Sunday, December 9, 2012

የወያኔ ፌደራል ፖሊስ በዩኒ ቨርሲቲው ቅጥር ግቢ በመግባት የጅማ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎችን ደበደበ

በጂማ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ላነሷቸው የመብት ጥያቄዎች እንደተለመደው የጨካኙ ወያኔ አገዛዝ ፌድረአል ፖሊሶች ዩኒቨርሲቲው ቅጥር ግቢ ድረስ በመግባት ለቀረቡት ጥያቄዎች ምላሽ ተማሪዎች በቆመጥ መደብደባቸዉን በዩኒቨርሲቲው ውስጥ የሚገኝ ምንጮችን በመጥቀስ የግንቦት ሰባት ዘጋቢ በላከልን ዜና አመለከተ። የጂማ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ጥያቄዎቻችን ይመለስልን በሚል ለዩኒቨርሲቲው አስተዳደር ጥያቄ ያቀረቡ ቢሆንም ለጥያቄአቸው ተገቢ ምላሽ ሳይሆን የ ጠበቃቸው የወያኔ ፈደራል ፖሊሶች ዱላ መሆኑን ዘጋቢያችን አክሎ ገልጿል። ተማሪዎቹ በዋናነት ካነሷቸው ጥያቄዎች በዋነኛነት የምንማረው ትምህርት ጥራት በጣም የወረደና ደረጃንም ያልጠበቀ በመሆኑ ሊስተካከል ይገ ባል፡ የሚል እንደሆነ የደረሰን ዘገባ ያመለክታል።
በዚሁና ተያያዥ በሆኑ የመብት ጥያቄዎች ምክንያት የወያኔ ፌደራል ፖሊሶች ዩኒ ቨርሲቲው ግቢ ውስጥ ገብተው ተማሪዎችን ደብድበዋል፣ መስኮቶችም ተሰባብረዋል፡፡ ከዚሁ የወያኔ አገዛዝ መረን የለቀቀ ተግባር ጋር በተያያዘ ተማሪዎችም ቁጣቸው እየጨመረ መሄዱ የታወቀ ሲሆን በተመሳሳይ መልኩ ይህ ጥያቄ በወልቂጤና ነቀምት ዩኒ ቨርሲቲዎች በመቀጣተል ላይ መሆኑን ዘጋቢያችን ገልጿል።
ከዚሁ ዘገባ ጋር በተያያዘ ዓንድ ስሙ እንዳይገለጽ የጠየቀ የዩኒቨርሲቲው ተማሪ ለዘጋቢያችን እንደገለጸው ወያኔ በ2004 ዓ.ም ባካሄደው የዩኒቨርሲቲዎች ጉባኤ ላይ ጅማ ዩኒቨርሲቲ በትምህርት ጥራት አንደኛ ደረጃ ላይ ይገ ኛል በሚል እንዲመረጥ አድርጎ የነበረ ሲሆን በትምህርት ጥራት አንደኛ ተብሎ ተመረጠ ዩኒቨርሲቲ ላይ ይህ ጥያቄ መነ ሳቱ ችግሩ ምን ያህል ስር የሰደደ እንደሆነ እና የ ወያኔ ድራማ ምን ያህል እየ ተጋለጠ ለመሆኑ ታላቅ ማሳያ ነ ው፡ በማለት አስተያየቱን ሰጥቷል።
ዘረኛው የወያኔ አገዛዝ በአንዳን ዩኒቨርሲቲዎች አንድም የቤተ መጽሃፍና የላብራቶር አገልግሎት ሳይኖራቸው ተማሪዎች ገብተውና ምንም እውቀትን ሳይቀስሙ እንዲመረቁ በማድረግ ተግባር ላይ ተጠምዶ እንደሚገኝ ቀደም ብሎ መዘገቡ ይታወሳል።
ዘረኛው የወያኔ አገዛዝ በኢትዮጵያዊያን ላይ እያደረሰ ያለው ግፍና በደል መጠኑን ካለፈ እጂግ በርካታ ዓመታት ያለፉ ሲሆን፣ በተለይም ባሁኑ ወቅት ኢትዮጵያ ውስጥ በድንገት ምን ሊፈጠር እንደሚችል መገመት የሚያዳግት ሁኔታ ላይ እንደሚገኝ ዘገባዎች እያመለከቱ ነው። የኢትዮጵያ ሳተላይት ቴሌቪዥን ኢሳት ከታዋቂው የኢኮኖሚክ ባለሙያ ፕ/ር በፈቃዱ ደግፌ ባደረገው ቃለምልልስ የወያኔ አገዛዝ የህዝብን ብሶት አልሰማ በማለቱ አንድ ቀን ያልጠበቀው አደገኛ ሁኔታ ሊፈጠርበት እንደሚችል ማስጠንቀቃቸው ታውቋል። ዶር በፈቃዱ በቃለ ምልልሳቸው “ህዝቡ የሚሄድበት ቦታ አጥቷል፣ ብሶታል” ያሉ ሲሆን ከአረብ አብዮት የምንማረው ህዝብ መሪ ሳያስፈልገው በብሶቱ ብቻ ሆ ብሎ ሊነሳ የሚችል መሆኑን ነው ሲሉ ገልጸዋል። ፕ/ር በፈቃዱ ደግፌ በቃለ ምልልሳቸው ባሁኑ ሰአት የኢትዮጵያ ባለቤት የኢትዮጵያ ህዝብ ሳይሆን ወያኔ ኢህአዴግ ነው ያሉ ሲሆን በኢትዮጵያ ውስጥ ያለሙስና ስራ መስራት እንደማይቻል ገልጸዋል።
 
 

No comments: