Monday, February 3, 2014

የአቶ አለምነው መኮነን ጭንቅላት ወይንም ጭንቅላት አልባነት !

Feb. 2/2014
አንዱ ዓለም ተፈራ
በዕርግጥ የአንድን የሀገራችን ክፍል ነዋሪዎች ጉዳይ አንስቶ በአንድ መንገድ ወይንም በሌላ መንገድ መነጋገር፤ ወደድንም ጠላንም፤ ያለንበት ዘመን ግዴታ ሆኗል። ትናንት አኝዋኮች ተረሸኑ፣ የኦጋዴን ወገኖቻችን ተከበው ተሰቃዩ፣ ኦሮሞዎች በእስር ቤት ታጎሩ እያልን እንደጮህን ሁሉ፤ ዛሬ ደግሞ በአማራዎች ላይ የሚደርሰውን በደል አንስተን መነጋገር ግዴታችን ሆኗል። የክርስትና እምነት ተከታዮች እንዲህ ሆኑ፤ የእስልምና እምነት ተከታዮች እንዲያ ሆኑ ስንል ብዙ ዓመታት ቆጠርን።በማይዘነጋ መንገድ ደግሞ እያንዳንዱን ለይተን እያነሳን፤ ይኼኛውን ብቻ የሚያደርጉ የዚህኛው ክፍል ብቻ ተወላጆችና ለዚያ ክፍል ብቻ ተቆርቋሪዎች ተደርጎ ስለሚወሰድ፤ እያንዳንዱን ጉዳይ “ለሌሎች” መተውና ጠቅላላ ኢትዮጵያዊንን በሚነኩ ጉዳዮች ላይ ብቻ መቆም፤ የታጋይነት ምልክት ተደርጎ የተወሰደ ፈሊጥ ሆኗል። እኔ ይኼን ትክክል ብዬ አልወስደውም። ለእያንዳንዱ ጉዳይ ቆሜ እቆጠራለሁ።
በኢትዮጵያዊነቴ የምኮራና በዚያ ብቻ ሀገራዊ የፖለቲካ ተሳትፎዬን የምለካ ስለሆነ፤ ይህ ጉዳይ ከአእምሮዪ ውጪ ነው። አማራው አማራ በመሆኑ ብቻ ለሚደርስበት በደል መቆርቆር፤ የግድ ከአማራ መወለድ አለበት የሚል ካለ፤ ዘረኛ ነው። በኢትዮጵያዊነቱ አያምንም። ለአማራው የሚቆረቆረውን ሁሉ ደግሞ ትምክህተኛ አማራ የሚል ሁሉ፤ ዘረኛ ነው። አማራን ይጠላል። ማንኛውም ኢትዮጵያዊ ላይ የሚደርሰውን በደል የኔ ብሎ ያልተነሳ ታጋይ ነኝ ባይ፤ ባይ እንጂ ኢትዮጵያዊ ታጋይ ነኝ ሊል አይገባውም። በአኝዋኩ ወገናችን፣ በኦሮሞው ወገናችን፣ በአማራው ወገናችን፣ በኦጋዴኑ ወገናችን የሚደርሰው በደል፤ የእያንዳንዳችን በደል ነው ብለን መውሰድ ካልቻልንና፤ የአንዱን ወገን በደል ብቻ ይዘን የምናቅራራ ከሆነ፤ ውሸታምና ዘረኛ ለመሆናችን ሌላ መረጃ አያስፈልግም። በዚህ ጽሑፍ፤ የአማራ ክልል ም/ፕሬዚዳንት እና የብሔራዊ የአማራ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ ጽ/ቤት ሃላፊ የሆኑት አቶ አለምነው መኮንን የተናገሩት፤ ምን ያህል ፀረ-ኢትዮጵያና፤ ውሃው የተቀዳበት ምንጭ የወገንተኛው አምባገነን ሕገወጥ ፓርቲና መንግሥት የፖለቲካ ፍልስፍናና የአስተዳደር መመሪያ እንደሆነ አሰምራለሁ። እናም ደግሞ ይህ አደገኛ መርዝ፤ ጠንቀኝነቱን አሳያለሁ።















                 የአማራው ሕዝብ

በወገንተኛው አምባገነን ሕገወጥ ገዢ ቡድን የፖለቲካ ስሌት፥ አማራውን ማጥቃት፤ ከሥር መሠረቱ ሲፈጠር ምሰሶዬ ብሎ የያዘው የትግል ምሰሶው ነው። ቀጥሎም የመንግትነቱን ካባ ካጠለቀ ወዲህ፤ ከራሱ አልፎ ለማንኛውም ኢትዮጵያዊ የሥልጣን መቆናጠጫ ዋና መሰላሉ፤ ይኼን መቀበልና መተግበር ሆኗል። ይህ ደግሞ ከአማራው ወገን ተወለድን ለሚሉትም ሆነ ከአማራው ወገን አልተወለድንም ለሚሉት ሁሉ የሚሠራ መለኪያ ሚዛን ነው። አንድ ጭንቅላት ብቻ ነው ያለው፤ የገዢው ቡድን ጭንቅላት። ስለዚህ አቶ አለምነው መኮነን ተናገሩት ወይንም አቶ ደሳለኝ ሀይለ ማርያም ተናገሩት ለውጥ የለውም። ሁሉም አፋቸው እንጂ ጭንቅላታቸው የነሱ አይደለምና! እናም የግለሰቡን የአቶ አለምነውን ሰውነት ሳይሆን፤ የአቶ አለምነው መኮነንን ጭንቅላት ነው ማስመዘን የምፈልገው። ቀደም አድርጎ ግን አቶ አለምነው ጭንቅላት አላቸው ወይ? ወይንስ ጭንቅላት የላቸውም? ብሎ መጠየቁ ተገቢ ነው። በዕርግጥ በዚህ ወራሪ በመሰለ አስተዳደር ለመዘፈቅ፤ በመጀመሪያ ደረጃ ማንነትን ሽጦ መቆም ግዴታ ነው። ይህ በአእምሯቸው ሳይሆን በሆዳቸው የሚመሩ ሰዎች ብቻ የሚሰበሰቡበት አስተዳደር ለመሆኑ ማስረጃ፤ የራሳቸውን ነፃነት አለማግኘታቸው ነው። ወይንም በትክክለኛው አነጋገር፤ ራሳቸውን መሸጣቸው ነው። አእምሮ ማጣታቸው ማለቱ ይቀላል።

ወንጀል ከተፈፀመ፤ እከሌ ወይንም እከሌና እከሌ ይኼን ሠሩ ወይንም ያንን ሳይሠሩ ቀሩ ብሎ አንድን ወይንም የተወሰኑ ግለሰቦችን መወንጀል፤ ተገቢ ነው። በአንድ ሀገር ያሉትን የአንድ የኅብረተሰብ ክፍል አባላትን ግን ለይቶ ይኼን አደረጉ በተለይም እንዲህ ናቸው ብሎ መወንጀል፤ ከግልብነቱ በላይ የኅብረተሰብን ምንነት አለማወቅን የሚያሳይ አጉሊ መነፅር ነው። ከዚህ ተነስቼ ነው የአቶ አለምነው መኮነንን ንግግር የምረዳው። እስኪ ከአቶ አለምነው መኮነን ንግግር ጠቀስ አድርጌ፤ ጭንቅላት አላቸው ወይንስ የላቸውም? ያስባለኝን ላሳያችሁ፤
፩ኛ፤ “ የአማራው ህዝብ በቅድሚያ እንዳይሰደድ ለማድረግ ስራ እየተሰራ ነው፣ ነገር ግን ከተሰደደ በሁዋላም ቢሆንም ሰንፋጭ የሆነውን ትምክህተኝነቱን በመተው ከሌላው ጋር ለመኖር መልመድ አለበት። ”
፪ኛ፤ “ የአማራው ህዝብ ሰንፋጭ የሆነ ትምክተኝነት የተጠናወተው በመሆኑ በቤንሻንጉልና በሌሎችም ቦታዎች ለመሰደዱ ምክንያት ሆኖታል። ”
፫ኛ፤ “ በባዶ እግሩ እየሄደ የሚናገረው ንግግር ግን መርዝ ነው። ይሄ መርዝ ንግግሩ አንድ የሚያደርግ አይደለም። ”
፬ኛ፤ “ ከኢትዮጵያውያን ጋር አብሮ ለመኖር አማራው የትምክህት ለሃጩን ማራገፍ አለበት። ይሄ ለሃጭ ሳይራገፍ በጋራ መኖር አይቻልም። ”
፭ኛ፤ “ ማንኛውም ስም ያወጣ ሙትቻ ፓርቲ ሁሉ መንገሻው አማራ ክልል ነው። ትምክህትን እንደ ምግብ ስለሚመገበው ነው። ያንን ምግብ እየተመገበ ያቅራራል። ”
እዚህ ላይ አቶ አለምነው መኮነን ሁለት መልዕክት ባንድ ላይ አስተላልፈዋል። የመጀመሪያው፤ የአማራውን ጠባየ ቢስነት አመልክቶ፤ አማራውን መኮነን ሲሆን፤ በሥር አስደግፎ ደግሞ፤ አማራው ከሌሎች ቦታዎች በተሰደደበት ምክንያት መንግሥታዊ አካላት ተጠያቂ አይደሉም ብሎ ለማሳመን የተቀመመ መርዝ ነው። ለመሆኑ አቶ አለምነው መኮነን ኢሕአዴግ ራሱ፤ የአማራውን ከሌሎች መፈናቀል ትክክል አልነበረም ሲል፤ የት ነበሩ? መንግሥት በየደረጃው፤ “ደን ስለጨፈጨፉ ነው” ሲል፤ የት ነበሩ? ይኼ የናንተ ቦታ አይደለም ሲባሉ፤ የት ነበሩ? ወይንስ ኢሕአዴግ የአቶ አለምነው መኮነንን ጭንቅላት በመጠቀም፤ ያመነበትን ባደባባይ ተናግሮ በጓሮ በር ራሱን ነፃ ለማውጣት የለከካት መልዕክት ናት? የተፈናቀሉት በትምክህተኛነታቸው ሳይሆን በአማራነታቸው ነው። ሕፃናት፣ ወጣቶች፣ አዛውነት፣ ሴቶች፣ ወንዶች፣ ደሃዎች፣ ባለፀጎች፣ ሁሉም ታታሪ ሠራተኞች ተባረዋል። ያካባቢው ሰዎች በተቻላቸውና መንግሥታዊ መዋቅሩ በማያውቀው መንገድ ድጋፍና ሐዘኔታ ሠጥተዋቸዋል። ይህ መንግሥታዊ ተግባር ትክክል ስላልሆነ ወደ መጡበት ይመለሱ ሲል ኢሕአዴግ ራሱ ወስኗል። አቶ አለምነው መኮነን! በኢሕአዴግኛ አነጋገር ወንጀለኛው እርስዎና እንደርስዎ ያሉት አፈናቃዮች ናቸው። ተራዎ ደርሶ፤ እርስዎም መጠቀሚያነትዎ አብቅቶ፤ እስኪባረሩ ወይንም ዘብጥያ እስኪወረወሩ ድረስ፤ ከወገብዎ በደንብ ልምጥ ይበሉ!
አማራው እንዲህ ነው ብሎ መጮህ፤ አማራውን ሌሎች እንዲበድሉት ፍቃድ ፈርሞና ታርጋ ለጥፎ መሥጠት ብቻ ሳይሆን፤ አማራው በተፈጥሮ ጎደሎ ስላለበት፤ ከአማራ የተገኘ ሁሉ፤ አብሮ ለመኖር አይመችምና፤ ከያለበት አባሩት ማለት ነው፤ ከኢትዮጵያዊነትም! ይህ ፀረ-ኢትዮጵያዊነትና ፀረ-ሰብዓዊነት ነው። ለነገሩ በዚህ ሹመት ከተመደበ በሆዱ ተንፏቆ በሆዱ ከሚያድር ሹም ሌላ ምን ይጠበቃል? አቶ አለምነው መኮነን ከአማራው ወገን ተወላጅ መሆናቸው ዋጋ የለውም። የአቶ በረከት ስምዖንም የአማራው ተወላጅነትና ተወካይነታቸው እንደተጠበቀ ሆኖ! እንዲህ ነው በአማራው ላይ መሾም ማለት!
በሌላ በኩል ስለ አንቀጽ 39 ጥያቄ ቀርቦላቸዋል። እስኪ ለምን ቀረበላቸው የሚለውን እናጢን! አንቀጽ 39 አማራውን ለብቻው እንደ አማራነቱ የሚጎዳው ነው ወይ? አማራውን ማጥቂያ መሣሪያ በመሆኑ ነው ወይ? የአማራ ክልል ሰዎች እንዲጠይቁ የተገደዱት? ጥያቄውን ማንሳታቸው የሚያመለክተው፤ አንድም አማራን ማጥቂያ መሣሪያ በመሆኑ፤ ወይንም የኢትዮጵያን አንድነት አማራው አጥብቆ ስለያዘ ነው። ከዚህ ሌላ ምንም ምክንያት የለውም። ታዲያ አማራው የሚጠቃበት መንገድ፤ በኢትዮጵያዊነቱ ነው ማለት ነው። በተለይም ኢትዮጵያዊነትን ስላጠበቀና በመላ ኢትዮጵያ ተበትኖ ስለኖረ። እናም አንቀጽ 39፤ “ኢትዮጵያን ለመጉዳት የታሰበ ወይንም አማራን ከማጥቃት ጋር የተያያዘ ነው።” ብለው ቢያንስ በአማራው ክልል ያሉት የራሱ የገዥው ካድሬዎች ያምናሉ ማለት ነው። ይኼ ራሱን ችሎ የሚታይ በመሆኑ እዚህ ላይ አስተያየት አልሠጥበትም። ለዚህ ጥያቄ የአቶ አለምነው መኮነን መልስ ደግሞ፤
፮ኛ፤ “ አንቀጽ 39 ባይኖር ኖሮ ኢትዮጵያ ደቡብ ሱዳን እንደሆነቸው ትሆን ነበር። አንቀጽ 39 በህዝቦች ዘንድ መተማመን መፍጠሩን፣ አቶ መለስ ዜናዊ በሞቱበት ጊዜ በገሃድ ታይቷል። ”
በዚህ መልስ የምረዳው፤ አቶ አለምነው መኮነን እንደ አቶ ደሳለኝ ሀይለማርያም የራሳቸውን ጭንቅላት ተጠቅመው የሚሠሩ ሳይሆን፤ በሟቹ “ባለራዕይ” መሪያቸው የሚጎተት መሆኑን ነው። ሟቹ ቢኖሩ ከዚህ የተለዬ እንደማይናገሩ ስለምናውቅ፤ አቶ አለምነው መኮነን ማስተላለፊያ ቀፎ መሆናቸውን ተረዳሁ። ታዲያ የአቶ መለስ ዜናዊን ቀሚስ ለምን አያጠልቁም? አዎ አምባገነኖች ከነሱ ሌላ በራሱ ጭንቅላት አስቦ የሚሠራ እንዲኖር አይፈልጉም። ታሪክም ይኼንኑ ነው የሚያስረዳን።
እንግዲህ አንደኛ፤ አቶ አለምነው መኮነን የራሳቸው ጭንቅላት የላቸውም ወይንም አከላቱ እንደ ግንድ በድኖ ከራሳቸው ውስጥ ቢኖርም፤ የገደል ማሚቶ ሆኖ ከማስተጋባት ሌላ ሙያ የለውም ማለት ነው። ሁለተኛ፤ ፀረ-ኢትዮጵያዊ የሆነን ተግባር፤ በአማራው ትምክህነት ማመካኘት፤ አደገኛና ለወደፊቱ የአማራውን ኢትዮጵያዊነት ብቻ ሳይሆን፤ የአማራውን የኅብረተሰብ አካልነት ጥያቄ ውስጥ ያስገባ መርዝ ነው። በሶስተኛ ደረጃ ልጠቁም የምፈልገው፤ ራሱ ኢሕአዴግ ሳይወድ ተገዶ ያመነበትን የአማራውን የማፈናቀል ወንጀል፤ ከኢሕአዴግ አሳልፎ በአማራው ላይ ለመለከክ የተደረገ የብልጠት ቅሌት ነው። ማሳረጊያው ግን፤ ይኼን መዘርዘሩ ሳይሆን፤ ይኼን ማውገዙ ሳይሆን፤ ይህ እንዳይደገም ሆነ ለዚህ ተጠያቂዎችን በሕግ ፊት ለማቅረብ፤ የታጋዩ ወገን ምን እያደረገ ነው? ነው። ይህ ትግል የኢትዮጵያዊያን፤ በኢትዮጵያዊነታችን አንድ ራዕይ ኖሮን በአንድ ድርጅት ተሰባስበን የምንነሳበት ትግል ነው። ይህ የአማራው ብቻ እንጂ፣ የትግሬው፣ የኦሮሞው፣ የደቡቡ፣ የኦጋዴኑ፣ የአኙዋኩ የግል ጉዳይ ያልሆነ አይደለም። የኢትዮጵያዊያን ጉዳይ ነው።
ኢትዮጵያዊያን የኔ ብለን በአንድነት እስካልተነሳን ደረስ፤ መፍትሔው የውሃ ውቀጥ መፍትሔ ነው፤ ውሃን ቢወቅጡት መልሶ እምቦጭ ነውና! ከነአቶ አለምነው መኮነን ሆነ ከአሽከርካሪዎቻቸው ተወግዘውም ሆነ ተለምነው መፍትሔ እንዲሠጡን መጠበቅ፤ ላም አለኝ በሰማይ ነው።

Sunday, February 2, 2014

በሚኒሶታው ደብረሰላም መድሃኔዓለም ቤ/ክ የባንክ አካውንት፣ ዝማሬ፣ ስብከትና ማንኛውም የቦርድ ስብሰባ በፍርድ ቤት ታገደ

Feb.2/2014

እየተካረረ የመጣው የሚኒሶታው ደብረሰላም መድሃኔዓለም ቤ/ክ ጉዳይ ወደ ፍርድ ቤት ማምራቱ ተገለጸ። ዛሬ ጃንዋሪ 2 ቀን 2014 ዓ.ም እንደወትሮው ምዕመናን ከቅዳሴ በኋላ ዝማሬ እና ስብከት ሳይሰማ የጠበቆች መልዕክት ብቻ ተሰምቶ ህዝቡ ወደ እቤቱ ተመልሷል።

ባለፈው ሳምንት በቤተክርስቲያኑ በሁለቱም ወገኖች ማለትም “ወደ ሃገር ቤቱ ሲኖዶስ መጠቃለል አለብን” በሚለው እና “በሃገር ቤት እና በውጭ ያሉት ሲኖዶሶች አንድነት እስኪፈጥሩ ድረስ በገለልተኝነታችን መቆየት አለብን” በሚሉት ወገኖች መካከል የተነሳው አለመደማመጥ በቤተ መቅደሱ ውስጥ አተካሮ ፈጥሮ እንደነበር የተለያዩ ሰዎች በዘ-ሐበሻ ድረገጽ ላይ በጻፏቸው አስተያየቶች ለንባብ መብቃቱ ይታወሳል።


ዲሴምበር 15 ቀን 2013 በሚኒሶታው ደብረሰላም ቤ/ክ በተጠራ ጠቅላላ ጉባዔ ቤተክርስቲያኑ በነበረበት በገለልተኛነቱ እንዲቆይ መወሰኑ የሚታወስ ሲሆን፤ ወደ ሃገር ቤት ሲኖዶስ እንዲጠቃለል የሚፈልገው ወገን “ምርጫው ኮረም አልሞላም፤ ውሳኔውም ህጋዊ ስላለሆነ አንቀበልም” በማለት አለመግባባቱ እየተካረረ መምጣቱን ሁለቱም ወገኖች በዘ-ሐበሻ መድረክ ላይ በጻፏቸው አስተያየቶች መረዳት ይቻላል። ይህን ተከትሎም የቦርዱ ሊቀመንበር “የቦርድ አባላቱ የሕዝቡን ውሳኔ አናስፈጽምም በማለታቸው ጠቅላላ ጉባኤ እስከሚጠራ ድረስ ማንኛውንም ስብሰባና ቦርዱን ማገዳቸውን” በቤተመቅደሱ ውስጥ የተናገሩ ሲሆን ባለፈው እሁድ ቦርዱ አዲስ የቦርድ ሊቀመንበር በመምረጥ የቀድሞው ሊቀመንበርን በድምጽ ብልጫ ከስልጣናቸው አውርጃለሁ ማለቱና ይህም ደብዳቤ በዘ-ሐበሻ መነበቡ አይዘነጋም።

ከሁለቱም ወገኖች ያሉ ጠበቆች ዛሬ ከቅዳሴ በኋላ ለሕዝቡ መዝሙር እንዳይዘመር፣ ስብከት እንዳይደረግ መታገዱን የገለጹ ሲሆን በአሁኑ ወቅት ፍርድ ቤት የቀድሞውን ሊቀመንበርም ሆነ፤ አዲሱን በቦርድ የተሾሙትን ሊቀመንበር እንደማይቀበል፤ ቦርዱ ምንም ዓይነት ስብሰባ እንዳያደርግ መከለክሉን፤ ሁሉም ውሳኔ በፍርድ ቤት እስኪሰጥ ድረስ የቤተክርስቲያኑ አካውንት ውስጥ ያለ ገንዘብ እንዲታገድ መደረጉን ለምዕመናኑ ገልጸዋል። በዚህም መሠረት ዛሬ ስርዓተ ቅዳሴ የተካሄደ ሲሆን፤ እንደወትሮው ሳይዘመር፣ ስብከት ሳይሰጥ ምእመኑ ወደ ቤቱ መመለሱን በሥፍራው የነበሩ የዘ-ሐበሻ ዘጋቢዎች ገልጸዋል።

የደብረሰላም መድሃኔዓለም ቤ/ክ ጉዳይ የፊታችን ማክሰኞ ወይም ረቡዕ በፍርድ ቤት መታየት እንደሚጀመር የሚጠበቅ ሲሆን ዘ-ሐበሻ ጉዳዩን ተከታትላ ለሕዝብ ለማድረስ ትሞክራለች።

በአሁኑ ወቅት በሚኒሶታው ደብረሰላም መድሃኔዓለም ቤ/ክ የባንክ አካውንት ውስጥ በሚሊዮን የሚቆጠር ዶላር እንዳለ በተደጋጋሚ የተገለጸና በሕዝብ መነጋገሪያ የሆነ ጉዳይ ሆኗል።

ዘ-ሐበሻ ከዚህ ቀደም በሁለቱም ወገኖች ላሉ ኢትዮጵያውያን ሰላም እንዲፈጥሩ እና ቁጭ ብለው በመነጋገር ችግሩን ሊፈቱት እንደሚገባ ስትመክር የቆየች ቢሆንም ጉዳዩ እየተካረረ ሄዶ እዚህ መድረሱ ጉዳዩን ከውጭ ሆነው ለሚከታተሉ አሳዛኝ ክስተት ሆኗል ተብሏል።

ሌንጮ ለታ – ታሪክ ሊሰሩ ወይንስ ታሪክ ሊጽፉ…?

February 2, 2014
ክንፉ አሰፋ
Former OLF chairman Lencho Leta
ኦቦ ሌንጮ ለታ
ኢትዮጵያዊው ቱጃር ለለውጥ ብለው በኮንትራት ታክሲ በመሄድ ላይ ናቸው። እሳቸውን የጫነው ታክሲ መስቀል አደባባይ ላይ ሲደርስ በድንገት ቀጥ ብሎ ቆመ። ሾፌሩ ተደናጋጠ። መኪናውን እንደገና ለማስንሳት ብዙ ሞከረ። ከብዙ ሙከራ በኋላ ጥረቱ ስላልተሳካለት ቱጃሩን ለትብብር ጠየቃቸው። እንዲህ ሲል። “ወጣ ብለው ይግፉ።”  ቱጃሩ በመገረም ሾፌሩን አዩት።  ”ይግዙ” ማለትህ ነው ሲሉም መለሱለት። እኚህ ሰው መኪናውን ከመግፋት ይልቅ አዲስ መኪና መግዛት ይቀላቸዋል።  የቤቶች ድራማ ላይ እከ ደከ አስር ጊዜ “እኔን ነው?” የሚለው ወዶ አይደለም። ማመን የሚቸግሩንን ነገሮች ማጣራት ስንፈልግ እንደጋግማለን።
በዚያን ሰሞን በኦቦ ሌንጮ ለታ የወጣው ዜና ብዙዎችን አስገርሟል።
“ሃገር ቤት ገብተን በመታገል አዲስ ታሪክ እንሰራለን።” የሚል ነበር የዜና እወጃው ርዕስ። ይህን ርዕስ እንዳየሁ አይኔን በደንብ ጠረግ ጠረግ አደረግኩና እንደገና አነበብኩት።
“ታሪክ እንሰራለን” የሚለው ሃረግ በስህተት የሰፈረ ነበር የመሰለኝ።  ሌንጮ ለማለት የፈለጉት “ታሪክ እናነባለን” ይሆናል በሚል ጥርጣሬ ደጋግሜ ያየሁት።  ያነበብኩት ነገር ትክክል ነው። ይህንኑ ቃል ከራሳቸው አንደበትም ሠማሁ።  በስህተት የሰፈረ ዜና አልነበረም።  ታሪክን ማንበቡም ሆነ መስራቱ ቀርቶ “ሃገር ቤት ገብተን አዲስ ታሪክ እንጽፋለን።” የሚል ቢሆን እንኳን ግርታውን ይቀንሰው ነበር።
በፍትህ ሳይሆን ይልቁንም በአዋጅ በምትተዳደር ኢትዮጵያ፤ እጅና እግራቸውን ብቻ ይዘው በመግባት ታሪክ መስራት የሚችሉ ከሆነ በምትሃት አልያም በመለኮታዊ ሃይል ብቻ መሆን አለበት። ሌንጮ ሃገር ቤት ገብተው ሰላማዊ ትግል ለማድረግ መወሰናቸው ላይ ምንም ችግር የለብኝም። የዚህ ውሳኔ ትክክለኝነት የሚዳኘው አስቀድመው በሚተቹ እና በሚተነብዩ የፖለቲካ ነብያት አይደለም። ፍርድ የሚሰጠው ሂደቱ በተግባር ሲፈተን ብቻ ይሆናል። ይህን ለማየት ደግሞ ብዙም ሩቅ አይሆንም።  በጎረበጠ የፖለቲካ መንገድ ላይ ጉዞ ለማድረግ ወደ ሃገር ቤት ለመግባት መወሰናቸው ግን አስመራ ላይ፤ በሻእቢያ ከታገቱት የኦነግ መሪዎች የተሻለ ውሳኔ ይመስላል።  ታሪክ ለመስራት አስመራ የመሸጉት እነ ዳውድ ኢብሳ ታሪክ ሆነው ቀርተዋል።
ችግሩ ያለው “ታሪክ እንሰራለን” ማለቱ ላይ ነው። እንደዚህ አይነት የፖለቲካ ትግል ውሳኔ ላይ መድረስ ቀላል ነገር አይደለም። ከመቅጽበት የመጣው ይህ ውሳኔ ልክ እንደ ኦሎምፒክ ውድድር ዝግጅቱን እንዳጠናቀቀ አትሌት ይመስላል። አትሌቲክስም ቢሆን የአካል ብቃትና በቂ ዝግጅትን ይጠይቃል።  ፖለቲካ ደግሞ ዘው ብለው ገብተው ታሪክ የሚሰሩበት በኦሎምፒክ የውድድር መድረክ አይደለም። እነ ሌንጮ እየነገሩን ያሉት አዲስ አበባ ገብተው በባላገሩ አይደል ላይ ለመወዳደር አይደለም። በባላገሩ የጫወታ ደንብ ጥሩ ስራ የሰራም፤ አስቀያሚ ስራ የሰራም ይሸለማል። ሌንጮ ታሪክ እንሰራለን የሚሉት “ስልጣን ወይንም ሞት!” የሚል መፈክር አንግቦ እስካፍንጫው የታጠቀ ሃይልን በመጋፈጥ ነው።
ታሪክን ለመስራት ብቃት ያላቸው ድርጅቶች በኢትዮጵያ የፖለቲካ መድረክ ጠፍተው አያውቁም። ከኦሮሞ ድርጅቶችም ቢሆን እነ ኦቦ ቡልቻ ደመቅሳ እና ፕ/ር መረራ ጉዲና አሉ።  የኦሮሞን ህዝብ አደራጅተው በምርጫም፣ በፓርላማም፣ በሰልፍም፣ በእርግማንም፣ በጸሎትና ምልጃም፣  በወረቀትም … ብዙ ተጉዘዋል። የእነዚህ ድርጅቶች አባላት እንደጥጃ እየተለቀሙ እስር ቤቱን ከማጨናነቃቸው በቀር ታሪክ ሲሰሩ አላየንም። አንድ እርምጃ ወደፊት፤ አስር እርምጃ ወደኋላ እየተጓዙ ሄደው…ሄደው በመጨረሻ ራሳቸውም ታሪክ ከመሆን አላለፉም። ይህ ለአቶ ሌንጮ ለታ እንግዳ ነገር አይደለም። አቶ ሌንጮ በኢትዮጵያ የፖለቲካ መድረክ በከባድ ሚዛን ደረጃ የሚመደቡ ናቸው።
በዛሬይቱ ኢትዮጵያ በፖለቲካ ታግሎ ታሪክ ከመስራት ይልቅ ነድጅ ቆፍሮ ታሪክ መስራት እንደሚቀል ለሌንጮም አዲስ ነገር አይደለም። እርግጥ ነው።  የታሪክ ትርጉም አሰጣጣችን ላይ እንለያይ ይሆናል። የገዥው ፓርቲ የታሪክ ትርጉምም ከልማት ጋር ይያያዛል። በዘመናችን ብዙ ታሪኮችን እየሰማን ነው። ልማታዊ አስተሳሰብ ያለው ሰው ሁሉ ዛሬ ታሪክ ሰሪ ይባላል። ታሪክ ሰርተው የሚሸለሙ የልማት አርበኞችን በቴሌቭዥን እናያለን።  በአነስተኛና ጥቃቅን እየተደራጁ የኮብል-ስቶን ድንጋይን እያናገሩ ያሉ ወጣት ምሁራንም በታሪክ መዝገብ ላይ እየሰፈሩ ይገኛል።
ኦቦ ሌንጮ ታሪክ የሚሉን እንዲህ አይነቱን ድራማ እንደማይሆን እርግጠኞች አይደለንም።  እኝህ የፖለቲካ መሪ ታሪክ መስራት ከነበረባቸው ግዜው አሁን አይደለም። በሽግግሩ ዘመን 20 ሺህ ጦር እና 20 መቀመጫ ይዘው በነበሩበት ጊዜ ለዚህ እድሉ ነበራቸው። ያንን እድል ይዘው ታሪክ ከመስራት ይልቅ ድርጅታቸው ጥቁር ነጥብ ጥሎ ነበር ያለፈው።  አቶ ሌንጮ ታሪክ መስራት ከነበረባቸው በሽግግሩ መንግስት የኢትዮጵያ መሪ ሆነው በተመረጡ ግዜ ነበር። በወቅቱ ምን ነበር ያሉት?  “በዚህ ላይ አልተዘጋጀሁበትም።” ሲሉ የእድሉን በር ራሳቸው ዘጉት። በርግጥ ያን ጊዜ ከኦሮሚያ የመገንጠል አዙሪት ውስጥ አልወጡም ነበር። ትልቅ ህዝብን ይዘናል እያሉ፤ የመገንጠል ጥያቄን ሲያነሱ በአለም ላይ የመጀመሪያዎቹ ብቻ አይደሉም። የኦሮሞን ህዝብ በፖለቲካ አናሳ ማድረጋቸው የታያቸውም ከ40 አመታት በኋላ መሆኑ ነው።  በዚያን ወቅት ኢትዮጵያን መምራት እንችላለን ለማለት በራስ መተማመን አልነበራቸውም።  አንድ ሰው አንድ ድምጽ በሚል መርህ ምርጫ አድርገው ከመጓዝ ይልቅ፤ እንደ አናሳ ጎሳ “መገንጠል አለብን” የሚል ያታሪክ ስህተት ውስጥ ነበሩ።
ከኦሮሞ ነጻ አውጭ ግንባር ወጥተው የኦሮሞ ዲሞክራቲክ ግንባርን መመስረታቸው ከታሪክ ተወቃጭሽነት ሊያድናቸው ይችላል ። ይህንን በማድረጋቸው የሰማይና የምድርን ያህል ርቆ የነበረውን የፖለቲካ መስመር ሊያጠበው እንደሚችል ግልጽ ነው። ዛሬ የመገንጠልን ጥያቄውን ውድቅ አድርገው ለዲሞክራሲና ለፍትህ መታገል መምረጣቸው ታሪክ ሰሪ ሊያደርጋቸው አይችልም። ይህ ሊሆን የሚችለው ለውጥ አምጥተው ፍትሃዊ ስርዓት ማስፈን ሲችሉ ብቻ ነው።
ሌንጮ ለታ አዲስ አበባ በመግባት ታሪክ እሰራለሁ ሲሉ ይህ የመጀመርያቸውም አይደለም። እ.ኤ.አ. 1993 የስራ ባልደረባቸውን ከከርቸሌ ለማስፈታት አዲስ አበባ ዘው ብለው ገብተው ነበር። እኝህ ሰው ሲገቡ ቦሌ ላይ ልዩ አቀባበል ተደረገላቸው። በብረት ተጠፍረውም ከርችሌ ተወረወሩ። በወቅቱ አዲስ አበባ ላይ ተካሂዶ በነበረው የግዮኑ የሰላም እና እርቅ ጉባዔ ላይ ለመሳተፍ ሲገቡ የታሰሩ ልኡካንን እዚያው ተቀላቀሉ።
ሌንጮ በዚያ ሰዓት ታሪክ ይሰራሉ ብለን ጠብቀን ነበር። ግን ይቅርታ ጠይቀው ከእስር ለመውጣት አንድ ሳምንትም አልፈጀባቸውም።  በወቅቱ ከአቶ ሌንጮ ለታ ጋር ረጅም ቃለ-መጠይቅ አድርጌ ይህንን ታሪክ በማሳትመው ጋዜጣ ላይ ለህዝብ ይፋ አድርጌዋለሁ። እርግጥ ነው። የሌንጮ ለታ ፖለቲካ እውቀት የሚደነቅ ነው። በፖለቲካ ብስለታቸውና ትንተናቸው ከማደንቃቸው የፖለቲካ ሰዎች አንዱ ናቸው።  ፖለቲካ ማወቅ እና ህዝብን መምራት ግን በጣም የተለያዩ ነገሮች ናቸው። ብዙውን ግዜ የሰዎችን የፖለቲካ ብቃት የምንለካው በንግግር ችሎታው ብቻ ነው። ጥሩ የፖለቲካ መሪ አስተዋይም መሆን አለበት። የመሪ አስተዋይ አለመሆን ደግሞ ችግር የመፍታት ብቃታ ማጣቱን ነው የሚያሳየን።  ኦነግ ከ40 አመታት በላይ በትግል ላይ እንደሆነ ይነገረን እንጂ ድርጅቱ ድል አድርጎ አይተን አናውቅም። የሽግግሩን መንግስት ላይም ቢሆን የተገኘው በድል አድራጊነት ሳይሆን ከህወሃት እና ከሻእቢያ ጥሪ ተደርጎለት ነበር።
በአሁኑ የአዲስ አበባ ጉዞ ሌንጮ እንደቀድሞው ልዩ አቀባበል ላይገጥማቸው ይችላል። በእርግጠኝነት ለመናገር ከጉዞው በፊት አንዳች ቅድመ ሁኔታዎች ወይንም ስምምነቶች ይኖራሉ።  ይህ ካልሆነ ግን እኝህን ሰው በቀይ መስመር ላይ ማስቆም ወይንም ደግሞ ማኖ ማስነካቱ አይቀሬ ነው። እሳቸውን ቀይ መስመር ላይ ለማቆስም በጣም ቀላል ነው። የበደኖው፣ የዋተሩና የአርባጉጉ ፋይሎች እየተመዘዙ ማውጣት ብቻ ይበቃል። አልያም ቦሌ ላይ እነ ዋልታ ብቅ ብለው በካሜራ ይቀበሏቸዋል። ልማቱን እንዲያደንቁ ይጠየቃሉ። በእስር ያሉ ወገኖችና “ሽብርተኞች”ን ማውገዛቸውም የግድ ነው። በዚህ መስመር ላይ ከሄዱ  ”አባ ጸበል ይርጩን” ብለው እንደገቡት እንደነ ስም አይጠሬ ተዋርደው ይመለሱና የፖለቲካ ሞትን ዳግም ይቀምሷታል።
ለእንደዚህ አይነቱ “ልማታዊ” የተቃውሞ አስተሳሰብ ሳይገዙ ታሪክ መስራት ከተቻለ ግን ተአምር ይሆናል።  ለማንኛውም መልካም ጉዞ…

ትራፊክ ጥሶ ለመሄድ በሞከረ ሚኒባስ ላይ በተተኮሱ ጥይቶች ሦስት ሰዎች ተጎዱ

Feb. 2/2014

ባለፈው ሐሙስ ከምሽቱ አራት ሰዓት አካባቢ በተሳፋሪዎች ተሞልቶ ደሴ ሊጓዝ ነበር የተባለ አንድ ሚኒባስ፣ ለትራፊክ ዝግ የሆነ መንገድ ጥሶ ለማለፍ ሲሞክር በፀጥታ አስከባሪዎች በተተኮሱ ጥይቶች ሦስት ሰዎች መጎዳታቻውን ምንጮች ለሪፖርተር ገለጹ፡፡

ጥር 22 ቀን 2006 ዓ.ም. የተጀመረውን የአፍሪካ መሪዎች ስብሰባ ምክንያት በማድረግ፣ በተለያዩ ሰዓታት መሪዎቹ የሚተላለፉባቸው መንገዶች ለተወሰነ ጊዜ ለትራፊክ ዝግ የሚደረጉ መሆኑ ቢታወቅም፣ ከምሽቱ አራት ሰዓት ሲሆን ከአዲስ አበባ ከተማ ሊወጣ እንደነበር የተገለጸው ኮድ 3 የሆነና ለከተማ ትራንስፖርት ድጋፍ ከሚሰጡ ሚኒባሶች አንዱ የሆነው ተሽከርካሪ ሾፌር፣ ለምን ትራፊክ ጥሶ ለማለፍ እንደፈለገ በቁጥጥር ሥር ውሎ በምርመራ ላይ መሆኑን ለማወቅ ተችሏል፡፡

ሚኒባሱ ከካዛንቺስ ወደ አራት ኪሎ በሚወስደው መንገድ ከፊት በር ሁለት መቶ ሜትር በላይ አለፍ ብሎ ከፓርላማ መቶ ሜትር ያህል ዝቅ ብሎ በሚገኘው የታላቁ ቤተ መንግሥት መግቢያ በር አካባቢ በፀጥታ አስከባሪዎች ተኩስ ሊቆም ቢችልም፣ ከተሳፋሪዎቹ መካከል ባልና ሚስትን ጨምሮ ሌላ አንድ ግለሰብ በመቁሰላቸው፣ ወደ ዳግማዊ ምኒሊክ ሆስፒታል ተወስደው ሕክምና እየተደረገላቸው መሆኑን ምንጮች ገልጸዋል፡፡

ባጋጠመው ድንገተኛ ሁኔታ የሞቱም ሆነ በከባድ ሁኔታ የተጎዱ ተሳፋሪዎች ባይኖሩም፣ በወቅቱ በሚኒባሱ ውስጥ የነበሩት ተሳፋሪዎች በድንጋጤ ራሳቸውን ስተው እንደነበሩ በሥፍራው የተገኙ የዓይን እማኞች ተናግረዋል፡፡

የሚኒባሱ አሽከርካሪ መንገዱ ለትራፊክ ዝግ መሆኑን እያወቀ ጥሶ ለማለፍ የፈለገበትን ምክንያትና በምርምራ ወቅት የተገኘ ሌላ ምክንያት ካለ፣ እንዲሁም ጉዳት ደርሶባቸዋል ስለተባሉት ሦስት ግለሰቦች ሁኔታ ማብራሪያ እንዲሰጡን የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽንና የፌደራል ፖሊስን ለማነጋገር የተደረገው ጥረት፣ ‹‹ጉዳዩ በምርመራ ላይ ስለሆነ ምንም ማለት አንችልም›› በሚል ምላሽ ሊሳካ አልቻለም፡፡

ከወራት በፊት ከምሽቱ 12 ሰዓት በኋላ ከአዲስ አበባ ውጪ የሚደረጉ የሕዝብ ትራንስፖርት ጉዞዎች መታገዳቸው የሚታወቅ ሲሆን፣ ቁጥጥሩ በመላላቱ ምክንያት ጉዞዎች እንዳልተገቱ እየተነገረ ነው፡፡

ሪፖርተር

Leaked audio: Amhara region leader insulting the Amhara people [video] የብአዴን ምክትል ፕሬዝዳንት ፣ የአማራን ሕዝብ ሲሳለቁበት

Feb.1/2014
የአማራ ክልል ም/ ፕሬዚዳንት እና የብአዴን ጽ/ቤት ሃላፊ የሆኑት አቶ አለምነው መኮንን “የአማራው ህዝብ ሰንፋጭ የሆነ ትምክተኝነት የተጠናወተው በመሆኑ በቤንሻንጉልና በሌሎችም ቦታዎች ለመሰደዱ ምክንያት ሆኖታል” በማለት፣ ለብአዴን ነባርና አዳዲስ ካድሬዎች ተናግረዋል።
ካድሬዎቹ “የአማራው ህዝብ ለምን ይሰደዳል? ለምን በእየክልሉ ጥቃት ይደርስበታል? አማራውን ከጥቃት ለመከላከል ለምን ሙከራ አይደረግም በማለት ጥያቄ ያቀረቡ ሲሆን፣ ም/ል ፕሬዚዳንቱ የአማራው ህዝብ በቅድሚያ እንዳይሰደድ ለማድረግ ስራ እየተሰራ ነው፣ ነገር ግን ከተሰደደ በሁዋላም ቢሆንም ሰንፋጭ የሆነውን ትምክህተኝነቱን በመተው ከሌላው ጋር ለመኖር መልመድ አለበት ብለዋል።
አማራው “በባዶ እግሩ እየሄደ የሚናገረው ንግግር ግን መርዝ ነው” ያሉት ምክትል አስተዳዳሪውና የብአዴን የጽህፈት ቤት ሃላፊው፣ ይሄ መርዝ ንግግሩ አንድ የሚያደርግ አይደለም ሲሉ አክለዋል።
ከኢትዮጵያውያን ጋር አብሮ ለመኖር አማራው  የትምክህት ለሃጩን ማራገፍ አለበት ያሉት አቶ አለምነው፣ ይሄ ለሃጭ ሳይራገፍ በጋራ መኖር አይቻልም ሲሉ ድምድመዋል።
ማንኛውም ስም ያወጣ ሙትቻ ፓርቲ ሁሉ መንገሻው አማራ ክልል ነው ያሉት ምክትል ፕሬዚዳንቱ፣ ምክንያቱንም ሲገልጹ ትምክህትን እንደ ምግብ ስለሚመገበው ነው ብለዋል። ያንን ምግብ እየተመገበ እንደሚያቅራራም ገልጸዋል።
አንዳንድ የብአዴን አባላት የምክትል ፕሬዚዳንቱ ንግግር እጅግ እንዳበሳጫቸው ለኢሳት ተናግረዋል።
የብአዴን ካድሬዎች አንቀጽ 39 ለምን አይወጣም በማለት ላነሱት ጥያቄ፣ እኝሁ ፕሬዚዳንት ሲመልሱ አንቀጽ 39 ባይኖር ኖሮ ኢትዮጵያ  ደቡብ ሱዳን እንደሆነቸው ትሆን ነበር በማለት መልሰዋል ። አንቀጽ 39 በህዝቦች ዘንድ መተማመን መፍጠሩን፣ አቶ መለስ ዜናዊ በሞቱበት ጊዜ በገሃድ መታየቱን ም/ፕሬዚዳንቱ ገልጸዋል
የድምጽ ማስረጃውን ቀርጸው ለላኩለን በስብሰባው ላይ የተካፈሉ የህክምና ባለሙያዎችን ለማመስገን እንወዳለን።

Saturday, February 1, 2014

ልፋ ያለው በሕልሙ ዳውላ ይሸከማል! ጠርናፊና ተጠርናፊ

Feb. 1/2014

መስፍን ወልደ ማርያም

ሰሞኑን እንደአዲስ ሆኖ የሚወራው ስለጥርነፋ ነው፤ ጥርነፋ ከዲያብሎስ ፋብሪካ የወጣ የክፋትና የጭቆና መሣሪያ ነው፤ ሰዎችን በመጨቆንና በማሰቃየት፣ ምቾትና እንቅልፍ በማሳጣት፣ ፍርሃትንና ስጋትን በማሰራጨት ሕዝብን ለጥ-ጸጥ አድርጎ ለመግዛት የሚፈልጉ ጠርናፊዎች፣ አምባ-ገነኖች፣ ጨቋኞች፣ አፋኞች፣ ዘራፊዎች፣ ወሮበሎች፣ ምድራዊም ሆነ ሰማያዊ ሕግ የማይገዛቸው፣ አምላካቸው አድርገው የሚያገለግሏቸው ሎሌዎችን በሆዳቸው ገዝተው የሚያሰልፉ ናቸው፤  እንኳን የገጠር ልጆችና አኛም የአዲስ አበባዎቹ መሰንከል ምን እንደሆነ እናውቃለን፤ እንስሳትን (በቅሎዎችንና አህዮችን፣ አንዳንዴ በገግና ፍየልም) የፊት እግር ከኋላ እግር ጋር በአጭር ገመድ እያሰሩ እንደልባቸው እንዳይንቀሳቀሱ ማድረግ ነው፤ ሀብት በመሆናቸው ቢጠፉ ባለቤቶቹ ይጎዳሉ፤ ስለዚህ በየአካባቢያቸው ያለውን እየጋጡ ችለው እንዲኖሩ ለማድረግ ቀላሉ ዘዴ መሰንከል ነው፡፡
ለሰውም ቢሆን ዓላማውም ዘዴውም አንድ ነው፤ ልዩነቱ የሰው ልጅ እንቅስቃሴው አካላዊ ብቻ ሳይሆን አእምሮም መንፈስም ስላለው መሰንከሉ አካላዊ ብቻ አይሆንም፤ እንዳያስብ አእምሮውን ማፈን ግዴታ ይሆናል፤ ለአምባ ገነኖች ችግር የሚመጣው የሰዎች አእምሮ ሲያስብ ነው፤ ያሰበውንም መናገርና መጻፍ ሲጀምር ነው፤ ‹‹መጥፎ ሀሰብ››፣ ማለትም ለጨቋኞቹ የማይበጅ ጥሩ ሀሳብ በንግግር፣ በጽሑፍ፣ በራድዮና በቴሌቪዥን ቢተላላፍና ብዙ ሰዎች ቢሰሙት አገር ይረበሻል፤ ሰው ሁሉ ሽብርተኛ ይሆናል፤ አገዛዙ ሕዝቡን ለመሰንከል ብዙ ዘዴዎች አሉት፤ በስም ማጥፋት እንዳልከሰስ ዘዴዎቹን አልናገርም፤ ነገር ግነ ክፉ እንቅልፍ ይዞት የሄደ ካልሆነ በቀር የማያውቃቸው የለም፤ የማያውቅ ካለ በየቤቱ እየመጡ ይተዋወቁታል፡፡
ወያኔ የትግራይን ሕዝብ አንድ ለአሥር ጠርንፎ ከሃያ ዓመታት በኋላ ውሉ ጠፋበትና ጥርነፋው ላላ! የቂል ነገር ለትግራይ ያልተሳካውን ጥርነፋ በቀረው የኢትዮጵያ ሕዝብ ላይም ለመዘርጋት አቅዷል ይባላል፤ የወያኔ መሪዎች በአዲስ አበባ ቤቶችን አፍርሰው መንገድ ከሠሩ በኋላ ባቡር ትዝ ሲላቸው መንገዱን አፍርሰው ሀዲድ ለመሥራት ይሞክራሉ፤ ጥርነፋ በትግራይ እንዳልሠራ እያዩ በቀሩት ክልሎች ያሉትን ሰዎች ለመጠርነፍ ይፈልጋሉ፤ ጭንቅላተቸው ውስጥ ያለው ምንድን ነው ያሰኛል፤ እንኳን እንዲህ መክሸፉ በተግባር እየታየ ይቅርና ማሰብ ለሚችል በሀሳብም ደረጃ የከሸፈ ነገር ነው፤ እንስሳትን መሰንከል ቀላል ነው፤ ጉልበትን በበለጠ ጉልበት ማሸነፍ ነው፤ መናገርን መሰንከል ግን አይቻልም፤ ምላሱ ቢቆረጥበትም ሰው ሌላ መንገድ ይፈልጋል፤ በደርግ ዘመን ከኤንሪኮ በር ላይ የማይጠፋ ወፍራም ድሪቶ የሚለብስ ዲዳ ሰው ነበር፤ አንዳንድ ቀን ያየውን ‹‹ሲያወራ›› አንዳንዶች ያስይዘናል በማለት ይሸሹት ነበር፤ ያያቸው ወታደሮች መሆናቸውን በራሱ ላይ መለዮ በእጁ ያሳይና ሹመታቸውን ደግሞ በትከሻው ወይም በክንዱ ላይ እያመለከተ ሰዎችን ጨረሷቸው ለማለት በእጁ አፉን ጥርግ ያደርጋል፤ እኛ እንደሰማነው ወታደሮቹም እየገባቸው በየጊዜው ይደበድቡት ነበር፡፡
ማሰብን መሰንከል ደግሞ ከመናገርን ወይም መጻፍን ከመሰንከል የበለጠ አስቸጋሪ ነው፤ ለኢጣልያ የገበረው ባንዳ ሁሉንም አየነው፤ አማኑኤል ደግ ነው፤ እያለ የኢጣልያኑን ቄሣር አሞገሰና በጊዜው በላበት፤ በኋላ የአጼ ኃይለ ሥላሴ አገዛዝ ሲመለስና ሲቋቋም ባንዳው ተገልብጦ ኢየሱስ ክርስቶስን ማለቴ ነው አለ! ሰምና ወርቅ የሚባለው የተፈጠረው ሀሳብን የመግለጽ መሰንከልን ለማክሸፍ ነው፤ ማሰብን መሰንከል እስካልተቻለ ድረስ ሀሳብን መግለጽን መሰንከል አይቻልም፡፡
የሰንካዮችን ጭንቅላት አልፎ ሊሄድ የማይችል አንድ ታሪክ ደጋግሞ ያረጋገጠው ነገር አለ፤ ልፋ ያለው ዳውላ ይሸከማል፤ እንደሚባለው ጨቋኞችና አፋኞች እንደእንስሳ ለሆዳቸው ብቻ የሚገዙ ታማኝ አገልጋዮችን እየመለመሉ ዙሪያቸውን ያጥራሉ፤ ነገር ግን የሆዳሞቹ አገልጋዮች በሀሳብ ወረርሺኝ ሲመታና ሲነቃ አፋኞች ማሰብን ለመሰንከል ባለመቻላቸው የራሳቸው ታማኝ አገልጋዮች ይገለብጧቸዋል፤ ይህ የታሪክ እውነት ቢገባቸው ማሰብን መሰንከል መሞከሩ ቀርቶ ሀሳብን መግለጽንም ለመሰንከል አይሞክሩም ነበር፤ ምክንያቱም ማሰብ በሚቻልበትና ሀሳብን በነጻነት መግለጽ በሚቻልበት አገር ሀሳብ አይፈነዳም፤ ሀሳብ እንደሚፈነዳ፣ ከፈነዳም በኋላ እንደወረርሺኝ መንደር ሳይመርጥ፣ ጎሣ ሳይመርጥ፣ የቋንቋና የሃይማኖት ልዩነት ሳያግደው፣ ሀሳብ ብቻ ሊያግደው የሚፈልገውን ኃይል ሁሉ በዘዴ እያሽመደመደ ይንቀለቀላል፤ ይስፋፋል፡፡
አብርሃም ሊንከን አለ እንደሚባለው ‹ጥቂት ሰዎችን ሁልጊዜ ማታለል ይቻላል፤ ሁሉንም ሰው ለጥቂት ጊዜ ማታለል ያቻላል፤ ነገር ግን ሁሉንም ሰው ሁልጊዜ ማታለል አይቻልም፤› ለጥቂት ጊዜ የታለሉት ማታለልን ይማሩና ያታልላሉ! የተኙ መስለው ያሸልባሉ፤ የሚያለብሱ መስለው ያራቁታሉ፤ የሚያከብሩ መስለው ያዋርዳሉ፡፡
በመጨረሻም ተጠርናፊዎች ጠርናፊዎች ይሆኑና መክሸፍ ይቀጥላል! ጠርናፊም እስኪጠረነፍ ሌላ ነገር አላስተማረም፤ ተጠርናፊም ራሱን ከጥርነፋ እስኪያወጣ የተማረው ሌላ ነገር የለም፤ ማስረጃ ከተፈለገ ተቃዋሚ በሚባሉት ቡድኖች ውስጥ ሞልቶአል!!
መጨረሻም በኢጣልያ የአገዛዝ ዘመን አምስት ለአንድ ጥርነፋ ማለት አንድ ኢጣልያዊ ለአምስት አበሻ ማለት ይሆንና አንድ ጠርናፊና አምስት ተጠርናፊዎች በቋንቋና በባህል የማይግባቡ፣ በታሪክም ሆነ በማኅበረሰብ ኑሮ ዝምድና የሌላቸው፣ የወደፊቱም ሕይወታቸው በተረጋገጠ የበላይነትና የበታችነት ደረጃ የተወሰነ ስለሚሆን ጥርነፋው ትርጉም ያለው ሊመስል ይችላል፤ አምስት አበሻ ለአንድ አበሻ መጠርነፍ ግን በጠርናፊም ሆነ በተጠርናፊ በኩል ብርቱ የማሰብ ችግር (ከመንግሥተ ሰማያትም ቢሆን አመጣሃለሁ! ያለው ሰውዬ ዓይነት) ከሌለ በቀር ከንቱ ነው፤ በቀላሉ አንድ ለአምስት በማድረግ ዓላማውን መገልበጥ ይቻላል!አንድና አምስት ስድስት ነው፤ እንዲሁም አምስትና አንድ ስድስት ነው፤ ሁለትና አራት ስድስት ነው፤ ሦስትና ሦስትም ስድስት ነው፤ በነዚህ ቁጥሮች ውስጥ ሰው የምንለው ማንን ነው? ከብት የምንለው ማንን ነው? ሁሉም ሰዎች ከሆኑ ጠርናፊና ተጠርናፊ አይኖርም፡፡

የቀድሞው የጋምቤላ ክልል ፕሬዚዳንት ከሃገር ፈረጠጡ

February 1/2014


(ዘ-ሐበሻ) ራሳቸው በጠሩት ግምገማ፣ ራሳቸውን አስገምግመው ከፓርቲው ሊቀመንበርነታቸው መነሳታቸው የንጽህናቸው ውጤት መሆኑን ሲናገሩ እንደነበረ የሚነገርላቸውና በአንድ ወቅት በጋምቤላ ስለነበረው ጭፍጨፋ ተጠያቂ ነህ ሲባሉ “መሳሪያውን ያቀበለው መለስ ዜናዊም መጠየቅ አለበት” ብለዋል የተባሉት የቀድሞው የጋምቤላ ክልል ፕሬዚዳንትና የአሁኑ የፌዴል ጉዳዮች ሚ/ር ደኤታ አቶ ኦሞት ኦባንግ ከሃገር መፈርጠጣቸው ተሰማ።

በስልጣን ዘመናቸው ፕሬዚዳንቱ የክልሉን ደን እያስጨፈጨፈና ህዝቡን እያፈናቀለ ስላለው የመሬት ሽያጭና ነጠቃ የክልሉ እጅ የለበትም በሚል የተናገሩት ኦሞት ሂይውማን ራይትስ ዎች ባወጣው ሪፖርት ላይ በክልሉ ስለሚካሄደው የመሬት ነጠቃ አቶ በረከት ስምኦን በበኩላቸው ምላሽ ሲሰጡ በክልሉ ከሶስት ሚሊዮን ሄክታር በላይ ባለቤት የሌለው መሬት መኖሩን መናገራቸው አይዘነጋም።

ኦሞት ኦባንግ ከሃገር እንዳይወጡ ከፍተኛ የሆነ ጥበቃ ሲደረግባቸው እንደነበር የሚታወስ ሲሆን በተለይም በጋምቤላ ክልል ስለተፈጸሙት የጅምላ ጭፍጨፋዎች በዓለም አቀፉ ፍርድ ቤት ምስክር ይሆናሉ በሚል ፍራቻ በሕወሓት/ኢሕአዴጎች ከሃገር እንዳይወጡ ይፈራ እንደነበርና የፌደራል ጉዳዮች ሚ/ር ደኤታ የተደረጉትም “ጠላትህን አታርቀው፤ አቅርበውና እንስቅቃሴውን ተከታተለው” በሚለው የፖለቲካ አካሄድ እንደነበር የውስጥ መረጃዎች ይጠቁማሉ።

ይህን በማስመልከትም አዲሲቷ ኢትዮጵያ ለጋራ ንቅናቄ በአንድ ወቅት ባወጣው መረጃ “አቶ ኦሞት ካገር ከወጡ አቶ መለስና መንግስታቸው ላይ ምስክር ይሆናሉ። አቶ ኦሞት ከተሰደዱ በአካል ለዓለም አቀፉ የወንጀለኞች ፍርድ ቤት ምስክርነታቸውን መስጠት ግዳጃቸው በመሆኑ የህወሃት ሰዎች ስጋት አለባቸው። ስለዚህ አቶ ኦሞት በተቀመጠላቸው የስድስት ወር የሃላፊነት ዘመናቸው አድርጉ የተባሉትን እየፈጸሙ ይኖራሉ። የህወሃት ሂሳብ ይህ ቢሆንም በመጨረሻ ያልታሰበ ሁኔታ ሊፈጠር እንደሚችል እገምታለሁ። ምክንያቱም ነገሮች ተነካክተዋል” የሚል አስተያየት አስነብቦ እንደነበር ይታወሳል።

የሚኒስትር ዲኤታውን ኩብለላ በተመለከተ በአዲስ አድማስ ጋዜጣ የተጠየቁት የፌደራል ጉዳዮች ሚኒስትር ዶ/ር ሽፈራው ተክለማርያም አቶ ኡመt በስራ ገበታቸው ላይ እንደሌሉ ማረጋገጣቸውን ገልጸው መስሪያ ቤታቸው ጉዳዩን እያጣራ እንደሚገኝ ሲናገሩ አቶ ኡመትም ወደ ሃገራቸው መመለስ እንደማይፈልጉ መናገራቸውን ጨምሮ የመጣው መረጃ ሲጠቁም፤ አሁን ግን የት ሃገር እንዳሉ ለጊዜው ማረጋገጥ እንዳልተቻለ ተጠቁሟል።

በጋምቤላ በተፈፀመው ጭፍጨፋ የሚከተሉት ሰዎች በዋነኝነት ለፍርድ መቅረብ አለባቸው የሚሉ አስተያየት ሰጪዎች አሉ።

1. አባይ ፀሀዬ (በጊዜው የፌደራል ጉዳዮች ሚኒስትር የነበረ)
2. ዶ/ር ገብረአብ ባርናባስ (በጊዜው ሚኒስትር ደኤታ የነበረና በቦታው በመገኘት ጭፍጨፋውን ያስተባብር የነበረ)
3. ኮለኔል ፀጋዬ (በጊዜው በቦታው የነበረው ወታደራዊ ሀይል አዛዥ)
4. ኡመት ኦባንግ (አሁን ከሃገር የፈረጠጡት የቀድሞው የጋምቤላ ክልል አስተዳዳሪ)።

አስገራሚ ዜና – ሽመልስ ከማል ተሳደቡ፣ አስፈራሩ

January31/2014


አስገራሚ ዜና – ሽመልስ ከማል ተሳደቡ፣ አስፈራሩ “በአብዛኛዎቹ የህትመት ሚዲያዎች ላይ የሚታየው ማስታወቂያ እንጥል እቆርጣለሁ፣ ግግ እቧጥጣለሁ የሚል የአንድ ደብተራ ማስታወቂያ ነው” አቶ ሽመልስ ከማል መንግስት የህትመት ውጤቶች አከፋፋዮች ላይ እርምጃ እንደሚወስድ ፍንጭ ሰጠ በዘሪሁን ሙሉጌታ የመንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ፅ/ቤት ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ሽመልስ ከማል በሀገሪቱ ውስጥ ፈርጀ ብዙ ኀሳቦች ለህብረተሰቡ እንዳይደርስ እያደረጉ ነው ባሉዋቸው የጋዜጣና መፅሔት አከፋፋዮች ላይ መንግስት በፍጥነት የማስተካከያ እርምጃ እንደሚወስድ አስታወቁ። ሚኒስትር ዴኤታው ይሄህን የተናገሩት “የዴሞክራሲያዊ ልማታዊ መንግስትና የመገናኛ ብዙኃን ግንኙነት” በሚል ርዕስ የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የጆርናሊዝምና ኮሙኒኬሽን ትምህርት ቤት በኢንተርኮንቲነታል ሆቴል ሰሞኑን ባዘጋጀው የአንድ ቀን ሲምፖዚየም መዝጊያ ላይ ነው። የፕሬስ ነፃነት አፈና ሲነሳ በአከፋፋዮች አማካኝነት የሚደረግ አፈና አንዱ መሆኑን በመጥቀስ ጥቂት መፅሔቶችንና ጋዜጦችን በባለቤትነት የያዙ ግለሰቦች የማከፋፈል ስራውን በሞኖፖል ይዘው የአመለካከት ፈርጀ ብዙነት እንዳይኖር በማድረግ፣ በርካታ ህትመቶችን በለጋነታቸው ለሞት እንዲበቁ በማድረግ የአፈና ስራ ውስጥ የገቡ ወገኖች አሰራራቸው በፍጥነት መስተካከል አለበት ብለዋል።

“ሚዲያን የመደጎምና የማስተካከሉ ስራ መንግስት በአግባቡ በተጠና ሁኔታ መግባት እንዳለበት ያምናል” ያሉት ሚኒስትር ዲኤታው በሚዲያ የኀሳብ ገበያ ውስጥ ምቹ ሁኔታዎችን በማዘጋጀት ለኢንዱስትሪው ቀና እድገት አስፈላጊ መሆኑን ጠቅሰዋል።

በአከፋፋዮች በኩል በርካታ ችግሮች ተለይተው እየተጠኑ መሆኑንም ጠቁመዋል። የህትመት ሚዲያው ብቻ ሳይሆን የሕዝብ የመገናኛ ብዙኀን አውታሮች ከችግሮች ነፃ አለመውጣታቸውንም የጠቀሱት አቶ ሽመልስ መንግስት ፈጣን መረጃ የሚሰጥ የሚዲያ ስርዓት እንዲፈጠር እንደሚፈልግ ገልጸዋል። መንግስት መረጃዎችን በገፍ የሚያቀርብ፣ ጥራት ባለውና ወቅታዊ በሆነ መንገድ የሚሰራ የሚዲያ ስርዓት እንዲገነባ ይፈልጋልም ብለዋል። ብሔራዊ የሚዲያ ፖሊሲው በመድብለ ፓርቲ ስርዓት ማዕቀፍ ውስጥ ሆኖ የህብረተሰቡን የፖለቲካ ብዙሃነት፣ ባህላዊና ሀይማኖታዊ ፈርጀብዙነት ከመቀበል የሚነሳ መሆኑ አስታውሰው፤ ነገር ግን ሚዲያው በማንኛውም የባለቤትነት ውስጥ ቢሆንም ብሔራዊ መግባባትን ለማስረፅ መተኪያ የሌለው ቀዳሚ ሚና እንዲጫወት ፍላጎት እንዳለው ገልፀዋል። ሚዲያው በብሔራ ዊ መግባባት ላይ እንዲሰራ መንግስት ቢፈልግም ከማንኛውም ርዕዮተዓለም ተፅዕኖ ነፃ እንዲሆን ይፈልጋል ብለዋል። አሁን ያለው የሚዲያ ችግር በንግድ ሚዲያ መርህ ወይም በገበያ መርህ መንቀሳቀስ አለመቻል መሆኑን የጠቆሙት አቶ ሽመልስ አብዛኛዎቹ ሚዲያዎቻቸው ገበያቸውን ከማስታወቂያ የሚሸፍኑ አይደሉም ብለዋል።

 “በአብዛኛዎቹ የህትመት ሚዲያዎች ላይ የሚታየው ማስታወቂያ “እንጥል እቆርጣለሁ፣ ግግ እቧጥጣለሁ” የሚል የአንድ ደብተራ ማስታወቂያ ነው። ከዚህ ውጪ ሌላ ማስታወቂያ የላቸውም። ኮሜርሺያል አይደሉም፤ ኮሜሪሻያል ካልሆኑ ይደጎማሉ። በድጎማ የሚተዳደሩ ከሆነ ታማኝ አንባቢ ነው ያላቸው። ከተወሰኑ ርዕዮተአለማዊ አጥሮች አልፈው መጓዝ አይፈልጉም። ስለሆነም የህትመት ሚዲያ እድገት ላይ አንድ ትልቅ ጋሬጣ የሆነው ከነፃ ሚዲያ ህግጋት ውጪ ተንጋዶ የበቀለ የሚዲያ አካሄድ ነው” ያሉት አቶ ሽመልስ ይህንን ለማስተካከል መንግስትን ጨምሮ ሁሉም ወገኖች ሊተባበሩ ይገባል ብለዋል። የሰንደቅ ዜናዎች (ጥር 21/2006)

ጎልጉል: የድረገጽ ጋዜጣ

Friday, January 31, 2014

“ታሪክ ለባለ ታሪኩ”

January 31, 2014
ገብረመድህን አርአያ፣ አውስትራሊያ
Ato Gebremedhin Araya is one of former Tigray People Liberation Front (TPLF) leaders
አቶ ገብረመድህን አርአያ የቀድሞ የሀወሀት ገንዘብ ያዥ
ኢትዮጵያ ሃገራችን ትልቁ እድሏ ከጥንት ዘመን ጀምሮ እስከ ዛሬ ድረስ ብዙ የታሪክ ሊቃውንትና ጸሓፍት ያፈራች ሃገር መሆኗ ነው።
በጥንቱ ዘመን በኢትዮጵያ መቀመጫቸውን አክሱም ያደረጉት ነገሥታት ታሪካቸውን እና ጥበባቸውን በሳብኛና በግእዝ እያጻፉ አዘጋጀተዋል። በመቀጠልም መቀመጫቸውን ወደ ዛጔ፣ ላስታ ላሊበላ፣ ወሎ ሲተላለፍ በዚያ የነገሡ ነገሥታትም ታሪካቸውን እና ጥበባቸውን በግእዝና በአማርኛ እያዘጋጁ አልፈዋል። የነገሥታቱ መቀመጫ ከወሎ ወደ ሸዋ፤ ከዛም ወደ ጎንደር ሲሸጋገር፣ የነበረው ታሪክ፣ ጥበብና የነገሥታቱ ዝርዝር ሁኔታ ተዘጋጅተው ተመዝግበዋል።
የታሪክ ሊቃውንት የነጋሥታቱን ብርቱና ደካማ ጎኖቻቸውን እና የሰሩትን ታሪክና ገድል ለኢትዮጵያ ሕዝብ በማሳወቅ፣ ሕዝቡም በተራው ያለፉት ነገሥታት የጣሉበትን የጀግንነት አደራ እንዲጠብቅ አድርጎታል። የኢትዮጵያን ሉአላዊነት፣ ዝና እና ክብር እንዲሁም ታሪክና የታሪክ ቅርሶቿ በክብር እንዲንከባከባቸው በሰጡት አደራ መሰረት ኢትዮጵያ ለማንም ቅኝ ገዢ ሳትንበረከክ በዓለም ደረጃ ዝነኛ ሆና የወጣች ሃገር እንድትሆን አድርገዋታል።
የታሪክ ሊቃውንት በ845 በኢትዮጵያ አክሱም ዘመነ መንግሥት በኢትዮጵያ ንጉሥ አንበሳ ውድም ልታወድም የተነሳችው ዮዲት ጉዲት ዙፋኑን ገልብጣ፣ አብያተ ክርስቲያናቱን በማቃጠል፣ ሃውልቶችን እያፈረሰች ታሪካዊ ቅርሶችን በማውደም፣ ክርስቲያኖችን በመጨፍጨፍ ብዙ ከባድ ግፎችን ፈጽማለች። ቀጥሎም በ1515 በአፄ ልብነ ድንግል ዘመን መንግሥት ግራኝ አህመድ የተባለ ጠላት ተነስቶ ብዙ አብያተ ክርስቲያናትን፣ ታሪካዊ ገዳማትን እና ታሪካዊ መዛግብትን ከማውደሙም በላይ፣ ክርስቲያኖችንም አንገታቸውን በሰይፍ እየቀላ ሕዝብ ጨርሷል። ታሪክ ጸሐፊዎችም በዮዲት ጉዲትና በግራኝ አህመድ የተፈጸመውን ግፍ በጥቁር ታሪክነቱ ከትበው ለትውልደ ኢትዮጵያውያን አስተላልፈዋል።
አሁን ባለንበት ዘመን ከሰሜን ኢትዮጵያ ትግራይ የመጣው ገዢ፣ ህዝባዊ ወያኔ ሓርነት ትግራይ (ህወሓት) ኢትዮጵያን እና ሕዝቧን ከላይ ከተጠቀሱት የኢትዮጵያ ጠላቶች እጅግ በጣም ተወዳዳሪ የማይገኝለት፣ በክፉ መልኩ ኢትዮጵያን እና ሕዝቧን ያወደመ፣ የሃገር ሉአላዊነትን ያፈረሰ፣ ሃገር የሸጠ፣ ወጣት ሴቶችን እና ወንዶችን ለባርነትና ለስደት የዳረገ ነው። ከየት መጣ ሳይባል ኢትዮጵያን በቅኝ ግዛት በመቆጣጠር ሃገር በማፍረስ፣ ሕዝብን ከተወለደበት በማፈናቀል የሚፈጽመውን ፋሽስታዊ ተግባራቱን የታሪክ ጸሐፊዎችና የኢኮኖሚ ሊቃውንት ኢትዮጵያውያን እየጻፉት ነው።
በህዳር 2006 መጨረሻ አስደንጋጭ ዜና በዓለም ሚዲያዎች ተነገረ። የደቡብ አፍሪካው የነፃነት አባት ኔልሰን ማንዴላ ከዚች ዓለም በሞት እንደተለየ ተገለጸ። የዓለም ሕዝብና መሪዎቹ የተሰማቸውን ጥልቅ ሃዘን በማስተላለፍ የኔልሰን ማንዴላን አንጸባራቂ ታሪክና ኤ.ኤን.ሲን በመምራት የከፈሉትን መስዋእትነት፣ በተካሄደው መራራ ትግል ደቡብ አፍሪካን ከአፓርታይድ ስርዓት አላቀው ሃገሪቷን እና ሕዝቧን ነፃ ምውጣታቸውን፣ እስከ ግባተ መሬታቸው ድረስ በትግል የፈጸሙትን አኩሪ ታሪካቸውን እና ገድላቸውን ካለምንም ማቋረጥ በዓለም ዙሪያ ነግሮላቸዋል፣ የሰላምና የእርቅ አባትም ተብለዋል።
በቀብራቸው እለትም ከ100 በላይ የዓለም መሪዎች ደቡብ አፍሪካ ድረስ በመጓዝ ለመጀመሪያ ጊዜ በዓለም ያልታየ እጅግ የደመቀ የቀብር ስነስርዓት ተፈጽሞላቸዋል። የዚህ ሁሉ ድምር ውጤት ማንዴላ የፈጸሙት የትግል ድልና ታሪክ ነው። ስለሆነም ታሪክ ለባለ ታሪኩ እንደሆነና እንደሚገባ በኔልሰን ማንዴላ ታይቷል። ጥቁር ታሪክ የተሸከመው ወያኔ ህወሓት ደግሞ ከትወልድ ወደ ትውልድ እየተላለፈ፣ እየተረገመና እየተወገዘ ልክ እንደ ዮዲት ጉዲት በሳጥናኤል ምስል እየታወሰ ይኖራል።
የኔልሰን ማንዴላን ህልፈት ተከትሎ የዓለም መሪዎች የተሰማቸውን ሃዘን ሲገልጹ፣ የዓለም ብዙሃን መገናኛዎችም ለሶስት ሳማንታት የቆየ ሰፊ ሽፋን ሰጥተውታል። በዚህም የተነሳ ለህወሓት አመራርና ካድሬዎቹ፣ እንዲሁም የፋሽስቱ ስርዓት መሳሪያ በመሆን የሚያገለግሉት ብአዴን፣ ኦህዴድ፣ ደቡብ ህዝቦች ተብለው በሚታወቁት የገዢው አጎብዳጆች ላይ የራስ ምታት ለቆባቸው ሰንብቷል። ምክንያቱም የህወሓት መሪ ከዚህ ዓለም በሞት ሲቀጠፍ ማንም የዓለም መሪም ሆነ ሕዝብ ከግምት ውስጥ ስለአላስገባው። ሚዲያውን በተመለከተ አልጀዚራና ቢቢሲ ከ2 ደቂቃ ባነሰ ጊዜ መለስ ዜናዊ የኢትዮጵያው አምባገነን መሪ ሞተ ብለው ከመናገር የዘለለ ምንም አልጨመሩም።
በ24/12/2013 በአይጋ ፎረም ርእሰ አንቀጽ “ማንዴላን በማሳበጥ የመለስ ራእይ አይሟሽሽም”!! በሚል ርእስ ስር የተጻፈውን አንኳር አንኳሩን ልዳስስ፤
ከመነሻው ጀምሮ ኔልሰን ማንዴላን በመጥፎ ስምና ተግባር እያብጠለጠለ የመለስ ራይእይን እና ጀግንነት፤ ሀገር ወዳድነት ወዘተ. እያለ ሙግስናውን ይቀጥላል፤
- ጀግናው መለስ ዜናዊ ጦርነት ሳይንስ እንጂ በእድል የሚገኝ አይደለም ብሎ የተነተነ ምሁር ሲሆን፣ ፋሽስት በሆነው ደርግ ላይ ያረጋገጠ ጀግናና የብዙ ጀግኖች ፈጣሪ ነው ይላል፤
በመሰረቱ የዚህ ርእሰ አንቀጽ ጸሐፊ የመለስ ዜናዊን ማንነት የማያውቅ፣ ለጥቅሙ ብሎ በአየር ላይ የሚንሳፈፍ ፊኛ ፍጡር ነው። መለስ ዜናዊ ከተሓህት/ህወሓት ለትግል ከተደባለቀበት ጊዜ አንስቶ በጦርነት ተሳተፍ ተብሎ በግዴታ በተሰለፈባቸው ጦርነቶች ገና የመጀመሪያዋ ጥይት ስትተኮስ ፈርቶ የሸሸ ለመሆኑ በጊዜው የነበሩ የተሓህት ታጋዮች በሚገባ እናውቃለን። በተሓህት ህግና ስነሥርአት መሰረት ከጦርነት ያፈገፈገ ሞት ይፈረድበታል። መለስ ዜናዊ በአደዋ፣ ፈረሰማይ፣ አዲደእሮ፣ ማይቅንጣል፣ ሃገረሰላም፣ አዲ-ኮኸብ፣ ገለበዳ ወዘተ. በተደረጉት ጦርነቶች ፈርቶ የሸሸና ያፈገፈገ ግለሰብ ነው። ለምን እንደሌሎቹ አፈገፈጋችሁ ተብለው እንደተገደሉት መለስ ዜናዊ ስላልተገደለበት ምክንያት በቀዳሚነት የሚጠየቅበትና መልስ የሚሰጠው አረጋዊ በርሄ ነው። ጀግኖች የፈጠረ ማለት ቀልድና ቧልት ነው። ሌቦችን እና ዘራፊዎችን የፈጠረና ራሱም ቀንደኛ ዘራፊ የሆነ ሰው ጀግኖች ሊፈጥር አይችልም። መለስ ዜናዊ ምንም የጦርነት ሳይንስም ሆነ ወታደራዊ ጥበብ የለውም።
- የባለ ራእይነትና አርባኝነት ትልቁ ዓላማው ኢትዮጵያን በአጭር ጊዜ ከበለጽጉት ሃገሮች ጋር እንድትቀላቀል ማድረግ ነው። የትራንስፎርሜሽን እቅዱም የዚሁ ራእይ አካል ነው ይላል። ቀጠል በማድረግም፣ የታላቁ መሪ ራእይ ስኬታማ እየሆኑ መምጣታቸውን እየተመለከትን ነው። የኢትዮጵያን ሕዝብ ከጭቆና በማላቀቅ የኢኮኖሚ ባለቤትነቱን ያረጋገጠ ጀግና ነው ብሎም ያትታል።
ባለርእሰ አንቀጹ ይህን ሲጽፍ ከጠባብ አስተሳሰብ በመነሳት ነው። ህወሓት ኢትዮጵያን በቅኝ ግዛት ከተቆጣጠረበት ከግንቦት 1983 እስከ አሁን ድረስ በሃገሪቱና በሕዝቧ የወረደው ፋሽስታዊ አገዛዝ ረሃብ፣ በሽታ፣ እንክርት፣ መፈናቀል፣ እስራት፣ የሃገር መሬትና ድነበር ለባእዳን መሸጥ፣ ሰቆቃ፣ አፍኖ ማጥፋት ወዘተ. እየተፈጸሙ ያሉት የመለስ ዜናዊ ራእይና የህወሓት አመራሮች እቅድ መሆኑን ማወቅና መገንዘብ መቻል ያለበት ይመስለኛል። በመሰረቱ የርእሰ አንቀጹ ጸሐፊ ህወሓት ማነው? ሲፈጥርስ ዲሞክራሲያዊ ድርጅት ሆኖ የተፈጠረ ነው ወይ? የሕዝብ ፍቅርና ስሜት መስፈርቱ ነበር ወይ? በኢትዮጵያ ሉአላዊነት ያምን ነበር ወይ? የሚሉትን ጥያቄዎች ያላገናዘበ ከጠባብ ዘርኝነት ስሜት የመነጨ ነው። ውሸት በመደርደር መለስንም ሆነ የህወሓት አመራርን ለልማት የቆሙ አስመስሎ መጻፍ የጸሐፊው አባላት ሳይቀሩ ይታዘቡታል፣ ይንቁታል። ለምን ቢባል፣ ጸረ-ሕዝብና ጸረ-ሃገር የሆነውን የህወሓትን ጥቁር ታሪክ በወርቃማ ቀለም መለወጥ አይቻልምና። ኢትዮጵያን ለማፍረስ ትልእኮው አድርጎ የተነሳ ድርጅት ነው። ከላይ የተጠቀሱትን ኢትዮጵያን ወሮ ከተቆጣጠረ ጀምሮ በተግባር ታይተዋል። ስለሆነም የመለስ ራእይ ለእድገትና ትራንስፎርሜሽን የሚበጅ ሊሆን አይችለም። የመለስና ግብረአበሮቹ ባህሪና የፖሊሲ አቋመቸው ጸረ-ዲሞክራሲ፣ ጸረ-ሃገርና ሕዝብ ነው። በቅጽበት ተለውጠው ለሕዝብና ለሃገር ተቆርቋሪ ሊሆኑ አይችሉም። ዲሞክራሲ ገና ከጅምሩ አንድ ድርጅት ሲፈጠር መሰረታዊ የዲሞክራሲ መሰሶዎች አበጅቶ የሚዳሰስ፣ የሚታይ ጠንካራ የህንጻ ብረት መሳሪያ መሰረቱን የጣለ ከሆነ ነው። ህወሓት ግን ከዚህ ያፈነገጠ ጠባብና ዘረኛ ፋሽስት ድርጅት የዲሞክራሲ መድረኩ አይፈቅድለትም። ስለዚህ፣ የኢኮኖሚ ባለቤትነትን ያረጋገጠ የመለስ ዜናዊ የጀግንነት መግለጫ ነው የሚለው አባባል ከእውነት የራቀ የጠባብ ዘረኝነት አስተሳሰብ ነው። ውሃ የማይቋጥር ቀዳዳ ጣሳ እንበለው።
- መለስ ዜናዊ ከድህነት በላይ አዋራጅ ከድህነት በላይ ክፉ ጠላት የለም የሚለው ራእይ በወሰደው ቆራጥ አመራር የከተማና የገጠር ልማት ፖሊሲዎችና የአፈጻጸም ስልቶች የመለስን የልማት አርበኝነትና ጀግንነት በትክክል የሚያሳይና የሚያርጋግጡ ናቸው ይላል።
የመለስ ዜናዊ የልማት፣ የእድገት አርበኝነት እያሉ በየቀኑ ሕዝብን የሚያደነቁሩ የህወሓት ካድሬዎች ብአዴን፣ ኦህዴድ፣ ደቡብ ህዝቦች ናቸው። ህወሓት የፈጠራቸው ቅጥረኛ ድርጅቶች ሃገር እያፈረሱ፣ ሕዝብን እየጨፈጨፉ ሲሆን፣ መሪያቸው የህወሓት አመራር ድህነትን የተዋጋ፣ ሰፊ የልማት አውታር በመዘርጋት ኢትዮጵያን የለወጠ ብሎ መናገር ከሃዲነት ነው። ወያኔ ህወሓት በ1983 ሃገር ወሮ በቅኝ ግዘቱ ስር ባደረጋት ማግስት የኢትዮጵያ ሁኔታ ሙሉ በሙሉ ተለዋወጠ። ሕዝቡ በርካሽ እየገዛ የሚጠቀምባቸው የምግብ አይነቶች ጤፍ፣ ስንዴ፣ ቅቤ፣ ሥጋ ወዘተ. ዋጋ የሰማይ ጣራ ነካ። እስከ ደርግ ዘመን ፍጻሜ ድረስ ጤፍ በኩንታል ብር 45-60 ይሸጥ ነበር። ቅቤ፣ ዘይት፣ ስጋ ወዘተ. በተመጣጣኝ ዋጋ ይገበይ ነበር። በወያኔ ህወሓት አገዛዝ ቅቤ፣ ዘይት ወዘተ. ከገበያ ጠፍቷል። ጤፍ በኩንታል ብር 1500-1800 ደርሷል። ከአፄ ኃ/ሥላሴ እስከ ደርግ ዘመን ማንኛውም ኢትዮጵያዊ በቀን ሶስት ጊዜ መብላት ይችል ነበር። በአሁኑ ስርዓት ግን በቀን አንድ ጊዜ ለመብላት የሚታገለው ሕዝብ ቁጥሩ በርካታ ሆኗል። የኢትዮጵያ ሕዝብ በታሪክ አይቶት ለማያውቀው ድህነት ከተዳረገ 23 ዓመት አስቆጥሯል። መራሹ ገዢ ህወሓት የኢትዮጵያን ሕዝብ ለከፋ ረሃብ፣ በሽታና ስደት ዳርጓል። “እንኳንስ ዘንቦብሽ ዱሮውንም ጤዛ ነሽ” እንደሚባለው፣ ከትግሉ መነሻ ጀምሮ እስከ መጨረሻው ወያኔ ህወሓት ለኢትዮጵያና ህዝቧ ጠላት ሆኖ የተፈጠረ ድርጅት ነው። ከ1967 ጀምሮ ሕዝቧን በጎሳና በዘር ከፋፍዬ አጠፋታለሁ ብሎ የተነሳ ድርጅት ነው። ይህንን ከመጠን ያለፈ ጥላቻ ከትግሉ መነሻ ጀምሮ ሲያራምደው የመጣና ዛሬ በተግባር እያሳየው ነው። ምክንያቱ፣ ህወሓት ኢትዮጵያዊ አይደለምና።
የህወሓት ካድሬዎችና ደጋፊዎች የምትናገሩትና የምትጽፉት ገደብ የለሽ ውሸት፣ በሙስና እና በዝርፊያ ባገኛችሁት ንብረት ከነቤተሰባችሁ እየተንደላቀቃችሁ ጠግባችሁ ብታድሩም፣ ለኢትዮጵያ ሕዝብ የምትነግሩትና የምትጎስሙትን የውሸት ነጋሪት ውድቅ ካደረገው ዓመታት አልፈዋል። ህወሓት፣ ብአዴን፣ ኦህዴድ፣ ደቡብ ህዝቦች በሕዝብ ፊት ቀርባችሁ ፍርዳችሁን የምታገኙበት ጊዜ ተቃርባለች።
ህወሓት ኢትዮጵያን ሲቆጣጠር ተሸክሞት የመጣውን በቀል አማራው፣ ኦሮሞው፣ ጋምቤላው፣ አፋሩ፣ ኦጋዴኑ ወዘተ. ዘር የማጥፋት ተግባሩን ፈጽሞታል። አሁንም እያጠፋ፣ እየገደለ በየወህኒ ቤቶቹ እየማገደው ነው። ይዞት የመጣው ድህነትና በሽታን ብቻ ነው። ፖሊሲው የኢትዮጵያን ሕዝብ ከዓለም ሃገሮች በድህነት ከወለል በታች ያደረገ ስርዓት ነው። የኢትዮጵያ ገበሬ የመሬቱ ባለቤት በነበረበት ወቅት እራሱን እና ቤተሰቡን አብልቶ ቀሪውን ለገበያ በማቅረብ ሕዝቧ እንደአቅሙ በልቶና ጠጥቶ ያድር ነበር። የህወሓት አስተዳደር መሬት የመንግሥት ነው ብሎ በማወጁ የኢትዮጵያ ሕዝብ በገጠሩም በከተማም መሬት አልባ ሆኗል። የኢትዮጵያ ሕዝብ በገዛ ሃገሩ ሁለተኛ ዜጋ ከመሆኑ የተነሳ ሲሞት እንኳን የሚቀበርበት ቦታ ያጣ ሕዝብ ሆኗል። የመለስ ራእይ እድገትና ልማት ነው ተብሎ የተጻፈው፣ የኢትዮጵያ ሕዝብ በዚህ ሁኔታ ይቀጥላል የሚል አመለካከት ካለው ፈጽሞ ተሳስቷል። የኢትዮጵያ ሕዝብ ለገዢው ስርዓት መቃብር ቆፍሮ እየጠበቃቸው ነው። የሚተርፋቸው ጥቁር ታሪካቸው ከትውልድ ትውልድ መተለለፉ ብቻ ይሆናል።
ይህንን በዚሁ ላብቃ። በሌላ መልኩ ደግሞ መልስ ልስጥህ። “ማንዴላን በማሳበጥ የመለስ ዜናዊ ራእይ አይሟሽሽም” ያልከው ጸሐፊ ይህንን አንብብ።
ለመለስ ዜናዊ ከድህነት በላይ ክፉ ጠላት የለውም ብሎ መጻፉ ትክክል ነው፣ እስማማበታለሁ። መለስ ዜናዊ የድሃ ቤተስብ ልጅ መሆኑ እንዳይታወቅበት ብዙ ጊዜ ሲከላከል እንደነበር የምናውቀ ሃቅ ነው። መለስ ዜናዊ የሹምባሽ አስረስ ተሰማ የልጅ ልጅ ነው። የሴት አያቱም ወ/ሮ ዘውዲቱ መንገሻ ይባላሉ። አድዋ አውራጃ የተወለደው አስረስ ተሰማ ደግሞ ኤርትራዊ ሲሆን፣ መለስ ዜናዊ በትግራይ ያለው ትውልድ በሴት አያቱ ብቻ ነው። ወራሪው ጣልያን ለሁለተኛ ጊዜ በአፄ ኃ/ሥላሴ ዘመነ መንግሥት በተሸነፈበት ጊዜ የጣልያን ባንዳው ሹምባሽ አስረስ ተሰማ በግዞት አድዋ ውስጥ ነበር። በ6 ወራት ጣልያን ሙሉ በሙሉ ተሸንፎ ኢትዮጵያ ነጻነቷን ስትቀዳጅ አስራስ ተሰማ በደረሰበት ድንጋጤ ታሞ ሞተ። ዜናዊ አስረስም ከአድዋ ከተማ ወደ ኤርትራ አልተመለሰም። ቀደም ብሎ በጣሊያን ጊዜ ያገባቺው ሚስቱም አንዴ አድዋ፣ ሌላ ጊዜ ደግሞ አዲኳላ እየተመላለሱ ኖረዋል። ዜናዊ አስረስ ከወ/ሮ አለማሽ ወ/ልኡል መለስ ዜናዊን ጨምሮ 5 ልጆች ወልደዋል። ሌሎች ሁለት ኤርትራውያን ሴቶች ስለነበሩት በጠቅላላው 13 ልጆች አሉት። ዜናዊ አስረስ ጣልያንኛ በመጠኑ ይናገራል፣ ግን አይጽፍም። ዜናዊ አስረስ ሥራ ያልነበረው ድሃ ስለነበር ማመልከቻ ጸሐፊ በመሆን ኑሮውን ይገፋ ነበር። በኤርትራዊነቱ ስለሚታወቅ በአድዋ አውራጃ ውስጥ የእርሻ መሬት አልነበረውም። አባቱ ሹምባሽ አስረስ ተሰማ በሕዝብ ላይ ብዙ ግፍ የፈጸመና በጣሊያን ባንደነቱ የተነሳ አድዋ ውስጥ በጣም የተጠላና የተገለለ ነበር። ይህንን ሁሉም የአድዋ ሰው የሚያውቀው ሃቅ ነው። ድህነት የሚያሳፍርና የሚያሸማቅቅ አይደለም። የዚህ ጽሑፍ አቅራቢ የድሃ ልጅ ነኝ፣ ስለሆነም አላፍርበትም። በድህነቴ እኮራለሁ እንጂ የሌለኝን አለኝ ብዬ አልመጻደቅም።
መለስ ዜናዊ ግን ይህን አይቀበልም፣ ቤተሰቦቹም ይህን አይቀበሉም። ወንድሞቹ በክፉ ድህነት ያደጉ፣ እህቶቹ እነ ገርግስ ዜናዊ በአሁኑ ጊዜ ሚሊየነር ብትሆንም እንጀራ እየሸጠች ያደገች፣ ኒቆዲሞስ ዜናዊም እንቁላል እየቀቀለና እንጀራ በየጠላ ቤቱ ማታ ማታ እየሸጠ ያደገ ነው። ይህ ሁሉም ሥራ ነው፣ የሚያስከብር እንጂ የሚያሳፈር አይደለም። ዜናዊ አስረስ በአፄ ኃ/ሥላሴ ዘመን የአድዋ አውራጃ ገዢ ነበር ብሎ ዋሸ። የተናገረውን ሁሉ ረስቶ ለሞቱ በተቃረበ ጊዜ አፄ ኃ/ሥላሴ አዲስ አበባ ድረስ አስጠርተው የአባትህን ሥራ ልስጥህ፣ በአታሼ ድረጃ ሥራ ልመድብህ ሲሉኝ አልቀበልም አልኩ በማለት ተናግሯል። የወላጅ አባቴን ሃብትና ንብረት ጠብቄ ለልጆቼ አወርሳለሁ ብዬ ወደ አድዋ ተመልስኩ ብሎ የተናግረውን በድረ ገጾች አይቸዋልሁ። ይህ ሁሉ ደረቅ ውሸት ነው። የሚኖረው ተወልደን ባደግንበት አድዋ ከተማ ነው። እስከምናውቅ ድረስ ምንም አይነት ሃብት የሌለው፣ በማመልከቻ ጸሐፊነት የሚተዳደር ደሃ መሆኑን የወቅቱ የአድዋ ከተማ ሕዝብ ያውቀዋል። መለስም ሥልጣን እንደጨበጠ የደሃ ልጅ እንዳይባል በተክለ ሰውነቱ እንዳትጠጋው አደረጋት። ድህነት አያሳፍርም። በዚህ ዓለም አሳፋሪ ነገር ውሸት፣ ዝርፊያ፣ ሙስና፤ የንጹሃን ደም ማፈሰስ፣ ባጠቃላይ ወንጀል ናቸው። መለስ ዜናዊ የዚህ ሁሉ ቀንደኛ ተዋናይ ነው።
አንድ እውነተኛ ታሪክ ላቅርብ። የታሪኩ ባለቤት የአድዋ ሰው ሲሆኑ አሁን ግን አልፈዋል። ታሪኩን በጊዜው የነበሩ የአድዋ ከተማ ኗሪ የሚያውቁት ትክክለኛ የታሪክ ሃቅ ነው። አባቶቻችን ለኛ ለልጆቻቸው ነግረውና አስተምረው አልፈዋል።
አስረስ ተሰማ የታወቀ የጣሊያን ባንዳ ነበር። ጣሊያን ኢትዮጵያን እንደወረረ አስረስ ተሰማ የጣሊያኖች ታማኝ አሽከር ነበር። በጣሊያኖች የተሰጠው ማእረግ መጀመሪያ ኮማንዳቶሪ ሲሆን፣ ቀጥሎም ካባሌሪ ሆነ። ትንሽ እንደቆየም ሹምባሽ አስረስ ተብሎ ይጠራ ነበር። በአድዋ፣ አዲግራትና አክሱም በርካታ ግፎችን ፈጽሟል። ግለሰቦችን ሁለት እግራቸውን፤ እጆቻቸውን እና ጆሯቸውን በመቁረጥ እስከግድያ በሚደርስ ድርጊት አስቃይቷል። በገበያ ቀን ኢትዮጵያውያንን ሰላይ እያለ ሴት ከወንድ ሳይለይ ለገበያ በወጣው ሕዝብ ፊት አርባ አርባ ጅራፍ በመግረፍ ስፍር ቁጥር በሌለው ሕዝብ ላይ ስቃይ አድርሷል። በዚህ መጥፎ ተግባሩ የታወቀው ሹምባሽ አስረስ ተሰማ ለዓመታት በዚህ አይነት ሲቀጥል፣ የሕዝቡ አቤቱታ ለራስ ስዩም መንገሻ ይደርስ ነበር። ጣልያን ውድቀቱ በተቃረበበት ወቅት፣ ራስ ሥዩም ደጃዝማች ገ/ህይወት መሸሻን ይህንን ሰው እንደምንም ብለህ ይዘህ አምጣልኝ የሚል ትእዛዝ ሰጥተዋቸው ነበር። ደጃዝማቹ አካባቢውን ስለሚያውቁት በሶስት ሳምንት ክትትል አዲኳላ በምትገኘው ማይጫአት፣ ልዩ ስሟ አዲአዝማቲ ከምትባል ቦታ በሌሊት ተከታትለው ሹምባሽ አስረስ ተሰማን ከልጃቸው ዜናዊ አስረስ ጋር ማርከው ያዟቸው። በሌሊት ወደ አድዋ አሸጋግረው ለፊታውራሪ ገ/አምላክ ከነልጁ በግዞት እንዲቆይና ለፍርድ እንዲቀርብ አደረጉ። ፊታውራሪ ገ/አምላክ ማለት የወያኔ ህወሓት መሪ የነበረው በ1993 ከነስየ አብርሃ ጋር የተባረረው የአለምሰገድ ገ/አምላክ ወላጅ አባት ናቸው። አስረስ ተሰማ ለጥቂት ወራት በግዞት ላይ እንዳለ ኢትዮጵያ ጣልያንን አሸንፋ ነጻነቷን ተቀዳጀች። አስረስ ተሳማና ዜናዊ አስረስን የራስ ሥዩም አሽከሮች ይኖሩበት ወደነበረው አድዋ እንዳሥላሴ አዘዋወሯቸው። የጣልያንን ሽንፈት በሰማ ጊዜ ታሞ ከትንሽ ጊዜ በኋላ ሞተ። ሹምባሽ አስረስ በሞተ ጊዜ የሚቀበርበት ቦታ ታጥቶለት ነበር። ጥቂት የሆኑት ቀባሪዎቹ እንዳሥላሴ ቤተ ክርስቲያን በመሄድ በቦታው እንዲቀበር ቢማጸኑም፣ ንብሰ ገዳይና የጣልያን አሽከር በቤተ ክርስቲያናችን አናስቀብርም ብለው ከለከሉ። አስረስ ተሰማ ከቆየባት ቤቱ በግመት 300 ሜትር ርቀት ላይ በምትገኘው እንዳጽዮን ቤተ ክርስቲያን ሂደው ሲጠይቁ፣ ለምን እንዳሥላሴ አትቀብሩትም፣ የቤተ ክርስቲያኑ አለቃ አስረስ ተሰማ በዚች ቅድስት ማርያም ቦታ፣ ገዳይና ከሃዲ የጣልያን አሽከር አናስቀብርም የሚል መልስ ሰጥተው አሰናበቷቸው። በቀሪዎቹ ቤተ ክርስቲያናት እንደ እንዳ መድሃኔዓለም፣ እንዳ ገብርኤል፣ እንዳ ሚካኤል ፈጽሞ የማይታሰብ ሆነ። ያላቸው አማራጭ በረሃ ውስጥ ጉድጓድ ቆፍረው ምቅበር ብቻ ነበር። ማይ ምድማር ውሰዱ ተባሉ። ይህ ቦታ ደግሞ የወንድሞቻችን እስላሞች መካነ መቃብር ነው። በአጥር የተከለለ በጣም ሰፊ ሜዳ ነው። ቦታው በክብር የሚጠበቅ ስለሆነ ማንም ዝር አይልበትም። ስለሆነም እዛም አልተቻለም። እንደ አማራጭ ብለው ያሰቡት ማይ ምድማርን ተሻግሮ በሚገኝ ቦታ ላይ ሆነ። ማይ ምድማር ማለት፣ ከሰሜን በኩል ማይጓጓ ወንዝ፤ በፀሃይ መውጫ በኩል አሰብ ወንዝ የአድዋን ከተማ ለሁለት ሰንጥቆ የሚያልፍ ሲሆን፣ ሁለቱ የሚገናኙበት ቦታ ማይምድማር ተብሎ ይጠራል። አንዳንድ ጊዜም ጉራንጉር ተብሎ ይጠራል። ከማይምድማር ተሻግሮ የሚገኘው ቦታ ደግሞ የእንዳ ጊዮርጊስ መሬት ነው። ብዙ የመስኖ እርሻ ስላለበት ቀባሪዎቹ እዚያ ማድረግ እንደማይችሉ ስለተገነዘቡ፣ ሬሳውን ተሸክመው ወደ ተምቤን በሚያቀና መንገድ ተጉዘው አንድ በማይታወቅ ቦታ ቀበሩት። ከቀባሪዎቹ ከማስታውሳቸው መካከል አቶ ግብረቱ፣ አቶ ገብሩ፤ ልጃቸው ዜናዊ አስረስ ሲሆኑ ቀሪዎቹን ማስታውስ አልቻልኩም። የሹምባሽ አስረስ ተሰማ ሬሳ በረሃ እንደተጣለ አባቶቻን ነግረውናል። ይህንንም በወቅቱ የነበረው የአድዋ ሕዝብ በግልጽ የሚያውቀው ነው። ዜናዊ አስረስ ከሕዝብ የተገለለ፣ ልጆቹም ከሰው ተገልለው ማደጋቸው ሁሉም የሚያውቀው ሃቅ ነው።
መለስ ዜናዊ በቤልጂየም ሆስፒታል መሞቱን ለኢትዮጵያ ሕዝብ ያበሰረው ኢሳት ነበር። ሕይወቱ ያለፈችው ከብዙ ስቃይ ብኋላ ነው። ነብስ ይማር ያለው ኢትዮጵያዊ አልነበረም፣ እሰይ አምላክ ፍርድህን ሰጠህ ከማለት በስተቀር። ሬሳው ኢትዮጵያ ውስጥ ይቀበር አይቀበር አይታወቅም። የአያቱ ሹምባሽ አስረስ ተሰማ ሬሳ የገጠመው አይነት እድል እንደገጠመው እገምታለሁ። የማይቀረው ጊዜ ሲደርስ ስላሴ የተቀበረው ባዶ ሳጥን የአያቱን አይነት እድል እንዲሚያገኝ አልጠራጠርም። መለስ ዜናዊና ግብረ አበሮቹ ኢትዮጵያን ሲቆጣጠሩ በእናቱም በአባቱም የደጃዝማች ልጅ ነው ብለው በድረ ገጽ ተጽፎ አንብቤአለሁ። ከላይ እንደዘረዘርኩት ከእውነት የራቀ ነው። ባንዳዎቹ ኢትዮጵያ ወደ ነፃነቷ እያመራች በነበረችበት ጊዜ አስመራ ለነበረው ጄነራል ደቦኖ አቤቱታ አቅርበው ነበር። የኢትዮጵያ መንግሥት ለራሱ ሰዎች ራስ፣ ደጃዝማች፣ ፊታውራሪ ወዘተ. እያለ ማእረግ ሰጥቷቸዋል። እኛ የጣሊያን አሽከሮች ግን ምንም አይነት ማእረግ አልተሰጠንም። እኛም ልክ እንደ ኢትዮጵያውያኖቹ አይነት ማእረግ እንዲሰጠን እንፈልጋለን ብለው አቤት ብለው ነበር። አቤቱታቸውን ግራዚያኒ ወደ ሮም መንግሥት በማስተላለፍ ሹመቱን እንዲሰጥ ተፈቀደለት። በዚያም መሰረት የጣሊያኑ ባለሥልጣን ለባንዳዎቹ ደጃዝማች፣ ፊታውራሪ ወዘተ. እያለ አምበሸበሻቸው። ለአጭር ጊዜም ቢሆን፣ የዚህ ተጠቃሚ የሆኑት፣ የዜናዊ አስረስ ባለቤት የነበረች አለማሽ ገ/ልኡል፣ አባቷ ደጃዝማች ገ/ልኡል ሲሆኑ፣ ሹምባሽ አስረስም ደጃዝማችነት ተችሮት ነበር። ይሁንና ሳይጠራበት በኢትዮጵያ ጀግኖች ተይዞ ግዞት ገባ። ሌላው የዚህ ተጠቃሚ የነበሩት የስብሃት ነጋ አባት ፍታውራሪ ነጋ ነበሩ። ማእረጉን ባገኙ በጥቂት ወራት ጣልያን ተሸንፎ ሲወጣ፣ እስከ እለተ ሞታቸው ድረስ የአድዋ ሕዝብ በጣልያን የተሰጠውን ፊታውራሪነት አልተቀበለላቸውም። አብዛኛው ኗሪ አቶ ነጋ ሲላቸው፣ ጥቂት የቅርብ ጓደኞቻቸውና ዘመዶቻቸው በጣልያኑ ሹመት ፊታውራሪ ነጋ እያሉ ሲጠሯቸው አውቃለሁ።

ይድረስ ለህወሓት አመራር አባላት፣ ለብአዴን እና የደቡብ ኢትዮጵያ ብሔር ብሔረሰቦች እና ሕዝቦች ዲሞክራሲይዊ ንቅናቄ

የደቡብ አፍሪካው መሪ ኔልሰን ማንዴላ በሞቱ ጊዜ የዓለም ሕዝብና መሪዎቻቸው መራራ ሃዘናቸውን ገልጸዋል። የዓለም ብዙሃን መገናኛዎችም ሶስት ሳምንታት ሙሉ የኔልሰን ማንዴላን አርበኝነት፣ የንፃነት መሪነታቸውን፣ የሰላምና የፍቅር አባትነታቸውን እና አንጸባራቂ ታሪካቸውን በስፋት ዘግበዋል። ይህ ነው እንግዲህ ታሪክ ለሰሪው፣ ታሪክ ለባለታሪኩ የሚባለው።
መለስ በሞተበት ጊዜ ሕዝብ በቀበሌ ተገዶና ብር 100 የውሎ አበል እየተሰጠው ነው ለቀብር የወጣው። ከዓለም መሪዎች መካከል የተገኙትም ጥቂቶች ናቸው። አብዛኛዎቹም ከነአካቴው የሃዘን መግለጫ እንኳን አልላኩም። ሚዲያውም ቢሆን፣ በጣም ጥቂቶቹ፣ አምባገነኑ መሪ መለስ ዜናዊ ሞተ ብለው ከመዘብ ያለፈ አላደረጉም። የኢትዮጵያ ገዢው መደብ ግን በዚህ ተናዷል። በዚህ የተነሳ፣ “ማንዴላን በማሳበጥ የመለስ ራእይ አይሟሽሽም” ብለው ጽፈዋል። እናንተ በየጊዜው የነበራችሁ የህወሓት አመራር አብሎችና አባላት ሆይ፣ መሪዎቻችሁ የፈጸሙት ግፍና ግድያ ለናንተ ደስታ ይሰጣችኋል። በትግልና በአመራር ዘመናቸው ዘርፈዋል፣ በሙስና ተጨማልቀዋል፣ የኢትዮጵያን ሕዝብ ለስደት፣ ለረሃብና ለሰቆቃ ዳርገዋል። እናንተም የዚህ ሁሉ ግፍ ተሳታፊዎች ናችሁ። ድርጊታችሁና ታሪካችሁ በደም የተጨማለቀ መሆኑን ዘንግታችሁ መለስ ዜናዊን ከኔልሰን ማንዴላ ጋር ማወዳደራችሁ በጣም አሳፋሪ ነው። በሁለቱ መካከል ያለው ልዩነት የሰማይና የምድርን ያክል ነው። ባለፉት ጽሑፎቼ እንደገለጽኩት፣ አጠር ባለ መልኩ፣ ሕወሓት ኢትዮጵያን ተቆጣጥሮ ያለ ድርጅት ነው። ስርዓቱም ፋሽስት፣ አምባገነን፣ ጠባብ ዘረኛ፣ ሽብርተኛ፣ ጸረ-ኢትዮጵያ ሉዓላዊነት፣ ጸረ-ኢትዮጵያ ሕዝብና የባእዳን ቅጥረኛ ነው።
ከ1969 መጀመሪያ ጀምሮ በትግራይ ሰላማዊ ዜጋ ላይ ግድያውን አቀጣጠለው። ግድያው ሳያንሰው ሃብትና ንብረቱም ተወረሰ። ከደደቢት በረሃ የጀመረውን አማራ የትግራይ ሕዝብ ጠላት ነው በማለት በተለያዩ ጊዜያትና ቦታዎች አማራውን በመጨፍጨፍ የዘር ማጥፋት ወንጀል ፈጽመዋል። ለሴቶች በግዳጅ የማምከኛ መድሃኒት በመስጠት የአማራው ቁጥር እንዳይጨመር አድርገዋል። ከኖርበት ቀየውና መሬቱ በግዳጅ እንዲፈናቀል አድርገዋል።
ህወሓት ኢትዮጵያን እንደተቆጣጠረ ከ1985 መጀመሪያ ጀምሮ በኦሮሞ ሕዝብ ላይ ሰፊ የጥቃት ዘመቻ በመክፈት የግድያ፣ የቤት ማቃጠል፣ ንብረቱን መዝረፍና ከፍ ያለ ሰቆቃ አድርሶባቸዋል። እንደ አማራው ሁሉ ከመኖሪያ ቦታውና ከመሬቱ ላይ ተፈናቅሏል። የኦነግ አባል ናችሁ እየተባሉ በሺዎች የሚቆጠሩ ያለምንም የፍርድ ውሳኔ ወደ ወህኒ ወርደዋል። በየቦታው በከፍተኛ ትምህርት ተቋሟት የሚማሩት የኦሮም ልጆች ከትምህርታቸው ተባረዋል። የተባረሩትም፣ መባረራቸው አልበቃ ብሎ ለእስር ተዳርገዋል። ደጉና ሩህሩሁ የኦሮሞ ሕዝብ ከእርሻው ተፈናቅሎ የረሃብና የበሽታ ሰለባ ሆኗል።
ህወሃት በጋምቤላ አኝዋኮች ላይ በፈጸመው የዘር ማጥፋት ወንጀል ተጠያቂ ነው። ሕዝቡ ከመሬቱ ተፈናቅሎ አብዛኛው በጎረቤት ሃገሮች ስደተኛ ሆነው በየሃገሩ እየተንከራተተ በችግር ላይ ነው።
የኦጋዴን ሕዝብም የዘር ማጥፋት ወንጀል ተፈጽሞበታል። ቤት ንብረቱ በህወሓት ወታደሮች ተቃጥሎበታል። ሴት ልጆቹና ሚስቶቹ ተደፍረውበታል። በተጨማሪም ከመሬቱ ላይ ተፈናቅሎ ለስደት ተዳርጓል።
የአፋር ሕዝብም በሌሎቹ የኢትዮጵያ ጎሳዎች የደረሰው ደርሶበታል፣ እየደረሰበትም ነው። የኢትዮጵያን ሕዝብ ከማሰቃየት ባለፈ ደግሞ የኢትዮጵያን ዳር ድንበር ለሱዳን መንግሥት ሸጠዋል። ሃገሪቱን ካለባህር በር አስቀርተዋል። የሃገር ሃብትና ታሪካዊ ቅርሶችን አውደመዋል፣ ሸጠዋል። ጊዜው ሲደርስ በኢትዮጵያ ሕዝብና በሃገሪቱ ላይ ለፈጸማችሁት ወንጀል ለፍርድ ያቀርባችኋል።

ይድረስ ለትግራይ ሕዝብ

ውድ የትግራይ ሕዝብ ሆይ!! ተሓህት ደደቢት በረሃ እንደወረደ በየሰበብ አስባቡ በየቤተ ክርስቲያናት እየመጡ፣ የትግራይ ሕዝብ በደመኛ ጠላትህ በአማራው የተጠቃህ ነህ። ነፃ የነበረችው ትግራይ ሃገርህ ወድቃልችና ተነስ። ከመሪ ድርጅተህ ተሓህት ጎን ተሰልፈህ አማራው ጠላትህን ደምስስ፣ ሲሉህ የሰጠኸው መልስ፣ አማራ የትግራይ ሕዝብ ጠላት አይደለም፣ ሆኖም አያውቅም፤ አብረን ተባብረን እና ጎን ለጎን ተሰልፈን፣ በአድዋና በማይጨው ጦርነት ጠላት የደመሰስን እና በደማችን አንድ የሆንን ኢትዮጵያውያን ነን። የአማራ ጠላት የሚባል አናውቅም። ትግራይ ኢትዮጵያ፣ ኢትዮጵያም ትግራይ ናት፣ የቅኝ ግዛት አይደለችም። ስለዚህ ኢትዮጵያዊነታችንን የሚነፍገን ምንም ሃይል አይኖርም። ድርጅታችሁ ትሓህት የምትሉትንም አናውቀውም፣ አንቀበለውም ብለህ መልሰሃል።
ይህንን ዓላማቸውን ለማዛመት በየቦታው የተንቀሳቀሱት የተሓህት መሪዎች በሁሉም ቦታ ተመሳሳይ ተቃውሞ ገጠማቸው። ተቃውሞው በሁሉም ከተሞች ሲበዛባቸው በብስራት አማረ የሚመራው የፈዳያን ቡድን በጠራራ ፀሃይ ሕዝቡን ፈጀው። ከየከተማው ሰዎችን እያጋዙ በየእስር ቤቱ እያጎሩ ገደሉት። የገጠሩን ሕዝብ ደግሞ ‘ትግራዋይ ሸዋዊ’ (የትግራይ ሸዋ)፣ ፊውዳል፣ ጸረ-ትሓህት፣ ጸረ-ኤርትራ ትግል ወዘተ. በማለት በውሽት በመወንጀል በቀንና በሌሊት በአፋኝ ቡድን እየተያዘ፤ ሃብት ንብረቱ እየተወረሰ ሃለዋ 06 ተወረወረ። እዚያም ገብቶ በብዙ ሺህ የሚቆጠሩት እንደተገደሉ አንተው እራስህ የምታውቀው ሃቅ ስለሆነ ምስክር አያስፈልግህም። ልጆችህ በተሓህት እየታፈኑ ወደ ሜዳ ወጥታችሁ ታገሉ እየተባሉ ብዙ ሺዎች ወንድና ሴት ልጆችህን ለሻእቢያ አሻግሮ ሸጠብህ። በቀይ ኮከብና በተለያዩ ዘመቻዎች ለሻእቢያ ተሰልፈው በማያውቁት የኤርትራ በረሃ ማለትም በሳህል፣ አቁርደት፣ ከርከበት፣ ናቅፋ፣ ሰሎሞና ወድቀው ቀሩብህ። በወቅቱ አንተው የትግራይ ሕዝብ ተሓህት/ህወሓትን በግለጽ የተቃወምከውና ያወገዝከው ስለነበረ መስካሪ አያሻህም። ኢትዮጵያዊነትህን እና ለሰንደቅዓላማዋ ያለህን ፍቅር አስመስክረሃል፣ ታሪክም ዘግቦታል።
ውድ የትግራይ ሕዝብ ሆይ፤ የህወሓት አመራሮችን ማንነት ጠንቅቀህ ታውቃለህ። ዛሬ ኢትዮጵያ ሃገራችን በሰቆቃና በችግር ውቅያኖስ ውስጥ ሰምጣለች። ይህ የሆነበት ምክንያት የህወሓት መሪዎች ኤርትራውያን እና የትግራይ ባናዳዎች ተሰባስበው በህወሓት ስም ሃገር አውድመዋል። ባንተ ስም ብዙ ሸቅጠዋል። በስምህ የመጣውን ሰፊ እርዳታ የህወሓት መሪዎች ዘርፈው ሸጠዋል። ይህም ካንተ የተደበቀ አይደለም። ወያኔ በጠነሰሰው ተንኮል በጠራራ ፀሃይ ያለረህራሄ በቦምብ ተደብድበሃል፣ ይህ ነው የማይባል የሰውና የንብረት ውድመት ደርሶብሃል። ከኢትዮጵያውያን ወገኖችህ ጋር ቅራኔ ውስጥ ሊከቱህም ብዙ ጥረዋል። በቆራጥ ኢትዮጵያዊነትህ ቁጣህን በማሳየት የወያኔ መሪዎችን አሳፍረሃቸዋል፣ አሁንም በርታበት፣ ቀጥልበት። የህወሓት መሪዎች 40 ዓመት ሙሉ አሰቃይተውሃል፣ አሁን በቃኝ በል። ከኢትዮጵያዊ ወገነህ ጎን ተሰልፈህ ግንባር ቀደም በመሆን ይህንን የህወሓት ገዳይና ሽብርተኛ ቅጥረኛ ፋሽስት ስርዓት በተበባረው ሕዝባዊ አመጽ መቃብር አስገብተን የኢትዮጵያን ሉአላዊነት፣ አንድነታችንን እና ነፃነታችንን እንጎናጸፍ።
የተከበርክ የኢትዮጵያ ሕዝብ ሆይ፤ ሰላማዊ ትግል እያልን ጊዜ አንስጠው። የተጀመረውን ሕዝባዊ ቁጣ በማቀጣጠል እጅ ለእጅ ተያይዘን በሕዝባዊ ማእበል ወያኔን ደምስሰን ሃገራችን ኢትዮጵያን ነፃ እናውጣት።
የተቃዋሚ ፓርቲ መሪዎች ለመስዋእትነት ቁርጠኛ ሁናችሁ ውጡ፣ ሕዝቡን ምሩት። በውጭ ሃገር ያለህ ኢትዮጵያዊም የትግሉ የጀርባ አጥንት ስለሆንክ አስፈላጊውን ሁሉ ለማቅረብ ተዘጋጅ።
በበረሃ ያላችሁ የትጥቅ ታጋዮችም ውጡ፣ የፋሽስቱን የወያኔ ሰራዊት በምታውቁት የውጊያ ስልት አጥቁት። የኢትዮጵያ ሕዝብ ያልተቆጠበ ድጋፉን ይሰጣችኋል። ጊዜው አሁን ነው፣ ሕዝቡም የናንተው ነው።
ድል ሊትዮጵያ እናታችን!!
ጥር 2006

ኢህአዴግ ሚኒስትሮቹን የግንባሩን ስራ እንዲያከናውኑ መደበ

January31/2014

ጥር ፳፫ (ሃያ ሦስት) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ኢህአዴግ ፓርቲውን እንዲመሩ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን እና ሌሎች ሁለት ሚኒስትር ዴኤታዎችን ባለፉት ወራት መሾሙን ውስጥ አዋቂ ምንጮች ጠቆሙ፡፡

ኢህአዴግ የመንግስት መዋቅርን ከፓርቲው መዋቅር ጋር አደበላልቆ በመስራት ላይ እንደሚገኝ ተደጋጋሚ ወቀሳዎችና ትችቶች እየቀረቡበት የቆየ ሲሆን በዚህ መልኩ ግልጽ የሆነ አደረጃጀት በመያዝ የመንግስት ከፍተኛ አመራሮችን ሲመድብ ከአቶ መለስ ሞት በሃላ ይህ ለመጀመሪያ ጊዜ ነው ተብሎአል፡፡

ቀደም ሲል የግንባሩ ሊቀመንበርና ምክትል ሊቀመናብርት የግንባሩንና የአባል ፓርቲዎችን የሚመሩበት ሁኔታ የተለመደ ሲሆን የአሁኑ አደረጃጀት ግን ለየት የሚያደርገው በሚኒስትር ዴኤታ ማእረግ ጭምር በመንግስት ሃላፊነት ላይ የተመደቡ ሹማምንት ከነጥቅሞቻቸው ወደ ፓርቲው ሃላፊነት ተመድበው የመምጣታቸው ጉዳይ ነው፡፡ ሰዎቹ አብዛኛውን ጊዜያቸውን በፓርቲው ስራዎች እንደሚያጠፉ የጠቆሙት ምንጮቻችን ይህም ከመጪው ምርጫ ጋር በቀጥታ የተያዘ ነው፡፡
በዚሁ መሰረት አቶ ደመቀ መኮንን ምክትል ጠ/ሚኒስትርና የኢህአዴግ ጽ/ቤትን በበላይነት የሚመሩ ሲሆን አቶ ደስታ ተስፋው እና አቶ አማኑኤል አብርሃም በሚኒስትር ዴኤታ ማዕረግ በጠ/ሚኒስትር ጽ/ቤት ሆነው ግንባሩን በተለያዩ ሃላፊነቶች እንዲመሩ ተመድበዋል፡፡ እነዚህ ሹማምንት በመንግስት ገንዘብ፣ ነዳጅና ጊዜ የፓርቲ ስራዎችን ማከናወናቸው ፖለቲካዊ ሙስና መሆኑን ስለጉዳዩ ያነጋገርናቸው ወገኖች አስተያየታቸውን ሰጥተዋል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ ኢህአዴግ የተማሩ አባሎች የሉትም በሚል የሚደርስበትን ትችት አስተባብሎአል። ገዥው ፓርቲ ኢህአዴግ የመልካም አስተዳደር ችግሮችን መፍታት ያልቻለው የተማሩ አባላትና ተሿሚዎች ስለሌሉት ነው በሚል ከተቃዋሚዎችና ከሌሎች ወገኖች የሚቀርብበትን ተደጋጋሚ ትችት ሃሰት ነው ብሎአል፡፡

በጠቅላ ሚኒስቴር ቢሮ የሕዝብ ተሳትፎና አደረጃጀት ሚኒሰትር ዴኤታና የኢህአዴግ ጽ/ቤት የህዝብና የውጪ ግንኙነት ዘርፍ ኃላፊ የሆኑት አቶ ደስታ ተስፋው ለመንግስታዊው አዲስ ዘመን ጋዜጣ የዛሬ ዕትም በሰጡት መግለጫ በአሁን ወቅት የመልካም አስተዳደር ችግር አለባቸው የሚባሉት ስላልተማሩ ነው የሚል ድምዳሜ ላይ መድረስ አያግባባም ካሉ በሃላ በአሁኑ ወቅት የኢህአዴግ አባላት የትምህርት ደረጃቸውን እያሻሻሉ ነው ብለዋል፡፡

ተቃዋሚ ፓርቲዎች አጀንዳ አድርገው የሚያቀነቅኑት በፍጹም የተሳሳተ ነው ያሉት ሚኒስትር ዴኤታው በአባላት መካከል ውድድር ቢካሄድ የኢህአዴግ አባላት በትምህርትና በብቃት እንደሚበልጡ ምስክርነታቸውን ሰጥተዋል፡፡

አንድ የኢህአዴግ ተሹዋሚ ሲያጠፋ እርምጃ ከመውሰድ ይልቅ ወደሌላ ቦታ ማዛወር ሁኔታ እንዳለ ለቀረበላቸው ጥያቄም ሲመልሱ በኢህአዴግ ውስጥ አንድ ቦታ ብቁ ሆኖ ያልተገኘ ሌላ ቦታ ሄዶ እንዲሰራ እንደሚደረግ አምነዋል፡፡“በኢህአዴግ ድርጅት ውስጥ ባለው አሰራር መሰረት እያንዳንዱ ግለሰብ ተግባር ይሰጠዋል፡፡  የተሰጠውን ተግባር እንዴት እንደፈጸመ ይገመገማል፡፡በግምገማ ውጤቱ ስራውን በብቃት የፈጸመ አባል ተመስግኖ ለቀጣይ ስራ እንዲዘጋጅ ይደረጋል፡፡በአንጻሩ ደግሞ ድክመት የታየበት አባል እንዲያስተካክል የተለያዩ ተግባራት ይከናወናሉ፡፡ለምሳሌ ያህል ሂስ ይደረጋል፣እንደየሁኔታው በማስጠንቀቂያም ይታለፋል፡፡ የተመደበበት የስራ ቦታ ከብቃቱ ጋር የማይመጣጠን ሆኖ ከተገኘ ከቦታው ተነስቶ የሚችለው ስራ መደብ ላይ ይቀየራል ”ሲሉ አስረድተዋል፡፡

ድርጅቱ በአሁኑ ወቅት ትልቅ ችግር አድርጎ የሚያየው የኪራይ ሰብሳቢነት አስተሳሰብን ነው ያሉት አቶ ደስታ የመልካም አስተዳደር ችግሮች እየተባባሱ አለመምጣታቸውን፣እንዲያውም ወደመልካም አስተዳደር በጉዞ ላይ ነን በማለት እርስ በርሱ የተምታታ መግለጫ ሰጥተዋል፡፡

በጎንደር ክ/ሃገር ሳንጃ ወረዳ የልዩ ሃይል አዛዥ ሻለቃ ቀለሙ ክብረት መገደላቸው ተሰማ

January 31/2014

በጎንደር ክ/ሃገር ሳንጃ ወረዳና አካባቢው ሕዝብን ሲያሰቃይ ነበሩ የተባለት የልዩ ሃይል አዛዥ ሻለቃ ቀለሙ ክብረት መገደሉ ተሰማ። የአርበኞች ግንባር ለግድያው ሃላፊነቱን ወስዶ “ግለሰቡ የተገደለው በጥር 21-2006 ዓ.ም ከቀኑ 12 ሰዓት ላይ በኢትዮጵያ ሕዝብ አርበኞች ግንባር ሰርጎ ገቦች ማሰሮ ደንብ የተባለ ቦታ በጥይት ተደብድቦ ቆስሎ ወዲያውኑ ወደ ጎንደር ቸቸላ ሆስፒታል ቢወሰድም በማግስቱ ማለትም በጥር 22-2006 ዓ,ም ህይወቱ አልፏል።” ብሏል።



                                              (የአርበኞች ግንባር ወታደር – ፎቶ ፋይል)


እንደ አርበኞች ግንባር ገለጻ ከሆነ “ይህ ግለሰብ በወረዳው የሚገኙ የህብረተሰብ ክፍሎችን የአርበኞች ደጋፊ ናችሁ በሚል ሲያሰቃይ የነበረ ሲሆን፣ ብዙ ንፁሃን ግለሰቦችን በድርጅቱ ደጋፊነት ስም እየፈረጀ እንደገደለ፣ እንዳሰረና እንዲሰደዱ ሲያደርግ የነበረ መሆኑ ይታወቃል ። ይህን ተከትሎ የኢትዮጵያ ሕዝብ አርበኞች ግንባር ግለሰቡ ከድርጊቱ ታቅቦ ሰላማዊ ኑሮውን እንዲኖር ካልሆነ ግን አስፈላጊው እርምጃ እንደሚወሰድበት የፅሁፍ መልዕክት የደረሰው ቢሆንም ሊታረም ባለመቻሉ የኢትዮጵያ ሕዝብ አርበኞች ግንባር ሰርጎ ገቦች እርምጃ እንዲወስዱበት ተደርጓል።” ብሏል።


  (የአርበኞች ግንባር ሠራዊት በምረቃ ላይ – ፎቶ ከፋይል)

“በጎንደር አካባቢ ምንም አይነት ወታደራዊ እርምጃ በኢትዮጵያ ሕዝብ አርበኞች ግንባር ሠራዊት ሲወሰድ የአካባቢውን ሕዝብ ማንገላታቱ የተለመደ ቢሆንም ሻለቃ ቀለሙ ክብረት ከሞተበት ከትናንት ጀምሮ ግን በህዝቡ ከፍተኛ ስቃይ እያደረሰበትና ገዳዮቹን ታውቃላችሁ እናንተ ናችሁ እየደበቃችሁና ቀለብ እየሰፈራችሁ የምታስጨርሱን በሚል ብዙ ሰዎች እንደታሰሩ ታውቋል።” የሚለው የአርበኞች ግንባር ዜና “የኢትዮጵያ ሕዝብ አርበኞች ግንባር ወታደራዊ መምሪያ በበኩሉ ወደፊትም ቢሆን ወያኔና ተላላኪዎቹን ከዚህም በከፋ ሁኔታ አይቀጡ ቅጣት እንደሚቀጣ አስታውቆ ሕዝቡም ከመሬቱና ከንብረቱ እየተፈናቀለ መኖሩ ያበቃ ዘንድ ከኢትዮጵያ ሕዝብ አርበኞች ግንባር ሰራዊት ጎን በመሰለፍ ይህን አፋኝ ስርዓት ለመገርሰስ የበኩሉን አስተዋፅዖ ማበርከት እንዳለበት ጥሪያችንን እናስተላልፋለን” ብሏል።

በዚህ ዜና ዙሪያ የመንግስትን ምላሽ ለማካተት ያደረግነው ጥረት አልተሳካም።


ምንጭ.  ዘ-ሐበሻ

የመሬት ሽያጭ በኢትዮጵያ አልጀዚራ ( Ethiopia Land to Sale Aljaazra )

የኢትዮጵያ ሕዝብ አርበኞች ግንባር ሰራዊት መተማ አካባቢ ጥቃት ፈጸምኩ አለ

January 31/2014

(ዘ-ሐበሻ) የኢትዮጵያ ህዝብ አርበኞች ግንባር የአገራችን ኢትዮጵያን ዳር ድንባር ለሱዳን ለማስረከብ ሽር ጉድ እያለ የሚገኘውን የወያኔን አገዛዝ ጸረ-አገርና ጸረ-ህዝብ እንቅስቃሴ በመቃወም በመተማ አካባቢ ልዩ ስሙ ዘባጭ ባህር በተባለ ቦታ ከወያኔው 24ኛ ክፍለ- ጦር ጋር በጥር 21- 2006 ዓ.ም ከቀኑ 6 ሠዓት ላይ ባደረገው ውጊያ 14(አስራ አራት) ገድሎ 12(አስራ ሁለት) ማቁሰሉን አርበኛ ኑርጀባ ለዘ-ሐበሻ በላከው መረጃ አስታውቋል::

“በመተማና አካባቢው በተደጋጋሚ በአርበኛው ጥቃት እየተፈፀመበት የሚገኘው የወያኔው ቅጥረኛ ሠራዊት ህይወቱን ለማትረፍ እግሩ ወደመራው እየፈረጠጠ መሆኑ ሲታወቅ በደረሰበትም ጉዳት ማካካሻ ይሆነው ዘንድ ሰላማዊውን ነዋሪ በእናንተ ምሽግነት ነው እየተመታን ያለነው በሚል እንግልት እያደረሱበት መሆኑ ታውቋል።” የሚለው የአርበኛ ኑርጀባ ዘገባ “በተያያዘ ዜናም በጭልጋ ወረዳ ጫቁ የተባለ አካባቢ ነዋሪዎች ከብት፣በግና ፍየል በአካባቢው የወያኔ ታጣቂዎች እየታረደ እየተበላባቸው መሆኑ ታውቋል” ብሏል።

አርበኛ ኑርጀባ ዘገባውን ቀጥሎ “በዚሁ አካባቢና አጎራባች ወረዳዎች የወያኔው ተላላኪዎች ተደጋጋሚ ንብረትን የመዝረፍ ሂደት የተቆጣው ነዋሪ ለምንድን ነው ንብረታችንን የምትዘረፉት ምን አደረግናችሁ ብለው ሲጠይቁ እናንተ የኢትዮጵያ ሕዝብ አርበኞች ግንባር ደጋፊዎች ፣መንገድ መሪዎች እንዲሁም ስንቅ አቀባዮች ናችሁ የሚል ምክንያት ሰጥጧቸዋል። ሕዝቡም እኛ የአርበኛው አባልም ደጋፊም አይደለንም ከፈለጋችሁ እነሱን ተከታትላችሁ መዋጋት ትችላላችሁ እኛን ምን አድርጉ ነው የምትሉ? ሲሉ ምሬታቸውን ቢገልፁም እንግልቱ እንዳላበራ” ከአርበኛ ኑርጀባ መረጃ መረዳት ተችሏል።

ዘገባው ቀጥሎም “የወያኔው ተላላኪዎች በሕዝቡ ላይ እያደረሱ ያለው እንግልት ያስቆጣቸው ብዛት ያላቸው የአካባቢው አርሶ አደሮች የኢትዮጵያ ሕዝብ አርበኛች ግንባር ሠራዊትን እየተቀላቀሉ መሆኑን አስታውቋል።” ብሏል።

“በሌላ ዜና የአማራ ክልል ፀጥታ ዘርፍ ሃላፊ የሆነው ሙሉጌታ ወርቁ የተባለው ግለሰብ በክልላችን ቢሮዎች በሙሉ የኢትዮጵያ ሕዝብ አርበኞች ግንባር ሰዎች ተሰግስገዋል በሚል ምክንያት ሰሞኑን በየወረዳው ፅ/ቤት የማፅዳት ዘመቻ በሚል ከፍተኛ ስብሰባ እያደረገ ነው” ሲል አርበኞች ግንባር አስታወቀ። ግንባሩ ለዘ-ሐበሻ በላከው ዜና ” የኢትዮጵያ ሕዝብ አርበኞች ግንባር ተደጋጋሚ ጥቃት እያሰጋው የመጣው ሆድ አደሩ የአማራው ክልል ባልስልጣናት ሕዝቡን በተለያየ ምክንያት ማሰቃየቱ ሳያንሰው የራሱ ታማኝ የሆኑ ቅጥረኞቹ ላይ እምነት በማጣት የሚያደርገውም የጠፋበት መሆኑ ግልፅ እየሆነ መምጣቱን አመላካች እንደሆነ የዚሁ ችግር ሰለባ ልንሆን እንችላለን ያሉ ወገኖች ጠቁመዋል። በይበልጥ አማራዉን በማይወክሉት የወያኔ አገልጋዮች እየተሰቃየው ያለው ሕዝቡ ሲሆን ፣ እነሱም ሕዝቡ ከጎናችው አለመኖሩን በመረዳታቸው የተፈጠረው ክፍተት በፈጠረባቸው ጭንቀት የመንግስት ሠራተኛውንም ሆነ ነጋዴውን ማመሱን እንደቀጠሉበት ለማወቅ ተችሏል።” በማለት ዘግቧል:፡

የአርበኞች ግንባር ሰራዊት በመተማ አካባቢ አደረስኩት ስላለው ጥቃት ከመንግስት በኩል የተሰጠ ማስተባበያም ሆነ መረጃ የለም።

Ethiopia: Can you trust the news media?

January31/2014

Baile Derseh Mihrete

A large number of people doubt what they read, what they see and hear in the news of EPRDF`s media. Governments want to convince the public to support of polices and their officials. Because the media draws on the content from the government.The media of Ethiopia is among the most strictly controlled in the world.




























The constitution notionally provides for freedom of speech and the press, however, the government prohibits the exercise of these rights in practice, unless it is in praise of government/EPRDF/.The government not only tightly control all information coming in and out, but seeks to mould information at its source.

A typical examples of this was the death of Meles Zenawi news of which was not divulged until many days after it occurred .It is no surprise that woyanne controlled medias are allowed to lie and distort the truth as much as they want ,even if they risk looking ridiculous. The Woyanne cadre journalists behind those terrorizing institution may be getting promotion for their act of deception and lie. I remember the woyanne officials who lied about bademe and the border demarcation some years ago and never retraction or show remorse until now for his deception.

Reporters without borders have consistently ranked Ethiopia near the bottom of its yearly press freedom index. The press is tightly controlled by the state; Article 19 of the Ethiopian constitution protects freedom of speech and freedom of the press. In practice, the government only allows speech supports it and the ruling party/tplf or EPRDF party/.Media report in Ethiopia are often one sided and exaggerated playing little or no role in gathering and disseminating vital information, true to facts and providing propaganda for the regime. The EPRDF/TPLF/media effectively paints the country and vision of the regime in a fake positive light and showing the Ethiopian public as to the outside world`s perception of the country.

Ethiopia has repeatedly drawn fire for the harsh treatment and lengthy jail terms it has given to bloggers who criticised the regime .like Eskinder Nega, Reeyot Alemu,Woubeshete Taye…,The number of arrests and conventions has soared in year to year .I think the fact that Ethiopia`s government uses social media to spread propaganda and lies to the public is a great examples of how something that`s supposed to encourage free speech is doing the complete opposite. State administration of radio and television to make sure content promotes party /EPRDF/ doctrine. The Ethiopia government employs a diverse range of methods to induce journalists to censor themselves rather than risk punishment.
The Ethiopia medias called ERTA is now become officially the propaganda machine to the EPRDF party secrete agenda in Ethiopia brain washing and laying Ethiopians how EPRDF is good for the country. The Ethiopian Medias and the government journalists need to act as human and competent and have to stop doing a propaganda job for the EPRDF Party, spreading their secret agenda to damage the nation, you will know when you are already damaged and there will be no turn back. There are millions of Ethiopians and friends of Ethiopians all over the world watching the situations very closely and seriously .Don`t be corrupted by them/EPRDF/.Find and trust them is the biggest challenge until their true being is seen with practical and use full actions, not taking one things sounds good while doing bad things which are accustomed to get from them for so long and this time to say enough is enough and stop it.

RECOMMENDATION

EPRDF should respect freedom of expression

- The government of Ethiopia /EPRDForTPLF/should take positive measures to stop the arrest and other forms of harassment of journalists.

- The right to freedom of expression and information cannot be restricted by the government.
- State owner ship of the press should be prohibited, and the independence of the media guaranteed.
- Should reflect the principles that the right to freedom of expression and information applies irrespective of boundaries.

- The offences of criminal defamation should be abolished

- Everyone has the right to freedom to freedom of opinion and expression, this right the right to hold opinions without interference.

- EPRDF/TPLF should stop inaccurate and inflammatory media reports
- Protection should be provided to all journalists working in the country and extended to media workers in general, such as editors publishers, photographers…,.

- The press should be encouraged to self-regulate rather than have rules imposed by the state/EPRDF/
Journalists and press out lets should be free to adopt and voluntarily follow professional standard of ethics

ህወሓት የፈሪዎችና የጨካኞች ስብሰብ መሆኑ አውቅ ነበረ::(አብርሃ ደስታ )

January 30/2014

በሌሎች ላይ የምትፈፅሙት ተግባር ሁሉ በራሳቹ ላይ እንደምትፈፅሙ ( እንደሚፈፀም ) አስቡ . በስልጣን ላይ ያለ ሁሉ በስልጣን አይኖርም . የስልጣን ዕድምያቹ በጣም አጪር መሆኑ እናንተም ታውቁታላቹ . በሰዎች ላይ ግፍ ስትፈፅሙ ሰዎች ይጠሏችኋል . በሰዎች ስትጠሉ የስልጣን ዕድምያቹ ያጥራል . እናንተ ያላቹ የህዝብ ድጋፍ ሳይሆን ጠመንጃ ነው . ጠመንጃ ስልጣን ለመያዝ ይረዳ እንደሆነ እንጂ በስልጣን ለመቆየት አያስችልም . ስለዚህ በጠመንጃ አፈሙዝ የስልጣን ዕድምያቹ ለማራዘም የምታደርጉት ጥረት ከንቱ ልፋት ነው . እናንተ ከስልጣን ወርዳቹ ስልጣን የህዝብ ሲሆን , ፍትሕ ሲነግስ , እኩልነት ሲሰፍን ለፈፀማችሁት ወንጀልና ላደረሳችሁት በደል በሕግ እንደምትጠየቁ አያጠራጥርም . በስልጣን የኖረ የለም . እንኳን አምባገነኖች ዴሞክራሲያዊ ስርዓቶችም በስልጣን ኮረቻ ተቀምጠው ለዘላለም አይኖሩም .

ምናልባት እናንተ ምግባራችሁ አውቃቹ በህዝብ ስትተፉ ሀገር ለቃችሁ በመውጣት ለማምለጥ ትሞክሩ ይሆናል . ገንዘቡም አላቹ . ሁሉም ካድሬዎች ( በሰዎች ላይ ግፍ እንዲፈፅሙ እየታዘዙ ያሉ የህወሓት አባላት ) ግን እንደናንተ ( እንደ ህወሓት መሪዎች ) ከሀገር ወጥተው ለማምለጥ ዓቅሙ የላቸውም . ደግሞ ዓቅሙ ቢኖራቸውስ ለምን በሰሩት ጥፋት ከሀገራቸው ለመሰደድ ይወሰንባቸባል ? የህወሓት ባለስልጣንናት ከስልጣን ወርደው በሀገራቸው በሰላም የሚኖሩበት ሁኔታ ለምን አያመቻቹም ? ለምን መርሃቸውን ከ « ስልጣን ወይ ሞት » ወደ « ስልጣን ለህዝብ አስረክቦ በሀገር በሰላም መኖር » አይቀይሩም ? ለካድሬዎቹስ አያስቡም እንዴ ? የህወሓት ዕድሜኮ ትንሽ ነው . ህወሓት ሲሞት የህወሓት አባላትም ከህወሓት ድርጅት ጋር አብረው መሞት የለባቸውም . ህወሓትም ስልጣን ለህዝብ አስረክቦ ተቃዋሚ ፓርቲ ሁኖ መቀጠል ይችል የለ ? ! ዕድምያችሁ ከህወሓት ድርጅት ዕድሜ በላይ እንዲሆን አድርጉ .

እኛ ሰለማዊ ታጋዮች ነን . ያላቹ ሃብትና ጠመንጃ በመጠቀም እኛን መደብደብ , ማሳሰር , ማሰቃየት , መግደል ትችላላቹ . አምባገነን ስርዓት የሚችለው ነገር ቢኖር ሰው ማሳሰርና መግደል ነው . የዓላም አምባገነን መሪዎች በማሳሰርና በመግደል የስልጣን ዕድምያቸው ዘለአለማዊ ማድረግ ከቶ አይቻላቸውም . ዛሬ እኛን ብትደበድቡና ብትገድሉ ዕድምያቹ እያሳጠራቹ እንጂ እያሸነፋቹ አይደላችሁም . እኛ ብንገደል ሌላ ሰው አለ . ሁሉም ሰው መግደል አይቻልም . ምክንያቱም ሁሉም ሰው ከተገደለ ማንን ትጨቁናላቹ ? የሚጨቆን ሰው ያስፈልጋችኋል . ሰው ጭቆና ሲበዛት በመሪዎቹ ላይ ያምፃል . እናም ትሸነፋላቹ . አምባገነን ተሸናፊ ነው . የማይሸነፍ ህዝብ ብቻ ነው . ምክንያቱም ህዝብ ለጭቆና አይነሳም . እኛን በማሰቃየት ሰለማዊ ትግሉ መግደል አይቻልም . ሰለማዊ ትግሉ በመግደል የሰዎች የነፃነት ጥያቄ መግደል አይቻልም . የሰዎች የነፃነት ጥያቄ በመግደል ሰዎችን ለዘላለም መጨቆን አይቻልም . ስለዚህ መሸነፋቹ አይቀርም .

የሰለማዊ ትግል በር ባትዘግቡን መልካም ነው . ምክንያቱም ደም መፋሰሱ , ጦርነቱ , መጠፋፋቱ አንፈልገውም መንገዳችንም ሰለማዊ ነው . የሰላም በር ሲዘጋብን እጆቻችንና እግሮቻችን አጣጥፈን እንቀመጣለን ማለት ግን አይደለም . አንድ በር ሲዘጋ ሌላ በር ማንኳኳታችን ግድ ነው . ነፃነት እንፈልጋለንና . « . እኛ የምንፈልገው ሰላም ነው . መታፈን ! ይብቃን » ብለን ተነስተናል ስለዚህ ትግላችን በምንም ዓይነት ስትራተጂ ማስቆም አይቻልም የሚቻለው ስልጣን ለህዝብ ማስረከብ ነው ዴሞክራሲ ማስፈን ነው ገዢዎች በሐሳብ መከራከር ሳይችሉ ሲቀሩ ወደ ሀይል እርምጃ እንደሚወርዱ እናውቃለን ሐይል መጠቀም የሽንፈት ምልክት ነው ህወሓት የፈሪዎችና የጨካኞች ስብሰብ መሆኑ አውቅ ነበረ ; . . . . . . ወደ ድንጋይ ውርወራ ፖለቲካ ይወርዳል የሚል ግምት ግን ፈፅሞ አልነበረኝም . መንግስት ወንጀልን መከላከል ሲገባው ወንጀል ፈፃሚ ሆነ . ህወሓት ዉስጧ መበስበሱ እየሸተተን ነው . ምናለ ድንጋይ ባለመወርወር ገመናችሁ ባታጋልጡ ? ለማንኛውም አደብ ግዙ የምትሰሩትን እወቁ . በሃይል የሚሆን ነገር እንደሌለ ተረዱ . ካለፉ ስርዓታት ታሪክ ተማሩ . ህዝብ እያያቹ ነው .

it is so!

ማንነት (ፕ/ር መስፍን ወ/ማርያም )

January 30, 2014
መስፍን ወልደ ማርያም
ኅዳር 21/2006
በ1996 ዓ.ም. የክህደት ቁልቁለት በሚል ጽሑፌ ውስጥ ‹‹ማንነት ምንድን ነው፤ በሚል ንዑስ ርእስ ስር ከገጽ 98 ጀምሮ በተቻለኝ መጠን አፍታትቻለሁ፤ የሪፖርተር ጋዜጠኛ ይህንን ለማንበብ ጊዜ አላገኘም፤ ወይም የተገለጠለት ዱሽ ቅንጫቢ በቅቶት ይሆናል፤ የምጠቅሰውም ለሱ ሳይሆን ለሌሎች ነው፡፡Prof. Mesfin Woldemariam : is an Ethiopian Human Rights activist and philosopher
በቅርቡ በፌስቡክ ላይ አንድ አውቀቱ ይሁን ጤንነቱ፣ ወይም ኪሱ የተቃወሰበት ሰው በትግርኛ ስለማንነት ጽፎ ነበር፤ ከዚህ በፊትም ጽፎ አስተሳሰቡ ሁሌም የተወላገደ በመሆኑ አልፌው ነበር፤ አሁን ደግሞ ሲጽፍና በአንዳንድ የሱ ቢጤዎች አበጀህ! አበጀህ! ሲባል ሳይ አደገኛነቱን ተገነዘብሁ፤ አንዱን ጎባጣ ሀሳብ ቶሎ ካላስተካከሉት ብዙ ጎባጦችን ያፈራል፤ የተጣራና ቀና የሆነ ሀሳብን ለመግለጽ በጣም ያስቸግራል፤ ማሰብ መጨነቅን፣ ማበጠርን፣ ማጣራትን ይጠይቃል፤ አፍ እንዳመጣ መልቀቅ ቀላል ነው፤ በተለይ የሚዳኝ ከሌለ!
በመጀመሪያ ሀሳብን ለመግለጽ የተመረጠው ቋንቋ ጠበብ ያለና የተፈለጉ አድናቂዎች ዘንድ ለመድረስ ብቻ ከተፈለገ ሀሳቡም እንደቋንቋው ለተወሰኑ ሰዎች የተመጠነ ይሆናል፤ በዚህ ዓይነት የቀረበው ቅንጣቢ ሀሳብ በሌላ ቋንቋ ሊተረጎም አይቻልም፤ ደንቆሮነትን ማጋለጥ ይሆናል፤ ለምሳሌ በትግርኛ ‹‹ኢትዮጵያዊ ዝበሃል መንነት የለን፤›› የሚለውን ‹‹ኢትዮጵያዊ የሚባል ማንነት የለም፤›› በማለት፣ በእንግሊዝኛ ደግሞ ‹‹There is no identity called Ethiopian.›› ተብሎ ሊተረጎም ነው፤ እንግዲህ ይህ አወቀች፤ አወቀች ሲሏት መጽሐፉን አጠበች እንደተባለችው ሴትዮ፣ ወይም ደግሞ አላዋቂ ሳሚ እንትን ይለቀልቃል! የሚባል ነው፤ ‹‹ኢትዮጵያዊ ዝበሃል መንነት የለን፤›› ብሎ በትግርኛ የጻፈው ሰው የአለማወቁ አዘቅት ዓለምን በሙሉ የሚያናጋ መሆኑን አልተገነዘበም፤ (አሜሪካን፣ እንግሊዝ፣ ፈረንሳይ፣ ኢጣልያን … የሚባል ማንነት የለም ሊለን ነው፤) የመንደር ማንነትን በሁለት እጆቹ ይዞ፣ አእምሮውን በመንደር ማንነት ጨቅጭቆ በየፓስፖርቱ ላይ የማንነት መግለጫ ተብሎ የተሰየመውንና በዓለም አቀፍ ደረጃ የታወቀውን ማንነት ካደው፡፡
በፍጹም ያልገባውን የፈረንሳዩን ፈላስፋ፣ የሩሶን ሀሳብ አበለሻሽቶ ከቆሻሻ መጣያ ውስጥ ያገኘው ቡትቶ ሊያደርገው ይከጅላል! ከጥራዝ-ነጠቅም አጉል ጥራዝ-ነጠቅ! ትግራይን የመገንጠል ዓላማ ያለው ሰው በእውነትና በግልጽ ዓላማውን ቢያራምድ በበኩሌ አልደግፈውም እንጂ አልቃወምም፤ መብቱ ነው፤ ነገር ግን በሰንካላ አስተሳሰብና በተንኮል ወጣቶችን ለመመረዝ የሚፈልገውን ሰው አጥብቄ እቃወማለሁ፤ ትግራይን እንደኤርትራ ካስገነጠለ በኋላ እንደኤርትራ ለትግራይም የኢትዮጵያዊነት ማንነትንን ማገድ ይቻላል፤ ከዚያ በፊት ግን ተንኮል ይቅር፡፡
ኢትዮጵያዊነትን ለማጥፋት የሚደረገው ሙከራ አዲስ ኤደለም፤ ኢጣልያኖች በሰፊው ዘርተውት የሄዱት ጉዳይ ስለሆነ የአባቶቻቸውን ውርስ የሚከተሉ ዛሬም ይኖራሉ፤ ኢትዮጵያዊነትን ለማጥፋት ብዙ ገንዘብና ሌላም የሚከፍሉ ብዙ የተለያዩ ድርጅቶች መኖራቸው የታወቀ ነው፤ ዱሮ የኢጣልያ ወኪሎች ተጠቅመውበታል፤ ዛሬ ደግሞ ሌሎችም ተጨምረው ያንኑ ተልእኮ የሚያራምዱ አሉ፤ በየዋህነት እንደበፊቱ እንዳናስተናግዳቸው እንጠንቀቅ!