Thursday, May 15, 2014

ጁነዲን ሰዶ አትላንታ አሜሪካ ገቡ

May 14, 2014

Junedin Sado“ይሄ ፋሽስት መንግሥት!” ማለት ጀምረዋል!

አገር ለቀው የኮበለሉትና የኦሮምያ ፕሬዚዳንትነትን ጨምሮ በተለያዩ የመንግሥት መስሪያ ቤቶች በሚኒስትርነት ማዕረግ ያገለገሉት እንዲሁም የኦህዴድና የኢህአዴግ ሥራ አስፈጻሚ የነበሩት አቶ ጁነዲን ሰዶ አሜሪካ መግባታቸውን በዋሺንግተን ዲሲ የሚታተመው ዘ-ኢትዮጵያ የተባለው የአማርኛ ጋዜጣ ይፋ አድርጓል። ኬንያ ለአንድ ዓመት ያህል በስደተኝነት ተቀምጠው የአሳይለም ወረቀታቸውን አግኝተው አትላንታ ከገቡ ሁለት ወራት እንደሆናቸውም የዘኢትዮጵያ ጋዜጣ ምንጮች ገልጸዋል።

አቶ ጁነዲን በአባ ዱላ ገመዳ እስኪተኩ ድረስ ከኦክቶበር 28/2001 እስከ ኦክቶበር 6 /2005 የኦሮምያ ክልል ፕሬዚዳንት ነበሩ። ከዚያም የትራንስፖርትና መገናኛ ሚኒስትር በመሆን እስከ ኦክቶበር 2008 አገልግለዋል። በመቀጠልም በሳይንስና ቴክኖሎጂ ሚኒስትርነት ከሠሩ በኋላ በመጨረሻም በ2010 የሲቪል ሰርቪስ ሚኒስትር በመሆን የቀድሞ ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ መለስ ዜናዊን መንግሥት አገልግለዋል። የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲም የቦርድ ሊቀመንበር ነበሩ። መንግሥታቸው ብዙ ዓመት ከኖሩበት የሚኒስትሮች ካቢኔ ያሰነባታቸው የአቶ ኃይለማርያም የጠቅላይ ሚኒስትርነት ዘመን ሲጀመር ነው።የስደት ኑሯቸውን ማቃናት የያዙት አቶ ጁነዲን ከወዳጆቻቸው ጋር ሲያወጉ “ይሄ ፋሽስት መንግሥት እኮ የሚያደርገውን አያውቅም” በሚል መገረም ሲናገሩ መደመጣቸውን ምንጮቻችን ገልጸዋል። ባለቤታቸው ወ/ሮ ሀቢባ መሀመድ “በሽብር ተግባር ተጠርጥረዋል፣ ከሳዑዲ ኤምባሲ ገንዘብና መጽሐፍት ይዘው ሲወጡ ሐምሌ 9 ቀን 2004 እጅ ከፍንጅ ተይዘዋል” በሚል ተዘውታሪ ሰበብ በእስር መቆየታቸው ይታወሳል። ከሥልጣናቸው በመስመጥ ላይ ለነበሩት አቶ ጁኒዲም ይህ የባለቤታቸው እስር ተጨምሮ ከአገር ለመኮብለል መንስኤ መሆኑ ሲዘገብ መሰንበቱ ይታወቃል።

ባለቤታቸውና ልጃቸው አሁንም በኢትዮጵያ የሚገኙ በመሆኑ አቶ ጁኒዲን በይፋ ምንም አስተያየት ሳይሰጡ ተቆጠበው መቀመጡን መምረጣቸው ተነግሯል። ሰሞኑን በኦሮምያ ክልል ተማሪዎች ላይ እየደረሰው ያለው ግድያና ሁከት በአንድም ሆነ በሌላ መንገድ የሚመለከታቸው ቢሆንም፣ እንደ ተራ ሰው “ይሄ ፋሽስት መንግሥት ምን እያደረገ ነው” ብለው መገረማቸው መልሶ ማሰገረሙን ምጮቻችን ገልጸውልናል። የኦሮምያ ክልል ፕሬዘዳንት ከነበሩት ውስጥ ሀገር ጥለው የኮበለሉ ፕሬዘዳንቶች ከአቶ ሀሰን ዓሊ ጋር አቶ ጁነዲን ሲደመሩ ሁለተኛ መሆናቸው ነው። ሁለቱም አትላንታ መሆናቸው ሲገለጽ አቶ ጁነዲን በአንድ ዩኒቨርስቲ መምርህነት ሥራ ለማግኘት ማመልከቻ ማስገባታቸውም ተነግሯል።

Wednesday, May 14, 2014

ወለጋ ዩኒቨርስቲ ነቀምት ዋናው ካምፓስ በድጋሚ ተቃውሞ ተነስቷል (ፎቶዎች ይዘናል)

May 14/2014
ሚኒሊክ ሳልሳዊ
በነቀምቴ በሚገኘው የወለጋ ዩንቨርስቲ የሚማሩ የኦሮሞ ተማሪዎች ባነሱት ተቃውሞ የወያኔ ፖሊሶች አጸፋውን የወሰዱ ሲሆን በዚሁም አጸፋ የተጎዱ በርካታ ተማሪዎች ወደ ህክምን ጣቢያ ሄደዋል። ከተደበደቡት ተማሪዎች በከፊል ምስሎቻቸውን ይመለክቱ። እነዚህ የምታይዋቸው ተማሪዎች በዛሬው የተቃውሞ ሰልፋቸው ላይ ይተጎዱ ናቸው።
nekemte1
nekemte2
nekemte3
nekemte4
nekemte5
nekemte6
nekemte7

የኢሕአዴግ አጋዚ ጦር በወለጋ ዜጎችን እያሰረ ነው – ጊምቢም እየወደመች ነው !

May 14/2014
«አበሾች አዲስ አበባን በመጠቀም የኦሮሚያን መሬት እየወረሩ ነው» በሚል በቅርቡ ይፋ የሆነውን የአዲስ አበባ ማስተር ፕላን በመቃወም በተለያዩ የኦሮሚያ ከተሞች በሚገኙ ዩኒቨርሲቲዎች ተቃውሞ ማሰማታቸው ይታወቃል። ከተቃዉሞው ጋር በተገናኘ በርካታ ዜጎች የሞቱ ሲሆን፣ በንብረትም ላይ ከፍተኛ ጥፋት ደርሷል።

በተነሳው ቀውስ ሰለባ ከሆነቸው ከተማ አንዷ የጊምቢ ከተማ ናት። ከጊምቢ የተላኩ ፎቶዎችን ይመልከቱ
gimbi6
gimbi5
gimbi4
gimbi3
gimbi2
gimbi1
Gim2

እናስራችኋለን? ለካንስ የነአጅሬ ጋጠወጥነት ከድንበርም ተሻግሯልና!

May 14, 2014
ነፃነት ዘለቀ (ከአዲስ አበባ)
በሀገራችን ባደመነው አጠቃላይ የሀዘን ድባብ ሳቢያ ፈገግታ እያማረኝ ፈገግ ለማለት ምንም ዕድል ሳላገኝ ብዙ ሰሞኖችን ባጀሁ፡፡ ዕድሜ ለዚህ ነገረኛ ኢሳት የሚባል ቴሌቪዥን ዛሬ ማታ ግና በሣቅ የሚያፈርስ ዜና ሰማሁና ምሽቱን ብቻ ሳይሆን ትዝ ባለኝ ቁጥር ሌቱን ሁሉ በሣቅ ስፈርስ አደርኩ – የግራ ጎን አጥንቶቼ ክፋይ ጉድ እስክትለኝ፡፡ ሣቅ ጥሩ ነው፡፡ አንዳንዴ በሣቅ የሚገድል ነገር ማግኘት የመታደል ያህል ነው፡፡ እውነተኛው ሣቅ ሞቶ ቢቀበርም ወያኔን መሰል ጅላንፎ ጉጅሌ የሚሠራቸው አንዳንድ ነገሮችን በመታዘብ ለጊዜውም ቢሆን ፈገግ መሰኘት ሲያስፈልግም ሆድን ያዝ አድርጎ በሣቅ መንፈርፈር ሰውነትን ያፍታታል፤ ወቅታዊ እፎይታንም ይሰጣል፡፡ እኔ – እውነቴን ነው – ለብዙ ጊዜ ያጣሁትን ሣቅ ዛሬ አገኘሁትና ከልቤ ተዝናናሁ፡፡ ወያኔ እኮ አልታወቀለትም እንጂ ደምበኛ የኮሜዲ መፍለቂያ ውድብ ነው፡፡ ልዩ የኢትዮጵያ ቻርሊ ቻፕሊን ሆነው የለም እንዴ!President Salva Kir of Sudan
ይህን የወያኔን ሞኝነት ጉዳዩ ለሚመለከተው የዓለም ክፍል ያንጸባረቀ ጉዳይ ለፖለቲካችን ቅርብ የሆነ ሰው ባያጣውም ለእንደኔ ዓይነቶች የማይሞላላቸው አንዳንድ ባዘኔዎች ማስታወሱ ደግ ይመስለኛል – ‹ቦዘኔ› እንዳላልኩ ይታወስልኝ፡፡ ብዙ ሰው እኮ የማይሞቀው የማይበርደው ሆኗል፡፡ ደንዘናል፤ በቁም ሞተናል፤ ‹ብታምኑም ባታምኑም› ብዙዎቻችን ከሰውነት ተራ ወጥተን የአምልኮተ ንዋይ ሰለባዎች ሆነናል፡፡ በሀገር ውስጥ ትንሽ ትልቁን ብታዩት ከሞላ ጎደል ሁሉም ሊባል በሚችል ሁኔታ ገንዘብ እንዴት ሊያገኝና በአቋራጭ ሊከብር እንደሚችል ሲጨነቅና ሲጠበብ ይታያል፡፡ ኅሊና ብሎ ነገር ጠፍቷል፡፡ ወንድም ወንድሙን፣ እህት እህቷን እስከመግደል በሚደርስ ሰይጣናዊ ጭካኔ ተሞልተን እየተፋጀን ነው፡፡ ወያኔ በቀደደው የጥፋት ጎዳና እየተመምን ከሰውነት ደረጃ በሚያስወጣ የሀብት ፍቅር ተነድፈን ልንጨራረስ የቀረን ጊዜ ሩብ ሐሙስ ቢሆን ነው፡፡ አልተነሳሁበትም እንጂ በዚህስ ትንሽ ባወራሁ፡፡
ወያኔም ባቅሙ አስታራቂና የሰላም አባት ሆኖ የደቡብ ሱዳን ተፋላሚዎችን በዕርቅ ለማስማማት አዲስ አበባ ይጠራቸዋል፡፡ ሳልቫኪር የሚሉት ባለባበሱና በዐይነ ውኃው ፊውዳላዊ አምባገነን የሚመስለኝ አማቻችን ሰውዬና ዶክተር ማቻር የሚባለው ሞገደኛ ሰውዬ ወደ አዲስ አበባ መጥተው (እንዳሁኑ ሁኔታ ደግሞ በመስፈራርቾ ተጠርተው) ሼራተን ሆቴል ሁለት ክፍሎች ውስጥ ይመሽጋሉ – ‹አማቻችን› ያልኩት የሳልቫኪር ይሁን የማቻር ልጅ የኛን ሀገር ልጅ እንዳገባ/ች በሚዲያ ስለሰማሁ ነው፡፡ ድርድሩም በወያኔ ጉጅሌ አማካይነት ተከናወነ ይባልና የዕርቁ ስምምነት ተፈረመ ተብሎ በወያኔው ቱሪናፋ ሚዲያዎች ይለፈፋል – (ከብቱ ወያኔ በሰሞኑ ጭፍጨፋው የጠለሸ ስሙን ያደሰ መስሎት በገባበት ወጥመድ የኋላ የኋላ ራሱ ገብቶበት ተተበተበበት እንጂ)፡፡ የወያኔ ኢትዮጵያ ለራሷ ብቻ ሣይሆን ለጎረቤት የሚተርፍ ሰላምና ዴሞክራሲ መጋዘኗ ውስጥ ጢም ብሎ እንዳለና ለሱዳንም፣ ለሶማሊያም፣ ለግብጽም፣ ለሦርያም፣ ለአፍጋኒስታንም፣ ለኢራቅም፣ ለቬንዝዌላም፣ ለ“ዴሞክራክ ሪፓብሊክ” ኮንጎም፣ ለሤንትራል አፍሪካ “ሪፓብሊክ”ም፣ ለሃይቲም፣ ለኡክሬንና ራሽያም፣ ለሰሜን ኮሪያም፣ ለ‹ኤርትራ›ም፣ ለሊቢያም፣ ለፓኪስታንም፣ ለበርማም፤ ለፍልስጥኤምም፣ (እንዴ፣ ዓለም ለካንስ በትርምስ ላይ ናትና ጎበዝ – የወያኔ የሰላም በረከት የሚላክላቸው ሁከት የነገሠባቸው ሀገሮች ዝርዝር አላልቅልኝ እኮ አለ!) ኤክስፖርት ለማድረግ ዝግጅቷን እንዳጠናቀቀች በነዚሁ በእውነት ዕርሙ የወያኔ ሚዲያዎች ከጥንፍ እስከ ጥንፍ ተስተጋባ፡፡ እኛም ይሄ የቤት ቀጋ የውጪ አልጋ የሆነ የወሮበሎች ቡድን ምን መተት ቢኖረው ይሆን እንዲህ ዓለምን ጉድ ባሰኘ መልክ የሰላም አባት ሊሆን የበቃው ብለን ተገረምን፡፡ የገዛ “ዜጎቹ”ን ባልተወለደ አንጀት እየጨፈጨፈና የስምንት ዓመት ሕጻን ሣይቀር ደረቱን በጥይት ዝናብ እየበሳሳ ባለበት ወቅት እንዲህ ያለ ሰላም ለሱዳናውያኑ ማስገኘቱ በርግጥም አንዳች ነገር አለው አልንና በጣም ተደነቅን፡፡ ኢትዮጵያችንም ስሟ ታደሰልን ብለን ደስ አለን – ደስታችን አንድ ጀምበር እንኳን ሳይዘልቅ ጠወለገብን እንጂ፡፡
ነገሩ ለካንስ ሌላ ኖሯል፡፡ ሳልቫኪር ሀገሩ እንደገባ ለሀገሩ መገናኛ ብዙኃንና ለባለሥልጣናቱ ሲናገር እንደተደመጠውና በሚዛናውያን ሚዲያዎች ሲዘገብ እንደተከታተልነው የሰላሙ ስምምነት የተፈረመው በወያኔ አስገዳጅነት ነበር፡፡ የአስገዳጅነቱ አካሄድም ነው በአስቂኝነቱ ወደር ያልተገኘለት፡፡
ከፍ ሲል እንደተገለጸው ወያኔ ሁለቱን ሰዎች ሼራተን ውስጥ በሁለት የተለያዩ ክፍሎች ያስቀምጣቸዋል፡፡ ፊት ለፊት ሳይገናኙም በተላላኪ ሃሳብ እንዲለዋወጡ ያደርጋል፡፡ መገናኘት ያልፈለጉት ምናልባት ራሳቸው ሊሆኑ እንደሚችሉ እንገምት፡፡ ወያኔ ግን የሁለቱ ሰዎች ያለመታረቅና ዕርቁን በፊርማ ያለማጽደቅ አዝማሚያ ሲገባው ያቺን የጫካ ህግ በመምዘዝ “ካልፈረማችሁ እዚሁ አስራችኋለሁ፤ ወደ ሀገራችሁ መሄድ ህልም እንደሆነባችሁ እንደነ እስክንድር ነጋና ርዕዮት ዓለሙ ከርቸሌ ትወረወራላችሁ፤ ከዚህ የሚያወጣችሁ አንድም ኃይል የለም” ብሏቸው ያርፋል፡፡ ይህ ያላሳቀ ምን ሊያስቅ ይችላል? እንዴ፣ በዚህማ ድዳችንን ተወቅረንም ሆነ ተነቅሰን መሣቅ አለብን፡፡ ግሩም እኮ ነው እናንተ ሆዬ!
ትርፋ ትርፉን እንተወውና ቃል በቃል ወያኔ ያላቸው “ስምምነቱን በፊርማችሁ ካላጸደቃችሁ ትታሰራላችሁ!” የሚል ነው – ከሌሎች የማስፈራሪያ አንድምታዎች ጋር፡፡ አስገዳጁ ደግሞ ራሱ ተገድዶ ቤት ጠባቂ የሆነው ደሳለኝ ነው አሉ – ማነው – ኃይለማርያም – ከአለቆቹ በተነገረው ጥብቅ ማስጠንቀቂያ መሠረት፡፡
ልብ አድርጉ! እነዚህ ሰዎች – እነሳልቫኪር – አነሰም አደገም የአንዲት ሉዓላዊት ሀገር መሪዎች ናቸው – አሁን ቢጣሉምና ከሁለት አንድኛቸው ዓለም አቀፍ ተቀባይነት ያለው መንግሥት በመምራት ላይ መገኘቱ እንዳለ ሆኖ፡፡ ወያኔን ታዲያ ምን ገጠመው? ይህችን እጅ እየጠመዘዙ ማስፈረምን ከሀገር ደረጃ አውጥቶ አህጉራዊ ቅርጽ እንዲኖራት የማድረግን ከፍተኛ ጉጉት ማን አሳደረበት? “የገቡበት የፖለቲካ ቀውስ የሚሠሩትን አሳጥቷቸው ለአንዳች የፖለቲካ ትርፍ ብለው ይሆን እንዲህ ያለ ‹ሪስክ› ውስጥ የገቡት?” ብዬም ተጨንቄላቸዋለሁ – ለወያኔዎቹ – እንዲያ ካልሆነ መቼም ጡት ያልጠባ ማለቴ ያልጣለ ሕጻን ሣይቀር መዘዙን ጠንቅቆ ሊገምተው የሚችለውን ይህን የመሰለ ጅልነት ውስጥ ባልገቡ ነበር፡፡ አሁን አስገድዶ ቢያስፈርማቸው ወደሀገራቸው ሲመለሱ ጉዱን ማለትም ምሥጢሩን እንደሚያወጡት እንዴት ወያኔዎች ሊገምቱ አልቻሉም? እንዴትስ ቢንቋቸው ነው? በኛ የለመዱትን ንቀት እኮ ነው በ‹ኮፒ ፔስት› እነሱም ላይ እውን ያደረጉት፡፡ በውነቱ እነዚህን የመርገምት ፍሬዎች ሰው ናቸው ብሎ መቀበል እንዴት ይቻላል? ኢትዮጵያ በታሪኳ እንዲህ ያለ አሣፋሪ ነገር የፈጸመባት በስሟ የተቀመጠ “መንግሥት” የለም፡፡ እዚህ ላይ አንዲት ብጫቂ ማሳሰቢያ አለችኝ፡- በተለይ ኢሳቶች ይህንን የወንበዴ ጥርቃሞ ቡድን “የኢትዮጵያ መንግሥት” እያላችሁ በዜና ዕወጃችሁ የምትናገሩትን ነገር ባፋጣኝ ብታርሙ ይሻላል፡፡ ይህ ‹መንግሥት› መንግሥት ሣይሆን የከተማ ሽፍታ ነው፤ በአንድ ጎሣ የተዋቀረ፣ ለአንድ ጎሣ ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ ጥቅም ያደረ፣ ለዓለም አቀፍ የውንብድና ተቋማት የሰገደና አንዲትን ሀገር ከነሕዝቧ መቀመቅ ለማውረድ ታጥቆ የተነሣን ወሮበላ የአማጊዶዎችን ስብስብ መንግሥት ማለት በመንግሥት ተቋማዊ ምንነት ላይ መቀለድ ነው፡፡ ስለዚህ ቢያንስ “የኢትዮጵያ መንግሥት ተብዬው” በሚል ቢነገር የተሻለ ነውና አንዳንድ ወገኖች አታቁስሉን፡፡ የነሱው ይበቃናል፡፡
አንድ ፈረንጅኛ አባባል አሁን ትዝ አለኝ፡፡ A man cat take a horse to a river; but twenty cannot make it drink. ወዳማርኛው ሲመለስ – አንድ ሰው አንድን ፈረስ ወደ ወንዝ ሊወስደው ይችላል፤ ሃያ ሰዎች ግን ውኃ(ውን) እንዲጠጣ ሊያደርጉት አይችሉም፡፡ የወያኔ ቂልነት፣ የወያኔ ባልጩት ራስነትና አባጉልቤነት እዚህ ላይ ነው፡፡ እነሱ የሚያስቡት ነገር ሁሉ ገዢ ይመስላቸዋል፡፡ የድንቁርናቸው መጠን በምንም ምድራዊ መለኪያ የሚሠፈር አይደለም፡፡ በመንግሥትነት ለሃያ ሦስት ዓመታት የቆዬ አንድ ኃይል የዚችን ፊርማ መነሻና መድረሻ ከነመዘዟ ጭምር ካላወቀ ትልቅ የአስተሳሰብም እንበለው የአመለካከት ችግር አለ ማለት ነው፡፡ እንዲያው ግን ኢትዮጵያ ምን ያህል ብትረገም ፣ እኛም ምን ያህል ባንታደል ይሆን ፈጣሪ እነዚህን ሰዎች የሰጠን? አይጨንቅም? ሳስበው በጣም ይጨንቀኛል – ማይግሬይን የተሰኘውን ከፍተኛ ራስ ምታት የሚለቅ ችግር ነው የገጠመን፡፡
የዚህ ችግር መባቀያ ደግሞ ውስብስብ ነው፡፡ ምዕራባውያንም ይጠየቁበታል – አሉበትና፡፡ ማፈሪያ የሰውነት አካል እንደወያኔው የላቸውም እንጂ ካላቸው በእጅጉ ሊያፍሩበት ይገባል፡፡ በብዙ ነገር እየደገፉ ከበረሃ ወደ ቤተ መንግሥት ያስገቡ ኃይሎች ቆም ብለው ሊያስብቡበት የሚገባ ወቅት ላይ መድረስ የሚገባቸው ይመስለኛል፡፡ እኛን ማመን ስላልፈለጉ እስካሁን አላመኑንም፡፡ የወያኔን ጉድ ቢያውቁትም እንደዚህ ቁልጭ ብሎ የወጣበት ዘመን ባለመኖሩ ይህን ሃቅ ማመን ባይፈልጉና በቆዬ ወያኔን የመደገፍ አቋማቸው የሚጸኑ ከሆነ ከሌላ ከማንም ጋር ሣይሆን ከገዛ ኅሊናቸው ጋር የሚጣሉበት ጊዜ እየደረሰ መሆኑን እየመረራቸውም ቢሆን መገንዘብ አለባቸው፡፡ ወያኔ የአንድን ሉዓላዊ ሀገር ፕሬዝደንት “አስርሃለሁ!” ካለና ካለውድ በግዱ ካስፈረመ ከዚህ በላይ ዓለም አቀፍ ውንብድናና ማፊያነት የለም፤ ወያኔ በዓለም አቀፍ ደረጃ ፕሬዝደንታዊ ስብዕናንና ሀገራዊ ክብርን የሚነካ እንዲህ ያለ ጠያፍ የማንአለብኝነት ተግባር ከፈጸመ የገዛ ምድሩን ዜጎች ምን ሊያደርግ እንደሚችል ማንም ወገን በዚህ ኹነት አማካነት ሊረዳ ይገባዋልና ይህ የሰሞኑ ወያኔያዊ ቅሌት ውርደታዊ ክስተት ለሀገራችን በጎ ገጽታ አለው (ፈረንጆቹ blessing in disguise እንደሚሉት ማለቴ ነው)፡፡ ይህ ነገር እንደሚመስለኝ ወያኔን ብቻ ሣይሆን ምዕራባውያንንም ከነሤራዊ ተንኮላቸው ለማጋለጥ ፈጣሪ ያመቻቸው ነገር መሆን አለበት፡፡ ከፍ ሲል እንደጠቆምኩት ዓለም እስኪታዘበን ድረስ የወያኔን አምባገነንነትና ገዳይነት ስናጋልጥ ብንቆይም ያመነን አልነበረም፡፡ የማቻርንና የሳልቫኪርን ምስክርነት ግን ሊጠራጠር የሚገባ ሰው አይኖርም ብዬ እገምታለሁ ፤ ምንም እንኳን እነሱ ራሳቸውም የአፍሪካዊ አምባገነንነት ወረርሽኝ ሰለባ ቢሆኑም፡፡
አሁን ፈረሱም ሜዳውም ያለው በወያኔ ደጋፊዎች ደጅ ነው፡፡ እስካሁን ያርመጠምጡት የነበረውን የኢትዮጵያ ፖለቲካ ማቃናት የሚያስችላቸው ወርቃማ ዕድል አሁን እፊታቸው አለ፡፡ አንዳንድ ልፍስፍስ ፖለቲከኞቻችንንና ወያኔ ተከል ተቃዋሚ ተብዬዎችን እንዲሁም በወያኔ ቅኝት የሚዘምሩ የነገ ራስ ምታቶችን ትተው ሁነኛ ዴሞክራሲ በሀገራችን የሚመጣበትን መንገድ ሊደግፉ የሚችሉበት ዕድል አሁንም አለ፡፡ አለበለዚያ በኃይል የሚመጣ ሥልጣን ለነሱም ሆነ ለሀገራት እንደማይበጅ የታወቀ ነውና እነዚህ ምዕራባውያን የእጃቸውን የሚያገኙበት ጊዜ ሩቅ አይሆንም፡፡ ብዙዎቹ በዓለም የሚታዩ አመፆችና የሽብር ተግባራት ሥረ መሠረታቸው ሲጠና መነሻቸው እነሱው ራሳቸው ምዕራባውያኑ ናቸው፡፡ ለዐይን ይበጃል ብለው የሚኳሉት ኩል ዐይንን እንደሚያጠፋ ሁሉ ለአንዳንድ ሤራዎቻቸው ስኬታማነት ብለው – ለምሳሌ እንደ አዲሱ የዓለም ሥርዓት (NWO) – የሚተልሟቸው ዕቅዶች በጊዜ ሂደት ወደነሱው እየዞሩ በመተኮሳቸው ባላስፈላጊ ጥቃቶች ዜጎቻቸውንና ንብረታቸውን አስፈጅተዋል፤ እያስፈጁም ነው – 9/11ን፣ 5/7ንና የናይሮቢን የሽብር ጥቃት ማስታወስ በቂ ነው፡፡ ቢን ላደንን ማነው እዚያ ላይ አድርሶት የነበረው? አዎ፣ ሁሉም የሥራውን ነው የሚያገኘው፡፡ የተከልካት ተክል ትጸድቃለች፤ ጠቃሚ ከሆነች ትጠቀምባታለህ፤ ጎጂ ከሆነች ግን ትጎዳባታለህ፤ ሰውን አለኃጢኣቱ ልታጠቃ ብለህ የወረወርካት ጦር ዞራ ተመልሳ ወዳንተው እንደምትመጣ ካላወቅህ ተሳስተሃል፤ ጊዜ ይፍጅ እንጂ በቆፈርከው ጉድጓድ የመግባት ዕድልህ እጅግ ሰፊና የማይቀርም የመጨረሻ ዕጣ ፋንታህ መሆኑን ማወቅ አለብህ፡፡ የበግ ግልገል መስላህ መንገድ ላይ ያገኘሃትን የጅብ ግልገል ቤትህ ውስጥ ብታሳድጋት ተፈጥሯዊ ባህርይዋን አትለቅምና የኋላ ኋላ የምትጎዳው አንተው ነህ፡፡ እናም ወያኔም ሆነ የስምሪት ኃላፊዎቹ ሁሉ የዘሩትን ያጭዳሉ፤ የጊዜና የቋት መሙላት/አለመሙላት ካልሆነ በስተቀር ወያኔ በኢትዮጵያ ምድርና ሰማይ እንደፏለለ የሚኖርበት ዘመን ያከትማል፤ ጦስ ጥምቡሱ ግን ለብዙዎች ይተርፋል፡፡ አርቆ ማሰብ የሚያስፈልገው ለዚህ ነው፡፡ ዛሬ ለምሳሌ አማራውና ኦሮሞው እንዲሁም ሌላው በገርጂም ሆነ በሰሚትና በቦሌ ከመሬቱና ከንብረቱ እየተነቀለ ለባለጊዜው የጎሣ አባላት እንደልብ ቢታደል ይህ ዘመን ሲገለበጥ ተከፍሎ የማያልቅ ዕዳ ይመጣል፡፡ ይህን የምለው ውሻ ሆድ ውስጥ ቅቤ አያድርምና ሰሞኑን ወደሰሚት ሄጄ ሰዎች ያሳዩኝ ትልቅ መንደር ውስጥ ካለሀብቶምና ካለአብረኸት በስተቀር አንድም – ለውርርድ ያህል እንኳን – አንድም ዘበርጋና ደቻሳ ወይም ሸዋርካብሽና አሰጋኸኝ የሚባሉ ዜጎች የማይኖሩበት ምድረ ገነት በአዲስ አበባ መኖሩን ስለተረዳሁ ነው፤ አዲስ አበባና መቀሌን መለየት የማንችልበት አስገራሚ የታሪክ አንጓ ላይ መድረሳችንን የምገልጥላችሁ ነገ ሊከሰት የሚችለውን አደጋ ከወዲሁ በማጤን በታላቅ ፍርሀት ተውጬ ጭምር ነው – ወያኔና ይሉኝታ የማይተዋወቁ መሆናቸውን ቀድሜ ባውቅም ተጋሩ(ትግራውያን) ወገኖቼ ይህን ያህል ኅሊናቸውን ስተው የወያኔን የአድልዖ አሠራር በጭፍን ይከተላሉ ብዬ አምኜ አላውቅም – አዝናለሁ – ሀዘነይ ካብ ልበይ ኢዩ፡፡ ይህ ሁሉ ግፍ ጊዜው ሲደርስ የሚያስከትለውን ጠንቅ የማይረዳ ሰው ካለ የመጨረሻው ከንቱ ነው፡፡ “ፍቅር ያዘኝ ብለህ አትበል ደንበር ገተር፤ እኛም አንድ ሰሞን እንዲህ አርጎን ነበር” አለች አሉ ያቺ ምስኪን አቀንቃኝ፡፡ የተራ ጉዳይ ነው፡፡ ተራ ሲባል ደግሞ እንደወያኔ ያለ ዐይን ያወጣ አድልዖና ፍርደ ገምድልነት በእስካሁኑ ታሪካችን በግልጽ ታይቷል ለማለት እንዳልሆነ ይሰመርበት፡፡ በአፄው ዘመን በፊውዳላዊ መድሎ፣ በደርጉም በወታደራዊ መድሎ የተወሰነ ብልሹ አሠራር እንደነበር መናገር በደልን ያጥባል እንጂ ክፋት የለውም፡፡ የአሁኑ ግን በሀገራችን ቀርቶ በየትም ሀገር ያልተመዘገበ የአንድ ጎሣ ሁሉንም ነገር የማግበስበስ ሁኔታ በግልጽና ክፉኛ በሚያሳፍር አኳኋን እየታዬ ነው፡፡ በነዚህ ልጆቿ የነገይቷ ትግራይ እንዴት እንደምትሸማቀቅ ሳስበው የትግራይ መሬት ራሷ ታሳዝነኛለች፡፡ በርግጥም ላም እሳት ወለደች፡፡ አሁንም አዝናለሁ፡፡ እግዚአብሔርና አስተዋይ የአብራኳ ክፋይ የሆኑ ልጆቿ ይሁኗት ከማለት ውጪ ምን እላለሁ፡፡ እየታዬ ካው አሰቃቂ መድሎ አኳያ ለጊዜው ከዚህ የዘለለ ነገር መናገር አይቻለኝም – ችግር አለ!!!!!!!!….
ሕዝብን የሚመለከት፣ የሕዝብን ዕንባ የሚጠርግ፣ የሕዝብን ብሶት የሚያዳምጥ፣ ሕዝብን ማዕከል ያደረገ ዓለማቀፋዊ ዘመቻ ያስፈልገናል፡፡ የየሀገሩ ሕዝብ በአንድ ወይ በሌላ ምክንያት እያለቀሰ ነው፡፡ ጥቂቶች በሚፈጥሩት ችግር ቢሊዮኖች እየተሰቃዩ ነው፡፡ ይህ የጥቂቶች የበላይነትና ችግር ፈጣሪነት እስካልተወገደ ድረስ መዘዙ ለሁሉም ነው፡፡ ያስለቀሰ እያለቀሰ፣ ያለቀሰም እያስለቀሰ የሚሄድበት መጥፎ አዙሪት እስካልተወገደ ድረስ ዘላቂ መፍትሔ የለም፡፡ … የሰው ልጅ አእምሯዊ ይዘቱ የተዛባ ይመስለኛል፡፡ ራስህን በማለፊያ ምግብ አጥግበህ ሌላውን ስታስርብና ስታሰቃይ የምትደሰት ከሆነ ከእንስሳነትም ወርደሃል ማለት ነውና ሰብኣዊ ዕድገትህ ላይ ችግር መከሰቱን ልብ ማለት ሊኖርብህ ነው፡፡ አሳዛኝ ወቅት ላይ እንገኛለን፡፡
ወያኔን ግን በደምብ ዐወቅናት አይደል? እስኪ እዚች ላይም ትንሽ እንሳቅና እንዝናና – “ካልፈረማቸሁ እናስራችኋለን!!!” ጥጃ ገዝተው ወይም ወደማርካቶ ወጣ በማለት አንድ አምስትና ስድስት ሺህ ኢትዮጵያውያን የሰው እንስሳትን እንደለመዱት አያስሩም? ቅብጠታቸው ግን ለከትና ድንበር አጣ፡፡ ለነገሩ በጌታዋ የተማነች በግ ላቷን ቀለበት መንገድ ላይና አባይ ላይ ታስራለች ይባል የለም? ዘይገርም ሻሸመኔ ትብስ ኮፈኔ፡፡ ጉድ ነው፡፡
የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር በሰሞኑ ግርግር በአምቦና በሌሎች የሀገራችን አካባቢዎች ሕይወታቸውን ያጡ ወገኖቻችንን ነፍሳት በአብርሃምና በያዕቆብ ነፍሳት አጠገብ ያኑርልን፣ በጠባቡ ቃሊቲ የታሰሩትንም፣ በሰፊው “ዞን 9” የታሰርነውን እኛንም ፈጣሪ በቸርነቱ ይጎብኘን፡፡ አስቡ – ቀኒቷ ቀርባለች፡፡ ምልክቶች ሁሉ ታይተዋልና “ፕሊዝ” ወደየኅሊናችን በመመለስ ውስጣችንን እናጽዳ፡፡ ተመልሰን ሰው እንሁን፡፡ ሰው መሆን እንችላለን፤ መብትም አለን፤ ሰው ለመሆን ደግሞ በሕይወት እስካለን ድረስ ሁላችንም ልንሞክረው የሚገባን ታላቅ አምላካዊ ፀጋ እንጂ ቀነ ገደብ የተጣለበት ለማንም የተከለከለ ጉዳይ አይደለም፤ እናም ተስፋ ሳንቆርጥ ሰው ለመሆን እንሞክር፡፡ ያኔ ነው ከነዚህ ጉግማንጉጎች ነጻ የምንወጣው፡፡ አለበለዚያ በባርነት እየዳከርን ብዙ ጊዜ እንቆያለን – የባርነቱ ዘመን ይረዝምብናል፡፡ እናም ሰው በመሆን ፈጣሪን እናግዘው – የነጻነታችንን ጊዜም እናቅርብ፡፡

መሠረታዊ የአገልግሎት ማሻሻያ ፕሮግራም የክልልና የፌደራል መንግሥታትን አከራከረ

May14/2014

-ለጋሾች በበጀት አጠቃቀም ላይ ጥያቄ እያነሱ ነው
የመሠረታዊ አግልግሎቶች ማሻሻያ ፕሮግራም በኢትዮጵያ መተግበር የጀመረው ከ1997 ዓ.ም. ምርጫ ማግሥት ለጋሽ አገሮች መንግሥት ላይ ባሳደሩት ጫና ነበር፡፡
በተለይ የአውሮፓ ኅብረት ከምርጫው ማግሥት በኋላ በተፈጠረው አለመረጋጋት ሳቢያ መንግሥትን በመኮነን ለአንድ ዓመት ያህል ዕርዳታ ከመስጠት ታቅቦ ቆይቶ ነበር፡፡

ሆኖም ለጋሽ አገሮች በቀጥታ ድሀ ተኮር የሆኑ ፕሮግራሞች በአግባቡ ስለመተግበራቸው እርግጠኛ ለመሆን፣ በጋራ ከማቀድ ጀምሮ አፈጻጸማቸውና ያስገኙትን ውጤት በጋራ መገምገም የሚያስችላቸውን መድረክ ከመንግሥት ጋር በመፍጠር ባለፉት ሦስት ዓመታት፣ በያመቱ የአሥር ቢሊዮን ብር ዕርዳታ ሲሰጡ ቆይተዋል፡፡

ለሦስተኛ ጊዜ የተተገበረውንና በ2005 ዓ.ም. የተጠናቀቀውን የመሠረታዊ አገልግሎቶች ማሻሻያ ፕሮግራም የግማሽ ዓመት የበጀትና ዕርዳታ አፈጻጸም ግምገማ ከለጋሽ አገሮች ጋር በግዮን ሆቴል ማካሄድ የተጀመረው ሰኞ ግንቦት 4 ቀን 2006 ዓ.ም. ሲሆን፣ በመጪው ግንቦት 8 እንደሚጠናቀቅ ይጠበቃል፡፡

በግምገማው መክፈቻ ወቅት የገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስቴር ይፋ እንዳደረገው የመሠረታዊ አገልግሎቶች ማሻሻያ ፕሮግራም በጤና፣ በትህምርት፣ በግብርና፣ በውኃና በመንገድ ንዑስ ዘርፎች ላይ ለጋሾች ለአፈጻጸማቸው የገንዘብ ድጎማ ያደርጋሉ፡፡ የሠራተኞችን ደመወዝ፣ የሥራ ማስኬጃ በጀትና ሌሎች ወቅታዊ በጀት የሚያካትታቸውን የፕሮግራሙን ወጪዎችን ይደጉማሉ፡፡ በተለይም በሰው ኃይልና በአስተዳዳራዊ ዘርፎች፣ በፋይናንስና በጀት ግልጽነትና ተጠያቂነት ላይ ያተኩራሉ፡፡ በመሠረታዊ አግልግሎቶች ማሻሻያ ፕሮግራም ላይ  እስካሁን የታዩ ለውጦች ጥሩ የሚባሉ ቢሆኑም፣ በታዳጊ ክልሎች የተመዘገቡት ለውጦች ከታቀደው በታች ነው በማለት መረጃዎችን አቅርቧል፡፡

ከዕድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅዱ ተውጣጥቶ የቀረበው የ2005 በጀት ዓመት የመሠረታዊ አገልግሎቶች ማሻሻያ ፕሮግራም ውጤቶች ሪፖርት ላይ ጥቂት የማይባሉ መስኮች ላይ ከታቀደው በታች ውጤት መመዝገቡን ቢገልጽም፣ ክልሎች ሳይቀበሉት ቀርተዋል፡፡

በትምህርት መስክ በአንደኛ ደረጃ የትምህርት ሽፋን ላይ የተመዘገቡትን ውጤቶች በማስመልከት ገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስቴር እንዳቀረበው፣ ባለፈው በጀት ዓመት ከአንደኛ እስከ ስምንተኛ ክፍል የተመዘገው የተጣራ የተማሪዎች ቁጥር 86 ከመቶ አቅራቢያ ነው፡፡ በዕቅድ ይመዘገባል የተባለው መጠን ግን 94 ከመቶ ገደማ ነው፡፡ ይህም ማለት በመላ አገሪቱ ከአንድ እስከ ስምንት የሚሰጠው የትምህርት አገልግሎት ሽፋን 94 ከመቶ ይደርሳል የሚል ነበር፡፡ ከአምስተኛ እስከ ስምንተኛ ክፍል ባለው የትምህርት ዕርከንም ይጠበቅ የነበረው የተማሪ ቁጥር 69 ከመቶ አቅራቢያ ሲሆን፣ በተጨባጭ የተመዘገበው ግን 47 ከመቶ በመሆኑ ከዕቅዱ በብዙ ርቆ ታይቷል፡፡ የስምንተኛ ክፍልን የሚያጠናቅቁ ተማሪዎች ቁጥር በአገር አቀፍ ደረጃ 53 ከመቶ አቅራቢያ ሲሆን፣ ይጠበቅ የነበረው ግን 78 ከመቶ ይደርሳል ተብሎ ነበር፡፡

ከ86 ከመቶው አገራዊ አማካይ ውጤት በታች ውጤት አስመዝግበዋል የተባሉት ክልሎች፣ አፋር ክልል 42 ከመቶ በማስመዝገብ ዋናው ሲሆን፣ አዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር 69 ከመቶ፣ ሐረሪ ክልል 75 ከመቶ በማስዝገብ ወደኋላ መቅረታቸው ተመልክቷል፡፡ ከዚህ ባሻገር በመምህራን ሥልጠናና ብቃት ላይም አማራ፣ አፋር፣ ሶማሌና ደቡብ ሕዝቦች በዝቅተኛ ደረጃ ውጤት ያሳዩ ተብለው ተተችተዋል፡፡

የቀረቡትን አኃዞች የአዲስ አበባ አስተዳደርም ሆነ የአፋርና የሶማሌ ክልሎች አጣጥለዋል፡፡ የአፋር ክልል ያጣጣለው የራሱን መረጃ በማጣቀስ ሲሆን፣ በክልሉ የሠለጠኑ የአንደኛ ደረጃ መምህራን ቁጥር 95 ከመቶ ደርሶ እያለ ገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስቴር 53 ከመቶ አቅራቢያ ነው ማለቱ ከምን በመነሳት እንደሆነ እንዲገለጽለት ጠይቋል፡፡ የአዲስ አበባ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ በበኩሉ በተማሪዎች ቁጥር ላይ ያለበትን ችግር ይፋ አድርጓል፡፡ ለአንደኛ ደረጃ ትምህርት ዕድሜያቸው የደረሱ ሕፃናት ትምህርት የሚጀምሩት በሰባተኛ ዓመታቸው ነው፡፡ ቢሮው አንደኛ ደረጃ ትምህርታቸውን የሚያጠናቅቁበት ዕድሜም 14 ዓመት መሆኑን ገልጾ፣ በአዲስ አበባ ከሚገኙ አንደኛ ደረጃ ተማሪዎች ውስጥ 40 ከመቶው በግል ትምህርት ቤቶች የሚማሩና ከተቀመጠው የትምህርት ዕድሜ በታች የአንደኛ ደረጃ ትምርትን የሚጀምሩና የሚያጠናቅቁ በመሆናቸው፣ ስታቲስቲካዊ መረጃ አያያዝ ላይ መቸገሩን አመልክቷል፡፡

በግል ትምህርት ቤቶች ውስጥ የሚማሩት ሕፃናት አንደኛ ደረጃ ትምህርት የሚጀምሩት በስድስት ዓመታቸው ሲሆን፣ የሚያጠናቅቁትም በ13ኛ ዓመታቸው ነው፡፡ ይህንን የገለጸው የአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ፣ ከዚህ ባሻገርም ከመደበኛው የትምህርት ዕድሜ በላይ የሆኑ ታዳጊዎች በማታው ክፍለ ጊዜ ትምህርታቸውን የሚከታተሉ በመሆኑ እነሱም የሚያካትት አኃዝ እንዳልቀረበ ይፋ አድርጓል፡፡

የትምትርት ሚኒስቴር ዴኤታ አቶ ፉአድ ኢብራሒም በበኩላቸው በአሁኑ ወቅት 22 ሚሊዮን ተማሪዎች በአገሪቱ እንደሚገኙ ገልጸው፣ ሁለት ሚሊዮን አዲስ ተማሪዎች ወደ ትምህርት ገበታው መምጣት እንደቻሉ ተናግረዋል፡፡ ትምህርት ማቋረጥና መቅረት አሳሳቢ መሆኑን ያመኑት አቶ ፉአድ፣ ይህም ሆኖ በመረጃ አሰባሰብ ላይ ከማዕከላዊ ስታቲስቲክስ ኤጀንሲ ጋር ልዩነት እየታየ በመሆኑ የአኃዝ ተቃርኖ መፈጠሩን ገልጸዋል፡፡ ኤጀንሲው የሚሰበስበው መረጃ በቤሰተብ ደረጃ ሲሆን ትምህርት ሚኒስቴር ግን ከየትምርት ቤቶቹ መረጃ የሚሰበስብ በመሆኑ በመረጃ ምንጭ ላይ ያለው ልዩነት ችግር እየፈጠረ መሆኑን አስታውቀዋል፡፡ በአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ ከቀረበው የዕድሜ ጉዳይ በተጨማሪ 44 ትምህርት ቤቶች ለግምገማው አለመካተታቸውን አቶ ፉኣድ ተናግረዋል፡፡

በግብርና በኩል የታየው ችግር በኤክስቴንሽን ሠራተኞች ቁጥር ላይና በምርታማነት ላይ ያተኮረ ነው፡፡ ባለፈው ዓመት በሔክታር ይጠበቅ የነበረው ምርት ከ19 ኩንታል በላይ ቢሆንም፣ ውጤቱ ግን በሔክታር 18 ኩንታል አልሞላም፡፡ በዋና ዋና ሰብሎች ላይ የታየው አዝጋሚ ምርታማነት በዕድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅዱ መሠረት ወደ ኋላ ሊቀር ችሏል ተብሏል፡፡ በዚህ አኃዝ ላይ ደስተኛ ያልሆኑት የግብርና ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታው አቶ ወንድይራድ ማንደፍሮ ያለፈው ዓመት መረጃ የዚህን ዓመት አፈጻጸም ሊገልጽ የማይችል ከመሆኑም በላይ፣ ባለፈው ላይ ከመነጋገር አሁን ባለው ላይ መወያየት እንደሚመርጡ ተናግረዋል፡፡ በዚያም ላይ ባለፈው ዓመት የተዘራው በዚህ ዓመት ውጤት የሚሰጥ በመሆኑ ምክንያት፣ ያለፈው ዓመት ዝቅተኛ ነው ብሎ መደምደም አስቸጋሪ መሆኑን ተናግረዋል፡፡ በጤና በኩልም በጤና ኤክስቴንሽን ሠራተኞች ቁጥር ከጊዜ ወደ ጊዜ እያሽቆለቆለ መምጣት ላይ ሪፖርት ቀርቦ ጤና ጥበቃ ማብራሪያ ሰጥቷል፡፡ በድኅረ ወሊድ እንቅብካቤና በፀረ አምስት ሦስተኛ ዙር ክትባት አግልግሎት ላይም የታዩ ለውጦች ለቤቱ ቀርበዋል፡፡  ጤና ጥበቃ የመረጃ ጥራትና ብዛት፣ የአስተዳደር ችግር፣ ከታሰበው ዓላማ ማፈንገጥ የመሳሰሉት ችግሮች በክልሎች እያጋጠመው መሆኑን አስታውቋል፡፡

በመንገድ ዘርፍ ላይ የታውን በተመለከተ እንደቀረበውም ከዚህ በፊት በሁሉም ዓይነት የአየር ጠባይ የሚያገለግሉ መንገዶች ሽፋን እተሸሻለ መምጣቱ ታይቷል፡፡ ከአራት ዓመት በፊት ከነበረው ወደ እነዚህ መንገዶች ለመድረስ 3.7 ኪሎ ሜትር መንገድ መጓዝ ይጠይቅ የነበረ ሲሆን፣ ባለፈው ዓመት ወደ 2.1 ኪሎ ሜትር ዝቅ ማለቱ ተጠቁሟል፡፡ በጥሩ ደረጃ ላይ የሚገኙ መንገዶች ሽፋን 90 ከመቶ የደረሰ ሲሆን፣ በዕቅድ የሚጠበቀው ግን 85 ከመቶ ገደማ ነበር፡፡

ከገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስቴር ባሻገር የእንግሊዝ ዓለም አቀፍ የልማት ትብብር ተቋም (ደፊድ)ም በበጀት፣ በፋይናንስ ግልጽነትና ተጠያቂነት እንዲሁም በሌሎች መስኮች ላይ ታይተዋል ያላቸውን ጉድለቶችና ጥሩ ውጤቶችን አስገኝተዋል ያላቸውን አፈጻጸሞች ገምግሟል፡፡

በኢትዮጵያ የዓለም ባንክ ዳይሬክተርና የለጋሽ አገሮች ተወካይ ጉዋንግ ዚ ቼን እንደተናገሩት፣ ምንም እንኳ ላለፉት ሦስት ዙሮች ሲተገበር የቆየው ፕሮግራም ለውጦችን ቢያስመዘግብም ችግሮች ግን አልተለዩትም፡፡ በመሠረታዊ አገልግሎት ማሻሻያ ፕሮግራሙ ላይ ከሚቀርቡ ዕቅዶች ውስጥ በበጀት አጠቃቀም ላይ የታዩ ችግሮች መኖራቸውን ጠቁመዋል፡፡ በመንገድ ዘርፉ ላይ የሚመደብ ፈንድ በአግባቡ ጥቅም ላይ አለመዋሉ፣ የሀብት አመዳደብ ችግር፣ የበጀት አደላደል፣ የመረጃ ምንጭ ላይ ችግሮች መኖራቸውን ጠቁመዋል፡፡ ጥራት ያለው መረጃ በወረዳና በቀበሌ ደረጃ ባሉ መዋቅሮች ላይ ማግኘት አስቸጋሪ መሆኑን የጠቆሙት ቼን፣ የአገልግሎት አሰጣጡ በሠራተኛው ላይ የሚንጠለጠል በመሆኑም የሰው ኃይል ላይ ትኩረት ሊደረግ ይገባል ብለዋል፡፡

በትምህርት፣ በጤና፣ በግብርናና በውኃ አቅርቦቶች ላይ የፌደራል መንግሥት ድጋፍ በሚሰጣቸው ታዳጊ ክልሎች ላይ ጎልቶ ታይቷል፡፡ ይህንን በተመለከተ ሪፖርተር ያነጋራቸው የዓለም ባንክ ዳይሬክተር፣ ክልሎቹ ራሳቸው ከዝቅተኛ ደረጃ ላይ እየተነሱ ያሉ በመሆኑ ነው ብለዋል፡፡

የገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስትር ዴኤታ ዶክተር አብርሃም ተከስተ ምንም እንኳ የመሠረታዊ አገልግሎቶች አቅርቦት እየተሻሻለም ቢሆንም፣ ዕርዳታ ሰጪ አገሮች ቃል ከገቡት ውስጥ የተወሰነ መጠን እስካሁን እንዳልቀቁና በቀሩት ወራት ውስጥ በጀቱን እንዲለቁ አሳስበው ነበር፡፡ ስለዚህ ጉዳይ ሪፖርተር ጥያቄ ያቀረበላቸው ቼን በበኩላቸው አልተቀቀም የተባለው በጀት በዝቅተኛ አፈጻጸም ጋር የተያያዘ መሆኑን ይፋ አድርገዋል፡፡ በተለይ የተመደበው ገንዘብ እንዴትና በምን አኳኋን ሥራ ላይ እንደዋለ በአግባቡ መረጃ ስለማይገኝ፣ የሚሰጠው ዕርዳታ ሊዘገይ መቻሉን ቼን ተናግረዋል፡፡

በገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስቴር የቻናል አንድ ፕሮግሞች አስተባባሪ አቶ ጌታቸው ነገራ ግን በታቀደው መሠረት ገንዘብ መለቀቁን ይናገራሉ፡፡ ለ2005/2006 በጀት ዓመት ፈሰስ ይደረጋል የተባለው በሙሉ ተለቅቋል ያሉት አቶ ጌታቸው፣ ከግንቦት ወር በኋላ መለቀቅ አለበት ተብሎ በሚጠበቀው የበጀት መጠን ላይ ያተኮረ ግምገማ እየተካሄደ መሆኑን ገልጸዋል፡፡ 

Tuesday, May 13, 2014

ለመላው የኢትዮጵያ ህዝብና በተለይ ለሀገር ተረካቢ ወጣትና ምሁራን ብሎም በውጪ ለሚገኙ ዜጎች!! ከባለራዕይ ወጣቶች ማህበር የተሰጠ መግለጫ

May 13/2014

ስፊው የኢትዮጵያ ሕዝብ በሀገራቸው ሉአላዊነት እና በህዝቦች መፈቃቀድ መፈቃቀርና መኖር ዙሪያ ማንም ሰንካላ ምክንያት በማቅረብ እንዲበታትነው መፍቀድ የለበትም በተለይ ይመራናል ያስተዳድረናል በምንለው መንግስት ከህዝቦች ፍቃድና እውቅና ውጪ በማስተዳደርና በመግዛት ዙሪያ ያለው የተራራቀ ልዩነትና የመንግስታችን አተያየም የመግዛት በመሆኑ የግዛት ጊዜውን በማራዘም የጭቆና ቀንበሩን ለማፅናት ሲል ለ3 ሺ ዘመናት የነበራትን ታሪክ በማበላሸትና በዚያ አኩሪ ታሪኳም ለዜጎች ብቻ ሳይሆን ለአፍሪካ የነፃነት ተምሳሌትና ኩራት የሆነች ባላት ታሪክና ትሩፋት በተለይ በህዝቧ ያኗኗር ዘይቤ በኢትዮጵያ እድገት ውስጥ ያበበና ጎልቶ የወጣ ልዕልናዋም ከአጉረ አፍሪካ ተሻግሮ ለአለም መደነቂያ የሆነች ሀገራችን ላይ ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ አጥልቶ ያለው የተቃርኖ እዳ የእርስ በርስ ግጭት እንዲፈጠር እየተጠነሰሰ ያለና በተግባራዊነቱም ጎልቶ የታየበት ጊዜ አይታወስንም በመሆኑም ዜጎች በመንግስት ትንኮሳና ሸር እየተፈፀሙ ያሉት ዜጎችን ከቦታቸው የማፈናቀል ለጠየቁት ጥያቄ አወንታዊ እርምጃ መውሰድ በጋዜጠኞችና በጦማሪያን ላይ የእስር እንዲሁም በቶፎካካሪ ፓርቲ አባላትና መሪዎች ላይ የሚደርሰው እንግልትና ወከባ የዚህች ሀገር ጎዞ ወዴት እያመራ ነው የሚለው እጅግ አሳሳቢ ነው ከዚህም በተረፈ በሚፈጠረው ግርግር ሰፊው የሀገራችን ህዝብ ተጎጂ የሚሆን በመሆኑና በተለይም በግንባር ቀደምነት የሀገራችን አምራችና አንቀሳቃሽ ብሎም ሀገር ተረካቢና አንቀሳቃሽ በምንለው ወጣት እጅጉን እየከፋ በመሄዱና ለጥቃትም ተጋላጭ በመሆኑ ይህን መግለጫ ለማውጣት ተገደናል፡፡
1. የሀገራችንን ህዝቦች ለመከፋፈልና ወደ ማያቋርጥ እልቂት ለመምራት በፈጠራ ታሪክ ላይ ተመስርቶ እየተሰራበት ያለው ሴራ ባስቸኳይ እንዲቆም እና የእልቂት መነሻ የሚሆን በተለይም አኖሌ የተገነባው ሀውልት ባስቸኳይ እንዲፈርስ በምትኩም ህዝቦች በጋራ ተቻችለው የሚኖሩበትና የጋራ አሴት ሊፈጥር የሚችል የመደጋገፍና የመረዳዳት ህልውናውን የሚያጠናክር መዘከር እንዲሰራ እንጠይቃለን፡፡
2. መንግስት በህዝቡ ዘንድ መግባባትና መፋቀር እንዲሰራና ሀገራችን ለዜጎችም ብሎም ለወጣቶች ምቹ ማድረግ ሲጠበቅበት ዜጎችን ኢ.ህገ መንግስታዊ እና ኢ-ፍታዊ በሆነ መልኩ በሀገራቸው በየትኛውም ክፍለ ሀገር የመኖርና ሀብት የማፍራት መብታቸውን በመጣል ከቄያቸው እና ተከባብረው እና ተፋቅረው ከኖሩት ህዝብ በሀይል የማፈናቀል እርምጃ ባስቸኳይ እንዲቆም ይህን ያደረጉም የመንግስት ባለስልጣናት ለህግ እንዲቀርቡ እንጠይቃለን፡፡
3. መንግስት በሀገሪቱ ህገ-መንግስት አንቀጽ 29 ላይ የአመለካከትና ሐሳብን በነፃ የመያዝና የመግለፅ መብትን በመጣስ በጋዜጠኞች በጦማሪያንና በፅሑፎች ላይ በቅርቡ የጅምላ እስር አከናውኗል በመሆኑም በሀገሪቱ የህጎች ሁሉ የበላይ የሆነው ህገ-መንግስት ለዜጎች ህልውና በሚል ያዘጋጀው መንግስት እራሱ ጥሰት በመፈፀም የወሰደው ኢ-ፍታዊ እርምጃ ዜጎች የመናገር ሀሳባቸውን በነፃነት በመግለፅና የመፃፍ መብትን በመተላለፍ የተወሰደ እርምጃ በመሆኑ ባስቸኳይ እንዲፈቱ እየጠየቅን ዜጎች የሚያከብሩትን ህገ-መንግስት ያዘጋጀው አካል መንግስትም ህገ-መንግስቱን እንዲያብብ አለበለዚያ ግን ሰፊው የኢትዮጵያ ህዝብ መብቶችን ለማስከበር በሚያደርገው ትግል ከሚከተለው አላስፈላጊ እልቂትና ጉዳት በፊት ከወዲሁ እልባት እዲበጅለት እናሳስባለን፡፡
4. መንግስት የአዲስ አበባን ከተማ ማስተር ኘላን ተከትሎ ቤተሰቦቻችን ያፈና ቀላል እርስት አልባ እና ቀጣሪ እንዲሁም ስራ ፈት በማድረግ ለድህነት ይዳርጋል በሚል ዩንቨርስሪቲዎች ለተጠየቀው ስላማዊ ጥያቄ በሰላማዊ መንገድ በጠረጴዛ ዙሪያ መፍታት ሲቻል ዜጎች ላይ ሊያውም የሀገሪቱ ኢፍታዊ እርምጃ አግባብነት የሌለውና ይህን ያደረጉ አካላትም ሆነ ትዛዝ ያስተላለፈ አካል፡፡
የተማረ ብሎም ወጣትና ትኩስ እንዲሁም ሀገር ተረካቢ በሆነው ትውልድ ላይ የተወሰደው ኢፍታዊ እርምጃ አግባብ አይደለም ስንል እያወገዝን ይህ ድርጊት በንፁዋን ዜጎች ላይ እርምጃው እንዲወሰድ ያዘዙና እርምጃውን የወሰደ ባለስልጣናትም ሆነ ፌደራል ፓሊስ አባላት ለህግ እንዲቀርቡ እንጠይቃለን፡፡
5. በተለይ ከዚህ ጥያቄ ጋር ተያይዞ ችግሩን የብሔር ችግር ለማስመሰልና ወደ አላስፈላጊ ቀውስ ለመምራትና የእርስ በርስ ግጭት እንዲሆን ለማድረግና የመብትና የህይወት ጥያቄን በሌላ መልኩ ጥላሸት በመቀባት ለማጥቆር መምከር እጅግ አሳስቦናል በአሰቃቂ ጭፍጨፋ በአለም ሆነ በውጭ የሚገኘው አንዳንድ ፅንፈኛና ጎጠኛ ሰዎች እየተካሄደ ያለው ደባ ባስቸኳይ እንዲቆም እየጠየቅን ለሀገራችን እድገትና ብልፅግና ከጥላቻ ፓለቲካ እና ዘር መሠረት ካደረገ አድሎ በመቆጠብ ፍታዊ አሰራር እንዲሰፍን ዜጎችም ለ3ሺ ዘመን ተፋቃቅረውና ተቻችለው በመኖር ለተቀረው አለም ምሳሌ መሆን እንደተጠበቀ ሆና ቢስራ የተሻለ ነው እንላለን፡፡
6. የዜጎች ሰብአዊና ህገ-መንግስታዊ መብታቸው ተጠብቆ በመፈቃቀደና በመፈቃቀር ላይ የተመሠረተችዋን ኢትዮጵያችንን ደግሞ ለማየት የተፍካከረ ፓርቲዎች በሰላማዊ መንገድ የሚያደርጉት ትግል ክልከላና እንቅፋት መደርደር ኋላ ለሚመጣው ችግር ተጠያቂ የሚሆን መንግስት በመሆን በዋነኝነትም ተጎጂው እና የችግሩ ግንባር ቀደም ገፈት ቀማሽ ወጣቱ ትውልድ ነውና ይህ ችግር ከመከሰቱ በፊት የፖለቲካ ምህዳሩ ሰፈር ክፍት እንዲያደርግ መንግስትን እየጠየቅን አማራጭ ያለውና እኔ እበልጥ እኔ ብሎ በሚፎካከሩ የፓለቲካ ፓርቲ መካከል ምርጫው ለህዝብ ትቶ በጠላትነት መታየትና መወነጃጀል ለሀገራችንም ሆነ ለህዝባችን ስለማይበጅ ከወዲሁ የመግባባት መድረክ እንዲኖር እንጠይቃለን፡፡
ኢትዮጵያዊ አንድነታችን ከልዩነታችን በላይ ነው!! ባለራዕይ ወጣቶች ማህበር፡፡
ግንቦት 02/08/2006 ዓ.ም

አቶ አሥራት አብርሃ ለምን አንድነት ፓርቲን ተቀላቀሉ? – በዘሪሁን ሙሉጌታ

May 13/2014

ቀደም ሲል በአረና ትግራይ ለዲሞክራሲና ለሉአላዊነት ፓርቲ (አረና) ውስጥ የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ የነበሩትና በኋላ ከፓርቲው ጋር በተፈጠረ “የስትራቴጂክ ልዩነት” ከአረና ፓርቲ ወጥተው በግል ሲንቀሳቀሱ የነበሩት አቶ አሥራት አብርሃም ከሰሞኑ ወደ አንድነት ፓርቲ ገብተዋል። አቶ አሥራት በቋንቋና ስነ-ፅሁፍ ከዲላ ዩኒቨርስቲ የመጀመሪያ ዲግሪ ያላቸው ሲሆን በአሁኑ ወቅት በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የፍልስፍና ትምህርት የሁለተኛ ዲግሪአቸውን በማጠናቀቅ ላይ ናቸው። አቶ አስራት ወደ አንድነት ፓርቲ ስለተቀላቀሉበት ምክንያት ለሰንደቅ ጋዜጣ አስተያየታቸውን ሰጥተዋል።
አቶ አሥራት ወደፓርቲው ስለገቡበት ምክንያት ተጠይቀው፤ ሲመልሱ ከአንድ ዓመት በፊት ከአረና ወጥተው ከቆዩ በኋላ ከፖለቲካ ስሜት ውጪ ሆነው አለመቆየታቸውን፣ በጋዜጣና በመፅሔት ከሚያቀርቡት መጣጥፍ ባሻገር ወደፓርቲዎች አካባቢ ጎራ በማለት የራሳቸውን ኃሳብ ሲያቀርቡ ከቆዩ በኋላ በግል ከመንቀሳቀስ በፓርቲ ታቅፈው መታገል ስለመረጡ፣ በአንድነት አካባቢ ያሉ ጓደኞቻቸው ባደረጉባቸው ገንቢ ግፊት አንድነት ፓርቲንም በቅርብ ስለሚያውቁት መሆኑን አስረድተዋል።
አቶ አሥራት ወደ አንድነት ፓርቲ የተቀላቀሉት በጓደኞቻቸው ግፊት ብቻ ሳይሆን ፕሮግራሙንም በማየት እንደሆነ ተናግረዋል። በተለይም አቶ ስዬ አብርሃ ጋር በትግራይ ክልል ተምቤን ወረዳ ሲወዳደሩ በትግርኛ ቋንቋ የተተረጎመውን የአንድነት ፓርቲ ፕሮግራም ቅጂ በማንበባቸውና በመድረክ ፓርቲ ውስጥ በነበራቸው ተሳትፎ ወቅት ከአንድነት ፕሮግራም ጋር በመተዋወቃቸው እንደሆነ ገልጸዋል። በተጨማሪም ቀደም ሲል ከነበሩበት የአረና ፓርቲ ፕሮግራም በብዙ መልኩ ተቀራራቢ ሆኖ ስላገኙትም እንደሆነ ይናገራሉ።
በአቶ አሥራት እምነት የአንድነት ፓርቲ ፕሮግራም በሀገሪቱ ተጨባጭ ሁኔታ ሲያዩት ለእኛ ሀገር ሁሉንም አስተሳሰቦችና ድምፅ ሊያሰባስብ የሚችል ፕሮግራም ስለሆነ ወደ ፓርቲው መግባታቸውን የሚያስረዱት አቶ አሥራት የአንድነት ፕሮግራም የግለሰብንና የቡድንን (Group) መብት መኖርን የተቀበለ፣ ከአማርኛ በተጨማሪ ኦሮምኛም የሀገሪቱ ተጨማሪ የፌዴራል መንግስት የስራ ቋንቋ እንዲሆን በፕሮግራሙ ያስቀመጠና በብዙ መንገድ ተራማጅ ሊባል የሚችል ፕሮግራም በመሆኑ ነው ብለዋል። ፓርቲው ባዘጋጀው የአምስት ዓመት የስትራቴጂ እቅድ ዘጠና በመቶ ስለሚስማሙ ፓርቲው ታግሎ ስለሚያታገል እንደሆነም ያስረዳሉ።
“በእኔ እምነት መካከለኛ በሆነው የፖለቲካ አስተሳሰብ እስማማለሁ። ቀኝና ግራ ጠርዝ ያልያዘ ፖለቲካ በሀገራችን ስለሚያስኬድ በዚህ ምክንያት ነው የገባሁት” ሲሉ አቶ አሥራት ያስረዳሉ።
የአንድነት ፕሮግራምና የአረና ፕሮግራም ተቀራራቢ ከሆነ ለምን ከአረና ወጥተው ወደ አንድነት እንደገቡም አቶ አስራት ተጠይቀው ሲመልሱ፤ “ከአረና ወጥቼ ወደ አንድነት አልገባሁም። ከአረና ወጥቼ ወደ ልጄና ሚስቴ ነው የተመለስኩት። ከአረና እንደወጣሁ ወደ አንድነት እገባለሁ ብዬ አላሰብኩም። ከአረና የወጣሁትም በአንዳንድ የስትራቴጂ አካሄድ ላይ መግባባት ባለመኖሩ፣ አዳዲስ ባህሪያትን በፓርቲው በመመልከትና የዛ ችግር አካል ላለመሆን ነው የወጣሁት። ከወጣሁም በኋላ የግል ስራ ስሰራ ቆየው እንጂ አንድነት ከአረና ስለሚሻል አይደለም ወደ አንድነት የገባሁት” ሲሉ መልሰዋል። በተጨማሪም ሰው እንደመሆናቸው በሂደት አቋማቸውን በመቀየራቸው እንዲሁም በቀጣይ አረና እና አንድነት ይዋሃዳሉ ከሚል ተስፋ በመነሳት ጭምር እንደሆነ ገልጸዋል።
የእሳቸው ወደ አንድነት መግባት አረና እና አንድነትን በማዋሃድ ረገድ ስለሚፈጥረው የፖለቲካ አቅም የተጠየቁት አቶ አሥራት፤ ቀደም ሲል ከአረና ጋር ያላቸው ግንኙነት የተሻለ በመሆኑ የእሳቸውን አስተዋፅኦ እንደሚያደርጉ፣ እንዲሁም የአረና ፓርቲ አባላት የእሳቸውን ወደ አንድነት ፓርቲ መቀላቀል በቴሌፎን በመደወል እንዳበረታታቸው ጭምር ተናግረዋል። ሁለቱን ፓርቲዎች እንዲዋሃዱም የተሻለ ነገር ሊፈጠር እንደሚችል ተስፋ እንዳላቸው ነው የጠቀሱት። የእሳቸውም አገባብ “ከአንድ ጢስ ወደ አንድ ጢስ” የመቀያየር ካልሆነ በስተቀር አንድነትና አረና ያንያህል ልዩነትና እርቀት አለን ብለን አናስብም ብለዋል።
ይሁን እንጂ አረና በክልል የተደራጀ የብሔር ፓርቲ ከመሆኑ አንጻር ከአንድነት ጋር ስለሚያቀራርባቸው ጉዳይ የተጠየቁት አቶ አሥራት ሁለት ነገር ጠቅሰዋል። የመጀመሪያው አረና የክልል ፓርቲ የሚያስብለውና የብሔር ፓርቲ የሚያስብለውን ልዩነት አስቀምጠዋል። አረና የአንድ ብሔር ሳይሆን የአንድ ክልል ፓርቲ ነው። አብዛኛዎቹ የፖለቲካ አቋሞቹ ላይ በተለይም የመድረክ ሁለተኛው ጉባኤው ላይ የመድረክን ፕሮግራም ሲቀበል በመድረክ ደረጃ የተቀበልነውን በተወሰነ ደረጃ በአረና በሚስማማ መልኩ ነው የወሰደው። እና ብዙ ከአንድነት የሚራራቅ ነገር የለውም” ሲሉ የገለፁት።
የእሳቸው ወደ አንድነት መግባት በመጠኑ የአለመተማመን ስሜት የሚንፀባረቅበትን የሰሜን ፖለቲካና የመሀል ሀገር ፖለቲካ በማቀራረብ ረገድ ስለሚያኖራቸው ሚና ተጠይቀውም ሁኔታው የበለጠ ወደፊት የሚታይ ቢሆንም አንድነት ከዚህ ቀደም ከሚታወቁ የመሃል ሀገር የፖለቲካ ፓርቲዎች በተወሰነ መጠን ለየት የሚልበት የራሱ አሳታፊ (accommodate) ባህሪ አለው። ፓርቲው የተለያየ ብሔርና አስተሳሰብ በአንድ ዓላማ ዙሪያ ለማሰባሰብ የሚጥር ፓርቲ ሆኖ የአስተሳሰብና የሰዎች ብዙህነት የሚንፀባረቅበት ፓርቲ ነው። አንድነት ፓርቲ ስትገባ ሁሉንም ኢትዮጵያዊ የምታገኝበት የተለያዩ ቋንቋዎች የሚነገርበት ሰፋ ያለ የብሔር ስብጥርና አይነት ያለው ፓርቲ ስለሆነ ከሌሎች የመሃል ሀገር ፖለቲካ ፓርቲዎች ይለያል ብለዋል። ችግሩ ያለው ከአንድነት ፓርቲ አደረጃጀት አንጻር ሳይሆን ከገዢው ፓርቲ መሆኑን የሚጠቅሱት ገዢው ፓርቲ በህብረብሔር የተደራጁ ፓርቲዎችን አንድ አይነት ቀለም እንዲኖራቸው ከመፈለጉም በላይ ወደ አንድ ጥግ ሊያሲዛቸው እንደሚፈልግ ጠቅሰዋል። በዚያው መጠን አንድነት ፓርቲንም የአንድ ብሔር ፓርቲ አድርጎ የመፈረጅ ዝንባሌና ፍላጎት እንዳለ ጠቅሰዋል። በአንፃሩ አንድነት የሚለይበት የራሱ የሆነ ብዙ ቀለማት ያሉት ፓርቲ ነው ብለዋል።
ቀደም ሲል በአንድነት ፓርቲ ውስጥ “የአማራ ብሔር የበላይነት አለው” የሚለው የአንዳንድ ልሂቃንን አስተያየት በተጨማሪ የቀድሞ የአንድነት ሊቀመንበር ዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳ መድረክን በተመለከተ በአንድነት ፓርቲ ውስጥ የነበራቸው አቋም በሌሎች የፓርቲው አመራሮች የሃሳብ የበላይነት ከመሸነፋቸው አንጻር እሳቸው (አቶ አሥራት) ወደአንድነት የመግባታቸው እንደምታም ምን እንደሆነ ተጠይቀው፤ አንድነት ፓርቲ የአማራ ብሔር የበላይነት አለው ብለው የሚያስቡ ልሂቃን በቁጥር ምንያህል ብዙ ስለመሆናቸው ጥርጣሬ እንዳላቸው ገልፀዋል። ይልቁኑ ይህ አመለካከት ከኢህአዴግ አካባቢ የሚደመጥ መሆኑን ጠቅሰው ዋናው ነገር ግን የፓርቲው ፕሮግራም ነው ብለዋል።
ከዚህ በተጨማሪ ወደ ፖለቲካ ትግል የሚገባ ሰው የእገሌ ብሔር ስለበዛና ስላነሰ እያለ ወደ ትግል መግባት የለበትም። ዋናው ነገር በፕሮግራሙና በሕገ ደንቡ ይመራል የሚለው ነው። በተጨባጭ አሁን ባለው ሁኔታ የአንድነት የስራ አስፈፃሚ አባላት ስብጥር ከአብዛኛዎቹ የኢትዮጵያ ክፍሎች የተውጣጡ ናቸው። በፓርቲው የአማራ የበላይነት አለ ቢባል እንኳ ጫፍ ይዞ ውጪ መቅረት ሳይሆን ገብቶ ተመጣጣኝ ውክልና እንዲኖርና የሁሉንም ኢትዮጵያዊ የሚወክል አመራርና አባል እንዲኖር መታገል ነው ብለዋል።
አቶ አሥራት ከአረና ፓርቲ ከወጡ በኋላ በዩኒቨርስቲ ቆይታቸው ወቅት የኀሳብ አመንጪ ምሁራን (Think thank) ለማቋቋም ጥረት ሲያደርጉ እንደነበር ይታወቃል። ጥረቱ ስላልተሳካ ወደ ፓርቲ ፖለቲካ ተመልሰው እንደሆነም ተጠይቀው ነበር። እሳቸውም የተባለው ሃሳብ አመንጪ አካል በተፈለገው መጠን ባይሄድም በቅርቡ ግን ፍልስፍና የሚያጠኑ ምሁራን ዶ/ር ዳኛቸው አሰፋ ጭምር ያሉበት “Think Ethiopia” የሚል ቡድን መቋቋሙን ገልጸዋል። ቡድኑ በአመዛኙ ፍልስፍና ላይ እንዲያተኩር መደረጉንም አስረድተዋል። ወደ አንድነትም የገቡት ታስቦ የነበረው ሰፋያለ ፖለቲካ ሃሳብ አመንጪ ቡድን ባለመሳካቱም እንደሆነም ጠቅሰዋል።
በምርጫ ዋዜማ ወደ ፖለቲካ ፓርቲ መግባታቸው ከስልጣን ፍለጋ ጋር ስለመያያዙም አቶ አሥራት ተጠይቀው ማንኛውም ፖለቲከኛ ትክክለኛ ስልጣን እንደማይጠላ ጠቅሰው፣ ነገርግን ስልጣን ያለው ኢህአዴግ ጋር መሆኑን አስረድተዋል። በእሳቸው እምነት በአረና ፓርቲ ውስጥ እያሉ ትልቅ ስልጣን እንደነበራቸው አስታውሰው ነገር ግን ፓርቲዎቹ ውስጥ ከስልጣን ይልቅ ትግል ወይም የስራ ክፍፍል ብቻ ነው ያለው ሲሉ መልሰዋል። በፓርቲው ውስጥ ለታችኛውም ሆነ ለላይኛው የአመራር አካል ኀሳብ በመስጠት በማንኛውም የፓርቲው ደረጃ ላይ በመሆን ለመስራት መዘጋጀታቸውን ገልጸዋል።
1619254_634234963328108_581967544042254518_n

ዶ/ር ሼክስፒር ፈይሳ የሃይለመድህን አበራን ጉዳይ ለመከታተል ወደ ጄኔቫ አመራ

May 13, 2014
 የኢትዮጵያ አየር መንገድ ረዳት ፓይለት ሃይለመድህን አበራን ጉዳይ ለመከታተል ኢትዮጵያዊው የህግ ባለሞያ ዶ/ር ሼክስፒር ፈይሳ ባለፈው ሳምንት ወደ ጄኔቭ-ስዊዘርላንድ ተጉዟል።
Ethiopian lawyer Shakespear Feyissa in Switzerland
ዶ/ር ሼክስፒር ፈይሳ ጄኔቭ-ስዊዘርላንድ
ሼክስፒር ፈይሳ የረዳት ፓይለቱን ጉዳይ ከሚኖርበት ከሲያትል ከተማ በቅርብ ሲከታተል ቆይቶ ነው ወደ ጄኔቭ ያመራው። ጄኔቭ እንደደረሰም የሃይለመድህን አበራን ጠበቃና ጉዳዩን ከሚከታተሉ አካላት ጋር በስፋት ተወያይቷል። በተለይ ከረዳት ፓይለቱ ጠበቃ ጋር ረጅም ሰዓታት በመውሰድ በበርካታ የህግና የቴክኒክ ጉዳዮች ላይ በጥልቅ ተነጋግሯል።
ረዳት ፓይለቱ ሙሉ በሙሉ ጤነኛ እንደሆነም ለማወቅ ተችሏል።
ኢትዮጵያዊ የህግና እንዳስፈለጊነቱ የህክምና ባለሞያዎች ጋር እንዲገናኝም ዶ/ር ሼክስፒር ምክር ሰጥቷል።
የረዳት ፓይለቱ ጠበቃ የስዊስ መንግስት ሃይለመድህን አበራን ለኢትዮጵያ አሳልፎ እንደማይሰጥና ግዚያዊ የስደት ፈቃድ እንዲሰጠው ውሳኔ መተላለፉን ያረጋገጠ ሲሆን – ጉዳዩ በቅርብ ጊዜ በሚሰየመው ግልጽ ችሎት እልባት እንደሚያገኝ አመላክቷል።
የሃይለመድህን አበራን ወደ ኢትዮጵያ ለማስመለስ በአቶ አስመላሽ ወልደ-ስላሴ የተመራ ከፍተኛ የኢህአዴግ ቡድን ጄኔቭ፣ ከርሞ ጥያቄው በስዊዘርላንድ መንግስት ውድቅ መደረጉ ይታወሳል።
ቡድኑ የስዊስ ፌዴሬሽን የህግ አካላትን ለማሳመን ካቀረበው ምክንያት ዋነኛው፣ ረዳት ፓይለት ሃይለመድህን አበራ የአእምሮ በሽተኛ መሆኑን እና ይህንንም የራሱ ቤተሰብ አባላት እንዳረጋገጡላቸው ገልጸዋል። የስዊዝ መንግስት ግን ጥያቄውን ውድቅ አድርጎታል። ለዚህም የሰጠው ዋነኛ ምክንያት፤ የሞት ፍርድን ተግባራዊ ለሚያደርግ መንግስት ማንንም አሳልፌ አልሰጥም የሚል ሲሆን ይህ ባይሆንም፣ በስዊዘርላንድ እና በኢትዮጵያ መሃል ተጠርጣሪ እስረኛን የማስመለስ ውል የለም ብለዋል።Ethiopian lawyer Shakespear Feyissa
ረዳት ፓይለቱ ለግዜው ሰው ማግኘት እንደማይፈልግ የተነገረ ሲሆን: ወንድሙ ዶ/ር እንዳላማው አበራ እና በጀርመን የምትኖር እህቱ ሃይማኖት አበራ ጄኔቭ ድረስ በመሄድ ሃይለመድህን አበራን ከሚገኝበት እስር ቤት ጎብኝተውታል።
ወጣት ሃይለመድህን አበራ ባለፈው የካቲት 10፣ 2006 ዓ.ም. የኢትዮጵያ አየር መንገድ ንብረት የሆነውን ቦይንግ 767 አግቶ ጄኔቭ ስዊዘርላንድ ላይ በማሳረፍ እዚያው የፖለቲካ ጥገኝነት መጠየቁ ይታወሳል። የአለም ዜና ርዕስ ሁሉ ትኩረት ስቦ የነበረው ይህ ልዩ ክስተት የኢትዮጵያን የሰብአዊ መብት ሁኔታና የአስተዳደር በደል አደባባይ በማውጣቱ የገዢው ፓርቲ አባላትን እጅግ እንዳበሳጨ ይነገራል።
አንዳንድ መገናኘ ብዙሃን እንደገለጹት የአጎቱ ድንገተኛ ህልፈት ርዳት ፓይለቱን አስቆጥቶት ነበር። የሃይለመድህን አበራ አጎት፤ ዶ/ር እምሩ ሥዩም ህይወት በድንገት ማለፍ ለብዙዎች ያልተፈታ እንቆቅልሽ ነው። ዶ/ር እምሩ ሥዩም የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ መምህር ነበሩ።
በአለም ዙሪያ ያሉ ኢትዮጵያውያን ወጣቱ ፓይለት ሃይለመድህን አበራን መደገፋቸውን እንደቀጠሉ ሲሆን በረዳት ፓይለቱ ስም የተከፈቱ ድረ-ገጾች እና የፌስቡክ መድረኮች ላይ አሁንም ሰፊ ዘመቻ በማድረግ ላይ ይገኛሉ።
ዶ/ር ሼክስፒር ፈይሳ በረዳቱ ጉዳይ ላይ ማንኛውንም ትብብር ለማድረግ ቃል የገባ ሲሆን የስዊስ ጠበቆችም በዚህ ከክፍያ ነጸ የሆነ ትብብሩ አድናቆታቸውን ገልጸዋል።

ETHIOPIA Government quietly disintegrating

May13/2014
Indian Ocean Newsletter
1034675
The general election looming ahead in 2015 is already casting a shadow over the Ethiopian government, whose sole uniting bond would seem to be its praise for the memory of its late Prime Minister Meles Zenawi.

His portraits are on all the walls in Addis Ababa, which was not the case when he was alive, and in the Federal Assembly a video projector plays his - See more at: http://satenaw.com/ethiopia-government-quietly-disintegrating/#sthash.AguStlIl.dpuf
speeches with the aim of inspiring the new MPs. And yet, since Meles Zenawi died in August 2012, the federal government has been rudderless, lacking a descendent.

His successor as Prime Minister, Haile Mariam Desalegn, has neither the grip nor the political clout and has not managed to impose himself on the other political leaders. He frequently has to be content with merely dealing with everyday business. While it is true the Ethiopian State, whose tradition goes back a long way, has not fallen into decadence, the different factions and regionalist tendencies are making federal power increasingly fragmented.

Divisions produce inertia ; Going beyond appearances, the ruling coalition Ethiopian People Revolutionary Democratic Front (EPRDF) is in an embryonic crisis state. Its central core, the Tigray People Liberation Front (TPLF), is deeply divided between the faction led by Tigray Regional State President Abay Woldu, and the faction headed by Deputy Prime Minister Debretsion Gebremichael, not to forget the various other Tigrayan sub-factions such as those of the elderly Marxist Sebhat Nega and the Meles Zenawi’s widow Azeb Mesfin.

Facing this inter-Tigrayan squabble, the Amhara in the ANDM and the Oromo in the OPDO (two of the parties in the ruling coalition) are watching from the wings, biding their time before they go into the arena. This freezes the decision-making power, as each faction does not want to make the wrong decision and yield an advantage to its rivals. In early April, speaking on a live TV debate (a rare event in itself), Amare Aregawi the editor of The Reporter asked the Prime Minister who is it that makes the decisions in his office and whether he is capable of making any himself. Much to the surprise of the viewers who are used to seeing decisiveness on their screens, Haile Mariam Desalegn mumbled an unconvincing response, confirming that the question had indeed struck home.

The economy and diplomacy are broken Ethiopian diplomacy suffers from a lack of leadership at the top of country. Questions about the situation in Somalia are left to the head of the Ethiopian army which is intervening directly in its neighbour territory. In the case of the IGAD mediation in the South Sudan crisis, the former foreign affairs minister Seyoum Mesfin was recalled from his post of ambassador to Beijing to lead the mediation. He nevertheless played a fairly effective role of mediator, which was largely taken over by the Ugandan President Yoweri Museveni even though Ethiopia did at the time hold the presidency of IGAD.

Similar blockages have produced similar effects in the management of the State-owned companies. The telephone network run by Ethio Telecom (formerly ETC) provides a very poor service, mainly because of frequent electricity outages which also affect the water distribution system when the electric pumps stop running. The cause is breakdowns of the aging transformers purchased from India by the Ethiopian Electric Power Corporation (EEPCO) several years ago. Today, EEPCO and ETC are squabbling over who should pay the cost of renovating the electricity system, a problem which Debretsion Gebremichael, the chairman of the EEPCO and ETC boards, has been unable to settle.

Regionalism becoming more intense Since the end of April, the federal police have brutally repressed student protests against the Master Plan in several universities in the Oromia Regional State. This Master Plan involves the expansion of Addis Ababa whose mayor, Diriba Kuma, is also an Oromo.
In the students view, this project would eat into Oromo land and reduce the area their language is used. This regionalist exacerbation is illustrated by certain of the student slogans, proclaiming “Oromia for the Oromos and by the start of misdemeanours against Amhara farmers obliged to leave their land and take refuge in Addis Ababa.

Certain TPLF officials have no qualms to explain that in their view, some ultra-regionalist elements of the ruling OPDO are discreetly fuelling this student protest movement against the Master Plan. - See more at: http://satenaw.com/ethiopia-government-quietly-disintegrating/#sthash.AguStlIl.dpuf

በሪያድ የአባይ ግድብ 3ኛ አመት ከብረ በዓል ላይ ኢትዮጵያውያን የሃገር ሽማግሌዎች እና የሃይማኖት አባቶች በአሸባሪነት መፈረጃቸው ተቃውሞ አስነሳ

May 13/2014

saudi11


በቅርቡ በሪያ የኢትዮጵያ ኮሚኒቲ አዳራሽ የተከበረውን የአባይ የኤሌክትሪክ ሃይል ማመንጫ ግደብ 3ኛ አመት  ክብረ በዓል አሰመልክቶ ኤምባሲው በጠራው ስብሰባ ላይ  ሪያድ ከተማ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን የሃይማኖት አባቶች እና የሃገር ሽማግሌዎች እንዳይገኙ  በሳውዲ አረቢያ የኢትዮጵያው አምባሳደር መሃመድ ሃሰን ባስተላለፉት ቀጨን ተዕዛዝ አዛውንቱ በአሸባሪነት ተፈርጀው በአሉን እንዳይታደሙ መታገዳቸው ሪያድ በሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ዘንድ ከፈተኛ ቁጣን ቀስቅሷል።
በተለይ ሰሞኑን  ውስጥ ወስጡን ሲነገር የነበረው የአምባሳደሩ መሃመድ ሃሰን ነውረኝነት ተግባር አርብ ሜይ 9 2014 ምሸት በሪያድ የኢትዮጵያ ኮሚኒት አዳራሽ ውስጥ ለአንድ ኢትዮጵያዊ በተዘጋጀ የእርዳታ ገቢ ማሰባሰቢያ ፕሮግራም ላይ ህዝቡ ተቃውሞውን ማሰማቱን ለማወቅ ተችሏል። በወቅቱ አንድ የሃይማኖት አባት ሪያድ ከተማ ውስጥ መኖር ከጀመሩ 35 አመታትን እንዳስቆጠሩ በማውሳት በሪያድ የሚኖረው ኢትዮጵያዊ ማህበረሰብ በተለያዩ ግዜያት ከሚፈራረቁ መንግስታት አምባሳደሮች እና ዲፕሎማቶች ጋር በተለያዩ የሃገር ጉዳዮች ከኤንባሲው ጎን ቆመው ህዝብን በማስተባበር በሰላም እና በፍቀር እየሰሩ ማሳለፋቸውን ጠቅሰው ዛሬ በማን አለብኝነት የሚከተሉትን የተሳሳተ አቅጣጫ እንዲያርሙ የሚመክሯቸውን ሁሉ በጠላትነት በሚፈርጁ ስረአት አልበኛ የመግስት ሹማምንቶች ኤምባሲያችን እየተመራ በፀረሰላም እና በአሸባሪነት መፈረጃችን በህግ ደረጃ አነጋጋሪነቱ እንደተጠበቀ ሆኖ የስም ስያሜው የተለመደ እና ለታላላቅ ኢትዮጵያውያን እየተሰጠ የሚገኝ የኢትዮጵያውያን መለያ በመሆኑ ልንኮራበት እንጂ ልንሸማቀቅ እና ልናፍርበት አይገባም በለው እምባ እየተናነቃቸው ባሰሙት ንግግር በተሰብሳቢው የድጋፍ ጭብጨባ የአዳራሹ ድባብ ተለውጦ መዋሉን  ለማወቅ ተችሏል።
saudi 13የዛሬውን የገቢ ማሰባሰቢያ ፕሮግራም ለጨቆኞች መልዕክታችንን በግልጽ የምናስተላለፍበት መልካም  አጋጣሚ በመሆኑ ፈጣሪን ልናመስግነው የገባል በማለት የመናገር እደል አግኝተው ተቃውሞቸውን ማሰማት የጀመሩ  አንድ በዕድሜ የገፉ የሃገር ሽማግሌ  በአምባሳደር  እርምጃ የተሰማቸውን ቅሬታ ሲገልጹ ለህዳሴው ግድብ 20 ሺህ ሪያል (1 መቶ ሺህ ብር) የቦንድ ግዢ መፈጸማቸውን ጠቅሰው ወዳጅ እና ጠላቶቻቸውን መለየት በተሳናቸው የመንግስት ተወካዮች ኢትዮጵያውያን ወገኖቼ የተሰጣቸው ስም ተችሮኝ ሰንደቃላማችን የተሰቀለበት ግቢ እንዳልገባ መታገዴ መንግስት  በተለያዩ ሃገራት የሚልካቸውን ሹማምንቶች የአምባሳደርነት ብቃት ትዝብት ውስጥ የከተተው ብቻ ሳይሆን የኮሚኒቲውን ንብረት ለግል ለመቆጣጠር አምባሳደሩ በማን አላበኝነት በግሉ የወሰደው እርምጃ ሊሆን እንደሚችል ጥርጣሬያቸውን ገልጸው ህዝብን በአሸባሪነት ፈርጆ  በብሄር እና በሃይማኖት በማተራመስ  ኢትዮጵያውያን በሃገራቸው ጉዳይ ተሳታፊ እንዳይሆኑ በንጹሃን ላይ የሚለጥፍው የአሸባሪነት ውንጀላ በፍጹም ህጋዊ መስረት እና ምክንያት  የሌለው መሆኑን በተጨባጭ አረጋግጫለሁ ብለዋል።
አንዳንድ የልማት ማህበር ስራ አመራር አባላት በአምባሳደር መሃመድ ሃሰን የተቀንባበረውን ስረአት አልበኝነት ለማስፈፀም  በህዳሴው ግድብ 3ኛ አመት  ከበረ በአል ላይ የሚገኙ እና የማይገኙ ኢትዮጵያውያን ስም ዘርዘር በማውጣት ንጹሃን ኢትዮጵያውያንን በአሸባሪነት በማፈርጅ ተግባር ላይ ተስማርተው የልማት አጋር የሆነውን ህዝብ   እየለዩ የጥሪ ወረቀት በማዘጋጀት ሲያከፋፍሉ እንደነበር  ከውስጥ አውቂ ምንጮች ለመረዳት ተችሏል። ይህ በእንዲህ  እንዳለ በአማራ ልማት ማህበር በኩል  በአሉን እንዲታደሙ የጥሪ ደብዳቤ ደርሷቸው  የነበሩ በሪያድ ነዋሪዎች ዘንድ  የተጣላን በማስታረቅ የተራበን በማብላት የታረዘን በማልበስ በአጠቃ ላይ  በሰው ሃገር የቤት ኪራይ ላጣ ገንዘብ በመለገስ እና ማህበረሰቡን በማስተባበር እርዳታ እንዲዋጣ በማድረግ የሚታወቁ እንደነ ፊት አውራሪ አሊ ሙሃመድ (አሊ ደሴ) አይነቱን  የህገር ሽማግሌ እና መስል ታላላቅ የሃይማኖት አባቶች የበአሉ ተሳታፊ  እንዳይሆኑ መታገዳቸውን ተከትሎ  የህዝብ አገልጋይ ነን እያልን  ስለልማት እንዴት መናገር ያስችለናል በሚል አንዳንድ የአማራ ልማት ማህበር  አመራር አባላቶች በአምባሳደሩ ላይ ቅሬታ ማሰማታቸውን ለማወቅ  ተችሏል።
የሰሞኑንን እርምጃ  በሪያድ የኢትዮጵያ ኮሚኒቲ መስራች  እንደነበሩ የሚነገር ላቸውን  የኮሚኒቲው አንጋፋ አባላት እና ደጋፊዎች ወደ ኮሚኒቲው ቀጥር ግቢ እንዳይደርሱ እየተደረገ ያለው ጥረት አንዱ አካል መሆኑን የሚናገሩ ምንጮች ሪያድ ከተማ ውስጥ ተደረገ በተባለው የአባይ ግድብ 3ኛ አመት በዓል ላይ እንዳይገኙ  የታገዱ ኢትዮጵያውያን በአሸባሪነት በመፈረጃቸው በህዝብ ዘንድ የቀሰቀሰው ቁጣ ወደ ከፍተኛ ደረጃ ሊያመራ እንደሚችል አክለው ገልጸዋል።saudi 12
አምባሳደር መሃመድ ሃሰን በሪያድ ህዝብ ዘንድ ተቀባይነት የሌላቸው ከወገኖቻቸው ይልቅ ለጥቂት የዓረብ ሃብታሞች የሚያጎበድዱ በቅርቡ መፉሃው ውስጥ በተነሳው ሁከት  የዜጎቻቸውን ክቡር ያስደፈሩ ለንዋይ ያደሩ አምባሳደር መሆናቸው ይታወቃል። አምባሳስደር መሃመድ ሃሰን የሃገሪቷን በሄራዊ ክበር ከሚፈታተኑ የተለያዩ ህገወጥ የሃዋላ ነጋዴ የአስሪ እና ሰራተኛ ኤጀንሲ ባለቤቶች ጋር የጥቀም ግንኙነት ፈጥረው በኢትዮጵያውያኑ ህይወት ዶላር ሲሰበስቡ የከረሙ በወገኖቻቸው ሬሳ ገንዘብ የሚበሉ ጨካኝ ሰው መሆናቸው በአብዛኛው ኢትዮጵያዊ የሪያድ ነዋሪ ይነገራል።
ኢትዮጵያውያን የሃይማኖት አባቶች እና የአገር ሽማግሌዎችን በአሸባሪነት በፈረጀው አወዛጋቢው የአባይ ግደብ 3ኛ አመት ክብረ በአል ዙሪያ አርብ ሚይ 09 ምሸት ኢትዮጵያኑ ያሰሙትን ተቃውሞ  አስመልክቶ የዲያስፖራውን ሃላፊ አቶ ተመስገን ኡመር ማብራሪያ እንዲሰጡኝ በስልክ ለማነጋገር ያደረኩት ሙከራ ለግዜው አልተሳካም።
ይህ ሥዕላዊ መግለጫ በዓሉን ለመታደም የመጡ ኢትዮጵያውያን ወደ ኮሚኒቲ ግቢ እንዳይገቡ ታግደው ጥቂቶች የህዳሴውን ግደብ 3ኛ አመት ክብረ በዓል ሲያደርጉ  የሚያሳይ ነው!
Ethiopian Hagere ጅዳ በዋዲ ለጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ የላኩት

የእስረኛው ‹‹ጋዜጠኝነት›› ሌላ ፈተና

May 12/2014
ጽዮን ግርማ
(ፋክት መጽሔት ላይ የታተመ)
የ2012ቱ የአሜሪካ ፕሬዝዳታዊ ምርጫ ከመከናወኑ ጥቂት ቀናት ቀደም ብሎ ስለምርጫውና የአሜሪካ የጋዜጠኝነት ኹናቴ
እንዲወያዩ በአሜሪካ ስቴት ዲፓርትመንት አዳራሽ ከተጋበዙና ከሰማንያ የዓለም አገሮች ከተውጣጡ አንድ መቶ ሠላሣ ተሳታፊ
ጋዜጠኞች መካከል አንዷ ነበርኹ፡፡ ልምዳቸውን እንዲያካፍሉ ከተጋበዙ የአሜሪካ አንጋፋ ጋዜጠኞች መካከል ታዋቂው
የዋሽንግተን ፖስት ጋዜጠኛ ቦብ ውድዋርድ አንዱ ነበር፡፡

ቦብ በስቴት ዲፓርትመንት ሕንፃ አዳራሽ ከሌላ አገር ለመጡ ጋዜጠኞች፤ በምርመራ ጋዜጠኝነት ሥር አጨቃጫቂና አንገብጋቢ
ጉዳዮችን ሲዘግቡ በአሜሪካ መንግሥት የሚያጋጥማቸውን ፈተና እየዘረዘረ፣ ዓለም የሚደነቅበትን የአገሩን የመናገርና የመጻፍ
ነፃነትና ‹ዴሞክራሲያዊ› የምርጫ ሂደት የፕሬዝዳንት ኦባማን ስም ሳይቀር በስም እየጠቀሰ በሒስ ሲሰልቀው ከፍርሃት ነፃ በኾነ
ከፍተኛ የራስ መተማመን መንፈስ ተሞልቶ ነበር፡፡

በወቅቱ የስቴት ዲፓርትመንት ከፍተኛ ባለሥልጣናት “The price of politics” የሚለውን ባለሠላሳ ዶላር መጽሐፉን ፈርሞ
በቦታው ለተገኘነው ጋዜጠኞች በስጦታ እንዳበረከተልን ተናግረው ሲያስጨበጭቡን ቦብ በስጨት ብሎ በማቋረጥ፣ ‹‹መጽሐፌን
ለማንም በነፃ አልሰጠኹም፤ ስቴት ዲፓርትመንቱ ነው ገዝቶ የሰጣችኹ›› በማለት ሲያሸማቅቃቸው በፈገግታ ነበር ያለፉት፡፡
እንግዲህ የዓለም ጋዜጠኞች በተሰበሰቡበት በኢትዮጵያው ጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት አዳራሽ አንድ አንጋፋ ኢትዮጵያዊ ጋዜጠኛ
መሪውንና ሥርዓቱን ሲተች በምናብ ማየት ነው!!

ውይይቱ ሲያበቃም ለጋዜጠኛው ክብር ሲባል በየቡድናችን እየተጠራንባለበት ሔደንየማስታወሻፎቶእንድንነሣስንጋበዝባለሥልጣናቱለጋዜጠኛው ያላቸውክብር በግልጽ ይታይ
ነበር፡፡ ሞጋች ጋዜጠኞችከሚሰደዱበት፣ከሚታሰሩበት አልያም በፍራቻ ሥራከሚያቆሙበት ወይምከፍ ዝቅ ተደርገውእየተመናጨቁ መረጃ

ከሚከለከሉበት፣ ከፖለቲካዊና ገዢዎችን ከሚነካ ዘገባ ይልቅ ወደ ማኅበራዊና መዝናኛ ጉዳዮች እንዲያተኩሩ በእጅ አዙር
ከሚገደድበት አገር ለሔደች ለእንደኔ ዓይነቷ ጋዜጠኛ የስቴት ዲፓርትመንቱ ባለሥልጣናት ለአንጋፋው የዋሽንግትን ፖስት
ጋዜጠኛ ቦብ ውድዋርድ የቸሩት አክብሮት ቢያስደምመኝም የጋዜጠኝነት ሞያ እንዲያ ተከብሮ የሚያስከብር መኾኑን
አላጣኹትም ነበር፡፡

ጋዜጠኝነት እንደሞያ እጅግ የተከበረ ነው፡፡ ጋዜጠኝነት በአቀራረቡ ባለብዙ መልክ ቢኾንም የብልሹ አስተዳደርና አሠራር
ችግሮችን ነቅሶ ለማውጣት፣ ከሕዝብ የተሰወሩ በደሎችን ለማጋለጥ፣ ከሕግና ሥርዓት ውጭ የኾኑ ባለሥልጣናትን በዐደባባይ
ለመተቸትና ለማጋለጥ፣ ለሕዝብ ዋስ ጠበቃ በመኾን የሚያገለግል በተለምዶ አአጠራር ‹አራተኛ መንግሥት› ነው፡፡

ከሚዛናዊነት፣ እውነትና ፍትሕ ጋር የሚሠራ “ሞያዊ ጋዜጠኛነት” (Professional journalism) ለዴሞክራሲዊ አስተሳሰብና
ተግባር ዋናው አንቀሳቃሽ ሞተር ነው፡፡ ከፍርሃትና ስጋት የተጠበቀ፣ ከተገዢነትና አገልጋይነት የጸዳ ጋዜጠኝነት የሚወደድ ሞያ
ነው፡፡ ሞያዊ ጋዜጠኝነት አገልጋይነቱ በቀጥታ ለሕዝብ ስለኾነ ኹሌም ለውጥ በማምጣት ሒደት ውስጥ ዋና ተሳታፊ ነው፡፡
ሞያው ነጻ በወጣባቸው አገሮችም ልክ እንደ ቦብ ውድዋርድ ተከብረው የሚያስከብሩ ጋዜጠኞች ይፈጠራሉ፡፡

በጋዜጠኝነት ሞያ የኢትዮጵያን ነባራዊ ኹኔታ ብናይ፤በሥልጣን ላይ ያለው መንግሥት በአገሪቱ ሐሳብን በነጻነት የመግለጽ መብት
እንደተከበረ በተለያየ መንገድ ያውጃል፡፡ መልሶ ደግሞ ይህን መብት ገደብ አልባ በኾኑ የተለያዩ መንገዶች ሲያፍነውና ሲጨቁነው
ይታያል፡፡ ኢትዮጵያ ውስጥ ባለው አሠራር በተለይ የኤሌክትሮኒክስ ሚዲያው ነጻነት ሙሉ በሙሉ በመንግሥት ቁጥጥር ሥር
ወድቋል፡፡ ለግል የተፈቀዱት ከአንድ እጅ ጣቶች የማያልፉ ሬዲዮ ጣቢያዎችም ቢኾኑ ነፃነታቸው የተረጋገጠው በመዝናኛ
ዝግጅቶችና በጥቂት የማኅበራዊ ጉዳይ ዘገባዎች ብቻ ነው፡፡ የኅትመት ብዙኃን መገናኛን በሚመለከትም በርካታ ጋዜጣና
መጽሔቶች በየወቅቱ ቢታዩም በተለያየ ምክንያት ስለሚቋረጡ በገበያው ረዘም ላለ ጊዜ የሚቆዩት ጥቂቶቹ ናቸው፡፡

እስረኛው ‹‹ጋዜጠኝነት›› በኢትዮጵያ

ኢትዮጵያ ውስጥ የጋዜጠኝነት ሞያ በራሱ ነፃ ያልወጣ እስረኛ ነው፡፡ በገዢው ግንባር ቁጥጥር ሥር የሚገኙ ብዙኃን መገናኛዎች
በመንግሥት ጥቅም ልክ የሚሠሩና ድጋፍ ብቻ የሚሰጡበት ‹‹ጋዜጠኝነት›› ነው፡፡ ከግንባሩ አስተሳሰብና አሠራር የሚነጨው
ይኸው የሞያው እስረኝነት ላለፉት ኻያ ሦስት ዓመታት ሲሠራበት የቆየ ነውና አያጠያይቅም፡፡ በግለሰብ ባለቤትነት በሚመሩ
የኅትመት ብዙኃን መገናኛዎችና ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በተጀመረው የዲጂታል ሚዲያ ላይ ተግባራዊ የሚደረገው ጋዜጠኝነትም
በበርካታ ተጽዕኖች ሥር የወደቀ ጋዜጠኝነት ነው፡፡ በተለይ ከምርጫ 97 ጀምሮ ጠንካራ ክንድ ተጭኖ ይዞታል፡፡
የመንግሥት ባለሥልጣናት በሚሰጧቸው መግለጫዎች ጋዜጠኛውን የሚያንቋሽሹ ቃላትን በመጠቀም በግል ብዙኃን መገናኛ ላይ
የሚሠሩ ጋዜጠኞች አገሪቷን ወደተሳሳተ መንገድ የሚመሩ አጥፊዎች አድርጎ መሣል የተለመደ ነው፡፡ የወንጀል ሕጉ ውስጥ
ጋዜጠኛን በሚመለከት የተካተቱት አንቀጾች፣ የመገናኛ ብዙኃን ዐዋጅና የፀረ ሽብር ዐዋጁ ጋዜጠኝነትን አስረው የሚያስቀምጡ
መቆጣጠሪያ መሣሪያዎች ናቸው፡፡

በመንግሥት ቁጥጥር ሥር ባሉ የኤሌክትሮኒክስና የኅትመት ሚዲያ አማካይነት በየዕለቱ በጋዜጠኞች ላይ የወቀሳ ናዳ በማውረድ
ሞያው ነፃነቱን እንዲያጣ ያደርጉታል፡፡ በመንግሥት ብዙኃን መገናኛዎች ውስጥ ያሉ ጋዜጠኞች የነፃነታቸው ጉዳይ ሳያሳስባቸው
በግል የሚሠሩ ጋዜጠኞችን የሚያንኳስስ ተደጋጋሚ ዘገባ ማቅረብን ለአለቆቻቸው እንደ እጅ መንሻ ይጠቀሙበታል፡፡
በኾነው ባልኾነው ጋዜጠኞችን እየጠሩ ማስፈራራት፣ መክሠሥና ማሰር ሞያውን የበለጠ እንዲኮሰምን ያደርገዋል፡፡ መተቸትን
አብዝቶ የሚጠላው መንግሥት በአገዛዙና በሥርዓቱ ላይ ጠንካራ ትችት የሚያቀርቡ ጋዜጠኞች ሲወጡ ‹‹ከጀርባቸው እገሌ
የሚባል አሸባሪ ድርጅት አለ›› ወይም ደግሞ ‹‹እገሌ ከሚባል አገሪቱን ለማተራመስ ከሚሠራ አካል ላይ ገንዘብ ተቀብለዋል››
በሚል ፈርጆ ሞያውን አስሮ ያስቀምጠዋል፡፡ ለመረጃ ነፃነትና ለጋዜጠኝነት ሞያ ድጋፍ በመስጠት ከማሳደግ ይልቅ ገና ብቅ ሳይል
አናት አናቱን በማለት እዛው ያስቀረዋል፡፡

በሌላ በኩል የመንግሥት ተፎካካሪ የኾኑ የተቃዋሚ ፓርቲ ድርጅቶችም ምንም እንኳን ራሳቸው በበርካታ የመንግሥት ጫና ሥር
የሚገኙ ቢኾኑም ትችት የሚያቀርብባቸውን ጋዜጠኛ ላይ ተጽዕኖ ለማሳረፍ አይሰንፉም፡፡ እነርሱን የሚተች ጋዜጠኛ ቅጥያ
ይለጠፍበትና የመንግሥት ደጋፊ ተደርጎ ይፈረጃል፡፡ በተለይ እርስ በርስ ስምምነት በሚያጡበት ጊዜ ኹሉም ጋዜጠኛውን ወደ
ራሳቸው ጎራ ለመጎተት ይሞክራሉ፡፡ እንቢተኝነትን ያሳየ ወይም ደግሞ ድርጊቱን የተቃወመ ጋዜጠኛ ስሙ ከአንዱ ድርጅት
ወይም ግለሰብ ጋር ተዳብሎ ሞያዊ ክብሩን ይገፈፋል፡፡

ጥቂት በማይባሉ አንባብያን ዘንድ ደግሞ ጋዜጠኛው ያቀረበውን መረጃ ትክክለኛነት በሒደት መዝኖ እውነቱን ከማወቅ ይልቅ
ፍረጃውን ተከትሎ አብሮ የመዝመም ዝንባሌ ይታያል፡፡ በፍረጃ ፍዳውን ባየ ጋዜጠኛ ላይ ውግዘት ይጨምርበታል፡፡ የማንበብ
ፍላጎቱም የሚዘልቀውም የኾነውን የተፈጠረውን ሳይኾን እርሱ እንዲኾን የሚፈልገውን ብቻ ነው፡፡ ጉዳያቸው ብዙኃን መገናኛ
ላይ ለመቅረብ ብቁ የኾነም ያልኾነም ግለሰቦች፣ የንግድ ተቋማት፣ አርቲስቶችና ሌሎች አካላትም የሚጻፉት ነገሮች ኹሉ በእነርሱ
ፍላጎት ልክ እንዲኾን ይወተውታሉ፡፡ ከፍላጎታቸው ውጭ ከተጻፈና ከተዘገበ ደግሞ ከቻሉ መክሰስ ካልኾነ ደግሞ ጋዜጠኛውን
ማንቋሸሽና ጠልፎ ለመጣል ሙከራ ያደርጋሉ፡፡ ምንም እንኳን ሕትመቱ ከመውጣቱ በፊት ቅድመ ምርመራ (censorship)
ባይኖርም ከማቀድና ከመጻፍ በፊት ጋዜጠኛው በግሉ ፤የራስ በራስ ምርመራ (self censorship) በማድረግ የሞያውን ነጻነት
አሳልፎ ይሰጣል፡፡

ሞያው ነጻነት ባጣ ቁጥር ዕድገቱ እየኮሰመነ ስለሚሄድ የሞያው ተፈላጊነት ይቀንሳል፡፡ በዕውቀትና በክህሎት ብቁ የኾኑ አብዛኞቹ
ባለሞዎች ሥራቸውን ይቀይራሉ አሊያም አገር ጥለው ይሰደዳሉ፡፡ ዕለት ከዕለት ሞያውን የሚቀላቀሉት ባለሞያዎችም ብቃት
አነስተኛ ስለኾነ ቁንጽል የሆኑ የጋዜጠኝነት መርሆዎችን ብቻ አንጠልጥለው በመያዝ ሞያውን የበለጠ ያዘቅጡታል፡፡ እንደነዚህ
ያሉ ሰዎች ሞያውን በተቀላቀሉ ቁጥር ገዢው ፓርቲ ይደሰታል፡፡ የጋዜጠኝነት መርሕ ተጥሶ ዘገባ ሲቀርብ የመናገርና የመጻፍ ነፃነት
መብት በአገሪቱ ላይ መከበሩንና ጋዜጠኞቹ ግን ይህን መብት እንዴት እየተጠቀሙበት እንደኾነ ለዓለም ሕዝብ ለማሳያነት ይጠቀምበታል፡፡

በጋዜጠኝነት ዘርፍ ወደ ተለያየ የዓለም አገራት ተጉዘው ትምሕርት ቀስመው የመጡ ምሑራንም ስለ ጋዜጠኝነት ሞያ አስተያየት
ሲጠየቁ ችግሩ ከሥሩ መርምረው ሞያው ነፃነት ያጣበትን ምክንያት ከእነ መፍትሔው በማስቀመጥ ለመቀየር ከመሞከር ይልቅ
በነፃነት ዕጦት በኮሰመነው የግል ብዙኃን መገናኛ የሕትመት ውጤትና ጋዜጠኝነት ላይ ውርጅብኝ ያወርዱበታል፡፡ በከፍተኛ
ትምሕርት ተቋማት የጋዜጠኝነትና ሥነ ጹሑፍ ዕጩ ተመራቂ ተማሪዎች እንኳን ሳይቀሩ በአብዛኛው ለመመረቂያ ጹሑፋቸው
የሚመርጡት ርእስና የሚሠሩት ጥናት የጋዜጠኝነትን ነፃነት የበለጠ የሚያሳጣ ነው፡፡

እነዚህ ኹሉ ችግሮች ተደማምረው ሞያውን አክስመውታል፡፡ አኹን ኢትዮጵያ ውስጥ ያለው ጋዜጠኝነት
ከእስር፣ከስደት፣ከፍረጃ፣ከፍርኃት የተረፈ ‹‹እስረኛ›› ጋዜጠኝነት ነው፡፡ ጋዜጠኝነት በአብዛኛው የራስ በራስ ቅድመ ምርመራ
ራሱን ጠፍንጎ ባሰረ ባለሞያና ለሞያው የጠለቀ ዕውቀት በሌላቸው ሰዎች የመጨረሻ እስትንፋስ እየተንገታገተ ያለ ሞያ ነው፡፡
በመንግሥት በኩል ደግሞ ይቺኑ ትንሽ እስትፋስ እስከ መጨረሻው ለማጥፋት በሚደረገው ጫና ያሉት ጋዜጠኞች ሞያው
የሚጠብቅባቸውን መረጃን ለሕዝብ የማስተላፍ ሥራን ከመሥራት ይልቅ ራስን ወደ መከላከል ሥራ ተሸጋግረዋል፡፡ በተለይ
ካለፉት አራት ዓመታት ጀምሮ ያሉት ጋዜጦችና መጽሔቶች የፊት ገጽ ሽፋንና የድረ ገፆች ዋና መነጋገሪያ ርእስ ጋዜጠኞች ላይ
የሚደረግ እስርና ጫና ላይ ያተኮረ ነው፡፡ ይህ ደግሞ አንዱ የማዳከሚያ ስልት ሊኾን ይችላል፡፡

በየአራት ዓመቱ በሚካሄደውና ለሦስተኛ ጊዜ በተደረገው የተባበሩት መንግሥታት የሰብዓዊ መብት ምክር ቤት መድረክ ላይ
ኢትዮጵያ ለሁለተኛ ጊዜ ተሳታፊ ኾና ቀርባ ነበር፡፡ ስብሰባው የሚደረገው በ197 የዓለም አገሮች መካከል ሲኾን ሲኾን አገራቱ
የሰብዓዊ መብት አያያዛቸውን በሚመለከት ሪፖርት የሚያቀርቡበት እንዲኹም የሚቀርብባቸውን ወቀሳና ትች አዳምጠው
የሚያሳሽሉትን ‹‹አሻሽላለሁ›› የሚሉበት ያልተስማሙበትን ደግሞ ያልተስማሙበትን ምክንያት የሚያስረዱበት ስብሰባ ነው፡፡
ኢትዮጵያ በዚህ ስብሰባ ላይ በ2010 ላይ ስትሳተፍ የመጀመሪያዋ ቢኾንመ የሰብዓዊ መብት ጉዳዮችን በሚመለከት 159
ጉዳዮችን እንድታሻሽል ተነግሯት ዘጠኛ ዘጠኙን መቀበሏን ስልሳውን ግን እንደማትቀበለው ተናግራ ነበር፡፡ስብሰባው በቀጥታ
ከጄኔቭ በቴሌ ኮንፍረንስ የተመራ ሲኾን እያንዳንዱ አገራት ከሚገኙበት አገር ኾነው በስብሰባው እንደተሳተፉት ኹሉ ማክሰኞ
ዕለት በተደረገውና ኢትዮጵያ ለሁለተኛ ጊዜ በተሳተፈችበት በዚህ የምክር ቤቱ ስብሰባ ላይም በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ሚኒስትር
ዴኤታ አምባሳደር ብርሃነ ገብረክርስቶስ የተመራና ከአምስት በላይ የሚኒስቴር መስሪያ ቤት ምክትል ሚኒስትሮችን የያዘ ቡድን
አዲስ አበባ በሚገኘው የተባበሩት መንግሥታት ጽ/ቤት ተገኝተቶ በውይይቱ ተሳትፎ ነበር፡፡

በልኡካን ቡድኑ አማካኝነት የኢትዮጵያ ሪፖርት ከቀረበ በኋላ፤ኢትዮጵያ ውስጥ ያለውን የሰብዓዊ መብት አያያዝ ፣ የበጎ
አድራጎትና ማኅበራት ዐዋጅን በተለመከተና የፀረ ሽብር ሕጉን በሚመለከት በከፍተኛ ተቃውሞ ገጥሟታል፡፡ በስብሰባው ላይ
የተሳተፉት አብዛኛው አገራት ኢትዮጵያ ላይ በሰጡት አስተያየት፤ኢትዮጵያ የፀረ ሽብር ሕጉን የመናገርና የመጻፍ ነፃነትን
እንዲሁም የፖለቲካን ተቃውሞ ለማፈን እየተጠቀመችበት ስለኾነ ሕጉን እንድታሻሽልና ሕጉም ሲሻሻል የፖለቲካ ተቃውሞን
ለማፈን እንዳትጠቀምበት ዋስትና የሚሰጥ መኾን እንዳለበት በመግለጽ ጠንካራ ወቀሳቸውን ሰንዝረዋል፡፡

የልኡካን ቡድኑ አባል የነበሩት የኮሚዩኒኬሽን ምክትል ሚኒስትሩ አቶ ሽመልስ ከማል በአገራቱ የቀረበውን ወቀሳ
አጣጥለው፤ኢትዮጵያ ውስጥ በሽብር ሕጉ ሰበብ ተደርጎ የታሰረ አንድም ጋዜጠኛ እንደሌለ ጠንከር አድርው በመናገር የሽብር
ተግባር ሲፈጽሙ ተይዘው የታሠሩና ከዚህ ቀደም በጋዜጠኝነት ሥራ ላይ ይሠሩ ነበር የሚባሉ እስረኞች ቢኖሩ እንኳን የታሰሩት
ከጋዜጠኝነት ሞያቸው ጋር በተያያዘ ሳይኾን በፈጸሙት የሽብር ወንጀል መኾኑን አበክረው ተናግረዋል፡፡

አቶ ሽመልስ እንዲህ ያለ መከራከሪያ ሲያቀርቡ የመጀመሪያቸው አይደለም፡፡ በዚህ ጉዳይ ላይ አገር ውስጥ ያሉም የውጭ
ጋዜጠኞች ሲጠይቋቸውም ይህንኑ ነው የሚመልሱት፡፡ ዓለም አቀፍ የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ድርጅቶች ሪፖርት ሲያወጡም
የሚመልሱት ይህኑ ነው፡፡ አሁን ደግሞ የዓለም አገራት ተሰባስበው ኢትዮጵያ የመናገርና የመጻፍ ነፃነት አፈናን
እንድታቆም፣በፖሊስ፣በመከላከያና በደህንንት ሰዎች የሚፈጸመው ‹‹ቶርቸር›› እንዲቆም ፀረ ሽብር ሕጉን ጋዜጠኞችን ለማሠር
እንዳትጠቀምበት የዓለም አገራት ተሰባስበው ቢመክሩም የአቶ ሽመልስ ከማል ምላሽ ተመሳሳይ ኾኗል፡፡ በርካታ ችግሮችን
ተቋቁሞ የሚውተረተረው የእስረኛው ‹‹ጋዜጠኝነት›› ትልቁ ፈታናም እዚህ ጋር ኾኗል፡፡ ጋዜጠኛ ይታሰራል ሲታሰር ደግሞ
‹‹በጻፈው ጹሑፍ ሳይኾን በሽብር ተግባር ላይ ስለተሳተፈ ነው›› የሚል ታፔላ ይለጠፍለታል፡፡ ይህ ደግሞ ሞያውን የበለጠ
ችግር ውስጥ ይዘፍቀዋል፡፡ የ‹‹እስረኛው›› ጋዜጠኝነት ሌላ ፈተና ማብቂያ እንደተባለው ኢትዮጵያ የፀረ ሽብር ሕጉን፣ የመናገርና
የመጻፍ ነፃነትን እንዲሁም የፖለቲካን ተቃውሞ ለማፈን እየተጠቀመችበት ነው በሚል እየተወቀሰችበት ያለውን ሕግ ስታሻሻ ይኾን?

Monday, May 12, 2014

የአንድነታችን ደወል!! ማንኛውም ኢትዮጵያዊ ሊያነበው የሚገባ፡፡

May 12/2014
የአንድነታችን ደወል!!


አንድነት ከመቼውም በላይ እንደሚያስፈልገን ፤ አይደለም አሁን ላይ ወደኋላ ከመቶ ዓመታት በላይ ተጉዘን ብንመለከት እንኳ አስፈላጊነቱ ቁልጭ ብሎ የሚታይ ነው፡፡ ሸዋ፣ ወላይታ፣ ከፋ፣ ትግሬ፣ሶማልያ፣ጎጃም፣ ጎንደር ከመቶ ዓመታት በፊት አንድነትን ከሃይል በፊትም ሆነ በኋላ ቢሰብኩልን፤ At the surface level /ህዝቡ/ በኢትዮጵያዊነት ጥላ ስር መጠለል እየፈለገም ቢሆን የተነሳውና የፈረጠመው ገዥ ለማደብዘዝ ቢሞክርም፤ አንድነትን የመሰለ ጠቃሚ እና ብቸኛ አማራጭ አልተገኘም፡፡

በታሪካችን አንድነት የለም ብለን መደምደም የሚያስችል ልሳን የት አገኘን? የክህደት የቅጥፈት ልሳን እንደምን እንዲህ ተንሰራፋ? ኢህአዴግ በአብዮታዊ ዲሞክራሲና ልማታዊ መንግስት አስተሳሰብ እድገት  ከትግል ጀምሮ፣ በሽግግር መንግስት ሂደት፣ በተሃድሶ  ዋዜማ፣ በተሃድሶ እንቅስቃሴ ብሎ በሰየመው አራት ዓስርታት ውስጥ ልማት ቁልፍ መጠሪያ እና መዳረሻው እነደሆነ ሰብኮናል፡፡ ይህንንም በ24 ሰዓታት ውስጥ ከ24 ጊዜ በላይ እንድንሰማው በእቅዱ አቅርቧል፡፡

የትም ፍጪው ዱቄቱን አምጪው እንዳለው ባል፤ ኢህአዴግም ከልምታዊ መንግስትነት መጠሪያ እስከ ታች ድረስ ልማታዊ ሌባን በሚያበረታታ መልኩ ማንነቱን የመሰከረበት ሂደቱ የማንክደው ሐቅ ነው፡፡ እስኪ ይህን ሐሳብ ማስረጃ እናቅርብበት
‹‹ለፍጆታ የሚውሉ የፍጆታ ዕቃዎች እስከ 12% የሚደርስ ጉቦ ይከፍሉ እንደነበር ታውቋል፡፡ ይህም ከመንግስት ኢኮኖሚያዊ ፓሊሲ ጋር የማይጋጭ የጉምሩክ ሰራተኞች የጣሉት የግል ግብር ነበር ማለት ይቻላል፡፡ ሌባ ሣይቀር ሌብነቱን ልማትን በማይጎዳ መልኩ ለመፈጸም መሞከሩ የልማታዊነት አስተሳሰብ በህብረተሰቡ ውስጥ ምን ያህል ሰርፆ እንደነበር ሊያመለክት ይችላል፡፡ መንግስትም ህዝብም በልማታዊነት አላማ ዙሪያ በአንድ ልብ መሥራታቸው ለስራው ስኬታማነት አስተዋጽኦ እንዳበረከተ ጥርጥር የለውም፡፡ ገጽ 52
ይታያችሁ በተለይ ‹‹ሌባ ሳይቀር…›› ከሚለው ጀምራችሁ በድጋሜ አንብቡት…. ይህ እንግዲህ የተባለው ከዋናው ባለራዕይ መሪ ነው፡፡ በሌብነት የሚደገፍ ልማትንም እውቅና ከመስጠት ባሻገር ለአንድነት ተብሎ የሚደረግን የነገስታት ዘመቻ ቅኝ ግዛት ብሎ መፈረጅ፤ በሌብነት ልማት ላይ የተንጣለለን የምጣኔ ሐብት እድገት ምን ብለን እንፈርጀው? ሌባ ካልተያዘ ሌባ አይደለምን ልብ ይሏል!!

በእጅጉ የሚገርመው ጥላቻው ከሰላማዊ/ከፍትሃዊ ልማቱ ሳይሆን ከአንድነቱ ነው፡፡ ይህንም በዚህቹ መጽሐፍ ላይ በሚገባ የምንመለከተው ነው፡፡ እንዲህ ይላል፡፡

“ተሃድሶውና የብሔር እኩልነት” በሚለው ንዑስ ርዕስ ስር በገጽ 99 እንዲህ ተቀምጧል፡፡ ካድሬዎች የታወረባቸውን የልብ ዓይን እንዲበራላቸው ተማጽነው ቢያበሩ እና ቢያነቡት ትልቅ እድገት የሚመጣ ይመስለኛል፡፡ ይህ ሁሉ የሚገኘው በባለራዕዩ መሪ በተጻፈው እና የአብዮታዊ ዴሞክራሲ ዶግማ ወ ቀኖና ተብሎ ከሚነገረው ‹‹ልማት፣ ዴሞክራሲና አብዮታዊ ዴሞክራሲ›› መጽሐፍ ውስጥ ነው፡፡

‹‹ኢህአዴግ መጀመሪያ መመለስ የነበረበት ጉዳይ የኢትዮጵያ ህዝቦች አንድነት ለምን ያስፈልጋል የሚለውን ጥያቄ ነበር፡፡ ›› /አንድነት ለምን እንደሚያስፈልግ መጠየቁ ምን አይነት ፍቺ አለው?/ ቀጠል ያደርግና
‹‹ይህንን ያህል ጊዜ አብረን የነበርን ስለሆን ለወደፊቱም አብረን መኖር አለብን ብሎ ታሪክን ያለፈው ሂደት መግለጫ ብቻ ሳይሆን የወደፊቱም ጉዞ የሚወስን አገር አድርጎ ማቅረብ የሚያስኬድ አይደለም፡፡ ታሪክ በራሱ ድርሻ ቢኖረውም ህዝቦች በዛሬውና በነገው ጉዳይ ላይ ተመስርተው እንጂ ያለፈውን ለማኖር ብቻ ብለው የሚወስኑት ነገር አይኖርም፡፡ በዚሁ ሂደት ብዝቡ ተዋውቋል፣ ተዋልዷል፣ ተሰባጥሮ መኖር ጀምሯል ስለዚህ አንድ ሆኖ መቀጠል አለበት ሚሉም አልጠፉም፡፡ ይህ ክስተት የራሱ ክብደት የሚሰጠው ቢሆንም፣ በእንደዚህ አይነት ሁኔታ መለያየት የራሱ ጣጣ ሊኖረው እንደሚችል ቢጠቁምም ለአንድነት በቂ ነው ሊባል አይችልም፡፡›› “በዛሬውና በነገው ጉዳይ ላይ ተመስርተው እንጂ ያለፈውን ለማኖር ብቻ ብለው የሚወስኑት ነገር አይኖርም…” የሚለው ሐሳብ የአባቶቻችንን ተጋድሎ ባለዕዳ የሚያደረግ ነው፡፡ ይህንን ሐሳብ ከፋሺሽት በቀር ማን ሰብከዋል??

 ልብ ይበሉ፡፡ የመዋለድ፣የመተዋወቅ እና የመሰበጣጠር ትርጓሜ ኢትዮያዊነት መሆኑን ጸሐፊው እንደማይዘነጋው እንዳንሸወድ!! የመዋሃድ እና አድነትን የመፍጠር ማንነት ኢትዮያዊነት መሆኑን እንዳንክድ! ኢትዮጰያዊነት ለአንድነት መሰረት መሆኑ ባይጠቀስልን፣ ተድበስብሶ እና ተጨቁኖ ቢታለፍም አዳማዊነት/ሰብአዊነት ለአንድነት በቂ ምክንያትን ሊፈጥርልን ይችላል፡፡ በባቢሎን ውድቀት በደረሰው መለያየት/ቋንቋ፣ጎሳ…./ ላይ ተኮፋፍሰን/ተከፋፍለን ልዩነትን የምንሰብክ ከሆነ ከዲያቢሎስ ቁራጭነት የተለየ ስያሜ የሚያሰጠን ነገር አይኖርም፡፡ የሰው ልጅ በቀለም፣ በዘር፣ በቋንቋ እና በጎሳ ቢለያይ ‹‹የሰውነቱ›› ማንነት አንድ ሊያደርገው ይችላል፡፡ ፍትሃዊ፣ የሁሉም ዘር፣ ቋንቋ ጎሳ ስብጥር የሆነ መንግስታዊ አስተዳደር ከተፈጠረ ሊያበታትነን የሚችለው ምክንያት ምንድን ነው? ከኋላ ታሪካችን ውስጥ ያለያዩንን ህጸጾች እየጠቀስን አንድታችንን ከማናጋት እና የወደፊት እኛነታችንን ከማበላሸት ከኋላ ታሪካችን አንድነትን የሚፍሩብንን እሴቶች እየሰበክን አንድነትን ለምን አልመሰረትንም?
አጼ ዮሐንስ በቦሩ ሜዳ የቆረጡትን ምላስ ሀውልት ከምንሰራ፣ አጼ ዮሐንስ አንገታቸውን የተቆረጡበትን ቦታ ሐውልት ብንሰራ አንድነታችን አይሰብክልንምን? አኖሌ ላይ ጡት እና እጅ ከምንገነባ አድዋ ላይ የአንድነታችንን ምስጢር ሐውልት ብንገነባ አይመረጥምን? ጣልያን አድዋን ሲያስብ እንደሚያንገፈግፈው ሁሉ እኛን ለምን አንገፈገፈን?

አለም እየከዳው እና እየከደነው የሚሄደውን የአድዋን ድል በአፍሪካ አገራት ሁሉ ሐውልት ማስቆም ሲገባን አንድ የሚያደርገን በቂ ምክንያት የለም ብሎ መደምደም ኢትዮጵያዊነት ወይስ ጣልያናዊነት? አንድነታችንን እንደማይፈልጉት በግልጽ እየተነገረን እና ጊዜ እያሳየን እኛ ለምን አንድ አንሆንም? ከቦንጋ አድዋ የሚወስደው የንግድ መስመር ለአንድነታችን መሰረት ሆኖ ሊገነባ፣ ሊሰበክ እንዲሁም በርካታ የጥበብ ትሩፋቶች ሊለቀሙበት ሲገባው ለምን መስመሩ እንዲህ በእሾህ ታጠረብን? የአንድነታችን መሰረት ኋላቀርነትን ለማስወገድ ልማታዊነታችንን ለማስቀጠል ብሎ የሚሰብክ መሪ/ የሌባውን ልማታዊነትም ሳንዘነጋው/ ለዚህች አገር መሰረት ‹‹ትላንት ሳይሆን ዛሬ›› ብሎ መሸምጠጥ  ‹‹የአንድነታችን መሰረትም ኢህአዴግ፣ አብዮታዊ ዴሞካራሲ ነው!›› ብሎ ማፍጠጥ ምን የሚሉት የዘመን ውራጅ ነው?

ከፋ፣ ቅማትን፣ ወይጦ፣ ወላይታ፣ ሲዳማ፣ ቦንጋ፣ አርሲ፣ ሸዋ፣ ጅግጅጋ፣ ሀድያ፣ ሐረር፣ ጎንደር፣ መቀሌ፣ አስመራ፣ አፋር፣ ጎጃም፣ ወሎ፣ በአራቱ ብቻ ሳይሆን በስምንቱም ማዕዘን የምትገኝ ሰው መሰረትህ አዳም መሰረትህ ሰብኣዊነት፣ አንድነትህ ኢትዮጵያዊነት ነው!! ትላንትም ነበረ፣ ዛሬም አለ፣ ነገም የሚቀጥል ነው፡፡ የሚሰበክልንን ዘመነኛ ፖለቲካ ትተን አንድ ቀይ ደማችን፣ ስጋችን እና አጥንታችን በሰብኣዊነት መንፈስ ተዋህዶ አትዮጳዊነትን ሊፈጥርልን ይገባል!! እኔ ትግሬ ሆኘ ስለምን ኦሮምኛ ቋንቋን ለመቻል እና አንድ ለመሆን አይረዳኝም? ኢትዮጵያዊነት የኦሮሞት እና የትግራይነት ውህደት ነው!! “አማራ” እና ቅማንት ከሚያገናኛቸው እልፍ መስተጋብሮች አልፎ ልዩነቱ ለምን ተለይቶ ይሰበካል? ጎንደሬው ቅማንትኛ ለማጥናት እና ቅማንቱ ጎንደሬ ነኝ ብሎ መዋሃድን ለምን አልተሰበከም??

ነገሩ ሁሉ ግልጽ ነው! ጨቋኝ መሪዎቻችን የአንድነታችንን መሰረት እነደማይሰብኩልን 2 ዓስርታት መስክረውልናል፡፡ ከመቼውም የበለጠ የአንድነት ትርጉም እና ዘላለማዊ ዋጋ አሁን የምንንረዳበት ጊዜ ነው፡፡ ዋለልኝ መኮንን እንዲያ ጽፎ ያቀረበው የብሔር ጥያቄ የአንድነት መሰረት ቢታከልበት ኢትዮጵያ እንዲህ ባልተፈረካከሰች ነበር፡፡

አሁን ግልጽ ነው፡፡ የአንድነታችን መሰረት በተናጋ ቁጥር ገዥዎቻችን የጭቆና ወንበሮቻቸው ይበረታሉ፡፡ አንድነት አሁን ይደውላል!! ከተለያየን አለያዮቻችን በደወሉ ይጨፍራሉ፣ በእኛ እንባ እና ደም ይሰክራሉ… ኢትዮጵያ ትጮሃለች!! የአንድነታችን ደወል…!!

ከኢትዮጵያዊነት የአንድነትና የፍቅር መንፈስ ጋር የሚጣሉ ሁለ ይደቃሉ!

May 12, 2014
በዲ/ን ኒቆዲሞስ (ምንጭ ፋክት) መጽሔት

“… ኢትዮጵያን አምላኬ ምትለው እግዚአብሔር ከኃያሉና ከብርቱ መዳፌ የሚያድናት፣ የሚታደጋት ከሆነ የእኔንም እግዚአብሔር ልጨምርላት እችላለሁ …፡፡” ቤኒቶ ሞሶሎኒ

ይህን ንግግር በሮማ አደባባይ የተናገረው ኢጣሊያዊ የፋሽስት መሪ ቤኒቶ ሞሶሎኒ ነው፡፡ ሞሶሎኒ ሮማውያኑ አያቶቹና አባቶቹ በዓድዋ የጦር ግንባር የተከናነቡትን ሽንፈትና ውርደት ከታሪክ መዛግብት እየቀፈፈውና እየዘገነነውም ቢሆን አንብቦ ነበር፡፡ ከዚህ ለማሰብ ቀርቶ ለማለም እንኳን ከሚከብድ የታሪክ ሐቅ ጋር የተፋጠጠው ሞሶሎኒ አምኖ ሊቀበለው የከበደውን ግን ደግሞ ሊፍቀው ያልቻለውን ይህን የታሪክ ውርደት፣ ይህን የታሪክ ስብራትና ክፉ ጠባሳ በሮማና በመላው አውሮጳ ምድር ይሻር ዘንድ ራሱን ታሪክን አዳሽ፣ ኃያልና ብርቱ የዘመኑ ጦረኛ ጎልያድ መሆኑን ለራሱም ለሕዝቡም አሳመነ፡፡
ሞሶሎኒ ሮማውያንን ብቻ ሳይሆን የመላውን አውሮጳውያን ቅኝ ገዢ ኃይሎችን ያዋረደ፣ ልክና ወደር ያጣውን ትዕቢታቸውንና ንቀታቸውን እንደ እንቧይ ካብ የናደውን ይህን የዓድዋውን ሽንፈት በመበቀል በአውሮጳ አዲስ አንጸባራቂ የድል ታሪክ ሊያስመዘግብ ቆርጦ ተነሣ፡፡ ሞሶሎኒ ሮማና መላው የአውሮጳ ቅኝ ገዢ ኃይሎች በኢትዮጵያና በኢትዮጵያውያን የደረሰባቸውን የውርድትና የሽንፈት አሳፋሪ ታሪክ ለማደስ በሮማ አደባባይ ለተሰበሰቡ የኢጣሊያ ሕዝብ እንዲህ ሲል በእብሪት ተሞልቶ ሮማ ዛሬም ኃያልና ታላቅ መሆኗን ለራሱና ለሕዝቡ ዳግም አበሰረ፡፡
ሞሶሎኒ ለ700 ዓመታት የዘለቀውን ታላቁን የሮማን ሥልጣኔና ታላቅነት እያስታወሰ ይህን አይደፈሬ የሆነውን የሮማን ታላቅነትና ክብር የተደፋፈሩትን ኢትዮጵያንና ኢትዮጵያውያንን ለመቅጣት ጊዜው አሁን መሆኑን በአደባባይ አወጀ፡፡ ይህ በኢትዮጵያውያን የደረሰውን የሮማን የታሪክ ስብራት ለመጠገን ሞሶሎኒ የኢጣሊያ ሕዝብ ሁሉ ከጎኑ ይቆም ዘንድ ቀጭን ትዕዛዝ አስተላለፈ፡፡
እናም ይህ አረመኔና ያልተገራ የኢትዮጵያን/ጥቁር ሕዝብን እንደ ሰም አቅልጬ፣ እንደ ገል ቀጥቅጬ በባርነት እገዛው ዘንድ የሚያግደኝ ማን ነው፣ የትኛው ጎበዝ፣ የትኛውስ ኃይል ነው ሲል ሮማዊው ጎልያድ፣ ሞሶሎኒ እንዲህ በኢትዮጵያና በኢትዮጵያዊነት ላይ ተሳለቀ፡፡ በኢትዮጵያ አምላክም ላይ በድፍረት አፉን አላቀቀ፡፡ እናም እንዲህ ሲል በሮማ አደባባይ ላይ ከፍ ባለ ድምፅ አወጀ፡፡
‹‹… ኢትዮጵያን አምላኬ ምትለው እግዚአብሔር ከኃያሉ መዳፌ የሚያድናት ከሆነ የእኔንም አምላክ ልጨምርላት እችላለሁ …፡፡›› ሲል በኢትዮጵያ አምላክ ላይ ተሳለቀ፣ በልዑል እግዚአብሔር ላይ የትእቢትንና የድፍረትን ነገርን ተናገረ፡፡ በሮማ ምድርም በእምዬ ኢትዮጵያ ላይ የጥፋት ቀን ተቀጠረላት፡፡ ማን ኃያል፣ ማን ብርቱ ነው ሊያቆመን የሚቻለው ያሉ የሮማ የጥፋት አበጋዝ፣ ታላቅ ሠራዊት በኢትዮጵያ ምድር ላይ ያለ ምንም ከልካይና ሃይ ባይ ተመመ፣ ዘመተ፤ ምድሪቷንም ክፉኛ አስጨነቋት፡፡
ኢትዮጵያንና ኢትዮጵያዊነትን የአንድነትና የፍቅር መንፈስ እንደ ከንቱነት የቆጠሩ፣ የኢትዮጵያን አምላክም ያቃለሉ እብሪተኞች በበቀል መንፈስ የጥፋት ሰይፋቸውን በሕዝባችን ላይ መዘዙት፡፡ ይህ የጥፋት ሰይፋቸውም ሕፃን፣ ሽማግሌ፣ ሴት ወንድ ሳይል ሁሉንም ያጭደው ያዘ፡፡ የመርዝ ጋዝን፣ የሞት አረርን የጫኑ አውሮፕላኖችም በኢትዮጵያ ሰማይ ላይ እየተገለባበጡና እያጓሩ ሰውና እንሰሳ ሳይሉ ይሄ ነው የማይባል ዘግናኝና አሰቃቂ የሆነ መአትንና መቅሰፍትን በሕዝባችን ላይ አወረዱበት፡፡
እነዚህን የኢትዮጵያን ሰማይ እያረሱ፣ እየሰነጠቁና እያጓሩ የሞት መርዝን የሚረጩ አካላትን አይቶም ሰምቶም የማያውቀው የአገሬ ሕዝብና ባለ ቅኔም፡-
የለህም እንዳልል ይመሻል ይነጋል፣
አለህም እንዳልል እንዲህ ይደረጋል፡፡
አምላክ ለአንተው ፍራ፣
በቤትህ አግድመት ጎዳና ተሠራ፡፡
ሲል ጭንቅ ጥበብ ብሎት ይህን አቤቱታ ለአምላኩ በቅኔው አሰማ፡፡
እማማ ኢትዮጵያ በሰይፍ ለወደቁ፣ በመርዝ ጋዝ ጭስ ላላቁ ልጆቿ፣ ወገቧን በገመድ ታጥቃ ብርቱ ጩኸትን ጮኸች፣ እንደ አይሁዳዊቷ ራሄል ያለ ብርቱ እንባዋንም ወደ አርያም፣ ወደ ፀባዖት ረጨችው፡፡ የሕፃናት፣ የጎበዛዝቱ፣ የእናቶችና የሽማግሌዎች ደም ምድሪቱን አጨቀየው፡፡ ዕንባ በሥፍር ተቀዳ፣ ደም እዚህም እዛም እንደ ጎርፍ ጎረፈ፡፡ ቅዱሳት መካናትና ገዳማት ሳይቀሩ በሮማውያኑ ሠራዊቶች ተደፈሩ፣ መነኮሳት፣ ካህናትና ዲያቆናት ያለ ምንም ርኅራኄ በጭካኔ ታረዱ፣ ተጨፈጨፉ፡፡
በወቅቱ ግራዝያኒ በኢትዮጵያውያን ላይ መጠቀም ስለሚገባው የመሣርያ ዓይነት በሚስጥር ያስተላለፈውን መልእክት የአሜሪካው ‘ላይብረሪ ኦፍ ኮንግረስ’ የሚገኝ አንድ ዶሴ እንደሚከተለው በሚስጢር ጽፎ እንደነበር ያጋልጣል፡፡ “ተልእኳችን እንዲሳካ ከተፈለገ በኢትዮጵያውያን/በጠላት ላይ እጅግ ከፍተኛ ውድመት ከዚህም በላይ የሞራል ስብራት የሚያስከትለውን ልዩ የሆነ ፈሳሽ ቦምብና መርዝ ሼል እንደፈለጉ በስፋት መጠቀም ያስፈልጋል፡፡”
የአገሬን ክብርና ነፃነት ለባዕድ አሳልፌ አልሰጥም፣ በኢትዮጵያዊነት ልዑላዊነትና የአንድነት መንፈስ ላይ በጭራሽ አልደራደርም ያሉት አቡነ ጴጥሮስም በሮማውያኑ መትረየስ በአደባባይ በጭካኔ ተደብደበው ሰማዕት ሆነው አለፉ፡፡ ኢትዮጵያ ፈጽማ በኀዘን ድባብ ተዋጠች፣ ክፉኛም አነባች፡፡
የኢትዮጵያ ታላቅ ባለውለታ የነበሩትና የኢጣሊያን ፋሽስት ግፍ ለዓለም ሁሉ በመግለጽ ከኢትዮጵያውያን ጎን የቆሙት ሲሊቪያ ፓንክረስት፣ የፋሽስቱ መሪ ቤኒቶ ሞሶሎኒ በኢትዮጵያውያን የሃይማኖት አባቶች ላይ እየተወሰደ ያለው እርምጃ ሌሎች ኢትዮጵያውያንን ሊያሸማቅቅ እንደሚችልና ጭፍጨፋውም ውጤታማ እንደሆነ በወቅቱ ለቅኝ ግዛት ሚ/ሩ ለግራዚያኒ ያስተላለፈውን ምስጢራዊ የቴሌግራም መልእክት Ethiopia and Eritrea በሚለው መጽሐፋቸው እንዲህ ገልጸውታል፡-
…The execution of Abune Petros, one of the four Ethiopian bishops, has terrified the leaders and the public. The work of repression against armed groups dispersed in the forest continues.
አቡነ ጴጥሮስም በመጨረሻ ቃላቸው፡- እምዬ ኢትዮጵያ … እናት አገሬ … ደሜ ለነፃነትሽ፣ ለክብርሽ፣ ለአንድነትሽ ንጹሕ የፍቅር መሥዋዕት ሆኖ የፈሰሰ ነውና ጽኑና ኃያል በሆነው አምላክሽ ፊት ልክ እንደ አቤል ደም ፍርድን የሚሻ፣ ፍትሕን የሚጠይቅ ይሁን፡፡ ሲሉ ዓይናቸውን ወደ ሰማየ ሰማይ አቅንተው አምላካቸውን እግዚአብሔርን በዕንባ ተለማመኑት፣ ተማጠኑት፡፡
እመብርሃን፣ ድንግል ሆይ … ይኸው ለቃል ኪዳን ምድርሽ እንባዬን ከደሜ ጋር ቀላቅያለሁና… ይህን በሕዝብሽ፣ በአገልጋዮችሽ ላይ እየወረደ ያለውን ግፍና መከራ በልጅሽ ፊት አዘክሪ፣ አሳስቢ፡፡ እናቴ ሆይ አዛኝቱ ያለ አንቺ ማን አለኝ፤ ድንግል ሆይ ‹‹ስምዒ ሐዘና ወብካያ ለሀገሪትነ ኢትዮጵያ!›› ሲሉ የኢትዮጵያን ሰቆቃዋን፣ ጣሯንና ጭንቀቷን አሳስቢ ሲሉ ተማፀኑ፡፡
ያ ለነጻነት ክቡር መንፈስ የፈሰሰ ዕንባቸውና ደማቸው በኢትዮጵያ ተራሮች፣ ሸንተረሮች፣ ዱርና ጫካ ታላቅ የሆነ የነጻነት ደወልን አሰማ፣ አስተጋባ፡፡ እምቢ ለነጻነቴ ያሉ የኢትዮጵያ የቁርጥ ቀን ልጆች ዘር፣ ጎሳ፣ ቋንቋና ሃይማኖት ሳይለያቸውና ሳይከፋፍላቸው ነፃነታቸውን በደማቸው ለማስመለስ ዱር ቤቴ ብለው ከተሙ፡፡ የእናት ኢትዮጵያን ህመሟን፣ ስቃይዋንና መከራዋን በዕንባቸውና በላባቸው፣ በደማቸውና በአጥንታቸው ታላቅ መሥዋዕትነት ይካፈሉ ዘንድ ዱር ቤቴ አሉ፡፡
የኢትዮጵያዊነትን የአንድነትንና የፍቅር ቅዱስ መቅደስ በደማቸው ዳግም ሊቀድሱና ሊያከብሩ በነፍሳቸው የተወራረዱ ኢትዮጵያውያን ጀግኖች በሮም አደባባይ በደማቸው ሕያው ታሪክን ጻፉ፡፡ የኦሮሞ ምድር ፍሬ የሆኑት ጀግናው ኮ/ል አብዲሳ አጋና ኤርትራዊው ዘርአይ ደረስ፡- በባዕድ ምድር፣ በግዞት እንኳን ሆነው፡- ‹‹ኢትዮጵያ ሆይ ብረሳሽ ቀኜ ትርሳኝ፣ ባላስብሽ ምላሴ በጉሮዬ ይጣበቅ፡፡›› በማለት የእናት ምድራቸውን አረንጓዴ፣ ቢጫና ቀዩ ሰንደቀ ዓላማቸውን በሮም አደባባይ ከፍ አድርገው በማውለብለብ ኢትዮጵያዊነት የአንድነት እና የፍቅር ቅዱስ መቅደስ መሆኑን በደማቸው መሰከሩ፡፡
በርካታ ኢትዮጵያውያን በአርበኝነት በአገራቸው ዱርና ተራራ ተሰደዱ፣ ሌሎች ደግሞ በዕንባና በለቅሶ እግዚአብሔር ኢትዮጵያን ይታደጋት ዘንድ ሱባኤ ገቡ፡፡ በኢየሩሳሌምም በሚገኘው የዴር ሱልጣን ገዳምም የተሰደዱ በርካታ ኢትዮጵያውያን መነኮሳት፣ ካህናትና ሹማምንቶች የኢትዮጵያ አምላክ ለአገራቸው ነጻነትን ይመልስላት ዘንድ በጸሎት መጋደል ያዙ፡፡
ኢየሩሳሌምን በሚገኘው ገዳማችንን ተሳልመው የጥቂት ቀናት ቆይታ አድርገው መንገዳቸውን ወደ ጄኔቭ ያደረጉት ዓፄ ኃይለ ሥላሴም በሊግ ኦፍ ኔሽን አቤቱታቸውን አቀረቡ፡፡ ንጉሡ በንግግራቸውም የኢጣሊያ የፋሽስት መንግሥት በአገራቸው ሕዝብ ላይ እያደረሱ ያሉትን ግፍና በዓለም መንግሥታት የተከለከለ መርዛማ ጭስ በአገራቸው ሕዝብ ላይ እያወረደ መሆኑን በመጥቀስ ይሄን ዘግናኝና አሰቃቂ መዓት ኃያላኑ ጣልቃ ገብተው እንዲያስቆሙ በብርቱ ተማፀኑ፡፡ የሕዝባቸውም አቤቱታ አሰሙ፡፡
የቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ አቤቱታና የሕዝባቸው ለቅሶና መከራ ግን ለአውሮጳውያኑ እምብዛም የሚያስጨንቃቸው ጉዳይ አልነበረም፡፡ እንደውም ለአንዳንዶቹ አውሮጳውያን ራሷን ከነጭ እኩል አድርጋ ለምታስበው ኢትዮጵያ ይህ ቅጣት የሚገባ፣ ልኳን እንድታውቅ የሚያደርግ መሆኑን በማመን ለሞሶሎኒ በግልጽና በስውር በርታ ሲሉ ቀኝ እጃቸውን አዋሱት፡፡
በሊግ ኦፍ ኔሽን መድረክ ተግባራዊ ምላሽ ያላገኙት ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴም፣ ‹‹… ይህን የአገሬንና የሕዝቤን ግፍና መከራ ችላ ብላችሁ ብታልፉት ታሪክና እግዚአብሔር ፍርዳችሁን ይሰጣችኋል … ፡፡ ሲሉ ትንቢታዊ የሚመስል ታሪካዊ ንግግርን አደረጉ፡፡ የኢትዮጵያን በአምባገነኑ የፋሽስት ሠራዊት መወረርና የሕዝባችንም ግፍ በዝምታ ያለፉ አውሮጳውያኑ አገራት ብዙም ሳይቆይ ከጀርመን በተነሳው በናዚ ሂትለርና በፋሽስቱ መሪ ሞሶሎኒ የጦር ክተት ታወጀባቸው፡፡
አምባገነኖችን በጊዜው ተው፣ እረፉ ለማለት የሞራል ብቃት፣ ጉልበት ያነሰውና ‹‹ጥርስ የሌለው አንበሳ›› የሚል ፖለቲካዊ ስላቅን ያተረፈው ‹‹ሊግ ኦፍ ኔሽንም›› በዓይኑ ፊት በአምባገነኖቹ ሂትለርና ሞሶሎኒ አገራት በግፍ ሲወረሩ የኃይለ ሥላሴ ትንቢታዊ ንግግር እየተፈጸመ እንደሆነ በወቅቱ ቀውሱን የታዘቡ ፖለቲከኞችና የታሪክ ምሁራን በሰፊው ጻፉ፣ መሰከሩ፡፡ በኢትዮጵያ ላይ የደረሰውን ኢፍትሐዊ ወረራና ግፍ በዝምታ ያለፉ አውሮጳውያን በራሳቸው ሲመጣ ግን ለመታገሥ አልቻሉም ነበር፡፡ ሳይወዱ ተገደው ወደ ጦርነት ገቡ፣ እናም የሁለተኛው የዓለም ጦርነት በአውሮጳ ሊፈነዳ ግድ ሆነ፡፡
የታሪክ ምሁራንና የፖለቲካ ተንታኞች እንደጻፉት ለሁለተኛው የዓለም ጦርነት መፈንዳት ሊግ ኦፍ ኔሽን ኢትዮጵያ በፋሽስት ኃይል ስትወረር ያሳየው መለሳለስና ደካማ አቋም እንደ አንድ ትልቅ ምክንያት ከሚጠቀሱት መካከል መሆኑን ያስመሩበታል፡፡ ‹‹አክሲስ ፓወር›› በሚል በጀርመኑ ሂትለር፣ በፋሽስቱ ሞሶሎኒና በቶኪዮ/ጃፓን የተባባረ ኃይል ዓለምን በራሳቸው ቁጥጥር ስር ለማድረግ የተነሡ ሮምንና ጀርመንን ለመመከት እንግሊዝና ፈረንሳይ ሌሎችን አገሮችን በማስተባበር ወደ ጦርነት ከተቱ፡፡
የኢትዮጵያና የሕዝቦቿም ለቅሶ በእግዚአብሔር ፊት ታሰበ፡፡ የግፍ ጽዋም ሞልቶ ፈሰሰ፡፡ እናም፣ ‹‹ስለ ድሆች፣ ስለ ምድሪቱ ግፉአን፣ ፍትሕንና ፍርድን ስለተነፈጉ ምንዱባን እግዚአብሔር አሁን ይነሳል፡፡››፣ ‹‹እግዚአብሔር ተዋጊ ነው ስሙም እግዚአብሔር ነው፡፡›› ተብሎ በአባቶቻችን ቅዱሳን ነቢያት የተነገረለት የሠራዊት አምላክ እግዚአብሔር የመዓቱን ጽዋ በአውሮጳ ምድር ላይ አፈሰሰው፡፡ አውሮጳ እስከዛሬ አይታው በማታውቀው መከራና ሰቆቃ ውስጥም ተዘፈቀች፡፡
በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሰዎች ያለቁበትና የአካል ጉዳተኛ የሆኑበት የሁለተኛው የዓለም ጦርነት ከፍተኛ የሆነ ፖለቲካዊ፣ ኢኮኖሚያዊ፣ ማኅበራዊና ሥነ ልቦናዊ ቀውስ አስከትሎ የናዚውን ሂትለርና የፋሽስቱን ሞሶሎኒ ታሪክ በውርደት ደመደመው፡፡ የትኛው አምላክ ነው ኢትዮጵያን ከኃያሉ ክንዴ የሚያስጥላት ያለው ሞሶሎኒም በሮም አደባባይ አይወርዱ ውርደትን ተዋርዶ የሞት ስቅላት ተፈረደበት፡፡
‹‹ኢትዮጵያን ከሕዝቦቿ ጋር ካልሆነም ኢትዮጵያን ገጸ-በረከት አድርጌ አቀርብልሃለሁ፡፡›› ብሎ ለአለቃው ለሞሶሎኒ ቃል የገባው ማርሻል ግራዚያኒም በአርበኞቻችንና በእንግሊዛውያን የጦር ሠራዊት ዕርዳታ ከነሠራዊቱ አፍሮና ተዋርዶ አገራችንን ለቆ ወጣ፡፡ በኢትዮጵያ ሰማይ ላይ በልጆቿ ደም የተቀደሰው አረንጓዴ፣ ቢጫና ቀዩ ሰንደቀ ዓላማዋ ዳግመኛ ከፍ ብሎ ተውለበለበ፡፡ እነ ዘርአይ ደረስ፣ እነ አብዲሳ አጋ፣ እልፍ ኢትዮጵያውያን አርበኞች በሮም አደባባይ ሳይቀር በደማቸው ከፍ ያደረጓት ሰንደቀ ዓላማችን ሚያዚያ 27 ቀን 1933 ዓ.ም. በክብር ዳግመኛ ከፍ ብላ ተውለበለበች፡፡
ዳግመኛ ኢትዮጵያዊነት ለጊዜው የሚያንቀላፋ እንጂ የማይሞት ጽኑና ሕያው ቃል ኪዳን መሆኑ ተበሰረ፡፡ ከኢትዮጵያና ከኢትዮጵያዊነት ጽኑ ቃል ኪዳን ጋር የተገዳዳሩ ሁሉ ዕድል ፈንታቸው፣ ጽዋ ተርታቸው ድቀት፣ ውርደትና ጥፋት ሆነ፡፡ የኢትዮጵያዊነትን የአንድነትና የፍቅር ቅዱስ መቅደስን ሊያረክሱና ሊያራክሱ የተነሡ ሁሉ ለድቀት፣ ለውርደትና ለአሳፋሪ ሽንፈት መዳረጋቸው የታወቀ ሐቅ መሆኑ ተመሰከረም፡፡ በምንም የማይረታና የማይሸነፍ በዓድዋ የተበሰረው ጽኑ የኢትዮጵያዊነት ታላቅ መንፈስም ዳግመኛ በሮማ ውርደት የተነሣ ከዓለም ጫፍ እስከ ጫፍ ተሰማ፡፡
ይህ የኢትዮጵያዊነት ክቡር የአንድነትና የፍቅር መንፈስ የቋራው ካሣ/ቴዎድሮስ በመቅደላ አፋፍ የተሰውለት፣ አፄ ዮሐንስ፣ ‹‹ኢትዮጵያ አገርህ ልጅህ፣ ሚስትህ፣ እናትህ፣ ዘውድህ፣ ክብርህና መቃብር ናት፡፡› በሚል በመተማ አንገታቸውን ለሰይፍ፣ ደረታቸውን ለጦር የሰጡለት፣ እምዬ ምኒልክ፣ እቴጌ ጣይቱ፣ እልፍ የኢትዮጵያ ጀግኖች በዓድዋ ጦር ግንባር በደማቸው የቀደሱት፣ ያከበሩትና ያወደሱት ነው … ይህ ዘመን የማይሽረው የኢትዮጵያዊነት ቃል ኪዳን፣ ክቡርና ታላቅ መንፈስ!!
በየዓመቱ የምናከብረው፣ የምንዘክረው ሚያዚያ 27 ቀንም ክቡር አባቶቻችንና እናቶቻችን ለኢትዮጵያ ነጻነት፣ ልዑላዊነት፣ ለሰንደቀ ዓላማዋ ክብርም ያለ ምንም መሳሳት ውድ ሕይወታቸውን የከፈሉበት ነጻነታችንን ምናስታውስበት ታላቅ ቀን ነው፡፡
ደግሞም የኢትዮጵያዊነትን የአንድነትንና የፍቅርን ሸማ የተላበስን ሁሉ በኢትዮጵያዊነት የአንድነትና የፍቅር መንፈስ ላይ ለመገዳዳር ለሚነሡ ሁሉ ሌሎች የደረሰባቸውን ውርደትና ድቀት ከታሪክ ይማሩ ዘንድ የምናሳስብበት ቀንም ነው፡፡ የኢትዮጵያዊነት ክቡር መንፈስ የዘር፣ የነገድ፣ የቋንቋ፣ የሃይማኖት ድንበር የማያግደው ሕያውና ጽኑ ቃል ኪዳን፣ ቅዱስ የፍቅር መቅደስ መሆኑን ያስታውሱና ራሳቸውንም ከውርደት፣ ከጥፋትና ከድቀት ያድኑ ዘንድም እንነግራቸዋለን፣ ግድ እንላቸዋለንም!!