Wednesday, December 5, 2012


በጅማ ዩኒቨርስቲ በተነሳው ተቃውሞ የታሰሩት ተማሪዎች ቁጥር ከ100 በላይ መድረሱን የፖሊስ ምንጮች ገለጹ

 
 
ህዳር ፳፮ (ሃያ ስድስት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም
ኢሳት ዜና:-ስማቸው እንዳይገለጥ የፈለጉ ፖሊሶች ለኢሳት እንደገለጡት በእስር ላይ የሚገኙት ተማሪዎች ቁጥር 115 ሲሆን፣ ከእነዚህም መካከል የተወሰኑት ትናንት ተለቀዋል። 2 ተማሪዎች ለህይወት አስጊ በሆነ ሁኔታ ላይ እንደሚገኙ ምንጮች ጠቁመዋል። መጠነኛ ጉዳት የደረሰባቸው ተማሪዎች በመቶዎች የሚቆጠሩ መሆኑን የገለጡት ፖሊሶች፣ ትምህርት አንጀምርም ያሉትን ተማሪዎች ከሙስሊም እንቅስቃሴና ከተቃዋሚዎች ጋር በማያያዝ ለመክሰስ መታቀዱን ገልጸዋል።
ተማሪዎች ያነሱት ጥያቄ ከምግብ ጋር የተያያዘ ቢሆንም ፣ መንግስት ግን ጉዳዩን ፖለቲካዊ አንድምታ ሊሰጠው በመፈለግ ፌደራል ፖሊሶችን በመላክ ተማሪዎችን እንዳስደበደ መዘገባችን ይታወሳል።

No comments: