Saturday, December 29, 2012

የመከላከያ ሚኒስቴር በድንጋጤ እየታመሰ ነው ::በርካታ ወጣት መኮንኖች ታስረዋል

የመከላከያ ሚኒስቴር በድንጋጤ እየታመሰ ነው ::በርካታ ወጣት መኮንኖች ታስረዋል
በአንድ ወገን የታጠረው የመከላከያ ሚኒስቴር መስርያ ቤት የወያኔ ጄኔራሎችን ሹመት ተከትሎ በ መኮንኖች መሃል በተነሳው ክፍፍል እና አለመግባባት እየበጠበጡ ናቸው ያላቸዉን መኮንኖች እያሰረ መሆኑን የምንሊክ ሳልሳዊ ምንጮች ከወደ አገር ቤት ተናግረዋል::

ይህ እያፈጠጠ እና ገሃድ እየወጣ ያለው ክፍፍል እና አለመግባባት በተለያዩ የጦር ክፍሎች ውስጥ የሚሰሩ ወጣት መኮንኖች ያለውን አድሎዋኢ አሰራር እየተቃወሙ ጥያቄ በማንሳታቸው ከተቃዋሚ ሃይላት ጋር ግንኙነት ፈጥረው ነው ተብለው እየታሰሩ ነው::
በ97 በተደረገው ምርጫ ወያኔው መሸነፉን አምነው ያልተቀበሉ ጄኔራሎች የአማራ እና የኦሮሞ ብሄር መኮንኖችን ቅንጅትን ደግፋችዋል በሚል ሰበብ ከ ሰራዊቱ መባረራቸዉን ያወሱት የሳልሳዊ ምንጮች አሁንም የሚደረገውን አድልዎ በመቃወም ተበሳጭተው የመብት ጥያቄ ያነሱትን ወታደራዊ ወጣት መኮንኖችን እያፈኑ ወደ እስር ቤት እየወረወሩ ነው::(www.facebook.com/minilik.salsawi) ይመልከቱት !!

ከምእራብ እዝ እና ከአዲስ አበባ የተለያዩ የጦር ክፍሎች ቁጥራቸው በርከት ያሉ ወጣት መኮንኖች ተይዘው አዲስ አበባ መኮንኖች ክበብ አከባቢ ካለው ወታደራዊ እስር ቤት ውስጥ የታሰሩ ሲሆን አብዛኛዎቹ የአማራ እና የ ኦሮሞ ተወላጆች ሲሆኑ የትግራይ ተወላጅ የሆኑ መኮንኖች ተለይተው ወደ ትግራይ እስር በት ተልከዋል::

እንዲሁም በመከላከያ ኢንጂነር ስር ያሉ የምህንድስና መኮንኖች አብዛኛዎቹ እስር ቤት ያሉ ሲሆን ከአምቦ ጋፋት ኢንጂነሪንግ.. ከደብረዘይት መኪና መገጣጠሚያ ..ከ አየር ሃይል እና ከተለያዩ ከተሞች ወጣት የጦር መኮንኖች እየታፈሱ እየታሰሩ መሆኑን የሚኒሊክ ሳልሳዊ የዉስጥ ምንጮች ገልጠዋል::

በቅርብ የተሾሙትን የ34 ጄኔራሎች ሹመት ተከትሎ የተነሳው ይህ ተቃውሞ የወያኔ ጀኔራሎች ያተኮሩባቸው የተማሩ ወጣት መኮንኖች ላይ ሲሆን ይህ ዘመቻ በመከላከያ ዉስጥ ትርምስን ፈጥሮዋል; ...
ያንድ ወገን የበላይነት ይወገድ...ተቃውሞ ብሄራዊ እንጂ ክልላዊ አይደለም....ለሃገር እንጂ ለግል የሚል አቁዋም ይወገድ ...የሚሉ እና ሌሎች የመብት ጥያቄዎችን ወጣት መኮንኖቹ በማንሳታቸው የወያኔ ጄኔራሎች በመደናገጣቸው የመከላከያ ደህንነት ሃይሉን አጠናክረውታል::

ይህ በእንዲህ እንዳለ በመከላከያ ዉስጥ ባለው ዝርክርክ እና ብልሹ አሰራር የሃገር ንብረት እና የህዝብ ሃብት በጀኘራል መኮንኖቹ እየተዘረፈ ሲሆን ዘመዶቻቸውን እያመጡ በተለያየ መንገድ እያሸሹ መሆኑን ታውቑል::
በተለያዩ የመከላከያ ግቢዎች ዉስጥ የቆሙ የተበላሹ መኪኖች እየተሰበሰቡ ለብረት ማቅለጫ ፋብሪካዎች በኪሎ እየተሸጡ ሲሆን ገንዘቡንም ጀነራሎቹ በሚስቶቻቸው እና በልጆቻቸው ስም እንዲሁም በዲያስፖራ ዘመዶቻቸው ስም በውጭ አገራት ባንኮች እያስቀመጡት ሲሉ የምንሊክ ሳልሳዊ ምንጮች አሳብቀዋል::

በተለያዩ መንገዶች ከመንግስት ካዝና ወጪ እየተደረገ በቢዝነሱ እንዲሳተፉ የሚደረጉት የጄኔራሎቹ ሚስቶች ሲሆኑ ደርግን ለመጣል የታገልነው እኛ ብቻ ነን በኢል መዘባበት የተለያዩ ንብረቶችን ከመስሪያቤቱ በዱቤ እያወጡ የማይከፍሉ ሲሆን ልጆቻቸው በዉጭው አለም በዉድ ዋጋ እየተማሩ መሆኑን የምንሊክ ሳልሳዊ ምንጮች ተናግረዋል::

የአድዋ ተወላጅ የሆኑ ጄኔራሎች በተለየ ሁኔታ በወርቅ ንግድ ዉስጥ የገቡ ሲሆን የተለያዩ የማእድን
አገር በቀል ድርጅቶችን እያባረሩ ራሳቸው ዘመዶቻቸዉን በማስቀመጥ ከጨረታ ውጪ ስራዉን እየሰሩት መሆኑን ጥቆማው ሲያስረዳ ከዚህም ተጠቃሚ እና ወኪል አንዱ ፒያሳ የሚገኘው አፍሪካ ወርቅ ቤት ተጠቃሽ ነው::

No comments: