Saturday, May 31, 2014

አረብሳት ከኢትዮጵያ የሞገድ አፈና እየተደረገብኝ ነው አለ

May 31/2014
አረብሳት ከኢትዮጵያ የሞገድ አፈና እየተደረገብኝ ነው አለ
ካቻምናም ታፍኛለሁ፣ ዘንድሮ ግን በህግ እጠይቃለሁ ብሏል

ተቀማጭነቱን በሳዑዲ አረቢያ ያደረገውና በርካታ የቴሌቪዥን ጣቢያዎችን በተለያዩ የዓለም ክፍሎች የሚያሰራጨው የአረብ ሳተላይት ኮሙኒኬሽን ተቋም (አረብሳት) ካለፈው ሳምንት ጀምሮ እየተፈጸመበት ያለው ዓለማቀፍ የሳተላይት ሞገድ አፈና (Jamming) ምንጩ ከኢትዮጵያ መሆኑን እንዳረጋገጠ ገለጸ፡፡
ሳትኒውስ የተባለው የአገሪቱ የዜና ምንጭ ከትናንት በስቲያ እንደዘገበው፣ አረብሳት በሚያስተላልፋቸው በርካታ የቴሌቪዝን ጣቢያዎቹ ላይ መታየት የጀመረውን የስርጭት መስተጓጎል መነሻ ለማወቅ ባደረገው በረቂቅ ቴክኖሎጂ የታገዘ ጥናት፣ ከኢትዮጵያ ግዛት ውስጥ የሚነሳና ሆን ተብሎ የሚፈጸም የሳተላይት ሞገድ አፈና (Jamming) እየተደረገበት መሆኑን ማረጋገጡን አስታውቋል፡፡ ይህን መሰሉ ህገወጥ ድርጊት መፈፀሙ መሆኑ እጅግ እንዳሳዘነው ያስታወቀው አረብሳት፤ ከኢትዮጵያም ሆነ ከኤርትራ የሚተላለፍ ምንም አይነት ስርጭት ሳይኖረው፣ የሳተላይት ሞገድ አፈና መደረጉ እንቆቅልሽ እንደሆነበት ገልጿል፡፡ 
የሳተላይት ሞገድ አፈናው፣ ምናልባትም ከሁለቱ አገራት የአንዱ ተቀናቃኝ የሆኑና ከአረብሳት ሳተላይቶች አቅራቢያ በሚገኙ ሳተላይቶች አማካይነት የሚሰራጩ የቴሌቪዝን ጣቢያዎችን ለማፈን የታለመ ሊሆን እንደሚችል ያለውን ግምትም ሰጥቷል፡፡
እየተፈጸመበት ያለውን ህገወጥ ተግባር ለመመከት በብሄራዊና በአለማቀፍ ደረጃ እየተንቀሳቀሰ መሆኑን የገለጸው አረብሳት፣ ጉዳዩን ለዓለማቀፉ የቴሌኮምኒኬሽን ህብረት እና ለአረብ ሊግ ማሳወቁንም ጠቅሷል፡፡አረብሳት ጉዳዩን በቀጣይ ከመረመረ በኋላ፣ ከአለማቀፍ የህግ  ተቋማትና የአገሪቱ የህግ አካላት ጋር በመቀናጀት ወደ ህግ እንደሚያመራና እየተቃጣበት ባለው የሳተላይት ሞገድ አፈና ለደረሰበትም ሆነ ለሚደርስበት ጉዳት ካሳ እንደሚጠይቅ  ማቀዱን ተናግሯል፡፡ከሁለት አመታት በፊት ከኢትዮጵያ ተመሳሳይ የሳተላይት ሞገድ አፈና እንደተፈጸመበትም አስታውሷል።

International broadcasters protest against intentional jamming from Ethiopia

May 31, 2014
Due to intentional jamming from Ethiopia the reception of TV programs by Deutsche Welle and numerous other international broadcasters is currently severely impacted in large parts of the Arab world.Germany’s international broadcaster Deutsche Welle (DW)
BBC, France 24 and Voice of America are also among the broadcasters affected by the jamming.
The satellite provider Arabsat has identified Ethiopia as the source of the strong jamming signals on all its three satellites. Ethiopian authorities have not responded to the incident yet.
Peter Limbourg, director general of Deutsche Welle: “This is a gross violation of the internationally recognized right of freedom of speech and freedom of the press. Deutsche Welle, BBC, France 24 and Voice of America strongly condemn this action against the free flow of impartial information. We urge the Ethiopian authorities to immediately cease the jamming.”
While Deutsche Welle’s short wave programs have been repeatedly target of jamming from Ethiopia, the current incident appears not to be aimed at specific broadcasters or programs. The jamming of satellite programs constitutes a violation of international agreements, but the practice is nevertheless on the rise. The most recent incidents occurred in 2011 and 2012 via Iran.
In the Arab world Deutsche Welle is available through its TV channel “DW Arabia.” Selected radio programs in Arabic are available via partner stations throughout the region.

ታፍኖ የተወሰደው የዩኒቨርሲቲ ተማሪ ማእከላዊ መታሰሩ ታወቀ

May 30/2014
ግንቦት ፳፪(ሃያ ሁለት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ከቀናት በፊት  ከትምህርት ገበታው ታፍኖ ተወስዶ የነበረው የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ 1ኛ አመት ተማሪ እና  የአንድነት ፓርቲ  አባል የሆነው መልካሙ አምባቸው በማእከላዊ ወንጀል ምርመራ መታሰሩ ታወቀ።
በጎንደር ምዕራብ አርማጨሆ ነዋሪ የሆነውና በአሁኑ ወቅት አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ 6 ኪሎ የአካውንቲግ 1ኛ ዓመት ተማሪ እና በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የአንድነት መዋቅር ስራአስፈጻሚ አባል የሆነው ወጣት መልካሙ አምባቸው ሰኞ ግንቦት 18 ቀን 2006 ዓ.ም ማታ ራት ከበላ በኋላ  ከዩኒቨርስቲ ግቢ ባልታወቁ ኃይሎች ታፍኖ ተወስዷል።
ወጣት መልካሙ  የአካባቢው ነዋሪ እንደመሆኑ መጠን በጎንደር ስለ ሚደረገው የድንበር ማካለል የሚያውቀውን መረጃ በመስጠቱ በመንግስ ሀይሎች ክትትል ይደረግበት እና አንዳንዴም ማስፈራሪያ ይሰነዘርበት እንደነበር ለፍኖተ ነፃነት በተደጋጋሚ ይገልጽ ነበር።
ተማሪ መልካሙ ሰሞኑን ከዩኒቨርሲቲው ቅጥር ግቢ ታፍኖ የተወሰደው  ከድንበር ማካለሉ ጋር በሰጠው መረጃ እንደሆነ በቦታው የነበሩ የዓይን ምስክሮች  ገልጸዋል፡፡
ባለፉት ቀናት አንድነትፓርቲ ወጣት መልካሙ ያለበትን ሁኔታ ለማጣራት በዩኒቨርስቲው አካባቢ ወደ ሚገኙ ፖሊስ ጣቢያዎች ተወካዮችን  በመላክ ጥረት  ቢያደርግም፤የሚገኝበት ቦታ እና ሁኔታ  ሊታወቅ አለመቻሉን መግለጹ ይታወሳል።
መልካሙን የሚያወቁት አብሮ አድጎቹ በሰጡት አስተያየት  ከ 2001 አመተ ምህረት ጀምሮ  ማለትም  ገና  በልጅነት እድሜው የአገሬ ጉዳይ ያገባኛል በማለት የመኢአድ አባል ሆኖ መታገል እንደጀመረ ጠቅሰው፤ ሆኖም ላለፉት አመታት በደረሰበት ተደጋጋሚ እስር እና ድብደባ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርቱን ለሁለት ዓመታት ለማቁዋረጥ ተገዶ እንደነበር አውስተዋል።
ታስሮ ሳለ የ 50 ሺህ ብር ዋስትና ሲጠየቅ የሚከፍለው በማጣቱ የ አካባቢው ህብረተስብ አዋጥቶ በመክፈል ከ እስር እንዳስፈታው የገለጹት አብሮ አደጎቹ፤ በስንት ስቃይና መከራ ውስጥ አልፎ ትምህርቱን ጨርሶ ወደ ዩኒቨርሲቲ በገባበት ዐመት እንደገና ለተመሳሳይ መከራ መዳረጉ እንዳሳሰኛቸው ተናግረዋል።

የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ 1ኛ ዓመት ተማሪ ከዩኒቨርስቲ ግቢ ባልታወቁ ኃይሎች ታፈነ

May30/2014
10426
በጎንደር ምዕራብ አርማጨሆ ነዋሪ የሆነውና በአሁኑ ወቅት አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ 6ኪሎ የአካውንቲግ 1ኛ ዓመት ተማሪ የሆነው እንዲሁም በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የአንድነት መዋቅር ስራ አስፈጻሚ አባል ወጣት መልካሙ አምባቸው ሰኞ ግንቦት 18 ቀን 2006 ዓ.ም ማታ ራት ከበላ በኋላ ከዩኒቨርስቲ ግቢ ባልታወቁ ኃይሎች ታፍኖ ተወስዷል፡፡ ወጣት መልካሙ በጎንደር የሚደረገውን የድንበር ማካለል የአካባቢው ነዋሪ እንደመሆኑ መጠን የሚያውቀውን መረጃ በመስጠቱ ክትትል አንዳንዴም ማስፈራሪያ ይደረግበት እንደነበር ለፍኖተ ነፃነት ዘጋቢ ይገልጽ ነበር፣ አሁንም የተያዘው ከድንበር ማካለሉ ጋር በሰጠው መረጃ እንደሆነ በቦታው የነበሩ የፍኖተ ነፃነት ምንጮች ጠቁመዋል፡፡ ፓርቲው ወጣት መልካሙ ያለበትን ሁኔታ ለማጣራት በዩኒቨርስቲው አካባቢ ያሉ ፖሊስ ጣቢያዎች ቢሞከርም እስካሁን ድረስ ያለበት አልታወቀም፡፡  

Friday, May 30, 2014

The Swiss government granted asylum to Co-pilot Hailemedhin Abera

May 30/2014
Ethiopian Airlines Boeing 787
Ethiopian Airlines Boeing 787
(EMF) — The Switzerland government has granted asylum to the Ethiopian co-pilot who seized control of the Boeing 767-300 on 17 February 2014 and flew it to Geneva, according Ethiopian attorney who closely following the case.
The Ethiopian government has pushed the Swiss government to extradite the Co-pilot Hailemedhin Aberaby labeling him as a “traitor”. The regime has also opened file to try him in absentia, sources said.
The Swiss Federal Office of Justice has confirmed that it has refused the extradition request by the Ethiopian government.
Hailemedhin Abera can freely move now and defend his case out of confinement.
The pro-democracy Ethiopian Diaspora and, attorneys, like Shakespeare Feyissa, are trying to defend the rights of the co-pilot.
The airliner’s second-in-command, Hailemedhin Abera Tegegn, 31, took control of the plane when the pilot left the cockpit to use the toilet. He then sent a coded signal announcing he had hijacked his own aircraft. The plane landed safely, and none of the 202 passengers and crew members on Flight ET-702, which originated in Addis Ababa, the Ethiopian capital, were injured.
The Co-pilot has exposed the gross human rights violations in Ethiopia at a global scale.
Diaspora Ethiopians took the streets of American and European cities in Support of the Co-pilot Hailemedhin Abera.

ግንቦት 20- የመከራ የስደትና ዘረኝነት አዲስ ምዕራፍ መጀመሪያ

May 30/2014

























ወያኔ ለንግሥና የበቃበትን ግንቦት 20 ቀን 1983 ዓመተ ምህረት መታሰቢያ በአል ለ23ኛ ጊዜ ለማክበር ሰሞኑን ደፋ ቀና ሲል ሰንብቷል። በኢትዮጵያ ግብር ከፋይ ህዝብ የሚተዳደሩ መገናኛ ብዙሃንና በተለያዩ የውጪ አገራት የተመደቡ የወያኔ ቆንስላ ጽ/ቤቶች በዚሁ የግንቦት 20 በአል አከባበር ሥራ ተጠምደው ከርመዋል። ለኢትዮጵያ አገራችንንና ለህዝቦቿ ባርነትን ለህወሃትና ለግብረ አበሮቹ ደግሞ አልመውት የማያውቁትን ድሎትና ብልጽግናን ያጎናጸፈው ግንቦት 20 በየአመቱ ሲዘከር ልብ ልንላቸው ከሚገቡ በርካታ ትሩፋቶቹ ጥቂቶቹ ማስታወስ ይችላል፦
  1. ኢትዮጵያ አገራችን ለመጀመሪያ ጊዜ ከአብራኳ በተገኙ ከሃዲዎች መዳፍ ውስጥ ወድቃ ሉአላዊነቷና አንድነቷ የተናጋበት ሁኔታ መፈጠሩ፤
  2. በዘመናት ጥረት የተቋቋመው ህብረ ብሄር የአገር መከላኪያ ሠራዊታችን ፈርሶ በምትኩ ለጠባብ የዘውግ ጥቅም የተሰባብሰቡ መንደርተኞች ሙሉ በሙሉ የሚቆጣጠሩት ተቋም መመስረቱ፤
  3. በከፈሉት የህይወት መስዋዕትነት አገራችንን ከውጪ ጠላት ተከላክለው ነጻነት ያወረሱን ጀግኖች አባቶቻችን ታሪክ እየተብጠለጠለ በታሪካችን እንድናፍር መደረጉ፤
  4. ዜጎች በብሄር ማንነታቸው ከመንግሥት ሥራና የግል ይዞታ የሚፈናቀሉበት ዘመን መፈጠሩ፤
  5. የመንግሥትና የህዝብ ሃብት የነበሩ የንግድና የአገልግሎት መስጫ ተቋሞች በሙሉ ወደ ህወሃት የግል ይዞታነት መዛወራቸው፤
  6. የዘር የሃይማኖትና የቋንቋ ልዩነት መስፈርት የሆነበት ሥርዓት ተቋቁሞ ዜጎች እርስ በርስ የሚላተሙበት ፤ ለዘመናት በሰላም ከኖርበት ቀያቸው በነቂስ የሚፈናቀሉበት ሁኔታ ደጋግሞ መከሰቱ፤
  7. በልማትና እድገት ሥም ሰፋፊ የእርሻ መሬቶቻችን ለህንድ፤ ለቻይናና ለአረብ ከበርቴዎች በመቸብቸቡ የነገው ትውልድ የእጅ አዙር ቅኝ አገዛዝ ውስጥ እንዲወድቅ መንገዶች መመቻቸታቸው፤
  8. በሚሊዮን የሚጠጉ ለጋ ወጣቶች ተስፋቸው ተሟጦ ለአሽከርነትና ለግርድና ወደ አረብ አገር የሚፈልሱበት ችግር እየተባባሰ መምጣቱ፤
  9. በታሪካችን ታይቶ የማይታወቅ ስደትና እንግልት ሰለባ መሆናችን ወዘተ
  10. ሃሳብን በነጻነት የመግለጽና የመደራጀት መብት ተጥሶ በርካታ ኢትዮጵያውያን በአስተሳሰባቸውና በአመለካከታቸው በእስር ቤት እንዲማቅቁ፣ እንዲገደሉና እንዲሰደዱ ተደርገገዋል ።
ወያኔ ሰሞኑን ባወጣው “የእንኳን አደረሳችሁ መግለጫ” የግንቦት 20 ድል በሀገራችን ለዘመናት ተንሰራፍቶ የነበረውን የዓፈናና የጭቆና ስርዓት የተወገደበትና በምትኩ ልማታዊና ዴሞክራሲያዊ ስርዓት ለመገንባት የሚያስችል ፅኑ መሰረት የተጣለበት ፣የሰብአዊና ዴሞክራሲያዊ መብቶችና ነፃነቶች በተለይ ደግሞ የብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ህዝቦች እኩልነት የማረጋገጥ ቁልፍ ጥያቄ ምላሽ ያገኘበትበመሆኑ ልዩ ቦታና ክብር ይሰጠዋል። የግንቦት 20 ድል ሀገራችን ተደቅኖባት የነበረውን የመበታተን አደጋ በመታደግ የኋልዮሽ ጉዞዋን በአስተማማኝ ሁኔታ በመቀልበስ ድሮ ወደነበረችው የስልጣኔ ማማዋ ለመመለስ የሚያስችል በህዝቦች ይሁንታና መከባበር ላይ የተመሰረተ የዴሞክራሲያዊ ስርዓት መሰረት የተጣለበት የህዳሴአችን ጮራ የፈነጠቀበት የድል ቀን ነው።” ብሏል።
ይህንን መግለጫ እንዳነበብን ወይም እንደሰማን የሚከተሉትን ጥያቄዎች መልሰን እንድንጠይቀው ግድ ይለናል።
  • በአገራችን ተንሰራፍቶ የነበረው አፈናና ጭቆና ደጋግመህ እንደምትነግረን ተወግዶአል ለማለት የአንድ ብሄር የበላይነት የሰፈነበት መከላከያ ሠራዊትህ መላው አገሪቱን በመቆጣጠር በአሶሳ፤ በአርሲ፤በሃረር ፤ በኦጋዴን ፤ በጋምቤላ ፤ በአዋሳ፤ በዋካ፤ በአረካ ፤ በኦሮሚያ የተለያዩ ዞኖች ፤ በጎንደር፤ በአዲስ አበባና በሌሎችም በርካታ ቦታዎች በሰላማዊ ዜጎች ላይ የፈጸማቸው ግዲያዎች፤ እስርና እንግልት በምን ቋንቋና መስፈርት ነው በቀድሞ ስራዓቶች ከተፈጸሙት ተሽለው የተገኙት?
  • የደህንነት ሃይሎችህ በዜጎች ላይ የሚወስዱት ዘግናኝ እርምጃዎችና አብዛኛውን ህዝብ በፍርሃት ቆፈን ውስጥ የከተተው አንድ ለአምስት ጥርነፋህ እንዴት ተደርጎ ነው የሰብአዊና የዲሞክራሲ መብቶች ግንባታ ጽኑ መሠረት የሆነው?
  • ትናንት በበረባሶ ጫማ አዲስ አበባ የዘለቀው ወታደርህና ቤሳ በስቲን ያልነበራቸው መሪዎቹ ዜጎችን ከቄያቸው በማፈናቀል በተቀራመቱት የከተማ ቦታዎች የጦፈ ንግድና በጨበጥከው የመንግሥት ሥልጣን በተመቻቸ ዘረፋ የገነቡት የንግድ ድርጅቶች፤ ህንጻና ከአለም አቀፍ አበዳሪዎች በተገኘ ገንዘብ የተሠሩ መንገዶች እንዴት የዲሞክራሲና የልማት መሠረት ሊሆኑ ይችላሉ ?
  • በምስሌኔዎችህ የምታስተዳድራቸው ብሄር ብሄረሰቦች የእጅ አዙር አገዛዝህን አንፈልግም በስማችን አትነግድብን እያሉህ ከትውልድ መንደርህ ጀምሮ ነፍጥ እያነገቡ እያየህና እየሰማህ ስለየትኛው የብሄር ብሄርሰብ እኩልነትና ነጻነት ነው የምትደሰኩረው?
  • ከውጭ በተገኘ የመሳሪያና የትጥቅ ድጋፍ የሰሜኑን የአገራችንን ክፍል ለማስገንጠል 17 አመት ሙሉ አገራችንን የወጋህ አንተው ሆነህ እያለህ ከየትኛው የአገር መበታተን አደጋ ነው እንደታደከን መላልሰህ እየነገርክ የምትደነቁረን ?
  • የኢትዮጵያ ታሪክ የመቶ አመት ታሪክ ነው በማለት የኩራት መሠረታችንን ስታፈርስ ከኖርክና በተለይ አዲሱን ትውልድ ታሪክ አልባ አድርገህ ካበቃህ ቦኋላ በየትኛው ዘመን ወደነበረው የሥልጣኔ ማማ ልትመልሰን ነው ባለ አዲስ ራዕይ የሆንክልን ?
” ጆሮ ለባለቤቱ …” እንዲሉ እነዚህ ጥያቄዎች ሲነሱ ወያኔ እንደለመደው ” የቀድሞ ሥርዓት ናፋቂዎች ፤ጸረ ሠላምና ጸረ ልማት ሃይሎች ፤ የብሄር ብሄረሰብ መብት የማይዋጥላቸው የአማራ ትምክህተኞች ፤ የኤርትራ የጥፋት መልዕክተኞች ፤ ሽብርተኞች” የሚሉ አራምባና ቆቦ የሆኑ መልሶችን እንደሚሰጥ መጠራጠር አይቻልም። የወያኔ ታሪክ ሁሌም የክህደት፣ የውሸት፣ የማስመሰል እና የማጭበርበር መሆኑን ሁሉም ህዝብ ጠንቅቆ የሚያውቀው ነው።
ግንቦት 7 የፍትህ የነጻነትና የዲሞክራሲ ንቅናቄ ወያኔ በየአመቱ የሚያከብረው ግንቦት 20 ደርግ የንጉሰ ነገሥቱን ዘውድ ገርስሶ ሥልጣን ከተቆናጠጠ በኋላ ተገፍቶ ከስልጣን እስከወደቀበት ዕለት ድረስ ያከብረው ከነበረው መስከረም 2 የተለየ ነው ብሎ አያምንም። ወያኔ ደርግን በሃይል ከሥልጣን የገረሰሰበትን ግንቦት 20ን በመስከረም 2 እንደተካው ሁሉ ህዝብ ለነጻነቱ የጀመረው ትግል ተጠናክሮ ወያኔን በሃይል ከሚቆጣጠረው ሥልጣን ሲያሽቀነጥረው የግንቦት 20 በአከባበርም አብሮት እንደሚያከትም ነጋሪ አያሻውም። ህዝብ በዘር በተሰባሰቡ ባንዳዎች መዳፍ ውስጥ የገባበትን ዕለት ፤ብሄራዊ ኩራቱንና ማንነቱን የተነጠቀበት ቀን፤ በገዛ አገሩ የበይ ተመልካች የሆነበትን የወያኔ የድል ቀን መልሶ የሚዘክርበት ምክንያት አይኖረውም። ወያኔ በየአመቱ የሚያከብረው ግንቦት 20ንና የድል ፍሬዎቹን ህዝብ እንደማይጋራው ግንቦት 7 ቀን 1997 ህዝብ በግልጽ ተናግሯል።
የግንቦት 7 የፍትህ የነጻነትና የዲሞክራሲ ንቅናቄ ዋና የትግል አላማ ነጻነት ናፋቂው የኢትዮጵያ ህዝብ በነቂስ ወጥቶ ግንቦት 7 ቀን 1997 ያስመዘገበውን ድል መልሶ እንዲቀዳጅ ማድረግ ነው። ስለዚህም ሰላም ፍትህና እኩልነት የተጠማኸው ሰፊው የኢትዮጵያ ህዝብ ፤ በገዛ አገርህ ሠርቶ የመኖር ተስፋህ ተሟጦ ለስደት በባህርና በየብስ ለማምለጥ እያኮበኮብክ ያለህ ወጣት፤ በየስፍራው የተቀጣጠለውን ህዝባዊ አመጽ ለማፈን እየተላክ ከገዛ ወገንህ ጋር ደም እየተቃባህ ያለኸው ወታደር፤ የገዥዎችን የሥልጣን ዕድሜ ለማራዘም በፖሊሲ ሃይል፤ በደህንነትና ጸጥታ ጥበቃ የተሰማራሃው ወገን ፣ ግንቦት 7 የጀመረው የነጻነት ትግል እናንተንም ጭምር ከአፈናና ከጉስቁልና ነጻ ለማውጣት ስለሆነ ዛሬውኑ ትግሉን ትቀላቀሉ ዘንድ ድርጅትህ ግንቦት 7 ወገናዊ የትግል ጥሪውን ያቀርብልሃል።
የግንቦት 20 ድል መቀሌ ውስጥ የአፓርታይድ ሠፈር የገነቡ የሥርዓቱ ቅምጥሎች ፤ አዲስ አበባ ውስጥ የመቀሌ ሠፈር ተብሎ የተሰየመውን ህንጻ ያሳነጹ ሌቦች ፤ በጋምቤላ፤ በአፋር፤ በቤነሻንጉልና ማሃል ኦሮሚያ የእርሻ መሬት እየዘረፉ የተቀራመቱ ህወሃቶችና የጥቅም ተካፋዮች እንጂ የሰፊው የኢትዮጵያ ህዝብ አለመሆኑን በተግባር ለማሳየት ሁላችንም እጅ ለእጅ ተያይዘን የወያኔን የአገዛዝ ሥርዓት ከላያችን ላይ አሽቀንጥረን ለመጣል ከምንጊዜውም በላይ መነሳት ያለብን ጊዜው አሁን ነው።
ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ!!!

ግንቦት 20…ከአንድ አምባገነን ወደ ሌላ አምባገነን!

May 29/2014
 ነገረ ኢትዮጵያ

ባለፉት ሁለት አስርት አመታት ዓለም በቴክኖሎጅና በኢኮኖሚው በእጅጉ የተለወጠበት፣ ለሰብአዊ መብትና ዴሞክራሲ መከበር በር የተከፈተበት፣ በሉላዊነት ምክንያት የዓለም ህዝቦች ከመቼውም ጊዜ በላይ የተሳሰሩበትና ለመተሳሰርም እድል የተገኘበት ጊዜ ነው፡፡ ይህን ነጻነታቸውን ካገኙ 20 አመት ያልበለጣቸው አገራትም ነጻነታቸውን በአግባቡ ተጠቅመውበት ህዝባቸውን ለመቀየር ችለዋል፡፡ ለአብነት ያህልም ደቡብ አፍሪካን መጥቀስ ይቻላል፡፡ ከደቡብ አፍሪካ በተጨማሪ እ.ኤ.አ በ1991 የራሷን አስተዳደር የመሰረተችውና ዓለም እውቅና ያልሰጣት ሶማሊ ላንድ እንኳ በፍትሃዊ ምርጫ፣ በሰላም መሪዎቿን በመምረጥ በአፍሪካ ቀንድ ብቸኛዋና በዓለም መንግስታት በአገርነት እውቅና ላገኙትም በምሳሌነት እየተጠቀሰች ትገኛለች፡፡

በሌላ በኩል አገራችን ኢትዮጵያ ረዥም የነጻነትነት እድሜ ያላት ብትሆንም አሁን ላይ ቀደም ብላ ከቅኝ አገዛዝና ጭቆና ነጻ እንዲወጡ ካገዘቻቸው የአፍሪካ አገራት ባነሰ ሁኔታ ውስጥ ትገኛለች፡፡ ለዚህ ኋላ ቀርነቷ ደግሞ ባለፉት 23 አመታት ያገኘቻቸውን አጋጣሚዎች ገዥዎቹ መጠቀም ባለመቻላቸው እንደዋነኛ ምክንያት የሚጠቀሱ ናቸው፡፡ በአሁኑ ወቅት ስልጣን ላይ የሚገኘው ህወሓት/ኢህአዴግ መጀመሪያ ላይ የዓለምን ማህበረሰብ ቀልም ለመሳብ መሰረታዊ ለውጦችን አድርጎ የነበርና እነዚህንም በህገ መንግስቱ ላይ ያስቀመጠ ቢሆንም ሲተገብራቸው ግን አልታየም፡፡ በተለይ ስልጣን ከያዘ ከአራትና አምስት አመት በኋላ ወደ ነበረበት ‹‹ግራ ዘመምነት›› በመመለስ በህገ መንግስቱ የፈቀዳቸውን መብቶች እንደገና በግልጽ ሲደፈጥጥ ተስተውሏል፡፡

ህወሓት/ኢህአዴግ ስልጣን እንደያዘ በመቶዎቹ የሚቆጠሩ የህትመት ሚዲያዎች ፈቃድ አግኝተው ለህዝብ መረጃ በማድረስ ላይ የነበሩ ቢሆንም ሚዲያ ህዝብን ማንቃቱን ያልወደደው ገዥው ፓርቲ እየቆየ አፈናውን ተያይዞታል፡፡ በመሆኑም በርካታ ሚዲያዎች ወደ አደባባዩ ወጥተው እንደገና ለመዘጋት ተዳርገዋል፡፡ ጋዜጠኞች ታስረዋል፤ እየታሰሩም ነው፡፡ በጫናው ምክንያት ተሰደዋል፤ እየተሰደዱም ይገኛሉ፡፡ በተለይ ህወሓት/ኢህአዴግ የደነገጠበት የ1997 ምርጫን ተከትሎ በርካታ የህትመት ሚዲያዎች ሲዘጉ፣ ጋዜጠኞች በአገር ክህደት ወንጀል ተከሰው ዘብጥያ ወርደዋል፡፡ በርካቶቹ ተሰደዋል፡፡ ይህን ሁሉ ጫና ችለው ለህዝባቸው መረጃ ለማድረስ የጣሩት እንደ እስክንድር ነጋ፣ ርዕዮት ዓለሙና ውብሸት ታየ ያሉት ደግሞ በአሁኑ ወቅት ‹‹አሸባሪ›› ተብለው እስር ቤት ውስጥ ይገኛሉ፡፡ በቅርቡ ከዞን ዘጠኝ አባላት ጋር የታሰሩት ሶስት ጋዜጠኞች ስርዓቱ ባለፈው 23 አመት ያደበረውን የአፈና ባህል አጠናክሮ እንደቀጠለ የሚያሳይ ሆኗል፡፡

በተመሳሳይ የመደራጀት፣ የመሰብሰብና ሌሎች መብቶች ባለፈው 23 አመት ህገ መንግስቱ ላይ ከሰፈረው በተቃራኒ እየተደፈጠጡ ቀጥለዋል፡፡ በአንድ ወቅት ጠንካራ ተቃዋሚ እንዳጣ በግልጽ ሲናገር የነበረው ገዥው ፓርቲ ከ1997 በኋላ ለተቃዋሚዎች መፈናፈኛ ላለመስጠት በርካታ ፀረ ህገ መንግስታዊና አፋኝ አዋጆችን አጽድቆ በህግ መሳሪያነት እየገዛ ቀጥሏል፡፡ ባለፉት 8 አመታት ህገ መንግስቱ የፈቀደው ሰላማዊ ሰልፍ በገዥው ፓርቲ ተከልክሎ ቆይቷል፡፡ በአሁኑ ወቅትም በተቃዋሚዎች ግፊት የተጀመሩ የተቃውሞ ሰልፎች በገዥው ፓርቲ የደህንነትና የፖሊስ ኃይል የሚጠበቅባቸውን ያህል ሚና እንዳይወጡ ተከልክለዋል፡፡
ተቃዋሚ ፓርቲዎች ህጋዊ በሆነ መንገድ የስብሰባ አዳራሽና ሌሎቹንም ለትግሉ ሊያገኙዋቸው የሚገቡ አገልግሎቶችን እንዳያገኙ ገዥው ፓርቲ ጠንክሮ እየሰራ ይገኛል፡፡ ይህም የፖለቲካ ኃይሎች በሰላማዊ ትግሉ ተስፋ እንዲቆርጡና ሌሎች ሰላማዊ ያልሆኑ አማራጮችን እንዲከተሉ እስከማድረግ ደርሷል፡፡ ከተቃዋሚ ፓርቲዎች በተጨማሪ ሲቪክ ማህበራትና ሌሎችም ለህዝብ ጥቅም የሚቆሙ የህዝብና የመንግስትን ተቋማት አንድም ለራሱ መጠቀሚያ ማድረጉ ከዚህም በተጨማሪ ስራቸውን እንዳይተገብሩ መሰናክል መፍጠሩ ህዝብ ድምጹን የሚያሰማበት መድረክ እንዲያጣ ተደርጓል፡፡

ሚዲያ፣ ተቃዋሚዎችና ተቋማት በመዳከማቸው ገዥው ፓርቲና ፖለቲከኞቹ ያለምንም ተጠያቂነት የአገሪቱን ሀብት ተጠቅመውበታል፡፡ በመሆኑም ባለፉት 23 አመታት ከአገርና ከህዝብ ጥቅም ይልቅ ግለሰባዊ፣ የፓርቲና ቤተሰባዊ ጥቅምን ማጋበስ የስርዓቱ ባህሪ እንደሆነ ታይቷል፡፡ በዚህም ምክንያት ህዝብ ከአገሩ ኢኮኖሚ የሚገባውን እንዳያገኝ ተደርጓል፡፡ በሙስና፣ በስርዓቱ ደጋፊነትና በመሳሰሉት ካልሆነ ህጋዊ መንገድን የያዘ ዜጋ ስራ መስራት ባለመቻሉ አገሪቱ ማግኘት የሚገባትን ኢኮኖሚያዊ ጥቅም እንዳታገኝ ተደርጋለች፡፡ ምሩቃን፣ ከስርዓቱ ጋር ግንኙነት የሌላቸው ምሁራንና ሌሎችም የህብረተሰብ ክፍሎች ህጋዊ በሆነው መንገድ ጥቅም ባለማግኘታቸው ለስደት፣ ለድህነት ተዳርገዋል፡፡

በተቃራኒው ግን ይህ ያፈጠጠ እውነታ ተገልብጦ የግንቦት 20 ፍሬዎች እየተባለ ህዝብ ባዶ ፕሮፖጋንዳ ይጋታል፡፡ በመሆኑም ገዥው ፓርቲ እንደሚለው ግንቦት 20 የኢትዮጵያ ህዝብ ነጻነቱን ያገኘበት ሳይሆን ከአንዱ አምባገነን ስርዓት ወደ ሌላ መልኩን የቀየረ አምባገነን ስርዓት የተሸጋገርንበት መሆኑን ልብ ማለት ያስፈልጋል፡፡ እናም ያለንበትን ትክክለኛ መልክ ሸፋፍኖ ስለሌለ ለውጥ ህዝብን በፕሮፖጋንዳ ከማደንቆር ይልቅ ወደ ትክክለኛ የህዝብ ተጠቃሚነትና ነጻነት የሚያደርሰውን መንገድ ይዞ ለአዲስ ለውጥ መታገል እንደሚገባ መገንዘብ ይገባል፡፡

Thursday, May 29, 2014

በቡራዩ ኦሮሚያ ፖሊስ የታፈነው አስራት አብርሃም “ፍትህ እፈልጋለሁ” አለ

May29/2014
(ኢ.ኤም.ኤፍ) ባለፈው ሳምንት በቡራዩ የኦሮሚያ ፖሊስ ከታሰረ በኋላ፤ ፖሊስ “የት እንዳለ አላቅም” ማለቱ ይታወሳል። በወቅቱ ታስሮ የነበረው አስራት አብርሃም፤ አሁን በህይወት መኖሩ ተረጋግጧል። ከአገር ቤት ባስተላለፈውም መልእክት “ፍትህ እፈልጋለሁ” የሚል አጭር ጽሁፍ ልኳል። ከዚህ የሚከተለው ነው።
Asrat Abraha
Asrat Abraha
ቡራዩ ከተማ ፖሊስ ጣቢያ “አስራት አብርሃም የሚባል ሰው አላሰርኩም” እያለ ሲምል ሲገዘት ሰንብቶ በኋላ ከየት አምጥቶ ወደ ፍርድ ቤት ሊያቀርበኝ እንደቻለ በህግ መጠየቅ እፈልጋለሁ። አንድን ሰው ወንጀል ካለበት አስሮ ወደ ፍርድ ቤት ማቅረብ እንጂ ይዞ መሰወር ከባድ ወንጀልና የሰብአዊ መብት ጥሰት መሆኑ መታወቅ አለበት።
እኔ ደግሞ እስረኞች ለመጠየቅ በሄድኩበት ፖሊስ ጣቢያ ነው የተያዝኩት፤ ከፖሊስ ጣቢያ አውጥተው በማይታወቅ ቦታ ያሰሩኝ፤ ቤተሰብና የፓርትዬ የአመራር አባላት እኔን ለመጠየቅ ሲመጡ ደግሞ “እኛ ጋ የለም፤ አላሰርነውም” በማለት የፈለጉትን ሰው ማሰርና ደብዛውን ማጥፋት እንደሚችሉ ያሳዩበት አጋጣሚ ነው። በዚህ ላይ የፖሊስ ጣቢያው ኮማንደር ተስፋስላሴ ነገራ በራሱ ቢሮ ውስጥ እንድደበደብ አድርጓል። ይሄ ነገር በእኔ ላይ የተጀመረ ነው ብዬ አላስብም፤ እንደሚታወቀው በዚህች ሀገር በተለይ በኦሮሚያ ክልል ሰዎች በየጊዜው ደብዛቸው እንደሚጠፋ ነው የሚነገረው፤ በየከተማው የምናየው “የአፈልጉን” ማስታወቂያዎችም አለምክንያት አልበዙም። ምን ይታወቃል በመንግስት የድህንት ኃይሎች ታፍነው ደብዛቸው እንዲጠፋ ተደርጎ ቢሆንስ!
ስለዚህ እኔ ይህን ጉዳይ ከዳር ለማድርስና በዚያም በሀገሪቱ ያሉት የህግና የሰብአዊ መብት ተቋማት ለመፈተሽ በህግ ሊሄድበት እያሰብኩ ነው። በመሆኑም የህግ ድጋፍ የሚያደርግልኝ ግለሰብም ሆነ ተቋም እፈልጋሁና ሞያውና እድሉ ያላችሁ ሁሉ ሞያዊ ድጋፍ እንድታደርጉልኝ እጠይቃለሁ፤ ይሄ ነገር ዝም ብለን ካፍነው በዚሁ ሊቆም አይችልም፤ በሌሎችም ላይ ሊቀጥል የሚችል ጉዳይ ነው። በአግባቡ መወገዝና በሰብአዊ ተቋማት ሁሉ መታወቅ አለበት የሚል እምነት ነው ያለኝ፤ እኔ ደግሞ አቅሜን የፈቀደው ሁሉ ይሄ ነገር ዳር ለማድረስ ወደኋላ አልልም። በዚህ ጉዳይ ላይ ከጎኔ የሚቆሙ ወገኖች እንደሚኖሩ ተስፋ አደርጋለሁ።

በደብረማርቆስ ከተማ ከ400 በላይ ቤቶች በዶዘር እየፈረሱ ነው

May 29/2014

በዛሬው ዕለት ደብረ ማርቆስ ከተማ ውስጥ ህገ ወጥ ናቸው የተባሉ ቤቶች በዶዘር እየፈረሱ እንደሚገኙ ከቦታው የደረሰን መረጃይጠቁማል፡፡ በተለይ ቦሌ እየተባለ የሚጠራው ሰፈር የሚገኙ ቤቶች በዛሬው ዕለት እየፈረሰ እንደሚገኝና ህዝብ ይቃወማልበሚል ቡችሌ፣ ሚሊሻ፣ ህዝባዊና ልዩ ፖሊስ ከፍተኛ ጥበቃ እያደረገ እንደሚገኝ የነገረ ኢትዮጵያ ምንጮች ተናግረዋል፡፡(ደብረማርቆስ ከተማ)ይህ ቦሌ ተብሎ የሚጠራው ሰፈር ትናንት ሊፈርስ የነበረ ቢሆንም በግንቦት 20 ምክንያት እንደታለፈ ተገልጾአል፡፡

ደብረ ማርቆስ ውስጥ ቤቶችን ማፍረስ የተጀመረው ግንቦት 18ና 19/2006 ዓ.ም ሲሆን ቀበሌ አራት (4) በተለይም ሞንቃተብሎ በሚጠራው ሰፈር 400 ያህል ቤቶች እንደፈረሱ ታውቋል፡፡ በተመሳሳይ ቦሌ የተባለው ሰፈር እንዳይፈርስ በተደረገበትበትናንትናው ቀን ከ23 አመት በላይ ግብር ሲከፈልበት የኖረ የአንድ ግለሰብ ቤት መፍረሱም ታውቋል፡፡

 አፍራሽ ግብረሃይሉየቤቱን ጣራ ካፈረሰ በኋላ ግለሰቡ ለ23 ዓመት ግብር ሲከፍልበት የነበረ መሆኑንበመገለጹግድግዳው ብቻ እንደቆመ ወደአቤቱታ መመራቱን ምንጮች ጨምረው ገልጸዋል፡፡

ደብረ ማርቆስ ውስጥ አብዛኛዎቹ ቤቶች ከ1997 ጀምሮ የተሰሩ ሲሆኑ አብዛኛዎቹ ቤቶች አርሶ አደሮች በአሁኑ ወቅት ወደከተማ በተከለለው መሬታቸው ላይ የሰሯቸው እንደሆኑ ታውቋል፡፡ ‹‹የአርሶ አደሮቹ መሬቶች ወደ ከተማ ሲከለሉ መንግስትተለዋጭ ወይንም ካሳ የመስጠት ግዴት የነበረበት ቢሆንም በአሁኑ ወቅት በህገ ወጥነት እያፈረሰ እያፈረሰ ይገኛል›› ያሉት አንድየከተማዋ ነዋሪ እርምጃው ህገ ወጥ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

Ethiopia holds editor-in-chief without charge – CPJ

May 29,2014

New York, May 28, 2014–The Committee to Protect Journalists condemns the detention of a journalist without charge since Monday and calls on Ethiopian authorities to release him immediately. An Ethiopian court on Tuesday extended by 14 days the pre-trial detention of Elias Gebru, according to news reports.

Ethiopia’s federal police in the capital, Addis Ababa, summoned Elias, editor-in-chief of the independent news magazine Enku, for questioning in connection with a column published in his paper, according to news reports. The Awramba Times reported that the column discussed a monument recently erected outside the capital in honor of ethnic Oromos massacred in the 19th century by Emperor Menelik’s forces. The monument has ignited divisions between some Oromos and supporters of the emperor’s legacy.

Local journalists said authorities were attempting to link the paper’s publication to the deadly clashes between Oromo student protesters and security forces last month. Ethiopian authorities claimed eight protesters were killed in the violence, while news outlets and human rights groups cited witnesses as saying that security forces killed more than a dozen protesters.

At least 17 other journalists are in jail in Ethiopia in connection with their journalistic work, according to CPJ research. Only Eritrea holds more journalists behind bars in Africa, CPJ research shows.

“The detention without charge of Elias Gebru is the latest move by the Ethiopian government to tighten the noose on the country’s independent press,” said CPJ Africa Advocacy Coordinator Mohamed Keita. “We call on authorities to release Elias immediately and to stop arresting journalists as a means to quell information and debate.”

Elias is being held at the Maekelawi detention center, according to local journalists.

In 2008, thousands of copies of Enku magazine were seized by Ethiopian authorities in connection with the paper’s independent coverage of the trial of a pop singer who had been critical of the government, according to news reports. The copies were later returned.

በግንቦት7 ስም የተከሰሱ ጥፋተኞች ተባሉ

May 28/2014

 ኢሳት ዜና :-የግንቦት7  ህዝባዊ  ሃይል የአመራር አባልና የቀድሞው የአማራ ክልል ወጣቶች ሊቀመንበር ዘመነ ካሴን ጨምሮ 10 ወጣቶች በተከሰሱበት የሽብረተኝነት ወንጀል ጥፋተኞች ተብለዋል።

ሰንደቅ እንደዘገበው አቃቢ ህግ ተከሳሾች ከግንቦት ሰባት ድርጅት ጋር በህቡዕ ግንኙነት በመፍጠር፤ ኤርትራ ድረስ በመሄድ የጦር ስልጠና በመውሰድና ተልዕኮ ተቀብለው በመምጣት በጦር መሳሪያ የታገዘ የሽብር ወንጀል ሊፈፅሙ ነበር ብሎአል።

የፌዴራሉ  ከፍተኛ  ፍርድ  ቤት  4ኛ  ወንጀል ችሎት ግንቦት 19 ቀን 2006 ዓ.ም ተከሳሾች እንዲከላከሉ ሲበይን፣ ዐቃቤ ሕግ ተከሳሾቹ ህገ-መንግስቱንና ህገ መንግስታዊ ስርዓቱን በሃይል ለመናድ በማሴር ከጎረቤት አገሮች ስልጠና በመውሰድ፤ የጦር መሳሪያ ግዢን በመፈፀምና የሽብር እቅድ በማውጣት በተለይም በአማራ ክልል በሚገኙ ባለስልጣናት ላይ ግድያ ለመፈፀም አሲረው መንቀሳቀሳቸውን ጋዜጣው ዘግቧል።አንደኛ ተከሳሽ ዘመነ ካሴ “በዐቃቤ ህግ ክስ ስር ከቀረቡበት ክሶች መካከል ኤርትራ ሄዶ የጦር ስልጠና ወስዶ መምጣቱን ፣ መንግስት አሸባሪ ብሎ ከሰየመው የግንቦት ሰባት ድርጅት አመራሮች በተለይም ከጄኔራል ተፈራ ማሞ እና ከአቶ አንዳርጋቸው ፅጌ ጋር በአካል ተገናኝቶ የሽብር ተልዕኮ መቀበሉን፣  በፌስ ቡክና በተለያዩ የኢንተርኔት ግንኙነቶች ከሌሎች አባላቱ ጋር በመገናኘትና መልዕክት በማስተላለፍ ተጠያቂ ” መሆኑን ገልጿል።

ከ1ኛ እስከ 5ኛ ተከሳሾች ማለትም  ዘመኑ ካሴ፣  አሸናፊ አካሉ፣  ደናሁን ቤዛ፣  ምንዳዬ ጥላሁን እና  አንሙት ይሄይስ በማህበራዊ ድረ-ገፆች ግንኙነትን በመፍጠር ተልዕኮና ትዕዛዝን በመቀበልና የሽብር ጥቃት ለመፈፀም የሚረዳቸውን የመሳሪያ ግዢ እንዲከናወን ማድረጋቸውን አቃቢ ህግ ገልጿል።

“በአንፃሩ ደግሞ ከ6ኛ እስከ 9ኛ ድረስ ያሉት ተከሳሾች ደሳለኝ አሰፋ፣  ምክትል ኢንስፔክተር ሙልዩ ማናዬ፣  ጠጋው ካሳና  ይህአለም አካሉ በሽብር እንቅስቃሴው ውስጥ አውቀውም ይሁን ሳያውቁ እርዳታ ሰጥተዋል” የሚለው አቃቢ ህግ፣ ከተከሳሾች መካከል  10ኛ ተከሳሽ ሆና ጉዳዩዋን ስትከታተል የቆየችው ሙሉ ሲሳይ በነፃ እንድትሰናበት ተደርጓል።
ተከሳሾች  ከመጪው ሰኔ 17 እስከ 20 ቀን 2006 ዓ.ም በተከታታይ የመከላከያ ማስረጃዎቻቸውን በፌዴራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት 4ኛ ወንጀል ችሎት እንዲያቀርቡም መታዘዛቸውን ጋዜጣው ዘገባውን አጠቃሏዋል። ዘመነ ካሴ የተከሰሰው በሌለበት ነው::

ውሸት ሲደጋገም ዕውነት እንዳይመስል፣ ስንናገርም ሆነ ስንጽፍ ልንጠነቀቅ ይገባል!

May 28/2014
ተክሌ የሻው
ዛሬ ከአገራችን አውራ ችግሮች መካከል ዋናው፣ የተደጋገሙ ውሸቶች ዕውነት የመሰሏቸው ቡድኖች የሚያጎኑት በጥላቻ ላይ የተመሠረተ የዘር ፖለቲካ እና አንድን ነገድ፣ በኢትዮጵያ ተፈጠሩ ለሚባሉ ችግሮች ሁሉ ተጠያቂ የሚያደርገው ነው ብዬ አምናለሁ። አይደለም የሚለኝ ከመጣም የሚለውን ለመስማት ዝግጁ ነኝ። የተደጋገሙ ውሸቶች ሀውልት ሲያስቆሙ እያዬን ነው። የአኖሌን ሀውልት ለአብነት መመልከት ነው። የከተሞችን ስም ሲያስለውጥ እያዬን ነው። አዲስ አበባን ፊንፊኔ፣ ናዝሬትን አዳማ፣ ደብረዘይትን ቢሸፍቱ፣ አዋሣን ሀዋሣ፣ ዝዋይን —ሌላ ሌም አለ። ወደ ኋላ እንይ ከተባለ ወለጋ፣ ቢዛምን፣ ኢሉባቡር እናርያ፣ አርሲ ፈጠጋር፣ ወሎ ላኮመልዛ ወዘተ ማለት ይቻላል። ይህ ግን አይጠቅምም። የኋሊት ጉዞ ያስከትላል። ይህ ደግሞ ወደ አንጋዳ በራስ ኃይል መውደቅን ያመጣል። ይህ ሁሉ የሆነው ውሸት በመደጋገሙ ነው።
ለዚህ መነሻ ሀሳብ የዳረገኝ ተደጋጋሚ ውሸተቶችን በጋዜጠኞችና በፖለቲከኞች ሲራገብ በማዬቴና በመስማቴ ነው። የትኛው ዐማራ በተናጠልም ሆነ በቡድን« የዐፄዎቹ ሥርዓት እንዲመለስ» እንደሚታገል መረጃ ሳይቀርብ፣ ዐማራውን በድፍኑ ያለፈው ሥርዓት ናፋቂ ነው ብሎ መፈረጅ ተገቢ ካለመሆኑም በላይ ውሸት ስለሆነ የወሬውን አባቶች ለመሞገት ነው። ፍረጃው ኢትዮጵያውያን ለአንድነት ለሚያደርጉት ትግል ዐማራው ዋነኛ ችግር እንደሆነ ማሳዬት መሆኑ የአፈራረጁ ሁኔታ ቁልጭ አድርጎ ያሳያል። የዚህ የመጨረሻ ግብ ደግሞ፣ ከወዲሁ ዋስ ጠበቃ የሌለውን ዐማራ በአውላላ ሜዳ ላይ ማንም ስጥ(ስጦ) እንደበላ አህያ ከመወገር አልፎ፣በኢትዮጵያ ምድር የመኖርና የመሥራት መብቱን ተገፎ በስቃይ ላይ የሚኖረውን ገበሬ፣ «ከነፍጠኝነት፣ ትምክህተኛ፣ገዥ፣ ጨቋኝ መደብና ብሔረሰብነት » ከሚሉት የማዋረጃና አንገት የማስደፊያ ስሞች በተጨማሪ ፣ለኢትዮጵያ አንድነት ፀር ነው ወደሚል አዲስ ታርጋ እየተለጠፈለት መሆኑን አእምሮዬ ስለነገረኝ ነው።Tekle Yeshaw Ethiopian author and politician
የነገሩ ፈልሳሚ ዶ/ር መረራ ጉዲና ናቸው። እርሳቸውም «የኢትዮጵያ ፖለቲካ ምስቅልቅል ጉዞና የሕይዎቴ ትዝታዎች» በሚል ርዕስ ባሳተሙት መጽሐፋቸው፣መደምደሚያ ላይ አንባቢያቸው አጽንዖት ሰጥተው እንዲመለከቱላቸው በሰጡት የማሳረጊያ ሀሳብ ላይ እንዲህ ብለዋል። “ በመጽሐፌ መደምደሚያ ላይ ለታሪክም፣ ለሕዝቡም አስቀምጨ ማብቃት የምፈልገው መሠረታዊ ነጥብ፣አብዛኛው የትግሬ ልሂቃን ሥላጣን ላይ የሙጥኝ እስካሉ ድረስ፣ አብዛኛው የአማራ ልሂቃን በአፄዎች ዘመን የነበረውን የበላይነት መልሸ አገኛለሁ ብሎ የሚጋፋውን የሕልም ፖለቲካ እስካልተዎ ድረስ፣ ብዙኃኑ የኦሮሞ ልሂቃን ኦሮሚያን ለብቻ የማውጣቱን ሕልም እስካልተዎ ድረስ ሀገራችን ከአደጋ ቀጠናና ቀውስ የምትወጣ አይመስለኝም።“ በማለት የዐማራውን ልሂቃን በሞጭ የዐፄዎች ሥርዓት ናፋቂ አድርገው ስለውታል። ስለኦሮሞዎቹ ከእርሳቸው በላይ ኦሮሞ ልሆን ስለማልችል፣ በኦሮሞ ልሂቃን ላይ ያቀረቡትን ትችት ውሸት ነው አልልም። እርሳቸውም የዚሁ አካል ናቸውና። ለዚህም ነው «የኦሮሞ ብሔራዊ ኮንግረስ» የሚል ፓርቲ መሥርተው የብሔር ፖለቲካውን ከሚያጦዙት በኦሮሞ ስም ከተደራጁት 12 የፖለቲካ ድርጅቶች አንዱ የሆኑት።
ስለትግሬዎች የተነሳው ሥልጣንን የሙጢኝ ብሎ የመያዙ ጉዳይ፣ ጥያቄ የሚያስነሳ አይመስለኝም። ምክንያቱም 17 ዓመት በትጥቅ ትግል፣ ዐማራውን በጠላትነት ፈርጀው፣ ለትግራይ የበላይነት ሞተው፣ ቆስለው፣ ሌሎች ብሔርተኞችን አሰልፈው ለሥልጣን የበቁት ሥልጣን ስለሚወዱና በሥልጣን የሚገኘውን ጥቅም ስለሚያውቁ ነው። ሥልጣን መውደዳቸው በራሱ ወንጀልም ኃጢያትም አይደለም። ወንጀልና ኃጢያት የሚሆነው ሥልጣንን መከታ በማድረግ የሚሠሩት አገርና ትውልድ አጥፊ የሆነው ፖሊሲያቸው ነው። ከፋፋይነታቸው፤ ዘረኝነታቸው፣ ሁሉን ለትግሬ ብቻ ማለታቸውና የኢትዮጵያን ታሪክ መካዳቸው ነው። ዐማራን በዘር ጠላትነት ፈርጀው የዘር ማጥፋትና የዘር ማጽዳት ወንጀል መፈጸማቸው ነው። የኢትዮጵያን ብሔራዊ ጥቅም ለባዕዳን አሳልፈው በመስጠታቸው ነው። ወዘተ ወዘተ–
አያሌ ዘመን ተጉዘው፣ ስንት መከራ አሳልፈው፣ሕይዎት ገብረውና ሺበሺ ገድለው፣ሕይዎት ነሰሺ፣ ሀብት አደላዳይና ነጣቂ የመሆንን፣ ኃይልን በፈለጉት ቦታና ጊዜ የመጠቀም መብትን ከሚያጎናጽፍ የሥልጣን ማማ ላይ የወጡ ሰዎች፣ ተገደው ካልሆነ ወደው ሊለቁ እንደማይችሉ ግልጽ ነው። ይህ ደግሞ የፖለቲካል ሣይንስ ተማሪ ፣ያውም ፕሮፌሰር ነኝ ለሚል ሰው የሚገድና ብዙ የሚያመራምር ጥያቄ አይደለም። በሠራችሁት ወንጀል አትጠየቁም፣ ብቻ ሥልጣኑን ልቀቁ እንኳ ቢባሉ፣ ወደው አይለቁም። ሥልጣን በመልቀቅ የሚያጡት የኢኮኖሚ፣ የፖለቲካና የማኅበራዊ የበላይነትን እንዳለ በቅጡ ያውቃሉ ። ይህም በመሆኑ ወደው ሥልጣን አይለቁም። ሥልጣን ደግሞ እንኳን በኋላቀር አገሮች ቀርቶ ፣ የሰለጠኑ ናቸው በሚባሉትም የሚነጠቅ እንጂ ወዶ ሥልጣኑን የሚሰጥ ግለሰብም ሆነ ድርጅት የለም። ስለሆነም የትግሬ ልሂቃንን ከሥልጣን ለማውረድ በሚያመቸው መንገድ ለመንጠቅ መዘጋጀት እንጂ፣ ይሰጡናል፣ ሥልጣን ሙጢኝ ብለዋል ብሎ ማልቀስ ከዓለም ነባራዊ ሁኔታ ውጭ ነው።
ወያኔዎችን (በዶ/ር መረራ አባባል የትግሬ ልሂቃኑ) ለምኒልክ ቤተመንግሥት ካበቋቸው ዋና ዋና ምክንያቶች አንዱ ኦነግ ለወያኔ እጁን ሰጥቶ የሽግግር መንግሥት እንዲመሠረት ያደረገውና ኢትዮጵያን በመናድ የተጫወተው ጉልህ ሚና የሚዘነጋ አይደለም። ኦነግ ከወያኔ ጋር የፈጠረው ሽርክና፣ ኢትዮጵያን አፍራሽ የሆነው ሕገ-መንግሥት ተጠቃሚ እሆናለሁ ከሚል እሳቤ በመነሳት እንደሆነ ማንም የሚስተው አይደለም። ሌሎቹም መሰል በኦሮሞ ስም የተደራጁት ድርጅቶች ከኦብኮ ጭምር ይህን አዲሱን በዘር ላይ የተመሠረተ ፌደራላዊ አደረጃጀትን ከልብ የተቀበሉ ናቸው። ምክንያቱም ክላምፍ የጫናቸውን በኢትዮጵያ ታሪክ የማይታወቅ « ኦሮሚያ» የሚል ግዛት ሰጥቷቸዋልና ነው። አብዛኝዎቹ የኦሮሞ ልሂቃን ከወያኔ ጋር ያላቸው ጠብ የሕዝብ ቁጥራችን ከፍተኛ ነው፤ ክልላችን በተፈጥሮ ሀብት የበለጸገ ነው፣ ስለሆነም ወሣኝ የሥልጣን ቦታዎች በኦሮሞ ልጆች መያዝ አለባቸው ወይም ይገባናል የሚለው የሥልጣን ጥያቄ ነው። ይህ ጥያቄ ደግሞ የወታደራዊ የበላይነት ባለው ወያኔ የሚዋጥ አልሆነም ። እኛ ታግለን፣ እኛ ሞተን፣ ጥንት የማታውቁትንና በሕልማችሁ የነበረ ክልል ኦሮሚያ ብለን ሰጥተን፣ በቋንቋችሁ እንድትስተዳደሩ ፈቅደን፣ ጠላታችን ነው የምትሉትን፣ የእኛም ጠላት የሆነውን ዐማራ እያሳደድን እየፈጀንላችሁ እያለ ከወሣኝ የፖለቲካ ቦታዎች ለቃችሁ አስረክቡን ማለት የማይታሰብ ነው አሏቸው። ስለዚህ ለወያኔዎቹ ሥልጣን መጨበጥ ጉልህ ሚና የተጫዎቱት የኦሮሞ ልሂቃን፣ ይህን የትግሬዎቹ ልሂቃን ከጨበጡት ሥልጣን በውድ ሊለቁ አለመቻላቸውን መገንዘብ አለመቻላቸው፣ ስለሥልጣንና መንግሥት ባህሪያት ባይተዋር መሆናቸውን ከማሳየቱ በላይ፣ የበለጠ ደግሞ “ሥልጣን ሙጢኝ ብለው ይዘዋል“ ይህም የኢትዮጵያ ችግር ነው፣ የሚለው ከቀድሞው የከፋ ጅልነት ነው። ይህ የትግራይ ልሂቃን ሥልጣን ሙጢኝ ብለው መያዛቸው የሚያስገርም ወይም የሚያስደንቅ አይደለም። ሥልጣንን ሙጢኝ ብለው መያዛቸውንም ለኢትዮጵያ ሕዝብ ነጋሪ አያሻውም። የወያኔ ባለሥልጣኖች የደም ዋጋ የከፈልንበትን በሕዝብ ድምፅ ለመልቀቅ ፈቃደኞች እንዳልሆኑ ደጋግመው ከመናገራቸውም በላይ፣ ምርጫ 97 ታሪካዊ ትምህርት አስተምሮን አልፏል። መቼምና ምንጊዜም ቢሆን ወያኔ ወዶ ሥልጣኑን አይሰጥም። ሥልጣን የፈለገ በሕዝብ የተባበረ አመጽ፣ ወይም ወያኔ በመጣበት መንገድ ተጉዞ መንጠቅ አለበት። ይህ ነባራዊ ዕውነት ነው።
ወደተነሳሁበት ፍሬ ነገር ሳልገባ ብዙ አስጓዝኳችሁ። ጉዞዬ ዓላማዬን መሠረት ለማስያዝ በመሆኑ አንባቢዎቼ ትረዱልኛለችሁ ብዬ አስባለሁ። በመረራ ጉዲና ከተነሱት “ ሀገራችንን ከአደጋ ቀጠናና ቀውስ ውስጥ የምትወጣ አይመስለኝም“ብለው ላቀረቡት በከፍተኛ ጥርጣሬ የተሞላ ሀሳብ የችግሩ ምንጮች ናቸው በተባሉት፣ በትግሬ ልሂቃንና በኦሮሞ ልሂቃን ላይ የቀረበውን ትችት ፣በአብዛኛው በመሬት ላይ ያለና አንድ ሁለት ተብሎ ማስረጃ የሚቀርብበት ነው። ይህም የአገራችን ችግር እንደሆነ ይረዳኛል። ሆኖም ስለዐማራው ልሂቃን የቀረበው ትችት ግን ማስረጃ ያልቀረበበት፣ በመሬት ላይም የሚታይ ምንም ነገር የሌለው ስለሆነ ይህን ልሞግት ተነስቻለሁ። ሙግቴን በነቃሽ ልጀምር፣ የለውጥ አቀንቃኝ በነበረው የ60ዎቹ የተማሪዎች እንቅስቃሴም ሆነ፣ በዛሬው የኢትዮጵያ ነባራዊ ሁኔታ የዐፄዎች ሥርዓት ይመለስ ወይም የዐማራ የበላይነት ይንገሥ ያሉ በግለሰብም ሆነ በድርጅት ደረጃ፣ በዶ/ር መረራ እና ባድናቂው አቶ ተመስገን ደሣለኝ ኅሊና ውስጥ ካልሆነ በቀር፣ በምድር ላይ የለም። ስላለፈው የዐፄዎች ሥርዓት መመለስና ለዐማራ የበላይነት የሚታገል የዐማራ ልሂቃን በድርጅት ቀርቶ በግለሰብ ደረጃ አንድ ሰው መጥራት የሚችል ይኖራል ብየ አላምንም። መረጃ የለም። ካለ በተጨባጭ ይቅረብ። አለ ከተባለ በቅድሚያ ዶ/ር መረራ ጉዲና ቀጥሎም ይህን በመረራ ኅሊና ውስጥ ያለ ጉዳይ፣ በገሐዱ ዓለም እንዳለ አስመስለው ለሕዝብ የሌለና በመረጃ ያልተደገፈ «የአባቶቻችን ስንብት» በሚል ርዕስ በዘሐበሻ ደረገጽ ላይ የጻፈው ጋዜጠኛ ተመስገን ደሣለኝ አለን የሚሉት ያለፈ,ው ሥርዓት ናፋቂ፣ የዐፄዎችን ሥርዓት ለመመለስ የሚጥር፣ የዐማራን የበላይነት ለማምጣት የሚታገል ድርጅትና ግለሰብ የዐማራ ልሂቃን የት እንዳለ/እንዳሉና ማን/ እነማን እንደሆኑ ሊነግሩን ይገባል። “ አብዛኛው የዐማራው ልሂቃን በዐፄዎች ዘመን የነበረውን የበላይነት መልሸ አገኛለሁ ብሎ የሚጋፋውን የሕልም ፖለቲካ እስካልተው፣—ሀገራችን ከአደጋ ቀጠናና ከቀውስ የምትወጣ አይመስለኝም፤“ ሲል የደመደመውን ሀሳብ ዕውነት ነው በማለት፣ ተመስገን ሀሳቡን አራግቧል፤ አሰራጭቷል።ይህ ደግሞ ዕውነት የመፈለግ ኃላፊነት ካለው ሙያተኛ የሚጠበቅ አይመስለኝም። ሁልጊዜ ዐማራውን ለምን ዓላማ ተጠቂ እንዲሆን እንደሚፈለግ ምክንያቱ ይገባኛል። ራሱ ዐማራው ለራሱ ኅልውና መቆምና መከራከርን አልደፈረም። በመሆኑም ሁሉም አጥፊነው እያለ ዘመቻ ይከፍትበታል። የዘመቻው ግብም ኢትዮጵያን ማጥፋት መሆኑ ግጽል ነው።
ማንም የኢትዮጵያን ተማሪዎች ንቅናቄ የተከታተለ ሰው በግልጽ እንደሚረዳው፣ ከሁሉም በላይ በውስጡ ያለፉ ሰዎች በቅጡ እንደያሚያውቁት የንቅናቄው ፈር ቀዳጅ የሆነው የ1953 በነመንግሥቱ ንዋይ የተመራው መፈንቅለ መንግሥት መሆኑ ዕውነት ነው። የመፈንቅለ መንግሥቱ መሠረታዊ ዓላማም የዘውዳዊ ሥርዓቱን በዘመናዊ መንገድ ለማሻሻል የሚል እንደነበር ይታወሳል። የዚህ ንቅናቄ መሪዎች ደግሞ የደጃዝማች ገርማሜ የልጅ ልጆች የሆኑት፣ የንዋይ ልጆች ዐማራዎች ናቸው። ኮሎኔል ወርቅነህ ገበዬሁ ዐማራ ነው። ሁሉም ይህ ቀረብን የማይሉ፣ የንጉሡ ባለሟሎችና ባለሥልጣኖች የነበሩና የሥርዓቱ ተጠቃሚዎች ነበሩ። እነርሱ ግን ለዘመናዊነትና ለሕዝብ ሁለተናዊ ጥቅም ለውጥ ያስፈልጋል ብለው በማሰባቸው ለለውጥ ተነሱ። የኋላ ውጤቱ ምን ሊሆን እንደሚችል ማወቅ ባልችልም፣ጥያቄአቸው ዘውዳዊ ሥርዓት ለለውጥና ለመሻሻል በር ይክፈት ሲሉ ባነሱት የለውጥ ሀሳብ፣ ራሳቸውን ቤዛ ያደረጉ ኢትዮጵያውያን ዐማሮች መሆናቸው ግልጽ ነው። እነዚህ ሰዎች በዚያ ጊዜ የዐማራው የበላይነት ይጠበቅ ብለው ቢያምኑና ቢያስቡ ኖሮ፣ ሥርዓቱም የዐማራ መሆኑን ቢያምኑ ኖሮ፣ መኮንን ሀብተወልድን፣ብላታ አየለ ገብሬን፣ሊቀመኳስ ታደሰ ነጋንሺ፣አቶ ገብረወልድ እንግዳ ወርቅን፣ደጃዝማች ለጥ ይበሉ ገብሬን፣አቶ ክብረት አጥናፉን ወዘተ የመሰሉ ሰዎችን ባልገደሉም ነበር። ከመጀመሪያውም ለለውጥ ባልተነሱ፤ ሥርዓቱንም አሳልፈው ባላጋለጡ ነበር።
በኢትዮጵያ ተማሪዎች ንቅናቄ ጉልህ ቦታ አለው የሚባለው ዋለልኝ መኮንን ዐማራ ነው። ያን ሥርዓት ኮንኖ ለኮናኞች አቀብሎ አገሪቱ ዛሬ ለምትገኝበት ምስቅልቅል ሁኔ ብቻ ሳይሆን፣ የጥፋቷን መንገድ ያመቻቸውን የዐማራ ልሂቃንን ያን ሥርዓት ሊመልሱ፣ የዐማራውን የበላይነት ሊያነግሡ ይታገላሉ የሚሉን። መረራና ተመስገን እንደሚሉት ልሂቃኑ ለዐማራ የበላይነትና ለዐፄዎች ሥርዓት ጸንቶ መኖር ቢሹና ለዚህም መጠበቅ ቢያስቡ ኖሮ፣ ዋለልኝ መኮንን፣« ኢትዮጵያ የብሔረሰቦች እስር ቤት ናት» የሚለውን፣ አገሪቱ ዛሬ ለምትገኝበት ምስቅልቅል ሁኔታና ለኢትዮጵያ ባሕር አልባ መሆን የዳረጋትን መነሻ ሀሳብ ሊጽፈውና ሊያሰራጨው ቀርቶ፣ በኅሊናው ቦታ አይሰጠው እንደነበር መገንዘብ አይገድም። ከዚሁ ጋር ተያይዞ የዐማራው ልሂቃን ለዐፄዎች ሥርዓት መቀጠል ፍላጎቱና ምኞቱ ቢኖራቸው ኖሮ፣ ወያኔ ከበቀለበት ቀዬ የበቀሉት፣ ጥላሁን ይግዛው፣ ብርሃነ መስቀል ረዳ፣ ዘሩ ክሸን፣ ተስፋዬ ደበሳይ፣ አታክልቲ ቀጸላ፣ ወዘተ በመሩት ኢሕአፓ እና ኢሕአሠ ፣በተሰኙት ወታደራዊና ፖለቲካ ድርጅቶች የዐማራው ልሂቃን ገብተው ውድ ሕይዎታቸውን ባልከፈሉም ነበር። ኃይሌ ፊዳ በመራው መኢሶን፣ ሰናይ ልቄ በመራው ወዛደር ሊግ ዕንቁ የነበሩት የዐማራ ልሂቃን ባልገቡና የሕይዎት ዋጋ ባልከፈሉ ነበር።
እነኮሎኔል እምሩ ወንዴ፣ ኮሎኔል አስናቀ እንግዳ፣ መቶ አለቃ አያልሰው ደሴ፣ ዶ/ር ዓለም አንተገብረሥላሴ፣ ዶ/ር ማሞ ሙጨ፣ ጌታቸው ማሩ፤ ወዘተ ወዘተ ቆጥሬ የማልጨርሳቸው ዐማሮች፣ የብሩኅ አዕምሮ ባለቤቶች የትግሉ አጋር ይሆናሉ ተብሎ አይታሰብም ነበር። መረራ ጉዲና ካልዘነጉ « ለመሬት ላራሹ ጥያቄ መልስ ማግኘት የዐማራው ምሁራን ከሌሎች ብሔረሰብ አባሎች በፊት ግንባር ቀደም ሚና ተጫውተዋል፤ ዛሬ ግን እኛ በየራሳችን ብሔር ጎጆ ገብተን የዐማራውን ልሂቃን ካድነው» ማለታቸውን አስታውሳለሁ። ሀቁ ይህ ነው። ዐማራው በሌሎች ተክዶም መካዱን አያውቅም ወይም ለማመን ይቸግረዋል። በዚህም የተነሳ የኢትዮጵያ ችግሮች ሁሉ ፈጣሪ ተደርጎ ይሳደዳል፣ ይወቀሳል።
በመጀመሪያስ ዛሬ የትግራይ ልሂቃን እንደሚያደርጉት የሁለንተናዊ ሀብትና ሥልጣን ባለቤት የሆነ ፣በሁለንተናው የዐማራው ነገድ የበላይነት የነገሠባት ኢትዮጵያ ነበረች ወይ? ብለን ብንጠይቅ አማርኛ ቋንቋ በአገሪቱ ከመነገሩ ውጭ፣ ዐማራው ከሌሎች የተለየ መብትና ሥልጣን ጠቅሎ የያዘባት ፣ኢትዮጵያ በብሔርተኞቹ ኅሊና የተሳለች ካልሆነች በዕውኑ ዓለም የለችም። ነገሥታቱ ካንድ ብሔር የተወለዱ አልነበሩም። ከበርካታ ነገዶች የተወለዱ ኢትዮጵያውያን ነበሩ። ዝርዝር መረጃውን ለማወቅ የሚፈልግ« ሥልጣን ተሻሚዎች ትግሬዎች እና የኢትዮጵያ አንድነት» የሚለውን በዚህ ጸሐፊ የተጻፈውን መጽሐፍ ይመልከቱ። ለአብነት ያህል፣ ዐፄ ቴዎድሮስ ቅማንትና ዐማራ ናቸው። አፄ ተክለጊዮርጊስ አገው ናቸው። ዐፄዮሐንስ 4ኛ ትግሬ ናቸው። ዳግማዊ ዐፄ ምኒልክ ጉራጌና ዐማራ ናቸው። ከፍ ስንልም የበርካታ ነገዶች ደም ቅልቅል አለባቸው። ቀዳማዊ ኃይለሥላሴ ጉራጌ፣ ኦሮሞና ዐማራ ደም ያለባቸው ናቸው። ኮሎኔል መንግሥቱ ኃይለማርያም ኦሮሞና ዐማራ ናቸው። ቀዳማዊ ኃይለስላሴ የዘርም ልዩነት ስለሌለባቸውም ልጆቻቸውን ያጋቡትት፣ ለጉራጌ፣ ለኦሮሞ፣ ለትግሬ ነው።
በዐማራነት የሚከሰሱትን የምኒልክን መኳንንቶች ብንወስድ አብዛኞቹ ዐማራዎች አይደሉም። ወሣኝ የሚባሉት የምኒልክ መኳንንቶችና አካባቢያዊ ገዥዎች የሚከተሉት ነበሩ።የማን ነገድ አባል እንደሆኑ አንባቢ በስማቸው ማወቅ ይችላል። እነዚህም የሚከተሉት ናቸው፦
1. ንጉሥ ተክለሃይማኖት ጎጃም፣
2. ራስ ( በኋላ ንጉሥ) ሚካኤል አሊ ወሎ፣
3. ራስ ወልደጊዮርጊስ አቦዬ ከፋ፣
4. ካዖ ጦና ወላይታ፣
5. ራስ ዳርጌ ሣህለሥላሴ አርሲ፣
6. ራስ መኮንን ወልደሚካኤል ጉዲሳ ሐረርጌ፣
7. ራስ ጎበና ዳጬ የጦር አበጋዝ፣
8. ራስ መሸሻ ቴዎድሮስ ደንቢያ፣
9. ራስ መንገሻ ዮሐንስ ትግራይ( ምዕራብ)፣
10. ራስ ተሰማ ናደው ኢሉባቡር፣
11. ራስ አባተ ቧያለው ሀዲያናገምባታ፣
12. ራስ ቢትወደድ መንገሻ አቲከም አገው ምድር፣
13. ራስ ጉግሳ አራኣያ ትግራይ ( ምስራቅ )
14. ራስ አሉላ አባነጋ(አሉላ ቁምቢ) የጦር አበጋዝ፣
15. ራስ ናደው አባወሎ፣
16. ራስ ወሌ ብጡል የጁ፣
17. አፈንጉሥ ነሲቡ መስቀሎ ሚኒስቴር፣
18. ፊታውራሪ ገበየሁ ጎራ( ተክሌ) የጦር መሪ፣
19. ፊታውራሪ ሀብተጊዮርጊስ ዲነግዲ የጦር ሚኒስቴር፣
20. ሱልጣን አባ ጅፋር ጅማ፣
21. ሱልጣን ሞሐመድ አንፍሬ አፋር፣
22. ደጃዝማች ገብረእግዚአብሔር ሞረዳ ወለጋ ነቀምት ዙሪያ፤
23. ደጃዝማች ባልቻ ሣፎ ( አባነፍሶ) ሲዳሞ፣
24. ደጃዝማች ጆቴ ቱሉ ወለጋ ጊንቢ አካባቢ፣
25. ደጃዝማች ሞረዳ በከሬ ወለጋ፣
26. ደጃዝማች ደምሰው ነሲቡ፣
27. ደጃዝማች መሸሻ ወርቄ ዲፕሎማት፣
28. ደጃዝማች ገብረሥላሴ ባርያ ጋብር ፣
29. ሸህ ሆጄሌ አሊ ሐሰን አሶሳ፣
30. ቢትወደድ አልፈርድ ኢልግ አማካሪ የውጭ ዜጋ
ካላይ ካለው የስም ዝርዝር መገንዘብ እንደሚቻለው፤ራስ ጎበና፣ ፊታውራሪ ሀብተጊዮርጊስ፣ ፊታውራሪ ገበዩሁ ተክሌ(ጎራ) ፣ወዘተ ከሚጠቀሱት የኦሮሞ ተወላጆች ዋነኞቹ ናቸው። የአካባቢ ገዥዎች የየአካባቢው ተወላጆች ነበሩ። ወለጋ ደጃዝማች ጆቴ፣ እና ደጃዝማች ኩምሳ( ገብረእግዚአብሔር) ፣ወላይታ ካዎ ጦና፣ ወሎ ራስ ሚካኤል(ዓሊ) ጎጃም ንጉሥ ተክለሃይማኖት(አዳል ተሰማ)፣ ትግሬ ራስ መንገሻ ወዘተ ነበሩ። ወደ ቀኃሥ ስንመጣም ዋና ዋና ባለሥላጣኖቹ ከተለያዩ ነገዶ የሚወለዱ ናቸው። ለአብነት ራስ ካሣ የአገው የደጃዝማች ኃይሉ ልጅ ናቸው። ራስ ደስታ ዳምጠው በእናታቸው ጉራጌ ናቸው። ራስ አበበ አረጋይ የራስ ጎበና ዳጨ የልጅ ልጅ ናቸው። ይልማ ደሬሣ ፣ጄኔራል ሙሉጌታ ቡሊ፣ጀኔራል ታደሰ ብሩ፣ ጄኔራል ጃጋማ ኬሎ፣ደጃዝማች ደረሱ ዱኬ፣ ወዘተ ኦሮሞዎች ናቸው። እንዲህ እያልን ዘር መቁጠር ከጀመርን ዐማራው በብቸኝነት ኢትዮጵያ የገዛበት ወቅት አለመኖሩን እንረዳለን። ውሸት ተደጋግሞ ሲነገር ዕውነት መስሎ ዐማራው ቋንቋው የመንግሥት የሥራ ቋንቋ በመሆኑ ብቻ፣ እንደገዥ ተቆጥሮ ነገዱ ባላየውና ባልበላው ዕዳ ከፋይ እየሆነ ይገኛል። መረራ እንዳለውና ተመስገን ደሣለኝም እንዳጸደቀው፣ የዐማራ ልሂቃን ለዐፄዎቹ ሥርዓት መጠበቅና ለዐማራው የበላይነት የሚታገሉና የታገሉ ቢሆን፣ያን ሥርዓት ለመጣል መራር መስዋዕትነት ለመክፈል ሳንጃ ወድረው፣ ቃታ ስበው ፣በርሃውን ሜዳዬ፣ ዱሩን ቤቴ ባላሉ ነበር። ይህ መረጃ ያልቀረበበት የመረረና የከረ፣ በዐማራ ልሂቃን ላይ የተሰነዘረ በቋሚ ሰነድ ላይ የሰፈረ ትችት ፣ለኢትዮጵያና ለኢትዮጵያዊነት ሲሉ ውድ ሕይዎታቸውን የከፈሉትን የዐማራ ነገድ ልጆች አጽም ያስቆጣል። በሕይዎት ያሉትምን ያስቆጫል። ለካ ለዚህ ኖሯል የደከምነው ብለው የወጣትነት ሕይዎታቸውን ያሳለፉበትን የትግል ዘመን እንዲረግሙ ያደርጋል። ይህ ደግሞ ደግ አይደለም።
ዶ/ርመረራ ያመነጨው፣ አቶ ተመስገን ደሣለኝ ያስፋፋው ይህ በዐማራው ላይ የተሰነዘረው ያለፈ ሥርዓት ናፋቂነት፣ «የዐማራን የበላይነት መልሸ አገኛለሁ ብሎ የሚገፋው የሕልም ፖለቲካ» ሲል የደመደመው ቃል የዐማራው ልሂቃን የሌሎች ነገዶች ልሂቃን እንዴት እንደሚያዩዋቸውና እንደሚንቋቸው የሚጠቁም ነው። ዐማራው እንደ መረራና መሰሎቹ በሄዱበት መንገድ መጓዝ ኢትዮጵያዊነትን ይጎዳል፣ አብሮነትን ይሸረሽራል፣ አንድነትን ይጎዳል ከሚል ሠፊ የአመለካከት ባሕር ውስጥ ገብቶ፣ በአድሮ እንዬው ፣ነገሮች ይብላሉ ብሎ በትብዝት ብሔርተኞቹን እዬተመለከተ እንጂ፣ የበላይነቱን ከፈለገውና ሥልጣን ለመረከበ በነገዱ ዙሪያ ከተደራጀ ብሔርተኞቹ ከተጓዙበት የጊዜ ርዝመት ባጠረ የፈለገውን ማድረግ የሚያስችል ሁለንተናዊ የአቅም ባለቤት እንደሆነ ያጡታል አይባልም። ይህ ግን ሰው በሰውነቱ ዕኩል ነው፤ ሰዎች በተግባራቸው እንጂ፣ በነገዳቸው መመዘን የለበትም፣ የሕግ የበላይነት እንጂ፣ የነገድ የበላይነት መኖር የለበትም ብሎ ለሚያምነው አብዛኝው ኢትዮጵያዊ የሚፈልገው አይደለም። በመሆኑም እባካችሁ ዐማራውን ባልዋለበት ስም እየሰጣችሁ ወደ ማይፈልገውና ወደማያምንበት አቅጣጫ አትግፉት።
ርዕሴን ለማጠቃለል፣ እባካችሁ ይህን የመረራ ጉዲናን ሀሳብ የምትጋሩ ሰዎች የት? መቼ? ማን? የዐፄዎች ሥርዓትን ለመመለስና ያልነበረ የዐማራ ሥርዓት ሊመልስ የቆመ ግለሰብ ወይም ድርጅት እንዳለ ጠቁሙኝ። በልዑል ኤርሚያስ ሣህለሥላሴ የሚመራውን የዘውድ ምክር ቤት ካላችሁኝ አልስማማም። ምክንያቱም ልዑሉ እናቱ ልዕልት ማኅፀንተ ድብልቅ ያልሆነ የወለጋ ኦሮሞ ናቸው። አባታቸው ልዑል ሣህለሥላሴም ባባታቸው የኦሮሞ፣ የጉራጌ ተወላጅ ሲሁኖ፣ በእናታቸው በእቴጌ መነን አስፋውም የንጉሥ ሚካኤል የልጅ ልጅ በመሆናቸው ኦሮሞነት አለባቸው። እርሳቸው ዘውዳዊ ሥርዓትን እንደ እንግሊዝ፣ ጃፓን፣ ስዊድን በባህላዊና ታሪካዊ ፋይዳው ይኑር የሚሉ እንጂ፣ እንደአባታቸው በሁለንተናው መልኩ ፈላጭ ቆራችነት ልቀጥል የሚሉ አይመስለኝም። የእርሳቸው ፍላጎት ደግሞ የአብዛኛው የዐማራ ልሂቃን ፍላጎት ነው ማለት የሚቻል አይመስለኝም። በዚህም የዐማራው ልሂቃን የኢትዮጵያ ችግሮች ናቸው ለማለትና የችግሩ አካሎች አድርጎ መቁጠር ተገቢም፣ ትክክልም ካለመሆኑም በላይ ታላቅ ስህተትና ድፍረት ነው።
በሌላ በኩል ዕድገት ወደፊት እንጂ ፣ወደኋላ አይጓዝም። የተፈጥሮም ሕግ እንዲሁ ወደፊት እንጂ ፣ወደኋላ አይሄድም። ዛሬ ዓለም ከደረሰበት የካፒታሊስት ሥልተምርት ወደ ባሪያ አሳዳሪው ወይም ወደ ፊውዳሉ ሥልተምርት እንመልስህ ቢሉት የሚቻል ብቻ ሳይሆን ፣ለማሰብም የማይቻል ነው። ከዚህ አንጻር « አብዛኛው የዐማራ ልሂቃን በዐፄዎች ዘመን የነበረውን የበላይነት መልሸ አገኛለሁ ብሎ የሚጋፋውን የሕልም ፖለቲካ እስካልተወ ድረስ፣—-ሀገራችን ከአደጋ ቀጠናና ቀውስ የምትወጣ አይመስለኝም» ሲል መረራ ጉዲና የደረሰበት ድምዳሜ የታሪክንና የኅብረተሰብን የጉዞ አቅጣጫ ያጤነው አይመስልም። የተቃጠለን ወረቀት መልሶ ወረቀት ማድረግ የሚቻል አይሆንም። የዐፄዎች ሥርዓትም ላይመለስ ሁሉም የኢትዮጵያ ልጆች እገሌ ከገሌ ሳይባል፣ አውቀውም ሆነ ሳያውቁ በዘመቻ ንደውታል። ያ ይመለሳል ብሎ ማሰብ ራስን አለማመን ነው። በሌልም በኩል ከፍ ሲል ለመጥቀስ እንደሞከርኩት የዐማራ የበላይነት ከቋንቋው መነገር ውጭ አልነበረም ፣ ኖሮም አያውቅ። እንዲኖርም የሚታገል የለም። ካለ ይነገረን ፤እንወቀው። የሀሳቡ አፍላቂና አድናቂዎች ይኸ ይጠፋቸዋል አይባልም። ሀሳቡ እንዲሰራጭ የተፈለገው ለዐማራው ተጨማሪ መክሰሻ ወንጀል መፈለጉ ነው። ይህ ደግሞ መረራ እንዳሉት አንድነት የሚያመጣ ሳይሆን፣ ዐማራው ለካ በዚህም ዘመን እንደዚህ የሚከሱን አሉ? በሌለንበት መከሰሳችንና የኣንድነት ፀሮች መባላችን ካልቀረ በነገዳችን ዙሪያ እንሰባሰብ የሚለውን የሞረሽ ወገኔን ዐማራ ድርጅት ጥሪ የሚያስተጋባ ነው። በዚህ መልኩ ለተኛው ዐማራ መቀስቀሻ እሳት ለጫሩልን ወገኖች ጉዳዩ ከዕውነት ያልተነሳ ቢሆንም ልሂቃኑ ማንነቱን እንዲያውቅና ከነማን ጋር እንደቆመ ራሱን እንዲመረምር የሚገፋፋ ስለሆነ በሉ ከግፉ ጨምሩበት እላለሁ። መገፋት አመጽን፣ አመጽ መሰባሰብንና የሀሳብ አንድነትን ይፈጥራልና!

Wednesday, May 28, 2014

Scores Reported Killed in Deadly Battle Near Ethiopia Border

May28/2014


Villagers in Modmoday 40 kms east ofBaidoa

Ato — At least 40 people had been killed in deadly battle that ensued near Somalia’s southwestern border with Ethiopia according to officials, Garowe Online reports. On Tuesday morning, heavily armed Al Shabaab fighters raided bases in a village on SomaliaEthiopia border, killing 28 vigilantes, the Governor of Bakool region of southwestern Somalia said on VOA Somalia Service during Tuesday interview.

He added that militants estimated to be 12 were also killed in stiff resistance from the local forces manning the bases. Meanwhile, Ato village head told BBC Somali Service that Al Shabaab fighters launched the deadly assault on local soldiers. Ethiopia maintains military presence near the attacked village of Ato, sources revealed.

Ethiopian-AMISOM troops have been fighting alongside Somali National Army (SNA) in support of Somali Federal Government’s stabilization efforts. Al Shabaab which has been driven underground in military campaign honed guerilla insurgency, targeting military and soft structures with military-style ambushes and suicide bombings 

ሰበር ዜና:- ጋዜጠኛ ተሰማ ደሳለኝ ሀገር ጥሎ ተሰደደ መንግስት አሁንም ሌላ ጋዜጠኛ አስሯል

May 28/2014


የኢትዮጵያ መንግስት በቅርቡ በጋዜጠኞች እና ብሎገሮች ላይ የፈፀመውን እስር ተከትሎ የኢቦኒ መፅሔት መስራች እና ማኔጂንግ ዳይሬክተር የነበረው ጋዜጠኛ ተሰማ ደሳለኝ ሀገር ጥሎ ተሰደደ፡፡ጋዜጠኛው በሀገሪቱ ያለው የፕሬስ ነፃነት አፈና ተጠናክሮ በመቀጠሉ እናመንግስት ሊወስደው ያሰበውን እርምጃ በመሸሽ እንደተሰደደ ምንጮቻችን አረጋግጠዋል፡፡ በተለይ የኢትዮጵያ ሬዲዮና ቴሌቪዥን፣ አዲስ ዘመን ጋዜጣ፣ ዛሚ ኤፍ ኤም፣ እና በሌሎች የኢህአዴግ ደጋፊ ናቸው በሚባሉ እንደነ አይጋ ፎረም እና ሆርን አፌይርስ የመሳሰሉ ድህረ-ገሮች የተለያዩ ጋዜጠኞች እና የኢትዮጵያ ዞን 9 ብሎገሮች እንዲታሰሩ እና እንደሚታሰሩ ፍንጭ መስጠታቸው ለስደቱ ምክንያት መሆኑ ተጠቁሟል፡፡ከመጪው ምርጫ 2007 ዓ.ም. በፊት የመንግስትን ብልሹ አሰራር እና ኢሰብዓዊ ድርጊት በመኮነን ያጋልጣሉ የተባሉ የነፃው ፕሬስ ጋዜጠኞች እና ብሎገሮች እንደሚታሰሩ በተለያየ ጊዜ የተነገረ ቢሆንም፤ በቅርቡ 3 ጋዜጠኞች እና 6 ብሎገሮች መታሰራቸው ይታወቃል፡፡ በመንግስት የተወሰደው የጋዜጠኞ እና ብሎገሮች እስር ተከትሎ ሌሎችም ሊታሰሩ እንደሚችሉ በተዘዋዋሪ መንገድ መገለፁን ተከትሎ ከጋዜጠኛ ተሰማ ደሳለኝ በፊት ጋዜጠኛ በትረ ያዕቆብ እና ፍስሃ ያዜን ጨምሮ አራት ጋዜጠኞች መሰደዳቸው ታውቋል፡:

 ጋዜጠኞቹ ከሀገር ጥለው መሰደዳቸው በስተቀር እስካሁን ያሉበትን ሁኔታ ማረጋገጥ አልተቻለም፡፡ ይህ በእንዲህ እንዳለ የእንቁ መፅሔት ዋና አዘጋጅ ጋዜጠኛ ኤልያስ ገብሩ ከስራው ጋር በተያያዘ በእንቁ መፅሔት በተፃፈ ፅሑፍ ከማዕከላዊ ቃሉን እንዲሰጥ በስልክ በተደረገለት ጥሪ ትናንት ሰኞ ግንቦት 18 ቀን 2006 ዓ.ም. ወደስፍራው ቢያቀናም ማረፊያው እዛው ማዕከላዊ እስር
ቤት ሆኗል፡፡ ይሁን እንጂ ዛሬ በዋስ ይለቀቃል ተብሎ ቢጠበቅም እስር ቤቱ ፍርድ ቤት አቅርቦት የዋስ መብት ሳይከበርለት ለተጨማሪ 7 ቀናት እዛው ማዕከላዊ ታስሮ እንዲቆይ ተጠይቆበት በእስር ላይ ይገኛል፡፡

የወያኔ ጥላቻ ፍሬ -ፕ/ር መስፍን ወ/ማርያም

May 28/2014
Prof. Mesfin Woldemariam
Prof. Mesfin Woldemariam
ወያኔ ለትግራይ ሕዝብ ሀብትንና ብልጽግናን አመጣ ብለው የሚያምኑ ሰዎች ብዙ ናቸው፤ ወያኔ የሥልጣን ወንበሩ ላይ በመውጣቱ ትግሬዎች ሁሉ አልፎላቸዋል ተብሎ ይታመናል፤ በተለይ በአውሮፓና በአሜሪካ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን በዚህ ላይ የጠነከረ እምነት አላቸው፤ በዚህ ጉዳይ ላይ ከኢትዮጵያ ውጭ ብዙ ውይይትም ይሁን ንትርክ ይደረጋል፤ በኢትዮጵያ ውስጥ ግን የተፈራ ርእስ ነው፤ ውስጥ-ውስጡን እንጂ አደባባይ አይወጣም፤ ይህንን ጉዳይ በኢትዮጵያ ውስጥ አደባባይ ለማውጣት ጊዜው የደረሰ ይመስለኛል፤ አረጋዊ በርሄ፣ ገብረ መድኅን አርአያ፣ አስገደ ገብረ ሥላሴ፣ አብርሃ ደስታ (አሥር ቢሞሉልኝ ደስ ይለኝ ነበር!) እየደጋገሙ ቢያነሡትም ሌሎች በቁም-ነገር የተቀበሉት አይመስልም፤ ሕዝቡ ግን በራሱ መንገድ እየተናገረና ምስክርነቱን እየሰጠ ነው፤ በመቀሌ የተሠራውን የመኳንንት መንደር ሕዝቡ አፓርቴይድ ብሎ ሲሰይመው፣ በአዲስ አበባ የተሠራውን መንደር መቀሌ ብሎ ሲሰይመው እየመሰከረ ነው፤‹‹የለሁበትም!›› እያለ ነው። 
የትግራይ ሕዝብ መደህየቱ አልበቃ ብሎት ሲለምንም እየተሳቀቀ ነው፤ የሚለምነው ትግሬ ለብዙ ሰዎች ትግሬና ወያኔ አንድ መስሎ እንደሚታየው ያውቃል፤ አብዛኛው ሰው በወያኔ ላይ ያለውን ስሜት ያውቃል፤ ስለዚህም ሲለምን ሰዎች በወያኔ ላይ ያላቸውን ስሜት ስለሚያራግፉበት እየተሸማቀቀ ነው፤ አንድ የትግራይ ቄስ ከአርሲ ነኝ አሉኝና ለምን እውነቱን አይናገሩም ስላቸው እውነቱን ስናገር የማገኘው ስድብ ብቻ ነው አሉኝ፤ እኒህ ሰው ምን በወጣቸው የወያኔን ኃጢአት ተሸካሚ ይሆናሉ፤ በሌላ በኩል ደግሞ በትግሬነቱ የተጠቀመ አለ፤ እኔ የማውቀው የደርግ ወታደር የነበረ ትግሬ ቆስሎ ከውትድርና ወጣና በአንድ የመንግሥት መሥሪያ ቤት የጥበቃ ሥራ ላይ ነበር፤ በጣም ይቸግረው ነበር፤ ሚስቱ ሕመምተኛ ነበረች፤ የቤት ኪራይ መክፈል ይቸገር ነበር፤ ዛሬ ግን የሚለብሰው ልብስ ሌላ ነው፤ ከኑሮውም ተርፎ ለሲጃራና ለጫት እያወጣ ነው፤ ወይም ሌሎች እያወጡለት ነው፤ ትግሬነታቸው ብቻ እንዲህ የደላቸው በጣም፣ በጣም ጥቂቶች ናቸው፤ ስለዚህም በወያኔ አገዛዝ ትግሬ ሁሉ ተጠቅሞአል ማለት ከጉልሁ እውነት ጋር የሚጋጭ ስሕተት ነው፤ አብርሃ ሰዎች ትግሬ ሁሉ ተጠቃሚ ሆኗል ሲሉ ‹‹ያመኛል›› ማለቱ ይገባኛል። 

 ወያኔ ትግሬ በመሆኑ ብቻ ትግሬ ሁሉ ዕዳ አለበት ማለት እንደወያኔ ማሰብ ነው፤ ወንጀል በዘር አይተላለፍም፤እያንዳንዱ ሰው ለሠራው ሥራ ሁሉ ኃላፊነትን ይወስዳል፤ ጊዜው ሲደርስ ውጤቱንም ለመቀበል ይገደዳል፤ ይህ የሚሆነው ሰው ሁሉ በመንፈሳዊ ኃይል በጎ መንፈስ አድሮበት፣ አእምሮው በትምህርት ተገርቶ በትክክል ማሰብ ሲችል ነው፤ የኢትዮጵያ ሕዝብ አሁን በአለበት ሁኔታ በጎ መንፈስ የራቀው ይመስላል፤ አእምሮም ጭራሹኑ በእኩይ መንፈስና በጥላቻ እየዛገ ነው፤ ስለዚህ ያስፈራል፤ በደቡብ ሱዳን ሁለት መቶ ሰዎች በዘር ተለይተው ታረዱ ሲባል ያስፈራል፤ በናይጂርያ፣ በኮንጎ የሚካሄደውን የዘርና የሃይማኖት እልቂት ስንሰማ ያስፈራል፤ በ1997 ዓ.ም. መለስ ዜናዊና አዲሱ ለገሰ እንዳስታወሱን የሩዋንዳ የጎሣ እልቂት በብዙ ሰዎች አእምሮ ውስጥ አለ፤ የቅርብ ተኳሽ የሆነው የአግዓዚ ጦርም አድፍጦ መጠበቅ ያስፈራል፤ ሌላውም ይህንን አውቆ አድፍጦ መጠበቁ ያስፈራል፤ ሰማይ ጠቀስ የሠሩት፣ የሥልጣን ኃላፊነትን ችላ ብለው በሥልጣን የሚነግዱና የሚከብሩት፣ የማይኖሩበትን ሕንጻ የሚክቡት፣ ከሕዝብ ጋር ያላቸው የአይጥና የድመት ኑሮ ያስፈራል፤ አቶ አስገደ ወያኔ መደንገጡን ይነግረናል፤ መደንገጥ የማይቆጣጠሩት ፍርሃት ነውና አደጋ ያመጣል፤ አደጋው አደጋን ይጠራል፤ ይህም ያስፈራል።

በትግራይ ዙሪያ ያለው ምንድን ነው? የትግራይ ሕዝብ በየትኛው አቅጣጫ ነው አንደልቡ እየተዘዋወረ ለመሥራትና ለመኖር የሚችለው? ወያኔ የትግራይን ሕዝብ ከሰሜን ከወገኑ ከኤርትራ ሕዝብ ጋር ደም አቃብቶታል፤ በደቡብ-ምሥራቅ ከወሎ መሬት ቆርሶ የወሎን ሕዝብ ቂም አስቋጥሯል፤ በደቡብ-ምዕራብ ከጎንደር መሬት ቆርሶ የጎንደርን ሕዝብ ቂም አስቋጥሯል፤ የራስን ወገኖች አስቀይሞ ሱዳንን በመሬት ለመደለል የሚደረገው ጥረት ሁሉ ፋይዳ የለውም፤ ሱዳን ለራሱም ያልበጀ አገር መሆኑ እየታየ ነው፤ ወደፊት ደግሞ ይበልጥ ይታያል፤ በትግራይ ውስጥ ደግሞ ወያኔ የፈጠረው አፓርቴይድ የወያኔን የኑሮ ደረጃ ወደሰማይ ሲያስጠጋው፣ የቀረውን ወደአንጦርጦስ የደሀነት ገደል ውስጥ ከቶታል፤ በዚህም ምክንያት በአዲስ አበባ ከተማ ከነልጆቻቸው እየተዘዋወሩ የሚለምኑ ሞልተዋል፤ ይህ ልመናም ለወያኔ ለመገበር ነው፤ ብዙዎቹ እንደሚናገሩት የሚለምኑት የማዳበሪያ ዕዳቸውን ለወያኔ ለመክፈል ነው። 

 ወያኔ ከሀያ ዓመታት በላይ አፍንጫ እየያዘ ያስከፈለውን የሚመልስበት ጊዜ እየተቃረበ ነው፤ ጥያቄው ወያኔ እንዲመልስ የሚገደደው እንዴት ነው? የሚል ነው፤ጥላቻ ወደንዴት፣ ንዴት ወደቁጣ ተለውጦ ሲገነፍል ምጽዓት ደረሰ ማለት ነው፤ ሁሉም ሰው ራቁቱን ይሆናል፤ አንደአውሬ ከጥፍሩና ከጥርሱ በቀር ሌላ መሣሪያ አይኖረውም፤ ሰው ሁሉ በክፋት ወደአውሬነት ይለወጣል፤ ጠመንጃና ቦምብ አያገለግሉም፤ ሕንጻው ምሽግ አይሆንም፤ መኪናው፣ ባቡሩ፣ ታንኩ ከቆመበት አይነቃነቅም፤ የትም አያደርስም፤ ጭፍራ ሁሉ በየራሱ ፍዳ ታንቆ እንኳን ለሌላ ሊተርፍ ለራሱም የማይበቃ ይሆናል፤ ለነገሩ ጌታና ሎሌም የለም፤ ሁሉም በአውሬ እኩልነት የተፋጠጠ ነው፤ ርኅራኄ ተሟጦ፣ መግል ያዘለ ልብ ፈርጦ፣ ውይይትና ክርክር አብቅቶ፣ ጥርሱን ያገጠጠና ጥፍሩን የሳለ መንጋ በደም የሚራጭበት ሁኔታ ነው። 

 ሌላ አገር እንዲህ አልሆነም፤ እዚያ አገር እንዲህ አልሆነም፤ የሚባል ነገር የለም፤ እኛ ዘንድ ሌላ ነው፤ የኢትዮጵያ ደሀዎች እንባ የእግዚአብሔርን ሰማይ አጨቀየው!  ክፋት እንደ እሳት ይቃጠላል፤ ኵርንችቱንና እሾሁን ይበላል፤ጭፍቅየሆነውንም ዱር ያቃጥላል፤ ጢሱም ተትጐልጕሎ እንደ ዓምድ ይወጣል፤በሠራዊት ጌታ በእግዚአብሔር ቁጣም ድር ተቃጥላለች፤ ሕዝቡም እሳትእንደሚበላው እንጨት ሆኖአል፤ ሰውም ለወንድሙ አይራራም፤ ሰው በቀኙ በኩልይነቅላል፤ ይራብማል፤ በግራም በኩል ይበላል፤ አይጠግብምም፤ እያንዳንዱምየ ክንዱን ሥጋ ይበላል፤ ምናሴ ኤፍሬምን፣ ኤፍሬምም ምናሴን ይበላል፤ …ኢሳይያስ 9/18-21  ትንቢተ ኢሳይያስ ለሩዋንዳውያን ብቻ አይደለም፤ ጥላቻና ክፋት በተዘራበት ቦታ ሁሉ ውጤቱ ጥፋት ነው፤ ምናሴ ኤፍሬምን በልቶ አይቀርም፤ ኤፍሬምም ምናሴን ይበላዋል።

Tuesday, May 27, 2014

ግንቦት ሃያ ለኢትዮጵያ ሕዝብ ምኑ ነው...........? (ገዛኸኝ አበበ ከኖርዌ ሌና)

 Gezahegn Abebe Norway Lena

ግንቦት ሃያ የጥቂት የአረመኔዎችና ሆዳሞች የደስታ ቀን ሲሆን የመላው ኢትዮጵያ ሕዝብ ደግም የሃዘን እና የጭቆና ቀን ነው!

ወያኔ ኢሕአዴግ ኢትዮጵያን በሀይል መግዛት ሕዝብን በአፈናና በእንግልት ማሰቃየት ከጀመረ ሀያ ሶስተኛ አመት የሆነው ሲሆን ይህንንም ወያኔዎች የድል ቀን ብለው የሚጠሩት ለመላው ኢትዮጵያ ደግም የሃዘንና የጭቆና ቀን የሆነው ግንቦት ሃያን ቀን ለሃያ ሶስተኛ ጊዜ  ለማክበር ሽር ጉድ እያሉ ሲሆን  ግንቦት ሃያ በመጣ ጊዜ ወያኔዎቸ በየአመቱ የሚያደርጉት የተለያዩ አይን ያወጣ የሀሰት ፕሮፓጋንዳዎችን  ዘንድሮም ተያይዘውት በኢትዮጵያ ሕዝብ አይምሮ ላይ እየቀለዱ  በወያኔ የግፍ ጅራፍ እየተገረፈ ያለውን  ሕዝብ ይበልጥኑ እያቆሰሉት ይገኛሉ : :በዚህ የወያኔ ግንቦት ሃያ ኢህአዲግ ለኢትዮጵያ ሕዝብ አሰገኛውላቸው የሚላቸውን ጥቅሞችንና ያላፉት ሃያ ሁለት አመታቶች ወደ ኋላ ዞር ብለን በምናይበት ጊዜ  ለኢትዮጵያ ሕዝቦች ምንም ያስገኙለት ጥቅም የለም ብል ድፍረት አይሆንብኝም ::ይልቁንም የኢትዮጵያን ሕዝ ለአስቸጋሪና ከባድ ችግር እንዲዳረግ አደረገው እንጂ:: በኢትዮጵያ ላይ የሚደረጉ አለም ዓቀፍ ጥናቶች እና ሐሀዞች ሳይቀር  እንደሚያሳዩት ወያኔ በስልጣን በቆየባቸው በእነዚህ ዓመታቶች በአገሪቷ ላይ አስከፊ ድህነት እንደሰፈነ ፣ የስራ አጥ ቁጥር እንዳሻቀበ ፣ ሰበዓዊ እና ፣ ዲሞክራሳዊ መብቶች ክብር አልባ ሆነው ፣ የገአሪቷ ዜጕች የኖሮ ደረጃ ከቀነ ወደ ቀን እንዳሽቆለቆለ ነው:: ስለሆነም ግንቦት ሃያ ለኢትዮጵያ ሕዝብ ይዞለት የመጣው ነገር ቢኖር እስራት፣ ግድያ፣ መከራና ሃዘን ፣ ድህነት፣ችግር፣ ፣ስቃይና ስደትን ብቻ ነው::በጣም የሚገርማችው ወያኔዎች ለኢትዮጵያ ሕዝብ ድልን አስገኘለት ብለው በሚያምኑበትን ቀን ዳንኪራ በመምታት ሊያከብሩት ሽር ጉድ በሚሉበት በዚህ የግንቦት ሃያ ዋዜማ በብዙ ሺ የሚቆጠሩ ኢትዮጵያኖች የወያኔ ስርዓት በፈጠረው የኑሮም ሆነ የፖለቲካ ጫና በመሸሽ አገራቸውን ትተው ለስደት እና ለመከራ ሲዳረጉ አብዛኞቹም ያሰቡበት ሳይደርሱ ሕይወታቸው እንደዋዛ አልፉል :: 

መረጃዎች እንደሚያመለክቱት የኢትዮጵያ ሕዝብ ከቀን ወደ ቀን በብዛት አገሪቷን በመተው ባገኘው አጋጣሚ ወደተለያዩ አገሮች በመሰደድ ላይ ሲሆን በአለም ላይ ዜጓቻቸው ከሚሰደዱባቸው  አገራት ተርታ ኢትዮጵያ በቀዳሚዎች ውስጥ እንደምትመደብ ነው:: ስርአቱም በፈጠረው የኑሮ ፣ቀውስ ምክንያት በብዙ ሚሊዮን የሚቆጠሩ የነገ ሀገር ተረካቢ ዜጎቻችን ሀገሪቷን በመልቀቅ ወደ ተለያዩ ሀገራት ለስደት ሲዳረጉ አንዳንዶቹም ለተለያየ ስቃይና ህልፈተ ህይወት ተዳርገዋል:: በተለይም ወደ ተለያዩ አረብ ሀገራት የተሰደዱ ወገኖቻችን ለከፋ ችግር እየተዳረጉ እንዳለ ይታወቃል::

 ወያኔ ኢሕአዴግ ሕዝብን ለማታለል በስልጣን በቆየባቸው አመታቶች በሀገሪቷ ላይ አመርቂ ውጤት እንዳስመዘገበና እያስመዘገበ እንደል ይለፍልፍ እንጂ አሁንም እየታየ ያለው ሀቁ ግን እንደሚያሳየው በአገሪቷ ላይ የአንድ ብሔር  የበላይነት ብቻ የሚነጸባረቀበት መሪዎች የፖለቲካ ስልጣንን ለግል ጥቅም ማካበቻ የሚጠቀሙበት ዘረኛ እና ጨቆኝ ስርዓት የነገሰባት ሀገር አንዷ ኢትዮጵያ እንደሆነች ነው:: ይህንንም ብልሹ እና አስከፊ ስርዓት የሚቃወሙ እና የሚተቹ ሰዎች በማን አለብኝነት  በየእስር ቤቱ እየተወረወሩ ሲሆን ከሰማንያ ሺህ በላይ የሚሆኑ ንጹህ ኢትዮጵያን ዜጎቻችን  በፖለቲካ አቋሟቸው ብቻ ከቤተሰቦቻቸው ተነጥለው በወያኔ እስር ቤት ውስጥ  የተለያዩ ስቃዮችና በደሎች እየደረሰባቸው  በመማቀቅ ላይ እንደሚገኙ ይታወቃል :: በጣም የሚያሳዝነው ደግሞ አንዳንዱችም  በእስር ላይ እንዳሉ እዛው እስር ቤት ውስጥ እንዳሉ  ህይወታቸው እያለፈ ሲሆን ከእነዚህ እስረኞች መካከል  ስድሳ ከመቶው የሚሆኑት አእምሮቸውን ስተው እንደሚገኙ  በቅርቡ ከውጭ የተገኘ ምንጮጭ ያስረዳሉ:: ይህ እንዲህ ባለበት ሁኔታ ነው እንግዲህ የኢትዮጵያኖች መብት የተከበረበት ቀን የሚባልለት ግንቦት ሃያ በየአመቱ በኢትዮጵያ የሚከበረው::

ወያኔዎች እንደሚሉት ግንቦት ሃያ የኢትዮጵያ ብሔር ብሔረሰቦች አንድነታቸውን  ያጠናከሩበት ቀን እንደሆነ ነው እኔ አኮ የማይገባኝ ነገር ኢህአዲግ ስልጣን ከያዘ ጀምሮ የቱ ላይ ነው ብሔር ብሔረሰቦች አንድነታቸው የጠነከረው በየቦታው የምናየውና የምንሰማው እርስ በእርስ መጣላት፣ እንደ ጠላት መተያየትና ፣መገዳደል ካልሆነ በቀር::  ወያኔ እንደሚያወራው ሳይሆን እውነታውና ሀቁ ግን ይኼ ግንቦት ሃያ ኢትዮጵያ አንድነቷ የፈረሰበትና ሕዝቡም አንድነቱን በማጣት በዘር፣ በጓሳ፣ በሃይማኖት የተከፋፈለበት ዘረኝነት ወደ ኢትዮጵያ የገባበት የጨለማ ቀን ነው::ታሪክ እንደሚያሳየን ከወያኔ መንግስት በፊት ኢትዮጵያን ሲመሩ የነበሩ መንግስታቶች ሁሉ ስለ ኢትዮጵያ አንድነት ስለዜጎችም እኩልነት የቆሙና ይሰብኩ የነበሩ መንግስታቶች እንደነበሩ ታሪክ ምስክር ነው:: ነገር ግን አሁን ላይ እንደምናየው በኢትዮጵያ በመቼውም ጊዜ ታይቶ በማይታወቅ ሁኔታ ሕዝቡ አንድነቱን ያጣበት በዘር የተከፋፈለበት ጊዜ ነው:: የወያኔ መንግስት በሀይል ወደ ስልጣን ከመጣባቸው ጊዜያቶች ጀምሮ ማለትም በእነዚህ ሃያ ሶስት አመታቶች ግንቦት ሃያ ካፈራቸው ፍሬዎች አንዱ ዘረኝነት ሲሆን ይህ የግንቦት ሃያ የዘረኝነት መዘዝ በእነዚህ ሃያ ሶስት አመታቶች በስፋት በኢትዮጵያ ተንሰራፍቶ ብዙዎች ኢትዮጵያኖች ዘረኝነት ባመጣው መዘዝ ሕይወታቸው እንዲያልፍ ምክንያት ሆኖል::

 በመጀሪያም ማወቅ ያለብን ነገር ወያኔዎች ከዛሬ ሃያ ሁለት አመት በፊት በግንቦት ሃያ ወደ ስልጣን ሲመጡ ቀደምት እንደነበሩ መሪዎች የኢትዮጵያን ሕዝብ አንድነትንና ኢትዮጵያዊነትን እየሰበኩን ሳይሆን አንዱን ብሔር  እያዋረዱና እየረገጡ ሌላውን ብሔር ከፍ እያደረጉና ተጠቃሚ እያደረጉ ሲሆን ይህንንም እስከዛሬ  በኢትዮጵያ በየቦታው በስፋት ተንሰራፍቶ እየተተገበረ የምናየው የግንቦት ሃያ ፍሬ እውነታ ነው::

 ሌላው በግንቦት ሃያ ወያኔ ሕዝብን አቀዳጀውት የሚለው ቴሌፎን፣ መንገድ፣ንጹህ መጠጥ ውሃ፣የጤና፣የትምህረትና ሌሎችም መሰረተ ልማት ከተሞችን አልፎ ገጠር ቀበሌ ድረስ በሰፊው መስፋፋት ሲሆን እዚህ ላይ ከእውነት የራቀ የወያኔን አይን ያወጣ የሀሰት ፕሮፓጋንዳ እንመለከታለን::በእነዚህ ሃያ ሶስት አመታቶች ወያኔዎች በኢትዮጵያ ላይ ብዙ ለውጦች እንዳመጣ እና የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ወደ ተሻለ የእድገት ደረጀ እያመራ እንዳለ የሕዝቡም የኖሩ አቀጣጫ እንደተለወጠ አፋቸውን ሞልተው ሲናገሩ እየሰማን ነው  ወያኔ ኢሕአዴግ የፖለቲካ ስልጣኑን ለማስረዘመ ይህንን ይበል እንጂ ሀቁና እውነታው ግን ይህ አይደለም::የተለያዩ ጥናቶችና ሪፖርቶ እንደሚያሳዩት አገሪቷ ከታች ካሉ የደሃ አገሮች ግንባር ቀደም እንደሆነች እና አገሪቷ ወደ መጥፎ አቅጣጫ እያመራች እንዳለ ነው:: የኢትዮጵያ ህዝብ የኑሮን ፈተና መወጣት ባልቻለበት በአሁኑ ወቅት የግንቦት ሃያ ድልን ሳይሆን እያሰበ ያለው የግንቦት ሃያ ቀን በመርገም ከዚህ ከአስከፊው የወያኔ ስርአት እንዲት እንደሚላቀቅ በማሰብ ከመከራና ከባርነት ነጻ የሚወጣበትን ቀናቶች በመናፈቅ እንደሆነ ግልጽ ነው :: ይህንንም የኢትዮጵያ ሕዝብ በተለያዩ ጊዚያቷች ከሚያሰማው ሮሮ ማወቅ ይቻላል :: 

በርግጥ በአሁን ሰአት ወያኔዎችና ጥቂት ሆዳሞ የወያኔ ካድሬዎች  የስርአቱ ተጠቃሚ ከመሆናቸው የተነሳ ግንቦት ሃያ ይዞላቸው የመጣውን ጥቅም በማየት በደስታ የግንቦት ሃያ ቀንን ለማክበር ሽር ጉድ እያሉ ሲሆን የኢትዮጵያ ሕዝብንም የግንቦት ሃያ ተጠቃሚ ለማስመሰል ወያኔ ግንቦት ሃያ በመጣ ቁጥር በሕዝቡ ላይ የተለያዩ ድራማዎችን እየሰራ እንዳለ ይታወቃል:: ከእነዚህም መካከል የገጠሩን ነዋሪ በሀይል እያስፈራሩ በግድ ስለ ስርአቱ ጥሩ ነገር እንደስገኘለትና ያንን በማሰብ ግንቦት ሃያን ደስ እያለው እንደሚያከብር  በግዳጅ እንዲናገር ማድረግ እንዲሁም በገጠርም በከተማም የሚኖረውን ሕዝብ ከየቀበሌው፣ ከየህድሩ፣ ከየመስሪ ቤቱ፣ ተማሪው፣ ገበሬው፣ ነጋዴው በተለያዮ ጥቃጥቅሞች በማታለልና እንዲሆም በማስፈራራት  በግዳጅ ሰለፍ እንዲወጣ በማድረግ በየአመቱ ይህን ተግባር እንደሚፈጽም የሚታወቅ ሲሆን ከአንዳንድ ሰዎች እንዳገኘውት መረጃ ዘንድሮም በየመስሪያ ቤቱ የግንቦት ሃያ ቀን ሰልፍ ላይ እንዲገኙና ሕዝቡ ከኢህአዲግ ጋር እንዳለ ለማስመሰል ግዳጃዊ ትህዛዝ እንደተላለፈላቸው ለማወቅ ችያለው የዛሬ ሁለት አመት አስታውሳለው አንድ በጣም የማውቀው ሰው በአንድ ትልቅ የመንግስት መስሪያ ቤት ተቀጥሮ የሚሰራና ነገር ግን በሚሰራበት መስሪያ ቤት ከሚያየው የዘር መጠቃቀምና ወያኔ ሕዝቡ ላይ እያደረሰ ካለው በደሎች የተነሳ ስርአቱን ክፎኛ የሚጠላና የሚቃወም ሰው ስለሆነ በመስሪያ ቤቱ ውስጥ የሚሰሩ ሰራተኞች ሁሉ በግንቦት ሃያ ቀን ሰልፍ ላይ እንዲገኙ ሲነገራቸው በሰልፉ ላይ እንደማይገኝ በመናገሩና ባለመገኘቱ በተለያየ ነገሮች በማሳበብ ከስራ መባረሩን አውቃለው:: አሁን ላይም ሁላችንም ኢትዮጵያኖች ስርአቱ ይዞብን የመጣውን ዘረኝነት፣ ድህነት፣ ስደትና ጭቆና ባለመቀበል ለኢትዮጵያ ሕዝብ ምኑም ላልሆነው  ግንቦት ሃያ  ማድመቂያ የወያኔ የሀሰት  ፕሮፖጋንዳ እንዳንሆን  እንጠንቀቅ ለማለት እወዳለው::

ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር!!!
gezapower@gmail.com

Monday, May 26, 2014

በወልቂጤ ዩኒቨርስቲ በተከሰተ የእሳት አደጋ አንድ የተማሪዎች ማደሪያ ህንጻ ከጥቅም ውጭ ሆነ

 May26/2014
አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 18 ፣ 2006 (ኤፍ.ቢ.ሲ.) ትላንት ሌሊት በወልቂጤ ዩኒቨርስቲ በተከሰተ የእሳት አደጋ አንድ የተማሪዎች ማደሪያ ህንጻ ከጥቅም ውጭ ሆነ ።
በአደጋው በተወሰኑ ተማሪዎች ላይም መጠነኛ የአካል ጉዳት ደረሷል ።
የዩኒቨርሰቲው  ፕሬዝዳንት ዶክተር አድማሱ ሽብሩ ለፋና ብሮድካስቲን ኮርፖሬት እንደተናገሩት ፤ አደጋው ከሌሊቱ 10 ሰዓት ላይ የተነሳ ሲሆን ፤ መንስኤው ግን እስካሁን ድረስ አልታወቀም ።
እሳቱን በአካባቢው ህብረተሰብና በአዲስ አበባ የእሳትና ድንገተኛ አደጋዎች መከላከያና መቆጣጠሪ ኤጀንሲ ሰራተኞች ትብብር በቁጥጥር ስር ማዋል ተችላል ያሉት ዶክተር አድማሱ ፤ አደጋው በሰው ህይወት ላይ ምንም ዓይነት ጎዳት አለማድረሱን ተናግረዋል።
በቃጠሎው ወቅት ከህንጻው ለመውጣት በሚያደረጉት ግፊያ ቁጥራቸው ለጊዜው ያልታወቁ ተማሪዎች ከግድግዳ ጋር በመጋጨትና በመውደቅ ቆስለዋል።
ተማሪዎቹም በአካባቢው በሚገኝው አጣጥ ሆስፒታል ህክምና እየተደረገላቸው ይገኛል።

 

ለኢትዮጵያ ሙስሊሞች መፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴ የመሰከሩ ዛቻ እና ማስፈራሪያ ተፈጸመባቸው።

May 26/2014
ምንሊክ ሳልሳዊ

የአወሊያ ትምህርት ቤት ኮሌጅና ሀይ ስኩል መምህራኖች ለትምህርት ቤቱ አስተዳደር ያነሱት የደመወዝ ጭማሪ ጥያቄን ከአመፅ ጋር በማያያዝ ለኮሚቴዎቹ በመሰከሩ መምህራኖች ላይ ዛቻና ማስፈራሪያ እየተፈፀመባቸው እንደሆነ ተገለፀ ።
FITH RADIO [ፍትህ ሬዲዮ]
ከኑሮው ውድነት ጋር ተያይዞ የሚከፈላቸው ደመወዝ ከእጅ ወደ አፍ የሆነባቸው የአወሊያ ትምህርት ቤት መምህራን ግንቦት 4\2006 በአወሊያ ትምህርት ቤት ቅጥር ግቢ ውስጥ በመሰባሰብ የአወሊያ ትምህርት ቤት አስተዳደር እስከዛሬ በሰሩት ስራና ውጤት ፍትሃዊ የደመወዝ ጭማሪ እንዲደረግላቸው መጠየቀቸው የሚታወስ ነው ፡፡
መምህራኖቹ ለትምህርት ቤቱ አስተዳደር ይህን ጥያቄ በሰላማ መንገድ ሲጠይቁ ትምህርት ቤቱ ከቻለጥያቄያቸውን ሰምቶ ምላሽ እንዲሰጣቸው ካልሆነ ደግሞ መጪው የትምህርት ዘመን ከመድረሱ በፊት የተሻለ ነው የሚሉትን አማራጭ ለመወሰን እንዲያመቻቸው ፈጣን ምላሽ መጠየቃቸው እየታወቀ የመንግስት ደህንንቶችና የፀጥታ ሰዎች ግን ሂደቱን የመምህራን አመፅ አስመስለው በማቅረብ አንዳንድ መምህራንን እያሸማቀቁና እያስፈራሩ መሆኑን ምንጮች ለፍትህ ሬዲዮ ገልፀዋል ፡፡
ከ 5 እስከ 30 አመታት ባገለገልንበት ተቋም እየተከፈለን ያለው ደመወዝ በቂ ባለመሆኑ አስተዳደሩ ማሻሻያ ያድርግልን የሚል ጥያቄ ከማንሳታቸው በቀር አንድም ማስፈራሪያ እንዳልሰነዘሩ በወቅቱ ተሰብስበው በነበረ ጊዜ የያዙት ቃለ ጉባኤ አስርጂ እንደሆነ የፍትህ ሬዲዮ ምንጮች ጠቁመዋል ፡፡ በቅርቡ በፍርድ ቤት ተገኝተው ለኮሚቴዎቻችን የመከላከያ ምስክር የነበሩ መምህራኖችን ታርጌት ያደረገ የሚመስለው ይህ ማስፈራሪያ ሆን ተብሎ በመንግስት የተቀነባበረ ሴራ እንደሆነ ተገልፇል ፡፡ ይህን የመምህራኖች የደመወዝ ጭማሪ ጥያቄ አስተዳደሩ ፍትሃዊና ሰላማዊ መሆኑን ቢያምንበትም አንዳንድ የመንግስት ሃላፊዎች ግን የትምህርት ቤቱን አስተዳደር መምህራኖቹ እንደረበሹ አስመሰለው ክስ እንዲያቀርቡ በመጎትጎት በስብሰባው ላይ የተሳተፉትንና ለኮሚቴቻችን መከላከያ ምስክርነት የቀረቡትን መምህራኖች ለማሸማቀቅ እየተሞከረ ለመሆኑ ለአስተዳደሩ ቅርበት ያላቸው ወገኖች ለፍትህ ሬዲዮ አጋልጠዋል ፡፡

Sunday, May 25, 2014

የመጨረሻዉ ካርድ

May 25/2014

አገራችን ኢትዮጵያ ባለፉት ሃያ ሦስት አመታት ያለፈችበትን የግፍና የመከራ ዉጣ ዉረድ ወደ ኋላ መለስ ብሎ መመለክት መፈጠርን የሚያስጠላና ልብን የሚያደርቅ እራሱን የቻለ ሌላ በጭንቅና በመከራ የተሞላ ዉጣ ዉረድ ነዉና አለመሞከሩ ይመረጣል። ሆኖም አገራችንን ከዚህ ሳትወድ በግድ እጇን ታስራ ከገባችበት የጥፋት ቁልቁለትና የመከራ አዘቅት ዉስጥ ላንዴና ለመጨረሻ ግዜ ጎትቶ ለማዉጣት የግድ እዘህ ድቅድቅ ጨለማ ዉስጥ እንዴት ገባች ብሎ እራስን መጠየቅ ያስፈልጋልና ወደድንም ጠላን የሃያ ሦስቱን አመት ጉዟችንን ወደ ኋላ ዞር ብለን በጥሞና ማጤኑ አማራጭ የሌለዉ መንገድ ነዉ። የወያኔ ዘረኞች ፋሺስቱን ደርግ ጣልን ይበሉ፤ በ99.6 በመቶ ድምጽ ተመርጥን ይበሉ ወይም እድገት አመጣን ይበሉ የእነሱ ፍላጎት ምን ግዜም ቢሆን የኢትዮጵያን ህዝብ ረግጦ መግዛት ነዉ እንጂ ህዝብን በጨዋነት ማስተዳደር አይደለም። አንድን ህዝብ ረግጦ ለመግዛት የሚያስፈልገዉ ደግሞ ጠመንጃና ባዶ ጭንቅላት ብቻ ነዉ፤ ጠመንጃና ባዶ ጭንቅላት በገፍ የሚገኝበት ድርጅት ነዉና ወያኔ ደግሞ በዚህ በፍጹም አይታማም። የወያኔ ዘረኞች ፍላጎት የኢትዮጵያን ህዝብ ከጣሊያን ፋሺስቶች ባልተለየ መንገድ እየረገጡ መግዛት ቢሆንም አንድን ህዝብ ዝንተ አለም ረግጦ መግዛት አንደማይቻል በሚገባ ያዉቃሉ፤ ለዚህ ነዉ የኢትዮጵያ ህዝብ ሙሉ ኃይሉን እነሱ ላይ ለማሳረፍ በቆረጠ ቁጥር ህዝብን ከህዝብ የሚለያይና የሚያራርቅ ካርዳቸዉን እየመዘዙ ጸረ ህዝብና ጸረ አገር ጨዋታቸዉን የሚጫወቱት። በእርግጥም ወያኔዎች በስልጣን በቆዩባቸዉ ባለፉት ሃያ ሦስት አመታት የተለያዪ ካርዶችን መዝዘዋል – ፌዴራሊዝም እያሉ በፌዝራሊዝም ቀልደዉብናል፤ እድገትና ልማት እያሉ ጠብ ያለዉን ሁሉ እነሱ እራሳቸዉ እየዋጡ ሌሎቻችንን የበይ ተመልካቾች አድርገዉናል፤ በጎሳ ከፋፍለዉናል፤ በዘር አጥር አጥረዉናል። ዛሬ ደግሞ ለእነዚህ ተራ በተራ ለመዘዟቸዉ የክፋት ካርዶች አልታለልም ያለዉን የኢትዮጵያ ህዝብ ካዝናቸዉ ዉስጥ የቀረችዉን የመጨረሻ ካርድ መዝዘዉ በጎሳና በዘር ከመለያየት አልፈዉ በዘር ለማጋጨትና ደም ለማፋሰስ ጉድ ጉድ እያሉ ነዉ።
ኢትዮጵያ ዉስጥ ማንም ኃይል በምርጫ ሥልጣን ያዝኩ ብሎ አፉን ሞልቶ ለመናገር ኦሮሚያና አማራ ክልል ዉስጥ ምርጫዉን ጉልህ በሆነ ብልጫ ማሸነፍ አለበት፤ ወይም አማራና ኦሮሚያ ዉስጥ ተሸንፎ ፓርላማ ዉስጥ አብዛኛዉን ወንበር ተቆጣጥሮ መንግስት መመስረት አይቻልም። ወያኔ ዛሬ ያንን የእንቅልፋሞች ፓርላማዉ ተቆጣጥሮ መንግስት ነኝ ብሎ የሚፏልለዉ ሁለቱን የአገራችንን ግዙፍ ብሄረሰቦች ለያይቶና አንዱ ሌላዉን በጥርጣሬ አይን እንዲመለከት አድርጎ ነዉ እንጂ ወያኔ በየቀኑ የሚያስራቸዉ፤ የሚደበድባቸዉ፤የሚያሳድዳቸዉና የሚገድላቸዉ የአማራና የኦሮሞ ህዝቦች በፍላጎታቸዉ መርጠዉታማ አይደለም። ወያኔ ዛሬ ከሚታይበት የፖለቲካ ኪሳራና ህዝባዊ መተፋት አንጻር እንደቀድሞዉ ኦሮሞንና አማራን በመከፋፈልና በመለያየት ብቻ ስልጣን ላይ መቆየት እንደማይችል ስለተረዳ እነዚህ ሁለት የአገራችን ግዙፍ ብሄረሰቦች እርስ በርሳቸዉ ተጋጭተዉ እንዲተላለቁ የሚቻለዉን ሁሉ እያደረገ ነዉ። ወይም ቀለል ባለ አማርኛ ወያኔ ከጫካ ይዞት የመጣዉን የመጨረሻ ካርድ መዝዞ አገራችንን በቀላሉ ወደ ማትወጣዉ የዘርና የጎሳ ግጭት ዉስጥ ለመክተት ቁጭ ብድግ እያለ ነዉ።
ወያኔ የመሬት ባለቤትነትን ጉዳይ ህገ መንግስቱ ዉስጥ ሸንቁሮ ኢትዮጵያ ዉስጥ መሬት የግል ንብረት የሚሆነዉ በእኔ መቃብር ላይ ነዉ ያለዉ አለምክንያት አይደለም። ወያኔ ኢትዮጵያ ዉስጥ መሬት የህዝብና የመንግስት ነዉ ይበል እንጂ ዛሬ ኢትዮጵያ ዉስጥ ትክክለኛዉ የመሬት ባለቤት ህዝብም መንግስትም ሳይሆን ህወሀት ወይም ወያኔ ነዉ። ይህንን ወያኔ የሚባል የዘረኞች ስብስብ ባስቸኳይ ጠራርገን በገዛ አፉ እንደተናገረዉ በወያኔ መቃብር ላይ የአገራችንን የተዛባና ጎታች የመሬት ይዞታ በፍጥነት ካልቀየርን ሁላችንም የወያኔ ገባር መሆናችን የማይቀር ነዉ:። ዛሬ ወደድንም ጠላን አገራችን ዉስጥ ልክ እንደፊዉዳሉ ዘመን መሬት እንደ ስጦታ ለዘመድና ለቤተዘመድ የሚሰጥ ደሃዉንና ሀብታሙን የሚለይ የመጨቆኛ መሳሪያ ነዉ። መሬት መብት መርገጫ ነዉ፤ መሬት አፍ ማስዘግያ ነዉ፤ መሬት ማማለያ መሳሪያ ነዉ፤ መሬት የማይወዱትናን የኛ አይደለም የሚሉትን ማግለያና መድረሻ ማሳጫ ነዉ። ባጠቃላይ ዛሬ ኢትዮጵያ ዉስጥ መሬት የወያኔ ቂም በቀል መወጫ አይነተኛ መሳሪያ ነዉ። ወያኔ እኔን አይደግፈኝም ከሚለዉ ከማንም ሰዉ መሬት ቀምቶ ላሰኘዉ ሰዉ መስጠት ይችላል። ይህንን ለማረጋገጥ ደግሞ ብዙ መጓዝ አያስፈልግም፤ አዲስ አበባን ጨምሮ በየክልሉ አዳዲሶቹን የከተማ ቦታና ሰፋፊ የእርሻ መሬት ባለቤቶች እነማን እንደሆኑ መመልከቱ ይበቃል።
በቅርቡ አምቦ ዉስጥ በግፍ የተጨፈጨፉት የኦሮሞ ተማሪዎች እንደዚህ አይነቱን አግላይ የሆነ የወያኔ የመሬት ፖሊሲ የተቃወሙ ተማሪዎች ናቸዉ። ዘረኛዉ የወያኔ አገዛዝ በልማት ስም በአዲስ አበባ ዙሪያ የሚኖሩ የኦሮሞ ገበሬዎችን እያፈናቀለ መሬቱን ለራሱ ወገኖች መስጠቱን በመቃወም አምቦ፤ ጅማ፤ ወለጋ፤ አዳማና ሐሮማያ ዩኒቨርሲቲ ዉስጥ የሚማሩ የኦሮሞ ተማሪዎች ወያኔንና ደጋፊዎቹን ክፉኛ ያስደነገጠ ከፍተኛ የተቃዉሞ ሰልፍ ያደረጉትና ምትክ የሌለዉን ህይወታቸዉን የገበሩት ይህ እጅግ በጣም አደገኛ የሆነ የወያኔ የመሬት ፖሊሲ ስለገባቸዉ ነዉ። በዚህ በተለያዩ ቦታዎች በተካሄደዉ የተቃዉሞ ስልፍ ላይ የኦሮሞ ተማሪዎች ያነገቡት አንድ ጥየቄ ብቻ ነበር፤ እሱም ህዝብን ያላካተተ ልማት የለምና ወላጆቻችንን እያፈናቀላችሁ መሬታችንን መከፋፈል አቁሙ የሚል ጥያቄ ነበር። ለዚህ የኦሮሞ ተማሪዎች በሰላማዊ መንገድ ላቀረቡት ጥያቄ ወያኔ የሰጠዉ መልስ እንደተለመደዉ በአግአዚ ነብሰ ገዳዮች ወጣቶችን በየአደባባዩ በጥይት መጨፍጨፍ ነበር – አዎ! የወያኔ ስራ ጥያቄ ሲጠይቁት መግደል፤ ምርጫ ሲሸነፍ መግደል፤ ለምን ጻፍክ ብሎ መግደል፤ ለምን ተናገርክ ብሎ መግደል ነዉ።
ወያኔ በሃያ ሦስት አመታት የስልጣን ዘመኑ እንደ ዘንድሮ ተገፍቶ ተገፍቶ ዳር የደረሰበትና እንደ ዘንድሮ መዉጪያና መግቢያዉ ጠፍቶበት አያዉቅም። እኛ ብናምንም ባናምንም ወይም ብናዉቅም ባናዉቅም ወያኔ የተከበበ አዉሬ ሆኗል፤ ግን ከዚህ በፊት አንዳደረገዉ ሁሉ የከበቡት ኃይሎች ፊት ለፊት የሚተያዩና አብረዉ የሚሰሩ ኃይሎች ባለመሆናቸዉ ወያኔ ከበባዉን ጥሶ ለመዉጣት እየሞከረ ነዉ። ከላይ ከፍ ሲል ለመጥቀስ እንደሞከርነዉ ወያኔ እንደ ዘንድሮ ተዋክቦና እንደዘንድሮ የመጨረሻዉ ሸትቶት አያዉቅም። ሆኖም እንድ መርሳት የሌለብን ነገር ቢኖር ወያኔ ከገጠመዉ ህዝባዊ ቁጣ ለማምለጥና ስልጣን እንደጨበጠ ለመቀጠል እንደዛሬ የዘር መለያየትና ማጋጨት ሴራዉን ተግባራዊ ያደረገበት ግዜም የለም። እዉነቱን ለመናገር በአንድ በኩል ምንም ጥርጥር በሌለዉ መልኩ ወያኔ ተከብቦ ህልዉናዉ አደጋ ላይ ወድቋል፤ በሌላ በኩል ደግሞ ወያኔ ከዚህ ተገፍቶ ከገባበት አደጋ ለመዳን አገራችን ዉስጥ ዘርና ጎሳ ለይቶ ህዝብን ከህዝብ ጋር የሚያባላ የእርስ በርስ ጦርነት ለመቀስቀስ ዝግጅቱን ጨርሷል።
የኦሮሞ ተማሪዎች ባካሄዱት የተቃዉሞ ሠልፍ ዉስጥ አልፎ አልፎ የተሰማዉ “የሚኒልክ ሃዉልት ይፍረስ” የሚለዉ ጩኸትና ጊምቢና በአንዳንድ የኦሮሚያ ክልል ወረዳዎች አማራ ይዉጣልን የሚለዉ ጥያቄ የህዝብ ጥያቄ ሳይሆን ወያኔ ሆን ብሎ ከትኩቶ ባሳደጋቸዉ ካድሬዎቹ አማካይነት ህዝብ ዉስጥ ይዞት የገባዉ የእርስ በርስ እልቂት መቀስቀሻ ጥያቄ ነዉ። ሁለቱ ዝሆኖች ሲጣሉ የሚሰቃየዉ ሳሩ ነዉ እንደሚባለዉ ወያኔ የአማራንና የኦሮሞን ብሄረሰቦች በማጋጨት እነዚህ ሁለት የአገራችን ብሄረሰቦች እርስ በርስ ሲፋጩና የኢትዮጵያ ህዝብ ሲሰቃይ እሱ የስልጣን ዘመኑን ማራዘምና የዘረፋ ተልዕኮዉን እንደገና ማደስ ይፈልጋል። ይህ “እኔ ከሞትኩ ስርዶ አይብቀል” አይነቱ የወያኔ ሴራ ለወደፊት ሊከናወን በዕቅድ የተያዘ ጥንስስ ሳይሆን ከአመታት በፊት ጫካ ዉስጥ ታቅዶ ዛሬ ተግባራዊ በመሆን ላይ ያለ የወያኔ ተንኮል ነዉ።
ወያኔ የኦሮሞና የአማራ ብሄረሰቦች እጅ ለእጅ ተያይዘዉ ከተነሱበት የስልጣን ዘመኑ በቀኖች እንደሚቆጠር በሚገባ ያዉቃል፤ በሌላ በኩል ደግሞ እነዚህ አብዛኛዉን የኢትዮጵያ ህዝብ ያቀፉት ሁለት ግዙፍ ብሄረሰቦች በመካላቸዉ ስምምነት ከሌለና አንዱ ሌላዉ ላይ በቂም በቀል ከተነሳ ማንም በቀላሉ ከስልጣን እንደማያባርረዉ ጠንቅቆ ያዉቃል፤ ለዚህም ነዉ ባገኘዉ አጋጣሚ ሁሉ እንዚህ ሁለት ብሄረሰቦች እንዲጋጩ ክብሪት የሚጭረዉ። አምቦ፤ ጊምቢ፤ አኖሌና ምስራቅ ኢትዮጵያ ዉስጥ በተደጋጋሚ የተጫረዉ የዘር ግጭት መቀስቀሻ እሳት ወያኔ አማራዉንና ኦሮሞዉን ለማጋጨት ሆን ብሎ የለኮሰዉ እሳት ነዉ። ዛሬ የኦሮሞን ተወላጆች ስልጣን መድረክ አካባቢ እንዳይቀርቡ አድርጎ የኦሮሚያን መሬትና የመሬት ላይና ዉስጥ ኃብት በገፍ የሚዘርፈዉና የአገሪቱን እስር ቤቶች በኦሮሞ ተወላጆች የሞላዉ ወያኔ ነዉ እንጂ ግዑዙና የማይናገረዉ የምኒልክ ኃዉልት አይደለም። ኦህዴድ የሚባል ተለጣፊ ባቡር ሰርቶ የኦሮሞን ህዝብ የሚገድለዉና በገዛ መሬቱ ላይ ባይተዋር ያደረገዉ ወያኔ ነዉ እንጂ ከመቶ አመት በፊት ሞተዉ የተበሩት ዳግማዊ ምኒልክ አይደሉም። ስለዚህ የኦሮሞ ህዝብ ከአማራዉና ከሌሎቹ ወንድሞቹና እህቶቹ ጋር ሆኖ ማፍረስ ያለበት የምኒልክን ኃዉልት ሳይሆን ወያኔንና ወያኔ የፈጠረዉን ዘረኛ ስርዐት ነዉ።
ባለፈዉ ወር አምቦ ላይ ያየነዉ የአግአዚ ጭፍጨፋ ወያኔ ከደገሰልን ጥፋት ጋት ሲነፃፀር እጅግ በጣም ትንሽ ነዉ፤ ወያኔ እያንዳንዳችንን በተናጠል በመታና በገደለ ቁጥር ቁጣችንን የምንገልጸዉና የምንከላከለዉ በተናጠል ከሆነ ወያኔ እያንዳንዳችንን በተናጠል እየገደለም ሆነ እያሰረ ጭጭ የማስደረግ ኃይል አለዉ። ይብዛም ይነስ የወያኔን ጥቃት ተቋቁመን ወያኔን ማስወገድ የምንችለዉ በጋራ አንድ ሆነን ስንቆም ብቻ ነዉ። እያንዳንዳችን ሺ ጠመንጃ ይዘን ወያኔን በተናጠል ብንገጥመዉ አናሸንፈዉም፤ ሁላችንም ተባብረን እንደ አንድ ሰዉ መቆም ከቻልን ግን ወያኔን ለማሸነፍ ጠመንጃም አያስፈልገንም። ስለዚህ ዛሬ ለኛ ለኢትዮጵያዉያን የትብብር ጥያቄ የትግል አማራጭ ሳይሆን በፍጹም ልናልፈዉ የማይገባን የህልዉና ጥያቄ ነዉ። እኛ ኢትዮጵያዉያን – ኑ አብረን እንታገል እያልን የትግል ጥሪ ስናስተላልፍ ወያኔ ደግሞ አገር እያፈረሰና ህዝብ እየገደለ ከሃያ አመት በላይ ተጉዘን ዛሬ ላይ ደርሰናል። የእኛ ጩኸት ከሃያ አመት በኋላ ዛሬም እንተባበር የሚል ነዉ፤ ሃያ አመት ሙሉ አገር ሲንድና ህዝብ ሲገድል የከረመዉ ወያኔ ግን ዛሬ የተቃወመዉን ሁሉ ቢቻል ለመግደል አለዚያም ለማሰር እየተንቀሳቀሰ ነዉ። እንደ አገርና እንደ ህዝብ በአንድነታችን ፀንተን ለመቀጠል ካሁን በኋላ ያለን ብቸኛ አማራጭ ጥቂቶች ታስረን፤ ጥቂቶች ተሰድደን ጥቂቶች ደግሞ ሞተን ወያኔን ማስወገድ ወይም በተናተል ሁላችንም ተራ በተራ መሞት ነዉ።
አባቶቻችን ያስተማሩንና እኛም በነጋ በጠባ እንደ ዳዊት የምንደግመዉ ይህንኑ ለእናት አገሬ እሞታለሁ የሚለዉን የአባቶቻችንን ትምህርት ነዉ።
ወገን ለኢትዮጵያ መሞት ካለብን ቀኑ ዛሬ ነዉ . . . . ኑና ለእዉነት ሞተን በህይወት እንኑር!