Friday, December 7, 2012

መንግሥት ሕገ-መንግሥቱን ጥሶ በሐይማኖታዊ ጉዳያችን ጣልቃ ገብቷል የሚሉት ኢትዮጵያዉን ሙስሊሞችም ሕገ-መንግሥቱ እንዲከበር አበክረዉ እየጠየቁ ነዉ

Muslime feiern das Ende des Ramadans im Nationalstadium von Addis Abeba, Äthiopien
Copyright: Getachew Tedla/DW, 
19.08.2012, Addis Abeba, Äthiopien

 

 መንግሥት ሕገ-መንግሥቱን ጥሶ በሐይማኖታዊ ጉዳያችን ጣልቃ ገብቷል የሚሉት ኢትዮጵያዉን ሙስሊሞችም ሕገ-መንግሥቱ እንዲከበር አበክረዉ እየጠየቁ ነዉ።የአዲስ አበባ ሙስሊሞች ዛሬ ከጁመዓ ሶላት በኋላ በተለይ የሐይማኖት ነፃነት የተደነገገበት አንቀፅ ሃያ-ሰባት መጣሱን አዉግዘዋል።
የኢትዮጵያን ሕገ-መንግሥት የማስከባሩ ሐላፊነት ከሐገሪቱ መንግሥት ይልቅ የመብት፥ ነፃነት ተሟጋቾችና ሐላፊነት የሚሰማቸዉ ወጣቶች የመሆኑ እንቆቅልሽ ገሐድ እየወጣ ነዉ።ዞን-ዘጠኝ በሚል መጠሪያ የተደረጁ የድረ-ገፅ ወጣቶት ታዳሚዎች ሕገ-መንግሥቱ የፀደቀበትን አስራ-ስምተኛ ዓመት ምክንያት በማድረግ «ሕገ-መንግሥቱ ይከበር» የሚል ዘመቻ ትናንት ጀምረዋል።መንግሥት ሕገ-መንግሥቱን ጥሶ በሐይማኖታዊ ጉዳያችን ጣልቃ ገብቷል የሚሉት ኢትዮጵያዉን ሙስሊሞችም ሕገ-መንግሥቱ እንዲከበር አበክረዉ እየጠየቁ ነዉ።የአዲስ አበባ ሙስሊሞች ዛሬ ከጁመዓ ሶላት በኋላ በተለይ የሐይማኖት ነፃነት የተደነገገበት አንቀፅ ሃያ-ሰባት መጣሱን አዉግዘዋል።

No comments: