Tuesday, January 29, 2013

ሕወሐት ለሁለት ተሰነጠቀ፤ ወረቀት ለአባለት ተበተነ
ከኢየሩሳሌም አርአያ
ዛሬ በመቀሌ ለአባላ ትና አልፎም ለህዝቡ በተበተነ የትግርኛ ፅሁፍ እነ ስዩም መስፍን፣ አባይ ፀሐዬ፣ ፀጋዬ በርሔ ከነባለቤታቸው እንዲሁም ሌሎች ከድርጅቱ እንዲባረሩTigray People Liberation Front Split በተበተነው መግለጫ ተጠቁሞዋል። በመግለጫው፥ ከጀርባ አሉ የተባሉትና « የዚህ መኅንዲስ» ተብለው የተፈረጁት ስብሃት ነጋ እርምጃ እንዲወሰድባቸው ከተባሉት መካከል በዋነኛነት ተፈርጀዋል። እነ ቴውድሮስ ሃጎስ፣አዜብ መስፍንና በረከት እጃቸው እንዳለበት የተነገረለት ይኸው መግለጫ ተከታዩን ይመስላል፤
«ተቆርቋሪ ለሆናችሁ የትግራይ ተወላጆ በሙሉ፤
«ድርጅትህ ሕወሐት እስከ ዛሬ ታግላ እዚህ ደረጃ አድርሰሃለች። በተለይም የሁሉም ነገር አድራጊና ፈጣሪ የነበረው ባለ ራዕይው መሪህ በቅርብ ጊዜ አጥተኽል።
ዛሬ እነዚህን ደካማ ጐኖች ተጠቅመው ለጠላት አሳልፈው ሊሰጡህ የሚፈልጉ ያውም ደግሞ የእኔ የምትላቸው ጅቦች ተነስተውብህ ይገኛሉ። ይህንን ግልፅ ለማቅድረግ አሁን በቅርብ ጊዜ በመቀሌ የድርጅቱ ማ/ኰሚቴ ስብሰባ አካሄደን ነበር። በዚህ ስብሰባ ላይ ነው እንግዲህ ተከታዩ ነገር የተነሳው። ይኽውም፥ እነ ስዩም መስፍን፣ አባይ ፀሐዬ፣ ፀጋዬ ከሚስቱ ጋርና ሌሎችም ያሉበት ይህን አሉ፤
«ድርጅታችን ጨርሶ ተዳክሞዋል። እኛ የኢትዮጲያ ሕዝብ ትግል መስራች ሆነን ሳለ ወደኋላ ተገፍትረን በአንፃሩ ሌሎች ከእኛ ኋላ የተፈጠሩና ራሳችን ያሳደግናቸው ሲጠናከሩ ድርጅታችን ግን እየተዳከመ በመሄድ ላይ ነው። ባዛው መጠን ሕዝባችን እየተጎዳ ነው። ስለዚህ አሁን ካጋጠመን አደጋ መውጣት ካለብን ከድርጅቱ -የተወገዱትን ግን በመጥፎ ጎዳና ያልተሰማሩትን መልሰን ወደ ፓርቲው ማስገባት አለብን። ይህ ካልሆነ ግን የሕዝብ ትግል አውላላ ሜዳ ላይ ጅብ በልቶት ሊቀር ነው።» በማለት ከጠላቶቻችን ጋር እንታረቅ እያሉን ነው።
“ሕዝባችን አስተውል። በዚህ አይነት ዳግመኛ በድርጅታችን ተኃድሶ እንደሚያስፈልገን ነው የተገነዘብነው። በሚቀጥለው የካቲት ወር በሚካሄደው ጉባኤያችን ይህንን ጉዳይ ትኩረት ሰጥቶና አጥርቶ (ውሳኔ አሳልፎ) እንደሚወጣና እነዚህንና መሰሎቻቸው ከሚያራምዱት አቋም ጋር ጠራርጐ እንደሚያስወግድልን ተስፋ እናደርጋለን። በዚህም እያንዳንዱ እንደከዚህ ቀደሙ የተለመደ አስተዋፅኦ (ሚና) እንደሚያበረክት አንጠራጠርም።
በተጨማሪ ከጀርባ ሆኖ የዚህ አፍራሽ ዋና ቀያሽ መሃንዲስ ስብሃት ነጋ መሆኑን ደርሰንበታል።”

Monday, January 28, 2013

ኢትዮጵያ በወታደራዊ እንቅስቃሴዎች እየታመሰች ነዉ::
ኢትዮጵያ ዉስጥ ዳር አገርም ሆነ መሀል አገር በየቦታዉ የሚታየዉ ወታደራዊ እንቀስቃሴ ከቀን ወደ ቀን እየጨመረ መምጣቱን አዲስ አበባና በየክልሉ የሚገኙ ወታደራዊ ምንጮቻችን ገለጹ። በተለይ የመለስ ዜናዊ ሞት ለህዝብ ይፋ ከሆነበት ግዜ ጀምሮ ኢትዮጵያ ከደርግ ዘመን ወዲህ ታይቶ በማይታወቅ ከፍተኛ ወታደራዊ እንቅስቃሴ እየታመሰች መሆኗን በየክልሉ የሚገኙ ዘጋቢዎቻችን የመከላከያ ምንጮችን ዋቢ በማድረግ የላኩልን ዜና ያስረዳል።
ከሁለት ሳምንት በፊት ከ35 በላይ ታንኮችን የጫኑ ከባድ ተሽከርካሪዎች ወደ ምስራቅ የአገሪቱ ክፍል የተጓዙ ሲሆን፣ ከአራት ቀን በፊት ደግሞ ከ30 ያላነሱ ታንኮች በከባድ ተሽከርካሪዎች ተጭነዉ ወደ ሰሜናዊዉ የአገራችን ክፍል ተጉዘዋል። ጠብ አጫሪዉ የወያኔ አገዛዝ የጦር መሳሪያዎችን ለምን በዚህ አይነት ፍጥነትና ብዛት እንደሚያንቀሳቅስ በትክክል ለማወቅ ባይቻልም በብዙ ምዕራባዉያንና የአገር ዉስጥ ወታደራዊ ጠበብቶች ግምት አገሪቱ ውስጥ በየክልሉ በሁሉም መስክ የሚታየው ህዝባዊ አመጽና አለመረጋጋት ወያኔን ክፉኛ ስላስደነገጠዉ ህዝባዊ እንቅስቃሴዉን በወታደራዊ ሀይል ለመቆጣጠር የታለመ ሊሆን ይችላል ተብሎ ይታናል። በሌላ በኩል ደግሞ የተለያዩ ስርዐቱን በትጥቅ ትግል የሚፋለሙ ሀይሎች በተለይ በቅርቡ የተቋቋመዉ እራሱን “የግንቦት ሰባት ሀይል” ብሎ የሚጠራዉ የተለያዩ ሀይሎች ስብስብ ወያኔን ክፉኛ እንዳስደነገጠዉ ብዙ ለአገዛዙ ቅርበት ያለቸዉ ምንጮች በመናገር ላይ ናቸዉ።

Friday, January 18, 2013

ሰበር ዜና መንግስት በምስክር እጦት ጭንቅ ውስጥ ገብቷል፡፡ የብዙዎች ምላሽ ‹‹በሐሰት አንመሰክርም›› የሚል ሆኗል፡፡     
በእስር ላይ የሚገኙ መሪዎቻችን እና ሌሎች ወንድሞቻችንን በአሸባሪነት ከስሶ ሲያንገላታ የቆየው መንግስት በምስክር እጦት ችግር ውስጥ መግባቱ ታወቀ፡፡ መንግስት ኮሚቴዎቻችን ላይ በመሰረተው ክስ በሐሰት ሊያስመሰክራቸው ያዘጋጃቸው 197 (አንድ መቶ ዘጠና ሰባት) ሰዎች መኖራቸውን ለፍርድ ቤት ቢያሳውቅም የተገለጸውን ቁጥር ያህል ምስክሮች ማግኘት አልቻለም፡፡ ይህም ሊሆን የቻለው ለምስክርነት የታሰቡት ብዙዎቹ ግለሰቦች ምስክር ለመሆን ፈጽሞ ፈቃደኛ አለመሆናቸውን ተከትሎ ነው፡፡ መሪዎቻችን ባልዋሉበት እና በማያውቁት ወንጀል የከሰሳቸው መንግስት በየአካባቢው ‹‹ድጋፍ ይሰጡኛል፤ እተማመንባቸዋለሁ›› የሚላቸውን ግለሰቦች ለምስክርነት ተደጋጋሚ ጥሪ ቢያደርግላቸውም በሐሰት አንመሰክርም የሚል ቆራጥ አቋም ማሳየታቸው ተሰምቷል፡፡
ሙስሊሙ ህብረተሰብ ያነሳቸውን የመብት ጥያቄዎች ለመንግስት እንዲያደርሱለት በአስር ጣቱ አምኖባቸው የመረጣቸው ኮሚቴዎቻችን እና ሌሎች ዳኢዎች መንግስት እውቅና ሰጥቷቸውና ስለ ሰላማዊነታቸውም በመንግስት ብዙሀን መገናኛዎች መስክሮላቸው፤ ከአገሪቱ ከፍተኛ ባለሥልጣናት ጋር ድርድር ሲያደርጉ እንደቆዩ ይታወሳል፡፡ ሆኖም መንግስት የቀረቡትን የመብት ጥያቄዎች ለመመለስ አለመፈለጉና እነሱም ጥያቄዎቹ እንዲመለሱ ተደጋጋሚ ጥያቄ በማቅረባቸው ‹‹አሸባሪ›› የሚል ታፔላ ተለጥፎባቸው ከሐምሌ 2004 ጀምሮ በእስር እና ስቃይ ላይ የሚገኙት መሪዎቻችን ንጹህ መሆናቸውን የተረዱ ብዙዎች በሀሰት እነሱ ላይ ለመመስከር ፈቃደኛ አለመሆናቸውን በቀጥታ መግለጽ ችለዋል፡፡
መንግስት ይህን የመስካሪዎች እምቢታ ተከትሎ አዳዲስ ምስክሮችን ለመመልመል ቀን ከሌት እየሰራ እንደሚገኝ ምንጮች አረጋግጠዋል፡፡ የመንግስት ደህንነቶች ቁጣና ንዴት በተሞላበት መልኩ ሰዎችን ምስክር እንዲሆኑ በአካልም ጨምር እየሄዱ በማስፈራራት ላይ ይገኛሉ፡፡ በተጨማሪም ደህንነቶቹ በአዲስ አበባ አንድ አንድ መስጊዶች በመገኘት ግለሰቦችን በግድ በመያዝ ምስክር እንዲሆኑ እየጠየቁ ሲሆን፤ ፈቃደኛ አልሆንም ያሉ ሰዎችንም ‹‹የማትመሰክር ከሆነ አንተን ነው የምንከስህ›› በማለት በማስፈራራት ላይ ይገኛሉ፡፡ የሀሰት ምስክርነትን (ሸሀደተ ዙር) አስከፊ ወንጀልነት የተረዱ በርካታ ሙስሊሞች አሁንም በእምቢታቸው የዘለቁ ሲሆን፤ አሁንም ግን ጥቂት የማይባሉ ‹‹ተገደን ነው የምንመሰክረው›› የሚል ምላሽ እየሰጡ ያሉ ግለሰቦች በመኖራቸው ከዚህ ከድርጊታቸው እንዲታቀቡና ከአስከፊው የሀሰት ምስክርነት መዘዝ እራሳቸውንና ቤተሰባቸውን እንዲጠብቁ አደራ እንላለን፡፡
አቡበከር ሲዲቅ (ረ.ዓ) የአላህ መልዕክተኛ (ሶ.ዐ.ወ) እንዲህ ማለታቸውን ዘግበዋል፡- ‹‹የከባዶች ከባድ የሆነውን ሀጢአት አልነግራችሁንም›› እኛም ‹‹አዎ! የአላህ መልዕክተኛ እንዴታ!›› አልን፡፡ እሳቸውም ‹‹በአላህ ማጋራት (ሽርክ) እና ወላጅን ያለመታተዝ ናቸው›› አሉና ተደላድለው ከተቀመጡበት ድንገት ተነስተው እንዲህ አሉ ‹‹አዋጅ! ውሸት መናገር እና በሐሰት መመስከ›› እያሉ የሚያቆሙት አልመስልህ እስኪለኝ ድረስ ደጋገሙት ፡፡ ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል

Thursday, January 17, 2013

‹‹አላሁ አእለም! ይቅርታ አንጠይቅም››
ሁለት ወቅታዊ ጉዳዮች
1. ከመለስ ሞት በኋላ መረጋጋት የተሳነው ኢህአዴግ ከበርካታ ችግሮች ጋር ፊት ለፊት ተፋጧል፡፡ ከችግሮቹ በከፊልም የሚከተሉት ይጠቀሳሉ፡፡ …በረከት ስምኦን የነበራው ተደማጭነት እየተሸረሸረ ነው፣ የበረከት ባለቤት የበረከትን መፅሃፍ ለመሸጥ (ገዥ ፍለጋ) በየተቋማቱ እየተንከራተቱ ነው፤ አዲሱ ለገሰ የተደማጭነት መስመሩን ‹‹ኢህአዴግን ለማጠናከር›› በሚል ምክንያት ይበልጥ እያደረጀ ነው፤ ደብረፅዮን ገ/ሚካኤል ከቀን ወደ ቀን በህወሓት ውስጥ ተሰሚነቱ እየጨመረ ነው፣ በእርግጥም ከድርጅቱ ከፍተኛ አመራሮች የአስጊ ህመም ችግር የሌለባቸው ተብለው የሚመደቡት ደብረፅዮን፣ አባይ ፀሀዬና ቴውድሮስ አድሃኖም ናቸው፣ አቦይ ስብሃት ነጋ ‹‹መፈንቅለ ፓርቲ›› በህወሓት ውስጥ ለማድረግ ቀን ከለሌት እያሴሩ ነው፣ ከሁለት ወርበኋላ የሚደረገው የኢህአዴግ ጠቀላላ ጉባኤ አዲስ ነገር ያስተናግዳል ተብሎ ይጠበቃል፤ ኦህዴድ በሹም ሽር ሊናጥ ነው፣ አለማየሁ አቱምሳ በሩቅ ምስራቅ ለሚከታተለው ህክምና እስከአሁን ያለውንም ሆነ በቀጣይ የሚያስፈልገውን ወጪውን እየሸፈነ ያለው ሼክ መሀመድ አላሙዲ ነው፤ ለምን? አለማየሁ የመንግስት ባለስልጣን ነው፣ በተጨማሪም ሆን ተብሎ በተሰጠው መርዝ ነው ታማሚ የሆነው የሚባለውን ወሬ ይዘን፣ ከዚህ ጀርባ ማን ነው ያለው? የሚል ጥያቄ መቀርቡ አይቀርም (የሰማሁት መረጃ ጆሮ ያቃጥላል) ግን ለምን? ኩማ ደመቅሳ መልካም አስተዳደር ባለማስፈንና ሙስናን መቆጣጠር ባለመቻል እየተወቀሰ ሲሆን፣ በተቃራኒው አባዱላ ገመዳ በኦህዴድ ውስጥ መረጋጋትን በማስፈንና ስራውን በብቃት በመወጣት በሚል ተመስግኗል፣ (የማኪያቬሊ ከፋፍለ ግዛ ማለት ይህ ይሆን?) በሚያዚያ ወር የሚደረገውን ምርጫ ተከትሎ የቱኒዝያንና የግብፅን መሰል ህዝባዊ አመፅ ይቀሰቀሳል በሚል አገዛዙ ፍርሃት አድሮበታል፣ 33ት ፓርቲዎች ነገ በምርጫው ላይ የሚኖራቸውን አቁም በሰማያዊ ፓርቲ ፅፈት ቤት ከጠዋቱ አራት ሰአት ላይ የፋ ያደርጋሉ (በእርግጥ የደረሱበት ውሳኔን ብግሌ ትክክል ነው ብዬ አምናለሁ፣ ከዚህ ውጪም ገዥው ፓርቲን ለድርድር የሚያስገድድ ዕድል የላቸውም)፣ በአማራ ክልል ደቡብ ጎንደር ኦስትሪያዊውን አገር ጎብኚ ማን ገደለው? ለምን ተገደለ? የደብረማርቆስ ማረሚያ ቤት ድራማስ በማን የተቀነባበረ ነው? ኃላፊነቱንስ ማን ነው የሚወስደው? የብሄራዊ መረጃና ደህንነት ኤጀንሲ ¬¬‹‹ለሽብር ድርጊት ሊውል ሲል ደረስኩበት›› በማለት ከተቀበረበት እንዳወጣው የነገረንን የጦር መሳሪያ ማነው የቀበረው? ይህ መሳሪያስ በእነማን የክስ መዝገብ ላይ ማስረጃ ሆኖ ሊቀርብ ነው የታቀደው? በቀጣይስ የቦንብ ፍንዳታ በየትኛው ከተማ፣ መቼ፣ ስንት ሰዓት ላይና በምን ሁኔታ ይደርስ ይሆን? …ይህኛው መንገድስ የት ድረስ ያስኬዳል? ‹‹አዲስ ታይምስ›› መፅሄትን ማፈኑስ ለምን አስፈለገ?
2. በሽብርተኝነት የተከሰሱትን የህዝብ ሙስሊም መሪዎችን በይቅርታ ለመፍታት መንግስት የማጭበርበሪያ ስልቱን እየተጠቀመ ነው፡፡ በዕለት ሀሙስ ጥር 2 ቀን 2005 ዓ.ም በፕሮፌሰር ኤፍሬም ይሳቅ ይመሩ ከነበሩት ሽማግሌዎች ውስጥ የተዘጋጀ ሶስት ሰዎች ያሉት አንድ ቡድን በቃሊቲ ማረሚያ ቤት ተገኝቶ ነበር፡፡ ከቡድኑ አባላት ፓስተር ዳንኤል እና ፕሮፌሰር አህመድ ዘካርያስ ለታሳሪዎቹ እንዲህ የሚል የማጭበርበሪያ መደራደሪያ አቅርቦ ነበር፡- ‹‹ጉዳያችሁ በፍርድ ቤት እየታየ ነው፤ ስለዚህም ክሱ አሁን ባለበት ደረጃ ሊቋረጥ አይችልም፡፡ እናም ክርክራችሁን አቋርጡና ጥፋተኛ ነን በሉ፣ ከዛም ፍርድ ቤቱ ከፈረደባችሁበኋላ ‹ይቅርታ› ጠይቃችሁ እናስፈታችኋለን›› ሆኖም የሙስሊሙ መሪዎች ‹‹ይህንን በጭራሽ አንቀበለውም፣ ጥፋተኛ ነኝም አንልም፣ አላሁ አእለም! ይቅርታ አንጠይቅም›› ሲሉ በድፍረትና በቁርጠኝነት መልሰውላቸው ወደ እስር ክፍላቸው ተመልሰዋል፡፡ በእርግጥም የኮሚቴው አባላት ትክክለኛ ውሳኔ ነው የወሰኑት፡፡ ምክንያቱም ይህ የሽምግልና ቡድን ቀንደኛ የስርአቱ ደጋፊ ሲሆን፣ መደራደሪያ ብሎ የሚያቀርበው ሁሉም ነገር የአገዛዙን የፖለቲካ ጥቅም የሚያስከብር ነውና፡፡ በድህረ ምርጫ 97 የታሰሩትን የቅንጅት አመራርንም በዚህ አይነት መልኩ መሸወዱ ይታወሳል፡፡(በነገራችን ላይ ሽማግሌዎቹ በተጠቀሰው ዕለት አንዱአለም አራጌን ጠርተው አናግረውታል፤ እስክንድር ነጋን ግን ዘለውታል፡፡ ለምን? ሌላው አስገራሚ ጉዳይ ደግሞ የሽማግሌ ቡድኑ ለሙስሊሙ መሪዎች ‹‹የመጣነው አንዱአለምን ፈልገን ነው፣ እናንተን እግረ መንገዳችንን ሰላም እንበላችሁ ብለን ነው›› ሲሏቸው፣ ለአንዱአለም ደግሞ የዚህን ግልባጭ ምክንያት ሰጥተውታል፡፡
http://www.ecadforum.com

Thursday, January 3, 2013


Ethnic clash among AAU 4 Kilo students causes damages

Listen to this article. Powered by Odiogo.com


Addis Abeba
3/1/13

A violent ethnic based conflict among Addis Abeba University (AAU) College of Natural Sciences/4 Kilo Campus students that started yesterday afternoon (02-01-2013) 4PM resulted in the damage of properties and injuries of students.
According to De Birhan's sources the violent conflict had reportedly started after "unidentified students posted a poster containing a derogatory message on the College's main Library and two other places about Oromo ethnic students". The conflict continued until mid night when Oromo ethnic students non violently blocked and banned most students from entering or leaving their dormitories. The tension turned out violent when a student was severely attacked around mid night.

The violent clash that continued until early morning had restarted after it was contained several times by the Federal Police who surrounded the Campus and tried to quell the situation. Several students from the conflicting groups that form along ethnic lines were severely wounded and were taken to Zewditu and Yekatit 12 Hospitals. Windows, doors and other properities of the Univeristy and many students' dormitories were damaged in the clash that continued until 3AM this morning.

Students that have been suspected to have had direct involvement in the violence are now under Police custody. Although there is Police presence and calamity in the Campus, students are still barred from either leaving or entering the Campus.

Similarly, De Birhan has learnt that there was a fall out between students and the College's Administration for the past two weeks over grading issues.

The College had introduced a new Grading System/scale, which requires students to score more than 95 out of 100 to get an "A", however students protested the new scale and class representatives had to meet with the College Administration on the matter. Due to disagreement, some representatives had even walked out of the meeting. After tense meeting and talks, the Administration finally agreed to reduce the required score to get an 'A' to 85 points out of 100.

The College was founded on March 20, 1950 by Emperor Haile Silassie I who declared the foundation of the University College of Addis Ababa, including the faculties of Arts and Science. At the time there were only 33 students enrolled. At present, over 5000 undergraduate, 3000 extension, over 1000 MSc and 50 PhD students are enrolled in the College. The Faculty today comprises six departments: Biology, Chemistry, Physics, Earth Sciences,Mathematics and Statistics and four programs namely Biothechnology, Food Science, Computational Science, Matreials Science and Environmental Science.
Breaking News: Protest erupts at Addis Ababa University

Addis Ababa University main campus
Awramba Times (Addis Ababa) – Protest sparked at the College of Natural Sciences, Arat Kilo Campus of the Addis Ababa University. According to our sources in Addis Ababa, The main cause of the protest is due to an ethnic derogatory poster against Oromo-ethnic students placed at the College’s main Library and two other places.
So far, more than 20 students from the conflicting ethnic groups were wounded and were taken to government hospitals. On the other hand Police have accused several students of causing damage to university property, including broken windows and doors. More details to come…
http://www.awrambatimes.com

Saturday, December 29, 2012

የመከላከያ ሚኒስቴር በድንጋጤ እየታመሰ ነው ::በርካታ ወጣት መኮንኖች ታስረዋል

የመከላከያ ሚኒስቴር በድንጋጤ እየታመሰ ነው ::በርካታ ወጣት መኮንኖች ታስረዋል
በአንድ ወገን የታጠረው የመከላከያ ሚኒስቴር መስርያ ቤት የወያኔ ጄኔራሎችን ሹመት ተከትሎ በ መኮንኖች መሃል በተነሳው ክፍፍል እና አለመግባባት እየበጠበጡ ናቸው ያላቸዉን መኮንኖች እያሰረ መሆኑን የምንሊክ ሳልሳዊ ምንጮች ከወደ አገር ቤት ተናግረዋል::

ይህ እያፈጠጠ እና ገሃድ እየወጣ ያለው ክፍፍል እና አለመግባባት በተለያዩ የጦር ክፍሎች ውስጥ የሚሰሩ ወጣት መኮንኖች ያለውን አድሎዋኢ አሰራር እየተቃወሙ ጥያቄ በማንሳታቸው ከተቃዋሚ ሃይላት ጋር ግንኙነት ፈጥረው ነው ተብለው እየታሰሩ ነው::
በ97 በተደረገው ምርጫ ወያኔው መሸነፉን አምነው ያልተቀበሉ ጄኔራሎች የአማራ እና የኦሮሞ ብሄር መኮንኖችን ቅንጅትን ደግፋችዋል በሚል ሰበብ ከ ሰራዊቱ መባረራቸዉን ያወሱት የሳልሳዊ ምንጮች አሁንም የሚደረገውን አድልዎ በመቃወም ተበሳጭተው የመብት ጥያቄ ያነሱትን ወታደራዊ ወጣት መኮንኖችን እያፈኑ ወደ እስር ቤት እየወረወሩ ነው::(www.facebook.com/minilik.salsawi) ይመልከቱት !!

ከምእራብ እዝ እና ከአዲስ አበባ የተለያዩ የጦር ክፍሎች ቁጥራቸው በርከት ያሉ ወጣት መኮንኖች ተይዘው አዲስ አበባ መኮንኖች ክበብ አከባቢ ካለው ወታደራዊ እስር ቤት ውስጥ የታሰሩ ሲሆን አብዛኛዎቹ የአማራ እና የ ኦሮሞ ተወላጆች ሲሆኑ የትግራይ ተወላጅ የሆኑ መኮንኖች ተለይተው ወደ ትግራይ እስር በት ተልከዋል::

እንዲሁም በመከላከያ ኢንጂነር ስር ያሉ የምህንድስና መኮንኖች አብዛኛዎቹ እስር ቤት ያሉ ሲሆን ከአምቦ ጋፋት ኢንጂነሪንግ.. ከደብረዘይት መኪና መገጣጠሚያ ..ከ አየር ሃይል እና ከተለያዩ ከተሞች ወጣት የጦር መኮንኖች እየታፈሱ እየታሰሩ መሆኑን የሚኒሊክ ሳልሳዊ የዉስጥ ምንጮች ገልጠዋል::

በቅርብ የተሾሙትን የ34 ጄኔራሎች ሹመት ተከትሎ የተነሳው ይህ ተቃውሞ የወያኔ ጀኔራሎች ያተኮሩባቸው የተማሩ ወጣት መኮንኖች ላይ ሲሆን ይህ ዘመቻ በመከላከያ ዉስጥ ትርምስን ፈጥሮዋል; ...
ያንድ ወገን የበላይነት ይወገድ...ተቃውሞ ብሄራዊ እንጂ ክልላዊ አይደለም....ለሃገር እንጂ ለግል የሚል አቁዋም ይወገድ ...የሚሉ እና ሌሎች የመብት ጥያቄዎችን ወጣት መኮንኖቹ በማንሳታቸው የወያኔ ጄኔራሎች በመደናገጣቸው የመከላከያ ደህንነት ሃይሉን አጠናክረውታል::

ይህ በእንዲህ እንዳለ በመከላከያ ዉስጥ ባለው ዝርክርክ እና ብልሹ አሰራር የሃገር ንብረት እና የህዝብ ሃብት በጀኘራል መኮንኖቹ እየተዘረፈ ሲሆን ዘመዶቻቸውን እያመጡ በተለያየ መንገድ እያሸሹ መሆኑን ታውቑል::
በተለያዩ የመከላከያ ግቢዎች ዉስጥ የቆሙ የተበላሹ መኪኖች እየተሰበሰቡ ለብረት ማቅለጫ ፋብሪካዎች በኪሎ እየተሸጡ ሲሆን ገንዘቡንም ጀነራሎቹ በሚስቶቻቸው እና በልጆቻቸው ስም እንዲሁም በዲያስፖራ ዘመዶቻቸው ስም በውጭ አገራት ባንኮች እያስቀመጡት ሲሉ የምንሊክ ሳልሳዊ ምንጮች አሳብቀዋል::

በተለያዩ መንገዶች ከመንግስት ካዝና ወጪ እየተደረገ በቢዝነሱ እንዲሳተፉ የሚደረጉት የጄኔራሎቹ ሚስቶች ሲሆኑ ደርግን ለመጣል የታገልነው እኛ ብቻ ነን በኢል መዘባበት የተለያዩ ንብረቶችን ከመስሪያቤቱ በዱቤ እያወጡ የማይከፍሉ ሲሆን ልጆቻቸው በዉጭው አለም በዉድ ዋጋ እየተማሩ መሆኑን የምንሊክ ሳልሳዊ ምንጮች ተናግረዋል::

የአድዋ ተወላጅ የሆኑ ጄኔራሎች በተለየ ሁኔታ በወርቅ ንግድ ዉስጥ የገቡ ሲሆን የተለያዩ የማእድን
አገር በቀል ድርጅቶችን እያባረሩ ራሳቸው ዘመዶቻቸዉን በማስቀመጥ ከጨረታ ውጪ ስራዉን እየሰሩት መሆኑን ጥቆማው ሲያስረዳ ከዚህም ተጠቃሚ እና ወኪል አንዱ ፒያሳ የሚገኘው አፍሪካ ወርቅ ቤት ተጠቃሽ ነው::

በቡሬ ግንባር የሚገኘው የኢትዮጵያ ሰራዊት እርስ በርሱ ተዋጋ



ታህሳስ ፲፱ (አስራ ዘጠኝ) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም
ኢሳት ዜና:-የኢሳት የመከላከያ ምንጮች እንደገለጡት በቡሬ ግንባር በሚገኙ የመከላከያ ሰራዊት አባላት መካከል ማንዳ እየተባለ በሚጠራው አካባቢ ማክሰኞ ሌሊት የተጀመረው የእርስ በርስ ጦርነት እስከ እኩለቀን ዘልቆ እንደነበርና አሁንም ውጥረቱ እንዳለ መሆኑን ለማወቅ ተችሎአል።
የእርስ በርስ ጦርነቱ እንደተጀመረ የአካባቢው ነዋሪ ኢትዮጵያ እና ኤርትራ ጦርነት ጀመሩ በሚል ቀየውን ለቆ የተንቀሳቀሰ ሲሆን፣ ከፍተኛ ወታደራዊ ባለስልጣናት በሄሊኮፕተር እየተንቀሳቀሱ ጦርነቱን ለማስቆም ጥረት ሲያደርጉ እንደነበር ምንጮቻችን ገልጸዋል።
40 ወታደሮች መሞታቸውን እንዲሁም ከ39 በላይ ደግሞ መቁሰላቸውን ከማንዳ ሆስፒታል የተገኘ መረጃ ያመለካተ ሲሆን፣ ሆስፒታል ሳይደረሱ የሞቱ፣ ወደ መቀሌ ሆስፒታል በሄሊኮፕተር የተወሰዱ ወታደራዊ አዛዦች መኖራቸውንም ለማወቅ ተችሎአል።
ዘግይቶ በደረሰን ዜና ደግሞ 15 ወታደሮች ወዲያውኑ መሞታቸውን ፣ 12ቱ ደግሞ ለሞት ሲያጣጥሩ በአይናቸው ማየታቸውን አንድ ስማቸውም ድምጻቸውም እንዳይተላለፍ የጠየቁ በሆስፒታሉ ውስጥ የሚሰሩ ነርስ ተናግረዋል።

የግጭቱን መንስኤ በትክክል ለማወቅ አልተቻለም። አንዳንድ ወገኖች ግጭቱ በህወሀት ወታደራዊ ባለስልጣናት መካከል በተፈጠረ አለመግባባት የተነሳ ነው ሲሉ ሌሎች ወገኖች ደግሞ በህወሀት ደጋፊ ወታደሮችና በተቀረው ሰራዊት መካከል የተፈጠረው አለመግባባት ነው ይላሉ። ኢሳት የግጭቱን ትክክለኛ ምንጭ ለማወቅ ጥረት እያደረገ ነው።
ማንዳ ከቡሬ ግንባር 21 ኪሎሜትር የሚርቅ ሲሆን፣ ግጭቱ በትክክል የተነሰባት ቦታ አሊ ፉኑ ዳባ እየተባለ በሚጠራው የጎሳ መሪ ስም በተሰየመ አሊ ፉኒ አካባቢ ነው። ግጭቱ በዚሁ ስፍራ ይጀመር እንጅ ወደ አራት አጎራባች አካባቢዎች ተሰራጭቶ እንደነበር ምንጮች አመልከተዋል።
ከትናንት በስቲያ እና ትናንት ውጥረቱ እንደነበር ለማወቅ የተቻለ ሲሆን፣ ምናልባትም ግጭቱ እንደገና ሊያገረሽ ይችላል በሚል ስጋት የአካባቢው ሰዎች ቀያቸውን እየለቀቁ ነው።
የቡሬ ግንባር ዋና እዝ መቀሌ የሚገኝ ሲሆን፣ በሰሜን እዝ አዛዥ ጄነራል ሳእረ መኮንን እንደሚመራ ይታወቃል።
ቡሬ ግንባር የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት ከባድመ ቀጥሎ ሀይሉን በብዛት ያሰማራበት ቦታ መሆኑ ይታወቃል። ኢሳት በቅርቡ በሰሜን ግንባር የተመደበን አንድ የመከላከያ ሰራዊት አባል በማናገር በሰራዊቱ ውስጥ ያለውን ችግር መዘገቡ ይታወሳል።
በሌላ ዜና ደግሞ በአካባቢው ለሚንቀሳቀሰው የአፋር ጋድሌ ሚሊሺያ ሀይል ወጣቶችን ትመለምላላችሁ የተባሉ የሚሊሺያው ወታዳራዊ አዛዥ የሆኑት የኮሎኔል ሙሀመድ አህመድ 4 የቅርብ ዘመዶች ተይዘው ታስረዋል። በአካባቢው ከፍተኛ ውጥረት መንገሱንና መንግስትም ካለፉት ሁለት ሳምንታት ጀምሮ በርካታ ወታደሮችን ማስፈሩን መዘገባችን ይታወሳል።

Friday, December 28, 2012

መንግሰት የኢንተርኔት ድረገጾችን እና ብሎጎችን እንደሚያፍን በይፋ አመነ
ታህሳስ ፲፱ (አስራ ዘጠኝ) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም
ኢሳት ዜና:-አንዳንድ የኢንተርኔት ድረገጾች እና ብሎጎች በኢትዮጽያ እንደሚታገዱ የኢንፎርሜሽን ደህንነት ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር ብርጋዴር ጄኔራል ተክለብርሃን ወልደአረጋይ በይፋ አረጋገጡ፡፡
ብ/ጄኔራሉ ሰሞኑን ለንባብ ከበቃው መንግስታዊው “ዘመን” መጽሔት ጋር ባደረጉት ቃለምልልስ እንዳረጋገጡት አንዳንድ አስጊ ናቸው ያሏቸውን የኢንተርኔት ድረገጾችና ብሎጎችን ማገድ የኤጀንሲው ዋንኛ ስራ አለመሆኑን፤ ነገር ግን በመርህ ደረጃ መደረግ አለባቸው ብሎ ማስቀመጡን ጠቅሰዋል፡፡“ለዚህ ደግሞ ቴሌ እንዲያጣራቸው አቅም
የመገንባት ስራ እንሰራለን፡፡ከተቻለ ደግሞ ከሃይማኖት፣ከዘር፣ከሽብርተኝነት፣ከሕዝብ ሞራል ጋር የተያያዙ ድረገጾች ወደ ኢትዮጽያ እንዳይገቡ ጥረት ይደረጋል” ሲሉ ተናግረዋል፡፡
“የሃይማኖት አክራሪነት አንድ ስጋት ነው፡፡ከዚያ አልፎ ሽብርተኝነት አለ፡፡ሕዝቡ በስነልቦና እንዲሸበር ፍርሃት፣ጭንቀት፣አለመተማመን እንዲሰፋ፣ ወጣቱ በሙሉ አቅሙ ወደ ልማትና ዴሞክራሲ ግንባታ እንዳይገባ የሚያደርጉ ኃይሎች አሉ ” ያሉት ብ/ጄኔራሉ ”ይህን ለመቆጣጠር ኢንተርኔትን መሰረት ያደረገ የመከላከያ አቅም መገንባት
ያስፈልጋል ሲሉ ገልጸዋል፡፡
ብ/ጄኔራሉ በዚሁ ቃለምልልሳቸው መረር ብለው “የኢትዮጽያ ቴሌኮምኒኬሽን የኀብረተሰቡን ሰላም የሚያጠፉ ዌብሳይቶችን የመቆጣጠር አቅም ሊኖረው ይገባል፡፡መርሁ ይህ ነው፡፡ለኀብረተሰቡ የሰላምና የልማት አጀንዳ እንቅፋት ሊሆኑ የሚችሉ የመቆጣጠር ብቃት አስፈላጊ ነው” ብለዋል፡፡
“ስርዓት ያልተበጀለት ኢንተርኔት ጉዳቱ ሰፊ ነው” የሚሉት ብ/ጄኔራል ተክለብርሃን “ሕገመንግስቱን ም ሆነ የሕዝቡን ሰላም የሚጻረሩ እንቅስቃሴዎች ሊፈቀድላቸው አይገባም” ብሎ አስቀምጧል ሲሉ አስረድተዋል፡፡
የኢትዮጽያ መንግስት በኢንተርኔት ድረገጾች እና ብሎጎች ላይ አፈና በማድረግ የዜጎችን ኀሳብን በነጻ የመግለጽ ነጻነት የሚጻረሩ ሕገወጥ እርምጃዎችን ይወስዳል በሚል የሚቀርብበትን ተደጋጋሚ ክሶች፤ መሰረተ ቢስ ናቸው በሚል ሲያጣጥል መቆየቱ አይዘነጋም፡፡

ግራ የሚያጋባ የወቅቱ ሐቅ! ማብቂያውን እናፍቃለሁ፡፡

ማሕሌት ፋንታሁንበሕይወታችን የምናደርጋቸውን እንቅስቃሴዎች ከመከወን እንድንቆጠብ ለራሳችን ስንነግር ወይም ውስጣችን ሲሰማው የፍርሐት ስሜት ተሰማን ልንል እንችላለን፡፡ የፍርሐትን ምንጭ በሁለት ከፍለን ማየት እንችላለን፡፡ የመጀመሪያው ፍርሐታችንን የምናምንበት፣ ምክንያቱም ከራሳችን የመነጨ ድክመት በሚሆንበት ጊዜ ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ ድርጊቱን በመፈፀማችን ሊደርስብን ይችላል ብለን የምናሰላው አግባብ ያልሆነ ጉዳት/በደል በማሰብ ድርጊቱን ከመፈፀም ስንቆጠብ ነው፡፡

ከላይ እንዳልኩት የለት ተለት እንቅስቃሴዎቻችን ውስጥ ምንጫቸው ከሁለት አንዱ ወይም ከሁለቱም የሆነ ፍርሐት ሊያሳድሩብን የሚችሉ ጉዳዮች ብዙ ናቸው፡፡ ይህ ጽሑፍ የሚያጠነጥነው በአሁን ሰዓት በሀገራችን የሚታየውን የፖለቲካ ጉዳዮች ላይ ሐሳብን የመሰንዘር፣ የመወያየት፣ የመሳተፍ እና የመተቸት ፍርሐትን ሲሆን፤ በሁለተኛ ደረጃ ደግሞ በተጠቀሰው የፍርሐት ምንጭ የሚከሰተውን ነው፡፡

ተማሪዎች

ተማሪዎች ስል ዕድሜያቸው ለአቅመ ማገናዘብ ከደረሱት ጀምሮ ማለቴ ነው፡፡ እነዚህ ተማሪዎች ወደ ከፍተኛ ትምህርት ለመግባት ዕድሉ ያላቸው ወይም ለቴክኒክና ሙያ ስልጠና የሚገቡ ወይም በግል ኮሌጅ ገብተው የሚቀጥሉና ውጤታቸው ትምህርታቸውን የማያስቀጥላቸው ሲሆኑ ሁሉንም የሚያመሳስላቸው አንድ ነገር አለ፡፡ ትምህርታቸውን የቀጠሉትም ያልቀጠሉትም በደረጃቸው ሥራ የመያዝ እና ራሳቸውን ለማኖር የመጣር ግዴታ አለባቸው፡፡ ሥራ ለማግኘት ደግሞ ያልተጻፈው ሕጋችን በኢሕአዴግ መጠመቅን ይጠይቃል፡፡ ሥራ አጥ ሆኖ ኢሕአዴግን መቃወም ወይም ስህተቶቹን እየነቀሱ መተቸት የማይታሰብ ነው፡፡ ይህን ጠንቅቀው ስለሚያቁ ተማሪዎች ቀደም ብለው አባል ወይም በደጋፊነት መዝገብ መስፈርትን እና የሚፈለገውን ሟሟላት ሌላው ተግባራቸው ይሆናል፡፡ ምክንያቱም ዋናው ነገር እንጀራ ነው፡፡ ምናልባትም ከተደላደሉና የትም ተቀጥረው የመሥራት ዕድላቸው የሰፋ ሲሆን ወደራሳቸው ሊመለሱ የሚችሉ ቢሆንም በጣም ኢሕአዴግ በሆኑ ቁጥር ጥቅማ ጥቅሞቹም በዛው ልክ ስለሚጨምሩ እዛው ሰምጠው የሚቀሩ ይበዛሉ፡፡ ለዚህም ነው በብዙ መጽሐፍት ያነበብነውን የሀገራቸውን ፖለቲካ የሚተነትኑ እና የራሳቸው የሆነ አቋም ያላቸው ተማሪዎች ማየት ሕልም የሆነብን፡፡

ሠራተኞች

ደረጃው ይለያይ እንጂ የመንግሥት የሆኑም ሆነ መንግሥታዊ ያልሆነ መሥሪያ ቤት ሠራተኞች ፖለቲካዊ ጉዳዮች ላይ በግልፅ ሐሳባቸውን ለመሰንዘር አይደፍሩም፡፡ በመንግሥት መስሪያ ቤቶች ውስጥ የኢሕአዴግ አባል ወይም ደጋፊ የሆኑ ሰራተኞች የሚያገኙትን እድገትና የተለያዩ ዕድሎች በማየት ሌሎች ገለልተኛ ሆነው የነበሩ ሠራተኞች አባል እንዲሆኑ ይገደዳሉ፡፡ ሁሉም ሰው የሚሠራው ለለውጥ እና ለዕድገት መሆኑ የማይካድ ሐቅ ነው፡፡ ለዚህም ለውጥ እና ዕድገት የሚያስገኘውን መንገድ አልቀበልም ብለው በራሳቸው ሐሳብ የፀኑ ብዙዎች በነሱ መያዝ ያለበት የኃላፊነት ቦታ ለቦታው በማይመጥን ሰው እንደሚያዝ በተደጋጋሚ የምንሰማው ስሞታ ነው፡፡

የመንግሥት መሥሪያ ቤቶች ከተመሰረቱበት ዋና ዓላማ ጎን ለጎን መንግሥቱን የሚመራው ፓርቲን ዓላማ የማስፈፀም ኃላፊነትም ያለባቸው ይመስላል፡፡ እንዲያውም አንዳንድ ጊዜ የመንግሥት መሥሪያ ቤቶች የኢሕአዴግ ፓርቲ ጽ/ቤት የሚመስሉበት አጋጣሚ አለ፡፡ በፓርቲው ያለው መዋቅር እና አሠራር አባል በሆኑ (ያው አብዛኞቹ አባል ናቸው) ሠራተኞች በመሥሪያ ቤቱም ተፈፃሚ ነው፡፡ የ1 ለ 5 የውይይት አደረጃጀትን ጨምሮ ሌሎች ፓርቲውን የሚመለከቱ ስብሰባዎች በሥራ ሰዓት ቢካሄዱም ችግር የለውም፡፡
መንግሥታዊ ያልሆኑ መሥሪያ ቤት የሚሠሩ ሠራተኞችም አባል መሆን ላይጠበቅባቸው ይችል ይሆና እንጂ መንግሥትን መቃወም እና መተቸታቸው በአሠሪዎቻቸው አይወደድላቸውም፡፡ ምክንያቱም አሠሪዎች ከመንግሥት ጋር መነካካት አይፈልጉም፡፡

አሠሪዎች

ከላይ አሠሪዎች ከመንግሥት ጋር መነካካት አይፈልጉም ብያለሁ፡፡ አባል ወይም ደጋፊ መሆን ሥራዎችን እንደሚያፋጥን እና ከመንግሥት ጋር በሚያገናኛቸው ጉዳይ ሁሉ እንግልት እንደማይኖርባቸው ስለሚያውቁ ብዙ አሠሪዎች አባል ወይም ደጋፊ ይሆናሉ፡፡ ወይም ከዳር ሆነው የሚመለከቱ ይሆናሉ፤ ግን አይቃወሙም ወይም አይተቹም፡፡ ስለሆነም ሠራተኞቻቸው አባል ቢሆኑላቸው እሰየው ነው፤ ተቃዋሚ ወይም የሚተቹ ባይሆኑ ግን ምርጫቸው ነው፡፡ ባጠቃላይ ከመንግሥት ጋር እሰጣ ገባ ውስጥ መግባት ስለማይፈልጉ መንግሥት የሚያስደስተውን ነገር ቢያደርጉ ይመርጣሉ፡፡

ባለሀብቶች

በድህነት ወይም በአቅም ማነስ ምክንያት ብቻ መንግሥትን ለመደገፍ የምንገደድ ቢመስለንም በሚገርም ሁኔታ ይህን ፍርሐት ገቢያቸው ከፍተኛ የሆኑ ባለሀብቶችም ይጋሩታል፡፡ ዓላማቸው ባላቸው ሀብት ላይ ሌላ ሀብት መጨመር ስለሆነ ምንም ቢሆን ከመንግሥት ጋር ተስማምቶ መስራት ይፈልጋሉ፡፡ ከመንግሥት ትዕዛዝ ባይቀበሉም (የተቀበሉም ሊኖሩ ይችላሉ)፤ ለተቃዋሚ ድርጅች እና ፓርቲዎች ንብረታቸውን ባለማከራየት፣ መንግሥትን የሚተቹ ማንኛቸውም ዓይነት ሥራዎችን ስፖንሰር ለማድረግ ፈቃደኛ ባለመሆን፣ ተቃዋሚ ፓርቲዎችን ባለመርዳት እና በመሳሰሉት ድርጊታቸው ፍርሐታቸውን መገንዘብ ይቻላል፡፡

እንግዲህ ማን ቀረ? ዋና ዋናዎቹን ጠቀስኩ እንጂ ይህ ዓይነቱ ፍርሐት ያልገባበት ቦታ የለም፡፡ አብዛኛው ዜጋ በሀገራችን የፖለቲካ ጉዳይ መወያየት፣ መሳተፍ እና መተቸትን እርግፍ አድርጎ ትቶታል፡፡ ሐሳቡን በአደባባይ ቢናገርም ቢወያይም መንግሥትን የማያስከፋውን እየመረጠ ነው፡፡ የመንግሥት መ/ቤት ደጅ ሳንረግጥ መኖር አለመቻላችን ባልከፋ ነገር ግን ጉዳያችን በአግባቡ እንዲፈፀም ደግሞ የመንግሥት ወዳጅ መሆን እንደመስፈርት መጠየቁ፤ ካልሆንን የሚደርስብን እንግልት እና በደል ተደማምረው የፍርሐታችን ልክ መድረሻ በማሳጣት የመንግሥት አጎብዳጅ እንድንሆን አድርጎናል፡፡ ሲጠሩን አቤት ሲልኩን ወዴት ሆኗል ነገሩ፡፡ የመንግሥትን ስህተት በግልፅ የሚናገር፣ የሚወያይ፣ የሚተች፣ የሚቃወም፣ የተቃዋሚ ፓርቲ አባል የሆነና በነዚህ ሰዎች ዙሪያ ያለ ሰው ደግሞ መንግሥት ወዳጅ አይደለም፡፡ ወዳጅ ካልሆነ ደግሞ መንገዱ ቀና አይሆንም፡፡ ይህ እንግዲህ በሕገመንግሥቱም ሆነ በማናቸውም የኢሕአዴግ ሕጎች ያልተጻፈ ነገር ግን ዜጎችን አግባብ ወዳልሆነ የፍርሐት ቀጠና እየወሰደ ያለ አስተሳሰብ ነው፡፡ የተቃዋሚ ፓርቲዎችም የአባላት ቁጥር ያለመጨመር እና እንቅስሴዎች መቀዛቀዝ ምክንያት አንዱ ይሄ ነው፡፡ ሕዝባዊ ስብሰባዎችን ሲያካሂዱ የሚገኘው ሰው በጣም ጥቂት ነው፡፡ አብዛኛዎቹን ኢሕአዴግ በሰበብ አስባቡ አባል ያደረጋቸው ሲሆን፤ የቀሩት ደግሞ ስብሰባው ላይ ቢገኙ የሚደርስባቸውን ነገር በማሰብ እና በመፍራት ብቻ አይገኙም፡፡

ይህን ስጋት እና ፍርሐት አስወግደው በራሳቸው ሐሳብ ብቻ በመመራት መንግሥትን እየተቃወሙ እና እየተቹ የሚደርስባቸውን ጫና ተቋቁመው እስካሁን ያሉ ጥቂቶች ቢኖሩም ብዙዎቹ እስር ቤት እና በስደት ናቸው፡፡ የተለያዩ ማኅበራዊ አውታሮች ላይ የምናያቸውን መንግሥትን በግልፅ የሚተቹ ጽሑፎች እና አስተያየቶችን አይተን ጸሐፊው ወይም አስተያየት ሰጪው ከኢትዮጵያ ውጪ እንደሆነ መታሰቡም ሀገር ውስጥ ያለውን ሐሳብን በነጻነት የመግለጽ ፍርሐት በግልጽ ያሳያል፡፡ አንዳንዴም ከሀገር መውጣት እንደፈለገ ተደርጎ ሊቆጠር ይችላል፡፡ ከአሠሪ ወይም ከመንግሥት ሰው ከሚደርስ ማስጠንቀቂያ ወይም ማስፈራሪያ በተጨማሪ የጸሐፊው ቤተሰብ፣ ጓደኛ ወይም የቅርብ ሰው ነኝ ባይ ምክር፣ ማስፈራሪያ እና ተግሳፅ ሊያስተናግድ ግድ ይለዋል፡፡ ከኛ ሐሳብ ጋር የሚመሳሰል ሐሳብ ያለው ሰው አጋጥሞን እንኳን በግልጽ ሊያወራን ቢሞክር ‹ተልኮብኝ ይሆን› በሚል ጥርጣሬ እንጂ በሙሉ ልባችን ለማውራት ፍርሐት አለብን፡፡ በፌስቡክና ሌሎች ማኅበራዊ አውታሮች ራሳችንን ገልጸን የተሰማንን እና የምናቀውን ሐቅ ለማውራት እንፈራለን፡፡ ሌላም ሌላም ብዙ ፍርሐቶች አሉብን፡፡

ምክንያቱም እንፈራለን፡፡

ግራ የሚያጋባ የወቅቱ ሐቅ! ማብቂያውን እናፍቃለሁ፡፡
----------
የዚህ ጽሑፍ ዋና ቅጂ በኢትዮጵያ እንዳይነበብ በታገደው በዞን ዘጠኝ ጦማር ላይ ይገኛል፡፡

Thursday, December 27, 2012

አስገድዶ መድፈር በጎንደር ዩኒቨርሲቲ

ጎንደር ዩኒቨርሲቲ ከአምስት ዓመታት በፊት በመምህሯ መደፈሯ የተገለፀ አንዲት ተማሪ ሁኔታዉን ለሚመለከተዉ አካል አቤት ብትልም እስካሁን መፍትሄ አማግኘቷ አነጋጋሪ እንደሆነ የደረሰን ዘገባ ያመለክታል።
ጎንደር ዩኒቨርሲቲ ከአምስት ዓመታት በፊት በመምህሯ መደፈሯ የተገለፀ አንዲት ተማሪ ሁኔታዉን ለሚመለከተዉ አካል አቤት ብትልም እስካሁን መፍትሄ አማግኘቷ አነጋጋሪ እንደሆነ የደረሰን ዘገባ ያመለክታል። በዩኒቨርሲቲዉ የተማሪዎች አገልግሎት ዲን ተፈፀመ የተባለዉን አስገድዶ የመድፈር ወንጀል ጥርጣሬ ደብዛ ለማጥፋት ተጎጂዋ ሃኪም ቤት የታከመችበትን ማስረጃ ምግኘት እንዳልቻሉ አንድ ስማቸዉ እንዳይገለጽ የጠየቁ የሰብዓዊ መብቶች ተሟጋች ለዶቼ ቬለ ገልጸዋል።

Monday, December 17, 2012


በማረቃ ወረዳ አንድ ግለሰብ በፖሊስ ተገደለ

ታህሳስ ፮(ስድስት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም

ኢሳት ዜና:- ታህሳስ 4 ቀን 2005 ዓም ማንነቱ ያልታወቀው ግለሰብ የተገደለው በወንጀል ተጠርጥሮ ከተያዘ በሁዋላ ነው። ግለሰቡን ተኩሶ የገደለው ፖሊስ በስም አልታወቀም። ይሁን እንጅ የወረዳው ፖሊስ ግለሰቡ ሊያመልጥ ሲል ተገደለ የሚል ምክንያት መስጠቱን ለማወቅ ተችልኦል።
...

የተርጫ ዞን የፖሊስ አዛዥ የሆኑት ኮሚሽነር አለማየሁ ጦፉ ግድያ መፈጸሙን ባይሸሽጉም ፣ ዝርዝሩን ከስብሰባ እንደወጡ እንደሚሰጡ ቢገልጹም ስቱዲዮ እስከገባንበት ጊዜ ድረስ ልናገኛቸው አልቻልንም።

በማረቃ ወረዳ የሚፈጸመው የሰብአዊ መብቶች ጥሰት ከፍተኛ ደረጃ በመድረሱ ህብረተሰቡ በተደጋጋሚ ሲያማርር ይሰማል። መምህር የኔሰው ገብሬ ፍትህና ዲሞክራሲ በሌለበት አገር አልኖርም በማለት ራሱን አቃጥሎ ከገደለ ወዲህ ፣ ከ6 ያላነሱ ሰዎች ራሳቸውን በመስቀል እና ወደ ገደል በመወርወር መግደላቸው ይታወሳል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ በአራት ኪሎ አካባቢ ቤታችሁን ልቀቁ በሚል ሰዎች መደብደባቸውን ነዋሪዎች ገልጸዋል። ከአሰብ አካባቢ ተፈናቅለው በአራት ኪሎ አካባቢ የሰፈሩ አንድ 70 አመት አዛውንት መደብደባቸውን የአይን እማኞች ገልጸዋል።
 


Thursday, December 13, 2012

BREAKING NEWS: Susan Rice Dropping Out




U.N. envoy Susan Rice is dropping out of the running to be the next secretary of state. Brian Williams will have an exclusive interview with Rice on tonight’s “Rock Center With Brian Williams” at 10p/9c.
By Tracy Connor, NBC News
Embattled U.N. envoy Susan Rice is dropping out of the running to be the next secretary of state after months ofEmbattled U.N. envoy Susan Rice is dropping out of the running to be the next secretary of state after months of criticism over her Benghazi comments, she told NBC News on Thursday. criticism over her Benghazi comments, she told NBC News on Thursday.
“If nominated, I am now convinced that the confirmation process would be lengthy, disruptive and costly – to you and to our most pressing national and international priorities,” Rice wrote in a letter to President Obama, saying she’s saddened by the partisan politics surrounding her prospects.
“That trade-off is simply not worth it to our country…Therefore, I respectfully request that you no longer consider my candidacy at this time,” she wrote in the letter obtained by NBC News.
Brian Williams will have an exclusive interview with Rice on tonight’s “Rock Center With Brian Williams” at 10p/9c.
In a statement, Obama said he accepted her decision to remove her name from consideration for secretary of state and he praised her as “an extraordinarily capable, patriotic, and passionate public servant.”

The president added: “While I deeply regret the unfair and misleading attacks on Susan Rice in recent weeks, her decision demonstrates the strength of her character, and an admirable commitment to rise above the politics of the moment to put our national interests first. The American people can be proud to have a public servant of her caliber and character representing our country. ”
Rice had been viewed as one of the front-runners to replace Hillary Clinton as the nation’s top foreign policy official.
She has been under intense fire from Republicans for initially characterizing the Sept. 11 assault on the U.S. consulate in Benghazi, Libya, as a spur-of-the-moment response to a crude anti-Muslim film.
“What happened in Benghazi was in fact initially a spontaneous reaction to what had just transpired hours before in Cairo, almost a copycat of the demonstrations against our facility in Cairo, which were prompted, of course, by the video,” Rice said on NBC’s “Meet the Press” five days after the attack.
“Opportunistic extremist elements came to the consulate as this was unfolding. They came with heavy weapons, which unfortunately are readily available in post-revolutionary Libya, and it escalated into a much more violent episode.”
As more details emerged suggesting it was a premeditated terrorist action, GOP critics accused Rice of misleading the public at the height of the presidential campaign.
She countered that she went with the best information available about the attack, in which Ambassador Chris Stevens and three other Americans were killed.
“I relied solely and squarely on the information provided to me by the intelligence community. I made clear that the information was preliminary and that our investigations would give us the definitive answers,” she said on Nov. 21 at the United Nations.
By then, Obama had already expressed strong support for Rice, warning Sens. John McCain (R-Ariz.) and Lindsay Graham (R-S.C.) to stop slamming her and vowing to block her confirmation.
“They should go after me,” he said at his first press conference after his re-election.
And last week, Clinton praised Rice as a “stalwart colleague” who had done a “good job” at the U.N.
Questions from lawmakers
Despite a series of closed-door meeting with Capitol Hill lawmakers to drum up support, Rice continued to face questions from senators key to her confirmation.
After a Nov. 28 sitdown with Rice, Sen. Susan Collins (R-Maine) said she couldn’t yet endorse the veteran diplomat and raised a new point of concern: her role in protecting American embassies in Kenya and Nairobi that were bombed by terrorists in 1998.
Sen. Bob Corker (R-Tenn.) suggested Rice was seen as too much of an Obama loyalist and the GOP preferred “someone of independence.”
In her letter to Obama, Rice took aim at her GOP critics.
“The position of secretary of state should never be politicized,” she wrote, adding, “I’m saddened that we have reached this point, even before you have decided whom to nominate. We cannot afford such an irresponsible distraction from the most pressing issues facing the American people.”
Her withdrawal leaves Sen. John Kerry (D-Mass.) as a possible candidate for the job, and Republicans have said he would have a smoother run.
“I think John Kerry would be an excellent appointment and would be easily confirmed by his colleagues,” Collins said last month.
Rice, 48, has been the United States’ permanent representative to the United Nations since 2009, after serving as a senior advisor to the Obama campaign , working at the Brookings Institution and holding other diplomatic and national security positions dating back to 1993.
13,December 2012
ECADF NEWS.

Wednesday, December 12, 2012

በሁለት ቀናት ልዩነት ሦስት ጊዜ ቀብሯ የተፈጸመው ወላድ ጉዳይ እያነጋገረ ነው

በሁለት ቀናት ልዩነት ሦስት ጊዜ ቀብሯ የተፈጸመው ወላድ ጉዳይ እያነጋገረ ነው
- አስከሬኗ ከመቃብር ወጥቶ ተገኝቷል
በታምሩ ጽጌ

የመጀመርያ ልጇን በቀዶ ሕክምና ከተገላገለች በኋላ ደም ፈሷት ሕይወቷ ያለፈው የ27 ዓመት ወጣት የቀብር ሥርዓቷ ባለፈው ቅዳሜ፣ እሑድና ከትናንት በስቲያ ሰኞ የመፈጸሙ ጉዳይ እያነጋገረ ነው፡፡ ሟች ቤተልሔም ሰለሞን ልጅ ወልዳ ለመሳም ዘጠኝ ወራትን ስትጠብቅና የእርግዝናዋንም ሁኔታ ስትከታተል ቆይታ የመውለጃዋ ዕለት በመድረሱ፣ ጎፋ ማዞሪያ ወደሚገኘው ሮያል የጽንስና የማኅፀን ሕክምና ከፍተኛ ክሊኒክ የሄደችው ኅዳር 27 ቀን 2005 ዓ.ም. ነበር፡፡

ክትትል ስታደርግበት የነበረው ክሊኒክ ተቀብሎአት ወደ ማዋለጃ ክፍል ካስገባት በኋላ የምጥ መርፌ ቢወጋትም፣ በዕለቱ ልትወልድ አለመቻሏንና ወደ ቤቷ መመለሷን ወላጅ እናቷ ወይዘሮ በለጡ አበበና ባለቤቷ አቶ ፍስሐ እሸቴ ገልጸዋል፡፡

ቤተሰቦቿ እንደሚሉት፣ ቤተልሔም ምጧ እየተፋፋመ በመምጣቱ ኅዳር 28 ቀን 2005 ዓ.ም. ተመልሳ ወደ ክሊኒኩ ትሄዳለች፡፡ የክሊኒኩ ሐኪሞች ተቀብለዋት ወደ ማዋለጃ ክፍል ካስገቧት ከጥቂት ደቂቃዎች በኋላ፣ ቤተሰቦቿ ተጠርተው “እንኳን ደስ ያላችሁ፤ በሰላም ተገላግላለችና የሕፃኗን ማቀፊያ አምጡ፤” ይባላሉ፡፡ በክሊኒኩ የተገኙት እናቷና ባለቤቷ ደስታቸውን በእልልታና እርስ በርስ በመሳሳም ገልጸው ለጥቂት ደቂቃዎች እንደቆዩ፣ ቤተልሔም “እናቴን፣ ባለቤቴንና ልጄን አሳዩኝ፤” ብላለች ተባሉና ሁሉም ገቡ፡፡ ቤተልሔም ከማደንዘዣ ነቅታ በደንብ እንዳነጋገረቻቸው ተናግረው፣ “ጠብቁ አሁን ትወጣለች” በመባላቸው ሕፃኗን ይዘው ከነበረችበት ክፍል ወጥተው መጠባበቅ መጀመራቸውን አስረድተዋል፡፡ ሐኪሞቹ “ትንሽ ቆዩና ባለቤቷን ጠሩት” የሚሉት የቤተልሔም እናት፣ እሳቸው ግራ ገብቷቸው በመጠባበቅ ላይ እያሉ፣ ባለቤቷ መኪናቸውን ይዘው ሲወጡ መመልከታቸውንና በዚያው መቅረታቸውን ተናግረዋል፡፡

ልጃቸው ምን እንደሆነች ያላወቁትና ግራ ተጋብተው ሲንቆራጠጡ ለነበሩት የቤተልሔም እናት፣ አንዲት ነርስና ዶክተር መጥተው የባለቤቷን ስልክ ሲጠይቋቸው፣ “ምነው ልጄ ምን ሆነች?” ሲሏቸው፣ “ደም ስላነሳት ደም እንዲሰጥ ነው” እንዳሏቸው ተናግረዋል፡፡

የቤተልሔም ባለቤትና ጓደኞች ደም ቢሰጡም እየደከመች ስለመጣችባቸው ያዋለዷት ዶክተር ሪፈር ጽፈው በመስጠት ኦክስጂን የተገጠመለት አምቡላንስ እንዲያመጡ ይነግሯቸዋል፡፡ ደክማለች በተባለችው ልጃቸው የተጨናነቁት ቤተሰቦች፣ ሩጫቸውን ወደ ተክለሃይማኖት ሆስፒታል እንዳደረጉ ይናገራሉ፡፡ የተጻፈውን ሪፈር ወረቀት የተመለከቱት የተክለሃይማኖት ሆስፒታል ሐኪም፣ “ብዙ ደም ስለፈሰሳት አንሠራም፤ ኃላፊነት አንወስድም፤” ሲሏቸው እግራቸው ሥር ቢወድቁም ሌላ ምላሽ ሊሰጧቸው እንዳልቻሉ ገልጸዋል፡፡

ግራ የተጋቡት ቤተሰቦች ጉዟቸውን ሜክሲኮ ገነት ሆቴል አካባቢ ወደሚገኘው ላንድማርክ ሆስፒታል በማድረጋቸው፣ የታዘዙትን ኦክስጂን የጫነ አምቡላንስ ማግኘታቸውን ተናግረዋል፡፡ የሆስፒታሉ ሠራተኞች፣ “እናንተ እዚህ ጠብቁን፤ እኛ ይዘናት እንመጣለን፤” ብለው ቤተልሔም ወደተኛችበት ሮያል የጽንስና የማኅፀን ሕክምና ከፍተኛ ክሊኒክ በማምራት ይዘዋት መምጣታቸውን እናቷ ወይዘሮ በለጡ ተናግረዋል፡፡ የቤተሰቦቿ መሯሯጥና እሷን ለማትረፍ ያደረጉት ጥረት ውጤት ሳያገኝ ቤተልሔም ላንድማርክ ስትደርስ ማረፏን እናቷና ባለቤቷ አስረድተዋል፡፡

ይኼ ሁሉ የሆነው ኅዳር 28 ቀን 2005 ዓ.ም. ሙሉቀን እስከ ምሽት ድረስ በመሆኑ፣ የቤተልሔም አስከሬን ላንድማርክ ሆስፒታል እንዲያድር ይደረግና ቤተሰቦቿ በቀዶ ሕክምና የተወለደችውን ሕፃን ታቅፈው ወደ ቤታቸው ይመለሳሉ፡፡

“ማንኛውም እናት በወሊድ ምክንያት መሞት የለባትም” የሚለው መሪ ቃል ባልሠራበት ሁኔታ ደም ፈሷት ሕይወቷን መታደግ ሳይቻል በመቅረቱ ቤተልሔም ሕይወቷ ማለፉንም አስረድተዋል፡፡ ቤተሰቦቿና ወዳጅ ዘመዶቿ በተገኙበት የቀብር ሥርዓቷ ገርጂ በሚገኘው ደብረገነት ቅዱስ ጊዮርጊስና ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ኅዳር 29 ቀን 2005 ዓ.ም. ከቀኑ ዘጠኝ ሰዓት መፈጸሙን ቤተሰቦቿ አረጋግጠዋል፡፡

የቀብር ሥርዓቷን ፈጽመው በሐዘን እየተብሰለሰሉ የዋሉትና ያደሩት የቤተልሔም ቤተሰቦች፣ በማግሥቱ ኅዳር 30 ቀን 2005 ዓ.ም. የተነገራቸውን ማመን አቅቷቸው ወደ ቀብር ቦታዋ ተሯሩጠው ይሄዳሉ፡፡

ቤተሰቦቿ የቀብር ቦታው ሲደርሱ የቤተልሔም አስከሬን ከተቀበረበት ጉድጓድ ወጥቶ ዳር ላይ በፊቱ ተደፍቶ ማየታቸውን ይገልጻሉ፡፡ አስከሬን ጉድጓድ ውስጥ ከገባ በኋላ በባዞላ ድንጋይ ጉድጓዱ ተደፍኖ በላዩ ላይ በሲሚንቶ ይለሰናል፡፡ ከዚያም በላይ አፈር ይለብሳል፡፡ ይኼንን ሁሉ አልፎ እንዴት ሊፈጸም እንደቻለ የቤተ ክርስቲያኑ አስተዳዳሪ ሊቀ ማዕምራን ጽጌ ከበረ ምላሽ እንዲሰጡ በሪፖርተር ተጠይቀው ነበር፡፡

አስተዳዳሪው እንደነገሩን፣ ሟች የኦርቶዶክስ እምነት ተከታይ በመሆኗ ሥርዓተ ፍትኃት ተፈጽሞላት ኅዳር 29 ቀን 2005 ዓ.ም. ከቀኑ ዘጠኝ ሰዓት የቀብር ሥርዓቷ ተከናውኗል፡፡ በዚያኑ ቀን ለእሑድ አጥቢያ እሳቸው ቅዳሴ ላይ እያሉ የቤተ ክርስቲያኑ ጥበቃዎች አስከሬን ከጉድጓድ ወጥቶ መገኘቱን ነግረዋቸዋል፡፡

ጥበቃዎቹ እንደነገሯቸው አስከሬን ከተቀበረበት ወጥቶ በመገኘቱ ለፖሊስ ተደውሎለት መጥቷል፡፡ የሟች ቤተሰቦችም መጥተዋል፡፡ ውጭ ላይ የተገኘው አስከሬን የተገነዘበት ጨርቅም የለም፡፡ አስከሬኑ ልብስ ባለመልበሱ ምክንያት ነጠላ ተሸፍኖ አባዲና እስኪመጣ ቢጠበቅም ሊመጣ ባለመቻሉ፣ ፖሊስና የሟች ቤተሰቦች ተመካክረውና ተስማምተው ለሁለተኛ ጊዜ ኅዳር 30 ቀን 2005 ዓ.ም. ከጠዋቱ አምስት ሰዓት አካባቢ በድጋሚ ቀብሩ መፈጸሙን አስረድተዋል፡፡

አስተዳዳሪው ያዩትን እንደተናገሩት፣ አስከሬኑ የወጣው ባንድ በኩል አንድ ባዞላ ድንጋይ ተፈንቅሎና በጠባብ ቀዳዳ ውስጥ ሲሆን፣ ቀብር የተፈጸመበት ሳጥንም ጉድጓዱ ውስጥ መሆኑንና አስከሬኑ በማበጡ ምክንያት እንዴት በዚያ ቀዳዳ ውስጥ እንደወጣ ተዓምር እንደሆነባቸው ነው፡፡

አስተዳዳሪው እንደገለጹት ሁሉ የሟች ቤተሰቦች ያዩትን ተናግረዋል፡፡ በሲሚንቶ የተደፈነ መቃብርን ደም ፈሷት የሞተች፣ ከ12 ሰዓታት በላይ ታፍና የቆየችና አቅም የሌላት ወላድ፣ ቀጭን ሰው በማያስወጣ ቀዳዳ እንዴት እንደወጣች፣ አፈሩ ሳይነሳና ከአንድ ባዞላ በስተቀር ሌላው ሳይነካ አስከሬን ወጥቶ በደረቱ ተደፍቶ መገኘቱ ግራ እንዳጋባቸው ተናግረዋል፡፡

የሟች ቤተልሔም አስከሬን ጉዳይ በሁለት ጊዜ ቀብር ሳያበቃ ከተቀበረ ከሰዓታት በኋላ “ጩኸት ይሰማል፤ ሳጥን እየተንኳኳ ነው፤” በማለት ፖሊሶች፣ የወረዳ አስተዳዳሪዎችና ሕዝቡ አካባቢውን አጥለቅልቆት እንደገና መጠራታቸውን ቤተሰቦቿ ገልጸዋል፡፡ እነሱ ሲደርሱ “ሆን ብለው ከነነፍሷ ቀብረዋት ነው፤ አምልኮ ቢኖር ነው፤ ስትጮህ ሰምተናታል፤ ውኃ ስጡኝ ስትል ነበር፣ ወዘተ” ከሚል ሹክሹክታና ትርምስ በስተቀር የቀብር ቦታው እንዳልተከፈተ መመልከታቸውን ቤተሰቦቿ ተናግረዋል፡፡

ፖሊሶች የሟች ቤተሰቦችን “እኛም ምንም የሰማነውና ያየነው ነገር የለም፤ ፈቃደኛ ከሆናችሁ ይቆፈርና ይውጣ፤” የሚል ጥያቄ ሲያቀርቡላቸው፣ “የተሰበሰበው ሰው የተለያየ ነገር ሲል እየሰማን እንዴት አይሆንም እንላለን? ይቆፈርና ይውጣ፤” በማለት መፍቀዳቸውን ተናግረዋል፡፡

አስከሬኑ በፖሊስ ተቆፍሮ እንዲወጣ ከተደረገ በኋላ ሳጥኑ ሲከፈትና አባዲና ሲመረምረው መሞቷ መረጋገጡን፣ ነገር ግን ሰውነቷ ፎርማሊን የተወጋ ቢሆንም፣ መተጣጠፍና መዘረጋጋት እንደሚችል የገለጹት ቤተሰቦቿ፣ ሕይወቷ ለማለፉ የመጨረሻ ማረጋገጫ ለማግኘት አስከሬኑ ዳግማዊ ምኒልክ ሆስፒታል ገብቶ እንዲመረመር ከተደረገ በኋላ፣ ለሦስተኛ ጊዜ ታኅሣሥ 1 ቀን 2005 ዓ.ም. ለመጨረሻ ጊዜ ቀብሯ መፈጸሙን አስታውቀዋል፡፡

ልጃቸው በሕክምና ጉድለት ደሟ ፈሶ መሞቷ አንሶ አስከሬኗ ሲንገላታ መክረሙ የበለጠ መሪር ሐዘን እንደሆነባቸው የገለጹት እናቷ፣ አንድ ልጃቸው መሆኗንና እሳቸውም ሆኑ ልጃቸው ከማንም ጋር ፀብም ሆነ ቅያሜ የሌላቸው በመሆኑ የልጃቸውን አስከሬን ከጉድጓድ ያወጣውን ማወቅ እንደሚፈልጉ ተናግረዋል፡፡ መንግሥት “ሰምተናል፣ አይተናል፤” በማለት ሕዝቡንና ሐዘንተኞችን ሲያሸብሩ የነበሩትን በደንብ እንዲመረምርና ያለውን እውነት እንዲገልጽላቸውም ጠይቀዋል፡፡

የባለቤታቸውን የአስከሬን ምርመራ ውጤትና በቁጥጥር ሥር የዋሉትን ተጠርጣሪ ሰዎች የምርመራ ውጤት አንድ ላይ ለቤተሰብና ለሕዝቡ ፖሊስ ይፋ እንዲያደርግ አቶ ፍሰሐ እሸቴ ጠይቀዋል፡፡

ፖሊስ ስለደረሰበትና ስለተደረገው ነገር ሁሉ ማብራርያ እንዲሰጥ በሪፖርተር ጥያቄ ቀርቦለት፣ የአስከሬኑ ምርመራ ውጤት ገና እንዳልደረሰ ገልጾ፣ ሕዝብንና ቤተሰብን በተደጋጋሚ ሲያሸብሩ የነበሩትን በቁጥጥር ሥር ማዋሉንና በምርመራ ላይ መሆኑን አስታውቋል፡፡ በምርመራ ላይ በመሆኑም ተጨማሪ ማብራርያ መስጠት እንደማይችል ገልጿል፡፡
 

Monday, December 10, 2012

በእብሪተኛው የወያኔ አገዛዝ የተፈናቀሉ ኢትዮጵያዊያን ከሁለት ሰው በላይ ሆነው ማውራት ተከለለክሉ

በአዲስ አበባ በተለያዩ አካባቢዎች ጎጆ ቀልሰው ከሚኖሩበት ሰፈር ህገወጦች ናችሁ በሚል ሰበብ በማንአለብኝነት እብሪት በተወጠረው ወያኔ ትእዛዝ ጎጇቸው ፈርሶ እንዲፈናቀሉና ሜዳ ላይ እንዲወድቁ የተደረጉት ዜጎች በሀገራችን መኖር ካልቻልን ወደ ሌላ ሀገር ሄደን በስደተኝነት ለመኖር እንችል ዘንድ ሁኔታዎች ይመቻቹልን ማለታቸው ተሰማ።
ተፈናቃዮቹ በየአካባቢዎቹ በመዘዋወር ላነጋገራቸው የግንቦት 7 ዘጋቢ ሲገልጹ ህገወጡ ወያኔ ህጋዊ ሰነድ ይዘን ህገወጦች ናችሁ ይለናል በጣም የሚገርም ነው፤ ሌላው ቀርቶ በህገ ወጥ መንገድ የሰፈሩ አንዳንድ እንኳን ቢኖሩ ሃላፊነት የሚሰማው መንግስት ቢሆን ኖሮ አስቀድሞ መጠለያ በማዘጋጀት ሊያዛውራቸውና መሬቱን ሊጠቀምበት ይችል ነበር።ነገር ግን ለዜጎች አንዳችም ደንታ የሌለው ዘረኛውና ስግብግቡ ወያኔ ማንንም ከማንም ሳይለይ ከመሬቱ የሚያገኘውን ጥቅም ብቻ በመመልከት ቤቶቻችንን በላያችን ላይ በማፍረስ ሜዳ ላይ ጥሎናል ብለዋል።
አሁን ደግሞ ይግረማችሁ ብሎ ለችግራችን ተወያይተን መፍትሄ እንኳን እንዳንሻ ከሁለት በላይ ሆናችሁ መነጋገር አትችሉም በማለት የግፉን መጠን በላይ በላዩ እየደረበብን ይገኛል በመሆኑም በሃገራችን መጠለያ የማግኘት መብት ከተነፈግን፣ ሁለት ሆነነ መነጋገር ከተከለከልን፣ በግፍ ከተደበደብን፣ ልጆቻችን ለሞት አደጋ እንዲጋለጡ ከተደረጉ እንደምን የዚች ሀገር ዜጎች ነን ማለት እንችላለን? ያሉት ተፈናቃዮች የትም ብንሄድ ከዚህ የባሰ ነገር ስለማይመጣ ዜጎቹ መሆናችንን የሚቀበል መንግስት እስኪመጣ ወደ ሌላ ማንኛውም ሀገር ለመሰደድ ወስነናል በማለት አብራርተዋል።
አንዲት እናት በበኩላቸው ይሄን ሁሉ ገንዘብ የሚያግበሰብሱት መቼ ሊበሉት እንደሆን አላውቅም፤ቤታችንን በላያችን ላይ በማፍረስ አውላላ ሜዳ ላይ የጣሉን መሬቱን ለመሸጥ ነው፤ እኔ የሚገርመኝ ከመለስ እንኳን አይማሩም፤እሱ ይሄው ከሰበሰበው ጥቂቱን እንኳን ሳይበላ አፈር ገባ፤ድሃን ቢንቁትም አምላክ አለው፤ የሱ ፍርድ የመጣ ቀን መግቢያ ይጠፋል፤ እናም ያክፉ ቀን ሳይመጣ እባካችሁ ግፍ ይብቃችሁ፤ስግብግብነት ይብቃችሁ፤ለወገኖቻችሁ አስቡ በልልኝ እንዳሉት ዘጋቢያችን ገልጿል።
በዚህ የሰሞኑ የቤት ማፍረስና ዜጎችን ሜዳ ላይ የመጣል ዘመቻ ከሰባ ሺህ በላይ ዜጎች መፈናቀላቸው፣መደብደባቸውና ሜዳ ላይ መበተናቸው መዘገቡ ይታወሳል።
Source: Ginbot 7

‹አሜሪካ የመጣሁት ከቃሊቲ ስለሚሻል ብቻ ነው›› ዳዊት ከበደ (የቀድሞው የአውራምባ ታይምስ ጋዜጣ ማኔጂንግ ኤዲተር)

‹አሜሪካ የመጣሁት ከቃሊቲ ስለሚሻል ብቻ ነው›› ዳዊት ከበደ (የቀድሞው የአውራምባ ታይምስ ጋዜጣ ማኔጂንግ ኤዲተር)
‹‹አሜሪካ የመጣሁት ከቃሊቲ ስለሚሻል ብቻ ነው››
ዳዊት ከበደ
የቀድሞው የአውራምባ ታይምስ ጋዜጣ ማኔጂንግ ኤዲተር
በ97 ዓ/ም. በሀገራችን ተከስቶ በነበረው ፖለቲካዊ ቀውስ ሣቢያ ለእስር ከተዳረጉ ጋዜጠኞች መካከል አንዱ ነው፡፡ ከአንድ ዓመት ከዘጠኝ ወራት እስር በኋላ በሂደት አውራምባ ታይምስ ጋዜጣን በየካቲት ወር 2ዐዐዐ ዓ.ም. አቋቁሞ ማሳተም ጀመረ፡፡ የሲፒጄ የ2ዐ1ዐ የኘሬስ ነፃነት ዓለም አቀፍ ተሸላሚ የነበረው – ጋዜጠኛ ዳዊት ከበደ፡፡ ህዳር 9 ቀን 2ዐዐ3 ዓ/ም. ግን “ይቅርታዬ ተነስቶ እንድታሠር በመወሰኑ ከፍትህ ሚኒስቴር አስተማማኝ ምንጭ መረጃ አገኘሁ” በማለት ከሀገሩ ወደ አሜሪካ መሰደዱ ይታወሳል፡፡
ኤልያስ ገብሩም ለቀድሞው የአውራምባ ታይምስ ጋዜጣ ማኔጂንግ ኤዲተር ጋዜጠኛ ዳዊት ከበደ በተለያዩ ርዕሠ ጉዳዮች ዙሪያ ጥያቄ በማንሣት ተከታዩን ቃለ-ምልልስ አድርጓል፡፡
አድዋ እንደተወለድክ አውቃለሁ፤ እስቲ ስለትውልድህና ስለልጅነት ህይወትህ ጠቅለል አርገህ ንገረኝ፡፡ አድዋ በመወለድህስ ምን ይሰማሀል?
በቅድሚያ እድሉን ስለሰጣችሁኝ እጅግ በጣም አመሰግናለሁ፡፡ ያው የተወለድኩት አድዋ
ነው፡፡ ያደግኩት ደግሞ አዲስ አበባ፡፡ አንዳንድ ሰዎች አድዋ መወለዳቸውን ብቻ እንደ ትልቅ ስኬት አድርገው ይቆጥሩታል፡፡ እኔ ግን አይታየኝም፡፡ ሰው ፈልጎ ባመጣው ነገር ነው መኩራት ያለበት፡፡ እውነትም ፈልጌና መርጬ አድዋ ብወለድ ኖሮ እንደ ስኬት እቆጥረው ነበር፡፡ በተረፈ ከተወለድኩ በኋላ ነው የት እንደተወለድኩ ያወቅኩት፡፡ ስለዚህ አጋጣሚ እኔ የተወለድኩበት አካባቢ የተወለዱ ጠቅላይ ሚኒስትር ኢትዮጵያን ለ21 ዓመታት ስለመሩ የዚህ ኩራቱ አይታየኝም፡፡ ከዛ ይልቅ መኩራት ያለብኝ አድዋ ላይ በተሰራው የጥቁር ህዝቦች ታላቅ ታሪክ ነው፡፡ ያ ታሪክ ደግሞ በሌላ የኢትዮጵያ ክፍልም ብወለድ ኖሮ ኩራቱ እኩል ነው የሚሰማኝ፡፡
ጋዜጠኝነትን መቼ ጀመርከው? ወደዚህ ሙያ እንድትገባስ ምክንያት የሆነህ ምንድነው?
ጋዜጠኝነትን መቼ እንደጀመርኩት ከመናገር ይልቅ፤ ለሙያው ትኩረት መስጠት የጀመርኩት ከመቼ ጀምሮ እንደሆነ መናገሩ ይሻላል፡፡ የጋዜጠኝነት ፍቅር በውስጤ ማደር የጀመረው ገና የአራት አመት ልጅ እያለሁ ጀምሮ ነው፡፡ በወቅቱ ምንም የማውቀው ነገር ባይኖርም አባቴ አንድ አነስተኛ ሬዲዮ ይዞ የአሜሪካ ድምጽ ሬዲዮ በተመስጦ ሲሰማ በጣም ይገርመኝ ነበር፡፡ እና አስታውሳለሁ፡- በወቅቱ ለእኔ በጣም አስገራሚ የነበረው ‹‹እንዴት ነው የሰው ልጅ በእንደዚህ አይነት ትንሽዬ ነገር ውስጥ ሆኖ (ሬዲዮውን እያየሁ ማለት ነው) ሊያወራ የሚችለው›› የሚለው ነገር ነበር፡፡ ደግሞም በነገሩ ተገርሜ ዝም አልልም” አባቴንም እጠይቀው ነበር፡፡ ታዲያ ሁሌ እሱ በተመስጦ ሲሰማ እኔ ደግሞ ያንኑ ተመሳሳይ ጥያቄ ደጋግሜ እየጠየኩ ሳስቸግረው አንድ ቀን ‹‹ስማ ጋዜጠኞች ናቸው፤ የሚያወሩት እዚህ ውስጥ ገብተው ሳይሆን ሌላ ቦታ ሆነው ነው፡፡ ስለዚህ እንደነሱ መሆን ከፈለክ ትምህርትህን ጠንክረህ ተማር!›› አለኝ፡፡
ከዛ በኋላ በትምህርት ቤት ግጥም ማንበብ፣ የተለያዩ ክበባት ውስጥ መግባት፣ ሚኒ ሚዲያ መሳተፍ ጀመርኩ፡፡ 12ኛ ክፍል ጨርሼ የማትሪክ ውጤት እስኪመጣልኝ ድረስ ባለው የክረምት ወር ከአዲስ አበባ ማስታወቂያ ቢሮ የሦስት ወር የጋዜጠኝነት ስልጠና ወሰድኩ፤ እግረመንገዴንም በአንዳንድ ጋዜጦችና መጽሄቶች ጽሁፍ እንዲወጣልኝ መስጠት ጀመርኩ፡፡ ከዚህ በኋላ የማትሪክ ውጤት መጣ፡፡ የመጣው የማትሪክ ውጤት በመንግስት የትምህርት ተቋም ሊያስገባኝ የሚችል ቢሆንም እኔ ግን ሁሌ የማስበው ጋዜጠኝነት ብቻ ስለነበረ በወቅቱ የጋዜጠኝነት ትምህርት የሚሰጠውን ዩኒቲ ኮሌጅ መርጬ ገባሁ፡፡ እና በዚህ መልኩ ነው ወደ ሙያው የገባሁት፡፡

በጋዜጠኝነት ህይወትህ ውስጥ የገጠመህን ፈተናና ውጣ ውረድ ብትገልጽልን? (ከሐዳር ጋዜጣ ጀምሮ እስከ ፊኒክስ – አሪዞና ድረስ የነበረህን ጉዞ ብትነግረን)
እንግዲህ ፈተና ሲባል ከትልቁ ነው መጀመር ያለብኝ፡፡ እኔ መጀመሪያ ያጋጠመኝ ፈተና ትልቁ ፈተና ነው፡፡ እስኪ አስበው በአንድ የክስ መዝገብ ውስጥ በስድስት የተለያዩ ክሶች መከሰስ ብቻ ሳይሆን” የእያንዳንዱ ክስ ቅጣት ደግሞ እድሜ-ልክ እና ሞት የሚያስፈርድ ሲሆን ምን አይነት ፈተና ብለህ ትጠራዋለህ? የ1997ቱን ፈተና ዱብ እዳ ከማለት ውጪ ምን ትለዋለህ፡፡ ደግሞም ከዛ በፊት ታስሬ አላውቅም፡፡ አንዳንዴ ፕሬስን የመሰለ ተቋም በአንድ አገር ሊኖረው የሚገባው ሚና እጅግ በጣም ትልቅ ቢሆንም” ይህ አይነቱ ተቋም ድምጥማጡ እንዲጠፋ የሚያደርግ ፍጹማዊ ስልጣን በጣም ጥቂት በሆኑ ግለሰቦች እጅ ውስጥ ገብቶ እንዳሻቸው ሲጫወቱበት ታያለህ፡፡ ሙያውና ሙያተኛው የሚተዳደርበት ህግን የሚያረቁት እነሱ፣ ሙያተኛም ተሰብስቦ እስር ቤት እንዲገባና በሞት እንዲቀጣ አቃቤ ህግ ሆነው የሚከራከሩት እነሱ፣ የአለም የፕሬስ ቀን በተከበረ ቁጥርም ይሁን በተለያዩ ኮንፈረንሶች ተገኝተው ‹‹የኢትዮጵያ ጋዜጠኞች ያላቸው የኤዲቶሪያል ነጻነት ለአለም ሁሉ ምሳሌና ትምህርት ይሆናል›› የሚል ስብከት የሚሰብኩትም እነሱ ናቸው፡፡ አየህ ኢንዱስትሪው ኃላፊነት እንዲሰማው ለማድረግ ሁሉንም የሚያስማማ ግልጽ የሆነ ተቋማዊ አደረጃጀትና ሁሉም በእኩል የሚስተናገዱበት ጽኑ መሰረት ያለው የህግ ማዕቀፍ ሊኖር ይገባል፡፡ አለበለዚያ ግለሰቦች እንዳሻቸው በታማኝነት አሊያም በቂም በቀል ውሳኔ የሚያስተላልፉበት፤ በየጀበና ቤቱ ማን ፍቃድ ሊነጠቅ እንደሚገባ፣ ማን መባረር እንዳለበት የሚወስኑበት አገር ነው ያለን፤ ያሳዝናል፡፡
ጥያቄውን በትክክል አልመለስክልንም?
ያው ስለውጣ-ውረድ ነው እየጠየቅከኝ ያለኸው፡፡ ከአዲስ አበባ እስከ አሪዞና ድረስ ያለውን መንገድና ውጣ-ውረድ መዘርዘር አቅቶኝ አይደለም፡፡ ከዚህ ሁሉ ውጣ-ውረድ እና እንቅፋት በስተጀርባ ያለው መነሻ ምክንያት ምን እንደሆነ ነው መታወቅ ያለበት፡፡ አውራምባ ውስጥ ዘገባዎችን ሚዛናዊ ለማድረግ ምን ያህል ርቀት ስንጓዝ እንደነበር ታውቃለህ፡፡ ያንን እያደረግን ግን የግል ጥላቻ የነበራቸው ሰዎች ነበሩ፡፡ በመንግስታዊ መዋቅር ውስጥ ያላቸው ‹‹ስልጣን›› ደግሞ የግል ጥላቻቸውን ለማራመድ ምቹ ነበር፡፡ እናም ያላቸውን ኔትወርክ ተጠቅመው ሳንወድ በግዳችን ከጨዋታው እንድንወጣ አደረጉን፡፡ ከኮሚኒኬሽን ጽህፈት ቤት እስከ ፍትህ ሚኒስቴር፤ በጉዳይ ፈጻሚነት ከሚያገለግሏቸው የግል ሬዲዮኖች፤ እስከ መንግስታዊው አዲስ ዘመን ድረስ ተረባርበው ስራቸውን ሰሩ፡፡ ከዛ ደግሞ ክራቫታቸውን አሳምረው በኪሳራ እንደዘጋነው ሊሰብኩ አለም አቀፍ ሚዲያዎች ላይ ወጡ፡፡ ስለዚህ የውጣ-ውረዱ ማጠንጠኛ እዚህ ላይ ነው ያለው፡፡
አሁን ባለህበት አገር አሜሪካ ኑሮን እንዴት እየገፋኸው ( እየመራኸው) ነው? ለመሆኑ ምግብ ታበስላለህ?
ማንም እንደሚያውቀው ተገድጄ ነው የወጣሁት፡፡ በተደጋጋሚ እንደገለጽኩት አሜሪካ የመጣሁት ከቃሊቲ ስለሚሻል ብቻ ነው፡፡ የመንግስት ደጋፊ የሆኑ ወዳጆቻችን እንደሚሉት ሰው የሚሰደደው የተሻለ ኑሮ ለመኖር ነው፡፡ እኔ ያየሁት የተሻለ ኑሮ ምን እንደሆነ አላውቅም፡፡ ከሙያዬ ውጪ ሌላ ስራ እንኳን መስራት አልፈልግም፡፡ በመንፈስ ደረጃ ስደትም ሌላ እስር ቤት ነው፡፡ እንደምታውቀው ከአገሬ የወጣሁት በ 2004 ህዳር ወር መጀመሪያ ላይ ነው፡፡ ሁኔታዎች ይሻሻላሉ በሚል ተስፋ እስከ መጋቢት ድረስ የ‹‹አሳይለም›› (የጥገኝነት) ጥያቄዬን አላቀረብኩም ነበር፡፡ በኋላ ግን የግድ የሚዲያ ስራውን ስደት ላይ ሆኜ መቀጠል ስለነበረብኝ ህጋዊ የሆነ ማዕቀፍ ውስጥ ለመግባት ‹‹አሳይለም››(ጥገኝነት) ከመጠየቅ ውጪ ሌላ አማራጭ አልነበረኝም፡፡ ስደት ካከበድከው ይከብዳል” ካቀለልከውም ይቀላል፡፡ ምግብ አበስላለሁ፡፡ አንዳንዴ ደግሞ ሲሰለቸኝ ውጭ እመገባለሁ፡፡
እንደሚታወቀው አሁን ድረ-ገፅ አቋቁመሃል፤ ስራው አንዴት ነው? (ከጋዜጣ ስራ የሚለይበት ነገርስ ምንድን ነው?)
የድረ-ገጽ ስራ ከጋዜጣ ይለያል፡፡ ጋዜጣ በሳምንት አንዴ ነው የሚታተመው፡፡ ድረ-ገጽ ግን በየሰዓቱ የሚፈጠሩ አዳዲስ ነገሮችን እየተከታተልክ ማቅረብ የግድ ይላል፡፡ ሌላ ዌብ ሳይት ቀድሞ ሳያወጣው የመጀመሪያ ለመሆን የምታደርገው ትንቅንቅ ደስ ይላል፡፡ ለምሳሌ ከዌብሳይቶች መካከል የብጹዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስን ህልፈት፤ የአቶ መለስን ዜና እረፍት (ከኢቲቪ ቀጥሎ) ቀድሞ ያወጣው ዌብሳይት አውራምባ ነው፡፡ ለምሳሌ ኦባማ በድጋሚ ተመረጡ ተብሎ በቀጥታ (ላይቭ) ሲነገር በ1 ደቂቃ ከ 15 ሴኮንድ ውስጥ ዜናውን ፖስት በማድረግ አውራምባ የመጀመሪያው ነው፡፡ የእድል ጉዳይ ሆኖ የአውራምባ ድረ-ገጽ በተመረቀ በሁለት ወር ውስጥ ነው ከፍተኛ ጎብኝ ካላቸው አንጋፋ ድረ-ገጾች መካከል አንዱ ለመሆን የበቃው፡፡ የዳያስፖራ የፖለቲካ ሙቀት ከምትገምተው በላይ ነው፡፡ ነገሮችን በኃላፊነት መንፈስ መርምረህ ገለልተኛ የሆኑ አቋሞችና አመለካከቶችን መያዝ ካልቻልክ ፈታኝ ነው፡፡ ልክ አገርቤት ‹‹በዚህ ጉዳይ ላይ መዘገብ የለብህም›› የሚሉ አምባገነኖች እንዳሉ ሁሉ፤ እዚህም በተመሳሳይ መልኩ እኛ የምንፈልገው ነገር ብቻ ነው መቅረብ ያለበት የሚሉ ‹‹የዳያስፖራ ሽመልስ ከማሎች›› አሉ፡፡ ልክ አገር ቤት ጸያፍ ስድብ የሚሳደቡ የሬዲዮ ጣቢያ ባለቤቶች እንዳሉ ሁሉ እዚህም በመልክም በተግባርም እነሱን የሚመስሉ በሌላ ጽንፍ የተሰለፉ የፓልቶክ አድሚኖች አሉ፡፡ ይገርምሀል እንዲሁ ፈርዶብን የአምባገነንነት ችግር የትም ቦታ ነው የሚያጋጥመን፡፡ እጅ ላለመስጠት ቁርጠኛ መሆን ግን ግድ ይላል፡፡
ከዲሲ ወደ ኦሪዞና ግዛት ለምን ሄድክ? (ብዙ ኢትዮጵያውያን ካሉበት መራቁ ለስራህ ጥሩ ነው?)
አዎ! ዲሲ ብዙ ኢትዮጵያዊያን አሉ፡፡ የብዙ ፖለቲከኞችና ቲፎዞዎቻቸው መፈንጫ፤ የብዙ ፍላጎቶች መናኸሪያም ነው፡፡ ብዙ ዝግጅቶች፣ በርካታ ሰላማዊ ሰልፎችና ኮንፈረንሶችም ይከናወንበታል፡፡ ይህ ማለት ግን አገር ቤት ለሚደረገው ትግል አሊያም እንዲመጣ ለምንፈልገው ፖለቲካዊ መቻቻል የሚኖረው ፋይዳ እዚህ ግባ የሚባል አይደለም፡፡ በኢትዮጵያ ፖለቲካ ውስጥ ጽንፍ የያዘ የፖለቲካ አማራጭ አሉታዊ እንጂ አዎንታዊ ውጤት የለውም፡፡ ገና ለገና ነጻነት ያለበት አገር ላይ ነው ያለነው ተብሎ የሚደረገው ልቅ የሆነ የመጠፋፋት ዘመቻ፤ ገና በዳዴ ላይ ላለው የፖለቲካ ባህላችን መራዥ የሆነ ሚና ነው የሚኖረው፡፡
ስለዚህ ከዲሲ ወደ አሪዞና የመጣሁበት ዋናው ምክንያት ከዚሁ ጋር በተያያዘ ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ እዚሁ አሪዞና ስቴት ዪኒቨርስቲ ትምህርቴን ለመቀጠል አንዳንድ የሚያስፈልጉኝን ነገሮች እያሟላሁ ነው፡፡
የዳያስፖራውን ኑሮ፣ ማህበራዊ-ህይወትና፣ ፖለቲካ እንዴት ተመለከትከው? በተለይ ፖለቲካ አራማጆቹ የፅንፈኝነት ደረጃቸውን እንዴት ትገልጸዋለህ? የዳያስፖራ ፖለቲካ ሲባል ሚዲያዎቹንም ይመለከታልና አያይዘህ ብትመልስልኝ፡-
እንደው አለመታደል ሆኖ የፖለቲካ ባህላችን ከ1960ዎቹ ጀምሮ የጽንፍ ፖለቲካ ነው፡፡ የኢህአዴግ ደጋፊዎችም ሆኑ ተቃዋሚዎች በእኩል ደረጃ ሁለት ጫፍ ይዘው ነው ሲጠዛጠዙ የምታያቸው፡፡ ፍልሚያው ደግሞ በኢህአዴግና በተቃዋሚዎች መካከል ብቻ የሚቆምም አይደለም፡፡ አንዱ ተቃዋሚ ሌላውን በወያኔነት ለመፈረጅ ያለው ጥድፊያ ብዙ መጽሐፍ ይወጣዋል፡፡ <የአንድን ሰው የፖለቲካ አቋም ለመፈረጅ ብሄሩን ጠንቅቀህ ማወቅ በቂ ነው> ባዬች ብዙ አሉ፡፡ አንዳንዴ አገር ቤት ያለው እንዴት አይነት ስልጡን ህዝብ ነው ትላለህ፡፡ ሁለቱም ወገን ጋር የምትመለከተው ‹‹እኔ ጋ ካልሆንክ ጠላቴ ነህ›› አይነት አጥፊ ድምዳሜ ነው፡፡
ሚዲያዎቹም የዚህ አይነቱ አሰላለፍ ሰለባዎች ናቸው፡፡ በተለይ እዚህ የምታየው አስቀያሚ ነገር የፖለቲካ ልዩነትን የብሄር ካባ አልብሶ ድምዳሜ ላይ ለመድረስ ያለው ሩጫ ተአምር ነው፡፡ አንድ የፖለቲካ ድርጅት ‹‹ጸባችን ከስርዓቱ ጋር ነው” ከትግራይ ህዝብ ጋ አይደለም›› ሲል ትሰማውና ትንሽ ቆይቶ ደግሞ ‹‹አጼ ዮሐንስም እኮ ለአካባቢያቸው ተወላጆች ነበር ስልጣን የሚሰጡት፤ እነ ብርሀነ መስቀልና እነ ተስፋዬ ደበሳይም ለትግራይ የበላይነት ነው ሲታገሉ የኖሩት›› ሲሉ ትሰማቸዋለህ፡፡ ይህ አይነቱ አባባል ‹‹ጸባችን ከህዝቡ ጋር ሳይሆን ከስርአቱ ጋር ነው ለሚለው ፕሮፖጋንዳ እንዴት ግብአት ሊሆን እንደሚችል ግልጽ አይሆንልህም፡፡
እንደሚገባኝ ከሆነ ይህ አይነቱ የፖለቲካ ስትራተጂ ተግባራዊ እንዲሆን የተፈለገው ‹‹ህወሃት በትጥቅ ትግሉ ወቅት ደርግና አማራ አንድ እንደሆኑ አድርጎ ይቀሰቅስ ነበር፤ እናም በዚህ መንገድ ውጤታማ መሆን ችሏል›› በሚል የተሳሳተ ስሌት ምክንያት ይመስለኛል፡፡ ይህ አይነቱ የፖለቲካ ቀመር በ2012 ተግባራዊ ለማድረግ መሞከር ግን ምንኛ ኋላ ቀር አካሄድ እንደሆነ ለመገንዘብ ዝግጁነቱ የለም፡፡ አንዳንዴ ከአንዳንድ የተቃዋሚ መሪዎች ጋር ሳወራ ‹‹የትግራይ ተወላጆች የጸረ ኢህአዴግ ትግሉን የማይቀላቀሉት ለምንድነው›› የሚል የቁጭት ጥያቄ ሲጠይቁ ይደመጣል፡፡ ነገር ግን ደግሞ እነ ስዬና እነ ገብሩ አስራት አይነት ሰዎች ወደ ተቃዋሚው ጎራ መጥተው ‹‹ተባብረን አንድ ነገር እናድርግ›› የሚል ጥያቄ ሲያቀርቡ የተቃዋሚው ምላሽ ‹‹እናንተም ያው ወያኔዎች ናችሁ›› የሚል ሆኖ ታገኘዋለህ፡፡ ‹‹ታዲያ እሺ ምን ይደረግ ስትል›› ደግሞ መልስ የለም፡፡
አሁን አቶ መለስ በህይወት የሉም፤ ወደአገርህ ለምን አትመለስም?
ችግሩ እኮ በአቶ መለስ መኖርና አለመኖር የሚፈታ አይደለም፡፡ ከሆነም እናየዋለን፡፡ አውራምባን የማዘጋቱና እኔን የማባረሩ የቤት ስራ የተሰራው ቀደም ብዬ እንደገለጽኩልህ ይህ አይነቱን ሴራ እንዲያከናውን በተመደበው ቡድን አማካኝነት ነው፡፡ ይህ ቡድን የሚያቀርበው ሪፖርት ደግሞ ከእንደኛ አይነቱ ምስኪን ዜጋ የበለጠ በአቶ መለስ ዘንድ አቅምና ተሰሚነት የነበረው ነው፡፡ አሁንም እንዳለው ይሰማኛል፡፡ ለዚሁ ተብሎ የተዋቀረ የጥፋት ቡድን ነውና፡፡
የአቶ መለስን ህልፈት ስትሰማ ምን ተሰማህ? በቀብራቸው ቀን ተገኝተው ሱዛን ራይስ ተናግረው ነበር፤ ንግግሩን እንዴት አየኸው?
በአቶ መለስ ህልፈት አዝኛለሁ፡፡ ለምን አዘንክ የሚለኝ ሰው ካለ በሱም ጭምር አዝናለሁ፡፡ አቶ በረከት ስምኦን ህልፈታቸውን በተመለከተ በይፋ ሲናገሩ ‹‹21 ዓመት ሙሉ ያለ እረፍት ሲሰሩ..ወዘተ›› ብለዋል፡፡ አዎ! በረከት ያሉት እውነት ነው፡፡ ኢትዮጵያ በአገር ቤትና በውጭ መለስን የሚተካ ሰው አጥታ አንድ ሰው እሰኪሞት ድረስ እንዲመራት ሲደረግ ያሳዝናል፡፡ አቶ መለስ ምንም ጥያቄ የለውም አዋቂ ናቸው፡፡ እንኳን አቶ መለስ አልበርት አንስታይንም 21 ዓመት ሙሉ አንድን አገር በብቃት መምራት አይችልም፡፡ አሜሪካዊያን ከስምንት አመት በላይ አንድ ሰው እንዲመራቸው የማይፈልጉት ለምንድነው? በቃ አንድ ሰው በሙሉ አቅምና ኃይል (ፓሽን) ውጤታማ (ፐሮዳክቲቭ) ሆኖ አገርን መምራት የሚችለው ለትንሽ ጊዜ ብቻ ነው፡፡ ወደ ኢህአዴግ ስንመጣ ለፖለቲካ መቻቻል በሩ ዝግ ነው፡፡ እሱ ብቻ ነው ለአገር የሚያስበው” ሌላው አገር አጥፊ ነው፡፡ ይህ የተሳሳተ የፖለቲካ ባህላችን ለጤናችን እንኳን ተገቢውን ጊዜ እንዳንሰጥ እያደረገን ነው፡፡ መለስ ብዙ ሰው አልቅሶ እንደቀበራቸው አውቃለሁ፡፡ ሁሉም ሰው ግን አልቅሶ አልቀበራቸውም፡፡ ያ ግን እንዲሆን ማድረግ ይችሉ ነበር” እድልም ነበራቸው፡፡
የሱዛን ራይስን ንግግር በተመለከተ በወቅቱ አንድ አርቲክል ጽፌ ነበር፡፡ መለስ ሱዛን ራይስ እንደገለጽዋቸው አይነት ሰው ቢሆኑ ኖሮ በሱዛን ራይስ አገር ላይ በጥገኝነት ተቀምጨ የሱዛን ራይስን ንግግር በቴሌቭዥን አልመለከተውም ነበር፡፡ መቅረጸ-ድምጼን ይዤ መስቀል አደባባይ ሆኜ ነበር የምመለከታቸው፡፡ እውነትም መለስ ‹ዓለም አቀፍ ደረጃ ያላቸው መሪ> <<ወርልድ ክላስ ሊደር›› ቢሆኑ ኖሮ እኔም እስክንድርም በቅድስት ስላሴ ካቴድራል ተገኝተን አልቅሰን እንሸኛቸው ነበር፡፡ ያ ግን አልሆነም፡፡ ለምን አልሆነም? ካልከኝ መለስ ሱዛን እንደገለጽዋቸው አይነት አይደሉማ!
አንዳንድ ወገኖች እዚሁ ሆነህ የሚከፈለውን ሁሉ መስዕዋትነት መክፈል እንደነበረብህ ይገልጻሉ፡፡ ምን ትላለህ ስለዚህ ጉዳይ?
በመጀመሪያ ጥያቄውን አታድበስብሰው! ‹‹እስካሁን ኢትዮጵያ ውስጥ ሰዎች በበቂ ሁኔታ አልታሰሩም” የእነ እስክንድር መታሰር በቂ ስላልሆነ አንተም መጨመር ነበረብህ›› ማለት ነው ጥያቄው፡፡ የኢትዮጵያ ህዝብ 80 ሚሊዮን ነው፡፡ እንደዚህ አይነት ጥያቄ የሚያነሱ ሰዎች ቀላሉን ጥያቄ ከመጠየቅ ከባዱንም ኃላፊነት ቢጋሩ መልካም ነው፡፡ ሌላው እንዲታሰር የምንጓጓውን ያህል የታሰሩትን ለማስፈታት ምን ጥረት አድርገናል ለመሆኑ? እስከ መቼ ነው ዋጋ የሚከፍሉልንን ሰዎች በመብራት እየፈለግን የምንኖረው? ሁሌ ተመሳሳይ ሰዎች ብቻ እየታሰሩ በይቅርታ እየወጡ እንደገና እየታሰሩ እንዲኖሩልን የምንፈልገውስ እስከመቼ ነው? ለእንደዚህ አይነቱ ነገር ዝግጁ ካልሆንን እንዲታሰሩ የምንፈልጋቸው ሰዎች ታስረው ነው የሚቀሩት፡፡ ለታሰሩ ሰዎች አንድ ነገር ማድረግ የማንችል ከሆነና ‹‹እከሌ ለምን ታስሮ አልቀረም›› ለማለት ከሆነ እንቅልፍ የምናጣው፤ ጭካኔአችን የሰው ልጅ ሳይሆን የእንስሳ ጭካኔ ነው፡፡
እኔ በግሌ ለእንደ ተመስገን አይነቱ አክብሮት አለኝ፡፡ ተመስገን ሁለት አመት ታስሮ በይቅርታ ቢፈታና ከዛ በኋላ ‹‹ይቅርታህ ሊነሳ ነው›› የሚል መረጃ ቢደርሰው እና አገር ጥሎ ቢወጣ ‹‹ተመስገን ለምን አልታሰረም›› ብዬ አገር ይያዝልኝ አልልም፡፡
አዲስ መፅሐፍ እየፃፍክ እንደሆነ ሰምተናል፡፡ መቼ እንጠብቀው? ምንስ ነገሮችን አካቷል?
መጽሐፉን ጽፌ የጨረስኩት ባለፈው ነሐሴ ነው፡፡ ነገር ግን ከጠ/ሚኒስትሩ ህልፈት ጋር በተያያዘ ያኔ የነበረው የፖለቲካ ድባብ መጽሀፉን ገበያ ላይ ለማዋል አስቸጋሪ ስለሆነ ከማቆየት ውጪ አማራጭ አልነበረኝም፡፡ አሁን ሁኔታዎች ስለተረጋጉ ከዛ በኋላ የተፈጠሩ አዳዲስ ነገሮችንም ጭምር አካትቼ እንደ አዲስ ለመከለስ ተገድጃለሁ፡፡ አሁን እያለቀ ነው ማለት ይቻላል፡፡ እንደ እግዚአብሄር ፍቃድ በሁለት ወር ውስጥ ይፋ ይሆናል፡፡ ይዘቱን በተመለከተ፡- አጠቃላይ ፕሬሱ ያለፈበትን ውጣ-ውረድ ከራሴ ልምድ ጋር በማዛመድ እቃኘዋለሁ፡፡ ከፕሬስ ነጻነት አንጻር የአቶ መለስ ሚና ምን እንደነበረም ትዝብቴን አሰፍራለሁ፡፡ እንዴት ከአገር እንደወጣሁ፣ የነበሩት ፈታኝ ሁኔታዎች ምን ይመስሉ እንደነበር ለማቅረብ እሞክራለሁ፡፡
ከሀገር ከወጣህ በኋላ የተጻፉ መፅሀፍትን እንዴት አየሃቸው?
እኔ ከተሰደድኩ በኋላ የወጡት መጽሐፎች የአቶ በረከት ስምኦን (በወቅቱ ሪቪው ሰርቼበታለሁ)፤ የኮ/ል መንግስቱ ኃይለማሪያምና የጋዜጠኛ ሲሳይ አጌና ከዚሁ ከዳያስፖራ፤ የተመስገን ደሳለኝና የወሰንሰገድ ገብረኪዳንን አንብቤአቸዋለሁ፡፡ ሌላ ስለ አዲስ አበባ የዝሙት ህይወት እና የመሳሰሉት ነገሮች የሚተርክ መጽሐፍ ደግሞ ‹‹የአውራምባ ታይምስ ሎጎ ተለጥፎበት ወጥቷል›› የሚል ነገር ሰምቻለሁ፤አላየሁትም፡፡ እንደዚህ አይነት ይዘት ባለው መጽሐፍ ላይ የአውራምባን ሎጎ ማስቀመጥ ለምን እንዳስፈለገ እስከ ዛሬ ድረስ አልገባኝም፡፡ እስኪ አጣራለሁ፡፡
እስቲ ደግሞ በቅርቡ ባለህበት አሜሪካ ስለተካሄደው ምርጫ ትንሽ በለን፡፡ ከአገራችን ምርጫ ጋር ስታስተያየው (ማነፃፀሩ አዳጋች ቢሆንም) እንደ ኢትዮጵያዊ ጋዜጠኝነትህ ምን ተሰማህ? በነበርክበት ኦሪዞና ግዛትስ የነበረው የምርጫ ሂደት ምን ይመስላል?
የአሜሪካ ምርጫን በደንብ ተከታትየዋለሁ፡፡ ኦባማ በድጋሚ መመረጡ ብዙ ኢትዮጵያዊያንን አስደስቷል፡፡ ሁሌም የአሜሪካ ምርጫ ስትከታተል የሚያስቀናህ ነገር በእጩዎቹ መካከል ያለው መከባበር ነው፡፡ በተለይ ውጤቱ ከታወቀ በኋላ አንዱ ለሌላው የሚያስተላልፈው የእንኳን ደስ ያለህ መግለጫ ደስ ይላል፡፡ በተለይ ሚዲያዎቹ ያላቸው ነጻነት ይገርምሀል፡፡ ‹‹ሲ ኤን ኤን›› እና ‹‹ፎክስ››ን ጨምሮ በርካታ ሚዲያዎች በራሳቸው መንገድ የተለያዩ መረጃዎችን መሰረት አድርገው ማን እንዳሸነፈ አስቀድመው ይፋ ያደርጋሉ፡፡ እኛ አገር ግን ምርጫ ቦርድ ይፋ ከማድረጉ በፊት እንዲህ አይነቱን የሚዲያ ትንበያ ይፋ ማድረግ አይፈቀድም፡፡ በእርግጥ በአገራችን እንዲህ አይነቱን ትንበያ ለመስራት የቴክኖሎጂ እጥረትና የአቅም ውሱንነት ቢኖርም በጊዜ ሂደት ግን የማይቻልበት ምክንያት የለም፡፡ በአዋጅ መከልከሉ ግን ተገቢ አይደለም፡፡ እኔ ያለሁበት አሪዞና ‹‹ሬድ ስቴት›› ነው፡፡ ማለትም ሪፐብሊካኖች ናቸው ሁሌ የሚያሸንፉት፡፡ ለምሳሌ ከአራት አመት በፊት ከኦባማ ጋር የቀረቡት ጆ ማኬይን የዚህ አካባቢ ሰው ናቸው፡፡
አዲሱ የአቶ ኃ/ማርያም አስተዳደር በፕሬስ ጉዳዮች ላይ ለውጥ ያመጣል ብለህ ትጠብቃለህ?
እኔ ሁሌም ተስፈኛ ነኝ፡፡ አቶ ኃይለማሪያም እዚህ ለተባበሩት መንግስታት ስብሰባ የመጡ ጊዜ ለእንግሊዝኛው ቪ ኦ ኤ የሰጡትን ቃለምልልስ ሰምቼዋለሁ፡፡ ፓርላማም ላይ የተናገሩት ነገር ተመሳሳይ ነው፡፡ ትንሽ ራሳቸውን መሆን የቻሉ አይመስለኝም፡፡ ፓርላማ ላይ ከእጅ እንቅስቃሴያቸው ጀምሮ አነጋገራቸው፣ በምላሾቻቸው ላይ የሰነዘሯቸው ማስጠንቀቂያዎችና ዘለፋዎች ተገቢ ናቸው ብዬ አላምንም፡፡ እንደዛም ሆኖ ግን ተስፈኛ ነኝ፡፡ ከ38 ዓመት በኋላ እምነት ያለው ሰው ወደ መሪነት ቦታ መምጣቱ ትልቅ ነገር ነው፡፡ እግዚአብሄር ይርዳቸው!
ከኢትዮጵያ በመሰደድህ ምን ያጣኸው ነገር አለ? (የሚቆጭህ፣ የሚናፍቅህ፣ የሚፀፅትህ ነገር አለ?)
ቀደም ብዬ እንደገለጽኩት ስደት ላይ ስትሆን ቁጭት፣ ናፍቆትና ጸጸት ሁሌም ይኖራል፡፡ እኔ ማድረግ የምችለውን ሁሉ አድርጌአለሁ፡፡ ባልወጣና ባልሰደድ ደስ ይለኝ ነበር፡፡ ግን ምን ታረገዋለህ” ከዚህ በፊት እንደገለጽኩት ህይወት መቀጠል አለበት፡፡
የባልደረባህ የጋዜጠኛ ውብሸት ታዬ ከስዊድን ጋዜጠኞች ጋር በይቅርታ ያለመፈታት ጉዳይን እንዴት አየኸው?
የውብሸት ጉዳይ ብሄራዊ ክብርን የሚፈታተን ነገር ነው፡፡ ከስዊድኖቹ ጋር እንደሚፈታ ሙሉ እምነት ነበረኝ፡፡ እኩል ነው የይቅርታ ሰነዱን የፈረመው፡፡ በዚህ ጉዳይ ላይ ከፕ/ር ኤፍሬም ይስሐቅ ጋር ተነጋግሬአለሁ፡፡ አጥጋቢ ምላሽ አልሰጡኝም እንጂ፡፡ አለም አቀፉ ሚዲያ የሚጮኸው ለስዊድኖቹ ስለነበር የኢትዮጵያ የይቅርታ ህግ ከኢትዮጵያዊያን ይልቅ የውጭ ዜጎችን ተጠቃሚ ሊያደርግ ግድ ነበር፡፡ ትንሽ ግራ የሚያጋባው ውብሸትም ስዊድናዊያኑም ሲታሰሩ አቶ መለስ የነጭ እና የጥቁር ደም እኩል ነው ብለው ነበር በፓርላማ፡፡ ተመርጠው ሲፈቱ ግን እኩል እንዳልሆነ አረጋግጠናል፡፡ ለዚህም ነው ስዊድኖቹ በተፈቱ በማግስቱ ‹‹አድሏዊውና አሳፋሪው ይቅርታ›› ብዬ አርቲክል ለመጻፍ የተገደድኩት፡፡ ለነገሩ ውብሸት የተበደለው ባሰሩት ሰዎች ብቻ አይደለም፡፡ ምክንያቱ ግልጽ ባይሆንልኝም አገር ቤትም ውጭም ያለው ሚዲያ ሆን ብሎ ረስቶታል፡፡ ከታሰረበት ጉዳይ ቀጥተኛ የሆነ ትስስር አላቸው የሚባሉ ዌብሳይቶች እንኳን አንድ ነገር ትንፍሽ ለማለት አልፈቀዱም፡፡ በሌላ በኩል አገር ቤት ያሉ ሚዲያዎችም እንደዛው፡፡ አንድ የሚዲያ ተቋም የራሱን ባልደረባ ብቻ እየመረጠ ማግዘፍና ማጀገን የለበትም፡፡ እስርቤት ስለነበርኩ የሚዲያ ሽፋን ስታገኝና ሳታገኝ የሚሰማህ ብርታት እኩል እንዳልሆነ አውቀዋለሁ፡፡
በቅርቡ የተካፈልክበት ስብሰባ በ (National Endowment for Democracy) የተዘጋጀው ላይ ፅሁፍ አቅርበህ ነበር? ስለስብሰባው ምንነትና ዓላማ ብታብራራልን?
ናሽናል ኢንዶውመንት ፎር ዴሞክራሲ እዚህ ዋሽንግተን ዲሲ የሚገኝ የአሜሪካዊያን አለም አቀፍ የጥናትና ምርምር ተቋም ነው፡፡ የፌሎውሽፕ ፕሮግራምም ይሰጣል፡፡ እንደምታወቀው ወ/ሪት ብርቱካን ለአንድ አመት ገደማ የቆየችው በዚሁ ተቋም ውስጥ ነው፡፡ ይህ ተቋም ባለፈው ጥቅምት “Toward a Democratic Ethiopia” በሚል ርዕስ የኢትዮጵያ ዴሞክራሲ በምን ሁኔታ ላይ ይገኛል የሚል አለምአቀፍ ኮንፈረንስ አካሂዶ ነበር፡፡
ውይይቱ በሦስት ፓነል የተከፋፈለ ነው፡- የመጀመሪያው የፕሬስ ነጻነትና የሲቪክ ድርጅቶች እንቅስቃሴ እንዲሁም ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የወጡት አዋጆች ምን ተጽእኖ አላቸው በሚል ርዕስ የቀረበ ነው፡፡ እኔ (በፕሬስ ነጻነት)፣ ወ/ሮ ማህደር ጳውሎስ (በሲቪክ ድርጅቶች) እንዲሁም የሂዩማን ራይትስ ዎች የዋሺንግተን ዲሲ ተጠሪ ሳራ ሞርጋን (በአዋጆቹ ዙሪያ) ጥናታዊ ጽሁፎቻችንን አቅርበናል፡፡ ቀጥሎ ደግሞ የአሜሪካ መንግስት በኢትዮጵያ ላይ የሚከተለው ፖሊሲ ምን እንደሚመስል አምባሳደር ዴቪድ ሺን እና ፕ/ር ቴሬንስ ሊዮንስ በመጨረሻ ደግሞ የስቴት ዲፓርትመት አሲስታንት ሴክሬታሪ እንዲሁም ሌላው የዩኤስ ኮንግረስ ተወካይ በተከታታይ ጽሁፎቻቸውን አቅርበዋል፡፡ ከኛ ከጽሁፍ አቅራቢዎቹ ውጪ በዚሁ ስብሰባ ላይ አቶ ስዬ አብርሀ፣ አቶ ገብሩ አስራት፣ ዶ/ር መረራ ጉዲና እንዲሁም በዋሺንግተን ዲ.ሲ የኢትዮጵያ ኤምባሲ ተወካይ የስብሰባው ታዳሚዎች ሆነው ፕሮግራሙን ተከታትለዋል፡፡
አንተ ያቀረብከው ይዘቱ ምን ይመስላል፤ የኤምባሲው ተወካይስ ማን ናቸው? ምንስ አሉ?
እኔ ያቀረብኩት አጠቃላይ ሚዲያው አሁን ያለበትን ሁኔታ የሚያሳይ ነው፡፡ ፕሬዚዳንት ኦባማ ከስብሰባው ከሁለት ሳምንት በፊት በተባበሩት መንግስታት ስብሰባ ላይ ተገኝተው የመናገር ነጻነትን በተመለከተ በጣም ድንቅ የሆነ ንግግር አድርገው ነበር፡፡ እኔ ለንግግሬ መነሻ ያደረኩት ኦባማ ያደረጉትን ንግግር በማስታወስ ነው፡፡ ኦባማ ያሉት ‹‹ሰዎች በሚያራምዱት አመለካከት ምክንያት እስር ቤት መግባት የለባቸውም፡፡ እዚህ አሜሪካ በርካታ ፕሬሶች እኔን ሲያብጠለጥሉ ይውላሉ፡፡ እኔ የአሜሪካ ፕሬዚደንትና የጦር ኃይሎች ጠቅላይ አዛዥ ነኝ ብዬ ግን ምንም የማረገው ነገር የለም፡፡ እንደውም በህገ መንግስታችን የተረጋገጠውን መብት ተግባራዊ በማድረጋቸው ይበልጥ ደስ ነው የሚለኝ›› ነበር ያሉት ኦባማ፡፡ ይህንን መነሻ አድርጌ የእስክንድርን፣ የርዕዮትንና የውብሸትን ሁኔታ በንጽጽር ለማስቀመጥ ሞክሬአለሁ፡፡ ያው አምባሳደር ዴቪድ ሼን ሁሌም …ዴሞክራሲ እኮ ሂደት ነው ምናምን የሚሉት ነገር አለ…እኔ ደግሞ ‹‹አምባሳደር ዴቪድ ሺን፣ እርስዎ በኢትዮጵያ የአሜሪካ አምባሳደር እያሉ ስንት ጋዜጦች ነበሩ? አሁንስ ስንት አሉ? ሂደት ማለት ይሄ ነው? ሂደት ማለት እንደዚህ ከሆነ፤ ወደተሳሳተ አቅጣጫ የሚወስድ ሂደት ላይ ነው ያለነው፤ ‹‹እኤአ እዚሁ በዋሺንግተን ዲሲ ተገናኝተን ስናወራ ቢያንስ እኮ እነ አውራምባ ይታተማሉ ብለው ተከራክረውኝ ነበር፤ ዛሬ ግን እነ አውራምባም አይታተሙም፡፡ ይኼ ነው ሂደት? ባለፈው አመት የእርስዎ ዌብሳይት ሳይቀር ኢትዮጵያ ውስጥ እንደተዘጋ ነግረውኝ ነበር” እንዴት ነው ይህንን ማስታረቅ የሚቻለው?›› አልኳቸው፡፡ በጣም የሚያስቀው ነገር ዌብሳይታቸው ኢትዮጵያ ውስጥ ተዘግቶ እንደነበረና ከአቶ ኃይለማሪያም ጋር ተነጋግረው እንዳስከፈቱት ነገሩኝ፡፡ ከኢትዮጵያ ኢምባሲ አቶ ዋሕድ በላይ ናቸው የተገኙት፡፡ አጋጣሚ የእኔ ጽሁፍ ቀርቦ ቤቱ ለጥያቄና መልስ ክፍት ሲሆን አቶ ዋሕድ ተነስተው የኔ ጽሁፍ የደርግ አመለካከት እንደሚንጸባረቅበት ተናገሩ፡፡ እኔ ደግሞ ኢህአዴግ አዲስ አበባ ሲገባ የዘጠኝ አመት ልጅ እንደነበርኩ ተናግሬ በአዳራሹ የነበሩ ታዳሚዎችን ትንሽ ፈገግ አሰኘኋቸው፡፡ በነገራችን ላይ ከዛ በኋላ ከአቶ ዋህድ ጋር አድራሻ ተለዋውጠን ኢንተርቪው ሁሉ እንደሚሰጡኝ ቃል ገብተውልኛል፡፡
አገሬ መጥቼ ተወዳጇን አውራምባ ታይምስ ጋዜጣ ዳግም አሳትማለሁ ብለህ ታስባለህ?
ተስፋ አደርጋለሁ፡፡ ሌላው ቢቀር ቢያንስ ዌብሳይቴን ኢትዮጵያ ሆኜ ብሰራው እንዴት ደስ ይለኛል መሰለህ፡፡ ግን በጣም የሚያሳዝነው ነገር እንደዛ አይነት ሆደ ሰፊነት ኢህአዴግ ጋ የለም፡፡ ይገርምሃል ዌብሳይቱ የተመረቀው ሜይ 05/2012 እንግዶች በተገኙበት በዋሺንግተን ዲ.ሲ ነው፡፡ በተጠቀሰው ቀን ተመርቆ በማግስቱ ግን ኢትዮጵያ ውስጥ ተዘግቷል፡፡ ‹‹አውራምባ ታይምስ በኪሳራ ነው የተዘጋው፤ እኛ ጫና አላሳደርንም›› ያሉት ኃላፊዎች የአውራምባ ዌብሳይትን ግን ከ24 ሰዓታት በላይ ሊታገሱት አልፈቀዱም፡፡ ቢያንስ ይዘቱ ምን ይመስላል? ተብሎ እንኳን ዳሰሳ ለማድረግ አይሞከርም? እና እንዲህ እንዲህ አይነቱን ስመለከት ትንሽ ተስፋዬን ያደበዝዘዋል፡፡ ግን ይሁን እስኪ…………..

