December25,2015
ንግግራቸው የሱዳን ጠቅላይ ሚኒስትር አስመስሏቸዋል።
''በታሪካችን ያላየነው ረሃብ ላይ ነን'' አቶ ኃይለ ማርያም
አቶ ኃይለማርያም ደሳለኝ ዛሬ ታህሳስ 15/2008 ዓም በኢትዮጵያ ፓርላማ ቀርበው በሰጡት ማብራሪያ ላይ በተለይ በኦሮምያ ክልል ለተነሳው ሕዝባዊ አመፅ እና በሱዳን እና በኢትዮጵያ መካከል ስላለው የድንበር ጉዳይ ላይ የተለመደ አወዛጋቢ እና የበለጠ አወሳሳቢ ንግግሮችን ተናግረዋል።
በኦሮምያ የተነሳውን ሕዝባዊ አመፅ ችግሩን፣መነሻውን እና መፍትሄውን የጠቆሙበት አገላለፅ የእራሳቸውን እና የመንግስታቸውን መፍትሄ ቢስነት በአደባባይ በድጋሚ ያጋለጠ ነው።ችግሩ ገበሬው መረጃ አለማግኘቱ ነው ማለታቸው እና በውጭ ኃይሎች ቅስቀሳ ነው የሚለው እርስ በርሱ የተቃረነ አነጋገር በእራሱ ለእራሳቸውም በአግባቡ የገባቸው አይመስልም።ችግሩን መንግስት ስለ ፕላኑ አለመንገሩ ነው ያሉት እና አሁን መንግስታቸው እያናገረ ያለው በጥይት መሆኑን ለሚያስተውለው የኢትዮጵያ ሕዝብ ንግግራቸው በሕዝቡ ላይ ከመዘባበት ያለፈ አንዳች የሚሰጠው ፋይዳ የለም።በመፍትሄነት ያስቀመጡትም ምንም አዲስ ነገር የሌለው እና አሁንም መልሰን እንነግረዋለን የሚለው አባባል ንግግሩ በጥይት እንደሆነ አመላካች ነው።ሕዝብ የሚባለው እና የሚደረገው ስላልገባው ነው የሚለው አባባል በእራሱ ለሕዝብ ያለን የንቀት ደረጃ አመላካች ነው።በሰላማዊ ሰልፍ እጆቻቸውን ወደ ሰማይ እየሰቀሉ ድምፃቸውን ያሰሙ ታዳጊዎችን በጥይት አረር ከመቱ (እንደ አቶ ኃይለማርያም አነጋገር 'ካናገሩ') በኃላ አሁንም እናናግራለን እያሉ መዘባበት በእራሱ ህዝብን የአላዋቂነት ጥግ ነው።
በሌላ በኩል የሱዳን እና የኢትዮጵያን የድንበር ማካለል ጉዳይ ላይ የጀመሩበት አረፍተ ነገር እና በመካከል እና በመጨረሻ ላይ የደመደሙበት ንግግር ኢትዮጵያ በእዚህ አይነት ደረጃ የባዕዳንን ጉዳይ የሚያስፈፅም መንግስት ኖሯት እንደማያውቅ በግልፅ የሚያሳይ ነው።
''በመሬት ጉዳይ ላይ የተደረገ ድርድር የለም። በኢትዮጵያ እና በሱዳን መሃል ያለው ድንበር በደንብ ስላልተስተካከለ በእርሱ ላይ ነው እየሰራን ያለነው'' ካሉ በኃላ የሱዳን ጠቅላይ ሚንስትር የሚናገሩ እስኪመስል ድረስ የኢትዮጵያን ክብር በሚነካ መልኩ ሱዳንን እየረበሽን ያለነው የእኛ ገበሬዎች ናቸው።አሁን የሚያርሱት መሬት የሱዳን መሬት ነው ብለው ለመከራከር ሞክረዋል።ይህ ማለት ባጭሩ ኢትዮጵያውያን ለዘመናት ሲያርሱት የነበረው መሬት በእራሳቸው አገር ጠቅላይ ሚኒስትር መሬቱ የሱዳን ነው እየተባሉ ነው ማለት ነው።በተለይ የሱዳን ወታደሮች ለስራ በወሰዷቸው ኢትዮጵያውያን ላይ ባለፉት ሶስት ወራት ውስጥ ብቻ እጅግ አሰቃቂ በሆነ መንገድ ስለመገደላቸው አንዳች ያልተነፈሱት አቶ ኃይለማርያም ይልቁንም የኢትዮጵያን ገበሬዎች በሱዳን ተገብተው ሲወቅሱ እንዲህ ብለዋል-
''ከእኛ አካባቢ እየሄዱ ሱዳናውያንን እየገደሉ የሚመለሱ'' እንደሳቸው አገላለጥ ''ሽፍቶች''ናቸው ሲሉ ተደምጠዋል።በመቀጠል አቶ ኃይለማርያም እንዲህ አሉ: ''በርካታ ኪሎ ሜትሮች ሱዳን ውስጥ ገብተው የሚያርሱ እኛ የምናውቃቸው ኢትዮጵያውያን አርሶ አደሮች እና ባለሀብቶች አሉ'' በማለት እነኝህ መሬቶች ለጊዜው ለሱዳን አይሰጡ እንጂ የሱዳን መሆናቸውን ባረጋገጡበት ንግግራቸው በቀጣዩ የድንበር ማካለልም መንግስታቸው የሱዳን መሆናቸውን እንደሚያውቅ አሁንም እንደ ኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትርነት ሳይሆን እንደ ሱዳን ጠቅላይ ሚኒስትርነት ሲናገሩ ተደምጠዋል።
ባጠቃላይ ድንበሩን በተመለከተ ከተናገሩት መረዳት የሚቻለው ሁለት ጉዳይ ነው።አንዱ ኢትዮጵያ እና ሱዳን የድንበር ማካለል ሂደት ላይ ናቸው የሚለው ዜና ትክክል መሆኑን።በሁለተኛ ደረጃ ደግሞ አሁንም እንደ ኢትዮጵያዊ ጠቅላይ ሚኒስትር ሳይሆን በሱዳን ወገን ተገብተው የኢትዮጵያን ገበሬዎች እና ባለ ሀብቶች የሱዳንን መሬት አረሱ እያሉ ይህ መሬት ለሱዳን እንደሚገባ በአንደበታቸው ሲናገሩ ተሰምቷል።በሌላ አነጋገር ለብዙ ትውልዶች መሬቱን ሲያርሱ የነበሩ ኢትዮጵያውያን ከመሬታችን አንነቀልም ካሉ ከሱዳን ወታደሮች ጋር ተባብረው ገበሬዎቹን እና ባለ ሀብቶቹን የማባረር ሥራ እንደሚሰራ እየገለጡ ነው ማለት ነው።ምክንያቱም በአደባባይ መሬቱ የኢትዮጵያን አይደለም።ለጊዜው ነው ሱዳኖች የፈቀዱልን ካሉ በኃላ ይህንንም የሱዳን ውለታ መሆኑን ለኢትዮጵያ ሕዝብ ለማስረዳት ሲውተረተሩ ተሰምተዋል።
በመጨረሻም አቶ ኃይለማርያም ''በምግብ እራሳችንን ችለናል'' ብለው በተናገሩ በወራት ውስጥ በዛሬው እለት ደግሞ ካለ አንዳች እረፍት ''የገጠመን ድርቅ በታሪካችን ምናልባትም ባለፉት ሃምሳ ዓመታት ውስጥ አይተነው የማናውቅ በእኔ አመለካከት እጅግ የከፋ ድርቅ ነው'' ሲሉ ተደምጠዋል።ለድርቁ የሰጡት መፍትሄ ግን የበለጠ አስቂኝ ነው።መፍትሄዎቹ የሚመጡ እርዳታዎችን መቀበል እና የውሃ ጉድጓድ በመቆፈር ነው ይላሉ አቶ ኃይለማርያም።ጥያቄው ግን ከእሩብ ክ/ዘመን አምባገነናዊ እና የከፋፍለህ ግዛ የኢህአዴግ/ህወሓት አገዛዝ በኃላ ኢትዮጵያ በታሪክ ያላየችው ርሃብ ላይ ነች ማለት እና የውሃ እጥረት ችግር ለሆንባት አገር የውሃ ጉድጓድ መቆፈር መፍትሄ ነው ማለት ምን አይነት የአስተሳሰብ ድህነት ነው? የሚል ነው።ባጭሩ አቶ ኃይለማርያም ህወሃቶች ስልጣን እንዲለቁ እና የሽግግር መንግስት እንዲመሰረት ሿሚዎቻቸውን ቢመክሩ እና የመሸበት ቢያድሩ የተሻለ ነው።
ጉዳያችን GUDAYACHN