Saturday, June 14, 2014

ወጣቶቹና- ቅዳሜ፣ አንዷን ቅዳሜ በፍርድ ቤት

June14/2014
ጽዮን ግርማ

Jailed blog9 bloggers in court

ለአብዛኛው ወጣት አዲስ አበባ ላይ ‹‹ቅዳሜ›› ትርጉም አላት፡፡ የሣምንቱን የሥራ ቀናት በየፈርጁ ያሳለፈው ኹሉም ወጣት ‹‹ቅዳሜ››ን ደግሞ እንደየ ምድቡ ይውልባታል፡፡ እንደሰማኹት ከኾነ ለዞን ዘጠኝ አባላትና ጓደኞቻቸውም ቅዳሜ ልዩ ቀን ናት፡፡ ለወጣቶቹ አብሮነት የጡመራ መድረኩ ቢያግዛቸውም ከዛ በላይ ግን ጓደኝነታቸው ቤተሰባዊነትን ፈጥሮላቸው አብዛኛውን ቅዳሜ እንደየ ቅርበታቸው አብረው ያሳልፋሉ፡፡
አብረው እስረኛ ይጠይቃሉ፣የታመመን ያጽናናሉ፣በጋራ ምሳ ይቋደሳሉ፣የተለየ ዝግጅት ካለም አብረው ይሳተፋሉ፡፡ ከዚህ የተረፈ ጊዜ ካላቸው ደግሞ ፈጣንንና ነጻ የገመድ አልባ ኢንተርኔት አገልግሎት በሚገኝበት ሆቴል ገብተው ዓለም በምን ኹኔታ ላይ እንዳለች ለመከታተል ይሞክራሉ፡፡ አገሪቷ ውስጥ ባለው ከፍተኛ የኢንተርኔት ኮኔክሽን ችግር ምክንያት አብዛኛው ጋዜጠኛና ጥቂት ወጣቶች የእነዚህ ትልልቅ ሆቴሎች ገመድ አልባ ኢንተርኔት ተጠቃሚ ነው፡፡ በቅዳሜ ወደእነዚህ ሆቴሎች ጎራ ያለ ከጦማሪያኑ ወይም ከጋዜጠኛEthiopia bloggers in court አንድ ሰው ሊያገኝ ይችላል፡፡ በቃ ሲገናኙ ሰላም ተባብለው መቀላቀል ነው፡፡እናም በአንድ ጉዳይ ጨዋታ ጀመራል፡፡ አብዛኛው ጨዋታ በአገር ጉዳይ ላይ ያተኮረ ሊኾን ይችላል፡፡ ኮምፒዩተሮቻቸውን እየነካኩ ስለ አገራቸው ግድ ያላቸውን ይነጋገራሉ፣ይከራከራሉ አሊያም ይጨቃጨቃሉ፡፡መሄጃው ሰዓት የደረሰበት ደግሞ ተሰናብቶ ይሄዳል፡፡በእነዚህ ሆቴሎች በቀጠሮ የሚገናኝ ሰው የለም፡፡‹‹የት ነህ? የት ነሽ?›› የሚለው የስልክ ጥያቄም ለመገናኘት በቂ ነው፡፡
የተስፋዓለም ቅዳሜ ደግሞ ሌላ ነበረች፡፡ሥራ ከጀመረበት ጊዜ ጀምሮ አብዛኛውን አርቦች ከእነ ለሊታቸው በሥራ ያጠፋቸዋል፡፡ቅዳሜንም ረፈድ አድርጎ ይነሳል፡፡ እናም የመጀመሪያ ሥራው ለሕትመት የበቁ ጋዜጣና መጽሔቶችን አበጥሮ ማንበብ ነው፡፡ በማንበብ ብቻም አያቆምም፤ ከዘገባዎቹ አብዛኖቹ የተሠሩት በጓደኞቹ አሊያም በሚያውቃቸው ጋዜጠኞች ስለሚኾን ስልክ ይደውላል፡፡ ከዘገባዎች ውስጥ ተስፋዓለምን የሚያስደስቱት በጣም ጥቂቶቹ ብቻ ሊኾኑ ስለሚችሉ የስልክ ልውውጦቹ ‹‹እንዲህ ብታደርግ/ብታደርጊ ኖሮ፣እንትናን ብታናግረው በዚህ ጉዳይ ላይ መረጃ ይሰጥህ ነበር፣እዚህ ቦታ እኮ እንዲህ ዓይነት መረጃ ነበር፣ይሄ እኮ ከዚህ በፊት እንዲህ ያለ ሕትመት ላይ ወጥቷል፣እውነቱን ለመናገር ይሄ ለሕትመት የሚበቃ ዘገባ ነው ብዬ አላምንም›› በሚሉ አስተያየቶች የተሞሉ ነበሩ፡፡ በዚያው ልክ ደግሞ የሚያስደስተውን ዘገባ ሲያነብ ወይም ፕሮግራም ሲሰማ አዘጋጁን አወቀው አላወቀው ስልክ አፈላልጎ በመደወል ያበረታታል፡፡ የተስፋዓለም ግማሽ ቅዳሜ የምታልቀው ይህን ሲያደርግ ነው፡፡
አኹን እነዚህ ወጣቶች ቅዳሜያቸውን በፌደራል ወንጀል ምርመራ መምሪያ (ማዕከላዊ) ፖሊስ ተነጥቀዋል፡፡ ሃምሳ ቀናት ታስረው ዘጠኝ ቅዳሜን አጥተዋል፡፡ እንዳሻቸው የሚያደርጓትን ቅዳሜ አኹን እነርሱ አያዙባትም፡፡ ከጠዋቱ ዐስራ ሁለት ሰዓት ሲል ከእንቅልፋቸው ይቀሰቀሳሉ፡፡ ለቁርስ ዳቦ በሻይ ይሰጣቸዋል፡፡ (ቤተሰብ የሚያወስድላቸው ምግብ ቁርስ ከበሉ በኋላ ነው የሚደርሳቸው) እናም ተመልሰው ገብተው ይዘጋባቸዋል፡፡አብዛኞቹ ለየብቻ ከሌሎች እስረኛ ጋር የታሰሩ ሲኾን ሁለት፣ ሁለት ተደርገው የታሰሩም አሉ፡፡እናም ከምርመራ የተረፈ ቀናቸውን በዝጉና በጨለምተኛው ክፍል ያሳልፋሉ፡፡ በአንዷ ቅዳሜ ደግሞ እንደዛሬው ፍርድ ቤት ይቀርባሉ፡፡
አንዷን ቅዳሜ- በፍርድ ቤት
ሦስቱ ወጣቶቹ እነርሱ በማያዙባት ቅዳሜ እጆቻቸውን በካቴና ታስረው ፒያሳ በሚገኘው የፌደራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ ችሎት ግቢ ውስጥ ሲደርሱ ከሌላው ጊዜ የበለጠ ቁጥር ያለው በዐይን ግምት ሦስት መቶ የሚደርስ ችሎት ተከታታይ በግቢ ውስጥ ተገኝቶ ነበር፡፡ የዛሬዎቹ ጠባቂ የፌደራል ፖሊሶች ባለፈው ጊዜ ከነበሩት ሻል ያሉ ስለነበሩ ቤተሰቦች ችሎት ውስጥ ገብተው እንዲታደሙ ባይፈቀድላቸውም ግቢ ውስጥ ከመቆም የከለከላቸው ወይም ያመናጨቃቸው አልነበረም፡፡ bloggers in court Addis Ababa, Ethiopia
ከጠዋቱ አራት ሰዓት ከሃያ ደቂቃ አካባቢ ሲኾን ችሎቱ በሴት ዳኛ በመሰየሙ፤ጋዜጠኛ ኤዶም ካሳዬ፣የዞን ዘጠኝ ጦማሪዎቹ ናትናኤል ፈለቀና አጥናፉ ብርሃነ እጃቸውን በሰንሰለት እንደታሰሩ ወደ ግቢው ገቡ፡፡ ዛሬ ወጣቶቹ በስስ ፈገግታ ‹‹አይዞአችሁ ደህና ነን›› የሚል የተስፋ ምልክት ለቤሰተቦቻቸውና ለጓደኞቻቸው አሳይተዋል፡፡ ከእነርሱ ቀጥለው በፖሊስ ታጅበው የገቡት ጋዜጠኛ ተስፋዓለም ወልደየስ፣ጋዜጠኛ አስማማው ኃይለ ጊዮርጊስና የሕግ መምሕርና የዞን ዘጠኝ ጦማሪ ዘለዓለም ክብረት እጆቻቸው በካቴና እንደታሰረ ለቤተሰቦቻው ሰላምታን ሰጥተዋል፡፡ የእነርሱ ፈገግተኛ መኾን ለቤተሰቦቻቸው፣ለጓደኞቻቸውና ለወዳጆቻቸው ጥቂትም ቢኾን እፎይታን ሰጥቷል፡፡
ተጠርጣሪዎቹ ችሎት የቀረቡት እንደወትሮው ኹሉ በሁለት መዝገብ ተከፍለው ቢኾንም ፖሊስ ያቀረበው ምክንያትና መከራከሪያ አንድ ዓይነት ነበር፡፡ ችሎቱ ከተሰየመ በኋላ ፖሊስ በተሰጠው ጊዜ ቀጠሮ በርካታ ጉዳዮችን ሲመረምር መቆየቱንና አሁንም ያልተጠናቀቀ ምርመራ ስለሚቀረው ተጨማሪ ሃያ ስምንት ቀናት እንዲሰጠው ጠይቋል፡፡
ጠበቃው አቶ አመሐ፤‹‹ፖሊስ ከዚህ ቀደም በወሰደው ጊዜ ቀጠሮ ሰንድ ለማስተርጎም፣ የምስክሮችን ቃል ለመቀበል፣ኢሜሎቻቸውን ለመፈተሽ እንዲሁም ያልተያዙEthiopian Jailed bloggers ግብረአበሮቻቸውን ለመያዝ ብሎ እንደነበርና አሁን ዝም ብሎ በጥቅሉ በርካታ ሥራዎችን ሠርቼያለሁ እንደገና ይጨመርልኝ ማለቱ አግባብ አይደለም›› ሲሉ አመልክተው ነበር፡፡ ዳኛው ፖሊስ የሠራውን ሥራና የሚቀረውን ምርምራ እንዲያስረዳ በማዘዛቸው፣‹‹ከሠራናቸው በርካታ የምርመራ ሥራዎች መካከል የተባባሪዎቻቸውን ቤት ፈትሸናል፣ለተለያዩ ባንኮች የተጠርጣሪዎቹን ዝርዝር መረጃ እንዲሰጡን ጠይቀን ከተወሰኑት ምላሽ አግኝተናል፣የተወሱ ምስክሮችንን ቃል ተቀብለናል፣ ከትርጉም ሥራውም የተወሰነውን ሠርተናል፡፡ ግብረአበሮቻቸው ወደ ክፍለ ሃገርና ወደ ተለያዩ አገራት እየሸሹ መያዝ ስለተቸገርን የፖሊስ ኃይል አሰማርተን እያፈለግናቸው ነው እነርሱንም መያዝ ይቀረናል፡፡›› በማለት ተናግሯል፡፡
አቶ አመሐ በበኩላቸው፤‹‹ፖሊስ ተጠርጣሪዎቹን በቁጥጥር ስር ካዋለ ሃምሳ ቀናት ሞልቶታል፡፡ እነዚህ የሚላቸውን ነገሮች አጠናቆ ለመጨረስ የነበረው ጊዜ ከበቂ በላይ ነው፡፡አሁንም ቢኾን እነዚህን ምርመራዎች ለማድረግ የደንበኞቼን አስሮ ማስቀመጥ አስፈላጊ አይደለም ስለዚህም ፍርድ ቤቱ የዋስትና መብቻውን ሊያከብርላቸው ይገባል፡፡ ይህን ጥያቄ ፍርድ ቤቱ ባይቀበለው እንኳን ከዚህ በኋላ ፖሊስ በሚሰጠው ሃያ ስምንት ቀናት ጊዜ ውስጥ ምርመራውን አጠናቆ እንዲመጣ፤አጠናቆ ባይመጣ ደግሞ ጥያቄው ተቀባይነት እንደማይኖረው ተደርጎ ይመዝገብልን›› በማለት ጠይቀዋል፡፡
ዳኛዋ አቤቱታውን ካደመጡ በኋላ፤ፖሊስ ከዚህ በኋላ ሲቀርብ ለተጨማሪ የምርመራ ቀነ ቀጠሮ መጠየቂያ አሁን የጠቀሳቸውን ምክንያቶች በምክንያትነት ይዞ እንዳይቀርብ በማሳሰብ የጠየቀውን የሃያ ስምንት ቀናት ተጨማሪ የምርመራ ጊዜ ቀጠሮ ፈቅደዋል፡፡zone9 bloggers in court
በዛሬው ዕለት ችሎት ከቀረቡት መካከል ጋዜጠኛ አስማማው ኃይለ ጊዮርጊስ ፤ከፍተኛ የኾነ የጀርባ ሕመም ስላለበት ወንበር እንዲገባለት መጠየቁንና እስካኹን ሊገባለት እንዳልቻለ ጠቅሶ ፍርድ ቤቱ ትእዛዝ እንዲሰጥለት አመልክቷል፡፡ ዳኛዋ ከምንም ነገር በላይ የጤና ጉዳይ ቅድሚያ ሊሰጠው እንደሚገባ በማሳሰብ የጠየቀው ወንበር እንዲገባለት ሲሉ ተናግረዋል፡፡ በችሎት የተገኘው መርማሪ ፖሊስ፤‹‹በአጋጣሚ የእርሱ መርማሪ እኔ ነኝ የጀርባ ሕመም እንዳለበት ነግሮኛል፡፡ ወንበር እንዲገባለት ግን አልጠየቀኝም፡፡ አሁን ቢኾን ይህ በጣም ቀላልና እዛው እኛው ጋር ሊያልቅ የሚችል ነገር ነው፡፡ ችግር የለም እናስገባለታለን›› ሲሉ ቃላቸውን ሰጥተዋል፡፡
እስረኞቹ ከችሎት ሲወጡ እንደ አገባባቸው በፈገግታ ሰላምታ እየሰጡ ሲኾን ችሎቱን ለመከታተል መጥቶ ፍርድ ቤቱ ግቢ ውስጥ ቆመው ሰውም እጁን በማውለብለብ ተሰናብቷቸዋል፡፡ (ፎቶ አዲስ ስታንዳርድ)
tsiongir@gmail.com

የሕዝብ ሃብቶች በመንግስት ወጪዎች ሰበብ ያለርሕራሔ በወያኔ ባለስልጣናት እየተዘረፉ ነው።

June14/2014
ሓገራችን በጥቂት አደገኛ የገዢው ፓርቲ ዘራፊዎች እጅ ወድቃለች።

ምንሊክ ሳልሳዊ ፦ የወያኔ መራሹ ጁንታ ያዋቀራቸውና በተቋምነት የሚታወቁ መስሪያቤቶች ውስጥ እየተፈጸመ ያለው አግባብ ያልሆነ ስልጣንን መከታ በማድረግ በትእዛዝ ብቻ ካለማረጋገጫዎች እና ካለምንም ቅድመ ዝግጅት በመስፋፋቱ ከፍተኛ ዘረፋ እየተካሄደ ነው።በየተቋማቱ የሚደረጉ የበጀት ምደባዎች፤ኮንትራቶች ፤የንብረት ግዢዎች፤ ጨረታዎች ፡የውጪ ምንዛሬ እንቅስቃሲዎች እና የተለያዩ ወጪዎች አገሪቷ ላይ ከፍተኛ የኢኮኖሚ ውድቀት በማስከተል የኑሮ ውድነት እንዲስፋፋ እያደረጉ ነው።ይህ ዘረፋ ተቆጣጣሪ አካላት ማጣት የዘመድ አዝማድ የውስጥ አሰራር እና ግንኙነት በፓርቲ ባለስልጣናት መካከል የተፈጠረ አለመተማመን እና መፈራራት አገሪቷ በጥቂት አደገኛ ዘራፊዎች እጅ እንድትወድቅ ሆኗል።
የወያኔው መንግስት በተለያዩ የንግድ ስራ ላይ ተሰማርተው በሚገኙ ኢትዮጵያውያን ላይ ከፍተኛ የሆነ ቁጥጥር በማድረግ በግብር እና በቀረጥ ስም እየበዘበዛቸው ቢሆንም የመንግስት በጀት ተብሎ የተመደበ ሲባክን አገልግሎት ላይ ሳይውል ሲቀር አላስፈላጊ ግዢዎች ተደርገው ብክነት ሲታይ ዝምታን በመምረጥ በሃገሪቱ ከፍተኛ የሙስና ተግባራቶች እንዲስፋፉ እድል ከፍቷል። ሙሰኞችን ጸረ ሙሰኞችም የተወሰኑ ባለስልጣናት በሆኑባት ኢትዮጵያ የሚደረገውን ብዝበዛ ለመሸፋፈን በተለያዩ የፖለቲካ ስውር እጆች ብክነት እና ብዝበዛን በማስፋፋት ህዝብ በኑሮ ውድነት እንዲደናቆር አድርገዋል።
ከስራ አፈጻጸም ጋር የማይዋሃዱ የማይገናኙ እና የማይመጣጠኑ በተለያዩ መስሪያ ቤቶች የሚመደቡ በጀቶች ውጤት አልባ ለሆኑ ጉዳዮች ከፍተኛ ውጪ በመመደብ - ለስብሰባ- ለነዳጅ-ለሆቴል-ለመኪና ግዢ-ለአልተፈለገ ድግስ- ለፊልድ አበል -ወዘተ እየተባለ አላስፈላጊ እና የማይመጥን ወጪ በማውጣት የወያኔ ባለስልጣናት የህዝብን ሃብት ካለመራራት እየበዘበዙት ይገኛሉ። ባለስልጣናቱ ወደ ባንኮች በመሄድ በመደወል በጥቅም በመተሳሰር ከተለያዩ የንግድ ድርት ባለቤቶች እና ከባንክ ባለስልጣናት ጋር በመመሳጠር የውጪ ምንዛሬ በማውጣት የሃገሪቷን ካዝና በባዶ ለማስቀረት ሌት ከቀን እየሰሩ ሲሆን እንዲሁን ይህንን የዶላር ምንዛሬ ለማግኘት ለሚፈልጉ ነጋዴዎች በአንዱ ዶላር ሁለት ብር ጉቦ በማስከፈል ስልታናቸውን ለከፍተኛ ብዝበዛ እየተተቀሙበት ነው።
ስልጣናቸውን ያለአግባብ የሚጠቀሙት የወያኔ ሰዎች ከውጪ ሃገር በግዢ እንዲመጡ የሚወሰንባቸውን የተቋማት የሕዝብ ንብረቶች ጨረታዎች በሙሉ በከፍተኛ የሙስና ትሥሥር የሚፈጸሙ ናቸው። በኢትዮጵያ ውስጥ እስካሁን ከውጪ የተገዙ የተቋማት ንብረቶች ከሙስና የጸዱ እንዳልሆኑ እና በጥቅማጥቅም ውህደት በኮሚሽን የተገዙ እንደሆነ ማረጋገጫዎች በገሃድ እያየናቸው ነው፤ጨረታ የሚለውን ቃል እንደ ህጋዊነት በመጠቀም በመጠኑ አስደንጋጭ የሆነ ኮሚሽን በመያዝ የሃገር እና የህዝብ እየተበዘበዘ ሲሆን በዚሁ የኮሚሽን እና የጉቦ ትሥሥር ከተለያዩ አገሮች የሚገዙ ንብረቶች የተበላሹ እና የሚቀላልጡ ውጤት አልባ በመሆናቸው ምንም ሳይሰራባቸው በየቦታው እንደቆሙ እና እንደወዳደቁ ሲቀሩ ባለስልጣናቱ ሙስናቸውን በመቀጠል ተቆጣጣሪ አልባ ስለሆኑ ወደ ሌላኛው ብዝበዛቸው ይሻገራሉ። ይህ አደገኛ ዘረፋ በብዙ መልኩ ከአነስተኛ እስከ ከፍተኛ ዘረፋዎች እየተካሄዱ ነው በሂደት እያየነው እንሄዳለን ።

የዞን 9 ጦማሪዎች እና ጋዜጠኛው ተጨማሪ 28 ቀናት ቀጠሮ ተሰጠባቸው

June 14/2014

ያለምንም ክስ ላለፉት 50 ቀናት ፖሊስ የምርመራዬን አልጨርስኩምና ተጨማሪ ቀጠሮ ይሰጠኝ ጥያቄና በፍርድ ቤቱ መፍቀድ የተነሳ እየተጉላሉ የሚገኙት የዞን 9 ጦማሪያን እና ጋዜጠኛው ዛሬ ፍርድ ቤት የቀረቡ ሲሆን ተጨማሪ 28 ቀናት ፖሊስ ጠይቆ ፍርድ ቤቱ መፍቀዱን የዘ-ሐበሻ ዘጋቢዎች ከአዲስ አበባ አስታውቀዋል።

በፌደራል ፍርድ ቤት በአራዳ ምድብ ችሎት ዛሬ የቀረቡት ናትናኤል ፈለቀ፣ አጥናፍ ብርሃኔ፣ ዘላለም ክብረት፣ ኤዶም ካሳዬ፣ አስማማው ሃይለጊዮርጊስ እና ጋዜጠኛ ተስፋለም ወልደየስ ሲሆኑ ጉዳያቸውን ለመከታተልም በርካታ ሰዎች ፍርድ ቤት መገኘታቸውን የዘ-ሐበሻ ዘጋቢዎች ገልጸዋል። እንደዘጋቢዎቹ ከሆነ ባልተነገረ ክስ ላለፉት 50 ቀናት በእስር ቤት እየማቀቁ የሚገኙት ታሳሪዎቹ ፍርድ ቤት ሲቀርቡ መንፈሳቸው ጠንካራ እንደነበር ለማየት ተችሏል። የታሳሪዎቹ ወላጆችና ሴቶች በፍርድ ቤቱ ሲላቀሱ እንደነበር ያስተዋሉት ዘጋቢዎቻችን ተጨማሪ 28 ቀናት ቀጠሮ መሰጠቱ ብዙዎችን እንዳበሳጨ ጠቁመዋል።

ዘ-ሐበሻ

የኢትዪጲያ ህዝብ አኩረፎናል ምርጫውም ደርሶብናል የኢህአዴግ አባላት ችግር ውስጥ ነን'' ዶ/ር ሽፈራው

June14/2014
 BBN ቢቢኤን የናንተው ድምፅ
ወያኔ አስቁሜዋለሁ ያለው የህዝበ ሙስሊሙ ትግል ራስ ምትታ ሆኖበታል።
ዶ/ር ሽፈራውና አቶ በረከት ስምኦን የመሩት በዝግ የተካሄደው የ 3 ቀን ስልጠና ሙሉ መረጃ 

ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናት በሙስሊሙ ትግል ጭንቀት ውስጥ መግባታቸውን አመኑ
''ድምፃችን ይሰማ በጣም አስቸግሮናል እናንተ የተመረቃችሁ 24 ሰአት ተከታተሉት ''
አቶ በረከት ስምኦን
''ሙስሊሙ እኛ ስብሰባው ስንጠራው አይመጣም እኛ ኮሚቴው ነን እያለ ቂልንጦን እያጥለቀለቀ ተቸግረናል፡፡ ግማሹ የኢትዪጲያ ህዝብ አኩረፎናል ምርጫውም ደርሶብናል የኢህአዴግ አባላት ችግር ውስጥ ነን''
ዶ.ር ሽፈራው ተክለ ማሪያም

ባንቢስ ከሚገኘው የፍትህ ሚኒስቴር ግቢ ውስጥ በከፍተኛ ምስጢር የደህንነት ስራዎችን በተመለከተ ሲሰለጥኑ የነበሩት ወጣቶች በትላንትናው እለት በአቶ በረከት ስሞን እና በዶ/ር ሽፈራው ፊውታራሪነት በዝግ ስብሰባ መመረቃቸው ታውቋል። ይህንን ሙሉ መረጃ በተመለከተ ቢ ቢ ኤን ሙሉ ዘገባውን ይዞ ለአድማጮቹ እንደሚከተለው ያቀርባል።

ቢ ቢ ኤን በዝግ ስብሰባውና ምርቃቱ ላይ ከተሳተፉት አንዱን ለቃለመጠይቅ በመጋበዝ የወያኔ መንግስት የገባበትን አጣብቂኝ ፍርጥርጥ አድርጎ ዘግቦታል። ምርጫ ደረሰብን የኢትዮጵያ ሕዝብ ግማሽ ሙስሊም ነው ስብሰባ ስንጠራው አይመጣም ቂሊንጦ ወርዶ ግን እኛ ኮሚቴዎ ነን በማለት ቂሊንጦን ያጥለቀልቃል ስለዚህ ኢሕአዴግ ችግር ውስጥ ነው በማለት ባለስልጣናቱ የተማጽኖ ሮሮ እና ኢሕአዴግን እናድን የሚል መልእክት ያዘለ አቤቱታ ለተመራቂ ደህንነቶች አሰምተዋል።