Sunday, December 9, 2012

በእነ አንዷለም አራጌ የክስ መዝገብ የንብረት ውርስ ላይ ትእዛዝ ተሰጠ
ህዳር ፳፱ (ሃያ ዘጠኝ) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም
ኢሳት ዜና:-ከፍተኛው ፍርድ ቤት በ1ኛ ተከሳሽ በአቶ አንዷለም አራጌ ባለቤት ስም የተመዘገበው የቤት መኪና ፤ በ7ኛ ተከሳሽ አቶ እስክንድር ነጋ ስም የተመዘገበ 1 ቤትና ከእናታቸው በውርስ ያገኙት ተዳምሮ 2 መኖሪያ ቤቶች እና በባለቤታቸው ስም የተመዘገበ 1 የቤት መኪና ፤ እንዲሁም በሌሉበት በተከሰሱት በ16ኛ ተከሳሽ በአቶ አበበ በለው ባለቤት ስም ፥ የተመዘገበ መኖሪያ ቤት ላይ የቀረበውን የውርስ አቤቱታ ያደመጠ ሲሆን አቶ አንዱአለም ባለቤት በጠበቃቸው አማካኝነት መኪናዋ ልጆችን ትምህርት ቤት የምታመላልስ መሆኗን ጠቅሰዋል። የጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ ባለቤት ወ/ሮ ሰርካለም ፋሲል ችሎት ቀርበው እንዳማይከራከሩ በችሎቱ ላይ ተገልጿል።
የ አቶ አበበ በለው ባለቤትም ችሎት ስላልቀረቡ ለታህሳስ 18 መጥሪያ ደርሷቸው ችሎት እንዲገኙ ትዕዛዝ ሰጥቷል።
የፌዴራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት 4ኛ የወንጀል ችሎት ለታህሳስ 18 ቀን 2005 ዓ.ም ተለዋጭ ቀጠሮ መያዙ ታውቋል
በእነ አንዷለም አራጌ የክስ መዝገብ የንብረት ውርስ ላይ ትእዛዝ ተሰጠ
ህዳር ፳፱ (ሃያ ዘጠኝ) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም
ኢሳት ዜና:-ከፍተኛው ፍርድ ቤት በ1ኛ ተከሳሽ በአቶ አንዷለም አራጌ ባለቤት ስም የተመዘገበው የቤት መኪና ፤ በ7ኛ ተከሳሽ አቶ እስክንድር ነጋ ስም የተመዘገበ 1 ቤትና ከእናታቸው በውርስ ያገኙት ተዳምሮ 2 መኖሪያ ቤቶች እና በባለቤታቸው ስም የተመዘገበ 1 የቤት መኪና ፤ እንዲሁም በሌሉበት በተከሰሱት በ16ኛ ተከሳሽ በአቶ አበበ በለው ባለቤት ስም ፥ የተመዘገበ መኖሪያ ቤት ላይ የቀረበውን የውርስ አቤቱታ ያደመጠ ሲሆን አቶ አንዱአለም ባለቤት በጠበቃቸው አማካኝነት መኪናዋ ልጆችን ትምህርት ቤት የምታመላልስ መሆኗን ጠቅሰዋል። የጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ ባለቤት ወ/ሮ ሰርካለም ፋሲል ችሎት ቀርበው እንዳማይከራከሩ በችሎቱ ላይ ተገልጿል።
የ አቶ አበበ በለው ባለቤትም ችሎት ስላልቀረቡ ለታህሳስ 18 መጥሪያ ደርሷቸው ችሎት እንዲገኙ ትዕዛዝ ሰጥቷል።
የፌዴራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት 4ኛ የወንጀል ችሎት ለታህሳስ 18 ቀን 2005 ዓ.ም ተለዋጭ ቀጠሮ መያዙ ታውቋል

የወያኔ ፌደራል ፖሊስ በዩኒ ቨርሲቲው ቅጥር ግቢ በመግባት የጅማ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎችን ደበደበ

በጂማ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ላነሷቸው የመብት ጥያቄዎች እንደተለመደው የጨካኙ ወያኔ አገዛዝ ፌድረአል ፖሊሶች ዩኒቨርሲቲው ቅጥር ግቢ ድረስ በመግባት ለቀረቡት ጥያቄዎች ምላሽ ተማሪዎች በቆመጥ መደብደባቸዉን በዩኒቨርሲቲው ውስጥ የሚገኝ ምንጮችን በመጥቀስ የግንቦት ሰባት ዘጋቢ በላከልን ዜና አመለከተ። የጂማ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ጥያቄዎቻችን ይመለስልን በሚል ለዩኒቨርሲቲው አስተዳደር ጥያቄ ያቀረቡ ቢሆንም ለጥያቄአቸው ተገቢ ምላሽ ሳይሆን የ ጠበቃቸው የወያኔ ፈደራል ፖሊሶች ዱላ መሆኑን ዘጋቢያችን አክሎ ገልጿል። ተማሪዎቹ በዋናነት ካነሷቸው ጥያቄዎች በዋነኛነት የምንማረው ትምህርት ጥራት በጣም የወረደና ደረጃንም ያልጠበቀ በመሆኑ ሊስተካከል ይገ ባል፡ የሚል እንደሆነ የደረሰን ዘገባ ያመለክታል።
በዚሁና ተያያዥ በሆኑ የመብት ጥያቄዎች ምክንያት የወያኔ ፌደራል ፖሊሶች ዩኒ ቨርሲቲው ግቢ ውስጥ ገብተው ተማሪዎችን ደብድበዋል፣ መስኮቶችም ተሰባብረዋል፡፡ ከዚሁ የወያኔ አገዛዝ መረን የለቀቀ ተግባር ጋር በተያያዘ ተማሪዎችም ቁጣቸው እየጨመረ መሄዱ የታወቀ ሲሆን በተመሳሳይ መልኩ ይህ ጥያቄ በወልቂጤና ነቀምት ዩኒ ቨርሲቲዎች በመቀጣተል ላይ መሆኑን ዘጋቢያችን ገልጿል።
ከዚሁ ዘገባ ጋር በተያያዘ ዓንድ ስሙ እንዳይገለጽ የጠየቀ የዩኒቨርሲቲው ተማሪ ለዘጋቢያችን እንደገለጸው ወያኔ በ2004 ዓ.ም ባካሄደው የዩኒቨርሲቲዎች ጉባኤ ላይ ጅማ ዩኒቨርሲቲ በትምህርት ጥራት አንደኛ ደረጃ ላይ ይገ ኛል በሚል እንዲመረጥ አድርጎ የነበረ ሲሆን በትምህርት ጥራት አንደኛ ተብሎ ተመረጠ ዩኒቨርሲቲ ላይ ይህ ጥያቄ መነ ሳቱ ችግሩ ምን ያህል ስር የሰደደ እንደሆነ እና የ ወያኔ ድራማ ምን ያህል እየ ተጋለጠ ለመሆኑ ታላቅ ማሳያ ነ ው፡ በማለት አስተያየቱን ሰጥቷል።
ዘረኛው የወያኔ አገዛዝ በአንዳን ዩኒቨርሲቲዎች አንድም የቤተ መጽሃፍና የላብራቶር አገልግሎት ሳይኖራቸው ተማሪዎች ገብተውና ምንም እውቀትን ሳይቀስሙ እንዲመረቁ በማድረግ ተግባር ላይ ተጠምዶ እንደሚገኝ ቀደም ብሎ መዘገቡ ይታወሳል።
ዘረኛው የወያኔ አገዛዝ በኢትዮጵያዊያን ላይ እያደረሰ ያለው ግፍና በደል መጠኑን ካለፈ እጂግ በርካታ ዓመታት ያለፉ ሲሆን፣ በተለይም ባሁኑ ወቅት ኢትዮጵያ ውስጥ በድንገት ምን ሊፈጠር እንደሚችል መገመት የሚያዳግት ሁኔታ ላይ እንደሚገኝ ዘገባዎች እያመለከቱ ነው። የኢትዮጵያ ሳተላይት ቴሌቪዥን ኢሳት ከታዋቂው የኢኮኖሚክ ባለሙያ ፕ/ር በፈቃዱ ደግፌ ባደረገው ቃለምልልስ የወያኔ አገዛዝ የህዝብን ብሶት አልሰማ በማለቱ አንድ ቀን ያልጠበቀው አደገኛ ሁኔታ ሊፈጠርበት እንደሚችል ማስጠንቀቃቸው ታውቋል። ዶር በፈቃዱ በቃለ ምልልሳቸው “ህዝቡ የሚሄድበት ቦታ አጥቷል፣ ብሶታል” ያሉ ሲሆን ከአረብ አብዮት የምንማረው ህዝብ መሪ ሳያስፈልገው በብሶቱ ብቻ ሆ ብሎ ሊነሳ የሚችል መሆኑን ነው ሲሉ ገልጸዋል። ፕ/ር በፈቃዱ ደግፌ በቃለ ምልልሳቸው ባሁኑ ሰአት የኢትዮጵያ ባለቤት የኢትዮጵያ ህዝብ ሳይሆን ወያኔ ኢህአዴግ ነው ያሉ ሲሆን በኢትዮጵያ ውስጥ ያለሙስና ስራ መስራት እንደማይቻል ገልጸዋል።