Monday, January 28, 2013

ኢትዮጵያ በወታደራዊ እንቅስቃሴዎች እየታመሰች ነዉ::
ኢትዮጵያ ዉስጥ ዳር አገርም ሆነ መሀል አገር በየቦታዉ የሚታየዉ ወታደራዊ እንቀስቃሴ ከቀን ወደ ቀን እየጨመረ መምጣቱን አዲስ አበባና በየክልሉ የሚገኙ ወታደራዊ ምንጮቻችን ገለጹ። በተለይ የመለስ ዜናዊ ሞት ለህዝብ ይፋ ከሆነበት ግዜ ጀምሮ ኢትዮጵያ ከደርግ ዘመን ወዲህ ታይቶ በማይታወቅ ከፍተኛ ወታደራዊ እንቅስቃሴ እየታመሰች መሆኗን በየክልሉ የሚገኙ ዘጋቢዎቻችን የመከላከያ ምንጮችን ዋቢ በማድረግ የላኩልን ዜና ያስረዳል።
ከሁለት ሳምንት በፊት ከ35 በላይ ታንኮችን የጫኑ ከባድ ተሽከርካሪዎች ወደ ምስራቅ የአገሪቱ ክፍል የተጓዙ ሲሆን፣ ከአራት ቀን በፊት ደግሞ ከ30 ያላነሱ ታንኮች በከባድ ተሽከርካሪዎች ተጭነዉ ወደ ሰሜናዊዉ የአገራችን ክፍል ተጉዘዋል። ጠብ አጫሪዉ የወያኔ አገዛዝ የጦር መሳሪያዎችን ለምን በዚህ አይነት ፍጥነትና ብዛት እንደሚያንቀሳቅስ በትክክል ለማወቅ ባይቻልም በብዙ ምዕራባዉያንና የአገር ዉስጥ ወታደራዊ ጠበብቶች ግምት አገሪቱ ውስጥ በየክልሉ በሁሉም መስክ የሚታየው ህዝባዊ አመጽና አለመረጋጋት ወያኔን ክፉኛ ስላስደነገጠዉ ህዝባዊ እንቅስቃሴዉን በወታደራዊ ሀይል ለመቆጣጠር የታለመ ሊሆን ይችላል ተብሎ ይታናል። በሌላ በኩል ደግሞ የተለያዩ ስርዐቱን በትጥቅ ትግል የሚፋለሙ ሀይሎች በተለይ በቅርቡ የተቋቋመዉ እራሱን “የግንቦት ሰባት ሀይል” ብሎ የሚጠራዉ የተለያዩ ሀይሎች ስብስብ ወያኔን ክፉኛ እንዳስደነገጠዉ ብዙ ለአገዛዙ ቅርበት ያለቸዉ ምንጮች በመናገር ላይ ናቸዉ።

No comments: