ከፕሮፌሰር አለማየሁ ገብረማርያም
ትርጉም በነጻነት ለሀገሬ
በኢትዮጵያ የሰብአዊ መብት ወንጀል ፍፃሜ መሪ ተዋንያን ሆነው ከቆዩ በኋላበመሰደድ በአሜሪካ እራሳቸውን ደብቀው በተቀመጡ የሰብአዊ መብትደፍጣጮች ላይ የዩናይትድ ስቴትስ አሜሪካ የፍትህ መምሪያ ጥቆማእንዲቀርብለት ኢትዮጵያውያንን/ትን በማበረታታት ላይ ይገኛል፡፡
እነዚህ በሰው ልጆች ላይ ወንጀልን የፈጸሙ ጨካኞች በሰው አገር ሄደው ተደብቀዋል፡፡ እነዚህ ወንጀለኞች በዩናይትድ ስቴትስ አሜሪካ በበማታለል ገብተው ለ30 ዓመታት ተደብቀዋል፡፡ እነዚህ በሰው ደም የተዘፈቁ ወንጀለኞች በቀላሉ ሊያዙ በሚችሉበት አገር በመሄድ ለድፍን ሶስት ዓመታት የተደበቁም አሉ ፡፡
እነዚህ የሰብአዊ መብት ደፍጣጭ ወንጀለኞች ከኒዮርክ እስከ ሎስአንጀለስ ባሉ ታላላቅ ከተሞች እራሳቸውን ደብቀው ሲንቀሳቀሱ ቆይተዋል፡፡ እነዚህ የፉኝት ዘሮች ማንም አይነካንም በሚል የእብሪት ስሜት ህዝብ በሚሰበሰብባቸው የአደባባይ ቦታዎች እና በእምነት ተቋማት ሳይቀር ደረታቸውን ገልብጠው ይንፈላሰሳሉ፡፡ በየቡና ቤቶች እና ምግብ ቤቶች ሲወጡ ሲገቡ ይውላሉ፡፡ በጎዳናና በመንደር መንገድ ላይ ይንፏቀቃሉ፡፡ የተማሩም አሉባቸው ያልተማሩም አሉባቸው፡፡ በስልጣን ላይ በነበሩባቸው ጊዚያት የዘረፏቸውን ገንዘቦች በውጭ ባንኮች አጭቀዋል፡፡ በዩናይትድ ስቴትስ አሜሪካ የንግድ ተቋማትን በማንቀሳቀስ ንብረት አፍርተዋል፡፡ ሌሎቹም ኑሯቸውን ለመምራት እና ዓላማዎቻቸውን ለማሳካት የአገልግሎት ሰራተኞች ሆነው ህይወትን በችግር መግፋት ላይ ይገኛሉ፡፡ ከንጹሀን የግፍ ሰለባዎች ጋር የሞት ዋስትና ተፈራርመዋል፡፡ ንጹሀን ዜጎችን ጨፍጭፈዋል፣ አስጨፍጭፈዋል፣ ረሽነዋል፣ አስረሽነዋል፣ ገድለዋል፣ አስገድለዋል፣ ፈጅተዋል፣ አስፈጅተዋል፡፡
በምርመራ ላለመያዝ የሀሰት ስሞችን በመቀያየር ማንነታቸውን በመደበቅ ሲንገዋለሉ እና ሲንከላወሱ ይውላሉ፡፡ ሲገርፏቸው እና ሲያሰቃዩአቸው በነበሩት የወንጀል ሰለባዎቻቸው እና መብቶቻቸውን በተደፈጠጡት ወገኖች በውል ይታወቃሉ፣ ሆኖም ግን እነዚህ የግፍ ሰለባዎች እነዚህን ጨካኝ አረመኔ ወንጀለኞች ለዩናይትድ ስቴትስ አሜሪካ የፍትህ አካላት በምን ዓይነት መንገድ ለህግ እንደሚያቀርቧቸው አያውቁም፡፡ የግፍ ሰለባዎቹ እነዚህን ሲያሰቃዩአቸው የነበሩትን ወንጀለኞች በየቀኑ ባዩ ቁጥር የቅዥት ህይወትን በመምራት ላይ ሲሆኑ በሌላ በኩል ደግሞ ግድያ፣ ማሰቃየት፣ እና ሌሎች በሰው ልጆች ላይ ወንጀል የፈጸሙ ግፈኞች በእነርሱ የእውቀት ደረጃ ምንም የሚመጣብን ነገር የለም በሚል ትዕቢት በመታበይ በሰላም እና ደህንነታቸው ተጠብቆ እንደሚኖሩ እምነት አድርገዋል፡፡
እነዚህ ግፈኛ አረመኔዎች የሰው ልጆችን ሰብአዊ መብቶች የደፈጠጡ እና በአሁኑ ጊዜ በዩናይትድ ስቴትስ አሜሪካ እራሳቸውን ደብቀው የሚገኙ የቀድሞው የኢትዮጵያ የደርግ ወታደራዊ አምባገነን መንግስት ከፍተኛ እና ዝቅተኛ ባለስልጣናት ናቸው፡፡
እነዚህ ግፈኛ አረመኔዎች የሰው ልጆችን ሰብአዊ መብቶች የደፈጠጡ እና በአሁኑ ጊዜ በዩናይትድ ስቴትስ አሜሪካ እራሳቸውን ደብቀው የሚገኙ የህዝባዊ ወያኔ ሐርነት ትግራይ (ህወሐት) እና እራሱ ቀፍቅፎ የፈጠረው የይስሙላው እራሱን “የኢትዮጵያ ህዝቦች አብዮታዊ ዴሚክራሲያዊ ግንባር” እያለ የሚጠራው ቡድን ከፍተኛ እና ዝቅተኛ ባለስልጣናት ናቸው፡፡
እነዚህ የሰብአዊ መብት ደፍጣጮች በለመደው አጭበርባሪ አንደበታቸው የአሜሪካንን የጥገኝነት እና ዜግነት መስሪያ ቤት ተቋም ስርዓትን በማታለል የአሜሪካንን የኗሪነት ወይም የዜግነት ፈቃድ ያገኙ ናቸው፡፡
እነዚህ ወንጀለኞች የገዳይ እና አስገዳይነት ወንጀላቸው ተረስቶ ምንም ነገር እንደማያመጣባቸው በማሰብ በዩናይትድ ስቴትስ አሜሪካ በምቾት እና በተድላ መኖር እንደሚችሉ እምነት አላቸው፡፡
እነዚህግፈኞችለአሜሪካፍርድቤቶችለፍትህለፍርድ መቅረብአለባቸው!
እነዚህ በአሜሪካ አገር እራሳቸውን ደብቀው የሚገኙ በሰው ልጆች ላይ ወንጀልን የፈጸሙ የኢትዮጵያ ግፈኞች አንዳንድ ጊዜ ወንጀል ከፈጸሙባቸው የግፍ ሰለባዎቻቸው ጋር በአጋጣሚ ይገናኛሉ፡፡ እ.ኤ.አ ሜይ 2011 ከፈለኝ ዓለሙ ወርቁ (ተለዋዋጭ ስም የሚጠቀም ፣ ሀብታብ በርሄ ተማኑ፣ “ቱፋ“፣ ከፈለኝ ዓለሙ) የተባለው ጨፍጫፊ ወንጀለኛ ኢትዮጵያ በነበረበት ወቅት ሲያሰቃያቸው ከነበሩት የግፍ ሰለባዎች መካከል ከአንደኛው ጋር ዴንቨር ኮሎራዶ ከተማ ፊት ለፊት ተገናኙ፡፡ ከፈለኝ ወርቁ እ.ኤ.አ በጁላይ 2004 ሀብታብ በርሄ ተማኑ በሚል የሀሰት መታወቂያ በመጠቀም ነው ስደተኛ በመምሰል ወደ አሜሪካ የገባው፡፡ እ.ኤ.አ በ1970ዎቹ መጨረሻ አካባቢ እራሱን “ደርግ“ እያለ የሚጠራ ጨካኝ አረመኔ ወታደራዊ አምባገነን መንግስት በኢትዮጵያ ከህግ አግባብ ውጭ ንጹሀን ዜጎችን የሚገድል እና በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎችን የሚያሰቃይ “ቀይ ሽብር” የተባለ ዘመቻ አወጀ፡፡ በዚያን ጊዜ ከፈለኝ ዓለሙ ወርቁ የእስር ቤት የጥበቃ አባል ነበር፡፡ እ.ኤ.አ በ1978 ሳሙኤል ከተማ የተባሉ የፖለቲካ እስረኛ አብረዋቸው የነበሩትን እስረኞች ይህ ወርቁ የተባለ ጨፍጫፊ ሲያሰቃይ እና ሲገድል የነበረ መሆኑን የምስክርነት ቃላቸውን ሰጥተዋል፡፡ እ.ኤ.አ በ1977 አበበች ደምሴ የምትባል የ16 ዓመት የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማሪ የነበረች እስረኛ “ወርቁ እየተኮሰ ሰዎች ገና አካለ መጠን ያልደረሰ ልጅን ጨምሮ ሲገድል አይቻለሁ“ የሚል የምስክርነት ቃላቸውን ሰጥተዋል፡፡ ወርቁ “በወለሉ ላይ የፈሰሰውን የሟቾቹን ደም በተገኘው ሁሉ በምላሳችንም ጭምር እንድናጸዳው“ ለሌሎቻችን እስረኞች ትዕዛዝ ሰጥቷል ብለዋል፡፡ ወርቁ በአበበች ጭንቅላት ላይም ኤኬ – 47 አውቶማቲክ ጠብመንጃ አነጣጥሮ የነበረ ቢሆንም በእግዚአብሔር ታምር ህይወታቸው የተረፈ መሆኑን ገልጸዋል፡፡
እንደ ፍርደ ቤቶች ዘገባ ከሆነ እ.ኤ.አ በ2013 ወርቁ በህገወጥ መልክ ዜግነትን በመግዛት ወይም በማግኘት፣ ማንነትን በመደበቅ ወንጀል፣ በማጭበርበር እና ህገወጥ ቪዛ በመውሰድ እና በመጠቀም፣ እንዲሁም ሌሎች የተጭበረበሩ ሰነዶችን በማቅረብ የሚሉ የተለያዩ ክሶች ቀርበውበታል፡፡ በዩናይትድ ስቴትስ የወረዳ ፍርድ በ5 ቀናት የፍርድ ቀጠሮ ሂደት እ.ኤ.አ ሜይ 23/2014 በዋለው ችሎት ወርቁ በሁሉም ክሶችጥፋተኛ ሆኖ በመገኘቱ በ22 ዓመታት እስር እንዲቀጣ ተበይኖበታል፡፡ በአጠቃላይ ከዜግነት ጥያቄ ጋር በተያያዘ መልኩ ለሚሰሩ ወንጀሎች በፌዴራል እስር ቤት ከ18 ወራት በላይ የእስራት ብይን አይሰጥም፡፡ ሆኖም ግን ብይኑን የሰጡት ዳኛ የዩናይትድ ስቴትስ ፌደራል ዳኛ ጆን. ኤል. ካኔ የወርቁ የጥፋተኝነት ወንጀል በጣም አስደንጋጭ እና ከፍተኛ ነው ብለዋል፡፡ ዳኛ ካኔ እንዲህ በማለት ገለጻ አድርገዋል፣ “ይህችአሜሪካ አገር የሰብአዊ መብት ደፍጣጮች መጠለያ ዋሻ የመሆን አደጋ ጋር በተያያዘ መልኩ ከፍተኛው የእስር ብይን መሰጠቱ ተገቢ ነው“ ብለዋል፡፡
ከፈለኝ ዓለሙ ወርቁ የፍርድ ሂደት ጉዳይ ይዘውት የነበሩት የዩናይትድ ስቴትስ ፌዴራል ጠበቃ ጆን ዋልሽ እንዲህ በማለት አውጀዋል፣ “የእኛ የፍትህ ስርዓት በአንድ ወቅት አሸባሪው ወንጀለኛ ተከላካይ ሲያሸብረው ከነበረው ስደተኛ ማህበረሰብ ላይ በተሳካ ሁኔታ እንዲወገድ አድርጓል፣ እናም ይህንን በማድረግ የእኛን ህጎች ብቻ አይደለም ከጥፈተኝነት ነጻ ያደረግነው ሆኖም ግን እዚህ እኛ አገር ውስጥ እየኖሩ ያሉትን የተከላካዩን የግፍ ሰለባዎች መብት ማስከበር ጭምር እንጅ፡፡“ በአሁኑ ጊዜ ፍትህ ተረጋግጧል/ሰፍኗል፡፡ የወንጀሉ ተከላካይ የሆነው ከፈለኝ ዓለሙ ወርቁ ለሰራው ወንጀል ከፍተኛ የሆነውን የእስር ብይን በመወሰን “ዩናይትድ ስቴትስ አሜሪካ የኗሪነት እና የጥገኝነት ህጓን በማጭበርበር ከለላ ለማግኘት ከውጭ ሲገድሉ እና ሲያሰቃዩ ቆይተው ወደ አሜሪካ ለሚመጡት ወንጀለኞች በሰላም ለመኖር መደበቂያ ዋሻ አትሆንም” በማለት ዳኛ ጆን ካኔ ጠንካራ የሆነ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡
ባለፈው ሳምንት በስደት በአሜሪካ አገር የሚኖረው የኢትዮጵያ ታዋቂው የምርመራ ጋዜጠኛ አበበ ገላው አንድ ቴዎድሮስ ባህሩ የሚባል “የኢትዮጵያ ሰይጣናዊ አቃቤ ህግ የነበረ“ (አሜሪካ ሊታይ በሚችል ቦታ ላይ እራሱን ደብቆ) አግኝቷል፡፡ ቴዎድሮስ ባህሩ ሲልቨር ስፕሪንግ ሜሪላንድ በሚባል ቦታ ኗሪ የሆነውን “በሰላማዊ አመጸኞች፣ በነጻው ፕሬስ ጋዜጠኞች እና በተቃዋሚ የፖለቲካ አባላት ላይ የጸረ- ሽብር አዋጅ እየተባለ የሚጠራውን የንጹሀን ዜጎች ማጥቂያ መሳሪያ በማድረግ ፍትሀዊ ያልሆነ እና ከህግ አግባብ ውጭ የዘፈቀደ እስራት ላይ የሙሉ ፈቃደኝነት ተዋናይ ሆኖ በመስራት “ በሚል ክስ አበበ ገላው መስርቶበታል፡፡ እንደ አበበ ገለጻ ከሆነ ባህሩ “ወንጀላቸው የህወሐትን ሙስና እና አምባገነናዊ አገዛዝ መቃወማቸው ብቻ በሆኑት ንጹሀን ዜጎች ላይ ለቁጥር የሚያዳግቱ የፍብረካ የአገር ክህደት እና የሽብር ወንጀል ክሶችን በመዘርዘር ዜጎች ያለስራቸው በሀሰት አንዲሰቃዩ እና ስብዕናቸውም እንዲገፈፍ በማድረግ ታላቅ ወንጀል ሰርቷል የሚል ነው፡፡“
አበበ ውንጀላውን እንዲህ በማለት አቅርቦታል፣ “ቴዎድሮስ ባህሩ ከህወሐት (በኢትዮጵያ የገዥው አካል ፓርቲ) ዓቃብያነ ህጎች መካከል አንዱ ሲሆን በፖለቲካ እስረኞች ላይ ማለትም በእነ እስክንድር ነጋ፣ አንዷለም አራጌ፣ ናትናኤል መኮንን፣ ርዕዮት ዓለሙ፣ ውብሸት ታዬ፣ በቀለ ገርባ፣ ኦልባና ሌሊሳ፣ በሙስሊሙ ማህበረሰብ መሪዎች ላይ እና ጆሀን ፔርሰን እና ማርቲን ሽብዬ በተባሉ ሁለት የስዊድን ጋዜጠኞች ላይ የሽብር ክሶችን እንዲፈበርክ ሰልጥኖ እና ተቀጥሮ በወሰደው ስልጠና መሰረት ሲያስፈጽም የቆየ“ ተጠርጣሪ ነው የሚል ነው፡፡ አበበ በመቀጠልም “ባህሩ የዩናይትድ ስቴትስ ዜግነት ያገኙትን እና ሌሎችንም ንጹሀን ዜጎች ማለትም ኦባንግ ሜቶን፣ ኒያሚን ዘለቀ፣ ዶ/ር ብርሀኑ ነጋ፣ ኤፍሬም ማዴቦ፣ ፋሲል የኔዓለም፣ መስፍን ነጋሽ እና አብይ ተክለማርያምን በሽብርተኝነት ክስ እንዲመሰረትባቸው አድርጓል“ ብሏል፡፡
በኤሌክትሮኒክ በተደረገ ግንኙነት ባህሩ ለአበበ እንዲህ የሚል መልዕክት አስተላልፏል፣ በሀሰት የተፈረከውን የእስክንድር ነጋን እና የሌሎችን ከላይ የተጠቀሱትን ተከላካዮች ሳቀርብ “ስራዬ ትዕዛዞችን ብቻ መቀበል ነበር“፡፡ በሚያስገርም ሁኔታ ቴዎድሮስ ባህሩ የናዚ የሰብአዊ መብት ደፍጣጭ ወንጀለኞች “በኑርምበርጉ የጦር ፍርድ ቤት” ቀርበው በተጠየቁበት ጊዜ ያነሱትን መከላከያ ሀሳብ እንዳለ ደግሞታል፡፡ በዚያን ወቅት አዶልፍ ኤክማን የተባለው ወንጀለኛ በጦር ፍርድ ቤቱ የፍርድ ሂደት እየተካሄደ ለጥያቄ በቀረበበት ጊዜ እንዲህ የሚል የምስክርነት ቃል ሰጥቶ ነበር፣ “እራሴን ለስልጣን ስራዎቼ ለቢሮዬ ቃልኪዳን ታማኝ ሆኘ እራሴን ማስገዛቴ እና ታዛዥ ሆኘ በማስፈጸሜ ጥፋተኛ ነኝ፡፡ አይሁዶችን ሆን ብዬ በማጥቃት እና በስሜታዊነት እንዲገደሉ አላደረግሁም፡፡ ያንን ያደረገው መንግስት ነው፡፡“ ከዚህ ጋር በተመሳሰለ መልኩ ቴዎድሮስ ባህሩም ለስልጣን ስራው ሲል ንጹሀን ዜጎችን አልነካሁም ነው የሚለው፡፡ትእዛዝ ብቻ ነው የተቀበልኩት :: ለዚህ በሸፍጥ ለተሞላው የወንበዴ ቡድን ታማኝ ሎሌ እና አገልጋይ በመሆን ለሰራቸው ጥፋቶች ሁሉ ኃላፊነት የለኝም ነው የሚለው፡፡ እስክንድር ነጋን፣ ርዕዮት ዓለሙን፣ ውብሸት ታዬን ወይም ሌሎች በደርዘን የሚቆጠሩ ንጹሀን ዜጎችን “ሆን ብሎ እና በስሜታዊነት” አላጠቃሁም፣ ያንን የፈጸመው መንግስት ነው ይላል ቴዎድሮስ ባህሩ ፡፡
ሰርካለም ፋሲል በቴዎድሮስ ባህሩ ላይ የመሰረተቻቸው ክሶች፣
የህወሐት ገዥ አካል እርሷን እና ባለቤቷን እስክንድር ነጋን ወደ እስር ቤት እስከወረወረበት ጊዜ ድረስ በኢትዮጵያ የመጀመሪያዋ ሴት ጋዜጠኛ እና አሳታሚ ሆና ስትሰራ በቆየችው ሰርካለም ፋሲል በቴዎድሮስ ባህሩ ላይ በጣም ጠንካራና ማስረጃ የሞላው ክስ አቅረባለች፡፡ ሁለቱም ሰርካለም እና እስክንድር (በአሁኑ ጊዜ በሀሰት የሸፍጥ ክስ ተመስርቶበት የ18 ዓመታት እስራት ተበይኖበት ከመሀል ከተማ በጥቂት ኪሎ ሜትሮች ርቀት ላይ በሚገኘው በታዋቂው የ “መለስ ዜናዊ የቃሊ እስር ቤት”በመማቀቅ ላይ ያለው) በዘመናዊ የአፍሪካ የነጻ ጋዜጠኞች ታሪክ ታይቶ በማይታወቅ መልኩ በገዥው አካል ጥቃት የተፈጸመባቸው እና ከፍተኛ የሆነ ዓለም አቀፋዊ አድናቆትን ያገኙ ሰላማዊ ጋዜጠኞች እስክንድርና ሰርካለም ናቸው፡፡ ባለፉት ሶስት ዓመታት ውሰጥ እስክንድር እያንዳንዱን ታዋቂ እና ታላላቅ ዓለም አቀፋዊ የፕሬስ ሽልማቶች አሸናፊ ነበር :: ከሁለት ሳምንታት በፊት በተወካዩ አማካይነት የተቀበለውን የ2014 ወርቃማ የብዕር የነጻነት ሽልማት ጨምሮ በዓለም ታዋቂና ተወዳጅ ተሸላሚ ሆኗል፡፡ ሰርካለምም እንደዚሁ “ዓለም አቀፍ የሴቶች ሜዲያ ፋውንዴሽን” ከተባለው ዓለም አቀፍ የፕሬስ ድርጅት አደጋ ተደቅኖ ባለበት ሁኔታ የተለዬ ጀግንነትን ለሚያሳዩ ጋዜጠኞች ”ለደፋር ጋዜጠኝነት ሽልማት“ የሚለውን ጨምሮ በርካታ ዓለም አቀፍ የፕሬስ ሽልማቶችን አግኝታለች፡፡
በተቀዳ የድምጽ/ኦዲዮ ቃለ መጠይቅ ሰርካለም ቴዎድሮስ ባህሩ በቀላሉ “ትዕዛዝን ብቻ በመቀበል” የሰራ አይደለም፡፡ ይልቁንም ከፍርድ ቤቶች ውጭ ወደ እስር ቤት እንዲገባ እና እንዲወጣ ትዕዛዝ ከሚሰጡት ሰዎች አንዱ ነበር ብላለች፡፡ ሰርካለም በተጨባጭ እንዳስቀመጠችው ባህሩ ባለቤቷን የገዥውን አካል ትዕዛዝ ተቀብሎ ከመተግበርም ባሻገር “ሆን ብሎ እና ስሜታዊነት በተሞላበት ሁኔታ” ሲያሰቃየው እንደደነበረ ገልጻለች፡፡ እንደ ሰርካለም አባባል ከሆነ ባህሩ ቁጡ፣ ጨካኝ፣ ችግር ፈጣሪ፣ ምህረት የለሽ እና ሩህሩህነት የማይሰማው አረመኔ አቃቤ ህግ ነበር ብላለች፡፡ እንደ ባለሙያ ዓቃቤ ህግ የሚገባውን ህጋዊ ስርዓት ተከትሎ የሚሰራ ሳይሆን እንደ ፖለቲካ አቃቤ ህግ ተከላካዮችን ያድን ነበር፡፡ ባህሩ ተከላካዮችን አሳንሶ ለማሳየት በፍርድ ቤቱ ችሎት ፊት ሁሉንም አጋጣሚዎች ሁሉ ያደርግ ነበር፡፡ ተከላካዮች ምንም ዓይነት ወንጀል ያልሰሩ ነጻ መሆናቸውን ሊያስረዱ የሚችሉ ሰነዶችን እና ምስክሮችን በሚያቀርቡበት ጊዜ ሁሉ እነዚህን በሚያስተባብል መልኩ ተቃውሞዎችን እያቀረበ ይከላከል ነበር፡፡ ተከላካዮች ፍትሀዊ ብይን እንዳያገኙ እና ማለቂያ በሌለው ረዥም ቀጠሮ እየተመላለሱ እንዲጉላሉ በማሰብ እንዲሁም የፍርድ ሂደቱን ስርዓት በማጣመም ከፍትህ አካላት የአሰራር መርህ ውጭ በሆነ መልኩ ፍትህን ሲያዛበ ነበር፡፡ የጥፋተኝነት ውሳኔ ለማሰጠት በማሰብ የተፈበረኩ እና የሀሰት ማስረጃዎችን ያቀርብ ነበር ብላለች፡፡
ሰርካለም በተለየ መልኩ ቴዎድሮስ ባህሩ በእራሱ አቅም እና እንደ መንግስት ዓቃቤ ህግ እያወቀ ሆን ብሎ እና የያዘውን ስልጣን ለእኩይ ተግባር በማዋል በእርሷና በባሌቤቷ የክስ ሂደት ላይ የህግ የበላይነትን ሲያጣምም ቆይቷል በማለት ውንጀላ አቅርባበታለች፡፡ እ.ኤ.አ በ2011 ባህሩ በባለቤቷ ላይ መሰረተ ቢስ ክስ በመመስረት፣ የሀሰት ማስረጃ እና የሀሰት ምስክር በማቅረብ እውነታውን እያወቀ ሆን ብሎ ሲያጣምም ነበር በማለት ወንጅላዋለች፡፡ ሰርካለም ውንጀላዋን በመቀጠል ባህሩ እስክንድርን የግንቦት ሰባት ድርጅት አመራራ በመሆን ወጣቶችን እየመለመለ ለሽብር ጥቃት ሲዳርግ ነበር ብላለች፡፡ ባህሩ ይህንን ውንጀላ ለማስተባበል የሚያስችል ምንም ዓይነት ማስረጃ ለማቅረብ አልቻለም፡፡ ሆኖም ግን የሸፍጥ ስራውን ለማከናወን ከዳኞች ጋር የሸፍጥ ዱለታ በማካሄድ ጥፋተኛ እንዲባል አስደርጓል፡፡ ሰርካለም ባህሩ እና ብርሀኑ ወንድምአገኝ የተባሉ ሁለት ዓቃብያነ ህጎች በግል የቤተሰቦቿን ንብረቶች፣ ቤቶቻቸውን፣ መኪኖቻቸውን እና ሌሎችን የግል መጠቀሚያ ቁሳቁሶችን ጨምሮ ከህግ አግባብ ውጭ እንዲነጠቁ በማድረጉ ሂደት ላይ ተባባሪ ነበሩ በማለት ውንጀላ አቅርባባቸዋለች፡፡ ባህሩ እያወቀ ስልጣኑን ከህግ አግባብ ውጭ በመጠቀም ሆን ብሎ እና ሌሎችን የኢትዮጵያን የነጻውን ፕሬስ ጋዜጠኞች ለማጥቃት እንደ ሰርካለም አባባል ዓለም አቀፍ የፕሬስ አሸናፊ ተሸላሚ የሆኑትን እነ ርዕዮት ዓለሙ፣ ውብሸት ታዬ እና ሌሎችም ፍትሀዊ ዳኝነት እንዳያገኙ በማድረግ ደባ ፈጽሟል ብላለች፡፡
ሰርካለም በቴዎድሮስ ባህሩ ላይ ያቀረበችው ውንጀላ በተለይም የህግ የበላይነትን ከማስጠበቅ አኳያ እና የመንግስት ዓቃብያነ ህጎች ንጹሀን ዜጎች የሰብአዊ መብት ደፍጣጮች ሰለባ እንዳይሆኑ በመከላከል ሂደት ላይ የሚጫወቱትን ቁልፍ ሚና በሚመለከት በርካታ የህግ ጥያቄዎች እንዲነሱ አድርገዋል፡፡ ዓለም አቀፍ የሰብአዊ መብት ህግ ዓቃብያነ ህጎች የሰብአዊ መብት ጥበቃ ንቁ ተከላካይ መሆን እንዳለባቸው እና የአገር እና ዓለም አቀፍ ህጎች ታማኝነት እና የሰብአዊ መብት መርሆዎች በከፍተኛ ደረጃ መጠበቅ እንዳለባቸው ይጠይቃል፡፡ ዓቃብያነ ህጎች ለፍትሀዊ ዳኝነት ሂደት እና ለፖለቲካ ዓላማ ሲባል ኃላፊነቶቻቸውን በአግባቡ ሳይወጡ የሚቀሩ ቢሆን የህግ የበላይነት መርሆዎችን ብቻ አይደለም እየጣሱ ያሉት፣ ሆኖም ግን ቆመንለታል የሚሉትን የፍትህን ጠቅላላ መጨንገፍ የሚያመላክት ስለሆነ የእነርሱ መኖር በእጅጉ አስፈላጊ ነገር ነው፡፡
ሁለቱም ዓለም አቀፍ የሰብአዊ መብቶች ድንጋጌ እና ዓለም አቀፍ የሲቪል እና የፖለቲካ መብቶች ስምምነቶች/ሲፖመስ (ዩናይትድ ስቴትስ ሲፖመስን በኢትዮጵያ ህገመንግስት አንቀጽ 13(1)) ላይ የተቀመጠውን “እያንዳንዱ ሰው በነጻ እና ገለልተኛ በሆነ የፍትህ አካል ችሎት ፍትህን የማግኘት እና የመደመጥ መብት እንዳለው እና ማንኛውም በግለሰቦች ላይ የሚመሰረትን የወንጀል ክስ ለመከላክል መብት እንዳለው የሚደነግገውን እና እ.ኤ.አ በ1992 ያጸደቀችውን፣(ሰፖመስ በአንቀጽ 14፡ የአፍሪካ ቻርተር ሰዎች እና በህዝቦች መብቶች (አቻሰህመ) ከአንቀጽ 6-8 የተዘረዘሩትን መመልከት ይቻላል)፡፡ የሮማ ዓለም አቀፍ የወንጀለኞች ፍርድ ቤት (አይሲሲ) የወንጀለኞች ፍትህ የማግኘት መብት መርሆዎችን በግልጽ ያስቀምጣል (ከአንቀጽ 22-33) እና የፍትሀዊ ዳኝነት (ከአንቀጽ 62 – 67) በግልጽ ተመልክቷል፡፡ ለሰብአዊ መብት ድፍጠጣ ሰላባዎች ካሳ ዓለም አቀፍ የሰብአዊ መብቶች ህግ እና ዓለም አቀፍ የሰብአዊ መብቶች ህግ መጣስን አስመልክቶ (በተባበሩት መንግስታት የጠቅላላው ጉባኤ የዴሴምበር 16/2005 ጉባኤ ውሳኔ ቁጥር 60/147) እንደሚገልጸው መንግስታት በሰብአዊ መብት ድፍጠጣ ወንጀል ፈጽመዋል በሚል የተጠረጠሩትን እና ዓለም አቀፍ የሰብአዊ መብቶችን ጥሰዋል የሚባሉትን መብት ደፍጣጮች የመዳኘት ኃላፊነት እንዳለባቸው በግልጽ ተደንግጓል፡፡“
በሰው ልጆች ላይ ወንጀልን ፈጽመው በዩናይትድ ስቴትስ አሜሪካ ተደብቀውበሚገኙ የኢትዮጵያ ወንጀለኞች ላይ ጥቆማ እንዲደረግ የቀረበ ጥሪ፣
እ.ኤ.አ ጃንዋሪ 2012 “የአፍሪካ አምባገነኖች፡ የትም ሮጠው ሊያመልጡ አይችሉም፣ የትም ተደብቀው ሊያመልጡ አይችሉም!“ በሚል ያቀረብኩት ፅሁፍ በኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶችን ደፍጥጠው ወደ ውጭ በመኮብለል በአሁኑ ጊዜ በአሜሪካ እየኖሩ የሚገኙትን መብት ደፍጣጮች አሳድዶ በማደን ስማቸውን እና ያሉበትን ልዩ ቦታ ለአሜሪካ ባለስልጣኖች ጥቆማ በመስጠት የዜግነት ግዴታዎቻችሁን እንድትወጡ እና የወገኖቻችሁ ደም ደመከልብ ሆኖ እንዳይቀር የሚል ጥሪ አስተላልፌ ነበር፡፡ በአሁኑ ጊዜ እየተጠናከሩ በመጡት ምርመራዎች እና የሰብአዊ መብቶችን በመደፍጠጥ ወደ አሜሪካ በማታለል እና በህገወጥ መልክ የገቡትን ወንጀለኞች አሳድዶ በመያዝ በተለይም ለአሜሪካ ባለስልጣኖች ለህግ ማቅረብ በጣም አስፈላጊ ጉዳይ ነው፡፡ እነዚህን የሰብአዊ መብት ደፍጣጮች ለዜግነት እና ለጉምሩክ አስፋጻሚ ፣ ለአገር ውስጥ ደህንነት ጉዳይ ፣ ለሰብአዊ መብት ደፍጣጮች እና ለጦር ወንጀለኞች ቡድኖች እና ለብሄራዊ ደህንነት የምርመራ ክፍል መ/ቤቶች መጠቆም ትችላላችሁ፡፡ ያሜሪካ መንግስት የጦር ወንጀለኞች፣ የዘር ማጥፋት ወንጀለኞች፣ የአሰቃዮች እና ሌሎች በዓለም ላይ ግጭትን ሊያመጡ የሚችሉ የሰብአዊ መብቶች ደፍጣጮች ኮሚሽን መደበቂያ ገነት እንዳትሆን ለመከላከል ጠንካራ ምርመራዎችን ያደርጋል፡፡ የውጭ ተጠርጣሪ የጦር ወንጀለኞች፣ አሰቃዮች እና የሰብአዊ መብት ድፍጣጮች ዩናይትድ ስቴትስ አሜሪካ የግዛት ክልል ውስጥ መኖራቸው በሚታወቅበት ጊዜ የምርመራ ቡድን ሙሉ የህግ ኃይሉን እና ስልጣኑን በመጠቀም ለማጣራት፣ ለመዳኘት እና በሚቻልት ሁኔታ ሁሉ እንደዚህ ያሉ ሰብአዊ መብት ደፍጣጮችን ከአሜሪካ ለማስወገድ ጥረት ያደርጋል፡፡
ባለፉት አስርት ዓመታት ያሜሪካ መንግስት በመቶዎች በሚቆጠሩ ከሰብአዊ መብት ጥሰት ጋር በተያያዘ መልኩ በወንጀለኛ እና/ወይም ስደተኞች ምርመራ ላይ ስኬታማ ሆኗል፡፡ የዚህ ቡድን የዳታ መሰረት በርካታ የታወቁ ተጠርጣሪ የሰብአዊ መብት ደፍጣጮችን ስም ዝርዝር አካትቶ ይዟል፡፡ የዳታ ቋቱ የታወቁ የሰብአዊ መብት ደፍጣጮች ወደ አሜሪካ እንዳይገቡ ለማድረግ ጠቃሚ መሳሪያ ሆኖ ያገለግላል፡፡ በአሁኑ ጊዜ ዜጉአ ወደ100 አካባቢ ከሚሆኑ ከተለያዩ አገሮች የመጡ በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ የሰብአዊ መብት ደፍጣጮች ላይ ክትትል በማድረግ ላይ ይገኛል፡፡ ባለፉት ስምንት ዓመታት በመቶዎች የሚቆጠሩ ከሰብአዊ መብት ድፍጣጮች እና ከተለያዩ የወንጀለኛ እና/ወይም ከስደተኝነት ጋር በተያያዘ መልኩ በቁጥጥር ስር አውሎ ሌሎች በመቶዎች የሚቆጠሩትን ታዋቂ ወይም ተጠርጣሪ ግለሰቦችን ደግሞ ከዩናይትድ ስቴትስ አሜሪካ በማስወጣት ወደ አገራቸው እንዲጋዙ አድርጓል፡፡
በሰው ልጆች ላይ ወንጀልን የፈጸሙ እና በአሜሪካ እየኖሩ ያሉ የኢትዮጵያወንጀለኞች ለምርመራ ለዜጉአ ሰመደጦወቡ ጥቆማ መቅረብ ይኖርባቸዋል፣
በኢትዮጵያ በሰው ልጆች ላይ የተፈጸሙ የሰብአዊ መብት ድፍጠጣዎች እና የጦር ወንጀሎች መረጃዎች በተሟላ ሁኔታ ተተንትነው እና ተጠቃለው ተዘጋጅተው ተይዘዋል፡፡ እ.ኤ.አ በ2007 በኢትዮጵያ ያለው የህወሐት ገዥ አካል አጣሪ ኮሚሽን ባቀረበው ዘገባ መሰረት የ2005 ድህረ ምርጫ ውዝግብን ተከትሎ በአገሪቱ ውስጥ ከህግ አግባብ ውጭ በዘፈቀደ 193 ሰላማዊ ዜጎች የተገደሉ፣ ሌሎች 763 ሰዎች ቁስለኛ እና ሌሎች ወደ 30 ሺህ የሚሆኑት ደግሞ ከህግ አግባብ ውጭ ለዘፈቀደ እስራት የተዳረጉ መሆናቸውን በተጨባጭ መረጃ አስደግፎ አቅርቧል፡፡ በዚህ የወንጀል ድርጊት ውስጥ ተዋንያን የነበሩ 237 ግለሰቦች ታውቀዋል፣ እንዲሁም ከዚሁ ጋር ንክኪ ያላቸው ተጠርጣሪዎች ተለይተዋል፡፡ እ.ኤ.አ ዴሴምበር 2003 በኢትዮጵያ በጋምቤላ 424 ንጹሀን ዜጎች ከህግ አግባብ ውጭ በዘፈቀደ ለህወሐት ታማኝ በሆኑ የደህንነት ኃይሎች ተገድለዋል፡፡ በኦጋዴን ላይ በሚደረገው ጭቆና እ.ኤ.አ በ2008 ሂዩማን ራይትስ ዎች ባወጣው ዘገባ መሰረት “150 የተገደሉ ግለሰቦች“ እና ሌሎች 37 ተጨማሪ ሰላማዊ ዜጎች በጦር ወንጀለኝነት ተጠያቂ በሚሆኑ በኢትዮጵያ ወታደሮች ትዕዛዝ እና ተሳታፊነት በተደረገ ጥቃት የተገደሉ ሰዎች ስም ዝርዝር ተመዝግቦ ተይዟል፡፡ ይህንን የጦር ወንጀል የሚያወቁት ወይም ደግሞ እንደዚህ ያለ ወንጀል እንደሚፈጸም ማወቅ ያለባቸው ሆኖም ግን ምንም ዓይነት እርምጃ ያልወሰዱ ከፍተኛ የጦር መኮንኖች እና የሲቪል ባለስልጣኖች እንደ ትዕዛዝ ሰጭነታቸው በወንጀሉ ተጠያቂዎች ናቸው፡፡ በአሁኑ ጊዜ የተስፋፋው እና ስልታዊ በሆነ መልክ በሶማሊ ክልል በእያንዳንዱ መንደር ላይ እየተካሄደ ያለው ከህግ አግባብ ውጭ በዘፈቀደ የሚደረገው ግድያ፣ ማሰቃየት፣ አስገድዶ መድፈር፣ እና አፍኖ መሰወር በስልጣን ላይ ያለው የኢትዮጵያ ገዥ አካል የመጨረሻውን ተጠያቂነት ሊወስድ የሚችልባቸው እና ሊጠየቅባቸው የሚችሉ በሰው ልጆች ላይ እየፈጸማቸው ያሉ ወንጀሎች ጠንካራ ማስረጃዎች ናቸው፡፡ እነዚህ ከብዙው በጥቂቱ የሚጠቀሱ ናቸው፡፡
በዩናይትድ ስቴትስ አሜሪካ ተደብቀው በሚገኙ የኢትዮጵያ ወንጀለኞች ላይጥቆማ ለማድረግ ለምን ተነሳሽነት ማሳየት እንዳለብን፣
ምናልባትም ባለፉት በርካታ ዓመታት በኢትዮጵያውያን/ት ዘንድ በተደጋጋሚነት ሲቀርቡልኝ ከነበሩት ጥያቄዎች ውስጥ “እኔ እንደ ግለሰብ በኢትዮጵያ ያለውን የሰብአዊ መብት ለማሻሻል ምን ማድረግ እችላለሁ?“ የሚሉ ነበሩ፡፡
በርካታ ኢትዮጵያውያን/ት በተለይም የዲያስፖራው ማህበረሰብ በግለሰቦች አቅመቢስነት ተስፋ እየቆረጡ የመጡ ይመስላል፡፡ በተቃዋሚ የፖለቲካ ቡድኖች መካካል የሚታዩትን የአንድነት መላላት በመመልከት እና መቋጫ በሌለው መልኩ እየተሰነጣጠቁ ሲፈረካከሱ በማየታቸው በሀዘን በመሞላት ከዳር ቆመው በመመልከት ላይ ይገኛሉ፡፡
ባለፈው ሳምንት በኮካ ኮላ ኩባንያ እና በሚያመርታቸው 114 ምርቶቹ ላይእንዳንጠቀም የሚቀሰቅስ ጥሪ አቅርቤ ነበር፡፡ ኮካ ኮላ 32 የዓለም ለዓለም እግርኳስ የመክፈቻ ስነስርዓት ማድመቂያ የሚሆን ምርጥ አገራዊ ሙዚቃቸውንእንዲያቀርብ ለ32 ታዋቂ ሙዚቀኞች ጋብዞ ከእነዚህ ውስጥ 31ዱን በመምረጥ ሲለቅቅ አንዱን ብቻ ነጥሎ በማውጣት የኢትዮጵያውን ወደ ጎን አሽቀንጥሮበመጣሉ ኮካ ኮላን “ገሀነብ ግባ!!!” በማለት እቅጩን ነግሬዋለሁ፡፡ በምንምዓይነት መልኩ የኮካ ኮላን ምርት አልገዛም፣ በፍጹም አልጠቀምም፣ እንዲሁምሌሎች የኮካ ኮላን ምርት እንዲገዙ ወይም እንዲጠቀሙ አላበረታታም፡፡ግለሰቦች በተናጠል እና እንዲሁም በጋራ በሚያደርጓቸው እንቅስቃሴዎችያለምንም ጥርጥር ለውጥ ያመጣሉ፡፡ ኮካ በጭራሽ በፊቴ አይዞርም!
ባለፈው ሳምንት በኮካ ኮላ ምርት ላይ ላለመጠቀም የሚቀሰቅሰው ጥሪ መተላለፉን ተከትሎ በእስፔን አገር ከፍተኛ የሆነ የኮካ ኮላ ምርት ሽያጭ ቅነሳ ተስተውሏል፡፡ በእስፔን የኮካ ኮላ ምርት ሽያጭ በግማሽ ቀንሷል ምክንያቱም የእስፔን ህዝብ የኮካ ኮላ ኩባንያን ገሀነም እንዲገባ ስለነገረው ነው!!!
(በኢትዮጵያ ኮካ ኮላን ባለመጠቀም ጸጥ በማለት ውጤታማ እንቅስቃሴዎች እየታዩ መሆኑን ተጨባጭ መረጃዎች ያመላክታሉ)፡፡
እስፔኖች ኮካ ኮላን አሽቀንጥረው ከጣሉት ኢትዮጵያውን/ትስ ምን ይሳናቸዋል?
ኢትዮጵያውያን/ት የኢትዮጵያን የሰብአዊ መብት ደፍጣጮች ለአሜሪካ የዜጎች እና ጉምሩክ አስፈጻሚ የሰብአዊ መብት ደፍጣጮች እና የጦር ወንጀለኞች ቡድን ለምን መጠቆም እንዳለባቸው በማስረጃ እና በመረጃ የተደገፉ በርካታ ምክንቶች አሉ፡፡
1ኛ) በኢትዮጵያ ህዝብ ላይ ወንጀል ሰርተው በዩናይትድ ስቴትስ አሜሪካ ሄደው ተደብቀው የሚኖሩትን መጠቆም በምንም ዓይነት ሊታለፍ የማይችል በቀጥታ የጥቃቱ ሰለባ የሆነው የእያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ/ት ወይም ደግሞ በሌሎች ወገኖቻችን ላይ የተፈጸመ ለመሆኑ እውቀቱ ያለው የሞራል ሰብዕና ተግባር በመሆኑ ነው፡፡ በሰው ልጆች ላይ እንደዚህ ያለ ወንጅልን የሚፈጽሙ ወንጀለኞች መጋለጥ እና ከአሜሪካ ህብረተሰብ መካከል መወገድ ይኖርባቸዋል፡፡
2ኛ) በእነዚህ የሰብአዊ መብት ደፍጣጮች ላይ ጥቆማ ማካሄድ በኢትዮጵያ በስልጣን ወንበር ላይ ተጣብቀው ላሉት ባለስልጣኖች አሜሪካ የሰብአዊ መብትን እየደፈጠጡ ለሚመጡ ወሮበላ ወንጀለኞች የሀሰት እና የተጭበረበረ የጥገኝነት ቪዛ እያመጡ በሰላም ለመኖር አሜሪካ በተጨባጭ መደበቂያ ገነት የማትሆን መሆኗን የሚገልጽ ጠንካራ መልዕክት ያስተላልፋል፡፡ እነዚህ ወንጀለኞች አሜሪካ ቢገቡ እንኳ ወደ እስር ቤት እንደሚጋዙ ዝግጅት ማድረግ አለባቸው ምክንያቱም ለፖሊስ ጥቆማ በማቅረብ ለፍትህ ይቀርባሉ፡፡
3ኛ) በዚህ ጥቆማ ላይ የሚደረግ ሰፊ የሆነ ተሳትፎ ኢትዮዮጵያ በስልጣን ላይ ላሉት የገዥው አካል አባላት አስቀያሚ የሆነ የሰብአዊ መብት ጥሰት ፈጽመው ወደ ዩናይትድ ስቴትስ አሜሪካ በመሄድ አሜሪካንን የሚረግጡ ከሆነ በአሜሪካ ባንኮች የደለበውን የባንክ ሂሳቦቻቸውን ብቻ አይደለም የሚያጡት፣ ሆኖም ግን የእራሳቸውን ነጻነትም እንደሚያጡ ጠንካራ የሆነ መልዕክት ያስተላልፋል፡፡ የመጨረሻዎቹን ቀናት በአሜሪካ እስር ቤቶች ሊያሳልፉ እንደሚችሉ ዝግጅት ማድረግ ይኖርባቸዋል፡፡
4ኛ) የኢትዮጵያ የሰብአዊ መብት ደፍጣጮች አሜሪካ የእነርሱ መደበቂያ ገነት ዋሻ እንደማትሆን እሰካመኑ ድረስ በኢትዮጵያ ህዝብ ላይ የሰብአዊ መብቶችን ጥሰት ከመፈጸም እኩይ ተግባራት ይታቀባሉ፡፡ ሁሉም የገዥው አካል አመራር አባላት በሚባል መልኩ እና የእነርሱ ታማኝ ሎሌዎች በአሁኑ ጊዜ ነገሮች በዚህ ሁኔታ የሚቀጥሉ ከሆነ እና በኢትዮጵያ ለውጥ ከመጣ ወደ አሜሪካ የሚያደርጉትን የፍርጠጣ ጉዞ በመሰረዝ ወደ ሌላ አዲስ ቦታ ጉዞ እንደሚያርጉ ይታመናል፡፡ እንደገና ቢያስቡ የተሻለ ይሆናል!
በኢትዮጵያ ወንጀል ፈጽመው ወደ አሜሪካ በመሄድ ተደብቀው የሚኖሩወንጀለኞች እንዳሉ እያወቁ አለመጠቆም እና ለፍትህ እንዲቀርቡ አለማድረግእና እንዲኖሩም መፍቀድ በእራሱ ወንጀል ነው፡፡ ወንጀል ከተሰራ በኋላለወንጀለኞች ተባባሪ መሆን ወንጀል ከመስራት ጋር እኩል ነው፡፡ እነዚህ በሰው ልጆች ላይ ወንጀልን ፈጽመው በአሜሪካን አገር ተደብቀው የሚገኙ ወንጀለኞች ፍትህ እንደዘገዬ ባቡር መሆኑን ሊገነዘቡ ይገባል፡፡
የጥቃት ሰለባዎች ለጥቂት ጊዜ መታገስ ይኖርባቸዋል፣ ሆኖም ግን በመጨረሻው ሰዓት ፍትህ በሙሉ ኃይሉ ታጅቦ ይመጣል፡፡ እ.ኤ.አ ሜይ 23/2014 ከፈለኝ ዓለሙ ወርቁ የተማረው ይህንን ሀቅ ነው፡፡ ያ በአሜሪካ ግልጽ ተደብቆ እየኖረ ያለው እያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ/ት የሰብአዊ መብት ደፍጣጭ በየዕለቱ ሊማርበት የሚገባ አብይ ትምህርት ነው፡፡ ያ ሁኔታ አሁኑ ጊዜ በኢትዮጵያ ሰብአዊ መብትን እየደፈጠጡ ያሉ እና አሜሪካ ሄዶ ከመደበቅ ይልቅ ወደ ሌላ አዲስ ቦታ ለመሸሽ ዕቅድ የሚያወጡት ወንጀለኞች ሊማሩበት የሚገባ ጉዳይ ነው፡፡
ለሁሉም ኢትዮጵያውያን/ት የሚሆን ፍትህ ትምሀርት
ባለፈው ሳምንት በፊላደልፊያ ግዛት ለ65 ዓመታት ከኖረ በኋላ በሁለተኛው የዓለም ጦርነት የናዚ የእስር ቤት ጥበቃ አባል በመሆን በታዋቂው አውሽውዝ እየተባለ ይጠራ በነበረው የጦር ካምፕ እና በሌሎች ቦታዎች ላይ በሰራው ወንጀል በጦር ወንጀለኛነት በመጠርጠር ጆሀን ብሪየር የተባለው የ89 ዓመት አዛውንት ወንጀለኛ በፖሊስ ቁጥጥር ስር ውሏል፡፡ ብሪየር እ.ኤ.አ 1952 ወደ አሜሪካ በመሄድ ተፈናቃይነት በሚል ምክንያት ዜግነትን ጠይቋል፡፡ ይህ ወንጀለኛ 1.1 ሚሊዮን ወንዶች፣ ሴቶች እና ልጆች ያለቁበትን ወንጀል ተሳታፊ ነበር ፡፡ የጀርመን ባለስልጣኖች ከ216, 000 በላይ የሚሆኑ የአውሮፓ አይሆዶችን በመግደል በሚል በጥፋተኝነት በመንጀል በሪየር ላይ ክስ መስርተዋል፡፡
ከፈለኝ ዓለሙ ወርቁ የናዚ እስር ቤት የጥበቃ አባል የነበረው ጆሀን ሪየር ከሰራው ወንጀል በምንም ዓይነት መንገድ አይለይም፡፡ ከፈለኝ ዓለሙ ወርቁ የደርግ ወታደራዊ አምባገነን መንግስት የእስር ቤት ጥበቃ አባል ነበር፡፡ እንደ ብሪየር ሁሉ ወርቁም የሰብአዊ መብት እልቂትን ፈጽሟል ወይም ደግሞ ያልተነገረ የሰብአዊ መብት ደፍጣጭ ነው፡፡ በማሰቃየት እና በመግደል በርካታዎቹን የግፍ ሰለባ አድርጓል፡፡ እንደ ሪየር ሁሉ ወርቁ በዩናይትድ ስቴትስ ጥገኝነት በጠየቀበት ጊዜ የእራሱን ማንነት እና ጥፋተኝነት ለመደበቅ እንዲሁም በቀይ ሽብር በተካሄደው እልቂት የእራሱን ሚና አሳንሶ ለማቅረብ ጥረት አድርጓል፡፡ ወርቁ እንደ ሪየር ሁሉ ከፍትህ ለማምለጥ ሙከራ አድርጓል፣ ሆኖም ግን እንደ ሪየር ሳይሆን ፍትህ በ10 ዓመታት የጊዜ ገደብ ውስጥ አሳድዳ ያዘችው፡፡
እውነታው ሲገመገም ግን በአሜሪካ የሚኖሩት የኢትዮጵያ የሰብአዊ መብት ደፍጣጮች በደርግ ወታደራዊ አምባገነን መንግስት የቆሸሸ ስራ የሰሩት ብቻ አይደሉም፡፡ እንደዚሁም ሁሉ ሌሎች በአሁኑ ጊዜ ኢትዮጵያ ያለው ገዥ አካል የህወሐት ወይም ተባባሪዎቻቸው በርካቶች አባላት ተመሳሳይ የሰብአዊ መብት ደፍጠጣ በማካሄድ ላይ ይገኛሉ፡፡ ሁሉም በተጠናከረ ጥቆማ እና ምርመራ እየተለቀሙ ለፍርድ መቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
የስድስት ዓመትም ይሁን የስድሳ አምስት ዓመታት እነዚህ የህወሐትም ይሁኑየደርግ የሰብአዊ መብት ደፍጣጮች ለፍትህ መቅረብ አለባቸው፡፡
በፍትህ ላይ የሚሰናሰል ምንም ዓይነት ነገር እንደሌለ ሊገነዘቡ ይገባል! በእነዚህ በመሀከላችን በነጻነት በሚኖሩ ወንጀለኞች ላይ የሚደረግ ልዩነት ማብቃት አለበት!
ሁሉንም ኢትዮጵያውያንን እና ኢትዮጵያውያትን አንድ ቀላል የሆነ ጥያቄ ላቀርብላቸው እወዳለሁ፡፡ ይህም የዩናይትድ ስቴትስ አሜሪካ የፍትህ መምሪያ በሰው ልጆች ላይ ወንጀልን ሰርተው በአሜሪካ አገር እራሳቸውን ደብቀው የሚኖሩ ተጠርጣሪ ወንጀለኞችን ለህግ ለማቅረብ ጥረት እያደረገ ባለበት ሁኔታ ኢትዮጵያውያን/ት እነዚህን በደም የተጨማለቁ ወንጀለኞች ከእያሉበት በመጠቆም ለምርመራ መምሪያው ተባባሪ መሆን ሊበዛብን ይችላልን?
እራሳቸውን በአሜካ ደብቀው የሚኖሩ የሰብአዊ መብት ደፍጣጮችን እየጠቆሙ ማሳወቅ ቀላል ነገር ነው፣ ጥቆማ በምታደርጉበት ጊዜ ስማችሁን መስጠትአይጠበቅባችሁም፡፡
በሰብአዊ መብት ደፍጣጮች ወይም በሰብአዊ መብት ረገጣ ወይም በጦር ወንጀለኝነት በሚጠረጠሩ በውጭ ዜጎች ላይ ማስረጃ ወይም መረጃ ካላችሁ የICE HISንየስልክ ቁጥር 1-866- 347- 2423ን በመጠቀም እና online tip formን ያጠናቅቁ፡፡
ጥቆማ በምታካሂዱበት ጊዜ ስም መስጠት አስፋለጊ አይደለም!
በሰብአዊ መብት ደፍጣጮች እና የጦር ወንጀለኞች ቡድን ያላችሁን ማስረጃ እና መረጃ በኢሜል አድራሻ
VRV.ICE@ice.dhs,gov ማቅረብ ትችላላችሁ፡፡
ለሰብአዊ መብት ድፍጠጣ ሰለባዎች እገዛ አለ፡፡ ለICE confidential victim/witness hotline toll free number at 1-866- 872- 4973 ጥሪ ያድርጉ፡፡
“ዩናይትድ ስቴትስ የእራሷን ሰላማዊ የዜግነት መብት ህጎቿ አታላዮች እና አጭበርባሪዎች ተበውዘው ከውጭ የሚመጡ ገዳዮች እና አሰቃዮች መደበቂያ ዋሻ አትሆንም“ (የዩናይትድ ስቴትስ ፌደራል ጠበቃ ጆን ዋልሽ)
ኢትዮጵያ በክብር ለዘላለም ትኑር!
ሰኔ 17 ቀን 2006 ዓ.ም