Monday, May 19, 2014

ዘር ማጥራት ወይስ ኢህአዴግን ማፍረስ? (ተመስገን ደሳለኝ)

May19/2014
Temesgen Desalegn "Fact" Ethiopian Amharic newspaper editor

ኢህአዴግ ያነበረውን ቋንቋንና ዘውግን መሰረት ያደረገ ፌዴራሊዝም አደገኛነት በተመለከተ  በርካታ ምሁራን፣ ፖለቲከኞች፣ ጋዜጠኞች… ሳያሰልሱ ለመምከርና ለማስጠንቅቅ መዋተታቸውን  አልዘነጋሁም፡፡ እኔም ከ“ፍትህ” ጋዜጣ እስከ “ፋክት” መጽሔት ድረስ ችክ ያልኩበትም ሆነ ዛሬ በዚህ ተጠየቅ የተመለስኩበት ምክንያት ችግሩ እያደር እየተባባሰ በመምጣቱና ከምንጊዜውም በላይ  አዘናግቶ ወደተፈራው የእርስ በእርስ እልቂት ሊዘፍቀን እየተንደረደረ በመሆኑ፣ ቅድሚያ ሰጥተን  በሕብረ-ድምፅ ‘የሀገር ያለህ!’ ብለን መጮህ እንዳለብን ስለማምን ነው፡፡

አርባ አራት ዓመት ወደኋላ…

በኢትዮጵያ የዘውግ ጥያቄ ለአደባባይ የበቃው በ60ዎቹ መጀመሪያ እንደነበረ ይታወሳል፡፡ ከዘመነኞቹ የተማሪ እንቅስቃሴ መሪዎች ይህንን ጥያቄ አለቅጥ ለጥጦና አጋንኖ በማቅረብ ግንባር ቀደሙ ዋለልኝ መኮንን ነው፡፡ በ1962 ዓ.ም በአራት ገፅ  ቀንብቦ ባዘጋጀው ታሪካዊ ጽሑፉ አማካኝነት “የብሔሮች ጥያቄ” ይፋ ሆኖ ለውይይት ከመቅረቡ በፊት፣ የተማሪው ዋነኛ  የመታገያ አጀንዳ የመሬት ጉዳይ እንደነበር የታሪክ ድርሳናት ያወሳሉ (በደብዛዛውም ቢሆን ይንፀባረቅ የነበረውን መደብ ተኮር  መንፈስ ሳንረሳ)፡፡ ዋለልኝ የሀገሪቱን መንግስታዊ አወቃቀርም ሆነ ባሕልን በአማራና በትግሬ ተፅእኖ ስር ስለመውደቁ  በተቸበት በዚያ “ዝነኛ” ጽሑፉ ላይ እንዲህ ይላል፡-

“…ማንንም ሰው የኢትዮጵያውያን ቋንቋ ምንድን ነው ብላችሁ ጠይቁ፤ የኢትዮጵያውያን ሙዚቃ የቱ ነው ብላችሁ ጠይቁ፤ የኢትዮጵያውያን ባሕል የቱ ነው ብላችሁ ጠይቁ፤ ብሔራዊ ልብሳችሁ የቱ ነው ብላችሁ ጠይቁ፤ የአማራ  ወይም የትግሬ ይላችኋል፡፡”

ይህ ሀቲት በወቅቱ በአብዛኛው ተማሪ ዘንድ ቁጣ ከመቀስቀሱም በላይ ዋለልኝን በ‹ፀረ-አማራና ትግሬነት› አስፈርጆ  ለውግዘት ዳርጎት ነበር፡፡ እራሱም ቢሆን በአንድ የዩንቨርስቲው መድረክ ላይ የተሰነዘረበት ከባድ ተቃውሞ በፈጠረበት ብስጭት ‹‹እኔም አማራ ነኝ፤ ያውም ከአማራ ሳይንት-ቦረና›› ማለቱ ይታወሳል (ቦረና በተለምዶ አማራ መጥቶበታል  የሚባለው አካባቢ መሆኑን ልብ ይሏል)፡፡ ግና፣ ዋናው ጥያቄ የእርሱ አማራ መሆን ያለመሆን አይደለም፤ እዚህ ድምዳሜ ላይ  የደረሰበት ምክንያት ከተጨባጩ እውነታ ጋ ምን ያህል ይዛመዳል? የሚል ነው፡፡ ሌላው ነገር ደግሞ ከዚህ ጽሑፍ በፊት  ብሔር ተኮር ጎዳዮችን አንስቶ ካለማወቁም በዘለለ፣ ሌሎች ሲያነሱ ፅንፈኛ ተቃዋሚ ስለነበረ ነው፡፡ ለምሳሌ ተማሪ ኢብሳ  ጉተማ (ኋላ ላይ የኦነግ መስራችና አመራር የሆነው) ‹‹ኢትዮጵያዊ ማነው?›› በሚል ርዕስ ባቀረበው ግጥም እጅግ ተናድዶ  ‹‹እንዴት እንዲህ አይነት ግጥም ታቀርባለህ? ዘረኛ ነህ፤ ኢትዮጵያውያንን የመከፋፍል ዓላማ ነው ያለህ?›› በማለት  እስከመቃወም መድረሱ የክርክሩ አንዱ ጭብጥ ነው፡፡

ታዲያ ዋለልኝ መኮንን ድንገት እዚህ ድምዳሜ ላይ የደረሰው ከምን የተነሳ ይሆን? በርግጥ ለዚህ ድንገቴ የአቋም ለውጥ ሶስት  መላ-ምቶች ሲነገሩ ቆይተዋል፡፡ የመጀመሪያው ‹በአፄው ሥርዓት ላይ አሴረዋል› ተብለው ከተከሰሱትና ‹ኦሮሞ እየተጨቆነ ነው› የሚል እምነት ከነበራቸው ጄነራል ታደሰ ብሩ ጋር በታሰረበት ወቅት፣ በጄነራሉ ስብከት አመለካከቱ ተቀይሮ ሊሆን  ይችላል የሚለው ሲሆን፤ ሁለተኛው ደግሞ ‹‹መገንጠልን መደገፍ በመጨረሻ የማትገነጠል ሀገር እንድትኖር ያደርጋል››  በማለት ከተከራከረበት ከራሱ አቋም ጋር የሚያያዝ ነው፤ ሶስተኛው ‹የሻዕቢያ (ኤርትራውያን ተማሪዎች) አሊያም የአሜሪካኑ  የስለላ ተቋም (ሲ.አይ.ኤ) መጠቀሚያ ሆኖ ነው› የሚሉት ዋነኞቹ ናቸው፡፡ ይሁንና ከዋለልኝ ጀርባ ‹ስውር እጅ›ን ለመፈለግ  ያስገደደው በጊዜው ብዙሁ ተማሪ ለሀገሪቱ ዘርፈ-ብዙ ችግሮች ‹የንጉሣዊው አስተዳደር ኋላቀርነት እና ስግብግበነት ነው› ብሎ  ከማመኑም ባለፈ፣ ከፌዴራላዊ ይልቅ የቻይና ኮሙኒስታዊ ሥርዓት አድናቂ የመሆኑ ጉዳይ ነው፡፡ ሌላው ቀርቶ የተማሪውን  እንቅስቃሴ በመምራት በዘመኑ ከዋለልኝ የላቀ ተሰሚነት የነበረው ጥላሁን ግዛው ‹‹ጎሰኝነትን›› በአደባባይ አጥብቆ ይቃወም እንደነበረ፣ በ1968 እ.ኤ.አ የታተመው ‹‹Struggle›› ቅፅ 3፣ ቁጥር 1 መጽሔት ጋር ያደረገውን ቃለ-መጠይቅ መጥቀስ ይቻላል፡-

‹‹በመጀመሪያ ደረጃ በጎሰኝነትና በሶሻሊዝም መካከል ያለውን ልዩነት ማሳየት እፈልጋለሁ፡፡ ጎሠኝነት በተወሰነ አካባቢ ብቻ  የሚቀርና አካባቢ ቀመስ ነው፡፡ ሶሻሊዝም ግን ዓለም ዓቀፋዊ ነው፡፡ …እንደ ዩንቨርስቲ ተማሪነታችንና እንደ እጩ  ምሁርነታችን የሕብረተሰባችንን አቋም ከመደብ አንፃር መተንተን እንጂ በጎሣ መከፋፈል አይገባም›› ማለቱ ይታወሳልና፡፡

የህወሓት-ውልደት

ዋለልኝ መኮንንን ‹‹የብሔር ጭቆና›› ትንተናን መሰረት ያደረጉ ጥቂት የማይባሉ የፋኖ ድርጅቶች መመስረታቸው  አይካድም፡፡ ከእነዚህም መንግስታዊውን ሥልጣን ለመጨበጥ የበቃው ህወሓት አንዱ ነው፡፡

የአማራና ትግሬ ጨቋኝነትን የሚያውጀው ጽሑፍ በተሰራጨ በአምስተኛው ዓመት የትግርኛ ተናጋሪውን ብሔራዊ ጭቆና ለማስረገጥ ጽሑፉን እንደ ሰነድ ማስረጃ ቆጥረው ‹‹ትግራይን ነፃ እናወጣለን!›› ያሉ ፋኖዎች ነፍጥ አንግበው በረሃ ቢወርዱም፣ በመጀመሪያዎቹ ጥቂት ዓመታት አካባቢ ‹‹እንታገልለታለን›› በሚሉት ዘውግ ተወላጆች ሳይቀር መናፍቅ ተደርገው መወገዛቸው ይታወሳል፡፡ ደራሲና ገጣሚ አስማማው ኃይሉም ‹‹ኢህአሠ›› በተባለው መጽሐፉ እንዲህ ይለናል፡-

‹‹በ1969 ዓ.ም አጋማሽ አካባቢ በእምባ ሰገንይቲ ወረዳ ነበለት አካባቢ ሽምዕጭ ተብሎ በሚጠራው መንደር የህወሓትና የኢሕአሠ አባላት ሕዝብን ለመቀስቀስ ተገኝተው ነበር፡፡ ሁለቱም ቡድኖች የድርጅታቸውን ዓላማ ካስረዱ በኋላ ያካባቢው አዛውንት ማሳረጊያውን ንግግር አደረጉ፡፡ አዛውንቱ መሔድ የሚሳናቸው ስለነበሩ ሰዎች ደግፈው ወደ በቅሏቸው እንዲያወጧቸው ከጠየቁ በኋላ የሚከተለውን ንግግር አደረጉ፡፡ ወደ ህወሓት አባላት እጃቸውን ዘርግተው ‹እናንተ ከሆዳችን የወጣችሁ ልጆቻችን ናችሁ›፤ ወደ ኢሕአሠ አባላትም ፊታቸውን አዙረው ‹እናንተ ደግሞ ከሁሉም የኢትዮጵያ ግዛት መጥታችሁ ለእኛ ስትሉ ነው የምትታገሉት፡፡ የሆነው ሆኖ እኛ የትግራይ ሰዎች ሆነን ስንቀር ኢትዮጵያ ከማን ጋር ልትቀር ነው? ስለሆነም እኛ ኢትዮጵያዊ ከሚል ጋር ነው የምንወግነው› ሲሉ ሃሳባቸውን ሰነዘሩ፡፡›› (ገፅ 235)

ህወሓት በትግራይም ሆነ በተቀረው የሀገሪቱ ክፍል የነበረውን አገዛዛዊ ጭቆና፣ የብሔር አስመስሎ እስከ መገንጠል ቢንደረደርም፣ የገጠመው ተቃውሞ ፕሮግራሙን ለመከለስ አስገድዶታል፡፡ ዘግይቶ ላገኘው ድጋፍም ቢሆን ከዘውግ ተኮሩ ተረት-ተረት ይልቅ አምባ-ገነናዊው የደርግ አስተዳደር የወለደው ሽብርና ጭፍጨፋ የተሻለ ጠቅሞታል፡፡ ለዚህም በዛሬይቷ ትግራይ ከሶስት ያላነሱ ፀረ-ህወሓት ድርጅቶች መኖራቸው ማሳያ ይሆናል ብዬ አስባለሁ፡፡

በሌላ በኩል ከህወሓት ምስረታ አንድና ሁለት ዓመት አስቀድሞ ወደ አደባባይ የመጡት ኢህአፓና መኢሶን የትግል አጀንዳቸው የመደብ ቅራኔ ላይ የተመሰረተ ነበር፡፡ ይህ ግን በወቅቱ ከህወሓትም በከረረ መልኩ ‹‹የብሔር ጥያቄ በመገንጠል ብቻ ነው የሚፈታው›› የሚል እምነት ተከታዩ ኦነግን ህልውና አያስክድም፡፡ እዚህ ጋ የምንመለከተው ሌላኛው ግራ አጋቢ ጉዳይ የመጀመሪያው የቀዳማዊ ኃ/ስላሴ ዩንቨርስቲ ተማሪዎችን የ‹‹መሬት ላራሹ››ን ሠልፍ (በ1957 ዓ.ም) አስተባብሮ የሕግ-መወሰኛው ምክር ቤት ድረስ የመራው ባሮ ቱምሳም (በአብዮቱ ሰሞን የኢጭአት የአመራር አባል ነበር) ሆነ፤ የመኢሶኑ ቁልፍ ሰው እንደሆነ የሚነገርለት ኃይሌ ፊዳን የመሳሰሉ የኦሮምኛ ቋንቋ ተናጋሪ ልሂቆች፣ ከኦነግ በተቃራኒው ከብሔር ይልቅ የመደብ ጥያቄ አቀንቃኝ የነበሩ መሆኑን ነው፡፡ በነገራችን ላይ በግሌ ዛሬም ቢሆን ኢትዮጵያዊ ብያኔ እነዋለልኝ የለጠጡትንና ያጎኑትን ያህል እንኳ ባይሆንም እንደገና መከለስ እንደሚያስፈልገው አምናለሁ፡፡

የሆነው ሆኖ ህወሓት መንግስታዊውን ሥልጣን በጨበጠ ማግስት ‹የሰነበተውን የብሔር ቅራኔ በማያዳግም ሁኔታ የሚፈታ› ሲል ያንቆለጳጰሰውን ቋንቋ ተኮር ፌዴራሊዝም ቢተገብርም፤ ከዚሁ ጋር ተያይዘው የሚነሱ ችግሮችን የመግታት አቅም እንደሌለው ለማረጋገጥ የአንድ እጅ ጣቶች ያህል ዓመታት እንኳን አልፈጀም፡፡ በደቡብ በጉጂ እና ጌዲዮ፣ በጉጂ እና ቡርጂ፤ በጋምቤላ በአኝዋክ እና ኑዌር፤ በቤንሻንጉል በጉምዝ እና በርታ መካከል የተከሰቱት የይገባኛል ግጭቶች በማሳያነት ይጠቀሳል፡፡

የፌዴራሊዝሙ ቀዳዳዎች

ዘውግ ተኮር ፌዴራሊዝሙ፣ ገና ከጠዋቱ ለከፋ ዕልቂት ሊዳርግ እንደሚችል በማስታወስ ይሰሙ የነበሩ የተራዘሙ ጩኸቶችን ችላ ብሎ ዛሬ ላይ ቢደርስም፤ ለፕሮፓጋንዳ በሸነቆራቸው ቀዳዳዎች እየገባ ያለው ከባድ ንፋስ ከራሱ አልፎ ሀገሪቷንም ከበታኝ አደጋ ፊት አቁሟታል፡፡ ለዚህም አገዛዙ የፈጠራ ትርክቱን ለማስረፅ የሄደበት የኑፋቄ መንገድ የአንበሳውን ድርሻ ይወስዳል፡፡ በፓርቲው ካድሬዎች በኩል በየዕለቱ የሚዘራው የጥላቻ ፖለቲካ፣ ሐውልት ማነፅ፣ ከፋፍሎ ማቆም እና መሰል ስልቱ በተጨማሪ ሜጋ በሚያሳትማቸው መጻሕፍት እልቂት ጠሪ ዘውግ ተኮር ቅስቀሳዎችን እስከማሰራጨት መድረሱን ተመልክተናል፡፡ ለአብነትም የሚከተለውን ግጥም ልጥቀስ፡-

“ነፍጠኞች እቤታቸው በክብር ይጎለታሉ፣
እኛን በኃይል አስገድደው ያሰራሉ፣
ቁጥቋጦ እንደምትመነጥረው መንጥራቸው
ወደመጡበት ወደ ሸዋ አባራቸው፡፡” (“ተራሮችን ያንቀጠቀጠ ትውልድ” ቅፅ 3፤ ገፅ 145)

ግና ‹‹ሸዋ›› ሱዳን ወይም ግብፅ አይደለምና ዛሬ ከጉራፈርዳ እስከ ደንቢዶሎና ጊምቢ ለተተገበረው የማባረር ዘመቻ ዋነኛው ተጠያቂ የሥርዓቱ ኤጲስ ቆጶሳት መሆናቸውን ግጥሙ ያስረግጣል፡፡ በግልባጩ እነዚህ ሰዎች በ97ቱ ምርጫ ዋዜማ፣ ሚያዚያ 30 ቀን መስቀል አደባባይ ቅንጅት በጠራው ሕዝባዊ ስብሰባ ላይ፣ አቶ በድሩ አደም ‹‹ወደመጡበት እንመልሳቸዋለን›› ማለታቸውን፣ ወደ ዘውግ ጥላቻ ከመቀየራቸውም በላይ፣ የቅንጅቱን አመራሮች ለቅመው ካሰሩ በኋላ የሰውየውን ንግግር ‹‹የዘር ማጥፋት ሙከራ!›› ሲሉ ለመሰረቱባቸው ክስ በማስረጃነት ማቅረባቸውን አስታውሳለሁ፡፡ በዚያው ሰሞን አቦይ ስብሃት ነጋም የብአዴን ጓዶቻቸውን ‹‹እኛ ወደመቀሌ ስንባረር፤ እናንተን መንዝ ላይ አራግፈን ነው የምንሄደው!!›› አሉ መባሉም ጉዳዩ በራስ ላይ ሲደርስ ምን ያህል አሳማሚ እና ለበቀል እንደሚያነሳሳ ሁነኛ ጥቁምታ ቢሰጥም፣ ገዥዎቻችን ተቃውሞዎች ዘውግ-ተኮር ወደመሆን ነበር የተሸጋገሩት፡፡ ኢህአዴግም ቢሆን በዩንቨርስቲዎች በተናጠል (በህወሓት፣ ብአዴን፣ ኦህዴድ እና ደኢህዴን) ስር ማደራጀት የጀመረው ከዚሁ ምርጫ በኋላ እንደነበረ አይዘነጋም፤ ለእንዲህ አይነቱ የፓርቲው ተልዕኮ ደግሞ እንደ ዶ/ር አድማሱ ፀጋዬ አይነት የገዥው-ፓርቲ መንፈስ የሰረፀበት ‹‹ምሁር›› ጠቀሜታን ለመረዳት አሁን አዲስ አበባ ዩንቨርስቲ ያለበትን ሁኔታ መቃኘቱ ብቻ በቂ ነው፡፡ በርግጥ ባለፉት ሁለት አስርታት የህወሓት አባልና ደጋፊ ተማሪዎች የግቢውን መንፈስ አይመረምሩም (አይሰልሉም) ነበር እያልኩ አይደለም፤ በግላጭ የጓደኞቻቸውን እንቅስቃሴ እየተከታተሉ ሪፖርት ያደርጉ ነበርና፡፡ በአናቱም የዘውግ ተኮር ፖለቲካው መተግበር በጀመረበት ወቅት ወደ ትምህርት ቤት የተላኩ ልጆች፣ ዛሬ ለዩንቨርስቲ መብቃታቸው፣ አጀንዳው በቅፅበት ሊፈፀም የመቻሉን እውነታ በኦሮሚያ ሰሞኑን የተመለከትነው ቀውስ በቂ ማሳያ ይሆናል፡፡

የተጭበረበረው አጀንዳ

‹የብሔር ጥያቄ ዋነኛው የቅራኔ ቅርፅ ነው› የሚለው ህወሓት ይህን ጥያቄ መፍታት ሥርዓታዊ ግብ እንደሆነ እስኪሰለቸን ቢደሰኩርም፤ አጀንዳውን ከማጭበርበሪያነት የዘለለ ዋጋ አልሰጠውም፡፡ እናም ታሪክ ቢያንስ በዚህ በኩል በበጎ እንደማያስታውሰው ለመናገርም ብዙ ማስረገጫዎችን መጥቀስ አይገድም፡፡ አሁንም ኢትዮጵያን እየናጣት ያለው፤ ጥያቄያችን አልተመለሰም› የሚሉ ብሔርተኛ ቡድኖች መበርከት መሆኑ ይታወቃል፡፡ በስያሜ ደረጃ እንኳን (መሬት ላይ ያላቸውን ጉልበት ትተን) ከአስራ አንድ የማያንሱ ተገንጣይ ንቅናቄዎች መኖራቸው እውነት ነው፡፡ የእነዚህን ከኦጋዴን እስከ ጋምቤላ፤ ከቤንሻንጉል እስከ አፋር ድረስ ያሉ አማፅያን እንቅስቃሴን የጥቂት ልሂቃን ቅብጠት አድርጎ መውሰድ ርትዕ አይሆንም (ስለምን ቢሉ ደርግም ህወሓትን የሚያስበው እንዲያ ነበርና)፡፡ እናም ከትልቁ ኦሮሞ ጥያቄ መጠለፍ ጀምሮ፤ እነዚህ ጉዳዮች አስቀድሞ ግንባሩ የብሔር ጥያቄን ለሥልጣን መወጣጫ ብቻ ለመጠቀም ማስላቱን ይጠቁሙናል፡፡

ሌላኛው ጭብጥ አሁንም ድረስ ማንነት ተኮር ጥያቄዎች አለመቆማቸው ነው፡፡ ከቅማንት እስከ ወለኔ እና ቁጫ ድረስ ያሉት ‹‹ማንነታችን ታውቆ ዞን ይሰጠን›› ጩኸቶች ማቆሚያቸው የቱ ጋ እንደሆነ ራሱ ኢህአዴግም የሚያውቅ አይመስለኝም፡፡ በግልባጩ ለእነዚህ ሶስት የማህበረሰብ ክፍሎች ጥያቄ በቅርቡ የሠጠው ምላሽ ጭፍለቃ መሆኑን ስናስተውል፤ ‹ተነሳሁለት› ከሚለው የብሔር ጭቆናን ማጥፋት አኳያ የሚነግረን ሀቅ ሥርዓቱ የሄደበትን ቁልቁለት ብቻ ነው፡፡

በሶስተኛነት ከዚሁ ጋር አያይዘን ልናነሳው የምንችለው ርዕሰ ጉዳይ የመገንጠል መብት ነው፡፡ ከዋለልኝ እስከ ጥላሁን ታከለ እና ቱሞቱ ሌንጮ (ፕ/ር እንድሪያስ እሸቴ) ድረስ የነበሩ የዘመኑ ትውልድ መንፈስ ተርጓሚዎች መገንጠልን ሕብረ-ሱታፌ (ሶሻሊስታዊ) ሥርዓት ለመገንባት መዳረሻ መንገድ አድርገው ቢያቀርቡትም፤ ጥራዝ ነጠቆቹ ህወሓቶች ሕገ-መንግስቱ ውስጥ ቀርቅረውታል፡፡ ለዚህም እንደምክንያት ‹‹መገንጠልን ለመከላከል ነው›› ቢሉም፤ ከፌደራሊዝሙ አወቃቀር አኳያ ‹የማይተገበር መብት› ስለመሆኑ ብዙ ተብሏል፡፡ ይህንን ለማስረገጥ በዋናነት ሁለት ነጥቦች ይነሳሉ፤ ‹እንደ ስታሊኒስቷ ሩሲያ ሁሉ መብቱ በሕገ-መንግስቱ ውስጥ ቢካተትም፣ የማዕከላዊ መንግስቱ ሥልጣን ፍፁማዊ መሆን እንዳይተገበር ያደርገዋል› የሚለው የመጀመሪያው ነጥብ ነው፡፡ ሁለተኛው የመብት አፈፃፀሙ ራሱ በተለያዩ አስገዳጅ ተዋረዳዊ ትግበራዎች መጠላለፉ ነው፡፡ በተለይም ሁለትና ከዚያ በላይ ዘውጎችን ያቀፉ ክልሎች የመገንጠል ጥያቄ ቢያነሱ ተፈፃሚነት እንደማይኖረው ለመረዳት የክልሎቹን አወቃቀር መመልከቱ ብቻ በቂ ይመስለኛል፡፡ ከእነዚህ ሁለት ነጥቦች ስንነሳ የመገንጠል ግብ ያላቸው እንቅስቃሴዎች በትጥቅ ትግል አገዛዙን ካላስወገዱት በቀር በሕገ-መንግስቱ መሰረት በሰላማዊ መንገድ ሊተገበሩ አለመቻላቸውን እንገነዘባለን፡፡ ይህ ሁነትም ሥርዓቱ ቋንቋን መሰረት ያደረገ ፌዴራሊዝም ያነበረው ከፋፍሎ ለመግዛት እንጂ፤ እስክንደነቁር በጩኸት ስለሚነግረን ‹‹ጭቁን ብሔር ብሔረሰቦች›› መብት ደንታ ኖሮት እንዳልሆነ ያስረግጥልናል ብዬ አስባለሁ፡፡

ግን እስከመቼ?

በዘመናዊቷ ኢትዮጵያ ታሪክ ከአፄ ኃይለስላሴ ቀጥሎ ረዘም ላለ ዓመታት ሀገሪቱን የመምራት ዕድል ያገኘው ኢህአዴግ የተሻለች ሀገር የመገንባት በርካታ ዕድሎችን አምክኗል፡፡ ወደሥልጣን በመጣ ማግስት ዘውገኝነትን የመንግስታዊ መዋቅሩ ብቸኛ ገፅ ሲያደርገው፣ ከብዙ ጫፎች ከተነሳበት ከባባድ ተቃውሞዎች መሀል፡- ቋንቋ ተኮር ፌዴራሊዝሙ ማሕበረ-ባሕላዊ መሰረቱ በጣም የተሳሳተ መሆኑን እና የዘውግ ማንነትን ብቸኛው የክልሎች ድንበር አሰማመር መነሻ ማድረግ ለእርስ በእርስ የዜጎች ትንቅንቅ ያጋልጣል የሚሉት ዋነኞቹ ነበሩ፡፡ ሥርዓቱ ይህን ጆሮ ሰጥቶ ከማዳመጥ ይልቅ ቢያፈገፍግም፣ ያሳለፍናቸው ሃያ ሶስት ዓመታት በሞቶችና በመከራዎች የተፃፉ ኩነቶችን አሳይተውናል፡፡ ‹‹ባለሥልጣን›› እና ‹‹ሥልጣን የለሽ›› (ባለቤትና መጤ) በሚል ጨዋታ፣ በየክልሎቹ የሚገኙ የሌላ ቋንቋ ተናጋሪዎች ከክልሉ የሥራ ቋንቋ ውጪ በመናገራቸው ብቻ፣ አንዳችም ተቋማዊ ውክልና እንዳያገኙ ማድረጉ፣ ከየአካባቢዎቹ በግፍ ለተፈናቀሉት የማሕበረሰብ ክፍሎች ዋነኛው መነሻ ሆኗል፡፡ አዲሱን የአዲስ አበባ የማስፋፊያ ዕቅድ ተከትሎ የተነሳው የኦሮሞ ተማሪዎች ተቃውሞም ሌላ ቅርፅ ወደመያዝ መሻገሩ አንዱ ሰሞነኛ ማሳያ ነው፡፡ በምዕራብ ወለጋ ለረዥም ጊዜ ኑሯቸውን መስርተው የነበሩት የአማርኛ ቋንቋ ተናጋሪዎች አካባቢውን ለቀው እንዲወጡ መገደዳቸው የሚቀጥል ከሆነ ደግሞ፣ የአማራ ክልልን ጨምሮ የየክልሎቹ ዘውጎች ‹‹መጤ›› ያሏቸውን ማባረር ላለመጀመራቸው እርግጠኛ መሆን የምንችልበት ምንም አይነት ዋስትና የለንም፡፡ እናሳ! ይህ አይነቱ ክልልን ከ‹‹መጤ›› ዘውግ የማንፃት ሂደት ማቆሚያው የቱ ጋ እንደሆነ ማን ሊገምት ይቻለዋል? ዘግናኝ ደም መፋሰስስ ሳያስከትል ይህንን ክፉ ድርጊት መሻገር የምንችለው እንዴት ነው?

እንግዲህ ይህ ሁሉ የፍርሰት መርዶ እየተሰማ ያለው፣ የሥርዓቱ ሰዎችና የጥቅም ተጋሪዎቻቸው ለዚህ ከፍታ የበቁበትን ሃያ ሶስተኛ የድል ዓመት በፌሽታ ለማክበር ደፋ ቀና በሚሉበት ዋዜማ ላይ ቆመን ቢሆንም ‹‹ጊዜው ከቶም ቢዘገይ አልረፈደም›› እንዲሉ፤ ተገፍቶ ገደል ጠርዝ የተንጠለጠለውን የኢትዮጵያን ህልውና በደለደለ መሰረት አፅንተን ለቀጣዩ ትውልድ ለማሻገር አንዳች እርምጃ መውሰዱ ብቸኛ አማራጭ ነው ብዬ አምናለሁ፡፡ ለዚህ ዘመን ለጣለው ትውልዳዊ የማንነት ዕዳ ክንውን ቀዳሚው ተግባር ኢህአዴግን ‹‹በቃህ!›› ብሎ ማስቆም እንደሆነም መቀበል የሚያስቸግር አይመስለኝም፡፡ ግና፣ ይህ ሳይሆን በወታደራዊ ጡንቻ ካሳለፍናቸው ዓመታት ጥቂቱን እንኳ እንዲሰነብት ከፈቀድንለት፣ የደም ባሕር ሲያጥለቀልቀን ቆመን ለመመልከት ተስማምተናል ማለት ነው፡፡

Sunday, May 18, 2014

አዜብ አከርካሪዋ በስብሃት ነጋ ተሰባብሮዋል። /እየሩሳሌም አርአያ/

May 18,2014
የአዜብ ነገር


ከሰሞኑ ኢህአዴግ ባካሄደው ጉባኤ ላይ አዜብ መስፍን ነበሩ። ከኋላ ፈንጠር ብለው ተቀምጠው ነበር። በሽተኛ ይመስላሉ። “እንኳንስ ዘንቦብሽ..” እንደሚባለው ያ ፊታቸው ገርጥቶ፣ የፉጨት አስተማሪ መስለው፣ ያ ሁሉ መኮፈስና ትእቢት ተንፍሶ ታይተዋል። አንዲት የአባይ ፀሐዬ ስጋ ዘመድ በቅርቡ ልጅ ለመውለድ ዲሲ መጥታ ስትናገር፥ « አዜብ አከርካሪዋ በስብሃት ነጋ ተሰባብሮዋል። ስብሃት አዜብን እንዳንታንሰራራ አድርጐ ከነተከታዮችዋ ከጨዋታ ውጭ አድርጓታል። የአዜብ ነገር አክትሞዋል፤ መልቀቂያ ብትጠይቅም ተቀባይነት አላገኘም። ስብሃት እያሳቀቀ በቁም እያሰቃያት ነው» ብላለች። ስብሃት ነጋ ይህን ማድረጋቸው እርግጥ ቢሆንም ነገር ግን ሁሉም አገሪቱን ቁልቁል የሚሰዱና በተለይ ስብሃት የዘርና ጐሳ መሐንዲስ እንደሆኑ ይታወቃል።….አዜብ “እበላዋለሁ” ብለው ከህዝብ ዘርፈው ያከማቹትን በቢሊዮን የሚቆጠር ገንዘብ- እያስጐመዠ በሰቀቀን የጨረሳቸው ይመስላል። ነፃ ፍ/ቤት ቢኖር ኖሮ አዜብ፣ አባይ ፀሐዬ፣ ስብሃት፣ በረከት…ወዘተ በሙስና ወንጀል መጠየቅ ነበረባቸው። ግን የለም!!… ጋዜጠኛ ሲሳይ አጌና በ1995ዓ.. በኢትኦጵ ጋዜጣ ላሰፈረው ርእሰ አንቀጽ የሰጠው ርእስ ሁሌም ያስገርመኛል፤ « የሙስና ኮሚሽን!» ነበር ያለው። በወቅቱ በዩኒቨርሲቲ ምሁራን፣ በገዢው ባለስልጣናትና መሰል አካላት ከፍተኛ መነጋገሪያ ሆኖ ነበር። እንዳውም የኮሚሽኑ ከፍተኛ ባለስልጣናት ጠርተው እንዳነጋገሩት አስታውሳለሁ። ..ለማንኛውም “የአዜብ ጥጋብ ሲተነፍስ ላሳየኸን ፈጣሪ ምስጋና ይድረስህ!!” ቀጣዩ ደግሞ….

ከሳዑዲ የተባረሩ ስደኞች ተመልሰው እየሄዱ ነው

May 17/2014

በአንድ ወር ከ700 በላይ ስደተኞች ድንበር ሲያቋርጡ ተይዘዋል አብዛኞቹ ተባርረው የመጡ ናቸው

      በሶማሌ ላንድ በኩል ቀይ ባህርን በጀልባ ተሻግረው ወደ ሳዑዲ አረቢያና ወደ የመን ለመሄድ ጉዞ የጀመሩ ከ700 በላይ ወጣቶች ሀረር አካባቢ እንደተያዙ የክልሉ ፖሊስ ገለፀ፡፡ ከ700 በላይ የሚሆኑት የተያዙት በአንድ ወር ውስጥ መሆኑን የጠቀሱት የሐረሪ ክልል ፖሊስ የህዝብ ግንኙነት ሃላፊ ኮማንደር ጣሰው ቻለው ለአዲስ አድማስ እንደገለጹት አብዛኞቹ ከ4ወር በፊት የሳዑዲ አረቢያ ከሳዑዲ የተባረሩ ስደኞች ተመልሰው እየሄዱ ነው በአንድ ወር ከ700 በላይ ስደተኞች ድንበር ሲያቋርጡ ተይዘዋል አብዛኞቹ ተባርረው የመጡ ናቸው መንግስት ህገወጥ ናችሁ በሚል ወደ ኢትዮጵያ የመለሳቸው ናቸው፡፡

ወጣቶች ከባሌ፣ ከጅማ፣ ከአርሲ፣ ከትግራይ ክልል ከተሞችና፣ ከደሴ በመነሳት ለህገወጥ አስኮብላዮች እስከ 5ሺ ብር በመክፈል በቅብብሎሽ ከከተማ ከተማ የተሸጋገሩ ሃረር የደረሱ መሆናቸው ታውቋል፡፡ ፖሊስ፣ የህገወጥ ስደት ሰንሰለቱ ቦሳሶ ድንበርን በመሻገር በጀልባ ከ40 ሠዓት በላይ በመጓዝ ሳዑዲ አረቢያና የመን ድረስ እንደሚዘልቅ ፖሊስ አስረድቷል፡፡ ህገወጥ ስደትን መከላከል የፖሊስ የእለት ተእለት ስራ እየሆነ መምጣቱን የጠቆሙት ሃላፊው፤ ከሐረር ከተማ ወጣቶችን በድብቅ በአይሱዙ በመጫን ወደ ሶማሌ ላንድ የሚያጓጉዙ ህገወጥ ሰዎች በፖሊስ ቁጥጥር ስር እያዋሉ ነው፤ በሚያዚያ ወር ግን ህገወጥ የስዎች ዝውውር በከፍተኛ ሁኔታ ጨምሯል ብለዋል፡፡ በሶማሌ ላንድ በኩል ባህሩን ለማቋረጥ በጀልባ ቀንና ሌሊቱን የሚደረገው ጉዞ እንደሆነ የጠቆመው ፖሊስ፣ ሰሞኑንም 80 ሰዎችን ጭኖ ይጓዝ የነበረ ጀልባ ተገልብጦ በርካታ ስደተኞች ህይወት ማለፉን አስታውሷል፡፡ በየዕለቱ ከአራት በላይ ጀልባዎች ህገወጥ ስደተኞችን በመጫን ወደ የመን ድንበር እንደሚደርሱና አንድ ጀልባ ከ80 እስከ 90 የሚደርሱ ስደተኞች እንደሚጫንም ገልጸዋል፡፡

ኢትዮጵያና ግብፅ ያቋረጡትን ድርድር እንዲጀምሩ የአሜሪካ መንግሥት ጥሪ አቀረበ

May 17/2014

ኢትዮጵያ ለጀመረችው የታላቁ ህዳሴ ግብድ ግንባታ የአሜሪካ መንግሥት ትልቅ ትኩረት እንደሚሰጠውና ግድቡን በተመለከተ የኢትዮጵያና የግብፅ መንግሥታት ያቋረጡትን ውይይት እንዲጀምሩ ጥሪ አቀረበ፡፡ 

የአሜሪካ ረዳት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሊንዳ ቶማስ ግሪንፊልድ ባለፈው ረቡዕ የአሜሪካ መንግሥት ከሰሐራ በታች ላሉ የአፍሪካ አገሮች የሚሰጠውን ትኩረት አስመልክቶ፣ ከተለያዩ የአፍሪካ አገሮች ከተወጣጡ ጋዜጠኞች ጋር ከአሜሪካ ሆነው በቀጥታ ቪዲዮ ኮንፈረንስ ተነጋገረው ነበር፡፡ ‹‹የአሜሪካ መንግሥት ከታላቁ የህዳሴ የኃይል ማመንጫ ግድብ ጋር በተገናኘ ከኢትዮጵያና ከግብፅ መንግሥታት ጋር ትልቅ ውይይት በማካሄድ፣ ሁለቱ አገሮች ልዩነታቸውን አቻችለው በጋራ እንዲሠሩ ጥሪ አቅርቧል፤›› ሲሉ ከሪፖርተር ለቀረበላቸው ጥያቄ ምላሽ ሰጥተዋል፡፡

የአሜሪካ መንግሥት ኢትዮጵያ በመገንባት ላይ ባለችው የታላቁ ህዳሴ የኃይል ማመንጫ ግድብ ላይ ያለውን አቋም አስመልክቶ በተጨማሪ ለቀረበላቸው ጥያቄ በሰጡት ምላሽ፣ በመጀመሪያ በኢትዮጵያና በግብፅ መካከል የሚስተዋለው የቃላት ጦርነት የአሜሪካ መንግሥትን እንደሚያሳስበው ገልጸዋል፡፡

ግድቡን በተመለከተ የአሜሪካ መንግሥት አቋም ሁለቱ መንግሥታት ወደ ንግግር መምጣት እንዳለባቸውና ተገናኝተው ሊወያዩ ይገባል፣ ያሉት ረዳት የውጭ ጉዳይ ሚንስትሯ፣ ልዩነታቸውን ሊያስታርቁ ይገባል ሲሉ በአፅንኦት አስረድተዋል፡፡

ከዚህ ቀደም በሁለቱ ኢትዮጵያና ግብፅ መካከል የተወሰነ ድርድር እንደነበር የአሜሪካ መንግሥት የሚገነዘብ መሆኑን የገለጹት ረዳት የውጭ ጉዳይ ሚንስትሯ፣ አሁንም ሁለቱ መንግሥታት ያቋረጡትን ድርድር በድጋሚ በመጀመር ለሁለቱ አገሮች የጋራ ጥቅም የሚበጅ መፍትሔ ላይ ቢደርሱ እንደሚሻል አስረድተዋል፡፡

ረዳት ሚንስትሯ ሊንዳ ቶማስ ከአፍሪካ ከተወጣጡ ጋዜጠኞች ጋር በቪዲዮ ኮንፈረንስ ያደረጉት ውይይት ከውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ጆን ኬሪ፣ የአፍሪካ ጉብኝት በቅርቡ በአሜሪካ በሚካሄደው የአፍሪካ መሪዎች ጉባዔ ዙሪያ ለተነሱ ጥያቄዎች ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡

በቅርቡ በሚካሄደው የአፍሪካ መሪዎች ጉባዔ ላይ የኤርትራ፣ የዚምባቡዌ፣ የሱዳንና የዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ መሪዎች እንደማይጋበዙ ገልጸዋል፡፡

በአሁኑ ወቅት በደቡብ ሱዳን የሚስተዋለውን የእርስ በእርስ ግጭት አስመልክቶ ሁለቱ የግጭቱ ተዋናዮች የሰላም ስምምነቱን ወደ መተግበር እንዲገቡ፣ ካልሆነ ግን የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የፀጥታው ምክር ቤት የአሜሪካ መንግሥት ማዕቀብ እንደሚጠብቃቸው አስታውቀዋል፡፡

የህህዋት የዘረኝነት ፓለቲካና መዘዙ ( ገዛኸኝ አበበ ከኖርዌ ሌና)

May20/2014
By Gezahegn Abebe (Norway Lena)

 ወያኔ /ኢህአዲግ የስልጣን እድሜውን ለማራዘም ትልቁ የፖለቲካ አጀንዳ አድርጎ የተነሳው ሕዝብን ከሕዝብ ጎሳን ከጎሳ ሀይማኖትን ከሀይማኖት የፖለቲካ ድርጅትን ከፖለቲካ ድርጅት  በማጋጨትና በማጣላት ላይ ሲሆን ህሕዋት እያራመደ ባለው የዘርና የጎሳ ፖለቲካ የተነሳ በኢትዮጵያ ታሪክ ከመቸውም ጊዜ በላቀ እና ታይቶ በመይታወቅ ሁኔታ የወያኔ መንግስት አሁን የኢትዮጵያን ህዝብ በሁሉም የኢትዮጵያ ክልልና አካባቢ  ሕዝቡ ኢትዮጵያዊነቱን እንዳያይ በዘር እየከፋፈለው ነው:. የህህዋት/ኢህአዴግ ገና ወደ ስልጣን ብቅ ሲል በጦርነት ከደርግ የሚረከባቸውን ቦታዎች ፣ዳገትና ቀበሌዎች ሁሉ በቤተሰብ ሳይቀር እየከፋፈለ በተለያዩ ጥቅማጥቅሞች እያሰረ ልዩነታቸውን ብቻ እያሳየ ሌላ አማራጭ ያልነበረው ህዝብ ሲቀበለው ቆይቶ አሁን በክልል በዞን በወረዳ በቀበሌ እና ሰፈር ድረስ በዘርና በጎሳ ከፋፍሎ ይህ ወያኔ ከደደቤት በረሃ ይዞት የመጣው የዘረኝነት ፖለቲካ መዘዝ  ዘሬም በኢትዮጵያ ውስጥ ተንሰራፍቶ  በየሰፈሩ አሁን የእንትን ሰፈር ልጅ ከእንትን ሰፈር ልጅ ጋር በጩቤ በድንጋይ ሲፈነካከት ሲተራረድ ማየት ምንም አዲስ ነገር አይደለም፡፡

የአንዱን ወረዳ ነዋሪ ከሌላኛው ወረዳ ነዋሪ ጋር በሆነ ባልሆነው ሲኮራረፍ ሲገዳደል ሲቀጣቀጥ ማየት ምንም አዲስ አደለም፡፡ አንዱ ዞን ከሌላኛው ዞን ጋር በስራቸው በሚያስተዳድሩት ህዝብ ስም ጥቅም እየነገዱ አንዱን ከአንዱ አባትን ከልጁ እናትን ከልጇ ወንድምን ከወንድሙ ምን አለፋችሁ በቃ በአሁኑ ሰአት በኢትዮጵያ ውስጥ እንደምታዩት ጠላቶች ሆነን ስንጨራራስ ስንተራረድ እንገኛለን፡፡ሰው ከሰው ጋር ለምን ይጋጫል ለምን ይገዳደላል የሚለው እውነተ ውስጥ አልገባሁም እርሱ ራሱን የቻለ ተፈጥሯዊ ክስተት ስለሆነ፡፡በዛም አለ በዚህ የመከፋፈላችን የመጨረሻ ውጤትና ምክንያት ፍጅት ነው፡፡ ሆኖም ፍጅት ሲባል ግን ኢትዮጵያ ውስጥ ሊነሳ የሚችለው ፍጅት እንደሁቱና ቱትሲ ይሆናል ብላችሁ ግን አታስቡት፡፡ መቸም ቢሆን ይህ ጉዳይ ሊከሰት አይችልም፡፡ በብሄር ግጭት ተነስቶ ኢትዮጵያ ሃገራችን ትጠፋለች አንድ ዘር ይጠፋል ማለት አይቻልም፡፡ ለዚህ ራሱን የቻሉ እውነተኛ ምክንያቶች አሉ፡፡ ሌላው ዓለም ላይ የሌሉ ሃገራችን ውስጥ ግን እንደ ዕድል ብቻ ሆኖ ያሉ ነገሮች ሕዝባችን ሳይማር ተፈጥሮ ብቻ አስተምራ ያኖረችው ትውልድና ትስስር በመሆኑ ብቻ አብረውን የሚኖሩ እውነቶች አሉ፡፡

ወያኔ ኢህአዴግ ግን ከዞን እና ቀበሌ ባለፈ የመጨረሻ ሴራውን በክልል በቋንቋ፣ ዘር ፣ቀለም ወዘተ እያለ በባህል፣ በእምነት እያለ የሚታዩና የማይታንን ልዩነቶች እየፈጠረ በመካከላችን ምንም አይነት ችግርና  ሳይኖር በፍቅር የኖረን ሆነን ሳለን ህህዋት ከጅምሩ ይዞ የተነሳውን  በቋንቋና በዘር ልዩነት ላይ የተመሰረተው የፌደራል ሥርአትና ኢትዮጵያን የመሰነጣጠቅ ሴራው  አሁን ላይ ስር እየሰደደ መጥቶ በኦህዴድ፣ ብአዴንና ደህዴድን የመሳሰሉ የመሳሰሉ የወያኔ አለቅላቂዎችና  አሽከሩች ተጨምረውበት በእነዚህ የኢትዮፖያን ሕዝብ ደም መጣጭ ድርጅቶች በኩል እየተገበረ ያለውን ኢትዮጵያን የመሰነጣጠቅ እና ለአስተዳደር ለማመቻቸት በመሰለ ሴራና ተንኮል ህዝባችን አንድነቱ ፍርሶ ፣ አሞቱ ፈሶ ኢትዮጵያዊው ወኔ እንዲደርቅ በማድረግ ለራሳቸውየሚጠቅማቸውን ለህዝባችን እና ሃገራችን ግን ትልቅ የአንድነት ነቀርሳን ተክለውብን ምኞታቸውን እያሳኩ ይገኛሉ፡:

ይህ የወያኔ የዘረኝነት ፖለቲካ መዘዝ ስር እየሰደደ በጣም በአሳሳቢ ሁኔታ ከጊዜ ወደ ጊዜ እጅግ አስከፊና አሳዛኝ የሆኑ የተለያዩ ችግሮች እየወለደ፤ ጸብና ግጭቶችን እያበራከተ የዜጎችን ሕይወት በቀላሉ እየቀጠፈና የሕዝቦችን ሀብት በማውደም፣ቤቶችን በማቃጠል መጥፎ ክስተት  እየተከሰተ ይገኛል። ከተለያዩ ምንጮች እንዳገኛውት ከሆነ በምሥራቅ ኢትዮጵያ ደገሃቡርና ጅጅጋ፤ በምሥራቅ ሀረርጌ ጋራሙለታ፤ በደኖ አንስቶ በባሌና በአርሲ በሚገኙ አካባቢዎች በዘር ላይ የተመሰረቱ ግጭቶችና የሰው ሕይወትና ንብረት የወደሙበት በምሳሌነት ሊጠቀሱ የሚችሉ ናቸው። በምዕራብ ኢትዮጵያም ቢሆን በተለያዩ ወቅቶች በአሶሳ በባምባሲ፤ በሰሪ፤ በጋምቤላ በምዕራብ ወለጋ ጊምቢ፤ ነቀምት፤ አምቦም ለዚሁ አስከፊ ሁናቴ የሚጠቀሱ ናቸው። በአርሲ ክፍለ ሀገር በአርባጉጉ አውራጃ ውስጥ በሚገኙ ጎሎልቻ፤ ጨሌ፤ ጃጁ፡ መርቂ በተሰኙ ወረዳዎችና አካባቢዎች በርካታ መኖሪያ ቤቶች የወደሙበት፤ ሕይወት የጠፋበት፤ የሰው ልጅ እንድ ከብት አንገትና ጡቶች የተቆረጡበት አሰቃቂና አሳዛኝ በድሎች ተካሂደዋል። በሌላ ቦታ ደግሞ ከነ ነፍሰሕይወታቸው ወደገደል ተውርውረው እንዲፈጠፈጡ ተደርገዋል።

በምንም መንገድ ከታሪካዊ አመጣጡም ቢሆን እንደተረዳነው ወያኔ ኢህአዴግ ለኢትዮጵያ አንድነት ሳይሆን የታገለው አሁንም የሚሮጠው ለእነዚህ አላማዎች ብቻ ነው፡፡ አንድም ታላቋ ትግራይን መመስረትና የአማራውን  ተሰሚነት አኮላሽቶ መቅበር ነው፡፡ለዚህም አማራውን ዝም ካልነው አያስቀምጠንም” የሚለው የመለስ መፈክር በቂ ምስክር ሲሆን ይህንን የሚያረጋግጡም በርካታ የምስልና የድምፅ ቅጅዎች በተለያዩ ነፃነት ናፋቂ የየትኛውም ብሄር ታጋዮች እጅ ይገኛል፡:

ከዚህ በፊት ኢትዮጵያን ሲመሩ የነበሩት መሪዎች ሁሉ የኢትዮጵያን ዳር ድንበር በማስከበረ ሕዝቡም አንድነቱን ጠብቆ እንዲኖር ብዙ መስዋትነትን  ከፍለዋል በወያኔ መንግስት እንደ አውሪ የሚቆጠረው ደርግ ሳይቀር ለኢትዮጵያ አንድነት ምሳሌ ናቸው ::ደርግ በርካታ አንቱ የሚያስብሉት ትግባራትን ፈፅሟል፡፡ በኋላም ለውድቀት የዳረገው በትክክል ደርግን ሁሉም ኢትዮጵያዊ ጠልቶት ሳይሆን በመካከላቸው በነበረው ተራ የስልጣን ሽኩቻ ምክንያት በነበራቸው የሃሳብ  መለያየት፣ ውስጣዊ ሴራ እና አማራጭ በማጣት አንድን የደርግ ወታደር በሁለት ብር ሂሳብ ለወያኔ በሰጡ ባስጨረሱ ጀኔራሎች ሴራ እንጅ በወያኔ ጥንካሬ እንዳልሆነ እውን ነው፡፡

የሚገርመው ግን የኢትዮጵያን አንድነት ለማጥፋት አላማ ይዞ የመጣው ወያኔ ስልጣን እንደያዘ የጀመረው የደርግን ጅማሮዎችን በሙሉ ከምድረ ኢትዮጵያ ማጥፋት እና ማቃጠል ፣ አንድነቷና ዳር ድንበሯ ተከብሮ የቆየውን ሀገሪቷን መሸጥና መቆራራጥ ሀገሪቷን ወደብ አልባ በማድረግ ለታሪክ መጥፎ የሆነ ጠባሳ ማስቀመጥ ነበር ይህንንም  ከሻቢያ ጋር በመሰማማት ሙሉ ለሙሉ ተግባራዊ አድርጎታል:: ወያኔ ኢህአዴግ አሁን የያዘው ስትራቴጅ ደግሞ የማያዋጣው ማጥ ውስጥ ስለከተተው የሚከተለው እንደ ትግሉ በግልፅ ራሱን በመገንጠል አላማ ማለትም የመሄድ ዓላማ ሳይሆን ተቃራኒውን ነው፡፡ ይህም ማለት አሁን በምኑም በምኑም ምንያት የከፋፈለውን ህዝብ የበለጠ በመከፋፈልና የመለያያ ታሪኮችን እንደመልካም አስተማሪ ታሪክ በመምዘዝ እና አደባባይ በማውጣት /ሆኑ አልሆኑ የሚለው ባይታወቅም ምንጭ ባይኖረውም/ አንዱን ከአንዱ በማፋጀት እራሱ መሄዱን ሳይጀምር ሌሎች በየአቅጣጫው እንዲሄዱ በማድረግ የተዳከመች ኢትዮጵያ የተፈረካከሰች ኢትዮጵያ ስትቀር…በሉ እኔም የድርሻየን እናንተ ከሄዳችሁማ…ብሎ ለመነሳት ነው ያሰበው፡፡

ይህ አላማውን ለማሳካት ደግሞ  አማራውን ከኦሮሞው አፋሩን ከሶማሌው ቀበሌን ከቀበሌ ፣ ዞንን ከዞን፣ ወረዳን ከወረዳ፣ ቋንቋን ከቋንቋ፣ ሃይማኖትን ከሃይማኖት ፣ ፓርቲን ከፓርቲ በማንኛውም ልዩነት አድርገው በወሰዱት መለያያ ሁሉ ለማፋጀት ቆርጠው ተነስተዋል፡፡ ለዚህም በትንሹም ቢሆን የተሳካላቸው ይመስላሉ ዘላቂ አይደለም እንጅ፡፡ ለዚህ ማሳያም አማራው ከቀየው እየተፈናቀለ ቤት ንብረቱ በየሜዳው እየተቃጠለ እየተዘረፈ እየተገደለ ነው:: ዛሬ ኦሮሚያ ክልል ውስጥ በርካታ ሚሊዮን አማሮች በርካታ መቶ ሽህ ትግሬዎች ሶማሌዎች አፋሮች ደቡቦች ጉሙዞች ጋምቤላዎች ይኖራሉ ግን የነፃነታቸው ጉዳይ አጠያያቂ ነው፡፡የህህዋት የዘረኝነት ፓለቲካ ባመጣው መዘዝ ዛሬ ላይ ኦሮሚያ ክልል ውስጥ የሚኖሩ አማሮች ችግር ውስጥ  ናቸው::  ከሰሞኑ እንዳየነው በምዕራብ ወለጋ ጊምቢ በወያኔ መሰሪና ተንኮል የአካባቢው ተወላጆች የሆኑ ኦሮሞዎች በአማራው ተወላጅ ሕዝብ ላይ እያደረሱት ያለው ግፍና በደል ምስክር ሲሆን ብዙዎች ኢትዮጵያኖችን ያሳዘነና ሁላችንም ልናወግዘው የሚገባ ድርጊት ሲሆን አሁን ብቻ ሳይሆን በተለያዩ ጊዛቶች ወያኔ ወደስልጣን ከገባ ጀምሮ አማሮች በኦሮሚያ ይገደላሉ ይታሰራሉ ንብረታቸው ይዘረፋል ይቃጠላል…ወዘተ ይህ ደግሞ የኦሮሚያ ህዝብ ለኢህአዴግ ሴራ ተገዥና ተጠቂ መሆኑ ነው፡፡ ነገር ግን ይህን ሁሉ በደልና ግፍ የኦሮሚያ ህዝብ ኢህአዴግን ለመደገፍ ፈልጎ እንዳልሆነ ግልፅ ጉዳይ ነው ሆኖም ግን  ስንት በርካታ ምሁራንን ያፈራው የኦሮሚያ ህዝብ ያላወቀው እና ለፀረ-ኢትዮጵያዊያን ተዘዋዋሪ አጋዥ ሆኗል ይህም ወያኔ ያመጣው የዘረኝነት ፖለቲካ መዘዝ ውጤት ነው::

አንድ ልናውቀው የሚገባ  እውነት  ይህች ሃገር በፍጹም ልትበታተንና ልትጠፋ አትችልም:: ይህንም ህህዋቶችና የወያኔ ተላላኪ፣ተለጣፊዎቹ ኦህዴድ፣ ብአዴንና ደህዴድ ያወቁት አይመስለኝም  ፡፡ ይህ ህዝብ አንድ ሆኗል በወያኔ ተንኳልና ሴራ አሁን ላይ በተለያዩ ነገሮች ቢጋጭም የተጋባ፣ የተዋለደ፣አብሮ የበላና ፣የጠጣ አብሮ ለኢትዮጵያ አንድነት ሲል የታዋጋ ፣ የደማና የቆሰለ ሕዝብ ነው :: ይህ እውነታና ሚስጥር ያልገባቸው አንዳንድ የወያኔ ኢህአዴግ ሴራ ማስፈጸሚያና መጠቀሚያ መሆናቸውን ያላወቁ በስሜት የሚነዱ ኢትዮጵያዊያን ብቻ ናቸው፡፡ስለሆነም የኦሮሞው፣የአማራው፣የአፋሩ፣የትግራዩ፣የጋምቢላው ........ሕዝብ የወያኔ የዘር ፖለቲካ ማስፈጸሚያ እንዳይሆን ሊጠነቀቅ ይገባል እያልኩኝ እዚህ ላይ ላጠቃልል:: ውድቀት ለዘረኛው የወያኔ አገዛዝ !!

የኢትዮጵያ አንድነት ለዘላለም ተጠብቆ ይኖራል!!
gezapower@gmail.com
       

Saturday, May 17, 2014

ግንቦት 7 ሕዝባዊ ሃይል ላለፉት ሶስት ወራት ያሰለጠናቸውን የአራተኛ ዙር ታጋዮችን አስመረቀ

May 17/2014

የኢትዮጵያዊያንን ስቃይና መከራ ሊያቅብና እንባቸውን ሊየብስ፤ ሀገራችን ኢትዮጵያ በጎጠኛው ሕወሃት የደረሰባትንና እየደረሰባት ያለውን ውርደት ወደ ክብር ለመለወጥና የናቋትና ያዋረዷት በፍትህ ሚዛን ላይ እንዲቀመጡና ፍርዳቸውን እንዲያገኙ ለማድረግ ዓላማየ ብሎ ምሎ ዱሩ ቤቴ ካለ ገና ሁለት ዓመት እንኳ ያልሞላው ግንቦት 7 ሕዝባዊ ሃይል በቃሉ መሰረት አራተኛውን ዙር የታጋዮች የምረቃ በአል ሚያዚያ 26 2006 ዓ/ም ጥሪ የተደረገላቸው የክብር እንግዶች በተገኙበት ማክበሩን አስታወቀ። ይህ የአራተኛው ዙር ስልጠና በሰልጣኞች ቁጥርም ሆነ በስልጠናው ጥንካሬ ካለፉት ሶስት ዙሮች በእጅጉ የተለየ እንደነበር የተገለጸ ሲሆን በአሁኑ ሰአት ያለውን የሀገሪቱን ነባራዊ ሁኔታ ያገናዘበና ወቅቱ የሚፈልገውን ቴክኖሎጅ በመጠቀም መረጃን መቀበልና ማስተላለፍን የጨመረም እንደነበር ተያይዞ ተጠቅሷል።
በሀገር ውስጥ ፋሽስት ወያኔ እያደረሰው ባለው መረን የወጣ ግፍ የተበሳጩና ሁሉም ልክ እንዳለው ለማሳየት ቆርጠው የተሰለፉት እነዚህ ምሩቅ ታጋዮች ከወታደራዊው ስልጠና በተጨማሪ የፖለቲካ፣ መረጃና ደህንነት እንዲሁም ሌሎችንም ተያያዥ ክህሎቶችን በበቂ ሁኔታ እንደቀሰሙም ተጠቁሟል። ስልጠናው ታጋዮቹ ወደፊት ከሚያጋጥማቸው ጠንካራ ፈተናና ከሚሰለፉበት ጥብቅ ግዳጅ አንጻር በቀላሉ ተስፋ እንዳይቆርጡ ለማድረግ በአካልም ሆነ በመንፈስ ዝግጁ እንደሚያደርጋቸው የተገለጸ ሲሆን የተጀመረው ሕዝባዊ ትግል በግለሰብ ደረጃ ሳይሆን በጋራና በተቀነባበረ ሃይል ለድል እንደሚበቃና ይህን የጋራ ሃይል በጠነካራ እጆች ላይ ላመስቀመጥም የተሰጠው ስልጠና ከበቂ በላይ ነበር ተብሏል።
ግንቦት 7 ሕዝባዊ ሃይል በሀገር ውስጥ እንደማእበል እየገነፈለ ያለውን የአታግሉን የሕዝብ ጣያቄ በተደራጀና በተቀነባበረ መንገድ በተገቢው መልኩ ለማስተናገድ እንዲችል እንደ ድርጅት ከመቼው በላይ ራሱን እያደራጀና እያጠነከረ እንደሚገኝና ምቹ አታጋይ ተቋም ሆኖ ለመውጣት ሌት ተቀን እየደከመ መሆኑም ተያይዞ ተጠቅሷል። በታጋዮች ስልጠና ወቅት የተገኙ አንዳንድ የክብር እንግዶች እንደጠቆሙትም ”ባሁኑ ሰአት በሀገር ውስጥ ያለው ሁኔታ ከመቼውም በላይ የተመቻቸ ነው” ካሉ በሗላ ”ሕወሃት የሚተማመንበት ወታደሩ እንኳ ቁጥሩ ካልሆነ በቀር ልቡም ሆነ መንፈሱ ከሕዝብ ጋር ነው፤ በሁሉም የሀገሪቱ አቅጣጫዎች እየሆነ ያለው ወያኔ በእርጅና ዘምኑ ማብቂያ ላይ መሆኑን ነው የሚያመለክተው። ስለሆነም በመረጃ መንቀሳቀስና በትብብር መስራት ባጭሩ ለድል ያበቃል። ለዚህ ደግሞ የዛሬ ምሩቅ ታጋዮች ያገኙት ስልጠና ለታሰበው ስኬት የሚያበቃቸው ነው” በማለት ትዝብታቸውን አጠቃለዋል።
በምረቃው ማብቂያ ላይ ራሱን ግንቦት 7 ሕዝባዊ ሃይል ብሎ ከሰየመበት ጊዜ ጀምሮ ለፋሽስት ወያኔ ከፍተኛ ስጋት እንደሆነ በማስረገጥ የጠቆሙት የሕዝባዊ ሃይሉ ሃላፊዎች፤ ከዚህ በፊት ፋሽስት ወያኔ በከፍተኛ ወጭና ጥንቃቄ ሕዝባዊ ሃይሉን ለማፈራረስና ለማትፋት በከፍተኛ ሁኔታ የሰራ ቢሆንም በሕዝባዊ ሃይሉ መረጃና ደህንነት ክፍል መክሸፉን አስታውሰው፤ ዓላማችንን ከዳር ለማድረስና የሕዝባችንን አርነት ለመመለስ ሀገራችንንም ከወያኔ አገዛዝ ነጻ ለማውጣት በምናደርገው ትግል የኢትዮጵያ ሕዝብ ከመቼውም ጊዜ በላይ ከጎናቸው እንዲቆም ጥሪ አስተላለፈዋል። ይህን ታሪካዊ ጥሪ ለመመለስና የሀገርና የትውልድ ጠላት የሆነውን ወያኔ ሕወሃትን ለማስወገድ አብረን እንቁም ሕዝባዊ ሃይላችንንም ተቀላቀሉ ሲሉም ጥሪያቸውን አስተላልፈዋል።



    የዛሬው የጋዜጠኞቹ እና የዞን 9 ብሎገሮቹ የፍርድ ቤት ውሎ – “ከሌሊቱ 8 ሰዓት እየተወሰድኩ ተደብድቤያለሁ”

    May 17/2014
    አዲስ ጉዳይ መጽሔት ዘገባ ከአዲስ አበባ)
    “የሥነልቡና ጫና ደርሶብኛል”
    ጋዜጠኛ አስማማው ኃ/ጊዮርጊስ
    “ከሌሊቱ 8 ሰዓት እየተወሰድኩ ድብደባ፣ ማስፈራራት እና ወከባ ተፈጽሞብኛል”
    አጥናፍ ብርሃኔ
    “ለምርመራ የምጠቀምበት አንድ ኮምፒውተር ነው ያለኝ፤ ጊዜ ይሰጠኝ”
    ፖሊስ

    ቅዳሜ ግንቦት 9፣ 2006 በቀጠሯቸው መሠረት አራዳ ምድብ ችሎት የቀረቡት 3 ጋዜጠኞች እና 3 ብሎገሮች ነበሩ፡፡ ፖሊስየተጠርጣሪዎቹን ጉዳዩ ከወንጀል ወደ ሽብር በማሻሻሉ እና ምርመራዬን አላጠናቀቀኩም በማለቱ የ28 ቀን ተጨማሪ የምርመራጊዜ እንዲሰጠው ጠይቆ ተፈቅዶለታል፡፡ ሦስት ሰዓት ይሰማል የተባለው ችሎት 4፡30 አካባቢ የተጀመረ ሲሆን በመዝገብ ቁጥር118721 የተከሰሱት ሦስት ተጠርጣሪዎች ኤዶም ካሣዬ፣ አጥናፍ ብርሃኔ እና ናትናኤል ፈለቀ በመጀመሪያ ቀርበዋል፡፡

    በዛሬው ችሎት ከእየአንዳንዱ ታሳሪ ሦስት የቤተሰብአባላት ወደ ችሎት ገብተው እንዲታደሙ ተፈቅዶነበር፡፡ ፖሊስ ክሱን ከወንጀል ወደ ሽብር ከፍ አድርጎቀርቧል፡፡ ምርመራዬን ስላላጠናቀቅኩ የተጨማሪ የ28ቀናት ጊዜ ይሰጠኝ ብሎም ለችሎቱ ጥያቄ አቅርቧል፡፡

    የተከሳሽ ጠበቆች ግን ከዚህ ቀደም በተሰጠው ሁለትቀጠሮዎች ውስጥ አጣራቸዋለሁ ያላቸው 6 ጉዳዮችአሁንም አልተሰሩም፤ ድርጊቱ ደንበኞቻችንን በቀጠሮማጉላላት ነው፣ ማስረጃ ባልተሰበሰበበት ሁኔታ ከወንጀል ወደ ሽብር የተቀየረበት መንገድም ተገቢአይደለም ሲሉ ተከራክረዋል፡፡ ፖሊስ መተርጎምያለባቸው ሰነዶች ወደ ትርጉም ቤት ተልከዋል፣ግብረአበሮቻቸው አድራሻ እየለዋወጡ ሊያዙልኝ አልቻሉም፣ አቀርባለሁ ያልኳቸውን
    ምስክሮችም እያስፈራሩብኝ ለማቅረብ አልተቻለኝም ሲልመልሷል፡፡ ፍርድ ቤቱም የተጠየቀውን የ28 ቀናትየጊዜ ቀጠሮ ፈቅዷል፡፡ በዚህም መሠረት ጋዜጠኞቹ እናብሎገሮቹ ቅዳሜ ሰኔ 7፣ 2006 ከጠዋቱ በ3፡30ሰዓት እንዲቀርቡ አዟል፡፡ አጥናፍ ብርሃኔ ከሌሊቱበስምንት ሰዓት ወደ ምርመራ ክፍሎች እየተወሰደበመርማሪዎች ወከባ፣ ድብደባ እና ማስፈራሪያ እንደደረሰበት ለፍርድ ቤቱ አስረድቷል፡፡

    ባለፈው ቀጠሮ ሚያዚያ 30 ቀርበው የነበሩት በፍቃዱ ኃይሉ እና አቤል ዋበላ ድብደባ እንደተፈጸመባቸው ለፍርድ ቤቱ
    ማስረዳታቸው ይታወሳል፡፡ ቀጥሎ በታየው መዝገብ 118722 ተጠርጥረው የቀረቡት አስማማው ኃ/ጊዮርጊስ፣ ተስፋዓለምወልደየስ እና ዘላለም ክብረት ክሳቸው ወደ ሽብር ተለውጦ በመቅረቡ እነሱም ሰኔ 7 ቀን 2006 እንዲቀርቡ ታዟል፡፡ ለችሎቱ የመናገር እድል እንዲሰጠው ጠይቆ የተፈቀደለት ጋዜጠኛ አስማማው ኃ/ጊዮርጊስ “መርማሪው የዞን 9 አባል አለመሆኔን ቢያምንም በተደጋጋሚ ጊዜ እየተጠራሁ አንድ ዓይነት በሆነ ጥያቄ ስለዞን 9 የምታውቀው ነገር አለና ተናገር እየተባልኩ ከፍተኛየሥነልቡና ጫና ደርሶብኛል፡፡ ጋዜጠኛ እንደሆንኩም ያውቃሉ፡፡” በማለት ቅሬታውን እንባ እየተናነቀው አሰምቷል፡፡

    የአስማማው ሁኔታ የችሎቱን ታዳሚያን እንባ አራጭቷል፡፡ ጠበቆቻቸውም ፖሊስ ከዚህ ቀደም በጠየቃቸው ቀጠሮዎች የሰራውነገር ስለሌለ የ28 ቀን ቀጠሮ ሊሰጠው አይገባም፤ ዋስትና ይፈቀድልን፤ ዋስትና አያሰጥም እንኳን ከተባለ ፖሊስ ከዚህ በኋላበጠየቀው ጊዜ ምን ሊሰራ እንዳሰበ ይግለጽልን ሲሉ ለችሎቱ ጥያቄ አቅርበዋል፡፡ መልስ የሰጡት መርማሪም በመረጃ ዴስካችንውስጥ ያለን ኮምፒዩተር አንድ ብቻ በመሆኑ የሁሉንም ተጠርጣሪዎች ፋይል ለማጣራት ጊዜ ወስዶብናል ብለዋል፡፡

    ተጠርጣሪዎቹ በሕቡዕ ተደራጅተዋል፤ ከእያንዳንዳቸው ኢ-ሜይል ለአመጽ የሚቀሰቅሱ ማስረጃዎች አግኝተናል እያንዳንዱለማስተርጎም ጊዜ ይወስዳል፤ በስማቸው ከውጭ የተላከ ገንዘብ እንዳለና ለሽብር ድርጊት ሊጠቀሙበት እንደሆነ ደርሰንበታል ያለቢሆንም ጠበቆቻቸው ግን ፖሊስ የጸረ-ሽብር ሕጉን አለአግባብ እየተጠቀመበት ነው፤ አስማማው ኃ/ጊዮርጊስ እና ተስፋለምወልደየስ የዞን ዘጠኝ አባላት አይደሉም፡፡ ጋዜጠኞች ናቸው፡፡

    ደንበኞቻችንን ሊያስጠረጥራቸው የሚችል ወንጀል አልተገኘባቸውም ሲሉ ተከራክረዋል፡፡ የዞን 9 አባላት ከውጭ የሽብር አካላትስልጠና አግኝተዋል የሚለው ልክ አይደለም፡፡ አርቲክል 19 እና ፍሪደም ሃውስ ሀሳብን የመግለጽ መብት እንዲከበር የሚንቀሳቀሱዓለም አቀፍ ተቋማት ናቸው፡፡ የትም ሀገር እና ቦታ የሽብር ተቋማት ተብለው አያውቁም፡፡ በኛም ሀገር በፓርላማ ሽብርተኛተብለው አልተወገዙም ሲሉ ጠበቆቻቸው ተናግረዋል፡፡ በመዝገብ ቁጥር 118720 የተካተቱት በፍቃዱ ኃይሉ፣ ማህሌትፋንታሁን እና አቤል ዋበላ እሁድ ግንቦት 10 ቀን 2006 ዓ.ም ጠዋት ይቀርባሉ፡፡ ጋዜጠኞቹ እና ብሎገሮቹ በቁጥጥር ሥርየዋሉት ሚያዚያ 18 እና 19 ቢሆንም ጠበቆቻቸው እንዲጎበኟቸው የተፈቀደው ግን ባሳለፍነው ረቡዕ ግንቦት 6 እና አርብ ግንቦት8፣ 2006 ነው፡፡

    አንቀጽ 19 በተግባር ተጥሷል – ሕገ መንግስቱን ሳያከብሩ ማስከበር አይቻልም የታሳሪዎች የምርመራ ሂደትን አስመልክቶ ከዞን 9 የተሰጠ መግለጫ

    May 16/2014

    አዘጋጅ 

    ከታሰሩ 22 ቀናትን ያስቆጠሩት የዞን ዘጠኝ አባላትና ጋዜጠኞች በቤተሰብም ሆነ በሕግ ባለሞያ የመገናኘት መብታቸውን ለማግኘት 19 ቀናትፈጅቶባቸዋል፡፡ ከታሰሩ እስከ 17 ቀን ድረስ ማንም የቤተሰብ አባል ሳይጎበኛቸውና በወዳጅ ዘመዶች ሳይጠየቁ የከረሙ ሲሆን ከጠበቆች ጋርለመገናኘት ደግሞ 19 ቀናት ፈጅቷል፡፡ አሁንም ከጠበቆቻቸው ጋር መገናኘት ያልቻሉ ቀሪ እስረኞች አሉ፡።

    በተለምዶው እነደሚደረገው የፓሊስ ማእከላዊ ምርመራ የቤተሰብ ጉብኝትን አይቻልም በሚል ቀላል ቃል የከለከለ ሲሆን ለጠበቆች ስብሰባ ላይነን የሚል ምክንያት ሲሰጥ ከርሟል፡፡ ይህ በመሆኑም የተነሳ የተያዙ ሰዎች መብት የሆነው የህገ መንግስቱ አንቀጽ 19 ሁለት ላይ ያለው የተያዙሰዎች ያለመናገር መብት ( the right to remain silent) በይፋ ተጥሶ ያለማንም የህግ ባለሞያ ምክር ለብዙ ቀናት ምርመራ ሲደረግባቸውቆይቷል፡፡

    ምርመራቸውን ጨርሰዋል ተብለው የታሰቡ ታሳሪዎቸን ካልሆነም በስተቀር በምርመራ ወቅት የህግ ባለሞያ ለማግኘት አልተፈቀደላቸውም፡፡
    መሰረቱ መሰረታዊ የሆነው ያለመናገር መብትና የሕግ ባለሞያ የማግኘት መብት መከልከሉ የተለመደውን ማእከላዊ ምርመራ
    የሚታማበትንየማስገደድ ምርመራ እውነተኛነት የሚያጋልጥ ነው፡፡ በተጨማሪም የአካልና የስነልቦና ጉዳት የማድረስ ምርመራ ሲፈጸምባቸው እነደነበረ የተያዙየዞን ዘጠኝ አባላት በተናገሩበት ወቅት ፍርድ ቤቱ የነዚህን ጉዳቶች መከልከል ላይ አስተያየት ከመስጠት ውጪ ይሄ ነው የሚባል እርምጃ እናማጣራት ለመውሰድ አልሞከረም፡፡

    ማዕከላዊ ምርመራ ከዚህ በፊት የሚታወቅበት ድብደባ፣ ምግብና እንቅልፍ መከልከል፣ የስነልቦና ጫና እና ማስፈራሪያ የተለያዩ ዛቻዎችሁሉም በተያዙ የዞን ዘጠኝ አባላትና ጋዜጠኞች ላይ በተለያየ መልኩ እነደደረሰ ተረድተናል፡፡ ይህም ምርመራውን ተከትሎ የሚመጣውንማንኛውንም ማስረጃ በሕግም በሞራልም ተቀባይነት እነዳይኖረው እነደሚያደርግ እናውቃለን፡፡
    ከታሳሪዎች የሚገኙ ማንኛውም መረጃዎች በከፍተኛ ተጽእኖ ስር እንደተሰጡ አንዲሁም ዝም የማለትና የሕግ ባለሞያ ምክር የማግኘት ሕገ-መንግስታዊ መብቶቻቸው ተጥሰው የተገኙ እንደሆኑ ዞን ዘጠኝ ያምናል፡፡

     በወንጀል ህግ ስነስርአት መሰረትእነዚህ ያለህግ ባለሞያ ጉብኝትያለመናገር መብታቸው (የህገ መንግስቱ አንቀጽ 19) ተጥሶ የተገኙ መረጃዎች በዚህ ምክንያት ብቻ ተቀባይነት እነደማይኖራቸውም የአገሪትዋሕግ ይደነግጋል፡፡

    በመሆኑም መንግስት ታሳሪዎቹን አንደፈታ እና ጉዳያቸው ሕገ መንግሰታዊ እና የወንጀል ህግ ሥነ-ስርአት ሕጉን ተከትሎ አንዲሆን እንዲያደርግናሌሎች እንዲያከብሩ የሚጠይቀውን ሕግ መንግስት ራሱን በማክበር አንዲጀምር አሁንም በድጋሚ ጥሪ እናቀርባለን ፡፡

    ህገ መንግስታዊ መብታቸው ተጥሶ ማእከላዊ ምርመራ የሚገኙ የዞን ዘጠኝ አባላት እና ጋዜጠኛ ወዳጆቻችን ያለንን ክብር እና ፍቅር እየገለጽንጽናታቸው አስተማሪ ሲሆን በሚከተሉት ቀናት በሚኖሩት ማንኛውም የህግ ሂደቶች ውስጥ የሚኖሩትን አዳዲስ መረጃዎች ለዞን ዘጠኝ ነዋሪያንእንገልጻለን፡፡ነገ ቅዳሜ ግንቦት 9 እና እሁድ ግንቦት 10 የሚደረጉ የፍርድ ቤት ሄደቶችን አራዳ ፍርድ ቤት አንደኛ ወንጀል ችሎት ጠዋትበመገኘት መከታተልና አጋርነታችሁን ማሳየት ትችላላችሁ፡፡

    የዞን ዘጠኝ ስብስብ አባላቶቹ ምንም አይነት ህገ ወጥ ተግባር ላይ ተሰማርተው እንደማያውቁ በድጋሚ ለማረጋገጥ ይወዳል፡፡

    Friday, May 16, 2014

    ትኩረት በህወሓት፣ ኦህዴድ፣ ብአዴንና ደህዴድ ላይ ይሁን!!!

    May 16/2014

    ዛሬ አገራችን ኢትዮጵያ መንታ መንገድ ላይ ትገኛለች። በአንድ በኩል ህወሓት እና አገልጋይ ድርጅቶቹ በተለይም ኦህዴድ፣ ብአዴንና ደህዴድ የተነሳባቸው ሕዝባዊ ተቃዉሞ ለመሸፈን የሕዝብ ለሕዝብ ጠብ ለመጫር የተቻላቸውን ሁሉ እያደረጉ ነው። በየተገኘው አጋጣሚ ሁሉ ዘርን መሠረት ያደረጉ ስድቦች፣ ዘለፋዎችና ጥቃቶች እንዲኖሩ በካድሬዎቻቸውና በቅጥረኞች አማካይነት እየጣሩ ነው። በዚህ እኩይ ተግባር ውስጥ ባለማወቅ በስሜት ብቻ የሚነዱ የወያኔ ደጋፊ ያልሆኑ ወገኖችም እየተሳተፉበት ነው። በሌላ በኩል ደግሞ በዘውግም ይሁን በአገር ደረጃ የተደራጁ የፓለቲካ ድርጅቶች መሪዎች የጋራ ጠላቶቻችን ወያኔና ግብረአበሮቹ ስለመሆናቸው የጠራ አቋም እየያዙ ነው። ወያኔና ግብረአበሮቹን ለማስወገድ በጋራ መታገል የሚያስፈልግ መሆኑ እና ከወያኔ አገዛዝ በኋላ በእኩልነት ላይ የተመሠረተ አገር የመገንባት የጋራ ኃላፊነት ያለብን መሆኑ ሰፊ ግንዛቤ እያገኘ መጥቷል።
    ይህ መንታ መንገድ በሁሉም ቦታ በባሰ ኦሮሚያ ውስጥ ጎልቶ እየታየ ነው። በኦሮሚያ አካባቢዎች የሚደርሰው ጥቃትና መፈናቀል ያስቆጫቸው ወጣቶች የሚያደርጉት ፍትሃዊ ተቃውሞ ቀጥሏል። በአምቦ፣ በነቀምት፣ በጊምቢ፣ በሀረር፣ እና ሌሎችም አካባቢዎች በተለይም የዩኒቨርስቲ ተማሪዎች ሥርዓቱን በመቃወማቸው ከፍተኛ ጥቃት እየደረሰባቸው ነው። በመቶዎች የሚቆጠሩ ሕይወታቸውን አጥተዋል፤ በሺዎች የሚቆጠሩ ታስረዋል። በእነዚህ ቦታዎች ሁሉ የእንተባበር ጥሪዎች ጎልተው እየተሰሙ ነው። በኦሮሚያ በሚገኙ ዩኒቨርስቲዎች የሌሎች አካባቢዎች ተማሪዎች ከጎናቸው እንዲቆሙ የኦሮሞ ተማሪዎች ተደጋጋሚ ጥሪዎችን አቅርበዋል። የሌሎች አካባቢዎች ተማሪዎችም ከኦሮሞ ወንድሞቻቸውና እህቶቻቸው ጎን ቆመዋል። ይህ ተስፋ የሚሰጥ እና መበረታታት ያለበት ነገር ነው። ሆኖም ግን ከዚሁ ጎን ለጎን ህወሓትና ኦህዴድ የሕዝቡን ጥያቄ ወደ ዘር ግጭት ለማዞር እየሠሩ ነው። በተማሪዎች መፈክሮች ውስጥ ዘርን ለይተው የሚያንቋንሽሹ መልዕክቶች ሰርገው እንዲገቡ እየተደረገ ነው። ኦሮሞ ባልሆኑ በተለይም በአማራ ተወላጆች ላይ ጥቃት እየደረሰ ነው። የወያኔ ጆሮ ጠቢዎችና ካድሬዎች በስሜት የተገፋፉ ወጣቶችን ወደ ዘር ግጭት እየመሯቸው ነው።ይህ እጅግ አሳሳቢና በአስቸኳይ መቆም የሚኖርበት ነገር ነው።
    ከመንታ መንገዶቹ ለአገርና ለወገን እንዲሁም ለወደፊቱ ትውልድ ደህንነት የሚበጀውን የመረዳዳት፣ የመደጋገፍ እና የመተባበርን መንገድ መርጠን እርምጃችንን ካላፋጠንን አሁን የደረስንበት ደረጃ እጅግ አስጊ ነው። ማሰብ፣ ማስተዋል እና ጠላትን መለየት በሚያፈልግበት ወሳኝ ወቅት ላይ ነው የምንገኘው። ድሃ አማራ ለድሃ ኦሮሞ ወገኑ ብቻ ሳይሆን የትግል አጋሩ ነው። ኦህዴድ ውስጥ ያሉ የወያኔ አገልጋዮች ደግሞ ኦሮሞች ስለሆኑ የድሃ ኦሮሞ ወዳጆች አይደሉም። እነሱ የወያኔ ተቀጥላዎች ናቸው። የትውልድ መንደራቸውን ሳይቀር አዘርፈው የሚዘርፉ ስግብግቦች ናቸው።
    የኦሮሞ ሕዝብ ትግል በወያኔ እና ተቀጥላዎቹ ድርጅቶች እንጂ በአማራና በኦሮሞ ወይም በኦሮሞና በትግሬ ሕዝብ መካከል አይደለም። የአማራ ሕዝብ ትግል በወያኔ እና ተቀጥላዎቹ ድርጅቶች እንጂ ከማንኛውም አካባቢ ሕዝብ ጋር አይደለም። ወደ እርስ በርስ ቅራኔ ሊዘፍቁን የሚፍጨረጨሩትን ህወሓት፣ ኦህዴድ፣ ብአዴንና ደህዴድን ከሕዝብ መነጠል መቻል አለብን። እዚህ እኩይ ኃይሎች ሥልጣን ላይ እስካሉ ድረስ ፍትህና ሰላም ማግኘት አንችልም። እዚህ እኩይ ኃይሎች እርስ በርሳችን ሊያጫርሱን እየሠሩ መሆኑን አውቀን ኃይላችንን በማስተባበር እንመክታቸው።
    ግንቦት 7: የፍትህ፣ የነፃነትና የዲሞክራሲ ንቅናቄ በማናቸውም የኢትዮጵያ ግዛት የሚደርስን የሰብዓዊ መብት ጥሰትን በፍጹም ቁርጠኝነት በጋራ እንታገል፤ በስሜት ከተሞሉና ለእርስ በርስ ግጭቶች ከሚዳርጉ ነገሮች እንቆጠብ፤ አርቆ አስተዋይነትና ታጋሽነት በተላበሰ መንገድ የጋራ ጠላቶቻችን በሆኑትን በህወሓት እና አጫፋሪዎቹ ኦህዴድ፣ ብአዴን እና ደህዴድ ላይ በጋራ እንነሳ ሲል ለመላው ኢትዮጵያ ሕዝብ ጥሪ ያደርጋል።
    ድል ለኢትዮጵያ ሕዝብ!!!

    Thursday, May 15, 2014

    ዝክር ለግንቦት 7 1997 እና ለግንቦት 7 ቀን 2000 ዓ.ም.

    May 15/2014
    ዘንድሮ፣ የታሪካዊው ግንቦት 7 ቀን 1997 አገር ዓቀፍ ምርጫ ዘጠነኛ ዓመት እና ንቅናቄዓችን የተመሠረተበት ስድስተኛ ዓመት የምንዘክረው ከመችውም በላይ አገራችን አሳሳቢ ሁኔታ ላይ ሁና ነው። ወያኔ የማይገዛትን አገር እንዳትኖር ለማድረግ እማትወጣው አረንቋ ውስጥ ከመክተት የማይመለስ ኃይል መሆኑን ዛሬ በአምቦ፣ በጉደር፣ በጊምቢ እና መሰል ቦታዎች በተግባር እያስመሰከረ ነው።
    የኢትዮጵያ ሕዝብ በታሪኩ ለመጀመሪያ ጊዜ እውነተኛ ፍላጎቱን የመግለጽ አንፃራዊ ነፃነት አግኝቶ የነበረበት የግንቦት 7 ቀን 1997 ዓ.ም. ምርጫን ስናስብ ዛሬ ያለንበት ሁኔታ መመዘናችን አይቀርም። ያኔ ለአብዛኛው የኢትዮጵያ ሕዝብ እንደ እጁ መዳፍ ቀርባ ትታየው የነበረችው ድል እስከዛሬ አልጨበጣትም። ትግሉ ግን ቀጥሏል። የዛሬው ትግላችን የኢትዮጵያ ሕዝብ ከያኔው በበለጠ ከታሪክና ከራስዋ ጋር የታረቀች አገር የመመሥረትን ርዕይ አስፈላጊነት ላይ ትኩረት መስጠትን የሚጠይቅ ሆኗል።
    ወያኔ ከተፈጠረበት ጊዜ ጀምሮ ለአለፉት አርባ ዓመታት ሲያብላላው የቆየው፤ በመንግሥት ሥልጣን በቆየባቸው ሃያ ሶስት ዓመታት ውስጥ ደግሞ በፓሊሲ ደረጃ ሲያስፈጽመው የቆየውን የዘር ፓለቲካ አስከፊ ውጤት አሁን እየታየ ነው። ይህ የዘር ፓለቲካ ራሱ ወያኔን ያጠፋዋል። ችግሩ ግን የዘር ፓለቲካ ወያኔን ነጥሎ አያጠፋም፤ ከወያኔ ጋር አገራችንንም ሊያጠፋ ይችላል። ከሁሉም በላይ አሳሳቢው ጉዳይ ደግሞ የዘር ፓለቲካ የበርካታ ኢትዮጵያዊያንን ሕይወት አደጋ ላይ ሊጥል ይችላል። በጎረቤት አገራት ውስጥ ያየነውን ዓይነት የእርስ በርስ እልቂት ወደ አገራችን ለማምጣት ህወሓትና ኦህዴድ ተግተው እየሠሩ ነው። ሌሎች የወያኔ ተቀጥላ ድርጅቶችም የዚህ ትልቅ የጥፋት ፕሮጀክት አካል ናቸው።
    የግንቦት 7 1997ቱ ብሩህ ተስፋ በፋሺስቱ ወያኔ የግፍ አፈና ሲጨልም፤ ያ ተስፋ እንዲያንሠራራ በግንቦት 7 2000 ዓ.ም. የተቋቋመው ግንቦት 7: የፍትህ፣ የነፃነትና የዲሞክራሲ ንቅናቄ ዛሬ የኢትዮጵያን ተስፋ ለማጨለም ከተነሱ ኃይሎች በተፃራሪ በመቆም የሕዝብና የአገር አለኝታነቱ ማረጋገጥ ይኖርበታል።
    በዚህም ምክንያት፣ በዚህ ወሳኝ ወቅት የግንቦት 7 አባላትና ደጋፊዎች የሆንን ሁሉ በከፍተኛ የኃላፊነት ስሜት መንቀሳቀስ ይኖርብናል። በግራም ይሁን በቀኝ ያለ ጽንፈኝነት አገራችን አይጠቅምም፤ የምንመኛትን ኢትዮጵያ አያመጣልንም። ሕዝባችንና አገራችንን ከዚህ አረንቋ ማውጣት የሚቻለው የአንድነትና የእኩልነት ፓለቲካን አሸናፊ ማድረግ ስንችል ነው።
    በአሁኑ የኢትዮጵያ ፓለቲካ ለሀገራችን የሚጠቅማትና ትክክለኛ ነው ብለን የምናምነው ለኢትዮጵያ ሉዓላዊነት የሚታገል፤ የተለያዩ የኅብረሰተሰብ ክፍሎች በመሰላቸው መንገድ ለመደራጀት መብታቸው እውቅና የሚሰጥ፤ በኢትዮጵያ የሚገኙ ማኅበረሰቦች በሙሉ በእኩልነት የሚስተናገዱበት ሥርዓትን የሚያልም፤ መሰማማት፣ መቻቻል እና ከዚያም አልፎ መተጋገዝ ያለበት የኢኮኖሚና የፓለቲካ ሥርዓት እንዲኖር የሚታገል፤ የእምነቶች እኩልነትን የሚያከብር፤ በታሪክ ውስጥ የተፈፀሙ በደሎችን መርምሮ ማኅበራዊ እርቅ ለመፍጠር ፍላጎት ያለው ፓለቲካ ነው።
    ይህ ዓይነቱ የአንድነትና የእኩልነት ፓለቲካ በአሸናፊነት እንዲወጣ ማድረግ ይቻላል ብሎ ግንቦት 7: የፍትህ፣ የነፃነትና የዲሞክራሲ ንቅናቄ ያምናል። ይህ ለሁላችንም የሚበጀው ፓለቲካ አሸናፊ ለማድረግ የሚከተሉትን መፈፀም ይጠበቅብናል።
    1. በማንኛውም የኢትዮጵያ ክፍል ውስጥ የሚደርስ የሰብዓዊ መብት ጥሰት በፍጹም የማንታገስ መሆኑን ማመንና በተግባሮቻችንም ይህንኑ መግለጽ፤
    2. ኢትዮጵያ ከገባችበት ችግር መውጫው መንገድ ወያኔን ማስወገድና በምትኩ የዜጎችን እኩልነት የሚያረጋግጥ፣ ሕዝብን ከሕዝብ የሚያስታርቅና የሚያስተሳስር መንግሥት መመሥረት መሆኑን ማመንና በተግባሮቻችን ማሳየት፤
    3. የኢትዮጵያ ዋነኛ ጠላቶች ወያኔ እና ተቀጥላዎቹ፣ በተለይም ህወሓት፣ ኦህዴድ፣ ብአዴን እና ደህዴድ መሆናቸውን በማመን ትኩረታችንን ነቀሎ ወደሌላ ከሚወስዱ አስተሳሰቦችና ድርጊቶች መቆጠብ፤
    4. በብሔር ከተደራጁ ኃይሎች ጋር በሚለያዩን ነገሮች ላይ ሳይሆን በሚያስተባብሩን ጉዳዮች ላይ በማተኮር የወያኔን የከፋፍለህ ግዛ አጀንዳ ማክሸፍ፤
    5. በስሜትከተሞሉ የአጭር ጊዜ እይታዎች ለእርስ በርስ ግጭቶች ከሚዳርጉ አስተሳሰቦችና ተግባራት መቆጠብ፤ እና
    6. አርቆ አስተዋይነትና ታጋሽነት በተላበሰ መንገድ ለኢትዮጵያ ሕዝብና ለኢትዮጵያ ደህንነት፣ለፍትህና ለነፃነት በግንባር ቀደምትነት መቆም፤
    የግንቦት 7 ንቅናቄ አባላትና ደጋፊዎች ከላይ የተዘረዘሩትን ለመፈጸም የሚቻለንን ሁሉ ለማድረግ ያለንን ዝግጁነት እየገለጽን፣ መላው የኢትዮጵያ ሕዝብ ወያኔና ግብር አበሮቹ ከፊቱ የደቀኑበትን ከፍተኛ አደጋ ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ተባብሮ እንዲያስወግድ ግንቦት 7: የፍትህ፣ የነፃነትና የዲሞክራሲ ንቅናቄ ጥሪውን ያቀርባል።
    አስቸጋሪ ወቅት ላይ የምንገኝ ቢሆንም እንኳን በርትተን ከታገልን የተረጋጋች፣ ዲሞክራሲያዊ ሉዓላዊ አገር – ኢትዮጵያ – ይኖረናል። ለዚህ ውጤት በርትተን እንታገል።
    ክብር የግንቦት 7 1997 ሀገራዊ ተስፋን እውን ለማድረግ ለወደቁ ሰማዕታት!
    ድል ለኢትዮጵያ ሕዝብ !!!

    የኢትዮጵያ አየር ኃይል ካፒቴን አስመራ ላይ ተቃዋሚዎችን ተቀላቀለ፤ * መንግስት አላስተባበለም

    May 15/2014

     የኢትዮጵያ አየር ሃይል አባላት ገዢውን የኢሕአዴግን መንግስት በመክዳት ወደ ተለያዩ ሃገራት የሚያደርጉትን ስደትቀጥለዋል። የኤርትራ ሚዲያዎች የመንግስታቸውን ቃል አቀባይ በመጥቀስ እንዳስነበቡት ሰሞኑን የኢትዮጵያ ሚግ 23 አብራሪየሆነው ካፒቴን ዳንኤል የሽዋስ ስርዓቱን ጥሎ አስመራ ገብቷል።

    እንደኤርትራ ሚዲያዎች ገለጻ ከሆነ ካፒቴን ዳንኤል የሺዋስ ኤርትራ ከሚገኙ የኢትዮጵያ ተቃዋሚ ኃይሎች ጋር ተቀላቅለዋል።ሚዲያዎቹ በምን መልኩ ወደ አስመራ እንደገባ የገለጹት ነገር ባይኖርም ማዕዶት የተባለው የኤርትራውያን የመረጃ መረብየኤርትራን መንግስት ቃል አቀባይ በመጥቀስ ካፒቴኑ ለኢሳያስ አፈወርቂ መንግስት እጁን የሰጠው ከነ አውሮፕላኑ ነው ሲል ዘግቧል።

    የኢሕአዴግ መንግስት በመከላከያ ውስጥ ያለውን የዘር አድልዎና በኢትዮጵያ ህዝብ ላይ እየፈጸመ ያለውን የሰብአዊ መብት ጥሰትበቸልታ መመልከት እያንገፈገፋቸው የሚገኙ የሠራዊቱ አባላት በተለያዩ ጊዜያት እየሸሹ ወደ ኤርትራ በመግባት ተቃዋሚዎችንእንደሚቀላቀሉ በተደጋጋሚ መዘገቡ ይታወሳል።
     ምንጭ ዘ-ሐበሻ


    Hailemariam Desalegn again at odds with TPLF on oromo protests

    May15/2014

    Ethiopian Prime Minister Hailemariam Desalegn is once again at odds with the powerful TPLF branch of EPRDF ruling party, according to sources connected to his adminstration. This time the dispute is on government response to Oromo protests in Oromia region, according to a journalist of an English weekly paper who asked to remain anonymous for fear of reprisals.
    Hailemariam, an ethnic Welayta native, does not have the military background and the political power that former Tigrayan Prime Minister Meles zenawi had. Meles was the executive head of the Tigrayan Peoples Liberation Front (TPLF) for over thirty years. Even though various ethnic groups are well represented inside the Ethiopian military, most of the top executive positions are held by Tigrayans. Some reports claim that around 70 percent of the country’s top generals and military leaders are still ethnic Tigrayan today, even though Tigrayans makeup only 6 percent of the Ethiopian population.
    The Govt source said TPLF military chiefs wanted to stop the peaceful Oromo student protest early before it turned into riots, but there was “lack of leadership and policy from Arat Kilo,” (refering to the Menelik Palace were the PM resides. )
    Despite their small numbers in the country, Hailemariam’s ethnic Welaytas are said to have significant presence in the mid-level positions in the army and federal force. However, TPLF’s military heads complain that Hailemariam portrays a “soft leader” image and the police has been overstretched with nonstop demonstrations for months. They say the public is emboldened to take their angers to the streets since Meles died. Since 2013, millions of Muslim Ethiopians have been protesting in the cities while the “legal opposition” groups have also organized various protests, sometimes without permit. But the recent Oromo protests have irritated the TPLF military authorities the most, as some OPDO (another EPRDF branch) members have provided covert support.
    The source said Hailemariam’s chances of being re-elected to lead EPRDF ruling party are slim. Hailemariam has also been under American pressure to deliver a peace deal in South Sudan, though some TPLF army officials are suspicious of the Sudanese opposition.
    TPLF military chiefs claimed South Sudan peace deals signed in Addis Ababa are symbolic but meaningless on the ground because the rebel leader Riek Machar does not have full control of opposition fighters.

    ጁነዲን ሰዶ አትላንታ አሜሪካ ገቡ

    May 14, 2014

    Junedin Sado“ይሄ ፋሽስት መንግሥት!” ማለት ጀምረዋል!

    አገር ለቀው የኮበለሉትና የኦሮምያ ፕሬዚዳንትነትን ጨምሮ በተለያዩ የመንግሥት መስሪያ ቤቶች በሚኒስትርነት ማዕረግ ያገለገሉት እንዲሁም የኦህዴድና የኢህአዴግ ሥራ አስፈጻሚ የነበሩት አቶ ጁነዲን ሰዶ አሜሪካ መግባታቸውን በዋሺንግተን ዲሲ የሚታተመው ዘ-ኢትዮጵያ የተባለው የአማርኛ ጋዜጣ ይፋ አድርጓል። ኬንያ ለአንድ ዓመት ያህል በስደተኝነት ተቀምጠው የአሳይለም ወረቀታቸውን አግኝተው አትላንታ ከገቡ ሁለት ወራት እንደሆናቸውም የዘኢትዮጵያ ጋዜጣ ምንጮች ገልጸዋል።

    አቶ ጁነዲን በአባ ዱላ ገመዳ እስኪተኩ ድረስ ከኦክቶበር 28/2001 እስከ ኦክቶበር 6 /2005 የኦሮምያ ክልል ፕሬዚዳንት ነበሩ። ከዚያም የትራንስፖርትና መገናኛ ሚኒስትር በመሆን እስከ ኦክቶበር 2008 አገልግለዋል። በመቀጠልም በሳይንስና ቴክኖሎጂ ሚኒስትርነት ከሠሩ በኋላ በመጨረሻም በ2010 የሲቪል ሰርቪስ ሚኒስትር በመሆን የቀድሞ ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ መለስ ዜናዊን መንግሥት አገልግለዋል። የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲም የቦርድ ሊቀመንበር ነበሩ። መንግሥታቸው ብዙ ዓመት ከኖሩበት የሚኒስትሮች ካቢኔ ያሰነባታቸው የአቶ ኃይለማርያም የጠቅላይ ሚኒስትርነት ዘመን ሲጀመር ነው።የስደት ኑሯቸውን ማቃናት የያዙት አቶ ጁነዲን ከወዳጆቻቸው ጋር ሲያወጉ “ይሄ ፋሽስት መንግሥት እኮ የሚያደርገውን አያውቅም” በሚል መገረም ሲናገሩ መደመጣቸውን ምንጮቻችን ገልጸዋል። ባለቤታቸው ወ/ሮ ሀቢባ መሀመድ “በሽብር ተግባር ተጠርጥረዋል፣ ከሳዑዲ ኤምባሲ ገንዘብና መጽሐፍት ይዘው ሲወጡ ሐምሌ 9 ቀን 2004 እጅ ከፍንጅ ተይዘዋል” በሚል ተዘውታሪ ሰበብ በእስር መቆየታቸው ይታወሳል። ከሥልጣናቸው በመስመጥ ላይ ለነበሩት አቶ ጁኒዲም ይህ የባለቤታቸው እስር ተጨምሮ ከአገር ለመኮብለል መንስኤ መሆኑ ሲዘገብ መሰንበቱ ይታወቃል።

    ባለቤታቸውና ልጃቸው አሁንም በኢትዮጵያ የሚገኙ በመሆኑ አቶ ጁኒዲን በይፋ ምንም አስተያየት ሳይሰጡ ተቆጠበው መቀመጡን መምረጣቸው ተነግሯል። ሰሞኑን በኦሮምያ ክልል ተማሪዎች ላይ እየደረሰው ያለው ግድያና ሁከት በአንድም ሆነ በሌላ መንገድ የሚመለከታቸው ቢሆንም፣ እንደ ተራ ሰው “ይሄ ፋሽስት መንግሥት ምን እያደረገ ነው” ብለው መገረማቸው መልሶ ማሰገረሙን ምጮቻችን ገልጸውልናል። የኦሮምያ ክልል ፕሬዘዳንት ከነበሩት ውስጥ ሀገር ጥለው የኮበለሉ ፕሬዘዳንቶች ከአቶ ሀሰን ዓሊ ጋር አቶ ጁነዲን ሲደመሩ ሁለተኛ መሆናቸው ነው። ሁለቱም አትላንታ መሆናቸው ሲገለጽ አቶ ጁነዲን በአንድ ዩኒቨርስቲ መምርህነት ሥራ ለማግኘት ማመልከቻ ማስገባታቸውም ተነግሯል።

    Wednesday, May 14, 2014

    ወለጋ ዩኒቨርስቲ ነቀምት ዋናው ካምፓስ በድጋሚ ተቃውሞ ተነስቷል (ፎቶዎች ይዘናል)

    May 14/2014
    ሚኒሊክ ሳልሳዊ
    በነቀምቴ በሚገኘው የወለጋ ዩንቨርስቲ የሚማሩ የኦሮሞ ተማሪዎች ባነሱት ተቃውሞ የወያኔ ፖሊሶች አጸፋውን የወሰዱ ሲሆን በዚሁም አጸፋ የተጎዱ በርካታ ተማሪዎች ወደ ህክምን ጣቢያ ሄደዋል። ከተደበደቡት ተማሪዎች በከፊል ምስሎቻቸውን ይመለክቱ። እነዚህ የምታይዋቸው ተማሪዎች በዛሬው የተቃውሞ ሰልፋቸው ላይ ይተጎዱ ናቸው።
    nekemte1
    nekemte2
    nekemte3
    nekemte4
    nekemte5
    nekemte6
    nekemte7

    የኢሕአዴግ አጋዚ ጦር በወለጋ ዜጎችን እያሰረ ነው – ጊምቢም እየወደመች ነው !

    May 14/2014
    «አበሾች አዲስ አበባን በመጠቀም የኦሮሚያን መሬት እየወረሩ ነው» በሚል በቅርቡ ይፋ የሆነውን የአዲስ አበባ ማስተር ፕላን በመቃወም በተለያዩ የኦሮሚያ ከተሞች በሚገኙ ዩኒቨርሲቲዎች ተቃውሞ ማሰማታቸው ይታወቃል። ከተቃዉሞው ጋር በተገናኘ በርካታ ዜጎች የሞቱ ሲሆን፣ በንብረትም ላይ ከፍተኛ ጥፋት ደርሷል።

    በተነሳው ቀውስ ሰለባ ከሆነቸው ከተማ አንዷ የጊምቢ ከተማ ናት። ከጊምቢ የተላኩ ፎቶዎችን ይመልከቱ
    gimbi6
    gimbi5
    gimbi4
    gimbi3
    gimbi2
    gimbi1
    Gim2

    እናስራችኋለን? ለካንስ የነአጅሬ ጋጠወጥነት ከድንበርም ተሻግሯልና!

    May 14, 2014
    ነፃነት ዘለቀ (ከአዲስ አበባ)
    በሀገራችን ባደመነው አጠቃላይ የሀዘን ድባብ ሳቢያ ፈገግታ እያማረኝ ፈገግ ለማለት ምንም ዕድል ሳላገኝ ብዙ ሰሞኖችን ባጀሁ፡፡ ዕድሜ ለዚህ ነገረኛ ኢሳት የሚባል ቴሌቪዥን ዛሬ ማታ ግና በሣቅ የሚያፈርስ ዜና ሰማሁና ምሽቱን ብቻ ሳይሆን ትዝ ባለኝ ቁጥር ሌቱን ሁሉ በሣቅ ስፈርስ አደርኩ – የግራ ጎን አጥንቶቼ ክፋይ ጉድ እስክትለኝ፡፡ ሣቅ ጥሩ ነው፡፡ አንዳንዴ በሣቅ የሚገድል ነገር ማግኘት የመታደል ያህል ነው፡፡ እውነተኛው ሣቅ ሞቶ ቢቀበርም ወያኔን መሰል ጅላንፎ ጉጅሌ የሚሠራቸው አንዳንድ ነገሮችን በመታዘብ ለጊዜውም ቢሆን ፈገግ መሰኘት ሲያስፈልግም ሆድን ያዝ አድርጎ በሣቅ መንፈርፈር ሰውነትን ያፍታታል፤ ወቅታዊ እፎይታንም ይሰጣል፡፡ እኔ – እውነቴን ነው – ለብዙ ጊዜ ያጣሁትን ሣቅ ዛሬ አገኘሁትና ከልቤ ተዝናናሁ፡፡ ወያኔ እኮ አልታወቀለትም እንጂ ደምበኛ የኮሜዲ መፍለቂያ ውድብ ነው፡፡ ልዩ የኢትዮጵያ ቻርሊ ቻፕሊን ሆነው የለም እንዴ!President Salva Kir of Sudan
    ይህን የወያኔን ሞኝነት ጉዳዩ ለሚመለከተው የዓለም ክፍል ያንጸባረቀ ጉዳይ ለፖለቲካችን ቅርብ የሆነ ሰው ባያጣውም ለእንደኔ ዓይነቶች የማይሞላላቸው አንዳንድ ባዘኔዎች ማስታወሱ ደግ ይመስለኛል – ‹ቦዘኔ› እንዳላልኩ ይታወስልኝ፡፡ ብዙ ሰው እኮ የማይሞቀው የማይበርደው ሆኗል፡፡ ደንዘናል፤ በቁም ሞተናል፤ ‹ብታምኑም ባታምኑም› ብዙዎቻችን ከሰውነት ተራ ወጥተን የአምልኮተ ንዋይ ሰለባዎች ሆነናል፡፡ በሀገር ውስጥ ትንሽ ትልቁን ብታዩት ከሞላ ጎደል ሁሉም ሊባል በሚችል ሁኔታ ገንዘብ እንዴት ሊያገኝና በአቋራጭ ሊከብር እንደሚችል ሲጨነቅና ሲጠበብ ይታያል፡፡ ኅሊና ብሎ ነገር ጠፍቷል፡፡ ወንድም ወንድሙን፣ እህት እህቷን እስከመግደል በሚደርስ ሰይጣናዊ ጭካኔ ተሞልተን እየተፋጀን ነው፡፡ ወያኔ በቀደደው የጥፋት ጎዳና እየተመምን ከሰውነት ደረጃ በሚያስወጣ የሀብት ፍቅር ተነድፈን ልንጨራረስ የቀረን ጊዜ ሩብ ሐሙስ ቢሆን ነው፡፡ አልተነሳሁበትም እንጂ በዚህስ ትንሽ ባወራሁ፡፡
    ወያኔም ባቅሙ አስታራቂና የሰላም አባት ሆኖ የደቡብ ሱዳን ተፋላሚዎችን በዕርቅ ለማስማማት አዲስ አበባ ይጠራቸዋል፡፡ ሳልቫኪር የሚሉት ባለባበሱና በዐይነ ውኃው ፊውዳላዊ አምባገነን የሚመስለኝ አማቻችን ሰውዬና ዶክተር ማቻር የሚባለው ሞገደኛ ሰውዬ ወደ አዲስ አበባ መጥተው (እንዳሁኑ ሁኔታ ደግሞ በመስፈራርቾ ተጠርተው) ሼራተን ሆቴል ሁለት ክፍሎች ውስጥ ይመሽጋሉ – ‹አማቻችን› ያልኩት የሳልቫኪር ይሁን የማቻር ልጅ የኛን ሀገር ልጅ እንዳገባ/ች በሚዲያ ስለሰማሁ ነው፡፡ ድርድሩም በወያኔ ጉጅሌ አማካይነት ተከናወነ ይባልና የዕርቁ ስምምነት ተፈረመ ተብሎ በወያኔው ቱሪናፋ ሚዲያዎች ይለፈፋል – (ከብቱ ወያኔ በሰሞኑ ጭፍጨፋው የጠለሸ ስሙን ያደሰ መስሎት በገባበት ወጥመድ የኋላ የኋላ ራሱ ገብቶበት ተተበተበበት እንጂ)፡፡ የወያኔ ኢትዮጵያ ለራሷ ብቻ ሣይሆን ለጎረቤት የሚተርፍ ሰላምና ዴሞክራሲ መጋዘኗ ውስጥ ጢም ብሎ እንዳለና ለሱዳንም፣ ለሶማሊያም፣ ለግብጽም፣ ለሦርያም፣ ለአፍጋኒስታንም፣ ለኢራቅም፣ ለቬንዝዌላም፣ ለ“ዴሞክራክ ሪፓብሊክ” ኮንጎም፣ ለሤንትራል አፍሪካ “ሪፓብሊክ”ም፣ ለሃይቲም፣ ለኡክሬንና ራሽያም፣ ለሰሜን ኮሪያም፣ ለ‹ኤርትራ›ም፣ ለሊቢያም፣ ለፓኪስታንም፣ ለበርማም፤ ለፍልስጥኤምም፣ (እንዴ፣ ዓለም ለካንስ በትርምስ ላይ ናትና ጎበዝ – የወያኔ የሰላም በረከት የሚላክላቸው ሁከት የነገሠባቸው ሀገሮች ዝርዝር አላልቅልኝ እኮ አለ!) ኤክስፖርት ለማድረግ ዝግጅቷን እንዳጠናቀቀች በነዚሁ በእውነት ዕርሙ የወያኔ ሚዲያዎች ከጥንፍ እስከ ጥንፍ ተስተጋባ፡፡ እኛም ይሄ የቤት ቀጋ የውጪ አልጋ የሆነ የወሮበሎች ቡድን ምን መተት ቢኖረው ይሆን እንዲህ ዓለምን ጉድ ባሰኘ መልክ የሰላም አባት ሊሆን የበቃው ብለን ተገረምን፡፡ የገዛ “ዜጎቹ”ን ባልተወለደ አንጀት እየጨፈጨፈና የስምንት ዓመት ሕጻን ሣይቀር ደረቱን በጥይት ዝናብ እየበሳሳ ባለበት ወቅት እንዲህ ያለ ሰላም ለሱዳናውያኑ ማስገኘቱ በርግጥም አንዳች ነገር አለው አልንና በጣም ተደነቅን፡፡ ኢትዮጵያችንም ስሟ ታደሰልን ብለን ደስ አለን – ደስታችን አንድ ጀምበር እንኳን ሳይዘልቅ ጠወለገብን እንጂ፡፡
    ነገሩ ለካንስ ሌላ ኖሯል፡፡ ሳልቫኪር ሀገሩ እንደገባ ለሀገሩ መገናኛ ብዙኃንና ለባለሥልጣናቱ ሲናገር እንደተደመጠውና በሚዛናውያን ሚዲያዎች ሲዘገብ እንደተከታተልነው የሰላሙ ስምምነት የተፈረመው በወያኔ አስገዳጅነት ነበር፡፡ የአስገዳጅነቱ አካሄድም ነው በአስቂኝነቱ ወደር ያልተገኘለት፡፡
    ከፍ ሲል እንደተገለጸው ወያኔ ሁለቱን ሰዎች ሼራተን ውስጥ በሁለት የተለያዩ ክፍሎች ያስቀምጣቸዋል፡፡ ፊት ለፊት ሳይገናኙም በተላላኪ ሃሳብ እንዲለዋወጡ ያደርጋል፡፡ መገናኘት ያልፈለጉት ምናልባት ራሳቸው ሊሆኑ እንደሚችሉ እንገምት፡፡ ወያኔ ግን የሁለቱ ሰዎች ያለመታረቅና ዕርቁን በፊርማ ያለማጽደቅ አዝማሚያ ሲገባው ያቺን የጫካ ህግ በመምዘዝ “ካልፈረማችሁ እዚሁ አስራችኋለሁ፤ ወደ ሀገራችሁ መሄድ ህልም እንደሆነባችሁ እንደነ እስክንድር ነጋና ርዕዮት ዓለሙ ከርቸሌ ትወረወራላችሁ፤ ከዚህ የሚያወጣችሁ አንድም ኃይል የለም” ብሏቸው ያርፋል፡፡ ይህ ያላሳቀ ምን ሊያስቅ ይችላል? እንዴ፣ በዚህማ ድዳችንን ተወቅረንም ሆነ ተነቅሰን መሣቅ አለብን፡፡ ግሩም እኮ ነው እናንተ ሆዬ!
    ትርፋ ትርፉን እንተወውና ቃል በቃል ወያኔ ያላቸው “ስምምነቱን በፊርማችሁ ካላጸደቃችሁ ትታሰራላችሁ!” የሚል ነው – ከሌሎች የማስፈራሪያ አንድምታዎች ጋር፡፡ አስገዳጁ ደግሞ ራሱ ተገድዶ ቤት ጠባቂ የሆነው ደሳለኝ ነው አሉ – ማነው – ኃይለማርያም – ከአለቆቹ በተነገረው ጥብቅ ማስጠንቀቂያ መሠረት፡፡
    ልብ አድርጉ! እነዚህ ሰዎች – እነሳልቫኪር – አነሰም አደገም የአንዲት ሉዓላዊት ሀገር መሪዎች ናቸው – አሁን ቢጣሉምና ከሁለት አንድኛቸው ዓለም አቀፍ ተቀባይነት ያለው መንግሥት በመምራት ላይ መገኘቱ እንዳለ ሆኖ፡፡ ወያኔን ታዲያ ምን ገጠመው? ይህችን እጅ እየጠመዘዙ ማስፈረምን ከሀገር ደረጃ አውጥቶ አህጉራዊ ቅርጽ እንዲኖራት የማድረግን ከፍተኛ ጉጉት ማን አሳደረበት? “የገቡበት የፖለቲካ ቀውስ የሚሠሩትን አሳጥቷቸው ለአንዳች የፖለቲካ ትርፍ ብለው ይሆን እንዲህ ያለ ‹ሪስክ› ውስጥ የገቡት?” ብዬም ተጨንቄላቸዋለሁ – ለወያኔዎቹ – እንዲያ ካልሆነ መቼም ጡት ያልጠባ ማለቴ ያልጣለ ሕጻን ሣይቀር መዘዙን ጠንቅቆ ሊገምተው የሚችለውን ይህን የመሰለ ጅልነት ውስጥ ባልገቡ ነበር፡፡ አሁን አስገድዶ ቢያስፈርማቸው ወደሀገራቸው ሲመለሱ ጉዱን ማለትም ምሥጢሩን እንደሚያወጡት እንዴት ወያኔዎች ሊገምቱ አልቻሉም? እንዴትስ ቢንቋቸው ነው? በኛ የለመዱትን ንቀት እኮ ነው በ‹ኮፒ ፔስት› እነሱም ላይ እውን ያደረጉት፡፡ በውነቱ እነዚህን የመርገምት ፍሬዎች ሰው ናቸው ብሎ መቀበል እንዴት ይቻላል? ኢትዮጵያ በታሪኳ እንዲህ ያለ አሣፋሪ ነገር የፈጸመባት በስሟ የተቀመጠ “መንግሥት” የለም፡፡ እዚህ ላይ አንዲት ብጫቂ ማሳሰቢያ አለችኝ፡- በተለይ ኢሳቶች ይህንን የወንበዴ ጥርቃሞ ቡድን “የኢትዮጵያ መንግሥት” እያላችሁ በዜና ዕወጃችሁ የምትናገሩትን ነገር ባፋጣኝ ብታርሙ ይሻላል፡፡ ይህ ‹መንግሥት› መንግሥት ሣይሆን የከተማ ሽፍታ ነው፤ በአንድ ጎሣ የተዋቀረ፣ ለአንድ ጎሣ ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ ጥቅም ያደረ፣ ለዓለም አቀፍ የውንብድና ተቋማት የሰገደና አንዲትን ሀገር ከነሕዝቧ መቀመቅ ለማውረድ ታጥቆ የተነሣን ወሮበላ የአማጊዶዎችን ስብስብ መንግሥት ማለት በመንግሥት ተቋማዊ ምንነት ላይ መቀለድ ነው፡፡ ስለዚህ ቢያንስ “የኢትዮጵያ መንግሥት ተብዬው” በሚል ቢነገር የተሻለ ነውና አንዳንድ ወገኖች አታቁስሉን፡፡ የነሱው ይበቃናል፡፡
    አንድ ፈረንጅኛ አባባል አሁን ትዝ አለኝ፡፡ A man cat take a horse to a river; but twenty cannot make it drink. ወዳማርኛው ሲመለስ – አንድ ሰው አንድን ፈረስ ወደ ወንዝ ሊወስደው ይችላል፤ ሃያ ሰዎች ግን ውኃ(ውን) እንዲጠጣ ሊያደርጉት አይችሉም፡፡ የወያኔ ቂልነት፣ የወያኔ ባልጩት ራስነትና አባጉልቤነት እዚህ ላይ ነው፡፡ እነሱ የሚያስቡት ነገር ሁሉ ገዢ ይመስላቸዋል፡፡ የድንቁርናቸው መጠን በምንም ምድራዊ መለኪያ የሚሠፈር አይደለም፡፡ በመንግሥትነት ለሃያ ሦስት ዓመታት የቆዬ አንድ ኃይል የዚችን ፊርማ መነሻና መድረሻ ከነመዘዟ ጭምር ካላወቀ ትልቅ የአስተሳሰብም እንበለው የአመለካከት ችግር አለ ማለት ነው፡፡ እንዲያው ግን ኢትዮጵያ ምን ያህል ብትረገም ፣ እኛም ምን ያህል ባንታደል ይሆን ፈጣሪ እነዚህን ሰዎች የሰጠን? አይጨንቅም? ሳስበው በጣም ይጨንቀኛል – ማይግሬይን የተሰኘውን ከፍተኛ ራስ ምታት የሚለቅ ችግር ነው የገጠመን፡፡
    የዚህ ችግር መባቀያ ደግሞ ውስብስብ ነው፡፡ ምዕራባውያንም ይጠየቁበታል – አሉበትና፡፡ ማፈሪያ የሰውነት አካል እንደወያኔው የላቸውም እንጂ ካላቸው በእጅጉ ሊያፍሩበት ይገባል፡፡ በብዙ ነገር እየደገፉ ከበረሃ ወደ ቤተ መንግሥት ያስገቡ ኃይሎች ቆም ብለው ሊያስብቡበት የሚገባ ወቅት ላይ መድረስ የሚገባቸው ይመስለኛል፡፡ እኛን ማመን ስላልፈለጉ እስካሁን አላመኑንም፡፡ የወያኔን ጉድ ቢያውቁትም እንደዚህ ቁልጭ ብሎ የወጣበት ዘመን ባለመኖሩ ይህን ሃቅ ማመን ባይፈልጉና በቆዬ ወያኔን የመደገፍ አቋማቸው የሚጸኑ ከሆነ ከሌላ ከማንም ጋር ሣይሆን ከገዛ ኅሊናቸው ጋር የሚጣሉበት ጊዜ እየደረሰ መሆኑን እየመረራቸውም ቢሆን መገንዘብ አለባቸው፡፡ ወያኔ የአንድን ሉዓላዊ ሀገር ፕሬዝደንት “አስርሃለሁ!” ካለና ካለውድ በግዱ ካስፈረመ ከዚህ በላይ ዓለም አቀፍ ውንብድናና ማፊያነት የለም፤ ወያኔ በዓለም አቀፍ ደረጃ ፕሬዝደንታዊ ስብዕናንና ሀገራዊ ክብርን የሚነካ እንዲህ ያለ ጠያፍ የማንአለብኝነት ተግባር ከፈጸመ የገዛ ምድሩን ዜጎች ምን ሊያደርግ እንደሚችል ማንም ወገን በዚህ ኹነት አማካነት ሊረዳ ይገባዋልና ይህ የሰሞኑ ወያኔያዊ ቅሌት ውርደታዊ ክስተት ለሀገራችን በጎ ገጽታ አለው (ፈረንጆቹ blessing in disguise እንደሚሉት ማለቴ ነው)፡፡ ይህ ነገር እንደሚመስለኝ ወያኔን ብቻ ሣይሆን ምዕራባውያንንም ከነሤራዊ ተንኮላቸው ለማጋለጥ ፈጣሪ ያመቻቸው ነገር መሆን አለበት፡፡ ከፍ ሲል እንደጠቆምኩት ዓለም እስኪታዘበን ድረስ የወያኔን አምባገነንነትና ገዳይነት ስናጋልጥ ብንቆይም ያመነን አልነበረም፡፡ የማቻርንና የሳልቫኪርን ምስክርነት ግን ሊጠራጠር የሚገባ ሰው አይኖርም ብዬ እገምታለሁ ፤ ምንም እንኳን እነሱ ራሳቸውም የአፍሪካዊ አምባገነንነት ወረርሽኝ ሰለባ ቢሆኑም፡፡
    አሁን ፈረሱም ሜዳውም ያለው በወያኔ ደጋፊዎች ደጅ ነው፡፡ እስካሁን ያርመጠምጡት የነበረውን የኢትዮጵያ ፖለቲካ ማቃናት የሚያስችላቸው ወርቃማ ዕድል አሁን እፊታቸው አለ፡፡ አንዳንድ ልፍስፍስ ፖለቲከኞቻችንንና ወያኔ ተከል ተቃዋሚ ተብዬዎችን እንዲሁም በወያኔ ቅኝት የሚዘምሩ የነገ ራስ ምታቶችን ትተው ሁነኛ ዴሞክራሲ በሀገራችን የሚመጣበትን መንገድ ሊደግፉ የሚችሉበት ዕድል አሁንም አለ፡፡ አለበለዚያ በኃይል የሚመጣ ሥልጣን ለነሱም ሆነ ለሀገራት እንደማይበጅ የታወቀ ነውና እነዚህ ምዕራባውያን የእጃቸውን የሚያገኙበት ጊዜ ሩቅ አይሆንም፡፡ ብዙዎቹ በዓለም የሚታዩ አመፆችና የሽብር ተግባራት ሥረ መሠረታቸው ሲጠና መነሻቸው እነሱው ራሳቸው ምዕራባውያኑ ናቸው፡፡ ለዐይን ይበጃል ብለው የሚኳሉት ኩል ዐይንን እንደሚያጠፋ ሁሉ ለአንዳንድ ሤራዎቻቸው ስኬታማነት ብለው – ለምሳሌ እንደ አዲሱ የዓለም ሥርዓት (NWO) – የሚተልሟቸው ዕቅዶች በጊዜ ሂደት ወደነሱው እየዞሩ በመተኮሳቸው ባላስፈላጊ ጥቃቶች ዜጎቻቸውንና ንብረታቸውን አስፈጅተዋል፤ እያስፈጁም ነው – 9/11ን፣ 5/7ንና የናይሮቢን የሽብር ጥቃት ማስታወስ በቂ ነው፡፡ ቢን ላደንን ማነው እዚያ ላይ አድርሶት የነበረው? አዎ፣ ሁሉም የሥራውን ነው የሚያገኘው፡፡ የተከልካት ተክል ትጸድቃለች፤ ጠቃሚ ከሆነች ትጠቀምባታለህ፤ ጎጂ ከሆነች ግን ትጎዳባታለህ፤ ሰውን አለኃጢኣቱ ልታጠቃ ብለህ የወረወርካት ጦር ዞራ ተመልሳ ወዳንተው እንደምትመጣ ካላወቅህ ተሳስተሃል፤ ጊዜ ይፍጅ እንጂ በቆፈርከው ጉድጓድ የመግባት ዕድልህ እጅግ ሰፊና የማይቀርም የመጨረሻ ዕጣ ፋንታህ መሆኑን ማወቅ አለብህ፡፡ የበግ ግልገል መስላህ መንገድ ላይ ያገኘሃትን የጅብ ግልገል ቤትህ ውስጥ ብታሳድጋት ተፈጥሯዊ ባህርይዋን አትለቅምና የኋላ ኋላ የምትጎዳው አንተው ነህ፡፡ እናም ወያኔም ሆነ የስምሪት ኃላፊዎቹ ሁሉ የዘሩትን ያጭዳሉ፤ የጊዜና የቋት መሙላት/አለመሙላት ካልሆነ በስተቀር ወያኔ በኢትዮጵያ ምድርና ሰማይ እንደፏለለ የሚኖርበት ዘመን ያከትማል፤ ጦስ ጥምቡሱ ግን ለብዙዎች ይተርፋል፡፡ አርቆ ማሰብ የሚያስፈልገው ለዚህ ነው፡፡ ዛሬ ለምሳሌ አማራውና ኦሮሞው እንዲሁም ሌላው በገርጂም ሆነ በሰሚትና በቦሌ ከመሬቱና ከንብረቱ እየተነቀለ ለባለጊዜው የጎሣ አባላት እንደልብ ቢታደል ይህ ዘመን ሲገለበጥ ተከፍሎ የማያልቅ ዕዳ ይመጣል፡፡ ይህን የምለው ውሻ ሆድ ውስጥ ቅቤ አያድርምና ሰሞኑን ወደሰሚት ሄጄ ሰዎች ያሳዩኝ ትልቅ መንደር ውስጥ ካለሀብቶምና ካለአብረኸት በስተቀር አንድም – ለውርርድ ያህል እንኳን – አንድም ዘበርጋና ደቻሳ ወይም ሸዋርካብሽና አሰጋኸኝ የሚባሉ ዜጎች የማይኖሩበት ምድረ ገነት በአዲስ አበባ መኖሩን ስለተረዳሁ ነው፤ አዲስ አበባና መቀሌን መለየት የማንችልበት አስገራሚ የታሪክ አንጓ ላይ መድረሳችንን የምገልጥላችሁ ነገ ሊከሰት የሚችለውን አደጋ ከወዲሁ በማጤን በታላቅ ፍርሀት ተውጬ ጭምር ነው – ወያኔና ይሉኝታ የማይተዋወቁ መሆናቸውን ቀድሜ ባውቅም ተጋሩ(ትግራውያን) ወገኖቼ ይህን ያህል ኅሊናቸውን ስተው የወያኔን የአድልዖ አሠራር በጭፍን ይከተላሉ ብዬ አምኜ አላውቅም – አዝናለሁ – ሀዘነይ ካብ ልበይ ኢዩ፡፡ ይህ ሁሉ ግፍ ጊዜው ሲደርስ የሚያስከትለውን ጠንቅ የማይረዳ ሰው ካለ የመጨረሻው ከንቱ ነው፡፡ “ፍቅር ያዘኝ ብለህ አትበል ደንበር ገተር፤ እኛም አንድ ሰሞን እንዲህ አርጎን ነበር” አለች አሉ ያቺ ምስኪን አቀንቃኝ፡፡ የተራ ጉዳይ ነው፡፡ ተራ ሲባል ደግሞ እንደወያኔ ያለ ዐይን ያወጣ አድልዖና ፍርደ ገምድልነት በእስካሁኑ ታሪካችን በግልጽ ታይቷል ለማለት እንዳልሆነ ይሰመርበት፡፡ በአፄው ዘመን በፊውዳላዊ መድሎ፣ በደርጉም በወታደራዊ መድሎ የተወሰነ ብልሹ አሠራር እንደነበር መናገር በደልን ያጥባል እንጂ ክፋት የለውም፡፡ የአሁኑ ግን በሀገራችን ቀርቶ በየትም ሀገር ያልተመዘገበ የአንድ ጎሣ ሁሉንም ነገር የማግበስበስ ሁኔታ በግልጽና ክፉኛ በሚያሳፍር አኳኋን እየታዬ ነው፡፡ በነዚህ ልጆቿ የነገይቷ ትግራይ እንዴት እንደምትሸማቀቅ ሳስበው የትግራይ መሬት ራሷ ታሳዝነኛለች፡፡ በርግጥም ላም እሳት ወለደች፡፡ አሁንም አዝናለሁ፡፡ እግዚአብሔርና አስተዋይ የአብራኳ ክፋይ የሆኑ ልጆቿ ይሁኗት ከማለት ውጪ ምን እላለሁ፡፡ እየታዬ ካው አሰቃቂ መድሎ አኳያ ለጊዜው ከዚህ የዘለለ ነገር መናገር አይቻለኝም – ችግር አለ!!!!!!!!….
    ሕዝብን የሚመለከት፣ የሕዝብን ዕንባ የሚጠርግ፣ የሕዝብን ብሶት የሚያዳምጥ፣ ሕዝብን ማዕከል ያደረገ ዓለማቀፋዊ ዘመቻ ያስፈልገናል፡፡ የየሀገሩ ሕዝብ በአንድ ወይ በሌላ ምክንያት እያለቀሰ ነው፡፡ ጥቂቶች በሚፈጥሩት ችግር ቢሊዮኖች እየተሰቃዩ ነው፡፡ ይህ የጥቂቶች የበላይነትና ችግር ፈጣሪነት እስካልተወገደ ድረስ መዘዙ ለሁሉም ነው፡፡ ያስለቀሰ እያለቀሰ፣ ያለቀሰም እያስለቀሰ የሚሄድበት መጥፎ አዙሪት እስካልተወገደ ድረስ ዘላቂ መፍትሔ የለም፡፡ … የሰው ልጅ አእምሯዊ ይዘቱ የተዛባ ይመስለኛል፡፡ ራስህን በማለፊያ ምግብ አጥግበህ ሌላውን ስታስርብና ስታሰቃይ የምትደሰት ከሆነ ከእንስሳነትም ወርደሃል ማለት ነውና ሰብኣዊ ዕድገትህ ላይ ችግር መከሰቱን ልብ ማለት ሊኖርብህ ነው፡፡ አሳዛኝ ወቅት ላይ እንገኛለን፡፡
    ወያኔን ግን በደምብ ዐወቅናት አይደል? እስኪ እዚች ላይም ትንሽ እንሳቅና እንዝናና – “ካልፈረማቸሁ እናስራችኋለን!!!” ጥጃ ገዝተው ወይም ወደማርካቶ ወጣ በማለት አንድ አምስትና ስድስት ሺህ ኢትዮጵያውያን የሰው እንስሳትን እንደለመዱት አያስሩም? ቅብጠታቸው ግን ለከትና ድንበር አጣ፡፡ ለነገሩ በጌታዋ የተማነች በግ ላቷን ቀለበት መንገድ ላይና አባይ ላይ ታስራለች ይባል የለም? ዘይገርም ሻሸመኔ ትብስ ኮፈኔ፡፡ ጉድ ነው፡፡
    የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር በሰሞኑ ግርግር በአምቦና በሌሎች የሀገራችን አካባቢዎች ሕይወታቸውን ያጡ ወገኖቻችንን ነፍሳት በአብርሃምና በያዕቆብ ነፍሳት አጠገብ ያኑርልን፣ በጠባቡ ቃሊቲ የታሰሩትንም፣ በሰፊው “ዞን 9” የታሰርነውን እኛንም ፈጣሪ በቸርነቱ ይጎብኘን፡፡ አስቡ – ቀኒቷ ቀርባለች፡፡ ምልክቶች ሁሉ ታይተዋልና “ፕሊዝ” ወደየኅሊናችን በመመለስ ውስጣችንን እናጽዳ፡፡ ተመልሰን ሰው እንሁን፡፡ ሰው መሆን እንችላለን፤ መብትም አለን፤ ሰው ለመሆን ደግሞ በሕይወት እስካለን ድረስ ሁላችንም ልንሞክረው የሚገባን ታላቅ አምላካዊ ፀጋ እንጂ ቀነ ገደብ የተጣለበት ለማንም የተከለከለ ጉዳይ አይደለም፤ እናም ተስፋ ሳንቆርጥ ሰው ለመሆን እንሞክር፡፡ ያኔ ነው ከነዚህ ጉግማንጉጎች ነጻ የምንወጣው፡፡ አለበለዚያ በባርነት እየዳከርን ብዙ ጊዜ እንቆያለን – የባርነቱ ዘመን ይረዝምብናል፡፡ እናም ሰው በመሆን ፈጣሪን እናግዘው – የነጻነታችንን ጊዜም እናቅርብ፡፡

    መሠረታዊ የአገልግሎት ማሻሻያ ፕሮግራም የክልልና የፌደራል መንግሥታትን አከራከረ

    May14/2014

    -ለጋሾች በበጀት አጠቃቀም ላይ ጥያቄ እያነሱ ነው
    የመሠረታዊ አግልግሎቶች ማሻሻያ ፕሮግራም በኢትዮጵያ መተግበር የጀመረው ከ1997 ዓ.ም. ምርጫ ማግሥት ለጋሽ አገሮች መንግሥት ላይ ባሳደሩት ጫና ነበር፡፡
    በተለይ የአውሮፓ ኅብረት ከምርጫው ማግሥት በኋላ በተፈጠረው አለመረጋጋት ሳቢያ መንግሥትን በመኮነን ለአንድ ዓመት ያህል ዕርዳታ ከመስጠት ታቅቦ ቆይቶ ነበር፡፡

    ሆኖም ለጋሽ አገሮች በቀጥታ ድሀ ተኮር የሆኑ ፕሮግራሞች በአግባቡ ስለመተግበራቸው እርግጠኛ ለመሆን፣ በጋራ ከማቀድ ጀምሮ አፈጻጸማቸውና ያስገኙትን ውጤት በጋራ መገምገም የሚያስችላቸውን መድረክ ከመንግሥት ጋር በመፍጠር ባለፉት ሦስት ዓመታት፣ በያመቱ የአሥር ቢሊዮን ብር ዕርዳታ ሲሰጡ ቆይተዋል፡፡

    ለሦስተኛ ጊዜ የተተገበረውንና በ2005 ዓ.ም. የተጠናቀቀውን የመሠረታዊ አገልግሎቶች ማሻሻያ ፕሮግራም የግማሽ ዓመት የበጀትና ዕርዳታ አፈጻጸም ግምገማ ከለጋሽ አገሮች ጋር በግዮን ሆቴል ማካሄድ የተጀመረው ሰኞ ግንቦት 4 ቀን 2006 ዓ.ም. ሲሆን፣ በመጪው ግንቦት 8 እንደሚጠናቀቅ ይጠበቃል፡፡

    በግምገማው መክፈቻ ወቅት የገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስቴር ይፋ እንዳደረገው የመሠረታዊ አገልግሎቶች ማሻሻያ ፕሮግራም በጤና፣ በትህምርት፣ በግብርና፣ በውኃና በመንገድ ንዑስ ዘርፎች ላይ ለጋሾች ለአፈጻጸማቸው የገንዘብ ድጎማ ያደርጋሉ፡፡ የሠራተኞችን ደመወዝ፣ የሥራ ማስኬጃ በጀትና ሌሎች ወቅታዊ በጀት የሚያካትታቸውን የፕሮግራሙን ወጪዎችን ይደጉማሉ፡፡ በተለይም በሰው ኃይልና በአስተዳዳራዊ ዘርፎች፣ በፋይናንስና በጀት ግልጽነትና ተጠያቂነት ላይ ያተኩራሉ፡፡ በመሠረታዊ አግልግሎቶች ማሻሻያ ፕሮግራም ላይ  እስካሁን የታዩ ለውጦች ጥሩ የሚባሉ ቢሆኑም፣ በታዳጊ ክልሎች የተመዘገቡት ለውጦች ከታቀደው በታች ነው በማለት መረጃዎችን አቅርቧል፡፡

    ከዕድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅዱ ተውጣጥቶ የቀረበው የ2005 በጀት ዓመት የመሠረታዊ አገልግሎቶች ማሻሻያ ፕሮግራም ውጤቶች ሪፖርት ላይ ጥቂት የማይባሉ መስኮች ላይ ከታቀደው በታች ውጤት መመዝገቡን ቢገልጽም፣ ክልሎች ሳይቀበሉት ቀርተዋል፡፡

    በትምህርት መስክ በአንደኛ ደረጃ የትምህርት ሽፋን ላይ የተመዘገቡትን ውጤቶች በማስመልከት ገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስቴር እንዳቀረበው፣ ባለፈው በጀት ዓመት ከአንደኛ እስከ ስምንተኛ ክፍል የተመዘገው የተጣራ የተማሪዎች ቁጥር 86 ከመቶ አቅራቢያ ነው፡፡ በዕቅድ ይመዘገባል የተባለው መጠን ግን 94 ከመቶ ገደማ ነው፡፡ ይህም ማለት በመላ አገሪቱ ከአንድ እስከ ስምንት የሚሰጠው የትምህርት አገልግሎት ሽፋን 94 ከመቶ ይደርሳል የሚል ነበር፡፡ ከአምስተኛ እስከ ስምንተኛ ክፍል ባለው የትምህርት ዕርከንም ይጠበቅ የነበረው የተማሪ ቁጥር 69 ከመቶ አቅራቢያ ሲሆን፣ በተጨባጭ የተመዘገበው ግን 47 ከመቶ በመሆኑ ከዕቅዱ በብዙ ርቆ ታይቷል፡፡ የስምንተኛ ክፍልን የሚያጠናቅቁ ተማሪዎች ቁጥር በአገር አቀፍ ደረጃ 53 ከመቶ አቅራቢያ ሲሆን፣ ይጠበቅ የነበረው ግን 78 ከመቶ ይደርሳል ተብሎ ነበር፡፡

    ከ86 ከመቶው አገራዊ አማካይ ውጤት በታች ውጤት አስመዝግበዋል የተባሉት ክልሎች፣ አፋር ክልል 42 ከመቶ በማስመዝገብ ዋናው ሲሆን፣ አዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር 69 ከመቶ፣ ሐረሪ ክልል 75 ከመቶ በማስዝገብ ወደኋላ መቅረታቸው ተመልክቷል፡፡ ከዚህ ባሻገር በመምህራን ሥልጠናና ብቃት ላይም አማራ፣ አፋር፣ ሶማሌና ደቡብ ሕዝቦች በዝቅተኛ ደረጃ ውጤት ያሳዩ ተብለው ተተችተዋል፡፡

    የቀረቡትን አኃዞች የአዲስ አበባ አስተዳደርም ሆነ የአፋርና የሶማሌ ክልሎች አጣጥለዋል፡፡ የአፋር ክልል ያጣጣለው የራሱን መረጃ በማጣቀስ ሲሆን፣ በክልሉ የሠለጠኑ የአንደኛ ደረጃ መምህራን ቁጥር 95 ከመቶ ደርሶ እያለ ገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስቴር 53 ከመቶ አቅራቢያ ነው ማለቱ ከምን በመነሳት እንደሆነ እንዲገለጽለት ጠይቋል፡፡ የአዲስ አበባ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ በበኩሉ በተማሪዎች ቁጥር ላይ ያለበትን ችግር ይፋ አድርጓል፡፡ ለአንደኛ ደረጃ ትምህርት ዕድሜያቸው የደረሱ ሕፃናት ትምህርት የሚጀምሩት በሰባተኛ ዓመታቸው ነው፡፡ ቢሮው አንደኛ ደረጃ ትምህርታቸውን የሚያጠናቅቁበት ዕድሜም 14 ዓመት መሆኑን ገልጾ፣ በአዲስ አበባ ከሚገኙ አንደኛ ደረጃ ተማሪዎች ውስጥ 40 ከመቶው በግል ትምህርት ቤቶች የሚማሩና ከተቀመጠው የትምህርት ዕድሜ በታች የአንደኛ ደረጃ ትምርትን የሚጀምሩና የሚያጠናቅቁ በመሆናቸው፣ ስታቲስቲካዊ መረጃ አያያዝ ላይ መቸገሩን አመልክቷል፡፡

    በግል ትምህርት ቤቶች ውስጥ የሚማሩት ሕፃናት አንደኛ ደረጃ ትምህርት የሚጀምሩት በስድስት ዓመታቸው ሲሆን፣ የሚያጠናቅቁትም በ13ኛ ዓመታቸው ነው፡፡ ይህንን የገለጸው የአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ፣ ከዚህ ባሻገርም ከመደበኛው የትምህርት ዕድሜ በላይ የሆኑ ታዳጊዎች በማታው ክፍለ ጊዜ ትምህርታቸውን የሚከታተሉ በመሆኑ እነሱም የሚያካትት አኃዝ እንዳልቀረበ ይፋ አድርጓል፡፡

    የትምትርት ሚኒስቴር ዴኤታ አቶ ፉአድ ኢብራሒም በበኩላቸው በአሁኑ ወቅት 22 ሚሊዮን ተማሪዎች በአገሪቱ እንደሚገኙ ገልጸው፣ ሁለት ሚሊዮን አዲስ ተማሪዎች ወደ ትምህርት ገበታው መምጣት እንደቻሉ ተናግረዋል፡፡ ትምህርት ማቋረጥና መቅረት አሳሳቢ መሆኑን ያመኑት አቶ ፉአድ፣ ይህም ሆኖ በመረጃ አሰባሰብ ላይ ከማዕከላዊ ስታቲስቲክስ ኤጀንሲ ጋር ልዩነት እየታየ በመሆኑ የአኃዝ ተቃርኖ መፈጠሩን ገልጸዋል፡፡ ኤጀንሲው የሚሰበስበው መረጃ በቤሰተብ ደረጃ ሲሆን ትምህርት ሚኒስቴር ግን ከየትምርት ቤቶቹ መረጃ የሚሰበስብ በመሆኑ በመረጃ ምንጭ ላይ ያለው ልዩነት ችግር እየፈጠረ መሆኑን አስታውቀዋል፡፡ በአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ ከቀረበው የዕድሜ ጉዳይ በተጨማሪ 44 ትምህርት ቤቶች ለግምገማው አለመካተታቸውን አቶ ፉኣድ ተናግረዋል፡፡

    በግብርና በኩል የታየው ችግር በኤክስቴንሽን ሠራተኞች ቁጥር ላይና በምርታማነት ላይ ያተኮረ ነው፡፡ ባለፈው ዓመት በሔክታር ይጠበቅ የነበረው ምርት ከ19 ኩንታል በላይ ቢሆንም፣ ውጤቱ ግን በሔክታር 18 ኩንታል አልሞላም፡፡ በዋና ዋና ሰብሎች ላይ የታየው አዝጋሚ ምርታማነት በዕድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅዱ መሠረት ወደ ኋላ ሊቀር ችሏል ተብሏል፡፡ በዚህ አኃዝ ላይ ደስተኛ ያልሆኑት የግብርና ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታው አቶ ወንድይራድ ማንደፍሮ ያለፈው ዓመት መረጃ የዚህን ዓመት አፈጻጸም ሊገልጽ የማይችል ከመሆኑም በላይ፣ ባለፈው ላይ ከመነጋገር አሁን ባለው ላይ መወያየት እንደሚመርጡ ተናግረዋል፡፡ በዚያም ላይ ባለፈው ዓመት የተዘራው በዚህ ዓመት ውጤት የሚሰጥ በመሆኑ ምክንያት፣ ያለፈው ዓመት ዝቅተኛ ነው ብሎ መደምደም አስቸጋሪ መሆኑን ተናግረዋል፡፡ በጤና በኩልም በጤና ኤክስቴንሽን ሠራተኞች ቁጥር ከጊዜ ወደ ጊዜ እያሽቆለቆለ መምጣት ላይ ሪፖርት ቀርቦ ጤና ጥበቃ ማብራሪያ ሰጥቷል፡፡ በድኅረ ወሊድ እንቅብካቤና በፀረ አምስት ሦስተኛ ዙር ክትባት አግልግሎት ላይም የታዩ ለውጦች ለቤቱ ቀርበዋል፡፡  ጤና ጥበቃ የመረጃ ጥራትና ብዛት፣ የአስተዳደር ችግር፣ ከታሰበው ዓላማ ማፈንገጥ የመሳሰሉት ችግሮች በክልሎች እያጋጠመው መሆኑን አስታውቋል፡፡

    በመንገድ ዘርፍ ላይ የታውን በተመለከተ እንደቀረበውም ከዚህ በፊት በሁሉም ዓይነት የአየር ጠባይ የሚያገለግሉ መንገዶች ሽፋን እተሸሻለ መምጣቱ ታይቷል፡፡ ከአራት ዓመት በፊት ከነበረው ወደ እነዚህ መንገዶች ለመድረስ 3.7 ኪሎ ሜትር መንገድ መጓዝ ይጠይቅ የነበረ ሲሆን፣ ባለፈው ዓመት ወደ 2.1 ኪሎ ሜትር ዝቅ ማለቱ ተጠቁሟል፡፡ በጥሩ ደረጃ ላይ የሚገኙ መንገዶች ሽፋን 90 ከመቶ የደረሰ ሲሆን፣ በዕቅድ የሚጠበቀው ግን 85 ከመቶ ገደማ ነበር፡፡

    ከገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስቴር ባሻገር የእንግሊዝ ዓለም አቀፍ የልማት ትብብር ተቋም (ደፊድ)ም በበጀት፣ በፋይናንስ ግልጽነትና ተጠያቂነት እንዲሁም በሌሎች መስኮች ላይ ታይተዋል ያላቸውን ጉድለቶችና ጥሩ ውጤቶችን አስገኝተዋል ያላቸውን አፈጻጸሞች ገምግሟል፡፡

    በኢትዮጵያ የዓለም ባንክ ዳይሬክተርና የለጋሽ አገሮች ተወካይ ጉዋንግ ዚ ቼን እንደተናገሩት፣ ምንም እንኳ ላለፉት ሦስት ዙሮች ሲተገበር የቆየው ፕሮግራም ለውጦችን ቢያስመዘግብም ችግሮች ግን አልተለዩትም፡፡ በመሠረታዊ አገልግሎት ማሻሻያ ፕሮግራሙ ላይ ከሚቀርቡ ዕቅዶች ውስጥ በበጀት አጠቃቀም ላይ የታዩ ችግሮች መኖራቸውን ጠቁመዋል፡፡ በመንገድ ዘርፉ ላይ የሚመደብ ፈንድ በአግባቡ ጥቅም ላይ አለመዋሉ፣ የሀብት አመዳደብ ችግር፣ የበጀት አደላደል፣ የመረጃ ምንጭ ላይ ችግሮች መኖራቸውን ጠቁመዋል፡፡ ጥራት ያለው መረጃ በወረዳና በቀበሌ ደረጃ ባሉ መዋቅሮች ላይ ማግኘት አስቸጋሪ መሆኑን የጠቆሙት ቼን፣ የአገልግሎት አሰጣጡ በሠራተኛው ላይ የሚንጠለጠል በመሆኑም የሰው ኃይል ላይ ትኩረት ሊደረግ ይገባል ብለዋል፡፡

    በትምህርት፣ በጤና፣ በግብርናና በውኃ አቅርቦቶች ላይ የፌደራል መንግሥት ድጋፍ በሚሰጣቸው ታዳጊ ክልሎች ላይ ጎልቶ ታይቷል፡፡ ይህንን በተመለከተ ሪፖርተር ያነጋራቸው የዓለም ባንክ ዳይሬክተር፣ ክልሎቹ ራሳቸው ከዝቅተኛ ደረጃ ላይ እየተነሱ ያሉ በመሆኑ ነው ብለዋል፡፡

    የገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስትር ዴኤታ ዶክተር አብርሃም ተከስተ ምንም እንኳ የመሠረታዊ አገልግሎቶች አቅርቦት እየተሻሻለም ቢሆንም፣ ዕርዳታ ሰጪ አገሮች ቃል ከገቡት ውስጥ የተወሰነ መጠን እስካሁን እንዳልቀቁና በቀሩት ወራት ውስጥ በጀቱን እንዲለቁ አሳስበው ነበር፡፡ ስለዚህ ጉዳይ ሪፖርተር ጥያቄ ያቀረበላቸው ቼን በበኩላቸው አልተቀቀም የተባለው በጀት በዝቅተኛ አፈጻጸም ጋር የተያያዘ መሆኑን ይፋ አድርገዋል፡፡ በተለይ የተመደበው ገንዘብ እንዴትና በምን አኳኋን ሥራ ላይ እንደዋለ በአግባቡ መረጃ ስለማይገኝ፣ የሚሰጠው ዕርዳታ ሊዘገይ መቻሉን ቼን ተናግረዋል፡፡

    በገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስቴር የቻናል አንድ ፕሮግሞች አስተባባሪ አቶ ጌታቸው ነገራ ግን በታቀደው መሠረት ገንዘብ መለቀቁን ይናገራሉ፡፡ ለ2005/2006 በጀት ዓመት ፈሰስ ይደረጋል የተባለው በሙሉ ተለቅቋል ያሉት አቶ ጌታቸው፣ ከግንቦት ወር በኋላ መለቀቅ አለበት ተብሎ በሚጠበቀው የበጀት መጠን ላይ ያተኮረ ግምገማ እየተካሄደ መሆኑን ገልጸዋል፡፡ 

    Tuesday, May 13, 2014

    ለመላው የኢትዮጵያ ህዝብና በተለይ ለሀገር ተረካቢ ወጣትና ምሁራን ብሎም በውጪ ለሚገኙ ዜጎች!! ከባለራዕይ ወጣቶች ማህበር የተሰጠ መግለጫ

    May 13/2014

    ስፊው የኢትዮጵያ ሕዝብ በሀገራቸው ሉአላዊነት እና በህዝቦች መፈቃቀድ መፈቃቀርና መኖር ዙሪያ ማንም ሰንካላ ምክንያት በማቅረብ እንዲበታትነው መፍቀድ የለበትም በተለይ ይመራናል ያስተዳድረናል በምንለው መንግስት ከህዝቦች ፍቃድና እውቅና ውጪ በማስተዳደርና በመግዛት ዙሪያ ያለው የተራራቀ ልዩነትና የመንግስታችን አተያየም የመግዛት በመሆኑ የግዛት ጊዜውን በማራዘም የጭቆና ቀንበሩን ለማፅናት ሲል ለ3 ሺ ዘመናት የነበራትን ታሪክ በማበላሸትና በዚያ አኩሪ ታሪኳም ለዜጎች ብቻ ሳይሆን ለአፍሪካ የነፃነት ተምሳሌትና ኩራት የሆነች ባላት ታሪክና ትሩፋት በተለይ በህዝቧ ያኗኗር ዘይቤ በኢትዮጵያ እድገት ውስጥ ያበበና ጎልቶ የወጣ ልዕልናዋም ከአጉረ አፍሪካ ተሻግሮ ለአለም መደነቂያ የሆነች ሀገራችን ላይ ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ አጥልቶ ያለው የተቃርኖ እዳ የእርስ በርስ ግጭት እንዲፈጠር እየተጠነሰሰ ያለና በተግባራዊነቱም ጎልቶ የታየበት ጊዜ አይታወስንም በመሆኑም ዜጎች በመንግስት ትንኮሳና ሸር እየተፈፀሙ ያሉት ዜጎችን ከቦታቸው የማፈናቀል ለጠየቁት ጥያቄ አወንታዊ እርምጃ መውሰድ በጋዜጠኞችና በጦማሪያን ላይ የእስር እንዲሁም በቶፎካካሪ ፓርቲ አባላትና መሪዎች ላይ የሚደርሰው እንግልትና ወከባ የዚህች ሀገር ጎዞ ወዴት እያመራ ነው የሚለው እጅግ አሳሳቢ ነው ከዚህም በተረፈ በሚፈጠረው ግርግር ሰፊው የሀገራችን ህዝብ ተጎጂ የሚሆን በመሆኑና በተለይም በግንባር ቀደምነት የሀገራችን አምራችና አንቀሳቃሽ ብሎም ሀገር ተረካቢና አንቀሳቃሽ በምንለው ወጣት እጅጉን እየከፋ በመሄዱና ለጥቃትም ተጋላጭ በመሆኑ ይህን መግለጫ ለማውጣት ተገደናል፡፡
    1. የሀገራችንን ህዝቦች ለመከፋፈልና ወደ ማያቋርጥ እልቂት ለመምራት በፈጠራ ታሪክ ላይ ተመስርቶ እየተሰራበት ያለው ሴራ ባስቸኳይ እንዲቆም እና የእልቂት መነሻ የሚሆን በተለይም አኖሌ የተገነባው ሀውልት ባስቸኳይ እንዲፈርስ በምትኩም ህዝቦች በጋራ ተቻችለው የሚኖሩበትና የጋራ አሴት ሊፈጥር የሚችል የመደጋገፍና የመረዳዳት ህልውናውን የሚያጠናክር መዘከር እንዲሰራ እንጠይቃለን፡፡
    2. መንግስት በህዝቡ ዘንድ መግባባትና መፋቀር እንዲሰራና ሀገራችን ለዜጎችም ብሎም ለወጣቶች ምቹ ማድረግ ሲጠበቅበት ዜጎችን ኢ.ህገ መንግስታዊ እና ኢ-ፍታዊ በሆነ መልኩ በሀገራቸው በየትኛውም ክፍለ ሀገር የመኖርና ሀብት የማፍራት መብታቸውን በመጣል ከቄያቸው እና ተከባብረው እና ተፋቅረው ከኖሩት ህዝብ በሀይል የማፈናቀል እርምጃ ባስቸኳይ እንዲቆም ይህን ያደረጉም የመንግስት ባለስልጣናት ለህግ እንዲቀርቡ እንጠይቃለን፡፡
    3. መንግስት በሀገሪቱ ህገ-መንግስት አንቀጽ 29 ላይ የአመለካከትና ሐሳብን በነፃ የመያዝና የመግለፅ መብትን በመጣስ በጋዜጠኞች በጦማሪያንና በፅሑፎች ላይ በቅርቡ የጅምላ እስር አከናውኗል በመሆኑም በሀገሪቱ የህጎች ሁሉ የበላይ የሆነው ህገ-መንግስት ለዜጎች ህልውና በሚል ያዘጋጀው መንግስት እራሱ ጥሰት በመፈፀም የወሰደው ኢ-ፍታዊ እርምጃ ዜጎች የመናገር ሀሳባቸውን በነፃነት በመግለፅና የመፃፍ መብትን በመተላለፍ የተወሰደ እርምጃ በመሆኑ ባስቸኳይ እንዲፈቱ እየጠየቅን ዜጎች የሚያከብሩትን ህገ-መንግስት ያዘጋጀው አካል መንግስትም ህገ-መንግስቱን እንዲያብብ አለበለዚያ ግን ሰፊው የኢትዮጵያ ህዝብ መብቶችን ለማስከበር በሚያደርገው ትግል ከሚከተለው አላስፈላጊ እልቂትና ጉዳት በፊት ከወዲሁ እልባት እዲበጅለት እናሳስባለን፡፡
    4. መንግስት የአዲስ አበባን ከተማ ማስተር ኘላን ተከትሎ ቤተሰቦቻችን ያፈና ቀላል እርስት አልባ እና ቀጣሪ እንዲሁም ስራ ፈት በማድረግ ለድህነት ይዳርጋል በሚል ዩንቨርስሪቲዎች ለተጠየቀው ስላማዊ ጥያቄ በሰላማዊ መንገድ በጠረጴዛ ዙሪያ መፍታት ሲቻል ዜጎች ላይ ሊያውም የሀገሪቱ ኢፍታዊ እርምጃ አግባብነት የሌለውና ይህን ያደረጉ አካላትም ሆነ ትዛዝ ያስተላለፈ አካል፡፡
    የተማረ ብሎም ወጣትና ትኩስ እንዲሁም ሀገር ተረካቢ በሆነው ትውልድ ላይ የተወሰደው ኢፍታዊ እርምጃ አግባብ አይደለም ስንል እያወገዝን ይህ ድርጊት በንፁዋን ዜጎች ላይ እርምጃው እንዲወሰድ ያዘዙና እርምጃውን የወሰደ ባለስልጣናትም ሆነ ፌደራል ፓሊስ አባላት ለህግ እንዲቀርቡ እንጠይቃለን፡፡
    5. በተለይ ከዚህ ጥያቄ ጋር ተያይዞ ችግሩን የብሔር ችግር ለማስመሰልና ወደ አላስፈላጊ ቀውስ ለመምራትና የእርስ በርስ ግጭት እንዲሆን ለማድረግና የመብትና የህይወት ጥያቄን በሌላ መልኩ ጥላሸት በመቀባት ለማጥቆር መምከር እጅግ አሳስቦናል በአሰቃቂ ጭፍጨፋ በአለም ሆነ በውጭ የሚገኘው አንዳንድ ፅንፈኛና ጎጠኛ ሰዎች እየተካሄደ ያለው ደባ ባስቸኳይ እንዲቆም እየጠየቅን ለሀገራችን እድገትና ብልፅግና ከጥላቻ ፓለቲካ እና ዘር መሠረት ካደረገ አድሎ በመቆጠብ ፍታዊ አሰራር እንዲሰፍን ዜጎችም ለ3ሺ ዘመን ተፋቃቅረውና ተቻችለው በመኖር ለተቀረው አለም ምሳሌ መሆን እንደተጠበቀ ሆና ቢስራ የተሻለ ነው እንላለን፡፡
    6. የዜጎች ሰብአዊና ህገ-መንግስታዊ መብታቸው ተጠብቆ በመፈቃቀደና በመፈቃቀር ላይ የተመሠረተችዋን ኢትዮጵያችንን ደግሞ ለማየት የተፍካከረ ፓርቲዎች በሰላማዊ መንገድ የሚያደርጉት ትግል ክልከላና እንቅፋት መደርደር ኋላ ለሚመጣው ችግር ተጠያቂ የሚሆን መንግስት በመሆን በዋነኝነትም ተጎጂው እና የችግሩ ግንባር ቀደም ገፈት ቀማሽ ወጣቱ ትውልድ ነውና ይህ ችግር ከመከሰቱ በፊት የፖለቲካ ምህዳሩ ሰፈር ክፍት እንዲያደርግ መንግስትን እየጠየቅን አማራጭ ያለውና እኔ እበልጥ እኔ ብሎ በሚፎካከሩ የፓለቲካ ፓርቲ መካከል ምርጫው ለህዝብ ትቶ በጠላትነት መታየትና መወነጃጀል ለሀገራችንም ሆነ ለህዝባችን ስለማይበጅ ከወዲሁ የመግባባት መድረክ እንዲኖር እንጠይቃለን፡፡
    ኢትዮጵያዊ አንድነታችን ከልዩነታችን በላይ ነው!! ባለራዕይ ወጣቶች ማህበር፡፡
    ግንቦት 02/08/2006 ዓ.ም

    አቶ አሥራት አብርሃ ለምን አንድነት ፓርቲን ተቀላቀሉ? – በዘሪሁን ሙሉጌታ

    May 13/2014

    ቀደም ሲል በአረና ትግራይ ለዲሞክራሲና ለሉአላዊነት ፓርቲ (አረና) ውስጥ የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ የነበሩትና በኋላ ከፓርቲው ጋር በተፈጠረ “የስትራቴጂክ ልዩነት” ከአረና ፓርቲ ወጥተው በግል ሲንቀሳቀሱ የነበሩት አቶ አሥራት አብርሃም ከሰሞኑ ወደ አንድነት ፓርቲ ገብተዋል። አቶ አሥራት በቋንቋና ስነ-ፅሁፍ ከዲላ ዩኒቨርስቲ የመጀመሪያ ዲግሪ ያላቸው ሲሆን በአሁኑ ወቅት በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የፍልስፍና ትምህርት የሁለተኛ ዲግሪአቸውን በማጠናቀቅ ላይ ናቸው። አቶ አስራት ወደ አንድነት ፓርቲ ስለተቀላቀሉበት ምክንያት ለሰንደቅ ጋዜጣ አስተያየታቸውን ሰጥተዋል።
    አቶ አሥራት ወደፓርቲው ስለገቡበት ምክንያት ተጠይቀው፤ ሲመልሱ ከአንድ ዓመት በፊት ከአረና ወጥተው ከቆዩ በኋላ ከፖለቲካ ስሜት ውጪ ሆነው አለመቆየታቸውን፣ በጋዜጣና በመፅሔት ከሚያቀርቡት መጣጥፍ ባሻገር ወደፓርቲዎች አካባቢ ጎራ በማለት የራሳቸውን ኃሳብ ሲያቀርቡ ከቆዩ በኋላ በግል ከመንቀሳቀስ በፓርቲ ታቅፈው መታገል ስለመረጡ፣ በአንድነት አካባቢ ያሉ ጓደኞቻቸው ባደረጉባቸው ገንቢ ግፊት አንድነት ፓርቲንም በቅርብ ስለሚያውቁት መሆኑን አስረድተዋል።
    አቶ አሥራት ወደ አንድነት ፓርቲ የተቀላቀሉት በጓደኞቻቸው ግፊት ብቻ ሳይሆን ፕሮግራሙንም በማየት እንደሆነ ተናግረዋል። በተለይም አቶ ስዬ አብርሃ ጋር በትግራይ ክልል ተምቤን ወረዳ ሲወዳደሩ በትግርኛ ቋንቋ የተተረጎመውን የአንድነት ፓርቲ ፕሮግራም ቅጂ በማንበባቸውና በመድረክ ፓርቲ ውስጥ በነበራቸው ተሳትፎ ወቅት ከአንድነት ፕሮግራም ጋር በመተዋወቃቸው እንደሆነ ገልጸዋል። በተጨማሪም ቀደም ሲል ከነበሩበት የአረና ፓርቲ ፕሮግራም በብዙ መልኩ ተቀራራቢ ሆኖ ስላገኙትም እንደሆነ ይናገራሉ።
    በአቶ አሥራት እምነት የአንድነት ፓርቲ ፕሮግራም በሀገሪቱ ተጨባጭ ሁኔታ ሲያዩት ለእኛ ሀገር ሁሉንም አስተሳሰቦችና ድምፅ ሊያሰባስብ የሚችል ፕሮግራም ስለሆነ ወደ ፓርቲው መግባታቸውን የሚያስረዱት አቶ አሥራት የአንድነት ፕሮግራም የግለሰብንና የቡድንን (Group) መብት መኖርን የተቀበለ፣ ከአማርኛ በተጨማሪ ኦሮምኛም የሀገሪቱ ተጨማሪ የፌዴራል መንግስት የስራ ቋንቋ እንዲሆን በፕሮግራሙ ያስቀመጠና በብዙ መንገድ ተራማጅ ሊባል የሚችል ፕሮግራም በመሆኑ ነው ብለዋል። ፓርቲው ባዘጋጀው የአምስት ዓመት የስትራቴጂ እቅድ ዘጠና በመቶ ስለሚስማሙ ፓርቲው ታግሎ ስለሚያታገል እንደሆነም ያስረዳሉ።
    “በእኔ እምነት መካከለኛ በሆነው የፖለቲካ አስተሳሰብ እስማማለሁ። ቀኝና ግራ ጠርዝ ያልያዘ ፖለቲካ በሀገራችን ስለሚያስኬድ በዚህ ምክንያት ነው የገባሁት” ሲሉ አቶ አሥራት ያስረዳሉ።
    የአንድነት ፕሮግራምና የአረና ፕሮግራም ተቀራራቢ ከሆነ ለምን ከአረና ወጥተው ወደ አንድነት እንደገቡም አቶ አስራት ተጠይቀው ሲመልሱ፤ “ከአረና ወጥቼ ወደ አንድነት አልገባሁም። ከአረና ወጥቼ ወደ ልጄና ሚስቴ ነው የተመለስኩት። ከአረና እንደወጣሁ ወደ አንድነት እገባለሁ ብዬ አላሰብኩም። ከአረና የወጣሁትም በአንዳንድ የስትራቴጂ አካሄድ ላይ መግባባት ባለመኖሩ፣ አዳዲስ ባህሪያትን በፓርቲው በመመልከትና የዛ ችግር አካል ላለመሆን ነው የወጣሁት። ከወጣሁም በኋላ የግል ስራ ስሰራ ቆየው እንጂ አንድነት ከአረና ስለሚሻል አይደለም ወደ አንድነት የገባሁት” ሲሉ መልሰዋል። በተጨማሪም ሰው እንደመሆናቸው በሂደት አቋማቸውን በመቀየራቸው እንዲሁም በቀጣይ አረና እና አንድነት ይዋሃዳሉ ከሚል ተስፋ በመነሳት ጭምር እንደሆነ ገልጸዋል።
    የእሳቸው ወደ አንድነት መግባት አረና እና አንድነትን በማዋሃድ ረገድ ስለሚፈጥረው የፖለቲካ አቅም የተጠየቁት አቶ አሥራት፤ ቀደም ሲል ከአረና ጋር ያላቸው ግንኙነት የተሻለ በመሆኑ የእሳቸውን አስተዋፅኦ እንደሚያደርጉ፣ እንዲሁም የአረና ፓርቲ አባላት የእሳቸውን ወደ አንድነት ፓርቲ መቀላቀል በቴሌፎን በመደወል እንዳበረታታቸው ጭምር ተናግረዋል። ሁለቱን ፓርቲዎች እንዲዋሃዱም የተሻለ ነገር ሊፈጠር እንደሚችል ተስፋ እንዳላቸው ነው የጠቀሱት። የእሳቸውም አገባብ “ከአንድ ጢስ ወደ አንድ ጢስ” የመቀያየር ካልሆነ በስተቀር አንድነትና አረና ያንያህል ልዩነትና እርቀት አለን ብለን አናስብም ብለዋል።
    ይሁን እንጂ አረና በክልል የተደራጀ የብሔር ፓርቲ ከመሆኑ አንጻር ከአንድነት ጋር ስለሚያቀራርባቸው ጉዳይ የተጠየቁት አቶ አሥራት ሁለት ነገር ጠቅሰዋል። የመጀመሪያው አረና የክልል ፓርቲ የሚያስብለውና የብሔር ፓርቲ የሚያስብለውን ልዩነት አስቀምጠዋል። አረና የአንድ ብሔር ሳይሆን የአንድ ክልል ፓርቲ ነው። አብዛኛዎቹ የፖለቲካ አቋሞቹ ላይ በተለይም የመድረክ ሁለተኛው ጉባኤው ላይ የመድረክን ፕሮግራም ሲቀበል በመድረክ ደረጃ የተቀበልነውን በተወሰነ ደረጃ በአረና በሚስማማ መልኩ ነው የወሰደው። እና ብዙ ከአንድነት የሚራራቅ ነገር የለውም” ሲሉ የገለፁት።
    የእሳቸው ወደ አንድነት መግባት በመጠኑ የአለመተማመን ስሜት የሚንፀባረቅበትን የሰሜን ፖለቲካና የመሀል ሀገር ፖለቲካ በማቀራረብ ረገድ ስለሚያኖራቸው ሚና ተጠይቀውም ሁኔታው የበለጠ ወደፊት የሚታይ ቢሆንም አንድነት ከዚህ ቀደም ከሚታወቁ የመሃል ሀገር የፖለቲካ ፓርቲዎች በተወሰነ መጠን ለየት የሚልበት የራሱ አሳታፊ (accommodate) ባህሪ አለው። ፓርቲው የተለያየ ብሔርና አስተሳሰብ በአንድ ዓላማ ዙሪያ ለማሰባሰብ የሚጥር ፓርቲ ሆኖ የአስተሳሰብና የሰዎች ብዙህነት የሚንፀባረቅበት ፓርቲ ነው። አንድነት ፓርቲ ስትገባ ሁሉንም ኢትዮጵያዊ የምታገኝበት የተለያዩ ቋንቋዎች የሚነገርበት ሰፋ ያለ የብሔር ስብጥርና አይነት ያለው ፓርቲ ስለሆነ ከሌሎች የመሃል ሀገር ፖለቲካ ፓርቲዎች ይለያል ብለዋል። ችግሩ ያለው ከአንድነት ፓርቲ አደረጃጀት አንጻር ሳይሆን ከገዢው ፓርቲ መሆኑን የሚጠቅሱት ገዢው ፓርቲ በህብረብሔር የተደራጁ ፓርቲዎችን አንድ አይነት ቀለም እንዲኖራቸው ከመፈለጉም በላይ ወደ አንድ ጥግ ሊያሲዛቸው እንደሚፈልግ ጠቅሰዋል። በዚያው መጠን አንድነት ፓርቲንም የአንድ ብሔር ፓርቲ አድርጎ የመፈረጅ ዝንባሌና ፍላጎት እንዳለ ጠቅሰዋል። በአንፃሩ አንድነት የሚለይበት የራሱ የሆነ ብዙ ቀለማት ያሉት ፓርቲ ነው ብለዋል።
    ቀደም ሲል በአንድነት ፓርቲ ውስጥ “የአማራ ብሔር የበላይነት አለው” የሚለው የአንዳንድ ልሂቃንን አስተያየት በተጨማሪ የቀድሞ የአንድነት ሊቀመንበር ዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳ መድረክን በተመለከተ በአንድነት ፓርቲ ውስጥ የነበራቸው አቋም በሌሎች የፓርቲው አመራሮች የሃሳብ የበላይነት ከመሸነፋቸው አንጻር እሳቸው (አቶ አሥራት) ወደአንድነት የመግባታቸው እንደምታም ምን እንደሆነ ተጠይቀው፤ አንድነት ፓርቲ የአማራ ብሔር የበላይነት አለው ብለው የሚያስቡ ልሂቃን በቁጥር ምንያህል ብዙ ስለመሆናቸው ጥርጣሬ እንዳላቸው ገልፀዋል። ይልቁኑ ይህ አመለካከት ከኢህአዴግ አካባቢ የሚደመጥ መሆኑን ጠቅሰው ዋናው ነገር ግን የፓርቲው ፕሮግራም ነው ብለዋል።
    ከዚህ በተጨማሪ ወደ ፖለቲካ ትግል የሚገባ ሰው የእገሌ ብሔር ስለበዛና ስላነሰ እያለ ወደ ትግል መግባት የለበትም። ዋናው ነገር በፕሮግራሙና በሕገ ደንቡ ይመራል የሚለው ነው። በተጨባጭ አሁን ባለው ሁኔታ የአንድነት የስራ አስፈፃሚ አባላት ስብጥር ከአብዛኛዎቹ የኢትዮጵያ ክፍሎች የተውጣጡ ናቸው። በፓርቲው የአማራ የበላይነት አለ ቢባል እንኳ ጫፍ ይዞ ውጪ መቅረት ሳይሆን ገብቶ ተመጣጣኝ ውክልና እንዲኖርና የሁሉንም ኢትዮጵያዊ የሚወክል አመራርና አባል እንዲኖር መታገል ነው ብለዋል።
    አቶ አሥራት ከአረና ፓርቲ ከወጡ በኋላ በዩኒቨርስቲ ቆይታቸው ወቅት የኀሳብ አመንጪ ምሁራን (Think thank) ለማቋቋም ጥረት ሲያደርጉ እንደነበር ይታወቃል። ጥረቱ ስላልተሳካ ወደ ፓርቲ ፖለቲካ ተመልሰው እንደሆነም ተጠይቀው ነበር። እሳቸውም የተባለው ሃሳብ አመንጪ አካል በተፈለገው መጠን ባይሄድም በቅርቡ ግን ፍልስፍና የሚያጠኑ ምሁራን ዶ/ር ዳኛቸው አሰፋ ጭምር ያሉበት “Think Ethiopia” የሚል ቡድን መቋቋሙን ገልጸዋል። ቡድኑ በአመዛኙ ፍልስፍና ላይ እንዲያተኩር መደረጉንም አስረድተዋል። ወደ አንድነትም የገቡት ታስቦ የነበረው ሰፋያለ ፖለቲካ ሃሳብ አመንጪ ቡድን ባለመሳካቱም እንደሆነም ጠቅሰዋል።
    በምርጫ ዋዜማ ወደ ፖለቲካ ፓርቲ መግባታቸው ከስልጣን ፍለጋ ጋር ስለመያያዙም አቶ አሥራት ተጠይቀው ማንኛውም ፖለቲከኛ ትክክለኛ ስልጣን እንደማይጠላ ጠቅሰው፣ ነገርግን ስልጣን ያለው ኢህአዴግ ጋር መሆኑን አስረድተዋል። በእሳቸው እምነት በአረና ፓርቲ ውስጥ እያሉ ትልቅ ስልጣን እንደነበራቸው አስታውሰው ነገር ግን ፓርቲዎቹ ውስጥ ከስልጣን ይልቅ ትግል ወይም የስራ ክፍፍል ብቻ ነው ያለው ሲሉ መልሰዋል። በፓርቲው ውስጥ ለታችኛውም ሆነ ለላይኛው የአመራር አካል ኀሳብ በመስጠት በማንኛውም የፓርቲው ደረጃ ላይ በመሆን ለመስራት መዘጋጀታቸውን ገልጸዋል።
    1619254_634234963328108_581967544042254518_n