የሙስሊሙን ትግል ለማክሸፍ ማድረግ ያለባቸውን በተመለከት መመሪያ የሰጡት ባለስልጣናቱ በድህረ ገጽ ላይ ለሚንቀሳቀሱ አክቲቪስቶች ማጥፊያ ዘዲም መክረዋል ቢቢ ኤን እና ድምጻችን ይሰማ እጅግ አስቸግሮናልም ብለዋል። ድምጻችን ይሰማ አሊያ ቢቢ ኤን ዘንድ ሪፖርቶች ሳይደርሱ ከመንገድ በማስቀረት ሕዝቡ የሚደናበርበት ስራ እየተሰራ እንደሆነም ተናግረዋል ሽፈራው እና በረከት ።

ሙሉ መረጃ ደርሶናል እዚህ ላይ ያዳምጡት ። የወያኔ አጣብቂኝ ይስሙት ።
-http://goo.gl/8IAAvN
-http://goo.gl/8IAAvN
-http://goo.gl/8IAAvN
መንግስት ትግሉን ለማዳመከም ያሰበው ሁሉ በዚህ ሚስጥራዊ ስብሰባ ተጋልጥዋል የዛሬውን የኮሚቴዎቻችን ውሎ በሰፊው ተዳስዋል ሌሎችም ጠቃሚ መረጃዎች ተካተዋል ፕሮግራሙን ሼር ዳውንሎድ በማድረግ ያስተላልፉ።

Friday, June 13, 2014

ከህወሀት/ኢህአዴግ ጓዳ በሀብታሙ አያሌው ላይ የተወረወረች ቀስት

June13/2014
ከዘላለም ደበበ

ይህን ፅሁፍ በሎሚ መፅሄት ላይ ባለፈው ሳምንት አወጣሁት፡፡ መፅሄቱ ላልደረሳችሁ ይኸው እዚህ ለጠፍኩት፡፡
በቅድሚያ እንኳን ወታደራዊ አምባገነኖች ተደምስሰው ‹‹ዴሞክራሲያዊ›› አምባገነኖች ለተተኩበት የግምቦት 20 በአል አደረሳችሁ፡፡ ዛሬ ዝምታ ሲበዛ ፍርሀት፣ ውሸት ደግሞ ሲደጋገም እውነት ይሆናልና የማውቀውንና የተሰማኝን ለአምባቢም ግልፅ ሊሆንለት የሚገባ ጉዳይን በወፍ በረር ላስቃኝ ወደድኩ፡፡

ለፅሁፌ መነሻ የሆነኝ ሎሚ መፅሄት አቤል ኤፍሬም በተባለ ግለሰብ የቀረበውንና መፅሄቱ ይዞት የወጣው ፅሁፍ ነው፡፡ ፅሁፉም በአንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ሀብታሙ አያሌው ላይ ያነጣጠረ ግልፅ የሆነ የስም ማጥፋት ዘመቻ ነው፡፡ እኔም ይህንን ፅሁፍ ያዘጋጀሁት የአቶ ሀብታሙ ተሟጋች ሆኜ ሳይሆን እውነታው ግን በፅሁፉ ከቀረበው ጋር ፍፁም የተለያየ ስለሆነ እና የፅሁፉ ‹‹ሞቲቭ›› አላማ ስም በማጉደፍ አምባገነኑ ስርዓት እንዲቀጥል ማስቻል ስለሆነ ነው፡፡ በሌላ ቋንቋ ከህወሃት/ ኢህአዴግ መንደር ወደ ወጣቱ ፖለቲከኛ የተወረወረች ትንሽ ቀስት መሆኗን መጠቆም ስለሚገባ ነው፡፡

በፅሁፉ ላይ በኢህአዴግ ስልጣን እንደነበራቸው ለህብረተሰቡ ለማሳወቅ ነው በማለት ለመጠቃቀስ ተሞክሯል፡፡ ነገርግን ምነው እነዚህን ዘለላችኋቸው ሌሎቹ ስልጣኖቹ እነዚህ ነበሩ በትምህርት ቢሮ የትምህርት ካውንስል ቦርድ አባል፣ የመገናኛ ብዙሀን ቦርድ አባል፣ የአፍሪካ እርስ በእርስ መገማገሚያ አህጉራዊ ገምጋሚ ምክር ቤት አባል፣ የወጣቶች ፌደሬሽን ፕሬዚዳንት፣ የጃልሜዳ ስፖርት ማእከል የቦርድ አባል፣ የአዲስ አበባ ኤች አይ ቪ መቆጣጠሪያ ቢሮ ቦርድ አባል ሌላም ሌላም እንደነበሩስ መረጃው የለዎትም? እሳቸው ግን እነዚህን ሁሉ ኃላፊነት እንደነበራቸው በቃለ መጠይቃቸው ወቅት ገልፀዋል ታዲያስ ይህንን ሁሉ ጥለው የወጡ ጥቂቶች ብቻ ስለሆኑ ብትረበሹ አይደንቅም፡፡ እርግጥ ነው ሀብታሙ ኢህአዴግ ቤት ነበር፡፡ ይህንንም ሲክድ ሰምቸ አላውቅም፡፡ ነገር ግን ፈንጅ አምካኝ ስላልነበረ ኢህአዴግ የሚከተለው መስመር ለህዝብ እንደማይጠቅም ተሎ በመማር ለሁለት አመታት የዘለቀውን ኢህአዴጋዊ ጋብቻ ለመቅደድ ፈጥኖ መወሰኑ ሊያስመሰግነው እንጂ ሊያስወቅሰው ባልተገባ ነበር፡፡

እዚህች ጋር አንድ ነገር ማንሳት እፈልጋለሁ አቶ ሀብታሙ አያሌው ራሱን ከኢህአዴግ አባልነቱ ያገለለው ከምርጫ 2002 ማግስት ነው፡፡ ለዚህም ደግሞ ሀገር ውስጥ በሚታተሙ ሁሉም ሊባል በሚቻል መልኩ በተለያዩ የህትመት ውጤቶች ላይ እንዲሁ ቃለመጠይቅ አድርጓል፡፡ በተለያዩ የሀገር ውስጥና የውጭ ሀገር ኤሌክትሮኒክስ ሚድያዎችም ጭምር ከስርአቱ እንዴትና በምን አይነት ሂደት እንደወጣ ከቃለ መጠይቆቹ ተረድተናል፡፡ ልብ በሉ አቶ ሀብታሙ ላይ በቅድሚያ የተጀመረው ዘመቻ እጅግ በጣም የተቀነባበር ነበር፡፡ በ2002 ዓ.ም. አቶ ሀብታሙ በግልፅ መልቀቂያ አስገብተው ከፓርቲው ከለቀቁ በኋላ ወደ ደቡብ አፍሪካ ለትምህርት ከሄዱ በኋላ በሀገር ውስጥ ያሉት የኢህአዴግ ከፍተኛ ባለስልጣኖች ጭንቀት ላይ ወደቁ፡፡ የጭንቀታቸውም መንስኤ ከሀገር ከወጣ በኋላ ለኢሳትና ለተለያዩ ሚድያዎች ጉዳችንን ያዝረከርክብናል፤ ይህ ደግሞ ለእኛ ትልቅ ኪሳራ ነው ምክንያቱም የሀገሪቱ የወጣቶች ፎረም ሰብሳቢ እንዲሁም ዘርፈ ብዙ ስልጣን እና ጥቅማ ጥቅም ሰጥተውት ጓዳቸው ድረስ ገብቶ የወደፊቱ የግፍ መሀንዲስ እንዲሆን ከፍ ከፍ ያደረጉት ሰው ድንገት ባላሰቡት ሰዓት ከድርጅቱ ለቅቄያለሁ ብሎ ወደ ውጭ ሀገር ሲሄድ መደናገጣቸው አይቀሬ ነበር፡፡ ደንግጠውም ግን አልቀሩም በአቤል ኤፍሬም አይነት ጥላሸት መቀባት በሚችሉ ግለሰቦች አማካኝነት አንድ ነገር ጀመሩ፡፡ ከፍተኛ የሆነ የስም ማጥፋት ዘመቻ አካሄዱ:: ሀብታሙ በ2010 እ.ኤ.አ. በደቡብ አፍሪካ አስተናጋጅነት የተካሄደውን የአለም ዋንጫ በማስመልከት አሁን በእስር ላይ ከሚገኘው አስካሉካን ትሬዲንግ ከተባለው ድርጅት ባለቤት ጋር በመሆን የብዙ ኢትዮጵያውያን ገንዘብን ዘርፎ ነው የሄደው ስለዚህም ይህ ሰው በስርቆት ወንጀል ተሳትፏል የሚል ዘመቻ ነው፡፡ ይህንንም ያደረጉበት ምክንያት በዛው ወደ አሜሪካን እና ሌሎች አገሮች ሄዶ ከቀረ ተአማኒነቱን እናሳጣዋለን ተመልሶ ከመጣ ግን ዝም ብለን ነገሩን አድበስብሰን ተመልሶ የፓርቲው አባል እንዲሆን ጥረት እናደርጋለን የሚል ዘዴ ነበር፡፡ ታዲያ በዚህን ጊዜ የአዲስ አበባ ወጣቶች ፎረም ስብሰባ እንደሚያደርግ አቶ ሀብታሙ በተለያዩ ሚድያዎች ሲናገሩ ሰምቻለሁ፡፡ እኔም ይህን ፅሁፍ ሳዘጋጅ ግልፅ ያልሆኑልኝ ነገሮች ግልፅ እንዲሆኑልኝ አነጋግሬያቸው ምላሻቸውን አግኝቻለሁ፡፡ እንግዲህ የአዲስ አበባ ፎረም በአሁኑ ሰዐት በከፍተኛ የሚኒስትርነት ማዕረግ ላይ ያሉት አቶ ሬድዋን ሁሴንን ጨምሮ ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣኖች እና የፎረሙ አባላት በማዘጋጃ ቤት አዳራሽ ሞልተዋል ስብሰባውን የሚመራው የወቅቱ የአዲስ አበባ ወጣቶች ፎረም ፀሀፊ ኤልያስ ባህሩ ነበር፡፡ እንግዲህ ወሳኙ ነገር እዚህ ጋር ነው ያለው፡፡

ቀድሞውኑ ስብሰባው ይደረግ እንደነበር ኢንፎርሜሽኑ የነበራቸው አቶ ሀብታሙ በስብሰባው ዋዜማ ከደቡብ አፍሪካ አዲስ አበባ ገብተው ነበርና ቀጥታ በዚህ ስብሰባ ላይ ለመገኘት ወደ አዳራሽ ሲገቡ በአዳራሹ ውስጥ የነበረው ተሰብሳቢ ከወንበሩ በመነሳት በፉጨት እና በጭብጨባ ነበር የተቀበላቸው፡፡ እዚህ ጋር በነሬድዋን እና በሌሎቹ ባለስልጣናት ፊት ላይ ይነበብ የነበረውን ድንጋጤ ግን አንባቢ እንዲረዳልኝ እፈልጋለው፡፡ ታዲያ አቶ ሀብታሙ በአዳራሹ ውስጥ ተገኝተው መናገር እንደሚፈልጉ ይናገራሉ አሁንም እድሉ እንዲሰጣቸው እና እንዲናገሩ የጉባኤተኛው ሙሉ ፍቃድ ነበርና ይናገሩ የሚሉ ድምፆች ሲበረክቱ ተፈቅዶላቸው ወደ መድረኩ ወጡ፡፡ አቶ ሀብታሙንም ሆነ ሌሎች በጉባኤው ላይ የነበራችሁ በሙሉ የቀናነስኩት እና የዘነጋሁት ነገር ካለ ልታርሙኝ ትችላላችሁ፡፡ አቶ ሀብታሙም ወደ መድረኩ ወጥተው መነጋገሪያውን እንዳነሱ እንዲህ አሉ ‹‹እኔ ፍትህን በመሸሽ ሳይሆን በመጋፈጥ ነው የማምነው፡፡ ዘርፎ ነው ሀገር ጥሎ የሄደው፤ የብዙ ኢትዮጵውያንን ንብረት ዘርፏል እያለችሁ የስም ማጥፋት ዘመቻ ከፍታችሁ ነበር፡፡ እውነት ዘርፌ ከሆነ ይኸው እጄን ለካቴና አንገቴን ለገመድ ለመስጠት ዝግጁ ነኝ፡፡ እውነት ዘርፌ ከሆነ በአደባባይ ስቅላትም ቢሆን ቢፈረድብኝ ወስኜ ነው የመጣሁት፤ አሁኑኑ ልታስሩኝ ትችላላችሁ፡፡ ማጭበርበር ሌብነት አስተዳደጌም ኢትዮጵያዊ ማንነቴም አይፈቅድልኝም ነግር ግን አብሬያችሁ ለሁለት አመት መቆየቴ ለኔ ስህተት እንደሆነ ተሰምቶኛል፤ በሀገር አንድነት ጉዳይ የማይታረቅ ልዩነት እንዳለን ልታውቁት ይገባል፡፡ በኢትዮጵያ ህዝብ ጥቅም ላይ እጀን አላነሳም›› ካለ በኋላ አዳራሹን ለቆ ወጣ፡፡

በዚህም ምክንያት አቶ ሀብታሙ በዛ ስብሰባ ላይ እንዲገኙ መረጃ ሰታችኋል የተባሉ የአዲስ አበባ ፎረም አባላት ከሃላፊነታቸው እንዲነሱ ተደርገዋል፤ የወቅቱ ምክትል ሊቀመንበር ወጣት ዳዊት ግርማ፤ ዋና ጸሐፊ ወጣት ኤልያስ ባህሩ እና ሌሎችም በህይወት ስላሉ ምስክርነቱን ለመስጠት ምስክርነት ለመስጠትም ወደ ኋላ እንደማይሉ ላረጋግጥ እወዳለሁ፡፡ እንግዲህ ይህ ሁሉ የሆነው 2002 ዓ.ም ላይ ሆኖ ሳለ ከ3 አመት በኋላ ምን ተገኝቶ ነው ይህ የስም ማጥፋት ዘመቻ እንዲህ የተበራከተው የሚለው ነገር በአፅንኦት መታየት ያለበት ጉዳይ ነው፡፡

በ2010 የአለም ዋንጫም ገንዘብ አጭበርብሮ ከሆነ የዛኔውኑ ለፍርድ አቅርቦ ውሳኔ ማሰጠት እየተቻለ በአቶ አቤል ኤፍሬምና መሰሎቻቸው አንዴ በፌስ ቡክ ሌላ ጊዜ በህትመት ሚዲያ በአሁኑ ሰአት ምን ፍለጋ ይሄ ዘመቻ ተጀመረ የሚለውን ነገር ካየነው በግልፅ ከህወሓት ጓዳ የወጡ የሀሰት ፕሮፓጋንዳ እና የስም ማጥፋት ዘመቻ ለመሆናቸው እራሱን የሰማያዊ ፓርቲ አባል እንደሆነ አድርጎ የሚያየው (እዚህ ጋር ሰማያዊ እንዲህ አይነት አባል ይኖረዋል ብዬ ስለማላስብ ነው) አቤል ኤፍሬም የተባለ ቀንደኛ የስርአቱ ደጋፊ ተቆርቋሪ በመምሰል የሚያሰራጫቸው ፅሁፎች ማሳያዎች ናቸው፡፡ ምክንያቱም ፀሀፊው ይሄንኑ ፅሁፉን በአዲስ ዘመን ገፅ 3 ላይ እንዲሁም ደግሞ በአይጋ ፎረም ላይ የተለያዩ ሰዎች ሀሳብ በማስመሰል አውጥቶታል፡፡ አንባቢ ግን ልብ ሊል የሚገባው ነገር ኢህአዴግ ይህንን ዘመቻውን የጀመረው አንድነት ፓርቲ በሚያደርጋቸው ከህዝብ ጋር በሚያገኛኙ ጉዳዮች ላይ ሀብታሙ ግምባር ቀደም በመሆን የአምበሳውን ድርሻ ይዞ ጠንካራ ተቃዋሚነቱን ሲያሳይ ኢህአዴግ ህዝብ እየጨቆነ የሚገዛበት ጊዜ ሩቅ እንዳይሆን በማድረግ በኩል ጉልህ ድርሻ ይኖረዋል ብሎ እንደሆነ ግልፅ ነው፡፡ ህወሃት/ኢህአዴግ በተለያዩ ሰዎች ላይ ይሄንን የስም ማጥፋት ዘመቻ ተያይዞት ነበር፡፡ የቅርብ ጊዜ ትዝታ ብናነሳ ሀሳቡን ያለ ፍርሀት በመግለጽ የኢትዮጵያ ህዝብ አፍና ጆሮ የሆነው ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ ላይ እንዲህ አይነት ከፍተኛ የስም ማጥፋት ዘመቻዎች ተከፍተውበት ነበር፡፡ ተመስጌን ኢህአዴግ ነው፣ ካልሆነ ለምን እስካሁን አልታሰረም፣ የህወሓት ተላላኪ ነው፣ አብረውት ያሉትን ጋዜጠኞችን እንዲሰልልላቸው ነው በማለት በተለያዬ መንገድ በተከፈተው የስም ማጥፋት ዘመ እጅግ ብዙ ብዙ ነገሮችን…… ተባለ፡፡ ነገር ግን ኢህአዴግ በዚህ የስም ማጥፋት ዘመቻ ከኪሳራ በቀር ትርፍ ሲያጣበት ተመስገን ደሳለኝን ነውጠኛ፣ አሸባሪ፣ አብዮት ናፋቂ፣….. በማለት በተለያዩ ክሶች ሊበላው እያዘጋጀው እንዳለ ሁላችንም እናውቃለን፡፡ ታዲያ ፍርሃት የማያውቀው ብርቱ ታጋይ ሀብታሙ አያሌው ላይ የተጀመረው ይህ ዘመቻም ሊበሏት ያሰቧትን አሞራ ይሆን እንዴ? ሀብታሙን በልደቱ ጫማ ለማስረገጥ መሞከር ህልም እንጂ እውን እንደማይሆን መረዳት ጠቃሚ ይመስለኛል፡፡ የስም ማጥፋት ዘመቻው ተጠናክሮ ሊቀጥል የከፋው እርምጃም ሊከት ግድ ነውንና ሀብታሙ ፅናቱን ይስጥህ ልልህ እወዳለሁ፡፡ ፅናትህን አውቃለሁና ለቀስት ወርዋሪዎቹ የህወሓት ስውር እጆች …..ውሾቹ ይጮሀሉ ግመሎቹም ጉዟቸውን ቀጥለዋል በልልኝ ፡፡ ቸር ያሰንብተን፡፡

የመሬት ወረራን በመቃወሜ የተፈፀመብኝ በደል – አበበ ሆንጃ (ከሰበታ)

June13/2014

ነዋሪነቴ በሰበታ ከተማ አስተዳደር ወለቴ 03 ቀበሌ ጎጥ አራት ነው፡፡ የጎጥ ሰብሳቢ ሆኜ ለሁለት ዓመት ሰርቻለሁ፡፡ የቀበሌው የምክር ቤት አባል እና የኦህዴድ ኢህአዴግ አባል ሆኜ አገልግያለሁ፡፡ ድርጅታዊ እና ማንኛውንም ከላይ የሚወርደውን የመንግሥት መመሪያና ደንብ በህገ መንግሥቱ መሰረት እንደ ዝቅተኛ አመራር ከድጋፍ ሰጪ አመራሮች በሚሰጠኝ መመሪያ እና ደንብ መሠረት በመፈጸም እና በማስፈፀም ሰርቻለሁ፡፡የህዝብን ጥቅም ለማስከበር ለአካባቢ ፀጥታ፣ ልማት እና የህዝብን አደረጃጀት በቀበሌው ውስጥ ከየትኛውም የጎጥ አመራሮች በበለጠ ስሰራ ቆይቻለሁ፡፡ በ23/07/06 ዓ.ም ለቀበሌው የፀጥታ ዘርፍ በጎጡ ውስጥ ባለው ከፍታ ቦታም መሬት እየተወረረ ነው በማለት ሪፖርት ባደርግም የሚሰማኝ አላገኘሁም፡፡ የሚሰማኝ በማጣቴ መሬት እየወረሩ የነበሩትን ‹‹እየተሰራ ያለውን አቁሙ!›› ስላቸው ‹‹አንተ ምንድነህ? ከአንተ የበላይ የሚገኙት ባለስልጣናት ናቸው ያዘዙን!›› በማለት ስራቸውን ቀጠሉበት፡፡

በማግስቱ ዓርብ ቀን 25/07/06 ዓ.ም ጧት 2፡00 ሰዓት አካባቢ ለቀበሌ 03 ሊቀመንበር ደውዬ ስለሁኔታው አስታውቄያለሁ፡፡ሊቀመንበሩም ለደንብ አስከባሪዎች ደውሉላቸው በማለት መልስ ሰጥተውናል፡፡ ይህም በእንዲህ እንዳለ አንድ ምንም የሥራ ዓይነት የሌለው ደላላና የግንባታ ፈቃድ ሌላቸው የመንግስትና የህዝብ ሀብት የሆነውን መሬት በመቸብቸብ ሀብት ያካበተ ግለሰብ ረቡዕ ማታ የደንብ አስከባሪዎች እየጠራ ገንዘብ ሲያፍስ እንደዋለ በዓይኔ አይቻለሁ፡፡ ይህ በሆነበት ማግሥት እርስ በእርሳቸው ጀርባ በመግጠም አራቱ ቤቶች ወደ ሰሜን፣ አራቱ ቶች ደግሞ ወደ ደቡብ፣ አራቱ ተዋቅረው አልቀው ቆርቆሮ ሊመቱ ሲል፣ አራቱ ደግሞ ገና ጉድጓድ ተቆፍረው እያሉ ተደረሰባቸው፡፡ ዓርብ ቀን በ25/07/06 ዓ.ም ከሰበታ ከተማ አስተዳደር የቀበሌያችን ደጋፊ ሰው አመራር የሆነውን ግለሰብ ደውዬ በግምቱ 5፡00 ሰዓት አካባቢ በህገ ወጥ መንገድ የተሰሩት ቤቶች አስፈርሻለሁ፡፡

ይህንን የመንግስትና የህዝብ ሀብት የሆነውን መሬት ከመሬት ወራሪዎች እጅ አስፈርሼ ስላስመለጥኩ የጥቅሙ ተካፋይ የቦታዎቹ ባለቤትነት ማረጋገጫ ካርታ እና ምንም ዓይነት የግንባታ ፈቃድ የሌላቸው ግለሰቦችና ባለስልጣናት ሥልጣናቸወን ተጠቅመው በደል አድርሰውብኛል፡፡ የመሬት ወረራ ያደረጉ ግለሰቦች በእኔ ላይ ተደራጅተው በደል እያደረሱብኝ ይገኛሉ፡፡ ዐቃቤ ሕግ፣ ፖሊስ እና አስተዳደር እና ፀጥታ ከፍተኛ አድማ፣ ተፅዕኖ፣ ማዕቀብ እና በኑሮዬ ላይ ችግር በመፍጠር ከቤቴ እንድወጣ አድርገውኛል፡፡ አሁን ተባባሪ ሆኛለሁ፡፡ ህገ ወጥ ቤትን በማስፈረሴና የመሬት መቀራመቱን ለማስቆም በጣርኩ በ8/8/06 ዓ.ም ስምንት ኦሮሚያ ልዩ ኃይል አባላት እንዲሁም 11 አባላት የያዘ የከተማዋ ፖሊሶችን በመያዝ እንዲሁም 10 የሚደርሱትን የቀበሌ 03 ደንብ አስከባሪዎችን ግደሉት ተብለው መኖሪያ ቤቴን ከበው ውለዋል፡፡ እነዚህ አካላት የታዘዙት ከከተማው የፖሊስ አዛዥ ሲሆን በእኔ ላይ የሚወሰደው እርምጃ ምክንያታዊ ባለመሆኑ ‹‹ለምን እንገድለዋለን?›› ብለው ከአዛዡ ጋር የተከራከሩ የፖሊስ አባላት እንዳሉም ሰምቻለሁ፡፡ ባለቤቴ ‹‹ባልሽን አምጭ!›› ተብላ ያለአግባብ የዋስትና መብትዋን በመንፈግ ያለምንም የፍርድ ቤት ትዕዛዝ ታስራ ትገኛለች፡፡ ‹‹የመንግስት ያለህ›› በማለት ለህዝብ እና ለሀገር ታማኝ ሆኜ መሥራቴ፣ ከኪራይ ሰብሳቢዎች ጋርለመተባበር ህገ-ወጥ ግንባታዎችን ማስፈረስ፣ አጥፉት፣ ግደሉት ያስብላል ወይ?

የአስተዳደር ፀጥታ ኃይሉ በሙሉ በእኔ ላይ ከፍተኛ አድማ፣ ተፅዕኖ፣ በመፍጠር ሊያጠፉኝ ተነስተዋል፡፡ ዛሬ ባለቤቴ ከመንግሥት ስራ ተፈናቅላ፣ እኔም እንዳይገሉኝ ሸሽቼ እገኛለሁ፡፡ ለአቅመ አዳም ያልደረሱ አራት ልጆች ያሉኝ ሲሆን ሁለቱ ልጆቼ የወለድኳቸውና ሌሎች ወላጅ አልባዎች በመሆናቸው የማሳድጋቸው ልጆቼ ዛሬ ለጎዳና አዳሪነት ሊዳረጉ ስለሆነ ለሚመለከተው ሁሉ ከጎኔ እንዲሰለፉ የድረሱልኝ ጥሪዬን አቀርባለሁኝ፡፡

በግንደ በረት በተማሪዎች እና በክልሉ ፖሊስ መካከል ከፍተኛ የሆነ ግጭት ተከሰተ

June13/2014

ምእራብ ሸዋ ዞን በኦሮሚያ ክልል በግንደበረት ወረዳ በተማሪዎች እና በወያኔ የፖሊስ ሃይሎች መካከል በተከሰተ ግጭት አንድ
ተማሪ ሞቶ አራት መቁሰላቸውን የአከባቢው ምንጮች ገልጸዋል።

ከትላንትና ጀምሮ ሲንከባለል የመጣው ግጭት ከዚህ ቀደም በኦሮምያ ክልል ውስጥ ከተነሱ የተማሪዎች አመጽ ጋር ተያያዥነት ያለው እና ጥያቂውም የአዲስ አበባ ማስተር ፕላን እና የሞቱ የኦሮሞ ተማሪዎች ጋር የተያያዘ ሲሆን ዛሬ በቀጠለው ተቃውሞ ወደ 10 ሺህ የሚጠጉ ተማሪዎች እና የወረዳው ነዋሪ በጋራ ሰልፍ በመውጣት ቁጣቸውን የገለጹ ሲሆን አስተዳደሩ ድረስ በመሄድ ድምጻቸውን ሲያሰሙ የፌዴራል ፖሊስ በመምጣት የበተናቸው ቢሆንምቀኑን ሙሉ በከተማው ከባድ ረብሻ እንደነበር እና ከቆሰሉ ተማሪዎቹም አንዱ መሞቱን የወረዳው ነዋሪዎች ተናግረዋል ሲሉምንጮቹ ጠቁመዋል።

በነገው እለት የ12ኛ ክፍል መሰናዶ ፈትና ከወሰደ በኋላ የተገደለውን ተማሪ ለመቅበር ይወጣል የተባለው ሕዝብ ተቃውሞ
እንዳያሰማ የወረዳው እና የከተማው ባለስልጣናት በመስጋት ፖሊሶች ያሰፈሩ ሲሆን ሕዝቡ ቁጣው እንዳልበረደ እና

በዞን 1 የሚገኙት ጀግኖቻችን በዛሬው እለት ተበታትነው እንዲደለደሉ ተደረገ! በህዝበ ሙስሊሙ ወኪሎች ላይ በማረሚያ ቤት እየተደረገ ያለው ወከባ በአስቸኳይ ይቁም ! (ድምፃችን ይስማ)

June 12, 2014
በሐሰት የሽብር ክስ ህገ መንግስታዊ መብቶችን በጣሰ ሁኔታ መሪዎቻችንን እያጉላላ የሚገኘው መንግስት በማረሚያ ቤት ውስጥ የሚያደርገውን ወከባ ቀጥሎበታል፡፡ ገና ወደማረሚያ ቤት ከተዛወሩበት ጊዜ አንስቶ ጠያቂዎችን በማጉላላት፣ የጥየቃ ሰአትን ከሌሎች በተለየ መልኩ በመገደብ፣ እንዲሁም በጠያቂዎች ቁጥር ላይ ገደብ በማድረግ በተለያዩ ወቅቶች መብታቸውን ሲነግፍ የቆየው መንግስት ዛሬ ደግሞ በታሪካዊው የካንጋሮ ፍርድ ቤት የችሎት ሂደት ምስክሮቻቸውን እያቀረቡና ትክክለኛው የህዝበ ሙስሊሙ ትግል ገጽታ በችሎት እየተመሰከረ ባለበት በዚህ ወቅት በፍርድ ቤት እየደረሰበት ያለውን ሽንፈት ለመቋቋም ወኪሎቻችን ላይ የተለያዩ ወከባዎችን እየፈጸመ ይገኛል፡፡ እስካሁን ድረስ በእስር ቤቱ ታሪክ በምንም መልኩ የማያስጠይቅን፣ ይልቁንም በማረሚያ ቤቱ ደንብ ጥበቃ የተደነገገለትን ገንዘብ የመያዝ መብት እንደወንጀል በመቁጠር በኮሚቴው ሰብሳቢ ኡስታዝ አቡበከር አህመድ እና በሸኽ መከተ ሙሄ ላይ፣ እንዲሁም በሌሎች ታሳሪዎች ላይ ሲያደርስ የነበረውና በቅርቡ የተረጋጋው ወከባ መሪዎቻችንን የማጥቂያ ሰበብ ፍለጋ እንጂ ሌላ እንዳልሆነ ግልጽ ነበር፡፡Ethiopian Musilms
አሁንም ይህንኑ ህገወጥ ድርጊቱን የቀጠለበት የእስር ቤቱ አስተዳደር በዞን አንድ በሚገኙ ጀግኖቻችን፣ (ማለትም በሸኽ መከተ ሙሄ፣ በኡስታዝ አቡበከር፣ በኡስታዝ ካሚል ሸምሱ፣ በኡስታዝ አህመድ ሙስጠፋ፣ በጋዜጠኛ አቡበከር ዓለሙ፣ በወንድም አብዱረዛቅ አክመል እና በወጣት ሙባረክ አደም) ላይ በዞን አንድ በሚገኙት 8 ክፍሎች እንዲበታተኑና እንዲለያዩ ትእዛዝ አስተላልፏል፡፡ ጓዞቻቸውንም ወደየተመደቡበት ክፍሎች እንዲቀይሩ እንደተነገራቸው ታውቋል፡፡ ባለበት የጤና ችግር ምክንያት ልዩ ትኩረትና ረዳት ጓደኛ የሚያስፈልገውን ወንድም አብዱረዛቅን ድጋፍ ለማግኘት አስቸጋሪ እንደሚሆንበት እያወቁ ብቻውን መድበውታል፡፡ ኡስታዝ አህመድ ሙስጠፋንም እንዲሁ ጊዜያዊ ማቆያ ተብሎ በሚታወቀውና በእስረኞች ቶሎ ቶሎ ተለዋዋጭነት ምክንያት ማህበራዊ ትስስር መመስረት አስቸጋሪ በሆነበት ክፍል ሆን ተብሎ እንዲመደብ ተደርጓል፡፡
የማረሚያ ቤቱ ደንብ በአንድ የክስ መዝገብ ችሎት የሚከታተሉ ታራሚዎች በችሎታቸው ዙሪያ በየጊዜው መነጋገርና መወያየት እንዲችሉ በአንድ ዞን የመታሰር መብት የሚሰጥ ቢሆንም አስተዳደሩ ግን ይህንን የሚያደርገው ሆን ብሎ የችሎታቸውን ፍሰት ለማስጓጎል እንደሆነ የአደባባይ ምስጢር ሆኗል፡፡ ሆነ ተብሎ እነሱን ብቻ የለየ ጥቃትና የመብት ጥሰት የሚፈጸምባቸውም በእስር ቤት ውስጥ ባለቻቸው ውስን ነጻነት የገነቧትን ማህበራዊ ትስስር ለማፍረስና የመጪውን ረመዳን ጾምም ተረጋግተው መጾም እንዳይችሉ ጫና ለማሳደር መሆኑ አያጠራጥርም፡፡ አወዛጋቢው የፍርድ ሂደት ቀጥሎ የሰው ምስክርነት እየተደመጠ ባለበት ሁኔታ የመጨረሻ ውሳኔ የማስለወጥ ሃይል ባይኖረውም እየተደመጠ ያለው ምስክርነት እጅግ እንዳደናገጣቸውና በዚህም ይህንን እርምጃ ለመውሰድ እንደተገደዱም የሚያሳብቅ ሆኗል፡፡ መንግስት በሃሰት የሽብር ክስ ማንገላታቱ ሳያንሰው በእስር ቤት ውስጥ እንኳን ታራሚዎች ላይ የሚያደርሰው በደል በእርግጥም የአገሪቱ የፍትህ ስርአት የቁልቁለት ጉዞውን እያፋጠነ ለመሆኑ ከበቂ በላይ ምስክር ነው፡፡
የእስር ቤቱ አስተዳደር ውስጥ ያሉት አንዳንድ ሀላፊዎች በግፍ እስር ላይ ለሚገኙት የህዝበ ሙስሊሙ ወኪሎች ያላቸውን ጥላቻ በተለያዩ አጋጣሚዎች ሲያሳዩ መቆየታቸው ይታወቃል፡፡ ካሁን ቀደም የደሴ ወጣት ታሳሪዎች ወደጨለማ ክፍል እንዲገቡ መወሰኑን ተከትሎ ሌሎች እስረኞች ተቃውሟቸውን ለማሰማት በተሰበሰቡበት ወቅት በቅጽል ስሙ ሻእቢያ ተብሎ የሚጠራው የማረሚያ ቤቱ የጸጥታ ሀላፊ ‹‹እኒህን አሸባሪዎች ይህን አጋጣሚ ተጠቅሞ መረሸን ነበር!›› ብሎ ቁጭቱን ሲገልጽ በግላጭ የተሰማ ሲሆን በተለያዩ አጋጣሚዎችም ጥቃት ከመፈጸም ወደኋላ እንደማይሉ መታዘብ ተችሏል፡፡ በማረሚያ ቤቱ ግቢ ውስጥ ካሁን ቀደምም በሌሎች በርካታ ታሳሪዎች ላይ አሰቃቂ የጅምላ ድብደባ ሲፈጸም የነበረ መሆኑ የቅርብ ጊዜ ትውስታ ነው፡፡
ህዝበ ሙስሊሙ ይህን መሰል የህገ መንግስቱን የእስረኛ አያያዝ ደንብ በግላጭ የሚጥሱ ወከባዎችና በደሎች በአስቸኳይ እንዲቆሙ ይጠይቃል! ህዝበ ሙስሊሙ ላይ ያወጁትን ጦርነት ሲያስፈጽሙ የቆዩት ደህንነቶችና የመዋቅራቸው አካላት ከህግ በላይ የሆነ አካሄዳቸውን በአስቸኳይ እንዲያቆሙም ያሳስባል! በህዝበ ሙስሊሙ ወኪሎች ላይ የሚፈጸም ማንኛውም ወንጀል በህዝበ ሙስሊሙ ላይ የሚፈጸም ወንጀል ነው፡፡ እነርሱ ላይ የሚደርስ በደል ፈርሞ ወደመንግስት በላካቸው ሰፊው ህዝበ ሙስሊም ላይ የሚደርስ በደል ነው፡፡ በመሆኑም በወኪሎቻችን ላይ አንዳች ነገር ቢደርስ ሃላፊነቱን ሙሉ በሙሉ የሚወስደው መንግስት መሆኑን እያስታወቅን ሰላማዊው ህዝበ ሙስሊምም ይህን መሰሉን ድንበር ያለፈ ጥቃት እስከመጨረሻው የሚፋረደው መሆኑን በጥብቅ እናሳውቃለን!
በህዝበ ሙስሊሙ ወኪሎች ላይ በማረሚያ ቤት ውስጥ እየተደረገ ያለው ወከባ በአስቸኳይ ይቁም!
የእስር ቤቱ አስተዳደር ከህግ በላይ መሆኑን በአስቸኳይ ያቁም!
የህዝብ ወኪሎችን ማጉላላት ይብቃ!
ድምፃችን ይሰማ!
አላሁ አክበር!

የወያኔ ግፍ ለከቱን አልፏል!

June12/2014
የወያኔ ጉጅሌ ራሱ ከሳሽ፣ ፖሊስና ዳኛ ሆኖ በሚገዛት ሀገራችን ውስጥ የሚያካሂደው ግፍ አንድ ህዝብ ሊሸከመው ለሚችለው በላይ ሆኗል።
የወያኔ ሹማምንትና በዘር ለዝርፊያ የተሰማራው ድርጅታቸው በቅርቡ ደግሞ ስዘርፍ አያችሁኝ በሚል ቁጣ ከአንደበታቸው በላይ ምንም ባልታጠቁ የኦሮሞ ተማሪዎች ላይ ከአካሄደው ጅምላ ጭፍጨፋ አልፎ ግለሰብ ተማሪዎችን በማሳደድ ሰቆቃ መፈጸሙን ቀጥሎበታል። በዚህ ሰአት በርካታ ተማሪዎች በታወቁና ባልታወቁ እስር ቤቶች ታጉረዋል። ብዙዎቹ ከትምህርት ገበታ ካላንዳች ጥያቄ ተባረዋል እየተባረሩም ይገኛሉ።
ከወያኔ ግፎች ሁሉ በእጅጉ የሚዘገንነው ሌሎችን በመወንጀል ማሰቃየትና መግደል በፈለገ ቁጥር ራሱ ወንጀል ከፈጸመ በኋላ ወንጀሉን በሌሎች ላይ ለማመኻኘትና ለመቅጣት የሚጠቀሙበት የሃሳብ ዘዴ ነው።
በአለምያ ዩኒቨርስቲ ተማሪዎች በተሰበሰቡበት አዳራሽ ውስጥ የደህንነት አባሎች ቦንብ አፈንድተው ጉዳት ካደረሱ በኋላ የሚፈልጓቸውን ወጣቶች ቦንብ ሲያፈነዱና ሲጠምዱ ያዝናቸው በማለት ከዚህ በፊት በዊክሊክ መረጃ እንደተለቀቀው የተለመደ በሰው ልጆች ላይ ሰቆቃ ይፈጽማሉ። ሌላው ቀርቶ ቦምብ አፈነዱ ተብለው የተከሰሱት ተማሪዎች በገዛ ጓደኞቻቸው ላይ ቦምብን የሚወረውሩበት ምክንያት የላቸውም።
ወያኔ ተማሪዎቹን አረመኔና እብድ ለማስመሰል የሰራው የራሱ ትንሽዪ ድራማ ወይም ሌላኛው አኬልዳማ መሆኑ ግልጽ ነው።
ወያኔ ደግሞ እንዲህ አይነት የወሮበላ ስራ እንደሚሰራ እንዳላዪ የሚያዩት ለጋሽ ሀገሮች ሁሉ ያጋለጡት፣ የሚያውቁት የአደባባይ ሚስጥር ከሆነ ሰንብቷል።
በዚህ መሰሪ ወንጀል ያዝናቸው ብለው ከአሰሯቸው ተማሪዎች ውስጥ የቦኮ ትቤ ተወላጅ የሆነ ኑረዲን ሃሰን የተባለ የአለመያ ዩኒቨርስቲ ተማሪ በድብደባ አሰቃይተው ከገደሉት በኋላ ራሱን ገደለ ብለው አስክሬኑን ለቤተሰቦቹ ሸጠውታል፡፡ በአሁኑ ወቅት ብዙ ተማሪዎች የደረሱበት እና የገቡበት ተፍጧል።
ይህ ሰቆቃ መጠኑን አልፏል! ግፍ በዚሁ እንዲቀጥል ከሆነ ደግሞ መቆም የሚችልበት ተግባር ባለመፈጸማችን ሁላችንም የዚያች ሀገር ልጆች ከታሪክ ወቀሳ እና ከህሊና ጸጸት አናመልጥም። ወያኔዎች በዘር ከፋፍለው በየተራ ስለሚያጠቁን ነው ይህ የሽብር አገዛዛቸው እድሜ ያገኘው። ይህን አደገኛ ክፍተት ካልዘጋነው መከራው ቀጥሎ ያሰቃየናል።
ግንቦት 7 የፍትህና የዴሞክራሲ ንቅናቄ አገራችን ይህን ሁሉ ግፍና መከራ ማስተናገድ እንዲበቃት ልጆቿ ተባብረን እንድንነሳ ደጋግሞ ጥሪውን ያቀርባል።
ለወያኔ የተመቸነው በየተራ ለመጠቃት አንዱን ብሄረሰብ በሌላው በማስፈራራትና ጥርጣሬ በመንዛት ለመግዛት የቀየሰው ዘዴ ሰለባ መሆናችን ነው።
ግንቦት 7 ንቅናቄ፤ የወያኔ የግፍ ቀንበር እንዲሰበር ሰፊ ህብረት ፈጥረን ከመታገል ውጪ አማራጪ የለንም ይላል።
የወያኔ ግፍ ይብቃ!
ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ!!!

Thursday, June 12, 2014

ህወሓት የቤተክስያን ገንዘብ ዘረፈ! (አብርሃ ደስታ – ከትግራይ)

June 12/2014

በትግራይ ምስራቃዊ ዞን ክልተ አውላዕሎ ወረዳ “አይናለም” የተባለ ጣብያ (ንኡስ ወረዳ) አለ። በዛ አከባቢ ያለው ደን “የመለስ ፓርክ” ተብሎ ተከልሏል። ኗሪዎቹ “የመለስ ፓርክ” መባሉ አልተዋጠላቸውም፤ ተቃውመውታል።
ባለፈው ወር ነው። “ከመለስ ፓርክ” የተወሰነ ዛፍ ይቆረጣል። በዚህ ጉዳይ የተቆጡ ካድሬዎች የአይናለም ኗሪዎችን ሰብስበው ዛፉ የቆረጠው ማን እንደሆነ ይጠይቃሉ። አውጫጭ መሆኑ ነው። ህዝቡ ላለመናገር አደመ። ህዝቡ ስላልተናገረ ለስምንት ተከታታይ ቀናት ታሰረ፤ ቅጣት መሆኑ ነው። ህዝቡ የታሰረው ፖሊስ ጣብያ አልነበረም፤ ፖሊስ ጣብያ አይበቃውማ። በብዙ ሺ የሚቆጠር ህዝብ (ወጣቶች፣ አዛውንቶች፣ እናቶች በቃ ሁሉም) በረኻ ላይ በፖሊሶች ተከቦ ታስሮ ይውላል። ዝናብ ይደበደባል፤ ፀሓይ ይመታል። ህዝቡ ግን ይህን ሁሉ ስቃይ ችሎ በቃሉ ፀና። ካድሬዎቹ ከስምንት ቀናት በኋላ ተስፋ ቆርጠው ተውት። ህዝቡ ግን ተቀይሟል።
ከተወሰነ ግዜ በኋላ የማዳበርያ ጉዳይ መጣ። መዳበርያ ዉሰዱ ተባሉ። አንወስድም አሉ፤ በአንድ ቃል። ህዝቡ ያቀረበው ምክንያት መዳበርያ ለመግዛት ገንዘቡም ፍላጎቱም የለንም የሚል ነው። ካድሬዎች ህዝቡን ለማስፈራራት ሞከሩ፣ አሰሩ፣ አዋረዱ። አልተሳካላቸውም። የካድሬዎች የመጨረሻ ሓሳብ ህዝቡ ለማዳበርያ የሚሆን ገንዘብ ከሌለው ከቤተክርስያን ታቦት እንዲበደር ጠየቁት። ህዝቡ አሻፈረኝ አለ። ከታቦት ተበድረን ማዳበርያ አንገዛም፣ ከእግዚአብሄር ቤት ተበድረን ለመንግስት አንሰጥም አሉ።
ካድሬዎችም ማዳበርያው በተሽከርካሪ ጭነው ጣብያው (ቀበሌው) ላይ አራገፉት። ህዝቡም የምንከፍለው ገንዘብ የለንም አለ። ካድሬዎቹ ደግሞ የአይናለም ህዝብ ታቦት የሚገኝበት “መድሃኔዓለም ቤተክርስትያን” ጋ በመሄድ ለማዳበርያው ዋጋ የሚሆን ገንዘብ ይወስዳሉ። የታቦቱ ቄሶች ዝርፍያ ተፈፅሞብናል በሚል ተግባሩን ይቃወማሉ። ቄሶቹ አርፈው እንዲቀመጡ ይነገራቸዋል። አሁን ለማዳበርያው የሚሆን ገንዘብ በቤተክርስትያኑ ተወስዷል። ህዝቡም ተቃውሟል። አሁን የተቃውሞ ሰለማዊ ሰልፍ ለማድረግ እየሞከሩ ነው። ህወሓትም እያስፈራራቸው ነው። ቤተክርስትያን ተዘርፏል ብለው ተቃውሞ ያሰሙ ቄሶች ግን ታስረው ይገኛሉ።
ይህ በንዲህ እንዳለ፤ በኢንደርታ ትግራይ ውስጥ የህወሓት መሪዎች ከ3000 በላይ የሚሆን የእግሪሓሪባ (እንደርታ) ኗሪ ለማምበርከክ በዚህ ሳምንት ከታሰሩ ስድስት ሰዎች በተጨማሪ ያከባቢው ቤተክርስትያን አገልጋይ ቄሶችም ለማሳሰር ወስነዋል። በዚህ መሰረት (1) ቀሲስ ብርሃኑ ቆባዕ፣ (2) ቀሲስ ንጉስ ወልደትንሳኤ እና (3) ቀሲስ ኃይሉ ገብረሂወት የእግሪሓሪባ ህዝብ የህወሓት ካድሬዎች ያዘዙትን እንዲሰማ እንዲያስፈራሩ፣ ካልሆነ ህዝቡን እንዲያወግዙ የሚያዝዝ ደብዳቤ ተሰጥቷቸዋል። ቄሶቹ ህዝብን በሀይማኖት አስፈራርተው ይሁን አታለው ዓረናን ትተው የህወሓትን ትእዛዝ እንዲቀበሉ ካላደረጉ ግን ቄሶቹ ራሳቸው እንዲታሰሩ ተወስኗል። ደብዳቤም ደርሷቸዋል።
ኢይደንግጥ ልብክሙ! ልባቹ አይደንግጥ! ልብኹም አይደንግፅ!

ሚሚ ስብሐቱ እና የሙታን ዲሞክራሲ (በዶ/ር ዳኛቸው)

June12/2014

የዚህ ጽሑፍ ዓላማ ሚሚ ስብሐቱና ጓደኞቿ “የጋዜጠኞች ክብ ጠረጴዛ” በተሰኘ ፕሮግራም እኔ ላይ ለሰነዘሩት ስድብ በዋናነት መልስ ለመስጠት ሳይሆን ዘለፋቸውን በሚካሄዱበት ሰዓት እግረ መንገዳችውን ባነሱት የፖለቲካ አተያይ ላይ ሒስ ለማቅረብ ነው፡፡ይህንንም እንድል ያስገደደኝ እኔ ከአዲስ አድማስ ጋዜጣ ዝግጅት ክፍል ተደውሎ ለቀረበልኝ ጥያቄ በሰጠሁት መልስ ላይ ወይም ባነሳሁት ሐሳብ ላይ ትችት በማቅረብ ፈንታ በእኔ ስብዕና ላይ አሉታዊ በሆነ መልኩ ዘለፋ በመሰንዘራቸው ነው፡፡

ለአዲስ አድማስ ጋዜጣ የሰጠሁት አስተያያት ዋና ፍሬ ነገር እንደሚከተለው ይነበባል፡፡ “በሁለተኛ ሹም ሽር የተከናወኑትን የስልጣን መደላደል በምናይበት ጊዜ ህወሓት እንደ ቀድሞው በእጅጉ ተጠናክሮ ብቸኛ የሆነውን ስልጣኑን ተመልሶ ይዟል፡፡”
እንግዲህ እነ ወ፨ሮ ሚሚ ስብሐቱ በዚህ መሠረታዊ ሐሳብ ላይ ትችት በመሰንዘር ፋንታ የተሾሙትን ሰዎች ስም እየጠቀሱ ግነት በተሞላበት አኳኋን ማንነታቸውን ማለትም ችሎታቸውን፣ክህሎታቸውን ፣ዕውቀታቸውን ሲክቡ በአንፃሩ እኔ ያቀረብኩትን ሐሳብ ሳይተቹ ለአንድ የዩኒቨርሲቲ መምህር የማይመጥን (የወረደ) አስተያየት በማለት አልፈውታል፡፡

እሑድ በሚተላለፈው ፕሮግራም ላይ የሚቀርቡት ወ፨ሮ ሚሚ እና ሌሎች ሁለት ግለሰቦች ቢሆኑም ሁለቱ ሰዎች እንደ ሰው በፕሮግራሙ ላይ የሚያንፀባርቁት የራሳቸው የአስተሳሰብ ልዕልና የሌላቸውና ለሚሚ ልሳን ለማዋስ ወይም “ለማከራየት” የተሠማሩ ስለሆነ ይህ ጽሑፍ እነርሱን ሳይሆን በቀጥታ እርሷን የሚመለከት ይሆናል፡፡

ከሁሉ አስቀድሞ ግን ትችቴን ከመጀመሬ በፊት አንድ ነጥብ አንስቼ ማለፍ እፈልጋለሁ፡፡ይኸውም እነሚሚ በግለሰብ ደረጃ ለሰነዘሩት ዘለፋ በአደባባይ መልስ መስጠቱ ተገቢ አይደለም፡፡በመሆኑም “እኔ እንዲህ ነኝ፤እንዲያ ነኝ” ብሎ ስለራስ መናገር ከባሕልም አኳያ ሆነ ከሞራል እይታ አንፃር ተገቢ ሆኖ አናገኘውም፡፡ሆኖም ግን ሚሚ ካነሳችው “ዳኛቸው ‘ይገባኛል’ የሚለው ሹመት ስላልተሰጠው ነው፡፡ ኢሕአዴግን የሚተቸው” ለሚለው ገለፃ ፅብቴን ጥዬ ማለፍ እፈልጋለሁ፡፡

ከላይ እንደጠቀስኩት ራሴን በመከላከል “አይ እኔ ሹመት አልፈልግም” የሚል መልስ ለመስጠት ሳይሆን እዚህ በቆየሁባቸው ፮ ዓመታት ሹመት የሚፈልግ ሰው ማድረግ የሚገባውን ነገር አጥቼው ወደ ሒስና በመንግስት ላይ ትችት ወደ መሰንዘር የሄድኩበት እንዴት ሊመስላት እንደቻለ መገረሜን ለመግለፅ ያክል ነው፡፡

ምናልባትም በመንግስት ለመሾም፣ለመደጎምና ለመመስገን ያለውን መንገድ በሞኖፖል “እኔ ብቻ ነኝ የማውቀው” የምትል ከሆነ ስለ እኔ ሹመት ከጃይነት ያለችው እውነት ሊሆን ይችላል፡፡

የሙታን ዲሞክራሲ
በገዢው ፓርቲ ልሂቃን አስተሳሰብ አሁን በኢትዮጵያ የተዘረጋው ሥርዓት ወሳኝ የሆኑትን የፖለቲካ ጥያቄዎች ስለፈታ ጊዜው የፖለቲካ ማቀንቀኛና “የማብጠልጠል” ሳይሆን ወደ ልማት የሚተኮርበት ነው፡፡

የዚህ ሐሳብ ዋነኛ ተጋሪ የሆነችው ሚሚ ስብሐቱ ጥያቄ በሚያነሱ ሰዎች ላይ ቁጣዋ የሚነሳው ከዚህ የመነጨ ነው፡፡የነሚሚ ስብሐቱ “የዚህ ጥያቄ አልቋል” የሚለው አስተያየት ጥያቄውን ለማፈንና ለመግደል ከመከጀል የመነጨ ነው፡፡

አንዳንድ ሰዎች እንደሚሉት እነሚሚ ማድረግ የሚፈልጉት ደርግ እንዳደረገው ጠያቂውን ሳይሆን ጥያቄውን እንደ ጥያቄ መግደል መፈለጋቸው ነው፡፡የዚህ ጽሑፍ ማተኮሪያ በሆነው ፕሮግራሟ ላይም ካነሳቻቸው ነጥቦች አንዱ “የብሔር ፖለቲካ መልስ ተሰጥቶበት ያበቃ ጉዳይ ነው የሚለው በምሳሌነት መቅረብ ይችላል፡፡”

“ፖለቲካ አልቋል”፣“ጥያቄዎች ተፈትተዋል”፣“ለአገሩቱ የሚበጅ ሐሳቦች ተገኝተዋል”፣“አሁን ትኩረታችን ከውይይት፣ከምክክር እና ከንትርክ ወጥተን ያገኘናቸውን የሚበጁ ሐሳቦች መተግበር ላይ ማድረግ ብቻ ነው የሚያስፈልገው”የሚል አካሄድ ነው የተያዘው፡፡እንዲህ ዓይነቱን አስተሳሰብ አንዳንድ ጸሐፍት ሕይወት አልባ እና የሙታን ዴሞክራሲ ይሉታል፡፡

በአንፃሩ ግን አንድ ማህበረሰብ ዴሞክራሲያዊና ሕያው እንዲሆን የሚከተሉትን ሦስት ንድፈ ሐሳቦች አቅፎ የያዘ መሆን አለበት፡፡እነርሱም አውጥቶ ማውረድና ምክክር (ደሊበራቲኦን) ፣ሐሳብን ማብላላት (ረፈለችቲኦን) እንዲሁም የሒስ መንፈስ (ጭሪቲቻል ጽፒሪት) ናቸው፡፡

ይህ እንግዲህ የሚያመለክተን ጉዳይ ማንኛውም ፍልስፍና ወይም የፖለቲካ ሂደት የሚነሱትን የኑሮ ተግባራዊ ችግሮች፣የሚታዩትን የፖለቲካ መሰናክሎች እንዲሁም የሚደቀኑትን የሞራል ክፍተቶች ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ መፍታት ስለማይቻል ከላይ የጠቀስናቸው ሦስት ነጥቦች ለዴሞክራሲያዊ ማሕበረሰብ በጣም አስፈላጊ መሆናቸውን ነው፡፡

እንደሚሚ ስብሐቱ አቀራረብ ግን የኢሐአዲግ የፖለቲካ አካሄድ ብዙ ማሕበረሰባዊ ጥቄዎችን እየፈታ የሚሄድ ስለሆነ እንደገና ወደ ኃላ እየተመለሱ ጥያቄ ማንሳት የአድኃሪ ጠባይ ነው፡፡
በተለይም “አገሪቱ የብሔር ጥያቄን ተሻግራ ካለፈች በኃላ እንደ ዳኛቸው ዓይነቱ ሰዎች ለምን ወደ ኃላ እንደሚመልሱን አናውቅም” ማለቷ ፖለቲካ ማለቂያ የሌለው የሐሳብ ፍጭት የሚያስተናግድ መድረክ መሆኑን ነው የዘነጋችው፡፡ለውይይትና ለሐሳብ ፍጭት ደግሞ አቀጣጣዩ ነዳጅ ጥያቄ ነው፡፡በመሆኑም ውይይት፣ጥያቄ፣ምክክር፣ነቀፊታ፣ትችት ወዘተ።።ለአንድ ዴሞክራሲያዊ ማሕበረሰብ ወሳኝና አስፈላጊ ነገሮች ናቸው፡፡

“አትናገሩ”፣“አትጠይቁ”፣“አታንገራግሩ”፣“አትተቹ”፣“ዝም ብላችሁ ተገዙ” የሚለውን የጉልበተኞች ጥሪ ይበልጥ ለማብራራት የ፳ ኛው ክ፨ዘመን ታላቅ ደራሲ ከሆነው ፍራንስ ካፍካ ሥራዎች መካከል ትንሽ ትረካ ልጥቀስ፡፡በአንድ እስር ቤት ውስጥ የሞት ፍርድ ተላልፎባቸው ቅጣቱን የሚጠባበቁ እስረኞች አንድ ቀን ከሰዓት በኃላ አመፅና ረብሻ ጀመሩ፡፡የከሰዓቱ ፈረቃ የዘብ አለቃ ካመፁት እስረኞች ዘንድ ቀርቦ “የእናንተ ጓደኞች ከዚህ በፊትም ሆነ ዛሬ ጠዋት እንኳ በነበሩት ረሻኞች ላይ ምንም ዓይነት ረብሻ ሳያነሱ ተረሽነው ሳለ እናንተ ግን በእኛ ተራ ላይ ረብሻ ማንሳታችሁ ተገቢ ያልሆነና አድልዎን የሚያሳይ ነው፡፡እንዲያውም ከሞራል አኳያ የሚያስጠይቃችሁን ሥራ እየፈፀማችሁ ነው፡፡የማታዳሉና ረብሻ ፈላጊ ባትሆኑ ኖሮ እንደዚህ ባለ የብጥበጣ ተግባር ውስጥ ሳትሳተፉ ዝም ብላችሁ ትገደሉ ነበር፡፡” ብሎ ወቀሳቸው፡፡

እነ ሚሚም አሁን የሚሉን “ባለፉት ስርዓታት ዝም ብላችሁ እኛ ስልጣን ስንይዝ በፊት ያላነሳችሁትን የጭቆናና የበደል አቤቱታ አሁን በእኛ ተራ ማንሳታችሁ ተገቢ አይደለም፡፡ጥሩ ሰዎች ብትሆኑ አርፋችሁ ትገዙ ነበር” እንደማለት ነው፡፡

ሚሚ ስብሐቱ ጋዜጠኛ ወይስ ሶፊስት
ጥንታዊው ትልቁ የግሪክ ፈላስፋ ፕሌቶ ዕድሜ ልኩን በሐሳብ ሶፊስቶችን ሲታገል ነው የኖረው፡፡በመሠረቱ ሶፊስት ማለት በተቀዳሚ አስመሳይ ማለት ነው፡፡ወይም አስመስሎ የሚያድር ማለት ነው፡፡

በዚህ ዙሪያ ዶ፨ር እጓለ ገ፨ዮሐንስ “የከፍተኛ ትምህርት ዘይቤ” በተባለ መጽሐፋቸው “የቀድሞ ዘመን ሶፊስቶች ያቀረቡት የጥቅም አገልጋይ የሆነ አሳሳች ትምህርት በጊዜአችንም ዘመናዊ ዳቦ ለብሶ ወደ እልፍኝ አዳራሽ ለመግባት ይጠይቃል፡፡ዳቦና ቆዳ ከለየን ግን ቆየን” ብለዋል፡፡እኛም ታግለው የመጡትን ፋኖዎችና የከተማ “ፋኖዎች” ከለየን ቆይተናል፡፡በተጨማሪም እውነተኛ ጋዜጠኞችንና ፕሮፓጋንዲስቶችንም ጠንቅቀን ካወቅንም ውለን ከርመናል፡፡እንደ እኔ አስተያየት ሚሚ ስብሐቱ በፕሮፓጋንዳ ሥራ ላይ የተሰማራች እመቤት ነች፡፡ሚሚ ተቀዳሚ ሥራዋ ፕሮፓጋንዳ ነው በምንልበት ጊዜ ምን ማለታችሁ ነው፧ ለዚህ ጥያቄ ቀጥተኛ መልስ ከመስጠታችን በፊት የእርሷ ሬዲዮ በአመለካከትና በአቀራረብ ከመንግስት ሚዲያ ጋር ዝምድና አለው ብለን ስለምናምን ከዛሚ በፊት ትንሽ ስለ ኢትዮጵያ ሬድዮና ቴሌቪዥን ብንናገር ጋሪውን ከፈረሱ ማስቀደም አይሆንብንም፡፡

ሚዲያና አታላዩ ጂኒ
በመሠረቱ የሚዲያው ዋና ሚናና ግብ ሥርዓቱ እራሱን እየወለደ (ረፕሮዱቸ እያደረገ) እንዲሄድና ሕልውናውን ለዘለቄታው ማስጠበቅ ነው፡፡ለዚህም ተልዕኮው መረጃ ከማቀበል መደበኛ ሥራው ጎን ለጎን የፕሮፓጋንዳ ተግባራትን ያከናውናል፡፡ለፕሮፓጋንዳ ሥርጭቶቹም ማሳነስ፣መጨመር፣ማጋነን፣ማንኳሰስ፣መደመር፣መቀነስ፣መፍጠር፣ማንፀባረቅ፣መወንጀል፣ማወደስ ዓይነተኛ መሣሪያዎች ናቸው፡፡

እነዚህን የፕሮፓጋንዳ ተግባራት ትንሽ ለማብራራት በአንድ ርዕስ ዙሪያ የተካሄደውን የሁለት ፈረንሳዮች ወግ መጥቀስ ተገቢ መስሎ ይታየኛል፡፡አንደኛው ፈረንሳዊ ሬኔ ዴካርት የተባለው የ፩፯ኛው ክ፨ዘመን ፈላስፋ ነው፡፡ይህ ፈላስፋ የሰው ልጅ ወደ ትክክለኛው ሐሳብ እንዳይደርስ የሚያደርጉ መሰናክሎች አሉ ይልና ከነኚህ መካከል ባህል፣ወግና የመሪዎች ጫና ተጠቃሾች መሆናቸውን ያስረዳል፡፡

ይኸውም የሚሆንበት ምክንያት በዋናነት የሰው ልጅ በስሎና ዐውቆ ስለማይወለድ የራሱን የአመለካከት ልዕልና እስከሚያገኝ ድረስ በማሕበረሰቡ ስለሚቀረጽ ውጫዊ የሆኑት የባሕል፣የወግ የታሪክ ጫናዎች በላዩ ላይ ያርፋሉ፡፡በመሆኑም በአንድ ማሕበረሰብ ውስጥ ያሉ ግለሰቦች ወደ እውነት እንዲቀርቡ ከተፈለገ በተቀዳሚነት የማሕበረሰቡ አመለካከት መታከምና መጽዳት አለበት ብሎ ያምናል፡፡

በተጨማሪም እንደሬኔ ዴካርት መላምት እንዲያውም ከባህል ውጭ አንድ ሆነ ብሎ አሳሳች የሆነ እርኩስ ሰይጣን ሊኖር ይችላል፡፡ማኅበረሰቡ ውስጥ ያሉ አሳሳች ነገሮች ዐውቀው ለማሳሳት ሳይሆን ካለማወቅ እና የጠቀሙ እየመሰላቸው የሚያሳስቱ ሲሆን፣በአንፃሩ የአሳሳቹ ጂኒ ተግባር ግን አስቦና ሆነ ብሎ የሚያደርገው ነው፡፡ከሬኔ ዴካርት አስተምህሮት የምናገኘው ስሕተት እንደ ስሕተት የግለሰቡ ጉዳይ ብቻ ሳይሆን ከማኅበረሰቡ አመለካከት ጋር የተቆራኘ መሆኑን ነው፡፡

በሌላ በኩል በ፳ኛው ክ፨ዘመን መባቻ ላይ የመጣው ፈረንሳው የማሕበረሰብ ጥናት ተመራማሪ ኤሚል ዴርካም፣ለዴካርት “አሳሳች ጂኒ ሊኖር ይችላል” ለሚል አስተያየት ሲመልስ “ጂኒውም ከጉም ፣ ከሰማይ ፣ከወንዝ፣ከተራራ ስር ከምትፈልገው እዚያ የፖለቲካ ማኅበረሰብ ውስጥ ብትፈልገው ታገኘዋለህ” በማለት ነበር፡፡ወደ እኛ ጉዳይ በምንመጣበት ጊዜ እኛም አታላዩ ጂኒ እንደ ዴርካይም የፖለቲካ ሥርዓቱ አካባቢ በተለይም በሚዲያ ክፍል ሊገኝ ይችላል ብለን እናምናለን፡፡ከዚህ አኳያ እህታችን ከተሰማራችበት የፕሮፓጋንዳና የማነሁለል ተግባራት ስንነሳ የሬኔ ዴካርትን ጂኒ ሚና እንደምትጫወት ይሰማናል፡፡
ይህንኑ አሳሳች ጂኒ በመፍራት ማንኛቸውም የዴሞክራሲያዊ አገራት መንግስታት የራሳቸው ሚዲያ እንዳይኖራቸው በሕግ ተከልክሏል፡፡እንደ ቪኢኤ የመሰሉ የሚዲያ ተቋማት ዜናዎቻቸውን ለውጭ አድማጮችና ተመልካቾች እንጂ ለአገር ውስጥ ታዳሚያን ማሠራጨት የማይችሉት ለዚህ ነው፡፡

ህወሓት እና የትግራይ ሕዝብ
በመሠረቱ ህወሓት ትግርኛ የሚናገሩ ሰዎች የፈጠሩት የፖለቲካ ፓርቲ እንጂ የትግራይ ሕዝብ ማለት አይደለም፡፡ በሌላ በኩል ፓርቲው የተወሰኑ የትግሪኛ ተናጋሪዎች እንጂ የሁሉም የትግራይ ሰዎች ፓርቲ ማለትም አይደለም፡፡ይህንን ለመለየት በጣም የላቀ ትምህርት አስፈላጊ ሆኖ አናገኘውም፡፡ሁለቱን መለያየት ካልቻልን እንደ ሚሚ ስብሐቱ ህወሓት ሲነካ ትግራይ ተነካ፤ስለ ህወሓት ሲወራ ስለ ትግራይ ማውራት ተደርጎ መቁጠር ይሆናል፡፡ለዚህም ማሳያነት እንዲሆን ለጋዜጣው በሰጠሁት አስተያየት “ስልጣን ተመልሶ ወደ ህወሓት እጅ ገባ” ማለቴን “ዳኛቸው ስልጣን ወደ ትግራይ ተመለሰ አለ” ብላ አቅርባዋለች፡፡እዚህ ላይ አፅንዖት ለመስጠት የምፈልገው ያላልኩትን ማለቷ ላይ ብቻ ሳይሆን ፓርቲና ዘርን አንድ አድርጎ የሚያቀርብላት አዕምሯዊ ቀረፃ እንዳላትም ለማሳየት ጭምር ነው፡፡

ይህንንም ስል የሽተቷ ምንጭ ከአቀራረብ ወይንም ከማወቅ አለማወቅ (ዐፒስተሞሎጊቻል) ሳይሆን ያላት አዕምሯዊ ኑባሬ (ኦንቶሎግይ) ከዘርና ከነገድ ውጭ እንዳታይ እንደሚያደርጋት መግለፄ ነው፡፡ ሽተቷ “ያጋጣሚ” ሳይሆን “የተፈጥሮ” መሆኑን ልብ ይሏል፡፡እንደዚህ ዓይነት አዕምሯዊ ኩነት የግድ ሚሚ ስብሐቱን ህወሓት ሲነካ ትግራይ ተነካ እንድትል፤ስለ ህወሓት ሲወራ ስለ ትግራይ የተወራ አድርጋ እንድትቆጥር ያደርጋታል፡፡በዚህ ረገድ ሚሚ ብቸኛ ሳትሆን በዛ ያሉ የአመለካከት ወንድምና እህቶችም እንዳሏት በእርግጠኛነት መናገር ይቻላል፡፡ከአዕምሯዊ ግንዛቤ ውጭ የፖለቲካ ደጀን ይሆነናል ከማለትም ሆነ ተብሎ የትግራይን ሕዝብ “መጡባችሁ” በሚል ፈሊጥ እንደመሸሸጊያ ይጠቀሙበታል፡፡ከዚህ ጋር ተያያዥ ያለው የተማሪነት ገጠመኜን በምሳሌነት ማቅረብ እፈልጋለሁ፡፡

በአፄ ኃ፨ሥላሴ ዘመነ፡መንግስት የሁለተኛ ደረጃ ተማሪዎች ሳለን ብዙ ጊዜ በፖለቲካ ምክንያት ረብሻ ይነሳ ነበር፡፡አንድ ቀን ከሰዓት በኃላ የት፨ቤቱ አሜሪካዊ ዳሬክተር ሁላችንንም ሰብስበው ተግሳፅና ቁጣ ከሰነዘሩብን በኃላ ከመሐከላችን የነበረውን በጣም የታወቁ የአፄ ኃ፨ሥላሴ የቅርብ ዘመድ የራስነት ማዕነግ ያላቸውን ሰው የልጅ ልጅ ከሁላችንም በተለየ ነጥለው የሚከተለውን ተናገሩት፡፡

“አንተ ብዙ ጊዜ ረብሻ ላይ እፊት ፊት ትቀድማህ ሆኖም ግን ችግር በሚመጣብህ ጊዜ ከዚህ ቀደም ደጋግመህ እንዳደረግኸው አያጥ ጫማ ውስጥ ገብተህ ትደበቃለህ ፡፡”አሁንም እኔ እንደሚታየኝ አንዳንድ የህወሓት አቀንቃኞች ፓርቲው ላይ ለሚሠነዘረው ሒስ መልስ መስጠት ሲቸግራቸውና የአመለካከት አጣብቂኝ ውስጥ ሲወድቁ ሮጠው የትግራይ ሕዝብ “ጫማ” ውስጥ ይደበቃሉ፡፡በመሆኑም ለእርሷ ህወሓትን የተቸ ሁሉ ፀረ፡ትግሬና ትምክህተኛ ነው፡፡በፕሮግራሙ ላይ ከተነሱት ነገሮች በጣም የገረመኝ ሚሚ ስብሐቱ ሳትሆን ከተወያዮቹ አንዱ “እኔ የምፈራው አሁን እነዚህ ሰዎች(እነ ዳኛቸው) ክቡር ዶ፨ር ቴዎድሮስ አድኃኖምን ትግሬ ብለው እንዳያዋርዷቸው ነው፡፡” ሲል መስማቴ ነው፡፡ “እንዳያዋርዷቸው” የሚለው መቼስ የሚገርም ቃል ነው፡፡ እኔ እስከገባኝ ድረስ በዚህ አነጋገር ለማለት የተሞከረው ሦስት ጉዳኞችን ነው፡፡አንደኛ፡፡“የተሾሙትን ትግሬዎች እንበላቸው ” በማለት ሹመቱ የት ቦታ እንደሄደ ለማድበስበስ ነው፡፡ሁለተኛው፡፡ደግሞ የተሾሙትን ከብሔር በላይ የሆኑ ሰዎች አድርጎ ለማቅረብ ነው፡፡በሦስተኛ ደረጃ ትግርኛ የሚናገርን ሰው “ኤርትራዊ ነኝ” እስካላለ ድረስ ትግሬ ነው ብለን ብንገልፀው ሰውየውን “ማዋረድ” የት ላይ እንደደሆነ ሊገባኝ አይችልም፡፡

መደምደሚያ
ጤናማ የሆነ የፖለቲካ ውይይት ለማካሔድ ከስድብና ከዘለፋ ባሻገር በአስተያየትና በሐሳብ ላይ የተሞረኮዘ ሙግትና ውይይት ምንጊዜም ለዴሞክራሲ ማበብ ትልቅ አስተዋፅዖ ያደርጋል የሚል እምነት አለኝ፡፡ከዚህም በተጨማሪ ዴሞክራሲ ተመራጭ የሆነው የሐሳብ ልዩነት የሚያስተናገድበትን መድረክ አመቻችቶ ስለሚያቀርብ ነው፡፡ሆኖም ከዚህ አኳያ የሚሚ ስብሐቱን የቅርብ የፖለቲካ አካሄድ ስንፈትሽ ለዴሞክራሲ ይበጃሉ ተብለው ከተቀመጡት ወሳኝ መርሆችዎች ያፈነገጠች መሆኗን እንገነዘባለን፡፡
አንደኛ፡፡የሐሳብ ልዩነትን በኃይልና በዘለፋ ለመወሰን መሞከር ኢ፡ዴሞክራሲያዊ መሆኑን ትዘነጋለች፡፡

ሁለተኛ፡፡የዴሞክራሲ ግብ ሄዶ ሄዶ ነጻነትን (ሊበርትይ) መጎናፀፍ ነው፡፡ነፃነት ስንል ደግሞ የቡድን ብቻ ሳይሆን የግለሰብም ነፃነት ማለታችን ነው፡፡እነ ሚሚ እንደሚያደርጉት ከእነርሱ ሐሳብ ውጪ የቀረበን ድምፅ እንዳይሰማ ለማፈን ከመሞከር በተጨማሪ “የብዙኃን መገናኛ በእጃችን አለ” በማለት የሐሳብ ብዝኃነትን ገድሎ አንድን ሐሳብ በብቸኝነት ለማንገስ የሚደርግ ሙከራ የነፃነት ገፈፋ ብቻ ሳይሆን ትልቅ የመብት ጥሰት መሆኑን መገንዘብ ያስፈልጋል፡፡

ሦስተኛ፡፡ዴሞክራሲ ከሁሉም በላይ በሥነ፡ምግባር ፣በፖለቲካ እንዲሁም በማህበረሰብ ጉዳይ የተኮተኮተ መልካም ዜጋ ለማፍራት የሚያስችል ሥርዓት ነው፡፡ከዚህም አኳያ ስናየው ዴሞክራሲ ትልቅ ት፨ቤት ነው፡፡
ለዚህ የማስተማር ተግባሩ ሬዲዮን ጨምሮ ሎሎች መገናኛ ብዙኃን ዓይነተኛ መሳሪያዎች ናቸው፡፡ሚሚ ስብሐቱ ግን ይህንን መልካም ሚና ሙሉ በሙሉ ለመጫወት የፖለቲካ ድባቡ ባይፈቅድላትም በራሷ ተነሳሽነት ትንሽም እንኳ ጥረት ስታደርግ አይስተዋልም፡፡እንዲያውም የሚሚን ፕሮግራም በምናይበት ጊዜ የመንግስት ሚዲያ የራሱን ሐሳብ ለማቅረብ የተሳነው ይመስል፤ እርሷም ተጨማሪ የግል ሬዲዮ በብዛት ሳይሆን በጥቂቱ በሌለበት አገር ውስጥ በሞኖፖል ለተያዘው የዜና አውታር አጋር መሆኗ የሚያሳዝን ነው፡፡

ዓለማየሁ ገ፨ሕይወት “እታለም” በተሰኘ ስብስብ ግጥሞች “በምድር ማሕፀን” በሚለው ግጥሙ በዋናነት የቀይሽብር ሰለባ የሆኑት ሰማዕታት አጽም ተቆፍሮ ሲወጣ በወቅቱ የተሰማውን ስሜት የገለጸ ሲሆን፣ወደፊትም ይኼ ነገር እንዳይደገም ያሰጠነቀቀበትን ምክር ያካተተ ግጥም ነው፡፡ዓለማየሁ በግጥሙ በተለይም ስለወደፊቱ ያሰጠነቀቀበት እኔ ካነሳሁት ሐሳብ ጋር ተያያዥነት ስላላው ጥቂት ስንኞች “ከምድር ማሕፀን” ተውሼ ለአንባቢያን እጋብዛለሁ፡፡

…።አፈር ያደረግነው፤
ጭንጫ መሬት ያልነው
ያገራችን ምድር ፣ተራራው ሜዳችን
ሰርጡ ወጣ ገባው፣ለምለሙ መስካችን
በተማሰ ቁጥር፣ወጣ ታሪካችን፡፡
…ሰርዶና ቄጠማ
ሰንበሌጥ አክርማ
እሚያበቅለው አፈር፣
ዋንዛና ባህርዛፍ፣
ዳጉሳና ነጭ ጤፍ
እሚያፈራው ምድር ፣
ዳግም ተማሰና፣ተገኝ ሌላ እውነት
የአንድ ትውልድ ታሪክ
የአንድ ትውልድ ሃፍረት፦
ሕጻንና አዛውንት
ኮረዳና አሮጊት
ጎልማሳና ወጣት
እንበለ ርህራሄ፣የተጨፈጨፋ የተቀበሩበት፦
…ነገ እሚቆፈረው ፣እሚማሰው አፈር
ከህሊና ንቅዘት፣
እንዲሆን የጸዳ፣ከዘመን ቸነፈር
በምንወጥነው ግብር፣በምንተክለው ችግኝ
ተንኮል እንዳይገኝ፣
ህፀፅ እንዳይገኝ፣
ሰርክ ፀሎታችን፣
ነገ እሚነበበው፣ታሪክ ሕይወታችን
የሚያስደስት እንጂ ፣ላይሆን እሚያስከፋ
አንገት እሚያስደፋ፣
ሀገር እሚያለማ፣እንጂ እማያጠፋ
መሆኑን ማሳየት፣አለብን በይፋ፦
ከእንግዲህ ምድራችን፣ማሕፀኗ ሲቃኝ
በወርቅና በአልማዝ፣ ተገጥግጦ እንዲገኝ
ለእውነት እንቁምና፣ቸር ቸረሩን እንመኝ፡፡

ይህ ጽሑፍ በአዲስ ጉዳይ መጽሔት ቅጽ 7 ቁጥር 145 ጥር 2005 ዕትም ለንባብ የበቃ ነው፡፡ሪ – 6ኛ ፓትርያርክ ለመሾም የሚደረገውን ጊዜውን ያልጠበቀ ሩጫ ለማትደግፉ በሙሉመፈክራችን – “የቤተ ክርስቲያኔ ጉዳይ ያገባኛል” የሚል ነው።

(ደጀ ሰላም ታኅሣሥ 11/2005 ዓ.ም፤ ዲሴምበር 20/2012)፦ በጥቂት የቅዱስ ሲኖዶስ አባላት ፍላጎት በመዘወር ላይ ያለው የ6ኛው ፓትርያርክ ምርጫ ተጠናክሮ በመቀጠል አሁን “አስመራጭ ኮሚቴ” በማቋቋም ትልቅ ርምጃ ተስፈንጥሯል። ለዕርቅና ለሰላም ወደ አሜሪካ የላካቸውን ልዑካን መምጣት ሳይጠብቅ፣ ይዘው ለሚመጡት ምላሽ ቦታ ሳይሰጥ አዲስ ፓትርያርክ ወደ መምረጡ እየተጓዘ ነው።

ይህንን ጉዳይ በተመለከተ በአገር ውስጥም፣ ከአገር ውጪም፣ በመላው ዓለም ያለው ኦርቶዶክሳዊ ድምጹን ማሰማት እንደሚፈልግ ይታወቃል። የአቅሙን የመፍትሔው አካል መሆን ይፈልጋል። ታዲያ ምን ይሻላል? ከጥቃቅን የጽዋ ማኅበራት እስከ ግዙፎቹ፣ ከማኅበረ ካህናት እስከ ማኅበረ ምዕመናን ስለ ቤተ ክርስቲያናችን እንደሚገደን መናገር የሚገባን አሁን ነው። ስለዚህም ነው ይህንን የመወያያ ርዕስ የከፈትነው። መፍትሔ የምትሏቸውን ሐሳቦች በማቅረብ፣ በየአካባቢያችሁና በየአጥቢያችሁ በአካል በመሰባሰብና በመነጋገር ለእናት ቤተ ክርስቲያናችሁ ያላችሁ አለኝታነት እንድታሳዩ ይጠበቃል። እምነት በሥራ እንጂ በምን ይገለጻል? ለመነሻ እንዲሆን ይህንን እንጠቁም። እናንተም አክሉበት።መረጃውን ለመላው ሕዝበ ክርስቲያን ማድረስ፣ (በስልክ የኤስ.ኤም.ኤስ መልእክቶች፣ በፌስቡክ፣ በትዊተር)፣በየአጥቢያችን ድምጻችንን ልናሰማ የምንችልበት ስብስብ መፍጠር፣ዜናውን ለመገናኛ ብዙኃን ማድረስ፣ብፁዓን አባቶችን በስልክም በአካልም በመቅረብ ስለ ጉዳዩ ማነጋገር፣ በውሳኔው እንደማንስማማ ማሳወቅ፣ (አስፈላጊ ነው ብለን በምናምነው ጊዜ ስልኮቻቸውን በይፋ ለማቅረብ እንገደዳለን)ጉዳያችን እና ዓላማችን “ድብቅ የፖለቲካ አጀንዳ” ሳይሆን የቤተ ክርስቲያናችን አባት የመምረጥ ጉዳይ መሆኑን ለሚመለከታቸው አካላት አለ ፍርሃትና ያለ ሥጋት መግለጽ፣ከመንግሥት አካላት የተደበቀ የመሥራት ፍላጎት እንደሌለን ከወዲሁ በተደጋጋሚ መግለጽ፣በአገር ውስጥ ያሉ ጋዜጦችና መጽሔቶች ለጉዳዩ ሽፋን እንዲሰጡት ማበረታታት፣የውጪ አገር ኢትዮጵያውያን ሚዲያዎችም በአንድ ድንጋይ ሁለት ወፍ በሚል በዚሁ ሰበብ ኢሕአዴግን ለመተቸት ሳይሆን ጉዳዩን ለክርስቲያኑ ሕዝብ በማይጎረብት መልክ እንዲያቀርቡት ማገዝ፣ኦርቶዶክሳውያን ጡመራ መድረኮችም ዜናዎችን በትብብርና በኅብረት ለምእመኑ ማድረስ፣

የኢትዮጵያ ነፃ ጋዜጠኞችንና ጦማርያንን ማን ይፈራቸዋል? (ፕ/ር አለማየሁ ገብረማርያም)

June 12, 2014
ከፕሮፌሰር አለማየሁ ገብረማርያም
ትርጉም በነጻነት ለሀገሬ
የእስክንድር ነጋን፣ ርዕዮት ዓለሙን፣ ውብሸት ታዬን፣ የዞን ዘጠኝ ጦማሪዎችን…የዴሞክራሲያዊ መብት የመጠቀም የትግል እንቅስቃሴ ሲመለከት እንደሚዳቋ እየበረገገ የሚስፈነጠረው ማን ነው?Ethiopian government scared of bloggers and journalists
የኢትዮጵያ የነጻው ፕሬስ እና ጦማርያን ቁንጮ የሆነው እስክንድር ነጋ ሀሳቡን በነጻ በመግለጹ ብቻ በአምባገነኑ የወሮበላ ቡድን ስብስብ የይስሙላው የዝንጀሮ ፍርድ ቤት የ18 ዓመታት እስር ተበይኖበት በገዥው አካል የማጎሪያ እስር ቤት በመማቀቅ ላይ ይገኛል፡፡ ሟቹ መለስ ዜናዊ ልዩ ትዕዛዝ እስክንድር ነጋ በቁጥጥር ስር እንዲውል እና የ18 ዓመቱ የሸፍጥ እስራት እንዲበየንበት ተደርጓል፡፡ መለስ ዜናዊ በኢትዮጵያ ከሚገኙ ማናቸውም ጋዜጠኞች የበለጠ እስክንድር ነጋን ይፈራዉና ይጠላው ነበር፡፡ ዝሆን አይጦችን “ይፈራል” ከሚለው ኢ-ስነ አመክንዮ አንጻር በተመሳሳለ መልኩ መለስም እስክንድር ነጋን እንደጦር ይፈራው ነበር፡፡
በቅርቡ እስክንድር ከማጎሪያው እስር ቤት ለ8 ዓመት ልጁ ለናፍቆት እንዲህ የሚል ግልጽ ደብዳቤ ጽፏል፣ “እንዲያው ሁኔታውን ሳየው እያለሁ የሌለሁ የዘፈቀደ አባት ሆኛለሁ፣ ምክንያቱም በ18ኛው መቶ ክፍለ ዘመን ፈረንሳዮች ነጻነት፣ እኩልነት፣ ፍቅር እያሉ ደጋግመው ይጠሯቸው የነበሩትን ሶስት ቀላል ቃላትን በመውሰድ እኔም በሀገሬ ነጻነት፣ እኩልነት እና ፍቅር እንዲሰፍን በማሰብ እነዚህን ቃላት በማስተጋባቴ ነው በሸፍጠኞች ለእስር የተዳረግሁት“ ብሏል፡፡ እስክንድር ለነጻነት፣ ለእኩልነት እና ለአብሮነት ፍቅር ጦማሪ ነው፡፡ ለዚህም ነው ለእኔ የጀግናዬ ተምሳሌት የሚሆነው!
የኢትዮጵያ የፕሬስ ነጻነት ቀንዲል ጀግናዋ የ34 ዓመቷ ወጣት ርዕዮት ዓለሙ በተመሳሳይ መልኩ በአቶ መለስ ዜናዊ የ14 ዓመታት እስር በይኖባታል፡፡ ይህች ጀግና ወጣት በዓለም አቀፉ ህብረተሰብ ዘንድ “እውነት ተናጋሪዋ ኢትዮጵያዊት እስረኛ” በመባል ትታወቃለች፡፡ ርዕዮት ለእስር የተዳረገችው የግድብ ፕሮጀክት የገንዘብ ማሰባሰቢያ ዘዴዎችን በተመለከተ በገዥው የፖለቲካ ፓርቲ ላይ ጠንካራ ትችት በማቅረቧ እና በቅርቡ በህይወት የተለዩት የሊቢያ አምባገነን መሪ ሙአማር ጋዳፊ እና መለስ ዜናዊ ከአንድ ባህር የሚቀዳ ተመሳሳይ ባህሪ ያላቸው መሆናቸውን በይፋ በመግለጿ ነው፡፡ ርዕዮት በእስር ቤት ተዘግቶባት እና አፏን ተሸብባ ለመቀመጥ ባለመፍቀድ በድፍረት አንገቷን ቀና አድርጋ ስልጣኖቻቸውን ከህግ አግባብ ውጭ በህገወጥነት ለሚጠቀሙት ህገወጦች እና ትዕቢተኞች እውነት እውነቱን እንዲህ በማለት እቅጬን ተናግራለች፣ ”የተሻለች ኢትዮጵያን ለማየት እኔ በግሌ የሚጠበቅብኝን ሁሉ ማበርከት አለብኝ የሚል እምነት አለኝ፣ በአሁኑ ጊዜ በኢትዮጵያ ውስጥ በርካታ ኢፍትሀዊነቶች እና ጭቆናዎች ተንሰራፍተው ስለሚገኙ እነዚህን እኩይ ተግባራት በምጽፋቸው ትችቶቸ ማጋለጥ እና ከንቱ መሆናቸውን መቃወም አለብኝ… ለዚህ በጎ ዓላማ በድፍረት ትግል በማካሂድበት ወቅት ሊያስከፍለኝ የሚችለውን ዋጋ ሁሉ ለመቀበል ዝግጁ ነኝ“ በማለት ከእስር ቤት አፈትልከው በሚወጡ የእጅ ጽሁፎቿ ገልጻለች ጀግናዋ ርዕዮት ዓለሙ፡፡ በማይበገረው እና በማይንበረከከው ትክክለኛ የጽናት አቋሟ ምክንያት ገዥው አካል ሰብአዊነት የሚባለውን ክቡር ነገር በመደፍጠጥ የህክምና አገልግሎት እንዳታገኝ ቅጣት ጥሎባታል፡፡ መቀመጫውን ሎንዶን ያደረገ የህግ መከላከል የተነሳሽነት ሜዲያ/Media Legal Defense Initiative የተባለ ተቋም በአልጃዚራ ባቀረበው ዘገባ መሰረት ርዕዮት “በሰውነት አካሏ ላይ የተከሰተ እብጠት የተገኘ ቢሆንም ተገቢ የሆነ ህክምና እየተሰጣት እንዳልሆነ ግልጽ አድርጓል፡፡ ምንም ዓይነት የሰመመን መስጫ ማደንዘዣ ሳይሰጣት በጡቷ ላይ የቀዶ ህክምና ስራ በማከናወን የቀዶ ህክምና መስፊያ ክሩ ከጡቷ ሳይወጣ ከዓመት በላይ ከመቆየቱም በላይ ከደህረ ቀዶ ህክምናው በኋላም ቢሆን ተገቢ የሆነ ህክምና የተሰጣት አይደለም“ ብሏል፡፡ ለእኔ ርዕዮት የጀግና ተምሳሌታዬ ናት!
የማይበገረው ጋዜጠኛ እና አርታኢ ውብሸት ታዬ የመናገር አንደበቱን ተሸብቦ በመለስ ዜናዊ ዝዋይ በሚባል አስፈሪ እና ጭራቃዊ የማጎሪያ እስር ቤት በመማቀቅ ላይ ይገኛል፡፡ በእርሱ ላይም የ14 ዓመታት እስራት ተበይኖበታል፡፡ ውብሸት የገዥውን አካል ሙስና እና ስልጣንን ከህግ አግባብ ውጭ መጠቀምን አስመልክቶ በጋዜጣ ላይ የሚያቀርባቸውን ትችቶች እና አስተያየቶች በፍጹም አያቋርጥም፡፡ ውብሸት ለሚጠዘጥዝ የኩላሊት ህመም ተጋልጦ የሚገኝ ቢሆንም እርሱም ህክምና እንዳያገኝ ተደርጎ በመሰቃየት ላይ ይገኛል፡፡ በኢትዮጵያ በማጎሪያው እስር ቤት ለሚገኙት የህሊና እስረኞች የህክምና አገልግሎት መንፈግ በኢትዮጵያ ያለው ገዥ አካል እለት በእለት የሚፈጽማቸው በሰው ልጆች ላይ የሚፈጸሙ የቅጣት ወንጀሎች ናቸው፡፡ ፍትህ እየተባለ የሚጠራው የውብሸት የአምስት ዓመት ልጅ እንዲህ በማለት ጥያቄ በማቅረብ ላይ ይገኛል፣ “ሳድግ እና ለአቅመ አዳም ስደርስ እኔም እንደ አባቴ ሁሉ ወደ እስር ቤት እጋዛለሁን?“ ሕፃኑ ፍትህ በአሁኑ ጊዜ አጥር የሌለው እስር ቤት ውስጥ እየኖረ መሆኑን ሊገነዘብ አይችልም፡፡
ከጥቂት ሳምንታት በፊት “የኢትዮጵያ የዞን ዘጠኝ ጦማሪዎች” (የፖለቲካ እስረኞችን ከያዘው ከመሀል ከተማ በጥቂት ኪሎ ሜትሮች ርቀት ላይ የሚገኘው የ “መለስ ዜናዊ ታዋቂው የቃሊቲ እስር ቤት” ህንጻዎች ቀጥሎ የተሰየመ) እና ሌሎች ጋዜጠኞች በስም አጥናፍ ብርሀኔ፣ ዘላለም ክብረት፣ በፍቃዱ ኃይሉ፣ አቤል ዋቤላ፣ ማህሌት ፋንታሁን፣ ናትናኤል ፈለቀ፣ አስማማው ኃይለጊዮርጊስ፣ ተስፋለም ወልደየስ እና ኤዶም ካሳዬ የክሱ ጭብጥ ባልታወቀበት ሁኔታ ከህግ አግባብ ውጭ በዘፈቀደ በቁጥጥር ስር ውለው ለእስር ተዳርገዋል፡፡ ፖሊስ በእነዚህ ጦማሪያን እና ጋዜጠኞች ላይ ምን ዓይነት ክስ መመስረት እንዳለበት ገና በመለግ ላይ ይገኛል፡፡
(የገዥው ፖሊስ የሚጠረጥረውን ዜጋ በዘፈቀደ በቁጥጥር ስር አውሎ እና እስር ቤት በማጎር እያሰቃዬ ተሰራ ለተባለው ጥፋት ማስረጃ እና መረጃ በመፈለግ በዜጎቿ ላይ ሰብአዊ መብትን በመደፍጠጥ ኢትዮጵያ በዓለም ላይ ብቸኛዋ አገር ናት!!! የይስሙላዎች የዝንጀሮ ፍርድ ቤቶች በዘፈቀደ ከህግ አግባብ ውጭ በቁጥጥር ስር ለዋሉት ዜጎች ዋስትና በመንፈግ ፖሊስ እና አቃቤህግ የሚባሉ የገዥው አካል የማጥቂያ መሳሪያ ሎሌዎች የሚፈበረኩ የፈጠራ ውንጀላዎችን አቀነባብረው እስኪያቀርቡ ድረስ የተንዛዙ እና አሰልቺ የሆኑ ማያልቅ ቀጠሮዎችን በመስጠት እና የይስሙላውን ፍርድ ቤት የፍርድ ሂደት ከሚገባው በላይ በማዘግየት በንጹሀን ዜጎች ላይ የቁማር ጨዋታ በመጫወት ላይ ይገኛሉ፡፡ በዚህም ምክንያት ነው አነዚህን ፍርድ ቤቶችን “የይስሙላ የዝንጀሮ ፍርድ ቤቶች እያልኩ የምጠራቸው፡፡” እውነተኛው የዞን ዘጠኝ ጦማሪያን ወንጀል ሀሳብን በነጻ በመግለጽ የሚያምኑበትን ነገር በነጻ ማራመዳቸው እና እነርሱ የተሻለች ኢትዮጵያ በማለት ስለሚጠሯት ኢትዮጵያ ህልም ማለማቸው ነው፡፡ የዞን ዘጠኝ ጦማሪያንን ጉዳይ የሚመለከተው በቅርቡ ቀጠሮ ተይዞለት የነበረው የዳኝነት ችሎት ለህዝቡ እና ጉዳዩን በቅርበት ለሚከታተሉት የዲፕሎማቲክ ማህበረሰብ አባላት ዝግ ነበር፡፡
እስክንድር ነጋን፣ ርዕዮት ዓለሙን፣ ውብሸት ታዬን፣ የዞን ዘጠኝ ጦማሪያንን… የሚፈሯቸው ለምንድን ነው?
ናፖሊዮን ቦና ፓርት የተባሉት የፈረንሳይ አምባገነን መሪ በዚያች አገር የነጻው ፕሬስ ላይ ጦርነት ባወጁበት ወቅት “ከአንድ ባታሊዮን ጦር ይልቅ አራት ተቃዋሚ ጋዜጦች የበለጠ ይፈራሉ“ የሚለውን እውነታ የበለጠ ግልጽ አድርጎታል፡፡ ላለፉት 23 ዓመታት በኢትዮጵያ ጫንቃ ላይ እንደ መዥገር በስልጣን ላይ ተጣብቆ ለሚገኘው ገዥ አካል ኤኬ – 47 ከታጠቀ አንድ ባታሊዮን ጦር ይልቅ ብዕር እና የኮምፒውተር ኪይ ቦርድ የያዙ ጥቂት ነጻ ጋዜጠኞች እና ጦማሪያን የበለጠ ያስፈሩታል፣ በፍርሀት ቆፈን ውስጥ እንዲወሸቅ ያደርጉታል፣ ያርዱታል፣ ያስደነብሩታል፣ የሚይዝ የሚጨብጠውን ያሳጡታል፣ የቀን ቅዠት ይፈጥሩበታል፣ በላብ እንዲጠመቅም ያደርጉታል፡፡ በታሪክ መነጽር ሲታይ እና ሲገመገም ሁሉም አምባገነኖች እና ጨቋኞች የነጻውን ፕሬስ የእውቀት እና የክህሎት ኃይል አጥብቀው ይፈሩታል፡፡ በኢትዮጵያ በስልጣን ላይ ተንፈራጥጠው የሚገኙት አምባገነኖች ዘመናዊ የጦር መሳሪያ እስከ አፍንጫው ከታቀው እና በልዩ ልዩ የጦር ክፍሎች ተዋቅሮ በጠላት ላይ ቅጽበታዊ ድልን የመቀዳጀት አቅም ካለው እና የጠላትን ኃይል በማያንሰራራ መልኩ ከሚያደባይ የጦር ኃይል ይልቅ የነጻውን ፕሬስ የዕውቀት እና የክህሎት ኃይል አጥብቀው ይፈራሉ፡፡
ጠቅላላ የብዙሀን መገናኛዎችን እና ነጻውን ፕሬስ መቆጣጠር የገዥዎች እኩይ ምግባር ነው፡፡ የመረጃ ፍሰቶችን በመቆጣጠር በኃይል የሚገዙትን ህዝብ ልብ እና አእምሮ የተቆጣጠሩ እንደሚመስላቸው እምነት አላቸው፡፡ የብዙሀን መገናኛ ዘዴዎችን በመቆጣጠር እንደ በቀቀን እየደጋገሙ ከሚቀፈቅፉት ነጭ ውሸታቸው እውነትን የሚፈበርኩ ይመስላቸዋል፡፡ ነጻውን ፕሬስ አፈር ድሜ በማብላት ሁሉንም ህዝብ ሁልጊዜ ማሞኘት የሚችሉ ይመስላቸዋል፡፡ ሆኖም ግን “እውነት ለዘላለም ተቀብራ እንደማትቀር እና ግፈኞችም በጉልበት ነጥቀው በያዙት የስልጣን ዙፋን ወንበር ላይ ለዘላለም ተጣብቀው እንደማይቆዩበት ድንጋይ በሆነው ልባቸው ያውቁታል፡፡“ ሁልጊዜም ስልጣናቸውን የሚያጡ እየመሰላቸው እለት በእለት የውሸት ድሪቷቸውን እየደረቱ ኑሮ አድርገው ይዘውታል፡፡
በአሁኑ ጊዜ በኢትዮጵያ በስልጣን ወንበር ላይ ተጣብቆ የሚገኘው አረመኔ አምባገነን ገዥ ከብዙ ዓመታት በፊት ናፖሊዮን ተጋፍጦት የነበረውን ዓይነት ሁኔታ ተጋፍጦ ይገኛል፡፡ “ጋዜጠኛ የህዝቡን እሮሮ የሚያሰማ፣ ስህተትን አራሚ፣ ምክርን የሚለግስ፣ የሉዓላዊነት ወኪል እና የአገሮች መምህር ነው፡፡“ ጋዜጠኛ “አገርን የሚያስተምር” ነው፣ መረጃን ለህዝብ የሚሰጥ ነው፣ ህዝቡን በእውቀት የማነጽ እና የማስተማር ኃላፊነት አለው፡፡ እንግዲህ እነዚህ እውነታዎች ነበሩ ናፖሊዮን ነጻውን ፕሬስ እንዲፈሩት ያስገደዳቸው፡፡ የነጻው ፕሬስ ኃይል የናፖሊዮንን አምባገነናዊ አገዛዝ ትርጉም ባለው መልኩ እንደሚያጋልጠው እና በህዝቡ ዘንድ ተጠያቂ እንደሚያደርገው ናፖሊዮን ይገነዘቡ ነበር፡፡ ናፖሊዮን የፈረንሳይን ህዝብ ለማስፈራራት በማሰብ መጠነ ሰፊ የሆነውን የስለላ መረባቸውን በመዘርጋት ሲያካሂዱት የነበረውን ስለላ ሲያጋልጡ የነበሩትን ጋዜጠኞች ለማስፈራራት፣ በእስር ቤት ለማጎር፣ በስራዎቻቸው ላይ ቁጥጥር ለማድረግ እና አንደበታቸውን ለመሸበብ ጊዜ አላባከኑም፡፡ ነጻው ፕሬስ የናፖሊዮን ወታደራዊ እቅድ መክሸፉን አጋልጧል፡፡ ምንም ዓይነት የጦር መሳሪያ ባልታጠቁ ሰላማዊ ዜጎች ላይ ማንንም ሳይለይ በጅምላ በዋና ዋና መንገዶች ላይ የተካሄዱትን ጭፍጨፋዎች እና የእርሳቸው የፖለቲካ ተቀናቃኝ በሆኑት ቡድኖች እና ግለሰቦች ላይ የተካሄደውን እስራት፣ ማሰቃየት እና ግድያ አውግዟል፡፡ በኢትዮጵያ እንደ መዥገር በስልጣን ወንበር ላይ ተጣብቀው የሚገኙት አምባገነኖች በናፖሊዮን ቅዠት በመውደቅ በተመሳሳይ መልኩ ወጣት ጦማሪያንን እና የነጻው ፕሬስ አባላትን ያስራሉ፣ ያሰቃያሉ፡፡ እውነታውን በመፍራት እንቅልፋቸውን አጥተው በነጭ ላብ ተዘፍቀው ያድራሉ!
የኢትዮጵያ ጦማሪያን እና ጋዜጠኞች ልዩ የኢትዮጵያ ጀግናዎች እና ጀግኒቶች ናቸው፡፡ የእውነት ተናጋሪ ተዋጊዎች ናቸው፡፡ አረመኔ አምባገነኖችን በብዕሮቻቸው እና በኮምፒውተር ኪቦርዶቻቸው ይዋጋሉ፡፡ የእነዚህ ወጣቶች ጥይቶች እውነት፣ ቃላት፣ ሀሳቦች፣ እውነታዎች እና እምነቶች ብቻ ናቸው፡፡ የተንሰራፉትን ውሸቶች በእውነት ጎራዴ ይከትፏቸዋል፡፡ መጥፎ እና መሰሪ ሀሳቦችን በጥሩ ሀሳቦች ያሳድዷቸዋል፣ እናም ያረጁ እና ያፈጁ፣ እንዲሁም የጃጁ፣ እና የበከቱ አሮጌ አስተሳሰቦችን በአዲስ እና ተራማጅ በሆኑ አስተሳሰቦች ለመተካት የማስተማር ጥረታቸውን ቀጥለዋል፡፡ የህዝቦችን ተስፋቢስነት በመዋጋት በተስፋ ቃላት ያለመልማሉ፡፡ ፍርሀት በጀግንነት እና በደፋርነት ድል እንደሚመታ ለህዝቡ ያስተምራሉ፡፡ ድንቁርናን እና ኃይለኛ ደንቆሮዎችን በእውቀት እና በምክንያታዊነት ይዋጋሉ፡፡ በእብሪት እና ትእቢት ለተወጠሩት የገዥው አካል አባላት በሰለጠነ መልኩ ለማስተማር እና ለማግባባት ጥረት ያደርጋሉ፡፡ ትዕግስትየለሽነትን በታጋሽነት፣ ጭቆናን ከመሸከም በጽናት ታግሎ በማስወገድ እና በጥርጣሬ ከመሸነፍ በሙሉ እምነት አሳድሮ ድል በመምታት ለመቀየር ይፈልጋሉ፡፡ የህዝቡን ልብ እና አእምሮ ለመያዝ በሚደረገው የትግል አውድ እንደ ወሮበላው የገዥ አካል ስብስብ በተራ የውሸት ፕሮፓጋንዳ እና በኃይል በጉልበት ጨፍልቆ ለመያዝ ሳይሆን እውነታውን እና እውነቱን ብቻ ለወገኖቻቸው በማሳየት በብዕሮቻቸው እና በኮምፒውተር ኪቦርዶቻቸው ይታገላሉ፡፡
ክህደት፣ ውሸት እና ፍርሀት በተንሰራፋባት ምድር ላይ መኖር፣
በኢትዮጵያ ያለው ገዥ አካል እውነት ውሸት በሆነባት፣ እውነት በእየለቱ በምትደመሰስባት እና ሸፍጠኛ አታላዮች በፍርሀት ተዘፍቀው የሚኖሩባት የእራሳቸውን ምድር ፈጥረዋል፡፡ ገዥው አካል እንዲህ የሚለውን የካርቴሲያንን መርህ አዛብቷል፣ “በኛ አስተሳሰብ ብቻ ነገሮች ሁሉ ህልውና ይኖራቸዋል ወይም ደግሞ ህልውና አልባ ይሆናሉ“፡፡ መለስ ዜናዊ የክህደት አለቃ ነበር፡፡ ሁልጊዜ በሱ የማጎሪያ አስር ቤቶች ውስጥ ምንም ዓይነት የፖለቲካ እስረኛ የለም በማለት ሽምጥጥ በማድረግ ይክድ ነበር፣ እንዲህ በማለት፣ “በአሁኑ ጊዜ በኢትዮጵያ ምንም ዓይነት የፖለቲካ እስረኛ የለም፡፡ በእስር ቤት ያሉት አመጸኞች እና አሸባሪዎች ናቸው፡፡ እናም በእስር ቤቶቻችን የፖለቲከ እስረኞች አሉ ብሎ ለመግለጽ አስቸጋሪ ነው የሚሆነው ምክንያቱም የፖለቲካ እስረኞች አይደሉምና፡፡ በሱ የንጉስነት ወቅት ምንም ዓይነት ረሀብ እና ቸነፈር እንዳልነበረ ሙልጭ አድርገው በመካድ እንዲህ ብሎ ነበር፣ በጣም ጥቂት የሆኑ በጣት የሚቆጠሩ በምግብ እጥረት ጉዳት የደረሰባቸው በደቡብ የሀገሪቱ ክፍል በሚገኙ የወረዳ ኪስ ቦታዎች እና በሶማሊ ክልል አካባቢ የአስቸኳይ ጊዜ ሁኔታ ብቻ ነው የነበሩት በማለት ዓይኔን ላፈር ብለዋል፡፡ በአገሪቱ ላይ ተንሰራፍቶ የሚገኘውን ያፈጠጠ እና ያገጠጠ እውነታ ሙልጭ አድርገው በመካድ በኢትዮጵያ ውስጥ ምንም ዓይነት የሰብአዊ መብት ጥሰት የለም“ ብለዋል፡፡ ይህንን ለማስረገጥ በማሰብ እንዲህ ብለው ነበር፣ “ኦጋዴን አካባቢ መንደሮችን አቃጥለዋል እየተባለ ውንጀላ ቀርቦብናል፡፡ ሆኖም ግን በእርግጠኝነት ልነግራችሁ እፈልጋለሁ፤ ኑስ አንድ መንደር እንኳ አልተቃጠለም፡፡ እናም እኔ እስከማውቀው ድረስ አንዲት ጎጆ አልተቃጠለችም፡፡ እኛ እየተከሰስን ያለነው በሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎችን ቀድሞ ከነበሩባቸው መንደሮች በማንቀሳቀስ ወደ መጠለያ ካምፖች በማስገባታችን ነው፡፡ በዚህ ጉዳይ ላይ ቅንጣት መረጃ ሊቀርብ አይችልም“ ብሎ ነበር፡፡ የአሜሪካ የሳይንስ እድገት ማህበር/American Association for the Advancement of Science በኦጋዴን መንደሮች ላይ የተካሄደውን የጅምላ የመንደሮች ማቃጠል ወንጀል በሳቴላይት ምስሎች የተረጋገጠው እውነታ ለመለስ ምድር ምናባዊ ህይወት ምንም አይደለም፡፡ አደናጋሪ የፕሬስ ህግ አዋጅ በማውጣት በደርዘን የሚቆጠሩ ምርጥ የኢትዮጵያ ነጻ ጋዜጠኞች እና ጦማሪያን ለእስር እና ግዞት ሲዳረጉ የሌባ አይነ ደረቅ እንዲሉ በሀሰት በነተበው አንደበታቸው መልሰው “ከዓለም የተሻለ ምርጥ የፕሬስ ህግ” በማለት ያደናግራሉ፡፡ እ.ኤ.አ በ2010 የተካሄደውን አገር አቀፋዊ “ምርጫ” ተከትሎ አቶ መለስ ፓርቲያቸው ምርጫውን በ99.6 በመቶ ያሸነፈ መሆኑን በኩራት ተናግረው ነበር፣ ምክንያቱም ህዝቡ ፓርቲያቸውን የሚወደው ስለሆነ ነው በማለት አፋቸውን ሞልተው ተናግረው ነበር፡፡ አቶ መለስ የኦርዌላን/Orwellian የእንስሳት ትረካ ዓይነት እውነታን የሚያራምዱ ሰው ነበሩ፡፡ ውሸታቸውን ለመንዛት ሲፈልጉ “የፖለቲካ ቋንቋን በመጠቀም የለየለትን ነጭ ውሸት እውነት እንዲመስል አድርገው በማቅረብ፣ ግድያ መፈጸም ወንጀል እና የስነምግባር ዝቅጠት መሆኑ ቀርቶ የሚያስከብር እንደሆነ አድርገው በማቅረብ ነጩን ውሸት የእውነት ቅርጽን እንዲላበስ አድርገው በማስመሰል የማቅረብ የባዶ ብልጣብለጥነት አካሄድ መንገድን ይጠቀሙ ነበር፡፡”
በአሁኑ ጊዜ በኢትዮጵያ በስልጣን ወንበር ላይ ተቀምጠው አገሪቱን እያተራመሱ በመግዛት ላይ ስለሚገኙት ስብስቦች አንድ የማይካድ ሀቅ አለ፡፡ ሁሉም በፍርሀት ቆፈን ውስጥ ተወሽቀው ነው እየኖሩ ያሉት፡፡ ያገጠጠውን እና ያፈጠጠውን እውነታ አየፈሩ ነው በመኖር ላይ ያሉት፡፡ የነጻው ፕሬስ ኃይል እውነታውን የሚያጋልጥ ስለሆነ የነጻውን ፕሬስ ኃይል በመፍራት ነው እየኖሩ ያሉት፡፡ በአንድ ወቅት የእነርሱ የአመለካከት ፍልስፍና አለቃ ቁንጮ የነበሩት ቪላድሚር ሌኒን “የመናገር ነጻነት እና የፕሬስ ነጻነት ለምንድን ነው የሚፈቀደው? ለምንድን ነው መንግስት ትክክል ነው ብሎ ያመነበትን ነገር ሲሰራ ትችት እንዲቀርብበት የሚፈቅደው? ተቃዋሚዎችን የጠላት መሳሪያ እንዲሆኑ መንግስት መፍቀድ የለበትም፣ ሀሳቦች ከጠብመንጃ የበለጠ የገዳይነት ባህሪ አላቸው፡፡ ለምንድን ነው ማንም ሰው የማተሚያ ቤት እንዲገዛ እና የሚቀርቡ ሀሳቦችን አትሞ በማሰራጨት በስልጣን ላያ ያለውን መንግስት በተቀነባበረ ስሌት ለመተቸት እና ለማሳፈር እንዲችል የሚፈቀደው?“ እንዳሉት ማለት ነው፡፡
እውነታውን በሚገባ ያውቁታል ምክንያቱም እውነታው ህዝቡን ነጻ እንዲሆን ያግዘዋል፡፡ ነጻነትን ይፈራሉ ምክንያቱም አዲስ ሀሳቦችን ይፈራሉ፡፡ አዲስ ሀሳቦችን ይፈራሉ ምክንያቱም ለውጥን ይፈራሉ፡፡ ነጻ የሆነ ህዝብ የእውነትን ጥሩር ታጥቆ የሀሳብ ነጻነትን ተጎናጽፎ በእራሱ ፈቃድ የእራሱን የመንግስት ዓይነት ለመመስረት ሙሉ ነጻነት አለው፡፡
በኢትዮጵያ ላይ ስላለው ገዥ አካል ያለው እውነታ ምንድን ነው? እውነታው በሰው ልጆች ላይ ግፍን የፈጸሙ ወንጀለኞች ናቸው፡፡ ምንም ዓይነት ህጋዊነት የላቸውም፡፡ በጠብመንጃ ኃይል በጉልበት በስልጣን ወንበር ላይ እንደ መዥገር ተጣብቀው የሚገኙ አምባገነኖች ናቸው፣ ምርጫዎችን በመስረቅ እና በመዝረፍ ተመርጠናል እያሉ በማታለል ተክነዋል፣ በጥልቅ የሙስና ማእበል ውስጥ ተዘፍቀው የአገሪቱን ሀብት በማውደም ላይ ይገኛሉ፣ ስልጣናቸውን ከህግ አግባብ ውጭ በህገወጥ መንገድ በመጠቀም ላይ ይገኛሉ፣ የህግ የበላይነትን በመደፍጠጥ በጫካው ህግ የሚገዙ ህገወጦች ሆነዋል፣ እውነታው ሲታይ በአጠቃላይ በሸፍጥ የታወሩ የጫካውን አስተዳደር ወደ መንግስታዊ አስተዳደርነት አዙረው ህዝብን በማተራመስ ላይ የሚገኙ የስግብግብ ወሮበላ ቡድን ስብሰቦች ናቸው፡፡ እውነታው በአጠቃላይ ሲታይ የአፍሪካን የጨካኝ ዘራፊነት ስርዓት በሀገራችን ላይ የሚተገብሩ ወሮበላ ዘራፊዎች ናቸው፡፡
እነዚህ ወሮበላ ዘራፊዎች ነጻ ጋዜጠኞችን እና ጦማሪያንን ይፈራሉ ምክንያቱም እነዚህ ነጻ ጋዜጠኞች እና ጦማሪዎች አምባገነኖቹ የሚሰሯቸውን ወንጀሎች እና ሙስናዎች፣ የመከኑ እና የወደቁ ፖሊሲዎቻቸውን፣ የአቅም ድሁርነታቸውን እና ድንቁርናቸውን በማጋለጥ እውነታውን ያወጡባቸዋል፡፡ እነዚህ ጭራቃዊ ፍጡሮች በጫማቸው ስር እረግጠው የያዟቸው የግፍ ሰለባዎች ነጻ ቅዱስነት እና የያዙት ጸበል ስለሚያቃዣቸው ነጻ ጋዜጠኞችን እና ጦማሪያንን አጥብቀው ይፈራሉ፡፡ በያዙት ሁሉ ኃይል በመጠቀም እውነቱ ወጥቶ ለህዝብ እንዳይደርስ እና እንዳይታወቅባቸው ማንኛውንም ነገር ከማድረግ ወደ ኋላ አይሉም፡ የሳቴላይት ስርጭቶችን ሳይቀር አፍነዋል፣ የኢንተርኔት ግንኙነቶችን አቋርጠዋል፣ ጋዜጦችን በመዝጋት ጋዜጠኞችን በእየእስር ቤቶች አጉረዋል፡፡ ባለፈው ሳምንት የአረብሳት ለዓለም አቀፉ የግንኙነት ህብረት/International Communication Union እና ለአረብ ሊግ/Arab League ኢትዮጵያ ስርጭቱን ያፈነች መሆኗን እና “ወንጀለኛውን ለመቅጣት አስፈላጊው እርምጃ እንዲወሰድ” እና በዚህ ህገወጥ ድርጊት ምክንያት ለደረሰው ጉዳት ወይም በዚህ ህገወጥ የአፈና ተግባር ምክንያት ወደፊት ለሚደርስ ማንኛውም አደጋ ተገቢውን ካሳ እንድትከፍል እንዲደረግ ተማጽዕኖውን አቅርቧል፡፡ በአሁኑ ጊዜ ገዥው አካል በገበያ ላይ የቀሩትን እና በገዥው አካል ላይ ጠንካራ ጥችት የሚያቀርቡትን ጥቂት ጋዜጦች በየመንገዶች እያዞሩ የሚሸጡትን ጋዜጣ አዟሪዎችን እያሳደደ፣ እያስፈራራ እና በቁጥጥር ስር እያዋለ ይገኛል፡፡
እውነታው በኢትዮጵያ ሀሳብን በነጻ ከመግለጽ ጉዳይ ጋር በተያያዘ መልኩ እየተካሄደ ላለው ጭቆና እና አፈና የቻይናዎች ስውር እጆች ያሉበት መሆኑ ነው፡፡ ቻይናዎች ለገዥው አካል የማፈኛ የቴክኖሎጂ መሳሪያዎችን ማቅረብ ብቻ አይደለም የሚያከናውኑት፡፡ ሆኖም ግን ለተንቀሳቃሽ ስልኮች እና ለኢንተርኔት አገልግሎት የመሰረተ ልማት ስራዎችም ግንባር ቀደም ተዋንያን ናቸው፡፡ የመረጃ ፍሰት ከኢትዮጵያ እንዳይወጣ እና ወደ ኢትዮጵያም እንዳይገባ ለመገደብ እና ለማቋረጥ የአንድ መስኮት ፈጣን የአግልግሎት መስጫ ኪቶችን ይዘዋል፡፡ ከዛሬ ሁለት ዓመታት ገደማ በፊት የቀድሞዋ የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር የነበሩት ሄላሪ ክሊንተን ዛምቢያን በመጎብኘት ላይ ሳሉ የቻይናውያን በአፍሪካ አህጉር ላይ ያላቸውን ሚና በማስመልከት እንዲህ ብለው ነበር፣ “በቅኝ ግዛት ዘመን ጊዜ መምጣት እና ለመሪዎቹ ገንዘብ በመስጠት የተፈጥሮ ሀብቶችን ከአፍሪካ መውሰድ ቀላል ነበር፣ በምትለቅቅበት ጊዜ እዚህ ላለው ህዝብ ምንም ነገር ትተህ አትወጣም፣ በአሁኑ ጊዜ አዲስ ቅኝ ተገዥነት በአፍሪካ ማየት አንፈልግም“ ብለው ነበር፡፡ እውነታው ግን ቻይናውያን በኢትዮጵያ መቆየታቸው እና የእጅ አዙር ቅኝ ግዛት መያዛቸው ብቻ ሳይሆን ለገዥው አካል የቴክኒክ እገዛ በመስጠት፣ የኦዲዮ እና ቪዲዮ መሳሪያዎችን በማቅረብ የመረጃ ምርመራ በማድረግ እና በኤሌክትሮኒክ መገናኛ ብዙሀን ላይ አፈናዎችን በማካሄድ ነጻ አሰተሳሰብን በመጨቆን በዋናነት ተጠያቂዎች ናቸው፡፡
ነጻነትን ይፈራሉ፡፡ ነጻነት ምንድን ነው? የሁሉም የሰው ልጆች ነጻነቶች ባህሪያት ከፍርህት የሚገኙ ነጻነቶች ናቸው፡፡ በተግባራዊ ሁኔታ ሲታይ አንድ ሰው ያሰበውን ለመናገር መፍራት ወይም ደግሞ አንድ ሰው ደስ ያለውን መጻፍ መፍራት ወይም በአንድ ሀሳብ ማለትም ሀይማኖት ወይም ፍልስፍና ላይ ማመን እና አለማመንን መፍራት ወይም ደግሞ አንድ ሰው ከመረጠው ሰው ጋር አብሮ መምጣት መፍራት ማለት አይደለም፡፡ ዋናው እና የመጨረሻው የሰው ልጅ ሁሉ ሊያደርገው የሚገባው ህዝቡ እራሱ ስልጣን የሰጣቸው በስልጣን ወንበር ላይ ያሉት ሰዎች ናቸው በህብረተሰቡ የኑሮ ሂደት ላይ መፍራት እና ህዝቡን ማክበር ያለባቸው፡፡
ሀሳብን ይፈራሉ፡፡ “ሀሳቦች ከጠብመንጃ የበለጠ ገዳዮች ናቸው“ በማለት ሌኒን አስጠንቅቀዋል፡፡ ሀሳቦች ሳይንስን፣ ፖለቲካን እና ማናቸውንም የሰው ልጅ የሚያደርጋቸውን እንቅስቃሴዎች ሁሉ የመለወጥ ኃይል አላቸው፡፡ ከምንም በላይ ዓለም ጠፍጣፋ አይደለችም፡፡ ሆኖም ግን በኢትዮጵያ ያሉ ገዥዎች የአዲስ ጠፍጣፋ መሬት ባለቤቶች ናቸው፡፡ እንደ ጥንቱ ንጉሶች፣ ዛሮች፣ እና ማሃራጃሆዎች ሆነው ከህዝቡ ፈቃድ ውጭ ( በተሰረቀ ስምምነት) መሰረት መግዛት ይፈልጋሉ፡፡ ጥቂት ሞራላዊ ጠቀሜታ ያላቸው ሀሳቦች ሲኖሯቸው ነገሮችን በቀላሉ ለመገንዘብ እና አዳዲስ ሀሳቦችንም ለማድነቅ እና ተቀብሎ ወደ ተግባር ለማዋል የምሁርነት አቅሙ የሌላቸው የመንፈስ የአስተሳሰብ ድሁሮች ናቸው፡፡ ሆኖም ግን የጎሳ ክፍፍልን ለማራመድ፣ ስግብግብነት እና ጥላቻን ለማምጣት፣ የጥላቻ ከባቢን የመፍጠር፣ ግጭትን የመጫር፣ ሙስናን ለማስፋፋት እና ለማጠናከር፣ ህብረትን በመናድና የጥላቻ መንፈስን በመዝራት እንዲሁም በሰዎች መካከል ጥርጣሬ እና አለመተማመን እንዲነግስ በማድረግ ጭንቅላቶቻቸው ዋና የዲያብሎሳዊነት ቤተሙከራዎች ናቸው፡፡ ህዝብን ሊያስተባብሩ እና ሊያፋቅሩ የሚችሉ ሀሳቦችን ለማመንጨት፣ በጎሳዎች መካከል ፍቅርን የማስፈን፣ ብሄራዊ አንድነትን የማምጣት፣ የጋራ መግባባትን የመፍጠር፣ የጓዳዊነት መንፈስ የማጠናከር እና እምነትን የማራመድ አቅመቢሶች ናቸው፡፡
አዳዲስ ሀሳቦችን የሚፈሩ በኢትዮጵያ በስልጣን ወንበር ላይ ተቆናጥጠው የሚገኙ አምባገነኖች የአዲስ ሀሳብ አመንጭ እና ባለራዕይ መስለው ለመታየት ይሞክራሉ፡፡ ህዝቡ እና ዓለም ወደፊት ጥሩ ነገር የሚያስቡ መልካም ነገር አላሚዎችና ፈጣሪዎች እንደሆኑ አድርጎ እንዲመለከታቸው እና እምነት እንዲኖረው ይፈልጋሉ፡፡ ሆኖም ግን በህልም የቅዠት ፍርሀት ተዘፍቆ ያለ ማንም ሰው መልካም አላሚ ሊሆን አይችልም፡፡ ባለራዕይ መሪዎች ለሚያደርጓቸው ማለትም ታማኝነት፣ ኃላፊነትነትን የመሸከም ብቃት፣ ሌሎችን አነቃቅቶ እና አሳምኖ በስራ የማሳተፍ ችሎታ፣ ያለፉትን ስህተቶች በግዴለሽነት እንዳሉ ከመድገም ይልቅ ከስህተት እና ከውድቀት መማርን፣ ስህተት በሚሰሩበት ጊዜ ይቅርታ አድርጉልኝ ብሎ መጠየቅን፣ ግልጽነት፣ ትክክለኛውን ነገር ለመስራት ፍትሀዊነት እና በፍቅር ላይ የተመሰረተ ሆኖ ከመገኘት ተግባራት ጋር ሁሉ አይተዋወቁም፡፡ መጥፎ እና ዕኩይ ተግባራትን ለማድረግ ፍቅር ያላቸው መሰሪ መሪዎች ናቸው፡፡ ኪሶቻቸውን የሚወጥሩትን የተዘረፉ በርካታ ገንዘቦችን ዓይኖቻቸው በቀላሉ ማየት ይችላሉ፡፡ ሆኖም ግን አሁን እየፈጸሟቸው ያሏቸው በርካታ ወንጀሎች በዘለቂነት ለወደፊት ሊያስከትሉት የሚችሏቸውን እንደምታዎች ለማየት የታወሩ ናቸው፡፡ ጠንካራን ሀሳብ ጊዜው እየመጣ ያለውን ሀሳብ የሚያቆመው ምድራዊ ኃይል የለም፡፡ የኢትዮጵያ ህዝብ ለነጻነት የሚያደርገውን ተጋድሎ የሚያቆመው ኃይል የለም፡፡ አንዴ ከተጀመረ በመንገዱ ላይ ያለውን ጋሬጣ ሁሉ እየጠራረገ ወደፊት ይገሰግሳል፡፡
ለውጥን ይፈራሉ፡፡ ለውጥ ምንድን ነው? ለውጥ በሁሉም ነገር የሚከሰተውን የዕድገት እና የመበስበስ ዓለም አቀፋዊ ዘላለማዊ የለውጥ ህግ የሚገዛ ሂደት ነው፡፡ በኢትዮጵያ በስልጣን ላይ ያለው ገዥ አካል ለውጥን አጥብቆ ይፈራል ምክንያቱም በህበረተሰቡ ላይ ያላቸውን የኢኮኖሚ እና የፖሎቲካ የበላይነት ቦታ ስለሚያሳጣቸው ነው፡፡ ለውጥን ሊያመጡ የሚችሉ ነገሮችን በሰላማዊ መንገድ ለውጥ ለማምጣት የሚንቀሳቀሱትን ማናቸውንም ሙከራ ሁሉ ይደመስሳሉ፡፡ ከዚህ አንጻር “በሰላማዊ መንገድ የለውጥ አብዮት እንዳይመጣ የሚከለክሉ ሁሉ የአመጽ ለውጥ በኃይል እንዲመጣ ይገደዳሉ“ የሚለውን ሀቅ ለመገንዘብ የተሳናቸው ይመስላል፡፡
በፖለቲካ ህጋዊነት ማጣት እና በመንግስት አቅም ማጣት ምክንያት ኢትዮጵያ በአሁኑ ጊዜ በፖለቲካ መበስበስ የመጨረሻ ጠርዝ ላይ ያለችበት ሁኔታ ነው የሚታየው፡፡ የጨነገፈ መንግስት ሆናለች፡፡ ባለፉት ሩብ ምዕተ ዓመታት የጎሳ ክፍፍል ፖሊሲ (የጎሳ ፌዴራሊዝም) “ልማታዊ መንግስት” ባለሁለት አሀዝ የኢኮኖሚ እድገት አስመዘገብን በማለት የሚራገበው እርባናየለሽ ፕሮፓጋንዳ ቢኖርም እንኳ ኢትዮጵያን በሁለት አማራጮች ላይ ጥሏታል፡፡ የእነርሱ ነጭ ውሸት ብቻ ነው በባሁለት እና በባለሶስት አሀዝ እድገት ያስመዘገበው፡፡
ኢትዮጵያ በአሁኑ ጊዜ በመስቀለኛ መንገድ ላይ ቆማለች፡፡ እንደተባበረች ሀገር አንድ ሆና ወደፊት ተገሰግሳለች ወይም ደግሞ ወደተለያዩ ትናንሽ የተበጣጠሱ ክልሎች ትገነጣጠላለች፡፡ የአፓርታይድ ዓይነት ባንቱስታንስ በኢትዮጵያ ክልል እየተባለ በዘር እና በቋንቋ የተቀየደ የአገዛዝ ስርዓት ነው፡፡ ኢትዮጵያ የተበጣጠሱ ግዛቶች ስብስብ የምትሆን ከሆነ የመጀመሪያው ቸግር ቀማሽ የሚሆኑት አሁን በስልጣን ላይ ተጣብቆ የሚገኘው ገዥው አካል፣ የእነርሱ ጋሻጃግሬዎች እና ደጋፊዎች ናቸው፡፡ በፖቲካ ስልጣን ማጣት ብቻ የሚቆም ሳይሆን ቢያንስ እስከ አሁን ድረስ በአገር ውስጥ የሚደረግ ለውጥ ዘግይቶ እንደደረሰ ባቡር ይቆጠራል፡፡ በምስራቅ አውሮፓ በመካከለኛው ምስራቅ ሲነፍስ የነበረው የለውጥ ነፋስ ያለምንም ጥርጥር በኢትዮጵያም መንፈሱ የማይቀር ጉዳይ ነው፡፡ ሊነሳ የሚችለው ብቸኛ ጥያቄ ግን እነዚህ ነፋሶች ተስማሚ እና በሰላም የሚያልፉ ወይስ ደግሞ ሁሉንም ነገር እየገነደሱ እና እየቦደሱ የሚጥሉ ኃይለኛ የሁሪኬን/hurricane-force ሞገዶች ይሆናሉ የሚለው ነው፡፡
እውነት ነጻ ያወጣሀል ነጻ አስከሆንክ ድረስ ሆኖም ግን ነጻ ያልሆኑት ይሰቃያሉ፣
“እውነት ነፃ ታወጣሀለች” ተብሎ ተጽፏል፡፡ ነጻነት እና ፍርሀት ለእየራሳቸው ተነጥለው የሚኖሩ ናቸው፡፡ የነጻው ፕሬስ እና ጦማሪያን ብቸኛው ተግባራቸው እንዳዩት እውነታውን ወዲያውኑ መናገር ነው፡፡ ስለ እውነታው ያላቸውን ሀሳብ የለምንም ፍርሀት የመግለጽ ነጻነት አላቸው፡፡ ሆኖም ግን ህዝቡ እውነታውን ቀድሞም ቢሆን ያውቀዋል፡፡ ኢትዮጵያ በባለሁለት አሀዝ የኢኮኖሚ እድገት አስመዝግባለች የሚለው ነጭ ውሸት ቢሆንም ህዝቦች እውነታውን ያውቁታል፡፡ የሚበላ በቂ ምግብ እንደሌለ ያውቃሉ፣ እናም ሚሊዮኖች በየቀኑ እየተራቡ እንዳሉ ያውቃሉ፡፡ እንዲሁም በቂ የውኃ አገልግሎት ወይም የኤሌክትሪክ ኃይል እንደሌለ ያውቃሉ፡፡ አናሳ የህክምና አገልግሎት ነው እየተሰጠ ያለው፣ ወጣቶች ጥራት ያለው ትምህርት አያገኙም እናም ስራ አጦች ናቸው፡፡ ገዥው አካል በሙስና ማጥ ውስጥ የተዘፈቀ እና የበከተ ነው፣ እንዲሁም በሰው ልጆች ላይ ወንጀልን ይፈጽማል፡፡ ህዝቦች በግልጽ የአየር ድባብ ውስጥ እስረኛ ሆነው እንደሚኖሩ ያውቃሉ፡፡
የነጻ ጋዜጠኞች እና የጦማሪዎች ወንጀል የሚያውቁትን ነገር ለማያውቁት ወገኖቻቸው መግለጻቸው ብቻ ነው፡፡ የእነርሱ ወንጀል የማዕድን ሙስና እና ስልጣንን ከህግ አግባብ ውጭ መጠቀምን፣ እንዲሁም በሰው ልጆች ላይ የሚፈጸሙትን ወንጀሎች እየቆፈሩ በማውጣት ማስረጃ በማቅረባቸው ነው፡፡ ለዚህም በስልጣን ላያ ያለው ገዥ አካል እየፈራቸው ያለው፡፡ ገዥው አካል እውነታው ሳይታወቅ ተቀብሮ እንዲቀር እና እንዲረሳ ይፈልጋል፡፡ ገዥው አካል እውነታው እንዳይታወቅ በመደበቅ፣ እውነት ተናጋሪዎችንም ጸጥ በማስደረግ እና በየእስር ቤቶች በማጎር ለዘላለም ጸጥ በማድረግ ትንፍሽ እንዳይሉ በማድረግ እውነትን የመግደል እምነት አለው፡፡ ጆርጅ ኦርዌል እንደጠቆሙት፣ ”የማጨበርበር እና የሀሰት ሸፍጥ በተንሰራፋበት ጊዜ እውነትን መናገር አብዮተኛነት ድርጊት ነው“ ብለው ነበር፡፡ በአሁኑ ጊዜ የኢትዮጵያ ጦማሪያን የኢትዮጵያ የማይበገሩ አብዮተኞች ናቸው፡፡
ፍርሀትን በብዙሀን መገናኛ እንደ መሳሪያ መጠቀም፣
በስልጣን ላይ ያለው ገዥ አካል ከብዙ ጊዜ ጀምሮ ዋና ድክመትን እንደ ትልቅ መጠቀሚያ መሳሪያ አድርጎ ይጠቀምበታል፡፡ ህዝብን ግራ ለማጋባት፣ እርስ በእርስ ለመከፋፈል፣ ለማታለል፣ ጥላሸት ለመቀባት እና ሀሳብን ከዋናው ጉዳይ አቅጣጫውን ለማስቀየስ ፍርሀትን በዋና መሳሪያነት ይጠቀምበታል፡፡ ማቋረጫ የሌለው የፍርሀት ዘመቻ በህብረተሰቡ ላይ ለመንዛት ሲፈልግ፣ ጥላሸት ለመቀባት እና ለማጠልሸት ሲፈልግ በህዝብ የግብር መዋጮ የሚተዳደረውን መገናኛ ብዙሀን ለእኩይ ምግባር ሌት ቀን ይጠቀማል፡፡ ገዥውን አካል የሚቃወሙትን ቡድኖች እና ግለሰቦች ጸጥ ለማድረግ ሲፈልግ እርባናየለሽ በውሸት ላይ ተመስርተው የተቀነባበሩ ዘጋቢ ፊልሞችን በመፈብረክ “አሸባሪ” የሚል ታፔላ በመለጠፍ በአሰልችው የመገናኛ ብዙሀን እንደበቀቀን ይደጋግማቸዋል፡፡ የውሸት ሸፍጥ በታጨቀበት እና ለመስማት እና ለማየትም አስቀያሚ በሆነው “አኬልዳማ” ብሎ በሰየመው ለምንም የማይውል እርባናየለሽ ዘጋቢ ፊልም ኢትዮጵያ በዲያስፖራው ተቃዋሚ ኃይል እና በአገር ውስጥ ባሉ የእነርሱ የግብር ተመሳሳዮች አማካይነት እንዲሁም ሌሎች አሸባሪ ቡድኖች ትብብር እና ርብርብ አደገኛ የሽብር አደጋ ተደቅኖባት እንደሚገኝ አደንቋሪ ጩኸታቸውን አሰምተዋል፡፡ “አኬልዳማ” በዓለም ላይ የተደረጉትን በጣም አስፈሪ እና አስቀያሚ ምስሎችን ሁሉ ለቃቅሞ በቪዲዮ በማሳየት በቅርቡ በህይወት የተለዩት አቶ መለስ ዜናዊ ተቃዋሚዎቻቸውን ጥላሸት በመቀባትና በሶማሌ የሚንቀሳቀሰው የአልቃይዳ እና አልሻባብ ቅጥረኞች ናቸው ብለው በአሸባሪነት በመፈረጅ የጥቃት ብቀላቸውን በንጹሁነ ዜጎች ላይ በሰፊው ተግብረውታል፡፡
በሌላ “ጅሃዳዊ ሀራካት” በተባለ እርባናየለሽ ዘጋቢ ፊልም በክርስቲያን እና በሙስሊሙ ህብረተሰብ መካከል ፍርሀት እና ጥላቻን ለማስፋፋት በማሰብ ጸረ እስልምና እሳትን የመጫር ሙከራ አድርገው በህዝቡ አርቆ አስተዋይነት እና የንቃት ደረጃ ምክንያት እኩይ ምግባራቸው ሳይሳካ መክኖ ቀርቷል፡፡ ለዘመናት አብሮ እና ተከባብሮ እየኖረ ያለውን የክርስቲያን እና የሙሰሊም ማህበረሰቡን በማጋጨት የእስልምና አሸባሪዎች በድብቅ ጅሀዳዊ መንግስት ለመመስረት ዕቅድ አውጥተው ተንቀሳቅሰዋል በማለት በሁለቱ ታላላቅ ኃይማኖቶች እምነት ተከታዮች መካከል የማያባራ እልቂት እና የደም ጎርፍን ለማዝነብ የታቀደ ዲያብሎሳዊ የድርጊት ዕቅድ ነድፈው ነበር፡፡ አሁንም ህዝቡ የነቃባቸው እና ከእነርሱ እኩይ አስተሳሰብ ውጭ የመጠቀ ሀሳብ ስላለው እና ስላወቀባቸው ዕቅዳቸው አሁንም መክኖ ቀርቷል፡፡
ፍርሀት እና ጥላቻን በህዝቡ ውስጥ ለማስፋፋት እና ምናባዊ የሆነ የዘር እና የጎሳ እልቂት እንዲሁም የኃይማኖት ጽንፈኝነት እልቂት እንደሚከሰት በመስበክ ይህንንም እልቂት ለማስወገድ ብቸኛ ቅዱሶች እነርሱ እንደሆኑ አድርገው በማቅረብ እና በማደናገር ጸረ ኢትዮጵያ እና ዘረኛ አስተሳሰብ የተጠናወታቸው ጎጠኞች መሆናቸውን በአደባባይ አስመስክረዋል፡፡ አሁንም ተስፋ ባለመቁረጥ አንዱን ጎሳ በሌላው ላይ በማስነሳት ለማጋጨት ሌት ቀን በመስራት ላይ ይገኛሉ፡፡ “የጎሳ ፌዴራሊዝም/ethnic federalism” በሚል እኩይ ስልት የዘር ማጽዳት ዘመቻቸውን ቀጥለውበታል፡፡ የጎሳ ጥላቻን ለመቀስቀስ ታሪካዊ ብሶቶችን እየፈበረኩ እና ጥቃቅን ነገሮችን እያጋነኑ በህዝቡ ዘንድ አለመተማመን እና ግጭቶች እንዲነሱ አበርትተው በመስራት ላይ ይገኛሉ፡፡ ህዝቡ ግን ስለነቃባቸው በባዶነታቸው ቀልበቢስ በመሆን እንደ አበደ ውሻ ከወዲያ ወዲህ በመቅበዝበዝ ላይ ይገኛሉ፡፡ የእራሳቸውን ፍርሀት እንደ መሳሪያ በመጠቀም ህዝቡን ለማደናገር ይሞክራሉ፡፡
በኢትዮጵያ ትንታግ ጋዜጠኞች እና ጦማሪያን ላይ የተከፈተው ጦርነት በእራሷ በእውነት ላይ የተከፈተ ጦርነት ነው፣
በኢትዮጵያ በስልጣን ላይ እንደ መዥገር ተጣብቆ የሚገኘው ገዥ አካል በነጻው ፕሬስ ጋዜጠኞች እና በጦማሪያን ላይ ያወጀው ጦርነት በእውነት በእራሷ ላይ ያወጀው ጦርነት ነው፡፡ ገዥው አካል ላለፉት ሩብ ምዕተ ዓመታት በተደረጉት ጦርነነቶች እና ግጭቶች ሁሉ በድል አድራጊነት ተወጥቷል፡፡ ሆኖም ግን በአሁኑ ጊዜ ጎራዴ እና ኤኬ 47 አውቶማቲክ ጠብመንጃዎችን በታጠቁ አምባገነኖች እና ብዕሮች እና የኮምፒውተር ኪቦርዶችን በሚጠቀሙ ጋዜጠኞች እና ጦማሪያን መካከል የሚደረገው ወሳኙ ፍልሚያ ተቃርቧል፡፡ ያ ጦርነት እና ፍልሚያ በኢትዮጵያውያን/ት ልብ እና አእምሮ ውስጥ ሰርጾ ሁሉንም ዜጎች ለወሳኙ ፍልሚያ እና ለድል ጉዞ ጥርጊያ መንገዱን የሚያመቻች ይሆናል፡፡ የዚያ ጦርነት እና ፍልሚያ ውጤቱ ምንም ይሁን ምን በእርግጠኝነት የምናገረው ነገር ቢኖር ፍልሚያው የሀገሪቱን የወደፊት ዕጣ ፈንታ የሚወስን ይሆናል፡፡ በእርግጥ ያ ጦርነት በእውነት አራማጅ ወገኖች አሸናፊነት እንደተደመደመ እምነት አለኝ፡፡ ኤድዋርድ ቡልዌር ሊቶን የተባሉት ገጣሚ በትክክል እንዳስቀመጡት ጎራዴ በታጠቁት እና ብዕርን በጨበጡት ተዋጊዎች መካከል በሚደረግ የጦርነት ፍልሚያ በመጨረሻ ሁልጊዜ የወሳኙ ድል ባለቤት የሚሆኑት ብዕርን የጨበጡት ናቸው፡፡ እውነትን ጨብጠዋልና!
እውነት፣ ይህ!
ከሰዎች አገዛዝ ስር ሌላ ታላቅ ነገር አለ፣
ብዕር ከጎራዴ የበለጠ ኃይል አለው፡፡ አስተውል/ይ
ቀስት ተሸካሚዎች ይፈነድቃሉ፣ ግን ምንም የሚመጣ ነገር የለም!-
ልዩ ታምር ከጌታቸው እጀ ይቀበላሉ፣
እናም ቄሳሮችን በድን ለማድረግ ያምጻሉ
ታላቋ መሬት ትንፋሽ ያጥራታል!- ጎራዴውን ከዚህ ወዲያ ውሰዱ-
መንግስታት ከእርሱ ውጭ ሊጠበቁ ይችላሉና!
ሆኖም ግን በኢትዮጵያ ያለውን ገዥ አካል ማዳን ወይስ ደግሞ የኢትዮጵያን ነጻ ፕሬስ እና ጦማሪያንን ማዳን የሚል ወሳኝ ጥያቄ ቢቀርብልኝ ቶማስ ጃፈርሰን እንደመረጡት ሁሉ እኔም የኋለኛውን ማዳን የሚለው እንዲጠበቅልኝ እመርጣለሁ፡፡ ቶማስ ጃፈርሰን እንዲህ የሚል ጥያቄ ቀርቦላቸው የሚከተለውን መልስ ሰጥተው ነበር፣ ”የእኛ መንግስት መሰረቱ የህዝብ ሀሳብ እንደመሆኑ መጠን የመጀመሪያው ዓላማ መሆን ያለበት ያንን መብት ማስከበር ነው፡፡ እናም ጋዜጦች የሌሉበት መንግስት ከሚኖር ወይም ደግሞ መንግስት በሌለበት ጋዜጦች ብቻ ከሚኖሩ የትኛው የተሻለ ነው የሚል ምርጫ ቢቀርብልኝ የኋለኛውን ለመምረጥ ለሰከንድ እንኳ ጥርጣሬ አይኖረኝም፡፡ ሆኖም ግን ይህን ስል ማንኛውም ሰው እነዚህን ጋዜጦች መቀበል እና ማንበብ መቻል አለበት፡፡“
በተመሳሳይ መልኩ ለእኔም ነጻ ጋዜጠኞች እና ጦማሪያን የሌሉበት ገዥ አካል ከሚኖር ወይም ደግሞ ገዥ አካል በሌለበት ነጻ ጋዜጠኞች እና ጦማሪያን ብቻ ከሚኖሩ የትኛው የተሻለ ነው የሚል ምርጫ ቢቀርብልኝ የኋለኛውን ለመምረጥ ለሰከንድ እንኳ ጥርጣሬ አይኖረኝም፡፡ ከሁሉም በላይ ለዓላማ በጽናት የቆምኩ፣ ለምሰራው ትክክለኛ ስራ ሁሉ ኩራት የሚሰማኝ፣ ላመንኩበት ዓላማ ከልብ እና በወኔ የቆምኩ፣ ዓላማየን ለማስፈጸም በከባድ እርምጃ ወደፊት የምገሰግስ፣ ላልሰራሁት ወንጀል ይቅርታን የማልጠይቅ፣ በምሰራው ስራ ሁሉ የማላፍር፣ ቆራጥ እና የማያወላውል ባህሪን የተላበስኩ የኢትዮጵያ ጦማሪ ነኝ!!!
ኃይል ለነጻ ጋዜጠኞች እና የኢትዮጵያ ጦማሪያን!
ውድቀት እና ሞት ህዘብን በጠብመንጃ ኃይል አስገድደው ለመግዛት ለተነሱ የዕኩይ ምግባር አራማጆች!
ኢትዮጵያ በክብር ለዘላለም ትኑር!
ሰኔ 3 ቀን 2006 ዓ.ም

አደጋ ላይ ነን!! (ስለግብረ ሰዶማዊነት ትምህርት እየተሰጠ ነው)

June 12/2014

(ኢ.ኤም.ኤፍ) በአዲስ አበባ በሚገኙ ትምህርት ቤቶች ውስጥ ከግብረ ሰዶማዊነት ጋር በተያያዘ ለተማሪዎች ክብረ ነክ ትምህርት እየተሰጠ መሆኑ ታወቀ። የትምህርት ቤት መዘጋትን ጠብቀው በፍጥነት እየተገበሩ ያሉት ትምህርት በኢትዮጵያ የወንጀለኛ መቅጫ ጭምር የሚያስከስስ ነው። ይህንን ግምት ውስጥ በመክተት በየትምህርት ቤቱ በአስቸኳይ እየተሰጠ ያለው ትምህርት እንዲቆም፤ ይህ ትምህርት ተግባራዊ እንዲሆን የሚያደርጉ ግለሰቦች፣ የውጭ ድርጅቶች እና ትምህርት ሚንስቴር ለዚህ ተጠያቂዎች ናቸው። በመሆኑም ጉዳዩ የሚመለከታቸው የሲቪክ እና የፖለቲካ ድርጅቶች አቋም እንዲወስዱ በዚህ አጋጣሚ ጥሪያችንን እናቀርባለን። ለዛሬው “አደጋ ላይ ነን” በማለት፤ ስማቸው እንዲገለጽ ያልፈለጉ መምህር የላኩትን መልእክት ከዚህ በታች አስፍረናል። አንብበው ለሌሎችም ያካፍሉ።
ካስደነገጥኳችሁ አዝናለሁ ግን በጣም መደንገጥ አለባችሁ፡፡በመላው የአዲስ አበባ የመንግስት ሁለተኛ ደረጃ ትምርህት ቤቶች ማለት ይቻላል በነSave The Children ፊት አውራሪነት እየተሰጠ ያለው የግብረሰዶማዊነት ትምህርት ተጠናክሮ እየቀጠለ መሆኑን ሳረዳችሁ ከፍተኛ ሀዘን እየተሰማኝ ነው፡፡እስካሁን ከ40 በላይ የሚሆኑ የአዲስ አበባ ት/ቤቶች ውስጥ ለውስጥ በአንድ ክፍለ ጊዜ በ120 ብር በተቀጠሩ የየትምህርት ቤቱ የባዮሎጂና የአይሲቲ መምህራን አማካኝነት እየተሰጠ ነው፡፡ሁለት አይነት ነው ትምህርቱ፡፡Life Skill (ላይፍ እስኪል) እና Comprehensive Sexuality Education (ከምፕሬኤንሲቭ ሴክሽዋሊቲ ኤጁኬሽን) የሚባሉ፡፡በሁሉም ትምህርት ቤቶች የመጀመሪያ ዙር ስልጠናው አልቋል፡፡ሁለተኛ ዙሩ የተግባር ትምህርት ነው፡፡ በቪዲዮና በተግባር እንቅስቃሴ የተደገፈ፡፡ ከሚሰጡት ትምህርቶች መካከል FREE KISSING (በፍሪ ኪሲንግ) እና MASTURBATION (ማስተርቤሽን)የሚባሉ የልቅ ወሲብ አይነቶች አሉበት፡፡ ልቅ ስል በ FREE KISSING (በፍሪ ኪሲንግ) ጊዜ ጾታ ሳይለይ የፈለጉትን ደፍሮ መሳም ሲሆን በ MASTERBATION (ማስተርቤሽን) የሚለው ደግሞ ሴቶችም ወንዶችም በቪዲዮ የታገዘ የ Pornography (የፖርኖ) ፊልሞች እያዩ እንዲተገብሩት የታሰበ ነው፡፡ ለዚህም አላማ ከየትምህርት ቤቱ ጎበዝ የተባሉ ተማሪዎች ተመርጠው ተዘጋጅተዋል፡፡
ጉዳዩ እስከ ትምህርት ሚኒስተርና ቢሮ ቢደርስም እስካሁን መልስ ሊሰጡ አልቻሉም፡፡አንዳንድ የክፍለ ከተማ ሀላፊዎች እንዳሉት እነSave The Children (ሴቭ ዘቺልድረን) በኢትዮጵያ የተለያዩ ስራዎች ስለሚሰሩልን አቁሙ ብንላቸው ግንኙነታችን ይበላሻል፡፡በላይ አመራሩም ዘንድ ያለው እሳቤና አቋም ይሄ ነው ብለዋል፡፡የተከበራችሁ የአዲስ አበባና በመላው ኢትዮጵያ የምትገኙ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማሪዎች ፤ ወላጆች ፤ቤተሰቦች ይህ የምነግራችሁ ነገር ተራ አሉባልታ አለመሆኑን በተለያየ ጊዜ ለማሳያ የተለጠፉ መረጃዎችን አይታችሁ መፍረድ ትችላላችሁ፡፡ የተከበራችሁ ተማሪዎች ወላጆች እና በዚህ ጉዳይ እንደ እኔ የተንገበገባችሁ ሁሉ አደጋ ላይ ነን፡፡በተለይ ድርጅቶቹ ነገሩን እንዲሰሩላቸው የመረጧቸውን ሰዎች ለመግዛት እያወጡት ያለው ምራቅ የሚያስውጥ ገንዘብ በየክፍሉ ከሚያስተምሩላቸው መምህራንና ከተባባሪ የትምህርት ቤት አስተዳደሮችም አልፎ እስከ ላይ ድረስ ኪስ ሳያሞቅ አልቀረም፡፡ የእናንተ እርዳታ ቆፍጠን ያለ ውሳኔ ያስፈልጋል፡፡
ተማሪዎችና ወላጆች በአዲስ አበባ በብዛት የሁለተኛ ደረጃ ተማሪዎች ላይ ቢያነጣጥርም ነገሩ በኦሮሚያ፣ በአማራና በሌሎች ክልልሎች ግን እስከ ታችኛው ክፍል ድረስ በስነተዋልዶ፣በጸረኤድስና በስርአተ ጾታ ሰበብ የግብረሰዶማዊነት ትምህርት እየተሰጠ መሆኑን ሳረጋግጥላችሁ በአውነት ነው፡፡ ስለዚህም ተማሪዎች፣ ወላጆች የሚመለከታችሁ ሁሉ አይናችሁን ወደ ትምህርት ቤት አንሱ!! ተማሪዎች በገንዘብ በተደለሉ ግለሰቦች እተረጨባቸው ያለውን መርዝ አስቁሙ፡፡በተለይ በአሁኑ ወቅት አስረኛና አስራ ሁለተኛ ክፍሎች ትምህርት በጨረሱበት ጊዜ እየሆነ ያለው ተማሪዎችን በክረምት ትምህርትና ስልጠና ሰበብ ለዚህ ተግባር እየመዘገቡ ያሉ ትምህርት ቤቶች እንዳሉ ልነግራችሁ እችላሁ፡፡ሴቭ ዘቺልድረን በክረምት ወራት ትምህርት ቤቶችን በክረምት ትምህርት አሳቦ በመከራየት የሰዶማዊነት ትምህርት ሊሰጥ መሆኑን ስነግራችሁ ያለምንም ጥርጥር ነው፡፡አስካሁን የግብረሰዶማዊነት ትምህርት ሁለተኛ ዙር ለመስጠት ፈቃደኛ ሆነው ካሉ ትምር ቤቶች መካከል፡ ሚኒሊክ፤መድሀኒአለም፣ባልቻ አባነፍሶ፣ኤስኦኤስ፣ህዳሴ፣አፍሪካ ህብረት፣የካቲት 23 ፣መነን፣አየርጤና እና ሌሎችም ይገኙበታል፡፡ይህ ነገር ሀሰትነው ብላችሁ የምትጠራጠሩ ከሆነ በተለይ ለአዲስ አበባ ነዋሪዎች በተለይ ወላጆች አንደኛ በየክፍለ ከተማ የሚገኙ የስርአተ ጾታ ሀላፊዎችን ፣በአዲስ ትምህርት ቢሮ በተለይ አቶ ሀይለ ስላሴ የተባሉ የስራ ሀላፊን መጠየቅ ይቻላል፡፡በተጨማሪም በኢትዮጵያዊነት ድምጽ ላይ የተለጠፉ የመማሪያ ሰነዶችን ማየት ይቻላል፡፡ወላጆች ልጆቻችሁን አድኑ!!
የተከበራችሁ ተማሪዎች በየትኛውም አጋጣሚ በትምህርት ቤትም ሆነ ከትምህርት ቤት ውጪ በስነተዋለዋልዶና ስርአተ ጾታ ስም የሚሰጠውን ፍጹም የግብረሰዶማዊነት ትምህርት አንማርም ንድትሉ ብትሉም እራስን የማዳንና የመከላከል ተግባርና እርምጃ መሆኑን አውቃችሁ በዚህ ተግባር ላይ የተሳተፉ መምህራንም ሆኑ በገንዘብ ተደልለው ሊያስተምሩ የተዘጋጁ ተማሪዎችን አምርራችሁ እንድታገሉ ሁላችንም በፈጠረን አምላክ ስም እለምናቿለሁ!!
ኢትዮጵያ የግብረሰዶማዊነት መቀበሪያ ትሆናለች እንጂ መቼም ከግብረሰዶማዊነት ጋር አትጋባም!!
ጭንቀት ካደረበት መምህር

Wednesday, June 11, 2014

ቅድመ-ውህደቱና ልዩ ገጠመኞቹ

June11/2014
የመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት (መኢአድ) እና አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ (አንድነት) የቅድመ ውህደት ስምምነት ሰኔ 1 ቀን 2006 ዓ.ም በመኢአድ ጽ/ቤት በተካሄደው የግማሽ ቀን ስነ-ስርዓት ተከናውኗል። በስነስርዓቱ ላይ በርካታ ታዋቂ ሰዎች፣ ፖለቲከኞች፣ የሚዲያ ባለሙያዎችና ዲፕሎማቶች ተገኝተው ነበር

የቅድመ-ውህደቱ አጠቃላይ ይዘት
የውህደቱ የፊርማ ስነ-ስርዓት በተካሄደበት ወቅት የሁለቱ ፓርቲ አመራሮች ሰፋ ያለ ንግግር አድርገዋል። የሁለቱም መሪዎች ንግግር ውህደቱ ከመዘግየቱ በስተቀር አስፈላጊ መሆኑን አፅንኦት ሰጥተው ተናግረዋል። ከቅድመ ውህደት ስነ-ስርዓት ፊርማው በኋላ ለጋዜጠኞች አጠር ያለ ጋዜጣዊ መግለጫ ፕሮግራም ተዘጋጅቶ ስለነበር በፕሮግራሙ ላይ የተለያዩ ጋዜጠኞች ለሁለቱ ፓርቲ መሪዎች ጥያቄ አቅርበውላቸው ነበር።
ከቀረቡት ጥያቄዎች መካከል በቀጣይ በአንድ ወር ውስጥ ጠቅላላ ጉባኤ ተጠርቶ የሚመሰረተው ፓርቲ ስያሜ ምን ይሆናል የሚል ነበር። ለዚህ ጥያቄ ምላሽ የሰጡት ኢንጅነር ግዛቸው ሽፈራው ስያሜው የሁለቱን ፓርቲዎች ስያሜ ባቆራኘ መልኩ አዲስ ስም ይወጣል ብለዋል። ስያሜው የሚፀድቀው በአዲሱ ውህድ ፓርቲ ጠቅላላ ጉባኤ መሆኑንም አስረድተዋል።
በተመሳሳይ ሌሎች ፓርቲዎችን ታሳትፋላችሁ? ለሚለው የጋዜጠኞች ጥያቄ መኢአድና አንድነት በመዋቅር ጥንካሬና በአባላት ብዛት በአንፃራዊ ደረጃ ከሌሎች ፓርቲዎች የተሻሉ መሆናቸውን ጠቅሰው፤ ይህ ብቻ በቂ ባለመሆኑ ሌሎች ፓርቲዎች እንዲገቡበት በማድረግ ኢህአዴግን የሚፎከር አብይ ብሔራዊ ፓርቲ ለማቋቋም መታሰቡን ገልፀዋል። የአሁኑም የአንድነትና የመኢአድ ቅድመ-ውህደት እንደ ውህደት ማዕከል ሆኖ እንደሚያገለግል ያላቸውን ተስፋ ገልፀዋል።
በተጨማሪም በአንድ ወር ውጥ ጠቅላላ ጉባኤ ተጠርቶ አዲሱን ውህድ ፓርቲ ለመፍጠር የአቅም ጉዳይ በጋዜጠኞች ተነስቶ የነበረ ሲሆን፤ “ችግራችን የአመራር እና ድርጅታዊ አቅምን የማንቀሳቀስ እንጂ የአቅም አይደለም። አባላቶች በከፊልም ቢሆን የራሳቸውን ወጪ በመሸፈን ወደ አዲስ አበባ በመምጣት የሁላችንንም ፍላጎት እናሳካለን” ሲሉ ኢንጂነር ግዛቸው መልሰዋል። በቅርቡም የሁለቱም ፓርቲዎች ብሔራዊ ም/ቤት የጠቅላላ ጉባኤ አዘጋጅ በመሰየም ሁኔታውን ያፋጥናል ብለዋል። አዲሱ ውህድ ፓርቲም ከሁለቱ ፓርቲዎች የተውጣጣ 400 የጠቅላላ ጉባኤ አባላት ይኖሩታል ብለዋል።
ቀደም ሲል በመኢአድ በኩል “አንድነት ከመድረክ ካልወጣ ውህደቱ አይሳካም” የሚለውን ጥያቄ በተመለከተ ከጋዜጠኞች ለተነሳው ጥያቄ ጉዳዩ በሕግ ባለሙያዎች ታይቶ በመድረክም ሆነ አዲስ በሚፈጠረው ውህድ ፓርቲ ላይ የሚፈጥረው ተፅዕኖ እንደሌለ መረጋገጡ፣ አንድነት ከመኢአድ ጋር ውህደት በሚፈፅምበት ወቅት ሕጋዊ ሰውነቱን ወዲያውኑ ስለሚያጣ ከመድረክ ጋር የሚኖረው ግንኙነት ወዲያውኑ የሚቋረጥ በመሆኑ ችግር እንደማይፈጠር ተረጋግጧል ሲሉ ኢንጂነር ግዛቸው ተናግረዋል።
ሌላው ከጋዜጠኞች የቀረበው ጥያቄ፤ ቅድመ ውህደቱ የተሳካው በፓርቲዎቹ አመራሮች ሳይሆን፤ በሽማግሌዎች ግፊት ስለሆነ ምን ያህል ዘላቂነት ይኖረዋል የሚል ነበር። ለዚህ ጥያቄ ምላሽ የሰጡት ኢንጂነር ግዛቸው፤ በሁለቱ ፓርቲዎች መካከል የውህደት ፍላጎት መንፀባረቅ የጀመረው ከአራት ዓመት በፊት መሆኑን አስታውሰው፤ ለመዋሐድ ፍላጎቱ የመጣው ከአባሉና ከአመራሩ መሆኑን ጠቅሰዋል፤ ነገር ግን ሽማግሌዎቹ የመጡት በመጨረሻ ውህደቱ እንዲፋጠን ድጋፍ ለማድረግ ነው ብለዋል።
አቶ አበባው መሐሪ (የመኢአድ ሊቀመንበር) በበኩላቸው አንድነት ከመድረክ ጋር ስላለው ግንኙነት ሲመልሱ፤ እስካሁን ድረስ ውህደቱን ሲያጓትት የቆየው የአንድነትና የመድረክ ግንኙነት የጠራ ባለመሆኑ ነው ብለዋል። መኢአድ ከአንድነት ጋር ሲዋሐድ ይሄው ችግር ወደ ውህዱ ፓርቲ እንዳይሄድ በመፍራት ጥያቄው በመኢአድ በኩል መነሳቱን ገልፀዋል። ሆኖም ችግሩን የሚያጠና ሁለት ገለልተኛ የሕግ ባለሙያዎች ተመድበው የመድረክና የአንድነት እንዲሁም የመኢአድ ከምርጫ ቦርድ ሕግና ደንብ ጋር ታይቶ በመጨረሻ ወደ ውህዱ ፓርቲ ሊተላለፍ የሚችለው የገንዘብና የንብረት እንጂ የፖለቲካ ባለመሆኑ በዚሁ በመተማመን የቅድመ-ውህደት ሰነዱ ሊፈረም መብቃቱን ተናግረዋል።
ሽማግሌዎቹ በአደራዳሪነት ይሳተፉ እንደነበር የጠቀሱት አቶ አበባው፤ የሽማግሌዎቹ በጎ አስተዋፅኦ ቢኖርም፤ አሁን ግን ሁለቱ ፓርቲዎች ድርድሩን በራሳቸው የጨረሱት መሆኑን ገልፀዋል።
በተጨማሪነት ከጋዜጠኞቹ የቀረበው ጥያቄ ፓርቲዎቹ የውስጥ ችግራቸውን ሳይፈቱ ወደ ቅድመ-ውህደት ፊርማ ለምን መጡ? የቅድመ-ውህደት ፊርማው ከማካሄዱ በፊት በር ላይ ቅሬታ ሲያሰሙ የነበሩ ወገኖች ነበሩ ለሚለው ጥያቄ፤ አቶ አበባው ሲመልሱ በዚህ ወቅት ፓርቲዎቹ በውስጥ ችግር ላይ አለመሆናቸውን ይልቁኑ ቅድመ ውህደቱን እንዳይፈረም ሁከት የፈጠሩት የመኢአድ አባላት ሳይሆኑ የአዲስ አበባ የኢህአዴግ አባላት ናቸው ብለዋል። “የኢህአዴግ አባል የመኢአድን የውስጥ ችግር ይፈታ የማለት መብት የለውም” ሲሉ በመግለፅ ጉዳዩ ፓርቲዎቹን ውህደት እንዳይፈፅሙ በመንግስት በኩል የተቀናጀ ጥረት መኖሩን የሚያመለክት ከመሆኑም በላይ ኢህአዴግ ጠንካራ ፓርቲ እንዳይፈጠርና በሕዝባችን ላይ የጭቆና ቀንበር ጭኖ ለመቀጠል መፈለጉን የሚያመላክት ነው ብለዋል።
ፓርቲዎቹ ከሚያደርጉት ውህደት ጎን ለጎን በ2007ቱ ምርጫ የሚኖራቸው ተሳትፎና ለዚያም የሚሆን ስትራቴጂ ምን እንደሆነ ከጋዜጠኞች ተጠይቀው የነበረ ሲሆን፤ ምርጫውን በተመለከተ የውህዱ ፓርቲ የሚወስነው እንደሆነ ኢንጂነር ግዛቸው ጠቅሰው፤ በአጠቃላይ ሁለቱም ፓርቲዎች የምርጫ ፓርቲዎች እንደመሆናቸውና በሰላማዊ ትግል የሚያምኑ በመሆኑ ምንጊዜም ለምርጫ ዝግጁ መሆናቸውን አስረድተዋል። በአንድነት ፓርቲ በኩል አማራጭ ፖሊሲ የምርጫ ስትራቴጂ፣ ማኒፌስቶ፣ ማዘጋጀት ዕጩዎችንና ታዛቢዎችን እየፈተሸ መሆኑንና በመኢአድም በኩል ይሄው ጉዳይ ስለሚኖር የሁለቱንም አጣምረን እንቀጥላለን ብለዋል። በምርጫ መሳተፍ፣ አለመሳተፉ ግን ወደፊት እንደሚወሰንና የዴሞክራሲ ተቋማቱ ነፃ መሆንና መጠናከር ወሳኝ መሆኑን አብራርተዋል።
በጋዜጠኞች ከተነሱ ሌሎች ጥያቄዎች መካከል ከፓርቲዎች ውህደት በኋላ አንጃዎች የመፈጠር ሁኔታዎች ስለሚስተዋል ለዚህ ችግር የተቀመጠ ስትራቴጂ አላችሁ ወይ የሚል ነበር። ለዚህ ጥያቄ ምላሽ የሰጡት ኢንጂነር ግዛቸው፤ ውህደቱን ተከትሎ አንጃ መውጣቱ ፓርቲዎቹን እንደማያሳስባቸው ነገር ግን የሚወጣው አንጃ ስርዓት አልበኛ ሲሆን ነው ችግሩ ብለዋል። አንጃ የሚወጣ ከሆነም ሁለቱ ፓርቲዎች በተቀመጠው መዋቅር በዴሞክራሲያዊና በሰለጠነ መንገድ መወጣት ይቻላል። ነገር ግን በስርዓት አልበኝነት ቢሮ በመውረር ከኢህአዴግ ጋር በመገናኘት መሰናክል የመፍጠሩ አካሄድ አንጃ መፍጠር አይደለም ብለዋል።
“ውህደቱ አልተስማማኝም የሚል ቡድን ካለ መብቱ ነው። ሌላ ፓርቲ ማቋቋም ይችላል። የሰለጠነ ፖለቲካ ለማካሄድ የጉልበት፣ የመደባደብና ከባህል ውጪ የሆነ ነገር ሲሆን ግን ያሳፍራል” ሲሉ ኢንጂነሩ የገለፁ ሲሆን፤ በአሁኑ ወቅት ከዚህ አንፃር በአንድነት በኩል የሚያሰጋ ነገር የለም ብለዋል።
ውህደቱ በመዘግየቱ እንደተቋም ሁለቱን ፓርቲዎች በፍጥነት ባለመስራታቸው ኃላፊነቱን እንደሚወስዱ ሁለቱም አመራሮች ገልፀዋል። በተለይ አቶ አበባው መሐሪ ውህደቱ ለምን ዘገየ ለሚለው የጋዜጠኞቹ ጥያቄ ሲመልሱ፤ የፓርቲዎችን መዋቅርና የፖለቲካ ፕሮግራም በማጣጣም ሂደት እንጂ ከግል ፍላጎት አለመመቸት ጋር የተያያዘ አይደለም ብለዋል። በአጠቃላይ ከአንድ ወር በኋላ በሚጠራው ጠቅላላ ጉባኤ ከመኢአድ 200 ከአንድነት 200 የጠቅላላ ጉባኤ አባላት አዲስ ውህድ ፓርቲ ይፈጠራሉ ተብሎ ይጠበቃል።
የቅድመ-ውህደቱ ልዩ ገጠመኞች
የቅድመ-ውህደት ስነ-ስርዓቱን ልዩ ካደረጉት አጋጣሚዎች መካከል የኢትዮጵያውያን ዴሞክራሲ ፓርቲ (ኢዴፓ) አመራር አባል የሆኑት አቶ ሞሼ ሰሙ በፕሮግራሙ ላይ መገኘት አንዱ ነበር። የእሳቸው በቦታው መገኘት ከምርጫ 97 በኋላ ከፖለቲካ ልዩነት ባሻገር በግለሰብ ደረጃ የተፈጠረውን መቃቃር ሊያለዝብ የሚችል ጥሩ ጅምር እንደሆነም እየተገለፀ ነው። የአንድነትም ሆኑ የመኢአድ የፓርቲ አመራር አባላት ለአቶ ሞሼ ሰሙ ያሳዩት አዎንታዊ አቀባበል በዕለቱ የነበሩ ጋዜጠኞችን ትኩረት ስቦ ነበር። አብዛኛዎቹ የአንድነትና የመኢአድ አመራሮች አቶ ሞሼን ያገኙዋቸው ከምርጫ 97 በኋላ መሆኑን በአድናቆት ሲናገሩ ታይተዋል።
አቶ ሞሼ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ሰፊ የፖለቲካ ተሳትፎ እያሳዩ የመጡ ፖለቲከኛ ናቸው። በገዢው ፓርቲ ፖሊሲዎች ላይ ከሚያነሱዋቸው የሰሉ ትችቶች ባሻገር ለሀገሪቱ ፕሬስ መጠናከር የሚሰጡዋቸው ገዢ ኀሳቦች በመስኩ ባለሙያዎችና አጋሮቻቸው ጭምር እውቅና እየተሰጠው ነው። አቶ ሞሼ በሰኔ አንዱ የመኢአድና የአንድነት የቅድመ ውህደት ስምምነት ስነ-ስርዓት ላይ በድፍረት በመገኘታቸውም በኢዴፓ እና በሌሎች ተቃዋሚዎች መካከል ለረጅም ጊዜ የቆየውን ያለመተማመን ስሜት በመጠኑም ቢሆን እንዲለዝብ ምክንያት ሊሆን ይችላል ብሎ መገመት ይቻላል።
ሌላው በዕለቱ ስነ-ስርዓት ላይ ከታዩ አወዛጋቢ ጉዳዮች መካከል ሊጠቀስ የሚገባው የቅድመ ውህደት ስምምነቱን ለመረበሽ የተደረገው ጥረት ነው። የውህደቱን ስነ-ስርዓት ለማወክ የተደረገው ጥረት እንደ ሀገር የሚያሳፍር፣ እንደ ዜጋም የሚያሳዝን ነው።
ከአስተባባሪዎቹ ገለፃ መረዳት እንደሚቻለው የውህደት ስምምነቱ እንዳይካሄድ በር በመደብደብና ፀያፍ ቃል በመናገር ሲበጠብጡ የነበሩት ሦስት ግለሰቦች ነበሩ። በእርግጥ ስነ-ስርዓቱ ወደሚከናወንበት ስፍራ እንዲገቡ የተፈለገው አስቀድመው የተጠሩ እና ለዚያም ልዩ ባጅ ያደረጉ ብቻ ነበሩ። ሆኖም የተወሰኑ ሰዎች “ልግባ፣ አትገባም” የሚል ውዝግብ በሩ ላይ ይስተዋል ነበር። በመጨረሻም ውዝግቡ ተባብሶ በር እስከመገንጠልና ድንጋይ እስከመወራወር ተደረሰ። በመሀሉም በተወረወረ ድንጋይ በመኢአድና በአንድነት ከፍተኛ አመራሮች ላይ የጥርስ መውለቅ አደጋ በመድረሱ ሁኔታውን አሳዛኝ ትዕይንት አድርጎታል። በዕለቱም ስብሰባውን ከረበሹ ሦስት ሰዎች መካከል አንዱ የኢህአዴግ አባል መሆኑ ተገልጿል፡፡
በቅርቡ ሃያ ሦስተኛው የግንቦት ሃያ በዓል ሲከበር ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ ከተናገሩዋቸው በርካታ ርዕሰ ጉዳዮች መካከል ለሀገሪቱ መድበለ ፓርቲ መዳበርና ለተቃና የምርጫ ስርዓት ከተቀመጡ ሕጎችና አሰራሮች ባሻገር ኢህአዴግ አባላቱን በስነ-ምግባር በማነፅ ተከታታይ ስልጠና እየሰጠ መሆኑን፣ በሂደቱም የሚያጠፉ አባላቱን ለመቆጣጠር ከድርጅቱ የማንንም ምክር ሳይፈልግ በራሱ የእርምት እርምጃ እንደሚወሰድ መግለፃቸው አይዘነጋም።  

የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ሠራተኛ በጥይት ተመትተው ሕይወታቸው አለፈ

June 11/2014
የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ሠራተኛ በጥይት ተመትተው ሕይወታቸው አለፈ
-በመግደል የተጠረጠረው ግለሰብ አልተያዘም

የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ሠራተኛ ናቸው የተባሉት አቶ በላይነህ ዳምጠው፣ ሰኔ 1 ቀን 2006 ዓ.ም. ከምሽቱ ሁለት ሰዓት ሲሆን ቤላ አካባቢ በሚገኘው የባለቤታቸው ቤተሰቦች ቤት ውስጥ በአንድ ግለሰብ በጥይት ተመትተው ሕይወታቸው ማለፉ ታወቀ፡፡

ባለትዳርና የአንድ ልጅ አባት መሆናቸው የተነገረው አቶ በላይነህ፣ ከሰኔ 1 ቀን 1992 ዓ.ም. ጀምሮ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በተለያዩ ኃላፊነቶች ላይ ይሠሩ እንደነበር፣ ሕይወታቸው ባለፈበት ዕለትም ቀን በሥራ ገበታቸው ላይ እንደነበሩ የምክር ቤቱ ሠራተኞች ለሪፖርተር ተናግረዋል፡፡

አቶ በላይነህ ሰኔ 1 ቀን 2006 ዓ.ም. ሥራ ውለው ቤላ አካባቢ ወደሚገኘው የባለቤታቸው ቤተሰቦች ቤት መሄዳቸውን የገለጹት የሥራ ባልደረቦቻቸው፣ ምክንያቱን በማያውቁትና ባላሰቡት ሁኔታ ሰኔ 2 ቀን 2006 ዓ.ም. ጠዋት ወደ ሥራ ሲገቡ የሥራ ባልደረባቸው መሞታቸውን መስማታቸውን አስረድተዋል፡፡

ግለሰቡ የተገደሉት በጥይት ተመትተው መሆኑንና ለመሞታቸውም ምክንያት የሆነችው አንዲት የፖሊስ ባልደረባ መሆኗን የአካባቢው ነዋሪዎች ገልጸዋል፡፡ የፖሊስ ባልደረባዋ፣ የሟች ባለቤት ቤተሰቦች ግቢ ውስጥ ተከራይታ እንደምትኖር የገለጹት ምንጮች፣ በዕለቱ እሷ ዘንድ የመጣ አንድ ተጠርጣሪ ግለሰብ ባልታወቀ ምክንያት እሷን እያባረረ ሟች ወደነበሩበት ክፍል ሲገባ፣ መጀመሪያ የሟችን ባለቤት ያገኛል፡፡ እሷን ሁለት እጆቿን በጥይት መትቶ ከጣላት በኋላ ወደ ውስጥ ሲዘልቅና ሟች ሲወጡ በመገናኘታቸው በተደጋጋሚ በጥይት ደብድቦ ሕይወታቸው እንዲያልፍ እንዳደረጋቸው አስረድተዋል፡፡

ተጠርጣሪው በአካባቢው የነበሩትን ነዋሪዎች በማስፈራራት የያዘውን ተሽከርካሪ አስነስቶ ከነመሣሪያው መጥፋቱንም የአካባቢው እማኞች ገልጸዋል፡፡

የ44 ዓመት ጐልማሳ የነበሩት የአቶ በላይነህ የቀብር ሥርዓትም ሰኔ 3 ቀን 2006 ዓ.ም. በፈረንሳይ አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ቤተ ክርስቲያን መፈጸሙ ታውቋል፡፡ የሟች ባለቤት በዳግማዊ ምኒልክ ሆስፒታል የሕክምና ዕርዳታ እንደተደረገላቸውና ለደረሰው አደጋ ምክንያት ናት የተባለችው የፖሊስ ባልደረባ በቁጥጥር ሥር ውላ በምርመራ ላይ መሆኗም ታውቋል፡፡ ተጠርጣሪ ገዳይም ለጊዜው ማምለጡ ተጠቁሟል፡፡ ጉዳዩ በምርመራ ላይ በመሆኑ ፖሊስ ማብራሪያ ከመስጠት ተቆጥቧል፡፡