Thursday, June 19, 2014

ጋዜጠና እስክንድር ነጋን እና ሌሎችንም በሃስት በመክሰስ እና በመመስከር ለዕስር ከዳረጉ ህሊና የሌላቸው ግለሰቦች በትቂቱ ይህን ይመሰላሉ ::

June 19/2014
ጋዜጠና እስክንድር ነጋን እና ሌሎችንም በሃስት በመክሰስ እና በመመስከር ለዕስር ከዳረጉ ህሊና የሌላቸው ግለሰቦች በጥቂቱ ይህን ይመሰላሉ ::
አሽባሪው አቃቤ ህግ ቴድሮስ ባህሩ በታማኝነት ህውሃቶችን በማገልገል በርካታ ንጽሃን በሃስት ከሶ ለዕስር እና መከራ ዳርጎ በአሁኑ ግዜ ከቤተሰቡ ጋር በአሜሪካ ሃገር በሜሪላንድ ሲልበርስፕሪንግ በሰላም ኑሮውን እየመራ ይገኛል:: አቃቤ ህግ ቴድሮስ ባህሩ እስክንድር ነጋን ጋዜጠኛ ርዮት አለሙን እንዲሁም በሙስሊሙ መፍትሄ አፈላላጊና ዋና ዋና በተባሉት ላይ ታላቅ ሚና የተጫወተ ግለሰብ ነው::
የጋዜተኛን እስክንድር ነጋን ንብረት እንዲወረስ ታላቅ ሚና የተጫወተው አቃቢ ህግ ብርሃኑ ወንድማገኝ ... በተደጋጋሚ ፍርድ ቤት በመቅረብ በዚህ ንብረት ላይ ለሚመለከታቸው በአድራሻቸው ልናገኛቸው አልቻልንም ፣:: የጥሪ ወረቀት ለመላክ አልቻልኩም ሲል ደጋግሞ ለፍርድ ቤቱም ገልጻል:: ፍርድ ቤቱም ተጨማሪ ቀናት ሲሰጠው ቆይቷል :: ንብረቷ እንደታገደ በዜና ሲነገር የሰማችው የጋዜጤኛ እስክንድር ባለቤት ጋዜጠኛ ሰርካለም ፍሲል፣ ይህ ግለሰብ በተደጋጋሚ ሲዋሽ በቦታው በመገኘት ሰትከታተል ከቆየች በኋላ አቶ ብርሃኑ በተደጋጋሚ የሚመለከታቸውን ልናገኝ አልቻልንም ሲል ጋዜተኛ ሰርካለም ፍሲል ከታዳሚው መሃከል እጇን በማውጣት ለፍርድ ቤቱ ማንነቷን ከገለፀች በኋላ በዚህ ጉዳይ ላይ ማንም እንዳላናገራት ለፍርድ ቤቱ በመግለጽ ፍርድ ቤቱም ሌላ ቀጠሮ ለመሰጠት ሲሞክርም ሰርካለም ሁሉንም እንደተከታተለች እና ንብረቱን እሷም ሆነች ባለቤቷ እስክንድር ነጋ እንደማይፈልጉት በመግለጽ ንብረቱን መውሰድ እንደሚችሉ ለፍርድ ቤቱ አሳውቃለች ::
ዜጎች ላይ ግፍ ሲሰሩ ከከረሙ በኋላ በውጭ አለም የራሳቸውን ህይወት በተደላደለ ሁኔታ "ሀ "ብለው የሚጀምሩ እንደ ቴድሮስ ባህሩ አይነት ግለሰቦች በርካታ ናቸው :: እነዚህን ወንጀለኞች በመረጃ ለፍርድ የሚቀርቡበት ግዜ ዕሩቅ አይሆንም ::
ታላቅ ምስጋና
ለጋዜጠኛ አበበ ገላው
ልትዮጵያ ለዘላለም ትኑር !!!
በተጨማሪ ለማዳመጥ ይህንን ሊንክ ይጫኑ

አሽባሪው ቴድሮስ ባህሩ እና ግብረአበሮቹ !!!





ጦማሪያኑን እና ጋዜጠኞቹን በተመለከተ ችሎቱ ለፖሊስ ጠንካራ ትዕዛዝ አስተላለፈ

June 19/2014

በቁጥጥር ስር ከዋሉ ባለፈው ቅዳሜ (ሰኔ 7 ቀን 2006 ዓ.ም) 50ኛ ቀናቸውን በእሰር ያሳለፉት ስድስቱ ጦማሪያንና ጋዜጠኞች ለአራተኛ ጊዜ የ28 ቀን የጊዜ ቀጠሮ ተፈቅዶባቸዋል። ለአራተኛ ጊዜ ፍርድ ቤት የቀረቡት ከዞን 9 ጦማሪያን መካከል ዘላለም ክብረት፣ ናትናኤል ፈለቀና አጥናፉ ብርሃኔ ሲሆኑ፤ ጋዜጠኞቹ ደግሞ ተስፋለም ወልደየስ፣ ኤዶም ካሳዬ እና አስማማው ወ/ጊዮርጊስ ናቸው። በዕለቱ ችሎቱ መርማሪ ፖሊስ የሚያቀርባቸውን ተደጋጋሚ ምክንያት አጠንክሮ በመፈተሽ በቀጣይ ቀጠሮ ፈፅሟቸው ሊመጣ የሚገቡ አራት ተግባራትን በግልፅ በማስቀመጥ ትዕዛዝ ሰጥቷል።
በፌዴራሉ የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ 1ኛ ወንጀለ ችሎት በዕለቱ የቀረቡት ጦማሪያንና ጋዜጠኞች ፖሊስ የመሰረተባቸውን የሽብርተኝነት ክስ በተመለከተ የደረሰበትን ማስረጃዎች ለፍርድ ቤቱ ለማሰማት ነበር። በችሎቱ ጥበት ምክንያት አንዳችም የውጪ ሰው ወደ ውስጥ ሳይዘልቅ የተከናወነው ችሎቱ በብዙዎች ዘንድ “የዝግ ችሎት ነው ወይ?” የሚያሰኝ ጥያቄን ቢያስነሳም ለጦማሪያኑና ጋዜጠኞቹ በጥብቅና የቆሙት ጠበቃ አመሃ መኮንን ግን ችሎቱ ጠባብ በመሆኑ ነው የሚል ምላሽ ሰጥተዋል። በዕለቱ በግቢው ውስጥ በርካታ ቁጥር ያላቸው ጋዜጠኞች ዲፕሎማቶችና የታሳሪዎቹ ወዳጅ ዘመዶች ተገኝተው ነበር።
ፍርድ ቤቱ የማዕከላዊ ፖሊስ በታሳሪዎቹ ላይ ካለፈው ቀጠሮ መልስ አገኘዋቸው የሚላቸውን መረጃዎችና ሰራዋቸው የሚላቸውን ተግባራት በተመለከተ ለፍርድ ቤቱ ሲያስረዳ፤ በከፊል ሰነዶችን ማስተርጐሙን፤ በከፊል የባንክ ማስረጃዎችን ማግኘቱንና በከፊል የቴክኒክ ማስረጃዎችን ስለማሰባሰቡ ቢገልፅም በደፈናው ግን “ብዙ ስራ ሰርተናል፤ ብዙ ስራም ይቀረናል” ሲል ለፍርድ ቤቱ ማስታወቁን ጠበቃው ከችሎት መልስ ተናግረዋል።
በዚህም ጉዳይ ላይ ፍርድ ቤቱ ማስረጃዎች ሲቀርቡ፤ በጥቅል መቅረብ እንደሌለባቸውና በዝርዝር እንዲቀርብለት ትዕዛዝ የሰጠ ሲሆን፤ ከዚህ በኋላም ጥቅል ማስረጃን ማድመጥ እንደማይፈልግ አስታውቋል። ፖሊስ ለስራው መጓተት አሁንም እንደቀደመው ጊዜ ካቀረባቸው ምክንያቶች ውስጥ የምስክሮችን ቃል ስለአለመቀበሉ፤ ተባባሪዎችን በቁጥጥር ስር ለማዋል መቸገሩንና ወደ ክልል ሀገር ሄደውብኛል በሚል አባሎቹን ልኮ በቁጥጥር ስር ለማዋል እየተከታተለ መሆኑን ከመግለፁም በተጨማሪ አሁንም ሰነዶችን አስተርጉመን አልጨረስንም ሲል አብራርቷል።
የተከሳሽ ጠበቆች በበኩላቸው ለፍርድ ቤቱ ሲያስረዱ ለአራተኛ ጊዜ በጊዜ ቀጠሮ ፍርድ ቤት መቅረባቸውን አስታውሰው፤ የቱንም ያህል ውስብስብ ወንጀል ቢሆን ተጠርጣሪዎቹ እጃቸው ከተያዘበት ጊዜ ጀምሮ ያለው 50 ቀናት በቂ ናቸው የሚል መከራከሪያ አሰምተዋል። ጠበቃው አክለውም ይህ የሚያሳየው ፖሊስ ከመነሻው አንድም ማስረጃ ሳይሰበስብ ልጆቹን የያዛቸው መሆኑና ይህም ሕግን የጣሰ ተግባር ነው ሲሉ አስረድተዋል። ሌላው በጠበቆች በኩል የቀረበው አቤቱታ ፖሊስ በተደጋጋሚ የሚያነሳቸው ተመሳሳይ ምክንያቶች በመሆናቸው የቀረቡትን ምክንያቶች ውድቅ አድርጐ ተጠርጣሪዎቹን በዋስ እንዲለቅ፤ አልያም ፍርድ ቤቱ ሕጋዊ ምክንያት አለኝ ብሎ የሚያምን ከሆነ ይህ የመጨረሻ የጊዜ ቀጠሮ ይሁንልን ሲሉ ስለመጠየቃቸው ጠበቃው ተናግረዋል።
የግራ ቀኙን ኀሳብ ያዳመጠው ፍርድ ቤቱም፤ ፖሊስ በተደጋጋሚ ከሚያነሳቸው ምክንያቶች ውስጥ አራት ጉዳዮችን በመምረጥ በቀጣዩ ቀጠሮ እልባት ሰጥቷቸው እንዲመጣ ትዕዛዝ የሰጠ ሲሆን፤ እነዚህ አራት ተግባራትም ተባባሪዎቻቸውን አልያዝንም፣ የምስክሮችን ቃል አልተቀበልንም፣ ሰነዶች ተተርጉመው አልመጡልኝምና ከሽብርተኝነት ጋር በተያያዘ በባንክ የተላከላቸውን ገንዘብ በተመለከተ ደብዳቤ ጽፈን ምላሽ እየተጠባበቅን ነው የሚሉትን ጉዳዮች በተመለከተ ከዚህ በኋላ ለጊዜ ቀጠሮ መጠየቂያ ምክንያት ሆነው ሊቀርቡ እንደማይችሉ በመግለፅ ትዕዛዝ የሰጠ ሲሆን፤ ይሁን እንጂ ፍርድ ቤቱ የጊዜ ቀጠሮውን የመጨረሻ ነው እንዳላለ ጠበቃው ተናግረዋል።
በሌላም በኩል የተጠርጣሪዎቹ ቤተሰብ እንዳይጠይቃቸው መሰናክል መኖሩንና፤ በተለይም ጋዜጠኛ አስማማው ወ/ጊዮርጊስ የወገብ ሕመም ያለበት መሆኑን በመግለፅ ወንበር ወደክፍሉ እንዲገባለት መጠየቁን ነገር ግን አሁንም ድረስ አለመፈፀሙን ለፍርድ ቤቱ አስረድተዋል። ፍርድ ቤቱም በበኩሉ መርማሪ ፖሊሶቹ በዚህ ላይ ምላሽ እንዲሰጡ ያዘዙ ሲሆን፤ የተጠርጣሪዎቹን ቤተሰብ መጐብኘትን በተመለከተ ከተደራራቢ ስራና ከአስተደደር ጋር የተያያዘ መሆኑን በመጥቀስ የመከልከል ደረጃ ግን አልተደረሰም ሲል የተፈጠሩት ክፍተቶች እንደሚያሻሽሉ አስረድቷል። የጋዜጠኛ አስማማው ወ/ጊዮርጊስን ጥያቄ በተመለከተ ፍርድ ቤቱ በጤና ጉዳይ ላይ ምንም አይነት ድርድር የለም በሚል የሰጠውን ትዕዛዝ ለመፈፀም እንደሚቻል አሳውቀዋል።
     የፌዴራሉ የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ ችሎት ፖሊስ የጠየቀውና ተጨማሪ 28 ቀናት የምርመራ ጊዜ በመፍቀድ ለሐምሌ 5 ቀን 2006 ዓ.ም እንዲቀርቡ አዟል።

Honorees of the Fourth Ethiopian Heritage Festival

June 19, 2014

Poet Laureate, Young Scholar and Journalists to be honored:

• An Ethiopian Poet Tsegaye Gebremedhin will be honored for his Contribution to the Advancement of Humanity
• The Zone Nine bloggers: Free press Journalist for reporting the truth, corruption, and the human rights condition in Ethiopia at great personal sacrifice and risk.
• Nahom Marie, a 17 Years old, software and iOS app developer who will be attending MIT.
Poet Laureate, Young Scholar and Journalists to be honored
These are among those who will be primarily honored, celebrated, and remembered at the upcoming Ethiopian Heritage Fourth annual Festival to be held from Friday, July 25 to 27th 2014.
Laureate Tsegaye “Giant” and “Icon”
Poet Laureate Tsegaye Gebremedhin was a renaissance man. He was poet, playwright, essayist, historiographer, philologist, art director, humanist, and peace activist. Born in 1936 Ambo, Ethiopia, Tsegaye Gebremedhin’s artistic talent was noticed early on by his grade school teacher. Into adulthood, he advanced to become a prolific playwright and poet. Throughout his life time, he has published over 11 research papers, over 40 plays and poetry in Amharic, and translated more than 16 plays in Amharic and English, some being his work.
Moreover, he has also held several positions such as was General Manager of the Ethiopian National Theatre, Vice-Minister of Culture and Sports, editor at the office of Oxford University Press, assistant professor at department of Education at Addis Ababa university from (1977-1978) and much more. His awards include the following: Emperor Haile-Selassie I International Prize for Amharic Literature in 1966, The Gold Mercury Ad Persona Award in 1982, 4 Fulbright Senior Scholar Resident Fellowship Award; Human Rights Watch Free Expression Award in New York in 1994, and Honorable Poets Laureate Golden Laurel Award. In addition, his literary contribution particularly to Ethiopia is immense and remains as an icon etched not only in Ethiopian history and identity, but to Africans as well.
Unsung Heroes- Zone9 bloggers
Zone9bloggers are a group of bloggers dedicated to presenting the various pertinent social issues such as political repression and human rights activism. The six bloggers are Atnaf Berahane, Mahlet Fantahun, Natnael Feleke, Befeqadu Hailu, Zelalem Kiberet, Abel Wabela, and 3 journalists; Edom Kassaye, Tesfalem Weldeyes and Asmamaw Hailegorgis of Addis Guday magazine. After much surveillance and harassment, as of April 26th they have been charged with terrorism and imprisoned at Maeklawi prison which is notorious for torture. The ESHNA acknowledges the diligent work zone9bloggers have contributed to human rights and the idea of free expression.
Young scholar- Nahom Marie
Nahom Marie is a bright 16 years old high school student whose academic achievement is exemplary. Nahom’s exceptional academic began whilst in Kindergarten where he exhibited a higher understand that advanced him to several classes beyond his age.
Nahom Marie is an aspiring software and iOS app developer from San Jose, California. He has worked on different types of apps from BOOM, a music recognition app that utilizes the capabilities of the Pebble smart watch, to an in-progress tutoring app that looks to make the process of tutoring and/or finding a tutor tailored to compatibility and several preferences.
Graduating this summer, Nahom has received several awards and scholarships to various universities such as Princeton, Sanford, Harvard, MIT and many more. Besides his academic achievement, he has engaged himself in working within the Ethiopian community. He often volunteered after school to help students with their homework’s, and acting not only as their tutor but as mentor as well.
Ethiopian Heritage Festival to be an Interesting Event
Along with the ceremonial honorees, the Ethiopian Heritage Festival will offer venues for members of the Ethiopian Diaspora Community and their American neighbors to learn about and celebrate the Ethiopian experience. These include art, crafts, and jewelry exhibitions. Plenty of delicious Ethiopian cuisine, traditional music and dancing, soccer and running sports, and plenty of activities for the youngsters will keep everybody interested.
Main days of the Ethiopian Heritage Festival: Opening Friday, July 25 at Silver Spring Civic building 1 Veterans Pl, Silver Spring, MD 20910 and Saturday July 26 through Sunday, July 27, 2014, on the campus of Georgetown University in Washington, D.C
For more info please visit our website www.ehsna.org
Or email us @-pr@ehsna.org

የኦክስፎርድ ዩኒቨርሲቲ ጥናት ኢትዮጵያን ከዓለማችን ደሃ ሀገራት ከመጨረሻው ሁለተኛ ደረጃ ላይ አስቀምጧታል፡፡

June19/2014
 Multidimensional Poverty Index (MPI) የተባለውና የዓለማችንን 108 በማደግ ላይ ያሉ ሀገራትን የድህነት ደረጃ የፈተሸው የኦክስፎርድ ዩኒቨርሲቲው ጥናት ኢትዮጵያን ከ108ቱ ሀገራት ከኒጀር ብቻ በልጣ ከመጨረሻው ሁለተኛ ደረጃ ላይ አስቀምጧታል፡፡ ደረጃው በትምህርት፣ ጤና እና የኑሮ ሁኔታ ላይ የሚያጠነጥኑ 10 መስፈርቶች ሲኖሩት ከ10ሩ መስፈርቶች አንድ ሦስተኛውን እንኳ ያላገኘን ደረጃው ዘርፈብዙ ደሃ (Multi-dimensionally poor)ሲለው፣ ከመስፈርቱ ዝርዝር ውስጥ አንድ ሦስተኛው ያህል የተሟላለትን ደግሞ ለኑሮ መሰረታዊው ነገር ያልተሟሉለት (Destitute) ይለዋል፡፡ በዚህም መሰረት ከኢትዮጵያ አጠቃላይ ህዝብ 87.3% ያህሉ ዘርፈብዙ ደሃ በሚለው ክልል ውስጥ ሲገኝ 58.1%ቱ ደግሞ መሰረታዊው ነገር ያልተሟሉለት (Destitute) በሚለው ክልል ውስጥ እንደሚገኝ የጥናት ውጤቱ ያስረዳል፡፡ ኢትዮጵያ ባለፉት ዓመታት ውስጥ መሰረታዊው ነገር ያልተሟሉላቸው (Destitute) ዜጎቿን ቁጥር በመቀነስ ረገድ ጥሩ ውጤት ብታስመዘግብም ኢትዮጵያ አሁንም የ76 ሚሊየን ዘርፈብዙ ደሃ ህዝብ ሀገር ናት ይላል የጥናት ውጤቱ፡፡ ይህም ቁጥር በዓለማችን ካሉ መሰል በርካታ እጅግ ደሀ ሕዝብ ከያዙ ሀገራት ማለትም ከህንድ፣ ቻይና፣ ባንግላዴሽ እና ፓኪስታን በመቀጠል ኢትዮጵያ በ5ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጣለች፡፡ የደረጃው ዝርዝር የገጠሪቱን ኢትዮጵያ አስመልክቶ 96.3% የገጠሪቱ ኢትዮጵያ ህዝብ በድህነት ውስጥ እንደሚገኝ ሲገልጽ በአንጻሩ ከከተማ ነዋሪው 46.4 %ቱ በድህነት ውስጥ እንዳለ ያስረዳል፡፡ በኢትዮጵያ የተለያዩ ክልሎች የሚስተዋለውን የድህነት ደረጃ አስመልክቶም በሶማሊያ 93% በኦሮሚያ 91.2% በአፋር 90.9 % በአማራ 90.1 % በትግራይ 85.4 % ህዝብ በድህነት ውስጥ እንዳለ ይገልጻል፡፡ ከተሞችንም በተመለከተ አዲስ አበባ ከሌሎች ከተሞች ይልቅ አነስተኛ ደሃ (20%)ያለባት ስትሆን ድሬዳዋና ሐረር ደግሞ አነስተኛ ደሃ በመያዝ በ54.9% እና በ57.9% ይከተላሉ፡፡

http://www.diretube.com/articles/read-ethiopia-ranks-second-poorest-country-in-the-world-%E2%80%93-oxford-university-study_5513.html#.U6Kj2_l_tSQ

Ethiopia ranks second poorest country in the world – Oxford University Study


ዜጎችን መታደግ የማይችሉ በአስቸኳይ ቆባቸውን አውልቀው ከተራው ሕዝብ የመቀላቀል ግዴታ አለባቸው።:-ምንሊክ ሳልሳዊ

June 18/2014
ቤተክርስቲያን እና መንግስት በኢትዮጵያ ውስጥ እጅና ጓንት ሆነው በኢትዮጵያውያን ላይ የማያባራ ጭቆና ማካሄድ ከጀመሩ ረዥም ዘመናት ተቆጥረዋል። ይብልጡኑ የመንግስቶች ጎህ ከቀደደ ጀምሮ በተለይ የተዋህዶ ሃይማኖት መሪዎች አስፈሪ እና አስደንጋጭ እንዲሁም አሳዛኝ ደግሞም አሳፋሪ ቃላቶችን በመጠቀም ስጋዊ እና ምድራዊ ስልጣኖችን ለገዢዎች ለማደላደል ይህ ነው የማይባል ግፍ በምእመናኖቻቸው እን በሌሎች አማኞች ላይ ፈጽመዋል አስፈጽመዋል፤ እየፈጸሙ ነው፤ እያስፈጸሙ ነው። ይህ የማይዋጥለት አሊያም የሚክድ ካለ እውነት የማይደላው ብቻ ነው።
Co_existanceየኢትዮጵያ ጨቋኝ መንግስታት የሆኑ ከጥንት እስከ ዛሬ የተንሰራፉ በህዝብ ላይ የሚያደርጉት ጭቆና እና በደል ታሪክ የማይሽረው ጠባሳ በሰው ልጆች የትውልድ ሂደት ላይ መፍጠሩ እንደተጠበቀ ሆኖ የሃይማኖቶች ሚና ግን እጅግ በሚያሳዝን መልኩ ዜጎች በግፍ በጨቋኝ መንግስቶች ሲታረዱ በመባረክ የመንግስታቱን እድሜ አስረዝመዋል አሁንም እያስረዘሙ ነው። የመንግስት እና የሃይማኖት ቁርኝት የሚፈለገው ስልጣንን አደላድሎ ለመያዝ እና ህዝብን ረግጦ ለመግዛት ካለ ምኞት እንጅ ለዜጎች ከመቆርቆር የመነጨ አይደለም። የሃይማኖት አባቶች በሃይማኖታዊ የመንፈስ ጥኡም ሰበካና ዜማ ጋር በማጣፈጥ የጨቋኞችን የበላይነት በመስበክ ማስፈራራት እና ማሸማቀቅ የጳጳሳት እና የሼህዎች አብይ ተግባር ነው።
በኢትዮጵያ ውስጥ ተገዝተው አሊያም አድርባይ ሆነው በመስራት ላይ ያሉ የሁሉም ሃይማኖት መሪዎች እጅግ ጥንቃቄ በጎደለው ሁኔታ በዜጎች ላይ የሚደርሱ ግድያዎች ድብደባዎች እስሮች እና መንገላታቶችን እንደ አንድ መንፈሳዊ የሃይማኖት መሪ እንደ ሰብአዊ ተፈጥሮ አሊያም መጽሃፋቸው እንደሚያዛቸው ለዚጎች ሲደራደሩ ሲከራከሩ ሲዋያዩ ሲሆንም አንተም ተው አንተም ተው ሲሉ አልታዩም ከዚህ በከፋ መልኩ በልማታዊ ዲሞክራሲ የፖለቲካ ፉጨት ስር ተደብቀው በለው በሚል አብዮታዊ ዜማ ዜጎችን እያስፈጁ ይገኛሉ።
አንድ የሃይማኖት አባት የታመመ ሲጠይቅ፤ የሞተ ሲቀብር ፤የተቸገር ሲረዳ ፤የታሰረ ዞሮ በመጎብኘት ሲያጽናና እንጂ ሲፖተልክ አሊያም ሲወሸክት ማየት ያማል። በሃገራችን ምእመናንን እንምራለን የሚሉ ሕዝብን መንፈስ እንመግባለን የሚሉ የለሊት ወፍ የሆኑ የክርስትና እና እስልምና የሃይማኖት መሪዎች ዜጎችን መታደግ የማይችሉ ከሆነ በአስቸኳይ ቆባቸውን አውልቀው ከተራው ሕዝብ መቀላቀል ግዴታ አለባቸው። ይህ ጉዳይ የብዙሃኑ የዜጎች ጉዳይ ስለሆነ ክርስቲያን እስላም የሚባልበት ሳይሆን የኢትዮጵያውያን የጋራ ጉዳይ ነው።
በሃገሪቱ ዜጎች በአለም ላይ ታይቶ በማይታወቅ ሁኔታ በነጻነት በመጻፋቸው የእኩልነት እና የነጻነት ጥይቄ በማንሳታቸው ብቻ አሸባሪ ተብለው እስር ቤት በታጎሩባት ኢትዮጵያ ጉዳዩን እስኪ ላስጠናው ላጥናው ያለ የሃይማኖት መሪም ይሁን የሃይማኖት ሃራጥቃ የለም። እንዲሁም በታሰሩ ሰዎች እና በአሳሪዎች መካከል እርቀ ሰላም እንዲወርድ ለወደፊቱ ስህተቶች ካሉ እንዳይደገሙ ነገሮችን ለማግባባት እና ለማቻቻል የፈቀደ አንድም የሃይማኖት መሪ የለም። ይብስኑ የሃይማኖት መሪዎቹ በየስብሰባው እና በየጭብጨባው ዜጎች የመንግስታዊ ሽብር ዱላ ሰለባ እንዲሆኑ እያበረታቱ ይገኛሉ ።
የዜጎች ሁኔታ ያሳሰባቸው የሃይማኖት መሪዎች በከፍተኛ ዛቻ እና ማስፈራራት እንዲሁም በጥቅም በማሰር እንዳይንቀሳቀሱ አሊያም በተዘዋዋሪ ባልሰሩት ወንጀል ለማጥመድ ሴራ በመጎንጎን እያስፈራሩ የህዝቦችን የሰብ አዊ መብት ጥያቄዎች እንዳያነሱ በማስደንገጥ እንዲሁም በጥቅማ ጥቅም እና በገንዘብ በመደለል አባትነታቸውን ለስጋዊ ባለስልጣናት እንዲሸጡ እና የፖለቲካ ምንዝር እንዲፍጽሙ እየተደረገ ሲገኝ ይህንን የምንዝር ጌጥ ከመለማመዳቸው የመጣ የሃይማኖት አባቶች ከጨቋኞች ብሰው በሕዝብ ላይ ከፍተኛ በደል እንዲፈስም ከባዱን ሚና እየተቻውቱ ይገኛሉ ።
የሃይማኖት አባቶች ሰጥ ለጥ ብለው ስለልማት ብቻ እንዲሰብኩ የእስላሙንም ሆነ የክርስቲያኑን ጥያቄዎች በተገኙበት እንድያስተጋቡ ማስጠንቀቂያ ከተሰጣቸው አባቶች መካከል አቡነ ማትያስ አቡነ ሉቃስ እና ሌሎችም ተጠቃሾች ናቸው እንዲሁም የወያኔ መንግስት በቅርቡ ለሾማቸው የእስልምና ምክር ቢት ሼሆችን ከፍተኛ የሆነ ምክር አዘል ማስጠንቀቂያ አስተላልፏል። እኔ ስጨፈጭፍ እናንተ አጨብጭቡ የሚለው አሸባሪው የወያኒ መንግስት ሃይማኖቶችን በራሱ አይዲኦሎጂ በመቀጽ ቀሚሳቸውን ያንዥረገጉ ሰላዮችን እና የሃይማኖት ነቅእዞችን በመመደብ ዜጎችን በተመለከተ የሚደርሱ በደሎች እና ገፈፋዎች ጠያቂ እንዳያገኙ አስታራቂ እንዳይሹ አድርጓል። ፓትርያርኩ ተንገላተው ከተለቀቁ በኋላ በማህበራዊ ድህረገጾች ላይ ብዕራቸው ለምን ታቀበ? ከፋሲካ ክብረ በአል በኋላ በትዊተር ላይ እንዳልተገኙ የሚነገርላቸው ፓትርያርኩ ራሳቸውን ከማንኛውም አንደፋዳፊ ንግግር በመቆጠብ በተረጋጋ መልኩ አንገታቸውን እንዲሰብሩ እና በቅርባቸው ለተመደቡላቸው የመንግስት ደህንነቶች /አማካሪዎች ተገዢ እንዲሆኑ ተደርጓል።
7d2898c3630feea92ec1553d16389ff6_XLዜጎቹን የማይታደግ የሃይማኖት መሪ ቆቡን አውልቆ ከፖለቲካው ጎላ ይቀላቀል አሊያም ገለልተኛ ሰው ሆኖ እንዲቀመጥ ለመምከር እንፈልጋለን ። በኢትዮጵያ ውስጥ ያሉ ሃይምኖቶች ለመንግስታዊ ሽብር ተገዢ እና ታዛዥ እንዲሁም የሽብር ሰባኪ ሆነው ዜጎችን በአደባባይ እያስግደሉ ዜጎች ከሞቱ በኋላ በሃይማኖታቸው ስር አት እና ደንብ እንዳይቀበሩ ተጽእኖ በማድረግ ለምድራዊው የጨቋኝ ምደብ ተባባሪ እና አስተባባሪ በመሆን ከባድ ወንጀል እየፈጸሙ ይገኛሉ። ስለዚህ በዜጎች ላይ የሚደርሱ በደሎች የማይቆረቁራቸው የሃይማኖት አባቶች ሊወገዱ ይገባል።
ማሳሰቢያ ፦ በዛሬው እለት በኦርቶዶክስ በእስልምና በካቶሊክ እና ከመካነ እየሱስ ቤተክርስቲያን የተዘዋወረው የበጎ አድራጎት ድርጅቶች ቡድን ያሰባሰበውን ጉድ የያዘ መረጃ በቅርቡ በይፋ እናወጣዋለን ይጠብቁን። ‪

Wednesday, June 18, 2014

ጋዜጠኞቹና ጦማሪያኑ ያለምንም ማስረጃ መታሰራቸውን የፖሊስ የምርመራ ሒደት እንደሚያሳይ ጠበቃቸው አሳወቁ

June18/2014

ፖሊስ በየቀጠሮው የሚያነሳቸው የምርመራ ምክንያቶች በፍርድ ቤት ታገዱ

በሽብርተኝነት ተጠርጥረው በእስር ላይ የሚገኙት ጋዜጠኞችና ጦማሪያን ያለምንም ማስረጃ መያዛቸውን፣ ፖሊስ ለአራት ጊዜ ፍርድ ቤት በመቅረብ ለችሎት ከሚያስረዳው የምርመራ ሒደት መረዳት መቻሉን ጠበቃቸው አስታወቁ፡፡

የተጠርጣሪዎቹ ጠበቃ አቶ አመሐ መኰንን ይህንን የተናገሩት ሰኔ 7 ቀን 2006 ዓ.ም. ለአራተኛ ጊዜ በፌዴራል የመጀመርያ ደረጃ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ ወንጀል ችሎት ቀርበው በነበሩት ጋዜጠኞች ተስፋለም ወልደየስ፣ አስማማው ኃይለ ጊዮርጊስ፣ ኤዶም ካሳዬ፣ ጦማሪያንና መምህር ዘለዓለም ክብረት፣ አጥናፍ ብርሃኔና ናትናኤል ፈለቀ ላይ ፖሊስ ለፍርድ ቤቱ ቀድሞ በተፈቀደለት 28 ቀናት ውስጥ ‹‹ሠርቻለሁ›› ያለውን የምርመራ ሒደት ተከትሎ ነው፡፡

ተጠርጣሪዎቹ በቁጥጥር ሥር ውለው በፌደራል ወንጀል ምርመራ ማዕከል (ማዕከላዊ) በእስር ላይ በቆዩባቸው 50 ቀናት ውስጥ አራት ጊዜ ፍርድ ቤት ሲቀርቡ፣ በአንድ ቀጠሮ የተጠርጣሪዎቹ ቤተሰቦች የሆኑ ብቻ ሁለት ሁለት ሰዎች ችሎቱን እንዲታደሙ የተደረገ ቢሆንም፣ ሰኔ 7 ቀን 2006 ዓ.ም. ግን ማንም ሰው ወደ ችሎት እንዳይገባ ተከልክሏል፡፡ በመሆኑም ተጠርጣሪዎቹ የፍርድ ቤት ውሎአቸውን ጨርሰው ሲወጡ ጠበቃቸውን አቶ አመሐን የአገር ውስጥና የውጭ መገናኛ ብዙኃን፣ እንዲሁም ከቤተሰብ ጀምሮ ዲፕሎማቶች፣ ጓደኞቻቸውና ሌሎች በፍርድ ቤቱ ቅጥር ግቢ ውስጥ የተገኙ ታዳሚዎች ከበቧቸው፡፡

‹‹ምን ተባሉ? ፖሊስ ምን ተጨማሪ ምርመራ አቀረበ?›› ለሚለው የሁሉም ታዳሚዎች ጥያቄ ምላሽ መስጠት የጀመሩት ጠበቃ አመሐ፣ ‹‹ፖሊስ አዲስ ነገር አላቀረበም፤›› ካሉ በኋላ፣ ባለፉት 28 ቀናት ውስጥ ምን ምን ሥራዎችን እንደሠራ ፍርድ ቤቱ ጠይቆት የተወሰኑ የትርጉም ሥራዎችን እንዳሠራ፣ የተወሰኑ የባንክ ማስረጃዎችን እንዳገኘ፣ የተወሰኑ የቴክኒክና ሌሎች በርካታ ሥራዎችን መሥራቱን እንዳስረዳ ገልጸዋል፡፡ በርካታ ሥራዎች የሠራ ቢሆንም ከሥራው ውስብስብነትና ስፋት አንፃር በርካታ ሥራዎች እንደሚቀሩት በመግለጽ፣ ለተጨማሪ ምርመራ 28 ቀናት እንዲፈቀድለት ፍርድ ቤቱን መጠየቁን አቶ አመሐ ተናግረዋል፡፡

መርማሪ ፖሊስ ‹‹በርካታ ሥራዎች›› በማለት በጥቅል የተናገረውን በሚመለከት የሠራውንና ያልሠራውን አንድ ሁለት ብሎ እንዲያስረዳ ፍርድ ቤቱ እንዳዘዘው የገለጹት ጠበቃው፣ የተወሰኑትን የምስክሮች ቃል ተቀብሎ የተወሰኑትን መቀበል እንደሚቀረው፣ ተባባሪዎች ወደ ክልል በመሄዳቸው የምርመራ አባላትን ልኮ እየተጠባበቀ መሆኑን፣ አዲስ አበባ ውስጥም ያልያዛቸው ተባባሪዎች እንዳሉና ለመያዝ እየሠራ መሆኑን፣ የተወሰነ ሰነድ ማስተርጐም እንደሚቀረው አስረድቶ የጠየቀው ጊዜ እንዲፈቀድለት በድጋሚ መጠየቁን አስረድተዋል፡፡

ጠበቃ አመሐ በበኩላቸው፣ መርማሪ ፖሊሶቹ ያቀረቡትን ሪፖርት በመቃወም መከራከራቸውን ተናግረዋል፡፡ ተጠርጣሪ ደንበኞቻቸው ከታሰሩ 50 ቀናት እንዳለፋቸው፣ አራት ጊዜ ፍርድ ቤት ቀርበው ጊዜ ቀጠሮ ተጠይቆባቸው እንደተፈቀደ፣ የፈለገ ውስብስብ ወንጀል ቢሆን እንኳን ከተያዙ ጊዜ ጀምሮ ምርመራ ቢጀመር 50 ቀናት ምርመራ ለማጠናቀቅ በቂ መሆኑን ለፍርድ ቤቱ ማስረዳታቸውን ገልጸዋል፡፡

‹‹ይኼ የሚያሳየው ፖሊስ ተጠርጣሪዎቹን የያዛቸው ምንም ዓይነት ማስረጃ ሳይኖረው መሆኑን ነው፤›› ያሉት ጠበቃ አመሐ፣ ተጠርጣሪዎቹን ዋጋ እያስከፈላቸውና ሕግን የጣሰ ተግባር በመሆኑ የመርማሪ ፖሊስን የምርመራ ውጤት ፍርድ ቤቱ ሊቀበለው እንደማይገባ በመናገር መከራከራቸውን አብራርተዋል፡፡

መርማሪ ፖሊስ በተደጋጋሚ ለፍርድ ቤት የሚያነሳቸው የምርመራ ሒደቶች ማለትም ትርጉም ማስተርጐም በተርጓሚውና በፖሊስ መካከል የሚከናወን መሆኑን፣ የቴክኒክ ምርመራውም በራሱ በፌዴራል ፖሊስ ውስጥ የሚሠራ በመሆኑ፣ ተጠርጣሪዎቹን በእስር የሚያቆያቸው አለመሆኑን ለፍርድ ቤቱ በማስረዳት፣ በቂ ምክንያቶች አለመሆናቸውንና ተጠርጣሪዎቹም ቀሩ በተባሉት የምርመራ ሒደቶች ላይ ተፅዕኖ ሊያደርሱ ስለማይችሉ ዋስትና እንዲፈቀድላቸው መጠየቃቸውን ጠበቃ አመሐ አስረድተዋል፡፡ ፍርድ ቤቱ የመርማሪ ፖሊሱ ሪፖርት ትክክል ነው ብሎ የሚያምን ከሆነም፣ የመጨረሻ የምርመራ ጊዜ ብሎ ትዕዛዝ እንዲሰጥ መጠየቃቸውን አክለዋል፡፡

ፍርድ ቤቱ ከሌሎቹ ጊዜ በተለየ ሁኔታ ለመርማሪ ፖሊሱ ተገቢ ጥያቄዎችን በማንሳት፣ ቀደም ብሎ ፖሊስ ለተጨማሪ ቀጠሮ ማስፈቀጃ ይጠቀምባቸው የነበሩትን፣ ‹‹ተባባሪ መያዝ ይቀረናል፣ ምስክሮች አልተቀበልንም፣ ሰነዶችን ለትርጉም ልከን አልመጣልንምና አሸባሪዎች ከላኩላቸው ገንዘብ ጋር በተገናኘ ከባንክ ማስረጃ ጠይቀን እየጠበቅን ነው፤›› የሚሉ ምክንያቶችን ማቅረብ እንደማይችል ማስታወቁን ገልጸዋል፡፡

ፍርድ ቤቱ ከላይ ከተጠቀሱት ውጪ ከሆነ ግን ሊቀበል እንደሚችል የሚያሳይ ትዕዛዝ መስጠቱ፣ ፍርድ ቤቱ የምርመራ ሒደቱን ‹‹የመጨረሻ›› ብሎ ለመናገር አለመድፈሩን እንደሚያሳይ ጠበቃ አመሐ ተናግረዋል፡፡ ፍርድ ቤቱ ጉዳዩን በግልጽ ችሎት ለምን ማየት እንዳልቻለ የተጠየቁት ጠበቃ አመሐ፣ በዝግ ችሎት መታየቱን ፖሊስ የሚፈልገው ቢሆንም፣ ፍርድ ቤቱ ግን ‹‹ዝግ ችሎት ነው›› አለማለቱን ገልጸዋል፡፡ ነገር ግን ችሎቶቹ በጣም ጠባብ መሆናቸውን እሳቸውም እንደተገነዘቡ አስረድተዋል፡፡

ከተጠርጣሪዎቹ መካከል አንዱ ጋዜጠኛ አስማማው ኃይለ ጊዮርጊስ፣ የወገብ ሕመም እንዳለበት በተደጋጋሚ ገልጾ ወንበር እንዲሰጠው ቢጠይቅም፣ ምላሽ የሚሰጠው እንዳጣ ለፍርድ ቤቱ በማስረዳት ትዕዛዝ እንዲሰጥለት ጠይቆ፣ ፍርድ ቤቱ ‹‹በጤና በኩል ምንም ድርድር የለም›› በማለት የምርመራ ማዕከሉ እንዲፈጽም ትዕዛዝ ማስተላለፉንም አስረድተዋል፡፡ ቤተሰብም የመጐብኘት መብት እንዳለው ፍርድ ቤቱ አስረድቶ፣ ይኼም ተግባራዊ እንዲሆን ትዕዛዝ መስጠቱን አክለዋል፡፡

አንዳንድ የአስተዳደራዊ ችግሮች ካልሆኑ በስተቀር የምርመራ ማዕከሉ ሁሉንም ተገቢ የሚባሉ ነገሮችን እንደሚያደርግ መርማሪ ፖሊሱ ገልጾ፣ የፍርድ ቤቱን ትዕዛዝ እንደሚያከብርም መናገሩን ጠበቃ አመሐ ለታዳሚዎች አስረድተዋል፡፡ በመጨረሻም ፍርድ ቤቱ ፖሊስ የጠየቀውን ተጨማሪ የ28 ቀናት ጥያቄ በመፍቀድ ለሐምሌ 5 ቀን 2006 ዓ.ም. ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል፡፡  

ተባበር ወይንስ ተሰባበር!?

June 18, 2014

ተባበር ወይንስ ተሰባበር!?

ተባበር ወይንስ ተሰባበር!?

በኢትዮጵያ ሃገራችን በፍቅር፣ በመተሳሰብና፣ በመቻቻል ለዘመናት የኖረ ህዝብ እርስ በርሱ በጥርጣሬና በጥላቻ ሲጎሻሸም፤ ቤተሰብ ከቤተሰብ መተማመን ጠፍቶ ግለኝነት ሲነግስ፤ የአብሮነታችን ማሰሪያ የሆነው ፍቅራችን ጠፍቶ አንዱ ብሄር በሌላው ብሄር ላይ ጥላቻን ሲዶልት፤ መከባበራችን ረክሶ አንዱ ሃይማኖት ሌላውን ሲጠራጠር፤ ባጠቃላይ በሃገሪቱ ፍቅር ጠፍቶ ጥላቻ ሲነግስ በማየቴ አዘንኩ። ገዢው የኢህአዴግ ከፋፋይ ሥርዓት የዘረጋው አፋኝ መዋቅር ህዝብ ከጥላቻ ውጪ ሌላ ምንም አይነት መረጃ እንዳያገኝ አፍኖ፤ በሃገሪቷ ሰላምና መረጋጋት እንዳይሰፍን፤ ብሎም ኢትዮጵያዊነት ቀስ በቀስ እየተሸረሸረና እየጠፋ እንደሆነ ሳስተውል ደግሞ ፈራሁ። በአንፃሩ ደግሞ ይህ አደገኛ ሁኔታ ለመናገር በሚዘገንን መልኩ አስከፊ በሆነበት በዚህ የጨለማ ዘመን፤ በተቃዋሚ ስም ራሳቸውን ሰይመው ‘እኔ ካልኩት በላይ ምንም ሊሆን አይችልም’ በሚል አምባገነናዊ አስተሳሰብ፤ በህዝብ ስም ለህዝብ ነፃነት ሳይሆን የራሳቸውን የግል ፍላጎት ለማሳካት የህዝብን በደል በማባባስ ላይ የተሰማሩ ስብስቦች እንደ አሸን በዝተው ስመለከት ተረበሽኩ። በመሆኑም በሃገራችን በጎ ነገር እንዲሰፍን በመመኘት፤ ያላስተዋለ ተገንዝቦ፣ አይቶ ዝም ያለም የሃገርና የህዝብ ውድቀት ነውና ማፈግፈጉን ትቶ ወደ እውነተኛው የህዝብ ነፃነት መንገድ ይራመድ ዘንድ፤  በዚህች አጭር ፅሁፍ ጥቆማዬን ለአንባቢያን ማቅረብን ፈቀድኩ።
ሁላችንም እንደምናውቀው የኢትዮጵያ ህዝብ ደህንነትና የሃገሪቱ ህልውና በኢህአዴግ መንግስት በጎ ፍቃድ ብቻ የሚወሰን መሆኑ ለሁሉም ኢትዮጵያዊ ግልፅ ነው። በመሆኑም መንግስት እንዳሻው ሃላፊነት በጎደለው አካሄድ ህዝብን ለዘመናት ሲያፈናቅል፤ ንጹሃን ዜጎችን መጥፎ ስም በመስጠት ባልሰሩት ሃጥያትና በተፈበረከ የሃሰት ውንጀላ በየእስር ቤቱ እንዲማቅቁ ሲያደረገ፤ የሃገሪቱን መሬት በፈቀደው መልኩ ለባእዳን ሃገራት ሲያድልና ሲሸጥና ብዙ ሌሎች በደሎችን በህዝብና በሃገር ላይ በተደጋጋሚ ሲፈፅም ማየት የተለመደ ሆኗል። በኔ አስተሳሰብ ኢህአዴግ ይህንን ማድረግ የቻለበት ዋንኛው ምክንያት የሚዲያ ተቋማትን ሙሉ ለሙሉ መቆጣጠር በመቻሉ ነው። በሃገራችን የሚገኙት መንግስታዊ የሚዲያ ተቋማት የኢህአዴግን የዘረኝነት ፖሊሲ ብቻ በመስበክ በተለይ ወጣቱ ትውልድ ስለ ሃገሩ አንድነት፣ ስለ ህዝቧ ፍቅርና፣ በሃገሪቱ ስላሉት የተቃዋሚ ድርጅቶች እንቅስቃሴ እንዳይሰማና እንዳያውቅ በማድረግ አስተሳሰቡ ከአካባቢው የማያልፍ ጠባብ አድርጎታል። ለዚህም በቅርቡ በኦሮሚያ ክልል በዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ሲተውኑት ያየነው ትእይንት አይነተኛ ምስክር ነው። ለአንድ ሃገርና ህዝብ የወደፊት አቅጣጫና ህልውናን በመወሰኑ ረገድ ሚዲያ እጅግ ወሳኝ ድርሻ አለው።ኢህአዴግ በሚቆጣጠራቸው የሚዲያ ተቋማት የሚያሰራጨውን የዘረኝነትና የእርስ በርስ የጥላጫ መርዝ በመቋቋም የነፃነት ትግሉን ወደፊት መግፋትና ለውጤት ማብቃት የሚቻለው፤ ኢህአዴግ እየፈፀማቸው የሚገኙትን በደሎች ከማጋለጡ ባሻገር፤  ህዝቡ በተቃራኒው ስለአንድነትና ፍቅር እንዲሁም ስለተቃዋሚዎች በቂ እውቀት እንዲኖረውና፣ ልዩነቶቻቸውን አጥብበው በጋራ እንዲሰሩ የሚገባውን ጫና እንዲያደርግ፣ አልያም የመረጠውን መቀላቀል ይችል ዘንድ ሁለገብ መረጃዎችን በስፋት ለህዝብ ለማድረስ የሚሰራ የሚዲያ ተቋም መገንባት ሲቻል ብቻ እንደሆነ ይሰማኛል። በተለይ እንደ ኢህአዴግ የሚዲያ ጠላት በሆነና ህዝብን በዘር፣ በጎሳ፣ በሃይማኖት፣ ከፋፍሎ የእርስ በርስ ጥላቻና ቂም ለማስፋፋት ታትሮ በሚሰራ አረመኔአዊ አገዛዝ ስር ለወደቀ ህዝብ ነፃ የመረጃ ስርጭት እጅግ አስፈላጊ ነው።
ሁላችንም እንደምናየው የኢትዮጵያ ህዝብ በአሁኑ ወቅት የተቃዋሚ ቡድኖች ከመጠን በላይ በመብዛታቸው ምክንያትና መረጃ በብቃት ስለማይደርሰው፤ የድርጅቶቹን አላማ፣ ግብ፣ ራእይ፣ በጎ ጎኖችና ግድፈቶች፣ እንዲሁም ሌሎች ልዩነቶቻቸውን በቅጡ መለየት ተስኖት፤ ምኑን ከምኑ፣ የትኛውን ከሌላኛው መለየት ባለመቻሉ ግራ በመጋባቱ ‘የነፃነት ትግል የውሸት፤ ፖለቲካ አይንህ ላፈር’ በሚል የተሳሳተ አስተሳሰብ ተወስኖ፤ የሚደርስበትን ችግር ለማስቆም በጋራ ከመታገል ይልቅ በዝምታ መቀመጥን መርጦ ይገኛል። በመሆኑም የተቃዋሚ ድርጅቶች ያለ ህዝብ ተሳትፎ ብቻቸውን ሲያጨበጭቡ ይታያሉ።
ከላይ ለመግለጽ የሞከርኳቸውንና ሌሎች መሰል ችግሮችን ለመቅረፍ ዋንኛ መሳሪያው ብቃት ያለው የሚዲያ ተቋም መኖር በመሆኑ የተለያዩ የተቃዋሚ ቡድኖች ተቋማትን መስርተው ሲንቀሳቀሱ እናያለን። ነገር ግን እዚህጋ ሊሰመርበት የሚገባው ጉዳይ ተቋማቱን መመስረት ብቻ ሳይሆን የሚያስተላልፉት የመረጃ ይዘቶችና አይነቶች እጅግ ወሳኝ መሆናቸውን ነው። በኔ እይታ የሚዲያዎች አትኩሮት በተለየ ሁኔታና በስፋት፤ በተቃዋሚዎች መካከል ያሉትን ልዩነቶች፣ የተቃዋሚዎችን በጎ ጎኖችና ግድፈቶች፣ ከገዢው መደብ ጋር ያላቸውን ልዩነቶች በመረጃ ማቅረብ፣  ለሁሉም የፖለቲካ ሃይሎች ያለ አድልዖ እኩል መድረክ የሚሰጡና በሃገሪቷ ታሪካዊ፣ ፖለቲካዊና ማህበራዊ ጉዳዮች ላይ ተቃራኒ አመለካከቶች ያሏቸውን ምሁራንንና የፖለቲካ ሰዎችን በማወያየት ህዝብ በስነልቦና በእውቀት እንዲጎለብት በስፋት የሚሰሩ ሊሆኑ ይገባል። ከዚህ መነሾነት ሲስተዋሉ በአሁኑ ወቅት ለኢትዮጵያ ህዝብ እውነተኛ መረጃን ለማስተላለፍ በሚል አላማ ከሚሰሩት የሚዲያ ተቋማት አብዛኛዎቹ በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ የኢህአዴግን መሰረታዊ አላማዎች ከማስተጋባት ያለፈ የሚጨበጥ ስራ ሲያከናውኑ አይታዩም። በእርግጥ አንፃራዊ በሆነ ሁኔታ ስመለከታቸው እንደ Addis Dimts Radio፣ SBS Australia፣ የVOA እሰጥ-አገባና እንወያይ የራዲዮ ዝግጅቶች ሊመሰገኑ  የሚገባ መሆኑን ለመጠቆም እወዳለሁ።
esat-radio-tv-logo
ከአድማጮችና ከደጋፊዎች ብዛት አንፃር የኢሳት ራዲዮና ቴሌቪዥን ከፍተኛውን ድርሻ የሚይዝ ስለሚመስለኝ ሃሳቤን ለመሰብሰብ ይሆን ዘንድ፤ ታዋቂ ሰዎችና የፖለቲካ መሪዎች ከአድማጮች ለሚቀርቡ ጥያቄዎች በኢሳት ራዲዮ ምላሽ የሚሰጡበት፤ የ “ጥያቄ አለኝ” ዝግጅት ላይ፤ የኢሳት ቴሌቢዥንና ራዲዮ በማኔጅመንት ዳሬክተሩ በአቶ ነአምን ዘለቀና በጋዜጠኛ ብሩክ ይባስ ትብብር መላሽ የነበረበትን ለሁለት ሳምንታት የተላለፈ ዝግጅት ላይ ከአንድ አድማጭ የቀረበ ጥያቄንና ከኢሳት የተሰጡ መልሶችን እንደምሳሌ ማንሳት አስፈላጊ ነውና ከዝግጅቱ ከታዘብኩት ጥቂት ልበል። እኝህ ኢትዮጵያዊ የኢሳት አድማጭ ለኢሳት ያቀረቡት ጥያቄ ከላይ ካነሳሁት መሰረታዊ ሃሳብ ጋር በፅኑ ስለሚገናኝና አድማጩ ኢሳትን ሊያስገነዝቡ የሞከሯቸው ጭብጦች በአምባገነን ስርዓቶች ለአመታት ሲሰቃይ ለኖረው ህዝብ ነፃነት መጎናፀፍ ጉልህ ሚና ስለሚኖራቸው፤ ጥያቄያቸውም የበርካታ ኢትዮጵያውያንም ጥያቄ እንደሆነ ስለምገምት ለአንባቢያን ጥያቄውን አቀርባለሁ።
ምስጋና ይህን ወሳኝ ጥያቄ ላቀረቡት ለእኝህ ቀና ኢትዮጵያዊ የኢሳት አድማጭ ይድረስና፤ ባይሳካም የጉዳዩን ወሳኝነት ለማሳሰብ አቀራረቡን የበለጠ ግልፅ አድርገው በሁለተኛው ሳምንትም በድጋሚ ጠይቀዉት ነበር።  ወደ ተነሳሁበት ጉዳይ ልመለስና፤  እንደኔ አረዳድ የጥያቄያቸው መንፈስ ይህን ይመስላል፤ “እስካሁን ድረስ የተለያዩ መረጃዎችን ስትሰጡን ኖራችኋል። ነገር ግን የምትሰጡን መረጃዎች የኢትዮጵያ ህዝብን ወደ ድል ሊያበቁ አልቻሉም። ሁላችንም እንደምናየው ወያኔ የሚፈልገዉን ነገር ከማድረግ የሚያግደው ምንም ሃይል ሊፈጠር አልቻለም። የዚህ ዋና ምክንያት ደግሞ የምትሰጡት መረጃ ወያኔ በደሉን ከህዝብ ለመደበቅ የጭቆና ስልቱን በመቀየር ስህተቱን እንዲያርም ከማድረግና ከማገልገል በስተቀር ለህዝብ የረባ ፋይዳ አላስገኘም።  ለወያኔ ደካማ ጎኑን እንደምትነግሩት ሁሉ፤ ለተቃዋሚዎችም ስህተታቸውን እንዲያርሙ እንድታሳስቧቸው ዘንድ፤ ብሎም ተቃዋሚዎች እየሰሩት በሚገኙት በደል ምክንያት ለነፃነቱ ላለመቆም ሳይወድ እንዲሸሽ ለተገደደው የኢትዮጵያ ህዝብ ብርታት እንደሚሆነው በማስገንዘብ ከብዙ አድማጮች አስተያየት ቢሰጣችሁም፤ ተግባራዊ ልታደርጉ አልቻላችሁም። የኢትዮጵያ የተቃዋሚ ሃይሎች ኢህአዴግ ከሚያጠፋው በላይ በኢትዮጵያ ላይ ትልቅ ጥፋት እያደረሱ ይገኛሉ፤ ምክንያቱም እኔ ካልኩት ሃሳብ በላይ ማንም ሊሆን አይችልም ብለው ስለሚያምኑ፤ ልስራ ብሎ የሚመጣውን አንዱ ሲያዳክም፤ አንደኛው ሌላኛውን ሲያጠፋ እያየን እንገኛለን።  ፊትለፊት አምጥታችሁ አገናኝታችሁ በጋራ እንዲሰሩ ልዩነቶቻቸውን ህዝብ አውቆ እንዲፈርድና የመረጠውን እንዲቀላቀል የማትረዱት ለምንድነው?”።
ለጥያቄው በትብብር የሰጡትን መልስ መሰረት በማድረግ ለአቶ ነአምን ዘለቀና ለጋዜጠኛ ብሩክ ይባስ ማሳሰብ የምፈልጋቸው ነጥቦች፤ የእኚህ  አድማጭ ጥያቄ የሁሉም ኢትዮጵያዊ ጥያከ መሆኑን፣ የተጠየቀው ጥያቄ እርስዎ(አቶ ነአምን) አስረግጠው እንዳስገነዘቡን የኢሳትን ነፃ ሚዲያነት የሚጋፋ ሳይሆን በተቃራኒው ኢሳት እንደ አንድ ለኢትዮጵያ ህዝብ መረጃ ለማቀበል የሚሰራ ነፃ የሚዲያ ተቋም በስፋትና በከፍተኛ ትኩረት ሊሰራበት የሚገባዉን ወሳኝ ጭብጥ የያዘ መሆኑን፣ ለህዝብ ነፃነት የሚበጀው አንድ የተቃዋሚ ድርጅት ትእይንት ባዘጋጀ ቁጥር ብቻ ወይንም ገዢው መንግስት በህዝቡ ላይ በደል በፈጠመ ጊዜ ብቻ የተቃዋሚ መሪዎችኒና ታዋቂ ግለሰቦችን ማነጋገር ሳይሆን፣ የህዝቡን የመረጃ ክፍተት መሰረት ያደረገና ዘላቂነት ያላቸው የተጠኑ ውይይቶችን ለህዝብ ጆሮ ማቅረብ እንዳለበት ለማስገንዘብ የቀረበ መሆኑን አውቃችሁ ግዴታችሁን ለመወጣት ብታተኩሩ መልካም ነው፣ የሚሉ ናቸው።
በዚህ አጋጣሚ የኢሳት ራዲዮና ቴሌቪዥን ገዢው የኢህአዴግ መንግስት በኢትዮጵያ ህዝብ ላይ የሚያደርሳቸውን በደሎች በማስተጋባት ብሶቱን ለማሰማት እለት ተለት የሚያደርገውን ጥረት ለማድነቅ እወዳለሁ። ሆኖም በኔ እይታ ይህ የኢሳት ራዲዮና ቴሌቪዥን ጥረት ብቻውን፤ ለህዝብ ብሶቱን ከማሰማት ያለፈ አስተዋዕፅዎ ይኖረዋል ብዬ አላምንም። በመሆኑም ኢሳት እንደ ነፃ የሚዲያ ተቋም ህዝቡ በቂ መረጃን አግኝቶ እየደረሱበት የሚገኙትን ከመጠን ያለፉ ችግሮች ለማስቆምና፤ ብሎም ለነፃነቱ በጋራ ትግሉን ይቀላቀል ዘንድ ለማስቻል፤ የህዝብ ብሶትን ከማሰማት ባለፈ እጅግ በጣም ብዙ መስራት የሚጠበቅበት መሆኑን በማስገንዘብ፤ የህዝብ ነፃነትን  እውን ለማድረግ በሚደረገው ትግል ላይ እንደ ሚዲያ ሃላፊነቱን ለመወጣት መጠነ ሰፊ የሆነ የዝግጅትና የአቀራረብ ለውጥ ማድረግ እንደሚኖርበት ጥቆማዬን አቀርባለሁ።
ይህን ሃሳብ ሳካፍል ፅሁፌን ያየ ያነበበ የኢትዮጵያ ልጅ ሁሉ፤  እኔ የተረዳሁትን ተረድቶ መፍትሄውን እንዲፈልግ፤ አልያም ሃሳቤን ለማካፈል የሞከርኩት ነፃ ሚዲያ ያጎናፀፈኝን እድል’ ተጠቅሜ ነውና፤ ከተሳሳትኩ የመታረም መብቴ የተጠበቀ መሆኑን እንዲረዳልኝ እጠይቃለሁ። ስለሆነም የኔ ማጠቃለያ የነፃ ሚዲያዎች ትኩረትና የአንባቢያን ጠቃሚ አስተያየት እንደሚሆን በእጅጉ ተስፋ አደርጋለሁ።
ቸር እንሰንብት
ከዋስይሁን ተስፋዬ

Ethiopia ranks second poorest country in the world – Oxford University Study

June 17, 2014
According to The Global Multidimensional Poverty Index (MPI), published by Oxford University, Ethiopia ranks the second poorest country in the world just ahead of Niger. The study is based on analysis of acute poverty in 108 developing countries around the world. Despite making progress at reducing the percentage of destitute people, Ethiopia is still home to more than 76 million poor people, the fifth largest number in the world after India, China, Bangladesh and Pakistan. India has the world’s largest number of poor people at more than 647 million.
87.3% of Ethiopians are classified as MPI poor, while 58.1% are considered destitute. A person is identified as multidimensionally poor (or ‘MPI poor’) if they are deprived in at least one third of the weighted MPI indicators. The destitute are deprived in at least one-third of the same weighted indicators, The Global MPI uses 10 indicators to measure poverty in three dimensions: education, health and living standards.
In rural Ethiopia 96.3% are poor while in the urban area the percentage of poverty is 46.4%. Comparing the poverty rate by regions, Somali region has the highest poverty rate at 93% followed by Oromiya (91.2%) and Afar (90.9%). Amhara region has 90.1% poverty rate while Tigray has 85.4%.
Addis Ababa has the smallest percentage of poverty at 20% followed by Dire Dawa at 54.9% and Harar (57.9%).
Multidimensional Poverty Index Data bank. OPHI, University of Oxford
Ethiopia (MPI 0.564)
graph_mpi_nationals_headcont_loc
The boundaries and names shown and the designations used on this map do not imply official endorsement or acceptance by OPHI or the University of Oxford. This map is intended for illustrative purposes only.
Complementary data are taken from the closest available year to the year of the survey used to calculate the MPI. Income poverty is only shown where the data available are taken from a survey fielded within three years of the MPI survey year.
 graph_mpi_subnationals_decom

MPI – Overview

A person is identified as multidimensionally poor (or ‘MPI poor’) if they are deprived in at least one third of the weighted MPI indicators.
The proportion of the population that is multidimensionally poor is the incidence of poverty, or headcount ratio (H). The average proportion of indicators in which poor people are deprived is described as the intensity of their poverty (A). The MPI is calculated by multiplying the incidence of poverty by the average intensity of poverty across the poor (MPI = H x A).
If a person is deprived in 20-33.3% of the weighted indicators they are considered ‘Vulnerable to Poverty’, and if they are deprived inmore than 50% they are identified as being in ‘Severe Poverty‘. (The destitute) are deprived in at least one-third of the same weighted indicators, but according to more extreme criteria than those used to identify the MPI poor, while the level of inequality among the poor is calculated using a separate, decomposable inequality measure.
SurveyYearMultidimensional Poverty Index(MPI = HxA)Percentage of Poor People (H)
(k = 33.3%)
Average Intensity Across the Poor (A)Percentage of Population:Inequality Among the MPI Poor
Vulnerable to
Poverty
K=20%-33.3%
In Severe
Poverty
K=50%
Destitute
DHS20110.56487.3%64.6%6.8%71.1%58.1%0.290
graph_mpi_headcont_loc
graph_mpi_percnt_poor_deprvd
Population breakdown: Urban = 17.9% of population, Rural = 82.1% of population

MPI – Composition of Poverty

The Global MPI uses 10 indicators to measure poverty in three dimensions: education, health and living standards. This bar chart reports the proportion of the population that is poor and deprived in each indicator in the country selected. (The deprivation of non-poor people is not included.)
You can see the incidence of censored deprivation in each indicator at the national level, or compare the incidence in urban and rural areas by selecting ‘Urban/Rural’. (See the table below for the urban/rural population breakdown.)
Where subnational data are available, you can also compare the percentage contribution of each indicator to overall poverty across regions.
graph_mpi_deprivatn_each_ind
Percentage
of population
Multidimensional
Poverty Index (MPI)
=Percentage of Poor
People (H)
xAverage Intensity
Across the Poor (A)
Total100%0.564=87.3%x64.6%
Urban17.9%0.230=46.4%x49.5%
Rural82.1%0.637=96.3%x66.2%
graph_combined_mpi_contr_ovrall_povty_Abs
 graph_mpi_subnationals_decom_ind_wise
MPI – Intensity
A person who is deprived in 90% of the weighted MPI indicators has a greater intensity of deprivation, or poverty, than someone who is deprived in 40% of the indicators. The graphs below show the percentage of MPI poor people who are experiencing different intensities of deprivation, at the national level or in urban/rural areas. (See table above for the urban/rural population breakdown.)
In both graphs, people who are deprived in 50% or more of the indicators are identified as in ‘Severe Poverty‘.
 graph_mpi_intnsty_amng_poor
graph_mpi_prcnt_weghtd_ind_total (1)
Disclaimers:
This Databank presents the results of the Global Multidimensional Poverty Index (MPI) and explains key findings graphically. For an explanation of the MPI, along with more information, international comparisons and details of the resources available, please click here.
For information on the original MPI methodology and on the updates that took place in 2011, 2013 and 2014, please click here.
Please cite this data as: Oxford Poverty and Human Development Initiative (2014) Global Multidimensional Poverty Index Databank. OPHI, University of Oxford.

The Global MPI Database was last updated in June 2014

Tuesday, June 17, 2014

Woyane is a dead and deadly regime walking

June 17, 2014
Ethiopians must be very attentive to safeguard the safety of our people

Ethiopians must be very attentive to safeguard the safety of our people and the integrity of our country from a dead and deadly regime walking. We must warn the officials and the cadres of the regime to abandon Woyane like their colleagues or ultimately pay for all the crimes of the Woyane. There would be no excuses not to abandon the regime and expect a safe haven to hide or run.

by Teshome Debalke

The defection rate of Woyane’s officials and cadres are increasing faster than ever. In recent news several individuals including the Deputy Communication Minster Ermias Legesse, the Federal Prosecutor Tewodros Behar, the Ethiopian Commodity Exchange Executive Director Anteneh Assefa, and the General Manager of the Endowment Fund for Rehabilitation of Tigray (EFFORT) Getachew Belay Wendimu is the sign of a dead and deadly regime walking.

The testimony of the former Deputy Communication Minster Ermias Legesse 1 2 3 / alone is sufficient to the extent of the crimes of Woyane to abandon it. Others choose to remain silent as cowards from telling what they know. They will be sought out as conspirators of the regime’s crime for the rest of their lives.

Things are not going well for Woyanes. Desperation is setting in among the officials and the rank and file of the cadres of ruling regime Woyane. They are searching for a place to run for dear life.

There are no armed oppositions surrounding them to surrender yet. There is no popular uprising to overthrow the regime yet. They are afraid of the same regime they have been serving most of their adult life going to use them as fall guys for its extensive crimes to buy time.

The inner circles of TPLF are scared to their pants from each other and are in a no-way-in no-way-out position the regime put them in. It is like being in hard place and a rock. The grandfather of Woyane Sibhat Nega is seen shuttling back-and-forth to calm down the Gangs of Adwa to stick with each other or else.

The ethnic puppets Woyane assembled and use to justify its crimes are in more crises than ever. Used and abused as front men by TPLF’s ethnic agenda, they sensed they are disposable to get out of the jam the regime got itself in to save face. Stuck from getting out of their predicament of serving the criminal enterprise of TPLF they are looking for escape route out of the reach of the regime’s assassins.

The vocal Diaspora apologists are also looking for an easy way out of their association with Woyane. With very little options for their transgression against the people of Ethiopia for far too long, economic growth and peace and stability became the only safe things to say to feel better. The popular badmouths of Woyane are also toning down their insult of Ethiopians on behalf of TPLF– sounding more patriotic that unite Ethiopians than Woyane lovers. If it wasn’t for the perk, they would have bailed out sooner than later singing Tobia Hagre woy mot.

The top enchiladas of the regime are also scrambling to stop the bleeding of Woyane by throwing all kinds of bizarre propaganda as they go. Accordingly, terrorist are surrounding us is becoming the quick way of buying time until they find a better diversion.

Other developments are, the numbers of Woyane’s officials’ family abounding the country to settle around the world. ’According to the advocacy groups that follow up these case most of the families of high officials are seeking residency permits as investors while the low ranked cadres are applying for political asylum. Sources inside the regime reviled the operatives of the regime are issuing passport and legal papers for substantial fee to smuggle officials to preferred destination of Western countries.

Others that fear Diaspora oppositions in Western countries prefer to migrate in African countries, South Africa in Africa and Thailand and Malaysia in Asia being the preferred destination.

As much as many corrupt officials and their families are free to migrate anywhere around the world with stolen public money without much challenge, oppositions rarely challenge them with all legal means available in the countries of their destinations.

Ethiopians have a long way to go to setup legal groups to challenge the officials of the regime and their families that committed crimes of atrocities and corruptions. Medias can’t any longer seat ideal and watch when the regime officials and their family launder public money in front of our nose. Political parties can no afford to squabble over minor differences than saving their country and protecting their people they want to rule. Individual Ethiopians no longer can pretend the little benefit they may have gotten from Woyane in a form of land is sufficient to abandon their people and country for the criminal enterprise of TPLF.

It is time to standup and be counted

የጀኔራሎቹ የጓዳ ሽኩቻ! – ቀጣዩ ኢታማዦር ማን ነው?

June17/2014

‹‹ደመወዝ አነሰኝ ብሎ ጭማሪ የሚጠይቅ ካለ አሁንኑ ከሰራዊቱ መልቀቅ ይችላል፡፡›› ይህ የጦር ኃይሎች ኢታማዦር ሹምየሆነው ጀኔራል ሳሞራ የኑስ ሁለተኛው የሰራዊት ቀን በተከበረበት ሰሞን ባህር ዳር ከተማ ሙሉዓለም አዳራሽ ከተሰበሰቡት የሰራዊቱ አባላት መካከል የደመወዝ ጭማሪን በተ መለከተ ለተነሳለት ጥያቄ ምላሽ ሲሰጥ የተናገረው ነው፡፡ ኢትዮጵያ ከአጼ ኃይለስላሴ ዘመነ መንግስት ጀምሮ ዘመናዊ ውትድርናና የጦር ስልት ሰልጣኝ ወታደሮችንና መኮንኖችን በተደራጀ ስልጠና ማፍራት መጀመሯ ይጠቀሳል፡፡ በሀረርና ሆለታ የጦር አካዳሚዎች በመታገዝ ዘመናዊ የውትድርና ሳይንስ ትምህርት መሰጠት የተጀመረው በዚሁ በንጉሱ ዘመን ነበር፡፡ በዚህ መልኩ እየተደራጀ የመጣው የሀገሪቱ ሰራዊት እስከ ኢህአዴግ ወደ ስልጣን መምጣት ዘመን ድረስ የሀገሪቱ ብሄራዊ ሰራዊት ሆኖ ለመዝለቅ ችሏል፡፡ ሆኖም የደርግ ውድቀትን ተከትሎ በነበረው ጊዜ አያሌ የሰራዊቱ አባላት ለስደትና ሞት እንዲሁም ለብተና ለመዳረግ በቅተዋል፡፡

(በእርግጥ ቀደም ብለው የተማረኩትን የቀድሞው የሰራዊቱ አባላት በኢህአዴግ ውስጥ ማግኘት እንደሚቻል ኩማ ደመቅሳ (የፖሊስ መቶ አለቃ እነደነበር ይነገርለታል)፣ እና ተራ ሚሊሻ እንደነበር የሚነገርለት አቶ አባዱላ ገመዳን ከፊት መስመር ላይ በማስቀመጥ መጥቀስ ይቻል ይሆናል፡፡ እንደነዚህ ያሉት የቀድሞው ሰራዊት አባላት ደርግ ከመውደቁ በፊት ከድተው የህወሓትንና የኢህዴንን ታጋዮች የተቀላቀሉት ናቸው፡፡) እናም በጊዜው ታጋዮች ሀገሪቱን በሙሉ ለመቆጣጠር መቻላቸውን ተከትሎ የኢትዮጵያ ሰራዊት (የደርግ ሰራዊት ብቻ ብሎ ማቃለሉን አልፈለግሁትም) ሜዳ ላይ ተበትኖ እንደቀረ ይታወሳል፡፡ ስለሆነም የኢህአዴግ ሰራዊት ሲያሸንፍ ሊያስተምሩት የሚችሉ አንዳንድ የቀድሞው ሰራዊት አባላት መኮንኖችን ብቻ አስቀርቶ ሌላውን ወደጎን ገፍቶታል፡፡ በተለይም የኢትዮጵያ የባህር ኃይል ሙሉ ለሙሉ ሲፈርስ ያለቀው ሰራዊት አልቆ በዚያው የሸሸውም የመን ላይ ለእስር ተዳርጎ ከፍተኛ ስቃይ መጋፈጡ የአደባባይ እውነት ሆኖ ተመዝግቦ ይገኛል፡፡ በዚህም ኢትዮጵያ አሁን ላይ ያለ አንዳች ባህር ኃይል፣ ያለ አንዳች የተፈጥሮ የባህር በር የቀረች ሀገር ለመሆን ተዳርጋለች፡፡ አሁን ያለው መከላከያ ሰራዊታችን የምድርና የአየር ኃይልን ብቻ ያቀፈ ነው፡፡ የምድር ኃይሉ ሙሉ ለሙሉ ለማለት በሚያስደፍር ሁኔታ በቀድሞ ታጋዮችና በቅርብ ጊዜ ምልምሎች የተደራጀ እንደሆነ ሲነገርለት፣ አየር ኃይሉ ላይ ግን ኢህአዴግ እንደገባ የአየር ኃይል ሳይንስን እንዲያስተምሩት የመረጣቸውን ጥቂት የቀድሞው የኢትዮጵያ ሰራዊት አባላትን በውስጡ የኋላ ደጀን አድርጎ ይዞ መቆየቱ ይነገራል፡፡ በአጠቃላይ ህወሓት/ኢህአዴግ ደርግን አሸንፎ ስልጣን ላይ እንደወጣ በትግል ይዞት የመጣውን ሰራዊት ‹‹ብሄራዊ ሰራዊት›› ለማድረግ ችሏል፤ ወዲያውም እዙ በመለስ ዜናዊ ስር እንዲሆን መደረጉ ታወቀ፡፡ ኢህአዴግ እንደገባ አካባቢ ብዙ ሰዎች ሰራዊቱን ‹የገበሬ ሰራዊት› እያሉ ይጠሩት እንደነበር ይታወሳል፡፡ በሂደት ግን ቀድሞ የነበሩትንና ሌሎች አዳዲስ የወታደራዊ ትምህርት ቤቶችን በመጠቀም ሰራዊቱን የማዘመን ስራ ተሰርቷል፤ አዳዲስ የሰራዊቱ አባላትን በአዲስ ዘመናዊ ስልጠና ኮትኩቶ ወደሰራዊቱ ማካተት ተችሏል፡፡ አሁን ላይ የኢትዮጵያ ሰራዊት ልክ እንደ አያቶቹና አባቶቹ ሁሉ ግዳጁን በብቃት የመወጣት ተፈጥሮአዊ የጀግንነትና የግዳጅ ስብዕናን የተላበሰ እንደሆነ ብዙዎች ምስክርነታቸውን ይሰጡታል፡፡

በእርግጥም የሰራዊቱ ጀግንነት ሊካድ የሚችል አይደለም፤ ሀቅ ነውና፡፡ አንዱ ማሳያ የሚሆነንም በተለያዩ ዓለም አቀፍ የሰላም ማስከበር ግዳጆች ላይ አመኔታን አትርፎ በመመረጥ በተ ሰማራበት ግንባር ሁሉ በሚገባ ግዳጁን ለመወጣት መቻሉ ነው፡፡ አሁን ያለው ሰራዊት በአዲስ መልክ ‹ብሄራዊ ሰራዊት› ሆኖ በአዋጅ የተደራጀው የካቲት 7/1988 ዓ.ም እንደነበር ይታወሳል፡፡ (ይህን ቀን ከዛሬ ሁለት ዓመት በፊት ጀምሮ የሰራዊት ቀን በሚል ሰራዊቱ እንዲያከብረው ተወስኖ ሁለት ጊዜ ለማክበር ችሏል፤ የአድዋ ድል የተመዘገበበት ታሪካዊ ቀን እያለ ይህኛው እንዴት ‹‹የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት ቀን›› ተብሎ እንደተመረጠ አወዛጋቢ ቢሆንም ቅሉ!) ለማነኛውም በማደራጃ አዋጁ ላይ የመከላከያ ሰራዊቱን ግዳጅና ‹የማንነት› ተዋጽኦ በአጭሩ ለመግለጽ ተሞክሯል፤ ‹‹የሐገሪቱን ሉዓላዊነት የሚያስከብር፣ የኢትዮጵያን ብሔር ብሔረሰቦች ሚዛናዊ ተዋጽኦ ያካተተ፣ ከማናቸውም ፖለቲካ ድርጅት ወገንተኝነት ነጻ በሆነ ሁኔታ ተግባሩን የሚያከናውን ሰራዊት ማደራጀት…›› በሚል፡፡ ቃል የሚዋሸከው እንግዲህ እዚህ ጀምሮ ነው፡፡ ‹‹ሚዛናዊ ተዋጽኦ›› እና ‹‹ከማናቸውም ፖለቲካ ድርጅት ወገንተኝነት ነጻ…›› የሚሉትን ሀረጎች ወስደን ተግባር ላይ ያለውን ስናይ እውነታው ለየቅል መሆኑን እንገነዘባለን፡፡

በመጀመሪያ ደረጃ ኢህአዴግ ነባሩን የኢትዮጵያ ሰራዊት አፍርሶ በምትኩ ተሸክሞ ይዞት የመጣውንና ለስልጣኑ ያበቃውን ሰራዊት ‹ብሄራዊ ሰራዊት› ነው ሲል ወገንተኛነቱ እንደምን ያለ ሊሆን እንደሚችል ቀድሞ የሚያውቀው ጉዳይ ይሆናል፡፡ ሲቀጥል ደግሞ ካሉት አጠቃላይ የሐገሪቱ የጦር ጀኔራሎች መካከል ስንቶቹ የህወሓት ቀኝ እጅ እንደሆኑ ከኢህአዴግም ሆነ ኢትዮጵያ ህዝብ የተሰወሩ አለመሆናቸውን ኢህአዴግ ሊያጣው የሚችለው እውነታ አይደለም፡፡ እስካሁን ከነበሩትና አሁን ካለው የመከላከያ ሰራዊቱ ኢታማዦር ሹሞች መካከል ስንቶቹ የህወሓት እንደሆኑስ የማያውቅ ማን ነው? በእርግጥ አሁን ላይ በጣም አስቸጋሪ በሚባሉ የጦር ግዳጆች ላይ የትኞቹ የሰራዊቱ ክፍሎች በቀዳሚነት እንደሚመደቡ ይታወቃል፡፡ በመከላከያ ሰራዊት ኢንዶክትሪኔሽን ክፍል ውስጥ የሚሰራ አንድ ባለማዕረግ የሰራዊቱ አባል ስለዚህ ሁኔታ ሲገልጽ፣ ‹‹ያስፈልገኛል የምትለውን መሰረታዊ ነገር ለማግኘት እንኳ በጣም አዳጋች ነው፡፡ ሌላው ቢቀር በተለያዩ የሀገሪቱ የልማት ፕሮጀክቶች ላይ ጥበቃ የሚያደርጉ በረሃ አካባቢ ያሉ የሰራዊቱ አባላት ምን አይነት የግዳጅ ሁኔታ ላይ እንዳሉ የሚያውቀው ያውቀዋል፡፡ ስለሰራዊቱ ብዙ መናገር አይቻልም እንጂ ስንት ነገር አለ መሰለህ? አድራጊ ፈጣሪዎቹ ግን እዚህ አዲስ አበባ ላይ ያሉት ሰዎች ናቸው፡፡ ምደባው ጎጠኝነትና ጎሰኝነትንም እንደ ስውር መስፈርት ያስቀመጠ ነው፡፡›› ይላል፡፡ በእርግጥ የእነዚህ በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ ሆነው ግዳጃቸውን የሚወጡ የሰራዊቱ አባላት ሁኔታ እዚህ መሀል ሀገርና አንጻራዊ ሰላም ባለበት ቦታ ላለነው ኢትዮጵያውያን በግልጽ ባይታየንም፣ በከፍተኛ የሀገርና የወገን ፍቅር ስሜት ሆነው ግዳጃቸውን ስለሚወጡ ግን ምስጋና ይገባቸዋል፡፡

የእነዚህ ቆራጥ ወገኖቻችን ጥረት ነው ሀገርንና ህዝብን የሚ ያስከብረው፡፡ ዳሩ ግን እንዲህም ሆነው ግዳጃቸውን ሲፈጽሙ ትንሽ እንኳ የደመወዝና የጥቅማጥቅም ጥያቄ ሲያነሱ፣ ‹‹ደመወዝ አነሰኝ ብሎ ጭማሪ የሚጠይቅ ካለ አሁንኑ ከሰራዊቱ መልቀቅ ይችላል፡፡›› የሚል አግባብ ያልሆነና አሳፋሪ መልስ ይሰጣቸዋል፡፡ ይህን መሰሉን መልስ የሚሰጡት ጀኔራሎች እዚህ አዲስ አበባ ላይ የተንደላቀቀ ኑሮ እየኖሩ፣ ምንጩ ያልታወቀ ሀብት እያፈሩ መሆኑ ደግሞ ግርምትን የሚያጭር ነው፡፡

 አሁን አሁን ጄኔራሎቻችን የብዙ ኃብት ባለቤቶች እንደሆኑ ይነገራል፤ ይህ ፎቅ የጀኔራል እገሌ ነው፣ ያኛው ደግሞ የጀኔራል እገሌ ነው የሚሉ በርካቶች ናቸው፡፡ ለመሆኑ እነዚህ ጀኔራሎች ገቢያቸው ምን ያህል ነው ብለን ስንጠይቅ ግን ምላሽ አናገኝም፤ ገቢያቸው ይሆናል ብለን ከምናምነው ጋር ለማገናዘብ ከሞከርን ደግሞ ሰዎቹ ሙስና ውስጥ መዘፈቃቸውን ለመናገር እንደፍራለን፡፡ (በነገራችን ላይ የኢትዮጵያ ኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት መስሪያ ቤት ኃላፊ ተደርጎ የተሾመው ሰው ራሱን ከሙስና ያራቀ እንደሆነ የሚነገርለት ሲሆን በሌሎች ሰዎች ላይ ያለውን አሰራር በቅርበት እየተከታተለ እንደሆነ ምንጮች ያነሳሉ፡፡ ‹‹ተውአቸው የሰሩትን ፎቅ ይስሩ፤ በባንክም የሚያስቀምጡትን ያህል ያስቀምጡ፤ በቅርብ ጊዜ ግን ሀብቱ ለሚመለከተው የኢትዮጵያ ህዝብ ይመለሳል›› በማለት መናገሩንም የሚያስታውሱ አሉ፡፡ ይህን የሰውየውን ባህርይ ያጤኑት አንዳንድ ጀኔራሎችና ባለስልጣናት ታዲያ ሰውዬውን ከሙስናና ሌሎች ተያያዥ ጉዳዮች ጋር ለማነካካት ሙከራ ማድረጋቸው አልቀረም፤ እስካሁን እየተሳካላቸው እንዳልሆነ ቢነገርም ቅሉ፡፡) ዝሆኖቹ ጀኔራሎች ይህ ሁሉ ነገር አያሳስባቸውም፤ ተቆጭም ያላቸው አይመስሉም፡፡ እነሱን የሚያሳስባቸው በመካከላቸው ያለውና ሊኖር የሚገባው የእርስ በእርስ የበላይነት ነው፤ በስልጣንም በሀብትም፡፡ ባለ አራት ኮከብ ጀኔራሉ ሳሞራ የኑስ በመለስ ዜናዊ ምርጫ የጦር ኃይሎች ኢታማዦር ሹም ተደርጎ የተሾመው የዛሬ ሰባት አመት ገደማ እንደነበር ይታወሳል፡፡ (የመጀመሪያው ባለ ሙሉ ጀኔራል ማዕረግ ያገኘ በሚል ምስሉ ብሄራዊ ሙዚየም የተቀመጠለት የጦር ሰው ሳሞራ የኑስ ነው፡፡) ይህ ሰው እስካሁን በስልጣን ላይ ለመቀመጡ ዋነኛ ምክንያት የሚባለው ለመለስ ዜናዊ የነበረው ቅርበትና ታዛዥነት ነው፡፡ በእርግጥ ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ሞት ባይቀድመው ኖሮ ሳሞራን ከኢታማዦርነቱ የማንሳት እቅድ እንደነበረው ይነገራል፡፡

ይህንን ጠንቅቆ ያውቅ የነበረው ጀኔራል ሳሞራ ታዲያ የሚሻርበትን ቀን ሲጠብቅ መለስ ህይወቱ በማለፉ በያዘው ቦታ ለመደላደል ስራዎችን መስራት እንደጀመረ ይወሳል፡፡በመለስ ዜናዊ እቅድ ውስጥ ሳሞራን እንዲተካው ተዘጋጅቶ የነበረው ደግሞ ሳሞራ የሙሉ ጀኔራልነት ማዕረግ ሲደፋለት በሁለተኛነት ደረጃ የሌትናት ጀኔራልነት ማዕረግን የተጎናጸፈው የ‹ብአዴኑ› ወጣቱ የጦር ሰው አበባው ታደሰ ነበር፡፡ ይህን የአበባው ወደ ኢታማዦር ሹምነት መምጣትን አጥብቀው ከማይፈልጉት ሰዎች ደግሞ ጀኔራል ሳሞራ ዋነኛው እንደሆነ ይነገራል፡፡ በዚህም የተነሳ የመለስን ህልፈት ተጠቅሞ ሳሞራ አበባውን ከሰራዊቱ የማግለል ስራ እንደሰራ የሚጠቅሱ አልጠፉም፡፡ እናም የማዕከላዊ እዝ ዋና አዛዥ የነበረውን ሌትናንት ጀኔራል አበባው ታደሰን በቦታው መቆየት ሳሞራ የፈለገው አይመስልም፡፡ አበባው ከማዕከላዊ እዝ አዛዥነት እንዲነሳ ተደረገ፡፡ ይህም ብቻ ሳይሆን ሳሞራ እምብዛም ቅርብ እንዳልሆነ የሚነገርለትን ሌላው ‹ጠንካራ› ሰው ሌትናንት ጀኔራል ሳዕረ መኮንን (የሰሜን እዝ ዋና አዛዥ የነበረ) ከኃላፊነቱ እንዲነሳ ተደረገ፡፡ አሁን ጀኔራል ሳሞራ ስጋቶቹን ያቃለለ መሰለ፡፡

ሂደቱ በዚህም የሚያበቃ እንዳልሆነ ነው ምንጮች የሚጠቁሙት፡፡ በተለይም በሌትናት አበባው ታደሰ ላይ ያለው ስጋት እሱን ከኃላፊነት በማንሳት ብቻ የሚያበቃ አልሆነም፡፡ በማዕከላዊ እዝና በሌሎችም በሰራዊቱ ከፍተኛ ተቀባይነት እንዳለው የሚነገርለት በእድሜ ትንሹ ጀኔራል አበባው ታደሰ ኃላፊነቱ ከተነሳም በኋላ ከፍተኛ ክትትል እንደሚደረግበት ነው የሚነገረው፡፡ በተለይም ከሰራዊቱ ከአዛዥነቱ ከተነሳ በኋላ ምዕራብ ጎጃም አዊ ከሁለት ሲቪሎች ጋር አንድ ሻይ ቤት እንደታዬ መነገሩ ከፍተኛ ጥርጣሬ እንዲነሳበት አስችሎአል፡፡ ይህን ተከትሎ በማዕከላዊ እዝ ሲደረግ በነበረው ግምገማ ወቅት አንዳንድ የሰራዊቱ አባላትን በጎጠኝነት ሰበብ የማደናገር ሁኔታ እንደታዬ ይጠቀሳል፡፡ አንዳንዶች በግልጽ ‹‹የአበባው አሽከር ነበርኩ ብለህ ሂስህን ዋጥ!›› እየተባሉ እንደተገመገሙ ምንጮች ያወሳሉ፡፡

በእርግጥም አሁን ጀኔራል ሳሞራ ጡረታ የሚወጣበትን ጊዜ በሚገባ ያራዘመ ይመስላል፤ ስጋት ያላቸውን ሰዎችም ከቁልፍ ቦታቸው ለማሸሽ ችሏል፡፡ በመከላከያ ሰራዊት ደንብ መሰረት ቅድሚያነትና ብቃት (ሲኔሪቲ) ትልቅ ተጽዕኖ አላቸው፡፡ ይህን ካየን ደግሞ አሁን ላይ ሰራዊቱ ውስጥ ካሉ ጀኔራሎች መካከል የሳሞራ ምትክ ሊሆን የሚችለው በቀዳሚነት ከሳሞራ አንድ ደራጃ ወረድ ብሎ የሚገኘውና ከሌሎቹ ቀደም ብሎ ሌትናት ጀኔራልነትን ያገኘው አበባው ታደሰ ነበር፡፡ ይህ እንዲሆን ያልፈለገው ሳሞራ ግን ሰውዬውን ገለል ማድረጉን መርጧል፡፡ ሳዕረንም እንዲሁ፡፡ መረጃዎች እንደሚጠቁሙት ጀኔራል ሳሞራ እንዲተካው የሚፈልገው አሁን በአብዬ የሰላም ማስከበር ግዳጅን በአዛዥነት የሚመራው ሌትናት ጀኔራል ዮሃንስ ገብረመስቀል ነው፡፡ ይህ ሰው ሌትናት ጀኔራልነቱን ያገኘው በቅርብ ቢሆንም የእሱን ሲኔየሮች ከኃላፊነት ገለል በማድረግ እሱ ወደመሪነቱ እንዲመጣ የተፈለገ ይመስላል፡፡ ሌትናት ጀኔራል ዮሃንስ ገብረመስቀል ከጄኔራል ሳሞራ ጋር ጥብቅ ወዳጆች እንደሆኑ ይነገርላቸዋል፡፡ ዮሃንስ ከፍተኛ ሀብት እንዳካበቱ ከሚነገርላቸው ጀኔራሎች መካከል ሲሆን በአሁኑ ጊዜ ደመወዙ በአስራ ሺ የሚቆጠር ዶላር እንደሆነ ይጠቀሳል፡፡ ቢሆንም ግን ሀብታምነቱ አሁን የዚህ ደመወዝ ባለቤት ከመሆኑም የቀደመ ለመሆኑ መረጃዎች ያሳብቃሉ፡፡ (ሌትናት ጀኔራል ዮሐንስ የደህንነቱን ስራ በኃላፊነት የሚዘውረው ጌታቸው አሰፋም ድጋፍ እንዳለው ይጠቀሳል፡፡)

 በዚያም አለ በዚህ ግን አሁን ላይ ሳሞራ መለስ በህይት እያለ ከነበረው እቅድ በወጣ መልኩ በኢታማዦር ሹምነቱ መቆየቱ ሀቅ እንደሆነ ይገኛል፤ የጡረታ ጊዜውን ማንም ቆርጦ ማስቀመጥ የተቻለው የለም፡፡ በስብሰባዎች ወቅት በድፍረት እያንዳንዱን ነጥብ እያነሳ ይገስጻቸው ነበር የሚባልለት ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ አሁን የለም፡፡ ስለዚህም አሁን ሳሞራም ሆነ ሌሎች ጄኔራሎች ተቆጭ የሌላቸው እንደሆኑ ነው የሚነገረው፡፡ በትንሹም ቢሆን አቶ በረከት ስምዖን የመለስን ቦታ ተክቶ ለመገሰፅ የሚሞክርበት አጋጣሚ ቢኖርም እንደመለስ ግን አይደነግጡለትም፤ በስልጣናቸውም ላይ ለውጥ የሚያመጣ መስሎ አይሰማቸውም ነው የሚባለው፡፡ በመጨረሻም፣ የጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝን ሚና እዚህ ላይ ማንሳቱ እምብዛም አስፈላጊ አይመስለኝም፡፡ በእርግጥ የጦር ኃይሎች ጠቅላይ አዛዥ ናቸው፡፡ ያም ቢሆን ግን ጀኔራሎቹ ለሰውዬው እንደቀድሞው አዛዣቸው መለስ ዜናዊ አድርገው የሚመለከቷቸው አይመስለኝም፡፡ እናም አሁን በሰራዊቱ ውስጥ ወሳኙ አድራጊ ፈጣሪው ሰው ሳሞራ የኑስ ለመሆኑ ጥርጥር የለውም፡፡ ለዚያም ይመስላል ከሰራዊቱ ለተነሳለት ጥያቄ ‹‹ካልፈለግህ ልቀቅ…›› ምላሽ ለመስጠትየበቃው፡፡ ለዚያም ይመስላል ለቀጣይ የስልጣን ጊዜው ‹ስጋቴ› ናቸው ያላቸውን ሲኒየር ጀኔራሎችን ከአዛዥነት ያነሳቸው፡

ለምን የሳሙኤል ዘሚካኤል ጉዳይ ያን ያህል ያስደንቀናል? (በትረ ያዕቆብ)

June17/2014
ሰሞኑን በማህበራዊ ድረ ገፆች አካባቢ የህዝብን ቀልብ መሳብ የቻለና አሁንም ዋና መወያያ አጀንዳ ሆኖ የቀጠለ ጉዳይ ተከስቷል የሳሙኤል ዘሚካኤልየሀሰትዶክተር እናኢንጂነርነት፡፡ ጉዳዩ ብዙዎችን አጃኢብ አስብሏል ፤ አሁን በርካቶች ብስጭታቸዉን እና ቁጣቸዉን በተለያየ መንገድ እየገለፁ ይገኛል፡፡ ብዙ ሰዎች በአንድ ወቅት የስኬት ምልክታቸዉ እስከ መሆን የደረሰና አድናቆታቸዉን ያጎረፉለት ሰዉ ድንገት የሀሰት ሆኖ ሲያገኙት መደናገጣቸዉ አልቀረም፡፡

እርግጥ ነዉ ነገሩ ትንሽ የሚያስገርም ነዉ፡፡ ወጣቱ የሄደበት እርቀት ግራ የሚያጋባና ድፍረቱ የሚያስገርም ነዉ፡፡ ሌላዉን ትተን በሀገር ዉስጥ የሚገኙትን ዩንቨርሲቲዎች ስም ደጋግሞ እያነሳ ይህንን ሸለሙኝ ፣ ይህንን ሰጡኝ ፣ የረዳት ፐሮፌሰርነት ማዕረግ ተበረከተልኝ ወዘተ ማለቱ በእርግጥም ከማሰገረም አልፎ ብዙ ያስብላል፡፡ ያም ሆኖ ግን እኔን ይበልጥ ያስገረመኝ ጉዳዩ ዚያን ያልህ እንደ ተዓምር የመታየቱ ነገር ነዉ፡፡ በጉዳዩ ዙሪያ እየተደረገ ያለዉን ዉይይት ስመለከት እንዴ ነዉ ነገሩ ብየ መደነቄ አልቀረም፡፡

በዚህ ወጣት የተፈፀመዉ አሳፋሪ ተግባር ዛሬ የተከሰተ አዲስ ክስተት አይደለም ፤ የነበረና አሁንም እየተፈፀመ ያለ ነገር ነዉ፡፡ እዉነቱን መነጋገር ካለብን መሰል ማጭበርበር ቤተ-መንግስት አካባቢ በጣም የተለመደ እና ብዙዎች የተጨማለቁበት ተግባር ነዉ፡፡ ይታያችሁ ፣ ቤተ-መንግስት ነዉ ያልኩት፡፡ ይህንን ስናይ ወጣቱ የፈፀመዉ ተግባር የሚደንቅ አይመስለኝም፡፡ እንዴትስ ያስደንቃል፡፡

ዛሬ ሳሙኤልዘሚካኤልእድል ጥሎት ሁሉም ተረባረበበት እንጅ የኢህአዴግ ባለስልጣናት የትምህርት ማስረጃ ቢመረመር ስንት ከሱ የባሰ ጉድ ይገኝ ነበር፡፡ እንግዲህ ሀገርን ያህል ትልቅ ነገር እንመራለን የሚሉ ግለሰቦች መሰል ተግባር በሚፈፅሙበት አገር የዚያ ወጣት ተግባር ጉድ የሚያስብልበት ምክንያት አይታየኝም፤፤ እንዴትስ ሊያስብል ይችላል፡፡ ከዚህ ይልቅ ቤተ-መንግስት ተቀምጠዉ አገርን የሚዘዉሩ ግለሰቦች ፣ በያንዳንዳችን እጣ ፈናታ ላይ የመወሰን ስልጣን በጉልበት የጨበጡ ባለስላጣናት የሀሰት ማስረጃ ሊያስደንቀን ፣ ሊያበሳጨን ፣ ሊያስደነግጠን ይገባ ነበር፡፡

ዛሬ በርካታ የኢህአዴግ/ህወሀት ጉምቱ ባለስልጣናት እንከዋን ትምህርት ቤት ገብተዉ ሊማሩ በበሩ እንኳን ሳይልፉ ባለሁለተኛ እና ሶስተኛ ድግሪ የመሆናቸዉ ጉዳይ ለብዙዎቻችን ሚስጥር አይመስለኝም፡፡ ዛሬ የአዲስ አበባ ዩንቨርሲት ድግሪና ማስትሬት በቀጭን ትእዛዝ እንዳሻቸዉ የሚሰበስቡት ተራ ነገር ነዉ፡፡ ሲያሻቸዉም ከዉጭ በገንዘብ ይሸምቱታል፡፡ ሲልም እድሜ በሙያዉ ለተካኑ የቻይና እና የህንድ ዜጎች እንደፈለጉት አሳምረዉ አዘጋጅተዉ ኮንግራ ይሏቸዋል፡፡ከዛም ከለታት አንድ ቀን ብቅ ብለዉ ይህ አለን ይላሉ፡፡ ይህ ነዉ ለኔ አሳፋሪዉ ፣ አስደንጋጩ፡፡ በእንዲህ አይነት መልኩ በርካታ ትልልቅ ባለስልጣናት የሀሰት የክብር ካባ ለመደረብ ሞክረዋል፡፡ አሁንም ብዙዎች ይህንን መንገድ ቀጥለዉበታል፡፡ ከብዙ ወራት በፊት አንድ አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ዉስጥ የሚሰራ ወዳጄ ሲያጫዉተኝ “ዩንቨርስቲዉ በካድሬ መመራት ከጀመረበት እለት አንስቶ በርካታ የኢህአዴግ መኳንንቶችን በማዕረግ” አመርቋል” ነበር ያለኝ፡፡ ይታያችሁ እርሱ ያለዉ “በማዕረግ” ነዉ፡፡ ይህ ማለት ሳይማሩ ፣ ሳያጠኑ ፣ ሳይፈተኑ ኤ በ ኤ ይሆናሉ ማለት፡፡ ለኔ ይሄ ነዉ አስደንጋጩ ጉዳችን፡፡ ይህ ወዳጄ እንደነገረኝ አልፎ አልፎም በዉጭ ዩኒቨርስቲ መማር የሚፈልጉ ከተገኙም የሚፈልጉትን የትምህርት መስክ መርጠዉ የመዓረግ ተመራቂ ተብሎና ሁሉም ነገር ተሟልቶለት ይሰጣቸዋል፡፡ እኒህ ሰዎች ናቸዉ ዛሬ ሀገሪቱን የሚመሩት ፤ ከእኛ በላይ አዋቂ የለም የሚሉን ፣ የጭቆና ቀምበር ጭነዉ ፍዳችንን የሚያሳዩን፡፡
 ከዚህ ጋር በተያያዘ ሁለት ግለሰቦች ማንሳት እዉዳለሁ፡፡ ይህ ለምሳሌ ያህል ብቻ ነዉ፡፡ የመጀመሪያዉ በአንድ ወቅት እንደ ምሁር ለመፈላሰፍ ሲቃጣዉ የነበረዉ የቀድሞዉ ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ መለስ ዜናዊ ነዉ፡፡ ሰዉየዉ ትምህርቱን ከዩንቨርሲቲ አቋርጦ በረሀ እንደ ወረደ እና ከ17 አመት የትጥቅ ትግል በኋላ በለስ ቀንቶት ቤተ-መንግስት እንደገባ ነዉ ነበር የምናዉቀዉ፡፡

ሆኖም ከእለታት በአንዱ ቀን አቶ ምን ይሳነዋል ባለሁተኛ ድግሪ ምሁር ነዉ ሲባል ሰማን ፣ ያም አልበቃ ብሎ ሌላም እንዳከሉበት የቀብሩ እለት ተነገረን፡፡ የአቶ ሳሞራ የኑስም ታሪክ ተመሳሳይ ነዉ፡፡ 11ኛ ክፍል አቅርጠዉ በረሀ ገብተዉ እንደታገሉ እንጅ ሌላ የምናዉቀዉ ነገር አልነበረም፡፡ ሆኖም እርሳቸዉ ከ11 ክፍል በአቋራጭ ከፈለጉት ቦታ ላይ ጉብ አሉ፡፡በሀዉልታቸዉ ላይም ባለ ሁለተኛ ድግር ምሁራ ናቸዉ ተብሎ ተፃፈ፡፡ እንዴት ብሎ የጠየቀም አልነበረም፡፡ እስከማዉቀዉ ድረስ በጉዳዮ ላይ ጥያቄ ያነሳ ብቸኛ ሰዉ ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ ብቻ ነዉ፡፡ ዛሬ “ለእዉነት ቆሜያለሁ” የሚለዉ ሬድዮ ፋናም ያኔ አዳች ነገር ትንፍስ አላለም ነበር፡፡ ይህ ብቻ አይደለም በቅርቡ ብዙ አፍሪካዊ ጋዜጠኞች የተሳለቁበት በሀሰት የትምህርት ማሰረጃ በመንግስት ሴራ የአፍሪካ ህብረት አካል በሆነ ድርጅት ዉስጥ ትልቅ ስልጣን እስከመጨበጥ የበቃዉ የኢህአዴግ ካድሬም በምሳሌነት ሊጠቀስ ይችላል፡፡

እንግዲህ ይታያችሁ እነዚህ ሰዎች ሀገር መሪ ነን ይላሉ፡፡ እነዚህ ናቸዉ የሀገሪቱን ፖሊሲና እስትራቴጅ ቀራፂያን ፣ እነዚህ ናቸዉ ሀገሪቱ እና እኛን ወክለዉ ከሌሎች ጋር የሚደራደሩት ፣ እነዚህ ናቸዉ ዛሬ በእያንዳንዳችን ህልዉን ላይ ወሳኝ ሆነዉን የሚገኙት፡፡ ይህ ነዉ እኔን ይበልጥ የሚያሳፍረኝ ፣ የሚያሰገርመኝ፡፡ ይህ ነዉ ለኔ ትልቁ ጉድ፡፡ እንዴት ነዉ እንዲህ አይነት የሀገር መሪዎች ባሉበት ሀገር አንድ ከደሀ ቤተሰብ የወጣ ልጅ የፈፀመዉ የማጭበርበር ተግባር የሚደንቀዉ፡፡ ነዉ ወይስ አላዉቅም ልንል ነዉ፡፡

ከባለስላጣናቶቻችን እና ከእኛ ዜጎች አልፎ ተርፎ እንኳ በየዩንቨርስቲዉ በዶክተር እና ፕሮፌሰርነት ማዕረግ ስም የሚያጭበረብሩት የዉጭ ዜጎች በርካታ አይደሉም? የመጀመሪያ ድግሪ ይዘዉ በዶክተር ስም የነገ ሀገር ተረካቢ በሆኑ ወጣት ልጆች ላይ ሲቀልዱ አላየንም ፣ አልሰማንም ? ለምሳሌ እንኳን በቅርቡ ወደ አንድ የዉጭ ዩንቨርስቲ ሁለተኛ ድግሪዉን ለመማር ያቀና ወጣት ዶክተር ነኝ ብሎ ካስተማረዉ የዩንቨርሲቲ መምህሩ ጋር በአንድ ክፍል ዉስጥ ለትምህርት እንደተገናኙ ሲተረክ ሰምተናል፡፡

በጥቅሉ እንነጋገር ከተባለ በርካታ ጉድ በዙሪያችን አለ፡፡ ዘርዝረን አንጨርሰዉም፡፡ በመሀከላችን በርካታ የቀበሮ ባህታዊያን እንዳሉ ልብ ልንል ያገባል፡፡ ይህ እየሆነ ባለበት አገር የሳሙኤልተግባር ለኔ ብዙ የሚያስደንቅ ነዉ ብየ አላስብም፡፡ እንዴዉም በአንድ ግለሰብ የማጭበርብር ተግባር ላይ ብቻ ማፍጠጡ ችግሩ እንደሌለ ያስመስለዋል ፤ ወደ መፍትሄም አይወስድም፡፡ ስለዚህም ችግሩን ሰፋ አድርጎ ማየትና አፍረጥርጦ መነጋገር ተገቢ ነዉ እላለሁ፡፡ ሬድዮ ፋናም ቢሆን “ለእዉነት ቆሜያለሁ” የሚል ከሆነ በአንድ ግለሰብ ተግባር ላይ ብቻ ከማንባረቅ በዘለለ የሌሎችንም በተለይም ሀገር እንመራለን በሚሉ የኢህአዴግ/ ህወሀት አምባገነን ባለስልጣናት እየተፈፀሙ ያሉ ማጭበርበሮችን ሊያጋልጥ ይገባል፡፡ እርግጥ ኢህአዴግ አምጦ ከወለደዉ ተቋም ይህን መጠበቅ ሞኝነት ነዉ፡፡

ለሁሉም ቸር እንሰንብት !