሉ ኤደፓዎች አቶ ኃይለማሪያም ደሳለኝ በላያቸው ላይ ያለፈው የአቶ መለስ ጥላ ገፈው ፣ ህዝብን አክብረው ፣ “ዴሞክራሲ የሕልዉና ጉዳይ ነው “ ብለው ብዙ ጊዜ የሚናገሩት ተግባራዊ እንዲያደርጉ አሳስበዋል።
አቶ ኃይለማሪያም ደርጅታቸው ብዙ ስህተት ያለው፣ ብዙ ነገሮችን ማስተካከል ያለበት እንደሆነ ያመኑ ሲሆን፣ ከተቃዋሚዎች ጋር እየደጋገሙ በመነጋገገር ያሉትን ችግሮች ለመፍታት እንደሚሞክሩም ቃል ገብተዋል።
በስብሰባው ያልተካፈሉ ደርጅቶችም ስብሰባዉ ላለመካፈልል የወሰኑትን ዉሳኔ እንደሚያከብሩ የገለጹት አቶ ኃይለማሪያም፣ በስብሰባው ካልተገኙ ደርጅቶች ጋር ለመወያየትና ለመነጋገር ፍላጎትና ፍቃደኝነቱ እንዳላቸዉም በስብሰባው ወቅት ገልጸዋል።
በኢዴፓና መድድረኩ ላይ በነበሩት በኢሕአዴግ ባለስልጣናት መካከል የጦፈ ክርክርና ምልልሶች የነበብሩ ቢሆንም በሕወሃቱ ጌታቸው ረዳ የሚመራው ኢቢሲ/ኢቲቪ ግን በስብሰባው የነበረዉን ሁኔታ በግልፅ ለሕዝብ ከማቅረብ፣ እንደ አቶ ትግስቱ አወሉ ያሉትን የሕወሃት አሻንጉሊቶች በማቅረብ፣ የዉሸት ዘገባን ማቅረቡን መርጧል።

No comments: