Friday, July 3, 2015

በህወሓት አገዛዝ እየተሰቃዩ ላሉ ወገኖቻችን ደህንነት የሚደረገው ዓለም አቀፍ ጫና ይቀጥል!

July 3, 2015
def-thumbከሣምንት በፊት የብሪታኒያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አቶ አንዳርጋቸው ጽጌን የሚመለከት አንድ መግለጫ አውጥቷል። በዚህ መግለጫው፣ አንዳርጋቸው ጽጌ ለአንድ ዓመት ሙሉ መሠረታዊ የሆኑ የታሳሪዎች መብት እንኳን ተነፍጎት ባልታወቀ እስር ቤት የሚገኝ መሆኑ እና በእንግሊዝ ባለሥልጣናትና በቤተሰቦቻቸው እንዲጠየቅ፣ ቋሚ የቆንስላና የህግ ምክር እንዲያገኝ በተደጋጋሚ የቀረበው ጥያቄ በወያኔ አገዛዝ ውድቅ መደረጉ በሁለቱ አገራት መካከል ያለው መልካም ግንኙነት የሚያሻክር መሆኑ ከወትሮው ጠንከር ባሉ ቃላት ገልጿል። አዲስ አበባ የሚገኘው የብሪታኒያ አምባሳደርም እንደዚሁ ከተለመደው ዲፕሎማሲያዊ ለስላሳነት ወጣ ያለ ያለ መግለጫ አዲስ አበባ ውስጥ ለሚታተመው ሪፓርተር ጋዜጣ ሰጥቷል። እነዚህ የሰሞኑ የእንግሊዝ መንግሥት መግለጫዎች በቀና የሚታዩ ቢሆንም የብሪታኒያ መንግሥት ማድረግ ይገባው ከነበረው እና ማድረግ ከሚችለው አንፃር ሲታይ ብዙ ይቀረዋል። የአውሮፓ ኅብረት የአቶ አንዳርጋቸው ጽጌ ጉዳይ በተደጋጋሚ አንስቷል። የተባበሩት መንግሥታትም የአቶ አንዳርጋቸው ጽጌ አያያዝ ጉዳይ ምርመራ እንዲደረግበት እንቅስቃሴ ጀምሯል። ከላይ የተዘረዘሩት ኩነቶች፣ በመላው ዓለም የሚገኙ ኢትዮጵያዊያን ያለሟቋረጥ የሚያደርጉት ውትወታ ውጤት እያመጣ መሆኑ ያሳያል። ይህ ጥረት ለወደፊቱም ተጠናክሮ መቀጠል ይኖርበታል።
በሌላ በኩል ደግሞ ኢትዮጵያ ውስጥ “አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ አስልጥኖ አሰማርቷችኋል” ተብለው እንደተለመደው በሀሰት የተከሰሱ ወገኖቻችን “አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ ኢትዮጵያ ውስጥ ስለሚገኙ መከላከያ ምስክር እንዲሆኑን ይታዘዝልን“ ብለው ሲጠይቁ ዳኛ ተብየው “የት እንደሚገኙ የማይታወቁ ሰውን በመከላከያ ምስክርነት ማቅረብ ይከብዳል” ብሎ ሲናገር ተደምጧል። አቶ አንዳርጋቸው ለምስክርነት ይቅረብ አይቅረብ ብይን ሊሰጥበት ቀጠሮ ተይዟል።
አርበኞች ግንቦት 7፡ የአንድነትና ዲሞክራሲ ንቅናቄ፣ የነፃነት አርበኛው የአቶ አንዳርጋቸው ጽጌ የእስር አያያዝ ሁኔታ ዓለም ዓቀፍ የዲፕሎማሲ አጀንዳ በሆነበት በዚህ ወቅት በህወሓት አገዛዝ በተሾመ ዳኛ “የት እንደሚገኙ የማይታወቁ” መባሉ አሳሳቢ ጉዳይ አድርጎ ይመለከተዋል። አርበኞች ግንቦት 7፣ በመላው ዓለም የሚገኙ ኢትዮጵያዊያን የተከሳሾች፣ የአቃቤ ህጉና የዳኛው ምልልስ ለተባበሩት መንግሥታት፣ ለአውሮፓ ኅብረትና ለእንግሊዝ መንግሥት እንዲደርስ እንዲያደርጉም ያሳስባል።
አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ ብቻ ሳይሆን በህወሓት እስርቤቶችና ከእስር ቤቶች ውጭ ባልታውቁ ቦታዎች ታስረው እየተሰቃዩ የሚገኙ ወገኖቻችን ሁሉ እና መላው የኢትዮጵያ ሕዝብ ነፃ የሚወጣው፣ ኢትዮጵያዊያን በሚያደርጉት ሁለገብ ትግል ነው ብሎ አርበኞች ግንቦት 7 ያምናል። ስለሆነም ራሳችንን፣ ወገኖቻችንና አገራችን ነፃ ለማውጣት የምናደርገው ትግል ማጠናከር ግዴታችን ነው። እኛ ራሳችን እንጂ ማንም ነፃነታችንን አያጎናጽፈልንም።
ይህ እንዳለ ሆኖ ግን የህወሓትን እኩይ ተግባራት በዓለም አደባባዮች ማጋለጥ፤ የህወሓት አገዛዝን ወዳጅ ማሳጣት እና በእስር ላይ የሚገኙ ወገኖቻችንን ደህነት የሚያሻሽሉ ተጽዕኖዎችን መፍጠር እጅግ አስፈላጊ ተግባር በመሆኑ፣ በመላው ዓለም የሚገኙ ኢትዮጵያዊያን፣ በህወሓት እጅ ለወደቁ ወገኖቻችን ድጋፍ የሚያሰሙትን ድጋፍ አጠናክረው እንዲቀጥሉ ያሳስባል።
ድል ለኢትዮጵያ ሕዝብ!!!

Thursday, July 2, 2015

Ethiopia: Respect court rulings and release opposition members

July2, 2015
Amnesty International
Semayawi party members have been rearrested repeatedly
Woyneshet Molla (left), Ermias Tsegaye, Daniel Tesfaye(right) and Betelehem Akalework( not in the picture) have been rearrested repeatedly on the same charges.
Ethiopian authorities must stop harassing two men and two women linked to the opposition Semayawi (Blue) Party, and immediately release them from detention, Amnesty International said as they were expected to face fresh charges in court today in the capital Addis Ababa.
“On five separate occasions over the course of the last 10 days, three different courts have ordered the police to release these four people,” said Michelle Kagari, Deputy Regional Director for East Africa, the Horn and Great Lakes. “Their continued detention is blatantly unlawful and in clear violation of their rights to liberty and a fair trial.”
Woyneshet Molla, Ermias Tsegaye, Daniel Tesfaye and Betelehem Akalework were arrested in April this year and charged with inciting violence during a rally in the capital. They remained in custody awaiting trial. The four were convicted at the Federal First Instance Criminal Court at Kirkos on 22 June 2015 and sentenced to two months in prison. The judge however ordered their immediate release on the basis that they had already served their time, but the police ignored court orders and returned them to Kality and Kilinto prisons.
They were released the following morning, but police and security officials immediately re-arrested the four without a warrant and brought them to Kasanchiz 6th police station. On 25 June, they were presented on the same charges before the same judge that had ordered their release. He dismissed the case and again ordered their immediate release but the police did not comply and instead unsuccessfully sought to have another judge in the same court accept the case.
The following day the police brought the four before a new judge at Keraa Federal First Instance Court, on new charges of threatening witnesses to their original case. In a hearing on 30 June the court accepted the case, but ordered that the accused be released on bail pending the case’s resumption today. Again, the police disregarded court orders and the four remain in custody.
Separately, the Federal High Court Lideta Branch on 29 June accepted to hear the public prosecutor’s appeal against the original verdict, but refused their request to keep the four in custody. The appeal has been adjourned until 3 July.
“This charade must come to a halt. These four men and women have already served their jail term. This blatant disregard for judicial orders, and attempts to press fresh charges amounts to persecution, and takes harassment and intimidation to new heights,” said Michelle Kagari.
“By keeping Woyneshet Molla, Ermias Tsegaye, Daniel Tesfaye and Betelehem Akalework in detention, the Ethiopian authorities are undermining the credibility and authority of the court process and eroding the rule of law. They must stop harassing opposition members and ensure that the right to a fair trial is upheld.”

Wednesday, July 1, 2015

አለም አቀፍ ድጋፍ የተቸረው “ልማታዊ” አንባገነናዊነት በኢትዮጵያ

July2,2015
Time_oppress_FLAT.JPG

“የአፍሪቃ ድሃ ባይጠግብም እንኳ ቀምሶ ካደረ ይበቃዋል” አይነት ንቀት የተሞላው የምዕራቡ አለም ምልከታ ከመቼውም ጊዜ በከፋ መልኩ አፍጦና አግጦ እየታየ ነው፡፡ በርሃባችንና በእርስ በእርስ መናቆራችን ለዘመናት ሲነግዱበትም ሲማረሩበትም ቆይተዋል፡፡ ዛሬ ዛሬ የመጫወቻው ካርድ ተቀይሮ ለአፍሪቃ አንባገነኖች አንድ ቃል ተለጥፎላቸው ካሳላፍነው ታሪክ ምናልባትም በከፋ መልኩ ጉዟችንን ቀጥለናል፤ የኋሊት ይሁን ወደፊት እርግጠኛ አይደለሁም፡፡ ነገር ግን የምዕራቡ አለም “ልማታዊ” በሚል ካባ የተከናነበውን የለየለት አንባገነናዊነት ሙሉ ድጋፋቸውን እየሰጡ ለመሆኑ የኦባማን የኢትዮጵያ ጉዞ ጨምሮ በርካታ ምልክቶችን እያየን ነው፡፡ ከምርጫው በፊትም ሆነ ከተጠናቀቀ በኋላ የአውሮፓ ኅብረትና የአሜሪካን መንግስት ያሳዩትም ድጋፍ የእዚሁ መገለጫ ነው፡፡

በአፋኝ አገዛዝ ውስጥ ላለ ሕዝብ ዲሞክራሲን፣ ሰብአዊ መብቶችን፣ ፍትሕን እና የሕግ የበላይነትን ለማረጋገጥ የሚደረግ ድጋፍ ለተራበ ሕዝብ ስንዴና ዘይትን እንደመርዳት ቀላል አይደለም፡፡ እህል ተርፏቸው ወደ ባሕር የሚጨምሩ አገሮች የተራበ ሲያገኙ የተረፋቸውን መወርወራቸው አንድም እርዳታ በመስጠትና ለጋሽ በመሆን የሚገኝው የመንፈስ እርካታና በዋነኝነት ደግሞ የተጠኑ ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ ትርፎችም አሉት፡፡ ዞሮ ዞሮ ግን ላለፉት አስርት አመታት በርካታ የአፍሪቃ አገራት፤ የኛዋ አገር ደግሞ በግናባር ቀደምነትነት የዚህ የእህልና የገንዘብ ድጎማ ተጠቃሚ ሆና ቆይታለች፡፡ በዚህ የቁስ እርዳታ ማን እንዳተረፈ በጥልቅ መመርመር የግድ ይላል፡፡ በእርግጠኝነት ግን መናገር የሚቻለው አገርንና ሕዝብን ለውርደት የዳረገና ክፉ የታሪክ ጠባሳም መሆኑን ነው፡፡ ዘንድሮ ስንዴና ዘይት የሚላክለት ድሃ ሕዝብ ያለችውን ቅሪት እየሸጠ በርሃና ባሕር አቋርጦ በራሱ ጥረት “ምና አደከማችሁ እኔ እዛው እምጣለሁ” ብሎ ለጋሾቹ ደጃፍ ደርሷል፡፡ ለዚህም በየአመቱ ከኢትዮጰያ፣ ከኤርትራ፣ ከሱዳን እና ከሱማሌ የሚሰደደው ሕዝብ ጥሩ ማሳያ ነው፡፡ የምዕራቡ አለም እርዳታውን በመርከብ ከማጓጓዝ ሳይድን አልቀረም፡፡ ስንዴ የሚጭኑ መርከቦች ሽብርን ለመዋጋት በሚል ሽፋን የጦር መሳሪያ በማጓጓዝ ስራ የተጠመዱ ይመስለኛል፡፡

ዛሬ ላይ የቻይና ቢዝነስ ተኮር ወረራ ያስደነበራቸው የምዕራቡ አለም አገራት የአፍሪቃን አንባገነኖች ከነ ወንጀሎቻቸውና ስንክሳራቸው ተቀበለው አብረው ለመዝለቅ የተገደዱበትና መለማመጥ የጀመሩበት ሁኔታ ነው የሚታየው፡፡ “ልማት” እና “ደህንነት” (security) ብቸኛዎቹ የምዕራቡና የአፍሪቃ አንባገነኖች የመወያያና የመደራደሪያ አጀንዳዎች ሆነዋል፡፡ ሰብአዊ መብቶች፣ ዲሞክራሲንና የሕግ የበላይነትን በዋነኝነት ያነሱ የነበሩት አውሮፓዊያን ሳይቀሩ እነዚህን አጀንዳዎች ወደጎን የገፉዋቸው መሆኑን በግልጽ እየታየ ነው፡፡ ለዚህም በኢትዮጵያ የ2007 ምርጫ ዙሪያ ያሳዩት የዳር ተመልካችነት ሚና እና ከምርጫውም በኋላ የሰጡዋቸው መግለጫዎች በግልጽ እንደሚያሳዩት ሁሉን ነገር ወደ ጎን ተትው “ሰላም” በሚለው አጀንዳ ላይ ብቻ ያተኮሩ ናቸው፡፡ ምርጫው በሰላማዊ መንገድ በመጠናቀቁ የተሰማቸውን ደስታ በመግለጽ ከ”ልማታዊው” አንባገነናዊ ሥርዓት ጋር ያላቸውን ጥብቁ ቁርኝት አድሰው እንደሚቀጥሉ በግልጽ የሚያሳየውን የአጋርነት መግለጫቸውን አንብበናል፡፡

በአገዛዝ ሥርዓቱና በአለም አቀፉ ማኅበረሰብ መካከል፤ የአፍሪቃ ኅብረቱንም ጨምሮ በኢትዮጵያ ምርጫ ላይ ቀደም ብሎ የተደረሰበት አንድ አይነት ስምምነት እንዳለ የሚያሳየው የምርጫ ቦርድና ገዢውን ቡድን ጨምሮ ሁሉም መፈክራቸው “ምርጫዉ ሰላማዊ በሆነ መልኩ ተጠናቋል” የሚል ነበር:: ይህ መሪ መፈክር ተደጋግሞ በሁሉም ሚዲያዎችም እነቪኦኤን ጨምሮ እስክንደነቁር ድረስ ሲነገርን ቆይቷል፡፡ ይህ ሆን ተብሎ ቅድመ ሥራ የተሰራበት ነገር ስለመሆኑ ምንም አያጠራጥርም፡፡ አንደኛ ሰላም ባለበት አገር ልክ ምርጫውን ተከትሎ አንዳች የመተላለቅ ዳመና እንዳንጃበበ ተደርጎ የተሰራው ዘገባ ሁሉ ሕዝቡ ስጋት ውስጥ እንዲገባና እንዲሸበር አድርጎታል፡፡ ይህ ተንኮል ያልገባውና ቀላል ግምት የማይሰጠው ሕዝብም ሊመጣ ይችላል ከተባለው አደጋ እንኳን ወያኔ አንዳች ኃይል ያለው ሰይጣንም ቢያስጥለው አይጠላም፡፡ ይህም ሆን ተብሎ የተቀነባበረ ነገር ነው፡፡ የሌለን ነገር እንዳለ አድርጎ ፈጥሮ ሕዝብን ማስጨነቅና ማስሸበር የተፈለገበት ዋነኛ አላማም የገዢውን ኃይል ብቸኛ የሰላም አስከባሪ አካል አድርጎ ሕዝብ እንዲያየውና ወያኔ ከሌለ ያልቅልናል የሚል ስጋት በብዙዎች ዘንድ እንዲፈጠር አድርጓል:: ይህ ደግሞ ከአመታት በፊት ቀድሞ የተወሰነና የምዕራቡንም አለም ቅቡልነት ያገኘውን የገዢውን ቡድን በስልጣን የመቆየት እቅድና ሕዝብ ባይዋጥለትም ሳያንገራግር እንዲቀበል ለማደረግ ቀላሉና ብቸኛው መንገድ ነበር፡፡ ስለሆነም “ነጻና ፍትሐዊነት” በምንም መልኩ የዚህ ምርጫ መሪ መፈክር አልነበሩም፡፡ ወያኔም ይህን ለማሟላት ዝግጁ አይደለም፡፡ ስለዚህ ምርጫውን ተከትሎ አንዳች የመተላለቅ አደጋ እንዳንጃበበ አድርጎ የማቅረቡ ፋይዳ ለወያኔም ሆነ ለምዕራቡ አለም ብቸኛው የማደናገሪያ ካርድና የመውጫ ቀዳዳ ነበር፡፡

ድምጽ በሚሰጥበት ዕለት እንኳን በርካታ የተቃዋሚ ፓርቲ አባላት፣ ዕጩዎችና ደጋፊዎቻቸው ሲጉላሉ፣ ሲደበደቡ፣ ሲታሰሩና አልፎም በአንዳንድ ቦታዎች ሲገደሉ የበርካታ ሚዲያዎች፣ የአፍሪቃ ሕብረት ታዛቢዎችና አለም አቀፍ ሚዲያዎች ሳይቀሩ አንድ አይነት ነጠላ ዜማ ነበር የሚያዜሙት፤ “የምርጫው ሂደት ሰላማዊ ነው፡፡ … በሰላምም ተጠናቋል፣ ወዘተ…”፡፡ ይህ ከላይ እንዳልኩት አንድም የአገዛዝ ሥርአቱን ብቃትና ጥንካሬ ለማጉላት ያለው ብቸኛ መንገድ ስለሆነ በሌላ መልኩም ቀድሞ የተዶለተበትንና አለም አቀፍ ቅቡልነት ያገኘውን በምርጫ ስም የአንባገነን ሥርዓቱን የአገዛዝ ዘመን የማደስ ስልት ለመሸፈን የተደረገ የትብብር ዘመቻ ነው፡፡

ምርጫ የዜጎች ዲሞክራሲያዊ መብቶችና ነጻነቶች ከሚረጋገጡባቸው መንገዶቹ አንዱ ነው፡፡ ልማት ደግሞ የአንድ አገር ሕዝብ ኢኮኖሚያዊና ማኅበራዊ መበቶች በተሟላ መልኩ እንዲረጋገጡ የሚያስችል ሌላው መንገድ ነው፡፡ ልማትና ዲሞክራሲ ተጣጥመው በሚሄዱበት ስፍራ ሁሉ ማህበራዊ ፍትሕም ይሰፍናል፣ ዘላቂና አስተማማኝ ሰላምም ይኖራል፡፡ ለዚህም ነው በተባበሩት መንግስታት የሰብአዊ መብቶች ድንጋጌ ውስጥ በሁለት ማዕቀፍ የተቀመጡት መብትና ነጻነቶች፤ የሲቪልና የፖለቲካ እንዲሁም የኢኮኖሚ፣ የማኅበራዊና የባሕላዊ መበቶች ሳይነጣጠሉ መተርጎምና መከብር እንዳለባቸው የተደነገገው:: ይሁንና ለድሃ አገራት ስንዴና ዘይት እየረዳ ስለ ሰብአዊ መብቶችና ነጻነቶች መከበር ካንገት በላይም ቢሆን ይሟገት የነበረው የምዕራቡ አለም ‘ድሃ በል’ በሆነው የገበያ መርህና በግሎባላይዜሽን ስም የዝርፊያ ጋሪውን አስቀድሞ ዜማውን በመቀየር ከ”ልማታዊ” አንባገነኖች ጋር ተስማምቶ የእጃዙር ቅኝ ግዛት መረቡን አፍሪቃ ላይ ጥሏል፡፡ እኛንም ከገዢዎቻችሁ የተራረፈውን ቀምሳችሁ ማደር ከቻላችሁ ዲሞክራሲንና ሰብአዊ መብቶችን ቀስ ብላችሁ በመቶ አመት ሂደት ትቀዳጃላችሁና ተረጋጉ እያሉን ነው፡፡ ለጊዜው አለማችን እኛው በፈጠርናቸው ሽብርተኞች ተወጥራለችና እጃቸው ከመውደቋ በፊት እነሱን ለማጥፋት እንተባበር እያሉን ነው፡፡ እንግዲህ የሚበጀንን እንምረጥ::

በቸር እንሰንብት!

ከያሬድ ኃይለማርያም
ሰኔ 16፣ 2007 ዓ.ም. ከብራስልስ
yhailema@gmail.com


Tuesday, June 30, 2015

ህወሃት/ኢህአዴግ በሰማእታት በአል ቀን መነገድ አይችልም!!

June30,2015
ህወሃት/ ኢህአዴግ በሰማእታት ስምና በጀግኖች ሰማእታት ቤተሰቦች እየነገደ በራሱ ጥቅም አስተሳሰብ ብቻ ተጠምዶ መንቀሳቀስ ከጀመረ እንሆ 24 ዓመታት አስቆጥሯል። የህወሃት/ማሌሊት ካድሬዎች በየአመቱ ሰኔ 15 ቀን በትግራይ ክልል ደረጃ የሰማእታት ቀን ብለው በመዘከር የአዞ እንባ ቢያነቡም ሃቁ ግን አስመሳይነታቸውን ይበልጥ አጉልቶ ያሳየና፣ በተለይ ለትግራይ ህዝብ ባጠቃላይ ደግሞ ለመላው የኢትዮጵያ ህዝብ አፍነውና አደናግረው ለመያዝ እየተጠቀሙበት ያለ ብልሃት መሆኑ ሲበዛ ግልፅ ነው።
የትግራይ ህዝብ ልጆቹን ወደ ትግል መርቆ ሲልክ፣ በላዩ ላይ የጭቆናው ግፍ ሲፈፅም የነበረውን ፍሽስታዊ የደርግ ስርዓት አስወግዶ ከኢትዮጵያ   ብሄር ብሄረሰቦችበ ጋር መብቱ ተከብሮለት ብሰላም አብሮ ለመኖርና   ኮርቶ የሚኖርባት አገር ለማየት ከነበረው ፍላጎት ነበር፣ ነገር ግን በህወሃት ማሌሊት ከሃድያን አመራሮች ምኞቱ ሊሳካ አልቻለም።
ህወሃት ማሌሊትና ስርአቱን የሚመሩት የበላይ ባለስልጣኖች፣ የህዝብና የሃገር ገንዘብ በመዝረፍ ያሰባሰቡት ሃብት ተጠቅመው ራሳቸውና ቤተሰቦቻቸው ሲፈነጥዙበት፣ የሰማእታት ወላጆች ግን ደጋፊና ጧሪ አጥቶው በከፋ ችግር ስኖሩ በሰማእታት ደም እየነገዱ ያሉት ባለስልጣኖች ግን በተጓዳኝ፣ በምንም ዓይነት ድንጋጤ አልተሰማቸውም ብቻ ሳይሆን፣ በሰማእታት ላይ ያላቸው ክዳትና ጭካኔ በሚያሳዝን ሁኔታ እየቀለዱ ይኖራሉ።
ህወሃት/ኢህአዴግ ባለፈው ግንቦት 16/2007 ዓ/ም ያካሄደው ፍፁም ፍትሃዊ ያልሆነ ምርጫ፣ “ዝሆን ቂጡን ተማምኖ ግንድ ይውጣል እንደሚባለው ” የስርዓቱ መሪዎች በሚያወርዱት ቀጥታዊ ትእዛዝ፣ በንጹሁ ህዝብ ላይ ታጣቂዎቻቸው የተለያዩ ተፅእኖዎች፤ ድብደባና የመግደል እርምጃዎች እየወሰዱ ባሉበት ግዜ፣ የተካሄደውን አስመሳይና የተጭበረበረ ምርጫ፣ የሰኔ 15 የሰማእታት ቀን ውጤት ነው ማለታቸው፣ አሁንም ባገራችን ውስጥ እውነተኛው የዴሞክራሲ ስርዓት ለማምጣት ብለው ውድ ህይወታቸውን በከፈሉ ሰማእታት ላይ መቀለድ ከመሆን አልፎ፣ ሌላ ትርጉም የሚያሰጠው አይደለም።
ፀረ ህዝብ የህወሃት ኢህአዴግ ስርዓት ባለፉት 24 የአገዛዝ ስልጣኑ፣ የመፃፍ፤ የመናገርና የመደራጀት መብት መከልከሉ፤ በተለያዩ የተቃዋሚ ድርጅት አመራሮችና አባሎቻቸው ላይ አሰቃቂ በደሎች እየፈጸመ በሚገኝበት ወቅት ዴሞክራሲ ለመገንባት ጥረት እያደረግን ነን ቢልም የኢትዮጵያ ህዝብ ግን ፍትህና መልካም አስተዳደር ማየት አልቻለም ብቻ ሳይሆን፣ እስከ አሁንን የተካሄደውን አስመሳይ ምርጫ በጠበንጃ አፈሙዝ ታጅቦና የተለያዩ ተንኮሎች ተዘጋጅቶበት የንፁሃን ዜጎወቻችንን ደም የፈሰስበትን ፍፁም ኢ-ዴሞክራሲያዊ በሆነ መንገድ ለተገባደዱት በሰማእታት ቀን ሰኔ 15 ለመነገድ እንደማይችል መታወቅ አለበት።

Monday, June 29, 2015

እነ ወይንሸት ሞላ ይግባኝ ተጠየቀባቸው

 June29,2015
በነገረ ኢትዮጵያ ሪፖርተር
መንግስት አይ.ኤስ.አይ.ኤስን ለመቃወም በጠራው ሰልፍ ሰበብ እስር ላይ ቆይተው ሰኔ 15/2007 ዓ.ም በቄራ ፍርድ ቤት በዋለው ችሎት እንዲፈቱ ተወስኖላቸው ሰኔ 16/2007 ዓ.ም ከእስር ቤት ሲወጡ እንደገና በፖሊስ ተይዘው የታሰሩት ወንይሸት ሞላ፣ ኤርሚያስ ፀጋዬ፣ ዳንኤል ተስፋዬና ቤትሄልየም አካለወርቅ ዛሬ ሰኔ 22/2007 ልደታ ፍርድ ቤት 11ኛ ምድብ ችሎት ቀርበው ቀደም ሲል ‹‹ሁከትና ብጥብጥ አስነስተዋል›› በሚል በተከሰሱበትና ከእስር በተለቀቁበት ክስ ላይ ይግባኝ ተጠየቀባቸው፡፡
አቃቤ ህግ እነ ወይንሸት የዋስትና መብታቸውን ተነጥቀው ጉዳያቸውን ማረሚያ ቤት ሆነው እንዲከታተሉ የጠየቀ ቢሆንም ዳኛዋ ‹‹በተከሰሱበት ጉዳይ ላይ ከእስር የተፈቱ በመሆናቸው ዋስትና ሊከለከሉ አይገባም፡፡›› ብለዋል፡፡ ዳኛዋ እነ ወይንሸት እንደተለቀቁ እንጅ በእስር ላይ መሆናቸውን እንደማያውቁ ገልጸው 3 ወር ተፈርዶበት ቂሊንጦ የሚገኘው ማስተዋል ፈቃዱ ባለመቅረቡ፣ ከእሱ ጋር ረቡዕ ሰኔ 24/2007 ዓ.ም ቀርበው ክርክር እንዲጀምሩ ቀጠሮ ሰጥተዋል፡፡ ሰኞ ሰኔ 29/2007 ዓ.ም ውሳኔ እንደሚሰጡም አሳውቀዋል፡፡
ሰኔ 15/2007 ዓ.ም በዋለው ችሎት ኤርሚያስ ፀጋዬ በነፃ፣ እንዲሁም ወይንሸት ሞላና ዳንኤል ተስፋዬ ሁለት ወር እስር ተወስኖባቸው ሁለት ወር በመታሰራቸው እንዲፈቱ ተፈርዶላቸው ከእስር ሲለቀቁ እስር ቤት በር ላይ በፖሊስ ተይዘው ወደ 6ኛ ፖሊስ ጣቢያ መዛወራቸው ይታወቃል፡፡ ወይንሸት፣ ኤርሚያስና ዳንኤል ሰኔ 19/2007 ዓ.ም በቄራ መጀመሪያ ፍርድ ቤት ቀርበው ፖሊስ ‹‹ከእስ እንዲለቀቁ በተወሰነላቸው ወቅት ምስክሮችና የምስክሮቹ ጓደኞች ላይ ዛቻና ማስፈራሪያ አድርሰውብኛል›› የሚል አዲስ ክስ አቅርቦባቸው 6ኛ ፖሊስ ጣቢያ ታስረው ይገኛሉ፡፡ በዚህ አዲስ ክስ ላይ የፖሊስን ምስክር ለመስማት ነገ ሰኔ 23/2007 ቄራ ፍርድ ቤት ይቀርባሉ፡፡

Saturday, June 27, 2015

ሙሱናን እንደባህል የሚጠቀሙ መሪዎች! የኢኮኖሚ እድገት አያረጋግጡም!!

 June 27,2015

የኢህአዴግ መሪዎች የህዝቡን የኑሮ ደረጃ በእጥፍ እንደጨመረ አስመስለው ቢናገሩም ሃቁ ግን በተቃራኒው አሰከፊ የኑሮ ደረጃ ከቀን ወደ ቀን እየጨመረና ህዝቡ በድህነት አለንጋ እየተገረፈ ያለበት ሁኔታ ነው ያለው። ከ 24 ዓመት በፊት በቀን ሦስት ግዜ ትመገባለህ ተብሎ ቃል የተገባለትድሃው ህዝብ እስካሁን ድረስ ራሱን መቻል አቅቶት እርዳታ ጠባቂ ሆኖ ሂወቱ ለመምራት ተገዷል።
በአሁኑ ወቅት በመንግስት ስራ ተቀጥሮ የሚሰራው ሲቪል አገልግሎት ሰጪም ቢሆን ምሳ በልቶ ራት የማያገኝ፤ ቁርስ በልቶ ምሳ የማይበላ እጅግ በርካታ ህዝብ መኖሩን የሚካድ አይደለም፣ የሸቀጦች ዋጋ እጅግ በመጨመሩ፤ የሚኖርበት የቤት ኪራይ ዋጋ ከሚከፈለው ደመወዙ ጋር የሚመጣጠን ስላልሆነ በርካሽ ዋጋ ለማግኘት ብሎ ወደ ከተማው ጫፍ እየሄደ ደረጃቸው በወረዱ መኖርያ ቤቶች ውስጥ የሚኖረው ወገን እጅግ በርካታ ነው።
በእርግጥ የኢህአዴግ መሬዎችና አጃቢዎቻቸው ኑሮአቸው ተሻሽለዋል፤ አይተውት የማያውቁት አፓርታማዎች አሰርቷል። እነሱ ከሚኖሩበት ዘመናዊ መኖርያ ቤት ውጭ ለውጭ ዜጎች እያከራዩ በሚልዮን የሚገመት ገንዘብ ውጭ በሚገኙ ባንኮች የሚያስቀሙጥበት ሁኔታ ነው ያለው።
ባለፈው ወር የፀደቀው የአገሪቱ አጠቃላይ የ 2008 ዓ/ም በጀት እጅግ በሚያስገርም ሁኔታ ካለፈው ዓመት ትልቁን የሃገሪቱ በጀት ለመከላከያና ለደህንነት ተመድበዋል፣ ይህ በጀት በሰራዊቱ ደመወዝ ላይ ለውጥ ያመጣበት መንገድም የለም፣ በመሆኑም የተመደበው በጀት ለመሳርያዎች ግዢ፤ ንፁሃን ሰዎችን ለማፈን፤ የህዝቡን ሰብአዊና ዴሞክራሲያዊ መብት ለማኮላሸትና የሰራዊቱ አዛዦችን የተንደላቀቀ ሂወት እንዲያሳልፉበት ተብሎ የሚባክን ሃብት ነው።
ባሁኑ ግዜ አገራችን ለዜጎቿ የምትጠቅም ሳትሆን ለውጭ ዜጎች የምትመችና በርካታ የውጭ ባለሃብቶች በኢንቨስትመንት ምክንያት በርካሽ ዋጋ መሬት እያከራዩና እዚህ ግባ በማይባል ዋጋ የህዝቡን ጉልበት እየበዘበዙ እንደ ፈለጉ ተንደላቅቀው እንዲኖሩና ከፍተኛ ሃብት እንዲሰበስቡ እድሉ ተፈጥሮላቿል። እነዚህ የውጭ ባለሃብቶች ከውጭ የሚያስገቡትን ከፍተኛ ንብረት ኢንቨስተሮችን ለማነሳሳት ተብሎ ተገቢ ግብርና ታክስ እንዲከፍሉ አይደረግም። ኑሮውን ከእጅ ወደ አፍ የሆነው ጭቁኑ ህዝቡ ግን እዚህ ግባ የማይባሉ የንግድ ስራዎች በሚጀምርበት ግዜ ከገቢው ጋር የማይመጣጠን ከፍተኛ ግብር እንዲከፍል ስለሚገደድ እጅና እግሩ አስሮ እንዲቀመጥና ከስራ ውጭ እንዲሆን ተፈርዶበታል።
በሌላ መንገድ ከለጋሽ ሃገሮች የሚመጣ ብድርና እርዳት ተስፋ ተደርጎ የሚገኘውን በጀት። ወደ ልማት ስራዎች ከማዋል ይልቅ ከፍተኛ ገንዘብ በሙሱና መልክ ወደ አመራሮቹ ኪስ እንዲገባ ይደረጋል። ሙሱና ዋነኛውና የማይድን የኢህአዴግ በሽታ መሆኑ የስርዓቱ ከፍተኛ አመራሮች በተለያዩ መድረኮች አምኖውበት ያለፉ የተረጋገጠ ጉዳይ’ዩ።
የአገራችን አብዛኛው በጀት በልማት ስራዎች መዋል ሲገባው ከኢንተርፖል ጋር ተሳስሮ ስርዓቱን የሚቃወሙ ሰዎች ወንጀሎኞች እንደሆኑ አስመስሎ መረጃ በማስተላለና ግለሰቦችን ለመያዝ በሚልዮን የሚገመት ገንዘብ ወጪ በማድረግ፤ ሃቀኛ የሆነ መረጃ የሚያስተላልፉትና የስርዓቱ ብልሹ አሰራርን የሚያጋልጡት የብዙሃን መገናኛዎች በሚልዮን የሚገመት ያገሪቱን ሃብት በማፍሰስ፤ የአገራችን ኢኮኖሚ እድገትና ኑሮ ሊሻሻል የሚችልበት አጋጣሚ ሊኖር አይችልም፣ እናም! በህዝባችን ኑሮ ላይ ለውጥና እድገት ሊረጋገጥ ከተፈለገ ፀረ ልማትና እድገት የሆነው የኢህአዴግ ስርዓት በህዝቡ ትግል ሲገረሰስ ብቻ እንደሆነ አውቀን ለማይቀረው ድል ትጥቃችን አጠናክረን መቀጠል ይገባናል።

5 የአጋዚ ክፍለጦር አባላት ኤርትራ ገብተው የአማራ ዴሞክራሲያዊ ሃይል ንቅናቄን ተቀላቀሉ

June27, 2015

(ዘ-ሐበሻ) የአማራ ብሔር ተወላጆች የሆኑ 5 የአጋዚ ጦር አባላት የነበሩ የስርዓቱ ታጋዮች የሕወሓትን መንግስት በመክዳት አስመራ ገቡ:: እነዚሁ 5 ታጋዮች ኤርትራ የሚገኘውን የአማራ ዴሞክራሲያዊ ሃይል ንቅናቄን ተቀላቅለዋል:: ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በሰላማዊ ትግል ይታገሉ የነበሩም ሆነ የሕወሓት ጦርን ሲያገለግሉ የነበሩ በርካታ ወጣቶች የትጥቅ ትግሉን በመምረጥ ወደ ኤርትራ በመሄድ የአማራ ዴሞክራሲያዊ ሃይል ንቅናቄን እየተቀላቀሉ መሆኑን ለዘ-ሐበሻ የሚደርሱ መረጃዎች ያመለክታሉ:: ሰሞኑን ይህንኑ ንቅናቄ የተቀላቀሉት 5ቶ የአጋዚ ጦር አባላት
1ኛ. ግራማ ተላይነሕ
2ኛ. ሄኖክ እንዳልካቸው
3ኛ ስለሺ ተስፋሁን
4ኛ. ምርት ይሁን መንገሻ
5ኛ ስማቸው ካሴ ይባላሉ። 

Saturday, June 20, 2015

የሰማያዊ ፓርቲ ከፍተኛ አመራሮችና አባላት ከሳሙኤል አወቀ ለቅሶ እንዳይደርሱ ታገዱ

June 20,2015
የሰማያዊ ፓርቲ ከፍተኛ አመራሮችና አባላት ከሳሙኤል አወቀ ለቅሶ እንዳይደርሱ ታገዱ
• ከአዲስ አበባ ወደ ጎጃም ለሌላ ለቅሶ በመሄድ ላይ የነበሩ ዜጎች ተደብድበው ተመልሰዋል


በነገረ ኢትዮጵያ ሪፖርተር

የሰማያዊ ፓርቲ ከፍተኛ አመራሮችና አባላት ሰኔ 8/2007 ዓ.ም ደብረማርቆስ ከተማ የተገደለው የሳሙኤል አወቀ ለቅሶ እንዳይደርሱ ታገዱ፡፡ አመራሮቹና አባላቱ ዛሬ ሰኔ 13/2007 ዓ.ም በጠዋት ከአዲስ አበባ ተነስተው የሳሙኤል አቀወ ቤተሰቦች ወደሚገኙበት ምስራቅ ጎጃም ዞን ግንደወይን እያቀኑ በነበረበት ወቅት አባይ ድልድይ ላይ በፌደራል ፖሊስ ታፍነው ከቀኑ 8 ሰዓት ጀምሮ ጎሃ ፂዮን ከተማ ውስጥ እስከ ምሽቱ 2 ተኩል ድረስ ታግተው ውለዋል፡፡ የሰማያዊ ፓርቲ አመራሮችና አባላትን ወደ ለቅሶ እንዳይሄዱ ያገዱት ከአዲስ አበባ የሄዱና ከቦታው ተዘጋጅተው ሲጠብቁ የነበሩ የፌደራል ፖሊሶች እንደሆኑ ለማወቅ ተችሏል፡፡

አመራሮቹና አባላቱ ለፖሊስ ቃል ሲሰጡ ከሳሙኤል አወቀ ጋር የነበራቸውን ግንኙነት፣ በፓርቲው ውስጥ ያላቸውን ኃላፊነት፣ ሳሙኤልን ማን እንደገደለው የሚመለከቱ ጥያቄዎች ቀርበውላቸዋል፡፡ ለቅሶ እንዳይደርሱ ከተከለከሉትና ታተው የዋሉት
1. ኢ/ር ይልቃል ጌትነት/ የፓርቲው ሊቀመንበር
2. ይድነቃቸው ከበደ/ የፓርቲው የህግ ጉዳይ ኃላፊ
3. ወሮታው ዋሴ /የፓርቲው የፋይናንስ ጉዳይ ኃላፊ
4. ሀብታሙ ደመቀ/ የኦዲትና ኢንስፔክሺን አባል
5. ጌታቸው ሺፈራው/ የነገረ ኢትዮጵያ ዋና አዘጋጅ
6. ጋሻው መርሻ/ የብሄራዊ ምክር ቤት አባል
7. እምላሉ ፍስሃ/ የብሄራዊ ምክር ቤት አባል
8. ሜሮን አለማየሁ/ አባል
9. ጥላሁን አበጀ/ አባል
10. ጠና ይታየው/ አባል
11. እስጢፋኖስ በኩረጽዮን /አባል
12. ኃይለማሪያም ተክለ ጊዮርጊስ/ አባል
13. ጋሻነህ ላቀ/ አባል
14. ግርማ ቢተው አባልና
15. የመኪናው ሾፌር ናቸው
ከምሽቱ 2 ሰዓት ተኩል ከአዲስ አበባ በመንገድ ትራንስፖርት ሰራተኞችና ትራፊክ ፖሊሶች ህጋዊ መሆኑ ተረጋግጦ ያለፈው እንዲሁም ለአራት ቀን ከፓርቲው ጋር ውል የያዘው መኪና እንዳይንቀሳቀስ ተከልክሎ ከፍተኛ አመራሮቹና አባላቱ ከእስር ተለቀዋል፡፡ በተጨማሪም የሰማያዊ ፓርቲ ልዑካን ይዘዋቸው የነነበሩ ቁሳቁሶች ለምርመራ በሚል በፖሊስ ተይዘዋል፡፡


በሌላ ዜና ከአዲስ አበባ ተነስተው ምስራቅ ጎጃም ዞን ደብረ ኤልያስ ወደ ሌላ ለቅሶ ሲሄዱ የነበሩ ዜጎች የሰማያዊ ፓርቲ አመራሮችና አባላት ከታፈኑ በኋላ ደጀን ላይ ተይዘው ከፍተኛ ድብደባ ተፈፅሞባቸው በግዳጅ ወደ አዲስ አበባ እንዲመለሱ ተደርገዋል፡፡ ተመልሰው ወደ ለቅሶው ቢሄዱ እስከ 10 ሺህ ብር ሊቀጡ እንደሚችሉ ማስጠንቀቂያ ተሰጥቷቸዋል፡፡ እነዚህ ዜጎች በተያዙበት ወቅት ሰማያዊ ፓርቲ ደብረማርቆስና ባህርዳር ላይ ሰላማዊ ሰልፍ ሊያደርግ እንደሆነ እንደተገለጸላቸው እነሱም የሰማያዊ ፓርቲ ሰልፍ ላይ ትገኛላችሁ ተብለው ተጠርጥረው እንደሆነ ለነገረ ኢትዮጵያ ገልጸዋል፡፡ 


ይህ በእንዲህ እንዳለ ይህ ዜና እየተሰራ ባለበት ወቅት ማረፊያ ክፍል እየፈለጉ የሚገኙት የሰማያዊ ፓርቲ አመራሮችና አባላት በፌደራል ፖሊስና በደህንነቶች ከፍተኛ ክትትል እየደረሰባቸው መሆኑ ታውቋል፡፡

Friday, June 19, 2015

ኢህአዴግን አልመረጣችሁም በሚል ቤታቸው እንደፈረሰባቸው የለገጣፎ ነዋሪዎች ገለጹ

June 19,2015
‹‹በምርጫው ምክንያት ሊበቀሉን ነው ቤታችን በክረምት ያፈረሱት›› ነዋሪዎቹ
በ2007 ዓ.ም ሀገራዊ ምርጫ ኢህአዴግን አልመረጣችሁም በሚል ቤታቸው እንደፈረሰባቸው በለገጣፎ አባኪሮስ፣ ገዋሳ አካባቢ ነዋሪዎች ለነገረ ኢትዮጵያ ገልጸዋል፡፡ ነዋሪዎቹ በተለያዩ ጊዜያት ፖሊስና ካድሬዎች ቤታቸውን በቀይ ቀለም ከቀቡ በኋላ በተደጋጋሚ ገንዘብ ሲቀበሏቸው እንደቆዩና ከሰኔ 09/2007 ዓ.ም ጀምሮ በምርጫው ሰበብ ቤታቸውን እያፈረሱ መሆኑን ገልጸዋል፡፡ የአካባቢው ህዝብ ‹‹ቤትክን እናፈርሳለን!›› እየተባለ በደተጋጋሚ በሚከፍለው ሙስና የተማረረው እንደሆነ የገለጹት ነዋሪዎቹ በአካባቢው ኢህአዴግ እንዳልተመረጠ ገልጸዋል፡፡ ይህን ተከትሎም ኢህአዴግን ያልመረጡ በተለይም ሰማያዊ ፓርቲን መርጠዋል የተባሉ ነዋሪዎች ቤት ቀይ ምልክት ተቀብቶ እንዲፈርስ መደረጉን ገልጸዋል፡፡ ከምርጫው ጋር በተያያዘ ቤታቸው እንዲፈርስ ቀይ ምልክት ከተቀባባቸው መካከል ለፖሊስና ካድሬዎች ጠቀም ያሉ ገንዘብ የከፈሉ ነዋሪዎች እንዳይፈርስባቸው ሲደረግ ገንዘብ መክፈል ያልቻልነው ቤታችን ፈርሶብናል ብለዋል፡፡ 
ነገረ ኢትዮጵያ ቢሮ ድረስ በመምጣት መረጃውን ያቀበሉን ነዋሪዎቹ ‹‹ኢህአዴግን አልመረጣችሁም፣ ሰማያዊ ፓርቲን ነው የመረጣችሁት በሚል ቤታችን ፈርሶ በአሁኑ ወቅት ከእነ ልጆቻችን ጎዳና ላይ ወድቀናል፡፡›› ብለዋል፡፡ ‹‹እስካሁን ቤታችሁን እናፈርስባችኋለን ብለው በማስፈራራት ከፍተኛ ገንዘብ ሲያስከፍሉን ቆይተዋል፡፡ ቆርቆሮ ገንጥለው ለቆርቆሮው እስከ 2 ሺህ ብር አስከፍለው እንደገና ቆርቆሮውን ይመልሱልን ነበር፡፡ አሁን ደግሞ በምርጫው ምክንያት በአካባቢው ህዝብ ቂም ይዘዋል፡፡ በምርጫው ምክንያት ሊበቀሉን ነው ቤታችን በክረምት ያፈረሱት›› ያለው አንድ ወጣት ሙስና ከፍለው ቤታቸው እንዳይፈርስ ካደረጉት ባሻገር እየዞሩ ቤት የሚያፈርሱት ፖሊሶችና ደህንነቶች በአካባቢው በርካታ ቤቶችን ማስገንባታቸውና የእነሱ ቤት እንደማይፈርስባቸው ገልጾአል፡፡ የካድሬዎች፣ የፖሊሶችና ገንዘብ የሚከፍሉት ሲቀር ‹‹ኢህአዴግን አልመረጣችሁም፡፡ የመረጣችሁት ተቃዋሚዎችን በተለይም ሰማያዊ ፓርቲን ነው›› ተብለው ቤታቸው እንደሚፈርስ ተነግሯቸው ሙስና መክፈል ያልቻሉት ነዋሪዎች ቤት ተመርጦ እየፈረሰባቸው መሆኑን ገልጸዋል፡፡
ገዋሳ፣ ጪሚሲና ሚሽን የተባሉ አካባቢዎች ቤቶች እየፈረሱ መሆኑን የገለጹ በለገጣፎ የሰማያዊ ፓርቲ ዕጩ የነበሩት አቶ አበበ አካሉ ‹‹የነዋሪዎች ቤት እየፈረሰ የሚገኘው በምርጫው ምክንያት ነው፡፡ ለገጣፎ አካባቢ ምርጫው መጭበርበሩን ያጋለጡ ሰዎች ከፍተኛ ጫና ደርሶባቸዋል፡፡ እኔ ጋርም እንዳይገናኙም ወከባ ይፈፀምባቸዋል፡፡ አሁን ደግሞ ህዝቡ ኢህአዴግን ባለመምረጡ ቤቱን እያፈረሱበት ነው፡፡›› ብለዋል፡፡
ምንጭ ነገረ ኢትዮጵያ 

Wednesday, June 17, 2015

የሰማዕታት ደም ይጮሃል፤ ይጣራል!!! (ከሰማያዊ ፓርቲ የተሰጠ ጥልቅ የሐዘን መግለጫ)

June 17,2015
አንድ በስልጣን ላይ የተቀመጠ አካል ተቀዳሚ ተግባር የዜጎችን ደህንነት መጠበቅ መሆኑን ጤነኛ አዕምሮ ያለው የሰው ልጅ የሚገነዘበው ጥሬ ሃቅ ነው፡፡ እንደ እርግማን ዛሬ በኢትዮጵያ የስልጣን እርካቡን የተቆጣጠረው ቡድን የሚገዛቸውን ዜጎች የሚያያቸው እንደጠላት እንጅ የመንግስትን ጥበቃ እንደሚፈልጉ፤ በጠላትነት የፈረጃቸው ዜጎች በከፈሉት ግብር ስልጣን ላይ መቆየት መቻሉን እንኳን ባለስልጣናቱ መረዳት ተስኗቸዋል፡፡
ሰኔ 8 ቀን 2007 ዓ.ም በደብረ ማርቆስ ከተማ እጅግ በሚሰቀጥጥ ጭካኔ እንደ እባብ ተቀጥቅጦ የተገደላው የሰማያዊ ፓርቲ ቆራጥ ታጋይ ሳሙኤል አወቀ የስርዓቱ አገልጋዩች ለዓመታት ሲያስፈራሩት፣ ሲደበድቡት፣ ሰርቶ የመኖር መብቱን ሲጋፉት፣ ያልተሳከ የመግደል ሙከራ በተደጋጋሚ ጊዜ ሲፈፅሙበት መቆየታቸውን የሚያረጋግጡ በርካታ ማስረጃዎች ተይዘዋል፡፡ ሳሙኤል ሕይወቱ አደጋ ላይ እንደሆነችና ጥበቃ እንዲያደርጉለት የጠየቃቸው የፀጥታና የፍትህ አካላት በተገላቢጦሽ ተጨማሪ ዛቻና ማስፈራሪያ ያደርሱበት እንደነበር አይዘነጋም፡፡ አንድ ወጣት በተወለደበት ምድር በሕይወት የቆየባቸውን ጊዚያት በስጋት እንዲኖር ከተፈፀመበት ግፍ በተጨማሪ በሕይወት የመኖር መብቱ በአረመኔዎች እጅ ስትነጠቅ የህዝብን ፀጥታና ደሕንነት እናስከብራለን የሚሉ አካላት በመሃል ከተማ እንኳን ደርሰው ለመታደግ አቅሙም ሆነ ፍላጎቱ አልነበራቸውም፡፡
ሳሙኤል በአሰቃቂ ሁኔታ ከመገደሉ በፊት በተለያዩ ጊዚያት ለሚመለካታቸው አካላትና ለኢትዮጵያ ሕዝብ ያስተላልፋቸው የነበሩ መልዕክቶች እንደተጠበቁ ሆነው በተለይ ግንቦት 25 2007 ዓ.ም በራሱ ገፅ በሆነው “የፌስ ቡክ” ማህበራዊ ሚዲያ ካስተላለፈው መልዕክት መረዳት እንደሚቻለው በተደራጀ ሁኔታ ሕይወቱ አደጋ ላይ እንደሆነች አስረግጦ ተናግሯል፡፡ ሆኖም የሚሰማውና የሚጠብቀው ምንም አካል እንዳልነበረ ይልቁንም ለመገደሉ ተባባሪ የሆኑ የመንግስት አካላት እንደነበሩ ስጋቱን በገለፀ በቀናት ውስጥ ሕይወቱ በአሰቃቂ ሁኔታ መቀጠፏ ጉልሕ ማስረጃ ነው፡፡
በሰላማዊ ትግል ፅኑዕ እምነት የነበረው ሳሙኤል አወቀ ይደርስበት የነበረውን ለቁጥርና ለዓይነት አታካች የሆነ በደል ተቋቁሞ፣ ትግሉን እንዲያቆም ወይም የሚወዳትን ሕይወቱን አሳልፎ የሰጠላትን ሐገሩን ለቆ እንዲሰደድ ይህ ካልሆነ ግን የእሱን ሕይወት ለማጥፋት እጅግ ቀላል መሆኑን የስርዓቱ ባለስልጣናት እና ካድሬዎች ደጋግመው ቢነግሩትም በጭቆና ስር ለሚማቅቀው የኢትዮጵያ ሕዝብ የገባውን ቃል ከማጠፍ ይልቅ ሕይወቱን ለመሰዋት እንደሚቀለው የገባውን ቃል በተግባር አስመስክሮ አልፏል፡፡ በማሰርና በመደብደብ አላማውን እንደማያስቀይሩት፤ ከገደሉት ግን ቀሪ ታጋዮች በተለይም የእድሜ አቻዎቹ የሆኑ የእርሱ ትውልድ የሚሰዋለትን ዓላማ ከግብ እንዲያደርሱ “ትግሌን አደራ!! አደራ!!” በማለት ተማፅኖ አስቀምጧል፡፡
እኛም እንላለን፡፡ አደራህ ከባድ ነው፡፡ ቃልህን እናከብራለን፡፡ አላማህንም እናሳካለን!!!!
ይህ ስርዓት በህግም በሞራልም ኢትዮጵያን የማስተዳደር ብቃት የለውም፡፡ ወንጀለኞች ለፍርድ ይቅረቡ እያልንም አናላዝንም፤ ወንጀለኞቹ የመንግስት አካላት ናቸውና፡፡ በወንድማችንና ገና በለጋ እድሜው በተቀጨው የትግል አጋራችን ላይ የተፈፀመውን ግፍ አይቶ እንዳላዬ ዝም ያለ መንግስት ከዚህ የተሻለ መልካም ነገር ያመጣል ብለን አንጠብቅም፡፡ ለኢትዮጵያ ሕዝብ ግን መልዕክት አለን፡፡ እስከ መቼ በግፍ እንገደላለን?!! ሸፍጠኞችስ እስከ መቼ ይዘባበቱብናል?!! ትግል ለውጤት የሚበቃው በተወሰኑ ቡድኖች ወይም ግለሰቦች መፍጨርጨር ብቻ ባለመሆኑ የግፍ ስርዓት እንዲያበቃ ሁላችንም የሚገባንን የዜግነት ድርሻ እንድንወጣ ጥሪ እናቀርባለን፡፡ ሰማያዊ ፓርቲ በአባላቱና በደጋፊዎቹ በአጠቃላይም የተለየ አስተሳሰብ ስላላቸው ብቻ በካድሬዎች የሚታሰሩ፣ የሚገረፉ፣ የሚሳደዱ፣ የሚዋረዱና የሚገደሉ ዜጎች ለከፈሉት መራራ ፅዋ ክብር ይሰጣል፡፡ መስዋዕትነታቸውም በከንቱ እንዳይሆን እሰከመጨረሻው ይታገላል፡፡
ሳሙኤል “ብታሰርም፣ ብገደልም ይህን ሁሉ የማደርገው ለሐገሬና ለነፃነቴ ነው” ያልከው ቃልህ ከመቃብር በላይ ነው!!!! ቃልህን እናከብራለን፡፡ አላማህንም እናሳካለን!!! ትግል ይቀጥላል . . .
ሰኔ 10 ቀን 2007 ዓ.ም
አዲስ አበባ

ኣቶ ታደሰ ኣብርሃ የተባሉ የዓረና-መድረክ ኣባልና የምዕራባዊ ዞን የዓረና ኣመራር ኣባል በሶስት ሰዎች ታንቀው ተገደሉ።

June 17,2015
ኣቶ ታደሰ ኣብርሃ የተባሉ የዓረና-መድረክ ኣባልና የምዕራባዊ ዞን የዓረና ኣመራር ኣባል ትናንት ማታ 09 / 10 / 2007 ዓ/ም
በሶስት ሰዎች ታንቀው ተገደሉ።
ኣቶ ታደሰ ኣብራሃ በቓፍታ ሑመራ ወረዳ ማይካድራ ቀበሌ ኑዋሪ ሲሆኑ በዘንድሮው ምርጫ ወቅት በቀበሌው ኣስተዳዳሪዎች፣ ካድሬዎች፣ የሚቀርቧቸው ሰዎች ከዓረና-መድረክ ኣባልነታቸው እንዲለቁ የተሸመገሉ፣ የተለመኑና በመጨረሻም ዛቻዎች ሲደርስባቸው እንደነበረ ይታወቃል።
ኣቶ ታደሰ ማታ 03:00 በ 3 ሰዎች ኣንገታቸው የታነቁ ሲሆን ሶስቱ ሰዎች ሙቷል ብለው የተዋቸው ቢሆኑም ሂወታቸው እስከ 09:15 ኣላለፈችም ነበር። ኣቶ ታደሰ ኣብራሃ የ48 ዕድሜ ጎልማሳ ነበሩ።
ኣደጋው 3 ሰዎች እንደፈፀሙባቸው፣ በኪሳቸውም 300 ብር የነበረ ቢሆንም ሰዎቹ ሊወስዱት እንዳልቻሉ ተናገረው ነበር።
የኣቶ ታደሰ ሬሳ በሑመራ ሆስፒታል ላለማስመርመር የማይካድራ ፖሊስ ትራፊክ በዓረና ኣባላት ላይ ከፍተኛ ጫና የፈጠሩ ሲሆን የተለያዩ የመንግስት ኣካላትም ምርመራው እንዳይካሄድ የተለያዩ ጫናዎች እንደፈጠሩ ኣባሎቻችን ከስፍራው ገልፀውልናል።
ሬሳው ወደ ሑመራ ወስዶ ለማስመርመር የሚጠቅም መኪና ለመከራይ ሲባል ኣባሎቻችን የተካራት ሞተር ሳይክ በፖሊስት ትራፊክ ተከልክላለች።
የኣቶ ታደሰ ኣብራሃ ቤት ኣካራይና ሌሎች ሰዎች ከኣደጋው በተያያዘ ጫና እየተፈጠረባቸው እንደሆነ ለማወቅ ተችለዋል።
የኣቶ ታደሰ ኣብራሃ ግድያ በሳምንት ውስጥ የወጣት ሳሙኤል ኣወቀን ጨምሮ ለሁለተኛ ግዜ በፖለቲከኞች ላይ የተፈፀመ ግድያ ሲሆን ከ2007 ዓ/ም በዓረና-መድረክ ኣባላት ለሁለተኛ ግዜ የተፈፀመ ግድያ ያደርገዋል።
ባለፈው ታህሳስ ወር የደቡባዊ ዞን የዓረና-መድረክ ኣስተባባሪና የማእከላይ ኮሚቴ ኣባል የነበረው ኣቶ ልጃለም ኻልኣዩ በኣዲስ ኣበባ ማንነታቸው ባልታወቁ ሰዎች መገደሉ ይታወቃል።
ይህ ተግባር በስፁም የሚወገዝና በሰላማዊ ትግል ላይ ሽብር የሚፈጥር ተግባር ነው።
በሰለማዊ መንገድ የሚታገሉ ፖለቲከኞች የሚፈፀም ግድያ ይቁም...!
መንግስት ነብሰገዳዮች ወደ ፍርድ ያቅርብ...!
ፈጣሪ ነብሳቸው ገነት ውስጥ ያኑርልን ኣሜን።
ነፃነታችን በእጃችን ነው።
IT IS SO..!
ምንጭ አምዶም ገብረስላሴ

ብርሃነ ገብረ ክርስቶስ በድብቅ ጅዳ ገቡ

June 17,2015
ልማታዊ “ዲፕሎማት” በምስጢር ካድሬዎችን ሰብስበዋል
berhane

የውጭ ጉዳይ ምክትል ሚ/ር አቶ ብርሃነ ገ/ክርስቶስ በድብቅ ጅዳ ማምሻውን ገብተዋል፡፡ ወደ ሳዑዲ አረቢያ የመጡበት ምክንያት ባይታወቅም በዚያው የሚገኙ የኢህአዴግ ሹሞችና ልማታዊ ዲፕሎማቶች ድንገተኛውን ጉብኝት ተከትሎ ከብርሃነ ጋር ለመወያየት ሽርጉድ ይሉ ለነበሩ የጅዳና አካባቢው ካድሬዎች፣ ለልማት ማህበራት ተወካዮችና ለደጋፊዎቻቸው በሚስጥር ጥሪ አስተላልፈዋል፡፡

ምስጢራዊውን ጥሪ የሚቃወሙ ኢትዮጵያውያን አንድ ባለስልጣን በዚህ መልክ ወደ ጃዳ መግባታቸው ዲፕሎማት ብለው ለሾሟቸው አገልጋዮቻቸው ያላቸውን ንቀት የሚያሳይ ብቻ ሳይሆን በዲፕሎማቱ ላይ እምነት እንደሌላቸው አመላካች መሆኑን ይናገራሉ።
berhane jeddah
ልማታውያንና የልማት አጋሮች ብርሃነን ለውይይት ሲጠብቁ
ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የኢህአዴግ ከፍተኛ ባለሥልጣናት ለስራ ጉብኝትም ይሁን ለህክምና ወደ ሳውዲ አረቢያ ሲገቡ የኤምባሲው ዲፕሎማቶች መረጃ የሚያገኙት ከተለያዩ ድህረ ገጾች መሆኑን የሚናገሩ ውስጥ አዋቂዎች ከዚህ በፊት በረከት ስምዖን በምስጢር ለህክምና ሲገቡ ዲፕሎማቱ በተመሳሳይ ሁኔታ መረጃ እንዳልነበራቸው ያስታውሳሉ፡፡
ከአንድ ዓመት በፊት በረከት በመሐመድ አላሙዲን የግል አውሮፕላን ተጭንው እኩለ ሌሊት ሳውዲ ገብተው ጅዳ ከተማ በሚገኝ አንድ ሆስፒታል ውስጥ በህክምና ላይ መሆናቸውን የቆንሳላ ጽ/ቤቱም ይሁን በሪያድ የኢትዮጵያ ኤምባሲ ያወቁት ጎልጉል እና ዘሃበሻ ሚዲያ ላይ በተለቀቀው መረጃ መሆኑን የሚያስታውሱ እነዚህ ወገኖች በዲፕሎማቱና በኢህአዴግ መሃከል ከፍተኛ የሆነ የመረጃ ክፍተት መኖሩን ያወሳሉ፡፡ በመሆኑም የመረጃ ክፍተቱን ለማሟላት ዲፕሎማቱ ሚስጥራዊ መረጃዎችን ለማግኘት የተጠቀሱትን ሚዲያዎች መከታተል አማራጭ የሌለው መፍትሄ እንደሆነባቸው ይነገራል።
ዛሬ በጅዳ ቆንስላ ጽ/ቤት በተደረገው ስብሰባ ላይ የታዩት ብርሃነ ገብረክርስቶስ በሙስና ስለሚታመሰው በጅዳ የኢትዮጵያ ኮሚኒቲ ት/ቤትና ህልውናው ስላከተመው በሪያድ የኢትዮጵያ ኮሚኒቲ ማህበር ንብረት መባከን ምንም መረጃ እንደሌላቸው ለማወቅ ተችሏል።
አንድ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መ/ቤት ሠራተኛ አስከትለው ትላንት ጅዳ ሳውዲ አረቢያ ስለገቡት አቶ ብርሃነ ገብረክርስቶስ ጉብኝት በሳውዲም ሆነ አገር ቤት ከሚገኘው የኢህአዴግ ጽ/ቤትና መገናኛ ብዙሃን እስካሁን ምንም የተባለ ነገር የለም፡፡ አሁን ዘግይቶ በደረሰን ዜና ብርሃነ ወደ ሪያድ ከተማ ያቀናሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡ (Ethiopian Hagere Jed Bewadi )

Monday, June 15, 2015

በማዕከላዊ እዝ የሚገኝ አንድ የኦሮሞ ተወላጅ የሆነ የአስር አለቃ ማዓረግ አይገባህም በመባሉ የተነስ እራሱን አጠፋ

June 15,2015
maekelay ezi ye mareg asetat የሚገኙ የሰራዊት አባላት ለሃምሌ ወር 2007 ዓ/ም የቆይታ ጊዜአቸውን ጨርሰው በሚገኙ የሰራዊት አባላት ላይ እየተካሄደ ባለው የከፋ የዘረኝነት ምልመላ ምክንያት አንድ የኦሮሞ ተወላጅ የሆነ የአስር አለቃ ማዓረግ አይገባህም በመባሉ የተነስ እራሱን እንዳጠፋ ተገለፀ።
በደረሰን መረጃ መሰረት- የ23 ክፍለ ጦር የ2 ሬጅመንት በ3 ሃይል ውስጥ የቲም ምክትል አዛዥ የነበረ አስር አለቃ ጫላ ጋዲሳ የተባለው ወታደር በተለያዩ መድረኮች ላይ ተቃራኒ የሆነ ሃሳቦችን ያቀርባል ለህገ መንግስቱ ታማኝ አይደለም መንግስትን ያማርራል የሚሉ ነጥቦችን አስቀምጠው ማዕረግ አይገባህም ተብሎ ከሃይል አመራር በላይ ያሉ አዛዦች ውሳኔውን በማስተላለፋቸው ምክንያት ስሜቱ የተጎዳው ይህ ወታደር ስብሰባው እንዳለቀ ዋርዲያ ነኝ በሎ በመውጣት እራሱን እንዳጠፋ ከእዙ የደረሰን መረጃ አመለከተ።
በአሁኑ ጊዜ በኢህአዴግ የሰራዊት አባላት ውስጥ ያለው የከፋ የዘረኝነት አድሎዎ ለማዕረግ እድገትና ለተለያዩ ጥቅማጥቅሞች ሲባል በሚደረጉ ምልመላዎች ላይ የሰራዊቱ ከፍተኛ አመራሮች በሰራዊት ውስጥ ኢ- ፍትሃዊ የሆነ አሰራር እየሰሩ መሆናቸውን በተለያዩ የሰራዊት እዞች ውስጥ የሚገኙ ምንጮቻችን የላኩልን መረጃ ያስረዳል።
ምንጭ ዴምህት

Sunday, June 14, 2015

የፍቅር ትርያንግል አዙሪት(Lovers Triangle)፤ ሼህ መሐመድ አላሙዲ-ከመንግስት ባለስልጣናት-ከልማታዊ አርቲስቶቻችን

June 14, 2015
በሥዩም ወርቅነህ
ቱጃሩ ‘ሼክ’ መሐመድ አል አሙዲን፤ጋጠወጦቹ የወያኔ መንግስት ሹማምንቶች፦ የሃገሪቱ ፕሬዚደንት ዶ/ር ሙላቱ ተሾመ፣ የፌደረሽን ምክር ቤት አፈ-ጉባዔ፣ የጠቅላይ ሚኒስትሩ አማካሪ አቶ በረከት ስምዖን፣ እንዲሁም ታላላቅ ‘የተከበሩ’ እንግዶችና የአርቲስት ቤተሰቦች በተገኙበት፤ በትላንትናው እለት የትዝታው ንጉስ ጋሽ ማህሙድ አህመድ 50ኛ ዓመት የሙያ ጉዞ በማስመልከት የተዘጋጀ ዝግጅት ሲከበር፤ ከወጣቷ አክትረስ ማህደር አሰፋ ጋር ከትዳራቸው ውጭ ሲማግጡ ታይተዋል። ይህ ከሃገራችን ባህልና ወግ በእጅጉ የሚፃረርና የወደፊት ተተኪውን ትውልድን ወደ አልባሌ ድርጊት የሚገፋፋ ነውረኛ ተግባር ነው።Sheikh Mohammed Hussein Ali Al Amoudi
ማህደርና ሼሁ ለብዙ ጊዜ ሲታሙ መቆየታቸው ይታወቃል። ነገር ግን ንቀት ካልሆነ በቀር እንደዚህ ጋጠወጥ የሆነን ድርጊት በአደባባይ ማድረጉ ለምን አስፈለገ? የወያኔ ሊቀመናብርት ባለስልጣናትን በመዳፋቸው በማስገባት የሃገሪቱን ሃብት የሚዘርፋት ሼክ መሃመድ አል አሙዲን በልማታዊ አርቲስቶቻችን ሰይፉ ፋንታሁን፣ ሰራዊት ፍቅሬ፣ ሙሉዓለም ታደሰ፣ ማዲንጎ አፈወርቅና በሌሎችም አማካኝነት ታዳጊ ወጣት የሃገራችን ልጃገረዶችን በሃብታቸው በማማለል ከአላማቸው በማሰናከል ንፅህናቸውን እንዲያረክሱ ያስገድዷቸዋል። ይህን ህገ-ወጥ ድርጊት የሚያውቁት የወያኔ ቁንጮ ባለስልጣናት ከድርጊታቸው እንዲቆጠቡ ከማድረግ ይልቅ በተጋበዙበት ግብዣ እንኳን ከትዳራቸው ውጭ እየማገጡ እያዩ በጭብጨባ አጅበዋቸዋል።
ወያኔና ጀሌዎቹ ላለፉት 24 ዓመታት የኃገራችን ሃብትና ንብረትን የዘረፉት አንሷቸው፤ ታሪካችንን ሲያጠለሹ፣ ሲያጠፉ፣ የታሪክ መፅሃፍትና ቅርስ ለባዕድ ሲሸጡ፣ ሲያቃጥሉ፣ ባህልና ወጋችንን ሲያንኳስሱ፣ የእምነትና ሃይማኖት ስፍራዎችን ሲያረክሱና ሲያቃጥሉ፣ እንዲሁም አያሌ ወንጀሎችን ሲፈፅሙ መቆየታቸው ፀሃይ የሞቀው የአደባባይ ሚስጥር ነው። እንደ አንድ ኢትዮጵያዊ ለእኔ በዚህ ደረጃ ተንኮታኩታ ጥበብ በአደባባይ ረክሳ፣ ሃገር ተደፍራና አንገታችንን አስደፍታ ማየት ያመኛል። ልማታዊ አርቲስቶቹና የወያኔ ቁንጮ ባለስልጣናት በሼሁ ፍርፋሪ ገንዘብ ህሊናቸው ታውሯል። ልማታዊ አርቲስቶቹም በጥቅም በመደለል የወያኔ ሎሌ ሆነዋል። በቅኝ ግዛት ተገዝታ የማታውቀው ሃገራችን ኢትዮጵያም ሼክ መሐመድ አል አሙዲን እንደፈለጉ የሚፈነጩባትና እሚያዙባት ሃገር ሆናለች።
ሼህ መሐመድ አል አሙዲን 28 ክርስቲያን ወንድሞቻችን ISIS በሚባለው እስላማዊው አሸባሪ ቡድን ከታረዱ ወዲህ ለብዙ አርስቲስቶች በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ብሮች በስጦታና በሽልማት መልክ አበርክተዋል። ለአብነት ያህል ለአርቲስት ማዲንጎ አፈወርቅና ለንዋይ ደበበ ሁለት ሁለት ሚሊዮን ብር፣ ለመሳፍንት 9 ሚሊዮን ብር እንዲሁም በትላንትናው ዕለት ለአርቲስት ማህሙድ አህመድ 5 ሚሊዮን ብር በሽልማት መልክ ለግሰዋል። እውን ይህን ሁሉ የሚያደርጉት ለአርቲስቶቻችን እውነተኛ አክብሮት ኖሯቸው ይሆን!? እውነተኛ ምክንያታቸው ይህ ቢሆን ኖሮ በርካታ ታላላቅ አርቲስቶቻችንና እውቅ ዜጐቻችን በሼሁ ብሮች በተጥለቀለቁ ነበር። ይልቁኑስ በዙሪያቸው የተሰባሰቡት አርቲስት ተላላኪዎቻቸውና ሎሌዎቻቸው በወንጀል ያደፈ ልባቸውን፣ በዝርፊያ የተጨማለቀ እጃቸውንና፣ ውስጠ ሚስጥራቸውን ስለሚያውቁ በውለታ መልክ ጠፍረው ለመያዝና አንዳንድ የዋህ ዜጐችን ለማምታታት ይመስላል።
ሼሁ በእውነት ለሃገራችን ደራሽ የሆኑ ቅን ሰው ቢሆኑ ኖሮ፤ መላው የኢትዮጵያ ሕዝብ በሃዘን ቅስሙ በተሰበረበት፣ መሪር ሃዘኑ በከፋበት፣ የልጆቹ አንገት በቢላዋ ሲቀላ በአደባባይ ተመልክቶ ባዘነበት በዛ ድቅድቅ ጨለማ፣ ለኢትዮጵያ ህዝብ ሃዘናቸውን በገለፁ ነበር፤ እንደሌላውም ቅን ኢትዮጵያዊ ልጆቻቸው ለታረደባቸው ቤተሰቦች እርዳታ ባደረጉ ነበር። ዛሬ ደግሞ አይናቸውን በጨው አጥበውና የኢትዮያን ህዝብ ንቀው፤ የልጅ ልጃቸው ከምትሆነው ከወጣት ተዋናይት ማህደር አሰፋ ጋር፤ ከኢትዮጵያ ባህልና ወግን ባልተከተለ መልኩ ባደባባይ ባልባለጉ ነበር። ሼሁ በISIS ልጆቻቸው ለተጎዳባቸው ቤተሰቦች ሃዘናቸውን ያልገለፁትና ያለመርዳታቸው፣ ያለሃፍረትም እንዲህ ያስፈነጠዛቸው ምክንያት በሃዘናችን ተደስተው ይሆን!? ወይንስ ሌሎችም እንደሚታሙት ለISIS አጋርነታቸውን እየገለፁ!?~መጠርጠር አይከፋም!።
የኢትዮጵያ ታሪክና ወግን አስጠብቀን ለተተኪ ትውልድ ለማስተላለፍ ወያኔን ማስወገድ አማራጭ የሌለው መፍትሄ ነው።
ኢትዮጵያ ለዘላለም በልጆቿ ተከብራ ትኑር!
እናቸንፋለን!

Saturday, June 13, 2015

ቴድሮስ አድሐኖም በጆሐንስበርግና በፕሪቶሪያ ዙሪያ እንዳይዘዋወሩ ጥብቅ መልእክት እንደደረሳቸው ተነገረ

June 13,2015

በደቡብ አፍሪካ የሚደረገዉን የአፍሪካ ህብረት ስብሰባ ለመካፈል ወደዚያዉ ያመራዉ የወያነኔ የዉጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቴድሮስ አድሐኖም በጆሐንስበርግና በፕሪቶሪያ ዙሪያ እንዳይዘዋወሩ ጥብቅ መልእክት ከወያኔ መረጃ ቢሮ በፕሪቶሪያ ለሚገኘዉ የወያኔ ኢንባሲ መተላለፉን ከዉስጥ የወጣ መረጃ አመለከተ::

ተላላኪዉ ቴድሮስ አድሐኖም በደቡብ አፍሪካ የሚገኙ የወያኔ ደጋፊዎችን ሰብስቦ ሊያነጋግር በሞባይል ስልክ መልክት (text)እያደረገ ሳንድተን ሪክሬሽን ሴንተር ቀጠሮ እያስያዘ መሆኑን የደረሱበት በደቡብ አፍሪካ የሚገኙ ተቃዋሚዎች በንቃት እየተጠባበቁት ሲገኙ ተላላኪዉ ቴድሮስ በማንኛዉም ስፍራዎች ለመዟዟር እንዳይችል ተደርጓል።

በተጨማሪ ኢትዮጵያዊያን በሙሉ ሚኒስተሩን በመቃወም በተገኘበት ስፍራና ቦታ ሁሉ መረጃ ለመስጠት በተጠንቀቅ መቆማቸዉን አሳዉቀዋል። ወያኔና ወያኔይያዊያን በሙሉ በደረሱበት ሁሉ ከመዋረዳቸዉንና ከመሸማቀቃቸዉን በዘለለ መልኩ ህዝብን በመፍራት መደበቃቸዉ በራሱ አንድ ታላቅ ድል ነዉ ሲሉ ከወደ ሳንድተን አንድ ግለሰብ ተናግረዋል፤

መርጋ ደጀኔ እንደዘገበው

የትጥቅ ትግል የሚያካሂዱ የተቃዋሚ ድርጅቶችን ዲሞክራሲያዊ ናቸው ብላችኋል የተባሉ ዜጎች እየታሰሩ ነው

June 13,2015

በአዲስ አበባ ከተማ የሚኖሩ ህዝቦችን የትጥቅ ትግል የሚያካሂዱ የተቃዋሚ ድርጂቶች ዲሞክራሲያዊ ናቸው ብላችኋል በማለት ንፁሃን ዜጎችን እያሰረ መሆኑን ከስፍራው የሚገኙ ምንጮቻችን አስረድተዋል።
በአዲስ አበባ ከተማ ጀሞ በተባለው አካባቢ ግንቦት 7 እና ሌሎችም የትጥቅ ትግል የሚያካሂዱ ድርጂቶች ዲሞክራሲያዊ ናቸው የሚል በራሪ ወረቀት መበተኑን ተከትሎ ለጊዜው ስሙ ያልታወቀ የጀሞ አካባቢ ነዋሪ ግንቦት 22 ቀን 2007 ዓም ይህንን ንግግር አንተም ደግመህዋል ተብሎ የታሰረ ሲሆን በተመሳሳይ ግንቦት 15 ቀን 2007 ዓ/ም ቅዳሜ ምሽት ሁለት አውሮፕላን አብራሪዎች ሸራተን ሆቴል አምሽተው ወደ ቤታቸው ሲሄዱ ምነው የምርጫው ዕለት ቀዘቀዘ ሰው የት ሄደ ብላችሁ ተነጋግራችኋል ተብለው በበርካታ የደህንነትና የፌድራል ፖሊስ ታጣቂዎች ታጅበው ወደ እስርቤት መወሰዳቸውን ምንጮቻችን ከቦታው ገልፀዋል።
ሁለቱ ኢትዮጵያዊያን የትግራይና የአዲስ አበባ ተወላጅ ፓይለቶች ምንም የሰሩት ወንጀል ሳይኖራቸው በጥርጣሬ አይን በመታየት ግንቦት 17 ቀን 2007 ዓ/ም ካሳንቺስ ምድብ ችሎት ቀርበው በተወሰነ ውሳኔ መሰረት ምነው የምርጫው ዕለት ቀዘቀዘ ሰው የት ሄደ ብለሃል የተባለው የትግራይ ክልል ተወላጅ ፓይለት 10ሺህ ብር እንዲከፍል የተወሰነ ሲሆን ሁለተኛው ምንም መልስ ባለመስጠቱ በነፃ ተሰናብቷል።

Thursday, June 11, 2015

ከቴፒ ወጣቶች የምንማራቸው ቁም ነገሮች

June 10, 2015
def-thumbበደቡብ ኢትዮጵያ ሸካ ዞን የሚገኙ የቴፒ ወጣቶች በህወሓት አገዛዝ የሚደርስባቸው በደል አንገሽግሿቸው ራሳቸውን አደራጅተው በአገዛዙ ላይ እርምጃ መውሰድ ከጀመሩ በርካታ ወራት ተቆጥረዋል። እነዚህ ወጣቶች ግንቦት 27 ቀን 2007 ዓ.ም. በአካባቢያቸው የሚገኝን አንድ የፓሊስ ጣቢያ ወረው እስረኞችን ማስፈታታቸው በመላው ኢትዮጵያ እንዲታወቁ ምክንያት ሆኗል፤ የአገዛዙ ሚዲያም ድርጊቱ መፈፀሙ በተዘዋዋሪም ቢሆን አምኗል።
ለፍትህ፣ ለነፃነት፣ ለዲሞክራሲ፣ ለእኩልነት እና ለአገር አንድነት ግድ ያለን ኢትዮጵያዊያን ሁሉ ከቴፒ ወጣቶች የምንማራቸው በርካታ ቁም ነገሮች ያሉ ቢሆንም የሚከተሉት ዋና ዋናዎቹ ናቸው ብለን እናምናለን።
1. “ጥቂቶች ነን፤ ምንም ማድረግ አንችልም” ብለው ተስፋ ቆርጠው በደልን ለመቀበል አልመረጡም፤
2. ዓላማቸው ትልቅና ሀገራዊ ቢሆንም እርጃዎቻቸው አካባቢ ተኮር አድርገዋል፤
3. የሚወስዷቸው እርምጃዎች በአቅማቸው መጠን እንዲሆኑ በማድረግ በራሳቸው ላይ ያለው መተማመን እንዲጎለብት ማድረግ ችለዋል፤
4. እንደሁኔታው በፍጥነት መሰባሰብና መበታተን የሚችል ቀልጣፋስብስብ ማደራደት ችለዋል፤ እና
5. በከፍተኛ ሥነሥርዓት በመታነጽ ከቴፒ ሕዝብ ጋር ያላቸውን ትስስር አጠናክረዋል።
ሁላችንም ከእነዚህ ወጣቶች ልንማር ይገባል። በአምባገነን አገዛዝ ጉያ ውስጥ የሚደራጅ የአመጽ ኃይል የተለያዩ አደረጃጀቶች ሊኖሩት ይችላል። አንዱ አደረጃጀት የቴፒ ወጣቶች በተግባር ያሳዩን ነው – ተንቀሳቃሽ፣ ለግዳጅ ተሰባስቦ በፍጥነት የሚበተን፤ መልሶ ደግሞ የሚሰባሰብ ቀልጣፋ ድርጅት።
በምርጫ 97 በሰላማዊ መንገድ የሰጡትን ድምጽ ይከበርን ያሉ ወገኖታችን በአዲስ አበባ ከተማ በግፍ የተጨፈጨፉበት ሰኔ 1 ቀን 1997 ዓም 10ኛ ዓመት በሀዘን አስታውሰናል። ከዚያ ወዲህ በርካታ ወገኖቻችንን በሰላማዊና ህጋዊ ትግል አጥተናል፤ ብዙዎች ቆስለዋል፤ በሺዎች የሚገመቱ በእስር እየማቀቁ ነው። ሆኖም ግን ያ የትግል መስመር የትም አላደረሰንም። የህወሓት አገዛዝ እንዲያበቃ እና በምትኩም ሕዝብ በነፃነት የመረጠው አስተዳደር እንዲኖር የምንፈልግ ወገኖች ሁሉ ወደግባች የሚያደርሱንን አማራጮችን መፈለግ ግዴታችን ሆኗል።
አርበኞች ግንቦት 7: የአንድነትና የዲሞክራሲ ንቅናቄ “ሁለገብ ትግልን” እንደ ትግል ስትራቴጂ ሲመርጥ በውስጡ ብዙ አማራጭ ስልቶች መኖራቸውን እግንዛቤ በማስገባት ነው። የቴፒ ወጣቶች በተግባር ያሳዩን የተለያዩ የሁለገብ ትግል ስትራቴጂ አካል የሆኑ በርካታ የትግል ስልቶች መኖራቸውን ነው። ቴፔ የተደረገው እንዳለ ሌላ ቦታ ይደረጋል ማለት አይደለም። ከቴፒ የምንማረው ዋናው ቁምነገር በፈጠራ እና በአካባቢ እውቀት በታገዘ ስልት ወያኔ መፋለም ያለብን መሆኑ ነው።
አርበኞች ግንቦት 7 የቴፒ ወጣቶች ላሳዩት ተግባራዊ መነሳሳት አድናቆት እና ለከፈሉት መስዋዕትነት ያለውን ክብር እየገለፀ በሌላው የአገራችን ክፍሎች ያሉ ወጣቶችም ከቴፒ ወንድሞቻቸው ትምህርት እንዲቀስሙ ያበረታታል።
በዚህ አጋጣሚም በየቦታው በራስ አነሳሽነት የሚጀመሩ ተግባራዊ እንቅስቃሴዎች አካባቢ ተኮር ቢሆኑም እንኳን አገራዊ እይታ እንዲኖራቸው፤ ከሌሎች መሰል እንቅስቃሴዎች ጋር እንዲቀናጁና እንዲደጋገፉ ብሎም የሀገራዊ ትግሉ አካል እንዲሆኑ ማድረግ የሚያስፈልግ መሆኑን በዚህ አጋጣሚ ያስገነዝባል፤ ይህ ተግባራዊ እንዲሆንም ይሠራል።
ድል ለኢትዮጵያ ሕዝብ!!!

Wednesday, June 10, 2015

ምርጫ ሲባል፣ መሳይና አስመሳይ (ፕ/ር መስፍን ወልደ ማርያም )

June 10, 2015
ምርጫ ሲባል የነጻነት ዓየር አለ፤ ምርጫ ሲባል ተፎካካሪዎች አሉ፤ ምርጫ ሲባል ተፎካካሪዎች በእኩልነትና በነጻነት የቆሙበት መድረክ አለ፤ ምርጫ ሲባል የራሱን ፍላጎት በትክክል የሚያውቅና ከፍርሃት ነጻ የሆነ መራጭ አለ፤ ምርጫ ሲባል የተፎካካሪዎቹን እኩልነትና ነጻነት፣ የመራጮቹን እኩልነትና ነጻነት የሚያከብሩና የሚያስከብሩ ዳኞች አሉ፤ ምርጫ ሲባል የመራጮቹን ፍላጎት በትክክልና ያለአድልዎ የሚያሳይ ሰነድ የሚያዘጋጁ እግዚአብሔርን የሚፈሩ፣ ሕግን የሚያከብሩ፣ ለሕዝብና ለአገር የሚቆረቆሩ ሰዎች አሉ፤ ምርጫ ሲባል ይኸኛው ከዚህኛው ይሻለኛል ብለው የመወሰን ችሎታ ያላቸው ሰዎች አሉ፤ ምርጫ ሲባል መራጮቹ ተመራጮቹን ማገላበጥ አለ።Prof. Mesfin Woldemariam
ታዲያ እኛ ምርጫ የምንለው ይህንን ሁሉ የያዘ ነው? ከዚህ በላይ ከተዘረዘሩት ውስጥ አንዱም እንኳን ቢጎድል፣ ምርጫ አንለውም፤ ምርጫ-መሳይ ልንለው እንችል ይሆናል፤ አንድ የሁለት ጓደኞች የቆየ ቀልድ ትዝ አለኝ፤ አንዱ ስሙ መሳይ ነው፤ ፊታውራሪ ነው፤ ሌላው ስሙ በፈቃዱ ነው፤ ሀኪም ነው፤ አንድ ቀን በፈቃዱ መሳይን ሲያገኘው በፊታውራሪነቱ ለማሾፍ ፊታውራሪ መሳይ አለ፤ መሳይን ጫን ብሎ፤ መሳይም ሲመልስ በዶክተርነቱ እያሾፈ ዶክተር በፈቃዱ ብሎ ዶክተርን ጫን ብሎ መለሰለት! የኛን ምርጫ-መሳይ ምን ብለን፣ አንዴት ብለን እናሹፍበት? ያውም ማሾፍ ከተፈቀደ! በባህላችን በጣም የተወደደ ምግብ አለ፤ ያንን ምግብ አቅርበው መሣሪያው ሲነፍጉ ሥጋውን ሰጥቶ ቢላዋውን መንሣት ይባላል፤ ንፉግነት ብቻ አይመስለኝም፤ ክፋትም አለበት፤ የደርግና የወያኔ ምርጫ-መሳዮች በአለማወቅና በንፉግነታቸው ይመሳሰላሉ፤ በክፋት ግን አይመሳሰሉም።
ደርግም ሆነ ወያኔ ከሌኒን ለመማር አልቻሉም እንጂ አስመስለዋል፤ ምርጫ-መሳዩንም ያገኙት ከዚያው ነው፤ ሌኒን ጉሮሮን ግጥም አድርጎ በብረት ሰንሰለት አስሮ ነጻ ነህ ይላል! መገንጠል ትችላለህ! ይላል፤ ወያኔም ሲሉ ሰምቶ መገንጠል-መሳይ ሕግ-መሳይ አወጣ! ችግር ነው ጌትነት! ዱሮ ተረት ነበር፤ ዛሬ ግን በእውነት ሲቸግር እያየን ይመስለኛል፤ አንድ ሰው ራሱ ባፈራው ሀብትና በደረሰበት የጌትነት ደረጃ ችግር አይሰማውም፤ ሀብቱ ከየት እንደመጣ፣ እንዴት እንደመጣ፣ ምን ያህል ልፋት እንዳስከተለ መገመት ይቻላል፤ በተዘረፈ ሀብት ጌትነት ሲመጣ ግን ችግርን አዝሎ ነው፤ አንድ ሰው አራት ሚልዮን ብር ወድቆ ቢያገኝ አራት መቶ ካሬ ሜትር መሬት ቢገዛበት አያስደንቅም፤ የገንዘብ አያያዝን ስለማያውቅና በስጋት ስለሚከሳ መሬቱ ላይ መቀመጥ አስተማማኝ መስሎ ይታየዋል፤ ከካስትሮ በፊት የነበረውን የኪዩባ ሁኔታ በትንሹም ቢሆን የሚያውቅ በዛሬው ጊዜ በኢትዮጵያ ካለው ሁኔታ ጋር ተመሳሳይነቱን ለመረዳት አያዳግትም፤ በኪዩባም ሆነ በኢትዮጵያ በተዘረፈ ሀብት ጌትነትን ያስፋፋው አሜሪካ ነው፤ ሕዝብ የሚደኸየውና የሚከብረው በጉልበትና በዝርፊያ ብቻ በሆነበት አገር ጊዜውን ጠብቆ ከሁለት አንዱን አርግዞ ይወልዳል፤ ወይ ዘራፊዎችን ሁሉ ዘርፎ ሙልጭ የሚያወጣቸው ጉልበተኛ ይመጣል፤ ወይ በሕጋዊ መንገድ ከዘራፊዎች እየገፈፈ ሀብትን ለሕዝብ የሚያደላድል ሕጋዊ ሥርዓት ይመሠረታል፤ ሁለቱንም በማስረገዝ ላይ ያሉት በግፍ ሀብታም የሚሆኑት ናቸው።
ሕዝብ የሥልጣን ባለቤት እንደሆነ ለማስመሰል ምርጫ መሳይ አለ፤ ሕዝብ የሀብት ባለቤት እንደሆነ ለማስመሰል ግን ትንሽ ያስቸግራል፤ በኮንዶሚንየም ለማስመሰል ቢሞከርም አልሆነም፤ ለሎሌዎች ሹሞችም አልተዳረሰም! በምርጫ መሳዩ ማሸነፍ ቀላል ነው፤ እንዲያውም መቶ በመቶ ማሸነፍ ይቻላል፤ ችግሩ የሚመጣው ከዚያ በኋላ ነው፤ ደካሞች የፖሊቲካ ቡድኖችንና ደካማውን ሕዝብ ማሸነፍ እንደሚቻል ጉልበተኛው አስመስክሯል፤ ሌላው ቀርቶ ‹‹የኔ›› የሚላቸውን ቡድኖችም አፈር ላይ ሊያስተኛቸው ይችላል፤ እንዲያውም አፈሩ ምቹ ፍራሽ ነው ብለው በደስታ እንዲቀበሉ ሊያደርጋቸው ይችላል፤ አሁን የጉልበተኛው መድረክ እየጠበበ መጣ፤ ችግሩ የሚፈጠረው እዚህ የጠበበው መድረክ ውስጥ ባሉት ጉልበተኞችና ጉልበተኛ መሳዮች ነው፤ በአንድ በኩል በጉልበተኞች መሀከል፣ በሌላ በኩል በጉልበተኛ መሳዮች መሀከል፤ በሌላ በኩል በጉልበተኞችና በጉልበተኛ መሳዮች መሀከል፣ ይህ ትግል ዳካማዎች የፖሊቲካ ቡድኖችን እንደማሸነፍ ቀላል አይደለም፤ በአጥር ላይ እየተንጠለጠሉ የጣሉትን ለመልቀም እየተሻሙ ነው፤ በጉልበተኞቹ መሀከል ክፉ የሥልጣን ችጋር ገብቷል ማለት ነው፤ ጦር መማዘዝ ኪስን እንደሚያራቁት ያውቃሉ፤ ያለሥልጣን ኪስ ሙሉ እንደማይሆንም ያውቃሉ፤ ታዲያ ምን ይሻላል?

Tuesday, June 9, 2015

ገዳይና ሟች – አየር ኃይልና ህውሃት

June 9, 2015
አዲስ (ከሲልቨር ስፕሪንግ)
ለኢትዮጵያ አየር ኃይል ቀናዒነት ስላለኝ በቅርብ እርቀት እከታተላለሁ ። ከአባላቱም ጋር በስደት የቅርብ ወዳጅነት መስርቼ ከልብ ትርታቸው ጋ የእኔን አዛምጄ ፣ በአዘኑበት አዝኜ ፣ ሲደሰቱ ተደስቼ ለማንኛውም ጥሪያቸው በግምባር ቀደምትነት ምላሽ በመስጠት በሁሉም ቦታ ታድሜ እነሆ ዘመናት ተቆጠሩ።Ethiopian air force
እማውቀው – እኔ ከብዙዎቹ አንዱ እንደሆንኩ ነው ። የቀድሞው የኢትዮጵያ አየር ኃይል በብዙሃኑ ኢትዮጵያዊ ልብ ውስጥ በቁጭት አክብሮትና አድናቆትን እንደተጐናፀፈ ከትውልድ ትውልድ እያንፀባረቀ ቢመጣም ፤ የኋላ ኋላ ዕጣ ፋንታው ግን መበተን ፣ መሰደድ ፣ ያለ ፍርድ ለዘመናት መታሰርና ፣ ለሞት ፍርድ ተላልፎ መሰጠት ሆነ ። ይህም እንኳ ሳያግደው ዝናው በጠላቶቹም ጭምር ሳይቀር ከዳር እስከዳር እንደናኘ ዛሬም አለ።
ታድያ ዛሬ የዚህን ታላቅ ወታደራዊ ተቋም ታሪክ በመፅሃፍ ተፅፎ ማየት በህይወት ላሉት ክብር ፣ ለሰፊው ህዝብ ማስታወሻ ፣ ለመጪውም ትውልድ መማሪያ መሆኑ የማንኛውም ቅን ዜጋ ህልም ነው ፤ ለአባላቱና ለቤተሰቦቻቸውም ደግሞ ኩራትና እፎይታ ነው።
ለዚህም ነበር ይህንን ታላቅ አላማ ሰንቀው ለተንቀሳቀሱ የቀድሞው የኢትዮጵያ አየር ኃይል አንጋፋ አባላት በከፍተኛ ሁኔታ ድጋፍ የተሰጠው ። ድጋፍ በገንዘብ ፣ ድጋፍ በማቴሪያል ፣ ድጋፍ በሞራል …. ወዘተ።
የታሪክ መፅሃፉን እውን ለማድረግ ለዘመናት ሲዳክሩ የነበሩት ፣ በአየር ኃይሉ ውስጥ ቀደምትነት ያላቸው የተከበሩ ፣ ስመጥርና ገናና የመሆናቸውን ያክል ፤ አጨራረሱ ላይ ግን በፊት አውራሪነት በኢትዮጵያችን እየተለመደ የመጣው የገዢው ስርዓት ተዋላጆች ዋነኛ ባለቤት እየሆኑ የብዙሃኑን ቀና ግምት ወደ ትዝብት ፣ ሃዘንና ጥርጣሬ የወሰደ አልነበረም ብሎ መደምደም አይቻልም።
ከዚሁ ጋር ተያይዞም የመፅሃፉ ይዘት በምን መልኩ ይቀርብ ይሆን የሚለው ከአገር ቤት እስከ ዲያስፖራው የቀድሞው አባላቱ መካከል የተለያየ ሃሳብ ከየአቅጣጫው ተነስቶ በመግባባትም ፣ ባለመግባባትም እንደተናጠ ነበር መፅሃፉ ከመደብር ሳይሆን በውስጥ አወቆች እዚህ ደጃችን የደረሰው።
ስለዚህ የጥያቄውና የውይይቱ መሰረተ ሃሳብ ለምን የአየር ኃይሉ የታሪክ መፅሃፍ ተፃፈ የሚል አይመስለኝም ። በፍፁም አደለምም ። የተወሰኑ ግለሰቦች ግን ለምን የአየር ኃይል ታሪክ ተፃፈ የሚል ጥያቄ እንደተነሳ አስመስለው ለማቅረብ ሲታገሉ በቅርብ አስተውያቸዋለሁ ። ጥያቄው ለምን መፅሃፉን ወደ ጠላት ጉያ ከተቱት (ምክንያቱም የአየር ኃይልን ቁስልና ጥቃት ለመግለፅ አመቺ ቀጠና ስላልመረጡ) ነው እንጂ ለምን ታሪኩ ተፃፈ አይደለም ብዬም ደጋግሜ አስረድቻቸውም ይህንን ይዘሉታል ። ስለዚህ ሆን ተብሎ የሚሰራ ነገር አለ ማለት ነው።
እንደ ግለሰብ ማንኛውም ሰው ፖለቲካዊም ሆነ ሃይማኖታዊ ወዘተ አመለካከቶች ሊኖሩት ይችላል ። ይህም ሊከበርለትና ሊበረታታም ይገባል ። ሆኖም ግን የዚህ የኢትዮጵያ አየር ኃይል ታሪክ አካሎች የኢትዮጵያ አየር ኃልይ አባላት ናቸው ። ባለቤቱ ደግሞ የኢትዮጵያ ህዝብ ነው ። እንግዲያውስ በዚህ መፅሃፍ ዝግጅት ዙርያ የተለያየ ሃሳብ ቢነሳ ሊደመጥና ከግንዛቤ ውስጥ ገብቶ ትኩረት ተሰጥቶት በሃሳብ ተፋጭቶም ነጥሮ ሊወጣ ይገባዋል ፤ ለመፅሃፉም ግብዓት አስተዋፅዖው ቀላል አይሆንም ፤ የታሪኩንም ሙልዓዊነት ሲያዳብረው ተዓማኒነቱንም ከፍተኛ ያደርገዋል ። ይህንንም ስል እንዲያው መቋጠሪያ በሌለው ውዝግብ ውስጥ ገብቶ መቧቸሩ አስፈላጊ ያለመሆኑን እየተረዳሁ ቢያንስ ግልፀኝነትና ታማኝነት በተሞላበት ሁኔታ በተደራጀ መልኩ (በየአካባቢው) በቡድን ኰፒውን የማየትና ሃሳብ የመለዋወጥ ዕድሉ ሊኖር በተገባ ነበር ። አለፍም ሲል በእድሜም ሆነ በልምድ የተከበሩ የሰራዊቱ አባላት እንደዚህ አይነቱን የግራ ቀኝ የሃሳብ ፍጭት ሃላፊነት ወስደው ማወያየትና ሁሉንም በተቀራረበ ግንዛቤ ሸክፎ በአንድነት እንዲጓዝ ማድረግ ታሪክ የጣለባቸው ትልቅ ሃላፊነት መሆን በተገባው ነበር።
ለመሆኑ ችግሩ ምንድነው ? ለምንስ ወደ አላስፈላጊ ጭቅጭቅ በሚል መሸፈኛ እነዚህ ከስርዓቱ ጋር ወስደው ያጣበቁን ሰዎች የፈለጉትን ለማድረግ በር የሚከፍት አካሄድ ተመረጠ ? ትላልቅ የሚባሉት ሰዎችስ ሃላፊነት በሚሰማው መልኩ መሃል ገብተው ማወያየትና መዳኘት ለምን ወኔ ከዳቸው ? ይህ ሃላፊነት ተወስዶ ቢሆን ኖሮ ቢያንስ ዛሬ ላይ ለተነሳው የክህደት ጥያቄ ባልተጋለጠን ነበር።
አገራችን ኢትዮጵያ በረዥም ዘመን ታሪኳ ውስጥ አሁን እንዳለችበት ጊዜ ችግር ገጥሟት አያውቅም ። ለእናት አገራቸው ደከመን ሰለቸን ሳይሉ በሙያቸው እያገለገሉ ሲዋደቁ የነበሩ ፣ ጊዜው በደረሰበት ቴክኖሎጂ የታነፁ ፣ በአፍሪካ ግምባር ቀደሙን አየር ኃይል የአኩሪ ገደል ባለቤት ያደረጉ ፣ ለኢትዮጵያ አየር መንገድ ፣ ለኢትዮጵያ ሲቪል አቬየሽን ጥንስስና መሰረት የጣሉ ፣ ለተለያዩ ሲቪል ተቋማትና አምራች ድርጅቶች አመራር መፍለቂያ የሆኑ ፣ በጤና ፣ በስፖርት የአገሪቷን ስም በዓለም እንዲናኝ ያደረጉ ወዘተ ታላላቅ ሰዎች ሁሉ ሲዋረዱና እንዲሸማቀቁ ሲደረግ በዓይናችን እንድናይ የተገደድንበት ዘመን ላይ ነን ያለነው።
በኢትዮጵያ የአብዮት ዘመንም ተነሳ ተራመድ ብለው በግንባር ቀደምትነት የህዝብን የለውጥ ፍላጐት በመምራት የህዝብ ዕምባ ጠባቂ በመሆን ያገለገሉ ፤ ረዥሙ የእርስ በርስ ጦርነትም ማብቂያ ይበጅለት ብለው በግንቦት 8፣ 1981 ብርቅዬና ውድ አመራሮቻቸውን የገበሩ ፤ ለእናት አገሩ ዘብ በመቆሙና በማገልገሉ ጀግኖቹ አባላቱ ተዋርደው ፣ ታስረው ፣ ተሰደው ፣ ተገልለውና ተሸማቀው እንዲኖሩ የተደረገበት ። የሞት ፍርድ እንኳ ሳይቀር የተበየነበት ዘመን ነው።
ዛሬም እንኳ ይህቺን ፅሁፍ እየጫጫርኩ ባለሁበት አጋጣሚ የግንቦት 20 ድል እየተከበረ ስለ ጨፍጫፊው የኢትዮጵያ አየር ኃይል ሲያላዝኑ ይሰማል ። ሌላው ቢቀር በአንድ ወቅት አየር ኃይሉን እንዲጐበኙ ለተደረጉት አርቲስቶች እንዳሉት የሞተ ፣ የተማረከ ፣ የተንኰታኰተና የተሽመደመደ አየር ኃይል እንደተረከቡና ዛሬ ግን እነሱ አየር ኃይሉን ከፍተኛ ደረጃ እንዳደረሱ ሲገልፁ መስማት ምንኛ ያማል ? እነዚህ የመፅሃፉ አዘጋጆች እንደዚህ አይነቱ የመንግስት ዘለፋ ሊሞቃቸውም ሆነ ሊበርዳቸውም እንዳልቻለ ማስተዋል ገረሜታን መፍጠሩ አልቀረም።
ታድያ ዛሬ መነሻው በተድበሰበሰ ሁኔታ ተጀቡኖ ፣ በአሳዳጆቹ ዳንኪራ ቤት (ሸራተን) በተሰጠ የችሮታ ድግስ የተጀመረው የመፅሃፍ ዝግጅት ፣ የሌላውን ሃሳብ ባለማዳመጥ በድንገት የምረቃው ዜና አሁንም በአሳዳጆቹ አጋፋሪነት መሰማቱ ከፍተኛ ሃዘንና ድንጋጤ ቢፈጥር ምን ይገርማል ? ክህደትስ ነው ቢባል ምን ያጠራጥራል?
ደግሞስ የመፅሃፉ አወጣጥና አካሄድ አላግባብ በማን አለብኝነት ብሎ መተቸት ከመፅሃፉ ይዘት ጋር ምን ያገናኘዋል ? አዎ ወደ አይቀሬው የመፅሃፉ ይዘት ወደድንም ጠላንም እንገባለን! አወጣጡ ግን የተሽመደመደ ፣ በክህደት የተሞላ ፣ ለአፍራሾቹ በበቂ ሁኔታ ምላሽ ሊሰጥ የማይችል መሆኑን በድፍረት እናገራለሁ ። ወደፊት በመፅሃፉ ባህሪና ይዘት ላይ ብዙ ለማለት እንድችል ከወዲሁ ይህንን ሳልጠቁም ማለፍ ስላልፈለኩ ነው።